የዋናው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ጀምሮ ይካሄዳል - የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን - ኢዜአ አማርኛ
የዋናው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ጀምሮ ይካሄዳል - የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን
አዲስ አበባ ፤ ሰኔ 5/2018(ኢዜአ)፦ የዋናው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ጀምሮ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የዋናው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሀን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ዋናውን የምክክር ጉባኤ ለማካሄድ ስኬታማ ሥራ መሰራቱን ገልጸዋል።
በአጀንዳ ማሰባሰብና ተሳታፊ ልየታ የነበረው የህዝብና የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ከፍተኛ እንደነበር ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር የእስካሁኑ ሂደት አካታች፣ ነጻ እና ዴሞክራሲያዊ እንደነበር አንስተዋል።
የዋናው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ጀምሮ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ጠቁመዋል።
ጉባኤው ለሶስት ሳምንት ያህል እንደሚካሄድ ይጠበቃል ብለዋል።