ፈረንሳይ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፈች - ኢዜአ አማርኛ
ፈረንሳይ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፈች
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 18/2018 (ኢዜአ)፦ ፈረንሳይ የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ በስኬት መጠናቀቁን በማስመልከት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፋለች።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ይፋዊ ውጤት ማስታወቁን ተከትሎ፣ ፈረንሳይ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክቷን አስተላልፋለች።
ለኢትዮጵያ ባለሥልጣናትና ለምርጫው ሂደት መሳካት አስተዋጽኦ ላበረከቱ ባለድርሻ አካላትም ዕውቅና የሰጠች ሲሆን በምርጫው ሂደት ተሳትፎ ለነበራቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች እና ታዛቢዎች ምስጋና አቅርባለች።
ፈረንሳይ ከምንም በላይ ምርጫው በስኬት እንዲካሄድ ከፍተኛ ሚና ለተወጣው የኢትዮጵያ ህዝብ እንኳን ደስ አላችሁ ስትል መልዕክቷን አስተላልፋለች።