ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሰባተኛ ሳምንት ዛሬ ይጀመራል  

አዲስ አበባ፤ ህዳር 18/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሰባተኛ ሳምንት ኢትዮጵያ ቡና ከሀላባ ከተማ  ዛሬ በሚያደርጉት ጨዋታ ይጀመራል።
 
ጨዋታው ከቀኑ 9 ሰዓት ከ30 በአዲስ አበባ ስታዲየም ይካሄዳል።
 
ኢትዮጵያ ቡና በሰባት ነጥብ 11ኛ ደረጃን ይዟል። አዲስ አዳጊው ሀላባ ከተማ በስምንት ነጥብ 9ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በስድስተኛ ሳምንት ወላይታ ድቻን 2 ለ 1 በመርታት ከሶስት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ኢትዮጵያ ቡና በድል ጉዞው ለመቀጠል ይፋለማል።
 
በኢትዮ ኤሌክትሪክ የ1 ለ 0 ሽንፈት ያስተናገደው ሀላባ ከተማ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ይጫወታል።
 
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሰባተኛ ሳምንት እስከ ህዳር 21 2019 ዓ.ም ይቆያል።

 
የባህር ዳር ከተማው አንተነህ ተፈራ በሰባት ጎሎች የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን እየመራ ነው።
 
የወላይታ ድቻው መሳይ ሰለሞን በአምስት ግቦች ይከተላል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም