ቀጥታ፡

ስዊዘርላንድ፣ ካናዳ እና ቦሲኒያ ሄርዞጎቪና ጥሎ ማለፉን ተቀላቀሉ

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 19/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ የምድብ ሁለት የመጨረሻ ጨዋታዎች ትናንት ማምሻውን ተደርገዋል።

በቢሲ ፕሌስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ስዊዘርላንድ ካናዳን 2 ለ 1 አሸንፋለች።

ሩበን ቫራጋስ እና የካናዳው ጆሃን ማዛምቢ  የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ፕሮሚስ ዴቪድ የካናዳን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ውጤቱን ተከትሎ ስዊዘርላንድ በሰባት ነጥብ የምድቡ መሪ በመሆን ወደ ጥሎ ማለፉ ገብታለች።




ከአዘጋጅ ሀገራት መካከል አንዷ የሆነችው ካናዳ በአራት ነጥብ ተመሳሳይ ነጥብ ያላትን ቦሲኒያ ሄርዞጎቪናን በግብ ክፍያ በልጣ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ በማጠናቀቅ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥሎ  ማለፉን መግባቷን አረጋግጣለች።

በዚሁ ምድብ በሲያትል ስታዲየም በተካሄደው ሌላኛው ጨዋታ ቦሲኒያ ሄርዞጎቪና ኳታርን 3 ለ 1 አሸንፋለች።

ከሪም አላጅቤጎቪች፣ ኤርሚን ማህሚች እና የኳታሩ ሱልጣን አል ብሬክ በራሱ ላይ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

ሀሰን አል ሃይዶስ የኳታርን ብቸኛ ጎል አስቆጥሯል።

ቦሲኒያ ሄርዞጎቪና በአራት ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ በምርጥ ሶስተኛነት ወደ ጥሎ ማለፍ ገብታለች።

ኳታር በአንድ ነጥብ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ በመያዝ ከውድድሩ ተሰናብታለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም