ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
ቼልሲ ሊያም ሮሲኒየርን አሰናበተ
Apr 22, 2026 351
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 14/2018 (ኢዜአ)፦ የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ዋና አሰልጣኙን ሊያም ሮሲኒየርን ከኃላፊነት ማሰናበቱን በይፋ አስታውቋል። አሰልጣኙ በስታምፎርድ ብሪጅ በነበራቸው ቆይታ ክለቡን መምራት የቻሉት ለአራት ወራት ብቻ ሲሆን፣ ይህ ውሳኔ የተላለፈው ቡድኑ እያሳየ ባለው እጅግ ደካማ ውጤት ምክንያት መሆኑን ቢቢሲ ክለቡን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል። በሮሲኒየር መሪነት ቼልሲ ካለፉት ዘጠኝ የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው በአንዱ ብቻ ሲሆን፣ በተለይም ባለፉት አምስት ጨዋታዎች ቡድኑ ምንም አይነት ግብ ሳያስቆጥር መሸነፉ ለአመራሮቹ ትዕግስት ማጣት ዋነኛ ምክንያት መሆኑ ተገልጿል። ቼልሲ ትናንት በሊጉ በብራይተን 3 ለ 0 መሸነፉ ይታወቃል። ሮሲኒየር የስድስት ዓመት ተኩል ረጅም ኮንትራት ፈርመው ወደ ክለቡ ቢመጡም፣ ቼልሲን በደረጃ ሰንጠረዡ ወደ ሰባተኛ ደረጃ ዝቅ ማድረጋቸው እና የቻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎ እድላቸውን አደጋ ላይ መጣላቸው ለስንብቱ ምክንያት ሆኗል። ክለቡ ለሮሲኒየር እና ለረዳቶቻቸው በቆይታቸው ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋናውን አቅርቧል። በመጪው እሁድ ቼልሲ ከሊድስ ዩናይትድ ጋር ለሚያደርገው የኤፍ ኤ ካፕ (FA Cup) የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ፣ ካሉም ማክፋርሌን ቡድኑን በጊዜያዊ አሰልጣኝነት እንደሚመሩ ክለቡ አስታውቋል። ቼልሲ በአሁኑ ወቅት ቋሚ አሰልጣኝ ለመቅጠር ጥረት እያደረገ ሲሆን፣ ይህም በባለቤቱ ቶድ ቦህሊ ዘመን አምስተኛው አሰልጣኝ እንደሚሆን ቢቢሲ ዘግቧል።
ተሻሽሎ የፀደቀው የኢትዮጵያ አቪዬሽን ሴኪዩሪቲ አዋጅ የሀገራችንን የአየር ትራንስፖርት ዕድገት አንድ ደረጃ ከፍ ያደርገዋል
Apr 22, 2026 476
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 14/2018(ኢዜአ)፦ ተሻሽሎ የፀደቀው የኢትዮጵያ አቪዬሽን ሴኪዩሪቲ አዋጅ የሀገራችንን የአየር ትራንስፖርት ዕድገት አንድ ደረጃ ከፍ እንደሚያደርገው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ገለጸ። 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 15ኛ መደበኛ ስብሰባ የኢትዮጵያ አቪዬሽን ሴኪዩሪቲ አዋጅን ለማሻሻል የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ 1412/18 መርምሮ አጽድቋል፡፡ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለኢዜአ በላከው መረጃ እንዳመለከተው፤ ከ21 ዓመታት በኋላ ተሻሽሎ የፀደቀው የኢትዮጵያ አቪዬሽን ሴኪዩሪቲ አዋጅ ተቋሙ የአቪዬሽን ደኅንነት ሥራዎችን በበላይነት ለመምራት እና ለማስተባበር የተሰጠውን ሀገራዊ ተልዕኮ ከስያሜው አንስቶ በግልፅ ያካተተ ሲሆን፤ የሀገራችንን የአየር ትራንስፖርት ዕድገት አንድ ደረጃ ከፍ ለማድረግ ያግዛል፡፡ የአቪዬሽን ደኅንነትን ለማጠናከር ትኩረት ከሚሰጣቸው ጉዳዮች ውስጥ የመጀመሪያው የሕግ ማዕቀፍ መሆኑንም አገልግሎቱ በመረጃው አመላክቷል። በዚህ ረገድ ነባሩ አዋጅ ኢንዱስትሪውን በሚፈለገው ደረጃ ለማሳደግ ተግዳሮት ሆኖ ከመቆየቱም በላይ የዓለም አቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት (ICAO) ተቀጽላ 17 ስታንዳርዶችን ሳያካትት መቆየቱንም ጠቁሟል፡፡ ተሻሽሎ የፀደቀው አዋጅ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የተሰጠውን የአቪዬሽን ደኅንነትን የማረጋገጥ ሀገራዊ ተልዕኮ በላቀ ብቃት ከመወጣት አንፃር የጥራትና የቁጥጥር ስራዎች ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን ጠብቀው እንዲከናወኑ የሚያስችሉ ሕጎችን መያዙም ተመላክቷል፡፡ አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ በአቪዬሽን ደኅንነት ረገድ ላስቀመጠው ራዕይ እና ስትራቴጂክ ግብ ስኬት መሰረት የሚጥል መሆኑም ጠቅሷል፡፡ ከቴክኖሎጂ አንፃር ኢንዱስትሪውን ለማዘመን አስፈላጊ የሆኑ ባለድርሻ አካላትን በኮሚቴነት መጨመሩ፤ የዓለም አቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ስታንዳርዶችን በአዲስ መልክ ማካተቱ፤ የአየር መንገዱን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ እገዛ የሚያደርግ መሆኑና ከኢንዱስትሪው ፈጣን እድገት ጎን ለጎን ለመጓዝ አቅም መፍጠር የሚያስችል የሕግ ድጋፍ መስጠቱ በፋይዳነት የሚጠቀሱ መሆናቸውንም በመረጃው ተገልጿል፡፡ የተሻሻለው የኢትዮጵያ አቪዬሽን ሴኪዩሪቲ አዋጅ ቁጥር 1412/18 በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሚያዝያ 13 ቀን 2018 ዓ.ም በአብላጫ ድምጽ መጽደቁንም አገልግሎቱ በመረጃው አመልክቷል፡፡
በተተገበሩ የሪፎርም ስራዎች የግብርና ዘርፉን ወደ ሜካናይዜሽን ማሸጋገር ያስቻሉ ተጨባጭ ወጤቶች ተመዝግበዋል
Apr 22, 2026 335
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 14/2018 (ኢዜአ)፡- ባለፉት የለውጥ ዓመታት በኢትዮጵያ የተተገበሩ የሪፎርም ስራዎች የግብርና ዘርፉን ወደ ሜካናይዜሽን ማሸጋገር ያስቻሉ ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸውን የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ ገለጹ። የ2018 በጀት ዓመት ሦስተኛው የመቶ ቀናት እና የዘጠኝ ወራት ስራ አፈጻጸም ሪፖርት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተገምግሟል። የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ በሰጡት ማብራሪያ፣ በኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት የተተገበሩ የሪፎርም ስራዎች የግብርና ዘርፉን ወደ ሜካናይዜሽን ማሸጋገር የሚያስችሉ ተጨባጭ ለውጦች መመዝገባቸውን ገልፀዋል። በዚህም አጠቃላይ ኢኮኖሚው ወደ ፊት እንዲራመድ፣ ፈጣንንና ጥራት ያለው ኢኮኖሚ እንዲመዘገብ በማስቻል ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ እድገት መመዝገቡን ጠቁመዋል። ከዚህ ቀደም ዝቅተኛ የግብርና ማሽነሪ ቁጥር ለማሳደግ መንግሥት የፖሊሲ ማበረታቻ በማድረግ አርሶ አደሮቹ ማሽነሪዎችን ከቀረጥ ነፃ እንዲያስገቡ እና የብድር አቅርቦት በማመቻቸት ሰፊ ስራ መሰራቱን አንስተዋል። በዚህም ባለፉት የለውጥ ዓመታት በተሰራው ስራ ወደ 27 ሺህ ትራክተሮች ከ8 ሺህ በላይ ኮምባይነሮች እንዲሁም ከ280 ሺህ በላይ በሞተር የሚሰሩ ፓምፖች ተደራሽ ማድርግ መቻሉን ተናግረዋል። በዚህም የግብርናው ስራ ከዝማላዳዊ አሰራር ተላቆ ወደ ሜካናይዜሽን እየተሸጋገረ መሆኑን ጠቅሰው፤ ባለፉት አመታት በተሰራ ስራ የሜካናይዜሽን እድገቱ 72 በመቶ መድረሱን ያሳያል ነው ያሉት። አጠቃላይ በኢትዮጵያ በትራክተር የሚለማ መሬት 7 ሚሊየን ሄክታር መሬት የደረሰ ሲሆን ይህ ማለት ከሚለማው መሬት አንድ ሶስተኛውን በትራክተር ማልማት እንደተቻለ ገልፀዋል። ይህም ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ለገበያ የሚቀርበውን ምርት በማሳደግ የአርሶ አደሩን ህይወት በመቀየር ረገድ ትልቅ ለውጥ ማስመዝገቡን ጠቁመዋል። በመሆኑም ባለፉት የለውጥ አመታት ተግባራዊ የተደረገው ሪፎርም የግብርና ትራንስፎርሜሽንን ለማረጋገጥ ትልቅ አቅም የፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህም ግብርናውን ከዝናብ ጥገኝነት ወደ መስኖ ለማሸጋገር በተደረገው ጥረት የመስኖ ልማት ሽፋኑ ከዓመት ወደ ዓመት እየጨመረ መጥቷል ነው ያሉት። በዘንድሮው ዓመት ብቻ 4 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር መሬት በመስኖ ስንዴ ለማልማት ታቅዶ እስካሁን ወደ 3 ነጥብ 87 ሚሊየን ሄክታር ማልማት መቻሉን ጠቅሰዋል። ይህም አርሶ አደሩ ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ በዓመት ሁለትና ከዚያ በላይ እንዲያመርት በማድረግ እንደ ሀገር የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የተያዘውን ግብ ለማሳካት ተጨባጭ ለውጥ ማሳየቱን ተናግረዋል። በተጨማሪም ለዜጎች ሰፋፊ የስራ እድል እየፈጠረ እንደሚገኝም ገልጸዋል። አርሶ አደሩ ከምግብነት ባለፈ በመጠንም በጥራትም ተወዳዳሪ ምርቶችን በማምረት ለዓለም ገበያ ተደራሽ እያደረጉ መሆኑን ተናግረዋል።
አትሌት ገመኔ ማሚቴ ምትኩ በተከለከለ አበረታች ቅመም ምክንያት የስድስት ዓመት እገዳ ተጣለባት
Apr 22, 2026 219
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 14/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን አትሌት ገመኔ ማሚቴ ቱኩ የተከለከሉ አበረታች ቅመሞችን (Doping) ተጠቅማ በመገኘቷ የስድስት ዓመት የእገዳ ቅጣት እንደተጣለባት አስታወቀ። ባለስልጣኑ በሁለት የተለያዩ ውድድሮች ላይ ባካሄዳቸው ምርመራዎች፣ አትሌቷ ኤሪትሮፖይቲን (EPO) እና ዴክሳሜታሶን (Dexamethasone) የተባሉ የተከለከሉ ንጥረ ነገሮችን መጠቀምዋን ማረጋገጡን አመልክቷል። በዚህም መሠረት አትሌት ገመኔ ማሚቴ ቱኩ ጊዜያዊ እገዳ ከተጣለባት ጥቅምት 2 ቀን 2018 ዓ.ም (November 11, 2025) ጀምሮ ለስድስት ዓመታት የሚጸና፣ በማንኛውም ስፖርታዊ ውድድር እንዳትሳተፍ እገዳ መጣሉን ገልጿል። በተጨማሪም አትሌቷ ከግንቦት 3 ቀን 2017 ዓ.ም (May 11, 2025) ጀምሮ በተካሄዱ የተለያዩ ውድድሮች ያስመዘገበቻቸው ውጤቶች በሙሉ እንዲሰረዙ ተወስኗል። ይህም ሜዳሊያዎችን፣ የማዕረግ ስሞችን፣ ደረጃዎችን እና የሽልማት ገንዘቦችን መመለስን እንደሚጨምር ነው ባለስልጣኑ ያስታወቀው። በቀጣይም በሀገሪቱ በየደረጃው የሚደረገው የምርመራና ቁጥጥር ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተመልክቷል። የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን የስፖርት አበረታች ቅመሞችን በመጠቀምም ሆነ በተለያየ መልኩ የፀረ-አበረታች ቅመሞች የህግ ጥሰት በሚፈጽሙ አትሌቶችና ከጀርባ ሆነው በሚያበረታቱ ሌሎች ግለሰቦች ላይ የሚወሰደው የእርምት እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።
ባለፉት ዘጠኝ ወራት 4 ነጥብ 85 ቢሊየን ዶላር የሚያወጡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ መተካት ተችሏል
Apr 22, 2026 355
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 14/2018 (ኢዜአ)፡- ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ 4 ነጥብ 85 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ ገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ መተካት መቻሉን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ገለጹ። የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ለዘርፉ ትልቅ መሰረት መጣሉን የገለጹት ሚኒስትሩ፣ በገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን 754 ኢንዱስትሪዎች ወደ ማምረት መግባታቸውን ጠቁመዋል። የ2018 በጀት ዓመት ሦስተኛው የመቶ ቀናት እና የዘጠኝ ወራት ስራ አፈጻጸም ሪፖርት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተገምግሟል። የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል በሰጡት ማብራሪያ የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግርን በማሳካት ረገድ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸውን አንስተዋል። የሪፎርም ሥራዎቹ ምርትና ምርታማነትን በመጨመር እንዲሁም የዜጎችን ኑሮ በማሻሻል ስኬታማ መሆናቸውን አንስተዋል። ቀደም ሲል 4 ነጥብ 8 በመቶ ብቻ የነበረው የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ዕድገት አሁን ላይ በሁለት አሃዝ አድጎ ከ13 በመቶ በላይ ደርሷል ነው ያሉት። የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶች ገቢ ምርትን በመተካትና በወጪ ንግድ ዘርፍ አመርቂ ለውጥ ማምጣታቸውን ጠቁመዋል። ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ 433 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ የኢንዱስትሪ ምርቶች ለውጭ ገበያ የቀረቡ ሲሆን የዘርፉ የኃይል አጠቃቀምም ማደጉን ተናግረዋል። የገቢ ምርትን በሀገር ውስጥ ለመተካት በተሠራው ሥራ 4 ነጥብ 85 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ ተኪ ምርቶችን ማምረት መቻሉን አስታውቀዋል። ይህ ውጤት የኑሮ ጫናን በማቅለል እና የኢኮኖሚ መነቃቃትን በማምጣት ረገድ ትልቅ ሚና መጫወቱን አስገንዝበዋል። የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ለዘርፉ ትልቅ መሰረት መጣሉን የገለጹት ሚኒስትሩ፣ በገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን 754 ኢንዱስትሪዎች ወደ ማምረት መግባታቸውን ጠቁመዋል። በቀጣይም የምርት አቅምን ለማሳደግ የፋይናንስ፣ የግብዓት፣ የኃይል አቅርቦት እና ምቹ የገበያ ሁኔታዎችን በመፍጠር ላይ በትኩረት እንደሚሰራ አስረድተዋል።
ፖለቲካ
የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሪፎርም በፓርቲዎች መካከል የትብብርና የፉክክር ሚዛን ማስጠበቅ ያስቻለ ምኅዳር ፈጥሯል
Apr 22, 2026 808
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 14/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሪፎርም በፓርቲዎች መካከል የትብብርና የፉክክር ሚዛን ማስጠበቅ ያስቻለ ምኅዳር መፍጠሩን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ ገለጹ። የ2018 በጀት ዓመት ሦስተኛው የመቶ ቀናት እና የዘጠኝ ወራት ስራ አፈጻጸም ሪፖርት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተገምግሟል። በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ በሰጡት ማብራሪያ፤ ባለፉት ስምንት ዓመታት በሁሉም ዘርፎች የተወሰዱ የሪፎርም እርምጃዎች ተጨባጭ ውጤቶች አስገኝተዋል ብለዋል። በዚህም በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ የተወሰዱ የሪፎርም እርምጃዎች በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ በመፈጸም ተጠባቂ ውጤቶች እንዲመዘገቡ ማድረጉን ገልጸዋል። ይህም የኢትዮጵያና ህዝቦቿን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ እመርታዊ የኢኮኖሚ ዕድገት እንዲመዘገብ ማስቻሉንም ተናግረዋል። ገዥው ፓርቲ በፖለቲካው መስክ የወሰዳቸው የሪፎርም እርምጃዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የትብብርና ፉክክር ሚዛንን ማስጠበቅ ያስቻለ ምኅዳር መፍጠሩን አስረድተዋል። በዚህም ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅምና ወሳኝ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በትብብር የሚሰሩበትን ጤናማ የፉክክር መድረክ መፈጠሩን አንስተዋል። ገዥው ፓርቲም በየደረጃው የሥራ ኃላፊዎችን የመመደብ ሥልጣንና ኃላፊነት እንዳለው አስታውሰው፤ የትብብርና የሃሳብ ልዕልና ባህልን ለማዳበር የኢትዮጵያን የመግባባት ዴሞክራሲን ማጠናከር የሚያስችል የተሳትፎ ምኅዳር መፍጠሩን ገልጸዋል። ከፌዴራል እስከ ወረዳ በሚገኙ የመንግስት መዋቅሮችም ከ275 በላይ የሚሆኑ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ተመድበው ህዝባቸውንና ሀገራቸውን እያገለገሉ መሆኑን አንስተዋል። የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሪፎርም በመሠረታዊ ጉዳዮች ላይ ብሔራዊ መግባባትና አንድነትን ለመፍጠር አካታች ሀገራዊ ምክክሩ የተሻለ የምክክር ምዕራፍ ላይ መድረሱንም ጠቁመዋል። በቀጣይም የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሪፎርም ውጤታማነትን በማስቀጠል በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መግባባትን ለመፍጠር የተጀመሩ ጥረቶች የበለጠ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አቶ አደም አረጋግጠዋል። መንግስትና ገዥው ፓርቲም መርህን በጠበቀ መልኩ ሀገራዊ ምክክሩ በህዝብና ባለድርሻ አካላት የላቀ ተሳትፎ ግቡን እንዲመታ በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል። በሌላ መልኩ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሪፎርም ሌሎች ሀገራት በአርዓያነት የሚወስዱት ተጨባጭ ውጤቶች እያስገኘ መሆኑን ተናግረዋል። ለአብነትም የኢትዮጵያ ብዝኅ ኢኮኖሚ ልማት የሀገር ውስጥ ፍጆታን በማሟላት የዓለም አቀፍ ወጪ ንግድ ተወዳዳሪነትን ማሳደግ የሚያስችል ስኬት ማስገኘቱን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት እንዲመረት እና የተለያዩ አምራች ኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም በማሳደግ ንግድና ኢንቨስትመንትን የሚያበረታታ እመርታዊ ውጤት ማስገኘቱን ጠቅሰዋል። በማህበራዊ ዘርፍም ፍትሕዊ የመሰረተ ልማት ተደራሽነቶች ጥራትና አካታችነትን በማስጠበቅ የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማሳደጉን አስገንዝበዋል። በተለይም የትምህርት ለትውልድ መርሃ ግብር የቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን በመገንባት የትምህርት ጥራትን የሚያስጠብቅ ውጤት እየተገኘበት መሆኑን አስታውቀዋል። በአጠቃላይ በፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና በዲፕሎማሲው መስክ የኢትዮጵያና ህዝቦቿን ክብር በማስጠበቅ ሁለንተናዊ ብልፅግናን የሚያረጋግጡ የልማት ድሎች መገኘታቸውን አብራርተዋል። በቀጣይም የመንግስት፣ የግሉ ዘርፍና የህዝብን ተሳትፎና አቅሞችን በመደመር ሁለንተናዊ ብልፅግና፣ የዳበረ ዴሞክራሲና መልካም አስተዳደር የሰፈነባት፣ ዘላቂና አዎንታዊ ሰላም ባለቤት ኢትዮጵያን መገንባት ይጠበቅብናል ብለዋል።
የኢትዮጵያን የተጽዕኖና የትብብር አድማስ ያሳደጉ ስትራቴጂካዊ የዲፕሎማሲ ስኬቶች ተመዝግበዋል
Apr 22, 2026 438
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 14/2018 (ኢዜአ)፡- ባለፉት የለውጥ ዓመታት የኢትዮጵያን የተጽዕኖና የትብብር አድማስ ያሳደጉ ስትራቴጂካዊ የዲፕሎማሲ ስኬቶች መመዝገባቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ገለፁ። በኢኮኖሚ፣ በተቋም ግንባታና በአካባቢ የተከናወኑ ተግባራትም ለኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ስኬት የጀርባ አጥንት መሆናቸውን ሚኒስትሩ አስታውቀዋል። የ2018 በጀት ዓመት ሦስተኛው የመቶ ቀናት እና የዘጠኝ ወራት ስራ አፈጻጸም ሪፖርት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተገምግሟል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) በዲፕሎማሲ መስክ የተገኙ ውጤቶችን አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በዚህም ባለፉት የለውጥ ዓመታት አበረታች የዲፕሎማሲ ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ በአህጉራዊና በዓለም አቀፍ መድረኮች ያላት ተጽዕኖ በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ መምጣቱን አስታወቀዋል። የኢትዮጵያን አንኳር ስትራቴጂካዊ ፍላጎት የሆነው የባህር በር አጀንዳ በዓለም አቀፍ መድረኮችና በሁለትዮሽ ግንኙነቶች ትልቅ ትኩረት እንዲያገኝ ተደርጓል ብለዋል። ይህም የተለያዩ አካላት የኢትዮጵያን ጥያቄ እንዲገነዘቡና ለጉዳዩ በጋራ መፍትሔ መፈለግ አስፈላጊ መሆኑን እንዲረዱ በማድረግ ረገድ ትልቅ ድል መገኘቱን ገልጸዋል። ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ጫናዎች ቢኖሩም፣ የኢትዮጵያ መንግሥትና ህዝብ ጫናዎቹን በመቋቋም የታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናቆ ወደ ስራ እንዲገባ ማድረግ መቻሉ ሌላኛው ትልቅ የዲፕሎማሲ ስኬት መሆኑን ጠቅሰዋል። ኢትዮጵያ የብሪክስ ሙሉ አባል ሀገር ሆና መመረጧና ንቁ ተሳትፎ መጀመሯ የሀገሪቱን ዓለም አቀፍ ተቀባይነት የሚያሳይ መሆኑንም ነው ያብራሩት። ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንትና ለኢኮኖሚ አጋርነት ያላት ተፈላጊነት እየጨመረ መምጣቱንም ጠቅሰዋል። የቅርብና የሩቅ ሀገራት ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለማጠናከር ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙም አስረድተዋል። የከፍተኛ አመራሮች የጉብኝት ልውውጦችና የሚፈረሙ ስምምነቶች የኢትዮጵያ የትብብር አድማስ መስፋቱን የሚያሳዩ ተጨባጭ ውጤቶች ናቸው ብለዋል። ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ ኢትዮጵያ በተለያዩ ዓለም አቀፍ የውሳኔ ሰጪ ተቋማት ውስጥ በከፍተኛ ድምፅ ስትመረጥ መቆየቷን ሚኒስትሩ ጠቁመዋል። በተለይም በግለሰብ ደረጃ የሚወከሉ የኢትዮጵያ እጩዎች በአፍሪካም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተመራጭ መሆናቸው የሀገሪቱ ተጽዕኖ ፈጣሪነት እያደገ መምጣቱን የሚያረጋግጥ እንደሆነ ገልፀዋል። የዲፕሎማሲ ስኬቱ በተጨባጭ የሀገር ውስጥ ስራዎች ላይ የተመሰረተ መሆኑንም አብራርተዋል። የኢኮኖሚ ሪፎርሙ የሀገሪቱን ተቋማት በማጠናከር ለውጤት የበቁ አቅሞች እንዲሆኑ ማስቻሉንም አንስተዋል። በአካባቢ ጥበቃና በታዳሽ ኃይል ኢንቨስትመንት የተሰሩ ስራዎች ለሌሎች ሀገራት እንደ ተምሳሌት እየታዩ መሆናቸውን ነው የተናገሩት። የከተማና የገጠር ልማት እንቅስቃሴዎች ተደምረው ኢትዮጵያ ለትብብርና ለኢንቨስትመንት ተመራጭ እንድትሆን አድርገዋታል ብለዋል። በኢኮኖሚ፣ በተቋም ግንባታና በአካባቢ ጥበቃ የተከናወኑ ተግባራት ለኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ስኬት የጀርባ አጥንት መሆናቸውንም ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል።
በያዝነው ካርድ ዴሞክራሲያዊ መብታችንን ለመጠቀም የምርጫውን ዕለት እየጠበቅን ነው
Apr 22, 2026 493
ሀዋሳ/ቦንጋ ፤ሚያዝያ 14/2018 (ኢዜአ)፡- በያዝነው ካርድ ዴሞክራሲያዊ መብታችንን ለመጠቀም የምርጫውን ዕለት እየጠበቅን እንገኛለን ሲሉ የሀዋሳና የቦንጋ ከተሞች ነዋሪዎች ገለጹ። በመጪው ግንቦት 24 ቀን 2018 ለሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት የመራጮች ምዝገባ ዛሬ ይጠናቀቃል። አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የሃዋሳና የቦንጋ ከተሞች ነዋሪዎች ፤ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በያዝነው ካርድ ዴሞክራሲያዊ መብታችንን ለመጠቀም የምርጫውን ዕለት እየጠበቅን እንገኛለን ብለዋል። አቶ አሸናፊ አለሙ የሀዋሳ ከተማ ነዋሪ ሲሆኑ ፣ የዜግነት ግዴታቸውን ለመወጣትና ይበጀኛል ያሉትን ፓርቲ ለመምረጥ የምርጫ ካርድ በመውሰድ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል፡፡ ምርጫ ቦርድ ያመቻቸው ተጨማሪ የምዝገባ ቀን በስራ መደራረብ ምክንያት ጊዜ ላላገኙ ዜጎች መልካም እድልን የፈጠረ በመሆኑ ካርድ ለመውሰድ አስችሎኛል ነው ያሉት፡፡ በምርጫው ንቁ ተሳታፊ ለመሆን የምርጫ ካርድ መውሰድ አስፈላጊ መሆኑን በማመን በመጨረሻው ቀን ካርድ ወስጃለሁ የሚሉት ደግሞ የከተማዋ ነዋሪ አቶ ታረቀኝ ድቃሶ ናቸው፡፡ ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ተጠቅመው ለሀገር የሚጠቅም ፓርቲን ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን ተናግረው የፓርቲዎቹን የምረጡኝ ቅስቀሳ እየተከታተሉ መሆኑን ተናግረዋል። ሌላው የከተማው ነዋሪ አቶ ሙሴ ኤልያስ በበኩላቸው፤ በተመቻቸላቸው ቀን ተጠቅመው የምርጫ ካርድ መውሰዳቸውን ተናግረው ለሀገር ልማት ይጠቅማል የሚሉትን ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል፡፡ የቦንጋ ከተማ ነዋሪዎች በበኩላቸው ፤ለጠቅላላ ምርጫው ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ለመጠቀም የሚያስችላቸውን ካርድ በመያዝ ድምጽ የመስጫ ቀኑን እየጠበቁ መሆናቸውን ተናግረዋል። በከተማው 03 ሸታ ምርጫ ጣቢያ ካርድ ሲወስዱ ያነጋገርናቸው የቦንጋ ትምህርት ኮሌጅ ተማሪዎች መቅደስ መኮንን እና መሠለች ወንድሙ ለመጀመሪያ ጊዜ በምርጫ ለመሳተፍ የመራጭነት ካርድ መውሰዳቸውን ገልጸዋል። በመጨረሻ ቀንም ቢሆን ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን ለመጠቀም የሚያስችላቸውን ካርድ በመውሰዳቸው መደሰታቸውን ጠቁመው፣ ይበጀናል ያሉትን ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል። ተማሪ ምናሉሽ አቱሞና ሰለሞን ኮያ በበኩላቸው በወሰዱት ካርድ ለሀገር ሰላምና ልማት ይበጃል ያሉትን ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተናል ብለዋል። ሌላው የቦንጋ ከተማ ነዋሪ አቶ አብዱልቃድር አደም በበኩላቸው፤ ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ለመጠቀም መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።
ቦርዱ ለመራጮች ምዝገባ ያስቀመጠው ጊዜ ከመጠናቀቁ በፊት የምርጫ ካርድ እየወሰድን ነው
Apr 22, 2026 313
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 14/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው ቀነ ገደብ መሠረት የመራጮች ምዝገባ ከመጠናቀቁ በፊት ዛሬ የምርጫ ካርዳችንን እየወሰድን ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት የመራጮች ምዝገባ እየተከናወነ ሲሆን፤ እስከ ዛሬ ሚያዚያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም የተራዘመው የጊዜ ገደብ በተለያየ ምክንያት ምርጫ ካርድ ያላወጡ ዜጎች እንዲመዘገቡ መልካም አጋጣሚን ፈጥሯል። ኢዜአ በመዲናዋ ተዘዋውሮ በምርጫ ጣቢያዎች ባደረገው ቅኝት የመጨረሻዋን ቀን በመጠቀም ዜጎች ካርድ እየወሰዱ መሆኑን ተመልክቷል። በመዲናዋ በተለያዩ የመራጮች ምዝገባ ጣቢያዎች ተዘዋውሮ ካርዳቸውን ሲወስዱ ያገኛቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የምርጫ ካርድ ማውጣታችን ዴሞክራሲያዊ መብታችንን ለመጠቀም ያስችለናል ብለዋል። የምርጫ ካርድ ሲያወጣ ያገኘነው ዘሪሁን ፍቃዱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለመራጮች በቂ ጊዜ ለመስጠት የምዝገባ ጊዜውን በማራዘሙ ዛሬ የድምፅ መስጫ ካርድ መውሰዱን ተናግሯል፡፡ ማርሸት ጠንክር የተባለች አስተያየት ሰጪ በበኩሏ፤ የወሰደችውን የምርጫ ካርድ በመጠቀም ግንቦት 24 በሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ይበጀኛል የምትለውን እጩ ለመምረጥ መዘጋጀቷን ገልጻለች፡፡ ሌላኛው አስተያየት ሰጪ የመዲናዋ ነዋሪ አቤል ኃይሉ በበኩሉ መምረጥ የሚያስችለኝን የመራጭነት ካርድ ወስጃለሁ ብሏል። ግንቦት 24/2018 ዓ.ም በሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ለሀገርና በተለይም ለወጣቶች ተጠቃሚነት የተሻለ ፖሊሲ ያቀረበውን ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀቱን የተናገረው ደግሞ ካሳሁን ጉልማ የተባለ አስተያየት ሰጪ ነው።
የመራጮች ምዝገባ ቀን መራዘሙ በምርጫው እንድንሳተፍ ተጨማሪ እድል ፈጥሮልናል
Apr 22, 2026 283
ደብረ ብርሃን ፤ሚያዝያ 14/2018 (ኢዜአ)፡- የመራጮች ምዝገባ ቀን መራዘሙ በምርጫው እንድንሳተፍ ተጨማሪ እድል ፈጥሮልናል ሲሉ የደብረ ብርሃን ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ። በደብረ ብርሃን ከተማ በተለያዩ ምክንያቶች የምርጫ ካርድ ሳይወስዱ የቆዩ ነዋሪዎች ለመራጭነት የሚያበቃቸውን የምርጫ ካርድ በመውሰድ ላይ ናቸው፡፡ የከተማዋ ነዋሪዎች ለኢዜአ እንዳሉት፤ ቦርዱ ለመራጮች ምዝገባ ቀን ያስቀመጠውን የጊዜ ሰሌዳ ማራዘሙ በሀገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ ተሳትፎ ለማድረግ ሁኔታዎችን ያመቻቸ ነው ብለዋል። የመራጭነት ካርድ ለመውሰድ በመመዝገብ ላይ የነበሩት የ65 ዓመት የእድሜ ባለፀጋ የሆኑት ወይዘሮ ጥሩነሽ ገብረወልድ ተጨማሪ የመራጮች ምዝገባ ቀናት እንዲኖር መደረጉ በምርጫው ተሳትፎ ለማድረግ እንድንችል አድርጓል ብለዋል ። በምርጫው ይጠቅመኛል ያሉትን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል። በአሁኑ ወቅትም በምርጫው የሚወዳደሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በመገናኛ ብዙሃን የሚያደርጉት የምረጡኝ ቅስቀሳ በእውቀት ላይ ተመስርተን ለምርጫው እንድንዘጋጅ አድርጎናል ብለዋል። የከተማዋ ነዋሪ የሆኑት አንዋር ደረጀ እና ወይዘሮ ሰላም ሹመት ፤በተለያዩ ምክንያቶች የመራጭነት ካርድ ለመውሰድ ሳይችሉ የቆዩ ቢሆንም በዛሬው እለት በተሰጣቸው የመጨረሻ እድል ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ የመራጮች ምዝገባ ቀን መራዘሙ በምርጫው በመሳተፍ ለሀገር ሰላም ልማትና እድገት የሚጠቅም ፓርቲ ወደ ስልጣን ለማምጣት እንድንዘጋጅ አድርጎናል ነው የሚሉት። ወይዘሮ ጽጌ ታየ በበኩላቸው በመጨረሻው የምዝገባ ቀን የወሰዱትን የምርጫ ካርድ በጥንቃቄ በማስቀመጥ መብቴንና ጥቅሜን ያስጠብቅልኛል የሚሉትን ፓርቲ ወደ ስልጣን ለማምጣት እንደሚጠቀሙበትም ነው ያነሱት። ካርድ ያላወጡ ዜጎች በዛሬው እለት በሚካሔደው የመጨረሻው የመራጮች ምዝገባ ቀን ተጠቅመው የዜግነት ግዴታቸውን ለመወጣት መዘጋጀት እንዳለባቸውም ነው አስተያየት ሰጪዎቹ የተናገሩት።
የመመዝገቢያ ቀን መራዘሙን ተጠቅመን የምርጫ ካርድ ወስደናል- የወላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪዎች
Apr 22, 2026 300
ወላይታ ሶዶ፤ሚያዝያ 14/2018 (ኢዜአ)፡- የመመዝገቢያ ቀን መራዘሙን ተጠቅመው የምርጫ ካርድ መውሰዳቸውን የወላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እስከ ሚያዝያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ያራዘመው የመራጮች ምዝገባ ቀነ ገደብ ዛሬ ይጠናቀቃል። የወላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪዎች የመራጮች ምዝገባ ቀን መራዘሙ ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን በመጠቀም የሚበጃቸውን ፓርቲ ለመምረጥ የሚያስችላቸውን እድል የፈጠረላቸው መሆኑን ተናግረዋል ። በዚህም ዘግይተውም ቢሆን በዘንድሮው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ተሳትፈው መምረጥ የሚያስችላቸውን ካርድ መውሰዳቸውን ገልጸዋል። የከተማው ነዋሪ አቶ አብነት ኤልያስ፤ በስራ ምክንያት ካርድ ሳይወስዱ መቆየታቸውን ጠቁመው ጊዜው ሳይጠናቀቅ የመምረጥ መብታቸውን ለመጠቀም ካርድ መውሰድ በመቻላቸው ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል። የምርጫ ቦርድ ባመቻቸው ተጨማሪ ቀን በወሰዱት የመራጭነት ካርድ የመምረጥ መብታቸውን ለመጠቀም መዘጋጀታቸውን አመልክተዋል። የምርጫ ካርድ በመውሰድ መብቴን ለመጠቀም ስጠባበቅ ቆይችያለሁ ያለችው ደግሞ ወጣት ቤዛ አዲላ ናት። የመምረጥ ዲሞክራሲያዊ መብት የሚወሰነው በምርጫ ካርድ ብቻ በመሆኑ ጊዜው ሳይጠናቀቅ ካርድ በመውሰዴ ዕድለኛ ነኝ ብላለች። የምርጫ ሂደቱ ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የዜግነት ግዴታዋን እንደምትወጣም አስረድታለች። ወጣት ታምራት ደስታ በበኩሉ ተጨማሪ ቀኑን በመጠቀም ለመራጭነት የሚያበቃውን ካርድ መውሰዱን ገልጿል። በካርዱ ለሀገር ልማትና ዕድገት ይበጃል ያለውን ፓርቲ የመምረጥ መብቱን እንደሚጠቀምም ነው የገለጸው፡፡ በምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት 7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል።
በተለያዩ ምክንያቶች የምርጫ ካርድ ሳይወስዱ የቆዩ ነዋሪዎች በመራጮች ምዝገባ ማጠናቀቂያ ቀን የምርጫ ካርድ እየወሰዱ ነው
Apr 22, 2026 300
ባሕርዳር፤ሚያዝያ 14/2018 (ኢዜአ)፡- በባህርዳር ከተማ በስራ መደራረብና በተለያዩ ምክንያቶች የምርጫ ካርድ ሳይወስዱ የቆዩ ነዋሪዎች በመራጮች ምዝገባ ማጠናቀቂያ ቀን ተገኝተው ለመራጭነት የሚያበቃቸውን የምርጫ ካርድ እየወሰዱ ነው። በባህርዳር ከተማ የራስ አገዝ ቀበሌ ነዋሪ አቶ ለሚ ጉርሙ በስራ መደራረብ ምክንያት ተመዝግበው የምርጫ ካርድ ሳይወስዱ መቆየታቸውን ገልፀዋል። የመራጮች ምዝገባ ማጠናቀቂያ ቀን ዛሬ በመሆኑ የምፈልገውንና ለሀገሪቱ እድገት ይበጃል ብዬ ያመንኩበትን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ የሚያስችለኝን የምርጫ ካርድ ወስጃለሁ ብለዋል። የሽምብጥ ቀበሌ ነዋሪ የሆነው ወጣት አለባቸው አባት በበኩሉ በግንዛቤ እጥረት ፈጥኖ የመራጭነት ካርድ ሳይወስድ መቆየቱን ተናግሯል። ይሁንና የመራጮች የምዝገባ ጊዜ ሰሌዳ ተራዝሞ መቆየቱ ዲሞክራሲያዊ መብቱን እንዲጠቀም እድል እንደፈጠረለት ጠቁሞ በመራጮች የምዝገባ ማጠናቀቂያ ቀን ተገኝቼ ለመራጭነት የሚያበቃኝን ካርድ ወስጃለሁ ብሏል። በወሰድው የምርጫ ካርድ በመጠቀም ለወጣቶች የስራ እድል ያመቻቻል፤ ለሀገር እድገት ይሰራል ያለውንና የተሻለ የፖሊሲ አማራጭ ይዞ የሚቀርበውን ፓርቲ እንደሚመርጥ አመላክቷል። የሴቶችን ሁለንተናዊ መብት ያስከብራል ብለው ያመኑበትን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ የሚያስችላቸውን የምርጫ ካርድ ዛሬ ተመዝግበው መውሰዳቸውን የገለፁት ደግሞ የከተማው ነዋሪ ወይዘሮ የሽበር ካሳ ናቸው። የሀገር ዕድገትና ብልፅግና የሚረጋገጠው የመምረጥ ዴሞክራሲያዊ መብታችንን ተጠቅመን የምንፈልገውን የፖለቲካ ፓርቲ መምረጥ ስንችል ነው፤ ለዚህም ዝግጁ ነኝ ብለዋል። ሌላው የከተማው ነዋሪ ወጣት እሱባለው አስፋው በበኩሉ ዛሬ የመራጮች ምዝገባ መጨረሻ ቀን በመሆኑ ዲሞክራሲያዊ መብቴን ተጠቅሜ ለመራጭነት የሚያበቃኝን የምርጫ ካርድ ወስጃለሁ ብሏል። በወሰድኩት የምርጫ ካርድ የሀገርን አንድነት አስጠብቆ ያስቀጥላል ብዬ ያመንኩበትን ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅቻለሁ ሲል አመላክቷል።
አርሶ አደሮችና ወጣቶች በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለሀገር ይበጃል የሚሉትን ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተዋል
Apr 22, 2026 320
አምቦ/ጭሮ፤ ሚያዝያ 14/2018 (ኢዜአ)፦ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለሀገር ይበጃል የሚሉትን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን በምዕራብ ሸዋ ዞን የአምቦ ወረዳ አርሶ አደሮች እና የጭሮ ከተማ ወጣቶች አስታወቁ። በአምቦ ወረዳ የጎሱ ቆራ ቀበሌ አርሶ አደሮች፤ በምርጫው ለሀገርና ለወገን ይጠቅማል ያሉትን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል። አስተያየታቸውን ለኢዜአ ከሰጡት መካከል አርሶ አደር ጋሻው ሹም፤ ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን በመጠቀም በአካባቢያቸው የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን የሚያስቀጥል ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል። አርሶ አደር ኡርገሳ ታደሰም በተመሳሳይ፤ የያዙትን የመራጭነት ካርድ በመጠቀም ለሕዝብ ጥቅም ይቆማል ብለው ላመኑበት ፓርቲ ድምፅ ለመስጠት የምርጫውን ዕለት በጉጉት እየጠበቁ መሆኑን ገልጸዋል። በግንቦት ወር በሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ይወክለኛል ላሉት ፓርቲ ድምፅ ለመስጠት ካርድ መውሰዳቸውን የገለጹት ደግሞ አርሶ አደር ደመሳ መገርሳ ናቸው። የአምቦ ወረዳ የጎሱ ቆራ ምርጫ ጣቢያ አስተባባሪ አቶ ካቤ ገታታ፤ ከየካቲት 28 ቀን ጀምሮ ሲከናወን የቆየው የመራጮች ምዝገባ በተያዘለት ዕቅድ መሠረት በስኬት እየተጠናቀቀ መሆኑን አስታውቀዋል። በሌላ በኩል የጭሮ ከተማ ወጣቶች ፌዴሬሽን ሰብሳቢ መሐመድ ሀሰን፤ በከተማው ሲካሄድ የቆየው የመራጮች ምዝገባ ሰላማዊ፣ ዲሞክራሲያዊና ከፍተኛ የወጣቶች ተሳትፎ የታየበት መሆኑን ገልጿል። ፌዴሬሽኑ ለምርጫው ስኬታማነት በ26 የምርጫ ጣቢያዎች 62 ታዛቢዎችን መመደቡንም ጠቁሟል። ካለፉት ምርጫዎች በተሻለ መልኩ በምዝገባው ሂደት የወጣቶች ተሳትፎ ከፍተኛ እንደነበር የገለጸው ሰብሳቢው፤ ወጣቶች በንቃት በመሳተፍ ለተጠቃሚነታቸው የሚሠራን አካል እንዲመርጡ ግንዛቤ እየተሰጠ መሆኑንም ተናግሯል። የከተማው ወጣት ማህበር ሰብሳቢ ወጣት አብደላ መሐመድ በበኩሉ፤ ማህበሩን በመወከል የምዝገባ ሂደቱን ሲታዘብ መቆየቱን ገልጾ፤ ሂደቱ ቀልጣፋ፣ የቁሳቁስ አቅርቦት የተሟላና የሕዝብ ተሳትፎ የጎላበት መሆኑን አመልክቷል። የከተማው ወጣቶች ማህበር እንደ አንድ የሲቪክ ማህበር የምርጫ ሂደቱ ፍጹም ሰላማዊ፣ ፍትሐዊና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የሚጠበቅበትን ሚና እንደሚወጣም አረጋግጧል። ወጣቶች በምዝገባ ሂደቱ የነበራቸውን ንቁ ተሳትፎ በድምፅ አሰጣጥ ዕለቱም በመድገም የመራጭነት መብታቸውን እንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርቧል።

ማህበራዊ
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የቴክኖሎጂ ዳኝነት አገልግሎቶች ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው
Apr 22, 2026 87
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 14/2018 (ኢዜአ)፡- የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የቴክኖሎጂ ዳኝነት አገልግሎቶች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳሰበ። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸምን ገምግሟል። የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ቴዎድሮስ ምህረት፤ የፍርድ ቤቶችን የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈፃጸም ዝርዝር ሪፖርት ለቋሚ ኮሚቴው አቅርበዋል። በሪፖርታቸው የኢትዮጵያን የዳኝነት አገልግሎት ለማዘመን የተወሰዱ የማሻሻያ እርምጃዎች በበጀት ዓመቱ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውጤት ማስመዝገብ መቻላቸውን ገልጸዋል። በዚህም በዲጂታል ክስ መስተንግዶ፣ በተዘዋዋሪ ችሎትና የቆዩ መዝገቦችን በማጥራት በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ትርጉም ያለው ስኬት መገኘቱን ተናግረዋል። የሰው ሃብት ልማት ተግባራትም የዳኞችንና የሕግ ሙያተኞችን አቅም በማጎልበት በመዝገብ ክምችት ቅነሳ፣ በጊዜ ቀጠሮና ቀልጣፋ የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ እየዳበረ መምጣቱን አንስተዋል። የምክር ቤቱ አባላትም በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዘጠኝ ወራት ዝርዝር የአፈፃጸም ሪፖርት ዙሪያ ምላሽ የሚሹ ጥያቄና አስተያየቶችን አቅርበዋል። በአርዓያነት የሚወሰደውን የፌደራል ፍርድ ቤቶች የዲጂታል ዳኝነት አገልግሎት በክልል ፍርድ ቤቶች ጭምር ለማስፋት እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን በተመለከተ ማብራሪያ ጠይቀዋል፡፡ የዳኝነት አገልግሎቱን ለማሳለጥ ተግባራዊ የተደረገው ቴክኖሎጂ ተጠያቂነትን ከማረጋገጥ አኳያ ስላመጣው እምርታ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ቴዎድሮስ ምህረት በምላሻቸው፤ ዲጂታል የዳኝነት የአገልግሎት ጥራትና ተደራሽነትን በማስፋት ወሳኝ መፍትሔ ሆኖ እያገለገለ ነው። አክለውም ተግባራዊ እየሆነ ያለው ዲጂታላይዜሽን ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለው አገልግሎት ተግባራዊ እንዲሆን ማስቻሉን ነው የተናገሩት፡፡ በቀጣይም የዳኝነት ሥርዓቱን የሚያሳልጡ አገልግሎቶችን የበለጠ በማስፋት በክልሎች ጭምር የተገልጋዮችን እርካታ ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እፀገነት መንግስቱ በሰጡት ማጠቃለያ፤ የፌዴራል ፍርድ ቤት የሥራ አፈፃጸም በሪፖርትና በመስክ ምልከታ መታየቱን ገልጸዋል። በመስክ ምልከታና ሪፖርቱም የፍርድ ቤቶች ፈጣንና ጥራት ያለው የቴክኖሎጂ የዳኝነት አገልግሎት ውጤታማነትን በማሳደግ በአርዓያነት የሚወሰዱ መሆናቸውን አረጋግጠናል ብለዋል። በቀጣይም ዘመናዊና ግልፅ የዳኝነት ምኅዳርን በማስፋት የተመዘገቡ አበረታች ውጤቶች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የክልል የሕዝብና የማህበረሰብ መገናኛ ብዙሃን ሀገራዊ አጀንዳዎችን ተደራሽ እያደረጉ ነው
Apr 22, 2026 84
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 14/2018 (ኢዜአ)፡- የክልል የሕዝብና የማህበረሰብ መገናኛ ብዙሃን ለሀገራዊ መግባባትና ትርክት ግንባታ መሰረት የሚሆኑ መረጃዎችን ተደራሽ በማድረግ ረገድ ገንቢ ሚና እየተወጡ መሆኑን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እውነቴ አለነ ገለጹ። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ባለፉት ሶስት ወራት በክልል የሕዝብ እና የማህበረሰብ መገናኛ ብዙኃን ላይ ያደረገውን የይዘት ስርጭት ክትትልና ግምገማ ውጤት ይፋ ማድረጊያ መርሃ ግብር "መገናኛ ብዙሃን ለሀገር ግንባታና ለማህበረሰብ አመለካከት ቀረፃ" በሚል መሪ ሃሳብ ተካሂዷል፡፡ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እውነቴ አለነ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን በመገናኛ ብዙሃን ላይ አበረታች ክትትልና ቁጥጥር እያደረገ ነው። የክልልና የማህበረሰብ መገናኛ ብዙሃን የህዝብን ፍላጎትንና ችግሮችን በቅርበት በመለየት ተደራሽ ማድረግ የሚችሉ መሆናቸውን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በክልሎች ማህበረሰቡን በሚያወያይበት ወቅት ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ ተደራሽ በማድረግ የጎላ አበርክቶ እንደነበራቸውም ተናግረዋል። እነዚህ የክልል የሕዝብና የማህበረሰብ መገናኛ ብዙሃን እውነተኛ የኢትዮጵያን ብዝሃነት ስዕል የምናይባቸው ተቋማት ናቸው ብለዋል። የማህበረሰብ መገናኛ ብዙሃን ያላቸውን አቅም አሟጠው በመጠቀም በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መልካም ጥረት እያደረጉ ነው ያሉት የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ፤ የክልል የሕዝብ መገናኛ ብዙሃን አቅማቸውን የሚያጠናክሩበት ድጋፍ ሊደረግላቸው እንደሚገባ አሳስበዋል። የክልል የሕዝብ መገናኛ ብዙሃን ወጥ ዘገባ በመስራት ብሔራዊ መግባባት ላይ የጋራ አቋም መያዝ መጀመራቸውን የገለጹት የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ፤ አስተሳሳሪ ትርክት ለመገንባት በቁልፍ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተናብበው እየሰሩ ነው ብለዋል፡፡ በድህረ እውነት ዘመን የሐሰተኛ መረጃ ስርጭት ፈታኝ በመሆኑ የመገናኛ ብዙሃን ቁልፍ ሥራ እውነትን ፈልጎ ማውጣት መሆን እንዳለበትም አስገንዝበዋል። የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራልና የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የቦርድ ሰብሳቢ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፤ በክልል የሕዝብ መገናኛ ብዙሃን መካከል የዜና እና የተሞክሮ ልውውጥ ማድረግ ከተቻለ ኢትዮጵያን በጋራ እንገነባለን ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ማስጠበቅ ሲባል ማን ሰራ ሳይሆን እንዴት በጋራ እንቋደሰዋለን የሚለው ነው ያሉት አምባሳደር ሬድዋን፤ የክልል ሥራዎችን በትብብር በመስራት ኢትዮጵያን መገንባት እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ዴሲሳ፤ የክልል መገናኛ ብዙሃን ከክልል አጥር በመውጣት በተለያዩ ቋንቋዎች የተለያዩ ይዘቶችን ማሰራጨት መቻላቸው ትልቅ ለውጥ መሆኑን አንስተዋል፡፡ ይሁን እንጂ የክልል የሕዝብ መገናኛ ብዙሃን በጋራ ታሪክ፣ በአስተሳሳሪ ጉዳዮችና በጋራ እሴት ግንባታ ላይ ከዚህ በላይ መሥራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ፤ አሁን ያለንበት የድህረ እውነት ዘመን እውነት የቀጨጨችበትና በብዙ የምትፈተንበት ወቅት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም የክልል የህዝብና የማህበረሰብ የመገናኛ ብዙሃን እውነትን ለማጽናት ደጋግመውና በተለያየ ሥልት መሥራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡ በመርሃ ግብሩ ላይ የተሳተፉ የመገናኛ ብዙሃን ተወካዮች በበኩላቸው፤ የክልል የህዝብና የማህበረሰብ የመገናኛ ብዙሃን የለውጡ አካል ተደርገው የብሔራዊ ጥቅምና ሀገራዊ መግባባት ላይ ተሳታፊ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ ሀገራዊ አጀንዳዎችን እንዲጋሩ፣ የአጀንዳዎቹ ባለቤቶች እንዲሆኑ መደረጉን በማንሳት፤ ይሄውም በጋራ እንዲቆሙ አስችሏቸዋል ብለዋል፡፡ የክልል የህዝብና የማህበረሰብ የመገናኛ ብዙሃን በሰው ሀይልም ሆነ በቴክኖሎጂ የአቅም ልዩነት ስላላቸው ሁሉም ፈጣን መረጃዎችን ተደራሽ ማድረግ እንዲችሉ መተጋገዝ እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡
የሚበጀንን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ የምርጫ ካርድ ወስደናል - የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች
Apr 22, 2026 81
ጎንደር፤ ሚያዝያ 14/2018 (ኢዜአ)፡- በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለሀገር እድገትና ብልጽግና ይበጃል የሚሉትን ፓርቲ ለመምረጥ የሚያስችላቸውን የምርጫ ካርድ መውሰዳቸውን የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡ አቶ አገኘሁ አበራ ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት፤ ሰላማዊና ዴሞክራሲዊ ምርጫ ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ የሚኖረውን ፋይዳ በመገንዘብ ዛሬ የምርጫ ካርድ ወስደዋል። ካርድ ያልወሰዱ የሕብረተሰብ ክፍሎችም ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ተጠቅመው ለመምረጥ ዕድሉ ሳያመልጣቸው የምርጫ ካርድ እንዲወስዱ መክረዋል። አቶ ሽፈራሁ ተስፋሁን በበኩላቸው ሳልመርጥ ቀረሁ ብሎ ከመቆጨት ይልቅ ዛሬ ካርድ በማውጣት መብትን መጠቀም የሥልጡን ማኅበረሰብ መገለጫ በመሆኑ፤ ያላወጡ ግለሰቦች ዕድሉን እንዲጠቀሙ አሳስበዋል። በሥራ መደራረብ ምክንያት የምርጫ ካርድ ሳላወጣ ብዘገይም የመጨረሻውን ቀን በመጠቀም ካርዴን እጄ ላይ አስገብቻለሁ ያሉት ደግሞ አቶ በላይ መንግሥቴ ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የፊታችን ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል፡፡
የኢትዮጵያን የባሕር በር ባለቤትነት ለማረጋገጥ የዜጎች ንቁ ተሳትፎ ያስፈልጋል
Apr 22, 2026 126
ጅማ፤ ሚያዝያ 14/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያን የባሕር በር ባለቤትነት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የዜጎች ንቁ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ምሁራን አስገነዘቡ። በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የጂኦግራፊ እና አካባቢ ጥናት ትምህርት ክፍል መምህር መንግሥቱ መላ እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ ያላትን ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር ሊሸከም የሚችል ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባት የባሕር በር ባለቤትነት መሠረታዊ ጉዳይ ነው። ሀገሪቱ ቀደም ሲል የነበራትን የባሕር በር ያጣችው ያለ ሕጋዊ መንገድ መሆኑን ገልጸው፤ አሁን ባለቤትነቷን ለማረጋገጥ የምታደርገው ጥረት በቂ የታሪክ እና የሕግ መሠረት እንዳለው አመላክተዋል። የባሕር በር ባለቤትነትን ማረጋገጥ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን፣ ለቀጣናው የጋራ ልማትም ወሳኝ ፋይዳ እንዳለው አስገንዝበዋል። መንግሥት የጀመረውን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ለማሳካትም የሁሉም ዜጎች የተቀናጀ ድጋፍ እና ተሳትፎ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። የባሕር በር ጉዳይ ከኢኮኖሚ ባሻገር የሀገርን ደኅንነት የማረጋገጥ ጉዳይ መሆኑን ያስገነዘቡት ደግሞ በጅማ ዩኒቨርሲቲ የሃይድሮሊክስ እና የውኃ ሀብት ኢንጂነሪንግ ትምህርት ክፍል መምህር ዋቅጅራ ታከለ (ዶ/ር) ናቸው። ባለቤትነትን ማረጋገጥ የሀገሪቱን የወጪና ገቢ ንግድ እንቅስቃሴ በማሳለጥ፣ የተጀመረውን ዕድገት በማፋጠን ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባት እንዲሁም ቀጣይነት ያለው ቀጣናዊ ተወዳዳሪነትን ይፈጥራል ብለዋል። መንግሥት የጀመረውን ዲፕሎማሲያዊ መርኅ መቀጠል እንዳለበት ጠቅሰው፤ ሀገሪቱ ለቀይ ባኽር ያላት ቅርበትና ከመልማት መብቷ ጋር ያለው ጥብቅ ቁርኝት ጉዳዩ የትውልዱ የማይቋረጥ ጥያቄ ሆኖ እንዲቀጥል እንደሚያደርገው አስገንዝበዋል።
ኢኮኖሚ
ተሻሽሎ የፀደቀው የኢትዮጵያ አቪዬሽን ሴኪዩሪቲ አዋጅ የሀገራችንን የአየር ትራንስፖርት ዕድገት አንድ ደረጃ ከፍ ያደርገዋል
Apr 22, 2026 476
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 14/2018(ኢዜአ)፦ ተሻሽሎ የፀደቀው የኢትዮጵያ አቪዬሽን ሴኪዩሪቲ አዋጅ የሀገራችንን የአየር ትራንስፖርት ዕድገት አንድ ደረጃ ከፍ እንደሚያደርገው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ገለጸ። 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 15ኛ መደበኛ ስብሰባ የኢትዮጵያ አቪዬሽን ሴኪዩሪቲ አዋጅን ለማሻሻል የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ 1412/18 መርምሮ አጽድቋል፡፡ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለኢዜአ በላከው መረጃ እንዳመለከተው፤ ከ21 ዓመታት በኋላ ተሻሽሎ የፀደቀው የኢትዮጵያ አቪዬሽን ሴኪዩሪቲ አዋጅ ተቋሙ የአቪዬሽን ደኅንነት ሥራዎችን በበላይነት ለመምራት እና ለማስተባበር የተሰጠውን ሀገራዊ ተልዕኮ ከስያሜው አንስቶ በግልፅ ያካተተ ሲሆን፤ የሀገራችንን የአየር ትራንስፖርት ዕድገት አንድ ደረጃ ከፍ ለማድረግ ያግዛል፡፡ የአቪዬሽን ደኅንነትን ለማጠናከር ትኩረት ከሚሰጣቸው ጉዳዮች ውስጥ የመጀመሪያው የሕግ ማዕቀፍ መሆኑንም አገልግሎቱ በመረጃው አመላክቷል። በዚህ ረገድ ነባሩ አዋጅ ኢንዱስትሪውን በሚፈለገው ደረጃ ለማሳደግ ተግዳሮት ሆኖ ከመቆየቱም በላይ የዓለም አቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት (ICAO) ተቀጽላ 17 ስታንዳርዶችን ሳያካትት መቆየቱንም ጠቁሟል፡፡ ተሻሽሎ የፀደቀው አዋጅ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የተሰጠውን የአቪዬሽን ደኅንነትን የማረጋገጥ ሀገራዊ ተልዕኮ በላቀ ብቃት ከመወጣት አንፃር የጥራትና የቁጥጥር ስራዎች ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን ጠብቀው እንዲከናወኑ የሚያስችሉ ሕጎችን መያዙም ተመላክቷል፡፡ አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ በአቪዬሽን ደኅንነት ረገድ ላስቀመጠው ራዕይ እና ስትራቴጂክ ግብ ስኬት መሰረት የሚጥል መሆኑም ጠቅሷል፡፡ ከቴክኖሎጂ አንፃር ኢንዱስትሪውን ለማዘመን አስፈላጊ የሆኑ ባለድርሻ አካላትን በኮሚቴነት መጨመሩ፤ የዓለም አቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ስታንዳርዶችን በአዲስ መልክ ማካተቱ፤ የአየር መንገዱን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ እገዛ የሚያደርግ መሆኑና ከኢንዱስትሪው ፈጣን እድገት ጎን ለጎን ለመጓዝ አቅም መፍጠር የሚያስችል የሕግ ድጋፍ መስጠቱ በፋይዳነት የሚጠቀሱ መሆናቸውንም በመረጃው ተገልጿል፡፡ የተሻሻለው የኢትዮጵያ አቪዬሽን ሴኪዩሪቲ አዋጅ ቁጥር 1412/18 በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሚያዝያ 13 ቀን 2018 ዓ.ም በአብላጫ ድምጽ መጽደቁንም አገልግሎቱ በመረጃው አመልክቷል፡፡
በተተገበሩ የሪፎርም ስራዎች የግብርና ዘርፉን ወደ ሜካናይዜሽን ማሸጋገር ያስቻሉ ተጨባጭ ወጤቶች ተመዝግበዋል
Apr 22, 2026 335
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 14/2018 (ኢዜአ)፡- ባለፉት የለውጥ ዓመታት በኢትዮጵያ የተተገበሩ የሪፎርም ስራዎች የግብርና ዘርፉን ወደ ሜካናይዜሽን ማሸጋገር ያስቻሉ ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸውን የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ ገለጹ። የ2018 በጀት ዓመት ሦስተኛው የመቶ ቀናት እና የዘጠኝ ወራት ስራ አፈጻጸም ሪፖርት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተገምግሟል። የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ በሰጡት ማብራሪያ፣ በኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት የተተገበሩ የሪፎርም ስራዎች የግብርና ዘርፉን ወደ ሜካናይዜሽን ማሸጋገር የሚያስችሉ ተጨባጭ ለውጦች መመዝገባቸውን ገልፀዋል። በዚህም አጠቃላይ ኢኮኖሚው ወደ ፊት እንዲራመድ፣ ፈጣንንና ጥራት ያለው ኢኮኖሚ እንዲመዘገብ በማስቻል ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ እድገት መመዝገቡን ጠቁመዋል። ከዚህ ቀደም ዝቅተኛ የግብርና ማሽነሪ ቁጥር ለማሳደግ መንግሥት የፖሊሲ ማበረታቻ በማድረግ አርሶ አደሮቹ ማሽነሪዎችን ከቀረጥ ነፃ እንዲያስገቡ እና የብድር አቅርቦት በማመቻቸት ሰፊ ስራ መሰራቱን አንስተዋል። በዚህም ባለፉት የለውጥ ዓመታት በተሰራው ስራ ወደ 27 ሺህ ትራክተሮች ከ8 ሺህ በላይ ኮምባይነሮች እንዲሁም ከ280 ሺህ በላይ በሞተር የሚሰሩ ፓምፖች ተደራሽ ማድርግ መቻሉን ተናግረዋል። በዚህም የግብርናው ስራ ከዝማላዳዊ አሰራር ተላቆ ወደ ሜካናይዜሽን እየተሸጋገረ መሆኑን ጠቅሰው፤ ባለፉት አመታት በተሰራ ስራ የሜካናይዜሽን እድገቱ 72 በመቶ መድረሱን ያሳያል ነው ያሉት። አጠቃላይ በኢትዮጵያ በትራክተር የሚለማ መሬት 7 ሚሊየን ሄክታር መሬት የደረሰ ሲሆን ይህ ማለት ከሚለማው መሬት አንድ ሶስተኛውን በትራክተር ማልማት እንደተቻለ ገልፀዋል። ይህም ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ለገበያ የሚቀርበውን ምርት በማሳደግ የአርሶ አደሩን ህይወት በመቀየር ረገድ ትልቅ ለውጥ ማስመዝገቡን ጠቁመዋል። በመሆኑም ባለፉት የለውጥ አመታት ተግባራዊ የተደረገው ሪፎርም የግብርና ትራንስፎርሜሽንን ለማረጋገጥ ትልቅ አቅም የፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህም ግብርናውን ከዝናብ ጥገኝነት ወደ መስኖ ለማሸጋገር በተደረገው ጥረት የመስኖ ልማት ሽፋኑ ከዓመት ወደ ዓመት እየጨመረ መጥቷል ነው ያሉት። በዘንድሮው ዓመት ብቻ 4 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር መሬት በመስኖ ስንዴ ለማልማት ታቅዶ እስካሁን ወደ 3 ነጥብ 87 ሚሊየን ሄክታር ማልማት መቻሉን ጠቅሰዋል። ይህም አርሶ አደሩ ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ በዓመት ሁለትና ከዚያ በላይ እንዲያመርት በማድረግ እንደ ሀገር የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የተያዘውን ግብ ለማሳካት ተጨባጭ ለውጥ ማሳየቱን ተናግረዋል። በተጨማሪም ለዜጎች ሰፋፊ የስራ እድል እየፈጠረ እንደሚገኝም ገልጸዋል። አርሶ አደሩ ከምግብነት ባለፈ በመጠንም በጥራትም ተወዳዳሪ ምርቶችን በማምረት ለዓለም ገበያ ተደራሽ እያደረጉ መሆኑን ተናግረዋል።
ባለፉት ዘጠኝ ወራት 4 ነጥብ 85 ቢሊየን ዶላር የሚያወጡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ መተካት ተችሏል
Apr 22, 2026 355
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 14/2018 (ኢዜአ)፡- ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ 4 ነጥብ 85 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ ገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ መተካት መቻሉን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ገለጹ። የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ለዘርፉ ትልቅ መሰረት መጣሉን የገለጹት ሚኒስትሩ፣ በገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን 754 ኢንዱስትሪዎች ወደ ማምረት መግባታቸውን ጠቁመዋል። የ2018 በጀት ዓመት ሦስተኛው የመቶ ቀናት እና የዘጠኝ ወራት ስራ አፈጻጸም ሪፖርት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተገምግሟል። የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል በሰጡት ማብራሪያ የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግርን በማሳካት ረገድ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸውን አንስተዋል። የሪፎርም ሥራዎቹ ምርትና ምርታማነትን በመጨመር እንዲሁም የዜጎችን ኑሮ በማሻሻል ስኬታማ መሆናቸውን አንስተዋል። ቀደም ሲል 4 ነጥብ 8 በመቶ ብቻ የነበረው የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ዕድገት አሁን ላይ በሁለት አሃዝ አድጎ ከ13 በመቶ በላይ ደርሷል ነው ያሉት። የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶች ገቢ ምርትን በመተካትና በወጪ ንግድ ዘርፍ አመርቂ ለውጥ ማምጣታቸውን ጠቁመዋል። ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ 433 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ የኢንዱስትሪ ምርቶች ለውጭ ገበያ የቀረቡ ሲሆን የዘርፉ የኃይል አጠቃቀምም ማደጉን ተናግረዋል። የገቢ ምርትን በሀገር ውስጥ ለመተካት በተሠራው ሥራ 4 ነጥብ 85 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ ተኪ ምርቶችን ማምረት መቻሉን አስታውቀዋል። ይህ ውጤት የኑሮ ጫናን በማቅለል እና የኢኮኖሚ መነቃቃትን በማምጣት ረገድ ትልቅ ሚና መጫወቱን አስገንዝበዋል። የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ለዘርፉ ትልቅ መሰረት መጣሉን የገለጹት ሚኒስትሩ፣ በገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን 754 ኢንዱስትሪዎች ወደ ማምረት መግባታቸውን ጠቁመዋል። በቀጣይም የምርት አቅምን ለማሳደግ የፋይናንስ፣ የግብዓት፣ የኃይል አቅርቦት እና ምቹ የገበያ ሁኔታዎችን በመፍጠር ላይ በትኩረት እንደሚሰራ አስረድተዋል።
ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከማዕድን ዘርፍ ወጪ ንግድ አራት ቢሊዮን ዶላር ገደማ ገቢ ተገኝቷል
Apr 22, 2026 227
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 14/2018 (ኢዜአ)፡- ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከማዕድን ዘርፍ ኤክስፖርት አራት ቢሊዮን ዶላር ገደማ ገቢ መገኘቱን የማዕድን ሚኒስትር ኢንጅነር ሀብታሙ ተገኝ ገለጹ፡፡ የ2018 በጀት ዓመት ሦስተኛው የመቶ ቀናት እና የዘጠኝ ወራት ስራ አፈጻጸም ሪፖርት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተገምግሟል። የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጅነር ሀብታሙ ተገኝ በሰጡት ማብራሪያ፣ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ ከማዕድን ወጪ ንግድ ወደ አራት ቢሊዮን ዶላር ገደማ ገቢ መገኘቱን ይፋ አድርገዋል። እንደ ሚኒስትሩ ማብራሪያ፣ በዘርፉ የታየው ውጤት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ87 በመቶ እድገት አሳይቷል። ይህ የአራት ቢሊዮን ዶላር ገቢ ከሦስት ዓመታት በፊት የሀገሪቱ አጠቃላይ ዓመታዊ የኤክስፖርት ገቢ የነበረውን ያህል መሆኑ፣ ዘርፉ በአጭር ጊዜ ውስጥ ያመጣውን ግዙፍ ለውጥ ያመላክታል ብለዋል። ለዘርፉ ስኬት ዋነኛው ምክንያት የሀገሪቱ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያ መሆኑን ጠቁመዋል። በተለይም ባለሀብቶች ያገኙትን ትርፍ በውጭ ምንዛሬ ወደ ውጭ ማውጣት መቻላቸው፤ የኢንቨስትመንት ስጋቶች መቀነሳቸው እና መንግሥት ለዘርፉ የሰጠው ልዩ የማበረታቻ ሥርዓት በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ ግዙፍ ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ አድርጓል ነው ያሉት። ከወርቅ ባለፈ ሌሎች ማዕድናትም ትኩረት እንደተሰጣቸው አንስተዋል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከፍተኛ የወርቅ ሀብት ካላቸው ሀገራት ተርታ እየተሰለፈች ሲሆን፥ ከወርቅ በተጨማሪ ሌሎች ማዕድናት ላይ ትኩረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል። እስካሁን በፍለጋ ደረጃ የነበሩ እንደ ጋዝ፣ ፖታሽ፣ ሊቲየም እና ኒኬል ያሉ ማዕድናት ወደ ምርት እንዲገቡ እየተደረገ መሆኑን ነው ያነሱት። እነዚህ ማዕድናት በቀጣይ የዘርፉን የኤክስፖርት ገቢ በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያሳድጉትም አንስተዋል። ከማዕድን ወጪ ንግድ ባሻገር እንደ ብረት፣ ሲሚንቶ እና ድንጋይ ከሰል ያሉ ማዕድናት የሀገር ውስጥ ፍላጎትን በማሟላት የውጭ ምንዛሬን ለማዳን ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ ነው ያሉት። ከሀገር ውስጥ ፍላጎት የሚተርፈው ምርት ደግሞ ወደ ውጭ ገበያ እንደሚላክ አስረድተዋል። አዲስ የተረቀቀው የማዕድን ፖሊሲ ሲጸድቅ እና አሁን የተጀመረው የሪፎርም ስራ ተጠናክሮ ሲቀጥል፣ ዘርፉ ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ይበልጥ እንደሚያድግ አብራርተዋል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
የአፍሪካ የዲጂታል ድምጾች ለጠንካራ ዓለም አቀፍ ትርክት ግንባታ ወሳኝ ናቸው
Apr 22, 2026 122
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 14/2018(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ የዲጂታል ድምጾች ለጠንካራ ዓለም አቀፍ ትርክት ግንባታ ወሳኝ መሆናቸውን የ ፐልስ ኦፍ አፍሪካ ሚዲያ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍጹምሸት ሽመልስ ገለጹ። አዲስ አበባ እ.አ.አ 2026 በመጪው ግንቦት 7 እና 8 ቀን የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤን (ASMIS-2026) በዓድዋ ድል መታሰቢያ ለማስተናገድ ዝግጅት እያደረገች ይገኛል። አህጉራዊ ጉባኤውን በስኬት ለማስተናገድም ፐልስ ኦፍ አፍሪካ (Pulse of Africa-POA) እና ኤጂኤ ቴክ (AGA-Tech) የባለድርሻና ተባባሪ አካላት የምክክር መድረክ አካሂደዋል። የመድረኩ ዓላማም ጉባኤውን በስኬት ማስተናገድ በሚቻልባቸው የዝግጅት ሂደትና የትብብር ድጋፎች ላይ ትኩረት አድርጓል። በዚሁ ጊዜ የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ በተፅዕኖ ፈጣሪዎች፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ በአፍሪካ ዳያስፖራዎችና የግሉ ዘርፍ ተዋናዮች የረጅም ጊዜ ትብብር የሚፈጠርበት መሆኑ ተገልጿል። የፐልስ ኦፍ አፍሪካ ሚዲያ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍጹምሸት ሽመልስ በዚሁ ወቅት፤ የአፍሪካ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የአህጉሪቱን ዓለም አቀፍ አመለካከት የሚቀይር ታሪካዊ ዕድል ነው ብለዋል። በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች በአፍሪካ ዙሪያ የሚፈጠሩ፣ የሚቀረጹና የሚሰራጩ ትርክቶች ዓለም ለአህጉሪቱ የሚሰጠውን የተሳሳተ ግምት ለመቀየር ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ገልጸዋል። የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤም የአፍሪካን ትክክለኛ ታሪክ፣ ስኬትና ምኞት የበለጠ ለማጉላት የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎችን አቅም ማጎልበት እንደሚያስችል ተናግረዋል። ኤጂኤ ቴክ (AGA-Tech) ኢንተርፕራይዝ ሥራ አስኪያጅ ገመዳ ኦላና በበኩላቸው፤ በርካታ የአፍሪካ ማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች በጉባኤው ለመሳተፍ ከፍተኛ ፍላጎት እያሳዩ መሆኑን ገልጸዋል። በጉባኤው የአፍሪካን ትርክት የሚያጎላ ጠንካራና ተቀባይነት ያለው የይዘት ፈጠራ ሥነ-ምኅዳር ግንባታ ላይ ትኩረት እንደሚደረግ ተናግረዋል። መድረኩ የባለድርሻ አካላትን ትብብር በማጠናከር የአህጉሪቱን የይዘት ጥራትና ፈጠራ በማሻሻል ተወዳዳሪ የዲጂታል ኢኮኖሚን ለመደገፍ ያለመ ነው ብለዋል። በተሳታፊዎች መካከልም በአጋርነት፣ ቅንጅት፣ ተግባቦት፣ ስትራቴጂክ አመራርና በሃብት ማሰባሰብ ጉዳዮች ላይ ጥልቅ ምክክር እንደሚደረግ አስረድተዋል። በአጠቃላይ ጉባኤው የዲጂታል ድምጾችን በማስተሳሰር የአህጉሪቱን ታሪክ የመንገር አቅም የሚያጎለብትና ዓለምአቀፍ ተፅዕኖ ፈጣሪነትንና ንቁ ተዋናይነትን የሚያጠናክር መሆኑን አብራርተዋል። በውይይቱ ጉባኤው ትርጉም ያለውና ዘላቂ ተጽዕኖ እንዲያሳድር ትብብርና የጋራ ጥረት አስፈላጊ መሆኑንና ባለድርሻ አካላት ለጉባኤው ስኬት ገንቢ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠቁመዋል።
መሶብ የአንድ ማዕከል ተንቀሳቃሽ አገልግሎት ዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባት ቁልፍ ሚና ይጫወታል
Apr 22, 2026 133
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 14/2018(ኢዜአ)፦ መሶብ የአንድ ማዕከል ተንቀሳቃሽ አገልግሎት ዜጎች የመንግሥትን አገልግሎት በቅርበት እንዲያገኙ በማድረግ ዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባት ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ(ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መሶብ የአንድ ማዕከል ተንቀሳቃሽ አገልግሎትን አስጀምረዋል። በዚሁ ወቅት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ(ዶ/ር)፤ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ በኢትዮጵያ አጠቃላይ ለመንግሥት አገልግሎት መሳለጥ ወሳኝ መሰረት ጥሏል ብለዋል። በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂም በቅርቡ ወደ ስራ በማስገባት የኢትዮጵያን የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ እያሳለጠ እንደሚገኝ ገልጸዋል። በኢትዮጵያ ከዓመታት በፊት የሚሰጡ የመንግሥት አገልግሎቶች የዜጎች እንግልት ምንጭ እንደነበሩ አስታውሰዋል። ለዚህም ከዓመት ወዲህ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን በማስጀመር ዜጎች የመንግሥት አገልግሎቶችን ፈጣን፣ ዘመናዊና ግልፅ በሆነ አሰራር እንዲያገኙ እያስቻለ መሆኑን ተናግረዋል። የዲጂታል እመርታ መንግሥት የአገልግሎት ቅልጥፍና መገለጫ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፤ የአንድ ማዕከል አገልግሎትም ዜጎች በርካታ አገልግሎቶችን በአንድ ቦታ የሚያገኙበትን ዕድል ፈጥሯል ብለዋል። ይህም እንግልትን በማስቀረት የመንግሥትን የሥራ ሂደት በማፋጠን የተሻለ የኢኮኖሚ ሥርዓት ለመገንባት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት አስረድተዋል። ለአብነትም የዲጂታል መታወቂያን ጨምሮ የተበታተኑ የመንግሥት አገልግሎቶች በአንድ ማዕከል መሰጠት ሲችሉ ከፍተኛ ሀገራዊ ፋይዳ እንዳላቸው አብራርተዋል። በአዲስ አበባ የተጀመረው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በክልሎች ጭምር የተደራሽነት አድማሱን በማስፋት ከፍተኛ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እያበረከተ መሆኑን አንስተዋል። በቀጣይም በዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ ዕቅድ መነሻነት የተገኘውን እመርታ በማስፋት የኢትዮጵያን ታላቅነት የሚመጥን አቅም ለመገንባት መትጋት ይጠይቃል ብለዋል። የአዲስ አበባ መሶብ የአንድ ማዕከል ተንቀሳቃሽ አገልግሎት መንግሥት አገልግሎቶችን ወደ ዜጎቹ ለማቅረብ ታስቦ ሥራ ላይ የዋለ ወሳኝ እርምጃ መሆኑንም ገልጸዋል። ይህም ዜጎች ባሉበት ቦታ የሚቀርብላቸውን የመንግሥት አገልግሎቶች በጥራት እንዲያገኙ በማስቻል ዲጂታል ኢኮኖሚና ሀገር ለመገንባት ቁልፍ ሚና እንደሚጫወቱ አብራርተዋል።
መሶብ የአንድ ማዕከል ተንቀሳቃሽ አገልግሎት የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ለሚታዩ ችግሮች ወሳኝ መፍትሔ ነው
Apr 22, 2026 122
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 14/2018 (ኢዜአ)፦ በመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ለሚታዩ መሠረታዊ ችግሮች መሶብ የአንድ ማዕከል ተንቀሳቃሽ አገልግሎት ወሳኝ መፍትሔ የሚሰጥ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መሶብ የአንድ ማዕከል ተንቀሳቃሽ አገልግሎትን አስጀምረዋል። የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በዚሁ ወቅት፤ ከዓመታት በፊት የመንግሥት አገልግሎቶች ዜጎችን ለብልሹ አሰራርና እንግልት በመዳረግ የዘመናት ጥያቄ ሆነው መቆየታቸውን አስታውሰዋል። ይህም የዜጎችን ምሬት በማባባስ የኢትዮጵያን ዕድገት የሚጎትት እንደነበር አስገንዝበዋል። በዚህም ለአገልግሎት የጥራት ችግር መፍትሔ ለማበጀት በመንግስት ደረጃ ተከታታይ ምክክር በማድረግ የዲጂታላይዜሽን ምኅዳር መፍጠር እንደተቻለ አንስተዋል። መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትም የመንግሥትን አገልግሎት ከደላላና ከሰው ንክኪ ነፃ የአሰራር ሥርዓት ለዜጎች በማቅረብ አገልግሎትን የሚያሳልጥ ምኅዳር መፍጠሩን ገልጸዋል። ይህም የሥራ ቅልጥፍን በማሳለጥ ከፍተኛ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ እንዳለው ተናግረዋል። መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትም ትላልቅ የመንግሥት አገልግሎቶችን ወደ ዜጎች በማቅረብ የተገልጋዮችን ፍላጎት የሚያሳልጥ ወሳኝ እርምጃ መሆኑን አንስተዋል። ዜጎች የመንግሥትን አገልግሎት በነፃነት የማግኘት መብት አላቸው ያሉት ሚኒስትሩ፤ በዚህም ዜጎች መንግሥት የዘረጋቸውን ዘመናዊ የአሰራር ስርዓቶች በመጠቀም ግብርን በግልፀኝነት መክፈል እንደሚጠበቅም አስገንዝበዋል። በአጠቃላይ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ ይስተዋል የነበረውን መሠረታዊ ችግር መፍትሄ የሚሰጥ ወሳኝ አሰራር መሆኑን አስረድተዋል። ዜጎችም የመንግሥትን ዘመናዊ፣ ግልፅና ቀልጣፋ የአሰራር ሥርዓት ሊጠቀምበት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
መሶብ የአንድ ማዕከል ተንቀሳቃሽ አገልግሎት ለህዝቡ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ትልቅ የምስራች ነው
Apr 22, 2026 140
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 14/2018 (ኢዜአ)፦ መሶብ የአንድ ማዕከል ተንቀሳቃሽ አገልግሎት ለህዝቡ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ትልቅ የምስራች ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዓይነቱ ልዩና የመጀመሪያ የሆነውን የአዲስ መሶብ ተንቀሳቃሽ ዲጂታል አገልግሎት አስጀምረዋል። ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ የከተማ አስተዳደሩ የአገልግሎት አሰጣጥ ቢሮክራሲን ለመቀነስ እና ተገልጋዮችን ከእንግልት ለመታደግ ያስቻሉ የመሶብ የተቀናጀ አገልግሎት መስጫ ማዕከላትን በስፋት ወደ ስራ አስገብቷል። ይህ አዲስ አሰራር ከቢሮ ወጥቶ አገልግሎትን ወደ ህዝብ ተደራሽ የሚያደርግ ነው ብለዋል። ይህ ዘመናዊ የዲጂታል አገልግሎ አሰጣጥ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መመሪያ ከተሰጠ በኋላ የከተማ አስተዳደሩ በከተማው የመጀመሪያውን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ጳጉሜን 5 ቀን 2017 ዓ.ም በይፋ ማስጀመራቸውን አስታውሰዋል። በዚህም እስካሁን በቦሌ፣ ልደታ፣ ቂርቆስ፣ አዲስ ከተማ እና ጉለሌ ክፍለ ከተሞች ስድስት የአገልግሎት ማዕከላት ተከፍተው ለሕዝቡ ፈጣን አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኙም ተናግረዋል። በእነዚህ ማዕከላት ውስጥ ከ150 በላይ የተለያዩ የመንግስት አገልግሎቶች በአንድ ማዕከል እንዲሰጡ ተደርጎ የተደራጁ ሲሆን፤ ይህም የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደቱን ፈጣንና ቀልጣፋ እንዲሆን አስችሏል ብለዋል። እስካሁን 150 ሺህ የሚሆኑ ነዋሪዎች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን መቻላችውን ጠቅሰው፤ ይህም የተገልጋዩን እርካታ 98 በመቶ ማድረስ መቻሉን ተናግረዋል። አስቸጋሪ የነበረውን ቢሮክራሲ ያቀለለው የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ለህዝቡ ትልቅ እፎይታ የፈጠረ ሲሆን፤ በቀጣይም ተጨማሪ አገልግሎቶች በዚሁ ሥርዓት ውስጥ ተካተው እንደሚቀጥሉ ከንቲባዋ አረጋግጠዋል። ከንቲባ አዳነች እንደገለፁት፤ እስከ ግንቦት አጋማሽ ድረስም አምስት አዳዲስ የመሶብ አንድ ማዕከል ዲጂታል አገልግሎት መስጫዎች ተከፍተው በይፋ ወደ ሥራ ይገባሉ። አዲሱ ተንቀሳቃሽ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መንግስት ህዝብ ድረስ በመቅረብ አገልግሎት እንዲሰጥ በማስቻል አዲስ የአገልግሎት አድማስ የከፈተ ትልቅ የምስራች ነው ብለዋል። ይህ ተነሳሽነት አገልግሎት አሰጣጥን ይበልጥ ተደራሽ እና ዘመናዊ በማድረግ፣ ነዋሪዎች ያለምንም እንግልት ፍላጎታቸውን እንዲያሟሉ የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል። ተንቀሳቃሽ የመሶብ አገልግሎት የሚሰጡ አውቶቢሶች አስተማማኝ የኤሌክትሪክና የኢንተርኔት መሰረተ ልማት የተሟላላቸው መሆኑን ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት ስምንት የተለያዩ ተቋማትን በማሰባሰብ 36 አገልግሎቶች በአንድ ላይ በማቀናጀት ለህዝቡ በቅርበት እየተሰጠበት ይገኛልም ነው ያሉት። ይህ ዘመናዊ የዲጂታል አሰራር የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደቱን ግልጽና ቀልጣፋ ከማድረጉም በላይ፣ አድሎአዊ አሰራሮችን በማስቀረት ረገድ የማይተካ ሚና እንደሚጫወት ከንቲባዋ ገልጸዋል።
ስፖርት
ቼልሲ ሊያም ሮሲኒየርን አሰናበተ
Apr 22, 2026 351
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 14/2018 (ኢዜአ)፦ የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ዋና አሰልጣኙን ሊያም ሮሲኒየርን ከኃላፊነት ማሰናበቱን በይፋ አስታውቋል። አሰልጣኙ በስታምፎርድ ብሪጅ በነበራቸው ቆይታ ክለቡን መምራት የቻሉት ለአራት ወራት ብቻ ሲሆን፣ ይህ ውሳኔ የተላለፈው ቡድኑ እያሳየ ባለው እጅግ ደካማ ውጤት ምክንያት መሆኑን ቢቢሲ ክለቡን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል። በሮሲኒየር መሪነት ቼልሲ ካለፉት ዘጠኝ የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው በአንዱ ብቻ ሲሆን፣ በተለይም ባለፉት አምስት ጨዋታዎች ቡድኑ ምንም አይነት ግብ ሳያስቆጥር መሸነፉ ለአመራሮቹ ትዕግስት ማጣት ዋነኛ ምክንያት መሆኑ ተገልጿል። ቼልሲ ትናንት በሊጉ በብራይተን 3 ለ 0 መሸነፉ ይታወቃል። ሮሲኒየር የስድስት ዓመት ተኩል ረጅም ኮንትራት ፈርመው ወደ ክለቡ ቢመጡም፣ ቼልሲን በደረጃ ሰንጠረዡ ወደ ሰባተኛ ደረጃ ዝቅ ማድረጋቸው እና የቻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎ እድላቸውን አደጋ ላይ መጣላቸው ለስንብቱ ምክንያት ሆኗል። ክለቡ ለሮሲኒየር እና ለረዳቶቻቸው በቆይታቸው ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋናውን አቅርቧል። በመጪው እሁድ ቼልሲ ከሊድስ ዩናይትድ ጋር ለሚያደርገው የኤፍ ኤ ካፕ (FA Cup) የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ፣ ካሉም ማክፋርሌን ቡድኑን በጊዜያዊ አሰልጣኝነት እንደሚመሩ ክለቡ አስታውቋል። ቼልሲ በአሁኑ ወቅት ቋሚ አሰልጣኝ ለመቅጠር ጥረት እያደረገ ሲሆን፣ ይህም በባለቤቱ ቶድ ቦህሊ ዘመን አምስተኛው አሰልጣኝ እንደሚሆን ቢቢሲ ዘግቧል።
አትሌት ገመኔ ማሚቴ ምትኩ በተከለከለ አበረታች ቅመም ምክንያት የስድስት ዓመት እገዳ ተጣለባት
Apr 22, 2026 219
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 14/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን አትሌት ገመኔ ማሚቴ ቱኩ የተከለከሉ አበረታች ቅመሞችን (Doping) ተጠቅማ በመገኘቷ የስድስት ዓመት የእገዳ ቅጣት እንደተጣለባት አስታወቀ። ባለስልጣኑ በሁለት የተለያዩ ውድድሮች ላይ ባካሄዳቸው ምርመራዎች፣ አትሌቷ ኤሪትሮፖይቲን (EPO) እና ዴክሳሜታሶን (Dexamethasone) የተባሉ የተከለከሉ ንጥረ ነገሮችን መጠቀምዋን ማረጋገጡን አመልክቷል። በዚህም መሠረት አትሌት ገመኔ ማሚቴ ቱኩ ጊዜያዊ እገዳ ከተጣለባት ጥቅምት 2 ቀን 2018 ዓ.ም (November 11, 2025) ጀምሮ ለስድስት ዓመታት የሚጸና፣ በማንኛውም ስፖርታዊ ውድድር እንዳትሳተፍ እገዳ መጣሉን ገልጿል። በተጨማሪም አትሌቷ ከግንቦት 3 ቀን 2017 ዓ.ም (May 11, 2025) ጀምሮ በተካሄዱ የተለያዩ ውድድሮች ያስመዘገበቻቸው ውጤቶች በሙሉ እንዲሰረዙ ተወስኗል። ይህም ሜዳሊያዎችን፣ የማዕረግ ስሞችን፣ ደረጃዎችን እና የሽልማት ገንዘቦችን መመለስን እንደሚጨምር ነው ባለስልጣኑ ያስታወቀው። በቀጣይም በሀገሪቱ በየደረጃው የሚደረገው የምርመራና ቁጥጥር ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተመልክቷል። የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን የስፖርት አበረታች ቅመሞችን በመጠቀምም ሆነ በተለያየ መልኩ የፀረ-አበረታች ቅመሞች የህግ ጥሰት በሚፈጽሙ አትሌቶችና ከጀርባ ሆነው በሚያበረታቱ ሌሎች ግለሰቦች ላይ የሚወሰደው የእርምት እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።
መቀሌ 70 እንደርታ ለኢትዮጵያ ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜ አለፈ
Apr 22, 2026 113
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 14/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ የመጀመሪያ ጨዋታ መቀሌ 70 እንደርታ ቦዲቲ ከተማን 3 ለ 2 አሸንፏል። በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ፍጹም ዓለሙ፣ ፕሪንስ ኦፎሪ እና ቦና ዓሊ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል። ሙሉቀን ተስፋዬ እና ቴዎድሮስ በለጠ ለቦዲቲ ከተማ ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። ውጤቱን ተከትሎ መቀሌ 70 እንደርታ ግማሽ ፍጻሜ የገባ የመጀመሪያ ቡድን ሆኗል። የኢትዮጵያ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ መርሐ ግብር እስከ ሚያዚያ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።
በክልሉ ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት በትምህርት ቤቶች ውስጥ ቅንጅታዊ ተግባራት እየተከናወኑ ነው
Apr 22, 2026 74
ጅማ ፤ሚያዝያ 14/2018 (ኢዜአ)፡-በኦሮሚያ ክልል ከመማር ማስተማር ሥራው ጎን ለጎን ብቁ እና ተወዳዳሪ ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት በትምህርት ቤቶች ውስጥ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን የማጠናከር ሥራ በቅንጅት እየተከናወነ መሆኑ ተገለጸ። የጅማ ዞን ትምህርት ቤቶች ስፖርታዊ ውድድር በጅማ ከተማ የተጀመረ ሲሆን፣ በውድድሩ ላይ ከዞኑ የተለያዩ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ከ530 በላይ ተማሪዎች ይሳተፋሉ። ውድድሩ ለሚቀጥሉት 10 ቀናት እንደሚቆይም ተገልጿል። በመክፈቻ ፕሮግራሙ ላይ የታደሙት የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ካሳሁን ገላና (ዶ/ር)፣ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት የሚረጋገጠው በትምህርት እና በቴክኖሎጂ ነው ብለዋል። ጠንካራ የትምህርት ተቋማትን መገንባት የሚቻለው በዕውቀትም ሆነ በአካል የጎለበቱ ተማሪዎችን ማፍራት ሲቻል መሆኑን ጠቅሰው፣ ይህንን ግብ ለማሳካትም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እየተሠራ ይገኛል ብለዋል። በክልሉ የመማር ማስተማር ሥራውን ውጤታማ ከማድረግ ጎን ለጎን ትምህርት ቤቶች ተተኪ ስፖርተኞች ማፍሪያ ስፍራ እንዲሆኑ ትኩረት ተደርጓል ነው ያሉት። የጅማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቲጃኒ ናስር በበኩላቸው፣በዞኑ የስፖርት ማዘውተሪያዎችን የማስፋፋት፣ ምቹ ሁኔታዎችን የመፍጠርና የስፖርት ትጥቆችን የማሟላት ሥራ በትኩረት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። የጅማ ዞን ትምህርት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሚፍታ አብዱልቃድር እና የዞኑ ወጣቶችና ስፖርት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ነጉማ መኮንን፣ በዞኑ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ስፖርትን የማጠናከር ሥራ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል። ከዚህ ቀደም ከትምህርት ቤቶች የወጡ ወጣቶች በዓለም አቀፍ መድረክ ኢትዮጵያን ማስጠራት መቻላቸውን አስታውሰው፣ ነገ አገርን የሚያስጠሩ ስፖርተኞችን ለማፍራት የትምህርት ተቋማትን የመደገፍና የማበረታታት ሥራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ ከሲጊሞ ወረዳ የመጣው ተማሪ መሀመድ ከሊፋ እና ከሰቃ ጨቆርሳ የመጣችው ተማሪ ተንዚላ ዛኪር በሰጡት አስተያየት፤ በትምህርት ቤቶቻቸው ውስጥ እንደ ፍላጎታቸውና ተሰጥኦዋቸው በሳምንት ሦስት ቀን ልምምድ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል። አስፈላጊው ስፖርታዊ ትጥቅና የመለማመጃ ስፍራም እንደተመቻቸላቸው ተናግረዋል።
አካባቢ ጥበቃ
የአረንጓዴ ዐሻራ ልማት በአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት በምሳሌነት የሚጠቀስ ነው
Apr 22, 2026 107
ሐዋሳ፤ ሚያዝያ 14/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ዐሻራ ልማት በአፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት በምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን የአፍሪካ አረንጓዴ አብዮት ጥምረት (AGRA) የቦርድ ሊቀመንበር ኃይለማርያም ደሳለኝ ገለጹ። ሊቀመንበሩ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂ ከሀገር ባለፈ አህጉራዊ የልማት ትብብርና ትስስርን መሰረት ባደረገ መልኩ በስኬት መቀጠሉን አንስተዋል። ኢትዮጵያ የአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂዋ ከተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ እና የአየር ንብረት ለውጥን ከመከላከል ባለፈ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችል መሆኑንም ገልጸዋል። በተለይም ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ የልማት ሥራዎች አስደናቂ መሆናቸውን አውስተው፤ እንደ ሀገር ትልቅ ስኬት የተመዘገበበት መሆኑን ተናግረዋል። ባለፉት ዓመታት በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ችግኞች መተከላቸው የተፈጥሮ ሃብትን ከመጠበቅና የአየር ንብረት ለውጥን ከመከላከል ባለፈ የምግብ ዋስትና መሰረት መሆናቸው በተግባር ታይቷል ብለዋል። በመሆኑም የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ዐሻራ ልማት በአፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት በምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን ነው ያመላከቱት። ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ላይ ትኩረት ተደርጎ መሠራቱም ለግብርና ልማትና ምርታማነት መሰረት እየሆነ መጥቷል ነው ያሉት። የዘርፉ ልማት ቀጣይነትን የሚጠይቅ በመሆኑ ችግኞችን መትከል እንዳለ ሆኖ፤ የተተከሉትን የመጠበቅና የመንከባከብ ልምድ እየዳበረ መሄድ እንዳለበትም ጠቁመዋል።
በከተማ አስተዳደሩ የተከናወኑ የአረንጓዴ አሻራ ሥራዎች አርሶ አደሩን ተጠቃሚ አድርገዋል
Apr 21, 2026 305
ወላይታ ሶዶ፤ሚያዚያ 13/2018(ኢዜአ)፦በወላይታ ሶዶ ከተማ በአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር የተከናወኑ የልማት ሥራዎች የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት እያረጋገጡ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ። በከተማ አስተዳደሩ "አረንጓዴ አሻራ ለተምሳሌት ሀገር ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ቃል የዘንድሮ የበልግ ወቅት የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በመርካቶ ክፍለ ከተማ ቦሳ ዝጋ ቀበሌ ተካሂዷል። የከተማው ከንቲባ ወይዘሮ እታገኝ ኃይለማርያም በመርሃ ግብሩ ላይ እንደገለጹት ባላፉት የለውጡ ዓመታት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተከናወኑ የልማት ሥራዎች የአርሶ አደሮችን ተጠቃሚነት አረጋግጠዋል። በመርሀ ግብሩ የተተከሉ ችግኞች የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ በተጨማሪ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከልና ሚዛኑን ለመጠበቅ እያገዙ መሆናቸውን ተናግረዋል። በዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርም የችግኝ ተከላ ሥራውን ለማስቀጠል የቡና፣ የእንሰት የአቮካዶና ሌሎች የፍራፍሬ ችግኞችን ለመትከል ሙሉ ዝግጅት በማድረግ ወደ ሥራ መገባቱንም ተናግረዋል። የወላይታ ሶዶ ከተማ ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ንጋቱ ቡሹራ በበኩላቸው ባለፉት ዓመታት በተሰሩ የአረንጓዴ አሻራ ስራዎች የአርሶ አደሩን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማሳደግ ተችሏል። ለዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር ለተከላ ከተዘጋጁ ችግኞች ውስጥ 150 ሺህ የሚሆኑት የተሻሻሉ የቡና ዝርያ ችግኞች መሆናቸውንም አመልክተዋል። ከዚህ በተጨማሪ ምርታማነታቸው በምርምር የተረጋገጡ የእንሰት፣ የአቮካዶ እና ሌሎች የፍራፍሬ ችግኞች መዘጋጀታቸውን ነው የገለጹት። የሚተከሉ ችግኞች ውጤታማ እንዲሆኑም የተጠናከረ የባለሙያዎች ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል። በመርሀ ግብሩ ላይ ከተሳተፉ አርሶ አደሮች አቶ ደበላ ዳና እና አቶ ኤልያስ ጁና በውሃ ገብ መሬቶችና እና በእርሻ ማሳቸው ላይ ባህር ዛፎችን እና ያረጁ ቡናዎችን በመተካት ልማቱን ማከናወናቸውን ጠቁመዋል። በችግኝ ተከላው ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው ፍራፍሬዎችን በመትከል ተጠቃሚ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ በበኩላቸው በዞኑ ባለፉት ዓመታት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች መተከላቸውን አንስተዋል። በዘንድሮ የአረንጎዴ አሻራ መርሃግብርም የቡና ችግኝ በስፋት ለመትከል ዝግጅት መደረጉን ነው የገለጹት። አርሶ አደሮችም በመርሀግብሩ ቡናና ሌሎች ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው የፍራፍሬ ችግኞችን ተክለው በመንከባከብ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን እንዲያሳድጉ አሳስበዋል። በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ላይ የዞንና የከተማ የመንግስት ሥራ ኃላፊዎች፣ ባለሙያዎች እንዲሁም አርሶ አደሮች ተገኝተዋል።
ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የወሰደቻቸው ተጨባጭ እርምጃዎች ውጤት እያስገኙ ነው
Apr 21, 2026 161
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 13/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የወሰደቻቸው ተጨባጭ እርምጃዎች ውጤት እያስገኙ መሆኑን የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ገለጸ። ኢንስቲትዩቱ ከአፍሪካ የሚቲዎሮሎጂ ሶሳይቲ ጋር በመተባበር ለመጀመሪያ ጊዜ ያዘጋጀውን ሳይንሳዊ ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ እያካሄደ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተርና በዓለም ሚቲዎሮሎጂ ድርጅት የአፍሪካ አህጉር ፕሬዚዳንት አቶ ፈጠነ ተሾመ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት፤ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም ለዘርፉ ተስማሚ የሆኑ የኃይል አማራጮችንና የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችን በተግባር እያከናወነች ትገኛለች፡፡ ለዚህም እንደ አብነት ከሚጠቀሱት መካከልም ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የታዳሽ ኃይል ልማት ተምሳሌትና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ ግንባታ ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተተገበረ ያለው የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃና የደን ልማት ስራዎች ተጨባጭ መፍትሄዎች መሆናቸውን ጠቅሰዋል። የአየር ንብረት ለውጥ ድንበር ተሻጋሪ በመሆኑ ተጽዕኖውን ለመቋቋም የጋራ ጥረትና ትብብር መሰረታዊ ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ከኮንፈረንሱ ለአፍሪካ ውጤታማ የሆኑ ሳይንሳዊ መፍትሄዎች እንደሚገኙም ገልጸዋል፡፡ የአፍሪካ የሚቲዎሮሎጂ ሶሳይቲ የቦርድ ሰብሳቢ ቡሩሃኒ ናይንዚ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ ሶሳይቲው የተቋቋመው ሀገር አቀፍ የሚቲዎሮሎጂ ማህበራትን ለማጠናከርና በዘርፉ ያሉ ባለሙያዎችን ለማስተሳሰር መሆኑን ገልጸዋል። ሳይንሳዊ ኮንፈረንሱ በአካባቢ ጥበቃ፣ በአየር ትንበያና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የሚሰሩ ተቋማትና ባለድርሻ አካላትን እንደሚያገናኝም ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም የልምድና የዕውቀት ልውውጥ በማድረግ የባለሙያዎችን አቅም እንደሚገነባ ጠቅሰው በአፍሪካ የሚቲዎሮሎጂ ሳይንስ እድገት ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም ጠቁመዋል፡፡ ይህ ኮንፈረንስ ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ ያላትን ተሞክሮ ለማካፈል እንደሚረዳም ተጠቁሟል፡፡
በሚቀጥሉት አስር ቀናት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ አካባቢዎች የዝናብ ቀጣይነት ይኖራል
Apr 20, 2026 103
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 12/2018(ኢዜአ)፦ በሚቀጥሉት አስር ቀናት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የዝናብ ቀጣይነት እንደሚኖረው የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ። ኢንስቲትዩቱ ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው ከሚቲዎሮሎጂ ክስተቶች ጋር ተያይዞ ወቅታዊ ዝናብ ቀስ በቀስ ወደ ምዕራብ አጋማሽ የሀገሪቱ ክፍሎች እየተስፋፋ እንደሚሄድ ገልጿል። በዚህም በደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ምስራቅ እንዲሁም በስምጥ ሸለቆ አካባቢዎች የተሻለ ገጽታ ይኖራቸዋል ብሏል። በመሆኑም በበልግ አብቃይ አካባቢዎች በርካታ ቦታዎችን የሚሸፍን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ ገልጿል። በተጨማሪም በውሃ አካላትና በአካባቢ አየር ውስጥ ከሚጠናከሩት የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በመነሳት በደቡብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ ብሏል። አርሶ እና አርብቶ አደሮች እንዲሁም የሚመለከታቸው አካላት የሚጠበቁ መልካም ሁኔታዎችን በአግባቡ እንዲጠቀሙና የግብርና ተኮር ሚቲዎሮሎጂ ምክረ ሀሳቦችን መተግበር እንደሚገባ አስታውቋል። ይህም ለበልግ ሰብሎች እና ቋሚ ተክሎች እድገት አዎንታዊ ሚና ያለው ሲሆን ለአፈር እርጥበት በመጨመር ለእርሻ እንቅስቃሴ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል ነው ያለው። በሚቀጥሉት አስር ቀናት በአብዛኞቹ የሀገሪቱ ተፋሰሶች ላይ የሚጠበቀው ዝናብ የገጸ ምድር ውሃ ፍሰትን እንደሚያሻሽልም ጠቁሟል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
አምባሳደር ቆንጂት ስነጊዮርጊስ የአፍሪካ ዲፕሎማሲ እሴቶች ተምሳሌት ነበሩ
Apr 7, 2026 471
አዲስ አበባ፤መጋቢት 29/2018 (ኢዜአ)፦አምባሳደር ቆንጂት ስነጊዮርጊስ የአፍሪካ ዲፕሎማሲ ከፍተኛ እሴት በተግባር ያሳዩ ታላቅ ዲፕሎማት ነበሩ ሲሉ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። ሊቀመንበሩ በኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ታሪክ ውስጥ ስመጥር በሆኑት አምባሳደር ቆንጂት ስነጊዮርጊስ ህልፈት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል። ሊቀመንበሩ አምባሳደሯን የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት አገልግሎት ፈር ቀዳጅ፣ ታላቅ ዲፕሎማት እና ህይወታቸውን ለሀገራቸውና ለአህጉሪቱ እድገት የሰጡ ጽኑ አፍሪካዊት ሲሉ አወድሰዋቸዋል። አምባሳደር ቆንጂት ስነጊዮርጊስ ለበርካታ አስርተ አመታት የዘለቀ አርአያነት ያለው ሙያዊ ስኬት ማስመዝገባቸውንና ከኢትዮጵያ ቀዳሚ ሴት አምባሳደሮች አንዷ በመሆንም ለአፍሪካውያን ሴት ዲፕሎማቶች የብርሃን ፋና መሆናቸውን አመልክተዋል። የአፍሪካን ጥቅም ለማስከበርና ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጠናከር የነበራቸው የማይናወጥ ቁርጠኝነት ለአህጉራዊ የጋራ ግቦች መሳካት የጎላ ሚና እንደነበረውም አውስተዋል። ሊቀመንበሩ አምባሳደር ቆንጂት በታማኝነት፣ በልዩ ብቃት እና ለጋራ የወደፊት እጣ ፈንታ የነበራቸው ጽኑ ቁርጠኝነት የአፍሪካ ዲፕሎማሲ እሴቶች ያላቸውን ጽኑ አቋም ያሳየ መሆኑንም ነው ያነሱት። የአምባሳደሯ የዲፕሎማሲ አሻራ ለቀጣይ ትውልድ ዲፕሎማቶች፣በተለይም ለሴቶች፣በድፍረትና በዓላማ እንዲያገለግሉ ዘላቂ መነሳሳት ሆኖ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል። ሊቀመንበሩ በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ስም ለአምባሳደር ቆንጂት ቤተሰቦች፣ ለኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ፣ እንዲሁም ለሁሉም አፍሪካውያን ልባዊ መጽናናትን ተመኝተዋል።
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት የሰላምና የፀጥታ ምክር ቤት ሊቀ መንበርነትን ተረከበች
Apr 3, 2026 381
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 25/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የእ.አ.አ አፕሪል 2026 የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና ፀጥታ ምክር ቤት (AU PSC) ተዘዋዋሪ ሊቀመንበርነትን በይፋ መረከቧን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። ኢትዮጵያ ሊቀ መንበርነቱን የተረከበችው ከኮትዲቯር ነው። ኢትዮጵያ መጋቢት 29 ቀን 2018 ዓ.ም የምክር ቤቱን አጀንዳዎች በሊቀመንበርነት መምራት እንደምትጀምር ሚኒስቴሩ አመልክቷል። በዚህም ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በ2025 በድጋሚ የምክር ቤቱ አባል ሆና ከተመረጠች በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊቀ መንበር መሆን ችላለች። በሊቀመንበርነት ቆይታዋ ኢትዮጵያ በአህጉሪቱ በሚገኙ አገራዊ እና ወቅታዊ የሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ላይ የሚደረጉ ውይይቶችን እንደምትመራ ሚኒስቴሩ አስታውቋል። የኢትዮጵያን ሊቀ መንበርነት በይፋ ለማብሰር እና አዲስ የተመረጡ የምክር ቤቱን አባላት ለመቀበል መጋቢት 29 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሰብሳቢነት የሰንደቅ ዓላማ የማውለብለብ ሥነ-ሥርዓት ይከናወናል። ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በ2004 ምክር ቤቱ ከተመሰረተ ጀምሮ በአባልነት ስታገለግል የቆየች መሆኑን የጠቀሰው የሚኒስቴሩ መግለጫ፤ እ.አ.አ በ2025 በድጋሚ ለሦስት ዓመታት አባል ሆና መመረጧን አውስቷል። ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም አራት ጊዜ የምክር ቤት አባል ሆና ተመርጣ በንቃት ስትሳተፍ መቆየቷ ተወስቷል።
ድርጅቱ የብዙኃነት አቅም ያለው በመሆኑ ይህን አቅም ወደ ስትራቴጂያዊ ጥቅም ማምጣት ያስፈልጋል
Mar 28, 2026 670
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 19/2018(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ሀገራት ድርጅት የብዙኃነት አቅም ያለው በመሆኑ ይህን አቅም ወደ ስትራቴጂያዊ ጥቅም ማምጣት እንደሚያስፈልግ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ አስገነዘቡ። 11ኛው የአፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ሀገራት ድርጅት የመሪዎች ጉባኤ በማላቡ ኢኳቶሪያል ጊኒ እየተካሄደ ይገኛል። በጉባኤው እየተሳተፋ የሚገኙት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ድርጅቱ የብዙኃነት አቅም ያለው በመሆኑ ይህን አቅም ወደ ስትራቴጂያዊ ጥቅም ማምጣት ያስፈልጋል ብለዋል። ተለዋዋጭ በሆነው የአለም የኢኮኖሚ እና ፖለቲካ ውስጥ የአባል ሀገራቱን ጥቅም የሚያስከብር ጠንካራ ድርጅት ሆኖ መቀጠል እንዳለበትም በአፅንኦት ተናግረዋል። ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በንግግራቸው ለድርጅቱ ጥንካሬ ይበጃሉ ያላቸውን ሀሳቦችም አካፍለዋል። በዚህም ድርጅቱ የብዙኃነት አቅም ያለው በመሆኑ ይህን አቅም ወደ ስትራቴጂያዊ ጥቅም ማምጣት ያስፈልጋል ነው ያሉት። ለዚህም የደቡብ - ደቡብ ግንኙነትን ማጠናከር ቁልፍ ሚና ይኖረዋል ያሉ ሲሆን መካከለኛ እና ከፍተኛ ኢኮኖሚን ከገነቡ ሀገራትና ድርጅቶች ጋር ያለን ግንኙነት ከቀደመው የእርዳታ ሰጭ እና ተቀባይ ግንኙነት ወደ የጋራ ተጠቃሚነት ለማሸጋገር መስራት ያስፈልጋል ብለዋል። የድርጅቱ አባል ሀገራት ተመሳሳይ የባለቤትነት ስሜትን ማዳበር እንዳለባቸውም ፕሬዚዳንቱ ጠቁመዋል። ቀጣይነት ያለው ልማት ማረጋገጥ፣ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ መገንባትና ሰላምና ፀጥታን ለማስፈን መስራት የአባል ሀገራት የጋራ የትኩረት አቅጣጫዎች መሆን እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል። የአፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ሀገራት ድርጅት አባል ሀገራት ዲጂታል ቴክኖሎጂ ላይ ያላቸው ሚና ከተጠቃሚነት ወደ ፈጣሪነት(አምራችነት) መሸጋገር እንዳለበትም ተናግረዋል። የሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ ሳይበር ደህንነት እና የዲጂታል ቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት ጉዳይ በልዩ ትኩረት ሊሰራባቸው እንደሚገባም ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ በመገንባት ረገድ ባስመዘገበቻቸው ውጤቶች ቀጣዩን የአለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤን (ኮፕ 32) እንድታስተናግድ መመርጧን አስታውሰዋል። ይህም የአፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ሀገራት ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ልማት በመገንባት ሂደት ያላቸውን ተሞክሮ የሚያቀርቡበት ትልቅ ዕድል እንደሆነም ፕሬዚዳንቱ አስረድተዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በበኩላቸው ሶስቱም ቀጣናዎች የጎላ አስተዋጽኦ ባላደረጉበት የአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛ ጉዳት እያስተናገዱ መሆናቸውን አንስተዋል። የአየር ንብረት ፍትህ እንዲረጋገጥ የተባበረ እንቅስቃሴ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል። በጉባኤው አፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ክልሎችን የወከሉ መሪዎች ንግግር ያደረጉ ሲሆን አፍሪካን በመወከል የወቅቱ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር እና የቡሩንዲ ፕሬዚዳንት ኤቫሪስት ንድዪሺሚዬ መልእከት አስተላልፈዋል። የድርጅቱን የፋይናንስ ምንጭ ቀጣይነት ማረጋገጥ፣ የድርጅቱን መዋቅራዊ አሰራር ማጠናከር እንዲሁም በአየር ንብረት ለውጥ ላይ የጋራ አቋም መያዝ በጉባኤው ጎልተው የተሰሙ ድምፆች መሆናቸውን ኢዜአ ከስፍራው ዘግቧል። በማላቡ ኢኳቶሪያል ጊኒ እየተካሄደ የሚገኘው 11ኛው የአፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ሀገራት ድርጅት የመሪዎች ጉባኤ እስከ ነገ መጋቢት 20/2018 ዓም ድረስ ይቆያል። በጉባኤው ከሶስቱም ክልሎች የሚገኙ የሀገራት መሪዎች እንዲሁም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ የአፍሪካ ህብረት እና የአውሮፓ ህብረት ተወካዮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
የዓለም የውሃ ቀን እየተከበረ ነው
Mar 22, 2026 364
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 13/2018 (ኢዜአ)፦ 34ኛው የዓለም የውሃ ቀን ዛሬ በዓለም ደረጃ እየተከበረ ይገኛል። “ውሃ እና ስርዓተ ጾታ” የዘንድሮ መሪ ቃል ነው። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የውሃ ቀን ቁልፍ መልዕክቶችን ይፋ አድርጓል። ተመድ የዓለም የውሃ ቀውስ ለሁሉም ሰው የሚተርፍ ቢሆንም ተፅዕኖው ግን እኩል እንዳልሆነ አመልክቷል። ሰዎች ደህንነቱ የተጠበቀ የመጠጥ ውሃ እና የንጽሕና መጠበቂያ አገልግሎቶችን የማግኘት ሰብአዊ መብታቸው በማይከበርባቸው ቦታዎች ላይ ኢ-ፍትሃዊነት ጎልቶ እንደሚታይ ገልጿል። በዚህም ሴቶችና ልጃገረዶች የችግሩ ዋነኛ ሰለባ እንደሚሆኑ ጠቅሶ ሴቶችና ልጃገረዶች የውሃ መፍትሔዎች ማዕከል የምናደርግበት ጊዜ አሁን ነው ብሏል። ሴቶች የውሃን የወደፊት ዕጣ ፈንታ መቅረጽ አለባቸው ያለው ተመድ ለዚህም የሴቶች ድምፅ፣ አመራር እና ተሳትፎ ማሳደግ እንደሚገባ ነው ያስታወቀው። በዘንድሮው የዓለም ውሃ ቀን ከሚተላለፉ መልዕክቶች አንዱ ውሃ ባለበት እኩልነት ያብባል የሚለው እሳቤ ነው። ሴቶችና ልጃገረዶች በውሃ ውሳኔዎች ላይ እኩል ድምፅ ሲኖራቸው፣ አገልግሎቶቹ ይበልጥ አካታች፣ ቀጣይነት ያላቸው እና ውጤታማ እንደሚሆኑ ተመድ አመልክቷል። ለሁሉም የሚተርፍ ጤናማ፣ የበለጸገ እና እኩልነት የሰፈነበት መጻኢ ጊዜን ለመገንባት፤ የሴቶች የውሃ ዘርፍ አመራር ሰጪነት ለማሳደግ የሚያስችል ስራን ማከናወን እንደሚገባም አስታውቋል። የዓለም የውሃ ቀን ከእ.አ.አ 1993 ጀምሮ እየተከበረ ይገኛል። እ.አ.አ 1992 በብራዚል ሪዮ ዴጄኔሮ በተካሄደው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የከባቢ አየር እና ልማት ኮንፍረንስ (ሪዮ ኮንፍረንስ) የዓለም መሪዎች የውሃ ሀብቶችን መጠበቅ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አንስተዋል። ከኮንፈረንሱ ውጤቶች መካከል አንዱ ውሃን አስመልክቶ ግንዛቤ መፍጠር ላይ ያተኮረ ቀን የመሰየም ምክረ ሀሳብ ነው። በዚሁ መሰረት ተመድ እ.አ.አ 1992 ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ በዓለም አቀፍ ደረጃ በማርች 22 እንዲከበር ውሳኔ አስተላልፏል። ውሳኔውን ተከትሎ የዓለም የውሃ ቀን ከእ.አ.አ 1993 ጀምሮ እየተከበረ ይገኛል። በዓለም በላይ ከሁለት ቢሊዮን በላይ ሰዎች ደህንነቱ የተጠበቀ የመጠጥ ውሃ እንደማያገኙ መረጃዎች ያመላክታሉ። የአየር ንብረት ለውጥ እና ፈጣን የህዝብ እድገት ለውሃ እጥረት ዋንኛ መንስኤዎች ናቸው።
ሐተታዎች
በኢዜአ ዐይን …!
Apr 19, 2026 319
የምግብ ሉዓላዊነት - ከተረጂነት መላቀቂያው መንገድ በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ ከተረጂነትና ጠባቂነት መፋቻ መንገዶች መካከል የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ አንዱ ብልኀት አድርጋ እየታተረች ነው። ይህን ተከትሎም የዜጎችን የምግብ ፍላጎት በራስ የምርት ዐቅም የመሸፈን ሥራ በመከወን ከጠባቂነት ለመላቀቅ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎች ስኬታማ ናቸው። ለዚህም ኢትዮጵያ በስንዴ ልማት ከልመና ወጥታ ወደ ውጭ ገበያ መላክ መጀመሯ አሥረጅ ነው። በመሆኑም ከውጭ የኢኮኖሚ ጥገኝነት በመላቀቅ የዜጎችን የምግብ ሉዓላዊነት ለማስከበር በስንዴ ልማት የተመዘገበውን ስኬት በሌሎች የግብርና ዘርፎች ለመድገም ርብርብ እየተደረገ ነው። በዚህም መሠረት በሩዝ፣ አትክልትና ፍራፍሬን ጨምሮ ሻይ ቅጠል እና ሌሎች የተለያዩ ሰብሎች ላይ እየተከናወነ ያለው ሥራ አበረታች ውጤት እያስገኘ ነው። የተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና የግብርና ድርጅት (ፋኦ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በምግብ ዋስትናና በተመጣጠነ የምግብ አቅርቦት ላሳዩት ርዕይ፣ የአመራር ቁርጠኝነት የአግሪኮላ ሜዳሊያ በ2016 ዓ.ም ማበርከቱ ለምግብ ሉዓላዊነት ጥረት የተሰጠ ዕውቅና ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት፤ የኢትዮጵያ መንግሥት ረሃብን ከማስቀረት ባለፈ የምግብ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ብሔራዊ ብልጽግናን ዕውን ለማድረግ እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በርካታ ያልተነኩ ጥሬ ሃብቶች፣ተስማሚ የዓየር ንብረት፣ ለሥራ ትጉ የሆነ ወጣት እንዳላት እና እነዚህን ሃብቶች ታሳቢ በማድረግ የታሪክ ዐውራ የሆነችውን ሀገር ልማት ወደፊት ለማራመድ የሚያስችሉ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም አስረድተዋል። በአንድ ወቅት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስከበር ዋጋ እንደከፈልን ሁሉ፤ ከምግብ ጥገኝነት ለመላቀቅ በትጋት መሥራት ይገባል ሲሉ ማስገንዘባቸው ይታወሳል። የምግብ ሉዓላዊነት፣የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት፣ የበጀት ሉዓላዊነት ታላቁን የሀገር ሉዓላዊነት በጽናት የሚያቆሙ መሆናቸውንም አብራርተዋል። እነዚህን የሉዓላዊነት ዘርፎች ለማስከበርም ብሔራዊ ዐርበኝነት እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል። ሀገራዊ ትልሙ ኢትዮጵያን ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለተሟላ ሀገራዊ ክብር፣ ነጻነት እና ሉዓላዊነት የሚያሸጋግር መልካም ጅማሮ ነው።
የክልሎች ቅኝት በወፍ በረር
Apr 19, 2026 149
ክልሎች፤ሚያዝያ 11/2018 (ኢዜአ)፡-የክልሎች ቅኝት በወፍ በረር በዚህ ዝግጅታችን በሳምንቱ በክልሎች የተከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮችን በወፍ በረር በመቃኘት ማስታወስ ይሆናል። በመሆኑም በዚህ ሳምንት በሀገራችን ሁሉም ክልሎች ምን ምን ዋና ዋና ጉዳዮች ነበሩ ስንል እንጠይቃለን? የንፋስ ሃይል በቀጥታ የምናመራው በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሄጦሳ ወረዳ ኢተያ አካባቢ ነው። በኢተያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተገኝተው የመረቁትን የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫን እንመለከታለን። የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ 100 ሜጋ ዋት ኃይል የሚያመነጭ ሲሆን ኢትዮጵያ በታዳሽ ሃይል ልማት ወደ ፊት እየተራመደች መሆኑን በተግባር ያረጋገጠ ሥራ ነው። ኢትዮጵያ ዘንድሮ ከጉባ እስከ አሰላ፣ ገናሌ እና አይሻ በሃይል ልማት ዘርፍ ትልቅ ትርጉም ያላቸውን ፕሮጀክቶች አስመርቃለች። የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ደግሞ በዚህ ሳምንት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ተመርቆ በይፋ ሥራ ጀምሯል። ጠቅላይ ሚኒስትሩም በምርቃቱ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት ከለውጡ በፊት የነበረው 4 ሺህ ሜጋ ዋት የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅም አሁን ላይ ወደ 10 ሺህ ሜጋ ዋት በመድረስ ከእጥፍ በላይ እድገት የተመዘገበበትን ትልቅ ስኬት አንስተዋል። የስንዴና ገብስ ሰብሎችን በከፍተኛ መጠን የሚያመርተው አርሲና አካባቢው አሁን ላይ የኤሌክትሪክ ሃይል የሚመረትበት አካባቢ መሆኑንም ገልጸዋል። በመሆኑም በሁሉም መስክ የኢትዮጵያን የብልፅግና ጉዞ እናስቀጥላለን ሲሉ አረጋግጠዋል። ቢሾፍቱ የኦሮሚያ ክልል መንግስት የዘጠኝ ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማም በዚህ ሳምንት በቢሾፍቱ ሀርሰዴ አዳራሽ መካሄዱ ይታወቃል። በዚህ መድረክ ላይ የተገኙት የክልሉ ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ፤ በክልሉ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በርካታ ስኬታማ የልማት ተግባራት መከናወናቸውን አንስተዋል። በተለይም የክልሉን ሕዝብ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት በተሻለ መልኩ ያሳደጉ የከተማ እና የገጠር የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን ነው ያስረዱት። ከዚህ ባለፈ የክልሉን የልማት ሥራዎች ለማቀላጠፍ የሚያግዙ በቴክኖሎጂ የተደገፉ የአገልግሎት አሰጣጥ አሰራሮች መተግበራቸውንም ተናግረዋል። የቢሾፍቱ መድረክ በድምሩ የግብርና፣ የገጠርና የከተሞች ልማት፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ክንውን በዝርዝር የታየበት ውጤታማ መድረክ እንደነበረም ተመላክቷል። የአሎማ ክላስተር ሌላ የሳምንቱ ዓበይት ጉዳይ ወደ አማራ ክልል ደቡብ ወሎ ይወስደናል። የሎጎ ሐይቅ ሪዞርት በይፋ አገልግሎት መስጠት የጀመረው በዚህ ሳምንት ነው። በመስኖ የለማ የስንዴ ክላስተር የተጎበኘበትና በተሁለደሬ ወረዳ በክላስተር ለሚከናወነው የተቀናጀ የፍራፍሬ ልማት የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር በይፋ የተጀመረበት እንዲሁም የክልሉ የ10 ዓመት የግብርና ሽግግር ፍኖተ ካርታ ይፋ የተደረገበትን ሁነት እናገኛለን። በእነዚህ ሁነቶች ላይ መልዕክት ያስተላለፉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፤ የመደመር መንግሥት በሁሉም ዘርፎች ለሀገር እድገትና ማንሰራራት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ለዚህም በግብርና፣ በመስኖ ልማት፣ በቱሪዝምና ሌሎች መስኮች በተግባር የተመለከትናቸው የልማት ሥራዎች ተጨባጭ ማሳያዎች ናቸው ሲሉ ተናግረዋል። የአሎማ ክላስተር የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት፣ የሓይቅ ዳር አትክልትና ፍራፍሬ ልማት ምርታማነትን በማሳደግ በምግብ ራስን የማቻል ጥረት በስኬት መንገድ ላይ መሆኑን የሚያሳዩ መሆኑን ጠቅሰው፤ ሀገርን የማሻገር ሥራችን ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። የታሪክ መሰነጃ የሳምንቱ በረራችን እንደቀጠለ ሲሆን አሁን ደግሞ የሰው ልጅ መገኛ፣ የኤርታሌ ትኩሳት የሚገነፍልባትና የአዋሽ ወንዝ የተንጣለለባት አፋር ክልል ገብተናል። በአፋር ቆይታችን ትኩረታችንን ሰመራ በማድረግ በስፍራው ሊገነባ የታሰበውን የሉሲ ሙዚየም እንመለከታለን። ሙዚየሙን ለመገንባት የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን እና የአፋር ክልል ቱሪዝም ቢሮ የፕሮጀክት ግንባታ ስምምነት አድርገዋል። ለሉሲ አፋር ቤቷ ነው፤ ሀዳር የተባለው ስፍራ ደግሞ መገኛዋ ነው። በመሆኑም በዚህ ከሰው ልጅ መገኛ ጋር የተቆራኘን ስፍራ ሙዚየም ገንብቶ፣ የቱሪስት መስህብ አልምቶና አካባቢውን በስፋት አስተዋውቆ የገቢ ምንጭ ማድረግ ሲቻል ለምን ተዘንግቶ ቆየ? የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ይሆናል። የጊዜ ጉዳይ ሆኖ አሁን አፋር ሰመራ ላይ በሉሲ የተሰየመ የሀገር ታሪክና ቅርስ ማጣቀሻ፤ የአፋር ክልል ህዝብ ቱባ ባህሎች ማሳያ የሆነ ሙዚየም ለመገንባት ዝግጅት መደረጉ ትልቅ ትርጉም ይኖረዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አበባው አያሌው (ረዳት ፕሮፌሰር)፤ የሚገነባው ሙዚየም የሀገር ታሪክና ቅርስ የሚሰነድበት፣ የአፋር ክልል ህዝብ ቱባ ባህሎች ተጠብቀው የሚዘልቁበት፣ የሰው ልጅ አመጣጥና ዝግመተ ለውጥ የሚያሳይ ዐውደ ርዕይ የሚካሄድበት ይሆናል ብለዋል። እሳቸው እንዳሉት የሙዚየሙ ግንባታ በ18 ወራት ውስጥ ተጠናቆ ለአገለግሎት የሚበቃ ይሆናል። የአፋር ክልል በመስኖ ቢያለሙበት፣ የጥጥ እና የቴምር ልማት ቢካሄድበት ተዝቆ የማያልቅ እምቅ አቅም ያለው መሆኑን አንስተዋል። በመሆኑም በለውጡ ሰፊ የልማት እንቅስቃሴ እየተደረገ ሲሆን እምቅ የቱሪዝም ሃብቱንም በማልማትና በመጠበቅ የሃገር ሃብት የማድረግ ጥረት ተጠናክሮ መቀጠሉን የሉሲ ሙዚየም ግንባታ ሁነኛ ማሳያ ነው። የሳምንቱ ቅኝታችን እንደቀጠለ ሲሆን አሁን ደግሞ በቀጥታ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ አሶሳ ተገኝተናል። አሶሳ በሳምንቱ በሃይማኖት አባቶች ጸሎትና ዱአ ተባርካ ስለ ሰላምና አብሮነት የሚመከርባት ከተማ ሆና እንግዶቿን ተቀብላ አስተናግዳለች። የተለያዩ የኃይማኖት አባቶች፣ የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች፣ ምሁራንና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት 7ኛው ሀገር አቀፍ የሰላም ኮንፈረንስ "ሰላምን ይበልጥ ለማስፋት እና ለማስረጽ የሃይማኖቶች ሚና" በሚል መሪ ሃሳብ በአሶሳ ከተማ ተካሂዷል። በመድረኩ አባቶች ስለ ሰላም እና አብሮነት እንትጋ ለትውልድ ግንባታም መስራት ግድ ይለናል በማለት አፅንኦት በመስጠት መክረዋል። የኢትዮጵያ ሐይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጠቅላይ ፀሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ኃይማኖቶች ለሰላም እና ለህዝቦች አብሮነት ያላቸውን አስተምህሮ በመጠቀም ለዘላቂ ሰላም ግንባታ እና ሀገራዊ የልማት ስራዎች ግንባር ቀደም ተሳታፊ መሆን አለባቸው ብለዋል። በኢትዮጵያ ሰላምን ለማጽናት እና የወንድማማችነት ድልድይን ለመገንባት እንስራ በማለትም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። ከአሶሳ ወደ ሀዋሳ ከአሶሳ ወደ ሀዋሳ ስንጓዝ የአፍሪካ አረንጓዴ አብዮት ጥምረት (አግራ-AGRA) ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች የኤልቶ ገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን የሥራ እንቅስቃሴን መጎብኘታቸውን እናገኛለን። በጉብኝቱ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትርና የጥምረቱ የቦርድ ሊቀ መንበር ኃይለማርያም ደሳለኝ፤ አርሶ አደሮች ምርታማነትን በማሳደግ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ የሚያደርጉት ጥረት ጥሩ ተስፋ የተሰነቀበት መሆኑን ተመልክተናል ብለዋል። የግብርና ልማትን የማዘመን፣ ምርታማነትን የማሳደግና የአርሶ አደሮችን ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ስራ ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ተግባር መሆኑንም አፅንኦት ሰጥተዋል። የጥምረቱ ፕሬዚዳንት አሊስ ሩህዌዛ፤ በአፍሪካ የግብርና ስርዓት ሽግግርን ለማጠናከር በተለይም አነስተኛ ማሳ ያላቸው አርሶ አደሮች ተጠቃሚ እንዲሆኑ የማስቻል ስራ ውጤት እያመጣ ይገኛል ብለዋል። በአፍሪካ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ሂደት ውስጥ ደግሞ የኢትዮጵያ ለውጥ አስደናቂ ስለመሆኑ አንስተዋል። ሌሎች በዚህ ሳምንት በሁሉም ክልሎች ባደረግነው ምልክታ በተለይም የምርጫ ጉዳይ ዋነኛ አጀንዳ ሆኖ ዜጎች የምርጫ ካርዳቸውን እየወሰዱ ሲሆን የፖለቲካ ፓርቲዎችም የምረጡኝ ቅስቃሳ ማድርጋቸውን ቀጥለዋል። የግብርና ልማት ስራዎች፣ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ዝግጅት እና ሌሎችም የልማት ሥራዎች በተጠናከረ መልኩ የቀጠሉበት ሳምንት ነበር ማለት ይቻላል።
የጤና ነገር …
Apr 17, 2026 345
በዮሐንስ ደርበው ማዲያት ታክሞ ይድናል? እነማንንስ ያጠቃል? የሥነ-ውበት ባለሙያ የሆኑት ዶክተር ሱመያ ኑርሁሴን ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ስለማዲያት መንስዔ፣ ምልክቶች እና ሕክምና ሙያዊ ሐሳባቸውን አጋርተዋል። እንደ ባለሙያ ቢደረግ ያሉትንም መክረዋል። • ማዲያት እነማንን ያጠቃል? ማዲያት ማንኛውንም ሰው እንደሚያጠቃ ያነሱት ዶ/ር ሱመያ፤ በብዛት ግን በሴቶች ላይ እንደሚከሰት ያስረዳሉ። በዚህም መሠረት ይላሉ፤ እርግዝና ላይ ያሉ እንዲሁም የወሊድ መከላከያ የሚወስዱ ሴቶች እና ሆርሞናል ቴራፒ ላይ ያሉ ሰዎች በስፋት ለማዲያት ተጋላጭ ናቸው። በተጨማሪም በብዛት ምግብ ማብሰል (ኪችን) ላይ የሚሠሩ ሰዎች ለማዲያት እንደሚጋለጡ ጠቁመዋል። ባብዛኛው ማዲያት የሚያጠቃው በዕድሜ ከ25 ወይም ከ30ዎቹ በላይ የሆኑትን መሆኑንም አንስተዋል። • መንስዔ እንደ ዶክተር ሱመያ ገለጻ፤ ለማዲያት ከሚያጋልጡ መንስዔዎች መካከል ዋነኛው የፀሐይ ጨረር ነው። በተጨማሪም ሆርሞናል ፋክተር (የወሊድ መከላከያ መጠቀም፣ እርግዝና ላይ መሆን፣ ሆርሞናል ቴራፒ መውሰድ) ለማዲያት አጋላጭ መንስዔ ሆነው ይጠቀሳሉ ይላሉ። ጭንቀት እንዲሁም ቆዳን የሚያስቆጡ ነገሮች ለማዲያት አጋላጭ መሆናቸውንም ነው ያብራሩት። • ምልክቶች ማዲያት ቀላ፣ ጠቆር ወይም ደብዘዝ ያለ ቀለም (መልክ) ይዞ ከትንሽ ጀምሮ የሚሰፋ መሆኑን ዶክተር ሱመያ አስገንዝበዋል። ለምሳሌ ይላሉ፤ ጉንጭ ላይ መውጣት ቢጀምር ወደ ሁለቱም ጉንጮች ከዚያም ወደ ግንባር እንዲሁም አገጭ እና አፍንጫ ሊደርስ እንደሚችል ገልጸዋል። በሂደትም የማቃጠል፣ የመቆጥቆጥ እና ማሳከክ ሁኔታ ሊኖረው እንደሚችል ነው ያነሱት። • ሕክምና መንስዔዎቹን ዐውቆ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ የሕክምናው አካል መሆኑን ያስገነዘቡት ዶክተር ሱመያ፤ የፀሐይ ጨረር መከላከያዎችን መጠቀም፣ በሕክምና የሚሰጡ መድኃኒቶችን ሳያቋርጡ በትዕግስት መጨረስ (ቶሎ ለውጥ አላየሁበትም ብሎ አለማቋረጥ) እንደሚገባም መክረዋል። የማዲያት ሕክምና ስኬታማነቱ ለሁሉም ሰው በዕኩል ጊዜ እንደማይታይ በመግለጽ፤ እንደተከሰተበት ጊዜ ከሰው ሰው እንደሚለያይ በአጽኦት ተናግረዋል። ለምሳሌ አሉ፤ ዓመታት ያለፉት ማዲያት እና 2 ወራት የሆኑት ሕክምና እኩል ቢጀመርም በተመሳሳይ ጊዜ ላይድኑ እንደሚችሉ አመላክተዋል። ስለዚህ የሌላኛው ድኖ የኔ አልዳነም በሚል ሕክምናን ማቋረጥ ስህተት መሆኑንም ነው ያስረዱት። በሌላ በኩል ማዲያትን አስቀድሞ መከላከል እንደሚቻል አረጋግጠው፤ ይህም የሚሆነው መንስዔዎቹን በማወቅ የማዲያት ተጋላጭ ባለመሆን ነው ብለዋል። ከተቻለ በየሥድስት ወሩ ወይም በየዓመቱ የቆዳ ጤና ምርመራ ማድረግ እና ያለበትን ደረጃ ማወቅም የሚከሰት ችግር ቢኖር እንኳ ሥር ሳይሰድድ በማከም ቶሎ እንዲድን ማድረግ ይቻላል ነው ያሉት።
በኢዜአ ዐይን …!
Apr 13, 2026 224
በምግብ ራስን የመቻል ጉዞ አንዱ ምሰሶ - የስንዴ ልማት በሙሴ መለሰ ስንዴ በኢትዮጵያ በከፍትኛ ደረጀ ከሚመረቱና ለግብይት ከሚውሉ የሰብል ምርቶች መካከል በቀዳሚነት ይጠቀሳል። በዚህም መሠረት ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከፍተኛ የስንዴ አምራች ከሆኑ ሀገራት መካከል በግንባር ቀደምነት ትጠቀሳለች። ከ2011/2012 የምርት ዘመን በፊት ኢትዮጵያ በመኸር የምታለማው ስንዴ ከ1 ነጥብ 7 ሚሊየን ሔክታር ያልበለጠ ነበር። የበጋ መስኖ ስንዴ ሲጀመርም 3 ሺህ ሔክታር ብቻ እንደነበር መረጃዎች ያመላክታሉ። በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ በመኸር፣ በበጋ መስኖ እና በበልግ ወቅት 7 ነጥብ 4 ሚሊየን ሔክታር መሬት ላይ ስንዴ እያለማች እንደምትገኝ የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ያስረዳል። ሚኒስቴሩ የ2018 ዓ.ም የበጋ መስኖ ስንዴ ልማትን አስመልክቶ ባወጣው መረጃ፤ 4 ነጥብ 29 ሚሊየን ሔክታር መሬት ላይ ስንዴ በማልማት ከበጋ መስኖ ስንዴ 175 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለማግኘት መታቀዱን መግለጹ ይታወሳል። በኢትዮጵያ በአብዛኛው የስንዴ ምርት የሚመረተው በአነስተኛ አርሶ አደሮች ነው። ባለፉት ዓመታት ግን የሜካናይዝድ እርሻ የስንዴ ምርቱን በእጥፍ እንደጨመረው ይገለጻል። መንግሥት መስኖን በመጠቀም ስንዴን በዓመት አንድ ጊዜ ከማምረት ወደ ሦስት ጊዜ ማምረት የሚቻልበትን አሰራር በመፍጠር የሀገሪቱን ምርታማነት ለማሳደግ እየሠራ ይገኛል። ኢትዮጵያ ዓመታዊ የስንዴ ፍላጎቷ ከ107 ሚሊየን ኩንታል በላይ ነው። ይህንን ፍላጎቷን ለመሙላት ለዓመታት ከ700 ሚሊየን ዶላር እስከ 1 ቢሊየን ዶላር ለስንዴ ግዥ ወጪ ታደርግ ነበር። ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ከዓመታዊ የስንዴ ፍላጎቷ ከ25 እስከ 30 በመቶ የሚሆነውን ትሸፍን የነበረውም ከውጭ በምትገዛው ስንዴ ነበር። መንግሥት የበጋ መስኖ ስንዴ ልማትን በማስፋፋትና በየዓመቱ የሚመረትበትን ዙር በመጨመር ኢትዮጵያ የስንዴ ፍጆታዋን ሙሉ በሙሉ እንድትሸፍን በትኩረት ሲሠራ ቆይቷል። በዚሁ በ2014 ዓ.ም ኢትዮጵያ ከውጭ ሀገር ስንዴ ማስገባት አቆመች። ኢትዮጵያ በስንዴ ልማት ያገኘችው ውጤት ከውጭ ማስገባትን ማስቆም ብቻ አልነበረም። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ራስን ብቻ ሳይሆን ኤክስፖርት የማድረግ ዐቅም እንዳላት በመግለጽ፤ ስንዴ ወደ ውጪ መላክ እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጠዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስቀመጡት ሀገራዊ ግብ መሰረት ኢትዮጵያ የካቲት 5 ቀን 2015 ዓ.ም ወደ ውጭ የመላክ ተግባርን በይፋ አስጀምራለች። የስንዴ ኤክስፖርቱ ኢትዮጵያ ገጽታዋን የሚለውጥ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ውስጥ መግባቷን የሚያመላክት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅቱ ገልጸው ነበር። ኢትዮጵያ በ2015 ዓ.ም የሀገር ውስጥ ፍጆታዋን ሸፍና 32 ሚሊየን ኩንታል ስንዴ ለውጭ ገበያ የማቅረብ ዐቅም እንዳላት ብሔራዊ የማክሮ ኢኮኖሚና የኤክስፖርት ኮሚቴ አረጋግጧል። ኮሚቴው የሀገራዊ የነፍስ ወከፍ ፍጆታና የሀገሪቱን አጠቃላይ የምርት ሚዛን በማጥናት ከፍጆታ የሚተርፍ 32 ሚሊየን ኩንታል ስንዴ ወደ ውጭ መላክ እንደሚቻልም ተገልጿል። 38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ባሳለፍነው የካቲት ወር በሕብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ መካሄዱ የሚታወስ ነው። በወቅቱም የአፍሪካ ሕብረት የግብርና፣ የገጠር ልማት፣ ብሉ ኢኮኖሚ እና የዘላቂ አካባቢ ኮሚሽነር ሞሰስ ቪላካቲ ከጉባዔው ጎን ለጎን በሰጡት መግለጫ፤ ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ያስመዘገበችው ስኬት ለአፍሪካ ተምሳሌታዊ የሆነ ተግባር መሆኑን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በአጭር ጊዜ ውስጥ የስንዴ ምርታማነቷን በማሳደግ የሀገር ውስጥ ፍላጎትን ከመሸፈን ባለፈ ለውጭ ገበያ ማቅረብ መቻሏን ሕብረቱ መመልከት መቻሉንም ተናግረዋል። የአፍሪካ ሀገራት በዓመት ውስጥ ለምግብ ምርቶች ከሚያወጡት የውጭ ምንዛሬ ስንዴ ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚይዝም ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ ከውጭ የሚገባውን ምርት በሀገር ውስጥ ስንዴ መተካት እንደሚቻል በተግባር ያሳየችበት መንገድ የሚደነቅ ነው ብለዋል። ኮሚሽነሩ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የኢትዮጵያን ተሞክሮ ወስደው ወደ ተግባር እንዲገቡ ጥሪ አቅርበዋል። ኢትዮጵያ በስንዴ ልማት ሥራ ላይ እያሳየች ያለውን ሥራ አስፍታ ከቀጠለች በምግብ ራሷን የመቻል ሕልሟን የማሳካት እድሏ ሰፊ መሆኑንም ማመላከታቸው ይታወሳል።
ትንታኔዎች
ኢትዮጵያ በአዕምሯዊ ንብረት ጥበቃ መንገድ
Apr 21, 2026 1420
(በዮሐንስ ደርበው) ታሪክ እንደሚነግረን፤ የአዕምሯዊ ንብረት ጥቅም ለመጀመሪያ ጊዜ ዕውቅና ያገኘው የኢንዱስትሪያዊ ንብረት ጥበቃን በሚመለከተው በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1883 በተፈረመው የፓሪስ ስምምነት እንዲሁም፤ በ1886 የተፈረመውን የሥነ-ጽሑፍና ሥነ-ጥበብ ሥራዎች ጥበቃን የተመለከተውን የበርን(ስዊዘርላንድ) ስምምነት ተከትሎ ነው። እነዚህ ስምምነቶችም በዓለም አዕምሯዊ ንብረት ድርጅት የሚተዳደሩ መሆናቸው ይታወቃል። ኢትዮጵያ የአዕምሯዊ ንብረት ባለሥልጣንን፤ በ2022 ዓ.ም ፈጠራንና ኢኖቬሽንን በማበረታታት የፈጠራ ሐሳቦችን ወደ ዕሴት በመለወጥ ሂደት ለሀገራዊ ብልጽግና ቁልፍ ሚና የሚጫወት በአፍሪካ ተምሳሌት የአዕምሯዊ ንብረት ተቋም ለማድረግ እየታተረች ነው። ለዚህ ርዕይ መሳካትም፤ ተቋሙ የአዕምሯዊ ንብረት ሥርዓት ለሀገራዊ ፈጠራ መጎልበት፣ የኢኖቬሽን፣ ቴክኖሊጂ ሽግግር እና የሥራ ዕድል ፈጠራ ማደግ ጥቅም ላይ የሚውልበትን ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ሀገራዊ የመዋቅር ሽግግርን መደገፍ የሚል ተልዕኮ አንግቦ እየሠራ ይገኛል። የእስካሁኑ የንግድ ምልክት፣ ቅጅና ተዛማጅ መብቶች እና የፈጠራ ባለቤትነት (ፓተንት) ምዝገባ የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ብሩክ ወርቅነህ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ2015 ዓ.ም እስከ ያዝነው በጀት ዓመት ያለፉት ዘጠኝ ወራት ድረስ በንግድ ምልክት፣ በቅጅና ተዛማጅ መብቶች እና በፈጠራ ባለቤትነት (ፓተንት) 20 ሺህ 476 ምዝገባዎች መከናወናቸውን አስረድተዋል። በዚህም መሠረት ይላሉ፤ 14 ሺህ 729 የንግድ ምልክቶች፣ 5 ሺህ 254 የቅጅና ተዛማጅ መብቶች እንዲሁም 1 ሺህ 781 የፈጠራ ሥራ ባለቤትነት ምዝገባ በተቋማችን አማካኝነት ተከናውኗል። የአዕምሯዊ ንብረት መብቶች ምንድን ናቸው? አዕምሯዊ ንብረት ማለት በሰው ልጅ አዕምሮ የሚፈጠሩ የፈጠራ ሥራዎችን የሚመለከት መሆኑን የገለፁት አቶ ብሩክ፤ እነዚህ የፈጠራ ሥራዎች እንደማንኛውም ቁሳዊ ሀብት በንብረትነት የሚታወቁበትን አግባብ የያዘው ሥርዓት ደግሞ የአዕምሯዊ ንብረት መብት እንደሚሰኝ ያስረዳሉ። በዚህ አግባብ፤ የአዕምሯዊ ንብረት መብቶች እንደማንኛውም ቁሳዊ ንብረት ሁሉ የፈጠራ ሥራዎችን ለሚያመነጩ ባለመብቶች የሚሰጡ የባለቤትነት መብቶች መሆናቸውን እንረዳለን። ለዚህም እንደ ምክንያት የሚቀርበው እንደ አቶ ዳንኤል ገለጻ፤ ወጥ ሥራዎችን ለማመንጨት የፈጠራ ባለመብቶች ዕውቀታቸውን፣ ገንዘባቸውንና ጊዜያቸውን መስዋዕት በማድረግ ከብዙ ድካም በኋላ ያገኟቸው የፈጠራ ውጤቶች በመሆናቸው ነው። ለአዕምሯዊ ንብረት ጥበቃ ማድረግ ለምን አስፈለገ? አንድም፤ የሰው ልጅ ቀጣይ ዕድገትና የኑሮ ደኅንነት ዋስትና መሠረት የሚያርፈው በቴክኖሎጂና ባሕል ዘርፎች በሚያሳርፋቸው ፈጠራዊ ብቃቶቹ በመሆኑ እንዲሁም የምርምርና የፈጠራ ሥራዎችን ለማካሄድ ተጨማሪ ሀብት የሚያስገኝ በመሆኑና ይህም የኢኖቬሽን ሥርዓቱን ስለሚያሳድግ ነው ይላሉ አቶ ብሩክ። እንዲሁም፤ የአዕምሯዊ ንብረት ጥበቃና ዘርፉን ለሕዝብ የማስተዋወቅ ተግባር ሀገራዊ የኢኮኖሚ ዕድገትን በማረጋገጥ የድርሻውን ስለሚወጣና የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት በአጠቃላይ የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ በተሻለ ደረጃ ላይ እንዲቆም ስለሚያደርግ መሆኑን ገልጸዋል። በተጨማሪም፤ ሀገራት ጠንካራ የአዕምሯዊ ንብረት ሥርዓት በፈጠሩ ቁጥር ዘርፉ ለኢኮኖሚ ዕድገት ቁልፍ የልማት መሣሪያ መሆኑን ይገነዘባሉ። ጠንካራና ፍትሐዊ የአዕምሯዊ ንብረት ሥርዓት በፈጠራ ባለቤቶችና በተጠቃሚው ሕዝብ ዘንድ ሚዛናዊ ነው ያሉት አቶ ብሩክ። በአጠቃላይ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ በመሆኑ ለአዕምሯዊ ንብረት ጥበቃ ማድረግ በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑን በአጽነዖት አንስተዋል። ዜጎች በአዕምሯዊ ንብረት ሥርዓት እንዴት ተጠቃሚ ይሆናሉ? ባለብዙ ቢሊየን ዶላር የፊልምና ድምጽ ሪከርድስ አሳታሚዎችና ሶፍትዌር ኢንዱስትሪዎች ለብዙ ሚሊየኖች የመዝናኛ ሥራዎች የሚያበረክቱት የቅጅ መብት ጥበቃ በመኖሩ መሆኑን መገንዘብ እንደሚገባም አቶ ብሩክ ይናገራሉ። በሌላ በኩል ተጠቃሚዎች የሚፈልጓቸውን ምርቶችና አገልግሎቶችን መለየት የሚያስችላቸው ብሔራዊና ዓለም አቀፋዊ የንግድ ምልክቶች ጥበቃና የመብት ማስከበር ሥርዓቶች ባይኖሩ ኖሮ ተመሳስለው በሚቀርቡ ምርቶችና አገልግሎቶች መታለልና ሌሎችም ችግሮች ያጋጥማቸው እንደነበርም ጠቁመዋል። ስለዚህ ምርቶችን በመሸመት ሂደትም በምርቶችና አገልግሎቶች ላይ ያለምንም ግራ መጋባት ግብይቱን ማከናወን እንደሚያስችላቸው መገንዘብ ይቻላል። እንደ አቶ ብሩክ ገለጻ፤ ለፓተንት የፈጠራ ሥራዎች ጥበቃ በመደረጉ መሰጠት የሚገባቸው ማበረታቻዎች የማይሰጡ ከሆነ፤ የፈጠራ ባለሙያዎች ቀጣይ የምርምር ሥራዎችን ማሳደግና ማስፋት እንደማይችሉ ይገመታል። በቀጣይነት የሚገኙ የተሻሻሉ የፈጠራ ሥራዎች አለመኖራቸው ደግሞ፤ በምርቶች ተጠቃሚና አጠቃላይ የኑሮ መሻሻል ሂደት ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ተፅዕኖ ይኖረዋል። የአዕምሯዊ ንብረት ዓይነቶች እንዴት ይመደባሉ? የአዕምሯዊ ንብረት፤ የኢንዱስትሪያዊ ንብረት (Industrial Property) እና የቅጅና ተዛማጅ መብቶች (Copyright and Related Rights) በሚሉ ሁለት ዋና ዋና ክፍሎች እንደሚመደብ ያስረዳሉ። አክለውም፤ ኢንዱስትሪያዊ ንብረት በውስጡ፤ የፓተንት፣ የንግድ ምልክት፣ የኢንዱስትሪያዊ ንድፍ እና የጂኦግራፊያዊ ምንጭ አመላካቾች የተሰኙ አራት ክፍሎችን እንደሚይዝ ያብራራሉ። ፓተንት ምንድን ነው?፡- ፓተንት ማለት በአንድ ቴክኒካዊ ባሕርይ ባለው የፈጠራ ሥራ ላይ የሚኖር የፈጠራ ባለቤትነት ብቸኛ መብት መሆኑን አቶ ብሩክ አስረድተዋል። የፓተንት መብት በአንድ ምርት (ለምሳሌ ማሽን ወይም የአመራረት ሂደት (Process) ሊሰጥ የሚችል ሲሆን፤ ፈጠራውም ለአንድ ቴክኒካዊ ችግር መፍትሔ የሚያስገኝ መሆን ይኖርበታል ይላሉ። ከፈጠራ ሥራው አመንጪ ይሁንታ ውጭ ሥራውን ገበያ ላይ ማዋል፣ መጠቀም፣ ማሰራጨት፣ መሸጥ ወዘተ… እንደማይቻልም አክለዋል። ፓተንት ለባለ መብቱ የጥበቃ መብት የሚያስገኝ ሲሆን፤ የጥበቃው ዘመንም በአጠቃላይ እስከ 20 ዓመት ሊደርስ ይችላል። ፓተንት የሚያስገኛቸው ሕጋዊ (የጥበቃ) መብቶች፡- የፈጠራ ሥራውን መጠቀም የሚችሉና የማይችሉ ሰዎችን መወሰን፤ ሦስተኛ ወገኖች ሥራውን እንዲጠቀሙ የመፍቀድ ወይም የፈቃድ ውል ስምምነት የመስጠት እንዲሁም የፈጠራ ሥራውን የመሸጥ (ለአዲስ የፓተንት ባለመብት) የሚሉት ይገኙበታል ብለዋል ሥራ አስፈጻሚው። የፓተንት ሥራዎች ለምን ያስፈልጋሉ?፡- ይህን ሲያብራሩም፤ ፓተንት ለፈጠራ ባለመብቶች ዕውቅናንና ሽልማቶችን (ማበረታቻዎችን) የሚሰጥ በመሆኑ፣ ፈጠራዎቹ የኢኖቬሽን ሥራዎችን ስለሚያጠናክሩና በዚህም ቀጣይነት ያለው የሰው ልጅ ሕይወት መሻሻልን የሚያረጋግጥ በመሆኑ እና በሌሎችም በጎ አስተዋጽዖዎች ፓተንት በዕጅጉ አስፈላጊ ነው ብለዋል። የንግድ ምልክት ምንድን ነው?፡- የንግድ ምልክት ማለት አንድን ምርት ወይም አገልግሎት ከሌላው ምርትና አገልግሎት እንዲለይ ለማስቻል በንግድ ምልክት ባለቤቶች ለምርታቸውና አገልግሎታቸው መለያ እንዲሆን ጥቅም ላይ የሚውል ልዩ ምልክት መሆኑን ተናግረዋል። የንግድ ምልክት ሸማቹ ሕብረተሰብ የሚፈልገውን ምርትና አገልግሎት በቀላሉ ለይቶ እንዲገዛ ከማስቻሉም በላይ በሚገዛው ምርትና አገልግሎት ጥራት ላይ በመተማመን ፍላጎቱን እንዲያሟላ ያደርጋል። የንግድ ምልክት ለባለመብቱ ምን ጥቅም ያስገኛል?፡- ምርቶቹ (አገልግሎቶቹ) በተጠቃሚዎች እንዲለዩለት ወይም እንዲታወቁለት ያደርጋል፣ ክፍያን መሠረት አድርጎ ሦስተኛ ወገን እንዲጠቀምበት የመፍቀድ፣ የንግድ ምልክቶች በራሳቸው ዋጋ አላቸው (የአዕምሯዊ ንብረት ዋጋ ትመና (IP Valuation) ለምሳሌ በፈረንጆቹ በ2026 የመጀመሪያ ወራት አፕል (Apple) 600 ቢሊየን ዶላር፣ ማይክሮሶፍት (Microsoft) 565 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር፣ ጉግል (Google) 433 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ዋጋ ግምት እንደነበራቸው ተብራርቷል። በተጨማሪም፤ የንግድ ምልክት በሕግ በሚቀመጥ የጊዜ ገደብ መሠረት እየታደሠ ለዘላለም ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል፤ የንግድ ምልክት ባለቤቱን በማስተዋወቅ ዕውቅናና የገንዘብ ትርፍን ያስገኛል፤ የንግድ ምልክት ተገቢ ያልሆኑ የንግድ ውድድሮችን በመግታት ረገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል (ተመሳስለው የሚሠሩና ለገበያ የሚቀርቡ ሥራዎችን (Counterfieited Products) ለመዋጋት ዓይነተኛ መሣሪያ ሆኖ ያገለግላል፤ የንግድ ምልክት ሰዎች ምርቶቻቸውንና አገልግሎቶቻቸውን ሚዛናዊ በሆነ አግባብ እንዲያቀርቡ በማድረግና በብሔራዊና ዓለም አቀፍ ደረጃ የተሳለጠ የንግድ ሥርዓት እንዲኖር ምቹ ሁኔታ በመፍጠር አስተዋጽዖው የላቀ ነው ብለዋል። ኢንዱስትሪያዊ ንድፍ ምንድን ነው?፡- ኢንዱስትሪያዊ ንድፍ በምርቶች ሥነ-ውበት (Esthetics) ላይ ተመስርቶ ቅርጽን፣ መስመሮችን ወይም ቀለምን በመጠቀም ለገበያ የሚቀርቡ ምርቶች የገዥዎችን (ሸማቾችን) ቀልብ ለመሳብ እንዲችሉ በምርቶች ላይ የሚገለጽ የንድፍ ጥበብ ዘርፍ ነው ያሉት አቶ ብሩክ፤ ኢንዱስትሪያዊ ንድፎች በኢንዱስትሪና ዕደ-ጥበብ ምርቶች ላይ ተዘጋጅተው ሊወጡና ለገበያ ሊቀርቡ ይችላሉ ይላሉ። ዘርፉ ከቴክኒካልና ሕክምና መሣሪያዎች አንስቶ እንደ ሠዓት፣ ጌጣጌጦችና ሌሎች የቅንጦት ምርቶች ዕቃዎችን ሊያካትት ይችላልም ብለዋል። የቤት ዕቃዎችን፣ የኤሌክትሪክ መሣሪያዎችን፣ ተሽከርካሪዎችና የሕንጻ ንድፎችን እንዲሁም የጨርቃጨርቅ ንድፍ ውጤቶች በኢንዱስትሪያዊ ንድፍ ሥር የሚወድቁ ይሆናሉ ይላሉ። ኢንዱስትሪያዊ ንድፎች ጥበቃ የሚደረግላቸው አዲስ ወይም ወጥ ከሆኑ ብቻ መሆኑን ገልጸው፤ በዲዛይኑ ውስጥ ከሚገለጸው ምርት ጋር ተያያዥ የሆኑ የቴክኒክ ጉዳዮች ጥበቃ እንደማይደረግላቸው አስታውቀዋል። ለኢንዱስትሪያዊ ንድፍ ጥበቃ ማድረግ ለምን ያስፈልጋል?፡- በምርቶች ውበት ላይ የሚገለጽ በመሆኑ የተጠቃሚውን ዐይን ይስባል፣ የምርቶችን ዋጋ ይጨምራል፣ ፈጠራንና ውድድርን ያበረታታል፣ ለባለመብቱ ብቸኛ መብትን ያጎናጽፋል፣ በኢንዱስትሪዎች፣ ባሕላዊ ጥበብና በዕደ ጥበብ ዘርፍ ፈጠራ በማሻሻል ኢኮኖሚ እንዲያድግ ያደርጋል፣ የወጭ ንግድን (Export Trade) ያሳድጋል በማለት የኢንዱስትሪ ንድፍ ጥበቃ አስፈላጊነትን ያብራራሉ። የጂኦግራፊያዊ ምንጭ አመላካች ምንድን ነው?፡- የጂኦግራፊያዊ ምንጭ አመላካቾች በምርቶች ላይ የሚቀርቡ ምልክቶች ሆነው እነዚህ ምልክቶች አንድ የተወሰነ አካባቢን በምርቱ ምንጭነት የሚያመላክቱና ጥራትንና ዝናን ከቦታው ጋር አስተሳስረው የሚያንጸባርቁ መሆናቸውን አቶ ብሩክ ያስረዳሉ። በአብዛኛው የጂኦግራፊያዊ ምንጭ አመላካቾች ልዩ ምርቱ የሚገኝበትን የቦታ ስም (Specific Local Geographyical Factors – Climate, Soil) ይይዛሉ። ለምሳሌ፡- Roquefort for Cheese -France፣ የማረቆ በርበሬ፣ የሸኖ ቅቤ፣ የዓድኣ ጤፍ … የመሳሰሉት ምርቶች ተጠቃሾች ናቸው። የጂኦግራፊያዊ ምንጭ አመላካቾችን መጠበቅ ለምን ያስፈልጋል?፡- ተጠቃሚዎች ምርቶች የሚገኙበትን ሀገር ወይም አካባቢ በቀላሉ ለመለየት፣ ሕጋዊነት በሌላቸው ወገኖች የምርቱ መገኛ አካባቢ እና የምርቱ ዝና በተሳሳተ መልኩ ለሌላ ምርት መጠሪያ እንዳይውል ለመከላከል ይረዳል ይላሉ። የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ምንድን ናቸው?፡- የቅጅ መብት በሥነ-ጽሑፍ እና ሥነ-ጥበብ ዘርፍ ወጥ የፈጠራ ሥራዎችን ለሚያመነጩ ደራስያን፣ አርቲስቶች ወዘተ… የባለቤትነት መብት የሚሰጥ የሕግ ማዕቀፍ መሆኑንም ነው ሥራ አስፈጻሚው የሚያስረዱት። በአንጻሩ ተዛማጅ የቅጅ መብት ማለት ይላሉ አቶ ብሩክ፤ በወጥ የፈጠራ ሥራዎች ላይ ተመስርተው የሚሠሩ ተዛማጅ (Related) የፈጠራ ሥራዎችን ያካትታል። ለምሳሌ፡- ከዋኞቹ (ተዋንያን እና ዘፋኞች)፣ ድምጽ ሪከርዲንግስ፣ አሳታሚዎች (ኮምፓክት ዲስኮች)፣ የብሮድካስት ተቋማት፣ (ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን) የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ ሲሉ ዘርዝረዋል። የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ምን ዓይነት መብቶች ያስገኛሉ?፡- ባለመብቶች ሥራዎቻቸውን ለመጠቀም ወይም ሦስተኛ ወገኖች እንዲጠቀሙባቸው የመፍቀድ፣ ሥራዎች እንዲባዙ፣ ለሕዝብ እንዲዳረሱ፣ እንዲሠራጩ፣ እንዲተረጎሙ ወይም ወደሌላ ሥራ እንዲቀየሩ የመፍቀድ ወይም የመከልከል፣ የደራሲነት (የአመንጭነት) መብት ዕውቅና እንዲያገኙ፣ በብዕር ስም የመጠቀም መብት፣ ክብሩንና መልካም ስሙን የሚያጎድፍ የሥራ መዛባት እንዳይኖር የመጠበቅ ወይም የሥራው ወደሌላ መቀየር የሚያስከትለውን ጉዳት የመቃወም ወዘተ መብቶችን ያስገኛሉ ብለዋል። የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ ምን ጥቅሞች ያስገኛል?፡- የሰውን ልጅ የፈጠራና ኢኖቬሽን ጥረቶችን ያሳድጋል፣ ለፈጠራ አመንጭዎች መበረታታትን ይፈጥራል፣ የሕጋዊ ተፈጻሚነትን በማረጋገጥ አመንጭዎችና በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች መዋዕለ-ነዋይ እንዲያፈሱ የፈጠራ ሥራዎችን በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚኖራቸውን የሥርጭት ሽፋን ያሳድጋል ነው ያሉት አቶ ብሩክ። የፓሪስ ስምምነት አባል ኢትዮጵያ ግንቦት 7 ቀን 2017 ዓ.ም የፓሪስ ስምምነት አባል ሀገር ለመሆን ለዓለም አዕምሯዊ ንብረት ድርጅት (WIPO) ያስገባችው ጥያቄ ተቀባይነት በማግኘቱና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስምምነቱን ነሐሴ 9 ቀን 2017 ዓ.ም በማጽደቁ ከዚሁ ዕለት ጀምሮ ለስምምነቱ ተገዢ ሆናለች። አቶ ብሩክ እንዳብራሩት፤ የፓሪስ ስምምነት በጥቅሉ የኢንዱስትሪያዊ ንብረቶችን ጥበቃ የሚመለከት ነው። የፓተንት፣ የንግድ ምልክት፣ ኢንዱስትሪያዊ ንድፍ፣ የግልጋሎት ሞዴል (በአንዳንድ ሀገራት ሕግ ኢትዮጵያን ጨምሮ “የአነስተኛ ፈጠራ የባለቤትነት መብት” በመባል የተደነገገ)፣ የአገልግሎት ምልክት፣ የንግድ ስም (የኢንዱስትሪ ወይም የንግድ እንቅስቃሴ የሚካሄድባቸው ስያሜዎች)፣ ጂኦግራፊያዊ አመላካች እና ፍትሐዊ ያልሆነ ውድድርን መከላከል ያካተተ ነው። የስምምነቱ መሠረታዊ ድንጋጌዎች በሦስት ዋና ዋና መርሆዎች እንደሚከፈሉ ጠቁመው፤ እነሱም፡- የፓሪስ ስምምነት አባል ሀገር መሆን በሌሎች አባል ሀገራት ውስጥ እንደ ዜጋ የመስተናገድ መብት፣ የቀዳሚነት መብት የማግኘት፣ በቀላሉ ዓለም አቀፍ ጥበቃ የማግኘት አሠራር እና መሰል ጉልህ ጥቅሞችን የማግኘት ዕድል ይሰጣል ሲሉ ይገልጻሉ። በመሠረቱ የፓሪስ ስምምነት የአዕምሯዊ ንብረት መብት ጥበቃን በማቀላጠፍ አዳዲስ ግኝቶችንና ፈጠራዎችን እንዲሁም የንግድ ሥራዎች ድንበር ሳይገድባቸው የፓተንትና የንግድ ምልክት መብቶች በቀላሉ እንዲጠበቁ በማድረግ ፈጠራን፣ ንግድን እና ኢኮኖሚያዊ እድገትን እውን ያደርጋል ብለዋል። የዘንድሮው የአዕምሯዊ ንብረት ቀን የፊታችን ሚያዝያ 17 ቀን 2018 ዓ.ም “አዕምሯዊ ንብረትና ስፖርት፤ እንዘጋጅ፣ እንጀምር፣ እንፍጠር!” በሚል መሪ ሐሳብ ዓለም አቀፉ የአዕምሯዊ ንብረት ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል። በስፖርት ዓለም ውስጥ የሚከሰቱ ተወዳዳሪዎች የግልና የጋራ ፈጠራዎች፣ ንድፎች፣ ብራንዶችና የመልካም ዝና ታሪኮችን ለመጠበቅና ሀገራትን ጭምር ለማስተዋወቅ የአዕምሯዊ ንብረት መብት ጥበቃ ሥርዓት ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ይታመናል። ምክንያቱም ስፖርት በባሕርይው በውድድር ላይ ብቻ ተወስኖ የሚቀር ሳይሆን፤ ከሀገራት ዝና፣ ከፋሽን ዲዛይን፣ ከመዝናኛ፣ ከሚዲያ ሥርጭት፣ ከጤናና ከዕለት ተዕለት መገልገያ ቁሶች ጋር የሚገናኝ በመሆኑ ነው።
ባሳለፍነው ሳምንት …
Apr 18, 2026 942
ከሚያዝያ 5 እስከ ሚያዝያ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች መካከል … • የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ መመረቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት ኢትዮጵያ በንፋስ ኃይል አማካኝነት ጨለማን ለመግፈፍ፣ ዐቅምን በለየ የቅድመ ጥናት እና ልዩ ዕቅድ የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫን ዕውን አድርጋለች ብለዋል። ይህ ፕሮጀክት 100 ሜጋ ዋት ንጹህ የኃይል አቅርቦት በመጨመር ወደ ዘርፈ-ብዙ እና ቀጣይነት ባለው የኃይል መጻዒ ዕጣ ፈንታ ለመገንባት የምናደርገውን ጉዞ ያጠናክረዋል ሲሉም ገልጸዋል። ይህም አስተማማኝ የኃይል አቅርቦትን ለማረጋገጥና የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመገንባት ያለንን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ አብነት ነው ብለዋል በወቅቱ። በሁሉም ዘርፎች የምናስመዘግበው የኢትዮጵያ የዕድገት ጉዞ ተጠናክሮ እየቀጠለ ይበልጥም እየለማ ይሄዳል፤ ከምንጊዜውም በላይ ታላቅ የምንሆንበት ጊዜ ሩቅ አይደለም ሲሉም አመላክተዋል። • ከኮፕ32 አስተናጋጅነት ጋር በተያያዘ ምክክር መደረጉ የኮፕ32 አስተናጋጇ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ኮሚቴ በማቋቋም ዝግጅቷን ቀደም ብላ መጀመሯን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታውቀዋል። ከብሔራዊ ኮሚቴው ጋር በነበረን ስብሰባ፤ በተለያዩ ዘርፎች የተከናወኑ ሥራዎችን በመገምገም ክፍተቶችን የመለየት እና ሁሉም ጥረቶቻችን ከሀገራዊ ርዕያችን ጋር የተጣጣሙ መሆናቸው ተዳሷል ሲሉ ገልጸዋል። ከግምገማ ባሻገር የቀጣይ አቅጣጫ መቀመጡን ጠቅሰው፤ ትኩረታችን ግልጽ ነው፤ በጠንካራ ትብብር፣ በተዋሃደ ታላቅ ርዕይ እና የጋራ ጽኑ ትጋት ተናበን ይህን ዓለም አቀፍ ሁነት በልኅቀት በማስተናገድ የሀገርን ታላቅነት ዳግም ማሳየት ነው ብለዋል። • የላይቤሪያ ፕሬዚዳንት በኢትዮጵያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ማድረጋቸው ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ባሳለፍነው ሳምንት ወደ ኢትዮጵያ ለመጡት የላይቤሪያ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ከዚያም በብሔራዊ ቤተ-መንግሥት አቀባበል አድርገውላቸዋል። በነበራቸው የሁለትዮሽ ውይይትም፤ ኢትዮጵያ እና ላይቤሪያ በቅኝ ያልተገዙ፣ ለአኅጉሩ ነፃነትና አንድነት ድምፅ በመሆን ከጋራ የጽናት ታሪክ የሚመነጭ ጥልቅና ዘመናትን የተሻገረ ግንኙነት አላቸው ያሉት ጠላይ ሚኒስትሩ፤ ዛሬም እንደ ሁሌው ኢትዮጵያ ከሰፊ ገበታዋ ያላትን ታላቅ ዐቅምና ዘላቂ ወዳጅነት አብረዋት ለሚጓዙ ሁሉ ለማካፈል ዝግጁ ናት ብለዋል። ጉብኝቱም በተለያዩ ዘርፎች ያለንን የቆየ አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከርና ለማስፋት ወሳኝ ምዕራፍን ከፍቷል ሲሉ ገልጸዋል። ከሁለትዮሽ ስብሰባው በመቀጠልም በሁለቱ ሀገራት በኩል ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች ለማሳካት ያለንን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጡ የመግባቢያ ስምምነቶች እንዲፈረሙ አድርገናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ስምምነቶቹ ኢትዮጵያ በፈጣን የለውጥ ጉዞ ያካበተችውን ልምድ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ለማካፈል እንዲሁም ከአጋሮቻችን የተለያዩ ዕይታዎችን በመቅሰም ለአኅጉሩ ዕድገት ዘላቂና አፍሪካዊ መፍትሔዎችን በጋራ ለማፍለቅ እንደ ወሳኝ መሠረት ያገለግላሉ ነው ያሉት። • የፖርቹጋል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከፖርቹጋል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፓውሎ ራንገል ጋር ባሳለፍነው ሳምንት በጽሕፈት ቤታቸው ተወያይተዋል። በዚሁ ወቅትም፤ የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን እና ቀጣይ ትብብሮችን በምናጠናክርባቸው ቁልፍ መስኮች ላይ መክረናል ብለዋል። • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከኢቢሲ ጋር ቆይታ ማድረጋቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “የሉዓላዊነት ልብ” በሚል ርዕሰ ጉዳይ ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር ቆይታ አድርገዋል። በቆይታቸውም፤ ሉዓላዊነትን ለማስጠበቅ፣ የተሻገረ ኢኮኖሚ ለመፍጠር፣ በበቂ ሁኔታ ዜጎችን ሥራ ለማስያዝ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ሚና አይተኬ መሆኑን በአጽንኦት አንስተዋል። በዚሁ ወቅትም፤ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ሥራ ይፈጥራል፣ ኢኮኖሚ ያሸጋግራል፣ ወደሚቀጥለው ደረጃ ለመሻገር እንደ መስፈንጠሪያ ሆኖ ያገለግላል በማለት አብራርተዋል። በእነዚህ እና በሌሎች ምክንያቶች ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ የኢኮኖሚ ብቻ ሳይሆን የሉዓላዊነት አንዱ አንጓ ነው በማለት አስረድተዋል። የብዙ መንግሥታትና የእኛም ትኩረት ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ላይ የሆነበት ዋናው ምክንያት፤ ኢንዱስትሪ ማደግ ለሚያስብ ሀገር በጣም ወሳኝ ነገር ስለሆነ ነው ብለዋል። አክለውም፤ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ የኢኮኖሚ ልብ መሆኑን አስገንዝበዋል። አንድ ሰው ልቡ ካልሠራ ሌላው አካላቱ ጤነኛ ቢሆንም ውጤታማ እንደማይሆን ሁሉ፤ ኢኮኖሚን ኢኮኖሚ የሚያደርገው የኢኮኖሚ ልብ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ነው ብለዋል። እንዲሁም የከተማ እና የከተሜነት እሳቤ ለሀገረ መንግሥት ግንባታ ስኬት ያለውን ወሳኝ ሚና አንስተው፤ የሀገረ መንግሥት ግንባታ ሊከናወንና ሊሳካ የሚችለው በጥግግት የሚኖሩ ሰዎች ሲኖሩ መሆኑን አስገንዝበዋል። የሕዝብ ጥግግት ለልማት እጅግ ወሳኝ መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ልማትንና ብልጽግናን የሚያስብ ማንኛውም መንግሥት ከተማን፣ ከተሜነትን፣ ግብር መክፈልንና አገልግሎት መስጠትን ማዕከሉ ካላደረገ ልማት ሊያመጣ እንደማይችል አብራርተዋል። ከተማ አያስፈልግኝም፤ የእኔ ትኩረት አርሶ አደር ብቻ ነው የሚል እሳቤ ካለ ልማትን ማሰብ እንደማይቻልም አመላክተዋል። • ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን በወሎ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ባሳለፍነው ሳምንት በደቡብ ወሎ ዞን ተሁለደሬ ወረዳ አሎማ ክላስተር በበጋ መስኖ የለማውን የደረሰ የስንዴ ማሳ በጎበኙበት ወቅት፤ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ሀገራችን በምግብ ራሷን ለመቻል የጀመረችው ጉዞ በተግባር ሥር እየሰደደ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል። የመደመር መንግሥት ለበጋ መስኖና ለስንዴ ምርታማነት የሰጠው ትኩረት የዜጎችን ሕይወት እየቀየረና የሀገርን የምግብ ሉዓላዊነት እያረጋገጠ ይገኛል ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የተመለከትነው የስንዴ ልማትም የራዕያችንን ውጤት፣ የሐሳባችን መሬት መንካትና ፍሬ የማግኘታችን ተጨባጭ ማሳያ ነው በማለት ገልጸዋል። እንዲሁም በ "ገበታ ለትውልድ" መርሐ ግብር የተገነባውን የሎጎ ሐይቅ ሪዞርት ሥራ ማስጀመራቸውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል። የሎጎ ሐይቅ ሪዞርት ጸጋን የመለየት፣ የማልማትና ወደ ሀብት የመቀየር ማሳያ እና የወሎ የብልጽግና ተስፋ ነው ብለዋል። ይህ ፕሮጀክት ከግንባታው ጅማሮ እስከ ፍጻሜው የ"መደመር" ዕሳቤ በተግባር የታየበት፣ የመንግሥት ሐሳብ፣ የባለ ሀብቱ ታታሪነት እና የሕዝቡ ትጋት የተሰባጠረበት ድንቅ ውጤት ነው ሲሉም ገልጸል። ያየነው ልማት የሰላም ውጤት ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የሐይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ወጣቶች ሰላማቸውን አጥብቀው እንዲጠብቁ አደራ በማለት፤ በአንድነት እና በትጋት ከሠራን ይህ ቀጣና የዕድገትና ብልጽግና መዳረሻ መሆኑ አይቀሬ ነው ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። እንዲሁም የኢትዮጵያ የመሠረተ-ልማት እና ኮንስትራክሽን ሳምንትን የከፈቱት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን፤ በዚሁ ወቅት መሠረተ-ልማት ለሀገር ዕድገት ወሳኝ ግብዓቶችን በማመላለስ የኢኮኖሚያችን የደም ሥር፣ የብልጽግናችን መሠረት ነው ብለዋል። በዐውደ ርዕዩ የተመለከትነውም ወሳኝ የልማት ተቋሞቻችን፣ መሠረተ-ልማትን እንደ ሀገር በቅንጅትና በትብብር የመምራት አዲስ የሥራ ባህል እየገነቡ መሆናቸው ነው ሲሉም ገልጸዋል። መንግሥት በመንገድ፣ በኃይል፣ በመስኖ፣ በባቡርና በዲጂታል መሠረተ-ልማት ዘርፍ ፈጣንና ፍትሐዊ ልማት ለማረጋገጥ የሚሠራውን ሥራ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አመላክተዋል። አሁን ያለንበት ወቅት የሥራ፣ የውጤት እና የተስፋ ዘመን ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ትናንት የተገነባው ለዛሬ፣ ዛሬ የምንገነባው ደግሞ ለነገው ትውልድ ኩራት እና የብልጽግና ዋስትና ነው ብለዋል። #ባሳለፍነው_ሳምንት #ኢዜአ #Ethiopian_News_Agency
የንፋስ ኃይል፤ የኢትዮጵያ የብርሃን አድማስ የአረንጓዴ ልማት ሌላኛው ብስራት!!
Apr 18, 2026 150
በቁምልኝ አያሌው የሰው ልጅ የታዳሽ ኃይል ምንጮችን መጠቀም የጀመረው በጥንታዊ ሥልጣኔዎች ዘመን እንደነበር የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ። ለአብነትም፤ ግብፃውያን ከአምስት ሺህ ዓመታት በፊት ጀልባዎችን በባሕር ላይ ለመንዳት የንፋስ ኃይልን ይጠቀሙ ነበር። በሰባተኛው ክፍለ ዘመን መባቻ ደግሞ ፋርስ (የአሁኗ ኢራን) የመጀመሪያውን በንፋስ ኃይል የሚሠራ የጥራጥሬ መፍጫ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ ማዋል ጀመረች። ግሪኮችና ሮማውያን የውሃ መንኮራኩሮችን በመጠቀም እህል መፍጨት የሚያስችል ፈጠራን እንዳስጀመሩ የታዳሽ ኃይል የታሪክ ማኅደሮች ይጠቁማሉ። ጥንታዊያን ሕዝቦች የፀሐይ ኃይልን ለብርሃንና ለሙቀት ምንጭነት ከመጠቀም ባለፈ፣ የፀሐይ ጨረርን በማሰባሰብ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚጠቀሙባቸውን ጥበቦች ነበሯቸው። ምንም እንኳን የ19ኛው ክፍለ ዘመን የኢንዱስትሪ አብዮት በድንጋይ ከሰልና በተፈጥሮ ዘይት የበላይነት ቢያዝም፤ በዚሁ ወቅት ለታዳሽ ኃይል ቴክኖሎጂ ልማት መሠረት መጣሉን ታሪክ ያስትውሰናል። ለዚህም ማሳያ የሚሆነው እ.አ.አ በ1839 ፈረንሳዊ የፊዚክስ ሊቅ ኤድመንድ ቤኩረል፤ የፀሐይ ብርሃንን ወደ ኤሌክትሪክ መቀየር የሚቻልበትን የ'ፎቶቮልታይክ' (Photovoltaic effect) ክስተት ማገኘቱ ነው። በተጨማሪም እ.አ.አ በ1882 የመጀመሪያው በውሃ ኃይል የሚሰራ የኤሌክትሪክ ማመንጫ በአሜሪካ ሥራ ጀመረ። እ.አ.አ በ1883 ደግሞ በኦስትሪያ ቪየና በተካሄደው ዓለም አቀፍ የኤሌክትሪክ ኤግዚቢሽን፣ የንፋስ ኃይልን ወደ ኤሌክትሪክ የሚቀይሩ ተርባይኖችን ለመትከል የሚያስችሉ ወሳኝ የቴክኖሎጂ ዕድሎች ታይተዋል። በ20ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ ለታዳሽ ኃይል የሚሰጠው ትኩረት መቀዛቀዝ ቢያሳይም፣ በ1970ዎቹ የተከሰተው ዓለም አቀፍ የነዳጅ እጥረት ዓለም አማራጮችን እንድታማትር አስገድዷታል። በዚህም ምክንያት የነዳጅ ዋጋ መናር ሀገራት ከነዳጅ ጥገኝነት ለመውጣት ወደ ውሃ፣ ፀሐይና ንፋስ ኃይል ፊታቸውን እንዲያዞሩና በዘርፉ ለሚካሄድ ጥናትና ምርምር ከፍተኛ መነሳሳት እንዲፈጠር አድርጓል። የንፋስ ኃይል ታሪካዊ ዳራና የቴክኖሎጂ እድገት የንፋስ ኃይልን ወደ ኤሌክትሪክ የመቀየር ታሪክ እ.አ.አ በ1883 በኦስትሪያ ቪየና በተካሄደው ዓለም አቀፍ የኤሌክትሪክ ኤግዚቢሽን ላይ ፍሬድላንድ በተሰኙ ሳይንቲስት አማካኝነት የመጀመሪያው የንፋስ ኤሌክትሪክ ተርባይን ለእይታ መቅረቡ ይነገራል። ይህ የፈጠራ ሥራ በየጊዜው እየተሻሻለ መጥቷል። በ1887 ስኮትላንዳዊው የኮሌጅ ፕሮፌሰር ጄምስ ብሊዝ የቤታቸውን መብራት ለማብራት የተጠቀሙበት የንፋስ ተርባይን በዘርፉ ትልቅ እመርታ ተደርጎ ይወሰዳል። ፕሮፌሰሩ ቀስ በቀስ የፈጠራ ውጤታቸውን አሳድገዋል። የአካባቢው ማኅበረሰብም የቴክኖሎጂው ተጠቃሚ እንዲሆን ያቸሉትን አድርገዋል። የንፋስ ኃይል ማመንጫ ግንባታ በበርካታ ሀገራት የተለያዩ ሙከራዎች መደረጉን ድርሳናት ሲፈተሹ የሚያሳዩት እውነት ነው። ሆኖም ዘርፉ ትኩረት አግኝቶ እንዲያድግ ያደረገው በ1973 በዓለም ላይ የተከሰተው የነዳጅ ቀውስ ነው። ይህ ክስተት ሀገራት ወደ አማራጭ ኃይል ምንጮች እንዲያተኩሩ ዕድል ፈጥሮላቸዋል። ይህን ተከትሎም አሜሪካ መጠነ ሰፊ የንፋስ ኃይል እርሻዎችን (Wind Farms) በመገንባት ግንባር ቀደም መሆን ችላለች። እ.አ.አ እስከ 2008 ድረስ ከዘርፉ የምታመነጨውን የኃይል መጠን ወደ 24.4 ጊጋ ዋት አሳድጋለች። የንፋስ ኃይል የማመንጨት ሂደት የንፋስን የተፈጥሮ እንቅስቃሴ በተርባይኖች አማካኝነት ወደ ሜካኒካዊ ኃይል፣ በመቀጠልም ወደ ኤሌክትሪክ ኃይል የሚቀይር ዘመናዊ የታዳሽ ኃይል ቴክኖሎጂ ነው። ሂደቱም የተርባይን ክንፎች በንፋስ ግፊት አማካኝነት በሚፈጥሩት ሽክርክሪት ጀኔሬተሩን በማንቀሳቀስ ኤሌክትሪክ እንዲመነጭ ያደርጋል። የዓለማችን ግዙፍ የንፋስ ኃይል ማመንጫዎች የት ይገኛሉ? በአሁኑ ወቅት በዓለማችን ከ350 ሺህ በላይ የንፋስ ተርባይኖች ተተክለው ኃይል እየሰጡ ይገኛል። ቻይና በንፋስ ኃይል ማመንጨት የዓለማችን ቀዳሚ ሀገር ስትሆን፤ አሜሪካ እና ጀርመን በቅደም ተከተል ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል። የቻይናው ጂኳን (Gansu) የንፋስ ኃይል ማመንጫም ከ20,000 ሜጋ ዋት በላይ የማመንጨት አቅም እንዲኖረው ታቅዶ እየተገነባ ያለ ግዙፍ ፕሮጀክት ነው። የንፋስ ኃይል በኢትዮጵያ ዓለም ለታዳሽ ኃይል ልማት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል። ኢትዮጵያም በአፍሪካ የንፋስ ኃይል ልማት ቀዳሚ ተዋናይ የሚያደርጋትን ስራዎች እያከናወነች ነው። ሀገሪቷ በምስራቅ አፍሪካ ያላት ስትራቴጂካዊ መልክዓ-ምድራዊ አቀማመጥ የታደለችውን የተፈጥሮ ፀጋ ወደ አማራጭ ኃይል ለመቀየር ሰፊ ዕድል ፈጥሮላታል። በንፋስ ኃይል ልማት የመጣው ከፍተኛ ለውጥም የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ፍላጎትን በመሙላት የብዝኅ ታዳሽ ኃይል አማራጭ ልማት እንዲጎለብት እያደረገ ይገኛል። የተፈጥሮ ስጦታና ያልተነካው የኢትዮጵያ እምቅ የንፋስ ኃይል ፀጋ ኢትዮጵያ ከምስራቅ አፍሪካ ሀገራት አኳያ በንፋስ ኃይል አማራጭ እምቅ የመልማት ፀጋን ተችሯታል። በተለይም የታላቁ ስምጥ ሸለቆ፣ ሰሜናዊ ተራራማ ስፍራዎችና ምስራቃዊ ቆላማ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የንፋስ ፍጥነት ኃይልን ለማመንጨት ተስማሚ መልክዓ ምድሮች ናቸው። በዚህም ኢትዮጵያ እስከ አንድ ነጥብ ሦስት ሚሊዮን ሜጋ ዋት የንፋስ ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳላት ጥናቶች ያመለክታሉ። ይህ አሃዛዊ መረጃም ከአሁኑ ወቅት አጠቃላይ ኃይል የማመንጨት አቅም ጋር ሲነፃጸር ሰፊ የልማት ዕድል መኖሩን ያረጋግጣል። ከጅምር እስከ ዛሬ የስኬት ጉዞ ምዕራፍ የኢትዮጵያ የንፋስ ኃይል ልማት በ2001 ዓ.ም አሸጎዳ ፕሮጀክት ግንባታ ተጀምሯል። በአዳማ 1 እና 2 ስራውን በማስፋት አሁን ላይ እስከ አይሻ 1 እና አሰላ ፕሮጀክቶች ደርሷል። እነዚህ የአዳማ፣ የአሸጎዳ፣ የአይሻ እና የአሰላ ፕሮጀክቶች የኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል አድማስ መስፋፋትን የሚያረጋግጡ ናቸው። ለሀገሪቷ አረንጓዴ ልማት ብስራት የሆኑ ታላላቅ ስራዎች ናቸው። አዳማ-1 እና ሁለት፡- በአጠቃላይ 204 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያላቸው የአዳማ የኤሌከትሪክ ማመንጫዎች የኢትዮጵያን የንፋስ ኃይል የማመንጨት አቅም በተግባር ያረጋገጡ ፋና ወጊዎች ናቸው። አሸጎዳ፡- በፈረንሳይ መንግስት የገንዘብ ድጋፍ የተገነባ ሁለተኛው የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ነው። 120 ሜጋ ዋት የሚያመነጨው ይህ ጣቢያ በሰሜን ኢትዮጵያ ለሚገኙ ዜጎች ከሚሰጠው ብርሃን በተጨማሪ የኢንዱስትሪ አቅም ሆኗል። አይሻ-2፡- በቅርቡ ተመርቆ ወደ ስራ የኃይል ማመንጫ ጣቢያ 80 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጫል። በኢትዮ-ጅቡቲ ድንበር አቅራቢያ መገናባቱም ቀጣናዊ የኃይል ትስስርን ለማጠናከር ጉልህ ፋይዳ አለው። አሰላ፡- በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን የምትገኝ የኢትዮጵያ ብርቅየ አትሌቶች መፍለቂያ ስፍራ ናት። በስንዴና ገብስ የግብርና ምርታማነትም በተምሳሌትነት ትጠቀሳለች። ነፋሻማ የአየር ሁኔታዋም ለኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ አቅም የሚሆን ፀጋን ተችሯታል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሚያዚያ 08 ቀን 2018 ዓ.ም 100 ሜጋ ዋት ማመንጨት የሚያስችለውን የአሰላ ንፋስ ኃይል መርቀዋል። በዚሁ ወቅትም አርሲ በስንዴና ገብስ ብቻ ሳይሆን በንፋስ ኃይልም የኢትዮጵያ ብልፅግና ማዕከል መሆኗን የአካባቢውን የብዝኅ ፀጋ አረጋግጠዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ የአሰላ ንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትም ኢትዮጵያ ከዕዳና ኪሳራ ወጥታ ፕሮጀክቶችን በታቀደላቸው ጊዜ ማጠናቀቅና ማትረፍ መጀመሯን በተግባር ያሳየ ነው። ከዚህም በላይ በንፋስ እና በጂኦተርማል ኃይል ማመንጫዎች የኢነርጂ ማዕከል እየሆነ መምጣቷን ያረጋግጣል። "አርሲ በኃይል ዘርፍ ልክ እንደ ስንዴ እና ገብስ ተጨማሪ አቅም ያለው አካባቢ መሆኑን ማየት ችለናል" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በንግግራቸው። የአሰላ ንፋስ ኃይል ማመንጫ በ145 ሚሊዮን ዩሮ ወጪ የተገነባ መሆኑን በመጥቀስ፤ ፕሮጀክቱ በአዋጭነት ደረጃ ሲታይ እጅግ ስኬታማ ነው ብለዋል። ከዚህ ቀደም የሚወሰዱ ብድሮች ለትውልድ ዕዳ ትተው የሚያልፉ እንደነበሩ በማስታወስ፣ የአሁኑን ፕሮጀክት የተለየ የሚያደርገውን ነጥብ ሲያነሱ ይህ ፕሮጀክት ቢበዛ በሁለት ዓመት ሙሉ ወጪውን ሸፍኖ ትርፋማ ስለሚሆን ልጆቻችን ትርፍ ሀብት የሚያገኙ እንጂ ዕዳ የሚረከቡ አይሆኑም በማለት ነው የገለጹት። ፕሮጀክቱ እውን እንዲሆን ግማሹን በእርዳታ እንዲሁም ቀሪውን ከወለድ ነጻ በሆነ ብድር ላቀረበችው የዴንማርክ መንግሥት የላቀ ምስጋና አቅርበዋል። የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቱም ቢበዛ በሁለት ዓመት ሙሉ ወጪውን ሸፍኖ ትርፋማ ስለሚሆን ልጆቻችን ምንዳ እንጂ ዕዳ የሚረከቡ እንደማይሆን አስገንዝበዋል። በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሄጦሳ ወረዳ ኢተያ ላይ በደማቅ ሁኔታ የተመረቀው የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ኢትዮጵያ በታዳሽ ኃይል ልማት የጀመረችውን ጉዞ ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ሌላኛው ታሪካዊ አሻራ ነው። በመደመር መንግስት መፅሐፍ ገፅ 206 ላይ እንደተጠቀሰው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦትን ለማስፋፋት ባለፉት ዓመታት ሰፊ ኢንቨስትመንት ተካሂዷል። ለአምራች ኢንዱስትሪው የሚቀርበው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦትም ከፍተኛ ለውጥ አሳይቷል። የታላቁ ሕዳሴ የኃይል ማመንጫን ጨምሮ ሌሎች በጅምር ያሉና በሚገባ አገልግሎት እየሰጡ ያልነበሩ ማመንጫዎችን ወደ መስመር ለማስገባት ተችሏል። በዚህም ሀገራችን ለአምራች ኢንዱስትሪው የሚያስፈልጋትን የኃይል አቅርቦት በሚገባ መሸፈን ችለናል በማለት ተከትቧል። በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች 504 ሜጋ ዋት ኃይል ብሔራዊ የኃይል ቋትን በመመገብ የኃይል አቅርቦት የጀርባ አጥንት ሆነዋል። በኢትዮጵያ የንፋስ ኃይል ልማት የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ ቀደም ሲል የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች በመንግስት ብቸኛ ይዞታነት ብቻ ሲካናወኑ ቆይተዋል። በአሁኑ ወቅት ግን ይህን አሰራር የሚቀይር የፖሊሲ ማሻሻያ ተደርጓል። ባለሃብቶች በመንግስትና የግል አጋርነት (PPP) ማዕቀፍ የሚሳተፉበት ሰፊ ዕድል ለመፍጠር ተችሏል። ይህም የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን ከማበረታታቱም በላይ፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርን በማፋጠን ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። የግሉን ዘርፍ በኃይል ልማት ላይ ለማሳተፍ የተወሰዱት የፖሊሲ እርምጃዎች አሁን ላይ ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገብ ጀምረዋል። ለአብነትም፤ በሶማሌ ክልል በመንግስትና በግል አጋርነት የሚገነባው የአይሻ-1 እና 3 የንፋስ ኃይል ፕሮጀክት ከ300 ሜጋ ዋት በላይ ኃይል የማመንጨት አቅም አለው። የኢትዮጵያ የንፋስ ኃይል ልማት የሀገር ውስጥ ፍላጎትን ከመሸፈን ባለፈ፣ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያለውን የኃይል ትስስር በማጠናከር ለጋራ ዕድገት መፋጠን ጉልህ ፋይዳ አለው። ኢትዮጵያ አረንጓዴ ኢኮኖሚ በመገንባትና የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን በመቀነስ ረገድ የምትከተለው የልማት መንገድ ለሌሎች ሀገራትም ተምሳሌት የሚሆን ነው። የኢትዮጵያ የንፋስ ኃይል ከብርሃን ባሻገር የንፋስ ኃይል የኢትዮጵያን የኃይል አቅርቦት በማሟላት ለሁለንተናዊ የብልፅግና ጉዞ ስትራቴጂክ መሰረት እየጣለ ይገኛል። ለአብነትም በኢትዮጵያ የዕድገት ጉዞ እያበረከተ ያለውን ፋይዳ መጥቀስ ይቻላል። የኢነርጂ ዋስትና እና የኃይል ምንጭ ስብጥር፡- በኢትዮጵያ ከውሃ ኃይል የማመንጨት ተግባር ቀዳሚውን ድርሻ ይይዛል። ይህም በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ በሚከሰት የድርቅ አደጋ የኃይል አቅርቦት ተጋላጭነት በማስፋት ተፅዕኖ ያሳድራል። የንፋስ ኃይልም የአቅርቦት ተጋላጭነትን ለመቀነስ ጉልህ ስትራቴጂክ ፋይዳ አለው። በበጋ ወራት የውሃ መጠን ሲቀንስ የንፋስ ኃይልን በመጠቀም ደግሞ የተፈጥሮ ሚዛንን የጠበቀ አስተማማኝ የኃይል ስብጥር ለመገንባት ጉልህ ፋይዳ ያበረክታል። የኢንዱስትሪ መፋጠንና የሥራ ዕድል፡- የኃይል አቅርቦት ለአስተማማኝ የኢንዱስትሪ ምርታማነት የጀርባ አጥንት ነው። የኢንዱስትሪው ዘርፍ ደግሞ ለሀገር ዕድገት ወሳኝ ሚና አለው። በተለይም በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚገነቡ የንፋስ ኃይል ፕሮጀክቶች የዕውቀትና የምርታማነት ሽግግርን በማፋጠን ረገድ ፋይዳቸው የጎላ ነው። እነዚህ ፕሮጀክቶች በንፋስ ኃይል ማመንጫ ተርባይኖች ተከላና ጥገና ወቅት የዜጎችን የምህንድስና ክህሎት በማጎልበት፣ የቴክኖሎጂ ሽግግሩን በተጨባጭ ያጠናክራሉ። ፋብሪካዎች አስተማማኝ ኃይል እንዲያገኙ በማድረግ የገቢ ምርቶችን የመተካትና የወጪ ንግድ አቅማቸውን በማሳደግ ለሀገር ኢኮኖሚ ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረክታሉ። ቀጣናዊ ትስስርና የውጭ ምንዛሬ ግኝት፡- የኢትዮጵያን የምስራቅ አፍሪካ የኃይል ማዕከልነት አቅም የሚያጎለብቱ ከአነስተኛ እስከ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ተገንብተዋል፤ በመገንባታ ሂደትም ናቸው። የንፋስ ኃይል ልማትም ቀጣናው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦትን እየደገፈ ይገኛል። ይህም የዕድገት ትስስርን በማፋጠን በየዓመቱ የሚገኘውን የውጭ ምንዛሬ ገቢን ለማሳደግ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያበረክታል። የአረንጓዴ አሻራና የአካባቢ ጥበቃ፡- የንፋስ ኃይል ከብክለት የፀዳ ንፁህ የኃይል ምንጭ ነው። ይህም ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ልማት የተቸራትን ዓለም አቀፍ ዕውቅና ለማፅናት በቀላሉ አይታይም። የአየር ንብረት ለውጥ ፈንድ የፋይናንስ ገቢን በማሳደግም ተጨማሪ የታዳሽ ኃይል ልማትን ለማጠናከር ያስቻላል። የገጠሩን ማህበረሰብ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚነት በማስፋትም የአካባቢና የደን መራቆትን ለመቀነስ ያስቻል። የንፋስ ኃይል ልማት ለኢትዮጵያ ቅንጦት አይደለም፤ ይልቁንስ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ዕድገትን የማፋጠን የህልውና ጉዳይ ነው። ለዚህም የንፋስ ኃይል ፀጋዎችን በማልማት ኢትዮጵያን አፍሪካዊት የንፁህ ኢኮኖሚ ግንባታ ፋና ወጊነት የሚያረጋግጥ የልማት አቅጣጫ ተተልሞ እየተሰራበት ነው። የኢትዮጵያ የንፋስ ኃይል ልማትም አዲስ ተስፋን የፈነጠቀ የብርሃን አድማስና የአረንጓዴ ልማት ሌላኛው ብስራት እየሆነ ይገኛል።
በፈተናዎች ሁሉ የጸናው የኢትዮጵያና የላይቤሪያ ወዳጅነት
Apr 14, 2026 1185
በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያና ላይቤሪያ ዘመናትን የተሻገረ ወዳጅነት አላቸው። ይሄ ወዳጅነት በፈተናዎች ጊዜ ሁሉ ጸንቶ የዘለቀም ነው። ሁለቱ ሀገራት በአፍሪካ ውስጥ ብቸኛ ነፃ ሀገራት በመሆናቸው፣ በዓለም አቀፍ መድረኮች (ለምሳሌ በሊግ ኦፍ ኔሽንስ) የአፍሪካውያን ድምፅ ሆነው በጋራ ይቆሙም ነበር። የሀገራቱ የወዳጅነት እና የትብብር ስምምነትም እ.አ.አ በ1950ዎቹ መጨረሻ ላይ የጀመረ ሲሆን፣ በመካከላቸው ያለው ዘላቂ ወዳጅነት እና በዓለም አቀፍ መድረኮች (እንደ ተባበሩት መንግሥታት ድርጅት) በጋራ ለመቆም ቃል የተገባበት ሰነድም ተደርጎ ይወሰዳል። የዘመናዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መሠረት የጣሉትም ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ እና ፕሬዝዳንት ዊሊያም ቱብማን ናቸው። እ.ኤ.አ. በ1954 ፕሬዝዳንት ቱብማን ወደ አዲስ አበባ ያደረጉት ጉብኝት በሁለቱ ሀገራት መካከል ይፋዊ ግንኙነት እንዲጀመር በር ከፍቷል። ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ እ.አ.አ. 1958 ጉብኝት ወደ ሞንሮቪያ በማድረግ፣ በምዕራብ አፍሪካ የሚገኙ የነፃነት ንቅናቄዎችን በጋራ ለመደገፍ ተወያይተዋል። እነዚህ ጉብኝቶች የሁለትዮሽ ብቻ ሳይሆኑ አህጉራዊ ፋይዳም ነበራቸው። እ.አ.አ በ1963 የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (OAU) ሲመሰረት፣ ሁለቱ ሀገራት "የሞንሮቪያ" እና "የካዛብላንካ" ቡድኖችን ልዩነት በውይይት በመፍታት ለአህጉሪቱ አንድነት የጀርባ አጥንት መሆናቸውን አስመስክረዋል። በ1960ዎቹ መጀመሪያ ላይ በ”ሞንሮቪያ ቡድን” እና "የካዛብላንካ ቡድን" መካከል የነበረውን ልዩነት ለማጥበብ ኢትዮጵያ እና ላይቤሪያ በጋራ በመስራታቸው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ሊመሰረት ችሏል። የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት በችግር ውስጥ የተፈተነ ወዳጅነት ነው የሚል ሀሳብ በብዙዎች ይነሳል። የዚህም ምክንያት ኢትዮጵያ በላይቤሪያ የነበራት የሰላም ማስከበር ሚና ነው። ላይቤሪያ ለ14 ዓመታት በዘለቀው አውዳሚ የእርስ በርስ ጦርነት ምክንያት መንግሥታዊ መዋቅሯ ፈርሶ ነበር። እ.ኤ.አ. በ2003 የተፈረመውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (UN) ሰላም እንዲያስከብሩ ከጠራቸው አገራት መካከል ኢትዮጵያ ቀዳሚዋ ነበረች። ኢትዮጵያ በላይቤሪያ በርካታ ሰራዊቷን በማሰማራት ለሀገሪቷ ሰላም ዋጋ ከፍላለች። ሰራዊቱ አማፂያንን ትጥቅ በማስፈታት፣ ተዋጊዎች ከማህበረሰብ ጋር እንዲቀላቀሉ በማድረግ እና የቀድሞ ታጣቂዎች ወደ ሰላማዊ ህይወት እንዲመለሱ ከፍተኛ ስራ ሰርቷል። ዋና ከተማዋ ሞንሮቪያ እና በገጠራማ አካባቢዎች የተኩስ አቁም ስምምነቱ እንዳይጣስ ጥብቅ ቁጥጥር አድርጓል። የኢትዮጵያ ሰራዊት የጤና ቡድን በየሰፈሩ በመዘዋወር ለላይቤሪያውያን ነፃ የህክምና እርዳታ እና መድሃኒትም ይሰጥ ነበር። ሰራዊቱ የራሱን ስንቅ ለተቸሩ ዜጎች በማካፈል ወንድማማችነትን በተግባር አሳይቷል። እ.ኤ.አ በ2014 የኢቦላ ወረርሽኝ በላይቤሪያ በከፋ ሁኔታ በተከሰተበት ወቅትም፣ ሌሎች ሀገራት ሰራዊታቸውን ሲያስወጡ ኢትዮጵያ ግን የህክምና ቡድኖችን እና ሰራዊቷን በማቆየት ከላይቤሪያ ህዝብ ጎን ቆማች። ኢትዮጵያ በላይቤሪያ ሶስት ተከታታይ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ምርጫዎች እንዲካሄዱ በሰላም ማስከበሩ ረገድ ከፍተኛ ሚና ተጫውታለች። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና የላይቤሪያ መንግሥት ለኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪዎች የላቀ አገልግሎት ሜዳሊያ እና የምስጋና የምስክር ወረቀት ሰጥተዋል። ኢትዮጵያ በላይቤሪያ የነበራት የሰላም ማስከበር ሚና ከወታደራዊ ተልዕኮ ባለፈ የደም እና የአጥንት መስዋዕትነት ከፍላለች። ይህ የሰራዊቱ ተሳትፎ ዛሬም ድረስ በሁለቱ ሀገራት ህዝቦች መካከል ላለው ጥብቅ ወዳጅነት ዋነኛው ምክንያት ተደርጎ ይወሳል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሀገራቱ መካከል የሚደረጉ የጉብኝት ልውውጦች እና ውይይቶች ለሁለትዮሽ ትብብሩ መጠናከር አስተዋጽኦ አድርገዋል። የቀድሞዋ የላይቤሪያ ፕሬዝዳንት ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ እ.አ.አ በ2006 ስልጣን በያዙ ማግስት አዲስ አበባን ጎብኝተዋል። ይህም ኢትዮጵያ በላይቤሪያ ሰላም ለማስፈን ላደረገችው ድጋፍ እውቅና የሰጡበት ነበር። ሰርሊፍ በላይቤሪያ የተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ ሲያበቃ እ.አ.አ ጁላይ 2015 ኢትዮጵያን በመጎብኘት ለተደረገላቸው የህክምና ቡድን ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል። የቀድሞዋ ፕሬዝዳንት እ.አ.አ በ2017 ለሶስት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳላኝ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል። ፕሬዝዳንቷ በወቅቱ የሃዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክን የጎበኙ ሲሆን ላይቤሪያ ከኢትዮጵያ የጨርቃ ጨርቅ ልማት ዘርፍ ልምድ መቅሰም እንደምትፈልግ በወቅቱ ገልጸው ነበር። የላይቤሪያ የእግር ኳስ ኮከብ እና የቀድሞው ፕሬዝዳንት ጆርጅ ዊሃ እ.አ.አ በ2018 ስልጣን ከያዙ በኋላ በአዲስ አበባ በተካሄደው 30ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የተሳተፉ ሲሆን ከጉባኤው ጎን ለጎን ከወቅቱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር ተገናኝተው በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ላይ ተወያይተዋል። የቀድሞው የላይቤሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲ-ማክስዌል ሳህ ከማያህ እ.አ.አ በ2022 በአዲስ አበባ ጉብኝት በማድረግ በሁለቱ ሀገራት መካከል የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን (Joint Ministerial Commission) እንዲቋቋም ስምምነት ተፈራርመዋል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በላይቤሪያ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ (UNMIL) ላይ በነበረበት ወቅት፣ የተለያዩ የመከላከያ ሚኒስትሮች እና የጦር አዛዦች የኢትዮጵያን ሰላም አስከባሪ ኃይል ለመጎብኘት እና ከላይቤሪያ ባለስልጣናት ጋር ለመወያየት በተደጋጋሚ ወደ ሞንሮቪያ ተጉዘዋል። ኢትዮጵያ እና ላይቤሪያ በተለያዩ ጊዜያት ባደረጓቸው ውይይቶች በተለያዩ ዘርፎች በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነቶችም ተፈራርመዋል። ሰላም ፣ ደህንነት፣ ጤና፣ የአየር አገልግሎት፣ የቪዛ ነፃ መብት ፣ የንግድ ትብብር ማዕቀፍ፣ ግብርና፣ ትምህርት፣ ባህል እና ስፖርት ስምምነት ከተደረገባቸው ዘርፎች መካከል ይጠቀሳሉ። የአየር አገልግሎት ስምምነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሞንሮቪያ ያለምንም ገደብ እንዲበር እና ላይቤሪያን ከቀሪው ዓለም ጋር ማገናኘት የሚያስችል ህጋዊ ማዕቀፍ ነው። የሰላም ማስከበር ስምምነቱ በተባበሩት መንግሥታት ማዕቀፍ ውስጥ የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል እንድትልክ የተደረገው ስምምነት በላይቤሪያ መረጋጋት እንዲመጣ ትልቅ ድርሻ ነበረው። በኪነ-ጥበብ እና በስፖርት ዘርፍ (በተለይም በእግር ኳስ) የሁለቱ ሀገራት ወጣቶች ልምድ እንዲለዋወጡ የሚያስችሉ የመግባቢያ ሰነዶች ተፈርመዋል። የወቅቱ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ቦአከይ እ.አ.አ 2023 ፕሬዝዳንት ሆነው በተመረጡበት ወቅት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የቆየ ግንኙነት ለማደስ እና በንግድ ዘርፍ በጋራ ለመስራት ፍላጎታቸውን ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በየካቲት ወር 2018 ዓ.ም ከተካሄደው 39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ከላይቤሪያ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ቦአካይ ጋር ውይይት አድርገዋል። የሁለትዮሽ ውይይቱ በቴክኖሎጂ፣ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እና ኢትዮጵያ ለመገንባት ባቀደችው የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዩኒቨርሲቲ ላይ ያተኮረ ነበር። በውይይቶቹ ላይ ኢትዮጵያ እና ላይቤሪያ በንግድ እና ኢንቨስትመንት ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ገልጸዋል። የላይቤሪያው ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ ለስራ ጉብኝት ትናንት ማምሻውን አዲስ አበባ ሲገቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክትም የላይቤሪያ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ የነገ ብሩህ ተስፋ እየተሰራባት ወደ ምትገኘው ምድረ ቀደምት ኢትዮጵያ እንኳን በሰላም መጡ ብለዋል። በፕሬዝዳንቱ ቆይታ እጅግ ፍሬያማ ውይይት እንደሚኖራቸውም ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። የፕሬዝዳንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ የስራ ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት ታሪካዊ ወዳጅነት የበለጠ እንደሚያጠናክርም ታምኖበታል። የኢትዮጵያ እና የላይቤሪያ መጻኢ ግንኙነት ከታሪካዊ ወዳጅነት ወደ ስትራቴጂካዊ የኢኮኖሚ አጋርነት የማሳደግ ፍላጎት በሁለቱም ወገን በኩል አለ። በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው የአቪዬሽን ትስስር፣ የቴክኖሎጂ ልውውጥ እና በአህጉራዊ የነፃ ንግድ ቀጠና (AfCFTA) ማዕቀፍ የሚደረግ ትብብር ለጋራ ብልጽግና መሰረት ይጥላል።
ልዩ ዘገባዎች
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 3911
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 2665
በዮሐንስ ደርበው በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 8455
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 6943
ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
መጣጥፍ
ፋሲካ -አብሮነት የሚደምቅበት የደስታ በዓል
Apr 12, 2026 527
በኢትዮጵያ የፋሲካ በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ድምቀት የሚከበር በዓል ነው። የትንሳኤ በዓል የሚከበረው ከ55 ቀናት የጾም ወቅት በኋላ ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች እነዚህን ቀናት ፈጣሪያቸውን በጾምና ጸሎት ከመለመን ባለፈ ከሥጋ፣ ከወተትና መሰል የእንስሳት ተዋጽኦ ምግቦች ታቅበው ነው የሚያሳልፉት። የትንሣኤ በዓል ከመድረሱ በፊት ያለው አንድ ሳምንት "ሰሞነ ሕማማት" በመባል ይታወቃል። የእምነቱ ተከታዮች በሰሞነ ሕማማት ኢየሱስ ክርስቶስ ያሳለፈውን መከራና ስቃይ በማሰብ በቤተ ክርስቲያን በስግደት፣ በጸሎትና በጾም በተለየ ሁኔታ ያሳልፋሉ። ምእመናን በእለተ አርብ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች መዳን ብሎ በቀራኒዮ አደባባይ የከፈለውን መከራ፣ ግርፋትና ስቅላት በማሰብ በስግደት፣ በጸሎትና በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርዓቶች ያሳልፋሉ። የትንሳኤ (የፋሲካ) በዓልም ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትል ድል አድርጎ መነሳቱን ተከትሎ የሚከበር ነው። ትንሳኤው ይቅርታ፣ ለሰው ለጆች መዳን የተከፈለ ፍቅርና መስዋዕትነት ጎልቶ የሚታይበት ነው። በመሆኑም ፋሲካ ሞትን ድል በመንሳት በትንሳኤ የምስራች የተበሰረበት ታላቅ በዓል ነው ማለት ይቻላል። ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን በትንሳኤ የለወጠበት ለሰው ልጅም ፍቅርን በቤዛነት ተክቶ ያሳየበት ዕለት ነው። ዕለቱ ትንሳኤ ብርሀን የታየበት በመሆኑ በትንሣኤ ዋዜማ ቅዳሜ ምሽት ምዕመናን ነጭ ልብስ ለብሰው ወደ ቤተ ክርስቲያን በመሄድ ሌሊቱን በጸሎትና በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርአቶች ያሳልፋሉ። የሌሊቱ ቅዳሴና ስርአተ ፀሎት ከተጠናቀቀ በኋላ ምዕመናን ወደ ቤታቸው ሲመለሱ ጾም ይፈታሉ። ከቅባት ምግቦች ለሁለት ወራት በመቆጠብ ያሳለፉበት ወቅት በመሆኑም በትንሳኤ ሌሊት ዶሮ በመብላት ጾማቸውን ይፈስካሉ። በበዓሉ ቀንም በነጭ የሀበሻ ልብስ ደምቀው ይታያሉ። በዓሉ ከሃይማኖታዊ ሥርአቱ ባለፈ የአብሮነት፣ የፍቅርንና የመተሳሰብ እሴት ያለው ነው። ዘመድ አዝማድ በመጠራራትና ከጎረቤት ጋር አብሮ በመብላትና በመጠጣት የሚያሳልፉት ነው። ቤት ያፈራውን በመቋደስ በዓሉን በአብሮነት በደስታ ያሳልፋሉ። የፋሲካ በዓል ማህበራዊ ትስስር የሚገለጥበትና አብሮነት የሚደምቅበት የደስታ በዓል ነው። በተለይ በፋሲካ በዓል ለዶሮ ወጥ ልዩ ትኩረት ይሰጣል። ፋሲካና ዶሮ ወጥ ጥብቅ የሆነ ባህላዊ ቁርኝት ያላቸው በመሆኑ አንዱ የበዓሉ ማድመቂያ ተደርጎ ይወሰዳል። ከዚህ በተጨማሪ የበሬ ቅርጫ፣ በግ፣ ፍየል፣ ዳቦና ጠላ እንደየ አቅም በማዘጋጀት ይከበራል። በአንዳንዶች ዘንድም ከገብስ ብቻ የሚዘጋጅ "ኬኔቶ" የተሰኘ (ከአልኮል ነፃ የሆነ መጠጥ) በማዘጋጀት በአማራጭነት ይቀርባል።
በኅብረትና ጽናት የሚቀረጽ ብርሃን፤ የኢትዮጵያ ትንሣኤ
Apr 12, 2026 1009
በኅብረትና ጽናት የሚቀረጽ ብርሃን፤ የኢትዮጵያ ትንሣኤ በቀበኔሳ ገቢሳ ትንሣኤ ለሰው ልጅ ተስፋን፣ ዘለዓለማዊ ሕይወትን እና ከኃጢአት ነፃ መውጣትን የሚያበስር ኃይማኖታዊ በዓል ነው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ በመነሳቱ የሰው ልጅ የዘለዓለም የሕይወት አክሊልን ተስፋ ያደረገበት፣ የእግዚአብሔር ፍቅር የተገለጠበት እንዲሁም የሰው ልጅ ከዘለዓለም ሞትና ከኃጢአት ባርነት ነፃ የወጣበት የድኅነት፣ የፍቅር፣ የጽናትና የተስፋ ብርሃን ብስራት ነው፡፡ የትንሣኤ በዓል ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ የመነሳቱ ታላቅ ምሥጢር የሚታሰብበት ብቻ አይደለም፤ ይልቁንስ የሰው ልጅ ከውርደት ወደ ክብር፣ ከኃጢያት ባርነት ወደ ድኅነት እንዲሁም ከጉስቁልና ወደ ብሩህ ተስፋ የተሸጋገረበት የድል አዋጅ ነው። በዕለቱም በሞት ላይ ሕይወት፣ በሐዘን ላይ ደስታ፣ በቂም ላይ ይቅርታ ተበስሮበታል። ከበዓላት ሁሉ የላቀ የነጻነት ተምሳሌት ነው ትንሣኤ። 👉የትንሣኤ ሕያው አስተምሮ በዕለት ተዕለት ሕይወት ትንሣኤ ሲከበር ከሥርዓተ አምልኮ ባለፈ፣ በዓሉ የሚሰጠውን ታላቅ አስተምሮ ማጤን ይገባል። ትንሣኤ በየቀኑ ካለንበት ድካምና ውድቀት በአዲስ መንፈስ የመነሳት አቅም ነው። በዓሉ የሚያስተምረንን የጽናት፣ የተስፋና የአብሮነት ዕሴት በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ መኖር ያስፈልጋል። ለዚህም የተቸገሩን መርዳት፣ የታመሙትን መጠየቅና የተጣሉትን ማስታረቅ የበዓሉን ትርጉም እውነተኛ ያደርገዋል። 👉የኢትዮጵያ ትንሣኤ፤ በፈተና የጸና ብርሃን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዓሉን በማስመልከት ባስተላለፉት መልዕክት፤ "የዘንድሮውን የትንሣኤ በዓል የምናከብረው ሀገራችን ኢትዮጵያ በፈታኝ የታሪክ ምዕራፍ ውስጥ ሆና እያለች ነው። መንገዳችን ረጅም፣ ጉዟችንም እሾህ የበዛበት ሊሆን ይችላል። ብርሃን እንዳናይ የሚጋርዱ፣ በጨለማ ወጥመድ ሊያሥሩን የሚሞክሩ መሰናክሎች ቢበዙም፣ እምነታችን ግን ከሕማማት በኋላ ትንሣኤ እንደሚመጣ ነው" ብለዋል፡፡ "ኢትዮጵያ ዛሬም ትንሳኤዋን እያየች ነው። መቃብሯ ተከፍቷል፤ ማኅተሙም ተሰብሯል። የትንሣኤውን ዜና ሊያደበዝዙ የሚሞክሩ የውሸት ወሬዎችና ተስፋ አስቆራጭ ትረካዎች የሀገራችንን የብርሃን ጉዞ ሊገቱት አይችሉም። ትንሳኤው እውነት ነው፤ ብርሃኑም የማይቀለበስ ሀቅ ሆኗል" ሲሉም አረጋግጠዋል፡፡ 👉ዴሞክራሲ እና ብሔራዊ ምክክር፤ የተስፋ ምዕራፎች የኢትዮጵያ ትንሣኤ አንዱ መገለጫ ዴሞክራሲን የመገንባት ጽናት ነው። ትንሣኤ ያለ ሕማማት እንደማይገኝ ሁሉ ዴሞክራሲ ያለ ፈተና በቀላሉ የሚታይ አይደለም። ዴሞክራሲ የሚገነባው በጽናት እንጂ በፍርሃት አይደለም። ዴሞክራሲን እየገነባን በትዕግሥትና በቆራጥነት ወደ ተስፋዋ ምድር እንደርሳለን። አሁን ያለው የዓለም ነባራዊ ሁኔታ ጦርነት፣ የኢኮኖሚ ቀውስና ማህበራዊ አለመረጋጋት የትንሳኤን ትምህርት ከመቼውም ጊዜ በላይ አስፈላጊ ያደርገዋል፡፡ ችግሮችን በብቸኝነት የምንወጣበት ጊዜ አብቅቷል። ዛሬ እንደህዝብ የሚያስፈልገን ከ"እኔ" ወደ "እኛ" መሸጋገር፣ የግል ፍላጎትን ለጋራ ስኬት መስዋዕት ማድረግ ግድ የሚልበት ወቅት ላይ ነን። የአንድነት ጉዟችንን በማጠናከር ዓለም አቀፋዊና ሀገራዊ ጫናዎችን ለመቋቋም በጋራ መቆም ይገባናል። የተቸገሩትን በመርዳት፣ የታመሙትን በመጠየቅና የተጣሉትን በማስታረቅ የተግባር አብሮነትን በማሳየት የበዓሉን እውነተኛ ትርጉም መግለጥ ይገባል፡፡ 👉ምርጫ፤ ከኢትዮጵያን ትንሣኤ ማብሰሪያዎች አንዱ ምዕራፍ ትንሣኤ ሞት ድል የተነሳበትና ተስፋ የታደሰበት ዕለት ነው። እኛም በምርጫ ካርዳችን የሃሳብ ልዩነትን በዴሞክራሲያዊ አንድነት ድል በማድረግ የኢትዮጵያን የብልፅግና ትንሳኤ እናረጋግጣለን። በትንሣኤ በዓል የምንማረው ይቅርታና ጽናትም ለምርጫችን ስኬት አቅም ይሆናል። በኅብረት የምንሰጠው ድምፅም የነገዋን ብሩህ ኢትዮጵያ የመቅረጽ ኃይል በእጃችን መሆኑን ያሳያል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመልዕክታቸው "ምርጫ የኢትዮጵያን ትንሣኤ ማብሰሪያዎች አንዱ ምዕራፍ ነው። ትንሣኤን ያለ ሕማማት እንደማናስበው ሁሉ ዴሞክራሲንም ከውጣ ውረድ ነጥሎ ማየት አይቻልም። በዓለም ላይ በደልዳላ መንገድ ተጉዞ ዴሞክራሲን የገነባ ሀገር የለም። ዴሞክራሲና ብልፅግና ያለ ጽናት አይሳኩም። ከእኛ በፊት ዐመጻውን በትዕግሥት የመከቱ ተሻግረዋል፤ ሑካታውን በጽናት ያለፉ አሳክተዋል። ብንመኝም ፈተናውን አናስቀርም፤ መጽናት ግን እንችላለን። ከድኅነት መውጫው ብርታታችን፣ ወደ ዴሞክራሲ መድረሻችው ትዕግሥታችን እንደሆነ አምነን ለኢትዮጵያ ትንሣኤ በሙሉ ልባችን እንትጋ!!" ብለዋል። 👉የወደፊት እጣ ፈንታችን በእጃችን ከፊታችን የሚጠብቁን ሀገራዊ ምክክርና የ2018 ዓ.ም ጠቅላላ ምርጫ የኢትዮጵያን የወደፊት መጻኢ ዕድል የሚወስኑ ታላላቅ ሁነቶች ናቸው። እነዚህ ሂደቶች ስኬታማ የሚሆኑት እያንዳንዱ ዜጋ የድርሻውን ሲወጣ ብቻ ነው። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር በልባችን ውስጥ ይቅርታና አብሮነት ሲነግስ ብቻ ግቡን ይመታል። ትንሣኤ ሞት ድል የተነሳበት እንደሆነው ሁሉ፣ በምክክሩም ጥልን፣ ጥርጣሬን፣ ያለመግባባት መንፈስን ድል መንሳት ይገባል፤ ቅንነት፣ ተስፋና መተሳሰብ ለምክክሩ ስኬት የመተማመኛ ቁልፎች ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ 2018 ዓ.ም ደግሞ የዜጎች ዴሞክራሲያዊ ተሳትፎ ማሳያ አንጓ ነው፤ የዜጎች ነፃ ተሳትፎ መብታቸውን የሚያስከብሩበት ፍላጎታቸውን የሚያረጋግጡበት ማረጋገጫ ማህተም ጭምር፡፡ ዜጎች የመምረጥና የመመረጥ መብታቸውን የሚያስከብሩበት፤ የሌላውን ሃሳብ አክብረው የራሳቸውን የሚያስከብሩበት ለኢትዮጵያ ትንሣኤ በጋራ የሚቆሙበት መድረክ ነው፡፡ ትንሣኤ የድልና የነጻነት በዓል ነው። ይህንን ታላቅ ዕለት ስናከብር ያለፈውን ቁስል ሽረን፣ ለነገ ተስፋ ሰንቀን መሆን አለበት። እርስ በእርስ በመደጋገፍ፣ ችግሮችን በንግግር በመፍታት ለሀገራዊ ምክክር ሂደቱ ስኬታማነት የድርሻችንን መወጣት ይገባናል። የተሻለችና የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመገንባት በጋራ እንቁም! መልካም የትንሳኤ በዓል!!