ቀጥታ፡

1 ሺህ 131 የምርጫ ክልል ውጤቶች ወደ ማረጋገጫ ማዕከል ደርሰዋል

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 4/2018 (ኢዜአ)፦ ከ1 ሺህ 139 የምርጫ ክልል ውጤቶች 1 ሺህ 131 ያህሉ ወደ ማረጋገጫ ማዕከል መድረሳቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ ገለጹ።

ሰብሳቢዋ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አሁን ላይ ከ501 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ ክልሎች ውስጥ 497ቱ ወደ ማረጋገጫ ማዕከል ደርሰዋል፡፡

እንዲሁም ከ638 የክልል ምክር ቤት ምርጫ ክልሎች 634ቱ ወደ ቦርዱ ማረጋገጫ ማዕከል መድረሳቸውንም አስታውቀዋል።

በዚህም መሰረት ከ1 ሺህ 139 የምርጫ ክልሎች ውጤት 1 ሺህ 131 ያህሉ ወደ ማረጋገጫ ማዕከል መድረሳቸውንም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም