ቀጥታ፡
አርእስተ ዜና
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤዎች የሥራ ርክክብ አካሄዱ
Oct 9, 2026 75
አዲስ አበባ፤ መስከረም 29/2019 (ኢዜአ) ፦ የኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አህመድ ሺዴ ከቀድሞው አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ጋር የሥራ ርክክብ አካሂደዋል። በርክክቡ ወቅትም አፈ ጉባኤ አህመድ ሽዴ እንደገለጹት የቀድሞ አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ እና የቀድሞ ምክትል አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ሎሚ በዶ ላለፉት አመታት የተጣለባቸውን ምክር ቤታዊ ኃላፊነት በቅንነት፣ በታታሪነት እና በመግባባት መንፈስ ተወጥተዋል። ሁለቱም አፈ-ጉባኤዎች ለህዝብና ለሀገራቸው ላበረከቱት አስተዋፅኦ ያመሰገኑት አቶ አሕመድ ሽዴ በቀጣይም ምክር ቤቱ የተጀመሩ ስራዎችን ይበልጥ በማጠናከር እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡   የቀድሞ አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ እና የቀድሞ ምክትል አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ሎሚ በዶ በምክር ቤት ቆይታቸው የተለያዩ ተግዳሮቶችን በመወጣት የሪፎርም ስራዎችን ጨምሮ በርካታ ተግባራትን ማከናወናቸውን አብራርተዋል፡፡ በምክር ቤቱ በነበራቸው ቆይታ ምክር ቤቱን እና የምክር ቤቱን ጽሕፈት ቤት አመራሮችን በማመስገን፤ የ7ኛው ምክር ቤት አፈ-ጉባኤዎችም መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡   በስራ ርክክቡ ወቅት ምክትል አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ አየለች እሸቴ እና የምክር ቤቱ ጽሕፈት ቤት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
የሚታይ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤዎች የሥራ ርክክብ አካሄዱ
Oct 9, 2026 75
አዲስ አበባ፤ መስከረም 29/2019 (ኢዜአ) ፦ የኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አህመድ ሺዴ ከቀድሞው አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ጋር የሥራ ርክክብ አካሂደዋል። በርክክቡ ወቅትም አፈ ጉባኤ አህመድ ሽዴ እንደገለጹት የቀድሞ አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ እና የቀድሞ ምክትል አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ሎሚ በዶ ላለፉት አመታት የተጣለባቸውን ምክር ቤታዊ ኃላፊነት በቅንነት፣ በታታሪነት እና በመግባባት መንፈስ ተወጥተዋል። ሁለቱም አፈ-ጉባኤዎች ለህዝብና ለሀገራቸው ላበረከቱት አስተዋፅኦ ያመሰገኑት አቶ አሕመድ ሽዴ በቀጣይም ምክር ቤቱ የተጀመሩ ስራዎችን ይበልጥ በማጠናከር እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡   የቀድሞ አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ እና የቀድሞ ምክትል አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ሎሚ በዶ በምክር ቤት ቆይታቸው የተለያዩ ተግዳሮቶችን በመወጣት የሪፎርም ስራዎችን ጨምሮ በርካታ ተግባራትን ማከናወናቸውን አብራርተዋል፡፡ በምክር ቤቱ በነበራቸው ቆይታ ምክር ቤቱን እና የምክር ቤቱን ጽሕፈት ቤት አመራሮችን በማመስገን፤ የ7ኛው ምክር ቤት አፈ-ጉባኤዎችም መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡   በስራ ርክክቡ ወቅት ምክትል አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ አየለች እሸቴ እና የምክር ቤቱ ጽሕፈት ቤት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

Pulse Of Africa

POA English

POA English

Pulse Of Africa - English Language

Your news, current affairs and entertainment channel

Join us on

POA Arabic

POA Arabic - عربي

Pulse Of Africa - Arabic Language

قناتكم الاخبارية و الترفيهية

Join us on

ፖለቲካ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤዎች የሥራ ርክክብ አካሄዱ
Oct 9, 2026 75
አዲስ አበባ፤ መስከረም 29/2019 (ኢዜአ) ፦ የኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አህመድ ሺዴ ከቀድሞው አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ጋር የሥራ ርክክብ አካሂደዋል። በርክክቡ ወቅትም አፈ ጉባኤ አህመድ ሽዴ እንደገለጹት የቀድሞ አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ እና የቀድሞ ምክትል አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ሎሚ በዶ ላለፉት አመታት የተጣለባቸውን ምክር ቤታዊ ኃላፊነት በቅንነት፣ በታታሪነት እና በመግባባት መንፈስ ተወጥተዋል። ሁለቱም አፈ-ጉባኤዎች ለህዝብና ለሀገራቸው ላበረከቱት አስተዋፅኦ ያመሰገኑት አቶ አሕመድ ሽዴ በቀጣይም ምክር ቤቱ የተጀመሩ ስራዎችን ይበልጥ በማጠናከር እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡   የቀድሞ አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ እና የቀድሞ ምክትል አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ሎሚ በዶ በምክር ቤት ቆይታቸው የተለያዩ ተግዳሮቶችን በመወጣት የሪፎርም ስራዎችን ጨምሮ በርካታ ተግባራትን ማከናወናቸውን አብራርተዋል፡፡ በምክር ቤቱ በነበራቸው ቆይታ ምክር ቤቱን እና የምክር ቤቱን ጽሕፈት ቤት አመራሮችን በማመስገን፤ የ7ኛው ምክር ቤት አፈ-ጉባኤዎችም መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡   በስራ ርክክቡ ወቅት ምክትል አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ አየለች እሸቴ እና የምክር ቤቱ ጽሕፈት ቤት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
ፖለቲካ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤዎች የሥራ ርክክብ አካሄዱ
Oct 9, 2026 75
አዲስ አበባ፤ መስከረም 29/2019 (ኢዜአ) ፦ የኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አህመድ ሺዴ ከቀድሞው አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ጋር የሥራ ርክክብ አካሂደዋል። በርክክቡ ወቅትም አፈ ጉባኤ አህመድ ሽዴ እንደገለጹት የቀድሞ አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ እና የቀድሞ ምክትል አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ሎሚ በዶ ላለፉት አመታት የተጣለባቸውን ምክር ቤታዊ ኃላፊነት በቅንነት፣ በታታሪነት እና በመግባባት መንፈስ ተወጥተዋል። ሁለቱም አፈ-ጉባኤዎች ለህዝብና ለሀገራቸው ላበረከቱት አስተዋፅኦ ያመሰገኑት አቶ አሕመድ ሽዴ በቀጣይም ምክር ቤቱ የተጀመሩ ስራዎችን ይበልጥ በማጠናከር እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡   የቀድሞ አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ እና የቀድሞ ምክትል አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ሎሚ በዶ በምክር ቤት ቆይታቸው የተለያዩ ተግዳሮቶችን በመወጣት የሪፎርም ስራዎችን ጨምሮ በርካታ ተግባራትን ማከናወናቸውን አብራርተዋል፡፡ በምክር ቤቱ በነበራቸው ቆይታ ምክር ቤቱን እና የምክር ቤቱን ጽሕፈት ቤት አመራሮችን በማመስገን፤ የ7ኛው ምክር ቤት አፈ-ጉባኤዎችም መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡   በስራ ርክክቡ ወቅት ምክትል አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ አየለች እሸቴ እና የምክር ቤቱ ጽሕፈት ቤት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
ማህበራዊ
በአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖ ምክንያት ድጋፍ ለሚፈልጉ ወገኖች የሰብአዊ ድጋፍ እየተጓጓዘ ነው
Oct 9, 2026 80
አዳማ ፣መስከረም 29/2019 (ኢዜአ)፡- በአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖ ምክንያት ድጋፍ ለሚፈልጉ ወገኖች መንግስት በራስ አቅም የሰብአዊ ድጋፍ ተደራሽ እያደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ። በዛሬው እለት ከአዳማ የእህል ማከማቻ ማእከላዊ መጋዘን የተጫነ አስቸኳይ ሰብአዊ ድጋፍ ወደተለያዩ የሀገሪቷ አካባቢዎች በመጓጓዝ ላይ ይገኛል። ለተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ክልሎች በራሳቸው አቅም ምላሽ ለመስጠት እየተረባረቡ ሲሆን ኮሚሽኑም የቅድሚያ ቅድሚያ በሚሰጣቸው አካባቢዎች ተጨማሪ የሰብአዊ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል።   ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም ሲያደርግ የነበረውን ድጋፍ በማጠናከር ለተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ፈጣን ምላሽ እየሰጠ መሆኑን ገልጿል። በዚህም የቅድሚያ ቅድሚያ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች የተለየ ትኩረት በመስጠት ሰብአዊ ድጋፍ የማድረስ ስራ እየተሰራ መሆኑን ኮሚሽኑ አመላክቷል። ክልሎች በራሳቸው አቅም የሚያደርጉት ድጋፍና ክትትል እንደተጠበቀ ሆኖ ኮሚሽኑም የሚመከታቸውን የፌዴራል መንግስት ሴክተር መስሪያ ቤቶች በማስተባበር የቅርብ ድጋፍና ክትትል እያደረገ ይገኛል። በዛሬው እለትም ከአዳማ የመጠባበቂያ መጋዘን ሰብአዊ ድጋፍ የጫኑ ተሽከርካሪዎች የቅድሚያ ቅድሚያ ወደተሰጣቸው አካባቢዎች ተንቀሳቅሰዋል።  
በደቡብ ኦሞ ዞን በክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ከ450 ሺህ በላይ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል
Oct 9, 2026 117
ጂንካ፤ መስከረም 29/2019(ኢዜአ)፡-በደቡብ ኦሞ ዞን በክረምት ወራት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ከ450 ሺህ በላይ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ያደረጉ የልማት ተግባራት መከናወናቸውን የዞኑ በጎ ፈቃድ አገልግሎት ጽሕፈት ቤት አስታወቀ። በዞኑ በክረምት ወራት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ግለሰቦችና ተቋማት ዛሬ በዲመካ ከተማ እውቅና ተሰጥቷል።   የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ እንዳሉት የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት እርስ በርስ የመረዳዳት ባህልን እያሳደገ መጥቷል፡፡ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ የአንድ ሰሞን ርብርብ ብቻ ሳይሆን በተቋማዊ አሰራር እና ዕቅድ ተካቶ ሁልጊዜ የሚተገበር መሆን እንዳለበት አንስተዋል። በዞኑ በጎ ፍቃደኞች በክረምት ወራት ላበረከቱት አስተዋጽኦ አመስግነው፤ ወጣቶች፣ ሴቶችና የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ የተጀመሩ በጎ ሥራዎችን ዘላቂ ማድረግ ይገባል ብለዋል። የደቡብ ኦሞ ዞን በጎ ፈቃድ አገልግሎት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኤልያስ ሰዕሲ፤ የ2018 የክረምት ወራት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት በ20 የትኩረት መስኮች ሲከናወን መቆየቱን አንስተዋል። በልማት ሥራዎቹም ከ143 ሺህ በላይ ወጣቶችን እና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎችን ለማሳተፍ መቻሉን ጠቅሰዋል። በልማት ስራዎቹ ከ450 ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ያሉት ኃላፊው፣ በዚህም ከመንግሥት ሊወጣ የነበረን ከ93 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ማዳን ተችሏል ብለዋል። የአረጋውያን ቤት እድሳት፣ የአረንጓዴ አሻራ፣ የደም ልገሳ፣ የአካባቢ ፅዳት፣ ለአቅመ ደካሞች ማዕድ ማጋራት እና ሌሎችም ተግባራት ከተከናወኑት የልማት ሥራዎች መካከል በዋናነት እንደሚጠቀሱም ገልጸዋል። በበጎ ፍቃድ ስራዎች ላይ የተሳተፉት ወጣት ስጦታው አመዴ እና ራሔል ታደሰ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ለህሊና እርካታ የሚሰጥና በፈጣሪ ዘንድም ዋጋ ያለው አበርክቶ መሆኑን ተናግራለች። በክረምት ወራት ወጣቶች የአረጋውያንን ቤት በማደስ፣ ደም በመለገስ እና በተራቆቱ አካባቢዎች ችግኝ በመትከል ተሳትፎ ማድረጋቸውን ጠቁመው፣ በዚህም ደስተኛ መሆናን ገልጻለች።   በዞኑ የተሰጠው ዕውቀትና ሽልማትም ተግባሩን በበጋ ወራት አጠናክረው እንዲቀጥሉ መነሳሳት እንደፈጠረላቸውም ተናግራለች።፡ በበጎ ፍቃድ አገልግሎቱ የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የዞኑ የሥራ ኃላፊዎች፣ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች እንዲሁም ተቋማት ዕውቅና ሽልማት ተሰጥቷል።      
በክልሉ የዳኝነት አገልግሎት ተደራሽና ፍትሐዊ ለማድረግ የተጀመረው የሪፎርም ስራ ውጤት አስገኝቷል
Oct 9, 2026 206
ባህርዳር፤ መስከረም 29/2019 (ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል የዳኝነት አገልግሎትን ፍትሐዊና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ተግባራዊ የተደረገው የሪፎርም ስራ ውጤታማ መሆኑን የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት አቶ ቴዎድሮስ ምህረት ገለጹ። "የዳኝነት ተደራሽነትን ማስፋት፤ አገልግሎትን ማላቅ" በሚል መሪ ሐሳብ ለ10 ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆየው የአማራ ክልል ፍርድ ቤት ዳኞች 2ኛው ዓመታዊ ጉባኤ ዛሬ ተጠናቋል።   ፕሬዝዳንቱ አቶ ቴዎድሮስ ምሕረት በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ባለፉት ዓመታት የዳኝነት ሥርዓቱን ዘመናዊና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ለማድረግ በሀገር አቀፍ ደረጃ ሪፎርም ተካሂዷል። ሪፎርሙ ተግባራዊ በማድረግም የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች በአጭር ጊዜ ውስጥ ያሳዩት መሻሻል እና ለውጥ ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን ነው ብለዋል። ፍርድ ቤቶች ተቀራራቢ በሆነ ደረጃ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል እና ለዚህ የሚሆን ቁመና ላይ እንዲገኙ ለማድረግም በትኩረት ሲሰራ እንደነበር አመልክተዋል። የክልሉ ፍርድ ቤቶች ከተደራሽነት፣ ከዲጂታላይዜሽን፣ ከአገልግሎት አሰጣጥ፣ ከቅልጥፍና እና አመቺ የሥራ ቦታ ከመፍጠር አንጻር እመርታዎች ማሳየታቸውን አስረድተዋል። ዜጎች ቀልጣፋ እና ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲያገኙ ዲጂታላይዜሽንን ማጠናከር እንደሚገባም ነው የተናገሩት። የዳኞችን ሙያዊ ሥነ ምግባርና ክህሎት በማሳደግ ነፃ፣ ከአድሎና ከብልሹ አሰራር የጸዳ ፍትሕን ተደራሽ ማድረግ እንደሚገባም ነው አቶ ቴዎድሮስ ያብራሩት። የዲጂታል አሠራርን ወደ ታች በማውረድ ሁሉንም ሕብረተሰብ የፍትሕ አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ የክልሉ መንግሥት የጀመረውን ድጋፍ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ነው ያሳሰቡት።   የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ዓለምአንተ አግደው በበኩላቸው የዳኝነት አገልግሎቱን በቴክኖሎጂ በማስደገፍ እየተከናወነ ባለው ሥራ አመርቂ ውጤት መመዝገቡን ገልጸዋል። የፍርድ ቤቶችን የአገልግሎት አሰጣጥ ፈጣን፣ ፍትሐዊና ተአማኒነት ያለው ለማድረግ የተጀመረውን የሪፎርም ሥራ ዳር ለማድረስ በተለይ ትኩረት እየተሠራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በሁለንተናዊ የልማት ጉዞዋ እና በቀዳማይ ልጅነት ልማት ያስመዘገበችው ስኬት ለአፍሪካ አዲስ የተስፋ ምዕራፍ ነው
Oct 9, 2026 168
አዲስ አበባ፤ መስከረም 29/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በሁለንተናዊ የልማት ጉዞዋ እና በቀዳማይ ልጅነት ልማት ያስመዘገበችው አስደናቂ ስኬት አፍሪካን ሊያስተሳስር የሚችል አዲስ የተስፋ ምዕራፍ ነው ሲሉ የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዚዳንት ካሺም ሸቲማ ገለጹ። በናይጄሪያ ምክትል ፕሬዚዳንት ካሺም ሸቲማ የሚመራ ሉዑክ በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛል። ልዑኩ በዛሬው እለት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጋር በህጻናት እድገትና በከተማ ልማት ዙሪያ የልምድ ልውውጥ መድረክ አካሂደዋል፡፡   የናይጄሪያው ምክትል ፕሬዚዳንት ካሺም ሸቲማ በውይይቱ ወቅት፤ ስለኢትዮጵያ እና አዲስ አበባ ውጤታማ የልማት ሥራዎች እንዲሁም በቀዳማይ ልጅነት ልማት ለተመዘገበው ውጤት አድናቆታቸውን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ እድገት የሚታይና የሚጨበጥ መሆኑን በመጠቆም የኢትዮጵያ መንግሥት ለልጆች እንክብካቤ እና ለቀዳማይ ልጅነት ልማት የሰጠውን ትኩረት አድንቀዋል። በኢትዮጵያ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎችና የሕፃናት እንክብካቤ አሰራሮች ለብዙዎች ሕይወት መሻሻል ትልቅ አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ መሆናቸውን ተናግረዋል።   ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሕዝባቸው ተጠቃሚነትና ደህንነት ቅድሚያ ሰጥተው መሥራታቸውንም ምክትል ፕሬዝዳንቱ አወድሰዋል። ናይጄሪያ እና ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች በጋራ በመስራት አወንታዊ ተጽዕኖ መፍጠር ከቻሉ ይህ ክፍለ ዘመን የአፍሪካ ክፍለ ዘመን እንደሚሆንም እምነታቸውን ገልጸዋል። አፍሪካ ከቀድሞው የግብርና እና የኢንዱስትሪ ዘመን አልፋ አሁን በእውቀት ላይ በተመሰረተው ሰው ሰራሽ አስተውሎትና በትላልቅ መረጃዎች ዘመን ውስጥ እንድትገባ የወጣቶችን አእምሯዊ አቅም ማሳደግ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል። የናይጄሪያ መንግሥትና ሕዝብ ውጤታማ ከሆኑ ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎች ለመማር እና ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ትብብር ለማጠናከር ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል።
ኢኮኖሚ
የሕንድና አፍሪካ የረጅም ዘመን ትብብር በሕንድ ቪክሲት 2047 ርዕይና በአፍሪካ ሕብረት አጀንዳ 2063 ትብብር ተጠናክሮ የሚቀጥል ነው
Oct 9, 2026 143
አዲስ አበባ፤ መስከረም 29 /2019 (ኢዜአ)፦ የሕንድና አፍሪካ የረጅም ዘመን ትብብር በሕንድ ቪክሲት 2047 ርዕይና በአፍሪካ ሕብረት አጀንዳ 2063 ትብብር ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን የሕንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሱብራህማንያም ጃይሻንካር (ዶ/ር) ገለጹ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር በሕንድ-አፍሪካ ትብብር ላይ ያተኮረ መድረክ በዓድዋ ድል መታሰቢያ አዘጋጅቷል።   በመድረኩ ላይ የመከላከያ ሚኒስትር መሀመድ ኢድሪስን ጨምሮ አምባሳደሮችና የዘርፉ ምሁራን የተገኙ ሲሆን የሕንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሱብራህማንያም ጃይሻንካር (ዶ/ር) ንግግር አድርገዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው፤ በታሪካዊው የዓድዋ ድል መታሰቢያ በመገኘታቸው ኩራት እንደተሰማቸው ገልጸዋል። የዓድዋ ድል የኢትዮጵያ የድል ታሪክ ብቻ አይደለም ያሉት ሚኒስትሩ፤ የአፍሪካና የመላው ጥቁር ሕዝቦች የነፃነትና የአሸናፊነት ምልክት መሆኑን ተናግረዋል። ዓድዋ ለሰብዓዊ ክብር መዋደቅ፣ ለሉዓላዊነት መታገል፣ ለፖለቲካ ነፃነት መሟገት በራስ አቅም የመወሰን ማሳያ መሆኑንም አንስተዋል። ሕንድና አፍሪካ በቅኝ ገዥዎች አማካኝነት ሰብዓዊ ኪሳራ እንደደረሰባቸው፣ ሀብታቸው እንደተመዘበረባቸው ገልጸው፤ በመካከላቸው የሕንድ ውቅያኖስ የማይጋርደው ዘመን ተሻጋሪ ግንኙነት አላቸው ብለዋል። የሕንድ ውቅያኖስ ውኃ ብቻ ሳይሆን የሕንድና አፍሪካ የሰብዓዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ግንኙነት ማሳለጫ የፍጥነት መንገድ መሆኑን ገልጸዋል። ሕንድና አፍሪካ በሙዚቃ፣ በባህል፣ በአስተሳሰብና በአገር በሕንድ ውቅያኖስ የተሳሰሩ ናቸው ብለዋል። በመካከላቸው ያለው የነፃነት ታሪክ የተሳሰረ መሆኑን በማንሳት፤ በተቋማት ግንባታና በመሠረተ ልማት ዝርጋታ ያላቸው ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። የዓለም ነባራዊ ሁኔታ መቀየሩን ገልጸው፤ ትብብራቸውም በደቡባዊ ዓለም ማዕቀፍ በዚያው ልክ ማደግ አለበት ብለዋል።   የሕንድ ቪክሲት (VikSit Bharat) 2047 ርዕይ ከአፍሪካ ሕብረት አጀንዳ 2063 ጋር ጎን ለጎን የሚሄድ ሳይሆን ተጣጥሞ የሚመራ ትልቅ ግብ መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም የአፍሪካና የሕንድ የንግድ ግንኙነት መገደብ የለብንም፤ በመሠረተ ልማት፣ በቴክኖሎጂ፣ በግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በቴሌኮም እና በመሰል ዘርፎች ያለውን ትብብር ማጠናከር ይገባል ብለዋል። በኢትዮጵያና በሕንድ መካከል ያለው የንግድ ግንኙነት ደግሞ በአክሱማዊት ሥልጣኔና በአዱሊስ ወደብ ንግድ የሚመነጭ የረጅም ጊዜ ትብብር መሆኑን አንስተዋል። በኢትዮጵያና በሕንድ መካከል ያሉት የትምህርትና ሥልጠና ግንኙነት ከመደበኛ ዲፕሎማሲ የተሻገረ መሆኑን ገልጸው፤ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሁለቱ ሀገራት ሁለንተናዊ ግንኙነት እየተጠናከረ መጥቷል ብለዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና በሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሙዲ መሪነት የሁለቱ ሀገራት የግንኙነት ሽግግር በፍጥነት እየተጓዘ መሆኑን ገልጸዋል። በኢትዮጵያ 600 በላይ የሕንድ ኩባንያዎች በተለያዩ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፎች ተሰማርተው እንደሚገኙ ገልጸው፤ ከ75 ሺህ በላይ የሥራ ዕድል ፈጥረዋል ብለዋል። ከኢትዮጵያ ጋር በኢነርጂ፣ በግብርና፣ በሕክምና መገልገያና መድኃኒት፣ እንዲሁም በስኳር ፕሮጀክት በጋራ እየሠሩ መሆኑን ገልጸዋል። ሕንድና ኢትዮጵያ በብሪክስ እና በአየር ንብረት ለውጥ እርምጃ ያላቸውን ትብብር አጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።
ሀገራዊ ቀጣይ የልማት ግቦችን ለማሳካት ሁሉም ዜጋ በተደመረ አቅምና ትብብር መስራት አለበት-ምሁራን
Oct 9, 2026 112
ጋምቤላ፤ መስከረም 29/ 2019 (ኢዜአ)፡- ሀገራዊ ቀጣይ የልማት ግቦችን ለማሳካት ሁሉም ዜጋ በተደመረ አቅምና በትብብር ሊሰራ ይገባል ሲሉ የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ገለጹ። ትልቅ ሀገር፤ ትልቅ ህዝብ፤ ታላቅ ርዕይ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመደመር መንግስት ምስረታ ዳግም በጠቅላይ ሚኒስትርነት ሲሰየሙ በሚቀጥሉት ዓመታት መንግስት ለመተግበር ያቀዳቸውን ዋና ዋና የልማት ግቦች ይፋ አድርገዋል። በጉዳዩ ላይ ኢዜአ ያነጋገራቸው የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ምሁራንም ሀገርን ወደ ተሻለ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ መዋቅራዊ ሽግግር የሚያደርሱ እነዚህን የልማት ግብች ለማሳካት ዜጎች በተደመረ አቅምና ትብብር ሊሰሩ ይገባል ብለዋል። ባለፉት አምስት ዓመታት በሁሉም ዘርፎች የታዩ የልማት ስኬቶችን አጠናክሮ ማስቀጠል የሀገሪቱን እድገትና ብልጽግና ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግርም ተናግረዋል። ከዩኒቨርሲቲው ምሁራን መካከል ጀምበሩ ዓለሙ (ዶ/ር) እንዳሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ ያደረጓቸው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የልማት አቅጣጫዎች በተደመረ አቅምና በትብብር እውን ማድረግ ይገባናል ብለዋል። በተለይም በምግብ ዋስትና፣ በመኖሪያ ቤት ግንባታ፣ በመሰረተ ልማትና በሌሎችም ዘርፎች የታለሙትን የልማት ግቦች ዳር ለማድረስ የሁሉም ዜጋ ትብብር ያስፈልጋል ብለዋል። በመደመር መንግስት የተያዙ የልማት ግቦች ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ ስኬቶችን የሚያጠናክሩና ለሀገሪቱ ህዝቦች ትልቅ ተስፋን የሚሰጡ መሆናቸውንም ገልጸዋል። እንደሀገር በቀጣይ ለማከናወን የተያዙ የልማት ግቦችን ውጤታማ ለማድረግ ዘመኑ የሚጠይቀውን የቴክኖሎጂ ክህሎት የተላበሰ ማህበረሰብ መገንባት ወሳኝ መሆኑን ገልጸው፣ ለዚህም ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የድርሻችንን እንወጣለን ብለዋል። መንግስትም የህዝብን አንድነትና አብሮነት በማጠናከር ህዝቡ በተደመረ አቅም ልማት ላይ እንዲረባረብ ማድረግ ይኖርበታል ሲሉም ምሁሩ ገልጸዋል።   ሌላው የዩኒቨርሲቲ ምሁር ጌታቸው በቀለ (ዶ/ር) እንዳሉት በቀጣይ ዓመታት ሊተገበሩ የታቀዱት የልማት ግቦች ዘላቂና ቀጣይነት ያለው ሀገራዊ ልማትን የሚያረጋግጡ ናቸው። የልማት ዕቅዶቹ በተለይም ባለፉት ዓመታት የተጀመሩ የአርንጓዴ አሻራ፣ የመንገድ፣ የኢነርጂና ሌሎች የልማት ሥራዎችን ይበልጥ የሚያጎለብቱ መሆናቸውንም ገልጸዋል። በመሆኑም በመንግስት የተያዙ የልማት ዕቅዶችን ስኬታማ ለማድረግ ሁሉም ዜጋ በትብብርና በአንድነት ሊሰራ እንደሚገባ አመልክተዋል። ለዕቅዱ መሳካት የበኩላቸውን ለመወጣት እንደሚሰሩም ጌታቸው (ዶ/ር) አክለው ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በሰጥቶ መቀበል መርህ የባህር በር ባለቤት ለመሆን የምታደርገው ጥረት ለቀጣናው ሰላም ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው
Oct 9, 2026 208
ዲላ፤ መስከረም 29/2019 (ኢዜአ) ፦ኢትዮጵያ በሰጥቶ መቀበል መርህ የባህር በር ባለቤት ለመሆን እያደረገች ያለው ጥረት ለቀጠናው ሰላምና መረጋጋት ያላትን ቁርጠኝነት ያሳያል ሲሉ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ገለጹ። የኢትዮጵያን ባህር በር ባለቤትነት ለማሳካት በተለያየ መስክ እየተደረገ ያለውን ጥረት ለማገዝ ዝግጁ መሆናቸውንም ምሁራኑ አረጋግጠዋል። በሰጥቶ መቀበል መርህ በሰላማዊ መንገድ የባህር በር ባለቤት ለመሆን እያደረገች ያለው ጥረት ለቀጣናው ሰላም መጠበቅ ያላትን ቁርጠኝነት ያሳያል ሲሉም ምሁራን ገልጸዋል። በዲላ ዩኒቨርሲቲ የታሪክና ቅርስ አስተዳደር መምህርና ተመራማሪ ገመቹ ኦላኒ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ በሴራ የባህር በር ባለቤትነቷን ማጣቷን አንስተዋል።   ያጣቸውን ሃብቷን መልሳ ለማግኘት በሰላማዊ መንገድ የምታደርገውን ጥረት ዓለም አቀፍ ማህበረሰቡ ተረድቶ ድጋፉን እያሳየ መምጣቱን አስረድተዋል። በተለይ በሰጥቶ መቀበል መርህ፣ በጋራ ተጠቃሚነትና ዲፕሎማሲያዊ በሆነ መንገድ የባህር በር ባለቤት ለመሆን እያደረገች ያለው ጥረት ዓለም አቀፍ ህግን ያከበረ ከመሆን ባለፈ ለቀጣናው ሰላም ያላትን ፍላጎት ያሳያል ብለዋል።   የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ለዜጎች የዘመናት ቁጭት ምላሽ የሚሰጥ ነው ያሉት ደግሞ በዩኒቨርሲቲው የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ መምህርና ተመራማሪ ረዳት ፕሮፌሰር ማስረሻ ኤራጓ (ዶ/ር) ናቸው። ኢትዮጵያ የባህር በሯን ያጣችበት መንገድ አግባብ እንዳልሆነ ገልጸው፣ የተፈጥሮን ሃብት በሰጥቶ መቀበል መርህ በጋራ የመጠቀም ዓለም አቀፍ የሕግ ድጋፍ ጭምር እንዳላት ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በሰላማዊና ዲፕሎማሲያዊ መንገድ የባህር በር ባለቤት ለመሆን የምታደርገው ጥረት ዓለም አቀፍ ተቀባይነት እያገኘ መምጣቱንም ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ተገቢ ምላሽ እንዲያገኝ መንግስትና ህዝብ እያደረጉ ያሉትን ጥረት ማጠናከር እንዳለባቸው የገለጹት ፕሮፌሰር ማስረሻ (ዶ/ር)፣ ለዚህም የበኩላቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል።
የመንግሥት እቅዶችና የወደፊት ትልሞች የዜጎችን ህይወት መለወጥ የሚያስችሉ ናቸው
Oct 9, 2026 270
አምቦ፤ መስከረም 29/2019 (ኢዜአ) ፦ የመደመር መንግሥት የያዛቸው እቅዶችና የወደፊት ትልሞች ሀገርን ከድህነት የሚያወጡና የዜጎችን ህይወት መለወጥ የሚያስችሉ መሆናቸውን የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ገለጹ። በብዝሃ ዘርፍ እየተመራ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከስብራት ወደ እድገትና ማንሰራራት እያመራ መሆኑን ተጨባጭ ውጤቶቹ ያመላክታሉ። በግብርና ዘርፍ ከሀገር ውስጥ ፍጆታ ያለፈ የስንዴ ምርት ማምረት የተቻለበት፤ የቡና ምርት በታሪክ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ገቢ የተገኘበት እንዲሁም የማእድን ዘርፍ የሀገር ኢኮኖሚ አቅም ሆኗል። በቱሪዝም፣ ዲጅታላይዜሽንና የኢንዱስትሪ ዘርፍም የሚታዩና የሚጨበጡ ውጤቶች እየተመዘገቡበት መሆኑ ይታወቃል። በኢትዮጵያ አጠቃላይ ምጣኔ ሃብትና የልማት እንቅስቃሴ በተመለከተ ኢዜአ ያነጋገራቸው የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን በብዝሃ ዘርፎች የሚታዩ ውጤቶች እየተመዘገቡ ስለመሆኑ ገልጸዋል። በዩኒቨርሲቲው የምጣኔ ኃብት መምህር ታደለ መላኩ (ደ/ር)፤ በመደመር መንግስት በተለይም በግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ቱሪዝም፣ ማእድን፣ ዲጅታላይዜሽንና ሌሎችም እየተመዘገበ ያለውን ስኬት አድንቀዋል። በአዳዲስ ኢንሸቲቮች እየታገዘ የቀጠለው የግብርና ዘርፍ ምርታማነትን በማሳደግ በምግብ እራስን የመቻል እቅድ ለማሳካት የሚያስችል መሆኑን አንስተዋል። በስራ እድል ፈጠራ፣ በከተሞችና የገጠር ልማት፣ በአካባቢ ጥበቃና የአረንጓዴ ልማት እመርታዊ ስኬት መመዝገቡንም ገልጸዋል። በመሆኑም የመደመር መንግሥት የያዛቸው እቅዶችና የወደፊት ትልሞች ሀገረን ከድህነት የሚያወጡና የዜጎችን ህይወት መለወጥ የሚያስችሉ መሆናቸውን ተናግረዋል። በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክተር ናኦል በቀለ (ዶ/ር)፤ በዲጅታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ የመጣው ለውጥና የተመዘገበው ስኬት ብዙ ሊባልለት የሚችል መሆኑን ገልጸዋል። በጥቂት ዓመታት የዲጅታል ልማት ስትራቴጂው በመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ፣ በፋይናንስ ተቋማትና ሌሎችም ሴክተሮች ላይ ያመጣውን ፈጣን ለውጥ በቀላሉ ማየት አይቻልም ብለዋል። በመተግበር ላይ የሚገኘው ዲጅታል ኢትዮጵያ 2030 በዘርፉ ትልቅ እመርታ የሚያመጣ መሆኑን በማንሳት በዚህ ረገድ የመንግስትን ተግባራዊ እንቅስቃሴ አድንቀዋል።
ቪዲዮዎች
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
ኢትዮጵያ ለሰው ሰራሽ አስተውሎት የሰጠችው ትኩረት ለአፍሪካ ሀገራት ትልቅ አርዓያነት ያለው ስራ ነው
Oct 9, 2026 67
አዲስ አበባ፤ መስከረም 29/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ለሰው ሰራሽ አስተውሎት የሰጠችው ትኩረት ለአፍሪካ ሀገራት ትልቅ አርዓያነት ያለው ተግባር መሆኑን የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዝዳንት ካሺም ሼቲማ ገለጹ። ምክትል ፕሬዝዳንቱ በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጉብኝት አድርገዋል። የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) በጉብኝቱ ወቅት ተቋሙ በአገልግሎት፣ በግብርና፣ በጤና፣ በትምህርት እና በሌሎች ዘርፎች የሰው ሰራሽ አስተዉሎት ቴክኖሎጂ የምርምርና ልማት ስራዎች ያስመዘገባቸውን ስኬቶች አስመልክቶ ገለጻ አድርገዋል። በተጨማሪም ኢንስቲትዩቱ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂን ለማሳካት እያከናወነ የሚገኘውን የቴክኖሎጂ ምርምርና ልማት ስራዎችን በተመለከተም ማብራሪያ ሰጥተዋል። የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዝዳንት ካሺም ሼቲማ ኢትዮጵያ ለአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ የሰጠችው ትኩረት ለአፍሪካ ሀገራት ትልቅ አርዓያነት ያለው ስራ መሆኑን አመልክተዋል። የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት መጠናከር ለአፍሪካ የሚተርፍ ትሩፋት እንዳለው መግለጻቸውን የኢንስቲትዩቱ መረጃ ያመለክታል።
ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር ከጥቅምት 1 ጀምሮ ለአንድ ወር ይከበራል
Oct 9, 2026 128
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 29/2019 (ኢዜአ) ፦ የማህበረሰቡን የሳይበር ደህንነት ግንዛቤ ማሳደግን ዓላማ ያደረገው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር ከጥቅምት 1 እስክ 30 ቀን 2019 ዓም እንደሚከበር የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር አስታወቀ። ‎ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) “ንቁ ዜጋ ደህንነቷ ለተጠበቀ ሀገር” በሚል መሪ ሀሳብ ለቀጣይ አንድ ወር የሚከበረውን 7ኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወርን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሃሚድ በመግለጫቸው፣ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት በፍጥነት ማደጉን ተከትሎ በዜጎች፣ በተቋማትና ቁልፍ መሠረተ ልማቶች ላይ የሳይበር ጥቃት የሚጨምርበት ሁኔታ እንደሚታይ ገልጸዋል።‎‎በመሆኑም የሳይበር ደህንነት ወር የተቋማትንና የማህበረሰቡን የሳይበር ደህንነት ግንዛቤ በማጎልበት ራሳቸውን ከሳይበር ጥቃት መከላከል እንዲችሉ ማድረግ ወሳኝ መሆኑን አመልክተዋል። ‎ዘንድሮ በሚከበረው ወር የተቋማትን እና የማህበረሰቡን የሳይበር ደህንነት ግንዛቤ በማጎልበት ለጉዳዩ ተገቢ ትኩረት እንዲሰጡና ራሳቸውን ከሳይበር ጥቃት መከላከል እንዲችሉ ከማድረግ አንጻር ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው አጽንኦት ሰጥተዋል።‎‎ የዘንድሮው የሳይበር ደህንነት ወር በህጻናት የበይነ-መረብ ጥበቃ ላይ ትኩረት ማድረጉን አመልክተው የህጻናት የበይነ-መረብ አጠቃቀምና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚከበር ተናግረዋል። ‎በወሩ ታዳጊዎችና ወጣቶችን የሚያሳትፍ ውድድርና በሰው ሰራሽ አስተውሎት እና በሳይበር ደህንነት ላይ የውይይት መድረክ እንደሚካሄድም ገልጸዋል። ‎‎ዋና ዳይሬክተሯ ኢመደአ የኢትዮጵያን የሳይበር ደህንነት የማስጠበቅ ሚናውን እየተወጣ እንደሚገኝ ገልጸው፤ የሳይበር ደህንነት የማስጠበቅ ስራ ላይ ሁሉም በጋራ ሊሰራ ይገባል ብለዋል። ‎በመሆኑም የጥቅምት ወርን የመንግስትና የግል ተቋማት በዘርፉ የሰራተኞቻቸውን ግንዛቤ በሚያሳድጉ ተግባራት እንዲያከብሩ ጥሪ አቅርበዋል። ‎‎ከጥቅምት 1 አስከ 30 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ 7ኛውን ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወርን በደመቀ ሁኔታ ማክበር የሚያስችል ዝግጅት መጠናቀቁንም አስታውቀዋል። የሳይበር ደህንነት ወር በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ23ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለሰባተኛ ጊዜ እንደሚከበርም ተመላክቷል።
የመደመር መንግስት ቀጣይ ዕቅዶች እንዲሳኩ በጥናትና ምርምር ለማገዝ ዝግጁ ነን- ምሁራን 
Oct 9, 2026 93
ሀዋሳ፤ መስከረም 29/2019 (ኢዜአ) ፦የመደመር መንግስት በቀጣይ ለማከናወን ያቀዳቸውን ተግባራት ለማሳካት ብቁ ባለሙያ ከማፍራት ባሻገር በጥናትና ምርምር ሥራዎች ለማገዝ ዝግጁ መሆናቸውን የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ገለጹ። የመደመር መንግስት በቀጣይ ዓመታት ጥራትን መሰረት ያደረገ ሁለንተናዊ መዋቅራዊ ሽግግር ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀስላሴ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመንግስት ምስረታ ወቅት ለምክር ቤት አባላት ባደረጉት ንግግር መግለጻቸው ይታወሳል። በተለይ የትምህርት፣ የጤና እና የማህበራዊ ጥበቃን ዘርፍ ከስፋት ወደ ጥራት በማሸጋገር ዜጋን ማዕከል ያደረገ የልማት ሥራዎች እንደሚከናወኑም ተገልጿል። የመደመር መንግስት ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች በአግባቡ እንዲተገበሩና ስኬታማ እንዲሆኑ ከማድረግ አንጻር ብቁ ባለሙያ የማፍራትና የተለያዩ ችግር ፈቺ ምርምሮችን የማድረግ ሚናቸውን እንደሚወጡ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ገልፀዋል። የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ትብብር ምክትል ፕሬዚዳንት መምህርና ተመራማሪ ታፈሰ ማቲዮስ (ዶ/ር) እንዳሉት፤ ባለፉት ዓመታት መንግስት ባከናወናቸው ሰው ተኮር የልማት ሥራዎች በርካታ ዜጎች ተጠቃሚ ሆነዋል። ዩኒቨርሲቲውም የመደመር መንግስት በቀጣይ ለማከናወን የያዛቸው ዕቅዶች እውን እንዲሆኑ የሰለጠነ ሰው ሀይል ከማፍራት ባለፈ በመንግስት የትኩረት መስኮች ላይ ችግር ፈቺ የምርምር ሥራዎችን በመስራት የበኩሉን እንደሚወጣም ገልጸዋል። ልማት ስኬታማ እንዲሆን የዜጎች ሚናም ከፍተኛ እንደሆነ ያነሱት ታፈሰ (ዶ/ር)፣ ህብረተሰቡም ለሀገራዊ ዕቅዶቹ መሳካት የበኩሉን መወጣት እንዳለበት አመልክተዋል። የዲጅታላይዜሽን ትግበራ የመንግስትና የግል አገልግሎቶችን ቀልጣፋ ከማድረግ ባሻገር ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለማስቀረትም ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የዩኒቨርሲቲው አስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዚዳንት መምህርና ተመራማሪ ሳሙኤል ጂሎ (ዶ/ር) ናቸው። መንግስት ያቀዳቸውን ተግባራት በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የለውጥ ሥራዎች ውስጥ በማካተት በውጤታማነት እንዲተገበሩ የራሳቸውን አስተጽኦ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል። ዩኒቨርሲቲው በግብርናው ዘርፍ የካበተ አቅምና ብቁ ተመራማሪዎች እንዳሉት ሳሙኤል (ዶ/ር) ገልጸው፣ ይህንን በመጠቀም መንግስት በግብርናው ዘርፍ የያዘውን ዕቅድ ለማሳካት ምርታማነትን የሚያሳድጉ ምርምሮችን በማድረግ ያግዛል ብለዋል። ምሁራኑ የመደመር መንግሥት የያዛቸው ግቦች እንዲሳኩ በምርምር፣ በመማር ማስተማርና በማህበረሰብ አገልግሎት የድርሻቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውንም አረጋግጠዋል።
የመደመር መንግሥት የዲጂታላይዜሽን አቅጣጫ  ለወጣቶች ሰፊ የሥራ ዕድል ይፈጥራል
Oct 9, 2026 103
ጅማ ፤ መስከረም 29/2019 (ኢዜአ) ፦ የመደመር መንግሥት የዲጂታላይዜሽን አቅጣጫ ለወጣቶች ሰፊ የሥራ ዕድል ለመፍጠር አቅም እንደሚሆን ተገለጸ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመደመር መንግሥት ምስረታ ወቅት ባደረጉት ንግግር፣ መንግሥት ከዚህ ቀደም ኢ-ኮደርስ ሥልጠና፣ዲጂታል መታወቂያን ጨምሮ የተለያዩ የዲጂታል ልማት ሥራዎችን ማከናወኑን አንስተዋል። በኢትዮ ኮደርስ ሥልጠና የወሰዱ የጅማ ከተማ ወጣቶችም፣ የመንግሥት የዲጂታላይዜሽን አቅጣጫ በተለይ ለወጣቶች ሰፊ የስራ ዕድል የሚፈጥር መሆኑን ተናግረዋል። አስተያየታቸውን ከሰጡ የከተማዋ ነዋሪዎች መካከል በግሉ በሶፍትዌር ማበልፀግ የተሰማራው ወጣት አደም ሰይድ እንዳለው በወሰደው የኢ-ኮደርስ ሥልጠና እውቀትና ክህሎቱን በማሳደግ ወደ ስራ እንዲገባ አድርጎታል።   አዲስ የተመሰረተው መንግስትም የዲጂታላይዜሽን ሥራዎችን ለማስፋፋት የያዘው አቅጣጫ የወጣቶችን የስራ እድል እንደሚያሰፋው ተናግሯል። በመንግሥት አገልግሎቶቹን ዲጂታላይዝ በማድረግ የተገልጋይን ጊዜና ጉልበት ለመቆጠብ የተዘረጉ አሰራሮች ውጤት ማምጣታቸውን የገለጸችው ደግሞ የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ባለሙያ የሆነችው ወጣት ሀናን አሙቲ ናት።   በቀጣይም ሥራዎቹን ለማስፋፋት መንግስት የያዘው እቅድ ሀገራዊ እድገትን ለማፋጠን ተደማሪ አቅም እንደሚሆን ጠቅሳለች። በኢ-ኮደርስ ሥልጠና ራሷን በማብቃት ለህብረተሰቡ የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት እንዳስቻላት የጠቆመችው ደግሞ ሌላዋ የመሶብ አንድ ማዕከል ባለሙያ አሲያ አባፊራ ናት።   መሰል የዲጂታል መሰረተ ልማት ሥራዎች የቴክኖሎጂ እውቀትና ክህሎት ለወጣቶች የበለጠ ተደራሽ በማድረግ ተወዳዳሪነታቸውን ለማሳደግ እንደሚያስችል ገልጻለች። ሌላው የጅማ ከተማ ነዋሪ መሀመድ ሀይደር በበኩላቸው እንዳሉት፤ የኢትዮጵያ የዲጂታላይዜሽን እቅዶች የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን ለማሳለጥ ተግባራዊ የተደረጉ እንደ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ያሉ ተቋማት አጋዥ ናቸው።   በጅማ ዩኒቨርሲቲ ኤሌክትሪካልና ኮምፒውተር ምህንድስና ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ መሀመድ ሙንታዝ (ዶ/ር) ፤ የመንግስት የዲጂታላይዜሽን ስራዎች ለወጣቶች ትልቅ የስራ እድል የሚፈጥሩ ናቸው ብለዋል።   ተግባሩ በቴክኖሎጂ ብቁ የሰው ኃይል ለማፍራት ትልቅ አቅም በመፍጠር ተወዳዳሪነትን ለማስፋት እንደሚያስችል ገልጸዋል። የኢትዮ ኮደርስ ስልጠናና የቴክኖሎጂ መሠረተ ልማት ስራዎች ወጣቶችን በዓለም የሥራ ገበያ ተወዳዳሪ እንደሚያደርጋቸው አብራርተዋል።
ስፖርት
ሀላባ ከተማ እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ አቻ ተለያዩ
Oct 9, 2026 95
አዲስ አበባ፤ መስከረም 29 /2019 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት መርሐ ግብር ሀላባ ከተማ እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል። በሀላባ ኢንተርናሽናል ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሽመክት ጉግሳ በ48ኛው ደቂቃ ያስቆጠረው ጎል ሀላባን መሪ አድርጓል። ካርሎስ ዳምጠው በ94ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት ከመረብ ላይ ባሳረፋት ጎል ወልዋሎ አቻ ሆኗል። አዲስ አዳጊው ሀላባ ከተማ ሶስት ነጥብ ሊያገኝበት የሚችልበትን እድል መጠቀም አልቻለም። በፕሪሚየር ሊጉ ለመጀመሪያ ጊዜ ተሳትፎ እያደረገ ያለው ሀላባ ከተማ የመጀመሪያ ነጥቡን አግኝቷል። በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ኢትዮጵያን ወክሎ እየተሳተፈ የሚገኘው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በተመሳሳይ አንድ ነጥብ አሳክቷል። ዛሬ በተደረገ የፕሪሚየር ሊጉ የመክፈቻ ጨዋታ አዳማ ከተማ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 1 ለ 0 አሸንፏል። የሊጉ የመጀመሪያ ሳምንት መርሐ ግብር እስከ ጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም ይቆያል።
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ይጀመራል
Oct 9, 2026 181
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 29/2019 (ኢዜአ) ፦ የ2019 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ በሚደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ጅማሮውን ያገኛል። የሊጉ የመክፈቻ ጨዋታ በኢትዮ ኤሌክትሪክና አዳማ ከተማ መካከል ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም ይካሄዳል። በ2019 ዓ.ም የውድድር ዓመት ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ54 ነጥብ አምስተኛ፣ አዳማ ከተማ በ46 ነጥብ 15ኛ ደረጃን ይዘው ማጠናቀቃቸው የሚታወስ ነው። በሌላኛው መርሐ ግብር አዲስ አዳጊው ሀላባ ከተማ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከቀኑ 10 ሰዓት በሃላባ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ይጫወታሉ። ሁለቱ ክለቦች በሊጉ ሲገናኙ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። የፕሪሚየር ሊጉ የመጀመሪያ ሳምንት መርሐ ግብር እስከ ጥቅምት 1 2019 ዓ.ም ይቆያል። የሊጉ ጨዋታዎች በሰባት የተመረጡ ስታዲየሞች ይደረጋሉ። አዲስ አበባ ስታዲየም፣ አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም፣ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም፤ ባህርዳር አለም አቀፍ ስታዲየም፣ሀላባ ስታዲየም፣ ሆሳዕና አብዩ ኤርሳሞ ስታዲየም እና አርባምንጭ ዩንቨርሲቲ አባያ ካምፓስ ስታዲየም ውድድሩ የሚካሄድባቸው ሜዳዎች ናቸው። በውድድሩ ላይ 18 ክለቦች ይወዳደራሉ።
አካባቢ ጥበቃ
አረንጓዴ ዐሻራ የኢትዮጵያን የደን ሽፋን በማሳደግ ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊ ትሩፋት እያስገኘ ነው
Oct 9, 2026 116
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 29/2019 (ኢዜአ) ፦የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የኢትዮጵያን የደን ሽፋን በማሳደግ ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊ ትሩፋት እያስገኘ መሆኑን የኢትዮጵያ ደን ልማት ገለጸ። ትልቅ ሀገር፤ ትልቅ ሕዝብ፤ ታላቅ ርዕይ የመደመር መንግሥት ምሥረታ እና ሰባተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መክፈቻ ሥነ ሥርዓት መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም ተካሂዷል። በዚህም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ን ለቀጣይ አምስት ዓመታት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰይሟል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት፤ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የተተከሉት 56 ቢሊዮን ችግኞች የተራቆቱ መሬቶችን በማገገም ጉልህ ፋይዳ እያስገኙ መሆኑን ገልጸዋል። የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብሩም የግብርና ምርታማነትን በማገዝ ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጠቀሜታ ያስገኘ ዓለም አቀፍ ተነሳሽነት ነው።   በኢትዮጵያ ደን ልማት የተፈጥሮ ደን መሪ ሥራ አስፈጻሚ ካብታሙ ግርማ ለኢዜአ እንዳሉት፤ ደን የአካባቢ መራቆትና የሥነ-ምኅዳር ደህንነትን በመጠበቅ ለግብርና ምርታማነት ጉልህ ጠቀሜታ አለው። የደን ሽፋን ዕድገትም አየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን በመቀነስ ብርቅዬ እንስሳትና የብዝኅ ሕይወት ደኅንነትን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ እንደሚኖረው ገልጸዋል። የመደመር መንግሥት በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ለደን ልማት የሰጠው ትኩረት የአካባቢ ተጽዕኖ ውጤታማነትን በማሻሻል ተጨባጭ ውጤት እያመጣ መሆኑን ተናግረዋል። ይህም ዜጎች በአትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም ተያያዥ የልማት መስኮች የሚሰማሩበትን ዕድል በመፍጠር ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ፋይዳ እያስገኘ መሆኑን አንስተዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሐሳብ አመንጭነት በ2011 ዓ.ም. የተጀመረው የአረንጓዴ ዐሻራም 17 ነጥብ 2 በመቶ የነበረውን ደን ሽፋን ወደ 23 ነጥብ 6 በመቶ ማሳደጉን አስታውሰዋል።   የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የደን ጥበቃ ውጤታማነትን በማላቅ የተስተካከለ ሥነ-ምኅዳርና የብዝኅ ሕይወት እንዲፈጠር እያደረገ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል። በተለይም የተራቆቱ አካባቢዎች እንዲያገግሙ በማድረግ ለምግብነት የሚውሉ የፍራፍሬ እፅዋት ልማትን በማስፋፋት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ መሠረት እየጣለ መሆኑን አብራርተዋል። የህብረተሰቡን የደን ጥበቃና እንክብካቤ ባህል በማሻሻል የደን አስተዳደር ሥርዓት ውጤታማነትን ማሳደግ የሚያስችል አቅም መፈጠሩንም አስረድተዋል። የኢትዮጵያ ደን ልማትም የተራቆቱ አካባቢዎች እንዲያገግሙ፣ የደን ሀብት በዘላቂነት እንዲጠበቅና እንዲለማ የሚያስችል ሥራ እየተሠራ እንደሚገኝ አንስተዋል። በተጨማሪም የደን ውጤቶች ምርታማነትን በማሻሻል የደን ሀብት ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ተጠቃሚነትን በማላቅ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን መቋቋም የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሀ ግብር ያስመዘገበችው ውጤት ለሌሎች ሀገራት ምሳሌ ሆኗል
Oct 7, 2026 168
አዲስ አበባ፤መስከረም 27/2019(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሀ ግብር ያስመዘገበችው ውጤት ለሌሎች ሀገራት አርዓያ የሆነ ታላቅ ተግባር መሆኑን የዘርፉ ሙያተኞች ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ህዝብ፣ ታላቅ ርዕይን አንግባ በትኩረት እየሰራችባቸው ከሚገኙ ውጤታማ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች መካከል አረንጓዴ ዐሻራ አንዱ ነው። ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ መዛባትን ለመከላከል፣ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ባለፉት ዓመታት በአርንጓዴ ዐሻራ መርሀ ግብር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን ተክላለች። የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመሥረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባውን መካሄዱ ይታወቃል። በዚህ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሀ ግብርን ከጀመረችበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን 56 ቢሊዮን ችግኞችን በመትከል የተራቆቱ መሬቶችን አረንጓዴ ማልበስ ተችሏል። በተጨማሪም ይህ መርሀ ግብር የመሬት መሸርሸርን እንዲቀንስ፣ ስነ ምህዳራን መጠበቅ እንዳስቻለም መግለጻቸው ይታወሳል። በተባበሩት መንግስታት የደን ፎረም ሴክሬታሪያት ዳይሬክተር ዶክተር ጁሊያት ቢያኦ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ የደን ሽፋንን ለመጨመር የሚከናወኑ ተግባራት በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ጉልህ ሚና እንደሚያበረክቱም ገልጸዋል። የደን መራቆትን ለመቅረፍና የመሬት ገጽታ ለመጠበቅ መንግስት ከሚያከናውናቸው ተግባራት በተጨማሪ የዘርፉን ተዋንያን ርብርብ የሚጠይቅ መሆኑን አብራርተዋል። የኢትዮጵያ መንግስት የአረንጓዴ ዐሻራ መርሀ ግብርን ነድፎ ባለፉት ዓመታት በመተግበር የአረንጓዴ ሽፋንን ለማሳደግ ያከናወነው ተግባር ውጤት ማስመዝገቡንም አክለዋል።   የአፍሪካ የደን ፎረም የደን ተመራማሪ የሆኑት ዶሪስ ሙታ (ዶ/ር) በበኩላቸው የአካባቢ ስነ ምህዳርን ለመጠበቅና በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚከሰቱ ችግሮችን ለመከላከል የሚከናወኑ ተግባራት የመንግስትን ቁርጠኝነት የሚጠይቅ መሆኑን አንስተዋል። በመሆኑም ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ያከናወነቻቸው ውጤታማ ተግባራት ከደን ሽፋን መመናመን ጋር ተያይዞ የሚከሰት የአየር ንብረት ለውጥ መዛባትን በመከላከል በኩል ጉልህ ሚና አለው ብለዋል። ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሀ ግብር ያስመዘገበችው ውጤት በዘርፉ በትኩረት ከተሰራ ታሪክ መቀየር እንደሚቻል ለዓለም ጥሩ ምሳሌ እንደሚሆን ተናግረዋል። እንደ አረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር አይነት ፕሮጀክት ነድፎ መተግበር ፋይዳው አካባቢን በደን ከመሸፈን በላይ መሆኑንም ነው የተናገሩት። በመሆኑም መሰል ምሳሌ የሚሆን ተግባር ሰዎች በምቹ ስነ ምህዳር እንዲኖሩ ዕድል የሚፈጥርና ምርታማነትን የሚያሳድግ አርዓያነት ያለው ተግባር እንደሆነም ነው ዶሪስ ሙታ ( ዶ/ር) የገለጹት።    
በአማራ ክልል የግሪሳ ወፍ መንጋ በሰብል ላይ ጉዳት እንዳያደርስ የኬሚካል ርጭት እየተካሄደ ነው
Oct 7, 2026 152
ባህር ዳር፤ መስከረም 27/2019 (ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል የተከሰተው የግሪሳ ወፍ መንጋ በሰብል ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ለመከላከል የኬሚካል ርጭት እየተካሔደ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው የሰብል ልማትና ጥበቃ ዳይሬክተር ማንደፍሮ አስላከ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ከነሐሴ ወር 2018 ዓ.ም መጨረሻ ጀምሮ የተከሰተውን የግሪሳ ወፍ መንጋ በዘመናዊና ባህላዊ መንገድ የመከላከል ሥራ እየተሠራ ይገኛል።   በደቡብና ሰሜን ወሎ፣ በሰሜን ሸዋ እና በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞኖች በሚገኙ 15 ወረዳዎች የተከሰተው የግሪሳ ወፍ መንጋ በደረሰ ሰብል ላይ ጉዳት እንዳያደርስ በተቀናጀ አግባብ የመከላከል ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። መንጋው የማሽላ፣ የጤፍ፣ የስንዴ፣ የገብስ፣ የዳጉሳ፣ የሩዝ እና የመሳሰሉ ሰብሎችን በእሸትነት ደረጃ ፍሬውን በመብላትና በማራገፍ ጥፋት የሚያስከትል ነው። በዚህም 74 የግሪሳ ወፍ መንጋ ማደሪያ ቦታዎችን በመለየት ከመስከረም 4 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ በአውሮፕላን የታገዘ የኬሚካል ርጭት በማከናወን አብዛኛውን የግሪሳ ወፍ ማስወገድ ተችሏል።   በተቀናጀ መንገድ በተካሄደ የመከላከል ሥራ ሰብሉን ሙሉ በሙሉ ከግሪሳ ወፍ ጉዳት መታደግ እንደተቻለ ነው ዳይሬክተሩ ያስገነዘቡት። አርሶ አደሩ በየእለቱ ሰብሉን አሰሳ በማድረግ ከግሪሳ ወፍ ጉዳት የመከላከል ሥራውን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል። የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ግብርና መምሪያ የሰብል ልማት ቡድን መሪ አቶ ደጀኔ ከበደ በበኩላቸው፤ መንጋው የተከሰተው በከሚሴ ከተማ አስተዳደር፣ በዳዋ ጨፋ፣ በአርጡማ ፉርሲ፣ በጅሌ እና ባቲ ወረዳዎች መሆኑን ተናግረዋል። መንጋውን በአውሮፕላን የኬሚካል ርጭት ፈጥኖ በማከናወን የመከላከል ሥራ በመሠራቱ ከ70 በመቶ በላይ የሚሆነውን የግሪሳ ወፍ ማስወገድ መቻሉን ገልጸዋል። አሁንም መንጋውን የመከላከል ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን አመልክተው፤ አርሶ አደሩም በባህላዊ መንገድ ድምፅ በማሰማት መንጋው በደረሱ ሰብሎች ላይ ጉዳት እንዳያደርስ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
አረንጓዴ ዐሻራ ከተሞችን ለኑሮ ምቹና ሳቢ በማድረግ ረገድ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው
Oct 3, 2026 276
አዲስ አበባ ፤መስከረም 23/2019 (ኢዜአ)፦የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር የሀገሪቱን የአረንጓዴ ልማት ግቦች ከማሳካት ባለፈ፣ ከተሞችን ለኑሮ ምቹ እና ተስማሚ እያደረገ እንደሚገኝ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ገለጸ። ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባት በ2011 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መሪነት የጀመረችው ታሪካዊ የአረንጓዴ ዐሻራ መርኃ ግብር ለአፍሪካም ሆነ ለዓለም ትልቅ አርአያ መሆን ችሏል። በዚህ ግዙፍ ሀገራዊ ተነሳሽነት አማካኝነት ባለፉት 8 ዓመታት ውስጥ 56 ቢሊዮን ችግኞች ለመትከል ተችሏል። በመርሃ ግብሩ የተተከሉ ችግኞች ስነ-ምህዳርን ከማስጠበቅና ከተሞችን አረንጓዴ ከማላበስ ባለፈ ለምግብነት እና ለቱሪስት መዳረሻነት ምቹ ሁኔታን ፈጥረዋል። ይህ ሁሉን አቀፍ ጥረት ሀገሪቱ የተፈጥሮ ጸጋዎቿን ጠብቃ የምግብ ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ ለምታደርገው ብሩህ ጉዞ ጠንካራ እና አዲስ መሰረት ጥሏል። በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የፖሊሲና ስትራቴጂ ጥናት ምርምር መሪ ስራ አስፈጻሚ አማን አሰፋ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንደገለጹት፣ በከተሞች የሚካሄዱ የአረንጓዴ ዐሻራ ልማት ስራዎች ከተሞች ለኑሮ ምቹ፣ ዘመናዊና ማራኪ አድርጓቸዋል። በከተሞች አካበቢ ከፍተኛ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ መኖር እና የኢንዱስትሪ ማዕከል መሆናቸው ለከፍተኛ ካርቦን ልቀትና ብክለት ተጋላጭ ናቸው ብለዋል። በመሆኑም የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ይህንን ችግር በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን አንስተዋል። በዚህም የሙቀት መጠንን በመቀነስ፣ የአካባቢ ስነ-ምህዳርን በመጠበቅ እና በከተሞች አካባቢ ጎርፍ እንዳይከሰት በመከላከል ለአየር ንብረት ለውጥ ትልቅ አዎንታዊ ድርሻ እያበረከተ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለአረንጓዴ ዐሻራ ልማት ልዩ ትኩረት በመስጠት አዳዲስ የከተማ ፕላን አሠራር ላይ ማሻሻያ ማድረጉንም ተናግረዋል። በዚህም አዲስ የሚዘጋጁ የከተማ ፕላኖች 30 በመቶ ለአረንጓዴ ልማት፣ 30 በመቶ ለመሠረተ ልማት እና 40 በመቶው ደግሞ ለመኖሪያነት እንዲውሉ የሚያስችል ሞዳሊቲ እንዲከተሉ ትኩረት ተሰጥቷል ብለዋል። በዚህ መሰረት የሚከናወኑ የከተማ ፕላን ዝግጅቶች የሀገሪቱን አረንጓዴ የልማት ግቦች ለማሳካት ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖራቸው ተገልጿል።      
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የአፍሪካ ህብረት እና ተመድ ያላቸውን የጋራ ውጥኖች በቁርጠኝነት ለመተግበር እንደሚሰሩ ገለጹ  
Sep 21, 2026 1046
አዲስ አበባ፤ መስከረም 10/2019 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሰላም፣ ኢኮኖሚና ፍትሃዊ ዓለምን ለማስፈን በጋራ እያከናወኑ የሚገኘውን ስራ ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰሩ አስታወቁ። 81ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ከመስከረም 8 ቀን 2019 ዓ.ም አንስቶ በኒው ዮርክ እየተካሄደ ይገኛል። “መተማመንን ዳግም መገንባት እና አዳዲስ ለውጦችን በአግባቡ መምራት፣ ለሁሉም የሚሰራ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን መፍጠር” የጉባኤው መሪ ሀሳብ ነው። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በጉባኤው ላይ ለመታደም ኒው ዮርክ ይገኛሉ። ከጠቅላላ ጉባኤው ጎን ለጎን ስትራቴጂካዊ ትብብር ማጎልበት፣ የሰላምና ደህንነት ማዕቀፎችን ማጠናከርና አፍሪካን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ሪፎርሞች ላይ ያተኮረ ከፍተኛ የምክክር መድረክ ተካሄዷል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ እና የተባበበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ መድረኩን በጋራ መርተውታል። ስብስባው ሁለቱ ተቋማት አፍሪካ መዋቅራዊ ፈተናዎችን ለመፍታት እያደረገች ያለቻቸውን ጥረቶች ለመደገፍና ፍትሃዊ የዓለም ስርዓትን ለመፍጠር ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት ይበልጥ ያረጋገጠ መሆኑን የአፍሪካ ህብረት መረጃ ያመለክታል። የዓለም አቀፍ የፋይናንስ አወቃቀርን ማሻሻል፣ ዘላቂ የእዳ አስተዳደር እና የአፍሪካ ሀገራት ከቁልፍ የማዕድን ሀብቶች ይበልጥ ተጠቃሚ ማድረግ ውይይት ከተደረገባቸው አጀንዳዎች መካከል ይጠቀሳሉ። ሁለቱ ወገኖች በስብሰባው ላይ የአፍሪካ ህብረት እና የተመድን ትብብር ያለውን ስትራቴጂካዊ ፋይዳ አጽንኦት ሰጥተዋል። የተቋማቱ ሶስት ነባር የትብብር ማዕቀፎች በአዲስ መልክ ለማደስ እና እ.አ.አ በ2026 ትግበራው የሚጠናቀቀውን የጋራ ፍኖተ ካርታ የተፈጻሚነት ገደብ ለማራዘም መስራት እንደሚገባ ተመላክቷል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአፍሪካ ያሉ የሰላም እና የደህንነት ተግዳሮቶችን ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ውስጥ የአፍሪካ ህብረት ቁልፍ አጋር ሆኖ እንደሚቀጥል ዳግም አረጋግጧል። የአፍሪካን የሰላምና ደህንነት መዋቅር ማጠናከር፣ ግጭትን አስቀድሞ የመከላከል ዲፕሎማሲና የእርቅ ሂደትን በሚገባ መተግበርና ለአፍሪካ ፈተናዎች አፍሪካዊ መፍትሄዎችን ማረጋገጥ የሚያስችል በቂ አቅም መገንባት እንደሚያስፈልግ በስብሰባው ላይ ተነስቷል። በውይይቱ በሳሄል ቀጠና፣ በሊቢያ፣ በሱዳን፣ በደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያና ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ያሉ ወቅታዊ ጉዳዮችና የሰላም ጥረቶች ተገምግመዋል። በስብስባው ላይ ግጭቶች፣ በዓለም አቀፍ የአቅርቦት ሰንሰለት ላይ የተፈጠሩ መስተጓጎሎች እና የባህር በር መስመሮችን መዝጋትን ጨምሮ ሌሎች ውጫዊ ሁኔታዎች በአፍሪካ ኢኮኖሚ እና ምግብ ዋስትና ላይ ተጨማሪ ጫና እየፈጠሩ መሆኑ ተነስቷል። የአየር ንብረት ለውጥ እያደረሰ ያለው ጉዳትም ምክክር ተደርጎበታል። ሁለቱ ወገኖች በውይይቶች ጠንካራ የጋራ ግብረ መልስ መስጫ ማዕቀፍ ለመፍጠር ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። የአፍሪካ ህብረት እና ተመድ ፍኖተ ካርታ ዝግጅን ለማጠናቀቅ፣ በአፍሪካ ሀገራት የሰላም ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር፣ የምግብ ዋስትና ተግዳሮቶችን ለመፍታትና ለድንገተኛ አደጋዎች ምላሽ መስጠት የሚያስችሉ የአሰራር ማዕቀፎችን ለመቅረጽ በቅርበት እንደሚሰሩ መግለጻቸውን የአፍሪካ ህብረት መረጃ ያመለክታል። 81ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ እስከ መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ይቆያል።
በቀጣናው ያሉ ፈተናዎችን በዘላቂነት ለመፍታት የሀገራት የጋራ ቁርጠኝነት ወሳኝ ነው - ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር)
Sep 15, 2026 1113
አዲስ አበባ፤ መስከረም 5/2019 (ኢዜአ)፦ በቀጣናው እያጋጠሙ የሚገኙ ፈተናዎች በዘላቂነት እንዲፈቱ የአባል ሀገራት አብሮነትና የጋራ ቁርጠኝነት ወሳኝ መሆኑን የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ገለጹ። የኢጋድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት 74ኛው አስቸኳይ ስብሰባውን ዛሬ በጅቡቲ አካሂዷል። በስብሰባው ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እና የኢጋድ አባል ሀገራት ተወካዮች ተሳትፈዋል። በቀጣናው ሰላም እና ጸጥታ እንዲሁም በሌሎች አበይት ጉዳዮች ላይ ምክክር ተደርጓል። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ በቀጣናው እያጋጠሙ ያሉ ፈተናዎችን በዘላቂነት ለመቋቋም የአባል ሀገራት አብሮነትና የጋራ ቁርጠኝነት ወሳኝ ነው።   በኢጋድ ሴክሬታሪያት በኩል የተከናወኑ የልማትና የሰላም ሥራዎች አበረታች ውጤቶችን እያስገኙ መሆናቸውን በመግለጽ፣ ተቋሙ ለቀጣናው ህዝቦች ብልጽግና መረጋገጥ የጸና አቋም እንዳለው አመልክተዋል። ምንም እንኳን የተለያዩ ጂኦፖለቲካዊ ፈተናዎች ቢኖሩም፣ የኢጋድ ሴክሬታሪያት ያለፉት ስድስት ወራት አፈጻጸም አበረታች የሚባል መሆኑን ተናግረዋል። በቀጣናዊ መሠረተ ልማት እና የጤና ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶችን ያነሱት ዋና ፀሐፊው፤ የቀጣናው የከርሰ ምድር ውሃ መረጃ ሥርዓት የአገልግሎት ተደራሽነት የላቀ ውጤት ማስመዝገቡን ጠቁመዋል። እንዲሁም የቀጣናው ዓለም አቀፍ የጤና ሽፋን መረጃ ጠቋሚ (ኢንዴክስ) ከ60 ወደ 65 በመቶ ከፍ ማለቱንና ይህም እ.አ.አ በ2027 70 በመቶ ለማድረስ የተያዘውን እቅድ ለማሳካት የሚያስችል መሆኑን ነው ያነሱት። በሌላ በኩል ሱዳን ወደ ኢጋድ ሙሉ አባልነቷ መመለሷ የቀጣናውን ትብብርና አንድነት ይበልጥ እንደሚያጠናክረው ገልጸዋል። ዋና ፀሐፊው እ.አ.አ ጁላይ 2026 ወደ ሱዳን ባቀኑበት ወቅት የኢጋድ የሱዳን ልዑክ ቢሮ በድጋሚ በይፋ መከፈቱን አስታውሰው ይህ እርምጃ ከቀጣናው ሕዝቦች ጋር ያለውን ቀጥተኛና ዘላቂ ትስስር አጠናክሮ የሚያስቀጥል መሆኑን አመላክተዋል። ኢጋድ ከአፍሪካ ሕብረት፣ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኤጀንሲዎች እና ከሌሎች ስትራቴጂካዊ አጋሮች ጋር ያለው ግንኙነት ለቀጣናው ዘላቂ ልማት ወሳኝ ነው ብለዋል። አጋርነቱ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትን አቅም በማጠናከር ረገድ የጎላ ድርሻ እንደሚያበረክትም ነው ያነሱት። በቀጣይ ሊከሰቱ የሚችሉ የአየር ንብረት ለውጥ አደጋዎችን የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓትን በማጠናከር ለመቋቋም የሚያስችሉ አሰራሮች እየተቀረፁ መሆናቸውን ተናግረዋል። ሀገራት የኤልኒኖ (El Niño) የአየር ንብረት መዛባት የሚያስከትለውን ስጋት ለመቀነስ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከር እንዳለባቸው አሳስበዋል። በሌላ በኩል ቀጣናውን ከሰው ሰራሽ አስተውሎት ጋር ለማስተሳሰርና በቴክኖሎጂ የታገዘ የልማት መሠረት ለመጣል የተጀመሩ ስራዎች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን ገልጸዋል። ስብሰባው የቀጣናውን ሰላም፣ ደህንነት እና ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማፋጠን በሚያስችሉ ሀገራዊና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ በመምከርና ውሳኔዎችን በማሳለፍ መጠናቀቁን ኢዜአ ከኢጋድ ሴክሬተሪያት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። የኢጋድ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ከተቋሙ ቁልፍ የፖሊሲ አደረጃጀቶች መካከል አንዱ ሲሆን፣ የድርጅቱን ሥራዎች በመምራትና በአባል ሀገራት መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር ረገድ ጉልህ ሚና የሚጫወት ነው።
አፍሪካ በዓለም ፊት ቦታ ለማግኘት አትማጸንም ፤ ይልቁንም የሚገባትን ስፍራ በባለቤትነት እየያዘች ነው
Sep 9, 2026 1009
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ):- አፍሪካ በዓለም ፊት ቦታ ለማግኘት አትማጸንም ፤ የሚገባትን ስፍራ እና ክብር በራሷ እያረጋገጠች ነው ሲሉ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። የአፍሪካ ህብረት ቀን ዛሬ እየተከበረ ይገኛል። የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ቀኑን በማስመልከት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ሊቀ መንበሩ የአፍሪካ ህብረት ቀን እ.አ.አ በ1999 የቀድሞ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ለመተካት ይፋዊ ውሳኔ የተላለፈበት የሰርጥ ድንጋጌ (Sirte Declaration) የሚታወስበት እንደሆነ ገልጸዋል። በዚያን ወቅት የአፍሪካ መሪዎች አህጉራዊ ትስስርን ለማፋጠን እና የአፍሪካን ድምጽ በዓለም አቀፍ መድረክ ከፍ ለማድረግ የአፍሪካ ህብረትን ለመመስረት ወሳኝ እና ታሪካዊ እርምጃ የወሰዱበት ምዕራፍ ነው ብለዋል። የዘንድሮው የአፍሪካ ህብረት ቀን ለአህጉሪቱ እጅግ ልዩ ትርጉም ባለው ወቅት ላይ እየተከበረ እንደሚገኝ አውስተዋል። ከጥቂት ቀናት በፊት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ የአፍሪካን እውነተኛ ቁመና እና ትክክለኛ መጠን የሚያሳይ የዓለም ካርታ አጠቃቀምን የሚደግፍ፣ በአፍሪካ መሪነት የቀረበ የውሳኔ ሀሳብ አፅድቋል። በቶጎ ሃሳብ አመንጪነትና በአፍሪካ ህብረት ድጋፍ እውን የሆነው ይህ እርምጃ ከቀላል የካርታ ማስተካከያ በላይ ትርጉም አለው ብለዋል ሊቀ መንበሩ። አፍሪካ በዓለም ፊት እንዴት እንደምትታይ ትኩረት የሚሰጠው መሆኑን እና አፍሪካ ራሷን የምትገመግምበትንና የምታሳይበትን ትርክት ራሷ መቅረጽ እንዳለባት አበክሮ የሚያስታውስ ነው። ይህ ውሳኔ አፍሪካ በዓለም ፊት በምን መልኩ መታየት እንዳለባት ከማሳየቱም በላይ፤ አፍሪካ ራሷን የምትመዝንበትንና እውነታዋን ለዓለም የምታሳይበትን ትርክት በራሷ መቅረጽ እንዳለባት በግልጽ የሚያሳይ መሆኑን ነው ያነሱት። የአፍሪካ እጣ ፈንታ የሚወሰነው በአፍሪካውያን የራሳቸው እይታ ነው። አፍሪካን በእውነተኛ ቁመናዋ፣ኃይሏ እና አቅሟ የምንመለከትበት ጊዜ አሁን ነው ብለዋል። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር አያይዘውም ካርታውን የማስተካከል እርምጃ አፍሪካ ወደ ላቀ የጋራ ራዕይ የምታደርገው አህጉራዊ ጉዞ አካል መሆኑን አንስተዋል። ይህም በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጠና (AfCFTA) አማካኝነት የኢኮኖሚ ትስስር ማጠናከርን፣ ሰላም እና ፀጥታን ማረጋገጥን፣ ዘላቂ ልማትን እውን ማድረግን እና በዓለም አቀፍ ውሳኔ ሰጪ አካላት ውስጥ የአፍሪካን ተሳትፎ ማሳደግን እንደሚያካትት በዝርዝር አስረድተዋል። የአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 የተሳሰረች፣ የበለጸገች እና ሰላማዊት አፍሪካን ለመገንባት የማዕዘን ድንጋይ ሆኖ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል። ሰላም እና ፀጥታን ማረጋገጥ፣ የኢኮኖሚ ትስስርን በማፋጠን እና የአፍሪካን ዓለም አቀፍ ተሰሚነት መጨመር የአፍሪካ ህብረት ቀዳሚ ትኩረቶች ናቸው ብለዋል። አፍሪካ በዓለም ፊት እውቅና ለማግኘት አትለምንም፤ ይልቁንስ በዓለም አቀፍ መድረክ የሷ የሆነውን ትክክለኛ ስፍራ በራሷ ባለቤትነት እየያዘች ነው። አሁን የሚጠበቅብን ይህንን ጠንካራ እምነት ወደ ህብረት፣ ሀብትና ብልጽግና፣ ሰላም እና ተደማጭነት መለወጥ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ሊቀመንበሩ አፍሪካ የምታስመዘግበው እድገት በዓለም አቀፍ መድረኮች በሚኖራት ውክልና ብቻ ሳይሆን፣ በዜጎቿ ላይ የኑሮ ጥራት መሻሻል ጭምር መለካት እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል። በዚህም መሰረት የአፍሪካ ህብረት የ2026 ዓመት ትኩረቱን በዘላቂ የንጹህ ውሃ አቅርቦት እና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አገልግሎት ላይ ማድረጉ፣ ህብረቱ አህጉራዊ ራዕዮችን ከዕለት ተዕለት የዜጎች ህይወት ጋር ለማያያዝ ያለውን ጽኑ ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ አመልክተዋል። በአፍሪካ ህብረት ቀን አከባበር አባል ሀገራት፣ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማህበረሰቦች፣ የአፍሪካ ተቋማት፣ የግሉ ዘርፍ፣ የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ ሴቶች እና ወጣቶች ተባብረው ይበልጥ የተሳሰረች፣ በራሷ አቅም የምትተማመን እና የራሷን እጣ ፈንታ በራሷ መወሰን የምትችል አፍሪካን እንዲገነቡ ሊቀመንበሩ ጥሪ አቅርበዋል። የምንፈልጋት አፍሪካ የሚለውን አህጉራዊ ራዕይ እውን ለማድረግ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ እና የሰርት ድንጋጌ ለቀጣዩ የአፍሪካ ትውልድ ዘላቂ የትምህርት እና የዕድገት መሰረት ሆኖ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። የነገዋ አፍሪካ በካርታ ላይ ብቻ የተሻለ ውክልና ያላት ብቻ ሳትሆን፤ በዓለም አቀፍ መድረክ ሉዓላዊነቷ የጸና፣ ጠንካራ ውስጣዊ አንድነት ያላት፣ ለህዝቦቿም ዘላቂ ብልጽግናን የምታጎናጽፍ አህጉር መሆን ይኖርባታል ነው ያሉት። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ለመላው አፍሪካውያን እና በውጭ ሀገር ለሚገኙ የአፍሪካ ዳያስፖራዎች ሰላማዊ እና የትብብር መንፈስ የተሞላበት የአፍሪካ ህብረት ቀን እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
የአፍሪካ ህብረት እና አሜሪካ አጋርነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ
Sep 4, 2026 1187
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ)፡- የአፍሪካ ህብረት እና አሜሪካ ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን እና ሁሉን አቀፍ ትብብራቸውን የበለጠ ለማላቅ እንደሚሰሩ አስታወቁ። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሺያን ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። ውይይቱ በአፍሪካ ህብረትና አሜሪካ መካከል ያለውን ለረጅም ጊዜ የቆየ አጋርነት ማጠናከር እና በአህጉሪቱ ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር የአፍሪካና አሜሪካን ትብብር ታሪካዊ መሆኑን አውስተው በህብረቱ፣ በአባል ሀገራት እና በአሜሪካ መካከል የሁለቱንም ወገኖች ጥቅም በሚያስጠብቅ መልኩ ጠንካራ አጋርነት መገንባት እንደሚገባ አሳስበዋል። በምስራቅ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ሱዳን እየተደረጉ ላሉ አፍሪካ መር የሰላም ጥረቶች አሜሪካ እያደረገች ላለው ገንቢ አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሺያ በበኩላቸው አፍሪካ አሜሪካ ቀዳሚ ትኩረት የምትሰጣት አህጉር እንደሆነች ገልጸዋል። የጋራ ፍላጎቶችንና ግቦችን ከህብረቱ ኮሚሽንና ከአባል ሀገራት ጋር በመሆን ለማሳካት ያላቸውን ጽኑ ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል። በንግድ እና ኢንቨስትመንት፣ በመሰረተ ልማት ዝርጋታ፣ በዲፕሎማሲ፣ እንዲሁም በሰላምና ጸጥታ ያለውን ትብብር ማጠናከር እንደሚገባም አመልክተዋል። በውይይቱ ላይ በሱዳን ጉዳይ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ፣ የሰብአዊ እርዳታ ያለ ገደብ እንዲገባ እና በሲቪሎች የሚመራ ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ሂደት እንዲጀመር አጽንዖት ተሰጥቷል። በአፍሪካ ባለቤትነት የሚመሩ የሰላም ጥረቶች እና አሜሪካ የምትደግፋቸው የሰላም ሂደቶች በተቀናጀ መልኩ ለመተግበር ከስምምነት ላይ ተደርሷል። በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በመሰረተ ልማት እና በሰላም መስኮች የሁለቱን ወገኖች ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችሉ የትብብር መስኮች ተገምግመዋል። ሁለቱ ወገኖች በአፍሪካ ህብረትና በአሜሪካ ስትራቴጂክ ኢንቨስትመንት ማዕቀፍ ውስጥ የተደረጉ ስምምነቶችን ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። በሊቢያ ጉዳይ ዘላቂ የፖለቲካ መፍትሄ ማግኘት እንደሚያስፈልግም ተነስቷል። የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር እና ረዳት ሚኒስትሩ የሁለቱን ወገኖች ስትራቴጂካዊ አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከርና የትብብር አድማሱን ለማስፋት የጋራ ቁርጠኝነታቸውን መግለጻቸውን ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ሐተታዎች
የኢትዮጵያ አዲስ የዕድገት ምዕራፍ - የመደመር መንግሥት እሳቤ ትሩፋቶች
Oct 9, 2026 75
ትልቅ ሀገር፤ ትልቅ ሕዝብ፤ ታላቅ ርዕይ የመደመር መንግሥት እሳቤ የሀገሪቱን ሁለንተናዊ የልማት አቅጣጫዎችን ወደ አዲስ የዕድገት ምዕራፍ እያሸጋገረ ይገኛል። በዚህም በግብርና ዘርፍ ብቻ ተወስኖ የቆየውን የኢኮኖሚ መሰረት ወደ ባለብዙ ዘርፍ የኢኮኖሚ ልማት ለማስፋት ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርሙ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል። በዚህም በግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ቱሪዝም፣ ማዕድንና ቴክኖሎጂ ዘርፎች በተከናወኑ በርካታ ተግባራት ተጨባጭ ውጤቶች እየተመዘገቡ ይገኛሉ፡፡ የመደመር መንግሥት ምሥረታና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መክፈቻ ሥነ ሥርዓት፣ አዲሱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ን ለቀጣይ አምስት ዓመታት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ የሰየመ ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩም የሀገሪቱ የልማት ስኬቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል። የበጋ መስኖ ልማትና የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብሮች የስንዴ፣ ሩዝ፣ ወተትና እንቁላል ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የተያዘውን ግብ እያሳኩ መሆኑን፤ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ፣ በዲጂታሉም የፋይዳ ማንነት፣ የገበታ፣ የወንዝ ዳርና የማዕድን ልማት ፕሮጀክቶችም የምርትና አገልግሎት አሰጣጥ ባህልን ወደ ላቀ አዲስ ምዕራፍ እንዲሸጋገሩ ማድረጋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምክር ቤቱ ባደረጉት ንግግር አንስተዋል። የብዝሃ ዘርፍ ኢኮኖሚ ትግበራና ስኬቶቹ የመደመር መንግሥት እሳቤ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ የልማት እንቅስቃሴዎች ወደ አዲስ ምዕራፍ እንዲሸጋገር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገ እና ውጤቶችም እንዲመዘገቡ እያስቻለ ይገኛል። በዚህም በግብርና ዘርፍ በዘመናዊ የመስኖ ልማት፣ በበጋ ስንዴ ምርት እና በኩታ-ገጠም የአስተራረስ ዘዴዎች የተገኙ ውጤቶች የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥና የውጭ ጥገኝነትን ለመቀነስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛሉ። በተጨማሪም በሌማት ትሩፋት፣ በከተማ ግብርና፣ በግብርና ምርቶች ላይ እሴት መጨመርና ሌሎች ውጤታማ ተግባራትም ተከናውነዋል። በግብርናው ዘርፍ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እየተከናወኑ በሚገኙ ዘርፈ ብዙ ተግባራት ለዜጎች በተለይም ለወጣቶችና ለሴቶች አዳዲስ የሥራ ዕድሎችን እየፈጠረ ይገኛል። በመደመር መንግሥት እሳቤ በመመራት በዘርፉ እየተከናወኑ የሚገኙት ውጤታማ ተግባራት ለውጭ ምንዛሬ ግኝትና ለኢንዱስትሪዎች ግብዓት ከማቅረብ አንጻርም አበርክቷቸው ከፍተኛ ሆኗል። ከሀገሪቱ ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ግብርና ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዝ በመሆኑ ይህን ዘርፍ ማዘመን፣ ሜካናይዜሽንን ማስፋፋትና የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋሙ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም የኢትዮጵያን የልማትና የዕድገት ጉዞ ስኬታማ ለማድረግ ወሳኝ መንገድ ነው። በኢንዱስትሪው ዘርፍ ሀገራዊ የማምረት አቅምን በማሳደግ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ለመቀነስ እና የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ለማሳደግ እና ለማዳን እንዲሁም ለዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ወሳኝ ሀገራዊ እርምጃዎች ተወስደዋል። ለዚህ እንደጥሩ ምሳሌ የሚጠቀሰው በስፋት ተተግበሮ ተጨባጭ ውጤቶች የተመዘገቡበት የ"ኢትዮጵያ ታምርት" ንቅናቄ ነው። ይህ ሀገራዊ ንቅናቄ በዘርፉ ለዓመታት ተግዳሮት ሆነው የቆዩ ጉዳዮችን በመፍታት ተጨባጭ ለውጦችን በማምጣት የሀገሪቱን የማምረት አቅም ወደ አዲስ ምዕራፍ እንዲሸጋገር አስችሏል። የኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም ለማሳደግ በተወሰዱ ተግባራዊ እርምጃዎች አሁን ላይ የማምረት አቅማቸው ከ69 በመቶ በላይ ማደጉን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ሀሰን መሐመድ መግለጻቸው የንቅናቄውን ውጤታማነት በግልጽ የሚያመላክት ነው። ንቅናቄው ተዘግተው የነበሩ ፋብሪካዎች ወደ ሥራ እንዲመለሱ፣ የሰው ኃይል እንዲሰባሰብና ምርታማነት እንዲያድግ በማድረግ ረገድ የአንበሳውን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል። ቀደም ሲል ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለመተካት በተሰጠው ከፍተኛ ትኩረትም በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ማዳን ተችሏል። ለዚህም የኢንዱስትሪ ፓርኮች ማስፋፋትና ማጠናከር፣ ሀገር በቀል የመድኃኒት አምራቾች አቅም እንዲጎለብት በተሰራ ስራም እንዲሁ ከውጭ የሚገቡ መድኃኒቶች በሀገር ውስጥ እንዲመረቱ መደረጉ ለዚህ ጥሩ ማሳያ ነው። የመደመር መንግሥት በኢንዱስትሪ ዘርፍ እንዲመዘገብ ያስቀመጠውን አቅጣጫ ስኬታማ ለማድረግ በርካታ የፖሊሲ እና የአሰራር ማሻሻያዎችን አድርጓል። በዚህም የአገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍናን የሚጨምሩ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ጥቅም ላይ እንዲውሉ እና የኃይል አቅርቦትና ሌሎች ማሻሻያዎች ተደርገዋል። እነዚህ የተግባር እርምጃዎች የዘርፉን ምርታማነት በማሳደግ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቱ እንዲጨምርና ከፍተኛ ኢንቨስትመንት መሳብ አስችለዋል። የመደመር መንግሥት ትኩረት ከሰጣቸው እና ውጤቶች ካስመዘገበባቸው ዘርፎች መካከል የዲጂታል ዘርፍ ተጠቃሽ ነው። ይህ ዘርፍ ለሀገሪቱ ሁለንተናዊ ዕድገት ካለው ከፍተኛ አስተዋጽኦ አንጻር የዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ ተቀርጾ ተግባራዊ ተደርጓል። ባለፉት ዓመታት ተግባራዊ ተደርጎ የሚጠበቀውን ውጤት ማስመዝገቡ ይታወቃል። በዚህም ዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ 2025 የኢትዮጵያን የልማትና የዕድገት ጉዞ በማፋጠን፣ ሀገሪቱን በቴክኖሎጂ ወደሚመራ ኢኮኖሚ ለማሸጋገር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ የሚገኝ አዲስ የዕድገት ሞተር ነው። ለዚህም ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ማጠናቀቂያ እና በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ይፋ ማድረጊያ መርሃ ግብር ላይ "ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ መቶ በመቶ በሚባል ደረጃ የተሳካ ነው" ሲሉ መግለጻቸው። ይህም ብቻ ሳይሆን ከአምሥት ዋና ዋና ዘርፎች መካከል አንዱ ስትራቴጂ መሆን አለበት ለኢትዮጵያ ብልጽግና አይተኬ ሚና አለው ነው ያሉት። ዲጂታል ቴክኖሎጂ የመደመር መንግሥት ለነደፋቸው ሌሎች ዋና ዋና ዘርፎች ውጤታማነትም አጋዥ ሆኖ እያገለገለ እንደሚገኝና ለበርካታ ወጣቶች ሰፊ የሀገር ውስጥ እና የውጭ የሥራ ዕድል እየፈጠረ ነው። በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘረፍ እየተገኙ ካሉ ውጤቶች መካከል የፋይናንስ ዘርፉን ቀልጣፋ እያደረገ መምጣቱ ተጠቃሽ ነው። በዚህም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ዲጂታል የክፍያ ስርዓትን በመጠቀም ግብይት እየፈጸሙ መሆኑ ለውጤታማነቱ ጥሩ ማሳያ ነው። የጥሬ ገንዘብ ዝውውርን መቀነስ፣ ሥራንና ንግድን ማቀላጠፍ እንዲሁም ሰዎች ገንዘብ በሚያስፈልጋቸው ጊዜና መጠን እንዲጠቀሙ እያስቻለ ይገኛል። ይህም ከባንክ ውጭ የሚዘዋወር የገንዘብ መጠንና የህትመት ወጪ እንዲቀንስና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እንዲጨምር አስችሏል። ከዚህ አኳያ በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፉ እንዲመጣ የታቀደው ግብ እየተሳካ ነው። በፋይዳ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያና መሶብ የአንድ ማዕከል የመንግሥት አገልግሎት መስጫ ማዕከላትን ለማስፋት በተሰራ ስራ አመርቂ ውጤቶች ተመዝግበዋል። እነዚህ ወሳኝ የመንግስት ውሳኔዎች የተቀናጀ የመንግሥት አገልግሎት ምህዳርን በመፍጠር ዜጎች አገልግሎቶችን ፈጣን፣ ግልጽ እና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ እንዲያገኙ እያስቻሉ ይገኛሉ። እነዚህ በቴክኖሎጂ የተደገፉ አሰራር ስርዓቶች አገልግሎት ለማግኘት ይባክን የነበረውን ጊዜና ወጪ ከመቀነሳቸው ባለፈ ቢሮክራሲንና ብልሹ አሰራረን በመቀነስ በኩል ከለፍትኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛሉ። በመደመር መንግሥት እሳቤ ከተገለጡ የሀገር ሀብቶች መካከል ለቱሪዝም ዘርፉ በተሰጠው ትኩረት የተገኙ አመርቂ ስኬቶች ይጠቀሳሉ። በዚህም አቧራ ለብሰው የቆዩ እና ለቱሪዝም መስህብነት ቢውሉ ከፍተኛ ጠቀሜታ የነበራቸውን ሀገራዊ ሀብቶች በመግለጥና በማልማት ወደ ወረት የተቀየሩበት አስደማሚ ስራዎች ለዚህ ትልቅ ማሳያዎች ናቸው። ይህ ውጤታማ ተግባራም ዘርፉ እንዲነቃቃ በማድረግ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እንዲያድግ በር ከፍቷል። በዚህም ኢትዮጵያ በባለፈው 2018 በጀት ዓመት ከቱሪዝም ዘርፍ ከ5 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ገቢ አግኝታለች። በሌላ በኩል ለበርካታ ዜጎችን ሰፊ የሥራ ዕድል ፈጥሯል። በመላ ሀገሪቱ ለመሠረተ ልማት መስፋፋት የተሰጠው ትኩረትም የከተሞች ውበትና መስህብነት እንዲያድግ ጉልህ ሚና ተጫውቷል። በዚህም የሀገር ውስጥና የውጭ ጎብኚዎች ፍሰት ጨምሯል። ለውጭ ምንዛሬ ግኝት ማደግም እንዲሁ አስተዋጽኦው የጎላ ነው። የየአካባቢዎቹ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች ተነቃቅተዋል። የኢትዮጵያም የቱሪዝም ገጽታ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲጎላ አስችሏል። የመደመር መንግሥት በሀገር በቀል ኢኮኖሚ ሪፎርም ለማዕድን ልማት እንዲሁ በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረግ የሚያስችል ምህዳር ተፈጥሯል። ባለፉት አመታት ለዘርፉ ትኩረት ተሰጥቶ በመሰራቱ ተጨባጭ ውጤቶች ተገኝተዋል። ቀደም ሲል በጥሬው ወደ ውጭ ይላኩ የነበሩ የወርቅ፣ ድንጋይ ከሰል፣ ኦፓልና ሌሎች ማዕድናት ላይ እሴት ተጨምሮባቸው ለወጪ ንግድ እንዲውሉ ለማድረግ አዳዲስ አሰራሮች በመዘርጋታቸው ስኬቶች ተመዝግበዋል። ለአብነትም ከወርቅ ምርት የሚገኘው የውጭ ምንዛሬ ገቢ በከፍተኛ መጠን አድጓል። ለምሳሌ በ2018 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ ከወርቅ ወጪ ንግድ ከ5 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ገቢ አግኝታለች። በሲሚንቶ፣ ድንጋይ ከሰል፣ ሴራሚክ ምርቶች ለኢንዱስትሪና ለግንባታ ዘርፍ ግብዓት በመሆን በርካታ ፋይዳዎች ተገኝተዋል። የማዕድን ዘርፍ ለሥራ ዕድል ፈጠራና የአካባቢ ኢኮኖሚ መነቃቃት እንዲሁም የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ለመሳብ ጉልህ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። በጥቅሉ የመደመር መንግሥት የግብርና፣ የኢንዱስትሪ፣ የዲጂታል ቴክኖሎጂ፣ የቱሪዝም እና የማዕድን ዘርፎች ለሀገር ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የየድርሻቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ለማስቻል የወሰዳቸው የፖሊሲ እና የስትራቴጂ እርምጃዎች ሀገሪቱ በአዲስ የዕድገት አቅጣጫ እንድትጓዝ እያስቻላት ይገኛል። ይህም ለወጭ ንግድ የሚሆኑ ምርቶች በስፋት እንዲመረቱ፣ ከውጭ ይገቡ የነበሩ ምርቶች በሀገር ውስጥ እንዲመረቱ በዚህም የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ለማሳደግና ለማዳን እንዲሁም የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥና አዳዲስ የሥራ ዕድሎችን ከመፍጠር ባለፈ የመንግሥትን አገልግሎት አሰጣጥ ስራዓት በማዘመን፣ ሀገሪቱ ዘላቂና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ብልጽግና እንድታስመዘግብ ጠንካራ መሠረት ጥሏል።
ዴሞክራሲያዊ ምርጫ፤ የመደመር መንግሥት ገለልተኛ ተቋማት ግንባታ ተጨባጭ ፍሬ!!
Oct 8, 2026 263
ምርጫ የሥልጣን ማሸጋገሪያ፣ የዜጎች የፖለቲካ ይሁንታ ችሮታና የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ በተግባር የሚፈተንበት የአደባባይ መድረክ ነው። በዚህ ሂደት የዜጎች ተሳትፎ፣ የተቋማት አቅምና የፖለቲካ ተዋናዮች የፉክክር ልምምድ በጋራ ሲጣመሩ የሀገርን የዴሞክራሲ ግንባታ ያጎለብታል። ዴሞክራሲያዊ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጤናማ ፉክክር ማዕከል ያደርጋል። የፉክክር ሂደቱም በሕግ፣ በተቋማት ግንባታና በዜጎች የነቃ ተሳትፎ እየፈካ የሚሄድ የዴሞክራሲ ልምምድ ነው። ይህም በኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ-8 ንዑስ አንቀጽ-3 ላይ የሕዝቦች ሉዓላዊነት በተመረጡ ተወካዮችና በቀጥታ ዴሞክራሲያዊ ተሳትፎ የሚገለጽ መሆኑን ይደነግጋል። በተመሳሳይም በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ-38 ንዑስ አንቀጽ-1 (ሀ) መሰረት ዜጎች በቀጥታና በነፃ በመረጧቸው ተወካዮች በኩል በሕዝባዊ ጉዳዮች አስተዳደር የመሳተፍ ሙሉ መብት አላቸው። ምርጫ የሥልጣን ማሸጋገሪያ መንገድ፣ ዜጎች የፖለቲካ ፈቃዳቸውን የሚገልጹበት፣ ተቋማት የዴሞክራሲ አሰራራቸውን የሚፈትኑበትና ከሂደቱ የሚገኘው ልምምድ ለቀጣይ የዴሞክራሲ ግንባታ መሠረት የሚሆንበት የአደባባይ መድረክ ነው። ከዚህ አንጻር የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የዜጎችን ንቁ ተሳትፎ በመግለጥ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ተሞክሮዎችንና የተቋማትን አቅምን የሚያሳይ የአስቻይ ልምምድ ሆኖ አልፏል። በሰባተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአንደኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመሥረቻ ስብሰባውን ባካሄደበት ወቅት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ን በድጋሚ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰይሟል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ የዴሞክራሲ ባህል የሚፈተነው በምርጫ ወቅት በሚካሄድ ልምምድ መሆኑን ገልጸዋል። ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫም እንደማንኛውም ሕዝባዊ ምርጫ ተካሄደ ተብሎ ብቻ የሚገለጽ የሰርክ ክንውን እንዳልነበረ በመጠቆም፤ ዜጎች ፈቃዳቸውን ለመግለጽ በብዙ ውዥንብሮች መካከል ማለፋቸውን አንስተዋል። የምርጫው አጠቃላይ ሂደትም የኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ መሰረቱ እየጠነከረ መምጣቱን በግልጽ በማሳየት ወደፊት ታሪክ በደማቅ ብዕር እንደሚጽፈውና ትውልድም ደጋግሞ እንደሚዘክረው ገልጸዋል። ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ምርጫን ከአንድ የሥልጣን ውድድር ባሻገር የዴሞክራሲ ልምምድን ለማጠናከር የሚያልፍበትን ሂደት በጉልህ ያመላክታል። በኢትዮጵያ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ ከ54 ሚሊየን በላይ መራጮች በመሳተፍ ዜጎች ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ያላቸውን ጽኑ ፍላጎት በተግባር አስመስክረዋል። የኢትዮጵያውያን በምርጫው የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ከሌሊት እስከ ሌሊት ያሳዩት ቁርጠኝነት ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ ያላቸውን ቀናኢነት በግልጽ አሳይተዋል። ይህም ዜጎች የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ የሩቅ ተመልካች ሳይሆኑ ሕገ-መንግሥታዊ መብታቸውን በመጠቀም በሂደቱ ውስጥ በቀጥታ የሚሳተፉ ባለቤቶች መሆናቸውን አረጋግጧል። በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የታየው የወጣቶች ተሳትፎም የኢትዮጵያ ወጣቶች ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ያላቸውን ከፍተኛ ሚና በተግባር አንጸባርቋል። ወጣቶች በመራጭነት፣ ተመራጭነት፣ በአስተባባሪነትና አስፈጻሚነት የነበራቸው ንቁ ተሳትፎም የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አካል መሆናቸውን አንጸባርቋል። የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫም የቅድመ ምርጫ፣ ምርጫና የድህረ ምርጫ ሂደት ውጤታማነት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን የገለልተኛ ተቋማት የማስፈጸም አቅም እየጎለበተ መምጣቱን ልብ ይሏል። ምርጫ በተፈጥሮው የፖለቲካ ፓርቲዎች በሃሳብ ጠረጴዛ ተገናኝተው የሚፎካከሩበት ሂደት ሲሆን በመጨረሻ ሀገር አሸናፊ የምትሆንበትን አማራጭ በጸጋ የሚቀበሉበት ስልጡን መድረክ ነው። ለዚህም ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሰባተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአንደኛ ዓመት የሥራ ዘመን ስብሰባ ላይ፤ ማንኛውም ምርጫ አሸናፊና ተሸናፊ ፓርቲ ሊኖረው ቢችልም ኢትዮጵያ ግን አሸናፊ እንጂ ተሸናፊ ዜጋ እንደማይኖራት መናገራቸው። የምርጫ ሂደት የሚመዘነው በአሸናፊና ተሸናፊ ፓርቲዎች ብቻ ሳይሆን ዜጎች የፖለቲካ ፈቃዳቸውን በሕጋዊ መንገድ መግለጽ መቻላቸውና ተቋማት ሂደቱን በአግባቡ መምራታቸው ጭምር ነው። የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ በአንድ ምርጫ ሂደት የሚጠናቀቅ አይደለም። ይልቁንም የዜጎች ተሳትፎ፣ የወጣቶች ሚና፣ የፖለቲካ ተዋናዮች ልምምድና የምርጫ ተቋማት አቅም በተከታታይ ሲጠናከር የሚገኝ ውጤት እንጂ። ከዚህ አንጻር የኢትዮጵያ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ከውጤት ባሻገር በዜጎች ተሳትፎ፣ በወጣቶች ሚና፣ በመንግሥትና የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ተቋማዊ ልምምድ የተገኙ ተሞክሮዎችን ለቀጣይ የዴሞክራሲ ግንባታ ማዋል ላይ ይመሰረታል። የመደመር መንግሥት የዴሞክራሲ ተቋማትን ገለልተኛነት የሚያስጠብቅ ውጤታማ የሪፎርም እርምጃ ውስዷል። ፍሬውም በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የማስፈጸም አቅም በተግባር ታይቷል። ዜጎችም ነጻ፣ ፍትሐዊ፣ ተዓማኒና ዴሞክራሲያዊ ምርጫን በማካሄድ መንግሥታቸውን እንዲመሰርቱ አስችሏል። የምርጫ ቀን ሲያበቃ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ሂደት የሚያበቃ አይደለም። የተገኘውን ልምድ ወደ ቀጣዩ ምርጫ፣ ወደ ቀጣዩ ትውልድና ወደ ቀጣዩ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ሂደት ምዕራፍ እየተላለፈ ይቀጥላል።
የኢትዮጵያን መሻት የሚያሳካ- የመደመር መንግሥት  
Oct 8, 2026 113
በሰውነት ጀምበሩ ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ ኢትዮጵያ በዘመናት መካከል በተለያዩ የመንግሥት አስተዳደር ሥርዓቶች ያለፈች ጥንታዊት ሀገር ነች። ይህ የመንግሥት ሥርዓተ ታሪክ የመሪዎችን ርዕይ፣ የሕዝቦችን አብሮነት፣ የሥልጣን ፍላጎትና የሀገር ግንባታ ሕልምን አጣምሮ የያዘ ሕያውና የዘመናት ጉዞ ነው። የኢትዮጵያ ታሪክ ከንጉሠ ነገሥቱ ፍጹማዊ ማዕከላዊነት ጀምሮ እስከ ደርግ ሶሻሊስታዊ ሙከራ፣ ከኢሕአዴግ የብሔር ፌዴራሊዝም እስከ አሁኑ ሀገር በቀል የመደመር ፍልስፍና ያለው ሂደት እያንዳንዱ ሥርዓት በሀገሪቷና በሕዝቦች ላይ የራሱን ዐሻራ አሳርፏል፤ እያሳረፈም ይገኛል። የንጉሠ ነገሥቱ ዘመን በዘመናዊ ተቋማት ግንባታና በማዕከላዊ ጠንካራ መንግሥት ምስረታ የሚታወስ ቢሆንም የሰፊውን ሕዝብ መሠረታዊ የነፃነት፣ የመሬት ባለቤትነት እና የማንነት ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት ባለመቻሉ በለውጥ ማዕበል ተናግቶ በደርግ ወታደራዊ ሥርዓት ተተካ። ደርግ "መሬት ላራሹ" አዋጅን የመሳሰሉ ጅምሮችን ቢያደርግም፣ ዴሞክራሲያዊ መብቶችን በመርገጡ እና የቀይ ሽብርን አሰቃቂ ጭፍጨፋ በማካሄዱ ኢትዮጵያን ረጅም የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ ከቷታል። ደርግ የ1987 ዓ.ም ሕገ-መንግሥት ሀገሪቱን በብሔር፣ በቋንቋና በመልክዓ ምድር ላይ በተመሠረቱ 9 ክልሎችና 2 የከተማ አስተዳደሮች በመክፈል አስተዳደራዊ መዋቅሩን ዘረጋ። ይሁን እንጂ ጠንካራ የሕዝብ አገልግሎት ፍላጎት የሚያረካ፣ ለልማትና ለዕድገት ቅድሚያ የሚሰጥ ተቋም መገንባት ተስኖት ቆይቷል። በእርግጥ የኢሕአዴግ በሕገ-መንግሥት አስተዳደር ለዘመናት ታፍነው የነበሩ ብሔሮችና ብሔረሰቦች ቋንቋቸውን እንዲያደራጁ፣ ባህላቸውን እንዲያሳድጉና አካባቢያቸውን በራሳቸው የሚያስተዳድሩበትን ዕድል ለመፍጠር ጥረት አድርጓል። ነገር ግን የፖለቲካ ምኅዳሩን አንዱን አጋር ሌላውን እህት በሚል አግላይና ከፋፋይ ስልት አስተዳደር የዘረጋው ሕወሓት መራሹ ሥርዓት በሀገሪቷ ላይ ፈላጭ ቆራጭ በመሆን ሥልጣነ መንበሩን ተቆናጦ ቆይቷል። ይህም አብዮታዊ ዴሞክራሲ ሥርዓት ሰዎችን ከሀገራዊ ዜግነታቸው ይልቅ በብሔር አጥር ውስጥ ብቻ እንዲወሰኑ አድርጎ ቆይቷል። የፖለቲካ ምኅዳሩን በመዝጋት፣ የዜጎችን መሰረታዊ ሰብዓዊ መብቶች በመጨቆንና በየአካባቢው የብሔር ግጭቶች እንዲባባሱ በማድረጉ ተቃውሞ ገጠመው። አልቻለም እንጂ የሕዝብን ተቃውሞ በማፈን ለጥቂት ጊዜ ለመራመድም ሙከራ አድርጎ ነበር። ሕዝባዊ እምቢተኝነትና ማዕበሉም በአራቱም አቅጣጫ ገደፉን አልፎ ኢትዮጵያ በ2010 ዓ.ም ለውጥን አምጣ ወልዳለች። ይህ ለውጥ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሚመራውን የመደመር መንግሥትን እንዲተዋወቅ አድርጓል። ይህ በሀገር በቀል ዕውቀት የሚመራው የመደመር መንግሥት ስብራቶችን የመጠገንና አዲስ አቅጣጫ የመቀየስ ባሕሪ የነበሩ ጭቆናዎችን በማስቀረት፣ የፖለቲካ ምኅዳሩን በመቀየር አጋርና ዋና የሚለውን ሥርዓት በማስቀረት ሁሉም ዜጋ በሀገሩ ላይ የመወሰንና የመጠቀም መብትን የሚያጎናጽፍ ሥርዓት ፈጥሯል። ዛሬ "መደመር" የሚለውን ሀገራዊ ፍልስፍና መሪ ፍኖት አድርጎ በመውሰድ የመደመር ዕይታ እያሰረጸ መልካም ነገሮችን ማስቀጠል፣ የተበላሹትን ማረምና አዳዲስ የጎደሉ ነገሮችን ማሟላትን እንደ ዋና መርህ አድርጓል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመደመርን አስተሳሰብ ሲያብራሩ "መደመር ማለት ያለንን መልካም ነገር አቀናጅተን፣ የጎደለንን ሞልተን፣ የተበላሸውን አርመን ወደፊት መራመድ ነው። በጽንፈኝነትና በከፋፋይ ፖለቲካ ሀገር አትገነባም። ኢትዮጵያ ሁላችንንም አቅፋ የምትይዝ ሀገር ናት" ብለዋል። መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም የለውጥ መንግሥት ኢትዮጵያን ከተረከበ ወዲህ ባለፉት ስምንት ዓመታት በኢትዮጵያ በርካታ ማሻሻያዎችን በማድረግ ሁሉን አቀፍ ለውጦች አስመዝግቧል። ለአብነት ሀገር በቀል የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን በማድረግ ኢኮኖሚው ከነበረበት ስብራት የሚያገግምበትን ዕድል ፈጥሯል። ይህም ግብርና መር የነበረውን የኢኮኖሚ ሥርዓት ወደ ብዝኅ የኢኮኖሚ ልማት አቅጣጫን በመቀየስ በርካታ ለውጦችን አስመዝግቧል። ባለፉት ዓመታት በርካታ ሀገራዊ ንቅናቄዎች በመተግበር በየዘርፉ እመርታዊ ውጤቶች የሚመዘገብበትን መንገድ ቀይሷል። ይህም ከገበታ ለሸገር ጀምሮ ገበታ ለሀገር፣ ገበታ ለትውልድ በሚል የተፈጠሩ ንቅናቄዎች የቱሪስት መስህቦችና መዳረሻዎችን በማስፋፋትና በማደስ ኢትዮጵያን የቱሪዝም ማዕከል እያደረጋት ይገኛል። ዜጎች የተትረፈረፈና የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኙ የሚያስችል የሌማት ትሩፋት መርሃ-ግብር ተግባራዊ በማድረግ ብዙዎች ተጠቃሚ ሆነዋል። ከራሳቸው አልፎም ለገበያ በማቅረብ ትሩፋታቸውን አጋርተዋል። በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር ከ56 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል፣ በዲጂታል ኢትዮጵያ፣ በመሶብ የአንድ ማዕከልና ሌሎችም የተጀመሩ ንቅናቄዎች በርካታ ለውጦችን መመዝገብ ችለዋል። ለውጡ ኢኮኖሚያዊ ለውጦችን ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ ፓርቲዎችን ስም ከተቃዋሚነት ወደ ተፎካካሪነት በመቀየር በፖለቲካው መስክ ሁሉም እኩል እንዲሳተፍ በማድረግ የፖለቲካ ምኅዳሩን አስፍቷል። በዚህም ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች በሀገር ጉዳይ ላይ እኩል የሚሳተፉበትን አውድ ፈጥሯል። ለዚህም ነው በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በርካታ የተፎካካሪ ፓርቲዎች ሰላማዊና የተረጋጋ ተሳትፎ ያደረጉት። ሕዝብ የሰጣቸውን ድምፅ ተቀብለው ለሀገር መጽናት በአብላጫ ድምፅ ካገኘው ፓርቲ ጋር በጋራ ለመሥራት ጽኑ አቋማቸውን በመግለጽ በኢትዮጵያ ታሪክ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ አርዓያ የሚሆን ገድል የፈጸሙት። በሀገር ደረጃ የተመዘገቡትን ድንቅ ለውጦች በጥሞና የተመለከተው ሕዝብ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ለብልፅግና ፓርቲ ድምፅ በመስጠት አድናቆቱን ገልጿል፤ ተግባሩንም እንዲቀጥል አደራ ሰጥቷል። በሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ገዥው ፓርቲ የሕዝብ ተወካዮችን ምክር ቤት 428 ወንበሮችን በማሸነፍ ቀሪዎችን ደግሞ የተፎካካሪ ፓርቲዎች ድምፅ አግኝተው ምክር ቤት ገብተዋል። ከአብላጫው ሕዝብ ድምፅ ያገኘውና አደራውን የተቀበለው ብልፅግና በጠንካራ መንፈስ፣ በጸና አደራ የመደመር መንግሥትን መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም በይፋ መስርቷል። ምክር ቤቱም በአካሄደው ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) ለሁለተኛ ጊዜ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ሰይሟል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በምክር ቤቱ ለሁለተኛ ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በተሰየሙበት ወቅት እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ሥርዓትን የመገንባት ሙከራዎች የቁጭት ችግር ባይኖርባቸውም የእፎይታና የስክነት ችግር ይስተዋልባቸው ነበር። ባለፉት ዓመታት የሌሎችን ተሞክሮ ከራሳችን ጋር ስናስማማ ቆይተናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)፤ መደመር የኢትዮጵያ ሥልጣኔ ማሰቢያ ቋንቋ መሆን እንደሚችል አረጋግጠናል ብለዋል። አዲሱ የመደመር መንግሥት መጪውን ዘመን ታሳቢ ያደረገ የፌዴራል መንግሥት አስፈጻሚ አካላት ስያሜ፣ አደረጃጀት፣ ሥልጣንና ተግባር በመቀየር በምክር ቤቱ አዋጅ እንዲጸድቅ አድርጓል። የአዋጁ መውጣትና ተግባራዊ መሆን የተቋማትን የማስፈጸም አቅም ያጎለብታል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመደመር መንግሥት የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላትን አቅርበው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲያሾሙ እንደገለጹት፤ ትምህርት ብቻውን የመፈጸም አቅምን ሊተካ ስለማይችል፣ የተማሩ ነገር ግን ተግባር ላይ ውጤት የማስመዝገብ፣ የመከታተልና ከፍተኛ ዲሲፕሊን ያላቸውን ግለሰቦች ማጣጣም ላይ ትኩረት ተደርጓል ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደገለጹት የአሁኑ ሹመት ከመቼውም ጊዜ በተለየ መልክ ከባድ ኃላፊነት ነው። ሌት ተቀን በመሥራት የሕዝብን ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ለውጡ በእያንዳንዱ ሰው ዘንድ ጥቅም የሚያስከትል መሆኑን የማረጋገጥ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል። ይህ ሲታይ የመደመር መንግሥት ተሿሚዎቹ ኃላፊነቱን ለመወጣት እንደሚችሉ በተሰማሩበት የሥራ መስክ የተሻለ አፈጻጸምና ውጤት ያስመዘገቡ አካላት በሥራ ልምዳቸው ተመዝነዋል። የመደመር መንግሥት ተሿሚዎችም በመጪዎቹ አምስት ዓመታት በርካታ ሀገራዊ ግቦችን ለማሳካት ከፍተኛ ጥረትና ሩጫ የሚጠይቅ በመሆኑ ያንን ኃላፊነት ለመወጣት የሚያስችል አቅም ያላቸው መሆኑ በሚገባ ተፈትሿል። በዚህም በምርጫው ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ድምፅ በመስጠት የሰጡትን ታላቅ አደራና የመንግሥትን ቁመና የማጠናከር ፍላጎት ለመሸከም ዝግጁ የሆኑ ሙስናን የሚጸየፉና ሕዝብን ማገልገል እንደ ታላቅ ጸጋ የሚቆጥሩ መሆናቸው በጠቅላይ ሚኒስትሩም በምክር ቤት አባላትም ታምኖባቸዋል። ይህ አዲስ አደረጃጀትም የኢትዮጵያን የማንሰራራት ጉዞ እውን ለማድረግ የሚረዳ ፍኖት ነው። ነገር ግን ይህ የመንግሥት አደረጃጀት እንደ ሀገር የታሰበውን ሀገራዊ ዓላማ ማሳካት እንዲችል ሁሉም የማኅበረሰብ አካል በየተሰማራበት መስክ መትጋት ይገባል። ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የመንግሥትን የትኩረት አቅጣጫ ለሁለቱም ምክር ቤቶች ባቀረቡበት ወቅት፤ የኢትዮጵያን ሰላም ለማጽናትና ልማትን ለማረጋገጥ ሁሉም የሚጠበቅበትን ኃላፊነት መወጣት እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል። እናም የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ዕድገትና ብልፅግና ለማረጋገጥ በሚደረገው ሀገራዊ ጥረት የበኩላችንን ኃላፊነት እንወጣ- መልዕክታችን ነው።
ገቢር-ነበብ ዲፕሎማሲ፤ የመደመር መንግሥት ብሔራዊ ጥቅምን የማስጠበቅ መርህ
Oct 8, 2026 118
ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ ፣ ታላቅ ርዕይ ባለቤቷ ኢትዮጵያ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲዋ አንድ ጉልህ ለውጥ- ዲፕሎማሲው ከምላሽ ሰጪ አቀራረብ ወደ ገቢር ነበብነት፣ ተሳታፊና ሀገራዊ ጥቅምን በግልጽ ወደሚያስቀምጥ አቅጣጫ ተሸጋግሯል። የመደመር መንግሥት የውጭ ግንኙነት አቀራረብ የሀገሪቱን ጥቅም ከጎረቤት ሀገራት ጥቅም፣ ከቀጣናዊ ሰላም፣ ከአህጉራዊ ትብብርና ከዓለም አቀፍ አጋርነት ጋር በማስተሳሰር የሚጓዝ ነው። ይህም ሀገራዊ ጥቅምን መተው ሳይሆን፣ የራስን ጥቅም ከሌሎች ጋር በሚያጣጥም መንገድ ማሳካትን የሚያስችል የጋራ ተጠቃሚነት አስተሳሰብ ነው። 👉ቅድሚያ ለጎረቤት፤ የጋራ ጥቅም የዲፕሎማሲው መሠረት የኢትዮጵያ የውጭ ፖሊሲ ግንኙነት ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያለውን ግንኙነት በቀዳሚነት ማስቀመጡ የዲፕሎማሲው አንዱ ጉልህ መገለጫ ነው። በአፍሪካ ቀንድ ያለው የሰላምና ደህንነት ሁኔታ፣ የንግድ ትስስር፣ የህዝብ እንቅስቃሴ፣ የውሃና የኃይል ሀብት፣ የመሠረተ ልማት ትስስርና የባህር መዳረሻ ጉዳዮች በአንድ ሀገር ብቻ ሊፈቱ የሚችሉ አይደሉም። ስለዚህም ነው የመደመር መንግሥት የጎረቤት ፖሊሲ ሀገራዊ ጥቅምን ከቀጠናዊ ጥቅም ጋር በማጣመር እያስኬደው የሚገኘው። ይህም የጎረቤት ሀገር መረጋጋት ለኢትዮጵያ መረጋጋት፣ የጎረቤት ኢኮኖሚ መጠናከርም ለኢትዮጵያ ንግድና ኢኮኖሚ እድል ነው ከሚለው አስተሳሰብ ይነሳል። ይህንኑ አቅጣጫ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመጀመሪያ ዓመት የሥራ ዘመን መጀመሪያ መደበኛ ስብሰባ ላይ ሲናገሩ ኢትዮጵያ በሁለትዮሽና በባለብዙ ወገን ግንኙነቶች ብሔራዊ ጥቅሟን መሠረት አድርጋ እንደምትሰራ ነው የገለጹት። በዚህም ጎረቤት ሀገራት በተፈጥሮ የተገናኙ ወዳጆች መሆናቸውን ጠቅሰው፣ ከሁሉም ጋር በሰላም፣ በጋራ ጥቅምና በትብብር የመስራት መርህን እንደሚያስቀጥሉ ነው የገለጹት። 👉የባህር በር ባለቤትነት ጉዳይ፤ ሀገራዊ ጥቅም በዲፕሎማሲያዊ መንገድ የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ጉዳይ የሀገሪቷ የውጭ ፖሊሲ ከሚያተኩርባቸው ዋነኛ አጀንዳዎች አንዱ ነው። ኢትዮጵያ ከ130 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ያላት ሀገር እንደመሆኗ፣ ከዓለም ገበያ ጋር ያላትን የንግድ ትስስር ለማስፋትና የሎጂስቲክስ ወጪዎችን ለመቀነስ የባህር መዳረሻ የረጅም ጊዜ ሀገራዊ ጥቅም በማድረግ በትኩረት እየሰራችበት ትገኛለች። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንደሚገልጹት የመደመር መንግስት የኢትዮጵያ ስልጣኔ ያለ ባህር በር እውን ሊሆን እንደማይችል እና በሰጥቶ መቀበል መርህ ሀገሪቷ ወጥቶ መግቢያ በር እንዲኖራት እየሰራ ይገኛል። ይህም ጉዳዩን ከጎረቤት ሀገራት ሉዓላዊነትና ከቀጣናዊ ሰላም ጋር በማጣጣም በድርድርና በጋራ ጥቅም መርህ መፍትሔ ለመፈለግ ያለውን አቅጣጫ ያሳያል። የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ቁመና በሁለትዮሽ ግንኙነት ብቻ የሚወሰን አይደለም። አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ መሆኗ በአህጉራዊ የፖለቲካ፣ የሰላም፣ የደህንነትና የልማት አጀንዳዎች ላይ ለኢትዮጵያ ልዩ የዲፕሎማሲ ቦታ ይሰጣታል። በአፍሪካ ህብረት ያላት ተሳትፎም አህጉራዊ ትብብርን ከሀገራዊ ጥቅም ጋር ለማጣመር የሚያስችል መድረክ ነው። ይህም የመደመር እሳቤን ከሀገራዊ ድንበር አልፎ አፍሪካዊ ትብብርን እንደ የጋራ ልማትና ተጠቃሚነት መሠረት የሚመለከት መሆኑን ያሳያል። ኢትዮጵያ ከጃንዩወሪ 1 ቀን 2024 ጀምሮ የብሪክስ ሙሉ አባል መሆኗ በውጭ ግንኙነቷ የተጨመረ አዲስ የዲፕሎማሲ መድረክ ነው። አባልነቱ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ፣ ከእስያ፣ ከገልፍና ከሌሎች የግሎባል ሳውዝ ሀገራት ጋር ያላትን ትብብር ለማጠናከርና የዲፕሎማሲ አማራጮቿን ለማስፋት ዕድል ፈጥሯል። ብሪክስ ከኢኮኖሚና ከፋይናንስ ትብብር ባሻገር በዓለም አቀፍ ተቋማት ማሻሻያ፣ በደቡብ ደቡብ ትስስር ድምፅ መጠናከርና በብዙ ወገን ትብብር ዙሪያ የሚካሄዱ ውይይቶች መድረክ በመሆኑ ለኢትዮጵያ ተጨማሪ የዲፕሎማሲ አማራጭ ይፈጥራል። የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ከጎረቤትና ከአፍሪካ ደረጃ ባሻገር ከቻይና፣ ከህንድ፣ ከሩሲያ፣ ከቱርክ፣ ከገልፍ ሀገራት፣ ከአውሮፓና ከሌሎች የዓለም ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት እያሰፋች ትገኛለች። ግንኙነቱም በፖለቲካዊ ውይይት ብቻ ሳይወሰን ኢንቨስትመንት፣ ንግድ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኃይል፣ መሠረተ ልማትና የሰው ኃይል ልማትን ያካትታል። ይህ አቀራረብ ዲፕሎማሲው የውጭ ፖሊሲ ግቦችን ብቻ ሳይሆን የልማት ፍላጎቶችንም የሚያገለግል መሣሪያ እየሆነ መምጣቱን የሚያሳይ ነው። በዚህም የዲፕሎማሲ ስኬት በተፈረሙ ስምምነቶች ብዛት ብቻ ሳይሆን፣ በሚፈጠሩ የኢኮኖሚ እድሎች፣ የንግድና የኢንቨስትመንት ፍሰት፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርና የልማት ትብብር የሚመዘን ነው። በአጠቃላይ የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ጉዞ ሀገሪቱ የውጭ ግንኙነቷን ከሀገራዊ ጥቅም ጋር አጥብቃ በማስተሳሰር የዲፕሎማሲ አማራጮቿን እያሰፋች መምጣቷን ያሳያል። ከጎረቤት ሀገራት ጋር የጋራ ጥቅምን መሠረት ማድረግ፣ የባህር በር ባለቤትነት ጉዳይን በድርድር ለመፍታት መስመር መክፈት፣ በአፍሪካ ህብረት ተሳትፎን ማጠናከር፣ በብሪክስ መሳተፍና ከተለያዩ የዓለም ኃይሎች ጋር ግንኙነትን ማስፋት የዚህ አቅጣጫ ዋና መገለጫዎች ናቸው። የዛሬው የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ቁመና ከጎረቤት ግንኙነት ወደ ቀጣናዊ ፖለቲካል ኢኮኖሚ ትብብር፣ ከአህጉራዊ ተሳትፎ ወደ ዓለም አቀፍ የባለ ብዙ ወገን መድረኮች የሚዘልቅ ሰፊ አውታር እየገነባች መምጣቷ እውን ነው። የዚህ ጉዞ ዋና ገፅታም ሀገራዊ ጥቅምን በግልጽ ማስቀመጥ፣ የጎረቤቶችን ጥቅምና ሉዓላዊነት ማክበር፣ የቀጣናውን ሰላም ከሀገራዊ ጥቅም ጋር ማስተሳሰርና በተለያዩ የዓለም ዲፕሎማሲ መድረኮች ተሳትፎን ማስፋት ነው። በዚህ አንፃር የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ቁመና በገቢር ነበብ ዲፕሎማሲ እንዲሁም ኢትዮጵያ የራሷን ጥቅም እያስቀመጠች ከጎረቤት፣ ከአህጉርና ከዓለም ጋር የጋራ ጥቅም የሚፈጥር የዲፕሎማሲ መስመር እየገነባች መሆኗን የሚያሳይ አቅጣጫ ሆኗል።
ትንታኔዎች
ካለመችው ሸብረክ የማትል ኢትዮጵያ፤ ወጥቶ መግቢያ በሯን ታስከብራለች!!
Oct 9, 2026 101
በቤተልሔም ባህሩ ኢትዮጵያ የክንደ ብርቱዎች ምድርና የነጻነት ተምሳሌት መሆኗን ታሪክ ደጋግሞ ከትቦታል። በየዘመናቱ የተጎናጸፈቻቸው አኩሪ ገድልም የአፍሪካ ቀንዲልነቷን ደጋግማ እንድታረጋግጥ አስችለዋታል። ፈተናን ወደ ድል ተግዳሮትን ወደ ዕድል የምትቀይር በሕብርና ትብብር የተሸመነ አይበገሬ ሀገር መሆኗንም ታሪክ መዝግቧል፤ እየመዘገበም ይገኛል። ቅድመ አያቶቻችን በዓድዋ ሰንሰለታማ ተራሮች ላይ ባበሩት የነጻነት ጮራ የፈነጠቀው የድል ችቦ ለጭቁን የዓለም ሕዝቦች የነጻነት ተስፋን አብስሯል። ከዚያ የድል ታሪክ የተሸጋገረው የኢትዮጵያውያን አርበኝነትም በዚያ የሚያበቃ አይደለም። በእያንዳንዱ የትውልድ ምዕራፍ አዲስ የታሪክ ገጽ እየተጻፈ ቀጥሏል። ከጉሊት ነጋዴ እናት እስከ ሀገር ጠባቂ ሰራዊት፣ ከጎልማሳ እስከ ታዳጊ፣ ከሀገር ውስጥ እስከ የተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የጋራ ትጋትና ተሳትፎ የሀገራቸውን የልማት ሕልም እውን ለማድረግ የሚደርጉት ጥረት የዚህ ትውልድ አይበገሬነት መገለጫ ነው። በዚህ የጋራ ጥረት ውስጥ በጉባ ተራሮች ግርጌ የተገነባው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሕዝብ ትብብርና የብሔራዊ ቁርጠኝነት ተጨባጭ ተምሳሌት ሆኗል። በጳጉሜን 4 ቀን 2017 ዓ.ም የተመረቀው ሕዳሴም የኢትዮጵያን የልማት ጉዞ የሚያሳልጥ አቅም ፈጥሯል። ለአፍሪካውያኑም በራሳቸው አቅም ታላላቅ ፕሮጀክቶችን ማሳካት እንደሚችሉ የሚያመለክት የፓን አፍሪካኒዝም ሐውልት ሆኗል። የመደመር መንግሥት የልማት ፕሮጀክቶችን ለማሳካት የሚያደርገው ጥረትና የሚያሳየው ቁርጠኝነትም ኢትዮጵያ ህልሟን ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር ያላትን ጽኑ ፍላጎት ያመላክታል። በሰባተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሥራ ዘመን መክፈቻ ሥነ ሥርዓት ወቅት የሕዳሴ ግድብ የዘመናችን ትውልድ የአይበገሬነት ማሕተም መሆኑ መገለጹም ይህንኑ ያረጋግጣል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአዲሱ የመደመር መንግሥት ምሥረታ ወቅት ድጋሚ በጠቅላይ ሚኒስትርነት መሰየማቸውን ተከትሎ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ባስተላለፉት መልዕክት ኢትዮጵያ ካለመችው ትልም ሸብረክ ሳትል ዕድገቷን የምታስቀጥል ሀገር መሆኗን ገልጸዋል። ባለፉት ዓመታትም በርካታ ፈተናዎችን በማለፍ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ዕድገት የሚያፋጥኑ መሰረቶችን በመጣል ሀገርን የሚቀይሩ የልማት ትሩፋቶች መፍጠር መቻሉንም አብራርተዋል። ለአብነትም ኢትዮጵያ ተፈጥሮ የቸራትን የውሃ ሀብት በራሷ ጥረት ለማልማትና ለመጠቀም ያጋጠሟትን ፈተናዎች በመሻገር ታላቁን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እውን ማድረግ መቻሏን አንስተዋል። የግድቡ ስኬት የሀገሪቱን የኃይል ምርት አቅም ከማሳደግ ባሻገር ከጎረቤት ሀገራት ጋር በኃይልና በቀጣናዊ ኢኮኖሚያዊ ትስስር የሚያሳልጥ ዕድል ይፈጥራል። ይህም የመደመር መንግሥት በጋራ ተጠቃሚነትና በትብብር ላይ የተመሰረተ የውጭ ግንኙነት አቅጣጫን እመርታዊ ጉዞ ያመለክታል። ከሕዳሴ ግድብ ተሞክሮ በመነሳት ኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት መሻቷንም በሰላማዊ የዲፕሎማሲ ድርድርና በጋራ ጥቅም መርህ ለማሳካት ጥረት እየተደረገ ነው። ለኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ከኢኮኖሚያዊ ፍላጎትና ቀጣናዊ ትስስር ጋር የተቆራኘ ስትራቴጂክ የሕልውና ጉዳይ ነው። ለዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመደመር መንግሥት ምሥረታ ወቅት ካነሷቸው ዐበይት የልማትና የዕድገት ጉዳዮች አንዱ የባህር በር ጉዳይ ነው። ጎረቤቶቻችን በተፈጥሮ ያገኘናቸው ወዳጆቻችን ናቸው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)፤ ከሁሉም ጎረቤቶች ጋር በሰላም ፣ በጋራ ጥቅምና በትብብር የመስራት መርሃችንን እንገፋበታለን ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል። ነገር ግን የኢትዮጵያ ስልጣኔ ያለ ባህር በር እውን ሊሆን አይችልምና በሰጥቶ መቀበል መርህ ኢትዮጵያ ወጥቶ መግቢያ በር እንዲኖራት ተግተን እንሰራለን ሲሉ አስምረውበታል። በዚህም የኢትዮጵያን ታላቅነት፣ የዓለምና የአካባቢያችን ወቅታዊ ሁኔታ ብሎም የወደፊቱን የዓለም አካሄድ ያገናዘበ የመከላከያ ኃይል በመገንባት በቀጣናው የአየር የበላይነት ለመፍጠር የሚያስችል አቅም እንደሚገነባ አስታውቀዋል። የሚኖረን መከላከያ ዘመናዊ፣ ፈጣሪ፣ ሁሌም ዝግጁ ብቁና ንቁ በየአውዶቹ የመሰማራት አቅምና ቁመና ያለው እንደሚሆን በመጠቆም፤ ችግሮች ሳይፈጠሩ በፊት አስቀድሞ ማወቅና መግታት ከመጡም መከላከል ከባሰም እንደ አባቶቹ እንደልማዱ ማሸነፍ የሚችል ኃይል ሆኖ ይገነባል ብለዋል። የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በሁለቱ ምክር ቤቶች የሥራ ዘመን የጋራ መክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ የኢትዮጵያ ውጭ ግንኙነት ማዕከላዊ መርህ ብሔራዊ ጥቅምና የዜጎች ክብር መሆኑን አንስተዋል። የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት አቅጣጫ ከታዛቢነት ወደ አጀንዳ ቀራጭነትና ተፅዕኖ ፈጣሪነት እንዲሸጋገር የሚያስችሉ ስትራቴጂያዊ ምርጫዎችን ማጠናከር እንደሚገባም አብራርተዋል። በድንበር ተሻጋሪ ሀብቶች ላይ ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥና ኢትዮጵያ አስተማማኝ የባሕር በር የማግኘት መሻቷን በሰላማዊ መንገድ ማሳካት የውጭ ግንኙነቷ ትኩረት መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል። በዚህም መንግሥት በዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች ኢትዮጵያ የውሃ ሀብቶቿን በፍትሐዊነት የመጠቀም መብቷን እንድታረጋግጥና የባሕር በር ጥያቄዋን በጋራ ጥቅምና በሰላማዊ ድርድር እንደምታሳካ ገልጸዋል። ይህ አቋም የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ከጋራ ሰላምና ደኅንነት ጋር በማጣጣም በትብብርና በጋራ ተጠቃሚነት መርህ ቀጣናዊ ኢኮኖሚያዊ ትስስርን ለማጠናከር ያለውን ፍላጎት ያመለክታል። የዓባይን ውሃ በፍትሐዊነት የመጠቀም ቀጣይ መሻት፣ አስተማማኝ የባሕር በር የማግኘት ጥረት፣ ብሔራዊ ደኅንነትን ማረጋገጥና የዜጎችን ክብር የማስቀጠል ጥረት በሕዝብ ተሳትፎ፣ በመንግሥት ተቋማዊና በዜጎች አንድነት የሚጠናከሩ የጋራ ግቦች ናቸው። በመሆኑም የሕዝብ ትጋትና የመንግሥት ጥረት የኢትዮጵያን ትልቅ ሀገርነት፣ የሕዝቧን ታላቅነትና የሰነቀችውን ታላቅ ርዕይ እውን የሚያደርጉ ዋነኛ መሠረቶች ናቸው። የጠንካራ ሀገር መንግሥት ግንባታ ሂደት የመንግሥት ኃላፊነት ብቻ ሳይሆን የዜጎችን ተሳትፎ፣ የተቋማትን ብቃት፣ የሕዝብን ትጋትና የትውልድን ቁርጠኝነት የሚጠይቅ የጋራ ጉዞ ነው። ስለሆነም ኢትዮጵያውያን አንድነታችንን በማጎልበትና በብሔራዊ ጥቅም ዙሪያ በመተባበር የሀገራችንን ክብርና ጥቅም ለማስጠበቅ የሚጠበቅብንን ኃላፊነት መወጣት ግድ ይለናል። የዘመኑ አርበኛ ትውልድም ከቀደሙት አያቶች የወረሰውን የነጻነትና የክብር ታሪክ በእውቀት፣ በሥራና በልማት በማላቅ ብሔራዊ ጥቅምና የዜጎችን ክብር ለማስከበር የሚጠይቀውን የጋራ ጥረትና ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ መሆን ይጠበቅበታል። ኢትዮጵያም የትናንትን መሰረት አጽንታ፣ የዛሬን አቅም ወደ ተጨባጭ ውጤት በመቀየር ለተሻለ ነገ ትሰራለች። ምክንያቱም የትልቅ ሀገር ታላቅነት የሚረጋገጠው ከታሪክ ባሻገር በሕዝብ የጋራ ትጋት፣ በመንግሥት ተቋማዊ ጥረትና በትውልዱ የጋራ ቁርጠኝነት በሚገነባው የወደፊት ስኬትም ጭምር ነው። ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብና ታላቅ ርዕይ የሰነቀችው ኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት መሻቷንም በሕዝብና በመንግሥት የተቀናጀ ጥረት ታሳካለች። የዘመኑ አርበኛ ትውልድ ብሔራዊ ጥቅሙንና ክብሩን ለማስጠበቅ መትጋት ይጠበቅበታል።
ሀገራዊ ብልፅግናን ከውጭ ተፅዕኖ ፈጣሪነት ጋር የሚያስተሳስር አዲስ ምዕራፍ
Oct 9, 2026 74
የመደመር መንግሥት- ሀገራዊ ብልፅግናን ከውጭ ተፅዕኖ ፈጣሪነት ጋር የሚያስተሳስር አዲስ ታሪካዊ ምዕራፍ ኢትዮጵያ ዛሬ የምትገኝበት ምዕራፍ በታሪኳ ውስጥ ልዩ ቦታ የሚይዝ ነው። በአንድ ወቅት በፖለቲካዊ ውጥረት፣ በኢኮኖሚያዊ ጫና፣ በማኅበራዊ መለያየት እና በተለያዩ ሀገራዊ ፈተናዎች የተከበበች ሀገር፣ ዛሬ በራሷ አቅም እና በራሷ እሳቤ በመመራት የዕድገትና ብልፅግና ግስጋሴ ላይ ትገኛለች። ይህ ስኬት በአጋጣሚ የመጣ ሳይሆን፣ ባለፉት ስምንት ዓመታት በሕዝብ ፈቃድ ወደ ሥልጣን የመጣው አመራር በሀገር በቀል የመደመር እሳቤ ላይ ተመስርቶ ያከናወነው ጉዞ ውጤት ነው። የመደመር ፍልስፍና እንደ ፖለቲካ መርህ ብቻ ሳይሆን፣ እንደ ሀገር ግንባታ ስትራቴጂ ተቀርጾ የተተገበረ ነው። የዚህ እሳቤ አፍላቂ የሆኑት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተለያዩ ወቅቶች የተደቀኑ ውስብስብ ፈተናዎችን በመሻገር፣ ሀገሪቱን ከአስቸጋሪ ሁኔታዎች ወደ መረጋጋት፣ ከመቆም ወደ መንቀሳቀስ፣ ከጥርጣሬ ወደ ተስፋ እና ከተግዳሮት ወደ ዕድል የመቀየር ቁርጠኛ አመራር አሳይተዋል። ዛሬ ኢትዮጵያ የምትናገረው ስለ ሕልውና ጥያቄ ሳይሆን፣ ስለ ብልፅግና፣ ስለ ከፍታ እና ስለ ቀጣይ ትውልድ ዕጣ ፈንታ ነው። ይህን ለውጥ የሚመሰክሩ ተጨባጭ ውጤቶችም በስምንቱ ዓመታት ጉዞ በስፋት ተመዝግበዋል። የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከሀገራዊ ሕልም ወደ ተጨባጭ እውነት በመቀየር የኢትዮጵያን የልማት ፍላጎት እና የሕዝቧን ጽናት ለዓለም አስመስክሯል። የገበታ ለሸገር፣ የገበታ ለሀገር እና የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክቶች ደግሞ የቱሪዝም ሀብቶችን ከጥላ ወደ ብርሃን በማምጣት፣ ተፈጥሮን፣ ታሪክን እና ልማትን አስተሳስረው ኢትዮጵያን አዲስ የቱሪዝም መዳረሻ እንድትሆን መሠረት ጥለዋል። በተመሳሳይ ጊዜ ሀገሪቱ ከአንድ ዘርፍ ተመርኩዞ ከሚጓዝ ኢኮኖሚ ወደ ብዝሃ ዘርፍ ኢኮኖሚ የመሸጋገር ጉዞ ጀምራለች። በቱሪዝም ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶች፣ በማዕድን ዘርፍ የተፋጠነ እንቅስቃሴ፣ በግብርና የተመዘገበው የምርታማነት ዕድገት፣ በማኑፋክቸሪንግ የተፈጠሩ አዳዲስ አቅሞች፣ እንዲሁም በቴክኖሎጂ እና በዲጂታላይዜሽን ዘርፍ የተመዘገቡ ለውጦች ኢኮኖሚውን የበለጠ ተወዳዳሪ እና ዘመናዊ እያደረጉት ነው። ዲጂታል ኢትዮጵያ፣ የፋይናንስ ዘርፍ ሪፎርሞች፣ የኢንቨስትመንት መስክ ማሻሻያዎች እና የአምራች ኢንዱስትሪ ማስፋፊያዎች የሕዝብን ተጠቃሚነት በማሳደግ የኢኮኖሚ ዕድገትን ወደ ተጨባጭ ውጤት የቀየሩ ናቸው። በከተማ ልማት የተመዘገቡ ለውጦችም የመደመር መንግሥት እሳቤን ከቃል ወደ ተግባር የቀየሩ ግልጽ ማሳያዎች ናቸው። በተለይም የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶች ከተሞችን ዘመናዊ፣ ማራኪ እና ለኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ምቹ በማድረግ የከተማ አኗኗር ዘይቤን በአዲስ መልክ እያሻሻሉ ይገኛሉ። ይህ ደግሞ ልማት ማለት የሕዝብን አኗኗር ማሻሻል፣ የኢኮኖሚ ዕድሎችን ማስፋት እና የሀገርን ገጽታ መቀየር መሆኑን ያሳያል። እነዚህ ተጨባጭ ውጤቶች በመሆናቸው ነው ሕዝቡ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የወደፊት ዕጣ ፈንታውን በማሰብ ውሳኔ የሰጠው። የተጀመሩት ለውጦች እንዲቀጥሉ፣ የተገኙት ስኬቶች እንዲጠናከሩ እና የብልፅግና ጉዞው ወደ ላቀ ደረጃ እንዲሸጋገር በማመን ሕዝቡ የብልፅግና ፓርቲን በመምረጥ አዲሱ የመደመር መንግሥት እንዲመሠረት አድርጓል። ይህም ምርጫ የፖለቲካ ሂደት ብቻ ሳይሆን፣ ሕዝብ በተጨባጭ ውጤቶች ላይ የሰጠው እምነት እና ድጋፍ ነበር። በመሆኑም የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ተከትሎ የተመሠረተው አዲሱ የመደመር መንግሥት የአዲስ ካቢኔ ምሥረታ ብቻ ሳይሆን፣ ኢትዮጵያ ወደ ቀጣዩ የከፍታ ምዕራፍ የምትሸጋገርበት ታሪካዊ መድረክ ሆኗል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመንግሥት ምሥረታ ወቅት በምክር ቤት ባደረጉት ንግግር ያነሷቸው አንኳር ሀገራዊ ጉዳዮችም ይህንን እውነታ ያረጋግጣል። ኢኮኖሚያዊ ለውጥ፣ የከተማ ልማት፣ የግብርና ምርታማነት፣ የስልጣኔ ግንባታ እና የተቋማት ጥንካሬ እንደ ዋና ዋና የልማት ምሰሶዎች ቀርበዋል። በተለይም የሀገር ብልፅግና የሚገነባው በጠንካራ ኢኮኖሚ፣ በምርታማ ዜጎች፣ በዘመናዊ ከተሞች እና በጠንካራ ተቋማት መሆኑን በንግግራቸው አንስተዋል። ኢትዮጵያ በቀጣይ ዓመታት የምትከተለውን የልማት አቅጣጫም በግልጽ አመላክተዋል። ይህም በመደመር እሳቤ ላይ ተመስርቶ ልዩነቶችን ወደ ጥንካሬ፣ ችግሮችን ወደ ዕድል እና ሀብቶችን ወደ ብልፅግና የመቀየር መንገድ ያመላከተ ሆኗል። አዲሱ የመደመር መንግሥት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሞች ጠንካራ መሠረት እንዳለውም አረጋግጧል። ኢትዮጵያ በቀጣናው የምትጫወተውን ሚና ማጠናከር፣ የዲፕሎማሲ ተፅዕኖዋን ማሳደግ፣ የኢኮኖሚ ጥቅሞቿን ማስከበር እና የባህር በር ባለቤት የመሆን ጽኑ ፍላጎቷን በሰላማዊ እና በተቀናጀ መንገድ ለማሳካት ጠንካራ የውስጥ አቅም ያስፈልጋል። ያለ ኢኮኖሚያዊ ጥንካሬ፣ ያለ ተቋማዊ ብቃት እና ያለ ሀገራዊ አንድነት ብሔራዊ ጥቅሞችን ማስከበር አይቻልም። ስለዚህ የመደመር መንግሥት ምሥረታ የውስጥ ብልፅግናን ከውጭ ተፅዕኖ ፈጣሪነት ጋር የሚያስተሳስር ታሪካዊ እርምጃ ነው። በመሆኑም የመደመር መንግሥት ምሥረታ የፖለቲካ ክስተት ብቻ ሳይሆን፣ ከፈተና ወደ ዕድል፣ ከለውጥ ወደ ብልፅግና እና ከብልፅግና ወደ ከፍታ የሚወስደውን ሀገራዊ ጉዞ የሚያጠናክር አዲስ ታሪካዊ ውል ነው። ዛሬ የተጀመረው ጉዞ የአንድ መንግሥት ወይም የአንድ ትውልድ ጉዞ ብቻ አይደለም፤ የበለጸገች፣ የተረጋጋች፣ በቀጣናው ተፅዕኖ ፈጣሪ እና ብሔራዊ ጥቅሞቿን በሙሉ ማስከበር የምትችል ኢትዮጵያ የመገንባት ታሪካዊ ሂደት ነው።
የላቀች ኢትዮጵያ - የመደመር መንግስት
Oct 8, 2026 414
  የመደመር መንግስት ምስረታን ተከትሎ ሀገሪቱ ወደ አዲስ የፖለቲካና የዕድገት ምዕራፍ የሚያሸጋግራትን መንገድ ጀምራለች። ይህ ታሪካዊ ምዕራፍ አዲስ መንግስት ከመመስረት ባለፈ አዲስ አቅጣጫና ተስፋን ይዞ መጥቷል። ይህ ጉዞ ሀገሪቱ ካለፉት ውስብስብ ፈተናዎች ወጥታ ወደ ላቀ የስልጣኔ ማማ፣ ዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልጽግና ለመሻገር ያላትን ፅኑ ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው። አዲሱ መንግሥት ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎች በነፃና በዴሞክራሲያዊ መንገድ በሰጡት ድምፅ ላይ የቆመ መሆኑ፣ ከሕዝብ ጋር ያለውን ማህበራዊ ውል በአዲስ መልክ ያደሰበት የሉዓላዊነት ማረጋገጫ ተደርጎም ይወሰዳል። ይህ አዲስ አቅጣጫ የሕዝብን የነገ ብሩህ ተስፋ በፅኑ መሠረት ላይ ለመገንባት እንዲሁም የልማትና እድገት ስኬቶችን በላቀ የውጤታማነት ደረጃ ለማስቀጠል የተቀረፀ ታላቅ ራዕይ ነው። በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ሰላምና ጸጥታን ይበልጥ ማጽናት፣ የባህር በር ባለቤት መሆን፣ መዋቅራዊ የኢኮኖሚ ሽግግሩን ወደ ላቀ ደረጃ ማድረስ ፣ የማህበራዊ ልማትና ጥበቃ ሥራዎችን ማጠናከር እንዲሁም መሠረተ ልማትን ማስፋፋት የመንግሥት ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫዎች ናቸው። የተያዙት እቅዶች በሁሉም መስኮች የተመዘገቡ ስኬቶችን ይበልጥ ለማጠናከር፣ ተቋማዊ አቅምን ለማጎልበት እና የዜጎችን ተጠቃሚነት በተጨባጭ ለማረጋገጥ ምቹ መደላድል የሚፈጥሩ ናቸው። አዲሱ መንግሥት ለገበያ መረጋጋት፣ ለቤት አቅርቦት እና ለሀገራዊ ሁለንተናዊ ዕድገት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሠራ ተመልክቷል። የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል ሰፊ የሥራ ዕድል የሚፈጠርባቸውን መስኮች በማስፋፋት የሕዝቡን ተጠቃሚነት ወደ ላቀ ደረጃ ማሳደግ ትልቁ የቤት ሥራ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሹመታቸውን ተከትሎ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ ጠንካራና አይበገሬ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ስርዓት እየገነባች ያለች ሀገር መሆኗን ገልጸዋል። ማንኛውም የውስጥና የውጭ ፈተና የሀገሪቱን የሥልጣኔና የብልጽግና ጉዞ ሊያቆመው አይችልም ሲሉም ተናግረዋል። ኢትዮጵያ የያዘቻቸውን ታላላቅ እቅዶች እውን ለማድረግ የመንግሥትና የሕዝብ ትብብር ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩም ይሄንን ታላቅ ርዕይ እውን ለማድረግ ያስችላቸው ዘንድ በህዝብ ድምጽ የተመረጠውና አደራንም የተረከበውን መንግስት ካቢኔ በአዲስ መልክ አደራጅተዋል። የሃገርን ብሔራዊ ጥቅም የሚያስቀድሙ ለህዝብ ተጠቃሚነት ያለድካም በትኩረት የሚሰሩና በጥብቅ ዲሲፕሊን የተመረጡ አባላትን በማደራጀትና ሹመታቸውን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በማስጸደቅ ስራ ጀምረዋል። ከአመራሩ ባለፈ ደግሞ ዜጎችም በሀገር ግንባታ ሂደት ውስጥ ተመልካች ብቻ ሳይሆኑ የለውጡ ባለቤት በመሆን፣ የላቀች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡም ይጠበቃል። መሆንም አለበት። ይህ አዲሱ የመንግሥት ምሥረታና ግዙፍ ሀገራዊ ትልሞች፣ ኢትዮጵያን ወደ ላቀ የሥልጣኔና የብልጽግና ምዕራፍ ለማሻገር መሰረት ናቸው።
የመደመር መንግሥት የማይታለፍ ቀይ መስመር - ሙስና ሌብነትና የወገንተኝነት አሰራር!!
Oct 8, 2026 300
ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ ሙስና፣ ሌብነትና ወገንተኝነት የሀገርን ዕድገትና ብልፅግና ያኮሰምናል። የዜጎችን ፍትሐዊና ግልጸኝነት የሰፈነበት የአስተዳደር ሥርዓት መሻት የሚገዳደር የልማት ጠንቅም ነው። ለዚህም ነው የመደመር መንግሥት ጠንካራ አቋም የያዘው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን መክፈቻ ላይ ዳግም ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በተሰየሙበት ወቅት፤ ሙስናን፣ ሌብነትን፣ የዘመድ አሰራርንና ወገንተኝነትን ለማስወገድ መንግሥት መራር እርምጃዎችን እንደሚወስድ አስምረውበታዋል። ይህ የመደመር መንግሥት ግልጽ አቋም ሌብነትና ሙስና የማይታለፍ ቀይ መስመር መሆኑን ያሳያል። መልዕክቱም የመንግሥት ተቋማት አገልግሎቶችን በማዘመን ብልሹ አሰራርን ለመግታትና ለሙስና መንስኤ የሆኑ ክፍተቶችን ለመዝጋት ትኩረት እንደሚሰጡ ያመላክታል። ይህም ለዜጎች ተስፋ፣ ለሙሰኞች ደግሞ መርዶን የሚያሰማ ጥብቅ የማስጠንቀቂያ ደወል ነው። አንድ ዜጋ የመንግሥት አገልግሎት ሲፈልግ ከቢሮ ቢሮ መዞር፣ ረጅም ወረፋ መጠበቅ፣ የግለሰብ ግንኙነትን ማማተርም ሆነ ተገቢ ያልሆነ ክፍያ መጠየቅ የለበትም። የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ እንዝህላልነት ሙስናን፣ ወገንተኝነትንና የዘመድ አዝማድ አሰራርን ያበረታታሉ። የፌዴራል ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ያወጣው የሦስተኛው ብሔራዊ የሙስና ግንዛቤ ጥናትም በሙስና፣ በሌብነትና በብልሹ አሰራር ላይ ተከታታይና መራር እርምጃ የመውሰድ አስፈላጊነትን ያመላክታል። የመደመር መንግሥት ይህን ክፍተት ለመዝጋት የዲጂታል አብዮትን እንደ ዋና መሣሪያ የሚጠቀም ዘመናዊ የአገልግሎት ምኅዳር እየፈጠረ ይገኛል። ለዚህም መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ሥርዓት ተጨባጭ አብነት ነው። የተቋማት አገልግሎቶች በአንድ ማዕከል መቅረባቸው ዜጎች ከቢሮ ቢሮ መዞር ሳይጠበቅባቸው የአገልግሎት ሂደቱን ግልጽና ፈጣን ያደርገዋል። በፌዴራል ደረጃ የተጀመረው የመሶብ አንድ ማዕከል የዲጂታል አገልግሎት ምኅዳርም አሁን ላይ የተደራሽነት አድማሱን አስፍቷል። ለአብነትም በአዲስ አበባ በ2018 ዓ.ም ብቻ በ11 ክፍለ ከተሞች የመሶብ የዲጂታል አገልግሎት ማዕከላት ወደሥራ ገብተዋል። አሁን ይህ ሥርዓት ወደ ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች እየተስፋፋ ይገኛል። ከዚህም በላይ በተንቀሳቃሽና በእጅ ስልክ መተግበሪያ የተቀናጀ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ዜጎች በቤታቸውና በአቅራቢያቸው እንዲገለገሉ አስችሏል። የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያም የዚህ ጉዞ ወሳኙ አካል ሆኗል። አንድ ሰው አንድ ነው በሚል የተጀመረው መርሃ ግብሩም የግለሰብን የዲጂታል መለያ በማረጋገጥ የሐሰት ሰነድና የማጭበርበር ዕድልን በእጅጉ እንዲቀንስ አድርጓል። የተቀናጀና የተናበበ አገልግሎትን ለዜጎች በመስጠትም ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ማስገኘቱን ቀጥሏል። የዲጂታላይዜሽን ጉዞው የመንግሥት አገልግሎትን ከግለሰብ ተጽዕኖ ነፃ እንዲሆን አድርጓል። የዲጂታል አገልግሎቶች ግልጽነትን በማስፈን ተጠያቂነትን እያረጋግጡ ነው። የዲጂታል ግብይትና ክፍያ ሥርዓት መስፋፋቱም ተመሳሳይ፣ ፈጣንና ቀልጣፋ የአገልግሎት ምኅዳር ዕድልን ፈጥሯል። የገንዘብ ዝውውርና እንቅስቃሴ የግብይት ሥርዓት ከእጅ ንክኪ በጸዳ ቁጥር የሙሰኞችን ሸምቀቆ በማጥበቅ ተጋላጭነትን መቀነስ ያስችላል። ይህም የመደመር መንግሥት የዲጂታል አብዮት አንዱ ተጨባጭ እመርታ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መክፈቻ ሥነ-ስርዓት ባስተላለፉት መልዕክት እንዳሉት፤ የተጀመረውን የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም በማጠናከር የአገልግሎት አሰጣጥን የበለጠ ለማዘመን ትኩረት ይሰጣል። ብቃት ላይ የተመሠረተ የሥራ መመዘኛና የአፈጻጸም ክትትልም ሙስና፣ ሌብነት፣ የዘመድ አሰራርና ወገንተኝነትን የሚያከስም ሁነኛ መሠረት ነው። እነዚህ እርምጃዎችም የመደመር መንግሥት ሙስናን ከወንጀለኛ መቅጣት ባሻገር ሌብነት እንዳይፈጠር የሚያደርግ ሥርዓት ለመገንባት የሚያከናውነውን ተከታታይ ተግባር ያመላክታል። ይህን ቁርጠኝነት ወደ ተግባር ለመቀየርም በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የሚመራ ብሔራዊ ኮሚቴ ተዋቅሮ ተከታታይ ሥራ እየሰራ ይገኛል። ኮሚቴው የሙስና፣ የሌብነትና የወገንተኝነት ትግልን በተቀናጀና በተጠናከረ መልኩ በመምራት በሌብነት ላይ የሚወሰደውን መራር እርምጃ በሥርዓት እያስፈጸመ ነው። መራር እርምጃው ቃል ብቻ ሳይሆን ተቋማዊ ለውጥ መሆን አለበት። የፀረ-ሙስና ተቋማት አቅም፣ የሲቪል ሰርቪስ ብቃት፣ የዲጂታል አገልግሎት ስፋት፣ የመንግሥት ግዥ ግልጽነትና የፕሮጀክት ክትትል በአንድ ላይ ሲሰናሰሉ የሚለካ ውጤት ይመጣል። የመደመር መንግሥት ጽኑ ፍላጎትም ለዜጎች ያለአንዳች እጅ መንሻና ብልሹ አሰራር የመንግሥት አገልግሎት ማስገኘት ነው። ዜጎች በየቀኑ በመንግሥት ተቋማት የሚያገኙት ፍትሐዊና ግልጽ አገልግሎትም ሌብነትን የሚያደርቅ እውነተኛ መለኪያ ይሆናል። ትልቅ ሀገርና ትልቅ ሕዝብን የሚመጥን ታላቅ ርዕይ ለሰነቀችው ኢትዮጵያ ርዕይን በተግባር የሚያስፈጽም ታማኝ፣ ብቁ፣ ግልጽና ተጠያቂ ተቋም እየተገነባ ነው። የመደመር መንግሥት ሙስና፣ ሌብነትና ወገንተኝነትን የማይታለፍ ቀይ መስመር አድርጎ መበየኑም የሀገርንና የሕዝብን ሀብት ለተፈለገው ዓላማ ለማዋል ካለው ቁርጠኛ አቋም ይመነጫል። የፍትሐዊ የመንግሥት አገልግሎት ተደራሽነትና ጥራትም ለዜጎች ተስፋን፣ ለሌቦች ደግሞ መርዶን የሚያውጅ ጥብቅ የማስጠንቀቂያ ደወል ሆኗል። የሌብነት ቀይ መስመርነትም የሕዝብና መንግስትን መተማመን በማጎልበት የኢትዮጵያን መሻት በማላቅ ዕድገትና ብልፅግና ለማሳለጥ ተስፋን የፈነጠቀ ቀጣይነት ያለው ሥራ ሆኗል።
ልዩ ዘገባዎች
ከዓባይ እስከ ቀይ ባሕር 
Oct 9, 2026 78
ነጋሪ መጽሔት የዓባይ ውሃ አጠቃቀምና የኢትዮጵያን የባሕር በር ፍላጎት በስፋት ተንትናለች። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም በመደመር መንግሥት ምሥረታ ላይ፣ “የኢትዮጵያ ሥልጣኔ ያለ ባሕር በር እውን ሊሆን አይችልም” በማለት ሀገሪቱ የባሕር መዳረሻ እንድታገኝ በትጋት እንደሚሠሩ አረጋግጠዋል። ይህ ጥረት በሰላማዊ ውይይት፣ በጋራ ተጠቃሚነትና በ“ሰጥቶ መቀበል” መርሕ እንደሚመራ በማስገንዘብ፣ ጉዳዩን ከአፍሪካ ቀንድ፣ ከቀይ ባሕርና ከመካከለኛው ምሥራቅ እየተለወጡ ካሉ የጂኦፖለቲካና የኢኮኖሚ ሁኔታዎች ጋር አያይዘው አቅርበዋል። መጽሔቷም በመስከረም 2019 ዓ.ም. እትሟ “የኢትዮጵያ የትንሳኤ መንገድ፡ ከዓባይ እስከ ቀይ ባሕር ፖለቲካ የዘለቀው ፍጥጫ” በሚል ርዕስ ባቀረበችው ትንታኔ፣ የውሃ ሀብት፣ የባሕር መዳረሻ፣ የዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮችና የቀጣናዊ ደኅንነት ጉዳዮች በሀገራት መካከል ባለው የኃይል አሰላለፍ ላይ ያላቸውን ተጽዕኖ ዳስሳለች። እንደ መጽሔቷ ትንታኔ፣ ዓባይና ቀይ ባሕር በተፈጥሮ የተለያዩ የውሃ አካላት ቢሆኑም፣ በዘመናዊው የጂኦፖለቲካ ስሌት ውስጥ በውሃ አጠቃቀም፣ በኢኮኖሚያዊ ጥቅም፣ በባሕር መዳረሻና በደኅንነት ጉዳዮች የተሳሰሩ ናቸው። የዓባይ ወንዝ ለኢትዮጵያና ለተፋሰሱ ሀገራት ለኃይልና የልማት ጥቅም ሲኖረው፣ ቀይ ባሕር ደግሞ አፍሪካን፣ እስያንና አውሮፓን የሚያገናኝ ወሳኝ የዓለም አቀፍ የንግድና የባሕር መተላለፊያ ነው። በተለይም የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ፣ የዓባይ ውሃን በፍትሐዊነትና በጋራ ተጠቃሚነት የማስተዳደር ጥያቄና የኢትዮጵያ የባሕር በር ፍላጎት በቀጣናው የፖለቲካና የደኅንነት ስሌቶች ላይ የሚያሳድሩትን ተጽዕኖ መጽሔቷ በስፋት ተንትናለች። የ1929 እና የ1959 የውሃ ስምምነቶች የላይኛውን ተፋሰስ ሀገራትን ጥቅም በበቂ ሁኔታ እንዳልተካተቱ በመግለጽ፣ የወንዙ ውሃ አጠቃቀም በፍትሐዊነት፣ በትብብርና በጋራ ጥቅም ላይ በተመሠረተ ማዕቀፍ መመራት እንዳለበት አመልክታለች። ኢትዮጵያ በ1993 ዓ.ም በኋላ የባሕር በር መዳረሻዋን ማጣቷን ተከትሎ፣ ጉዳዩ ከኢኮኖሚያዊ ጥቅም ባለፈ ከብሔራዊ ደኅንነትና ከረጅም ጊዜ የልማት ፍላጎት ጋር እንደተያያዘ መጽሔቷ አትታለች። የባሕር በር መዳረሻ ማግኘት የንግድ ወጪን ለመቀነስ፣ የወደብ አማራጮችን ለማስፋትና የኢኮኖሚ ዕድገትን ለመደገፍ ወሳኝ መሆኑንም አብራርታለች። በሌላ በኩል፣ ቀይ ባሕር ከእስያ፣ ከአፍሪካና ከአውሮፓ የንግድ መስመሮችን የሚያገናኝ ስትራቴጂካዊ የባሕር መተላለፊያ በመሆኑ፣ በአካባቢው ያለው የደኅንነት ሁኔታ ከአካባቢያዊ ግንኙነቶች ባለፈ ዓለም አቀፋዊ የንግድ ፍሰትን ይነካል። መጽሔቷ የቀይ ባሕር የጂኦፖለቲካ አስፈላጊነት ከስዊዝ ቦይና ከባብ-ኤል መንደብ የባሕር መተላለፊያ ጋር በማያያዝ የዳሰሰች ሲሆን፣ በአካባቢው የሚካሄዱ የኃይል ፉክክሮች የንግድና የደኅንነት ስጋቶችን እንደሚያባብሱ ተንትናለች። መጽሔቷ በትንታኔዋ የኢትዮጵያን የባሕር በር ፍላጎት ከቀጣናው ሀገራት የፖለቲካ አቋሞች ጋር በማያያዝ የተለያዩ ትንታኔዎችን አቅርባለች። ሆኖም እነዚህ በመጽሔቷ የቀረቡ የፖለቲካ ትንታኔዎች ሲሆኑ፣ የተጠቀሱ አቋሞችንና ክሶችን ከተረጋገጡ እውነታዎች መለየት ያስፈልጋል። መጽሔቷ በዓባይ ውሃ አጠቃቀምና በባሕር መዳረሻ ጉዳይ ዙሪያ የሚነሱ አለመግባባቶች በግጭት ሳይሆን በውይይት፣ በድርድርና በጋራ ተጠቃሚነት መርሕ መፍትሔ ማግኘት እንዳለባቸው አጉልታለች። የውሃ ሀብትን በፍትሐዊነት ማስተዳደርና የባሕር መዳረሻ ጉዳይን በሰላማዊ ስምምነት መፍታት ለቀጣናዊ መረጋጋት፣ ለኢኮኖሚ ትብብርና ለዘላቂ ልማት ወሳኝ መሆናቸውን በትንታኔዋ አመልክታለች። የመጽሔቱ ሊንክ https://www.ena.et/web/negari/w/negari_9696604
ከአዲሱ መንግስት ምን ይጠበቃል?
Oct 5, 2026 300
ትልቅ ሀገር- ትልቅ ህዝብ- ታላቅ ርእይ አዲስ የሚመሰረተው መንግስት በሀገሪቷ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን የማስቀጠል፤ በተለይም የተጀመሩ ግዙፍ ሀገራዊ የልማት ፕሮጀክቶችን ለስኬት ማብቃት ትልቁ የቤት ስራ ነው የሚሆነው። በከተሞች እየተከናወነ ያለውን የኮሪደር ልማትና የስማርት ሲቲ ግንባታ፣ የዲጂታል አገልግሎቶችን የማስፋት፣ የአረንጓዴ አሻራ ልማትን ማስቀጠል ሌላኛው ሀገራዊ ሃላፊነት ነው የሚሆነው። የኢትዮጵያ ልማት በከተሞች ጋር ብቻ የሚወሰን ባለመሆኑ በገጠር አካባቢዎች የተጀመሩ የገጠር ትራንስፎርሜሽን የልማት ስራዎችንም ማስቀጠል የግድ ይላል። የገጠር ትራንስፎርሜሽን ዋነኛ ዓላማም የገጠሩን ህዝብ አኗኗር ማዘመን፣ የመሠረተ ልማትና የመሰረታዊ አገልግሎት ተደራሽነትን ማሻሻል፣ የገጠር ኢኮኖሚን ማጠናከርና የገጠር ነዋሪዎችን ከዘመናዊ የምርትና የገበያ ሥርዓት ጋር ማስተሳሰር መሆን አለበት። ኢትዮጵያ በተፈጥሮ፣ በታሪክ፣ በባህልና በሃይማኖት የበለፀገች ሀገር በመሆኗ አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎችን መፍጠር፣ ያሉትን የመጠበቅና የማልማት እንዲሁም ታሪካዊና ተፈጥሯዊ ሀብቶችን መጠበቅ፣ የቱሪስት ቆይታን ማራዘምና ከቱሪዝም ጋር የተሳሰሩ የስራ እድሎችን የማስፋት ጉዳይ የአዲሱ መንግስት ዋነኛ ትኩረት ሆኖ ይቀጥላል። በግብርናው ዘርፍም በምርትና ምርታማነት፣ በመስኖ ልማት፣ በስንዴ፣ በሌማት ትሩፋት፣ በቡና፣ በሆርቲካልቸርና በሌሎችም የግብርና ዘርፎች የተጀመሩ ስራዎች በዘላቂነት እንዲቀጥሉ ማድረግ ይጠበቃል። ከምርት መጨመር ባሻገር የግብርና ምርቶችን ማቀነባበር፣ የገበያ ትስስርን ማሻሻል፣ የማከማቻና የመጓጓዣ ስርዓትን ማዘመን እና የአርሶ አደሩን ገቢ የማሳደግ ጉዳይ ትኩረት ይፈልጋል። የምርትና ምርታማነት መጨመር በመጨረሻም ከውጭ የሚገቡ የምግብ ምርቶችን በመተካት፣ የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥና የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ አቅም በማሳደግ ከተረጅነት ለመውጣት የሚደረገውን ጥረት ማሳካት ይጠበቅበታል። የማዕድን ልማት፣ ዲጂታላይዜሽንና የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን የማዘመን ጉዳይም ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ይሆናል። የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር የምርትና የገበያ አቅርቦትን ማሳደግ፣ የአቅርቦት ሰንሰለትን ማሻሻል፣ ህገወጥ የገበያ አሰራሮችን መቆጣጠርና የዜጎችን የመግዛት አቅም ማሻሻል ይጠበቃል። የኑሮ ውድነት ችግር በአንድ መፍትሄ የሚፈታ ባለመሆኑ የገቢ፣ የምርት፣ የገበያና የፋይናንስ ፖሊሲዎችን በተቀናጀ መልኩ ማስኬድ ያስፈልጋል።
የአካታች ሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት ፅኑ መሰረት
Oct 5, 2026 193
መስከረም 25/2019 (ኢዜአ):- አዲሱ የመንግስት ምስረታ - አካታች የፖለቲካ ስርአት ግንባታ መሰረት ትልቅ ሀገር- ትልቅ ህዝብ- ታላቅ ርእይ በምክር ቤት አብላጫ መቀመጫ ያገኘው ብልጽግና ፓርቲ መንግስት የመመስረት ሃላፊነት ያለበት በመሆኑ በዛሬው እለት ይሄው የሚከናወን ይሆናል። በፓርላማው የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች መቀመጫ ያገኙ በመሆኑ የፖለቲካ ክርክሮችና የሃሳብ ብዝሃነት የሚስተናገዱበት እንደሚሆንም ይጠበቃል። በኢትዮጵያ አካታችና አሳታፊ የፖለቲካ ስርአት ግንባታ መሰረት ያኖረው አዲሱ የመንግስት ምስረታ ሂደት የክልሎች ተጠናቆ በዛሬው እለት የፌዴራል መንግስት ምስረታ እውን ይሆናል። ባለፉት ዓመታት የተመዘገበው የአካታችነት ስኬት የመንግሥት ከፍተኛ የአመራር እርከኖች፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤትና የፍትህ ተቋማት አመራሮች ላይ የተፎካካሪ ፓርቲ ተወካዮችን፣ የሴቶችንና የወጣቶችን ፍትሃዊ ስብጥር በተግባር ማሳየት ያስቻለ ነው። ከባለፉት አምስት አመታት ተሞክሮ በመነሳትም የዘንድሮው ምርጫ በብዙ መስፈርቶች ዴሞክራሲያዊ፣ አሳታፊ እና አካታች መሆኑን በተግባር ያሳየና የሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት ፅኑ መሰረት ያኖረ ሆኗል። በተቋማዊ አካታችነትና ሀገራዊ መግባባትን ለመፍጠር በተወሰዱ እርምጃዎችም ጉልህ ውጤቶች ተመዝግበዋል። ሁሉንም የፖለቲካና የኅብረተሰብ ክፍሎች ያቀፈው ሀገራዊ የምክክር ሂደት በሀገሪቷ የቆዩ ልዩነቶችን በምክክር ለመፍታት አዲስ ምእራፍ የከፈተ ሆኗል። ከዚህ ጎን ለጎን የጽንሰ-ሐሳብ፣ የቋንቋና የባህል ስብጥሮችን ያከበሩ የትምህርትና የባህል ፖሊሲዎች መተግበራቸው፣ ዜጎች በቋንቋቸው የመማርና አገልግሎት የማግኘት መብታቸው እንዲሰፋ በማድረግ ረገድም ትልቅ ስኬት ታይቷል። በመሆኑም በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አብላጫ ድምፅ ያገኘው የብልፅግና ፓርቲ የሚያቋቁመው አዲሱ መንግስት በቀጣይ ሁለንተናዊ አካታችነትን በማረጋገጥ ረገድ ብዙ እንደሚሰራ ይጠበቃል። ገዢው ፓርቲ መወዳደር የሚችልባቸውን አካባቢዎች በመተው ለተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች እድሉን መስጠቱ በምክር ቤቱ የተለያዩ ድምፆች እንዲስተጋቡ ምቹ ሁኔታ የፈጠረ ሆኗል። በመሆኑም ጠቅላላ ምርጫው የፖለቲካ ተሳታፊነትንና ውክልናን በማስፋት ረገድ ጉልህ ውጤቶች የተመዘገቡበት ነበር ማለት ይቻላል። በተጨማሪም በውሳኔ ሰጪነትና በፖለቲካ ውድድር ውስጥ የሴቶች፣ የወጣቶችና የልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፎ እንዲያድግ በመደረጉ ህዝባዊ ወካይነት ያለው የምርጫ ሂደትን ለማከናወን አስችሏል። ምርጫ አስተዳደሩንና አሰራሩን አሳታፊና ፍትሃዊ በማድረግ ረገድ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኩል የታዩት እርምጃዎች ሌላው የአካታችነት ማሳያዎች ናቸው። የድምፅ መስጫ ጣቢያዎችን ተዳራሽ ማድረግ፣ ለአካል ጉዳተኞች ምቹ የሆኑ የምርጫ ግብዓቶችን ማዘጋጀት እና በምርጫ ታዛቢነት የሲቪክ ማህበራትን፣ የሀገር ውስጥና የውጪ ምርጫ ታዛቢዎችን ማሳተፍ ተችሏል። ይህም የህብረተሰቡ ልዩ ልዩ ክፍሎች ያለምንም ገደብ የመምረጥ መብታቸውን እንዲጠቀሙና በሂደቱ ላይ ያላቸው እምነት እንዲጎለብት አድርጓል። በመሆኑም በዛሬው እለት የሚመሰረተው መንግሥት ልዩ ልዩ የፖለቲካና የማህበረሰብ ክፍሎችን ድምፅ በማስተናገድና ሀገራዊ መግባባትን በመፍጠር ጠንካራ የሀገረ መንግስት ግንባታ መሰረት የሚያኖር እንደሚሆን ይጠበቃል።
የመደመር መንግሥት-የብሔራዊ ጥቅም ዘብ
Oct 5, 2026 196
ኢትዮጵያ ዛሬ አዲስ መንግሥት ትመሠርታለች።ይህ መንግሥት የዛሬውን ትውልድ ብቻ ሳይሆን፤የመጪውንም ትውልድ ፍላጎት በጽኑ መሠረት ላይ የሚያቆም ሥራ የሚሠራ ነው። አዲሱ መንግሥት ትልቅ የሕዝብ አደራ የሚቀበልና የነገዋን ኢትዮጵያ በከፍታ ላይ የሚያስቀምጥ እንደሚሆን እሙን ነው። ኢትዮጵያ በታሪኳ እጅግ ውስብስብ የሆኑ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ ፈተናዎች አልፋ ዛሬ አዲስ የምዕራፍ ላይ ትገኛለች። አዲሱ መንግስት ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን፣ ሉዓላዊነቷን እና የሕዝቦቿን የጋራ እድገት ለማረጋገጥ ባደረገችው ያላሰለሰ ጥረት ውስጥ ቀጣይ ጉዞዋን በተሻለ መልኩ የሚያስቀጥል መንግሥት ይሆናል። ይህ ታሪካዊ ጉዞ በቀላሉ የተገኘ አልነበረም። ሕዝቡ የወደፊት ዕጣ ፈንታውን በቃላት ሳይሆን በተግባር ለመወሰን፣ መብቱን በድምፁ በመጠቀም ታሪካዊ አደራውን ለመወጣት ውስብስብ ፈተናዎችን አልፏል። በፈተና ውስጥ አልፎ የሰጠው ድምፅ ተራ የምርጫ ሂደት ሳይሆን፤ የሀገርን ሕልውና የማስከበር፣የብሔራዊ ጥቅምን የማስጠበቅ እና ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለች ሀገር የማስረከብ ጽኑ ፍላጎት መግለጫ ነበር። ዛሬ የሚመሠረተው አዲስ መንግሥት የዚሁ የሕዝብ አደራና የጽናት ውጤት ነው።ይህ የመደመር መንግሥት የሀገሪቱን ታሪካዊ፣ ተፈጥሯዊ እና ቀጣናዊ ጥቅሞች ያስከብራል፤ የኢትዮጵያን የሉዓላዊ ድንበር እና የወደፊት ሕልውና በጠንካራ ዲፕሎማሲና በውስጥ አንድነት ይጠብቃል። የዛሬዎቹን አጣዳፊ ጥያቄዎች ለመመለስ ብቻ ሳይሆን፣ መጪው ትውልድ የሚተማመንባት፣ በኢኮኖሚ የበለጸገች እና ብሔራዊ ጥቅሟን የምታስጠብቅ ሀገር መንግስት ይመሰርታል። ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን በሁለት ውኃዎች ላይ አድርጋ በጽናት እየተንቀሳቀሰች ትገኛለች። የአባይን ውኃ ለሁለንተናዊ እድገቷ መጠቀም ጀምራለች፤ ሕዳሴንም ጨርሳ የማድረግ አቅሟን አረጋግጣለች።ይህ ጉዞ ቀላል አልነበረም፤ሀገሪቱ በውስጥና በውጭ በርካታ ፈተናዎችን፣ ተፅዕኖዎችንና ጫናዎችን አልፋ ነው እዚህ ደረጃ ላይ የደረሰችው። ዛሬ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን የበለጠ የሚያስከብርላትን የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ አንሥታ ጉዳዩን ዓለም አቀፍ አጀንዳ አድርጋዋለች። የመደመር መንግሥት ኢትዮጵያ ኢ-ፍትሐዊና ባልተገባ መልኩ ያጣችውን የባሕር በሯን እንድታገኝ በትክክለኛው መንገድ ይጓዛል፤ ግቡንም ያሳካል። ዛሬ የሚመሠረተው አዲስ መንግሥት ለነገዋ ኢትዮጵያ ጠንካራ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ መደላደል የሚፈጥር ነው፤ የሀገሪቱን የባሕር በር ፍላጎት፣የዓባይ ወንዝ ፍትሐዊ ተጠቃሚነት፣የውስጥ ደኅንነትና የኢኮኖሚ ነፃነት አፅንኦት ሰጥቶ ማስጠበቅ ነው።ልዩነቶችን በማቀናጀትና አቅሞችን በመደመር የሀገርን ሕልውና አስተማማኝ ማድረግም ሌላው ከመደመር መንግስት የሚጠበቅ ነው። ከምንም በላይ ኢትዮጵያ የበርካታ ዘመናት ታሪካዊ ጠላቶቿንና ተላላኪዎቻቸውን እኩይ ሴራ ትበጣጥሳለች።የውስጥና የውጭ ጫናዎችን በህዝቦቿ ጽናት፣የአንድነት መንፈስና የማይናወጥ ሀገራዊ ወኔ እያሸነፈች ትቀጥላለች።ለነፃነቷና ሉዓላዊነቷ ሳትበገር በማንኛውም ጊዜና ሁኔታ ወደ ላቀ የልማት፣ የብልፅግናና የዕድገት ከፍታ ወደ ፊት መገስገሷን ትቀጥላለች። ዛሬ የሚመሰረተው አዲሱ የመደመር መንግሥትም የሕዝቡን ተስፋና እምነት ወደ መሬት በማውረድ፣የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም አክብሮና አስከብሮ ለመጪው ትውልድ የምትመችና በጽኑ መሠረት ላይ የተገነባች ሀገርን የማስረከብ ታሪካዊ ኃላፊነት አለበት።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 108655
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 81856
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 59974
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 57578
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ በአልሸባብ ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገለፁ
Feb 14, 2024 40850
አዲስ አበባ፤ የካቲት 6/2016 (ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ አሸባሪው አልሸባብ ከሰሞኑ በሶማሊያ በፈፀመው የሽብር ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሃዘን ገለፁ። አምባሳደር ታዬ ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት በሽብር ቡድኑ ጥቃት ምክኒያት በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት እና አካል ጉዳት ጥልቅ ሃዘን እንደተሰማቸው ገልፀዋል። በኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ እንዲሁም በራሳቸው ስም የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ለሶማሊያ መንግስት እና ህዝብ የገለጹት ሚኒስትሩ ፤ በልምምድ ወቅት ወታደራዊ መኮንኖችን ኢላማ በማድረግ የተፈፀመውን ጥቃት የወንጀል ተግባር ነው ብለዋል። የወንጀል ተግባሩን ኢትዮጵያ በፅኑ እንደምታወግዘውም ባስተላለፉት መልዕክት አስታውቀዋል። ጥቃቱ አልሸባብ የሽብር ቡድን በሶማሊያ እና በክፍለ አህጉሩ ደህንነት አደጋ መደቀኑን በግልፅ ያረጋገጠ መሆኑን በመግለፅ ፥ የአካባቢው ሀገራት በፀረ ሽብር የሚያደርጉትን ትብብር ሊያጠናክሩ እንደሚገባም አመልክተዋል። የሶማሊያን ሰላም እና ደህንነት በጋራ ለማረጋገጥ ኢትዮጵያ ትብብሯን አጠናክራ በቁርጠኛነት እንደምትቀጥልም ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት ማስታወቃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።    
በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈጸማል-ባለስልጣኑ
Apr 6, 2023 40784
አዲስ አበባ መጋቢት 28/2015(ኢዜአ)፡ በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ። የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ የሚፈፀምበትን የድርጊት መርሐ ግብር በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ተወያይቷል።   የውይይቱ ዓላማ በመዲናዋ የሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች በአሰራሩ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማስቻል መሆኑ ተነግሯል። በዚህ ወቅት የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ፤ ባለስልጣኑ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። በዚህም ቀደም ብሎ ከነዳጅ ማደያና አከፋፋይ ኩባንያዎች ጋር ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው፤ አሁን ደግሞ ለሙሉ ትግበራው ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ውይይት ተደርጓል ብለዋል። በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓቱ በአማራጭነት ለሙከራ እየተተገበረ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም ተናግረዋል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል። የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሀምሌ አንድ ጀምሮ በአስገዳጅነት እንደሚተገበርም ጠቁመዋል። በኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ሞባይል መኒ ኦፊሰር ብሩክ አድሃነ፤ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች በማድረግ ረገድ በቴሌ ብር ውጤታማ ስራ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። ለዚህም ባለፉት ዘጠኝ የሙከራ ወራት በቴሌ ብር ብቻ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈጸሙን አንስተዋል። የነዳጅ ግብይቱን በአግባቡ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መገንባቱንም እንዲሁ። የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማኅበር አባል የሆኑት አቶ ሚካኤል ገብረስላሴ እና የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ የነዳጅ ግብይት ስርዓቱ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ መሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ብለዋል። በተለይ ለነዳጅ አዳዮች ጥሬ ገንዘብ በመቁጠር የሚያባክኑትን ጊዜ ከመቅረፍ አንፃር እንዲሁም በማደያዎች የሚቀመጥ የግብይት ገንዘብ እንዳይኖር በማድረግ የደህንነት ስጋትን እንደሚፈታ ተናግረዋል። በተጨማሪም መንግስት የነዳጅ ምርት ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን ስርጭት ሂደት መረጃ እንዲኖረው እና ነጋዴዎችም ግብርና ታክስ እንዳያጭበረብሩ በማድረግ ቴክኖሎጂው ትልቅ ሚና አለው ነው ያሉት።  
ለላቀ ውጤት - የተማሪ መምህርና ወላጆች ጥምር ጥረት
Mar 27, 2023 40200
በሃብታሙ ገዜ ስልጡን የመንገድ ጠበብቶች በጥንቃቄ የከተማ ውብ ገፅታ አልበሰው ባነጿት ከዚራ አካባቢ የሚገኘው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አዳራሽ በሰው ተሞልቷል። የተሰበሰቡት ወጣት ተማሪዎች፣ የድሬደዋ አመራሮች፣ የትምህርት ዘርፍን የሚመሩ አካላትና ወላጆች በፈገግታ ተሞልተዋል። ይበልጥኑ ከወጣቶቹ ገፅታ የሚንፀባረቀው የደስታ ፈገግታ ለአዳራሹ የተለየ ብርሃን ደርቦለታል። የደስታቸው ምንጭ ደግሞ አምና የተፈተኑትን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በላቀ ውጤት አልፈው ሽልማት በመቀበል ላይ መሆናቸው ነው። የአዳራሹን የሽልማት መርሃ ግብር የሚመራው ሰው ድንገት "የዛሬው ልዩ ክስተት ከሚሸለሙት ተማሪዎቻችን መካከል ከ600 በላይ ውጤት በማምጣት ከወንድሞቿ ጋር ሦስት ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ የአንድ ቤተሰብ አባላት መገኘታቸው ነው" ሲል ተናገረ። ይሄኔ አዳራሹ በጭብጨባ ተናጋ፤ ሁሉም ተሰብሳቢ በአንድነት ቆሞ ጭብጨባውን አቀለጠው። ለሽልማት ወደ አደባባዩ የመጡት በደስታ ፀዳል የወረዙት የወላጅ ተወካይ እንጂ የድሉ ባለቤት የሆኑት እነዚህ ሦስት ተማሪዎቹ አይደሉም። በአዳራሹ የተሰባሰቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃርና የካቢኔ አባላት እንዲሁም ተሸላሚዎቹ ተማሪዎች "የዓመቱ የተለየ ክስተት የሆኑትን ተማሪዎች" ለማየት ዓይኖቻቸው ቢባዝንም አልተሳካም። ለምን ካላችሁ ተማሪዎቹ ወደ ተመደቡበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጓዛቸው ነው። የመድረኩ የድምፅ ማጉያ ባለቤትም ሆነ ተሰብሳቢዎቹ የዓመቱ ክስተት የሆኑት ኒያ ሰላሃዲን 602፤ አሊ ሰላሃዲን 556፣ አማን ሰላሃዲን 526 ያመጡት ተማሪዎች መንትዮች መሆናቸውን ቢያውቁ ኖሮ አዳራሹ ሌላ የግርምት ደስታን ባስተናገደ ነበር። ሽልማቱን ያበረከቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ተሸላሚዎች በጥረታቸው በትጋታቸው ባመጡት ውጤት መደሰታቸውን አብስረዋል። አገር በዜጎች አንድነትና መተባበር እንደሚፀናው፤ የተማሪዎች ውጤትም በተማሪዎችና በመምህራን ጥረት ብቻ ሳይሆን በወላጆች ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ጭምር የሚመጣ ነው። "በተለይ ከአንድ ቤተሰብ የበቀሉት ተማሪዎችና የዛሬው ሽልማት እና ውጤት ያስተማረን ይህንኑ ነው" ብለዋል ከንቲባው። በዚህ አደራሽ ውስጥ የሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰነ-መምህራን ታድመዋል። እንደ ድሬደዋ አስተዳደር ከተፈተኑት ከ3 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎች መካከል በቀጥታ ያለፉት 250 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። ለመጣው ውጤት ተሞጋሹም ተወቃሹም የዘርፉ አመራሮች፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና ወላጆች ናቸው። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉካ መሐመድ "ለመጣው ዝቅተኛ ውጤት በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ያለነው በሙሉ ተጠያቂዎች ነን" ብለዋል። ኃላፊዋ ሌላውም ከዚህ ትምህርት መውሰድ እንዳለበት ነው የገለጹት። እንደ አስተዳደሩም የትምህርት አመራሮች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራንና ወላጆች ያካተተ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩን አውስተዋል። በመንግስት የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ከኩረጃ ነፃ ለማድረግ የተወሰደው እርምጃ ተማሪዎች በጥረታቸውና በብቃታቸው የልፋታቸውን ውጤት እንዲያገኙ ያስቻለ ነው። የፈተና አሰጣጡና ውጤቱ እንደአገር ያለንበትን አዘቀት አስተምሮ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ፤ ብቁና በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማዋለድም ጥርጊያ መንገድ ሆኖ አልፏል ማለት ይቻላል። መንግስት የትምህርት ጥራትን ከታችኛው እርከን ጀምሮ ለማረጋገጥም በዘርፉ ሙሁራን ጥልቅ ጥናት ላይ ተመስርቶ ያዘጋጀውን የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት ቀርጾ ዘንድሮ እስከ 8ተኛ ክፍል ተግባራዊ አድርጓል። ለመማር ማስተማሩ መጻህፍት ተዘጋጅተው ለመምህራን ስልጠና በመስጠትም ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። በሚቀጥለው ዓመትም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው። በሽልማት ሥነስርዓቱ ላይ እንደታየው ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች ሚና የጎላ ነው። ወላጆች ተገቢውን ድጋፍ እና ጥብቅ ክትትል ካደረጉ የሚፈልገው ለውጥና ውጤት ማምጣት ይቻላል። ወይዘሮ ሙሉካ በአትኩሮት ከገለጹት ሃሶቦች መካከል ዋናዎቹን ሰበዞች መዝዤ፤ "ተጠያቂዎቹ እኛው ነን" የሚለውን ሃሳብ አንግቤ ለድሬዳዋና ለአገር ከፍ ሲል ለዓለም ህዝብ ጭምር በየዘርፉ ታላላቅ ሙሁራን ወደ አፈሩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሁ። ድንገት ሃሳቤን ቀለበስኩት። መነሻዬ የወላጆች ኃላፊነት እና ድጋፍ መሆኑን መርሳት ዞሮ ዞሮ የምፅፈው መዳረሻ መርሳት ይሆንብኛል ብዬ ነው። እናም ወደ ሦስቱዎቹ፤ የዓመቱ ክስተቶች አባት አመራሁ። ድሬዳዋን ለሁለት እኩሌታ የሚከፍላትን የደቻቱን ድልድይ ተሻግሬ ወደአንድ የግል የሕክምና አገልግሎት መስጫ ሆስፒታል ገባሁ። አምሮ በተሰናዳው ሆስፒታል ውስጥ ሙያዊ ኃላፊነታቸው እየተወጡ አገኘኋቸው፤ የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍን። የውጤታማ ተማሪዎቹ ወላጅ ናቸው፤ በ1970 ዎቹ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መዝለቅ በመርፌ ቀዳዳ የመሹለክ ያህል በሚቆጠርበት ዘመን በከፍተኛ ማዕረግ አልፈው በቀሰሙት ዕውቀትና ጥበብ የሰዎችን ሕይወት እየታደጉ ይገኛሉ። ዶክተር ሰላሃዲን ለትምህርት ጥራት መውደቅ ወደ ዩኒቨርሲቲ በስርቆትና ኩረጃ የመግባት ዝንባሌዎች እንደሆኑና ይሄም ሁሌም የሚያንገበግባቸው ጉዳይ መሆኑን አጫወቱኝ። መንግስት በተለይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ባልደረቦቻቸው በሁለተኛ ደረጃ የፈተና አሰጣጥ ላይ የወሰዱት እርምጃ አስደስቷቸዋል። "በተለይ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ከሚያሳልፉት ጊዜ በበለጠ ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸው ጊዜ ይበልጣል። ከሁሉም ነገር በላይ ለትምህርት ትኩረት ማድረጋቸውን መከታተልና መደገፍ የኛ ፋንታ ነው፤ አንዴ መስመር ከያዙ የሚመልሳቸው ችግር አይኖርም" ይላሉ። ሦስቱ ልጆቻቸውን በዚህ መንገድ በመደገፍ እና ከትምህርት ቤታቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ አስችለዋል። 604 ያመጣችው ስኮላርሽፕ ሺፕ አግኝታ ወደ ውጭ ሄዳለች፤ ሁለቱ ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው። "ለልጆቼ የፈለጉትን የማድረግ አቅም ቢኖረኝም ያለትምህርት የሚፈጠር አንዳች ነገር እንደሌለ ገብቷቸው ለውጤት በቅተዋል" ይላሉ ዶክተር ሰላሃዲን። ብዙ የመስራት እንጂ ብዙ የመናገር ዝንባሌ የማይታይባቸው እኚህ የታታሪዎች አባት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራት በሚደረግ ጥረት የወላጆች ክትትልና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ነው በአፅንኦት ያሳሰቡት። "የሽልማቱ መርሃ ግብር ወደሌላ አካባቢ በሄድኩበት አጋጣሚ በመካሄዱ ሳልገኝ ቀረሁ፤ በጣም የቆጨኝና ቅር ያለኝ ዕለት ሆኖ አልፏል" ብለዋል። እሳቸውን ጨምሮ አንቱ የተሰኙ ሙሁራን ያፈራው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ፍቃዱ ሰንበቶ፤ የማርያም ሰፈር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ኢጀታ መኮንን ካለፈው ክፍተት በመማር ዘንድሮ የተሻለ ውጤት እንዲመጣ የተማሪዎች አመለካከት ላይ ለውጥ እና እችላለሁ የሚል መርህ የማስረጽ ሥራ ተሰርቷል ብለውኛል። ለውጤቱ ቀዳሚ ባለቤት ተማሪዎች ቢሆኑም ከወላጆቻቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ የማካካሻና ለፈተና ዝግጁ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ነው ርዕሳነ መምህራኑ የገለጹት። ቅኝቴን በመቀጠል ሽቅብ ወደ ሳብያን ሁለተኛ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት አመራሁ። ይህ ትምህርት ቤት በከተማዋ ካሉት ትምህርት ቤቶች በውጤታማነት እና በብዛት ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማሳለፍ ረገድ ወደር አልነበረውም፤ ባለፉት ዓመታት። ከተመሠረተ 22 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ ትምህርት ቤት በምክትል ርዕሰ መምህርነት የሚመሩት አቶ በፍቃዱ ወልደሰማያትን አገኘኋቸው። ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተናቸው ከ800 በላይ ተማሪዎች መካከል ያለፉት 20 ናቸው። የመጣው ውጤት ያለንበትን ደረጃ ፍንትው አድጎ ያሳየን መሆኑን ተከትሎ መሠረታዊ የሆኑት ችግሮች በጋራ ተነቅሰው ለመጪው ጊዜ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ ተገብቷል። አቶ በፍቃዱ እንዳሉት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ትምህርት ቤቱን ሞዴል ትምህርት ቤት ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን ለዘንድሮው ተፈታኞች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ነው። እነዚህን ሥራዎች የተማሪ፣ መምህርና ወላጅ ህብረት በቅርበት እንዲከታተል ተደርጓል። ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች የቅርብ ክትትልና ደጋፍ መሠረታዊ ጉዳይ ነው የሚሉት አቶ በፍቃዱ፣ ለዚህ ጉዳይ ትምህርት ቤቱ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ነው የገለጹት። "በተለይ ወላጆች በትምህርት ውጤታማነት ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ልክ እንደ ዶክተር ሰላሃዲን አይነት ቤተሰቦች ተሞክሮ የማስፋት ሥራ ለመስራት ትምህርት ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል" ብለዋል። "ፍቃደኛ ከሆኑ የመጀመሪያው እንግዳችን ዶክተር ሰላሃዲን በማድረግ ለወላጆች ህብረት ተሞክሮን እንዲያካፍሉ እናደርጋለን " ብለዋል። በድሬዳዋ ታሪክ ከፍ ሲልም እንደ አገር በ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ1990 ዎቹ ዘመን ጀምሮ እንዲህ አይነት ዝቅተኛ ውጤት አለመምጣቱን የሚገልጹት ደግሞ የትምህርት ቤቱ አንጋፋ መምህር እዮብ ረታ ናቸው። የፊዚክስ መምህሩ እንደሚሉት የአምናው ክፍተት በሰከነ መንፈስ ታይቶ ዘንድሮ የተሻለ ሥራ ለመስራት መምህራን በጥሩ መንፈስ ጉዞ ጀምረዋል። ወላጆችም ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት መላክ ብቻ ሳይሆን የዕለት ተዕለት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው የገለጹት። "የተማሪዎች የትምህርት ቤት ቆይታ ለሰዓታት ብቻ የተወሰነ መሆኑን በመረዳት ወላጆች በስነ ምግባር የታነፀ በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማፍራት የተጀመረውን ጉዞ መደገፍ አለባቸው" በትምህርት ቤቱ የዘንድሮው የ12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪ ረደኤት ገነሙ በበኩሏ "እንደአገር በዩኒቨርሲቲዎች የተጀመረው የፈተና አሰጣጥ ኩረጃን የሚጠየፍ በራሱ ጥረት ውጤት ለማምጣት የሚተጋ ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል" ብላለች። በትምህርት ቤቱ የተጀመረው ልዩ ዕገዛ መጠናከርና መቀጠል እንዳለበት የምትገልጸው ተማሪ ረድኤት ወላጆቿ ተገቢውን ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ከመምህራን ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የልጆቻቸውን ትምህርት ሊከታተሉ እንደሚገባ አውግታኛለች። እኔም ሆንኩ የዘንድሮ ተፈታኞች ትምህርት ቤታችንንና ድሬዳዋን በውጤት ለማስጠራት ጠንክረን እያጠናን ነው ብላለች። ከገጠር ከተማ ተጉዞ የሚማረው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪ አላሙዲን አልይ በበኩሉ፤ መንግሥት የፈተና ኩረጃን ለማስቀረት የጀመረውን ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበት ነው የገለፀው። "የዘንድሮ የመምህራን ድጋፍ የተለየ ነው፤ እኛም ልዩ የጥናት ጊዜ እንዲጀመር ጫና እየፈጠርን ነው፤ ወላጆቼም በአቅማቸው እየደገፉኝ በመሆኑ ቀሪው ሥራ የኔ ጥረትና ብርታት ይሆናል፤ ልፋቴ ውጤት እንዲያስገኝ የስርቆትና የኩረጃ ሂደት መወገድ አለበት" ብሏል ተማሪ አላሙዲን። ከሳብያን ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ግቢ ለቅቄ ስወጣ ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍ ያሉኝ ትዝ አለኝ። "ለተሞክሮ የሚሆን ነገር እኔ ጋር ካለ ያለችኝን ጊዜ አብቃቅቼ ለዘንድሮው ተፈታኞች ሃሳቤን ለማካፈል ዝግጁ ነኝ" ያሉኝ በአዕምሮዬ ደጋግሞ እያቃጨለብኝ ጉዞዬን ቀጠልኩ። ለመውጫ ያህል፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ዘንድሮ በመንግሥት እና በግል 22 ትምህርት ቤቶች ከ5 ሺህ በላይ ተፈታኞች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው። እነዚህ ተፈታኞች በራሳቸው ጥረት የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ በየአቅጣጫው የተቀናጀ ድጋፍ የማድረግ ጅምር ተግባራት ተስተውለዋል፤ ይሄ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ይህን ዙሪያመለስ ድጋፍ በማጠናከር ተማሪዎቹን ለውጤት ማብቃት በሁሉም ዘንድ ለአፍታ መዘንጋት የለበትም። መድረሻውን ለማሳመር መነሻውን አድምቶ ማበጃጀት ግድ እንደሚልም እንዲሁ።
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 38696
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 108655
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 81856
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 59974
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 57578
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
መጣጥፍ
የከተሞች ትንሳኤ ምሥጢር - የመደመር መንግሥት 
Oct 9, 2026 92
በታዬ ለማ 👉አዲስ አበባ ዳግም አብባለች ጎህ ሲቀድ በአዲስ አበባ ላይ የሚወጣው ፀሐይ ዛሬ ሌላ ከተማ ያበራል። ሰፋፊ መንገዶቿ ላይ ብርሃን ሲያርፍ፣ በእግረኛ መንገዶቿ ላይ የማለዳ ተጓዦች ሲተላለፉ፣ በወንዞቿ ዳርቻ የተሠሩ ፓርኮች አረንጓዴ ሲለብሱ ማየት ይቻላል። ይህች ከተማ እንደ ስሟ አዲስ ሆናለች። ይህ ለውጥ ግን ድንገት የመጣ አይደለም፤ በትልቅ ቁጭት የተገነባ የትውልድ ተሻጋሪ አሻራ ነው፡፡ 👉አገር እየተቀየረች ነው የመደመር መንግሥት ባለፉት ዓመታት አገርን የሚቀይሩና ኢትዮጵያን ወደ ፊት ያራመዱ ውጤታማ ተግባራትን አከናውኗል። በኢኮኖሚው ዘርፍ ታሪካዊ ውጤት ተመዝግቧል። ኢትዮጵያ ስንዴን ከውጭ የምታስገባ አገር መሆኗ ቀርቶ ዛሬ ወደ ውጭ የምትልክ ሆናለች። በኢንዱስትሪው ዘርፍም ትልቅ ድል ተገኝቷል፤ ቀደም ሲል ብዙ የውጭ ምንዛሬ ያስወጡ የነበሩ ምርቶች አሁን እዚሁ ይመረታሉ፤ በዚህም ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ማዳን ተችሏል። በማዕድን ዘርፍ እስከ ዛሬ ታይቶ በማያውቅ መንገድ የኢትዮጵያ ማዕድናት እንዲወጡ እየተደረገ ነው፤ አገሪቱም ከዚህ ሀብቷ ተጠቃሚ እየሆነች ነው። በቴክኖሎጂው ዘርፍ የተሠሩት ሥራዎች አስደናቂ ናቸው፤ መንግሥት በቴክኖሎጂ የተገነባች የነገዋን ኢትዮጵያ ለመፍጠር ምን ያህል ርቀት እንደተጓዘ ያሳያሉ። በቱሪዝም ዘርፍ ደግሞ «ገበታ ለሀገር»፣ «ገበታ ለሸገር» እና «ገበታ ለትውልድ» በተሰኙ ማዕቀፎች አስደናቂ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል። በዚህ ሳቢያ አብዛኞቹ የአገሪቱ ክፍሎች በአስደናቂ ሁኔታ ተቀይረዋል። ታሪካቸው ተለውጦ አዲስ መልክ የያዙት እነዚህ ስፍራዎች ለዜጎቻቸው ኑሮ የተመቹ ከመሆናቸውም በላይ የውጭ አገር ዜጎች ጭምር ሊጎበኟቸው የሚናፍቋቸው ከተሞች እየሆኑ ነው። ከእነዚህ ሁሉ መካከል እንደ ስሟ በመደመር መንግሥት ዘመን አዲስ መሆን የቻለችው አዲስ አበባ ጎልታ ትታያለች። 👉«ውብ አበባ» የተባለችው አገር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 7ኛው የ1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመሥረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ይህንኑ እውነታ አንስተዋል። ከተሞቻችን የዘመናዊ ከተማ መልክ ለመያዝ በጀመሩት ጥረት ለመኖሪያ የተመቹ፣ ለንግድና ለኮንፈረንስ የተስማሙ፣ ተምሳሌት ተደርገው የሚጠቀሱም እየሆኑ መምጣታቸውን ገልጸዋል። «ዛሬ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ውብ አበባ ተብላ ብትጠራ እውነት እንጂ ባዶ ምኞት ተደርጎ አይወሰድም» ብለዋል። አያይዘውም የአዲስ አበባ ለውጥ የዓለም ጎብኚዎችን «ኑ ወደ እኔ» እያለ የሚጣራ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው የተናገሩት እውነት ነው። 👉ትናንት የነበረችው አዲስ አበባ ይህ ጥሪ ምን ያህል ትልቅ ለውጥ እንደሆነ ለመረዳት ወደ ኋላ መለስ ብሎ ማየት ያስፈልጋል። አዲስ አበባ የኢትዮጵያ መዲና፣ የአፍሪካም የዲፕሎማሲ ማዕከል ሆና ለዘመናት በአገሪቱ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ ሕይወት ውስጥ እጅግ ከፍተኛ ቦታ ይዛ ኖራለች። ይሁን እንጂ እድገቷ ከደረጃዋ ጋር ፈጽሞ አይጣጣምም ነበር። በአብዛኞቹ የከተማዋ ክፍሎች ደረጃውን የጠበቀና ከተሽከርካሪ መንገድ የተለየ የእግረኛ መንገድ አልነበረም። እግረኛው ከመኪና ጋር እየተጋፋ ይጓዝ ነበር፤ መንገዶቿም ለትራፊክ አደጋና ለእግረኞች እንግልት ዋና ምክንያት ነበሩ። የመንገድ ዳር መብራቶች ካሉበት ቦታ ይልቅ የሌሉበት አካባቢዎች በርከት ይሉ ነበር፤ በርካታ አደባባዮችና መንገዶችም ከፍተኛ ጥገና ይፈልጉ ነበር። ዘመናዊና አማራጭ የትራንስፖርት ዘዴዎችን የሚያበረታቱ መንገዶች ደግሞ ጨርሶ የሚታሰቡ አልነበሩም። ሌላው ጎልቶ የሚታይ ክፍተት የሕዝብ መዝናኛ ቦታዎች እጥረት ነበር። ነዋሪው ነፃ ጊዜውን የሚያሳልፍበት ሰፊ ቦታ አልነበረውም። በከተማዋ ውስጥ አቋርጠው የሚያልፉ በርካታ ወንዞችና የወንዝ ዳርቻዎችም ተንከባካቢ በማጣታቸው በቆሻሻ ተሞልተው የአካባቢ ጥበቃ ሥጋት ሆነው፣ የበሽታ ምንጭና የደህንነት ስጋትም ነበሩ፡፡ እንደ ካዛንቺስና አራት ኪሎ ባሉ የከተማዋ እምብርት ሰፈሮች ውስጥ በአንድ ወቅት ተደራርበው የቆሙ አሮጌ የጭቃ ቤቶች፣ ጠባብ ጥጋጥጎች እና የታጨቁ መንደሮች የተለመደ ገጽታ ነበሩ። የዘመናት ታሪክ የተሸከሙ ሕንፃዎችና መኖሪያዎች ተገቢውን እድሳትና እንክብካቤ ሳያገኙ በጊዜ ሲሸረሸሩ ኖረዋል። ከተማዋ ወጥ የሆነ የውበትና የቀለም መመሪያ ስላልነበራት ገጽታዋ የተበታተነ ነበር፤ የታሪካዊ ስፍራዎችና የሐውልቶች ዙሪያም በቂ ጽዳትና ብርሃን አላገኘም ነበር። ዛሬ ግን ያ ገጽታ ወደ ታሪክነት እየተሸጋገረ ነው። እነዚሁ ሰፈሮች በዘመናዊ ዕቅድ ተቃኝተው፣ ታሪካዊ ሕንፃዎቻቸው ታድሰውና ተጠብቀው፣ በተዋሃደ የቀለምና የዲዛይን ቅንብር አዲስ መልክ እየያዙ ነው። ሐውልቶችና ታሪካዊ ስፍራዎች በጽዳትና በምሽት ብርሃን ተውበው፣ ለነዋሪው ኩራት ለጎብኚውም መስህብ ሆነው ይታያሉ። 👉ትንሳኤ ዛሬ ግን ታሪኩ ተቀይሯል። አዲስ አበባ የትናንት ገጽታዋን በማይታመን ሁኔታ እየቀየረች ነው። ነዋሪው ለውጡን እያጣጣመው ነው፤ ዓለምም አድናቆቱን እየገለጸ ነው። ትናንት የነበረችው አዲስ አበባ ላትመለስ ተሰናብታለች። መዓዛዋ ተቀይሯል፤ ደስ የማይል ገጽታዋና ሽታዋም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተወግዷል። አዲስ አበባ በእርግጥም አዲስ ሆናለች። 👉የመደመር መንግሥት ለአዲስ አበባ ትንሳኤ ሆኗታል። ዛሬ እንደ ስሟ አዲስ ሆና ተገንብታለች። በኮሪደር ልማቷ፣ በስማርት ሲቲ ግንባታዋና በሰው ተኮር ልማቶቿ ለዜጎቿ ምቹ እየሆነች፣ የአፍሪካ መዲናነቷንም በትክክል እያረጋገጠች ትገኛለች። የኮሪደር ልማት አዲስ አበባን ከጊዜው ጋር የሚመጥንና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ መሠረተ ልማት ባለቤት ያደረገ ትልቅ የለውጥ ምዕራፍ ነው። ፕሮጀክቱ መንገድን ከማሻሻል ባለፈ የከተማዋን ሁለንተናዊ ገጽታ ሙሉ በሙሉ ቀይሯል። 👉ከመንገድ እስከ እግረኛ የከተማዋ ዋና ዋና አውታሮች ሰፊና ደረጃቸውን የጠበቁ ሆነው እንደገና ተገንብተዋል። ተሽከርካሪዎች ቀልጣፋ ፍሰት አግኝተዋል፤ የትራፊክ እንግልትም በከፍተኛ ደረጃ ቀንሶ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ቀሏል። ቀደም ሲል ትኩረት ተነፍጎት የነበረው እግረኛ አሁን ትክክለኛውን የመራመጃ ቦታ አግኝቷል። የእግረኛ መንገዶች ተስፋፍተዋል፤ ለአካል ጉዳተኞች ምቹ መተላለፊያዎች፣ ንጹሕና ውብ የእግረኛ መንገዶች እንዲሁም የብስክሌት መጋለቢያ መስመሮች ተካተዋል። ዜጎች ደኅንነታቸው በተጠበቀ፣ ምቹ በሆነ አካባቢ መንቀሳቀስ ጀምረዋል። ምሽት ሲመጣም ከተማዋ አትደበዝዝም። ዘመናዊና ኃይል ቆጣቢ የመብራት ሥርዓቶች፣ የዲጂታል መረጃ መስጫ ሰሌዳዎችና ውብ የመንገድ ዳር አረንጓዴ ልማቶች ውበቷንና ደኅንነቷን ይጨምራሉ። ይህ የተቀናጀ ልማት አዲስ አበባን የነዋሪዎቿን ፍላጎት የምታሟላ፣ ለኑሮና ለሥራ ምቹ፣ የአፍሪካ መዲናነቷንም በሥራ ያረጋገጠች ዘመናዊ ከተማ አድርጓታል። 👉ወንዞችና አረንጓዴ ስፍራዎች በአንድ ወቅት የቆሻሻ መጣያና የከተማዋ ሥጋት የነበሩት የወንዝ ዳርቻዎችና ክፍት ቦታዎች ዛሬ የከተማዋ ዋነኛ የመስህብ ሀብትና የጽዳት ማዕከል ሆነዋል። በከተማዋ ማዕከልና አካባቢ የሚያልፉ ጥንታዊ ወንዞች ከቆሻሻ ተነጥለው የተፈጥሮ ፍሰታቸውን ጠብቀው እንዲፈሱ ተደርገዋል። ዳርቻዎቻቸው በድንጋይና በኮንክሪት ግድግዳዎች ተጠብቀው ከጎርፍ ሥጋት ነፃ ሆነዋል። በወንዝ ዳርቻዎች ላይ የተገነቡት ውብ ፓርኮች፣ የመዝናኛ ስፍራዎች፣ የሕፃናት መጫወቻዎችና የስፖርት ማዕከላት ለነዋሪዎችና ለጎብኚዎች ሁለንተናዊ የዕረፍትና የመዝናኛ አማራጭ ፈጥረዋል። የዛፎችና አረንጓዴ ተክሎች መብዛት የከተማዋን የአየር ጥራት አሻሽሏል፤ የሙቀት መጠኑን አመጣጥኖ የተፈጥሮ ሥነ ምኅዳሩ እንደገና እንዲያንሰራራ አድርጓል። በዚህም አዲስ አበባ አረንጓዴ፣ ንጹሕና ለኑሮ እጅግ ተስማሚ ሆናለች። 👉ሰላምና ደኅንነት የኮሪደር ልማት የከተማዋን ውበትና ገጽታ ብቻ አልቀየረም፤ ወንጀልን በመከላከልም ትልቅ ሚና እየተወጣ ነው። ፍትሕ ሚኒስቴር «የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት በወንጀል መከላከልና ደኅንነት ማረጋገጥ ላይ ያለው ሚና» በሚል ርዕስ ባካሄደው ጥናት ይህንኑ አመልክቷል። በተለይ ለጎዳና ወንጀል ምቹ የነበሩ ስፍራዎች እንዲጠፉ በማድረግ አስተማማኝ ሰላምና ደኅንነት እንዲረጋገጥ ዕድል መፍጠሩን ጥናቱ ያሳያል። 👉ጉዞው ይቀጥላል ታላቅ ሕዝብን የሚመጥን ርዕይ የሰነቀችው ኢትዮጵያ፣ ዋና ከተማዋን አዲስ አበባን ይበልጥ የማደስ ተግባሯን አጠናክራ ትቀጥላለች። የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከተማዋን ለቀጣይ አምስት ዓመታት ለመምራት በተመረጡበት ወቅት ያረጋገጡትም ይህንኑ ነው። በቀጣዮቹ ዓመታት አዲስ አበባን ይበልጥ ጽዱ፣ ሳቢ፣ ምቹና ለነዋሪዎቿ ተስማሚ የማድረጉ የሪፎርም ሥራ ተጠናክሮ የሚቀጥል ነው በማለት አፅንኦት ሰጥታዋል። ትናንት የነበረችው አዲስ አበባ ተሰናብታለች። ዛሬ የምትታየው አዲስ አበባ ደግሞ ገና ጅማሬዋ ላይ ናት። 👉አዲስ አበባ የለኮሰችው የልማት ችቦ በሁሉም ይበራል ከአዲስ አበባ የተነሳው የልማት ብርሃን በዚያው አልተወሰነም፤ ወደ ሁሉም የአገሪቱ ማዕዘናት እየተሰራጨ ነው። በመዲናዋ የተጀመረው የኮሪደር ልማት፣ የወንዝ ዳርቻ ፓርኮችና የከተማ እድሳት ልምድ ወደ ሌሎች ከተሞች ተሸጋግሮ፣ ዛሬ ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ያሉ ከተሞች አዲስ መልክ እየያዙ ይገኛሉ። የመደመር መንግሥት የሚያከናውነው ልማት ማንንም ወደ ኋላ የማይተው፣ ሁሉንም አካባቢዎች በእኩል ዓይን የሚያይና ያቀፈ ነው። በ«ገበታ ለሀገር»፣ «ገበታ ለሸገር» እና «ገበታ ለትውልድ» ማዕቀፎች በተለያዩ ክልሎች የተገነቡ የቱሪዝም መዳረሻዎች፣ በየከተማው የሚታዩ ዘመናዊ መንገዶችና የመዝናኛ ስፍራዎች፣ እንዲሁም በገጠር የሚካሄዱ የግብርና እና የመሠረተ ልማት ሥራዎች አንድ እውነት ይናገራሉ፤ ልማቱ የአንድ ከተማ ሳይሆን የመላው አገር መሆኑን። አዲስ አበባ ለሌሎች ከተሞች አርአያ ሆና ስትቆም፣ ሌሎች ከተሞችም በየፊናቸው አብበው የአገሪቱን ውበት እያበዙ ነው። በዚህም ኢትዮጵያ በአንድ ማዕከል ብቻ የምታደምቅ ሳትሆን፣ በሁሉም ማዕዘኗ የምታበራ፣ ዜጎቿም በየትኛውም ቦታ የልማቱ ተካፋይና ተጠቃሚ የሆኑባት አገር እየሆነች ነው።
ብሔራዊ ጥቅምን ማዕከል ያደረገ ሀገራዊ የከፍታ ጉዞ
Oct 7, 2026 221
ብሔራዊ ጥቅምን ማዕከል ያደረገ ሀገራዊ የከፍታ ጉዞ ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ አዲስ ምዕራፍ ተከፍቷል።የመደመር መንግሥት ከትናንት በስትያ በይፋ በተመሠረተበት ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በፓርላማ ያቀረቡት ንግግር የመንግሥቱን አቅጣጫ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን የወደፊት ራዕይ በግልጽ የሚያሳይ ነው። የንግግራቸው ማዕከላዊ ጭብጥም ኢትዮጵያ ዘላቂ ችግሮቿን የምትፈታው በራሷ የሥልጣኔ መንገድ ስትጓዝ ብቻ መሆኑን አጽንኦት ሰጥቷል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው ኢትዮጵያ የብዝሃ ሥልጣኔ ሀገር መሆኗን አንስተዋል። ለዘመናት የታሪክ፣ የባህል፣ የእምነት እና የማንነት መገናኛ ሆና ቆይታለች። ለብዙ ሕዝቦች መነሻ፣ ለብዙ ትውልዶች መነቃቃት ምንጭ የሆኑ ታሪኮችን በውስጧ ይዛለች። ሆኖም ይህን ታላቅ ቅርስ ወደ ዘላቂ ልማትና ዕድገት በመቀየር ረገድ ፈተናዎች በተደጋጋሚ ያጋጥማሉ። የጀመርነውን ማስቀጠል፣ የተገነባውን ማስጠበቅ እና በትውልድ መካከል ቀጣይነትን ማረጋገጥ ትልቁ ፈተና መሆኑንም አስገንዝበዋል።አንድ ትውልድ የገነባውን ሌላው ትውልድ እያፈረሰ የሚሄድበት ሁኔታ ሥልጣኔን እንደማይፈጥር ፣ ሀገርንም እንደማያበለጽግ አብራርተዋል። በዚህ ምክንያት ኢትዮጵያ በብዙ ዘርፎች ያላትን አቅም ሙሉ በሙሉ መጠቀም አልቻለችም። ሀሳብን በውይይት ከመፍታት ይልቅ በኃይል ለማስፈጸም የተደረጉ ጥረቶች ሀገሪቱን ወደ ኋላ ጎትተዋል። በመሆኑም የመደመር መንግሥት መልዕክት ግልጽ ነው፤ የኢትዮጵያ ችግሮች መፍትሔ የሚገኘው በግጭት ሳይሆን በመግባባት፣ በመደመር እና በጋራ ግብ ዙሪያ በመሰባሰብ ነው። አዲሱ የኢትዮጵያ ሥልጣኔ ማለት የመከባበር ባህልን መገንባት፣ ሕግን ማክበር፣ ልዩነቶችን እንደ ጥንካሬ መቀበል እና የጋራ ሀገራዊ ራዕይ መፍጠር ነው። ይህ ደግሞ ስሜትን በማሸነፍ፣ ጥላቻን በመተው እና አቅምን በጋራ በማሰባሰብ የሚሳካ ታላቅ ሀገራዊ ርዕይ ነው። በዚህ አዲስ ምዕራፍ ውስጥ ብሔራዊ ጥቅምን ማስከበር የመንግሥት ቀዳሚው አጀንዳው ነው። ከሁሉም የዓለም ሀገራት ጋር የሚደረገው ግንኙነት የኢትዮጵያን ጥቅም እና ተጽዕኖ የሚያሳድግ መሆን አለበት ብለዋል። ይህ የሚያሳየው ኢትዮጵያ በሌሎች ፍላጎት የምትመራ ሳይሆን በራሷ ብሔራዊ ጥቅም ላይ ተመስርታ የምትወስን ጠንካራ ሀገር መሆኗን ነው። በቀጣናውም ኢትዮጵያ የመረጋጋት እና የትብብር ማዕከል ሆና ትቀጥላለች። ጎረቤቶቿ በተፈጥሮ ያገኘቻቸው አጋሮቿ በመሆናቸው የጋራ ጥቅም፣ የሰላም እና የትብብር መርሆዎች የውጭ ግንኙነቷ መሠረት እንደሚቀጥሉ አጽንዖት ሰጥተዋል። በዚህም ኢትዮጵያ የራሷን ጥቅም በማስከበር እና በጋራ ጥቅም መርህ ላይ ተመስርታ የቀጣናው ተፅዕኖ ፈጣሪ ሀገር ለመሆን ትሰራለች። በመሆኑም የመደመር መንግሥት ምሥረታ የአስተሳሰብ ለውጥ፣ የሥልጣኔ ግንባታ ጥሪ እና ብሔራዊ ጥቅምን ማዕከል ያደረገ አዲስ ሀገራዊ የከፍታ ጉዞ ነው። ይህ ጉዞ ስኬታማ የሚሆነው ደግሞ መንግሥት፣ ፓርላማ፣ ተቋማት እና ሕዝብ በአንድ ራዕይ ሲተባበሩ ብቻ ነው። ኢትዮጵያ ያላትን ታሪካዊ ቅርስ ወደ ዘመናዊ ሥልጣኔ በመቀየር፣ ብሔራዊ ጥቅሟን በማስከበር እና በቀጣናው የሰላም አርበኛ ሆና በመቆም አዲስ ታሪክ ለመጻፍ ተዘጋጅታለች። የኢትዮጵያ ዘላቂ ብልጽግና፣ የሕዝቦቿ አንድነት እና የቀጣናው ደህንነት የሚረጋገጠው አዲስ ኢትዮጵያዊ ሥልጣኔ በሚገነባበት መጠን ነው።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም