ቀጥታ፡

በፕሪሚየር ሊጉ ኢትዮጵያ መድን ከቅዱስ ጊዮርጊስ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው

አዲስ አበባ፤ የካቲት 18/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ21ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ዛሬ ይጀመራል።

 

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 15ኛ ሳምንት ዛሬ ይጀመራል

በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ኢትዮጵያ መድን ከቅዱስ ጊዮርጊስ ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ።

ኢትዮጵያ መድን በሊጉ ካደረጋቸው 20 ጨዋታዎች መካከል አራት ጊዜ ሲያሸንፍ ስምንት ጊዜ ሽንፈት አስተናግዷል። በስምንት ጨዋታዎች አቻ ተለያይቷል። በጨዋታዎቹ ላይ 12 ግቦችን ሲያስቆጥር 16 ጎሎች ተቆጥረውበታል። 

የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ መድን በ20 ነጥብ 17ኛ ደረጃን በመያዝ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። 

ተጋጣሚው ቅዱስ ጊዮርጊስ በበኩሉ 19 ጨዋታዎችን አከናውኖ በስድስቱ ድል ሲቀናው በሰባቱ ተሸንፏል። በቀሪ ስድስት ጨዋታዎች ነጥብ ተጋርቷል። 16 ግቦችን ከመረብ ጋር ሲያገናኝ 14 ጎሎችን አስተናግዷል።

የ16 ጊዜ የሊጉ አሸናፊ ቅዱስ ጊዮርጊስ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው በ24 ነጥብ 10ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ባለፉት ስድስት የሊጉ ጨዋታዎች ከድል የራቀው ኢትዮጵያ መድን ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ይጫወታል።
ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአራት ጨዋታዎች ያለማሸነፍ ጉዞ በኋላ ወደ ድል መንገድ ለመመለስ ይፋለማል።

ቡድኖች በመጀመሪያ ዙር ባደረጉት ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ 1 ለ 0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው።

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ21ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር እስከ የካቲት 21 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።

ሲዳማ ቡና በ36 ነጥብ ሊጉን እየመራ ነው።

የቅዱስ ጊዮርጊሱ አቤል ያለው እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንኩ አዲስ ግደይ የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን በተመሳሳይ ስምንት ግቦችን በማስቆጠር እየመሩ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም