በጠቅላላ ምርጫው ዕድሜያቸው ለመምረጥና ለመመረጥ የደረሱ አካል ጉዳተኞች ንቁ ተሳትፎ ያደርጋሉ - ኢዜአ አማርኛ
በጠቅላላ ምርጫው ዕድሜያቸው ለመምረጥና ለመመረጥ የደረሱ አካል ጉዳተኞች ንቁ ተሳትፎ ያደርጋሉ
ወላይታ ሶዶ ፤ የካቲት 18/2018(ኢዜአ)፦ በ7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ ዕድሜያቸው ለመምረጥና ለመመረጥ የደረሱ አካል ጉዳተኞች ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ እየሰራ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን ገለጸ።
መገናኛ ብዙኃን ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬት አገራዊ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ደነቀ ዳጮ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ፌዴሬሽኑ በጠቅላላ ምርጫው ዕድሜያቸው ለመምረጥና ለመመረጥ የደረሱ አካል ጉዳተኞች ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ እየሰራ ነው።
አካል ጉዳተኞች የምርጫ ካርድ ወስደው ድምፃቸውን እንዲሰጡና በታዛቢነት እንዲሳተፉ እንዲሁም ዕጩ ተመራጭ እንዲሆኑ ግንዛቤ ከመፍጠር ጀምሮ ከምርጫ ቦርድና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን እየተሰራ ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድም ለአካል ጉዳተኞች ምርጫውን አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጥ ተግባር እንዲያከናውን ዝግጅት መደረጉን ጠቅሰዋል።
በዞኑ የአካል ጉዳተኞችን ፖለቲካዊ ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን የገለፁት ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ህብስት መንክር ናቸው።
ለዚህም ከምርጫ ቦርድ ጋር በቅርበት እየሰሩ እንደሚገኙ ጠቁመው በምርጫ አዋጆች እና ደንቦች መሰረትም ታዛቢዎችን የመመልመል ስራ መሰራቱን አመልክተዋል።
ምርጫው አካታች፣ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ፍትሃዊ ሆኖ እንዲካሄድ የበኩላቸውን እንደሚወጡም ጠቁመዋል።
የጌዴኦ ዞን አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት መምህር ተሰማ ዎሬራ በበኩላቸው፤ በዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ ላይ ተሳትፎ የሚያደርጉ ሰባት ታዛቢዎችን ለይተው ማሳወቃቸውን ተናግረዋል።