ኢዜአ - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
በአማራ ክልል የአኩሪ አተር የግብይት ችግርን መንግስት እንዲያቃልል ተጠየቀ
Dec 6, 2023 28
ባህር ዳር፤ህዳር 26/2016 (ኢዜአ) ፡- በአማራ ክልል የአኩሪ አተር የዋጋ መቀነስን ለማስተካከል መንግስት የገበያ ትስስር እንዲፈጥር አርሶ አደሮችና ባለሃብቶች ጠየቁ። በክልሉ በአኩሪ አተር ሰብል ከለማው መሬት ስድስት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅም ተገልጿል። በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ የኩመር አውላላ ቀበሌ አርሶ አደር ይበልጣል አማረ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በዘንድሮው የመኸር ወቅት በአኩሪ አተር ካለሙት ሦስት ሄክታር መሬት 61 ኩንታል ምርት አግኝተዋል። ባለፈው ዓመት የአኩሪ አተር ምርት ዋጋ ከተገመተው በላይ በመውረዱ የማምረቻ ወጪያቸውን መሸፈን ሳይችሉ እንደቀሩም አስታውሰዋል። "የገበያ ችግር ዘንድሮ ይስተካከላል" በሚል ሰብሉን በስፋት ቢያመርቱም የገበያ ችግሩ ካለፈው ዓመት የተለየ እንዳልሆነ ገልጸዋል። ችግሩን ለመቅረፍም መንግስት የገበያ ትስስር እንደፈጥርላቸው አመልክተዋል። በዚሁ ወረዳ የደለሎ ቀበሌ አርሶ አደር ገብሬ አሻግሬ በበኩላቸው፤ ባለፈው ዓመት በነበረው የገበያ ችግር ተስፋ ሳይቆርጡ በአምስት ሄክታር መሬት ላይ የአኩሪ አተር ሰብል ማምረታቸውን አስታውሰዋል። ለአመረቱት ምርት ወጪያቸውን የሚያካክስ "የገበያ ዋጋ ይኖራል" ብለው ተስፋ ቢያደርጉም፤ አሁንም ዋጋው በኩንታል ከ2 ሺህ 500 ብር የማይበልጥ በመሆኑ ለኪሳራ እንዳይዳረጉ ስጋታቸውን ገልጸዋል። አሁን ያለው የገበያ ዋጋ ሰብሉን ለማምረት የወጣውን ወጪ የሚሸፈን እንዳልሆነ ጠቅሰው፤ የሚመለከተው አካል ሁሉ "ገበያ በማፈላለግ ሊያግዘን ይገባል" ብለዋል። ባለፈው ዓመት ያመረቱትን 470 ኩንታል አኩሪ አተር ገበያ ባለመኖሩ እስካሁን በመጋዘን ማስቀመጣቸውን የገለጹት ደግሞ በምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ በእርሻ ኢንቨስትመንት የተሰማሩት አቶ አምሳሉ ላቀው ናቸው። ዘንድሮም በአኩሪ አተር ካለሙት 20 ሄክታር መሬት 390 ኩንታል ምርት ማግኘታቸውን ጠቅሰው፤ መንግስት ከኢንዱስትሪዎችና ከላኪዎች ጋር በማስተሳሰር የገበያ ችግራቸውን እንዲፈታላቸው ጠይቀዋል። የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አጀበ ስንሻው በበኩላቸው እንደተናገሩት፤ ለኢንዱስትሪ ግብዓትና ለውጭ ገበያ የሚውለው የአኩሪ አተር ምርት ካለፈው ዓመት ጀምሮ በስፋት እየተመረተ ይገኛል። ሰብሉ ባለፈው ዓመት በስፋት ቢመረትም ምርቱ የታሰበውን ያህል ዋጋ ማውጣት ባለመቻሉ አርሶ አደሮችና በዘርፉ የተሰማሩ ባለሃብቶች የማምረቻ ወጪያቸውን መሸፈን ሳይችሉ ቀርተዋል። ዘንድሮም በ249 ሺህ 728 ሄክታር መሬት ለምቶ እየተሰበሰበ ከሚገኘው የአኩሪ አተር ሰብል ከስድስት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል። ምርቱ ተገቢውን ዋጋ አውጥቶ በዘርፍ የተሰማሩት ሁሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከአጋር አካላት ጋር ገበያ በማፈላለግ በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝም አመልክተዋል። በአኩሪ አተር ሰብል የተስተዋለውን የግብይት ችግር ከኢንዱስትሪዎችና ላኪዎች ጋር በማስተሳሰር ለመፍታት እየተሰራ መሆኑን የገለፁት ደግሞ የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ የሰብልና የኢንዱስትሪ ምርቶች ግብይት ዳይሬክተር አቶ ልንገረው አበሻ ናቸው። ከታህሳስ መግቢያ ጀምሮ ለሚጀመረው ግብይትም አቅራቢ ነጋዴዎች፣ ዘይት አምራች ኢንዱስትሪዎችና የእርሻ ውል ስምምነት የወሰዱ ባለሃብቶችና ላኪዎች ምርቱን በተገቢ ዋጋ እንዲገዙ ከወዲሁ በትብብር እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል። በአማራ ክልል ባለፈው ዓመት በአኩሪ አተር ከለማው መሬት ከአምስት ነጥብ ዘጠኝ ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት መገኘቱን ከግብርና ቢሮው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ለህዝቡ ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ በመስጠት ረገድ የሚስተዋሉ የአመራር ግድፈቶች ይታረማሉ
Dec 6, 2023 44
አዲስ አበባ፤ ህዳር 26/2016(ኢዜአ)፦ህዝቡ በሚፈልገው ልክ ምላሽ ለመስጠት በየደረጃው ባሉ አመራሮች ዘንድ የአስተሳሰብ፣ የአመለካከት እና በተግባር አፈጻጸም ላይ የሚታየውን ጉድለቶችን በየጊዜው በመገምገምና በማጥራት ችግሮችን መፍታት እንደሚያስፈልግ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ገለጹ። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ከክልል እስከ ወረዳ ያሉ አመራሮች ክልላዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ግምገማ መድረክ በቦንጋ ከተማ እያካሄደ ይገኛል። ርዕሰ-መስተዳድሩ የግምገማ መድረኩ ወቅታዊ ክልላዊ የፖለቲካ አዝማሚያ በመዳሰስና በመገምገም በየደረጃው በሚያከውናቸው ተግባራት ላይ የፖለቲካ አስተሳሰብና የተግባር አንድነት ለመፍጠር ታልሞ የተዘጋጀ እንደሆነም ገልጸዋል። የግምገማና የማጥራት መድረኩም እስከታችው መዋቅር ድረስ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል። የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ፀጋዬ ማሞ የብልጽግና ፓርቲ እሴትን፣ ራዕይ እንዲሁም ተልዕኮን በአግባቡ መፈፀምና መተግበር የሚችል አመራር ለመገንባት ክልሉ ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ተናግረዋል። አመራሩ አሁንም የሚታይበትን የአመለካከት ችግር በፍጥነት ማስተካከል እንደሚገባም አመልክተዋል። የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች የተሰጡ ቢሆንም አሁንም የሚታዩ ግድፈቶችን አንጥሮ ለማዉጣት ይህ መድረክ ተዘጋጅቷል ብለዋል። በግምገማ መድረኩ የክልል፣የዞን፣የወረዳና የከተማ አስተዳደር አመራሮች እየተሳተፉ ሲሆን መድረኩ በቀጣይ አራት ቀናት እንደሚቀጥል የደቡብ ምዕራብ ኢትየጵያ ህዝቦች ክልል የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ መረጃ ያመለክታል።
በምስራቅ ቦረና ዞን ባለፉት አራት ወራት ከ8 ሺህ ለሚበልጡ ወጣቶች የስራ እድል ተፈጥሯል
Dec 6, 2023 31
ነገሌ ቦረና፤ህዳር 26/2016 (ኢዜአ) ፦ በምስራቅ ቦረና ዞን በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ አራት ወራት በ532 ማህበር የተደራጁ ከ8 ሺህ በላይ ወጣቶች ወደ ስራ መግባታቸውን የዞኑ የክህሎትና የስራ እድል ፈጠራ ጽህፈት ቤት ገለጸ፡፡ በጽህፈት ቤቱ የስራ እድል ፈጠራ ባለሙያ አቶ ጎዳና ሳራ ዞኑ በተያዘው ዓመት ለ37 ሺህ 619 ስራ ፈላጊዎች የስራ እድል ለማመቻቸት አቅዶ ወደ ስራ መግባቱን ገልጸዋል፡፡ እስካሁን በተሰራ ስራም በ532 ማህበር ተደራጅተው ወደ ስራ የገቡ 8 ሺህ 21 ወጣቶች የማምረትና አገልግሎት የመስጠት ስራ መጀመራቸውን ገልጸዋል፡፡ በዞኑ ወደ ስራ ከገቡት ውስጥ 1ሺህ 200 የሚሆኑት የኮሌጂና የዩኒቨርስቲ ምሩቃን ወጣቶች እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ወጣቶቹ በግብርና፣ በንግድ፣ በአገልግሎት፣ በማንፋቸሪንግ፣ በግንባታ፣ በማዕድን ፍለጋና ግብይት የስራ ዘርፎች መሰማራታቸውን በማከል፡፡ ወደ ስራው ለተሰማሩት ወጣቶች በከተማና በገጠር አንድ ሺህ 800 ሄክታር መሬትና 27 የማምረቻና የመሸጫ ሼዶች መከፋፈላቸውንም አክለዋል፡፡ የወጣቶቹን ካፒታል ለማሳደግ እንዲረዳም 90 ሚሊዮን ብር የብድር አገልግሎት በሲንቄ ባንክ መመቻቸቱን ባለሙያው አመልክተዋል፡፡ በቅርቡ የስራ እድሉን ተጠቅመው በእንጨትና ብረታ ብረት ስራ ከተሰማሩት ወጣቶች መካከል የነገሌ ቦረና ከተማ ነዋሪና የቅድስተ ማሪያም ዩኒቨርስቲ ተመራቂ ወጣት ከነአን ብርሃኑ አንዱ ነው፡፡ ወጣቱ በመንግስት መስሪያ ቤት ተቀጥሮ ከመስራት ከሶስት ባልደረቦቹ ጋር ተደራጅተው የተሰማሩበት ስራ ከእራሳቸው አልፈው ለሌሎች 13 ወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠር እንዳስቻላቸውም ገልጸዋል፡፡ እሱና ባልደረቦቹ ከሲንቄ ባንክ በወሰዱት 100 ሺህ ብር ብድር የጀመሩት ስራ በአሁኑ ጊዜ ምርታችውን ለአከባቢው ገበያ እያቀረቡ እንደሆነ ገልጿል፡፡ አሁን ባለው የተሻለ የስራ እንቅስቃሴ በቀጣይ እስከ ሁለት ሚሊዮን ብር ብድር በመውሰድ የስራ ዘርፋቸውን ይበልጥ የማስፋት እቅድ እንዳላቸውም ተናግረዋል፡፡ የቤትና የቢሮ እቃ ምርታቸውን ለተጠቃሚ በማቅረብ ላይ መሆናቸውን የሚናገረው ደግሞ ሌላው የከተማው ነዋሪ ወጣት መሐመድ ሙሳና 14 ባልደረቦቹ ናቸው፡፡ ወጣቱና ባልደረቦቹ ስራ ሲጀምሩ ከመንግስት አንድ የመሸጫ ሼድ እና ከሲንቄ ባንክ ደግሞ የ50 ሺህ ብር ብድር መውሰዳቸውን ገልጿል፡፡
በኦሮሚያ ክልል 18ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በማያ ከተማ እየተከበረ ነው
Dec 6, 2023 34
ሐረር፤ ኅዳር 26/2016 (ኢዜአ)፡- በኦሮሚያ ክልል ደረጃ 18ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በምስራቅ ሐረርጌ ማያ ከተማ እየተከበረ ነው። "ብዝሃነትና እኩልነት ለአገራዊ አንድነት!" በሚል መሪ ሃሳብ እየተከበረ በሚገኘው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ላይ ቀኑን የተመለከቱ የተለያዩ ኪነ ጥበባዊና ሌሎች ዝግጅቶች እየቀረቡ ይገኛሉ። በክብር እንግድነት የተገኙት የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ሰዓዳ አብዱረህማን ቀኑን አስመልክተው መልዕክት እንደሚያስተላልፉ ይጠበቃል። በሥነ-ሥርዓቱ ላይ በጨፌ ኦሮሚያ የመንግስት ተወካይና የብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፈቃዱ ተሰማን ጨምሮ የፌዴራል፣ የአጎራባች እና የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ ምሁራን፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ታድመዋል።
የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ የማቋቋም ጥረትን ውጤታማ ለማድረግ የባለድርሻ አካላት ድጋፍ ተጠየቀ
Dec 6, 2023 42
አዲስ አበባ ፤ህዳር 26/2016 (ኢዜአ)፦ የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ የማቋቋም ጥረትን ውጤታማ ለማድረግ ባለድርሻ አካላት እገዛ እንዲያደርጉ የብሔራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን ጥሪ አቀረበ። የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ተሾመ ቶጋ የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ የማቋቋም ስራ ብዙ ተግባራትን ይጠይቃል ብለዋል። ለዚህም ኮሚሽኑ ተቋሙን በግብአት እና በሰው ሀይል የማደራጀት፣ወደ ተሀድሶ የሚገቡ የቀድሞ ተዋጊዎችን የመለየት እና ከክልሎች ጋር በስራዎቹ ላይ መግባባት የሚፈጥሩ መድረኮችን ማካሄዱን ተናግረዋል። በአሁኑ ጊዜ በሀገሪቱ ከ371 ሺህ በላይ የቀድሞ ተዋጊዎች መኖራቸውን ጠቁመው፤ መልሶ ወደ ማቋቋም ተግባር ውስጥ እንዲገቡ ከማድረግ በፊት በድጋሚ የማጣራት ስራ እንደሚሰራ ጠቁመዋል። ዋና ኮሚሽነሩ አክለውም፤ የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደ ሰላማዊ ህይወታቸው እንዲመለሱና እንዲቋቋሙ የማድረጉ ስራ ከፍተኛ ሀብት እንደሚጠይቅ ገልጸዋል። መንግሥት ለብሔራዊ ተሃድሶው ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ ከፍተኛ ሙዓለ ንዋይ ፈሰስ እያደረገ መሆኑን ጠቅሰው፤ ባለድርሻ አካላትም አስፈላጊውን እገዛ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደ ማህበረሰቡ የመቀላቀልና መልሶ የማቋቋም ስራ ለሀገሪቱ ልማትና ዘላቂ ሰላም መረጋገጥ ሚናው ቀላል እንዳልሆነ ጠቁመዋል። በተለይም በተለያዩ ግጭቶች ውስጥ ሲሳተፉ የነበሩ ተዋጊዎች ወደ ሰላም ተመልሰው የኢኮኖሚው ዋነኛ አምራች ሃይል እንዲሆኑ ማድረግ ለሀገር ጥቅሙ ትልቅ መሆኑን በማንሳት። በአስተሳሰብ ረገድም ልዩነቶችንና ችግሮችን በሰላም ከመፍታት የተለየ አማራጭ እንደሌለ ያስተምራል ሲሉም ነው ዋና ኮሚሽነር ተሾመ ቶጋ የተናገሩት። በመሆኑም የቀድሞ ተዋጊዎች ወደ የአካባቢያቸው ተመልሰው ተቋቁመው በዘላቂነት የሰላምና የልማት ሃይል እንዲሆኑ ሁሉም አካል እገዛ ማድረግ አለበት ብለዋል።
ፖለቲካ
ለህዝቡ ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ በመስጠት ረገድ የሚስተዋሉ የአመራር ግድፈቶች ይታረማሉ
Dec 6, 2023 44
አዲስ አበባ፤ ህዳር 26/2016(ኢዜአ)፦ህዝቡ በሚፈልገው ልክ ምላሽ ለመስጠት በየደረጃው ባሉ አመራሮች ዘንድ የአስተሳሰብ፣ የአመለካከት እና በተግባር አፈጻጸም ላይ የሚታየውን ጉድለቶችን በየጊዜው በመገምገምና በማጥራት ችግሮችን መፍታት እንደሚያስፈልግ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ገለጹ። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ከክልል እስከ ወረዳ ያሉ አመራሮች ክልላዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ግምገማ መድረክ በቦንጋ ከተማ እያካሄደ ይገኛል። ርዕሰ-መስተዳድሩ የግምገማ መድረኩ ወቅታዊ ክልላዊ የፖለቲካ አዝማሚያ በመዳሰስና በመገምገም በየደረጃው በሚያከውናቸው ተግባራት ላይ የፖለቲካ አስተሳሰብና የተግባር አንድነት ለመፍጠር ታልሞ የተዘጋጀ እንደሆነም ገልጸዋል። የግምገማና የማጥራት መድረኩም እስከታችው መዋቅር ድረስ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል። የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ፀጋዬ ማሞ የብልጽግና ፓርቲ እሴትን፣ ራዕይ እንዲሁም ተልዕኮን በአግባቡ መፈፀምና መተግበር የሚችል አመራር ለመገንባት ክልሉ ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ተናግረዋል። አመራሩ አሁንም የሚታይበትን የአመለካከት ችግር በፍጥነት ማስተካከል እንደሚገባም አመልክተዋል። የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች የተሰጡ ቢሆንም አሁንም የሚታዩ ግድፈቶችን አንጥሮ ለማዉጣት ይህ መድረክ ተዘጋጅቷል ብለዋል። በግምገማ መድረኩ የክልል፣የዞን፣የወረዳና የከተማ አስተዳደር አመራሮች እየተሳተፉ ሲሆን መድረኩ በቀጣይ አራት ቀናት እንደሚቀጥል የደቡብ ምዕራብ ኢትየጵያ ህዝቦች ክልል የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ መረጃ ያመለክታል።
በኦሮሚያ ክልል 18ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በማያ ከተማ እየተከበረ ነው
Dec 6, 2023 34
ሐረር፤ ኅዳር 26/2016 (ኢዜአ)፡- በኦሮሚያ ክልል ደረጃ 18ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በምስራቅ ሐረርጌ ማያ ከተማ እየተከበረ ነው። "ብዝሃነትና እኩልነት ለአገራዊ አንድነት!" በሚል መሪ ሃሳብ እየተከበረ በሚገኘው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ላይ ቀኑን የተመለከቱ የተለያዩ ኪነ ጥበባዊና ሌሎች ዝግጅቶች እየቀረቡ ይገኛሉ። በክብር እንግድነት የተገኙት የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ሰዓዳ አብዱረህማን ቀኑን አስመልክተው መልዕክት እንደሚያስተላልፉ ይጠበቃል። በሥነ-ሥርዓቱ ላይ በጨፌ ኦሮሚያ የመንግስት ተወካይና የብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፈቃዱ ተሰማን ጨምሮ የፌዴራል፣ የአጎራባች እና የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ ምሁራን፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ታድመዋል።
የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ የማቋቋም ጥረትን ውጤታማ ለማድረግ የባለድርሻ አካላት ድጋፍ ተጠየቀ
Dec 6, 2023 42
አዲስ አበባ ፤ህዳር 26/2016 (ኢዜአ)፦ የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ የማቋቋም ጥረትን ውጤታማ ለማድረግ ባለድርሻ አካላት እገዛ እንዲያደርጉ የብሔራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን ጥሪ አቀረበ። የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ተሾመ ቶጋ የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ የማቋቋም ስራ ብዙ ተግባራትን ይጠይቃል ብለዋል። ለዚህም ኮሚሽኑ ተቋሙን በግብአት እና በሰው ሀይል የማደራጀት፣ወደ ተሀድሶ የሚገቡ የቀድሞ ተዋጊዎችን የመለየት እና ከክልሎች ጋር በስራዎቹ ላይ መግባባት የሚፈጥሩ መድረኮችን ማካሄዱን ተናግረዋል። በአሁኑ ጊዜ በሀገሪቱ ከ371 ሺህ በላይ የቀድሞ ተዋጊዎች መኖራቸውን ጠቁመው፤ መልሶ ወደ ማቋቋም ተግባር ውስጥ እንዲገቡ ከማድረግ በፊት በድጋሚ የማጣራት ስራ እንደሚሰራ ጠቁመዋል። ዋና ኮሚሽነሩ አክለውም፤ የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደ ሰላማዊ ህይወታቸው እንዲመለሱና እንዲቋቋሙ የማድረጉ ስራ ከፍተኛ ሀብት እንደሚጠይቅ ገልጸዋል። መንግሥት ለብሔራዊ ተሃድሶው ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ ከፍተኛ ሙዓለ ንዋይ ፈሰስ እያደረገ መሆኑን ጠቅሰው፤ ባለድርሻ አካላትም አስፈላጊውን እገዛ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደ ማህበረሰቡ የመቀላቀልና መልሶ የማቋቋም ስራ ለሀገሪቱ ልማትና ዘላቂ ሰላም መረጋገጥ ሚናው ቀላል እንዳልሆነ ጠቁመዋል። በተለይም በተለያዩ ግጭቶች ውስጥ ሲሳተፉ የነበሩ ተዋጊዎች ወደ ሰላም ተመልሰው የኢኮኖሚው ዋነኛ አምራች ሃይል እንዲሆኑ ማድረግ ለሀገር ጥቅሙ ትልቅ መሆኑን በማንሳት። በአስተሳሰብ ረገድም ልዩነቶችንና ችግሮችን በሰላም ከመፍታት የተለየ አማራጭ እንደሌለ ያስተምራል ሲሉም ነው ዋና ኮሚሽነር ተሾመ ቶጋ የተናገሩት። በመሆኑም የቀድሞ ተዋጊዎች ወደ የአካባቢያቸው ተመልሰው ተቋቁመው በዘላቂነት የሰላምና የልማት ሃይል እንዲሆኑ ሁሉም አካል እገዛ ማድረግ አለበት ብለዋል።
ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ አገራዊ ምክክሩ ጉልህ ሚና አለው - ኮሚሽነር አቶ መላኩ ወልደማሪያም
Dec 6, 2023 60
ሶዶ፤ ህዳር 26/2016 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ሰላም ለማረጋገጥ አገራዊ የምክክር ሂደቱ ጉልህ ሚና እንዳለው የአገራዊ ምክክር ኮሚሽነር አቶ መላኩ ወልደማርያም ገለጹ። አገራዊ የምክክር ኮሚሽን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተባባሪ አካላት ስልጠና በወላይታ ሶዶ ከተማ መስጠት ጀመረ። ስልጠናውን ያስጀመሩት የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ መላኩ ወልደማሪያም የአገራችንን ሁለንተናዊ ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ ምክክሩ ጉልህ ሚና ይኖረዋል። "አለመግባባቶችና ግጭቶች እንዳይፈጠሩ ማድረግ እንዲሁም የተፈጠሩትንም በማርገብ የአገሪቷን ሁለንተናዊ ሰላምና ልማት ማረጋገጥ የምክክሩ ዋነኛ አጀንዳ ነው" ብለዋል። በመሆኑም ይሄ በኮሚሽኑ ስር በሚገኙ 11 ኮሚሽነሮች ብቻ የሚሳካ ባለመሆኑ ስልጠናው ተባባሪ አካላትን በጉዳዩ ዙሪያ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ያለመ መሆኑን አስረድተዋል። ምክክሩ አገራዊ መግባባት ላይ ለመድረስ የተሻለ አማራጭ መሆኑን አመልክተዋል። ምክክር ለየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ፣ ብሄርና ሀይማኖት የሚወግን ሳይሆን፤ "የአገርን ሁለንተናዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ያለመ ነው" ብለዋል። በስልጠናው በክልሉ ከሚገኙ ዞኖች፣ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ 700 ተባባሪ አካላት እየተሳተፉ ሲሆን፤ ለሶስት ቀናት እንደሚቆይ ተጠቁሟል።
የብሔር፣ ብሔረሰቦች መኖሪያ የሆነችው ጅግጅጋ እንግዶቿን በደማቅ ሁኔታ እየተቀበለች ነው-ከንቲባ ዚያድ
Dec 6, 2023 37
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 26/2016 (ኢዜአ)፡- ጅግጅጋ ከተማ ለ18ኛው ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ዝግጅቷን በማጠናቀቅ እንግዶችን በደማቅ ሁኔታ እየተቀበለች መሆኗን የከተማዋ ከንቲባ ኢንጂነር ዚያድ አብዲ ገለጹ። ከንቲባው ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ የጅግጅጋ ነዋሪዎች የበዓሉን ተሳታፊዎች በኢትዮጵያዊ እንግዳ ተቀባይነት እየተቀበሉ ነው ብለዋል። በጅግጅጋ ከተማ 18ኛውን የብሔር ብሔረሰብና ህዝቦች በዓል በድምቀት ለማክበር ሲደረግ የቆየው የቅድመ ዝግጅት ስራ መጠናቀቁን ገልጸዋል። በበዓሉ ለመታደም ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች እንግዶች ወደ ከተማዋ እየገቡ ነው ያሉት ከንቲባው፥ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦችን የወከሉ የባህል ቡድኖች ጅግጅጋ መግባታቸውን ተናግረዋል። የጅግጅጋ ከተማ ነዋሪዎችም ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የመጡ ኢትዮጵያውያን ወንድም እህቶቻቸውን በፍቅር ተቀብለው እያስተናገዱ እንደሚገኙ ገልጸዋል። የሶማሌ ክልል ህዝብና የጅግጅጋ ከተማ ነዋሪዎች በዓሉ በድምቀት እንዲከበር በከፍተኛ ጉጉት ሲጠባበቁ ቆይተዋል ብለዋል። ጅግጅጋ የኅብረ ብሔራዊነት መገለጫና ሰላማዊት ከተማ ናት ያሉት ከንቲባ ዚያድ፥ "የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል ተሳታፊዎች፤ እንኳን ወደ ከተማችሁ በሰላም መጣችሁ" ብለዋል። 18ኛው የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል "ብዝኅነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት" በሚል መሪ ሃሳብ ከትናንት ጀምሮ በጅግጅጋ ከተማ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል።
"የብዝኃነት" ቀን የኢትዮጵያውያንን ኅብረ ብሔራዊ አንድነት በሚያንጸባርቁ ዝግጅቶች በጅግጅጋ እየተከበረ ነው
Dec 6, 2023 50
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 26/2016 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓልን ምክንያት በማድረግ "የብዝኃነት" ቀን የኢትዮጵያውያንን ኅብረ ብሔራዊ አንድነት በሚያንጸባርቁ ዝግጅቶች በጅግጅጋ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው። በዝግጅቱ ላይ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የመጡ የባህል ቡድኖች ባህላዊ ትርዒታቸውን በማቅረብ ላይ ናቸው። 18ኛው የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል "ብዝኅነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት" በሚል መሪ ሃሳብ ከትናንት ጀምሮ በጅግጅጋ ከተማ በድምቀት መከበሩን ቀጥሏል። በዛሬው ዕለትም "የብዝኃነት" ቀን እየተከበረ ሲሆን፤ በስነ ስርዓቱ ላይም የኢትዮጵያዊያንን ኅብረብሔራዊ አንድነት የሚያንጸባርቁ የባህል የልምድ ልውውጥ ዝግጅቶች እየቀረቡ ነው። ትናንት ህዳር 25 ቀን 2016 ዓ.ም "የወንድማማችነት" ቀን የተከበረ ሲሆን፤ ቀኑን ምክንያት በማድረግ ጎዳና ላይ ሩጫ ውድድርና የባህል ትዕይንት ተካሂዷል። በዕለቱ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ኢብራሂም ዑስማን ለብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን የተዘጋጀውን የንግድ ትርኢትና ባዛር ከፍተዋል። በቀጣይ ኅዳር-27 የአብሮነት፣ ኅዳር-28 የመደመር፣ ኅዳር-29 የኢትዮጵያ ቀን በሚሉ ስያሜዎች በልዩ ልዩ መርሃ ግብሮች በድምቀት የሚከበር ይሆናል።
ህብረቱ ባለፈው ዓመት በደቡብ ክልል የተካሄደውን ህዝበ ውሳኔ አስመልክቶ የታዘባቸውን የምርጫ ኩነቶች ይፋ አደረገ
Dec 5, 2023 75
አርባ ምንጭ ፤ ህዳር 25/2016 (ኢዜአ) ፦ የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ህብረት ባለፈው ዓመት በደቡብ ክልል የተካሄደውን ህዝበ ውሳኔ አስመልክቶ የታዘባቸውን የምርጫ ኩነቶች በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል። ህብረቱ በደቡብ ክልል ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም በተካሄደው ህዝበ ውሳኔ ምርጫ የታዘባቸውን የምርጫ ኩነቶች በመገምገም የመጨረሻ ሪፖርቱን የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ዛሬ በአርባ ምንጭ ከተማ ይፋ አድርጓል። የህብረቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ አበራ ሃይለማሪያም በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የህዝበ ውሳኔው ሂደት ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ከምርጫ አስፈጻሚ አካላት ምልመላ፣ ስልጠናና ስምሪት ጋር በተያያዘ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጉልህ ድርሻ እንደነበረው ባደረጉት ትዝብት አረጋግጠዋል። በሁሉም የድምጽ መስጫ ጣቢያዎች አምስት አስፈጻሚዎችን መመደቡ ጨምሮ በወላይታ ዞን በተካሄደው ዳግም ምርጫ ስህተቶች እንዳይደገሙ ያበረከተውን አስተዋጽኦ በጥንካሬ አንስተዋል። በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የአገር ውስጥና የውጭ ታዛቢዎች ዴስክ ተጠባባቂ ሃላፊ አቶ ደረጀ ኃይለሚካኤል በበኩላቸው፤ ገለልተኛ የሆኑ አገር በቀል ተቋማት ምርጫው ዴሞክራሲያዊና ፍትሃዊ እንዲሆን ሂደቱን ከመታዘብም በላይ ማህበረሰቡን በማንቃቱ ረገድ የማይተካ ሚና እንደነበራቸው አመልክተዋል። የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ህብረት በህዝበ ውሳኔ ሂደቱ የታዘባቸውን ጉዳዮች በተመለከተ መድረክ አዘጋጅቶ በዚህ መልክ ማቅረቡን አመስግነዋል። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህዝበ ውሳኔው ተዓማኒና በህዝቡ ዘንድ ቅቡልነት ያለው እንዲሆን ገለልተኛ አካላትን በማሳተፍ የወሰደው እርምጃ የሚበረታታ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢና የወላይታ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ፓርቲ ሊቀ መንበር አቶ ጎበዘ ጎአ ናቸው። በመድረኩ ላይ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተወካይ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ በህዝበ ውሳኔው ሂደት የተሳተፉ ባለድርሻ አካላትና ሲቪል ማህበራት ተገኝተዋል።
በመደመር ፍልስፍና ገዥ ትርክቶቻችንን በማጎልበት አንድነታችንን ልናጠናክር ይገባል
Dec 5, 2023 61
ደሴ ፤ ህዳር 25/2016 (ኢዜአ) ፦በኢትዮጵያ "በመደመር ፍልስፍና የሚያሰባስቡን ገዥ ትርክቶቻችንን በማጎልበት አንድነታችንን ልናጠናክር ይገባል" ሲሉ በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት የጥናትና ምርምር ክፍል ሃላፊና የኮምቦልቻ ስልጠና ማዕከል አስተባባሪ አቶ ተተካ በቀለ ገለፁ። በኮምቦልቻ ከተማ የ4ኛው ዙር የአመራር አባላት ስልጠና የማጠቃለያ መርሃ ግብር ተካሄዷል። በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት የጥናትና ምርምር ክፍል ሃላፊና የወሎ ኮምቦልቻ ስልጠና ማዕከል አስተባባሪ አቶ ተተካ በቀለ እንደገለፁት፤ በተሳሳተ ትርክት ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚሰሩ ቡድኖችን በጋራ መመከት ይገባል። የተሳሳተ ትርክት አገርን ለአደጋ የሚያጋልጥ መሆኑን ጠቅሰው፤ በመደመር ፍልስፍና "የሚያሰባስቡንን ገዥ ትርክቶች አጎልብተን አንድነታችንና የእርስ በእርስ ግንኙነታችንን የበለጠ ማጠናከር ይገባናል" ብለዋል። ለዚህም አመራር አባላት የጠራና የጋራ ግንዛቤ እንዲኖረው በየደረጃው የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህም ተለዋዋጭ ሁኔታውን ተገንዝቦ ለህብረተሰቡ ጥያቄ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት እንደሚያግዝ ተናግረዋል። እንዲሁም ሀብት በማመንጨት ኢኮኖሚውን በማነቃቃት፣ ለዜጎች የስራ እድል በመፍጠርና የፋይናንስ አስተዳደሩን በማዘመን ሁለንተናዊ ለውጥ እንዲመጣ የሚያስችል ግንዛቤ መፈጠሩን ጠቁመዋል። ሰልጣኞች በቆይታቸው ያገኙትን እውቀትና አቅም በመጠቀም ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ እድገት በትጋት መስራት እንዳለባቸው ተናግረዋል። በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ የወጣቶች ዘርፍ አስተባባሪ ወይዘሮ ፈዲላ ቢያ በበኩላቸው፤ ስልጠናው አመራሩ የአካባቢውን ፀጋ ለይቶ እንዲያውቅና በአግባቡ መጠቀም እንዲችል እድል መፈጠሩን ገልጸዋል። ከዚህ ባለፈም "የእርስ በእርስ ግንኙነቱን በማሳደግ ጠንካራና አስተማማኝ ሰላም ለመገንባት ያግዛል" ብለዋል። ከሰልጣኞች መካከል አቶ ቃይራኒቶ ገመቹ በበኩላቸው፤ ስልጠናው ጠንካራ አንድነትን በመፍጠር የህብረተሰቡን የመልካም አስተዳደርና የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ አቅም ፈጥሯል ብለዋል። ያገኙትን እውቀት ተጠቅመውም በመደመር ፍልስፍና የጋራ ትርክቶችን በማጎልበት ለኢትዮጵያ አንድነትና ዘላቂ ሰላም የድርሻቸውን እንደሚወጡ አስታውቀዋል። ''ስልጠናው የተለያዩ ምልከታዎችና እይታዎች እንዲኖሩን ከማድረጉ ባለፈ አንድነታችንን ለማጠናከር አግዞናል'' ያሉት ደግሞ ሌላዋ ሰልጣኝ አንችንአሉ ዘውዱ ናቸው። ''ባህልና እሴቶቻችንን ጠብቀንና የወል ትርክቶቻችንን አጎልብተን የኢትዮጵያ ሁለተናዊ ብልጽግና በጋራ እናረጋግጣለንም'' ብለዋል። በማጠቃለያ መርሃ ግብሩ የፌዴራል፣ የክልል፣ የዞንና የከተማ አመራር አባላትን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ፖለቲካ
ለህዝቡ ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ በመስጠት ረገድ የሚስተዋሉ የአመራር ግድፈቶች ይታረማሉ
Dec 6, 2023 44
አዲስ አበባ፤ ህዳር 26/2016(ኢዜአ)፦ህዝቡ በሚፈልገው ልክ ምላሽ ለመስጠት በየደረጃው ባሉ አመራሮች ዘንድ የአስተሳሰብ፣ የአመለካከት እና በተግባር አፈጻጸም ላይ የሚታየውን ጉድለቶችን በየጊዜው በመገምገምና በማጥራት ችግሮችን መፍታት እንደሚያስፈልግ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ገለጹ። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ከክልል እስከ ወረዳ ያሉ አመራሮች ክልላዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ግምገማ መድረክ በቦንጋ ከተማ እያካሄደ ይገኛል። ርዕሰ-መስተዳድሩ የግምገማ መድረኩ ወቅታዊ ክልላዊ የፖለቲካ አዝማሚያ በመዳሰስና በመገምገም በየደረጃው በሚያከውናቸው ተግባራት ላይ የፖለቲካ አስተሳሰብና የተግባር አንድነት ለመፍጠር ታልሞ የተዘጋጀ እንደሆነም ገልጸዋል። የግምገማና የማጥራት መድረኩም እስከታችው መዋቅር ድረስ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል። የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ፀጋዬ ማሞ የብልጽግና ፓርቲ እሴትን፣ ራዕይ እንዲሁም ተልዕኮን በአግባቡ መፈፀምና መተግበር የሚችል አመራር ለመገንባት ክልሉ ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ተናግረዋል። አመራሩ አሁንም የሚታይበትን የአመለካከት ችግር በፍጥነት ማስተካከል እንደሚገባም አመልክተዋል። የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች የተሰጡ ቢሆንም አሁንም የሚታዩ ግድፈቶችን አንጥሮ ለማዉጣት ይህ መድረክ ተዘጋጅቷል ብለዋል። በግምገማ መድረኩ የክልል፣የዞን፣የወረዳና የከተማ አስተዳደር አመራሮች እየተሳተፉ ሲሆን መድረኩ በቀጣይ አራት ቀናት እንደሚቀጥል የደቡብ ምዕራብ ኢትየጵያ ህዝቦች ክልል የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ መረጃ ያመለክታል።
በኦሮሚያ ክልል 18ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በማያ ከተማ እየተከበረ ነው
Dec 6, 2023 34
ሐረር፤ ኅዳር 26/2016 (ኢዜአ)፡- በኦሮሚያ ክልል ደረጃ 18ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በምስራቅ ሐረርጌ ማያ ከተማ እየተከበረ ነው። "ብዝሃነትና እኩልነት ለአገራዊ አንድነት!" በሚል መሪ ሃሳብ እየተከበረ በሚገኘው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ላይ ቀኑን የተመለከቱ የተለያዩ ኪነ ጥበባዊና ሌሎች ዝግጅቶች እየቀረቡ ይገኛሉ። በክብር እንግድነት የተገኙት የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ሰዓዳ አብዱረህማን ቀኑን አስመልክተው መልዕክት እንደሚያስተላልፉ ይጠበቃል። በሥነ-ሥርዓቱ ላይ በጨፌ ኦሮሚያ የመንግስት ተወካይና የብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፈቃዱ ተሰማን ጨምሮ የፌዴራል፣ የአጎራባች እና የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ ምሁራን፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ታድመዋል።
የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ የማቋቋም ጥረትን ውጤታማ ለማድረግ የባለድርሻ አካላት ድጋፍ ተጠየቀ
Dec 6, 2023 42
አዲስ አበባ ፤ህዳር 26/2016 (ኢዜአ)፦ የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ የማቋቋም ጥረትን ውጤታማ ለማድረግ ባለድርሻ አካላት እገዛ እንዲያደርጉ የብሔራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን ጥሪ አቀረበ። የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ተሾመ ቶጋ የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ የማቋቋም ስራ ብዙ ተግባራትን ይጠይቃል ብለዋል። ለዚህም ኮሚሽኑ ተቋሙን በግብአት እና በሰው ሀይል የማደራጀት፣ወደ ተሀድሶ የሚገቡ የቀድሞ ተዋጊዎችን የመለየት እና ከክልሎች ጋር በስራዎቹ ላይ መግባባት የሚፈጥሩ መድረኮችን ማካሄዱን ተናግረዋል። በአሁኑ ጊዜ በሀገሪቱ ከ371 ሺህ በላይ የቀድሞ ተዋጊዎች መኖራቸውን ጠቁመው፤ መልሶ ወደ ማቋቋም ተግባር ውስጥ እንዲገቡ ከማድረግ በፊት በድጋሚ የማጣራት ስራ እንደሚሰራ ጠቁመዋል። ዋና ኮሚሽነሩ አክለውም፤ የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደ ሰላማዊ ህይወታቸው እንዲመለሱና እንዲቋቋሙ የማድረጉ ስራ ከፍተኛ ሀብት እንደሚጠይቅ ገልጸዋል። መንግሥት ለብሔራዊ ተሃድሶው ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ ከፍተኛ ሙዓለ ንዋይ ፈሰስ እያደረገ መሆኑን ጠቅሰው፤ ባለድርሻ አካላትም አስፈላጊውን እገዛ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደ ማህበረሰቡ የመቀላቀልና መልሶ የማቋቋም ስራ ለሀገሪቱ ልማትና ዘላቂ ሰላም መረጋገጥ ሚናው ቀላል እንዳልሆነ ጠቁመዋል። በተለይም በተለያዩ ግጭቶች ውስጥ ሲሳተፉ የነበሩ ተዋጊዎች ወደ ሰላም ተመልሰው የኢኮኖሚው ዋነኛ አምራች ሃይል እንዲሆኑ ማድረግ ለሀገር ጥቅሙ ትልቅ መሆኑን በማንሳት። በአስተሳሰብ ረገድም ልዩነቶችንና ችግሮችን በሰላም ከመፍታት የተለየ አማራጭ እንደሌለ ያስተምራል ሲሉም ነው ዋና ኮሚሽነር ተሾመ ቶጋ የተናገሩት። በመሆኑም የቀድሞ ተዋጊዎች ወደ የአካባቢያቸው ተመልሰው ተቋቁመው በዘላቂነት የሰላምና የልማት ሃይል እንዲሆኑ ሁሉም አካል እገዛ ማድረግ አለበት ብለዋል።
ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ አገራዊ ምክክሩ ጉልህ ሚና አለው - ኮሚሽነር አቶ መላኩ ወልደማሪያም
Dec 6, 2023 60
ሶዶ፤ ህዳር 26/2016 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ሰላም ለማረጋገጥ አገራዊ የምክክር ሂደቱ ጉልህ ሚና እንዳለው የአገራዊ ምክክር ኮሚሽነር አቶ መላኩ ወልደማርያም ገለጹ። አገራዊ የምክክር ኮሚሽን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተባባሪ አካላት ስልጠና በወላይታ ሶዶ ከተማ መስጠት ጀመረ። ስልጠናውን ያስጀመሩት የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ መላኩ ወልደማሪያም የአገራችንን ሁለንተናዊ ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ ምክክሩ ጉልህ ሚና ይኖረዋል። "አለመግባባቶችና ግጭቶች እንዳይፈጠሩ ማድረግ እንዲሁም የተፈጠሩትንም በማርገብ የአገሪቷን ሁለንተናዊ ሰላምና ልማት ማረጋገጥ የምክክሩ ዋነኛ አጀንዳ ነው" ብለዋል። በመሆኑም ይሄ በኮሚሽኑ ስር በሚገኙ 11 ኮሚሽነሮች ብቻ የሚሳካ ባለመሆኑ ስልጠናው ተባባሪ አካላትን በጉዳዩ ዙሪያ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ያለመ መሆኑን አስረድተዋል። ምክክሩ አገራዊ መግባባት ላይ ለመድረስ የተሻለ አማራጭ መሆኑን አመልክተዋል። ምክክር ለየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ፣ ብሄርና ሀይማኖት የሚወግን ሳይሆን፤ "የአገርን ሁለንተናዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ያለመ ነው" ብለዋል። በስልጠናው በክልሉ ከሚገኙ ዞኖች፣ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ 700 ተባባሪ አካላት እየተሳተፉ ሲሆን፤ ለሶስት ቀናት እንደሚቆይ ተጠቁሟል።
የብሔር፣ ብሔረሰቦች መኖሪያ የሆነችው ጅግጅጋ እንግዶቿን በደማቅ ሁኔታ እየተቀበለች ነው-ከንቲባ ዚያድ
Dec 6, 2023 37
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 26/2016 (ኢዜአ)፡- ጅግጅጋ ከተማ ለ18ኛው ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ዝግጅቷን በማጠናቀቅ እንግዶችን በደማቅ ሁኔታ እየተቀበለች መሆኗን የከተማዋ ከንቲባ ኢንጂነር ዚያድ አብዲ ገለጹ። ከንቲባው ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ የጅግጅጋ ነዋሪዎች የበዓሉን ተሳታፊዎች በኢትዮጵያዊ እንግዳ ተቀባይነት እየተቀበሉ ነው ብለዋል። በጅግጅጋ ከተማ 18ኛውን የብሔር ብሔረሰብና ህዝቦች በዓል በድምቀት ለማክበር ሲደረግ የቆየው የቅድመ ዝግጅት ስራ መጠናቀቁን ገልጸዋል። በበዓሉ ለመታደም ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች እንግዶች ወደ ከተማዋ እየገቡ ነው ያሉት ከንቲባው፥ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦችን የወከሉ የባህል ቡድኖች ጅግጅጋ መግባታቸውን ተናግረዋል። የጅግጅጋ ከተማ ነዋሪዎችም ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የመጡ ኢትዮጵያውያን ወንድም እህቶቻቸውን በፍቅር ተቀብለው እያስተናገዱ እንደሚገኙ ገልጸዋል። የሶማሌ ክልል ህዝብና የጅግጅጋ ከተማ ነዋሪዎች በዓሉ በድምቀት እንዲከበር በከፍተኛ ጉጉት ሲጠባበቁ ቆይተዋል ብለዋል። ጅግጅጋ የኅብረ ብሔራዊነት መገለጫና ሰላማዊት ከተማ ናት ያሉት ከንቲባ ዚያድ፥ "የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል ተሳታፊዎች፤ እንኳን ወደ ከተማችሁ በሰላም መጣችሁ" ብለዋል። 18ኛው የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል "ብዝኅነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት" በሚል መሪ ሃሳብ ከትናንት ጀምሮ በጅግጅጋ ከተማ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል።
"የብዝኃነት" ቀን የኢትዮጵያውያንን ኅብረ ብሔራዊ አንድነት በሚያንጸባርቁ ዝግጅቶች በጅግጅጋ እየተከበረ ነው
Dec 6, 2023 50
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 26/2016 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓልን ምክንያት በማድረግ "የብዝኃነት" ቀን የኢትዮጵያውያንን ኅብረ ብሔራዊ አንድነት በሚያንጸባርቁ ዝግጅቶች በጅግጅጋ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው። በዝግጅቱ ላይ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የመጡ የባህል ቡድኖች ባህላዊ ትርዒታቸውን በማቅረብ ላይ ናቸው። 18ኛው የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል "ብዝኅነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት" በሚል መሪ ሃሳብ ከትናንት ጀምሮ በጅግጅጋ ከተማ በድምቀት መከበሩን ቀጥሏል። በዛሬው ዕለትም "የብዝኃነት" ቀን እየተከበረ ሲሆን፤ በስነ ስርዓቱ ላይም የኢትዮጵያዊያንን ኅብረብሔራዊ አንድነት የሚያንጸባርቁ የባህል የልምድ ልውውጥ ዝግጅቶች እየቀረቡ ነው። ትናንት ህዳር 25 ቀን 2016 ዓ.ም "የወንድማማችነት" ቀን የተከበረ ሲሆን፤ ቀኑን ምክንያት በማድረግ ጎዳና ላይ ሩጫ ውድድርና የባህል ትዕይንት ተካሂዷል። በዕለቱ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ኢብራሂም ዑስማን ለብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን የተዘጋጀውን የንግድ ትርኢትና ባዛር ከፍተዋል። በቀጣይ ኅዳር-27 የአብሮነት፣ ኅዳር-28 የመደመር፣ ኅዳር-29 የኢትዮጵያ ቀን በሚሉ ስያሜዎች በልዩ ልዩ መርሃ ግብሮች በድምቀት የሚከበር ይሆናል።
ህብረቱ ባለፈው ዓመት በደቡብ ክልል የተካሄደውን ህዝበ ውሳኔ አስመልክቶ የታዘባቸውን የምርጫ ኩነቶች ይፋ አደረገ
Dec 5, 2023 75
አርባ ምንጭ ፤ ህዳር 25/2016 (ኢዜአ) ፦ የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ህብረት ባለፈው ዓመት በደቡብ ክልል የተካሄደውን ህዝበ ውሳኔ አስመልክቶ የታዘባቸውን የምርጫ ኩነቶች በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል። ህብረቱ በደቡብ ክልል ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም በተካሄደው ህዝበ ውሳኔ ምርጫ የታዘባቸውን የምርጫ ኩነቶች በመገምገም የመጨረሻ ሪፖርቱን የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ዛሬ በአርባ ምንጭ ከተማ ይፋ አድርጓል። የህብረቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ አበራ ሃይለማሪያም በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የህዝበ ውሳኔው ሂደት ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ከምርጫ አስፈጻሚ አካላት ምልመላ፣ ስልጠናና ስምሪት ጋር በተያያዘ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጉልህ ድርሻ እንደነበረው ባደረጉት ትዝብት አረጋግጠዋል። በሁሉም የድምጽ መስጫ ጣቢያዎች አምስት አስፈጻሚዎችን መመደቡ ጨምሮ በወላይታ ዞን በተካሄደው ዳግም ምርጫ ስህተቶች እንዳይደገሙ ያበረከተውን አስተዋጽኦ በጥንካሬ አንስተዋል። በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የአገር ውስጥና የውጭ ታዛቢዎች ዴስክ ተጠባባቂ ሃላፊ አቶ ደረጀ ኃይለሚካኤል በበኩላቸው፤ ገለልተኛ የሆኑ አገር በቀል ተቋማት ምርጫው ዴሞክራሲያዊና ፍትሃዊ እንዲሆን ሂደቱን ከመታዘብም በላይ ማህበረሰቡን በማንቃቱ ረገድ የማይተካ ሚና እንደነበራቸው አመልክተዋል። የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ህብረት በህዝበ ውሳኔ ሂደቱ የታዘባቸውን ጉዳዮች በተመለከተ መድረክ አዘጋጅቶ በዚህ መልክ ማቅረቡን አመስግነዋል። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህዝበ ውሳኔው ተዓማኒና በህዝቡ ዘንድ ቅቡልነት ያለው እንዲሆን ገለልተኛ አካላትን በማሳተፍ የወሰደው እርምጃ የሚበረታታ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢና የወላይታ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ፓርቲ ሊቀ መንበር አቶ ጎበዘ ጎአ ናቸው። በመድረኩ ላይ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተወካይ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ በህዝበ ውሳኔው ሂደት የተሳተፉ ባለድርሻ አካላትና ሲቪል ማህበራት ተገኝተዋል።
በመደመር ፍልስፍና ገዥ ትርክቶቻችንን በማጎልበት አንድነታችንን ልናጠናክር ይገባል
Dec 5, 2023 61
ደሴ ፤ ህዳር 25/2016 (ኢዜአ) ፦በኢትዮጵያ "በመደመር ፍልስፍና የሚያሰባስቡን ገዥ ትርክቶቻችንን በማጎልበት አንድነታችንን ልናጠናክር ይገባል" ሲሉ በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት የጥናትና ምርምር ክፍል ሃላፊና የኮምቦልቻ ስልጠና ማዕከል አስተባባሪ አቶ ተተካ በቀለ ገለፁ። በኮምቦልቻ ከተማ የ4ኛው ዙር የአመራር አባላት ስልጠና የማጠቃለያ መርሃ ግብር ተካሄዷል። በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት የጥናትና ምርምር ክፍል ሃላፊና የወሎ ኮምቦልቻ ስልጠና ማዕከል አስተባባሪ አቶ ተተካ በቀለ እንደገለፁት፤ በተሳሳተ ትርክት ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚሰሩ ቡድኖችን በጋራ መመከት ይገባል። የተሳሳተ ትርክት አገርን ለአደጋ የሚያጋልጥ መሆኑን ጠቅሰው፤ በመደመር ፍልስፍና "የሚያሰባስቡንን ገዥ ትርክቶች አጎልብተን አንድነታችንና የእርስ በእርስ ግንኙነታችንን የበለጠ ማጠናከር ይገባናል" ብለዋል። ለዚህም አመራር አባላት የጠራና የጋራ ግንዛቤ እንዲኖረው በየደረጃው የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህም ተለዋዋጭ ሁኔታውን ተገንዝቦ ለህብረተሰቡ ጥያቄ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት እንደሚያግዝ ተናግረዋል። እንዲሁም ሀብት በማመንጨት ኢኮኖሚውን በማነቃቃት፣ ለዜጎች የስራ እድል በመፍጠርና የፋይናንስ አስተዳደሩን በማዘመን ሁለንተናዊ ለውጥ እንዲመጣ የሚያስችል ግንዛቤ መፈጠሩን ጠቁመዋል። ሰልጣኞች በቆይታቸው ያገኙትን እውቀትና አቅም በመጠቀም ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ እድገት በትጋት መስራት እንዳለባቸው ተናግረዋል። በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ የወጣቶች ዘርፍ አስተባባሪ ወይዘሮ ፈዲላ ቢያ በበኩላቸው፤ ስልጠናው አመራሩ የአካባቢውን ፀጋ ለይቶ እንዲያውቅና በአግባቡ መጠቀም እንዲችል እድል መፈጠሩን ገልጸዋል። ከዚህ ባለፈም "የእርስ በእርስ ግንኙነቱን በማሳደግ ጠንካራና አስተማማኝ ሰላም ለመገንባት ያግዛል" ብለዋል። ከሰልጣኞች መካከል አቶ ቃይራኒቶ ገመቹ በበኩላቸው፤ ስልጠናው ጠንካራ አንድነትን በመፍጠር የህብረተሰቡን የመልካም አስተዳደርና የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ አቅም ፈጥሯል ብለዋል። ያገኙትን እውቀት ተጠቅመውም በመደመር ፍልስፍና የጋራ ትርክቶችን በማጎልበት ለኢትዮጵያ አንድነትና ዘላቂ ሰላም የድርሻቸውን እንደሚወጡ አስታውቀዋል። ''ስልጠናው የተለያዩ ምልከታዎችና እይታዎች እንዲኖሩን ከማድረጉ ባለፈ አንድነታችንን ለማጠናከር አግዞናል'' ያሉት ደግሞ ሌላዋ ሰልጣኝ አንችንአሉ ዘውዱ ናቸው። ''ባህልና እሴቶቻችንን ጠብቀንና የወል ትርክቶቻችንን አጎልብተን የኢትዮጵያ ሁለተናዊ ብልጽግና በጋራ እናረጋግጣለንም'' ብለዋል። በማጠቃለያ መርሃ ግብሩ የፌዴራል፣ የክልል፣ የዞንና የከተማ አመራር አባላትን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ማህበራዊ
የሸዋል ኢድ በዓል በዓለም ቅርስነት መመዝገብ የቱሪዝም ኢንዱስትሪውን ያጠናክረዋል - -አቶ አደም ፋራህ
Dec 6, 2023 52
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 26/2016(ኢዜአ)፦ የሸዋል ኢድ በአል በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ተቋም ዩኔስኮ መመዝገቡ በቱሪዝም ዘርፍ የምናደርገው እንቅስቃሴ እንዲጠናከርና አድማሱን እንዲያሰፋ ያደርገዋል ሲሉ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንትና የፓርቲው ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ አደም ፋራህ ገለጹ። አቶ አደም ፋራህ የሸዋል ኢድ በዓል በአለም ቅርስነት በመመዝገቡ የእንኳን ደስ ያለን መልዕክት አስተላለፈዋል። ፓርቲያችን ብልፅግና በትኩረት እና በልህቀት እፈፅማቸዋለው ብሎ ከያዛቸው አምስት የልማት መስኮች መሀል የቱሪዝም ዘርፉ ይገኝበታል ያሉት አቶ አደም በሀገራችን የሚገኙ ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ መስህቦችም ይበልጥ እንዲያድጉ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል። የሸዋል ኢድ በአል በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ተቋም ዩኔስኮ መመዝገቡ በቱሪዝም ዘርፍ የሚደረገውን እንቅስቃሴ በማጠናከር የተሻለ ተጠቃሚነትን እንደሚያሳድግም አስረድተዋል። ይህ ታሪካዊ ውሳኔ ሀረር ከተማን በዩኔስኮ ሁለት ቅርሶችን ያስመዘገበች ብቸኛዋ የሀገራችን ከተማ የሚያደርጋት ሲሆን ሀገራችን ኢትዮጵያንም በርካታ ቅርሶችን በአለም ቅርስነት በማስመዝገብ ከአፍሪካ ቀዳሚ ስፍራን እንድትይዝ የሚያደርጋት በመሆኑ ደስታችን ወደር የለውም ብለዋል። በቀጣይም የበአሉ አከባበር ይበልጥ ባማረ መልኩ እንዲቀጥልና ድምቀቱ አለምአቀፍ እውቅናውን በሚመጥን መልኩ እንዲካሄድ፣ ከተማዋም በቱሪስቶች ዘንድ ተመራጭ መዳረሻ እንድትሆን እንደ ብልፅግና ፓርቲ ሰፊ ስራዎችን መስራታችንን እንደምንቀጥል በዚህ አጋጣሚ ለመግለፅ እወዳለሁ ማለታቸውን ከብልጽግና ፓርቲ ማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
የመተከል ዞን ሠላም መመለስ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴን በነጻነት ለማከናወን አስችሎናል --ነዋሪዎች
Dec 6, 2023 38
አሶሳ ፤ኅዳር 26/2016 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል ዞን ሠላም መመለስ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴን በነጻነት ለማከናወን እንዳስቻላቸው የግልገል በለስ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ። በመተከል ዞን የግልገል በለስ ከተማ ነዋሪዎች መካከል ወይዘሮ ድርቤ ለማ ለኢዜአ እንዳሉት፣ ባለፉት ዓመታት በአካባቢው ተከስቶ በነበረ የጸጥታ ችግር በተለይ እናቶች እና ሕጻናት ለከፋ ጉዳት ተዳርገዋል። እሳቸውም በሰላም እጦቱ የሆቴል ሥራቸው ተስተጓጉሎ እንደነበር ያስታወሱት አስተያየት ሰጪዋ፣ በአሁኑ ወቅት በአካባቢው ሰላም መስፈነን ተከትሎ ሥራቸውን በአግባቡ እያከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል። ተማሪ ልጆቻቸውን ያለሀሳብ በነጻነት ወደትምህርት ቤት እየላኩ መሆኑንም ነው የገለጹት። "ከሠላም የሚጠቀመውም ሆነ በሠላም እጦት የሚጎዳው ህብረተሰቡ ነው" የሚሉት ወይዘሮ ድርቤ፣ በአካባቢው አሁን የሰፈነውን ሰላም ዘላቂ እንዲሆን የበኩላቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል። "የሰላም እጦት የሚያስከትላቸውን ችግሮች ስላየን በቀጣይ ችግሮች ቢከሰቱ እንኳ ተነጋግረን እንፈታለን" ያሉት ነዋሪዋ፣ ከሰላሙ ተጠቃሚ ስለሆንን ከመንግስት ጋር በመሆን ሰላማችንን እንጠብቃለን ብለዋል። ወጣት ጌታሁን ለገሰ በበኩሉ እንዳለው የብሔር ብሔረሰቦች በዓል በግልገል በለስ ከተማ በክልል ደረጃ መከበሩ የዞኑ ሠላም ዳግም ስለመመለሱ ዋነኛ ማሳያ ነው። "ከዚህ ቀደም በአካባቢው ተከስቶ ለነበረው የሠላም እጦት ዘረኝነት ዋነኛው ምክንያት ነው" ያለው ወጣቱ፣ ወንድማማችነትና አገራዊ አንድነትን በማጠናከር የተገኘውን ሠላም ለማስቀጠል የበኩሉን እንደሚወጣ ገልጿል። በሰላም እጦት ከግልገል በለስ ወደ ወምበራ፣ ማንኩሽ፣ ፓዌ እና ቻግኒ ከተሞች ተቋርጦ የነበረው የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት መጀመሩን የተናገሩት ደግሞ መምህር ታመነ ሚልኪያስ ናቸው። "አሁን ያለፈውን ረስተን ሥራ ላይ አተኩረን እየተንቀሳቀስን ነው፤ እርስ በርስ ገበያም እየተገበያየን ነው" ሲሉም የሰላምን ትሩፋት ገልጸዋል። የግልገል በለስ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ጊሳ ዚፋ በአካባቢው ሰላም በመስፈኑ በከተማው ተቋርጠው የነበሩትን የልማት ሥራዎች ለማስቀጠል እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። ወጣቱ የአካባቢ ጽዳትና ውበት ሥራን ጨምሮ በጥቃቅንና አነስተኛ የሥራ ዘርፎች አደራጅቶ ወደሥራ በማስገባት ከጠባቂነት እንዲላቀቅ መደረጉንም አመልክተዋል። ከእዚህ በተጨማሪ እንደ መንገድ፣ ውሃ፣ ኤሌክትሪክ ያሉ መሰረተ ልማቶችን በማሟላት አልሚ ባለሃብቶችን በስፋት ወደ ከተማ በማስገባት የከተማውን ኢኮኖሚ ለማነቃቃት ጥረት እየተደረገ መሆኑንም አቶ ጊሳ አስረድተዋል። በአካባቢው ለተገኘው ሠላም የሃይማኖት አባቶች፣ የሃገር ሽማግሌዎች፣ የወጣቶች ማህበራት እና ሌሎች የሠላም አደረጃጀቶች የጎላ ሚና እንደተጫወቱ የገለጹት ከንቲባው፣ እነዚህ አካላት አሁንም ከጸጥታ አስከባሪው ጋር ተቀናጅተው እየሰሩ መሆናቸውን አስረድተዋል። የመተከል ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ለሜሳ ዋውያ በበኩላቸው፣ በዞኑ ለመጣው ሠላም ህብረተሰቡና የጸጥታ አካላት ታላቅ መስዋዕትነት ከፍለዋል። በነበረው በጸጥታ ችግር የባከነውን የልማት ጊዜ ለማካካስ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፣ በእዚህም የተበላሹ መንገዶችን የመጠገንና የተቋረጠውን ትራንስፖርት አገልግሎት የማስጀመር ሥራ መሰራቱን ገልጸዋል። ለተደራጁ ወጣቶችና ለአርሶ አደሮች የእርሻ ትራክተሮችን ጨምሮ ዘመናዊ የግብርና ቁሶችን ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑንም አመልክተዋል። ለአካባቢው ሰላም መመለስ ቁልፍ ሚና የተጫወቱትን እርቀ ሠላም እና ህዝባዊ የውይይት መድረኮች በአሁኑ ወቅት ተጠናክረው ቀጥለዋል ሲሉም ገልጸዋል። ዞኑ የተለያዩ የተፈጥሮ ሃብቶች እንዳሉት ያመለከቱት ዋና አስተዳዳሪው፣ ይህን ሀብት በአግባቡ በማልማት ለአካባቢውና ለሀገር ጥቅም ለማዋል ህብረተሰቡ ሠላሙን ዘላቂ ማድረግ አለበት ብለዋል።
የማህበራዊ ሚዲያ ተዋናዮችና ማህበረሰብ አንቂዎች በጠንካራ እሴት በመመራት በአገር ግንባታ ውስጥ ሚናቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ
Dec 6, 2023 51
አዳማ፤ ህዳር 26/2016 (ኢዜአ)፡-የማህበራዊ ሚዲያ ተዋናዮችና ማህበረሰብ አንቂዎች በጠንካራ እሴት በመመራት በአገር ግንባታ ውስጥ ሚናቸውን እንዲወጡ የሰላም ሚኒስቴር አስገነዘበ። "የአገር ግንባታ መሰረታዊያን" በሚል ርዕስ ለማህበራዊ ሚዲያ አካላትና ማህበረሰብ አንቂዎች የተዘጋጀ የምክክር መድረክ በአዳማ በመካሄድ ላይ ይገኛል። የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንዳኣ በዚሁ ወቅት እንደገለፁት፤ ዜጎች የጋራ ማንነትና ጥቅም ላይ ጥልቅ ዕውቀትና ግንዛቤ እንዲኖራቸው ከማድረግ አኳያ የማህበራዊ ሚዲያ ባለሙያዎችና ማህበራዊ አንቂዎች ሚና የጎላ ነው። "አገር የሚገነባው አንድን መሪ ለማስደሰት ወይም ለአንድ የፖለቲካ ፓርቲ ተብሎ አይደለም" ያሉት አቶ ታዬ፤ የብሔር፣ የእምነት፣ የማንነት፣ የቋንቋ፣ የባህልና የሃሳብ ማንነትን የያዘ ብዝሃነት ቢኖረንም "በአገር ግንባታ፣ እና በጋራ እሴቶች ላይ የሁሉም የሆነች ኢትዮጵያን እውን ማድረግ አለብን" ብለዋል። በዚህም የማህበራዊ ሚዲያ ተዋናዮችና ማህበረሰብ አንቂዎች አገራዊ ማንነትና ዘላቂ ጥቅምን አውቀው በትክክለኛ እሴት በመመራት በአገር ግንባታ ውስጥ ሚናቸውን እንዲወጡ አቶ ታዬ አስገንዝበዋል። በተለይም "ህዝቡን በማስተሳሰርና አንድነትን በማጠናከር ላይ መስራት አለባቸው" ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፤ በዚህ ዙሪያ የየማህበራዊ ሚዲያ ባለሙያዎችና ማህበረሰብ አንቂዎች የጋራ አረዳድ ሊኖራቸው እንደሚገባም አመልክተዋል። ከመድረኩ ተሳታፊዎች መካከል የቅን ልቦና በጎ ስራ ድርጅት ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ስንሻው በበኩላቸው፤ ማህበራዊ ሚዲያን እንዴት ለአገር ግንባታና ሰላምን ለማፅናት ማዋል እንችላለን በሚለው ላይ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር እየሰራን ነው ብለዋል። ማህበራዊ ሚዲያዎችና አንቂዎች "በሃይማኖትና በማንነት ላይ ትኩረት በማድረግ አብሮ የመኖር እሴቶችን በሚሸረሽሩ አጀንዳዎች ላይ ሲሰሩ ይስተዋላል" ያሉት አቶ ተስፋዬ፤ ይኸ ዓይነቱ አካሄድ ለአገር ግንባታ እንደማይጠቅም ተናግረዋል። በተለይም ቲክቶከሮች፣ ማህበራዊ ገፅና ዩቱበሮች ሰፊ ተከታይ ለማግኘትና ለገቢያቸው በማሰብ ትኩረታቸው በብሔር፣ በፖለቲካ እሳቤ፣ በሃይማኖትና ማንነት መካከል የሚፈጠሩ ክፍተቶችን አጀንዳ በማድረግ ሲሰሩ እንደሚታዩ ገልጸዋል። "ሁሉም የማህበራዊ ሚዲያ ተሳታፊዎች አንቂዎች ከዚህ እሳቤ በመውጣት በአገርና ሰላም ግንባታ አዎንታዊ ሚና መጫወት እንደሚጠበቅባቸው አስረድተዋል።
በኦሮሚያ ክልል ህጻናትና አቅመ ደካማ እናቶችን ይበልጥ ተጠቃሚ ያደረጉ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት ተከናውነዋል
Dec 6, 2023 44
አዳማ ፤ ህዳር 26/2016(ኢዜአ)፦ባለፉት አራት ወራት በኦሮሚያ ክልል ህጻናትና አቅመ ደካማ እናቶችን ይበልጥ ተጠቃሚ ያደረጉ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት መከናወናቸውን የኦሮሚያ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ገለፀ ። የቢሮው ምክትል ሃላፊ ወይዘሮ ሰርካለም ሳኩሜ ለኢዜአ አንደገለጹት በተያዘው የበጀት ዓመት በክልሉ የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ የበጎ ፍቃድ አገልግሎቶች ተከናውነዋል። በክልሉ በየደረጃው ያሉ የሴቶች ማህበራት፣ የሴቶች ሊግና ፌዴሬሽን የመሳሰሉ የሴቶች አደረጃጀቶች የአካባቢያቸውን ባለሃብቶችና መላውን ህብረተሰብ በማስተባበር አበረታች ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል። በዚህም በተለይም "የእናቶች ቤት ሠርተን እንመረቅ" የሚል መሪ ሐሳብ ተይዞ 62ሺህ 294 የአቅመ ደካሞች ቤቶች እድሳትና ግንባታ ተከናውነዋል ብለዋል። የአረንጓዴ አሻራው የችግኝ ተከላና እንክብካቤ መርሃ ግብር፣ የደም ልገሳ፣ የጽዳት ስራ፣ የትምህርት ቤቶች እድሳትና ግንባታ፣ ለችግረኛ ተማሪዎች የተደረጉ የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ድጋፍ በቢሮው አስተባባሪነት ከተከናወኑ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች መካከል የሚጠቀሱ መሆናቸውን ገልጸዋል። በዚህም በተያዘው በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ አራት ወራት ብቻ 22 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር የሚገመት የዜግነት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መከናወኑን ምክትል ቢሮ ሃላፊዋ ገልጸዋል። በተከናወኑ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት ምንም ገቢ የሌላቸው ሴቶች የገቢ ምንጭ እንዲኖራቸውና ሠርተው ራሳቸውን እንዲችሉ ተደርገዋል ያሉት ደግሞ የቢሮው የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ወይዘሮ ሩቅያ በሹ ናቸው። 22ሺህ 802 የሪቢ በጎችና ፍየሎች እንዲሁም ለጭነት አገልግሎት የሚውሉ ጋሪዎች ተገዝተው ለእናቶች መሰጠታቸው ከተከናወኑት ተግባራት መሆናቸውን በማከል። በዚህም በተለይም በገጠር ውስጥ በጀርባቸው ተሸክመው ረዥም መንገድ ተጉዘው የሚሰሩ እናቶችን ለመደገፍ የተሰራው ስራ አበረታች መሆኑን በማከል። በተመሳሳይ 3 ነጥብ 2 ሚሊዮን የሚሆኑ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህፃናትና በመማር ላይ ለሚገኙ ልጆች የደንብ ልብስን ጨምሮ የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ በዚሁ መርሃ ግብር መደረጉን ወይዘሮ ሩቅያ ገልጸዋል። የዜግነት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የአንድ ወቅት ስራ ብቻ ሳይሆን በዘላቂነት የማህበረሰቡ ባህል ሆኖ እንዲሰራበትም ቢሮው ከክልሉ መንግስት እና ከቡሳ ጎኖፋ ጽህፈት ቤት ጋር በመተባበር እንደሚሰራ ተገልጿል።
ኢኮኖሚ
በአማራ ክልል የአኩሪ አተር የግብይት ችግርን መንግስት እንዲያቃልል ተጠየቀ
Dec 6, 2023 28
ባህር ዳር፤ህዳር 26/2016 (ኢዜአ) ፡- በአማራ ክልል የአኩሪ አተር የዋጋ መቀነስን ለማስተካከል መንግስት የገበያ ትስስር እንዲፈጥር አርሶ አደሮችና ባለሃብቶች ጠየቁ። በክልሉ በአኩሪ አተር ሰብል ከለማው መሬት ስድስት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅም ተገልጿል። በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ የኩመር አውላላ ቀበሌ አርሶ አደር ይበልጣል አማረ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በዘንድሮው የመኸር ወቅት በአኩሪ አተር ካለሙት ሦስት ሄክታር መሬት 61 ኩንታል ምርት አግኝተዋል። ባለፈው ዓመት የአኩሪ አተር ምርት ዋጋ ከተገመተው በላይ በመውረዱ የማምረቻ ወጪያቸውን መሸፈን ሳይችሉ እንደቀሩም አስታውሰዋል። "የገበያ ችግር ዘንድሮ ይስተካከላል" በሚል ሰብሉን በስፋት ቢያመርቱም የገበያ ችግሩ ካለፈው ዓመት የተለየ እንዳልሆነ ገልጸዋል። ችግሩን ለመቅረፍም መንግስት የገበያ ትስስር እንደፈጥርላቸው አመልክተዋል። በዚሁ ወረዳ የደለሎ ቀበሌ አርሶ አደር ገብሬ አሻግሬ በበኩላቸው፤ ባለፈው ዓመት በነበረው የገበያ ችግር ተስፋ ሳይቆርጡ በአምስት ሄክታር መሬት ላይ የአኩሪ አተር ሰብል ማምረታቸውን አስታውሰዋል። ለአመረቱት ምርት ወጪያቸውን የሚያካክስ "የገበያ ዋጋ ይኖራል" ብለው ተስፋ ቢያደርጉም፤ አሁንም ዋጋው በኩንታል ከ2 ሺህ 500 ብር የማይበልጥ በመሆኑ ለኪሳራ እንዳይዳረጉ ስጋታቸውን ገልጸዋል። አሁን ያለው የገበያ ዋጋ ሰብሉን ለማምረት የወጣውን ወጪ የሚሸፈን እንዳልሆነ ጠቅሰው፤ የሚመለከተው አካል ሁሉ "ገበያ በማፈላለግ ሊያግዘን ይገባል" ብለዋል። ባለፈው ዓመት ያመረቱትን 470 ኩንታል አኩሪ አተር ገበያ ባለመኖሩ እስካሁን በመጋዘን ማስቀመጣቸውን የገለጹት ደግሞ በምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ በእርሻ ኢንቨስትመንት የተሰማሩት አቶ አምሳሉ ላቀው ናቸው። ዘንድሮም በአኩሪ አተር ካለሙት 20 ሄክታር መሬት 390 ኩንታል ምርት ማግኘታቸውን ጠቅሰው፤ መንግስት ከኢንዱስትሪዎችና ከላኪዎች ጋር በማስተሳሰር የገበያ ችግራቸውን እንዲፈታላቸው ጠይቀዋል። የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አጀበ ስንሻው በበኩላቸው እንደተናገሩት፤ ለኢንዱስትሪ ግብዓትና ለውጭ ገበያ የሚውለው የአኩሪ አተር ምርት ካለፈው ዓመት ጀምሮ በስፋት እየተመረተ ይገኛል። ሰብሉ ባለፈው ዓመት በስፋት ቢመረትም ምርቱ የታሰበውን ያህል ዋጋ ማውጣት ባለመቻሉ አርሶ አደሮችና በዘርፉ የተሰማሩ ባለሃብቶች የማምረቻ ወጪያቸውን መሸፈን ሳይችሉ ቀርተዋል። ዘንድሮም በ249 ሺህ 728 ሄክታር መሬት ለምቶ እየተሰበሰበ ከሚገኘው የአኩሪ አተር ሰብል ከስድስት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል። ምርቱ ተገቢውን ዋጋ አውጥቶ በዘርፍ የተሰማሩት ሁሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከአጋር አካላት ጋር ገበያ በማፈላለግ በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝም አመልክተዋል። በአኩሪ አተር ሰብል የተስተዋለውን የግብይት ችግር ከኢንዱስትሪዎችና ላኪዎች ጋር በማስተሳሰር ለመፍታት እየተሰራ መሆኑን የገለፁት ደግሞ የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ የሰብልና የኢንዱስትሪ ምርቶች ግብይት ዳይሬክተር አቶ ልንገረው አበሻ ናቸው። ከታህሳስ መግቢያ ጀምሮ ለሚጀመረው ግብይትም አቅራቢ ነጋዴዎች፣ ዘይት አምራች ኢንዱስትሪዎችና የእርሻ ውል ስምምነት የወሰዱ ባለሃብቶችና ላኪዎች ምርቱን በተገቢ ዋጋ እንዲገዙ ከወዲሁ በትብብር እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል። በአማራ ክልል ባለፈው ዓመት በአኩሪ አተር ከለማው መሬት ከአምስት ነጥብ ዘጠኝ ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት መገኘቱን ከግብርና ቢሮው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
በምስራቅ ቦረና ዞን ባለፉት አራት ወራት ከ8 ሺህ ለሚበልጡ ወጣቶች የስራ እድል ተፈጥሯል
Dec 6, 2023 31
ነገሌ ቦረና፤ህዳር 26/2016 (ኢዜአ) ፦ በምስራቅ ቦረና ዞን በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ አራት ወራት በ532 ማህበር የተደራጁ ከ8 ሺህ በላይ ወጣቶች ወደ ስራ መግባታቸውን የዞኑ የክህሎትና የስራ እድል ፈጠራ ጽህፈት ቤት ገለጸ፡፡ በጽህፈት ቤቱ የስራ እድል ፈጠራ ባለሙያ አቶ ጎዳና ሳራ ዞኑ በተያዘው ዓመት ለ37 ሺህ 619 ስራ ፈላጊዎች የስራ እድል ለማመቻቸት አቅዶ ወደ ስራ መግባቱን ገልጸዋል፡፡ እስካሁን በተሰራ ስራም በ532 ማህበር ተደራጅተው ወደ ስራ የገቡ 8 ሺህ 21 ወጣቶች የማምረትና አገልግሎት የመስጠት ስራ መጀመራቸውን ገልጸዋል፡፡ በዞኑ ወደ ስራ ከገቡት ውስጥ 1ሺህ 200 የሚሆኑት የኮሌጂና የዩኒቨርስቲ ምሩቃን ወጣቶች እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ወጣቶቹ በግብርና፣ በንግድ፣ በአገልግሎት፣ በማንፋቸሪንግ፣ በግንባታ፣ በማዕድን ፍለጋና ግብይት የስራ ዘርፎች መሰማራታቸውን በማከል፡፡ ወደ ስራው ለተሰማሩት ወጣቶች በከተማና በገጠር አንድ ሺህ 800 ሄክታር መሬትና 27 የማምረቻና የመሸጫ ሼዶች መከፋፈላቸውንም አክለዋል፡፡ የወጣቶቹን ካፒታል ለማሳደግ እንዲረዳም 90 ሚሊዮን ብር የብድር አገልግሎት በሲንቄ ባንክ መመቻቸቱን ባለሙያው አመልክተዋል፡፡ በቅርቡ የስራ እድሉን ተጠቅመው በእንጨትና ብረታ ብረት ስራ ከተሰማሩት ወጣቶች መካከል የነገሌ ቦረና ከተማ ነዋሪና የቅድስተ ማሪያም ዩኒቨርስቲ ተመራቂ ወጣት ከነአን ብርሃኑ አንዱ ነው፡፡ ወጣቱ በመንግስት መስሪያ ቤት ተቀጥሮ ከመስራት ከሶስት ባልደረቦቹ ጋር ተደራጅተው የተሰማሩበት ስራ ከእራሳቸው አልፈው ለሌሎች 13 ወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠር እንዳስቻላቸውም ገልጸዋል፡፡ እሱና ባልደረቦቹ ከሲንቄ ባንክ በወሰዱት 100 ሺህ ብር ብድር የጀመሩት ስራ በአሁኑ ጊዜ ምርታችውን ለአከባቢው ገበያ እያቀረቡ እንደሆነ ገልጿል፡፡ አሁን ባለው የተሻለ የስራ እንቅስቃሴ በቀጣይ እስከ ሁለት ሚሊዮን ብር ብድር በመውሰድ የስራ ዘርፋቸውን ይበልጥ የማስፋት እቅድ እንዳላቸውም ተናግረዋል፡፡ የቤትና የቢሮ እቃ ምርታቸውን ለተጠቃሚ በማቅረብ ላይ መሆናቸውን የሚናገረው ደግሞ ሌላው የከተማው ነዋሪ ወጣት መሐመድ ሙሳና 14 ባልደረቦቹ ናቸው፡፡ ወጣቱና ባልደረቦቹ ስራ ሲጀምሩ ከመንግስት አንድ የመሸጫ ሼድ እና ከሲንቄ ባንክ ደግሞ የ50 ሺህ ብር ብድር መውሰዳቸውን ገልጿል፡፡
በሶማሌ ክልል የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎች ለተኪ ምርቶች ትኩረት እንዲሰጡ ልዩ ድጋፍ ይደረጋል-ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ኢብራሂም
Dec 6, 2023 33
አዲስ አበባ፤ ህዳር 26/2016(ኢዜአ)፦በሶማሌ ክልል የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎች የሚያጋጥማቸውን ችግር በመቅረፍ ለተኪ ምርት ትኩረት እንዲሰጡ ልዩ ድጋፍ የሚደረግ መሆኑን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ኢብራሂም ዑስማን ገለጹ። 18ኛውን የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል አስመልክቶ የንግድ ትርዒትና ባዛር በጅግጅጋ ከተማ ትናንት ተከፍቷል። የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ኢብራሂም ዑስማን፤ የንግድ ትርኢትና ባዛሩን በከፈቱበት ወቅት የዘንድሮው የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል አገራዊ አንድነትንና የህዝቦችን ትስስር ለማጠናከር ከፍተኛ አስትዋጽኦ ያበረክታል ብለዋል። የንግድ ትርኢትና ባዛሩ ለአልሚ ግለሰቦች፣ ድርጅቶችና ማኅበራት ምርትና አገልግሎታቸውን ለማስተዋወቅ እንዲሁም የግሉን ዘርፍ ተወዳዳሪነትና ተመጋጋቢነትን በማሳደግ የገበያ ትስስር ለመፍጠር እንደሚያስችል ነው ያብራሩት። በሆቴል ቱሪዝምና አገልግሎት ሰጪ ዘርፎች ላይ የጅግጅጋ ከተማን ለማነቃቃት ያለው በጎ ተጽዕኖ የጎላ መሆኑን ጠቁመዋል። በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ገቢ ምርቶችን በአገር ውስጥ በመተካት የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ለማሳደግ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል። በተያዘው በጀት ዓመትም ኢትዮጵያ ከውጭ የምታስገባቸውን ከ2 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር በላይ የሚገመቱ 96 የምርት አይነቶችን በአገር ውስጥ ለመተካት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ህብረተሰቡም የአገር ውስጥ ምርቶችን የመጠቀም ባህሉን በማሳደግ ተገቢውን ትኩረት ለመስጠት መሰል የንግድ ትርኢትና ባዛር ግብይቶች ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳላቸው ተናግረዋል። በሶማሌ ክልል በየደረጃው የሚገኙ አምራቾች የሚያጋጥማቸውን ችግር በመቅረፍ ለተኪ ምርቶች ትኩረት እንዲሰጡ ልዩ ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል። የዘንድሮው የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል "ብዝሃነትና እኩልነት ለሀገራዊ እንድነት በሚል መሪ ሀሳብ በተለያዩ ዝግጅቶች ከትናንት ጀምሮ በመከበር ላይ ነው።
በለሚ እንጀራ ፋብሪካ ለሚሰሩ ሴቶች የገበያ ትስስርን ለማጠናከር እገዛ ይደረጋል - ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል
Dec 6, 2023 33
አዲስ አበባ፤ ህዳር 26/2016(ኢዜአ)፦ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በለሚ እንጀራ ፋብሪካ በመገኘት የስራ እድል የተፈጠረላቸውን ሴቶች የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል። በጉብኝቱ ላይም የእንጀራ ፋብሪካው ለሴቶች የስራ እድል ከመፍጠር በተጨማሪ የሚያመርተው እንጀራ ደረጃውን የጠበቀ፣ የተሻለ ጥራት ያለውና ጤፍን በግብአትነት የሚጠቀም ከመሆኑም ባለፈ አመራረቱ ንጽህናውን የጠበቀ መሆኑን ማየታቸውን ሚኒስትሯ ተናግረዋል። በፋብሪካው የስራ እድል የተፈጠረላቸው ሴቶች ቤተሰብ አስተዳዳሪ በመሆናቸው ከመጠቀማቸውም ባለፈ ገበያ በማረጋጋት ረገድም አይነተኛ ሚና እንዲጫወት ገልጸው መስሪያ ቤታቸው የገበያ ትስስር ማጠናከር ላይ እንደሚያግዝም ቃል ገብተዋል። ከንቲባ አዳነችም ሚኒስትሯ በስፍራው ተገኝተው ሴቶቹን ስላበረታቱና ለማገዝም ስለፈቀዱ ምስጋና ማቅረባቸውን ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
በምስራቅ አፍሪካ ግዙፉ የንፋስ ሀይል ማመንጫ በኢትዮጵያ ሊገነባ ነው
Dec 3, 2023 145
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 23/2016 (ኢዜአ)፡- በምስራቅ አፍሪካ 300 ሜጋ ዋት የሚያመነጭ ግዙፉ የንፋስ ሀይል ማመንጫ በኢትዮጵያ ሊገነባ ነው። የሚገነባው የንፋስ ሀይል ማመንጫ 600 ሚሊየን ዶላር ወጭ የሚደረግበትና 300 ሜጋ ዋት የሚያመነጭ መሆኑም ተገልጿል፡፡ ይህንን እውን ለማድረግም የገንዘብ ሚኒስቴር አሜአ ፓወር ከተሰኘ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ኩባንያ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡ የንፋስ ሀይል ማመንጫው በሶማሌ ክልል አይሻ አካባቢ አሜአ ፓወር በተሰኘ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ኩባንያ እንደሚገነባ ከገንዘብ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡ ፕሮጀክቱን ተግባራዊ ለማድረግ የ3 አመታት ጥናት ቀድሞ መደረጉም በመረጃው ተጠቁሟል፡፡ ስምምነቱ በመንግስትና በግል አልሚዎች ማእቀፍ የሚሰራ ትልቁ ኢንቨስትመንት ሲሆን በንፋስ ሀይል ማመንጫ ከምስራቅ አፍሪካ ግዝፉ እንደሆነም ተመላክቷል፡፡ ስምምነቱ ኢትዮጵያ በታዳሽ ሀይል ላይ መሰረት ላደረገ የሀይል አቅርቦት ስትራቴጂዋ ተጨማሪ ግብአት ይሆናል፡፡
የቺካጎ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ስድስት ተቀራራቢ ፕላኔቶች ማግኘታቸውን ገለጹ
Nov 30, 2023 131
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 20/2016 (ኢዜአ)፦ ስድስት ተቀራራቢ ፕላኔቶች ማግኘት መቻላቸውን በአሜሪካ የቺካጎ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች አስታወቁ። ተገኙ የተባሉት ፕላኔቶች በራሳቸው የጸሃይ ስርአት ዙሪያ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ስርአቱን የጠበቀና ሙዚቃዊ ስልት ያለው መሆኑንም ተመራማሪዎቹ ይፋ ባደረጉት ምስል ገልጸዋል። ኤች ዲ 110067 የሚል ስያሜ የተሰጣቸው ፕላኔቶቹ ኮማ ቤሬኒሲስ ከተባለው የህብረ ክዋክብት ስብስብ በአንድ መቶ የብርሃን አመታት ይርቃሉ መባሉን ኔቸር የተባለውን የምርምር መጽሄት ጠቅሶ ዩ ፒ አይ በድረ ገጹ አስነብቧል። የፕላኔቶቹ መገኘት ስለፕላኔቶች አፈጣጠር እና ዝግመተ ለውጥ አዲስ እይታ ሊፈጥር ይችላል የሚሉት የጥናት ቡድኑ መሪ ራፋኤል ሊዩክ “መሰል ግኝቶች ኔፕቱን በተባለችው ፕላኔት ዙሪያ ያሉ አካላት እንዲታወቁ እድል ይፈጥራል” ማለታቸውን ዘገባው አስታውሷል። “ምድር ካለችበት የጸሃይ ስርአት ውጪ ያሉ ሌሎች ፕላኔቶች አፈጣጠር፣ ቆይታ፣ የተሰሩበት ነገር ውሃ ስለመያዛቸው እና ሌሎች ጉዳዮች የጥናቱ መነሻ እንዲሆን አስችሏል” ብለዋል ተመራማሪው። የአሜሪካው ብሄራዊ የጠፈር ምርምር ኤጀንሲ ናሳ ከአውሮፓ የጠፈር ጥናት ድርጅት ጋር በመሆን በተላኩት ሳተላይቶች የክዋክብቱን የብርሃን መጠን፣ ከሌሎች ከዋክብት ጋር ያላቸውን መስተጋብር መመልከት እንደተቻለም ተገልጿል። እንደ ተመራማሪዎቹ ገለጻ ፕላኔቶቹ እርስ በእርስ ያላቸውን ርቀት የሚያስጠብቁበት ሬዞናንስ የተባለው ስርአት ያላቸው በመሆኑ በጸሃይ ዙሪያ ያሉት በርካታ ክዋክብት በሚያደርጉት መሽከርከር የሚጋጩባቸው አጋጣሚዎች በእጅጉ አናሳ መሆኑን በዘገባው ተመላክቷል።
የጂንካ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ችግር ፈቺና ፈርጀ ብዙ ቴክኖሎጂዎችን በማፍለቅ ለተጠቃሚዎች እያሻገረ ነው
Nov 29, 2023 283
ጂንካ፤ ህዳር 19/2016 (ኢዜአ)፡- የጂንካ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ውጤታማ፣ ችግር ፈቺና ፈርጀ ብዙ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን በማፍለቅ ለተጠቃሚዎች ለማሻገር አትኩሮ እየሰራ መሆኑን ገለጸ ። ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የኮሌጁ ዲን አቶ ካሳሁን ጌታቸው እንዳሉት፤ ኮሌጁ ችግር ፈቺ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን በማፍለቅ ለማህበረሰቡ በማሸጋገር ተጠቃሚ ለማድረግ አልሞ እየሰራ ይገኛል። ኮሌጁ በአካባቢው የሚገኙ ያልተነኩ አቅሞችን ለመጠቀም የተጀመሩ ጥረቶችን ለማገዝ የማህበረሰቡን ድካም የሚቀንሱና ውጤታማነትን የሚያጎለብቱ ቴክኖሎጂዎች ማፍለቅና ማሸጋገር ላይ ዋናው ትኩረት አድርጎ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል ። በተለይ ኮሌጁ ''ኢትዮጵያ ታምርት'' በሚል መሪ ሀሳብ በተጀመረው አገራዊ ንቅናቄ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ማሽነሪዎችን በሀገር ውስጥ ምርቶች ለመተካት ባደረገው እንቅስቃሴ ውጤት እየተገኘ መሆኑን ጠቁመዋል። ለአብነት በኮሌጁ ከተሰሩ የፈጠራ ስራዎች መካከል ከ30 እስከ 40 ሜትር ጥልቅ ጉድጓድ መቆፈር የሚያስችል ማሽን መሰራቱን ያነሱት አቶ ካሳሁን ከውጭ ሲገባ ከሚጠይቀው ወጪ አንጻር እጅግ ዝቅተኛ በሆነ ዋጋ ለማህበረሰቡ እየቀረበ እንደሚገኝ ነው የተናገሩት። ኮሌጁ የአርሶ አደሮችን ድካም ለማቃለል ከፈጠራቸው ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎች መካከል የበቆሎ መፈልፈያ፣ የገብስና የጥራጥሬ መፈተጊያ ማሽኖች ይገኙበታል። የገብስና የጥራጥሬ መፈተጊያ ማሽኑም በባህላዊ መንገድ ጤፍ፣ ማሽላና ሌሎች ሰብሎችን በመውቃት የሚገጥመውን የምርት ብክነት መቀነስ የሚያስችል ቴክኖሎጂ መሆኑን አመላክተዋል። በኮሌጁ የቴክኖሎጂ ሽግግርና የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ባለሙያ አቶ እስጢፋኖስ እያሱ በኮሌጁ የፈለቁ ማሽኖች የኃይል አማራጭ ስላላቸው መብራት በሌለባቸው አካባቢዎች በነዳጅ የሚሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል። ይህም ከኃይል አቅርቦት ጋር የሚስተዋሉ ችግሮችን መቅረፍ የሚያስችል ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂ ነው ያሉት። ማሽኑ የኃይል አማራጭ እንዲኖረው መደረጉ አርሶ አደሮች እና በግብርና ላይ የተሰማሩ ኢንቬስተሮች ማሽኑን በተለያየ ቦታ በማንቀሳቀስ መጠቀም እንዲችሉ ታስቦ እንደተሰራም አስረድተዋል። በተለይ ተቋሙ የፈጠረው የጥራጥሬ መፈተጊያ ማሽን ስንዴ፣ ገብስ፣ ማሽላ እና ሩዝ መፈተግ የሚያስችል መሆኑን ጠቅሰዋል። ይህም የአርሶ አደሩን ጊዜና ጉልበት ከመቆጠቡም ባሻገር የምርት ብክነትን ያስቀራል ብለዋል። በገጠር አካባቢዎች በስፋት የሸክላ ሥራ የሚተገበርና አሰራሩም ሁዋላ ቀር በመሆኑ ከዘርፉ የሚገኘው ኢኮኖሚያዊ ጥቅም አነስተኛ መሆኑን የገለፁት አቶ እስጢፋኖስ፤ ስራው በሰው ጉልበት በመሰራቱ እጅግ አድካሚ እንደሆነም አንስተዋል። ኮሌጁ ይህን ችግር በማየት የሸክላ አፈር መፍጨት፣ ማቡካትና የተለያዩ ቅርፆችን እንዲይዝ የሚያደርግ ዘመናዊ የሸክላ መስሪያ ማሽን መስራት ችሏል ብለዋል። ኮሌጁ የእርሻ ስራውን ለማዘመን እና የከብት እርባታውን አዋጭ ለማድረግ ከሚያግዙ ቴክኖሎጂዎች መካከል አነስተኛ የእርሻ ትራክተር እና የወተት መናጫ ማሽን እና ሌሎችንም ማፍለቅ መቻሉንም ገልጸዋል ። በፈጠራ ስራዎች ላይ ከተሳተፉ የኮሌጁ ተማሪዎች መካከል ተማሪ ሙሉቀን አለማየሁ ለኢዜአ እንደገለፀው በኮሌጁ 30 በመቶ የንድፈ ሃሳብ፣ 70 በመቶ የሚሆነውን ደግሞ በተግባር ልምምድ እንደተማሩ ተናግሯል። የጂንካ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በአሁኑ ወቅት በግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በኮንስትራክሽን እና በሌሎች ተዛማጅ የትምህርት መስኮች 501 ነባር ተማሪዎችን እያሰለጠነ ሲሆን ለ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ደግሞ 600 ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር በዝግጅት ላይ ይገኛል። ከመደበኛ የመማር ማስተማር ሰራው ጎን ለጎን 1 ሺህ ለሚሆኑ ሰልጣኞች በገበያ አዋጭነትና ስራ ፈጠራ ላይ አጫጭር ስልጠናዎችን ለመስጠት መዘጋጀቱንም ከኮሌጁ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
የ5-ጂ ሞባይል ኔትዎርክ መስፋፋት የዲጂታል ልማትን ከማፋጠን ባለፈ ሀገራዊ የምጣኔ ኃብት እድገትን ለማረጋገጥ ሚናው የላቀ ነው
Nov 29, 2023 121
አዲስ አበባ ፤ህዳር 19/2016 (ኢዜአ):- በኢትዮጵያ የአምስተኛው ትውልድ (5-ጂ) የሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎት መስፋፋት የዲጂታል ልማትን ከማፋጠን ባለፈ ሀገራዊ የምጣኔ ኃብት እድገትን ለማረጋገጥ ሚናው የላቀ መሆኑን የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ገለጹ። ኢትዮ-ቴሌኮም የአምስተኛውን ትውልድ (5-ጂ) የሞባይል ኔትዎርክ በጅግጅጋ ከተማ በይፋ አስጀምሯል። የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ፤ በማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት በዓለም ላይ እጅግ ፈጣን የሚባለውን የአምስተኛው ትውልድ (5-ጂ) የሞባይል ኔትዎርክ ኢትዮጵያ መጠቀም ጀምራለች ብለዋል። የአምስተኛው ትውልድ (5-ጂ) ኔትዎርክ ተጠቃሚ ከሆኑ የዓለም አገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗንም ጠቅሰዋል። የ5-ጂ ኔትዎርክ ቀደም ሲል በአዲስ አበባ እና አዳማ በይፋ መጀመሩን አስታውሰው፤ አሁን ላይ በሱማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ በመጀመሩ እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል። በኢትዮጵያ የማስፋፋት ሥራው በልዩ ትኩረት እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰው፤ በቀጣይም ተጠናከሮ ይቀጥላል ሲሉ ተናግረዋል። የአምስተኛው ትውልድ (5-ጂ) የሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎት የማስፋፋት ሥራ ለዲጂታል ኢትዮጵያ እውን መሆን የላቀ አስተዋጽዖ እንዳለውም ገልፀዋል። የ5-ጂ ኔትዎርክ አገልግሎት በጅግጅጋ ከተማ መጀመሩም የንግድና የመረጃ ሥርዓቱን ለማሳለጥና የመንግሥትን አገልግሎት አሰጣጥ የሚያቀላጥፍ መሆኑን ጠቅሰዋል። የሱማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ-መስተዳድር ኢብራሂም ኡስማን፤ የቴክኖሎጂው እውን መሆን በክልሉ ለተጀመሩ የልማት ሥራዎች መፋጠን እንዲሁም በተለያዩ ሴክተሮች ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሚያግዝ መሆኑን ገልፀዋል። በጅግጅጋ ኢዜአ ካነጋገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች መካከል ወይዘሮ ራሁ ጠይብካስ እና አብዱረዛቅ ሐሰን የአምስተኛው ትውልድ (5-ጂ) የሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎት መጀመር በንግዱም ይሁን በሌሎች አገልግሎቶች ተጠቃሚ የሚያደርግ በመሆኑ ተደስተናል ብለዋል። የ5-ጂ የኔትዎርክ አገልግሎት በተለይም ለስማርት ሲቲ፣ ስማርት ትራንስፖርት፣ የትምህርት ሥርዓት፣ ለጤና፣ ለውሃ፣ የግብርና ልማት፣ ለንግድና የፋይናንስ ሴክተር፣ ለኢንዱስትሪ፣ ለስማርት የመንግሥት አስተዳደር እና ሌሎችም ሴክተሮች የላቀ አበርክቶ እንዳለው ይነገራል።
ስፖርት
18ኛውን የብሔሮች ፣ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓልን በማስመልከት በጅግጅጋ ከተማ የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ተካሄደ
Dec 5, 2023 72
ጅግጅጋ ፤ ህዳር 25/2016 (ኢዜአ) ፡- 18ኛውን የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓልን በማስመልከት በጅግጅጋ ከተማ የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ተካሄደ። ውድድሩ ከማለዳው 12 ከ30 ጀምሮ በከተማው ሰይድ መሀመድ አብደላ ሀሰን አደባባይ የተካሄደ ሲሆን የጅግጅጋ ከተማ ወጣቶች ተሳትፈዋል። 18ኛው የብሔሮች ፣ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ከዛሬ ህዳር 25 እስከ ህዳር 29/2016 ዓ.ም ድረስ በፌዴሬሽን ምክር ቤት አስተባባሪነትና በሶማሌ ክልል አስተናጋጅነት "ብዝኅነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት" በሚል መሪ ሃሳብ በጅግጅጋ ከተማ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ይከበራል። በዚህም ህዳር-25 የወንድማማችነት፣ ህዳር-26 የብዝሃነት፣ ህዳር-27 የአብሮነት፣ ህዳር-28 የመደመር፣ ህዳር-29 የኢትዮጵያ ቀን በሚሉ መሪ ስያሜዎች በተለያዩ ዝግጅቶች መከበሩን ጀምሯል።
“ኑ ባሌን ጎብኙ” የ6 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር ተካሄደ
Dec 3, 2023 82
ሮቤ ፤ ህዳር 23/2016 (ኢዜአ) ፦ “ኑ ባሌን ጎብኙ” በሚል መሪ ሐሳብ የባሌን የቱሪዝም መስህቦች ማስተዋወቅ ዓላማ ያደረገ የ6 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ዛሬ በሮቤ ከተማ ተካሄደ፡፡ ውድድሩን ያዘጋጁት የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽንና ሳዲያ መልቲ ሚዲያ በመተባበር ነው። ሩጫው በተለይ በቅርቡ በተባበሩት መንግስታት የትምህርትና የባህል ተቋም/ዩኔስኮ/ የተመዘገበውን የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክን ለማስተዋወቅ ዓላማ ያደረገ መሆኑም ተገልጿል። እንዲሁም ሌሎች በዞኑ ውስጥ የሚገኙ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ መስህቦችን ለማስተዋወቅና ለማልማት ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም እንዲሁ፡፡ ሩጫውን ያስጀመሩት የባሌ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አብዱልሀኪም አልይ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት የባሌ ዞን የብዙ ተፈጥሮና ሰው ሰራሽ የቱሪስት መስህብ ባለቤት በመሆኑ ዘርፉ የዞኑንም ሆነ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ እንዲደግፍ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቷል። በተለይም የአያሌ አዕዋፋት፣ አራዊትና የተለያዩ መልክዓ ምድርን ያቀፋው የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገብ መደረጉ የዚሁ ጥረት አካል ነው ብለዋል። አስተዳዳሪው እንዳሉት ዞኑ የአያሌ የመስህብ ስፍራዎች መገኛ ቢሆንም በሚገባ ለምቶ ለአገር መስጠት የሚገባውን አበርክቶ በመስጠት ረገድ ውስንነቶች አሉት። ዛሬ የተካሄደው የጎዳና ላይ ሩጫም በዞኑ የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎችን ለማስተዋወቅና ለማልማት ማነቃቂያ እንዲሆን ታስቦ ነው። የሮቤ ከተማ ከንቲባ አቶ ንጋቱ ሞቱማ በበኩላቸው አስተዳደሩ ሮቤን ለነዋሪዎቿ ምቹ ከማድረግ በተጓዳኝ የቱሪዝምና የንግድ ማዕከል ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው ብለዋል። ባለኃብቶች ከተማዋ ያላትን ምቹ እድሎች በመጠቀም በሆቴሎችና ሌሎች ዘርፎች ላይ ኢንቨስት እንዲያደርጉም ጠይቀዋል። "ክልሉ የብዙ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ መስህብ ባለቤት ቢሆንም ዘርፉ የክልሉን ኢኮኖሚ ትርጉም ባለው መልኩ እንዲደግፍ ለማድረግ ብዙ ስራዎች ይቀራሉ ያሉት ደግሞ የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽነር ወይዘሮ ለሊሴ ዱጋ ናቸው" ኮሚሽኑ በክልሉ የሚገኙ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ መስህቦችን በማልማትና እንዲተዋወቁ በማድረግ ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ መሪ እቅድ አውጥቶ እየሰራ መሆኑን በማከል። በባሌ ሮቤ የተዘጋጀው የጎዳና ላይ ሩጫም የቱሪዝም መስህቦችን የማስተዋወቅና የማህበረሰቡን ግንዛቤ ለማነቃቃት ዓላማ ያለው እንደሆነ አመልክተዋል፡፡ ውድድሩን በወንዶች ብርሃኑ ጌታሁን በሴቶች ደግሞ አበራሽ ከበደ ውድድሩን በአንደኝነት አጠናቀዋል ። ለሩጫው አሸናፊዎች የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። ከዞኑ አስተዳደር የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በዩኔስኮ በቋሚነት መመዝገቡን በማስመልከት ህዳር 25 ቀን 2016ዓ.ም የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በባሌ ሮቤ የሚካሄድ የእውቅና መርሃ ግብር እንደሚዘጋጅ ታውቋል። የዛሬው የጎዳና ላይ ሩጫው የዚሁ መርሃ ግብር አካል መሆኑንም ከዞኑ አስተዳደር መረጃው ያመለክታል። የባሌና ምስራቅ ባሌ ዞኖች የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ፣ የሶፍ ኡመር የተፈጥሮ ዋሻ፣ የድሬ ሼህ ሁሴን እንዲሁም ጥቅጥቅ የሀረና ጥብቅ ደንና ሌሎች የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ መስህቦች ናቸው፡፡
በ2024 በኳታር ዶሃ ለሚካሄደው የውሃ ዋና ሻምፒዮናና በፈረንሳይ ፓሪስ ለሚደረገው ኦሊምፒክ የሚወዳደሩ ዋናተኞች ተለዩ
Dec 2, 2023 87
አዲስ አበባ፤ ህዳር 22/2016(ኢዜአ)፡- በ2024 በኳታር ዶሃ ለሚካሄደው የውሃ ዋና ሻምፒዮናና በፈረንሳይ ፓሪስ ለሚደረገው ኦሊምፒክ በወንዶች በረከት ደምሴ በሴቶች ደግሞ ሊና ዓለማየሁ ተመረጡ። የኢትዮጵያ የውሃ ዋና ስፖርት ተሳትፎ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2012 በተከናወነው በለንደን ኦሊምፒክ የሚጀምር ሲሆን፤ በወቅቱ በሴቶች ያኔት ስዩም በወንዶች ደግሞ ሙሉዓለም ግርማ በ50 ሜትር ነፃ ቀዘፋ ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ ከለንደን ኦሊምፒክ ጀምሮ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2021 እስከተካሄደው የጃፓን ቶኪዮ ኦሊምፒክ ድረስ በውሃ ዋና በሦስት ኦሊምፒኮች እንደተሳተፈች የኢትዮጵያ ውሃ ስፖርቶች ፌዴሬሽን መረጃ ያመለክታል። ዘንድሮም ፌዴሬሽኑ በ2024 በኳታር ዶሃ ለሚካሄደው የውሃ ዋና ሻምፒዮና እና በፈረንሳይ ፓሪስ ለሚደረገው ኦሊምፒክ ተወዳዳሪዎችን ለመምረጥ በጊዮን ሆቴል ውድድር አካሂዷል። በዚህም ውድድር በሁለቱም ፆታ በነፃ ቀዘፋ እና በቢራቢሮ ውድድሮች ተካሂደው፤ በወንዶች በረከት ደምሴ ከአዲስ አበባ በሴቶች ሊና ዓለማየሁ ከኦሮሚያ አንደኛ ሆነው ተመርጠዋል። የተመረጡ አሸናፊ አትሌቶች በቂ ዝግጅት አድርገው ኢትዮጵያን በመወከል በዶሃ የዓለም ውሃ ስፖርቶች ውድድርና በፓሪስ ኦሊምፒክ እንደሚሳተፉ ፌዴሬሽኑ ገልጿል። የኢትዮጵያ ውሃ ስፖርቶች ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት መሠረት ደምስ ለኢዜአ እንደገለፁት፤ የውሃ ዋና ተወዳዳሪዎቹ ስለተለዩ በቀጣይ የአሰልጣኝ ምርጫ ተካሂዶ ዋናተኞቹ ይሰለጥናሉ። የተመረጡት ዋናተኞችም በየካቲት ወር በኳታር ዶሃ ለሚካሄደው የውሃ ዋና ሻምፒዮና የፌዴሬሽኑ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በሚወስነው መሠረት አዲስ አበባ ወይም ቢሾፍቱ ላይ ዝግጅት እንደሚያደርጉ ገልፀዋል። በፈረንሳይ ፓሪስ ለሚደረገው 33ኛው የኦሊምፒክ ውድድርም ዋናተኞቹ የሚያደርጉትን ዝግጅት ከኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ጋር በመነጋገር ልምምድ የሚያደርጉበት ሁኔታ እንደሚመቻች አስታውቀዋል። ኢትዮጵያ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2024 በፈረንሳይ ለሚካሄደው 33ኛው የኦሊምፒክ ውድድር እስካሁን በአትሌቲክስና በውሃ ዋና መሳተፏን እንዳረጋገጠች ከኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
በአዲስ አበባ ከተማ የቦክስ ስፖርት ውድድርን ለማስፋት እየተሰራ ነው
Dec 1, 2023 103
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 21/2016 (ኢዜአ) ፦ በአዲስ አበባ ከተማ የቦክስ ስፖርት ውድድር ለማስፋት በዘርፉ ስመ ጥር ስፖርተኞችን ለማፍራት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ገለፀ። "አዲስ ቦክስ ውድድር" በሚል ስያሜ የቦክስ ስፖርት ውድድር ትናንት ምሽት ላይ በአዲስ አበባ ከተማ ተከናውኗል ። በሁለቱም ፆታዎች ከ54 እስከ 81 ኪሎ ግራም ውድድር ተካሂዷል። በታዳጊዎች 54 ኪሎ ግራም ልዑልሰገድ ወንዱ አማኑኤል ታምራትን ሲረታ በአዋቂ ሴቶች 54 ኪሎ ግራም ሀገሪ እማኙ ሮማን አሰፋን አሸንፋለች። በተመሳሳይ በአዋቂ ወንዶች 54 ኪሎ ግራም ፍትዊ ጥኡማይ ዳዊት በቀለን ማሸነፍ ችሏል። በ57 ኪሎ ግራም የወንዶች ውድድር በዘንድሮው የኦሊምፒክ ማጣሪያ ከአፍሪካ ተወዳዳሪዎች ጋር ተፋልሞ ለአገሩ የብር ሜዳልያ ይዞ የተመለሰው ፍቅረ ማርያም ያደሳ ቢላል አስራርን አሸንፏል። በ63 ነጥብ 5 ኪሎ ግራም አዋቂ ወንዶች መስፍን ብሩና አብርሃም ዓለም ፍልሚያቸውን ያካሄዱ ሲሆን በመስፍን ብሩ አሸናፊነት መጠናቀቅ ችሏል። የውድድሩ የመጨረሻ ምድብ በሆነውና ብርቱ ፉክክር የታየበት 81 ኪሎ አዋቂ ወንዶች ፍልሚያ ሰይፉ ከበደ ከናትናኤል ነዋይ ጋር ተፋልሞ ማሸነፍ ችሏል። በየምድቡ አሸናፊ ለሆኑ ቦክሰኞች የ15ሺህ ብር ሽልማት ሲበረከትላቸው ለተጋጣሚዎች ደግሞ የ10ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ በላይ ደጀን በውድድሩ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር፤ ፤ እንደነዚህ ዓይነት ውድድሮች መዘጋጀታቸው ስፖርቱን እንደሚያነቃቃ ገልፀዋል። በዓለም አቀፍ የውድድር መድረኮች አገርን ወክለው የሚወዳደሩ ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት እንደሚረዳም ተናግረዋል። በከተማው የሚገኙ የስፖርት ማኅበራትን በመደገፍና ከባለድርሻ አካላት፣ ከባለሃብቶችና ስፖርትን ከሚወዱ አካላት ጋር ተቀናጅቶ በመስራት የቦክስ ውድድሮች በከተማ ደረጃ በስፋት እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል። የአዲስ አበባ ቦክስ ፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት ኢንጂነር አስቻለው ኃይለማርያም በበኩላቸው የቦክስ ስፖርት እየተዳከመ መምጣቱን ገልፀዋል። ስለሆነም የቦክስ ስፖርት እንዲነቃቃና አገርን በኦሊምፒክ የውድድር መድረክ የሚወክሉ ስፖርተኞችን ለማፍራት የቦክስ ውድድሮችን በስፋት ማከናወን እንደሚገባ ተናግረዋል።
አካባቢ ጥበቃ
አየር ጠባይ ለውጥ ምክንያት የሚያጋጥሙ የተለያዩ አደጋዎችን ለመቀነስ ኢትዮጵያ በትኩረት እየሰራች ነው
Dec 4, 2023 76
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 24/2016 (ኢዜአ) ፡- በአየር ጠባይ ለውጥ ምክንያት የሚያጋጥሙ የተለያዩ አደጋዎችን ለመቀነስ ኢትዮጵያ በትኩረት እየሰራች መሆኑን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ሃብታሙ ኢተፋ ገለጹ። የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ሃብታሙ ኢተፋ ከ28ኛው የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ጉባኤ ጎን ለጎን በተዘጋጀው የዓለም ሚቲዎሮሎጂ ድርጅት የሚኒስትሮች ውይይት ላይ ተሳትፈዋል። መድረኩ “የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት ለሁሉም በሚል መሪ ሀሳብ ነው የተካሄደው። ሚኒስትሩ በመድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት በአየር ጠባይ ለውጥ ምክንያት የሚያጋጥሙ የተለያዩ አደጋዎችን ለመቀነስ ኢትዮጵያ በትኩረት እየሰራች ነው ብለዋል። በተለይ ለሚቲዎሮሎጂ ምልከታ የሚያግዙ ዘመናዊ የመረጃ መሰብሰቢያ ጣቢያ እና መሰረተ ልማት በስፋት በመዘርጋት፤ ወቅቱን የጠበቀ ቦታ ተኮር እና ተደራሽ ትንበያና ቅድመ ማስጠንቀቂያ በመስጠት የአደጋ ተጋላጭነትን የሚቀንሱ በርካታ እርምጃዎችን እየወሰደች መሆኑንም አብራርተዋል። ሚኒስትሩ አክለውም የአደጋ ስጋትን ለመቀነስ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የሚመራ የብሄራዊ አደጋ መከላከል ካውንስል ተቋቁሞ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን በመጥቀስ በመድረኩ የኢትዮጵያን ልምድ ማካፈላቸውን ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ያሳየችው ለውጥ ለቀጣናውም ሆነ ለአፍሪካ በምሳሌነት የሚጠቀስ ነው
Dec 3, 2023 101
አዲስ አበባ ህዳር 23/2016 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ያሳየችው ለውጥ ለቀጣናውም ሆነ ለአፍሪካ በምሳሌነት የሚጠቀስ ነው ሲሉ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ጸሀፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ገለጹ። ኢትዮጵያ በዚህ መርሃ ግብር ከ30 ቢሊየን በላይ ችግኞችን መትከሏንም ጠቅሰዋል። በዱባይ እየተካሔደ በሚገኘው 28ኛው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ ያዘጋጀችው የአረንጓዴ አሻራና ሌሎች ተሞክሮዎቿን የምታካፍልበት አውደ ርእይ/ፓቪሊዮን/ በሃገራት መሪዎች፣ በጉባኤው ተሳታፊዎች በመጎብኘት ላይ ነው። የኢትዮጵያን የአረንጓዴ አሻራ አውደ ርእይ/ፓቪሊዮን/ የጎበኙት ዋና ጸሀፊው የምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥ ችግርን ከአየር ንብረት ለውጥ ኮንፈረንሶች እና መገናኛ ብዙሃን ገለጻ በላይ ችግሩን በተግባር ተከስቶ ማየታቸውን አስታውሰዋል። ቀጣናው በተለይም ባለፉት ሶስት አመታት የጎርፍ እና የድርቅ አደጋዎች ከማስተናገዱ ጋር በተያያዘ ሀገራቱ ችግሩን ለመፍታት የራሳቸውን መፍትሄ መውሰዳቸውን ሲገልጹ ለዚህም የኢትዮጵያ ተሞክሮ በአረአያነት መጠቀሱን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ አየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሀሳብ አመንጪነት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለቀጣናውም ሆነ ለአፍሪካ በምሳሌነት የሚጠቀስ ነው ብለዋል። የዱባዩ ጉባኤ ችግሩን ለመቋቋም የተደረጉ ተሞክሮዎች የሚቀርቡበትና ግብዓት የሚወሰድበት ነው ያሉት ዋና ጸሀፊው፤ ኢትዮጵያ ያቀረበችው መካነ ርዕይ ችግሩን ለመፍታት የፈጠረችው የህዝብ ንቅናቄው ወደ ውጤት መቀየሩን ያረጋገጠ እንደሆነ ተናግረዋል። በዚህም ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ክስተትን ለመቅረፍም ከ30 ቢሊየን በላይ ዛፎችን መትከሏን ተናግረዋል። ይህም ከዓለም የገንዘብ ተቋማት ምንም አይነት የገንዘብ ድጋፍ ሳትሻ መሪዎቿ ህዝብን በማነቃነቅ ለአካባቢ ጥበቃ በማዋል ለቀጣናው ሀገራት ጭምር ዛፎችን መስጠታቸውን ተናግረዋል። አፍሪካ ባልፈጠረችው የተዛባ ተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም ለአየር ንብረት ለውጥ ችግር መዳረጓን ከማስረዳቷም ባለፈ ኢትዮጵያ ከኢጋድ ጋር በመሆን አፍሪካን ወክላ ለጉዳቱ ማካካሻ ፈንድ በማምጣት ከፍተኛ እንቅስቃሴ ማድረጓን ጠቅሰዋል።
የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት የአርሶ አደሩን የምግብ ዋስትና ከማረጋገጥ አልፎ ተጨማሪ ገቢ እንዲያገኝ እያስቻለ ነው
Dec 2, 2023 82
ሮቤ ፤ ህዳር 22/2016(ኢዜአ)፡- የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት የአርሶ አደሩን የምግብ ዋስትና ከማረጋገጥ አልፎ ተጨማሪ ገቢ እንዲያገኝ እያስቻለ መሆኑን የሲናና ግብርና ምርምር ማዕከል ገለጸ። ማዕከሉ በተቀናጀ የተፈጥሮ ኃብት ልማት እንክብካቤ ላይ በባሌ ዞን አጋርፋ ወረዳ እያካሄደ የሚገኘው ሥራ በተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተጎብኝቷል። በምርምር ማዕከሉ እየተከናወኑ ከሚገኙ ምርምሮች መካከል የአፈር ለምነት ማሻሻል፣ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ዝግጅት፣ የንብ ማነብና የአፈር መሸርሸር መቀነስ ላይ ትኩረት ያደረጉ መሆኑም ተመልክቷል። በሲናና ግብርና ምርምር ማዕከል የአፈር ለምነት ተመራማሪ አቶ ሙሉጌታ እሸቱ እንዳሉት፣ የማዕከሉ የምርምር ስራዎች አርሶ አደሩን የምግብ ዋስትና የሚያረጋግጡና ተጨማሪ ገቢ የሚያስገኙ ሥራዎች ላይ ትኩረት ያደረጉ ናቸው። በተለይ በአፈር መሸርሸርና ጎርፍ ሳቢያ ስጋት ሆነው የቆዩ የተፋሰስ ልማቶች ላይ በተሰሩ ሥራዎች መሬቱ ዳግም ለልማት እንዲውል እየተደረገ ነው ብለዋል። በተለይ የምርምር ማዕከሉ ከ500 ሄክታር በሚበልጥ መሬት ላይ በአጋርፋ ወረዳ እያከናወነ የሚገኘው የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ሥራ ውጤት እያስመዘገበ መምጣቱን በማሳያነት አንስተዋል። አቶ ሙሉጌታ እንዳሉት፣ በማዕከሉ እየተከናወኑ ከሚገኙ ምርምሮች መካከል የአፈር ለምነት ማሻሻል፣ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ዝግጅት፣ የንብ ማነብና የአፈር መሸርሸር መቀነስ በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው። አርሶ አደሩ በተለይ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ዝግጅት ላይ ያገኘው የቁሳቁስ ድጋፍና የዕውቀት ሽግግር ለፋብሪካ ማዳበሪያ ያወጣ የነበረውን ወጪ እንደሚቀንስ ተናግረዋል። በዘመናዊ የቀፎ ዝግጅትና የጓሮ አትክልት ልማት ላይ ግንዛቤ በማግኘት ከሚያደርገው መደበኛ ልማት በተጓዳኝ ተጨማሪ ገቢ እንዲያገኙ እገዛ እያደረገ ነው ብለዋል። የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ተወካይ አቶ ተማሮ ገልገሎ በበኩላቸው፣ ማዕከሉ የአርሶና አርብቶ አደሩን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ የሚያግዙ በ8 የትኩረት መስኮች ላይ ያተኮሩ ምርምሮችን እያካሄደ ነው። ማዕከሉ በተለይ ከዚህ ቀደም በሰብል ልማት፣ የጥራጥሬና የእንስሳት መኖ ላይ ትኩረት በማድረግ የተገኙ ውጤቶችን በማስፋት በተቀናጀ የተፈጥሮ ኃብት ልማት ላይ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። አቶ ተማሮ እንዳሉት፣ የምርምር ማዕከሉ የተሻሻሉ ቴክኖሎጂዎችም አርሶና አርብቶ አደሩ ዘንድ እንዲደርሱ በራሱ ማሳ ላይ በማዕከሉ ተመራማሪዎች ከሚደረገው ሙያዊ ምክር በተጓዳኝ የአርሶ አደሮች የመስክ ቀን በማዘጋጀት እርስ በርስ እንዲማማሩ እየተደረገ ነው። አስተያየታቸውን ከሰጡ የአጋርፋ ወረዳ አርሶ አደሮች መካከል አቶ አበበ ከበዳ፤ ከማዕከሉ የሚለቀቁ ምርጥ ዘርና የተሻሻሉ የግብርና አሰራሮችን ተከታትለው እንደሚጠቀሙ ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅትም ከማዕከሉ በድጋፍ ያገኙትን ዘመናዊ የንብ ቀፎ በግቢያቸው ውስጥ በማዘጋጀት ከመደበኛ የሰብል ልማት በተጓዳኝ ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት እየሰሩ መሆኑን አመልክተዋል። በተለምዶ ሲያካሄዱ በነበረው የተፋሰስ ልማት ሥራ የማዕከሉ ተመራማሪዎች ያገኙትን ሙያዊ ድጋፍ ተጠቅመው የተፈጥሮ ማዳበሪያ በማዘጋጀት ለልማት እያዋሉ መሆኑን አክለዋል። የሲናና ግብርና ምርምር ማዕከል ከ1978 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁን ከ97 የሚበልጡ የሰብል ዝሪያዎችና የእንስሳት መኖ ላይ ትኩረት ያደረጉ የምርምር ውጤቶችን ለአርሶ አደሮች ማድረሱን ከምርምር ማዕከሉ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የኢትዮጵያ ብሪክስን መቀላቀል ከሩሲያ ጋር ያላትን ትብብር ያጠናክራል - ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን
Dec 5, 2023 158
አዲስ አበባ፤ ህዳር 25/2016(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ ብሪክስን መቀላቀሏ ከሩሲያ ጋር ያላትን ትብብር የበለጠ የሚያጠናክረው መሆኑን የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ገለጹ። በሩሲያ ፌዴሬሽን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ቻም ኡጋላ ኡሪያት የሹመት ደብዳቤያቸውን ለሩሲያው ፕሬዝዳንት አቀርበዋል ፡፡ አምባሳደሩ የሹመት ደብዳቤያቸውን ባቀረቡበት ወቅት ፕሬዝዳንት ፑቲን ባስተላለፉት መልዕክት ኢትዮጵያና ሩሲያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከመሰረቱ 125 ዓመታትን ያስቆጠሩ ወዳጅ አገራት መሆናቸውን አንስተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በቅርቡ በሩሲያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት በማድረግ የተለያዩ የትብብር ስምምነቶች መፈረማቸው ግንኙነቱን ከፍ ወዳለ ደረጃ እንዳሻገረው መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል። ኢትዮጵያ ብሪክስን መቀላቀሏ ደግሞ የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት የበለጠ እንደሚያጠናክረው ተናግረዋል፡፡
በታንዛንያ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት የ47 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ
Dec 4, 2023 70
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 24/2016 (ኢዜአ) ፦ በታንዛንያ ከባድ ዝናብ መጣሉን ተከትሎ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት በትንሹ የ47 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጿል። የአየር ንብረት ለውጥን ተከትሎ ከፓስፊክ ውቅያኖስ የሚነሳው ዝናብ አዘሉ የአሌ ኒኖ ክስተት ታንዛንያን ጨምሮ በኬኒያና በሶማልያ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል። በሰሜን ታንዛንያም ከቅዳሜ ጀምሮ እየጣለ የሚገኘው ነፋስ የቀላቀለ ዝናብ ባስከተለው የመሬት መንሸራተት አደጋ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን ዘጋርዲያን በዘገባው አስነብቧል። በሰሜናዊ ታንዛንያ ካቴሽ ከተማ በተከሰተው አደጋ እስከ ትላንት ምሽት ድረስ በተንሹ የ47 ሰዎች ህይወት ማለፉንና 85 ሰዎች መጎዳታቸውን ተጠቅሷል። በግዛቲቱ እየጣለ የሚገኘውን ነፋስ የቀላቀለ ዝናብ ተከትሎ የተጎጂዎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ያመለከተው ዘገባው ለአካባቢው ነዋሪዎች የማስጠንቀቂያ መልዕክት ከግዛቲቱ የአደጋ መከላከል ኮሚሽን መተላለፉንም ገልጿል።
የአየር ንብረት ለውጥ ቀውስ ከ 12 ሆስፒታሎች አንዱን የመዝጋት አደጋን ደቅኗል
Dec 4, 2023 78
አዲስ አበባ፤ ህዳር 24/2016 (ኢዜአ)፦የካርበን ልቀትን መቆጣጠር ካልተቻለ በአለማችን ካሉ 12 ሆስፒታሎች አንዱ በአየር ንብረት ቀውስ ሙሉ በሙሉ አለያም በከፊል የመዘጋት አደጋ መደቀኑን ጥናት አመለከተ። ይህ ጥናት የቀረበው በዱባዩ ኮፕ28 የመሪዎች የጤና ጉባኤ ላይ ነው። የካርበን ልቀትን መቆጣጠር ካልተቻለ በሚያስከትለው የአየር ንብረት ቀውስ በአለማችን ካሉ 12 ሆስፒታሎች አንዱ ሙሉ በሙሉ አለያም በከፊል የመዘጋት አደጋ አንደተደቀነበት የሲተቪ ኒውስ ዘገባ ያመለክታል። በክሮስ ዲፔንዳንሲ ኢኒሼቲቭ የሳይንስና ቴክኖሎሊ ዳይሬክተር ዶክተር ካረለ ማሎን በኮፕ 28 ዱባይ የጤና ጉባኤ ላይ ባቀረቡት ሪፖርት እንዳመለከቱት ለጥናት ከተወሰዱ ከ200ሺ 216 ሆስፒታል ናሙናዎች ከ12 አንዱ አደጋላይ ነው ። የአየር ንብረት ለውጡ ሆስፒታሎች ላይ የሚያስከትለው አውሎ ንፋስ፣ የጎርፍ መጥለቅለቅ ወይም የደን ቃጠሎ ስራቸውን ያስተጓጉላል አለያም ወደ ሌላ ቦታ እንዲቀይሩ ያስገድዳቸዋል እንደ ሪፖርቱ ገለጻ። ችግሩን መቅረፍ ካልተቻለም በምእተአመቱ መገባደጃ የአለማችን 16ሺ245 ሆስፒታሎች በአየር ንብረት ለውጡ ሙሉ በሙሉ አለያም በከፊል ይዘጋሉ ። የአየር ንብረት ለውጥ በጤና ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ለመቀነስም የቅሪተ አካላት ነዳጅ አጠቃቀምን መቆጣጠር አስገዳጅ ነው።
የታዳሽ ሃይል አቅርቦትን በሶስት እጥፍ ለማሳደግ ለቀረበው ጥሪ የበርካታ አገራት ድጋፍ አገኘ
Dec 3, 2023 85
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 23/2016 (ኢዜአ)፦ የታዳሽ ሃይል አቅርቦትን በሶስት እጥፍ ለማሳደግ ለቀረበው ጥሪ የበርካታ አገራት ድጋፍ ማግኘቱ ተገለጸ። በዱባይ እየተካሄደ ባለው የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት የአገራት መሪዎች የታዳሽ ሃይል አቅርቦትን በዓለም አቀፍ ደረጃ በሶስት እጥፍ ለማሳደግ መስማማታቸውን ተዘግቧል። ከአንድ መቶ አስር በላይ የሚሆኑ የአገራት መሪዎች እንደአውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2030 የታዳሽ ሃይል አቅርቦትን በሶስት እጥፍ ለማሳደግ ለቀረበው ጥሪ አዎንታዊ ምላሽ መስጠታቸውን የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዝደንት ኡርሱላ ቮንደር ሊይን ገልጸዋል። መንግስታትም ሆኑ ግዙፍ ኩባንያዎች ከፍ ያለ መዋእለ ንዋያቸውን ለዚሁ አላማ መሳካት ያውላሉ ወይ የሚለው ጥያቄ መመለስ እንደሚኖርበት አጽንኦት የሰጡት ፕሬዝደንቷ የግብአት አቅርቦት፣ የዋጋ ጭማሪ፣ በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ሃይል እንዲሁም የፕሮጀክቶች አፈጻጸምን የተመለከቱ ጉዳዮች ከውሳኔው በኋላ መፍትሄ የሚፈለግላቸው ይሆናል ብለዋል። በጉባኤው የሚነሳው ሃሳብ የሁለት መቶ አገራት ይሁንታ የሚፈልግ መሆኑን የተነገረ ሲሆን የአውሮፓ ህብረት፣ አሜሪካና ዩናይትድ አረብ ኤምሬት ጥሪውን በግንባር ቀደምነት የተቀበሉ ናቸው። ቻይናና ህንድ በይፋ ሃሳባቸውን ባይገልጹም በካይ የሚባሉትን የድንጋይ ከሰልና የነዳጅ ዘይት የሃይል ምንጮችን በመቀነስ የታዳሽ የኃይል አማራጮችን በ2030 በሶስት እጥፍ ማሳደግ በሚለው ሃሳብ ዙሪያ የመስማማት አዝማሚያ ማሳየታቸውን ተገልጿል። ደቡብ አፍሪካ፣ ቪየትናም፣ አውስትራሊያ፣ ጃፓን፣ ካናዳ፣ ቺሊና ባርባዶስ ሃሳቡን በይፋ መቀበላቸውን ከገለጹ አገራት መካከል ተጠቃሽ መሆናቸውን የኢነርጂ ዎርልድ ዘገባ ያመለክታል።
ሐተታዎች
"ድሽታ ግና'' የኣሪዎች የምስጋናና የምርቃት በዓል!
Nov 30, 2023 135
በጣፋጩ ሰለሞን (ኢዜአ) በኦሞ ሸለቆ አካባቢ በማጎ ብሔራዊ ፓርክ አቅራቢያ የሚገኙት አሪዎች በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከሚኖሩ ብሔር ብሔረሰቦች ውስጥ ይጠቀሳሉ፡፡ ''ኣሪ ኣፍ'' ወይም ''ኣሪኛ'' የተሰኘ የመግባቢያ ቋንቋም አላቸው፤ ከኦሞቲክ የቋንቋ ነገድ ይመደባል። የኣሪ ማህበረሰብ የኢኮኖሚ መሰረት ጥምር ግብርና ሲሆን፤ አካባቢውም ቆላ፣ ደጋ እና ወይና ደጋ የአየር ጠባይ አለበት። ኣሪዎች የቤት አሰራራቸው፣ የሙዚቃ ጥበባቸው፣ የአጨፋፈር ስልታቸው፣ አለባበስና አጋጌጣቸው እጅግ ማራኪና የቱሪስት ቀልብን የሚስብ ነው። እግር ጥሎት ወደ አካባቢው ያቀና እንግዳ ባይተዋርነት እንዳይሰማው የሚያደርገው የኣሪዎች የእንግዳ አቀባበል ባህል የሚደነቅ ነው። አሪዎች ለቤታቸው እንግዳ የሆነን ሰው ''አቦቶ፤ ደኣይቶ'' - ውይ በሞትኩልህ! እንደማለት ነው እያሉ ደረታቸውን እየደቁ ይቀበላሉ። ለእንግዳው አርደውና አብልተው ሲመሽ ደግሞ እግሩን አጥበው አልጋቸውን ለቀው መሬት አንጥፈው ያስተኛሉ። የራሳቸው የጊዜ ቀመር አቆጣጠር ያላቸው ኣሪዎች ''ሎንጋ'' በተሰኘው የታህሳስ ወር አሮጌውን ዓመት ሸኝተው አዲሱን ዓመት ይቀበላሉ። ይሄው አዲስ ዓመታቸው ደግሞ ''ድሽታ ግና'' የሚል መጠሪያ ያለው ትልቅ ዓመታዊ ክብረ በዓላቸው ነው። የኣሪ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ የባህል፣ የታሪክ፣ የቅርስ ጥናትና ልማት የሥራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ዳኜ ገብሬ እንደሚሉት የአዲስ ተስፋና ወንድማማችነት ተምሳሌት የሆነው ድሽታ ግና በማህበረሰቡ ዘንድ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው በዓል ነው። የብሔረሰቡ የዘመን መለወጫ የሆነው የ"ድሽታ ግና" በዓል የሁለት ቃላት ጥምር ሲሆን ''ድሽታ'' ምስጋና "ግና'' ደግሞ ምርቃትን ይወክላል። የ"ድሽታ ግና" በዓል አርሶ አደሩ የዘራው ዘር ፍሬ አፍርቶ ጎተራው፣ ከብቶች ተዋልደው ጋጥ ሲሞላና ቤቱ በበረከት ሲትረፈረፍ ፈጣሪን የሚያመሰግኑበት፤ በባህል መሪዎች ቡራኬ የሚሰጥበት ታላቅ የምስጋናና የምርቃት በዓል ነው። በባህሉ መሰረትም ወደ አዲሱ አመት ቂምና ቁርሾን ይዞ መሻገር አይቻልም። ስለዚህ ከበዓሉ በፊት በዳይና ተበዳይ "ይቅር" ተባብለው ቂም በቀልን ከአሮጌው ዓመት ጋር ሸኝተው በፍቅር አዲሱን ዓመት እንደሚቀበሉ ነው አቶ ዳኜ የሚናገሩት፡፡ በዚህም መሰረት አንድ የኣሪ ማህበረሰብ አባል በዓሉ ከመድረሱ በፊት "በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ያስቀየምኩት ካለ" በሚል በየቤቱ እየተዟዟረ ይቅርታ ይጠይቃል። በዚህ አጋጣሚ ምናልባት እስከ ህይወት መጥፋት ድረስ የሚደርስ በደል ከተፈፀመ በዳዩ ሽማግሌ ልኮ ፀፀቱን ገልፆ ተበዳይን ተማፅኖ ይቅርታ ይጠይቃል፤ ይቅርታም ይደረግለታል። በየቤቱ ይቅርታ የሚጠይቅበት ምክንያት ቂምና ቁርሾ ወደ አዲሱ ዓመት መተላለፍ ስለሌለበት ነው። ቂምና ቁርሾ በውስጡ ይዞ በዓሉን የሚያከብር አሊያም የበዓል ድግስ ደግሶ ጎረቤት ጠርቶ ማብላት በብሔረሰቡ ዘንድ በጥብቅ የተከለከለ እንደሆነ አቶ ዳኜ ይገልፃሉ። አንድ የኣሪ ማህበረሰብ አባል ዕርቅ ከፈፀመ በኋላ "አርሼ ጥሩ ምርት አግኝቻለሁ፤ ነግጄ አትርፊያለሁ፣ ከብቶቼ ጋጣ ሞልተውልኛል፣ ቤቴ በበረከት ተትረፍርፏል" ሲል ካገኘው ላይ ቀንሶ ድል ያለ ድግስ ይደግሳል። ድግሱ የተራበውን በማብላት፣ የተቸገረውን በመጎብኘት ፈጣሪ ላደረገላቸው በጎ ነገር ከሌሎች ጋር አብሮ ማዕድ በመቋደስ ለፈጣሪ ምስጋና የሚያቀርብበት እንደሆነም አቶ ዳኜ ይናገራሉ። የ"ድሽታ ግና" በዓል እሸት የሚቀመስበት ነው። በበዓሉ ዕለት የኣሪ ባላባቶች እሸቱን፣ ወተቱን፣ ማሩን ከቀመሱ በኋላ መጪው ዘመን የተባረከ፣ የጥጋብ፣ የሰላምና የጤና እንዲሆን ይመርቃሉ። የሰላምና የአብሮነት እንዲሁም ያለፈውን ዘመን በመተው በአዲስ ተስፋ እጅ ለእጅ በመያያዝ ወንድማማችነትን በማጠናከር ሰርቶ በመለወጥ እና ለሌላው መትረፍን ጭምር የሚያበረታታ በዓል ነው። የብሄረሰቡ ተወላጅ የሆኑት አቶ ፍቃዱ ጋሲ በእንደሚናገሩት፤ የ"ድሽታ ግና" በዓል የፍቅር፣ የአንድነትና የይቅርታ አስተምህሮ ያለው አብሮነትን የሚያጠናክር ነው። በዓሉ የተጣላውን የሚያስታርቅ የተራራቀውን የሚያቀራርብ በመሆኑ በየዓመቱ በጉጉት ይጠበቃል። የዕድገትና ለውጥ መሰረት ጭምር ተደርጎ የሚወሰድ ነው። የዘንድሮውን የ"ድሽታ ግና" በዓልም አብሮነትን፣ አንድነትን፣ መረዳዳትን በሚያጎላ ብሎም የባህሉን እሴት በጠበቀ መልኩ ለማክበር መዘጋጀታቸውን አቶ ፍቃዱ ይገልጻሉ። የ"ድሽታ ግና" በዓል ጠቃሚ ባህላዊ እሴቶች ያሉትና ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተሸጋገረ የመጣ ነው። አሁንም በዓሉ ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር በማስተማር ሃላፊነታቸውን እየተወጡ መሆናቸውን ነው በአጽንኦት የተናገሩት። የ"ድሽታ ግና" በዓል ከመድረሱ አስቀድሞ እናቶች ከእንሰት እና ከእንስሳት ተዋጽኦ የሚገኙ ለክብር እንግዶችና ለአባ ዎራዎች የሚቀርቡ ባህላዊ ምግቦችን የማዘጋጀት ስራ ላይ እንደሚጠመዱ የገለጹት ደግሞ የብሔረሰቡ አባል ወይዘሮ ደብሪቱ ኣዳዮ ናቸው። ወጣት ሴቶችና ወንዶች ደግሞ ቤት በማስዋብ እና ግቢ በማሳመር ስራ ላይ ይሳተፋሉ። በበዓሉ ወቅትም በቤት ውስጥ የተዘጋጁ ምግቦች በዓይነታቸው ተለይተው ይቀርባሉ። ጥሩ ምግብ ያዘጋጀችና ምግቧ ጣፋጭ የሆነላት ሴት በግጥምና በዜማ ትወደሳለች። የ"ድሽታ ግና" በዓል "የተጣሉትን በማስታረቅ፣ ከተቸገሩ ወገኖች ጋር ቤት ያፈራውን አብሮ በመቋደስ ፣የታመሙትን በመጠየቅ በጋራ የምናከብረው ልዩ በዓል ነው" ያሉት ወይዘሮዋ "ድሽታ ግና" ፍቅር፣ አንድነት እና በጎነት ጎልቶ የሚታይበት ዕለት እንደሆነም ነው የገለጹት። በድሽታ ግና በዓል "በዕርቅ የማይቋጭ ጥል፣ የማይድን ቁስል፣ የማይሽር ጠባሳ የለም" ብለዋል። በነዋሪው ዘንድም ለዘመናት ለዘለቀው ሰላምና አንድነት እንዲሁም ጠንካራ የስራ ባህል መሰረት ነው፡፡ የኣሪ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ አቶ ኤሊያስ ቃሾ በበኩላቸው፤ በዓሉ ከኣሪ ማህበረሰብ አልፎ ለመላው ኢትዮጵያዊያን የሚሆን "በርካታ ጠቃሚ እሴቶችን በውስጡ የያዘ ነው" ሲሉም ይገልጻሉ። "ድሽታ ግና" ሰላም፣ ፍቅር፣ አንድነትን፣ መረዳዳትን እና አብሮነትን የሚያስተምር ህዝብ ለህዝብ የሚያቀራርብ ዕሴት ያለው በዓል ነው፡፡ የ"ድሽታ ግና" በአል ከጥንት አባቶቻችን ጀምሮ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ በዓል ቢሆንም የተሰጠው ትኩረት አነስተኛ በመሆኑ ተደብቆ የኖረ ቱባ ባህል መሆኑን አንስተዋል። ሃላፊው እንዳሉት የ"ድሽታ ግና" በዓል ከለውጡ ማግስት በመንግስት በተሰጠው ትኩረትና ባገኘው ዕውቅና የአደባባይ በዓል ሆኖ በመከበሩ "የአገር ውስጥና የውጭ አገራት ቱሪስቶች እንዲጎበኙት በር ከፍቷል" ብለዋል። የ"ድሽታ ግና" በዓል እንደ ሌሎች ዕውቅና እንዳገኙ ክብረ በዓላት አድጎ፣ ጎልብቶ እንዲሁም ዕውቅና አግኝቶ ከአገራችን አልፎ የዓለም ቅርስ እንዲሆን የመላ ኢትዮጵያዊያንን እገዛ ያስፈልጋል። የዘንድሮው የድሽታግና በዓል ''ድሽታ ግና ለዘላቂ ሰላም እና ለፈጣን ልማት'' በሚል መሪ ሀሳብ በዞኑ ሁሉም አካባቢዎች በድምቀት እንደሚከበር የተናገሩት ደግሞ የኣሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም አታ ናቸው። በዓሉ "የመተሳሰብ፣ የመረዳዳትና የዕርቀ-ሰላም በመሆኑ የተጣላውን በማስታረቅ፣ የተቸገሩ ወገኖችን በመጎብኘትና ማዕድ በማጋራት ይከበራል" ብለዋል። ሰላምና ወንድማማችነትን የሚሰብከው "ድሽታ ግና" የአሮጌው ዘመን ማጠቃለያና አዲሱን ዘመን ብስራት ከአጎራባች ዞኖች እና ከመላው ኢትዮጵያዊያን ጋር ዕሴቱን በጠበቀ መልኩ በአደባባይ በጋራ ለማክበር አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቋል። የ"ዲሽታ ግና" ዕሴቶች አገር በቀልና በህዝቡ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት ያላቸው መሆኑን ያነሱት ዋና አስተዳዳሪው፤ እንደአገር ዘላቂ ሰላምና ልማት እንዲሁም የብልጽግና ጉዞን ለማጠናከር "ለተወጠኑ ግቦች ስኬት የሚኖረው ፋይዳ ከፍተኛ በመሆኑ ልንጠቀምበት ይገባል" ብለዋል። ከወርሃ ህዳር አጋማሽ ጀምሮ ከቤተሰብ እስከ ኣሪ ባላባቶች ቅደም ተከተሉን ጠብቆ የሚከበረው የ"ድሽታ ግና" በዓል ታህሳስ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ደግሞ የአዲስ ዓመት ብስራት ይታወጅበታል። በዕለቱ በጂንካ ከተማ በተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች በድምቀት ይከበራል። ''ዑሳ ዎም ዣዕሼ !'' እንኳን አደረሳችሁ!
ኢሬቻ የአብሮነት ማሰሪያ ሐረግ
Oct 6, 2023 708
ኢሬቻ የአብሮነት ማሰሪያ ሐረግ (አሸናፊ በድዬ) ኢሬቻ የምስጋና በዓል ነው፤ ከክረምት ወቅት መለያየትና መራራቅ በኋላ ሰዎች በአብሮነት ብርሃን ለማየት ያበቃቸውን ፈጣሪ የሚያመሰግኑበት። ስለ ሰላምና አንድነት የሚዘመርበት፣ ስለመጪው ጊዜ መልካም ምኞት የሚገለጥበት፣ ሁሉን ላደረገ ፈጣሪ ምስጋና የሚቸርበት የአብሮነት በዓል ነው። በልመናው፣ በምርቃቱ፣ በምስጋናው ሁሉ ሀዬ! ሀዬ! ሀዬ! (አሜን! አሜን! አሜን!) የሚሉ ድምፆች ይስተጋባሉ። "ሀዬ! ሀዬ! ሀዬ! ሀዬ! የእውነትና የሰላም አምላክ! ከስህተትና ከክፉ ነገሮች ሁሉ ጠብቀን! ለምድራችን ሰላም ስጥ! ለወንዞቻችን ሰላም ስጥ! ከጎረቤቶቻችን ጋር ሰላም ስጠን! ለሰውም ለእንስሳቱም ሰላም ስጥ!" በማለት ይመረቃል። ሕዝቡም ይሁንልን ይደረግልን ሲል "ሀዬ! ሀዬ! ሀዬ!" ይላል። የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል መስከረም 26 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሆራ ፊንፊኔ እንዲሁም በማግስቱ እሑድ መስከረም 27 ቀን በቢሾፍቱ ሆራ ሀርሰዲ ይከበራል። የክራምት ወራት እንዳበቃ የሚከበረው "ኢሬቻ መልካ" (በውሃ ዳርቻ የሚከበር) ሲሆን በዓመቱ አጋማሽ ላይ የሚከበረው "ኢሬቻ ቱሉ" ደግሞ በተራራማ ቦታ የሚከበር ነው። ኢሬቻ መልካ የሚከበረው በመስከረም ወር ከመስቀል በዓል በኋላ ሲሆን፤ የክረምት ወራት የዝናብ፣ የደመና፣ የጭቃና የረግረግ ወቅት አልፎ ለፈካው ወራት በመብቃቱ ምስጋና የሚቀርብበት ነው። ኢሬቻ ቱሉ የሚከበረው የበጋው ወራት አልፎ የበልግ ዝናብ በሚጠበቅበት ወቅት ነው። በዚህም ፈጣሪ ''እርጥበት አትንፈገን፣ ወቅቶች ጊዜያቸውን ጠብቀው ይምጡ፤ የዝናብ ንፋስ ስጠን'' በማለት ለፈጣሪ ተማጽኖ የሚቀርብበት ነው። "ይህን ተራራ የፈጠርክ ፈጣሪ ወቅቱን የሰላም አድርግልን፣ የሰላም ዝናብ አዝንብልን፣ ጎርፍን ያዝልን፣ የተዘራው ፍሬ እንዲያፈራ እንለምንሃለን" እያለ በኢሬቻ ቱሉ ላይ ፈጣሪውን ይለምናል፡፡ በኢሬቻ በዓል የፈጣሪ ምህረት፣ ዕርቅ፣ እዝነት እና በዓሉ የሰላም በዓል እንዲሆን ከላይ በተጠቀሰው መልኩ ኦሮሞ ፈጣሪውን ይጠይቃል፤ ይማፀናል፤ ለተደረገለትም ነገር ሁሉ ያመሰግናል። የኢሬቻ በዓል ከገዳ ሥርዓት ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያለው ሲሆን፤ በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ለዘመናት ሲከበር የቆየ በዓል ነው። በዓሉ በዋናነት በአዲስ አበባ ሆራ ፊንፊኔ፤ በቢሾፍቱ ከተማ በሆራ ሀርሰዲ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ ታድሞ የሚከበር ቢሆንም በተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖችና ወረዳዎች በድምቀት ይከበራል። የኦሮሞ ሕዝብ ምድርን እና ሰማይን ለፈጠረው ፈጣሪ "ዋቃ" ምስጋናውን ለማድረስ የኢሬቻ በዓልን ያከብራል ይላሉ አባገዳዎች። የኦሮሞ ሕዝብ በዕድሜ ልዩነት ሳይገደብ የኢሬቻ በዓልን ለዘመናት በጋራ፣ በአንድነትና በፍቅር ሲያከብር ቆይቷል። በዝናባማው የክረምት ወቅት በጅረቶችና ወንዞች መሙላት ምክንያት ተራርቆ የቆየው ዘመድ አዝማድ በኢሬቻ በዓል ማክበሪያ ሥፍራ ይገናኛል፤ ይጠያየቃል፤ ናፍቆቱንም ይወጣል። አባቶች ክረምት በለሊት ይመሰላል ይላሉ። ለሊት ደግሞ ጨለማ ነው። ጨለማው ሲነጋ ደግሞ ብርሃን ነው፤ ብርሃን ደግሞ ውበት ነው፤ መታያና መድመቂያም ነው። ለዚህ ነው በኢሬቻ በዓል አከባበር ላይ ሁሉም ውብ የባህል ልብሱን በመልበስ በደስታ በዓሉን ለማክበር የሚመጣው። ሕዝቡ በዓሉ ወደሚከበርበት ሥፍራ የሚሄደው በተናጠል ሳይሆን በሕብረትና በአንድነት ነው፡፡ ለዚህ ነው ኢሬቻ የአንድነትና የአብሮነት በዓል ነው የሚባለው። በኢሬቻ ልዩነት የለም፤ ፀብ የለም፤ ክፋት የለም፤ ይልቁንም ምስጋና ይጎርፋል፤ ፍቅር ይሰፍናል፤ አብሮነት ያብባል። ኢሬቻ በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው የሰላምና የአብሮነት ምልክት ሲሆን፤ የኢሬቻ በዓልን ለማክበር የሚወጣው ታዳሚም እንደ እርጥብ ሣር ወይም አበባ ያለ እርጥብ ነገር በእጁ ይዞ የበዓሉን ስነ-ስርዓት ያከናውናል። ይህን የሚያደርገውም "ፈጣሪያችን ሆይ አንተ ያፀደቅከው ነው አብቦ ፍሬ ያፈራው፤ ለዚህም እናመሰግንሃለን" በማለት የፈጣሪን መልካምነት ለማሳየት ነው። በሌላ በኩል እርጥብ ሣር የልምላሜ ምልክት በመሆኑ የመልካም ምኞት መግለጫም ጭምር በመሆኑ ነው በኢሬቻ በዓል እርጥብ ሣር የሚያዘው። የኦሮሞ ሕዝብ ለሰላም ትልቅ ሥፍራ ይሰጣል። ሰላም ካለ ሁሉም ነገር አለ ብሎም ያምናል። በምርቃቱም "ቡና ፊ ነጋአ ሂንደቢና" ብሎ ይመራረቃል። ቡናና ሰላም አያሳጣችሁ ማለት ነው። ለዚህም ነው በኢሬቻ በዓል ለመላው የሰው ልጅ ሰላምና ደኅንነት ፈጣሪ የሚለመነው። ሳል ይዞ ስርቆት፤ ቂም ይዞ ፀሎት እንዲሉ አበው በኢሬቻ የተጣላ ታርቆ፣ ቂሙን ረስቶ በንጹህ ልቦና ፈጣሪ ንጹህ ወዳደረገው የውሃ አካል ይሄዳል፤ በዚያም ፈጣሪውን ያመሰግናል። የኢሬቻ በዓል ሲከበር ከሚከወኑ ሥርዓቶች መካከል ሴቶች ሲቄ፣ እርጥብ ሣር እንዲሁም ጮጮ ይዘው ከፊት ሲመሩ አባ ገዳዎች ደግሞ ቦኩ፣ አለንጌ እና ሌሎችንም በበዓሉ ሥርዓት የሚፈቀዱትን ሁሉ በመያዝ ወደ ሥርዓቱ አከባበር ያመራሉ። ኦ ያ መሬሆ…………………መሬሆ መሬሆ………………… መሬሆ ያ ዋቃ ኡማ ሁንዳ መሬሆ…………………ያ መሬሆ መሬሆ………………… መሬሆ ያ ዋቃ ለፋ ኡምቴ መሬሆ………………… ያ መሬሆ መሬሆ………………… መሬሆ ያ ዋቃ መልካ ኡምቴ መሬሆ………………… ያ መሬሆ መሬሆ………………… መሬሆ እያሉ ያመራሉ። የሁሉ ፈጣሪ፣ ምድርን የፈጠርክ፣ ወንዙን የፈጠርክ . . . ምስጋና ለአንተ ይሁን በማለት ያመሰግናሉ፤ ይዘምራሉ። የኢሬቻ በዓል ሥነ-ሥርዓት በአባመልካ ተከፍቶ በአባ ገዳዎች ተመርቆ ከተጀመረ በኋላ መላው ሕዝብ በአንድነት ሥርዓቱን ያከናውናል። ኢሬቻ ሁሉም በጋራ የሚያከብረው፣ የሁሉም ማጌጫ፣ መድመቂያ እና የአብሮነት መገለጫ ነው። ብሔር ብሔረሰቦች የሚታወቁበትን ባህላዊ ልብስ በመልበስ በቋንቋቸው ፈጣሪን እያመሰገኑ በዓሉን በአንድነት ያከብራሉ። ለዚህም ነው ኢሬቻ ከኦሮሞ ሕዝብ አልፎ የመላው ኢትዮጵያውያን በዓልና መገለጫ ነው የሚባለው። በርካታ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን የሆራ ፊንፊኔ እና የሆራ ሀርሰዲ በዓላት ላይ ለመታደም ወደ አገር ቤት ይመጣሉ። የውጭ አገራት ጎብኚዎችና እንግዶችም በትዕይንቱ ይታደማሉ። ለአብነትም ባሳለፍነው ዓመት ከኬንያ አገር የመጡ ልዑካን በዚህ በዓል ላይ በመታደም የበዓሉን ትልቅነት እና የኢትዮጵያውያን የአብሮነት መገለጫ መሆኑን መመስከራቸው ይታወሳል። በዚህ ዓመትም የሦስት ጎረቤት አገራት ልዑካን በዚህ በዓል ላይ እንደሚታደሙ የተገለጸ ሲሆን፤ የኬንያ፣ ሩዋንዳ እና ታንዛኒያ አገራት ተወካዮች እንደሚታደሙ ይጠበቃል። አያሌ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳዎች ያሉት ይህ የምስጋና በዓል እውነተኛ ወንድማማችነት የሚታይበት፣ አንድነት የሚጎላበት፣ አብሮነት የሚጠናከርበት፣ ሰላምና ተስፋ የሚታወጅበት ትልቅ አገራዊ እሴት ነው። በባህል አልባሳትና ጌጣጌጦች፣ ባህላዊ ምግቦችና ሌሎች ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ግለሰቦችና ተቋማት ኢሬቻና መሰል የአደባባይ በዓላትን እንደመልካም የገበያ አማራጭ ይጠቀሙባቸዋል። ኢሬቻ ባህላዊ አልባሳትና ቁሳቁሶች በስፋት የሚተዋወቁበት ታላቅ መድረክ ነው። በእርግጥም ይህንን ውብ የጋራ እሴት ጠብቆ ለትውልድ ማስተላለፍ ያስፈልጋል። ኢሬቻ የምስጋና በዓል ነውና በምስጋና እንደጀመርን በምስጋናና ምርቃት እንሰነባበት። "ሀዬ! ሀዬ! ሀዬ! ከመጥፎ ነገር ጠብቀን! ንጹህ ዝናብ አዝንብልን! ከእርግማን ሁሉ አርቀን! እውነትን ትቶ ከሚዋሽ አርቀን! ከረሃብ ሰውረን! ከበሽታ ሰውረን! ከጦርነት ሰውረን! ሀዬ! ሀዬ! ሀዬ! (አሜን! አሜን! አሜን!)
"በገበታ ለትውልድ" የሚለማው የደንቢ ሀይቅ
Oct 4, 2023 669
"በገበታ ለትውልድ" ስለሚለማው የደንቢ ሰው ሰራሽ ሃይቅ ምን ያህል ያውቃሉ? (በቀደሰ ተክሌ ከሚዛን አማን) ደንቢ ሃይቅ ሰው ሰራሽ ሃይቅ ሲሆን በእኛ የዘመን ቀመር በ1970ዎቹ የተሠራ ነው። በተፈጥሮ መስህቦች የተከበበው የደንቢ ሰው ሰራሽ ሃይቅ ለአካባቢው ብርሃንን ይፈነጥቅ ዘንድ የተሰራውን የቀድሞ የደንቢ ኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድብን ተከትሎ የተፈጠረ ሃይቅ ነው። የደንቢ ሃይቅ ለአካባቢው ማህበረሰብ ባለውለታ ነው፤ የመጀመሪያውን የኤሌክትሪክ ብርሃን ያገኙበት ነውና። ኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድቡ ከመልክዓ ምድሩ ጋር እንዲስማማ ተደርጎ የተገነባ በመሆኑ ውሃው ከላይ ወደ ታች በሁለት ምዕራፍ ቁልቁል እንዲወረወር ዕድልን ፈጥሮለታል። የመጀመሪያው የኤሌክትሪክ ሃይልን ለማመንጨት በዝግታ የሚወርደው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ሃይል አመንጭቶ ሲወጣ እጅግ ውብ የሆነ ፏፏቴን ፈጥሮ ወደ ታች የሚወርደው ነው። የደንቢ ፏፏቴ ከሃይቁ ወረድ ብሎ ስለሚገኝ "ደንቢ ሃይቅና ፏፏቴ" እየተባለ ይጠራል። ሃይቁን አይቶ ፏፏቴውን ሳያዩ መመለስ የማይቻል ነገር ነው። የደንቢ ፏፏቴ ከላይ ከዓለት ዓለት እየተጋጨ ሲወረወር የሚያሰማውን በግርማ ሞገስ በታጀበ ድምጽ፤ በተራራ ቀበቶ ተገምዶ ወደ ማረፊያ ቦታው ሲምዘገዘግ በለመለመው መስክ ላይ አሻግረው የሚቃኙት የተፈጥሮ ውበት ነው። ያሻው ወደ ተራራው ጫፍ ጠጋ ብሎ እንደ ጢስ በሚተነው የውሃ አካል ፊቱን እያስመታ አልያም ከሃይቁ ፊት ለፊት ራቅ ብሎ ተቀምጠው እየተመለከቱ መንፈስን የሚያድሱበት ውብ የፏፏቴ ሥፍራ ነው። ከላይኛው የግድቡ አናት ወደ ታችኛው ለመውረድ 640 ደረጃዎችን አቆልቁሎ መጓዝን ይጠይቃል። ይህ ትዕይንት ደግሞ የደንቢ ሃይቅ ሌላኛው መስህብ ነው። የደረጃዎቹን የመውጣትና የመውረድን ድካም አረንጓዴ ካባ የደረበው የሥፍራው ልምላሜ እንዲዘነጋ ያደርጋል። የደንቢ ሃይቅ አካባቢ ቀልብን ስቦ ድካምና ሌላ ሃሳብን አስትቶ ሃሴትን የሚያጎናጽፍ የተፈጥሮ ፀጋን የታደለ ነው። የደንቢ ሃይቅና ፏፏቴ ግርማ ሞገስ ምስጢሩ የአካባቢው ደን ነው። በረጃጅም እድሜ ጠገብ የሃገር በቀል ዛፎች የተከበበ ነው። በእምቅ ደኑ ውስጥ የሚገኙ አዕዋፋት ለሚገባ ለሚወጣው ሁሉ እንደየ ፀጋቸው ያዜማሉ። ጉሬዛዎችና ጦጣዎች ከዛፍ ወደ ዛፍ እየዘለሉ እጅ ይነሳሉ። ይህ አካባቢ የተጎናጸፈው የቱሪዝም ፀጋ ከብዙዎች ዐይን ርቆ ቆይቷል። አሁን ግን በቃ ብሎ ሚሊዮኖች ሊጎበኙት ጊዜው ተቃርቧል። አካባቢው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምሥረታን ተከትሎ ወደ ሥፍራው ጎራ ለሚሉ ሚኒስትሮችና የሃገር መሪዎች የማስተዋወቅ ሥራ በመሠራቱ "የገበታ ለትውልድ" ፕሮጀክት አንዱ አካል ሊሆን ችሏል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ቦታው ድረስ በመሄድ፣ በማየትና ለዓለም ጭምር በማስተዋወቅ የደንቢ ሎጅ ግንባታን የመሠረት ድንጋይ አስቀምጠዋል። በመድረኩ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የሚለማው የደንቢ ሃይቅ ሎጅ ፕሮጀክት በአንድ ዓመት ተኩል የጊዜ ገደብ ውስጥ የሚጠናቀቅ ነው። በተጨማሪም በደንቢ ሃይቅ ሎጅ አቅራቢያም ሌላው በጠቅላይ ሚኒስትሩ የመሰረት ድንጋይ የተቀመጠለት የአየር ማረፊያ ግንባታ ፕሮጀክት ይበልጥ አካባቢውን የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የሚያስችል ነው። የሎጅ ግንባታው ተጠናቆ ወደ ሥራ ሲገባ፤ ደንቢ ላይ ያረፈ ጎብኚ ከ40 በላይ የሚፍለቀለቁ የዑሲቃ ፍል ውሃ ቦታዎችን፣ የጋርንናንሳ ተራራን እና ሌሎች የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ የቤንች ሸኮ ዞን የተፈጥሮ ፀጋዎችን በቅርብ ርቀት መጎብኘት ይችላል። የቤንች ሸኮ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ እና የፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ሃላፊ አቶ ሳሙኤል አሰፋ በርካታ የቱሪዝም ሃብቶችን በዙሪያው አቅፎ የያዘው ደንቢ በቅርቡ የቱሪዝም ኢኮኖሚ አነቃቂ ሃይል ይሆናል የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በነደፉት የ"ገበታ ለትውልድ" ፕሮጀክት ሲለማ ከሃገር ውስጥ ባሻገር ከሃገር ውጭ በርካታ ጎብኚዎችን በማስተናገድ የውጭ ምንዛሬ የሚገኝበት ፕሮጀክት መሆኑንም ሳይዘነጉ። እንደዚህ አይነት ሃገራዊ ፕሮጀክቶች በአካባቢያቸው የተለመዱ አለመሆናቸውን ጠቅሰው የመንግስትን እይታና በአካባቢው ያለውን ሃገራዊ አቅም ወደ ኢኮኖሚ ለመቀየር ትልቅ ትርጉም ያለው መሆኑንም አድንቀዋል። የቤንች ሸኮ ዞን በርካታ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ መስህብ ሃብቶች እንዳሉት ገልጸው የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ያለውን ወደ ዓለም አቀፍ ገበያ ለመቀላቀል መንግስት የከፈተውን መልካም አጋጣሚ መጠቀም እንደሚገባ ነው የጠቆሙት። ከአንድ ዓመት ተኩል በፊት መሠረት ተቀምጦለት እየተገነባ ያለውን የሚዛን አማን ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ግንባታን መልካም አጋጣሚውን ለመጠቀም አንዱ ዕድል እንደሆነም ጠቅሰዋል። ፕሮጀክቶቹ ሲጠናቀቁ ለመጎብኘት የሚመጡ እንግዶችን ቆይታ ለማራዘም እና ወደውት ተደስተው እንዲመለሱ ለማስቻል ከወዲሁ በቂ ዝግጅት እናደርጋለን ያሉ ሲሆን በቅርብ ርቀት ያሉ የቱሪስት መዳረሻዎችን ምቹ የማድረግ ሥራም በትኩረት ይከናወናል ብለዋል። የሚዛን አማን ከተማ ነዋሪው አቶ ያሬድ ካንጃ ደንቢ በቅርብ ርቀት ቢገኝም ያልለማ በመሆኑ ብዙዎች የመጎብኘት ዕድል እንዳላገኙ ተናግረዋል። ደንቢ ሃይቅ እና ፏፏቴ ከሃይቅነትና የቱሪስት መስህብነት ባሻገር በሥራ ዕድል ፈጠራም ጭምር ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ አለው ነው ያሉት። የሎጁ መገንባት የዞኑን የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ወደ ዓለም ገበያ ያስገባል የሚል ተስፋ መሰነቃቸውንም አቶ ያሬድ አልሸሸጉንም። "እንደ አካባቢው እምቅ የተፈጥሮ ሃብት አቅም አንጻር ይህ ጅምር ነው፤ በቀጣይ በርካታ ፕሮጀክቶችን እንጠብቃለን" ብለዋል።
የብርቅዬዎችን አምባ በዩኔስኮ መዝገብ ላይ እናቆይ!
Sep 30, 2023 900
በመሐመድ ረሻድ ባሌ ሮቤ(ኢዜአ) ኢትዮጵያ የብዙ ሕብረ ብሔራዊ ባህልና ማንነት ያሏቸው ሕዝቦች ሀገር ነች። የተፈጥሮ ገፅታዋ በልዩነት ውስጥ አንድነትን፣ በብዝሃነት ውስጥ ህብረትን አጎናጽፏታል። ከህዝቦቿ ጥምር ውበት ባለፈ ተፈጥሮ ያደላት የበርካታ ጸጋዎች ባለቤትም ናት። መስራት የሚገባውን ያክል ሳይሰራበት ቢቆይም አሁን ላይ እነዚህን ተፈጥሯዊ ሃብቶች የቱሪዝም ኢንዱስትሪውን ለማሳደግና የዘርፉን ተጠቃሚነትም ለማሳደግ እየተሰራባቸው ይገኛል። በዚህ ረገድ ሥሙ በቀዳሚነት ጎልቶ የሚነሳው ባለብዙ የተፈጥሮ ውበት ባለቤት የሆነውና "አንድ ፓርክ ብዙ ዓለማት (One Park Many World)" ተብሎ የሚታወቀው የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ አንዱና ዋነኛው ማሳያ ነው። በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ባሌ ዞን የሚገኘው ይህ ብሔራዊ ፓርክ ከአዲስ አበባ በ411 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል። በድንቅ የተፈጥሮ ጸጋ የታደለው ይህ ስፍራ እንኳን ደህና መጣችሁ የሚያሰኝ ሃሴትን የሚሞላ ግርማ ሞገስን የተላበሰ ነው። ፓርኩ በሀገራችን ከሚገኙ 27 ብሄራዊ ፓርኮችና ሌሎች ጥብቅ ደን ስፍራዎች አንዱ ነው። በውስጡ በርካታ የብዝሃ-ህይወት ሃብትን የያዘና የጎብኚዎችን ቀልብ የሚስብ ነው። የደጋ አጋዘን፣ቀይ ቀበሮ፣ትልቁ ፍልፈል፣ የሳነቴ አምባ፣ የሀረና ጥቅጥቅ ደን ፓርኩ ከሚታወቅባቸው ብርቅዬዎች መካከል በዋነኞቹ ናቸው። የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በ2 ሺህ 150 ካሬ ኪሎ ሜትር ስፋት ላይ ተከልሎ የተመሰረተው በ1962 ዓ.ም ሲሆን በውስጡ ከ1 ሺህ 600 በላይ የተለያዩ የእጽዋት ዝርያዎች፣ ከ78 ዓይነት በላይ አጥቢ የዱር እንስሳት እና 300 የሚደርስ ዝርያ ያላቸው አዕዋፍን ይዟል። ከነዚህ መካከል 32 የእጽዋት ዝርያዎች እና በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙ 31 ብርቅዬ የዱር እንስሳት እንደሚገኙበትም ከብሔራዊ ፓርኩ ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያስረዳል፡፡ ጥቂት ስለ ብሔራዊ ፓርኩ ጸጋዎች፦ ⦁ የሰማይ ላይ ደሴት(The Island in the Sky) - የሳነቴ አምባ የሳነቴ አምባ የተፈጥሮ ድንቅ ስራ የሚታይበት የፓርኩ ልዩ ገፅታ የሚንፀባረቅበት ነው። ስፍራው በአፍሪካ ካሉት ፕላቶዎች በስፋቱ 17 በመቶ የሚሸፍን ሜዳማና ትልቁ የአፍሮ አልፓይን አምባ ወይም የሰማይ ላይ ደሴት(The Island in the Sky) ነው፡፡ ይህ ውርጫማ ስፍራ የከፍተኛ ተራራዎች መገኛ ሲሆን፤ በሀገራችን በከፍታው ሁለተኛ የሆነውና ከባህር ጠለል በላይ 4ሺህ 377 ሜትር ከፍታ ያለው የቱሉ ዲምቱ ተራራ መገኛም ነው፡፡ የሳነቴ አምባ ከመልክዓ ምድሩ አቀማመጥ ባሻገር የዝናብ ውኃን የመሰብሰብና የማጥራት አቅም ያለው ድንቅ መልክዓ ምድር ነው። በተለይ በአካባቢው የሚገኙ የባሌ ፍልፈሎች ከጠላቶቻቸው ለማምለጥ ሲሉ የሚሰሯቸው እልፍ ጉድጓዶች ውኃው ወደ ከርሰ ምድር እንዲሰርግ ከፍተኛውን ሚና ይወጣሉ። ይህም ከ40 የሚበልጡ ጅረቶች ከፓርኩ እንዲፈልቁ ምክንያት ሆኗል። ጅረቶቹ አቅማቸውን በማሰባሰብ እንደ ዋቤ ሸበሌ፣ ገናሌ፣ ዌልመልና ዱማል የመሳሰሉ ትላልቅ ወንዞችም መነሻ ቦታ ነው፡፡ ከዚህ የተነሳ ሳነቴ የ'ውኃ ጋን' የሚል ስያሜንም እንዲያገኝ ምክንያት ሆኗል። ከሳነቴ አምባ የሚፈልቁት እነዚህ ድንበር ተሻጋሪ ወንዞች በዞኑ የደሎ መናና ሀረና ወረዳ ለሚገኙ የአርብቶ አደር ማህበረሰብ የዘመናዊ መስኖ ልማት ምንጭ እየሆኑም መጥተዋል። በተለይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) የግንባታ ሥራውን ከሶስት ዓመት በፊት ያስጀመሩትና ተጠናቆ ለአገልግሎት ሲበቃ ከ11 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ የማልማት አቅም ያለው የዌልመል ዘመናዊ የመስኖ ልማት ፕሮጄክት አንዱ ማሳያ ነው። ኢትዮጵያን ጨምሮ በኬንያና ሶማሊያ የሚኖረው ከ30 ሚሊዮን በላይ ህዝብ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ህልውው ከዚህ አካባቢ በሚፈልቁ ተፋሰሶች ላይ የተመሰረተ መሆኑን በብሔራዊ ፓርኩ የዱር እንስሳት ክትትልና የምርምር ቡድን መሪ አቶ ሴና ገሼ ያስረዳሉ። ⦁ "የሀረና የተፈጥሮ ደን ሀብት" የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በሀገራችን በጥቅጥቅ ደን ሽፋኑ ከያዮ ደን ቀጥሎ የሁለተኛነትን ስፍራ የያዘው የሀረና የተፈጥሮ ደን ሀብት መገኛም ነው፡፡ ደኑ የፓርኩን 1ሺህ ካሬ ኪሎ ሜትር ገደማ ይሸፍናል፡፡ ከሀገራችን አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ለካርቦን ንግድ ታጭተው ህብረተሰቡ ከዘርፉ ተጠቃሚ እንዲሆን እያገዙ ከሚገኙ የሀገራችን ድንቅ ደኖች ውስጥም አንዱ ሆኗል። የሀረና የተፈጥሮ ደንን በአሳታፊ የደን ልማት አስተዳደር አርሶ አደሩን በ38 የደን ማህበራት በማደረጃት ባለፉት አራት ዓመታት በተከናወኑ ሥራዎች ከ179 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ከከርቦን ንግድ ሽያጭ መገኘቱን በኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት የባሌ ዞን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የዕቅድ ክትትል የሥራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ቀነዓ ያደታ ይገልጻሉ። የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በውስጡ ባሉት የእጽዋት እና የእንስሳት ብዝሃ ህይወት ሲታይ ከዓለም በ34ኛ፣ ከአፍሪካ ደግሞ በ12ኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በተለይ ፓርኩ በውስጡ ከሚገኘው እጽዋትና የእንስሳት ብዝሃ ህይወት በተጓዳኝ ለአዕዋፍ ዝርያ ካለው ምቹ ሁኔታ የተነሳ “Bird Site International” የተሰኘ ዓለም አቀፍ ድርጅት "በዓለም ከሚገኙ ምቹ የአዕዋፍ መገኛዎች አንዱ ስለመሆኑም አብነቱን ይሰጣል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ከላይ የተጠቀሱ እውናታዎችን ጨምሮ ሌሎች የፓርኩ እምቅ አቅሞችን ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት እ.ኤ.አ. በ2009 በጊዜያዊ መዝገቡ ላይ ማስፈሩም ይታወሳል። መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ በርካታ ባለድርሻ አካላት ባለፉት ዓመታት ቅርሱ በቋሚነት በዩኔስኮ እንዲመዘገብ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ መቆየታቸውን የፓርኩ ኃላፊ አቶ ሻሚል ከድር ያስታውሳሉ። በተለይ ፓርኩ በድርጅቱ በቋሚ የቅርስ መዝገብ ላይ እንዳይሰፍር ማነቆ ሆነው ከቆዩት መካከል ልቅ ግጦሽ፣ የሰደድ እሳት፣ ህገ ወጥ ሰፈራ ሲሆኑ፤ ችግሮቹ አሁንም ያልተሻገርናቸውና የሁሉንም ትኩረት የሚሹ ናቸው ይላሉ። በተለይ በፓርኩ አልፎ አልፎ የሚያጋጥመው ሰደድ እሳት የብርቅዬ የዱር እንስሳትን መኖሪያና ምግባቸውን ስለሚያሳጣቸው በቀጣይነት በትኩረት ሊሰራበት እንደሚገባም ያስረዳለሁ። ⦁ "ፓርኩን ለማቆየት የተከፈለ የህይወት መስዋዕትነት" ይህ የብርቅዬዎች አምባ ተጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ በተላይም የባሌ ህዝብ፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አያሌ መስዋዕትነት ከፍለዋል። በተለይ በ2007 ዓ.ም ፓርኩ ላይ ተነስቶ የነበረው የሰደድ እሳት በባሌ ህዝብ ዘንድ የማይረሳ ጠባሳ ጥሎ ማለፉን ነው አቶ ሻሚል ያስታወሱት። በግንዛቤ ማነስ ጭምር ግለሰቦች ለከብቶቻቸው የተሻለ መኖ ለማግኘት በማሰብና ለማር ቆረጣ በፓርኩ ክልል ውስጥ እሳት በመለኮስ ያስነሱትን ቃጠሎ ከሌሎች ጓደኞቹ ጋር ለማጥፋት ጥረት ሲያደርግ ህይወቱን ያጣውን የፓርኩን ሰራተኛና የአካባቢ ተቆርቋሪ ወጣት ቢኒያም አድማሱን በማሳያነት አቅርበዋል፡፡ ወጣቱ የተፈጥሮ ሀብት ጀግና በሚል በፓርኩ ውስጥ የማስታወሻ ሀውልት ቆሞለታል። እንዲሁም በተጠናቀቀው የ2015 ዓ.ም የበጀት ዓመት የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን ባካሄደው ዓመታዊ ግምገማ የተፈጥሮ ሀብት ጀግና ለሆነው ለቢኒያም አድማሱ ቤተሰቦች ዕውቅናና ሽልማት ሰጥቷል። እንዲያም ሆኖ ግን ጠባሳው በብዙ የአካባቢ ተቆርቋሪዎች ዘንድ ሁሌም የሚታወስ ነው፡፡ ይህ በብዝሃ ህይወት ስብጥሩና በአያሌ ጸጋዎች የተንበሸበሸው የብርቅዬዎች አምባ በቅርቡ በሳውዲ አረቢያ ሪያድ ተካሂዶ በነበረው 45ኛው የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የዓለም ቅርስ ጉባኤ ላይ በኢትዮጵያ ሁለተኛው ታላቅ የተፈጥሮ ቅርስና በዓለም ደግሞ 11ኛው ቅርስ በመሆን በቋሚነት መመዝገቡ ሁሉንም የአገሪቱን ዜጎች አስደስቷል። ፓርኩ በዓለም ቅርስነት መመዝገቡ ለቅርሱ የሚደረግለትን ጥበቃ ለማጠናከርና መስህብነቱን ለመጨመር እድል እንደሚፈጥር የዞኑ ባህልና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ሮብዳ ጃርሶ ይገልጻሉ። እንዲሁም ፓርኩ በዩኔስኮ እውቅና ማግኘቱ የቱሪስት ፍሰቱን በማሻሻል ከቱሪዝም የሚገኘውን ዓመታዊ ገቢ በማሳደግ ሀገርና ሕዝብ ከዘርፉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዕድል የሚፈጥር ነው ይላሉ። ቅርሱን በዩኔስኮ ማስመዝገብ ብቻውን ግብ አይደለም ያሉት ወይዘሮ ሮብዳ ህብረተሰቡ ተንከባክቦ ለዛሬ ያቆየውን ቅርስ በዘላቂነት መጠበቁ ላይ እንዲበረታም አሳስበዋል። በፓርኩ ላይ የሚደርሰውን ሰው ሰራሽ ጫና ሊቀነሱ የሚያስችሉ ፕሮጀክቶችን በመቅረፅ ገቢራዊ እያደረጉ ከሚገኙ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት መካከል የፍራንክፈርት ዞሎጂካል ሶሳይቲ ድርጅት የባሌ ዞን ቅርንጫፍ አስተባባሪ አቶ አብዱርቃድር ኢብራሂም የፓርኩ የጥበቃ ሥራ የአካባቢውን ማህበረሰብ ያሳተፈ መሆን እንዳለበት ይናገራሉ። በተለይ በፓርኩ አጎራባች የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በፓርኩ ላይ እያደረሱሷቸው ያሉ ጫናዎችን ለመቀነስ ህይወታቸውን የሚመሩበት ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ተጽዕኖውን መቀነስ እንደሚቻል ያምናሉ። ፓርኩን በዩኔስኮ ቋሚ መዝገብ ላይ ለማስፈር የተደረገው የተቀናጀ ጥረት እንዳለ ሆኖ ይሄው ገጽታውና ክብሩ ተጠብቆ እንዲቆይ ከፍተኛ ጥረትና ቁርጠኝነትን እንደሚጠይቅም በአጽኖኦት ያስረዳሉ። ከአካባቢው ነዋሪዎች መካከል ወይዘሮ ነፊሳ መሐመድ እንዳሉት ፓርኩን ለመጎብኘት ለሚመጡ የሀገር ውስጥና የውጭ አገር ጎብኝዎች የዕደ ጥበብ ቁሳቁሶችን በመሸጥ በሚያገኙት ገቢ ህይወታቸውን እየመሩ ናቸው። እንደሳቸው እምነት በአሁኑ ወቅት ፓርኩ በቋሚነት በዓለም ቅርስነት በመመዝገቡ ለቅርሱ የሚያደርጉትን ጥበቃ ይበልጥ እንዲያጠናክሩ መነሳሳትን የሚፈጥር ነው። የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ መምህርና በአካባቢ ሳይንስ ላይ ምርምር የሚያደርጉት አቶ አልይ መሐመድ እንዳሉት በፓርኩ አካባቢ የሚኖሩ የማህበረሰብ ክፍሎች ከፓርኩ በሚፈለገው ደረጃ ተጠቃሚ ቢሆኑ የጥበቃውን ሥራ በእጅጉ ያቃልላል የሚል እምነት አላቸው። ይህ ደግሞ የባለቤትነት ስሜትን በሚፈለገው ደረጃ እንዲያዳብሩ የሚያደርግም ነው። በመሆኑም በፓርኩ ላይ እየደረሰ የሚገኘውን ጫና ለመቀነስ የአካባቢውን ማህበረሰብ ከብሔራዊ ፓርኩ በኢኮ-ቱሪዝምና ተያያዥ ጉዳዮች ተጠቃሚ በማድረግ የባለቤትነት አስተሳሰብን ማጎልበት እንደሚያስፈልግም ያስረዳሉ። በተለይ ለማህበረሰቡ አማራጭ የግጦሽና የሰፈራ ቦታ፣ የማገዶ፣ የኃይል አቅርቦትና ሌሎች አማራጮች በቀጣይ እንዲቀርቡለት የማድረግ ስራ ቢሰራ በፓርኩ ላይ የሚደርሰውን ጫና ትርጉም ባለው መልኩ መቀነስ እንደሚቻልም ይመክራሉ። ከሀገር አልፎ የዓለም ቅርስ የሆነውን የብርቅዬዎች አምባ የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በዩኔስኮ ቋሚ መዝገብ ውስጥ ለማቆየት የሚያግዙ ሥራዎችን ከወዲሁ አቅደው እየሰሩ መሆኑን የፓርኩ ኃላፊ አቶ ሻሚል ያስረዳሉ። ብሔራዊ ፓርኩን በሚያዋስኑ ወረዳዎች የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ስለብዝሃ ህይወት ጥቅምና ተጓዳኝ ጉዳዮች በቂ ግንዛቤ አግኝተው በጥበቃው የድርሻቸውን እንዲወጡ ተከታታይነት ያለው የግንዛቤ ማዳበሪያ ሥራዎች እየተከወኑ መሆናቸውንም ገልጸዋል። የዓለም ቅርስ የሆነው የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ብዝሃ ህይወትን በዘላቂነት መንከባከብና መጠበቅ የሚያስችሉ ሀገር በቀልና ዘመናዊ አሰራሮችን ተግባራዊ በማድረግ ፓርኩን በድርጅቱ ቋሚ መዝገብ ውስጥ ከማቆየት ባለፈ ከዘርፉ የሚገኘውን ዘላቂ ጥቅም ለማረጋገጥ ሁሉም የድርሻውን በቁርጠኝነትና በፅናት ሊወጣ ይገባል።
ትንታኔዎች
ከገበታ ወደ ገበያ
Sep 24, 2023 663
(ሰለሞን ተሰራ) ኢትዮጵያ ከ10 ሺ ዓመታት በፊት ከኒዮሊቲክ አብዮት ዘመን ጀምሮ የበርካታ አዝእርትና እንስሳት ሀብት መፍለቂያ ሆና ዛሬ ላይ ደርሳለች። ከዚያ ዘመን ጀምሮ የአገራችን ገበሬ በስራ ያካበተውንና በተፈጥሮ የተሰጠውን ችሎታ በመጠቀም ዘመናዊና ቴክኖሎጂ በወለዳቸው መሳሪያዎች ሳይታገዝ፣ በየጊዜው የአፈሩ ለምነት እየቀነሰ ከሄደው መሬትና ባህላዊ የአስተራረስ ዘዴ ጋር እየታገለ ቁጥሩ እየናረ የሚሄደውን ህብረተሰብ ከመመገብ ወደ ኋላ ብሎ አያውቅም። ግብርናው ከቀደሙት ጊዜያት በተለየ ሁኔታ ትኩረት ባገኘበት በዚህ ዘመንም ከተደቀኑበት እጅ ጠምዛዥ ጉዳዮች ጋር ግብግብ ውስጥ ነው። የአየር ንብረት ለውጥ፣ ድርቅ፣ የፖለቲካና የገበያ አለመረጋጋት፣ የዕውቀትና የቴክኖሎጂ ውስንነት፣ የተፈጥሮ አደጋ፣ የዘርፉ ኢንቨስትመንት አለመዳበር የዘርፉ ተግዳሮት ሆነው ቀጥለዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን በ78ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ባደረጉት ንግግር በተለይ የአየር ንብረት ለውጥን ተጽእኖ በሚገባ አመላክተዋል። የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ በተለይ በአፍሪካና በሌሎች በማደግ ላይ ያሉ አገራት ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ቀውስ ሁሉን አቀፍ መፍትሄ እንዲበጅ እየሰራች መሆኗን ተናግረዋል። በተለይ ኢትዮጵያዊያን ከጫፍ ጫፍ እየተሳተፉበት ያለው የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር የዚህ ቁርጠኝነት ማሳያ መሆኑን አንስተዋል። በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ ላለፉት ተከታታይ አራት ዓመታት በሰራችው ስራ በአካባቢ ጥበቃና በግብርናው ዘርፍም ውጤት ማግኘቷ እሙን ነው። ነገር ግን ፈተናዎቹን በድል ለመሻገር የሚደረጉ ጥረቶችና በዘርፉ የተገኙ አበረታች ውጤቶች እንደተጠበቁ ሆነው አሁንም ዘርፉን በሰለጠነ የሰው ሃይል፣ በተደራጀ የግብርና መሳሪያና ማቀነባበሪያ በመደገፍ አገርና ህዝብ ከግብርናው ዘርፍ ማግኘት ያለባቸውን ጥቅም እንዲያገኙ ለማስቻል ብዙ መስራት ይጠይቃል። በተለይ የግብርና ሜካናይዜሽንን ከማስፋፋትና ዘመናዊ የግብርና ግብዓቶችን በበቂ ሁኔታ ከማቅረብ አኳያ መንግስት እየሰጠ ያለው ትኩረት የበለጠ መጠናከርና ማደግ ይኖርበታል። የግብርናና የገጠር ልማት የፋይናንስና ብድር አቅርቦትን ማጠናከር እንዲሁም የአካባቢና ስነ ምህዳር ጥበቃ ስራዎችን በዘላቂነት መተግበር ያሻል። በተለይ ኢትዮጵያ በልዩ ትኩረት እየሰራችበት ያለውን የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ ጉዳይ ከዚህ ቀደም የነበረውን የግብርና አሰራር በመቀየርና አማራጮችን በማማተር እውን ማድረግ ይጠይቃል። ኢትዮጵያ በዝናብ ወይም በመስኖ መልማት የሚችል ያልተነካ ሰፊ መሬት እንዳላት የሚታወቅ ሲሆን ይህን ያልታረሰ መሬት በአግባቡ በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ አንዱ አማራጭ ነው። መረጃዎች እንደሚያሳዩት ግብርናው ከ34 በመቶ በላይ የጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት ድርሻ ይዟል፡፡ በተጨማሪም ዘርፉ 79 በመቶ የሚሆኑ ዜጎች መተዳደሪያ ሲሆን በተመሳሳይ 79 በመቶ የሚሆነውን የውጭ ንግድ ገቢ በመሸፈንና ለአገር ውስጥ ኢንቨስትመንትና ገበያ የጥሬ እቃ አቅራቢ በመሆንም ይታወቃል። መንግስት በግብርናው ዘርፍ የወሰዳቸው የሪፎርም ስራዎችና ግብርናን ከአረንጓዴ አሻራ ጋር በማስተሳሰር የሰራቸው ስራዎች ፍሬ ማፍራት ጀምረዋል። በተለይ የስንዴ ምርታማነትን በማሳደግ ከራስ ፍጆታ አልፎ ለውጭ ገበያ ለማቅረብ የተሰራው ስራ ቀዳሚ ተጠቃሽ ነው። ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት ብቻ የስንዴ ምርታማነቷን በ27 በመቶ ማሳደግ መቻሏ ስንዴ ከመሸመት ወደ መላክ የመሸጋገሯ ማረጋገጫ ሆኗል። በጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ አህመድ የተጀመረው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ በዚህ ረገድ የሚታይ ለውጥ እያሳየ ሲሆን በተሰራው ውጤታማ ስራ ባለፈው በጀት ዓመት ኢትዮጵያ ከውጭ ስንዴ አላስገባችም። በዚህም 1 ቢሊዮን ዶላር ማዳን መቻሏን የግብርና ሚኒስትሩ ዶክተር ግርማ አመንቴ በቅርቡ ማሳወቃቸው ይታወሳል። ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት 15 ነጥብ 4 ሚሊዮን ቶን ስንዴ ያመረተች ሲሆን በተያዘው ዓመት ደግሞ ምርቱን ወደ 19 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቶን ለማሳደግ እቅድ ተይዞ እየተሰራ ይገኛል። ይህንኑ ግብ ለማሳካት ደግሞ የስንዴ ማሳዋን በማሳደግ 5 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በስንዴ ሰብል ለመሸፈን እየሰራች ነው። ከዚህ ውስጥ በመስኖ የሚለማ ስንዴን በ2 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ላይ በመዝራት በመስኖ የሚለማውን ስንዴ በ54 በመቶ ለማሳደግ እየሰራች ነው። ይህ ደግሞ በቀጣይ ከሀገር ውስጥ ፍጆታ ባለፈ ምርቱን ለውጭ ገበያ ለማቅረብ እንደሚያስችል ዶክተር ግርማ አመንቴ ተናግረዋል። የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ያወጣው ሪፖርት እንደሚያመላክተው የግብርናው ዘርፍ በአስር ዓመቱ የልማት ዕቅድ የመጀመሪያዎቹ 3 ዓመታት (2013-2015) በዋና ዋና ተግባራት ከዕቅድ በላይ ዕድገት አስመዝግቧል። በዚህም ዘርፉ በ2013 ከነበረበት 5 ነጥብ 1 በመቶ በ2014 ወደ 5 ነጥብ 8 በመቶ ያደገ ሲሆን በ2015 ደግሞ 6 ነጥብ 3 በመቶ እድገት አስመዝግቧል። ግብርናውን ለማሳደግ ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዘው የሰብል ምርት ሲሆን ለዘርፉ ማደግ 65 ነጥብ 5 በመቶ አስተዋጽኦ አበርክቷል። ደን ልማት 8 ነጥብ 6 በመቶ እንዲሁም የእንሰሳት ሃብት ልማቱ 25 ነጥብ 9 በመቶ ድርሻ ይዘዋል። በ2015 ዓ.ም ጠቅላላ 627 ሚሊዮን ኩንታል ሰብል ለማምረት ታቅዶ ከተቀመጠው ግብ በላቀ ደረጃ 639 ሚሊየን ኩንታል ምርት ማግኘት ተችሏል። ከበጋ ስንዴ ልማት ጎን ለጎን በቅርብ ጊዜ የተጀመሩ የቡና፣ አቮካዶና አኩሪ አተር የመሳሳሉት ትላልቅ የግብርና ልማት ስራዎች በተመሳሳይ ውጤት ታይቶባቸዋል። የአዝርት፣ የአትክልት፣ ፍራፍሬና ስራስር ምርት ከፍተኛ የዕድገት ሽግግር የታየባቸው ናቸው። በአረንጓዴ አሻራ፣ በሌማት ትሩፋትና በከተማ ግብርና ተሞክሮ ሊወሰድበት የሚችል አፈጻጸም መመዝገቡ በሪፖርቱ ተመላክቷል። ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋትን የስንዴ ምርት ከውጭ ገበያ ስትገዛ የኖረች ሲሆን በተለይም በተለያዩ ጊዜያት የሚፈጠሩ ዓለም አቀፍ ተግዳሮቶች አቅርቦቱን ሲያስተጓጉሉት ቆይተዋል። አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ የስንዴና የገብስ ምርትን በሀገር ውስጥ ምርት መተካት የቻለች ሲሆን የሩዝ ፍላጎቷን ደግሞ 50 በመቶ መሸፈን ችላለች። በስንዴ ምርታማነት የተገኘውን ተሞክሮ ወደሌሎች ሰብሎች በማስፋት የገቢ ምርቶችን በቀጣይ ለመተካት በትኩረት እየተሰራበት ይገኛል። ይህንን ለማሳካት መንግሥት ለዘርፉ የሰጠው ትኩረት የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ እንደሚሆን ይታመናል። በተለይ ለግብርና ዘርፉ የተሻለ በጀት መመደቡ፣ እስካሁን ለመጣውና ለወደፊትም ይመጣሉ ተብለው ለሚታሰቡ ለውጦች ትልቅ ምክንያት ነው። ለምሳሌ የ2015 ዓ.ም. በአገሪቱ ለተለያዩ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ልማት ከተመደበው 786 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በጀት ውስጥ፣ ለግብርናው ዘርፍ 34 በመቶ የሚሆን በጀት ተመድቧል። ይህ ደግም ከለውጡ በፊት ከአሥር በመቶ ያልበለጠ በጀት ጋር ሲነፃፀር እጅግ ከፍተኛ ያደርገዋል። በተጨማሪም መንግሥት ለኩታ ገጠምና ለመስኖ እርሻ ከፍተኛ ትኩረት መስጠቱ፣ ሙሉ በሙሉ በዝናብ ላይ ጥገኛ የሆነውን የግብርና ስራ በመስኖ የታገዘ እንዲሆንና አርሶ/አርብቶ አደሩ በዓመት ከአንድ ጊዜ በላይ እንዲያመርት ማድረጉ ውጤቱን ጉልህ አድርጎታል። እንደ ስንዴ፣ በቆሎ፣ ሩዝ፣ ቡና፣ አቦካዶ ሁሉ በግብርና ሚኒስቴር ከተያዙና በልዩ ትኩረት ከሚከናወኑ ዕቅዶች አንዱ የማር ምርትን ማሳደግ ሲሆን፣ በአሥር ዓመቱ የልማት ዕቅድ ውስጥ እንደተመላከተውም የማር ምርትን በማዘመን ምርቱን ለማሳደግ በስፋት ይሰራል። በኢትዮጵያ ለማር ምርት ተስማሚ የሆነ አግሮ ኢኮሎጂና ብዛት ያላቸው ዕፅዋት መኖራቸው የሚመረተው ማር የተፈጥሮ ጥራት እንዲኖረው ያግዛል። ይህንኑ ዕምቅ ሀብት ትኩረት ሰጥቶ ማልማት ከተቻለ ከ500 ሺሕ ቶን በላይ ማርና ከ50 ሺሕ ቶን በላይ ሰም ማምረት እንደሚቻል ባለሙያዎች ያስረዳሉ። የኢትዮጵያ እንስሳት ሀብት ኢንስቲትዩት ባወጣው መረጃ በሀገሪቱ አለ ተብሎ ከሚገመተው ሰባት ሚሊዮን የንብ መንጋ ውስጥ 90 በመቶው በባህላዊ ቀፎ ውስጥ የሚገኝ ነው። የንብ መንጋዎቹ በባህላዊ ቀፎ ከመኖራቸው በተጨማሪ በጫካ መገኘታቸው ሃብቱ ለአገር ዕድገት በሚፈለገው ልክ እንዳይውል አድርጎታል። ያም ቢሆን ባለፈው ዓመት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የተጀመረው “የሌማት ትሩፋት” ለማር ምርት ትኩረት የሰጠ በመሆኑ ዘመናዊ የንብ ማነብ ዘዴ እንዲስፋፋ ተደርጓል። በዚህም የማር ምርታማነትን በዓመት ወደ 98 ሺህ ቶን ማሳደግ መቻሉ በቅርቡ መገለጹ ይታወሳል። ምርቱን በእጥፍ ለማሳደግ እቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑም እንዲሁ። ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የማር ምርት የማምረት አቅም ካላቸው አሥር ሀገሮች አንዷ በመሆኗ ሃብቱን ለማልማት ሁሉም ሊረባረብ ይገባል። በአጠቃላይ መንግሥት ለአረንጓዴ ልማት/አሻራ፣ ለአፈርና አካባቢ ጥበቃ የሰጠው ትኩረት ሁሉን አቀፍ የግብርና ዕድገት እንዲመጣ መሠረት ሆኗል። በተጨማሪም መንግስት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሌማት ትሩፋትና ምግባችን ከደጃችን መርሐ ግብር ኅብረተሰቡ የከተማ ግብርናን እንዲያስፋፉ በገጠርም ሆነ በከተማ ያከናወነው ተግባር ውጤት አስመዝግቧል። በአጠቃላይ ባለፉት አምስት ዓመታት ዘርፉን ለማዘመን የተከናወኑ የልማትና የሪፎረም ሥራዎች ግብርናውን ከአዝጋሚ ጉዞ በማውጣት ወደ ፈጣንና አስተማማኝ ጉዞ ማሸጋገር ችለዋል። ኢትዮጵያ አሁንም አያሌ ያልተነኩ ዕምቅ ሀብቶች ያሏት መሆኗን እንደ እድል በመውሰድ ቀጣይነት ያለው እድገት ማስመዝገብ ይጠበቅባታል። ይህን ማድረግ ስትችል የግብርና ሽግግር ይረጋገጣል። ግብርናውን ለማሻገር ደግሞ በፋይናንስ፣ በግብአት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በሰለጠነ የሰው ሀይል ልማት ላይ በትኩረት መስራት ያሻል። ወጣቱ ግብርናን እንደ ንግድ (Agri-Bussiness) ማየትና በዚያው ልክ መስራት ይጠበቅበታል። በዚህ ልክ በርብርብ ሲሰራ ግብርናን በማሸጋገር ገበታን ከመሙላት ወይም ከፍጆታ አልፎ ገበያን ማማተር ይቻላል።
ኢትዮጵያ እና መስከረም
Sep 22, 2023 661
(በአየለ ያረጋል) መቼስ ሀገሬው መስከረምን ሲናፍቅ ‘ለብቻ’ ነው። በባህሉ፣ በትውፊቱ፣ በስለ-ምኑ፣ በኪነ-ቃሉ እና ስነ-ቃሉ ልዩ ሥፍራ ይሰጠዋል ለመስከረም። እንደ መስከረም ክብር፣ ሞገስ እና ፀጋ የተቸረው የትኛው ወር ይሆን? ማንም! ሀገሬው ለቆንጆ ልጁ ስም ሲያወጣ ‘መስከረም’ እንጂ በሌላ ወር ሰይሞ ያውቃል? አያውቅም። በኢትዮጵያ ምድር መስከረም ለሰው ልጅ ብቻ ሳይሆን ለእንስሳት እና አዕዋፋት ራሱ ልዩ ጊዜ ነው። ‘ኢትዮጵያ ነይ በመስከረም…’ እንዲሉ መስከረም ለኢትዮጵያ ውበቷ፣ ቀለሟ፣ ትዕምርቷ፣ የባህር ሃሳቧ መባቻ ነው። ተናፋቂው መስከረም ዝም ብሎ ወር ብቻ አይመስልም። እውቁ ሠዓሊ እና ባለቅኔ ገብረክርስቶስ ደስታ መስከረምን “… በሽቱ መዓዛህ ለውጠው ዓመቱን፤ ይታደስ ያረጀው ፍጥረት ሌላ ይሁን…” ሲል የአዲስ ተስፋና መንፈስ መሻቱን አሳይቷል። ተወዳጇ ድምፃዊት እጅጋየሁ ሽባባው ደግሞ “… መስከረም ለምለሙ፣ መስከረም ለምለሙ፣ ብሩህ ዕንቁጣጣሽ ደስታ ለዓለሙ…” ትለዋለች መስከረምን ስታዜመው። እንደየ ንፍቀ ክበቡ ዓመታት በወራት ሲመነዘሩ የራሳቸው መልክና መገለጫ አላቸው። ኢትዮጵያም ከጎርጎሮሳዊያኑ የዘመን ቀመር በሰባት ዓመት ከስምንት ወራት ልዩነት ያለው የራሷ የዘመን ቀመር አላት። ኢትዮጵያ ብቸኛዋ ባለ 13 ወራት ሀገር ነች። ወራቱም መጸው(መኸር)፣ ሐጋይ(በጋ)፣ ፀደይ(በልግ) እና ክረምት በሚል በአራት ወቅቶች ይከፈላሉ። ወቅቶቹም የራሳቸው ጸባይ፣ ክዋኔ፣ ትውስታና ትዕምርት ይቸራቸዋል። እያንዳንዱ ወርም እንደዚሁ። ከዘመን መባቻው መስከረም እስከ ማዕዶተ-ዘመኗ ጳጉሜን ወራቱ በሰማይና በምድሩ ተፈጥሯዊ፣ ባህላዊና መንፈሳዊ ውቅራቸው ግላዊ ገጽታ ይነበብባቸዋል። የወራቱ ቅላሜ እና ሕብርነት ልዩ መልክዓ-ኢትዮጵያን ይፈጥራል። ‘የ13 ወር ፀጋ’ የሚለው መጠሪያም በ‘ምድረ ቀድምት’ እስኪተካ ድረስ ለብዙ አሥርት ዓመታት መለያ ሆኖ ዘልቋል። ይህን መለያ ስም ያወጡት እና የኢትዮጵያ ቱሪዝም አባት የሚሰኙት አቶ ኃብተሥላሴ ታፈሠ “ኢትዮጵያ የ13 ወራት ፀሐይ ባለቤት ናት። ስያሜው ከምንም የፖለቲካና ሃይማኖት ጋር ንክኪ የለውም” ብለው ነበር። የኢትዮጵያ ወራት ስያሜ ከመልክና ግብራቸው ይመነጫል። የወራት መባቻው መስከረም እንደዛው። ሊቃውንት መስከረምን ሲፈትቱት መስ - 'ዐለፈ፤ ከረመ' ይሉትና “ክረምቱን ማስከረሚያ፤ የጥቢ መባቻ" ወርኅ ሲሉ ያመሰጥሩታል። መስከረም ዘመን ያስረጃል፤ አዲስ ሕይወትና ተስፋ ደግሞ ይደግሳል። አንዳንዴም ይህ ወር ዘመን መለወጫ፣ ዕንቁጣጣሽ፣ ቅዱስ ዮሐንስ ተብሎም ይጠራል፡፡ 'አገር፣ ቀለም፣ ዘመን' እንደሸማው በድርና ማግነት ከሚሰባረቅባቸው ወራት አንዱ መስከረም ነው። መስከረም አገርኛ አለባበስ፣ አገርኛ ዝማሬ፣ አገርኛ ጨዋታ፣ አገርኛ ትውፊትና ቀለም በመስከረም በዓላት በተግባር ይታያል። መስከረም ሁለንተናዊ ውበቱ ድንቅ ነው፤ ትዕምርቱም ጉልህ ነው። የመልክዓ-መስከረም ድምቀት ማሳያዎች ዘመን መለወጫ በኢትዮጵያ ዘመን ስሌት ቀለበት መስከረም 1 ቀን ዘመን ይለወጣልና። የዘመን መለወጫ በዓል ‘ርዕሰ ዓውደ- ዓመት’ ይሰኛል። የባህር ሐሳብ ሊቃውንት መስከረም ለምን የዘመን መለወጫ እንደሆነ ሲያትቱ “ብርሃናት /ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት/ የዓመት ዑደታቸውን በጳጉሜ ወር ጨርሰው በመስከረም ወር ስለሚጀምሩ ነው” ይላሉ። በመስከረም ሌሊቱ ከቀኑ እኩል ነው። ደራሲ ካሕሳይ ገብረእግዚአብሔር “ቀዳማይ፣ ርዕሰ ክራሞት፣ መቅድመ አውርኅ፣ ርዕሰ ዐውደ-ዓመት፣ የክረምት ጫፍ መካተቻ፣ የመፀው መባቻ” ይሉታል ወርኃ መስከረምን። እናም ዘመነ ማዕዶቷን፤ ወርኅ ተውሳኳን ‘ጳጉሜን’ ተሻግሮ መስከረምን መሳም ይጓ'ጓ'ል። የመስከረም ጥባት በአያሌው ይሻታል። 'መስከረም ሲጠባ ወደ አገሬ ልግባ …’ እንዲሉ የተሰደዱት በአዲስ ዓመት መባቻ የአገራቸውን አፈር ለመሳም ያማትራሉ። ’አበባዬ ሆይ፤ አበባዬ ሆይ’ የሚሉ ሕፃናት ተስፋና ምኞታቸውን በወረቀት ያቀልማሉ፤ የአበባ ስዕላት ይዘው በየደጃፉ ይሯሯጣሉ፤ የ’ዕደጉ’ ምርቃት ያገኛሉ፤ በደስታ ይንቦጫረቃሉ። በዚህ ድባብ ነው እንግዲህ መስከረምን የግዑዛንም የሕይወታውያንም የነፃነት፣ የተስፋና የፍቅር ወርኅ ተደርጎ የሚናፈቀው። የብዙ ሺህ ዘመናት ባለታሪኳ ኢትዮጵያ ተፈጥሯዊ አዱኛ ሳይርቃት በእርስ በርስ ጦርነት፣ በጠላት ፍላፃዎች እና በድንቁርና ብዛት... ሰንኮፎቿ ሳይነቀሉ በመልከ-ብዙ ምስቅልቅሎሽ ውስጥ ዛሬ ደርሳለች። ጊዜው የኢትዮጵያን መስከረም ያስናፍቃል። ዕንቁጣጣሽ መስከረም በአደይ አበባ የሚያሸበርቅ ወር ነው። የነገረ-ዕንቁጣጣሽ የትመጣ መልከ-ብዙ አተያዮች ይጠቀሳሉ። ለምሳሌ “ዕንቁ – ዕፅ አመጣሽ” ብሎ የአበባ መፈንዳት ለማመላከት እንደሆነ የሚጠቅሱ አሉ። ንግሥት ሳባ /አዜብ/ ወደ ንጉሥ ሰሎሞን የእጅ መንሻ ይዛ ስትሄድ ንጉሡም “ዕንቁ ለጣትሽ ጌጥ ይሁንሽ” በሚል ቀንና ከሌሊት የሚያበራ ቀለበት ስለሰጣት ነው የሚል አፈታሪክም ይነገራል። የስያሜው መነሻ ያም ሆነ ይህ መስከረም ለመልክዓ-ምድሩ፣ ለሰውና ለእንስሳት ሁሉ ‘ፍስሐ ወተድላ’ የሆነ ወር ነው። በመስከረም ምድር በዕንቁጣጣሽ ትፈካለች፤ በአበቦች ታጌጣለች፤ ውኆች ይጠራሉ። ሰማዩም የክብረ-ሰማይ ብርሃኑን ያጎላል። ጥቁር ደመና ጋቢ ይገፈፋል፤ ክዋክብት እንደፈንዲሻ በዲበ-ሰማይ ይደምቃሉ። ዕጽዋትና አዝዕርት እንቡጦች ይፈነዳሉ። የመብረቅ ነጎድጓድ ተወግዶ የሰላምና የሲሳይ ዝናብ ይዘንባል። እንስሳት የጠራ ውሃ እየጠጡ፣ ለምለም ሳር እየነቸረፉ ይቦርቃሉ። እርሻ የከረሙ በሬዎች፣ ጭነት የከረሙ አህዮች መስከረም አንጻራዊ የእፎይታ ወራቸው ነው። ነጎድጓድ በአዕዋፋት ዝማሬ ይተካል። ንቦች አበባ ይቀስማሉ፤ ቀፏቸውን ያደራሉ። ቢራቢሮ ሳትቀር ‘በመስከረም ብራ ከኔ በላይ ላሳር..’ ብላ ትከንፋለች። በ’ዕንቁጣጣሽ’ ምድር ብቻ አይደለችም የምትዋበው። መስከረም ለሰው ልጆችም በተለይም ለወጣቶች የፍቅር፣ የእሸት እና የአበባ ወር ነው። የሰላም፣ የንጹህ አየር፣ የጤና ድባብ ያረብባል። የጋመ በቆሎ እሸት ጥብስ፤ ቅቤ ልውስ፤ ቅቤ በረካ ይናፈቃል። የተጠፋፋ ዘመድ አዝማድ ይገናኛል። ‘ሰኔ መጣና ነጣጠለን’ ብለው ወርኃ ሰኔን የረገሙ ተማሪዎች ተናፋቂያቸውን ያገኛሉና ‘መስከረም ለምለም’ ብለው ያሞካሹታል። የገበሬው የሰብል ቡቃያ ያብባል፤ እሸት ያሽታል። ጉዝጓዝ ሣር፣ ትኩስ ቡና ይሽታል። ደመራ ወመስቀል ሊቃውንት የደመራን የትመጣን ሲፈትቱ ‘ደመረ፣ ተሰባሰበ’ ይሉታል። ጎረቤት፣ የሩቅ የቅርብ ዘመድ አዝማድ ተደምሮ የሚከውነው ነውና። ነገረ መስቀሉ እምነቱ፣ ባህሉ፣ ትውፊቱ ብዙ ነው። መስቀል በሃይማኖተ-አበው ሀተታ ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ለማዳን፣ ለፍጡር የሰው ልጆች ያለውን ጥልቅ ፍቅር የገለጸበት ዓርማ ነው። በዚህም መስቀልን አማኝ ምዕመናን እና ካህናት የደኅንነትና የእምነት ምልክታቸው፤ የርኩስ መንፈስ ማባረሪያ መሳሪያቸው አድርገው ይመለከቱታል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መስከረም 10 ቀን ‘ተቀጸል ጽጌ’ በሚል የክርስቶት መስቀል ግማድ (ቀኝ እጁ ያረፈበት ክፋይ) ከኢየሩሳሌም ተነስቶ ኢትዮጵያ የገባበትን ቀን ታከብረዋለች፤ መስከረም 17 ቀን ደግሞ መስቀሉ የተገኘበትን። መስከረም 16 እና 17 ቀን የሚከበረው የደመራ መስቀል በዓል ከሃይማኖታዊ አስተምህሮው ባለፈ ባህላዊ ትውፊትነቱ የጎላ በመሆኑ በአብዛኛው ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ይናፈቃል። ደመራና መስቀል የአንድነት፣ የፍቅር፣ የይቅርታ፣ አብሮነት፣ የምስጋና፣ የተስፋ… እሴቶች የሚገለጹበት ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ ክብረ-በዓል ነው። ደመራ እና መስቀል በዓላት ሃይማኖታዊ የአደባባይ በዓል ቢሆንም እንደየ አካባቢው ባህል፣ መንፈሳዊነት፣ ትውፊት፣ ዕውቀት አገርኛ ህብር ጥበባት የሚጎሉበት፣ አገር የውበት አክሊል የምትደፋበት ዕለት ነው። መስቀል የዓለማችን የማይዳሰስ የኢትዮጵያ ወካይ ቅርስ መዝገብ ሥር ሰፍሯል። በመስቀል አገርኛ ቀለም ይጎላል። 'አገር፣ ቀለም፣ ዘመን' እንደሸማው በድርና ማግነት ይሰባረቃሉ። የባህር ማዶ ጎብኚዎች በአግራሞትና መደነቅ ሲናገሩ ይደመጣሉ። የዕንቁጣጣሽ ተከታይ የመስከረም መልክ ነው መስቀል። የደመራ አደማመር እና ማብራት ሥነ-ሥርዓት በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች ተመሳሳይ እንዳልሆነ ደራሲ ካሕሳይ ገብረእግዚአብሔር ይተርካሉ። በትግራይ፣ በጎንደር፣ በወሎ፣ በዋግኸምራ፣ በአዊና በከፊል ጎጃም ደመራ ማታ ላይ ተደምሮ ንጋት ላይ ይለኮሳል። በከፊል ጎጃም፣ በሸዋ፣ በአዲስ አበባ፣ በጉራጌ፣ በጋሞ፣ በወላይታና ሌሎች የደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች ደግሞ እንደየ አካባቢው ተለምዶ መስከረም 16 ከእኩለ ቀን ጀምሮ እስከ አመሻሽ ድረስ ደመራው ይለኮሳል። መስቀል በአንዳንድ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ርዕሰ ዓውደ-ዓመት ይመስላል። በደቡብ ኢትዮጵያ መስቀል ከሃይማኖታዊ ይዘቱ ባህላዊ ጎኑ ይጎላል። ጉራጌዎች፣ ጋሞዎችና ሌሎችም መስቀልን ከሁሉም በዓላት የበለጠ ይናፍቁታል። የተራራቁ ቤተሰቦች የሚገናኙበት የፍቅር፣ የደስታና የእርቅ በዓል ነው መስቀል። በጋሞ ብሔረሰብ ባህል በዋዜማው ሰው ቢሞት እንኳን በሌሊት ተወስዶ ይቀበራል እንጂ ለቅሶ እንደማይለቀስ ይነገራል፤ ለሰው ብቻ ሳይሆን ለእንስሳቱም ልዩ መኖ እንደሚቀርብላቸው ይነገራል። ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ እንደሚባለው በጋሞዎች ደግሞ ‘ለመስቀል ያልሆነ ዱንጉዛ ይበጣጠስ’ በሚመስል መልኩ የባህል ልብስ አለባበስ እንደሚዘወተር መምህር ካሕሳይ (በሕብረ-ብዕር ድርሰታቸው) ጽፈዋል። መስቀል በጉራጌዎች ዘንድ እንደ አውራው በዓል ይቆጠራል። ለመስቀል ዓመቱን ሙሉ ዝግጅት ይደረጋል። አባወራው ሰንጋ ለመግዛት፣ እማወራ ማጣፈጫውን ለማዘጋጀት፣ ወጣቶች ደመራና ደቦት ለማዘጋጀት፣ ልጆች ምርቃት ለመቀበል የየራሳቸውን ይዘጋጃሉ። ቤተሰብ ወዳጅ ዘመድ የሚጠያየቅበት፣ ለትዳር የደረሱ ሚስት የሚያጩበትና የሚመርጡበት ጥላቻና ቂም በፍቅርና በይቅርታ የሚታደስበት ነው። በጉራጌዎች ዘንድ መስቀል ትልቅ ቦታ ይቸረዋል። መስቀል እንደየአካባቢውና ባህሉ የሚናፈቅበት ዕልፍ ገጽታዎች አሉት። ለምሳሌ እኔ በተወለድኩበት ገጠራማ አካባቢ ያለውን በወፍ በረር እንቃኘው! በደመራ ዋዜማ ቀናት ልጆች ተራራ ለተራራ፣ ወንዝ ለወንዝ፣ ቋጥኝ ለቋጥኝ በልጅነት ወኔና ስስት በመዞር ለደመራ የሚሆን እንጨት፣ አደይ አበባ፣ ደቦት(ችቦ) ያጠራቅማሉ። ልክ መስከረም 16 አመሻሽ ከብቶች ወደ ግርግም ከገቡ የመንደሩ ወጣቶች ወደ ‘አፋፍ’ ይወጣሉ። ደመራ ወደሚደመርባት ሥፍራ። ሁሉም የአንድ ዕድር አባላት ቤተሰብ ተወካዮች ባሉበት እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት የደመራው ሥራ ይጠናቀቃል። ደመራው ሲጠናቀቅ ወደየ ቤታችን እንበታተናለን። (አዲስ አበባን ጨምሮ በከተሞች እንደሚደረገው በመስከረም 16 አመሻሽ ደመራው አይለኮስም። ይልቁኑ መስከረም 16 ለ17 አጥቢያ ጀምሮ ይለኮሳል እንጂ።) ለመስከረም 17 አጥቢያ ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ጀምሮ ሁሉም ሰው ከየቤቱ ደቦቱ (ችቦውን) እየለኮሰ ‘እዮሃ ደመራ’ እያለ ወደ ደመራው ሥፍራ ይተማል። እንደየ ግለሰቡ ቤት እስከ ሦስት ኪሎ ሜትር ድረስ መጓዝ ሊጠይቅ ይችላል። የመስከረም እኩሌታ አረንጓዴያማ ውብ ማሳ ከየቤቱ ከሚወጡ የችቦ እሳት ነበልባል ብርሃን ይታጀባል። ከሌሎች አጎራባች የመንደር ደመራዎች ቀድሞ ለመለኮስ ጉጉቱ የትየለሌ ነው። ከቤት እስከ ደመራው ሥፍራ እስኪደርሱ ድረስ ሰዎችን፣ በረት ያሉ ከብቶቹንና የጓሮ አዝመራውን ጨምሮ ሕይወታዊያንን በሙሉ “እንጎረጎባህ፤ እንጎረጎባችሁ” ይባላል። የተጠያቂው ሰው ምላሽ ደግሞ “ዓመት ዓመቱን ያድርስህ” የሚል ይሆናል። ከደመራ ግጥም ተዘውታሪ ስንኞች መካከልም፡- “እዮሃ አበባዬ፣ መስከረም ጠባዬ፣ እዮሃ አረሬ አረሬ፣ መስቀል ጠባ ዛሬ፣ በሸዋ በትግሬ…” የሚለው ይጠቀሳል። ከደመራው ሥፍራ ስንደርስ የ’እንጎረጎባህ!’ ድምፆች ይበረታሉ። የ’ዓመቱን ያድርስህ’ መልስ ካልሆነም እኩይ አፀፋ ይኖራል። ሁሉም ከተሰባሰበ በኋላ ደመራን የሚያሞካሹና የአዲሱን ዓመት መልካምነት የሚመኙ ‘እዮሃ አበባዬ” ግጥሞች እየተደረደሩ ደመራው ሦስት ጊዜ እንቧለሌ ይዞራል። በዕድሜ ታላቅ እና የተከበረ ሰው በቅድሚያ ደመራውን ይለኩሳል። ቀጥሎ ሁሉም ወደ ደቦቱን(ችቦውን) ወደ ደመራው ውስጥ ያስገባል። ደመራውም ይቀጣጠላል። የእሳቱ ነበልባል በመስከረም የንጋት ውርጭና ብርድ ላይ ያይላል። ሁሉም በደመራው ዙሪያ ተኮልኩሎ የክረምት ወራት ትዝታ ይነሳል፤ ሹፈት፣ ቀልድና ቁምነገር በየፈርጁ ይሰለቃል። ሌሊቱ የአህያ ሆድ እስኪመስል ይቀጥላል። የተጣላም ይታረቃል። የደመራው አምድ (ምሰሶ) አወዳደቅ ለማየት ሁሉም በጉጉት ይጠብቃል። ምሰሶው ወደ ምሥራቅ ከወደቀ የጥጋብ ዓመት፤ ወደ ምዕራብ ከሆነ ግን የችጋር ዓመት ተደርጎ ይታመናል። ከደመራው ሁነቶች አንዱ ባህሉ የበቆሎ እሸት ናፍቆት ነው። የደመራው ምሰሶ ከወደቀ በኋላ በአቅራቢያ ካለ የበቆሎ ማሳ በቆሎ እሸት ይመጣል። በመስቀል ደመራ ፍም ተጠብሶ ይበላል። ባለበቆሎው ሰው ዓመታዊ ደንብ ስለሆነ የበቆሎ ማሳዬ ተጎዳብኝ ብሎ አይቆጣም። ከደመራው ዓመድ ግንባራችን ላይ መስቀለኛ ምልክት ማድረግ እና ‘የዛሬ ዓመት አድርሰኝ’ ስለት ይቀጥላል። ሰማዩ የአህያ ሆድ ሲመስል ልጆች በደቦ ወደ መንደር ለመንደር በመዞር ‘እንጎረጎባችሁ’ እንላለን። የቤቱ ባለቤትም በሳህን፣ ጣሳ ወይም ሌላ ዕቃ ጤፍ ዱቄት ይሰጣል። የሰበሰብነውን ዱቄት ይዘን ወደ ደመራው ሥፍራ እንመለሳለን። በደመራው ጉባዔ ተወስኖ ከዕድሩ ለተመረጠች ቀጭን እመቤት (ባለሙያ ሴት) ዱቄት ይሰጣትና በ17 ምሽት ለሚኖረው የእራት ሰዓት ዝግጅት በአነባበሮ መልክ ዱቄት አብኩታና ጋግራ ታቀርባለች። መስቀል የወል ክብረ በዓል ነው። የመስቀል ዕለት (መስከረም 17) በግ ይታረዳል። እህል ውሃ ቀርቦ የመንደሩ ሰው በጋራ ሲጫወት ይውላል፤ በሕብረት ይበላል። ለመስቀል የተጣላ ጎረቤት ይታረቃል። ልጆች በሕብረት ይቦርቃሉ። የመስቀል ትዝታ በእኛ መንደር ይናፈቃል። ሁሉም እንደየ ቀየው ትውፊት እና ልማድ ይህን ሁነት ይናፍቃል….!! ጊፋታ ጊፋታ/ ግፋታ ማለት ትርጉሙ በኩር ወይም ታላቅ ማለት ሲሆን በለኬላ ትርጓሜው መሻገር ማለት ነው፡፡ በወላይታ ብሔረሰብ አዲስ ዓመት አንድ ብሎ የሚጀመርበት የአዲስ ዓመት መግቢያና የብርሃን ጊዜ ማብሰሪያ ነው፡፡ ከአሮጌ ወደ አዲስ፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን መሻገር የሚለውንም ይገልጻል፡፡ ጊፋታ የዓመቱ የመጀመሪያ ወር ስያሜ ነው፡፡ በወላይታ ብሔረሰብ ዘንድ መስከረም ወር በገባ ከቀን 14 እስከ 20 መካከል የሚውለው እሑድ አዲሱን ዓመት የሚቀበሉበር ዕለት ይሆናል፡፡ በዓሉ የሚውልበት እሑድ ስሙም ‹‹ሹሃ ወጋ›› የእርድ እሑድ ይባላል፡፡ እሑድ የአዲስ ቀን ብሥራትም ነው፡፡ ቀጣዮቹ የሳምንቱ ቀናት የየራሳቸው ስያሜና አከባበር አላቸው። ለአብነት ‹‹ጋዜ ኦሩዋ›› ማንሳት ይቻላል። የአዲስ ዓመት አራተኛ ቀን ነው። የሰፈሩ ወጣቶች በየመንደሩ በታዋቂ የአገር ሽማግሌዎች ደጅ ተሰባስበው የግፋታ በዓል ባህላዊ ጨዋታ የሆነውን ጋዜ በጋራ ሆነው ‹‹ሀያያ ሌኬ›› እያሉ ትከሻ ለትከሻ ተቃቅፈው የሚጫወቱበትና ልጃገረዶችን ሎሚ በመለመን የሚፈልጓትን የሚመርጡበት ጨዋታ የሚጫወቱበት ቀን ነው፡፡ በዕለቱ ልጃገረዶች አንድ ላይ ሆነው በየቡድን ቁጭ ብለው ወንዴና ሴቴን ከበሮ እየመቱ ‹‹ወላወላሎሜ›› እያሉ የሚመርጡትን ወንድ ሎሚ በመስጠት የሚመርጡበት፣ እንዲሁም ሴቶች ለሚዜነትና ለጓደኝነት ከመረጧት ሴት ጋር በጥርስ አንድ ሎሚን ለሁለት የሚከፋፈሉበትና ስማቸው ሲጠራሩ ‹‹ሎሜ ሎሜ›› የሚባባሉበት ጨዋታ የሚጫወቱበት ዕለት ጋዜ ኦሩዋ ነው፡፡ ግፋታ ሲሸኝ ጥቅምት በገባ በመጀመሪያው ሳምንት ማክሰኞ ሆኖ የሽኝት በሬ ታርዶ ከተበላ በኋላ ቶክ ጤላ የተባለውን ምሽት በችቦ ያባርራሉ፡፡ ዜማ በተቀላቀለበት ጩኸት ችቦ ይዘው ‹‹ኦሎ ጎሮ ባ! ሳሮ ባዳ ሳሮ ያ!›› ይላሉ፡፡ ትርጓሜውም ጊፋታ በሰላም ሄደሽ በሰላም ነይ! ማለት ነው፡፡ ዮ …ማስቃላ በጋሞዎች ዘንድ በየዓመቱ በጉጉት የሚጠበቀው «ዮ ማስቃላ» የዘመን መለወጫ በዓል በመስከረም ወር አጋማሽ ላይ ቅበላው ተከብሮ በዚሁ ወር መጨረሻ «ዮ ማስቃላ» ሽኝት በዓል በድጋሚ በድምቀት ይከበራል። መስከረም ወር የመጀመሪያው ቀን በጋሞ ዞን ”ሂንግጫ” ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ይህም አዲሱን ዓመት ለመቀበል ዝግጅት የሚደረግበት ቀን ነው። ጋሞዎች ዓመቱን ሙሉ ገንዘብ በመቆጠብ በዓሉን በድምቀት ለማክበር ዝግጅት ይደረጋል። ወንዶች ለበዓሉ የሚሆን ሠንጋ መግዣ፣ ለልጆች ልብስ እና ጌጣጌጥ ማሟያ፤ እናቶች ደግሞ ለቅቤ፣ ለቅመማቅመም፣ ለባህላዊ ምግቦች እና መጠጦች እህል መግዣ የሚሆን ገንዘብ ያጠራቅማሉ። በጋሞ ዞን የማስቃላ በዓል ለሰው ልጆች ብቻ ሳይሆን ለእንሳስት እና ለአዕዋፋትም ጭምር ነው ተብሎ ይታመናል፤ በዕለቱ ምግብ ከሰው አልፎ ለእንሳስት እና ለአዕዋፍም ይትረፈረፋል። ለከብቶችም የግጦሸ መሬት በየአካባቢው ይከለላል። በተለያዩ አጋጣሚዎች የተጣሉ ታርቀው፣ የተራራቁ ዘመድ አዝማድ እና ወዳጆች ተሰባስበው በዓሉን በጋራ እንዲያከብሩ ማድረግ የጋሞ ማስቃላ በዓል መገለጫ ነው። በጋሞ ብሔረሰብ የሚከበረው የማስቃላ በዓል በሶፌ ሥርዓት የታጀበ ነው። የቀደመው ዓመት ማስቃላ በዓል ከተከበረ በኃላ የተጋቡ ሙሽሮች ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ ማምሻውን በአደባባይ ከመላው ሕብረተሰብ ጋር የሚቀላቀሉበት እና ሁለቱም ተጋቢ ቤተሰቦች አንድ ላይ ሆነው ደስታቸውን የሚገልፁበት ሥርዓት ነው። የመጨረሻው የማስቃላ ሽኝት በዓል ነው፤ ይህ ሥርዓት እንደየአባወራው አቅም በፈቀደ መጠን የሚፈፀም ነው። በዚህ ዕለት ሁሉም ያለ ፆታ ልዩነት በአደባባይ ላይ ወጥተው ያኑረን እስከ ወዲያኛው እንኖራለን እያሉ ይጨፍራሉ። ከዚህ በኋላ ለመጪው ዓመት በሰላም በጤና ያድርሰን ተባብለው ፈጣሪን በመማፀን ዝግጅቱ ይቋጫል። ያሆዴ መስቀላ የክረምቱ ወራት አልፈው መስኩ በልምላሜና በአደይ አበባ ሲያሸበርቅ በሃድያዎች ዘንድ ትልቅ ዝግጅት አለ - ያሆዴ መስቀላ። “ያሆዴ“ ማለት እንደ ብሔሩ የባህል ሽማግሌዎች ትርጓሜ እንኳን ደስ አላችሁ፤ የሚል የብስራት ትርጉም ያለው ሲሆን ”መስቀላ” ማለት ደግሞ ብርሃን ፈነጠቀ ማለት ነው፡፡ በመሆኑም ያሆዴ መስቃላ ብርሃን ፈነጠቀ እንኳን ደስ አላችሁ የሚል ትርጉም አለው። በዓሉ በወርኃ መስከረም 16 የሚከበር ሲሆን ወሩ ብርሃን፣ ብሩህ ተስፋ፣ ሰላም፣ ፍቅር፣ ረድኤት፣ በረከት የሚሞላበት ተምሳሌት ወር ተደርጎ ይቆጠራል። የሃድያ አባቶች ”ከባለቤቱ የከረመች ነፍስ በያሆዴ መስቀላ ትነግሳለች“ የሚል ብሂል አላቸው። የሃድያ አባቶች እንደ ዘመን መለወጫ የመጀመሪያ ቀን አድርገው በመውሰድ ማንኛውንም ዓይነት ክስተት ከዚያ ጋር አያይዘው እንደሚቆጥሩ ይነገራል። በዓሉ ከመድረሱ በፊት ሁሉም የቤተሰብ አባላት በዓሉን ለማድመቅ የየራሳቸው ድርሻ አላቸው። በብሔሩ አባቶች አብሮነታቸውን ከሚያጠናክሩባቸው ማኅበራዊ እሴቶች መካከል አንዱ ቱታ/ሼማታ/ሲሆን ይህ ማለት በዓሉን ምክንያት በማድረግ የተደራጀ ቋሚ የሆነ ከአራት እስከ ስምንት አባላትን የያዘና በሥጋ ቅርጫ የተደራጀ ማኅበር ነው። የዚህ ማኅበር አባላት ግንኙነት ያላቸው የሚተሳሰቡ የኢኮኖሚ አቅማቸውም ተቀራራቢነት ያለው ሲሆን በመቀናጀት የበዓሉ እለት ከመድረሱ በፊት በጋራ ገንዘብ ማስቀመጥ ይጀምራሉ፤ በበዓሉ ወቅትም ለእርድ የሚሆን በሬ መግዣ ገንዘብ እንዳይቸገሩና በዓሉን በደስታ እንዲያሳልፉ ሕብረታቸው ትልቅ ሚና ይጫወታል። ከመጋቢት ወር ጀምሮ ለከብቶች የግጦሽ ሳር የሚሆን ቦታ ከልሎ በማስቀመጥ የበዓሉ ቀን ከብቶች ተለቀውበት እንዲጠግቡ የሚደረግ ሲሆን በአዲስ ዓመት መግቢያ እንኳን የሰው ልጅ እንሰሳትም ቢሆኑ መጥገብ እንዳለባቸው እንዲሁም የጥጋብ ዘመን እንዲሆን በብሔሩ በዓሉ ለሰው ብቻ ሳይሆን እንሰሳትም ሆዳቸው ሳይጎድል አዲሱን ዓመት መቀበል እንዳለባቸው በመታመኑ ልዩ ትኩረት ይሰጣቸዋል። ኢሬቻ ኢሬቻ ከመስከረም ደማቅ መልኮች አንዱ ነው። ኢሬቻ የዘመነ መፀው መጀመሪያ ሁነት ነው። የኢሬቻ ክብረ በዓል ኢሬቻ ቢራ (መልካ) በሐይቆች ወይም በወንዞች ዳር የሚከበር ነው። ከክረምት ወደ መፀው መሸጋገርን ምክንያት በማድረግ የሚከወን የምስጋና በዓል ነው። በኦሮሞ ዘንድ ለዘመናት የሚከበር እና ከገዳ ሥርዓት ጋር የተቆራኘ እንደሆነ ይነገራል። ኢሬቻ ከመስቀል በኋላ ይከበራል። በቢሾፍቱ ከተማ የሚከበረው የ'ሆራ አርሰዲ' እንዲሁም ‘ሆራ ፊንፊኔ’ ከፍተኛ ሕዝብ ቁጥር በታደመበት በድምቀት ይከበራል። በሌሎችም የኦሮሚያ አካባቢዎች በተለያዩ ክዋኔዎች እንዲሁ ይከበራል። ኢሬቻ ለፈጣሪ (ዋቃ) የክረምት ወቅትን በማሳለፉ፣ ወይንም ወደ አዲስ ዓመት በማሸጋገሩ የሚቀርብ ምስጋና ነው። ‹‹ዋቃ›› ፍጥረተ ዓለምን ያስገኘውና ሒደቱንም የሚያስተናብረው አንድ አምላክ ማለት ነው፡፡ ‹‹ኢሬቻ ሰላም ነው፣ ሰላም ጥልቅ ትርጉም አለው፣ ሰው ከሰው ጋር፣ ሰው ከራሱ ጋር፣ ሰው ከተፈጥሮ ጋርና ሰው ከፈጣሪው ጋር ሰላም ሊኖረው ይገባል፤›› የሚለው ጽንሰ ሐሳብ የክብረ በዓሉ ጭብጥ ነው፡፡ ለሕዝቡና ለአገሩ ምርቃትና መልካም ምኞት የሚገለጽበትም ነው-ኢሬቻ። ታዲያ ማንኛውም ሰው ወደ በዓሉ ሥፍራ ሲሄድ አለባበሱን ማሳመር ይጠበቅበታልኢሬቻ ከመስቀል በኋላ ይከበራል። በቢሾፍቱ ከተማ የሚከበረው የ'ሆራ አርሰዲ' እንዲሁም ‘ሆራ ፊንፊኔ’ ከፍተኛ ሕዝብ ቁጥር በታደመበት በድምቀት ይከበራል። በሌሎችም የኦሮሚያ አካባቢዎች በተለያዩ ክዋኔዎች እንዲሁ ይከበራል። ኢሬቻ እንደ ዕንቁጣጣሽ በመስከረም ጥባት ውሃ ጎድሎ፣ የተራራቀ ዘመድ አዝማድ የሚገናኝበት ነው። በተለያዩ ጸሐፍት እንደተጠቀሰው፣ ኢሬቻ አንድም ‘ዋቃ’ ከብርድና መብረቅ፣ ከጎርፍ፣ ከአውሎ ነፋስ እና መሰል የክረምት ተፈጥሯዊ ክስተቶች ጠብቆ ወደ ብራ እና ፀሐያማው የመፀው ወቅት በሰላም ስላሸጋገረ፣ አንድም በዋቃ ፈቃድ ዝናብ ዘንቦ፣ መሬቱ ረስርሶ፣ አዝመራው ለምልሞ፣ መልካም ፍሬ በመታየቱ፣ እሸት በመስጠቱ ስለማያልቀው ቸርነቱ ለማመስገን ነው። ከክረምቱ ጨለማ ወደ ብርሃን የማለፍ ብሥራት ነው ኢሬቻ። በሌላ በኩል ደግሞ መጪው አዲሱ ዓመት የተባረከና የተቀደሰ፣ የደስታና የብልፅግና፣ የተድላና ፍስሃ ይሆን ዘንድ መልካም ምኞትን የመግለጫ በዓልም ነው። በኢሬቻ ክዋኔ አባ ገዳዎችና የሕዝብ መሪዎች ይመርቃሉ። በኦሮሞ ሕዝብ ባህላዊ አለባበሱን በማጌጥ ወደ ክብረ-በዓሉ የሚያመሩ ኢሬቻ አክባሪዎች እርጥብ ሳር እና አደይ አበባን ይይዛሉ። ከኢሬቻ ክብረ-በዓል የምርቃት ስንኞች መዘን እንሰናበት። “… ለምድራችን ሰላም ስጥ! ለወንዞቻችን ሰላም ስጥ! ከጎረቤቶቻችን ጋር ሰላም ስጠን! ለሰውም ለእንስሳቱም ሰላም ስጥ! ከእርግማን ሁሉ አርቀን! ከረሃብ ሰውረን! ከበሽታ ሰውረን! ከጦርነት ሰውረን! ሀዬ! ሀዬ! ሀዬ! (አሜን! አሜን! አሜን!)
ያሆዴ- የአዲስ ተስፋና ልምላሜ ምልክት
Sep 22, 2023 804
(በማሙሽ ጋረደው ከሆሳዕና) ያሆዴ የሃድያ ብሔር የአዲስ ዘመን መሸጋገሪያ በዓል ነው። በዓሉ ሲከበር ቂምና ቁርሾ ተወግዶ ያለፈው ዓመት መልካምና በጎ ያልሆነ ሁኔታ ታይቶ ለቀጣይ ስኬት አዲስ ተስፋና ልምላሜ ሰንቆ የሚሻገሩበት በዓልም እንደሆነ ይነገራል። ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡ የሃድያ ዞን አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ሃላፊ አቶ ታምሬ ኤርሚያስ እንዳሉት ሃድያ የራሱ የሆነ የጊዜ አቆጣጠር ባህል፤ ልማድ፤ ወግና ስርዓት አለው። ለዚህም እንደ ማሳያ በብሔሩ ዘንድ በከፍተኛ ድምቀት የሚከበረውን የያሆዴ ክብረ በዓል ለአብነት ጠቅሰዋል። በዓሉ የአዲስ ተስፋና ልምላሜ ምልክት ተደርጎ እንደሚወሰድ የተገለጸ ሲሆን በተለይም የሚመጣው ዘመን የስኬት እንዲሆን እያንዳንዱ ካለፈው ዓመት ስኬትና ውድቀት ልምድ እየቀመረ ሃገር ሰላም እንዲሆን ተመራርቀው በደስታ እየተበላ፤ እየተጠጣ የሚከበር በዓል መሆኑንም ተናግረዋል። በብሔሩ ዘንድ ልዩ ቦታ የሚሰጠው የያሆዴ ክብረ በዓል አሮጌውን ዓመት ሸኝተው አዲሱን ዓመት የሚጀምሩበትም ነው። በዓሉ ከነሐሴ አጋማሽ ጀምሮ በተለያዩ ክዋኔዎች የሚከበር ሲሆን በዓሉ መቅረቡን ታዳጊ ልጆች በተለያዩ ገላጭ በሆኑ ድርጊቶች እንደሚያበስሩ አቶ ታምሬ ተናግረዋል። በተለይም ታዳጊዎቹ ያሆዴ መድረሱን ለማብሰር ከነሐሴ አጋማሽ ጀምሮ እስከ ጳጉሜ መጨረሻ ድረስ በብሔሩ አጠራር ገምባቡያ ወይም (ዋሽንት) በመጠቀም የተለያዩ ጥዑመ ዜማዎችን በማሰማት በዓሉ መቅረቡን ያበስራሉ። በሃድያ ብሔር ዘንድ የአዲስ ዘመን ብስራት “ያሆዴ" የብሩህ ተስፋ፣ የሠላም፣ የፍቅር፣ የረድኤት፣ የበረከት ተምሳሌት ተደርጎ የሚወሰድ በዓል መሆኑንም አመልክተዋል። ይህም የሆነበት ምክንያት በመስከረም ሰውና እንስሳ ከዶፍ ዝናብ፣ ከውርጭ፣ ከጤዛና ከጭቃ፣ ከጉም፤ ከጭጋግና ጽልመት ነጻ ይሆናሉ። ምድሩ በሃምራዊ ቀለም ደምቆ ያሸበርቃል። ፀሐይ ሙሉ ገላዋን ገልጣ ጸዳሏን ትሰጣለች። በመሆኑም በስራ የደከመ ሰውነት ዘና፣ የታመመ ቀና ይልበታል፣ ልጅ አዋቂ የደስታ ነጋሪቱን ይጎስማል፣ የፍቅር ጽዋ ይጠጣል፣ የአእምሮ እርካታ ይነግሳል፣ በሁሉም ነገር ደስታ ይሰፍናል ወርሃ መስከረም በጥጋብና ደስታ ይጀመራል ። በዓሉ ከመግባቱ በፊት የራሱ የሆነ የሥራ ክፍፍል ኖሮት ቅድመ ዝግጅት የሚደረግበት መሆኑን ያነሱት ሃላፊው የቤተሰብ አባላት ሁሉም በየድርሻቸው ሃላፊነታቸውን እየተወጡ እንደሚጠብቁት ተናግረዋል። ለአብነትም ለበዓሉ መድመቅ በዓሉ ከመድረሱ ሦስትና አራት ወራት በፊት በአንድ ቤት ውስጥ የሚኖሩ የቤተሰብ አባላት የሚወጡት ድርሻ አላቸው። የሃድያ አባቶች የያሆዴን የዘመን መለወጫ በዓል የሚያከብሩት በቅንጅት አማካኝነት ከአራት እስከ ስድስት ሰው በመሆን ተቀናጅተው ሰንጋ በመግዛት ነው። ለበዓሉ ሰንጋ መግዣ የሚሆን ገንዘብ ማስቀመጥ የሚጀምሩትም ቀደም ብለው ነው ። እናቶች በዓሉ ከመቃረቡ ከሦስትና እና አራት ወራት በፊት ለበዓሉ የሚሆን ቅቤ ለማጠራቀም በሚገቡት (ዊጆ) በተሰኘ ዕቁብ ቅቤ ማከማቸት ይጀምራሉ። በተጨማሪም ለስጋ መብያና ለአተካና መስሪያ የሚሆን እንሰት በመለየትና በመፋቅ፣ ቆጮ፣ ሜሬሮና፣ ቡላን ጨምሮ የሚጠጣ ቦርዴ፣ ቃሪቦ፣ ጠጅ፣ ብርዝ የማዘጋጀት የድርሻቸውን ይወጣሉ። የደረሱ ልጃገረዶች የቤቱን ወለል ቆፍረው ይደለድላሉ፣ የተለያዩ ውበት የሚሠጡ ቀለማትንና የተለያዩ ኖራዎችን በመጠቀም የቤቱን የውስጥና የውጭ ግርግዳን በመቀባት ያስውባሉ። ወጣቶች ከነሐሴ መግቢያ ጀምሮ አባቶቻቸው የሚመርጡላቸውን ዛፍ፣ ግንድ ቆርጠው ለምግብ ማብሰያና ለደመራ የሚሆን ችቦ የማዘጋጀት ኃላፊነታቸውን እየተወጡ ይቆያሉ። ከመስከረም መግቢያ ጀምሮ ያሉ የቅዳሜ ገበያዎች ስያሜ (መቻል ሜራ ) የእብድ ገበያ በመባል ይጠራሉ።እነዚህ የግብይት ቀናት ከዚህ ቀደም እንደነበሩ የግብይት ቀናት በተረጋጋ መንገድ የሚተገበሩ ባለመሆኑና በጠዋት ቆሞ በጊዜ የሚበተን ገበያ በመሆኑ (መቻል ሜራ) የእብድ ገቢያ የሚል ስያሜ አሰጥቶታል ነው ያሉት አባቶች ሰንጋ ገዝተው ለመብላት ባደራጁት (ቱታ) ቅንጃ አማካኝነት ያጠራቀሙትን ገንዘብ በመያዝ ወደ መቻል ሜራ (እብድ ገበያ) በመሔድ የሚፈልጉትን ሰንጋ ገዝተው ይመለሳሉ። ገንዘብ ያላስቀመጡና በወቅቱ ማግኘት የማይችሉ አባወራዎች በዓሉን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተደስተው እንዲያሳልፉ ሌላኛው አማራጭ (ሃባ) በመባል የሚታወቅና ምንም ገንዘብ የሌላቸው ሰዎች ለበዓሉ የሚሆን ሰንጋ በብድር የሚወስዱበት በብሔሩ ተወላጆች ዘንድ የኖረ የመተጋገዝና የመተሳሰብ እሴት አንዱ ነው። የሚፈልጉትን ሰንጋ ከመረጡ በኋላ እህል በሚደርስበት በታህሳስና በጥር ለመክፈል በዱቤ ይወስዳሉ። የበሬ ነጋዴውም ያለ ማንገራገር ሰንጋውን በመስጠት ወቅቱ ሲደርስ ገንዘቡን ለመውሰድ ተስማምቶ ይሰጥና ወቅቱን ጠብቆ ገንዘቡን ይወስዳል። በትውስት ተወስዶ ገንዘብ ያልከፈለ አባወራ ለቀጣይ የዘመን መለወጫ አይደርስም ተብሎ በብሔሩ ዘንድ ስለሚታመን በተስማሙበት ወቅት ገንዘቡን የመስጠት ግዴታቸው የተጠበቀ ነው። ሌላኛው አስተያየት ሰጪ የመምሪያው ባለሙያ አቶ ይዲድያ ተስፋሁን እንዳሉት በዓሉ ያለው ለሌለው አካፍሎ በጋራ የሚበላበትና ወደ አዲስ ዘመን በጠንካራ አብሮነት የሚሻገሩበት ነው። በመሆኑም የያሆዴ በዓል በዜጎች መካከል ጠንካራ አንድነትና አብሮነትን መሰረት ያደረጉ ዕሴቶች ያሉበት መሆኑን አንስተው ለትውልድ ግንባታ የሚሆኑ ዕሴቶችን አጎልብቶ መጠቀም እንደሚገባ ተናግረዋል ። ለበዓሉ ዋዜማ ከሚዘጋጁ ሁነቶች መካከል አተካና ልዩ ቦታ የሚሰጠው ነው። አተካና በተለይም ለዚህ በዓል ከዚህ ባሻገር ለትልልቅ እንግዶች ከሚዘጋጁ ምግቦች መካከል አንዱ ነው። አተካና ከወተት፣ ከቅቤ፣ አይብና ቡላ የሚዘጋጅና በበዓሉ የምግብ ፍላጎትን የሚከፍት ተበልቶ የማይጠገብ በእናቶች የሚዘጋጅ ጣፋጭ ምግብ ነው። የበዓሉ ዋዜማ አተካን ሂሞ (የአተካና ምሽት) የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን በዓሉን ለማክበር ከሩቅም ከቅርብም የተሰበሰበ ቤተሰብና እንግዶች በናፍቆት የሚመገቡት ምግብ ነው። በዚሁ ዕለት በአካባቢው ትልቅ የሚባል አባወራ (አዛውንት) ቤት ችቦ (ሳቴ ) ተዘጋጅቶ ማምሻውን አባቶች ወይም የሃገር ሽማግሌዎች የማቀጣጠያ (ጦምቦራ) ደመራ ማቀጣጠያ ይዘው ይወጣሉ። ከዚያም የአካባቢው ማህበረሰብም የሃገር ባህል ልብስ ለብሰው እንዲሁም ወጣቶች ተሰብስበው ያሆዴ ይጨፍራሉ። የሃገር ሽማግሌዎች ይመርቃሉ፤ ከዚያም የተዘጋጀውን ችቦ በእሳት ለኩሰው ያበራሉ። ይህም አዲስ ዘመን መግባቱን ማብሰርና ዓመቱ የብርሃን ዓመት እንዲሆን መልካም ምኞት የሚገለፅበት ነው። ደመራው ከተቀጣጠለ በኃላ ወጣቶች ያሆዴ (ኦሌ) ጭፈራ ሲጫወቱ ያነጋሉ። ይህ ጭፈራ ከያሆዴ በዓል ውጭ አይጨፈርም። ወጣት ደመቀ አባቴ የሆሳዕና ከተማ ነዋሪ ሲሆን ስለ በዓሉ አስተያየቱን ሲሰጥ ''በአባቶች ደመራው ከተቀጣጠለ በኃላ እኛ ወጣቶች ያሆዴ ....ያህዴ....ሆያ ሆ... /ኦሌ/ ጭፈራ እየተጫወትን እናነጋለን፤'' ይህ ጭፈራ ከያሆዴ በዓል ውጭ ስለማይጨፈር በዓሉን ቀን በጉጉት እንደሚጠብቁት ተናግሯል። ተራርቀው የቆየ ወዳጅ ዘመድ ተሰብስቦ ያለምንም ልዩነት ችግርም ካለ በዕርቅና ሰላምን በማውረድ የሚመጣው ዘመን የልምላሜና የስኬት እንዲሆን ተመራርቀው የሚለያዩበት በዓል በመሆኑ በተስፋ የሚጠብቁት እንደሆነ ነው ወጣቱ የሚናገረው። የበዓሉ እለት ለዕርድ የተዘጋጀው ሠንጋ ከቀረበ በኃላ የባህል ሽማግሌዎች (ጋቢማ ) ሥርዓት ያከናውናሉ። ክዋኔውም የበሬውን ሻኛ በለጋ ቅቤና በሠርዶ ሳር በመቀባትና ወተት በማፍሰስ ይከናወናል። ይህም በሚከናወንበት ወቅትም ክፉ ቀን አይምጣ፣ ርሃብ ሰቀቀን ይጥፋ፣ ጥጋብ ይስፈን፣ በአካባቢው በሃገሩ ጥጃ ይቦርቅ፣ ልጅ ይፈንጭበት፣ አገር ሰላም፣ ገበያ ጥጋብ ይሁን፣ ሰማይና ምድሩ ይታረቁን በማለት (ፋቴ) ዳግም ምርቃት ፈጽመው በሬው ይጣልና የዕርድ ሥርዓት ይካሔዳል። በዕለቱም ከታረደው ሥጋ ቅምሻ በጋራ ይበሉና ቀሪውን ለማህበሩ (ለቱታ) አባላት ክፍፍል ይፈፀማል። ከእርድ ሥርዓቱ በኃላ በማግስቱ ልጆች ወደ ወላጆቻቸው ዘራሮ የሚባል አበባ ይዘው እየጨፈሩ ያስማሉ -ይመረቃሉ የመስቀል አበባ እንደሚኖር ኑሩ ይባባላሉ፤ ከስጋውም ፣ከቦርዴውም ፣ ከአተካናውም የሚመገቡበት ክዋኔ (ሚክራ) በመባል ይታወቃል። ትዳር የያዙ ሴት ልጆችም ከባሎቻቸው ጋር ሆነው ወደ ወላጆቻቸው ምግብ ሰርተው፣ የሹልዳ ስጋና (ዘራሮ) አደይ አበባ ጭምር ይዘው የሚሔዱበት እንዲሁም ያላገቡ ወጣቶች ለትዳር የሚሆናቸውን አጋር የሚፈልጉበትና የሚያጩበት ባህልም ያለው ነው ያሆዴ ክብረ በዓል። ከእርድ ስነ ስርዓቱ በኋላ ከሶስት ሳምንታት እስከ ወር ለሚሆን ጊዜ የመጠያየቂያና የመረዳጃ ወቅት ይሆናል። የያሆዴ በዓል ያሉ ዕሴቶች ለህዝብ ትስስር፣ ጠንካራ የስራ ባህልና ዘላቂ ሰላም ግንባታ ያላቸውን ሚና ለማላቅ በልዩ ትኩረት ሊሰራ እንደምገባ የሚያነሱት በዋቸሞ ዩኒቨርስቲ የህዝብ ግንኙነትና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የአቶ ዳንኤል ገዴ በዚህ ላይ በአከባቢው ያሉ የማህበረሰብ ልምዶችና ወጎች ለትውልድ እንዲሸጋገሩ መስራትና የሃገር በቀል ዕውቀትን ማጠናከር እንደምገበባ ተናግረዋል። በዚህ ረገድ የዋቸሞ ዩኒቨረሲቲ የሃድያን ብሔር የዘመን አቆጣጠር ታሪክ : ባህልና ቋንቋ እንዲሁም ሌሎች ዕሴቶች ተሰንደው እንዲቀመጡና ለማስተማሪያነት እንዲውሉ ለማስቻል በጥናትና ምርምርና የተደገፈ ስራ በመስራት ላይ መሆኑን አመላክተዋል። በተጨማሪም ባህሉ ይበልጥ እንዲታወቅና በዩኔስኮ ተመዝግቦ ለአካባቢው ማህበረሰብ የሚገባውን ጥቅም እንዲያመጣና ከቱሪዝም አንጻር ሚናውን እንዲጫወት ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛል ብለዋል።
የመኔ ሸድዬ ባሮ - የጠንካራ የስራ ባህል፣ የአብሮነትና የሰላም ተምሳሌት
Sep 20, 2023 1376
በሽመልስ ጌታነህ (ኢዜአ) የመኔ ሸድዬ ባሮ የካፈቾ ብሄር ከአሮጌው ዘመን ወደ አዲሱ የሚሸጋገሩበት፣ የአዲስ ዘመን ብስራትና የዘመን መለወጫ በዓል ነው። በዓሉ የጠንካራ የስራ ባህል፣ የአብሮነትና የሰላም ተምሳሌት በዓል እንደሆነ ይነገርለታል። በዚህም የካፋ ብሄር ለዘመናት የገነባውና ጠንካራ የስራ ባህል፤ ተፈጥሮን የመጠበቅና የመንከባከብ እንዲሁም ከተለያዩ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ጋር ተቻችሎና ተፈቃቅሮ የሚኖር ሲሆን ቱባ ዕሴቱ ዛሬም ላለው ትውልድ መሰረት መሆኑን ያምኑበታል። የተለያዩ የታሪክ ድርሳናት እንደሚያሳዩት ከሆነ የካፋ ህዝብ ጠንካራ ንጉሳዊ ሥርዓት የነበረው፤ የታሪክና የቱባ ባህል ባለቤትም ነው። ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የታሪክ ባለሙያና የሀገር ሽማግሌ አቶ አሰፋ ገብረማሪያም የካፈቾ ብሄር ዘመን መለወጫ በሃገሬው አጠራር ''የመኔ ሸድዬ ባሮ'' በዓል የካፋ ህዝብ ከሚያከብራቸው በርካታ በዓላት ውስጥ ትልቅ ሥፍራ የሚሰጠው መሆኑን አፅንኦት ሰጥተው ይናገራሉ። በዓሉ ያለውን ግዝፈት ሲያመለክቱ በሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በውጭ ፀሐፍት ጭምር “ታላቁ በዓል ወይም (ግሬት ፌስቲቫል)” ተብሎ እንደሚጠራም ተናግረዋል። በዓሉ ታሪካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ዳራ ያለው ሲሆን ከጥንት ካፋ ንጉስ ጀምሮ በየአመቱ በድምቀት የሚከበር በዓል እንደሆነም ጠቁመዋል። የካፋ ህዝብ ከ14ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ከጎሳ መሪነት አንስቶ ጠንካራ የመንግስት መዋቅር የነበረው ታላቅ ህዝብ እንደሆነ ያነሱት አቶ አሰፋ፣ በዚህም በዓሉ በዘመኑ የነበሩ መንግስታት በዓል እንደነበረም አብራርተዋል። ዓመታዊ የሥራ አፈፃፀም የሚገመገምበት ጥሩ የሠራና የተሻለ አፈጻጸም ያስመዘገበ የሚሸለምበትና ለበለጠ ሥልጣን የሚታጭበት፤ ሰነፉ ደግሞ የሚወቀስበትና ስልጣኑ የሚነጠቅበት ታላቅ በዓልም ነው ብለዋል። ይህም በብሄሩ ዘንድ ለዘመናት የተሻገረ የጠንካራ የሥራ ባህል ግንባታ መሰረት ሆኖ የቆየ መሆኑን አንስተዋል። ይህ ሁሉ ሲከናወን በማህበረሰባዊ የህግ ተገዥነት መሰረት መሆኑ የተለየ እንደሚያደርገው ገልጸው ከሁሉ በፊት ሰላምን በማስቀደም መንግስትንና ህግን ማክበር እንዲሁም ህግ የሚመራው ህዝብ የበላይ መሆኑን አመላካች ሥርዓት መሆኑን አንስተዋል። በዓሉ ከአዝመራ ጋር የተያያዘ የዘመን አቆጣጠርን ተከትሎ እንደሚከበርም የታሪክ ባለሙያው አቶ አሰፋ ይገልጻሉ። እንደ ታሪክ ተመራማሪው ገለጻ የካፋ ህዝብ አብዛኛው አርሶ አደር አልፎም አርብቶ አደር ሲሆን ለአዝመራ የተለየ ትኩረት ይሰጣል፤ በዓሉ ሊከበር 77 ቀናት ሲቀሩት ህዝቡ የአዲስ ዘመን መለወጫ ብሎ ሃምሌ አንድ አዝመራውን እንደሚጀምርም ጠቁመዋል። የአዝመራ ወቅት ሊገባደድ 25 ቀናት ሲቀሩት (ከሼ ዋጦ) ብሎ አዝመራውን ያጠናቅቃል። ወቅቱም ጨለማው አልፎ በብርሃን የሚተካበት፤ ክረምቱ ለበጋ ቦታውን የሚለቅበት በመሆኑ አዲስ አመት መድረሱን ያሳውቃል። ያን ጊዜ በጥንት የካፋ ምክርቤት ከሚገኙ ሰባት የሚክረቾ አባላት ውስጥ አንዱ የሆነው አዲዬ ራሾ ፤ የንጉሱ መቀመጫ በሆነው ቦንጌ ሸምበቶ በዓሉን ለማክበር ከየአቅጣጫው ለሚመጣው ህዝብ መንገዶችን በማፅዳት እና ለወንዞች ድልድይ በማበጀት በዓሉ መድረሱን ያበስራል። ያን ጊዜ በዓሉን ለማክበር ህዝብ ከያለበት አቅጣጫ ወደ ቦንጌ ሸምበቶ ይተማል። ህዝቡ በቦንጌ ሸምበቶ ከተሰበሰበ በኋላም ንጉሱ በተገኙበት የእያንዳንዱ ወራፌ ራሾ ሥራ ይገመገማል፤ ጥሩ ሥራ የሠራ ጠንካራ መሪ ይሸለማል፤ ለበለጠ ስልጣንም ይታጫል፤ ሀላፊነቱን በተገቢ ሁኔታ ያልተወጣው ደግሞ ይመከራል፣ ይወቀሳል አልፎም ስልጣኑን ይነጠቃል። ዛሬም ሀገራችን ይህ አይነቱን ጠንካራ የሥራ ባህል አብዝታ ትሻለች፤ እንዲህ አይነት ሀገር በቀል ዕውቀቶች ትውልዱን በጠንካራ ሥነ-ምግባርና የሥራ ባህል ለመገንባት ትልቅ ድርሻ አላቸው። በተጨማሪም በዓሉ ቅሬታዎችን ለመፍታትና ሰላምን ለማጠናከር ትልቅ አስተዋፅኦ አለው ፤ ቂምና ጥላቻን ይዞ ወደ ንጉሱ ፊት መቆምም ይሁን ወደ አዲሱ ዓመት መሻገር ነውር ተደርጎ የሚወሰድ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ወደ በዓሉ ከመምጣቱ አስቀድሞም ይሁን በበዓሉ ወቅት የተጣላ ይታረቃል፤ ጥላቻም በፍቅር ይተካል ብለዋል የታሪክ ተመራማሪው። እንዲህ አይነቱ ሀገር በቀል ዕውቀት ጠንካራ ባህል ለመገንባት፤ ቅራኔዎችን በሰላም ለመፍታትና ማህበራዊ ግኑኝነቶችን ለማጠናከር ትልቅ ፋይዳ ስላላቸው በትምህርት ሥርዓት ውስጥ አካቶ ማስተማርና ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ ይገባል ሲሉም ሃሳባቸውን አካፍለዋል። ሌላኛው የሀገር ሽማግሌና የካፋ፣ጫራ እና ናኦ የባህል ምክርቤት አባል አቶ ፀጋዬ ገብረማሪያም እንደሚሉት የካፋቾ ''የመኔ ሸድዬ ባሮ'' በዓል ማህበራዊ ግንኙነትን በማጠናከሩ ረገድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው በዓል ነው። ምክንያቱ ደግሞ፣ በዓሉን ለማክበር በአካባቢው ያሉ፣ በሌሎች የሃገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ እንዲሁም ባህር ማዶ የሚገኙ የአካባቢው ተወላጆች የሚሰበሰቡበት ታላቅ በዓል ስለሆነ ነው ብለዋል። በዚህም የተራረቀ የሚገናኝበት፤ የተጠፋፋ የሚጠያየቅበት ሲሆን ህዝቡ በአንድ ላይ ተሰብስቦ በንጉሱ ተመርቆ፣ በልቶ ጠጥቶ እንዲሁም ተጫውቶ ወደ ቀጣዩ አመት በደስታና በታላቅ ተስፋ የሚሸጋገርበት እንደሆነም አብራርተዋል። ይህ ባህል በተለያዩ ምክንያቶች ከ120 ዓመታት በላይ ሳይከበር እንደቆየ የገለፁት አቶ ፀጋዬ ገብረማሪያም ዳግም መከበር ከጀመረበት ስምንት ዓመታት ወዲህ የነበረውን ታሪክና ባህል በሚያስቀጥል መልኩ በየዓመት በድምቀት እየተከበረ መሆኑንም አንስተዋል። ወጣቱ ትውልድ ባህሉንና ታሪኩን አውቆ እንዲኖርና እንዲያስቀጥል ግንዛቤ የመፍጠርና የማስተማር ሥራ በሰፊው እየተሠራ እንደሆነም ገልፀዋል። ከዚህ ባለፈም ባህሉንና ታሪኩን ለማስቀጠል የባህል ምክር ቤቱ የወረዳ የባህል ምክር ቤቶችን የማጠናከር፣ ታሪካዊ ቅርሶችን የመሰብሰብና የማደራጀት ሥራ እየሠራ ነውም ብለዋል። በዓሉ አንድነትን የሚያጠናክር፣ ጠንካራ የሥራ ባህልን የሚያበረታታ እና የተፈጥሮ ጥበቃን የሚያጠናክር በመሆኑ ከካፋ ብሔረሰብ በዓልነቱ ባለፈ የሀገርና የአለም ቅርስና ሀብት እንዲሆን ሰፊ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባም አቶ ፀጋዬ አሳስበዋል። የካፋቾ ዘመን መለወጫ በዓል (የመኔ ሸድዬ ባሮ) መሠረቱን ሳይለቅ ለትውልድ እንዲተላለፍ በዞን ደረጃ እየተሠራ መሆኑን የገለፁት የካፋ ዞን ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ሃላፊ አቶ ተሾመ አምቦ ዘንድሮም ለዘጠነኛ ጊዜ በአደባባይ ለማክበር ሰፊ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል። በዓሉ በሁሉም የካፋ ህዝብ በጋራ ያለምንም ልዩነት የሚከበር ታሪካዊ በዓል ሲሆን አለም አቀፋዊ እውቅና አግኝቶ በዩኔስኮ እንዲመዘገብ ለማስቻል ከተለያዩ ምሁራንና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በመሆን የተለያዩ ጥናቶች እየተሠሩ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ በበዓሉ ንጉሱ የተራቡትን የሚመግቡበት (ጮንጎ) የተሰኘ ስርዓት የሚፈፀምበትና የተጣሉ የሚታረቁበት ስርዓት እንደሚፈፀም የገለፁት አቶ ተሾመ አሁንም በዓሉ በየዓመቱ ሲከበር ይህ ሥርዓት ይከወናል ብለዋል። ቀጣይ ይህን በዓል በሰፊው አስተዋውቆ ወደ ቱሪዝም በማሳደግ ህዝቡ ከዘርፉ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆን የሚያስችሉ ሥራዎች እንደተጀመሩም ሃላፊው ገልፀዋል። የዘንድሮው የ2016 ዓ.ም የካፊቾ ዘመን መለወጫ በዓል በቦንጋ ከተማ ከመስከረም 12 እስከ መስከረም 13/2016 ዓ.ም በፓናል ውይይትና በተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች በደማቅ ሁኔታ እንደሚከበርም ጠቁመዋል።
ልዩ ዘገባዎች
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 5621
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 10592
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት። እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
በጂንካ ከተማ የተመረተው 23 ኪሎ ግራም የሚመዝነው የስኳር ድንች "በአፍሪካ ትልቁ ስኳር ድንች" በሚል ተመዘገበ
Mar 13, 2023 4039
ጂንካ መጋቢት 4/2015 (ኢዜአ):- በጂንካ ከተማ ደሙዝ ሰፈር የተመረተው እና 23 ኪሎ ግራም የሚመዝነው ስኳር ድንች በአፍሪካ የድንቃ ድንቆች መዝገብ "በአፍሪካ ትልቁ ስኳር ድንች" በሚል መመዝገቡ ተገለጸ። በአዲስ አበባ በተካሄደው የእውቅና ስነስርዓት ላይ የአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ስራ አስኪያጅ አቶ አሸናፊ አለም ለስኳር ድንቹ ባለቤት አቶ ኢሳያስ ጊዜአለው የእውቅና ምስክር ወረቀት አስረክበዋል። ከዚህ ቀደም በአፍሪካ 10 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች መቅረቡን አቶ አሸናፊ ለኢዜአ ገልጸዋል። “ነገር ግን 23 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች በአፍሪካ ደረጃ ሲቀርብ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው” ብለዋል። በዓለም የድንቃ ድንቅ መዝገብ 37 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች መመዝገቡንና በደሙዝ ሰፈር የተገኘው ስኳር ድንች በ14 ኪሎ ግራም ዝቅ ብሎ ከዓለም የ”ሁለተኛነት” ደረጃ ላይ እንደሚያስቀምጠው አመልክተዋል። የስኳር ድንቹ ባለቤት አቶ ኢሳያስ ጊዜያለው ስኳር ድንቹ በአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ላይ በመስፈር የኢትዮጵያን ስም በማስጠራቱ መደሰታቸውን ገልጸዋል። ስኳር ድንቹ እውቅና እንዲያገኝ የዜና ሽፋን ለሰጠው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ምስጋቸውን አቅርበዋል። ኢዜአ የካቲት 19 ቀን 2015 ዓ.ም “በጂንካ ከተማ ደሙዝ ሰፈር 23 ኪሎ ግራም የሚመዝን አንድ የስኳር ድንች መመረቱ ተገለጸ” በሚል መዘገቡ የሚታወስ ነው።
ዶክተር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ እውቅና አገኙ
Mar 9, 2023 4894
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 30/2015 የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ በሩዋንዳ ኪጋሊ በተካሄደው በአፍሪካ ዓለም አቀፍ የጤና አጀንዳ ኮንፈረንስ (AHAIC)2023 ላይ እውቅና ተሰጣቸው። ሚኒስትሯ በሩዋንዳ ኪጋሊ ትላንት በተካሄደው Africa Health Agenda International Conference (AHAIC) 2023 ላይ የተበረከተላቸውን Women in Global Health Award የእውቅና ሽልማት በተወካያቸዉ በኩል ተቀብለዋል። እውቅናው በጤና ልማት ውስጥ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በመቋቋምና በመፍታት፣ የጤና አገልግሎት ጥራትና ፍትሀዊ ተደራሽነት እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ሽፋን ላይ ትኩረት ሰጥተው ለሚሰሩ አመራሮች የሚሰጥ መሆኑም ተመላክቷል። ለመጪዎቹ ትውልዶች አርዓያ ለሆኑ የአፍሪካ ሴት መሪዎች የሚሰጠው ሽልማቱ የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰም ለዜጎች የተሻለና ዘላቂ ጤናን ለማምጣት በሚደረግ ጥረት ውስጥ ላበረከቱት የላቀ የመሪነት ሚና ከአምሪፍ ሄልዝ አፍሪካ እውቅናውን አግኝተዋል።
መጣጥፍ
የዱርና የቤት እንስሳቱ ቤተሰባዊ ፍቅር
Dec 3, 2023 86
በፍሬዘር ጌታቸው (ወላይታ ሶዶ ኢዜአ) አብዛኛውን ጊዜ አንዳንድ የዱር እንስሳት ለሥጋቸው፣ ለቆዳቸው፣ ለጥርሳቸው ወዘተ እየተባለ እንደሚገደሉ የአደባባይ ምስጢር ነው። መንግሥት ይህንን ጥቃት ለመከላከል የተለያዩ የዱር እንስሳት ፓርኮችን በማቋቋም ጭምር የተለያዩ እርምጃዎችን ሲወስድ ይታያል። እርምጃው የዱር እንስሳቱን ከመጥፋት እንዲሁም መንግስት ዘርፉን በማስጎብኘት የሚያገኘውን ጥቅም ከመጨመር ባሻገር ሊኖረው የሚችለው ፋይዳ ብዙ ነው። የዱር እንስሳቱ ለአካባቢ ሥነ-ምህዳር የሚያበረክቱት አስተዋፅኦ ሳይዘነጋ ማለት ነው። ሆኖም ግን አሁንም በሀገራችንም ሆነ በሌላው ዓለም የዱር እንስሳት በሰው ሰራሽም ሆነ የተፈጥሮ አደጋ ስጋት ላይ ናቸው። ለዛሬ የፅሁፌ ማጠንጠኛ የዱር እንስሳቱ ስጋትና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ሳይሆን እነሱን በማላመድ ያልተለመደ ተግባርን እየፈፀመ ባለ ግለሰብ ላይ ይሆናል። ግለሰቡ ወጣት በረከት ብርሃኑ ይባላል፤ የወላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪ ነው። ወጣት በረከት አዘወትረን የምንሰማውን 'እንኳን ሰው ወፍ ያለምዳሉ' የሚለውን ብሂል በሚያስረሳ መልኩ እሱ አባባሉን 'እንኳን ሰው አውሬ ያለምዳሉ' ወደሚለው ቀይሮታል ማለት ይቻላል። በረከት “በጎሪጥ የሚተያዩ የዱር እንስሳትን በፍቅር እንዲኖሩ ያደረገበትን ሁኔታ በርካቶች በግርምት ሲመለከቱት ይታያል። የሰው ልጆች በተፈጥሮ ክፉ ሆነው አይወለዱም ዳሩ ግን በህይወት አጋጣሚ ከሚቀስሙት ክፉ ባህሪ የሚማሩትና የሚዋሃዱበት እንጂ ይላል በረከት። ''አብሪያቸው ለመሆን በመወሰኔ እውነተኛ ፍቅርን ከዱር እንስሳቱ ተምሬያለሁ'' የሚለው ወጣት በረከት ከሰባት ዓመት በፊት የዱርና የቤት እንስሳትን በተለይም ሰው ለመቅረብ የሚፈራቸውን ጭምር እንደ ዘንዶ፣ ጅብ፣ ዝንጀሮ፣ አዞ፣ ጦጣ፣ አሳማ እንዲሁም ውሻና የመሳሰሉትን በማሰባሰብ በአንድ ላይ እንዲኖሩ እያደረገ በአንድ ላይ ማኖር እንደጀመረ ይናገራል። በዚህም ምክንያት ሰው ሰራሽ ሐይቅን በውስጡ የያዘ የወጣቶች መዝናኛ ፓርክ በወላይታ ሶዶ ከተማ ማቋቋሙን ገልጿል። የዱር እንስሳቱን ከአባያ ብላቴ እንዳመጣቸው የሚናገረው በረከት በይበልጥ ግን በመኪናና መሰል አደጋዎች የተጎዱ የዱር እንስሳትን ከወደቁበት በማንሳት እንዲያገግሙ ለማድረግ በሚያደርግላቸው የእንክብካቤ ቆይታ ታዲያ የዱር እንስሳቱ ከቤት እንስሳት ጋር አብረው የማደር፣ አብረው የመዋል፣ አብረው የመብላት፣ በአንድ ላይ የመጫወት ዕድሉን እንዳገኙ ነው ለኢዜአ የተናገረው። የቤትና የዱር እንስሳቱ ህብረትና አንድነት የሚያስቀና እንደሆነም ወጣት በረከት ገልጿል። ኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ የዱር እንስሳት ሀብት እንዳለ የሚናገረው ወጣት በረከት በውስጡ ለተፈጥሮ ያለውን ፍቅር ወደ ስራ መቀየሩን ነው የገለፀው። ከሌሎች የዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ጋር በመሆን ስራውን ለመሥራት ወስነው በመግባታቸው የከተማው አስተዳደር የሥራ ቦታና መነሻ ካፒታል እንደረዳቸው ገልፆ በዚህም በመበረታታት ያልተለመደ የስራ ዘርፍ ለመፍጠር ወጥነው መጀመራቸውን ይናገራል። ስራውን ሲጀምር ቀላል ሁኔታ እንዳልገጠመው ያስታወሰው በረከት "ካባ ድንጋይ የሚፈነቀልበትን ስፍራ አልምቶና ችግኝ ተክሎ ወደ ዛፍ መቀየር እንዲሁም የሰው ሰራሽ ሐይቅ እንዲያመነጭ ማድረግ የማይቻል ይመስላል" ይላል። ቦታውን በባለሙያ በማስጠናትና ደባል አፈር ከሌላ ቦታ በማስመጣት ህልማቸውን እውን ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት ማድረጋቸውን አውስቶ ዓላማቸውን ለማሳካት የሄዱበት ርቀት ለሌሎች አስተማሪ መሆኑንም ይናገራል። ቦታውን አሁን ላይ የተለያዩ የዱርና የቤት እንስሳት በጋራ የሚኖሩበትና በርካታ የአገር ውስጥና ከሌላው ዓለም የሚመጡ ጎብኚዎች የሚዝናኑበትና የሚያርፉበት "ጁኒየር የወጣቶች መዝናኛ ፓርክ" መክፈት መቻላቸውን ነው የተናገረው። እንስሳቶች የሚሰጣቸውን ስያሜ ሳይሆን ተቀራርበው የሚኖሩበትን የፍቅር ህይወት ለማየት የሚመጣው ጎብኚ የቆይታ ጊዜ እንዲራዘም ማድረግ እንዳለበት በማመን የማረፊያ ቤቶች እና ተጨማሪ መዝናኛዎችን በማስፋፋት አሁን ላይ ጥሩ አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ አብራርቷል። በዚህም ''በፓርኩ ግቢ ውስጥ የወላይታ ሶዶ ከተማን ገጽታ የሚያሳይ ባለ ሰባት በር መግቢያና መውጫ ያለው ሆቴልና የጀልባ መዝናኛ አገልግሎት ለተጠቃሚዎች በመስጠት የተሻለ ስራ በመስራት ላይ እንገኛለን'' ብሏል። ፓርኩን ለመጎብኘት ለሀገር ውስጥ ጎብኚዎች ለአንድ ሰው 30 ብር፣ ለውጭ ዜጋ ደግሞ 100 ብር በማስከፈል አገልግሎት እየሰጡ ያነሳው ወጣቱ በአዘቦት ቀናት በቀን ከ400 በላይ ጎብኚ ፓርኩን እንደሚጎበኙ ፣ በሰንበት ቀናት እና በበዓላት ወቅት እስከ 1 ሺህ ድረስ ጎብኚዎች እንደሚመጡ ነው የተናገረው። ያንን ሁሉ አስቸጋሪ ጊዜ ለማለፍ ባደረጉት ብርቱ ጥረት ከቤተሰብና በጥቂቱም ቢሆን ከመንግሥት ጥገኝነት መላቀቃቸውን የሚናገረው ወጣቱ በህይወታቸው ጥሩ ኑሮ መኖር ከመጀመራቸውም በዘለለ በፓርኩ ውስጥ ላለው የእንስሳት እንክብካቤና ጎብኚዎችን የማስተናገድ ስራን ለሚያሳልጡ 22 ወጣቶች የስራ እድል መፍጠር በመቻላቸውም ስኬታማ እንደሆኑም ያነሳል። "አሁን እንስሳቶቹ ቤተሰቦቼ ሆነዋል በአንድ ቅጥር ግቢ ውስጥ አብሬያቸው ውዬ ነው የማድረው ይላል። ስራ ሩቅ አይደለም አጠገባችን እንዲያውም እጃችን ላይ ነው ያለው የሚለው ወጣት በረከት ሆኖም ሌላ አካል መጥቶ እንዲሰጠን እንጠብቃለን፣ ይኸ አስተሳሰብ የእድገታችን ፀር ነው '' ሲልም አፅንኦት ሰጥቶታል። ኢትዮጵያ በዱር እንስሳት ሀብት በዓለም አቀፍ ደረጃ ስሟ የሚነሳ መሆኑን ጠቁሞ ሀብቱን ለማሳደግና ሳቢ በማድረግ ተደራሽነቱን ለማስፋት እንዲያመች የሎጅ ግንባታ ስራ እንቅስቃሴ ጀምሬያለሁ ባይ ነው። ፓርኩ ውስጥ 62 ምንጮች እንደሚገኙ የገለፀው ወጣት በረከት ማስፋፊያ ቦታ ቢሰጠው የተሻሉ ስራዎችን ለመስራት እቅድ እንዳለው ተናግሯል። በሰዎች ዓለም ውስጥ ገዢ ሀይል ፍቅር ሊሆን እንደሚገባ ፓርኩ ትልቅ የፍቅር ተምሳሌት ፓርክ ‼ ነው የሚሉት ደግሞ የወላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪ አቶ ታዲዮስ ታንቱ ናቸው። ፓርኩ በሂደት ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስሟ እንዲጠራ ጉልህ ሚና ይኖረዋል የሚል ተስፋ እንዳላቸው በመግለጽ የሚመለከታቸው አካላት ተገቢውን ትኩረትና ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል። ፓርኩን ሲጎበኙ ያገኘናቸው የአዲስ አበባ ነዋሪው አቶ ለገሰ ቶማስ በበኩላቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየመነመነ ለመጣው የዱር እንስሳት ሀብት ማገገም የራሱን አስተዋጽኦ ሊያደርግ የሚችል ፓርክ መሆኑን ተናግረዋል። "ሁላችንም እንደዚሁ በእጃችን ያለውን ሀብት መጠቀም ካልጀመርን በቀር ሊለውጠን የሚመጣ ተዓምር አይኖርም'' ያሉት አስተያየት ሰጪው ከወጣት በረከት ሁሉም ብዙ ሊማር እንደሚገባም ጠቁመዋል።
“ዮ-ማስቃላ''- ሁሉም የሚደሰትበት በዓል
Sep 23, 2023 858
በሳሙኤል አየነው የሰላም፣ የአብሮነት፣ የፍቅር፣ የመቻቻልና የአንድነት ተምሳሌት የሆነው የጋሞ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል “ዮ-ማስቃላ” ከወርሃ መስከረም አጋማሽ ጀምሮ በተለያዩ ባህላዊ ሁነቶች በድምቀት ይከበራል ። በተለያየ ምክንያት በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ተራርቀው የነበሩ ወገኖች ወደ የአካባቢያቸው በመመለስ ከቤተሰቦቻቸው ብሎም ከቀየው ህብረተሰብ ጋር አብረው የሚያከብሩት የዓመቱ ታላቅ በዓል ነው ። ታዲያ በዓሉን በድምቀት ለማክበር ወንዶች ሰንጋ በሬ ለመግዛት እንዲሁም ለትዳር አጋሮቻቸውና ለልጆቻቸው ልብስና ጌጣ ጌጥ የሚሆን ገንዘብ መቆጠብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ሴቶችም ለባህላዊ ምግቦች፣ ለቅመማ ቅመም፣ ለቅቤና ለባህላዊ መጠጦች እህል ግዥ የሚሆን ገንዘብ ዓመቱን ሙሉ ሲቆጥቡ ይከርማሉ። መስከረም ወር ከገባበት ዕለት አንስተው ወንዶችም ሆኑ ሴቶቹ በቆጠቡት ገንዘብ በየፊናቸው ለበዓሉ የሚሆኑ ቁሳቁሶችን ማቅረብ ይጀምራሉ። ይህም የዝግጅት ጊዜ “እንግጫ” በመባል ይጥራል። በ”ዮ--ማስቃላ” ጊዜ አብሮነት እንጂ ግለኝነት የሚባል ነገር በጋሞዎች ዘንድ ፈጽሞ አይታሰብም፤ አብሮ እርድ ማካሄድ፣ አብሮ መመገብ፣ አብሮ መጠጣት፣ አብሮ መጫወት የጋሞዎች መገለጫ ነው። እንደ ሌሎቹ በዓላት ሁሉ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ወገኖችም በዓሉን እንዴት እናሳልፍ የሚል ስጋት አያድርባቸውም። ምክንያቱም የሌለውም ካለው ጋር አብሮ የሚቋደስበት፣ የሚደሰትበት፣ የሚተሳሰብበትና የሰብአዊነት ልክ የሚንጸባረቅበት ልዩ ድባብ ያለው በዓል ነውና ዮ-ማስቃላ ። የጋሞ የሀገር ሽማግሌ አቶ አመሌ አልቶ ስለ “ዮ--ማስቃላ” በዓል በትንሹ እንዲያወጉን ጠይቀናቸው በዓሉ ለሰው ልጆች ብቻ ሳይሆን እንስሳትና አዕዋፋት ሁሉ የሚደሰቱበት እንደሆነ ነግረውናል። በአካባቢው ቋንቋ ተፈጥሮ ሁሉ በዓሉን በደስታ እንደሚያሳልፍ ለመግለጽ “ካፎስ ካናስ ማስቃላ” በማለት የሚገለጽ ስሆን “ለሰው ብቻ ሳይሆን ለእንስሳትም መስቀል ነው” እንደማለት ነው ብለዋል። በዓሉ ከመድረሱ ከሶስት ወራት አስቀድሞ በየአካባቢው ለእንስሳት የግጦሽ ሥፍራ ተከልሎ የሚዘጋጅ ሲሆን ችቦው በሚለኮስበት በደመራው ዕለት የቤት እንስሳት በሙሉ በዚያው የሚሰማሩ ይሆናል። ዓመቱን ሙሉ ሲያርሱ የነበሩ የእርሻ መሣሪያዎችም በበዓሉ ጊዜ ታጥበውና በቅቤ ታሽተው በክብር ይቀመጣሉ። ክብር ለሰው ልጆች ብቻ ሳይሆን ለእንስሳትና ለእርሻ መሣሪያዎችም ይሰጣል። በባህሉ መሠረት ችቦ በሚወጣበት ሰዓት አባት የራሱን ችቦ ለኩሶ የቤቱን ምሰሶ፣ የከብቶችን ጋጣና የበር ጉበኖችን ግራና ቀኝ በችቦው ጫፍ በማነካካት ወደ ውጭ ካወጣ በኋላ ወንድ ልጆች የየራሳቸውን ችቦ ተራ በተራ እየለኮሱ አባታቸውን ተከትለው “ዮ---ማስቃላ” እያሉ ወደ ደመራ ቦታ ያመራሉ። ከዚያም አባት በቅድሚያ ችቦውን ከለኮሰ በኋላ ልጆች ደግሞ ተከትለው ደመራውን ይለኩሳሉ። ከዚህ ፕሮግራም መልስ ወደ ቤት ተመልሰው የተዘጋጀውን ገንፎ በአንድ ወጭት ላይ “ዮ--ማስቃላ”እያሉ ሁሉም የቤተሰብ አባላት፣ ዘመድ አዝማድና ጎረቤት ተሰባስበው በጋራ ይመገባሉ። በ”ዮ--ማስቃላ” በዓል በዋናነት እርድ የሚከወን ሲሆን ቁርጥ፣ ጎረድ ጎረድ፣ ክትፎና የወጣ ወጥ ዓይነቶች ተሠርተው ለምግብነት ይቀርባሉ። ከባህላዊ ምግቦች ደግሞ የገብስ ቅንጬ፣ የቆጮና ገብስ ውህድ ቂጣ፣ የቡላ ፍርፍር፣ ሀረግ ቦዬ፣ እንዲሁም ከመጠጥ አይነቶች ደግሞ ቦርዴ፣ ጠላ፣ የማርና የቦርዴ ጠላ ውህድና ሌሎች ተወዳጅ ምግቦችና መጠጦች ይዘጋጃሉ። በ”ዮ--ማስቃላ” በዓል ዕለት የሚቀራረቡ ጎረቤታሞች በጋራ ሆነው አማካይ በሆነ ሥፍራ ላይ የእርድ ሥነሥርዓት ያከናውናሉ። የእርድ ሥነ-ሥርአቱም በደመራው ዕለትና ማግስት እንደ ህብረተሰቡ ይሁንታ የሚፈጸም ይሆናል። ከማግስቱ ጀምሮ የተዘጋጀውን ሥጋ በጋራ እየበሉና እየጠጡ የበዓሉን ድባብ የሚያስቀጥሉ ሲሆን “ዱንግዛ” በተሰኘው የጋሞ ባህላዊ ጥበብ ልብስ ደምቀው በጌጣጌጥ አሸብርቀው ሁሉም በየአደባባዩ በባህላዊ ጫዋታዎች እየተደሰተ በዓሉን ያከብራል። ሰላም፣ ፍቅር፣ አንድነትና አብሮነት ካለ በአዲሱ ዓመት ምድሪቱ ተገቢውን ምርት እንደምትሰጥ ሁሉም ሰው በተሰማራበት መስክ ውጤታማ እንደሚሆን ይታመናል። ከዚም የተነሳ በአሮጌው ዓመት ሃዘን ላይ የነበሩ ወገኖች ሙሉ በሙሉ ሀዘናቸውን በመተው በአዲስ መንፈስ ወደ መደበኛው ህይወት ይመለሳሉ። የተጣሉ ወገኖች ቂም ይዘው አዲስ ዓመትን መሻገር በጋሞዎች ዘንድ ነውር በመሆኑ በባህላዊ ሸንጎ ሥርአት /ዱቡሻ/ በጋሞ አባቶች አሸማጋይነት እርስ በርስ ተነጋግረው በመታረቅ አዲሱን ዓመት በጋራ ያበስሩታል። በሌላ መንገድ “ዮ..ማስቃላ” በዓል ተጠብቆ ወጣቶች የሚተጫጩበት፣ የተጫጩት ደግሞ ጋብቻ የሚከውኑበት እንዲሁም ያገቡት በየገበያው ዕለት “ሶፌ” የሚባል ሥነ-ሥርዓት በማከናወን በማህበራዊ ህይወት ማህበረሰቡን በይፋ የሚቀላቀሉበት መሆኑን ጋሽ አመሌ አውግተውናል። ጋሞዎች ከሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ጋር በመሆን በአብሮነት ለሁለት ሳምንታት በደስታ ካሳለፉ በኋላ ወደ ግብርና ሥራቸው በመመለስ ቀደም ሲል በክብር ያስቀመጧቸውን የእርሻ መሣሪያዎች በማንሳት ወደ እርሻ ሥራ ይገባሉ። እስከ ታህሳስ ወር መውጫ ድረስ የበዓሉ ድባብ ሳይጠፋ ይቆይና በመጨረሻም የመሰናበቻ ድግስ ወይም “ጮዬ ማስቃላ” በማዘጋጀት በህብረት ከተመገቡና ከጠጡ በኋላ የዓመት ሰው ይበለን፣ ዓመቱ የሰላም፣ የጤና፣ የበረከት ይሁን በማለት በመመራረቅ “ዮ--ማስቃላ”ን ይሸኛሉ። በዓሉ የህዝቡን ሰላም ፣አንድነትና አብሮነት የሚያንጸባርቅ ልዩ በዓል ነው በማለት የጋሞ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ሃላፊ አቶ ሞናዬ ሞሶሌ የጋሞ የሀገር ሽማግሌ የሆኑት የአቶ አመሌ አልቶን ሃሳብ ይጋራሉ። ባህላዊ እሴቱ ከትውልድ ወደ ትውልድ ተጠብቆ እንዲቆይ “ዮ--ማስቃላ” ትልቅ ድርሻ አለው። የባህል እሴቶች ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፉ በጥናትና ምርምር በማስገፍና የቋንቋና ባህል አውደ ጥናት በየዓመቱ እየተደረገ እንደሆነም ነግረውናል። አባቶች በልዩነት ውስጥ ያለንን አንድነት እንዳቆዩልን ሁሉ ወጣቶችም ኢትዮጵያዊ ለዛ ያላቸው የጋራ እሴቶች ሳይበረዙና ሳይከለሱ ጠብቀው ለትውልድ የማስተላለፍ ሃላፊነት አለባቸው የሚለውን የንግግራቸው ማሳረጊያ አድርገዋል።