ቀጥታ፡

አዘጋጇ አሜሪካ ድል ቀንቷታል

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 6/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ አሜሪካ ፓራጓይን 4 ለ 1 ረታለች።

ማለዳ ላይ በተጠናቀቀው እና በሎስ አንጀለስ ስታዲየም በተካሄደው የምድብ አራት ጨዋታ ፍሎሪያን ባሎጉን ሁለት ግቦችን ሲያስቆጠር ጂኦቫኒ ሬይና እና የፓራጓዩ ዳሚያን ቦባዲላ በራሱ ላይ ቀሪዎቹን ጎሎች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

ማውሪሲዮ የፓራጓይን ብቸኛ ጎል አስቆጥሯል።

ባለሜዳዋ አሜሪካ በጨዋታው ከፍተኛ ብልጫ ወስዳለች።

ሁለት ግቦችን ያስቆጠረው ፍሎሪያን ባሎጉን የጨዋታው ኮከብ ሆኖ ተመርጧል።

አሜሪካ ያስመዘገበችው ድል በውድድሩ ተሳትፎ ታሪኳ ትልቁ የሚባለው ውጤት ነው።

ውጤቱን ተከትሎ ከአዘጋጅ ሀገራት መካከል አንዷ የሆነችው አሜሪካ ምድብ አራትን በሶስት ነጥብ መምራት ጀምራለች።

ፓራጓይ ያለ ምንም ነጥብ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ ይዛለች።

አውስትራሊያ ከቱርኪዬ በምድብ አራት የሚደረግ ሌላኛው ጨዋታ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም