ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
ከአፍሪካ የግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤቶች አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ የኢነርጂ፣ ሎጅስቲክስና የኢንዱስትሪ አቅሟን እያጠናከረች ነው- አሊኮ ዳንጎቴ
Sep 24, 2026 67
አዲስ አበባ፤ መስከረም 14/2019 (ኢዜአ):- አፍሪካ ውስጥ ካሉት የግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤቶች አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ የኢነርጂ፣ የሎጂስቲክስና የኢንዱስትሪ አቅሟን እያጠናከረች ትገኛለች ሲሉ ናይጄሪያዊው ባለሀብትና የዳንጎቴ ግሩፕ መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ አሊኮ ዳንጎቴ ገለጹ። አሊኮ ዳንጎቴ በጅቡቲ ዳመርጆግ እና በኢትዮጵያ ደወሌ መካከል የሚዘረጋው የ120 ኪሎ ሜትር የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ እና የ400 ሚሊዮን ሊትር ማከማቻ ተርሚናል ግንባታ ፕሮጀክት ይፋ መደረጉን ገልጸዋል። በምሥራቅ አፍሪካ ፈጣን ዕድገት እያስመዘገበች ያለችው ኢትዮጵያ የኢነርጂ፣ የትራንስፖርት፣ የሎጂስቲክስ እና የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ፍላጎቷ ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ የሚገኝና ትልቅ ኢኮኖሚ ያላት ሀገር መሆኗን ዳንጎቴ አመልክተዋል። የዳንጎቴ ግሩፕ በኢትዮጵያ ውስጥ ሰፊ ኢንቨስትመንቶችን እያከናወነ መሆኑን የገለጹት ዳንጎቴ፣ ሀገሪቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ማዳበሪያን ጨምሮ ሌሎች ወሳኝ ምርቶችን ከውጭ በማስገባት ፈንታ ለውጭ ገበያ ማቅረብ እንደምትጀምር ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ከነባረው የከባድ መኪና የትራንስፖርት ጫና በመላቀቅ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ፈጣን እና ቀልጣፋ የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ መስመር አጠቃቀም በመዘርጋት ጠንካራ የኢነርጂ ዋስትናን በዚህ ፕሮጀክት ታረጋግጣለች ብለዋል። ይህ የኢንቨስትመንት ማዕቀፍ ለኢትዮጵያ የሎጂስቲክስ ማነቆዎችን በእጅጉ እንደሚቀንስ፣ የምርት ጥራት ቁጥጥርን እንደሚያሻሽል እና እንደ ኢንዱስትሪ፣ አቪዬሽን፣ ትራንስፖርት፣ ግብርናና ኮንስትራክሽን ያሉ ቁልፍ ዘርፎችን በዘላቂነት እንደሚደግፍ ነው ያብራሩት። ፕሮጀክቱ ሙሉ በሙሉ በአፍሪካዊ ካፒታል እና በወጣት አፍሪካውያን መሐንዲሶች የሚገነባ መሆኑን የገለጹት ዳንጎቴ፣ ይህም አፍሪካ የራሷን የልማት ችግሮች በራሷ አቅም መፍታት እንደምትችል ትልቅ ማሳያ መሆኑን አመልክተዋል። ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ በመልክዐ ምድር፣ በጋራ ራዕይ እና በእጣ ፈንታ የተሳሰሩ መሆናቸውን ጠቅሰው የጅቡቲ ኮሪደር የሁለቱንም ሀገራት የንግድ እና የኢኮኖሚ ልውውጥ በማስተሳሰር ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል። አፍሪካ ከዕምቅ አቅም ባሻገር ወደ ተጨባጭ ምርት ልትሸጋገር እንደሚገባና በሌሎች ጥገኝነት የመሆን ሁኔታ ሊያበቃ ይገባል ብለዋል። በዚህ ረገድም አፍሪካ የኢነርጂ ዋስትናን ማረጋገጥ እና በራሷ አቅም መጠቀም እንዳለባት ተናግረዋል። የአፍሪካ ኤክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ (አፍሪ ኤግዚም ባንክ) እና የአፍሪካ ፋይናንስ ኮርፖሬሽን (ኤ.ኤፍ.ሲ) የመሳሰሉ አህጉራዊ የፋይናንስ ተቋማት ለዚህ ታላቅ ፕሮጀክት እያደረጉት ያለው ድጋፍ የአፍሪካን የገንዘብ አቅም የሚያሳይ ነው ብለዋል። ይህ ታሪካዊ የኢነርጂ መሠረተ ልማት ፕሮጀክት በወቅቱ፣ በጥራት እና በከፍተኛ ዓለም አቀፍ ደረጃዎች ተጠናቆ የሁለቱን አገራት ሕዝቦች እና የምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና የኢኮኖሚ ትስስር ለረጅም ዓመታት እንዲያገለግል ጥሪ ማቅረባቸውን ዳንጎቴ አመልክተዋል።
የተጣራ ነዳጅ ማስተላለፊያ ቱቦ መስመሩ ፓን-አፍሪካዊ ፕሮጀክት ነው - የጅቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦመር ጊሌ
Sep 24, 2026 91
አዲስ አበባ፤ መስከረም 14/2019 (ኢዜአ):- የተጣራ ነዳጅ ማስተላለፊያ የቱቦ መስመር የአፍሪካውያን የትብብር መንፈስ የገለጠ ፓን-አፍሪካዊ ፕሮጀክት መሆኑን የጅቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦመር ጊሌ ገለጹ። በጅቡቲ ዳመርጆግን ከኢትዮጵያ ደወሌ የሚያገናኝ እና ታላቅ ስትራቴጂካዊ ኢንቨስትመንት የሆነውን አዲስ የተጣራ ነዳጅ ማስተላለፊያ ቱቦ መስመር ዝርጋታ ዛሬ ይፋ ሆኗል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በፕሮጀክቱ መሠረተ ድንጋይ የማስቀመጥ ሥነ-ሥርዓት ላይ ታድመዋል። የጅቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦመር ጊሌ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ መገኘት በኢትዮጵያ እና በጅቡቲ መካከል ያለውን ጥልቅ እምነት እና የጋራ ጽኑ አቋም የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል። ይህ ኢንቨስትመንት የአፍሪካ መንግሥታትና የግሉ ዘርፍ ሲተባበሩ አፍሪካ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ መሆን እንደምትችል የሚያሳይ ፓን-አፍሪካዊ ፕሮጀክት መሆኑን አመልክተዋል። ፕሮጀክቱ ከ375 ሺህ ኪዩቢክ ሜትር በላይ የሚሆን የነዳጅ ማከማቻ ተርሚናል እንደሚኖረው እና በዓመት 5 ሚሊዮን ቶን ምርቶችን በማስተናገድ የትራፊክ ማነቆዎችን እንደሚፈታ ተናግረዋል። አፍሪካ ጥሬ ዕቃዎችን እየላከች የተጣራ ነዳጅ በውድ ዋጋ የመግዛት አዙሪት እና ጥገኝነት አሁን ሊጠናቀቅ እንደሚገባና እውነተኛ ነፃነት የሚገኘው በኢነርጂ ራስን በመቻል መሆኑን ነው የገለጹት። እርስ በእርስ ያልተሳሰሩ መሰረተ ልማቶች ድንበር ተሻጋሪ አይደሉም ያሉት ፕሬዝዳንቱ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና የደነገገውን ህጋዊ ማዕቀፍ በተጨባጭ መሠረተ ልማት መደገፍ እንደሚገባ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ እምቅ አቅም እና የጅቡቲ ወደቦች ሲቀናጅ የላቀ ስኬት ማስመዝገብ እንደሚቻል አመልክተዋል። ፕሮጀክቱ በአፍሪካዊ የካፒታል ወጪ የተገነባ መሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ ቴክኖሎጂውንና እውቀቱን ይዘው የሚሠሩት አፍሪካዊ መሐንዲሶችና ወጣቶች መሆናቸው ትልቅ እምርታ መሆኑን ነው የተናገሩት። ጅቡቲ መሠረተ ልማቶቿን በማዘመን፣ የኢኮኖሚ አማራጮቿን በማስፋት እና ለቀጣናዊ መረጋጋት አስተማማኝ አጋር ሆና እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል። ፕሬዝዳንቱ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ለአሊኮ ዳንጎቴ፣ ለጅቡቲ ወደቦች እና ነፃ የንግድ ቀጣናዎች ባለሥልጣን እንዲሁም ለፕሮጀክቱ ድጋፍ ላደረጉ ሌሎች አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰላም፣ መረጋጋት እና ኢኮኖሚያዊ ውህደት እንዲሳለጥ በቁርጠኝነት እየሰራች ነው-ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ
Sep 24, 2026 89
አዲስ አበባ፤ መስከረም 14/2019 (ኢዜአ):-ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰላምና መረጋጋት እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ውህደቶች እንዲሳለጡ በቁርጠኝነት እየሰራች መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ገለጹ። ፕሬዝዳንት ታዬ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 81ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት በዓለም ደረጃ ፍትሃዊ ሥርዓት ማንበር ሁሉንም ተጠቃሚ ለማድረግ ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል። ዘላቂ ሠላም የሚረጋገጠው በሉዓላዊ እኩልነት ላይ በተመሰረተ ትብብር ብቻ ነው ያሉት ፕሬዝዳንት ታዬ፣ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በጸጥታ ጉዳዮች ላይ በጋራ መሥራት ወሳኝ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል። በጸጥታ ጉዳዮች ላይ በሚጠበቀው ደረጃ በጋራ አለመሰራቱ የኃይል ፖለቲካ እያየለ መምጣት ጋር ተዳምሮ የዓለም አቀፉን ሥርዓት ተጽዕኖ ውስጥ እየከተተው መሆኑን አስገንዝብዋል። ለዚህ ችግር ሁነኛ መፍትሄ የባለብዙ ወገን ትብብር መሆኑን አንስተው ይህን ማድረግ ሲቻል ከግጭት ነጻ ዓለምን ማጽናት ያስችላል ሲሉ ተናግረዋል። ከ1 ነጥብ 6 ቢሊዮን በላይ ሕዝብ የሚኖርባትን አፍሪካ ትርጉም ያለው ውክልና መከልከል አግባብነት የሌለው መሆኑንም አጽንዖት ሰጥተዋል። ለዚህም በተለይም የጸጥታው ምክር ቤት ማሻሻያ እንዲደርግ ጥሪ አቅርበዋል። የሰው ሰራሽ አስተውሎት፣የአየር ንብረት ለውጥና በዓለም አቀፍ ደረጃ እየታየ ያለው የኢኮኖሚ አለመጣጣም ትልቅ ፈተና መደቀኑን ገልጸዋል። በዚህ ረገድ የሚፈልቁ ቴክኖሎጂዎች በማደግ ላይ ያሉ ሀገራትን ጨምሮ ሁሉንም የዓለም ሕዝብን ተጠቃሚ ማድረጋቸውን ማረጋገጥ ወሳኝ ጉዳይ ነው ብለዋል። በምሥራቅ አፍሪካ ሠላምና ቀጣናዊ የልማት ትብብር እውን እንዲሆን ኢትዮጵያ በቁርጠኝነት እንደምትሰራ ያረጋገጡት ፕሬዝዳንት ታዬ፤ በሱዳን ለተከሰተው ግጭት በሱዳናውያን ባለቤትነት የሚመራ መፍትሄ እንዲበጅለትም ጥሪ አቅርበዋል። የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለቀጣናዊ ዕድገት አስተዋጽኦ የሚያበረክት ታላቅ የፓን-አፍሪካ የኃይል ፕሮጀክት መሆኑንም አብራርተዋል። የኢትዮጵያን ኢኮኖሚያ ሽግግግር ለማስቀጠል አስተማማኝ የባህር በር ማግኘት ቁልፍ ጉዳይ ነው ያሉት ፕሬዝዳንት ታዬ፤ ኢትዮጵያ ከባህር በር ጋር የተያያዙ ዕድሎችን ለመጠቀም ሁሉንም ዲፕሎማሲያዊ አማራጮች እየተከተለች እንደሚገኝም አስረድተዋል። ኢትዮጵያ በምግብ ዋስትና፣ በታዳሽ የኃይል ምንጭ፣ በአረንጓዴ አሻራ እና አካባቢ ጥበቃ ሥራዎች ያስመዘገበቻቸውን አመርቂ ውጤቶችንም አንስተዋል። የዲጂታል ልማትን በማሳለጥ በኩል በርካታ ውጤታማ ተግባራት የተከናወኑ ሲሆን በ5 ሚሊዮን ኮደሮች ፕሮግራም የተመዘገበውን ስኬት በአብነት ጠቅሰዋል።
የነዳጅ ማስተላለፊያ ቱቦው የሎጂስቲክስ ወጪና ጊዜን ትርጉም ባለው መልኩ ይቀንሳል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
Sep 24, 2026 101
አዲስ አበባ፤ መስከረም 14/2019 (ኢዜአ):- በኢትዮጵያና ጅቡቲ መካከል የሚዘረጋው አዲስ የተጣራ ነዳጅ ማስተላለፊያ ቱቦ የሎጂስቲክስ ወጪና ጊዜን ትርጉም ባለው መልኩ የሚቀንስ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጅቡቲ ዳመርጆግ ከኢትዮጵያ ደወሌን የሚያገናኘውን የነዳጅ ምርቶች ማስተላለፊያ ቱቦ ግንባታ መሠረተ ድንጋይ የማስቀመጥ ሥነ-ሥርዓት ላይ ታድመዋል። በጅቡቲ ዳመርጆግን ከኢትዮጵያ ደወሌ የሚያገናኝ እና ታላቅ ስትራቴጂካዊ ኢንቨስትመንት የሆነውን አዲስ የተጣራ ነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ መስመር ዝርጋታ ዛሬ ይፋ ሆኗል። መልክዓ ምድር ለሁለቱ ሀገራት የሰጠው የጋራ ኮሪደር ጅቡቲን ከሰፊ ገበያ፣ ኢትዮጵያን ደግሞ ወደ ዓለም አቀፍ ንግድ የሚያገናኝ ድልድይ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል። የትራንስፖርት መዘግየቶች፣ ውስን የማጠራቀሚያ አቅሞች እና ውጤታማ ያልሆኑ የመጓጓዣ ዘዴዎች ለንግዱ ማህበረሰብ ከፍተኛ ወጪ ማስከተላቸውን አውስተዋል። ዛሬ አዲስ አበባ የሚገባ እያንዳንዱ ሊትር ነዳጅ በመኪና አምስት ቀናትን አሳልፎ እንደሚመጣ ጠቅሰው አዲሱ የቧንቧ መስመር ይህንን ጉዞ ወደ አንድ ቀን ገደማ ዝቅ እንደሚያደርገው አመልክተዋል። ጅቡቲ፣ ኢትዮጵያ እና የዳንጎቴ ግሩፕ በጋራ በመሆን ከዳመርጆግ እስከ ደወሌ 120 ኪሎ ሜትር የሚረዝም የነዳጅ ቧንቧ መስመር እንደሚዘረጉም ነው የጠቆሙት። በሁለቱም ወገኖች ከአንድ ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር በላይ የሚሆን የጋራ ማከማቻ ቦታ የሚዘጋጅ ሲሆን፣ ይህም ዓለም አቀፍ ቀውሶች ሲያጋጥሙ የኢነርጂ አቅርቦቱ እንዳይስተጓጎል ዋስትና ይሰጣል ብለዋል። መሠረተ ልማቱ ለኢትዮጵያ ኢንዱስትሪዎች እና ግብርና ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለጅቡቲ ደግሞ የትራንዚት መጠንን ከፍ በማድረግ እንደ ቀጠናዊ የሎጂስቲክስ ማዕከል ያላትን ቦታ እንደሚያጠናክር አብራርተዋል። ወደቦች፣ አውራ ጎዳናዎች፣ የባቡር መስመሮች፣ ሞጆ የሎጂስቲክስ ማዕከል እና የቧንቧ መስመሩ እንደ አንድ የተሳሰረ ሥርዓት መሥራት እንዳለባቸው ጠቁመዋል። አሊኮ ዳንጎቴ፣ የአፍሪካ ድርጅቶች ከታላቅ ራዕይ ጋር የሚመጥን ግብ አሳክተው በዓለም አቀፍ ደረጃ መወዳደር እንደሚችሉ ማስመስከር መቻላቸውን ጠቅሰዋል። ይህ ፕሮጀክት በአፍሪካዊ ካፒታል የተገነባ ለአፍሪካዊ ዕድገት የሚውል አፍሪካዊ መሠረተ ልማት ነው ብለዋል። ሥራውን ወደ መሬት አውርዶ ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባም አስገንዝበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዚህ ኢንቨስትመንት ፕሮጀክት እውን መሆን አስተዋፅኦ ላደረጉ አካላት ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በምንከፍለው ግብር ከተማችን በልማት እያደገችና እየተለወጠች በመሆኑ ተደስተናል- የደሴ ከተማ ነጋዴዎች
Sep 24, 2026 93
ደሴ፤ መስከረም 14/2019(ኢዜአ)፡-በምንከፍለው ግብር ከተማችን በልማት እያደገችና እየተለወጠች በመሆኑ ተደስተናል ሲሉ የደሴ ከተማ ነጋዴዎች ገለፁ። የደሴ ከተማ አስተዳደር በአዲሱ የፌዴራል ታክስ አስተዳደር ዙሪያ ከነጋዴዎች ጋር የግንዛቤ ማስጨበጫ የምክክር መድረክ አካሄዷል። በወቅቱም ነጋዴዎቹ የሚከፍሉት ግብር የከተማዋን ልማት ለማሳለጥ በመዋሉ ከተማዋ እየተለወጠች ትገኛለች ብለዋል። ከተሳታፊ ነጋዴዎች መካከል አቶ መሀመድ አሊ፤ የሚጠበቅባቸውን ግብር በወቅቱ በመክፈል የዜግነት ግዴታቸውን እየተወጡ መሆኑን ጠቁመው፣ "በምንከፍለው ግብር ከተማችን እያደገችና እየተለወጠች በመሆኑ ተደስተናል" ብለዋል። በዓመት በአማካይ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ግብር እንደሚከፍሉ የተናገሩት አቶ መሀመድ፣ ዘንድሮም የሚጠበቅባቸውን ግብር በወቅቱ በመክፈል በከተማዋ ልማት እየተሳተፉ መሆኑን ገልጸዋል። ሌላው ተሳታፊ አቶ ጋሻው አሰፋ በበኩላቸው፤ "የአካባቢያችንን ሰላም ነቅተን በመጠበቅ ለከተማችን ሁለንተናዊ እድገትና ልማት የድርሻችንን እየተወጣን እንገኛለን" ሲሉ ገልጸዋል። "ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በከተማችን በተሰሩልን ልማቶች ተጠቃሚ መሆን ችለናል" ያሉት አቶ ጋሻው፣ የሚከፍሉትን ግብር ጠቀሜታ በተግባር ማየት በመቻላቸው መደሰታቸውን ተናግረዋል። በሰሩት ልክ በየዓመቱ ከ100 ሺህ ብር በላይ ግብር በመክፈል ለሰላምና ልማት ስራው አስተዋጽኦ ማበርከታቸውንም አውስተዋል። በከተማዋ የተገነቡት የኮሪደር ልማትና ሌሎች የልማት ተግባራት የግብርን ፋይዳ እንዲገነዘቡ እንዳስቻላቸው ጠቁመው፣ የተጀመረውን ልማት ለማስቀጠል የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል። የደሴ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ አቶ መንግስቱ አበበ በበኩላቸው፤ በከተማዋ የሚካሄደው ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ የሚያመነጨውን ገቢ አሟጦ በመሰብሰብ ልማትና ዕድገቷን ለማፋጠን እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በአዲሱ የፌዴራል ታክስ አስተዳደር ዙሪያ ለንግዱ ማህበረሰብ ግንዛቤ በመፍጠር፣ አስተዳደሩ ያቀደውን ከ8 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ እየሰራ እንደሚገኝም ገልጸዋል። የደሴ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሽመልስ ጌታቸው በበኩላቸው፤ ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን የከተማዋን ሰላም በመጠበቅ ሰፋፊ የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን አብራርተዋል። የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ፍቅረ ማሪያም ደጀኔ በበኩላቸው፤ በክልሉ በሚንቀሳቀሰው ኢኮኖሚ ልክ ገቢ በመሰብሰብ የልማት ሥራዎችን ለማከናወን የግብር ከፋዩ ህብረተሰብ ድርሻ የጎላ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም ባለፉት ዓመታት ውጤታማ ተግባር መከናወኑን ጠቁመው፣ ዘንድሮም የተሻለ ለመስራት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። በምክክር መድረኩ የክልል፣ የከተማና የክፍለ ከተማ አመራሮችን ጨምሮ ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
ፖለቲካ
የኢትዮ-ጅቡቲ ወዳጅነት፡የመደመር መንግሥት የጎረቤት ተኮር ዲፕሎማሲ ህያው አብነት
Sep 24, 2026 166
የኢትዮጵያና የጅቡቲ ሕዝቦች በታሪክ፣በቋንቋ፣ በባህልና በማኅበራዊ እሴቶች እጅግ የተሳሰሩና በደም የተቆራኙ ወንድማማቾች ናቸው።የሀገራቱ የትብብር ታሪክም ከአንድ ክፍለ ዘመን በላይ የተሻገረ ሆኖ ይገኛል። ኢትዮጵያ በዳግማዊ አፄ ምኒሊክ ዘመነ መንግሥት የመጀመሪያውን ቆንስላ ጽሕፈት ቤት በጅቡቲ ከፍታለች።ለኢትዮጵያ በታሪኳ የመጀመሪያው የውጭ አገር ዲፕሎማሲያዊ ተልዕኮ ነበር። እ.አ.አ በ1897 የፈረንሳይ አስተዳደር ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በመስማማት ጅቡቲን ከአዲስ አበባ የሚያገናኘውን ታሪካዊ የባቡር መስመር ግንባታ አስጀምሯል። ይህ መሠረተ ልማት የሁለቱን አገራት የንግድና የሕዝብ ትስስር ከመነሻው ያጠናከረ ዋነኛ ምሰሶ ነው። የኢትዮጵያና የጅቡቲ ሕዝቦች በታሪክ፣ በቋንቋ፣ በባህልና በማኅበራዊ እሴቶች እጅግ የተሳሰሩና በደም የተቆራኙ ወንድማማቾች ናቸው። ይህ የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር የፖለቲካና የኢኮኖሚ ግንኙነቱ ጠንካራ መሠረት ተደርጎ የሚወሰድ ሲሆን ባለፉት አስርት ዓመታት ውስጥ በሀገራቱ መካከል ግዙፍ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች መገንባታቸው ትስስሩን ስትራቴጂካዊ መልክ እንዲይዝ አስችሏል። ይህንን ትስስር ይበልጥ ዘላቂ ለማድረግ ዘመናዊው የአዲስ አበባ-ጅቡቲ የኤሌክትሪክ ባቡር መስመር፣ የድንበር ማቋረጫ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች፣ የፍጥነት መንገዶች እና የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ተዘርግተዋል። ይህም አገራቱን በፖለቲካዊ ስምምነት ብቻ ሳይሆን በመሠረተ ልማት አስተሳስሯቸዋል። በአሁኑ ወቅት ደግሞ ትስስራቸው ይበልጥ እያደገ መጥቷል። በሁለቱ ሀገራት መሪዎች መካከል የሚደረጉ የጉብኝት ልውውጦችም ትስስሩን የማጠናከር ወሳኝ ሚና እየተወጣ ይገኛል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተለያዩ ጊዜያት ወደ ጅቡቲ በማቅናት እንዲሁም የጅቡቲው ፕሬዝዳንት እስማኤል ዑመር ጊሌ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት የሁለትዮሽና ቀጣናዊ ትስስሮችን የሚያጠናክሩ ውይይቶችን አድርገዋል። ኢትዮጵያ ቅድሚያ ለጎረቤት በሚሰጠው የመደመር መንግሥት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲዋ አማካኝነት በቀጣናው በምታደርገው የልማት ትስስር የኢትዮ-ጅቡቲ ወዳጅነት በአብነት የሚነሳ ነው። የኢትዮ-ጅቡቲ ወዳጅነት በጋራ ተጠቃሚነት መርህ ላይ የተመሠረተ ሲሆን፤ በሀገራቱ መካከል የተመሠረተው የሕዝብ ለሕዝብ መድረክ እንደ ፍልሰት እና የአየር ንብረት ለውጥ ያሉ የጋራ ተግዳሮቶችን በጋራ ለመፍታት ያስችላል። የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ ተሞክሮን በጅቡቲ ጭምር የማጋራትና የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሮች ተግባራዊ ማሳያ ናቸው። በዛሬው ዕለት ደግሞ ይህንን ጠንካራ ወዳጅነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ስትራቴጂካዊ ትስስር ተበስሯል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ የጅቡቲ ፕሬዚዳንት እስማኤል ዑመር ጊሌ እና አፍሪካዊው ባለሀብት አሊኮ ዳንጎቴ በጋራ ዛሬ አዲሱን የትብብር ምዕራፍ አስጀምረዋል። ይህም በጅቡቲ ዳመርጆግን ከኢትዮጵያ ደወሌ የሚያገናኝ አዲስ የተጣራ ነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ መስመር ዝርጋታ ፕሮጀክት ነው። ፕሮጀክቱ በሁለቱም ጫፎች የሚገነቡ የማከማቻ ተርሚናሎችን የሚያካትት ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስና በዳንጎቴ ግሩፕ ጥምረት የሚተገበር ነው። ዋና ዓላማው የነዳጅ ማጓጓዣ ወጪንና መዘግየትን በመቀነስ፣ የኢነርጂ አቅርቦትን ማሻሻል እና የኢትዮ–ጅቡቲ የንግድ ኮሪደርን ይበልጥ ማቀላጠፍ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንደገለጹትም፣ ፕሮጀክቱ የሎጂስቲክስ ወጪንና መዘግየትን በመቀነስ የኢነርጂ ዋስትናን ያጠናክራል፤ የኢትዮ–ጅቡቲ የንግድ መስመርንም ፍጥነትና ዘላቂነት ያሳድጋል። ነገር ግን ይህ መሠረተ ልማት ከነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ መስመር በላይ የሚታይ ትርጉም አለው። ከንግድና ከሎጂስቲክስ ባሻገር፣ በአፍሪካውያን ኢንቨስትመንትና በጋራ ልማት ላይ የተመሠረተ ቀጣናዊ ትስስርን የሚያጠናክር አዲስ የትብብር ደረጃ ነው። ይህም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሚመራው የመደመር መንግሥት የሚከተለው የቅድሚያ ለጎረቤት የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ጅቡቲን ጨምሮ በቀጣናው የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያጎለብቱ አስተሳሳሪ ልማቶችን በመተግበር ቀጣናዊ ትስስርን ለማጠናከር የሚከተለውን አቅጣጫ ያሳያል። የኢትዮጵያ እና የጅቡቲ የመጻኢ ጊዜ የሁለትዮሽ ትብብር በሀገራቱ መካከል የተጀመሩትን ግዙፍ የምጣኔ ሀብት እና የመሠረተ ልማት ትስስሮች ይበልጥ ወደ ላቀ የተሟላ ቀጣናዊ ትስስር የሚሸጋገርበት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። የሁለቱ አገራት መሪዎች እና ሕዝቦች ያላቸው ዘመን ተሻጋሪ ወዳጅነት፣ የጋራ ህልውና እና እምነት የወደፊት ወዳጅነታቸውን ይበልጥ አስተማማኝ እንደሚያደርገው ይታመናል።
ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር ያነሷቸው ዋና ዋና ጉዳዮች
Sep 24, 2026 267
ኢትዮጵያ 32ኛውን የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ በኃላፊነት ታዘጋጃለች፤ ጉባኤው የግሉን ዘርፍ እና ዓለም አቀፍ ባለድርሻ አካላትን ያካተተ እንዲሁም ውጤታማ መፍትሔ የሚያመጣ እንዲሆን ኢትዮጵያ በቁርጠኝነት ትሠራለች፤ ፕሬዝዳንቱ ሁሉም የዓለም መሪዎች በጉባኤው ላይ በመሳተፍ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ታሪካዊ አሻራቸውን እንዲያሳርፉ ጥሪ አቅርበዋል፤ ኢትዮጵያ እየገነባችው ላለው ጠንካራ ኢኮኖሚ አስተማማኝና ደህንነቱ የተጠበቀ የባህር በር ያስፈልጋታል፤ የኢትዮጵያ የባህር በር የማግኘት ጉዳይ ለሁሉም የቀጣናው ሀገራት ከሚያስገኘው የጋራ ጥቅም፣ ትብብርና ዕድገት አንጻር ሊታይ ይገባል፤ ኢትዮጵያ የባህር በር ፍላጎቷን ለማሳካትና ከዓለም አቀፍ የንግድ ሥርዓት ጋር በጥብቅ ለመተሳሰር ሁሉንም የዲፕሎማሲ አማራጮች ተጠቅማ እየሠራች ትገኛለች፤ 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን አፍሪካውያን እኩል ውክልና የማግኘት መብት ለዘመናት መነፈጋቸውን እንዴት የዓለም ህሊና ሊቀበለው ይችላል? የፀጥታው ምክር ቤት አስቸኳይ ሪፎርም ማድረግ የትውልዱ የእውነትና የሞራል ጥያቄ ነው፤ ድርጅቱ የዓለምን ነባራዊ እውነታ ያገነዘበ፣ በፍትሕና በእኩልነት ላይ የተመሠረተ መሠረታዊ ሪፎርም በማድረግ ወቅታዊ የዓለም ፈተናዎችን በተሻለ አቅም መወጣት አለበት፤ ኢትዮጵያ የሰዎች ሰብአዊ ክብር እንዲጠበቅ፣ ፍትሕ እንዲሰፍንና የነፃ ሕዝቦች አብሮነት እንዲከበር ባላት ታሪካዊ ቁርጠኝነት ጸንታ ትቀጥላለች፤ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በውሃ ሀብት የጋራ ቀጣናዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ እንደሚቻል ያሳየ ታላቅ ፕሮጀክት ነው፤ ኢትዮጵያ እስከ እ.ኤ.አ. 2030 ተጨማሪ 13,000 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት የምሥራቅ አፍሪካን የኢነርጂ ገበያ ፍላጎት ለማሟላት አቅዳ እየሠራች ትገኛለች፤ ኢትዮጵያ በመሠረተ ልማት፣ በንግድ እና በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ቀጣናዊ ትስስርን ለማጠናከር እየሠራች ነው፤ በምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና አለመረጋጋት ለመፍጠር የሚሠሩ የውጭ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስበዋል፤ ታዳጊ ሀገራት የቴክኖሎጂ አብዮቱ ተመልካች ሳይሆኑ ባለቤት መሆን አለባቸው፤ የኢትዮጵያ የ"5 ሚሊዮን ኮደሮች" መርሃ ግብር እና የሰው ሠራሽ አስተውሎት ዩኒቨርሲቲ ግንባታ አፍሪካ ለቴክኖሎጂው ዘመን ዝግጁ መሆኗን ማሳያ ነው ባለፉት 8 ዓመታት በተካሄደው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር 56 ቢሊዮን ችግኞች መተከላቸውንና ይህም በዓመት 9 ቢሊዮን ቶን ካርቦን የማመቅ አቅም ይኖራቸዋል፤ ኢትዮጵያ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከስንዴ አስመጪነት ወጥታ በአፍሪካ ከሚገኙ ትላልቅ የስንዴ አምራች ሀገራት አንዷ መሆን ችላለች፤ በምግብ ዋስትና ረገድም ከፍተኛ እመርታ ማስመዝገብ ችላለች፤ የአየር ንብረት ለውጥን የሚያቋቁሙ የተሻሻሉ የስንዴ ዝርያዎችን በስፋት በመጠቀም ረገድ አበረታች ስኬት አስመዝግባለች፤ የምግብ አቅርቦት የፖለቲካ አጀንዳ በሆነበት እና የዓለም የምግብ አቅርቦት ሰንሰለት በተፈተነበት ወቅት፣ የኢትዮጵያ የስንዴ ምርታማነት አፍሪካ ራሷን መመገብ እንደምትችል ማሳያ ሆኗል፤
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ጅቡቲ ገቡ
Sep 24, 2026 234
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 14/2019 (ኢዜአ):- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ጅቡቲ ገብተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጅቡቲ ሲደርሱ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦመር ጊሌ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ሁለቱ መሪዎች በኢትዮጵያ እና በጅቡቲ መካከል ያለውን ኢኮኖሚያዊ ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ የጋራ ፕሮጀክት ይፋ የሚሆንበትን መድረክ እንደሚታደሙ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።
ታላቁ የህዳሴ ግድብ ቀጣናዊ ብልጽግናን ማሳካት እንደሚቻል ያረጋገጠ ፓን-አፍሪካዊ ፕሮጀክት ነው-ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ
Sep 24, 2026 287
አዲስ አበባ፤ መስከረም 13/2019 (ኢዜአ):- የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በውሃ ሀብት የጋራ ቀጣናዊ ብልጽግና ልማት እውን ማድረግ እንደሚቻል ያረጋገጠ ታላቅ ፓን-አፍሪካዊ ፕሮጀክት መሆኑን ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ገለጹ። 81ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ በኒው ዮርክ እየተካሄደ ይገኛል። ፕሬዝዳንቱ ማምሻውን በጠቅላላ ጉባኤው ላይ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ በመሠረተ ልማት ዝርጋታ፣ በንግድ እና በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት በኩል በምስራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ ትስስርና ትብብርን ለማጠናከር በትጋት እየሠራች መሆኑን ፕሬዚዳንቱ ጠቁመዋል። አንዳንድ የውጭ አካላት በምስራቅ አፍሪካ ቀጣና አለመረጋጋት ለመፍጠር እየሰሩ መሆኑን አንስተው፤ እነዚህ አካላት ከድርጊታቸው መቆጠብ አለባቸው ብለዋል። ከኢነርጂ ጋር በተያያዘ፣ ኢትዮጵያ ከ60,000 ሜጋ ዋት በላይ ኃይል ማመንጨት አቅም እንዳላት የገለጹት ፕሬዝዳንቱ፤ እ.ኤ.አ. እስከ 2030 ድረስ ተጨማሪ 13,000 ሜጋ ዋት ለማመንጨት ማቀዷን ጠቁመዋል። ይህም የምሥራቅ አፍሪካን የኢነርጂ ገበያና ከዚያም አልፎ ያለውን ፍላጎት ለማሟላት እንደሚያስችል አስታውቀዋል። በዚህ ረገድም የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውሃ ሀብት የጋራ ቀጣናዊ ብልጽግና ዕድገትና ልማት መፍጠር እንደሚቻል ያረጋገጠ ታላቅ ፓን-አፍሪካዊ ፕሮጀክት ነውም ብለዋል። በሌላ በኩል በዲጂታል አብዮትና በሰው ሠራሽ አስተውሎት ዘመን አፍሪካ የምታነሳው ወሳኝ ጥያቄ የቴክኖሎጂው ዘመን ዓለም አቀፍ አለመመጣጠንን የሚያባብስ ወይስ የጋራ እድገት ማፋጠኛ ነው? የሚለውን ጥያቄ መሆኑን ፕሬዝዳንቱ አመልክተዋል። ዓለም አቀፉ የደቡብ ክፍለ ዓለም የቴክኖሎጂ አብዮቱን በባለቤትነት መምራት እንጂ ተመልካች መሆን የለበትም ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ የኢትዮጵያ የ"5 ሚሊዮን ኮደሮች" መርሃ ግብር እና የሰው ሠራሽ አስተውሎት ዩኒቨርሲቲ ግንባታ አህጉሪቱ ለቀጣዩ ጊዜ ዝግጁ መሆኗን ማሳያ ናቸው ብለዋል። ከአካባቢ ጥበቃ እና ከተፈጥሮ ሀብት አንፃርም፤ ከስምንት ዓመታት በፊት በተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር እስከ አሁን 56 ቢሊዮን ችግኞች መተከላቸውን ፕሬዝዳንቱ አስታውሰዋል። መርሃ ግብሩ የደን ሽፋን ከማስፋቱም በላይ የአካባቢ ሥነ-ምህዳርን ወደ ነበረበት እየመለሰ መሆኑን ጠቅሰው ፤ ይህም በዓመት 9 ቢሊዮን ቶን ካርቦን የማመቅ አቅም እንደሚኖረው ይጠበቃል ብለዋል።
አፍሪካውያን በተመድ ፍትሃዊ ውክልና መነፈጋቸው በአስቸኳይ መታረም ያለበት ጉዳይ ነው - ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ
Sep 23, 2026 395
አዲስ አበባ፤ መስከረም 13/2019 (ኢዜአ):- 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን አፍሪካውያን በተመድ ፍትሃዊ ውክልና መነፈጋቸው በአስቸኳይ መታረም ያለበት ጉዳይ ነው ሲሉ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ገለጹ። ተመድ የዓለምን ነባራዊ እውነታ ያገነዘበ መሰረታዊ ሪፎርም ሊያደርግ ይገባልም ብለዋል። 81ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ በኒው ዮርክ እየተካሄደ ነው። ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ማምሻውን በጠቅላላ ጉባኤው ላይ ንግግር አድርገዋል። ፕሬዝዳንት ታዬ በንግግራቸው ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአሁኑ ሰዓት ዓለም ላይ ፈታኝ ሁኔታዎችን በተሻለ አቅም መፍታት እንዲችል መሰረታዊ የሆነ ሪፎርም እንዲያደርግ አጥብቃ ታሳስባለች ብለዋል። ተመድ በእኩልነት እና ፍትሃዊነት ላይ የተመሰረተ እንዲሁም የዓለምን ነባራዊ እውነት ባገነዘበ መልኩ ማሻሻያ ሊደረግበት እንደሚገባ ተናግረዋል። አፍሪካ በዓለም አቀፍ ውሳኔ ሰጪነት ውስጥ ለረጅም ጊዜ ተግላ መቆየቷን አውስተው የፀጥታ ምክር ቤት አስቸኳይ ሪፎርም ማከናወን እንዳለበት አስገንዝበዋል። "እውነተኛ የፖለቲካ ፍላጎት ካለ፣ 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን አፍሪካውያን እኩል ውክልና የማግኘት መብት ለዘመናት መነፈጋቸውን እንዴት የዓለም ህሊና ሊቀበለው ይችላል?" ሲሉ ፕሬዝዳንቱ ጠይቀዋል። ይህ የትውልዱ የእውነት እና የሞራል ጥያቄ መሆኑንም ገልጸዋል። በሌላ በኩል ፕሬዚዳንቱ የባለብዙ ወገን ትብብርን አስፈላጊነት ሲያስረዱ፤ የጋራ ጸጥታ ምሰሶዎች ሙሉ በሙሉ ከመፍረሳቸው በፊት ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ቆራጥ እርምጃ በመውሰድ ግጭቶችን ለመከላከል አበክሮ ሊሠራ እንደሚገባ አሳስበዋል። ባለብዙ ወገን ትብብር እንደ ቀላል የዲፕሎማሲያዊ መሳሪያ አይደለም፤ ይልቁንም ዓለም አቀፍ የኃይል ፖለቲካን ለመቋቋም የሚያስችል እና በሉዓላዊ እኩልነት ላይ የተመሰረተ ህያው ጋሻችን ነው ሲሉ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ሰዎች ሰብአዊ ክብራቸው እንዲጠበቅ፣ ፍትሕ እንዲሰፍን እና የነፃ ሕዝቦች ጽኑ አብሮነት እንዲከበር ባላት ታሪካዊ ቁርጠኝነት ጸንታ እንደምትቀጥል ፕሬዝዳንቱ አረጋግጠዋል።
ኢትዮጵያ ኮፕ 32 ሁሉን አካታች እና መፍትሔ አምጪ እንዲሆን በቁርጠኝነት ትሠራለች – ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ
Sep 23, 2026 380
አዲስ አበባ፤ መስከረም 13/2019 (ኢዜአ):- ኢትዮጵያ 32ኛውን የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 32) ሁሉን አካታች እና መፍትሔ አምጪ እንዲሆን በቁርጠኝነት እንደምትሠራ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ገለጹ። 81ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ በኒው ዮርክ መካሄዱን ቀጥሏል። “መተማመንን ዳግም መገንባት እና አዳዲስ ለውጦችን በአግባቡ መምራት፣ ለሁሉም የሚሠራ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን መፍጠር” የጠቅላላ ጉባኤው መሪ ሐሳብ ነው። በፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የተመራ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ልዑካን ቡድን በጉባኤው ላይ እየተሳተፈ ይገኛል። ፕሬዝዳንቱ ማምሻውን በጠቅላላ ጉባኤው ላይ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ 32ኛውን የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 32) እንደምታዘጋጅ ገልጸዋል። ጉባኤው የግሉን ዘርፍ እና ዓለም አቀፍ ባለድርሻ አካላትን ጨምሮ ሁሉን አካታች እና መፍትሔ አምጪ እንዲሆን ኢትዮጵያ አበክራ እንደምትሠራ ተናግረዋል። ሁሉም የዓለም መሪዎች በኮፕ ጉባኤው ላይ እንዲሳተፉና የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ታሪካዊ አሻራቸውን እንዲያሳርፉ ጥሪ አቅርበዋል።
የትግራይ ክልላዊ መንግስት ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ሜጀር ጀነራል ገብረ አድሃና ወደ መንግስት ገቡ
Sep 23, 2026 424
አዲስ አበባ፤ መስከረም 13 /2019 (ኢዜአ)፦የትግራይ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት የሕወሃት ነባር አመራር ሜጀር ጀነራል ገብረ አድሃና የህወሓትን ከታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር በማበር ሀገር የማፍረስ ተልዕኮና የጦርነት አባዜን በመቃወም ወደ ፌዴራል መንግስት ገብተዋል። ጀነራል መኮንኑ በሀገር መከላከያ ሠራዊት ውስጥ በከፍተኛ የአመራር እርከን ላይ ያገለገሉ ሲሆን፣ ህወሓት በሀገር ላይ ክህደት እስኪፈጽም ድረስ የመከላከያ መረጃና ዘመቻ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል። ዕድሜያቸው ለውጊያ ያልደረሱ ህፃናትን አስገድዶ በመመልመል ለጦርነት በመማገድ ፣ የትግራይ ህዝብን ስቃይ እያበዛ ያለውን የህወሃት እኩይ ሴራ በመቃወም ጀኔራሉ ከድርጅቱ መለየታቸውም የህገ - ወጡን የህውሀት ቡድን ህልውና ማክተሙን በተግባር ያሳያል።
የአዲሱ መንግሥት ምስረታ እና የምክር ቤቱ መክፈቻ ሥነ ሥርዓት መስከረም 25 ይካሄዳል - አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ
Sep 23, 2026 596
አዲስ አበባ፤ መስከረም 13/2019 (ኢዜአ):- የአዲሱ መንግሥት ምሥረታ እና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መክፈቻ ሥነ ሥርዓት መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም እንደሚካሄድ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ገለፁ፡፡ አፈ-ጉባኤው ባስተላለፉት መልእክት፤ የተካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሃዊና ተዓማኒነት ያለው ሆኖ መጠናቀቁን ገልጸዋል። በዚሁ ምርጫ 42 የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ 10,438 እጩዎች እንዲሁም ከ54 ሚሊዮን በላይ መራጮች መሳተፋቸውንም አውስተዋል። በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 50 ንዑስ አንቀጽ 3 መሠረት የፌደራሉ መንግሥት ከፍተኛ የሥልጣን አካል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲሆን ተጠሪነቱም ለሀገሪቱ ሕዝብ መሆኑ ተደንግጓል። በተጨማሪም በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 58 ንዑስ አንቀጽ 2 የምክር ቤቱ የሥራ ዘመን በመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ እንደሚጀመር በተደነገገው መሠረት፣ የመንግሥት ምስረታውና የምክር ቤቱ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም ይከናወናል። በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 56 መሠረት በምክር ቤቱ አብላጫ መንበር ያገኘው የፖለቲካ ፓርቲ የፌደራሉን ሕግ አስፈጻሚ አካል የሚያደራጅ ሲሆን፣ በሕዝብ የተመረጠው አዲሱ ሕግ አስፈጻሚ አካል በዕለቱ በይፋ ኃላፊነት እንደሚረከብ ገልጸዋል። ለሥነ-ሥርዓቱ አስፈላጊው ዝግጅት ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን የጠቆሙት አፈ-ጉባኤው፤ መጪው ዘመን የሰላም፣ የጤና፣ የደስታ፣ የፍቅር፣ የአንድነትና የብልፅግና እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።

ማህበራዊ
የመስቀል በዓል ሀይማኖታዊ ፣ታሪካዊና ባህላዊ እሴትን በጠበቀ መልኩ ይከበራል
Sep 24, 2026 101
ጎንደር፤ መስከረም 14 /2019 (ኢዜአ)፡-የመስቀል በዓል ሃይማኖታዊ፣ታሪካዊና ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ የህዝብን አንድነትና ሰላም በሚያረጋግጥ መልኩ እንደሚከበር የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ገለፁ። የመስቀል በዓል አከባበርን አስመልክቶ ከጎንደር ከተማ ወጣቶች ጋር የውይይት መድረክ ተካሒዷል። የከተማዋ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ቻላቸው ዳኘው በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ የመስቀል በዓል የጎንደር ከተማ ታሪካዊና ባህላዊ እሴት፣ የህዝቦቿ አንድነትና የማንነት ማሳያ ነው። የበዓሉ መከበር ከመላው ኢትዮጵያና ከውጭ ሀገራት የሚመጡ እንግዶችንና ጎብኚዎችን በመቀበል የከተማዋን መልካም ገጽታ ለማስተዋወቅ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክትም ተናግረዋል። በዓሉ ይበልጥ አምሮና ደምቆ በሰላማዊ መንገድ እንዲከበር የከተማው ህዝብ፣ በተለይም ወጣቱ በባለቤትነት ስሜት እንዲሳተፍ አሳስበዋል። የከተማው ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ አለልኝ ዓለም በበኩላቸው፤ የመስቀል በዓል ሃይማኖታዊና ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ በሰላም እንዲከበር ወጣቶች የላቀ ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል። በመሆኑም ከዋዜማው ጀምሮ በሚካሔደው የደመራ በዓለልም ሆነ በመስቀል እለት ተቀጣጣይ ቁሶችን ይዞ መንቀሳቀስ በፍፁም የተከለከለ መሆኑን አሳስበዋል። የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ስልጣናት አባ ዮሴፍ ደስታ፤ በዓሉ ሲከበር ፍፁም ሃይማኖታዊና መንፈሳዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ ሊሆን እንደሚገባ ገልጸዋል። መስቀል የፍቅርና የሠላም መገለጫ በመሆኑ ከሃይማኖት ውጭ የሆኑ የተሳሳቱ ተግባራት እንዳይታዩ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ነው ያሳሰቡት። ክርስቶስ ጥልና ጥላቻን የገደለበት የተቀደሰ በዓል በመሆኑ በዓሉ በባህላዊ አልባሳት በመድመቅና መንፈሳዊ መዝሙሮችን በመዘመር እንደሚከበርም ነው የተናገሩት። በዓሉ የሃይማኖታዊ ትውፊቱን ጠብቆ እንዲከበር ወጣቱ የበኩሉን ሚና ለመወጣት ተዘጋጅቷል ያለው ደግሞ ከውይይቱ ተሳታፊዎች መካከል የሆነው ወጣት ሰለሞን አስፋው ነው።
የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓላት ሃይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶቻቸውን ጠብቀው በድምቀት እንዲከበሩ የተቀናጀ ዝግጅት ተደርጓል
Sep 24, 2026 89
አዲስ አበባ፤ መስከረም 14/2019 (ኢዜአ):-የ2019 ዓ.ም የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓላት ሃይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶቻቸውን ጠብቀው በድምቀት እንዲከበሩ የተቀናጀ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ገለፀ። ቢሮው በዓላቱን በድምቀት እንዲከበሩ የተደረገ ቅድመ ዝግጅትን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ምክትል ቢሮ ሃላፊ ፍስሀ ጥበቡ በመግለጫቸው እንዳሉት፥ የዕድገትና የልማት ጉዞ ዘላቂ የሚሆነው አስተማማኝ ሰላምና ማህበራዊ መተሳሰብ ሲኖር ነው። በዓላቱ ሃይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶቻቸውን ጠብቀው በድምቀት እንዲከበሩ ከፀጥታ አካላት፣ ከሃይማኖትና ባህል ተቋማት እንዲሁም ከኅብረተሰቡ ጋር የተቀናጀ ሥራ መከናወኑን ጠቁመዋል። የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት ከሃይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶቻቸው ባሻገር፣ በማህበራዊ ትስስር፣ በሰላም ግንባታ እና በህዝቦች አብሮነት ላይ ባላቸው የጎላ አስተዋጽኦ በዩኔስኮ በማይዳሰስ የዓለም ቅርስነት የተመዘገቡ መሆናቸው አመልክተዋል። በዚህም በዓላቱ በድምቀት መከበራቸው የባህል እሴቶችን ከማስቀጠል ባለፈ ለሀገራዊ እድገት፣ ለቱሪዝም፣ ለንግድና ለማህበራዊ ካፒታል መጠናከር አወንታዊ እድልን እንደሚፈጥር ገልፀዋል። ስለሆነም በዓላቱ ሲከበሩ አብሮነትን፣ መቻቻልንና የመከባበር ባህልን በሚያጠናክር መልኩ ሊሆን ይገባል ነው ያሉት። የፀጥታ መዋቅሩ የህዝብን ደህንነት ከመጠበቅ በተጨማሪ የትራፊክ ፍሰትን የማስተካከል፣ መጨናነቅን የመቆጣጠር እና ለአደጋ ጊዜ ምላሽ የመስጠት ዝግጅቱን ማጠናቀቁንም አስታውቀዋል። ቢሮው ከሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት፣ ከሃይማኖት ተቋማት፣ ከአባ ገዳዎች፣ ከአደስንቄዎች እንዲሁም ከህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በመተባበር ሰፊ የቅድመ ዝግጅት እና የንቅናቄ ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱን አስታውቋል። የፀጥታ መዋቅሩ የበዓላቱን ህዝባዊ ባህሪ፣ የህዝብ ብዛትና የሚጠበቁ እንቅስቃሴዎችን ታሳቢ ያደረገ ዝግጅት ማድረጉን ገልፀው፤ የከተማዋ ነዋሪዎችና የበዓላቱ ታዳሚዎች የፀጥታ አካላትን መመሪያዎች እንዲከተሉም መልዕክት አስተላልፈዋል። መገናኛ ብዙሃንም በበዓላቱ ወቅት ትክክለኛ፣ ሚዛናዊና የተረጋገጡ መረጃዎችን ለህዝቡ በማድረስ እንዲሁም የሰላምና የመቻቻል መልዕክቶችን በማስተጋባት ሙያዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል። የከተማዋ ነዋሪዎችና የበዓላቱ ታዳሚዎች ከፀጥታ አካላት ጋር የተለመደ ቅንጅቱን በማሳደግ ህግና ስርዓትን በማክበር እንዲሁም አጠራጣሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ ፈጣን ጥቆማ በመስጠት ሰላማዊነታቸውን እንዲያግዙ ጥሪ ቀርቧል። በመጨረሻም ህብረተሰቡ በበዓላቱ አከባበር ማንኛውንም አጠራጣሪ ሁኔታዎች ወይም የፀጥታ ስጋቶች ሲያጋጥሙ በነፃ የስልክ መስመር 8882 በመደወል እንዲያሳውቅ ቢሮው ጥሪ አስተላልፏል።
ሁሉም ቀና ቢያስብ፣ ሰው ለሰው ቢፋቀር፣ ሁሉም ቢተባበር የት እንደርስ ነበር!
Sep 24, 2026 120
ለዓመታት ነዋሪዎቻችን የጎርፍ እና የእሳት አደጋ ደጋግሞ እየጎበኛቸው በከፍተኛ ሰቀቀን፣ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይኖሩ ነበር። ዛሬ ግን የዜጎቻችንን ክብር ወደ ጠበቀ ውብ የመኖሪያ ቤትና ስፍራ ተሸጋግረው በደስታ ሲኖሩ ማየት ወደር የሌለው ደስታ ይሰጣል። ግን ዋናው ጥያቄ በሀገራችን ዋና ከተማ ውስጥ እንዴት ብዙ ዜጎቻችን እንደዛ አይነት አስቸጋሪ አኗኗር ውስጥ ለዓመታት ኖሩ? ዛሬስ ሁሉም በዚህ ፍጥነት እየተለወጠ ያለው እንዴት ነው? የሚለው ነው፡፡ መልሱ ፡- ይህን ስራ እውን ያደረግነው ብዙ አካላትን በማስተባበርና በመደመር ነው። ከያለበት ያለውን እውቀት፣ ሀብትና ጉልበት ሳንሰስት ደምረናል። የተወሰኑት በፋይናንስ ሲደግፉን፣ ሌሎቹ ደግሞ በእውቀታቸው፣ በጉልበታቸው፣ በዲዛይን እና በግንባታ ስራው ላይ በንቃት በበጎ ፍቃድ ተሳትፈዋል። ነዋሪዎቻችንም ለተሻለ ልማት የለውጥን ተስፋ ሰንቀው ትልቅ ትብብር አድርገዋል። ይህ ሁሉ ጥረት አንድ ላይ ተደምሮ ትልቅ አቅም በመሆን ይህን የመሰለ የመኖሪያ መንደር እና አካባቢን ፈጠረ። ቅጠል ተራም ታሪኩ ተቀየረ። ውድ ወገኖቼ፤ አንድ ላይ ተደምሮ ይህንን አዲስ ሰፈር የፈጠረው መሬት፣ ሰዉም፣ ገንዘቡም፣ እውቀቱም የእኛው ነው። ትርጉሙ አንድ ቦታ ላይ ንፁህ የመኖሪያ ስፍራ ከማግኘት እጅግ የላቀ ነው። ይልቁንም ለጋራ ራእይ እየተባበርን፣ በቅንነት፣ በትጋት እና እውነተኛ አገልጋይነት አብረን ስንሰራ ብዙ ሀብቶቻችን ተደምረው የሁላችንንም የጋራ ተጠቃሚነት እንደሚያረጋግጡ፣ የዜግነትን ክብር የሚያልቁ ፣ አዳዲስ እድል እና ሀብት ይፈጥራሉ። ስለዚህ በማንኛውም ነገር በጋራ እንቁም፤ ትብብራችንንም ይበልጥ እናጠናክር። ለበለጠ ሀገራዊ ስኬት በመተማመን አብረን እንትጋ!
የአዲስ አበባ ፈጣን ለውጥ ለአደባባይ በዓላት ድምቀት እና ለቱሪዝም ዕድገት ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል
Sep 24, 2026 238
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 14/2019 (ኢዜአ):-በአዲስ አበባ ከተማ የተገነቡ የኮሪደርና ሌሎች ዘመናዊ መሰረተ ልማቶች እንደ መስቀል፣ ኢሬቻ እና የዒድ አልፈጥር ሶላት ያሉ የአደባባይ በዓላትን በድምቀት ለማክበር እና ለቱሪዝም ዕድገት ምቹ ሁኔታ መፍጠራቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች ገለጹ። አዲስ አበባ ከተማ በኮሪደር ፣ በወንዝ ዳርቻዎች ፣ በዘመናዊ መናፈሻዎች፣ በስፖርት ማዘወተሪያ ስፍራዎች እና በሌሎችም ሁለገብ ስራዎች እጅግ ፈጣን እና አስደናቂ ለውጥ በማስመዝገብ ላይ ትገኛለች። እነዚህ ተጨባጭ የልማት ስራዎች መዲናችንን በአህጉራዊ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍ ከማድረጉም በላይ፣ የሀገራችንን ገጽታ በእጅጉ ቀይረውታል። ከተማዋ አሁን ላይ የያዘችው ማራኪ ገጽታና ዘመናዊ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ በአደባባይ ለሚከበሩ የተለያዩ ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ ክብረ በዓላት ልዩ ድምቀት አጎናጽፈዋል። ይህም ከሀገር ውስጥም ሆነ ከውጭ ሀገር የሚመጡ ቱሪስቶች ፍሰት እንዲጨምር በማድረግ ረገድ ትልቅ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። አስተያየታቸውን ለኢዜአ ከሰጡት የመዲናዋ ነዋሪዎች መካከል አቶ ነመራ በርሲሳ፤ ዘንድሮ በመዲናዋ የሚከበሩ የአደባባይ በዓላት በርካታ መሠረተ ልማቶች በተገነቡበት ወቅት መከበራቸው ልዩ እንደሚያደርጋቸው ገልጸዋል። እነዚህ የተገነቡ መሰረተ ልማቶች በዓላቱን በድምቀት ለማክበር ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥሩ ጠቁመው በእነዚህ ወቅቶች ለመሠረተ ልማቶቹ ደህንነት ትኩረት በመስጠት መጠበቅና መንከባከብ እንደሚገባም ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ከተማ የተከናወኑት እና እየተከናወኑ የሚገኙት የልማት ስራዎች ከአካባቢ ጥበቃ እና ከፅዳት አንጻር እጅግ የተሻሻሉና ለማህበረሰቡ ምቹ ሁኔታን የፈጠሩ መሆናቸውን ያብራሩት ደግሞ ወይዘሮ ወገኔ ኃይሌ ናቸው። ኮሪደርን ጨምሮ በመዲናዋ የተገነቡት መሰረተ ልማቶች በዓላቱን ለመታደምም ሆነ ለጉብኝት ወደ መዲናዋ የሚመጡ ጎብኚዎች በሚመለከቱት እና በሚያገኙት ጥሩ መስተናግዶ ተደስተው እንደሚመለሱ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። ሌላኛው አስተያየት ሰጪ ፍቅሩ እንዳለው፤ በበኩሉ በአዲስ አበባ የተሰሩ የልማት ሥራዎች ከተማዋ የአፍሪካ መዲና መሆኗን በተጨባጭ የሚያስመሰክሩ ናቸው ብለዋል። ይህም በዓላቱን የሚታደመው ህዝብ እንዲሁም የሀገር ውስጥና የውጭ ጎብኚዎች እንደ ልባቸው ተዝናንተውና ተደስተው የሚመለሱባት ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን የሚያሳይ እንደሆነም ተናግረዋል። አቶ መስፍን ገዛኸኝ በበኩላቸው፤ በአዲስ አበባ ከተማ የበዓላትና የቱሪስት ፍሰቱን በሚመጥን መልኩ የተገነቡ መሰረተ ልማቶች በዓላቱን በጥሩ መንፈስ ለማክበር የሚያስችሉ መሆናቸውን ተናግረዋል። እነዚህ የተገነቡ አዳዲስ የልማት ስራዎች የሀገሪቱ መልካም ገጽታ በላቀ ደረጃ ጎልቶ እንዲታይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱም ጠቁመዋል። አቶ ፀሃይ መላኩ የተባሉ የከተማዋ ነዋሪ በበኩላቸው፤ ቀደም ሲል አዲስ አበባ የነበራት የፅዳትና የውበት ሁኔታ ዝቅተኛ እንደነበር አስታውሰው በዓላትን ምቹ እና ደማቅ በሆነ መልኩ ለማክበር አስቸጋሪ ነበር ይላሉ። በአሁኑ ወቅት ግን በከተማዋ በተከናወኑ የኮሪደር እና ሌሎች የመሰረተ ልማት ግንባታዎች አዲስ አበባ እጅግ ውብ፣ ፅዱና ማራኪ በመሆኗ በዓላቱን ደስ በሚል መልኩ ማክበር እንችላለን ነው ያሉት። ሌላኛዋ የመዲናዋ ነዋሪ ወይዘሮ ማሪያ አንጋ በበኩላቸው፣ አዲስ አበባ በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ የለውጥ ጎዳና ላይ ትገኛለች ብለዋል። ይህም ዘንድሮ የሚከበሩ የአደባባይ በዓላትን ከምንጊዜውም በላይ ለየት ባለ እና በደመቀ ሁኔታ ለማክበር እንደሚያስችሉ ተናግረዋል።
ኢኮኖሚ
ከአፍሪካ የግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤቶች አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ የኢነርጂ፣ ሎጅስቲክስና የኢንዱስትሪ አቅሟን እያጠናከረች ነው- አሊኮ ዳንጎቴ
Sep 24, 2026 67
አዲስ አበባ፤ መስከረም 14/2019 (ኢዜአ):- አፍሪካ ውስጥ ካሉት የግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤቶች አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ የኢነርጂ፣ የሎጂስቲክስና የኢንዱስትሪ አቅሟን እያጠናከረች ትገኛለች ሲሉ ናይጄሪያዊው ባለሀብትና የዳንጎቴ ግሩፕ መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ አሊኮ ዳንጎቴ ገለጹ። አሊኮ ዳንጎቴ በጅቡቲ ዳመርጆግ እና በኢትዮጵያ ደወሌ መካከል የሚዘረጋው የ120 ኪሎ ሜትር የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ እና የ400 ሚሊዮን ሊትር ማከማቻ ተርሚናል ግንባታ ፕሮጀክት ይፋ መደረጉን ገልጸዋል። በምሥራቅ አፍሪካ ፈጣን ዕድገት እያስመዘገበች ያለችው ኢትዮጵያ የኢነርጂ፣ የትራንስፖርት፣ የሎጂስቲክስ እና የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ፍላጎቷ ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ የሚገኝና ትልቅ ኢኮኖሚ ያላት ሀገር መሆኗን ዳንጎቴ አመልክተዋል። የዳንጎቴ ግሩፕ በኢትዮጵያ ውስጥ ሰፊ ኢንቨስትመንቶችን እያከናወነ መሆኑን የገለጹት ዳንጎቴ፣ ሀገሪቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ማዳበሪያን ጨምሮ ሌሎች ወሳኝ ምርቶችን ከውጭ በማስገባት ፈንታ ለውጭ ገበያ ማቅረብ እንደምትጀምር ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ከነባረው የከባድ መኪና የትራንስፖርት ጫና በመላቀቅ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ፈጣን እና ቀልጣፋ የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ መስመር አጠቃቀም በመዘርጋት ጠንካራ የኢነርጂ ዋስትናን በዚህ ፕሮጀክት ታረጋግጣለች ብለዋል። ይህ የኢንቨስትመንት ማዕቀፍ ለኢትዮጵያ የሎጂስቲክስ ማነቆዎችን በእጅጉ እንደሚቀንስ፣ የምርት ጥራት ቁጥጥርን እንደሚያሻሽል እና እንደ ኢንዱስትሪ፣ አቪዬሽን፣ ትራንስፖርት፣ ግብርናና ኮንስትራክሽን ያሉ ቁልፍ ዘርፎችን በዘላቂነት እንደሚደግፍ ነው ያብራሩት። ፕሮጀክቱ ሙሉ በሙሉ በአፍሪካዊ ካፒታል እና በወጣት አፍሪካውያን መሐንዲሶች የሚገነባ መሆኑን የገለጹት ዳንጎቴ፣ ይህም አፍሪካ የራሷን የልማት ችግሮች በራሷ አቅም መፍታት እንደምትችል ትልቅ ማሳያ መሆኑን አመልክተዋል። ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ በመልክዐ ምድር፣ በጋራ ራዕይ እና በእጣ ፈንታ የተሳሰሩ መሆናቸውን ጠቅሰው የጅቡቲ ኮሪደር የሁለቱንም ሀገራት የንግድ እና የኢኮኖሚ ልውውጥ በማስተሳሰር ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል። አፍሪካ ከዕምቅ አቅም ባሻገር ወደ ተጨባጭ ምርት ልትሸጋገር እንደሚገባና በሌሎች ጥገኝነት የመሆን ሁኔታ ሊያበቃ ይገባል ብለዋል። በዚህ ረገድም አፍሪካ የኢነርጂ ዋስትናን ማረጋገጥ እና በራሷ አቅም መጠቀም እንዳለባት ተናግረዋል። የአፍሪካ ኤክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ (አፍሪ ኤግዚም ባንክ) እና የአፍሪካ ፋይናንስ ኮርፖሬሽን (ኤ.ኤፍ.ሲ) የመሳሰሉ አህጉራዊ የፋይናንስ ተቋማት ለዚህ ታላቅ ፕሮጀክት እያደረጉት ያለው ድጋፍ የአፍሪካን የገንዘብ አቅም የሚያሳይ ነው ብለዋል። ይህ ታሪካዊ የኢነርጂ መሠረተ ልማት ፕሮጀክት በወቅቱ፣ በጥራት እና በከፍተኛ ዓለም አቀፍ ደረጃዎች ተጠናቆ የሁለቱን አገራት ሕዝቦች እና የምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና የኢኮኖሚ ትስስር ለረጅም ዓመታት እንዲያገለግል ጥሪ ማቅረባቸውን ዳንጎቴ አመልክተዋል።
የተጣራ ነዳጅ ማስተላለፊያ ቱቦ መስመሩ ፓን-አፍሪካዊ ፕሮጀክት ነው - የጅቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦመር ጊሌ
Sep 24, 2026 91
አዲስ አበባ፤ መስከረም 14/2019 (ኢዜአ):- የተጣራ ነዳጅ ማስተላለፊያ የቱቦ መስመር የአፍሪካውያን የትብብር መንፈስ የገለጠ ፓን-አፍሪካዊ ፕሮጀክት መሆኑን የጅቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦመር ጊሌ ገለጹ። በጅቡቲ ዳመርጆግን ከኢትዮጵያ ደወሌ የሚያገናኝ እና ታላቅ ስትራቴጂካዊ ኢንቨስትመንት የሆነውን አዲስ የተጣራ ነዳጅ ማስተላለፊያ ቱቦ መስመር ዝርጋታ ዛሬ ይፋ ሆኗል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በፕሮጀክቱ መሠረተ ድንጋይ የማስቀመጥ ሥነ-ሥርዓት ላይ ታድመዋል። የጅቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦመር ጊሌ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ መገኘት በኢትዮጵያ እና በጅቡቲ መካከል ያለውን ጥልቅ እምነት እና የጋራ ጽኑ አቋም የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል። ይህ ኢንቨስትመንት የአፍሪካ መንግሥታትና የግሉ ዘርፍ ሲተባበሩ አፍሪካ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ መሆን እንደምትችል የሚያሳይ ፓን-አፍሪካዊ ፕሮጀክት መሆኑን አመልክተዋል። ፕሮጀክቱ ከ375 ሺህ ኪዩቢክ ሜትር በላይ የሚሆን የነዳጅ ማከማቻ ተርሚናል እንደሚኖረው እና በዓመት 5 ሚሊዮን ቶን ምርቶችን በማስተናገድ የትራፊክ ማነቆዎችን እንደሚፈታ ተናግረዋል። አፍሪካ ጥሬ ዕቃዎችን እየላከች የተጣራ ነዳጅ በውድ ዋጋ የመግዛት አዙሪት እና ጥገኝነት አሁን ሊጠናቀቅ እንደሚገባና እውነተኛ ነፃነት የሚገኘው በኢነርጂ ራስን በመቻል መሆኑን ነው የገለጹት። እርስ በእርስ ያልተሳሰሩ መሰረተ ልማቶች ድንበር ተሻጋሪ አይደሉም ያሉት ፕሬዝዳንቱ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና የደነገገውን ህጋዊ ማዕቀፍ በተጨባጭ መሠረተ ልማት መደገፍ እንደሚገባ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ እምቅ አቅም እና የጅቡቲ ወደቦች ሲቀናጅ የላቀ ስኬት ማስመዝገብ እንደሚቻል አመልክተዋል። ፕሮጀክቱ በአፍሪካዊ የካፒታል ወጪ የተገነባ መሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ ቴክኖሎጂውንና እውቀቱን ይዘው የሚሠሩት አፍሪካዊ መሐንዲሶችና ወጣቶች መሆናቸው ትልቅ እምርታ መሆኑን ነው የተናገሩት። ጅቡቲ መሠረተ ልማቶቿን በማዘመን፣ የኢኮኖሚ አማራጮቿን በማስፋት እና ለቀጣናዊ መረጋጋት አስተማማኝ አጋር ሆና እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል። ፕሬዝዳንቱ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ለአሊኮ ዳንጎቴ፣ ለጅቡቲ ወደቦች እና ነፃ የንግድ ቀጣናዎች ባለሥልጣን እንዲሁም ለፕሮጀክቱ ድጋፍ ላደረጉ ሌሎች አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰላም፣ መረጋጋት እና ኢኮኖሚያዊ ውህደት እንዲሳለጥ በቁርጠኝነት እየሰራች ነው-ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ
Sep 24, 2026 89
አዲስ አበባ፤ መስከረም 14/2019 (ኢዜአ):-ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰላምና መረጋጋት እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ውህደቶች እንዲሳለጡ በቁርጠኝነት እየሰራች መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ገለጹ። ፕሬዝዳንት ታዬ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 81ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት በዓለም ደረጃ ፍትሃዊ ሥርዓት ማንበር ሁሉንም ተጠቃሚ ለማድረግ ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል። ዘላቂ ሠላም የሚረጋገጠው በሉዓላዊ እኩልነት ላይ በተመሰረተ ትብብር ብቻ ነው ያሉት ፕሬዝዳንት ታዬ፣ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በጸጥታ ጉዳዮች ላይ በጋራ መሥራት ወሳኝ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል። በጸጥታ ጉዳዮች ላይ በሚጠበቀው ደረጃ በጋራ አለመሰራቱ የኃይል ፖለቲካ እያየለ መምጣት ጋር ተዳምሮ የዓለም አቀፉን ሥርዓት ተጽዕኖ ውስጥ እየከተተው መሆኑን አስገንዝብዋል። ለዚህ ችግር ሁነኛ መፍትሄ የባለብዙ ወገን ትብብር መሆኑን አንስተው ይህን ማድረግ ሲቻል ከግጭት ነጻ ዓለምን ማጽናት ያስችላል ሲሉ ተናግረዋል። ከ1 ነጥብ 6 ቢሊዮን በላይ ሕዝብ የሚኖርባትን አፍሪካ ትርጉም ያለው ውክልና መከልከል አግባብነት የሌለው መሆኑንም አጽንዖት ሰጥተዋል። ለዚህም በተለይም የጸጥታው ምክር ቤት ማሻሻያ እንዲደርግ ጥሪ አቅርበዋል። የሰው ሰራሽ አስተውሎት፣የአየር ንብረት ለውጥና በዓለም አቀፍ ደረጃ እየታየ ያለው የኢኮኖሚ አለመጣጣም ትልቅ ፈተና መደቀኑን ገልጸዋል። በዚህ ረገድ የሚፈልቁ ቴክኖሎጂዎች በማደግ ላይ ያሉ ሀገራትን ጨምሮ ሁሉንም የዓለም ሕዝብን ተጠቃሚ ማድረጋቸውን ማረጋገጥ ወሳኝ ጉዳይ ነው ብለዋል። በምሥራቅ አፍሪካ ሠላምና ቀጣናዊ የልማት ትብብር እውን እንዲሆን ኢትዮጵያ በቁርጠኝነት እንደምትሰራ ያረጋገጡት ፕሬዝዳንት ታዬ፤ በሱዳን ለተከሰተው ግጭት በሱዳናውያን ባለቤትነት የሚመራ መፍትሄ እንዲበጅለትም ጥሪ አቅርበዋል። የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለቀጣናዊ ዕድገት አስተዋጽኦ የሚያበረክት ታላቅ የፓን-አፍሪካ የኃይል ፕሮጀክት መሆኑንም አብራርተዋል። የኢትዮጵያን ኢኮኖሚያ ሽግግግር ለማስቀጠል አስተማማኝ የባህር በር ማግኘት ቁልፍ ጉዳይ ነው ያሉት ፕሬዝዳንት ታዬ፤ ኢትዮጵያ ከባህር በር ጋር የተያያዙ ዕድሎችን ለመጠቀም ሁሉንም ዲፕሎማሲያዊ አማራጮች እየተከተለች እንደሚገኝም አስረድተዋል። ኢትዮጵያ በምግብ ዋስትና፣ በታዳሽ የኃይል ምንጭ፣ በአረንጓዴ አሻራ እና አካባቢ ጥበቃ ሥራዎች ያስመዘገበቻቸውን አመርቂ ውጤቶችንም አንስተዋል። የዲጂታል ልማትን በማሳለጥ በኩል በርካታ ውጤታማ ተግባራት የተከናወኑ ሲሆን በ5 ሚሊዮን ኮደሮች ፕሮግራም የተመዘገበውን ስኬት በአብነት ጠቅሰዋል።
የነዳጅ ማስተላለፊያ ቱቦው የሎጂስቲክስ ወጪና ጊዜን ትርጉም ባለው መልኩ ይቀንሳል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
Sep 24, 2026 101
አዲስ አበባ፤ መስከረም 14/2019 (ኢዜአ):- በኢትዮጵያና ጅቡቲ መካከል የሚዘረጋው አዲስ የተጣራ ነዳጅ ማስተላለፊያ ቱቦ የሎጂስቲክስ ወጪና ጊዜን ትርጉም ባለው መልኩ የሚቀንስ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጅቡቲ ዳመርጆግ ከኢትዮጵያ ደወሌን የሚያገናኘውን የነዳጅ ምርቶች ማስተላለፊያ ቱቦ ግንባታ መሠረተ ድንጋይ የማስቀመጥ ሥነ-ሥርዓት ላይ ታድመዋል። በጅቡቲ ዳመርጆግን ከኢትዮጵያ ደወሌ የሚያገናኝ እና ታላቅ ስትራቴጂካዊ ኢንቨስትመንት የሆነውን አዲስ የተጣራ ነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ መስመር ዝርጋታ ዛሬ ይፋ ሆኗል። መልክዓ ምድር ለሁለቱ ሀገራት የሰጠው የጋራ ኮሪደር ጅቡቲን ከሰፊ ገበያ፣ ኢትዮጵያን ደግሞ ወደ ዓለም አቀፍ ንግድ የሚያገናኝ ድልድይ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል። የትራንስፖርት መዘግየቶች፣ ውስን የማጠራቀሚያ አቅሞች እና ውጤታማ ያልሆኑ የመጓጓዣ ዘዴዎች ለንግዱ ማህበረሰብ ከፍተኛ ወጪ ማስከተላቸውን አውስተዋል። ዛሬ አዲስ አበባ የሚገባ እያንዳንዱ ሊትር ነዳጅ በመኪና አምስት ቀናትን አሳልፎ እንደሚመጣ ጠቅሰው አዲሱ የቧንቧ መስመር ይህንን ጉዞ ወደ አንድ ቀን ገደማ ዝቅ እንደሚያደርገው አመልክተዋል። ጅቡቲ፣ ኢትዮጵያ እና የዳንጎቴ ግሩፕ በጋራ በመሆን ከዳመርጆግ እስከ ደወሌ 120 ኪሎ ሜትር የሚረዝም የነዳጅ ቧንቧ መስመር እንደሚዘረጉም ነው የጠቆሙት። በሁለቱም ወገኖች ከአንድ ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር በላይ የሚሆን የጋራ ማከማቻ ቦታ የሚዘጋጅ ሲሆን፣ ይህም ዓለም አቀፍ ቀውሶች ሲያጋጥሙ የኢነርጂ አቅርቦቱ እንዳይስተጓጎል ዋስትና ይሰጣል ብለዋል። መሠረተ ልማቱ ለኢትዮጵያ ኢንዱስትሪዎች እና ግብርና ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለጅቡቲ ደግሞ የትራንዚት መጠንን ከፍ በማድረግ እንደ ቀጠናዊ የሎጂስቲክስ ማዕከል ያላትን ቦታ እንደሚያጠናክር አብራርተዋል። ወደቦች፣ አውራ ጎዳናዎች፣ የባቡር መስመሮች፣ ሞጆ የሎጂስቲክስ ማዕከል እና የቧንቧ መስመሩ እንደ አንድ የተሳሰረ ሥርዓት መሥራት እንዳለባቸው ጠቁመዋል። አሊኮ ዳንጎቴ፣ የአፍሪካ ድርጅቶች ከታላቅ ራዕይ ጋር የሚመጥን ግብ አሳክተው በዓለም አቀፍ ደረጃ መወዳደር እንደሚችሉ ማስመስከር መቻላቸውን ጠቅሰዋል። ይህ ፕሮጀክት በአፍሪካዊ ካፒታል የተገነባ ለአፍሪካዊ ዕድገት የሚውል አፍሪካዊ መሠረተ ልማት ነው ብለዋል። ሥራውን ወደ መሬት አውርዶ ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባም አስገንዝበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዚህ ኢንቨስትመንት ፕሮጀክት እውን መሆን አስተዋፅኦ ላደረጉ አካላት ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
"አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የመጨረሻ ፈጠራ ወይስ የፈጠራ መጨረሻ?" በሚል ርዕስ በሰለሞን ሙሉጌታ የተጻፈ መጽሐፍ ለንባብ በቃ
Sep 23, 2026 201
አዲስ አበባ፤ መስከረም 13/2019 (ኢዜአ):- "አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የመጨረሻ ፈጠራ ወይስ የፈጠራ መጨረሻ?" በሚል ርዕስ በሰለሞን ሙሉጌታ የተጻፈ መጽሐፍ ለንባብ በቃ። "አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የመጨረሻ ፈጠራ ወይስ የፈጠራ መጨረሻ?" በሚል ርዕስ የተዘጋጀው መፅሀፍ ሲሆን፤ የመንግሥት የስራ ሃላፊዎች፣ የጸሀፊው ቤተሰቦችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በሳይንስ ሙዚየም ተመርቋል። የመጽሐፉ ጸሀፊ ሰለሞን "ቴክ ቶክ ዊዝ ሰለሞን" በሚል ርዕስ በሚያዘጋጀው ፕሮግራም የቴክኖሎጂ ዜናዎችን፣ አዳዲስ የፈጠራ ስራዎችን እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ ስኬታማ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎችና ሳይንቲስቶች በማስተዋወቅ ትልቅ ሚና ተጫውቷል። በአዲስ አበባ ባቋቋመው የቴክኖሎጂ የፈጠራ ማዕከልም ወጣት የፈጠራ ሃሳብ ያላቸው ስታርታፖችን በመደገፍ በስራ ዕድል ፈጠራ እና ዲጂታል ሽግግርን ማፋጠን እንዲሁም ለቴክኖሎጂው ዕድገት የበኩሉን ሚና እየተወጣም ይገኛል። ሰለሞን ሙሉጌታ ያስመረቀው መጽሐፍ በኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ እና ዲጂታል ሽግግር ውስጥ ትልቅ አሻራ የሚያሳርፍ መሆኑ ተጠቁማል። የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢኒስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ታዬ ግርማ (ዶ/ር) በቪዲዮ ባስተላለፉት መልዕክት፤ መጽሐፉ ሰው ሰራሽ አስተውሎትን በቀላል ቋንቋ የሚያስረዳ በመሆኑ ግንዛቤን ለማስፋት መሰረት ይጥላል ብለዋል። የሰው ሰራሽ አስተውሎትን ጥቅምና ስጋቶች በአግባቡ እንደሚተነትን ጠቁመው፤ በዘርፉ ውጤታማ ሆኖ ለመዝለቅ አመላካች ሃሳቦች የተካተቱበት በመሆኑ ጠቀሜታው የጎላ እንደሆነ ገልጸዋል። ጂኦ ፖለቲካ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘመን ያለውንም ቦታ በተመለከተ ጥልቅ ጽንሰ ሃሳብ የያዘ በመሆኑ ለዘርፉ ዕድገት ጉልህ አበርክቶ እንደሚኖረው ተናግረዋል። የስነ አዕምሮ ሀኪሙ ዶክተር ምህረት ደበበ በበኩላቸው፤ ሰው ሰራሽ አስተውሎት ትምህርት፣ ጤና፣ ፖለቲካ፣ ወታደራዊ መስኮችን ጨምሮ በሁሉም የህይወት መስኮች በሚባል ደረጃ ሚና መጫወት መጀመሩን አንስተዋል። ስለሆነም ከሰው ሰራሽ አስተውሎት መራቅ እንደማይቻል አንስተው፤ ሰው ሰራሽ አስተውሎትን እንዴት ጠቃሚ በሆነ መንገድ ልንጠቀም ይገባል የሚለው ቁልፍ ጉዳይ ነው ብለዋል። መጽሐፉ ለእነዚህ ጉዳዮች በቂ ምላሽ የሚሰጥ በመሆኑ ጠቀሜታው ከፍ ያለ ነው ሲሉም ተናግረዋል። ሰው ሰራሽ አስተውሎትን ከሞራል ጋር ባስተሳሰረ መልኩ የመጠቀምን አስፈላጊነትንም መጽሐፉ እንደሚዳስስ ጨምረው አብራርተዋል። የመጽሐፉ ጸሀፊ ሰለሞን በበኩሉ፤ ሰው ሰራሽ አስተውሎት ለአፍሪካ የህክምና፣ የአየር ንብረት ለውጥን ጨምሮ የህልውና ጥያቄ መፍቻ ቁልፍ እንደሚሆን አብራርቷል። የስራ ዕድል ፈጠራ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘመን በምን መልኩ ሊቃኝ ይገባል? የአፍሪካ ሀገራትም በምን መልኩ ሊያዩት ይገባል? የሚለውንም ጥያቄ በማንሳት መጽሐፉ እንደሚያብራራ ገልጸዋል። በሰው ሰራሽ አስተውሎት ውስጥ የአፍሪካ ዕጣ ፈንታ እንዴት ይሆናል? የሚለው ጉዳይ በመጽሐፉ ውስጥ መካተቱን ጠቁሞ፤ ከዘርፉ የአፍሪካን የተጠቃሚነት ድርሻ ለማሳደግ በቁርጠኝነት መረባረብ እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥቷል ነው ያለው። ጸሀፊው ሰለሞን ሙሉጌታ ከዚህ ቀደም "ግርመተ ሳይቴክ" የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ ማብቃቱ ይታወሳል።
በአስተዳደሩ የተዘረጋው የዲጂታል አሠራር የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት አስችሏል
Sep 22, 2026 178
ድሬደዋ፣ መስከረም 12/2018 (ኢዜአ)፡- በድሬዳዋ አስተዳደር የተዘረጋው የዲጂታል አሠራር የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በፍጥነትና ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ ለመፍታት ማስቻሉ ተገለፀ። በድሬደዋ አስተዳደር የተገልጋዮችን ቅሬታና አቤቱታ ለመፍታት በተዘረጋው የዲጂታል ቴክኖሎጂ አሠራር ላይ የግንዛቤ ማሳደጊያ ሥልጠና ተሰጥቷል። በወቅቱም የአስተዳደሩ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ ሰዓዳ አዋሌ እንደገለጹት፤ በአስተዳደሩ የተዘረጋው የዲጂታል አሠራር የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በፍጥነትና ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ ለመፍታት አስችሏል። ዘመናዊ የዲጂታል አሠራሩ በከንቲባው ጽሕፈት ቤት የቅሬታ አቀራረብና አፈታት ዳይሬክቶሬት ሥር በሚገኙ ተቋማት ተተግብሮ ውጤታማ መሆኑንም አስረድተዋል። በከንቲባው ጽሕፈት ቤት የተገኘውን ውጤት ሕዝብ በብዛት በሚገለገልባቸው የወረዳ ተቋማት ውስጥ ለማስጀመር የዛሬው ሥልጠና መሰጠቱን ገልጸዋል። ሥልጠናው የዲጂታል አሠራሩን በዚህ ሳምንት በሁሉም ወረዳዎች ለማስጀመር ያለመ መሆኑን ጠቅሰው፤ በቀጣይም በገጠር ክላስተሮች እንደሚቀጥልም አስረድተዋል። የዲጂታል አሠራር መተግበሪያውን አስተዳደሩ ከድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመቀናጀት ለተለያዩ ተቋማት እያበለጸገ መሆኑንም ገልጸዋል። በከንቲባ ጽሕፈት ቤት የሕዝብ ቅሬታ፣ አቤቱታና ሥልጠና ቡድን መሪ አቶ አሻግሬ ታደሰ በበኩላቸው፤ በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የበለጸገው ዲጂታል መተግበሪያ የሕዝብን ቅሬታ በፍጥነት ለመፍታት ማገዝ እንደሚያስችል ተናግረዋል። የዲጂታል አሠራሩ በየደረጃው የሚገኘው አመራር የሚቀርቡለትን የትኛውንም ቅሬታዎች ባለበት ቦታ ሆኖ በፍጥነት ለመመለስ የሚያስችል መሆኑንም ገልጸዋል። በሶፍትዌር አተገባበሩ ላይ የተሳተፉት ሰልጣኞች በበኩላቸው፤ ሥልጠናው የዲጂታል አሠራሩን በፍጥነት ወደ ተግባር በማውረድ የተሻለ አገልግሎትን ለነዋሪው ለመስጠት እንደሚያግዛቸውም ጠቁመዋል።
ዩኒቨርሲቲው የሚያካሄደው የምርምርና ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት የአካባቢውን ህብረተሰብ ተጠቃሚ እያደረገ ነው
Sep 21, 2026 349
ሮቤ፤ መስከረም 11/2019 (ኢዜአ)፦ የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የሚያካሄዳቸው የምርምርና ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎቶች የአካባቢውን ህብረተሰብ ተጠቃሚ እያደረጉ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ብርሃነመስቀል ጠና (ዶ/ር) ገለጹ። ዩኒቨርሲቲው የጭብጥ ተኮር የምርምርና ማህበረሰብ ልማት ንድፈ ሀሳቦችን የሚገመግም የአቅም ግንባታ ዐውደ ጥናት እያካሄደ ነው። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ብርሃነመስቀል ጠና (ዶ/ር) እንዳሉት፤ ዩኒቨርሲቲው ከመማር ማስተማር ጎን ለጎን ለማህበረሰቡ ችግሮች መፍትሔ የሚያመላክቱ ምርምሮችን እያካሄደ ይገኛል። በተለይም የዩኒቨርሲቲው የልህቀት ማዕከል የሆኑት የግብርና፣ ጤና፣ ቱሪዝም፣ ብዝሃ-ሕይወትና የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ዘርፎች ዋና ዋና የምርምር ትኩረት መስኮች መሆናቸውን አክለው ገልጸዋል። የዩኒቨርሲቲው ምሁራንም ባለፉት ዓመታት ባካሄዷቸው የምርምርና ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎቶች የበርካታ ዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ እመርታዊ ውጤቶች መገኘታቸውን ገልጸዋል። በተለይም በግብርናው የኩታ-ገጠም አሰራር፣ በካንሰር ህክምናና ህብረተሰቡን ግንዛቤ በማስጨበጥ ረገድ በተከናወኑ ተግባራት ተጨባጭ ለውጦች መመዝገባቸውን በማሳያነት ጠቅሰዋል። ዩኒቨርሲቲው የሚያከናውናቸው የምርምርና ማህበረሰብ ልማት አገልግሎቶች የህዝብን ችግሮች በተሻለ ሁኔታ ለመፍታት እንዲችሉ በዘርፉ ለተሰማሩ ተመራማሪዎችና ገምጋሚዎች የሚሰጠው ቀጣይነት ያለው የአቅም ግንባታ ስልጠናም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ፕሬዝዳንቱ አውስተዋል። የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ፣ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት በዛብህ ወንድሙ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የአቅም ግንባታ ዐውደ ጥናቱ በምርምር ዘርፍ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን በመለየት የተሻለ ተፅዕኖና ውጤት የሚያመጣ ምርምር ለማከናወን እንደሚረዳ ገልጸዋል። በተለይም ተመራማሪዎቹ በስልጠናው ቆይታቸው በጭብጥ ተኮር የምርምር ንድፎች ምንነትና አዘገጃጀት፣ በማህበረሰብ ተኮር ልማት ስራዎች ንድፈ-ሀሳብ አዘገጃጀትና በዓለም አቀፋዊ ነባራዊ ሁኔታዎች ላይ በቂ ግንዛቤ እንደሚያገኙ ተናግረዋል። የዩኒቨርሲቲው ምሁራን በ2018 የበጀት ዓመት በተለያዩ የትኩረት መስኮች ላይ ያተኮሩ ከ24 በላይ ምርምሮችን ማካሄዳቸውን በማስታወስ፤ በአዲሱ የበጀት ዓመት ደግሞ 96 የምርምር ንድፈ-ሀሳቦች ለግምገማ መቅረባቸውን አመልክተዋል። ዩኒቨርሲቲው የሚያካሄዳቸው የምርምርና ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎቶች የአካባቢውን ህብረተሰብ ችግሮች በመቅረፍ ተጠቃሚነቱን ይበልጥ ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አመልክተዋል።
በክልሉ ተቋማት ላይ ተግባራዊ የተደረገው የመንግሥት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም የተገልጋይን እርካታ እያረጋገጠ ነው
Sep 19, 2026 447
ባህር ዳር፤ መስከረም 9/2019 (ኢዜአ):- በአማራ ክልል ተቋማት ላይ ተግባራዊ የተደረገው የመንግሥት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም የተገልጋይን እርካታ እያረጋገጠ መሆኑ ተገለፀ። በክልሉ በመጀመሪያው ዙር ወደ መንግሥት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም የገቡ ስምንት ተቋማት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ተካሄዷል። በአማራ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተሞች ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ሪፎርም አብይ ኮሚቴ ሰብሳቢ አሕመዲን መሐመድ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ሪፎርሙ የመንግሥት አገልግሎትና አስተዳደር የተገልጋይን እርካታ እያረጋገጠ መምጣቱን ገልጸዋል። ይህም የመንግሥትን ተቋማት ነፃና ገለልተኛ እንዲሆኑ ከማድረግ ባሻገር የሠራተኛውን ችሎታና ብቃት ለማረጋገጥ የሚያስችል ነው ብለዋል። በተቋማት በቴክኖሎጂ የታገዘ የዲጂታል አሠራርን እውን በማድረግ ፈጠራና ፍጥነት የታከለበት አገልግሎትን በፍትሐዊነት ተደራሽ መሆኑ ውጤት እያስገኘ ነው ያሉት። በተለይም የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ፈጣንና ዘመናዊ አገልግሎት ተደራሽ ማድረግ ማስቻሉን ጠቅሰው፤ በዚህም በስድስት ማዕከላት በተሰጠ አገልግሎት የተገልጋይ እርካታን 99 ነጥብ 7 በመቶ ማድረስ እንደተቻለም ገልጸዋል። የክልሉ ሲቪል ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ባንችአምላክ ገብረማርያም በበኩላቸው፤ ሪፎርሙ የመንግሥትን አገልግሎትና አስተዳደር በውጤታማነት ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል ነው ብለዋል። በተለይም ከዚህ ቀደም በተቋማት ይስተዋሉ የነበሩ የሕዝብ አገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን በዘላቂነት በመፍታት ወጪ ቆጣቢ በሆነ አግባብ ውጤታማ ተግባራትን ማከናወን ማስቻሉን ጠቁመዋል። ሪፎርሙ አሠራሮችን ዲጂታል በማድረግ ሥራን የማቅለልና የማዘመን ብሎም ብቁና ተወዳዳሪ የሰው ኃይል መገንባትን ዓላማ ያደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል። እስካሁን በተደረገ ጥረት ተቋማትን ለአሠራር ምቹ ከማድረግ ባለፈ የሕግ ማዕቀፎችን፣ ስትራቴጂዎችን፣ ደንቦችንና መመሪያዎችን በማዘጋጀት ወደ ሥራ መገባቱን ገልጸዋል። በክልል ደረጃ 69 ተቋማት 361 አገልግሎቶቻቸውን ዲጂታላይዝድ በማድረግ ከ183 ሺህ 300 በላይ ደንበኞች ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኙ ተደርጓል ብለዋል። በሪፎርሙ የግዥ፣ የንብረት አስተዳደርና የክፍያ ሥርዓትን ዲጂታላይዝድ በማድረግ ውጤታማ ሥራ መከናወኑን ጠቅሰው፤ የገቢ ሥርዓቱን ከማኑዋል ወደ ዲጂታል በማሳደግ ገቢ የመሰብሰብ አቅም ከፍ እንዲል ማድረጉን አብራርተዋል። ትምህርት፣ ጤና፣ ግብርና፣ ፕላንና ልማት እና ሥራና ክህሎት ቢሮዎች ሪፎርሙን በመተግበር የተሻለ ሥራ ማከናወናቸውን ተናግረዋል። የተገኙ ውጤቶችን በማጠናከርም በየደረጃው የተሻለ ግንዛቤ ተፈጥሮ ወደ ተሟላ አፈጻጸም ለመግባት በቅንጅት መረባረብ እንደሚገባም አሳስበዋል። በመድረኩ በሪፎርሙ ወደ ተግባር የገቡ ተቋማት አመራሮች የተሳተፉ ሲሆን የየተቋማቱ የሪፎርም አፈጻጸም ግምገማ ተካሄዷል።
ስፖርት
የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ተጋጣሚዎቹን አውቋል
Sep 23, 2026 188
አዲስ አበባ፤ መስከረም 13/2018 (ኢዜአ)፦ የ17ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ የዕጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ዛሬ በታንዛንያ ዳሬ ሰላም ተካሄዷል። በማጣሪያው ላይ የምትሳተፈው ኢትዮጵያ በምድብ ሁለት ከዩጋንዳ እና ብሩንዲ ጋር ተደልድላለች። አዘጋጇ ሩዋንዳ፣ ሱዳን፣ ሶማሊያ እና ደቡብ ሱዳን በምድብ አንድ የሚገኙ ሀገራት ናቸው። ታንዛንያ፣ ጅቡቲ እና ኬንያ በምድብ ሶስት ተደልድለዋል። የማጣሪያ ውድድሩ ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም በሩዋንዳ ይካሄዳል። በውድድሩ ከአንድ እስከ ሶስት የሚወጡ ሀገራት ሴካፋ ዞንን ወክለው በአፍሪካ ዋንጫ ይሳተፋሉ። 17ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ እ.አ.አ በ2027 በሞሮኮ አስተናጋጅነት ይካሄዳል። በውድድሩ ላይ 16 ሀገራት ይሳተፋሉ።
ሲዳማ ቡና እና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዙር የሜዳ ጨዋታቸውን በድሬዳዋ ስታዲየም ያደርጋሉ
Sep 23, 2026 156
አዲስ አበባ፤ መስከረም 13/2019 (ኢዜአ):- በአህጉራዊ የክለቦች ውድድሮች ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት ሲዳማ ቡና እና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዙር ማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን የሚያደርጉበት ቀን እና ቦታ ይፋ ሆኗል። በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ቅድመ ማጣሪያ የቻዱን ኤጌሎን በድምር ውጤት 3ለ0 በማሸነፍ ወደ ሁለተኛው ዙር ያለፈው ሲዳማ ቡና፤ ከሱዳኑ አል ሂላል ኦምዱርማን ጋር የሚያደርገውን የመጀመሪያ ጨዋታ ጥቅምት 8 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ በድሬዳዋ ስታዲየም ያደርጋል። በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ የሱዳኑን ሂሊል አል ሳህል በመለያ ምት ያሸነፈው ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ፤ የሁለተኛ ዙር ማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታውን ከሊቢያው አል አህሊ ትሪፖሊ ጋር ጥቅምት 6 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ በድሬዳዋ ስታዲየም ያከናውናል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጁባ ደርሷል
Sep 22, 2026 403
አዲስ አበባ፤ መስከረም 12 /2019 (ኢዜአ):- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በ36ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከሱዳን ጋር ለሚያደርገው የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታ ደቡብ ሱዳን ጁባ መግባቱን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ። ዋልያዎቹ መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም ከሱዳን ጋር ይጫወታሉ። በአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ የሚመራው ብሔራዊ ቡድኑ ከሱዳን እና ሴኔጋል ለሚያደርገው የማጣሪያ ጨዋታ ከአንድ ወር በላይ በሀገር ቤት ዝግጅቱን አድርጓል። ኢትዮጵያ ሁለተኛ ጨዋታዋን ከሴኔጋል ጋር መስከረም 19 ቀን 2019 ዓ.ም በባህር ዳር ስታዲየም ታከናውናለች። በምድብ 10 የምትገኘው ኢትዮጵያ በማጣሪያው ከሱዳን፣ ሴኔጋል እና ሞዛምቢክ ጋር ተደልድላለች።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን አቀባበል ተደረገለት
Sep 22, 2026 198
አዲስ አበባ፤ መስከረም 12/2019 (ኢዜአ)፦ በዴንማርክ ኮፐንሃገን በተካሄደው ሁለተኛው የዓለም አትሌቲክስ የጎዳና ሩጫ ሻምፒዮና ላይ የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑክ ቡድን ዛሬ አዲስ አበባ ገብቷል። ልዑኩ ቡድኑ አዲስ አበባ ሲደርስ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን እና የፌዴሬሽኑ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የኮሙኒኬሽን ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ቢኒያም ምሩፅ አቀባበል አድርገውላቸዋል። የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን በኮፐንሃገን የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ከፍ በማድረግ ሀገራችሁን አኩርታችኋል ሲሉ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው አንድ የወርቅ፣ ሁለት የብር እና አንድ የነሐስ በድምሩ አራት ሜዳሊያዎችን በማግኘት ከዓለም ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ሻምፒዮናውን አጠናቃለች።
አካባቢ ጥበቃ
በሐረሪ ክልል ለተፈጥሮ አደጋዎች አፋጣኝ ምላሽ መስጠት የሚያስችል የተሟላ ዝግጅት ተደርጓል
Sep 24, 2026 974
ሀረር፤ መስከረም 14/2019 (ኢዜአ):- ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ ለሚያጋጥሙ አደጋዎች ፈጣን ምላሽ መስጠት የሚያስችል የተሟላ ዝግጅት መደረጉን የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ልማት ቢሮ ሃላፊ ሮዛ ኡመር ገለጹ። በአየር ንብረት መለዋወጥ ሳቢያ በዓለም አቀፍ ደረጃ የኤልኒኖ ክስተት ጋር የተያያዘ ችግር ስለመኖሩ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ሰሞኑን አመላክቷል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ በዘንድሮው የበጋ ወቅት በደቡብና ደቡብ ምሥራቅ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የተሻለ የዝናብ መጠን እንደሚኖር ይጠበቃል ብሏል፡፡ በአንጻሩ በመካከለኛውና በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍሎች አልፎ አልፎ ያልተጠበቀ ዝናብ ሊኖር ይችላል ሲልም አሳውቋል። በመሆኑም ለሚያጋጥሙ ችግሮች ፈጣን ምላሽ በመስጠት ረገድ በሐረሪ ክልል ያለውን ዝግጁነት በተመለከተ ኢዜአ የክልሉን ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አነጋግሯል። የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ልማት ቢሮ ሃላፊ ሮዛ ኡመር፤ በማብራሪያቸው በክልሉ በአየር ንብረት ለውጥ ሊያጋጥም የሚችልን ችግር ለመቋቋም የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት ስለመደረጉ ገልጸዋል። በራስ አቅም የተቀናጀ ቅድመ ዝግጅት ስራ ሲከናወን መቆየቱን በማስታወስ ለሚያጋጥሙ አደጋዎች አፋጣኝ ምላሽ መስጠት የሚያስችል የተሟላ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል። በክልሉ ለድርቅ ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎችን ቀደም ብሎ በመለየት የመስኖና የከርሰ ምድር ውሃ በመጠቀም የማልማትና የምርት አማራጮችን የማስፋት ስራ መከናወኑን ገልጸዋል። በዚህም በቤተሰብ ደረጃ ጭምር በምግብ ራስን የመቻል ስኬት መኖሩን አንስተው የሌማት ትሩፋትና ሌሎችም ኢንሸቲቮች መሰረታዊ ለውጥ ያመጡ መሆኑንም ተናግረዋል። የምርትና ምርታማነት አቅምን በማሳደግ ከተረጅነት ለመላቀቅ በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤት መመዝገቡንም ተናግረዋል። በዚህም በተለይ የዝናብ እጥረት ሲያጋጥም ክስተቱን በራስ አቅም ለመቋቋም የሚያስችል አቅም እየተፈጠረ መሆኑን ጠቁመው ፈጥነው የሚደርሱ ምርጥ ዘሮች በመለየት የውሃ እጥረትን የሚቋቋሙ ሰብሎች በስፋት ጥቅም ላይ እንዲውሉ እየተደረገ መሆኑን ለአብነት ጠቅሰዋል። በተጨማሪም የምርት ክምችት የማድረግና ድጋፍ የመስጠት እንዲሁም የከብት መኖ የማቅረብ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል። አሁን ላይም እየጣለ የሚገኘውን ዝናብ በማጠራቀም አርሶ አደሩ ባለው መሬት እንዲያለማ እየተደረገ መሆኑን አመልክተዋል። በቀጣይም የአየር ንብረትና ሁኔታ መረጃን ለአርሶ አደሩ የማድረስና የመስኖና የከርሰ ምድር ውሃ ሃብትን በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን የበለጠ የማሳደግ ስራዎች እንደሚጠናከሩ አስታውቀዋል። የሐረሪ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ቢሮ ሃላፊ አቶ ኤልያስ መሀመድ በበኩላቸው የኤልኒኖ ክስተት በአንዳንድ አካባቢዎች ጉዳት እንዳያስከትልና አፋጣኝ ምላሽ መስጠት እንዲቻል የአደጋ መከላከልና ፈጣን ምላሽ ሰጪ ምክር ቤት መቋቋሙን ተናግረዋል። በዚህም ችግሩ የታየባቸውን አካባቢዎች የመለየትና ምርጥ ዘር በማከፋፈል ወደ ምርት እንዲገቡ መደረጉን ጠቅሰዋል። በተለይም የምግብ እጥረት እንዳይከሰት በራስ አቅም መቋቋም የሚያስችል የምርት ክምችት የማድረግ ስራም መከናወኑን ገልጸዋል።
አረንጓዴ ዓሻራ፡ የመደመር እሳቤ አብነት
Sep 24, 2026 119
በሀገራችን አንዱ የማድረግ ዐቅም ማሳያ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ነው።የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በዓለም በስፋት እየተስተዋለ ካለው የአየር ንብረት ግብዝነት (Greenwashing) ፍጹም ተቃራኒ በሆነ መንገድ ከንግግር ተግባርን ያስቀደመ መርሐ ግብር ዓላማው የደን ሽፋንን ማሳደግና የደን መጨፍጨፍ፣ የመሬት መራቆትና የአየር ንብረት ለውጥ ችግሮችን መፍታት የሆነው የኢትዮጵያ አረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር፤ የአካባቢ መራቆትና የአየር ንብረት ለውጥ ተግዳሮቶችን ተጨባጭ በሆኑ ተግባራት ለመፍታት መሰጠ ሰፊና የላቀ ውጤት የተመዘገበበት ተግባራዊ ጥረት ነው። እንዲህ ያለው ትልቅ ፕሮጀክት በፌዴራል፣ በክልልና በአካባቢ ደረጃና ልዩ የሆነ የአመራር ቁርጠኝነትና ቅንጅትን ይፈልጋል። ይህ የአመራር ጥበብና ቅንጅት የተለያዩ ማኅረሰቦችን፣ ትምህርት ቤቶችን፣ የንግድ ተቋማትና ዓለም አቀፍ አጋሮችን ያሳተፈ አካታች መርሐ ግብር ነው። የአረንጓዴ ዐሻራ ፕሮግራም የጋራ የኃላፊነት ስሜትን በማጎልበት፣ ተነሣሽነቱ ከዛፍ ተከላ በላይ ሆኖ ወደ ሀገራዊ ንቅናቄ አድጓል። የተለያዩ ቡድኖች ለጋራ ዓላማ ተባብረው እንዲሠሩ አስችሏል። የማስፈጸም ሂደቱ ዛፍ በመትከል ላይ ብቻ ያተኮረ አልነበረም። ሁሉንም ማኅበረሰብ ያሳተፈ ነበር። አካሄዱም ሊላካ የሚችል ከባቢያዊ ጥቅም የሚያስገኝ እንቅስቃሴ መፍጠር ነበር። የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ስኬት ሀገራዊ ኩራትና ጽናት እንዲጎለብት አስችሏል። አጣዳፊ ሀገራዊና ዓለም አቀፍ ተግዳሮቶችን ለመፍታት በመደመር ስሌት ጠንካራ የአፈጻጸም ጥበብ ያለውን ዐቅምም አሳይቷል። የመደመር መንግሥት ገጽ 127 እና 128
የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለምግብ ዋስትና መረጋገጥ ትልቅ አቅም እየሆነ ነው
Sep 24, 2026 128
ሀዋሳ፤ መስከረም 14/2019 (ኢዜአ):- የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ተፅዕኖ በመቋቋም ለምግብ ዋስትና መረጋገጥ ትልቅ አቅም እየሆነ መምጣቱን በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የዘርፉ ምሁራን ገለጹ። በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ የዘርፉ ተመራማሪዎች ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ ልማት የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ተፅዕኖ በመቋቋም ዘላቂ የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ እያስቻለ ነው። ችግኞችን መትከል ብቻ ሳይሆን ለመንከባከብ የተሰጠው ሀገራዊ ትኩረት ሁለንተናዊ ዕድገትን ለማፋጠን ጉልህ ሚና እየተጫወተ መሆኑንም አመልክተዋል። በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ መምህርና ተመራማሪ ፕሮፌሰር ፀጋዬ በቀለ እንዳሉት፤ በኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት የአረንጓዴ አሻራ ልማት ንቅናቄን በመፍጠር መላውን ማህበረሰብ በማሳተፍ የተከናወነው ተግባር በዘርፉ አስደናቂ ውጤት አስመዝግቧል። በሀገር አቀፍ ደረጃ ችግኝን የመትከልና የመንከባከብ ባህል እያደገ በመምጣቱ ዘርፍን የተሻለ ውጤት እንዲታይበት አድርጓል ብለዋል። ይህም ተፈጥሮን በመጠበቅ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ችግር በመቋቋም የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ የጎላ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ፕሮፌሰር ፀጋዬ ተናግረዋል። መርሃ ግብሩ የመሬት ለምነትና የውሃ አቅም በማሻሻል የግብርና ምርትና ምርታማነት ለመጨመር ማስቻሉንም ተናግረዋል። ንብ ማነብን ጨምሮ አዳዲስ የስራ ዘርፎች በስፋት እንዲፈጠሩ በማድረግ የዜጎች ተጠቃሚነት እንዲጎለብት ማስቻሉንም ጠቁመዋል። የኮሌጁ ዲን ተሻለ ወልደአማኑኤል (ዶ/ር) በበኩላቸው እንዳሉት፤ ባለፉት ዓመታት የተከናወነው የአረንጓዴ አሻራ ልማት አመርቂ ውጤቶች እያስገኘ ነው። ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባት የምታከናውነው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለአፍሪካም ሆነ ለዓለም ትልቅ አርአያ መሆኑን ተናግረዋል። የስነ-ምህዳር እና ብዝሃ ህይወት በዘላቂነት እንዲጠበቅ በማድረግ ረገድ መርሃ ግብሩ የማይተካ ሚና እየተጫወተ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ ኮሌጁ ከሀገሪቱ መልክአ ምድርና ስነምህዳር ጋር የሚስማሙ ችግኞችን በምርምር በማውጣት እንዲሁም በማፍላትና በማሰራጨት መርሃ ግብሩን በመደገፍ የሚጠበቅበትን ሀላፊነት እየተወጣ መሆኑን ጠቅሰዋል። ኮሌጁ የኢትዮጵያን የአረንጓዴ አሻራ ልማት ልምድ ወደ ሌሎች ሀገራት እንዲስፋፋ በጥናት የተደገፉ ሰነዶች በማዘጋጀት የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተሻለ (ዶ/ር) አስታውቀዋል።
በሚቀጥሉት አስር ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብና እርጥበት ይኖራል
Sep 22, 2026 211
አዲስ አበባ፤ መስከረም 12/2019 (ኢዜአ)፦በሚቀጥሉት አስር ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብና እርጥበት እንደሚኖር የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ። ኢንስቲትዩቱ ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳመለከተው፤ በሚቀጥሉት ቀናት በምዕራብ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ አብዛኛዎቹ ቦታዎች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው የአፈር ውስጥ እርጥበት ይኖራል። በተመሳሳይ በሰሜን ምስራቅ እና ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ቀላል መጠን ያለው እርጥበት እንደሚኖርና በክረምት ዝናብ ተጠቃሚ ተፋሰሶች ላይ ደግሞ ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው የገጽ ምድር የውኃ ፍሰት እንደሚኖር መግለጫው ጠቅሷል። ምዕራብ ወለጋ፣ ኢሉባቦር፣ አርሲ፣ አብዛኞቹ የሸዋ ዞኖች፣ የምዕራብ፣ መካከለኛ፣ ደቡብ እና ሰሜን ጎንደር፣ የሰሜን፣ የምዕራብ እና የምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ማኦ ኮሞ፣ ምዕራብ ኦሞ እና አሶሳ ከመካከለኛ እስከ ከባድ እርጥበት የሚያገኙ አካባቢዎች መሆናቸውን አስታውቋል፡፡ በተጨማሪም ምስራቅ እና ምዕራብ ሀረርጌ፣ ደቡብ እና ሰሜን ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ወረዳ፣ ምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ ትግራይ፣ የሲዳማ ሁሉም ዞኖች እና የወላይታ አካባቢዎች ከቀላል እስከ መካከለኛ እርጥበት የሚያገኙ አካባቢዎች መሆናቸውን ጠቅሷል፡፡ ይህ የአየር ሁኔታ የአፈር እርጥበትን ለማሻሻል፣ ለረጅም እና መካከለኛ ጊዜ ሰብሎች እድገት እንዲሁም ዘግይተው ተዘርተው በተለያየ የእድገት ደረጃ ላይ ለሚገኙ ሰብሎች ፍሬያማነት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለውም አስታውቋል፡፡ በተጨማሪም ለቋሚ ተክሎች ልምላሜ፣ ለእንስሳት መኖና ለመጠጥ ውኃ አቅርቦት መጎልበት እንዲሁም የዝናብ ውኃን አሰባስቦ ለማስቀረት ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል ብሏል። የመኸር ሰብል አብቃይ አከባቢዊች አርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች ምርታማነትን ለመጨመር የሰብል በሽታና አረምን አስቀድመው እንዲከላከሉ፤ ፀረ-አረምና ፀረ-ተባይ ኬሚካሎችንም የግብርና ባለሙያዎችን በማማከር ብቻ እንዲጠቀሙ አሳስቧል። የውኃ ትነትን ለመቀነስ የሚያስችሉ የግብርና ስራዎችን ማከናወን፣ የሚገኘውን እርጥበት በአግባቡ ለልማት ማዋል፣ ለእንስሳት ግጦሽ ሳርን በተቆጠበ መንገድ መጠቀም እና የዝናብ ውኃን አጠናክሮ ማከማቸት እንደሚገባ መክሯል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የአፍሪካ ህብረት እና ተመድ ያላቸውን የጋራ ውጥኖች በቁርጠኝነት ለመተግበር እንደሚሰሩ ገለጹ
Sep 21, 2026 522
አዲስ አበባ፤ መስከረም 10/2019 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሰላም፣ ኢኮኖሚና ፍትሃዊ ዓለምን ለማስፈን በጋራ እያከናወኑ የሚገኘውን ስራ ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰሩ አስታወቁ። 81ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ከመስከረም 8 ቀን 2019 ዓ.ም አንስቶ በኒው ዮርክ እየተካሄደ ይገኛል። “መተማመንን ዳግም መገንባት እና አዳዲስ ለውጦችን በአግባቡ መምራት፣ ለሁሉም የሚሰራ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን መፍጠር” የጉባኤው መሪ ሀሳብ ነው። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በጉባኤው ላይ ለመታደም ኒው ዮርክ ይገኛሉ። ከጠቅላላ ጉባኤው ጎን ለጎን ስትራቴጂካዊ ትብብር ማጎልበት፣ የሰላምና ደህንነት ማዕቀፎችን ማጠናከርና አፍሪካን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ሪፎርሞች ላይ ያተኮረ ከፍተኛ የምክክር መድረክ ተካሄዷል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ እና የተባበበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ መድረኩን በጋራ መርተውታል። ስብስባው ሁለቱ ተቋማት አፍሪካ መዋቅራዊ ፈተናዎችን ለመፍታት እያደረገች ያለቻቸውን ጥረቶች ለመደገፍና ፍትሃዊ የዓለም ስርዓትን ለመፍጠር ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት ይበልጥ ያረጋገጠ መሆኑን የአፍሪካ ህብረት መረጃ ያመለክታል። የዓለም አቀፍ የፋይናንስ አወቃቀርን ማሻሻል፣ ዘላቂ የእዳ አስተዳደር እና የአፍሪካ ሀገራት ከቁልፍ የማዕድን ሀብቶች ይበልጥ ተጠቃሚ ማድረግ ውይይት ከተደረገባቸው አጀንዳዎች መካከል ይጠቀሳሉ። ሁለቱ ወገኖች በስብሰባው ላይ የአፍሪካ ህብረት እና የተመድን ትብብር ያለውን ስትራቴጂካዊ ፋይዳ አጽንኦት ሰጥተዋል። የተቋማቱ ሶስት ነባር የትብብር ማዕቀፎች በአዲስ መልክ ለማደስ እና እ.አ.አ በ2026 ትግበራው የሚጠናቀቀውን የጋራ ፍኖተ ካርታ የተፈጻሚነት ገደብ ለማራዘም መስራት እንደሚገባ ተመላክቷል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአፍሪካ ያሉ የሰላም እና የደህንነት ተግዳሮቶችን ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ውስጥ የአፍሪካ ህብረት ቁልፍ አጋር ሆኖ እንደሚቀጥል ዳግም አረጋግጧል። የአፍሪካን የሰላምና ደህንነት መዋቅር ማጠናከር፣ ግጭትን አስቀድሞ የመከላከል ዲፕሎማሲና የእርቅ ሂደትን በሚገባ መተግበርና ለአፍሪካ ፈተናዎች አፍሪካዊ መፍትሄዎችን ማረጋገጥ የሚያስችል በቂ አቅም መገንባት እንደሚያስፈልግ በስብሰባው ላይ ተነስቷል። በውይይቱ በሳሄል ቀጠና፣ በሊቢያ፣ በሱዳን፣ በደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያና ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ያሉ ወቅታዊ ጉዳዮችና የሰላም ጥረቶች ተገምግመዋል። በስብስባው ላይ ግጭቶች፣ በዓለም አቀፍ የአቅርቦት ሰንሰለት ላይ የተፈጠሩ መስተጓጎሎች እና የባህር በር መስመሮችን መዝጋትን ጨምሮ ሌሎች ውጫዊ ሁኔታዎች በአፍሪካ ኢኮኖሚ እና ምግብ ዋስትና ላይ ተጨማሪ ጫና እየፈጠሩ መሆኑ ተነስቷል። የአየር ንብረት ለውጥ እያደረሰ ያለው ጉዳትም ምክክር ተደርጎበታል። ሁለቱ ወገኖች በውይይቶች ጠንካራ የጋራ ግብረ መልስ መስጫ ማዕቀፍ ለመፍጠር ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። የአፍሪካ ህብረት እና ተመድ ፍኖተ ካርታ ዝግጅን ለማጠናቀቅ፣ በአፍሪካ ሀገራት የሰላም ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር፣ የምግብ ዋስትና ተግዳሮቶችን ለመፍታትና ለድንገተኛ አደጋዎች ምላሽ መስጠት የሚያስችሉ የአሰራር ማዕቀፎችን ለመቅረጽ በቅርበት እንደሚሰሩ መግለጻቸውን የአፍሪካ ህብረት መረጃ ያመለክታል። 81ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ እስከ መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ይቆያል።
በቀጣናው ያሉ ፈተናዎችን በዘላቂነት ለመፍታት የሀገራት የጋራ ቁርጠኝነት ወሳኝ ነው - ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር)
Sep 15, 2026 817
አዲስ አበባ፤ መስከረም 5/2019 (ኢዜአ)፦ በቀጣናው እያጋጠሙ የሚገኙ ፈተናዎች በዘላቂነት እንዲፈቱ የአባል ሀገራት አብሮነትና የጋራ ቁርጠኝነት ወሳኝ መሆኑን የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ገለጹ። የኢጋድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት 74ኛው አስቸኳይ ስብሰባውን ዛሬ በጅቡቲ አካሂዷል። በስብሰባው ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እና የኢጋድ አባል ሀገራት ተወካዮች ተሳትፈዋል። በቀጣናው ሰላም እና ጸጥታ እንዲሁም በሌሎች አበይት ጉዳዮች ላይ ምክክር ተደርጓል። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ በቀጣናው እያጋጠሙ ያሉ ፈተናዎችን በዘላቂነት ለመቋቋም የአባል ሀገራት አብሮነትና የጋራ ቁርጠኝነት ወሳኝ ነው። በኢጋድ ሴክሬታሪያት በኩል የተከናወኑ የልማትና የሰላም ሥራዎች አበረታች ውጤቶችን እያስገኙ መሆናቸውን በመግለጽ፣ ተቋሙ ለቀጣናው ህዝቦች ብልጽግና መረጋገጥ የጸና አቋም እንዳለው አመልክተዋል። ምንም እንኳን የተለያዩ ጂኦፖለቲካዊ ፈተናዎች ቢኖሩም፣ የኢጋድ ሴክሬታሪያት ያለፉት ስድስት ወራት አፈጻጸም አበረታች የሚባል መሆኑን ተናግረዋል። በቀጣናዊ መሠረተ ልማት እና የጤና ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶችን ያነሱት ዋና ፀሐፊው፤ የቀጣናው የከርሰ ምድር ውሃ መረጃ ሥርዓት የአገልግሎት ተደራሽነት የላቀ ውጤት ማስመዝገቡን ጠቁመዋል። እንዲሁም የቀጣናው ዓለም አቀፍ የጤና ሽፋን መረጃ ጠቋሚ (ኢንዴክስ) ከ60 ወደ 65 በመቶ ከፍ ማለቱንና ይህም እ.አ.አ በ2027 70 በመቶ ለማድረስ የተያዘውን እቅድ ለማሳካት የሚያስችል መሆኑን ነው ያነሱት። በሌላ በኩል ሱዳን ወደ ኢጋድ ሙሉ አባልነቷ መመለሷ የቀጣናውን ትብብርና አንድነት ይበልጥ እንደሚያጠናክረው ገልጸዋል። ዋና ፀሐፊው እ.አ.አ ጁላይ 2026 ወደ ሱዳን ባቀኑበት ወቅት የኢጋድ የሱዳን ልዑክ ቢሮ በድጋሚ በይፋ መከፈቱን አስታውሰው ይህ እርምጃ ከቀጣናው ሕዝቦች ጋር ያለውን ቀጥተኛና ዘላቂ ትስስር አጠናክሮ የሚያስቀጥል መሆኑን አመላክተዋል። ኢጋድ ከአፍሪካ ሕብረት፣ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኤጀንሲዎች እና ከሌሎች ስትራቴጂካዊ አጋሮች ጋር ያለው ግንኙነት ለቀጣናው ዘላቂ ልማት ወሳኝ ነው ብለዋል። አጋርነቱ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትን አቅም በማጠናከር ረገድ የጎላ ድርሻ እንደሚያበረክትም ነው ያነሱት። በቀጣይ ሊከሰቱ የሚችሉ የአየር ንብረት ለውጥ አደጋዎችን የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓትን በማጠናከር ለመቋቋም የሚያስችሉ አሰራሮች እየተቀረፁ መሆናቸውን ተናግረዋል። ሀገራት የኤልኒኖ (El Niño) የአየር ንብረት መዛባት የሚያስከትለውን ስጋት ለመቀነስ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከር እንዳለባቸው አሳስበዋል። በሌላ በኩል ቀጣናውን ከሰው ሰራሽ አስተውሎት ጋር ለማስተሳሰርና በቴክኖሎጂ የታገዘ የልማት መሠረት ለመጣል የተጀመሩ ስራዎች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን ገልጸዋል። ስብሰባው የቀጣናውን ሰላም፣ ደህንነት እና ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማፋጠን በሚያስችሉ ሀገራዊና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ በመምከርና ውሳኔዎችን በማሳለፍ መጠናቀቁን ኢዜአ ከኢጋድ ሴክሬተሪያት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። የኢጋድ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ከተቋሙ ቁልፍ የፖሊሲ አደረጃጀቶች መካከል አንዱ ሲሆን፣ የድርጅቱን ሥራዎች በመምራትና በአባል ሀገራት መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር ረገድ ጉልህ ሚና የሚጫወት ነው።
አፍሪካ በዓለም ፊት ቦታ ለማግኘት አትማጸንም ፤ ይልቁንም የሚገባትን ስፍራ በባለቤትነት እየያዘች ነው
Sep 9, 2026 705
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ):- አፍሪካ በዓለም ፊት ቦታ ለማግኘት አትማጸንም ፤ የሚገባትን ስፍራ እና ክብር በራሷ እያረጋገጠች ነው ሲሉ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። የአፍሪካ ህብረት ቀን ዛሬ እየተከበረ ይገኛል። የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ቀኑን በማስመልከት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ሊቀ መንበሩ የአፍሪካ ህብረት ቀን እ.አ.አ በ1999 የቀድሞ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ለመተካት ይፋዊ ውሳኔ የተላለፈበት የሰርጥ ድንጋጌ (Sirte Declaration) የሚታወስበት እንደሆነ ገልጸዋል። በዚያን ወቅት የአፍሪካ መሪዎች አህጉራዊ ትስስርን ለማፋጠን እና የአፍሪካን ድምጽ በዓለም አቀፍ መድረክ ከፍ ለማድረግ የአፍሪካ ህብረትን ለመመስረት ወሳኝ እና ታሪካዊ እርምጃ የወሰዱበት ምዕራፍ ነው ብለዋል። የዘንድሮው የአፍሪካ ህብረት ቀን ለአህጉሪቱ እጅግ ልዩ ትርጉም ባለው ወቅት ላይ እየተከበረ እንደሚገኝ አውስተዋል። ከጥቂት ቀናት በፊት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ የአፍሪካን እውነተኛ ቁመና እና ትክክለኛ መጠን የሚያሳይ የዓለም ካርታ አጠቃቀምን የሚደግፍ፣ በአፍሪካ መሪነት የቀረበ የውሳኔ ሀሳብ አፅድቋል። በቶጎ ሃሳብ አመንጪነትና በአፍሪካ ህብረት ድጋፍ እውን የሆነው ይህ እርምጃ ከቀላል የካርታ ማስተካከያ በላይ ትርጉም አለው ብለዋል ሊቀ መንበሩ። አፍሪካ በዓለም ፊት እንዴት እንደምትታይ ትኩረት የሚሰጠው መሆኑን እና አፍሪካ ራሷን የምትገመግምበትንና የምታሳይበትን ትርክት ራሷ መቅረጽ እንዳለባት አበክሮ የሚያስታውስ ነው። ይህ ውሳኔ አፍሪካ በዓለም ፊት በምን መልኩ መታየት እንዳለባት ከማሳየቱም በላይ፤ አፍሪካ ራሷን የምትመዝንበትንና እውነታዋን ለዓለም የምታሳይበትን ትርክት በራሷ መቅረጽ እንዳለባት በግልጽ የሚያሳይ መሆኑን ነው ያነሱት። የአፍሪካ እጣ ፈንታ የሚወሰነው በአፍሪካውያን የራሳቸው እይታ ነው። አፍሪካን በእውነተኛ ቁመናዋ፣ኃይሏ እና አቅሟ የምንመለከትበት ጊዜ አሁን ነው ብለዋል። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር አያይዘውም ካርታውን የማስተካከል እርምጃ አፍሪካ ወደ ላቀ የጋራ ራዕይ የምታደርገው አህጉራዊ ጉዞ አካል መሆኑን አንስተዋል። ይህም በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጠና (AfCFTA) አማካኝነት የኢኮኖሚ ትስስር ማጠናከርን፣ ሰላም እና ፀጥታን ማረጋገጥን፣ ዘላቂ ልማትን እውን ማድረግን እና በዓለም አቀፍ ውሳኔ ሰጪ አካላት ውስጥ የአፍሪካን ተሳትፎ ማሳደግን እንደሚያካትት በዝርዝር አስረድተዋል። የአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 የተሳሰረች፣ የበለጸገች እና ሰላማዊት አፍሪካን ለመገንባት የማዕዘን ድንጋይ ሆኖ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል። ሰላም እና ፀጥታን ማረጋገጥ፣ የኢኮኖሚ ትስስርን በማፋጠን እና የአፍሪካን ዓለም አቀፍ ተሰሚነት መጨመር የአፍሪካ ህብረት ቀዳሚ ትኩረቶች ናቸው ብለዋል። አፍሪካ በዓለም ፊት እውቅና ለማግኘት አትለምንም፤ ይልቁንስ በዓለም አቀፍ መድረክ የሷ የሆነውን ትክክለኛ ስፍራ በራሷ ባለቤትነት እየያዘች ነው። አሁን የሚጠበቅብን ይህንን ጠንካራ እምነት ወደ ህብረት፣ ሀብትና ብልጽግና፣ ሰላም እና ተደማጭነት መለወጥ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ሊቀመንበሩ አፍሪካ የምታስመዘግበው እድገት በዓለም አቀፍ መድረኮች በሚኖራት ውክልና ብቻ ሳይሆን፣ በዜጎቿ ላይ የኑሮ ጥራት መሻሻል ጭምር መለካት እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል። በዚህም መሰረት የአፍሪካ ህብረት የ2026 ዓመት ትኩረቱን በዘላቂ የንጹህ ውሃ አቅርቦት እና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አገልግሎት ላይ ማድረጉ፣ ህብረቱ አህጉራዊ ራዕዮችን ከዕለት ተዕለት የዜጎች ህይወት ጋር ለማያያዝ ያለውን ጽኑ ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ አመልክተዋል። በአፍሪካ ህብረት ቀን አከባበር አባል ሀገራት፣ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማህበረሰቦች፣ የአፍሪካ ተቋማት፣ የግሉ ዘርፍ፣ የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ ሴቶች እና ወጣቶች ተባብረው ይበልጥ የተሳሰረች፣ በራሷ አቅም የምትተማመን እና የራሷን እጣ ፈንታ በራሷ መወሰን የምትችል አፍሪካን እንዲገነቡ ሊቀመንበሩ ጥሪ አቅርበዋል። የምንፈልጋት አፍሪካ የሚለውን አህጉራዊ ራዕይ እውን ለማድረግ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ እና የሰርት ድንጋጌ ለቀጣዩ የአፍሪካ ትውልድ ዘላቂ የትምህርት እና የዕድገት መሰረት ሆኖ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። የነገዋ አፍሪካ በካርታ ላይ ብቻ የተሻለ ውክልና ያላት ብቻ ሳትሆን፤ በዓለም አቀፍ መድረክ ሉዓላዊነቷ የጸና፣ ጠንካራ ውስጣዊ አንድነት ያላት፣ ለህዝቦቿም ዘላቂ ብልጽግናን የምታጎናጽፍ አህጉር መሆን ይኖርባታል ነው ያሉት። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ለመላው አፍሪካውያን እና በውጭ ሀገር ለሚገኙ የአፍሪካ ዳያስፖራዎች ሰላማዊ እና የትብብር መንፈስ የተሞላበት የአፍሪካ ህብረት ቀን እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
የአፍሪካ ህብረት እና አሜሪካ አጋርነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ
Sep 4, 2026 895
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ)፡- የአፍሪካ ህብረት እና አሜሪካ ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን እና ሁሉን አቀፍ ትብብራቸውን የበለጠ ለማላቅ እንደሚሰሩ አስታወቁ። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሺያን ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። ውይይቱ በአፍሪካ ህብረትና አሜሪካ መካከል ያለውን ለረጅም ጊዜ የቆየ አጋርነት ማጠናከር እና በአህጉሪቱ ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር የአፍሪካና አሜሪካን ትብብር ታሪካዊ መሆኑን አውስተው በህብረቱ፣ በአባል ሀገራት እና በአሜሪካ መካከል የሁለቱንም ወገኖች ጥቅም በሚያስጠብቅ መልኩ ጠንካራ አጋርነት መገንባት እንደሚገባ አሳስበዋል። በምስራቅ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ሱዳን እየተደረጉ ላሉ አፍሪካ መር የሰላም ጥረቶች አሜሪካ እያደረገች ላለው ገንቢ አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሺያ በበኩላቸው አፍሪካ አሜሪካ ቀዳሚ ትኩረት የምትሰጣት አህጉር እንደሆነች ገልጸዋል። የጋራ ፍላጎቶችንና ግቦችን ከህብረቱ ኮሚሽንና ከአባል ሀገራት ጋር በመሆን ለማሳካት ያላቸውን ጽኑ ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል። በንግድ እና ኢንቨስትመንት፣ በመሰረተ ልማት ዝርጋታ፣ በዲፕሎማሲ፣ እንዲሁም በሰላምና ጸጥታ ያለውን ትብብር ማጠናከር እንደሚገባም አመልክተዋል። በውይይቱ ላይ በሱዳን ጉዳይ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ፣ የሰብአዊ እርዳታ ያለ ገደብ እንዲገባ እና በሲቪሎች የሚመራ ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ሂደት እንዲጀመር አጽንዖት ተሰጥቷል። በአፍሪካ ባለቤትነት የሚመሩ የሰላም ጥረቶች እና አሜሪካ የምትደግፋቸው የሰላም ሂደቶች በተቀናጀ መልኩ ለመተግበር ከስምምነት ላይ ተደርሷል። በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በመሰረተ ልማት እና በሰላም መስኮች የሁለቱን ወገኖች ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችሉ የትብብር መስኮች ተገምግመዋል። ሁለቱ ወገኖች በአፍሪካ ህብረትና በአሜሪካ ስትራቴጂክ ኢንቨስትመንት ማዕቀፍ ውስጥ የተደረጉ ስምምነቶችን ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። በሊቢያ ጉዳይ ዘላቂ የፖለቲካ መፍትሄ ማግኘት እንደሚያስፈልግም ተነስቷል። የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር እና ረዳት ሚኒስትሩ የሁለቱን ወገኖች ስትራቴጂካዊ አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከርና የትብብር አድማሱን ለማስፋት የጋራ ቁርጠኝነታቸውን መግለጻቸውን ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ሐተታዎች
የባሌ ተራሮች እውነታ
Sep 24, 2026 254
በኢትዮጵያ ከሚገኙ ውብ እና አስደናቂ የተፈጥሮ መስህቦች መካከል የባሌ አካባቢ ልዩ ስፍራ የሚሰጠው ነው። የባሌ የተፈጥሮ ሀብት ከማራኪ መልክዓ ምድር ባለፈ የብርቅዬ እንስሳትና አእዋፋት መገኛም መሆኑ ይታወቃል። ከሰማይ ጠቀስ ተራሮቹ እስከ ጥቁር አንበሳ መኖሪያው የሃረና ደን፣ ከገዳ ስርዓት የጥበቃ እሴት እስከ ካርቦን ንግድ ተጠቃሚነቱ ባሌ በተፈጥሮ የታደለ እውነተኛ ድንቅ ምድር ነው፤ በአንድ አባባል፡ 'ባሌ፡ አንድ ፓርክ፣ የብዙ ዓለማት መገኛ! (Bale: One Park Many Worlds) እየተባለ የሚጠራው። የባሌ መልክዓ-ምድር የተፈጥሮ ድንቅ ጥበብ ማሳያ ነው፤ የበርካታ ወንዞች ምንጭ፣ የጥቅጥቅ ደኖችና የአረንጓዴ ምድር ነፃብራቅ። ከባህር ጠለል በላይ ሰማይን በሚነኩ ግዙፍ ተራሮቹ፣ ሰፋፊ አምባዎቹና ውብ ሸለቆቹ የታጀበው ይህ አስደናቂ ስፍራ፣ በተፈጥሮ ለጋስነት ከተጎናፀፋቸው እምቅ የውሃ ሀብቶች ጋር ተደምሮ እውነተኛ የምድር ላይ ገነት ያደርገዋል። የባሌ ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ከ2 ሺህ 150 ካሬ ኪሎ ሜትር በላይ ስፋት ያለው ሲሆን በከፍተኛ ቦታዎች ላይ የተለያዩ የዕፅዋት ዝርያዎችን የያዘ እምቅ የደን ሀብትም አለው። መልክዓ ምድራዊ አቀማመጡም ሲታይ ከባህር ጠለል በላይ ዝቅተኛው 1 ሺህ 500 ሜትር እንዲሁም ከፍተኛው ጫፍ የቱሉ ዲምቱ ተራራ በ4 ሺህ 377 ሜትር ከፍታ ላይ የሚገኝ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ። በፓርኩ ከ260 በላይ የአእዋፍ ዝርያዎች እና ልዩ ልዩ ብርቅዬ የዱር አንስሳት የሚገኙ መሆኑም ይታወቃል። በዚህም ድንቅ ተፈጥሯዊና ብዝሃ-ሕይወታዊ ሀብቱ ምክንያት፣ የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በዩኔስኮ የዓለም የተፈጥሮ ቅርስ ሆኖ በቋሚነት መመዝገቡ ይታወቃል። በባሌ ተጠቃሽ ከሆኑት የቱሪስት መዳረሻዎች መካከል ከ4 ሺህ ሜትር በላይ ከፍታ ላይ የሚገኘው በረዷማው የሳነቴ አምባ ይጠቀሳል። በዚህ አስደናቂ የተፈጥሮ እይታ ባለው አካባቢ ብርቅዬ የሆኑ ቀይ ቀበሮዎችን በቀላሉ ማየት ይቻላል። የሃረና ጥቅጥቅ ደን ደግሞ ከሳነቴ አምባ በስተደቡብ በኩል የሚወርድ ሰፊና እርጥበታማ አካባቢ ሲሆን በዛፎች የተሞላ፣ በርካታ የዱር እንስሳት የሚገኙበት እንዲሁም ኩልል ያሉ አስደናቂ ፏፏቴዎች የሚገኙበት ነው። የሀገራችን ጋሻና መከታ የሆነው የጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን ተምሳሌት የሆነው ብርቅዬው ጥቁር አንበሳ፣ በዚህ አስደናቂ የሃረና ተፈጥሮ ደን ውስጥ ይገኛል። የአካባቢው ማህበረሰብ ከገዳ ስርዓት በወረሰው ድንቅ ባህላዊ እሴትና ተፈጥሮን የመንከባከብ እውቀቱ ደኑን ጠብቆ በማቆየቱ፣ ከስነ-ምህዳሩ ከሚያገኘው በርካታ አገልግሎት ባሻገር፣ ዛሬ ላይ በአሳታፊ የደን አስተዳደር አማካኝነት ከካርቦን ሽያጭ ቀጥተኛ ተጠቃሚ መሆን ችሏል። ለተራራ ላይ የእግር ጉዞ አፍቃሪ ጎብኚዎች ደግሞ የቱሉ ዲምቱ ተራራ ከነ ግርማ ሞገሱ የሚጠብቃቸው ይሆናል። ብርቅዬው ቀይ ቀበሮ ዋነኛ ምግቡ የሆነውን ፍልፈል የዓይጥ ዝርያ በቀስታ ሲያድንና ዘሎ በሹል አፉ ሲይዝ ማየት ለናፈቀው ጎብኚም ሳነቴ ተመራጩ ቦታ ነው። ባለ ክራቫቱ የደጋ አጋዘን ከእነግርማሞገሱ ቆሞ ፊትለፊት የሚታየው ደግሞ የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ አካል በሆነው ዲንሾ ጫካ ውስጥ ነው። የባሌ እና አካባቢው መልክዓ ምድር በአብዛኛው የሁለት ጊዜ የዝናብ ወቅት በመሆኑ ይህም ለምለምና አረንጓዴ እንዲሆን አድርጎታል። ከጎኑ እየታረሰ፣ በሌላ በኩል ደግሞ የደረሰ ሰብል የሚሰበሰብበት ባሌ ለስንዴና ለቢራ ገብስ ልማት እጅግ ተመራጭና ተስማሚ የአየር ጠባይ እንዲሁም የመልክዓ-ምድር አቀማመጥ ያለው ምድር ነው። የእነዚህ ሁሉ ድምር ውጤቶች ባሌን እና የባሌ ተራሮች ብሄራዊ ፓርክን ተመራጭና ተወዳጅ የቱሪስት መዳረሻ ያደርገዋል። በቅርብ ዓመታት እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎች ባሌ ያለውን የተፈጥሮና የቱሪዝም አቅም ወደ ተጨባጭ የኢኮኖሚ ጥቅም ለመለወጥ እያስቻለ ይገኛል። ወደ ቱሪስት መዳረሻዎች የሚወስዱ የመንገድ ግንባታዎች፣ የኤሌክትሪክ እና የቴሌኮም መሰረተ ልማት ዝርጋታዎች በስፋት በመከናወን ላይ ይገኛሉ። ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመቀናጀት የሎጅ ግንባታዎች፣ የዕደ-ጥበብ ስራዎች ማስተዋወቅ እና እንግድነትን መሰረት ያደረጉ የኢኮ-ቱሪዝም ስራዎች ደረጃቸውን ጠብቀው እየተሰሩ መሆኑ ይታወቃል። እንደ አጠቃላይ የባሌ የተፈጥሮ ሀብት፣ አስደናቂ መልክዓ ምድር፣ ብርቅዬ እንስሳትና አእዋፋት እንዲሁም የውሃ ሃብት ተደምሮ ለኢትዮጵያ ትልቅ የቱሪዝም ሃብት መሆን የሚችል ነው። ከባሌ ሰፊ የተፈጥሮ ጸጋ ባለፈ በታሪክ፣ በባህል እሴቶችና በጠንካራ ማህበራዊ ትስስርም የሚጠቀስ ሲሆን የአካባቢው ማህበረሰብ ተፈጥሮን በማስጠበቅና በመንከባከብ ረገድ የዳበረ ልምድ እንዳለው ይታወቃል።
ከባህር በር ጥያቄ እስከ ፍትሃዊ ውክልና በተመድ ጉባኤ የተንጸባረቁ የኢትዮጵያ አቋሞች
Sep 24, 2026 155
በኒውዮርክ እየተካሄደ የሚገኘው 81ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ የዓለምን ትኩረት የሳበና በርካታ አንገብጋቢ ጉዳዮች እየተነሱበት ይገኛል። “መተማመንን ዳግም መገንባት እና አዳዲስ ለውጦችን በአግባቡ መምራት፣ ለሁሉም የሚሰራ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን መፍጠር” የጠቅላላ ጉባኤው መሪ ሀሳብ ነው። በዚህ ዓለም አቀፍ መድረክ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ከፍተኛ ልዑካን ቡድን መሪ እና የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ያደረጉት ንግግር የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ አቋም፣ የልማት ጉዞ እና አህጉራዊ ራዕይ በሰፊው ያንጸባረቀ ነበር። የፕሬዝዳንቱ መልዕክት የኢትዮጵያን ፍላጎቶች ከዓለም አቀፉ ነባራዊ ሁኔታ ጋር ያጣጣመና የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ አቅጣጫ ግልጽ ያደረገም ጭምር ነው። ኢትዮጵያ 32ኛውን የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ-32) በታላቅ ዝግጅት እንደምታስተናግድ አብስረዋል። ይህ ጉባኤ ከንግድ ተቋማት እስከ ዓለም አቀፍ ባለድርሻ አካላት ድረስ ሁሉን አካታች እና ተጨባጭ መፍትሄዎችን የሚያመጣ እንዲሆን ኢትዮጵያ በቁርጠኝነት እንደምትሰራ አረጋግጠዋል። የአየር ንብረት ቀውሱን ለመከላከል ዓለም አቀፍ መሪዎች በኮፕ-32 ጉባኤ ላይ እንዲገኙ ጥሪ ያቀረቡት ፕሬዝዳንቱ፣ ሁሉም አካላት ታሪካዊ አሻራቸውን እንዲያሳርፉ አሳስበዋል። መልዕክታቸውም በኢትዮጵያ በ8 ዓመታት ውስጥ የተተከሉት 56 ቢሊዮን ችግኞች፣ ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ጥበቃ ላይ ንግግር ብቻ ሳይሆን በቢሊዮን የሚቆጠሩ ዛፎችን በመትከል ከፍተኛ የካርቦን የመምጠጥ አቅም የፈጠረች ሀገር መሆኗን በሚገባ ያሳየ ነው። የአየር ንብረት ርዕሰ ጉዳይን ተከትሎ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ እድገትና የባህር በር ጥያቄን በማንሳት ጠንካራ ሀሳቦችን አቅርበዋል። ጠንካራና የጸና ኢኮኖሚ ለመገንባት አስተማማኝ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የባህር በር ማግኘት ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል። የኢትዮጵያ የባህር በር ፍላጎት ከማንኛውም ሌላ ወገን ጥቅም ጋር የማይጋጭና ለቀጣናው ሀገራት የጋራ ፕሬዝዳንቱ የባህር በር ማግኘት የሌሎችን ጥቅም እንደማይጎዳና ሁሉንም ወገኖች ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ማብራራታቸው፣ ጥያቄው በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ህጋዊና ሰላማዊ የልማት ጥያቄ ሆኖ እንዲወሰድ ትልቅ እድል የሚፈጥር ነው። ዕድገትና ትብብር ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክት መሆኑን በግልጽ አስምረውበታል። ይህንን ፍላጎት እውን ለማድረግም ሀገሪቱ ያላትን የዲፕሎማሲ አማራጮች በሙሉ በመጠቀም ከዓለም አቀፍ የንግድ ሥርዓት ጋር ለመተሳሰር እየሰራች መሆኑንም ገልጸዋል። ይህም ኢትዮጵያ የባህር በር ማግኘት የሌሎችን ጥቅም እንደማይጎዳና ሁሉንም ወገኖች ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ማብራራታቸው፣ ጥያቄው በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ህጋዊና ሰላማዊ የልማት ጥያቄ ሆኖ እንዲወሰድ መንገድ ይከፍታል። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አወቃቀር ላይ ሀሳባቸውን የሰነዘሩት ፕሬዝዳንት ታዬ፣ አንድ ነጥብ ስድስት ቢሊዮን የሚሆኑ አፍሪካውያን ተገቢውን ፍትሃዊ ውክልና ማጣታቸው በአስቸኳይ ሊታረም የሚገባው የሞራል ጥያቄ መሆኑን ተናግረዋል። ተመድ የዓለምን ነባራዊ እውነታዎች ባገናዘበ መልኩ መሠረታዊ ሪፎርም ሊያደርግ እንደሚገባው አጥብቀው ያሳሰቡ ሲሆን፣ የአፍሪካን አህጉር በዓለም አቀፍ ውሳኔ ሰጪነት ውስጥ ማካተት የዘመኑ ግዴታ መሆኑን አብራርተዋል። እውነተኛ የፖለቲካ ፍላጎት ካለ የአፍሪካ ህዝቦች የረጅም ጊዜ የውክልና መነፈግ አግባብነት እንደሌለው ጠቁመው፣ ይህ ጉዳይ የትውልዱ ትልቁ የህሊና እና የሞራል ጥያቄ መሆኑን አመልክተዋል። የፕሬዝዳንቱ መልዕክት የአህጉሪቱን የጋራ አቋም የሚያጠናክር እና ኢትዮጵያ የቀደመች የተመድ መስራች አባልነቷን በመጠቀም የአፍሪካን ድምፅ በዓለም አቀፍ ደረጃ በግንባር ቀደምነት ተሞጋች ሆና እንድትቆም ያደርጋታል። ከምግብ ዋስትና አንፃር ኢትዮጵያ ያስመዘገበችው ስኬት ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ መልዕክት አስተላልፈዋል። በአጭር ጊዜ ውስጥ ከስንዴ አስመጪነት ወጥታ በአፍሪካ ግንባር ቀደም የስንዴ አምራች ሀገር መሆን የቻለችው ኢትዮጵያ፣ አፍሪካ በራሷ አቅም ራሷን መመገብ እንደምትችል በተግባር ማሳየቷን ተናግረዋል። በተጨማሪም የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በውሃ ሀብት አጠቃቀም ዙሪያ የጋራ ቀጣናዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ እንደሚቻል ያረጋገጠ ታላቅ ፓን-አፍሪካዊ ፕሮጀክት መሆኑን አንስተዋል። ኢትዮጵያ ከ60 ሺህ ሜጋዋት በላይ የኃይል ማመንጨት አቅም እንዳላት ጠቅሰው፣ በቅርብ ዓመታት ውስጥ ተጨማሪ ኃይል በማመንጨት የምስራቅ አፍሪካን የኢነርጂ ፍላጎት ለማሟላት እቅድ ይዛ እየተንቀሳቀሰች መሆኑን አብራርተዋል። ግድቡ የምስራቅ አፍሪካ የጋራ ብልጽግና እና የታዳሽ ኃይል ምንጭ ተደርጎ መቅረቡ የሀገሪቱን የልማት አተያይ ላይ መግባባት ለመፍጠርና የኢትዮጵያን ቀጣናዊ ተጽዕኖና ኢኮኖሚያዊ ትስስር የሚያጎላ ነው። በቴክኖሎጂ እና በዲጂታል አብዮት ዘመን አፍሪካውያን ተመልካች ብቻ ሳይሆን የለውጡ ባለቤት መሆን እንደሚገባቸው አጽንኦት ሰጥተዋል። የኢትዮጵያ የአምስት ሚሊዮን ኮደሮች መርሃ-ግብር እና የሰው ሰራሽ አስተውሎት ዩኒቨርሲቲ ግንባታ አህጉሪቱ ለዲጂታል ዘመን ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳዩ መሆናቸውን አስገንዝበዋል። በአካባቢ ጥበቃ ረገድም ባለፉት ዓመታት የተከናወነው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርም ከሀገር አልፎ ዓለም አቀፍ ትኩረት የሰበሰበ ስኬት መሆኑን አብራርተዋል። በስምንት ዓመታት ውስጥ 56 ቢሊዮን ችግኞች መተከላቸው የደን ሽፋንን ከማሳደግም በላይ ከፍተኛ መጠን ያለው ካርቦን የመምጠጥ አቅም በመፍጠር የዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ቀውስን ለመታገዝ የላቀ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። ኢትዮጵያ ሰብአዊ ክብርን በሚያስከብር፣ ፍትሕ በሚያሰፍን እና በነጻ ህዝቦች ጽኑ አብሮነት ላይ በተመሰረተ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲዋ ጸንታ እንደምትቀጥል ፕሬዝዳንቱ አረጋግጠዋል። በአጠቃላይ፣ የፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ንግግር ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ መድረክ መፍትሔ አመንጪ፣ የቀጣናው የኢኮኖሚ ትስስር መሪ እና የአፍሪካ ፍትሃዊ ውክልና ተሞጋች መሆኗን ያረጋገጠ መልዕክት ነው።
የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግርን እያረጋገጠ የሚገኘው አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ
Sep 24, 2026 108
የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ለሀገር የኢኮኖሚ እድገት፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራ እና ለውጭ ምንዛሬ ግኝት ዋና ማዕከል ነው። በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ታሪክ ውስጥ ዘርፉ የፖሊሲ እና መዋቅራዊ ፈተናዎች ሲያጋጥሙት የቆየ ቢሆንም፣ በየጊዜው በተወሰዱ የማሻሻያ እርምጃዎች፣ በኢንዱስትሪ ፓርኮች መስፋፋት እና በቅርብ ጊዜ በተጀመረው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም አማካኝነት ወደ አዲስ የስኬት እና የእድገት ምዕራፍ እየተሸጋገረ ይገኛል። 👉በኢንዱስትሪ ዘርፉ የነበሩ ፈተናዎች በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ዘርፉ ተገቢው እድገት እንዳይመዘገብ በርካታ መዋቅራዊ ችግሮች ነበሩበት። የአምራች ኢንዱስትሪዎች የጥሬ፣ የካፒታል ዕቃዎች እና የፋብሪካ ማሽኖች እንዲሁም የማሽኖች መለዋወጫዎች ግዢ በውጭ ምንዛሬ ላይ የተመሰረቱ ናቸው። የውጭ ምንዛሬ እጥረት ደግሞ የማምረቻ ዘርፉ ብቻ ሳይሆን ሀገሪቷ ትልቁ ፈተና እንደነበር ይታወቃል። ይህ የውጭ ምንዛሬ እጥረት በአምራች ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም ላይ ከፍተኛ ችግር ሆኖ ቆይቷል። ለኢንዱስትሪዎች ግብዓት የሚሆኑ የግብርና ምርቶች በሚፈለገው ጥራት እና መጠን አለመመረትም እንዲሁ አንዱ ተግዳሮት ሆኖ ይጠቀሳል። የግብርናው ዘርፍ ከኢንዱስትሪዎች ጋር ያለው የአቅርቦት ሰንሰለት በደላላ የተተበተበ፣ አምራቹንና ተቀባይ ኢንዱስትሪዎችን በቀጥታ ለማገናኘት እንቅፋት ሆኖ የቆየ ነበር። ከአቅርቦት ሰንሰለቱ መበታተን በተጨማሪ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ፣ የመንገድ እና የሎጂስቲክስ ቀልጣፋ አለመሆን የምርታማነት ወጪን ከፍ አድርጎት መቆየቱም ይነሳል። አዳዲስ የኢንዱስትሪ ባለሀብቶች እና ነባር ፋብሪካዎች ለማስፋፊያ የሚሆን የረጅም ጊዜ ብድር የማግኘት እድላቸው ጠባብ ሆኖ መቆየቱም እንዲሁ ፋብሪካዎች ሙሉ አቅማቸውን እንዳይጠቀሙ አድርጓል። 👉ከችግር ወደ መፍትሔ መዋቅራዊ ሽግግር እና የፖሊሲ ማሻሻያዎች ባለፉት ዓመታት በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርሙ በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ይታዩ የነበሩ ስር የሰደዱ መዋቅራዊ ችግሮችን ለማቃለል እና የዘርፉን የኢኮኖሚ ዋና አንቀሳቃሽነት ሚና ለማሳደግ የመደመር መንግስት በርካታ የፖሊሲ እና የተግባር እርምጃዎችን ወስዷል። አጠቃላይ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ የማምረት አቅም ከነበረበት 47 በመቶ ወደ 67 በመቶ ከፍ እንዲል ሰፊ ጥናቶችና የድጋፍ ስራዎች መከናወናቸውንና የወጪ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት የመተካት ስትራቴጂ ተግባራዊ መደረጉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 30ኛው መደበኛ ስብሰባ ላይ መግለጻቸው ዘርፉን ለማሳደግ መንግስት የወሰዳቸውን እርምጃዎች የሚያመላክት ነው። መንግስት ከነባሮቹ የኮምቦልቻ፣ የመቀሌ እና የሐዋሳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች በተጨማሪ አስር አዳዲስ የኢኮኖሚ ዞኖችን በመገንባት ከ80 በመቶ በላይ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን መሳብ መቻሉን መጥቀሳቸውም ይህንኑ ያስረግጣል። የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ምርቶች ዓለምአቀፍ ተወዳዳሪነትን የማሳደግና ለውጭ ገበያ የማቅረብ አቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ ማደጉን እንዲሁም የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ በሀገሪቷ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ላይ የላቀ ሚና እያበረከተ መምጣቱን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል መግለጻቸው እንዲሁ የዘርፉን ውጤታማነት ያረጋግጣል። በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው ምክንያት በተነደፈው በ”ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ ዘርፉን ከመቼውም ጊዜ በላይ በማነቃቃቱ ለወጪ ንግድ የሚሆኑ ምርቶችን በመጠንም ሆነ በጥራት በማሳደግ የውጭ መንዛሬ ግኝት ላይ ትርጉም ያለው እድገት ተመዝግቧል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ ከውጭ የምታስገባቸውን የተለያዩ ምርቶች በሀገር ውስጥ በማምረት ወደ ሀገር ይገቡ ለነበሩ ምርቶች ይወጣ የነበረውን የውጭ ምንዛሬ ማዳን የተቻለበት አቅምም ተፈጥሯል። ኢትዮጵያ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን መሳብ የሚያስችሉ መሰረተ ልማቶችን ከማሟላት በተጨማሪ የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ስርዓትን በመዘርጋት የሀገር ውስጥ እና የውጭ ባለሀብቶችን በኢትዮጵያ ኢንቨስት የማድረግ ተነሳሽነት ማሳደግና ውጤት ማስመዝገብ አስችሏታል። በተለይ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በተገነቡ የኢንደስትሪ ፓርኮች በተፈጠሩ የኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታዎችና በተሟሉ መሰረተ ልማቶች ተጠቅመው ምርቶቻቸውን ለውጭ ገበያ እያቀረቡ የሚገኙ አምራቾች ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደጉ መምጣታቸውን መረጃዎች ይጠቁማሉ። እነዚህ የኢንዱስትሪ ፓርኮች የውጭ ኢንቨስትመንትን በመሳብ፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር በማምጣትና ለዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠር በኩል ትልቅ ሚና እየተጫወቱም ይገኛሉ። ፓርኮቹ የተቀናጀ መሰረተ ልማት እና ደረጃቸውን የጠበቁ አሰራሮች በማቅረብ ባለሀብቶች በፋብሪካ ግንባታ ላይ የሚያባክኑትን ጊዜ ቀንሰዋል። 👉የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ትሩፋቶች የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በኢትዮጵያ የማኑፋክቸሪንግ እና የኢንዱስትሪ ዘርፍ ላይ የተደቀኑ ችግሮችን ለመፍታት፣ የሀገር ውስጥ ምርታማነትን ለማሳደግና ኢንዱስትሪውን የኢኮኖሚው ዋና አንቀሳቃሽ ለማድረግ የተጀመረ ሀገራዊ ንቅናቄ ሲሆን አጠቀላይ በዘርፉ ያሉ ተግዳሮችን በመቅረፍ በኩል ጉልህ አስተዋጽኦ አበርክቷል። በዚህም ኢንደስትሪዎች ሲገጥማቸው የነበሩ የመሬት፣ የኃይል እና የፋይናንስ ችግሮችን በመፍታት የማምረት አቅማቸውን ወደ ከፍተኛ ደረጃ ማሸጋገር ተችሏል። በጨርቃጨርቅ፣ በቆዳ፣ በሲሚንቶ፣ በኬሚካል፣ በምግብ እና መጠጥ ዘርፎች የሚመረቱ የሀገር ውስጥ ምርቶች ከውጭ የሚገቡትን በመተካት ከፍተኛ ሀገራዊ ወጪን አስቀርተዋል። ሲሚንቶ፣ ብረት፣ ብርጭቆ እና ሴራሚክስን የመሳሰሉ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በማምረት ብቻ ወደ 5 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የውጭ ምንዛሬ መቆጠብ መቻሉን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ዘርፉ እያስመዘገበ ባለው ፈጣን እድገትም በማዕድን ዘርፍ 24 በመቶ፣ በማኑፋክቸሪንግ 20 ነጥብ 3 በመቶ እና በኢነርጂ ዘርፍ ደግሞ 23 በመቶ ጭማሪ መታየቱን ማንሳታቸው ዘርፉ በተደረገለት ድጋፍ ወደ ውጤታማነት መሸጋገሩን ያሳያል። በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና በባለሃብቶች መካከል የተደረጉ ተከታታይ ውይይቶች በዘርፉ የሚስተዋሉ ማነቆዎችን የሚፈቱ ትልልቅ ውሳኔዎች እንዲወሰኑ አስችለዋል። የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የሀገር ውስጥ ምርቶች ዕድገት እንዲጨምር አስችለዋል፤ የአምራቾችና የሸማቾችን ትስስር አጠናክረዋል እንዲሁም የህብረተሰቡን የሀገር ውስጥ ምርት የመጠቀም ባህል አሳድገዋል። በአጠቃላይ ንቅናቄው አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ከነበረበት ፈተና ተላቆ ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል። 👉የሀገር በቀል የማክሮ ኢኮኖሚ እና የፋይናንስ ዘርፍ ሪፎርም በኢትዮጵያ የተደረጉ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያዎችና የውጭ ምንዛሬ አስተዳደር ስርዓት ለወጥ የኢንዱስትሪው ዘርፍ የነበረበትን የውጭ ምንዛሬ እጥረት ለማቃለል፣ የውጭ ኢንቨስትመንትን ለመሳብና የሀገር ውስጥ አምራቾች ጥሬ ዕቃዎችን በነፃነት እንዲያስገቡ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል። 👉የግብርና እና ኢንዱስትሪ ትስስር በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ትስስር ለዘላቂ እድገት፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራ እና ለውጭ ምንዛሬ ግኝት ዕድገት መሠረታዊ ምሰሶ ናቸው። ግብርናው ለኢንዱስትሪው ጥሬ ዕቃ የሚያቀርብ ሲሆን፣ ኢንዱስትሪው ደግሞ የግብርና ምርቶችን እሴት በመጨመርና መልሶ ለግብርናው ዘርፍ ግብዓቶችን በማቅረብ ባለሁለት ወገን ትስስር ይፈጥራሉ። 👉በተወሰዱ እርምጃዎች የተመዘገቡ ውጤቶች የመደመር መንግስት እና ባለድርሻ አካላት የኢንደስትሪ ዘርፉን ውጤታማነት ለማሳደግ ባደረጉት የተቀናጀ ጥረት እና በተወሰዱ መዋቅራዊ ማሻሻያዎች የፋብሪካዎች የማምረት አቅምን 67 በመቶ ማድረስ ተችሏል። ይህ ቀደም ሲል 30 እና 40 በመቶ ከነበረው የፋብሪካዎች የማምረት አቅም አንጻር ሲታይ ከፍተኛ ለውጥ መምጣቱን የሚያመላክት ነው። ኢትዮጵያ በመደመር እሳቤ በመመራት ባለፉት ዓመታት የኢንደስትሪ ዘርፏን ለማሳደግ በርካታ ተግባራትን በማከናወን እና የማሻሻያ እርምጃዎችን በመውሰድ በዘርፉ እምርታዊ ውጤት አስመዝግባለች። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የ2018 “ኢትዮጵያ ታምርት” ኤክስፖን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልእክት በውጤት ተኮር አመራር ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ መልኩ የኢንዱስትሪ መስፋፋት መንጸባረቁን መናገራቸው ይህንኑ የሚገልጽ ነው፡፡ እመርታውን በተጨባጭ ማሳያ ሲያቀርቡም የአምራች ኢንዱስትሪዎችን አማካይ የማምረት አቅም ከ47 በመቶ ወደ 67 በመቶ ከፍ ማድረግ መቻሉን፣ ከ2 ሺህ 800 በላይ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንቶችን መሳብ መቻሉን እንዲሁም አዳዲስ ኢንዱስትሪ ፓርኮች መገንባታቸውንና በሀገር ውስጥ ምርትን በማስፋፋት እስከ 5 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የውጭ ምንዛሬ መቆጠቡን መግለጻቸውም እንዲሁ። የመደመር መንግስት በአምራች ኢንዱስትሪዎች ላይ ይስተዋል የነበረውን የፋይናንስ ማነቆ ለመፍታት በወሰደው እርምጃ፣ ቀደም ሲል 40 ቢሊዮን ብር የነበረውን የብድር መጠን ወደ 115 ቢሊዮን ብር ከፍ ማድረግ መቻሉንና የኢንዱስትሪዎችን ተወዳዳሪነት፣ ምርታማነት፣ ትርፋማነት እና የመስፋፋት ዕድል ከፍ እያለ መምጣቱን የኢንደስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል መግለጻቸው የመንግስት ውሳኔዎች ውጤታማነትን የሚያረጋግጡ ናቸው። የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ የንግድ ሚዛንን በማጣጣም በኩል ያለውን አስተዋጽኦ ሲገልጹም የኢትዮጵያን ዘላቂ ተወዳዳሪነት ለማረጋገጥ ከፍተኛ ድርሻ አበርክቷል። በዚህ መነሻነትም መንግስት በ2019 በጀት ዓመት ከወጭ ንግድ የሚገኘውን ገቢ ወደ 1 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ዕቅድ ነድፎ ለስኬታማነቱ እየታተረ ይገኛል። እነዚህ የፖሊሲም ሆነ ሌሎች የመንግስት እርምጃዎች በሙሉ የዘርፉን ውጤታማነት ለማሳደግ ያለውን ቁርጠኝነት ያረጋግጣሉ። 👉ማጠቃለያ የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ጉዞ ከብዙ መሰናክሎች በኋላ በተለይ የመደመር መንግስት ለዘርፉ በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት እና በወሰዳቸው የፖሊሲና የመዋቅራዊ ማሻሻያ እርምጃዎች፣ የሀገር ውስጥ ምርታማነትን በማስቀደም በሂደት ወደ ጠንካራ መዋቅር እየተሸጋገረ ይገኛል። አሁን የተጣጣሙት የፖሊሲ እርምጃዎች እና የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎች ተጠናክረው ሲቀጥሉ፣ ዘርፉ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በጽኑ መሰረት ላይ በመገንባት በአፍሪካ የማኑፋክቸሪንግ ማዕከል የሚያደርግ ትልቅ አቅም አለው።
አዲስ መንግሥት፣ የላቀ ድል!
Sep 23, 2026 146
ኢትዮጵያውያን በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በድምጻቸው ይሁንታ የሰጡት ፓርቲ መንግሥት የሚመሰርትበት ቀን ይፋ ሆኗል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ዛሬ ይፋ እንዳደረጉት፤ በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 58 ንዑስ አንቀጽ 2 የምክር ቤቱ የሥራ ዘመን በመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ እንደሚጀመር በተደነገገው መሠረት፣ የመንግሥት ምስረታውና የምክር ቤቱ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም ይከናወናል። በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 56 መሠረት በምክር ቤቱ አብላጫ መንበር ያገኘው የፖለቲካ ፓርቲ የፌደራሉን ሕግ አስፈጻሚ አካል የሚያደራጅ ሲሆን፣ በሕዝብ የተመረጠው አዲሱ ሕግ አስፈጻሚ አካል በዕለቱ በይፋ ኃላፊነት ይረከባል። ይህም የፖለቲካ ሕጋዊነትን በጽኑ መሰረት ላይ የመገንባት እና ተቋማዊ ሽግግርን በተሳካ ሁኔታ የማረጋገጥ ሀገራዊ እርምጃ ነው። ኢትዮጵያ ወደ እዚህ ታሪካዊ ምዕራፍ ለመሸጋገር በርካታ መንገዶችን ተጉዛለች። ከ54 ሚሊዮን በላይ መራጮች፤ 42 የፖለቲካ ፓርቲዎችና 10 ሺህ 438 ዕጩዎች የተሳተፉበት ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ደግሞ በዚህ ረገድ በጉልህ የሚጠቀስና የኢትዮጵያ የማድረግ አቅም የተገለጸበት ሀገራዊ ሁነት ነው። ምርጫው በትልቅነቱ ብቻ ሳይሆን በትርጉሙም ኢትዮጵያ በቀጣናው ታላቅ ሀገር መሆኗን በተግባር ያሳየ ነው። ውስብስብ ሂደት የሚጠይቀውን ይህንን ምርጫ ነጻ፣ አሳታፊ፣ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን አድርጋ በውጤታማነት ያጠናቀቀችበት ሂደትም በበርካቶች አድናቆት የተቸረው ስኬት ነው። ከሀገራዊ ድንበር ባሻገር፣ ኢትዮጵያ በምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና የምትጫወተው የጂኦ-ፖለቲካዊ ሚና ከፍተኛ እንደመሆኑ መጠን፣ በሀገሪቱ የተካሄደው ዴሞክራሲያዊ ምርጫ የቀጣናውን የፖለቲካ መረጋጋት የሚያጎለብት ታላቅ አወንታዊ ምልክት ነው። አሁን ደግሞ ኢትዮጵያ ሕገ መንግሥቱን መሠረት በማደረግ አዲስ መንግሥት በመመስራት ወደ ሥራ ለመግባት ቀን ቆርጣ ዝግጅቷን አጠናቃለች። መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም የሚመሰረተው አዲስ መንግሥት ከ130 ሚሊዮን በላይ ከሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር አዲስ ማህበራዊ ውል (Social Contract) የሚፈጸምበት ታሪካዊ ምዕራፍ ነው። አዲስ መንግሥት መመሥረቱ ደግሞ የታቀዱ ታላላቅ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን፣ መዋቅራዊ ለውጦችን እና የልማት ፕሮጀክቶችን በሙሉ ራስ መተማመን ለማስፈጸም ተጨማሪ ዕድልና ጉልበት ይፈጥራል። ለ2019 በጀት ዓመት የሚውል 2 ነጥብ 34 ትሪሊዮን ብር የፌዴራል መንግሥት በጀት በይፋ መጽደቁ ይታወሳል። ይህ በጀት በሀገር ውስጥ የሚመነጭ ኢኮኖሚን በማጠናከርና የውጭ የንግድ ብድርን በመቀነስ ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ የሀገር ውስጥ ጠቅላላ ምርት (GDP) ዕድገት ተጠናክሮ እንዲቀጥል መሠረት እንደሚጥልም ታምኖበታል። እየተተገበሩ ያሉ የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃዎች፣ የዋጋ ንረትን ባለ አንድ አሃዝ ለማድረስ የተጀመረው ጥረት ውጤት እያደረጉ ሲሆን ማሻሻያዎቹ እንደሚቀጥሉም ይጠበቃል። ለሴቶችና ለገጠር ማኅበረሰብ የሚደረጉ የሥራ ዕድል ፈጠራና የኑሮ ማሻሻያ ስራዎች፤ የቤት እጥረት ችግርን ለመቅረፍ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ መኖሪያ ቤቶችን የመገንባት እና የኃይልና የመስኖ ማመንጫ ፕሮጀክቶችን ሙሉ በሙሉ የማጠናቀቅ ሥራዎችም በአዲሱ መንግሥት ከሚጠበቁ ስራዎች መካከል ይጠቀሳሉ። የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታን እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ ተደራሽ ማድረግ እንዲሁም ዜጎች ቀልጣፋ የመንግሥት አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ በቢሮክራሲ የሚፈጠሩ እንግልቶችን ማስወገድና ጊዜን ወደ ምርታማነት መቀየር የአዲሱ ዘመን መለያ እንደሚሆን ይጠበቃል። ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲው መስክ ያገኘቻቸውን ስኬቶች የማስቀጠል እንዲሁም የኮፕ 32 የዝግጅት ሂደትም ሌላኛው የትኩረት መስክ ይሆናል። ኮፕ 32 የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ዲፕሎማሲ ስኬቷን የሚያሳይ ሲሆን፤ በቀይ ባሕር እና በዓባይ ወንዝ ፍትሐዊ አጠቃቀም ላይ ሰላማዊና ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶቿ ተጠናክረው ይቀጥላሉ።
ትንታኔዎች
የሌማት ትሩፋት- ከምግብ ዋስትና እስከ ዘላቂ ምርታማነት
Sep 24, 2026 155
የሌማት ትሩፋት በዋናነት የእንስሳት ተዋጽኦ ምርቶችን ማለትም ወተት፣ ሥጋ፣ እንቁላልና ማርን በስፋት በማምረት የኢትዮጵያን የምግብ ሉዓላዊነትና የሥርዓተ-ምግብ ዋስትና ማረጋገጥን አላማ በማድረግ እየተተገበረ ያለ ሀገራዊ ኢኒሼቲቭ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሌማት ትሩፋትን በጥቅምት ወር 2018 ዓ.ም በአርባምንጭ ከተማ በይፋ አስጀምረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክት በምግብ ራስን አለመቻል የሀገርን ክብር እንደሚነካና፣ ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን ካልቻለች ሙሉ ነፃነት ሊኖራት እንደማይችል ገልጸዋል። በስንዴ ምርት የታየውን ስኬት በሌማት ትሩፋት መደገም እንዳለበትም አሳስበዋል። ጤናማና አምራች ትውልድ ለመፍጠርም ሀገራዊ ሌማታችንን በተመጣጠነ ምግብ ማሟላት እንደሚገባ አብራርተዋል። የሌማት ትሩፋት ዋና ግብ በቤተሰብ ደረጃ የተመጣጠነ ምግብን ተደራሽ በማድረግ የህፃናት መቀንጨርን መቀነስ፣ ለወጣቶችና ለሴቶች ሰፊ የሥራ ዕድል መፍጠር፣ እንዲሁም የዜጎችን ኑሮ ማሻሻል መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። ይህ ሀገራዊ መርሐ ግብር የተለያዩ እና አጋዥ የሆኑ የትኩረት መስኮችን ይዞ መንቀሳቀሱን ቀጥሏል። የወተት ላሞችን ዝርያ በማሻሻል የወተት ምርትን ማሳደግ፣ የዶሮ ሥጋና እንቁላልን በቤተሰብ ደረጃ ተደራሽ ማድረግ፣ እንዲሁም ዘመናዊ ቀፎዎችን በመጠቀም የማር ጥራትና ምርት መጨመር ቁልፍ ምሰሶዎች ናቸው። ከዚህ ጎን ለጎንም ግብርናንና የእንስሳት እርባታን የከተማ ግብርና አካል የማድረግ ሰፊ የንቅናቄ እንቅስቃሴ መፈጠሩ ትልቅ መሻሻል ነው። የዶሮና የእንቁላል ምርት በከፍተኛ ሁኔታ ማደጉ ብቻ ሳይሆን፣ በብዙ ክልሎች የወተት ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎችና የመሰብሰቢያ ማዕከላት በስፋት ተስፋፍተዋል። የሌማት ትሩፋት ለወጣቶችና ለሴቶች ሰፊ የሥራ ዕድል በመፍጠር አስተማማኝ የገቢ ምንጭ ሆኗል። አርሶ አደሩ ከመደበኛው የሰብል ምርቱ በተጓዳኝ በየዕለቱ ገቢ ማግኘት መቻሉ የኑሮ ደረጃውን በከፍተኛ መጠን እንዲያሻሽል አግዞታል። በፕሮቲን በበለጸጉ ምግቦችን በተለይም እንቁላልና ወተትን ለህጻናትና ለነፍሰ ጡር እናቶች ተደራሽ በማድረግ ረገድ አበረታች ለውጦች ታይተዋል። በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የአንድ ቀን ጫጩቶች፣ ዝርያቸው የተሻሻሉ የወተት ላሞችና ዘመናዊ የንብ ቀፎዎች ለአርሶ አደሩና ለከተማ ነዋሪው ተደራሽ መደረጋቸው ተችሏል። ይህም ቀደም ሲል በግዢ ብቻ ይሟሉ የነበሩ የምግብ ምርቶች አሁን ላይ በብዙ ቤተሰቦች ጓሮ በራሳቸው እንዲመረቱ አድርጓል። ይህ ተሞክሮ በቤተሰብ ደረጃ የፕሮቲን አቅርቦትን በማሳደግ በሕፃናት ላይ የሚታየውን የምግብ እጥረትና መቀንጨር ለመቀነስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። በተለይም የከተማ ግብርናን በማስፋት ነዋሪው በውስን ቦታ ምርታማ መሆን እንደሚችል በተግባር የታየበትና በምግብ ራስን የመቻል ጉዞ ተስፋ ሰጪ ውጤቶች ታይተዋል። በተጨማሪም ጥራት ያለው የማርና የሥጋ ምርት ለውጭ ገበያ ለማቅረብ የተጀመሩ ጥረቶች የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ ግኝት ለማሳደግ አዲስ በር ከፍተዋል። የሌማት ትሩፋት ኢትዮጵያ በምግብ ራስን ለመቻልና የዜጎቿን የአመጋገብ ሥርዓት ለማሻሻል የጀመረችው ስትራቴጂካዊ ጉዞ ዋና አካል ነው። መርሐ ግብሩ ከመነሻው አንስቶ በምርት ዕድገት፣ በሥራ ዕድል ፈጠራና በሥራ ባህል ለውጥ ረገድ እጅግ ተስፋ ሰጪ ውጤቶችን አሳይቷል። ይህ ንቅናቄ በተለይ የእንስሳት ተዋጽኦን በየጓሮውና በየቤቱ ተደራሽ በማድረግ በሕፃናት ላይ የሚታየውን የመቀንጨር ችግር ለመቅረፍ አስችሏል። እንዲሁም አነስተኛ አምራቾችን የዕለት ገቢ ባለቤት በማድረግ የኢኮኖሚ አቅማቸውን እንዲገነቡ አድርጓል። በአጠቃላይ የሌማት ትሩፋት ኢትዮጵያ በታሪክ አጋጣሚዎችና በተለያዩ ውጫዊና ውስጣዊ ምክንያቶች የሚገጥሟትን የምግብ ዋስትና ተግዳሮቶች በጽናት ለመቀልበስ መንግስት ተግባራዊ ካደረጋቸው ቁልፍ ስራዎች መካከል አንዱ ማሳያ ነው። መርሐ ግብሩ የሀገሪቱን ነባር ችግሮች ወደ ታላቅ የኢኮኖሚ እድል በመቀየር ረገድ እጅግ የላቀ ድርሻ እያበረከተ የሚገኝ ሲሆን፣ ለዘላቂ ብልጽግና መሠረት የሚጥል ታላቅ ብሔራዊ ስኬትም ነው።
ስንዴ ከመሸመት ወደ ላኪነት - የኢትዮጵያ የአምራችነት ማሳያ
Sep 23, 2026 287
በኢትዮጵያ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከፍተኛ እመርታ ካስመዘገቡ የግብርና ዘርፎች አንዱ የስንዴ ምርት ነው ። የራሷን ፍጆታ በስንዴ ምርት ማሳካት ባለመቻሏ ለረጅም ጊዜ ከውጭ ታስገባ የነበረችው ኢትዮጵያ ዛሬ ላይ ይሄንን ጉዳይ ወደ ታሪክነት ቀይራዋለች። በየዓመቱ እስከ አንድ ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወጭ በማድረግ የስንዴ ምርትን ወደ ሀገር ውስጥ ስታስገባ የነበረው ታሪክም እንዲሁ ተለውጧል። የተለመደውን አካሄድ የቀለበሰና የስንዴ ልማቱን በውጤት ያጀበው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ኢኒሼቲቭ ስንዴን በበጋና በክረምት በስፋት በማልማት የሃገር ውስጥ ፍጆታ በማሟላት የዜጎችን የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ እንዲሁም ስንዴን ከውጭ ለማስገባት የሚወጣውን የውጭ ምንዛሪን በማዳን በስንዴ ልማት ላይ በትኩረት በመሰራቱ ተጨባጭ ውጤት ተመዝግቧል፡፡ ቀደም ሲል በአነስተኛ ማሳና በተበጣጠሰ መልኩ ይከናወን የነበረውና የክረምት ዝናብ ጥገኛ የነበረው የምርት ሒደት አሁን ላይ ሙሉ ለሙሉ በሚባል መልኩ ተቀይሮ የመስኖ ስንዴ በአብዛኛው የሃገሪቱ አካባቢዎች የሚከናወን መደበኛ ስራ ሆኗል። ከዚሁ ጎን ለጎን ማሳዎች ከተለመደው ኋላ ቀር የግብርና ዘዴዎች በመላቀቅ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎችም እየተተገበሩባቸው ነው። የተሻሻሉ ዝርያዎችን ከመጠቀም ባለፈ የግብርና ሜካናይዜሽን ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችን ለመሸፈን የሚያስችል አቅም እንዲፈጠር አድርጓል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ የስንዴ ፕሮግራም ምርታማነትን በመጨመር፣ የመስኖ ሥርዓትን በማስፋት፣ የዘር አቅርቦት ሥርዓትን በማጠናከር ብሎም በዋና ዋና አካባቢዎች አነስተኛ አርሶ አደሮችን በመደገፍ የሀገራችንን ራስን የመቻል ጉዞ ግብ ላይ የተመሠረተ ነው ማለታቸው ይታወሳል። በምስራቅ ሐረርጌ ቆላማ አካባቢዎች እየለማ የሚገኝ የበጋ ስንዴ ልማትን በጎበኙበት ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት መሬት ጦም ማደር የለበትም ብለን አስበን የጀመርነው ስራ እያስገኘ ያለው ፍሬ በጣም ተስፋ ሰጪ ነው ማለታቸው አይዘነጋም። በስንዴ ልማት የተገኘው እመርታ ፈጣን እና አስደማሚም ነው። በጣም ዝቅተኛ የነበረው የስንዴ ማሳ የመስኖ ሽፋን ከጊዜ ወደ ጊዜ ፈጣን እድገት እያሳየ ነው ። ለምሳሌ በ2012 ዓ.ም 20 ሺህ ሄክታር ብቻ በነበረው የመስኖ ስንዴ ልማት 600 ሺህ ኩንታል ምርት ተሰብስቦ ነበር። ይሄ ግን በጥቂት ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ ለውጥ ከማስመዝገቡም በላይ ምርታማነትን በተጨባጭ ለውጦታል ። የመስኖ ስንዴ ልማት በ 2017 ዓ.ም. ምርት ዘመን ወደ 3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሔክታር ያደገ ሲሆን ከ 128 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት መገኘቱንም የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። ይሄ እንግዲህ የስንዴ የመስኖ ልማቱ ማሳያ ነው የመኸር ምርቱንም ስንመለከት በ2012 ዓ.ም ከነበረበት 1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ሄክታር በ2017 ምርት ዘመን ወደ 4 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሄክታር ማደጉን ያሳያል። በምርት ረገድም ከ53 ሚሊዮን ኩንታል ወደ 152 ሚሊዮን ኩንታል ከፍ ማድረግ ተችሏል። በአጠቃላይ በ2017 በጀት ዓመት በስንዴ የለማ መሬት 7 ነጥብ 8 ሚሊዮን ሄክታር በመሸፈን 280 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ተመርቷል፡፡ በዚህም መሰረት ኢትዮጵያ በየዓመቱ ከውጭ ለምታስገባው ስንዴ ታወጣ የነበረውን የውጭ ምንዛሬም ሙሉ በሙሉ ማዳን ተችሏል። በስንዴ ምርት ራስን የመቻል ስኬታማ ኢኒሼቲቭ ላደረጉት መሪነት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጣሊያን ሮም የተከበረውን የአለም የምግብ እና እርሻ ድርጅት አግሪኮላ ሜዳሊያ ሽልማት ጥር 19 ቀን፣ 2016 ዓ.ም ማግኘታቸው ይታወሳል።
ሀገር ያጸና ጀግና የመከላከያ ሠራዊት!
Sep 23, 2026 257
ኢትዮጵያውያን አገራቸውን የሚያዩበት መነጽር እጅግ ልዩ ነው። የገዘፈ ምስል በታላቅ ግርማ ሞገስ የሚመለከቷትን አገራቸውን በታላቅ የሀሳብ ልዕልና አክብረው፣ አስከብረውና እያከበሩት የሚኖሩት ምሰጢሩ የሚመነጨው በአእምሯቸው ካለው ሀገራዊ ምስል ነው። በታላቅ የሀሳብ ልዕልና የተገነባ የአገር ፍቅር ከጥንት ጀምሮ ያለ፣ የሚኖርና ለዘመናት የሚዘልቅ ነው። ይህ የኢትዮጵያዊነት መሰረት ነው እንግዲህ አገራቸውን በሉዓላዊነት ጠብቀው እንዲኖሩ ያደረገው። የጀግንነት ምስጢራቸው እና የነጻነት ልዕልናቸው ከዚህ በቀላሉ ከማይነካ ትስስራቸው የሚመነጭ ነው። የውጭ ጠላቶቻቸው ጦር ሰብቀው፣ ገስግሰውና “ድል የእኛ ነው” ብለው ሲመጡም አፍረውና ተዋርደው እንዲመለሱ የሚያደርጋቸው በጠንካራ መሰረት ላይ በተገነባው የሀገር ፍቅር ስሜታቸው፣ በደምና ባጥንታቸው መከታ ነው። ደርቡሽ ቢመጣ አፍሮ የተመለሰው፣ ግብጽ ጦሯን አሰልፋ አገር ለመውረር ደጋግማ ብትመጣ አፍራና ተሸማቃ የሄደችው በኢትዮጵያዊያን ጠንካራ ክንድ ነው። ጣሊያን የቀኝ ገዥነት ህልሙን እውን ሊያደርግ በወቅቱ በያዛቸው ድንቅ መሳሪያዎች ተማምኖ ባሕር አቋርጦ ገስግሶ ቢመጣም፣ በአራት ሰዓታት ውጊያ ዓለምን ባስደመመ ቅጽበት ድል ተነስቶ፣ ወታደሮቹ ሞተው፣ ከፊሎቹ ተማርከው የተመለሱት በጀግንነት በተዋጓቸው ኢትዮጵያዊያን ነው። ይህ የታሪክ ልዕቀት የተመዘገበው ነገሮች አልጋ ባልጋ ሆነው አይደለም። ለአብነት ያህል፣ አስደናቂው የዓድዋ ድል ሲመዘገብ ኢትዮጵያውያን በውስጥ የራሳቸው ችግር ነበረባቸው፤ ረሃብ ያስከተለው ድርቅ ሀገራዊ ችግሩን አግዝፎት ነበር። ይህ እውነታ ግን ለኢትዮጵያውያን አንድነትና ጠላትን ድል ለመንሳት አላገዳቸውም፤ ነጻነታቸውን አስቀጥሎ ለማስኬድም ተግዳሮት አልሆነም። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት “ኢትዮጵያ የሚለው ስም ከነፃነት፣ ከክብር፣ ልቆ ከመታየት፣ ስለ ሀገር፣ ስለ ህዝብ ራስን ከመሰዋት ጋር በቀጥታ የተያያዘ ነው” በማለት የኢትዮጵያዊያንን አንድነትና ለሀገራቸው መስዋዕት ስለመሆን ያላቸውን ቁርጠኝነት አመላክተዋል። የኢትዮጵያውያን ጀግንነት መገለጫው በውስጣቸው እርስ በርስ በሃሳብ ሊለያዩ፣ ሊጋጩና አንዱ ሌላውን ሊቆጣ ይችላል፤ ይህ ተፈጥሯዊ ነው። ሆኖም ጠላት ሲመጣ የራሳቸውን የውስጥ ችግር ወደ ጎን በመተው ለአንድ ዓላማና ግብ ወደ ፊት ይገሰግሳሉ። ሌላውን የማሸናፍ ምስጢራቸው የሚፈለቀቀው ከዚህ እውነት ነው። የቅርቡን የሱማሊያ ወረራ መነሻ እንኳን ብንወስድ፣ “ኢትዮጵያውያን በለውጥ ማዕበል እየተመቱ ነው፣ በሰሜን ችግር አለባቸው፤ ስለዚህ ወረራ በመፈጸም እናጥቃ፣ አዋሽን እንሻገር” በሚል የተሳሳተ ስሌት የተጀመረውን ጦርነት ኢትዮጵያውያን ከአርሶ አደር እስከ ተማሪ በአንድነት በመዝመት ድል ነስተው አስወጥተውታል። ይህ ሲባል ግን ባንዳ አልተፈጠረም፣ የሀገሩን ጥቅም ለግልም ሆነ ለቡድን ፍላጎት አሳልፎ የሚሰጥ የለም ማለት አይደለም። “በታሪካችን በሙሉ ግን ሊነኩን የመጡትን ከቅርብም ከሩቅም አሳፍረን መመለስ ደግሞ ተግባራችን፣ መገለጫችንና ማንነታችን ነው። አንነካም፤ ከመጡብን ግን ማንንም፣ ማንንም በኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ክብር አንደራደርም። ማንም ኢትዮጵያን መድፈር ቢፈልግ አንዴ ሳይሆን አስር ጊዜ ማሰብ ይኖርበታል፤ ምክንያቱም ኢትዮጵያውያን የምንችለው አንዱና ትልቁ ነገር ራሳችንን መከላከል ነው” በማለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ያስቀመጡትን ሀሳብ እዚህ ላይ ማንሳት ይቻላል። የኢትዮጵያውያን የጦር ውሎ ጀግንነት ለሀገራቸው ካላቸው ቀናኢ የሀሳብ ልዕልና የሚመነጭ ነው። ለእነርሱ ሀገር ማለት ልዩ ትርጉም አለው። ከሁሉም ነገር በላይ የገዘፈና ጠንካራ መገለጫ ያለው፣ ጠላቶች መጥተው ሲጋጩት ተሰባብረው የሚበታተኑበት ልዩ ምስጢር ያለው ነው። የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት በመዳፈር፣ እንድትበታተን በመስራት ታሪክ ሊያደርጓት ብዙዎች ጥረዋል። ነገርግን ጠላቶቿ የተላተሟት የገዘፈ ልዕለ ሀሳብ ከሚመራው ኢትዮጵያዊ ጋር ነው። ድል ነስቷቸው የሚመለሱትም ይህንን ግዝፈት ቀለል አድርገው በማየታቸው ነው። የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በአንድ ወቅት እንደገለጹት፤ ታሪካዊና ወቅታዊ ጠላቶቻችን ሀገራችንን ከምስራቅ አፍሪካ ካርታ ለማጥፋት ለዘመናት ቢሞክሩም አልቻሉም። ይህ የታሪክ ድርሳናት የሰነዱት ጠንካራ የሉዓላዊነት ልዕለ ሀሳብ ከሊቅ እስከ ደቂቅ የሚገዛለት መሆኑን የተረዱት ጠላቶች፣ ለራሳቸው ጥቅምና ለቡድን ፍላጎት የተንበረከኩ፣ ራሳቸውን ለጥቅም አሳልፈው በሰጡ ባንዳዎች በኩል እጃቸውን አስረዝመው መምጣታቸው አልቀረም። 21ኛው ክፍለ ዘመን ዓለም እጅግ በተሳሰረችበትና ጥብቅ ግንኙነት በፈጠረችበት ምህዳር ላይ፣ ጠላቶቻችን አልተኛም ብለው ስምሪት በሰጧቸው ባንዳዎች በኩል እየመጡ ነው። “ስለዚህ በእጅ አዙር መዋጋትን መርጠው በራሳችን ባንዳ ልጆች እየሞከሩ ነው። ምክንያት እየደረደረ ጫካ የገባው ባንዳ፣ ስደተኛ ባንዳ እና ሰርጎ ገብ ባንዳ የገዛ ሀገሩን አደጋ ላይ ለመጣል የሚወራጨው፣ በታሪክ የለመደውን የውጭ ጠላቶች ጉዳይ ተጭኖ ኢትዮጵያን የማዳከምና የማፍረስ ተግባር መተዳደሪያው ስላደረገው ነው።" በማለት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የገለጹት ሐሳብ የኢትዮጵያ ጠላቶች በቀጥታ ሳይሆን በእጅ አዙር ለመውጋት ተኝተው እንደማያድሩ ማረጋገጫ ነው። ዛሬ ኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሏን በሪፎርም ጠንካራና የማይበገር በማድረግ ለማንኛውም ጉዳይ ዝግጁ አድርጋለች። የመከላከያ ኃይሏን ዘመኑን በሚዋጅ ዘመናዊነት እየገነባች ነው። ሰላሟን ለማረጋገጥና በአስተማማኝ ኃይል ላይ ለመሆን ኢኮኖሚዋን እያሳደገች ነው። ከውጭው ዓለም ጋር ያላት የዲፕሎማሲ ግንኙነትም በከፍታ ላይ ይገኛል። የመከላከያ ሰራዊት በተግባር የተፈተሸ ኃያልነቱን ያረጋገጠ፣ የማድረግ አቅሙን ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋገረ፣ በጠላት ፊት ጀርባውን መስጠት የሚባል ታሪክን የማያውቀው እና አስደናቂ ታሪክ በደሙ የጻፈና የሚጽፍ የማይበገር ኃይል ያለበት ነው። መከላከያ ሰራዊት በየትኛውም ቦታና ጊዜ ከመንግስት፣ ከህዝብና ከተቋሙ የሚሰጡትን ማንኛውንም ግዳጅ ከትናንት በላይ በሆነ በላቀ ደረጃ ለመወጣት በከፍተኛ ዝግጁነት ላይ ይገኛል። ዛሬ ጠላቶቻችንና እግራቸው ስር ሆነው ለሚላላኩት የምንለው፦ “ኢትዮጵያን ተዋት፤ 21ኛውን ክፍለ ዘመን ለመዋጀት ትስራ፤ በጦርነት ስም አትጎትቱ፤ ማጣፊያው እንዳያጥራችሁ” የሚል ነው። “ኢትዮጵያን አትንኳት፤ ኢትዮጵያ መልማትና መበልፀግ ተፈልጋለች፤ በግራም በቀኝም ኢትዮጵያን ለማዳከም የምትሰሩ እኛን ከመንካታችሁ በፊት ደጋግማችሁ አስቡበት” በማለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የገለጹት ሐሳብ የኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን የጸና አቋም በግልጽ ያሳያል።
የግብፅ የውሃ አባካኝነት እና ያረጀው የቅኝ ግዛት እሳቤ
Sep 22, 2026 226
ግብፅ ለዓባይ ወንዝ ፍሰት ምንም ዓይነት አስተዋጽኦ የሌላት ብትሆንም፣ የዓባይን ውኃ በማባከን ትታወቃለች። ይህ በዓባይ ወንዝ እውነት ላይ ያለ አስገራሚ ተቃርኖ ነው። በርካታ የውሃ ሃብት ተንታኞችና ድንበር ተሻጋሪ የውኃ ባለሙያዎች እንደሚናገሩት፤ በግብፅ ግድቦች ውስጥ የሚከማቸው ውኃ ሀገሪቱ ባላት እጅግ ሞቃታማ የአየር ንብረት ምክንያት በትነት ይባክናል። የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የድንበር ተሻጋሪ ውኃዎች እና የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ (GERD) አማካሪ ቡድን ሰብሳቢ፣ እንዲሁም የምሥራቅ ናይል አህጉራዊ የቴክኒክ ኮሚቴ ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ፈቅአህመድ ነጋሽ እንደሚገልጹት፣ የታላቁ አስዋን ግድብ የፈጠረው የናስር ሀይቅ የሚገኘው በዓለም ላይ በጣም ሞቃት እና ደረቅ ከሆኑት የሰሃራ በረሃ ክፍሎች ውስጥ ነው። በዚህም አስዋን ግድብ በየዓመቱ በትነት ምክንያት ብቻ ከ15 እስከ 16 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ ውኃ ያጣል። ከዚህ በተጨማሪ በግብፅ የዓባይ ሸለቆ እና ዴልታ አሁንም ከ80 በመቶ በላይ የሚሆነው የግብርና መሬት የሚጠጣው በባህላዊ የጎርፍ/የቦይ መስኖ ዘዴ ነው። ይህም ከ40 እስከ 50 በመቶ የሚሆነውን በትነት፣ በመሬት ሰርገት እና ባልተጣጠመ ስርጭት ምክንያት ያባክናል። በግብጽ እንደ ጠብታ መስኖ እና ረጭ መስኖ (Sprinkler) ያሉ ዘመናዊና ውሃ ቆጣቢ ቴክኖሎጂዎች ትግበራ አሁንም አነስተኛ ነው። በሌላ በኩል በረሃን ወደ እርሻ መሬት ለመቀየር የተቀረፁ ትልልቅ ፕሮጀክቶች በረጅም ክፍት ካናሎች ውሃን ወደ በረሃ በመሳብ ለማልማት የሚደረገው ጥረት፣ ውሃው ክፍት በሆኑ ካናሎች በሚጓዝበት ወቅት በከፍተኛ ሙቀት ምክንያት በትነት እና ወደ አሸዋማ መሬት በመስረግ ከፍተኛ ውሃም ለዘመናት እያባከነች ትገኛለች። ይህ አልበቃት ብሎ ግብፅ በደረቅና ከፍተኛ የትነት መጠን ባላቸው አካባቢዎች ከፍተኛ የውሃ ፍጆታ ያላቸውን ሰብሎች በስፋት ታመርታለች። እንደ ሩዝ እና የሸንኮራ አገዳ ያሉ ከፍተኛ ውሃ የሚፈልጉ ሰብሎችን በበረሃማ የአየር ጠባይ ውስጥ በጎርፍ መስኖ ማልማት በቢሊዮን የሚቆጠሩ ሜትር ኪዩብ ውሃን ታባክናለች። በተቃራኒው ውኃን በኢትዮጵያ ጥልቅ፤ ጠባብ ሸለቆዎች ውስጥ እና አመቺ የአየር ንብረት ባለበት አካባቢ ማከማቸት የትነት መጠንን ለመቀነስ እጅግ ከፍተኛ ሚና አለው። ዋናው የውኃ ማከማቻ በኢትዮጵያ መሆኑ በሙቀት ሊባክን የሚችለውን በርካታ መጠን ያለው ውኃ ከማዳኑም በላይ፣ ወደ ታችኛው ተፋሰስ ሀገራት የሚለቀቀውን የውኃ መጠን አስተማማኝና የተረጋጋ እንዲሆን ያደርገዋል። የታላቁ ህዳሴ ግድብ የሚገኝበት ቦታ ቀዝቃዛና ጥልቅ ሸለቆ በመሆኑ፣ ውሃን በከፍተኛ ሙቀት ውስጥ ከሚገኘው የአስዋን ግድብ ይልቅ እዚያ መያዝ በትነት የሚባክነውን የውሃ መጠን በእጅጉ ይቀንሳል። ይህም ለግብፅም ጭምር ውሃን የሚቆጥብ ሳይንሳዊ እውነታ ነው። ሳይንሳዊ እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ግብፅ አሁንም ያረጀና የፈጀ የቅኝ ግዛት እሳቤን በመያዝ በዓባይ ወንዝ ላይ የተሳሳተ አቋም ማራመዷን ቀጥላለች። ግብፅ አሁንም በ1929 እና 1959 በቅኝ ግዛት ዘመን በተደረጉ፣ ኢትዮጵያን ያገለሉ ፍትሃዊ ያልሆኑ ውሎች ላይ በመመስረት የከልካይነት መብት አለኝ የሚል ጊዜ ያለፈበት እሳቤ ለማራማድ እየጣረች ነው። የኢትዮጵያን ዕድገትና የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ለግብፅ እንደ ስጋት አድርጎ በመሳል፣ የዓባይን ጉዳይ የደህንነት ስጋት በማስመሰል ጫና ለመፍጠር የምታደረግው ከንቱ ሙከራም ከዚህ ካረጀ እሳቤ የመነጨ ነው። ነገር ግን ካይሮ በኢትዮጵያ ሉዓላዊ መብት ላይ ጫና ለማሳደር ከምታደርገው ከንቱ ጥረት ይልቅ፣ የራሷን የውሃ አጠቃቀም ማዘመን፣ ዘመናዊ የመስኖ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም እና ከኢትዮጵያ ጋር በጋራ ጥቅም እና በመከባበር ላይ የተመሠረተ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ትብብር ማድረግ የረጅም ጊዜ መፍትሔ ነው።
ልዩ ዘገባዎች
በታዳጊው የተሰራችው መኪና
Jun 17, 2026 13723
ለአዳዲስ ፈጠራ የማይታክተው ልጅዓለም ንጉሱ ትውልድና እድገቱ በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ወረዳ ፀመራ ቀበሌ ነው። ከሕጻንነቱ ጀምሮ ፈትቶ መግጠምና አፍርሶ መስራትን እየተለማመደ የመጣው ልጅዓለም፤ ከቤት እስከ ትምህርት ቤት ያልተቋረጠ ፈጠራውን አጠናክሮ ቀጥሏል። ከዚህ ቀደም ለሚማርበት ፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከወዳደቁ ቁሶች የተለያዩ ቅርፃ ቅርፆችን በመስራት የፈጠራ አሻራውን አኑሯል። በትምህርትና በፈጠራ ሥራው ገፍቶበት አሁን ላይ የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ልጅዓለም እንጨት ገጣጥሞ መኪና በመስራት ያለውን የጥበብና ፈጠራ ክህሎት አሳይቷል። በታዳጊው የተሰራችውና በፔዳል የምትነዳው መኪና ሁለት ሰዎችን የማያዝ አቅም አላት። በቀጣይ ተጨማሪ ቁሶችን በማቅረብና በተለያየ መንገድ የሚያግዘው ካገኘ መኪናዋ በዲናሞ እንድትንቀሳቀስ ለማድረግ መዘጋጀቱን ተናግሯል። የተሽከርካሪውን አካል የገጣጠመው በአካባቢው አጠራር "እንቋ" የተሰኘ ዛፍ እንጨትን በመጠቀም ሲሆን የተሽከርካሪውን እግር ለማዘጋጀት ደግሞ የዋርካ ዛፍ ተጠቅሟል። በዚህም መሰረት የልጅዓለም መኪና የመብራትና የመሪ ስራዋ ተጠናቆ ሁለት ሰዎችን ጭና መንቀሳቀስ እንደምትችል በተግባር አሳይቷል። "በቀጣይ የሚያግዘኝና የሚደግፈኝ ካገኘሁ በዲናሞ የሚሰራ ተሽከርካሪ ለመስራት ዝግጁ ነኝ" ያለው ጥበበኛው ተማሪ ወደ ፊት ለሀገሬ ብዙ የመፍጠር ህልም አለኝ ብሏል። የፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ግርማ ጌቴ፤ ከዚህ በፊት ተማሪ ልጅዓለም በትምህርት ቤቱ የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎች እንዳሉት አስታውሰው ትምህርቱንም ፈጠራውንም አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል። የፈጠራ ክህሎቱን፣ ተሰጥኦውንና ፍላጎቱን ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ ተከታትያለሁ ያሉት መምህሩ የሳይንስ ትምህርቱንና የግል ክህሎቱን ደምሮ ለአዳዲስ ሥራዎች እየተጋ መሆኑን አንስተው፣ የመኪና ፈጠራውም ይህንኑ በተግባር ያሳየበት ነው ብለዋል። የግብዓት አቅርቦት ድጋፍ ከተደረገለት የተሻለና ውጤታማ ሥራ መስራት እንደሚችል ገልጸው ለሚፈጥሩ ወጣቶች በጥሩ ምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን ተናግረዋል። በእንጨት የተገጣጠመችው መኪና በሁላችንም ድጋፍ የዲናሞ፣ የብረትና ሌሎች አስፈላጊ ቁሶች ከተሟሉላት በታዳጊው ጥበብ የተሻለች መኪና ሆና ልትሰራ ትችላለች ሲለም እምነታቸውን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 22696
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 15718
በዮሐንስ ደርበው በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 21462
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
መጣጥፍ
የጉራጌ መስቀል- 'ከወሬት የኸና' እስከ 'አዳብና'
Sep 24, 2026 166
የጉራጌ መስቀል- 'ከወሬት የኸና' እስከ 'አዳብና' (በእንዳልካቸው ደሳለኝ ከኢዜአ ወልቂጤ ቅርንጫፍ) በኢትዮጵያ ከሚከበሩ ታላላቅና ደማቅ ሃይማኖታዊ በዓላት መካከል መስቀል ይጠቀሳል። የመስቀል በዓል ሃይማኖታዊ ቢሆንም በተለያዩ ባህላዊ እሴቶች ጎልቶ የሚታይበት ነው፡፡ በቤተ ጉራጌ መስቀል ከሃይማኖታዊ ሥርዓት ባሻገር ሰፊ ማህበራዊ ክዋኔ ያለው ሲሆን፣ የተቀያየመ የሚታረቅበት፣ የተራራቀ ወዳጅና ዘመድ የሚገናኝበት፣ ጋብቻ የሚፈፀምበት እንዲሁም የፍቅርና የአንድነት ማንፀባረቂያ ነው። በዓሉ በዋናነት በቤተ ጉራጌዎች መስከረም 15 ቀን የሚከበር ቢሆንም፣ የዝግጅት ሂደቱና አከባበሩ ከነሐሴ አጋማሽ ጀምሮ እስከ ጥቅምት ወር መጀመሪያ ድረስ የተዘረጋ ረጅም የደስታና የምስጋና ወቅት ነው። የመስቀል ዝግጅት በይፋ የሚጀምረው ነሐሴ 12 ቀን እንደሆነ የሚናገሩት የሀገር ሽማግሌ አቶ በለጠ ወልዴ፣ በዚህ ዕለት የዓመቱ የመስቀል ደመራ የሚቆምበት እንደሆነ ያብራራሉ። ከዚህ ዕለት ጀምሮ በቤተሰቡ ውስጥ የሥራ ክፍፍል ተደርጎ አጠቃላይ የዝግጅት እንቅስቃሴው ይፋ ይሆናል። በዚህም መሰረት የስራ ኃላፊነቶችን ሲጠቅሱ፤ ልጃገረዶች የቤቱን የውስጥ ክፍል ማፅዳት፣ በባህላዊ ቀለማትና ጌጣጌጦች ቤት ማስዋብ እንዲሁም ለበዓሉ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን ያዘጋጃሉ። የወጣት ወንዶች ዋነኛ ኃላፊነት ደግሞ ጀፎረን በማስዋብ አጥር ማጠር፣ ለበዓሉ የሚሆን የማገዶ እንጨት ማዘጋጀትና ለደመራ የሚሆኑ እንጨቶችን አስቀድሞ ማደራጀት ነው። አባወራዎች ለበዓሉ የእርድ ሰንጋዎችን የመግዛትና የማዘጋጀት ኃላፊነት ሲኖርባቸው፤ የእናቶች ድርሻ ደግሞ ለባህላዊ ምግቦች የሚያስፈልጉ እንደ ቆጮ፣ ቡላ፣ አይብ፣ ቅቤ እና የመገልገያ ባህላዊ ቁሳቁሶችን የማደራጀትና የማዘጋጀት ኃላፊነት ነው። በቤተ ጉራጌ ከመስከረም 12 እስከ ጥቅምት 5 ባለው ጊዜ ውስጥ በዓሉ በየቀኑ ልዩ ልዩ ባህላዊ ስያሜዎችና ሥርዓቶች ተሰጥተውት በደመቀ ሁኔታ ይከበራል። በጋራ ሆነው ክትፎና መሰል ባህላዊ ምግቦችን እየተመገቡ በጭፈራና በፈንጠዝያ የመስቀልን በዓል ያከብራሉ። የቀናቶቹን ስያሜና ባህላዊ ክዋኔ በተመለከተ ያነጋገርናቸው የሀገር ሽማግሌ ጐታ ኩየ እንደገለጹት፤ መስከረም 13 ቀን ‘ወሬት የኸና’ (እንቅልፍ ከልካዩ ቀን) ሲሆን በዚህ ቀን ሴቶች ለበዓሉ ዝግጅት ለማድረግ የሚጓጉበት ቀን ከመሆኑ ጋር በተያያዘ እንደሆነ ይነገራል። በዚህ ቀን ለበዓሉ ለመመገቢያነት የሚያገለግሉ ባህላዊ ቁሳቁሶች ለዓመት ከተሰቀሉበት ቦታ ወርደው በጥንቃቄ ተጣጥበው ዝግጁ ይሆናሉ። ቀኑ ከአፈር በተዘጋጁ ቀለማት ግድግዳዎች የሚያሸበርቁበትና አዳዲስ ጅባዎች ተነጥፈው ለበዓሉ ዝግጁ የሚሆኑበት ቀን ነው። መስከረም 14 ቀን ደግሞ ‘ደንጔሳት’ የሚል ስያሜ ያለው ሲሆን ዕለቱ ልጆች ደመራ ደምረው ባህላዊ ጭፈራዎቻቸውን የሚያቀልጡበት ነው። ከደመራው በኋላም ሴቶች የጎመን ክትፎ በማዘጋጀት በእያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ውክልና በተዘጋጀ ጣባ አድርገው ለምግብነት ያቀርባሉ። ባለትዳር የሆኑ አባላት በአንድ ጣባ የጎመን ክትፎው ተዘጋጅቶ ይሰጣቸዋል። ተምሳሌትነቱም የትዳር አጋሮች "አንድ አካል፣ አንድ አምሳል ናቸው" ተብሎ ስለሚታመን የሚፈፀም ነው። ጉራጌዎች ‘ወኸምያ’ ብለው የሚጠሩት መስከረም 15 ዋናው የመስቀል በዓል የሚውልበት ቀን ነው። በዚህ ዕለት ከሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች በተለየ በሁሉም የቤተ ጉራጌ አካባቢዎች የእርድ ቀን ነው። በሌሎች አካባቢዎች ዕለቱ መስከረም 17 ቀን ላይ እንደሚከበር ልብ ይሏል። በ 'ወኸምያ' ቀን የሚታረደው በሬም ሆነ ወይፈን በሽማግሌዎች ፊት ቀርቦ ስለ ሀገር ሰላም እንዲሁም በዓሉ መልካም ነገር እንዲያመጣ ምርቃት ይወርዳል። የቤተሰቡ አባላትም በእያንዳንዱ ምርቃት መጨረሻ ላይ “ኬር ኬር ኬር ይሁን” (ሰላም ይሁን) በማለት ምርቃቱን ይቀበላሉ። በዚህ ባህላዊ የምርቃት ሥነ ሥርዓት አብዛኛውን ጊዜ እንዲመርቁ የሚጋበዙት በዕድሜያቸው ገፋ ያሉ አረጋውያን ሲሆኑ፣ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች እኩል ተሳትፎ ይኖራቸዋል። መስከረም 16 ቀን (‘ያባንዳ እሳት’ ወይም 'የጉርዝ ኧሳት') የሚል ስያሜ ያለው ሲሆን ዕለቱ አባቶች ደመራ ይዘው የሚወጡበት ነው። በዚህ ዕለት ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍል ተሳትፎ የሚያደርግበት የደመራ በዓል ይከወናል። በዕለቱ አባቶች የተለየ ክብር ተሰጥቷቸው የደመራ በዓሉን በምርቃት ያስጀምሩታል። ቀኑ ከባህላዊ ይልቅ መንፈሳዊ ይዘትን ተላብሶ ይከበራል። ጎረምሶችና ልጃገረዶች ደመራውን በመክበብ በተለያዩ ጭፈራዎች አካባቢውን ያደምቁታል። ከጭፈራው በኋላም ሁሉም ወደ ቤቱ በመመለስ በራሱ ጣባ የተዘጋጀለትን ክትፎ ይመገባል። ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ በአንድ አካባቢ የሚገኙ የቤተ ጉራጌ ነዋሪዎች ደመራው ወደተቃጠለበት ቦታ በመሄድ የአካባቢያቸውን የዕድር ዳኛ በመቀየር አዲስ የሚመርጡበትና ቃለ መሐላ የማስፈፀም ተግባር የሚያከናውኑበት ቀን የሚከበረው መስከረም 17 ቀን ሲሆን ይህም ‘ንቅባር’ ወይም 'የከሰል ማይ' በሚል ስያሜ ይጠራል። በዕለቱም ሁሉም የአካባቢው የቤተሰብ አባላት የተቃጠለውን የደመራ ከሰል እየዘለሉ በመጪው ዘመን መልካም ነገር እንዲገጥማቸው ይመኛሉ፤ ይማፀናሉም። ወጣቶች ንጋት ላይ ተቀጣጥለው የቀሩ ጉማጅ እንጨቶችን ተሽቀዳድመው በመውሰድ እርሻ ላይ ያቆማሉ፤ ይህም እርኩስ መናፍስትን ይከላከላል ተብሎ ይታመናል። መስከረም 18 ቀን ‘የፊቃቆ ማይ’ ይባላል። በዚህ ቀን የአካባቢው ልጃገረዶች ሰፌድ ለመስራት የሚያገለግል ስንደዶዎችን ይሰበስባሉ። የስንደዶ ለቀማው በባህላዊ ዜማዎች ታጅቦ ይከናወናል። ከመስከረም 17 እስከ መስከረም 23 ያለው ጊዜ ደግሞ የዘመድ መጠየቂያ ወቅት ሲሆን ‘የጀወጀ’ ወይም ‘የጀመቸ’ ተብሎ ይጠራል። ለዓመት ተነፋፍቀው የቆዩ ቤተሰቦች ተገናኝተው ናፍቆታቸውን የሚገልፁበት፣ የባልና ሚስት እናትና አባት የሚጠየቁበት እንዲሁም ስጦታ የሚቀበሉበት ዕለት ነው። ሴት ልጆች ለእናቶቻቸው የፀጉር ቅቤ፣ ባርኔጣ፣ ጭራ እና ሌሎች ስጦታዎችን ሲያቀርቡ፣ ባሎቻቸው ደግሞ የበግ ሙክት በመያዝ ይጠይቋቸዋል። ስጦታው የቀረበላቸው እናትና አባቶችም የልጆቻቸውን ባሎችና ሚስቶች በየተራ ይመርቋቸዋል። የጉራጌ ጋብቻ በብዛት የሚከወነው በዚሁ በመስቀል ሰሞን በመሆኑ፣ ከመስከረም 16 እስከ ጥቅምት 5 ያለው ጊዜ በቤተ ጉራጌ ወጣቶች ዘንድ እጅግ ተወዳጅ ነው። በዚህ ጊዜ በተለያዩ የገበያ ቦታዎችና አብያተ ክርስቲያናት ወጣቶች ባህላዊ ጭፈራዎቻቸውን ያሳያሉ፤ እግረ መንገዳቸውንም ለትዳር የምትሆናቸውን ጉብል መልከት መልከት ያደርጋሉ። የወጣቶቹ ባህላዊ ጨዋታ “አዳብና” በሚል ስያሜ የሚታወቅ ሲሆን፣ በንግድና በተለያዩ ምክንያቶች ቆይተው ስለመጡባቸው ቦታዎች ተገናኝተው የሚያወጉበትም ነው::
ከጨበራ እስከ ጎርጎራ
Sep 22, 2026 299
አዲስ አበባ፤ መስከረም 12/2019 (ኢዜአ)፦ከጨበራ እስከ ጎርጎራ ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ጸጋዎች እንዲሁም በታሪክ፣ በባህል እና በታሪካዊ ቅርሶች የታደለች ሀገር መሆኗ ይታወቃል። ይሁን እንጂ እነዚህ እምቅ ሃብቶች ለበርካታ ዓመታት ተገቢውን ትኩረት ሳያገኙ፣ ሳይለሙና የሀብት ምንጭ ሳይሆኑ ተዘንግተው መቆየታቸው የሚታወቅ ነው። የመደመር መንግስት ለቱሪዝም ዘርፉ በሰጠው ትኩረት ዘርፉ በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ከተካተቱ አምስት ሴክተሮች አንዱ ሆኖ መተግበር ጀምሯል። በዚህም በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ነባር የቱሪዝም መዳረሻዎችን የማሻሻልና አዳዲስ መዳረሻዎችን የማልማት ስራ በስፋት ተከናውኗል፤ እየተከናወነም ይገኛል። በዚህም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሃሳብ አመንጭነት በጥቂት ዓመታት ውስጥ የተከናወኑ የ"ገበታ ለሸገር"፣ "ገበታ ለሀገር" እና "ገበታ ለትውልድ" የልማት መርሃ-ግብሮች የቱሪዝም ዘርፉ ከፍተኛ እመርታና ማንሰራራት አምጥተዋል። በእነዚህ ኢንሸቲቮች ተደብቀው የቆዩና በሁሉም ማእዘናት የነበሩ መሠረተ ልማቶችን በማልማት ጥቅም ላይ ማዋል ተችሏል። ለኢትዮጵያ ተፈጥሮ የለገሳትን ውብ መልክዓ ምድሮች፣ ሀይቆች፣ ብሔራዊ ፓርኮች እና ታሪካዊ ስፍራዎች ይበልጥ በማልማት የዓለም አቀፍ እና የሀገር ውስጥ ቱሪዝም መዳረሻነቷን ከፍ አድርጓል። የቱሪዝም ልማቱ ሀገርን እና ትውልድን መሰረት አድርጎ በሁሉም አካባቢዎች በርካታ ግንባታዎችን እውን አድርጓል። ከቀድሞው የተገደበ የቱሪስት እንቅስቃሴ ወጥቶ፣ አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎችንና ሪዞርቶችን በመገንባት ረገድ አስደናቂ ስራዎች ተከናውነዋል። በጣና ሐይቅ ዳርቻ ላይ የተገነባው የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት ለቱሪስቶች ምቾትና ለሐይቁ ውበት ግርማ ሞገስ ሆኖ የተገነባ ነው። የጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክ ጋር ተሰናስሎ የተገነባው ሎጅም የተፈጥሮን ውበት ከዘመናዊ የቅንጦት አገልግሎት ጋር ያሰናሰለ አስደናቂ ስፍራ መሆኑ ይታወቃል። የ«ገበታ ለትውልድ» ሁለተኛ ምዕራፍ ማሳያ የሆነው ሎጎ ሐይቅ ሪዞርት ደግሞ የወሎን ማህበራዊ መስተጋብር እና የአብሮነት እሴት የሚያጎለብት፣ ለአይን ማራኪ እና ዘመናዊ መዝናኛ ሆኖ የታነጸ ነው። በአጭር ጊዜ ውስጥ ተገንብተው ትኩረት ከሰበሰቡ አዳዲስ የቱሪዝም እና የልማት መዳረሻዎች መካከል ቤኑና መንደር አንዱ ነው። የ«ይቻላል» እምነት ቋሚ ምስክር ተብሎ የሚታወቀው ይህ አካባቢ፣ አካባቢው ያለውን የተፈጥሮ ስበት በመጠቀም የሀገር ውስጥ እና የውጭ ቱሪስቶችን ትኩረት የሳበ ውብ መናኸሪያ ሆኗል። በእሳተ ገሞራ ፍንዳታ የተፈጠረው እና ውብ ውበቱን የያዘው የወንጪ ሐይቅ፣ ዛሬ ላይ ከማህበረሰቡ ጋር በተቀናጀ መልኩ በለማው ኢኮ-ሎጅ ዓለም አቀፍ ዕውቅናን ያገኘ መዳረሻ መሆኑ ይታወቃል። በሶማሌ ክልል ከጅግጅጋ ከተማ በ385 ሄክታር መሬት ላይ የተገነባው ታላቁ የሸበሌ ሪዞርትም የክልሉን የቱሪዝም ልማት በእጅጉ ያነቃቃ ታላቅ ፕሮጀክት መሆኑ ይታወቃል። የዳናክል በረሃ እና ኤርታአሌ ያሉ ድንቅ የተፈጥሮ ጸጋዎችን የያዘው የአፋር ክልል ቱሪዝምን ለማነቃቃትና የጎብኚዎችን ቆይታ ለማራዘም "ከፈንታሌ እስከ ኤርታአሌ" የተሰኘ የቱሪዝም ልማት ፕሮጀክት ጨምሮ ዘመናዊ ሪዞርቶችና መዳረሻዎች እንዲስፋፉ ተደርጓል። በድምሩ ከጨበራ እስከ ጎርጎራ፣ ቤኑና፣ ወንጪ፣ ሎጎ ሃይቅ እንዲሁም የሀሮ ደንዲ ሎጅ የሀገሪቱን ገጽታ የቀየሩና የቱሪዝም ዘርፉን እድገትና ማንሰራራት እውን ካደረጉት መካከል የሚጠቀሱ ናቸው። የህዳሴ ግድብም ከሃይል ልማት ባለፈ አይነተኛ የቱሪዝም መሰህብ ስፍራ ሆኖ የንጋት ሃይቅ ዓሳ የሚመረትበትና ቱሪስቶች የሚስተናገዱበት ተመራጭ ስፍራ ሆኗል። በመደመር መንግስት አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ከመገንባት ባለፈ የቆዩትን የማደስና ቅርሶችን የመጠበቅ እንዲሁም የመንከባከብ ስራ በስፋት ተከናውኗል። በሁሉም ክልሎች እምቅ ሃብቶችን በመለየት የማልማትና የነበሩትን የመጠበቅ ስራ ተሰርቷል። ለትውልድ የሚሻገር የቅርስ ጥበቃና መዳረሻዎችን የማልማት ተግባር የኢትዮጵያን ብዝሃ-ሃብት በማስተዋወቅ ረገድ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል። በአጠቃላይ ባለፉት አምስት ዓመታት የተከናወኑ የልማት ኢኒሼቲቮች በተለይም በቱሪዝም ሴክተር መሰረታዊ ለውጥና ስኬት ማስመዝገብ የቻሉ ተጨባጭ ውጤቶችም ያመጡ መሆናቸውን መናገር ይቻላል።