ቀጥታ፡

ኖቲንግሃም ፎረስት ከቼልሲ : የ12ኛ ሳምንት የመጀመሪያ መርሐ ግብር


አዲስ አበባ፤ ህዳር 18 /2019 (ኢዜአ)፦ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 12ኛ ሳምንት ዛሬ ይጀመራል።

ምሽት አምስት ሰዓት ላይ ኖቲንግሃም ፎረስት ከቼልሲ  በሲቲ ግራውንድ ስታዲየም ይጫወታሉ።

ባለሜዳው ኖቲንግሃም ፎረስት በዘጠኝ ነጥብ 17ኛ ደረጃን ይዟል። ቼልሲ በ16 ነጥብ 8ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በ11ኛ ሳምንት መርሐ ግብር  ፎረስት በቦርንማውዝ  የ2 ለ 0 ሽንፈት አስተናግዷል።

የምዕራብ ለንደኑ ቼልሲ ባለፉት ሁለት የሊግ ጨዋታዎች  ተሸንፏል። በተለይም በ11ኛ ሳምንት በሜዳው በሊድስ ዩናይትድ የ4 ለ 1 ሽንፈት ያስተናገደበት ውጤት ያልተጠበቀ ነበር።

ሁለቱም ክለቦች ወደ አሸናፊነት ለመመለስ የሚያደርጉት ፍልሚያ ተመጣጣኝ ፉክክር ይታይበታል ተብሎ ይጠበቃል።

የ43 ዓመቱ አንዲ ማድሊ ጨዋታውን በዋና ዳኝነት ይመሩታል።


የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ  12ኛ ሳምንት  እስከ ህዳር 20 2019 ዓ.ም ይቆያል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም