ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
ኢንተር ሚላን የሴሪአውን ዋንጫ ለ21ኛ ጊዜ ማንሳቱን አረጋገጠ
May 3, 2026 75
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 25/2018 (ኢዜአ)፦ በጣልያን ሴሪአ የ35ኛ ሳምንት ጨዋታ ኢንተር ሚላን ፓርማን 2 ለ 0 አሸንፏል። ማምሻውን በሳንሲሮ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ማርከስ ቱራም እና ኤነሪክ ሚኪታሪያን ግቦቹን አስቆጥረዋል። በሊጉ 26ኛ ድሉን ያስመዘገበው ኢንተር ሚላን በ82 ነጥብ ሶስት ጨዋታዎች እየቀየሩት የሴሪአው ዋንጫ ባለቤት መሆኑን አረጋግጧል። ኢንተር የሊጉ ዋንጫ ሲያነሳ የአሁኑ ለ21ኛ ጊዜ ነው። በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 13ኛ ሽንፈቱን የቀመሰው ፓርማ በ42 ነጥብ 12ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት
May 3, 2026 88
ባሕር ዳር ጥንታዊነትን ከዘመናዊነት። በዚህ አካባቢ ታሪክ መጻፍ ከጀመረ መቶዎች ዓመታት አልፈዋል። ዛሬ ደግሞ ታሪክ ወደፊት እየሄደ ነው። የባሕር ዳር የኢንዱስትሪ፣ የመዝናኛ እና የመሠረተ ልማት ለውጦች ታሪክን ወደ ነገ እየወሰዱት ነው። ዛሬ ከባለ ሀብቶች እና ከአባ ገዳዎች ጋር ሆነን የባሕር ዳርን ስታዲየም፣ አዲሱን የአውሮፕላን ተርሚናል፣ የክልሉን ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የኮሪደር ልማትን ጎብኝተናል። በጉብኝታችን መንገዳችን ትክክል፣ መዳረሻችን አይቀሬ መሆኑን አረጋግጠናል። ባሕር ዳር የሥልጣኔ ዳር ሳትሆን ዕረፍት አይኖረንም።
ቶተንሃም ሆትስፐርስ አስቶንቪላን በማሸነፍ ከወራጅ ቀጠና ወጣ
May 3, 2026 76
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 25/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ35 ሳምንት መርሐ ግብር ቶተንሃም ሆትስፐርስ አስቶንቪላን 2 ለ 1 አሸንፏል። ማምሻውን በቪላ ፓርክ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኮኖር ጋላገር እና ሪቻርልሰን ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። ኤሚሊያኖ ቡንዲያ ለአስቶንቪላ ብቸኛውን ጎል አስቆጥሯል። በሊጉ ተከታታይ ድሉን ያስመዘገበው ቶተንሃም ሆትስፐርስ በ37 ነጥብ ደረጃውን ከ18ኛ ወደ 17ኛ ከፍ በማድረግ ከወራጅ ቀጠና ወጥቷል። በሊጉም ዘጠነኛ ላይ አሳክቷል። በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 11ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አስቶንቪላ በ58 ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዟል። ቡድኑ ሻምፒዮንስ ሊግ ለመግባት በሚያደርገው ፉክክር ወሳኝ ሶስት ነጥብ አጥቷል።
የጣና ሐይቅ ተቀድቶ የማያልቅ የልማት ምንጭ፤ የማይደበዝዝ የውበት ጮራ ነው - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
May 3, 2026 115
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 25/2018(ኢዜአ)፦ የጣና ሐይቅ ተቀድቶ የማያልቅ የልማት ምንጭ፤ የማይደበዝዝ የውበት ጮራ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳስታወቁት ለባሕር ዳርና ለአካባቢው ዘርፈ ብዙ ትሩፋት ይዞ የመጣውን ፈለገ ግዮን ኢኮ ሪዞርት ዛሬ መርቀን ለአገልግሎት ከፍተናል። ዳርቻ የለሽ የተፈጥሮ ውበት ከሰው ልጆች ትጋት ጋር ሲደመር ምን ውጤት እንደሚገኝ ባሕር ዳር ማሳያ ናት ሲሉም ተናግረዋል። ባሕር ዳር በኢትዮጵያ ትልቁ ሐይቅ እና በዓለም ትልቁ ወንዝ የሚገናኙባት ከተማ ናት ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዙሪያዋ ፈጣሪ የሰውን መንፈስ በነፍስም በሥጋም ለማደስ የፈጠረው አካባቢ ነው በወዲያ የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት አለ ብለዋል በመልዕክታቸው። ተሻግሮ የጎንደር ፋሲለደስ ደረቱን ነፍቶ ይታያል መነሻ በወዲህ በገበታ ለሀገር ኢኒሼቲቭ ተጠንስሶ በአቶ ካሣሁን(ቢአይካ) የተገነባው የፈለገ ግዮን ኢኮ ሪዞርት ይገኛል፤ በመሐል ዓባይና ጣና ናቸው ሲሉም ገልጸዋል። ዛሬ የመረቅነው የፈለገ ግዮን ኢኮ ሪዞርት ለከተማዋና ለሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ተጨማሪ የውበት እና የልማት ከፍታ ነው ብለዋል። መንግሥት ለቱሪዝም መዳረሻዎች የሰጠው ትኩረት ምን ውጤት እንዳመጣ በገሐድ የሚነበብበት ፕሮጀክት ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአካባቢውን የቱሪዝም መሥመርና ሠንሠለት የሚያጠናክር ማረፊያና መዳረሻም ነው። ሪዞርቱ ዘመናዊ እና ቅንጡ የእንግዳ ማረፊያዎች፣ የመዝናኛ ሥፍራዎች፣ ሱቆች ፣ አምፊ ቴአትር እና መሰል መሠረተ ልማቶችን አሟልቶ፣ ጣናን ተንተርሶ የተሠራ ሪዞርት ነውም ብለዋለ። በባሕር ዳር ኢንቨስት ለማድረግ ሥራ የጀመሩና መሬት የተረከቡ ኢንቨስተሮች እንደ ፈለገ ግዮን ሥራዎቻቸውን በፍጥነት እንዲፈጽሙ አደራ እንላለን ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው።
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ተመርቆ የተከፈተው ፈለገ ግዮን ኢኮ ሪዞርት…
May 3, 2026 115
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርትን መነሻ በማድረግ በገበታ ለሀገር ፕሮጀክት አካል ሆኖ በግል ኢንቨስትመንት በባህር ዳር ከተማ የተገነባውን የፈለገ ግዮን ኢኮ ሪዞርት በዛሬው ዕለት መርቀው ከፍተዋል፡፡ ስለፈለገ ግዮን ኢኮ ሪዞርት በጥቂቱ፦ ✅በባህር ዳር ከተማ በጣና ሐይቅ ደቡባዊ ዳርቻ ላይ ተገንብቷል፤ ✅በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) "ገበታ ለሀገር" እቅድ መሰረት በሐይቁ ሌላኛው አቅጣጫ ከሚገኘው የጎርጎራ ብርሃን (ጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት) ጋር በመቀናጀት የጣናን የቱሪዝም ቀጣና ለማነቃቃት የታለመ ነው፤ ✅ 4 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ወጪ ተደርጎበታል፤ ✅ በሁለት ዓመት ከስድስት ወር (30 ወራት) ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለምረቃ በቅቷል፤ ✅በሀገር በቀሉ ባለሀብት በአቶ ካሳሁን ምስጋናው (የቤአኢካ ንግድና ኢንቨስትመንት መሥራች) አማካኝነት በግል ኢንቨስትመንት የተገነባ ነው፤ ✅ሪዞርቱ አዲስ በተቋቋመው ሮዳ ሆስፒታሊቲ ግሩፕ ስር ይተዳደራል፤ ✅ሮዳ ሆስፒታሊቲ ግሩፕ ይህንን አዲስ ሪዞርት እና የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርትን በአንድ ላይ በማስተዳደር የቀጣናውን የሆስፒታሊቲ አገልግሎት ይመራል፤ ✅ኢኮ-ሪዞርቱ፦ የተፈጥሮ አካባቢን በጠበቀ መልኩ የተገነባ የቱሪስት መዳረሻ ነው፤ ✅በግል ኢንቨስትመንት ቢገነባም፣ በመንግሥት የገበታ ለሀገር ማዕቀፍ ኢኒሼቲቮች ውስጥ ተካትቶ የተመራና ትኩረት የተሰጠው ፕሮጀክት ነው፤ ✅ሪዞርቱ ለአማራ ክልልም ሆነ ለሀገሪቱ የቱሪዝም ኢንዱስትሪ አዲስ የገቢና የሥራ ዕድል ምንጭ እንደሚሆንም ይጠበቃል።
ፖለቲካ
በለውጡ መንግስት የክልሉ ተጠቃሚነትና ተሳታፊነት እያደገ መጥቷል
May 3, 2026 168
ሰመራ፤ ሚያዝያ 25/2018 (ኢዜአ)፦በለውጡ መንግስት የክልሉ ተጠቃሚነትና ተሳታፊነት እያደገ መጥቷል ሲሉ በብልጽግና ፓርቲ የአፋር ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ መሐመድ ሁሴን ገለጹ። ''ከዳር እስከ መሃል ውጤታማ የብዝሃ ዘርፍ'' በሚል መሪ ሐሳብ የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትና የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በመተባበር ያዘጋጁት የውይይት መድረክ ተካሄዷል። በመድረኩ በመገኘት ውይይቱን ያስጀመሩት በብልፅግና ፓርቲ የአፋር ክልል ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መሐመድ ሁሴን ፤ ኢትዮጵያ በእኩልነት የምንኖርባት የሁላችንም የጋራ ቤት ሆናለች ብለዋል። በተለይም አገራዊ ለውጡን ተከትሎ በርካታ የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ድሎች መመዝገባቸውን ገልጸው የአግላይነት ፖለቲካ ተወግዶ ህዝቦች የራሳቸውን ዕድል በራሳቸው እኩል የመወሰን መብትን ተጎናፅፈዋል ብለዋል። በለውጡ ዓመታት በአፋር ክልል በተለያዩ ብዝሃ ዘርፎች ውጤታማ የሚባሉ መከናወናቸውን አስረድተዋል። በፓናል ውይይቱ ላይ የተገኙት በቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ መሐመድ አህመድ በበኩላቸው የአፋር ክልል የለውጡ ዕውን መሆንን ተከትሎ ፖለቲካዊ ድሎችን መጎናፀፍ ችሏል ብለዋል። እውነተኛ ፌዴራሊዝም ተግባራዊ በመደረጉም የክልሉ ተጠቃሚነትና ተሳታፊነት እያደገ መምጣቱን ገልጸዋል። ከለውጡ ማግስት አንስቶ በተለያዩ ዘርፎች ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል ያሉት ደግሞ የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አህመድ አብዱልቃድር ናቸው። በክልሉ ለዘመናት ጥቅም ላይ ሳይውሉ የቆዩ ወንዞችን በአግባቡ በመጠቀም የእርሻ ስራዎችን በማስፋፋት እንደ ቆላ ስንዴ፣ ሙዝ፣ ፓፓያና ሸንኩርት በስፋት በማምረት የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የተሰሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን አንስተዋል። በተጨማሪም ከዚህ ቀደም በአካባቢው እምብዛም የማይዘወተሩ አዳዲስ አዝዕርቶችን የማላመድ ስራ መሰራቱንም ገልጸዋል። ህብረተሰቡ በእንስሳት ሀብቱ የበለጠ ተጠቃሚ የሚሆንበት የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውንም አመልክተዋል። በኢንቨስትመንት ዘርፍ አበረታች ለውጦች መኖራቸውን ጠቅሰው ክልሉ ከጨው ሀብት ዘርፉ በተገቢው መጠቀም መቻሉንም አብራርተዋል። የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ያሲን ሀቢብ በበኩላቸው፤ በጤናና በትምህርት መስኮች የተሻሉ ስራዎች በመሰራታቸውና ተደራሽነትን ማስፋት በመቻሉ ተጠቃሚነት ማደጉን ገልጸዋል። በፓናል ውይይቱ ላይ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የጎሳ መሪዎችና የአገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል።
ለሰው ተኮር ፕሮጀክቶች በተሰጠው ልዩ ትኩረት የህብረተሰቡ ተጠቃሚነት እያደገ ነው
May 3, 2026 186
ደሴ፤ሚያዝያ 25/2018 (ኢዜአ)፦ብልጽግና ፓርቲ ለሰው ተኮር ፕሮጀክቶች በሰጠው ልዩ ትኩረት የህብረተሰቡ ተጠቃሚነት እያደገ መሆኑን በብልጽግና ፓርቲ የደሴ ከተማ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሸናፊ አለማየሁ አመለከቱ። "ብልጽግና ለሴቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት" በሚል መልእክት ሴቶች ብቻ የተሳተፉበት የብልጽግና ፓርቲ የድጋፍና የምርጫ ቅስቀሳ መርሃ ግብር ዛሬ በደሴ ከተማ ተካሄዷል። በወቅቱም በብልጽግና ፓርቲ የከተማዋ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሸናፊ አለማየሁ እንደገለፁት፤ ፓርቲው ለሰው ተኮር ፕሮጀክቶች በሰጠው ልዩ ትኩረት የህብረተሰቡ ተጠቃሚነት እያደገ ነው። ፓርቲው የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተግባር እየሰራ ያለውን ስራ ሴቶች ተገንዝበው በሰልፍ መደገፋቸው በቀጣይ ለበለጠ ስራ የሚያነሳሳ መሆኑን ገልጸዋል። በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የደሴ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ በበኩላቸው፣ በከተማው ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል። በቅስቀሳና ድጋፍ ሰልፉ ላይ ከተገኙት መካከል ወይዘሮ ደህንነት ጫኔ እንደገለፁት፣ በብልጽግና ፓርቲ መሪነት ባለፉት የለውጥ ዓመታት በከተማው ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ስራዎች ተከናውነዋል። በተለይም ለሰው ተኮር ፕሮጀክቶች በተሰጠው ትኩረት የሴቶች ተጠቃሚነትና ተሳትፎ ማደግ በመቻሉ ይህ ተግባር ተጠናክሮ እንዲቀጥል በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተናል ብለዋል። ሌላዋ ተሳታፊ ወይዘሮ ላቀች አበበ በበኩላቸው፣ የብልጽግና ፓርቲ በሌማት ትሩፋት፣ ለአቅመ ደካሞች ቤቶች ግንባታና በሌሎች ታላላቅ ፕሮጀክቶች ህብረተሰቡን ተጠቃሚ እያደረገ ነው ብለዋል። የተጀመሩ ተስፋ ሰጪ ፕሮጀክቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ፓርቲውን በመደገፍ የድርሻችንን እንወጣለን ብለዋል። የጤና አገልግሎቱን በማዘመን፣በተማሪዎች ምገባ፣ በኮሪደር ልማትና በሌሎችም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ሴቶች በተግባር ተጠቃሚ መሆን ችለናል ያሉት ደግሞ ወይዘሮ ሶፊያ መሀመድ ናቸው። በደሴ ከተማ ከልማት ስራዎች በተጓዳኝ ገበያውን ለማረጋጋት፣ በቱሪዝምና በሌሎችም አበረታች ስራዎች እየተከናወኑ በመሆኑ ዛሬ እዚህ ተገኝተናል ብለዋል። በመርሃ ግብሩ ላይ የደሴ ከተማ አመራሮች፣ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ደሴን የሚወክሉ ተመራጮችና ሌሎችም ተሳትፈዋል።
በሶማሌ ክልል በለውጡ ዓመታት የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል
May 3, 2026 157
ጎዴ፤ ሚያዝያ 25/2018 (ኢዜአ)፦ በሶማሌ ክልል በለውጡ ዓመታት የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን በብልጽግና ፓርቲ የሶማሌ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካ እና የአቅም ግንባታ ዘርፍ ሃላፊ አቶ አብዱራህማን አህመድ ተናገሩ። የብልፅግና ፓርቲ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የምረጡኝ ቅስቀሳ መርሃግብር በሶማሌ ክልል ሸበሌ ዞን፣ ጎዴ ከተማ አካሄዷል። በፓርቲው የሶማሌ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካ እና የአቅም ግንባታ ዘርፍ ሃላፊ አቶ አብዱራህማን አህመድ በመርሃ ግብሩ ላይ እንደገለጹት ብልጽግና ፓርቲ ባለፋት የለውጥ ዓመታት በሀገረ መንግሥት ግንባታ የተለያዩ ስኬቶች አስመዝግቧል። ፓርቲው የሀገሪቱን ዜጎች በሁሉም ዘርፎች የሚያሳትፍ አካታችና አሳታፊ ፓርቲ ነው ሲሉም ገልጸዋል። በተለይም በሶማሌ ክልል በለውጡ ዓመታት የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል። ብልጽግና ፓርቲ በክልሉ እያከናወነ በሚገኘው የልማት ሥራዎች አበረታች ለውጦች ማምጣታቸውን ገልጸው በክልሉ የተጀመረው ልማት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል። በምረጡኝ ቅስቀሳው ብልጽግና ፓርቲን በክልልና በፌዴራል ምክር ቤት የሚወክሉ እጩዎች ተገኝተዋል።
በጠቅላላ ምርጫው የፖሊሲ አማራጮቻችንን በተለያዩ ሚዲያዎች ሳንገደብ ማቅረብ ችለናል
May 3, 2026 202
ሰመራ፤ ሚያዝያ 25/2018 (ኢዜአ)፦ በዘንድሮው አገራዊ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች የፖሊሲ አማራጮቻቸውን ያለ ምንም ገደብ ለህዝብ ማቅረብ የሚችሉበት ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን የአፋር ነፃ አውጭ ግንባር ፓርቲ (አነግፓ) ሊቀ መንበርና የክልሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ሃንፈሬ አሊሚራህ ገለጹ። ለዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ የሚሳተፉ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች አማራጭ የፖሊሲ ሃሳቦቻቸውንና ማኒፌስቶዋቸውን ለህዝብ እንዲያስተዋውቁ የመገናኛ ብዙኃን እኩል የአየር ሰዓትና ሰፊ መድረክ መመደባቸው ይታወቃል። ይህም ሚዲያዎች ብዝሃነትን በማስተናገድ ረገድ ያላቸውን ሚና በተግባር እያሳዩ መሆኑን አመላካች ሆኗል። ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የአፋር ነፃ አውጭ ግንባር ፓርቲ(አነግፓ) ሊቀ መንበር አቶ ሃንፈሬ አሊሚራህ፤ በዘንድሮው ምርጫ የመወዳደሪያ ምህዳሩ ከቀደምት የምርጫ ዘመናት የተለየና የተሻሻለ መሆኑን ገልፀዋል። ከዚህ ቀደም የነበረው ለክልል ተወዳዳሪዎች አምብዛም ሽፋን ያልሰጠ መሆኑን ጠቅሰው፤ በአሁኑ ጊዜ ግን አማራጭ ሐሳቦቻቸውን በተለያዩ የመንግስትና የግል ሚዲያ አውታሮች እያቀረቡ መሆናቸውን ተናግረዋል። ፓርቲያቸው ከሰባት በላይ መድረኮችን በመጠቀም የመወዳደሪያ ሐሳቡን ማቅረቡን ገልጸው፤ በዚህም የመወዳደሪያ ምህዳሩ የሰፋ መሆኑን አስረድተዋል። በዚህ ወቅት በክልሉ ሁሉም ወረዳዎች በነፃነት ቅሰቀሳ በማድረግና በማሰተዋወቅ ላይ መሆናቸውንም አክለዋል። የአፋር ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የምርጫውን ሂደት በመገምገም አስፈላጊ የሆኑ የእርማት እርምጃዎችን የሚጠቁም ኮሚቴ አቋቁሞ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልጸዋል። ምክር ቤቱ ይህን ኮሚቴ ያዋቀረው ምርጫው ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ እንዲጠናቀቅ ያለውን ድርሻ ለመወጣት እንደሆነም አስታውቀዋል።
የኢትዮጵያ ሕብረ-ብሔራዊ አንድነትንና ፌዴራላዊ ሥርዓትን የማፅናት አዲስ አቅጣጫ
May 2, 2026 384
ከለውጡ በፊት ሕብረ-ብሔራዊ አንድነትን በተሟላ ሁኔታ አለማረጋገጥ በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ መዋቅሮች ላይ ጥልቅ ጠባሳ ጥሎ አልፏል ፡፡ ቀደምት ግጭቶች፣ የመሠረተ ልማት ውድመትና የማኅበራዊ ትስስር መላላት የዚሁ አንድነት አለመረጋገጥ ውጤቶች ናቸው ፡፡ የመደመር መንግስት እየገነባ ያለው ሥርዓት ልዩነቶችን እንደ ጌጥ፣ አንድነትን ደግሞ እንደ መሠረት የሚቀበል "ባለ ሚዛን" ሥርዓት ነው ። ይህ አዲስ ጉዞ የቡድን መብትንና የግለሰብ ነፃነትን ሳያጋጭ በማጣጣም፣ የሀገረ መንግሥቱን ፅናት ለማረጋገጥ ያለመ ነው። ይህ ዕሳቤ ኅብረ-ብሔራዊነትን እንደ ነባር ሀገራዊ እውነታ የሚቀበል እንጂ ከአንድነት ጋር የሚጋጭ አድርጎ አይመለከተውም። በዚህም መሠረት የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማኅበረሰቡ የሚገነባው በወል ትርክትና ለብዝኃነት እውቅና በሚሰጡ እሴቶች ላይ ይሆናል። መንግሥት "በኅብረት ሆነን እንበለጽጋለን" በሚል መርሕ፣ በቀጣይ ዓመታት የብዝኃ ቋንቋ ፖሊሲን ወደ ተግባር በማስገባትና የፌዴራል ሥርዓቱን ዋና ምሶሶ የሆነውን ብዝኃነትን በማስተናገድ ረገድ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል ። ባለፉት የለውጥ አመታት ከተከናወኑት መካከል ቀደም ሲል "አጋር" ተብለው ከውሳኔ ሰጪነት ተገልለው የነበሩ የዳር አካባቢ ሕዝቦችን እንደ ሀገር ግንባታ ዋና ምሰሶ በማየት ማካተቱ ትልቅ እርምጃ ነው ፡፡ በተጨማሪም፣ በፌዴራልና በክልሎች መካከል ያለውን ግንኙነት በሕግ ለመምራት የወጣው አዋጅ (1231/2013) እና ለዘመናት ታፍነው የነበሩ የማንነት ጥያቄዎች በሕገ-መንግሥታዊ መንገድ ምላሽ ማግኘታቸው እንደ ስኬት ይጠቀሳሉ ። እነዚህ እርምጃዎች በዜጎች መካከል የመተማመን መንፈስ እንዲጎለብትና ክልሎች እርስ በእርሳቸው የሚደጋገፉበት የ"እህትማማችነት" ፖለቲካ እንዲሰፍን አድርገዋል ፡፡ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳን በተመለከተ፣ መንግሥት የፌዴራል ሥርዓቱን የክልሎችን ጸጋ ለጋራ ብልጽግና ማዋያ መሣሪያ አድርጎ እየተጠቀመበት ይገኛል። ለዚህም እንደ ሕዳሴ ግድብ ያሉ የሕዝብ ትስስር ምልክቶች፣ የ"ገበታ ለሀገር" ፕሮጀክቶች እና በቆላማ አካባቢዎች የተመዘገበው የስንዴ ልማት ተሞክሮዎች በዋቢነት ቀርበዋል። እነዚህ ፕሮጀክቶች ክልሎች ያላቸውን አቅም ወደ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ከመቀየር ባለፈ፣ የጋራ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ብሔራዊ አንድነትን አፅንተዋል። አዲስ አበባን ጨምሮ በክልል ከተሞች የሚከናወኑ የኮሪደር ልማቶችና የታሪክ መዘክሮች ግንባታም የኢትዮጵያን ብዝኃነትና የጋራ ማንነት የሚያንፀባርቁ ናቸው። መንግሥት ተቋማዊ ሪፎርሞችን በማጠናከር ሲቪል ሰርቪሱ ከፖለቲካ ወገንተኝነት ነፃ ሆኖ እንዲያገለግል ለማድረግ እሰራ ይገኛል ። የብዝኃ-ልሳን ፖሊሲን ማስፋፋት፣ የክልሎችን የኢኮኖሚ ትስስር ማጠናከርና በብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን በኩል የሚመጡ የመፍትሔ ሀሳቦችን ተግባራዊ ማድረግ የትኩረት አቅጣጫዎች ናቸው። በተጨማሪም፣ ፍትሐዊ የሀብት ክፍፍል ቀመርን በማሻሻል አነስተኛ አቅም ያላቸውን አካባቢዎች የሚደግፍ አሠራር ይዘረጋል ። የመደመር መንግሥት የሚከተለው የፌዴራሊዝም አቅጣጫ ኢትዮጵያን ጠንካራ ተቋማት ያሏት፣ ብዝኃነቷ ለልማት የሚውልባትና እያንዳንዱ ዜጋ በነፃነት የሚኖርባት ሀገር ለማድረግ ያለመ ነው ። ብልፅግና ፓርቲ
የምንፈልገውን ፓርቲ ለመምረጥ ግንቦት 24ን እየጠበቅን ነው - የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች
May 2, 2026 306
ጂንካ፤ ሚያዝያ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በተመቻቸልን ዕድል ተጠቅመን የምንፈልገውን ፓርቲ ለመምረጥ የሚያስችለንን የምርጫ ካርድ በመውሰዳችን ግንቦት 24ን በጉጉት እየጠበቅን ነው ሲሉ የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ገለፁ። ተማሪ በቀለ ባሪሶ ለኢዜአ እንደገለጸው፤ ምርጫው የሀገራችንን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ለመወሰን ከፍተኛ ሚና ያለው በመሆኑ በንቃት ተሳትፎ ለማድረግ መቻል ልዩ ስሜት አለው። ምርጫው የዴሞክራሲ ልምምድ ሥርዓት አካል በመሆኑ ሁሉም ዜጋ መሳተፍ አለበት ያለው ደግሞ ተማሪ አምሳሉ ዓባይነህ ነው። በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለመሳተፍ የሚያበቃውን የድምፅ መስጫ ካርድ በመውሰዱ ይበጀኛል ለሚለው ፓርቲ ድምጹን ለመስጠት ዝግጁ መሆኑንም አንስቷል። የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ኅብረት ፕሬዚዳንት መቅደስ አድማሱ በበኩሏ አብዛኛው ተማሪ በምርጫው ለመሳተፍ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው በመግለጽ፤ ይህም ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት ለሚደረገው ጥረት ተስፋ ሰጪ መሆኑን አስረድታለች። ዩኒቨርሲቲው የኢንፎርሜሽ ኮሙኒኬሽን እና የቤተ ሙከራ ማዕከላትን በበይነ መረብ በማስተሳሰር ተማሪዎች ዲጂታል የምርጫ ካርድ እንዲወስዱ ማድረጉን የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዚዳንት መልካሙ ዘሮ (ዶ/ር ) ተናግረዋል።
የተመቻቸውን ዕድል በመጠቀም የመራጭነት ካርድ ወስደናል - የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች
May 2, 2026 406
አሶሳ፤ ሚያዝያ 24/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ያመቻቸውን ዕድል በመጠቀም የመራጭነት ካርድ መውሰዳቸውን የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተናገሩ። ቦርዱ የምርጫ ካርድ ላልወሰዱ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች፣ ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና በካምፕ ለሚገኙ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት በልዩ ሁኔታ እስከ ሚያዝያ 24 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆይ የመራጮች ምዝገባ እያካሄደ ነው። የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችም ባገኙት የመራጭነት ዕድል ድምጽ ለመስጠት የሚያበቃቸውን የመራጭነት ካርድ መውሰዳቸውን ለኢዜአ ተናግረዋል። የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ኅብረት ፕሬዚዳንት ተማሪ መልካሙ መላኩ እንደገለጸው፤ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ተጠቅመው ለሀገር ግንባታ፣ ለሰላም እና ልማት አስተዋጽኦ የሚያደርግ ፓርቲ እንዲመርጡ ዕድል መመቻቸቱ የሚበረታታ ነው። ተማሪዎች ባሉበት ሆነው በቴክኖሎጂ ታግዘው መመዝገብ የሚችሉበት ሁኔታ መፈጠሩም በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሂደት የታየ ትልቅ መሻሻል መሆኑን ጠቁሟል። ተማሪ አበባ የኛነው በበኩሏ፤ ተማሪዎች በምርጫው እንድንሳተፍ መደረጉ የመምረጥ መብታችንን ተጠቅመን ሀገርን በልማትና በሰላም ግንባታ ወደፊት የሚያራምድ ፓርቲ ለመምረጥ ዕድል ይሰጠናል ብላለች። ለተማሪዎች የተመቻቸውን ዕድል በመጠቀም የምርጫ ካርድ መውሰዱን የገለጸው ተማሪ አቢያን ኩኩ፤ ባሉበት ሆነው ካርድ ማውጣት መቻላቸው ጊዜና ጉልበት በመቆጠቡ ሊበረታታ ይገባል ብሏል። ግንቦት 24 ቀን 2018 በሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ድምጹን ለሚፈልገው የፖለቲካ ፓርቲ በመስጠት የዜግነት ኃላፊነቱን ለመወጣት መዘጋጀቱንም አረጋግጧል።
የሚበጀንን ፓርቲ ለመምረጥ የምርጫውን ዕለት እየጠበቅን ነው - የሰመራ ከተማ ነዋሪዎች
May 2, 2026 356
ሰመራ፤ ሚያዝያ 24/2018 (ኢዜአ)፡- ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ ወሳኝ በሆነው ምርጫ ላይ በንቃት በመሳተፍ ለሀገር ግንባታ የሚበጅ ፖሊሲ ያለውን ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን የሰመራ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ። ኢዜአ በሰመራ ከተማ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች እንዳሉት፤ በምርጫ ካርዳቸው የተሻለ ሐሳብ አለው፣ ሀገርና ሕዝብንም ወደፊት ያራምዳል ለሚሉት የፖለቲካ ፓርቲ ድምጻቸውን ለመስጠት ተዘጋጅተዋል። አቶ ዘይኑ ሙሳ ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ ምርጫ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበው፤ ለሕዝብ ሁለንተናዊ የልማት ተጠቃሚነትና ዘላቂ ሰላም አበክሮ ይሠራል ለሚሉት የፖለቲካ ፓርቲ ድምጻቸውን ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል። ፓርቲዎች በተለያዩ የሚዲያ አማራጮችና ቋንቋዎች ሐሳባቸውን ለሕዝብ እንዲያቀርቡ መደረጉ እንደ መራጭ በቂ ግንዛቤ ለመያዝ እንዳስቻላቸው አስረድተዋል። ምርጫ ይበጀኛል ብለን ድምጻችንን ለምንፈልገው የፖለቲካ ፓርቲ የምንሰጥበት በመሆኑ ሁሉም ሰው ዴሞክራሲያዊ መብቱን ለመጠቀም መዘጋጀት አለበት ያሉት ደግሞ አቶ ሙሳ አብዱ ናቸው። የምርጫውን ቀን እየጠበቁ መሆናቸውን ጠቁመው፤ ለሰላምና ልማት መቀጠል የተሻለ ሐሳብ ያለውን ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን አረጋግጠዋል። አቶ መሐመድ ይመር በበኩላቸው፤ የፓርቲዎችን አማራጭ ሐሳቦች ሕብረተሰቡ በተለያዩ ቋንቋዎች እንዲያገኝ መደረጉ የተሻለ ሐሳብ ያለውን ፓርቲ ለመለየት እንዳስቻላቸው ተናግረዋል። የምርጫ ካርዳቸውን በወቅቱ ወስደው ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን በመጠቀም ድምጻቸውን ለመስጠት መጪውን ግንቦት 24 እየጠበቁ መሆናቸውን አመላክተዋል።

ማህበራዊ
ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሀገራት የሕክምና ባለሙያዎች ሥልጠና በመስጠት ረገድ የበኩሏን ሚና እየተወጣች ነው
May 3, 2026 103
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 25/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሀገራት የሕክምና ባለሙያዎች ሥልጠና በመስጠት ረገድ የበኩሏን ሚና እየተወጣች እንደምትገኝ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ገለጹ። የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ለ13ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን 556 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመርቋል። የኮሌጁ ተመራቂዎች በጠቅላላ ሕክምና፣ በስፔሻላይዜሽንና በተለያዩ የጤና ሳይንስ ዘርፎች የሰለጠኑ መሆናቸው ተገልጿል። ከተመራቂዎቹ መካከል 204ቱ ሴቶች ሲሆኑ፤ 14ቱ ደግሞ ከተለያዩ የአፍሪካ አገራት የመጡ ናቸው። ዶክተር መቅደስ ዳባ በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ እንደገለጹት፤ መንግሥት ለጤናው ዘርፍ በሰጠው ልዩ ትኩረት አመርቂ ውጤቶች እየተመዘገቡ ይገኛሉ። ዘርፉ በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ የለውጥ ሂደት ላይ እንደሚገኝ የጠቀሱት ሚኒስትሯ፣ ለሕክምናው ወሳኝ የሆኑ ዘመናዊ የሕክምና ቴክኖሎጂዎችና የምርመራ መሣሪያዎች ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ እየተደረገ መሆኑንም አንስተዋል። ብቁ የሕክምና የሰው ኃይል በማፍራት ረገድ በርካታ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን አመልክተው፤ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ እያከናወነ ያለው ተግባር ለአብነት የሚጠቀስ መሆኑን ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በአህጉሪቷ የጤና ዘርፍ ላይ ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱ ከ400 በላይ አፍሪካውያን የጤና ባለሙያዎችን ማሰልጠን መቻሏንም የጤና ሚኒስትሯ አረጋግጠዋል። የኮሌጁ ፕሮቮስት ዶክተር ሙሉቀን ተስፋዬ በበኩላቸው እንደገለጹት፣ ኮሌጁ ባለፉት 13 ዓመታት በጤናው ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ያሉ ባለሙያዎችን አፍርቷል። ተቋሙ ጥራቱን የጠበቀ ትምህርትና ሥልጠና በመስጠት ረገድ ውጤታማ ሥራዎችን ሲያከናውን መቆየቱንም አመልክተዋል። በአሁኑ ወቅት በኮሌጁ የሰለጠኑ ባለሙያዎች በተለያዩ የጤና ተቋማት ተሰማርተው የኅብረተሰቡን የጤና ችግር በማቃለል ረገድ ትልቅ ሚና እየተወጡ እንደሚገኙ ዶክተር ሙሉቀን አስታውቀዋል። ከተመራቂዎች መካከል የወርቅ ተሸላሚው ዶክተር ይከበር ቴዎድሮስ እንደገለጸው፤ ባገኘው እውቀት ያስተማረውን ማኅበረሰብ በትጋትና በታማኝነት ለማገልገል ዝግጁ ነው። ዶክተር ህሊና ዳዊት በቆይታዋ በንድፈ ሐሳብና በተግባር የተደገፈ በቂ እውቀት ማግኘቷን ገልጻለች። በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።
ሕክምና ኮሌጁ በተለያዩ የሕክምና ሙያ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 556 ተማሪዎች አስመረቀ
May 3, 2026 135
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 25/2018 (ኢዜአ)፦የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ በተለያዩ የሕክምና ሙያ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 556 ተማሪዎች ዛሬ አስመረቀ። የኮሌጁ ተመራቂዎች በሕክምና፣ በስፔሻላይዜሽንና በተለያዩ የጤና ሳይንስ ዘርፎች የሰለጠኑ መሆናቸው ተገልጿል። ከተመራቂዎቹ መካከል 204ቱ ሴቶች ሲሆኑ፤ 14ቱ ደግሞ ከተለያዩ የአፍሪካ አገራት የመጡ መሆናቸው ታውቋል። በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፣ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል። የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ፕሮቮስት ዶክተር ሙሉቀን ተስፋዬ በወቅቱ እንደገለጹት፤ ኮሌጁ ባለፉት 13 ዓመታት በጤናው ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ያሉ ባለሙያዎችን አፍርቷል። ተቋሙ ጥራቱን የጠበቀ ትምህርትና ሥልጠና በመስጠት ረገድ ውጤታማ ሥራዎችን ሲያከናውን መቆየቱንም አመልክተዋል። በአሁኑ ወቅት በኮሌጁ የሰለጠኑ ባለሙያዎች በተለያዩ የጤና ተቋማት ተሰማርተው የኅብረተሰቡን የጤና ችግር በማቃለል ረገድ ትልቅ ሚና እየተወጡ እንደሚገኙ ዶክተር ሙሉቀን አስታውቀዋል። የኮሌጁ የዛሬው የምረቃ መርሐ-ግብር ለ13ኛ ጊዜ መሆኑ ታውቋል።
በድሬዳዋ የወባ በሽታን ለመከላከል በተከናወኑ ስራዎች ውጤቶች ተመዝግበዋል
May 3, 2026 206
ድሬዳዋ፤ ሚያዝያ 25/2018 (ኢዜአ)፦በድሬዳዋ አስተዳደር ወባን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተከናወኑ የተቀናጁ ተግባራት በሽታውን በመቀነስ ረገድ ተጨባጭ ውጤት እያመጡ መሆኑን የጤና ባለሙያዎችና የዘርፉ አመራሮች ገለጹ። ድሬዳዋ በጂኦግራፊያዊ አቀማመጧና በሞቃታማ የአየር ንብረቷ ምክንያት ለወባ በሽታ ተጋላጭ ከሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች አንዷ መሆኗ ይታወቃል። ይህንን ተጋላጭነት ለመቀነስና የህዝቡን ጤና ለመጠበቅም የተለያዩ የመከላከያ ስራዎች ሲከናወኑ የቆዩ ሲሆን በዚህም ውጤቶች መመዝገባቸው ተገልጿል። በሳቢያን ወረዳ የጎሮ ጤና ጣቢያ ስራ አስኪያጅ የጤና መኮንን እንዳለማው እርቅይሁን እንዳሉት፤ ለወባ በሽታ መንስኤ የሆኑ የትንኝ መራቢያ አካባቢዎች በተቀናጀ መንገድ በማዳረቅና ኬሚካል በመርጨት ወባን በተጨባጭ መከላከል ተችሏል። በተለይም የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ለህብረተሰቡ ተገቢውን የመከላከያ ትምህርት በመስጠት በመከላከሉ ስራ ላይ በባለቤትነት በማሳተፍ የተከናወኑት ተግባራት ፍሬያማ ሆነዋል ብለዋል። ነዋሪው ጊቢውንና አካባቢውን በማፅዳት፣ ውሃ ያቆሩ አካባቢዎችን በማፋሰስና በማዳረቅ እያከናወነ የሚገኘው ስራ በአብነት የሚጠቀስ መሆኑን በመግለፅ። ከመከላከሉ ጎን ለጎን ባለፉት ዘጠኝ ወራት በወባ በሽታ ለተያዙ 2ሺህ 900 ሰዎች ተገቢውን ህክምና በመስጠት የማዳን ስራ መሰራቱን አንስተዋል። አምናና ዘንድሮ ወባን ለመከላከልና ለማጥፋት የተሰሩ ስራዎች በወባ የሚያዙ ሰዎች በከፍተኛ ደረጃ እንዲቀንሱ ማስቻሉንም ገልጸዋል። የመልካ ጀብዱ ወረዳ ጤና ጣቢያ ባለሙያ ቤተልሄም እንዳለ በበኩላቸው፤ ዘንድሮ ወባን ለመከላከልና ለማጥፋት የተከናወኑ ተግባራት የበሽታውን ስርጭት እንዲገታ አስችሏል። በተለይም የትንኝ መራቢያ ወንዞችና የኢንዱስትሪ አካባቢዎች ላይ ኬሚካል ርጭት በማካሄድ አካባቢዎችን ከስጋት ነፃ ማድረግ ተችሏል ብለዋል። ለታመሙትም አስፈላጊው ህክምና እየተሰጠ መሆኑን በማስታወስ አንድም በወባ የተያዘ ታካሚ በጤና ጣቢያው እንደሌለም ገልጸዋል። ወባን ለመከላከል በተሰሩ ስራዎች የመጡ ለውጦችን ይበልጥ በማሳደግ ከወባ ነፃ የሆነ መልካጀብዱን ዕውን ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል። የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ፅጌረዳ ክፍሌ በበኩላቸው፤ የወባ በሽታን በመከላከልም ሆነ በየጤና ተቋማት በወባ ለተያዘ ሰው እየተሰጠ የሚገኘው ህክምና አበረታች ውጤት ማምጣቱን ገልጸዋል። ህብረተሰቡ በሽታውን ለመከላከል እያደረገ የሚገኘው ተሳትፎ እየተጠናከረ መምጣቱ እና በሁሉም ጤና ተቋማት የፀረ ወባ መድኃኒት እና ፈጣን መመርመሪያ ኪት እንዲሟላ መደረጉ የበሽታውን ስርጭት በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ አስችሏል ብለዋል። ባለፉት ዘጠኝ ወራት በወባ በሽታ ህይወቱ ያለፈ አንድም ነዋሪ አለመኖሩን ጠቅሰው ይህን ውጤታማ ጉዞ በማስቀጠልና ድሬዳዋን ከወባ ነፃ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል።
ባሳለፍነው ሳምንት …
May 2, 2026 363
ከሚያዝያ 18 እስከ ሚያዝያ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች መካከል … • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በሁዋጂያን ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በአዲስ አበባ በሁዋጂያን ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ውስጥ የሚገኘውን "ጎበዝ ሶላር ሴል" ማምረቻን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት የጎበኙ ሲሆን፤ በዚሁ ወቅትም ይህ ፋብሪካ በ2025 ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንቨስት ያድርጉ ፎረም (Invest in Ethiopia Forum) አማካኝነት በተፈረመው ስምምነት መነሻ በ100 ሚሊየን ዶላር የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ የተቋቋመ ነው ብለዋል። በውጤታማ ድጋፍ እና ክትትል በስድስት ወራት ብቻ እውን የሆነው "ጎበዝ ሶላር ሴል" ማምረቻ ዘመናዊ ማሽኖች እና በቴክኖሎጂ የተዋቀረ መሆኑን ገልጸው፣ ማምረቻው ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድልም ፈጥሯል ነው ያሉት። በመጀመሪያ ምዕራፍ 2 ጌጋዋት ዓመታዊ የማምረት ዐቅም ያለው ፋብሪካው የኢትዮጵያን የኃይል ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ከታዳሽ ኃይል ለማድረግ ለተጀመረው ሀገራዊ ርዕይ እውን ለማድረግ ተደማሪ ዐቅም ፈጥሯል ሲሉም ተናግረዋል። በተጨማሪም በኢንዱስትሪ ፓርኩ ውስጥ የሚገኘውን የጫማ ማምረቻ እና ንዑስ የኤሌክትሪክ ጣቢያን ተመልክቻለው ብለዋል በመልዕክታቸው። • ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአራዳ ፓርክን መመረቃቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት አራዳ ፓርክን በመረቁበት ወቅት፤ ፓርኩ አዲስ አበባን ለመለወጥ ያለንን ርዕይ በተግባር ያሳየንበት አንዱ ሥራችን ነው ብለዋል። ቀደም ሲል ተዘንግቶና ለአደጋ ተጋልጦ የነበረው የአራዳ አካባቢ፤ ዛሬ ተመልሶ ተገንብቶ አስደናቂ የከተማ አካል መሆን ችሏል ሲሉም ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለእኛ በምናብ የምትሳል ህልም ብቻ ሳትሆን በተግባር የምትገነባ እውነታ ናት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ጤናማ፣ ጽኑ፣ ለመጭው ትውልድ ተስፋን ከተጨባጭ ሀብት ጋር የምትሰጥ፣ በአፍሪካ መሪ፣ በዓለም መድረክ ደግሞ ተወዳዳሪ የሆነች ሀገር እየገነባን እንገኛለን ብለዋል። በየቀኑም ተስፋን ወደ እውነታ የመለወጥ ተግባራችንን እንቀጥላለን ሲሉ ተናግረዋል። • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማኅበራዊ ልማት እመርታ ለሀገር ግንባታ መድረክ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተገኝተው ሐሳባቸውን ያጋሩበት “የማኅበራዊ ልማት እመርታ ለሀገር ግንባታ” በሚል መሪ ሐሳብ የተዘጋጀውና በማኅበራዊ ዘርፍ ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ ዐበይት ውጤቶች የቀረቡበት የምክክር መድረክ ባሳለፍነው ሳምንት ተካሂዷል። በዚሁ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የማኅበራዊ ዘርፍ ግንባታ እንደ ሌሎች መሠረተ-ልማቶች ውጤቱ ወዲያው የሚታይና የሚጨበጥ ባይሆንም፤ ለሀገር ዘላቂና ወሳኝ መሠረት የሚጥል ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ በሚገጥሟት ተግዳሮቶች ሳትገደብ ከሚገመተው በላይ በከፍተኛ ፍጥነት እየተገነባች መሆኗን ገልጸው፤ ምንም እንኳ የዐቅም ውስንነቶች ቢኖሩብንም ለማሻሻል ያልተሞከረ የማኅበራዊ ዘርፍ የለም ሲሉም አስረድተዋል። በየዘርፎች የታለመው ሁሉ በተግባር እንዲተረጎምና ተገቢውን ዓላማቸውን እንዲያሳኩ ብዙ ሥራ ይጠበቅብናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ለዚህም አንድ እጅ ብቻውን ማጨብጨብ እንደማይችል ሁሉ፤ መንግሥት የሚጀምራቸውን ሥራዎች ሌላው የማኅበረሰብ ክፍል እንደ አንድ ባለ ድርሻ ኃላፊነት ወስዶ በጋራ መቆም እንዳለበት አስገንዝበዋል። • የሞዛምቢክ ፕሬዚዳንት በኢትዮጵያ ባሳለፍነው ሳምንት የሞዛምቢክ ፕሬዚዳንት ዳንኤል ፍራንሲስኮ ቻፖ ለጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በክብር ተቀብለዋቸዋል። የፕሬዚዳንቱ ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት የጋራ ልማትና የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር ትርጉም ባለው መልኩ ሊለውጡ የሚችሉ ተጨባጭ ሥራዎችን ቅድሚያ የሰጠ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለእውነተኛ አፍሪካዊ አጋርነት ያላትን የማይናወጥ ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ መሆኑንም አስረድተዋል። ከዚያም ባደረጉት ቆይታ ዘላቂ እና ተጨባጭ ለውጥ ለሚያመጣ አጋርነት መሠረት የጣለ ፍሬያማ የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በስትራቴጂካዊ ዘርፎች ያለንን ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግሩና የአሠራር ማዕቀፍ የሚሆኑ ልዩ ልዩ የመግባቢያ ሠነዶችን ልውውጥ አካሂደናል ብለዋል። • የበጋ መስኖ እርሻ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት ባስተላለፉት መልዕክት፤ የበጋ መስኖ እርሻ በምግብ ራሳችንን ለመቻል በሚደረገው ጉዞ ውስጥ የጸና መሠረት የጣልንበት ምዕራፍ ነው ብለዋል። የውኃ ሀብታችንን በአግባቡ በመጠቀም፣ ባልተቋረጠ ጥረት እና ቁርጠኝነት፣ የመልማት ጉዟችን አስተማማኝና ዘላቂ የሆነ የምግብ ዋስትና ወደምናረጋግጥበት ብሩህ ተስፋ እንደሚያሸጋግረን ጥርጥር የለውም ሲሉም አስገንዝበዋል። • ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ባሳለፍነው ሳምንት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሆሞሻ ወረዳ የሚገኘውን ፍቃዱ ነመራ የተቀናጀ የእርሻ ልማት ጎብኝተዋል። ጉብኝታቸውን ተከትሎም፤ ፍቃዱ ነመራ የተቀናጀ የእርሻ ልማት በኢትዮጵያ የግሉን ዘርፍ ያሳተፈ የግብርና ሥራ እንዲስፋፋ ለሚደረገው ሥራ አንድ ማሳያ ነው ብለዋል። ይህ በግል ባለሀብት እየለማ ያለው የግብርና ሥራ እንደ ሶላር ያሉ የኃይል አማራጮችን እና የከርሰ ምድር ውኃን በመጠቀም በመስኖ በማልማት ኢትዮጵያ ለጀመረችው የግብርና ልማት እና የገጠር ሽግግር ሰፊ አስተዋጽኦ ያበረክታል ሲሉም ገልጸዋል። በተመሳሳይ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግራናይት የሚያመርተውን የኦርላመንት (3ኤም) ማርብልና ቴራዞ ማኑፋክቸሪንግ የሥራ እንቅስቃሴ የጎበኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ መንግሥት የግሉ ዘርፍ በማዕድን ልማት ላይ በስፋት እንዲሳተፍ የፈጠረው ምቹ ሁኔታ፣ ማበረታቻና ድጋፍ እንዲህ ያሉ ተጨባጭ ውጤቶችን እያመጣ ነው ብለዋል። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከወርቅ እስከ ግራናይት በተፈጥሮ የታደለ መሆኑን ገልጸው፤ ይህን ፀጋ ለሀገር ብልጽግና ለማዋል የተጀመሩ የልማት ሥራዎች ይበልጥ እንዲጠናከሩ የፌደራል መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረጉን ይቀጥላል ሲሉ አረጋግጠዋል።
ኢኮኖሚ
የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት
May 3, 2026 88
ባሕር ዳር ጥንታዊነትን ከዘመናዊነት። በዚህ አካባቢ ታሪክ መጻፍ ከጀመረ መቶዎች ዓመታት አልፈዋል። ዛሬ ደግሞ ታሪክ ወደፊት እየሄደ ነው። የባሕር ዳር የኢንዱስትሪ፣ የመዝናኛ እና የመሠረተ ልማት ለውጦች ታሪክን ወደ ነገ እየወሰዱት ነው። ዛሬ ከባለ ሀብቶች እና ከአባ ገዳዎች ጋር ሆነን የባሕር ዳርን ስታዲየም፣ አዲሱን የአውሮፕላን ተርሚናል፣ የክልሉን ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የኮሪደር ልማትን ጎብኝተናል። በጉብኝታችን መንገዳችን ትክክል፣ መዳረሻችን አይቀሬ መሆኑን አረጋግጠናል። ባሕር ዳር የሥልጣኔ ዳር ሳትሆን ዕረፍት አይኖረንም።
የጣና ሐይቅ ተቀድቶ የማያልቅ የልማት ምንጭ፤ የማይደበዝዝ የውበት ጮራ ነው - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
May 3, 2026 115
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 25/2018(ኢዜአ)፦ የጣና ሐይቅ ተቀድቶ የማያልቅ የልማት ምንጭ፤ የማይደበዝዝ የውበት ጮራ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳስታወቁት ለባሕር ዳርና ለአካባቢው ዘርፈ ብዙ ትሩፋት ይዞ የመጣውን ፈለገ ግዮን ኢኮ ሪዞርት ዛሬ መርቀን ለአገልግሎት ከፍተናል። ዳርቻ የለሽ የተፈጥሮ ውበት ከሰው ልጆች ትጋት ጋር ሲደመር ምን ውጤት እንደሚገኝ ባሕር ዳር ማሳያ ናት ሲሉም ተናግረዋል። ባሕር ዳር በኢትዮጵያ ትልቁ ሐይቅ እና በዓለም ትልቁ ወንዝ የሚገናኙባት ከተማ ናት ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዙሪያዋ ፈጣሪ የሰውን መንፈስ በነፍስም በሥጋም ለማደስ የፈጠረው አካባቢ ነው በወዲያ የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት አለ ብለዋል በመልዕክታቸው። ተሻግሮ የጎንደር ፋሲለደስ ደረቱን ነፍቶ ይታያል መነሻ በወዲህ በገበታ ለሀገር ኢኒሼቲቭ ተጠንስሶ በአቶ ካሣሁን(ቢአይካ) የተገነባው የፈለገ ግዮን ኢኮ ሪዞርት ይገኛል፤ በመሐል ዓባይና ጣና ናቸው ሲሉም ገልጸዋል። ዛሬ የመረቅነው የፈለገ ግዮን ኢኮ ሪዞርት ለከተማዋና ለሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ተጨማሪ የውበት እና የልማት ከፍታ ነው ብለዋል። መንግሥት ለቱሪዝም መዳረሻዎች የሰጠው ትኩረት ምን ውጤት እንዳመጣ በገሐድ የሚነበብበት ፕሮጀክት ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአካባቢውን የቱሪዝም መሥመርና ሠንሠለት የሚያጠናክር ማረፊያና መዳረሻም ነው። ሪዞርቱ ዘመናዊ እና ቅንጡ የእንግዳ ማረፊያዎች፣ የመዝናኛ ሥፍራዎች፣ ሱቆች ፣ አምፊ ቴአትር እና መሰል መሠረተ ልማቶችን አሟልቶ፣ ጣናን ተንተርሶ የተሠራ ሪዞርት ነውም ብለዋለ። በባሕር ዳር ኢንቨስት ለማድረግ ሥራ የጀመሩና መሬት የተረከቡ ኢንቨስተሮች እንደ ፈለገ ግዮን ሥራዎቻቸውን በፍጥነት እንዲፈጽሙ አደራ እንላለን ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው።
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ተመርቆ የተከፈተው ፈለገ ግዮን ኢኮ ሪዞርት…
May 3, 2026 115
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርትን መነሻ በማድረግ በገበታ ለሀገር ፕሮጀክት አካል ሆኖ በግል ኢንቨስትመንት በባህር ዳር ከተማ የተገነባውን የፈለገ ግዮን ኢኮ ሪዞርት በዛሬው ዕለት መርቀው ከፍተዋል፡፡ ስለፈለገ ግዮን ኢኮ ሪዞርት በጥቂቱ፦ ✅በባህር ዳር ከተማ በጣና ሐይቅ ደቡባዊ ዳርቻ ላይ ተገንብቷል፤ ✅በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) "ገበታ ለሀገር" እቅድ መሰረት በሐይቁ ሌላኛው አቅጣጫ ከሚገኘው የጎርጎራ ብርሃን (ጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት) ጋር በመቀናጀት የጣናን የቱሪዝም ቀጣና ለማነቃቃት የታለመ ነው፤ ✅ 4 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ወጪ ተደርጎበታል፤ ✅ በሁለት ዓመት ከስድስት ወር (30 ወራት) ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለምረቃ በቅቷል፤ ✅በሀገር በቀሉ ባለሀብት በአቶ ካሳሁን ምስጋናው (የቤአኢካ ንግድና ኢንቨስትመንት መሥራች) አማካኝነት በግል ኢንቨስትመንት የተገነባ ነው፤ ✅ሪዞርቱ አዲስ በተቋቋመው ሮዳ ሆስፒታሊቲ ግሩፕ ስር ይተዳደራል፤ ✅ሮዳ ሆስፒታሊቲ ግሩፕ ይህንን አዲስ ሪዞርት እና የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርትን በአንድ ላይ በማስተዳደር የቀጣናውን የሆስፒታሊቲ አገልግሎት ይመራል፤ ✅ኢኮ-ሪዞርቱ፦ የተፈጥሮ አካባቢን በጠበቀ መልኩ የተገነባ የቱሪስት መዳረሻ ነው፤ ✅በግል ኢንቨስትመንት ቢገነባም፣ በመንግሥት የገበታ ለሀገር ማዕቀፍ ኢኒሼቲቮች ውስጥ ተካትቶ የተመራና ትኩረት የተሰጠው ፕሮጀክት ነው፤ ✅ሪዞርቱ ለአማራ ክልልም ሆነ ለሀገሪቱ የቱሪዝም ኢንዱስትሪ አዲስ የገቢና የሥራ ዕድል ምንጭ እንደሚሆንም ይጠበቃል።
በአማራ ክልል ተፈጥሯዊና ታሪካዊ ጸጋዎችን ለዓለም የሚያስተዋውቁ አዳዲስ የቱሪስት መዳረሻዎች እውን እየሆኑ ነው - ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ
May 3, 2026 104
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 25/2018(ኢዜአ)፦ መንግሥት ለቱሪዝም ዘርፍ በሰጠው ልዩ ትኩረት የአማራ ክልልን ተፈጥሯዊና ታሪካዊ ጸጋዎች ለዓለም የሚያስተዋውቁ አዳዲስ የቱሪስት መዳረሻዎች ግንባታ እውን እየሆነ ነው ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩመህ በገበታ ለሀገር ኢኒሼቲቭ የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርትን መነሻ በማድረግ በባህር ዳር ከተማ ጣና ዳርቻ በባለሀብቱ ካሳሁን ምስጋናው የተገነባውን ፈለገ ግዮን ኢኮ ሪዞርት ዛሬ መርቀው ከፍተዋል። በመርኃ ግብሩ የአማራ ክልል እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ አባ ገዳዎች፣ ባለሀብቶችና የባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ተገኝተዋል። በባህር ዳር ከተማ በጣና ሐይቅ ደቡባዊ ዳርቻ ላይ የተገነባው ፈለገ ግዮን ኢኮ ሪዞርት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) "ገበታ ለሀገር" እቅድ መሰረት በሐይቁ ሌላኛው አቅጣጫ ከሚገኘው የጎርጎራ ብርሃን (ጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት) ጋር በመቀናጀት የጣናን የቱሪዝም ቀጣና ለማነቃቃት የታለመ ነው። ይሄው በአራት ነጥብ አምስት ቢሊየን ብር ወጪ የተገነባው ሪዞርት፤ ሁለት ዓመት ከስድስት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ግንባታው ተጠናቆ ለምረቃ መብቃቱ ታውቋል። የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ እንደገለጹት፤ በአሁኑ ወቅት እየተገነቡ የሚገኙት የቱሪዝም መዳረሻዎች የክልሉን ውበት ከመግለጽ ባለፈ፣ እስካሁን በበቂ ሁኔታ ያልታወቁ ጸጋዎችን ይፋ እያደረጉ ይገኛሉ። ቀደም ሲል የተገነባው የጎርጎራ ፕሮጀክት፣ ፈለገ ግዮን ኢኮ ሪዞርት እና ሌሎች ግንባታዎች የክልሉን ውበትና የኢትዮጵያን የብልጽግና ከፍታ የሚያሳዩ ተጨባጭ ማስረጃዎች መሆናቸውንም ገልጸዋል። አዲሱ ፈለገ ግዮን ኢኮ ሪዞርት የጣና ሐይቅን ደህንነት በጠበቀ መልኩ የተገነባ፣ የጥራትና የምቾት መለኪያ ተደርጎ የሚወሰድ መሆኑን አመልክተዋል። ሪዞርቱ በታላቁ ወንዝ ስም የተሰየመ የጎብኚዎች መዳረሻ መሆኑን አመልክተው፤ ክልሉ ከቱሪዝም ዘርፍ ተገቢውን ጥቅም እንዲያገኝ ያስችላል ብለዋል። ፕሮጀክቱ በመንግሥትና በግለሰቦች በጋራ የመሥራት ባህል የተገኘ ውጤት መሆኑን ጠቅሰው፤ በዚህም አዳዲስ የቱሪስት መዳረሻዎች ግንባታ እውን እየሆነ መሆኑንና በቀጣይም መሰል የልማት ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል። ለትውልድ የሚተርፉና ሀገርን የሚያስከብሩ ሥራዎች መሥራታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
በአማራ ክልል ብቁ የሰው ኃይል በመፍጠር የኅብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ ነው
May 3, 2026 245
ደሴ ፤ ሚያዝያ 25/2018 (ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን የተላመደ ብቁ የሰው ኃይል በማፍራት፣ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ስራና ክህሎት ቢሮ ገለጸ። ቢሮው ለዘርፉ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና በኮምቦልቻ ከተማ መስጠት ጀምሯል። በአማራ ክልል ስራና ክህሎት ቢሮ የተቋማት አግባብነትና ጥራት ማረጋገጥ ዳይሬክተር አቶ ሙላው ልመንህ እንደገለፁት፣ የገበያ ፍላጎትንና የመልማት ፀጋን መሰረት በማድረግ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት በመከናወን ላይ ናቸው። ለዚህም ቴክኖሎጂን የተላመደ ብቁ የሰው ሃይል በመፍጠር የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ስልጠናው በተሻሻለው የቴክኒክና ሙያ ስትራቴጂ፣ በፖሊሲ፣ በደንብና አዳዲስ እሳቤዎች ዙሪያ ግንዛቤ ከመፍጠር ባለፈ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምና በፈጠራ ሥራዎች ላይ እውቀት የሚያስጨብጥ ይሆናል ብለዋል። በዚህም ሁሉም ባለድርሻ አካላት ዓለም የደረሰበትን በቴክኖሎጂ የተደገፈ የአገልግሎት አሰጣጥ ተረድቶ ተፎካካሪና ተወዳዳሪ ለመሆን መነሳሳት የሚፈጥርለት ነው ብለዋል። በቴክኖሎጂው ዘርፍ ባለፉት ዓመታት አበረታች ውጤቶች መገኘታቸውን ጠቁመው በስራ እድል ፈጠራውም ዙሪያ የተሻለ ማከናወን መቻሉን አስረድተዋል። በዋግኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ስራና ክህሎት መምሪያ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ተሞክሮ ቅመራ ባለሙያ ወይዘሮ እምዬ ጌታቸው በበኩላቸው፣ አሰራሩን በቴክኖሎጂ በማስደገፍ የተሻለ ለመስራት ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል። ስልጠናው እውቀታቸውንና ክህሎታቸውን በማሰደግ ብቁና ተወዳዳሪ ለመሆን እንደሚያግዛቸው ጠቁመው፣ ስልጠናውን በአግባቡ ተከታትለው የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል። የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት መምሪያ የትምህርትና ስልጠና ቡድን መሪ አቶ ዓሊ ኢብራሂም በሰጡት አስተያየት በቴክኖሎጂ ታግዘን ለዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር ስልጠናው አስፈላጊ ነው ብለዋል። ለአንድ ሳምንት በሚቆየው በዚሁ ስልጠና የክልል፣ የዞንና የከተማ፣ የፖሊ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ አመራሮች፣ ቡድን መሪዎች፣ ባለሙያዎችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ነው።
የምርምር ኢንስቲትዩት የኢትዮጵያን የሕክምና ምርምር ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋገረ ነው
May 3, 2026 116
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 25/2018 (ኢዜአ)፦በአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት የተገነባው ዘመናዊው የምርምር ላቦራቶሪ ኮምፕሌክስ የኢትዮጵያን የሕክምና ምርምር ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋገረ የልህቀት ማዕከል መሆኑን የአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተቋሙን በመረቁበት ወቅት እንደገለጹት፣ በአርማወር ሐንሰን የምርምር ተቋም ቅጥር ግቢ ውስጥ የተገነባው ይህ ዘመናዊ ማዕከል ከመሠረተ ልማት ግንባታ ባለፈ፣ ራሷን የቻለችና ጤናማ የሆነች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የሚተጋ የላቀ የዕውቀት ማዕከል ነው። ተቋሙ ምርምርን ወደ ፖሊሲ፣ ፈጠራን ደግሞ ወደ ተግባራዊ መፍትሔ በመቀየር፤ በመድኃኒት ምርት ራሳችንን ለመቻል፣ ዘላቂ የጤና ደህንነትን ለማረጋገጥ እና ከሁሉም በላይ ደግሞ እስካሁን ያስመዘገብናቸውን ስኬቶች ይበልጥ ለማሳደግ የሚረዳ ትልቅ እርምጃ ነው ሲሉ ገልጸዋል። ይህ ማዕከል በኢትዮጵያና በአፍሪካ የሳይንስ ሥነ-ምሕዳር ውስጥ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ዘመናዊ የምርምር ተቋም መሆኑንም አረጋግጠዋል። የአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ኢንስቲትዩቱ በበሽታዎች ምርምር፣ ምርመራ እና በወረርሽኝ መልክ የሚከሰቱ የጤና ስጋቶችን ለመለየት የሚያስችል ትልቅ አገራዊ አቅም ገንብቷል። ተቋሙ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እና በሰለጠነ የሰው ኃይል ታግዞ የኢትዮጵያን የሕክምና ምርምር ወደ ላቀ ከፍታ የሚያሸጋግር ሥራ እያከናወነ መሆኑንም ጠቁመዋል። በቅርቡ የተመረቀው የምርምር ኮምፕሌክስ ዘመናዊ የላቦራቶሪ መሠረተ ልማትና የሰለጠነ የሰው ኃይልን ያካተተ መሆኑን አመልክተው፤ በኢትዮጵያ ያለውን የሕክምና ምርምር ደረጃ ማሳደጉን ገልጸዋል። አዳዲስና ነባር በሽታዎችን በትክክል የመለየት አቅሙም ለሕክምናው ዘርፍ ትልቅ እገዛ እያደረገ ይገኛል ብለዋል። በወረርሽኝ መልክ የሚከሰቱ በሽታዎችን በምርምር ለመተንተንና ለመለየት፣ እንዲሁም የሕዝብ ጤና ደህንነትን ለመጠበቅ ዝግጁነቱን ማጠናከሩን ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል። ኢንስቲትዩቱ የሚከተላቸው የምርምር ስልቶች ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ መሆናቸው ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለምስራቅ አፍሪካ ቀጣናም ትልቅ ፋይዳ እንዳለው አክለዋል። አዲሱ የላቦራቶሪ ኮምፕሌክስ በርካታ ላቦራቶሪዎችን በአንድ ላይ የያዘና ትልቅ አገራዊ አቅም የፈጠረ መሆኑን ገልጸው፤ በተለይም የዘርመል (Genetic) ትንተና ለማከናወን የሚያስችል አቅሙ ከዚህ ቀደም ወደ ውጭ አገር ተልከው የሚሠሩ ምርመራዎችን በአገር ውስጥ ለማከናወን ያስችላል ብለዋል። በማዕከሉ የተለያዩ የምርምርና የትንተና ሥራዎችን በአገር ውስጥ አቅም ለመሥራት የሚያስችሉ የተለያዩ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች መሟላታቸውን ገልጸው፤ አሁን ላይ ከኢትዮጵያ አልፎ የአፍሪካ አገራትን ማገልገል የሚያስችል ሥራ እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል። ተቋሙ መጀመሪያ ላይ የሥጋ ደዌ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተመሰረተ ቢሆንም፣ አሁን ላይ መድኃኒት የተለማመደ የቲቢ በሽታን፣ የወባ በሽታንና ሌሎች በርካታ የምርምር ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል። ከምርምር በተጨማሪ በአገር ውስጥ የሚመረቱ መድኃኒቶች ጥራታቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ ለማድረግ በምርመራ የመለየት ሥራ መከናወኑን ተናግረዋል። የምርምር ማዕከሉ 40 ላቦራቶሪዎችን፣ የላቁ የጂኖሚክስ (genomics) እና የባዮኢንፎርማቲክስ (bioinformatics) ክፍሎችን፣ እንዲሁም በሀገር ውስጥ የሚመረቱ መድኃኒቶችን ጥራትና ብቃት የሚያረጋግጥ የባዮኢኩዊቫለንስ (bioequivalence) ማዕከልን አካትቷል። በኢትዮጵያ እና በመላው አፍሪካ ለሳይንስ ሥነ ምሕዳር መስፋፋትና አቅም ግንባታ አዲስ መለኪያ ያስቀመጠው ተቋም ለሥልጠና እና ለምርምር የተመደቡ ቦታዎችን መያዙ ተገልጿል።
አገልግሎቱ ከአላስፈላጊ የገንዘብ ወጪ እና እንግልት ታድጎናል - ተገልጋዮች
May 3, 2026 158
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 25/2018 (ኢዜአ)፦የአዲስ መሶብ ተንቀሳቃሽ ዲጂታል የመንግሥት አገልግሎት ከአላስፈላጊ ወጪ እና እንግልት ታድጎናል ሲሉ ኢዜአ ያነጋገራቸው ተገልጋዮች ገለጹ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግሥት ተንቀሳቃሽ አገልግሎትን በይፋ ማስጀመራቸው ይታወሳል። የአዲስ መሶብ ተንቀሳቃሽ ዲጂታል የመንግሥት አገልግሎት ሥራ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ፣ ሰው በሚበዛባቸው አካባቢዎችና ወደ ንግድ ተቋማት በመንቀሳቀስ ለዜጎች ቀልጣፋና እንግልት የሌለው አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። ኢዜአ አገልግሎቱ በሚሰጥባቸው የከተማዋ ስፍራዎች በመዘዋወር ያነጋገራቸው ተገልጋዮች፤ አሠራሩ ከአላስፈላጊ የገንዘብ ወጪና እንግልት እንደታደጋቸው ገልጸዋል፡፡ ከተገልጋዮች መካከል መንጃ ፈቃድ ሲያሳድስ ያገኘነው ወጣት ታምራት መንግሥቱ፤ አገልግሎቱ ደጃፉ ድረስ በመምጣት ተገቢውን ምላሽ እንደሰጠው ተናግሯል፡፡ ቀደም ሲል መንጃ ፈቃድ ለማሳደስ በርካታ ቀናትን ይፈጅ እንደነበር አስታውሶ፣ አሁን በፍጥነትና በጥራት ማግኘት መቻሉን ገልጿል። ይህም ጊዜና ገንዘብ ሳይባክን፣ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ሳይገታ የተቀላጠፈ አገልግሎት ለማግኘት እንዳስቻለው አስረድቷል። ሌላኛው መንጃ ፈቃድ ለማሳደስ የመጡት አቶ ክፍሌ ዳባ በበኩላቸው፤ "አገልግሎቱ ጊዜ ቆጣቢና እንግልትን ያስቀረ ሆኖ አግኝቼዋለሁ" ብለዋል። መስተንግዶው እጅግ ትሕትና የተሞላበት፣ ቀልጣፋ፣ አስተማማኝና እንከን የማይወጣለት መሆኑንም መስክረዋል፡፡ የልደት ምስክር ወረቀት ሲያወጣ ያገኘነው ወጣት መኮንን ይማም በበኩሉ፤ ከአገልግሎት አሰጣጡ ፍጥነትና ጥራት ባሻገር፣ ሠራተኞቹ በመልካም ሥነ-ምግባር የታነጹ መሆናቸውን በአካል መታዘቡን ገልጿል። "የመንግሥት አገልግሎት በዚህ ልክ ይዘምናል፣ ወደ ደጃፍም ይቀርባል ብዬ አስቤም አልሜም አላውቅም" ያሉት ደግሞ የንግድ ፈቃድ ለማደስ የተገኙት አካል ጉዳተኛው አቶ መኮንን ወርቁ ናቸው። የአዲስ መሶብ ተንቀሳቃሽ ዲጂታል የመንግሥት አገልግሎት በተለይ ለአካል ጉዳተኞች ትልቅ በረከት መሆኑንም ተናግረዋል። ሌላኛው መታወቂያ ሲያሳድስ ያገኘነው ወጣት ሚኪያስ ወንድማገኝ፤ አዲስ መሶብ ቢሮክራሲንና የተገልጋዮችን እንግልት ሙሉ በሙሉ ያስቀረ መሆኑን ገልጿል። የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግሥት አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ማስረሻ፤ በመዲናዋ እስካሁን የ25 ተቋማት 150 አገልግሎቶች ዲጂታላይዝ መደረጋቸውን ገልጸዋል፡፡ ከእነዚህ በተጨማሪ ባለጉዳይ የሚበዛባቸው የስምንት የተለያዩ ተቋማት አገልግሎቶችን በተንቀሳቃሽ መልክ ተደራሽ ማድረግ መቻሉን ጠቁመዋል። ተንቀሳቃሽ ዲጂታል የመንግሥት አገልግሎቱ ዜጎች ጊዜና ገንዘባቸውን ሳያባክኑ የዕለት ተዕለት ሥራቸውን እያከናወኑ አገልግሎት እንዲያገኙ እያስቻለ መሆኑን ገልጸው፤ እስካሁን በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎችን ተደራሽ ማድረግ መቻሉንና በደንበኞች ግብረ-መልስ መሠረት የእርካታ ደረጃቸው እያደገ መምጣቱን አረጋግጠዋል። ይህም ቀደም ሲል በመንግሥት ተቋማት ይስተዋል የነበረውን የአገልግሎት ስብራት ሙሉ በሙሉ ያስቀረ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በቀጣይም የአገልግሎቱን አድማስ ለማስፋት በትኩረት እየተሠራ መሆኑን አንስተዋል።
በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ተወዳዳሪ ትውልድ ለማፍራት የሚያስችሉ ተግባራት ተጠናክረዋል
May 2, 2026 223
ድሬደዋ፤ ሚያዚያ 24/2018(ኢዜአ)፦ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ተወዳዳሪ ትውልድ በመገንባት ዲጂታል ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸውን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ተናገሩ። በአስተዳደሩ ለሶስት ቀናት የተካሄደው የትምህርት ቤቶች የሳይንስና የቴክኖሎጂ የፈጠራ ውጤቶች አውደ ርዕይ ዛሬ ተጠናቋል። የድሬደዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት ፤በአውደ ርዕዩ ላይ የቀረቡት የፈጠራ ውጤቶች ዲጂታል ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ የተጀመሩ አበረታች ጉዞዎችን ለማሳካት የጎለ አስተዋጽኦ ይኖራቸዋል ብለዋል። በትምህርት ቤቶች የሳይንስና ቴክኖሎጂ ክህሎትና ጥበብ ያላቸውን ታዳጊ ተማሪዎችን ለማፍራት የሚከናወኑ ጥረቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል። በአውደ ርዕዩ የቀረቡ ችግር ፈቺ የሳይንስና የቴክኖሎጂ የፈጠራ ውጤቶች ጥቅም ላይ እንዲውሉ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በቅንጅት ይሰራል ብለዋል። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሱልጣን አልይ በበኩላቸው፤ የሳይንስና የቴክኖሎጂ ዕውቀት፣ ክህሎትና ጥበብ የተላበሱ ታዳጊዎችን ለማፍራት የተጀመሩ ጥረቶች ፍሬያማ እየሆኑ መምጣታቸውን ተናግረዋል። በአውደ ርዕዩ በየዘርፉ የቀረቡ የቴክኖሎጂ የፈጠራ ውጤቶች የዚሁ መገለጫ መሆናቸውን በመግለፅ ። በቀጣይም የፈጠራና የምርምር ስራዎችን በጥራት፣ በስፋት እና በተሻለ ከፍታ ለማሳደግ ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ እና ከድሬዳዋ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ምሁራን ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል ። የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የዘርፉ ምሁራን የፈጠራ ውጤቶቹን በመገምገም በየዘርፉ የተሻሉትን የፈጠራ ውጤቶች ደረጃ መለየቻቸውም ታውቋል። በአውደ ርዕዩ ላይ በድሬደዋ አስተዳደር የሚገኙ የ1ኛ እና 2ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች የሳይንስና የቴክኖሎጂ የፈጠራ ውጤቶች ናቸው የቀረቡት። በአውደ ርዕዩ በየዘርፉ የተሻለ የፈጠራ ሃሳቦችን እና ውጤቶችን ይዘው ለቀረቡት ተማሪዎች ሽልማት ተሰጥቷል።
ስፖርት
ኢንተር ሚላን የሴሪአውን ዋንጫ ለ21ኛ ጊዜ ማንሳቱን አረጋገጠ
May 3, 2026 75
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 25/2018 (ኢዜአ)፦ በጣልያን ሴሪአ የ35ኛ ሳምንት ጨዋታ ኢንተር ሚላን ፓርማን 2 ለ 0 አሸንፏል። ማምሻውን በሳንሲሮ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ማርከስ ቱራም እና ኤነሪክ ሚኪታሪያን ግቦቹን አስቆጥረዋል። በሊጉ 26ኛ ድሉን ያስመዘገበው ኢንተር ሚላን በ82 ነጥብ ሶስት ጨዋታዎች እየቀየሩት የሴሪአው ዋንጫ ባለቤት መሆኑን አረጋግጧል። ኢንተር የሊጉ ዋንጫ ሲያነሳ የአሁኑ ለ21ኛ ጊዜ ነው። በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 13ኛ ሽንፈቱን የቀመሰው ፓርማ በ42 ነጥብ 12ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ቶተንሃም ሆትስፐርስ አስቶንቪላን በማሸነፍ ከወራጅ ቀጠና ወጣ
May 3, 2026 76
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 25/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ35 ሳምንት መርሐ ግብር ቶተንሃም ሆትስፐርስ አስቶንቪላን 2 ለ 1 አሸንፏል። ማምሻውን በቪላ ፓርክ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኮኖር ጋላገር እና ሪቻርልሰን ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። ኤሚሊያኖ ቡንዲያ ለአስቶንቪላ ብቸኛውን ጎል አስቆጥሯል። በሊጉ ተከታታይ ድሉን ያስመዘገበው ቶተንሃም ሆትስፐርስ በ37 ነጥብ ደረጃውን ከ18ኛ ወደ 17ኛ ከፍ በማድረግ ከወራጅ ቀጠና ወጥቷል። በሊጉም ዘጠነኛ ላይ አሳክቷል። በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 11ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አስቶንቪላ በ58 ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዟል። ቡድኑ ሻምፒዮንስ ሊግ ለመግባት በሚያደርገው ፉክክር ወሳኝ ሶስት ነጥብ አጥቷል።
መቻል በድል ጉዞው ቀጥሏል
May 3, 2026 73
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 25/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 24ኛ ሳምንት መቻል ባህር ዳር ከተማን 3 ለ 2 አሸንፏል። በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቱሪስት ለማ፣ ትዕግሥት ወርቁ እና መዲና አወል ለመቻል ግቦቹን አስቆጥረዋል። ሳሮን ሰመረ እና ማናዩሽ ተስፋዬ ለባህር ዳር ከተማ ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። የመቻሏ ቱሪስት ለማ የጨዋታው ኮከብ ሆና ተመርጣለች። በሊጉ ተከታታይ ሶስተኛ ድሉን ያስመዘገበው መቻል በ54 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል። በውድድር ዓመቱ 16ኛ ድሉን አሳክቷል። በሊጉ 17ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ባህር ዳር ከተማ በ19 ነጥብ 10ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ዛሬ አስቀድመው በተደረጉ የ24ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ጨዋታዎች ሸገር አርባምንጭ ከተማን 4 ለ 0፣ ሲዳማ ቡና ልደታ ክፍለ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፈዋል።
ማንችስተር ዩናይትድ ሊቨርፑልን 3 ለ2 በሆነ ውጤት አሸነፈ
May 3, 2026 91
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 25/2018 (ኢዜአ)፦በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በተደረገው ተጠባቂ ጨዋታ ማንችስተር ዩናይትድ ሊቨርፑልን 3 ለ2 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል። የቀያይ ሰይጣኖቹን የማሸነፊያ ግቦች ኩንያ ፤ ቤንጃሚን ሴስኮ እና ኮቢ ማይኖ አስቆጥረዋል። ለሊቨርፑል ግቦችን ስቦዝላይ እና ኮዲ ጋክፖ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል። ማንችስተር ዩናይትድ ማሸነፉን ተከትሎ ወደ አውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ መመለሱን አረጋግጧል። ማንችስተር ዩናይትድ በዚህ አመት ሊቨርፑልን በሁለቱም ዙር ጨዋታዎች ማሸነፍ ችሏል። ማንችስተር ዩናይትድ በ64 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ያስጠበቀ ሲሆን ሊቨርፑል በ58 ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ሁለቱ ክለቦች እስከ አሁን በሁሉም ውድድሮች 245 ጊዜ ተገናኝተው ማንችስተር ዩናይትድ 93 ጊዜ በማሸነፍ የበላይነቱን ሲይዝ ሊቨርፑል 82 ጊዜ አሸንፏል።70 ጊዜ ደግሞ አቻ ተለያይተዋል። ማንችስተር ዩናይትድ ማሸነፉን ተከትሎ በቀጣይ ወደ አውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር መመለሱንም አረጋግጧል።
አካባቢ ጥበቃ
የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት አተገባበር በምሳሌነት የሚጠቀስ ነው
May 3, 2026 122
ጅማ ፤ ሚያዝያ 25/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት አተገባበር በምሳሌነት የሚጠቀስና ተጨባጭ መሆኑ ተመላከተ። ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ስትራቴጂን በመከተል ላይ ትገኛለች። ስትራቴጂው በዋናነት ዘላቂነት ባለው የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም እና በፈጠራ የታገዙ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ልምዶችን በማስፋፋት ላይ ያተኩራል። ለአብነትም የአፈር እና ውሃ ጥበቃን ማጠናከር፣ ድርቅ የሚቋቋሙ የሰብል ዝርያዎችን መጠቀም እና ከበካይ ጋዝ ነፃ የሆኑ የኃይል ምንጮችን ማስፋፋት የስትራቴጂው አካላት ናቸው። ይህም ኢትዮጵያ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ ለመሰለፍ በምታደርገው ጉዞ ከበካይ ጋዝ ልቀት የጸዳ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት ለማስመዝገብ የያዘችው ግብ አካል ነው። ለተግባራዊነቱም የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር፣ የታዳሽ ኃይል ልማት፣ ዘመናዊና አረንጓዴ ትራንስፖርት እንዲሁም የግብርና እና ተፋሰስ ልማት ላይ በትኩረት እየሰራች ትገኛለች። በዚሁ ጉዳይ ላይ ኢዜአ በኢትዮጵያ የግሎባል ግሪን ግሮዝ ኢንስቲቲዩት (GGGI) ዳይሬክተር እና በኢትዩጵያ የምግብ ስርዓት ሽግግር እና ኒውትሪሽን የአየር ንብረት አስተባባሪ ጋር ቆይታ አድርጓል። የግሎባል ግሪን ግሮዝ ኢንስቲቲዩት በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት ሁሉን አቀፍና ለአካባቢ ጥበቃ ትኩረት የሚሰጥ ጠንካራ ኢኮኖሚን እንዲገነቡ እገዛ ያደርጋል። በኢትዮጵያ የኢንስቲትዩቱ ዳይሬክተር ኦኬቹኩ ዳንኤል ኦግቦናያ እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ተቋቁማ ያስመዘገበችው እድገት ቀጠናውን በልማት ለማስተሳሰር ተጨማሪ እቅም እየፈጠረ ነው። የአረንጓዴ የኢኮኖሚ ልማቱም የካርቦን ልቀትን በመቀነስ የስራ እድል እንዲስፋፋና ኢንቨስትመንትን ለመሳብም ተደማሪ አቅም በመፍጠሩ ተሞክሮ የሚወሰድበት መሆኑን ጠቁመዋል። ሀገሪቱ በታዳሽ ኃይል ልማት በውሃ፣ በነፋስና ጸሐይ ላይ የሚደረጉት ግዙፍ ኢንቨስትመንቶችም በአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚን ለመገንባት እንደሚያስችላት ተናግረዋል። በኢትዮጵያ የምግብ ስርዓት ሽግግር እና ኒውትሪሽን የአየር ንብረት አስተባባሪ ከፈለኝ ጌታሁን (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ አረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ የአየር ንብረት ለውጥን ታሳቢ ያደረገ እድገትን መገንባት እንደሚያስችላት ጠቁመዋል። ለዚህም በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ዘርፈ ብዙ ጥቅም የሚሰጡ ችግኞች ተከላና የአፈርና ውሀ ጥበቃ ስራዎች ምርታማነት እንዲጨምር ማገዛቸውን አንስተዋል። ኢትዮጵያ የሰሃራ በረሀ መስፋፋትን ተከትሎ በአፍሪካ ቀንድ በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የተደቀነውን ፈተና ለመቋቋም የሚያስችል አቅም አየገነባች መሆኗን አስተባባሪው ገልጸዋል። አትዮጵያ ቀጣናውን በጋራ ልማት ለማስተሳሰር የጀመረችው ተግባርም የሚበረታታ መሆኑንም አክለዋል።
ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን መቋቋም የሚያስችል አስደናቂ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ እየገነባች ነው - አምባሳደር ኦሊቪያ ሌስሊ
May 1, 2026 350
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 23/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን መቋቋም የሚያስችል አስደናቂ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ እየገነባች መሆኑን በኢትዮጵያ የአየርላንድ አምባሳደር ኦሊቪያ ሌስሊ ገለጹ። የኢትዮጵያ አረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ በአረንጓዴ አሻራ፣ የውሃ፣ የንፋስና የፀሐይ ታዳሽ ኃይል ምንጮችን በማስፋፋት ዓለም አቀፍ ዕውቅናን ያስገኘ ዕድገት እያመጣ ይገኛል። የበካይ ጋዝ ልቀትን የሚቀንሱ ዘመናዊ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ የትራንስፖርት አማራጮችን ማበረታታትና የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም ዘላቂ ግብርናን የሚያሳልጡ ስትራቴጂክ የልማት አቅጣጫዎች ናቸው። ይህ የተቀናጀ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ የተፈጥሮ ሃብትን በመጠበቅና ዕድገትን በማፋጠን ለቀጣዩ ትውልድ አስተማማኝ መሰረት እየጣለ ይገኛል። በኢትዮጵያ የአየርለንድ አምባሳደር ኦሊቪያ ሌስሊ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ አየርላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የተለያዩ የትብብር መስኮችን በማጠናከር የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ለመቀነስ እየሰራች ነው ብለዋል። ኢትዮጵያም ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ በመገንባት ተምሳሌትና ዓለምአቀፍ ተቀባይነት ያላቸው ስኬቶችን እያስመዘገበች እንደምትገኝ ገልጸዋል። በተለይም በታዳሽ ኃይልና በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተመዘገቡ ውጤቶች የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን መቋቋም የሚያስችሉ መሠረቶች መሆናቸውን ተናግረዋል። በቀጣይም አየርላንድ የኢትዮጵያ የልማት አቅጣጫዎችን ለማሳካት በሚደረገው ጥረት ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል። የኢትዮ-አየርላንድን የሁለትዮሽ ግንኙነት በሚያጠናክሩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ባላቸው የልማት መስኮች በአጋርነት እየተሰራ አንደሚገኝም አምባሳደሯ ገልጸዋል። ኢትዮጵያና አየርላንድ ያላቸውን ዲፕሎማሲያዊ ትብብር የበለጠ በማጠናከር በተለያዩ የልማት መስኮች የሚደረጉ ግንኙነቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል። አየርላንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ሁሉን አቀፍ ትብብር እንደምታጠናክርም አምባሳደሯ አረጋግጠዋል።
ዘንድሮ በሰሜን ሸዋ ዞን በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ከ36 ሺህ ሔክታር በሚልቅ መሬት ላይ ችግኝ ይተከላል
Apr 30, 2026 366
ደብረ ብርሃን፤ ሚያዝያ 22/ 2018 (ኢዜአ)፡- በመጪው ክረምት በሚካሄደው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ከ36 ሺህ ሔክታር በሚልቅ መሬት ላይ ችግኝ እንደሚተከል የሰሜን ሸዋ ዞን ግብርና መምሪያ አስታውቋል። ለመጪው ክረምት አረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር የሚተከሉ 294 ሚሊየን ችግኞች እስካሁን መዘጋጀታቸውን በመምሪያው የተፈጥሮ ሀብት ልማት ጥበቃና አጠቃቀም ቡድን መሪ ጌታነህ ተ/ማርያም ገልጸዋል። በቀሪ ወራትም ፈጥነው የሚደርሱ ችግኞች ላይ በማተኮር የማዘጋጀት ሥራው እንደሚቀጥል ጠቁመዋል። በአጠቃላይም በመጪው ክረምት ከ36 ሺህ 260 ሔክታር በሚልቅ መሬት ላይ ችግኞች እንደሚተከሉ ለኢዜአ ተናግረዋል። ከአሁን በፊት የተተከሉ ችግኞች አርሶ አደሩን በእንስሳት ዕርባታና ማድለብ፣ በንብ ማነብ፣ በመኖ አቅርቦትና በሌሎች የሥራ ዘርፎች በማሰማራት ጥምር ግብርናን ለማስፋፋት ምቹ ሁኔታ ፈጥረዋል ብለዋል። በዞኑ ባለፉት ዓመታት የለሙ 1 ሺህ 163 ተፋሰሶች የአፈር ለምነትን በማሻሻል፣ የገጸና ከርሰ ምድር ውኃን በማበልጸግና ለመስኖ ልማት በማዋል የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ማሳደጋቸውንም አክለዋል።
በአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ባለማነው የፍራፍሬ ችግኝ ተጠቃሚነታችን አድጓል-አርሶ አደሮች
Apr 29, 2026 306
ሃዋሳ ፤ ሚያዝያ 21/2018 (ኢዜአ)፦ በአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ያለሙት የፍራፍሬ ችግኝ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን እንዳሳደገላቸው በሲዳማ ክልል የሸበዲኖ ወረዳ አርሶ አደሮች ገለጹ፡፡ በሲዳማ ክልል የሸበዲኖ ወረዳ አርሶ አደሮች ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ባለፉት ዓመታት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ያለሙት የፍራፍሬ ችግኞች አድገው ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን እንዲያረጋግጡ እያስቻሉ ነው፡፡ በወረዳው የፉራ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አርሶ አደር መሃመድ ቦጋለ እና አርሶ አደር ሄርቲሞ ሬቢሶ የቡና ችግኝ በማልማት ውጤታማ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ ችግኞቹን በኩታ ገጠም በመትከል፣ የተፈጥሮ አፈር ማዳበሪያ በማዘጋጀትና ለጥላ የሚሆን እንሰት በመትከል ተገቢውን እንክብካቤ እያደረጉ እንደሚገኙም ተናግረዋል፡፡ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር አቮካዶን ጨምሮ ለምግብነት የሚውሉ ፍራፍሬዎችን በማልማት ተጠቃሚ መሆናቸውን የተናገሩት ደግሞ በአቮካዶ ልማት የተሳተፉት አርሶ አደር ሙሴ በቴሾ ናቸው፡፡ ላለፉት ስምንት ዓመታት ሁለት ሄክታር በሚጠጋ ማሳቸው ላይ የተሻሻሉ ዝርያ ያላቸው የአቮካዶ ችግኞችን ተክለው በማልማት ምርቱን ለኢንዱስትሪ ፓርኮች እንደሚሸጡም አክለዋል። የወረዳው እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ጽህፈት ቤት የቡና ፍራፍሬና ቅመማ ቅመም ባለሙያ አቶ ደሞዜ ሌዳሞ እንዳሉት በወረዳው በዘንድሮው ዓመት ከ726 ሄክታር በላይ መሬት ላይ የቡና ችግኝ ለመትከል ታቅዶ ወደ ስራ ተገብቷል። በተለይም ቡና በክላስተር በማልማት የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተሰራው ስራ ውጤታማ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ቡናን ጨምሮ ለፍራፍሬና ለምግብት ለሚውሉ ችግኞች ትኩረት መሰጠቱን የገለጹት ደግሞ የሲዳማ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ መምሩ ሞኬ ናቸው፡፡ በመርሃ ግብሩ ከሚተከሉ ችግኞች መካከል 60 በመቶ የሚሆኑት ለምግብነት የሚውሉ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡ በመርሃ ግብሩም አቮካዶ፣ አፕልና ሌሎች ፍራፍሬዎችን ጨምሮ ለእንስሳት መኖም ትኩረት ተሰጥቷል ብለዋል፡፡ በክልሉ ለዘንድሮ ዓመት የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ከ322 ሚሊዮን በላይ ችግኖች የተዘጋጁ ሲሆን በቡና ችግኝ ተከላ የተጀመረው መርሃ ግብር እስከ መጪው ሃምሌ ወር እንደሚከናወንም አስረድተዋል፡፡
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የአህጉሪቷን የልማት ግቦች ለማሳካት የአፍሪካ ሕብረትና አባል ሀገራትን የፖሊሲ አቅጣጫ አሰናስሎ መምራት ይገባል
Apr 28, 2026 634
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 20/2018(ኢዜአ)፦የአህጉሪቷን የልማት ግቦች ለማሳካት የአፍሪካ ሕብረትና አባል ሀገራትን የፖሊሲ አቅጣጫ አሰናስሎ መምራት እንደሚገባ የሕብረቱ ኮሚሽን ምክትል ሊቀ-መንበር አምባሳደር ሰልማ ማሊክ ሀዳዲ ገለጹ። በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ከአፍሪካ ሕብረት፣ ከአፍሪካ ልማት ባንክና ሌሎች አጋር አካላት ጋር በመተባበር "የአጀንዳ 2030 እና 2063 ግቦችን ለማሳካት የተቀናጀና አሻጋሪ አካሄድ መከተል" በሚል መሪ ሐሳብ ያዘጋጀው 12ኛው የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ቀጣናዊ ጉባኤ በአዲስ አበባ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን መካሄድ ጀምሯል። በየዓመቱ የሚካሄደው የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ቀጣናዊ ጉባኤ የአፍሪካ ሕብረትን የአጀንዳ 2030 እና 2063 የዘላቂ የልማት ግቦችን አፈፃጸም ይገመግማል። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ-መንበር አምባሳደር ሰልማ ማሊክ ሀዳዲ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ አጀንዳ 2030 እና 2063 ጎን ለጎን የሚሄዱ ሳይሆን እርስ በርስ የሚደጋገፉ ናቸው። የአፍሪካ ሕብረት የሁለተኛውን የአሥር ዓመት የአጀንዳ 2063 የትግበራ ዕቅድን ሀገር በቀል በማድረግ አካታች ዕድገትና ዘላቂ የኢኮኖሚ ሽግግርን የሚያፋጥን መሠረታዊ እርምጃ መውሰዱን ገልጸዋል። የሕብረቱ አባል ሀገራትም ብሔራዊ የልማት ዕቅዶችን ከአጀንዳው ጋር በማጣጣም የበጀት ድልድልና የፖሊሲ እርምጃዎችን ለአፍሪካ የትኩረት መስኮች ቅድሚያ እየሰጡ መሆናቸውን ተናግረዋል። በዚህም አፍሪካ የአጀንዳ 2030 እና 2063 ዘላቂ የልማት ዕቅዶችን በመተግበር ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ያላትን ቁርጠኝነት በተግባር እያሳየች መሆኑን ገልጸዋል። በአፍሪካ አጀንዳ 2030 እና 2063 ግቦች የበለጸገች አህጉርን እውን ለማድረግም የአባል ሀገራት ቅንጅትና ትብብር ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል ብለዋል። የአጀንዳ 2030 የዘላቂ ልማት ግቦችን በማሳካት የተሳለጠ የለውጥ ሽግግርን ለመፍጠርም ጠንካራና የተሰናሰለ ሀገራዊ፣ ቀጣናዊና አህጉራዊ የፖሊሲ ፍሰት ሊኖር እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ ለዚህም የመንግሥታት፣ የግሉ ዘርፍና የልማት አጋሮች በወሳኝ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ የሚኖራቸውን ትብብርና ቅንጅት የሚያበረታታ ምኅዳር መፍጠር እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። የዑጋንዳ ጠቅላይ ሚኒስትርና ተሰናባቿ የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ቀጣናዊ ጉባኤ ቢሮ ሊቀ-መንበር ሮቢናህ ናባንጃ በበኩላቸው፤ የአፍሪካውያን ድምፅ በወሳኝ የዓለም መድረኮች ላይ መንፀባረቅ እንዳለበት ገልጸዋል፡፡ አፍሪካውያን በዓለም አቀፍ መድረኮች በከፍተኛ ደረጃ ከሚደረግ ፖለቲካዊ ተሳትፎ ባለፈ በወሳኝ ስትራቴጂክ ሂደቶች ላይ በንቃት መሳተፍ ይገባቸዋል ብለዋል። የአፍሪካ ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካትም ሎጂስቲክስ፣ ትራንስፖርትና መሰል የትኩረት ዘርፎች ላይ በስፋት በመሰማራት ቀጣናዊ ትስስርን ማጠናከር እንደሚገባ ተናግረዋል።
አፍሪካ የአጀንዳ 2030 እና 2063 ዘላቂ የልማት ዕቅዶችን በመተግበር ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ያላትን ቁርጠኝነት በተግባር እያሳየች ነው
Apr 28, 2026 348
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 20/2018(ኢዜአ)፦ አፍሪካ የአጀንዳ 2030 እና 2063 ዘላቂ የልማት ዕቅዶችን በመተግበር ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ያላትን ቁርጠኝነት በተግባር እያሳየች መሆኑን የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ-መንበር አምባሳደር ሰልማ ማሊክ ሀዳዲ ገለጹ። በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ከአፍሪካ ሕብረት፣ ከአፍሪካ ልማት ባንክና ሌሎች አጋር አካላት ጋር በመተባበር "የአጀንዳ 2030 እና 2063 ግቦችን ለማሳካት የተቀናጀና አሻጋሪ አካሄድ መከተል" በሚል መሪ ሐሳብ ያዘጋጀው 12ኛው የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ቀጣናዊ ጉባኤ በአዲስ አበባ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን መካሄድ ጀምሯል። በየዓመቱ የሚካሄደው የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ቀጣናዊ ጉባኤ የአፍሪካ ሕብረትን የአጀንዳ 2030 እና 2063 የዘላቂ የልማት ግቦችን አፈፃፀም ይገመግማል። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ-መንበር አምባሳደር ሰልማ ማሊክ ሀዳዲ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ አጀንዳ 2030 እና 2063 በትይዩ የሚሄዱ ሳይሆን እርስ በርስ የሚደጋገፉ ናቸው። በአፍሪካ አካታች ዕድገትና ዘላቂነት ያለው የኢኮኖሚ ሽግግር ለመፍጠር ወሳኝ መሆናቸውንም ገልጸዋል። የአፍሪካ ሕብረት የሁለተኛውን የአሥር ዓመት የአጀንዳ 2063 የትግበራ ዕቅድ ሀገር በቀል እንዲሆን መሠረታዊ እርምጃ መውሰዱን ተናግረዋል። የሕብረቱ አባል ሀገራት ብሔራዊ የልማት ዕቅዶቻቸው ከአጀንዳው ጋር እየተጣጣመ መምጣቱን በማንሳት፤ የበጀት ድልድልና ፖሊሲዎቻቸው ለአፍሪካ የትኩረት መስኮች ቅድሚያ የሰጡ መሆናቸውን አስታውቀዋል። የአጀንዳ 2030 እና 2063 ግቦችን በማሳካት የበለጸገች አፍሪካን እውን ለማድረግ በሀገራት መካከል ያለው ቅንጅትና ትብብር ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባም አስገንዝበዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ #ENA
አፍሪካውያን የአረንጓዴ ኢንዱስትሪ አብዮትና ዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት የማዕድን ሀብታቸውን እሴት በመጨመር ለዓለም ገበያ ማቅረብ አለባቸው
Apr 27, 2026 371
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 19/2018 (ኢዜአ)፦ አፍሪካውያን የአረንጓዴ ኢንዱስትሪ አብዮትና ዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት የማዕድን ሀብታቸው ላይ እሴት በመጨመር ለዓለም ገበያ ማቅረብ እንዳለባቸው የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ጸሀፊ ክላቨር ጋቴቴ ገለጹ፡፡ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ከታንዛኒያ የአፍሪካ ዘላቂ ልማት አመራር ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር "የአፍሪካ ወሳኝ ማዕድናትን ለአረንጓዴ የኢንዱስትሪ አብዮትና ዘላቂ ልማት ማዋል" በሚል መሪ ሃሳብ ያዘጋጁት የ12ኛው የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ቀጣናዊ ቅድመ ጉባኤ ተካሂዷል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ጸሀፊ ክላቨር ጋቴቴ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ አፍሪካ እንደ ኮባልት፣ ሊቲየም፣ ግራናይት እና ሌሎች የከርሰ ምድር ሀብቶችን ጨምሮ የዓለምን 30 በመቶ ማዕድናትን ይዛለች፡፡ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ብቻዋን የዓለምን ከፍተኛ የኮባልት ማዕድን የያዘች መሆኑን ገልጸው፤ ይሄውም አፍሪካን የዓለም አቀፍ የኃይል ሽግግር /Energy Transition/ ማዕከል ያደርጋታል ብለዋል፡፡ አፍሪካ ዩራኒዬምና ሌሎች የከርሰ ምድር የከበሩ ማዕድናት ባለቤት መሆኗን በመጥቀስ፤ ለዓለም አቀፉ የኒውክሌር ኃይል አቅርቦት አስተዋጽኦ ከማድረግ ባለፈ ብዙ የአፍሪካ ሀገራት ወደ ኒውክሌር ኃይል ልማት እያመሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አፍሪካ የከበሩ ማዕድናት ባለቤት ብትሆንም አብዛኛው በጥሬ እቃ መልክ ወደ ውጭ የሚላክ በመሆኑ የአህጉሪቱ የእርስ በእርስ ግብይት ከሁለት በመቶ እንዳማይዘል ተናግረዋል፡፡ በአህጉሪቱ የማዕድናት ማምረቻና ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎችን መገንባት ቢቻል በየዓመቱ ከ24 ቢሊየን ዶላር በላይ ተጨማሪ ገቢ ማግኘትና ለ2 ነጥብ 3 ሚሊየን ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር ይቻላል ብለዋል፡፡ የአፍሪካ የማዕድን ፖሊሲ ለእሴት መጨመር፣ ኢንዱስትሪ ልማትና ሁሉን አቀፍ ልማት ቅድሚያ የሚሰጥ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም በአህጉሪቱ የተቀናጀ ቀጣናዊ ኢንዱስትሪ ለመገንባት ያለውን ፍላጎት በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ማዕቀፍ አህጉራዊ የማዕድን ሀብቶችን ወደ ዘላቂ ብልጽግና መለወጥ ይገባል ብለዋል፡፡ በዚህም የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ቀጣናዊ እሴት ሰንሰለትን በማጠናከር የማዕድን ጸጋዎችን ጥቅም ላይ ለማዋል በሚደረገው ጥረት ትብብሩን ማጠናከሩን እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡ የአፍሪካ ዘላቂ ልማት አመራር ኢንስቲትዩት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ካዳሪ ሲንጎ በአፍሪካ ሁሉን አቀፍና አካታች ዕድገት ለማስመዝገብ የማዕድን ሀብቶችን በአግባቡ ጥቅም ላይ ማዋል እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ አፍሪካውያን በተፈጥሮ ሀብታችን ላይ የሚኖረን ትብብርና ተሳትፎ ስትራቴጂያዊና መዳረሻ ግብ ያለው መሆን እንዳለበት ገልጸዋል፡፡ በአፍሪካ ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥና የአረንጓዴ ኢንዱስትሪ አብዮት ሽግግርን ለመፈጠር በአቅም ግንባታ ድጋፍ እናደርጋለን ብለዋል፡፡
አምባሳደር ቆንጂት ስነጊዮርጊስ የአፍሪካ ዲፕሎማሲ እሴቶች ተምሳሌት ነበሩ
Apr 7, 2026 748
አዲስ አበባ፤መጋቢት 29/2018 (ኢዜአ)፦አምባሳደር ቆንጂት ስነጊዮርጊስ የአፍሪካ ዲፕሎማሲ ከፍተኛ እሴት በተግባር ያሳዩ ታላቅ ዲፕሎማት ነበሩ ሲሉ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። ሊቀመንበሩ በኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ታሪክ ውስጥ ስመጥር በሆኑት አምባሳደር ቆንጂት ስነጊዮርጊስ ህልፈት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል። ሊቀመንበሩ አምባሳደሯን የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት አገልግሎት ፈር ቀዳጅ፣ ታላቅ ዲፕሎማት እና ህይወታቸውን ለሀገራቸውና ለአህጉሪቱ እድገት የሰጡ ጽኑ አፍሪካዊት ሲሉ አወድሰዋቸዋል። አምባሳደር ቆንጂት ስነጊዮርጊስ ለበርካታ አስርተ አመታት የዘለቀ አርአያነት ያለው ሙያዊ ስኬት ማስመዝገባቸውንና ከኢትዮጵያ ቀዳሚ ሴት አምባሳደሮች አንዷ በመሆንም ለአፍሪካውያን ሴት ዲፕሎማቶች የብርሃን ፋና መሆናቸውን አመልክተዋል። የአፍሪካን ጥቅም ለማስከበርና ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጠናከር የነበራቸው የማይናወጥ ቁርጠኝነት ለአህጉራዊ የጋራ ግቦች መሳካት የጎላ ሚና እንደነበረውም አውስተዋል። ሊቀመንበሩ አምባሳደር ቆንጂት በታማኝነት፣ በልዩ ብቃት እና ለጋራ የወደፊት እጣ ፈንታ የነበራቸው ጽኑ ቁርጠኝነት የአፍሪካ ዲፕሎማሲ እሴቶች ያላቸውን ጽኑ አቋም ያሳየ መሆኑንም ነው ያነሱት። የአምባሳደሯ የዲፕሎማሲ አሻራ ለቀጣይ ትውልድ ዲፕሎማቶች፣በተለይም ለሴቶች፣በድፍረትና በዓላማ እንዲያገለግሉ ዘላቂ መነሳሳት ሆኖ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል። ሊቀመንበሩ በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ስም ለአምባሳደር ቆንጂት ቤተሰቦች፣ ለኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ፣ እንዲሁም ለሁሉም አፍሪካውያን ልባዊ መጽናናትን ተመኝተዋል።
ሐተታዎች
የቴክኖሎጂ እምርታ -ሌላው የኢትዮጵያ ከፍታ ጉዞ አመላካች
May 3, 2026 124
የቴክኖሎጂ እምርታ -ሌላው የኢትዮጵያ ከፍታ ጉዞ አመላካች በሙሴ መለሰ በኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት የታየው የቴክኖሎጂ ለውጥ ወደ ዘመናዊው የዲጂታል ምህዳር እያሸጋገራት ይገኛል።የፖሊሲ ማሻሻያዎች፣ የመሰረተ ልማት እና የተቋማት ግንባታ ስራዎች ኢትዮጵያ ወደ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን በምታደርገው ጉዞ ውስጥ የሚጠቀሱ ዋንኛ ስራዎች ናቸው። ለውጡን ተከትሎ መንግስት "ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" የተሰኘውን ስትራቴጂ በመቅረጽ የዲጂታላይዜሽን ስራውን የሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት ምሰሶ አድርጎታል። የለውጡ መንግስት ስልጣን ከያዘ በኋላ ቴክኖሎጂን እንደ አንድ የኢኮኖሚ ምሰሶ በመቁጠር "ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" የተሰኘውን አጠቃላይ ስትራቴጂ ነድፎ ወደ ተግባር ገባ።ይህ ስትራቴጂ የሀገሪቱን የዲጂታል ጉዞ ከመሰረቱ የለወጠ ሲሆን፣የመጀመሪያው ትልቅ እርምጃም የቴሌኮም ዘርፉን ለውጭ ኢንቨስትመንት ክፍት ማድረግ ነበር። የቴሌኮም ዘርፉ ለውጭ ኢንቨስትመንት ክፍት መደረጉ የሳፋሪኮም ወደ ኢትዮጵያ መግባትና የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎቶችን የማዘመን ስራ የኢንተርኔት ተደራሽነት እንዲሰፋ ምክንያት ሆኗል።በተለይም የአምስተኛ ትውልድ (5G) ቴክኖሎጂ አገልግሎት መጀመር ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እንድትሆን አስችሏታል። የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ለውጡ የፋይናንስ ዘርፉ ላይ ውጤት አምጥቷል።እንደ ቴሌብር (telebirr) ያሉ የዲጂታል ክፍያ አማራጮች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ያለ ምንም የባንክ ሂሳብ በስልካቸው ብቻ ግብይት እንዲፈጽሙ በማድረግ፣ ሀገሪቱ ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚ እንድትሸጋገር ትልቅ መደላድል ፈጥረዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ረገድ የተመዘገቡት ስኬቶችም የኢትዮጵያን የቴክኖሎጂ አድማስ ይበልጥ አስፍተውታል። የኢትዮጵያ ሰው ሰራሽ አስተውሎት ኢንስቲትዩት መቋቋም ሀገሪቱ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ያላትን ራዕይ ለዓለም ያሳየችበት አጋጣሚ ነው።ኢንስቲትዩቱ በአሁኑ ወቅት በጤናው ዘርፍ የካንሰር ህመምንና የሳምባ በሽታዎችን ቀድሞ መለየት የሚያስችሉ የኤአይ ውጤቶችን አበልጽጓል። በግብርናውም ረገድ የአፈርን ለምነትና የሰብል በሽታን በቴክኖሎጂ የመለየት ስራዎች እየተከናወኑ ሲሆን፣ ይህም በምግብ ዋስትና ላይ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። ሌላው ትልቅ ስኬት የሀገር በቀል ቋንቋዎችን በዲጂታል ዓለም ውስጥ ተወዳዳሪ ለማድረግ የተሰሩ የቋንቋ ፕሮሰሲንግ (NLP) ስራዎች ናቸው። ይህም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች በዘመናዊ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎች ውስጥ እንዲካተቱና ለተጠቃሚው ምቹ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። የፋይዳ (Fayda) ብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ፕሮጀክት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎችን መረጃ በአንድ ማዕከል በመሰብሰብ፣ ለባንክ፣ ለጤናና ለሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶች አስተማማኝ መሠረት ጥሏል። በአሁኑ ወቅት ዜጎች እንደ ፓስፖርት ማደስ፣ የንግድ ፈቃድ ማውጣትና ግብር መክፈል ያሉ አገልግሎቶችን ከቤታቸው ሆነው በኢንተርኔት ማከናወን መቻላቸው የለውጡ ፍሬያማነት ማሳያ ነው።የሳይንስ ሙዚየምም የወጣቶችን የፈጠራ አቅም የሚያሳይና የሀገሪቱን ቴክኖሎጂ የሚደግፍ ትልቅ አቅም ሆኗል።የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 በቅርቡ መጠናቀቁ ይታወቃል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የ2025 ስትራቴጂው መጠናቀቁን ተከትሎ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ን ታህሳስ 11 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ ማስጀመራቸው ይታወሳል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክት ተደራሽነትን ማስፋት፣ ለዜጎች እኩል እድል መፍጠር እንዲሁም በዜጎችና ተቋማት መካከል መተማመንን ማጎልበት ደግሞ የስትራቴጂው ቁልፍ መሰረታዊ ትልሞች መሆናቸውን ገልጸዋል። ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ም ባለፉት አምስት ዓመታት የተከናወኑ ተግባራትን መሰረት በማድረግ መዘጋጀቱን አንስተዋል።ትልሞቹ እንዲሳኩም በተለይ የህዝብ ዲጂታል መሠረተ ልማት ማስፋት ላይ ትልቅ ስራ እንደሚከናወን ጠቁመው፤ ይህም ዲጂታል ቴክኖሎጂ ሰው ተኮር ሆኖ የዜጎችን ኑሮ እንዲያሻሽል ትልቅ አቅም ይፈጥራል ብለዋል። በአጠቃላይ በዲጂታል ኢትዮጵያ የሚከናወኑ ስራዎች የመደመር መንግስት በቀለለ ቢሮክራሲ ታላላቅ ስትራቴጂዎችን እውን ለማድረግ ከያዘው ግብ ጋር የተሳሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል። ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 እንዲሳካም ሁሉም በትብብር መስራት እንዳለበት ነው ጥሪ ያቀረቡት። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ዲጂታል 2030ን ይፋ ሲያደርጉ የነበረው ትልቁ መልዕክት ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂው ዓለም ተመልካች ሳይሆን ተሳታፊና መሪ ትሆናለች የሚል ነው። ስትራቴጂው በዋናነት"የፋይዳ" ዲጂታል መታወቂያን ከሁሉም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶች ጋር በማቀናጀት፣ ለዜጎች ቀልጣፋ አሰራርን መፍጠር፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የዲጂታል ስራ እድሎችን ለወጣቶች ማመቻቸት እና ኢትዮጵያን በአፍሪካ ቀዳሚ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ማዕከል (Innovation Hub) አድርጎ መገንባትን እንደ ዋነኛ ግብ አስቀምጧል። ይህም ሁሉን አቀፍ የኢንተርኔት ተደራሽነትን በማረጋገጥ፣ የመንግስት አገልግሎቶችን መቶ በመቶ ወረቀት አልባ በማድረግ እና የሰው ሰራሽ አስተውሎትን (AI) በግብርና፣ በጤናና በኢንዱስትሪ ዘርፎች ላይ በስፋት በመተግበር የምርታማነት አብዮት መፍጠርን ያለመ ነው። በዚህ ረገድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ሕብረት የሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence) እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ መሪ (Champion) ሆነው መሾማቸው ኢትዮጵያ በዘርፉ የጀመረችው ስራ በአህጉራዊ ደረጃ ያለውን ተቀባይነትና የተሰጣትን ትልቅ ኃላፊነት የሚያሳይ ነው።ኢትዮጵያ አሁን ላይ የደረሰችበት የቴክኖሎጂ ከፍታ፣ ሀገሪቱን በአፍሪካ የቴክኖሎጂ ተፎካካሪ ብቻ ሳይሆን የፈጠራ ምንጭ እንድትሆንም እያደረጋት ይገኛል። በዚህ ረገድም የቀጣዩ ዲጂታል 2030 ስትራቴጂ ስኬትም ኢትዮጵያን ሙሉ በሙሉ ወረቀት አልባና በቴክኖሎጂ የበለጸገች ሀገር የማድረግ ራዕይን ለማሳካት እና ለሀገራዊ ብልጽግና እንደ ቁልፍ ሞተር ሆኖ ያገለግላል።
የክልሎች ቅኝት በወፍ በረር
May 3, 2026 97
ክልሎች፤ሚያዝያ 25/2018 (ኢዜአ)፡-የክልሎች ቅኝት በወፍ በረር በሳምንቱ በክልሎች የተከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮች በወፍ በረር ሲቃኙ ይህንን ይመስላሉ!!! 👉ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የተገነቡትን የቶዮ ሶላር ኢነርጂ ምዕራፍ ሁለት፣ የኦሪጂን እና የሉሚንቴክ የሶላር ፋብሪካዎችን እንዲሁም የኤች.ዜድ ጋዝ ማምረቻ ፋብሪካን በይፋ መርቀዋል። እነዚህ የሶላር ፋብሪካዎች በጋራ በዓመት 11.3 ጊጋ ዋት ንጹሕ ኃይል የማመንጨት አቅም ያላቸው ሲሆን፣ የኤች.ዜድ ጋዝ ፋብሪካ ደግሞ በዓመት 900 ቶን ኦክስጅን፣ 40,000 ቶን ናይትሮጅን እና 7 ቶን ሃይድሮጅን ለገበያ ያቀርባል። ይህ ክንውን የኢትዮጵያን የታዳሽ ኃይል ልማት ለማፋጠን፣ የኢነርጂ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና ዘላቂ፣ የማይበገር ሁለንተናዊ እድገት ዕውን ለማድረግ የተነደፈውን ስትራቴጂ ለማሳካት ትልቅ ምዕራፍ ተደርጎ ይወሰዳል። 👉እንቁላልን ሳይበላሽ ለሁለት ዓመት የማቆየት ልምምድ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ፤ የዶሮ እንቁላል ሳይበላሽ ለሁለት ዓመት ያህል ማቆየት የሚያስችል ቴክኖሎጂን ወደ ተግባር ለማስገባት ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል። በዩኒቨርሲቲው የእንስሳት ሕክምናና ሳይንስ ኮሌጅ መምህርና ተመራማሪ ዶክተር ማስተዋል ብርሃን፤ ዩኒቨርሲቲው የእንቁላል ምርት ብክነትና ብልሽትን ለማስቀረት ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። በዚህም እንቁላልን እስከ ሁለት ዓመት ያለ ምንም ብልሽት ማቆየት የሚያስችለውን ቴክኖሎጂን የማላመድና የማስተዋወቅ ስራ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ቴክኖሎጂው በአንድ ሊትር ውሃ ውስጥ 30 ግራም የኖራ አፈር ወይም ላይም ስቶን ጨምሮ በማዋሃድ እስከ 12 እንቁላሎችን ሳይበላሽ የሚያስቀምጥ በመሆኑ ለአርሶ አደሩ ተመራጭ ነው ያሉት። ይህም እስካሁን ባለው አንድ ትኩስ እንቁላል ሳይበላሽ መቆየት የሚችለው እስከ ሁለት ሳምንት መሆኑን ጠቁመው ቴክኖሎጂው ይሄን ችግር በመሰረታዊነት የሚቀይር ነው።፡ ቴክኖሎጂውን በስፋት በማስተዋወቅና በማላመድ ረገድም ተግባር ተኮር ስልጠናዎችን በመስጠት ችግር ፈቺነቱን የማሳየት ስራ እየተሰራ መሆኑንም አስረድተዋል። 👉የአፋር ጥጥ ተስፋ ሰጪ ፀጋ! የአፋር ክልል የበርካታ የተፈጥሮ ፀጋዎች ባለቤት ነው፤ ሆኖም እነዚህን እምቅ ሀብቶች ወደ ልማት በመቀየር ከፀጋዎቹ ተቋዳሽ ለመሆን ሳይቻል ለረጅም ተቆይቷል። አሁን ግን ከፀጋዎቹ አንዱ የሆነውን ተፈጥሯዊ ጥጥ (Organic Cotton) ለማምረት ተስፋ ሰጪ ተግባራት እየተከናወኑ ነው። በሰመራ በተካሄደ የውይይት መድረክም በግብርና ሚኒስቴር የጥጥ ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ሳምሶን አሰፋ፤ የአፋር ክልል ጥጥን በመስኖ ማልማት የሚቻልበት አቅም ያለው በመሆኑ ልማቱን ማስፋፋት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ብለዋል። በሀገራችን የጥጥ ልማትን ለማስፋፋት ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን አንስተው፤ ባለፈው የምርት ዘመን እንደ ሀገር በስድስት ክልሎች 110 ሺህ ሄክታር መሬት በጥጥ መልማቱን ተናግረዋል።በዚህም 79 ሺህ ሜትሮክ ቶን የተዳመጠ ጥጥ በማምረት ለኢንደስትሪዎች ማቅረብ እንደተቻለ ነው የገለፁት። 👉የሸማቹ ሸክም ይቀላል! የኢትዮጵያ ህብረት ሥራ ኮሚሽን “ወደ ቀበሌ መድረስ” በሚል መሪ ሃሳብ በተለያዩ ስድስት ከተሞች ሀገር አቀፍ የህብረት ሥራ ማህበራት ሪፎርም የንቅናቄ መድረክ ሲያካሄድ የህብረት ስራ ማህበራት ከእንግዲህ የሸማቹን ሸክም ሊያቀሉ ይገባል የሚል ሀሳብ ተነስቷል። በሀዋሳው በተካሔደው የማጠናቀቂያ መርሃ ግብር ላይ የግብርና ሚኒስትሩ አዲሱ አረጋ በቪዲዮ ኮንፈረንስ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ባለፉት ስምንት ዓመታት በተለያዩ መስኮች የበለጸገችና ህብረ ብሔራዊት ሀገር ለመፍጠር ዘርፈ ብዙ የሪፎርም ስራዎች ተግባራዊ መደረጋቸውን አንስተዋል። በተከናወኑ ተግባራትም ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ በርካታ ለውጦች እየተመዘገቡ መሆኑን አክለዋል። የመንግስትን፣ የግሉ ዘርፍንና የዜጎችን የካፒታል አቅምና ዕውቀትን ደምረው የያዙት የህብረት ስራ ማህበራት ግብርናውን በማሻገር የአርሶና አርብቶ አደሩን ህይወት በመቀየር ረገድ ትልቅ አቅም እንዳላቸው ገልፀው የፋይናንስ አቅርቦት ችግርን በመፍታትና የግብይት ሰንሰለቱን በማሳጠር የሸማቹን ህብረተሰብ ሸክም ያቀላሉ ተብሎ እንደሚታመንም አስረድተዋል። 👉ምርምር ለቀጣናዊ ትስስር በጅማ ዩኒቨርሲቲ "ቀጠናዊ ሰላምና ትብብር ለዘላቂ ልማት" በሚል መሪ ሀሳብ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የምርምር ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ ባለችበት ቀጣና የሚታዩ ፍላጎቶችን ለማሟላትና ተግዳሮቶችን ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ ለመፍታት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰሩ ጥናቶች ትኩረት ሊሰጡ እንደሚገባ ተነስቷል። በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ኮራ ጦሽኔ ቀጣናውን በልማት ለማስተሳሰር በሚደረግ ጥረት የትምህርት ተቋማቱ የጥናትና ምርምር ድጋፍ ከፍተኛ ሚና አለው ያሉ ሲሆን ለዚህም ተቋማቱ ኢኮኖሚያዊ ትስስርን የሚያሳድጉ እና ማህበራዊ ፈተናዎችን ለመፍታት የሚያግዙ የፖሊሲ መነሻ ሀሳቦችን በጥናትና ምርምር እንዲያፈልቁ አሳስበዋል። የሚወጡ ጥናቶች በቀጣናው በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ እየተከሰቱ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችሉ ሊሆኑ እንደሚገባ የተጠቀሰ ሲሆን ከዚህ አኳያ ኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራን በመተግበር እያከናወነች ያለችው ተግባር በተመክሮነት ቀርቦ አድናቆትን አስገኝቶላታል። 👉ሻይ ቅጠል አሁን አሁን አርሶ አደሩ በተለያዩ ኢንሼቲቮች በሚከናወኑ የግብርና ልማት ትግበራዎች ተጠቃሚነቱን እያረጋገጠ ይገኛል። በርካታ አርሶ አደሮች በሻይ ቅጠል ልማት ኢንሼቲቭ በመሰማራት ገቢን ከማሳደግ ባለፈ ለሌሎችም ሰፊ የስራ ዕድል እየፈጠሩ ይገኛሉ። በጅማ ዞን የሻይ ቅጠል ልማትን ከማስፋፋት ባለፈ የበያ ትስስር የመፍጠርና ጥራቱን የጠበቀ ምርት ለፋብሪካ ለማቅረብ ለአርሶ አደሩ ግንዛቤ እየተሰጠ መሆኑም ተገልጿል። የዞኑ ግብርና ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ቲጃኒ ተማም፤ በዞኑ የሻይ ቅጠል ልማትን በኢኒሼቲቨን መልክ በመተግበር የአርሶ አደሩን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ከማሳደግ ባለፈ ለበርካቶች የስራ ዕድል እየተፈጠረ ነው። ዘንድሮም ስራውን ለማስቀጠል በተመረጡ 6 ወረዳዎች በመጪው ክረምት የሚተከሉ 50 ሚሊዮን ችግኞች የተዘጋጁ ሲሆን ህዝብን በማሳተፍም ወደ 2 ሺህ ሄክታር የሚጠጋ መሬትን ለመሸፈንም ታስቧል። ጥቅሙ የገባቸው አርሶ አደሮችም የሰብል ልማቱን ለጊዜው ተወት በማድረግ በሻይ ቅጠል ልማት ላይ እየተሳተፉ እንደሆነ ይናገራሉ። በዞኑ የሰቃ ጨቆርሳ ወረዳ አርሶ አደር ሲራጅ ሼክ ከድር በሻይ ቅጠል ልማት ላይ መሳተፍ ከጀመሩ ወዲህ ገቢያቸው መጨመሩን ተናግረዋል። አርሶ አደር ሱልጣን አባሞጋ በበኩላቸው ተሰማርተውበት ከነበረው የሰብል ልማት ወደ ሻይ ቅጠል ልማት በመሰማራት ተጠቃሚ መሆናቸውን አስረድተዋል። የአካባቢ ፀጋን ተገንዝቦ ወደ ስራ መግባት ተጠቃሚነትን እንደሚያመጣ ማሳያ ሊሆን ይችላል። 👉ተስፋዎች ከሳምንቱ አንኳር ጉዳዮች መካከል በሆሳዕና ከተማ የተካሄደው የሞዴል ኢንተርፕራይዞች ደረጃ ሽግግር እውቅና መርሃ ግብር ይጠቀሳል። "የኢንተርፕራይዞች ሽግግር ለእመርታዊ እድገት" በሚል መሪ ሀሳብ የተከናወነው የዕውቅና መድረክ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በተገኙበት ነው የተካሄደው። እሳቸው እንደገለፁት፤ ኢንተርፕራይዞቹ ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካትና ለውጪ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶችን ከማምረት በተጨማሪ ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል እየፈጠሩ ነው። በክልሉ በገጠርና በከተማ በአነስተኛና መካከለኛ አምራች ዘርፍ ከ25 ሺህ በላይ ኢንተርፕራይዞች በተለያዩ መስኮች መሰማራታቸው የተገለፀ ሲሆን ባለፉት ዘጠኝ ወራት በክልሉ በጥቃቅንና በአነስተኛ ደረጃ የሚገኙ 4 ሺህ 948 ኢንተርፕራይዞችን የማሸጋገርና 495 ሞዴል ኢንተርፕራይዞችን የመለየት ስራ መሰራቱም እንዲሁ። ከኢንተርፕራይዝ ወደ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሸጋገሩ አምራቾች እንደተናገሩት ሽግግሩ ስራቸውን በተሻለ ሁኔታ ለመከወን እንደሚያግዛቸው ገልጸዋል። 👉ትምህርትና አርብቶ አደሩ የወፍ በረር ቅኝታችንን ስንቀጥል ጋምቤላ እንደርሳለን፤ በሳምንቱ በጋምቤላ ከተማ በተካሄደ መድረክም የአርብቶ አደሩን የትምህርት ተደራሽነትና ጥራት ለማረጋገጥ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር የተለያዩ ተግባራት ሲከናወኑ መቆየታቸውም ተመልክቷል። በለውጡ ዓመታት የአርብቶ አደሩን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተሰሩ ስራዎች ውጤት መመዝገባቸውም እንዲሁ። በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ ስራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) በመድረኩ ላይ እንዳሉት የአርብቶ አደሩን የትምህርት ተደራሽነትና ጥራት ለማረጋገጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ሲሰራ ቆይቷል። በዚህም ረገድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚና የገዘፈ መሆኑም በመድረኩ መገለፁን ቅኝታችን ዳሶታል። 👉ልወቅሽ ኢትዮጵያ ሁነቶቹን ጠቅለል አድርጎ የዳሰሰው ቅኝታችን ደግሞ በስድስት ከተሞች ለማካሄድ ዕቅድ የተያዘለትና እስካሁን በጅማ፣ በሀዋሳና በደብረ ብርሃን ከተሞች የተካሄደው የ"ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ ታላቁ ሩጫ" ከተሞቹን ከማስተዋወቅ የዘለለ ፋይዳውን በመርሃ ግብሩ ላይ በተላለፉ መልዕክቶቹ አሳይቷል። ለአብነት በጅማ የተካሄደው ‘ፖሊዮን በጋራ እናጥፋ’ የሚለውን የጤና ጉዳይን ያነሳ ነበር። በአዳማ ከተማ የተከናወነው ሁነት ደግሞ በመኪና ውድድር ታጅቦ የተከናወነና የቱሪዝም መስህቦችን ማስተዋወቅን ታላሚ ያደረገ ነበር። ‘’ለሀዋሳ ከፍታ እንሮጣለን’’ በሚል መሪ ሃሳብ የተዘጋጀው ሁነትም ከጅማና አዳማው ሁነት የተለየ እሳቤንም ሆነ መልዕክትን አልያዘም። ሁሉም ሁነቶች ከዋነኞቹ አምስት ምጣኔ ሃብታዊ አምዶች መካከል አንዱ የሆነውን ቱሪዝም ልማት በማጠናከር የማህበረሰቡን የዘርፉ ተጠቃሚነት ማላቅን ታሳቢ ማድረጋቸውን መመልከት ተችሏል። ቅኝቶቻችን በወፍ በረር ይህንን ይመስላሉ!! የሳምንት ሰው ይበለን!!!
የክልሎች ቅኝት በወፍ በረር
Apr 26, 2026 491
ክልሎች፤ሚያዝያ 18 /2018 (ኢዜአ)፡-የክልሎች ቅኝት በወፍ በረር በዚህ ዝግጅታችን በሳምንቱ በክልሎች የተከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮችን በወፍ በረር የምንቃኝበት ነው። በዚህ ሳምንትም አንኳር የክልሎች ክንውኑን የሚያሳዩ መረጃዎች ቀርበዋል። የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጫ ማህተም! ኢትዮጵያ የበጋ መስኖ ልማት ስራ መደባኛ ስራዋ ካደረገች ወዲህ አያሌ ለውጦች እየተመዘገቡ ይገኛሉ። ባለፉት ዓመታት የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት በእቅድ እና በቁርጠኝነት በመከናወኑ ከውጪ የሚገባ ስንዴ ቀርቷል፤ የምግብ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ ጥረቱም ቀጥሏል። ከተረጂነት ወደ አምራችነት የሚደረገው ሽግግርም ዓመቱን ሙሉ በማልማት እየታጀበ ሲሆን የአንበሳውን ድርሻ የሚይዘው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ሥራ ነው። በዚህ ውስጥ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አበረታች ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑ ተደጋግሞ ይነሳል። በተያዘው ሳምንት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሱሉልታ ወረዳ ወሬርሶ ማሊማ፣ በጂዳ ወረዳ ሲባ ሲርቲ እና ቂምቢቢት ወረዳ ሰገሌና ደርማሙሳ ቀበሌ በኩታ ገጠም የለማ እና በመልካም ሁኔታ ላይ የሚገኝ የስንዴ ቡቃያ አስቃኝተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፎቶ ጋር ያያዙት መልዕክትም ''ይህ የበጋ የመስኖ ስንዴ ልማት በምግብ ራስን የመቻል እና የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጫ ማህተማችን ነው'' ይላል። ብሪክስ -- ከተሳትፎ ባለፈ መፍትሄ አቅራቢ ከሳምንቱ አንኳር ጉዳዮች መካከል በባህር ዳር ከተማ ''የብሪክስ አሁናዊ አቅሞች እና የኢትዮጵያ የልማት ትብብር ትኩረቶች'' በሚል መሪ ሃሳብ የተዘጋጀው ጉባኤ አንዱ ነው። ኢትዮጵያ በብሪክስ ማዕቀፍ ከተሳትፎ ባለፈ መፍትሄ አቅራቢ በመሆን ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነች መሆኑ ይታወቃል። የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር መሐመድራፊዕ አባራያ በመድረኩ እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ ሳትፎዋን በማሳደግ በጥናት ላይ የተመሰረቱ የተደራጁ የመፍትሔ ሀሳቦችን በማቅረብ ለኢትዮጵያ ብሎም ለአፍሪካ የሚጠቅሙ ተግባራትን እያከናወነች ትገኛለች። መድረኩም ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ፣ በፈጠራና በቴክኖሎጂ እድገት ውስጥ የራሷን ድርሻ ለመወጣት የሚያስችላት የሁለትዮሽ ትብብር ጭምር የተካሄደበት፤ በብሪክስ ማዕቀፋ በተለይም በግብርና እና ስንዴ ልማት፣ በአረንጓዴ ልማት፣ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስና መሰል ዘርፎች ልምድ የተሰጠበትም መሆኑ ተመላክቷል። ማረም እና ማነጽ የማረሚያ ተቋማት የሰብዕና እና የክህሎት ግንባታ ማዕከል እንዲሆኑ ለጉዳዩ ትኩረት መሰጠቱ የተገለጸውም በዚሁ ሳምንት ነው። የፌዴራልና የክልል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ኮሚሽነሮች የጋራ ጉባኤ “የማረሚያ ተቋማት ለሀገር ልማት" በሚል መሪ ሀሳብ በሆሳዕና ከተማ ተካሄዷል። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) የማረሚያ ተቋማት የሰብዕና እና የክህሎት ግንባታ ማዕከል ሆነው እንዲያገለግሉ እየተሰራ ነው ብለዋል። ከታራሚዎች የሰብአዊ መብት አያያዝ፣ የመሰረታዊ ፍላጎት አቅርቦት፣ ከማረሚያ ቤት የሪፎርም ሥራዎች እንዲሁም ከማረም የማነጽ ተሃድሶ ልማት አገልግሎት ጋር በተያያዘ ጉባኤው በልዩ ሁኔታ የመከረበት ነው። ኢትዮጵያ ማምረቷን ቀጥላለች በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥና የራስን አቅም የመገንባት ታሪካዊ ጉዞ እንደቀጠለ ነው። የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል "ድሬ ታምርት ኢትዮጵያ ትበልፅግ" በሚል መሪ ሃሳብ በድሬዳዋ በተዘጋጀ የአምራች ኢንዱስትሪ ኤክሲፖ ላይ በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ዘርፍ በተደረገው ድጋፍና ክትትል እመርታዊ ውጤቶች መመዝገባቸውን ተናግረዋል። በንቅናቄው የተዘጉ አምራች ኢንዱስትሪዎች ወደ ሥራ እንዲመለሱ በማድረግ ከውጭ የሚገቡ ምርቶች በጥራትና በስፋት እየተተኩ ነው ብለዋል። ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን በማምረት፣ አዳዲስ ኢንቨስትመንቶችን በመሳብ እና የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድም መሠረታዊ ውጤቶች ተገኝተዋል ነው ያሉት። ዘንድሮ ብቻ 13 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ያስመዘገቡ የውጭ ሀገራት ባለሃብቶች ወደ ኢትዮጵያ ገብተው በዘርፉ ለመሰማራት መዘጋጀታቸውም ተገልጿል። ውኃ ይበላል፤ ውኃ ይጠጣል በኢትዮጵያ ቆላማ እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ውኃ የህልውና ጉዳይ ነው። በእርግጥ ለፍጡራን ሁሉ ውኃ ህይወት ቢሆንም በእነዚህ አካባቢዎች ግን ውኃ ይበላል፤ ውኃ ይጠጣል። በሳምነቱም በአፋር ክልል ከ800 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የአይሳኢታ አፋምቦ የብዙሃን መንደር እና የአይሳኢታ ከተማ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት በቅተዋል።የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ የተከናወነው ልማት የህብረተሰቡን ጥያቄዎች በተግባር ከመመለሱ በላይ፣ በየደረጃው ያለውን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል። የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር)፤ መንግስት የውሃ ሽፋን አነስተኛ ለሆነባቸው አካባቢዎች ልዩ ትኩረት በመስጠት፣ በፕሮጀክቶች ታግዞ መስራት እንደሚገባ በጽኑ ያምናል፤ በተለይም የለውጡ መንግስት ለቆላማ እና አርብቶ አደር አካባቢዎች በሰራው ስራ የውኃ ተደራሽነት በእጅጉ ማደጉን አንስተዋል። ልምድ ልውውጥ እና ተሞክሮ -ለምክር ቤቶች ሌላው ቅኝታችን በዚህ በተጠናቀቀው ሳምንት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክር ቤትና የዞን ምክር ቤቶች የጋራ ምክክር መድረክ በሚዛን አማን ከተማ መካሄዱን የዳሰሰ ነው። የጋራ የምክክር መድረኩ ዓለማ የልምድ ልውውጥና የልማት ሥራዎችን በመመልከት ተሞክሮ መለዋወጫ ነው።የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ወንድሙ ኩርታ፤ መንግስት ሕዝቡ የሰጠውን ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት የምክር ቤቶችን አደረጃጀት ማጠናከርና የክልሉ ሕገ መንግስት ያስቀመጣቸውን ኃላፊነቶች መፈጸም ይገባል ብለዋል።የመንግስት የልማት ኢኒሼቲቮች የዜጎችን ኑሮ ለማሻሻል የሚያስችሉ በመሆናቸው በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ትኩረት ተሰጥቷቸው መተግበር እንዲችሉ ምክር ቤቶች ያለሰለሰ ጥረት እያደረጉ መሆኑ ተመልክቷል። የጤና ልማት ስራ እስከ አክሞ ማዳን የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ለማሳደግ በሚደረግ ጥረት የአጋር ድርጅቶች አስተዋጾ ትልቅ ድርሻ እንዳለውም የተመለከተው በዚህ ሳምንት ነው። ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጋር በመሆን በአርባ ምንጭ ከተማ ያስገነባው የኩላሊት እጥበት ማዕከል ተመርቆ ለአገልግሎት በቅቷል። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ፤ መሰል የጤና ዘርፍ የልማት ስራዎች መንግስት በዘርፉ የያዘውን ውጥን ከማሳካት አንጻር እገዛቸው ትልቅ መሆኑን አንስተዋል።ማዕከሉ ማህበረሰቡ በቅርበት ሕክምና እንዲያገኝ ከማስቻል ባለፈ ወደ ሌላ አካባቢ ሄዶ ሲታከም ሊያወጣ የሚችለውን ወጪ ያስቀራል። ማዕከሉ የኩላሊት እጥበት ማሽኖች፣ የመድሃኒት ቤት፣ መኝታ አልጋዎችና የህክምና አገልግሎት መስጫ ክፍሎች አሟልቶ የተገነባ መሆኑም ታውቋል። የከተሞች ኮሪደር- ከቱሪዝም እስክ ኮንፍረንስ ማዕከልነት በኮሪደር ልማት እጅግ ከተዋቡ እና ከደመቁ የኢትዮጵያ ከተሞች መካከል ሀዋሳ አንዷ ናት። በሳምንቱ የከተማዋ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ዙር የኮሪደር ልማት ሥራ ማጠናቀቂያ የምስጋናና ዕውቅና እንዲሁም የአራተኛ ዙር የኮሪደር ልማትና የሐይቅ ዳርቻ ፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ተካሄዷል፡፡ የሲዳማ ክልል መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አብርሃም ማርሻሎ ሀዋሳ ከተማን የቱሪዝምና የኮንፈረንስ ማዕከል በማድረግ ከተማዋ አለም አቀፍ ተወዳዳሪ ከተማ እንድትሆን ርብርቡ ቀጥሏል ብለዋል። በቀጣይ ለሚከናወነው የኮሪደር እና የሐይቅ ዳርቻ ልማት ስራዎች እንደሚቀጥሉ አንስተው የኮሪደር ልማት ስራ ከተማዋ ያላትን የተፈጥሮ ፀጋና ማህበራዊ ትስስር ይበልጥ የሚያጎላ መሆኑን ገልፀዋል። የከተማዋን የቱሪዝምና የኮንፈረንስ ማዕከልነት ለማጠናከር ሥራዎች በላቀ ፍጥነትና ጥራት መከናወናቸውን እንደሚቀጥሉም አረጋግጠዋል። ምርጫ -የዴሞክራሲ መሰረት ሳምንቱ በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያስቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ ከመጠናቀቁ በፊት መራጮች የምርጫ ካርድ ወስደው ለምርጫው ዝግጁ መሆናቸውን የገለጹበትም ነበር። ኢትዮጵያዊያን መጪውን ጊዜ የተሻለ የሚያደርግላቸውን መንግስት ለመመረጥ ዝግጅታቸውን በተግባር እያረጋገጡ ነው።
ከአፍሪካ አቪዬሽን መሪነት እስከ አህጉራዊ የኢኮኖሚ ትስስር
Apr 23, 2026 489
በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የአቪዬሽን ታሪክ ታይቶ የማይታወቅና በአህጉሪቱ ትልቁ የሆነውን የ12 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ግዙፍ የኤርፖርት ግንባታ ፕሮጀክት በቢሾፍቱ ከተማ በይፋ መጀመሯን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታውቋል። ጋዜጠኛ ዳንኤል ኦሊቫሬስ ጋሌጎ በሲኤንኤን የጉዞ ገጽ ላይ ባሰፈረው ጽሁፍ እንደገለጸው፣ ይህ ሜጋ ፕሮጀክት አፍሪካውያን ተጓዦች ከአህጉሩ ውጭ ባሉ እንደ ዱባይ፣ ፓሪስና ለንደን ባሉ ማዕከላት በኩል የሚያደርጉትን አድካሚ ጉዞ በማስቀረት፣ አዲስ አበባን የአህጉሪቱ ቀዳሚ የመገናኛ ማዕከል ለማድረግ ያለመ ነው። ከአዲስ አበባ ከተማ በስተደቡብ ምስራቅ 48 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው ይህ ግዙፍ ግንባታ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ታሪክ ትልቁ የአቪዬሽን መሰረተ ልማት ተብሎ መጠቀሱን ጋዜጠኛው በዚሁ ጽሁፉ አመልክቷል። ስራው በይፋ የተጀመረው ባለፈው ጥር ወር ሲሆን፣ አውሮፕላን ማረፊያው በ2023 ዓ.ም (2030 እ.ኤ.አ) የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር፣ በዓመት 60 ሚሊዮን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም እንደሚኖረው በሲኤንኤን የጉዞ ገጽ ላይ ተመልክቷል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ፣ ፕሮጀክቱ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ በዓመት እስከ 110 ሚሊዮን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም ይኖረዋል። ይህም አውሮፕላን ማረፊያውን በዓለም ላይ በርካታ ተጓዦችን ከሚያስተናግደው የአትላንታው ሀርትስፊልድ-ጃክሰን አውሮፕላን ማረፊያ ካለው አቅም በላይ እንደሚያደርገው ዳንኤል ኦሊቫሬስ ጋሌጎ ባሰፈረው ጽሁፍ አብራርቷል። አውሮፕላን ማረፊያው ከመንገደኞች አገልግሎት ባለፈ፣ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠናን (AfCFTA) በላቀ ሁኔታ ለመደገፍ ታቅዶ የተገነባ መሆኑን ጋዜጠኛው በሲኤንኤን የጉዞ ገጽ ላይ ባሰፈረው ጽሁፍ በዝርዝር አስቀምጧል። በዓመት 3 ነጥብ 73 ሚሊዮን ቶን ጭነት የማስተናገድ አቅም ያለው ይህ መሠረተ ልማት፣ በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ የመጣውን የአፍሪካን የጭነት በረራ ፍላጎት በሚገባ ምላሽ መስጠት የሚችል መሆኑን ተጠቁሟል። የአውሮፕላን ማረፊያው የተርሚናል ዲዛይን በዓለም አቀፍ ደረጃ ዝነኛ በሆነው ዛሃ ሃዲድ አርክቴክትስ የቀረበ መሆኑን የጠቀሰው ጋዜጠኛው፣ዲዛይኑ የኢትዮጵያን ታላቁ ስምጥ ሸለቆና የተለያየ መልክዓ ምድራዊ ውበትን የሚያንፀባርቅ መሆኑን በጽሁፉ አካቷል። ተጓዦች በአውሮፕላን ማረፊያው ውስጥ ሲዘዋወሩ የኢትዮጵያን ባህልና ተፈጥሮ እንዲመለከቱ በሚያስችል መልኩ የተዘጋጀ ሲሆን፣ለዘላቂነት ቅድሚያ በመስጠት የፀሐይ ብርሃን ኃይልንና የዝናብ ውሃ አሰባሰብ ስርዓትን እንዲጠቀም ተደርጎ ተቀርጿል። በአጠቃላይ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ መጠናቀቅ፣ኢትዮጵያ በአፍሪካ አቪዬሽን ያላትን መሪነት ከማረጋገጡ ባለፈ የአህጉሪቱን የኢኮኖሚ ትስስር ወደ አዲስ ምዕራፍ እንደሚያሸጋግረው ጋዜጠኛው በሲኤንኤን የጉዞ ገጽ ላይ ባሰፈረው ጽሁፍ ደምድሟል። ይህ ፕሮጀክት ከሌሎች የአፍሪካ አየር መንገዶች ጋር በመተባበር የነጠላ የአፍሪካ አየር ትራንስፖርት ገበያን (SAATM) ወደ ተግባር ለመቀየር የሚደረገውን ጥረት በእጅጉ እንደሚያግዝም ተመልክቷል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
ትንታኔዎች
ባሳለፍነው ሳምንት …
May 2, 2026 363
ከሚያዝያ 18 እስከ ሚያዝያ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች መካከል … • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በሁዋጂያን ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በአዲስ አበባ በሁዋጂያን ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ውስጥ የሚገኘውን "ጎበዝ ሶላር ሴል" ማምረቻን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት የጎበኙ ሲሆን፤ በዚሁ ወቅትም ይህ ፋብሪካ በ2025 ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንቨስት ያድርጉ ፎረም (Invest in Ethiopia Forum) አማካኝነት በተፈረመው ስምምነት መነሻ በ100 ሚሊየን ዶላር የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ የተቋቋመ ነው ብለዋል። በውጤታማ ድጋፍ እና ክትትል በስድስት ወራት ብቻ እውን የሆነው "ጎበዝ ሶላር ሴል" ማምረቻ ዘመናዊ ማሽኖች እና በቴክኖሎጂ የተዋቀረ መሆኑን ገልጸው፣ ማምረቻው ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድልም ፈጥሯል ነው ያሉት። በመጀመሪያ ምዕራፍ 2 ጌጋዋት ዓመታዊ የማምረት ዐቅም ያለው ፋብሪካው የኢትዮጵያን የኃይል ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ከታዳሽ ኃይል ለማድረግ ለተጀመረው ሀገራዊ ርዕይ እውን ለማድረግ ተደማሪ ዐቅም ፈጥሯል ሲሉም ተናግረዋል። በተጨማሪም በኢንዱስትሪ ፓርኩ ውስጥ የሚገኘውን የጫማ ማምረቻ እና ንዑስ የኤሌክትሪክ ጣቢያን ተመልክቻለው ብለዋል በመልዕክታቸው። • ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአራዳ ፓርክን መመረቃቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት አራዳ ፓርክን በመረቁበት ወቅት፤ ፓርኩ አዲስ አበባን ለመለወጥ ያለንን ርዕይ በተግባር ያሳየንበት አንዱ ሥራችን ነው ብለዋል። ቀደም ሲል ተዘንግቶና ለአደጋ ተጋልጦ የነበረው የአራዳ አካባቢ፤ ዛሬ ተመልሶ ተገንብቶ አስደናቂ የከተማ አካል መሆን ችሏል ሲሉም ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለእኛ በምናብ የምትሳል ህልም ብቻ ሳትሆን በተግባር የምትገነባ እውነታ ናት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ጤናማ፣ ጽኑ፣ ለመጭው ትውልድ ተስፋን ከተጨባጭ ሀብት ጋር የምትሰጥ፣ በአፍሪካ መሪ፣ በዓለም መድረክ ደግሞ ተወዳዳሪ የሆነች ሀገር እየገነባን እንገኛለን ብለዋል። በየቀኑም ተስፋን ወደ እውነታ የመለወጥ ተግባራችንን እንቀጥላለን ሲሉ ተናግረዋል። • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማኅበራዊ ልማት እመርታ ለሀገር ግንባታ መድረክ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተገኝተው ሐሳባቸውን ያጋሩበት “የማኅበራዊ ልማት እመርታ ለሀገር ግንባታ” በሚል መሪ ሐሳብ የተዘጋጀውና በማኅበራዊ ዘርፍ ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ ዐበይት ውጤቶች የቀረቡበት የምክክር መድረክ ባሳለፍነው ሳምንት ተካሂዷል። በዚሁ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የማኅበራዊ ዘርፍ ግንባታ እንደ ሌሎች መሠረተ-ልማቶች ውጤቱ ወዲያው የሚታይና የሚጨበጥ ባይሆንም፤ ለሀገር ዘላቂና ወሳኝ መሠረት የሚጥል ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ በሚገጥሟት ተግዳሮቶች ሳትገደብ ከሚገመተው በላይ በከፍተኛ ፍጥነት እየተገነባች መሆኗን ገልጸው፤ ምንም እንኳ የዐቅም ውስንነቶች ቢኖሩብንም ለማሻሻል ያልተሞከረ የማኅበራዊ ዘርፍ የለም ሲሉም አስረድተዋል። በየዘርፎች የታለመው ሁሉ በተግባር እንዲተረጎምና ተገቢውን ዓላማቸውን እንዲያሳኩ ብዙ ሥራ ይጠበቅብናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ለዚህም አንድ እጅ ብቻውን ማጨብጨብ እንደማይችል ሁሉ፤ መንግሥት የሚጀምራቸውን ሥራዎች ሌላው የማኅበረሰብ ክፍል እንደ አንድ ባለ ድርሻ ኃላፊነት ወስዶ በጋራ መቆም እንዳለበት አስገንዝበዋል። • የሞዛምቢክ ፕሬዚዳንት በኢትዮጵያ ባሳለፍነው ሳምንት የሞዛምቢክ ፕሬዚዳንት ዳንኤል ፍራንሲስኮ ቻፖ ለጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በክብር ተቀብለዋቸዋል። የፕሬዚዳንቱ ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት የጋራ ልማትና የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር ትርጉም ባለው መልኩ ሊለውጡ የሚችሉ ተጨባጭ ሥራዎችን ቅድሚያ የሰጠ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለእውነተኛ አፍሪካዊ አጋርነት ያላትን የማይናወጥ ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ መሆኑንም አስረድተዋል። ከዚያም ባደረጉት ቆይታ ዘላቂ እና ተጨባጭ ለውጥ ለሚያመጣ አጋርነት መሠረት የጣለ ፍሬያማ የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በስትራቴጂካዊ ዘርፎች ያለንን ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግሩና የአሠራር ማዕቀፍ የሚሆኑ ልዩ ልዩ የመግባቢያ ሠነዶችን ልውውጥ አካሂደናል ብለዋል። • የበጋ መስኖ እርሻ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት ባስተላለፉት መልዕክት፤ የበጋ መስኖ እርሻ በምግብ ራሳችንን ለመቻል በሚደረገው ጉዞ ውስጥ የጸና መሠረት የጣልንበት ምዕራፍ ነው ብለዋል። የውኃ ሀብታችንን በአግባቡ በመጠቀም፣ ባልተቋረጠ ጥረት እና ቁርጠኝነት፣ የመልማት ጉዟችን አስተማማኝና ዘላቂ የሆነ የምግብ ዋስትና ወደምናረጋግጥበት ብሩህ ተስፋ እንደሚያሸጋግረን ጥርጥር የለውም ሲሉም አስገንዝበዋል። • ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ባሳለፍነው ሳምንት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሆሞሻ ወረዳ የሚገኘውን ፍቃዱ ነመራ የተቀናጀ የእርሻ ልማት ጎብኝተዋል። ጉብኝታቸውን ተከትሎም፤ ፍቃዱ ነመራ የተቀናጀ የእርሻ ልማት በኢትዮጵያ የግሉን ዘርፍ ያሳተፈ የግብርና ሥራ እንዲስፋፋ ለሚደረገው ሥራ አንድ ማሳያ ነው ብለዋል። ይህ በግል ባለሀብት እየለማ ያለው የግብርና ሥራ እንደ ሶላር ያሉ የኃይል አማራጮችን እና የከርሰ ምድር ውኃን በመጠቀም በመስኖ በማልማት ኢትዮጵያ ለጀመረችው የግብርና ልማት እና የገጠር ሽግግር ሰፊ አስተዋጽኦ ያበረክታል ሲሉም ገልጸዋል። በተመሳሳይ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግራናይት የሚያመርተውን የኦርላመንት (3ኤም) ማርብልና ቴራዞ ማኑፋክቸሪንግ የሥራ እንቅስቃሴ የጎበኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ መንግሥት የግሉ ዘርፍ በማዕድን ልማት ላይ በስፋት እንዲሳተፍ የፈጠረው ምቹ ሁኔታ፣ ማበረታቻና ድጋፍ እንዲህ ያሉ ተጨባጭ ውጤቶችን እያመጣ ነው ብለዋል። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከወርቅ እስከ ግራናይት በተፈጥሮ የታደለ መሆኑን ገልጸው፤ ይህን ፀጋ ለሀገር ብልጽግና ለማዋል የተጀመሩ የልማት ሥራዎች ይበልጥ እንዲጠናከሩ የፌደራል መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረጉን ይቀጥላል ሲሉ አረጋግጠዋል።
ባሳለፍነው ሳምንት …
Apr 25, 2026 538
ከሚያዝያ 11 እስከ ሚያዝያ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች መካከል … • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከተለያዩ ሀገራት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች ጋር መምከራቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት ጋር ተወያይተዋል። በዚሁ ወቅትም፤ ቀጣናችንን መልክ በሚያሲዙ እና የጋራ መፃኢ የልማት ጉዳዮች ላይ የሁለትዮሽ ውይይት አድርገናል ብለዋል። በሁለቱ ሀገሮች በላቀ እድገትና ተጠቃሚነት ዙሪያ መረጃ የተለዋወጥን ሲሆን፤ የኢኮኖሚ ትስስርን በጠንካራ ትብብር እና በኢንቨስትመንት በመደገፍ እድሎችን የምናሰፋባቸውን የቀጣይ ስራዎች የተመለከተ ፍሬያማ ምክክር አድርገናል ሲሉም ገልፀዋል። ባሳለፍነው ሳምንት ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች አንዱ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአውሮፓ ኅብረት የዓለም አቀፍ ትብብር ኮሚሽነር ጆሴፍ ሲከላ ጋር መምከራቸው ነው። በዚሁ ወቅትም፤ ከአውሮፓ ኅብረት ጋር ስላለን የረጅም ጊዜ ትብብር መክረናል ብለዋል። በተመሳሳይም ከፕሬዚዳንት ኡመር ጌሌህ የተላከ መልዕክት ይዘው ከመጡት የጂቡቲ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር አብዱልቃድር ሁሴን ኦማር ጋር ተወያይተዋል። በዚሁ ወቅትም በሀገሮቻችን መካከል ስላለው ትብብር ተወያይተናል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። እንዲሁም የአፍሪካ በሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል (Africa CDC) ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዣን ካሴያ ጋር ውጤታማ ውይይት አድርገዋል። በዚሁ ወቅትም፤ በአፍሪካ ሕብረት የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ መሪ (Champion) በመሆን የተሰጠኝን አዲስ ኃላፊነት በሚመለከት በስፋት ተነጋግረናል ብለዋል። በጤናው ዘርፍ የሚገጥመንን ተለዋዋጭ ተግዳሮቶች ለመወጣት የሰው ሠራሽ አስተውሎትንና የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን ዐቅም መጠቀም የጤና ሥርዓታችንን ለማጠናከር፣ ተደራሽነትን ለማስፋፋት እና ለሕዝባችን የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ወሳኝ ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ ያላትን ልምድ ለአህጉሩ ለማካፈል እንዲሁም በፍጥነት ከሚለዋወጠው የቴክኖሎጂው ዓለም ጋር ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመራመድ የሚያስችሉ ጠንካራ አጋርነቶችን ለመመሥረት ያላትን ቁርጠኝነት ዳግም ታረጋግጣለች ሲሉም አስታውቀዋል። • በኢትዮጵያ የበቆሎ መስኖ ውጤታማነት ባሳለፍነው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ትኩረት ሰጥተን እየሠራንባቸው ከሚገኙት ምርቶች አንዱ የሆነው የበቆሎ መስኖ ሥራ፤ ከፍ ባለ ስኬት ላይ ይገኛል ማለታቸው ይታወሳል። የተገኘው ጅምር ውጤትም፤ ኢትዮጵያ የምግብ ዕርዳታ ከመቀበል ወጥታ ራሷን መመገብ የምትችል ሀገር የማድረግ ታላቁ ህልማችን ዕውን የሚሆንበት መንገድ ላይ ስለመሆኑ አመላካች ነው ብለዋል። • መሶብ የሞባይል አገልግሎት መመረቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት፤ ካቀድናቸው አምስት የልማት ምሰሶዎች መካከል ቴክኖሎጂን ለአገልግሎት ዘርፉ እንደ ዋነኛ መሣሪያ በመጠቀም፣ የአገልግሎት ቅልጥፍናንና ተደራሽነትን ለማሻሻል በቁርጠኝነት እየሠራን ነው ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። በመሶብ አገልግሎት የታየው ከፍተኛ የደንበኞች እርካታ የስራውን ውጤታማነት ያረጋገጠ መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአሰራሩን ይበልጥ መስፋፋት አስፈላጊነትም ገልጸዋል።ዜጎች ጊዜያቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙ የተቀናጁ አገልግሎቶችን ተደራሽ የማድረጉ ስራ ተጠናክሮ አንደሚቀጥልም ጠቁመዋል። በተመሳሳይ በዚሁ ጉዳይ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ባጋራው መረጃ ዛሬ ሥራ የጀመረው የመሶብ ተንቀሳቃሽ አውቶቡስ አገልግሎት፤ አስፈላጊ የሆኑ የመንግሥት አገልግሎቶችን በቀጥታ ወደ ማኅበረሰቡ ለማድረስ የተወሰደ ትልቅ እርምጃ ነው ብሏል። ለአገልግሎት የተደራጀው አውቶቡስ ሙሉ ቁሳቁስ የተሟላለትና ራሱን የቻለ የአገልግሎት ማዕከል ሆኖ የተዘጋጀ ሲሆን፤ ቀልጣፋና አስተማማኝ አሠራርን ለማረጋገጥ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችንና ሥርዓቶችን አቀናጅቶ የያዘ መሆኑን ገልጿል። አውቶቡሱ የአገልግሎት ፍሰቱን የሚያደራጅ የሰልፍ ማስተናገጃ ሥርዓት እንዳለውና የተለያዩ የክፍያ አማራጮች ማካተቱንም አመላክቷል። ለአገልግሎቱ የሚያስፈልገውን ኃይል በከፊል ከ8 ኪሎ ዋት የፀሐይ ብርሃን የሚያገኝ ሲሆን፤ አስተማማኝ ኢንተርኔትም ተገጥሞለታል። በተጨማሪም የአገልግሎት አሰጣጡን ደኅንነትና ግልፅነትን ለመከታተል ካሜራዎች ተገጥመውለታል፤ መፍትሔ አምጪ ሆኖ የተዘጋጀው የፈጠራ ውጤትና ተንቀሳቃሽ ክፍል፤ ከስምንት የተለያዩ የመንግሥት ተቋማት የሚገኙ የሚከተሉትን ወሳኝ አገልግሎቶች ይሰጣል፦ አዲስ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) መስጠት፣ የንግድ ፈቃድ ማውጣትና ማደስ፣ ለመንጃ ፈቃድ የሚያስፈልግ የሕክምና ምርመራ ማድረግ፣ የነዋሪነት መታወቂያ ማደስና የልደት ምዝገባ፣ የመንጃ ፈቃድ መስጠትና የተሽከርካሪ ታርጋ ማደስ፣ የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት የመንገድ ፈንድ ክፍያን ማከናወን፣ የብሔራዊ መታወቂያ ምዝገባና የመረጃ እርማት፣ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በኩል የሚሰጥ የቅድመ ክፍያ የኤሌክትሪክ አገልግሎቶችን ይሰጣል። በአጠቃላይ ይህ ተንቀሳቃሽ አውቶቡስ የስምንት ተቋማትን አገልግሎት በአንድ ላይ በማቀናጀት፣ ዜጎች ረጅም ርቀት ሳይጓዙ ወይም የተለያዩ ቢሮዎችን ማንኳኳት ሳያስፈልጋቸው ምቹ፣ ቀልጣፋና ተደራሽ የሆነ መፍትሔ ይሰጣል። • የ100 ቀናትና የ9 ወራት የመንግሥት ሥራ አፈጻጸም ግምገማ ባሳለፍነው ሳምንት የሥራ ዘመኑ 3ኛ የ100 ቀናት የመንግሥት ሥራ አፈፃፀም ከዘጠኝ ወራት አጠቃላይ አፈፃፀም ጎን ለጎን መገምገሙን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል። በዚሁ ወቅትም፤ የቀየስነው አዲሱ የኢኮኖሚ አካሄድ በአጭር ጊዜ ትግበራ ጠንካራ ባለሁለት አሃዝ የዕድገት ሂደትን አስመዝግቧል ብለዋል። ጥረቶቻችን የበለጠ ጽኑ፣ ተወዳዳሪ እና አካታች ኢኮኖሚ ለመገንባት ያለንን አቋም እና የመተግበር ዐቅም ያሳያሉ ሲሉም አስገንዝበዋል። • ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ስለ 3ኛው 100 ቀን አፈጻጸም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በተገኙበት፤ የ2018 በጀት ዓመት የ3ኛው የ100 ቀን አፈጻጸም ሪፖርት ከፌደራል ተቋማት አመራሮች ጋር ተገምግሟል። በዚሁ ወቅትም አቶ ተመስገን፤ ኢትዮጵያ ትልቅ ሀገር ናት፤ የሚገባትም ትልቅ ሥፍራ ነው፤ እኛ ደግሞ የዚህ ታሪክ ሠሪዎች የመሆን ዕድል በእጃችን ላይ ነው ሲሉ አዝገንዝበዋል። በኮሪደር ልማት፣ በገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶችና በዲጂታል ኢትዮጵያ ዘርፍ የተካሄደው የመሠረተ-ልማት አብዮት የሀገራችንን እንዲሁም የከተሞቻችንን ገጽታና አገልግሎት ቀይሯል ብለዋል። በስንዴ ልማትና በሌማት ትሩፋት አማካኝነት የተረጅነትን ቀንበር ሰብረን ወደ ምግብ ሉዓላዊነት እየተጓዝን ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በዲፕሎማሲው መስክም ኢትዮጵያ ከእርዳታ ጠባቂነት ወደ ንግድና ኢንቨስትመንት አጋርነት በመሸጋገር፣ በዓለም አቀፍ መድረክ ተደማጭነቷን ወደ ላቀ ምዕራፍ አሳድጋለች ብለዋል። • የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔዎች ባሳለፍነው ሳምንት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባካሄደው 54ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል። በዚህም መሠረት ምክር ቤቱ፤ በሁለት የፋይናንስ ድጋፍና ብድር ስምምነቶች፣ በሀገራችን የዩሪያ ማዳበሪያ ማምረቻና ማቀነባበሪያ ፋብሪካን የሚመለከት የኢንቨስትመንት ማበረታቻና ጥበቃ ስምምነት፣ የቁልፍ መሠረተ-ልማቶች የሳይበር ደኅንነት ረቂቅ አዋጅ፣ በሥድስት ዓለም አቀፍ የሁለትዮሽ ስምምነቶች እንዲሁም የኢትዮጵያ እሳት እና ሌሎች ቅጽበታዊ አደጋዎች አገልግሎት ማቋቋሚያ ደንብ ላይ መክሮ በማጽደቅ ውሳኔዎችን አሳልፏል። • ዓለምን በሚበይነው የዲጂታል ዘርፍ ሪፎርም የተገኙ ቁልፍ ውጤቶች የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ዓለምን በሚበይነው የዲጂታል ዘርፍ ሪፎርም የተገኙ ቁልፍ ውጤቶች ብሎ ባጋራው መረጃ፤ በመሠረተ-ልማት (የ5G እና የ4G ሽፋን መስፋፋት)፣ በዲጂታል መሳሪያዎች (ስማርት ስልኮችን በሀገር ውስጥ መገጣጠም)፣ በዲጂታል መንግሥት (በመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት 2 ሺህ 260 አገልግሎቶች በአንድ ቋት መደራጀት፣ ዲጂታል ክፍያዎች፣ የፍትሕ ተደራሽ ስማርት ችሎት እና ዲጂታል ፖሊስ) የሚሉትን አንስቷል። በተጨማሪም በዲጂታል ክኅሎት (5 ሚሊየን ኮደሮች ስልጠና፣ ትምህርት ቤቶችን በኢንተርኔት (SchoolNet)፣ በሦስተኛ ዲግሪ (PhD) ደረጃ የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ምርምር እና ስታርት አፖችን በዕውቀትና በፈጠራ ማብቃት፣ በተቋማት ግንባታ (ዲጂታል ስታቲስቲክስ እና ልማት አስተዳደር፣ AI ኢንስቲትዩት፣ AI ዩኒቨርሲቲ እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አሥተዳደር)፣ በሕግ ማዕቀፍ ተዓማኒነት (በፋይዳ መታወቂያ ከ40 ነጥብ 9 ሚሊየን በላይ ዜጋ ተካቷል፣ የግል መረጃ ጥበቃ አዋጅ፣ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ እና የኤሌክትሮኒክ ፊርማ ተግባራዊነት) የሚሉት ጉዳዮችን ጠቅሷል። • የልማት ዕቅድ ማስፈፀሚያ ኢንሼቲቮችን በመለየት መተግበር የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ባሳለፍነው ሳምንት ባጋራው መረጃ፤ በአረንጓዴ ዐሻራ የሀገሪቱ የደን ሽፋን 23 ነጥብ 6 በመቶ መድረሱን አስታውቋል። ሀገራዊ የስንዴ ልማትን በተመለከተም ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን እና ሉዓላዊነትን እያረጋገጠች ትገኛለች ያለው ጽሕፈት ቤቱ፤ አዳዲስ የግብርና ዕውቀቶች እየተስፋፉ፣ የሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎች ግብዓቶችን እያገኙ፣ ውድ የሆኑ የውጭ ምርቶች በሀገር ውስጥ እየተተኩ፣ የሥራ ዕድሎች እየሰፉና የአርሶ አደሮች ገቢ እየጨመረ ይገኛል ብሏል። ከሌማት ትሩፋት አንጻርም፤ የግብርና ግብዓቶች አቅርቦት እና ምርታማነት እየጨመረ ነው፤ የተመጣጠነ ምግብ በቀላሉና በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲገኝ ከማድረግ ባለፈ፣ አነስተኛ የንግድ እንቅስቃሴዎች እንዲሳለጡና አካባቢው ይበልጥ እንዲጠበቅ እያደረገ ይገኛል ሲል ገልጿል። ዲጂታል ኢትዮጵያን አስመልክቶም፤ የሕግ፣ የፋይናንስ እና የማንነት መታወቂያ (ID) ሥርዓቶች ወደ ዲጂታል እየተቀየሩ ነው። የኢንተርኔት ተደራሽነትና የኦንላይን አገልግሎቶች እየተስፋፉ፣ የሞባይል ክፍያ ሥርዓት እየተጠናከረ እንዲሁም የኢ-ኮሜርስ ንግድ የዜጎችን ጊዜና ገንዘብ እያተረፈ ነው ብሏል። የከተማና የገጠር ኮሪደር ልማትም፤ የከተሞች መሠረተ-ልማት በአረንጓዴ ትራንስፖርት እየዘመነ ነው ያለው ጽሕፈት ቤቱ፤ ይህም የዜጎችን የኑሮ ጥራት እያሻሻለ፣ የአካባቢ ንግድን እያነቃቃ እንዲሁም በከተማና በገጠር መካከል ያለውን ትስስር እያጠናከረ እንደሚገኝ አስታውቋል። ከኢትዮጵያ ታምርት አኳያም፤ የማምረት ዐቅምና የምርቶች እሴት የመጨመር ሂደት እየተሻሻለ ነው ብሏል። ከውጭ የሚገቡ ምርቶች በሀገር ውስጥ እየተተኩ፣ የውጭ ምንዛሪ ግኝት እያደገ፣ የግብዓት አቅርቦት እየተጠናከረና አዳዲስ የሥራ ዕድሎች እየተፈጠሩ ስለመሆኑም አመላክቷል። እያንዳንዱ ምሰሶ ፈተናዎችን ወደ መልካም አጋጣሚ በመቀየር፣ ጠንካራ እና ራሷን የቻለች ኢትዮጵያን ለመገንባት ጉልህ ሚና እየተጫወተ ነው ሲልም በአጽንዖት ገልጿል።
ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እና በዲጂታል ጤና ከሀገር በቀል ስኬት ወደ አህጉራዊ መሪነት
Apr 23, 2026 483
(በሙሴ መለሰ) ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ዘርፍ እያከናወነች ያለችው ስራ ውጤታማ እንዲሆን ስትራቴጂካዊ የሆኑ ተቋማዊና የፖሊሲ መሰረቶች ተጥለዋል። የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት መቋቋም ለሀገራዊ ችግሮች በቴክኖሎጂ የታገዘ መፍትሄ ለማግኘት ትልቅ አቅም የፈጠረ ሲሆን፣ ብሄራዊ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ፖሊሲ ተቀርጾ መጽደቁ ደግሞ የዘርፉን ልማትና አጠቃቀም በተደራጀ መንገድ ለመምራት አስችሏል። እነዚህ እርምጃዎች ሀገሪቱ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 እና 2030 ስትራቴጂ ውስጥ ቴክኖሎጂውን እንደ ቁልፍ የለውጥ አቅጣጫ እንድትጠቀም በማድረግ ላይ ይገኛሉ። የቴክኖሎጂ ሽግግሩን ዘላቂ ለማድረግም በሰው ኃይል ልማት ላይ ትኩረት ተሰጥቷል። በአሁኑ ወቅት አምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ወጣቶችን በኮዲንግ፣ በዳታ ሳይንስ እና በክህሎት ለማሰልጠን የተጀመረው ግዙፍ ፕሮግራም የለውጡ አንቀሳቃሽ ኃይል እየሆነ ነው። ከዚህም ባለፈ፣ በአፍሪካ የመጀመሪያው የሆነው የኤአይ ዩኒቨርሲቲ እንዲገነባ መታቀዱና በዚህ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ አባልነት ውስጥ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ስርዓት እንዲሳተፍ መወሰኑ፣ ሀገሪቱ ቴክኖሎጂውን ለውሳኔ ጥራትና ለምርምር በከፍተኛ ደረጃ እየተጠቀመችበት መሆኑን ያሳያል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ሕብረት የሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence) እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ መሪ (Champion) ሆነው መሾማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል። ጽህፈት ቤቱ እንደገለጸው፣ ሹመቱ የተሰጠው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዘርፉ ላሳዩት አመራር እና ኢትዮጵያ በአህጉሩ የሰው ሰራሽ አስተውሎትንና የፈጠራ ሥራዎችን ለማስፋፋት እየተገበረች ላለው የላቀ ሚና እውቅና ለመስጠት ነው። በሹመት ደብዳቤው ላይም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን ለማስፋፋት ያደረጉት አመራር፣ AI ለአፍሪካ ሉዓላዊነት፣ ለውጤታማነት እና ለአሳታፊ እድገት ቁልፍ መሣሪያ ሆኖ እንዲያገለግል በማስቻል ረገድ ትልቅ እገዛ ማድረጉ ተመልክቷል። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አክሎ እንደገለጸው፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልታዊ በሆነ መልኩ የቴክኖሎጂ ነጻነትን እና ዐቅምን ለመገንባት የሚያደርጉት ተከታታይ ቅስቀሳ፣ አህጉሩ በኃላፊነት እና በፍትሐዊነት በታጀበ የAI አጠቃቀም ረገድ በዓለም አቀፍ ደረጃ ግንባር ቀደም እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል። ባለፉት ጥቂት ዓመታት የዲጂታል መሰረተ ልማትን ማስፋፋት፣ የኤሌክትሮኒክስ የመንግሥት አገልግሎቶችን ሥራ ላይ ማዋል እና በፈጠራ ሥነ-ምህዳር ላይ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ ለሀገራዊ ለውጡ ጠንካራ መሰረት የጣሉ ተግባራት መሆናቸውን ጽህፈት ቤቱ በዝርዝር አስፍሯል። በተጨማሪም ራሱን የቻለ የAI ዩኒቨርሲቲ ለማቋቋም የተያዘው ሥራ ምርምርን፣ የክህሎት ልማትን እና አህጉራዊ ትብብርን ይበልጥ እንደሚያጠናክርም ተገልጿል። ይህ አህጉራዊ እውቅና በተለይ በጤናው ዘርፍ የታዩ ውጤቶችን ያካትታል። ኢትዮጵያ በኤአይ የታገዘ ዲጂታል ኤክስሬይን ለሳንባ ነቀርሳ ምርመራ ካዋሉ የአፍሪካ ሀገራት መካከል በቀዳሚነት ትጠቀሳለች። በተጨማሪም የ"HEP Assist" መተግበሪያን በሙከራ ደረጃ በማስጀመር፣ በገጠር የሚገኙ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ውስብስብ ምልክቶችን ሲያዩ ሙያዊ የሕክምና ውሳኔ እንዲሰጡ ድጋፍ እየተደረገ ነው። እነዚህ የዲጂታል ጤና ስራዎች በ7 ክልሎችና በ15 ወረዳዎች ተግባራዊ መደረግ መጀመራቸው፣ ቴክኖሎጂው በገጠርና በከተማ መካከል ያለውን የአገልግሎት ልዩነት ለማጥበብ ያለውን ፋይዳ ያሳያል። በአጠቃላይ፣ የኤአይ ቴክኖሎጂ በጤናው ዘርፍ ከሚሰጠው የጡት ካንሰር፣ የአንጎል እብጠትና የቆዳ በሽታዎች ምርመራ ባለፈ፣ በግብርና፣ በፋይናንስና በመንግስታዊ አገልግሎቶች ውስጥም በስፋት እየገባ ይገኛል። በ2030 በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ ሆስፒታሎችን ሙሉ በሙሉ ወደ ዲጂታል አገልግሎት ለመቀየር የተቀመጠው ግብ፣ ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትሩ አነሳሽነት የጀመረችውን የቴክኖሎጂ ነጻነትና የመሪነት ጉዞ ይበልጥ የሚያጠናክር ነው። በኢትዮጵያ እየተገነባ ያለው የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ሥርዓት በጤና፣ በግብርና እና በመንግስታዊ አገልግሎቶች ውስጥ ለውጥ እያመጣ ይገኛል። በጤናው ዘርፍ እንደ ካንሰር እና ሳንባ ነቀርሳ ያሉ በሽታዎችን ቀድሞ በመለየት የህክምና ጥራትን ሲያሻሽል፣ በግብርናው ደግሞ የሰብል ተባዮችንና የቡና በሽታዎችን በመለየት ምርታማነትን እያሳደገ ነው። ከዚህ ባለፈም ቴክኖሎጂው በመንግስት የአገልግሎት አሰጣጥ እና በፋይናንስ ዘርፍ ውስጥ ሰፊ የመረጃ ትንታኔዎችን በፍጥነት በማከናወን፣ የሥራ ፍጥነትን እና የውሳኔ አሰጣጥ ጥራትን ወደ ላቀ ደረጃ እያሸጋገረ ይገኛል። የዘርፉ ፋይዳ ከቴክኖሎጂ አጠቃቀም ባለፈ የሀገሪቱን የዲጂታል ሉዓላዊነት እና የሰው ኃይል አቅም በመገንባት ላይ ያተኩራል። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወጣቶችን በኮዲንግ እና በዳታ ሳይንስ በማሰልጠን እንዲሁም የፈጠራ ማዕከላትን (Startups) በመገንባት፣ ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂው ዘርፍ በሌሎች ላይ ጥገኛ ከመሆን ወጥታ የራሷን የዲጂታል ኢኮኖሚ መሠረት እየጣለች ትገኛለች። ይህም በአህጉር ደረጃ ለሚደረጉ የቴክኖሎጂ ሽግግሮች እንደ አርአያ በመሆን፣ ቴክኖሎጂውን ለኢኮኖሚ እድገትና ለማህበራዊ ፍትሃዊነት የመጠቀም ጥቅል ፋይዳው የጎላ እንዲሆን አድርጎታል። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሹመት ኢትዮጵያ በአፍሪካ የሰው ሰራሽ አስተውሎት እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ ያላትን የመሪነት ሚና ይበልጥ ያጎላል። በተጨማሪም ሹመቱ የኢትዮጵያ ተሞክሮ በአህጉር አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ማግኘቱንና አፍሪካ በኃላፊነትና በፍትሐዊነት በታጀበ የኤአይ አጠቃቀም ረገድ በዓለም አቀፍ ደረጃ ግንባር ቀደም እንድትሆን የመሪነት ሚናዋን እንድትወጣም ያደርጋታል።
ኢትዮጵያ በአዕምሯዊ ንብረት ጥበቃ መንገድ
Apr 21, 2026 1708
(በዮሐንስ ደርበው) ታሪክ እንደሚነግረን፤ የአዕምሯዊ ንብረት ጥቅም ለመጀመሪያ ጊዜ ዕውቅና ያገኘው የኢንዱስትሪያዊ ንብረት ጥበቃን በሚመለከተው በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1883 በተፈረመው የፓሪስ ስምምነት እንዲሁም፤ በ1886 የተፈረመውን የሥነ-ጽሑፍና ሥነ-ጥበብ ሥራዎች ጥበቃን የተመለከተውን የበርን(ስዊዘርላንድ) ስምምነት ተከትሎ ነው። እነዚህ ስምምነቶችም በዓለም አዕምሯዊ ንብረት ድርጅት የሚተዳደሩ መሆናቸው ይታወቃል። ኢትዮጵያ የአዕምሯዊ ንብረት ባለሥልጣንን፤ በ2022 ዓ.ም ፈጠራንና ኢኖቬሽንን በማበረታታት የፈጠራ ሐሳቦችን ወደ ዕሴት በመለወጥ ሂደት ለሀገራዊ ብልጽግና ቁልፍ ሚና የሚጫወት በአፍሪካ ተምሳሌት የአዕምሯዊ ንብረት ተቋም ለማድረግ እየታተረች ነው። ለዚህ ርዕይ መሳካትም፤ ተቋሙ የአዕምሯዊ ንብረት ሥርዓት ለሀገራዊ ፈጠራ መጎልበት፣ የኢኖቬሽን፣ ቴክኖሊጂ ሽግግር እና የሥራ ዕድል ፈጠራ ማደግ ጥቅም ላይ የሚውልበትን ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ሀገራዊ የመዋቅር ሽግግርን መደገፍ የሚል ተልዕኮ አንግቦ እየሠራ ይገኛል። የእስካሁኑ የንግድ ምልክት፣ ቅጅና ተዛማጅ መብቶች እና የፈጠራ ባለቤትነት (ፓተንት) ምዝገባ የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ብሩክ ወርቅነህ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ2015 ዓ.ም እስከ ያዝነው በጀት ዓመት ያለፉት ዘጠኝ ወራት ድረስ በንግድ ምልክት፣ በቅጅና ተዛማጅ መብቶች እና በፈጠራ ባለቤትነት (ፓተንት) 20 ሺህ 476 ምዝገባዎች መከናወናቸውን አስረድተዋል። በዚህም መሠረት ይላሉ፤ 14 ሺህ 729 የንግድ ምልክቶች፣ 5 ሺህ 254 የቅጅና ተዛማጅ መብቶች እንዲሁም 1 ሺህ 781 የፈጠራ ሥራ ባለቤትነት ምዝገባ በተቋማችን አማካኝነት ተከናውኗል። የአዕምሯዊ ንብረት መብቶች ምንድን ናቸው? አዕምሯዊ ንብረት ማለት በሰው ልጅ አዕምሮ የሚፈጠሩ የፈጠራ ሥራዎችን የሚመለከት መሆኑን የገለፁት አቶ ብሩክ፤ እነዚህ የፈጠራ ሥራዎች እንደማንኛውም ቁሳዊ ሀብት በንብረትነት የሚታወቁበትን አግባብ የያዘው ሥርዓት ደግሞ የአዕምሯዊ ንብረት መብት እንደሚሰኝ ያስረዳሉ። በዚህ አግባብ፤ የአዕምሯዊ ንብረት መብቶች እንደማንኛውም ቁሳዊ ንብረት ሁሉ የፈጠራ ሥራዎችን ለሚያመነጩ ባለመብቶች የሚሰጡ የባለቤትነት መብቶች መሆናቸውን እንረዳለን። ለዚህም እንደ ምክንያት የሚቀርበው እንደ አቶ ዳንኤል ገለጻ፤ ወጥ ሥራዎችን ለማመንጨት የፈጠራ ባለመብቶች ዕውቀታቸውን፣ ገንዘባቸውንና ጊዜያቸውን መስዋዕት በማድረግ ከብዙ ድካም በኋላ ያገኟቸው የፈጠራ ውጤቶች በመሆናቸው ነው። ለአዕምሯዊ ንብረት ጥበቃ ማድረግ ለምን አስፈለገ? አንድም፤ የሰው ልጅ ቀጣይ ዕድገትና የኑሮ ደኅንነት ዋስትና መሠረት የሚያርፈው በቴክኖሎጂና ባሕል ዘርፎች በሚያሳርፋቸው ፈጠራዊ ብቃቶቹ በመሆኑ እንዲሁም የምርምርና የፈጠራ ሥራዎችን ለማካሄድ ተጨማሪ ሀብት የሚያስገኝ በመሆኑና ይህም የኢኖቬሽን ሥርዓቱን ስለሚያሳድግ ነው ይላሉ አቶ ብሩክ። እንዲሁም፤ የአዕምሯዊ ንብረት ጥበቃና ዘርፉን ለሕዝብ የማስተዋወቅ ተግባር ሀገራዊ የኢኮኖሚ ዕድገትን በማረጋገጥ የድርሻውን ስለሚወጣና የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት በአጠቃላይ የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ በተሻለ ደረጃ ላይ እንዲቆም ስለሚያደርግ መሆኑን ገልጸዋል። በተጨማሪም፤ ሀገራት ጠንካራ የአዕምሯዊ ንብረት ሥርዓት በፈጠሩ ቁጥር ዘርፉ ለኢኮኖሚ ዕድገት ቁልፍ የልማት መሣሪያ መሆኑን ይገነዘባሉ። ጠንካራና ፍትሐዊ የአዕምሯዊ ንብረት ሥርዓት በፈጠራ ባለቤቶችና በተጠቃሚው ሕዝብ ዘንድ ሚዛናዊ ነው ያሉት አቶ ብሩክ። በአጠቃላይ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ በመሆኑ ለአዕምሯዊ ንብረት ጥበቃ ማድረግ በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑን በአጽነዖት አንስተዋል። ዜጎች በአዕምሯዊ ንብረት ሥርዓት እንዴት ተጠቃሚ ይሆናሉ? ባለብዙ ቢሊየን ዶላር የፊልምና ድምጽ ሪከርድስ አሳታሚዎችና ሶፍትዌር ኢንዱስትሪዎች ለብዙ ሚሊየኖች የመዝናኛ ሥራዎች የሚያበረክቱት የቅጅ መብት ጥበቃ በመኖሩ መሆኑን መገንዘብ እንደሚገባም አቶ ብሩክ ይናገራሉ። በሌላ በኩል ተጠቃሚዎች የሚፈልጓቸውን ምርቶችና አገልግሎቶችን መለየት የሚያስችላቸው ብሔራዊና ዓለም አቀፋዊ የንግድ ምልክቶች ጥበቃና የመብት ማስከበር ሥርዓቶች ባይኖሩ ኖሮ ተመሳስለው በሚቀርቡ ምርቶችና አገልግሎቶች መታለልና ሌሎችም ችግሮች ያጋጥማቸው እንደነበርም ጠቁመዋል። ስለዚህ ምርቶችን በመሸመት ሂደትም በምርቶችና አገልግሎቶች ላይ ያለምንም ግራ መጋባት ግብይቱን ማከናወን እንደሚያስችላቸው መገንዘብ ይቻላል። እንደ አቶ ብሩክ ገለጻ፤ ለፓተንት የፈጠራ ሥራዎች ጥበቃ በመደረጉ መሰጠት የሚገባቸው ማበረታቻዎች የማይሰጡ ከሆነ፤ የፈጠራ ባለሙያዎች ቀጣይ የምርምር ሥራዎችን ማሳደግና ማስፋት እንደማይችሉ ይገመታል። በቀጣይነት የሚገኙ የተሻሻሉ የፈጠራ ሥራዎች አለመኖራቸው ደግሞ፤ በምርቶች ተጠቃሚና አጠቃላይ የኑሮ መሻሻል ሂደት ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ተፅዕኖ ይኖረዋል። የአዕምሯዊ ንብረት ዓይነቶች እንዴት ይመደባሉ? የአዕምሯዊ ንብረት፤ የኢንዱስትሪያዊ ንብረት (Industrial Property) እና የቅጅና ተዛማጅ መብቶች (Copyright and Related Rights) በሚሉ ሁለት ዋና ዋና ክፍሎች እንደሚመደብ ያስረዳሉ። አክለውም፤ ኢንዱስትሪያዊ ንብረት በውስጡ፤ የፓተንት፣ የንግድ ምልክት፣ የኢንዱስትሪያዊ ንድፍ እና የጂኦግራፊያዊ ምንጭ አመላካቾች የተሰኙ አራት ክፍሎችን እንደሚይዝ ያብራራሉ። ፓተንት ምንድን ነው?፡- ፓተንት ማለት በአንድ ቴክኒካዊ ባሕርይ ባለው የፈጠራ ሥራ ላይ የሚኖር የፈጠራ ባለቤትነት ብቸኛ መብት መሆኑን አቶ ብሩክ አስረድተዋል። የፓተንት መብት በአንድ ምርት (ለምሳሌ ማሽን ወይም የአመራረት ሂደት (Process) ሊሰጥ የሚችል ሲሆን፤ ፈጠራውም ለአንድ ቴክኒካዊ ችግር መፍትሔ የሚያስገኝ መሆን ይኖርበታል ይላሉ። ከፈጠራ ሥራው አመንጪ ይሁንታ ውጭ ሥራውን ገበያ ላይ ማዋል፣ መጠቀም፣ ማሰራጨት፣ መሸጥ ወዘተ… እንደማይቻልም አክለዋል። ፓተንት ለባለ መብቱ የጥበቃ መብት የሚያስገኝ ሲሆን፤ የጥበቃው ዘመንም በአጠቃላይ እስከ 20 ዓመት ሊደርስ ይችላል። ፓተንት የሚያስገኛቸው ሕጋዊ (የጥበቃ) መብቶች፡- የፈጠራ ሥራውን መጠቀም የሚችሉና የማይችሉ ሰዎችን መወሰን፤ ሦስተኛ ወገኖች ሥራውን እንዲጠቀሙ የመፍቀድ ወይም የፈቃድ ውል ስምምነት የመስጠት እንዲሁም የፈጠራ ሥራውን የመሸጥ (ለአዲስ የፓተንት ባለመብት) የሚሉት ይገኙበታል ብለዋል ሥራ አስፈጻሚው። የፓተንት ሥራዎች ለምን ያስፈልጋሉ?፡- ይህን ሲያብራሩም፤ ፓተንት ለፈጠራ ባለመብቶች ዕውቅናንና ሽልማቶችን (ማበረታቻዎችን) የሚሰጥ በመሆኑ፣ ፈጠራዎቹ የኢኖቬሽን ሥራዎችን ስለሚያጠናክሩና በዚህም ቀጣይነት ያለው የሰው ልጅ ሕይወት መሻሻልን የሚያረጋግጥ በመሆኑ እና በሌሎችም በጎ አስተዋጽዖዎች ፓተንት በዕጅጉ አስፈላጊ ነው ብለዋል። የንግድ ምልክት ምንድን ነው?፡- የንግድ ምልክት ማለት አንድን ምርት ወይም አገልግሎት ከሌላው ምርትና አገልግሎት እንዲለይ ለማስቻል በንግድ ምልክት ባለቤቶች ለምርታቸውና አገልግሎታቸው መለያ እንዲሆን ጥቅም ላይ የሚውል ልዩ ምልክት መሆኑን ተናግረዋል። የንግድ ምልክት ሸማቹ ሕብረተሰብ የሚፈልገውን ምርትና አገልግሎት በቀላሉ ለይቶ እንዲገዛ ከማስቻሉም በላይ በሚገዛው ምርትና አገልግሎት ጥራት ላይ በመተማመን ፍላጎቱን እንዲያሟላ ያደርጋል። የንግድ ምልክት ለባለመብቱ ምን ጥቅም ያስገኛል?፡- ምርቶቹ (አገልግሎቶቹ) በተጠቃሚዎች እንዲለዩለት ወይም እንዲታወቁለት ያደርጋል፣ ክፍያን መሠረት አድርጎ ሦስተኛ ወገን እንዲጠቀምበት የመፍቀድ፣ የንግድ ምልክቶች በራሳቸው ዋጋ አላቸው (የአዕምሯዊ ንብረት ዋጋ ትመና (IP Valuation) ለምሳሌ በፈረንጆቹ በ2026 የመጀመሪያ ወራት አፕል (Apple) 600 ቢሊየን ዶላር፣ ማይክሮሶፍት (Microsoft) 565 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር፣ ጉግል (Google) 433 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ዋጋ ግምት እንደነበራቸው ተብራርቷል። በተጨማሪም፤ የንግድ ምልክት በሕግ በሚቀመጥ የጊዜ ገደብ መሠረት እየታደሠ ለዘላለም ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል፤ የንግድ ምልክት ባለቤቱን በማስተዋወቅ ዕውቅናና የገንዘብ ትርፍን ያስገኛል፤ የንግድ ምልክት ተገቢ ያልሆኑ የንግድ ውድድሮችን በመግታት ረገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል (ተመሳስለው የሚሠሩና ለገበያ የሚቀርቡ ሥራዎችን (Counterfieited Products) ለመዋጋት ዓይነተኛ መሣሪያ ሆኖ ያገለግላል፤ የንግድ ምልክት ሰዎች ምርቶቻቸውንና አገልግሎቶቻቸውን ሚዛናዊ በሆነ አግባብ እንዲያቀርቡ በማድረግና በብሔራዊና ዓለም አቀፍ ደረጃ የተሳለጠ የንግድ ሥርዓት እንዲኖር ምቹ ሁኔታ በመፍጠር አስተዋጽዖው የላቀ ነው ብለዋል። ኢንዱስትሪያዊ ንድፍ ምንድን ነው?፡- ኢንዱስትሪያዊ ንድፍ በምርቶች ሥነ-ውበት (Esthetics) ላይ ተመስርቶ ቅርጽን፣ መስመሮችን ወይም ቀለምን በመጠቀም ለገበያ የሚቀርቡ ምርቶች የገዥዎችን (ሸማቾችን) ቀልብ ለመሳብ እንዲችሉ በምርቶች ላይ የሚገለጽ የንድፍ ጥበብ ዘርፍ ነው ያሉት አቶ ብሩክ፤ ኢንዱስትሪያዊ ንድፎች በኢንዱስትሪና ዕደ-ጥበብ ምርቶች ላይ ተዘጋጅተው ሊወጡና ለገበያ ሊቀርቡ ይችላሉ ይላሉ። ዘርፉ ከቴክኒካልና ሕክምና መሣሪያዎች አንስቶ እንደ ሠዓት፣ ጌጣጌጦችና ሌሎች የቅንጦት ምርቶች ዕቃዎችን ሊያካትት ይችላልም ብለዋል። የቤት ዕቃዎችን፣ የኤሌክትሪክ መሣሪያዎችን፣ ተሽከርካሪዎችና የሕንጻ ንድፎችን እንዲሁም የጨርቃጨርቅ ንድፍ ውጤቶች በኢንዱስትሪያዊ ንድፍ ሥር የሚወድቁ ይሆናሉ ይላሉ። ኢንዱስትሪያዊ ንድፎች ጥበቃ የሚደረግላቸው አዲስ ወይም ወጥ ከሆኑ ብቻ መሆኑን ገልጸው፤ በዲዛይኑ ውስጥ ከሚገለጸው ምርት ጋር ተያያዥ የሆኑ የቴክኒክ ጉዳዮች ጥበቃ እንደማይደረግላቸው አስታውቀዋል። ለኢንዱስትሪያዊ ንድፍ ጥበቃ ማድረግ ለምን ያስፈልጋል?፡- በምርቶች ውበት ላይ የሚገለጽ በመሆኑ የተጠቃሚውን ዐይን ይስባል፣ የምርቶችን ዋጋ ይጨምራል፣ ፈጠራንና ውድድርን ያበረታታል፣ ለባለመብቱ ብቸኛ መብትን ያጎናጽፋል፣ በኢንዱስትሪዎች፣ ባሕላዊ ጥበብና በዕደ ጥበብ ዘርፍ ፈጠራ በማሻሻል ኢኮኖሚ እንዲያድግ ያደርጋል፣ የወጭ ንግድን (Export Trade) ያሳድጋል በማለት የኢንዱስትሪ ንድፍ ጥበቃ አስፈላጊነትን ያብራራሉ። የጂኦግራፊያዊ ምንጭ አመላካች ምንድን ነው?፡- የጂኦግራፊያዊ ምንጭ አመላካቾች በምርቶች ላይ የሚቀርቡ ምልክቶች ሆነው እነዚህ ምልክቶች አንድ የተወሰነ አካባቢን በምርቱ ምንጭነት የሚያመላክቱና ጥራትንና ዝናን ከቦታው ጋር አስተሳስረው የሚያንጸባርቁ መሆናቸውን አቶ ብሩክ ያስረዳሉ። በአብዛኛው የጂኦግራፊያዊ ምንጭ አመላካቾች ልዩ ምርቱ የሚገኝበትን የቦታ ስም (Specific Local Geographyical Factors – Climate, Soil) ይይዛሉ። ለምሳሌ፡- Roquefort for Cheese -France፣ የማረቆ በርበሬ፣ የሸኖ ቅቤ፣ የዓድኣ ጤፍ … የመሳሰሉት ምርቶች ተጠቃሾች ናቸው። የጂኦግራፊያዊ ምንጭ አመላካቾችን መጠበቅ ለምን ያስፈልጋል?፡- ተጠቃሚዎች ምርቶች የሚገኙበትን ሀገር ወይም አካባቢ በቀላሉ ለመለየት፣ ሕጋዊነት በሌላቸው ወገኖች የምርቱ መገኛ አካባቢ እና የምርቱ ዝና በተሳሳተ መልኩ ለሌላ ምርት መጠሪያ እንዳይውል ለመከላከል ይረዳል ይላሉ። የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ምንድን ናቸው?፡- የቅጅ መብት በሥነ-ጽሑፍ እና ሥነ-ጥበብ ዘርፍ ወጥ የፈጠራ ሥራዎችን ለሚያመነጩ ደራስያን፣ አርቲስቶች ወዘተ… የባለቤትነት መብት የሚሰጥ የሕግ ማዕቀፍ መሆኑንም ነው ሥራ አስፈጻሚው የሚያስረዱት። በአንጻሩ ተዛማጅ የቅጅ መብት ማለት ይላሉ አቶ ብሩክ፤ በወጥ የፈጠራ ሥራዎች ላይ ተመስርተው የሚሠሩ ተዛማጅ (Related) የፈጠራ ሥራዎችን ያካትታል። ለምሳሌ፡- ከዋኞቹ (ተዋንያን እና ዘፋኞች)፣ ድምጽ ሪከርዲንግስ፣ አሳታሚዎች (ኮምፓክት ዲስኮች)፣ የብሮድካስት ተቋማት፣ (ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን) የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ ሲሉ ዘርዝረዋል። የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ምን ዓይነት መብቶች ያስገኛሉ?፡- ባለመብቶች ሥራዎቻቸውን ለመጠቀም ወይም ሦስተኛ ወገኖች እንዲጠቀሙባቸው የመፍቀድ፣ ሥራዎች እንዲባዙ፣ ለሕዝብ እንዲዳረሱ፣ እንዲሠራጩ፣ እንዲተረጎሙ ወይም ወደሌላ ሥራ እንዲቀየሩ የመፍቀድ ወይም የመከልከል፣ የደራሲነት (የአመንጭነት) መብት ዕውቅና እንዲያገኙ፣ በብዕር ስም የመጠቀም መብት፣ ክብሩንና መልካም ስሙን የሚያጎድፍ የሥራ መዛባት እንዳይኖር የመጠበቅ ወይም የሥራው ወደሌላ መቀየር የሚያስከትለውን ጉዳት የመቃወም ወዘተ መብቶችን ያስገኛሉ ብለዋል። የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ ምን ጥቅሞች ያስገኛል?፡- የሰውን ልጅ የፈጠራና ኢኖቬሽን ጥረቶችን ያሳድጋል፣ ለፈጠራ አመንጭዎች መበረታታትን ይፈጥራል፣ የሕጋዊ ተፈጻሚነትን በማረጋገጥ አመንጭዎችና በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች መዋዕለ-ነዋይ እንዲያፈሱ የፈጠራ ሥራዎችን በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚኖራቸውን የሥርጭት ሽፋን ያሳድጋል ነው ያሉት አቶ ብሩክ። የፓሪስ ስምምነት አባል ኢትዮጵያ ግንቦት 7 ቀን 2017 ዓ.ም የፓሪስ ስምምነት አባል ሀገር ለመሆን ለዓለም አዕምሯዊ ንብረት ድርጅት (WIPO) ያስገባችው ጥያቄ ተቀባይነት በማግኘቱና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስምምነቱን ነሐሴ 9 ቀን 2017 ዓ.ም በማጽደቁ ከዚሁ ዕለት ጀምሮ ለስምምነቱ ተገዢ ሆናለች። አቶ ብሩክ እንዳብራሩት፤ የፓሪስ ስምምነት በጥቅሉ የኢንዱስትሪያዊ ንብረቶችን ጥበቃ የሚመለከት ነው። የፓተንት፣ የንግድ ምልክት፣ ኢንዱስትሪያዊ ንድፍ፣ የግልጋሎት ሞዴል (በአንዳንድ ሀገራት ሕግ ኢትዮጵያን ጨምሮ “የአነስተኛ ፈጠራ የባለቤትነት መብት” በመባል የተደነገገ)፣ የአገልግሎት ምልክት፣ የንግድ ስም (የኢንዱስትሪ ወይም የንግድ እንቅስቃሴ የሚካሄድባቸው ስያሜዎች)፣ ጂኦግራፊያዊ አመላካች እና ፍትሐዊ ያልሆነ ውድድርን መከላከል ያካተተ ነው። የስምምነቱ መሠረታዊ ድንጋጌዎች በሦስት ዋና ዋና መርሆዎች እንደሚከፈሉ ጠቁመው፤ እነሱም፡- የፓሪስ ስምምነት አባል ሀገር መሆን በሌሎች አባል ሀገራት ውስጥ እንደ ዜጋ የመስተናገድ መብት፣ የቀዳሚነት መብት የማግኘት፣ በቀላሉ ዓለም አቀፍ ጥበቃ የማግኘት አሠራር እና መሰል ጉልህ ጥቅሞችን የማግኘት ዕድል ይሰጣል ሲሉ ይገልጻሉ። በመሠረቱ የፓሪስ ስምምነት የአዕምሯዊ ንብረት መብት ጥበቃን በማቀላጠፍ አዳዲስ ግኝቶችንና ፈጠራዎችን እንዲሁም የንግድ ሥራዎች ድንበር ሳይገድባቸው የፓተንትና የንግድ ምልክት መብቶች በቀላሉ እንዲጠበቁ በማድረግ ፈጠራን፣ ንግድን እና ኢኮኖሚያዊ እድገትን እውን ያደርጋል ብለዋል። የዘንድሮው የአዕምሯዊ ንብረት ቀን የፊታችን ሚያዝያ 17 ቀን 2018 ዓ.ም “አዕምሯዊ ንብረትና ስፖርት፤ እንዘጋጅ፣ እንጀምር፣ እንፍጠር!” በሚል መሪ ሐሳብ ዓለም አቀፉ የአዕምሯዊ ንብረት ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል። በስፖርት ዓለም ውስጥ የሚከሰቱ ተወዳዳሪዎች የግልና የጋራ ፈጠራዎች፣ ንድፎች፣ ብራንዶችና የመልካም ዝና ታሪኮችን ለመጠበቅና ሀገራትን ጭምር ለማስተዋወቅ የአዕምሯዊ ንብረት መብት ጥበቃ ሥርዓት ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ይታመናል። ምክንያቱም ስፖርት በባሕርይው በውድድር ላይ ብቻ ተወስኖ የሚቀር ሳይሆን፤ ከሀገራት ዝና፣ ከፋሽን ዲዛይን፣ ከመዝናኛ፣ ከሚዲያ ሥርጭት፣ ከጤናና ከዕለት ተዕለት መገልገያ ቁሶች ጋር የሚገናኝ በመሆኑ ነው።
ልዩ ዘገባዎች
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 4300
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 2901
በዮሐንስ ደርበው በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 8691
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 7174
ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
መጣጥፍ
አዲስ ምዕራፍ- ከዜጎች ደጃፍ እስከ እጅ ስልክ
Apr 25, 2026 610
አዲስ ምዕራፍ- ከዜጎች ደጃፍ እስከ እጅ ስልክ በቁምልኝ አያሌው በአንድ ሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት ውስጥ የመንግሥት አገልግሎት ጥራት ከሰው ልጅ የደም ዝውውር ጋር ይመሰላል። በሌላ በኩልም፣ የአገልግሎት አሰጣጥ የዜጎች የሞራልና የፍትሕ ልዕልና መለኪያ ተደርጎ ይወሰዳል። መንግሥት ለዜጎቹ የሚያቀርባቸው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶች ጥራት፣ ፍጥነትና ፍትሐዊነትም የሀገርን ፖለቲካዊ መረጋጋትና የኢኮኖሚ አቅጣጫ የሚበይኑ መጋቢዎች ናቸው። ታዋቂው የፖለቲካል ኢኮኖሚ ምሁር ፍራንሲስ ፉኩያማ እንደሚሉት፤ "የመንግሥት ተቋማት ብቃት (State Capacity) ለኢኮኖሚ ዕድገትና ለዴሞክራሲ መረጋጋት መሠረት ነው።" መልካም አስተዳደር የሰፈነበት ሥርዓት የሕዝብ አመኔታን በመጨመርና ማህበራዊ እኩልነትን በማስፈን ለዘላቂ ሰላም የማይተካ ሚና ይጫወታል። ይህም ሀገርን በኢኮኖሚ ለማሳደግና ለማበልጸግ በሚደረገው ርብርብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል። ሌላኛው የኢኮኖሚክስ ምሁር ጆሴፍ ስቲግሊዝ በበኩላቸው፤ "ውጤታማ መንግሥት ማለት ዜጎቹን በግልጽነትና በተጠያቂነት የሚያገለግል፣ በሂደቱም የህዝብ አመኔታን መገንባት የሚችል ነው" ሲሉ አጽንኦት ይሰጣሉ። በአንፃሩ፤ የአገልግሎት ክፍተትና የአስተዳደር ጉድለት ለሀብት ብክነት፣ ለሙስና እና ብልሹ አሰራር በር በመክፈት ዜጎችን ለከፍተኛ ምሬት በማጋለጥ አመኔታን ያሳጣል። ይህንን እንግልት ለማቃለል ሀገራት አገልግሎትን የሚያዘምን ፈጣንና ቀልጣፋ የዲጂታል ሥርዓት እየዘረጉ ይገኛል። ኢትዮጵያም ይህንን መርህ በመከተል ዘገምተኛ አሰራር ከወለደው የ"እጅ መንሻ" (ሙስና) ልምምድ በመላቀቅ ዘመናዊና ግልጽ የዲጂታል ሽግግርን በማፋጠን ላይ ትገኛለች። ይህም ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባትና ሉዓላዊነትን የሚያጎናጽፍ ወሳኝ የልማት ምኅዳር እየፈጠረ ነው። የመደመር መንግሥት ዕሳቤ፤ በተቋማት ግንባታና አገልግሎት ጥራት!! በመደመር ፍልስፍና ውስጥ የመንግሥት ተቋማት ግንባታ የሀገር ግንባታ የጀርባ አጥንት ተደርገው ይወሰዳሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመደመር መንግሥት መጽሐፋቸው ገፅ-129 እንዳሰፈሩት፤ ''የመደመር መንግሥት ከውስብስብ ቢሮክራሲ ተላቀው የመደመር ለውጥ የሚያመጡ ተቋማት ውቅር ነው። በመሆኑም ተቋማት ከተለመደ ''የሥራ ሂደት መር'' አካሄድ መላቀቅ ይጠበቅባቸዋል። አደረጃጀታቸውንም ለሚያገለግሉት ሕዝብ ትርጉም ያለው ለውጥ እንዲያገኙ ወደሚረዳቸው አደረጃጀት መሸጋገር አለባቸው። ለመደመር መንግሥት ሕዝቡን ማገልገል ከቢሮክራሲ በላይ ነው'' በሚል አስገንዝበዋል። ለዚህም ነው ተቋማት የሰውን ልጅ አቅምና ዕውቀት አቀናጅተው ለጋራ ዓላማ የሚያውሉ ሕያው መዋቅሮች ናቸው የሚባለው። በመደመር ዕሳቤ ጠንካራ ተቋማት ማለት በግለሰቦች ፍላጎትና ስሜት ላይ ያልተመሰረቱ ይልቁንም በሕግና በሥርዓት የሚመሩ መሆን አለባቸው። በመደመር መንግሥት መፅሐፍ ገፅ-130 እንደሰፈረው፤ ''በየተቋማት ያሉ የመንግስት ሠራተኞች ሕዝቡን ከቢሮክራሲው በላይ የሚመለከቱ እንዲሆኑ ይጠበቃል። አገልጋይነትን የተላበሱ መሆን ይጠበቅባቸዋል።'' መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትም ይህንን ዕሳቤ በተግባር የሚተረጉም ነው። ግለሰባዊ ንክኪን በመቀነስና አሰራርን በቴክኖሎጂ በመተካት ተቋማት ከግለሰቦች መልካም ፈቃድ ይልቅ በሥርዓት ወደሚመራ ተቋማዊ ብቃት መሸጋገርን ያሳያል። የአገልግሎት ጥራትና የዜጎች ክብር በመደመር መንግሥት ትልቅ ትኩረት የተሰጠው ሰው ተኮር የልማት ነጥብ ነው። ''ለሕዝቡ ቅድሚያ የማይሰጥ አመራርም ሆነ ሠራተኛ የመደመር መንግሥት ወገን አይደለም። እንዲህ ዓይነቱን ግለሰብም ሆነ አይቶ እንዳላየ በማለፍ የማይታገል ሰው በመደመር መንግሥት ውስጥ ዕድል ፈንታ የለውም'' በሚል በመደመር መንግሥት መፅሐፍ የሰፈረው ግልፅ መልዕክትም መንግሥት የአገልጋይነት እንጂ የገዥነት መንፈስ ሊኖረው እንደማይገባ በጉልህ ያመላክታል። የአገልግሎት ጥራት መሻሻልም ዜጎች በሀገራቸው ተቋማት ክብራቸውና መብታቸው ተጠብቆ ያለ እንግልት የሚገለገሉበትን ምኅዳር ይፈጥራል። በተቋማት አገልግሎት የዜጋ እርካታ (Citizen Satisfaction) ዋነኛ የፖለቲካል ኢኮኖሚ ዕድገት ምንጭ ተደርጎ ይወሰዳል። በመደመር መንግስት ዕይታ የብልሹ አሰራር መታገያ ስትራቴጂ በጩኸትና በቅጣት ብቻ የሚመጣ ሳይሆን አሰራርን በማዘመን ጭምር ነው። የመሶብ ዲጂታል የአንድ ማዕከል አገልግሎትም ሌብነትን የማይጋብዝ ሥርዓት የፈጠረ (Systemic Prevention) ስትራቴጂክ አቅጣጫ ሆኗል። የኢትዮጵያ የዲጂታል ልማትና የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የመደመር መንግሥት መሠረታዊ የተቋማት ሪፎርም ትግበራን (Institutional Reform) የሚያሳዩ ናቸው። ይህም ተቋማትን ከመዋቅራዊ ሽግግርና ለውጥ ባለፈ የተቋማት ሠራተኞችን ከመንግሥት ሠራተኛነት ወደ ሕዝብ አገልጋይነት የአስተሳሰብ ለውጥ (Paradigm Shift)፣ ኋላ ቀር አሰራርን በዲጂታል የቴክኖሎጂ አማራጭ የሚተካ (Technology Integration)፣ አገልግሎትን ለሁሉም ዜጋ በእኩልነት፣ በቅርበትና ፍትሐዊነት የማዳረስ ፅንሰ ሃሳባዊ ግብን በተግባር ያረጋገጠ ሆኗል። ይህ ታላቅ ተግባርም ኢትዮጵያ በመደመር ዕሳቤ የጀመረችውን የብልፅግና ጉዞ የሚያፋጥንና ዜጎች በመንግሥታቸው ላይ ያላቸውን አመኔታ በጽኑ መሠረት ላይ የሚገነባ መሠረት ነው። የዲጂታል ኢትዮጵያ ርዕይና ስትራቴጂክ ሽግግር!! ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው ለግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን፣ ቱሪዝምና አይሲቲ ዘርፎች ወሳኝ የልማት ዕድሎችን ፈጥሯል። በዚህ ሰፊ መርሃ ግብር ውስጥ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ እንደ ዋነኛ የብልፅግና ምሰሶ ተወስዷል። በ"ዲጂታል ኢትዮጵያ-2025" ስትራቴጂ የተጀመረውና በስኬት የተጠናቀቀው ጉዞ ዛሬ ላይ ሀገሪቷን ወደ "ዲጂታል ኢትዮጵያ-2030" አሸጋግሯታል። ይህ ስትራቴጂ ዜጎች ካሉበት ቦታ ሆነው አገልግሎት የሚያገኙበትን ምኅዳር በመፍጠር በሰው ንክኪ የሚፈጠሩ ብልሹ አሰራሮችንና የአገልግሎት እንግልትን በማስቀረት ረገድ ታሪክ ቀያሪ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። የልማትና ዕድገት ምሁሩ አማርትያ ሴን፤ "ልማት የሰው ልጅ ምርጫና የመገልገያ አቅሙን ማስፋፊያ መሣሪያ ነው" በማለት የሚገልጹት ስለልማት ከፍ ያለ ትርጉም ይሰጠናል። የኢትዮጵያ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትም ዜጎች የሚያጋጥሟቸውን እንግልቶች በማስወገድ ትኩረታቸውን በልማት ላይ እንዲያደርጉ በማስቻሉ፣ ይህንን የልማት ፅንሰ-ሃሳብ በተግባር እየተረጎመ ይገኛል። የአንድ ጣሪያ በረከትና የቅልጥፍና ተምሳሌት - መሶብ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሚያዚያ 18/2017 ዓ.ም የተመረቀው የፌዴራል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፣ ለተቋማዊ ሽግግር መነሻ ሆኗል። ቁልፍ የመንግሥት አገልግሎቶች በአንድ ጣሪያ ስር መሰባሰባቸው የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራቱን ወደ ከፍተኛ ደረጃ አሸጋግሮታል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅቱ እንደገለጹት፤ ይህ ማዕከል ዜጎች ጊዜያቸውንና ሀብታቸውን በመቆጠብ ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ ለዘመናት የቆየውን ምሬት የሚቀለብስ የሪፎርም እርምጃ ነው። በወቅቱ ሲጀመር 12 የነበሩት ፌዴራል ተቋማት፤ አሁን ላይ 23 በመሻገር አገልግሎታቸውን እየሰጡ ይገኛል። ይህም የዜጎች እንግልት በማስቀረት ታላቅ እፎይታን ፈጥሯል። እነዚህ ተቋማት፦ የብሔራዊ መታወቂያ፣ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት፣ የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት፣ የገቢዎች ሚኒስቴር፣ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የትምህርት ስልጠና ባለስልጣን፣ ኢትዮ ፖስታ፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን፣ የኢትጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን፣ የጤና ሚኒስቴር፣ የፍትሕ ሚኒስቴር፣ ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ የትምህርት ምዘናና የፈተናዎች አገልግሎት ናቸው። መነሻውን አዲስ አበባ ከተማ የፌዴራል ተቋማት በአንድ በማሰባሰብ የጀመረው ይህ አገልግሎት አሁን ላይ በሁሉም ክልሎችና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች ተደራሽ እየሆነ ነው። ይህም የመልካም አስተዳደር እጦትን የሚያቃልል ታሪክ ቀያሪ መደላድል ፈጥሯል። አዲስ መሶብ - የተንቀሳቃሽ አገልግሎት ተስፋ!! በመዲናችን ሚያዚያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ የተጀመረው መሶብ የአንድ ማዕከል ተንቀሳቃሽ አገልግሎት፣ "መንግሥት ወደ ዜጋው ይሄዳል" (Citizen-Centric Governance) የሚለውን የዘመናዊ አስተዳደር ፍልስፍና በተግባር ያሳየ ነው። በፀሐይ ኃይልና በፈጣን ኔትወርክ የታገዘው ይህ ተንቀሳቃሽ አገልግሎት የስምንት ተቋማትን 36 ዓይነት አገልግሎቶች ወደ ህዝቡ ደጃፍ በማምጣት ረገድ ተምሳሌት ሆኗል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በወቅቱ እንደገለጹት፤ ከተማዋ ለዘመናት ስር በሰደደ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር ተተብትባ ብትቆይም፣ የመሶብ ዲጂታል አገልግሎት ግን ለተገልጋዩ እውነተኛ እፎይታን ይዞ መጥቷል። የቀጣዩ ዘመን ግብ - አገልግሎትን በእጅ ስልክ!! ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቀጣይ አገልግሎቱን ወደ ዜጎች የእጅ ስልክ የማሸጋገር ግብ መኖሩን አረጋግጠዋል። ይህ ሽግግር ሙሉ በሙሉ ስኬታማ እንዲሆን የዲጂታል መታወቂያ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። ዜጎችን በዲጂታል መታወቂያ መለየት መቻሉ የአሰራር ግልጽነትን ከመጨመሩም በላይ መንግሥት አገልግሎቱን ለማን እየሰጠ እንደሆነ በትክክል እንዲያውቅ ያስችለዋል። ተገልጋይን አክብሮ፣ ስርቆትና "እጅ መንሻን" አስቀርቶ አገልግሎት መስጠት የባህል ለውጥ ይጠይቃል። ለዚህም ሲቪል ሰርቪሱን በማዘመን፣ ቴክኖሎጂንና የባህል ለውጥን በማቀናጀት የእጅ መንሻን ባህል የሚያስቀር መሠረት እየተጣለ ይገኛል። ለዚህ ለውጥ ስኬት እያንዳንዱ ዜጋና ተቋም የበኩሉን ሊወጣ ይገባል። በአጠቃላይ የኢትዮጵያ የዲጂታል ልማት መርሃ ግብርና የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ሙስናን በማድረቅ ፍቱን መፍትሔ እየሰጡ ይገኛሉ። ይህም ሀገሪቷን ከቆየችበት የ"እጅ መንሻ" አዙሪት አውጥቶ፣ ተቋማት ለዜጎች ክብር ወደሚያሳዩበት አዲስ ምዕራፍ አሸጋግሯታል። ይህ ጉዞ እመርታ ነው፤ ግልጽነትን በማንገስና የህዝብን እርካታ በመጨመር የብልጽግና ጉዞውን የሚያፋጥን ነው።
ፋሲካ -አብሮነት የሚደምቅበት የደስታ በዓል
Apr 12, 2026 793
በኢትዮጵያ የፋሲካ በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ድምቀት የሚከበር በዓል ነው። የትንሳኤ በዓል የሚከበረው ከ55 ቀናት የጾም ወቅት በኋላ ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች እነዚህን ቀናት ፈጣሪያቸውን በጾምና ጸሎት ከመለመን ባለፈ ከሥጋ፣ ከወተትና መሰል የእንስሳት ተዋጽኦ ምግቦች ታቅበው ነው የሚያሳልፉት። የትንሣኤ በዓል ከመድረሱ በፊት ያለው አንድ ሳምንት "ሰሞነ ሕማማት" በመባል ይታወቃል። የእምነቱ ተከታዮች በሰሞነ ሕማማት ኢየሱስ ክርስቶስ ያሳለፈውን መከራና ስቃይ በማሰብ በቤተ ክርስቲያን በስግደት፣ በጸሎትና በጾም በተለየ ሁኔታ ያሳልፋሉ። ምእመናን በእለተ አርብ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች መዳን ብሎ በቀራኒዮ አደባባይ የከፈለውን መከራ፣ ግርፋትና ስቅላት በማሰብ በስግደት፣ በጸሎትና በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርዓቶች ያሳልፋሉ። የትንሳኤ (የፋሲካ) በዓልም ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትል ድል አድርጎ መነሳቱን ተከትሎ የሚከበር ነው። ትንሳኤው ይቅርታ፣ ለሰው ለጆች መዳን የተከፈለ ፍቅርና መስዋዕትነት ጎልቶ የሚታይበት ነው። በመሆኑም ፋሲካ ሞትን ድል በመንሳት በትንሳኤ የምስራች የተበሰረበት ታላቅ በዓል ነው ማለት ይቻላል። ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን በትንሳኤ የለወጠበት ለሰው ልጅም ፍቅርን በቤዛነት ተክቶ ያሳየበት ዕለት ነው። ዕለቱ ትንሳኤ ብርሀን የታየበት በመሆኑ በትንሣኤ ዋዜማ ቅዳሜ ምሽት ምዕመናን ነጭ ልብስ ለብሰው ወደ ቤተ ክርስቲያን በመሄድ ሌሊቱን በጸሎትና በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርአቶች ያሳልፋሉ። የሌሊቱ ቅዳሴና ስርአተ ፀሎት ከተጠናቀቀ በኋላ ምዕመናን ወደ ቤታቸው ሲመለሱ ጾም ይፈታሉ። ከቅባት ምግቦች ለሁለት ወራት በመቆጠብ ያሳለፉበት ወቅት በመሆኑም በትንሳኤ ሌሊት ዶሮ በመብላት ጾማቸውን ይፈስካሉ። በበዓሉ ቀንም በነጭ የሀበሻ ልብስ ደምቀው ይታያሉ። በዓሉ ከሃይማኖታዊ ሥርአቱ ባለፈ የአብሮነት፣ የፍቅርንና የመተሳሰብ እሴት ያለው ነው። ዘመድ አዝማድ በመጠራራትና ከጎረቤት ጋር አብሮ በመብላትና በመጠጣት የሚያሳልፉት ነው። ቤት ያፈራውን በመቋደስ በዓሉን በአብሮነት በደስታ ያሳልፋሉ። የፋሲካ በዓል ማህበራዊ ትስስር የሚገለጥበትና አብሮነት የሚደምቅበት የደስታ በዓል ነው። በተለይ በፋሲካ በዓል ለዶሮ ወጥ ልዩ ትኩረት ይሰጣል። ፋሲካና ዶሮ ወጥ ጥብቅ የሆነ ባህላዊ ቁርኝት ያላቸው በመሆኑ አንዱ የበዓሉ ማድመቂያ ተደርጎ ይወሰዳል። ከዚህ በተጨማሪ የበሬ ቅርጫ፣ በግ፣ ፍየል፣ ዳቦና ጠላ እንደየ አቅም በማዘጋጀት ይከበራል። በአንዳንዶች ዘንድም ከገብስ ብቻ የሚዘጋጅ "ኬኔቶ" የተሰኘ (ከአልኮል ነፃ የሆነ መጠጥ) በማዘጋጀት በአማራጭነት ይቀርባል።