ኢራን ከኒውዝላንድ ሳዑዲ አረቢያ ከኡራጓይ ያደረጓቸው ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀቁ - ኢዜአ አማርኛ
ኢራን ከኒውዝላንድ ሳዑዲ አረቢያ ከኡራጓይ ያደረጓቸው ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀቁ
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 9/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ ከእኩለ ሌሊት በኋላ ሁለት ጨዋታዎች ተደርገዋል።
በሎስ አንጀለስ ስታዲየም በተካሄደው የምድብ ሰባት ጨዋታ ኢራን እና ኒውዝላንድ ሁለት አቻ ተለያይተዋል።
ራሚን ሬዛን እና መሐመድ ሞሄቢ ለኢራን ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ኤሊጃህ ጀስት የኒውዝላንድን ግቦች አስቆጥሯል።
ኢራን በጨዋታው ላይ ሁለት ጊዜ ተመርታ የአቻ ውጤት ማስመዝገብ ችላለች።
በዚሁ ምድብ ትናንት ማምሻውን ቤልጂየም እና ግብጽ ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል።
ኒውዝላንድ ከግብጽ፣ ቤልጂየም ከኢራን ቀጣይ የሚደረጉ የምድብ ሰባት ጨዋታዎች ናቸው።
በተያያዘም በሚያሚ ስታዲየም በተካሄደው የምድብ ስምንት ሁለተኛ ጨዋታ ሳዑዲ አረቢያ እና ኡራጓይ ሁለት አቻ ተለያይተዋል።
አብዱሌላህ ኤል-አምሪ ለሳዑዲ አረቢያ፣ ማክሲ አራውጆ ለኡራጓይ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
በዚሁ ምድብ ትናንት በተደረገው ጨዋታ ኬፕቨርዴ ከስፔን ጋር ያለ ግብ አቻ በመውጣት ያገኘችው ውጤት ያልተጠበቀ ሆኗል።
በምድብ ስምንት ሁለተኛ መርሐ ግብር ኡራጓይ ከኬፕቨርዴ፣ ስፔን ከሳዑዲ አረቢያ ይጫወታሉ።