ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
አርሰናል ብሬንትፎርድን በማሸነፍ መሪነቱን አጠናከረ
Dec 3, 2025 71
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 24/2018(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ14ኛ ሳምንት መርሃ ግብር አርሰናል ብሬንትፎርድን 2 ለ 0 አሸንፏል። ማምሻውን በኤምሬትስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ማይክል ሜሪኖ በ11ኛው እና ቡካዮ ሳካ በ91ኛው ደቂቃ ላይ የማሸነፊያ ጎሎቹን አስቆጥረዋል። በጨዋታው አርሰናል ከተጋጣሚው ጠንካራ ፈተና ቢገጥመውም ወሳኝ ሶስት ነጥብ ይዞ ወጥቷል። በውድድር ዓመቱ 10ኛ ድሉን ያስመዘገበው አርሰናል በ33 ነጥብ መሪነቱን አጠናክሯል። ከተከታዩ ማንችስተር ሲቲ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ አምስት ከፍ አድርጓል። በአንጻሩ በሊጉ ሰባተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ብሬንትፎርድ በ19 ነጥብ ከነበረበት 10ኛ ደረጃ ወደ 13ኛ ዝቅ ብሏል።
በመደመር መንግስት የብዝኀ ዘርፍ ዕይታዎች የኢትዮጵያን ብልጽግና አይቀሬ መሆኑን ማረጋገጫ ናቸው
Dec 3, 2025 143
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 24/2018(ኢዜአ)፦ በመደመር መንግስት የብዝኀ ዘርፍ ዕይታዎች የኢትዮጵያ ብልጽግና አይቀሬ መሆኑን እንደሚያረጋግጡ የመንግስትና የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “በመደመር መንግሥት ዕይታ፣ የዘርፎች እመርታ” በሚል መሪ ሃሳብ ለቀናት ለብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አባላት የማጠቃለያ ስልጠና መስጠታቸው ይታወሳል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሥልጠናው ላይ እንደገለጹት፤ የመደመር መንግስት የሚፈጽማቸው የልማት ግቦች የሁሉንም ዜጋ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ታሳቢ ያደረጉ መሆናቸውን ነው ያረጋገጡት። የኢትዮጵያን ቀደምት ስልጣኔና ቀጣይ መዳረሻ ታሳቢ በማድረግም በመደመር መንግስት የመፍጠን፣ መፍጠር፣ ማባዛትና ማጥራት እሳቤ ለከፍተኛ አመራሩ አብራርተዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር ዴኤታ መሐመድ እድሪስ (ዶ/ር)፤ የመደመር መንግስት ኢትዮጵያ ትመራበት ከነበረ የተውሶ ሃሳብ በማላቀቅ ስኬታማ ስራዎችን እየሰራ ነው ብለዋል። የመደመር እሳቤም ከርዕዮተ ዓለማዊ ታማኝነት ወደ ህዝብና ሀገርን ማገልገል ታማኝነት፣ አካታች ካልሆነ የፓርቲ፣ የተቋምና የልማት ፖሊሲ እሳቤ ወደ አቃፊነት መቀየር እንዳስቻለ ተናግረዋል። የከፍተኛ አመራር አባላት ስልጠናም በጠራ የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት ልማትን ማሳካት የሚያስችል ተግባቦት የተፈጠረበት መሆኑን ገልጸዋል። የመደመር መንግስት ከሃሳብና ተቋም በመነሳት ሽግግርን በስኬት በመምራት የጸና መንግስት በመገንባት የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት የተፈጠረበት መሆኑን አስረድተዋል። የኢትዮጵያ ብዝኀ ዘርፍ ዕይታዎች የኢኮኖሚ ስኬት የመደመር መንግስት ወሳኝ ትሩፋት ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፤ የብዝኀ ኢኮኖሚ ሥርዓቱም አንደኛው የሌላኛው የልማት ደጀን መሆን አስችሏል ብለዋል። የብዝኀ ዘርፍ የልማትም የኢትዮጵያን ብዝኀ ጸጋና አቅሞች በማሰባሰብ በግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን፣ ቱሪዝምና ዲጂታል ሥርዓት ስኬቶችን ያመጣ የመደመር መንግስት ኢኮኖሚያዊ እሳቤ መሆኑን ገልጸዋል። የብልጽግና ፓርቲ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ዋና ዳይሬክተር አቶ ነብዩ ስሑል በበኩላቸው፤ የመደመር መንግስት መንገዱን መደመር መዳረሻው ደግሞ የኢትዮጵያን ብልጽግና ማረጋገጥ መርህ ያደረገ ነው ብለዋል። ባለፉት ጥቂት ዓመታትም በጠራ የመደመር መንግስት እሳቤ ትላልቅ ውጤቶችን በማስመዝገብ ለበርካታ ሀገራት ጭምር አርዓያ መሆን የቻለ ስኬት መምጣቱን አስረድተዋል። የብዝኀ ዘርፍ ኢኮኖሚ ልማት የኢትዮጵያን የመልማት አቅም ወደ ጥቅም የቀየር ሀገር በቀል የዕድገት እሳቤ ነው ያሉት አቶ ነብዩ፤ የብዝኀ ዘርፍ የኢኮኖሚ ሥርዓቱም የተሟላ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ መሠረት እየጣለ መሆኑን ገልጸዋል። የብዝኀ ዘርፍ የኢኮኖሚ ሥርዓትም የመንግስት፣ የህዝብና የግሉን ክፍለ ኢኮኖሚ የብዝኀ ተዋናይነት ሚና በማስፋት ውጤት ማምጣቱን አንስተዋል። ለአብነትም የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ዕድገት በአፍሪካና በዓለም አቀፍ ደረጃ የሀገርን ብልጽግና አይቀሬነት በሚያረጋግጥ መልኩ ዕድገት እያስመዘገበ መቀጠሉን አስረድተዋል።
የተከናወኑ ሪፎርም ስራዎች በሰው ሀብት ልማት ላይ የተሻለ ለውጥ እንዲመዘገብ አስችለዋል
Dec 3, 2025 103
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 24/2018 (ኢዜአ)፦በሥራና ክህሎት ልማት የተከናወኑ የሪፎርም ስራዎች በሰው ሀብት ልማት ላይ የተሻለ ለውጥ እንዲመዘገብ ማስቻሉን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ። የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደር ቢሮዎች እንዲሁም ተጠሪ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ለሶስት ቀናት በቢሺፍቱ ከተማ ያካሄደውን የምክክር መድረክ አጠናቋል። በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል፤ የሰው ሃብት ልማትን ለማሻሻል የተከናወኑ የሪፎርም ተግባራት ተጨባጭ ስኬት እያስመዘገቡ ነው ብለዋል። በተቋም ደረጃ የተወሰዱ የሪፎርም እርምጃዎችም በአዳዲስ የለውጥ እሳቤ የሀገር ውስጥ ምርታማነትና የቴክኖሎጂ ሃሳቦችን የማፍለቅ አቅም እያሻሻለ መሆኑን ገልጸዋል። በሰው ሃብት ልማት የተፈጠረው አቅም አምራች ኢንዱስትሪው በእውቀትና ክህሎት የበለጸገ የሰው ሃይል እንዲያገኝ ማስቻሉን አንስተዋል። በእውቀትና ክህሎት የበለጸገ የሰው ሃብት ለሥራ ኢንዱስትሪው ለማቅረብም በሰው ሰራሽ አስተውሎትና በሳይበር ቴክኖሎጂ የታገዘ ስልጠና እየተሰጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል። የቴክኒክ እና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማትም በሰው ሃብት ልማት ላይ የተሰጣቸውን ተልዕኮ በብቃት በመወጣት ትርጉም ያለው ሥራ እየሰሩ መሆናቸውን አንስተዋል። ባለፉት ጥቂት ዓመታት በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት የተሰጡ የአጭር፣ መካከለኛና የረጅም ጊዜ ስልጠናዎች ለሥራ ዕድል ፈጠራ ምቹ ምኅዳር መፍጠራቸውን አብራርተዋል። በእውቀትና ክህሎት የበለጸገ የሰው ሃብት የማሰልጠን ተግባርም ከገበያ ፍላጎትና ጥራት ጋር የተጣጣመ የቴክኖሎጂ ሽግግር በመፍጠር አመርቂ ውጤት መገኘቱን ጠቅሰዋል። በሥራ ዕድል ፈጠራ የተገኙ ስኬቶችም ዜጎች ከራሳቸው አልፎ ሃብትና ንብረት በማፍራት በሀገራቸው የኢኮኖሚ ዕድገት አሻራቸውን እንዲያሳርፉ እያደረገ መሆኑን አንስተዋል።
የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለን ከጥፋት መንገድ ተመልሰን መጥተናል - የቀድሞ ታጣቂዎች
Dec 3, 2025 90
ጎንደር፤ ህዳር 24/2018(ኢዜአ)፦ የህዝቡን የሰላም ጥያቄና የልማት ፍላጎት በመረዳት የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለን ከጥፋት መንገድ ተመልሰናል ሲሉ በአማራ ክልል የሰላምን ጥሪ ተቀብለው የመጡ የቀድሞ ታጣቂዎች ተናገሩ። የቀድሞ ታጣቂዎቹ የሰላም ጥሪውን በመቀበል በዛሬው እለት በጎንደር ከተማ ወደ ሰላማዊ ህይወት ለመኖር ገብተዋል። ከቀድሞ ታጣቂዎቹ መካከል አበጀ ገላው፤ በተሳሳተ መንገድ ጫካ በመግባት በህዝብ ላይ ጥፋት መፈፀሙን አንስቶ በድርጊቱ በመፀፀት ሰርቶና አገልግሎ ለመካስ መዘጋጀቱን ተናግሯል። ብዙዎቻችን ወደ ጫካ የገባነው የተሳሳተ አረዳድ ይዘን ነው ሲል ገልጾ አሁን ላይ እውነታውን በመገንዘብ ወደ ሰላማዊ ህይወት እየተመለስን እንገኛለን ብሏል። በዚህም መሰረት እርሱና ሌሎች ጓደኞቹ የመንግስትን የሰላም ጥሪ በመቀበል ሰላማዊ ህይወት ለመምራት መምጣታቸውን አረጋግጧል። የህዝቡን የሰላም ጥያቄና የልማት ፍላጎት በመረዳት ከጥፋት ወጥተን የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለን መጥተናል ብሏል። የበደልኩትን ህዝብ በልማት በመካስ ከዚህ በኋላ ከተሳሳተ መንገድ እራሴን በማግለል አዲስ ህይወት ለመምራት ቁርጠኛ በመሆን የሰላም ጥሪውን ተቀብዬ ገብቻለሁ ሲሉም ገልጿል፡፡ ቁርጠኛ በመሆን የሰላም ጥሪውን ተቀብዬ ገብቻለሁ ብሏ ሌላኛው የሰላምን መንገድ መርጦ የመጣው አማረ ምትኩ፤ በቆዩበት የተሳሳተ መንገድ ህዝብን ሰላም ከመንሳትም ባለፈ ብዙ በደሎችን ማድረሳችን እኔና መሰል ጓደኞቼን ጸጸት ላይ ጥሎናል ሲል ተናግሯል። በመሆኑም ከጥፋት በመውጣት ለሰላምና ልማት ዝግጁ በመሆን ህዝባችንን በስራ ለመካስ መጥተናል በማለት ሌሎችም በተሳሳተ መንገድ የሚገኙ ሁሉ የመንግስትን የሰላም ጥሪ በመቀበል እንዲመጡ መክሯል። የጎንደር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የወንጀል መከላከል ምክትል መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር ስማቸው አደመ፤ በከተማው በህብረተሰቡ ተሳትፎ ዘላቂ ሰላምን ማስፈን መቻሉን ተናግረዋል። በተሳሳተ መንገድ የባዳ ተልእኮ ፈፃሚ የነበሩና ህዝብን የበደሉ የቀድሞ ታጣቂዎች እየተመለሱና ሰላማዊ ህይወት እየመሩ መሆኑን ገልጸዋል። የቀድሞ ታጣቂዎቹን በማቋቋም ወደ ህብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ እየተደረገ መሆኑን አንስተው አሁን የመጡትም የተሃድሶ ስልጠና ወስደው በተመሳሳይ ሁኔታ ህይወታቸውን እንዲመሩ ይደረጋል ብለዋል። ከቀናት በፊት የመንግስትን የሰላም ጥሪ የተቀበሉ 15 የቀድሞ ታጣቂዎች በጎንደር ከተማ የሰላም አማራጭን በመቀበል ወደ ሰላማዊ ህይወት ለመመለስ በመወሰን መግባታቸው ይታወሳል።
ድርድርን በመግፋት የቅኝ ግዛት አስተሳሰብን ለማራመድ የሚደረገው የግብጽ እንቅስቃሴ ከወቅቱ እውነታ ጋር የማይሄድ ነው
Dec 3, 2025 102
አዲስ አበባ፤ሕዳር 24/2018(ኢዜአ)፦በህዳሴ ግድቡ ዙሪያ የሚደረጉ ድርድሮችን በመግፋትና የቅኝ ግዛት ዘመን አስተሳሰብን ለማራመድ የሚደረገው የግብጽ መንግስት ባለስልጣናት ተደጋጋሚ እንቅስቃሴ ከ21ኛው ክፍለ ዘመን እውነታ ጋር የማይሄድ ነው ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፤ የግብጽ መንግስት በአባይ ወንዝ ላይ የቅኝ ግዛት ዘመን የበላይነትን ለማስጠበቅ የሚያደርገው ተደጋጋሚ ጥረት ወቅቱን የማይመጥን ነው ሲል አውግዟል። ኢትዮጵያ ከተፋሰሱ ሀገራት ጋር በትብብር ለመልማት ሁሌም ቁርጠኛ መሆኗን የገለጸው ሚኒስቴሩ የፓን አፍሪካ የረጅም ጊዜ አሻራ እና ታሪክ ያላት ኢትዮጵያ የቆየ የቅኝ ግዛት እሳቤዎችን በፍጹም አትቀበልም ብሏል። ፍትሃዊ፣ ምክንያታዊና እኩልነትን መሰረት ያደረገ የውሃ ሀብት አጠቃቀም የዓለም አቀፍ ሕግ ገዢ ጽንሰ ሀሳብ መሆኑን አመልክቶ ኢትዮጵያም ሀብቷን ለመጠቀም ከማንኛውም አካል ፍቃድ መጠየቅ አያስፈልጋትም ሲል ገልጿል። መግለጫው ፤ግብጽ የሁለትዮሽ ድርድሩን ወደ ጎን በመተው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ኢትዮጵያ ላይ የምታሰራጨው መሰረት ቢስ ውንጀላ ተቀባይነት የለውም ብሏል። ዓለም አቀፉ ማህረሰብ የግብጽን ጸብ አጫሪ ባህሪ እንዲያወግዝም ሚኒስቴሩ ጠይቋል። የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ጨምሮ የኢትዮጵያ የልማት ፕሮጀክቶች የአፍሪካ ራስን መቻል የሚያሳዩ እንደሆኑም አመልክቷል። ኢትዮጵያ ለትብብርና ሁሉንም ተጠቃሚ ለሚያደርጉ የመፍትሄ ሀሳቦች በቁርጠኝነት እንደምትሰራ ነው በመግለጫው ላይ የተጠቀሰው። ኢትዮጵያ የአባይ ወንዝን አሁን ላለውና ለቀጣይ ትውልዶች በመጠቀም መብቷ ጸንታ እንደምትቀጥልም ሚኒስቴሩ አስገንዝቧል።
ፖለቲካ

ያሉንን ሃብቶች በማልማት ህብረተሰባችንን ተጠቃሚ ለማድረግ በቁርጠኝነት እንሰራለን
Dec 3, 2025 250
ሰመራ ፤ ህዳር 24/2018(ኢዜአ)፦ ያሉንን ሃብቶች በመጠቀምና በማልማት ህብረተሰባችንን ተጠቃሚ ለማድረግ ተዘጋጅተናል ሲሉ የአፋር ክልል ሰልጣኝ አመራሮች ተናገሩ። በክልሉ “በመደመር መንግስት ዕይታ የዘርፎች እመርታ” በሚል መሪ ሀሳብ ለመካከለኛና ከፍተኛ አመራሮች ስልጠና ሲሰጥ መቆየቱ ይታወሳል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በስልጠናው ማጠቃለያ በሰጡት ማብራሪያ ላይ ፤ መፍጠር፣ መፍጠን፣ ማብዛት እና ማጥራት ላይ ትኩረት በማድረግ ለውጤታማነት መስራት እንደሚገባ መናገራቸው ይታወሳል። በአፋር ክልል ኢዜአ ያነጋገራቸው የስልጠናው ተሳታፊ አመራሮች እንደገለጹት፤ በስልጠናው ያገኙትን እውቀት ከክልሉ ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማጣጣም ለክልሉ ህዝብ ተጠቃሚነት በቁርጠኝነት ይሰራሉ። ከአመራሮቹ መካከል የቡሩሞዳይቱ ወረዳ አስተዳደሪ አቶ መሐመድ ሐሰን፤ በወረዳው የሚገኘው ሐይቅና ሌሎች ሀብቶች ላይ ወጣቶችን አደራጅቶ ወደስራ ለማስገባት የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል። በቀጣይም የቱሪዝም ሀብቶችን እና ሌሎችን በማልማት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ይሰራል ብለዋል። በወረዳው ባሉ ሰፋፊ የእርሻ መሬቶች የተለያዩ የግብርና ልማት ሥራዎችን በመስራት ተጠቃሚነት ማሳደግ ላይ በፍጥነትና በጥራት ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል። የሰሙሮቢ ወረዳ ሲቪል ሰርቪስ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አይትሌ ማቴ በበኩላቸው ፤ መሬት፣ ውሃና የሰው ጉልበት እያለ የእርሻ መሬቶችን ጦም ላለማሳደር ተግተው እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል። ህብረተሰቡን በማሳተፍ ውጤታማ ሥራ ለመስራት ዝግጁ ነን ያሉት አመራሩ፤ በተለይም የተሰጠንን ኃላፊነት ተገንዝበን ምርታማነትን በማሳደግ ተረጂነትን ለመቀነስ የሚያስችሉ ስራዎችን እንሰራለን ብለዋል።ለስኬታማነቱም እስከ ታች ድረስ ያሉ መዋቅሮችን በመጠቀም እንደሚሰራ ነው የገለጹት። የተላላክ ወረዳ ትምህርት ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ በርኦ ዓሊ በበኩላቸው፤ በወረዳው ያሉትን አቅሞችና ሀብቶች አውቀን ወደልማት ለመቀየር ተዘጋጅተናል በማለት ተናግረዋል።
የመደመር መንግሥት ታሪክን እንደትምህርት በመውሰድ ታሪክ ሰሪ የሆነ እሳቤን ይከተላል
Dec 3, 2025 111
አዲስ አበባ፤ሕዳር 24/2018 (ኢዜአ)፦የመደመር መንግሥት ታሪክን እንደትምህርት በመውሰድ ታሪክ ሰሪ የሆነን እሳቤን እንደሚከተል የታሪክ ምሁሩ ታምራት ሃይሌ (ዶ/ር) ገለጹ። የመደመር መንግሥት የታሪክ አረዳድ በኢትዮጵያ ትናንት፣ ዛሬና ነገ መካከል ባለው አሰባሳቢና አስተሳሳሪ ዕይታ የተመሠረተ መሆኑንም ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “በመደመር መንግሥት ዕይታ፣ የዘርፎች እመርታ” በሚል መሪ ሃሳብ ለቀናት ለብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አባላት የማጠቃለያ ስልጠና መስጠታቸው ይታወሳል። በወቅቱም የመደመር መንግሥት የሚያሻግር ሃሳብ፣የሚሻገር ህዝብ ይዞ ለለውጥ የሚተጋ ስርዓት በመያዝ ታሪክን ከማውራት ይልቅ ታሪክን በመስራት እራሱን መግለጥ የሚሻ መሆኑን ገልጸዋል። የታሪክ ምሁሩ ታምራት ሃይሌ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንዳሉት፤ የሰው ልጆች ታሪክ አረዳድ በግለሰብ፣ በማህበረሰብ፣ በሀገረ መንግስትና ዓለም አቀፍ ደረጃ የተወሰነ መሆኑን ገልጸዋል። ታሪክም በዜጎች የትናንትና ዛሬ ማንነት እንዲሁም ከፖለቲካ ሥልጣንና አስተዳደር ጋር በእጅጉ የተቆራኘ መሆኑን ጠቁመዋል። በ1950 በተጀመረ የኢትዮጵያ ዘመናዊ የታሪክ አስተምህሮም በመልካምና በተግዳሮት የታጀበ ቢሆንም፤ ታሪክን በነጣጣይና ቆሞ ቀር ትርክትነት የሚጠቀሙ የፖለቲካ ኃይሎች ሀገርን ዋጋ ማስከፈላቸውን አስረድተዋል። የመደመር መንግሥት በታሪክ እሳቤ ላይ ያለው አተያይም በኢትዮጵያ ትናንት፣ ዛሬና ነገ መካከል ያለውን ሚዛን በልኩ በማየት የተመሰረተ መሆኑን አስገንዝበዋል። የመደመር መንግሥት የታሪክ ዕይታ ያለፉ ጥንካሬና ክፍተቶችን ነቅሶ በማውጣት መፍትሔ አመላካች እሳቤ ማስቀመጡን አብራርተዋል። በዚህም የመደመር መንግሥት በኢትዮጵያ ትናንት፣ ዛሬና ነገ መካከል ጥልቅ ትስስር መኖሩን የሚያመላክት እሳቤ መሆኑን አንስተዋል። ኢትዮጵያ ካላት የታሪክ ሃብት አኳያ የምትገኝበት ሁኔታ የሚመጥነን አይደለም ያሉት ምሁሩ፤ በዚህም የመደመር መንግሥት ታሪክን እንደ ትምህርት በመውሰድ ታሪክ ሰሪ የሆነ እሳቤን የመዘርጋት አካሄድ ይከተላል ብለዋል። በአጠቃላይ የመደመር መንግሥት የኢትዮጵያ ታሪክ በትናንት፣ ዛሬና ነገ ትስስርና ቅብብሎሽ የሚሰራ እንደሚረዳ አብራርተዋል። የመደመር መንግሥት ቀደም ካሉት የዘውዳዊ፣ የደርግ፣ የኢሕአዴግ የኢትዮጵያ ሥርዓቶች ጋር ሲነፃጸር ለየት ያለ አዲስ ሀገር በቀል ዕይታን እንደሚከተል አስረድተዋል። በዚህም የመደመር መንግሥት ሥርዓትም ትናንትን ከዛሬና ከነገ ጋር ተደማሪ በማድረግ የኢትዮጵያን የታሪክ ውስንነቶች እየፈታ እንደሚገኝ አብራርተዋል። በዚህም ቀደምት የኢትዮጵያ የመንግስት አስተዳደር ስርዓቶች የትናንትን ታሪክ ያዩበት የነበረውን የአረዳድ ውስንነቶችን በማረም የመደመር መንግሥት እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል። የመደመር መንግሥት የታሪክ ዕይታም ከቀደምት የኢትዮጵያ መንግስታት አኳያ አዲስ ዕይታን በማምጣት ሚዛኑን ለጠበቀ አሰባሳቢ ትርክት ግንባታ ትኩረት የሚሰጥ መሆኑን አስረድተዋል። የመደመር መንግሥት የታሪክ አረዳድም አሰባሳቢና አስተሳሳሪ ዕይታ ያለው መሆኑን አንስተዋል። ታሪክንም የአንድ ወገን ብቻ አድርጎ ባለመመልከት በስፋትና በጥልቀት፤ በዘመንና ሁኔታ፣ በባህልና ሃይማኖት የሁሉም መሆኑን የሚያትት አሰባሳቢ ዕይታ እንዳለው አንስተዋል። በመደመር መንግሥት መጽሐፍም የኢኮኖሚ፣ ፖለቲካና ማህበራዊ ጉዳዮች ኢትዮጵያ ያሉባትን ስብራት ታሪካዊ ዳራ በሚገባ የተረዳ እንደሆነም አስረድተዋል። ከቀደሙት የኢትዮጵያ መንግስታት ርዕዮተ ዓለምም ሆነ ፖሊሲዎችና አስተዳደራዊ አቅጣጫዎች ከውጭ የሚቀዱ እንደነበር አስታውሰዋል። በዚህ ረገድ የመደመር መንግሥት እራስን በመመርመር ሀገር በቀል እሳቤን በማስቀመጥ ወደ ተግባር መግባቱን አንስተዋል።
የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን መከበር ሀገራዊ አንድነትን በማጠናከር ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ የጎላ አስተዋጽኦ አበርክቷል
Dec 3, 2025 108
ደብረብርሃን፤ ህዳር 24/2018 (ኢዜአ)፦ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን መከበር ሀገራዊ አንድነትን በማጠናከር ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ የጎላ አስተዋጽኦ ማበርከቱን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አገኘሁ ተሻገር አስታወቁ። በአማራ ክልል ደረጃ 20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን ማጠቃለያ መርሀ ግብር በደብረብርሃን ከተማ በድምቀት ተከብሯል። በበዓሉ ላይ የተገኙት የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር እንዳሉት የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን የኢትዮጵያ ህዝቦች በጋራ ለመኖር የተስማሙበት ነው። ቀኑ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ባህላቸውንና እሴቶቻቸውን በአደባባይ ወጥተው የሚገልጡበት እንደሆነም ተናግረዋል። በመሆኑም ጠንካራ ሀገር ለመገንባት የሚያስችል የፌደራል ስርዓት እንዲኖር በማድረግ ህብረ ብሔራዊነትን በማጠናከር ህዝቦች በአንድነት ተሳስረው እንዲኖሩ የላቀ አስተዋጽኦ ማበርከቱን አመልክተዋል። የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ለፍትህ፣ ለእኩልነትና ለዲሞክራሲ ግንባታ መሰረት የጣለ ነው ሲሉም አክለዋል። የአማራ ክልል ምክር ቤት ፈጉባኤ ወይዘሮ ፋንቱ ተስፋየ፤ በዓሉ በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች በአስተምህሮት፣ በበጎፈቃድ አገልግሎት፣ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት በማጎልበት ህብረ ብሔራዊ አንድነትን በሚያጠናክር መንገድ ሲከበር መቆየቱን ተናግረዋል ። የቀኑ አከባበር ህግ እና ህገ መንግስታዊ መሰረት ያለው መሆኑን ጠቁመው፤ ህዝቦች ባህል፣ ወጋቸውንና እሴቶቻቸውን ተጠቅመው የወል ትርክት ለመገንባት እድል የፈጠረ ነው ብለዋል ። የዘንድሮ አከባበር የታላቁ ህዳሴ ግድብ የተጠናቀቀበትና የይቻላል መንፈስን የገነባንበት እና ሌሎች ለሀገር የሚጠቅሙ ሜጋ ፕሮጀክቶችን አቅደን ወደ ስራ የገባንበት ወቅት ላይ መሆኑ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል። የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን መከበር ከጀመረ ወዲህ የህዝቦች አብሮነት፣ የአንድነትና የመደጋገፍ አሴት እያደገ መምጣቱን የገለጹት ደግሞ የደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት ናቸው። በከተማው የኢንዱስትሪና የኢንቨስትመንት መስፋፋትና ማደግ የዜጎችን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ በመምጣቱ ከህገ መንግስቱ ቱሩፋት የተገኘ መሆኑን አስታውቀዋል። ከበዓሉ ተሳታፊዎች መካከል ወይዘሮ መሰረት ቀጸላ የቀኑ መከበር ህገመንግስታዊ አስተምህሮትን ይበልጥ ለማጎልበት ያግዛል ብለዋል። በተለይ ሴቶች በህገመንግስቱ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ዘርፎች ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸው እለቱ ለሴቶች ልዩ እንደሆነ ተናግረዋል። አቶ ብስራት ታደለ በበኩላቸው የቀኑ መከበር ዜጎች እርስ በእርሳቸው በመተዋወቅ የነገን ተስፋ በጋራ ለመሰነቅ የሚያስችል መሆኑን አመልክተዋል። በተለይም ባህልን ጨምሮ ማህበረሰባዊ እሴቶችን ለመጠበቅና ለትውልድ ለማስተላለፍ የጎላ ሚና እንዳለው ገልጸዋል። በዓሉ እንደሀገር በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳእና ከተማ የፊታችን ህዳር 29 ቀን 2018 ዓም እንደሚከበር ታውቋል።
የብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ህብረ ብሔራዊ አንድነትን እያጎለበተ ነው
Dec 3, 2025 99
ሐረማያ፤ ህዳር 24/2018 (ኢዜአ)፦ የብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ከፋፋይ ትርክቶችን በማስቀረት ህብረ ብሔራዊ አንድነትን እያጎለበተ መሆኑን አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ምሁር ተናገሩ። ኢትዮጵያ የብዝኃ ቋንቋ፣ ባህል፣ ታሪክና እምነቶች መገኛ ሀገር ናት፤ ብዝኃ ማንነት፣ ባህል፣ ታሪክና እምነት ያላቸው ብሔረሰቦች ተዋደውና ተቻችለው በፍቅር የሚኖሩባት የሕብረ-ብሔራዊነት ተምሳሌት አገር ናት። በዚህም 20ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን "ዲሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት" በሚል መሪ ሀሳብ በተለያዩ መርኃ ግብሮች በመከበር ላይ ነው። የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህርና ተመራማሪ መሀመድ ሐሰን(ዶ/ር) ለኢዜአ እንዳሉት የብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን መከበር በልዩነት ውስጥ ያለውን አንድነት እያጎለበተ መጥቷል። በተለይ እለቱ በአብሮነት መከበሩ ከፋፋይ ትርክቶችን በማስቀረት ህብረ ብሔራዊ አንድነትን እያጎለበተ መምጣቱንም ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች በታሪክ ውስጥ ባህልና ቋንቋን ተጋርተዋል፣ እሴቶቻቸውንም አጎልብተዋልያሉት ዶክተር መሀመድ፤ በዚህም የጋራ እድልና እጣ ፈንታ አላቸው ብለዋል። ይህም በኢትዮጵያ የብሔሮች ብሔረሰቦና ህዝቦች ዘንድ ከፋፋይ ትርክት ቦታ እንደሌለው ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል። በተለይም በዓሉ የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች የተለያዩ ቋንቋ፣ ባህል፣ እምነትና ሌሎች እንዳሏቸውና በልዩነታቸው ውስጥ በጋራ አብረው እንደሚኖሩ የሚያሳዩበት በዓል ነው ብለዋል። በዓሉ አብሮነትና የቆየ ትስስርን እያጎለበተና ጠንካራ ሀገረ መንግስት መገንባት እያስቻለ ነው ሲሉም ተናግረዋል። ምሁራንም በልዩነት ውስጥ ያለውን አንድነትና ውበት የማጎልበትና ጠንካራ አገረ መንግስት የመገንባት ስራውን በጠንካራ መሰረት ላይ የማሳረፍ ስራ ላይ አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚገባቸውና ይህም እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
የብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን መከበር አብሮነትን ከማጠናከር ባለፈ ልማትን ለማፋጠን ቃላችንን የምናድስበት ነው - ተሳታፊዎች
Dec 3, 2025 90
ዲላ፤ ህዳር 24/2018(ኢዜአ)፦ የብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን መከበር አብሮነትን ከማጠናከር ባለፈ ልማትን ለማፋጠን ዳግም ቃላችንን የምናድስበት ነው ሲሉ በቡሌ ሆራ ከተማ በተከበረው መርሃ ግብር የተሳተፉ ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ ተሳታፊዎች ገለጹ። 20ኛው የብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ ከተለያዩ አካባቢ የመጡ የብሔር ብሔረሰቦች ተወካዮች በተገኙበት በቡሌ ሆራ ከተማ በድምቀት ተከብሯል። በዓሉን በማስመልከት ኢዜአ ያነጋገራቸው ተሳታፊዎች እንደገለጹት በዓሉ የእርስ በርስ ትውውቃቸውን ከማሳደግ ባለፈ ልማትን ለማፋጠን ዳግም ቃላቸውን የሚያድሱበት መሆኑን ተናግረዋል። ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል የቡርጂ የባህል አባት መሐመድ ወሌ ቀኑ እርስ በርስ በመተዋወቅ ግንኙነትን በማጠናከር ሀገራዊ አንድነታችንን የምናጸናበት ነው ብለዋል። በበዓሉ ላይ ባህላዊ እሴቶቻችንን ከማስተዋወቅ ባለፈ በየአካባቢያችን የሚከናወኑ የልማት ሥራዎችን ለማፋጠን ዳግም ቃላችንን የምናድስበት ነው ሲሉም ተናግረዋል። የተለያዩ የብሔር ብሔረሰቦች ተወካዮች በተገኙበት በዓሉ በጋራ መከበሩ የተለየ ስሜት እንደፈጠረበቸው ያነሱት ሌላው የበዓሉ ተሳታፊ ደግሞ የቦረና ዞን ሃደ ሲንቄ ጡሩ ሞሉ ናቸው። ቀኑ የብሔር ብሔረሰቦችን ባህሎች እንዲሁም የአኗኗር ዘይቤያቸውን ለማወቅና የራሳቸውንም ለማስተዋወቅ ዕድል እንደፈጠረላቸው ጠቅሰዋል። ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን በጋራ ቆመን እንዳሳካነው ሁሉ ሌሎች ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን አጠናቀን ሀገራዊ ብልጽግናን ለማሳካት አንድነትን ማጠናከር አለብን ብለዋል። ከጉራጌ ዞን የመጣችው ወጣት በጽናት ተመስገን በበኩሏ የብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ሕብረ ብሔራዊ አንድነታችንን ለዓለም ለማሳየት ምቹ አጋጣሚ የሚፈጥር ነው ብላለች። በተለይ ኢትዮጵያ የተለያዩ ቀለሞች፣ ባህሎችና ቋንቋዎች ባለቤት መሆኗን ገልጸው፤ በዓሉ አብሮነታችንና አንድነታችንን በማጠናከር ለልማትና ለሰላም በጋራ ለመቆም ጠቀሜታው የጎላ መሆኑንም አንስታለች። በኦሮሚያ ክልል ደረጃ 20ኛው የብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር እና የተለያዩ የብሔር ብሔረሰቦች ተወካዮች በተገኙበት በቡሌ ሆራ ከተማ መከበሩ የሚታወስ ነው።

ማህበራዊ
ቀኑ በስኬት እንዲከበር ዝግጅት ተደርጓል
Dec 3, 2025 82
ሆሳዕና፤ ህዳር 24/2018(ኢዜአ)፦በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለሚከበረው የብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ስኬታማነት ማህበረሰቡንና በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችን ያሳተፈ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አስታወቀ፡፡ ቢሮው ለበዓሉ ስኬታማነት የተደረጉ ቅድመ ዝግጅቶች በማስመልከት ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥቷል፡፡ በመግለጫው የቢሮው ኃላፊ አቶ ተመስገን ካሳ እንዳሉት፣ 20ኛው የብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል በስኬት እንዲከበር ከሰላምና ጸጥታ ጋር የተያያዙ ዝግጅቶች ተደርገዋል። የዝግጅት ሥራው ማህበረሰቡን፣ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችንና የሰላምና ጸጥታ ተቋማትን ያሳተፈ መሆኑንም ነው የጠቆሙት። በዓሉን ለማክበር እንግዶች ወደ ክልሉ መግባት እንደጀመሩ የጠቆሙት ሃላፊው የማረፊያና ሌሎች የአገልግሎት መስጫ ስፍራዎችን የማዘጋጀት ስራ እየተከናወነ ነው ብለዋል፡፡ በተለይም የከተማው ነዋሪ የበዓሉ ታዳሚዎችን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል ለሚከናወኑ ተግባራት ተባባሪ እንዲሆን አስገንዝበዋል። በበዓሉ አከባበር ሂደት የሚያጋጥሙ ወንጀሎችን ፈጥኖ ለመፍታት ጊዜያዊ ችሎቶች መቋቋማቸውንም ጠቁመዋል።
ለዘላቂ ሰላም ግንባታ የበኩላችንን እንወጣለን - የኃይማኖት አባቶች
Dec 3, 2025 71
ደሴ ፤ ህዳር 24/2018(ኢዜአ)፦የመከባበርና የአብሮነት እሴቶችን በማጠናከር ለዘላቂ ሰላም ግንባታ የበኩላቸውን እንደሚወጡ የሃይማኖት አባቶች ገለጹ። የደሴ ከተማ አስተዳደርና የደቡብ ወሎ ዞን የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ "ሐይማኖቶች ለሰላም፣ ለአብሮነትና ለመከባበር" በሚል መሪ ሃሳብ ውይይት እየተካሄደ ነው። በደሴ ከተማ እየተካሄደ ባለው መድረክ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ሥራ አስፈጻሚ አባልና የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ቦርድ አባል ሸህ እንድሪስ አሊ፣ ሁሉም ለሰላም ዘብ መቆም እንዳለበት አንስተዋል። ሰላም እንዲጸና በእምነት ተቋማት የሰላምን ዋጋ አበክረን ማስተማር ይኖርብናል ብለዋል። የደቡብ ወሎ ዞን ሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሰብሳቢና የዞኑ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ቆሞስ አባ ለይኩን ወንድይፍራው ፤ ሰላምን በዘላቂነት ለማፅናት በቅንጅት የተጀመረው ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል። ሕብረተሰቡ የሰላም ባለቤትነቱን በተግባር እንዲያፀና እንደ ሀይማኖት አባት የሰላምን ዋጋ በማስገንዘብ ሚናቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል። የመከባበር፣ የአብሮነትና የመተጋገዝ ባህልን በማጠናከር ለዘላቂ ሰላም ግንባታ ሁሉም የበኩሉን መወጣት እንዳለበትም ቆሞስ አባ ለይኩን አንስተዋል። የደሴ ከተማ አስተዳደር ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ምክትል ሰብሳቢና የደሴ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሸህ ሀሰን ሀሚዲን በበኩላቸው እንዳሉት፤ የሁሉም እምነቶች አስተምህሮ ሰላምና አንድነትን መሰረት ያደረገ ነው።ሁሌም ስለሰላም አስፈላጊነት በማስተማር የድርሻችንን እንወጣለን ብለዋል። ዘላቂ ሰላም የሁሉ ነገር መሰረት ነው ያሉት ደግሞ የደቡብ ወሎ ዞን ሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ አባልና የመካነ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ማዕከላዊ ሰሜን ኢትዮጵያ ሲኖዶስ ፕሬዚዳንት ቄስ ዋኘው አንዳርጌ ናቸው። የአካባቢው ሰላም ተጠናክሮ እንዲቀጥል በመደገፍ የበኩላቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል። የሕዝብን ሰላም በመንሳት ግፍና በደል የሚፈጽሙ የጥፋት ተላላኪዎችን በጋራ በቃችሁ ልንላቸው ይገባል ያሉት ደግሞ የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ መኮንን ናቸው። የሐይማኖት አባቶች አጥፊዎችን በመምከር፣ በማስተማርና በመገሰፅ የሰላም አማራጭን እንዲከተሉ በማድረግ የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው አመልክተዋል። የደሴ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ በበኩላቸው፤ ለከተማው ዘላቂ ሰላምና ልማት መጠናከር ሁሉም ሀላፊነት አለበት ብለዋል። በተለይ የሀይማኖት አባቶች ምዕመናን በማስተማርና በመምከር ሰላም፣ አብሮነትና ልማትን አጠናክሮ ለማስቀጠል ቀጣይነት ያለው ሥራ መስራት እንዳለባቸው አመልክተዋል። ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀናት በሚቆየው የምክክር መድረክ ከፌዴራል፣ ከክልል፣ ደቡብ ወሎ ዞን እና የደሴ ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ የሀይማኖት አባቶች በመሳተፍ ላይ ናቸው።
በክልሉ አካል ጉዳተኞችን ተጠቃሚ በማድረግ ረገድ አበረታች ውጤት እየታየ ነው
Dec 3, 2025 104
ባህር ዳር ፤ ሕዳር 24/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል የአካል ጉዳተኞችን ተሳትፎና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት በማሳደግ ረገድ አበረታች ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን የክልሉ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን ገለጸ። “አካል ጉዳተኝነትን የሚያካትት ማህበረሰብ መገንባት ለተሻለ ማህበራዊ እድገት” በሚል መሪ ሃሳብ የአካል ጉዳተኞች ቀን በባህር ዳር ከተማ ዛሬ ተከብሯል። የክልሉ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ፍሬሰላም ዘገየ ለኢዜአ እንዳሉት፤ በክልሉ የአካል ጉዳተኞችን መብት በማስጠበቅና ተጠቃሚነታቸውን በማረጋገጥ ረገድ አበረታች ለውጦች እየታዩ ነው። በክልሉ የሚኖሩ አካል ጉዳተኞችን ተጠቃሚነታት ለማረጋገጥ አደረጃጀቶች ተፈጥረው እየተሰራ እንደሚገኝ አንስተዋል። የአካል ጉዳተኞችን መብት በማስከበር ረገድ ብዙ መሻሻሎች እንዳሉ ጠቁመው አሁን ላይ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል። የአማራ ክልል ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወይዘሮ ንጹህ ሽፈራው በበኩላቸው እንዳሉት፤ የአካል ጉዳተኞችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የበለጠ ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ ነው። አካል ጉዳተኞችን አካታች የሆነ የፖለቲካ፣ የልማትና የኢኮኖሚ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸው፤ አሁንም በአመለካከት ደረጃ ያልተፈቱ ችግሮች መኖራቸውንና ለዚህም በጋራ መስራት ይገባል ብለዋል። አካል ጉዳተኞች በሚችሉት አቅም ሁሉ ሰርተው ራሳቸውንም ሆነ ሀገራቸውን መጥቀም እንዲችሉ የቅንጅት ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ሲሉም አረጋግጠዋል። በባህር ዳር ከተማ አካል ጉዳተኞች በሚፈጠሩ የስራ እድሎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ በልዩ ትኩረት እየተሰራ ነው ያሉት ደግሞ የከተማ አስተዳደሩ ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ሰብለ ዘውዱ ናቸው። አካል ጉዳተኞች መብታቸውን በማስከበር ራሳቸውንና ሌሎችን የመጥቀም እምቅ አቅማቸውን በስራ ላይ እንዲያውሉ ለማድረግ የክትትልና ድጋፍ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። በመድረኩ የክልሉና የከተማ አስተዳደሩ የዘርፉ አመራሮችና የአካል ጉዳተኞች ተወካዮች ተሳታፊ ሆነዋል።
ድጋፉ የጤና አገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል ያግዛል
Dec 3, 2025 70
ሰመራ፤ ሕዳር 24/2018(ኢዜአ)፦ ለአፋር ክልል ጤና ቢሮ የተደረገው የህክምና መሳሪያዎች ድጋፍ የጤና አገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል ያግዛል ሲሉ የቢሮው ሃላፊ አቶ ያሲን ሃቢብ ተናገሩ። በካናዳ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ያሰባሰቡትን የህክምና መሳሪያዎች በተወካያቸው አማካኝነት ለአፋር ክልል ጤና ቢሮ አስረክበዋል። ድጋፉ ከ30 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ የወጣበት መሆኑም ተመላክቷል። በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የአፋር ክልል ጤና ቢሮ ኀላፊ አቶ ያሲን ሃቢብ እንዳሉት፤ ቢሮው በጎ ፈቃደኞችን እና አጋዥ አካላትን በማስተባበር የጤና አገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል ዘርፈ ብዙ ተግባራት በማከናወን ላይ ይገኛል። ዛሬ የተደረገው ድጋፍም በክልሉ በሚገኙ የጤና ተቋማት የጤና አገልግሎት አሰጣጡን በእጅጉ የሚያግዝና የአቅርቦት ዕጥረትን የሚያቃልል ነው ብለዋል። ለተደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን ያቀረቡት አቶ ያሲን፤ ሌሎች ግብረሰናይ ድርጅቶችና በጎ አድራጊዎችም ይኸንን አርአያ ተከትለው መሰል ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል። ድጋፉን ያስረከቡት የበጎ ፈቃደኞቹ ተወካይ ወይዘሮ ብርትኳን ካሳ በበኩላቸው፤ ወገን ለወገን የሚያደርገው ድጋፍ በእኛ በኢትዮጵያዊያን የነበረና አሁንም ያለ መልካም ባህላችን ነው ብለዋል። በካናዳ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በትብብር በመሆን የሚያደርጉት እገዛ በዚህ ብቻ የሚያበቃ ሳይሆን ቀጣይነት ያለው መሆኑን ገልፀዋል። በድጋፍ ከተበረከቱ የህክምና መሳሪያዎች መካከል ዘመናዊ የህሙማን አልጋዎች፣ ማሞቂያዎች፣ ዊልቸር፣ ስትሬቸር፣ ክራንች እንዲሁም ኮምፒውተሮች ይገኙበታል።
ኢኮኖሚ
የተከናወኑ ሪፎርም ስራዎች በሰው ሀብት ልማት ላይ የተሻለ ለውጥ እንዲመዘገብ አስችለዋል
Dec 3, 2025 103
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 24/2018 (ኢዜአ)፦በሥራና ክህሎት ልማት የተከናወኑ የሪፎርም ስራዎች በሰው ሀብት ልማት ላይ የተሻለ ለውጥ እንዲመዘገብ ማስቻሉን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ። የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደር ቢሮዎች እንዲሁም ተጠሪ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ለሶስት ቀናት በቢሺፍቱ ከተማ ያካሄደውን የምክክር መድረክ አጠናቋል። በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል፤ የሰው ሃብት ልማትን ለማሻሻል የተከናወኑ የሪፎርም ተግባራት ተጨባጭ ስኬት እያስመዘገቡ ነው ብለዋል። በተቋም ደረጃ የተወሰዱ የሪፎርም እርምጃዎችም በአዳዲስ የለውጥ እሳቤ የሀገር ውስጥ ምርታማነትና የቴክኖሎጂ ሃሳቦችን የማፍለቅ አቅም እያሻሻለ መሆኑን ገልጸዋል። በሰው ሃብት ልማት የተፈጠረው አቅም አምራች ኢንዱስትሪው በእውቀትና ክህሎት የበለጸገ የሰው ሃይል እንዲያገኝ ማስቻሉን አንስተዋል። በእውቀትና ክህሎት የበለጸገ የሰው ሃብት ለሥራ ኢንዱስትሪው ለማቅረብም በሰው ሰራሽ አስተውሎትና በሳይበር ቴክኖሎጂ የታገዘ ስልጠና እየተሰጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል። የቴክኒክ እና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማትም በሰው ሃብት ልማት ላይ የተሰጣቸውን ተልዕኮ በብቃት በመወጣት ትርጉም ያለው ሥራ እየሰሩ መሆናቸውን አንስተዋል። ባለፉት ጥቂት ዓመታት በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት የተሰጡ የአጭር፣ መካከለኛና የረጅም ጊዜ ስልጠናዎች ለሥራ ዕድል ፈጠራ ምቹ ምኅዳር መፍጠራቸውን አብራርተዋል። በእውቀትና ክህሎት የበለጸገ የሰው ሃብት የማሰልጠን ተግባርም ከገበያ ፍላጎትና ጥራት ጋር የተጣጣመ የቴክኖሎጂ ሽግግር በመፍጠር አመርቂ ውጤት መገኘቱን ጠቅሰዋል። በሥራ ዕድል ፈጠራ የተገኙ ስኬቶችም ዜጎች ከራሳቸው አልፎ ሃብትና ንብረት በማፍራት በሀገራቸው የኢኮኖሚ ዕድገት አሻራቸውን እንዲያሳርፉ እያደረገ መሆኑን አንስተዋል።
በክልሉ የአርሶ አደሩን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተሰራው ስራ ውጤታማ ነው
Dec 3, 2025 65
ሀዋሳ፤ ሕዳር 24/2018(ኢዜአ)፦በሲዳማ ክልል የአርሶ አደሩን የምግብ ዋስትናና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ውጤታማ መሆናቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ተናገሩ። በክልሉ በመኸር ወቅት በተለያዩ ሰብሎች ከለማው መሬት 3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ ተመላክቷል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በደቡባዊ ሲዳማ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች በመኸር ወቅት የለማ ሰብልን ተመልክተዋል። በዚህ ወቅት ርዕሰ መስተዳድሩ እንደገለጹት፤ በክልሉ የአርሶ አደሩን የምግብ ዋስትናና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ተግባራዊ እየተደረጉ ያሉ ሥራዎች ውጤታማ ሆነዋል። በመኸር ወቅት የለማ ሰብል በጥሩ ቁመና ላይ እንደሚገኝ የገለጹት አቶ ደስታ ይህም በምግብ ራስን ለማቻል፣ ገበያን ለማረጋጋትና ለኢንዱስትሪ ግብአት እንዲሆን የተቀመጠውን ግብ ማሳካት እንደሚያግዝ አመላካች ነው ብለዋል። ከዚህ በፊት ምርት የማይሰጡ መሬቶች ጭምር እንዲታረሱ የምርት ማሳደጊያ ቴክኖሎጂ አቅርቦትን ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራቱንም ጠቅሰዋል። መኸር አብቃይ በሆኑ የክልሉ ደጋማ አካባቢዎች መሬቱ በአሲዳማነት የመጠቃት እድሉ ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው አሲዳማ መሬትን በኖራ በማከም ምርታማነትን የማሳደግ ስራም በልዩ ትኩረት ተሰርቷል ብለዋል። በመኸር ወቅት በክልሉ ከ117 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በስንዴ፣ ገብስ፣ ጤፍ እና ሌሎች ዋና ዋና ሰብሎች መልማቱን የተናገሩት ደግሞ የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ መምሩ ሞኬ ናቸው። ከዚህም 3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ይሰበሰባል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል። እንደ ኃላፊው ገለጻ፤ በክልሉ በመኸር ወቅት ከለማው አጠቃላይ መሬት 45 በመቶ የሚሆነው በኩታ ገጠም የለማ ነው። በአሁኑ ወቅትም ምርትን በአግባቡ መሰብሰብ፣ የገበያ ትስስር መፍጠርና ለፋብሪካ ግብዓት ማቅረብ ትኩረት የተሰጣቸው መሆኑን አቶ መምሩ ጠቁመዋል። ከአሰላ ብቅል ፋብሪካ ጋር በተፈጠረ የገበያ ትስስር ከ35 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት በቢራ ገብስ እንዲለማ ተደርጓል ብለዋል። በዳራ ኦቲልቾ ወረዳ የአበራ ጌሌዴ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ደጋጋ ሀጣላ፣ ስምንት አርሶ አደሮች በጋራ ሆነው በ12 ሄክታር መሬት ላይ ስንዴ በኩታ ገጠም እያለሙ መሆናቸውን ገልፀዋል። ከአምስት ዓመት በፊት የምርት ማሳደጊያ እና ዘመናዊ የግብርና አሰራር ባለመጠቀማቸው የሚያገኙት ምርት ከቤት ፍጆታ ያለፈ እንዳልነበርና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ለገበያ ለማቅረብ ጭምር ተግተው እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል ። በዚህም ከማሳቸው በሄክታር ከ40 ኩንታል በላይ ምርት እንደሚሰበስቡ አስረድተዋል፡፡ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ ምልከታ ያደረጉት በዞኑ ሁላ እና ዳራ ኦቲልቾ ወረዳዎች በኩታ ገጠም የለማ የመኸር ሰብልን ነው።
ኢትዮጵያ ስታትስቲክስ በልማት ዕቅድና ትግበራ ሂደት ስትራቴጂክ ሚና እንዲኖረው አድርጋለች
Dec 3, 2025 102
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 24/2018(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ ብሔራዊ የስታትስቲክስ ልማት በልማት ዕቅዶችና በትግበራ ሂደት ስትራቴጂክ ሚና እንዲኖረው ማድረጓን የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር በከር ሻሌ(ዶ/ር) ገለጹ። ዋና ዳይሬክተሩ ይህን ያሉት 19ኛው የአፍሪካ ስታትስቲክስ ተቋማት ዋና ዳይሬክተሮች ኮሚቴ ስብሰባ ዛሬ በአዲስ አበባ በተከፈተበት መርኃ ግብር ላይ ነው። ኢትዮጵያ ለስታትስቲክስ ዘርፍ ከፍተኛ ትኩረት መስጠቷን በመግለፅ፥ በመተግበር ላይ ያለውን የሦስት ዓመት ብሔራዊ የስታትስቲክስ ልማት ፕሮግራም ለአብነት አንስተዋል። በዚህም የስታትስቲክስ አቅምን የማጠናከር፣ የዳታን ወቅታዊነትና ጥራት የማሻሻል እንዲሁም የግብርና ቆጠራ እና የኢኮኖሚ ተቋማት ቆጠራን ጨምሮ ስትራቴጂክ ጥናቶች እየተካሄዱ ነው ብለዋል። በመረጃ ላይ የተመሠረተ የፖሊሲ አወጣጥና ውሳኔ አሰጣጥን የሚደግፍ የተቀናጀና አስተማማኝ የስታትስቲክስ ሥርዓት እየተገነባ መሆኑን ጠቅሰዋል። ይህም ኢትዮጵያ የስታትስቲክስ አቅሟን ለማጠናከር ያላትን የማይናወጥ ቁርጠኝነት የሚያሳይና ስታትስቲክስን በልማት ዕቅድና ትግበራ ስትራቴጂካዊና ብሔራዊ ሚና እንዲኖረው ማድረጓን የሚያሳይ መሆኑን ተናግረዋል። የአፍሪካ ስታትስቲክስ ተቋማት ዋና ዳይሬክተሮች ኮሚቴ ሊቀመንበር ንያካሲ ሳንያንግ በበኩላቸው፥ የዳታ ፍላጎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ የስታትስቲክስ ባለሙያዎች ሚና ከመቼውም ጊዜ በላይ ወሳኝ ሆኗል ብለዋል። በአህጉሪቱ የስታትስቲክስ ስምምነቶችንና የተቋቋሙ የቴክኒክ ቡድኖችን በተሟላ ሁኔታ ወደ ተግባር ማስገባት እንደሚገባ ገልጸዋል። በዚህ ዘመን ዳታ ከመረጃነት ባለፈ የልማት አንቀሳቃሽ ኃይል በመሆኑ ጥራት ላለው ስታትስቲክስ በቅንጅት መትጋት እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተዋል። በተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን የአፍሪካ ስታትስቲክስ ማዕከል ዳይሬክተር ሳሙኤል ኮቢና፥ ስታትስቲክስ የአፍሪካን የልማት ችግሮች ለመፍታት ዋነኛው መሣሪያ መሆኑን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት በአስደማሚ የለውጥ ጎዳና ላይ መሆኑን ጠቅሰው፥ መንግሥት ለዘርፉ የሰጠውን ትኩረት አድንቀዋል። የስታትስቲክስ ማኅበረሰቡ ከቁጥር ባለፈ የአፍሪካውያንን መጻኢ እጣ ፋንታ የተሻለ የሚያደርጉና በትክክል የሚያመላክቱ መረጃዎችን ማመንጨት አለበት ብለዋል። በተለይም መንግሥታት የሚያሳልፏቸው ውሳኔዎች በመጪው ትውልድ ላይ የሚኖራቸውን ተጽዕኖ ታሳቢ እንዲያደርጉ ትክክለኛ መረጃዎችን በማቅረብ ማገዝ ያስፈልጋል ነው ያሉት። ማኅበራዊ አመልካቾች ከኢኮኖሚ አመልካቾች ጋር ያላቸውን ጠንካራ ትስስር በማሳየት ማንም ከዕድገትና ከልማት ወደ ኋላ እንዳይቀር ማረጋገጥ እንደሚገባም ገልጸዋል። የአፍሪካ ስታትስቲክስ ማዕከል ከዓለም አቀፉ የስታትስቲክስ ተቋም ጋር በመተባበር ለአባል ሀገራት የሚያደርገውን ድጋፍና ስትራቴጂያዊ አጋርነት እንደሚያጠናክር አረጋግጠዋል።
ኢትዮጵያ አረንጓዴ ፋይናንስን የረጅም ጊዜ ስትራቴጂ እንዲሆን በምታደርገው ጥረት የካፒታል ገበያ ቁልፍ ሚና አለው
Dec 3, 2025 65
አዲስ አበባ፤ ህዳር 24/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ አረንጓዴ ፋይናንስን የረጅም ጊዜ ስትራቴጂ እንዲሆን በምታደርገው ጥረት የካፒታል ገበያ ቁልፍ ሚና እንዳለው የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ በረከት ፍስሀጽዮን ገለጹ፡፡ በአዲስ ዓለም አቀፍ የስብሰባ ማዕከል እየተካሄደ ያለው ሁለተኛው ቀጣናዊ የካፒታል ገበያ ስብሰባ ዛሬ ሁለተኛ ቀኑን ይዟል፡፡ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ በረከት ፍስሀጽዮን በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ልማት መገንባት የሚየስችል ጥረት እያደረገች ነው፡፡ ኢትዮጵያ የዜጎች ብልጽግና መሰረት የሚጥል የአረንጓዴ ሥነ ምህዳር ለመፍጠር በርካታ ተግባራትን ማከናወኗን ገልጸዋል፡፡ በአረንጓዴ ፋይናንስ ስርዓት በትራንስፖርት፣ በግብርና፣ በኢነርጂ፣ በኢንዱስትሪና ከተማ መሰረተ ልማት የካርበን ልቀትን መቀነስ የሚያስችሉ ስራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ሪፎርም በአረንጓዴ ፋይናንስ እና በካፒታል ገበያ መካከል ትስስር በመፍጠር የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን መቋቋም የሚያስችል ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ መመሥረት እንደ ሀገር አዲስ የፋይናንስ ዝማኔን እንደሚፈጥር በመግለጽ፤ ይሄውም ከብሔራዊ የትኩረት አጀንዳዎች ጋር የተያያዘ መሆኑን አንስተዋል፡፡ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ አይበገሬነትን፣ ዘላቂነት እና የኢኮኖሚ ሽግግርን ብሔራዊ የትስስር አጀንዳ በማድረግ የአየር ንብረት ፖሊሲን መተግበር የሚያስችሉ ተግባራትን እውን ማድረጓን ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ተወዳዳሪነትን፣ ሥራ ፈጣሪና ፈጣን ዕድገትን በማስመዝገብ ለኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ ዕድገት ጉልህ አበርክቶ እንዳለው ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ የአረንጓዴ ፋይናንስ የረጅም ጊዜ ስትራቴጂ እንዲሆን በምታደርገው ጥረት የካፒታል ገበያ ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት ገልጸው፤ መንግሥት የተቋማትን የቁጥጥር ስርዓት በማጠናከር የፋይናንስ ዘርፉን እየደገፈ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ የኢኮኖሚ ሽግግሩን በማሳለጥ ዘላቂ ዕድገት ማረጋገጠ የሚያስችል ቁልፍ መሳሪያ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያን ዘላቂ ልማት ግቦች እውን ለማድረግ የግሉ ዘርፍ ወሳኝ መሆኑን ገልጸው፤ አጋር አካላት፣ ባለሃብቶችና የዘርፉ ተዋንያን በትብብር መሥራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
በዲጂታል ዘመን የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን ለመከላከልና መፍትሄ ለመስጠት አዲስና ዓለም አቀፋዊ የትብብር ሞዴል መገንባት ያስፈልጋል
Dec 3, 2025 88
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 24/2018(ኢዜአ)፦ በዲጂታል ዘመን የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን ለመከላከልና መፍትሄ ለመስጠት አዲስና ዓለም አቀፋዊ የትብብር ሞዴል መገንባት እንደሚያስፈልግ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ገለጹ። የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ያዘጋጀው የ2025 ዳይመንድ ክለብ ሲምፖዚየም "አካታች ወደፊትን ለመፍጠር ዓለም አቀፍ የዲጂታል አመራር ማጠናከር" በሚል መሪ ሃሳብ ተካሄዷል። በሲምፖዚየሙ መክፈቻ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር)፤ የኢትዮጵያ ዲጂታል እድገት አበረታች መሆኑን ገልጸው፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች በዲጂታል መለያ ሥርዓቶች ውስጥ እየተካተቱ መሆኑን አስታውቀዋል። የዲጂታል መሠረተ ልማቶች እየተስፋፉ እንዲሁም በኤሌክትሮኒክ የሚሰጡ የመንግስት አገልግሎቶች እያደጉ መምጣታቸውን በአብነት አንስተዋል። በቅርቡ የፀደቀው የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ አካታች የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማረጋገጥና የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማጎልበት ቁልፍ ሚና እንዳለው አጽንኦት ሰጥተዋል። በዓለም ላይ ቴክኖሎጂን በአግባቡ አለመጠቀም አዲስ ፈተና የመፍጠር አቅም እንዳለው ጠቁመው፤ ይህን ፈተና ለመሻገር ሀገራት ትብብራቸውን ማጠናከር አለባቸው ብለዋል። የመረጃ ግላዊነት፣ የሳይበር ደህንነት እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት ላይ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች በአንድ ሀገር አቅም ሊፈቱ እንደማይችሉ አመላክተዋል። በመሆኑም በዲጂታል ዘመን የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን ለመከላከልና መፍትሄ ለመስጠት አዲስና ዓለም አቀፋዊ የትብብር ሞዴል መገንባት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል። የአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ደረጄ እንግዳ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ዘመኑ ዲጂታል ቴክኖሎጂ ዓለምን ባልተጠበቀ ፍጥነት እየቀረጸ ያለበት ጊዜ መሆኑን ገልጸዋል። ዩኒቨርሲቲው ባሉት የልህቀት ማዕከላት በመታገዝ በአህጉር ደረጃ ተጽዕኖ ፈጣሪ ለመሆን እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ተቋሙ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ላይ ያተኮረ ፈር ቀዳጅ ዩኒቨርሲቲ መሆኑን አስታውሰው፤ የአፍሪካን ቴክኖሎጂ የሚቀርጹ ተመራማሪዎች እና ዲጂታል መሪዎች ለማፍራት ቁርጠኛ መሆኑን ጠቁመዋል። የዓለም አቀፉ የቴክኖሎጂ ፕሮፌሽናል ፕሮግራም ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ጁንሴኦክ ሀዋንግ መድረኩን ላዘጋጁ አካላት ምስጋና አቅርበዋል። ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር የተለያዩ ስራዎችን በጋራ እያከናወኑ መሆኑን ገልጸው፤ ትብብሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። በቀጣይም ትልቁን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ዩኒቨርሲቲ ለመክፈት አመራሩ ቁርጠኛ መሆኑን አመላክተዋል።
ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ አካታች የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማረጋገጥ ቁልፍ ሚና ይጫወታል
Dec 3, 2025 123
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 24/2018 (ኢዜአ)፦ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ አካታች የኢኮኖሚ ዕድገትን ይበልጥ ለማረጋገጥ ቁልፍ ሚና የሚጫወት መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ገለጹ። የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ያዘጋጀው የ2025 'ዳይመንድ ክለብ ሲምፖዚየም' Club Symposium) "አካታች ወደ ፊትን ለመፍጠር ዓለም አቀፍ የዲጂታል አመራር ማጠናከር" በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ነው። በሲምፖዚየሙ መክፈቻ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ባደረጉት ንግግር ቴክኖሎጂ የዓለምን ከባድና ወስብስብ ችግሮች ለመፍታት ዕድሎችን ይዞ መምጣቱን ተናግረዋል። በሌላ በኩል ቴክኖሎጂን በአግባቡ አለመጠቀም አዲስ ፈተናዎችን የመፍጠር አቅም እንዳለው ጠቁመው፤ ይህን ፈተና ለመፍታት ሀገራት ትብብራቸውን የበለጠ ማጠናከር አለባቸው ብለዋል። በቅርቡ የፀደቀው የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ አካታች የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማረጋገጥና የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማጎልበት ቁልፍ ሚና እንዳለውም ነው አጽንኦት የሰጡት። የኢትዮጵያ ዲጂታል እድገት አበረታች መሆኑን ገልጸው፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች በዲጂታል መለያ ሥርዓቶች ውስጥ እየተካተቱ መሆኑን ተናግረዋል። የዲጂታል መሠረተ ልማቶች እየተስፋፉ እንዲሁም ኤሌክትሮኒክ የመንግስት አገልግሎቶች እያደጉ መምጣታቸውን አንስተዋል። የመረጃ ግላዊነት፣ ሳይበር ደህንነት እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት ላይ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች በአንድ ሀገር ብቻ ሊፈቱ እንደማይችሉ አመላክተዋል። የሰዎች መብቶች የሚጠበቅበት እና ፈጠራን ከድንበር በላይ እንዲያድግ የሚያስችል አዲስ ዓለም አቀፍ የትብብር ሞዴሎች መገንባት እንደሚገባም ጠቁመዋል። የዛሬው ሲምፖዚየም ለመነጋገር ብቻ ሳይሆን ወደ ተግባር ለመሸጋገር የሚያስችል ጊዜ መሆን እንዳለበት ተናግረዋል።
በኢትዮ ኮደርስ ስልጠና አለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለመሆን የሚያስችል ዕውቀት ቀስመናል- የአሪ ዞን ሰልጣኞች
Dec 3, 2025 71
ጂንካ፤ ህዳር 24/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮ ኮደርስ ስልጠና አለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለመሆን የሚያስችል ዕውቀት መቅሰማቸውን የአሪ ዞን የኢትዮ ኮደርስ ሰልጣኞች ተናገሩ። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢንሺዬቲቭ በሀገሪቱ በዲጂታል ክህሎት የታገዘ ማህበረሰብን ለመፍጠርና ዲጂታል ኢትዮጵያን ለመገንባት የሚያግዝ የኢትዮ -ኮደርስ ስልጠና በሁሉም አካባቢዎች እየተሰጠ ነው። በስልጠናው ላይ እየተሳተፉ የሚገኙ የአሪ ዞን ወጣቶችም ስልጠናው የዲጂታል ክህሎታቸውን በማሳደግ በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሚያደርጋቸውን እውቀት አንደቀሰሙ ተናግረዋል። በዞኑ የጂንካ ከተማ ነዋሪ ገላዬ ስምዖን፥ መንግስት በነፃ ለዜጎች ያመቻቸው የ5 ሚሊዮን ኮደርስ ስልጠና የዲጂታል ክህሎታቸውን በማሳደግ በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሚያደርጋቸውን እውቀት ማግኘታቸውን ጠቁመዋል ። በአሁኑ ወቅት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዕውቀትን ማሳደግ ተወዳዳሪ ለመሆን የሚያስችል አቅም ለመፍጠር እንደሚያግዝ ጠቅሶ፥ ስልጠናው ዲጂታል ኢትዮጵያን በመገንባት ሀገራዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ ለተጀመረው ጥረት አጋዥ መሆኑንም ገልጸዋል። በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና በዳታ አናሊስስ ኮርሶችን ያጠናቀቀው ገላዬ ስምኦን፥ በተለይ የዳታ አናሊስስ ኮርስ ለሁለተኛ ዲግሪ ማሟያ ለሚሰራው የመመረቂያ ፅሁፍ በእጅጉ እንዳገዛቸው አስረድተዋል። ሌላኛው አስተያየት ሰጪ የጂንካ ከተማ ነዋሪው ወጣት ኬብሮም ዕቁባይ በበኩሉ የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ለወጣቱ ትልቅ እድል ይዞ መምጣቱን ተናግሯል። ስልጠናው ጠቃሚና አለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለመሆን የሚያስችል ዕውቀት እንደሚያስጨብጥ ገልፆ በዳታ ሳይንስ እና በፕሮግራሚንግ የሚሰጠውን ስልጠና በማጠናቀቅ ሰርተፊኬት ማግኘቱን ጠቁሟል ። በአሪ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ የማህበራዊ ሚዲያ ሪፖርተር እየሩሳሌም ይንቲሶ በበኩሏ ስልጠናው ለጋዜጠኝነት ሙያ እጅግ አጋዥና የዲጂታል ዕውቀትን የሚያልቅ እንደሆነም ጠቁማለች። በፕሮግራሙ ከሚሰጡ አራት ስልጠናዎች አርቲፊሻል ኢንተለጀንስና ዳታ አናሊስ ኮርሶችን ማጠናቀቋን ጠቁማ፥ በዌብ-ፕሮግራሚንግ እና የአንድሮይድ ማበልፀግ ኮርሶችን ለማጠናቀቅም ማቀዷን ገልፃለች። ሌሎች ወጣቶችም የዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማህበራዊ ሚዲያ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ እየሰራች እንዳለችም ተናግራለች። የአሪ ዞን ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ይኼነው ተስፋዬ በበኩላቸው የኢትዮ ኮደርስ ስልጠናን ውጤታማ ለማድረግ ከሌሎች ተቋማት ጋር በመቀናጀት በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም ገለጸዋል። በዞኑ በሶስት ዓመታት ውስጥ ከ12 ሺህ 400 በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች ስልጠናውን ለመስጠት መታቀዱን ጠቁመው ካለፈው ዓመት እስካሁን ከ4 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች ስልጠናው መሰጠቱን ጠቁመዋል። ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ቢሮ በተገኘ መረጃ መሰረት በክልሉ ከ235 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ለመስጠት እየተሰራ መሆኑም ተመላክቷል።
ተቋማት እና ዘርፎች የሰው ሰራሽ አስተውሎት አጠቃቀምን የውጤት መለኪያቸው ማድረግ አለባቸው
Dec 2, 2025 162
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 23/2018(ኢዜአ)፦ እያንዳንዱ ተቋም እና ዘርፍ የሰው ሰራሽ አስተውሎትን አጠቃቀምን የውጤት እና ግብ መለኪያ በማድረግ ሊሰራ እንደሚገባው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አስገነዘቡ። “በመደመር መንግሥት ዕይታ፣ የዘርፎች እመርታ” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ለብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች የማጠቃለያ ስልጠና በሰጡበት ወቅት ካነሷቸው ሀሳቦች መካከል አንዱ የዲጂታል ዘርፉን የተመለከተ ይገኝበታል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ዲጂታል ዘርፉን አስተሳሰሪ አቅም መሆኑን ገልጸው መንግስት የዲጂታል መታወቂያ፣ ሞባይል ባንኪንግ እና ዘመናዊ የክፍያ ዘዴዎች የማስፋት ስራ እያከናወነ መሆኑን አመልክተዋል። የሰው ሰራሽ አስተውሎት እና ኳንተም ሳይንስ የሰው ልጆች አኗኗር፣ ስራ እና እሳቤ እየየቀሩ እንደሚገኙም ገልጸዋል። ቴክኖሎጂን መቀበል አለብን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሰው ሰራሽ አስተውሎት የኃይልን፣ የምርት እና የተሳትፎ ሕግጋትን እንደገና እየጻፈ እንደሚገኝ አስረድተዋል። ፋይዳ፣ ፓስፖርት፣ መሶብ፣ ሞባይል ባንኪንግ፣ ዘመናዊ የክፍያ ዘዴ፣ የጉምሩክ እና ገቢዎች ዲጂታል አገልግሎት እንዲሁም የተቀናጀ የፋይናንስ አስተዳደር መረጃ ሥርዓት(ኢፍሚስ) በሀገር ውስጥ አቅም እየጎለበተ እና እያደገ መሄድ እንዳለበትም አስገንዝበዋል። የተለያዩ ዘርፎች ምን ያህል ሰው ሰራሽ አስተውሎትን ተጠቅመዋል? ብለን ከአሁኑ መለካት ካልጀመርን ዘመን መዋጀትን ብንፈልግም አንደርስበትም ነው ያሉት። ለሁሉም ስራ ቴክኖሎጂን መጠቀም እንደሚያስፈልግ ጠቁመው የተሟላ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎች ጋር ማስተሳሰር ግድ እንደሚል አስገንዝበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአንድ ግቦች በሚል ባነሱት ሀሳብ እያንዳንዱ ከተማ የአንድ መሶብ አገልግሎት መክፈት እንዳለበትም አንስተዋል። በ100 ፐርሰንት ግቦች ውስጥም የፋይዳ መታወቂያ ሙሉ ለመሉ በኢትዮጵያ መዳረስ እንዳለበት ገልጸው ለዚህም በሁሉም የአስተዳደር መዋቅሮች አበክሮ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል። የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ በጣም ወሳኝ ስራ መሆኑን ጠቁመውም ኢኒሼቲቩ መቶ ፐርሰን መሳካት አለበት ብለዋል። እያንዳንዱ ተቋም እና ዘርፍ የሰው ሰራሽ አስተውሎትን ምን ያህል ተጠቀምኩኝ? በሚል ግብ ማስቀመጥ እንደሚኖርበትም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለጹት። የሰው ሰራሽ አስተውሎት አጠቃቀም ካላደገ የሚታሰበውን ትራንስፎርሜሽንና ትስስር ማምጣት እንደማይቻልም አመልክተዋል። በፈጠራ እና ፍጥነት ጥራትንና ብዛትን እውን ለማድረግ መትጋት የመደመር መንግስት ቁልፍ ስራ ነው ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ተናግረዋል።
ስፖርት
አርሰናል ብሬንትፎርድን በማሸነፍ መሪነቱን አጠናከረ
Dec 3, 2025 71
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 24/2018(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ14ኛ ሳምንት መርሃ ግብር አርሰናል ብሬንትፎርድን 2 ለ 0 አሸንፏል። ማምሻውን በኤምሬትስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ማይክል ሜሪኖ በ11ኛው እና ቡካዮ ሳካ በ91ኛው ደቂቃ ላይ የማሸነፊያ ጎሎቹን አስቆጥረዋል። በጨዋታው አርሰናል ከተጋጣሚው ጠንካራ ፈተና ቢገጥመውም ወሳኝ ሶስት ነጥብ ይዞ ወጥቷል። በውድድር ዓመቱ 10ኛ ድሉን ያስመዘገበው አርሰናል በ33 ነጥብ መሪነቱን አጠናክሯል። ከተከታዩ ማንችስተር ሲቲ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ አምስት ከፍ አድርጓል። በአንጻሩ በሊጉ ሰባተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ብሬንትፎርድ በ19 ነጥብ ከነበረበት 10ኛ ደረጃ ወደ 13ኛ ዝቅ ብሏል።
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ አርባምንጭ ከተማ እና ሃዋሳ ከተማ ነጥብ አቻ ተለያዩ
Dec 3, 2025 61
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 24/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ10ኛ ሳምንት መርሃ ግብር አርባምንጭ ከተማ እና ሃዋሳ ከተማ ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል። በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የምስራች ፈለቀ በ57ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት ያስቆጠረችው ጎል ሃዋሳ ከተማን መሪ አድርጓል። ምህረት አለሙ በ67ኛው ደቂቃ ላይ ያሳረፈችው ግብ አርባምንጭ ከተማ አቻ ሆኗል። ውጤቱን ተከትሎ ሃዋሳ ከተማ በ22 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል። አርባምንጭ ከተማ በስምንት ነጥብ 11ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ዛሬ በተደረጉ በሌሎች ጨዋታዎች የሊጉ መሪ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ይርጋጨፌ ቡና 4 ለ 0 ሲያሸንፍ ሸገር ከተማ ሲዳማ ቡናን 1 ለ 0 ረቷል።
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮ ኤሌክትሪክ መሪነቱን ያጠናከረበት ወሳኝ ድል አስመዘገበ
Dec 3, 2025 57
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 24/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ10ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ኢትዮ ኤሌክትሪክ ይርጋጨፌ ቡናን 4 ለ 0 ረቷል። በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ትዕግስት ያደታ ሁለት ግቦችን ስታስቆጥር እየሩሳሌም ወንድሙ እና ማህሌት ምትኩ ቀሪዎቹን ጎሎች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። በሊጉ 10ኛ ድሉን ያስመዘገበው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ30 ነጥብ መሪነቱን አጠናክሯል። በውድድር ዓመቱ አራተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አዲስ አዳጊው ይርጋጨፌ ቡና በ10 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃን ይዟል።
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሸገር ከተማ ሲዳማ ቡናን አሸነፈ
Dec 3, 2025 68
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 24/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ10ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ሸገር ከተማ ሲዳማ ቡናን 1 ለ 0 አሸንፏል። በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሰርካለም ባሳ በ79ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥራለች። በውድድር ዓመቱ ስድስተኛ ድሉን ያስመዘገበው አዲስ አዳጊው ሸገር ከተማ በ18 ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዟል። በአንጻሩ በሊጉ አራተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሲዳማ ቡና በዘጠኝ ነጥብ 10ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ10ኛ ሳምንት መርሃ ግብር እስከ ሕዳር 26 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።
አካባቢ ጥበቃ
በኢሉባቦር ዞን በክረምቱ ወቅት የተተከሉ ችግኞችን የመንከባከብ ስራ እየተከናወነ ነው
Dec 2, 2025 143
መቱ ፤ሕዳር 23/2018 (ኢዜአ)፡-በኢሉባቦር ዞን በክረምቱ አረንጓዴ አሻራ መርሐግብር የተተከሉ ችግኞችን የመንከባከብ ስራ በዘመቻ መልክ እየተከናወነ መሆኑን የዞኑግብርና ጽሕፈት ቤት ገለጸ። የዞኑ የተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ሰራተኞች የተሳተፉበት በክረምቱ ወቅት የተተከሉ ችግኞችን በጋራ እየተንከባከቡ ናቸው። የኢሉባቦር ዞን ግብርና ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ አወል መሐመድ በዞኑ በክረምቱ ወራት ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች መተከላቸውን አስታውሰዋል። የችግኞቹን የጽድቀት መጠን ለማሳደግም ህብረተሰቡ እንክብካቤ እንዲያደርግ ግንዛቤ በመፈጠሩ የዞኑ የመንግስት ሰራኞችን ጨምሮ ሁሉንም የሕብረተሰብ ክፍሎች ባሳተፈ መልኩ እንክብካቤው በዘመቻ መልክ እየተካሄደ መሆኑን ጠቁመዋል። ይህም የጽድቀት መጠናቸው በአሁኑ ወቅት ከ95 በመቶ በላይ መድረሱን ተናግረዋል። ለችግኞቹ የሚደረገው እንክብካቤ ጽድቀታቸውን ከማረጋገጥ ባለፈ በአጭር ግዜ ደርሰው ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታቸው እንዲጎላ እንደሚያግዝም አመልክተዋል። በችግኝ እንክብካቤው ከተሳተፉ የመንግስት ሰራተኞች መካከል የዞኑ የፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ጽሕፈት ቤት ባለሞያ አቶ መላኩ ከበደ በበኩላቸው በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በአንድነት የተከልናቸውን ችግኞች በአንድነት የመንከባከብ ስራ እየሰራን ነው ብለዋል። በመንግስት አገልግሎት ለህዝብ ከሚሰጧቸው አገልግሎት ባለፈ በክረምቱ ወራት በበጎ ፈቃድ አገልግሎት የተከሏቸውን ችግኞች በመንከባከብ እንዲጸድቁ ለማድረግ በስፍራው መገኘታቸውን ገልጸዋል። በአረንጓዴ አሻራ የተከልሏቸው ችግኞች የሚጠበቀውን ውጤት ለማግኘት መትከል ብቻውን በቂ ባለመሆኑ የእንክብካቤ ስራውን ማጠናከር በማስፈለጉ ለዚሁ ተግባር መጥቻለሁ ያሉት ደግሞ ወይዘሮ ፋጡማ የሱፍ ናቸው። አቶ እንዳሻው ጆቴ በበኩላቸው የተተከሉ ችግኞችን በጋራ በመንከባከብ ለውጤት ለማብቃት ያልተቋረጠ ክትትል በማስፈለጉ በተከላ ወቅቱ የገቡትን ቃል በተግባር ለማዋል ስራው ላይ መገኘታቸውን ጠቁመዋል። በክረምቱ የተተከሉት ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ተገቢው እንክብካቤ ካልተደረገላቸው በመጥፋት የወጣባቸው ከፍተኛ ገንዘብ ለብክነት እንደሚዳረግም አክለዋል።
ኢትዮጵያውያን የደመቁበት የኢጋድ የሚዲያ አዋርድ
Dec 1, 2025 189
ሶስተኛው የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት ህዳር 20 እና 21 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ተካሂዷል። የሽልማት ስነ ስርዓቱ “ውጤታማ የአየር ንብረት ዘገባ ደህንነቱ ለተረጋገጠ፣ ጠንካራ እና የተረጋጋ ቀጣና” በሚል መሪ ሀሳብ ተከናውኗል። ኢጋድ ቀጣናዊ ሁነቱን ያዘጋጀው ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመተባበር ነው። ፐልስ ኦፍ አፍሪካ ሚዲያ የሽልማት መርሃ ግብሩ የሚዲያ አጋር ሲሆን የሁለት ቀኑን የሽልማት መርሃ ግብር የቀጥታ ስርጭት ሽፋን በመስጠት ለመላው አፍሪካውያን ተደራሽ አድርጓል። የአፍሪካ ኢምፖርት እና ኤክስፖርት ባንክ(አፍሪኤግዚም ባንክ) ለፕሮግራሙ ድጋፍ አድርጓል። የኢጋድ የሚዲያ አዋርድ ተሳታፊ የሚዲያ ባለሙያዎች ፐልስ ኦፍ አፍሪካ ሚዲያን ጎብኝተዋል። የ2025 የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት በ10 ዘርፎች ተከናውኗል። የህትመት ጋዜጠኝነት፣ የሬዲዮ ጋዜጠኝነት፣ የቴሌቪዥን ጋዜጠኝነት፣ ዲጂታል ሚዲያ፣ ፎቶግራፈር፣ ሀገር በቀል ዘገባ፣ የዓመቱ ተጽእኖ ፈጣሪ/ የይዘት ቀራጭ፣ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽእኖ ፈጣሪዎች እና የእድሜ ዘመን ሽልማት የሽልማት ዘርፎቹ ናቸው። 400 የሚሆኑ የኢጋድ አባል ሀገራት የሚዲያ ባለሙያዎች ስራዎቻቸውን ያስገቡ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 94 የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን የሚዲያ ባለሙያዎች መሆናቸውን ኢጋድ አስታውቋል። ከ94ቱ ኢትዮጵያውያን የሚዲያ ባለሙያዎች መካከል ሶስቱ በተለያዩ ዘርፎች ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ጋዜጠኛ ጌትነት ሸንቁጤ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የ2025 የሚዲያ ሽልማት በዲጂታል ሚዲያ ዘርፍ አሸናፊ በመሆን ሽልማቱን ተቀብሏል። ጋዜጠኛ ጌትነት ሸንቁጤ ሽልማቱን የተጎናጸፈው “Climate Intelligence for Survival: IGAD’s Push for Accurate, Actionable Data” በሚል ርዕስ በጻፈው ጽሁፍ ነው። የጋዜጠኛ ጌትነት ጽሁፍ በኢጋድ ቀጣና ያለውን የአየር ንብረት ለውጥ ፈተና የሚዳስስ ነው። በተደጋጋሚ ጊዜ የሚከሰት ድርቅ፣ የጎርፍ አደጋዎችና ኢ-ተገማች የአየር ጸባይ ለውጦች ዜጎችን በማፈናቀል እና በቁም እንስሳት ላይ ያደረሱትን ጉዳት ይቃኛል። ትክክለኛ፣ ጊዜውን የጠበቀና ለተግባር ምላሽ የሚያገለግሉ የአየር ንብረት መረጃዎች የማይበገር አቅም ለመገንባትና አደጋዎችን ለመከላከል ያላቸውን ሚናም ተዳሷል። በጽሁፉ ላይ የኢጋድ የአየር ንብረት ትንበያና ትግበራ ማዕከል(ICPAC) የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓትን በማጠናከር፣ የትንበያ አቅም ማሳደግና የረጅም ጊዜ የአየር ንብረት የመቋቋም አቅም ላይ እያከናወነ ያለው ስራ ተቀምጧል። የአየር ንብረት ለውጥ ፈተናዎች፣ የአንበጣ መንጋ፣ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብና ሌሎች ፈተናዎችን ለመከላከል ተአማኒነት ያለው የአየር ንብረት መረጃ ወሳኝ መሆኑም ተመላክቷል። በተለይም ኑሯቸው በተለያዩ ወቅቶች ላይ ለተመረኮዙ አርሶ እና አርብቶ አደሮች መረጃው ወሳኝ መሆኑን ያስቀምጣል። ሌላኛው ተሸላሚ የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ (ኦቢኤ) ጋዜጠኛ ሽመክት ጉግሳ ነው። የተሸለመበት ዘርፍ በኦሮምኛ ቋንቋ በሰራው ፕሮግራም ነው። ፕሮግራሙ ዛፎች ከሰው ህይወት ጋር ያላቸውን ቁርኝት በዋናነት ይቃኛል። መንደርደሪያውን ከዓለም የዛፍ ጠቀሜታና ጥበቃ በማድረግ በኦሮሚያ ክልል እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን ይዳስሳል። ዛፍ መትከል ተፈጥሮና የሰው ልጅን እንዴት እንደሚጠብቅ በተቃራኒው መቁረጥ የሚያደርሰውን ጉዳትም ያስቃኛል። የ21 ደቂቃ ፕሮግራሙ የኦሮሞ ህዝብ በዘመናት መካከል ዛፎችና የደን ሀብቶች እንዲጠበቁ ያደረገው አስተዋጽኦ ተወስቶበታል። በተለይም በገዳ ስርዓት ውስጥ ዛፍን መጠበቅ ያለው ሚና በስፋት ተነስቷል። አንድ ዛፍ ለአራት ሰዎች መኖር መሠረት ይሆናል፤ ዛፍ መቁረጥ አራት ሰዎችን እንዲሞቱ ያደርጋል የሚል የአባገዳ አስተያየትም ተጠቃሽ ነው። አባ ገዳዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ እናቶችና የአካባቢ ማህበረሰቦች ተፈጥሮን ጠብቆ በማቆየት ያላቸው ሚና ቁልፍ እንደሆነ ተመላክቷል። የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ራዲዮ መስራችና ስራ አስኪያጅ አንጋፋዋ ጋዜጠኛ መዓዛ ብሩም የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን(ኢጋድ) የህይወት ዘመን ጋዜጠኝነት ሽልማት ተበርክቶላታል። ጋዜጠኛ መዓዛ ብሩ በሬዲዮ ጋዜጠኝነት ግንባር ቀደምና በዘርፉ ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከቷንም ኢጋድ ገልጿል። በብሮድካስት ሚዲያው ከ40 ዓመት በላይ የቆየችው ጋዜጠኛ መዓዛ ሸገር ኤፍኤም 102.1ን ከ18 ዓመታት በፊት በማቋቋም በኢትዮጵያ ቀዳሚ የመረጃ እና የመዝናኛ ጣቢያ እንዲሆን ማድረጓ አመልክቷል። ከጋዜጠኛ መዓዛ ብሩ አበይት ፕሮግራሞች መካከል “ማንን ምን እንጠይቅልዎ?” እና “ሸገር ካፌ” ተጠቃሽ ናቸው። ጋዜጠኛዋ በፕሮግራሞቹ ህዝብን ከመንግስት አገልግሎቶች ጋር በማገናኘትና በማህበራዊ፣ የህግ እና የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ሀሳብ ላይ የተመረኮዙ ውይይቶች እንዲካሄዱ መድረክ መፍጠር መቻሏንም ነው የገለጸው። የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ራዲዮ መሪ ሀሳብ በሆነው የእናንተ ሬዲዮ መዓዛ በጋዜጠኝነት ሙያ ህዝብን ለማገልገልና የኢትዮጵያውያንን ድምጽ ለማጉላት ያላትን ቁርጠኝነት ኢጋድ አድንቋል። ሽልማቱ በቀጣናው ገንቢ ሚና ያለው ጋዜጠኝነት እንዲጎለብት አዎንታዊ ሚና እንደሚጫወትም ኢጋድ አመልክቷል።
በሚቀጥሉት አስር ቀናት ወደ ሀገሪቱ የሚነፍሰው ደረቅ እና ቀዝቃዛ አየር ተጠናክሮ ይቀጥላል
Dec 1, 2025 174
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 22/2018(ኢዜአ)፦ በሚቀጥሉት አስር ቀናት ከሳይቤሪያ ከፍተኛ የአየር ግፊት ላይ በመነሳት ወደ ሀገሪቱ የሚነፍሰው ደረቅ እና ቀዝቃዛ አየር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ገለፀ። ኢንስቲትዩቱ ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንደገለፀው በሚቀጥሉት አሥር ቀናት ዝናብ ሰጭ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት አካባቢዎች ላይ ቀጣይነት ይኖረዋል። ዝናብ ሰጭ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በጥቂት የደቡብ እና የደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች አልፎ አልፎ በሚኖሩት ቀናቶች ላይ በተዳከመ ሁኔታ ቀጣይነት ይኖራቸዋል። በዚህም የደቡብ ኦሮሚያ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡባዊ ዞኖች እና የሶማሌ ክልል ደቡባዊ ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ በጣም አነስተኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች እንደሚጠቁሙ ገልጿል። በሌላ በኩል ከሚኖረው የደመና ሽፋን ላይ በመነሳት በጥቂት የሰሜን፣ መካከለኛውና ደቡብ ጎንደር ዞኖች፣ ባህርዳር ዙሪያ፣ አዊ ፣ በምዕራብና ምስራቅ ጎጃም አልፎ አልፎ በሚኖሩት ቀናት ወቅቱን ያልጠበቀ አነስተኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙም ትንበያው አብራርቷል። የምዕራብ ኦሮሚያ ክልል ዞኖች፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፤ ባሌ እና ምስራቅ ባሌ ዞኖች፣ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሺ እና የማኦኮሞ ልዩ ዞን፤ የጋምቤላ ክልል ዞኖች፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ዞኖችም አልፎ አልፎ ወቅቱን ያልጠበቀ አነስተኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ። ስለሆነም በሚኖሩት ደረቅ ቀናቶች የደረሱ ሰብሎች መሰብሰብ አስፈላጊ መሆኑን ኢንስቲትዩቱ ጠቁሟል። በሌላ በኩል ከሳይቤሪያ ከፍተኛ የአየር ግፊት ላይ በመነሳት ወደ ሀገሪቱ የሚነፍሰው ደረቅ እና ቀዝቃዛ አየር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች እንደሚያሳዩም በመግለጫው ተብራርቷል። በዚህም የበጋው ደረቅ፣ ፀሐያማና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ በተለይም በሰሜን፣ ምስራቅ፣ መካከለኛውና ደቡብ ደጋማ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የለሊትና የማለዳው ቅዝቃዜ ከአምስት ዲግሪ ሴልሺየስ በታች እንደሚሆን ትንበያው ያሳያል።
የኢትዮጵያ የዓለም የአየር ንብረት ጉባኤን ለማስተናገድ መመረጥ በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ ላላት ቁርጠኝነት የተሰጠ ዕውቅና ነው
Nov 30, 2025 187
አዲስ አበባ፤ ህዳር 21/2018(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ የዓለም የአየር ንብረት ጉባኤን ለማስተናገድ መመረጥ ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ ላላት ቁርጠኝነት የተሰጠ ዕውቅና መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ገለጹ። የአየር ንብረት ለውጥ ለመከላከል በሚደረግ ሂደት የሚዲያ ሚና ወሳኝ መሆኑንም ሚኒስትሩ ገልጸዋል። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ''ውጤታማ የአየር ንብረት ዘገባ፤ ደኅንነቱ ለተረጋገጠ ጠንካራና የተረጋጋ ቀጣና” በሚል መሪ ሃሳብ የ2025 የሚዲያ ሽልማት በአዲስ አበባ በማካሄድ ላይ ይገኛል። በመድረኩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር)፣ የኢጋድ ዋና ፀሀፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር)፣ ቀጣናዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል። ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት ኢጋድ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ለቀጣናዊ የአየር ንብረት ለውጥ ምላሽ ለመስጠት በትኩረት እየሰራ ነው ብለዋል። የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ለመቀነስም በስትራቴጂክ ዕቅድ መምራት የሚያስችል የማስተባበር ሥራ እየሰራ አንደሚገኝ ገልጸዋል። ኢትዮጵያም የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ለመቀነስ በተግባር የተደገፈ ለውጥ አምጪ የመፍትሔ እርምጃዎች ላይ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች እንደምትገኝ ተናግረዋል። በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በቢሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞችን በመትከል ለጎረቤት ሀገራት ጭምር በማጋራት ውጤታማ ስራ ማከናወኗን አስረድተዋል። ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብም በአህጉሪቷ የታዳሽ ኃይል መስክ አዲስ ምዕራፍ በመክፈት የዲጂታል ሽግግር አንቀሳቃሽ ኃይል ለመሆን መብቃቱን አንስተዋል። ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እና ሌሎች የታዳሽ ሀይል የልማት ስኬቶች ለአፍሪካ የኢንዱስትሪና የዲጂታል ሽግግር በምሳሌነት የሚወሰዱ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። የኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የኢኮኖሚ ግንባታም 2ኛውን የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ በስኬት በማስተናገድ ቀርጠኝነቷን ለዓለም ማስመስከሯን ገልጸዋል። ከሁለት ዓመታት በኋላ የሚካሄደውን የመንግስታቱ ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤን (COP 32) በ2027 ለማስተናገድ በሙሉ ድምጽ መመረጧ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ለመቀነስ ላላት ቁርጠኝነት የተሰጠ እውቅና መሆኑን ተናግረዋል። የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ለመዋጋትም መገናኛ ብዙኃን ግንባር ቀደም ሚና እንዳላቸው የኢጋድ 2025 የጋዜጠኞች ዕውቅና ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ፀሀፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር)፤ እያደገ የመጣው የመገናኛ ብዙኃን ሙያተኞች ሽልማት ቀጣናዊ ድምፆችን ለማጉላት ጉልህ ፋይዳ አለው ብለዋል። መገናኛ ብዙኃን ሙያተኞችም የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ለመቀነስ፣ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ ሰላምና ደኅንነትን ለማስጠበቅ ወሳኝ ሚና እንዳላቸው አስረድተዋል። የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርም የቀጣናውን ማህበረሰብ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያሻሽል ወሳኝ የልማት እርምጃ መሆኑን ገልጸዋል። በብራዚል ቤለም በተካሄደው 30ኛ ጉባኤ ላይ ከሁለት ዓመታት በኋላ የሚካሄደውን 32ኛ የዓለም የአየር ንብረት ጉባኤ (COP-32) ኢትዮጵያ እንድታስተናግድ መመረጧ ይታወቃል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
ግድቡ አፍሪካውያን ለጋራ ራዕይ ከቆሙ ህልማቸውን ማሳካት እንደሚችሉ ያሳየ ነው - የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት አሸናፊዎች እና ተሳታፊ ጋዜጠኞች
Dec 1, 2025 187
አዲስ አበባ፤ ህዳር 22/2018(ኢዜአ)፦ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አፍሪካውያን ለጋራ ራዕይ ከቆሙ ህልማቸውን ማሳካት እንደሚችሉ ያሳየ ነው ሲሉየምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የሚዲያ ሽልማት አሸናፊዎች እና ተሳታፊ ጋዜጠኞች ገለጹ። የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የአፍሪካን ትርክት በመቀየር ትልቅ ሚና የሚወጣ ግዙፍ ፕሮጀክት መሆኑንም ተናግረዋል። ሶስተኛው የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ መካሄዱ ይታወቃል። የሶስተኛው የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት አሸናፊዎች እና ተሳታፊ ጋዜጠኞች ዛሬ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ጎብኝተዋል። በሴት ጋዜጠኞች ዘርፍ አሸናፊ ከሆኑት መካከል ዩጋንዳዊቷ ጋዜጠኛ አይባሬ ሲንደሬላ ኢትዮጵያ በዜጎቿ አስተዋጽኦ ህዳሴ ግድብን ለመገንባት ያሳየችውን ቁርጠኝነት አድንቃለች። በበርካታ ሀገራት ዜጎች ከሚከፍሉት ታክስ ተጨባጭ ውጤቶችን እምብዛም ሲያዩ አይስተዋልም ያለችው ጋዜጠኛዋ ኢትዮጵያ በግልጽነትና በጠንካራ ራዕይ የህዝብን ሀብቶች አሻጋሪ ብሄራዊ ፕሮጀክት መቀየሯን ተናግራለች። የአፍሪካ መሪዎች ከሕዳሴ ግድብ ጠቃሚ ተሞክሮዎችን ሊወስዱ ይገባል ብላለች። የኬንያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ከፍተኛ አዘጋጅ አሻ ሃሚሲ አፍሪካውያን የራሳቸውን ችግሮች ያለ ምንም ጣልቃ ገብነት መፍታት እንዳለባቸው ገልጻለች። ሕዳሴ ግድብ ዜጎች ለሀገራቸው መስዋዕትነት እንደሚከፍሉ የሚያሳይ ፕሮጀክት ነው ያለችው አሻ ይህም በህዝብ እና በመንግስት መካከል ያለ መተማመንና ነገን የተሻለ ለማድረግ ዛሬ ላይ መስራት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያመላከት ነው ብላለች። ግድቡ አፍሪካውያን ለጋራ ራዕይ ከቆሙ ህልማቸውን ማሳካት እንደሚችሉ ያሳየ እንደሆነም ተናግራለች። በኢጋድ ሚዲያ ሽልማት በዲጂታል ሚዲያ ዘርፍ ካሸነፉት ጋዜጠኞች መካከል አንዱ የሆነው ደቡብ ሱዳናዊው የፊልም ባለሙያ እና ተራኪ ጋብርኤል ጋትሉዋክ ዋል ኬት በበኩሉ ህዳሴ ግድብ አፍሪካ ያላትን አቅም በተግባር ያሳየ ነው ሲል ተናግሯል። ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን የመሰለ ግዙፍ ፕሮጀክት ካሳካች ሌሎች ሀገራትም ይህን ፈለግ ተከትለው ትላልቅ ፕሮጀክቶችን እውን ማድረግ ይችላሉ ብሏል። አፍሪካውያን ሀገራቸውን በራሳቸው መገንባት እንደሚችሉ ማመን አለባቸው ያለው ኬት የራሳቸውን ዕጣ ፈንታ ሌሎች እንዲወስኑላቸው መፍቀድ የለባቸውም ሲልም ገልጿል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው ለሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያን እና በውጭ የሚኖሩ ዳያስፖራዎች የከፈሉትን መስዋዕትነት አንስተዋል። ሕዳሴ ግድ የአፍሪካ የስኬት ተምሳሌት ፕሮጀክት እንደሆነ ገልጸው ከግድቡ የሚገኘው የኤሌክትሪክ ኃይል ጎረቤት ሀገራትን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ አመልክተዋል። ይህም ቀጣናዊ ትስስርን የሚያጠናክርና የአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 ራዕይ የሆነውን የበለጸገች እና የተሳሰረች አፍሪካን የመፍጠር ራዕይን እንደሚደግፍም ተናግረዋል። ግድቡ የአፍሪካን ትርክት የመቀየር ትልቅ ኃይል ያለው ፕሮጀክት ነው ብለዋል አምባሳደሩ።
የአፍሪካን ዘላቂ የልማት ግቦች ለማሳካት ዓለም አቀፍ ትብብርን በማጠናከር በቁርጠኝነት መስራት ያስፈልጋል
Nov 21, 2025 568
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 12/2018(ኢዜአ)፦ የአፍሪካን ዘላቂ የልማት ግቦች ለማሳካት በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ ዓለም አቀፍ ትብብርን በማጠናከር በቁርጠኝነት መስራት እንደሚያስፈልግ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ገለጸ። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዘጋጅነት የ2025 የአፍሪካ ዘላቂ የልማት ሪፖርት ዋና ዋና ግኝቶችና የፖሊሲ ምክረ ሃሳቦች ላይ የዌብናር ውይይት ተካሂዷል። በመድረኩም የአፍሪካ ሕብረት አባል ሀገራት ወሳኔ ሰጪዎች፣ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማህበረሰቦች፣ ዓለም አቀፍ ተቋማት፣ የገንዘብ ተቋማት፣ ተመራማሪዎችና የልማት አጋሮች ተሳትፈዋል። በመንግስታቱ ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የልማት ዕቅድ ክፍል ኃላፊ ኦዬባንኬ አበጂሪን፤ የምንፈልጋትን አፍሪካ ዕውን ለማድረግ በዘላቂ የልማት ግቦች ላይ በትብብር መስራት ያስፈልጋል ብለዋል። የአፍሪካ ሀገራት የ2030 ዘላቂ የልማት አጀንዳና የአፍሪካ ሕብረት አጀንዳ 2063 አፈፃጸም ሂደትን የሚከታተል የሪፖርት ሥርዓት መኖሩንም ገልጸዋል። እ.ኤ.አ በ2017 የተጀመረው የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ሪፖርት ክትትል ሥርዓትም የአህጉሪቷን ዘላቂና ቁልፍ የልማት ማዕቀፎች አፈፃጸም የሚገመገምበትን መድረክ በማመቻቸት ወሳኝ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ተናግረዋል። እ.ኤ.አ የ2025 የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ሪፖርት መድረክም የአህጉሪቷ ልማት በሳይንስና ማስረጃ የተመሰረቱ የመፍትሔ አፈፃጸሞችን ያመላከተ መሆኑን አስገንዝበዋል። ሪፖርቱም የአፍሪካ ዕድገት በጤና፣ በሥርዓተ ፆታ እኩልነት፣ በኢኮኖሚ ዕድገት፣ በውቅያኖስ ጥበቃና ዓለም አቀፍ ሽርክና ጋር በአፍሪካ ሀገራት እ.ኤ.አ የ2030 ዘላቂ የልማት ግብና የአፍሪካ ሕብረት አጀንዳ 2063 ወሳኝ አካል መሆኑን አስረድተዋል። የአህጉሪቷን ዘላቂ የልማት ግቦች ለማሳካትም በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ የትብብር ሥርዓትን በማጠናከር በቁርጠኝነት ሊሰሩ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። የ2025 የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ሪፖርትም ወሳኝ የአፈፃጸም ግኝቶችን በማረም የፖሊሲ ምክረ ሃሳቦችን በሚገባ ለመተግበር አቅም እንደሚፈጥር አስረድተዋል። በመድረኩም የአህጉሪቷን ዘላቂ የልማት ግቦችና አጀንዳዎች የአፈፃጸም ስኬት ልምድና ተሞክሮ በመለዋወጥ የፖሊሲ አቅጣጫዎችን ለመቅረጽ የሚችል ተግባቦት መፈጠሩን አስገንዝበዋል። በቀጣይም የአህጉሪቷን የልማት ግቦች ለማሳካትም አዲስ ዓለም የፋይናንስ ድጋፍ ማዕቀፍ አስፈላጊነትን ታሳቢ በማድረግ በትኩረት የሚሰራበት ጉዳይ መሆኑን አብራርተዋል። መድረኩም ብሔራዊና ቀጣናዊ የልማት ስኬት አፈፃጸም የአሰራር ስርዓቶችን በመፈተሽ ዕድሎችን በማስፋት የአህጉሪቷን ዘላቂ የልማት አጀንዳዎ ማሳካት እንደሚያስፈልግም አጽንኦት ሰጥተዋል።
የአፍሪካ ህብረት እና ማሌዥያ የአጋርነት አድማሳቸውን ለማስፋት እንደሚሰሩ ገለጹ
Nov 20, 2025 460
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 11/2018(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ህብረት እና ማሌዥያ በትምህርት እና ዲጂታል ዘርፍ ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ያላቸውን አጋርነት ለማጠናከር በቅርበት እንደሚሰሩ አስታወቁ። የማሌዥያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሰሪ አንዋር ቢን ኢብራሂም በአፍሪካ ህብረት ዋና ኮሚሽን ዛሬ ይፋዊ የስራ ጉብኝት አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ህብረቱን የጎበኙ የመጀመሪያ ማሌዥያ መሪ ሆነዋል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ከማሌዥያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሰሪ አንዋር ቢን ኢብራሂም ጋር ተወያይተዋል። ውይይቱ ሁለቱ ወገኖች በተለያዩ መስኮች ያላቸውን አጋርነት ማጠናከርን ያለመ ነው። ሊቀመንበሩ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት የአፍሪካ እና ማሌዥያ ትብበር ውስጥ ታሪካዊና የሁለቱን ወገኖች ስትራቴጂካዊ ትብብር እንደሚያጠናክር አመልክተዋል። እ.አ.አ በ2024 የአፍሪካ እና ማሌዥያ የንግድ ልውወጥ መጠን 7 ነጥብ 5 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር መድረሱን ጠቅሰው፤ ይህም በዘርፉ ያለው ትብብር እየተጠናከረ መምጣቱን የሚያሳይ ነው ብለዋል። ትምህርት የሁለቱ ወገኖች አጋርነት ዋነኛ ምሰሶ መሆኑንና ከእ.አ.አ 2012 አንስቶ ከ40 ሺህ በላይ አፍሪካውያን በማሌዥያ ትምህርታቸውን መከታተላቸውን ገልጸዋል። ማሌዥያ ቀጣይ የደቡብ ምስራቅ እስያ ሀገራት ሊቀ መንበር መሆኗ እና ብሪክስን ለመቀላቀል ያላት ፍላጎት ኢንቨስትመንትን ጨምሮ ከአፍሪካ ጋር ያለውን ትብብር ለማጠናከር መልካም አጋጣሚ ይፈጥራል ነው ያሉት። ሁለቱ ወገኖች በዲጂታል ኢኖቬሽን፣ በግብርና ማቀነባበሪያ ልማት፣ በደቡብ ደቡብ ንግድ እና ትምህርት ዘርፍ ያላቸውን አጋርነት ለማጠናከር ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት ገልጸዋል። ሊቀ መንበሩ የአፍሪካ ህብረት እና ማሌዥያ ዓመታዊ ምክክር እ.አ.አ በ2026 እንዲካሄድ ሀሳብ አቅርበዋል። የማሌዥያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሰሪ አንዋር ቢን ኢብራሂም በበኩላቸው፤ ማሌዥያ እና አፍሪካ ንግድ፣ ግብርና እና ትምህርትን ጨምሮ በቁልፍ ጉዳዮች ትብብር እያደገ መምጣታቸውን አመልክተዋል። ሁለቱ ወገኖች ያላቸውን የትብብር አድማስ በማስፋት የጋራ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ መስራት እንደሚገባቸው መግለጻቸውን ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። በውይይቱ ላይ የማሌዥያ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ተሳትፈዋል። የአፍሪካ ህብረት እና ማሌዥያ የአጋርነታቸውን አድማስ ለማስፋት እንደሚሰሩ ገልጸዋል::
ለሱዳን ግጭት ዓለም አቀፍ የተቀናጀ የተግባር ምላሽ ያስፈልጋል- ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር)
Nov 19, 2025 577
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 10/2018(ኢዜአ)፦ የሱዳን ግጭት ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኝ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የተቀናጀ ምላሽ እንዲሰጥ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ጥሪ አቀረቡ። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ያዘጋጀው ሁለተኛ የሱዳን የልዩ ልዑኮች ፎረም ዛሬ በጅቡቲ ተካሄዷል። በፎረሙ ላይ የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር)፣ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፍ ተዋንያን ተሳትፈዋል። ፎረሙ በሱዳን ላለው ቀውስ የተቀናጀ መልስ መስጠት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነው። የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) በፎረሙ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር የሱዳን ሰላም በሱዳናውያን የሚመራ፣ ቀጣናዊ ትብብር የተረጋገጠበት እና ዓለም በአንድ ድምጽ የሚደግፈው ሊሆን እንደሚገባ አመልክተዋል። በሱዳን ያለውን ግጭት ለማስቆም፣ ንጹሃን ዜጎችን ለመጠበቅ እና የኢጋድ ቀጣናን የተረጋጋ ለማድረግ በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። ዋና ፀሐፊው ኢጋድ ከአፍሪካ ህብረት እና ዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር በመሆን በሱዳን የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንዲደረስ፣ የሰብዓዊ እርዳታ መተላለፊያ እንዲከፈት እና ተአማኒነት ያለው የስልጣን ሽግግር እንዲኖር በቁርጠኝነት ይሰራል ብለዋል። ኢጋድ ሱዳናውያን በሀገራቸው ሰላም እና ደህንነት እንዲረጋገጥ እንዲሁም ክብራቸው እንዲጠበቅ ያላቸው መሻት እንዲሳካ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ በመረጃው አመልክቷል።
ሐተታዎች
ለቀጣናዊ የጋዜጠኝነት ሙያዊ ልህቀት እውቅና የሚሰጠው የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት
Nov 28, 2025 319
የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት የተጀመረው በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) አማካኝነት ነው። ሽልማቱ የኢጋድ የኮሙኒኬሽን ስትራቴጂ እና ተቋማዊ አቅምን የማጠናከር ጥረቶች አካል ነው። በኢጋድ ቀጣና በጋዜጠኝነት የላቀ ስራ ላከናወኑ የሚዲያ ባለሙያዎች በሽልማቱ እውቅና ይሳጣቸዋል። ሽልማቱ ቴሌቪዥን፣ ሬዲዮ፣ ህትመት፣ ፎቶግራፍ፣ ዲጂታል ሚዲያ እና ሌሎችም ተጓዳኝ መድረኮችን የሚሸፍን ነው። የሚዲያ ስራው በቀጣናው በተለይም የድርቅ አይበገሬነት፣ ሰላም፣ ደህንነት፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና ልማት ያሉ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆን ይኖርበታል። ዓመታዊው የኢጋድ ሽልማት የቀጣናዊ ተቋሙ አባል ሀገራት ውስጥ የሚገኙ ጋዜጠኞች፣ በግላቸው የሚሰሩ የሚዲያ ባለሙያዎች፣ የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች እና የፎቶ ጋዜጠኞች ጨምሮ አጠቃላይ የሚዲያ ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት ነው። በተጨማሪም የቀጣናውን ጉዳይ የሚሸፍኑ የውጭ ሀገራት ጋዜጠኞችም ይሳተፉበታል። በውድድሩ ላይ የሚሳተፉ ባለሙያዎች ስራቸውን በእንግሊዘኛ፣ ፈረንሳይኛ እና በኢጋድ አባል ሀገራት በሚገኙ ቋንቋዎች ያቀርባሉ። ከተለያዩ ሙያዎች የተወጣጡ የውሳኔ ሰጪ ወይም ገምጋሚ ቡድን ተቋቁሙ ስራዎቹን በመመዘን አሸናፊዎችን ይለያል። የመጀመሪያው የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት የተካሄደው እ.አ.አ በ2023 በጅቡቲ ነበር። “የድርቅ ተጽእኖዎችን መቋቋም የሚያስችል ትብብር መፍጠር” የሽልማቱ መሪ ሀሳብ ነው። መሪ ሀሳቡ በድርቅ፣ አይበገሬ አቅም መገንባት፣ የውሃ አስተዳደር እና ቀጣናዊ ትብብር ያተኮረ ነው። ቴሌቪዥን፣ ሬዲዮ፣ ህትመንት፣ ጦማር (ብሎግ) እና የፎቶ ጋዜጠኝነት የሽልማት ዘርፎቹ ናቸው። በመጀመሪያው ሽልማት ላይ ከቀጣናው 105 ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን 14 ባለሙያዎች በዘርፎቹ ተመርጠው ተሸልመዋል። የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት ተቋሙ ሚዲያን ለግንዛቤ መፍጠር እና ቀጣናዊ ትብብር እንደ መሳሪያ ለመጠቀም ያለውን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ በወቅቱ ገልጾ ነበር። በድርቅ እና በምግብ ዋስትና ላይ ያሉ የጋራ ፈተናዎችን ለመፍታት የሚዲያ ሚና ወሳኝ እንደሆነም አመልክቷል። ሁለተኛው የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት የተካሄደው እ.አ.አ በ2024 በኬንያ ናይሮቢ ነው። “የተስፋ ትርክቶች፤ የቀጣናውን መጻኢ ጊዜ ሰላማዊ፣ ደህንነቱ የተረጋገጠ እና ሁሉን አቃፊ ማድረግ” የሽልማቱ መሪ ሀሳብ ነው። ሽልማቱ በሰላም፣ ደህንነት፣ ሁሉን አሳታፊ የሆነ መጻኢ ጊዜን መፍጠር፣ ቀጣናዊ ትብብር እና መረጋጋት ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነው። ቴሌቪዥን፣ ሬዲዮ፣ ህትመት፣ ፎቶግራፍ፣ ዲጂታል ሚዲያ፣ ተጽእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች፣ የእድሜ ዘመን ተሻላሚ ከሽልማት ዘርፎቹ ውስጥ ናቸው። ለ2024ቱ ሽልማት 318 የሚዲያ ባለሙያዎች ስራቸውን ያቀረቡ ሲሆን 18 የሚዲያ ባለሙያዎች በዘርፎቹ ሽልማት አግኝተዋል። ሁለተኛው ሽልማት ከመጀመሪያው በዘርፎች እና በተሳታፊዎች ብዛት መሻሻል የታየበት ነበር። ይህም ሚዲያ በቀጣናዊ ሰላም፣ ደህንነት እና ቀጣናዊ ትስስር ላይ ያላቸውን ሚና የሚያሳይ ነው። ሶስተኛው የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት ወደ አፍሪካ መዲና አዲስ አበባ መጥቷል። ሽልማቱ ነገ ህዳር 20 እና 21 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል። የሽልማት ስነ ስርዓቱ “ ውጤታማ የአየር ንብረት ዘገባ ደህንነቱ ለተረጋገጠ፣ ጠንካራ እና የተረጋጋ ቀጣና” በሚል መሪ ሀሳብ የሚከናወን ነው። ኢጋድ ቀጣናዊ ሁነቱን ያዘጋጀው ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመተባበር ነው። ፐልስ ኦፍ አፍሪካ ሚዲያና የአፍሪካ ኢምፖርት እና ኤክስፖርት ባንክ (አፍሪኤግዚም ባንክ) ለፕሮግራሙ ድጋፍ እንደሚያደርጉም አስታውቋል። የዚህ ዓመት ሽልማት በአፍሪካ ቀንድ ውጤታማ የአየር ንብረት ትርክትን ለቀረጹ ጋዜጠኞች እና የፊልም ባለሙያዎች እውቅና የሚሰጥ ነው። የሁለት ቀን ሁነቱ የአየር ንብረት ጠንካራ ዘገባዎች እና ሀሳቦች የሚቀርቡበት እንዲሁም ቀጣናዊ ትብብር ጎልቶ የሚታይበት መሆኑን ኢጋድ ለኢዜአ በላከው መረጃ አመልክቷል። የ2025 የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት በ10 ዘርፎች የሚከናወን ነው። የህትመት ጋዜጠኝነት፣ የሬዲዮ ጋዜጠኝነት፣ የቴሌቪዥን ጋዜጠኝነት፣ ዲጂታል ሚዲያ፣ ፎቶግራፈር፣ ሀገር በቀል ዘገባ፣ የዓመቱ ተጽእኖ ፈጣሪ/ የይዘት ቀራጭ፣ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽእኖ ፈጣሪዎች እና የእድሜ ዘመን ሽልማት የሽልማት ዘርፎቹ ናቸው። 400 የሚሆኑ የኢጋድ አባል ሀገራት ባለሙያዎች ስራዎቻቸውን ማስገባታቸውን ጠቁመው፤ ከዚህ ውስጥ 94 የሚሆኑት ኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎች መሆናቸውን ኢጋድ አስታውቋል። ሽልማቱ በቀጣናው ገንቢ ሚና ያለው ጋዜጠኝነት እንዲጎለብት አዎንታዊ ሚና እንደሚጫወትም አመልክቷል። ኢትዮጵያ ሶስተኛውን የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የሚዲያ አዋርድ ማስተናገዷም ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ ስኬቶች ዕውቅና የሚሰጥ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። በሚዲያ ሽልማት ውድድሩ ላይ በርካታ የኢጋድ አባል ሀገራት የመገናኛ ብዙሃን ሙያተኞች እንደሚሳተፉም ገልጿል። የሽልማት ሥነ-ስርዓቱ በአዲስ አበባ መካሄዱም በፐብሊክ ዲፕሎማሲ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን በማጠናከር የኢትዮጵያን ገጽታ ለመገንባት አዎንታዊ ሚና እንደሚጫወትም ነው ሚኒስቴሩ ያመለከተው። የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት በቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ለሚሰሩ የሚዲያ ባለሙያዎች እውቅና ከመስጠት ባለፈ ሙያዊ ደረጃውን የጠበቁ እና ተጽእኖ ፈጣሪ ዘገባዎች እንዲጠናከሩ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል። ቀጣናዊ ትብብርን ለማጠናከር፣ የማህበረሰብን ግንዛቤ ለማሳደግ፣ ብዝሃ ድምጾች እንዲሰሙ በማድረግ፣ ለዴሞክራሲ እሴቶች መጎልበት እና ዘላቂ ልማት የበኩሉን ሚና ይወጣል።
የኢትዮጵያ የኮፕ 32 አዘጋጅነት
Nov 14, 2025 629
ለረጅም አስርት ዓመታት ኢትዮጵያ የአፍሪካ ጠንካራ የዲፕሎማሲ ምሰሶ ሆና ቆማለች። በሀገራት መካከል የግንኙነት ድልድል እና የአንድነት መልዕክተኛ መሆን ችለላች። ከምስረታው አንስቶ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ ናት። የአፍሪካ መዲና በመባል የምትጠራው አዲስ አበባ በርካታ ድርድሮች፣ የሰላም ውይይቶች እና አህጉራዊ ውሳኔዎች የተላለፈባቸው ሁነቶች ተስተናግደውባታል። ውሳኔዎቹ የአፍሪካ ቀጣና ፖለቲካ እና የልማት ጉዞ ላይ አሻራቸውን ያሳረፉ ናቸው። የኢትዮጵያ የመሪነት ሚና ከዲፕሎማሲውም የተሻገረ ነው። ሀገሪቷ የገባችውን ቃል ከተግባር ጋር በማጣጣም በአየር ንብረት ለውጥ ላይ እርምጃ በመውሰድ የሚለኩ ውጤቶችን እያስመዘገብች ትገኛለች። የተራቆቱ መሬቶች ወደ ነባር ይዞታቸው እንዲመለሱ በማድረግ እና የታዳሽ ኃይል አማራጮቿን በማስፋት ለአረንጓዴ ልማት እና እድገት ያላትን ቁርጠኝነት አሳይታለች። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረው አረንጓዴ አሻራ ሚሊዮኖችን ከዳር እስከ ዳር በማነቃነቅ ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ከችግር ተናገሪነት ወደ ተጨባጭ መፍትሄ አመንጪነት ሽግግር በማድረግ በአፍሪካ እና በዓለም ደረጃ ምሳሌ የሚሆን ተግባር አከናውናለች። ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ያስመዘገበቻቸው ስኬቶች በዓለም ደረጃ ያላትን ተአማኒነት እና ተቀባይነት እንዲያድግ አድርጎታል። ኢትዮጵያ በከባቢ አየር ጥበቃ ቁርጠኝነት እና አቅምን በማጣመር ለውጥ አምጥታለች። ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያገኘችው እምነት እና የመሪነት ሚና ውጤት የሚያሳይ ተጨማሪ ሃላፊነት ከሰሞኑ ከብራዚል የደን ከተማ ቤለም ተሰምቷል። 30ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 30) በቤለም እየተካሄደ ይገኛል። የዓለም ሀገራት በአንገብጋቢ የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳዮች እና ቀጣይ የመፍትሄ አቅጣጫዎች ላይ እየመከሩ ይገኛል። በጉባኤው ላይ እየተሳተፈች የምትገኘው ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2027 የሚካሄደውን 32ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ለማስተናገድ ይፋዊ ጥያቄ አቅርባለች። በብራዚል የኢትዮጵያ አምባሳደር ልዑልሰገድ ዓለም ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የገቡትን ቃል በተግባር ለመቀየር ቁርጠኝነት ባነሳቸው ወቅት ኢትዮጵያ ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን ተግባር መፈጸሟን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎችን በማዘጋጀት የረጅም ጊዜ ልምድ እንዳላት ገልጸው የዳበረ የትራንስፖርት አገልግሎት ከብዙ የዲፕሎማሲ ተቋማት መቀመጫነት ጋር ሲደመር የዝግጁነት አቅሟን በላቀ ሁኔታ እንደሚያሳድገው አመልክተዋል። ኢትዮጵያ 32ኛውን የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤን ለማዘጋጀት ኢትዮጵያ ልምዱም አቅሙም እንዳላት ገልጸው፣ ሀገራት ድጋፍ እንዲሰጡ ጠይቀዋል። ናይጄሪያም ጉባኤውን ለማስተናገድ ጥያቄ አቅርባ ነበር። የኢትዮጵያ የኮፕ 32 የማስተናገድ ፍላጎት ከአፍሪካ ሀገራት ሙሉ ድጋፍ አግኝቷል። የወቅቱ የአፍሪካ የአየር ንብረት ተደራዳሪዎች ቡድን ሊቀመንበር የሆነችው ታንዛንያ የኢትዮጵያ ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱን ገልጻለች። የአፍሪካውያን ውሳኔ ከቃል ባሻገር ኢትዮጵያ የአህጉሪቷን የአየር ንብረት የቅድሚያ ትኩረቶች የማራመድ እና የመወከል አቅም አላት ብለው ይሁንታ የሰጡበት ነው። ይህ ጠንካራ እምነት ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ ሁሉን አፍሪካውያን ያሳተፈ ውይይት እንዲደረግ እና አህጉሪቷን ያማከለ ውሳኔዎች በዓለም መድረክ እንዲተላለፍ እያደረገች ያለውን ጥረት ይበልጥ ውጤታማ የሚያደርግም ነው። በብራዚል የኢትዮጵያ አምባሳደር ልዑልሰገድ ታደሰ አፍሪካውያን ኢትዮጵያ ኮፕ 32ን እንድታስናግድ ድጋፍ በመስጠታቸው አመስግነው፤ ጉባኤውን በተሳካ ሁኔታ ለማስተናገድ አበክራ እንደምትሰራ ተናግረዋል። በቅርቡ በአዲስ አበባ የተካሄደው ሁለተኛው የአፍሪካ አየር ንብረት ጉባኤ ኢትዮጵያ መሰል አህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ሁነቶችን በብቃት ማስተናገድ እንደምትችል የሚያመላክት ነው ብለዋል። አዲስ አበባ እንግዶቿን በሚመጥን ደረጃ ጉባዔውን ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኗን ያረጋገጡት አምባሳደሩ፥ ለኢትዮጵያ ጥያቄ ሌሎች ሀገራትም ድጋፍ እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል። የኢትዮጵያ የኮፕ 32ን ለማስተናገድ መመረጧ በድንገት የመጣ ጉዳይ አይደለም። በተግባር የተረጋገጥ የአየር ንብረት ለውጥ መከላከል የመሪነት ሚና፣ አረንጓዴ እና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባት እያከናወነች ያለቻቸው ስራዎች እና የፖለቲካ ቁርጠኝነቷ፣ የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ድምጽ እና ምልክት መሆኗ ከቃል ባለፈ በተጨበጠ ስራ መታየቱ፣ ዓለም አቀፍ ሁነቶችን የማስተናገድ ውጤታማነቷ እና የዲፕሎማሲ ተሰሚነቷ ድምር ውጤቶች እንጂ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ኢትዮጵያ ኮፕ 32ን እንድታስተናግድ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ትልቅ ኃላፊነት ስለሰጠን ክብር ይሰማናል ብለዋል። አፍሪካ በ2025 በተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ኮንፈረንስ (COP 30) ላይ በብራዚል በአንድ ድምጽ ተናግራለች፤ ዓለምም አዳምጧል ብለዋል። እንዲሁም ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ በ2027 በአዲስ አበባ COP 32ን ለማስተናገድ ያቀረበችውን ጥያቄ ሙሉ በሙሉ ለደገፉ የአፍሪካ ሀገራት ተወካዮች ምሥጋና አቅርበዋል። በሰው ልጆች ኑሮ በጣም አንገብጋቢ ከሆኑት ተግዳሮቶች መካከል አንዱን ለመቅረፍ እንዲቻል የጋራ ጥረቶችን ለመምራት ዕድሉን ስላገኘንም አመሥጋኞች ነን ብለዋል። ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ይህን ትልቅ ኃላፊነት ስለሰጠንም ክብር ይሰማናል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ። ይህ ዕውቅና ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ላይ ያላትን ቁርጠኛ ርምጃ፣ አመራር ብሎም ዋና ዋና ዓለም አቀፍ ዝግጅቶችን የማስተናገድ የዳበረ ዐቅም ያሳያል ሲሉም በአጽንኦት ገልጸዋል። በመሆኑም ኢትዮጵያ በምታስተናግደው የኮፕ 32 መድረክ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ የጋራ ርምጃን የሚያበረታታ ጠንካራ እና ትርጉም ያለው ውጤት ለማምጣት ሙሉ በሙሉ ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል። ኢትዮጵያ ኮፕ 32ን ማዘጋጀቷ በዓለም አቀፍ እና ቀጣናዊ መድረኮች ኢትዮጵያ ያላትን የአየር ንብረት የመሪነት ሚና የበለጠ ያሳድጋል። የአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ስራ የሚያስፈልጋትን ፋይናንስ ለማግኘት እና ዓለም አቀፍ አጋርነትን ለማጠናከር መልካም አጋጣሚን ይፈጥርላታል። በሺህዎች የሚቆጠሩ የጉባኤው ተሳታፊዎች የቱሪዝም መስህቧቿንና መዳረሻዎቿን ሲጎበኙ ከዘርፉ የሚያገኘው ገቢ ያድጋል ይህም ኢኮኖሚውን በመደገፍ ቁልፍ ሚና ይጫወታል። በአፍሪካ ዲፕሎማሲ ውስጥ ያላትን ተጽእኖ ፈጣሪን ጉባኤው በማስተናገድ በኩል ጉልህ አበርክቶ የሚኖረው ሲሆን ዘላቂ የሆነ የከባቢ አየር ትብብርን ለመፍጠር ያስችላል። ለኢትዮጵያ ኮፕ 32ን ማስተናገድ ከክብር ባሻገር ኢትዮጵያ ለአፍሪካ እና ሰው ለሚኖርባት ምድር ጥበቃ ያላትን ቁርጠኝነት በተግባር የምታሳይበት ይሆናል። ኢትዮጵያ ጠንካራ የከባቢ አየር ጥበቃ ኢኒሼቲቮች፣ የማይበገር ዲፕሎማሲ እና የነገ አረንጓዴ እድገት ህልሟ ከጉባኤው ጋር ተዳምረው የተፈጥሮ ጠበቃነቷን እና የዓለም ትብብር ተምሳሌትና መሪነቷን የበለጠ ያሳድጉታል። ኢትዮጵያ እና ህዝቧቿ ከመቼውም ጊዜ በላይ የአየር ንብረት የረጅም ጊዜ ፈተናዎች እንዲፈቱ ከአፍሪካ ብሎም ከመላው ዓለም ጋር ለመፍታት ከመቼውም ጊዜ በላይ ዝግጁ እና ቁርጠኛ ናት።
" መሬት እና ፍትህ" - የአፍሪካ ሁሉን አቀፍ የእድገት ጉዞ
Nov 11, 2025 659
መሬት በአፍሪካ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ትርጉም ያለው ነው። መሬት ከአፍሪካውያን የአኗኗር ዘይቤ፣ ማንነት፣ ባህል እና ማህበራዊ መስተጋብር ጋር የተቆራኘ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። ከቅኝ ግዛት ዘመን በፊት የአፍሪካ በርካታ ማህበረሰቦች መሬት በልማዳዊ እና ባህላዊ ስርዓት ያስተዳድሩ ነበር። የቤተሰብ ጎሳዎች ወይም ማህበረሰቦች መሬት የመጠቀም፣ የማስተዳደር እና ባህላዊ መንገዶች በሰጣቸው መብት ሲያስተላልፉ ቆይተዋል። በእንደዚህ አይነት ስርዓት ውስጥ መሬት ከሀብት ባለፈ ከማህበራዊ ግንኙነቶች፣ መንፈሳዊ መስተጋብሮች እና የተፈጥሮ ሀብቶችን በጋራ የማስተዳደር ኃላፊነት ጋር ትስስር አለው። በቅኝ ግዛት ዘመን የአውሮፓ ኃይሎች በስምምነቶች፣ በአዋጆች እና ኃይል በመጠቀም መሬት የቁጥጥር፣ የብዝበዛ እና ሀብትን የመንጠቂያ መሳሪያ አድርገውታል። መሬት ፖሊሲ ኃይልን ማጠናከሪያ እና የኢኮኖሚ ብዝበዛ መንገድ ሆኗል። አፍሪካውያን በልማዳዊ እና ባህላዊ መንገዶች የነበራቸውን የመሬት መብቶች በመንጠቅ ከአፍሪካ ውጪ የሚገኙ ዜጎች ከፍተኛ የሰፈራ ፕሮግራም ማካሄጃ እንዲሆኑ በር ከፍቷል። በዚህም ከፍተኛ የሆነ የአፍሪካ ሀብት ሲበዘበዝ ቆይቷል። ሀገር በቀል ማህበረሰቦች ከመሬታቸው የመፈናቀል እና የመገለል ሰለባ ሆነዋል። በቅኝ ገዢዎች የወጡ የመሬት ፖሊሲዎች፣ የመሬት ምዝገባ እና የመሬት አስተዳደር ስርዓት የአፍሪካ መሬት ተጠቃሚዎችን መብት የነፈገ ነበር። የቅኝ ግዛት የቀረጸው የመሬት አስተዳደር ስርዓት አፍሪካውያንን ህጋዊ የመሬት ባለቤትነትን ያሳጣ ነው። የአፍሪካ ሀገራት ከነጻነታቸው በኋላ እኩልነት ያልተረጋገጠባቸውን የመሬት መብቶች እና ስርዓቶች ወርሰዋል። ሀገራት የመሬት ፖሊሲዎቹን አሁን ያሉ የልማት ግቦችን፣ የፍትህ ፍላጎቶች እና ወቅታዊ የአስተዳደር ማዕቀፎች ባማከለ ሁኔታ የመቀየር ስራ በማከናወን ላይ ናቸው። በቅኝ ግዛት ዘመን የመሬት መብታቸውን ላጡ ዜጎች በተለይም ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተመለሰላቸው ይገኛል። ይሁንና የቅኝ ግዛት የመሬት ቅድሚያ መጥፎ፣ በሀገራት ብሄራዊ ህግ ውስጥ ያሉ የተደባለቁ የህግ ማዕቀፎች (ለምሳሌ ልማዳዊ ህጎች ከመደበኛ ህጎች ጋር መደባለቅ) እና የተቋማት የአስተዳደር ስርዓት አለመናከር በአፍሪካ ፍትሃዊ እና እኩልነት የመሬት ስርዓት የማስፈን ጉዞ ላይ ጋሬጣ ሆኗል። ዛሬ ላይ አፍሪካ አጀንዳ 2063 እና ዘላቂ ልማት ግቦች እየተገበረች ትገኛለች። የአህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ አጀንዳዎች አንኳር ምሰሶ ተደርገው ከሚጠቀሱት ጉዳዮች መካከል አንዱ መሬት ነው። እኩል የመሬት መብት የምግብ ዋስትና እና ስርዓተ ጾታ እኩልነትን ለማረጋገጥ፣ ለከባቢ አየር ጥበቃ እና ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ እድገት ቁልፍ ሚና እንደሚጫወቱ የአጀንዳ 2063 ሰነድ ያስረዳል። የአፍሪካ ህብረት ከተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ኢሲኤ) እና የአፍሪካ ልማት ባንክ በመተባበር በአፍሪካ የመሬት ፖሊሲ ላይ ማዕቀፎች እና የህግ አሰራሮችን በመቅረጽ እያስተዋወቁ ይገኛሉ። የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት የመሬት ህጎችን የተሰናነሰኑ እንዲሆኑና የተቋማት አቅምን እንዲያጠናክሩ ጥሪ በማቅረብ ላይ ነው። “የመሬት አስተዳደር፣ ፍትህ እና ካሳ ለአፍሪካውያን እና ለዘርዓ አፍሪካውያን” በሚል መሪ ሀሳብ ስድስተኛው የአፍሪካ የመሬት ፖሊሲ ኮንፍረንስ ከህዳር 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ይገኛል። ኮንፍረንሱን ያዘጋጁት የአፍሪካ ህብረት፣ የአፍሪካ ልማት ባንክ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ኢሲኤ) በጋራ በመተባበር ነው። ከአፍሪካ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ታሪካዊ እና የአካባቢ ጉዳዮች ጋር የተጣጣሙ እና ለነባራዊ እውነታዎች ምላሽ የሚሰጡ የመሬት ፖሊሲ ምርጥ ተሞክሮዎች በኮንፍረንሱ ላይ እየቀረቡ ይገኛል። ህዳር 1 በነበረው የጉባኤው መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ጸኃፊ ክላቨር ጋቴቴ በአፍሪካ የመሬት ፖሊሲ ጉዳይ ላይ የሚመክረው ስብሰባ በወሳኝ ወቅት የተዘጋጀ ነው ብለዋል። አፍሪካውያን ያላቸውን ሰፊ የመሬት ሀብት በቅኝ ግዛት አሰራሮች ሳቢያ በአግባቡ መጠቀም ባለመቻላቸው በአፍሪካ መሬት ዛሬም የግጭትና የኢ-ፍትሐዊነት መገለጫ ሆኗል ብለዋል። በአፍሪካ የመሬት አስተዳደር በሴቶች፣ በወጣቶችና በዝቅተኛ አርሶ አደሮች ዘንድ ኢ-ፍትሐዊነትን በማንገስ ሰፊ የኢኮኖሚ ልዩነት መፍጠሩን ገልጸዋል። የአፍሪካ የመሬት ፖሊሲ ስብሰባ ከአፍሪካ ሕብረት 2025 "የማካካሻ ፍትህ ለአፍሪካውያን እና ዘርዓ አፍሪካውያን" መሪ ሀሳብ ጋር የተጣጣመ መሆኑን አንስተው፤ ዓላማው አፍሪካውያን ከዓለም ነባራዊ ሁኔታ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ነው ብለዋል። የአፍሪካውያንና ዘርዓ አፍሪካውያን የካሳ ጥያቄ ያለፈውን ማስመለስ ሳይሆን አሁን ባለው የዓለም የፋይናንስ ስርዓት ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ እንደሆነ ገልጸዋል። አፍሪካ 65 በመቶ ያልታረሰ መሬት፣ ከዓለም ኢንዱስትሪ ሁለት በመቶ ብቻ ድርሻ ያላት፣ ለአየር ንብረት ለውጭ ተፅዕኖ ያላት ድርሻ ከአራት በመቶ በታች የሆነ አህጉር መሆኗን አንስተዋል። በአፍሪካ የመሬት አስተዳደር ስርዓቱን በማዘመን ፍትሐዊነትን ማስፈን ጊዜው አሁን ነው ያሉት ዋና ጸኃፊው፣ ሴቶችን ወጣቶችና ዝቅተኛ አርሶ አደሮችን በማሳተፍ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥና ዘላቂ ሰላም ማስፈን እንደሚገባ ገልጸዋል። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን የዜጎችና ዳያስፖራ ዳይሬክተር አምር አልጆዋሊ የአፍሪካ የመሬት ፖሊሲ የአህጉሪቱን መፃኢ ጊዜ ለመቀየር ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑን ገልጸዋል። በአፍሪካና ዘርዓ አፍሪካውያን ላይ የደረሰው በደል ዕውቅና ማግኘት እንዳለበት ገልጸው፤ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ለሕብረቱ መሪ ሀሳብ ትግበራ ቁርጠኛ መሆኑን ተናግረዋል። የመሬት አስተዳደር የፍትሐዊነት ምልክት መሆኑን በማንሳት፤ የመሬት ፍትሐዊ ተጠቃሚነት መስፈን አለበት ብለዋል። የአፍሪካ ሕብረት አጀንዳ 2063 በማሳካት አካታች ብልፅግናና ሰላምን ለማረጋገጥ በትብብር መስራት ይገባል ብለዋል። ሕብረቱ በመሬት አስተዳደር ዙሪያ ግልፅ አሰራር እንዲሰፍን ለአባል ሀገራት አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን አንስተዋል። ስድስተኛው የአፍሪካ የመሬት ፖሊሲ ኮንፍረንስ እስከ ህዳር 5 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል። ውጤታማ እና ተጠያቂነት የሰፈነበት የመሬት አስተዳደር ስርዓት መገንባት፣ ተቋማዊ አቅምን መፍጠር እና የቁጥጥርና ክትትልን ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ምክክር እንደሚደረግ የአፍሪካ ህብረት መረጃ ያመለክታል። የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት የቅኝ ግዛት አሻራዎች እና ወቅታዊ የኢ-ፍትሃዊነት ጉዳዮች በመሬት ባለቤትነት እና አስተዳደር ያሳደሯቸውን ተጽእኖዎች ለመፍታት ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ይገልጻሉ። በመሬት ፖሊሲ ቀረጻ፣ ትግበራ እና ቁጥጥር አቅምን መገንባት፣ የእውቀት ሽግግርን ማሳደግ እና የፖሊሲ ቁርጠኝነትን ወደ ሚጨበጥ የተግባር ምላሽ የመቀየር ጉዳይም አጽንዖት የሚሰጣቸው አጀንዳዎች መሆናቸውን ህብረቱ ገልጿል። በአህጉራዊ ኮንፍረንሱ ላይ የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት፣ የህብረቱ ተቋማት እና አደረጃጀቶች ከፍተኛ አመራሮች፣ ተመራማሪዎች፣ የፖሊሲ ባለሙያዎች፣ የማህበረሰብ መሪዎች፣ ትውልደ አፍሪካውያንና ሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛል። የአፍሪካ የመሬት ፖሊሲ ኮንፍረንስ በየሁለት ዓመቱ የሚካሄድ ሁነት ነው። የመሬት ፖሊሲ ጉባኤው አፍሪካውያን ፍትሃዊ እና ዘላቂ የመሬት አስተዳደርን ለማስፈን ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነታቸውን እያሳዩበት የሚገኝ መድረክ ነው። ጉባኤው አፍሪካውያን ከባለፈው ታሪክ በመማር ፖሊሲ፣ ጥናት እና የማህበረሰብ ድምጾችን በማቀናጀት ረገድ ያለው ፋይዳ ወሳኝ ነው። ጉባኤው የመሬት ፍትህን የማስፈን፣ አይበገሬነትን የመገንባት እና ለሁሉም አፍሪካውያን የጋራ ብልጽግና የማረጋገጥ የጋራ ራዕይ በመደገፍ ረገድ የበኩሉን ድርሻ ይወጣል።
ለጆሮ ህመም አጋላጭ ምክንያቶች ምንድን ናቸው?
Nov 7, 2025 708
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የአንገት በላይ ሕክምና ስፔሻሊስት ሐኪም ኦሊያድ ታረቀኝ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ስለ ጆሮ ህመም መንስዔ እና መደረግ ስላለበት ጥንቃቄ አብራርተዋል። የጆሮ ህመም ምንድን ነው? እንደ ዶክተር ኦሊያድ ገለጻ፤ በጆሮ አካባቢ ያሉ የአካል ክፍሎችን የሚያጠቁ ህመሞች የጆሮ ህመም ሊባሉ ይችላሉ። በሳይንሱ የውጨኛው፣ የመካከለኛው እና የውስጠኛው የጆሮ ክፍል ህመም ተብለው እንደሚለዩ ጠቅሰው፤ እነዚህን ክፍሎች የሚያጠቁ የተለያዩ የህመም ዓይነቶች እንዳሉም አመላክተዋል። የጆሮ ህመም ዓይነቶች በተለያዩ መንስዔዎች የተለያዩ ህመሞች እንደሚከሰቱ ጠቁመው፤ ከእነዚህ መካከል በስፋት የሚከሰተው በኤንፌክሽን የሚከሰት የጆሮ ህመም መሆኑን ተናግረዋል። ከአደጋዎች፣ ህመሞችና ጉዳቶች ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ የጆሮ ክፍሎች ህመሞች እንዳሉም በመጠቆም። እንዲሁም ከዕባጮች (ዕጢዎች) ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ የጆሮ ህመሞች እንዳሉ አመላክተዋል። በውጨኛው የጆሮ ክፍል የሚከሰቱ ከአጥንትና ከቆዳ የሚነሱ ዕባጭና ዕጢዎች፣ ከመካከለኛው የጆሮ ክፍል የሚነሱ በአብዛኛው ከደም ሥር ጋር የተያያዙ ዕጢዎች እንዲሁም ከውስጠኛው የጆሮ ክፍል ከነርቭ የሚነሱ የተለያዩ ዓይነት ዕጢዎች ሊኖሩ እንደሚችሉም አብራርተዋል። ለጆሮ ህመም አጋላጭ ምክንያቶች የጆሮ ህመም በሁሉም ጾታና የዕድሜ ክልል ሊከሰት እንደሚችል ገልጸው፤ በአብዛኛው አጋላጭ ምክንያቶች ተብለው ከሚነሱት መንስዔዎች መካከል ከታች የተጠቀሱት ዋነኞቹ መሆናቸውን ያብራራሉ። o ባብዛኛው ዕድሜያቸው ከ14 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች (ልጆች ባላቸው ያልዳበረ በሽታዎችን የመከላከል ዐቅም እንዲሁም አንዳንድ የሰውነት ክፍሎቻቸው በደንብ ባለመዳበራቸው ሊከሰት የሚችል ነው።) o ዕድሜ ሲጨምር የጆሮ መዳከም ችግር ሊኖር ስለሚችል የመስማት ዐቅም እየቀነሰ ሊሄድ ይችላል። o ለተለያየ ከባድ ድምጽ መጋለጥ ለጆሮ ህመም ወይም የተለያየ ደረጃ ላላቸው የመስማት ችግሮች ሊዳርግ ይችላል። o ሲጋራ ማጨስ እንዲሁም የተለያዩ ዓይነት ጭሶች መጋለጥ ለጆሮ ህመም ሊያጋልጥ ይችላል ተብሎ እንደሚታሰብ አስረድተዋል። የጆሮ ህመም ምልክቶች ምልክቶቹ እንደ ህመሙና ህመሙ እንደተከሰተበት ቦታ የተለያዩ መሆናቸውን ዶክተር ኦሊያድ ይገልጻሉ። ለምሳሌ በኢንፌክሽን ምክንያት የሚከሰት የጆሮ ህመም ከሆነ እንደተከሰተበት የጆሮ ክፍል ምልክቱ ይለያያል ይላሉ። ለአብነትም የውጨኛው የጆሮ ክፍል ላይ የሚከሰት የጆሮ ኢንፌክሽን ከሚያሳያቸው ምልክቶች መካከል መጠዝጠዝ፣ ውጋትና ማሳከክ ዋናኞቹ ናቸው ብለዋል። ራሱ ይህ ህመም በመካከለኛው የጆሮ ክፍል ላይ ሲከሰት ደግሞ የመስማት ደረጃ መቀነስ፣ ትኩሳት፣ አልፎ አልፎ ከባድ የጆሮ ውጋት መኖር፣ የህመሙ ደረጃ እየጨመረ ሲሄድም የተለያዩ ፈሳሾችን ሊያሳይ ይችላል (ለምሳሌ እንደ ውኃ የቀጠነ ፈሳሽ፣ ወፍራም መግል የመሰለ ፈሳሽ፣ አንዳንድ ጊዜ ደም የቀላቀለ ፈሳሽ ሊሆን ይችላል ሲሉ አብራርተዋል።) በተለያዩ ዕባጮችና ዕጢዎች የሚከሰት የጆሮ ህመም ሲሆን ከሚያሳያቸው ምልክቶች መካከል፤ የጆሮ መደፈን ስሜት (ጆሮ ድፍን ብሎ ለመስማት መቸገር)፣ የተለያየ ዓይነት የጆሮ ውስጥ ድምጽና ጩኸቶች መኖር (አንዳንድ ጊዜ ከልብ ምት ጋር አብሮ ሊሰማ የሚችል የጆሮ ውስጥ ጩኸት ሊሆን ይችላል) ብለዋል። በውስጠኛው የጆሮ ክፍል ላይ የሚከሰት የዕጢ ዓይነት ደግሞ የመስማት ደረጃ መቀነስ፣ ማዞር እና ቫላንስ እስከ ማጣት (ሚዛንን ጠብቆ ለመንቀሳቀስ እስከመቸገር) የሚያደርሱ ምልክቶችን ሊያሳይ እንደሚችል ጠቁመዋል። ሰዎች ለጆሮ ህመም እንዳይጋለጡ ምን ያድርጉ? ሰዎች የተለያዩ ጥንቃቄዎችን ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው መክረው፤ ከእነዚህ ጥንቃቄዎች መካከልም፡- o በልማድ የሚደረጉ ጭራሽ ለጉዳት አጋላጭ የሆኑ ጆሮን የማጽዳት ተግባራት (‘የጆሮን ንጽህና እየጠበቅሁ ነው’ ብሎ በማሰብ ጆሮን ለማጽዳት የሚደረጉ ልማዶችን) ማስወገድ፤ o ጆሮ ለከባድ ድምጽ እንዳይጋለጥ ማድረግ። ለምሳሌ ለረጅም ሠዓት ‘ኤርፎን’ መጠቀም ለጆሮ ህመም እንደሚያጋልጥ በመገንዘብ የሠዓቱን እና የድምጹን መጠን መቀነስ እንደሚገባ መክረዋል። ‘ኤርፎን’ በአንድ ጊዜ ለ60 ደቂቃ የድምጽ መጠኑ ከ60 በመቶ ባልበለጠ ጊዜ መጠቀም ይመከራል ያሉት ዶክተር ኦሊያድ፤ ከዚህ ደቂቃ በላይ በአንድ ጊዜ መጠቀም ሲያስፈልግ በየመሀሉ ከ15 እስከ 20 ደቂቃ ጆሮን ማሳረፍ እንደሚገባ ይመክራሉ። በሌላ በኩል ማሳከክን ጨምሮ የጆሮ ህመም ስሜት ሲኖር በወቅቱ ተገቢውን የሕክምና ዕርዳታ በማድረግ ህመሙ ወደ ከፋ ደረጃ ሳይደርስ መታከም የጥንቃቄው አካል መሆኑን አስረድተዋል። የጆሮ ህመም ሕክምና ሕክምናው እንደ ህመሙ ዓይነት እንደሚለያይ አስገንዝበው፤ በአጠቃላይ በሚዋጡ፣ በመርፌ በሚሰጡ፣ በጆሮ ውስጥ በሚጨመሩ እንዲሁም በሚቀቡ አማራጮች ሕክምናው እንደሚሰጥ አብራርተዋል። ከላይ ከተጠቀሱት የሕክምና አማራጮች አልፎ የመስማት ደረጃ መቀነስና መቸገር ከተስተዋለ የቀዶ ሕክምና ማድረግ ብሎም የማዳመጫ ማገዣ መሣሪያ መጠቀም የሕክምናው አካል መሆናቸውን አስረድተዋል። የጆሮ ህመም በኢትዮጵያ በኢትዮጵያ ከ5 እስከ 14 ዓመት ዕድሜ ባላቸው ልጆች ላይ 8 በመቶ እንዲሁም ዕድሜያቸው ከ60 በላይ በሆኑ ሰዎች ደግሞ እስከ 73 በመቶ ድረስ የመስማት ችግር እንደሚያጋጥም ጥናት ማመላከቱን ጠቅሰዋል። ጆሮ ላይ የሚከሰቱ ህመሞች የመስማት ችግርን ሊያስከትሉ ስለሚችሉ ሕብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ መክረዋል።
ትንታኔዎች
ማድያት እና ህክምናው
Sep 29, 2025 2629
ማድያትን ለማከም አስቸጋሪ መሆኑንና በታካሚዎች ላይም የሥነ ልቡና እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ጫና ሊያመጣ የሚችል መሆኑን የቆዳ ሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ። ስለ ማድያት መንስዔ፣ ስለሚከሰትበት የሰውነት ክፍል፣ ማድያት ያለበት ሰው ማድረግ ስላለበት ጥንቃቄ፣ ቆዳን ስለሚያስቆጣ ሠርካዊ ልማድ እና ሕክምናውን በተመለከተ በራስ ደስታ ዳምጠው መታሰቢያ ሆስፒታል የቆዳ እና አባላዘር በሽታዎች ስፔሻሊስት ዶክተር አደራጀው ብርሃን ከኢዜአ ቆይታ አድርገዋል። በማብራሪያቸውም፤ በቆዳ ውስጥ ያሉ ቀለም አምራች ኅዋሶች(ሴሎች) ከመጠን በላይ ቀለም ሲያመርቱ ማድያት ተከሰተ እንደሚባል ገልጸዋል። ለዚህም መንስዔው የተፈጥሮ ተጋላጭነት ከተለያዩ ቀስቃሽ ምክንያቶች ጋር የሚያደርጉት መሥተጋብር መሆኑን አስረድተዋል። 👉 የማድያት መንስዔ ምንድን ነው? 1ኛ. የሆርሞን ለውጥ፡- በእርግዝና ወቅት ወይም የወሊድ መቆጣጠሪያ ሲጠቀሙ የሚኖር የሆርሞን ለውጥ ማድያት እንዲከሰት ወይም እንዲባባስ ያደርጋል ይላሉ የሕክምና ባለሙያው። 2ኛ. የፀሐይ ጨረር፡- ከልክ ያለፈ ፀሐይ ቀለም አምራች ኅዋሶች(ሴሎች) በብዛት ቀለም እንዲያመርቱ ስለሚያነቃቃ፤ የፀሐይ ጨረር ዋነኛ ቀስቃሽ እና አባባሽ ምክንያት መሆኑንም ገልጸዋል። 3ኛ. የዘር ሐረግ፡- በቤተሰብ ውስጥ ማድያት ካለ በዘር የመተላለፍ ዕድሉ ከፍተኛ መሆኑንም ይናገራሉ። 4ኛ. የቆዳ ዓይነት፡- ጥቁሮች (ከቡናማ እስከ ጥቁር የቆዳ ቀለም ያላቸው) ንቁ ቀለም አምራች ሴሎች ስላሏቸው ለማድያት የሚኖራቸው ተጋላጭነት ከፍተኛ መሆኑን ነው የተናገሩት። 5ኛ. ሌሎች መንስዔዎች፡- ሙቀት (የሚታዩ እና የማይታዩ ጨረሮች እንዲሁም የምድጃ እሳት)፤ የተለያዩ መድኃኒቶችና የመዋቢያ ምርቶች፤ የእንቅርት ዕጢ ህመሞች እንዲሁም ጭንቀት ማድያት እንዲከሰት ወይም እንዲባባስ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል መሆናቸውንም የሕክምና ባለሙያው አስገንዝበዋል። 👉 ማድያት በየትኛው የቆዳ ክፍል ላይ ይከሰታል? ማድያት ከሚከሰትበት የቆዳ እና የሰውነት ክፍሎች አንጻር በሁለት ከፍሎ ማየት እንደሚቻል ዶክተር አደራጀው አንስተዋል። እነሱም 1ኛ. ከሚከሰትበት የቆዳ ክፍል አንጻር፡- ማድያት በውስጠኛውም ሆነ በላይኛው የቆዳ ክፍሎች ላይ ወይም በሁለቱም ላይ ሊከሰት ይችላል ብለዋል። 2ኛ. ከሚከሰትበት የሰውነት ክፍሎች አንጻር፡- የሕክምና ባለሙያው እንዳሉት 60 በመቶ ማድያት ግንባር፣ ጉንጭ፣ አፍንጫ፣ የላይኛው ከንፈር እና አገጭ ላይ ይከሰታል ብለዋል። 30 በመቶው ደግሞ ጉንጭ እና አፍንጫ ላይ እንዲሁም 10 በመቶው የአገጭ መስመርን ተከትሎ እንደሚከሰት አስረድተዋል። በሌላ በኩል አልፎ አልፎ ከፊት የሰውነት ክፍሎች በተጨማሪ በደረት፣ አንገት እና ክንድ ላይ የሚከሰትበት ሁኔታ መኖሩንም ጠቁመዋል። 👉 የማድያት ባሕርይ ማድያት የቆዳ ቀለም ለውጥ ያመጣል፤ በግራና በቀኝ የፊት ክፍል ይወጣል። የማሳከክ ወይም የህመም ስሜት እንደሌለውም ዶክተር አደራጀው አስረድተዋል። • ማድያት በላይኛው የቆዳ ክፍል ላይ ሲከሰት፡- ነጣ ወይም ጠቆር ያለ ቡናማ የሆነ የቆዳ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይ አመላክተዋል። • ማድያት በውስጠኛው የቆዳ ክፍል ላይ ሲከሰት፡- ሰማያዊ ግራጫ ወይም ጠቆር ያለ ግራጫ የቆዳ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይ አንስተዋል። • ማድያት በሁለቱም የቆዳ ክፍሎች ላይ ሲከሰት፡- የተቀላቀለ የቡናማ እና ግራጫ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይም ባለሙያው አብራርተዋል። 👉 ማድያት ያለበት ሰው ምን ዓይነት ጥንቃቄዎችን ማድረግ ይገባዋል? 1ኛ. ወርቃማ ጥንቃቄ፡- • ተከታታይና ጥብቅ የሆነ የፀሐይ መከላከያ መጠቀም ይገባል ይላሉ የሕክምና ባለሙያው። በዚህም መሠረት ከቤት ከመውጣት ከ20 እስከ 30 ደቂቃ ቀደም ብሎ የፀሐይ መከላከያ ክሬሞችን መቀባትና በሁለት ሠዓት ልዩነት እየደረቡ መቀባት። • በሌላ በኩል ከ4 እስከ 10 ሠዓት ያለው የፀሐይ ሙቀት ለቆዳ ህመም አጋላጭ መሆኑን በመገንዘብ ከፀሐይ መከላከያ ክሬም በተጨማሪ ጥላና ኮፍያን መጠቀም እንደሚገባ መክረዋል። 2ኛ. ቆዳን የሚያስቆጣ የቆዳ እንክብካቤ (መስተካከል ያለበት ልማድ)• ቆዳን የሚያስቆጡ መታጠቢያዎች(ሳሙናን ጨምሮ ሌሎችም) እንዲሁም መዋቢያዎችና የሚቀቡ ነገሮች (ኮስሞቲክስን ጨምሮ ሌሎችም) አለመጠቀም ይገባል ይላሉ። • ለቆዳ ተስማሚ የሆኑ ማለስለሻዎችን በደንብ መጠቀም እንደሚገባም ይመክራሉ። 3ኛ. በሐኪም የታዘዙ መድኃኒቶችን በአግባቡ መጠቀም • በሐኪም የታዘዘ መድኃኒትን በአግባቡ(ሳያቆራርጡ) መጠቀም እንደሚመከር ያስረዱት ዶክተር አደራጀው፤ እንደ ማድያቱ እና እንደ ሰዎቹ ቆዳ ዓይነት መድኃኒቱ ለውጥ የሚያሳይበት ጊዜ ስለሚለያይና ከ8 እስከ 12 ሣምንት ሊወስድ ስለሚችል ታግሶ በደንብ ቢጠቀሙ መልካም ነው ይላሉ። 4ኛ. የተለያዩ የሕክምና አማራጮችን መጠቀም• የሕክምና ባለሙያው እንደሚመክሩት፤ በዘርፉ ያሉ የተለያዩ የሕክምና ዓይነቶችን ለምሳሌ እንደ ኬሚካል ፒልስ፣ የቆዳ ሕክምና እና ማይክሮ ኒድሊንግ ያሉትን በሐኪም ምርመራ መሠረት መጠቀም ይገባል። 5ኛ. ከወሊድ መቆጣጠሪያ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ የተከሰተ ማድያት ከሆነ ከሕክምና ባለሙያ ጋር በመመካከር ሌላ አማራጭ መጠቀም እንደሚገባም አንስተዋል። እንዲሁም ጭንቀትን መቀነስ እንደሚገባ መክረዋል። 👉 የማድያት ሕክምናን በተመለከተ የማድያት ሕክምና በጣም አስቸጋሪ ከሚባሉትና ረጂም ጊዜ ከሚወስዱ እንዲሁም በመመላለስ ከሚያስቸግሩ የቆዳ ሁኔታዎች አንዱ መሆኑን ዶክተር አደራጀው ገልጸዋል። በሕክምና ማድያቱ የጠፋላቸው ሰዎች መኖራቸውን አረጋግጠው፤ በሌላ በኩል በሕክምና ሂደት የማድያቱ ሁኔታ ከነበረበት እየቀነሰ ለውጥ የሚታይበት ሁኔታ አለ ብለዋል። ይህን ለውጥ የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ማስቀጠል እንደሚገባም ይመክራሉ። እንክብካቤው ከተቋረጠ ግን ማድያቱ እንደገና የሚመለስበት ሁኔታ መኖሩን አስገንዝበዋል። 👉 የማድያት ሕክምና አማራጮች የሚቀቡ መድኃኒቶች፣ የሚዋጡ መድኃኒቶች፣ ሌሎች የሕክምና አማራጮች(ኬሚካል ፒልስ፣ የቆዳ ሕክምና እና ማይክሮ ኒድሊንግ)፣ የፀሐይ መከላከያ አማራጮችን በአግባቡ አዘውትሮ መጠቀም እንደሚገባ ይመክራሉ።
በ600 ዓመታት አንድ ጊዜ 7 ቀናት የሚኖሯት ጳጉሜን…
Sep 5, 2025 2653
ጳጉሜን በሦስት ዓመታት አምስት፣ በአራት ዓመታት ውስጥ ስድስት እንዲሁም በ600 ዓመታት ውስጥ አንድ ጊዜ ሰባት ቀናት ይኖሯታል። 👉 ‘ጳጉሜን’ ማለት ምንድን ማለት ነው? ‘ጳጉሜን’ የሚለው ስያሜ “ኤፓጉሜኔ” ከሚለው የግሪክ ቃል መምጣቱን በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የነገረ መለኮትና የሥነ-ልቡና መምህር አባ ጌዴዎን ብርሀነ ይገልጻሉ። ትርጉሙም “ተውሳክ ወይም ተረፍ” ማለት መሆኑን ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ አስረድተዋል። (አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፤ መዝገበ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገብ ቃላት፤ ገጽ ፱፻፭) ላይም “በዓመቱ መጨረሻ ላይ አምስት ወይም ስድስት ቀን በመሆን ተጨማሪ ሆና የምትመጣ መሆኗ ተገልጿል። በዚሁ መሠረት በሦስት ዓመት አምስት፤ በአራት ዓመት (በዘመነ ዮሐንስ) ስድስት እንዲሁም በ600 ዓመታት አንድ ጊዜ ሰባት ቀናት እንደምትሆን ተመላክቷል። 👉 የጳጉሜን መሠረት? ይህን በተመለከተ መምህር አባ ጌዴዎን ሲያስረዱ፤ በየቀኑ የሚተርፉ ተረፈ ደቂቃዎችና ሰከንዶች ቀናትን እያስገኙ ተጠራቅመው ከዓመቱ በስተመጨረሻ አምስት ዕለታት ይተርፋሉ ይላሉ። በዚህም ጳጉሜን የተባሉ አምስት ዕለታት እንደሚገኙ ጠቁመው፤ አንድ ዓመት ደግሞ 365 ዕለት ከ15 ኬክሮስ ከ6 ካልኢት ይሆናል ሲሉ ይገልጻሉ። 15ቱ ኬክሮስ በአራት ዓመት ስድስት ጳጉሜንን ይወልዳል ያሉት መምህሩ፤ ስድስቱ ካልኢት ደግሞ በ600 ዓመት ሰባተኛ ጳጉሜንን ያስገኛሉ በማለት አብራርተዋል። 👉 ከጭማሬ ቀንነት በተለየ ያላት ትርጓሜ ምንድን ነው? እንደ መምህር አባ ጌዴዎን ገለጻ፤ ‘ጳጉሜን’ ከተጨማሪ ቀናትነት የተሻገረ ለኢትዮጵያውያን የማንነት ዐሻራ የእኩልነት ምልክት ናት። በዓለም ዘንድ ባለው የበላይነት እና ሌላውን አሳንሶ የማየት ዝንባሌ እንደነዚህ ያሉ የጥበብ መንገዶች የኢትዮጵያውያንን ማንነትና በዓለም ዘንድ የነበራቸውን የቀዳሚነት ቦታም ከሚያሳዩ ምልክቶች መካከል አንዱ በመሆኑ የማንነት መገለጫ ናት ይላሉ። ምክንያቱም ከማንም ያልተወሰደ የራስ ማንነት መኖሩ ኢትዮጵያውያን አባቶቻችን በዓለም ዘንድ የነበራቸውን የመፈላሰፍ፣ የስልጣኔና አካባቢያቸውን በንቃት የመገንዘብ አቅም የሚያሳይ ስለሆነ ብለዋል። ጳጉሜን ኢትዮጵያን ከቀደምት ስልጡን ሀገራት መካከል ቀዳሚ የስልጣኔ ፋና የፈነጠቀባት ለመሆኗ ማሳያ ስለመሆኗም ይናገራሉ። የሰው ልጅ አካባቢውን በንቃት መገንዘብ መጀመሩ እና የሰማያዊ አካላትን የማይዋዥቁ ክስተቶች በመከታተል የማይታየውንና የማይሰፈረውን የጊዜ ርዝማኔ በብርሃናት እየሰፈረና እየለካ፤ ዕለታትን፣ ሳምንታትን፣ ወራትን፣ ወቅትን፣ ዓመታትን፣ አዝማናትን እና ሌሎች ዐውዳትን መቀመሩን ጠቅሰዋል። በዚህም የጊዜ ልኬት ከሥነ-ፈለክ እና ከሐሳበ-ከዋክብት ጋር በእጅጉ የተቆራኘ እንዲሆን አድርጎታል ነው ያሉት። በአጭሩ ኢትዮጵያውያን አባቶቻችን ከሚያዩአቸው ተደጋጋሚ ሁነቶች በመነሳት የጊዜ አሃዶችን ወስነዋል፤ ክፍፍሎችንም በይነዋል ብለዋል መምህር አባ ጌዴዎን። በተለይም ለዕይታቸው ቅርብ የሆኑት የፀሐይ እና የጨረቃ ያለማቋረጥ መውጣት እና መግባት፣ የሚወጡበት እና የሚገቡበትም የጊዜ መጠን በአንጻራዊነት ቋሚ በመሆኑ ለቀን አቆጣጠራቸው ዋነኛ ግብዓቶች እንደሆኗቸው ተናግረዋል። በሂደትም የዑደታቸውን የጊዜ መጠን በሚገባ ተረድተው፣ የዑደታቸውን ህጸጾች ዐወቁ ይላሉ። በዚህ ብቻ ሳይገደቡ የሰማይ አሰሳን ከፀሐይ እና ጨረቃ ወደ ሌሎች አፍላካት፣ ወደ ከዋክብትም ጭምር ማስፋታቸውን ነው የሚገልጹት። በዚሁ መሠረት ኢትዮጵያ የራሳቸው የቀን መቁጠሪያ ቀመር ካላቸው ቀደምት ሀገራት መካከል አንዷ መሆን መቻሏን አስገንዝበዋል። ለዚህም በዋቢነት ከሚጠቀሱት ጥንታዊ መዛግብቶቿ መካከል መጽሐፈ ሄኖክን እና አቡሻኽርን አንስተዋል። 👉 ከነበረው ወደ ሌላኛው ዓመት መሻገሪያ እንደመሆኗ ሰዎች በዚህ ወቅት ምን አይነት ሥነ-ልቡናዊ ዝግጅት እንዲያደርጉ ይመከራል? ጊዜ የለውጥ መስፈሪያ (መለኪያ ወይም መለያ ድንበር) መሆኑን የሚገልጹት መምህር አባ ጌዴዎን፤ ለውጥ ያለጊዜ፣ ጊዜም ያለ ለውጥ አይሆኑም፤ ትርጉምም የለውም ይላሉ። ጊዜ በዚህ ዓለም የማይቋረጥ ሂደት፤ የማይቆም የለውጥ ጥያቄ መሆኑንም ያስገነዝባሉ። በዚህ የለውጥ ምክንያት የሰው ልጅ የሚኖረው ከተሰጠው ወይም ካለው እየቀነሰ እንጅ እየጨመረ እንዳልሆነም ይጠቅሳሉ። ስለዚህ ጳጉሜን የማንቂያ ደወል ናት፤ የአዲስ ዘመን ማብሰሪያ አዲስ ዘመን በለውጥ ምክንያት የተገኘ በመሆኑ ከነበረው የዕለታት ድምር ባሻገር አዲስ የሚል ቅጽል ይዞ መጥቷል ይላሉ። ስለዚህ ጳጉሜን ምን አዲስ ነገር አለ የሚል የሕይወት ጥያቄ አስከትላ የመጣች በልባችን ምኅዋር የምታቃጭል ናት ብለዋል። በጳጉሜን ብዙዎች በጽሞና ሆነው ራሳቸውን የሚያዳምጡባት ወደውስጥ በጥልቀት የሚመለከቱባት በመሆኗ ባለፉት ጊዜያት ያልተሳኩትን በቀጣይ ለማሳካት አዳዲስ ሐሳቦችን እና እቅዶችን በማዘጋጀት ለቀጣዩ ምዕራፍ የምታሻግር ናት በማለት ገልጸዋል።
የባሕር በር የሌላቸው ሀገራት አንገብጋቢው ጉዳይ
Aug 6, 2025 3552
የባህር በር ጉዳይ በሀገራት ዘንድ በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ግዙፍ ኢኮኖሚና ሰፊ ህዝብ ላላቸው ሀገራት ሕልውና ጉዳይ ሆኗል። በቱርክሜኒስታን አዋዛ ከተማ ሶስተኛው ባህር በር አልባ ታዳጊ ሀገራት ጉባዔ በመካሄድ ላይ ይገኛል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝም በጉባኤው መክፈቻ ላይ ቁልፍ መልዕክት አስተላለፈዋል። ዋና ፀሐፊው ባህር በር የሌላቸው ሀገራት በተለይም መልኩ እየተለዋወጠ ባለው ዓለም፤ በአየር ንብረት ለውጥና መሰል ተጽዕኖዎች ሳቢያ መልከ ብዙ ፈተና እንደተደቀነባቸው ገልጸዋል። በተለይ ለአንዳንዶቹ ህልውናቸውን እየተፈታተነ ስለመሆኑም አጽንኦት ሰጥተዋል። የዋና ጸሐፊው ንግግርም ፦ ዛሬ ከዚህ የተሰባሰብነው ለማንክደው አንድ ዕውነት ነው። መልክዓ ምድር መዳረሻን መወሰን የለበትም። ነገር ግን በአፍሪካ፣ በኤዥያ፣ በላቲን አሜሪካና በአፍውሮፓ 32 ሀገራት ባህር በር ስለሌላቸው የማደግ ዕድላቸው ተገድቧል፤ ኢ-ፍትሃዊነትንም አስፍቷል። ሀገራችሁ አያሌ ተግዳሮቶች ተጋርጦባቸዋል። ዕድገታቸው እንዲወሰን፣ በከፍተኛ የወጪ ንግድ ትራንስፖርት እንዲበዘበዙና በዓለም ገበያ ተደራሽ እንዳይሆኑ ፈተና ገጥሟቸዋል። በርካቶች በጥሬ ዕቃ ኤክስፖርት እንዲወሰኑ፣ ለተለዋዋጭ ዓለም አቀፍ ገበያ እንዲጋለጡ ብሎም በጠባብ ኢኮኖሚያዊ መሰረት እንዲታጠሩ አድርጓቸዋል። በሌላ በኩል የዕዳ ጫና ለመልከ ብዙና ዘላቂነት ላለው ችግር ዳረጓቸዋል። አንድ ሶስተኛው የዓለማችን ባህር በር አለባ ሀገራትም ለደህንነት እንዲጋለጡና የግጭት አዙሪት ችግር እንዲገጥማቸው ተገደዋል። ምንም እንኳን 7 በመቶው የዓላማችን ህዝብ ድርሻ ቢይዙም በዓለም ኢኮኖሚ አንድ በመቶ ብቻ ድርሻ ይዘዋል። ይህም ምንጊዜም ኢ-ፍትሃዊነትና መገለል ሁነኛ ማሳያ ነው። ይህ የኢ-ፍትሃዊነት መልክ ዘላለማዊ መሆን የለበትም። ባህር በር የሌላቸው ሀገራት በዓለም የፋይናንስና የንግድ መዋቅር ውስጥ ለከፍተኛ ችግር የተጋለጡ ናቸው። በበይነ-ዓለም ትስስር በገሀድ በሚታይበት የዛሬው የዓለም መልክ ስርዓታዊ መድሎና መገለል በይፋ የደረሰባቸው ሀገራት ናቸው። ይህም በብዙ ምክንያቶችም የቅኝ ግዛት አሻራ ምልክት ነው። በቅርብ ጊዜ ትውስታዎች እንኳን ከኮቪድ 19 እስከ አየር ንብረት ለውጥ ቀውሶች፣ ከአቅርቦት ሰንሰለት መስተጓጎል እስከ ግጭት እንዲሁም በጂኦፖለቲካዊ ውጥረቶች ሳቢያ ባህር በር የሌላቸው ሀገራት ዘላቂ የልማት ግቦችን ዕውን ለማድረግ ተቸግረዋል። ይህ ጉባኤ ችግሮችን ከማንሳት ባሻግር መፍትሄዎች ላይ ማተኮር አለበት። የቀጣይ ዘመን የእድገት መሻት ጉዞን መቀየስ ብሎም ባህር በር አልባ ታዳጊ ሀገራትን የማልማት ዕድሎች በጋራ መግለጥ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መምክር ይገባል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም በዚህ ረገድ ከሀገራቱ ጎን የቆመ ነው። በቀጣይ አስርት ዓመታት በትብብር መሰራት ካለባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ መዋቅራዊ ሽግግርን ማሳለጥ እና ኢኮኖሚያዊ ስብጥርን ማብዛት ላይ መተኮር ይገባል። ምክንያቱም እነዚህ ሀገራት በሰው ሃይል እና በተፈጥሮ ሀብት የታደሉ ቢሆንም በፋይናንስ እጥረትና በገበያ እጦት ይህን አቅም ተጠቅመው መልማት አልቻሉም። ወሳኝ የሆኑ እሴት ጨማሪ ኢንዱስትሪዎችን መገንባት፣ ሀገር ውስጥ ፈጠራዎችን ማጎልበት እንዲሁም ለቀጣናው ለትውልድ ትሩፋት የሚያቋድስ አካታች ልማትን ዕውን ማድረግ ይሻል። የሀገራቱን የገበያና የመልክዓ ምድር ተግዳሮቶችን ለማቅለል አንዱ መፍትሄ የዲጂታላይዜሸን ሽግግር ነው። በዲጂታል ምህዳር ተደራሽነት ለማቅለልም በሰው ሰራሽ አስተውሎት ስራዎች መጠንከር አለባቸው። የግል ዘርፉን ማጠናከርም ኢ-ፍትሃዊነትና ተደራሸነትን ችግርን ለማቅለል ያግዛል። ሀገራቱ በቋንቋ፣ በባህልና በጥበብ በጥልቅ የተቆራኙ ናቸው። በሀገራቱ መካከል ያለው የተቆራረጠ ሎጂስቲክስ፣ ያልተሳለጠ የድንበር ግብይት፣ የተሟላ መሰረተ ልማት አለመኖር በዓለም ገበያ ተወዳደሪና ተደራሽ ለመሆን አልቻሉም። በመሆኑም ድንበር ዘለል የሆኑ ትስስሮችን ማሳለጥ በተለይም ሀገራትን የሚያስተሳሰሩ ኮሪደሮችን መገንባት፣ የጭነት ሎጂስቲክስን ማሳለጥ፣ የሃይል እና የአየር ትራንስፖርት ትስስርን መጨመር ያስፈልጋል። ይህን መንገድ በመከተል በቀጣናውና በዓለም ገበያ መግባት ብሎም ከጥሬ ዕቃ አቅራቢነት ወደ እሴት የተጨመረባቸው ምርቶችን ማቅረብ መሸጋገር ይቻላል። በዓለም አቀፍ ደረጃ የንግድ ግብይት መልክን መለወጥ፣ የትብብርና የጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተቃኘ አካሄድ መከተል ይገባል። ዓለም አቀፍ የባለብዙ ወገን የፋይናንስ ተቋማትም የበይነ ሀገራት የድንበር ላይ ትስስርና የጋራ ልማት ላይ ተገቢውን የኢንቨስትመነት ልማት ፋይናንስ ማቅረብ ይገባቸዋል። ባህር በር የሌላቸው ሀገራት በቀጣናው ደረጃ ከተሰባሰቡ ልማትን ዕውን ማድረግ ያስችላልና። ባህር በር አልባ ሀገራት ምንም እንኳን ከዓለማችን ሀገራት የበካይ ጋዝ ልቀታቸው ለከ3 በመቶ ያነሱ ቢሆነም የአየር ንብረት ለውጥ ቀውስ ገፈት ቀማሾች ግን እንርሱ ናቸው። ከሰሃራ በርሃ መስፋፋት እስከ በረዶ የሚቀልጥባቸው ተራራማ ሀገራት፣ የኤስያ ሀገራት አስቸጋሪ የአየር ጸባይ ለውጥ፣ በከባድ ዝናብና አውሎንፋስ የሚመቱ የላቲን አሜሪካ ሀገራት ለዚህ ማሳያ ናቸው። የአየር ንብረት ለውጥ ባህር በር አልባ ሀገራትን እየበላቸው ነው። የአየር ንብረት ለውጥና ባህር በር አልባነት ተዳምሮ ዕድገታቸውን እንዲወሰን ለአንዳንዶቹም በህልውናቸው ላይ አደጋ ደቅኗል። በተባበሰው የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ሳቢያ በአንድ አዳር በሚደርስ የመሰረተ ልማት ውድመት የሀገራት ዓለም አቀፍ ንግድ ተሳትፎ አደጋ ውስጥ ይወድቃል። በመሆኑም ቃል የተገቡ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ መቋቋሚያ ፋየናንስ መተግበር፣ ተዕጽኖ የሚቋቋም መሰረተ ልማት መዘርጋት ይሻል” በማለት ነበር መልዕክታቸውን ያስተላለፉት። በአረንጓዴ ልማት፣ በፋይናንስ ማሰባሰብ፣ በብድር አቅርቦት እና ወለድ አያያዝና ትግበራ ጉዳይም ልብ መባል ያለበትን ጉዳይ ጠቅሰዋል። ባህር በር አልባ ሀገራት በጋራ ነጋቸውን ለማሳመርና ፈተናዎቻቸውን ለመሻገር በትብብር እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል። ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት ጥያቄዋን በይፋ ከገለጸች ውላ አድራለች፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የባህር በር ጥያቄ የህልውና ጉዳይ መሆኑን በተደጋጋሚ መግለጻቸው ይታወሳል።
ኢትዮጵያ የስርዓተ ምግብ ሽግግር ለምን አስፈለጋት?
Jul 19, 2025 3634
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቲኒዮ ጉቴሬዝ አነሳሽነት እ.አ.አ 2021 የተመድ የስርዓተ ምግብ ጉባኤ በኒው ዮርክ በበይነ መረብ አማራጭ ተካሄዷል። “የህዝቦች ጉባኤ” እና “የመፍትሄ ጉባኤ” የሚሉ ስያሜዎች የተሰጠው ጉባኤ ላይ ከ193 ሀገራት የተወጣጡ ከ51 ሺህ በላይ ሰዎች ተሳትፈውበታል። በምግብ ስርዓት ላይ የተዘጋጀ ይህ ታሪካዊ ጉባኤ ዓለም አቀፍ ሁነት ዋንኛ ግቡ የነበረው የተመድ አባል ሀገራት የምግብ ስርዓት ትራንስፎርሜሽን እንዲያመጡ እና ስርዓተ ምግብን ከዘላቂ ልማት ግቦች በተለይም ከግብ ሁለት ረሃብን ማጥፋት ጋር ማስተሳሰር ነው። ጉባኤው በአምስት ዓበይት የትኩረት ነጥቦች ላይ ያተኮረ ነበር። ለሁሉም ዜጋ ደህንነቱ የተጠበቀ እና የተመጣጠነ ምግብ ተደራሽ ማድረግ፣ ከብክነት ወደ ዘላቂ የምግብ አጠቃቀም መሸጋገር፣ ተፈጥሮን ያማከለ የምግብ ምርማነትን ማሳደግ፣ እኩልነትን መሰረት ያደረገ የአኗኗር ሁኔታን ማጠናከር እና ለአደጋዎችና ጫናዎች የማይበገር ጠንካራ የምግብ ስርዓት መገንባት ጉባኤው የተወያየባቸው ጉዳዮች ናቸው። ጉባኤው በወቅቱ አባል ሀገራት ሁሉን አቀፍ የምግብ ስርዓትን በመፍጠር የዘላቂ ልማት ግቦችን እንዲያሳኩ ጥሪ አቅርቧል። የተመድ የዓለም የምግብ ደህንነት ኮሚቴ የምግብ እና የስነ ምግብ ከፍተኛ የባለሙያዎች ፓናል የስርዓተ ምግብ አካሄድ ከባቢ አየር፣ ዜጎች፣ ግብአቶች፣ ሂደቶች፣ መሰረተ ልማቶችና ተቋማትን ጨምሮ ሁሉንም ተዋንያን ያሳተፈ መሆን እንዳለበት ያስቀምጣል። ስርዓተ ምግብ ምርት፣ ማቀነባበር፣ ስርጭት፣ ማዘጋጀት፣ መመገብ እና የተረፈ ምግብ አወጋገድን አቅፎ የያዘ እና ይህም ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ከባቢ አየር ላይ ቀጥተኛ ተጽእኖ ያለው ነው። የባለሙያዎች ፓናሉ የምግብ ስርዓት ትራንስፎርሜሽን ዜጎች፣ ምድር፣ ብልጽግና፣ ሰላም እና አጋርነት ላይ ያውጠነጠነ መሆኑን ይገልጻል። ፓናሉ ይህን ከግምት ውስጥ በማስገባት በምግብ ስርዓት ላይ ለውጥ ያመጣል ያላቸውን ስድስት ሀልዮታዊ ማዕቀፎችን ቀርጿል። ህይወት ያላቸው እና የቁስ አካላት ባህርያት፣ ከባቢ አየር የመጀመሪያው ነው። በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠው ቴክኖሎጂ፣ ኢኖቬሽንና መሰረተ ልማት ሲሆን ኢኮኖሚ እና ገበያ ሶስተኛውን ስፍራ ይይዛል። ፖለቲካ እና ተቋማዊ ሁኔታ፣ ማህበራዊ እና ባህላዊ ጉዳዮች እንዲሁም የስነ ሕዝብ ውቃሬ ሌሎች የምግብ ስርዓት ለውጥ አምጪ ምክንያቶች እንደሆኑ ተቀምጧል። ስድስቱ የምግብ ለውጥ አሳላጭ ሁኔታዎች ተፈጻሚ እና ውጤታማ የሚያደርጉ አራት ቁልፍ መስኮች እንዳሉም የባለሙያዎች ፓናሉ ያስቀምጣል። የምግብ ምርታማነትን የሚያሳድጉ ስርዓቶችን መደገፍ፣ የምግብ አቅርቦት ሰንሰለትን ማጠናከር፣ የዜጎችን የምግብ አጠቃቀም ባህሪያት ላይ ለውጥ ማምጣት እና የተመጣጠኑ ንጥረ ምግቦችን ብዝሃነት ማስፋት ቁልፍ የትኩረት ጉዳዮች ናቸው። የተቀመጡትን ማዕቀፎች፣ ለውጥን የመፍጠሪያ መንገዶች እና አስቻይ ሁኔታዎች ከፖሊሲ እና ሁሉን አቀፍ አስተዳደር ጋር በማቆራኘት የምግብ ስርዓት ላይ ለውጥ ማምጣት እንደሚገቡ ባለሙያዎቹ ምክረ ሀሳባቸውን ያቀርባሉ። የኢትዮጵያ የስርዓት ምግብ ራዕይ (EFS) መነሾም በስርዓተ ምግብ ጉባኤው እ.አ.አ በ2030 መሳካት አለባቸው ብሎ ያስቀመጣቸውን የስርዓተ ምግብ ግቦች እውን ለማድረግ ያሉ ፈተናዎች እና እድሎች ናቸው። እ.አ.አ በ2024 የወጣው የኢትዮጵያ የስርዓተ ምግብ ሁሉን አቀፍ ሪፖርት ኢትዮጵያ በጉባኤው የተቀመጡ የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት እና የጉባኤውን ምክረ ሀሳቦች ለመተግበር ቁርጠኛ እንደሆነች ይገልጻል። የኢትዮጵያ መንግስት እ.አ.አ ዲሴምበር 2020 የኢትዮጵያ ስርዓተ ምግብ የአሰራር ሂደት ይፋ ያደረገ ሲሆን ሂደቱ እ.አ.አ ጃንዋሪ 2021 ተጀምሯል። የስርዓተ ምግብ ማዕቀፉ የኢትዮጵያን የስርዓተ ምግብ ትራንስፎርሜሽን ራዕይን በግልጽ ያስቀመጠ ነበር። በወቅቱ ሂደቱን ለማስጀመር የቀድሞ የግብርና ሚኒስትር ኡመር ሁሴን እና የቀድሞ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ የመሯቸው የከፍተኛ ደረጃ ምክክሮች የተደረጉ ሲሆን ሰነዶችም ተቀርጸዋል። በስርዓት ምግብ ላይ ሁለት ብሄራዊ ምክክሮች የተደረጉ ሲሆን ምክክሮችን ተከትሎ የኢትዮጵያ ስርዓተ ምግብ ሂደት ይፋ ሆኗል። ምክክሮቹ የኢትዮጵያ ምግብ ስርዓት አሁናዊ ሁኔታ አና መጻኢ ሁኔታዎች፣ የኢትዮጵያን የምግብ ስርዓት የመለወጥ ጉዞ በሚል ርዕስ የተካሄዱ ናቸው። የስርዓተ ምግብ ሂደት ቀረጻው ላይ መንግስት፣ የግሉ ዘርፍ፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ የሲቪክ ማህረሰቦች፣ የምርምር ተቋማት፣ የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ተቋማት ያሉባቸው ከ120 በላይ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል። ይፋ የሆነውም የስርዓተ ምግብ ሂደት ሰነድ እ.አ.አ በ2021 በጣልያን ሮም በአካል ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስርዓተ ምግብ ጉባኤ ላይ ቀርቦ አዎንታዊ ምላሾችን አግኝቷል። የስርዓተ ምግብ ሂደት ማዕቀፉ ከሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም አጀንዳ፣ ከ10 ዓመት መሪ የልማት እቅድ እንዲሁም ከሌሎች የፖሊሲ እና አሰራሮች ጋር የተጋመደ ነው። የኢትዮጵያ የስርዓተ ምግብ ሁሉን አቀፍ ሪፖርት ኢትዮጵያ የስርዓተ ምግብ ለውጥ እና ሽግግር ያስፈለገባቸውን ምክንያቶች ያስቀምጣል። የምግብ እና የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት ተደራሽነት በሚፈለገው ደረጃ ማረጋገጥ አለመቻል፣ ፈጣን የህዝብ እድገት፣ የክትመት መጠን መስፋፋት፣ የከባቢ አየር ጉዳት እና የአየር ንብረት ለውጥ፣ እኩል ያልሆነ የዜጎች አኗኗር፣ ደካማ የምግብ ስርዓት መሰረት፣ ግብርናን ለኢኮኖሚ ያለውን ድርሻ ማሳደግ እና የምግብ ስርዓትን ከብሄራዊና ዓለም አቀፍ ግቦችን ጋር ማሰናሰን ማስፈለጉ የስርዓተ ምግብ ለውጡ መሰረታዊ ለውጥ መነሻ ናቸው። ኢትዮጵያ በስርዓተ ምግብ ሽግግር ውስጥ ስንዴን ጨምሮ በተለያዩ ሰብሎች ምርት እና ምርታማነትን በማሳደግ፣ የንጥረ ነገሮችን ብዝሃነት በማስፋት፣ የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት ተደራሽነትን በማሳደግ እና የግብርና ማቀነባበሪዎችን ቁጥር በመጨመር አመርቂ ውጤቶችን አስመዝግባለች። በዚህም በዜጎች ጤና እና ገቢ እድገት ላይ ለውጦች መምጣታቸውን ሪፖርቱ ያሳያል። ብሄራዊ የምግብ ስርዓት ማዕቀፎች፣ በምክክሮች የዘርፉ ተዋንያን የማሳተፍ ሁኔታ እያደገ መምጣት፣ በምግብ ስርዓቱ በሰባቱ ስትራቴጂካዊ የትኩረት አቅጣጫዎች ስር ለውጥ አምጪ ተብለው የተቀመጡ 24 መፍትሄዎች እና ተቋማዊ አቅም ግንባታ ሌሎች የታዩ አበረታች ለውጦች ናቸው። ሰባቱ ስትራቴጂካዊ የትኩረት አቅጣጫዎች ደህንነቱ የተጠበቀ እና የተመጣጠነ ምግብን ለሁሉም ተደራሽ ማድረግ፣ ጤናማ የአመጋገብ ሁኔታን መፍጠር፣ አሰራሮች እና ፖሊሲዎችን በተቀናጀ መንገድ መተግበር፣ በምግብ ስርዓቱ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች እና አሰራሮችን መተግበር፣ የገበያ ተደራሽነት ማስፋት እና መረጃ አሰጣጥን ማጠናከር፣ ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ ህብረተሰብ ክፍሎችን መጠበቅ እና የማይበገር አቅም መገንባት እንዲሁም መሰረተ ልማቶችን ማስፋፋት፣ ዘላቂነት ያለው የከተሜነት እድገትን መፍጠር እና ክህሎት ልማት ላይ ያተኮሩ ናቸው። ደህንነቱ የተጠበቀ እና የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦትን በሚፈለገው መጠን ተደራሽ አለማድረግ፣ ደካማ የምግብ ደህንነት መሰረተ ልማት፣ የግብርና ሜካናይዜሽን አለመስፋፋት፣ የከባቢ አየር ጉዳቶች፣ የቅንጅታዊ አሰራር ላይ ያሉ ክፍቶች እና የዜጎች የአኗኗር ሁኔታ ለይ ለውጦች ቢኖሩም አመርቂ አለመሆን፣ የፋይናንስ ውስንነት እና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገሩ ቴክኖሎጂዎች ተደራሽነት በምግብ ስርዓቱ ዋና ፈተናዎች ተብለው የተቀመጡ ናቸው። የምግብ ስርዓትን አስተዳደርን እና የባለድርሻ አካላት ቅንጅትን ማጠናከር፣ የቴክኒክ ድጋፍ ሰጪ መዋቅሮችን መዘርጋት፣ የመንግስት እና የግል አጋርነትን ማጠናከር፣ አቅምን መገንባት እና የምግብ ስርዓት አጀንዳ ዘላቂነት ባለው እና በተቀናጀ ሁኔታ ለማህበረሰቡ ማስገንዘብ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ተብለው ከተለዩ ጉዳዮች መካከል ይጠቀሳሉ። የገበያ ትስስርን ማጠናከር፣ የአየር ንብረት ለውጥ ማጣጣሚያ እቅዶች እና ስትራቴጂዎችን ማቀናጀት እንዲሁም ወጣቶች፣ ሴቶች እና ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን ጨምሮ የስርዓተ ምግብ ትግበራው ሁሉን አካታችነት የበለጠ ማረጋገጥ ቀጣይ የቤት ስራ ተብለው የተያዙ ናቸው። በአጠቃላይ የስርዓተ ምግብ ማዕቀፉን በየጊዜው በመፈተሽ እና የሁኔታዎችን ተለዋዋጭነት ከግምት ውስጥ ባስገባ ሁኔታ የአስተዳደር መዋቅርን በማሻሻል እ.አ.አ በ2030 የተያዙ ግቦችን ለማሳካት በትኩረት እንደሚሰራ ሁሉን አቀፍ ሪፖርቱ ያመለክታል። በአዲስ አበባ ከሐምሌ 20 እስከ 22 ቀን 2017 ዓ.ም በሚካሄደው ሁለተኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስርዓተ ምግብ ጉባኤ በስርዓተ ምግብ ላይ እያከናወነች ያለውን ስራ ለዓለም የማሳወቅ ስራ ታከናውናለች። በስርዓተ ምግብ ትራንስፎርሜሽን ያላትን ተሞክሮዎች በዋናው ጉባኤ እና በጎንዮሽ ሁነቶች ላይ ታቀርባለች። የጉባኤው ተሳታፊዎችም የኢትዮጵያን የስርዓተ ምግብ የተግባር ስራዎች እና ውጤቶች በመስክ ምልከታቸው ይቃኛሉ።
ልዩ ዘገባዎች
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 1883
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 1241
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 1/2018(ኢዜአ)፡- በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 7061
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 5549
ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
መጣጥፍ
በአረንጓዴ ልምላሜ ያጌጠው - የቤንቾች ቀዬ
Dec 3, 2025 138
በአረንጓዴ ልምላሜ ያጌጠው - የቤንቾች ቀዬ (በቀደሰ ተክሌ) -ከሚዛን ቅርንጫፍ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የሚገኘው የቤንች ምድር የሰጡትን የሚያበቅል ክረምት ከበጋ የማይጠወልግ ልምላሜን የታደለ ክልል ነው። በቤንች ሸኮ ዞን ባሉ የተለያዩ ወረዳዎች ደን የሚመስልና በመኖሪያ መንደሮች የሚታየው አብዛኛው አረንጓዴ ስፍራ ለምግብነት የሚያገለግሉ ፍራፍሬዎች፣ ቅጠሎችና ስሮችን የያዘ ነው። የቤንቾች ቤት ዙሪያው በአረንጓዴ ተፈጥሮ ያጌጠ ነው። የቤታቸው ሞገስ፤ የምግብ ዋስትናቸውም ጭምር ነው። ከዚህ ከፍ ሲል ደግሞ ቤንቾች ነፋሻማ አየር እየማጉ የመኖር ልምድን ያጎናጸፋቸው ይኸው አፈር ቆፍረው ዘር ተክለው ያበቀሉትና የተንከባከቡት አረንጓዴ ሀብት ነው። ከአንድ አርሶ አደር ማሳ እንሰት፣ ሙዝ፣ ጎደሬ፣ ፓፓያ፣ አቮካዶ፣ ብርቱካን እና ሌሎች ፍራፍሬዎች ማየት የተለመደ ነው። እግር ጥሎት ወደ ቀዬያቸው ያመራ እንግዳ ከፍራፍሬዎቹ የደረሰ ካለ ተቆርጦ ይሰጠዋል። በተጨማሪም ከብቶች፣ በጎችና ዶሮዎች የገቢ ምንጮቻቸው ናቸው። ወደ ቤታቸው ዘልቆ የገባ ሰው "ኪዥ" የተሰኘና የቤንች እናቶች ከወተት የሚያዘጋጁትን ''ጎደሬ'' ተብሎ ከሚጠራ የስራ ስር ምግብ ጋር ያጣጥማል። ቤንቾች በቆሎ፣ ማሽላ፣ ስንዴ፣ ባቄላ እንዲሁም ሌሎች የሰብል ዓይነቶችን ያለማሉ። ማር፣ ቡና፣ ኮረሪማ እና ሌሎች የተፈጥሮ ቅመማ ቅመሞችም ቤንቾች ከገበያ ገዝተው የሚያመጡት ሳይሆን ከማሳቸው የሚያፈሩት ነው። የተቀናጀ እርሻን ባህል ያደረጉት ብርቱ የቤንች አርሶ አደሮች ወደ ገበያ አውጥተው የሚሸጡት እንጂ የሚገዙት የለም ቢባል ማጋነን አይሆንም። የፋብሪካ ውጤቶችን ለመግዛትና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግም ከጓዳቸው ሞልቶ የተረፈውን ወደ ገበያ አውጥተው በመሸጥ ገበያን ያረጋጋሉ። በጠንካራ የእርሻ ባህላቸውም ምክንያት ልጆቻቸው የበሰለ ምግብን ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ፍራፍሬዎችንም ከጓሮና ከጫካ ቆርጠው ስለሚመገቡ ረሀብን አያውቁም። የቤንቾች ቤት ዙሪያ ውብና ጽዱ ነው። ለዚህ ደግሞ ሴቶቹ የቤታቸውን ግድግዳ በተፈጥሮ ቀለም ከማስዋብ ጀምሮ ይጠበቡበታል። በቤንቾች ዘንድ የአንድ አርሶ አደር ጉብዝና የሚለካው በቤቱ ነው። ይህም የቤቱ ዙሪያ ያለው ውበትና የቤቱ ጥንካሬ ብቻም ሳይሆን ገላጣ መሆን አለመሆኑም ጭምር ከግምት ውስጥ ይገባል። አባዎራው በማሳው ላይ የሰብል ስራውን ያከናውናል። ልጆችና እማውራዋ ደግሞ ይኮተኩታሉ ያርማሉ። ከዚህም በተጨማሪ የቤንች እናት ጎደሬና ሌሎች የጓሮ አትክልቶችን የማልማት ኃላፊነት አለባት። የቤታቸው ዙሪያና ቀዬው በሙሉ በአረንጓዴ ልምላሜ አጊጦ የሚታይበት ምስጢሩ ይሄው ነው። ከርቀት ደን መስሎ የሚታየው አረንጓዴው ቀዬአቸው የገቢ ምንጭም በመሆኑ አረንጓዴ ኢኮኖሚ ነውም ማለት ይቻላል። የሌማት ትሩፋት እሳቤ ቀድሞ የገባቸው ቤንቾች ማር አይገዙም፤ ለእንቁላል ሸመታም ገበያ አይወጡም። ወተት ቢያምራቸው በትኩሱ፤ ከዛም አለፍ ሲል በባህላዊ መንገድ እርሾ ጨምረው የሚያዘጋጁት "ኪዥ" የተሰኘ የወተት ውጤትን እንደ አይብም እንደ እርጎም አደርገው ይጠቀሙታል። የትኛውንም መልክዓ ምድር በሚስማማው የሰብል ዓይነት መሸፈን ያውቁበታል። መሬቱ ረግረጋማ ከሆነ ለጎደሬ፤ ዳገታማ ሆኖ ለማረስ የሚያስቸግር ከሆነ ደግሞ ለሙዝ ልማት ያውሉታል። የምግብ ዋስትናን በቤተሰብ ደረጃ ለማረጋገጥ ሥራ የሚሠራው በጓሮ ነው። ይህም ሁሉን ከአንድ ጓሮ ለማግኘት በመጣር የሚመጣ ነው። ይህም ካልሆነ ደግሞ አስተማማኝና ቋሚ ምርት ማሳ ላይ አልያም ጎተራው ላይ ማኖር ያስፈልጋል። እንደ ቤንቾች በቤተሰብ ደረጃ ምግብን በራስ አቅም ለመቻል የሚደረገው ጥረት እንደሀገር ሲጠናከር ለውጡ ቀጣይነት ባለው መልኩ ይፋጠናን። ሀገራችን ኢትዮጵያ ካላት የሕዝብ ቁጥር አብዛኛው አርሶ አደር ነው። ይሁን እንጂ ጾሙን የሚያድር ሰፊ መሬት እንዳለ መረጃዎች ያመለከታሉ። አንድም መሬት ጾም እንዳያድር በየአካባቢው ስራዎች ቢጀመረም ውጤቱ ቀሪ ሥራዎችን የሚጠይቅ ነው። ዛሬም በምርት እጥረት የኑሮ ውድነትና መሰል ችግሮች ይስተዋላሉ። በእነዚህ መሬቶች ላይ ሰርቶ ከመለወጥ ይልቅ ከተማ ቁጭ ማለትን የሚሻ ትውልድ ማየት የተለመደ ነው። የቤንች ሸኮ ዞን አርሶ አደሮች እጃቸው ብርቱ በመሆኑ እነዚህ ችግሮች በስራ አሽንፈዋል። ይህም በምግብ ራሳቸውን ከመቻል ባለፈ በኢኮኖሚም እንዲረጋጉ አድርጓቸዋል። ለሀብት ምንጭ የሆነን ማሳ ለቆ ከተማ በመዋል የሚገኝ ነገር አይኖርም። በከተማም ሆነ በገጠር ለመለወጥ እንደ ቤንቾች ብርቱ እጆች ያስፈልጋሉ። ካልተሰራ ገቢ ሳይሆን ወጪ እያደገ ወዳልተገባ መንገድ ለመሄድ ምክንያት ይሆናል። ለችግርም ሆነ ሰርቶ የመለወጥ ዕድሉ የሚወሰነው በምርጫችንና ለሥራችን በምንሰጠው ትኩረት ነው። እንደ ቤንች ሸኮ ዞን አርሶ አደሮች ሰርቶ ለመለወጥና ራስን ለመቻል በየአካባቢው ያለን የተፈጥሮ ሀብት ወደ ልማት ለመቀየር ተግቶ መስራት ያስፈልጋል ። ሰላም!
ብልህ ከችግር ይማራል!!
Dec 2, 2025 183
ብልህ ከደረሰበት ችግር ይማራል!! በማሙሽ ጋረደው ገራድ ተስፋዬ ተፈራ ትውልድና እድገታቸው በሀድያ ዞን ሌሞ ወረዳ ቃልሻ ቀበሌ ሲሆን በ1999 ዓ.ም በህገ ወጥ መንገድ ከፍተኛ ገንዘብ አውጥተው ወደ ደቡብ አፍሪካ ተጉዘው እንደነበር ያስታውሳሉ። ገንዘብ ለማግኘትና የመለውጥ ህልማቸውን ለማሳካት በሚል ሩቅ አስበው የጀመሩት ህገ ወጥ ጉዞ መዳረሻውን እስር ቤት አደረገው። ይህም ሁኔታ ''ሩቅ አሳቢ-ቅርብ አዳሪ'' አደረጋቸው። በባዕድ አገር በነበራቸው የ2 ዓመት የእስር ቤት ቆይታም የምግብ እጦትን ጨምሮ አካላዊ ጥቃትና ጉልበት ብዝበዛ እንዲሁም የተለያዩ ስነ-ልቦናዊ ጉዳቶችን እንዳስተናገዱ ይናገራሉ። ይህም አልበቃ ብሎ ከአካባቢው በህገወጥ መንገድ የሚሰደዱ ወጣቶችን ጉልበት በመጠቀም ሰፋፊ እርሻዎች ላይ እንዲሰማሩ በማድረግ የጉልበት ብዝበዛ ይፈፀምባቸው እንደነበርም ያስታውሳሉ። ብልህ ከደረሰበት ችግር ይማራል! የሚሉት ገራድ ተስፋዬ ሩቅ ሳይጓዙ፣ ገንዘብ ሳያወጡ ሰርተው መለወጥ የሚችሉበትን አካባቢያቸውን ፀጋ ሳያማትሩ ስደት መሄዳቸው ቁጭት ፈጥሮባቸው ነበር፡፡ ይህም በሀገራቸው እንኳንስ የለማን መሬት ይቅርና የተቦረቦረ መሬትን አልምቶ ጉልበትንና ጊዜን በአግባቡ ተጠቅሞ ለስኬት መብቃት እንደሚቻል ከእስር ቤት ቆይታቸው ተምረው ከእስር እንደተፈቱም ወዲያውኑ ወደ ሀገር ቤት መመለሳቸውን ተናግረዋል። በ2001 ዓ.ም ወደ ሀገር ቤት እንደተመለሱም በማህበር ተደራጅተው ከመንግሥት ባገኙት 70 ሺህ ብር ብድር በእንስሳት እርባታ ላይ ለመሰማራት 4 የወተት ከብቶችን ገዝተው የእርባታ ስራ መጀመራቸውን ይገልጻሉ፡፡ በዚህም የዞኑ አስተዳደር የሰጣቸውን መሬት አልምተው የእንስሳት እርባታውን አስፋፍተው መስራት ጀመሩ፡፡ አሁን ላይ የወተት ላሞቹን ቁጥር 37 በማድረስ የወተት ምርታማነታቸው አድጎ ከቤት ፍጆታ አልፎ ለሆሳዕና ከተማና አካባቢው በቀን ከ670 ሊትር በላይ ወተት እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡ ለ40 ወጣቶችም ቋሚና ጊዜያዊ የስራ እድል ከመፍጠራቸውም ባሻገር የተለያዩ የጭነትና የስራ ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ ከ250 ሚሊዮን ብር በላይ ሀብት ማፍራት መቻላቸውን ይናገራሉ። የጀመሩትን ስራ በጥምር ግብርና የማስፋትና የሚያገኙትን ወተት በማቀነባበር ምርቱን በተለያየ መልኩ ለገበያ የማቅረብ ራዕይን ሰንቀው በትጋት እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ በህገወጥ ስደት ካጋጠማቸው ችግር ተነስተው በተግባር ያዩትን ለሌሎች በማስተማር የስደትን አስከፊነት ለአካባቢያቸው ወጣቶች እያስገነዘቡ መሆኑን ገልጸዋል። ወጣቶች የስደትን አማራጭ ከመመልከታቸው በፊት የአካባቢያቸውን ፀጋ እንዲቃኙና ራዕይ ሰንቀው ራሳቸውን ለማሻሻል እንዲሰሩም መክረዋል። መለወጥ በውጪ ሀገር ብቻ ያለ የሚመስላቸው የቤተሰብ ኃላፊዎችም ልጆቻቸው በሀገራቸው ሰርተው መለወጥ እንደሚችሉ በማመን ሊያግዟቸው እንደሚገባም አቶ ገራድ አስገንዝበዋል። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትልና የእርሻና ሆርቲካልቸር ዘርፍ ኃላፊ አቶ አለምይርጋ ወልደስላሴ፤ በክልሉ በርካታ ወጣቶች ያልተጨበጠ ተስፋ ሰንቀው ለህገወጥ ስደትና ለተለያዩ ችግሮች ተጋላጭ እየሆኑ ይገኛሉ ብለዋል፡፡ በሀገር ሰርቶ ለመለወጥ የሚያስችል አቅም በግብርናው ዘርፍ መኖሩን ጠቅሰው በዘርፉ የተሰማሩ ከስደት ተመላሾች በአካባቢያቸው ሰርተው ለስኬት እየበቁ እንደሚገኙም ጠቁመዋል፡፡ በዚህም ከራሳቸው አልፈው ለበርካታ ስራ አጥ ዜጎች የስራ እድል በመፍጠር ላይ የሚገኙና የእነዚህን አካላት ተሞክሮ በመውሰድ በሀገር ሰርቶ ለመለወጥ መትጋት ይገባል ብለዋል፡፡