ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
ቻይና ለብልጽግና ፓርቲ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፈች
Jun 25, 2026 496
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 18/2018 (ኢዜአ):- ቻይና በ7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ ላሸነፈው እና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሚመራው የብልጽግና ፓርቲ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፋለች። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ የመጨረሻ ውጤት በቅርቡ ይፋ ማድረጉ የሚታወስ ነው። በዚህም መሠረት የብልጽግና ፓርቲ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 501 መቀመጫዎች መካከል 438ቱን አገኝቷል። የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጉዎ ጂያኩን በዕለታዊ ጋዜጣዊ መግለጫቸው ላይ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፤ ቻይና የኢትዮጵያ ታማኝና በሁኔታዎች የማይለዋወጥ ስትራቴጂክ አጋር (all-weather strategic partnership) መሆኗን ገልጸዋል። ቻይና ኢትዮጵያ የራሷን ተጨባጭ ብሔራዊ ሁኔታ ያገናዘበ የልማት ጎዳና እንድትከተል የምታደርገውን ድጋፍ እንደምትቀጥልና በቀጣይም የላቀ ሀገራዊ ዕድገት እንደምታስመዘግብ ያላትን ጽኑ እምነት ገልጸዋል። ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር ላላት ግንኙነት ትልቅ ቦታ እንደምትሰጥ የጠቆሙት ቃል አቀባዩ፤ የሁለቱ ሀገራት መሪዎች የደረሱባቸውን ታሪካዊ ስምምነቶች እንዲሁም በቤጂንግ በተካሄደው የቻይና-አፍሪካ ትብብር ፎረም (FOCAC) ጉባኤ ላይ የተላለፉ ውሳኔዎችን ተግባራዊ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል። በተጨማሪም በሁሉም ዘርፎች ያለውን ትብብር ይበልጥ በማጠናከር ለሁለቱም ሀገራት ሕዝቦች የላቀ ጥቅም ለማስገኘት እንዲሁም በቻይና-አፍሪካ እና በደቡብ ንፍቀ ክበብ (Global South) ሀገራት መካከል ያለውን አንድነትና ትብብር ይበልጥ ለማሳደግ ቻይና አበክራ እንደምትሠራ ቃል አቀባዩ መናገራቸውን የዥንዋ የዜና ወኪል ዘገባ ያመለክታል።
የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የዜጎችን መብት በማስከበር አስተዳደራዊ በደልን ለመከላከል የጀመረውን ሥራ ማጠናከር አለበት
Jun 25, 2026 266
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 18/2018 (ኢዜአ):-የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የዜጎችን መብት በማስከበር አስተዳደራዊ በደልን ለመከላከል የጀመራቸውን ተግባራት ማጠናከር እንዳለበት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳሰበ። ምክር ቤቱ ባካሄደው 28ኛ መደበኛ ስብሰባ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋምን የ2018 በጀት ዓመት የ11 ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን ገምግሟል። በዚሁ ወቅት ዋና እምባ ጠባቂ ስመኝ ውቤ በአፈፃጸም ሪፖርታቸው፤ የፍትሕ መጓደልንና የመልካም አስተዳደር ጉድለቶችን ቀድሞ በመከላከል የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን አስረድተዋል። የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በቀረበው ሪፖርት ላይ፤ በቅሬታ አፈታት፣ መልካም አስተዳደር ጉድለት ቅድመ መከላከል ተግባራት ተጠናክረው በሚቀጥሉበት ዙሪያ ጥያቄ አንስተዋል። ዋና እምባ ጠባቂ ስመኝ ለተነሱት ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽና ማብራርያ፤ በተቋማት ላይ ምርመራ በማድረግ የዜጎችን የአስተዳደር በደል የሚያስቀር አቅም እየተገነባ መሆኑን አስረድተዋል። በበጀት ዓመቱ 108 የመንግሥት ተቋማት ክትትልና ቁጥጥር ለማድረግ ታቅዶ በ201 መስሪያ ቤቶች ላይ ተፈፃሚ ማድረግ መቻሉን አስታውቀዋል። የዲጂታል አሰራሮችና በ9503 የአቤቱታ መቀበያ ነፃ መስመር መረጃ በመሰብሰብ የሕግ የበላይነትን ማረጋገጥ የሚያስችል የአሰራር ሥርዓት መፈጠሩን አብራርተዋል። በቀጣይም ምክር ቤቱ የሰጣቸውን ምክረ ሃሳቦች በግብዓትነት በመጠቀም የተሻለ አቅም ለመገንባት በትኩረት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ እውነቴ አለነ፤ በተቋማት ላይ የሚደረግን ክትትልና ቁጥጥር በማጠናከር አስተዳደራዊ በደሎችን ለመከላከል የተጀመሩ ሥራዎች መጠናከር እንዳለባቸው አሳስበዋል። ዓለም አቀፍ ልምዶችና ተሞክሮዎችን በመቀመር ጭምር የዲጂታል መረጃ መሰብሰቢያ አሰራሮችን በማጎልበት በዜጎች ላይ ሊደርሱ የሚችሉ በደሎችን ቀድሞ መከላከል እንደሚገባ አመልክተዋል። በሕፃናት፣ ሴቶች፣ አረጋዊያንና አካል ጉዳተኞች ላይ ሊደርሱ የሚችሉ አስተዳደራዊ በደሎችን ቀድሞ በመከላከል የተከናወኑ ተግባራትም የሚደነቁ መሆናቸውን አንስተዋል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 28ኛ መደበኛ ስብሰባው የመረጃ ነፃነት አዋጅን እና የፌዴራል ሸሪዓ ፍርድ ቤቶች ረቂቅ አዋጅን የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ አፅድቋል።
ብቁ ትውልድ ለማፍራት የተጀመረው የዘመናዊ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ግንባታ ይጠናከራል
Jun 25, 2026 263
ድሬዳዋ፤ሰኔ 18/2018 (ኢዜአ):-የነገዋን ኢትዮጵያ በአንድነት የሚገነባ ብቁ ትውልድ ለማፍራት የተጀመረው የዘመናዊ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ግንባታ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ። በድሬዳዋ በ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በጀት ለሚገነባው ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዛሬ የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል።በጠቅላላው10 ሄክታር መሬት ላይ ለሚገነባው የአዳሪ ትምህርት ቤት የመሰረት ድንጋይ በማስቀመጥ ግንባታውን ያስጀመሩት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የድሬዳዋ ከንቲባ ከድር ጁሃር ናቸው። ትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በወቅቱ እንደገለጹት፤ ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በሁሉም ክልሎች አንድ አንድ ለመገንባት ታቅዶ ወደሥራ ተገብቷል። በትምህርት ቤቶችም ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የሚማሩባቸው መሆኑንም ተናግረዋል። የትምህርት ቤቶቹ ግንባታ ሥራ አምና በአምስት ክልሎች መጀመሩን አስታውሰው ዘንድሮ ድሬዳዋን ጨምሮ በአራት የክልል ከተሞች የግንባታ ሥራ ይጀመራል ብለዋል። እንደ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ገለፃ እየተገነቡ በሚገኙት ዘመናዊ ሁለተኛ ደረጃ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ሲጠናቀቁ ከመላው አገሪቱ የሚሰባሰቡ ውጤታማ ተማሪዎች የተለያዩ የክህሎትና የቀለም ትምህርት ይቀስሙባቸዋል። ከመደበኛ ትምህርታቸው ጎን ለጎን የዲጂታል፣ የግብርናና ሌሎች ሙያዊ ክህሎትን በተግባር ጭምር ተምረው የሚወጡበት ነው ብለዋል። ዛሬ በድሬዳዋ በ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በጀት ግንባታው የተጀመረው ትምህርት ቤት የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታው በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅም አመልክተዋል። አዳሪ ትምህርት ቤቶቹ የነገዋን ኢትዮጵያ በህብረ ብሔራዊ አንድነት የሚገነቡ ብቁና ታታሪ ወጣቶች የሚፈሩባቸው መሆኑንም ፕሮፌሰር ብርሀኑ ገልጸዋል። የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር በበኩላቸው፤ የትምህርት ሚኒስቴር ለመጀመሪያ ጊዜ በራሱ በጀት አዳሪ፣ ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ እና የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት መገንባት በመጀመሩ አመስግነዋል። እነዚህ ፕሮጀክቶች የትምህርት ፍትሃዊ ተደራሽነትና ጥራትን ከማሳደግ ባሻገር አስተዳደሩ ያለውን ውስን በጀት ሌሎች የህዝብ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመፍታት እንዲያውል ያስችለዋል ብለዋል። ዛሬ ግንባታው የተጀመረው አዳሪ ትምህርት ቤት በሚፈለገው ጊዜና ጥራት ተገንብቶ እንዲጠናቀቅ በአስተዳደሩ በኩል የቅርብ ክትትልና ድጋፍ እንደሚደረግ አረጋግጠዋል።
የኢትዮጵያና ዩናይትድ ኪንግደም ታሪካዊ ግንኙነት ወደላቀ ስትራቴጂክ አጋርነት እየተሸጋገረ ነው
Jun 25, 2026 313
አዲስ አበባ፤ሰኔ 18/2018 (ኢዜአ):-የኢትዮጵያና ዩናይትድ ኪንግደም ታሪካዊ ግንኙነት ወደላቀ ስትራቴጂክ የዲፕሎማሲ አጋርነት እየተሸጋገረ መሆኑን በዩናይትድ ኪንግደም የኢትዮጵያ አምባሳደር ብሩክ መኮንን ገለጹ። በኢትዮጵያ እና እንግሊዝ መካከል ያለው ሁሉን አቀፍ ትብብር ለማሳደግ የተዘጋጀው የኢትዮ-እንግሊዝ የንግድና ኢንቨስትመንት ፎረም 2026 በለንደን ከተማ ተካሂዷል። በዩናይትድ-ኪንግደም የኢትዮጵያ አምባሳደር ብሩክ መኮንን በዚሁ ጊዜ፤ ኢትዮጵያና እንግሊዝ በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ ዘመናትን የተሻገር ታሪካዊ ግንኙነት ያላቸው ወዳጅ ሀገራት ናቸው ብለዋል። የሀገራቱ መልካም ግንኙነትም የንግድና ኢንቨስትመንት የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ትብብርን በማሳደግ የህዝብ ለህዝብ ትስስርን ጭምር እያጠናከረ እንደሚገኝ አስረድተዋል። በአሁኑ ወቅትም የኢትዮጵያና ዩናይትድ ኪንግደም ታሪካዊ ግንኙነት ወደላቀ ስትራቴጂክ የዲፕሎማሲ አጋርነት እየተሸጋገረ መሆኑን ተናግረዋል። የሀገራቱ የንግድና ኢንቨስትመንት ፎረምም የኢኮኖሚክ ዲፕሎማሲ አጋርነትን ለማጎልበት ጉልህ ፋይዳ እንደሚኖረው ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ሀገር በቀል የብዝኅ ዘርፍ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሪፎርሙ ለሀገራቱ ሁለንተናዊ የዲፕሎማሲ ትብብር አስቻይ ሁኔታ መፍጠሩንም አንስተዋል። በቀጣይም የሀገራቱን ሁለንተናዊ የዲፕሎማሲ ትብብር የበለጠ በማጠናከር የጋራ ተጠቃሚነትን ለማሻሻል በቁርጠኝነት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል። በዩናይትድ ኪንግደም የኢትዮጵያ ኤምባሲም የሁለቱን ሀገራት የንግድ፣ የኢንቨስትመንትን፣ የዲፕሎማሲና የኢኮኖሚ ትብብር ወደ ላቀ ስትራቴጂክ አጋርነት ለማሸጋገር በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል። በፎረሙ ላይ የሀገራቱ የፖሊሲ አውጪ ሙያተኞች፣ ባለሃብቶችና የተለያዩ ተቋማት ጋር የሃሳብ ልውውጦች መደረጋቸው ተመላክቷል።
በምዕራብ ሸዋ ዞን የህዝቡን የልማት ጥያቄዎች የሚመልሱ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ለአገልግሎት በቁ
Jun 25, 2026 282
አምቦ፤ሰኔ 18/2018 (ኢዜአ):- በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን የህዝቡን የቆዩ የልማት ጥያቄዎች ለመፍታት የተገነቡ የተለያዩ የመሰረተ ልማት አውታሮች በሁለት ዙር ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት መሆናቸውን የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ። በዞኑ ኢሉ ገላን ወረዳ ተገንብተው ለአገልግሎት የበቁት ኮሪደር ልማት፣ የእንስሳት ጤና ኬላ፣ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት እና ሌሎች የመሰረተ ልማት ተቋማትም ይገኙበታል። በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የምዕራብ ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ዲዳ ጉደታ እንደገለጹት፤ በዞኑ በሕዝብና በመንግሥት ትብብር የተገነቡ የልማት ፕሮጀክቶች ለአገልግሎት እየበቁ ነው። በበጀት ዓመቱ በመጀመሪያው ዙር 391 የልማት ፕሮጀክቶች ተመርቀው አገልግሎት መጀመራቸውን የገለጹት አስተዳዳሪው፤ የሁለተኛው ዙር ምረቃ በኢሉ ገላን ወረዳ መጀመሩን ጠቁመዋል። ግንባታቸው ተጠናቆ ምርቃታቸው የተጀመረው የሁለተኛ ዙር ፕሮጀክቶች ቁጥር 128 መሆኑንም ገልጸዋል። የኢሉ ገላን ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አሚን ነሻ በበኩላቸው፤ በወረዳው በመንግሥት በጀትና በሕብረተሰቡ ተሳትፎ ከ106 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡ 18 የልማት ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት መሆናቸውን አስታውቀዋል። የተገነቡት መሰረተ ልማቶች የአካባቢውን ሕብረተሰብ ዘመናት ያስቆጠሩ ጥያቄዎች የሚፈቱ መሆናቸውን የገለጹት የወረዳው አስተዳዳሪ፤ ሕዝቡ ለፕሮጀክቶቹ አስፈላጊውን እንክብካቤ በማድረግ ለመጪው ትውልድ ማስተላለፍ እንዳለበት አሳስበዋል። ኢዜአ ያነጋገራቸው የኢሉ ገላን ወረዳ ነዋሪዎችም በአካባቢያቸው ለአገልግሎት የበቁ ፕሮጀክቶች የረጅም ጊዜ ጥያቄያቸውን ከመመለስ ባለፈ፣ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸውን እንደሚያሳድጉት ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። አቶ ሁንዱማ ታረሳ "በቀበሌያችን የተገነባው ዲጂታል ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት መጀመሩ የአካባቢው ተማሪዎች በቴክኖሎጂ ታግዘው ዕውቀት እንዲቀስሙና በሀገር አቀፍም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ትልቅ እገዛ ያደርጋል" ብለዋል። ወጣት ደራርቱ ወጋሪ በበኩሏ፤ ለአገልግሎት የበቁት መሰረተ ልማቶች የአካባቢውን ሕብረተሰብ ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ ከመሆናቸውም በላይ፣ ለወጣቶች ሰፊ የሥራ ዕድል የሚፈጥሩ በመሆናቸው ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ገልጻለች።
ፖለቲካ

ከተጽዕኖ ፈጣሪነትና ተደማጭነት መጎልበት እስከ የአኅጉር ድምጽ መሆን - የኢትዮጵያን ታላቅነት የገለጠው የዲፕሎማሲው ዘርፍ ስኬት
Jun 25, 2026 539
በዮሐንስ ደርበው ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲያዊ ጥረቷ የፓን አፍካኒዝም ንቅናቄን በማንሳት አኅጉራዊ ተቋማት እንዲመሠረቱ ፊታውራሪ ከመሆን ጀምሮ ለጎረቤቶቿ ሰላም ጉልኅ ሚና ተጫውታለች፤ አሁንም ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔን እያሰረጸች በርካቶች እንዲጋሯት አድርጋለች። እንደ ሀገር ከለውጡ መንግሥት ወዲህ ከተገኙ በርካታ ትላልቅ ስኬቶች መካከል በዲፕሎማሲው ዘርፍ የተመዘገበው አንዱ ነው። ትውልዱ ዛሬንም ነገንም በሚጠቅመው የአረንጓዴ ዐሻራ ኢኒሼቲቭ ንቁ ተሳታፊ መሆን ይጠበቅበታል እየተስፋፋ ያለው የጉበት ስብን (ቅባት) እንዴት መከላከል ይቻላል? ምክክር - ወደ መግባባት መሸጋገሪያው ድልድይ! የለውጡ መንግሥት የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ ዋነኛ መለኪያም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ነው። የኢትዮጵያ ሁኔታዎችን የማሰብ፣ የመፈለግና የመከወን ሂደት ንጥል (ለራስ ብቻ የሚል) ሳይሆን፤ በወንድማማችነት/እህትማማችነት ዕሳቤ በጋራ ማደግን ያነገበ ነው። ይህ ሂደቷም በበርካታ ሀገራት፣ ዓለም አቀፍ እንዲሁም አኅጉር አቀፍ ተቋማት ተወድሷል። በዚህም ሐሳቦቿ ቅቡል ሲሆኑ ተመልክተናል። ኢትዮጵያ የ#BRICS አባል መሆን መቻሏ አንዱ ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። ይህም ተሰሚነቷን ያረጋገጠ ማስረጃ ሲሆን፤ በኢኮኖሚ፣ በንግድ፣ ኢንቨስትመንትና ተያያዥ ጉዳዮች ዘርፈ-ብዙ ጥቅም በማስገኘት የበለጸገች ኢትየጵያን ዕውን የማድረግ ጉዞው ያፋጥናል። ወዲህ ደግሞ በተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት አባልና አፍሪካን በመወከል ምክትል ፕሬዚዳንት ሆና መመረጧም የአኅጉሪቱ ድምጽ መሆኗን ይነግረናል። ዓለም አቀፍ ብሎም አኅጉር አቀፍ የሆኑ በርካታ ኮንፈረንሶችም በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት እንዲካሄዱ መደረጉ አንድምታው ብዙ ነው። በብቃት ማስተናገዷ ደግሞ ሌላኛው ጥንካሬዋ። ሌላው የሀገራችንን የተጨበጠ የአረንጓዴ ዲፕሎማሲ ስኬት የሚገልጽልን፤ የዓለም የዓየር ንብረት ለውጥ ጉባዔን (COP32) እንድታዘጋጅ መመረጧ ነው። ይህን ትልቅ ዕድል በርካቶች ስለተመኙት አላገኙትም፤ ኢትዮጵያ ግን ዜጎቿን አስተባብራ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ቁርጠኛ አመራር ሰጭነት ባከናወነችው ያላሰለሰ ትጋት አግኝታዋለች። ግጭት ባለባቸው የቀጣናው ሀገራትም በመንግሥታቱ እንዲሁም በአፍሪካ ሕብረት ሥር ከምታበረክተው ከፍተኛ አስተዋጽዖ ባለፈ፤ በግሏ የሰራችው ብዙ ነው። ከራሷ አልፋ ለጎረቤቶቿ ዘብ መሆኗ፤ በአብሮነት መኖርን እና በጋራ ማደግን በተግባር የገለጠች ሀገርም ያደርጋታል። ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ በሚለው ቅድሚያ ለሀገር በቀል ዕውቀቶች በሩን ክፍት ባደረገው ትጋቷም፤ በበርካታ የአኅጉሪቱ ሀገራት ዘንድ ምሥጋና አስችሯታል። በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲዋም በተለያዩ ሀገራት በችግር ውስጥ የነበሩ ዜጎቿን ከሀገራቱ እና ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመነጋገር በተሳካ ሁኔታ ልጆቿን ወደ ዕቅፏ መልሳለች፤ በቅርቡ በሳዑዲ ዓረቢያ ለእስር ተዳርገው የነበሩ ኢትዮጵያውያን የፍርድ ሂደታቸው ተቋርጦ የምኅረት ዐዋጅ እንዲሰጣቸው መደረጉ አንድ ማሳያ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ፤ ኢትዮጵያ አፍሪካን ጨምሮ በተለያዩ አኅጉራት በሚገኙ ሀገራት መሪዎችና ተወካዮች ዘንድ በስፋት የተመረጠችና የተጎበኘች ሀገር መሆኗን ማስታወስ ተገቢ ነው። ከጉብኝት ባለፈ ትላልቅ ስምምነቶችም የተፈራረመች መሆኗን ልብ ማለት ይገባል፤ ይህም የምታነሳውን ሐሳብ ገዥነትና የአፍሪካ መግቢያ በር መሆኗን ያሳያል። በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ከአጀንዳ ተቀባይነት ወደ አጀንዳ ሰጭነት በመሸጋገር ብሔራዊ ጥቅምን በሚያስጠብቅ ከፍታ እየተጓዘ መሆኑን መረዳት ይገባል። ኢትዮጵያ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ድርድር ሂደት የተጎናጸፈችው የዲፕሎማሲ ስኬት ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት መነቃቃት መፍጠሩንም ማጤን ያስፈልጋል። ይህ የተሳካው ሀገሪቱ ኢትዮጵያ መንገዷም የጋራ ልማትን የሰነቀ ዕውነት በመሆኑ ነው። በቀጣይ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለአንዲት ሀገራቸው አምባሳደር በመሆን፤ የዲፕሎማሲውን ሥራ በይበልጥ ማገዝ ይጠበቅባቸዋል። ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው ካልሠሩ ማን ለሀገራቸው ሊሠራ ይችላል?
ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በምክር ቤቱ ያገኙት መቀመጫ ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ መጠናከር ዕድል ይሰጣል
Jun 25, 2026 556
አዲስ አበባ፤ሰኔ 18/2018 (ኢዜአ)፦በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በምክር ቤቱ ያገኙት መቀመጫ፣ ለሀገሪቱ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ መጠናከር ዕድል የሚሰጥ መሆኑን የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አባላት ገለጹ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በተካሄደባቸው የምርጫ ክልሎች የተገኘውን ውጤት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። በዚህም የብልፅግና ፓርቲ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና በክልል ምክር ቤቶች አብላጫውን መቀመጫ ማግኘቱንና በምክር ቤቶቹ ተፎካካሪ ፓርቲዎችም መቀመጫ ማግኘታቸውን አረጋግጧል፡፡ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) አባል አወቀ አምዛዬ (ዶ/ር)፤ ምክር ቤቱ የተለያዩ ድምጾች የሚሰሙበት ዕድል ማግኘቱን ገልጸዋል። ከሌላው ጊዜ ይበልጥ የሕብረተሰብ ድምፅ የሚሰማበትና ለኢትዮጵያ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ መጠናከር በር የሚከፍት መሆኑንም ተናግረዋል። ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ከመቼውም ጊዜ በላይ የህብረተሰቡ ንቁ ተሳትፎ የታየበትና ከ54 ሚሊዮን በላይ መራጭ የተመዘገበበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የብልጽግና ፓርቲ አባል ኢንጅነሪ ስለሺ ኮሬ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ፍትሐዊና ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን የሚያስችል ዝግጅት አስቀድሞ መደረጉን ተናግረዋል፡፡ መንግሥት የፖለቲካ ምኅዳሩን ማስፋቱን ተከትሎ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሚዛናዊነት ላይ የተመሠረተ ፉክክርና ትብብር እንዲያደርጉ ያስቻለ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ይህም ዲሞክራሲን ለማጎልበት እና ሀገርን በጋራ ለመገንባት ያለውን ተነሳሽነትና ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በቀጣይም ከመረጣቸው ሕዝብና ከፓርቲያቸው ጋር በመሆን የተሰጣቸውን ኃላፊነት በተገቢው ለመወጣት መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል፡፡ አዲስ የሚመሠረተው መንግሥት የሕዝቡን ሰላም ማረጋገጥ፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት እና ከፍተኛ የኢኮኖሚ ዕድገትን የሚያመነጩ ፖሊሲዎችን ገቢራዊ ማድረግ ላይ በትኩረት መሥራት እንዳለበትም አስገንዝበዋል፡፡
የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የሚፃረሩ ኃይሎችን ስጋት የሚቀለብስ ዘመኑን የዋጀ አስተማማኝ የመከላከያ ሰራዊት ተገንብቷል
Jun 25, 2026 505
አዲስ አበባ፤ሰኔ 18/2018 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የሚፃረሩ ኃይሎችን ስጋት የሚቀለብስ ዘመኑን የዋጀ አስተማማኝ የመከላከያ ሰራዊት መገንባቱን የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ወታደራዊ አማካሪና የተኩስ አመራር ኃላፊ ጀነራል አለምእሸት ደግፌ አስገነዘቡ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ኮሌጅ "የኢትዮጵያ የብሔራዊ ደህንነት ተግዳሮቶችና የመፍትሔ አቅጣጫዎች" በሚል መሪ ሀሳብ ዓመታዊ የምክክር ጉባዔ እያካሄደ ይገኛል። ጀነራል አለምሸት ደግፌ በዚህ ወቅት እንደገለጹት፤ኢትዮጵያ በሁሉም መስክ ዕድገትን በሚያፋጥን ትክክለኛ የልማት አቅጣጫ ላይ ትገኛለች። የሀገሪቱን ዕድገት ለማደናቀፍ የሚሹ ጽንፈኛና ሽብርተኛ ኃይሎች የሚያደርጉት ከንቱ ሙከራም በጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊትና ሰላም ወዳዱ ህዝብ እየመከነ መሆኑን ገልጸዋል። ጽንፈኝነትና አክራሪነት የሀገር ልማትና አንድነት ጸር መሆኑን የጠቀሱት ጀነራል አለምእሸት፤ የጥፋት እንጂ የዓላማ አንድነት የሌላቸው ኃይሎች የኢትዮጵያ ዳግም ስጋት እንዲሆኑ ዕድል ሊሰጣቸው አይገባም ብለዋል። በዚህም የኢትዮጵያን ሰላምና ሉዓላዊ ክብር በማፅናት ዕድገቷን ማፋጠን የሁሉም ዜጋ ታሪካዊ ኃላፊነት መሆኑን አስገንዝበዋል። ዓለማችን ከነጠላ ልዕለ-ኃያል ወደ ብዙ ዋልታ የሽግግር ሂደት ላይ እንደምትገኝ የገለጹት ጀነራል አለምእሸት፤ ሂደቱ በርካታ ውስብስብና አስቸጋሪ የፀጥታና የደህንነት ሁኔታዎችን ማስከተሉን አብራርተዋል። አሁናዊው ቀጣናዊ ሁኔታ ዕድልም ስጋትም ይዞ የመጣ መሆኑን አመልክተው፤ እንደ ሀገር ዕድሉን ለመጠቀምና ስጋት ሆነው ለሚመጡ ችግሮች ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት ዘመኑን የዋጀ ጠንካራ መከላከያ ሰራዊት መገንባቱን ገልጸዋል። ምስራቅ አፍሪካ የኃይል አሰላለፍና የመካከለኛ ኃይሎች ተፅዕኖ የሚታይበት ቀጣና መሆኑን ጠቅሰው፤ሁኔታዎችን ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ጋር በማስታረቅ በሳል ስትራቴጂን መከተል እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል። በኢትዮጵያውያን የተባበረ ክንድ ተሰባብረው የነበሩ የሀገር ጠላቶች፣ ዛሬም ከብሔራዊ ጥቅሟ በተቃራኒ የቆሙ ኃይሎችን በማሰባሰብ ለዳግም የጥፋት ተልዕኮ እየተዘጋጁ መሆኑንም ጠቁመዋል። የመከላከያ ሰራዊትም በሙሉ ወታደራዊ ዝግጁነት የተለመደውን የጀግንነት ገድል ለመፈፀም በቂ አቅም እንዳለውም አረጋግጠዋል። የመከላከያ ትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ ሃላፊ ጀነራል ይመር መኮንን በበኩላቸው፤ በወቅታዊና ተለዋዋጭ በሆነው የዓለም ሁኔታ ውስጥ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ማስከበር ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ደህንነት ከአፍሪካ ቀንድ የጋራ ሰላም፣ ተጠቃሚነትና ደህንነት ጋር በእጅጉ የተቆራኘ ነው ያሉት ጀነራል ይመር፤ የኢትዮጵያን ሉዓላዊ አንድነት በማስቀጠል ብሔራዊ ጥቅምን ለማረጋገጥ በትብብር መስራት ወቅቱ የሚጠይቀው መሰረታዊ አጀንዳ መሆኑን አስረድተዋል። በጉባዔው ላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ቀነአ ያደታ (ዶ/ር)፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዲማ ኖጎ (ዶ/ር)፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ዘሪሁን አበበና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በኢትዮጵያ የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ባህል ወደ አዲስ ምዕራፍ እየተሸጋገረ ነው - አቶ መለሰ ዓለሙ
Jun 25, 2026 477
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 18/2018 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳሩን በማስፋት የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ባህል ወደ አዲስ ምዕራፍ እንዲሸጋገር እየተደረገ መሆኑን በብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ መለሰ ዓለሙ ገለጹ። ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በተካሄደው ጠቅላላ ምርጫ 42 ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችና በርካታ ሚሊዮን ዜጎች በድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ የተሳተፉበት ታሪካዊ ምርጫ ሆኖ ተጠናቋል። የአፍሪካ ህብረት፣ የኢጋድ፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና በርካታ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችም የምርጫውን ሂደት ነጻ፣ ፍትሐዊነትና ገለልተኝነት እማኝነታቸውን በመስጠት አረጋግጠዋል። በምርጫው ዕለትም ዜጎች ከማለዳው 10 ሰዓት እስከ እኩለ ሌሊት ድርስ በመሰለፍ ጭምር ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ያላቸውን ቁርጠኝነት አስመስክረዋል። በብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ መለሰ ዓለሙ ለኢዜአ እንዳሉት፤ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የፓርቲዎችና የፖሊሲ ብቻ ሳይሆን የሥርዓት ምርጫ ጭምር ነው። የዴሞክራሲ ተቋማትና ሉዓላዊ የሥልጣን ባለቤት የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ነፃና ገለልተኛነታቸውን በተግባር ያረጋገጡበት ምርጫ መሆኑን ገልጸዋል። ኢትዮጵያውያን እውነተኛ ዴሞክራሲ መሻታቸውን ለወዳጅም ለጠላትም ያሳዩበት መሆኑን ገልጸው፤ ከቅድመ ምርጫ እስከ ድህረ ምርጫ የተዋንያን ቅንጅት መንጸባረቁንም አድንቀዋል። ምርጫው ከፖለቲካ ፓርቲዎች ውድድር ባለፈ ብሔራዊ ክብርና ሉዓላዊነት የተንጸባረቀበት በመሆኑ ኢትዮጵያ አሸንፋለች ብለዋል። ከለውጡ ማግስት የተደረገው መጠነ ሰፊ የፖለቲካ ሪፎርም የፓርቲዎችን እንግልትና ስደት በማስቀረት ጤናማ የፖለቲካ የፉክክር ምኅዳር መፈጠሩን ገልጸዋል። የሕግና ፖሊሲ ማሻሻያም በስድስተኛውና በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የፓርቲዎችን ተሳትፎ በማሳደግ አዲስ የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ እንዲወለድ ማድረጉን አስረድተዋል። ይህም የፖለቲካ ፓርቲዎች የሥልጣን ምንጭ ከህዝብ የሚሰጥ ድምፅ መሆኑን በመገንዘብ በዴሞክራሲ ባህል ግንባታ የሚጠበቅባቸውን ገንቢ ሚና የሚወጡበትን ዕድል መፍጠሩን አብራርተዋል። በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫም የፖለቲካ ፓርቲዎች የውስጥና የውጭ ጫናን በመቋቋም ጭምር ለዴሞክራሲ ባህል ግንባታ አሻራቸውን ላሳረፉ አካላት ምሥጋና አቅርበዋል። የለውጡ መንግሥት በሀገራዊ የጋራ ጥቅሞች ላይ ከፉክክር ይልቅ በትብብር ላይ የተመሰረተ የፖለቲካ ሥርዓት በመዘርጋት በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ተፎካካሪ ፓርቲዎች በብሔራዊ ጥቅም ላይ ወጥ የሆነ አቋም እንዲይዙ አድርጓቸዋል ብለዋል። ይሄ ትልቅ የዴሞክራሲ ትሩፋት መሆኑን በማንሳት፤ ልዩነቶች እንደተጠበቁ ሆነው በፓርቲዎች መካከል መተማመን በመፍጠር የኢትዮጵያን መዳከም የሚሹ ኃይሎችና ታሪካዊ ጠላቶችን ማሳፈሩን ገልጸዋል።
ፈረንሳይ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፈች
Jun 25, 2026 481
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 18/2018 (ኢዜአ)፦ ፈረንሳይ የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ በስኬት መጠናቀቁን በማስመልከት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፋለች። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ይፋዊ ውጤት ማስታወቁን ተከትሎ፣ ፈረንሳይ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክቷን አስተላልፋለች። ለኢትዮጵያ ባለሥልጣናትና ለምርጫው ሂደት መሳካት አስተዋጽኦ ላበረከቱ ባለድርሻ አካላትም ዕውቅና የሰጠች ሲሆን በምርጫው ሂደት ተሳትፎ ለነበራቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች እና ታዛቢዎች ምስጋና አቅርባለች። ፈረንሳይ ከምንም በላይ ምርጫው በስኬት እንዲካሄድ ከፍተኛ ሚና ለተወጣው የኢትዮጵያ ህዝብ እንኳን ደስ አላችሁ ስትል መልዕክቷን አስተላልፋለች።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተሻሻሉ ረቂቅ አዋጆች መርምሮ በሙሉ ድምፅ አጸደቀ
Jun 25, 2026 473
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 18/2018 (ኢዜአ):- የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመረጃ ነፃነት አዋጅ እና የፌዴራል ሸሪዓ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የማሻሻያ ረቂቅ አዋጆችን አጽድቋል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 28ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል። ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የ2018 በጀት ዓመት የ11 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፓርት አዳምጧል። እንዲሁም የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የመረጃ ነፃነት አዋጅን አስመልክቶ ያቀረበውን የሪፓርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አፅድቋል። የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እውነቴ አለነ በወቅቱ፤ ረቂቅ አዋጁ የዜጎችን መረጃ የመጠየቅና ማግኘት መብት የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል። አዋጁ አለም አቀፍ መብቶችን በመጠበቅ ፈጣን ቀልጣፋና ወቅቱ የጠበቀ መረጃ ፍሰት የሚያረጋግጥ መሆኑን ጠቅሰዋል። እንዲሁም የሀገራችንን ብሄራዊ ደህንነት በሚያረጋግጥ መልኩ የተዘጋጀ በመሆኑ ምክር ቤቱ እንዲያጸድቀው ጠይቀዋል። ይህን ተከትሎም አዋጅ ቁጥር 1427/2018 ሆኖ ተሻሽሎ በሙሉ ድምፅ ፀድቋል። በሌላ በኩል ምክር ቤቱ የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የፌዴራል ሸሪዓ ፍርድ ቤቶች ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አዋጁን አፅድቋል። የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እፀገነት መንግስቱ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ የማሻሻያ ረቂቅ አዋጁ የኢትዮጵያን የፍትህ ሥርዓት በማሻሻል ረገድ እጅግ የጎላ ፋይዳ ይኖረዋል። የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ የፌዴራል ሸሪዓ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ለማቋቋም፣ የፍርድ ቤቶችን የሥራ ተደራሽነት ይበልጥ ለማስፋት እንደሚረዳም ጠቁመዋል። በዚህም አዋጅ ቁጥር 1428/2018 ሆኖ ተሻሽሎ በሙሉ ድምፅ ጸድቋል።
በምርጫው ካሸነፈው ብልፅግና ፓርቲ ጋር በብሔራዊ ጥቅም እና በትልልቅ ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ በትብብር ለመሥራት ቁርጠኛ ነን -የፖለቲካ ፓርቲዎች
Jun 25, 2026 509
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 18/2018 (ኢዜአ):- በምርጫው ካሸነፈው ብልፅግና ፓርቲ ጋር በብሔራዊ ጥቅም እና በትልልቅ ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ በትብብር ለመሥራት ቁርጠኛ መሆናቸውን የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች አስታወቁ። ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የተካሄደው 7ኛው የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ የተሳተፈበትና በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎች የፉክክር መድረክ የሆነበት ታሪካዊ ክስተት ሆኖ ተመዝግቧል። በምርጫው ሂደት ላይ የህዝቡም ሆነ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ብስለትና አስተዋይነት በግልጽ የታየበት በመሆኑ፣ ሂደቱ ፍጹም ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ሊጠናቀቅ ችሏል። የምርጫውን ውጤት ተከትሎም ተፎካካሪ ፓርቲዎች ለአሸናፊው ብልፅግና ፓርቲ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት እያስተላለፉ የሚገኙ ሲሆን፣ በቀጣይም ለሀገር ልማትና አንድነት በጋራ ለመስራት ያላቸውን ዝግጁነት በመግለጽ ላይ ናቸው። የኢዜአ ያነጋገራቸው የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች እንዳስታወቁት፤ የምርጫ ሂደቱ ጠንካራ የህዝብ ተሳትፎ የታየበት መሆኑን ህዝቡ ለምርጫው ውጤታማነት ከቅድመ ምርጫ ጀምሮ ያሳየው ተሳትፎ እጅግ አስደናቂ ነበር፡፡ በምርጫ ወቅትም በነቂስ በመውጣት በሰለጠነ አግባብ በሰላማዊ ሁኔታ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የመንግስት ስልጣን መያዝ የሚገባ መሆኑን ትልቅ ትምህርት መስጠት መቻላቸውን አስታውቀዋል። ኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የሴቶች መምሪያ ሃላፊና የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የሴቶች ክንፍ ስራ አስፈጻሚ እመቤት ቢራራ እንዳሉት፤ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በርካታ የማህበረሰብ ክፍሎች በነቂስ ወጥተው የመረጡበት ታሪካዊ ሂደት ነው። ሴቶችም ከማለዳው ጀምሮ በከፍተኛ ተነሳሽነት በምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት መሳተፋቸውን ጠቁመው፤ ሴቶች በከፍተኛ ቁጥር በምርጫው መሳተፋቸውን አንስተዋል፡፡ የወሎ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ፕሬዚዳንት ነጻነት ጣሰው በበኩላቸው፤ በጠቅላላ ምርጫው የታየው ሰፊ የሕዝብ ተሳትፎ ለዴሞክራሲ ስርዓት መጠናከርና ለሀገረ መንግስት ግንባታ ፅኑ መሰረት የጣለ መሆኑን አስታውቀዋል። መንግስት አካታችነት ላይ በትኩረት በመስራቱ በርካታ አመርቂ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል፡፡ በተለይም ሴቶች፣ ወጣቶች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በሂደቱ ላይ በንቃት እንዲሳተፉ የተደረገው ጥረት ለምርጫው ስኬታማነትና ተአማኒነት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክቷል ብለዋል። በቀጣይ ፓርቲው ህዝባዊ አደራን ተቀብሎ መንግስት ለመሆን ከበቃው ብልፅግና ፓርቲ ጋር በልማት እና በተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ እንደሚሰራ አስታውቀዋል፡፡ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የሴቶች መምሪያ ሃላፊና የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የሴቶች ክንፍ ስራ አስፈጻሚ እመቤት ቢራራ ኢዜማ በብሔራዊ ጥቅም በሌሎች ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ከአሸናፊው ብልፅግና ፓርቲ ጋር በቅርበትና በትብብር ለመስራት ሙሉ ቁርጠኝነት እንዳላቸው ገልጸዋል። ኢትዮጵያ የሁላችንም ተወዳዳሪዎች የጋራ መኖሪያ በመሆኗ ለላቀ እድገቷ በጋራ መስራት ይገባናል ያሉት ደግሞ የወሎ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ፕሬዚዳንት ነጻነት ጣሰው ናቸው፡፡

ማህበራዊ
የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የዜጎችን መብት በማስከበር አስተዳደራዊ በደልን ለመከላከል የጀመረውን ሥራ ማጠናከር አለበት
Jun 25, 2026 266
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 18/2018 (ኢዜአ):-የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የዜጎችን መብት በማስከበር አስተዳደራዊ በደልን ለመከላከል የጀመራቸውን ተግባራት ማጠናከር እንዳለበት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳሰበ። ምክር ቤቱ ባካሄደው 28ኛ መደበኛ ስብሰባ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋምን የ2018 በጀት ዓመት የ11 ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን ገምግሟል። በዚሁ ወቅት ዋና እምባ ጠባቂ ስመኝ ውቤ በአፈፃጸም ሪፖርታቸው፤ የፍትሕ መጓደልንና የመልካም አስተዳደር ጉድለቶችን ቀድሞ በመከላከል የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን አስረድተዋል። የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በቀረበው ሪፖርት ላይ፤ በቅሬታ አፈታት፣ መልካም አስተዳደር ጉድለት ቅድመ መከላከል ተግባራት ተጠናክረው በሚቀጥሉበት ዙሪያ ጥያቄ አንስተዋል። ዋና እምባ ጠባቂ ስመኝ ለተነሱት ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽና ማብራርያ፤ በተቋማት ላይ ምርመራ በማድረግ የዜጎችን የአስተዳደር በደል የሚያስቀር አቅም እየተገነባ መሆኑን አስረድተዋል። በበጀት ዓመቱ 108 የመንግሥት ተቋማት ክትትልና ቁጥጥር ለማድረግ ታቅዶ በ201 መስሪያ ቤቶች ላይ ተፈፃሚ ማድረግ መቻሉን አስታውቀዋል። የዲጂታል አሰራሮችና በ9503 የአቤቱታ መቀበያ ነፃ መስመር መረጃ በመሰብሰብ የሕግ የበላይነትን ማረጋገጥ የሚያስችል የአሰራር ሥርዓት መፈጠሩን አብራርተዋል። በቀጣይም ምክር ቤቱ የሰጣቸውን ምክረ ሃሳቦች በግብዓትነት በመጠቀም የተሻለ አቅም ለመገንባት በትኩረት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ እውነቴ አለነ፤ በተቋማት ላይ የሚደረግን ክትትልና ቁጥጥር በማጠናከር አስተዳደራዊ በደሎችን ለመከላከል የተጀመሩ ሥራዎች መጠናከር እንዳለባቸው አሳስበዋል። ዓለም አቀፍ ልምዶችና ተሞክሮዎችን በመቀመር ጭምር የዲጂታል መረጃ መሰብሰቢያ አሰራሮችን በማጎልበት በዜጎች ላይ ሊደርሱ የሚችሉ በደሎችን ቀድሞ መከላከል እንደሚገባ አመልክተዋል። በሕፃናት፣ ሴቶች፣ አረጋዊያንና አካል ጉዳተኞች ላይ ሊደርሱ የሚችሉ አስተዳደራዊ በደሎችን ቀድሞ በመከላከል የተከናወኑ ተግባራትም የሚደነቁ መሆናቸውን አንስተዋል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 28ኛ መደበኛ ስብሰባው የመረጃ ነፃነት አዋጅን እና የፌዴራል ሸሪዓ ፍርድ ቤቶች ረቂቅ አዋጅን የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ አፅድቋል።
ብቁ ትውልድ ለማፍራት የተጀመረው የዘመናዊ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ግንባታ ይጠናከራል
Jun 25, 2026 263
ድሬዳዋ፤ሰኔ 18/2018 (ኢዜአ):-የነገዋን ኢትዮጵያ በአንድነት የሚገነባ ብቁ ትውልድ ለማፍራት የተጀመረው የዘመናዊ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ግንባታ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ። በድሬዳዋ በ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በጀት ለሚገነባው ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዛሬ የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል።በጠቅላላው10 ሄክታር መሬት ላይ ለሚገነባው የአዳሪ ትምህርት ቤት የመሰረት ድንጋይ በማስቀመጥ ግንባታውን ያስጀመሩት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የድሬዳዋ ከንቲባ ከድር ጁሃር ናቸው። ትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በወቅቱ እንደገለጹት፤ ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በሁሉም ክልሎች አንድ አንድ ለመገንባት ታቅዶ ወደሥራ ተገብቷል። በትምህርት ቤቶችም ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የሚማሩባቸው መሆኑንም ተናግረዋል። የትምህርት ቤቶቹ ግንባታ ሥራ አምና በአምስት ክልሎች መጀመሩን አስታውሰው ዘንድሮ ድሬዳዋን ጨምሮ በአራት የክልል ከተሞች የግንባታ ሥራ ይጀመራል ብለዋል። እንደ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ገለፃ እየተገነቡ በሚገኙት ዘመናዊ ሁለተኛ ደረጃ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ሲጠናቀቁ ከመላው አገሪቱ የሚሰባሰቡ ውጤታማ ተማሪዎች የተለያዩ የክህሎትና የቀለም ትምህርት ይቀስሙባቸዋል። ከመደበኛ ትምህርታቸው ጎን ለጎን የዲጂታል፣ የግብርናና ሌሎች ሙያዊ ክህሎትን በተግባር ጭምር ተምረው የሚወጡበት ነው ብለዋል። ዛሬ በድሬዳዋ በ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በጀት ግንባታው የተጀመረው ትምህርት ቤት የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታው በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅም አመልክተዋል። አዳሪ ትምህርት ቤቶቹ የነገዋን ኢትዮጵያ በህብረ ብሔራዊ አንድነት የሚገነቡ ብቁና ታታሪ ወጣቶች የሚፈሩባቸው መሆኑንም ፕሮፌሰር ብርሀኑ ገልጸዋል። የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር በበኩላቸው፤ የትምህርት ሚኒስቴር ለመጀመሪያ ጊዜ በራሱ በጀት አዳሪ፣ ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ እና የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት መገንባት በመጀመሩ አመስግነዋል። እነዚህ ፕሮጀክቶች የትምህርት ፍትሃዊ ተደራሽነትና ጥራትን ከማሳደግ ባሻገር አስተዳደሩ ያለውን ውስን በጀት ሌሎች የህዝብ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመፍታት እንዲያውል ያስችለዋል ብለዋል። ዛሬ ግንባታው የተጀመረው አዳሪ ትምህርት ቤት በሚፈለገው ጊዜና ጥራት ተገንብቶ እንዲጠናቀቅ በአስተዳደሩ በኩል የቅርብ ክትትልና ድጋፍ እንደሚደረግ አረጋግጠዋል።
የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የወል ትርክት በሚገነባ እና ወንድማማችነትን በሚያጠናክር መልኩ ተግባራዊ ይደረጋል
Jun 25, 2026 183
አዲስ አበባ፤ሰኔ 18/2018 (ኢዜአ)፦የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የወል ትርክትን በሚገነባ እና ወንድማማችነትን በሚያጠናክር መልኩ ተግባራዊ እንደሚደረግ የብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽሕፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትርና የፌዴራል ተቋማት አደረጃጀት አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ፍቃዱ ተሰማ ገለፁ። የብልፅግና ፓርቲ አባል የፌዴራል ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የሰባተኛው የጠቅላላ ምርጫ የማጠቃለያ ሪፖርት መድረክ በአዲስ አበባ አካሂዷል። በመድረኩ ላይ የፓርቲው ዋና ጽሕፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትርና የፌዴራል ተቋማት አደረጃጀት አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ፍቃዱ ተሰማ ማጠቃለያ እና ቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጠዋል። በማጠቃለያቸው ለቀጣይ ተልዕኮዎች ስኬት የአመራርና አባላትን ቁርጠኝነት ማጥራት እንዲሁም ተቋማዊ ኃላፊነቶችን መወጣት እንደሚገባ አሳስበዋል። ለቀጣዩ ከባድ ተልዕኮ ግልፅነትና ዝግጁነት ያለው የሰው ኃይል ይዞ መንቀሳቀስ እንደሚገባ ገልጸው፤ አመራሩ ለዚህ ዝግጁ መሆን አለበት ብለዋል። የፓርቲው ማኒፌስቶ በየሚኒስቴሩ ዕቅድ ውስጥ ተካቶ መተግበር እንዳለበት ተናግረው፤ የፌዴራል ተቋማት ፖሊሲና ስትራቴጂ የሚያመነጩ፣ በጀትን የሚመሩ አጀንዳ ፈጣሪዎች በመሆናቸው ትልቅ ኃላፊነት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። በየተቋማት ያሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ተለይተው መፈታት አለባቸው ሲሉ አስገንዝበዋል። የዘንድሮው የፌዴራል ተቋማት የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ዕቅድ ለየት ባለ መልኩ መዘጋጀቱን ተናግረዋል። በዚህም ትርክት ግንባታን፣ የወል ትርክትን፣ ወንድማማችነትን በሚያጠናክር መልኩ ተግባራዊ እንደሚደረግ በአፅዕኖት ተናግረዋል። ኢትዮጵያን በጋራ እንገንባ በሚል መሪ ሐሳብ ህዝብን ያሳተፈና ዘላቂ የሀገር ግንባታን የሚያረጋግጥ መጠነ-ሰፊ ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡ ይህንን ታላቅ ሀገራዊ ራዕይ ከዳር ለማድረስ አካታችነትን፣ ሚዛናዊነትን፣ የሀሳብና የባህል ልዩነቶችን ማክበርን እንዲሁም በዋና ዋና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ አቋም መያዝን ማዕከል ያደረጉ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን በስኬት ለማጠናቀቅ በቅንጅት እየተሰራ ነው
Jun 25, 2026 179
ወልቂጤ፤ሰኔ 18/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን በስኬት ለማጠናቀቅ ባለድርሻ አካላት በቅንጅት እየሰሩ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ። የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ዝግጅትን አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር የተዘጋጀው የምክክር መድረክ በወልቂጤ ከተማ ተካሂዷል። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ በወቅቱ እንዳሉት፤ በክልሉ ፈተናውን በስኬት ለማጠናቀቅ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የተጣለባቸውን ኃላፊነት በቁርጠኝነት መወጣት ይኖርባቸዋል። በክልሉ በአጠቃላይ ከ31 ሺህ በላይ ተማሪዎች ለፈተና የሚቀመጡ ሲሆን፣ ፈተናው በክልሉ በተዘጋጁ 34 ማዕከላት ይሰጣል ብለዋል። ከአጠቃላይ ተፈታኞች ውስጥ 18 ሺህ 827 ተማሪዎች ፈተናውን በኢንተርኔት አማካኝነት የሚወስዱ ሲሆን፣ ለዚህም ስኬት ተማሪዎችን የማብቃት ሥራ ሲከናወን መቆየቱን ገልጸዋል። በምክክር መድረኩ ላይ የተገኙት የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ተወካይ አበበ ሎላሞ (ዶ/ር)፤ ዩኒቨርሲቲው ተፈታኝ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተናገድና ለማስፈተን አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን ገልጸዋል። የኢትዮ ቴሌኮም የሆሳዕና ዲስትሪክት ኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አለማየሁ አሰፋ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ በኦንላይን ፈተና በሚሰጥባቸው ማዕከላት ላይ አስተማማኝ የኔትወርክ ዝርጋታ መከናወኑን አረጋግጠዋል። በፈተና ወቅት የኢንተርኔት መቆራረጥን ጨምሮ ከቴሌኮም አገልግሎት ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ችግሮች ለመከላከል የሚያስችል ዝግጅት መደረጉንም አክለዋል። የክልሉ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተወካይ አቶ ፍሬው ገዛህኝ፣ ተፈታኞች ተረጋግተው ፈተናቸውን እንዲወስዱ በየማዕከላቱ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ እንዳያጋጥም ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል። በመድረኩ ላይ የክልሉ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ማስፈጸሚያና የኦንላይን ፈተና ዕቅድ ዝግጅት ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት የተደረገበት ሲሆን፣ ቀጣይ አቅጣጫዎችም ተቀምጠዋል። በዚሁ የምክክር መድረክ ላይ የክልል፣ የዞን፣ የወረዳና የልዩ ወረዳ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
ኢኮኖሚ
የኢትዮጵያና ዩናይትድ ኪንግደም ታሪካዊ ግንኙነት ወደላቀ ስትራቴጂክ አጋርነት እየተሸጋገረ ነው
Jun 25, 2026 313
አዲስ አበባ፤ሰኔ 18/2018 (ኢዜአ):-የኢትዮጵያና ዩናይትድ ኪንግደም ታሪካዊ ግንኙነት ወደላቀ ስትራቴጂክ የዲፕሎማሲ አጋርነት እየተሸጋገረ መሆኑን በዩናይትድ ኪንግደም የኢትዮጵያ አምባሳደር ብሩክ መኮንን ገለጹ። በኢትዮጵያ እና እንግሊዝ መካከል ያለው ሁሉን አቀፍ ትብብር ለማሳደግ የተዘጋጀው የኢትዮ-እንግሊዝ የንግድና ኢንቨስትመንት ፎረም 2026 በለንደን ከተማ ተካሂዷል። በዩናይትድ-ኪንግደም የኢትዮጵያ አምባሳደር ብሩክ መኮንን በዚሁ ጊዜ፤ ኢትዮጵያና እንግሊዝ በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ ዘመናትን የተሻገር ታሪካዊ ግንኙነት ያላቸው ወዳጅ ሀገራት ናቸው ብለዋል። የሀገራቱ መልካም ግንኙነትም የንግድና ኢንቨስትመንት የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ትብብርን በማሳደግ የህዝብ ለህዝብ ትስስርን ጭምር እያጠናከረ እንደሚገኝ አስረድተዋል። በአሁኑ ወቅትም የኢትዮጵያና ዩናይትድ ኪንግደም ታሪካዊ ግንኙነት ወደላቀ ስትራቴጂክ የዲፕሎማሲ አጋርነት እየተሸጋገረ መሆኑን ተናግረዋል። የሀገራቱ የንግድና ኢንቨስትመንት ፎረምም የኢኮኖሚክ ዲፕሎማሲ አጋርነትን ለማጎልበት ጉልህ ፋይዳ እንደሚኖረው ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ሀገር በቀል የብዝኅ ዘርፍ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሪፎርሙ ለሀገራቱ ሁለንተናዊ የዲፕሎማሲ ትብብር አስቻይ ሁኔታ መፍጠሩንም አንስተዋል። በቀጣይም የሀገራቱን ሁለንተናዊ የዲፕሎማሲ ትብብር የበለጠ በማጠናከር የጋራ ተጠቃሚነትን ለማሻሻል በቁርጠኝነት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል። በዩናይትድ ኪንግደም የኢትዮጵያ ኤምባሲም የሁለቱን ሀገራት የንግድ፣ የኢንቨስትመንትን፣ የዲፕሎማሲና የኢኮኖሚ ትብብር ወደ ላቀ ስትራቴጂክ አጋርነት ለማሸጋገር በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል። በፎረሙ ላይ የሀገራቱ የፖሊሲ አውጪ ሙያተኞች፣ ባለሃብቶችና የተለያዩ ተቋማት ጋር የሃሳብ ልውውጦች መደረጋቸው ተመላክቷል።
በምዕራብ ሸዋ ዞን የህዝቡን የልማት ጥያቄዎች የሚመልሱ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ለአገልግሎት በቁ
Jun 25, 2026 282
አምቦ፤ሰኔ 18/2018 (ኢዜአ):- በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን የህዝቡን የቆዩ የልማት ጥያቄዎች ለመፍታት የተገነቡ የተለያዩ የመሰረተ ልማት አውታሮች በሁለት ዙር ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት መሆናቸውን የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ። በዞኑ ኢሉ ገላን ወረዳ ተገንብተው ለአገልግሎት የበቁት ኮሪደር ልማት፣ የእንስሳት ጤና ኬላ፣ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት እና ሌሎች የመሰረተ ልማት ተቋማትም ይገኙበታል። በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የምዕራብ ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ዲዳ ጉደታ እንደገለጹት፤ በዞኑ በሕዝብና በመንግሥት ትብብር የተገነቡ የልማት ፕሮጀክቶች ለአገልግሎት እየበቁ ነው። በበጀት ዓመቱ በመጀመሪያው ዙር 391 የልማት ፕሮጀክቶች ተመርቀው አገልግሎት መጀመራቸውን የገለጹት አስተዳዳሪው፤ የሁለተኛው ዙር ምረቃ በኢሉ ገላን ወረዳ መጀመሩን ጠቁመዋል። ግንባታቸው ተጠናቆ ምርቃታቸው የተጀመረው የሁለተኛ ዙር ፕሮጀክቶች ቁጥር 128 መሆኑንም ገልጸዋል። የኢሉ ገላን ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አሚን ነሻ በበኩላቸው፤ በወረዳው በመንግሥት በጀትና በሕብረተሰቡ ተሳትፎ ከ106 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡ 18 የልማት ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት መሆናቸውን አስታውቀዋል። የተገነቡት መሰረተ ልማቶች የአካባቢውን ሕብረተሰብ ዘመናት ያስቆጠሩ ጥያቄዎች የሚፈቱ መሆናቸውን የገለጹት የወረዳው አስተዳዳሪ፤ ሕዝቡ ለፕሮጀክቶቹ አስፈላጊውን እንክብካቤ በማድረግ ለመጪው ትውልድ ማስተላለፍ እንዳለበት አሳስበዋል። ኢዜአ ያነጋገራቸው የኢሉ ገላን ወረዳ ነዋሪዎችም በአካባቢያቸው ለአገልግሎት የበቁ ፕሮጀክቶች የረጅም ጊዜ ጥያቄያቸውን ከመመለስ ባለፈ፣ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸውን እንደሚያሳድጉት ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። አቶ ሁንዱማ ታረሳ "በቀበሌያችን የተገነባው ዲጂታል ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት መጀመሩ የአካባቢው ተማሪዎች በቴክኖሎጂ ታግዘው ዕውቀት እንዲቀስሙና በሀገር አቀፍም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ትልቅ እገዛ ያደርጋል" ብለዋል። ወጣት ደራርቱ ወጋሪ በበኩሏ፤ ለአገልግሎት የበቁት መሰረተ ልማቶች የአካባቢውን ሕብረተሰብ ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ ከመሆናቸውም በላይ፣ ለወጣቶች ሰፊ የሥራ ዕድል የሚፈጥሩ በመሆናቸው ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ገልጻለች።
የሀረር ፌዴራል ፖሊስ ሆስፒታል ማስፋፊያ የክልሉን የሜዲካል ቱሪዝም የሚያጎለብት ነው
Jun 25, 2026 171
አዲስ አበባ ፤ ሰኔ 18/2018/(ኢዜአ) ፦ የሀረር ፌዴራል ፖሊስ ሆስፒታል ማስፋፊያ ፕሮጀክት የክልሉን የሜዲካል ቱሪዝም ይበልጥ የሚያጎለብት ነው ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ። ርዕሰ መስተዳድሩ የሀረር ፌዴራል ፖሊስ ሆስፒታል ማስፋፊያ የግንባታን የአፈጻጸም ሂደት ተመልክተዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ በጉብኝታቸው የሪፈራል ሆስፒታሉን ግንባታ በተያዘለት የጊዜ ገደብ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ስለመሆኑ ማየታቸውን ገልጸዋል። የሆስፒታሉ ማስፋፊያ ግንባታ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ሲጀምርም የህክምና አገልግሎቱን ወደ ተሻለ ደረጃ የሚያደርስ መሆኑን ነው የተናገሩት። በክልሉ ለጤና አገልግሎት ተደራሽነት ልዩ ትኩረት ተሰቶት ወደ ስራ መገባቱን የጠቆሙት ርዕሰ መስተዳድሩ የሆስፒታሉ ማስፋፊያም በክልሉ በጤና ዘርፍ የሚሰጠውን አገልግሎት ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ የራሱን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ገልፀዋል። በተለይ ሀረር ጎረቤት አገራትን ጨምሮ ከአጎራባች ክልሎች ለህክምና የሚመጡ በርካታ ተገልጋዮች የሚስተናገዱባት የሜዲካል ቱሪዝም ከተማ መሆኗን ጠቅሰው የሆስፒታሉ ማስፋፊያ የሜዲካል ቱሪዝሙን ይበልጥ የሚያጎለብት ነው ብለዋል። የማስፋፊያ ፕሮጀክቱ ጥሩ በሚባል አፈፃፀም ላይ እንደሚገኝ በማመላከት በፍጥነት ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት እንዲችል የክልሉ መንግስት ድጋፍ እንደሚያደርግም ርዕሰ መስተዳድሩ አረጋግጠዋል።
የኢትዮጵያ የብዝኅ ኢኮኖሚ እመርታ ለውጭ አልሚ ባለሃብቶች ምቹ የንግድና ኢንቨስትመንት ምኅዳርን ፈጥሯል
Jun 25, 2026 164
አዲስ አበባ፤ሰኔ 18/2018 (ኢዜአ):-የኢትዮጵያ ብዝኅ የኢኮኖሚ ልማት እመርታ ለውጭ አልሚ ባለሃብቶች ምቹ የንግድና ኢንቨስትመንት ምኅዳር መፍጠሩን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ ገለጹ። በኢትዮጵያ እና ዩናይትድ ኪንግደም መካከል ያለው ሁሉን አቀፍ ትብብርን ለማሳደግ የተዘጋጀው የኢትዮ-እንግሊዝ የንግድና ኢንቨስትመንት ፎረም 2026 በለንደን ከተማ ተካሂዷል። የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ በዚሁ ወቅት፤ ኢትዮጵያ አምራች የሰው ኃይል፣በዓመት ከሶስት ጊዜ በላይ የሚያመርት መሬትና የብዝኅ ጸጋ ምድር ናት ብለዋል። በሀገራዊ ለውጡ ማግስት ተግባራዊ የተደረገው የኢትዮጵያ የብዝኅ ኢኮኖሚ የልማት አቅጣጫም በግብርና፣ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን፣ቱሪዝምና ዲጂታል ኢኮኖሚ ዘርፎች ተጨባጭ ለውጥ እያመጣ መሆኑን ገልጸዋል። የግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚም በሁሉም ወቅቶች ዘመናዊ አስተራረስ ምኅዳርን በማስፋት የኢንዱስትሪ ሽግግርን እያፋጠነ እንደሚገኝ አስረድተዋል። የኢትዮጵያን የንግድና ኢንቨስትመንት ከባቢ ለማሻሻል ተግባራዊ የሆኑ የሕግና የአሰራር ማሻሻያዎችም ለውጭ ባለኃብቶች አስቻይ ምኅዳር መፍጠሩን አስረድተዋል። የኢትዮጵያ የግብርና ምርታማነት አቅም የምግብ ሉዓላዊነትን በሚያረጋግጥ ትክክለኛ አቅጣጫ ላይ እየተመራ እንደሚገኝ አስገንዝበዋል። የእንግሊዝ አልሚ ባለሃብቶችም የኢትዮጵያ የብዝኅ ኢኮኖሚ አስቻይ የንግድና ኢንቨስትመንት ምኅዳር መጠቀም የሚችሉበት ዕድል መፈጠሩንም አብራርተዋል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
የኢትዮጵያ የዲጂታል እመርታ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ዕድገትን በማሳለጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው
Jun 25, 2026 250
አዲስ አበባ፤ሰኔ 18/2018 (ኢዜአ):-የኢትዮጵያ የዲጂታል ዘርፍ እመርታ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ዕድገትን በማሳለጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬተሪያት ኃላፊ ቢልለኔ ስዩም ገለጹ። በኢትዮጵያ እና እንግሊዝ መካከል ያለው ሁሉን አቀፍ ትብብር ለማሳደግ የተዘጋጀው የኢትዮ-እንግሊዝ የንግድና ኢንቨስትመንት ፎረም 2026 በለንደን ከተማ ተካሂዷል። የኢትዮ-እንግሊዝ የንግድና ኢንቨስትመንት ፎረም ጎን ለጎንም በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂና ዲጂታላይዜሽን ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት ተካሄዷል። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬተሪያት ኃላፊ ቢልለኔ ስዩም በዚሁ መድረክ፤ በሀገራዊ ለውጡ ማግስት ኢትዮጵያ ስኬታማ የቴክኖሎጂና የኢኮኖሚ ማሻሻያ ማድረጓን አስረድተዋል። የግብርና፣ኢንዱስትሪ፣ ማዕድንና ቱሪዝም ዘርፍ የሚያስመዘግቡትን እመርታዊ ዕድገትም ዲጂታል ቴክኖሎጂ እያሳለጠ እንደሚገኝ አንስተዋል። የኢትዮጵያ አምስቱ የብዝኅ ኢኮኖሚ ዕድገት መሰሶዎችም በዲጂታል መሰረተ ልማት ታግዞ ፈጣን ዕድገት እያስመዘገበ መሆኑን ተናግረዋል። የዲጂታል ዘርፍ የኢትዮጵያ ብዝኅ ኢኮኖሚ መሰሶ አካል መደረጉም በአጠቃላይ የኢኮኖሚ ሥርዓት ላይ ሥር ነቀል ለውጥ እንዲመጣ ማድረጉን አስረድተዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሚመራው የዲጂታላይዜሽን ሂደት ዋና ስትራቴጂ ደረጃዎችን ወደ ላቀ ምዕራፍ ማሸጋገር እንዳስቻለም ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ ዘርፍ የበለፀጉ ሀገራት ያለፉበትን ልምድና ተሞክሮ በመውሰድና ከነባራዊ አውድ ጋር በማጣጣም በወሳኝ የሽግግር ሂደት ላይ እያለፈች መሆኗን ገልጸዋል። የዲጂታል ዘርፍ እመርታም ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ዕድገትን በማሳለጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን አስረድተዋል። በፓናል ውይይቱ አወያይ የነበሩት የምጣኔ ሃብት ባለሙያ ዘመዴነህ ንጋቱ እንዳሉት፤ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በአስደናቂ የዕድገት ምዕራፍ እያለፈች ነው። በዚህም በመሰረተ ልማትና በዲጂታል ዘርፍ የተመዘገበው እመርታዊ ውጤትም ንግድና ኢንቨስትመንትን የሚያበረታታ አስቻይ የትራንስፎርሜሽን ምኅዳር መፍጠሩን አስገንዝበዋል።
ዩኒቨርሲቲው ተመራቂ ተማሪዎች ስራ ፈጣሪ እንጂ ስራ ጠባቂ እንዳይሆኑ እየሰራ ነው
Jun 25, 2026 204
ባህር ዳር ፤ ሰኔ 18/2018 (ኢዜአ)፦ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በተግባር ተኮር ትምህርት ላይ በመመስረት ተመራቂ ተማሪዎች ስራ ፈጣሪ እንጂ ስራ ጠባቂ እንዳይሆኑ እየሰራ መሆኑን ገለጸ። የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ያዘጋጀውና ለሁለት ቀናት የሚቆየው "የስታርትአፕ፣ የቀጣሪ ድርጅቶችና የተመራቂዎች" ትስስር መድረክ ዛሬ መካሄድ ጀምሯል። የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት መንገሻ አየነ (ዶ/ር) በመድረኩ እንዳሉት፤ ተመራቂዎች ሥራ ከመጠበቅ ይልቅ በፈጠራ ላይ ተመስርተው የራሳቸውን ድርጅት በመመሥረት ለሌሎች የሥራ ዕድል የሚፈጥሩ እንዲሆኑ በትኩረት እየተሠራ ነው። ዩኒቨርሲቲው ካሉት 440 በላይ የትምህርት ፕሮግራሞች ውስጥ 70 በመቶ ያህሉ በድህረ-ምረቃ ደረጃ የሚሰጡ በመሆናቸው፣ ችግሮችን በምርምር ለመፍታትና ተወዳዳሪ ተመራቂዎችን ለማብዛት ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን ተናግረዋል። በዚህም ተማሪዎች ገና ሳይመረቁ የፈጠራ ሃሳባቸውን ወደ ተግባር ቀይረው ድርጅት በማቋቋም ሲወጡ ለሌሎች ተስፋ የሚሆኑ ተጨባጭ ውጤቶች እየተገኙ መሆኑን ገልጸዋል። ለዚህ ስኬትም ዩኒቨርሲቲው አስፈላጊውን የበጀትና የሰው ኃይል በመመደብ እንዲሁም መሠረተ ልማትን በማሟላት ላይ አተኩሮ እየሠራ መሆኑን ጠቁመው፣ የዛሬው መድረክም ፈጣሪዎችንና ቀጣሪዎችን ለማገናኘት ያለመ ነው ብለዋል። የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ምትኩ ዳምጤ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ አሁን ላይ ተማሪዎች ተመርቀው ሲወጡ ከትምህርት ማስረጃ በተጨማሪ የፈጠራ ባለቤትነት (ፓተንት) ይዘው እየወጡ መሆኑን ገልጸዋል። ይህ ውጤት ሊመዘገብ የቻለው ዩኒቨርሲቲው ባቋቋማቸው የቋንቋ፣ የሶፍት ስኪል እና የቢዝነስ ኢንኩቤሽን ማዕከላት አማካኝነት ተማሪዎች ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩ በመደረጉ መሆኑን አረጋግጠዋል። በዚህም የተቋሙ ምሩቃን እንደ ናሳ፣ ቦይንግ፣ ጎግልና አማዞን ባሉ ግዙፍ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ውስጥ እየሠሩ እንደሚገኙ ጠቁመው፣ በክህሎት የዳበሩ ተማሪዎችን የማፍራት ተልዕኮው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። በዕለቱ የፈጠራ ሥራዎቻቸውን ካቀረቡት መካከል በዩኒቨርሲቲው የኬሚካል ኢንጂነሪንግ መምህርና ተመራማሪው ኢዮሲያስ አለሙ፤ ከድንች የእንጀራና የዳቦ ዱቄት በማዘጋጀት የተሳካ የፈጠራ ሥራ ማቅረባቸውን ገልጸዋል። ፈጠራው ተገቢውን ዕውቅና ማግኘቱን ጠቅሰው፣ የድንች ዱቄትን በኪሎ 70 ብርና ከዚያ በታች በሆነ ዋጋ በማቅረብ አሁን የሚስተዋለውን የኑሮ ውድነት ለመቅረፍ የሚያስችል መሆኑን አስረድተዋል። ሌላው የሜካኒካል ኢንጂነሪንግ ተመራቂ ዳግም ደጉ በበኩሉ፤ የከተሞችን የኮሪደር ልማት ዘመናዊነት የሚመጥን፣ በአንድ ጊዜ 30 ጫማዎችን ማጠብ የሚችል ማሽን ሠርቶ አቅርቧል። በአሁኑ ወቅት ከአንድ ጓደኛው ጋር በመሆን ማሽኑን በትዕዛዝ አምርተው በማቅረብ ገቢ ማግኘት መጀመራቸውንና በቀጣይም ለሌሎች ወጣቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር መዘጋጀታቸውን ገልጿል። ለሁለት ቀናት በሚቆየው በዚህ የስታርትአፕና የሥራ ፈጠራ መድረክ ላይ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ የሥራ ፈጣሪዎች፣ ተማሪዎችና የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ አባላት በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
ዩኒቨርሲቲው የአካባቢውን ማህበረሰብ ኑሮ ለማሻሻል የሚያግዙ የምርምር ሥራዎችን እያከናወነ ነው
Jun 25, 2026 202
ወልቂጤ፤ ሰኔ 18/2018 (ኢዜአ)፦ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ከመማር ማስተማር ሥራው በተጓዳኝ የአካባቢውን ማህበረሰብ ኑሮ ለማሻሻል የሚያግዙ የምርምር ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን አስታወቀ። ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 363 ተማሪዎች ዛሬ አስመርቋል። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት አብዱልሙህሲን ሃሰን (ዶ/ር) በምረቃ ሥነ ስርዓቱ ላይ እንደገለፁት፤ ዩኒቨርሲቲው የኢንዱስትሪውን ችግር በቅርበት ተገንዝቦ የሚፈታ አምራች የሰው ሀይል እያፈራ ነው። ከመማር ማስተማሩ ሥራው በተጓዳኝ የአካባቢውን ማህበረሰብ ኑሮ ለማሻሻል የሚያግዙ የምርምር ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን ጠቁመው፣ የጀፎረን ሀገር በቀል እውቀት በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ የሚያስችል ጥናት ማካሄዱንም ገልጸዋል። የአካባቢውን ማህበረሰብ በኢኮኖሚና ማህበራዊ ዘርፎች ተጠቃሚነቱን ለማሳደግ የሚያከናውናቸውን የምርምር ስራዎች በቀጣይም እንደሚያጠናክር አመልክተዋል። የዛሬው ምሩቃንም በትምህርት ቆይታቸው ያገኙትን ዕውቀት ተጠቅመው በቀጣይ የራሳቸውንና የህብረተሰቡን ኑሮ ለመለወጥ መትጋት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። በምረቃ ሥነ ሥርአቱ ላይ የተገኙት የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነርና የዩኒቨርሲቲው የቦርድ ሰብሳቢ ደበሌ ቃበታ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ዩኒቨርሲቲው በእውቀት የበቃ ዜጋን ለማፍራት የጀመረውን ጥረት ማጠናከር እንዳለበት ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርስቲው በቅድመና ድህረ ምረቃ ትምህርት ሀገሪቱ የምትፈልገውን የሰው ሀይል እያፈራ መሆኑ ገልጸው፣ በተለይ የአለም ተለዋዋጭነትን ታሳቢ በማድረግ የምርምር ስራዎችን ማጠናከር እንዳለበት አመልክተዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው በተለይ በኢንዱስትሪ እና በቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸው፣ ምሩቃንም በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው የቀሰሙትን ዕውቀት ለሀገር ልማትና ብልጽግና እንዲያውሉ አሳስበዋል። በሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ ትምህርት የዋንጫ ተሸላሚው ባስያኤል ጌቱ፤ በትምህርት ቆይታው ሙሉ ጊዜውን ለትምህርት በመስጠቱ ውጤታማ ለመሆን መቻሉን ተናግሯል። በዩኒቨርሲቲው ሙሉ ጊዜውን ለንባብ እና ለአዳዲስ ፈጠራዎች ትኩረት መስጠቱና በትጋት በመማሩ ለሽልማት መብቃቱን ተናግሯል። በህግ ትምህርት ከፍተኛ ውጤት ያመጣው ኤፍሬም ሀይለማርያም በበኩሉ፣ በቀጣይም በህግ ትምህርት ባገኘው እውቀት ሀገሩንና ድጋፍ የሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎቸን ለማገልግል መዘጋጀቱን ተናግሯል። በተማሪዎች ምረቃ ሥነ ስርአቱ ላይ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።
የግብርናውን ዘርፍ በቴክኖሎጂ በመደገፍ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ረገድ ትልቅ እምርታ እየታየ ነው
Jun 25, 2026 308
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 18/2018 (ኢዜአ):- የግብርናውን ዘርፍ በቴክኖሎጂ በመደገፍ የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት በማሳደግ ረገድ ትልቅ እምርታ እየታየ መሆኑን በኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን የዲጅታል ግብርና አገልግሎት ፕሮጀክት ቡድን መሪ ተመስገን ገበየሁ ገለጹ፡፡ የኢኮኖሚው የጀርባ አጥንት የሆነውን የግብርና ዘርፍ በቴክኖሎጂ በመደገፍ የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የሚደረገው ጥረት ተስፋ ሰጪ ውጤቶችን አስመዝግቧል፡፡ በኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን የዲጅታል ግብርና አገልግሎት ፕሮጀክት ቡድን መሪ ተመስገን ገበየሁ ፤ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ አማካኝነት ግብርናን ለማዘመን ቴክኖሎጂ በስፋት ጥቅም ላይ መዋሉን ገልጸዋል። በዚህም አርሶ አደሮች በእጅ ስልካቸው በመጠቀም ስለ ግብዓቶች አቅርቦት፣ ዋጋ እና ጊዜ መረጃ እንዲሁም ስለ አፈር፣ ዝናብና የሰብል በሽታዎች የባለሙያ ምክር በቀላሉ እንዲያገኙ መደረጉን ተናግረዋል፡፡ ይህ የዲጂታል ስልት አርሶ አደሩ የገበያ ዋጋን አስቀድሞ አውቆ ምርቱን በቀጥታ እንዲያቀርብ በማገዝ ምርታማነቱንና ተጠቃሚነቱን በተግባር እንዲያረጋግጥ ማስቻሉን ጠቅሰዋል፡፡ ኢንስቲትዩቱ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂን የግብርና ትራንስፎርሜሽንን ቅርጽ ለማስያዝና ፕሮግራሞችን ለመደገፍ በከፍተኛ ሁኔታ ሲጠቀምበት መቆየቱን ተመራማሪው ጠቁመዋል። በተለይም የምክር አገልግሎትን ለማገዝ በተዘረጋው የ"8028" የስልክ መስመር ከ7 ሚሊየን በላይ አርሶ አደሮች በነጻ በመደወል የምክር አገልግሎት ማግኘታቸውን ጠቁመዋል፡፡ በተጨማሪም 344 ከሚሆኑ የገበያ ማዕከላት በየጊዜው እየተሰበሰበና ትክክለኛነቱ እየተረጋገጠ የሚሰራጨው የገበያ መረጃ እስካሁን 2 ሚሊየን የሚሆኑ ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረጉን ጠቁመዋል፡፡ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ የኢኮኖሚው የጀርባ አጥንት የሆነውን ግብርና ይበልጥ በማዘመን ለምግብ ሉዓላዊነት መረጋገጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክትም ገልጸዋል። በስትራቴጂው በከተማና በገጠር መካከል ያለውን የዲጂታል ልዩነት በማጥበብ የአርሶ አደሩን ምርታማነት ለማሳደግ የሚሰራ ሲሆን፣ ለዚህም የዲጂታል መሰረተ-ልማትና የእውቀት ማሳደጊያ ስልጠናዎች እንደሚሰጡ ጠቁመዋል፡፡ በ2030 አርሶ አደሮችን ቀልጣፋ አገልግሎት የሚያገኙበት ደረጃ ላይ ለማድረስ እንደሚሰራ ጠቁመው፤ የቴክኖሎጂ አቅሞችን ተደራሽ በማድረግ ምርትና ምርታማነትን ይበልጥ ለማሳደግ እንደሚሰራም ጠቁመዋል፡፡
ስፖርት
ሀገራት ከፍተኛ የገንዘብ መጠን የሚያጋብሱበት የዓለም ዋንጫ ክብረ ወሰን ሽልማት
Jun 25, 2026 317
በሙሴ መለሰ 23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ ጣምራ አዘጋጅነት መካሄድ ጀምሯል። የዘንድሮው የዓለም ዋንጫ በበርካታ ነገሮች «የመጀመሪያ» የተሰኙ አዳዲስ ነገሮችን ይዟል። ከነዚህም መካከል ለውድድሩ ተሳታፊ ሀገራት የሚበረከተው የገንዘብ ሽልማት ነው። የዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) ለዓለም ዋንጫው ተሳታፊ ሀገራት 871 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ሽልማት ማዘጋጀቱን ይፋ አድርጓል። ይህም በውድድሩ የ96 ዓመታት ታሪክ ከፍተኛ የሚባለው ነው። የፊፋ ምክር ቤቱ እ.አ.አ ዲሴምበር 2025 በኳታር ዶሃ ባካሄደው ስብሰባ፤ በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ላይ ለሚሳተፉ አገራት የሚከፋፈል የ727 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ታሪካዊ በጀት አጽድቆ ነበር። ይህ መጀመሪያ ላይ የጸደቀው የገንዘብ መጠን፣ በኳታር አስተናጋጅነት ከተካሄደው የ2022 የዓለም ዋንጫ ጋር ሲነጻጸር የ50 በመቶ ብልጫ ያለው እንደነበር ተገልጿል። በዚሁ የኳታር ስብሰባ ላይ በጸደቀው ስሌት መሠረት፣ የውድድሩ ሻምፒዮን (ባለድል) 50 ሚሊዮን ዶላር ሲያገኝ፣ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ የሚያጠናቅቀው ቡድን 33 ሚሊዮን ዶላር፣ ሦስተኛው 29 ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም አራተኛ ደረጃን የሚያገኘው 27 ሚሊዮን ዶላር ተመድቦለታል። በተመሳሳይ ከ5ኛ እስከ 8ኛ ደረጃ የሚይዙት 19 ሚሊዮን ዶላር፣ ከ9ኛ እስከ 16ኛ ደረጃ ላይ የሚቀመጡት 15 ሚሊዮን ዶላር፣ ከ17ኛ እስከ 32ኛ ደረጃ ያላቸው ቡድኖች 11 ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም ከ33ኛ እስከ 48ኛ ደረጃ ይዘው የሚያጠናቅቁት አገራት እያንዳንዳቸው 9 ሚሊዮን ዶላር የሽልማት ገንዘብ ያገኛሉ። በተጨማሪም በእያንዳንዱ ደረጃ ላይ ለሚገኙት ቡድኖች ከሚሰጠው የሽልማት ገንዘብ ውጪ፣ ለእያንዳንዱ ተሳታፊ አገር ለዝግጅት ወጪ (Preparation costs) 1.5 ሚሊዮን ዶላር ተመድቦ የነበረ ሲሆን፤ በዚህም ማንኛውም ተሳታፊ አገር ቢያንስ 10.5 ሚሊዮን ዶላር ማግኘቱ ተረጋግጦ ነበር። ነገር ግን ምክር ቤቱ ውድድሩ ከመጀመሩ 44 ቀናት በፊት፣ እ.አ.አ ኤፕሪልክ 2026 በቫንኩቨር ካናዳ ባደረገው ሌላኛው ስብሰባው ተጨማሪ ማሻሻያ አድርጓል። ውድድሩ ባስመዘገበው ከፍተኛ የንግድ ገቢ ምክንያት፣ ምክር ቤቱ ቀደም ሲል አጽድቆት በነበረው በጀት ላይ ተጨማሪ የ15 በመቶ ጭማሪ በማድረግ አጠቃላይ ድምሩን ወደ 871 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ከፍ አድርጎታል። በዚህ የቫንኩቨር ስብሰባ በተወሰነው አዲስ ማሻሻያ መሠረት፦ ለእያንዳንዱ አገር የሚሰጠው የዝግጅት ወጪ (Preparation money) ከ1.5 ሚሊዮን ዶላር ወደ 2.5 ሚሊዮን ዶላር እንዲያድግ ተደርጓል። ለውድድር ተሳትፎ (Qualification money) ከ9 ሚሊዮን ዶላር ወደ 10 ሚሊዮን ዶላር ከፍ ብሏል። ይህም በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ 48 አገራት በሚሳተፉበት በዚህ የዓለም ዋንጫ ላይ የሚሳተፍ ማንኛውም አገር፣ ከምድብ ማጣሪያው ባያልፍ እንኳ በትንሹ 12.5 ሚሊዮን ዶላር (የ2.5 ሚሊዮን ዝግጅት እና የ10 ሚሊዮን የተሳትፎ ክፍያ) ያገኛል። በተጨማሪም ለቡድኖች ልዑካን ቡድን ወጪ መሸፈኛ እና ለትኬት ድልድል ከ16 ሚሊዮን ዶላር በላይ ተጨማሪ ድጎማ መመደቡ ተገልጿል። የፊፋ ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ በጉዳዩ ላይ በሰጡት አስተያየት፤ ፊፋ በአሁኑ ወቅት በታሪኩ እጅግ ጠንካራ በሆነ የፋይናንስ አቋም ላይ እንደሚገኝ ጠቁመው፣ ይህም ሁሉንም አባል ማኅበራት ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ለመደገፍ እንዳስቻለ ገልጸዋል። ይህ ውሳኔም የፊፋ ሀብት እንዴት በቀጥታ ወደ እግር ኳሱና ለዘርፉ ዕድገት መልሶ ጥቅም ላይ እንደሚውል የሚያሳይ ትልቅ ማረጋገጫ ነው ብለዋል። ከተሳታፊ ቡድኖች ክፍያ የተረፈው አጠቃላይ ገቢ፣ በ211 የፊፋ አባል ማኅበራት አማካኝነት ለዓለም እግር ኳስ ዕድገት ማስፈጸሚያ በድጋሚ ጥቅም ላይ እንደሚውል ፊፋ አስታውቋል።
ኮትዲቯር ወደ ጥሎ ማለፍ ለመግባት ከኩራሳኦ ጋር ትጫወታለች
Jun 25, 2026 321
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 18/2018 (ኢዜአ):- በ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ የምድብ አምስት መርሐ ግብር ኮትዲቯር ከኩራሳኦ ጋር ጨዋታዋን ታከናውናለች። ጨዋታው ምሽት አምስት ሰዓት ላይ በፊላደልፊያ ስታዲየም ይካሄዳል። ከሁለት ጨዋታዎች ሶስት ነጥብ ያገኘችው ኮትዲቯር ማሸነፍ ቀጥታ ወደ ጥሎ ማለፍ ያስገባታል። አቻ መውጣት በምርጥ ሶስተኝነት ሊያሳልፋት ይችላል። በዓለም ዋንጫ የመጀመሪያ ተሳትፎዋን እያደረገች የምትገኘው ኩራሳኦ በአንድ ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። ኩራሳኦ ወደ ጥሎ ማለፍ ለመግባት ያላት ብቸኛ እድል ማሸነፍ ብቻ ነው። በዚሁ ምድብ ኢኳዶር ከጀርመን በኒው ዮርክ ኒው ጀርሲ ስታዲየም ከምሽቱ አምስት ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። አኳዶር በአንድ ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዛለች። የአራት ጊዜ የዓለም ዋንጫ አሸናፊዋ ጀርመን በስድስት ነጥብ ጥሎ ማለፍ መግባቷን አረጋግጣለች። የደቡብ አሜሪካዋ ኢኳዶር ወደ ጥሎ ማለፍ የመግባት ተስፋውን ለማለምለም ጨዋታውን ማሸነፍ ይጠበቅባታል። በተያያዘም በምድብ ስድስት የመጨረሻ የምድብ ጨዋታዎች ይደረጋሉ። ቱኒዚያ ከኔዘርላንድስ ከሌሊቱ ስምንት ላይ በካንሳስ ሲቲ ጨዋታቸውን ያከናውናሉ። በምድቡ ሁለት ጨዋታዎች የተሸነፈችው እና ከውድድሩ የተሰናበተችው ቱኒዚያ የመርሐ ግብር ማሟያ ጨዋታዋን ታደርጋለች። በአራት ነጥብ ምድቡን የምትመራው ኔዘርላንድስ ካሸነፈች ወይም አቻ ከወጣች ወደ ጥሎ ማለፍ መግባቷን ታረጋግጣለች። በዚሁ ምድብ ጃፓን ከስዊድን ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት ላይ በዳላስ ስታዲየም ይጫወታሉ። ጃፓን በአራት ነጥብ ሁለተኛ፣ ስዊድን በሶስት ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል። ጃፓን ማሸነፍ ወይም አቻ መውጣት ወደ ቀጣዩ ዙር ያሳልፋታል። በአንጻሩ ስዊድን ካሸነፈች በቀጥታ ወደ ቀጣዩ ዙር ታልፋለች። አቻ መውጣትም በምርጥ ሶስተኝነት ሊያሳልፋት ይችላል። በምድብ አራት በተመሳሳይ ሁለት ጨዋታዎች ከሌሊቱ 11 ሰዓት ላይ ይደረጋሉ። ቱርኪዬ ከአሜሪካ በሎስ አንጀለስ ስታዲየም ይጫወታሉ። በምድቡ በሁለት ጨዋታ የተሸነፈችው ቱርኪዬ ከውድደሩ መሰናበቷ ይታወቃል። በአንጻሩ ከአዘጋጅ ሀገራት መካከል አንዷ የሆነችው አሜሪካ በስድስት ነጥብ ወደ ጥሎ ማለፉ ገብታለች። በሌላኛው የምድቡ መርሐ ግብር ፓራጓይ ከአውስትራሊያ በሳን ፍራንሲስኮ ቤይ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። አውስትራሊያ እና ፓራጓይ በተመሳሳይ ሶስት ነጥብ በግብ ክፍያ ተበላልጠው ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል። ማሸነፍ ሀገራቱን ወደ ጥሎ ማለፉ ያስገባቸዋል። አቻ መውጣት አውስትራሊያን በቀጥታ ወደ ቀጣዩ ዙር እንድታልፍ ያስችላታል። ፓራጓይ ከጨዋታው አንድ ነጥብ ካገኘች በምርጥ ሶስተኝነት የማለፍ እድል ይኖራታል።
ሞሮኮ እና ደቡብ አፍሪካ ወደ ጥሎ ማለፍ ተሸጋግረዋል
Jun 25, 2026 360
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 19/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ የምድብ አንድ እና ሶስት የመጨረሻ የምድብ ጨዋታዎች ከእኩለ ሌሊት በኋላ ተደርገዋል። በአትላንታ ስታዲየም በተካሄደው የምድብ ሶስት ጨዋታ ሞሮኮ ሃይቲን ከመመራት ተነስታ 4 ለ 2 አሸንፋለች። አሽራፍ ሀኪሚ፣ እስማኤል ሳይባሪ፣ ሶፊያን ራህሚ እና ጌሲም ያሲን ግቦቹን አስቆጥረዋል። እስማኤል ሳይባሪ በውድድሩ ላይ ያስቆጠራቸውን ጎሎች ብዛት ሶስት አድርሷል። ዊልሰን ኢሲዶር እና የሞሮኮው ግብ ጠባቂ ያሲን ቦኖ በራሱ ላይ የሃይቲን ግቦች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። ውጤቱን ተከትሎ ሞሮኮ በሰባት ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ወደ ጥሎ ማለፍ ገብታለች። ሞሮኮ በዓለም ዋንጫው ታሪክ ግማሽ ፍጻሜ የገባች የመጀመሪያ አፍሪካዊት ሀገር መሆኗ ይታወቃል። አስቀድማ ከውድድሩ የተሰናበተችው ሀይቲ ያለ ምንም ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዛ ጨርሳለች። በሚያሚ ስታዲየም በተካሄደው የምድብ ሶስት ሌላኛው መርሐ ግብር ብራዚል ስኮትላንድን 3 ለ 0 አሸንፋለች። ሺኒሸስ ጁኒየር ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ማትያስ ኩንሃ ቀሪዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል። ቪኒሸስ ጁኒየር በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ያስቆጠራቸውን ጎሎች ብዛት አራት አድርሷል። በጉዳት ላይ የነበረው ኔይማር ተቀይሮ በመግባት የመጀመሪያ የዓለም ዋንጫ ጨዋታውን አድርጓል። ውጤቱን ተከትሎ ብራዚል በሰባት ነጥብ የምድቡ መሪ በመሆን ጥሎ ማለፍ ገብታለች። ስኮትላንድ በሶስት ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዛ ያጠናቀቀች ሲሆን ምርጥ ሶስተኛ ሆና ለማለፍ የሌሎች ምድቦችን ውጤት ትጠብቃለች። በተያዘዘም በምድብ አንድ የምትገኘው ደቡብ አፍሪካ ኮሪያ ሪፐብሊክን 1 ለ 0 አሸንፋለች። በሞንቴሬይ ስታዲየም በተካሄደው ታፔሎ ማሴኮ በ63ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል። ድሉን ተከትሎ ደቡብ አፍሪካ በአራት ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ለጥሎ ማለፉ አልፋለች። ኮሪያ ሪፐብሊክ በሶስት ነጥብ ሶሶተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። ምርጥ ሶስተኛ ሆኖ ለማለፍ የሌሎቹን ምድቦች ውጤት ትጠብቃለች። በዚሁ ምድብ በሜክሲኮ ሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሜክሲኮ ቼክ ሪፐብሊክን 3 ለ 0 አሸንፋለች። ማቲዮ ቻቬዝ፣ ጁሊያን ኪኖኔስ እና አልቫሮ ፊዳልጎ ግቦቹን አስቆጥረዋል። አስቀድማ ወደ ጥሎ ማለፉ መግባቷን ያረጋገጠችው ሜክሲኮ በዘጠኝ ነጥብ የምድቡ መሪ ሆና አጠናቃለች። በዓለም ዋንጫው ሁሉንም የምድቧን ጨዋታ ያሸነፈች ብቸኛ ሀገር ሆናለች። ሜክሲኮ ከዓለም ዋንጫ አዘጋጅ ሀገራት መካከል አንዷ ናት።
ስዊዘርላንድ፣ ካናዳ እና ቦሲኒያ ሄርዞጎቪና ጥሎ ማለፉን ተቀላቀሉ
Jun 25, 2026 302
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 19/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ የምድብ ሁለት የመጨረሻ ጨዋታዎች ትናንት ማምሻውን ተደርገዋል። በቢሲ ፕሌስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ስዊዘርላንድ ካናዳን 2 ለ 1 አሸንፋለች። ሩበን ቫራጋስ እና የካናዳው ጆሃን ማዛምቢ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል። ፕሮሚስ ዴቪድ የካናዳን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል። ውጤቱን ተከትሎ ስዊዘርላንድ በሰባት ነጥብ የምድቡ መሪ በመሆን ወደ ጥሎ ማለፉ ገብታለች። ከአዘጋጅ ሀገራት መካከል አንዷ የሆነችው ካናዳ በአራት ነጥብ ተመሳሳይ ነጥብ ያላትን ቦሲኒያ ሄርዞጎቪናን በግብ ክፍያ በልጣ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ በማጠናቀቅ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥሎ ማለፉን መግባቷን አረጋግጣለች። በዚሁ ምድብ በሲያትል ስታዲየም በተካሄደው ሌላኛው ጨዋታ ቦሲኒያ ሄርዞጎቪና ኳታርን 3 ለ 1 አሸንፋለች። ከሪም አላጅቤጎቪች፣ ኤርሚን ማህሚች እና የኳታሩ ሱልጣን አል ብሬክ በራሱ ላይ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። ሀሰን አል ሃይዶስ የኳታርን ብቸኛ ጎል አስቆጥሯል። ቦሲኒያ ሄርዞጎቪና በአራት ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ በምርጥ ሶስተኛነት ወደ ጥሎ ማለፍ ገብታለች። ኳታር በአንድ ነጥብ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ በመያዝ ከውድድሩ ተሰናብታለች።
አካባቢ ጥበቃ
የኢትዮጵያ ልዕልና በአረንጓዴው ከፍታ
Jun 25, 2026 568
(በዮርዳኖስ ዓባይነህ) የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከልና የተራቆቱ መሬቶችን መልሶ ለማልማት የጀመረችው ታሪካዊና አርአያነት ያለው ብሔራዊ ንቅናቄ ነው። ይህ ዘመቻ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ሕፃናት፣ ወጣቶች፣ አዋቂዎችና ልዩ ልዩ ተቋማት በነቂስ በመውጣት በየዓመቱ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞችን በከፍተኛ የሕዝብ ንቅናቄና በአንድነት መንፈስ ለመትከል ችለዋል። በዚህ ተከታታይ የችግኝ ተከላና እንክብካቤ ሥራ ምክንያት ለዓመታት ተራቁተው የነበሩ ተራራማና ኮረብታማ ቦታዎች እንዲሁም የሀገሪቱ የደን ሽፋን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲያገግም ሆኗል፤ ይህም የአፈር መሸርሸርን ከመከላከል ባለፈ የከርሰ-ምድር ውሃ መጠን እንዲጨምር ተጨባጭ አስተዋጽኦ አበርክቷል። አካባቢን ከመጠበቅ ባሻገር፣ መርሃ-ግብሩ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን የፍራፍሬ፣ የቡናና የቅመማ ቅመም ችግኞችን በማካተት አርሶ አደሩ ተጨማሪ ገቢ እንዲያገኝና የምግብ ዋስትናው እንዲረጋገጥ ትልቅ የኢኮኖሚ በር ከፍቷል። በተጨማሪም በዋና ዋና ከተሞች የተገነቡት ውብ አረንጓዴ ፓርኮች ከተሞችን ለነዋሪዎች ምቹ፣ ንጹህና ማራኪ ከማድረጋቸውም በላይ ተመራጭ የቱሪስት መዳረሻ እየሆኑ ይገኛሉ። በአጠቃላይ የኢትዮጵያ አረንጓዴ አሻራ ለአሁኑ ትውልድ የኢኮኖሚ ዋስትናን፣ ለወደፊቱ ደግሞ የተስተካከለ የአየር ንብረትና ለምለም ሀገርን የሚያስረክብ ታላቅ የትውልድ ቅርስ በመሆኑ፣ የተተከሉትን ችግኞች ተንከባክቦ ማሳደግና ዘላቂነታቸውን ማረጋገጥ የሁላችንም የጋራ ኃላፊነት ነው። 👉ከተፈጥሮ ጋር የተጻረረው የሰው ልጅ ስልጣኔ የሰው ልጅ በምድር ላይ መኖር ከጀመረበት ጥንታዊ ዘመን አንስቶ በሕይወት ለመቀጠልና ሕልውናውን ለማረጋገጥ ከተፈጥሮ ብሎም ከመሰሎቹ ጋር ጠንካራ እና ቀጣይነት ያለው መስተጋብር ሲያደርግ ቆይቷል። ነገር ግን ይህ መስተጋብር ሚዛኑን እየሳተ መጥቶ፣ ከጥንቱ የግብርና ስልጣኔ እስከ ዛሬው የኢንዱስትሪ መስፋፋት ድረስ በሰው ልጅ እጅ የተፈጸመው የተፈጥሮ መራቆት በምድር ላይ ከባድ ጠባሳ ጥሏል። የደን መጨፍጨፍ፣ የአፈር መሸርሸር እና የውሃ አካላት መናመን የዚሁ አውዳሚ ጉዞ ውጤቶች ናቸው። አግባብ ያለው የአካባቢ ጥበቃ ባለመደረጉም፣ በቢሊዮን የሚቆጠሩ አዕዋፋትና የዱር እንስሳት ለዘመናት ከኖሩበትና ለነሱ ከሚስማማቸው ቀያቸው ለመሰደድ ተገድደዋል። የተባበሩት መንግስታት የምግብ እና ግብርና ድርጅት (FAO) በ2016 እ.ኤ.አ ባወጣው ጥናት መሠረት፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ 92 ሺህ ሄክታር ደን ይጨፈጨፋል። ለዚህም የእርሻ መሬት ማስፋፋትና የማገዶ ፍላጎት መጨመር በዋና ምክንያትነት ይጠቀሳሉ። ይህ የዓለም አቀፍ ስጋት ለሀገራችን ለኢትዮጵያ ደግሞ የራቀ ሳይሆን የውስጥ ቁስል ነበር። በደን መጨፍጨፍና በአፈር መሸርሸር ምክንያት በተደጋጋሚ የተከሰቱት የድርቅ፣ የረሃብ፣ የመሬት መንሸራተት እና የሕዝቦች መፈናቀል ታሪኮች የቅርብ ጊዜ ትዝታዎቻችን ናቸው። 👉የ"ክፉ ቀን" ትርክት እና የስነ-ልቦና ጠባሳ ከ1888 እስከ 1892 እ.ኤ.አ በሀገራችን የተከሰተውና '’ክፉ ቀን'’ ተብሎ የሚታወቀው አሰቃቂ የረሃብ ታሪክ ፣ ከዚያም በኋላ በወሎና በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የታዩት ድርቆች በዓለም መገናኛ ብዙሃን ጎልተው ሲዘገቡ ቆይተዋል። ይህ አሳዛኝ ክስተት ለውጭ መገናኛ ብዙሃንና ተቋማት ተጨማሪ ዝና እና ገቢ ማግኛ ሰበብ ሲሆን፣ ለሕዝባችን ግን ለዘመናት ያልተሻረ የስነ-ልቦና ቁስል ጥሎ አልፏል። ኢትዮጵያን በዓለም መድረክ የድህነት እና የረሃብ ተምሳሌት አድርጎ በመሳል፣ ኢትዮጵያውያንን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን አንገት ያስደፋ ጥቁር ታሪክ ሆኖ ኖሯል። ታዲያ ይህንን የውርደት ትርክት የሚቀይር፣ ሀገራዊ ክብርን የሚመልስና ቀጣይነት ያለው የአካባቢ ጥበቃን የሚያረጋግጥ ወሳኝ እርምጃ መውሰድ የህልውና ጉዳይ ነበር። 👉አረንጓዴ አሻራ፦ ተግዳሮቶችን የመለወጥ የፅናት ጉዞ በ2011 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሃሳብ አመንጪነት፣ በተቋማት ቅንጅትና በተደራጀ የሕዝብ ንቅናቄ "የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር" ተጀመረ። በመጀመሪያው ዓመት “40 ዛፎች በነፍስ ወከፍ” በሚል መሪ ሃሳብ የተጀመረው ዘመቻ፣ ከዕቅድ በላይ 18 በመቶ ስኬት በማስመዝገብ የሕዝቡን የልማት ጥም አሳየ። በሁለተኛው ዓመት (2012 ዓ.ም) ዓለምን ያሸበረው የኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ወረርሽኝ ቢከሰትና ማኅበራዊ መራራቅ፣ ጥንቃቄዎች እንዲሁም ከቤት ሆኖ መሥራት ግዴታ ቢሆንም፣ የኢትዮጵያውያን የአረንጓዴ ጉዞ አልተገታም። “እየተጠነቀቅን እንተክላለን” በሚል መሪ ሐሳብ ፣ ማኅበረሰቡ ደህንነቱን ጠብቆ በመንቀሳቀሱ ከዕቅድ በላይ 14 በመቶ ችግኝ መትከል ተችሏል። 👉የሰባት ዓመታት ስኬቶች በቁጥር እና የስነ-ምህዳር መነቃቃት ይህ ስራ ለአንድና ለሁለት ዓመት የተደረገ ዘመቻ ሳይሆን የሰባት ዓመታት ተከታታይ የፅናት ጉዞ ነበር። ከ2011 እስከ 2017 ዓ.ም ባሉት ዓመታት ውስጥ በአጠቃላይ ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞች በኢትዮጵያ ምድር ላይ ተተክለዋል። የችግኞቹ የስብጥር ይዘትም ስልታዊ የደን ልማትን ያሳያል፦ 60 በመቶ የጥምር እርሻ ደን (Agroforestry) 35 በመቶ የተፈጥሮ ደን ሽፋን 5 በመቶ የከተማ ውበት ዛፎች ከተከናወኑት የክትትልና ቁጥጥር ሪፖርቶች መረዳት እንደሚቻለው፣ ከተተከሉት ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞች ውስጥ በአማካይ ከ75 በመቶ እስከ 80 በመቶ በላይ የመፅደቅ መጠን (Survival Rate) ማሳየት መቻላቸው የሥራውን ውጤታማነት በተጨባጭ ያረጋግጣል። ይህ መጠነ-ሰፊ ስራ ቀደም ሲል ከ2010 እስከ 2016 ዓ.ም ይከሰት የነበረውን የደን መጨፍጨፍ በ65 ሺህ ሄክታር በመቀነስ፣ የሀገሪቱን የደን ሽፋን በ11 ነጥብ 4 በመቶ ከፍ እንዲል አድርጓል። የተከናወነው የተቀናጀ የልማት ስራ የአፈር መሸርሸርን በመቀነስና የውሃ አካላትን በማንሰራራት ረገድ ትልቅ ሚና ተጫውቷል። ይህ የደን ሽፋን ዕድገት ሀገሪቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከካርቦን ሽያጭ (Carbon Trading) እና ከአየር ንብረት አረንጓዴ ፋይናንስ (Green Finance) ልታገኝ የምትችለውን የኢኮኖሚ ዕድል በከፍተኛ ደረጃ የሚያሰፋላት ነው። 👉ከስነ-ምህዳር ጥበቃ ወደ ቢሊዮን ዶላር ኢኮኖሚ ግንባታ እና የኮሪደር ልማት የአረንጓዴ አሻራ ስኬት ስነ-ምህዳሩን በማደስ ብቻ አልተገደበም፤ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ የጀርባ አጥንትም ጭምር ቀይሯል። መሬትን የማከምና የአፈር እርጥበትን የመመለስ ስራው በ2017 ዓ.ም 280 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ በሀገር ውስጥ ለማምረት አስችሏል። ይህ ውጤት ኢትዮጵያ ቀደም ሲል ለስንዴ ማስመጫ ታወጣ የነበረውን አንድ ቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ሙሉ በሙሉ ማስቀረት ያስቻለ ታሪካዊ ምዕራፍ ነው። በተጨማሪም ይህ አረንጓዴ ልማት ኢትዮጵያን በአፍሪካ 2ኛዋ የአቮካዶ ምርት ላኪ ሀገር ያደረጋት ሲሆን፣ በ2017 ዓ.ም የቡና ምርትን በማስፋፋትና ጥራትን በመጨመር 2 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ታሪካዊ የውጭ ምንዛሪ ለማስመዝገብ አስችሏል። ይህ ታላቅ ስኬት የተገኘው የኢኮ-ሲስተም ልማትን፣ የገጠር ልማትን፣ የወንዝ ዳርቻ ልማትን እና የከተማ ኮሪደር ልማትን (Urban Corridor Integration) ባካተተ የተቀናጀ ስትራቴጂ ነው። በተለይም በአዲስ አበባና በተለያዩ ከተሞች የተከናወኑት የኮሪደር ልማት ስራዎች የከተማዋን ገጽታ በከፍተኛ ደረጃ ከመቀየር ባለፈ፣ ለነዋሪዎች ምቹና ሰፊ የእግር መንገዶችን፣ ማራኪ የአረንጓዴ ስፍራዎችንና መናፈሻዎችን በመፍጠር ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገር ጎብኚዎች ደህንነቱ የተጠበቀና ማራኪ የከተማ ቱሪዝም (Eco-tourism) መዳረሻዎችን በተግባር መፍጠር ችሏል። 👉የአረንጓዴ ዲፕሎማሲ መሪነት እና ዓለም አቀፍ እውቅና ይህ ንቅናቄ በሀገር ውስጥ ካለው ፋይዳ ባለፈ፣ ኢትዮጵያ በአህጉራዊና በዓለም አቀፍ ደረጃ "የአረንጓዴ ዲፕሎማሲ" መሪ እንድትሆን አድርጓታል። እንደ ኤርትራ፣ ጅቡቲ፣ ፓኪስታን፣ ደቡብ ሱዳን እና ሩዋንዳ ያሉ ሀገራት ከኢትዮጵያ ተሞክሮ በመቅሰም በሀገራቸው የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር መጀመራቸው የዚህ ማሳያ ነው። በተጨማሪም የዓለም ምግብና ግብርና ድርጅት (FAO) ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የ"አግሪፎድ ሻምፒዮን" እና "የላቀ የአፍሪካ አመራር ሽልማት" መስጠቱ ፣ ኢትዮጵያ 2ኛውን የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ምግብ ጉባኤን ማስተናገዷ እና በ80ኛው የፋኦ ጉባኤ ላይ ለሀገሪቱ አጠቃላይ ዕድገት የተሰጠው እውቅና የዓለምን አድናቆት ያረጋገጡ ክስተቶች ናቸው። እነዚህ ዓለም አቀፍ ምስክርነቶች ኢትዮጵያ ቀደም ሲል ተስሎባት የነበረውን የድርቅ እና የረሃብ አፍራሽ ትርክት በአረንጓዴ ልማት፣ በአንድነት እና በምርታማነት በተግባር የቀለበሰችበት ታላቅ ድል ነው። 👉ስምንተኛው ዙር የአረንጓዴ ዐሻራ፡ "ተስፋን እንትከል!" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዲ ሐይቅ የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ማስጀመራቸው ይታወቃል። መርሃ ግብሩ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ሉዓላዊነትና ብልፅግና አሰናስሎ የሚያረጋግጥ ብሔራዊ የልማት አቅጣጫ መሆኑ ተመስክሮለታል። የዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ ዘመቻ "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ሐሳብ መጀመሩ ጥልቅ ትርጉም አለው። ተስፋ የነገን ብሩህ ምዕራፍ ዛሬ ላይ ለመጻፍ የሚያስችል አረንጓዴ መቀነት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉትም፤ አረንጓዴ ዐሻራ አፈራችንን ከስደት፣ የታላቁን ህዳሴ ግድባችንን ደግሞ ከደለል የሚታደግ ብሔራዊ ጋሻ ሆኗል። የአባቶቻችን የዓድዋ ድል ወራሪን ያሳፈረ ታላቅ ገድል እንደነበረ ሁሉ፣ የአሁኑ ትውልድ በአረንጓዴ ዐሻራ እያከናወነ ያለው ተግባርም ለቀጣዩ ትውልድ የሚሻገር አዲስ የታሪክ ገድል እየሆነ ይገኛል። ይህ ንቅናቄ የሀገሪቱን የተረጂነት ታሪክ ወደ ማድረግና ራስን ወደ መቻል ዘመን የሚያሸጋግር የመደመር መርህ መገለጫ ነው። የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ዐሻራ ጉዞ ቁጥራዊ መረጃዎች የህዝብ ቁርጠኝነት ማሳያ ናቸው። ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን ከ48 ቢሊየን በላይ ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ያላቸው ችግኞች ተተክለዋል። በዘንድሮው መርሃ ግብር ደግሞ ከ8 ቢሊየን በላይ ችግኞችን ለመትከል የታቀደ ሲሆን፤ ይህም አጠቃላይ የተተከሉትን ችግኞች ቁጥር ወደ 56 ቢሊየን ያደርሰዋል። ይህ ታላቅ ስኬት እዚህ ላይ አያበቃም፤ ሀገሪቱ በፈረንጆቹ 2029 የሚካሄደውን የዓለም አቀፉን የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (COP32) ስታስተናግድ፣ በአጠቃላይ 65 ቢሊየን ችግኞችን መትከል የቻለች መሪ ሀገር መሆኗን ለዓለም የምታበስርበት ታሪካዊ ምዕራፍ ይሆናል። በክረምቱ ወራት እያንዳንዱ ዜጋ "ተስፋን በመትከል" የዓድዋን የኩራት ስሜት በአረንጓዴ ልማት ሊደግመው ይገባል። የበለፀገችና የተከበረች ኢትዮጵያን ለቀጣዩ ትውልድ ለማስረከብ፣ የተተከሉትን ችግኞች ተንከባክቦ ማሳደግና የአረንጓዴ ዐሻራን ስኬት ማስፋትና ማስቀጠል የዛሬው ትውልድ የማይታጠፍ ብሔራዊ ጥሪ ነው። 👉የወደፊት ስትራቴጂካዊ አቅጣጫዎች በኢትዮጵያ እስከአሁን የተመዘገቡ ስኬቶችን ዘላቂ ለማድረግና የተፈጥሮ ቅርሶቻችንን ይበልጥ ለማጠናከር የወደፊት የትኩረት አቅጣጫዎች በግልጽ ተቀምጠዋል። መንግሥት የልማቱን የሕዝብ ባለቤትነት ማረጋገጥና ማቀናጀት፣ አረንጓዴ ልማትን እንደ ባህል መገንባት፣ የቴክኖሎጂ እሴቶችን በመጠቀም የሥራ ዕድሎችን ማስፋፋት፣ በተፈጥሮ ሀብት ላይ የሚደረገውን ጫና መቀነስ፣ እንዲሁም አዲስ የተገነቡ የኮሪደር ልማቶችንና ፓርኮችን በመጠበቅ የጎብኝዎችን ደህንነት ማረጋገጥና የተፈጥሮ ቅርስን አብሮ ማጠናከር ላይ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጧል።
በክልሉ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ አግዟል-ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ
Jun 25, 2026 193
ሀዋሳ፤ ሰኔ 18/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር የግብርና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ድርሻ ማበርከቱን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ገለጹ ። የሲዳማ ክልል የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር ዛሬ በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የጨፋ ሲኔ ቀበሌ ተጀምሯል። በመርሀ ግብሩ ማስጀመሪያ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ እንዳሉት፤ በክልሉ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር የግብርና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና አየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቋቋም አግዟል። በዘንድሮ ክረምትም ተግባሩን ለማስቀጠል የችግኝ ተከላ እና የእንክብካቤ ስራን ማጠናከር እንደሚገባ አሳስበዋል። የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ መምሩ ሞኬ በበኩላቸው፤ አረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ከቡና፣ ፍራፍሬ ልማትና ከሥራ ዕድል ፈጠራ ጋር በመተሳሰሩ የአርሶ አደሮች ምርታማነትና ተጠቃሚነት እያደገ መጥቷል። የፍራፍሬ ልማቱን ከግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎች ጋር በማስተሳሰር የአርሶ አደሩን የገበያ አማራጭ ማስፋት እንደተቻለም ጠቁመዋል። በተለያዩ ምክንያቶች የተራቆቱ አካባቢዎች በአረንጓዴ አሻራ ልማት እንዲያገግሙ መደረጉ የተደራጁ ወጣቶች በንብ ማነብ ሥራ ተሰማርተው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረጉንም ተናግረዋል። በሀዋሳ ከተማ አረንጓዴ አሻራን ከኮሪደር እና ከሀዋሳ ሐይቅ ዳርቻ ልማት ጋር እንዲተሳሰር መደረጉን የተናገሩት ደግሞ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጥራቱ በየነ ናቸው። በዚህም የሃዋሳ ከተማን የብልጽግና ተምስሌት ለማድረግ የተጀመሩ ሥራዎች ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆኑ ተፈጥሮን በመጠበቅና በመንከባከብ ሥራ ህብረተሰቡን በንቃት ለማሳተፍ እየተሰራ ነው ብለዋል። በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ቱላ ክፍለ ከተማ የጨፋ ሲኔ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ብርሀኑ ሻፋሞ እንዳሉት፤ ቀደም ባሉት ዓመታት ለተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ትኩረት ሳይሰጥ ቆይቷል። ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ለተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ በተሰጠ ትኩረት በአካባቢያቸው ላይ ተጨባጭ ለውጥ ማየታቸውን ገልጸው፣ በአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር የመጣውን ውጤት ለማስቀጠል በዛሬው የችግኝ ተከላ መርሀግብር ላይ መገኘታቸውን ተናግረዋል። ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ በተፋሰስ ልማት ሥራ እርከን በመስራትና በአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በተተከሉ ችግኞች የተራቆቱ መሬቶች ጭምር አገግመው ምርት መስጠት እንደቻሉ ገልጸዋል።
በዞኑ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የሚተከሉትን ችግኞች የመንከባከብ ስራ ትኩረት ተሰጥቶታል
Jun 25, 2026 225
ግምቢ፤ ሰኔ 18/2018 (ኢዜአ):-በምዕራብ ወለጋ ዞን በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የሚተከሉትን ችግኞች ለመንከባከብ ስራ ትኩረት መሰጠቱን የዞኑ አስተዳደር ገለጸ። የምዕራብ ወለጋ ዞን አመራሮች እና የዞኑ ነዋሪዎች የተሳተፉበት የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በመንዲ ከተማ ዛሬ ተጀምሯል። የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ተሊላ ተረፈ እንዳሉት፤ የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄን ስኬታማ ለማድረግ የተተከሉ ችግኞችን በአግባቡ መንከባከብ ከሁሉም ይጠበቃል። ለመርሃ ግብሩ ስኬታማነትም እንደ ዞን በቂ የችግኝ ዝግጅት፣ ተገቢው የቦታ መረጣ እና የችግኝ መትከያ ጉድጓድ መቆፈሩን ገልጸዋል። በዘንድሮው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ከተዘጋጁት 328 ሚሊዮን ችግኞች ውስጥ ለምግብነት እና ለገቢ ምንጭ የሚያገለግሉ የፍራፍሬ፣ የቡና እና የእንስሳት መኖ ችግኞች ከፍተኛ ትኩረት የተሰጣቸው መሆኑን አቶ ተሊላ አስገንዝበዋል። ባለፉት ዓመታት በመርሃ ግብሩ የተተከሉ ችግኞች አብዛኛዎቹ ጸድቀው ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታ ማስገኘታቸውንም ዋና አስተዳዳሪው አረጋግጠዋል። ከመርሃ ግብሩ ተሳታፊዎች መካከል አባገዳ አምቢሳ ሊካሳ በሰጡት አስተያየት፤ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ችግኞችን እንደ ሰው ልጅ ተንከባክቦ ማሳደግ የትውልዱ ኃላፊነት ሊሆን ይገባል ብለዋል። በየዓመቱ አሻራቸውን በማኖራቸው ልዩ ደስታ እንደሚሰጣቸው ገልጸው፣ ችግኞችን ከመትከል ባሻገር የጽድቀት ሂደታቸውን በአግባቡ እንደሚከታተሉም ተናግረዋል። አቶ ኤሊያስ ቱቾ በበኩላቸው፤ ችግኝ መትከል በርካታ ጠቀሜታ እንዳለው በመገንዘብ በችግኝ ተከላው እየተሳተፉ መሆኑን ገልጸዋል። በየዓመቱ በችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ የተናገረው ደግሞ ወጣት ኩርፈሳ ኦልጂራ ነው። በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸውን ከ200 በላይ የፍራፍሬ ችግኞችን በግሉ ለመትከል ማቀዱንም ጠቁሟል።
ችግኞችን አዘጋጅተን በማቅረብ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታችን አድጓል-ወጣቶች
Jun 25, 2026 239
ሀዋሳ፤ ሰኔ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሲዳማ ክልል ለአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብርና ለኮሪደር ልማት የተለያየ ጠቀሜታ ያላቸውን ችግኞች አዘጋጅተው በማቅረብ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን እያሳደጉ መሆኑን በችግኝ ብዜት ሥራ የተሰማሩ ወጣቶች ተናገሩ። በክልሉ የተለያየ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች አዘጋጅተው በማቅረብ ሥራ ላይ የተሰማሩ ወጣቶች ከኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸው ባለፈ የተራቆቱ መሬቶች እንዲያገግሙም በማድረግ በኩልም አስተዋጾ እያደረጉ ነው። በተለይ ለአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ስኬታማነት ወጣቶች በማህበር ተደራጅተው ችግኞችን እያቀረቡና የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እየሆኑም መጥተዋል። በማህበር ተደራጅተው የፍራፍሬ፣ የውበትና የጥላ ዛፍ ችግኞችን አዘጋጅተው በማቅረብ ተጠቃሚ ከሆኑ ወጣቶች መካከል የድሪመርስ ላንድ ስኬፒንግና ሲድሊንግ ማህበር አባላት ይገኙበታል። የማህበሩ ሥራ እስኪያጅ ኮከብ ቢያድግልኝ (ዶ/ር) አምስት ሆነው በ50 ሺህ ብር መነሻ ካፒታል የችግኝ ማፍላትና ማቅረብ ሥራቸውን ጀምረው በአሁኑ ወቅት ካፒታላቸውን 500 ሺህ ብር ማድረስ ችለዋል። በስራቸው የማህበሩ አባላት ተጠቃሚነት እያደገ መምጣቱን የገለጸችው ኮከብ (ዶ/ር)፣ በአሁኑ ወቅትም ለሌሎች አምስት ሰዎች የሥራ ዕድል መፍጠር እንደቻሉም ተናግራለች። በማህበሩ የሥራ ዕድል ከተፈጠረላቸው ወጣቶች መካከል ወጣት ባዩ በየነ እንዳለው፣ በማህበሩ በተፈጠረለት የሥራ ዕድል ገቢ እያገኘ ራሱን ማስተዳደር ችሏል። የሲዳማ ክልል የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ምክትል ሀላፊ አበባየሁ በየነ እንዳሉት፣ በክልሉ በየዓመቱ በአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር የተለያዩ ችግኞችን በመትከል የተራቆቱ አካባቢዎች መልሰው እንዲያገግሙና የግብርና ምርታማነት እንዲጨምር ለማድረግ እየተሰራ ነው። በዘንድሮው የክረምት አረንጓዴ አሻራ መረሀ ግብር የፍራፍሬ፣ የቡና፣ የቀርከሃና ሌሎች አገር በቀል ዝርያ ያላቸው ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት ተደርጎ ወደተግባር መገባቱን ገልጸዋል። በክልሉ በክረምት የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎችን ለማሳተፍ መታቀዱን ጠቅሰዋል። ለተከላ ከተዘጋጁት ችግኞች ውስጥ አቮካዶ፣ አፕል፣ ማንጎ፣ ቡናና ሌሎች የፍራፍሬ ችግኞች እንዲሁም ቀርከሀ፣ ቀረሮ፣ ዋንዛና መሰል ሀገር በቀል ችግኞች ይተከላሉ ብለዋል። ችግኞቹ በ316 የመንግስት፣ የማህበራትና አርሶ አደሮች የችግኝ ጣቢያዎች መዘጋጀታቸውን የተናገሩት አቶ አበባየሁ፣ ይህም አርሶ አደሩ ተጨማሪ ገቢ እንዲያገኝ ከማድረግ ባለፈ ለሥራ ዕድል ፈጠራና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ያስችላል ብለዋል። በአረንጓዴ አሻራ የሚተከሉት የፍራፍሬ ችግኞች በቀጣይ ለምርት ሲደርሱ ለኢንዱስትሪ ፓርክ ግብዓት እንዲሆኑ ታስቦ የተዘጋጁ መሆኑንም ገልጸዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የአፍሪካን አንድነት የበለጠ በማጎልበት የበለፀገች አህጉር መገንባት አለብን-መሐሙድ አሊ ዩሱፍ
May 25, 2026 12169
አዲስ አበባ፤ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፦የአፍሪካን አንድነት የበለጠ በማጎልበት የበለፀገች አህጉር መገንባት እንደሚያስፈልግ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። 63ኛው የአፍሪካ ቀን ''የ63 ዓመታትን ዓመታት አንድነት፣ ትስስርና ልማት፤ አብረን እናክብር” በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት ቅጥር ግቢ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል። በዝግጅቱም የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሀደራ አበራ ጨምሮ የሕብረቱ አባል ሀገራት ዲፕሎማቶችና ተጋባዥ እንግዶች ታድመዋል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ አፍሪካ በዓለም መድረክ ያላት ሚና በየ ጊዜው እየታደሰ መምጣቱን ገልጸዋል። የአህጉሪቷ የሕዝብ ቁጥርና የኢኮኖሚ ዕድገትም በጥቂት ዓመታት ውስጥ የአፍሪካን ጥቅል የሀገር ውስጥ ዕድገት ምጣኔ 10 ትሪሊዮን ዶላር ያደርሰዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል። የአፍሪካ ወጣቶችም ሌሎች አህጉራት ጭምር የሚመኟቸው የአህጉሪቷ ዕድገትና ብልፅግና አቅም መሆናቸውን አንስተዋል። በቀጣይም የአፍሪካዊያንን የአንድነት ኃይል የበለጠ በማጎልበት የአህጉሪቱን ዕምቅ ፀጋዎች ለሁለንተናዊ ዕድገትና ብልፅግና መቀየር እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሀደራ አበራ በበኩላቸው፥የአፍሪካዊያን ባህልና ዕሴት ለአህጉሪቷ መፃኢ ዕድል፣ ዕድገትና ብልፅግና የሚተርፍ የጥንካሬ ምንጭ ነው ብለዋል። የአፍሪካን የትብብር አቅም በማጎልበት የአህጉሪቷ ዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥና የራስን የተሻለ ዕድል መቅረፅ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። ለዚህም በሁሉም ዘርፍ የአፍሪካን የኢኮኖሚ ዕድገት በማስፋት የአህጉሪቱን ዕምቅ የልማት ፀጋ ወደ ዘላቂ ብልፅግና መቀየር እንደሚገባ ተናግረዋል። በአህጉሪቷ ላይ የደረሱ በደሎች ፍትሕ እንዲያገኙ ከማድረግ ባሻገርም ለአጀንዳ 2063 ስኬት በቁርጠኝነት በመስራት የወደፊት እጣ ፋንታ መወሰን እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል። በየዓመቱ የአፍሪካ ቀን መከበር የጀመረው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የአሁን የአፍሪካ ህብረት እ.ኤ.አ በ1963 መመስረቱን እንደሆነ ይታወቃል። የዘንድሮው የአፍሪካ ቀንም የህብረቱ ኮሚሽን ከህብረቱ ሰራተኞች ማኅበር፣ አባል ሀገራት፣ ከህብረቱ አደረጃጀቶችና ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማህበረሰቦች ጋር በመተባበር ተዘጋጅቷል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
የአፍሪካ ሕብረት ለታዳጊው ዓለም የፍትህ ድምፅ እና ለባለብዙ ወገን ግንኙነት ዋነኛ መገለጫ ነው
May 13, 2026 8744
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ሕብረት ለታዳጊው ዓለም የፍትህ ድምፅ እና ለባለብዙ ወገን ግንኙነት ዋነኛ መገለጫ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ገለጹ፡፡ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሰላም፣ በጸጥታ፣ በዘላቂ ልማት እና በሰብአዊ መብቶች ዙሪያ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ተቋማዊ ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቱን የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ፈርመውታል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በዚሁ ወቅት በሰጡት መግለጫ፣ የአፍሪካ ህብረት ለታዳጊው ዓለም የፍትህ ድምፅ እና ለባለብዙ ወገን ግንኙነት ዋነኛ መገለጫ መሆኑን ገልጸዋል። አጋርነታቸውን ይበልጥ ተቋማዊ የሚያደርገው ይህ ስምምነት በቁልፍ ዘርፎች ላይ የተመዘገቡ ስኬቶችንና የወደፊት ዕቅዶችን መነሻ ያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል። አፍሪካ በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ በቋሚ አባልነት አለመካተቷን ታሪካዊ ኢ-ፍትሃዊነት ነው ያሉት ዋና ጸሐፊው፣ ይህም የምክር ቤቱን ተቀባይነትና ውጤታማነት እንደሚጎዳው አስገንዝበዋል። በተጨማሪም ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት ሊስተካከል እንደሚገባ ጠቅሰው አፍሪካ ከጥሬ ዕቃ አቅራቢነት ወጥታ ለአረንጓዴ ኢነርጂ ሽግግር የማምረቻና የማጣሪያ ማዕከል መሆን እንዳለባት ጠቁመዋል፡፡ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በበኩላቸው፣ የአፍሪካ ህብረት የ2063 አጀንዳ እና የተባበሩት መንግሥታት የ2030 አጀንዳ የተጣጣሙ መሆናቸውን ገልጸዋል። በአፍሪካ ቀንድ ያሉ ፈተናዎችን ለመፍታት በቅርበት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት ማሻሻያ ተደርጎ የአፍሪካ ሀብቶች ጥቅም ላይ እንዲውሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በናይሮቢ የተካሄደው የ"አፍሪካ ፎርዋርድ" (Africa Forward) ጉባኤ ውጤቶች ክትትል እንዲደረግባቸው አሳስበዋል፡፡ አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብትን ጨምሮ ቋሚ መቀመጫና ፍትሃዊ ውክልና እንዲኖራት የሚለውን የአህጉሪቱን ጥያቄ በድጋሚ አረጋግጠዋል። ይህ ስምምነት በሁለቱ ድርጅቶች መካከል ያለውን ስልታዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው ይጠበቃል። 10ኛው የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የከፍተኛ ደረጃ ውይይት ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄዱ ይታወቃል፡፡
አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራት ማድረግ የዓለም አቀፍ ተቋማትን ኢ-ፍትሐዊነት የሚያንጸባርቅ ነው
May 13, 2026 7563
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018(ኢዜአ)፦ አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራት ማድረግ የዓለም አቀፍ ተቋማትን ኢ-ፍትሐዊነት የሚያንጸባርቅ ተግባር መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ገለጹ። የአፍሪካ ሕብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 10ኛ ዓመታዊ ኮንፍረንስ በአፍሪካ ሕብረት እየተካሄደ ነው። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ የመንግስታቱ ድርጅት በሁሉም ዘርፎች ቀዳሚ ተግባር አፍሪካን የማድረግ የፖለቲካም ሆነ የሞራል ግዴታ አለበት። አፍሪካ አህጉራዊ ግጭቶችን በማርገብ፣ አህጉራዊ ዕድገትና ብልፅግናን ለማረጋገጥ የምታደርገው ጥረት የሚደነቅ መሆኑን በመግለጽ፤ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣናና ሌሎች የሰላምና ጸጥታ ኢኒሼቲቮች አስደናቂ መሆናቸውን ገልጸዋል። አፍሪካ በዓለም ሁለንተናዊ እንቅስቀሴ ላይ ያላት ሚና የጎላ መሆኑን እንገነዘባለን ያሉት ዋና ጸሀፊው፤ በታሪክና በዓለም ኢ-ፍትሐዊ አሰራር የደረሰባትን በደል ለመቀልበስ የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ከቅኝ ግዛት ባልወጡበት ወቅት የተቋቋሙ ዓለም አቀፍ ተቋማት አህጉሪቱ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራት ማድረጋቸው ተገቢ አለመሆኑን ገልጸዋል። አፍሪካ ባልተሳተፈችበት የተቋቋሙ የዓለም አቀፍ ተቋማት ኢ-ፍትሐዊነት አፍሪካን ብዙ አሳጥቷታል ያሉት ዋና ጸሀፊው፤ አፍሪካዊ ችግሮችን በአፍሪካ ለመፍታት የተጀመሩ ኢንሼቲቮችን መደገፍ እንደሚገባ ተናግረዋል። የመንግሥታቱ ድርጅት አፍሪካዊ ግጭቶች በአፍሪካ ማዕቀፍ እንዲፈቱ በመሪነት ከመሳተፍ ባለፈ የአፍሪካ ሕብረትን ጥረት እንደሚደግፍ ጠቁመዋል። አፍሪካ በወሳኝ ማዕድናትና በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ትልቅ አቅም እንዳላት ገልጸው፤ ሀብቷን እሴት በመጨመር ለዓለም ገበያ የምታቀርብበትን መንገድ መቀየስ ይገባል ብለዋል።
አፍሪካ ለ2030 እና አጀንዳ 2063 ግቦች የሚያስፈልጋትን የልማት ፋይናንስ ለማግኘት የራሷን የብድር ደረጃ መመጠኛ ተቋም ለማቋቋም ወሰነች
May 13, 2026 7460
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018(ኢዜአ)፦ አፍሪካ ለ2030 እና አጀንዳ 2063 ግቦች የሚያስፈልጋትን የልማት ፋይናንስ ለማግኘት የተዛባውን የዓለም የፋይናንስ ስርዓት የሚያጣጥም የራሷን የብድር ደረጃ መመጠኛ ተቋም (African Rating Agency) ለማቋቋም መወሰኗን የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። የአፍሪካ ሕብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 10ኛ ዓመታዊ ኮንፍረንስ በአፍሪካ ሕብረት አዳራሽ እየተካሄደ ነው። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ መድረኩ በአፍሪካ ሰላምና ጸጥታ፣ ዘላቂ ልማት፣ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ አስተዳደርና በተለዋዋጭ ዓለም የአፍሪካ ፈተናዎች ዙሪያ የሚያተኩር ነው። የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነትን ጨምሮ የዓለም ነባራዊ ሁኔታ በአሕጉሪቱ ላይ የሚያደርሰውን ተፅዕኖ ለመቋቋም የሚደረግ ጥረት ቢኖርም በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች የሚሰቃዩበትና የሚሰደዱበት አስቸጋሪ ሁኔታ ተፈጥሯል ብለዋል። ይሄውም በአፍሪካ አስተማማኝና ዘላቂ መፍትሔ ለማበጀት በሚደረገው ጥረት ላይ እንቅፋት እየፈጠረ መሆኑን በመጥቀስ፣ ከጸጥታ ባለፈ በመልካም አስተዳደር፣ በልማትና የማይበገር ኢኮኖሚ በመገንባት አስቻይ ሁኔታ መፍጠር እንደሚገባ ገልጸዋል። በአፍሪካ የልማት ፋይናንስ አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑን የገለጹት የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር፤ ዓለም አቀፉ የፋይናንስ አስተዳደር የአጀንዳ 2063 እና 2030 ግቦችን ለማሳካት እንቅፋት ፈጥሯል ብለዋል። በተለይም ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የተቋቋሙና አሁንም ያለው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ስርዓት ለአፍሪካ ፍላጎትና እውነታ ምላሽ የማይሰጥ መሆኑንም ተናግረዋል። በመሆኑም አፍሪካን ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ ስርዓት ጋር ለማጣጣም የራሷን የብድር ደረጃ መመጠኛ ተቋም (Africa Rating Agency) ለማቋቋም መወሰኗን ገልጸዋል። ይሄውም የአፍሪካ ሕብረት በጉዳዩ ላይ በጥልቀት ሲሰራ ቆይቶ እ.አ.አ በመጪው ሰኔ ወር 2026 በሞሪሼስ በይፋ እንደሚጀመር አስታውቀዋል። የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት በአፍሪካ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩን ገልጸው፤ በብዙ ሀገራት የምግብ ሸቀጦች ዋጋ ንሯል፤ በአንዳንድ ሀገራት የነዳጅ ዋጋ ከ100 እስከ 150 በመቶ ጨምሯል ነው ያሉት። የአፍሪካ ሕብረት ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጋር በትብብር ሲሰራ መቆየቱን በመጥቀስ፣ የእርስ በርስ ትብብሩን ለማጠናከር በቅርበት እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል። ሁለቱ ተቋማት አጋርነታቸውን ማጠናከር እንዳለባቸው በመግለጽ፤ በተቋማቱ መካከል ያለውን ዘርፈ ብዙ ትብብር ወደፊት ማሻገር ያስፈልጋል ብለዋል።
ሐተታዎች
ከተጽዕኖ ፈጣሪነትና ተደማጭነት መጎልበት እስከ የአኅጉር ድምጽ መሆን - የኢትዮጵያን ታላቅነት የገለጠው የዲፕሎማሲው ዘርፍ ስኬት
Jun 25, 2026 539
በዮሐንስ ደርበው ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲያዊ ጥረቷ የፓን አፍካኒዝም ንቅናቄን በማንሳት አኅጉራዊ ተቋማት እንዲመሠረቱ ፊታውራሪ ከመሆን ጀምሮ ለጎረቤቶቿ ሰላም ጉልኅ ሚና ተጫውታለች፤ አሁንም ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔን እያሰረጸች በርካቶች እንዲጋሯት አድርጋለች። እንደ ሀገር ከለውጡ መንግሥት ወዲህ ከተገኙ በርካታ ትላልቅ ስኬቶች መካከል በዲፕሎማሲው ዘርፍ የተመዘገበው አንዱ ነው። ትውልዱ ዛሬንም ነገንም በሚጠቅመው የአረንጓዴ ዐሻራ ኢኒሼቲቭ ንቁ ተሳታፊ መሆን ይጠበቅበታል እየተስፋፋ ያለው የጉበት ስብን (ቅባት) እንዴት መከላከል ይቻላል? ምክክር - ወደ መግባባት መሸጋገሪያው ድልድይ! የለውጡ መንግሥት የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ ዋነኛ መለኪያም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ነው። የኢትዮጵያ ሁኔታዎችን የማሰብ፣ የመፈለግና የመከወን ሂደት ንጥል (ለራስ ብቻ የሚል) ሳይሆን፤ በወንድማማችነት/እህትማማችነት ዕሳቤ በጋራ ማደግን ያነገበ ነው። ይህ ሂደቷም በበርካታ ሀገራት፣ ዓለም አቀፍ እንዲሁም አኅጉር አቀፍ ተቋማት ተወድሷል። በዚህም ሐሳቦቿ ቅቡል ሲሆኑ ተመልክተናል። ኢትዮጵያ የ#BRICS አባል መሆን መቻሏ አንዱ ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። ይህም ተሰሚነቷን ያረጋገጠ ማስረጃ ሲሆን፤ በኢኮኖሚ፣ በንግድ፣ ኢንቨስትመንትና ተያያዥ ጉዳዮች ዘርፈ-ብዙ ጥቅም በማስገኘት የበለጸገች ኢትየጵያን ዕውን የማድረግ ጉዞው ያፋጥናል። ወዲህ ደግሞ በተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት አባልና አፍሪካን በመወከል ምክትል ፕሬዚዳንት ሆና መመረጧም የአኅጉሪቱ ድምጽ መሆኗን ይነግረናል። ዓለም አቀፍ ብሎም አኅጉር አቀፍ የሆኑ በርካታ ኮንፈረንሶችም በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት እንዲካሄዱ መደረጉ አንድምታው ብዙ ነው። በብቃት ማስተናገዷ ደግሞ ሌላኛው ጥንካሬዋ። ሌላው የሀገራችንን የተጨበጠ የአረንጓዴ ዲፕሎማሲ ስኬት የሚገልጽልን፤ የዓለም የዓየር ንብረት ለውጥ ጉባዔን (COP32) እንድታዘጋጅ መመረጧ ነው። ይህን ትልቅ ዕድል በርካቶች ስለተመኙት አላገኙትም፤ ኢትዮጵያ ግን ዜጎቿን አስተባብራ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ቁርጠኛ አመራር ሰጭነት ባከናወነችው ያላሰለሰ ትጋት አግኝታዋለች። ግጭት ባለባቸው የቀጣናው ሀገራትም በመንግሥታቱ እንዲሁም በአፍሪካ ሕብረት ሥር ከምታበረክተው ከፍተኛ አስተዋጽዖ ባለፈ፤ በግሏ የሰራችው ብዙ ነው። ከራሷ አልፋ ለጎረቤቶቿ ዘብ መሆኗ፤ በአብሮነት መኖርን እና በጋራ ማደግን በተግባር የገለጠች ሀገርም ያደርጋታል። ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ በሚለው ቅድሚያ ለሀገር በቀል ዕውቀቶች በሩን ክፍት ባደረገው ትጋቷም፤ በበርካታ የአኅጉሪቱ ሀገራት ዘንድ ምሥጋና አስችሯታል። በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲዋም በተለያዩ ሀገራት በችግር ውስጥ የነበሩ ዜጎቿን ከሀገራቱ እና ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመነጋገር በተሳካ ሁኔታ ልጆቿን ወደ ዕቅፏ መልሳለች፤ በቅርቡ በሳዑዲ ዓረቢያ ለእስር ተዳርገው የነበሩ ኢትዮጵያውያን የፍርድ ሂደታቸው ተቋርጦ የምኅረት ዐዋጅ እንዲሰጣቸው መደረጉ አንድ ማሳያ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ፤ ኢትዮጵያ አፍሪካን ጨምሮ በተለያዩ አኅጉራት በሚገኙ ሀገራት መሪዎችና ተወካዮች ዘንድ በስፋት የተመረጠችና የተጎበኘች ሀገር መሆኗን ማስታወስ ተገቢ ነው። ከጉብኝት ባለፈ ትላልቅ ስምምነቶችም የተፈራረመች መሆኗን ልብ ማለት ይገባል፤ ይህም የምታነሳውን ሐሳብ ገዥነትና የአፍሪካ መግቢያ በር መሆኗን ያሳያል። በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ከአጀንዳ ተቀባይነት ወደ አጀንዳ ሰጭነት በመሸጋገር ብሔራዊ ጥቅምን በሚያስጠብቅ ከፍታ እየተጓዘ መሆኑን መረዳት ይገባል። ኢትዮጵያ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ድርድር ሂደት የተጎናጸፈችው የዲፕሎማሲ ስኬት ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት መነቃቃት መፍጠሩንም ማጤን ያስፈልጋል። ይህ የተሳካው ሀገሪቱ ኢትዮጵያ መንገዷም የጋራ ልማትን የሰነቀ ዕውነት በመሆኑ ነው። በቀጣይ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለአንዲት ሀገራቸው አምባሳደር በመሆን፤ የዲፕሎማሲውን ሥራ በይበልጥ ማገዝ ይጠበቅባቸዋል። ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው ካልሠሩ ማን ለሀገራቸው ሊሠራ ይችላል?
እየተስፋፋ ያለው የጉበት ስብን (ቅባት) እንዴት መከላከል ይቻላል?
Jun 25, 2026 415
የጤና ነገር በዮሐንስ ደርበው በዝምታ እየተስፋፋ ያለው የጉበት ስብን (ቅባት) እንዴት መከላከል ይቻላል? የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት፤ የጨጓራ፣ አንጀትና ጉበት ሰብ ስፔሻሊስት ዶክተር ሚፍታህ ደሊል ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ የጉበት ጤናን እንዴት መጠበቅ እንደሚቻል፣ ለጉበት ጤና መታወክ ስለሚያጋልጡ ጉዳዮች፣ ስለጉበት ስብ (ቅባት) እንዲሁም ሕክምናው ሳይንሳዊ ማብራሪያዎችን ሰጥተዋል። · በሰው ልጅ ሕይዎት (ሠርካዊ እንቅስቃሴ) ውስጥ የጉበት ሚና ምንድን ነው? ዶክተር ሚፍታህ እንደገለጹት፤ ጉበት በሰውነታችን ውስጥ ኪሚገኙ ትላልቅ የውስጥ አካል ክፍሎች (ኦርጋኖች) አንዱ ነው። ከ1 ሺህ በላይ ተግባራትን የሚያከናውን ትልቁ እና ባተሌ የሆነ የአካል ክፍል መሆኑንም አስረድተዋል። የኪንታሮት በሽታ መንስዔ ይታወቃል? ካንሰር እንዴት ይከሰታል? · ለጉበት ህመም አጋላጭ ምክንያቶች ይታወቃሉ? ለጉበት ህመም አጋላጭ ከሆኑ መንስዔዎች መካከል፤ ቫይረሶች (ሄፓታይትስ ቢ፣ ሄፓታይትስ ሲ) እንዲሁም አልኮል (ከፍተኛ መጠን ያለው አልኮል መጠጣት) መሆናቸውን አንስተዋል። በአሁኑ ወቅት ደግሞ በስፋት የሚስተዋለው አጋላጭ መንስዔ የጉበት ስብ መጨመር መሆኑንም በአጽንዖት ገልጸዋል። በእኛ ሀገር ደረጃ ከሚከሰቱ የጉበት ህመሞች 50 በመቶው በሄፓታይትስ ቢ ምክንያት የሚከሰት ነው ይላሉ ዶክተር ሚፍታህ። ከ15 እስከ 20 በመቶ ያህሉ የጉበት ህመም የሚከሰተው ደግሞ በአልኮል ምክንያት መሆኑን ነው ያስረዱት። እንዲሁም በሄፓታይትስ ሲ ምክንያት የሚከሰተው የጉበት ህመም ከላይ ከተገለጹት ቀጥሎ በሦስተኛነት እንደሚቀመጥም አመላክተዋል። አሁን አሁን ደግሞ ይላሉ ዶክተር ሚፍታህ፤ በሥራም ሆነ ለመዝናናት ለረጂም ሠዓታት መቀመጥን ተከትሎ የጉበት ስብ (ቅባት) በከፍተኛ ደረጃ እየተስፋፋና ለጉበት ህመም እያጋለጠ መሆኑን አስገንዝበዋል። · የጉበት ፋት (ስብ፣ ቅባት) ለጉበት ህመም የሚያጋልጥበት ምክንያት ምንድን ነው? የጉበት ስብ በተለያዩ ሀገራት (በእኛም ሀገር በትላልቅ ከተሞች) በስፋት የሚከሰት ነው ያሉት ዶክተር ሚፍታህ፤ የጥናት ውጤቶች እንደሚያመላክቱት ከዓለም ሕዝብ 30 በመቶው (1/3ኛው ወይም ከ2 ቢሊየን በላይ ያህሉ) የጉበት ስብ ሊኖርበት ይችላል ይላሉ። በእርግጥ ሁሉም የጉበት ስብ ወደ ከፍተኛ የጉበት ቁስለት ይሸጋገራል ማለት እንዳልሆነ ገልጸው፤ የጉበት ስብ ካለባቸው መካከል ከ10 እስከ 15 በመቶ ያህሉ ብቻ ስቡ ከመብዛቱ የተነሳ ጉበቱን ማቁሰል እንደሚጀምር አስገንዝበዋል። ይህ ቁስለት ደግሞ እየዳነ እንደገና እያገረሸ ጠባሳ እየፈጠረ ይሄድና ጉበት ሥራውን ማከናወን የማይችልበት ደረጃ ሲደርስ የጉበት መድከም ይከሰታል፤ ሰዎችም ጉዳት ይደርስባቸዋል ይላሉ። የጉበት ስብ መንስዔም፤ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ አለማድረግ (መቀመጥን ማዘውተር)፣ ፋስት ፉድ ማዘውተር (የተጠበሱ ምግቦች፣ በርገር፣ ችብስ፣ ዘይት የበዛባቸው ምግቦች) እንዲሁም ከፍተኛ ስኳር ያላቸው ለስላሳ መጠጦች፣ አልኮል መሆናቸውን አብራርተዋል። · የጉበት ስብን እንዴት መከላከል ይቻላል? የጉበት ስብ ከፍ እያለ ሲሄድ በአልትራሳውንድ እንደሚታይ (ትንሽ ከሆነ አይታም) የገለጹት ዶክተር ሚፍታህ፤ እስካሁን ክትባት እንደሌለው አረጋግጠዋል። ይህ ኬዝ እንቅስቃሴ ባለማድረግ፣ ኮምፒውተርም ሆነ ቴሌቪዥን ለማየት ረጂም ሠዓት በመቀመጥና በውፍረት መጨመር የሚከሰት መሆኑን ጠቁመው፤ መከላከያ መንገዱም ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረግ (ቢያንስ በሳምንት እስከ 150 ደቂቃ በእግር መሄድ (ዎክ ማድረግ) ወይም በቀን ለ30 ደቂቃ ዎክ ማድረግ) መሆናቸውን ዘርዝረዋል። በተጨማሪም በፋብሪካ ፕሮሰስ የተደረጉ የታሸጉ ምግቦችን አለማዘውተር፣ ከስኳር ነጻ የሚሉ የሚበሉም ሆነ የሚጠጡ ነገሮችም ቢሆኑ በቀጥታም ባይሆን በሌላ መንገድ ጣፋጭ ስለሚኖራቸው አለማዘውተር፣ የተጠበሱ እንደ ችብስ እና መሰል ያሉ ምግቦችንም አለማዘውተር እንደሚገባ መክረዋል። ከልክ ያለፈ ውፍረት እንዳይኖር ማድረግም ለጉበት ስብ ተጋላጭነትን እንደሚቀንስ አስረድተዋል። · የጉበት በሽታ ምልክቶች እንደ ኬዙ ቢለያይም ጉበት 80 በመቶ ያህል ክፍሉ እስከሚጎዳ ምልክት ላያሳይ እንደሚችል ዶክተር ሚፍታህ ይገልጻሉ። 15 ወይም 10 በመቶ ጤናማ ክፍሉ ሲቀር (ከ85 በመቶ በላይ ክፍሉ በጣም ሲጎዳ) አንዳንድ ምልክቶች ሊያሳይ እንደሚችል ገልጸዋል። እነዚህ ምልክቶችም፤ ሆድ ላይ ውኃ መፍጠር (አሳይተስ)፣ ደም ማስመለስ መሆናቸውን እና በዚህ ወቅት የጉበት ንቅለ ተከላ ካልሆነ መፍትሔ እንደሌለው አንስተዋል። በአንጻሩ ግን፤ ‘አኪዩት ሄፓታይትስ’ የሚባለው ወይም አንድ ቫይረስ ጉበትን ሲያጠቃ ወዲያውኑ ሕክምና ይደረግለታል ሙሉ በሙሉም ይድናል ብለዋል።በዚህ ወቅት የሚየሳየው ምልክትም የዐይን ቢጫ መሆን፣ በቀኝ ደረት ሥር የውጋት ስሜት መኖር፣ ከፍተኛ ድካም መኖር፣ የምግብ ፍላጎት አለመኖር (ምግብ አስጠላኝ ማለት)፣ ማቅለሽለሽ እንዲሁም ማስመለስ መሆናቸውን አብራርተዋል። · የጉበት በሽታ አሳሳቢ ነው? የጉበት በሽታ በዓለም አቀፍ ደረጃም በተለያዩ ሀገራት ከ1 እስከ 10 ገዳይ (አሳሳቢ) ተብለው ከሚጠቀሱት መካከል መሆኑን ዶክተር ሚፍታህ አስረድተዋል። በእኛ ሀገር ደረጃም የጉበት ካንሰር ከ3 እስከ 4 ገዳይ ተብለው ከሚጠቀሱ በሽታዎች መካከል መሆኑን ነው የጠቆሙት። በዓለም በየዓመቱ እስከ 3 ሚሊየን ሰዎች በጉበት በሽታ እንደሚሞቱ ገልጸው፤ ይህ አኃዝ አሳሳቢነቱን ያስረዳል ብለዋል። ምንም እንኳን ቀድሞ በሚወሰድ ክትባት (ለሄፓታይትስ ቢ) ከተከሰተ በኋላም በሚወሰድ መድኃኒት (ለሄፓታይትስ ሲ) አበረታች ውጤቶች ቢኖሩም፤ የጉበት ስብ (ቅባት) ግን በሀገራችንም ሆነ በዓለም ላይ በተለይም በከተማ ነዋሪዎች ዘንድ በስፋት እየተስተዋለ ያለ በመሆኑ አሳሳቢ ነው ብለዋል። · የጉበት በሽታ በተለይም በየትኞቹ የዕድሜ ክልሎች ላይ በስፋት ይከሰታል? የጉበት በሽታው ዓይነት በስፋት የሚከሰትበትን ዕድሜ እንደሚወስን ጠቁመው፤ በዚህም መሠረት ለምሳሌ፡- ሄፓታይትስ ቢ ከ30 ዓመት በታች ባሉ ሰዎች ላይ፣ ሄፓታይትስ ሲ ከ20 እስከ 40 ዓመት (አንዳንድ ጊዜ ከ40 ዓመት በላይ ባሉ ሰዎች ላይም ሊከሰት ይችላል)፣ የጉበት ስብ (ቅባት) ደግሞ ከ40 ዓመት በላይ ባሉ ሰዎች ላይ በስፋት እንደሚስተዋል ያስረዳሉ። · የጉበት በሽታን አስቀድሞ መከላከል ይቻላል? ዶክተር ሚፍታህ እንዳሉት የጉበት በሽታን አስቀድሞ መከላከል የቻልባቸው የተለያዩ አማራጮች አሉ። ለምሳሌ፡- የሰውነት ክብደት (ውፍረት) ከልኩ እንዳያልፍ መቆጣጠር፣ ረጂም ሠዓት አለመቀመጥ፣ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ማዘውተር፣ አልኮል አለመጠጣት (በቀን ከአንድ ቢራ በላይ መጠጣት ለጉበት ስብ ያጋልጣል)፣ ጣፋጭ ምግብና መጠጦችን መቀነስ (ጭራሽ አለመጠቀም ቢቻል)፣ ዘይት የበዛባቸውና የተጠባበሱ ምግቦችንም አለማዘውተር የሚሉትን አንስተዋል። በተጨማሪም በእኛ ሀገር ቀዳሚው የጉበት በሽታ ሄፓታይትስ ቢ መሆኑን በመግለጽ፤ ለዚህም ከ95 በመቶ በላይ የመከላከል ዐቅም ያለው ክትባት ስላለው ሦስት ጊዜ በመከተብ አስቀድሞ መከላከል እንደሚቻል አረጋግጠዋል። · የሕክምና አማራጮች አሉት? ሄፓታይትስ ቢ ተከስቶ ጉበቱን ማቁሰል ከጀመረም የሚሰጥ ውጤታማ መድኃኒት መኖሩን አስታውቀዋል። ይህ መድኃኒት ምናልባት ዕድሜ ልክ ሊወሰድ ይችላል ነገር ግን ቁስለቱንም ሆነ ቫይረሱን በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል ነው ያሉት። ሄፓተይትስ ሲ ከሆነ ደግሞ በጣም ውጤታማ የሆነ ለሦስት ወር የሚሰጥ መድኃኒት አለ ብለዋል። ጠባሳ ከሆነ እና ከ85 በመቶ በላይ የሚሆነው የጉበት ክፍል ከተጎዳ (ከተበላሸ) ግን በውጭ ሀገር የጉበት ንቅለ ተከላ ማድረግ አስገዳጅ ይሆናል ብለዋል። · ምክረ ሐሳብ ተላላፊ ካልሆኑ የጉበት በሽታዎች አንዱ እና አሁን በስፋት እየተስተዋለ ያለውን የጉበት ስብ (ቅባት) ጨምሮ የጉበት ጤናን ለመጠበቅ፤ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በየቀኑ ማድረግን መክረዋል። በዓመት አንድ ጊዜ የጤና ምርመራ በማድረግ ያሉበትን ሁኔታ ማወቅም ቢለመድ ሲሉ ይመክራሉ። በወቅቱ ከተደረሰብት የጉበት በሽታ መዳን እንደሚችል ገልጸው፤ በቸልተኝነት ወደ ተወሳሰበ ደረጃ ከፍ ካለ ግን እስከ ጉበት ካንሰር ሊደርስ እንደሚችልም አመላክተዋል።
የጤና ነገር
Jun 24, 2026 1360
በዮሐንስ ደርበው የኪንታሮት ህመም እንዴት ይከሰታል? እንዳይከሰት መከላከል የሚቻልበት ብልኀት አለ? ከተከሰተ በኋላስ የሚድንበት ዕድል ይኖራል? · ኪንታሮት እንዴት ይከሰታል? አጠቃላይ የቀዶ ጥገና ሐኪም የሆኑት ዶክተር ቤተልሔም አበራ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ በፊንጢጣ ውስጥ የሚገኙ በጤናማ መንገድ ፊንጢጣ እንዲዘጋ (‘ኩሽን’ እንዲሆን) የሚያደርጉ ደም ሥሮች በተለያየ ምክንያት ሲያብጡ ኪንታሮት (ሄሞሮይድ) ተከሰተ እንደሚባል አስረድተዋል። · የኪንታሮት በሽታ መንስዔ ይታወቃል? እንደ ሕክምና ባለሙያዋ ገለጻ ለኪንታሮት በሽታ መንስዔ ተብለው ከሚጠቀሱት መካከል፤ የሰገራ ድርቀት በዋናነት ይነሳል። በተጨማሪም ይላሉ፤ በተለይም ሴቶች ላይ በእርግዝና ወቅት የጽንሱ መጠን (ክብደት) እየጨመረ በሚሄድበት ጊዜ ወደ መቀመጫ በሚያደርገው ጫና ምክንያት በፊንጢጣ ውስጥ የሚገኙ የደም ሥሮች እንዲያብጡ በማድረግ ለኪንታሮት መከሰት መንስዔ ይሆናል። በአሁኑ ጊዜ በስፋት ለሚከሰት የኪንታሮት በሽታ በመንስዔነት የሚነሳው ከመጠን ያለፈ ውፍረት መጨመር መሆኑንም ጠቁመዋል። ይህም ውፍረት ወደ መቀመጫ ጫና በማሳደር በፊንጢጣ ውስጥ ያሉ የደም ሥሮች እንዲያብጡ በማድረግ ኪንታሮት እንዲከሰት ያደርጋል ነው ያሉት። በሌላ በኩል እንደ ሥራ ባሕርያቸው ለረጂም ሠዓታት የሚቀመጡ ሰዎች ስለማይንቀሳቀሱና ይህን ተከትሎም ለድርቀት ስለሚጋለጡ ለኪንታሮት በሽታ ይዳረጋሉ ሲሉ አስገንዝበዋል። ከአመጋገብ ዘይቤ ጋር በተያያዘም፤ በቂ ውኃ አለመጠጣት እና በፋይበር የበለጸጉ ምግቦችን አለማዘውተር ለድርቀት ስለሚዳርግ የኪንታሮት በሽታ እንዲከሰት ያደርጋል ብለዋል። ሕጻናትን ለውስብስብ ችግር እየዳረገ ያለው የስኳር ህመም (Diabetes) የጡት ካንሰርን መከላከል ይቻላል? · የኪንታሮት በሽታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ ያለው ለምንድን ነው? ኪንታሮት የተለመዱ (‘ኮመን’) ከሚባሉ የቀዶ ሕክምና በሽታዎች መካከል አንዱ መሆኑን የገለጹት ዶክተር ቤተልሔም፤ በትክክል ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን መረጃ ለጊዜው መግለጽ ባይቻልም በዓለም አቀፍ ደረጃ እስከ 25 በመቶ ያህሉ ሕዝብ የኪንታሮት ተጠቂ እንደሆነ ጠቁመዋል። እዚህ ላይ ልብ መባል ያለበት ጉዳይ የኪንታሮት በሽታ ከቦታ ቦታ ከሀገር ሀገር እንደሚለያይ መሆኑን አስገንዝበው፤ ለዚህም ምክንያቱ ከውፍረት እና ለድርቀት ከሚያጋልጡ አመጋገቦች መዘውተር ጋር የተያያዘ በመሆኑ ነው ይላሉ። ለምሳሌ፡- በጣም ወፍራም ሰዎች በሚበዙባቸው እና ለድርቀት አጋላጭ ምግቦች በሚዘወተሩባቸው አካባቢዎች የኪንታሮት ተጋላጭነት ከፍተኛ ነው ይላሉ። የኪንታሮት በሽታ እየጨመረ (እየተስፋፋ) የሚሄድበት ምክንያትም ከአኗኗር ዘይቤ ጋር እንደሚያያዝ ገልጸው፤ ለምሳሌ አብዛኛውን ጊዜ ቁጭ ብሎ (ተቀምጦ) ማሳለፍ ለኪንታሮት አጋላጭ መንስዔ ነው ብለዋል። በተለይም ቢሮ አካባቢ የሚሠሩ ሰዎች ለበርካታ ሠዓታት ስለሚቀመጡ፣ ሥራ ሲበዛባቸውም ወደ መጸዳጃ ቤት መሄድ ባለባቸው ሠዓት ባለመሄድ (የሚሄዱበትን ጊዜ ስለሚያራዝሙ፣ ቆይ ይችን ልጨርስ…ትንሽ…የተወሰነ ደቂቃ እያሉ ማራዘም) ሰገራን ለድርቀት ያጋልጣል፤ ይህም የደም ሥሮች እንዲያብጡና ከፊንጢጣ ውጭ እንዲወጡ በማድረግ ለኪንታሮት መከሰት ያጋልጣል ብለዋል። · የኪንታሮት በሽታ ምልክቶች በፊንጢጣ ላይ ዕብጠት መኖር፣ መድማት፣ ማሳከክ እና የህመም ስሜት መኖር ከምልክቶቹ መካከል መሆናቸውን ዶክተር ቤተልሔም ያብራራሉ። የኪንታሮት በሽታ የውስጠኛው እና የውጨኛው ተብሎ እንደሚከፈል በመግለጽ፤ የበሽታው ደረጃም ከአንድ እስከ አራተኛ እንደሚመደብ ያስረዳሉ። ይህን ሲያብራሩም፤ በውስጠኛው የኪንታሮት በሽታ ባብዛኛው ህመም አይኖርም፣ የፊንጢጣ ደም ሥሮች ዕብጠትና መድማት ይኖራል፤ በውጨኛው የኪንታሮት በሽታ ግን የህመም ስሜት ይኖራል ይላሉ። · የኪንታሮት በሽታ ደረጃዎች ደረጃዎቹን በተመለከተ ሲያስረዱ፤ ምልክቶቹን እንዳስተዋሉ ቶሎ ወደ ሕክምና ባለመሄድ ከአንደኛ ወደ ሁለተኛ ከዚያም ወደ ሦስተኛ እና አራተኛ ደረጃ እየተባባሰ እንደሚሸጋገር ገልጸዋል። ስለዚህ ሰዎች ምልክቶቹን እንዳዩ ቢታከሙ ደረጃው ከፍ ሳይል በሽታውን የመግታት ዕድል ይኖራቸዋል ነው የሚሉት። የመጀመሪያ ደረጃ የኪንታሮት በሽታ፤ በዚህ ወቅት የኪንታሮት ህሙማን እንኳን የዕብጠቱን መኖር ባብዛኛው በእጃቸውም ነክተው እንደማያውቁት እና የመድማት ምልክት ሊኖር እንደሚችል ተናግረዋል። ሁለተኛ ደረጃ የኪንታሮት በሽታ፤ በዚህኛው ደረጃ ደግሞ ህሙማኑ በሚጸዳዱበት ወቅት ዕባጩ ወደ ውጭ እንደሚወጣ እና ሲጨርሱ በራሱ ጊዜ ዕባጩ ወደ ቦታው እንደሚመለስ አስገንዝበዋል። ሦስተኛ ደረጃ የኪንታሮት በሽታ፤ በሽታው ያለባቸው ሰዎች በሚጸዳዱበት ወቅት ወደ ውጭ የሚወጣውን ዕባጭ በእጃቸው ወደ ውስጥ ካላስገቡት በራሱ ጊዜ የማይመለስበት ደረጃ መሆኑን ይገልጻሉ። አራተኛ ደረጃ የኪንታሮት በሽታ፤ ይህ ደረጃ ዕባጩ ከፊንጢጣ ውጭ ይወጣና ተገፍቶም ወደ ውስጥ መግባት የማይችልበት ደረጃ ሲደርስ መሆኑን አስገንዝበዋል። ስለዚህ አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ላይ ያለ የኪንታሮት በሽታ፤ ያለ ቀዶ ሕክምና ሰዎች እቤታቸው እንዲያደርጉ የሚመከሩትን ሁኔታዎች በአግባቡ ካደረጉ ወደ ቀጣዩ ደረጃ እንዳይሸጋገር ማድረግ ይቻላል ይላሉ። · በወቅቱ ካልታከመ በአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ኪንታሮትን ከላይ በተገለጹ የኑሮ እና አመጋገብ ዘይቤዎች ማስተካከል እንደሚቻል (ወደ ቀጣዮቹ ሦስተኛ እና አራተኛ ደረጃ ሳይሸጋገር ባለበት እንዲቆይ) ማድረግ እንደሚቻል ያስረዳሉ። ወደ ሦስተኛ እና አራተኛ ደረጃ ከደረሰ ግን የቀዶ ሕክምና እንደሚሰጥ ጠቁመው፤ ይህ ደግሞ ጥቅምም የጎንዮሽ ጉዳትም እንዳለው አስገንዝበዋል። በተጨማሪም በመጀመሪያዎቹ ደረጃዎች ካልታከመ እና ወደ መጨረሻዎቹ ደረጃዎች ከደረሰ ከፍተኛ የደም መፍሰስ እንደሚኖረውና ይህም ከሰው ደም እስከመለገስ ሊያደርስ እንደሚችል ይገልጻሉ። ወደ ውጭ ወጥተው በሚቀሩ የፊንጢጣ ደም ሥሮች ውስጥ የደም መርጋት ሊያጋጥም እንደሚችልና ይህም ከፍተኛ ህመም እንደሚያመጣ ተናግረዋል። በዚህም ድንገተኛ ሕክምና የመፈለግ ደረጃ ላይ ሊደርሱ እንደሚችሉ ነው ያመላከቱት። · የኪንታሮት በሽታ ሙሉ በሙሉ ይድናል ወይስ አይድንም? በየትኛውም ደረጃ ላይ ያለ የኪንታሮት በሽታ በጊዜውና በአግባቡ ከታከመ ሙሉ በሙሉ እንደሚድን ዶክተር ቤተልሔም አረጋግጠዋል። በተለይም አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ላይ ያለ የኪንታሮት በሽታን ሰዎች እቤታቸው በሚያደርጉት ትሪትመንት (የአኗኗርና አመጋገብ ዘይቤያቸውን በማስተካከል) ሊያድኑት እንደሚችሉም አመላክተዋል። በተጨማሪም ወደ ሕክምና ተቋም ቢሄዱ፤ የሰገራ ማለስለሻ፣ ፊንጢጣ ላይ የሚቀባ የህመምና ዕብጠት መቀነሻ መድኃኒት እንደሚሰጥ በመግለጽ ይህ ከተስተካከለ የአኗኗር ዘይቤያቸው ብሎም በብዛት ውኃ ከመጠጣት ጋር ሲሠናሰል በመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ኪንታሮት የመዳን ዕድሉ ከፍተኛ መሆኑን አስገንዝበዋል። ይህንን አልፎ ወደ ሦስተኛ እና አራተኛ ደረጃ ላይ ቢደርስ እንኳን የተለያዩ የቀዶ ሕክምና አማራጮች እንዳሉ ጠቁመዋል። በዚህም መሠረት እንደ ኪንታሮቱ መጠን ‘ረበርባንድ’ (ዕባጩን ዙሪያውን በመቋጠር በጊዜ ሂደት ደርቆ እንዲረግፍ የማድረግ ሕክምና) እና ኪንታሮቱን (የደም ሥሮቹን ዕባጭ) በቀጥታ በቀዶ ሕክምና በማውጣት ማከም ይቻላል፤ መዳንም ይቻላል ብለዋል። · ኪንታሮት እና ባሕላዊ ሕክምና ከላይ እንደገለጽነው (የኑሮ ዘይቤን ማስተካከል፣ ውኃ በብዛት መጠጣት፣ በፋይበር የበለጸጉ ምግቦችን ማዘውተር፣ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረግ) ከዚያም ዘመናዊ ሕክምና መከታተል ተገቢ መሆኑን የሕክምና ባለሙያዋ መክረዋል። በአንጻሩ በባሕል (በልማድ) ፊንጢጣ ውስጥ የሆነ ነገር መቅበር፣ ኪንታሮትን በግለት መተኮስ ለካፋ ችግር ሊያጋልጥ ስለሚችል ይህን ከማድረግ መቆጠብ ይመከራል ብለዋል። ምክንያቱም ለፊንጢጣ መጥበብ (በሚጸዳዱበት ጊዜ ለመሰንጠቅና መድማት) ብሎም ለመሰል የጎንዮሽ ጉዳቶች ሊዳርግ እንደሚችል አስረድተዋል። ኪንታሮት በአግባቡ በቀዶ ሕክምና ካልወጣ በባሕል (ልማድ) መነካካቱ ለባክቴሪያ እንደሚያጋልጥ፤ ባክቴሪያው ደግሞ ከፊንጢጣ አልፎ ወደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች (ለምሳሌ ወደ ታፋና አካባቢው) የሚዛመት መግል የያዘ ከፍተኛ ኢንፌክሽን ያጋልጣል ብለዋል። በዚህ ጊዜ ወደ ሕክምና ሲመጡ ሕክምናውን በጣም ከባድ (ውስብስብና አስቸጋሪ) ያደርገዋል ነው ያሉት። · የፊንጢጣ ካንሰርና የኪንታሮት በሽታ ቀደም ብለን እንዳነሳነው የኪንታሮት በሽታ ምልክቶች፤ ማሳከክ፣ ዕባጭ፣ መድማት እና ህመም ናቸው ያሉት ዶክተር ቤተልሔም፤ የፊንጢጣ ካንሰርም ተመሳሳይ ምልክቶች ይኖሩታል ይላሉ። ስለዚህ ማንኛውም ሰው በፊንጢጣ በኩል ደም ሲመለከት ወዲያውኑ ወደ ሕክምና ተቋም እንዲሄድ መክረዋል። ምክንያቱም ይላሉ፤ በፊንጢጣ በኩል ደም የሚታየው አንድም በኪንታሮት በሽታ እንዲሁም በአንጀት ቁስለት፣ በፊንጢጣ ካንሰር፣ በጨጓራ ቁስለት እና በትልቁ አንጀት ካንሰር ምክንያት ሊሆን ስለሚችል ነው። ከመድማት በተጨማሪ የፊንጢጣ ቁስለት በስፋት ከታየ ካንሰር ሊሆን እንደሚችልም አመላክተዋል። ቁስለቱ ፊንጢጣ ውስጥ ስለሚሆን በእጅ መንካትና ማወቅ የማይቻልበት ሁኔታ እንደሚኖርም ጠቁመዋል። · ምክረ ሐሳብ ለኪንታሮት በሽታ ላለመጋለጥ ወይም ከመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ወደ ቀጣዮቹ ደረጃዎች እንዳይሸጋገር መንስዔዎቹን መቀልበስ ተገቢ መሆኑን በአጽንዖት አንስተዋል። በዚህም መሠረት ድርቀት እንዳይኖር ማድረግ ቀዳሚው መፍትሔ መሆኑን አስገንዝበዋል። ለዚህም በቂ ውኃ መጠጣት፣ ከ25 እስከ 30 ግራም ፋይበር በየቀኑ መውሰድ (በደንብ ፋይበር ያላቸው ምግቦችን መመገብ ለምሳሌ፡- ጎመን፣ ቆስጣ፣ ብርቱካን፣ ሙዝ፣ አፕል፣ ባቄላ፣ ገብስ፣ አጃ፣ ስንዴ) ይገባል ብለዋል። በተጨማሪም ድርቀትን ለመከላከል ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደሚገባ በመግለጽ፤ በሥራ ባሕርያቸው ቢሮ ውስጥም ሆነ ሌላ ቦታ መቀመጥ የሚያበዙ ሰዎች በመሐል በመነሳት መንቀሳቀስ እንዲሁም ከሥራ ሲወጡ በእግር መሄድ (ዎክ ማድረግ) እና ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ማድረግ ለአንጀት እንቅስቃሴ ዕገዛ በማድረግ ድርቀት እንዳይኖር ይጠቅማቸዋል ብለዋል። ከመጠን ያለፈ ውፍረት ያለባቸው ሰዎችም ክብደታቸውን እንዲቀንሱ መክረው፤ ይህ ሲሆን ከፊንጢጣ ውጭ የነበረው የደም ሥር ዕብጠት (የኪንታሮት በሽታ) ወደ ነባር ቦታው እንዲመለስ ወይም ባለበት እንዲቆይ (በይበልጥ ተገፍቶ እንዳይወጣ) ይረዳል ይላሉ። ከልማዳዊ ሕክምና በመራቅ ዘመናዊ ሕክምናን ቀዳሚ ምርጫ ለማድረግ በተለይም ቀድሞ መከላከል የሚቻልበትን ብልኀት ለማዳበር ስለ ኪንታሮት በሽታ በስፋት ግንዛቤ መፍጠር ተገቢ ነው ይላሉ። በፊንጢጣ በኩል ደም ሲታይ ሁሌም ኪንታሮት ላይሆን እንደሚችልና ካንሰር ሊሆን እንደሚችልም በመገንዘብ ቶሎ ወደ ሕክምና በመሄድ ወደ ሌሎች ደረጃዎች ሳይሸጋገር በማከም እንዲድን ማድረግ ተገቢ መሆኑን መክረዋል።
ትውልዱ ዛሬንም ነገንም በሚጠቅመው የአረንጓዴ ዐሻራ ኢኒሼቲቭ ንቁ ተሳታፊ መሆን ይጠበቅበታል
Jun 23, 2026 1766
በኢዜአ ዐይን…! በዮሐንስ ደርበው የአረንጓዴ ዐሻራ ኢኒሼቲቭ ጥቅም ንጥልም ቀላልም አይደለም፤ በተለያዩ ዐውዶች ገዝፎ ይገለጣል እንጅ። ለአብነትም፤ የደን ሽፋንን በማሳደግ የዓየር ንብረት ተጽዕኖን በመቀነስ ብሎም በመከላከል፣ የአፈር መሸርሸርን በመቀነስ እንዲሁም በመከላከል ምርታማነትን በመጨመር የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ፣ የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ የከተማ ውበት መጠበቅን ጨምሮ የተለያዩ ጥቅሞችን በቀጥታ ለሰው ልጆች ይቸራል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንዳሉት፤ አረንጓዴ ዐሻራ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ሉዓላዊነትና ብልጽግና አሠናሥሎ የሚያረጋግጥ ብሔራዊ ኢኒሼቲቭ ነው። የደን፣ የሰብልና ሁለንተናዊ ሉዓላዊነት የማረጋገጥ ወሳኝ የልማት አቅጣጫም ነው። የአረንጓዴ ዐሻራ ኢኮኖሚያዊ ትሩፋት አረንጓዴ ዐሻራ - ለዓየር ንብረት ለውጥ ላለመበገር የሚደረግ ትጋት ጽንሰ ሐሳቡ ከችግኝ ተከላ የተሻገረው አረጓዴ ዐሻራ የአረንጓዴ ዐሻራ ኢኒሼቲቭ መነሻ፤ የተራቆተ አካባቢን ችግኝ በመትከል አረንጓዴ ከማድረግ የላቀ ድርብርብ ግብ ያለው ሰፊ መርሐ-ግብር ነው። በዚህም መሠረት፤ እንደየ ሥነ-ምኅዳሩ የሚላመዱ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ላላቸው ችግኞች፣ ለደን ሽፋን ማደግ የጎላ ሚና ለሚኖራቸው ችግኞች፣ ለከተማ ውበትና ለማረፊያ ጥላ ለሚሆኑ ዛፎች፣ የአፈር መሸርሸርን ለመከላከል የሚችሉ ዛፎች የሚተከሉበት ነው። ይህም አንድን አካባቢ አረንጓዴ ከማድረግ ልቆ በረሃማነትንና የዓየር ንብረት ተጽዕኖን በመቀነስ፣ ምርታማነትን በመጨመር ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን በማሳደግ በቀጥታ ሕብረተሰቡን የሚጠቅም ትልቅ ኢኒሼቲቭ መሆኑን ያስረዳል። የተለያዩ ክፍላተ-ዓለማት አንድም በካፋ ቅዝቃዜ እንዲሁም መደበኛ የኑሮ ሁኔታን በሚያናጋ አደገኛ ሙቀት ብሎም በድንገተኛ ጎርፍ እና ሰደድ እሳት በሚታመሱበት ጊዜ፤ እነዚህንና መሰል ችግሮችን ቀድሞ ለማረቅ አንዱ መፍትሔ አረንጓዴ ዐሻራን በስፋት ማከናወን መሆኑ ይታመናል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሐሳብ አመንጭነትና ቁርጠኛ አመራር ሰጭነት ባለፉት ዓመታት በብርቱዎቹ ኢትዮጵያውያን ርብርብ ከ48 ቢሊየን በላይ ችግኞች ተተክለዋል፤ ውጤቱንም ሕዝቡ ዐይቷል። ከውጤቶቹ መከካልም ለአብነት፤ ከሀገራዊ ለውጡ በፊት 17 ነጥብ 2 በመቶ የነበረው የደን ሽፋን አሁን ወደ 23 ነጥብ 6 በመቶ ማደጉ፣ የምርታማነትና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት መጨመር ብሎም ውብና አረንጓዴ ከተሞች መስፋፋት የሚሉት ይነሳሉ። በሕዝቡ ዘንድ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ተፈጥሮን የመንከባከብ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን፤ የሀገርን የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትና የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ጉዳይ ጭምር ተደርጎ መወሰድ ይኖርበታል። የአረንጓዴ ዐሻራን ውጤት ላጣጣመ ሥራውን በንቃት እንዲከውን መካሪ ባያሻም፤ ካለፈው የበለጠ ውጤት እንዲገኝ ዛሬ ላይ ኢትዮጵያውያን ተጠቃሚነታቸውን በሚያረጋግጠው የአረንጓዴ ዐሻራ በነቂስ መሳተፍ እና ባሕላቸው ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። ከአረንጓዴ ዐሻራ ትሩፋቶች መካከል • በሰብል፣ ፍራፍሬ፣ ቡና ምርታማነት እና በሥራ ዕድል ፈጠራ ረገድ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ሐሳብ አመንጭነት በ2011 ዓ.ም ጅማሮውን ያደረገው የአረንጓዴ ዐሻራ ኢኒሼቲቭ አሁን ዘርፈ-ብዙ ጥቅሙ በተጨባጭ እየተገለጠ ነው። ከበርካታ ትሩፋቶቹ መካከልም የምርታማነት ማደግ ተጠቃሽ ነው። ይህን ተከትሎም የሕብረተሰቡ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት አድጓል። ይህን ሐሳብ በአኃዝ አስደግፎ ብናየው፤ ከአረንጓዴ ዐሻራ ኢኒሼቲቭ በፊት (በ2010 ዓ.ም) በሔክታር የሚመረተው ስንዴ 22 ኩንታል፣ በቆሎ 30 ኩንታል፣ ጤፍ 17 ኩንታል እንዲሁም ገብስ 23 ኩንታል ነበር። ከኢንሼቲቩ ትግበራ በኋላ ደግሞ (በ2017 ዓ.ም) ስንዴ በሔክታር 36 ኩንታል፣ በቆሎ 46 ኩንታል፣ ጤፍ 20 ኩንታል፣ ገብስ 30 ኩንታል ማምረት ተችሏል። በዚህም መሠረት በ2017 ዓ.ም 7 ነጥብ 8 ሚሊየን ሔክታር መሬት በስንዴ ሰብል በመሸፈን 280 ሚሊየን ኩንታል ማምረት ተችሏል። ስንዴን በትጋት በማምረትም ከውጭ ለማስገባት ይወጣ የነበረን 1 ቢሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማስቀረት ተችሏል። በሌላ በኩል ደግሞ፤ የአረንጓዴ ዐሻራ ኢኒሼቲቭ በፍራፍሬው ዘርፍ ዕድገትም ከፍተኛ አስተዋጽዖ አበርክቷል። በዚህም ገበያውን ከማረጋጋት ባለፈ ሕብረተሰቡ (አምራቹ) ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነቱ በዚያው ልክ እንዲያድግ አስችሏል። ኢትዮጵያም በአፍሪካ አቮካዶን በቀዳሚነት ወደ ውጭ የምትልክ ሁለተኛዋ ሀገር እንድትሆን አስችሏታል። ሌላኛው የአረንጓዴ ዐሻራ ኢኒሼቲቭ ትሩፋት የቡና ልማት መስፋፋትና የውጭ ምንዛሬ ማደግ ነው። ይህን በአሥረጂ አስደግፈን ብንመለከት፤ በ2011 ዓ.ም በ600 ሺህ ሔክታር ላይ ቡና ተተክሏል። 500 ሺህ ሜትሪክ ቶን የቡና ምርት ተሰብስቧል። 738 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ተገኝቷል። እንዲሁም በ2017 ዓ.ም 1 ነጥብ 4 ሚሊየን ሔክታር መሬት ላይ ቡና ተተክሏል። 1 ነጥብ 58 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን የቡና ምርት ተሰብስቧል። 2 ነጥብ 65 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢም ማግኘት ተችሏል። እንዲሁም ከአረንጓዴ ዐሻራ ኢኒሼቲቭ ጋር በተያያዘ ለ2 ነጥብ 5 ሚሊየን ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር ተችሏል። ከላይ የተጠቀሱ ማሳያዎችን (ናሙናዎችን) ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች የአረንጓዴ ዐሻራ ኢኒሼቲቭ በቀጥታ ለሕዝቡ ጥቅም የቆመ መርሐ-ግብር መሆኑን መገንዘብ አያዳግትም። ስለዚህ በቀጣይ ሕብረተሰቡ በዚህ ኢኒሼቲቭ ላይ ያለጠባቂነት በንቃት በመሳተፍ እና ባሕሉ በማድረግ ተጠቃሚነቱንም በዚያው ልክ ለማሳደግ መትጋት ይጠበቅበታል። እስከ ዓለም ከፍታ ሕጻናትን ለውስብስብ ችግር የሚዳርገው ህመም ከአረንጓዴ ዐሻራ ኢኒሼቲቭ አበርክቶዎች መካከል • በመሬት መራቆት መቀነስ፣ በደን ሽፋን ማደግ፣ በውኃማ አካላት መስፋፋት ረገድ የአረንጓዴ ዐሻራ ኢኒሼቲቭ፤ የአካባቢ መራቆትን በመቀነስና በመቅረፍ ከፍተኛ አስተዋጽዖ አበርክቷል፣ በደን መጨፍጨፍ ምክንያት ይከሰት የነበረን የበረሃማነት መስፋፋት ቀንሷል፣ የደን ሽፋንን ጨምሯል፣ የአፈር መሸርሸርን በመቀነስ መሬት እንዲያገግም በማድረግ ምርታማነትን ጨምሯል። በተጨማሪም የውኃማ አካላትን መመናመን ቀንሷል (ደርቀው የነበሩ ስፍራዎች ወደ ቀድሞ ውኃማ ይዘታቸው እንዲመለሱ አስችሏል)፣ የአካባቢ መራቆትና የዓየር ንብረት ፈተናዎችን በመቀነስ ረገድም የራሱን ከፍተኛ ሚና አበርክቷል። ኢትዮጵያ ለአረንጓዴ ዐሻራ ኢኒሼቲቭ ትግበራዋ ስኬታማነት ዓለም ዕውቅና ችሯታል በሀገር አቀፍ፣ አኅጉር አቀፍ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ተቋማትና መሪዎች ዘንድ የኢትዮጵያ አረንጓዴ ዐሻራ ትግበራ ተወድሷል። ከእነዚህ ዕውቅናዎች መካከል፤ የዓለም የምግብና እርሻ ድርጅት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአግሪኮል ሽልማት መስጠቱ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) Outstanding African Leadership Award ማግኘታቸው የሚሉት ይጠቀሳሉ። እንዲሁም፤ ኢትዮጵያ 2ኛውን የአፍሪካ የዓየር ንብረት ጉባዔ ተመርጣ ማስተናገዷ፣ ኢትዮጵያ 2ኛውን የተባበሩት መንግሥታት የሥርዓተ-ምግብ ጉባዔ ማስተናገዷ፣ በ80ኛው የዓለም ምግብና እርሻ ድርጅት ጉባዔ ለዘላቂ ደን ልማት የተሰጣት ዕውቅና እንዲሁም ኢትዮጵያ ኮፕ-32 (COP- 32) ለማስተናገድ መመረጧ በዘርፉ ላከናወነችው አርዓያነት ያለው ተግባር የተሰጡ ዕውቅናዎች ናቸው። ኢትዮጵያ ስኬታማውን የአረንጓዴ ዐሻራ ኢኒሼቲቭ ትልሟን ለሀገራት ማጋራቷ ኢትዮጵያ በራሷ ሐሳብ አመንጭነት ሕዝቧን አስተባብራ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) እየተሰጠ ባለ ያልተቆራረጠ ጠንካራ አመራር በአረንጓዴ ዐሻራ ዘርፍ ያስመዘገበችውን ስኬት፣ አሠራር (ልምድ) እና ችግኝ ለተለያዩ ሀገራት አጋርታለች። ይህም እየሄድችበት ያለው መንገድ ሁሉ ተባብሮ ማደግን ያነገበ ለመሆኑ አሥረጂ ነው። በዚህም መሠረት፤ በ2012 ዓ.ም ለፑንትላንድ፣ በ2012 ዓ.ም ለፓኪስታን፣ በ2012 ዓ.ም ለጂቡቲ፣ በ2013 ዓ.ም ለደቡብ ሱዳን፣ በ2013 ዓ.ም ለሩዋንዳ እና ለሌሎችም በዘርፉ ያላትን የተመሠገነ ልምድ አጋርታለች። የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ዐሻራ ኢኒሼቲቭ የተመራበት ሂደት የኢኒሼቲቩ ሐሳብ አመንጭ እና አመራር ሰጭ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ናቸው። ወደ ክልል፣ ዞን ወረዳ እና ቀበሌ በማውረድም በተቀናጀ ትጋት በመመራቱም ስኬታማ መሆን ችሏል። በዚህም መሠረት፤ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ሐሳብ አመንጭነትና አመራር ሰጭነት፣ በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች እና ባለድርሻ አካላት ቅንጅት፣ በክልል ርዕሳነ-መሥተዳድሮችና ሴክተር መሥሪያ ቤቶች ቅንጅት፣ በየደረጃው በተዋቀረ የቴክኒክ ኮሚቴ አማካኝነት፣ በተደራጀ የሕዝብ ተሳትፎ አማካኝነት የአረንጓዴ ዐሻራ ኢኒሼቲቭ በስኬት እየተተገበረ ይገኛል። ከአረንጓዴ ዐሻራ ጋር በተያያዘዘ የቀጣይ አቅጣጫዎች የአረንጓዴ ዐሻራ ኢኒሼቲቭ የለውጡ መንግሥት ከመጣ ወዲህ ላለፉት ዓመታት በተቀናጀ አግባብ ተመርቷል፤ አሁንም እየተተገበረ ነው። በቀጣይ ደግሞ ኢኒሼቲቩ እንዴት መከናወን እንዳለበት ግቦች ተቀምጠዋል። በዚህም መሠረት፤ የሕዝብ ባለቤትነትን አጠናክሮ ማስቀጠል (አረንጓዴ ባሕል መገንባት)፣ አማራጭ የኃይል አቅርቦት ሥራዎችን ማስፋትና በደን ላይ የሚደርሰውን ጫና መቀነስ፣ የሕግና የፖሊሲ ማሻሻያ የሚፈልጉ ጉዳዮችን ለይቶ በጥናት መመለስ የሚሉት የቀጣይ አቅጣጫዎች ናቸው። በተጨማሪም፤ ከአረንጓዴ ዐሻራ የሚገኘውን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት አጠናክሮ ማስቀጠል፣ የባለድርሻ አካላት እና የተቋማት ቅንጅታዊ አሠራርን ማጠናከር፣ በክረምት ወራት የሚተከሉ ችግኞችን በበጋ ወራት በአግባቡ መንከባከብ ከቀጣይ አቅጣጫዎች መካከል ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ሐሳብ በቢሾፍቱ ማስጀመራቸው ይታወቃል። በዚሁ ጊዜ ባስተላለፉት መልዕክትም፤ ከ8 ቢሊየን በላይ ችግኞች ለተከላ ዝግጁ በሆኑበት በዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ ወቅት አረንጓዴ ለሆነች ነገ፣ ሁላችንም ተስፋን እንትከል ሲሉ ለሀገሬው ጥሪ አቅርበዋል። ይህ ዘርፈ-ብዙ ጥቅሙ በተጨባጭ እየተገለጠ ያለው የአረንጓዴ ዐሻራ ኢኒሼቲቭ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ2011 ዓ.ም መጀመሩም የሚታወስ ነው። #አረንጓዴ_ዐሻራ #ኢዜአ #Ethiopian_News_Agency #ተስፋን_እንትከል
ትንታኔዎች
ምክክር - ወደ መግባባት መሸጋገሪያው ድልድይ!
Jun 24, 2026 1865
በዮሐንስ ደርበው በአመለካከት መለያየት ሥሪቱ ተፈጥሯዊ ነው። ሰዎች ልክ በመልክ፣ ቁመት ውፍረት ወይም ቅጥነት ሥብጥር፤ ምድርም በተፈጥሮ አቀማመጥ እና በዓየር ጠባይዋ ወጥ እንዳልሆኑት ሁሉ ማለት ነው። ለአንድ ሕዝብ እና ሀገር ብልጽግና ሲባል ከተበተነ ይልቅ የተደመረ ሐሳብ በእጅጉ ይጠቅማል። ሀገርኛ ብኂላችን “ከአንድ ብርቱ ሁለት መድኃኒቱ” ብሎ መሰባሰብን እንደሚሰብከው። የዋናው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ጀምሮ ይካሄዳል - የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ትውልዱ ዛሬንም ነገንም በሚጠቅመው የአረንጓዴ ዐሻራ ኢኒሼቲቭ ንቁ ተሳታፊ መሆን ይጠበቅበታል የአረንጓዴ ዐሻራ ኢኮኖሚያዊ ትሩፋት ከሥሪታቸው አንጻር ዕሳቤዎች የግድ ተጨፍልቀው አንድ እንዲሆኑ ባይጠበቅም፤ ሀገርና ሕዝብን ወዳስቀደመው በይበልጥ ገዥ ሐሳብ መቅረብ ግን ተገቢ ይሆናል። በአንጻሩ በተለያዩ ዋልታዎች ቆሞ መጓተት ለማን ይጠቅማል? በምክክር ሁሉንም አሸናፊ አድርጎ መቋጨት እየተቻለ ለበርካታ ዓመታት የሐሳብ ልዩነቶች የወለዷቸው ግጭቶች፤ እንደ ሀገር አያሌ ሰብዓዊ፣ ቁሳዊ፣ ሥነ-ልቡናዊ እና ማኅበራዊ ክስረቶች ማስከተላቸውን ታሪክ ይነግረናል። የለውጡ መንግሥት ለኢትዮጵያ ከቸራቸው ትልልቅ ጉዳዮች የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሙ አንዱ ነው። ሀገራዊ ምክክር በአንድ ሀገር ውስጥ የምንኖር ሕዝቦች ራሳችንን በታማኝነት ፈትሸን በሐሳብ ልዩነቶች ላይ ለመነጋገር መፍቀዳችንን የሚጠይቅ ሂደት እንደመሆኑ፤ በቁጥር የማይተመኑ ረቂቅ የሆኑ ዋጋዎች አሉት። ይህም ፍላጎትን በኃይል ለመተግበር ሕይወትና ንብረት ከሚያወድመው ጦርነት ይልቅ አዋጭ የመግባቢያ መንገድ መሆኑን ያሳያል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርአያ (ፕ/ር) ሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ.ም በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ ሀገራዊ የምክክር ጉባዔው ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ይካሄዳል። እዚህ ደረጃ ከመደረሱ በፊት በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ኮሚሽኑ በየጊዜው ማሳወቁም ይታወሳል። ሀገራዊ ምክክር በአካታችና አሳታፊ ውይይት ወደ የጋራ መግባባት መድረሻ አትራፊ መንገድ ነው። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽንም ኃላፊነቱን ለመወጣት ለምክክር በሩን ለሁሉም የማኅበረሰብ ክፍል ክፍት አድርጓል። በዚህም መሠረት ከዳያስፖራው፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ በተለያዩ ክልሎች ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ ከነበሩና ሰላምን ከመረጡ ብሎም ከመላው ኢትዮጵያውያን ጋር በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መክሮ፤ አጀንዳዎችንም ተቀብሏል። ኮሚሽኑ የመጨሻው የምክክር ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ የሚገልጹት ዋና ኮሚሽነሩ፤ አካታች የምክክር ጉባዔ ለማካሄድ በማንኛውም ጊዜ ወደ ምክክሩ ለሚመጡ አካላት በሩ ክፍት መሆኑንም አረጋግጠዋል። የኪንታሮት ህመም እንዴት ይከሰታል? እንዳይከሰት መከላከል የሚቻልበት ብልኀትስ አለ? 👉 ሀገራዊ ምክክር ምን ይጠግናል? የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሥራ በሆነው የመደመር መንግሥት መጽሐፍ ገጽ 384 ላይ እንደተቀመጠው፤ በሀገረ-መንግሥት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ሕዝብ ተመካክሮ፣ የጋራ መግባባት ላይ ደርሶ፣ የተግባባባቸውን በሕግና በሥርዓት አጽንቶ፤ ያልተግባባባቸውን ለወደፊት ምክክሮች አቆይቶ አልተጓዘም። በዚህ የተነሣ በየጊዜው ቅሬታ፣ ኩርፊያ፣ አብዮት፣ ዐመጽ ይፈጠራል። ነገሮች በተናጠል እየቀረቡ ለፖለቲካ ነጋዴዎች ምቹ ሁኔታ ይመቻቻል። ሁለንተናዊ ዕይታ ይጠፋል። ሀገራዊ ምክክር ይህን የዘመናት ስብራት ይጠግናል። 👉 ሀገሬው ለበለጸገችና ጠንካራ ሀገሩ ምን ይጠበቅበታል? መንግሥት በኢትዮጵያ የሐሳብ ገበያን ባሕል ለማድረግ እየተከተላቸው ካሉ መንገዶች አንዱ ሀገራዊ ምክክር ነው። በመደመር መንግሥት መጽሐፍ (ገጽ 383) ላይ እንደሰፈረው ደግሞ፤ በኢትዮጵያ የሚደረገው ሀገራዊ ምክክር የተለያዩ ሐሳቦች በአንድ መድረክ ቀርበው፤ በምክክርና ውይይት ጎልብተው አሰባሳቢና አስማሚ ሆነው የሚወጡበት መድረክ ነው። ስለሀገር የሚያገባው ሁሉም አካል በመሠረታዊ ጉዳዮች ላይ ሐሳብ አዋጥቶና ተነጋግሮ መግባባት የሚፈጥርበት ምኅዳር መሆኑም ተገልጿል። ስለዚህ ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሚከናወነው ለዚህ ታሪካዊ ሁነት መሳካት ኢትዮጵያውያን ከኮሚሽኑ ጎን በመሆን የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል። በሀገራዊ የምክክር ጉባዔው ለመሳተፍ የተመረጡ የማኅበረሰብ ክፍሎች እና የባለ ድርሻ አካላት ወኪሎችም ውጤታማ ጉባዔ ማካሄድ የሚችሉበትን ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቧል። ሀገራዊ ምክክር በአንድ በኩል፤ አንድነትና ኅብረትን በማጠናከር ልሂቃንና ሕዝብ ለአንድ ከፍ ላለ ዓላማ በአንድ ላይ እንዲቆሙ ያደርጋል። በዚህም ጥረቶች ሁሉ በአንድ አቅጣጫ እንዲፈስሱ ያደርጋል። በሌላ በኩል ፖለቲካዊ መረጋጋትና ሰላምን በመፍጠር የመንግሥት ትኩረት፣ ሀብትና ጊዜ ሳይበታተን ብልጽግናን ለማረጋገጥ ብቻ እንዲውል ያደርጋል (የመደመር መንግሥት መጽሐፍ ገጽ 403)። #እንመካከር! #በምክክር_ከሰፈር_እስከ_ሀገር_የተሻለ_ነገን_እንገንባ! #ኢዜአ #Ethiopian_News_Agency #የኢትዮጵያ_ዜና_አገልግሎት #ኢትዮጵያ_እየመከረች_ነው
የጡት ካንሰርን ለመከላከል …
Jun 16, 2026 3893
የጤና ነገር በዮሐንስ ደርበው የጡት ካንሰርን ለመከላከል … ለጡት ካንሰር ላለመጋለጥ መደረግ ስላለበት ጥንቃቄ፣ ስለ አጋላጭ ምክንያቶቹ እንዲሁም ምልክቶቹና ሕክምናው የካንሰር ሕክምና ስፔሻሊስት ዶክተር ቢኒያም ተፈራ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ አብራርተዋል። መነሻ - ካንሰር እንዴት ይከሰታል? እንደ ዶክተር ቢኒያም ገለጻ፤ ጤናማ የሰው ልጅ በሕይዎት ዑደት ሲያልፍ በሰውነቱ ውስጥ ያሉ ኅዋሶች (ሴሎች) በመደበኛ ሁኔታ ይራባሉ፤ ጊዜያቸውን ጠብቀውም ይሞታሉ። ይህን ሂደት በተፈጥሮ መቆጣጠር የሚቻልና የራሱ የሆነ የመቆጣጠሪያ መንገድ ያለው መሆኑንም ያስረዳሉ። ነገር ግን ይላሉ በአንዳንድ ምክንያቶች (በዘረመል ለውጥ ወይም በአካባቢያዊ ጉዳዮች ሊሆን ይችላል)፤ ከቁጥጥር ውጭ በሆነ ሁኔታ መራባት ሲጀምሩና ወይም መሞት ባለባቸው ጊዜ ሳይሞቱ ሲቀሩ፣ በራሳቸው አካባቢ ከመጠን በላይ በማደግ እንደ ዕጢ ያለ ነገር ሲፈጥሩ፤ ከዚህ አልፎ በአካባቢያቸው ያሉ ኦርጋኖችን መያዝ ሲጀምሩ እንዲሁም ወደ ሌላ የሰውነት አካል በመሄድ ባልተፈቀደላቸው ቦታ ላይ ማደግና ያለቁጥጥር መራባት የሚጀምሩበት ሂደት ካንሰር ተብሎ ይጠራል። ካንሰር ስሙ የሚሰየመው እንደተከሰተበት የሰውነት ክፍል መሆኑን አስገንዝበው፤ የጡት ካንሰር፣ የአንጀት ካንሰር፣ የቆዳ ካንሰር … እየተባለ የሚጠራው በዚሁ አግባብ መሆኑን አስረድተዋል። ለልብ ህመም አጋላጭ መንስዔዎች ምንድናቸው? እንደዋዛ የበርካቶችን በር የሚያንኳኳው ቨርቹዋል ኦቲዝም የጡት ካንሰር ምልክቶች በጡት ውስጥ ቀደም ሲል ያልነበረ (አዲስ) ዕብጠት መከሰት፣ የጡት ቆዳ ቀለም መለወጥ፣ ቁስለት መኖር፣ ከጡት ጫፍ ላይ መግል ወይም ደም መሰል ፈሳሽ መውጣት፣ በብብት ሥር አካባቢ የሚከሰት ዕብጠት በአብዛኛው የጡት ካንሰር ምልክቶች መሆናቸውን አብራርተዋል። እነዚህ ምልክቶች ኬዙ አድጎ መታየት ሲጀምር የሚስተዋሉ መሆናቸውን በመጠቆም፤ በአንዳንድ ሰዎች ላይ ምልክቶች ሳይኖሩ የጡት ካንሰር የመያዝ ዕድል መኖሩን አመላክተዋል። ወደ ጤና ተቋም መቼ መሄድ ይመከራል? የሕክምና ባለሙያው እንዳሉት፤ በአጠቃላይ አንዲት ሴት ጡቷ ላይ ቀደም ሲል ያልነበረ አዲስ ለውጥ ካለ ካንሰር ሊሆንም ላይሆንም እንደሚችል በመገመት ወደ ሕክምና ተቋም መሄድ ይጠበቅባታል። ነገር ግን ከካንሰር ጋር በተያያዘ ጥርጣሬን ሊጨምሩ የሚችሉ ሁኔታዎች እንዳሉ ጠቁመው ከነዚህም አንዱ በጡት ውስጥ ዕብጠት መኖርና ዕብጠቱም ምንም ዓይነት ህመም የሌለው መሆንን ጠቅሰዋል። አክለውም እስከ 80 በመቶ የሚሆነው በዕብጠት የሚመጣ የጡት ካንሰር ህመም እንደሌለው አንስተዋል። ህመም የለውም ብሎ ዕብጠትን ችላ ማለት እንደማይገባም በመምከር። በአጠቃላይ አንዲት ሴት ከላይ የጡት ካንሰር ምልክቶች ተብለው የተዘረዘሩትን ካየች በአፋጣች ወደ ሕክምና ተቋም መሄድ እንደሚጠበቅባት በአጽንዖት ገልጸዋል። በተጨማሪም በአጠቃላይ ዕድሜያቸው ከ20 ዓመት በላይ የሆኑ ሴቶች ጡታቸውን እየዳበሱ ከወትሮው የተለየ አዲስ ምልክት መኖሩን ማየት እንዳለባቸው መክረው፤ የተለየ (አዲስ) ነገር ሲኖር ወደ ሕክምና እንዲሄዱ አሳስበዋል። የአሳሳቢነት ደረጃ የጡት ካንሰር በጣም አሳሳቢ መሆኑን የሚገልጹት ዶክተር ቢኒያም፤ ከካንሰር ዓይነቶች ሁሉ በሀገራችን በቀዳሚነት ይቀመጣል ብለዋል። በተለይም ይላሉ፤ በሴቶች ላይ ከሚከሰቱ የካንሰር ዓይነቶች 1/3ኛ (31 በመቶ ገደማ) ያህሉ የጡት ካንሰር ነው። በእርግጥ ወንድንም ሴትንም ብንደምረው በብዛትም ሆነ በሽታ በማስከተል ረገድ በአንደኝነት የሚቀመጥ ነው ይላሉ። ስለ ጡት ካንሰር ያለ ግንዛቤ በሕብረተሰቡ ዘንድ ስለ ጡት ካንሰር አጠቃላይ ሁኔታዎች ሰፊ የግንዛቤ እጥረት መኖሩን ገልጸው፤ ለአብነትም ከ2/3ኛ በላይ የሚሆነው ታማሚ ወደ ሕክምና ተቋም የሚመጣው በሽታው በጣም ሥር ከሰደደ በኋላና ችግር መፍጠር ሲጀምር መሆኑን አንስተዋል። በወቅቱ ወደ ሕክምና ተቋም የሚሄዱት ሴቶች ቁጥር በሚፈለገው ልክ አለመሆኑን (ከ30 በመቶ በታች) መሆኑንም አመላክተዋል። ይህ ሁሉ የሆነው በግንዛቤ እጥረት እንደሆነ ይታመናል ብለዋል። በመንግሥታዊና በግል ተቋማት ጭምር ለአብነት የጥቅምት ወርን የጡት ካንሰር ወር አድርጎ ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ እየተከናወነ ቢሆንም በቂ አለመሆኑን ጠቁመዋል። በተለይም ስለጡት ካንሰር በአግባቡ አለማወቅ እንዲሁም በጡት ላይ የሚስተዋሉ ምልክቶችን ልብ አለማለት (ቀለል አድርጎ በማሰብ ሥር እንዲሰድ ዕድል መስጠት) እንዳለ አብራርተዋል። በጡት ካንሰር የሚከሰት ሞትን ከፍ ከሚያደርጉት አንዱ የግንዛቤ እጥረት እንደሆነ ይታመናል ይላሉ። በወንዶች ላይ የጡት ካንሰር በወንዶች ላይም የጡት ካንሰር ሊከሰት እንደሚችል የሚናገሩት የሕክምና ባለሙያው፤ የሚከሰትበት መጠን (ቁጥር) ግን በጣም ዝቅተኛ መሆኑን ነው ያስረዱት። ምንም እንኳን ኢትዮጵያ ላይ ቁጥሩ በዛ ቢልም በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ1 በመቶ በታች መሆኑንም ገልጸዋል። ዕድሜያቸው ከፍ ባሉ ወንዶች ላይ እንደሚከሰት በመግለጽ፤ ወንዶች በጡታቸው ላይ የተለየ ምልክትና ህመም ሲሰማቸው ወደ ሕክምና መሄድ እንደሚጠበቅባቸው መክረዋል። የጡት ካንሰር በሕጻናትና አዳጊዎች ላይ አይከሰትም ብሎ መደምደም ባይቻልም፤ የመከሰት ዕድሉ በጣም ዝቅተኛ መሆኑን ዶክተር ቢኒያም አስረድተዋል። እዚህ ላይ ብዙም አያሳስብም ይላሉ። ዕድሜና የጡት ካንሰር በአብዛኛው የጡት ካንሰር የሚከሰተው ዕድሜ እየጨመረ ሲሄድ መሆኑን የሚገልጹት ዶክተር ቢኒያም፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ በተለይም ከ50 ዓመት በላይ በሆናቸው ሰዎች ላይ የመከሰት ዕድሉ ከፍ እንደሚል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ ግን አብዛኛው ሕዝብ ወጣት ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ጠቁመው፤ ከ70 እስከ 80 የሚሆኑት የጡት ካንሰር ታማሚዎች ከ30 እስከ 50 ባለው ዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። ስለዚህ ዕድሜያቸው ገፋ ባሉም ሆነ በወጣቶች ጡት ላይ አዲስ ህመም ሲስተዋልና ምልክት ሲታይ ቶሎ ወደ ሕክምና መሄድ እንጅ፤ ከ50 ዓመት በላይ በሆናቸው ሰዎች ላይ የሚከሰት ነው ብሎ ችላ ማለት ተገቢ እንዳልሆነ አስገንዝበዋል። ለጡት ካንሰር አጋላጭ ምክንያቶች እንደ ሕክምና ባለሙያው ማብራሪያ፤ የጡት ካንሰር እኛ ቀድመን ብንሠራባቸው ተጋላጭነትን የምንቀንስባቸው እና ከቁጥጥራችን ውጭ በሆኑ (ተፈጥሯዊ) ሁኔታዎች የምንጋለጥባቸው ጉዳዮች አሉ። ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ሁኔታዎች የአካል እንቅስቃሴ አለማድረግ፣ ከመጠን ያለፈ ውፍረት፣ አልኮል መጠጣት፣ ሲጋራ ማጨስ፣ በፋብሪካ የተቀነባበሩ (ፕሮሰስ የተደረጉ) ምግቦችን ማዘውተር፣ አትክልትና ፍራፍሬ አለመመገብ ተጋላጭነቱን እንደሚጨምሩ አንስተዋል። እነዚህን በማስተካከል ተጋላጭነትን መቀነስ እንደሚቻል ገልጸዋል። በተፈጥሯዊ ሁኔታዎች ለጡት ካንሰር የሚያጋልጡ ሁኔታዎች የዕድሜ መጨመር፣ ሴት መሆን፣ በዘረመል (በጀኔቲክ) ለውጥ (በቤተሰብ ወይም በሕይዎት አጋጣሚ ከአካባቢያዊ ሁኔታ የሚመጡ የዘር መለወጦች) ለጡት ካንሰር ሊያጋልጡ እንደሚችሉ አብራርተዋል። እነዚህን ምንም ማድረግ እንደማይቻል በመግለጽ መፍትሔው ምልክት (ጥርጣሬ) ሲኖር ጊዜ ሳያባክኑ ወዲያውኑ ወደ ሕክምና ተቋም መሄድ ነው ይላሉ። ሕክምና እና የመዳን ተስፋ የጡት ካንሰር የመዳን ተስፋው ጥሩ መሆኑን ገልጸው፤ ይህ የሚወሰነው ግን ህመሙ እንደተገኘበት ደረጃ (ስቴጅ) ነው ይላሉ። [6/16/2026 9:29 AM] awe: በአጠቃላይ ሲታይም፤ ቶሎ ወደ ሕክምና በመሄድ የታከመ ካንሰር የመዳን ዕድሉ ከፍተኛ ነው ብለዋል። ባብዛኛው የሚሰጡ የሕክምና አማራጮችም፤ ኦፕሬሽን፣ ኬሞቴራፒ፣ የጨረር ሕክምና፣ የሆርሞን ሕክምና ሲሆኑ፤ አልፎ አልፎ ደግሞ እንደሁኔታው ታርጌትድ ቴራፒ እና ሚኖቴራፒ የሚባሉ የሕክምና አማራጮች መኖራቸውን ዘርዝረዋል። የሕክምና አማራጩን የሚወስነው በሽታው የተገኘበት ደረጃ (ስቴጅ) መሆኑንም አስገንዝበዋል። ምክረ ሐሳብ ሕብረተሰቡ እንዲገነዘበው የምንፈልገው ቶሎ ከታወቀ የጡት ካንሰር ታክሞ ይድናል፤ ለዚህ ደግሞ በጡት ላይ አዲስ ነገር ሲስተዋል ቶሎ ወደ ሕክምና መሄድ አዋጭ መሆኑን ነው ብለዋል። በጡት ላይ የሚስተዋል ዕብጠትና ህመም ሁሌም ካንሰር ነው ማለት ስላልሆነ ሴቶች ሳይደናገጡ ምርመራ እንዲያደርጉ መክረው፤ የምርመራ ውጤቱ ካንሰር መሆኑን ቢያሳይ እንኳ ቶሎ ወደ ሕክምና እስከሄዱ ድረስ በቀላሉ መዳን እንደሚችል መገንዘብ እንዳለባቸውም መክረዋል። ሕብረተሰቡ በአጠቃላይ ከጡት ካንሰር ጋር በተያያዘ ከሚሰራጩ የተሳሳቱ መረጃዎች መቆጠብ እንደሚገባውም ይመክራሉ። ቢያንስ ዕድሜያዋ ከ20 ዓመት በላይ የሆናት ሴት በወር አንድ ጊዜ ጡቷን በመዳበስ (ዕብጠትም ካለ እንዲታያት በመስታዎት ፊት ሆና በመመልከት) ቀደም ሲል ያልነበረ አዲስ ነገር መኖሩን መከታተል ይጠበቅባታል። ይህም ኬዙ ቢከሰት እንኳ ቶሎ ለመዳን ስለሚያግዝ ይላሉ። ዕድሜያቸው ከ40 ዓመት በላይ የሆኑ ሴቶች ደግሞ ቢቻል በዓመት አንድ ጊዜ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ የጡት ቅድመ ምርመራ እንዲደርጉ መክረዋል። #ኢዜአ #የጡት_ካንሰር #የጤና_ነገር
በኢዜአ ዐይን…!
Jun 15, 2026 2309
በዮሐንስ ደርበው ዜጎች ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ቁርጠኝነታቸውን ያረጋገጡበት ጠቅላላ ምርጫ • እንደ መነሻ ባሳለፍነው ወርኃ ግንቦት ኢትዮጵያ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አካሂዳለች። ምርጫ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መታያ፣ የመምረጥና የመመረጥ መብት ገቢራዊነት መገለጫ፤ ሕዝባዊ መንግሥትን አንባሪ ብሎም በሕዝባዊ ምርጫ ብቻ ወደሥልጣን የሚመጣበት መንገድ ነው። ለሀገራዊ መግባባትና ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታም ቁልፍ ነው። • ቅድመ ምርጫ ምርጫው ከመካሄዱ በፊት ባለድርሻ አካላት ምርጫውን ዴሞክራሲያዊ ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራትን አከናውነዋል። ለአብነትም፤ የምርጫ ሕጉን ከማሻሻል ጀምሮ በቴክኖሎጂ የታገዙ ሥርዓቶች ወደ ሥራ እንዲገቡ ተደርጓል። በተጨማሪም የምርጫ ትምህርትና ግንዛቤን ለማስፋት ለሚሠሩ በርካታ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ፈቃድ ተሰጥቷል። የምርጫ ሂደትን ፍትሐዊነት ለማረጋገጥም በርካታ ድርጅቶች በታዛቢነት ተመዝግበዋል። የመራጮች ምዝገባም፤ በመደበኛ የመራጮች ምዝገባ (ማኑዋል)፣ ምርጫዬ በተሰኘ የሞባይል መተግበሪያ እና በድረ ገጽ አማራጭ በመቅረቡ በርካታ መራጮችን አሳትፏል። በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለሚወዳደሩ የፖለቲካ ፓርቲዎችም በ24 ሬዲዮ፣ በ20 ቴሌቪዥን እና በ6 ጋዜጦች በሕዝብና በንግድ ሚዲያዎች ነጻ የአየር ሠዓት ተደልድሏል፤ ሐሳባቸውንም ተደራሽ አድርገዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያልተቋረጠ የስኬት ጉዞ በአረንጓዴ ዐሻራ ጸንቶና ተግቶ መሥራት ዘመኑ የሚፈልገው ዐርበኝነት • በምርጫ ወቅት በምርጫ ካርድ ሀገር የሚመራን የፖለቲካ ፓርቲ መምረጥ ከሥልጣኔ መገለጫዎች አንዱ ሆኖ ይጠቀሳል። የመራጮች ንቁ ተሳትፎም የሕዝቡን ዴሞክራሲያዊ ልምምድ ያጎለብታል። ምርጫ፤ ዜጎች ሕገ-መንግሥታዊ መብታቸውን እንዲጠቀሙ፣ ተቋማዊ አሠራሮች እንዲጠናክሩ ቁልፍ በመሆኑ ጠቅላላ ምርጫው ዜጎች ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ያላቸውን ቁርጠኝነት ያረጋገጡበት ነው። የሕዝቡን ትጋት አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባስተላለፉት መልዕክትም፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ አስደናቂም ተዓምረኛም ሕዝብ ነው፤ ከፈጣሪ በቀር ሕዝባችንን አሟልቶ ሊያውቅና ሊገመግም የሚችል ማን ነው? የዳበረ ባሕል፣ ሀገር ወዳድና የወል መሻቱን መጠበቅ የሚችል ሕዝብ መሆኑን በዘንድሮው ምርጫ ዳግም ለዓለም አሳይቷል ብለዋል። ታሪካዊ በሆነው ዕለትም፤ የሌሊቱ ብርድና ጨለማ ያላስፈራቸው፣ የቀትሩ ፀሐይና ድንገተኛ ዝናብ ያልበገራቸው፣ ሠርግ፣ ኀዘን፣ ወሊድና ሌሎች ማኅበራዊ ሁነቶች ያላገዳቸው፣ ረጃጅም ሰልፎች ያላታከታቸው፣ የአካል ጉዳት ድምጽ ለመስጠት ያልገደባቸው፣ ሕመም እና እርጅና የሀገር ተስፋን ከማየት ያላገዳቸው፣ የነገ ሀገር ተረካቢ ጨቅላ ልጃቸውን ማዘል ያላደከማቸው፣ ከምንም በላይ የጠላት ጩኸትና ማስፈራሪያ ያላስቆማቸው ዜጎች፤ በብዙ ውጣ ውረዶች መካከል ያሳዩት ጽናት ለዴሞክራሲና ለሀገር ሕልውና የተከፈለ መሆኑን ገልጸዋል። ከዚህ ሁሉ የሥልጡን ሕዝብ ትጋት በኋላ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ አሰጣጥ ሂደት በስኬት መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ አረጋግጠዋል። ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም በሰጡት መግለጫ ዜጎች በነቂስ ወጥተው ከማለዳው 12፡ 00 ሠዓት ጀምሮ ድምፃቸውን መስጠታቸውን አስታውቀዋል። ረጃጅም ሰልፍ የነበረባቸውን የምርጫ ጣቢያዎችም እስከ ሌሊቱ 6 ሠዓት በማራዘም መራጮች ድምፅ እንዲሰጡ መደረጉን አመላክተዋል። የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ ኡሁሩ ኬንያታ የ7ኛውን የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ሂደት በተመለከተ እንዳሉት፤ የኢትዮጵያ ዜጎች የመምረጥ መብታቸውን በነፃነት እና በሙሉ ፈቃዳቸው እንደተጠቀሙበትም ልዑካቸው ታዝቧል። ዜጎች ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን በተግባር አሳይተዋል፤ ያለምንም ጫና የሚፈልጉትን ፓርቲ መርጠዋል፤ ምርጫው ፍጹም ሰላማዊ እና በተዓማኒነት የተሞላ ሂደት ነው ብለዋል። የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ ስፔሲዮዛ ዋንዲራ (ዶ/ር)፤ ኢትዮጵያውያን የዜግነት መብታቸውን በመጠቀም ድምጻቸውን መስጠታቸውን ዐይተናል ብለዋል። የምርጫ ሂደቱ በተቀናጀ መንገድ መካሄዱን፣ በምርጫ ጣቢያዎችም ነፍሰ ጡር እናቶች፣ ልጆቻቸውን የያዙ እናቶች፣ ወጣቶች እና አዛውንቶች ሳይቀሩ ከማለዳው ጀምሮ ድምጽ ሲሰጡ እንደነበር መታዘባቸውን ተናግረዋል። በሁሉም አካባቢ የድምፅ መስጠት ሒደቱ በጥሩ ሁኔታ መካሄዱን በመጠቆም፤ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ የታየበት መሆኑን አስታውቀዋል። 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የዜጎች የነቃ ተሳትፎ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የማስፈፀም ዐቅም እያደገ መምጣቱ የታየበት ስኬታማ ምርጫ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አሕመድ ሁሴን ናቸው። ምርጫውን መታዘባቸውን በመጥቀስ፤ ምርጫው በርካታ ዜጎች የተሳተፉበት፣ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሂደትን የተከተለ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በምርጫው አረጋውያን፣ አካል ጉዳተኞች፣ ወጣቶች፣ ሴቶችን ጨምሮ በርካታ ዜጎች ድምጻቸውን እንደሰጡም ነው የገለጹት፡፡ ይኸውም የኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገና ይበልጥ አካታች ተሳትፎን እያጎለበተ መምጣቱን ማሳያ ነው ብለዋል። አክለውም፤ መንግሥት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ መገናኛ ብዙኃንና ሌሎችም አጋር አካላት ለምርጫው ስኬታማነት ሚናቸውን መወጣታቸውን ተናግረዋል፡፡ የዴሞክራሲና የፍትሕ ተቋማት እንዲጠናከሩ በትኩረት መሠራቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡ ቦርዱ ነፃና ገለልተኛ በመሆን የማስፈጸም ዐቅሙ እያደገ መምጣቱን በማንሳት፤ ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ ያበረከተውን አስተዋጽኦ በአብነት ጠቅሰዋል፡፡ • ድኅረ ምርጫ ሰኔ 3 ቀን 2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ በሰጡት መግለጫ፤ የ1 ሺህ 8 የምርጫ ክልሎች ውጤት ወደ ቦርዱ የማረጋገጫ ማዕከል መግባቱን ተናግረዋል። የምርጫ ጣቢያዎች የውጤት ቆጠራ ተጠናቅቆ በምርጫ ክልሎች የማዳመር ሥራ እየተከናወነ መሆኑንም አስታውቀዋል። ከ501ዱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የምርጫ ክልሎች 446ቱ ወደ ማዕከል መድረሳቸውንና ቀሪዎቹ የክልል ምክር ቤቶች መሆናቸውንም አብራርተዋል። በሌላ በኩል በመጠለያ ጣቢያዎችና በካምፖች የድምፅ አሰጣጥ መከናወኑን ጠቁመው፤ ውጤት የማዳመር ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ አስረድተዋል። #ምርጫ #ኢዜአ #የኢትዮጵያ_ዜና_አገልግሎት #Ethiopian_News_Agency #በኢዜአ ዐይን
ከአፍሪካ ሰማይ እስከ ዓለም ከፍታ፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያልተቋረጠ የስኬት ጉዞ!
Jun 12, 2026 7655
በኢዜአ ዐይን ...! በዮሐንስ ደርበው የኢትዮጵያ የዘመናት ስኬት መገለጫ፤የአፍሪካ አቪዬሽን ማዕከል እና በኢንዱስትሪው በዓለም ስመጥር ተቋማት መካከል አንዱ ነው ! የኢትዮጵያ አየር መንገድ። አየር መንገዱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ በማስገባት፣ የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ የኢትዮጵያን ወጪ ንግድ በመደገፍ፣ኢትዮጵያን በአቪዬሽን መሠረተ-ልማት ከፍ በማድረግ፣የቱሪዝም ዘርፉን በማገዝ እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ አፍተኛ አስተዋጽዖ እያበረከተ ነው። አየር መንገዱ ወደ ካይሮ "አንድ" ብሎ የጀመረው ታሪካዊ ጉዞ ዛሬ ላይ በአምስት አኅጉራት 145 መዳረሻዎችና በ147 ዘመናዊ አውሮፕላኖች አገልግሎቱን እያቀላጠፈም ይገኛል። አየር መንገድ የገነባው ዐቅም በዓለም መድረክ ላይ ተወዳዳሪ እንዲሆን ያስቻሉት ሲሆን የወደፊት ዕቅድና የዐቅም ግንባታ ትኩረቶቹ ለቀጣይ ስኬቱ ቁልፍ እንደሚሆኑም ይጠበቃል። በተለያዩ ጊዜያትም ዓለም አቀፍ፣አኅጉር አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ሽልማቶችን መሰብሰቡ ለዚህ ሁነኛ አስረጂ ይሆናል።የበረራ አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት፤የተቋማዊ ዕድገቱን ማስቀጠል እንዳስቻለውም ይገለጻል። አየር መንገዱ በታላቅነቱ ተፎካካሪ ሆኖ ለመዝለቅ የሀገር ውስጥ አቅሙን ማሳደግ እና የነበሩ አውሮፕላን ማረፊያዎችን በማደስ፣በማስፋፋት፣በማዘመን፣አዳዲስ በመገንባት ክልሎችን በአየር ትራንስፖርት በማስተሳሰር ለዜጎቹ ምቹ ሁኔታ እንዲኖር በልዩ ትኩረት እየሠራ ይገኛል። በሌሎች ዘርፎች የተመዘገቡትን ስኬቶች በቴክኖሎጂውም ለልብ ህመም አጋላጭ መንስዔዎች ምንድን ናቸው? በአረንጓዴ ዐሻራ ጸንቶና ተግቶ መሥራት ዘመኑ የሚፈልገው ዐርበኝነት የኢትዮጵያ አየር መንገድ 24ኛ የሀገር ውስጥ መዳረሻውን በቅርቡ አስመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ማድረጉም የእዚሁ ትጋት አንዱ ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል።ይህ መዳረሻ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመረቀው የነገሌ ቦረና ገዳ አውሮፕላን ማረፊያ ነው። ይህ መሠረተ-ልማትም ለአካባቢው ነዋሪ፣ የንግዱ ማኅበረሰብ እና ቱሪዝም ትልቅ ሥጦታ ነው። የምንገነባው እያንዳንዱ አዲስ የአውሮፕላን ማረፊያ ርቀትን በማጥበብ ትስስር ይፈጥራል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ይህም የክልሎችን ኢኮኖሚያዊ ዐቅም ያነቃቃል እንዲሁም ሕዝባችንን ይበልጥ ያቀራርባል ብለዋል። የአፍሪካ ኩራት የሆነውና 80ኛ ዓመቱን የያዘው አየር መንገዱ በእርግጥም “የአፍሪካ አዲሱ መንፈስ” (The New Spirit of Africa!”) ነው ሲሉ ገልጸውታል። በዚህም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአዳዲስ የመንገደኛ አውሮፕላን፣ የበረራ መዳረሻ በማስፋትና በሀገር ውስጥ የአውሮፕላን ማረፊያ መሠረተ-ልማት ግንባታ አስደናቂ ሥራ እየሠራ ነው። በሰፊ የአውታረ መረብ መስመሮች በርካታ ሀገራትን ተደራሽ በማድረግ ግንባር ቀደም ከሚባሉት ጥቂት አየር መንገዶች አንዱ ለመሆንም በቅቷል። አየር መንገዱ መንገደኞችን ከሀገር ሀገር ከማዘዋወር፤ከፍተኛ የካርጎ አገልግሎትን ከማቀላጠፍ ባሻገርም በሀገራት መካከል ንግድን፣ቱሪዝምን፣ኢንቨስትመንትን እና ውህደትን በመፍጠር በኩል ለአመታት የዘለቀ ዝናን አትርፏል። ይህ የተለያዩ አውሮፕላን ማረፊያዎችን የመገንባት ስትራቴጂ ኢትዮጵያን የወደፊቷ የአፍሪካ ግንባር ቀደም የአየር ትራንስፖርት በር የማድረግ ዓላማን ያነገበ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታን ባስጀመሩበት ወቅትም የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በአፍሪካ ታሪክ ትልቁ የአየር ትራንስፖርት መሠረተ-ልማት ፕሮጀክት እንደሚሆን መግለጻቸው ይታወሳል። ይህም የኢትዮጵያን ፈጣን የአየር ትራንስፖርት እድገት እና እየሰፋ የመጣውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፍ ትስስር ዘላቂ በማድረግ ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በተጨማሪ አዲስ ሜጋፕሮጀክት እየለማ ይገኛል ማለታቸው የዚሁ ማሳያ ነው። #በኢዜአ_ዐይን…! #ኢዜአ #የኢትዮጵያ_አየር_መንገድ #Ethiopian_News_Agency
ልዩ ዘገባዎች
በታዳጊው የተሰራችው መኪና
Jun 17, 2026 3280
ለአዳዲስ ፈጠራ የማይታክተው ልጅዓለም ንጉሱ ትውልድና እድገቱ በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ወረዳ ፀመራ ቀበሌ ነው። ከሕጻንነቱ ጀምሮ ፈትቶ መግጠምና አፍርሶ መስራትን እየተለማመደ የመጣው ልጅዓለም፤ ከቤት እስከ ትምህርት ቤት ያልተቋረጠ ፈጠራውን አጠናክሮ ቀጥሏል። ከዚህ ቀደም ለሚማርበት ፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከወዳደቁ ቁሶች የተለያዩ ቅርፃ ቅርፆችን በመስራት የፈጠራ አሻራውን አኑሯል። በትምህርትና በፈጠራ ሥራው ገፍቶበት አሁን ላይ የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ልጅዓለም እንጨት ገጣጥሞ መኪና በመስራት ያለውን የጥበብና ፈጠራ ክህሎት አሳይቷል። በታዳጊው የተሰራችውና በፔዳል የምትነዳው መኪና ሁለት ሰዎችን የማያዝ አቅም አላት። በቀጣይ ተጨማሪ ቁሶችን በማቅረብና በተለያየ መንገድ የሚያግዘው ካገኘ መኪናዋ በዲናሞ እንድትንቀሳቀስ ለማድረግ መዘጋጀቱን ተናግሯል። የተሽከርካሪውን አካል የገጣጠመው በአካባቢው አጠራር "እንቋ" የተሰኘ ዛፍ እንጨትን በመጠቀም ሲሆን የተሽከርካሪውን እግር ለማዘጋጀት ደግሞ የዋርካ ዛፍ ተጠቅሟል። በዚህም መሰረት የልጅዓለም መኪና የመብራትና የመሪ ስራዋ ተጠናቆ ሁለት ሰዎችን ጭና መንቀሳቀስ እንደምትችል በተግባር አሳይቷል። "በቀጣይ የሚያግዘኝና የሚደግፈኝ ካገኘሁ በዲናሞ የሚሰራ ተሽከርካሪ ለመስራት ዝግጁ ነኝ" ያለው ጥበበኛው ተማሪ ወደ ፊት ለሀገሬ ብዙ የመፍጠር ህልም አለኝ ብሏል። የፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ግርማ ጌቴ፤ ከዚህ በፊት ተማሪ ልጅዓለም በትምህርት ቤቱ የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎች እንዳሉት አስታውሰው ትምህርቱንም ፈጠራውንም አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል። የፈጠራ ክህሎቱን፣ ተሰጥኦውንና ፍላጎቱን ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ ተከታትያለሁ ያሉት መምህሩ የሳይንስ ትምህርቱንና የግል ክህሎቱን ደምሮ ለአዳዲስ ሥራዎች እየተጋ መሆኑን አንስተው፣ የመኪና ፈጠራውም ይህንኑ በተግባር ያሳየበት ነው ብለዋል። የግብዓት አቅርቦት ድጋፍ ከተደረገለት የተሻለና ውጤታማ ሥራ መስራት እንደሚችል ገልጸው ለሚፈጥሩ ወጣቶች በጥሩ ምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን ተናግረዋል። በእንጨት የተገጣጠመችው መኪና በሁላችንም ድጋፍ የዲናሞ፣ የብረትና ሌሎች አስፈላጊ ቁሶች ከተሟሉላት በታዳጊው ጥበብ የተሻለች መኪና ሆና ልትሰራ ትችላለች ሲለም እምነታቸውን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 16935
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 10008
በዮሐንስ ደርበው በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 15768
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
መጣጥፍ
የኢትዮጵያ ልዕልና በአረንጓዴው ከፍታ
Jun 25, 2026 568
(በዮርዳኖስ ዓባይነህ) የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከልና የተራቆቱ መሬቶችን መልሶ ለማልማት የጀመረችው ታሪካዊና አርአያነት ያለው ብሔራዊ ንቅናቄ ነው። ይህ ዘመቻ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ሕፃናት፣ ወጣቶች፣ አዋቂዎችና ልዩ ልዩ ተቋማት በነቂስ በመውጣት በየዓመቱ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞችን በከፍተኛ የሕዝብ ንቅናቄና በአንድነት መንፈስ ለመትከል ችለዋል። በዚህ ተከታታይ የችግኝ ተከላና እንክብካቤ ሥራ ምክንያት ለዓመታት ተራቁተው የነበሩ ተራራማና ኮረብታማ ቦታዎች እንዲሁም የሀገሪቱ የደን ሽፋን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲያገግም ሆኗል፤ ይህም የአፈር መሸርሸርን ከመከላከል ባለፈ የከርሰ-ምድር ውሃ መጠን እንዲጨምር ተጨባጭ አስተዋጽኦ አበርክቷል። አካባቢን ከመጠበቅ ባሻገር፣ መርሃ-ግብሩ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን የፍራፍሬ፣ የቡናና የቅመማ ቅመም ችግኞችን በማካተት አርሶ አደሩ ተጨማሪ ገቢ እንዲያገኝና የምግብ ዋስትናው እንዲረጋገጥ ትልቅ የኢኮኖሚ በር ከፍቷል። በተጨማሪም በዋና ዋና ከተሞች የተገነቡት ውብ አረንጓዴ ፓርኮች ከተሞችን ለነዋሪዎች ምቹ፣ ንጹህና ማራኪ ከማድረጋቸውም በላይ ተመራጭ የቱሪስት መዳረሻ እየሆኑ ይገኛሉ። በአጠቃላይ የኢትዮጵያ አረንጓዴ አሻራ ለአሁኑ ትውልድ የኢኮኖሚ ዋስትናን፣ ለወደፊቱ ደግሞ የተስተካከለ የአየር ንብረትና ለምለም ሀገርን የሚያስረክብ ታላቅ የትውልድ ቅርስ በመሆኑ፣ የተተከሉትን ችግኞች ተንከባክቦ ማሳደግና ዘላቂነታቸውን ማረጋገጥ የሁላችንም የጋራ ኃላፊነት ነው። 👉ከተፈጥሮ ጋር የተጻረረው የሰው ልጅ ስልጣኔ የሰው ልጅ በምድር ላይ መኖር ከጀመረበት ጥንታዊ ዘመን አንስቶ በሕይወት ለመቀጠልና ሕልውናውን ለማረጋገጥ ከተፈጥሮ ብሎም ከመሰሎቹ ጋር ጠንካራ እና ቀጣይነት ያለው መስተጋብር ሲያደርግ ቆይቷል። ነገር ግን ይህ መስተጋብር ሚዛኑን እየሳተ መጥቶ፣ ከጥንቱ የግብርና ስልጣኔ እስከ ዛሬው የኢንዱስትሪ መስፋፋት ድረስ በሰው ልጅ እጅ የተፈጸመው የተፈጥሮ መራቆት በምድር ላይ ከባድ ጠባሳ ጥሏል። የደን መጨፍጨፍ፣ የአፈር መሸርሸር እና የውሃ አካላት መናመን የዚሁ አውዳሚ ጉዞ ውጤቶች ናቸው። አግባብ ያለው የአካባቢ ጥበቃ ባለመደረጉም፣ በቢሊዮን የሚቆጠሩ አዕዋፋትና የዱር እንስሳት ለዘመናት ከኖሩበትና ለነሱ ከሚስማማቸው ቀያቸው ለመሰደድ ተገድደዋል። የተባበሩት መንግስታት የምግብ እና ግብርና ድርጅት (FAO) በ2016 እ.ኤ.አ ባወጣው ጥናት መሠረት፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ 92 ሺህ ሄክታር ደን ይጨፈጨፋል። ለዚህም የእርሻ መሬት ማስፋፋትና የማገዶ ፍላጎት መጨመር በዋና ምክንያትነት ይጠቀሳሉ። ይህ የዓለም አቀፍ ስጋት ለሀገራችን ለኢትዮጵያ ደግሞ የራቀ ሳይሆን የውስጥ ቁስል ነበር። በደን መጨፍጨፍና በአፈር መሸርሸር ምክንያት በተደጋጋሚ የተከሰቱት የድርቅ፣ የረሃብ፣ የመሬት መንሸራተት እና የሕዝቦች መፈናቀል ታሪኮች የቅርብ ጊዜ ትዝታዎቻችን ናቸው። 👉የ"ክፉ ቀን" ትርክት እና የስነ-ልቦና ጠባሳ ከ1888 እስከ 1892 እ.ኤ.አ በሀገራችን የተከሰተውና '’ክፉ ቀን'’ ተብሎ የሚታወቀው አሰቃቂ የረሃብ ታሪክ ፣ ከዚያም በኋላ በወሎና በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የታዩት ድርቆች በዓለም መገናኛ ብዙሃን ጎልተው ሲዘገቡ ቆይተዋል። ይህ አሳዛኝ ክስተት ለውጭ መገናኛ ብዙሃንና ተቋማት ተጨማሪ ዝና እና ገቢ ማግኛ ሰበብ ሲሆን፣ ለሕዝባችን ግን ለዘመናት ያልተሻረ የስነ-ልቦና ቁስል ጥሎ አልፏል። ኢትዮጵያን በዓለም መድረክ የድህነት እና የረሃብ ተምሳሌት አድርጎ በመሳል፣ ኢትዮጵያውያንን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን አንገት ያስደፋ ጥቁር ታሪክ ሆኖ ኖሯል። ታዲያ ይህንን የውርደት ትርክት የሚቀይር፣ ሀገራዊ ክብርን የሚመልስና ቀጣይነት ያለው የአካባቢ ጥበቃን የሚያረጋግጥ ወሳኝ እርምጃ መውሰድ የህልውና ጉዳይ ነበር። 👉አረንጓዴ አሻራ፦ ተግዳሮቶችን የመለወጥ የፅናት ጉዞ በ2011 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሃሳብ አመንጪነት፣ በተቋማት ቅንጅትና በተደራጀ የሕዝብ ንቅናቄ "የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር" ተጀመረ። በመጀመሪያው ዓመት “40 ዛፎች በነፍስ ወከፍ” በሚል መሪ ሃሳብ የተጀመረው ዘመቻ፣ ከዕቅድ በላይ 18 በመቶ ስኬት በማስመዝገብ የሕዝቡን የልማት ጥም አሳየ። በሁለተኛው ዓመት (2012 ዓ.ም) ዓለምን ያሸበረው የኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ወረርሽኝ ቢከሰትና ማኅበራዊ መራራቅ፣ ጥንቃቄዎች እንዲሁም ከቤት ሆኖ መሥራት ግዴታ ቢሆንም፣ የኢትዮጵያውያን የአረንጓዴ ጉዞ አልተገታም። “እየተጠነቀቅን እንተክላለን” በሚል መሪ ሐሳብ ፣ ማኅበረሰቡ ደህንነቱን ጠብቆ በመንቀሳቀሱ ከዕቅድ በላይ 14 በመቶ ችግኝ መትከል ተችሏል። 👉የሰባት ዓመታት ስኬቶች በቁጥር እና የስነ-ምህዳር መነቃቃት ይህ ስራ ለአንድና ለሁለት ዓመት የተደረገ ዘመቻ ሳይሆን የሰባት ዓመታት ተከታታይ የፅናት ጉዞ ነበር። ከ2011 እስከ 2017 ዓ.ም ባሉት ዓመታት ውስጥ በአጠቃላይ ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞች በኢትዮጵያ ምድር ላይ ተተክለዋል። የችግኞቹ የስብጥር ይዘትም ስልታዊ የደን ልማትን ያሳያል፦ 60 በመቶ የጥምር እርሻ ደን (Agroforestry) 35 በመቶ የተፈጥሮ ደን ሽፋን 5 በመቶ የከተማ ውበት ዛፎች ከተከናወኑት የክትትልና ቁጥጥር ሪፖርቶች መረዳት እንደሚቻለው፣ ከተተከሉት ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞች ውስጥ በአማካይ ከ75 በመቶ እስከ 80 በመቶ በላይ የመፅደቅ መጠን (Survival Rate) ማሳየት መቻላቸው የሥራውን ውጤታማነት በተጨባጭ ያረጋግጣል። ይህ መጠነ-ሰፊ ስራ ቀደም ሲል ከ2010 እስከ 2016 ዓ.ም ይከሰት የነበረውን የደን መጨፍጨፍ በ65 ሺህ ሄክታር በመቀነስ፣ የሀገሪቱን የደን ሽፋን በ11 ነጥብ 4 በመቶ ከፍ እንዲል አድርጓል። የተከናወነው የተቀናጀ የልማት ስራ የአፈር መሸርሸርን በመቀነስና የውሃ አካላትን በማንሰራራት ረገድ ትልቅ ሚና ተጫውቷል። ይህ የደን ሽፋን ዕድገት ሀገሪቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከካርቦን ሽያጭ (Carbon Trading) እና ከአየር ንብረት አረንጓዴ ፋይናንስ (Green Finance) ልታገኝ የምትችለውን የኢኮኖሚ ዕድል በከፍተኛ ደረጃ የሚያሰፋላት ነው። 👉ከስነ-ምህዳር ጥበቃ ወደ ቢሊዮን ዶላር ኢኮኖሚ ግንባታ እና የኮሪደር ልማት የአረንጓዴ አሻራ ስኬት ስነ-ምህዳሩን በማደስ ብቻ አልተገደበም፤ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ የጀርባ አጥንትም ጭምር ቀይሯል። መሬትን የማከምና የአፈር እርጥበትን የመመለስ ስራው በ2017 ዓ.ም 280 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ በሀገር ውስጥ ለማምረት አስችሏል። ይህ ውጤት ኢትዮጵያ ቀደም ሲል ለስንዴ ማስመጫ ታወጣ የነበረውን አንድ ቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ሙሉ በሙሉ ማስቀረት ያስቻለ ታሪካዊ ምዕራፍ ነው። በተጨማሪም ይህ አረንጓዴ ልማት ኢትዮጵያን በአፍሪካ 2ኛዋ የአቮካዶ ምርት ላኪ ሀገር ያደረጋት ሲሆን፣ በ2017 ዓ.ም የቡና ምርትን በማስፋፋትና ጥራትን በመጨመር 2 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ታሪካዊ የውጭ ምንዛሪ ለማስመዝገብ አስችሏል። ይህ ታላቅ ስኬት የተገኘው የኢኮ-ሲስተም ልማትን፣ የገጠር ልማትን፣ የወንዝ ዳርቻ ልማትን እና የከተማ ኮሪደር ልማትን (Urban Corridor Integration) ባካተተ የተቀናጀ ስትራቴጂ ነው። በተለይም በአዲስ አበባና በተለያዩ ከተሞች የተከናወኑት የኮሪደር ልማት ስራዎች የከተማዋን ገጽታ በከፍተኛ ደረጃ ከመቀየር ባለፈ፣ ለነዋሪዎች ምቹና ሰፊ የእግር መንገዶችን፣ ማራኪ የአረንጓዴ ስፍራዎችንና መናፈሻዎችን በመፍጠር ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገር ጎብኚዎች ደህንነቱ የተጠበቀና ማራኪ የከተማ ቱሪዝም (Eco-tourism) መዳረሻዎችን በተግባር መፍጠር ችሏል። 👉የአረንጓዴ ዲፕሎማሲ መሪነት እና ዓለም አቀፍ እውቅና ይህ ንቅናቄ በሀገር ውስጥ ካለው ፋይዳ ባለፈ፣ ኢትዮጵያ በአህጉራዊና በዓለም አቀፍ ደረጃ "የአረንጓዴ ዲፕሎማሲ" መሪ እንድትሆን አድርጓታል። እንደ ኤርትራ፣ ጅቡቲ፣ ፓኪስታን፣ ደቡብ ሱዳን እና ሩዋንዳ ያሉ ሀገራት ከኢትዮጵያ ተሞክሮ በመቅሰም በሀገራቸው የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር መጀመራቸው የዚህ ማሳያ ነው። በተጨማሪም የዓለም ምግብና ግብርና ድርጅት (FAO) ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የ"አግሪፎድ ሻምፒዮን" እና "የላቀ የአፍሪካ አመራር ሽልማት" መስጠቱ ፣ ኢትዮጵያ 2ኛውን የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ምግብ ጉባኤን ማስተናገዷ እና በ80ኛው የፋኦ ጉባኤ ላይ ለሀገሪቱ አጠቃላይ ዕድገት የተሰጠው እውቅና የዓለምን አድናቆት ያረጋገጡ ክስተቶች ናቸው። እነዚህ ዓለም አቀፍ ምስክርነቶች ኢትዮጵያ ቀደም ሲል ተስሎባት የነበረውን የድርቅ እና የረሃብ አፍራሽ ትርክት በአረንጓዴ ልማት፣ በአንድነት እና በምርታማነት በተግባር የቀለበሰችበት ታላቅ ድል ነው። 👉ስምንተኛው ዙር የአረንጓዴ ዐሻራ፡ "ተስፋን እንትከል!" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዲ ሐይቅ የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ማስጀመራቸው ይታወቃል። መርሃ ግብሩ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ሉዓላዊነትና ብልፅግና አሰናስሎ የሚያረጋግጥ ብሔራዊ የልማት አቅጣጫ መሆኑ ተመስክሮለታል። የዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ ዘመቻ "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ሐሳብ መጀመሩ ጥልቅ ትርጉም አለው። ተስፋ የነገን ብሩህ ምዕራፍ ዛሬ ላይ ለመጻፍ የሚያስችል አረንጓዴ መቀነት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉትም፤ አረንጓዴ ዐሻራ አፈራችንን ከስደት፣ የታላቁን ህዳሴ ግድባችንን ደግሞ ከደለል የሚታደግ ብሔራዊ ጋሻ ሆኗል። የአባቶቻችን የዓድዋ ድል ወራሪን ያሳፈረ ታላቅ ገድል እንደነበረ ሁሉ፣ የአሁኑ ትውልድ በአረንጓዴ ዐሻራ እያከናወነ ያለው ተግባርም ለቀጣዩ ትውልድ የሚሻገር አዲስ የታሪክ ገድል እየሆነ ይገኛል። ይህ ንቅናቄ የሀገሪቱን የተረጂነት ታሪክ ወደ ማድረግና ራስን ወደ መቻል ዘመን የሚያሸጋግር የመደመር መርህ መገለጫ ነው። የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ዐሻራ ጉዞ ቁጥራዊ መረጃዎች የህዝብ ቁርጠኝነት ማሳያ ናቸው። ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን ከ48 ቢሊየን በላይ ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ያላቸው ችግኞች ተተክለዋል። በዘንድሮው መርሃ ግብር ደግሞ ከ8 ቢሊየን በላይ ችግኞችን ለመትከል የታቀደ ሲሆን፤ ይህም አጠቃላይ የተተከሉትን ችግኞች ቁጥር ወደ 56 ቢሊየን ያደርሰዋል። ይህ ታላቅ ስኬት እዚህ ላይ አያበቃም፤ ሀገሪቱ በፈረንጆቹ 2029 የሚካሄደውን የዓለም አቀፉን የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (COP32) ስታስተናግድ፣ በአጠቃላይ 65 ቢሊየን ችግኞችን መትከል የቻለች መሪ ሀገር መሆኗን ለዓለም የምታበስርበት ታሪካዊ ምዕራፍ ይሆናል። በክረምቱ ወራት እያንዳንዱ ዜጋ "ተስፋን በመትከል" የዓድዋን የኩራት ስሜት በአረንጓዴ ልማት ሊደግመው ይገባል። የበለፀገችና የተከበረች ኢትዮጵያን ለቀጣዩ ትውልድ ለማስረከብ፣ የተተከሉትን ችግኞች ተንከባክቦ ማሳደግና የአረንጓዴ ዐሻራን ስኬት ማስፋትና ማስቀጠል የዛሬው ትውልድ የማይታጠፍ ብሔራዊ ጥሪ ነው። 👉የወደፊት ስትራቴጂካዊ አቅጣጫዎች በኢትዮጵያ እስከአሁን የተመዘገቡ ስኬቶችን ዘላቂ ለማድረግና የተፈጥሮ ቅርሶቻችንን ይበልጥ ለማጠናከር የወደፊት የትኩረት አቅጣጫዎች በግልጽ ተቀምጠዋል። መንግሥት የልማቱን የሕዝብ ባለቤትነት ማረጋገጥና ማቀናጀት፣ አረንጓዴ ልማትን እንደ ባህል መገንባት፣ የቴክኖሎጂ እሴቶችን በመጠቀም የሥራ ዕድሎችን ማስፋፋት፣ በተፈጥሮ ሀብት ላይ የሚደረገውን ጫና መቀነስ፣ እንዲሁም አዲስ የተገነቡ የኮሪደር ልማቶችንና ፓርኮችን በመጠበቅ የጎብኝዎችን ደህንነት ማረጋገጥና የተፈጥሮ ቅርስን አብሮ ማጠናከር ላይ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጧል።
የሀዋሳ ቀጣይ የዕድገትና የውበት ምዕራፍ
Jun 24, 2026 565
ሀዋሳ፤ ፤ ሰኔ 17/2018 (ኢዜአ)፦የሀዋሳ ቀጣይ የዕድገትና የውበት ምዕራፍ በእንዳለ ደበላ (ሀዋሳ ኢዜአ) ታቦር ተራራን በአንድ ጎኗ አላሙራ ተራራን ደግሞ በሌላው ጎኗ ታቅፋ የከተመችው ሀዋሳ ከተማ የፍቅር ሐይቅን ጨምሮ የተለያዩ የመስህብ ስፍራዎችንም በጉያዋ አቅፋ ይዛለች። ለባህላዊ ሕክምና አገልግሎት ጭምር የሚውሉት የወንዶገነት እና የይርጋለም የተፈጥሮ ፍል ውሀዎች ከሀዋሳ በቅርብ ርቀት ላይ መገኘታቸው ከተማዋ የቱሪስት መዳረሻ እንድትሆን በማድረግ በኩል የራሳቸው አስተዋጽኦ አላቸው። የሲዳማ ክልል ርዕሰ መዲናዋ ሀዋሳ ካሏት ተፈጥሯዊ የመስህብ ስፍራዎች በተጨማሪ የተለያዩ ባህላዊና ሀይማኖታዊ በዓላት በድምቀት የሚከበሩባት መሆኑም በጎብኚዎች ተመራጭ አድርጓታል። ሀዋሳ ባላት የተፈጥሮ ሀብት ላይ ተጨማሪ ውበትን ያላበሳት የኮሪደር ልማትም ከተማዋን ለኑሮ፣ ለሥራና ለኢንቨስትመንት ይበልጥ ምቹና ተመራጭ እያደረጋት ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወደከተማዋ የሚመጡ ጎብኚዎች ቁጥር እንዲበራከትና የቆይታ ጊዜያቸውንም እንዲያራዝሙ በማድረግ በኩል የኮሪደር ልማቱ አዎንታዊ ሚና መጫወት ጀምሯል። በከተማዋ ከሪፈራል ሰርክል እስከ መንቦ፣ ከሳውዝ ስፕሪንግ እስከ ፍቅር ሐይቅ፣ ከፍቅር ሐይቅ እስከ ሳውዝ ስታር ሆቴል የተከናወኑ የኮሪደር ልማት ሥራዎች በተፈጥሮ የታደለችውን ሀዋሳን የበለጠ አድምቋታል። ውበቷን አጉልቶ ከማውጣት በተጨማሪ የከተማዋ ገቢ በማሳደግ በኩልም ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ነው። የሲዳማ ክልል ገቢዎች ባለስልጣን ምክትል ሀላፊና የደንበኞች አገልግሎት የታክሰ አሰባሰብ ዘርፍ ሀላፊ ወይዘሮ ሙላት ዮሴፍ በእዚህ ሀሳብ ይስማማሉ። እሳቸው እንዳሉት ባለፉት 11 ወራት በከተማዋ 6 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰብ ተችሏል። አምና በተመሳሳይ ወቅት 5 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ገቢ እንደተሰበሰበ አስታውሰው የዘንድሮው 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ብልጫ አለው ብለዋል። ለገቢው መጨመር በምክንያትነት ከጠቀሷቸው አንዱ የኮሪደር ልማቱን ተከትሎ የንግድ እንቅስቃሴውና የጎብኚው ቁጥር እያደገ መምጣት ነው። ይህን የከተማዋን የገቢ አቅም የበለጠ ለማሳደግ ያስችላል የተባለለት ተጨማሪ የኮሪደር ልማትም በአሁኑ ወቅት ሥራው ተጀምሯል። ከሳውዝ ስታር ሆቴል በቀድሞው መናኸሪያ እስከ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተጀመረው የኮሪደር ልማት ሥራ አንዱ ሲሆን በፍጥነት ለማጠናቀቅም ታቅዶ እየተሰራ ነው። ሀዋሳ የቱሪዝምና የኮንፈረንስ ማዕከልነቷልን ይበልጥ ለማሳደግ አሁንም በትጋት እየሰራች ነው፤ አሁንም ልማት ላይ ነች። ከከተማዋ መግቢያ የሐይቅ ዳርቻ ጀምሮ እስከ ታቦር ተራራ ድረስ 12 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የሐይቅ ዳርቻ ልማት ተጀምሯል። ይህም የከተማዋን እድገት ከማስቀጠል ባለፈ ይበልጥ የሚያደምቃት ነው። ተመራጭነቷነም ከፍ ያደርገዋል። በስድስት ወራት ውስጥ እንዲጠናቀቅ ታቅዶ ወደሥራ የተገባው የሐይቅ ዳርቻ የኮሪደር ልማት በመጀመሪያ ምዕራፍ ሥራ የፍቅር ሐይቅ መግቢያ፣ አሞራ ገደል እና አሣ ገበያ አካባቢዎችን አካቶ የሚገነባ ነው። የሐይቅ ዳርቻ ልማቱ 60 ሜትር ወደ ሐይቁ ተገብቶ የሚከናወን ሲሆን ሰው ሰራሽ የውሀ ፏፏቴ፣ በሐይቁ ዳርቻ የእግረኛና የብስክሌት መንገድ፣ የተለያዩ ሱቆች፣ ሬስቶራንት፣ የመመልከቻ ማማዎች እንዲሁም ሌሎች መዝናኛዎችን አካቶ የሚሰራ ነው። ልማቱ ተጠናቆ ወደአገልግሎት ሲገባ በከተማዋ የቱሪዝም እንቅስቃሴ ላይ አዎንታዊ አበርክቶ ይኖረዋል። የከተማዋ የቱሪዝም መረጃ እንደሚያሳየው ካለፉት ዓመታት ወዲህ በሀዋሳ ከተማ የቱሪስት ፍሰት እየጨመረ መጥቷል። በተለይ በኮንፈረንስ ቱሪዝም ረገድ እና በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት በኩል እየታየ ያለው ለውጥ ከተማዋን በቱሪስቶች ይበልጥ ተመራጭ አድርጓታል። ሀዋሳ ከተማ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን ጨምሮ የተለያዩ ስፖርታዊ ውድድሮችን ለማስተናገድ ተመራጭ መሆኗ በስፖርት ቱሪዝም ዘርፍ ይበልጥ እንድትታወቅ እያደረገ ነው። ክለባቸውን ለመደገፍ ወደከተማዋ የሚመጡ ደጋፊዎች ዘርፉ እንዲነቃቃ የራሳቸውን አሻራም እያሳረፉ ይገኛሉ። በሀዋሳ ከተማ የሚከበሩ ሀይማኖታዊና ባህላዊ በዓላትም ከተማዋ በርካታ እንግዶችን እንድታስተናግድ ከማድረጋቸው ባለፈ ለከተማዋ ገቢ መጨመር የራሳቸውን አስተዋጽኦ አበርክተዋል። የዓለም ቅርስ ሆኖ የተመዘገበው የሲዳማ ዘመን መለወጫ በዓል (ፊቼ ጨምበላላ) ለእዚህ ጥሩ ምሳሌ ነው። የጎብኚዎችን ቀልብ የሚስበው ይሄ በዓል ሌላው የሀዋሳ ከተማ ድምቀት ነው። በየዓመቱ በፍቼ ጨምባላላ በዓል ላይ ለመታደም ከሀገር ውስጥና ከመላው ዓለም በርካቶች ወደሀዋሳ ከተማ ስለሚመጡ ዋነኛው የቱሪስት መስህብ ነው ማለት ይቻላል። እነዚህ ባህላዊ፣ ሀይማኖታዊና ተፈጥሯዊ እሴቶችን በአግባቡ በማልማትና በማጎልበት ሀዋሳን ይበልጥ የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው። በቅርቡ የግንባታ ሥራው የተጀመረው የሀዋሳ ፍቅር ሐይቅ ዳርቻ ልማት ለእዚህ አንድ ማሳያ ነው። ልማቱ ከተማዋን የሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ ብሎም የዓለም ኮንፈረንስ ማዕከል ለማድረግ ትልቅ ራዕይ ይዞ የተጀመረ ነው። ይህን የሀዋሳ ሐይቅ ዳርቻ የኮሪደር ልማት በይፋ ያስጀመሩት የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ናቸው። የፍቅርና የሕብር ተምሳሌት የሆነችውን ሀዋሳ ውበቷን ይበልጥ ለማውጣትና ተመራጭ ለማድረግ የክልሉ መንግስት አበክሮ ይሰራል ነው ያሉት። እንደእሳቸው ገለጻ የኮሪደር ልማት ሥራው በፍጥነት እየተከናወነ የሚገኝ ሲሆን በቀጣይም ከሀዋሳ ሐይቅ እስከ ሞኖፖል ድረስ ያለውን አካባቢ በአምስተኛ ዙር የኮሪደር ልማት ለማልማት ታቅዷል። ሀዋሳን የኮንፈረንስ፣ የስፖርትና የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ ትልቅ ዕድል ይዞ ለሚመጣው የሀዋሳ ሀይቅ ዳርቻ ልማት የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም ተናግረዋል። የሀዋሳ ከተማን በሀገር ውስጥና በአፍሪካ ተመራጭ የኮንፈረንስ ማዕከል ለማድረግ እንደሚሰራ የገለጹት ደግሞ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጥራቱ በየነ ናቸው። ከተማዋን ይበለጥ ተመራጭ ለማድረግ ለሚከናወነው የመጀመሪያ ዙር የሐይቅ ዳርቻ ልማት 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል። ከዚህ ውስጥ ደግሞ 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን የሚሆው ከማህበረሰቡ የሚሰበሰብ መሆኑን ነው ከንቲባው የገለጹት። ህዝቡም የከተማዋን ልማት ለመደገፍ የአቅሙን እያገዘ ነው። ለልማቱ በአይነት፣ በገንዘብና በዕውቀት እያደረገ ያለው ድጋፍ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አንስተዋል። የሀዋሳ ሐይቅ ዳርቻ ልማት ከ1 ሺህ ለሚበልጡ ሰዎች የሥራ ዕድል እንደሚፈጠር ያነሱት ደግሞ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የሀዋሳ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ሀላፊ አቶ ቸርነት ፍላቴ ናቸው። በሀዋሳ በተለያዩ ምዕራፎች የተከናወኑ የኮሪደር ልማት ሥራዎች እስካሁን ከ2ሺህ ለሚበልጡ ሰዎቸ የሥራ ዕድል በመፍጠር ለበርካቶች ተጨማሪ ጥቅምን አስገኝቷል። የልማት ሥራዎች ለከተማዋ ነዋሪዎች የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባለፈ ሀዋሳን ውብ፣ ምቹና ለኑሮ ተመራጭ ከተማ እያደረጓት በመሆኑ በቀጣይም ህብረተሰቡን በማሳተፍ ልማቱ እንደሚጠናከር ነው የገለጹት። ከታቦርና አላሙራ ተራሮች እግር ሥር የከተመችው ሀዋሳ ዛሬም በሥራ ላይ ናት፣ የሚሰሩ ልጇቿ ዛሬም ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ከተማዋን ይብልጥ ከፍ ለማድረግ እየታተሩ ነው። የከተማዋን የቀጣይ የዕድገትና የውበት ምዕራፏን እውን ለማድረግ ልጆቿ በአቅማቸው አሻራቸውን ለማሳረፍ ወደተግባራዊ ሥራ ገብተዋል። በማማዋ ላይ ከፍ ብላ ጎልታ እንድትታይ የሚያደርጉት ርብርብ በዚህ ከቀጠለ ራዕዩዋን በማሳካት ሀዋሳን ከሀገር ውስጥ ባለፈ የአፍሪካ ኮንፈረንስ ማዕከል የማድረግ ግብ መሳካቱ አይቀሬ ነው።