የኢትዮጵያ ዋንጫ የአንደኛ ዙር ድልድል ይፋ ሆነ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ዋንጫ የአንደኛ ዙር ድልድል ይፋ ሆነ
አዲስ አበባ፤ህዳር 18/2019 (ኢዜአ)፦ የ2019 የኢትዮጵያ ዋንጫ 2019 የአንደኛ ዙር ድልድል እጣ መውጣት ስነ ስርዓት ተካሄዷል።
በዚህ መሠረት በውድድሩ የመጀመሪያ ዙር የሚሳተፉ 36 ክለቦች በምድብ ሀ፣ በምድብ ለ እና በምድብ ሐ ተከፋፍለው በመጀመሪያው ዙር እርስ በርስ የሚገናኙባቸው መርሃ ግብሮች ታውቀዋል።
በመጀመሪያው ቋት ስር ስድስት የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች የሚደረጉ ሲሆን፣ ጊምቢ ከተማ ከነቀምቴ ከተማ፣ ቦሌ ክፍለ ከተማ ከሶማሌ ፖሊስ፣ ቴፒ ከተማ ከቦዲቲ ከተማ፣ ጊንጪ ከተማ ከቡታጅራ ከተማ፣ ሀድያ ሌሞ ከሲርጢ ከተማ እንዲሁም ሌቃ ከተማ ከሾኔ ከተማ ይገናኛሉ።
በሁለተኛው ቋት ጉለሌ ከተማ ከሐረር ከተማ፣ ሀላባ ሸገር ከወልቂጤ ከተማ፣ ስልጤ ወራቤ ከአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ፣ ቡልዲግሉ ዘምበረ ከዱራሜ ከተማ፣ ኮንሶ ኒውዮርክ ከኦሜድላ እንዲሁም ሮቤ ከተማ ከመቂ ከተማ ጋር የሚፋለሙ ይሆናል።
በሦስተኛው ቋት ደግሞ ከቀጣናው የሚያልፈው ክለብ ከባስኬት ቡና ጋር የሚገናኝ ሲሆን፣ ጂንካ ከተማ ከንፋስ ስልክ፣ አሰላ ከተማ ከደምቢ ዶሎ ከተማ፣ ኑዌር ዘን ከአረካ ከተማ፣ ፉሪ ክፍለ ከተማ ከሀሳሳ ከተማ እንዲሁም ነጌሌ ቦረና ከሆለታ ከተማ ይጫወታሉ።
በነዚህ ጨዋታዎች የሚያሸንፉ 18 ክለቦች ወደ ሁለተኛው ዙር የሚያልፉ ሲሆን፣ የጨዋታዎቹ ቀን፣ ሰዓት እና ስታዲየሞችን በቀጣይ ይፋ እንደሚያደርግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።
በሁለቱ ዙሮች የሚሳተፉ ክለቦች የከፍተኛ ሊግ፣ የአንደኛ ሊግ እና ከክልል ማጣሪያ (ቀጠና) ያለፉ ናቸው።
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች በሶስተኛው ዙር ውድድሩን ይቀላቀላሉ።