ቤልጂየም እና ግብጽ ነጥብ ተጋርተዋል - ኢዜአ አማርኛ
ቤልጂየም እና ግብጽ ነጥብ ተጋርተዋል
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 9/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ የምድብ ሰባት መርሐ ግብር ቤልጂየም እና ግብጽ አንድ አቻ ተለያይተዋል።
ትናንት ማምሻውን በሲያትል ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ኢማም አሹር በ20ኛው ደቂቃ ግብጽን መሪ ያደረገችውን ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል።
የግብጹ መሐመድ ሀኒ በ66ኛው ደቂቃ በራሱ ላይ ያስቆጠረው ጎል ቤልጂየምን አቻ አድርጓል።
በጨዋታ ቤልጂየም የተሻለ የኳስ ቁጥጥር ቢኖራትም ግብጽ የግብ እድሎችን በመፍጠር ብልጫ ወስዳለች።
ውጤቱን ተከትሎ ሀገራቱ በዓለም ዋንጫው የመጀመሪያው ነጥባቸውን አግኝተዋል።