ቀጥታ፡

ኒውካስትል ዩናይትድ ቦዶ ግሊምት እና ባየር ሌቨርኩሰን ወደ ጥሎ ማለፍ ገብተዋል

አዲስ አበባ፤ የካቲት 18/2018 (ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ማጣሪያ ሶስት የመልስ ጨዋታዎች ተደርገዋል።



ኒውካስትል ዩናይትድ ካራባግን 3 ለ 2 አሸንፏል።

አትሌቲኮ ማድሪድ ጥሎ ማለፉን ተቀላቀለ

በሴንት ጀምስ ፓርክ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሳንድሮ ቶናሊ፣ ጆሊንግተን እና ስቬን ቦትማን የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ካሚሎ ዱራን እና ኤልቪን ጃፋርኩሊየቭ ለካራባግ ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

ኒውካስትል ዩናይትድ በድምር ውጤት 9 ለ 3 በማሸነፍ ጥሎ ማለፉን ተቀላቅሏል።

በሌላኛው መርሐ ግብር ቦዶ ግሊምት ኢንተር ሚላንን 2 ለ 1 አሸንፏል።



በሳን ሲሮ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ጀንስ ፒተር ሃውግ እና ሃልኮን ኢቭጄን የማሸነፊያ ግቦችን አስቆጥረዋል።

አሌሳንድሮ ባስቶኒ ለኢንተር ሚላን ብቸኛውን ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ቦዶ ግሊምት በድምር ውጤት 5 ለ 2 በመርታት ጥሎ ማለፍ ገብቷል።

የሶስት ጊዜ የውድድሩ አሸናፊ ኢንተር ሚላን ጥሎ ማለፍ ሳይገባ ከውድድሩ ተሰናብቷል።

ባየር ሌቨርኩን ከኦሎምፒኮሶ ጋር ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።

የጀርመኑ ክለብ በአጠቃላይ ውጤት 2 ለ 0 በማሸነፍ 16 ውስጥ ገብቷል።

ዛሬ አስቀድሞ በተደረገ ጨዋታ አትሌቲኮ ማድሪድ ክለብ ብሩዥን በድምር ውጤት 7 ለ 4 አሸንፎ ጥሎ ማለፉን ተቀላቀለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም