ኢዜአ - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
“ዱቡሻ” የተሰኘው የጋሞ ብሔር ባህላዊ የሸንጎ ሥርዓት ችግሮችን ለመፍታት ከፍተኛ እገዛ እያደረገ ነው-የጋሞ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ
Oct 1, 2023 52
አርባ ምንጭ፤ መስከረም 20/2016(ኢዜአ)፦ “ዱቡሻ” የተሰኘው የጋሞ ብሔር ባህላዊ የሸንጎ ሥርዓት በማህበረሰቡ ውስጥ የሚፈጠሩ ችግሮችን በመቅረፍ ለማህበራዊ መረጋጋትና ሰላማዊ ህይወት ከፍተኛ ፋይዳን እንደሚያበረክት የዞኑ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ አቶ ሞናዬ ሞሶሌ ገለጹ። “ዱቡሻ” ን በዩኔስኮ ለማስመዝገብ እየተሠራ መሆኑንም አስታውቀዋል። አቶ ሞናዬ ሞሶሌ ለኢዜአ እንዳሉት “ዱቡሻ” የተሰኘው የጋሞ ብሔር ባህላዊ የሸንጎ ሥርዓት በማህበረሰቡ ውስጥ የሚፈጠሩ ችግሮችን በመቅረፍ ለማህበራዊ መረጋጋትና ሰላማዊ ህይወት ከፍተኛ ፋይዳን የሚያበረክት ነው ፡፡ በዚህም ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣው ይህ ሥርዓት የህዝቡን ሰላም፣ አብሮነት፣ መቻቻልና አንድነቱን በማጽናት ረገድ የማይተካ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል ብለዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ግጭቶች እንደሚስተዋሉ የጠቀሱት አቶ ሞናዬ እንደ ዱቡሻ ያሉ የሸንጎ ሥርዓቶች ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል ስሉም አክለዋል፡፡ ይህን ሥርዓት ለማሳደግና ለማበልጸግ ከፌዴራል ጀምሮ በየደረጃው ካሉ የባለድርሻ አካላት ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተዘጋጅቶ መፈራረማቸውን ጠቅሰዋል፡፡ እንደ አቶ ሞናዬ ገለጻ በያዝነው የበጀት ዓመት በእነዚህ ተቋማት አማካይነት በ”ዱቡሻ” ሥርዓት ዙሪያ ጥናት የሚደረግ ሲሆን ለጥናቱ ማስፈጸሚያ ደግሞ 6 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በጀት ተመድቧል፡፡ በአካባቢው ባህላዊ እሴቶች ዙሪያ ጥናታዊ ጽሑፍ ያቀረቡት የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሥነ-ጽሑፍ መምህርና ተመራማሪ ዶክተር ተመስገን ምንዋጋው “ዱቡሻ” ለሚያጋጥሙ ያለመግባባቶች ዘላቂ መፍትሔ በመስጠት ረገድ ሚናው የጎላ እንደሆነ ተናግረዋል። ''ዱቡሻ'' የህዝቡን ችግሮች በዘላቄታዊነት ከመፍታት ባለፈ ለፍትህ ሥርዓቱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል ብለዋል፡፡ ባህላዊ የሸንጎ ሥርዓት የሚካሔድባቸው ስፍራዎች በርካታ መሆናቸውን ጠቅሰው ባህላዊ እሴቱ ለህዝቡ ከሚያመጣው ዘላቂ ሰላም አንጻር ለመጪው ትውልድ መተላለፍ እንዳለበትም ጠቁመዋል፡፡ “ዱቡሻ” በሀገራችን ዘመናዊ የአስተዳደር ሥርዓት ከመምጣቱ በፊት የነበረና እስካሁን ድረስም ህዝቡ በሰላም፣ በመቻቻል፣ በመፋቀርና በመረዳዳት እንዲኖር ዘመን ተሻጋሪ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የጋሞ የሃገር ሽማግሌ አቶ አመሌ አልቶ ናቸው፡፡ "ዱቡሻ" ላይ የማይፈታ ማህበራዊ ችግር የለም ያሉት አቶ አመሌ አልቶ በሀቅ ላይ የተመሠረተ፣ ቂምና ቁርሾ የሌለው እንደሆነም አስረድተዋል፡፡
በምስራቅ ቦረና ዞን ድርቅን ለመቋቋም የሚያስችል ከ204 ሺህ በላይ ሜትሪክ ቶን የእንስሳት መኖ እየተዘጋጀ ነው
Oct 1, 2023 35
ነገሌ ቦረና (ኢዜአ) መስከረም 20.2016-- በምስራቅ ቦረና ዞን በተደጋጋሚ ጊዜ የሚያጋጥመውን ድርቅ ለመቋቋም የሚያስችል 204 ሺህ በላይ ሜትሪክ ቶን የእንስሳት መኖ እየተዘጋጀ መሆኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ፡፡ ይኸው የመስኖ ልማት ፕሮጀክቱ 1 ሺህ 500 ሄክታር መሬት የማልማት አቅም ያለው ሲሆን 3 ሺህ አርብቶ አደሮችንና 20 ሺህ የቤት እንስሳትን በመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ የሚያደርግ እንደሆነም በወቅቱ ተገልጾ ነበር። ከውሃ ሀብት ልማቱ ጎን ለጎን የእንሰሳት መኖን አዘጋጅቶ በማከመችት ድርቅን በዘላቂነት ለመከላከል እየተሰራ መሆኑን አቶ ዋሪዎ ጨምረው ገልጸዋል። በዚህ ዓመት ብቻ ከ116 ሺህ ሄክታር በላይ የግጦሽ መሬት ከንክኪ የተከለለ ሲሆን ከዚህ ከተከለለ መሬት ከ204 ሺህ 870 ሜትሪክ ቶን በላይ የእንስሳት መኖ እየተዘጋጀ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ የእንስሳት መኖ በማቅረብ በዞኑ ባለፉት አመታት የደረሰውን ድርቅ ለመከላከል ጥረት ቢደረግም ለሁሉም ማዳረስ እንዳልተቻለ ገልጸዋል፡፡ በድርቁ የግጦሽ ሳርን ጨምሮ ወንዞችና ምንጮች በመድረቃቸው በቤት እንስሳት ላይ ጉዳት መድረሱን በማስታወስ፡፡ ችግሩ ጎልቶ በታየባቸው 8 ወረዳዎች ለዘንድሮ በጋ 116 ሺህ 678 ሄክታር መሬት በዞኑ ህዝብ ተሳትፎ ከንክኪ መከለሉን ገልጸዋል፡፡ የግጦሽ ሳር ልማቱ ከ325 ሺህ በላይ የሚገመት የቤት እንስሳትን ተጠቃሚ የማድረግ አቅም እንዳለውም ገልጸዋል፡፡ የዘፈቀደና ልቅ የግጦሽ ሳር አጠቃቀምን ለማስቀረት አርብቶ አደሩ የቁጠባ አጠቃቀምን ባህል እንዲያዳብር ግንዛቤ የመስጨበጥ ስራም እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡ በጽህፈት ቤቱ የተፈጥሮ ሀብት ቡድን መሪ አቶ አልዪ አረባ በበኩላቸው በዞኑ በተፋሰስ ልማትና በአረንጓዴ አሻራ ድርቅን ለመከላከል የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል፡፡ ባለፈው አመት ችግሩን ለመቀነስ በቀጥታ ከ80 ሺህ በላይ ህዝብ በአፈርና ውሃ ጥበቃ የልማት ስራ መሳተፉን አስታውሰዋል፡፡ በዞኑ አሬሮ ወረዳ የመታ ገፈርሳ ቀበሌ ነዋሪ አቶ ዋቅሽማ ወጋሪ ከአከባቢያቸው ነዋሪዎች ጋር በመተባበር የግጦሽ ሳር መሬት እንደከለሉ ገልጸዋል፡፡ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችም በመኖ ልማት ዝግጅት እያገዟቸው መሆኑን አንስተዋል፡፡ በአከባቢያቸው ከንክኪ ከተከለለ መሬት ለበጋ ወራት የሚያገለግል ከ8 ሺህ 500 በላይ እስር ሳር መሰብሰባቸውንም ጠቅሰዋል፡፡ ለድርቅ ወቅት የሚሆነን የእንስሳት መኖና የዝናብ ውሃ በማዘጋጀት በግለሰብ ደረጃም ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ እንደሆኑም አመልክተዋል፡፡
በአዲስ አበባ የነዋሪዎችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት የማረጋገጥና የኑሮ ሁኔታ የማሻሻል ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Oct 1, 2023 36
አዲስ አበባ መስከረም 20/2016(ኢዜአ)፦ በመዲናዋ የነዋሪዎችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት የማረጋገጥና የኑሮ ሁኔታን የማሻሻል ሥራ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ። የከተማ አስተዳደሩ የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር አብርሃም ታደሰ፤ ከንቲባዋን በመወከል በጉለሌ ክፍለ ከተማ የተገነቡ መኖሪያ ቤቶችን ለተጠቃሚዎች አስተላልፈዋል፡፡ በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን በክፍለ ከተማው ቀጨኔ አካባቢ የተገነቡት ቤቶች 14 ሲሆኑ፤ አጠቃላይ 85 የቤተሰብ አባላትን ተጠቃሚ የሚያደርጉ መሆናቸው ተገልጿል። የከተማ አስተዳደሩ የነዋሪዎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑን ገልጸው፤ በተለይም የመኖሪያ ቤት ችግርን ለማቃለል ብዙ ጥረቶች ተደርገዋል ብለዋል። በዚህም ባለፉት አምስት ዓመታት ብቻ ከ22 ሺህ በላይ ቤቶች ተገንብተው ለተጠቃሚዎች ተላልፈዋል ሲሉ ተናግረዋል። በቀጣይም የሰው ተኮር ፕሮጀክቶችን ክንውን በማጠናከር የነዋሪዎችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት የማረጋገጥና የኑሮ ሁኔታ የማሻሻል ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ አረጋግጠዋል። የአዲስ አበባ ከተማ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ዘሪሁን አባተ፤ ተቋሙ ከሚያከናውናቸው ተግባራት በተጓዳኝ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ነው ብለዋል። በመሆኑም ባለሥልጣኑ በጎ ፈቃደኞችን በማስተባበር ከ31 ሚለየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ያስገነባቸውን ቤቶች ለአቅመ ደካሞች ማስተላለፉን ጠቅሰዋል። የቤት ልማቱ ተጠቃሚ የሆኑ አቅመ-ደካሞችችም በከተማ አስተዳደሩ ለተደረገላቸው ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። በአዲስ አበባ በዛሬው እለት በተለያዩ ክፍለ ከተሞች በድምሩ 203 መኖሪያ ቤቶች ለአቅመ ደካሞችና ለአገር ባለውለታዎች መተላለፋቸው ታውቋል።
በጎንደር ከተማ የ15 ሚሊዮን ብር የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ለሚሹ ቤተሰብ ተማሪዎች ድጋፍ ተደረገ
Oct 1, 2023 32
ጎንደር (ኢዜአ) መስከረም 20/2016 ፦ በጎንደር ከተማ በ2016 የትምህርት ዘመን 15 ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸው የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ለሚሹ ቤተሰብ ተማሪዎች ድጋፍ መደረጉን የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት መምሪያ አስታወቀ፡፡ መምሪያው መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶችና በጎ አድራጊ ግለሰቦች የሰበሰባቸውን የትምህርት ቁሳቁስ ነው በዛሬው እለት ድጋፍ ለሚሹ ቤተሰብ ተማሪዎች ያከፋፈለው፡፡ በድጋፍ አሰጣጥ ስነ-ስርአቱ ላይ የመምሪያው ሃላፊ አቶ ዳንኤል ውበት እንደተናገሩት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፉ ዋና አላማ ድጋፍ የሚሹ ተማሪዎች በትምህርት ቁሳቁስ እጥረት ትምህርታቻውን እንዳያቋርጡ ለማድረግ ነው፡፡ ከተማ አስተዳደሩን ጨምሮ 7 መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና በጎ አድራጊ ግለሰቦች ባደረጉት በዚሁ ድጋፍም በከተማው 44 ትምህርት ቤቶች የሚገኙ 10ሺህ የሚጠጉ ድጋፍ የሚሹ ቤተሰብ ተማሪዎችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አስረድተዋል፡፡ ድጋፍ ከተደረጉ የትምህርት ቁሳቁስ መካከል 40ሺህ የመማሪያ ደብተሮች፣ ከ16ሺህ በላይ የማጣቀሻ መጻህፍትን ጨምሮ የትምህርት ቤት የደንብ ልብሶች፣ ቦርሳዎችና የሳይንስ ቁሶች ይገኙባቸዋል፡፡ ከተማ አስተዳደሩ በበኩሉ በ1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር ወጪ የገዛቸውን 200 ማስደገፊያ ያላቸው ወንበሮች፣ 96 መደርደሪያዎችና ጠረጴዛዎችን ለ4 ትምህርት ቤቶች ማከፋፋሉን ተናግረዋል፡፡ ዛሬ የተደረገው የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ የተማሪዎችን የወደፊት ህልም የሚያሳካ ነው ያሉት የተማሪ ወላጅ የሆኑት አቶ ጌትነት መንግስቴ ናቸው፡፡ በኑሮ ውድነቱ ወላጆች ለተማሪዎች በውድ ዋጋ ደብተር ገዝተው ለማስተማር ተቸግረው እንደነበር አስታውሰው ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ የእውቀት በር 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ8ኛ ክፍል ተማሪ ኤልሳ አለማየሁ በበኩሏ የተደረገልን ድጋፍ በትምህርት ቁሳቁስ እጥረት ትምህርታችን እንዳናቋርጥ የሚያግዘን ነው ብላለች፡፡ ሌላው የ6ኛ ክፍል ተማሪ አብረሃም ክፍሌ የመማሪያ ደብተርን ጨምሮ የደንብ ልብስና የማጣቀሻ መጻህፍት ድጋፍ እንደተደረገለት ጠቅሶ በተረጋጋ መንፈስ ትምህርቱን ለመከታተል መዘጋጀቱን ተናግሯል፡፡ በጎንደር ከተማ በ2016 የትምህርት ዘመን በቅድመ መደበኛ በ1ኛና በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ትምህርታቸውን የሚከታታሉ ከ90ሺህ በላይ ተማሪዎች መመዝገባቸውን ከመምሪያው የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
የተፈጥሮ ጸጋዎች ላይ የሚከናወኑ የልማት ስራዎች ለኢትዮጵያ ብልጽግና እውን መሆን መሠረት ይጥላሉ- አፈ-ጉባዔ ታገሰ ጫፎ
Oct 1, 2023 54
አዲስ አበባ፤ መስከረም 20/2016(ኢዜአ)፦የተፈጥሮ ጸጋዎችን ከሰው ኃይል ጋር በማስተሳሰር እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎች ለኢትዮጵያ ብልጽግና እውን መሆን መሠረት የሚጥሉ መሆናቸውን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ታገሰ ጫፎ ተናገሩ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በጅማ እና አካባቢው እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡ በጉብኝታቸውም በዋናነት በአካባቢዎቹ የሚከናወኑ የሌማት ትሩፋት፣ እንዲሁም የግብርና ሥራዎችን የጎበኙ ሲሆን፤ በጅማ ከተማ በገበታ ለትውልድ አማካኝነት የሚከናወነው የቱሪዝም ልማት ሥራም የጉብኝቱ አካል ነው፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ታገሰ ጫፎ፤ በጉብኝታቸው በጅማ ዞን ሕዝብን ተጠቃሚ ያደረጉ በርካታ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን መመልከታቸውን ተናግረዋል፡፡ በአካባቢው በቡና፣ ሩዝ፣ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም በቱሪዝም ልማት አበረታች ሥራ እየተከናወነ ስለመሆኑም ጠቁመዋል፡፡ ይህም የፌደራል መንግሥት ከክልሎች ጋር በመቀናጀት እያከናወናቸው ያሉ የልማት ሥራዎች በውጤታማ መንገድ ላይ መሆናቸውን ያመላከተ ነው ብለዋል፡፡ በአገር አቀፍ ደረጃ እየተከናወኑ ያሉ መሰል የልማት ሥራዎች ለኢትዮጵያ ብልጽግና መሠረት የሚጥሉ መሆናቸውንም እንዲሁ፡፡ ሕዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ሥራዎች ለዘላቂ ሰላም ግንባታ ወሳኝ ሚና እንዳላቸውም አፈ- ጉባዔው አብራርተዋል፡፡ ኢትዮጵያውያን በርካታ ፈተናዎችን በጋራ በማለፍ አብሮነታቸውን አስጠብቀው መቀጠላቸውን አስታውሰው፤ ይህንን የሕዝብ አብሮነት በልማት ሥራዎች በማስተሳሰር ይበልጥ ማጠናከር እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ ከዚህ አኳያ በሌማት ትሩፋትና ቱሪዝም ልማት የተጀመሩ ሥራዎች አበረታች መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡ የቀድሞ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አባ ዱላ ገመዳ በበኩላቸው፤ በጉብኝታቸው በጅማ ከተማና አካባቢው በርካታ አዳዲስ የልማት ስራዎች መከናወናቸውን እንደተመለከቱ ተናግረዋል፡፡ ለአብነትም ከዚህ ቀደም በአካባቢው የማይመረቱ እንደ ሩዝ ያሉ ምርቶችን በስፋት ማልማት መቻሉን ጠቅሰው፤ የቡና ምርትና ምርታማነትን በመጨመር ረገድም ከፍተኛ ሥራ መከናወኑን ገልፀዋል፡፡ በተለይ በጅማ ከተማ በገበታ ለትውልድ አማካኝነት እየተከናወኑ ያሉ የቱሪዝም ልማት ሥራዎች ከተማዋን የቱሪስት መዳረሻ የማድረግ አቅም እንዳላቸውም ነው የገለጹት፡፡ በሌማት ትሩፋትና ግብርና ልማት እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎች የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ እድገት በማሳለጥ ረገድ ሚናቸው የጎላ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ ከዚህ አኳያ አመራሩ በሁሉም ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶችን በሁሉም አካባቢዎች በማስቀጠል ረገድ ይበልጥ መሥራት እንዳለበትም አቶ አባ ዱላ ገመዳ ተናግረዋል፡፡
ፖለቲካ
የክልሉን ፖሊስ በግብዓት፣ በክህሎትና በቴክኖሎጂ የማጠናከር ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል - አቶ ኦርዲን በድሪ
Oct 1, 2023 53
ሐረር መስከረም 20/2016 (ኢዜአ) ... የክልሉን ፖሊስ በግብዓት፣በክህሎትና በቴክኖሎጂ የማጠናከር ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለጹ። ርዕሰ መስተዳድሩ ይህን ያሉት በክልሉ በቅርቡ ከተመረቁ የፖሊስ አባላት ጋር የትውውቅ እና የስራ መመርያ በሰጡበት ወቅት ነው። የፖሊስ ተግባር ከራስ በፊት ለህዝብ ቅድሚያ መስጠት መሆኑን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ የፖሊስ አባላቱ የዜጎችን ደህንነት መጠበቅና የህግ የበላይነትን በማስፈን ለህዝብ ቅን አገልጋይ መሆን ይጠበቅባቸዋል ብለዋል። የፖሊስ ተቋማት ከማህበረሰቡ ጋር በቅንጅት ካልሰሩ ወንጀልን የመከላከል ተልዕኮ ውጤታማ እንደማይሆን ጠቅሰው፤ ለዚህም ሁሌም ዝግጁ መሆን እንደሚገባቸው አመልክተዋል። ዜጎች በየትኛውም ጊዜና አካባቢ በነጻነት ተንቀሳቅሰው በአገር ልማት ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ከማንኛውም ጥቃት በመጠበቅ ሰላምና ጸጥታ ለማስፈን በትኩረት መስራት እንደሚያስፈልግ ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ባከናወነው የሪፎርም ስራ በክልሉ አበረታች የሰላምና የጸጥታ ስራዎች መከናወናቸውን የጠቀሱት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ ተቋሙን በግብዓት፣ በክህሎትና በቴክኖሎጂ የማጠናከር ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ አረጋግጠዋል። ከኮሚሽኑ ተቋማዊ ሪፎርም ወዲህ "ቀድሞ ይታዩ የነበሩ ችግሮች መቅረፍ ተችሏል" ያሉት ደግሞ የሐረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ነስሪ ዘከርያ ናቸው። በዚህ ፖሊስ ከማህበረሰቡ ጋር በመቀናጀት በሚያከናውነው የሰላምና ጸጥታ ስራ አበረታች ውጤት እየተመዘገበ ይገኛልም ብለዋል። ዘንድሮ የተመረቁ ፖሊሶችም የክልሉንና የአካባቢውን ሰላም እና ፀጥታ በአስተማማኝ መንገድ ለመጠበቅ የሚከናወነውን ተግባራት ለማጠናከር ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል። የሐረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ. ም 491 የፖሊስ አባላትን አሰልጥኖ ማስመረቁ ይታወሳል።
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ ከሃይማኖት መሪዎች ጋር ተወያዩ
Sep 30, 2023 71
መስከረም 19/2016(ኢዜአ)፡- የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ ከተለያዩ የሃይማኖት መሪዎች ጋር በክልሉ ሰላም እና ፀጥታ ዙሪያ በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል። ክልሉ የተለያዩ የሃይማኖት ተከታዮች ተቻችለው፣ ተከባብረው እና ተዋድደው የሚኖሩበት የመቻቻል ተምሳሌት የሆነ ክልል መሆኑን አቶ አረጋ በምክክሩ ወቅት አንስተዋል። በሁሉም ሃይማኖቶች አስተምሮ ሰላም፣ ፍቅር፣ መቻቻል እና አብሮነት ዋነኛ መርሆዎች ናቸው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ ይህንን መልካም ተግባር የሃይማኖቱ መሪዎቻ እና ታላላቅ አባቶች በየጊዜው ተከታዮቻቸውን ያለመታከት እንደሚያስተምሩ ጠቅሰዋል። በአማራ ክልል ዜጎች ያለገደብ በሰላም ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰው ነግደው እንዲያተርፉ፣ ገበያው መረጋጋት እንዲችል፣ ሕሙማን ወደ ሕክምና ተቋማት መሄድ እንዲችሉ እና መድሃኒት እንዲያገኙ፣ ኢንዱስትሪዎች ጥሬ ዕቃቸውን አግኝተው እና አምርተው እንዲያከፋፍሉ፣ አርሶ አደሩ ምርቱን ያለምንም እንቅፋት አምርቶ ገበያ ባለበት ምርቱን እንዲሸጥ እና ያሰበውን እንዲያሳካ ሰላም ከሁሉም በላይ ትልቅ ዋጋ የሚከፈልበት እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ ርዕሰ መስተዳድሩ አፅንዖት ሰጥተዋል። በውይይቱ የታደሙ የተለያዩ የሃይማኖት መሪዎች በበኩላቸው፣ በክልሉ ሰላም እንዲሰፍን እና የዜጎች ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ እንዳይገታ የሰላም እና የፀጥታ መስፈን ወሳኝ በመሆኑ የሚችሉትን ሁሉ በማድረግ እና ለተከታዮቻቸው በማስተማር የድርሻቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል። የሃይማኖት መሪዎች እና ተከታዮቻቸው ለሰላም መስፈን ድርሻቸው እጅግ ከፍተኛ በመሆኑ የድርሻቸውን እንዲወጡ ርዕሰ መስተዳድሩ ማሳሰባቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
የመከላከያ ሰራዊቱ የአገርን ሉዓላዊነትና የዜጎችን ደህንነት የማረጋገጥ ተልዕኮውን በብቃት እየተወጣ ነው- ሌተናል ጀነራል ይመር መኮንን
Sep 30, 2023 107
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 19/2016(ኢዜአ)፡- የመከላከያ ሰራዊቱ የአገርን ሉዓላዊነት የማስጠበቅና የዜጎችን ደህንነት የማረጋገጥ ተልዕኮውን በብቃት እየተወጣ መሆኑን የመከላከያ ሰራዊት የትምህርትና ሥልጠና ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጀነራል ይመር መኮንን ገለጹ፡፡ በመከላከያ ትምህርትና ሥልጠና ዋና መምሪያ የውጊያ ምህንድስና ኮሌጅ በተዋጊ መሃንዲስ አመራርነትና በተዋጊ መሃንዲስ መሰረታዊ ሙያ ያሰለጠናቸውን ሰልጣኞች ዛሬ አስመርቋል። ተመራቂዎቹ በኮሌጁ ቆይታቸው የወገንን እንቅስቃሴ የሚያሳልጡና የጠላትን እንቅስቃሴ መግታት የሚያስችላቸውን ክህሎትና ሙያ ማግኘታቸውም ተጠቁሟል፡፡ በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የመከላከያ ሰራዊት የትምህርትና ሥልጠና ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጀነራል ይመር መኮንን፤ የውጊያ መሃንዲስ ዋነኛ ተልዕኮ የሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ መሰናክሎችን በማስወገድ የሰራዊቱን እንቅስቃሴ እንዲፋጠን ማድረግ ነው ብለዋል፡፡ ተመራቂዎች በኮሌጁ ቆይታቸው ያገኙትን የንድፈ ሃሳብና የተግባር እውቀት በመጠቀም የዕለት ተዕለት ስራዎቻቸውን ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባቸውም ገልጸዋል፡፡ በሰለጠኑበት ሙያ የአገርን ሉዓላዊነትና አንድነት እንዲሁም የሕዝብን ደኅንነት በመጠበቅ የተጣለባቸውን ኃላፊነት በብቃት ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል። የመከላከያ ሰራዊቱ የኢትዮጵያን አንድነትና ሰላም በማይፈልጉ የውጪ እና ውስጥ ኃይሎች የሚቃጡ ጥቃቶችን በአስተማማኝ ሁኔታ በመመከት አፍራሽ ተልዕኳቸውን መቀልበሱን ገልጸዋል። አንዳንድ አካላት የሀገር ማፍረስ ቅዠታቸውን ለማስፈጸም የሰራዊቱን ስም ለማጥፋትና በሀሰት ለመከፋፈል ያልሞከሩት ነገር እንደሌለ በመጥቀስ፤ ሰራዊቱ በፅናት፣ በአንድነትና በጀግንነት ሴራቸውን አክሽፏል ብለዋል። ሌተናል ጀነራል ይመር አክለውም የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከመቼውም ጊዜ በላይ የኢትዮጵያን ሉዓላዊ የግዛት አንድነትና የህዝቧን ደህንነት የማረጋገጥ ተልዕኮውን በብቃት እየተወጣ እንደሚገኝም ተናግረዋል። የውጊያ ምህንድስና ኮሌጅ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ኪታባ ሂንሰርሙ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት፤ ኮሌጁ የሰራዊቱን የመፈጸም አቅም ለማሳደግ እየሰራ ነው። የዛሬ ተመራቂዎችም በተዋጊ መሃንዲስ አመራርነት እና በተዋጊ መሃንዲስ መሰረታዊ ሙያ በንድፍና በተግባር የታገዙ ሥልጠናዎችን መከታተላቸውን አብራርተዋል። የወታደራዊ ምህንድስና ሙያ ተመራቂዎች በበኩላቸው፤ በስልጠናው ያገኙትን ዕውቀት ተጠቅመው የሰራዊቱን ተልዕኮ የመፈፀም አቅም ለመጨመር እንደሚሰሩ ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡ ሻለቃ ተስፋዬ ዘውዴ በኮሌጁ ቆይታቸው ባገኙት እውቀት አገራቸውን በብቃት ለማገልገል ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ የአገራቸውን ዳር ድንበር ለማስጠበቅና በሙያዊ ስነምግባር ለማገልገል ዝግጁ መሆናቸውን የገለጹት ደግሞ ምክትል አስር አለቃ ጤናው አሰሙ ናቸው። በመከላከያ ትምህርትና ሥልጠና ዋና መምሪያ የውጊያ ምህንድስና ኮሌጅ በ1934 ዓ.ም የተቋቋመ ሲሆን በአምስት የትምህርት መስኮች የተለያዩ ሥልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል።
የምስራቅ አፍሪካ ሠላምና ደኅንነትን ለማስጠበቅ በዘርፉ ያለውን ትብብር ማጠናከር ይገባል - የቀጣናው አገራት ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች
Sep 30, 2023 64
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 19/2016(ኢዜአ)፡- የምስራቅ አፍሪካ ሠላምና ደኅንነት ለማስጠበቅ በዘርፉ የሰው ኃይል ልማትን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ያለውን ትብብር ማጠናከር እንደሚያስፈልግ የቀጣናው አገራት ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ገለጹ። የኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ ሰላም ማስከበር ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በግጭት አፈታትና ሰላም ማስከበር መስክ በሁለተኛ ዲግሪ ከሰሞኑ ማስመረቁ ይታወሳል። ከተመራቂዎቹ መካከል የኬኒያ፣ የዩጋንዳና የደቡብ ሱዳን ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ይገኙበታል። ተመራቂ መኮንኖቹም በቆይታቸው ኢትዮጵያ ለዘመናት ያካበተችውን ስኬታማ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ግንዛቤ ያገኙበት መሆኑንም ተናግረዋል። የምስራቅ አፍሪካ ሠላምና ደኅንነት ለማስጠበቅ በዘርፉ የሰው ኃይል ልማት ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ያለውን ትብብር ማጠናከር እንደሚያስፈልግም ገልፀዋል። በኬንያ የአገር መከላከያ ሰራዊት የአየር ኃይል ባልደረባ ሌተናል ኮሎኔል ጂኦፈረይ የጎ፤ በቆይታቸው ያገኙት እውቀትና ክህሎት የቀጣናውን ሰላምና ደኅንነት በራስ አቅም ለማስጠበቅ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ገልጸዋል። በኢንስቲትዩቱ ያገኙት የግጭት አፈታትና ሰላም ማስከበር ሙያም የሚያጋጥሙ ቀጣናዊ የሰላምና ደኅንነት ችግሮችን በትብብር ምላሽ ለመስጠት እንደሚያግዝ ተናግረዋል። የደቡብ ሱዳን ወታደራዊ አታሼ በኢትዮጵያ ብርጋዴር ጄኔራል ጃክ አንጎክ ደንግ፤ የትምህርት እድሉ ኢትዮጵያ በሲቪልና በወታደራዊ የሰው ኃይል ግንባታ ዘርፍ ለደቡብ ሱዳን ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገች እንደሚገኝ ማሳያ ነው ብለዋል። በተለይም በሰላምና ደኅንነት ሙያ እየተሰጡ የሚገኙ የትምህርትና ስልጠና መስኮችም የቀጣናውን አገራት የሰላምና ደህንነት ትብብር የሚያጠናክር መሆኑን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ደቡብ ሱዳንን ጨምሮ በሌሎች አገራትም በሰላም ማስከበር ተልዕኮ ወሳኝ ሚና እንዳላት ገልጸው ከዚህም ልምድ ለመውሰድ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል። በዩጋንዳ የአገር መከላከያ ሠራዊት ዋና መምህር ሌተናል ኮሎኔል ዋታሳ ዴቪድ፤ ኢትዮጵያ በሰላም ማስከበር ተልዕኮ ውጤታማነት የካበተ ታሪክ አላት ብለዋል። ለአብነትም በኮሪያ፣ በኮንጎ፣ በሶማሌና ደቡብ ሱዳን አብዬ ቀጣና የሰላም ማስከበር ተልዕኮን በብቃት በመወጣት ከፍተኛ ልምድ ያካበተች አገር እንደሆነች ተናግረዋል። በኢትዮጵያ የትምህርት ቆይታቸው ያገኙትን ልምድም የአገራቸው ወታደራዊ አቅም ለማጎልበት እንደሚጠቀሙበት ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ፆታዊ እኩልነትን በማረጋገጥ ብቁ ሴት ወታደራዊ መኮንኖች ለማፍራት እያደረገች የሚገኘው ጥረት ለቀጣናው አገራት ትምህርት የሚሰጥ መሆኑንም ተናግረዋል። የኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ ሰላም ማስከበር ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ለአህጉራዊ የሰላምና ደህንነት ትብብር መጎልበት እንደሚሰራ አረጋግጧል።
በሀረር ከተማ እና የቻይናዋ ዉሻን ከተማ መካከል የእህትማማችነት ግንኙነት ለመመሰረት የሚያስችል ውይይት ተካሄደ
Sep 28, 2023 139
አዲስ አበባ፤ መስከረም 17/2016(ኢዜአ)፦በሀረር ከተማ እና በቻይናዋ ዉሻን ከተማ መካከል የእህትማማችነት ግንኙነት ለመመሰረት የሚያስችል ውይይት ተካሄደ። በውይይቱ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ እንደተናገሩት የሀረር ከተማ የጀጎል ቅርስን ጨምሮ በዩኔስኮ የተመዘገቡ አለም አቀፍ ቅርሶች መገኛ ናት። ከተማዋ ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ ከተሞች ብቸኛዋ የአለም ቅርስ ከተሞች ድርጅት (Organization of World Heritage Cities) አባል መሆኗንም ገልጸዋል። በተጨማሪም በተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) በሰላም ፣ በመቻቻልና በአብሮነት ከተማነት አለም አቀፍ ሽልማት እና እውቅናን ማግኝቷን ገልጸው ይህም የተለያዩ እምነት ፣ ባህልና ቋንቋ ያላቸው ህዝቦች ለዘመናት በሰላምና በፍቅር የኖሩባት ዛሬም የሚኖሩባት ከተማ በመሆኗ የተቀዳጀችው ክብር እና እውቅና ነው ብለዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ እንዳሉት ሀረር ከተማ ከቻይና ዉሻን ከተማ ጋር የእህትማማችነት ግንኙነት ለመመሰረት የሚያስችል ፍሬአማ ውይይት ማካሄድ መቻሉን ገልጸዋል። በውይይቱም ባህልን በማስተዋወቅ ታሪካዊ ቅርሶችንና ሙዚየሞችን በመጠበቅና እንክብካቤ በማድረግ ፣ የህዝብ ለህዝብ ግንኙኑትን በማጠናከርና በሌሎችም ጉዳዮች በትብብር ለመስራት መስማማታቸውን ተናግረዋል። የቻይና ዉሻን ከተማ አመራሮች በበኩላቸው የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ዘመናትን ያስቆጠረ እና በመልካም ወዳጅነት ላይ የተመሠረተ መሆኑን ተናግረዋል። የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪና የልኡካን ቡድናቸው የዉሻን ከተማን እንዲጎበኙም ጠይቀዋል። በውይይቱ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል።
በመስቀሉ ያገኘነውን ድኅነት እያሰብን የሀገራችንን ሠላም ልናስጠብቅ ይገባል- ብጹዕ አቡነ ኤርሚያስ
Sep 27, 2023 220
ወልዲያ/ ደሴ ፤ መስከረም 16/2016 (ኢዜአ) ፡- በመስቀሉ ያገኘነውን ድኅነትና ሠላም እያሰብን የሀገራችንን ሠላም ልናስጠብቅ ይገባል'' ሲሉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የሰሜን ወሎ ዞን ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ኤርሚያስ ገለጹ። በዓሉ በወልዲያ በተከበረበት ወቅት ሊቀ ጳጳሱ ብጹዕ አቡነ ኤርሚያስ ባስተላለፉት መልዕክት፤ መስቀል የሰላም አዋጅ የታወጀበት በመሆኑ አንዳችን በአንዳችን ላይ ክፉ ሳናወራ በመስቀሉ የተገኘውን ሰላም ልናስቀጥል ይገባል ብለዋል። ሃገር የምትገነባውና የምትቀጥለው በትውልዶች ቀና ትብብርና ትጋት በመሆኑ ዘላቂ ሰላም ለመገንባት አንዳችን ከአንዳችን ተሽለን በጎ ስራዎችን ልንሰራ ይገባል ሲሉ ገልጸዋል። የወልድያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ተወካይ አቶ አለማየሁ ካሳሁን በበዓሉ ሥነ-ሥርዓት ላይ ተገኝተው እንዳመለከቱት፤ የከተማውን ሰላም በማስቀጠል የተጀመሩ ልማቶች ተጠናቀው የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የህዝቡ የነቃ ተሳትፎ ወሳኝ ነው። የበዓሉ ታዳሚ አቶ ተመቸ ዘውዱ በሰጡት አስተያየት፤ በከተማችን ሰላም በመስፈኑ ታላቁን የደመራ በዓል በሰላም ለማክበር በቅተናል ብለዋል። ወይዘሮ ትኩነሽ አስፋው በበኩላቸው፤ የሠላም ዋጋው በገንዘብ የማይተመን የህልውና መሠረት በመሆኑ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ሁላችንም የድርሻችንን ልንወጣ ይገባል ሲሉ ገልፀዋል። በተመሳሳይ በዓሉ በደሴ ከተማ ሆጤ ስታዲየም ሲከበር የደቡብ ወሎ ዞን ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ መምህራን ብርሃነ ሕይወት እውነቱ ፤ ምዕመናኑ አንድነቱንና ሰላሙን ጠብቆ የመስቀሉን ፍቅርና አንድነት በመስበክ በዓሉን ማክበር አለበት ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። መስቀሉ ህዝብ ያዳነ የነፃነትና የፍቅር ምልክት ነው፤ ምዕመናኑ በዓሉን ሲያከብር አንድነቱንና ሰላሙን ጠብቆ እንደ መስቀሉ ፍቅርንና አንድነትን በመስበክ ኢትዮጵያ ማስቀጠል ይኖርበታል ብለዋል፡፡ የደሴ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ በበኩላቸው፤ በዓሉ የፍቅር፣ የሰላምና የአንድነት በመሆኑ ሁላችንም ለዘላቂ ሰላምና ብልጽግና የድርሻችንን መወጣት አለብን ሲሉ ገልጸዋል፡፡ ወጣቱም በሀሰት ትርክት ሳይወዛገብ እውነትን መፈለግና ኢትዮጵያን ለማጽናት የድርሻውን መወጣት እንዳለበት አመልክተዋል። ሰላማችንን እየጠበቅን በደሴ ከተማ የተጀመሩ ልማቶችን ከማስቀጠል ባለፈ በበጀት ዓመቱ አዳዲስ ልማቶችን ለማከናወን በማቀዳችን ህብረተሰቡ ከጎናችን ተሰልፎ የተለመደ ትብብር ሊያደርግ ይገባል ብለዋል። በዓሉን በደስታ፣ በፍቅርና አንድነት በማክበራችን ተደስተናል ያሉት ደግሞ የበዓሉ ተሳታፊ አቶ አውራሪስ ደጀኔ ናቸው፡፡ በወልዲያና ደሴ ከተሞች የተከበረው የመስቀል ደመራ በዓል በሰላም ተጠናቋል።
ከመስቀል በዓል አስተምህሮ በመነሳት ሁሉም ለፍቅር፣ ለሰላም እና አንድነት የበኩሉን ሊወጣ ይገባል -ሊቀ ጳጳስ አቡነ ፊሊጶስ
Sep 27, 2023 233
ጂንካ ፤ መስከረም 16 /2016 (ኢዜአ)፡- "መስቀል ስለፍቅር ለሌሎች ዋጋ መክፈልና ሰላምን አጥብቆ መሻት ስለሚያስተምር ሁሉም ለፍቅር፣ ለሀገር ሰላምና አንድነት የበኩሉን ሊወጣ ይገባል" ሲሉ የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ፊሊጶስ ተናገሩ። የመስቀል ደመራ በዓል በጂንካ ከተማ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥርአቶች በድምቀት ተከብሯል። በዓሉ በከተማው መስቀል አደባባይ ሲከበር የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅድስት ስላሴ ካቴድራል መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አቡነ ፊሊጶስ በክብረ በዓሉ ላይ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል። በእዚህ ጊዜም እንዳሉት የመስቀል በአል ሰላም፣ ፍቅር፣ መተሳሰብ፣ አንድነት እርቅን የሚያስተምር ታላቅ በአል ነው። በመሆኑም ምዕመናኑ ይህን ታላቅ ክብረ በዓል ሲያከብሩ በችግር ውስጥ ያሉ ወገኖችን በማሰብ ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል። "መስቀል ለሌሎች ማሰብን፣ ስለፍቅር ዋጋ መክፈልንና ሰላምን አጥብቆ መሻትን ያስተምራል" ያሉት አቡነ ፊልጶስ፣ የእምነቱ ተከታዮች ይህንን አስተምህሮ በመከተል መተግበር እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። የሀገር ሰላም፣ ፍቅርና የህዝቦች ትስስር እንዲጠናከር የበኩላቸውን ሊወጡ እንደሚገባም አስታውቀዋል። በዓሉ ያሉት ትውፊቶች ተጠብቀው ለትውልድ እንዲሸጋገር ሁሉም የበኩሉን መወጣት ይኖርበታል ሲሉም ገልጸዋል። የጂንካ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አስፋው ዶሪ በክብረ በዓሉ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የደመራ በዓል ለሌሎች ዋጋ መክፈልን ስለሚያስተምር አንድነታችንን በእጅጉ ያጎላል ብለዋል። "በዓሉ የህዝብ ለህዝብ ትስስርን ከማጠናከር አኳያ ትልቅ ሚና ያለው፣ ሀገራዊ ገጽታን የሚያጎላ እና በዓለም ቅርስነት የተመዘገበ ዕንቁ ቅርሳችን በመሆኑ ልንጠብቀውና ልንከባከበው ይገባል" ሲሉ ገልጸዋል። በመስቀል በዓል የሚታየውን የአንድነት ስሜት በሌሎች የልማት ስራዎች አጠናክሮ በመቀጠል ለአገር እድገት የድርሻን መወጣት እንደሚገባም ተናግረዋል። የአሪ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም አታ በበኩላቸው፤ የመስቀል ደመራ በአል የሰላም፣ የፍቅርና የአንድነት እሴት ያለው በአል በመሆኑ የበአሉን እሴት አጠናክረን ልንቀጥል ይገባል ብለዋል። ጥልን በማስወገድ በፍቅር፣ በአንድነት እና በመቻቻል ለሀገራዊ እድገት በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል። በበአሉ ላይ የታደሙት የጂንካ ዩኒቨርስቲ የታሪክ መምህርት እስከዳር አለልኝ፤ የመስቀል በዓል በውስጡ በርካታ ትውፊቶች ያለው ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ ክብረ በአል መሆኑን ተናግረዋል ። ይህ አኩሪ ሀይማኖታዊና ባህላዊ እሴት በዩኔስኮ የተመዘገበ የማይዳሰስ ቅርሳችን በመሆኑ ሳይበረዝና ሳይከለስ ለትውልድ እንዲሻገር ሁሉም የሚጠበቅበትን መወጣት አለበት ብለዋል። በዓሉ የመረዳዳት፣ የፍቅርና የአንድነት በዓል በመሆኑ ከተቸገሩ ወገኖች ጋር በመተሳሰብ እና በመረዳዳት እንደሚያከብሩት ተናግረዋል።
በጎንደር ከተማ ያለውን የጸጥታ ሁኔታ አስመልክቶ በማህበራዊ ሚዲያ የሚናፈሰው መረጃ ፈጽሞ ከእውነት የራቀ ነው- ብርጋዴር ጄኔራል ማርዬ በየነ
Sep 27, 2023 208
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 16/2016 (ኢዜአ)፦ በጎንደር ከተማ ያለውን የጸጥታ ሁኔታ አስመልክቶ በማህበራዊ ሚዲያ የሚናፈሰው መረጃ ፈጽሞ ከእውነት የራቀ መሆኑን የጎንደር ከተማ ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ብርጋዴር ጄኔራል ማርዬ በየነ ገለጹ፡፡ ኮማንድ ፖስቱ ጽንፈኛ ቡድኑ ላይ እየወሰደ ካለው እርምጃ ባሻገር የከተማዋን ነዋሪዎች በማወያየት ባከናወነው ስራ የከተማዋ የሰላም ሁኔታ መሻሻሉንም ነው የተናገሩት፡፡ ጽንፈኛ ቡድኑ የኢትዮጵያን ህልውና እና ሰላም ከማይፈልጉ አካላት የሚላክለትን ፍርፋሪ በመጠቀም ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጥቃት የሚፈጽም የህዝብ ጠላት መሆኑን አብራርተዋል፡፡ ኮማንድ ፖስቱ ከህዝብ ጋር ባደረገው ውይይትም ህብረተሰቡ የጽንፈኛ ቡድኑን እኩይ ድርጊት በግልጽ ማንሳቱን ጠቅሰዋል፡፡ ነገር ግን ከጽንፈኛ ቡድኑ ጎን የተሰለፉ አንዳንድ አካላት በማህበራዊ ሚዲያ የሃሰት መረጃዎችን በማሰራጨት ህዝብ ለማደናገር እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ለአብነትም ባለፉት ቀናት "ብርጋዴር ጄኔራል ማርዬ ተገድለዋል" በሚል በማህበራዊ ሚዲያ የሃሰት መረጃ ሲያሰራጩ መቆየታቸውን አንስተዋል፡፡ በተጨማሪም "ክፍለ ጦር ደመሰስን፤ ታንክ ማረክን፤ አውሮፕላን ጣልን" የሚሉ የበሬ ወለደ መረጃዎችን ሲያሰራጩ መቆየታቸውን ጠቁመዋል፡፡ በመሆኑም ህብረተሰቡ ሆነ ብለው የሃሰት መረጃ በሚያሰራጩ የጽንፈኛው ቡድን አባላት መደናገር የለበትም ነው ያሉት፡፡ ኮማንድ ፖስቱ በጽንፈኛ ቡድኑ ላይ ከሚወስደው እርምጃ ባሻገር ህዝብን በማወያየት ዘላቂ ሰላም ለማስፈን እየሰራ መሆኑንም ብርጋዴር ጄኔራል ማርዬ ተናግረዋል፡፡ በዚህም የመከላከያ ሰራዊቱ የተሰጠውን ግዳጅ በብቃት እየተወጣ ነው ብለዋል፡፡ በቅርቡ በጎንደር ከተማ በአንድ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ተኩስ በመክፈት ለማምለጥ በሞከሩ የጽንፈኛው ኃይል አባላት ላይ እርምጃ በመውሰድ የከተማዋን ሰላም ማስጠበቅ መቻሉንም ብርጋዴር ጄኔራል ማርዬ ገልጸዋል፡፡ ሰራዊቱ ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት ውጤታማ ስራ እያከናወነ ነው፤ ለዚህ ደግሞ ደጀኑ ህዝባችን ምስክር ነው ብለዋል፡፡

ማህበራዊ
“ዱቡሻ” የተሰኘው የጋሞ ብሔር ባህላዊ የሸንጎ ሥርዓት ችግሮችን ለመፍታት ከፍተኛ እገዛ እያደረገ ነው-የጋሞ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ
Oct 1, 2023 52
አርባ ምንጭ፤ መስከረም 20/2016(ኢዜአ)፦ “ዱቡሻ” የተሰኘው የጋሞ ብሔር ባህላዊ የሸንጎ ሥርዓት በማህበረሰቡ ውስጥ የሚፈጠሩ ችግሮችን በመቅረፍ ለማህበራዊ መረጋጋትና ሰላማዊ ህይወት ከፍተኛ ፋይዳን እንደሚያበረክት የዞኑ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ አቶ ሞናዬ ሞሶሌ ገለጹ። “ዱቡሻ” ን በዩኔስኮ ለማስመዝገብ እየተሠራ መሆኑንም አስታውቀዋል። አቶ ሞናዬ ሞሶሌ ለኢዜአ እንዳሉት “ዱቡሻ” የተሰኘው የጋሞ ብሔር ባህላዊ የሸንጎ ሥርዓት በማህበረሰቡ ውስጥ የሚፈጠሩ ችግሮችን በመቅረፍ ለማህበራዊ መረጋጋትና ሰላማዊ ህይወት ከፍተኛ ፋይዳን የሚያበረክት ነው ፡፡ በዚህም ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣው ይህ ሥርዓት የህዝቡን ሰላም፣ አብሮነት፣ መቻቻልና አንድነቱን በማጽናት ረገድ የማይተካ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል ብለዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ግጭቶች እንደሚስተዋሉ የጠቀሱት አቶ ሞናዬ እንደ ዱቡሻ ያሉ የሸንጎ ሥርዓቶች ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል ስሉም አክለዋል፡፡ ይህን ሥርዓት ለማሳደግና ለማበልጸግ ከፌዴራል ጀምሮ በየደረጃው ካሉ የባለድርሻ አካላት ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተዘጋጅቶ መፈራረማቸውን ጠቅሰዋል፡፡ እንደ አቶ ሞናዬ ገለጻ በያዝነው የበጀት ዓመት በእነዚህ ተቋማት አማካይነት በ”ዱቡሻ” ሥርዓት ዙሪያ ጥናት የሚደረግ ሲሆን ለጥናቱ ማስፈጸሚያ ደግሞ 6 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በጀት ተመድቧል፡፡ በአካባቢው ባህላዊ እሴቶች ዙሪያ ጥናታዊ ጽሑፍ ያቀረቡት የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሥነ-ጽሑፍ መምህርና ተመራማሪ ዶክተር ተመስገን ምንዋጋው “ዱቡሻ” ለሚያጋጥሙ ያለመግባባቶች ዘላቂ መፍትሔ በመስጠት ረገድ ሚናው የጎላ እንደሆነ ተናግረዋል። ''ዱቡሻ'' የህዝቡን ችግሮች በዘላቄታዊነት ከመፍታት ባለፈ ለፍትህ ሥርዓቱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል ብለዋል፡፡ ባህላዊ የሸንጎ ሥርዓት የሚካሔድባቸው ስፍራዎች በርካታ መሆናቸውን ጠቅሰው ባህላዊ እሴቱ ለህዝቡ ከሚያመጣው ዘላቂ ሰላም አንጻር ለመጪው ትውልድ መተላለፍ እንዳለበትም ጠቁመዋል፡፡ “ዱቡሻ” በሀገራችን ዘመናዊ የአስተዳደር ሥርዓት ከመምጣቱ በፊት የነበረና እስካሁን ድረስም ህዝቡ በሰላም፣ በመቻቻል፣ በመፋቀርና በመረዳዳት እንዲኖር ዘመን ተሻጋሪ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የጋሞ የሃገር ሽማግሌ አቶ አመሌ አልቶ ናቸው፡፡ "ዱቡሻ" ላይ የማይፈታ ማህበራዊ ችግር የለም ያሉት አቶ አመሌ አልቶ በሀቅ ላይ የተመሠረተ፣ ቂምና ቁርሾ የሌለው እንደሆነም አስረድተዋል፡፡
በአዲስ አበባ የነዋሪዎችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት የማረጋገጥና የኑሮ ሁኔታ የማሻሻል ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Oct 1, 2023 36
አዲስ አበባ መስከረም 20/2016(ኢዜአ)፦ በመዲናዋ የነዋሪዎችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት የማረጋገጥና የኑሮ ሁኔታን የማሻሻል ሥራ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ። የከተማ አስተዳደሩ የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር አብርሃም ታደሰ፤ ከንቲባዋን በመወከል በጉለሌ ክፍለ ከተማ የተገነቡ መኖሪያ ቤቶችን ለተጠቃሚዎች አስተላልፈዋል፡፡ በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን በክፍለ ከተማው ቀጨኔ አካባቢ የተገነቡት ቤቶች 14 ሲሆኑ፤ አጠቃላይ 85 የቤተሰብ አባላትን ተጠቃሚ የሚያደርጉ መሆናቸው ተገልጿል። የከተማ አስተዳደሩ የነዋሪዎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑን ገልጸው፤ በተለይም የመኖሪያ ቤት ችግርን ለማቃለል ብዙ ጥረቶች ተደርገዋል ብለዋል። በዚህም ባለፉት አምስት ዓመታት ብቻ ከ22 ሺህ በላይ ቤቶች ተገንብተው ለተጠቃሚዎች ተላልፈዋል ሲሉ ተናግረዋል። በቀጣይም የሰው ተኮር ፕሮጀክቶችን ክንውን በማጠናከር የነዋሪዎችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት የማረጋገጥና የኑሮ ሁኔታ የማሻሻል ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ አረጋግጠዋል። የአዲስ አበባ ከተማ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ዘሪሁን አባተ፤ ተቋሙ ከሚያከናውናቸው ተግባራት በተጓዳኝ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ነው ብለዋል። በመሆኑም ባለሥልጣኑ በጎ ፈቃደኞችን በማስተባበር ከ31 ሚለየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ያስገነባቸውን ቤቶች ለአቅመ ደካሞች ማስተላለፉን ጠቅሰዋል። የቤት ልማቱ ተጠቃሚ የሆኑ አቅመ-ደካሞችችም በከተማ አስተዳደሩ ለተደረገላቸው ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። በአዲስ አበባ በዛሬው እለት በተለያዩ ክፍለ ከተሞች በድምሩ 203 መኖሪያ ቤቶች ለአቅመ ደካሞችና ለአገር ባለውለታዎች መተላለፋቸው ታውቋል።
በጎንደር ከተማ የ15 ሚሊዮን ብር የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ለሚሹ ቤተሰብ ተማሪዎች ድጋፍ ተደረገ
Oct 1, 2023 32
ጎንደር (ኢዜአ) መስከረም 20/2016 ፦ በጎንደር ከተማ በ2016 የትምህርት ዘመን 15 ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸው የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ለሚሹ ቤተሰብ ተማሪዎች ድጋፍ መደረጉን የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት መምሪያ አስታወቀ፡፡ መምሪያው መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶችና በጎ አድራጊ ግለሰቦች የሰበሰባቸውን የትምህርት ቁሳቁስ ነው በዛሬው እለት ድጋፍ ለሚሹ ቤተሰብ ተማሪዎች ያከፋፈለው፡፡ በድጋፍ አሰጣጥ ስነ-ስርአቱ ላይ የመምሪያው ሃላፊ አቶ ዳንኤል ውበት እንደተናገሩት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፉ ዋና አላማ ድጋፍ የሚሹ ተማሪዎች በትምህርት ቁሳቁስ እጥረት ትምህርታቻውን እንዳያቋርጡ ለማድረግ ነው፡፡ ከተማ አስተዳደሩን ጨምሮ 7 መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና በጎ አድራጊ ግለሰቦች ባደረጉት በዚሁ ድጋፍም በከተማው 44 ትምህርት ቤቶች የሚገኙ 10ሺህ የሚጠጉ ድጋፍ የሚሹ ቤተሰብ ተማሪዎችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አስረድተዋል፡፡ ድጋፍ ከተደረጉ የትምህርት ቁሳቁስ መካከል 40ሺህ የመማሪያ ደብተሮች፣ ከ16ሺህ በላይ የማጣቀሻ መጻህፍትን ጨምሮ የትምህርት ቤት የደንብ ልብሶች፣ ቦርሳዎችና የሳይንስ ቁሶች ይገኙባቸዋል፡፡ ከተማ አስተዳደሩ በበኩሉ በ1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር ወጪ የገዛቸውን 200 ማስደገፊያ ያላቸው ወንበሮች፣ 96 መደርደሪያዎችና ጠረጴዛዎችን ለ4 ትምህርት ቤቶች ማከፋፋሉን ተናግረዋል፡፡ ዛሬ የተደረገው የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ የተማሪዎችን የወደፊት ህልም የሚያሳካ ነው ያሉት የተማሪ ወላጅ የሆኑት አቶ ጌትነት መንግስቴ ናቸው፡፡ በኑሮ ውድነቱ ወላጆች ለተማሪዎች በውድ ዋጋ ደብተር ገዝተው ለማስተማር ተቸግረው እንደነበር አስታውሰው ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ የእውቀት በር 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ8ኛ ክፍል ተማሪ ኤልሳ አለማየሁ በበኩሏ የተደረገልን ድጋፍ በትምህርት ቁሳቁስ እጥረት ትምህርታችን እንዳናቋርጥ የሚያግዘን ነው ብላለች፡፡ ሌላው የ6ኛ ክፍል ተማሪ አብረሃም ክፍሌ የመማሪያ ደብተርን ጨምሮ የደንብ ልብስና የማጣቀሻ መጻህፍት ድጋፍ እንደተደረገለት ጠቅሶ በተረጋጋ መንፈስ ትምህርቱን ለመከታተል መዘጋጀቱን ተናግሯል፡፡ በጎንደር ከተማ በ2016 የትምህርት ዘመን በቅድመ መደበኛ በ1ኛና በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ትምህርታቸውን የሚከታታሉ ከ90ሺህ በላይ ተማሪዎች መመዝገባቸውን ከመምሪያው የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
በምዕራብ ወለጋ ዞን ወባና ሌሎች ተላላፊ በሽታዎች በወረርሽኝ መልክ እንዳይከሰቱ ህብተሰቡን ያሳተፈ የመከላከል ስራዎች እየተከናወኑ ነው
Oct 1, 2023 28
ግምቢ/መስከረም 20/2016 (ኢዜአ)-- በምዕራብ ወለጋ ዞን የወባና ሌሎች ተላላፊ በሽታዎች በወረርሽኝ መልክ እንዳይከሰቱ ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ የመከላከል ስራ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ ጤና ጥበቃ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡ የጽሕፈት ቤቱ ሀላፊ አቶ ሰለሞን ጫላ እንደገለጹት በዞኑ የክረምቱን መውጣት ተከትሎ የወባ በሽታና ሌሎች ተላላፊ በሽታዎች በወረርሽኝ መልክ እንዳይከሰቱ ህብረተሰቡብን ባሳተፈ መልኩ ለአካባቢ ጽዳት ትኩረት ተሰጥቷል፡፡ በዞኑ ዘንድሮ የወባ ወረርሽኝ በ13 ወረዳዎች መከሰቱን ተናግረው፤ በሽታው የከፋ ጉዳት ሳያደርስ የመቆጣጠር ስራ በተቀናጀ መልኩ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በዞኑ በሁሉም ወረዳዎች ለወባ ትንኝ መራቢያ ሊሆኑ የሚችሉ ሥፍራዎችንና ውሃ የሚያቁሩ ቦታዎችን የማጽዳት ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በሕዝብ ተሳትፎ ዘመቻ ስራው የጸጥታ አካለት ጭምር እየተሳተፉ ሲሆን አካባቢን የማጽዳት ስራ በስፋት እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ከአካባቢ ጽዳት ጎን ለጎን በዞኑ በ13 ወረዳዎች በ100 ሺህ በላይ ቤቶች ላይ የኬሚካል ርጭት እየተከናወነ መሆኑንም ተናግረዋል። 678 ሺህ የአልጋ አጎበር ለተጠቃሚዎች አስቀድሞ እንዲደርስ ተደርጓል ያሉት ኃላፊው ከ74 ሺህ በላይ ዜጎች በበሽታው እንዳይጠቁ ማድረግ ተችሏል ብለዋል ፡፡ የጤና ባለሙያዎችም ህዝቡን ከበሽታው ለመታደግ ቤት ለቤት በመሄድ የግልና የአካባቢ ንጽሕና አጠባበቅ ላይ የግንዛቤ መስጨበጫ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ ብለዋል፡፡ የጊምቢ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘሮ ሉጬ መገርሳ፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየታየ ያለውን የወባ በሽታ ለመከላከል የግላቸውንና የአካባቢያቸውን ንጽሕና በአግባቡ በመጠበቅ ከበሽታው ራሳቸውን እየጠበቁ እንደሆነ ነው የገልጹት፡፡ ለወባ ትንኝ መራቢያ ሊሆኑ የሚችሉና ውሃ የሚያቁሩ ስፍራዎች የመደፍን ስራ ከሌሎች ጎረቤቶታቸው ጋር እያሰሩ መሆኑን ተናገረዋል። ''የግልም ሆነ የአካባቢ ንጽሕና መጠበቅ ለራስ ነው'' ያሉት የጊምቢ ከተማ ነዋሪው አቶ ናደው አምሳሉ የግላቸውንና አካባቢያቸውን ንጽህና ከመጠበቅ ባለፈ የአልጋ አጎበር በአግባቡ በመጠቀም በሽታውን እየተከላከሉ መሆኑን ገልጸዋል።
ኢኮኖሚ
በምስራቅ ቦረና ዞን ድርቅን ለመቋቋም የሚያስችል ከ204 ሺህ በላይ ሜትሪክ ቶን የእንስሳት መኖ እየተዘጋጀ ነው
Oct 1, 2023 35
ነገሌ ቦረና (ኢዜአ) መስከረም 20.2016-- በምስራቅ ቦረና ዞን በተደጋጋሚ ጊዜ የሚያጋጥመውን ድርቅ ለመቋቋም የሚያስችል 204 ሺህ በላይ ሜትሪክ ቶን የእንስሳት መኖ እየተዘጋጀ መሆኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ፡፡ ይኸው የመስኖ ልማት ፕሮጀክቱ 1 ሺህ 500 ሄክታር መሬት የማልማት አቅም ያለው ሲሆን 3 ሺህ አርብቶ አደሮችንና 20 ሺህ የቤት እንስሳትን በመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ የሚያደርግ እንደሆነም በወቅቱ ተገልጾ ነበር። ከውሃ ሀብት ልማቱ ጎን ለጎን የእንሰሳት መኖን አዘጋጅቶ በማከመችት ድርቅን በዘላቂነት ለመከላከል እየተሰራ መሆኑን አቶ ዋሪዎ ጨምረው ገልጸዋል። በዚህ ዓመት ብቻ ከ116 ሺህ ሄክታር በላይ የግጦሽ መሬት ከንክኪ የተከለለ ሲሆን ከዚህ ከተከለለ መሬት ከ204 ሺህ 870 ሜትሪክ ቶን በላይ የእንስሳት መኖ እየተዘጋጀ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ የእንስሳት መኖ በማቅረብ በዞኑ ባለፉት አመታት የደረሰውን ድርቅ ለመከላከል ጥረት ቢደረግም ለሁሉም ማዳረስ እንዳልተቻለ ገልጸዋል፡፡ በድርቁ የግጦሽ ሳርን ጨምሮ ወንዞችና ምንጮች በመድረቃቸው በቤት እንስሳት ላይ ጉዳት መድረሱን በማስታወስ፡፡ ችግሩ ጎልቶ በታየባቸው 8 ወረዳዎች ለዘንድሮ በጋ 116 ሺህ 678 ሄክታር መሬት በዞኑ ህዝብ ተሳትፎ ከንክኪ መከለሉን ገልጸዋል፡፡ የግጦሽ ሳር ልማቱ ከ325 ሺህ በላይ የሚገመት የቤት እንስሳትን ተጠቃሚ የማድረግ አቅም እንዳለውም ገልጸዋል፡፡ የዘፈቀደና ልቅ የግጦሽ ሳር አጠቃቀምን ለማስቀረት አርብቶ አደሩ የቁጠባ አጠቃቀምን ባህል እንዲያዳብር ግንዛቤ የመስጨበጥ ስራም እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡ በጽህፈት ቤቱ የተፈጥሮ ሀብት ቡድን መሪ አቶ አልዪ አረባ በበኩላቸው በዞኑ በተፋሰስ ልማትና በአረንጓዴ አሻራ ድርቅን ለመከላከል የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል፡፡ ባለፈው አመት ችግሩን ለመቀነስ በቀጥታ ከ80 ሺህ በላይ ህዝብ በአፈርና ውሃ ጥበቃ የልማት ስራ መሳተፉን አስታውሰዋል፡፡ በዞኑ አሬሮ ወረዳ የመታ ገፈርሳ ቀበሌ ነዋሪ አቶ ዋቅሽማ ወጋሪ ከአከባቢያቸው ነዋሪዎች ጋር በመተባበር የግጦሽ ሳር መሬት እንደከለሉ ገልጸዋል፡፡ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችም በመኖ ልማት ዝግጅት እያገዟቸው መሆኑን አንስተዋል፡፡ በአከባቢያቸው ከንክኪ ከተከለለ መሬት ለበጋ ወራት የሚያገለግል ከ8 ሺህ 500 በላይ እስር ሳር መሰብሰባቸውንም ጠቅሰዋል፡፡ ለድርቅ ወቅት የሚሆነን የእንስሳት መኖና የዝናብ ውሃ በማዘጋጀት በግለሰብ ደረጃም ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ እንደሆኑም አመልክተዋል፡፡
የተፈጥሮ ጸጋዎች ላይ የሚከናወኑ የልማት ስራዎች ለኢትዮጵያ ብልጽግና እውን መሆን መሠረት ይጥላሉ- አፈ-ጉባዔ ታገሰ ጫፎ
Oct 1, 2023 54
አዲስ አበባ፤ መስከረም 20/2016(ኢዜአ)፦የተፈጥሮ ጸጋዎችን ከሰው ኃይል ጋር በማስተሳሰር እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎች ለኢትዮጵያ ብልጽግና እውን መሆን መሠረት የሚጥሉ መሆናቸውን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ታገሰ ጫፎ ተናገሩ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በጅማ እና አካባቢው እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡ በጉብኝታቸውም በዋናነት በአካባቢዎቹ የሚከናወኑ የሌማት ትሩፋት፣ እንዲሁም የግብርና ሥራዎችን የጎበኙ ሲሆን፤ በጅማ ከተማ በገበታ ለትውልድ አማካኝነት የሚከናወነው የቱሪዝም ልማት ሥራም የጉብኝቱ አካል ነው፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ታገሰ ጫፎ፤ በጉብኝታቸው በጅማ ዞን ሕዝብን ተጠቃሚ ያደረጉ በርካታ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን መመልከታቸውን ተናግረዋል፡፡ በአካባቢው በቡና፣ ሩዝ፣ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም በቱሪዝም ልማት አበረታች ሥራ እየተከናወነ ስለመሆኑም ጠቁመዋል፡፡ ይህም የፌደራል መንግሥት ከክልሎች ጋር በመቀናጀት እያከናወናቸው ያሉ የልማት ሥራዎች በውጤታማ መንገድ ላይ መሆናቸውን ያመላከተ ነው ብለዋል፡፡ በአገር አቀፍ ደረጃ እየተከናወኑ ያሉ መሰል የልማት ሥራዎች ለኢትዮጵያ ብልጽግና መሠረት የሚጥሉ መሆናቸውንም እንዲሁ፡፡ ሕዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ሥራዎች ለዘላቂ ሰላም ግንባታ ወሳኝ ሚና እንዳላቸውም አፈ- ጉባዔው አብራርተዋል፡፡ ኢትዮጵያውያን በርካታ ፈተናዎችን በጋራ በማለፍ አብሮነታቸውን አስጠብቀው መቀጠላቸውን አስታውሰው፤ ይህንን የሕዝብ አብሮነት በልማት ሥራዎች በማስተሳሰር ይበልጥ ማጠናከር እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ ከዚህ አኳያ በሌማት ትሩፋትና ቱሪዝም ልማት የተጀመሩ ሥራዎች አበረታች መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡ የቀድሞ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አባ ዱላ ገመዳ በበኩላቸው፤ በጉብኝታቸው በጅማ ከተማና አካባቢው በርካታ አዳዲስ የልማት ስራዎች መከናወናቸውን እንደተመለከቱ ተናግረዋል፡፡ ለአብነትም ከዚህ ቀደም በአካባቢው የማይመረቱ እንደ ሩዝ ያሉ ምርቶችን በስፋት ማልማት መቻሉን ጠቅሰው፤ የቡና ምርትና ምርታማነትን በመጨመር ረገድም ከፍተኛ ሥራ መከናወኑን ገልፀዋል፡፡ በተለይ በጅማ ከተማ በገበታ ለትውልድ አማካኝነት እየተከናወኑ ያሉ የቱሪዝም ልማት ሥራዎች ከተማዋን የቱሪስት መዳረሻ የማድረግ አቅም እንዳላቸውም ነው የገለጹት፡፡ በሌማት ትሩፋትና ግብርና ልማት እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎች የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ እድገት በማሳለጥ ረገድ ሚናቸው የጎላ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ ከዚህ አኳያ አመራሩ በሁሉም ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶችን በሁሉም አካባቢዎች በማስቀጠል ረገድ ይበልጥ መሥራት እንዳለበትም አቶ አባ ዱላ ገመዳ ተናግረዋል፡፡
በኦሮሚያ ክልል የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማዕከል በማድረግ የተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች አበረታች ውጤት አስመዝግበዋል - አቶ ሽመልስ አብዲሳ
Oct 1, 2023 47
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 20/2016(ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል የህብረተሰብቡን ተጠቃሚነት ማዕከል በማድረግ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች አበረታች ውጤት እያስመዘገቡ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ባለፉት ሁለት ቀናት በጅማ እና አካባቢው ያሉ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡ በጉብኝታቸውም በዋናነት በአካባቢዎቹ የሚከናወኑ የሌማት ትሩፋት፣ እንዲሁም የግብርና ስራዎችን ተመልክተዋል። የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ በክልሉ የመደመር ዕሳቤን ማዕከል በማድረግ አራት መሰረታዊ የልማት ግቦችን ለማሳካት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። እነዚህም የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ፣ የገቢ ምርቶችን በአገር ውስጥ መተካት፣ ወደ ውጭ የሚላክን ምርት ማሳደግ፣ የስራ እድል ፈጠራን ማሻሻል መሆናቸውን ገልጸዋል። ከዚህ አኳያ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የተቀመጡ ኢንሼቲቮችን መነሻ በማድረግ በክልሉ በርካታ የልማት ስራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል። ለአብነትም በክልሉ በመኸር እና መስኖ የሚለማውን የመሬት ሽፋን በማሳደግ ረገድ ውጤታማ ስራ መከናወኑን ጠቁመዋል፡፡ የልማት ስራዎቹ በዋናነት የህዝብ ተጠቃሚነትን መሰረት ያደረጉ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡ ከአማራ ክልል ተሞክሮ በመውሰድ ከሶስት ዓመት በፊት የተጀመረው የሩዝ ምርትም ውጤት እየተመዘገበበት መሆኑንም አብራርተዋል፡፡ ይህም በአገር አቀፍ ደረጃ በሩዝ ምርት ራስን ከማቻል ባለፈ ለውጭ ገበያ ለማቅረብ የተጀመረውን ስራ በማገዝ ረገድ ትርጉም ያለው ለውጥ የሚያመጣ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ባለፉት አምስት ዓመታት ያረጁ የቡና ዛፎችን በአዲስ በመተካትና በአዲስ መልክ የቡና ችግኞችን በመትከል ረገድ አበረታች ስራ መከናወኑን ጠቅሰዋል፡፡ በዚህም ከ5 ቢሊዮን በላይ የቡና ችግኞችን መትከል መቻሉን ጠቅሰው፤ አርሶ አደሩ የቡና ምርትን በቀጥታ ለውጭ ገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ እንዲሆን እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል። በቀጣይም የምርት ጥራት ላይ ትኩረት በማድረግ የወጭ ንግድን ማሳደግ ላይ ያተኮሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል። በመኸርና በጋ መስኖ ስንዴ ልማት በተሰሩ ስራዎች ከፍጆታ አልፎ ለውጭ ገበያ ማቅረብ መቻሉን ጠቅሰው፤ በዚህም ኢትዮጵያ ለስንዴ ግዥ ታወጣው የነበረውን የውጭ ምንዛሬ ከማስቀረት ባለፈ ተጨማሪ ምንዛሪ ማስገኘት ተችሏል ብለዋል። በክልሉ ከፍተኛ የመልማት አቅም መኖሩን ገልጸው ይህንን አቅም በቴክኖሎጂ በማገዝ የበለጠ ውጤት ለማስመዝገብ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። ይህንን የአርሶ አደሩን ትጋት በአግባቡ በመደገፍ ጠንክሮ መስራት ከተቻለ በአጭር ጊዜ የላቀ ውጤት እንደሚረጋገጥም ነው የተናገሩት። በጅማ ዞን የተመዘገበው ስኬትም የዚሁ ማሳያ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል፡፡
የቱሪዝም ዘርፉን የሀገር ኢኮኖሚ ልማት መሠረት ለማድረግ የሚያስችሉ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው- የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት
Oct 1, 2023 55
አዲስ አበባ፤ መስከረም 20/2016 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያን የቱሪዝም ዘርፍ የሀገር ኢኮኖሚ ልማት መሠረት ለማድረግ የሚያስችሉ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት አስታወቀ። ቱሪዝም የሀገር በቀል ዕውቀትን በማበረታታት ለአዲሱ ሥርዓተ-ገቢራዊነት ገንቢ ሚና እንደሚወጣም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ገልጿል። በዓለም ለ44ኛ በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ36ኛ ጊዜ "ቱሪዝምና አረንጓዴ ኢንቨስትመንት" በሚል መሪ ሀሳብ የሚከበረው የቱሪዝም ቀን በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ በተለያዩ መርሃ-ግብሮች እየተከናወነ ነው። የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከስልጤ ዞን ጋር በመተባበር ባዘጋጁት መርሃ-ግብር ላይ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን ጨምሮ የክልሉና የዞኑ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ጌታቸው ነጋሽ፤ የቱሪዝም ዘርፍ የሀገር ኢኮኖሚ ልማት መሠረት ለማድረግ የሚያስችሉ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልፀዋል። በመንግሥት ለቱሪዝም ዘርፍ እድገትና ተጠቃሚነት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት የተለያዩ ተግባራት መጀመራቸውን ጠቅሰው፤ ካለው ሃብት አንፃር ተጠቃሚ ለመሆን በቀጣይ ብዙ መሥራት ይጠበቅብናል ሲሉ ተናግረዋል። የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ተሻለ በሬቻ፤ ኢትዮጵያ በርካታ የሰው ሰራሽና የተፈጥሮ ኃብቶች መስህብ ባለቤት ብትሆንም ጥቅም ላይ በማዋል ረገድ ውስንነቶች እንደነበሩ ጠቅሰዋል። አሁን ላይ ግን የቱሪስት መዳረሻዎች በትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲው ተካተው የሀገር ሀብትና ኢኮኖሚውን የሚደግፉና የሥራ ዕድል መፍጠሪያ መስክ በማድረግ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ገልፀዋል። የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አሊ ከድር፤ በዞኑ በርካታ ቅርሶች፣ ታሪካዊ ሥፍራዎችና ማራኪ የቱሪስት መዳረሻዎች ቢኖሩም እስካሁን እምብዛም ጥቅም አልተገኘባቸውም ብለዋል። የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ መደረጉን ተከትሎ የቱሪዝም ዘርፉ እየተነቃቃና በርካታ ጥቅሞች እየተገኙበት ነው ብለዋል። በዞኑ ያሉ ሙጎ ተራራ፣ የአባያ ጡፋ ሀይቅ፣ የሀጅ አሊዬ መስጂድ እና ሌሎችም የቱሪስት መዳረሻዎችን በመለየት ለጎብኚዎች ምቹ ማድረግ ተችሏል ሲሉ ተናግረዋል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
ለድሬዳዋ ልማት በገንዘብ የሚደረገውን ድጋፍ በቀላሉ ለማሰባሰብ የሚያግዝ ሶፍትዌር እና ድረ ገጽ አገልግሎት መስጠት ጀመረ
Sep 30, 2023 60
ድሬደዋ፤ መስከረም19/2016(ኢዜአ)፣- ለድሬዳዋ ልማት በገንዘብ የሚደረገውን ድጋፍ በቀላሉ ለማሰባሰብ የሚያግዝ ሶፍትዌር እና ድረ ገጽ አገልግሎት መስጠት ጀመረ። አገልግሎት መስጠት የጀመረው ሶፍት ዌር እና "ሄልፕድሬ ዶት ኮም" የተሰኘው የገቢ ማሰባሰቢያ ድረ ገጹ በውጭና በአገር ውስጥ ያሉ የድሬዳዋ የልማት ተባባሪዎች ካሉበት ሆነው ድጋፋቸውን በቀላሉ ተደራሽ ማድረግ እንደሚያስችላቸው በስነስርዓቱ ላይ ተገልጿል። የድሬዳዋ ወዳጅና ተወላጅ የሆኑ ባለሙያዎች አስተዳደሩ የህብረተሰቡን ማህበራዊ ችግሮች ለማቃለል ለሚያከናውናቸው ተግባራት አጋዥ እንዲሆን የሰሩትን ሶፍት ዌርና ድረ ገፅ ዛሬ ለአስተዳደሩ ከንቲባ አስረክበዋል። በድሬደዋ አስተዳደር የሚከናወኑ የልማት ፕሮጀክቶችን እና የአገልግሎት አሰጣጥ ተግባራትን በቴክኖሎጂ በማስደገፍ የተሻለ ውጤት ለማምጣት በቁርጠኝነት እንደሚሰራም ከንቲባው ከድር ጁሃር ተናግረዋል። "ቻፓ የፋይናንስ ተቋም" ላበረከተው ቴክኖሎጂ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ቴክኖሎጂው የድሬዳዋ ተወላጆችና ወዳጆች የድሬዳዋን ማህበራዊ ችግሮች ለመፍታት ከያሉበት የጀመሩትን ዘርፈ ብዙ ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል ብለዋል። "የድሬዳዋን ማህበራዊ ችግሮች በራሷ ልጆችና ተወላጆች የመፍታቱ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል" ያሉት ከንቲባ ከድር፣ በድረ ገጹ የሚሰበሰበው ሃብት ለትምህርት ቤት ምገባና በድሬዳዋ በተደራጀው የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል ነፃ የሕክምና አገልግሎት ለመስጠት እንደሚውል ገልጸዋል። እንደ ከንቲባ ከድር ገለፃ በዘንድሮ ዓመት በድሬዳዋ የሚከናወኑ የምጣኔ ሃብትና የማህበራዊ አገልግሎት ፕሮጀክቶች እንዲሁም የተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥ ተግባራት ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆኑ በቴክኖሎጂ ለመደገፍ በቁርጠኝነት ይሰራል። ሶፍትዌር እና የገቢ ማሰባሰቢያ ድረ ገፅ ፈጠራውን ለአስተዳደሩ ያስረከበው ቻፓ የፋይናንስ ተቋም ስራ አስኪያጅ ወጣት እስራኤል ጎይቶም በበኩሉ እንደተናገረው፣ ለድሬዳዋ ሁሉን አቀፍ ዕድገትና የነዋሪውን ማህበራዊ ችግሮች ለማቃለል የሚከናወኑ ተግባራት ውጤታማ እንዲሆኑ ተቋሙ በዕውቀት፣ በገንዘብና በጉልበት የሚያደርገውን ድጋፍ ያጠናክራል። በስነስርዓቱ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህን ጨምሮ የካቢኔ አባላት፣ የኃይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎችና ነዋሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል።
የአማራ ክልል የከተማ ልማት ክላስተር በክልሉ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን መተግበር የሚያስችለውን የሶስትዮሽ ስምምነት ተፈራረመ
Sep 29, 2023 85
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 18 /2016(ኢዜአ)፡- የአማራ ክልል የከተማ ልማት ክላስተር በክልሉ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን ለመተግበር የሚያስችለውን የሶስትዮሽ ስምምነት ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና ከኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር ተፈራረመ፡፡ ስምምነቱን በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የከተማ ዘርፍ ክላስተር አስተባባሪና የከተማ ልማት ቢሮ ሃላፊ ዶክተር አህመዲን ሙሐመድ፣ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ወርቁ ጋቸና እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ሰለሞን ሶካ ተፈራርመዋል፡፡ የሶስትዮሽ ስምምነቱ ለማህበራዊ፣ ኢኮኖሚ እና ሌሎች ዘርፎችን ፋይዳ ያላቸውን የቴክኖሎጂ ውጤቶች በመተግበር የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ያለመ ነው ተብሏል፡፡ የሚተገበሩት ቴክኖሎጂዎች በተለይም በመሬት ዘርፍ ያለውን ህገ-ወጥንነት ለመከላከል፣ ተቋማትን ከብክነት ለመታደግና ወንጀልን ለመከላከል ትልቅ ፋይዳ እንዳላቸው ተጠቁሟል፡፡ ይህም የክልሉን ህዝብ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያግዛል ነው የተባለው፡፡ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ሰለሞን ሶካ በዚሁ ወቅት፤ ስምምነቱ በአማራ ክልል ስማርት ሲቲን ለመተግበር፣ ንግድና ገቢዎች ዘርፍን ለማሳለጥና የቱሪዝም ሴክተሩን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ ያግዛል ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክር ኢንጅነር ወርቁ ጋቸና በበኩላቸው በስምምነቱ መሰረት በአርተፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፉ ክልሉን ለማገዝ በጋራ እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡ በክልሉ ህዝቡ ለሚያነሳቸው ጥያቄዎች በቴክኖሎጂ የተደገፈ ፈጣን ምላሽ በመስጠት ረገድ ኢንስቲትዩቱ የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣም ተናግረዋል፡፡ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የከተማ ዘርፍ ክላስተር አስተባባሪና የከተማ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አህመዲን ሙሐመድ፤ ስምምነቱ በቴክኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎት አሰጣጥን ተደራሽ ለማድረግ እንደሚያግዝ ገልጸዋል፡፡ በክልሉ ህገ-ወጥ ግንባታ፣ የመሬት ወረራ፣ የስራ አጥነትና መሰል ችግሮች መኖራቸውን ጠቁመው ችግሮቹን በዘላቂነት ለመፍታት በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት አሰጣጥ ወሳኝ ሚና እንዳለው ተናግረዋል፡፡ በስምምነቱ መሰረትም መሬት ስራን በካዳስተር እንዲመራ በማድረግ እንዲሁም የአገልግሎት ዘርፉን ማዘመን ላይ በትኩረት ይሰራሉ ብለዋል፡፡ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስን መሰረት ባደረጉ ተግባራትም በተለይ የክልሉን ዋና ከተማን ጨምሮ ሌሎችንም የሴኩሪቲ ካሜራ ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚሰሩም ጠቁመዋል፡፡
ኢትዮ-ቴሌኮም እና የአዲስ አበባ ከተማ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የስማርት የእሳትና አደጋ ስጋት አመራር ትግበራ ስምምነት ተፈራረሙ
Sep 26, 2023 153
አዲስ አበባ፤ መስከረም 15/ 2016 (ኢዜአ)፦ ኢትዮ-ቴሌኮም እና የአዲስ አበባ ከተማ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የስማርት የእሳትና አደጋ ስጋት አመራር ትግበራ ስምምነት ተፈራረሙ። ስምምነቱ ፈጣን የአደጋ መረጃ እና ምላሽ አሰጣጥ ስርዓትን ለማጎልበት የሚያግዝ ነው፡፡ ስምምነቱን የአዲስ አበባ ከተማ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ ሰለሞን አማረ እና የኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ቴክኖሎጂ ኦፊሰር ታሪኩ ደምሴ ተፈራርመዋል፡፡ በስምምነቱ መሰረት የተቀናጀ የግንኙነት እንዲሁም የመረጃ ስርዓት ተግባራዊ በማድረግ የአደጋ ስራ አመራር አገልግሎቶችን ለማዘመን ይሰራል፡፡ በዚህም ኢትዮ ቴሌኮም ዘመናዊና በቀላሉ ተደራሽ የሚሆን የአደጋ ጊዜ የጥሪ ማዕከል በማዘጋጀት አገልግሎቱን በጥራትና በቅልጥፍና እንደሚያቀርብ ተመላክቷል። በተጨማሪም የተቀናጀ የድንገተኛ አደጋ ጊዜ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ የሚያግዝ ስርዓት አቅርቦት እና የተከላ እንዲሁም ቀጣይነት ያለው ስልጠና እና ድጋፍ እንደሚደረግ ተመላክቷል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ ሰለሞን አማረ ስምምነቱ የእሳትና አደጋ ስጋት አመራርን በተሻለ መልኩ ለመምራት ያግዛል ብለዋል። ድንገተኛ አደጋዎችን ለመከላከልና በአጭር ጊዜ ለመቆጣጠር ወሳኝ ሚና እንዳለው አመላክተዋል። በስምምነቱ መሰረት በቀጣዮቹ አራት ወራት ዘመናዊ የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ እንደሚገባም ነው የገለጹት። የኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ቴክኖሎጂ ኦፊሰር ታሪኩ ደምሴ በበኩላቸው ኩባንያው ዲጂታል አገልግሎቶችን በስፋት ተደራሽ በማድረግ የዲጂታል ኢትዮጵያን ራእይ ለማሳካት የበኩሉን ሚና እየተወጣ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በዚህም ለተለያዩ ተቋማት የቴክኖሎጂ እና ዲጂታል አማራጮችን በማቅረብ የአገልግሎት አሰጣጣቸውን እንዲያዘምኑ እገዛ እያደረገ መሆኑን ጠቅሰው፤ የዛሬው ስምምነትም የዚሁ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡ ስምምነቱም የዜጎችን የእለት ተእለት እንቅስቃሴን በማሳለጥ ረገድ ጉልህ ሚና እንዳለው አመላክተዋል፡፡ የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ይክፈለው ወልደመስቀል፤ ኮሚሽኑ ላለፉት 90 አመታት የእሳት አደጋ ምላሽ እየሰጠ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ከዚህ አኳያ ስምምነቱ ከተማዋን የሚመጥን አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ያግዛል ብለዋል።
አውደ-ርዕዩ በዘርፉ ያካበተ ልምድ ካላቸው ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በትብብር ለመሥራት እድል ፈጥሯል - የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር
Sep 22, 2023 327
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 11/2016 (ኢዜአ)፦ በአዲስ አበባ ለአንድ ወር የተካሄደው የውኃና ኢነርጂ አውደ-ርዕይ በዘርፉ ያካበተ ልምድ ካላቸው ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በትብብር ለመሥራት እድል መፍጠሩን የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ገለጸ። የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር "የውኃ ኃብታችን ለብልጽግናችን" በሚል መሪ ኃሳብ በሳይንስ ሙዚየም ለአንድ ወር ያካሄደው አውደ ርዕይ ትላንት ተጠናቋል። አውደ ርዕዩ ምን አስገኘ? የሚለውን ለማወቅ ኢዜአ የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴርና በአውደ-ርዕዩ አገልግሎታቸውን ያቀረቡ ተቋማትን አነጋግሯል። በሚኒስቴሩ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ጌትነት ጌጡ፤ በአውደ-ርዕዩ ዘርፉን ለማዘመን በትግበራ ላይ ያሉ የተለያዩ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለዕይታ ቀርበዋል ብለዋል። ለአብነትም ኢትዮጵያ የውኃ መጠኗን በዲጂታል መተግበሪያ በመታገዝ እንዴት እንደምትከታተልና እንደምትቆጣጠር ማሳየት መቻሏን ጠቁመዋል። አውደ-ርዕዩን የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጨምሮ የዘርፉ ዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች እንዲሁም አምባሳደሮች መጎብኘታቸውን ነው ያረጋገጡት። በመሆኑም አውደ-ርዕዩ አገሪቱ በዘርፉ የምታከናውነውን ሥራ ለማስገንዘብ እድል ሰጥቷል ነው ያሉት። ከዚህ በተጠማሪም አውደ-ርዕዩ በዘርፉ ከተለያዩ ተቋማት ጋር አዳዲስ አጋርነትና ትብብር ለመመሥረት ምቹ ሁኔታ መፍጠሩንም ገልጸዋል። በመድረኩ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን ያቀረቡ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት በበኩላቸው አውደ-ርዕዩ የውኃና ኢነርጂ ዘርፍን በቴክኖሎጂ ለማዘመን የሠሯቸውን ሥራዎች ለሕዝብ ለማቅረብ እድል ሰጥቶናል ብለዋል። በኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት በመረጃና ክላይማቶሎጂ ክፍል ተመራማሪ የሆኑት ለታ በቀለ ተቋማቸው በአውደ-ርዕዩ በአገሪቱ ያለውን የአየር ፀባይ ሁኔታ ጥናት ለማካሄድ የሚጠቀምባቸውን የቴክኖሎጂ ውጤቶች ማቅረባቸውን ጠቅሰዋል። የተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች አውደ-ርዕዩን መጎብኘታቸው ገልጸው ይህም በቀጣይ በሚቲዎሮሎጂ ዘርፍ አብረው መሥራት የሚችሉባቸውን ሁኔታዎች ለመለየት ዕድል መፍጠሩን ነው የገለጹት። የአነጋ ኢነርጃይዝ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ የሽያጭ ባለሙያ እየሩሳሌም ደጀኔ በበኩሏ በአውደ-ርዕዩ ኅብረተሰቡ የሚጠቀምባቸውን ኃይል ቆጣቢ ምድጃዎች ማቅረባቸውን ተናግራለች። በዝግጅቱ ላይ መሳተፋቸው ኃይል ቆጣቢ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ለተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች በቀላሉ ለማስተዋወቅ እንደረዳቸው በመግለፅ እንደ አገር መሰል አውደ-ርዕዮች በተለያዩ አካባቢዎች ሊስፋፉ እንደሚገባ ተናግራለች። በሐፍ አስመጪና አቅራቢ ድርጅት የኦፕሬሽን ማናጀር ሃበን ገብሩ በአውደ-ርዕዩ ምንም አይነት ኤሌክትሪክ ኃይልና የውኃ ማጣሪያ ኬሚካል ሳይጠቀም ውኃን ማጣራት የሚችል ቴክኖሎጂ ለኅብረተሰቡ በስፋት አሳይተናል ብለዋል።
ስፖርት
አትሌት ድርቤ ወልተጂ በ1 ማይል የሴቶች የጎዳና ላይ ሩጫ ክብረ ወሰን በማሻሻል አሸነፈች
Oct 1, 2023 59
አዲስ አበባ፤ መስከረም 20/2016 (ኢዜአ)፦ በላቲቪያ ሪጋ በተካሄደው የዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ አትሌት ድርቤ ወልተጂ በ1ማይል የሴቶች የጎዳና ላይ ሩጫ የዓለም ክብረ ወሰንን በመስበር አሸንፋለች። ርቀቱን አትሌት ድርቤ ወልተጂ 4 ደቂቃ ከ21 ሰከንድ በሆነ ሰዓት ውድድሩን ስትጨርስ ፍሬወይኒ ኃይሉ ደግሞ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች፡፡ ቀደም ብለው በተደረጉ ውድድሮች በ5 ኪሎ ሜትር የዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ አትሌት ሀጐስ ገ/ሕይወት 12 ደቂቃ ከ59 ሰከንድ በመግባት 1ኛ ሲወጣ አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ ደግሞ 13 ደቂቃ ከ02 ሰከንድ በመግባት 2ኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ ይታወሳል። በተመሳሳይ አትሌት እጅጋየሁ በ5 ኪሎ ሜትር የዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ 14 ደቂቃ ከ40 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በመግባት 3ኛ ሆና ማጠናቀቅ ማጠናቀቅ መቻሏም እንዲሁ። በላቲቪያ ሪጋ ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ በሚደረገው የዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን ወክለው 13 አትሌቶች እየተሳተፉ ይገኛሉ። በሻምፒዮናው ከ57 አገራት የተወጣጡ 347 አትሌቶች የሚሳተፉ ሲሆን 1 ማይል፣ 5 ኪሎ ሜትር እና የግማሽ ማራቶን በሁለቱም ጾታዎች ውድድር የሚካሄድባቸው ርቀቶች ናቸው።
በዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ድል ቀናቸው
Oct 1, 2023 59
አዲስ አበባ፤ መስከረም 20/2016 (ኢዜአ)፡- ዛሬ በላቲቪያ ሪጋ በተካሄደው በ5 ኪሎ ሜትር የዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች 1ኛና 2ኛ በመውጣት ድል ቀንቷቸዋል። በውድድሩም አትሌት ሀጐስ ገ/ሕይወት 12 ደቂቃ ከ59 ሰከንድ በመግባት 1ኛ ሲወጣ አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ ደግሞ 13 ደቂቃ ከ02 ሰከንድ በመግባት 2ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል። በተመሳሳይ አትሌት እጅጋየሁ በ5 ኪሎ ሜትር የዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ 14 ደቂቃ ከ40 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በመግባት 3ኛ ሆና ማጠናቀቅ ችላለች። በዚሁ እርቀት የተሳተፈችው አትሌት መዲና ኢሳ ደግሞ አራተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች፡፡ ኬንያዊቷ አትሌተ ቢያትሬስ ቼቤት ውድድሩን በአንደኛነት አሸንፋለች።
በላቲቪያ ሪጋ በሚካሄደው የዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በ13 አትሌቶች ተወከላለች
Oct 1, 2023 45
አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2016(ኢዜአ)፡- በላቲቪያ ሪጋ ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ በሚደረገው የዓለም ጎዳና ላይ ሩጫ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን ወክለው 13 አትሌቶች ይሳተፋሉ። በሻምፒዮናው ከ57 አገራት የተወጣጡ 347 አትሌቶች የሚሳተፉ ሲሆን 1 ማይል፣ 5 ኪሎ ሜትር እና የግማሽ ማራቶን በሁለቱም ጾታዎች ውድድር የሚካሄድባቸው ርቀቶች ናቸው። ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው በ7 ሴቶች እና በ6 ወንዶች በድምሩ በ13 አትሌቶች ትወከላለች። በሴቶች 5 ኪሎ ሜትር እጅጋየሁ ታዬ እና መዲና ኢሳ ከቀኑ 5 ሰዓት ከ50 ላይ ውድድራቸውን ያደርጋሉ። ከቀኑ 6 ሰዓት ከ15 ላይ በሚካሄደው ወንዶች ውድድር ዮሚፍ ቀጄልቻ እና ሐጐስ ገብረ ሕይወት ይወዳደራሉ። ድርቤ ወልተጂና ፍሬወይኒ ኃይሉ 7 ሰዓት ላይ በሚካሄደው የአንድ ማይል እንዲሁም በወንዶች በተመሳሳይ ርቀት ከቀኑ 7 ሰዓት ከ10 ሰዓት ላይ በሚደረገው ውድድር ታደሰ ለሚ ይወዳደራል። በሴቶች የግማሽ ማራቶን ውድድር ከቀኑ 7 ሰዓት 30 ጽጌ ገብረሰላማ፣ ያለምጌጥ ያረጋል እና ፍታው ዘርዬ ይሳተፋሉ። ከቀኑ 8 ሰዓት ከ15 በግማሽ ማራቶን ወንዶች ጀማል ይመር፣ ንብረት መላክና ፀጋዬ ኪዳኑ የሚወዳደሩ ይሆናል። ለሻምፒዮናው ውድድር አትሌቶቹ ለሶስት ሳምንታት ዝግጅት ማድረጋቸውን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
የ2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ይጀመራል
Oct 1, 2023 42
አዲስ አበባ፤ መስከረም 20 /2016(ኢዜአ)፡- የ2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ በሚካሄዱ ሁለት ጨዋታዎች ይጀመራል። በ16 ክለቦች መካከል የሚከናወነው የወንዶች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የጨዋታ መርሃ ግብር ከዛሬ ጀምሮ መካሄዱን የሚቀጥል ይሆናል። በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም አዳማ ከተማ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ካደገው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ከቀኑ 9 ሰዓት የሊጉን የመክፈቻ ጨዋታ ያደርጋሉ። በመቀጠልም ሲዳማ ቡና ከኢትዮጵያ ቡና ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ። የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታዎች እስከ መስከረም 27 ቀን 2016 ዓ.ም የሚካሄዱ ይሆናል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ዙር ውድድር እስከ የካቲት 10ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚከናወን የፕሪሚየር ሊጉ አክሲዮን ማህበር አስታውቋል። የሊጉ የመጀመሪያ ዙር ውድድር በአዳማና ድሬዳዋ ከተሞች እንደሚደረግም ታውቋል። ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ሻሸመኔ ከተማና ሀምበሪቾ ዱራሜ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ያደጉ ክለቦች መሆናቸው ይታወቃል።
አካባቢ ጥበቃ
የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር የድሬደዋን አየር ንብረት ለኑሮና ለሥራ ምቹ ከማድረግ ባለፈ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እያገዘ ነው--ቢሮው
Sep 30, 2023 82
ድሬደዋ፤ መስከረም 19/2016(ኢዜአ)፡- የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀግብር የድሬደዋን የአየር ንብረት ለኑሮና ለሥራ ምቹ ከማድረግ ባለፈ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ አስተዋጾ እያደረገ መሆኑን የድሬደዋ አስተዳደር ግብርና፣ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ አስታወቀ። በድሬደዋ በሁለተኛው ዙር የመጀመሪያ ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር ለመትከል ከታቀደው 1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ችግኞች 94 በመቶ የሚሆኑት ተተክለው እንክብካቤ እየተደረገላቸው መሆኑ ተገልጿል። የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ኤሊያስ አልይ ለኢዜአ እንደተናገሩት በመርሀግብሩ የመጀመሪያ ዙር አራት ዓመታት በድሬዳዋ ገጠርና ከተማ 5 ነጥብ 7 ሚሊዮን የዛፍ እና የፍራፍሬ ችግኞች ተተክለዋል። ከተተከሉት ችግኞች 70 በመቶዎቹ የጸደቁ ሲሆን ችግኞቹም በገጠር በቤተሰብ ደረጃ የተጀመረውን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ አይነተኛ ሚና እየተጫወቱ መሆኑን ገልጸዋል። "በተለይ የተተከሉ ምርጥ የፓፓያ፣ የጊሽጣ፣ የአንበሾክ፣ የብርትኳን፣ የመንደሪን፣ የአፕል እና ሌሎች የፍራፍሬ ችግኞች አፍርተው ለገጠሩ ማህበረሰብ ተጨማሪ ገቢና የተመጣጠነ ምግብ እያስገኙ ናቸው" ብለዋል። በተጨማሪም ለድሬዳዋ የጎርፍ አደጋ መነሻ በሆኑ ወረዳዎች በቅንጅት የተተከሉት ችግኞች ጎርፍን በመቀነስና ውሃን ለልማት በማዋል የጎላ አስተዋጾ እያደረጉ መሆኑን አቶ ኤሊያስ ተናግረዋል። "የአረንጓዴ አሻራ ከጎረቤት ጅቡቲ ጋር ያለንን ሁለንተናዊ ጠንካራ ትስስር ይበልጥ እንዲያብብ እያገዘ ነው" ያሉት አቶ ኤሊያስ፣ ባለፉት ሁለት ዓመታት ከ140 ሺህ በላይ ችግኞች ለጅቡቲ በመላክና ሙያዊ ድጋፍ በመስጠት ትስስሩ እንዲጠናከር መደረጉንም ገልጸዋል። ዘንድሮም በቀጣይ ጥቅምት ወር 100 ሺህ ምርጥ ችግኞችን ለጅቡቲ ለመስጠት ዝግጅት መደረጉን ነው አቶ ኤሊያስ ያመለከቱት። የድሬዳዋ አስተዳደር የደንና አየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን የደን ልማትና ጥበቃ ዳይሬክተር አቶ ማስረሻ ይመር በበኩላቸው፣ ባለፉት ዓመታት የተተከሉት ችግኞች የድሬደዋ አየር ንብረት ለሥራና ለኑሮ ምቹ ማድረጉን ገልጸዋል። በተጨማሪም ነዋሪዎች ችግኝ ተክሎ መንከባከብ የህልውና ጉዳይ መሆኑን ይበልጥ እንዲገነዘቡ አድርጓል ብለዋል። አቶ ማስረሻ እንዳሉት በሁለተኛው ዙር የመጀመሪያው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻ ለመትከል ከተዘጋጁት 1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ችግኞች ውስጥ 94 በመቶ የሚሆኑት ተተክለዋል። አሁን በአካባቢው እየጣለ ያለውን ዝናብ በመጠቀም ቀሪዎቹ እንደሚተከሉም አመልክተዋል። የተተከሉትን ችግኞች ከመንከባከብ በተጨማሪ በክረምቱ ተተክለው በተለያዩ ምክንያቶች ያልበቀሉትን መልሶ የመተካት ሥራ እንደሚሰራም አቶ ማስረሻ ተናግረዋል። ችግኞችን መትከልና መንከባከብ ለድሬዳዋ ነዋሪዎች የህልውና ጉዳይ መሆኑን በአፅንኦት የተናገሩት ደግሞ የአረንጓዴ አሻራ አገር አቀፍ የድሬዳዋ ተሸላሚው አቶ በያን ምትኩ ናቸው። በደን መመናመን ምክንያት ጎርፍ ከ17 ዓመታት በፊት በድሬደዋና በነዋሪዎቿ ላይ ያደረሰውን አሰቃቂ አደጋ አስታውሰዋል። አምና በድሬዳዋ ገጠርና ከተማ በአንድ ጀንበር 880 ሺህ ችግኞች ሲተከሉ የአረንጓዴ አሻራ አርበኛው አቶ በያን በሺዎች የሚገመቱ ችግኞችን ተክለው በመንከባከብ ታሪካዊ ሥራ ሰርተው አርአያ ሆነዋል። "ሁሉም የድሬደዋ ነዋሪዎች ችግኞችን ተክለው በመንከባከብ አካባቢያቸውን መለወጥ አለባቸው" ሲሉም አስገንዝበዋል። በድሬደዋ አስተዳደር በሁለተኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻ ከ12 ሚሊዮን በላይ የጥላ፣ የፍራፍሬ እና የዛፍ ችግኞች ይተክላሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ታውቋል።
የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ሁነኛ መፍትሄ ነው - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን
Sep 23, 2023 211
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 12/2016(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እየተገበረች ያለው የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ሁነኛ መፍትሄ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ። አቶ ደመቀ መኮንን ይህንን ያሉት በአሜሪካ ኒው-ዮርክ እየተካሄደ ባለው በ78ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው። በንግግራቸውም የአየር ንብረት ለውጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተጽዕኖ እየፈጠረ መሆኑን ገልጸው ተጽዕኖው በአፍሪካና በሌሎች በማደግ ላይ ባሉ አገራት ከፍተኛ ነው ብለዋል። ያደጉ አገራት አፍሪካን ጨምሮ በማደግ ላይ ባሉ አገራት የአየር ንብረትን ለውጥን እንዲቋቋሙ ለመልቀቅ የወሰኑትን የገንዘብ ድጋፍ ሙሉ በሙሉ አለመለቀቁን አንስተዋል። እንዲያም ሆኖ ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ቀውስ ሁሉን አቀፍ መፍትሄ እንዲሰጥ እየሰራች መሆኑን ገልጸው አረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር የዚህ ቁርጠኝነት ማሳያ ነው ብለዋል። መርኃ ግብሩ የአረንጓዴ ልማትን ለማስፋት ዓላማ ያደረገ መሆኑን ገልጸው አሁን ላይ መርኃ ግብሩ በአገር አቀፍ ደረጃ ውጤታማ መሆኑን ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ በዘርፉ ያላትን ልምድ ለማካፈል እየሰራች መሆኑንም ተናግረዋል። በቀጣይ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የሚካሄደው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ችግሩን ለማቃለል ተጨባጭ እርምጃ ለመውሰድ መረባረብ እንደሚገባ አሳስበዋል። በሌላ በኩል አንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2030 ድኅነት ለመቀነስ እየተሰራ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች እነዚህ ችግሮች እየጨመሩ መምጣታቸውን ገልጸዋል። ጎን ለጎንም በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚስተዋለው የሸቀጦች የዋጋ ንረት የአብዛኛውን ተጋላጭ ማኅበረሰቦች ፈተና ይበልጥ እያወሳሰበው መሆኑንና ትኩረት እንደሚሻ ጠቁመዋል።
በሚቀጥሉት አሥር ቀናት ለመኸር እርሻ ሥራ አመቺ ዝናብ ይኖራል- የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት
Sep 22, 2023 191
አዲስ አበባ፤ መስከረም 11/2016(ኢዜአ)፦በሚቀጥሉት አሥር ቀናት በአብዛኞቹ የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ አካባቢዎች ለመኸር እርሻ አመቺ ዝናብ እንደሚዘንብ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ። ኢንስቲትዩቱ ለኢዜአ በላከው መግለጫ በሚቀጥሉት አሥር ቀናት በአብዛኞቹ የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ አካባቢዎች የሚኖረው ዝናብ ለመኸር እርሻ ሥራ አመቺ ሁኔታን እንደሚፈጥር ገልጿል። በተለይም ከክረምት አጋማሽ አካባቢ ጀምሮ የዝናብ እጥረት በነበረባቸው የምስራቅ እና የሰሜን ምስራቅ አካባቢዎች ዝናብ ያገኛሉ። በእነዚህ አካባቢዎች የሚገኘው ዝናብ በተለያዩ የውሃ ማቆያ ዘዴ ተጠቅሞ ለእርሻ ሥራ ማዋል እንደሚገባ ኢንስቲትዩቱ ጠቁሟል። በአንፃሩ የደቡብና የደቡብ ምሥራቅ ኢትዮጵያ አካባቢዎች ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ ከመጣው የደመና ሽፋን ጋር ተያይዞ ሊኖር የሚችል እርጥበት ለአርብቶ አደርና ለከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች በጎ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ተጠቅሷል። በተጨማሪም በሰሜን፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብና በመካከለኛው ምስራቅ ተፋሰሶች ላይ የተሻለ የእርጥበት ሁኔታ እንደሚኖር የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ሆኖም ግን በአንዳንድ አካባቢዎች የሚጠበቀው ከባድ ዝናብ በተዳፋትና ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ላይ የአፈር መሸርሸር ሊያስከትል ስለሚችል የሚመለከታቸው አካላት ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ኢንስቲትዩቱ አሳስቧል። ከቀን ወደ ቀን የውሃ መጠናቸው ከፍ እያለ በመጡት እንደ ቆቃ፣ አዋሽ ተፋሰስ፣ ጣና በለሰና ፊንጫ ግድቦች ላይ አስፈላጊውን ክትትል ማድረግ እንደሚገባ ትንበያው አመልክቷል።
የአየር ንብረት ለውጥ የሚያሳድራቸውን ተጽዕኖዎች ለመከላከል ዓለም አቀፍ ትብብርን ማጠናከር ያስፈልጋል - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን
Sep 21, 2023 235
አዲስ አበባ፤ መስከረም 10/2016 (ኢዜአ)፦ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያሳድራቸውን ተጽዕኖዎች ለመከላከል ዓለም አቀፍ ቅንጅታዊ ትብብርን ማጎልበት እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ። 78ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ “ሰላም፣ብልጽግና፣ለውጥና ዘላቂነት” በሚል መሪ ሀሳብ በኒው ዮርክ እየተካሄደ ነው። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከጉባኤው ጎን ለጎን በተካሄደ የአየር ንብረት ለውጥን የተመለከተ ጉባኤ ላይ ተሳትፈዋል። አቶ ደመቀ በጉባኤው ላይ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቋቋም በአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ከፍተኛ የሚባል መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ እየሰራች እንደምትገኝ ገልጸዋል። በመርሐ-ግብሩ እስከ አሁን ከ32 ቢሊዮን በላይ ችግኞች መተከላቸውንና የተለያዩ ውጤቶች እየተገኙበት መሆኑንም አመልክተዋል። የአደጋዎች ስፋት፣ መጠንና የሚከሰቱበት የጊዜ ገደብ ታሳቢ በማድረግ ኢትዮጵያ ፖሊሲዎቿን በመለወጥ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት የማጠናከር ስራ በማከናወን ላይ ነች ብለዋል። በዚህ ረገድም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉትዬሬዝ “ቅድመ ማስጠንቀቂያ ለሁሉም” በሚል የጀመሩትን ኢኒሺዬቲቭ አቶ ደመቀ አድንቀዋል። ዓለም አቀፍ ትብብር አስፈላጊውን ቅንጅትና ትስስር በመፍጠር የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ወሳኝ አስተዋጽኦ እንዳለውም ነው ያብራሩት። በአገር፣ በአህጉርና ዓለም አቀፍ ደረጃ ብቁና ውጤታማ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት ለመገንባት አስፈላጊው የፋይናንስ ድጋፍ እንዲደረግም ጥሪ አቅርበዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
ኢትዮጵያ ለቢዝነስ ምቹ ከሆኑ 10 የአፍሪካ ሀገራት አንዷ መሆኗ ተገለጸ
Sep 28, 2023 267
አዲስ አበባ ፤መስከረም 17/2016 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ለቢዝነስ ምቹ ከሆኑ10 የአፍሪካ ተመራጭ ሀገራት አንዷ መሆኗን የኦክስፎርድ ምጣኔ ኃብታዊ ሪፖርት ይፋ አደረገ። ቢዝነስ ኢንሳይደር አፍሪካ እ.ኤ.አ. በ2023 ቢዝነስ ለመስራት 10 ምርጥ የአፍሪካ ሀገራት ዝርዝርን የኦክስፎርድ የአፍሪካ ምጣኔ ኃብታዊ ሪፖርትን ዋቢ አድርጎ ይፋ አድርጓል። የኦክስፎርድ ምጣኔ ኃብታዊ ሪፖርት “የአፍሪካ ስጋትና ማነቃቂያ መጠቆሚያ” በሚል ርዕስ ገምግሞ 10 አገራትን በምርጥነት አስቀምጧል። ከአሥሩ አንዷ ደግሞ ኢትዮጵያ ሆና ተመርጣለች። እነዚህ አገራት ምቹ የንግድ ከባቢ፣ ጠንካራ መሠረተ ልማት፣ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት እና ጠንካራ የቁጥጥር ማዕቀፍ እንዳላቸው በግምገማ ተረጋግጦ መመረጥ መቻላቸው ተገልጿል። በተለይ አገራቱ ምቹ የኢንቨስትመንት ማዕከል መሆናቸው ለዚህ ተመራጭ እንዳደረጋቸውም ዘገባው አመልክቷል። ሪፖርቱ በእያንዳንዱ የአፍሪካ ሀገር ትርፍ እና ኪሳራ፣ የፀጥታ ሁኔታ እና የአፍሪካ ሀገራት ቀጣይ በኢንቨስትመንት የኃብት ፍሰት ምን አንደሚመስል ገምግሟል። ግምገማው የመካከለኛ ጊዜ የምጣኔ ኃብታዊ ዕድገት ትንበያዎችን፣ የምጣኔ ኃብት መጠንን፣ የምጣኔ ኃብታዊ መዋቅርን እና የሥነ-ሕዝብ አወቃቀርን ያካተተ መሆኑም ተመላክቷል። የምጣኔ ኃብታዊ ዕድገቱ ጠንካራ በሆነበት የኢንቨስትመንት እድሎች የሚለካ በመሆኑ የምጣኔ ኃብት ዕድገት ምልከታው በግምገማው ላቅ ያለ ክብደት እንደተሰጠውም ተገልጿል። እነዚህን መስፈርቶች በአብዛኛው አሟልተዋል የተባሉ አሥር የአፍሪካ አገራት መመረጥ ችለዋል። በዚህም ኢትዮጵያን ጨምሮ ሞሮኮ፣ ግብጽ፣ ታንዛንያ፣ ኬንያ፣ ኮቲዲቯር፣ ሴኔጋል፣ ናይጄሪያ፣ ዩጋንዳ እና ኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፓብሊክ በምርጥነት በዝርዝሩ ተካተዋል። ኦክስፎርድ የአፍሪካ ምጣኔ ኃብት መሰረቱን በኦክፎርድ ዩኒቨርስቲ ያደረገ ገለልተኛ የሆነ የምጣኔ ኃብት አማካሪ ድርጅት ነው።
የአማርኛ ቋንቋ በሞስኮ ከተማ ትምህርት ቤቶች መሰጠት ተጀመረ
Sep 20, 2023 269
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 09/2016 (ኢዜአ)፦ የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት በሩሲያ ሞስኮ ትምህርት ቤቶች መሰጠት ተጀምሯል። የሩሲያው ዜና አግልግሎት ስፑቲኒክ እንደዘገበው አማርኛን ጨምሮ የአፍሪካ ቋንቋዎችን በሩሲያ ትምህርት ቤቶች መሰጠት ተጀምሯል። የቋንቋዎቹ ትምህርት መጀመር በሩሲያ እና በአፍሪካ ሀገራት መካከል የሚኖረውን ኢኮኖሚያዊ፣ ዲፕሎማሲያዊና ባሕላዊ መስኮች የነበሩ ትስስሮችን ይበለጥ ለማሳድግ ሚናው የጎላ መሆኑን የትምህርት ቤቶች ርዕሰ መምህራን ተናግረዋል። አማርኛ ቋንቋን በሁለተኛ ቋንቋነት መማር የጀመሩ ተማሪዎች ለስፑቲኒክ እንደተናገሩት፣ የአማርኛ ቋንቋ ከማወቅ ባሻገር ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የህዝቡን ባህልና አኗኗር የማወቅ ጉጉት አሳድሮባቸዋል። ሩሲያ በሞስኮ ትምህርት ቤቶች ከመስከረም ጀምሮ አማርኛ ቋንቋ ማስተማር እንደምትጀምር ባለፈው ዓመት ማስታወቋ ይታወሳል።
የቡድን 20 የመሪዎች ጉባዔ የአፍሪካ ኅብረትን አባል በማድረግ ተጠናቀቀ
Sep 10, 2023 417
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 5/2015(ኢዜአ)፦በሕንድ አስተናጋጅነት ኒውዴልሂ ከተማ ውስጥ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የቡድን 20 አባል አገራት የመሪዎች ጉባዔ የአፍሪካ ኅብረትን 21ኛ አባል በማድረግ ዛሬ ተጠናቋል። በጉባዔው ማጠናቀቂያ ላይ የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ለብራዚሉ ፕሬዝዳንት ሉዊዝ ኢናሲዮ ዳ ሲልቫ የቡድን 20 ፕሬዝዳንትነት ቀጣይ መንበር አስረክበዋል። ሉላ ዳ ሲልቫ ማኅበራዊ አካታችነትን፣ ረሃብን መዋጋት፣ የኃይል ሽግግርን እና ዘላቂ ልማትን የቡድን 20 አገራት ቅድሚያ ትኩረት የሚሰጧቸው እንደሆነም ከወዲሁ ይፋ አድርገዋል። ጉባዔው 55 አባል አገራት ያቀፈውን የአፍሪካ ኅብረትን ታሪካዊ በተባለ ውሳኔ የቡድን 20 አባል አድርጎ ተቀብሏል። የአፍሪካ ኅብረት የቡድን 20 ሃያ አንደኛ አባል ሆኖ መቀላቀሉ የቡድኑን አካታችነት መርህ እንደሚያጎላው የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ተናግረዋል። ሕንድ ባስተናገደችው የቡድን 20 የመሪዎች ጉባዔ ላይ በተከፋፈሉ የዓለም ኃያላን መንግሥታት መካከል ስምምነትን መፍጠር ችላለች ተብሏል። ይህ ደግሞ ለአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ላቅ ያለ ዲፕሎማሲያዊ ስኬት እንደሆነም ተገልጿል። ጉባዔው የኒውዴልሂ የጋራ መግለጫ ሰነድ ይፋ በማድረግ ሲጠናቀቅ ሁሉም የቡድን 20 አባላት አገራት በዓለም ዙሪያ ሰላም፣ ደህንነት እና ግጭት በማስወገድ አንድ ሆነው ለመስራት ተስማምተዋል። ሰነዱ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት በአገር አቀፍ ደረጃ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ገቢራዊ ለማድረግ እኤአ እስከ 2030 ድረስ ከ5 ነጥብ 8 እስከ 5 ነጥብ 9 ትሪሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልጋቸው አመልክቷል። እንዲሁም እስከ 2030 ድረስ ለታዳሽ ኃይል ቴክኖሎጂዎች 4 ትሪሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልጋቸውና ይህም እኤአ በ2050 የካርባን ልቀትን ዜሮ ለማድረስ እንደሚረዳቸው ግልጽ አድርጓል። በተጨማሪም አባል አገራት የኃይል እርምጃን ከመውሰድ እንዲቆጠቡ መግባባት ላይ ተደርሷል ነው የተባለው።
በቴል አቪቭ የሚኖሩ ኤርትራዊያን ከፖሊስ ጋር በፈጠሩት ግጭት 160 ሰዎች መቁሰላቸው ተገለጸ
Sep 2, 2023 573
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 27/2015 (ኢዜአ) ፦ በእስራኤል ቴል አቪቭ የሚኖሩ ጥገኝነት ጠያቂ ኤርትራዊያን ከፖሊስ ጋር በፈጠሩት ግጭት ፖሊሶችን ጨምሮ 160 ሰዎች መቁሰላቸው ተገለጸ። እንደ እየሩሳሌም ፖስት ዘገባ የኤርትራ ኤምባሲ በቴል አቪቭ ያቀረበውን የባህል ዝግጅት ኤርትራዊያኑ ስደተኞች በመቃወማቸው ምክንያት በተነሳ ብጥብጥ ብዙዎቹ ጉዳት ደርሶባቸዋል። በተቃውሞው ላይ በነበራቸው ተሳትፎ ከቆሰሉት ጥገኝነት ጠያቂ ኤርትራዊያን መካከል ስምንቱ ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ናቸው። እየሩሳሌም ፖስት የሆስፒታልና የፖሊስ ምንጮችን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ከቆሰሉት መካከል 13ቱ መጠነኛ እንዲሁም 93 የሚሆኑት ደግሞ ቀላል ጉዳት ያጋጠማቸው ናቸው። ዛሬ ከቀትር በኋላ በቴል አቪቭ የኤርትራ ኤምባሲ ባሰናዳው ዝግጅት ላይ በተነሳው የተቃውሞ ብጥብጥ 50 የሚሆኑ ፖሊሶች መቁሰላቸውን ጨምሮ በንብረት ላይም ጉዳት መድረሱ ተዘግቧል። ኤርትራዊያኑ ስደተኞች የሃገራቸውን መንግስት በመቃወም በተነሳው ብጥብጥ የሱቆችን መስኮቶች፣ የፖሊስ ተሽርካሪዎችን የሰባበሩ ሲሆን ፖሊስም ሁኔታውን ለመቆጣጠር አስለቃሽ ጭስና ሌሎችንም አማራጮች መጠቀሙ ተዘግቧል።
ሐተታዎች
የብርቅዬዎችን አምባ በዩኔስኮ መዝገብ ላይ እናቆይ!
Sep 30, 2023 97
በመሐመድ ረሻድ ባሌ ሮቤ(ኢዜአ) ኢትዮጵያ የብዙ ሕብረ ብሔራዊ ባህልና ማንነት ያሏቸው ሕዝቦች ሀገር ነች። የተፈጥሮ ገፅታዋ በልዩነት ውስጥ አንድነትን፣ በብዝሃነት ውስጥ ህብረትን አጎናጽፏታል። ከህዝቦቿ ጥምር ውበት ባለፈ ተፈጥሮ ያደላት የበርካታ ጸጋዎች ባለቤትም ናት። መስራት የሚገባውን ያክል ሳይሰራበት ቢቆይም አሁን ላይ እነዚህን ተፈጥሯዊ ሃብቶች የቱሪዝም ኢንዱስትሪውን ለማሳደግና የዘርፉን ተጠቃሚነትም ለማሳደግ እየተሰራባቸው ይገኛል። በዚህ ረገድ ሥሙ በቀዳሚነት ጎልቶ የሚነሳው ባለብዙ የተፈጥሮ ውበት ባለቤት የሆነውና "አንድ ፓርክ ብዙ ዓለማት (One Park Many World)" ተብሎ የሚታወቀው የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ አንዱና ዋነኛው ማሳያ ነው። በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ባሌ ዞን የሚገኘው ይህ ብሔራዊ ፓርክ ከአዲስ አበባ በ411 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል። በድንቅ የተፈጥሮ ጸጋ የታደለው ይህ ስፍራ እንኳን ደህና መጣችሁ የሚያሰኝ ሃሴትን የሚሞላ ግርማ ሞገስን የተላበሰ ነው። ፓርኩ በሀገራችን ከሚገኙ 27 ብሄራዊ ፓርኮችና ሌሎች ጥብቅ ደን ስፍራዎች አንዱ ነው። በውስጡ በርካታ የብዝሃ-ህይወት ሃብትን የያዘና የጎብኚዎችን ቀልብ የሚስብ ነው። የደጋ አጋዘን፣ቀይ ቀበሮ፣ትልቁ ፍልፈል፣ የሳነቴ አምባ፣ የሀረና ጥቅጥቅ ደን ፓርኩ ከሚታወቅባቸው ብርቅዬዎች መካከል በዋነኞቹ ናቸው። የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በ2 ሺህ 150 ካሬ ኪሎ ሜትር ስፋት ላይ ተከልሎ የተመሰረተው በ1962 ዓ.ም ሲሆን በውስጡ ከ1 ሺህ 600 በላይ የተለያዩ የእጽዋት ዝርያዎች፣ ከ78 ዓይነት በላይ አጥቢ የዱር እንስሳት እና 300 የሚደርስ ዝርያ ያላቸው አዕዋፍን ይዟል። ከነዚህ መካከል 32 የእጽዋት ዝርያዎች እና በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙ 31 ብርቅዬ የዱር እንስሳት እንደሚገኙበትም ከብሔራዊ ፓርኩ ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያስረዳል፡፡ ጥቂት ስለ ብሔራዊ ፓርኩ ጸጋዎች፦ ⦁ የሰማይ ላይ ደሴት(The Island in the Sky) - የሳነቴ አምባ የሳነቴ አምባ የተፈጥሮ ድንቅ ስራ የሚታይበት የፓርኩ ልዩ ገፅታ የሚንፀባረቅበት ነው። ስፍራው በአፍሪካ ካሉት ፕላቶዎች በስፋቱ 17 በመቶ የሚሸፍን ሜዳማና ትልቁ የአፍሮ አልፓይን አምባ ወይም የሰማይ ላይ ደሴት(The Island in the Sky) ነው፡፡ ይህ ውርጫማ ስፍራ የከፍተኛ ተራራዎች መገኛ ሲሆን፤ በሀገራችን በከፍታው ሁለተኛ የሆነውና ከባህር ጠለል በላይ 4ሺህ 377 ሜትር ከፍታ ያለው የቱሉ ዲምቱ ተራራ መገኛም ነው፡፡ የሳነቴ አምባ ከመልክዓ ምድሩ አቀማመጥ ባሻገር የዝናብ ውኃን የመሰብሰብና የማጥራት አቅም ያለው ድንቅ መልክዓ ምድር ነው። በተለይ በአካባቢው የሚገኙ የባሌ ፍልፈሎች ከጠላቶቻቸው ለማምለጥ ሲሉ የሚሰሯቸው እልፍ ጉድጓዶች ውኃው ወደ ከርሰ ምድር እንዲሰርግ ከፍተኛውን ሚና ይወጣሉ። ይህም ከ40 የሚበልጡ ጅረቶች ከፓርኩ እንዲፈልቁ ምክንያት ሆኗል። ጅረቶቹ አቅማቸውን በማሰባሰብ እንደ ዋቤ ሸበሌ፣ ገናሌ፣ ዌልመልና ዱማል የመሳሰሉ ትላልቅ ወንዞችም መነሻ ቦታ ነው፡፡ ከዚህ የተነሳ ሳነቴ የ'ውኃ ጋን' የሚል ስያሜንም እንዲያገኝ ምክንያት ሆኗል። ከሳነቴ አምባ የሚፈልቁት እነዚህ ድንበር ተሻጋሪ ወንዞች በዞኑ የደሎ መናና ሀረና ወረዳ ለሚገኙ የአርብቶ አደር ማህበረሰብ የዘመናዊ መስኖ ልማት ምንጭ እየሆኑም መጥተዋል። በተለይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) የግንባታ ሥራውን ከሶስት ዓመት በፊት ያስጀመሩትና ተጠናቆ ለአገልግሎት ሲበቃ ከ11 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ የማልማት አቅም ያለው የዌልመል ዘመናዊ የመስኖ ልማት ፕሮጄክት አንዱ ማሳያ ነው። ኢትዮጵያን ጨምሮ በኬንያና ሶማሊያ የሚኖረው ከ30 ሚሊዮን በላይ ህዝብ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ህልውው ከዚህ አካባቢ በሚፈልቁ ተፋሰሶች ላይ የተመሰረተ መሆኑን በብሔራዊ ፓርኩ የዱር እንስሳት ክትትልና የምርምር ቡድን መሪ አቶ ሴና ገሼ ያስረዳሉ። ⦁ "የሀረና የተፈጥሮ ደን ሀብት" የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በሀገራችን በጥቅጥቅ ደን ሽፋኑ ከያዮ ደን ቀጥሎ የሁለተኛነትን ስፍራ የያዘው የሀረና የተፈጥሮ ደን ሀብት መገኛም ነው፡፡ ደኑ የፓርኩን 1ሺህ ካሬ ኪሎ ሜትር ገደማ ይሸፍናል፡፡ ከሀገራችን አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ለካርቦን ንግድ ታጭተው ህብረተሰቡ ከዘርፉ ተጠቃሚ እንዲሆን እያገዙ ከሚገኙ የሀገራችን ድንቅ ደኖች ውስጥም አንዱ ሆኗል። የሀረና የተፈጥሮ ደንን በአሳታፊ የደን ልማት አስተዳደር አርሶ አደሩን በ38 የደን ማህበራት በማደረጃት ባለፉት አራት ዓመታት በተከናወኑ ሥራዎች ከ179 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ከከርቦን ንግድ ሽያጭ መገኘቱን በኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት የባሌ ዞን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የዕቅድ ክትትል የሥራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ቀነዓ ያደታ ይገልጻሉ። የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በውስጡ ባሉት የእጽዋት እና የእንስሳት ብዝሃ ህይወት ሲታይ ከዓለም በ34ኛ፣ ከአፍሪካ ደግሞ በ12ኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በተለይ ፓርኩ በውስጡ ከሚገኘው እጽዋትና የእንስሳት ብዝሃ ህይወት በተጓዳኝ ለአዕዋፍ ዝርያ ካለው ምቹ ሁኔታ የተነሳ “Bird Site International” የተሰኘ ዓለም አቀፍ ድርጅት "በዓለም ከሚገኙ ምቹ የአዕዋፍ መገኛዎች አንዱ ስለመሆኑም አብነቱን ይሰጣል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ከላይ የተጠቀሱ እውናታዎችን ጨምሮ ሌሎች የፓርኩ እምቅ አቅሞችን ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት እ.ኤ.አ. በ2009 በጊዜያዊ መዝገቡ ላይ ማስፈሩም ይታወሳል። መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ በርካታ ባለድርሻ አካላት ባለፉት ዓመታት ቅርሱ በቋሚነት በዩኔስኮ እንዲመዘገብ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ መቆየታቸውን የፓርኩ ኃላፊ አቶ ሻሚል ከድር ያስታውሳሉ። በተለይ ፓርኩ በድርጅቱ በቋሚ የቅርስ መዝገብ ላይ እንዳይሰፍር ማነቆ ሆነው ከቆዩት መካከል ልቅ ግጦሽ፣ የሰደድ እሳት፣ ህገ ወጥ ሰፈራ ሲሆኑ፤ ችግሮቹ አሁንም ያልተሻገርናቸውና የሁሉንም ትኩረት የሚሹ ናቸው ይላሉ። በተለይ በፓርኩ አልፎ አልፎ የሚያጋጥመው ሰደድ እሳት የብርቅዬ የዱር እንስሳትን መኖሪያና ምግባቸውን ስለሚያሳጣቸው በቀጣይነት በትኩረት ሊሰራበት እንደሚገባም ያስረዳለሁ። ⦁ "ፓርኩን ለማቆየት የተከፈለ የህይወት መስዋዕትነት" ይህ የብርቅዬዎች አምባ ተጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ በተላይም የባሌ ህዝብ፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አያሌ መስዋዕትነት ከፍለዋል። በተለይ በ2007 ዓ.ም ፓርኩ ላይ ተነስቶ የነበረው የሰደድ እሳት በባሌ ህዝብ ዘንድ የማይረሳ ጠባሳ ጥሎ ማለፉን ነው አቶ ሻሚል ያስታወሱት። በግንዛቤ ማነስ ጭምር ግለሰቦች ለከብቶቻቸው የተሻለ መኖ ለማግኘት በማሰብና ለማር ቆረጣ በፓርኩ ክልል ውስጥ እሳት በመለኮስ ያስነሱትን ቃጠሎ ከሌሎች ጓደኞቹ ጋር ለማጥፋት ጥረት ሲያደርግ ህይወቱን ያጣውን የፓርኩን ሰራተኛና የአካባቢ ተቆርቋሪ ወጣት ቢኒያም አድማሱን በማሳያነት አቅርበዋል፡፡ ወጣቱ የተፈጥሮ ሀብት ጀግና በሚል በፓርኩ ውስጥ የማስታወሻ ሀውልት ቆሞለታል። እንዲሁም በተጠናቀቀው የ2015 ዓ.ም የበጀት ዓመት የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን ባካሄደው ዓመታዊ ግምገማ የተፈጥሮ ሀብት ጀግና ለሆነው ለቢኒያም አድማሱ ቤተሰቦች ዕውቅናና ሽልማት ሰጥቷል። እንዲያም ሆኖ ግን ጠባሳው በብዙ የአካባቢ ተቆርቋሪዎች ዘንድ ሁሌም የሚታወስ ነው፡፡ ይህ በብዝሃ ህይወት ስብጥሩና በአያሌ ጸጋዎች የተንበሸበሸው የብርቅዬዎች አምባ በቅርቡ በሳውዲ አረቢያ ሪያድ ተካሂዶ በነበረው 45ኛው የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የዓለም ቅርስ ጉባኤ ላይ በኢትዮጵያ ሁለተኛው ታላቅ የተፈጥሮ ቅርስና በዓለም ደግሞ 11ኛው ቅርስ በመሆን በቋሚነት መመዝገቡ ሁሉንም የአገሪቱን ዜጎች አስደስቷል። ፓርኩ በዓለም ቅርስነት መመዝገቡ ለቅርሱ የሚደረግለትን ጥበቃ ለማጠናከርና መስህብነቱን ለመጨመር እድል እንደሚፈጥር የዞኑ ባህልና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ሮብዳ ጃርሶ ይገልጻሉ። እንዲሁም ፓርኩ በዩኔስኮ እውቅና ማግኘቱ የቱሪስት ፍሰቱን በማሻሻል ከቱሪዝም የሚገኘውን ዓመታዊ ገቢ በማሳደግ ሀገርና ሕዝብ ከዘርፉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዕድል የሚፈጥር ነው ይላሉ። ቅርሱን በዩኔስኮ ማስመዝገብ ብቻውን ግብ አይደለም ያሉት ወይዘሮ ሮብዳ ህብረተሰቡ ተንከባክቦ ለዛሬ ያቆየውን ቅርስ በዘላቂነት መጠበቁ ላይ እንዲበረታም አሳስበዋል። በፓርኩ ላይ የሚደርሰውን ሰው ሰራሽ ጫና ሊቀነሱ የሚያስችሉ ፕሮጀክቶችን በመቅረፅ ገቢራዊ እያደረጉ ከሚገኙ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት መካከል የፍራንክፈርት ዞሎጂካል ሶሳይቲ ድርጅት የባሌ ዞን ቅርንጫፍ አስተባባሪ አቶ አብዱርቃድር ኢብራሂም የፓርኩ የጥበቃ ሥራ የአካባቢውን ማህበረሰብ ያሳተፈ መሆን እንዳለበት ይናገራሉ። በተለይ በፓርኩ አጎራባች የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በፓርኩ ላይ እያደረሱሷቸው ያሉ ጫናዎችን ለመቀነስ ህይወታቸውን የሚመሩበት ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ተጽዕኖውን መቀነስ እንደሚቻል ያምናሉ። ፓርኩን በዩኔስኮ ቋሚ መዝገብ ላይ ለማስፈር የተደረገው የተቀናጀ ጥረት እንዳለ ሆኖ ይሄው ገጽታውና ክብሩ ተጠብቆ እንዲቆይ ከፍተኛ ጥረትና ቁርጠኝነትን እንደሚጠይቅም በአጽኖኦት ያስረዳሉ። ከአካባቢው ነዋሪዎች መካከል ወይዘሮ ነፊሳ መሐመድ እንዳሉት ፓርኩን ለመጎብኘት ለሚመጡ የሀገር ውስጥና የውጭ አገር ጎብኝዎች የዕደ ጥበብ ቁሳቁሶችን በመሸጥ በሚያገኙት ገቢ ህይወታቸውን እየመሩ ናቸው። እንደሳቸው እምነት በአሁኑ ወቅት ፓርኩ በቋሚነት በዓለም ቅርስነት በመመዝገቡ ለቅርሱ የሚያደርጉትን ጥበቃ ይበልጥ እንዲያጠናክሩ መነሳሳትን የሚፈጥር ነው። የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ መምህርና በአካባቢ ሳይንስ ላይ ምርምር የሚያደርጉት አቶ አልይ መሐመድ እንዳሉት በፓርኩ አካባቢ የሚኖሩ የማህበረሰብ ክፍሎች ከፓርኩ በሚፈለገው ደረጃ ተጠቃሚ ቢሆኑ የጥበቃውን ሥራ በእጅጉ ያቃልላል የሚል እምነት አላቸው። ይህ ደግሞ የባለቤትነት ስሜትን በሚፈለገው ደረጃ እንዲያዳብሩ የሚያደርግም ነው። በመሆኑም በፓርኩ ላይ እየደረሰ የሚገኘውን ጫና ለመቀነስ የአካባቢውን ማህበረሰብ ከብሔራዊ ፓርኩ በኢኮ-ቱሪዝምና ተያያዥ ጉዳዮች ተጠቃሚ በማድረግ የባለቤትነት አስተሳሰብን ማጎልበት እንደሚያስፈልግም ያስረዳሉ። በተለይ ለማህበረሰቡ አማራጭ የግጦሽና የሰፈራ ቦታ፣ የማገዶ፣ የኃይል አቅርቦትና ሌሎች አማራጮች በቀጣይ እንዲቀርቡለት የማድረግ ስራ ቢሰራ በፓርኩ ላይ የሚደርሰውን ጫና ትርጉም ባለው መልኩ መቀነስ እንደሚቻልም ይመክራሉ። ከሀገር አልፎ የዓለም ቅርስ የሆነውን የብርቅዬዎች አምባ የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በዩኔስኮ ቋሚ መዝገብ ውስጥ ለማቆየት የሚያግዙ ሥራዎችን ከወዲሁ አቅደው እየሰሩ መሆኑን የፓርኩ ኃላፊ አቶ ሻሚል ያስረዳሉ። ብሔራዊ ፓርኩን በሚያዋስኑ ወረዳዎች የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ስለብዝሃ ህይወት ጥቅምና ተጓዳኝ ጉዳዮች በቂ ግንዛቤ አግኝተው በጥበቃው የድርሻቸውን እንዲወጡ ተከታታይነት ያለው የግንዛቤ ማዳበሪያ ሥራዎች እየተከወኑ መሆናቸውንም ገልጸዋል። የዓለም ቅርስ የሆነው የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ብዝሃ ህይወትን በዘላቂነት መንከባከብና መጠበቅ የሚያስችሉ ሀገር በቀልና ዘመናዊ አሰራሮችን ተግባራዊ በማድረግ ፓርኩን በድርጅቱ ቋሚ መዝገብ ውስጥ ከማቆየት ባለፈ ከዘርፉ የሚገኘውን ዘላቂ ጥቅም ለማረጋገጥ ሁሉም የድርሻውን በቁርጠኝነትና በፅናት ሊወጣ ይገባል።
አንጮቴ፣ ጩምቦና መስቀል በምዕራብ ኦሮሚያ
Sep 27, 2023 181
አንጮቴ፣ ጩምቦና መስቀል በምዕራብ ኦሮሚያ በአቤኔዘር ፈለቀ (ከነቀምቴ ኢዜአ) ወርሃ መስከረም ምድር በአደይ አበባ ፈክታ የምትደምቅበት፣ የአዕዋፍት ዝማሬ በተለየ ቅላጼ የሚደመጥበት፣ አርሶ አደሩ የልፋቱን ዋጋ ከደጅ-ከማሳው የበቆሎ፣የአተር፣ የባቄላ ወዘተ እሸት የሚቋደስበት፤ በክረምቱ ዝናብ ከአፍ እስከ ገደባቸው ሞልተው 'ከእኔ ወዲያ ላሳር' በሚል የሰዎችን እንቅስቃሴ ገድበው የቆዩ ድፍርስ ወንዞች ጎለውና ጠርተው ሰው ከወዳጅ ዘመዱ የሚገናኝበት "መስከረም ሲጠባ አደይ ሲፈነዳ እንኳን ሰው ዘመዱን ይጠይቃል ባዳ" ተብሎ የተቀነቀነለት የኢትዮጵያዋን የአዲስ ዓመት ብስራት የሚበሰርበት ነው። በመስከረም ወር ከሚከበሩ ሃይማኖታዊና ባህላዊ በዓላት አንዱ የደመራና የመስቀል በዓል ነው። መስቀል በተለይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት የሚከበር አውዳመት ነው። በተለይ የመስቀል ዋዜማ የሆነው የደመራ በዓል የእምነቱ ተከታዮች ችቦ ለኩሰው በደመቀ ሥነሥርዓት የሚያከብሩት ሲሆን፤ ከትውልድ ቀያቸው ርቀው የሚገኙና ኑሯቸውን ከኢትዮጵያ ውጭ ያደረጉ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሚሰባባሰቡበት፣ የተለያዩ አገሮች ቱሪስቶች የሚታደሙበት ነው። በዓሉ የእምነቱ ተከታዮች በየአካባቢያቸው የእምነቱ ተከታይ ካልሆኑ ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ጋር ተሰባስበው በአንድነትና በአብሮነት ለአውዳመቱ የተዘጋጀውን እና ቤት ያፈራውን ባህላዊ ምግቦችን በጋራ የሚቋደሱበት መጠጦች እየተጎነጩ በድምቅት የሚያከብሩት ነው። ለደመራና ለመስቀል እንደ የአካባቢው ወግና ሥርዓት የተለያዩ ባህላዊ ምግቦች ይዘጋጃሉ፤ ለአብነትም በጉራጌ ሕዝብ ዘንድ መስቀልና ክትፎ ያላቸውን ባህላዊ ትስስር ማንሳት ይቻላል። በምዕራብ ኦሮሚያ በወለጋና አካባቢው አንጮቴና ጩምቦ ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ለመስቀል በተለያየ መልክ ተሰናድተው ለምግብነት የሚቀርቡ ባህላዊ ምግቦች ናቸው። አንጮቴ እንደ ድንችና ሌሎች የሥራስር አትክልት ከመሬት ውስጥ ተቆፍሮ ወጥቶ በተለያዩ ዓይነት ተዘጋጅቶ በአዘቦቱ ቀን ለክብር እንግዳ፤ እንደመስቀል ላሉ ክብረ-በዓላት ደግሞ ከቤተሰብ፣ ዘመድ ወዳጅ በአብሮነት የሚቋደሰው ባህላዊ ምግብ ነው። በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ ጩምቦ ወይም 'ጮሮርሳ' በሚል ስያሜ የሚታወቀው ባህላዊ ምግብ ደግሞ ከአፍለኛ የቀይ ጤፍ በልዩ የአዘገጃጀት ሥርዓት ተዘጋጅቶ በተነጠረና ለሰውነት ተስማሚ በሆነ ለጋ ቅቤ የሚዘጋጅ ሲሆን በአዘቦቱ ቀን ለክብር እንግዳ፤ እንደ መስቀል ላሉ ክብረ-በዓላት ደግሞ ማህበረሰቡ ተጠራርቶ በአብሮነት የሚቋደሰው ነው። ወይዘሮ አጌ መንግሥቱ በነቀምቴ ከተማ አስተዳደር የኦሮሞን ባህላዊ ምግቦች አሰናድተው ለተጠቃሚው ህብረተሰብ በአካባቢው ባህል፣ ወግና ሥርዓት መሰረት የሚያቀርቡ የ'ኬኛ የኦሮሞ ባህላዊ ምግብ ማዕከል' ባለቤት ናቸው። እሳቸው እንዳሉት ለመስቀል በዓል ከሚቀርቡ ባህላዊ ምግቦች አንጮቴ አንዱና ዋነኛው ነው። አንጮቴና መስቀል የማይነጣጠሉ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው ብለዋል። እንደ ወይዘሮ አጌ ገለጻ አንጮቴን የተለየ የሚያደርገው ምርቱ በወርሃ መስከረም የሚደርስ በመሆኑ ማህበረሰቡ በመስቀል በዓል በጋራ ከሚቋደሰው እሸት አንዱ ስለሆነ ከደመራና መስቀል ክብረ-በዓላት ጋር የቆየ ባህላዊና ተለምዷዊ ትስስር ያለውና እንደ መስቀል በዓል ሁሉ ክብር የሚሰጠው ባህላዊ ምግብ መሆኑ ነው። አንጮቴ የአካል ጉዳት የደረሰበት ሰው የተጎዳው "ሰውነቱ ቶሎ እንዲጠገን ያደርጋል" ተብሎ ስለሚታመን ለፈውስነት እንዲሁም ለአራሶች ለወገብ መጠገኛነት፣ ገና ምግብ ለሚጀምሩ ጨቅላ ህፃናት ከምጥን እህል ጋር ተሰናድቶ ለዕድገትና ለአጥንት ጥንካሬ በገንቢነቱ ስለሚረዳና በተለየ ሁኔታ ለምግብነት ስለሚውል ከህብረተሰቡ ጋር ለዘመናት የዘለቀ ትስስር ያለው ባህላዊ ምግብ ነው። የመስቀል በዓልን በጥጋብ ማሳለፍ ዓመቱ በሙሉ የጥጋብ ዘመን ይሆናል ተብሎ ስለሚታመን በመስቀል በዓል ጠግቦ መብላት በማህበረሰቡ ዘንድ የተለመደ መሆኑን አንስተው፤ያለው ለሌለው በማካፈልም በመጠራራት ጭምር ጩምቦና አንጮቴን የመሳሰሉ ባህላዊ ምግቦችን በጋር በመቋደስ የደመራና መስቀል በዓልን በአብሮነት ያከብራል ይላሉ። የነቀምቴ ከተማ ነዋሪዎች ወይዘሮ ባጩ ተስፋዬ፣ አንጮቴ ተወዳጅ እና ተዘውታሪ የባህል ምግብ መሆኑና አዘውትረው እንደሚመገቡት ይገልጻሉ። የአንጮቴ ምርት ሳይበላሽ ለሁለት ለሶስት ዓመታት መሬት ውስጥ የመቆየት ባህርይ እንዳለውም ያስረዳሉ። መሬት ውስጥ ከሁለት ዓመት በላይ የቆየ አንጮቴም "ጉቦ" በመባል የሚታወቅ ሲሆን፤ ይህ ምርት በማህበረሰቡ ይበልጥ ተፈላጊ ነው ይላሉ። ወይዘሮ ባጩ አያይዘውም አርሶ አደሩም ሆነ ባለሃብቶች አንጮቴን በስፋት አልምተው ምርቱ በሁሉም ማህበረሰብ ዘንድ እንዲለመድ የማስተዋወቅ ስራ ቢሰራበት አንጮቴ ገበያ ተኮር ከሆኑ ምርቶች አንዱና ዋነኛው ሊሆን እንደሚችል ያላቸውን እምነት ይገልጻሉ። ሌላዋ የከተማዋ ነዋሪ ወይዘሮ አሼቴ ግርማ ተወልደው ያደጉት ገጠር ሲሆን፤ አንጮቴን ከመዝራት ጀምሮ በአሰራሩም ያደጉበት ስለሆነ የተለየ ፍቅር እንዳላቸው ያስረዳሉ። አንጮቴን ከገብስና ከአጃ እህል ጋር ደባልቆ በማስፈጨት ከወተት ጋር አፍልተው ልጆቻቸውን እያጠጡ ማሳደጋቸውንም እንዲሁ። የልጆቻቸው በሽታ መከላከል አቅምና ጥንካሬም ከፍተኛ እንደነበረም ያስታውሳሉ። የምስራቅ ወለጋ ዞን ባህልና ቱሪዝም ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አንዳርጌ ገለታ በአካባቢያቸው አንጮቴ፣ ጩምቦና ከደመራና መስቀል በዓል ጋር ጠንካራ ትስስር ያላቸው መሆኑን ያስረዳሉ። በአካባቢው በበዓላት ወቅት የተለያዩ ባህላዊ ምግቦች የሚዘወተሩ ቢሆንም፤ በመስቀል በዓል ግን እንደ አንጮቴና ጩምቦን በማህበረሰቡ ዘንድ ጥቅም ላይ የሚውል ባህላዊ ምግብ የለም ይላሉ። አቶ አንዳርጌ እንዳሉት ጽህፈት ቤቱ እነዚህን ባህላዊ ምግቦች ለማስተዋወቅና ለቀጣይ ትውልድ ለማሻገር ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ ተቋማትና አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ ነው። የመስቀል በዓልን ምክንያት በማድረግ በአካባቢው በሚከናወኑ ሕዝባዊ ኹነቶች አንጮቴ ዋና ምግብ ሆኖ እንዲቀርብ ዝግጅት ተደርጓል። አንጮቴ ድርቅና በሽታን ተቋቁሞ ጥሩ ምርት የሚሰጥና ሳይበላሽ ለረጅም ጊዜ መቆየት የሚችል የምግብ ዓይነት በመሆኑ፤ ይህን ምርት የማላመድና የማስተዋወቁ ስራ ትኩረት እንዲያገኝ በማድረጉ በኩል የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
የአባቱን የጀግንነት ፈለግ የተከተለው ዳግም ኤቢሳ
Sep 19, 2023 269
በኢትዮጵያ የሺህ ዘመናት ታሪክ ለሀገር ክብር፣ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነትን ጠብቆ ለማቆየት የተዋደቁ፣ ጀግንነትን የተዋረሱ እና መስዋዕትነት የከፈሉ ቤተሰቦች ማግኘት የተለመደ ነው። በየዘመኑ ለአገር ሉዓላዊነት፣ ለህዝብ ሰላምና ደህንነት ዘብ የቆሙ ወታደሮች ጀግንነታችውን ለልጆቻቸው አውርሰዋል፤ ልጆችም የአባትና አያቶቻቸውን ፈለግ በመከተል የራሳቸውን የጀግንነት አሻራ ያሳርፋሉ። ለእናት አገር ዘብ መቆምን በትውልድ ቅብብሎሽ ካስቀጠሉ ቤተሰቦች መካከል የወይዘሮ እሙዬ ፈለቀ ባለቤት ኮሎኔል ኤቢሳ ታይሳ እና ልጃቸው ዳግም ኤቢሳ ይገኙበታል። "እኛ የመከላከያ ሰራዊት ቤተሰብ ነን" የሚሉት ወይዘሮ እሙዬ ፈለቀ፣ ባለቤታቸው ኮሎኔል ኤቢሳ በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ አገልግሎ ለሀገሩ ክብር በጀግንነት መሰዋቱን ያነሳሉ። የጀግና አባቱን ገድል እየሰማ ያደገውና የሀገር ፍቅርን የወረሰው ልጃቸው ዳግም ኤቢሳ ደግሞ በጦላይ ከፍተኛ ባለሌላ ማዕረግተኛ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት በመሰረታዊ ወታደርነት ተመርቋል። ከአዲስ አበባ ተነስተው ወደ ጦላይ በመሄድ በልጃቸው ምርቃት ላይ ያገኘናቸው ወይዘሮ እሙዬ ፈለቀ፣ "ልጄ የአባቱን የኮሎኔል ኤቢሳ ታይሳ ጀግንነትና የሀገር ፍቅር ለመከተል ከፍተኛ ስሜት ነበረው" ይላሉ። "የጀግና ልጅ ጀግና ነውና ልጄም ሰራዊትን በመቀላቀል ጀግንነቱን በተግባር አረጋግጧል" ሲሉም ይናገራሉ። ባለቤታቸው እና ልጃቸው ለሀገር ክብር ዘብ በመሆናቸውም የላቀ ክብርና ኩራት እንደሚሰማቸው የሚያነሱት ወይዘሮ እሙዬ፤ ልጃቸውን "እንደ አባትህ ጀግና ሁን" እያሉ ጀግንነትን እንዲላበስ ማድረጋቸውንም ይገልጻሉ። "ልጄ የአባቱን ወታደራዊ የደንብ ልብስ ለብሶ በማየቴ ከፍተኛ ኩራት ተሰምቶኛል" ያሉት እናት፣ ሀገርን በቅንነትና ታማኝነት በማገልገል የአባቱን የጀግንነት ታሪክ እንዲያስቀጥል መምከራቸውንም አንስተዋል። ባለቤታቸው ለከፈለው መስዋዕትነትም የሀገር መከላከያ ሰራዊት ለቤተሰቡ ተገቢውን ድጋፍ እያደረገላቸው መሆኑን ጠቅሰዋል። መሰረታዊ ወታደር ዳግም ኤቢሳ በበኩሉ በማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ ወታደራዊ ትምህርትና ስልጠና ወስዶ ከጓዶቹ ጋር በመመረቁ ተደስቷል። "የእናት ሀገሬን ሉዓላዊነት አንድነት በመጠበቅ የአባቴን አሻራ ለማስቀጠል ዝግጁ ነኝ" ብሏል። ወታደራዊ ግዳጅን በብቃት መወጣት የሚያስችል ትምህርትና ስልጠና መውሰዱን የሚናገረው ዳግም ኤቢሳ፣ እንደ አባቱ እስከ ሕይወት መስዋዕትነት ከፍሎ ሀገሩን ለማገልገል ያለውን ወኔና ቁርጠኝነትም ገልጿል።
ችግር ፈቺ ፈጠራ
Sep 9, 2023 409
ባስልኤል የእንጨትና ብረታ ብረት ማህበር በጅንካ ከተማ በክላስተር ማዕከል ውስጥ ከተደራጁ 8 ማህበራት አንዱ ነው ። የማህበሩ ሰብሳቢ አቶ ጌታቸው ሙሐመድ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ማህበሩ ከኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ባገኘው 450 ሺህ ብር የብድር ድጋፍ በ2007 ዓ.ም ወደ ስራ መግባቱን አስታውሰዋል። ከብድር አቅርቦቱ በተጨማሪ በመንግስት የማሽነሪ እና የማምረቻ ሼድ ድጋፍ እንደተደረገላቸውም ተናግረዋል። ማህበሩ ከሚያመርታቸው የእንጨትና ብረታ ብረት ውጤቶች በተጨማሪ ከውጪ በከፍተኛ የዶላር ምንዛሪ የሚገቡ የተለያዩ ማሽነሪዎችን ያመርታል። ማህበሩ ካመረታቸው አዳዲስ የፈጠራ ሥራዎች አንዱ የጥልቅ ጉድጓድ መቆፈሪያ ማሽን ይጠቀሳል። ቀደም ሲል ማሽኑን ለመግዛት እስከ 2 ሚሊዮን ብር ይፈጅ እንደነበር የገለፁት የማህበሩ ሰብሳቢ ፤ ይህንኑ ማሽን በተሻለ ጥራት ማምረት በመቻላችን ለማሽኑ የሚወጣውን ከፍተኛ ወጪ ማዳን ችለናል ብለዋል። የጉድጓድ መቆፈሪያ ማሽኑንም በጅንካ ከተማ ለሚገኙ ለተለያዩ ተቋማት በተመጣጣኝ ዋጋ የጥልቅ ጉድጓድ በመቆፈር የንፁህ መጠጥ ውሃ ችግራቸውን መቅረፉንም ነው አቶ ጌታቸው የሚናገሩት። በተጨማሪ ኃይል ቆጣቢ የእህል ወፍጮ፣ ኃይል ቆጣቢ ምድጃ፣ በሰአት እስከ 10 ኪሎ ግራም ቡና የሚቆላ ማሽን፣የገብስ መፈተጊያና የአተር መቁያ ማሽን በአገልግሎት ላይ ከሚገኙ የማህበሩ የፈጠራ ውጤቶች ይጠቀሳሉ። ከተጠቀሱት ምርቶች ባለፈም ማህበሩ በሚሰራቸው የብረት ማቅለጫና ቅርፅ ማውጫ ማሽኖች የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎችንም ያመርታል። የማህበሩ የረጅም አመታት ደንበኛ እንደሆኑ የሚገልጹት የጅንካ ከተማ ነዋሪ አቶ አወቀ አይኬ፤ ''ማህበሩ የሚሰራቸው አዳዲስ የፈጠራ ቴክኖሎጂዎች የማህበረሰቡን ችግር በእጅጉ እያቃለሉ ናቸው'' ብለዋል። ከዚህ ቀደም የተሽከርካሪ የመለዋወጫ ዕቃዎችን ለማግኘት 730 ኪሎ ሜትር በመጓዝ ወደ አዲስ አበባ እንደሚሄዱ አስታውሰው አሁን ማህበሩ የምንፈልገውን ብሎንም ሆነ ሌሎች የመለዋወጫ ዕቃዎችን በፈለግነው ዲዛይን እዚሁ አምርቶ በማቅረቡ ወደ አዲስ አበባ በመሄድ የምናባክነውን ጊዜና ገንዘብ እንድንቆጥብ አስችሎናል ብለዋል። በተለይ የጥልቅ ውሃ ጉድጓድ መቆፈሪያ ማሽኑ በከተማዋ የሚስተዋለውን የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር ከማቃለል አኳያ ትልቅ ሚና እየተወጣ እንዳለም ተናግረዋል። ወይዘሮ ትዕግስት አባይነህ የተባሉ የጅንካ ከተማ ነዋሪ በበኩላቸው ማህበሩ የፈጠራቸው አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች በተለይ የሴቶችን ድካም በእጅጉ እንዳቃለለ ተናግረዋል። ቀደም ሲል ገብስ ለመፈተግ፣አተር ለመቁላት እና ሌሎች ቅመማ ቅመሞችን ለማዘጋጀት ብዙ ውጣ ውረዶች እንደነበር ገልፀው ይህም ከቢሮ የስራ ሰአት ውጪ ባለው ትርፍ ጊዜ ለማከናወን አስቸጋሪ እንደነበር ገልጸዋል ። በተለይ በቤት ውስጥ የበአልና ሌሎች ፕሮግራሞች ሲኖሩ እነኚህን ስራዎች መስራት አድካሚ እንደሆነ ገልፀው አሁን ማህበሩ በፈጠራቸው ዘመናዊ ማሽኖች አድካሚ ስራዎችን ግማሽ ሰአት ባልሞላ ጊዜ እንደሚያጠናቅቁ ተናግረዋል ። ማህበሩ የሰራቸው ወጪ ቆጣቢ ምድጃዎችም በቤት ውስጥ ምግብ ለማዘጋጀት አመቺና ጥራታቸውም ወደር እንደሌለው የገለፁት ወይዘሮ ትዕግስት እነዚህ ምርቶች በእጅጉ የማህበረሰቡን ችግር የሚቀርፉና ህይወትን ቀለል የሚያደደርጉ በመሆናቸው እንዲህ ያለ የፈጠራ ሀሳብ ያላቸው ግለሰቦች ሊበረታቱ እንደሚገባም ተናግረዋል ። የባስልኤል የእንጨትና ብረታ ብረት ስራ ማህበር ከማህበሩ አባላት በተጨማሪ ለ8 ሰራተኞች ቋሚ የስራ እድል ፈጥሯል፤ ቀደም ሲል በማህበሩ ይሰሩ የነበሩ አባላትም ከማህበሩ በቀሰሙት ዕውቀትና ልምድ የግል ድርጅት በመክፈት የራሳቸውን ገቢ እያመነጩ ለሌሎችም የሥራ ዕድልን ፈጥረዋል። በማህበሩ ተቀጥረው ከሚሰሩ ባለሙያዎች አንዱ አቶ ደረጀ ሙሐመድ ሲሆኑ በማህበሩ ውስጥ በመስራታቸው ተጠቀሚነታቸው የደሞዝ ብቻ እንዳልሆነና የዕውቀት ሽግግር ዕድልን ተጠቃሚ እንደሆኑ ያነሳሉ። ታዲያ የነዚህ የፈጠራ ሀሳቦች ባለቤት የሆነውና የማህበሩ መስራች አቶ ጌታቸው ሙሐመድ ይህን የፈጠራ ሀሳብ በማፍለቅ እውን የሚያደርገው እንደ ሙሉ ጤነኛ ሰው በእግሩ እንደ ልቡ እየተንቀሳቀሰ ሳይሆን በዊልቸር እየተገፋ ነው። አቶ ጌታቸው በ1990 ዓመተ ምህረት በድሬዳዋ ከተማ በስራ ላይ ባጋጠመው የኤሌክትሪክ አደጋ ከፎቅ ላይ በመውደቁ በእግሮቹ ላይ ጉዳት ሊደርስበት መቻሉን ተናግሯል። አደጋው ካጋጠመው ጊዜ አንስቶ በበርካታ ውጣ ውረዶች ውስጥ ማለፉን አስታውሶ ለፈተናዎች እጅ ባለመስጠቱ ለዚህ ስኬት መብቃቱን ይናገራል። ''ያጋጠመኝን የተሽከርካሪ ችግር ለመቅረፍ የወዳደቁ ሞተር ሳይክሎች በመጠገን ለራሴ እንድትመቸኝ አድርጌ የሰራኋት ተሽከርካሪ እዚህ ደረጃ ላይ እንድደርስ አድርጋኛለች'' ብለዋል። ማህበሩ አሁን ላይ ከቋሚ ንብረቶች በተጨማሪ ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ ሃብትእያንቀሳቀሰ እንደሚገኝ አቶ ጌታቸው ገልጿል። በቀጣይም እንደ አገር በተጀመረው የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በውድ ዋጋ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶችን በተሻለ ዲዛይን በማምረት የውጭ ምንዛሪውን ለማስቀረትና የማህበረሰቡንም ችግር ለማቃለል ማህበሩ በትጋት እንደሚሰራም ተናግረዋል። የአምራችነት ቀን '' ከሸማችነት ወደ አምራችነት'' በሚል መሪ ሃሳብ እየተከበረ በሚገኝበት በዛሬው ዕለት የመሰል ማህበራት ተሞክሮ የሚያስተምረው ነገር ብዙ ነው።
ትንታኔዎች
ከገበታ ወደ ገበያ
Sep 24, 2023 158
(ሰለሞን ተሰራ) ኢትዮጵያ ከ10 ሺ ዓመታት በፊት ከኒዮሊቲክ አብዮት ዘመን ጀምሮ የበርካታ አዝእርትና እንስሳት ሀብት መፍለቂያ ሆና ዛሬ ላይ ደርሳለች። ከዚያ ዘመን ጀምሮ የአገራችን ገበሬ በስራ ያካበተውንና በተፈጥሮ የተሰጠውን ችሎታ በመጠቀም ዘመናዊና ቴክኖሎጂ በወለዳቸው መሳሪያዎች ሳይታገዝ፣ በየጊዜው የአፈሩ ለምነት እየቀነሰ ከሄደው መሬትና ባህላዊ የአስተራረስ ዘዴ ጋር እየታገለ ቁጥሩ እየናረ የሚሄደውን ህብረተሰብ ከመመገብ ወደ ኋላ ብሎ አያውቅም። ግብርናው ከቀደሙት ጊዜያት በተለየ ሁኔታ ትኩረት ባገኘበት በዚህ ዘመንም ከተደቀኑበት እጅ ጠምዛዥ ጉዳዮች ጋር ግብግብ ውስጥ ነው። የአየር ንብረት ለውጥ፣ ድርቅ፣ የፖለቲካና የገበያ አለመረጋጋት፣ የዕውቀትና የቴክኖሎጂ ውስንነት፣ የተፈጥሮ አደጋ፣ የዘርፉ ኢንቨስትመንት አለመዳበር የዘርፉ ተግዳሮት ሆነው ቀጥለዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን በ78ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ባደረጉት ንግግር በተለይ የአየር ንብረት ለውጥን ተጽእኖ በሚገባ አመላክተዋል። የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ በተለይ በአፍሪካና በሌሎች በማደግ ላይ ያሉ አገራት ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ቀውስ ሁሉን አቀፍ መፍትሄ እንዲበጅ እየሰራች መሆኗን ተናግረዋል። በተለይ ኢትዮጵያዊያን ከጫፍ ጫፍ እየተሳተፉበት ያለው የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር የዚህ ቁርጠኝነት ማሳያ መሆኑን አንስተዋል። በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ ላለፉት ተከታታይ አራት ዓመታት በሰራችው ስራ በአካባቢ ጥበቃና በግብርናው ዘርፍም ውጤት ማግኘቷ እሙን ነው። ነገር ግን ፈተናዎቹን በድል ለመሻገር የሚደረጉ ጥረቶችና በዘርፉ የተገኙ አበረታች ውጤቶች እንደተጠበቁ ሆነው አሁንም ዘርፉን በሰለጠነ የሰው ሃይል፣ በተደራጀ የግብርና መሳሪያና ማቀነባበሪያ በመደገፍ አገርና ህዝብ ከግብርናው ዘርፍ ማግኘት ያለባቸውን ጥቅም እንዲያገኙ ለማስቻል ብዙ መስራት ይጠይቃል። በተለይ የግብርና ሜካናይዜሽንን ከማስፋፋትና ዘመናዊ የግብርና ግብዓቶችን በበቂ ሁኔታ ከማቅረብ አኳያ መንግስት እየሰጠ ያለው ትኩረት የበለጠ መጠናከርና ማደግ ይኖርበታል። የግብርናና የገጠር ልማት የፋይናንስና ብድር አቅርቦትን ማጠናከር እንዲሁም የአካባቢና ስነ ምህዳር ጥበቃ ስራዎችን በዘላቂነት መተግበር ያሻል። በተለይ ኢትዮጵያ በልዩ ትኩረት እየሰራችበት ያለውን የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ ጉዳይ ከዚህ ቀደም የነበረውን የግብርና አሰራር በመቀየርና አማራጮችን በማማተር እውን ማድረግ ይጠይቃል። ኢትዮጵያ በዝናብ ወይም በመስኖ መልማት የሚችል ያልተነካ ሰፊ መሬት እንዳላት የሚታወቅ ሲሆን ይህን ያልታረሰ መሬት በአግባቡ በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ አንዱ አማራጭ ነው። መረጃዎች እንደሚያሳዩት ግብርናው ከ34 በመቶ በላይ የጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት ድርሻ ይዟል፡፡ በተጨማሪም ዘርፉ 79 በመቶ የሚሆኑ ዜጎች መተዳደሪያ ሲሆን በተመሳሳይ 79 በመቶ የሚሆነውን የውጭ ንግድ ገቢ በመሸፈንና ለአገር ውስጥ ኢንቨስትመንትና ገበያ የጥሬ እቃ አቅራቢ በመሆንም ይታወቃል። መንግስት በግብርናው ዘርፍ የወሰዳቸው የሪፎርም ስራዎችና ግብርናን ከአረንጓዴ አሻራ ጋር በማስተሳሰር የሰራቸው ስራዎች ፍሬ ማፍራት ጀምረዋል። በተለይ የስንዴ ምርታማነትን በማሳደግ ከራስ ፍጆታ አልፎ ለውጭ ገበያ ለማቅረብ የተሰራው ስራ ቀዳሚ ተጠቃሽ ነው። ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት ብቻ የስንዴ ምርታማነቷን በ27 በመቶ ማሳደግ መቻሏ ስንዴ ከመሸመት ወደ መላክ የመሸጋገሯ ማረጋገጫ ሆኗል። በጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ አህመድ የተጀመረው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ በዚህ ረገድ የሚታይ ለውጥ እያሳየ ሲሆን በተሰራው ውጤታማ ስራ ባለፈው በጀት ዓመት ኢትዮጵያ ከውጭ ስንዴ አላስገባችም። በዚህም 1 ቢሊዮን ዶላር ማዳን መቻሏን የግብርና ሚኒስትሩ ዶክተር ግርማ አመንቴ በቅርቡ ማሳወቃቸው ይታወሳል። ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት 15 ነጥብ 4 ሚሊዮን ቶን ስንዴ ያመረተች ሲሆን በተያዘው ዓመት ደግሞ ምርቱን ወደ 19 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቶን ለማሳደግ እቅድ ተይዞ እየተሰራ ይገኛል። ይህንኑ ግብ ለማሳካት ደግሞ የስንዴ ማሳዋን በማሳደግ 5 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በስንዴ ሰብል ለመሸፈን እየሰራች ነው። ከዚህ ውስጥ በመስኖ የሚለማ ስንዴን በ2 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ላይ በመዝራት በመስኖ የሚለማውን ስንዴ በ54 በመቶ ለማሳደግ እየሰራች ነው። ይህ ደግሞ በቀጣይ ከሀገር ውስጥ ፍጆታ ባለፈ ምርቱን ለውጭ ገበያ ለማቅረብ እንደሚያስችል ዶክተር ግርማ አመንቴ ተናግረዋል። የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ያወጣው ሪፖርት እንደሚያመላክተው የግብርናው ዘርፍ በአስር ዓመቱ የልማት ዕቅድ የመጀመሪያዎቹ 3 ዓመታት (2013-2015) በዋና ዋና ተግባራት ከዕቅድ በላይ ዕድገት አስመዝግቧል። በዚህም ዘርፉ በ2013 ከነበረበት 5 ነጥብ 1 በመቶ በ2014 ወደ 5 ነጥብ 8 በመቶ ያደገ ሲሆን በ2015 ደግሞ 6 ነጥብ 3 በመቶ እድገት አስመዝግቧል። ግብርናውን ለማሳደግ ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዘው የሰብል ምርት ሲሆን ለዘርፉ ማደግ 65 ነጥብ 5 በመቶ አስተዋጽኦ አበርክቷል። ደን ልማት 8 ነጥብ 6 በመቶ እንዲሁም የእንሰሳት ሃብት ልማቱ 25 ነጥብ 9 በመቶ ድርሻ ይዘዋል። በ2015 ዓ.ም ጠቅላላ 627 ሚሊዮን ኩንታል ሰብል ለማምረት ታቅዶ ከተቀመጠው ግብ በላቀ ደረጃ 639 ሚሊየን ኩንታል ምርት ማግኘት ተችሏል። ከበጋ ስንዴ ልማት ጎን ለጎን በቅርብ ጊዜ የተጀመሩ የቡና፣ አቮካዶና አኩሪ አተር የመሳሳሉት ትላልቅ የግብርና ልማት ስራዎች በተመሳሳይ ውጤት ታይቶባቸዋል። የአዝርት፣ የአትክልት፣ ፍራፍሬና ስራስር ምርት ከፍተኛ የዕድገት ሽግግር የታየባቸው ናቸው። በአረንጓዴ አሻራ፣ በሌማት ትሩፋትና በከተማ ግብርና ተሞክሮ ሊወሰድበት የሚችል አፈጻጸም መመዝገቡ በሪፖርቱ ተመላክቷል። ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋትን የስንዴ ምርት ከውጭ ገበያ ስትገዛ የኖረች ሲሆን በተለይም በተለያዩ ጊዜያት የሚፈጠሩ ዓለም አቀፍ ተግዳሮቶች አቅርቦቱን ሲያስተጓጉሉት ቆይተዋል። አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ የስንዴና የገብስ ምርትን በሀገር ውስጥ ምርት መተካት የቻለች ሲሆን የሩዝ ፍላጎቷን ደግሞ 50 በመቶ መሸፈን ችላለች። በስንዴ ምርታማነት የተገኘውን ተሞክሮ ወደሌሎች ሰብሎች በማስፋት የገቢ ምርቶችን በቀጣይ ለመተካት በትኩረት እየተሰራበት ይገኛል። ይህንን ለማሳካት መንግሥት ለዘርፉ የሰጠው ትኩረት የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ እንደሚሆን ይታመናል። በተለይ ለግብርና ዘርፉ የተሻለ በጀት መመደቡ፣ እስካሁን ለመጣውና ለወደፊትም ይመጣሉ ተብለው ለሚታሰቡ ለውጦች ትልቅ ምክንያት ነው። ለምሳሌ የ2015 ዓ.ም. በአገሪቱ ለተለያዩ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ልማት ከተመደበው 786 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በጀት ውስጥ፣ ለግብርናው ዘርፍ 34 በመቶ የሚሆን በጀት ተመድቧል። ይህ ደግም ከለውጡ በፊት ከአሥር በመቶ ያልበለጠ በጀት ጋር ሲነፃፀር እጅግ ከፍተኛ ያደርገዋል። በተጨማሪም መንግሥት ለኩታ ገጠምና ለመስኖ እርሻ ከፍተኛ ትኩረት መስጠቱ፣ ሙሉ በሙሉ በዝናብ ላይ ጥገኛ የሆነውን የግብርና ስራ በመስኖ የታገዘ እንዲሆንና አርሶ/አርብቶ አደሩ በዓመት ከአንድ ጊዜ በላይ እንዲያመርት ማድረጉ ውጤቱን ጉልህ አድርጎታል። እንደ ስንዴ፣ በቆሎ፣ ሩዝ፣ ቡና፣ አቦካዶ ሁሉ በግብርና ሚኒስቴር ከተያዙና በልዩ ትኩረት ከሚከናወኑ ዕቅዶች አንዱ የማር ምርትን ማሳደግ ሲሆን፣ በአሥር ዓመቱ የልማት ዕቅድ ውስጥ እንደተመላከተውም የማር ምርትን በማዘመን ምርቱን ለማሳደግ በስፋት ይሰራል። በኢትዮጵያ ለማር ምርት ተስማሚ የሆነ አግሮ ኢኮሎጂና ብዛት ያላቸው ዕፅዋት መኖራቸው የሚመረተው ማር የተፈጥሮ ጥራት እንዲኖረው ያግዛል። ይህንኑ ዕምቅ ሀብት ትኩረት ሰጥቶ ማልማት ከተቻለ ከ500 ሺሕ ቶን በላይ ማርና ከ50 ሺሕ ቶን በላይ ሰም ማምረት እንደሚቻል ባለሙያዎች ያስረዳሉ። የኢትዮጵያ እንስሳት ሀብት ኢንስቲትዩት ባወጣው መረጃ በሀገሪቱ አለ ተብሎ ከሚገመተው ሰባት ሚሊዮን የንብ መንጋ ውስጥ 90 በመቶው በባህላዊ ቀፎ ውስጥ የሚገኝ ነው። የንብ መንጋዎቹ በባህላዊ ቀፎ ከመኖራቸው በተጨማሪ በጫካ መገኘታቸው ሃብቱ ለአገር ዕድገት በሚፈለገው ልክ እንዳይውል አድርጎታል። ያም ቢሆን ባለፈው ዓመት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የተጀመረው “የሌማት ትሩፋት” ለማር ምርት ትኩረት የሰጠ በመሆኑ ዘመናዊ የንብ ማነብ ዘዴ እንዲስፋፋ ተደርጓል። በዚህም የማር ምርታማነትን በዓመት ወደ 98 ሺህ ቶን ማሳደግ መቻሉ በቅርቡ መገለጹ ይታወሳል። ምርቱን በእጥፍ ለማሳደግ እቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑም እንዲሁ። ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የማር ምርት የማምረት አቅም ካላቸው አሥር ሀገሮች አንዷ በመሆኗ ሃብቱን ለማልማት ሁሉም ሊረባረብ ይገባል። በአጠቃላይ መንግሥት ለአረንጓዴ ልማት/አሻራ፣ ለአፈርና አካባቢ ጥበቃ የሰጠው ትኩረት ሁሉን አቀፍ የግብርና ዕድገት እንዲመጣ መሠረት ሆኗል። በተጨማሪም መንግስት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሌማት ትሩፋትና ምግባችን ከደጃችን መርሐ ግብር ኅብረተሰቡ የከተማ ግብርናን እንዲያስፋፉ በገጠርም ሆነ በከተማ ያከናወነው ተግባር ውጤት አስመዝግቧል። በአጠቃላይ ባለፉት አምስት ዓመታት ዘርፉን ለማዘመን የተከናወኑ የልማትና የሪፎረም ሥራዎች ግብርናውን ከአዝጋሚ ጉዞ በማውጣት ወደ ፈጣንና አስተማማኝ ጉዞ ማሸጋገር ችለዋል። ኢትዮጵያ አሁንም አያሌ ያልተነኩ ዕምቅ ሀብቶች ያሏት መሆኗን እንደ እድል በመውሰድ ቀጣይነት ያለው እድገት ማስመዝገብ ይጠበቅባታል። ይህን ማድረግ ስትችል የግብርና ሽግግር ይረጋገጣል። ግብርናውን ለማሻገር ደግሞ በፋይናንስ፣ በግብአት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በሰለጠነ የሰው ሀይል ልማት ላይ በትኩረት መስራት ያሻል። ወጣቱ ግብርናን እንደ ንግድ (Agri-Bussiness) ማየትና በዚያው ልክ መስራት ይጠበቅበታል። በዚህ ልክ በርብርብ ሲሰራ ግብርናን በማሸጋገር ገበታን ከመሙላት ወይም ከፍጆታ አልፎ ገበያን ማማተር ይቻላል።
ኢትዮጵያ እና መስከረም
Sep 22, 2023 185
(በአየለ ያረጋል) መቼስ ሀገሬው መስከረምን ሲናፍቅ ‘ለብቻ’ ነው። በባህሉ፣ በትውፊቱ፣ በስለ-ምኑ፣ በኪነ-ቃሉ እና ስነ-ቃሉ ልዩ ሥፍራ ይሰጠዋል ለመስከረም። እንደ መስከረም ክብር፣ ሞገስ እና ፀጋ የተቸረው የትኛው ወር ይሆን? ማንም! ሀገሬው ለቆንጆ ልጁ ስም ሲያወጣ ‘መስከረም’ እንጂ በሌላ ወር ሰይሞ ያውቃል? አያውቅም። በኢትዮጵያ ምድር መስከረም ለሰው ልጅ ብቻ ሳይሆን ለእንስሳት እና አዕዋፋት ራሱ ልዩ ጊዜ ነው። ‘ኢትዮጵያ ነይ በመስከረም…’ እንዲሉ መስከረም ለኢትዮጵያ ውበቷ፣ ቀለሟ፣ ትዕምርቷ፣ የባህር ሃሳቧ መባቻ ነው። ተናፋቂው መስከረም ዝም ብሎ ወር ብቻ አይመስልም። እውቁ ሠዓሊ እና ባለቅኔ ገብረክርስቶስ ደስታ መስከረምን “… በሽቱ መዓዛህ ለውጠው ዓመቱን፤ ይታደስ ያረጀው ፍጥረት ሌላ ይሁን…” ሲል የአዲስ ተስፋና መንፈስ መሻቱን አሳይቷል። ተወዳጇ ድምፃዊት እጅጋየሁ ሽባባው ደግሞ “… መስከረም ለምለሙ፣ መስከረም ለምለሙ፣ ብሩህ ዕንቁጣጣሽ ደስታ ለዓለሙ…” ትለዋለች መስከረምን ስታዜመው። እንደየ ንፍቀ ክበቡ ዓመታት በወራት ሲመነዘሩ የራሳቸው መልክና መገለጫ አላቸው። ኢትዮጵያም ከጎርጎሮሳዊያኑ የዘመን ቀመር በሰባት ዓመት ከስምንት ወራት ልዩነት ያለው የራሷ የዘመን ቀመር አላት። ኢትዮጵያ ብቸኛዋ ባለ 13 ወራት ሀገር ነች። ወራቱም መጸው(መኸር)፣ ሐጋይ(በጋ)፣ ፀደይ(በልግ) እና ክረምት በሚል በአራት ወቅቶች ይከፈላሉ። ወቅቶቹም የራሳቸው ጸባይ፣ ክዋኔ፣ ትውስታና ትዕምርት ይቸራቸዋል። እያንዳንዱ ወርም እንደዚሁ። ከዘመን መባቻው መስከረም እስከ ማዕዶተ-ዘመኗ ጳጉሜን ወራቱ በሰማይና በምድሩ ተፈጥሯዊ፣ ባህላዊና መንፈሳዊ ውቅራቸው ግላዊ ገጽታ ይነበብባቸዋል። የወራቱ ቅላሜ እና ሕብርነት ልዩ መልክዓ-ኢትዮጵያን ይፈጥራል። ‘የ13 ወር ፀጋ’ የሚለው መጠሪያም በ‘ምድረ ቀድምት’ እስኪተካ ድረስ ለብዙ አሥርት ዓመታት መለያ ሆኖ ዘልቋል። ይህን መለያ ስም ያወጡት እና የኢትዮጵያ ቱሪዝም አባት የሚሰኙት አቶ ኃብተሥላሴ ታፈሠ “ኢትዮጵያ የ13 ወራት ፀሐይ ባለቤት ናት። ስያሜው ከምንም የፖለቲካና ሃይማኖት ጋር ንክኪ የለውም” ብለው ነበር። የኢትዮጵያ ወራት ስያሜ ከመልክና ግብራቸው ይመነጫል። የወራት መባቻው መስከረም እንደዛው። ሊቃውንት መስከረምን ሲፈትቱት መስ - 'ዐለፈ፤ ከረመ' ይሉትና “ክረምቱን ማስከረሚያ፤ የጥቢ መባቻ" ወርኅ ሲሉ ያመሰጥሩታል። መስከረም ዘመን ያስረጃል፤ አዲስ ሕይወትና ተስፋ ደግሞ ይደግሳል። አንዳንዴም ይህ ወር ዘመን መለወጫ፣ ዕንቁጣጣሽ፣ ቅዱስ ዮሐንስ ተብሎም ይጠራል፡፡ 'አገር፣ ቀለም፣ ዘመን' እንደሸማው በድርና ማግነት ከሚሰባረቅባቸው ወራት አንዱ መስከረም ነው። መስከረም አገርኛ አለባበስ፣ አገርኛ ዝማሬ፣ አገርኛ ጨዋታ፣ አገርኛ ትውፊትና ቀለም በመስከረም በዓላት በተግባር ይታያል። መስከረም ሁለንተናዊ ውበቱ ድንቅ ነው፤ ትዕምርቱም ጉልህ ነው። የመልክዓ-መስከረም ድምቀት ማሳያዎች ዘመን መለወጫ በኢትዮጵያ ዘመን ስሌት ቀለበት መስከረም 1 ቀን ዘመን ይለወጣልና። የዘመን መለወጫ በዓል ‘ርዕሰ ዓውደ- ዓመት’ ይሰኛል። የባህር ሐሳብ ሊቃውንት መስከረም ለምን የዘመን መለወጫ እንደሆነ ሲያትቱ “ብርሃናት /ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት/ የዓመት ዑደታቸውን በጳጉሜ ወር ጨርሰው በመስከረም ወር ስለሚጀምሩ ነው” ይላሉ። በመስከረም ሌሊቱ ከቀኑ እኩል ነው። ደራሲ ካሕሳይ ገብረእግዚአብሔር “ቀዳማይ፣ ርዕሰ ክራሞት፣ መቅድመ አውርኅ፣ ርዕሰ ዐውደ-ዓመት፣ የክረምት ጫፍ መካተቻ፣ የመፀው መባቻ” ይሉታል ወርኃ መስከረምን። እናም ዘመነ ማዕዶቷን፤ ወርኅ ተውሳኳን ‘ጳጉሜን’ ተሻግሮ መስከረምን መሳም ይጓ'ጓ'ል። የመስከረም ጥባት በአያሌው ይሻታል። 'መስከረም ሲጠባ ወደ አገሬ ልግባ …’ እንዲሉ የተሰደዱት በአዲስ ዓመት መባቻ የአገራቸውን አፈር ለመሳም ያማትራሉ። ’አበባዬ ሆይ፤ አበባዬ ሆይ’ የሚሉ ሕፃናት ተስፋና ምኞታቸውን በወረቀት ያቀልማሉ፤ የአበባ ስዕላት ይዘው በየደጃፉ ይሯሯጣሉ፤ የ’ዕደጉ’ ምርቃት ያገኛሉ፤ በደስታ ይንቦጫረቃሉ። በዚህ ድባብ ነው እንግዲህ መስከረምን የግዑዛንም የሕይወታውያንም የነፃነት፣ የተስፋና የፍቅር ወርኅ ተደርጎ የሚናፈቀው። የብዙ ሺህ ዘመናት ባለታሪኳ ኢትዮጵያ ተፈጥሯዊ አዱኛ ሳይርቃት በእርስ በርስ ጦርነት፣ በጠላት ፍላፃዎች እና በድንቁርና ብዛት... ሰንኮፎቿ ሳይነቀሉ በመልከ-ብዙ ምስቅልቅሎሽ ውስጥ ዛሬ ደርሳለች። ጊዜው የኢትዮጵያን መስከረም ያስናፍቃል። ዕንቁጣጣሽ መስከረም በአደይ አበባ የሚያሸበርቅ ወር ነው። የነገረ-ዕንቁጣጣሽ የትመጣ መልከ-ብዙ አተያዮች ይጠቀሳሉ። ለምሳሌ “ዕንቁ – ዕፅ አመጣሽ” ብሎ የአበባ መፈንዳት ለማመላከት እንደሆነ የሚጠቅሱ አሉ። ንግሥት ሳባ /አዜብ/ ወደ ንጉሥ ሰሎሞን የእጅ መንሻ ይዛ ስትሄድ ንጉሡም “ዕንቁ ለጣትሽ ጌጥ ይሁንሽ” በሚል ቀንና ከሌሊት የሚያበራ ቀለበት ስለሰጣት ነው የሚል አፈታሪክም ይነገራል። የስያሜው መነሻ ያም ሆነ ይህ መስከረም ለመልክዓ-ምድሩ፣ ለሰውና ለእንስሳት ሁሉ ‘ፍስሐ ወተድላ’ የሆነ ወር ነው። በመስከረም ምድር በዕንቁጣጣሽ ትፈካለች፤ በአበቦች ታጌጣለች፤ ውኆች ይጠራሉ። ሰማዩም የክብረ-ሰማይ ብርሃኑን ያጎላል። ጥቁር ደመና ጋቢ ይገፈፋል፤ ክዋክብት እንደፈንዲሻ በዲበ-ሰማይ ይደምቃሉ። ዕጽዋትና አዝዕርት እንቡጦች ይፈነዳሉ። የመብረቅ ነጎድጓድ ተወግዶ የሰላምና የሲሳይ ዝናብ ይዘንባል። እንስሳት የጠራ ውሃ እየጠጡ፣ ለምለም ሳር እየነቸረፉ ይቦርቃሉ። እርሻ የከረሙ በሬዎች፣ ጭነት የከረሙ አህዮች መስከረም አንጻራዊ የእፎይታ ወራቸው ነው። ነጎድጓድ በአዕዋፋት ዝማሬ ይተካል። ንቦች አበባ ይቀስማሉ፤ ቀፏቸውን ያደራሉ። ቢራቢሮ ሳትቀር ‘በመስከረም ብራ ከኔ በላይ ላሳር..’ ብላ ትከንፋለች። በ’ዕንቁጣጣሽ’ ምድር ብቻ አይደለችም የምትዋበው። መስከረም ለሰው ልጆችም በተለይም ለወጣቶች የፍቅር፣ የእሸት እና የአበባ ወር ነው። የሰላም፣ የንጹህ አየር፣ የጤና ድባብ ያረብባል። የጋመ በቆሎ እሸት ጥብስ፤ ቅቤ ልውስ፤ ቅቤ በረካ ይናፈቃል። የተጠፋፋ ዘመድ አዝማድ ይገናኛል። ‘ሰኔ መጣና ነጣጠለን’ ብለው ወርኃ ሰኔን የረገሙ ተማሪዎች ተናፋቂያቸውን ያገኛሉና ‘መስከረም ለምለም’ ብለው ያሞካሹታል። የገበሬው የሰብል ቡቃያ ያብባል፤ እሸት ያሽታል። ጉዝጓዝ ሣር፣ ትኩስ ቡና ይሽታል። ደመራ ወመስቀል ሊቃውንት የደመራን የትመጣን ሲፈትቱ ‘ደመረ፣ ተሰባሰበ’ ይሉታል። ጎረቤት፣ የሩቅ የቅርብ ዘመድ አዝማድ ተደምሮ የሚከውነው ነውና። ነገረ መስቀሉ እምነቱ፣ ባህሉ፣ ትውፊቱ ብዙ ነው። መስቀል በሃይማኖተ-አበው ሀተታ ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ለማዳን፣ ለፍጡር የሰው ልጆች ያለውን ጥልቅ ፍቅር የገለጸበት ዓርማ ነው። በዚህም መስቀልን አማኝ ምዕመናን እና ካህናት የደኅንነትና የእምነት ምልክታቸው፤ የርኩስ መንፈስ ማባረሪያ መሳሪያቸው አድርገው ይመለከቱታል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መስከረም 10 ቀን ‘ተቀጸል ጽጌ’ በሚል የክርስቶት መስቀል ግማድ (ቀኝ እጁ ያረፈበት ክፋይ) ከኢየሩሳሌም ተነስቶ ኢትዮጵያ የገባበትን ቀን ታከብረዋለች፤ መስከረም 17 ቀን ደግሞ መስቀሉ የተገኘበትን። መስከረም 16 እና 17 ቀን የሚከበረው የደመራ መስቀል በዓል ከሃይማኖታዊ አስተምህሮው ባለፈ ባህላዊ ትውፊትነቱ የጎላ በመሆኑ በአብዛኛው ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ይናፈቃል። ደመራና መስቀል የአንድነት፣ የፍቅር፣ የይቅርታ፣ አብሮነት፣ የምስጋና፣ የተስፋ… እሴቶች የሚገለጹበት ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ ክብረ-በዓል ነው። ደመራ እና መስቀል በዓላት ሃይማኖታዊ የአደባባይ በዓል ቢሆንም እንደየ አካባቢው ባህል፣ መንፈሳዊነት፣ ትውፊት፣ ዕውቀት አገርኛ ህብር ጥበባት የሚጎሉበት፣ አገር የውበት አክሊል የምትደፋበት ዕለት ነው። መስቀል የዓለማችን የማይዳሰስ የኢትዮጵያ ወካይ ቅርስ መዝገብ ሥር ሰፍሯል። በመስቀል አገርኛ ቀለም ይጎላል። 'አገር፣ ቀለም፣ ዘመን' እንደሸማው በድርና ማግነት ይሰባረቃሉ። የባህር ማዶ ጎብኚዎች በአግራሞትና መደነቅ ሲናገሩ ይደመጣሉ። የዕንቁጣጣሽ ተከታይ የመስከረም መልክ ነው መስቀል። የደመራ አደማመር እና ማብራት ሥነ-ሥርዓት በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች ተመሳሳይ እንዳልሆነ ደራሲ ካሕሳይ ገብረእግዚአብሔር ይተርካሉ። በትግራይ፣ በጎንደር፣ በወሎ፣ በዋግኸምራ፣ በአዊና በከፊል ጎጃም ደመራ ማታ ላይ ተደምሮ ንጋት ላይ ይለኮሳል። በከፊል ጎጃም፣ በሸዋ፣ በአዲስ አበባ፣ በጉራጌ፣ በጋሞ፣ በወላይታና ሌሎች የደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች ደግሞ እንደየ አካባቢው ተለምዶ መስከረም 16 ከእኩለ ቀን ጀምሮ እስከ አመሻሽ ድረስ ደመራው ይለኮሳል። መስቀል በአንዳንድ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ርዕሰ ዓውደ-ዓመት ይመስላል። በደቡብ ኢትዮጵያ መስቀል ከሃይማኖታዊ ይዘቱ ባህላዊ ጎኑ ይጎላል። ጉራጌዎች፣ ጋሞዎችና ሌሎችም መስቀልን ከሁሉም በዓላት የበለጠ ይናፍቁታል። የተራራቁ ቤተሰቦች የሚገናኙበት የፍቅር፣ የደስታና የእርቅ በዓል ነው መስቀል። በጋሞ ብሔረሰብ ባህል በዋዜማው ሰው ቢሞት እንኳን በሌሊት ተወስዶ ይቀበራል እንጂ ለቅሶ እንደማይለቀስ ይነገራል፤ ለሰው ብቻ ሳይሆን ለእንስሳቱም ልዩ መኖ እንደሚቀርብላቸው ይነገራል። ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ እንደሚባለው በጋሞዎች ደግሞ ‘ለመስቀል ያልሆነ ዱንጉዛ ይበጣጠስ’ በሚመስል መልኩ የባህል ልብስ አለባበስ እንደሚዘወተር መምህር ካሕሳይ (በሕብረ-ብዕር ድርሰታቸው) ጽፈዋል። መስቀል በጉራጌዎች ዘንድ እንደ አውራው በዓል ይቆጠራል። ለመስቀል ዓመቱን ሙሉ ዝግጅት ይደረጋል። አባወራው ሰንጋ ለመግዛት፣ እማወራ ማጣፈጫውን ለማዘጋጀት፣ ወጣቶች ደመራና ደቦት ለማዘጋጀት፣ ልጆች ምርቃት ለመቀበል የየራሳቸውን ይዘጋጃሉ። ቤተሰብ ወዳጅ ዘመድ የሚጠያየቅበት፣ ለትዳር የደረሱ ሚስት የሚያጩበትና የሚመርጡበት ጥላቻና ቂም በፍቅርና በይቅርታ የሚታደስበት ነው። በጉራጌዎች ዘንድ መስቀል ትልቅ ቦታ ይቸረዋል። መስቀል እንደየአካባቢውና ባህሉ የሚናፈቅበት ዕልፍ ገጽታዎች አሉት። ለምሳሌ እኔ በተወለድኩበት ገጠራማ አካባቢ ያለውን በወፍ በረር እንቃኘው! በደመራ ዋዜማ ቀናት ልጆች ተራራ ለተራራ፣ ወንዝ ለወንዝ፣ ቋጥኝ ለቋጥኝ በልጅነት ወኔና ስስት በመዞር ለደመራ የሚሆን እንጨት፣ አደይ አበባ፣ ደቦት(ችቦ) ያጠራቅማሉ። ልክ መስከረም 16 አመሻሽ ከብቶች ወደ ግርግም ከገቡ የመንደሩ ወጣቶች ወደ ‘አፋፍ’ ይወጣሉ። ደመራ ወደሚደመርባት ሥፍራ። ሁሉም የአንድ ዕድር አባላት ቤተሰብ ተወካዮች ባሉበት እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት የደመራው ሥራ ይጠናቀቃል። ደመራው ሲጠናቀቅ ወደየ ቤታችን እንበታተናለን። (አዲስ አበባን ጨምሮ በከተሞች እንደሚደረገው በመስከረም 16 አመሻሽ ደመራው አይለኮስም። ይልቁኑ መስከረም 16 ለ17 አጥቢያ ጀምሮ ይለኮሳል እንጂ።) ለመስከረም 17 አጥቢያ ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ጀምሮ ሁሉም ሰው ከየቤቱ ደቦቱ (ችቦውን) እየለኮሰ ‘እዮሃ ደመራ’ እያለ ወደ ደመራው ሥፍራ ይተማል። እንደየ ግለሰቡ ቤት እስከ ሦስት ኪሎ ሜትር ድረስ መጓዝ ሊጠይቅ ይችላል። የመስከረም እኩሌታ አረንጓዴያማ ውብ ማሳ ከየቤቱ ከሚወጡ የችቦ እሳት ነበልባል ብርሃን ይታጀባል። ከሌሎች አጎራባች የመንደር ደመራዎች ቀድሞ ለመለኮስ ጉጉቱ የትየለሌ ነው። ከቤት እስከ ደመራው ሥፍራ እስኪደርሱ ድረስ ሰዎችን፣ በረት ያሉ ከብቶቹንና የጓሮ አዝመራውን ጨምሮ ሕይወታዊያንን በሙሉ “እንጎረጎባህ፤ እንጎረጎባችሁ” ይባላል። የተጠያቂው ሰው ምላሽ ደግሞ “ዓመት ዓመቱን ያድርስህ” የሚል ይሆናል። ከደመራ ግጥም ተዘውታሪ ስንኞች መካከልም፡- “እዮሃ አበባዬ፣ መስከረም ጠባዬ፣ እዮሃ አረሬ አረሬ፣ መስቀል ጠባ ዛሬ፣ በሸዋ በትግሬ…” የሚለው ይጠቀሳል። ከደመራው ሥፍራ ስንደርስ የ’እንጎረጎባህ!’ ድምፆች ይበረታሉ። የ’ዓመቱን ያድርስህ’ መልስ ካልሆነም እኩይ አፀፋ ይኖራል። ሁሉም ከተሰባሰበ በኋላ ደመራን የሚያሞካሹና የአዲሱን ዓመት መልካምነት የሚመኙ ‘እዮሃ አበባዬ” ግጥሞች እየተደረደሩ ደመራው ሦስት ጊዜ እንቧለሌ ይዞራል። በዕድሜ ታላቅ እና የተከበረ ሰው በቅድሚያ ደመራውን ይለኩሳል። ቀጥሎ ሁሉም ወደ ደቦቱን(ችቦውን) ወደ ደመራው ውስጥ ያስገባል። ደመራውም ይቀጣጠላል። የእሳቱ ነበልባል በመስከረም የንጋት ውርጭና ብርድ ላይ ያይላል። ሁሉም በደመራው ዙሪያ ተኮልኩሎ የክረምት ወራት ትዝታ ይነሳል፤ ሹፈት፣ ቀልድና ቁምነገር በየፈርጁ ይሰለቃል። ሌሊቱ የአህያ ሆድ እስኪመስል ይቀጥላል። የተጣላም ይታረቃል። የደመራው አምድ (ምሰሶ) አወዳደቅ ለማየት ሁሉም በጉጉት ይጠብቃል። ምሰሶው ወደ ምሥራቅ ከወደቀ የጥጋብ ዓመት፤ ወደ ምዕራብ ከሆነ ግን የችጋር ዓመት ተደርጎ ይታመናል። ከደመራው ሁነቶች አንዱ ባህሉ የበቆሎ እሸት ናፍቆት ነው። የደመራው ምሰሶ ከወደቀ በኋላ በአቅራቢያ ካለ የበቆሎ ማሳ በቆሎ እሸት ይመጣል። በመስቀል ደመራ ፍም ተጠብሶ ይበላል። ባለበቆሎው ሰው ዓመታዊ ደንብ ስለሆነ የበቆሎ ማሳዬ ተጎዳብኝ ብሎ አይቆጣም። ከደመራው ዓመድ ግንባራችን ላይ መስቀለኛ ምልክት ማድረግ እና ‘የዛሬ ዓመት አድርሰኝ’ ስለት ይቀጥላል። ሰማዩ የአህያ ሆድ ሲመስል ልጆች በደቦ ወደ መንደር ለመንደር በመዞር ‘እንጎረጎባችሁ’ እንላለን። የቤቱ ባለቤትም በሳህን፣ ጣሳ ወይም ሌላ ዕቃ ጤፍ ዱቄት ይሰጣል። የሰበሰብነውን ዱቄት ይዘን ወደ ደመራው ሥፍራ እንመለሳለን። በደመራው ጉባዔ ተወስኖ ከዕድሩ ለተመረጠች ቀጭን እመቤት (ባለሙያ ሴት) ዱቄት ይሰጣትና በ17 ምሽት ለሚኖረው የእራት ሰዓት ዝግጅት በአነባበሮ መልክ ዱቄት አብኩታና ጋግራ ታቀርባለች። መስቀል የወል ክብረ በዓል ነው። የመስቀል ዕለት (መስከረም 17) በግ ይታረዳል። እህል ውሃ ቀርቦ የመንደሩ ሰው በጋራ ሲጫወት ይውላል፤ በሕብረት ይበላል። ለመስቀል የተጣላ ጎረቤት ይታረቃል። ልጆች በሕብረት ይቦርቃሉ። የመስቀል ትዝታ በእኛ መንደር ይናፈቃል። ሁሉም እንደየ ቀየው ትውፊት እና ልማድ ይህን ሁነት ይናፍቃል….!! ጊፋታ ጊፋታ/ ግፋታ ማለት ትርጉሙ በኩር ወይም ታላቅ ማለት ሲሆን በለኬላ ትርጓሜው መሻገር ማለት ነው፡፡ በወላይታ ብሔረሰብ አዲስ ዓመት አንድ ብሎ የሚጀመርበት የአዲስ ዓመት መግቢያና የብርሃን ጊዜ ማብሰሪያ ነው፡፡ ከአሮጌ ወደ አዲስ፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን መሻገር የሚለውንም ይገልጻል፡፡ ጊፋታ የዓመቱ የመጀመሪያ ወር ስያሜ ነው፡፡ በወላይታ ብሔረሰብ ዘንድ መስከረም ወር በገባ ከቀን 14 እስከ 20 መካከል የሚውለው እሑድ አዲሱን ዓመት የሚቀበሉበር ዕለት ይሆናል፡፡ በዓሉ የሚውልበት እሑድ ስሙም ‹‹ሹሃ ወጋ›› የእርድ እሑድ ይባላል፡፡ እሑድ የአዲስ ቀን ብሥራትም ነው፡፡ ቀጣዮቹ የሳምንቱ ቀናት የየራሳቸው ስያሜና አከባበር አላቸው። ለአብነት ‹‹ጋዜ ኦሩዋ›› ማንሳት ይቻላል። የአዲስ ዓመት አራተኛ ቀን ነው። የሰፈሩ ወጣቶች በየመንደሩ በታዋቂ የአገር ሽማግሌዎች ደጅ ተሰባስበው የግፋታ በዓል ባህላዊ ጨዋታ የሆነውን ጋዜ በጋራ ሆነው ‹‹ሀያያ ሌኬ›› እያሉ ትከሻ ለትከሻ ተቃቅፈው የሚጫወቱበትና ልጃገረዶችን ሎሚ በመለመን የሚፈልጓትን የሚመርጡበት ጨዋታ የሚጫወቱበት ቀን ነው፡፡ በዕለቱ ልጃገረዶች አንድ ላይ ሆነው በየቡድን ቁጭ ብለው ወንዴና ሴቴን ከበሮ እየመቱ ‹‹ወላወላሎሜ›› እያሉ የሚመርጡትን ወንድ ሎሚ በመስጠት የሚመርጡበት፣ እንዲሁም ሴቶች ለሚዜነትና ለጓደኝነት ከመረጧት ሴት ጋር በጥርስ አንድ ሎሚን ለሁለት የሚከፋፈሉበትና ስማቸው ሲጠራሩ ‹‹ሎሜ ሎሜ›› የሚባባሉበት ጨዋታ የሚጫወቱበት ዕለት ጋዜ ኦሩዋ ነው፡፡ ግፋታ ሲሸኝ ጥቅምት በገባ በመጀመሪያው ሳምንት ማክሰኞ ሆኖ የሽኝት በሬ ታርዶ ከተበላ በኋላ ቶክ ጤላ የተባለውን ምሽት በችቦ ያባርራሉ፡፡ ዜማ በተቀላቀለበት ጩኸት ችቦ ይዘው ‹‹ኦሎ ጎሮ ባ! ሳሮ ባዳ ሳሮ ያ!›› ይላሉ፡፡ ትርጓሜውም ጊፋታ በሰላም ሄደሽ በሰላም ነይ! ማለት ነው፡፡ ዮ …ማስቃላ በጋሞዎች ዘንድ በየዓመቱ በጉጉት የሚጠበቀው «ዮ ማስቃላ» የዘመን መለወጫ በዓል በመስከረም ወር አጋማሽ ላይ ቅበላው ተከብሮ በዚሁ ወር መጨረሻ «ዮ ማስቃላ» ሽኝት በዓል በድጋሚ በድምቀት ይከበራል። መስከረም ወር የመጀመሪያው ቀን በጋሞ ዞን ”ሂንግጫ” ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ይህም አዲሱን ዓመት ለመቀበል ዝግጅት የሚደረግበት ቀን ነው። ጋሞዎች ዓመቱን ሙሉ ገንዘብ በመቆጠብ በዓሉን በድምቀት ለማክበር ዝግጅት ይደረጋል። ወንዶች ለበዓሉ የሚሆን ሠንጋ መግዣ፣ ለልጆች ልብስ እና ጌጣጌጥ ማሟያ፤ እናቶች ደግሞ ለቅቤ፣ ለቅመማቅመም፣ ለባህላዊ ምግቦች እና መጠጦች እህል መግዣ የሚሆን ገንዘብ ያጠራቅማሉ። በጋሞ ዞን የማስቃላ በዓል ለሰው ልጆች ብቻ ሳይሆን ለእንሳስት እና ለአዕዋፋትም ጭምር ነው ተብሎ ይታመናል፤ በዕለቱ ምግብ ከሰው አልፎ ለእንሳስት እና ለአዕዋፍም ይትረፈረፋል። ለከብቶችም የግጦሸ መሬት በየአካባቢው ይከለላል። በተለያዩ አጋጣሚዎች የተጣሉ ታርቀው፣ የተራራቁ ዘመድ አዝማድ እና ወዳጆች ተሰባስበው በዓሉን በጋራ እንዲያከብሩ ማድረግ የጋሞ ማስቃላ በዓል መገለጫ ነው። በጋሞ ብሔረሰብ የሚከበረው የማስቃላ በዓል በሶፌ ሥርዓት የታጀበ ነው። የቀደመው ዓመት ማስቃላ በዓል ከተከበረ በኃላ የተጋቡ ሙሽሮች ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ ማምሻውን በአደባባይ ከመላው ሕብረተሰብ ጋር የሚቀላቀሉበት እና ሁለቱም ተጋቢ ቤተሰቦች አንድ ላይ ሆነው ደስታቸውን የሚገልፁበት ሥርዓት ነው። የመጨረሻው የማስቃላ ሽኝት በዓል ነው፤ ይህ ሥርዓት እንደየአባወራው አቅም በፈቀደ መጠን የሚፈፀም ነው። በዚህ ዕለት ሁሉም ያለ ፆታ ልዩነት በአደባባይ ላይ ወጥተው ያኑረን እስከ ወዲያኛው እንኖራለን እያሉ ይጨፍራሉ። ከዚህ በኋላ ለመጪው ዓመት በሰላም በጤና ያድርሰን ተባብለው ፈጣሪን በመማፀን ዝግጅቱ ይቋጫል። ያሆዴ መስቀላ የክረምቱ ወራት አልፈው መስኩ በልምላሜና በአደይ አበባ ሲያሸበርቅ በሃድያዎች ዘንድ ትልቅ ዝግጅት አለ - ያሆዴ መስቀላ። “ያሆዴ“ ማለት እንደ ብሔሩ የባህል ሽማግሌዎች ትርጓሜ እንኳን ደስ አላችሁ፤ የሚል የብስራት ትርጉም ያለው ሲሆን ”መስቀላ” ማለት ደግሞ ብርሃን ፈነጠቀ ማለት ነው፡፡ በመሆኑም ያሆዴ መስቃላ ብርሃን ፈነጠቀ እንኳን ደስ አላችሁ የሚል ትርጉም አለው። በዓሉ በወርኃ መስከረም 16 የሚከበር ሲሆን ወሩ ብርሃን፣ ብሩህ ተስፋ፣ ሰላም፣ ፍቅር፣ ረድኤት፣ በረከት የሚሞላበት ተምሳሌት ወር ተደርጎ ይቆጠራል። የሃድያ አባቶች ”ከባለቤቱ የከረመች ነፍስ በያሆዴ መስቀላ ትነግሳለች“ የሚል ብሂል አላቸው። የሃድያ አባቶች እንደ ዘመን መለወጫ የመጀመሪያ ቀን አድርገው በመውሰድ ማንኛውንም ዓይነት ክስተት ከዚያ ጋር አያይዘው እንደሚቆጥሩ ይነገራል። በዓሉ ከመድረሱ በፊት ሁሉም የቤተሰብ አባላት በዓሉን ለማድመቅ የየራሳቸው ድርሻ አላቸው። በብሔሩ አባቶች አብሮነታቸውን ከሚያጠናክሩባቸው ማኅበራዊ እሴቶች መካከል አንዱ ቱታ/ሼማታ/ሲሆን ይህ ማለት በዓሉን ምክንያት በማድረግ የተደራጀ ቋሚ የሆነ ከአራት እስከ ስምንት አባላትን የያዘና በሥጋ ቅርጫ የተደራጀ ማኅበር ነው። የዚህ ማኅበር አባላት ግንኙነት ያላቸው የሚተሳሰቡ የኢኮኖሚ አቅማቸውም ተቀራራቢነት ያለው ሲሆን በመቀናጀት የበዓሉ እለት ከመድረሱ በፊት በጋራ ገንዘብ ማስቀመጥ ይጀምራሉ፤ በበዓሉ ወቅትም ለእርድ የሚሆን በሬ መግዣ ገንዘብ እንዳይቸገሩና በዓሉን በደስታ እንዲያሳልፉ ሕብረታቸው ትልቅ ሚና ይጫወታል። ከመጋቢት ወር ጀምሮ ለከብቶች የግጦሽ ሳር የሚሆን ቦታ ከልሎ በማስቀመጥ የበዓሉ ቀን ከብቶች ተለቀውበት እንዲጠግቡ የሚደረግ ሲሆን በአዲስ ዓመት መግቢያ እንኳን የሰው ልጅ እንሰሳትም ቢሆኑ መጥገብ እንዳለባቸው እንዲሁም የጥጋብ ዘመን እንዲሆን በብሔሩ በዓሉ ለሰው ብቻ ሳይሆን እንሰሳትም ሆዳቸው ሳይጎድል አዲሱን ዓመት መቀበል እንዳለባቸው በመታመኑ ልዩ ትኩረት ይሰጣቸዋል። ኢሬቻ ኢሬቻ ከመስከረም ደማቅ መልኮች አንዱ ነው። ኢሬቻ የዘመነ መፀው መጀመሪያ ሁነት ነው። የኢሬቻ ክብረ በዓል ኢሬቻ ቢራ (መልካ) በሐይቆች ወይም በወንዞች ዳር የሚከበር ነው። ከክረምት ወደ መፀው መሸጋገርን ምክንያት በማድረግ የሚከወን የምስጋና በዓል ነው። በኦሮሞ ዘንድ ለዘመናት የሚከበር እና ከገዳ ሥርዓት ጋር የተቆራኘ እንደሆነ ይነገራል። ኢሬቻ ከመስቀል በኋላ ይከበራል። በቢሾፍቱ ከተማ የሚከበረው የ'ሆራ አርሰዲ' እንዲሁም ‘ሆራ ፊንፊኔ’ ከፍተኛ ሕዝብ ቁጥር በታደመበት በድምቀት ይከበራል። በሌሎችም የኦሮሚያ አካባቢዎች በተለያዩ ክዋኔዎች እንዲሁ ይከበራል። ኢሬቻ ለፈጣሪ (ዋቃ) የክረምት ወቅትን በማሳለፉ፣ ወይንም ወደ አዲስ ዓመት በማሸጋገሩ የሚቀርብ ምስጋና ነው። ‹‹ዋቃ›› ፍጥረተ ዓለምን ያስገኘውና ሒደቱንም የሚያስተናብረው አንድ አምላክ ማለት ነው፡፡ ‹‹ኢሬቻ ሰላም ነው፣ ሰላም ጥልቅ ትርጉም አለው፣ ሰው ከሰው ጋር፣ ሰው ከራሱ ጋር፣ ሰው ከተፈጥሮ ጋርና ሰው ከፈጣሪው ጋር ሰላም ሊኖረው ይገባል፤›› የሚለው ጽንሰ ሐሳብ የክብረ በዓሉ ጭብጥ ነው፡፡ ለሕዝቡና ለአገሩ ምርቃትና መልካም ምኞት የሚገለጽበትም ነው-ኢሬቻ። ታዲያ ማንኛውም ሰው ወደ በዓሉ ሥፍራ ሲሄድ አለባበሱን ማሳመር ይጠበቅበታልኢሬቻ ከመስቀል በኋላ ይከበራል። በቢሾፍቱ ከተማ የሚከበረው የ'ሆራ አርሰዲ' እንዲሁም ‘ሆራ ፊንፊኔ’ ከፍተኛ ሕዝብ ቁጥር በታደመበት በድምቀት ይከበራል። በሌሎችም የኦሮሚያ አካባቢዎች በተለያዩ ክዋኔዎች እንዲሁ ይከበራል። ኢሬቻ እንደ ዕንቁጣጣሽ በመስከረም ጥባት ውሃ ጎድሎ፣ የተራራቀ ዘመድ አዝማድ የሚገናኝበት ነው። በተለያዩ ጸሐፍት እንደተጠቀሰው፣ ኢሬቻ አንድም ‘ዋቃ’ ከብርድና መብረቅ፣ ከጎርፍ፣ ከአውሎ ነፋስ እና መሰል የክረምት ተፈጥሯዊ ክስተቶች ጠብቆ ወደ ብራ እና ፀሐያማው የመፀው ወቅት በሰላም ስላሸጋገረ፣ አንድም በዋቃ ፈቃድ ዝናብ ዘንቦ፣ መሬቱ ረስርሶ፣ አዝመራው ለምልሞ፣ መልካም ፍሬ በመታየቱ፣ እሸት በመስጠቱ ስለማያልቀው ቸርነቱ ለማመስገን ነው። ከክረምቱ ጨለማ ወደ ብርሃን የማለፍ ብሥራት ነው ኢሬቻ። በሌላ በኩል ደግሞ መጪው አዲሱ ዓመት የተባረከና የተቀደሰ፣ የደስታና የብልፅግና፣ የተድላና ፍስሃ ይሆን ዘንድ መልካም ምኞትን የመግለጫ በዓልም ነው። በኢሬቻ ክዋኔ አባ ገዳዎችና የሕዝብ መሪዎች ይመርቃሉ። በኦሮሞ ሕዝብ ባህላዊ አለባበሱን በማጌጥ ወደ ክብረ-በዓሉ የሚያመሩ ኢሬቻ አክባሪዎች እርጥብ ሳር እና አደይ አበባን ይይዛሉ። ከኢሬቻ ክብረ-በዓል የምርቃት ስንኞች መዘን እንሰናበት። “… ለምድራችን ሰላም ስጥ! ለወንዞቻችን ሰላም ስጥ! ከጎረቤቶቻችን ጋር ሰላም ስጠን! ለሰውም ለእንስሳቱም ሰላም ስጥ! ከእርግማን ሁሉ አርቀን! ከረሃብ ሰውረን! ከበሽታ ሰውረን! ከጦርነት ሰውረን! ሀዬ! ሀዬ! ሀዬ! (አሜን! አሜን! አሜን!)
ያሆዴ- የአዲስ ተስፋና ልምላሜ ምልክት
Sep 22, 2023 208
(በማሙሽ ጋረደው ከሆሳዕና) ያሆዴ የሃድያ ብሔር የአዲስ ዘመን መሸጋገሪያ በዓል ነው። በዓሉ ሲከበር ቂምና ቁርሾ ተወግዶ ያለፈው ዓመት መልካምና በጎ ያልሆነ ሁኔታ ታይቶ ለቀጣይ ስኬት አዲስ ተስፋና ልምላሜ ሰንቆ የሚሻገሩበት በዓልም እንደሆነ ይነገራል። ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡ የሃድያ ዞን አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ሃላፊ አቶ ታምሬ ኤርሚያስ እንዳሉት ሃድያ የራሱ የሆነ የጊዜ አቆጣጠር ባህል፤ ልማድ፤ ወግና ስርዓት አለው። ለዚህም እንደ ማሳያ በብሔሩ ዘንድ በከፍተኛ ድምቀት የሚከበረውን የያሆዴ ክብረ በዓል ለአብነት ጠቅሰዋል። በዓሉ የአዲስ ተስፋና ልምላሜ ምልክት ተደርጎ እንደሚወሰድ የተገለጸ ሲሆን በተለይም የሚመጣው ዘመን የስኬት እንዲሆን እያንዳንዱ ካለፈው ዓመት ስኬትና ውድቀት ልምድ እየቀመረ ሃገር ሰላም እንዲሆን ተመራርቀው በደስታ እየተበላ፤ እየተጠጣ የሚከበር በዓል መሆኑንም ተናግረዋል። በብሔሩ ዘንድ ልዩ ቦታ የሚሰጠው የያሆዴ ክብረ በዓል አሮጌውን ዓመት ሸኝተው አዲሱን ዓመት የሚጀምሩበትም ነው። በዓሉ ከነሐሴ አጋማሽ ጀምሮ በተለያዩ ክዋኔዎች የሚከበር ሲሆን በዓሉ መቅረቡን ታዳጊ ልጆች በተለያዩ ገላጭ በሆኑ ድርጊቶች እንደሚያበስሩ አቶ ታምሬ ተናግረዋል። በተለይም ታዳጊዎቹ ያሆዴ መድረሱን ለማብሰር ከነሐሴ አጋማሽ ጀምሮ እስከ ጳጉሜ መጨረሻ ድረስ በብሔሩ አጠራር ገምባቡያ ወይም (ዋሽንት) በመጠቀም የተለያዩ ጥዑመ ዜማዎችን በማሰማት በዓሉ መቅረቡን ያበስራሉ። በሃድያ ብሔር ዘንድ የአዲስ ዘመን ብስራት “ያሆዴ" የብሩህ ተስፋ፣ የሠላም፣ የፍቅር፣ የረድኤት፣ የበረከት ተምሳሌት ተደርጎ የሚወሰድ በዓል መሆኑንም አመልክተዋል። ይህም የሆነበት ምክንያት በመስከረም ሰውና እንስሳ ከዶፍ ዝናብ፣ ከውርጭ፣ ከጤዛና ከጭቃ፣ ከጉም፤ ከጭጋግና ጽልመት ነጻ ይሆናሉ። ምድሩ በሃምራዊ ቀለም ደምቆ ያሸበርቃል። ፀሐይ ሙሉ ገላዋን ገልጣ ጸዳሏን ትሰጣለች። በመሆኑም በስራ የደከመ ሰውነት ዘና፣ የታመመ ቀና ይልበታል፣ ልጅ አዋቂ የደስታ ነጋሪቱን ይጎስማል፣ የፍቅር ጽዋ ይጠጣል፣ የአእምሮ እርካታ ይነግሳል፣ በሁሉም ነገር ደስታ ይሰፍናል ወርሃ መስከረም በጥጋብና ደስታ ይጀመራል ። በዓሉ ከመግባቱ በፊት የራሱ የሆነ የሥራ ክፍፍል ኖሮት ቅድመ ዝግጅት የሚደረግበት መሆኑን ያነሱት ሃላፊው የቤተሰብ አባላት ሁሉም በየድርሻቸው ሃላፊነታቸውን እየተወጡ እንደሚጠብቁት ተናግረዋል። ለአብነትም ለበዓሉ መድመቅ በዓሉ ከመድረሱ ሦስትና አራት ወራት በፊት በአንድ ቤት ውስጥ የሚኖሩ የቤተሰብ አባላት የሚወጡት ድርሻ አላቸው። የሃድያ አባቶች የያሆዴን የዘመን መለወጫ በዓል የሚያከብሩት በቅንጅት አማካኝነት ከአራት እስከ ስድስት ሰው በመሆን ተቀናጅተው ሰንጋ በመግዛት ነው። ለበዓሉ ሰንጋ መግዣ የሚሆን ገንዘብ ማስቀመጥ የሚጀምሩትም ቀደም ብለው ነው ። እናቶች በዓሉ ከመቃረቡ ከሦስትና እና አራት ወራት በፊት ለበዓሉ የሚሆን ቅቤ ለማጠራቀም በሚገቡት (ዊጆ) በተሰኘ ዕቁብ ቅቤ ማከማቸት ይጀምራሉ። በተጨማሪም ለስጋ መብያና ለአተካና መስሪያ የሚሆን እንሰት በመለየትና በመፋቅ፣ ቆጮ፣ ሜሬሮና፣ ቡላን ጨምሮ የሚጠጣ ቦርዴ፣ ቃሪቦ፣ ጠጅ፣ ብርዝ የማዘጋጀት የድርሻቸውን ይወጣሉ። የደረሱ ልጃገረዶች የቤቱን ወለል ቆፍረው ይደለድላሉ፣ የተለያዩ ውበት የሚሠጡ ቀለማትንና የተለያዩ ኖራዎችን በመጠቀም የቤቱን የውስጥና የውጭ ግርግዳን በመቀባት ያስውባሉ። ወጣቶች ከነሐሴ መግቢያ ጀምሮ አባቶቻቸው የሚመርጡላቸውን ዛፍ፣ ግንድ ቆርጠው ለምግብ ማብሰያና ለደመራ የሚሆን ችቦ የማዘጋጀት ኃላፊነታቸውን እየተወጡ ይቆያሉ። ከመስከረም መግቢያ ጀምሮ ያሉ የቅዳሜ ገበያዎች ስያሜ (መቻል ሜራ ) የእብድ ገበያ በመባል ይጠራሉ።እነዚህ የግብይት ቀናት ከዚህ ቀደም እንደነበሩ የግብይት ቀናት በተረጋጋ መንገድ የሚተገበሩ ባለመሆኑና በጠዋት ቆሞ በጊዜ የሚበተን ገበያ በመሆኑ (መቻል ሜራ) የእብድ ገቢያ የሚል ስያሜ አሰጥቶታል ነው ያሉት አባቶች ሰንጋ ገዝተው ለመብላት ባደራጁት (ቱታ) ቅንጃ አማካኝነት ያጠራቀሙትን ገንዘብ በመያዝ ወደ መቻል ሜራ (እብድ ገበያ) በመሔድ የሚፈልጉትን ሰንጋ ገዝተው ይመለሳሉ። ገንዘብ ያላስቀመጡና በወቅቱ ማግኘት የማይችሉ አባወራዎች በዓሉን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተደስተው እንዲያሳልፉ ሌላኛው አማራጭ (ሃባ) በመባል የሚታወቅና ምንም ገንዘብ የሌላቸው ሰዎች ለበዓሉ የሚሆን ሰንጋ በብድር የሚወስዱበት በብሔሩ ተወላጆች ዘንድ የኖረ የመተጋገዝና የመተሳሰብ እሴት አንዱ ነው። የሚፈልጉትን ሰንጋ ከመረጡ በኋላ እህል በሚደርስበት በታህሳስና በጥር ለመክፈል በዱቤ ይወስዳሉ። የበሬ ነጋዴውም ያለ ማንገራገር ሰንጋውን በመስጠት ወቅቱ ሲደርስ ገንዘቡን ለመውሰድ ተስማምቶ ይሰጥና ወቅቱን ጠብቆ ገንዘቡን ይወስዳል። በትውስት ተወስዶ ገንዘብ ያልከፈለ አባወራ ለቀጣይ የዘመን መለወጫ አይደርስም ተብሎ በብሔሩ ዘንድ ስለሚታመን በተስማሙበት ወቅት ገንዘቡን የመስጠት ግዴታቸው የተጠበቀ ነው። ሌላኛው አስተያየት ሰጪ የመምሪያው ባለሙያ አቶ ይዲድያ ተስፋሁን እንዳሉት በዓሉ ያለው ለሌለው አካፍሎ በጋራ የሚበላበትና ወደ አዲስ ዘመን በጠንካራ አብሮነት የሚሻገሩበት ነው። በመሆኑም የያሆዴ በዓል በዜጎች መካከል ጠንካራ አንድነትና አብሮነትን መሰረት ያደረጉ ዕሴቶች ያሉበት መሆኑን አንስተው ለትውልድ ግንባታ የሚሆኑ ዕሴቶችን አጎልብቶ መጠቀም እንደሚገባ ተናግረዋል ። ለበዓሉ ዋዜማ ከሚዘጋጁ ሁነቶች መካከል አተካና ልዩ ቦታ የሚሰጠው ነው። አተካና በተለይም ለዚህ በዓል ከዚህ ባሻገር ለትልልቅ እንግዶች ከሚዘጋጁ ምግቦች መካከል አንዱ ነው። አተካና ከወተት፣ ከቅቤ፣ አይብና ቡላ የሚዘጋጅና በበዓሉ የምግብ ፍላጎትን የሚከፍት ተበልቶ የማይጠገብ በእናቶች የሚዘጋጅ ጣፋጭ ምግብ ነው። የበዓሉ ዋዜማ አተካን ሂሞ (የአተካና ምሽት) የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን በዓሉን ለማክበር ከሩቅም ከቅርብም የተሰበሰበ ቤተሰብና እንግዶች በናፍቆት የሚመገቡት ምግብ ነው። በዚሁ ዕለት በአካባቢው ትልቅ የሚባል አባወራ (አዛውንት) ቤት ችቦ (ሳቴ ) ተዘጋጅቶ ማምሻውን አባቶች ወይም የሃገር ሽማግሌዎች የማቀጣጠያ (ጦምቦራ) ደመራ ማቀጣጠያ ይዘው ይወጣሉ። ከዚያም የአካባቢው ማህበረሰብም የሃገር ባህል ልብስ ለብሰው እንዲሁም ወጣቶች ተሰብስበው ያሆዴ ይጨፍራሉ። የሃገር ሽማግሌዎች ይመርቃሉ፤ ከዚያም የተዘጋጀውን ችቦ በእሳት ለኩሰው ያበራሉ። ይህም አዲስ ዘመን መግባቱን ማብሰርና ዓመቱ የብርሃን ዓመት እንዲሆን መልካም ምኞት የሚገለፅበት ነው። ደመራው ከተቀጣጠለ በኃላ ወጣቶች ያሆዴ (ኦሌ) ጭፈራ ሲጫወቱ ያነጋሉ። ይህ ጭፈራ ከያሆዴ በዓል ውጭ አይጨፈርም። ወጣት ደመቀ አባቴ የሆሳዕና ከተማ ነዋሪ ሲሆን ስለ በዓሉ አስተያየቱን ሲሰጥ ''በአባቶች ደመራው ከተቀጣጠለ በኃላ እኛ ወጣቶች ያሆዴ ....ያህዴ....ሆያ ሆ... /ኦሌ/ ጭፈራ እየተጫወትን እናነጋለን፤'' ይህ ጭፈራ ከያሆዴ በዓል ውጭ ስለማይጨፈር በዓሉን ቀን በጉጉት እንደሚጠብቁት ተናግሯል። ተራርቀው የቆየ ወዳጅ ዘመድ ተሰብስቦ ያለምንም ልዩነት ችግርም ካለ በዕርቅና ሰላምን በማውረድ የሚመጣው ዘመን የልምላሜና የስኬት እንዲሆን ተመራርቀው የሚለያዩበት በዓል በመሆኑ በተስፋ የሚጠብቁት እንደሆነ ነው ወጣቱ የሚናገረው። የበዓሉ እለት ለዕርድ የተዘጋጀው ሠንጋ ከቀረበ በኃላ የባህል ሽማግሌዎች (ጋቢማ ) ሥርዓት ያከናውናሉ። ክዋኔውም የበሬውን ሻኛ በለጋ ቅቤና በሠርዶ ሳር በመቀባትና ወተት በማፍሰስ ይከናወናል። ይህም በሚከናወንበት ወቅትም ክፉ ቀን አይምጣ፣ ርሃብ ሰቀቀን ይጥፋ፣ ጥጋብ ይስፈን፣ በአካባቢው በሃገሩ ጥጃ ይቦርቅ፣ ልጅ ይፈንጭበት፣ አገር ሰላም፣ ገበያ ጥጋብ ይሁን፣ ሰማይና ምድሩ ይታረቁን በማለት (ፋቴ) ዳግም ምርቃት ፈጽመው በሬው ይጣልና የዕርድ ሥርዓት ይካሔዳል። በዕለቱም ከታረደው ሥጋ ቅምሻ በጋራ ይበሉና ቀሪውን ለማህበሩ (ለቱታ) አባላት ክፍፍል ይፈፀማል። ከእርድ ሥርዓቱ በኃላ በማግስቱ ልጆች ወደ ወላጆቻቸው ዘራሮ የሚባል አበባ ይዘው እየጨፈሩ ያስማሉ -ይመረቃሉ የመስቀል አበባ እንደሚኖር ኑሩ ይባባላሉ፤ ከስጋውም ፣ከቦርዴውም ፣ ከአተካናውም የሚመገቡበት ክዋኔ (ሚክራ) በመባል ይታወቃል። ትዳር የያዙ ሴት ልጆችም ከባሎቻቸው ጋር ሆነው ወደ ወላጆቻቸው ምግብ ሰርተው፣ የሹልዳ ስጋና (ዘራሮ) አደይ አበባ ጭምር ይዘው የሚሔዱበት እንዲሁም ያላገቡ ወጣቶች ለትዳር የሚሆናቸውን አጋር የሚፈልጉበትና የሚያጩበት ባህልም ያለው ነው ያሆዴ ክብረ በዓል። ከእርድ ስነ ስርዓቱ በኋላ ከሶስት ሳምንታት እስከ ወር ለሚሆን ጊዜ የመጠያየቂያና የመረዳጃ ወቅት ይሆናል። የያሆዴ በዓል ያሉ ዕሴቶች ለህዝብ ትስስር፣ ጠንካራ የስራ ባህልና ዘላቂ ሰላም ግንባታ ያላቸውን ሚና ለማላቅ በልዩ ትኩረት ሊሰራ እንደምገባ የሚያነሱት በዋቸሞ ዩኒቨርስቲ የህዝብ ግንኙነትና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የአቶ ዳንኤል ገዴ በዚህ ላይ በአከባቢው ያሉ የማህበረሰብ ልምዶችና ወጎች ለትውልድ እንዲሸጋገሩ መስራትና የሃገር በቀል ዕውቀትን ማጠናከር እንደምገበባ ተናግረዋል። በዚህ ረገድ የዋቸሞ ዩኒቨረሲቲ የሃድያን ብሔር የዘመን አቆጣጠር ታሪክ : ባህልና ቋንቋ እንዲሁም ሌሎች ዕሴቶች ተሰንደው እንዲቀመጡና ለማስተማሪያነት እንዲውሉ ለማስቻል በጥናትና ምርምርና የተደገፈ ስራ በመስራት ላይ መሆኑን አመላክተዋል። በተጨማሪም ባህሉ ይበልጥ እንዲታወቅና በዩኔስኮ ተመዝግቦ ለአካባቢው ማህበረሰብ የሚገባውን ጥቅም እንዲያመጣና ከቱሪዝም አንጻር ሚናውን እንዲጫወት ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛል ብለዋል።
የመኔ ሸድዬ ባሮ - የጠንካራ የስራ ባህል፣ የአብሮነትና የሰላም ተምሳሌት
Sep 20, 2023 743
በሽመልስ ጌታነህ (ኢዜአ) የመኔ ሸድዬ ባሮ የካፈቾ ብሄር ከአሮጌው ዘመን ወደ አዲሱ የሚሸጋገሩበት፣ የአዲስ ዘመን ብስራትና የዘመን መለወጫ በዓል ነው። በዓሉ የጠንካራ የስራ ባህል፣ የአብሮነትና የሰላም ተምሳሌት በዓል እንደሆነ ይነገርለታል። በዚህም የካፋ ብሄር ለዘመናት የገነባውና ጠንካራ የስራ ባህል፤ ተፈጥሮን የመጠበቅና የመንከባከብ እንዲሁም ከተለያዩ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ጋር ተቻችሎና ተፈቃቅሮ የሚኖር ሲሆን ቱባ ዕሴቱ ዛሬም ላለው ትውልድ መሰረት መሆኑን ያምኑበታል። የተለያዩ የታሪክ ድርሳናት እንደሚያሳዩት ከሆነ የካፋ ህዝብ ጠንካራ ንጉሳዊ ሥርዓት የነበረው፤ የታሪክና የቱባ ባህል ባለቤትም ነው። ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የታሪክ ባለሙያና የሀገር ሽማግሌ አቶ አሰፋ ገብረማሪያም የካፈቾ ብሄር ዘመን መለወጫ በሃገሬው አጠራር ''የመኔ ሸድዬ ባሮ'' በዓል የካፋ ህዝብ ከሚያከብራቸው በርካታ በዓላት ውስጥ ትልቅ ሥፍራ የሚሰጠው መሆኑን አፅንኦት ሰጥተው ይናገራሉ። በዓሉ ያለውን ግዝፈት ሲያመለክቱ በሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በውጭ ፀሐፍት ጭምር “ታላቁ በዓል ወይም (ግሬት ፌስቲቫል)” ተብሎ እንደሚጠራም ተናግረዋል። በዓሉ ታሪካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ዳራ ያለው ሲሆን ከጥንት ካፋ ንጉስ ጀምሮ በየአመቱ በድምቀት የሚከበር በዓል እንደሆነም ጠቁመዋል። የካፋ ህዝብ ከ14ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ከጎሳ መሪነት አንስቶ ጠንካራ የመንግስት መዋቅር የነበረው ታላቅ ህዝብ እንደሆነ ያነሱት አቶ አሰፋ፣ በዚህም በዓሉ በዘመኑ የነበሩ መንግስታት በዓል እንደነበረም አብራርተዋል። ዓመታዊ የሥራ አፈፃፀም የሚገመገምበት ጥሩ የሠራና የተሻለ አፈጻጸም ያስመዘገበ የሚሸለምበትና ለበለጠ ሥልጣን የሚታጭበት፤ ሰነፉ ደግሞ የሚወቀስበትና ስልጣኑ የሚነጠቅበት ታላቅ በዓልም ነው ብለዋል። ይህም በብሄሩ ዘንድ ለዘመናት የተሻገረ የጠንካራ የሥራ ባህል ግንባታ መሰረት ሆኖ የቆየ መሆኑን አንስተዋል። ይህ ሁሉ ሲከናወን በማህበረሰባዊ የህግ ተገዥነት መሰረት መሆኑ የተለየ እንደሚያደርገው ገልጸው ከሁሉ በፊት ሰላምን በማስቀደም መንግስትንና ህግን ማክበር እንዲሁም ህግ የሚመራው ህዝብ የበላይ መሆኑን አመላካች ሥርዓት መሆኑን አንስተዋል። በዓሉ ከአዝመራ ጋር የተያያዘ የዘመን አቆጣጠርን ተከትሎ እንደሚከበርም የታሪክ ባለሙያው አቶ አሰፋ ይገልጻሉ። እንደ ታሪክ ተመራማሪው ገለጻ የካፋ ህዝብ አብዛኛው አርሶ አደር አልፎም አርብቶ አደር ሲሆን ለአዝመራ የተለየ ትኩረት ይሰጣል፤ በዓሉ ሊከበር 77 ቀናት ሲቀሩት ህዝቡ የአዲስ ዘመን መለወጫ ብሎ ሃምሌ አንድ አዝመራውን እንደሚጀምርም ጠቁመዋል። የአዝመራ ወቅት ሊገባደድ 25 ቀናት ሲቀሩት (ከሼ ዋጦ) ብሎ አዝመራውን ያጠናቅቃል። ወቅቱም ጨለማው አልፎ በብርሃን የሚተካበት፤ ክረምቱ ለበጋ ቦታውን የሚለቅበት በመሆኑ አዲስ አመት መድረሱን ያሳውቃል። ያን ጊዜ በጥንት የካፋ ምክርቤት ከሚገኙ ሰባት የሚክረቾ አባላት ውስጥ አንዱ የሆነው አዲዬ ራሾ ፤ የንጉሱ መቀመጫ በሆነው ቦንጌ ሸምበቶ በዓሉን ለማክበር ከየአቅጣጫው ለሚመጣው ህዝብ መንገዶችን በማፅዳት እና ለወንዞች ድልድይ በማበጀት በዓሉ መድረሱን ያበስራል። ያን ጊዜ በዓሉን ለማክበር ህዝብ ከያለበት አቅጣጫ ወደ ቦንጌ ሸምበቶ ይተማል። ህዝቡ በቦንጌ ሸምበቶ ከተሰበሰበ በኋላም ንጉሱ በተገኙበት የእያንዳንዱ ወራፌ ራሾ ሥራ ይገመገማል፤ ጥሩ ሥራ የሠራ ጠንካራ መሪ ይሸለማል፤ ለበለጠ ስልጣንም ይታጫል፤ ሀላፊነቱን በተገቢ ሁኔታ ያልተወጣው ደግሞ ይመከራል፣ ይወቀሳል አልፎም ስልጣኑን ይነጠቃል። ዛሬም ሀገራችን ይህ አይነቱን ጠንካራ የሥራ ባህል አብዝታ ትሻለች፤ እንዲህ አይነት ሀገር በቀል ዕውቀቶች ትውልዱን በጠንካራ ሥነ-ምግባርና የሥራ ባህል ለመገንባት ትልቅ ድርሻ አላቸው። በተጨማሪም በዓሉ ቅሬታዎችን ለመፍታትና ሰላምን ለማጠናከር ትልቅ አስተዋፅኦ አለው ፤ ቂምና ጥላቻን ይዞ ወደ ንጉሱ ፊት መቆምም ይሁን ወደ አዲሱ ዓመት መሻገር ነውር ተደርጎ የሚወሰድ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ወደ በዓሉ ከመምጣቱ አስቀድሞም ይሁን በበዓሉ ወቅት የተጣላ ይታረቃል፤ ጥላቻም በፍቅር ይተካል ብለዋል የታሪክ ተመራማሪው። እንዲህ አይነቱ ሀገር በቀል ዕውቀት ጠንካራ ባህል ለመገንባት፤ ቅራኔዎችን በሰላም ለመፍታትና ማህበራዊ ግኑኝነቶችን ለማጠናከር ትልቅ ፋይዳ ስላላቸው በትምህርት ሥርዓት ውስጥ አካቶ ማስተማርና ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ ይገባል ሲሉም ሃሳባቸውን አካፍለዋል። ሌላኛው የሀገር ሽማግሌና የካፋ፣ጫራ እና ናኦ የባህል ምክርቤት አባል አቶ ፀጋዬ ገብረማሪያም እንደሚሉት የካፋቾ ''የመኔ ሸድዬ ባሮ'' በዓል ማህበራዊ ግንኙነትን በማጠናከሩ ረገድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው በዓል ነው። ምክንያቱ ደግሞ፣ በዓሉን ለማክበር በአካባቢው ያሉ፣ በሌሎች የሃገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ እንዲሁም ባህር ማዶ የሚገኙ የአካባቢው ተወላጆች የሚሰበሰቡበት ታላቅ በዓል ስለሆነ ነው ብለዋል። በዚህም የተራረቀ የሚገናኝበት፤ የተጠፋፋ የሚጠያየቅበት ሲሆን ህዝቡ በአንድ ላይ ተሰብስቦ በንጉሱ ተመርቆ፣ በልቶ ጠጥቶ እንዲሁም ተጫውቶ ወደ ቀጣዩ አመት በደስታና በታላቅ ተስፋ የሚሸጋገርበት እንደሆነም አብራርተዋል። ይህ ባህል በተለያዩ ምክንያቶች ከ120 ዓመታት በላይ ሳይከበር እንደቆየ የገለፁት አቶ ፀጋዬ ገብረማሪያም ዳግም መከበር ከጀመረበት ስምንት ዓመታት ወዲህ የነበረውን ታሪክና ባህል በሚያስቀጥል መልኩ በየዓመት በድምቀት እየተከበረ መሆኑንም አንስተዋል። ወጣቱ ትውልድ ባህሉንና ታሪኩን አውቆ እንዲኖርና እንዲያስቀጥል ግንዛቤ የመፍጠርና የማስተማር ሥራ በሰፊው እየተሠራ እንደሆነም ገልፀዋል። ከዚህ ባለፈም ባህሉንና ታሪኩን ለማስቀጠል የባህል ምክር ቤቱ የወረዳ የባህል ምክር ቤቶችን የማጠናከር፣ ታሪካዊ ቅርሶችን የመሰብሰብና የማደራጀት ሥራ እየሠራ ነውም ብለዋል። በዓሉ አንድነትን የሚያጠናክር፣ ጠንካራ የሥራ ባህልን የሚያበረታታ እና የተፈጥሮ ጥበቃን የሚያጠናክር በመሆኑ ከካፋ ብሔረሰብ በዓልነቱ ባለፈ የሀገርና የአለም ቅርስና ሀብት እንዲሆን ሰፊ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባም አቶ ፀጋዬ አሳስበዋል። የካፋቾ ዘመን መለወጫ በዓል (የመኔ ሸድዬ ባሮ) መሠረቱን ሳይለቅ ለትውልድ እንዲተላለፍ በዞን ደረጃ እየተሠራ መሆኑን የገለፁት የካፋ ዞን ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ሃላፊ አቶ ተሾመ አምቦ ዘንድሮም ለዘጠነኛ ጊዜ በአደባባይ ለማክበር ሰፊ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል። በዓሉ በሁሉም የካፋ ህዝብ በጋራ ያለምንም ልዩነት የሚከበር ታሪካዊ በዓል ሲሆን አለም አቀፋዊ እውቅና አግኝቶ በዩኔስኮ እንዲመዘገብ ለማስቻል ከተለያዩ ምሁራንና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በመሆን የተለያዩ ጥናቶች እየተሠሩ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ በበዓሉ ንጉሱ የተራቡትን የሚመግቡበት (ጮንጎ) የተሰኘ ስርዓት የሚፈፀምበትና የተጣሉ የሚታረቁበት ስርዓት እንደሚፈፀም የገለፁት አቶ ተሾመ አሁንም በዓሉ በየዓመቱ ሲከበር ይህ ሥርዓት ይከወናል ብለዋል። ቀጣይ ይህን በዓል በሰፊው አስተዋውቆ ወደ ቱሪዝም በማሳደግ ህዝቡ ከዘርፉ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆን የሚያስችሉ ሥራዎች እንደተጀመሩም ሃላፊው ገልፀዋል። የዘንድሮው የ2016 ዓ.ም የካፊቾ ዘመን መለወጫ በዓል በቦንጋ ከተማ ከመስከረም 12 እስከ መስከረም 13/2016 ዓ.ም በፓናል ውይይትና በተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች በደማቅ ሁኔታ እንደሚከበርም ጠቁመዋል።
ልዩ ዘገባዎች
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 5008
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 9997
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት። እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
በጂንካ ከተማ የተመረተው 23 ኪሎ ግራም የሚመዝነው የስኳር ድንች "በአፍሪካ ትልቁ ስኳር ድንች" በሚል ተመዘገበ
Mar 13, 2023 3495
ጂንካ መጋቢት 4/2015 (ኢዜአ):- በጂንካ ከተማ ደሙዝ ሰፈር የተመረተው እና 23 ኪሎ ግራም የሚመዝነው ስኳር ድንች በአፍሪካ የድንቃ ድንቆች መዝገብ "በአፍሪካ ትልቁ ስኳር ድንች" በሚል መመዝገቡ ተገለጸ። በአዲስ አበባ በተካሄደው የእውቅና ስነስርዓት ላይ የአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ስራ አስኪያጅ አቶ አሸናፊ አለም ለስኳር ድንቹ ባለቤት አቶ ኢሳያስ ጊዜአለው የእውቅና ምስክር ወረቀት አስረክበዋል። ከዚህ ቀደም በአፍሪካ 10 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች መቅረቡን አቶ አሸናፊ ለኢዜአ ገልጸዋል። “ነገር ግን 23 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች በአፍሪካ ደረጃ ሲቀርብ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው” ብለዋል። በዓለም የድንቃ ድንቅ መዝገብ 37 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች መመዝገቡንና በደሙዝ ሰፈር የተገኘው ስኳር ድንች በ14 ኪሎ ግራም ዝቅ ብሎ ከዓለም የ”ሁለተኛነት” ደረጃ ላይ እንደሚያስቀምጠው አመልክተዋል። የስኳር ድንቹ ባለቤት አቶ ኢሳያስ ጊዜያለው ስኳር ድንቹ በአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ላይ በመስፈር የኢትዮጵያን ስም በማስጠራቱ መደሰታቸውን ገልጸዋል። ስኳር ድንቹ እውቅና እንዲያገኝ የዜና ሽፋን ለሰጠው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ምስጋቸውን አቅርበዋል። ኢዜአ የካቲት 19 ቀን 2015 ዓ.ም “በጂንካ ከተማ ደሙዝ ሰፈር 23 ኪሎ ግራም የሚመዝን አንድ የስኳር ድንች መመረቱ ተገለጸ” በሚል መዘገቡ የሚታወስ ነው።
ዶክተር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ እውቅና አገኙ
Mar 9, 2023 4323
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 30/2015 የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ በሩዋንዳ ኪጋሊ በተካሄደው በአፍሪካ ዓለም አቀፍ የጤና አጀንዳ ኮንፈረንስ (AHAIC)2023 ላይ እውቅና ተሰጣቸው። ሚኒስትሯ በሩዋንዳ ኪጋሊ ትላንት በተካሄደው Africa Health Agenda International Conference (AHAIC) 2023 ላይ የተበረከተላቸውን Women in Global Health Award የእውቅና ሽልማት በተወካያቸዉ በኩል ተቀብለዋል። እውቅናው በጤና ልማት ውስጥ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በመቋቋምና በመፍታት፣ የጤና አገልግሎት ጥራትና ፍትሀዊ ተደራሽነት እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ሽፋን ላይ ትኩረት ሰጥተው ለሚሰሩ አመራሮች የሚሰጥ መሆኑም ተመላክቷል። ለመጪዎቹ ትውልዶች አርዓያ ለሆኑ የአፍሪካ ሴት መሪዎች የሚሰጠው ሽልማቱ የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰም ለዜጎች የተሻለና ዘላቂ ጤናን ለማምጣት በሚደረግ ጥረት ውስጥ ላበረከቱት የላቀ የመሪነት ሚና ከአምሪፍ ሄልዝ አፍሪካ እውቅናውን አግኝተዋል።
መጣጥፍ
“ዮ-ማስቃላ''- ሁሉም የሚደሰትበት በዓል
Sep 23, 2023 208
በሳሙኤል አየነው የሰላም፣ የአብሮነት፣ የፍቅር፣ የመቻቻልና የአንድነት ተምሳሌት የሆነው የጋሞ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል “ዮ-ማስቃላ” ከወርሃ መስከረም አጋማሽ ጀምሮ በተለያዩ ባህላዊ ሁነቶች በድምቀት ይከበራል ። በተለያየ ምክንያት በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ተራርቀው የነበሩ ወገኖች ወደ የአካባቢያቸው በመመለስ ከቤተሰቦቻቸው ብሎም ከቀየው ህብረተሰብ ጋር አብረው የሚያከብሩት የዓመቱ ታላቅ በዓል ነው ። ታዲያ በዓሉን በድምቀት ለማክበር ወንዶች ሰንጋ በሬ ለመግዛት እንዲሁም ለትዳር አጋሮቻቸውና ለልጆቻቸው ልብስና ጌጣ ጌጥ የሚሆን ገንዘብ መቆጠብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ሴቶችም ለባህላዊ ምግቦች፣ ለቅመማ ቅመም፣ ለቅቤና ለባህላዊ መጠጦች እህል ግዥ የሚሆን ገንዘብ ዓመቱን ሙሉ ሲቆጥቡ ይከርማሉ። መስከረም ወር ከገባበት ዕለት አንስተው ወንዶችም ሆኑ ሴቶቹ በቆጠቡት ገንዘብ በየፊናቸው ለበዓሉ የሚሆኑ ቁሳቁሶችን ማቅረብ ይጀምራሉ። ይህም የዝግጅት ጊዜ “እንግጫ” በመባል ይጥራል። በ”ዮ--ማስቃላ” ጊዜ አብሮነት እንጂ ግለኝነት የሚባል ነገር በጋሞዎች ዘንድ ፈጽሞ አይታሰብም፤ አብሮ እርድ ማካሄድ፣ አብሮ መመገብ፣ አብሮ መጠጣት፣ አብሮ መጫወት የጋሞዎች መገለጫ ነው። እንደ ሌሎቹ በዓላት ሁሉ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ወገኖችም በዓሉን እንዴት እናሳልፍ የሚል ስጋት አያድርባቸውም። ምክንያቱም የሌለውም ካለው ጋር አብሮ የሚቋደስበት፣ የሚደሰትበት፣ የሚተሳሰብበትና የሰብአዊነት ልክ የሚንጸባረቅበት ልዩ ድባብ ያለው በዓል ነውና ዮ-ማስቃላ ። የጋሞ የሀገር ሽማግሌ አቶ አመሌ አልቶ ስለ “ዮ--ማስቃላ” በዓል በትንሹ እንዲያወጉን ጠይቀናቸው በዓሉ ለሰው ልጆች ብቻ ሳይሆን እንስሳትና አዕዋፋት ሁሉ የሚደሰቱበት እንደሆነ ነግረውናል። በአካባቢው ቋንቋ ተፈጥሮ ሁሉ በዓሉን በደስታ እንደሚያሳልፍ ለመግለጽ “ካፎስ ካናስ ማስቃላ” በማለት የሚገለጽ ስሆን “ለሰው ብቻ ሳይሆን ለእንስሳትም መስቀል ነው” እንደማለት ነው ብለዋል። በዓሉ ከመድረሱ ከሶስት ወራት አስቀድሞ በየአካባቢው ለእንስሳት የግጦሽ ሥፍራ ተከልሎ የሚዘጋጅ ሲሆን ችቦው በሚለኮስበት በደመራው ዕለት የቤት እንስሳት በሙሉ በዚያው የሚሰማሩ ይሆናል። ዓመቱን ሙሉ ሲያርሱ የነበሩ የእርሻ መሣሪያዎችም በበዓሉ ጊዜ ታጥበውና በቅቤ ታሽተው በክብር ይቀመጣሉ። ክብር ለሰው ልጆች ብቻ ሳይሆን ለእንስሳትና ለእርሻ መሣሪያዎችም ይሰጣል። በባህሉ መሠረት ችቦ በሚወጣበት ሰዓት አባት የራሱን ችቦ ለኩሶ የቤቱን ምሰሶ፣ የከብቶችን ጋጣና የበር ጉበኖችን ግራና ቀኝ በችቦው ጫፍ በማነካካት ወደ ውጭ ካወጣ በኋላ ወንድ ልጆች የየራሳቸውን ችቦ ተራ በተራ እየለኮሱ አባታቸውን ተከትለው “ዮ---ማስቃላ” እያሉ ወደ ደመራ ቦታ ያመራሉ። ከዚያም አባት በቅድሚያ ችቦውን ከለኮሰ በኋላ ልጆች ደግሞ ተከትለው ደመራውን ይለኩሳሉ። ከዚህ ፕሮግራም መልስ ወደ ቤት ተመልሰው የተዘጋጀውን ገንፎ በአንድ ወጭት ላይ “ዮ--ማስቃላ”እያሉ ሁሉም የቤተሰብ አባላት፣ ዘመድ አዝማድና ጎረቤት ተሰባስበው በጋራ ይመገባሉ። በ”ዮ--ማስቃላ” በዓል በዋናነት እርድ የሚከወን ሲሆን ቁርጥ፣ ጎረድ ጎረድ፣ ክትፎና የወጣ ወጥ ዓይነቶች ተሠርተው ለምግብነት ይቀርባሉ። ከባህላዊ ምግቦች ደግሞ የገብስ ቅንጬ፣ የቆጮና ገብስ ውህድ ቂጣ፣ የቡላ ፍርፍር፣ ሀረግ ቦዬ፣ እንዲሁም ከመጠጥ አይነቶች ደግሞ ቦርዴ፣ ጠላ፣ የማርና የቦርዴ ጠላ ውህድና ሌሎች ተወዳጅ ምግቦችና መጠጦች ይዘጋጃሉ። በ”ዮ--ማስቃላ” በዓል ዕለት የሚቀራረቡ ጎረቤታሞች በጋራ ሆነው አማካይ በሆነ ሥፍራ ላይ የእርድ ሥነሥርዓት ያከናውናሉ። የእርድ ሥነ-ሥርአቱም በደመራው ዕለትና ማግስት እንደ ህብረተሰቡ ይሁንታ የሚፈጸም ይሆናል። ከማግስቱ ጀምሮ የተዘጋጀውን ሥጋ በጋራ እየበሉና እየጠጡ የበዓሉን ድባብ የሚያስቀጥሉ ሲሆን “ዱንግዛ” በተሰኘው የጋሞ ባህላዊ ጥበብ ልብስ ደምቀው በጌጣጌጥ አሸብርቀው ሁሉም በየአደባባዩ በባህላዊ ጫዋታዎች እየተደሰተ በዓሉን ያከብራል። ሰላም፣ ፍቅር፣ አንድነትና አብሮነት ካለ በአዲሱ ዓመት ምድሪቱ ተገቢውን ምርት እንደምትሰጥ ሁሉም ሰው በተሰማራበት መስክ ውጤታማ እንደሚሆን ይታመናል። ከዚም የተነሳ በአሮጌው ዓመት ሃዘን ላይ የነበሩ ወገኖች ሙሉ በሙሉ ሀዘናቸውን በመተው በአዲስ መንፈስ ወደ መደበኛው ህይወት ይመለሳሉ። የተጣሉ ወገኖች ቂም ይዘው አዲስ ዓመትን መሻገር በጋሞዎች ዘንድ ነውር በመሆኑ በባህላዊ ሸንጎ ሥርአት /ዱቡሻ/ በጋሞ አባቶች አሸማጋይነት እርስ በርስ ተነጋግረው በመታረቅ አዲሱን ዓመት በጋራ ያበስሩታል። በሌላ መንገድ “ዮ..ማስቃላ” በዓል ተጠብቆ ወጣቶች የሚተጫጩበት፣ የተጫጩት ደግሞ ጋብቻ የሚከውኑበት እንዲሁም ያገቡት በየገበያው ዕለት “ሶፌ” የሚባል ሥነ-ሥርዓት በማከናወን በማህበራዊ ህይወት ማህበረሰቡን በይፋ የሚቀላቀሉበት መሆኑን ጋሽ አመሌ አውግተውናል። ጋሞዎች ከሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ጋር በመሆን በአብሮነት ለሁለት ሳምንታት በደስታ ካሳለፉ በኋላ ወደ ግብርና ሥራቸው በመመለስ ቀደም ሲል በክብር ያስቀመጧቸውን የእርሻ መሣሪያዎች በማንሳት ወደ እርሻ ሥራ ይገባሉ። እስከ ታህሳስ ወር መውጫ ድረስ የበዓሉ ድባብ ሳይጠፋ ይቆይና በመጨረሻም የመሰናበቻ ድግስ ወይም “ጮዬ ማስቃላ” በማዘጋጀት በህብረት ከተመገቡና ከጠጡ በኋላ የዓመት ሰው ይበለን፣ ዓመቱ የሰላም፣ የጤና፣ የበረከት ይሁን በማለት በመመራረቅ “ዮ--ማስቃላ”ን ይሸኛሉ። በዓሉ የህዝቡን ሰላም ፣አንድነትና አብሮነት የሚያንጸባርቅ ልዩ በዓል ነው በማለት የጋሞ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ሃላፊ አቶ ሞናዬ ሞሶሌ የጋሞ የሀገር ሽማግሌ የሆኑት የአቶ አመሌ አልቶን ሃሳብ ይጋራሉ። ባህላዊ እሴቱ ከትውልድ ወደ ትውልድ ተጠብቆ እንዲቆይ “ዮ--ማስቃላ” ትልቅ ድርሻ አለው። የባህል እሴቶች ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፉ በጥናትና ምርምር በማስገፍና የቋንቋና ባህል አውደ ጥናት በየዓመቱ እየተደረገ እንደሆነም ነግረውናል። አባቶች በልዩነት ውስጥ ያለንን አንድነት እንዳቆዩልን ሁሉ ወጣቶችም ኢትዮጵያዊ ለዛ ያላቸው የጋራ እሴቶች ሳይበረዙና ሳይከለሱ ጠብቀው ለትውልድ የማስተላለፍ ሃላፊነት አለባቸው የሚለውን የንግግራቸው ማሳረጊያ አድርገዋል።
የዕልፍ ሕጻናትን ዕጣ ፈንታ ከሞት ወደ ሕይወት የለወጠው ወጣት ላሌ ላቡኮ
Sep 8, 2023 611
በሀገራችን በርካታ አካባቢዎች የታዳጊዎችን ተስፋና ህልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የሚገዳደሩ ከባህላዊ እምነት ጋር የተቆራኙ አይነተ ብዙ ጎጂ ባህላዊና ልማዳዊ ድርጊቶች እና ክዋኔዎች አሉ። ለአብነትም ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የተለመደው እና ከህጻናት ጥርስ አበቃቅል ጋር የተያያዘው ’ሚንጊ' የሚሰኘው ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት ይጠቀሳል። በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣቸዋል። ከዚህ ጋር በማገናኘትም የሚወለዱ ህጻናት የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ከሆነ እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥመዋል። ይህ ልማድ “ሚንጊ” ተብሎ የሚጠራ ሲሆን አያሌ ህጻናትን ቀጥፏል። ይህ ብቻም ሳይሆን የማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። ሚንጊ ተብለው የተፈረጁ ህጻናት በማህበረሰቡ ዘንድ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… እንደሚያመጡ ስለሚቆጠር ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል ዕጣ ይገጥማቸዋል። ሚንጊንና መሰል በየማህበረሰቡ ዘንድ ለዘመናት የተለመዱ ጎጂ ድርጊቶችን ለማስቀረት እና ማህበረሰብ አቀፍ ለውጥ ለማምጣት ግን ውስብስብ እና ጊዜ የሚጠይቅ ጉዳይ ነው። ላሌ ላቡኮና መሰል ብርቱና አርቆ አሳቢ ሰዎች ግን ባደጉበት ብርቱ ጥረት የማህብረሰብን አስተሳስብ በመለወጥ ለዘመናት ለሚከወኑ ውስብስብ ችግሮችን መፍትኤ መስጠት ችለዋል። ላሌ ላቡኮ በተወለደበት ቀዬ እና አባል በሆነበት ደመ ከልብ ሆነው የሚቀሩ ህጻናትን ዕጣ ፈንታ ከወንዝ፣ ከገደልና ከጫካ ከመጣል ተርፈው ለወግና ማዕረግ እንዲበቁ አስችላል። በአጉል ባህል ሕይወታቸውን የሚነጠቁ ዕልፍ አዕላፍ ህጻናት ነፍስ እንዲዘሩ በማድረግ ትውልድ ያሻገረ፣ ማህበረሰብን የለወጠ አርበኛ ነው። ላሌ ላቡኮ ይህን ነባር ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት ለመቃወምና መፍትሄ ለማምጣት ያነሳሳው ሁለት እህቶቹን ጨምሮ ምንም ነፍስ ያላወቁ ሕጻናት በሚንጊነት ተፈርጀው ሲቀጠፉ በማየቱና በመስማቱ እንደሆነ ይናገራል። ከ17 ዓመታት በፊት ‘ኦሞ ቻይልድ’ በሚል ባቋቋመው ድርጅት 'ሚንጊ' የተባሉ 58 ሕፃናትን ከገዳዮች ፈልቅቆ ከሕልፈት ወደ ሕይወት ለውጧል፣ ለቁም ነገር ለማብቃትም እያስተማራቸው ይገኛል። እህቶቹን ጨምሮ የትውልድ መንደሩ ሕጻናትን ሕይወት ለመቀጠፍ የዳረጋቸው የሚንጊ ድርጊት የሚፈጸመው፣ በማህበረሰቡ ዕውቀት ማነስ ነው ብሎ ያምናል። በዚህም ይህን አስከፊ ድርጊት እና አስተሳሰብ ለመቀየር ቆርጦ በመነሳቱ ቤተሰቡን ጨምሮ ከማህበረሰቡ መገለል እስከ ማስፈራሪያ ጥቃቶች አስተናግዷል። እርሱ ግን ፈተናዎች ሳይበግሩት በዓላማው ጸንቶ፣ ትዕግስትና ብልሃት ተላብሶ ሸውራራ ማህበረሰብ አቀፍ አመለካከቶችን መስበር ችሏል። የሚንጊ ባህል አሁንም ሙሉ ለሙሉ እንዳልተቀረፈ የሚናገረው ላሌ፣ ስር ነቀል የአስተሳስብ ለውጥ ለማምጣት ለህብረተሰቡ አሁንም ብርቱ ግንዛቤ የመፍጠር ስራዎች እንደሚገቡ ገልጿል። ላሌ በመሰረተው ድርጅት ከሚማሩ ሕጻናት ባሻገር ከ300 በላይ ህጻናት ከቤተሰባቸው ዘንድ ሆነው ለመማር እንዲችለኩ ማድረጉንም ይናገራል። ሕፃናቱን ከሞት አፋፍ ታድጎ ከራሳቸው ሕልውና ባለፈ ለቁም ነገር እንዲበቁና ለሀገርና ለወገን የሚበጁ ሰዎች እንዲሆኑ በመስራቱ አዕምራዊ እርካታ እንደሚሰማው ይገልጻል። ላሌ የሚንጊን ጎጂ ድርጊት ከመታደጉ በተጨማሪ በደቡብ ኦሞ ትምህርት ቤት ገንብቶ ከ700 በላይ ተማሪዎችን እያስተማረ ይገኛል። ናሽናል ጂኦግራፊ፣ ቴድ ቶክ፣ የሰብዓዊ መብቶች ተቋም እና የበጎ ሰው ሽልማት ድርጅት የላሌን ትውልድ የመታደግ ተግባር ዕውቅና ከሰጡት ወስጥ ይጠቀሳሉ።