ቀጥታ፡

የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ህዳር 18/2019 (ኢዜአ)፦ የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ዛሬ መጀመሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት እንደገለፁት ዛሬ የተጀመረው የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ በዋናነት በፓርቲው ስትራቴጂካዊ አቅጣጫ እና በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ይሆናል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም