ቀጥታ፡

የእስራኤሉ ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 18/2018(ኢዜአ)፦ የእስራኤሉ ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።

ዘመናትን የተሻገረው የኢትዮ-እስራኤል ታሪካዊ ትስስር

ፕሬዝዳንቱ ቦሌ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) እና ሚኒስትር ዴኤታው አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ አቀባበል አድርገውላቸዋል።


 

ፕሬዝዳንቱ በአዲስ አበባ በሚኖራቸው ቆይታ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ዙሪያ ከመንግሥት ከፍተኛ መሪዎች ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም