ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ ቡና እና ሀላባ ከተማ ነጥብ ተጋሩ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 18/2019 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሰባተኛ ሳምንት የመጀመሪያ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና እና ሀላባ ከተማ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሩዋንዳዊው ታይባ ምቦኑዩምዋኒ በ49ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ጎል ኢትዮጵያ ቡና መሪ ሆኗል።

ሽመክት ጉግሳ በ55ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት የሀላባ ከተማን የአቻነት ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ ቡና በስምንት ነጥብ 10ኛ ደረጃን ይዟል።

አዲስ አዳጊው ሀላባ ከተማ በዘጠኝ ነጥብ 7ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም