አርእስተ ዜና
አምስት የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በቴክኖሎጂ የታገዘ (e-learning) የትምህርት መርኃ ግብር ወደ ሥራ አስገቡ
Mar 4, 2024 107
አዲስ አበባ፤ የካቲት 25/2016(ኢዜአ)፡-አምስት የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በቴክኖሎጂ የታገዘ (e-learning) የመማር ማስተማር የትምህርት መርኃ ግብር ወደ ሥራ አስገቡ። የትምህርት መርኃ ግብሩ የትምህርት ሚኒስቴር ከማስተርካርድ ፋውንዴሽን፣ ከአሜሪካው አሪዞና ስቴት ዩኒቨርሲቲና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ነው ወደ ሥራ የገባው። ትምህርቱን መስጠት የሚያስችሉ የአምስት ዩኒቨርሲቲዎች "ብሔራዊ መልቲ-ሚዲያ ስቱዲዎዮች" የትምህርት ሚኒስቴርና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራሮች በተገኙበት በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመርቀዋል። በምርቃ ሥነ-ሥርዓቱ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በተወካያቸው በኩል ባስተላለፉት መልዕክት፤ መንግሥት ባለፉት ዓመታት የከፍተኛ ትምህርት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የተለያዩ ተግባራት ሲያከናውን ቆይቷል ብለዋል። ይህንንም ተከትሎ አሁን ላይ በአገሪቱ 51 የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎችና ከ300 በላይ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተከፍተው የመማር ማስተማር ተግባር እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል። ይሁንና በተለይም የትምህርት ጥራትን ከማረጋገጥ አኳያ አሁንም ውስንነቶች መኖራቸውን ጠቁመዋል። በመሆኑም መንግሥት የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት ከትምህርት ማኅበረሰቡና ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በመሆን የተለያዩ የማሻሻያ እርምጃዎችን እየወሰደ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ከእነዚህም መካከል በዛሬው ዕለት ሥራ የጀመረው በቴክኖሎጂ የተገዘው (e-learning) የመማር ማስተማር የትምህርት መርኃ ግብር ተጠቃሽ መሆኑን ገልጸዋል። መርኃ ግብሩ ዋና ዓላማም በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ጥራት፣ አግባብነትና ተደራሽነትን ለማሳደግ ያለመ መሆኑን ተናግረዋል። ከዛሬ ጀምሮ በአዲስ አበባ፣በባህርዳር፣በአዋሳ፣በድሬዳዋና በጂማ ዩኒቨርሲቲዎች በተገነቡ የብሔራዊ መልቲ-ሚዲያ ስቱዲዮች አማካኝነት የትምህርት መርኃ ግብሩ በይፋ መጀመሩን ገልጸዋል። በዚህም የመጀመሪያና የሁለተኛ ዲግሪ የትምህርት መርኃ ግብሮች እንደሚሰጡ ጠቅሰው በቀጣይም መርኃ ግብሩ በሌሎች ዩኒቨርስቲዎች ተግባራዊ እንደሚሆን ተናግረዋል።   የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዘዳንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ በበኩላቸው፤ በቴክኖሎጂ የታገዘው ይህ የትምህርት መርኃ ግብር መጀመር በተለይም የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ተናግረዋል።  
ኢትዮጵያና ዴንማርክ በተለያዩ የትብብር መስኮች ላይ የተመሰረተውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር ይሰራሉ 
Mar 4, 2024 84
አዲስ አበባ፤ የካቲት 25/2016(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያና ዴንማርክ ለበርካታ ዓመታት የዘለቀውንና በተለያዩ የትብብር መስኮች ላይ የተመሰረተውን የሁለቱ አገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚሰሩ ገለጹ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከዴንማርክ ፓርላማ የውጭ ፖሊሲ ኮሚቴ አባላት ጋር ተወያይቷል። የውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶክተር ዲማ ኖጎ በዚሁ ጊዜ በኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በፖለቲካና ምጣኔ ኃብት ዘርፎች እየተከናወነ ያለውን የለውጥ ሥራ አብራርተዋል። ጎን ለጎንም ወቅታዊ የአገሪቱን የሰላምና ጸጥታ ጉዳይ በተለይም በአገሪቱ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት በፕሪቶሪያው የተደረሰውን የሠላም ሥምምነት ትግበራ አስመልክቶም ማብራሪያ ሰጥተዋል። መንግሥት ለዘላቂ ሰላም ቁርጠኛ አቋም በመያዝ በአማራና ኦሮሚያ ክልል የሚስተዋሉ የጸጥታ ችግሮችን በውይይትና በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚያከናውናቸውን ተግባራትም ዘርዝረዋል። በሂደት ላይ ያለው የሽግግር ፍትህ ፖሊሲን በተመለከተም ገለጻ አድርገዋል።   በፖለቲካ ሊሂቃንና የኃሳብ መሪዎች መካከል የሚስተዋሉ ልዩነቶችን በውይይት በመፍታት ጠንካራ አገረ መንግሥት ለመገንባት በአገራዊ የምክክር ኮሚሽን በኩል እየተሰራ መሆኑንም አብራርተዋል። ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካም ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን በሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን እንዲሁም ሶማሊያ ያላትን የሰላም አስተዋጽኦ በማብራሪያቸው ጠቅሰዋል። በቀጣናው ሰላምና መረጋጋት በመፍጠር የምጣኔ ኃብት፣ የመሰረተ ልማት፣ የንግድና ሌሎች ዘርፎች ትስስር ለመፍጠርም በትኩረት እየሰራች መሆኑንም ገልጸዋል። ለአብነትም የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት በማድረግ የተገነባውን የታላቁ የሕዳሴ ግድብን አንስተዋል። ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት ከሶማሌላንድ ጋር ያደረገችውን የመግባቢያ ሥምምነት ለቀጣናው ሠላምና ደኅንነት እንዲሁም ምጣኔ ኃብት እድገት ያለውን አስተዋጽዖም አብራርተዋል።   የዴንማርክ ፓርላማ የውጭ ፖሊሲ ኮሚቴ ሰብሳቢ ማይክል አስትረፕ በበኩላቸው ኮሚቴው በኢትዮጵያ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ለማወቅና የአገራቱን ግንኙነት ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ በሚቻልባቸው ምቹ ሁኔታዎች ዙሪያ ለመምከር ወደ ኢትዮጵያ መምጣቱን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት በምስራቅ አፍሪካ ሰላምና ደኅንነት እንዲረጋገጥ በአገር ውስጥ ያሉ ችግሮች በሰላማዊ መልኩ ለመፍታት የሚያከናውናቸውን ተግባራት በአድናቆት እንደሚመለከቱት የዴንማርክ ፓርላማ የውጭ ፖሊሲ ኮሚቴ አባላት ገልጸዋል። የኢትዮጵያና የዴንማርክ የፓርላማ ተወካዮች በፓርላማ የሴቶች ተሳትፎና በሌሎች የፓርላማ ግንኙነቶች ልምድ በመለዋወጥ በጋራ ለመሥራት ተስማምተዋል። ሁለቱ አገራት ግንኙነታቸውን በምጣኔ ኃብት፣ በፖለቲካና ማኅበራዊ ዘርፎች የበለጠ በሚያጠናክሩባቸው ጉዳዮች ላይም በስፋት መክረዋል። ለበርካታ ዓመታት የዘለቀውንና በተለያዩ የትብብር መስኮች ላይ የተመሰረተውን የሁለቱ አገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚሰሩ በመድረኩ ተገልጿል።                                      
በክልሉ አዳዲስ ባለሃብቶችን ከመሳብ ባለፈ፤ ነባር ኢንዱስትሪዎች የተሻለ ማምረት እንዲችሉ የተጀመሩ ስራዎች ይጠናከራሉ - አቶ እንድሪስ አብዱ
Mar 4, 2024 66
ደብረ ብርሃን፤ የካቲት 25/2016 (ኢዜአ)፦ የአማራ ክልል አዳዲስ ባለሃብቶችን ከመሳብ ባለፈ፤ ነባር ኢንዱስትሪዎች የተሻለ ማምረት እንዲችሉ የተጀመሩ ስራዎች የሚጠናከሩ መሆኑን የክልሉ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሃላፊ አቶ እንድሪስ አብዱ ገለጹ። በአማራ ክልል ደረጃ ''የኢትዮጵያ ታምርት'' ንቅናቄ መድረክ በደብረ ብርሃን ከተማ ዛሬ ተካሄዷል። አቶ እንድሪስ በመድረኩ ላይ እንደተናገሩት ንቅናቄው በአማራ ክልል የኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም በማሳደግ አበረታች ውጤት እያስመዘገበ ነው። በንቅናቄው ለረጅም ዓመታት ቆመው የነበሩ አምራች ኢንዱስትሪዎች ችግሮቻቸውን በመፍታት ወደ ሥራ መግባታቸውን አስረድተዋል። በዚህም ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅማቸውን በማሳደግ ምርቶቻቸውን ለሃገር ውስጥና ለውጭ ገበያ ለማቅረብ እንደተቻለ ሃላፊው ተናግረዋል። በቀጣይም አዳዲስ ባለሃብቶችን ከመሳብ ባለፈ፤ ነባር ኢንዱስትሪዎች የተሻለ ማምረት እንዲችሉ ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል።   የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ሃላፊ አቶ ብርሃን ገብረሀይወት፣ በከተማዋ በባለሀብቱና በአስተዳደሩ መካከል ያለው ቅንጅታዊ አሰራር እየተጠናከረ መምጣቱን ገልጸዋል። በከተማዋ ያሉትን የኢንዱስትሪዎችን ትስስር ለማጠናከር 3 ነጥብ 2 ኪሎ ሜትር መንገድ መገንባቱን ገልጸው በዚህም ባለሀብቶችም ወደ ምርት የመሸጋገር አቅማቸው ማደጉን አቶ ብርሃን ተናግረዋል። መድረኩ ችግሮችን በጋራ በመለየት ለቀጣይ የልማት እንቅስቃሴ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ታስቦ መዘጋጀቱንም ገልጸዋል። የደብረ ብርሃን መኪና መገጣጠሚያ ኢንዱስትሪ ሥራ አስኪያጅ አቶ መሐመድ አህመድ፣ መንግሥት ለባለሃብቶች እያደረገ ያለው እገዛ የሚያበረታታ መሆኑን አመልክተው፣ አሁንም በመሰረተ ልማት ዝርጋታ ረገድ የተጀመሩ ስራዎች እንዲጠናከሩ ጠይቀዋል። በኢትዮ ቴሌኮም የማዕከላዊ ሰሜን ሪጅን ዳይሬክተር አቶ አንተነህ ፋንታሁነኝ በበኩላቸው ተቋሙ በአካባቢው ያለውን የቴሌ መሰረተ ልማት ለማዘመን 210 ሚሊየን ብር መድቦ እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል። በየደረጃው የሚገኙ የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች ሪጅኑ የሚጠይቀውን የኔትወርክ ማስፋፊያ ቦታ ካቀረቡ የባለሀብቶቹ ጥያቄ በፍጥነት ምላሽ ያገኛልም ብለዋል።            
በህብረት ስራ ዘርፍ የተጀመረውን ሀገር አቀፍ ሪፎርም ወጤታማ ለማድረግ አመራሩ ተገቢውን ትኩረት እንዲሰጥ ተጠየቀ
Mar 4, 2024 78
አዳማ፤ የካቲት 25/2016 (ኢዜአ)፦ በህብረት ስራ ዘርፍ የተጀመረውን ሀገር አቀፍ ሪፎርም ወጤታማ ለማድረግና ግቡን ለማሳካት የፖለቲካ አመራሩ ተገቢውን ትኩረት እንዲሰጥ በዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል የአደረጃጀት ዘርፍ ሚኒስትር አቶ ሳዳት ነሻ አስገነዘቡ። የተጀመረውን የህብረት ስራ ሪፎርም ለማሳካት ላይ ያተኮረ የፌዴራልና የክልሎች የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች የተሳተፉበት መድረክ በአዳማ ከተማ ዛሬ ተካሄዷል።   በመድረኩ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል የአደረጃጀት ዘርፍ ሚኒስትር አቶ ሳዳት ነሻ ለህብረት ስራ ትኩረት መስጠት ካልቻልን የተሟላና የሚፈለገውን የኢኮኖሚ ልማትና እድገት ማምጣት አንችልም ብለዋል። በተለይ የኑሮ ውድነትና የስራ አጥነትን ለመቀነስና ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል እንዲረጋገጥ የህብረት ስራ ማህበራት ያላቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰዋል። እስካሁን ባለው ሂደት ዘርፉ በሀገር ልማትና እድገት ውስጥ የሚጠበቅበትን ያህል አስተዋጽኦ እያበረከተ አለመሆኑንም ተናግረዋል። በዚህም የህብረት ስራ ማህበራትና ዩኒየኖች የግብርና ግብዓት አቅርቦት ላይ ብቻ እንዲወሰኑ ማድረጉን የገለጹት ሚኒስትሩ በተለይ ገበያን በማረጋጋትና ስራ አጥነትን በመቀነስ ረገድ የሚጠበቅባቸውን ያህል መጓዝ እንዳልቻሉ ተናግረዋል። ዘርፉ በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ውስጥ የሚጠበቅበት አስተዋጽኦ ማበርከት እንዲችልና በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረው ሪፎርም እንዲሳካ በየደረጃው ያለው የፖለቲካ አመራር ተገቢውን ትኩረት እንዲሰጠው ሲሉ አሳስበዋል። ሪፎርሙን በመተግበር፣ አደረጃጀትና አሰራር በመዘርጋት፣ ዘርፉ ከማምረት እስከ ገበያ ድረስ ባለው የምርትና ግብይት ሰንሰለት ውስጥ መሪ ሚና እንዲኖረው ለማስቻል ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል። ወጥነት ያለው የህብረት ስራ ሪፎርም ትግበራ እንዲረጋገጥ ፓርቲው ተገቢውን ድጋፍና እገዛ ያደርጋል ያሉት ደግሞ በዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል የፖለቲካ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ሙሳ አህመድ ናቸው። ሪፎርሙ የአመራሩን ትኩረት ማግኘት አለበት ያሉት አቶ ሙሳ የህብረት ስራ ዘርፍ ረዥም ታሪክ ያለው ቢሆንም አሁን ሀገሪቷ ከደረሰችበትና የዋጋ ግሽበቱን ለመቆጣጠር በሚደረገው ጥረት ውስጥ የሚጠበቅበትን ያህል እያገዘ አይደለም ብለዋል። በመሆኑም የተጀመረው ሀገራዊ የህብረት ስራ ሪፎርም ንቅናቄ ተገቢው ትኩረት ከተሰጠው የዘርፉን ችግሮች የሚፈታ ነው ብለዋል። የኢትጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ጌታቸው መለሰ በበኩላቸው ሪፎርሙ አጠቃላይ የዘርፉ አሰራርና አደረጃጀት ከመሰረቱ ከመለወጡም ባለፈ ተወዳዳሪ የህብረት ስራ ማህበራትን ለመፍጠር ቁልፍ ሚና ያለው መሆኑን ተናግረዋል።   መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት የሀገር በቀልና ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎች የተካተቱበት አሰራሮች፣ የህግ ማእቀፎች፣ ማኑዋሎችና መመሪያዎች ተዘጋጅተው ወደ ትግበራ መገባቱን አመልክተዋል። በዚህም የአሰራር፣ የአደረጃጀት፣ የተጠሪነት፣ የቴክኖሎጂ፣ የክህሎት፣ የፋይናንስ አቅም ውስንነትን ጨምሮ በርካታ የዘርፉ ማነቆዎችን በመፍታትና ዘርፉን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ ያለመ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል።  
የሚታይ
ዩ.ኤን.ዲ.ፒ በኢትዮጵያ የግብርና ዘርፍ የመድን አገልግሎት ለማጠናከር የሚያስችል መርኃ-ግብር ይፋ አደረገ
Mar 4, 2024 80
አዲስ አበባ፤ የካቲት 25/2016(ኢዜአ)፦የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም (ዩ.ኤን.ዲ.ፒ) የግብርና ዘርፍ የመድን አገልግሎትን ለማጠናከር የሚያስችል መርኃ-ግብር ይፋ አደረገ። መርኃ-ግብሩ ሕብረተሰቡ የአደጋ ተጋላጭነትን ለመቆጣጠር አቅም እንዲያጎለብት እንደሚያስችለው ተጠቅሷል። ዛሬ ይፋ የሆነው ይኸው መርኃ-ግብሩ በቀጣይ አራት ዓመታት በኢትዮጵያ ገቢራዊ የሚሆን ሲሆን፤ 1 ነጥብ 9 ሚሊየን ዶላር በጀት የተያዘለት መሆኑም ተመላክቷል። በዩ.ኤን.ዲ.ፒ ኢትዮጵያ የአካታች ኢኮኖሚ ልማት መርኃ-ግብር አስተባባሪ ግዛቸው ሲሳይ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት፤ የግብርና መድህን ስርዓቱ በዋናነት ሁለት ዓላማዎች አሉት።   የመጀመሪያው አነስተኛ ይዞታ ያላቸው እንዲሁም በዘመናዊ መንገድ በግብርና የተሰማሩ አርሶ አደሮች የመድን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችል መሆኑን ገልፀዋል። ይህም የአደጋ ሥጋትን መቋቋም የሚችል ግብርና እንዲያከናውኑ የሚያስችላቸው መሆኑን ተናግረዋል። በአገሪቱ በአጠቃላይ የግብርና የመድን አገልግሎት ሥርዓት ውስጥ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር ደግሞ ሌላኛው የመርኃ-ግብሩ ዓላማ መሆኑን ጠቁመዋል።   በብሔራዊ ባንክ የኢንሹራንስ ሱፐርቪዥን ዳይሬክተር በላይ ቱሉ በበኩላቸው፤ መርኃ-ግብሩ የግብርና የመድን አገልግሎት ከመመሪያው ጀምሮ ያሉ ክፍተቶችን ለማረም ይረዳል ብለዋል። ይህም ብቻ ሳይሆን በዘርፉ የሚስተዋለውን የአቅም ክፍተት ለመሙላት እንደሚያግዝ ጠቁመዋል።   መርኃ-ግብሩ በዘርፉ የሚሰሩ ተግባራትን ይበልጥ ለማጎልበት ያስችላል ያሉት ደግሞ በግብርና ሚኒስቴር የግብርና ኢንቨስትመንትና ምርት ግብይት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ደረጀ አበበ ናቸው። የግብርና የመድን አገልግሎት በኢትዮጵያ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ መሆኑን አስታውሰው፤ መርኃ-ግብሩ የመድን አገልግሎት ሽፋኑን ለማስፋት አዎንታዊ አስተዋጽዖ እንዳለው ተናግረዋል። በኢትዮጵያ የግብርና የመድን አገልግሎት ተደራሽነትን ለማስፋት በተለይም ስለ አገልግሎቱ አስፈላጊነት ግንዛቤ ሊኖር እንደሚገባ ጠቁመው፤ በቀጣይ አርሶ አደሩን የማስገንዘብ ሥራ ይሰራል ብለዋል።
በጤናው መስክ የሚታዩ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት መፍትሔ አመላካች ስራዎች ከዘርፉ ባለሙያዎች ይጠበቃል
Mar 4, 2024 141
አዲስ አበባ፤ የካቲት 25/2016(ኢዜአ)፡- በጤናው መስክ የሚታዩ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት መፍትሔ አመላካች ስራዎች ከዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚጠበቅ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አየለ ተሾመ ገለጹ። የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ለሰባተኛ ጊዜ በስድስት የህክምና መስኮች ያስተማራቸውን የጤና ባለሙያዎች በትናንትናው ዕለት አስመርቋል። በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አየለ ተሾመ የጤና ባለሙያዎች ስኬት የሚለካው በሚታደጓቸው ህይወት፣ በሚለውጧቸው ማህበረሰብ ነው ብለዋል። በተለይም ለዘርፈ ብዙ ችግር ተጋላጭ የሆኑ ወገኖችን መርዳትና ማሻገር ከጤና ባሙያዎች ይጠበቃል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ሃብት ባነሰበት፣ ያልተሟሉ ነገሮች በበዙበት ሀገር መስራት ፈተና የሚሆነውን ያህል በፈተና ወቅት ለሀገር የሚከፈል ዋጋ ነው ሲሉም አስገንዝበዋል።   ይህም ሰፊ እድል ይዞ የሚመጣ በመሆኑ ተመራቂዎች መፍትሄ አመንጪ የፈጠራ ሰዎች በመሆን ችግርን ወደ እድል እንዲቀይሩ አደራ ብለዋል። በተለያዩ የህይወት ውጣ ውረድ ውስጥ አልፋችሁ ከባዱን የጤና ትምህርት ለማጠናቀቅ እና ያስተማራችሁን ማህበረሰብ ጤና ለማሻሻል የተጋችሁ ተመራቂዎች እንኳን ደስ አላችሁ ያሉት ደግሞ የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር መንግስቱ በቀለ ናቸው። ማህበረሰባችን የሚፈልገው የህክምና ጥበባችሁን እና የሚያክበረው ሙያችሁን ብቻ ሳይሆን ሰብዓዊነታችሁን ጭምር በመሆኑ የምታገለግሉት ህዝብ እንደ እናትና አባታችሁ፣ እህትና ወንድሞቻችሁ ቆጥራችሁ ማገልገል ያስፈልጋል ብለዋል። የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ፕሮቮስት አቶ ስንታየው ተክሌ በበኩላቸው ተመራቂዎች ያገኙትን እውቀትና ልምድ ወደ ተግባር በመቀየር በቁርጠኝነት መስራት አንደሚገባቸው አስገንዝበዋል። በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አወሉ አብዲ እና የአዳማ ከተማ ከንቲባ አቶ ሀይሉ ጀልዴ ተገኝተው ለተመራቂዎች ድግሪና ሜዳልያ ማበርከታቸውን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያ በአለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ከአፍሪካ አንደኛ ከዓለም አምስተኛ በመሆን አጠናቀቀች 
Mar 4, 2024 172
አዲስ አበባ፤ የካቲት 25/2016 (ኢዜአ)፡- በ19ኛው የአለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ከአፍሪካ አንደኛ ከዓለም አምስተኛ በመሆን አጠናቃለች። በስኮትላንድ ግላስጎ ሲካሄድ የነበረው 19ኛው የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ትናንት ሌሊት ተጠናቋል። በውድድሩ ከተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ ከ650 በላይ አትሌቶች የተሳተፉ ሲሆን ኢትዮጵያም በ800 ሜትር፣ በ1500 ሜትር እና በ3000 ሜትር ርቀቶች በ8 ሴቶች እና በ5 ወንዶች በድምሩ በ13 አትሌቶች ተሳትፋለች ፡፡ በሻምፒዮናው ኢትዮጵያ በሴቶች 800 ሜትር ፅጌ ዱጉማ እና በሴቶች 1500 ሜትር ፍሬወይኒ ሀይሉ የወርቅ ሜዳሊያን አሸንፈዋል።   በሴቶች 3000 ሜትር ጉዳፍ ፀጋዬ የብር እንዲሁም በወንዶች 3000 ሜትር ሰለሞን ባረጋ የነሃስ ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ ያስገኙ አትሌቶች መሆናቸውን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል። በዚህ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ሁለት ወርቅ አንድ ነሀስ በአንድ ብር በአጠቃላይ በአራት ሜዳሊያዎችን በማግኘት በሜዳልያ ሰንጠረዥ ከአፍሪካ አንደኛ ከአለም አምስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች።
ማስታወቂያ
ኢዜአ
Feb 7, 2023 12352
ኢዜአ
ፖለቲካ
ኢትዮጵያና ዴንማርክ በተለያዩ የትብብር መስኮች ላይ የተመሰረተውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር ይሰራሉ 
Mar 4, 2024 84
አዲስ አበባ፤ የካቲት 25/2016(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያና ዴንማርክ ለበርካታ ዓመታት የዘለቀውንና በተለያዩ የትብብር መስኮች ላይ የተመሰረተውን የሁለቱ አገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚሰሩ ገለጹ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከዴንማርክ ፓርላማ የውጭ ፖሊሲ ኮሚቴ አባላት ጋር ተወያይቷል። የውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶክተር ዲማ ኖጎ በዚሁ ጊዜ በኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በፖለቲካና ምጣኔ ኃብት ዘርፎች እየተከናወነ ያለውን የለውጥ ሥራ አብራርተዋል። ጎን ለጎንም ወቅታዊ የአገሪቱን የሰላምና ጸጥታ ጉዳይ በተለይም በአገሪቱ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት በፕሪቶሪያው የተደረሰውን የሠላም ሥምምነት ትግበራ አስመልክቶም ማብራሪያ ሰጥተዋል። መንግሥት ለዘላቂ ሰላም ቁርጠኛ አቋም በመያዝ በአማራና ኦሮሚያ ክልል የሚስተዋሉ የጸጥታ ችግሮችን በውይይትና በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚያከናውናቸውን ተግባራትም ዘርዝረዋል። በሂደት ላይ ያለው የሽግግር ፍትህ ፖሊሲን በተመለከተም ገለጻ አድርገዋል።   በፖለቲካ ሊሂቃንና የኃሳብ መሪዎች መካከል የሚስተዋሉ ልዩነቶችን በውይይት በመፍታት ጠንካራ አገረ መንግሥት ለመገንባት በአገራዊ የምክክር ኮሚሽን በኩል እየተሰራ መሆኑንም አብራርተዋል። ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካም ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን በሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን እንዲሁም ሶማሊያ ያላትን የሰላም አስተዋጽኦ በማብራሪያቸው ጠቅሰዋል። በቀጣናው ሰላምና መረጋጋት በመፍጠር የምጣኔ ኃብት፣ የመሰረተ ልማት፣ የንግድና ሌሎች ዘርፎች ትስስር ለመፍጠርም በትኩረት እየሰራች መሆኑንም ገልጸዋል። ለአብነትም የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት በማድረግ የተገነባውን የታላቁ የሕዳሴ ግድብን አንስተዋል። ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት ከሶማሌላንድ ጋር ያደረገችውን የመግባቢያ ሥምምነት ለቀጣናው ሠላምና ደኅንነት እንዲሁም ምጣኔ ኃብት እድገት ያለውን አስተዋጽዖም አብራርተዋል።   የዴንማርክ ፓርላማ የውጭ ፖሊሲ ኮሚቴ ሰብሳቢ ማይክል አስትረፕ በበኩላቸው ኮሚቴው በኢትዮጵያ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ለማወቅና የአገራቱን ግንኙነት ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ በሚቻልባቸው ምቹ ሁኔታዎች ዙሪያ ለመምከር ወደ ኢትዮጵያ መምጣቱን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት በምስራቅ አፍሪካ ሰላምና ደኅንነት እንዲረጋገጥ በአገር ውስጥ ያሉ ችግሮች በሰላማዊ መልኩ ለመፍታት የሚያከናውናቸውን ተግባራት በአድናቆት እንደሚመለከቱት የዴንማርክ ፓርላማ የውጭ ፖሊሲ ኮሚቴ አባላት ገልጸዋል። የኢትዮጵያና የዴንማርክ የፓርላማ ተወካዮች በፓርላማ የሴቶች ተሳትፎና በሌሎች የፓርላማ ግንኙነቶች ልምድ በመለዋወጥ በጋራ ለመሥራት ተስማምተዋል። ሁለቱ አገራት ግንኙነታቸውን በምጣኔ ኃብት፣ በፖለቲካና ማኅበራዊ ዘርፎች የበለጠ በሚያጠናክሩባቸው ጉዳዮች ላይም በስፋት መክረዋል። ለበርካታ ዓመታት የዘለቀውንና በተለያዩ የትብብር መስኮች ላይ የተመሰረተውን የሁለቱ አገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚሰሩ በመድረኩ ተገልጿል።                                      
ኢትዮጵያ እና ጂቡቲ ረጅም ዓመት ያስቆጠረ የባህል እና የቋንቋ ትስስር ያላቸው ወንድማማች ህዝቦች ናቸው - አቶ አደም ፋራህ
Mar 4, 2024 110
አዲስ አበባ፤ የካቲት 25/2016(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ እና ጂቡቲ ረጅም ዓመት ያስቆጠረ የባህል እና የቋንቋ ትስስር ያላቸው ወንድማማች ህዝቦች ከመሆናቸው ባሻገር በኢኮኖሚያዊ እና በመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ዝርጋታ የጠበቀ ግንኙነት እንዳላቸው የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የዋናው ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አደም ፋራህ ገለጹ። በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የዋናው ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አደም ፋራህ የተመራው ልዑክ በጂቡቲ የገዢው ፓርቲ 45ኛ ዓመት ክብረ በዓል ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።   በመርሃ-ግብሩ ላይ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የዋናው ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አደም ፋራህ የአጋርነት ንግግር አድርገዋል። በንግግራቸውም ብልጽግና ፓርቲን ወክለው ለገዢው ፓርቲ እና ለጂቡቲ ህዝብ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። ኢትዮጵያ እና ጂቡቲ ረጅም ዓመት ያስቆጠረ የባህል እና የቋንቋ ትስስር ያላቸው ወንድማማች ህዝቦች ከመሆናቸው ባሻገር በኢኮኖሚያዊ እና በመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ዝርጋታ የጠበቀ ግንኙነት እንዳላቸው አንስተዋል።   የብልጽግና ፓርቲ ለጂቡቲ ገዢው ፓርቲ ያለውን አብሮነት እና ወንድማማችነት ለማስቀጠል ያለውን ቁርጠኛ አቋምም ገልጸዋል። በክብረ በዓሉ ላይ የቻይና፣ የኬንያ እና የሩዋንዳ ልዑካን መገኘታቸውን በጂቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል።
የሀረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ
Mar 3, 2024 161
አዲስ አበባ፤ የካቲት 24/2016(ኢዜአ)፦ የሀረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት (ካቢኔ) ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል። መስተዳድር ምክር ቤቱ በዋናነትም በሀረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት የከተማ ተቋማዊ እና የመሰረተ ልማት ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ፅህፈት ቤት በ2016 በጀት አመት በተዘጋጀው የCIP እቅድ እና የሐረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት የገቢ ርዕሶችና ታሪፍ ማሻሻያ ረቂቅ ደንብ ላይ መወያየቱ ተመላክቷል።   በዚህም መስተዳድር ምክር ቤቱ በከተማ ተቋማዊና መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም የ2016 የበጀት አመት ካፒታል ኢንቨስትመንት እቅድን መርምሮ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል። ምክር ቤቱ በCIP እቅድ ከባለፈው በጀት አመት የዞሩ 12 ፕሮጀክቶች እና በ2016 ለማከናወን የተያዙ አዳዲስ 29 ፕሮጀክቶችን ማስፈጸሚያ የቀረበለትን 242 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በጀትም መርምሮ አጽድቋል። መስተዳደር ምክር ቤቱ የሐረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት የገቢ ርዕሶችና ታሪፍ ማሻሻያ ረቂቅ ደንብ ላይም ከተወያየ በኋላም ከዛሬ ጀምሮ ስራ ላይ እንዲውል መወሰኑ ተገልጿል፡፡ መስተዳድር ምክር ቤቱ ከዚህ በተጨማሪም በሌሎች አጀንዳዎች ዙሪያ ውይይት በማካሄድ ውሳኔ ማሳለፉን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።
ወጣቱ ትውልድ የአድዋን ታሪክ መነሻ በማድረግ አገሪቱን ወደ ተሻለ ከፍታ የሚያሻግር የራሱን ታሪክ መሥራት አለበት - ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ
Mar 2, 2024 309
አዲስ አበባ፤ የካቲት 23/2016(ኢዜአ)፦ወጣቱ ትውልድ የአድዋን ታሪክ መነሻ በማድረግ አገሪቱን ወደ ተሻለ ከፍታ የሚያሻግር የራሱን ታሪክ መሥራት አለበት ስትል የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሸን ፕሬዝዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ተናገረች። በዓለም አደባባይ የአገሯን ሰንደቅ ያውለበለበችው የኦሊምፒክ ባለድሏ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሸን ፕሬዝዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ፣ የአድዋ ድል በከባድ መስዋዕትነት የተገኘ ድል ነው ብላለች። በአድዋ የተገኘው ድል ለኢትዮጵያዊያን ትልቅ ትርጉም ያለው መሆኑንም ጠቁማ እያንዳንዱ ትውልድ የአገሪቱን ሥም በበጎ የሚያስጠራበት የራሱ ታሪክ የሚጽፍበት አድዋ ሊኖረው እንደሚገባም ተናግራለች።   ለዚህም ደግሞ ማንኛውም ግለሰብ በየዘመኑና በተሰማራበት ሙያ የሚጠበቅበትን አገራዊ ሃላፊነት በአግባቡ መወጣት ሲችል መሆኑን ገልጻ ይህም የሁሉም አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ሃላፊነት ነው ብላለች። ጎን ለጎንም ትውልዱ የቀደሙ አባቶችን የአንድነትና አብሮነት እሴቶች ለማጠናከር ከአድዋ ጀግኖች ጽናትና አገር ወዳድነት እሴት በመውረስ ለአገር ከፍታ በትኩረት መሥራት እንዳለበትም ነው ያሳሰበችው። የአድዋ ድል በትውልዶች ሁሉ ሊዘከር የሚገባው ደማቅ የጋራ ታሪክ መሆኑን ያነሳችው ደራርቱ፣ ኢትዮጵያዊያን በመተባበር የተሻለ አገር ለመገንባት መሥራት እንደሚገባቸው ተናግራለች። በተለይም በዚህ ዘመን የአገር ሰላም በማስጠበቅ ሁሉም ዜጋ ሃላፊነቱን እንዲወጣም ጥሪ አቅርባለች።    
የአድዋ ድል የኢትዮጵያን ዘመናዊ የጦር ሠራዊት አባላት የአገር ፍቅርና ጀግንነት ስሜት አውርሷል - የቀድሞ ጦር ሠራዊት አባላት
Mar 2, 2024 197
አዲስ አበባ፤ የካቲት 23/2016 (ኢዜአ)፦ የአድዋ ድል የኢትዮጵያን ዘመናዊ የጦር ሠራዊት አባላት የአገር ፍቅርና ጀግንነት ስሜት ያወረሰ ድል መሆኑን ኢዜአ ያነጋገራቸው የቀድሞ ጦር ሠራዊት አባላት ተናገሩ። 128ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል አድዋ የጥቁር ሕዝቦች ድል ዓርማ በሚል መሪ ሃሳብ ተዘክሯል። በተለያዩ ጊዜያት አገራቸውን በአርበኝነትና በውትድርና ሙያ ያገለገሉ የቀድሞ ሠራዊት አባላት ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ የጥቁር ህዝቦች ነጻነት ዓርማ የሆነው አድዋ ድል የአገር ፍቅር እሴት ለትውልድ አውርሷል። በዚህም ኢትዮጵያ ዘመናዊ ጦር ሰራዊት አባላትም በአድዋ ጀግኖችን ታሪክና እሴት በመጋራት እንደቻሉ ተናግረዋል። የቀድሞ የፖሊስ ሰራዊት ባልደረባ ሆነው በተለያዩ ግዳጆች አገራቸውን ያገለገሉት ብርጋዴር ጀኔራል አንዳርጌ መሸሻ፣ የአድዋ ድል ለህዝቡ ብዙ እሴቶችን እንዳወረሰ ይናገራሉ። በዚህም ኢትዮጵያ ድሕረ አድዋ ለተቃጣባት ወረራዎች ሁሉ መቀልበስ የቻለችው ሰራዊቷ ከአድዋ ጀግኖች በወረሰው ጀግንነትና የአገር ፍቅር ስሜት መሆኑን ተናግረዋል። አባት አርበኛ ኮሎኔል ጃል ዑመር በፋቪስት ኢጣሊያ ወረራ ወቅት በአርበኝነት እንዲሁም በዜያድባሬዋ ሶማሊያ ወረራን ክተት ጥሪ ተቀላቅለው ሀገራቸውን ከወረራ ለመታደግ መዋደቃቸውን ይናገራሉ። የአድዋ ኢትዮጵያዊያን ውስጣዊ ችግራቸውንም ወደጎን በመተው በሕብረት ዘምተው የሀገር ክብርና ሉላዓላዊነት ያረጋገጡበት ድል መሆኑንም ገልጸዋል። ጠላት ከ40 ዓመታት በኋላ ድጋሚ ሲመጣ በወቅቱ ክተት ጥሪ ሲደረግ የራሳቸውን ስንቅና ትጥቅ ይዘው በአርበኝነት ያገለገሉት በአድዋ ጀግኖች እሴትን በመውረስ ስለመሆኑ ይናገራሉ። የክብር ዘበኛ ጦር ክፍል አባል የነበሩትና የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር አባል ሃምሳ አለቃ ዲባባ ጫላ የአድዋ ድል የተገኘው በከባድ መስዋዕትነት እንደሆነ ያወሳሉ። ይህ አኩሪ ታሪክ ጀግንነትና የአገር ፍቅርም እርሳቸውና ቤተሰባቸው ለአገራቸው መስዋዕትነት በመክፈል በውትድርና ለማገልገል ትልቅ እርሾ እንደሆናቸው አንስተዋል።
የአድዋ ድል የሕዝብ አንድነትና ኅብረት የተንፀባረቀበት ልዩ የጥቁር ሕዝቦች ታሪክ ነው 
Mar 2, 2024 209
አዲስ አበባ፤ የካቲት 23/2016 (ኢዜአ)፦ የአድዋ ድል የሕዝብ አንድነትና ኅብረት የተንፀባረቀበት ልዩ የጥቁር ሕዝቦች ታሪክ መሆኑን በመታሰቢያ በዓሉ የተገኙ የተለያዩ አገራት ተወካዮች ገለጹ። በ128ኛ የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል ላይ ኢዜአ ያነጋገራቸው የተለያዩ ሀገራት ኤምባሲ ተወካዮች የአድዋ ድል የመላው ጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ድል መሆኑን አንስተዋል። በኢትዮጵያ የአርመንያ አምባሳደር ሳሃክ ሳርግስያን፤ የአድዋ ድል ለኢትዮጵያውያን እንዲሁም ለጥቁር ሕዝቦች ወሳኝ የድል ታሪክ ነው ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪም በአድዋ ድል ጥንካሬ፣ ትብብር፣ የአገር ፍቅር፣ መስዋዕትነት የተንፀባረቀበት ልዩ የጥቁር ሕዝቦች ታሪክ መሆኑን ገልፀዋል። በመሆኑም 128ኛ የአድዋ ድል መታሰቢያ ላይ በመገኘታቸው የተሰማቸውን ክብር ተናግረዋል። በኢትዮጵያ የዛምቢያ ኤምባሲ የፖለቲካና አስተዳደር አማካሪ ናዋ ሲቦንጆ፤ የአድዋ ድል ለአፍሪካ አህጉር ወሳኝ የታሪክ ምዕራፍ መሆኑን አንስተዋል። ኢትዮጵያውያን ዘር፣ ቀለም፣ ሃይማኖት፣ የፖለቲካ ልዩነት ሳይገድባቸው ለሀገር ሉዓላዊነት በሕብረት የተሳተፉበት በመሆኑ የአንድነት ምሳሌ ነው ብለዋል። በመሆኑም ከአድዋ ድል አፍሪካውያን ልዩነታቸውን በመቻቻል የበለፀገችና አንድነቷ የተጠናከረ አፍሪካን ለመፍጠር ትምህርት የምንወስድበት ነው ሲሉ ተናግረዋል። በኢትዮጵያ የባንግላዲሽ ኤምባሲ የመከላከያ አታሼ ብርጋዴር ጄኔራል ጂኤም ሻሪፉል፤ የአድዋ ድል ኢትዮጵያውያን ለቅኝ ግዛት ባለመንበርከክ ኃያልነታቸውን ያሳዩበት ወሳኝ የድል ታሪክ መሆኑን ገልፀዋል። ድሉም የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የመላው ጥቁር ሕዝቦች መሆኑን ጠቁመዋል። ኢትዮጵያውያን በአንድነት የፋሽስትን ወራሪ ኃይል ድል ያደረጉበት 128ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ የተለያዩ አገራት አምባሳደሮች፣ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች፣ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት በአድዋ ድል መታሰቢያ በተለያዩ ሁነቶች ተከብሯል።

ማህበራዊ
አምስት የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በቴክኖሎጂ የታገዘ (e-learning) የትምህርት መርኃ ግብር ወደ ሥራ አስገቡ
Mar 4, 2024 107
አዲስ አበባ፤ የካቲት 25/2016(ኢዜአ)፡-አምስት የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በቴክኖሎጂ የታገዘ (e-learning) የመማር ማስተማር የትምህርት መርኃ ግብር ወደ ሥራ አስገቡ። የትምህርት መርኃ ግብሩ የትምህርት ሚኒስቴር ከማስተርካርድ ፋውንዴሽን፣ ከአሜሪካው አሪዞና ስቴት ዩኒቨርሲቲና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ነው ወደ ሥራ የገባው። ትምህርቱን መስጠት የሚያስችሉ የአምስት ዩኒቨርሲቲዎች "ብሔራዊ መልቲ-ሚዲያ ስቱዲዎዮች" የትምህርት ሚኒስቴርና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራሮች በተገኙበት በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመርቀዋል። በምርቃ ሥነ-ሥርዓቱ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በተወካያቸው በኩል ባስተላለፉት መልዕክት፤ መንግሥት ባለፉት ዓመታት የከፍተኛ ትምህርት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የተለያዩ ተግባራት ሲያከናውን ቆይቷል ብለዋል። ይህንንም ተከትሎ አሁን ላይ በአገሪቱ 51 የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎችና ከ300 በላይ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተከፍተው የመማር ማስተማር ተግባር እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል። ይሁንና በተለይም የትምህርት ጥራትን ከማረጋገጥ አኳያ አሁንም ውስንነቶች መኖራቸውን ጠቁመዋል። በመሆኑም መንግሥት የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት ከትምህርት ማኅበረሰቡና ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በመሆን የተለያዩ የማሻሻያ እርምጃዎችን እየወሰደ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ከእነዚህም መካከል በዛሬው ዕለት ሥራ የጀመረው በቴክኖሎጂ የተገዘው (e-learning) የመማር ማስተማር የትምህርት መርኃ ግብር ተጠቃሽ መሆኑን ገልጸዋል። መርኃ ግብሩ ዋና ዓላማም በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ጥራት፣ አግባብነትና ተደራሽነትን ለማሳደግ ያለመ መሆኑን ተናግረዋል። ከዛሬ ጀምሮ በአዲስ አበባ፣በባህርዳር፣በአዋሳ፣በድሬዳዋና በጂማ ዩኒቨርሲቲዎች በተገነቡ የብሔራዊ መልቲ-ሚዲያ ስቱዲዮች አማካኝነት የትምህርት መርኃ ግብሩ በይፋ መጀመሩን ገልጸዋል። በዚህም የመጀመሪያና የሁለተኛ ዲግሪ የትምህርት መርኃ ግብሮች እንደሚሰጡ ጠቅሰው በቀጣይም መርኃ ግብሩ በሌሎች ዩኒቨርስቲዎች ተግባራዊ እንደሚሆን ተናግረዋል።   የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዘዳንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ በበኩላቸው፤ በቴክኖሎጂ የታገዘው ይህ የትምህርት መርኃ ግብር መጀመር በተለይም የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ተናግረዋል።  
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የማህፀን በር ካንሰር ቅድመ መከላከያ ክትባት ዘመቻ በይፋ ተጀመረ
Mar 4, 2024 86
ጂንካ ፤የካቲት 25/2016(ኢዜአ)፡- በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የማህፀን በር ካንሰር ቅድመ መከላከያ ክትባት ዘመቻ በይፋ ተጀመረ። ክትባቱ በክልሉ ለሚገኙ ዕድሜያቸው 14 ዓመት ለሆናቸው 154 ሺህ 848 ልጃገረዶች እንደሚሰጥም ተገልጿል። የክትባት ዘመቻው በክልሉ ኣሪ ዞን በጂንካ ከተማ በቄራ መጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ዛሬ በይፋ ተጀምሯል።   በማስጀመሪያ መረሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ እንዳሻው ሽብሩ፤ የማህፀን በር ካንሰር ከጡት ካንሰር ቀጥሎ እናቶችን ለሞትና ለስቃይ እየዳረገ ያለ ገዳይ በሽታ ነው።   በሽታውን ለመከላከል የቅድመ መከላከያ ክትባት መውሰድ እንደሚገባ ገልጸው፣ ክትባቱ በሽታውን 95 በመቶ የመከላከል አቅም እንዳለው ተናግረዋል። እድሜያቸው ከ30 በላይ የሆኑ እናቶች ደግሞ ምርመራ በማድረግ ራሳቸውን ከበሽታው እንዲጠብቁም ኃላፊው አሳስበዋል። አምና በክልሉ ከተመረመሩ 21 ሺህ እናቶች 1500 የሚሆኑት የበሽታው ምልክት እንደታየባቸው አስታውሰው፣ የበሽታውን ስርጭት ለመከላከል የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች በስፋት መካሄድ እንዳለባቸው ተናግረዋል። የማህፀን በር ካንሰር ቅድመ መከላከያ ክትባት ዘመቻ ከዛሬ ጀምሮ በትምህርት ቤቶች፣ በጤና ተቋማትና ለክትባት በተመረጡ ጊዜያዊ የክትባት ጣቢያዎች ይሰጣል።  
በትምህርት ምዘና እና የፈተና ማሻሻያ ላይ የተጀመሩ ሥራዎችን ውጤታማ ለማድረግ ምሁራን በጥናትና ምርምር እንዲደግፉ ተጠየቀ
Mar 4, 2024 86
አዲስ አበባ፤ የካቲት 25/2016(ኢዜአ)፡- በትምህርት ምዘና እና የፈተና ማሻሻያ ላይ የተጀመሩ ሥራዎችን ውጤታማ ለማድረግ ምሁራን በጥናትና ምርምር ሊደግፉ ይገባል ሲሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ። የመጀመሪያው የትምህርት ምዘና ብሔራዊ ጉባዔ "በኢትዮጵያ የትምህርት ምዘና እና የፈተና አሰጣጥ ሥርዓቶችን መለወጥ፤ የነገ ትልሞችን ለማሳካት" በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።   በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፤ በትምህርት ጥራትና ተደራሽነት ላይ መንግሥት በልዩ ትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል። የትምህርት ጥራትን ከማስጠበቂያ መንገዶች አንዱ የትምህርት ምዘና እና ፈተናን ማሻሻል መሆኑን ጠቅሰው፤ ለዚህም የተቀናጀ ጥረትና ድጋፍ ያስፈልጋል ብለዋል። በዚህ ረገድ በመንግሥት የተጀመሩ ሥራዎችን ለማሳካት በተለይም ምሁራን በጥናትና ምርምር እንዲደግፉ ጠይቀዋል። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ኃብት ልማት፣ ስራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶክተር ነገሪ ሌንጮ፤ በትምህርት ዘርፍ ላይ የሚስተዋሉ የጥራትና ተደራሽነት ችግሮችን በዘላቂነት መፍታት ይገባል ብለዋል።   የትምህርት ምዘና እና የፈተና አሰጣጥ ሂደት የሚፈለገውን የትምህርት ጥራት ለማምጣት አጋዥ መሆኑን ጠቅሰው፤ የተቀናጀ ጥረት መደረግ እንዳለበት አንስተዋል። ለዚህም የትምህርት ምዘና ብሔራዊ ጉባዔ መካሄዱ ትልቅ ግብአት የሚገኝበት እንደሚሆን ያላቸውን እምነት ገልፀዋል። የፖሊሲ፣ የሥርዓተ-ትምህርት፣ የመማር ማስተማር ሂደትና ሌሎችንም አሠራሮች በማሻሻል የተጀመረው ጥረት በዘርፉ የሚፈለገውን ውጤት ለማምጣት የሚያግዝ መሆኑንም ተናግረዋል። የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር እሸቱ ከበደ፤ የትምህርት ምዘና እና የፈተና አሰጣጥ ሂደት ውጤታማነት ለትምህርት ጥራት ማስጠበቅ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰዋል።   ለዚህም መሳካት በተለይም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ ሥራ መጠናከር እንዳለበት አንስተዋል። በጉባዔው ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎች፣ ሀገር አቀፍ ፈተናዎችና የትምህርት ምዘና ላይ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችሉ አዳዲስ ሃሳቦችና ልምዶች የሚቀርቡበት ይሆናል ብለዋል። የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፕሬዝዳንቶች፣ የክልል የትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች እንዲሁም የተለያዩ ምሁራን የተገኙበት የመጀመሪያው የትምህርት ምዘና ብሔራዊ ጉባዔ ዛሬ እና ነገ ይካሄዳል።  
በኢትዮጵያ  በማህጸን በር ካንሰር ምክንያት በዓመት ከ5ሺህ በላይ ሴቶች ህይወታቸው ያልፋል-  የጤና ሚኒስቴር
Mar 4, 2024 75
አዲስ አበባ፤ የካቲት 25/2016(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ በማህጸን በር ካንሰር ምክንያት በዓመት ከ5ሺህ በላይ ሴቶች ህይወታቸው እንደሚያልፍ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። የማህፀን በር ካንሰር በሽታ መከላከያ ክትባት “ክትባት የሁሉንም ማህበረሰብ ጤና ለማስጠበቅ” በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ ከዛሬ ጀምሮ በዘመቻ እየተሰጠ ይገኛል፡፡ የጤና ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ የመገናኛ ብዙሃን ለህብረተሰቡ ተዓማኒነት ያለውን መረጃ እንዲያገኝ በማድረግ በኩል የበኩላቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ጠይቋል፡፡ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ እንደተናገሩት በኢትዮጵያ በዓመት በማህጸን በር ካንሰር ምክንያት ከ5ሺህ በላይ ሴቶች ህይወታቸው ያልፋል። እድሜያቸው ከ14 ዓመት በላይ ከሆኑት ሴቶች ከአምስቱ አራቱ በህይወት ዘመናቸው ለማህፀን በር ካንሰር ተጋላጭ እንደሚሆኑም ተናግረዋል፡፡   የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ በዓመት 2 ጊዜ በ6 ወር ልዩነት ሁለት ዶዝ ክትባት ሲሰጥ መቆየቱን አንስተዋል። አለማቀፍ ጥናቶች መሰረት በማድረግ አንድ ጊዜ በተከተቡት እና ሁለት ጊዜ በተከተቡት ልጆች መካከል የክትባቱ ውጤታማነት ሲታይ ተመጣጣኝ የሚባል የመከላከል አቅም በማሳየቱ፣ ከዚህ ዓመት ጀምሮ አንድ ዶዝ ብቻ የሚሰጥ መሆኑንም ሚኒስትሯ አብራርተዋል፡፡ በ2016 አመት ብቻ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን የሚጠጉ እድሜያቸው 14 አመት የሆናቸው ሴቶች ልጆች ለመከተብ መታቀዱም የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። ክትባቱ በትምህርት ቤቶች፣ በጤና ተቋማት፣ በጊዜያዊ ክትባት መስጫ ጣቢያዎችም እንደሚሰጥም ተጠቁሟል። የሀይማኖት አባቶች፣ የጎሳ መሪዎች፣ የአካባቢ ሽማግሌዎች፣ የአካባቢው ማኅበረሰብ፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ድጋፍና ትብብር እንዲያደርጉም ተጠይቋል። ለክትባቱ ዘመቻ ውጤታማነት ቁልፍ አጋር የሆኑት መምህራን እና የትምህርት ቤት ማህበረሰብ የተለመደውን ድጋፍና ትብብር እንዲያደርጉ የጤና ሚኒስቴር ጥሪ አቅርቧል፡፡ ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች እድሜያቸው 14 ዓመት የሆናቸው ሴት ልጆች የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት እንዲወስዱ በማድረግ ግዴታቸውን እንዲወጡም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አሳስቧል፡፡
ኢኮኖሚ
በክልሉ አዳዲስ ባለሃብቶችን ከመሳብ ባለፈ፤ ነባር ኢንዱስትሪዎች የተሻለ ማምረት እንዲችሉ የተጀመሩ ስራዎች ይጠናከራሉ - አቶ እንድሪስ አብዱ
Mar 4, 2024 66
ደብረ ብርሃን፤ የካቲት 25/2016 (ኢዜአ)፦ የአማራ ክልል አዳዲስ ባለሃብቶችን ከመሳብ ባለፈ፤ ነባር ኢንዱስትሪዎች የተሻለ ማምረት እንዲችሉ የተጀመሩ ስራዎች የሚጠናከሩ መሆኑን የክልሉ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሃላፊ አቶ እንድሪስ አብዱ ገለጹ። በአማራ ክልል ደረጃ ''የኢትዮጵያ ታምርት'' ንቅናቄ መድረክ በደብረ ብርሃን ከተማ ዛሬ ተካሄዷል። አቶ እንድሪስ በመድረኩ ላይ እንደተናገሩት ንቅናቄው በአማራ ክልል የኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም በማሳደግ አበረታች ውጤት እያስመዘገበ ነው። በንቅናቄው ለረጅም ዓመታት ቆመው የነበሩ አምራች ኢንዱስትሪዎች ችግሮቻቸውን በመፍታት ወደ ሥራ መግባታቸውን አስረድተዋል። በዚህም ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅማቸውን በማሳደግ ምርቶቻቸውን ለሃገር ውስጥና ለውጭ ገበያ ለማቅረብ እንደተቻለ ሃላፊው ተናግረዋል። በቀጣይም አዳዲስ ባለሃብቶችን ከመሳብ ባለፈ፤ ነባር ኢንዱስትሪዎች የተሻለ ማምረት እንዲችሉ ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል።   የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ሃላፊ አቶ ብርሃን ገብረሀይወት፣ በከተማዋ በባለሀብቱና በአስተዳደሩ መካከል ያለው ቅንጅታዊ አሰራር እየተጠናከረ መምጣቱን ገልጸዋል። በከተማዋ ያሉትን የኢንዱስትሪዎችን ትስስር ለማጠናከር 3 ነጥብ 2 ኪሎ ሜትር መንገድ መገንባቱን ገልጸው በዚህም ባለሀብቶችም ወደ ምርት የመሸጋገር አቅማቸው ማደጉን አቶ ብርሃን ተናግረዋል። መድረኩ ችግሮችን በጋራ በመለየት ለቀጣይ የልማት እንቅስቃሴ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ታስቦ መዘጋጀቱንም ገልጸዋል። የደብረ ብርሃን መኪና መገጣጠሚያ ኢንዱስትሪ ሥራ አስኪያጅ አቶ መሐመድ አህመድ፣ መንግሥት ለባለሃብቶች እያደረገ ያለው እገዛ የሚያበረታታ መሆኑን አመልክተው፣ አሁንም በመሰረተ ልማት ዝርጋታ ረገድ የተጀመሩ ስራዎች እንዲጠናከሩ ጠይቀዋል። በኢትዮ ቴሌኮም የማዕከላዊ ሰሜን ሪጅን ዳይሬክተር አቶ አንተነህ ፋንታሁነኝ በበኩላቸው ተቋሙ በአካባቢው ያለውን የቴሌ መሰረተ ልማት ለማዘመን 210 ሚሊየን ብር መድቦ እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል። በየደረጃው የሚገኙ የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች ሪጅኑ የሚጠይቀውን የኔትወርክ ማስፋፊያ ቦታ ካቀረቡ የባለሀብቶቹ ጥያቄ በፍጥነት ምላሽ ያገኛልም ብለዋል።            
በህብረት ስራ ዘርፍ የተጀመረውን ሀገር አቀፍ ሪፎርም ወጤታማ ለማድረግ አመራሩ ተገቢውን ትኩረት እንዲሰጥ ተጠየቀ
Mar 4, 2024 78
አዳማ፤ የካቲት 25/2016 (ኢዜአ)፦ በህብረት ስራ ዘርፍ የተጀመረውን ሀገር አቀፍ ሪፎርም ወጤታማ ለማድረግና ግቡን ለማሳካት የፖለቲካ አመራሩ ተገቢውን ትኩረት እንዲሰጥ በዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል የአደረጃጀት ዘርፍ ሚኒስትር አቶ ሳዳት ነሻ አስገነዘቡ። የተጀመረውን የህብረት ስራ ሪፎርም ለማሳካት ላይ ያተኮረ የፌዴራልና የክልሎች የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች የተሳተፉበት መድረክ በአዳማ ከተማ ዛሬ ተካሄዷል።   በመድረኩ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል የአደረጃጀት ዘርፍ ሚኒስትር አቶ ሳዳት ነሻ ለህብረት ስራ ትኩረት መስጠት ካልቻልን የተሟላና የሚፈለገውን የኢኮኖሚ ልማትና እድገት ማምጣት አንችልም ብለዋል። በተለይ የኑሮ ውድነትና የስራ አጥነትን ለመቀነስና ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል እንዲረጋገጥ የህብረት ስራ ማህበራት ያላቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰዋል። እስካሁን ባለው ሂደት ዘርፉ በሀገር ልማትና እድገት ውስጥ የሚጠበቅበትን ያህል አስተዋጽኦ እያበረከተ አለመሆኑንም ተናግረዋል። በዚህም የህብረት ስራ ማህበራትና ዩኒየኖች የግብርና ግብዓት አቅርቦት ላይ ብቻ እንዲወሰኑ ማድረጉን የገለጹት ሚኒስትሩ በተለይ ገበያን በማረጋጋትና ስራ አጥነትን በመቀነስ ረገድ የሚጠበቅባቸውን ያህል መጓዝ እንዳልቻሉ ተናግረዋል። ዘርፉ በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ውስጥ የሚጠበቅበት አስተዋጽኦ ማበርከት እንዲችልና በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረው ሪፎርም እንዲሳካ በየደረጃው ያለው የፖለቲካ አመራር ተገቢውን ትኩረት እንዲሰጠው ሲሉ አሳስበዋል። ሪፎርሙን በመተግበር፣ አደረጃጀትና አሰራር በመዘርጋት፣ ዘርፉ ከማምረት እስከ ገበያ ድረስ ባለው የምርትና ግብይት ሰንሰለት ውስጥ መሪ ሚና እንዲኖረው ለማስቻል ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል። ወጥነት ያለው የህብረት ስራ ሪፎርም ትግበራ እንዲረጋገጥ ፓርቲው ተገቢውን ድጋፍና እገዛ ያደርጋል ያሉት ደግሞ በዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል የፖለቲካ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ሙሳ አህመድ ናቸው። ሪፎርሙ የአመራሩን ትኩረት ማግኘት አለበት ያሉት አቶ ሙሳ የህብረት ስራ ዘርፍ ረዥም ታሪክ ያለው ቢሆንም አሁን ሀገሪቷ ከደረሰችበትና የዋጋ ግሽበቱን ለመቆጣጠር በሚደረገው ጥረት ውስጥ የሚጠበቅበትን ያህል እያገዘ አይደለም ብለዋል። በመሆኑም የተጀመረው ሀገራዊ የህብረት ስራ ሪፎርም ንቅናቄ ተገቢው ትኩረት ከተሰጠው የዘርፉን ችግሮች የሚፈታ ነው ብለዋል። የኢትጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ጌታቸው መለሰ በበኩላቸው ሪፎርሙ አጠቃላይ የዘርፉ አሰራርና አደረጃጀት ከመሰረቱ ከመለወጡም ባለፈ ተወዳዳሪ የህብረት ስራ ማህበራትን ለመፍጠር ቁልፍ ሚና ያለው መሆኑን ተናግረዋል።   መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት የሀገር በቀልና ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎች የተካተቱበት አሰራሮች፣ የህግ ማእቀፎች፣ ማኑዋሎችና መመሪያዎች ተዘጋጅተው ወደ ትግበራ መገባቱን አመልክተዋል። በዚህም የአሰራር፣ የአደረጃጀት፣ የተጠሪነት፣ የቴክኖሎጂ፣ የክህሎት፣ የፋይናንስ አቅም ውስንነትን ጨምሮ በርካታ የዘርፉ ማነቆዎችን በመፍታትና ዘርፉን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ ያለመ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል።  
ዩ.ኤን.ዲ.ፒ በኢትዮጵያ የግብርና ዘርፍ የመድን አገልግሎት ለማጠናከር የሚያስችል መርኃ-ግብር ይፋ አደረገ
Mar 4, 2024 80
አዲስ አበባ፤ የካቲት 25/2016(ኢዜአ)፦የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም (ዩ.ኤን.ዲ.ፒ) የግብርና ዘርፍ የመድን አገልግሎትን ለማጠናከር የሚያስችል መርኃ-ግብር ይፋ አደረገ። መርኃ-ግብሩ ሕብረተሰቡ የአደጋ ተጋላጭነትን ለመቆጣጠር አቅም እንዲያጎለብት እንደሚያስችለው ተጠቅሷል። ዛሬ ይፋ የሆነው ይኸው መርኃ-ግብሩ በቀጣይ አራት ዓመታት በኢትዮጵያ ገቢራዊ የሚሆን ሲሆን፤ 1 ነጥብ 9 ሚሊየን ዶላር በጀት የተያዘለት መሆኑም ተመላክቷል። በዩ.ኤን.ዲ.ፒ ኢትዮጵያ የአካታች ኢኮኖሚ ልማት መርኃ-ግብር አስተባባሪ ግዛቸው ሲሳይ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት፤ የግብርና መድህን ስርዓቱ በዋናነት ሁለት ዓላማዎች አሉት።   የመጀመሪያው አነስተኛ ይዞታ ያላቸው እንዲሁም በዘመናዊ መንገድ በግብርና የተሰማሩ አርሶ አደሮች የመድን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችል መሆኑን ገልፀዋል። ይህም የአደጋ ሥጋትን መቋቋም የሚችል ግብርና እንዲያከናውኑ የሚያስችላቸው መሆኑን ተናግረዋል። በአገሪቱ በአጠቃላይ የግብርና የመድን አገልግሎት ሥርዓት ውስጥ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር ደግሞ ሌላኛው የመርኃ-ግብሩ ዓላማ መሆኑን ጠቁመዋል።   በብሔራዊ ባንክ የኢንሹራንስ ሱፐርቪዥን ዳይሬክተር በላይ ቱሉ በበኩላቸው፤ መርኃ-ግብሩ የግብርና የመድን አገልግሎት ከመመሪያው ጀምሮ ያሉ ክፍተቶችን ለማረም ይረዳል ብለዋል። ይህም ብቻ ሳይሆን በዘርፉ የሚስተዋለውን የአቅም ክፍተት ለመሙላት እንደሚያግዝ ጠቁመዋል።   መርኃ-ግብሩ በዘርፉ የሚሰሩ ተግባራትን ይበልጥ ለማጎልበት ያስችላል ያሉት ደግሞ በግብርና ሚኒስቴር የግብርና ኢንቨስትመንትና ምርት ግብይት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ደረጀ አበበ ናቸው። የግብርና የመድን አገልግሎት በኢትዮጵያ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ መሆኑን አስታውሰው፤ መርኃ-ግብሩ የመድን አገልግሎት ሽፋኑን ለማስፋት አዎንታዊ አስተዋጽዖ እንዳለው ተናግረዋል። በኢትዮጵያ የግብርና የመድን አገልግሎት ተደራሽነትን ለማስፋት በተለይም ስለ አገልግሎቱ አስፈላጊነት ግንዛቤ ሊኖር እንደሚገባ ጠቁመው፤ በቀጣይ አርሶ አደሩን የማስገንዘብ ሥራ ይሰራል ብለዋል።
ቪዲዮዎች
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
በዓመት ለኔትወርክ ግዢ የሚወጣውን 60 ሚሊየን ዶላር ማስቀረት የሚያስችል ፕሮጀክት ተግባራዊ ሊደረግ ነው
Mar 1, 2024 266
አዲስ አበባ፤ የካቲት 22/2016(ኢዜአ)፦ ሀገሪቱ በዓመት ለኔትወርክ ግዢ የምታወጣውን 60 ሚሊየን ዶላር ማስቀረት የሚያስችል ብሔራዊ የኔትዎርክ ማሳለጫ ፕሮጀክት ተግባራዊ ሊደረግ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ። ለአንድ ሳምንት ሲካሔድ የቆየው ሀገራዊ የዲጂታል አቅሞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሳምንት'ዛሬ ተጠናቋል። መርሃ ግብሩ ሀገሪቱ ያላትን የቴክኖሎጂ አቅም አሟጦ ለመጠቀምና በዘርፉ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን ለመፍታት ያለመ ነው ተብሏል። በመርሃ ግብሩ ላይ በሚኒስቴሩ የብሔራዊ ኔትወርክ ፕሮጀክት መሪ አቶ ዳንኤል አድነው የፕሮጀክቱን አስፈላጊነት የሚዳስስ ጽሁፍ አቅርበዋል። ኢትዮጵያ እየተጠቀመች ያለው ኢንተርኔት ቨርዠን ፕሮቶኮል አለም የደረሰበት የቴክኖሎጂ ደረጃ ላይ ለመድረስ አዳጋች እንዲሆን አድርጎታል ብለዋል። በተጨማሪም በቀላሉ መልማት የሚችል የኔትወርክ ስርጭት እያለ ሀገሪቱ ለኔትወርክ ብቻ አላስፈላጊ ወጪ እንድታወጣና ለሳይበር ጥቃት ተጋላጭ እንድትሆን አድርጓቷል ነው ያሉት። ተግባራዊ የሚደረገው ብሔራዊ የኔትዎርክ ማሳለጫ ፕሮጀክት ሀገሪቱን ከአላስፈላጊ ወጪና ከሳይበር ጥቃት የሚታደግ ነው ብለዋል። ፕሮጀክቱን በሙከራ ደረጃ በማልማት ተግባራዊ መደረጉን ገልጸው፤ በቀጣይ በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ተደራሽ በማድረግ የኢንተርኔት አገልግሎቱን ፈጣንና ቀልጣፋ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል። ፕሮጀክቱ በሀገሪቱ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች በቴክኖሎጂ እንዲደገፉ ለማድረግ፣ በትምህርት ስርዓቱ ላይ የተጀመረውን ቴክኖሎጂያዊ አሰራር ለማጠናከርና ተቋማት የሚሰጡትን አገልግሎቶች ለማቀላጠፍ የሚያግዝ ነው ብለዋል። ፕሮጀክቱ ሙሉ በመሉ ተግባራዊ ሲሆን በዋናነት እየተስፋፋ የመጣውን የሳይበር ጥቃት 80 በመቶ ለመቀነስ የሚያስችል መሆኑንም አክለዋል። እንዲሁም ለኢንተርኔት ግዢ ሀገሪቱ በዓመት የምታወጣውን ከ60 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ ማዳን ያስችላል ነው ያሉት። ብሔራዊ የኔትዎርክ ማሳለጫ ፕሮጀክት የተለያዩ የሙከራ ስራዎች ተደርጎለት ስኬታማ በመሆኑ በቅርቡ ተግባራዊ እንደሚደረግም አረጋግጠዋል።   የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ይሽሩን አለማየሁ በበኩላቸው ሀገራዊ የዲጂታል አቅሞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሳምንት በዲጂታል እና በአይሲቲ ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራትን ለማስተዋወቅ የተካሔደ ነው። በተጨማሪም ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን በማድረግ ሒደት ውስጥ ሀገሪቱ በዘርፉ ያላትን አቅም ለማስገንዘብና ቴክኖሎጂን አሟጦ ለመጠቀም የሚያግዝ እንደነበርም ገልጸዋል። በአጠቃላይ የዲጂታል ስርዓቱን ይበልጥ ተደራሽ በማድረግ ግብይቱን ለማስፋትና ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በትኩረት እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
የከተሞች ፎረም መዘጋጀቱ ችግር ፈቺ አዳዲስ የፈጠራ ሥራዎቻችንን ለማስተዋወቅ ዕድል ፈጥሮልናል - ተሳታፊዎች
Feb 25, 2024 341
ሶዶ፤ የካቲት 17/2016(ኢዜአ)፦ በዘጠነኛው የከተሞች ፎረም ላይ መሳተፋቸው የህብረተሰቡን ችግር የሚያቃልሉ አዳዲስ የፈጠራ ሥራዎቻቸውን ለማስተዋወቅ ዕድል እንደፈጠረላቸው በፎረሙ ላይ የተሳተፉ ሥራ ፈጣሪዎች ገለጹ። ከየካቲት 9 እስከ 15/2016 በወላይታ ሶዶ በተካሄደው 9ኛው የከተሞች ፎረም ላይ የተሳተፉ ሥራ ፈጣሪዎች እንደገለጹት በፎረሙ የተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች መሳተፋቸው አብሮነትን ለማጠናከር የሚያስችል ነው። የህብረተሰቡን ችግር የሚያቃልሉ አዳዲስ የፈጠራ ሥራዎቻቸውን ለማስተዋወቅ ፎረሙ የተሻለ ዕድል እንደፈጠረላቸውም ለኢዜአ ገልጸዋል። አስተያየታቸውን ለኢዜአ ከሰጡ ሥራ ፈጣሪዎች መካከል የወራቤ ከተማ ነዋሪው አቶ ረሻድ ከድር በእናቶች እና አርሶ አደሮች ላይ የሚስተዋለውን የሥራ ጫና ማቃለል የሚያስችል የእንሰትና የቆጮ መፋቂያ፣ የጤፍ መውቂያ እንዲሁም የቃጫ ማምረቻ ማሽኖች ማቅረባቸውን ጠቅሰዋል።   ይህም የፈጠራ ሥራዎቻችንን ለማስተዋወቅ የተሻለ እድል ፈጥሮልናል ሲሉም ገልጸዋል። በወላይታ ዞን የአረካ ከተማ ነዋሪውና በአውደ ርዕዩ ላይ የሰራውን መኪና ይዞ የቀረበው ወጣት አጃዬ ማጆር በበኩሉ ፎረሙ ያለንን የፈጠራ ውጤት ለሌሎች ለማስተዋወቅ ረድቶናል ብሏል።   የባለ ሁለት እግር ሞተር ሳይክል ሞተርን በመጠቀም መኪናውን እንደሰራ የተናገረው ወጣቱ፣ የፈጠራ ሥራዎች እየተጠናከረ መምጣት የውጭ ምንዛሬን ከማስቀረት ባለፈ ለዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር እነደሚያስችልም አክሏል።   በ8ኛው የከተሞች ፎረም ላይ በፈጠራ የተሰሩ መኪኖች ለእይታ እንዳልቀረቡ ያስታወሰው ወጣት አጃዬ፣ ዘንድሮ ለ9ኛ ጊዜ በተካሄደው የከተሞች ፎረም ላይ የተለያዩ መኪኖች ቀርበው መመልከቱን ተናግሯል። የፈጠራ ሥራዎች እያደጉ መምጣት ሥራ ፈጣሪዎችን በማነቃቃት ሀገራዊ አድገትን ለማፋጠን የራሱ ጠቀሜታ እንዳለውም ጠቁሟል። ፎረሙ ከተሞች ያላቸውን ሀብትና የሥራ ፈጠራ ውጤት እንዲያስተዋውቁ እድል መፍጠሩን የተናገሩት ደግሞ የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪው አቶ ዳዊት አብርሃም ናቸው።   በአካባቢው በስፋት የሚመረተውን የሙዝ ምርት ወደ ዱቄት፣ ገንፎ፣ ኬክና ሌሎች ጣፋጭ ምግቦች እንዲሁም ኮባውን ወደ ቃጫነት ቀይሮ የሚሰራ ማሽን ሰርተው ፎረሙ ላይ ለእይታ ማቅረባቸውን ጠቅሰዋል። ከዚህ በፊት ከእንሰት ውጤት ይገኝ የነበረውን ቃጫ በአሁኑ ወቅት ከሙዝ እያመረቱ መሆናቸውን የገለጹት አቶ ዳዊት፣ ፎረሙ ይሄንና አዳዲስ ፈጠራዎችን ከማቅረብ ባለፈ ሥራ ፈጣሪዎችን እርስ በእርስ ያስተዋወቀ መሆኑን ተናግረዋል። የከተሞች ፎረም "የዘመኑ ከተሞች ለኢትዮጵያ ብልጽግና" በሚል መሪ ሀሳብ ከየካቲት 9 እስከ 15 ቀን 2016 ዓ.ም በርካታ ከተሞች በተሳተፉበት በወላይታ ሶዶ ከተማ መካሄዱ የሚታወስ ነው።
አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ለሲዳማ ክልል የደህንነት ካሜራዎች ድጋፍ አደረገ
Feb 24, 2024 373
አዲስ አበባ፤ የካቲት 16/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ለሲዳማ ክልል የፀጥታ ተቋማትን ለማጠናከር የሚያገለግሉ የደህንነት ካሜራዎች ድጋፍ አደረገ፡፡ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ አቅምን የተላበሱት የደህንነት ካሜራዎቹ ግምታዊ ዋጋቸው 25 ሚሊዮን ብር መሆኑን የኢንስቲትዩቱ መረጃ ያመለክታል። ካሜራዎቹ የሐዋሳ ከተማን እንዲሁም የክልሉን ፖሊስ አሰራር በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በማዘመን የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ ጉልህ ሚና እንደሚኖራቸው በርክክቡ ወቅት ተጠቅሷል፡፡ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታገሱ ደሳለኝ ለሲዳማ ክልል የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ ካሜራዎቹን እና ተያያዥ የቴክኖሎጂ ቁሳቁሶችን አስረክበዋል።   በርክክቡ ወቅትም አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ ባስተላለፉት መልዕክት ኢንስቲትዩቱ ለክልሉ መንግሥት ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ የተረከቧቸው ቴክኖሎጂዎች ክልሉን ለማዘመን በሚደረገው ጥረት ላይ የሚኖራቸው ሚና ጉልህ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡  
ስፖርት
በሶማሌ ክልል በከተማ አስተዳደሮች እና በዩኒቨርስቲ ክለቦች መካከል ሲካሄድ የቆየው የእግርኳስ ውድድር ትናንት ምሽት ተጠናቀቀ
Mar 4, 2024 78
ጅግጅጋ ፤ የካቲት 25/2016(ኢዜአ)፦ በሶማሌ ክልል በስድስት ከተማ አስተዳደሮች እና በሁለት ዩኒቨርሲቲ ክለቦች መካከል በጅግጅጋ ስታድየም ሲካሄድ የቆየው የእግርኳስ ውድድር ትናንት ምሽት ተጠናቀቀ። ለሶስት ሳምንታት ሲካሄድ በቆየው ውድድር የተሳተፉት የጅግጅጋ፣ ጎዴ፣ ቀብሪደሃር፣ ቶግ ውጫሌ፣ ቀብሪበያህ፣ ደገሀቡር ከተማ አስተዳደሮች እና የጅግጅጋና ቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲዎች የእግር ኳስ ቡድኖች ናቸው። ትናንት በተካሄው የፍፃሚ ጨዋታ ጅግጅጋ ከተማ አስተዳደር የቀብሪ ደሃር ዩኒቨርሲቲን በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት ሆኗል። በፍጻሜ ጨዋታው ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዶክተር ሁሴን ሃሺ፣ የብልፅግና ፓርቲ የሶማሌ ክልል ቅርንጫፍ ኃላፊ ኢንጂነር መሀመድ ሻሌ፣ የጅግጅጋ ከተማ ከንቲባ ኢንጂነር ሻፊ አህመድን ጨምሮ የጅግጅጋ ከተማ እግር ኳስ አፍቃሪያን ተገኝተዋል።  
ኢትዮጵያ በአለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ከአፍሪካ አንደኛ ከዓለም አምስተኛ በመሆን አጠናቀቀች 
Mar 4, 2024 172
አዲስ አበባ፤ የካቲት 25/2016 (ኢዜአ)፡- በ19ኛው የአለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ከአፍሪካ አንደኛ ከዓለም አምስተኛ በመሆን አጠናቃለች። በስኮትላንድ ግላስጎ ሲካሄድ የነበረው 19ኛው የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ትናንት ሌሊት ተጠናቋል። በውድድሩ ከተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ ከ650 በላይ አትሌቶች የተሳተፉ ሲሆን ኢትዮጵያም በ800 ሜትር፣ በ1500 ሜትር እና በ3000 ሜትር ርቀቶች በ8 ሴቶች እና በ5 ወንዶች በድምሩ በ13 አትሌቶች ተሳትፋለች ፡፡ በሻምፒዮናው ኢትዮጵያ በሴቶች 800 ሜትር ፅጌ ዱጉማ እና በሴቶች 1500 ሜትር ፍሬወይኒ ሀይሉ የወርቅ ሜዳሊያን አሸንፈዋል።   በሴቶች 3000 ሜትር ጉዳፍ ፀጋዬ የብር እንዲሁም በወንዶች 3000 ሜትር ሰለሞን ባረጋ የነሃስ ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ ያስገኙ አትሌቶች መሆናቸውን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል። በዚህ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ሁለት ወርቅ አንድ ነሀስ በአንድ ብር በአጠቃላይ በአራት ሜዳሊያዎችን በማግኘት በሜዳልያ ሰንጠረዥ ከአፍሪካ አንደኛ ከአለም አምስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች።
የድሬዳዋ የከፍተኛ ዲቪዚዮን የክለቦች ውድድር ተተኪ ተጫዋቾች የተገኙበት ነው 
Mar 3, 2024 112
ድሬደዋ፤ የካቲት 24 /2016( ኢዜአ)፡- የድሬደዋ የከፍተኛ ዲቪዚዮን የክለቦች ውድድር ተተኪና የቀድሞ ዝና ለመመለስ የሚያስችሉ ተጫዋቾች የተገኙበት መድረክ መሆኑ ተገለጸ። በድሬዳዋ አስተዳደር በ14 የከፍተኛ ዲቪዚዮን ክለቦች መካከል ሲካሄድ የሰነበተው ዓመታዊ የእግርኳስ ጨዋታ በመስቀለኛ ክለብ አሸናፊነት ተጠናቋል። በውድድሩ ማብቂያ ላይ የተገኙት የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባና የስፖርት ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ከድር ጁሃር በወቅቱ ለኢዜአ እንደተናገሩት ፤ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ተጨማሪ ክለብ ለመፍጠር ለሚደረገው ጥረት ውድድሩ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል ። በተለይ ድሬዳዋ በኢትዮጵያ ደረጃ በእግር ኳስ የነበራትን ገናና ዝናና ስም ለመመለስ የሚያስችሉ ምርጥ ተጫዋቾች ያሏት መሆኑን በውድድሩ ተመልክተናል ብለዋል። እነዚህን ጅምር ስራዎች ይበልጥ ለማሳደግ በአዳጊ ወጣቶች ፕሮጀክቶች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል ብለዋል። የስፖርት ማዘውተሪያና መሠረተ ልማት በስፋት እየተከናወነ መሆኑንም ገልጸዋል። የውድድሩ ሻምፒዮና የሆነው የመስቀለኛ ክለብ ዋና አሰልጣኝና የውድድሩ ኮኮብ አሰልጣኝ ተብላ የተመረጠችው የ27 ዓመቷ ወጣት ምስጋና አበባየሁ ለኢዜአ እንደተናገረችው ፤በተናበበ ትጋትና ቁርጠኝነት የተገኘው ድል አስደሳች ነው።   ይህ ጅምር ውጤት በማስቀጠል በቀጣይ በድሬዳዋ ሆነ በአገር የእግርኳስ ሂደት ውስጥ ሴቶች ደማቅ አሻራ እንዲኖራቸው በአርአያነት እንደምትሰራ ገልፃለች ። " ምኞቴ ትላልቅ የአገራችንን ክለቦች አሰልጥኜ በአፍሪካ ውድድሮች ላይ ክስተት መሆን ነው የምፈልገው፤ ይሄን ደግሞ አደርገዋለሁ " ብላለች። እንደ ወጣቷ አሰልጣኝ ገለጻ፤ ወጣቶቹ የተሻለ ደረጃ እንዲደርሱ ላሉባቸው የትጥቅና የላብ መተኪያ ችግሮች የሚመለከታቸው አካላትና ስፖርት ወዳጁ የድሬዳዋ ባለሃብቶችና ህብረተሰብ ድጋፍ ማድረግ አለባቸው። በእውነት በተሰጠኝ ማዕረግ ተደስቻለሁ ፤ ችሎታዬን አሳድጌ ለድሬዳዋና ለብሔራዊ ቡድን የመጫወት ፍላጎቴን አሳካለሁ ያለው ደግሞ የውድድሩ ኮኮብ ተጫዋች ስንታየሁ አበባየሁ ነው። ከሶስት ወራት በፊት የተጀመረውና በ14 የድሬደዋ የከፍተኛ ዲቪዚዮን ክለቦች መካከል ሲካሄድ የሰነበተው ዓመታዊ ውድድር አሸናፊ የሆነው የመስቀለኛ ክለብ የወርቅ ሜዳሊያ ፣ የዋንጫና የ200ሺህ ብር ተሸላሚ ሆኗል። ሁለተኛ የወጣው ገንደ አብዲ ቦሩ የብር ሜዳሊያና የ150 ሺህ ብር ተሻላሚ ሲሆን ፤የነሐስ ሜዳሊያ ተሸላሚው የድሬ ካባ ደግሞ የ100 ሺህ ተበርክቶለታል ። የውድድሩ ኮኮብ አሰልጣኝ፣ግብ ጠባቂ ፣ተጫዋችና ግብ አስቆጣሪ የዋንጫና የዘመናዊ የስልክ ሞባይል ተሸላሚ ሆነዋል። የተዘጋጁትን ሽልማቶች የድሬዳዋ ከንቲባ ከድር ጁሃርና የካቢኔ አባላት እንዲሁም የአስተዳደሩ ስፖርትና ወጣቶች ኮሚሽን ከፍተኛ የአመራር አባላት አበርክተዋል።        
አካባቢ ጥበቃ
በምስራቅ ሐረርጌ ዞን የተከናወኑ ስኬታማ የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራዎች የህዝቡ ቁርጠኝነት የታየበት መሆኑ ተገለጸ
Mar 4, 2024 68
ሐረር ፤ የካቲት 25/2016 (ኢዜአ)፡ - በምስራቅ ሐረርጌ ዞን የተከናወኑ ስኬታማ የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራዎች የህዝብ ቁርጠኝነት የታየበትና ተሞክሮው ሊስፋፋ የሚገባ ነው ሲሉ የተለያዩ የክልል ግብርና ቢሮ ሃላፊዎች ተናገሩ። የክልል ግብርና ቢሮ የስራ ኃላፊዎች ይህን የተናገሩት በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ግራዋ ወረዳ በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ የተከናወኑ የልማት ስራዎችን በጎበኙበት ወቅት ነው። የሲዳማ ክልል የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ፍቅረየሱስ አሸናፊ እንደተናገሩት በዞኑ የተከናወኑ የተፋሰስ እና የተፈጥሮ ሃበትና ልማት ጥበቃ ስራዎች ህዝብ ሲተጋና በቁርጠኝነት ሲሰራ ሁሉንም ማከናወን እንደሚቻል በተግባር የተመለከቱበት ነው። በተለይ አርሶ አደሩና ማህበረሰቡ ያከናወኑት የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎች የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራን የህልውና ጉዳይ አድርገው የወሰዱበት መሆኑን ይገልጻል ብለዋል። በወረዳው ባለፉት ዓመታት በተፋሰሶች ላይ የተከናወኑት የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራዎች ወደ ለምነት መቀየራቸው፣ የደረቁ ምንጮች በመመለሳቸው እና ለወጣቶች የስራ እድል ፈጥሮ መመልከታቸውን ገልጸዋል። በዞኑ የተከናወኑ አበረታች የተፋሰስ ልማት እና የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራ ተሞክሮን ወደ ክልሉ ለማስፋፋት ይሰራል ብለዋል።   በዞኑ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎችን በስነ-ህይወታዊ ዘዴ የማጠናከርና ከሌሎች የሰብል ልማት፣ እንስሳት እርባታ እንዲሁም ከአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ጋር አያይዘው ያከናወኑት የተቀናጁ የግብርና ልማት ስራ አበረታች መሆኑን የተናገሩት በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የአማራ ክልል ገጠር ልማት አስተባባሪና የግብርና ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ድረስ ሳህሉ ናቸው። አሁንም በዞኑ የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራ በህዝብ ንቅናቄና በይቻላል መንፈስ በስፋት እየተከናወነና መሬቱም ለግብርና ልማት ስራ እንዲውል እየተደረገ እንደሚገኝ መመልከታቸውን ተናግረዋል። የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራን በጥራት ማከናወን እንደሚቻልና በስፍራውም የተቀናጀ የግብርና ልማትን በማከናወን ተጠቃሚ መሆን እንደሚቻል መመልከታቸውነና መነሳሳትንም የፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል። በዞኑ የተመለከቷቸው ነባርና አዲስ የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራ ልምድ ሊወሰድበትና ሊስፋፋ የሚገባው መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮዽያ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ውብሸት ዘነበ ናቸው። በተለይ በለሙ በተፋሰሶች ላይ የተከናወኑት የንብ ማነብ፣ የከብት እርባታና ሌሎች የግብርና ልማት ስራዎች የአካባቢው ማህበረሰብ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆን ማስቻሉንና ትምህርት የተገኘበት እንደሆነም አመልክተዋል። የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ወይዘሮ ሚስኪ መሀመድ በበኩላቸው በዞኑ በተከናወነው የተቀናጀ የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራዎች ውጤታማ ናቸው ብለዋል። በተለይ ባለፉት ሶስት ዓመታት በአመራሩ፤ ማህበረሰቡና የግብርና ባለሞያው ተቀናጅቶ ባከናወነው የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራ አካባቢው ወደ ለምነት ከመቀየሩ ባለፈ በርካታ ወጣቶች የስራ እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማስቻሉን ተናግረዋል። በዞኑ የተከናወነው የተፈጥሮ ሃበት ጥበቃ ስራ ተስፋ ሰጪና ለሌሎችም እንደ ተሞክሮ እየተወሰደና እየተስፋፋ ይገኛል ሲሉ ገልጸዋል። በምስራቅ ሐረርጌ ዞን በዘንድሮ የበጋ ወቅት በ477 ተፋሰሶች ላይ የተለያዩ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎች ተከናውነዋል።
የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ በግብርናው ዘርፍ ለሚከናወኑ የልማት ስራዎች ተጨባጭ ለውጥ አምጥቷል- ፕሮፌሰር እያሱ ኤሊያስ
Mar 3, 2024 120
ሐረር ፤ የካቲት 24 / 2016 (ኢዜአ) ፡- የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ተግባር በግብርናው ዘርፍ ለሚከናወኑት የልማት ስራዎች ተጨባጭ ለውጥ ማምጣቱን የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር እያሱ ኤሊያስ ገለጹ። የግብርና ሚኒስቴርና የክልል ግብርና ቢሮ የስራ ኃላፊዎች በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ግራዋ ወረዳ በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ የተከናወኑ የልማት ስራዎችን ተመልክተዋል።   በዚህ ወቅት ፕሮፌሰር እያሱ ኤልያስ እንደተናገሩት ባለፉት ዓመታት በተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ የተከናወኑ ተግባራት በግብርናው ዘርፍ ላይ ተጨባጭ ውጤት እንዲገኝ አስተዋጽኦ አድርገዋል። በተለይ በንብ ማነብ፣በከብት እርባታና ማድለብ ፣በሌማት ቱሩፋት እንዲሁም በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት፣ በአረንጓዴ አሻራና በሌሎች የግብርና ዘርፎች ለውጥ እንዲመጣ ያበረከተው አስተዋጽኦን ጠቅሰዋል። በአገሪቱ በተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ የሚከናወኑ ተግባራት ይደርሱ የነበሩ የጎርፍ አደጋዎች እንዲቀንሱ ከማስቻሉ ባለፈ አካባቢዎች አረንጓዴ እንዲላበስና ምግብ ዋስትና እንዲረጋገጥ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ተናግረዋል። በተለይ በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ግራዋ ወረዳ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑት የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራዎች የግብርና ልማት ስራዎችን ከማሳለጥ ባለፈ ወጣቶች በተለያየ መልኩ የስራ እድል እንዲያገኙ ማስቻሉን እንደተረዱም አውስተዋል። በሐምሌ ወር 2015 ዓም በወረዳው “ጋራ ጊሌ” ተፋሰስ ላይ የተተከሉ የአትክልትና ሌሎች ችግኞች ሙሉ በሙሉ እንደፀደቁ መመልከታቸውን ጠቅሰዋል። ዘንድሮም በወረዳ “አበል ቃሲም” ሌሎች ተፋሰሶች ላይ ከጥር አጋማሽ ጀምሮ ህብረተሰቡ በነቂስ ወጥቶ ያከናወነው የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎች ለተፈጥሮ ሃብት ጥበቃና ምርታማነትን ለማሳደግ ፋይዳው የጎላ መሆኑን እንደተረዱም ፕሮፌሰር እያሱ አመላክተዋል። የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ሃላፊ አቶ ጌቱ ገመቹ በበኩላቸው፤ ቢሮው ለተፋሰስ ልማት ስራዎች ትኩረት በመስጠት እየደገፈ መሆኑን ተናግረዋል።   በዚህም በክልሉ የሚከናወኑ የግብርና ስራዎች በትክክለኛው መንገድ እንዲሄዱ አስችሏል ያሉት ሃላፊው፤ በዚህም በየዓመቱ በተፋሰሶች የሚለማው መሬት ስፋት እየጨመረ መምጣቱን አመልክተዋል። ዘንድሮም የተፋሰስ ልማት ትግበራን በማስቀጠል የእርከንና ክትር ጨምሮ የተለያዩ የአፈርና ውሃ ዕቀባ ስራዎች ሲከናወኑ እንደቆየ አውስተዋል።   በተለይ ባለፈው ዓመት በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ግራዋ ወረዳ ጋራ ጊሌ ተፋሰስ ላይ የተከናወነው የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራ በአካባቢው የጠፉትን ምንጮች ጎልብተው የዓሳ ልማት ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል። በተፈጥሮ ሀብት ልማትና እንክብካቤ ስራው የተራቆተው መሬት አገግሞ በደን መሸፈኑን የገለጹት አቶ ጌቱ፤ በአሁኑ ወቅትም ማህበረሰቡ ንብ በማነብና በእንስሳት መኖ ልማት ተሰማርተው ውጤታማ በመሆን ላይ እንደሚገኝ መታየቱን ተናግረዋል። በዞኑ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ የተፋሰስ ልማት ተግባራት በርካታ የተራቆቱ ስፍራዎች ወደ ለምነት እንዲቀየሩ ማስቻሉን የገለጹት ደግሞ የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ወይዘሮ ሚስኪ መሐመድ ናቸው።   የከርሰ ምድር ውሃ እንዲጨምር፣የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት እንዲጎለብትና ምርታማነት እንዲጨምር ማገዙን ገልጸዋል። በምስራቅ ሐረርጌ ዞን በዘንድሮ የበጋ ወቅት በ477 ተፋሰሶች ላይ የተለያዩ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎች መከናወናቸውንም ወይዘሮ ሚስኪ ተናግረዋል።  
አዲሱ የደን ልማት ጥበቃና አጠቃቀም ደንብ የኢትዮጵያ የካርበን ሽያጭ በህግ እንዲመራ የሚያደርግ ነው
Mar 3, 2024 131
አዲስ አበባ፤ የካቲት 24/2016(ኢዜአ)፦ አዲሱ የደን ልማት ጥበቃና አጠቃቀም ደንብ የኢትዮጵያ የካርበን ሽያጭ በህግ እንዲመራ የሚያደርግና የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ የሚያሳድግ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ገለጹ። የሚኒስትሮች ምክር ቤት በ27ኛ መደበኛ ስብሳባው ላይ ተወያይቶ እንዲጸድቅ ውሳኔ ካሳለፈባቸው የህግ ማዕቀፎች መካከል አንዱ "የደን ልማት፣ ጥበቃና አጠቃቀም ረቂቅ ደንብ" ነው። ደንቡም ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ በመገንባት የካርቦን ክምችትን በዓለም አቀፉ ግብይት በማስገባት የኢትዮጵያን የደን ሃብት ለማልማትና ለመጠበቅ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል። በዚሁ ጉዳይ ላይ ኢዜአ ያነጋገራቸው ከፍተኛ የደን ባለሙያዎች፤ የኢትዮጵያ የደን ሃብት በሚገባ በማልማት የካርቦን ሽያጭ ገቢዋን በማሳደግ ረገድ አዲሱ ረቂቅ ደንብ ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል ብለዋል። በኢትዮጵያ ደን ልማት የብሔራዊ ‘’ሬድ ፕላስ’’ ፕሮግራም አስተባባሪ ይተብቱ ሞገስ (ዶ/ር)፤ ኢትዮጵያ የካርበን ሽያጭ ማከናወን የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ እስካሁን እንዳልነበራት ገልጸዋል። በመሆኑም የሚኒስትሮች ምክር ቤት በ27ኛ መደበኛ ስብሳባው ያጸደቀው የደን ልማት ጥበቃና አጠቃቀም ደንብ የደን ልማት፣ አጠቃቀምና የካርበን ሽያጭ የህጋዊነት ጥያቄን ምላሽ የሰጠ ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ የደን ሃብቷን በማልማት ከዘርፉ የሚገባትን ገቢ እንድታገኝና በህጋዊነት ላይ የነበረውን የአሰራር ክፍተት ምላሽ የሰጠ መሆኑንም አብራርተዋል።   የኢትዮጵያ ደን ልማት ከፍተኛ የደን ባለሙያና የአገር አቀፉ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር አስተባባሪ አደፍርስ ወርቁ (ዶ/ር)፤ በደን ልማት ላይ የመጣውን ተጨባጭ ውጤት በደንብና ህጋዊ የአሰራር ሥርዓት መምራት ተገቢ መሆኑን ገልጸዋል። የዘርፉን ልማት በማሳለጥ የአርሶ እና አርብቶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማሳለጥ እንዲሁም የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ለማሳደግ አዲሱ ደንብ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰዋል። የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያጸደቀው የደን ልማት፣ ጥበቃና አጠቃቀም ረቂቅ ደንብ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል ውሳኔ መተላለፉ የሚታወስ ነው።    
የግብርና ሚኒስቴርና የክልል ግብርና ቢሮ የስራ ኃላፊዎች በምስራቅ ሐረርጌ ዞን በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራ የተከናወኑ ተግባራትን እየጎበኙ ነው
Mar 2, 2024 151
ሀረር፤ የካቲት 23/2016(ኢዜአ)፦ የግብርና ሚኒስቴርና የክልል ግብርና ቢሮ የስራ ኃላፊዎች በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ግራዋ ወረዳ በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራ የተከናወኑ ተግባራትን እየጎበኙ ነው። በጉብኝቱ ላይ የግብርና ሚኒስትር ድኤታው ፕሮፌሰር እያሱ ኤልያስን ጨምሮ የተለያዩ ክልሎች የግብርና ቢሮ ኃላፊዎችና የተፈጥሮ ኃብት ጥበቃ ዘርፍ አስተባባሪዎች ተገኝተዋል። የአመራር አባላቱ በዞኑ ግራዋ ወረዳ በተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራ ጋር ተያይዞ የአካባቢው ነዋሪዎች በማር ምርት፣ በእንስሳት እርባታና ማድለብ እንዲሁም በአሳ ሃብት ልማትና በተፈጥሮ ማዳበርያ ዝግጅት ረገድ የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን እየጎበኙ ይገኛሉ። የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ግራዋ ወረዳ በዚህ ዓመት በተፋሰስ ልማትና በአካባቢ ጥበቃ ስራዎች የተሻለ ስራ ከተከናወነባቸው ስፍራዎች አንዱ መሆኑ ተገልጿል። አሁን ላይ በወረዳው በተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራ በለማው 'ጋራ ጊሌ' ተፋሰስ ላይ የተከናወኑ የተለያዩ የልማት ስራዎችን በመጎብኘት በልማቱ የተሳተፉ ወጣቶችን አበረታተዋል።  
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
በህንድ አንድ እቃ ጫኝ ባቡር ያለ አሽከርካሪ 70 ኪሎ ሜትሮች መጓዙ ተነገረ
Feb 26, 2024 343
አዲስ አበባ ፤የካቲት 18/2016 (ኢዜአ)፦በህንድ አንድ እቃ ጫኝ ባቡር ያለ አሽከርካሪ 70 ኪሎ ሜትሮች መጓዙን ተከትሎ የሀገሪቱ የባቡር አስተዳደር ምርመራ እያካሄደ መሆኑን ገልጿል። በህንድ አንድ እቃ ጫኝ ባቡር ያለ አሽከርካሪ መንቀሳቀሱን የሚያሳዩ ምስሎች በማህበራዊ ሚዲያ መሰራጨታቸውን ተከትሎ ጉዳዩ አነጋጋሪ ሆኗል። የህንድ የባቡር አስተዳደር ባለስልጣናት ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ መነሻውን ከካሽሚር ግዛት ወደ ጃሙ ያደረገ እቃ ጫኝ ባቡር ያለ አሽከርካሪ እሁድ ከቀኑ 7፡15 እስከ ቀኑ 9 ሰዓት ድረስ መጓዙን ተናግረዋል። በ53 ፍርጎዎች ለቤትና መንገድ ግንባታ የሚያገለግሉ የድንጋይ ጠጠሮችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረው ባቡሩ በሰዓት 100 ኪሎ ሜትር ፍጥነት እንደነበረውም ተነግሯል። ሆኖም በሰው ህይወት ላይ ምንም አይነት ጉዳት ሳያደርስ ባቡሩን ማስቆም እንደተቻለ ነው ሃላፊዎቹ የገለጹት። በካቱሃ ግዛት የአሽከርካሪዎችና ባለሙያዎች ቅይይር ሲደረግ ችግሩ ሊፈጠር እንደቻለ የተነገረ ሲሆን 70 ኪሎ ሜትሮችን ያለ አሽከርካሪ እንዴት ሊጓዝ ቻለ የሚለው ጉዳይ ላይ በጥብቅ ምርመራ እንደሚደረግ ቢቢሲ ዘግቧል። የቁጥጥር ባለሙያዎች ባቡሩን ለማስቆም የዛፍ ግንዶች እንደተጠቀሙ ያስነበበው ዘገባው በዚህም የባቡሩን ፍጥነት በመቀነስና በካቱሃ ግዛት እንዲቆም መደረጉን አስነብቧል።
የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የኢትዮጵያ ድል በአፍሪካ ታሪክ ጉልህ ስፍራ እንዳለው ማሳያ ነው
Feb 17, 2024 632
አዲስ አበባ፤ የካቲት 9/2016(ኢዜአ)፡- የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የኢትዮጵያን ድል የሚዘክር እና ድሉ በአፍሪካ ታሪክ ውስጥ አገሪቱ ያላትን ጉልህ ስፍራ የሚያሳይ መሆኑ ተገለጸ። የዓድዋ ድል ኢትዮጵያውያን ከ128 ዓመታት በፊት በአንድነት ተሰልፈው ድል በመንሳት ነፃነታቸውን ያስከበሩበት መሆኑን ሩሲያ የዜና አገልግሎት ስፑትኒክ ዘግቧል። ስፑትኒክ የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ምረቃን አስመልክቶ ከአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አማካሪ ልደት ሙለታ ጋር ቃለምልልስ አድርጓል። በዚሁ ቃለምልልስ ላይ ልደት ሙለታ ሙዚየሙ በመሀል አዲስ አበባ ላይ እንዲገነባ የተወሰነው ቦታው ለመላው ኢትዮጵያውያን ካለው ታሪካዊ ፋይዳ አንጻር መሆኑን አስረድተዋል። ሙዚየሙ የተገነባበት ቦታ ኢትዮጵያውያን ወደ አድዋ ከመዝመታቸው በፊት ከሁሉም የአገሪቱ አቅጣጫዎች በመትመም የተሰበሰቡበት መሆኑን አማካሪዋ አስገንዝበዋል። መታሰቢያ ሙዚየሙ የኢትዮጵያውያን የአንድነት ምልክት ሆኖ ከማገልገሉም በተጨማሪ የአድዋ ድል መነሻ መሆኑንም ያሳያል ብለዋል። በዚህ ታሪካዊ የአDዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በርካታ ታሪካዊ ቅርሶች የያዘ መሆኑን ያስረዱት ልደት ሙለታ ከእነዚህ መካከል በጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ከተሰረቀበት ጣሊያን አገር እንዲመለስ የተደረገው እ.አ.አ በ1935 ኢትዮጵያውያን ከጀርመን ኢንጂነሮች ጋር በመተባበር የሰሩት የመጀመሪያ የኢትዮጵያ አውሮፕላን እንደሚገኝበት አስረድተዋል። አማካሪዋ ከአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም መገንባት ማዕከላዊ ሀሳቦች መካከል አንዱ ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ወረራ ያሳየችውን ተቃውሞና አልገዛም ባይነት ለማስታወስ እና የሀገሪቱን ድል ለመዘከር ነው ብለዋል። ሁሉን አቀፍና አካታች የሆኑ ቀጠናዊና ዓለም አቀፋዊ ትብብሮችን በስፋት መጠቀም እንደሚያስፈልግ ያብራሩት አማካሪዋ ጂኦ ፖለቲካል አሰላለፎችን በመገንዘብ የታዳጊ ሀገራትን ድምጽ የሚያጎሉ ቁልፍ ዓለም አቀፍ መድረኮችን መጠቀም እንደሚገባም ጠቁመዋል። አማካሪዋ አክለውም፤ ኢትዮጵያ በቅርብ ጊዜ በብሪክስ (BRICS) ውስጥ በአባልነት መካተቷ በአለም አቀፍ ዲፕሎማሲ እና በአለም ዙሪያ ካሉ አገራት ጋር በሚደረገው የትብብር ሂደት እያደገ የመጣውን ተጽእኖ ፈጣሪነቷ ያሳያል ብለዋል።
ታንዛንያ አንድ ቢሊየን ዶላር የሚያስገኝ የካርበን ሽያጭ ፕሮጀክት ይፋ አደረገች
Feb 8, 2024 925
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2016 (ኢዜአ)፦ ታንዛንያ አንድ ቢሊየን ዶላር የሚያስገኝ የካርበን ሽያጭ ፕሮጀክት ይፋ ማድረጓ ተገለጸ፡፡ ስፑትኒክ ድረገጽ የአገሪቱን ምክትል ፕሬዝደንት ቢሮ ጠቅሶ እንደዘገበው ታንዛንያ ከተጠናቀቀው የአውሮፓውያኑ 2023 ወዲህ 35 የካርበን ሽያጭ ማመልከቻዎችን ተቀብላለች፡፡ በቢሮው የአካባቢ ደህንነት ኃላፊ ሴሌማኒ ጃፎ እንደተናገሩት የካርበን ሽያጭ ለአገሪቱ የገቢ ምንጭ እየሆነ ይገኛል፡፡ የካርቦን ሽያጭ ከ2018 እስከ 2022 ባሉት አመታት በተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ የተተገበረው የካርበን ሽያጭ ለአገሪቱ ከ12 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ማስገኘቱን ተናግረዋል። “የካርቦን ሽያጭ የታንዛንያን ምጣኔ ሃብታዊ እድገት ለማገዝና የተፈጥሮ አካባቢን ለመንከባከብ የራሱ አስተዋጽኦ አለው“ ያሉት ሴሌማኒ ጃፎ ጠቀሜታውን ለህብረተሰቡ በማስረዳትና በስፋት በማሳተፍ እየተሰራበት ይገኛል ብለዋል። በዱባይ በነበረውም የኮፕ 28 የአየር ንብረት ጉዳዮች ጉባኤ ላይ የሃገራቸውን መልካም ተሞክሮ በማቅረብ ዘርፉ ላይ ከሚሰሩ አካላት አዎንታዊ ግብረመልሶች ማግኘት መቻሉን አላፊው ገልጸዋል፡፡ በተገኘው ውጤትም ታንዛንያ የአንድ ቢሊየን ዶላር የሚያስገኝ የካርበን ሽያጭ ፕሮጀክት ይፋ መደረጉን ተናግረዋል፡፡ ታንዛንያ ከሶስት አመታት በፊት ብሔራዊ የካርበን ሽያጭ መመሪያ በማዘጋጀት ባለድርሻ አካላት እንዲመሩበት ማድረጓ ይታወቃል፡፡ ኢትዮጵያ በደን ልማት ዘርፍ እያከናወነች ባለው ሥራ እ.ኤ.አ እስከ 2030 ከካርበን ሽያጭ 100 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት እቅዳ እየሰራች ይገኛል፡፡
ሐተታዎች
አድዋን የዘከሩ ስንኞች
Feb 29, 2024 200
የታሪክ ድርሳናት የአድዋ ድልን በተለያየ መንገድ ዘክረውታል። ምሁራንም አንድምታውን በየዐውዱ ዘርዝረዋል። በዚህም ለሰው ልጆች በተለይም ለጥቁሮች አዲስ ምዕራፍ የከፈተ እንደሆነ ደምድመዋል። በርግጥም የአድዋ ድል ታሪክም፣ ትርክትም የለወጠ ትልቅ ሁነት ነው። በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ምዕራባዊያን 'አቢሲኒያ' በሚሏት ጥንታዊት አፍሪቃዊት ምድር የነበረው ክስተት ቀለምና ዘር ቀመስ በሆኑ በሰው ልጆች መካከል ድል መንሳትና መነሳት፣ ተስፋ እና ቀቢፀ ተስፋ፣ ሀሜትና ሀሞት፣ ብስራትና መርዶ... እያፈራረቀ አበሰረ። ለሀገሬው ዘመን-አይሽሬ አሻራ አነበረ። ውርስም ቅርስም ሆነ!! ይህ ክስተት በታሪኩ ልክ በኪነ ጥበብ ተዘክሯል ባይባልም ቅሉ በጥበብ ፈርጁ ተወስቷል። የኪነ-ጥበብ ሰዎች በየመክሊቶቻቸው ድሉን ለመዘከር ጥረዋል። ሙዚቀኞች በዜማዎቻቸው፣ የሲኒማ ሰዎች እና ፀሐፈ ተውኔቶች በተውኔታቸው፣ ሊቃውንት በቅኔዎቻቸው አድዋን ዘክረዋል። ዕውቅ ገጣሚያን ደግሞ ቃላት እያዋደዱ፣ በዘይቤና ዘመን እያዋሃዱ፣ ምዕናብና ገሀድ እያዛነቁ፣ ታሪክና ትዝብት እያሰባረቁ ... አድዋን በግሩም ስንኞቻቸው ከትበውታል። በአድዋ ድል ምርጥ ግጥሞች መካከል "ጥቂት ስንኞች" እየመዘዝን በወፍ በረር ቅኝት እንመልከት። ባለቅኔው ፀጋዬ ገብረመድህን በ‘እሳት ወይ አበባ’ ግጥም መድብሉ አድዋን መልክዓ ምድራዊና ሃሳባዊ ወሰኗን አድማስ ተሻጋሪ፣ ሰማይ ታካኪ፣ ታሪካዊ ስፍራዋ የአጽም ርስትና የደም ትቢያ የተሸበለለባት መቀነት አድርጎ መስሏታል። በዚህች ታሪካዊ ስፍራ በተከፈለው መስዋዕትነት ከባርነትና ነጻነት ስርየትን ሲያጎናጽፍ፣ የኩራት ቅርስ መሆኗንም ሰፊውን ታሪክ በጥቂት ስንኞች እንዲህ ቋጥሯል። ".... አድዋ ሩቅዋ፣ የዓለት ምሰሶ የአድማስ ጥግዋ፣ ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ... ዓድዋ የዘር አፅመ ርስትዋ- የደም ትቢያ መቀነትዋ ከሞት ከባርነት ሥርየት- በደም ለነጻነት ስለት አበው የተሰውብሽ እ’ለት የኩሩ ትውልድ ቅርስዋ- የኢትዮጵያዊነት ምስክርዋ..." ገጣሚው አለፍ ሲልም በጦርነቱ የዋሉ መሳሪያዎችን፣ የጦር መሪዎችን እጅና ጓንትነት በፈረስ ስሞቻቸው በመቋጠር /ለአብነትም የዳግማዊ ምኒልክ፣ የራስ መኮንን፣ የደጃች ባልቻ ሳፎ፣ የፊታውራሪ ገበየሁና ሌሎችም/ ኢትዮጵያዊያንን ጀግንነትና ወኔ በአጭሩ ቋጥሮታል። ...ድው-እልም ሲል ጋሻዋ- ሲያስተጋባ ከበሮዋ፣ ሲያስገመግም ዳኘው መድፍዋ፣ ያባ መቻል ያባ ዳኘው፤ ያባ ነፍሶ ያባ ቃኘው፣ ያባ ጎራው፣ ያባ በለው በለው ሲለው..." በሚል። ደራሲና ጋዜጠኛ ነብይ መኮነን ‘ስውር ስፌት’ በተሰኘ የግጥም መድብሉ የአድዋን ድል ሲያመሰጥረው አድዋን ‘በደም ግብርነት’ ይገልጸዋል፤ ታሪኩንም ላጥፋህ ቢሉት የማይጠፋ ሕያው ቀንዲል አድርጎታል። “አድዋ የደም ግብር ነው፤ አበው የለኮሱት ቀንዲል፣ አድዋ የአፍሪካ ዱካ ነው፤ አበሽ የከተበው ፊደል፣ ላጥፋህ ቢሉት መች ይጠፋል፤ ጠላት በልቶ ያፈራ ተክል፣ ለዛሬም ታሪክ ነው፣ ‘ነገም ሌላ ቀን ነው’ ለሚል...” የቀድሞው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቋንቋ ምሁር ሰይፉ መታፈሪያ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) “የተስፋ እግር ብረት” መጽሐፍ “የድል በዓል ማለዳ” በሚል ርዕስ የአድዋን ድባብ ከማለዳው ምናባዊ ትዕይንት ጀምሮ ይቃኛል። ገጣሚው የሰንደቁን መውለብለብ፣ የሕብረ ቀለሙን ድምቀት ከልክ በላይ ውስጥን ኮርኩሮ የሚያስፈግግ ሐሴት እንዳለው በዘይቤያዊ ቃላት ገልፆታል። ገጣሚው በቅኔው የሠራዊቱን ቆራጥነት፣ በወኔ በደም ሲቅላላ፣ የመድፍ አረር ሲያፋጭ ይስለዋል። በስሜት ስካር አድዋ ደፍርሶ በስዕለ ህሊናው የነበረውን የጦርነቱ ማለዳዊ ድባብም እንዲህ ያብራራዋል። ዐይነ-ልቦናዬ ዐጽም ያያል፤ የድል ሜዳውን ይቃኛል። ባድዋ ድል በዓሉ ማለዳ፤ የበዓል መድፍ ሲንዱዋዱዋ (ዱዋ ዱዋ ዱዋ ዱዋ!) ከሞት እንቅልፍ ተቀስቅሶ፤ ያ-ዐጽም ዙርያውን ደባብሶ ጉሮሮውን ጠረገ፣ እህህህህ! እህህህህ!... እያለ ይቀጥላል። በአድዋ ኮረብታማ ተራሮች የተኙ ጀግኖችን በሕይወት ተኝተው የሚያንኮራፉ አስመስሎም አቅርቧቸዋል። ...ድንጋይ ተንተርሶ፤ አፈር ቅጠሉን ለብሶ፣ ከዚያን ያንኮራፋል፤ እንደዚሁም በቅብልብል የወደቀበቱ ሜዳው፣ ተረተሩ፤ ቀን የማይለውጠው ምስክሩ የዚያ ጀግና፣ የዚያ ኩሩ። ገጣሚ አበረ አያሌው “ፍርድና ዕርድ” በተሰኘው የግጥም ስብስቡ ባሰፈራቸው ስንኞች ‘ነገረ አድዋ’ን ከመንደር ወደ አገር፣ ከአገር ወደ አህጉር በመጨረሻም ከአህጉር አተልቆ ‘ዓለም’ ያደርገዋል፤ አድዋን የአፍሪካ ብርሀን ፈንጣቂ፤ ለእብሪተኞች ደግሞ የትካዜና ቅስም መስበሪያ ምስጢር አድርጓታል። በተለይም ኢትዮጵያ ለገጠማት አሁናዊ የዘር ፖለቲካ አዙሪት አድዋን ለሚያሳንሱ ወገኖች በቅኔው ምላሽ ይሰጣል። "...እነ ምኒልክ ጦር ይዘው ከመድፍ የተዋደቁ ጎራዴ መዘው የሮጡ በጠብ-መንጃ አፍ ያለቁ ለጓጉለት ነጻነት -ደማቸውን ያፈሰሱ ለሰፈር ብቻ አይደለም- የአህጉር ድል አታሳንሱ። ... ዓድዋ ሰፈር አይደለም - ዓድዋ መንደር አይደለም እሱ ዓለም ናት ዓድዋ ቤቱ - ሃገር ናት የድል ትራሱ ለጠበበ የዘር ቅኔ - የደም ድል አታሳንሱ!..." በማለት ገልጾታል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ተግባቦት ምሁሩ ተሻገር ሽፈራው (ዶ/ር) ‘የነፍስ ርችቶች’ በተሰኘ የግጥም ስብስብ መፅሃፉ ከቋጠራቸው ስንኞች መካከል በአድዋ 100ኛ ዓመት ክብረ በዓል የግጥም ውድድር ያሸነፈበትን ረጅምና ድንቅ ግጥም አካቷል። የዶክተር ተሻገር ግጥም አንጓ እና ስንኞች የአድዋን ምጡቅነት፣ ዝና፣ ነቅዓ ፍትሕ፣ ውበትና ቅኔ በውብ ቃላት ገልጠውታል። "... ዓድዋ አንቺ የዝና አጽናፍ ሕዝቦች እፍ ያሉብሽ ቁጣ - የነበልባል እቶን ጫፍ እጹብ ክስተት፤ ደቂቅ ረቂቅ፤ ምጡቅ ጠሊቅ ኬላ ድንበር፣ አድማስ ሰበር፣ የቅርብ ሩቅ ለትንግርትሽ ብቻ መጥኔ ትንግርት እውነት፣ ታምር ሁነት፣ የብርቅ ብርቅ፣ የድንቅ ድንቅ ለሰጠሽው ፍትህ መጠን - ለፍርድሽ ሚዛን ብያኔ ለንግስትሽ ሥነ ውበት - ለታሪክሽ ምስጢር ቅኔ…" ገጣሚው "... በምን ቀሰም፣ በምን ቀለም - በምን ብዕራና ሊከትበው..." ሲል የአፍሪካዊያን ሁሉን አቀፍ ድል ለመግለጽ የቀለም፣ የአንደበትና የብራና ወኔ እንዳጣባት ይናገራል። በመጨረሻም ይህችን የድል ቁንጮ የማትሞቺ ህያው ጀንበር ሁልጊዜም ተዘመሪ፤ ተወደሽ" ይላታል። "… እና ዓድዋ አንቺ በኩር የድል መኸር የቅኝ ግዛት ቀንበር ሰንሰለቱ እንዲሰበር ተጠቂዎች አጥናፍ አጥናፍ የመረጡሽ የትግል ዘር ህይወት ከፍለው እልፍ - ያርጉሽ የመረጡሽ ከአገር አገር የማታልፊ የማትከስሚ - የማትሞቺ ህያው ጀንበር ሰብዓዊ ድል ነሽና - ስምሽ ይወደስ ይዘመር…" (በአየለ ያረጋል)  
ከተሜው ገበሬ - ኮማንደር ጥላሁን ጸጋዬ
Feb 20, 2024 571
የከተማ ግብርና ሥራ ኢኮኖሚን ከመደገፍ ባለፈ ጤናማ ማህበረሰብ እንዲፈጠር አበርክቶው የጎላ ነው። አዲስ አበባ በመኖሪያ እና በተቋማት ቅጥር ግቢዎች የጓሮ አትክልት፣ ፍራፍሬና መሰል የግብርና ልማት ስራዎች እየተስፋፉባቸው ከመጡ ከተሞች መካከል አንዷ ናት። በርካታ የመዲናዋ ነዋሪዎች በግቢያቸው በሚያለሟቸው አትክልትና ፍራፍሬዎች ራሳቸውን ከመመገብ ባለፈ ለሌሎች መትረፍ ችለዋል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እህት ኩባንያ የሆነው ኮሜርሻል ኖሚኒስ ዳይሬክተር ጄኔራል የሆኑት ኮማንደር ጥላሁን ጸጋዬ በከተማ ግብርና አርአያ የሆነ ስራ እያከናወኑ ይገኛሉ። በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ አካባቢ ተወልደው ያደጉት ኮማንደር ጥላሁን የጓሮ አትክልትና ፍራፍሬ በማምረት ተጠቃሚ ከመሆን ባለፈ የገቢ ምንጭም ሆኗቸዋል።   የከተማ ግብርና ስራን ከቤተሰቦቻቸው መውረሳቸውን ያስታወሱት ኮማንደር ጥላሁን የከተማ ግብርና የኑሮ ውድነትን ለመቋቋም ከማገዙ ባለፈ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እድል እንደሚፈጥር ይገልጻሉ። ከመደበኛ ሥራቸው ጎን ለጎን እንደ ጥቅል ጎመን፣ ቆስጣ፣ ሰላጣ፣ አፕል፣ ሙዝ፣ ቡና፣ ማር፤ ዘይቱን እና ሌሎች ተክሎችን በጓሯቸው በማምረት ለቤተሰቦቻቸው ፍጆታ እየተጠቀሙ ይገኛሉ። ከዚህም ባለፈ ቡና፣ ሸንኮራ፣ ማር በማምረት ከራስ ፍጆታ አልፎ ለሌሎችም መትረፍ መቻላቸውን ይናገራሉ።   በተለይም በከተማ ግብርና ለመሰማራት ወሳኙ ሰፊ ወይም ጠባብ ቦታ መኖር ሳይሆን ያለውን ሃብት በአግባቡ በመጠቀም በፍላጎት መስራት መሆኑን ያነሳሉ። በዶሮ እርባታም በስፋት ለመሰማራት እየሰሩ ሲሆን በዚህም ከራሳቸው ፍጆታ አልፈው ቢያንስ ለአካባቢው ማህበረሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ እንቁላል ለማቅረብ ተዘጋጅተዋል። አሁን ላይ በመንግስት እየተተገበረ ያለው የከተማ ግብርና ከድህነት ለማምለጥ ሁነኛ መፍትሄ መሆኑን ገልጸዋል። በቀጣይም በተለይም ስራውን ይበልጥ በማስፋት ከራሳቸው አልፈው ምርቶቻቸውን ለማህበረሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ እየሰሩ እንደሆነ ተናግረዋል። ማንም ሰው ምንም አይነት ስራ ለመስራት በመጀመሪያ ደረጃ ፍላጎት ሊኖረው እንደሚገባ የገለጹት ኮማንደር ጥላሁን፤ በፍላጎት ወደ ስራ ከተገባ ውጤታማ መሆን እንደሚቻል ተናግረዋል። ሁሉም የቤተሰቡ አባላት አትክልትና ፍራፍሬዎችን በመንከባከብ የሚያደርጉት አስተዋጽኦ ለውጤታማነታቸው መሰረት መሆኑን ገልጸው አንድን ነገር ለማሳካት በቤተሰብ ውስጥ የሀሳብ መግባባትና መተባበር ወሳኝ መሆኑንም ገልጸዋል።    
የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ትኩረት የሚያደረግባቸው ዋና ዋና አጀንዳዎች 
Feb 17, 2024 617
የዘንድሮው 37ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ ረፋዱ ላይ የሚጀመር ሲሆን የአህጉሪቱ የረጅም ጊዜ እቅድ የ2063 አጀንዳ (የምንፈልጋትን አፍሪካ) እውን ለማድረግ በተጣሉ አንኳር ግቦች ማዕቀፍ በአብይት ጉዳዮች ምክከር አድርጎ የመፍትሔ ኃሳቦችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል። 1. የትምህርት ተደራሽነትና ጥራት የዘንድሮ የፈረንጆች ዓመት የትምህርት ዘመን ተብሎ መሰየሙን ተከትሎ የኅብረቱ ጉባኤ በአህጉሪቱ የትምህርት ተደራሽነትና ጥራት ለማረጋገጥ ሊሰሩ በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል። የመንግሥታቱ ድርጅት መረጃ እንደሚያሳየው፤ በአፍሪካ በተለይም ከሰሃራ በታች በሚገኘው የአህጉሪቱ ቀጣና በዓለም የትምህርት ተደራሽነት ካልተረጋገጠበት አከባቢ ቀዳሚ ነው። ለአብነትም አጠቃላይ በአህጉሪቱ ከሚገኙ እድሜያቸው ከ15 እስከ 17 የመሆኑ ታዳጊ ወጣቶች 60 በመቶ የሚሆኑት ከትምህርት ገበታ ውጪ ናቸው። ትምህርታቸውን የሚያቋርጡ ታዳጊዎች ቁጥርም አጅግ ከፍተኛ ነው። ብቂ መምህራን የማሰማራት እንዲሁም አህጉሪቱን ለመለወጥ የሚያስችሉ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፉ የተግባር ትምህርቶች ተደራሽነትም ከሚፈለገው በታቸ ነው። ይህንን የተገነዘበው የመሪዎች ጉባኤውም የመፍትሄ ውሳኔዎች ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል። 2. አህጉራዊ ምጣኔ ኃብታዊ ትስስር የአፍሪካን ከውጭ የፋይናንስ ጥገኝነት ለማላቀቅና ዘርፈ ብዙ ማኅበራዊና ምጣኔ ኃብታው ችግሮችን ለመቅረፍ የውስጥ አቅምን አሟጦ መጠቀም በተመለከተ ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል። በዚህ ረገድ በተለይም ትልቅ ግምት የተሰጠው አሁን በሙከራ ደረጃ ላይ የሚገኘው አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና የእስካሁኑ ሂደትና ቀጣይ አቅጣጫ ላይ ምክክር እንደሚደረግ ይጠበቃል። ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ሲገባ በአህጉሪቱ 30 ሚለየን ሰዎችን ከድኅነት የማውጣት እንዲሁም እንደ አውሮፓውያኑ አቆጠጣር በ2035 በአፍሪካ ገቢን በ7 በመቶ እንደሚጨምር ተስፋ የተጣለበት ይኸው የንግድ ቀጣና በፍጥነት ወደ ሥራ እንዲገባ አገራት ከታሪፍና ከሌሎች የንግድ ሂደት ጋር ያሉ ውስብስብ አሰራሮችን እንዲያስወግዱ አቅጣጫ ይቀመጣል ተብሎ ይገመታል። የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርትና ምርታማነት እንዲሁም ጥራት የማረገጋጥ ጉዳይም ሌላው ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ ነው። 3. አፍሪካ በዓለም መድረክ ያላት ሥፍራ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ተቋማት ያላትን ውክልና ተገቢውን ሥፍራ እንድትይዝ በተለይም በመንግሥታቱ ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ያላትን ውክልና በተመለከተ ለበርካታ ዓመታት ስትጠይቅ ቆይታለች። ይህንን ጨምሮ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማትም የአፍሪካን ፍላጎት ያገናዘበ ቁመና ሊኖረው ይገባል የሚለውም አጀንዳ የዘንድሮው ጉባኤ ተጠባቂ አጀንዳ ይሆናል የሚል ግምት አለ። አፍሪካ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ የባለብዙ ወገን መድረኮች ጋር በተለይም አሁን አፍሪካ የቡድን 20 አገራት አባል መሆኗን ተከትሎ እንዲሁም ተጽዕኖ ፈጣሪነቱ እየገነነ ከመጣው ከብሪክስ ጋር ባላትና ሊኖራት በሚችለው ግንኙነት ዙሪያም ምክክር ይደረጋል። በተለይም አፍሪካ እንደ ተጨማሪ የቡድን 20 አባልነቷ፤ ምን ይዛ ልትሄድና ልታመጣ ትችላለች እንዲሁም አባልነቷን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ለበርካታ ዓመታት ተፈልጎ የታጣውን ውክልና ለመካስ ወይም የአህጉሪቱን ድምጽ ይበልጥ ለማሰማት በሚቻልባቸው ምቹ ሁኔታዎች ዙሪያ ምክክር እንደሚደረግ ይጠበቃል። 4. የሠላምና ደኅንነት ተግዳሮቶችና መፍትሄያቸው የመሪዎቹ ጉባኤ ዘንድሮም በአፍሪካ የጸጥታ ችግሮች ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል። አህጉሪቱን ከድኅረ -ነጻነት በኋላ በእጅጉ እየፈተኑ ከሚገኙ ከነገረ ፖለቲካዊ ጉዳዮች መካከል ቀዳሚውን ሥፍራየሚይዘው የጸጥታ መደፍረስ ነው። ሽብርተኝነት፣ ኢ-ሕገ-መንግሥታዊ የሥልጣን መቆናጠጥ፣ ግጭቶችና ከምርጫ ጋር የተያያዙ የፖለቲካ አለመረጋጋት እና ሌሎች መሰል ቸግሮች አሁንም ለአፍሪካ ፈተና ሆነው ቀጥለዋል። እነዚህ የፖለቲካ ቀውሶች አህጉሪቱ በየትኛውም ማኅበራዊና ምጣኔ ኃብታዊ መስክ ወደፊት ፈቅ እንዳትል ካደረጓት ምክንያቶ ዋነኛው መሆኑን ነው የተለያዩ ጥናቶች የሚያሳዩት። እነዚህን ግጭቶች ባሉበት ለማቆምና ሌሎችም በቀጣይ እንዳይከሰቱ በተለይም የሰለጠነ የፖለቲካ ባህል (ውይይት) ብቸኛ አማራጭ ለማድረግ ኅብረቱ ከዚህ ቀደም የጀመራቸውን ሥራዎችና ሌሎች ተግባራትን ለማጠናከር በሚያስቸሉ ጉዳዮች ላይ መሪዎቹ ውይይት እንደሚያደረጉና የመፍትሄ አቅጣጫ እንደሚያስቀምጡ ይጠበቃል። ጉባኤው "ለ21ኛው ክፍለ ዘመን የሚመጥን አፍሪካዊ ማስተማር፤ የማይበገሩ የትምህርት ስርዓቶች በመገንባት በአፍሪካ ሁሉን አቀፍ፣ የሕይወት ዘመን፣ ጥራትና አግባብነት ያለው የትምህርት ተደራሽነትን ማስፋት“ በሚል መሪ ሃሳብ ዛሬና ነገ የሚካሄድ ይሆናል።  
  በቅንጅት መስራት - ትውልድን ለማፍራት
Feb 15, 2024 719
(በእንዳለ ደበላ ከሃዋሳ) መልካም ስነምግባር፣ ዕውቀትና ክህሎት እንዲሁም የተሟላ ስብዕና ያለው ትውልድ ለሀገር ሁለንተናዊ ለውጥ የሚኖረው ፋይዳ የላቀ ነው። ሀገር ያሰበችውን፣ ያለመችውንና የነደፈችውን ዕቅድ ለማሳካትም የሚኖረው አስተዋጾም ቀላል አይደለም። ዛሬ ላይ በቴክኖሎጂ አድገውና ስልጣኔን ተጎናጽፈው ዓለምን እየዘወሩ ያሉ ሀገራት ለእዚህ ደረጃ የደረሱት በዕውቀትና በክህሎት የተካነና የተሟላ ስብዕና ያለው ዜጋ ለማፍራት ለትምህርት ልዩ ትኩረት ሰጥተው በመስራታቸው ነው። በኢትዮጵያም ቀደም ባሉት ዓመታት የትምህርት ተቋማትን በማስፋፋትና ተደራሽ በማድረግ የተማረ ዜጋ የማፍራት ሥራዎች ሲሰሩ ቆይተዋል። የትምህርት ተደራሽነትን ለማስፈን ተቋማትን የመገንባት ሥራ በስፋት ቢከናወንም ጥራት ያለው ትምህርት ከመስጠት አንጻር ግን ውስንነቶች ጎልተው ታይተዋል። በዚህም ምክንያት ተማሪዎች በዕውቀት የተሟላ ስብዕና ባለቤት እንዲሆኑ ለማድረግ የተሰራው ስራ ከፈተና ውጤት አንጻር ሲመዘን የጎላ ችግር ያለበት ሆኖ ተገኝቷል። አጥንቶና አውቆ ለፈተና ከመቀመጥ ይልቅ በኩረጃ ተማምኖ የሚፈተነው ተማሪ ቁጥር ከፍተኛ መሆኑ ባለፉት ሁለት ዓመታት በ8ኛ እና በ12ኛ ክፍል ሀገራዊ ፈተና የተማሪዎች ውጤት በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱ አንድ ማሳያ ነው። ይህን የትምህርት ስብራት ለመጠገንና የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ መንግስት የትምህርት ፍኖተ ካርታ በማዘጋጀት ወደሥራ ገብቷል። ይህን ሥራ ለማገዝም ክልሎች ለትምህርት ጥራት መጓደል ምክንያት የሆኑ ችግሮችን ለይተው በመፍታት ወጣቱ ትውልድ በዕውቀት፣ በክህሎትና በመልካም ስነምግባር ታንጾ የተሟላ ስብዕና እንዲኖረው ለማድረግ የራሳቸውን ሥራ ጀምረዋል። በቅርቡ የተመሰረተው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልልም መልካም ስነምግባር የተላበሰ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ለማፍራት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው። ለእዚህም የትምህርት ስብራትን መጠገን አንዱ የትኩረት መስክ በማድረግ ከወላጆች፣ ከመምህራንና ሌሎች የትምህርት ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት ጀምሯል። ከእነዚህ አካላት ባለፈ በክልሉ የሚገኙ የሴቶችና ወጣቶች ሊግና ሌሎች አደረጃጀቶችም ይህን ሥራ በማገዝ የድርሻቸውን እንዲወጡ ለማድረግ በክልሉ በሚገኙ ሰባት ዞኖችና ሦስት ልዩ ወረዳዎች በቅርቡ የውይይት መድረክ አካሂዷል። በመድረኩ የትምህርት ሥራ ትልቁ አጀንዳ ይሁን እንጂ በክልሉ ሴቶችና ወጣቶች የሚነሱ የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና የዴሞክራሲ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙም ተነስቶ ውይይት ተደርጎበታል። በመደረኩ ላይ የተገኙት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው በትምህርት ዘርፍ ለውጥ ለማምጣት በጋራ እንደሚሰራ ገልጸዋል። ባለፉት ዓመታት ያጋጠመውን የትምህርት ስብራት ለመጠገን የዕውቀትና የክህሎት ባለቤት የሆነ ዜጋ ለማፍራት ትኩረት ሰጥቶ በቅንጅት ይሰራል። አቶ እንዳሻው እንዳሉት “አምና በተሰጠው የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ፈተና እንደ ክልል የመጣው ውጤት ዝቅተኛ ነው። ዘንድሮ ይህን ውጤት ለማሻሻል ትኩረት ተሰጥቷቸው እየተከናወኑ ካሉ ተግባራት መካከል ትምህርት ቀዳሚው ነው። ውጤቱን ለመቀየር ከተከናወኑ ተግባራት መካከል የመምህራንና የትምህርት አመራሩን አቅም ማሳደግ በዋናነት ትኩረት የተሰጠው ነው። ለእዚህም በተያዘው ዓመት ለ10 ሺህ መምህራን በክልሉ በሚገኙ የዋቸሞ፣ ወልቂጤ እና ወራቤ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር ስልጠና መሰጠቱን ነው የገለጹት። መምህራን አቅማቸው በጎለበተ መጠን ለተማሪዎቻቸው የተሟላ ትምህርት በመስጠትና አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ የትምህርት ስብራቱን ለመጠገን ከማንም በላይ አስተዋጾ እንደሚኖራቸውም ነው አቶ እንዳሻው ያመለከቱት። እንደ እሳቸው ገለጻ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የሚከናወኑ ሥራዎችን ለማገዝ የዞንና የወረዳ መዋቅሮች የየራሳቸውን ዕቅድ አውጥተው ወደ ሥራ ገብተዋል። የክልሉ መንግስት የመማሪያ መጻህፍትን እያሰራጨ እንደሚገኝም ነው የገለጹት። ህብረተሰቡም ገንዘብ በማዋጣት ለትምህርት ዘርፉ አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ ይገኛል። ወጣቱ በመልካም ስነምግባር የታነጸ እንዲሆን ለማድረግ በክልሉ የሚገኙ የንባብና ሌሎች የክህሎት ማዕከላትን በቁሳቁስ በማደራጀት የማጠናከር ስራ እየተሰራም ይገኛል። ይህም በትምህርት ጥራት ላይ የሚሰሩ ሥራዎችን የሚያጠናክር ነው። የክልሉ ሴቶችና ወጣቶች ሊግ የትምህርት ስብራቱ ሊጠገን የሚችለው ሁሉም ቅንጅታዊ ሥራ መሆኑን አምነው ይህን ተግባር ለማገዝ ቁርጠኛ መሆናቸውን በመድረኩ አረጋግጠዋል። ሁለቱ ሊጎች ለትምህርት ሥራው ስኬታማነት በክልሉ የሚገኙ ከአንድ ሚሊዮን የሚልቁ የሴቶችና የወጣቶች ሊግ አባላት የድርሻቸውን እንዲወጡ ጠንክረው እንደሚሰሩም ገጸዋል። ወጣት ሰንበቶ አባባ የክልሉ ወጣቶች ሊግ ጽህፈት ቤት ሀላፊ ነው። ከትምህርት ጥራት ጋር ተያይዞ የገጠመ የውጤት ማሽቆልቆል እና የተማሪ ስነምግባር ላይ ለውጥ እንዲመጣ ወጣቱ ከመንግስት ጎን ሆኖ እንዲሰራ ሊጉ የሚጠበቅበትን ይወጣል። የሊጉ አባላት በበጎፍቃድ ሥራዎች ከሚያከናውኗቸው ተግባራት ውስጥ የትምህርት ሥራ አንዱ እንደሚሆንም ነው ያመለከተው። ወጣቶቹ በክፍል ደረጃ የሚበልጧቸውን ታናናሽ ወንድምና እህቶቻቸውን በማስጠናትና በእረፍት ቀናት የማጠናከሪያ ትምህርት በመስጠት የጀመሩትን ሥራ የበለጠ ለማጠናከር እንደሚሰራም ነው የገለጸው። ሴቶች ከልጆቻቸው ጋር ካላቸው ቀረቤታ አንጻር በመልካም ስነምግባር እንዲታነጹና ሀገር ተረካቢ ትውልድ እንዲሆኑ በማድረግ በኩል አስተዋጿቸው የጎላ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የክልሉ ሴቶች ሊግ ጽህፈት ቤት ሀላፊ ወይዘሮ ኤልሳ ሽመልስ ናቸው። እንደእሳቸው ገለጻ፣ ልጆች ከትምህርት ቤት መልስ የየዕለት የትምህርት ውሏቸውን በመፈተሽ ለጥናት ጊዜ እንዲሰጡና በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ በማድረግ በኩል ከማንም በላይ የሴቶች ሚና የላቀ ነው። የሊጉ አባላት በየአካባቢያቸው ይህን በማጠናከር ለትምህርት ዘርፍ ወጤታማነት የበኩላቸውን እንዲወጡ ሊጉ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል። ከእዚህ በተጨማሪ የሊጉ አባላትን በማስተባበር በገንዘብ፣ በጉልበትና በቁሳቁስ ድጋፍ ለማድረግ የተጀመረው ሥራ እንደሚጠናከር ነው ያመለከቱት። መንግስት የትምህርት ጥራትን በማምጣት ስብራቱን ለመጠገን የጀመረው ጉዞ ስኬታማ እንዲሆን ሊጎቹ ከመንግስት ጋር ተቀናጅተው እንደሚሰሩ ማረጋገጣቸው ይበል የሚያሰኝ ነው። በትምህርት ጥራት በተለይ ከተማሪዎች ውጤት ጋር በተያያዘ የተስተዋለውን ችግር መፍታት ለአንድ ወገን ወይም ለመንግስት ብቻ የሚተው አይደለም። በአገርኛ ብሂል "ከአንድ ብርቱ ሁለት መድሀኒቱ" እንደሚባለው የለውጥ ሥራው የሁሉንም አካላት ተሳትፎ የሚፈልግ ነው። ከቤት ከተማሪ ወላጆች ጀምሮ የመምህራን፣ የማህበረሰብ፣ የትምህርት ቤቶች፣ የአመራሩና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን ቅንጅታዊ ተሳትፎ ይጠይቃል። የትምህርት ስብራቱ እንዲጠገን እነዚህን ባለድርሻ አካላት አስተባብሮ ዘርፉን መምራት ደግሞ ሌላው ትኩረት የሚፈልግ ጉዳይ ነው። ከእዚህ አንጻር በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሴቶችና ወጣቶችን ሊግ በማስተባበር በቅንጅት ለመስራት የታየው ጅምር ይበል ያሰኛል። ሀገር በተማረ፣ በመልካም ስነምግባር በታነጸና የተሟላ እውቀትና ስብዕና ባለው ወጣት የምትገነባው በአሁኑ ወቅት በትምህርት ዘርፍ የገጠመውን ስብራት መለወጥ ሲቻል ነው። ለዚህ ደግሞ ባለድርሻ አካላት ሚናቸው የጎላ ነው። በመሆኑም ብቁ ሀገር ተረካቢ ዜጋ ለማፍራት ከቤተሰብ ጀምሮ የትምህርቱን ዘርፍ ማገዝ የሁላችንም መሆን አለበት።
ትንታኔዎች
ሞክሼዎቹ - የአድዋ መንገሻዎች
Mar 2, 2024 165
ሞክሼዎቹ - የአድዋ መንገሻዎች (ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም እና ራስ መንገሻ ዮሐንስ)   የአድዋ አድማስ ዘለል ገድል ሲወሳ የድሉ መገኘት የጦር አበጋዞች ከፊት ይመጣሉ። ከንጉሠ ነገሥቱ ጀምሮ ራስ፣ ደጃዝማች፣ ፊታውራሪ፣ ቀኛዝማች፣ ግራዝማች፣ ባላምባራስ እና ሌሎች ባለማዕረግ አዋጊዎች የድሉ የጀርባ አጥንት መሆናቸው እሙን ነው። ከመላ ሀገሪቷ ጠረፍ ተነቃንቆ ስንቅና ትጥቁን ታጥቆ፣ ድል ሰንቆ እስከ ግማሽ ዓመት ድረስ በባዶ እግሩ የተመመውን የሀገሬው ሰራዊት በቅጡ መርተው አዋግተዋል። ከመነሻ ሰፈር እስከ አድዋ ተረተር፣ ከአምባላጌ ኮረብቶች እስከ መቀሌ ጋራና ቁልቁለቶች፣ ከእንደአባ ገሪማ እስከ ማሪያም ሸዊቶ ሸለቋማ ቋጥኞች፣ ከምንድብድብ መስክ እስከ በገሠሦ አቆበቶች፣ .... ድልና ገድል በደምና በላብ ሲጻፍ የጠላትን የ'ክዱ' ማባባያ የጠሉ፣ ለሀገር ለመሰዋት የቆረጡ ጀግና አዋጊዎች፣ የሀገር ባለውለታዎች ነበሩ። በአድዋ ድል መታሰቢያ 12 የአድዋ ጦር አበጋዞች (ጀኔራሎች) ሀውልት ቆሞላቸዋል። እነሱም፤- ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ ጉርሙ (አባ ጎራው)፣ ልዑል ራስ መኮንን ወልደ ሚካኤል ጉዲሳ (አባ ቃኘው)፣ ንጉስ ተክለሃይማኖት ተሰማ ጎሹ (አባ ጠና)፣ ንጉስ ሚካኤል አሊ አባ ቡላ (አባ ሻንቆ)፣ ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ ሮቢ (አባ ጠለስ)፣ ራስ ቢተወደድ መንገሻ አቲከም ቢተርፉ (አባ ገድብ)፣ ራስ ወሌ ብጡል ሃይለማሪያም (አባ ጠጣው)፣ ዋግሹም ጓንጉል ብሩ ገብረመድህን (አባ መርከብ)፣ ራስ አባተ ቧያለው ንጉሱ (አባ ይትረፍ)፣ ራስ አሉላ እንግዳ ቁቢ (አባ ነጋ)፣ ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ (ቁሴ) ዲነግዴ ሁንዱል (አባ መቻል) እና ራስ መንገሻ ዮሃንስ ምርጫ (አባ ግጠም) ናቸው። ከነዚህ የአገር ባለውለታዎች መካከል ሁለት ስመ ሞክሼ ጀግኖችን እንዘክራለን። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም እና ራስ መንገሻ ዮሐንስን። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም ከዳግማዊ አፄ ምኒልክ ቀዳሚዎች ስምንት ራሶች መካከል ብቸኛው የራስ ቢትወደድ (ከንጉሥነት በታች) ባለማዕረግ ናቸው። በፈረስ ስማቸው አባ-ገድብ ይሰኛሉ። በልጅነታቸው የዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ ባለሟል ሳሉ ከእስረኛው ምኒልክ ጋር ተዋወቁ። ምኒልክ ከአፄ ቴዎድሮስ አምልጠው ሸዋ ከገቡ በኋላ ከእቴጌ ጣይቱ ብጡል ወንድሞች ራስ ወሌ እና ፊታውራሪ አሉላ ብጡልን ይዘው ከመቅደላ ወደ ሸዋ ተሻገሩ፤ የምኒልክ ሁነኛ ሰው ሆኑ። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም በሞት እስኪለዩ ድረስ በክፉም በደጉም ዘመን የአጼ ምኒልክ ከፍተኛ አማካሪና ተወዳጅ መስፍን እንደነበሩ፣ ከጦር ሜዳ እስከ ሽምግልናም ሁነኛ ሰው ሆነው ስለማገልገላችው በታሪክ ድርሳናት ተጠቅሷል። በሸዋ፣ ወሎ፣ ጎንደር፣ ዳሞት(ጎጃም) ተዘዋውረው በተለያዩ ግዛቶች በአስተዳዳሪነት ሰርተዋል። ድሕረ መተማ ጦርነት ምርኮኞች እንዲመለሱ፣ ድንበር እንዲካለል በመስራትም የዲፕሎማሲ ስራቸው ይጠቅሳል። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም ከተሳተፉባቸው ደማቅ ታሪኮች መካከል የአድዋ ድል ይጠቅሳል። ጦርነቱ አሀዱ ብሎ የጀመረው ሕዳር 28 ቀን 1888 አምባላጌ ነው። ለሁለት ሰዓታት በዘለቀው በዚህ ጦርነት ጀኔራል ቶዚሊ የተባለው የጠላት ጦር መሪ የተገደለበት ነው። በዚህ ዐውደ ውጊያ አባ ገድብ አንዱ ወሳኝ የጦር አበጋዝ ነበሩ። በተለያዩ የታሪክ ድርሳናት እንደተመዘገበው ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም ከግዛታቸው ከዳሞትና አገው ምድር የተውጣጣ ስድስት ሺህ እግረኛ እና ፈረሰኛ ጦር ይዘው አድዋ ዘምተዋል። “አባ ገደብ መንጌ እያለ ኧረ ጐራው አምባ ላጌን ሰብሮ ቶዘሊን አስጐራው” የተባለው ለዚህ ይመስላል። አባ ገድብ ጥቅምት 11 ቀን 1903 ምሸት ከራስ ቢትወደድ ተሰማ ናደው ጋር እየተጫወቱ ካለምንም ህመም ድንገት አርፈው ቅድስት ሥላሴ ተቀበሩ። ራስ ቢትወደድ መንገሻ ልጆቻቸውን ከተለያዩ መኳንንት ጋር በጋብቻ በማጣመር በኢትዮጰያ ታሪክ ተጠቃሽ መሆን ችለዋል። ለአብነትም ዘውዲቱ መንገሻ ጠቅላይ ሚኒስትር መኮንን እንዳልካቸውን፣ አስካለማርያም መንገሻ ልዑል ራስ ኅይሉን አግብተው የልጅ ኢያሱን ባለቤት ሠብለወንጌል ኅይሉን ወልደዋል። ደጃዝማች ጀኔራል አበበ ዳምጠውን ያገቡት ወሰንየለሽ መንገሻ ደግሞ የአልጋወራሽ አስፋወሰን ባለቤት ልዕልት መድፈሪያሽ ወርቅ አበበን ወልደዋል። ሌላው የአድዋ ጀግና የጦር መሪ ራስ መንገሻ ዮሐንስ (አባ ግጠም) ናችው። ትውልዳቸው ትግራይ፣ ዘመኑም 1857 ዓ.ም ነው። የአድዋ ጦር ውሎ ቁልፍ ሰው ራስ መንገሻ የአጼ ዮሐንስ (አባ በዝብዝ) ልጅ ናቸው። አጼ ዮሐንስ በተሰዉበት በመተማው ጦርነት ተሳትፈዋል። አባታቸው ከሞቱ በኋላም የትግራይ አገረ ገዥ ሆነዋል። በአድዋ ዘመቻ 12 ሺህ ጦር አሰልፈው በብርቱ ተዋግተዋል። ራስ መንገሻ ዮሐንስ ከአድዋ ጦርነት ቀደም ብሎ በአጼ ምኒልክ ላይ እንዲያምጹ ኢጣሊያኖች ሲገፋፋቸውና ሲያባብላቸው ቢቆዩም ከስልጣን ሽኩቻ ይልቅ የኢትዮጵያን ነጻነት መርጠዋል። ከአጼ ምኒልክ ጋር ቢኳረፉም በሀገር ሉዓላዊነት ግን አልተደራደሩም። የኢጣሊያ ወራሪ ጦር ትግራይ ሲገባም ራስ መንገሻ የወገን ደጀን ጦር እስኪደርስ ወደራያ አፈግፍገው፣ በአምባላጌ ጦር ሜዳ አንዱ ተሳታፊ የጦር ጀግና ነበሩ። ራስ መንገሻ የትግራይ ሀገረ ገዥ በመሆናቸውም የእርሳቸው እና በስራቸው የነበሩት የራስ አሉላ እንግዳ ጦር በጄኔራል አልቤርቶኔ ከሚመራው ጠላት ሃይል ቀዳሚው ተፋላሚ እንዲሆኑ አድርጎታል። “አይከፈት በሩ መግቢያ መውጫችን በል ተነስ መንገሻ ግጠም በር በሩን ይህን ጎሽ ጠላ ማን አይቀምሰው መንገሻ ዮሐነስ አንተን ገፍተው...” ተብሎ የተገጠመላቸውም ለዚህ ነው። የጠላት መግቢያ በር ዘብ በመሆናቸው። አባ ግጠም በአድዋው ታሪካዊ ጦርነት አሰላለፋቸው ማርያም ሸዊቶ በተሰኘው ተራራ በኩል ሲሆን ከራስ አሉላ፣ ከዋግሹም ጓንጉል ብሩና ከደጃዝማች ሀጎስ ጋር በመሆን ነበር። የጠላትን የመጀመሪያ ጥቃትን ያስተናገዱትም ራስ መንገሻ ዮሐንስ ናቸው። የአድዋ ድል ከተበሰረ በኋላ አጼ ምኒልክ ራስ መንገሻን ሹመውና ሸልመው ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል። አጼ ምኒልክ ከትግራይ ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ ማህበረሰቡ በጦርነት ስፍራ በመሆኑ ለደረሰበት ጉዳት 30 ሺህ ብር ድጋፍ ማድራገቸውን የንጉሠ ነገሥቱ ዜና መዋዕል የጻፉት ፀሐፊ ትዕዛዝ ገብረ ሥላሴ ወልደአረጋይ ተርከዋል። ከአድዋ ድል ከጥቂት ዓመታት በኋላ ራስ መንገሻ በአጼ ምኒልክ ላይ በማመጻቸው ተይዘው በቁጥጥር ስር ዋሉ። ሕዳር 6 ቀን 1899 ዓ.ም አንኮበር ግዞት ላይ አንዳሉ ማረፋቸውን የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ። ራስ መንገሻ ዮሐንስ ከራስ መንገሻ አቲከም ግዛት ከአገው ምድር እመይቴ ተዋበች ጋር ትዳር መስርተው ዕውቁን የትግራይ መስፍን ራስ ሥዩም መንገሻን እንዲሁም ከእቴጌ ጣይቱ የወንድም ልጅ ወይዘሮ ከፈይ ወሌ ብጡል አግብተው አስቴር መንገሻን፣ አልማዝ መንገሻንና ብርሃኔ መንገሻን ወልደዋል፡፡ ለአብነት ያክል የሞክሼዎቹን ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም እና ራስ መንገሻ ዮሐንስ አነሳን እንጂ የዛሬ የ128 ዓመት በአድዋ ጦርነት ዓለም የተደመመበትና ዛሬ ድረስ እንቆቅልሽ የሆነበት ደማቅ ታሪክ የጻፉ ጀግኖች ቁጥር ስፍር የላቸውም። ጀግኖቹን የመሩ የጦር መሪዎችም ብዙና ተጋድሏቸው የገዘፈ ነው። ከ11 ሺህ በላይ የጣሊያንን ሠራዊት ሙትና ቁስለኛ ያደረጉ፣ 4ሺህ የሚሆኑትን እጅ ያሰጡና የማረኩ እንዲሁም 56 መድፎች፣ በርካታ መትረየሶች እና ሌሎች አውቶማቲክ መሳሪያዎቹን ለወገን ጦር እንዲያስረክብ ያደረጉ ኢትዮጵያውያን ሁል ጊዜም ክብር ይገባቸዋል። የጣሊያን ወራሪ ኃይል ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ስር አድርጎ ለመበዝበዝ ቢመጣም ጀግንነት፣ ሕብረ ብሔራዊ አንድነት፣ እንዲሁም የአልገዛም ባይነት ወኔን የታጠቁ ኢትዮጵያውያን በሶሎዳ ተራሮች ግርጌ ቅስሙን በመስበር የአገራቸውን ክብርና ነጻነት አጽንተዋል። በዚህ አኩሪ ድል ኢትዮጵያ ለበርካታ አገራት በተምሳሌትነት ትጠቀሳለች። የአድዋ ድል ደግሞ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህዝቦች የጀግንነት ተምሳሌትና የነጻነት ዓርማ እንድትሆን ያስቻለ ታላቅ አፍሪካዊ ድል ነው። (በአየለ ያረጋል)      
ትላንትን ከዛሬ ባስተሳሰረው የአድዋ ድል መታሰቢያ የሚገኙ እውነታዎች 
Mar 2, 2024 290
ትላንትን ከዛሬ ባስተሳሰረው የአድዋ ድል መታሰቢያ የሚገኙ እውነታዎች ለመነሻ እኤአ በ1885 ጀርመን በተካሄደው የበርሊን ኮንፈረንስ አውሮፓውያን መላ አፍሪካን በካርታ ላይ የተከፋፈሉትን በተግባር መሬት ላይ ለመቀራመት ጦራቸውን ሰብቀው፣ ስንቃቸውን ጭነውና ትጥቃቸውን አጥብቀው ያካሄዱት ዘመቻና የወረራ ጉዞ የተገታባት አድዋ እና እለቷ ዛሬ ድረስ በተገፉ ህዝቦች ልብ ታትማ በአዕምሮ ውስጥ ተቀርጻ ትኖራለች። ጣሊያን የኢትዮጵያን መሬት፣ የአየር ንብረትና መልክዓ ምድር ተቆጣጥሮ ሀብቷን ለሮምና ለመላው አውሮፓ ለማቅረብ የቋመጠበት የዘመናት ህልሙ የተኮላሸበት ቦታ ጭምር ናት - አድዋ። ይህ ወራሪ ኃይል ሊቢያን በእጁ ካስገባ በኋላ ጉዞውን በቀይ ባሕር አስመራ አድርጎ መላ ኢትዮጵያን የመቆጣጠር ግብ ነበረው። ጄነራል ባራቴሪ የመደባቸው ጄነራል አልበርቶኒ፣ ጄኔራል አሪሞንዲ እና ጄነራል ቦርሜዳ በግንባር የተሰለፈውን ጦር ሲመሩ የኋላ ደጀንም እንደነበራቸው የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ። ከ17 ሺህ በላይ የጣሊያን ሠራዊት 66 የሚሆኑ መድፎች፣ በርካታ መትረየሶች እና አውቶማቲክ መሳሪያዎችን ታጥቆ የግንባር ሜዳው ላይ ስለመድረሱ "የኢትዮጵያ ታሪክ ከመጀመሪያው እስካሁኑ ዘመን" በሚል በአንድርዜይ ባርይትኒስኪ እና ዮዓና ማንቴል-ኒየችኮ ተጽፎ በዓለማየሁ አበበ የተተረጎመው መጽሐፍ ያስረዳል። የዛሬ የ128 ዓመት፤ ዕለቱም የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በአድዋ ጦርነት ዓለም የተደመመበትና ዛሬ ድረስ እንቆቅልሽ የሆነበት ደማቅ ታሪክ በጀግኖች አባቶች ተሰራ። በጦርነቱ የጣሊያን መንግስት የጎመጀውን የኢትዮጵያን መሬት ሊያገኝ ይቅርና ከ11 ሺህ በላይ ሠራዊቱ ሙትና ቁስለኛ ሆኑ። 4ሺህ የሚሆኑት ደግሞ ለጀግኖች አባቶቻችን እጃቸውን ሰጥተው ተማረኩ። እንዲሁም 56 መድፎች፣ በርካታ መትረየሶች እና ሌሎች አውቶማቲክ መሳሪያዎቹን ለወገን ጦር አስረከበ። የቀረው የፋሽስት ሠራዊትም ተንጠባጥቦ እግሬ አውጪኝ ብሎ ፈረጠጠ። ጀግኖች ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው ክብር፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት በአውደ ግንባሩ በፈጸሙት የጀግንነት ተጋድሎ ዓለምን ያስደመመና መላውን ጥቁር ሕዝብ ያኮራ ድል ተጎናጽፈዋል። በወቅቱ ነጭን ታግሎ ማሸነፍ አይቻልም የሚለውን አስተሳሰብ በይቻላል ተክቶ ሌሎችም ለነፃነታቸው እንዲታገሉ ያነሳሳ ደማቅ የታሪክ አሻራ አኑረዋል። የጣሊያን ወራሪ ኃይል ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ስር አድርጎ ለመበዝበዝ ቢመጣም ጀግንነት፣ ሕብረ ብሔራዊ አንድነት፣ እንዲሁም የአልገዛም ባይነት ወኔን የታጠቁ ኢትዮጵያውያን በሶሎዳ ተራሮች ግርጌ ቅስሙን በመስበር የአገራቸውን ክብርና ነጻነት አጽንተዋል። በዚህ አኩሪ ድል ኢትዮጵያ ለበርካታ አገራት በተምሳሌትነት ትጠቀሳለች። የአድዋ ድል ደግሞ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህዝቦች የጀግንነት ተምሳሌትና የነጻነት ዓርማ እንድትሆን ያስቻለ ታላቅ አፍሪካዊ ድል ነው። ኢትዮጵያውያን በብሔር፣ በሃይማኖት፣ በአካባቢና በሌሎች ልዩነቶች ሳይነጣጠሉ ለአገራቸው ክብርና ነጻነት በአንድነት ቆመውና መስዋት ከፍለው ያስመዘገቡት የጀግንነት ታሪክ ነው። በዓድዋ ድል ኢትዮጵያ ለአፍሪካና ለመላው የጥቁር ህዝቦች ኩራትና የነፃነት ምልክት ሆናለች፡፡ የሰው ልጆችን እኩልነት በደም ዋጋ አረጋግጣለች።   የአድዋ ድል መታሰቢያ የአድዋ ድል ደማቅና ታላቅ ቢሆንም በሚመጥነው ልክ መታሰቢያ አልነበረውም። ዛሬ ግን እነዚያ ዋጋ የከፈሉ ጀግኖችን በሚመጥን ሁኔታ በአዲስ አበባ ፒያሳ “የዓድዋ ድል መታሰቢያ” ተገንብቷል። ከአድዋ ድል 128 ዓመታት በኋላ፣ የተሰራው የአድዋ ድል መታሰቢያ በጠቅላይ ሚኒሰትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የካቲት 3 ቀን 2016 ዓ.ም ተመርቆ ተከፍቷል። የአድዋ ድል መታሰቢያ በአምስት ሄክታር ላይ ያረፈ ሲሆን በአንድነት የተከፈለውን መስዋትነት፣ የአርሶ አደሮችን ተሳትፎ፣ የሴቶችን ተጋድሎ በሚያሳይ መልኩ፣ በአስገራሚ የኪነ-ህንጻ ጥበብ የታነጸ ነው።   የአድዋ ድል መታሰቢያ የተገነባበት ስፍራ አገር በውጭ ወራሪ ኃይሎች እጅ እንዳትወድቅ የህይወት መስዋዕትነት የከፈሉ የዓድዋ ጅግኖች የዘመቻቸው መነሻ እንዲሁም ከድል በኋላ ተሰባስበው ደስታቸውን የተጋሩበት ታሪካዊ ስፍራ ነው። የአድዋ ድል በዓል 7ኛ ዓመት ዳግማዊ ምኒልክ፣ ከአርበኞች፣ ከየአካባቢው ገዢዎች፣ ከውጭ አገር ዲፕሎማቶችና ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጋር በደማቅ ሁኔታ በዚሁ ስፍራ አክብረውታል። ስፍራው ዛሬ የታላቁ የአድዋ ድል መታሰቢያ ሳይገነባበት በፊት በተለያዩ ጊዜያት ለተለያዩ የልማት ስራዎች ቢታጭም ውጤታማ ስራ ሳይሰራበት ቆይቷል። አካባቢው ለረጅም ዘመናት ታጥሮ ሳይለማ በመቆየቱ እጅግ የቆሸሸ፣ ሰዎች ለዝርፊያ የሚዳረጉበት ስፍራ ሆኖ ቆይቷል። ዘመናትን ተሻግሮ ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ በከተማዋ ከሚገነቡ ትላልቅ ፕሮጀክቶች በዓይነቱ ልዩ የሆነው የዓድዋ ድል መታሰቢያ እንዲሰራበት ተደረገ። የዓድዋ ድል መታሰቢያ እጅግ በሚስብ ኪነ ህንፃ፤ የኢትዮጵያውያንን ህያው የድል ታሪክ የሚዘክር ሆኖ ተሰርቷል።   የአድዋ ድል መታሰቢያ መግቢያ በሮች የኢትዮጵያውያን የድል ብስራት፣ የጥቁር ህዝቦች የነጻነት ኩራት የሆነው የአድዋ ድል መታሰቢያ መግቢያ በሮች የራሳቸው የሆነ ስያሜ ተሰጥቷቸዋል። የምሥራቅ ጀግኖች በር፣ የምዕራብ ጀግኖች በር፣ የሰሜን ጀግኖች በር፣ የደቡብ ጀግኖች በር፣ የፈረሰኞች በር፣ የአርበኞች በር፣ የፓን አፍሪካኒዝም በር ተብለው የተሰየሙ ናቸው። በአራቱም አቅጣጫዎች የተሰየሙ በሮች ተምሳሌትነት በዓድዋ ድል ከአራቱም አቅጣጫ ኢትዮጵያውያን በጋራ የተሳተፉበት የጋራ ድላቸው መሆኑን ያመለክታል፡፡   መታሰቢያው በውስጡ ምን ይዟል? በዋናው መግቢያ:- የኢትዮጵያውያንና አፍሪካውያን ነጻነት ድል መገለጫ የሆነው የአድዋ ድል መታሰቢያ ሃውልትና የሁሉም ከተሞች ርቀት ልኬት መነሻ የአድዋ ዜሮ ኪሎ ሜትር ምልክት ይገኛል። የዓድዋ ጦርነት ዘመቻን ያስተባበሩትና የወቅቱ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት የዳግማዊ አፄ ምኒልክ እና የባለቤታቸው እቴጌ ጣይቱ ብጡል ሀውልትም በዚሁ መግቢያ በኩል ይገኛል። ሃውልት የቆመላቸው 12 የጦር መሪዎች:- በመታሰቢያው የአድዋን ጦርነት በታላቅ ጀግንነት በመምራት ለጥቁር ህዝቦች ድል ያበሰሩ 12 ዋና ዋና የጦር መሪዎች ሃውልት ተቀምጧል፣ እነሱም፤- ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ ጉርሙ (አባ ጎራው)፣ ልዑል ራስ መኮንን ወልደ ሚካኤል ጉዲሳ (አባ ቃኘው)፣ ንጉስ ተክለሃይማኖት ተሰማ ጎሹ ( አባ ጠና)፣ ንጉስ ሚካኤል አሊ አባ ቡላ (አባ ሻንቆ)፣ ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ ሮቢ (አባ ጠለስ)፣ ራስ ቢተወደድ መንገሻ አቲከም ቢተርፉ (አባ ገድብ)፣ ራስ ወሌ ብጡል ሃይለማሪያም (አባ ጠጣው)፣ ዋግሹም ጓንጉል ብሩ ገብረመድህን (አባ መርከብ)፣ ራስ አባተ ቧያለው ንጉሱ (አባ ይትረፍ)፣ ራስ አሉላ እንግዳ ቁቢ ( አባ ነጋ)፣ ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ (ቁሴ) ዲነግዴ ሁንዱል (አባ መቻል) እና ራስ መንገሻ ዮሃንስ ምርጫ (አባ ግጠም) ናቸው። በስተቀኝ በኩል፤- እስከ 3 ሺ እንግዶችን ማስተናገድ የሚችል ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተገጠመለት የስብሰባ አዳራሽ የሚገኝ ሲሆን በመጀመሪያው ኮሪደር ላይ ደግሞ ህዝቡ የጦርነት ክተት አዋጅ ጥሪ ሲሰማ ሁሉም ልዩነቱን ወደ ጎን በመተው አገሩን ከወራሪ ለመታደግ በመወኔ መነሳቱን፣ ወደ ጦር ግንባር መትመሙን እንዲሁም በጀግንነት መፋለሙን የሚሳየዩ ትዕይንቶች በእስክሪኖች ይታያሉ። በክፍሉ መሐል ላይ፤- ጦርነቱ የተጎሰመበት ግዙፍ ነጋሪት የተቀመጠ ሲሆን በነጋሪቱ ግራና ቀኝ ለጦርነቱ መንስኤ የሆነው የውጫሌው ውል አንቀጽ 17፣ የአድዋ ታሪክ እንዲሁም ከድል ወደ ሰላም የሚለው የአዲስ አበባ ስምምነት ሰነድ ተዘርግቶ ይገኛል። ከድል መልስ ግልጋሎት ላይ የዋሉ ጋሻዎች፣ መሳሪያዎች፣ አልባሳት፣ መመገቢያ ቁሳቁሶችን ጨምሮ በርካታ ቅርሶች፣ ስዕሎች፣ ፎቶዎች ይገኛሉ። ወደ ውስጥ መግቢያ በሆነው በምዕራብ በር ላይ የወቅቱ የኢትዮጵያ መሪ የነበሩት አጼ ሚኒሊክ እና እቴጌ ጣይቱ ብጡል ሃውልት በክብር ተቀምጦ ይገኛል። በአድዋ ጦርነት ወቅት ጠላት ለመጠጥነት ይጠቀምበት የነበረውን የምንጭ ውሃ እቴጌ ጣይቱ ብልሃት በተሞላበት መልኩ በኢትዮጵያ ሰራዊት እንዲከበብና ጠላት በውሃ ጥም እንዲዳከም በማድረግ ማሸነፍ የተቻለበት የጦር እስትራቴጂ የሚዘክር ገንዳ ከእቴጌ ጣይቱ ሃውልት ፊት ለፊት ተቀምጦ ይገኛል። የአድዋ ሰንሰለታማ ተራሮች፤- ጦርነቱ የተካሄደበትን ቦታ የሚያሳየው የአሸዋ ገበታ ሌላው የአድዋ ድል መታሰቢያ ውበትም ታሪክም ነው፡፡ የአድዋ ሰንሰለታማ ተራሮች፣ መልከዓ-ምድር የሚሳየው የመሬት ላይ ንድፍ ስራ በዚሁ መታሰቢያ መቀመጡ ኢትዮጵያውያን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለነጻነት የከፈሉትን መስዋትነት ያመላክታል። ከተራሮች አጠገብ በጦርነት ወቅት ጥቅም ላይ ከዋሉ ጣሊያናዊ ስሪት የሆነ "ቶሪኖ 1883" የሚል ጽሁፍ ያለበት መድፍ ይገኛል። በጦርነቱ ተዋጊዎችን ያጓጓዙ 45 ሺህ ፈረሰኞች የሰሩትን ጀብድ ሊወክልና ሊዘክራቸው የሚችል ‘የአድዋ ፈረሰኞች የድል ሀውልት’ ቆሞላቸዋል፡፡ የአድዋ ጀግኖች ኢትዮጵያን ከወራሪው ጣሊያን ለማዳን ዘር፣ ቀለም፣ ሃይማኖት ሳይለዩ በአንድነት ተሰባስበው የተመሙበትን የሚወክል ‘የአንድነት ድልድይ’ በሚል ተሰርቷል፡፡ የሁሉንም ተሳትፎ የሚያሳዩ የተለያዩ ሁነቶች በጦርነቱ ወቅት ህዝብና አገርን በታማኝነት ሲያስተዳድሩ የነበሩ እንደራሴዎች የሚያሳይ ስዕላዊ በመታሰቢያ የተቀመጠ ሲሆን በጦርነቱ ወቅት የነበረውን የህዝቡን እንቅስቃሴ የሚገልጹ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችና የመገልገያ ቁሳቁሶች፣ ስዕሎችና ቅርጾችም ይገኛሉ።   የገበሬዎችና ሴቶች ተሳትፎ የሚያሳዩ ስራዎች በአድዋ ጦርነት ከ120 ሺህ በላይ ገበሬዎች የግብርና ስራቸውን አቋርጠው "አገራችን ተነካች" በማለት ታጥቀው ድል ያጎናጸፉ፣ ለጥቁር ህዝቦች ትልቅ ታሪክ ያስቀመጡ ጀግኖች ናቸው። በዚህ መታሰቢያ የአንድነት ማዕከል፣ የአፍሪካ ነጻነት ማስታወሻ የኢትዮጵያ ጀግኖችን ጉዞ የሚያሳዩ ምስሎች ይገኛሉ። በጦርነት ወቅት ሴቶች የቤት ሃላፊነትን ከመወጣት በተጨማሪ በአዋጊነት፣ በመረጃ ሰጪነት ቁስለኞችን በመንከባከብ ለሰሩት ስራ የተሰየመ ማስታወሻም በአድዋ ድል መታሰቢያ በክብር ተቀምጦ ይገኛል። የአሁኑ ትውልድ አሻራ፣- የኢትዮጵያ ልጆች በአንድነት ተባብረው አፍሪካ በራሷ አቅም መልማት እንደምትችል ያሳዩበት፣ አፍሪካዊ ተምሳሌት የሆነው የህዳሴ ግድብ ፏፏቴ በመታሰቢያው ይገኛል። ኢትዮጵያውያን ለጥቁር ህዝቦች ነጻነት ላደረጉት ተጋድሎ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ የፓን-አፍሪካ ሃውልትም ተካቷል።   ሌሎችም የአድዋ ድል መታሰቢያ የአድዋን ጦርነት ሁነቶች ብቻ ሳይሆን ለተለያያዩ ዝግጅቶች የሚሆኑ አዳራሾችን፣ ካፍቴሪያዎችን፣ ሲኒማ ቤቶችንና ሌሎች ለበርካታ አገልግሎት የሚውሉ ክፍሎችንን አካቶ የተሰራ ነው። ከ2500 በላይ እንግዶችን መያዝ የሚችል ፓን አፍሪካን አዳራሽ፣ 300 ሰዎች የሚይዝ የአድዋ አዳራሽ፣ 160 ሰዎች የሚይዝ መካከለኛ አዳራሽ፣ 300 ሰው በአንድ የሚያስተናግዱ ሬስቶራንቶች፣ ሁለት ካፍቴሪያዎችና የህጻናት ሙዚየም በውስጡ አካቷል። በሌላ በኩል በአንድ ጊዜ 1000 ተሽከርካሪ መያዝ የሚችሉ ፓርኪንግ፣ ዘመናዊ ጂምና ሌሎችም ተካተዋል። የአድዋ ድል መታሰቢያ አድዋ ጊዜ የማይሽረው፣ ዘመን የማይለውጠው የጀግንነትና የአንድነት ምልክት መሆኑን ማሳያ፣ ለነጻነት የታገሉና የተሰዉ ጀግኖች የሚታሰቡበት የታሪክ ማስታወሻ ነው። የአድዋ ድል ትሩፋቶችን ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለመላው ጥቁር ህዝብ በየትውልዱ ለማስተማር የሚያግዝ የዘመናት የነጻነት መንፈስን የሚያስተጋባ፣ ለመጪው ትውልድ የሚሻገር እውነት ነው። እናም የአድዋ ድል መታሰቢያ የወል ታሪካችንን የምንገነባበት የማዕዘን ድንጋይ ነው።  
ሴቶች - የአድዋ ድል ሁለንተናዎች
Mar 1, 2024 182
ሴቶች - የአድዋ ድል ሁለንተናዎች በአየለ ያረጋል "... መጨረሻም ድምሩን ስገምተው አድዋ ድል የተገኘው በሴቶች አገልጋዮችና በበቅሎዎች ብርታት መሆኑ ይታወቀኛል..." ይህን ያሉት ታላቁ ምሁር እና የአድዋ ዘማች ፊታውራሪ ተክለሐዋሪያት ተክለማርያም ናቸው። በርግጥ በአድዋ ዘመቻ ያልዘመተ የለም። የሀይማኖት መሪዎች፣ ንጉሱ፣ ንግስቲቱ፣ ገበሬው፣ አገሬው ከነማንነቱ… ገድል ፈጽሟል። በጦር ሜዳ ገድሎች የሴቶች አበርከቶ እምብዛም አይታወስም። ሴቶች የዋሉበት ግንባር አይዘከርም። ቅሉ ሴቶች በኪነ-አድዋ ያልተዘመረላቸው ‘’ደብዛዛዎቹ ጀግኖች” ናቸው። እቴጌ ጣይቱን መሰል የአድዋ ሴት የጦር ፊታውራሪዎች አሉ። አዝማሪ ጣዲቄና መሰል አዝማሪዎች የሰራዊቱ ስነ ልቦና ገንቢዎች ናችው። ሴቶች የሎጂስቲክስ አሳላጮች፣ የቁስለኛ ሀኪሞች፣ የጀግና አበርቺዎች፣ የስንቅ ሰናቂዎች፣….በጥቅሉ ሴቶች የአድዋ ድል ሁለንተናዎች ነበሩ። ለዚህ ደግሞ እቴጌ ጣይቱ ብጡል ቀዳሚ ምስክር ናቸው። እቴጌ ጣይቱ ከውጫሌ እስከ መቀሌ፣ ከእንጦጦ እስከ ማርያም ሸዊቶ መላ መቺም፣ ጦር አዝማችም ነበሩ። የዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዜና መዕዋል ከታቢ ጸሐፌ ትዕዛዝ ገብረሥላሴ ወልደአረጋይ ‘ታሪከ ዘመን ዘዳግማዊ ምኒልክ’ በተሰኘው መጽሐፋቸው የሴቶችን ሚና በተመለከተ እንዲህ ይላሉ። “እንዲህም እየሆነ፣ አጤ ምኒልክ ባዳራሹ እቴጌ ጣይቱ በእልፍኝ ባለሟሎችን ወይዛዝርቱን ይዘው ግብሩ አንድ ቀን ሳይጎድል፣ ይዘምታሉ። ከዘመቻ ላይ ጠጁ ማሩ አለመጉደሉ፣ ስለምንድነው ያልህ እንደሆነ ይህን ታሪክ መመልከት ነው። በስድስት ድንኳን እንጀራው ሲጋገር ሲያድር፣ በአራት ድንኳን ወጡ ሲሠራ ሲያድር፣ ጠጁ በቀንድ በኮዳ ደግሞ ሦስት መቶ ስድስት መቶ የሚሆን ገንቦኛ ሲጓዝ ግብሩ ይጎድል ይመስልሀል” (ገጽ-241) ፀሐፊ ትዕዛዝ ገብረስላሴ ይቀጥላሉ። “… ጥቂቱን ጻፍን እንጅ በአድዋ ጦርነት ዐይናቸን እንዳየው ጆሯችን እንደሰማው መጻፍ አይቻለንም። እቴጌ በዚያን ጊዜ በግምባርዎ ተደፍተው በጉልበትም ተንበርክከው ድንጋይ ተሸክመው እግዚአብሄር እያመለከቱ ሲያዝኑ ሲጨነቁ ነበር። … ሴት ወይዛዝርቱም የንጉሠ ነገሥቱ ልጅ ወይዘሮ ዘውዲቱም ደንገጡሮችንም ተከትለው ነበር። የኋላው ሰልፈኛ እንደመወዝወዝ ሲል ባዩ ጊዜ ቃልዎን አፈፍ አድርገው ተናገሩ። አይዞህ አንተ ምን ሆነሃል! ድሉ የኛ ነው በለው! አሉት… ጣሊያ ድል ከሆነ በኋላ ወንዱ በርኮር፣ ሴቱ በገንቦ ውሃ ያዙ ብለው አዘው ለተጠማውና ለቆሰለው ውሃ ሲያጠቱት ዋሉ። እንኳን ኢትዮጵያ ሰው የኢጣሊያው ስንኳ ቁስለኛ ከዚያ ስፍራ የተገኘ ከዚህ ከእቴጌ ካዘዙት ውሃ አልቀረበትም“ይላሉ። ከጽሁፉ መረዳት እንደሚቻለው እቴጌ ጣይቱና መሰሎቻቸው አንድም በጸሎታቸው፣ አንድም ተዋጊዎችን በማደፋፈር ወኔያቸው፣ አንድም በጦር መሪነት ሚናቸውን ተወጥተዋል። ዋናው ደግሞ ቁስለኞችን የማከምና ሰብዓዊነት ሙያቸው ነው። ፀሃፊ ትዕዛዝ ገብረስላሴ “… ሙሉ ግብር እየበላ የተጓዘ እንጂ ወታደር የስንቅ አቁማዳዉን አልፈታም“ ሲሉ የአድዋ ሴቶች ገድል ምንኛ ገናና እንደሆነ መገመት እንደሚቻል ይጠቅሳሉ። እንደ ፀሐፊ ትዕዛዝ ገብረስላሴ ስለዘመቻው አጓኳን በማስታወሻቸው እንደገለጡት ድንኳን ተካይ፤ ዕንጨት አቅራቢው፣ ወጥ ሰሪው፣ እንጀራ ጋጋሪው፣ እህል ውሃ ተሸካሚው፣ መልከኛው (አራጁ)፣ በቅሎ ጫኙ፤ ተዋጊው ሁሉም በየፊናው እንስሳቱም ሳይቀር ተደራጅቶ ዘምቷል። በርካታ የታሪክ ምንጮች የአድዋ ጦርነት ተሳታፊዎች ገሚሶቹ ሴቶች እንደሆኑ ይገልጻሉ። የታሪክ ምሁሩ ዶክተር አልማው ክፍሌ ደግሞ በአንድ ወቅት ሚዲያ ላይ ቀርበው “በአድዋ ጦርነት ዘማቾች 75 በመቶ ሴቶች ነበሩ” ብለው ነበር። በአድዋ ጦርነት ሴቶች በተለያዩ ሙያዎች ተመድበው ከካምፕ እስከ ጦር ሜዳ ከመመገብ እስከ ማጀገን፣ ከማከም እስከ መዋጋት ድንቅ ሚና ተወጥተዋል። ድርብ ድርብርብ ኃላፊነት ይዘው የዘመቱ፣ ለወንዶችም ልብ፣ ሞራልና ወኔ አቀባዮች ነበሩ። ደራሲ በዕውቀቱ ሥዩም ‘ከአሜን ባሻገር’ በተሰኘ መጽሐፉ ‘ሴቶች በዋሉበት’ በሚል ርዕስ የኢትዮጵያ ሴቶች ተጋድሎና ሚና “ከቁስ ባሻገር ከልብ ያቀርባሉ” ይላቸዋል። “ሴቶች ባዋላጅነት ከነበራቸው የማይተናነስ ሚና በጦር ሜዳ ተጫውተዋል። እናቶቻችን በጦር ወቅት፣ መሳሪያ ያቀርቡ ነበር። ምግብ ያቀርቡ ነበር። ሃሳብ ያቀርቡ ነበር። ልብ ያቀርቡ ነበር። ደስታ ያቀርቡ ነበር። ኧረ ምኑ ቅጡ። ሴቶች ባንድ በሙቀጫ ዙሪያ፣ ማኅበረሰቡን ኬሚስት፣ ገጣሚና የፖለቲካ ተንታኝ ሆነው ማገልገላቸውን ልብ እንበል” ይላል። (ገጽ-138) የራስ መኮንን ባለሟል የነበሩት ፊታውራሪ ተክለሐዋሪያት ተክለማሪያም ገና በ15 ዓመት ዕድሜያቸው አድዋ ዘማች ነበሩ። "የሕይወቴ ታሪክ’ (ኦውቶባዮግራፊ) በተሰኘው ግለ ታሪካቸው ከሐረር እስከ አድዋ በዘለቀው ጉዟቸው ሴቷ (አገልጋያቸው) የነበራትን ሚና ለማብራራት ቃላት ያጥርባቸውና እንዲህ ብለው የአንባቢን ህሊና ይነካሉ። “… ከቶ እሷ ባትኖር ኖሮ እንዴት እሆን ኖሯል! እያልኩ ዘወትር ሳስበው ያደንቀኛል። ዕቃ ተሸክማ ስትሄድ ትውላለች። ከሰፈርን በኋል ውሃ ቀድታ፣ እንጨት ለቅማ፣ ቂጣ ጋግራ፣ ወጥ ሰርታ፣ ታበላናለች። ወዲያውኑ እንዲዚህ ለማታ ታሰናዳለች። እንደዚህ የወለተ አማኑኤልን አገልግሎት እያሰብኩ ስደነቅ ደግሞ በየሰፈሩ እንደርሷ ስንት ሴቶች እንደሚያገለግሉ ይታሰበኛል። የሴቶቹን አገልግሎት ስገምት ደግሞ የበቅሎዎች አገልግሎት ይታወሰኛል። በመጨረሻም ድምሩን ስገምተው አድዋ ድል የተገኘው በሴቶች አገልጋዮችና በበቅሎዎች ብርታት መሆኑ ይታወቀኛል። ሁሉንም አያይዥ በደምሳሳው ስመለከተው የኢትዮጵያን መንግስት ነጻነቱን ጠብቀው፤ እዚህ አሁን የደረስንበት ኑሮ ያደረሱት እነዚህ የዘመቻ ሃይሎች መሆናቸውን አልስተውም። የኢትዮጰያ መንግስት የተባለው ተቋም፣ ላገልጋዮቹ ውለታ ምላሽ ሆኗል ወይ? የዚህን ምላሽ ለመስጠት ሳስበው እልቅ የሌለው መንገድ ይገጥመኛል። ሲሄዱ መኖር ይሆንብኛል። የማልዘልቀው እየሆነብኝ፣ እየተከዝኩ እተወዋለሁ” በማለት በቁጭት ጽፈዋል። በርግጥም ሴቶች በኪነ-አድዋ በልካቸው ያልተዘመረላቸው፣ ‘’ደብዛዛዎቹ ጀግኖች” ናቸው።  
በአጭር ጊዜ ትልቅ እመርታ በሌማት ትሩፋት
Feb 6, 2024 984
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 14ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቀረቡ ጥያቄዎች መካከል የምግብ ዋስትናን ለማረጋጥ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን የተመለከቱ ጥያቄዎች ይጠቀሳሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ በግብርና ልማት በተለይም በስንዴ ላይ እየተሰራ ያለው ስራ በምግብ እራስን ለመቻል ለሚደረገው ጥረት ውጤታማነት ትልቅ ድርሻ እንዳለው አብራርተዋል። በግብርና ልማት እየተከናወኑ ባሉ ውጤታማ ስራዎች ላይ የሌማት ትሩፋት ተግባራት ሲታከሉ ከምግብ ዋስትና ባለፈ ስርአተ ምግብን በማስተካከል ረገድ አይነተኛ ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል። ለመሆኑ የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና ስርአተ ምግብን ለማሻሻል በሚደረገው ጥረት ውስጥ የሚኖረው ፋይዳ እንዴት ይታያል? በእስካሁኑ አካሄድስ ምን ውጤቶች ተገኙ? ጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ.ም በአርባ ምንጭ ከተማ ‘የሌማት ትሩፋት’ መርሃ ግብርን ካስጀመሩ በኋላ በመህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ሌማት አርሶ አደሩን፣ አርብቶ አደሩን እና ሸማቹን የሚያገናኝ ድልድይ መሆኑን ገልጸው ነበር። በወቅቱ የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር በቂ እና አመርቂ ምግብ ማግኘት መሆኑን ገልጸው በቂ የመጠን፣ አመርቂ የይዘት ጉዳይ መሆኑን አብራርተዋል። አክለውም በምግብ ራስን መቻል ከሀገር ሉዓላዊነትና ክብር ጋር ጥብቅ ቁርኝት እንዳለው ገልጸዋል። የሌማት ትሩፋት መርኃ-ግብር ዓላማ የምግብ ሉዓላዊነት ማረጋገጥና ክብርን ማስጠበቅ ሲሆን በተለይም ስጋ፣ እንቁላል፣ ማር እና ወተት ትርፍ ምርት ሆነው እንዲገኙ ማልማትና መጠቀምን መሰረት ያደረገ ነው። መርኃ-ግብሩ የኢትዮጵያን ደካማ የአምራችነት ታሪክ በመቀየር የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥና የኢኮኖሚ እድገትን የማፋጠን ግብ የሰነቀ መሆኑ ይታወቃል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሌማት ትሩፋት ዘመቻው በቤተሰብ፣ ብሎም በሀገር ደረጃ በምግብ ራሳችንን ለመቻል የምናደርገውን ጥረት የሚያፋጥን ነው ብለዋል። የወተት፣ የዶሮ፣ የዕንቁላል፣ የማር፣ የዓሣ እና የሥጋ ምርቶችን ለማሻሻል ሀገራዊ የመንግሥት ፕሮግራም ሆኖ ከጥቅምት 2015 ዓ.ም ጀምሮ እየተተገበረ የሚገኘው የሌማት ትሩፋት በብዙ መልኩ ውጤት እያስገኘ ነው። በእርግጥም የሌማት ትሩፋት በአንድ ዓመት ጉዞው በተለይ በወተት፣ በእንቁላል፣ በዶሮና ስጋ ምርት መጠን አርሶ አደሩን፣ አርብቶ አደሩን እና ሸማቹን የሚያገናኝ ድልድይ መሆኑ የተረጋገጠበት ውጤት ተመዝግቧል። ጠቅላይ ሚኒስትሩም በ2015 ዓ.ም፣ የወተት፣ የዶሮ እና የሥጋ ምርት መጠን በዕቅዱ መሠረት ጥሩ ውጤት ማምጣቱንና በተያዘው ዓመትም በበለጠ ለማሳካት የሁሉም ጥረት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል። የግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና አሣ ሃብት ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ጽጌረዳ ፍቃዱ በሌማት ትሩፋት መርኃ-ግብር በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች በማር፣ በወተትና በዶሮ ልማት ከ20 ሺህ በላይ መንደሮችን በመለየት ወደ ስራ ማስገባት መቻሉን ለኢዜአ ገልጸዋል። ለአብነትም በወተት ልማት በተሰሩ ስራዎች 6 ነጥብ 9 ቢሊዮን ሊትር የነበረውን የማምረት አቅም ወደ 8 ነጥብ 6 በሊዮን ሊትር ከፍ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል። በመጪዎቹ ዓመታትም ወደ 11 ነጥብ 7 ቢሊዮን ሊትር ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል። በእንቁላል ምርት ውጤታማ ስራ መሰራቱን ጠቅሰው የጫጩቶች ስርጭት ከነበረበት 26 ሚሊዮን ወደ 42 ሚሊዮን ማደጉን ተናግረዋል። የሌማት ትሩፋት መርኃ- ግብር የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ አስተዋጽኦ የላቀ መሆኑን የሚናገሩት የግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና አሣ ሃብት ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ጽጌረዳ ፍቃዱ በእንስሳት ሃብት ልማት ብቻ በዓመት ለ259 ሺህ ዜጎች የስራ ዕድል መፈጠሩን ገልጸዋል። ከዚህ ቀደም ለዘርፉ ትኩረት ባለመሰጠቱ ምክንያት አመርቂ ውጤት ሳያገኝ መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን፤ ዘርፉ በቅንጅት ከተመራ፣ በቴክኖሎጂ ከታገዘ የምግብ አማራጭን ማብዛት ይቻላል። ወተት፣ ማር፣ ስጋ እና እንቁላል መሰል የእንስሳት ተዋጽኦ ምርቶችን በገበያ ላይ ማትረፍረፍ፣ የሌማቱ በረከት ማብዛት የሚለው የብዙሃኑ እምነት ነው። የምግብ ዋስትና ጉዳይ ከተመጣጠነ ምግብ ጋር ያለው ቁርኝት የማይነጣጠል በመሆኑ የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር ፋይዳው ብዙ ነው። በሌማት ትሩፋት ገበታን በተመጣጠነ ምግብ መሙላት ከተቻለ የእናቶችንና የህጻናትን ፍላጎት በማሟላት በአካል የዳበረና በአዕምሮ የበለጸገ ትውልድ መገንባት ይቻላል። በተቃራኒው ያልተመጣጠነ አመጋገብ ጤና ላይ ከሚፈጥረው ችግር ባለፈ በሰዎች መካከል ያለውን የኑሮ አለመመጣጠን በማስፋት፣ ማህበራዊ ቀውስን በመፈልፈልና ኢኮኖሚውን በመጉዳት ምርትና ምርታማነትን ወደ ኋላ የሚጎትት ይሆናል። ይህ ደግሞ እንደ ኢትዮጵያ ከድህነት ለመውጣት በከባድ ትግል ላይ የሚገኙ ሀገራትን የልማት ግስጋሴ በመግታት ቀድሞ ወደነበሩበት የድህነት አረንቋ እንዲመለሱ ያደርጋቸዋል። በኢትዮጵያ ከሚገኙና እድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች ከሆኑ ህፃናት ከ30 በመቶ በላይ የሚሆኑት በዕድሜያቸው ልክ ዕድገት የማያስመዘግቡ ወይም የመቀንጨር ችግር ያለባቸው መሆናቸውን መረጃዎች ያመላክታሉ። ለዚህ ነው በምግብ ራስን ከመቻል ጎን ለጎን የተመጣጠነ ምግብን ተደራሽ ማድረግ ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ የሚሆነው። በዚህ ረገድ የሌማት ትሩፋት እየተጫወተ ያለው ሚና ቀላል ግምት የሚሰጠው አይደለም። የተለያዩ ምግቦችን በገበታ ላይ ማካተት የሚያስችል ስልጠናን ከተግባራዊ የልማት ስራዎች ጋር ያካተተ ሲሆን አዲስ የአመጋገብ ባህልን የሚያለማምድ ነው። ከዚህ ጋር በተያያዘ ለተሰሩ ስራዎችና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ላሳዩት የአመራር ቁርጠኝነት በተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት የከበረውን የፋኦ አግሪኮላ ሜዳልያ ተሸልመዋል። ሽልማቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምግብ ዋስትና እና በተመጣጠነ የምግብ አቅርቦት ላሳዩት ርዕይ፣ አመራር እና ቁርጠኝነት፣ ብሎም ፈጣን፣ ተለዋዋጭ እና ፈታኝ በሆነው ከባቢያዊ ሁኔታ በስንዴ ምርት ራስን ለመቻል በተከተሉት ፈጠራዊ መፍትሔ ዕውቅና ለመስጠት የተበረከተ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በመርሃ-ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ ረሀብን ዜሮ ለማድረስ የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት ብቻ ሳይሆን የምግብ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ሀገራዊ ብልጽግናን እውን እንደምታደርግ ገልጸዋል። ባለፉት አምስት ዓመታት በኢትዮጵያ የተሰሩት ስራዎች ለመጪው ትውልድ ጥሩ መሰረት የሚጥሉ መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያን ለአብነት አንስተዋል። የምግብ ሉዓላዊነት የማረጋገጥ ጉዟችንን በፅናት እናስቀጥላለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግብርና ስራችን የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ የተመጣጠነ ምግብን ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ እንሰራለን ብለዋል። የሌማት ትሩፋት የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባሻገር የኢኮኖሚ ሉዓላዊነቷን ያስከበረች ነጻ አገር እውን ማድረግን ያለመ መሆኑን የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አመራሩ ይህንን ተገንዝቦ እንዲሰራ አስገንዝበዋል። ኢትዮጵያ ህልም የሚመስሉ በርካታ አገራዊ ፕሮጀክቶችን እውን ማድረግ የቻለችው በዜጎቿ የተባበረ ክንድ መሆኑ እሙን ነው። ከዚህ አኳያ በምግብ ራስን ከመቻል በላይ የኢትዮጵያን የአምራችነት ታሪክ የመቀየር ግብ ለሰነቀው የሌማት ትሩፋት መርሃ-ግብር ስኬታማነት ከመቼውም ጊዜ በላይ በትብብር መስራት ይጠበቃል።  
ልዩ ዘገባዎች
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 7788
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 12844
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
በጂንካ ከተማ የተመረተው 23 ኪሎ ግራም የሚመዝነው የስኳር ድንች "በአፍሪካ ትልቁ ስኳር ድንች" በሚል ተመዘገበ
Mar 13, 2023 6183
ጂንካ መጋቢት 4/2015 (ኢዜአ):- በጂንካ ከተማ ደሙዝ ሰፈር የተመረተው እና 23 ኪሎ ግራም የሚመዝነው ስኳር ድንች በአፍሪካ የድንቃ ድንቆች መዝገብ "በአፍሪካ ትልቁ ስኳር ድንች" በሚል መመዝገቡ ተገለጸ። በአዲስ አበባ በተካሄደው የእውቅና ስነስርዓት ላይ የአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ስራ አስኪያጅ አቶ አሸናፊ አለም ለስኳር ድንቹ ባለቤት አቶ ኢሳያስ ጊዜአለው የእውቅና ምስክር ወረቀት አስረክበዋል። ከዚህ ቀደም በአፍሪካ 10 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች መቅረቡን አቶ አሸናፊ ለኢዜአ ገልጸዋል።   “ነገር ግን 23 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች በአፍሪካ ደረጃ ሲቀርብ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው” ብለዋል። በዓለም የድንቃ ድንቅ መዝገብ 37 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች መመዝገቡንና በደሙዝ ሰፈር የተገኘው ስኳር ድንች በ14 ኪሎ ግራም ዝቅ ብሎ ከዓለም የ”ሁለተኛነት” ደረጃ ላይ እንደሚያስቀምጠው አመልክተዋል። የስኳር ድንቹ ባለቤት አቶ ኢሳያስ ጊዜያለው ስኳር ድንቹ በአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ላይ በመስፈር የኢትዮጵያን ስም በማስጠራቱ መደሰታቸውን ገልጸዋል።   ስኳር ድንቹ እውቅና እንዲያገኝ የዜና ሽፋን ለሰጠው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ምስጋቸውን አቅርበዋል። ኢዜአ የካቲት 19 ቀን 2015 ዓ.ም “በጂንካ ከተማ ደሙዝ ሰፈር 23 ኪሎ ግራም የሚመዝን አንድ የስኳር ድንች መመረቱ ተገለጸ” በሚል መዘገቡ የሚታወስ ነው።
ዶክተር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ እውቅና አገኙ
Mar 9, 2023 7127
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 30/2015 የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ በሩዋንዳ ኪጋሊ በተካሄደው በአፍሪካ ዓለም አቀፍ የጤና አጀንዳ ኮንፈረንስ (AHAIC)2023 ላይ እውቅና ተሰጣቸው። ሚኒስትሯ በሩዋንዳ ኪጋሊ ትላንት በተካሄደው Africa Health Agenda International Conference (AHAIC) 2023 ላይ የተበረከተላቸውን Women in Global Health Award የእውቅና ሽልማት በተወካያቸዉ በኩል ተቀብለዋል። እውቅናው በጤና ልማት ውስጥ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በመቋቋምና በመፍታት፣ የጤና አገልግሎት ጥራትና ፍትሀዊ ተደራሽነት እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ሽፋን ላይ ትኩረት ሰጥተው ለሚሰሩ አመራሮች የሚሰጥ መሆኑም ተመላክቷል። ለመጪዎቹ ትውልዶች አርዓያ ለሆኑ የአፍሪካ ሴት መሪዎች የሚሰጠው ሽልማቱ የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰም ለዜጎች የተሻለና ዘላቂ ጤናን ለማምጣት በሚደረግ ጥረት ውስጥ ላበረከቱት የላቀ የመሪነት ሚና ከአምሪፍ ሄልዝ አፍሪካ እውቅናውን አግኝተዋል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 17014
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 15735
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 12844
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 9728
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈጸማል-ባለስልጣኑ
Apr 6, 2023 8980
አዲስ አበባ መጋቢት 28/2015(ኢዜአ)፡ በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ። የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ የሚፈፀምበትን የድርጊት መርሐ ግብር በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ተወያይቷል።   የውይይቱ ዓላማ በመዲናዋ የሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች በአሰራሩ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማስቻል መሆኑ ተነግሯል። በዚህ ወቅት የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ፤ ባለስልጣኑ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። በዚህም ቀደም ብሎ ከነዳጅ ማደያና አከፋፋይ ኩባንያዎች ጋር ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው፤ አሁን ደግሞ ለሙሉ ትግበራው ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ውይይት ተደርጓል ብለዋል። በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓቱ በአማራጭነት ለሙከራ እየተተገበረ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም ተናግረዋል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል። የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሀምሌ አንድ ጀምሮ በአስገዳጅነት እንደሚተገበርም ጠቁመዋል። በኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ሞባይል መኒ ኦፊሰር ብሩክ አድሃነ፤ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች በማድረግ ረገድ በቴሌ ብር ውጤታማ ስራ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። ለዚህም ባለፉት ዘጠኝ የሙከራ ወራት በቴሌ ብር ብቻ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈጸሙን አንስተዋል። የነዳጅ ግብይቱን በአግባቡ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መገንባቱንም እንዲሁ። የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማኅበር አባል የሆኑት አቶ ሚካኤል ገብረስላሴ እና የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ የነዳጅ ግብይት ስርዓቱ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ መሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ብለዋል። በተለይ ለነዳጅ አዳዮች ጥሬ ገንዘብ በመቁጠር የሚያባክኑትን ጊዜ ከመቅረፍ አንፃር እንዲሁም በማደያዎች የሚቀመጥ የግብይት ገንዘብ እንዳይኖር በማድረግ የደህንነት ስጋትን እንደሚፈታ ተናግረዋል። በተጨማሪም መንግስት የነዳጅ ምርት ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን ስርጭት ሂደት መረጃ እንዲኖረው እና ነጋዴዎችም ግብርና ታክስ እንዳያጭበረብሩ በማድረግ ቴክኖሎጂው ትልቅ ሚና አለው ነው ያሉት።  
ለላቀ ውጤት - የተማሪ መምህርና ወላጆች ጥምር ጥረት
Mar 27, 2023 8686
በሃብታሙ ገዜ ስልጡን የመንገድ ጠበብቶች በጥንቃቄ የከተማ ውብ ገፅታ አልበሰው ባነጿት ከዚራ አካባቢ የሚገኘው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አዳራሽ በሰው ተሞልቷል። የተሰበሰቡት ወጣት ተማሪዎች፣ የድሬደዋ አመራሮች፣ የትምህርት ዘርፍን የሚመሩ አካላትና ወላጆች በፈገግታ ተሞልተዋል። ይበልጥኑ ከወጣቶቹ ገፅታ የሚንፀባረቀው የደስታ ፈገግታ ለአዳራሹ የተለየ ብርሃን ደርቦለታል። የደስታቸው ምንጭ ደግሞ አምና የተፈተኑትን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በላቀ ውጤት አልፈው ሽልማት በመቀበል ላይ መሆናቸው ነው። የአዳራሹን የሽልማት መርሃ ግብር የሚመራው ሰው ድንገት "የዛሬው ልዩ ክስተት ከሚሸለሙት ተማሪዎቻችን መካከል ከ600 በላይ ውጤት በማምጣት ከወንድሞቿ ጋር ሦስት ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ የአንድ ቤተሰብ አባላት መገኘታቸው ነው" ሲል ተናገረ። ይሄኔ አዳራሹ በጭብጨባ ተናጋ፤ ሁሉም ተሰብሳቢ በአንድነት ቆሞ ጭብጨባውን አቀለጠው። ለሽልማት ወደ አደባባዩ የመጡት በደስታ ፀዳል የወረዙት የወላጅ ተወካይ እንጂ የድሉ ባለቤት የሆኑት እነዚህ ሦስት ተማሪዎቹ አይደሉም። በአዳራሹ የተሰባሰቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃርና የካቢኔ አባላት እንዲሁም ተሸላሚዎቹ ተማሪዎች "የዓመቱ የተለየ ክስተት የሆኑትን ተማሪዎች" ለማየት ዓይኖቻቸው ቢባዝንም አልተሳካም። ለምን ካላችሁ ተማሪዎቹ ወደ ተመደቡበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጓዛቸው ነው። የመድረኩ የድምፅ ማጉያ ባለቤትም ሆነ ተሰብሳቢዎቹ የዓመቱ ክስተት የሆኑት ኒያ ሰላሃዲን 602፤ አሊ ሰላሃዲን 556፣ አማን ሰላሃዲን 526 ያመጡት ተማሪዎች መንትዮች መሆናቸውን ቢያውቁ ኖሮ አዳራሹ ሌላ የግርምት ደስታን ባስተናገደ ነበር። ሽልማቱን ያበረከቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ተሸላሚዎች በጥረታቸው በትጋታቸው ባመጡት ውጤት መደሰታቸውን አብስረዋል። አገር በዜጎች አንድነትና መተባበር እንደሚፀናው፤ የተማሪዎች ውጤትም በተማሪዎችና በመምህራን ጥረት ብቻ ሳይሆን በወላጆች ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ጭምር የሚመጣ ነው። "በተለይ ከአንድ ቤተሰብ የበቀሉት ተማሪዎችና የዛሬው ሽልማት እና ውጤት ያስተማረን ይህንኑ ነው" ብለዋል ከንቲባው። በዚህ አደራሽ ውስጥ የሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰነ-መምህራን ታድመዋል። እንደ ድሬደዋ አስተዳደር ከተፈተኑት ከ3 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎች መካከል በቀጥታ ያለፉት 250 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። ለመጣው ውጤት ተሞጋሹም ተወቃሹም የዘርፉ አመራሮች፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና ወላጆች ናቸው። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉካ መሐመድ "ለመጣው ዝቅተኛ ውጤት በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ያለነው በሙሉ ተጠያቂዎች ነን" ብለዋል። ኃላፊዋ ሌላውም ከዚህ ትምህርት መውሰድ እንዳለበት ነው የገለጹት። እንደ አስተዳደሩም የትምህርት አመራሮች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራንና ወላጆች ያካተተ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩን አውስተዋል። በመንግስት የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ከኩረጃ ነፃ ለማድረግ የተወሰደው እርምጃ ተማሪዎች በጥረታቸውና በብቃታቸው የልፋታቸውን ውጤት እንዲያገኙ ያስቻለ ነው። የፈተና አሰጣጡና ውጤቱ እንደአገር ያለንበትን አዘቀት አስተምሮ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ፤ ብቁና በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማዋለድም ጥርጊያ መንገድ ሆኖ አልፏል ማለት ይቻላል። መንግስት የትምህርት ጥራትን ከታችኛው እርከን ጀምሮ ለማረጋገጥም በዘርፉ ሙሁራን ጥልቅ ጥናት ላይ ተመስርቶ ያዘጋጀውን የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት ቀርጾ ዘንድሮ እስከ 8ተኛ ክፍል ተግባራዊ አድርጓል። ለመማር ማስተማሩ መጻህፍት ተዘጋጅተው ለመምህራን ስልጠና በመስጠትም ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። በሚቀጥለው ዓመትም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው። በሽልማት ሥነስርዓቱ ላይ እንደታየው ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች ሚና የጎላ ነው። ወላጆች ተገቢውን ድጋፍ እና ጥብቅ ክትትል ካደረጉ የሚፈልገው ለውጥና ውጤት ማምጣት ይቻላል። ወይዘሮ ሙሉካ በአትኩሮት ከገለጹት ሃሶቦች መካከል ዋናዎቹን ሰበዞች መዝዤ፤ "ተጠያቂዎቹ እኛው ነን" የሚለውን ሃሳብ አንግቤ ለድሬዳዋና ለአገር ከፍ ሲል ለዓለም ህዝብ ጭምር በየዘርፉ ታላላቅ ሙሁራን ወደ አፈሩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሁ። ድንገት ሃሳቤን ቀለበስኩት። መነሻዬ የወላጆች ኃላፊነት እና ድጋፍ መሆኑን መርሳት ዞሮ ዞሮ የምፅፈው መዳረሻ መርሳት ይሆንብኛል ብዬ ነው። እናም ወደ ሦስቱዎቹ፤ የዓመቱ ክስተቶች አባት አመራሁ። ድሬዳዋን ለሁለት እኩሌታ የሚከፍላትን የደቻቱን ድልድይ ተሻግሬ ወደአንድ የግል የሕክምና አገልግሎት መስጫ ሆስፒታል ገባሁ። አምሮ በተሰናዳው ሆስፒታል ውስጥ ሙያዊ ኃላፊነታቸው እየተወጡ አገኘኋቸው፤ የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍን። የውጤታማ ተማሪዎቹ ወላጅ ናቸው፤ በ1970 ዎቹ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መዝለቅ በመርፌ ቀዳዳ የመሹለክ ያህል በሚቆጠርበት ዘመን በከፍተኛ ማዕረግ አልፈው በቀሰሙት ዕውቀትና ጥበብ የሰዎችን ሕይወት እየታደጉ ይገኛሉ። ዶክተር ሰላሃዲን ለትምህርት ጥራት መውደቅ ወደ ዩኒቨርሲቲ በስርቆትና ኩረጃ የመግባት ዝንባሌዎች እንደሆኑና ይሄም ሁሌም የሚያንገበግባቸው ጉዳይ መሆኑን አጫወቱኝ። መንግስት በተለይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ባልደረቦቻቸው በሁለተኛ ደረጃ የፈተና አሰጣጥ ላይ የወሰዱት እርምጃ አስደስቷቸዋል። "በተለይ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ከሚያሳልፉት ጊዜ በበለጠ ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸው ጊዜ ይበልጣል። ከሁሉም ነገር በላይ ለትምህርት ትኩረት ማድረጋቸውን መከታተልና መደገፍ የኛ ፋንታ ነው፤ አንዴ መስመር ከያዙ የሚመልሳቸው ችግር አይኖርም" ይላሉ። ሦስቱ ልጆቻቸውን በዚህ መንገድ በመደገፍ እና ከትምህርት ቤታቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ አስችለዋል። 604 ያመጣችው ስኮላርሽፕ ሺፕ አግኝታ ወደ ውጭ ሄዳለች፤ ሁለቱ ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው። "ለልጆቼ የፈለጉትን የማድረግ አቅም ቢኖረኝም ያለትምህርት የሚፈጠር አንዳች ነገር እንደሌለ ገብቷቸው ለውጤት በቅተዋል" ይላሉ ዶክተር ሰላሃዲን። ብዙ የመስራት እንጂ ብዙ የመናገር ዝንባሌ የማይታይባቸው እኚህ የታታሪዎች አባት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራት በሚደረግ ጥረት የወላጆች ክትትልና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ነው በአፅንኦት ያሳሰቡት። "የሽልማቱ መርሃ ግብር ወደሌላ አካባቢ በሄድኩበት አጋጣሚ በመካሄዱ ሳልገኝ ቀረሁ፤ በጣም የቆጨኝና ቅር ያለኝ ዕለት ሆኖ አልፏል" ብለዋል። እሳቸውን ጨምሮ አንቱ የተሰኙ ሙሁራን ያፈራው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ፍቃዱ ሰንበቶ፤ የማርያም ሰፈር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ኢጀታ መኮንን ካለፈው ክፍተት በመማር ዘንድሮ የተሻለ ውጤት እንዲመጣ የተማሪዎች አመለካከት ላይ ለውጥ እና እችላለሁ የሚል መርህ የማስረጽ ሥራ ተሰርቷል ብለውኛል። ለውጤቱ ቀዳሚ ባለቤት ተማሪዎች ቢሆኑም ከወላጆቻቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ የማካካሻና ለፈተና ዝግጁ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ነው ርዕሳነ መምህራኑ የገለጹት። ቅኝቴን በመቀጠል ሽቅብ ወደ ሳብያን ሁለተኛ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት አመራሁ። ይህ ትምህርት ቤት በከተማዋ ካሉት ትምህርት ቤቶች በውጤታማነት እና በብዛት ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማሳለፍ ረገድ ወደር አልነበረውም፤ ባለፉት ዓመታት። ከተመሠረተ 22 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ ትምህርት ቤት በምክትል ርዕሰ መምህርነት የሚመሩት አቶ በፍቃዱ ወልደሰማያትን አገኘኋቸው። ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተናቸው ከ800 በላይ ተማሪዎች መካከል ያለፉት 20 ናቸው። የመጣው ውጤት ያለንበትን ደረጃ ፍንትው አድጎ ያሳየን መሆኑን ተከትሎ መሠረታዊ የሆኑት ችግሮች በጋራ ተነቅሰው ለመጪው ጊዜ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ ተገብቷል። አቶ በፍቃዱ እንዳሉት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ትምህርት ቤቱን ሞዴል ትምህርት ቤት ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን ለዘንድሮው ተፈታኞች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ነው። እነዚህን ሥራዎች የተማሪ፣ መምህርና ወላጅ ህብረት በቅርበት እንዲከታተል ተደርጓል። ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች የቅርብ ክትትልና ደጋፍ መሠረታዊ ጉዳይ ነው የሚሉት አቶ በፍቃዱ፣ ለዚህ ጉዳይ ትምህርት ቤቱ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ነው የገለጹት። "በተለይ ወላጆች በትምህርት ውጤታማነት ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ልክ እንደ ዶክተር ሰላሃዲን አይነት ቤተሰቦች ተሞክሮ የማስፋት ሥራ ለመስራት ትምህርት ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል" ብለዋል። "ፍቃደኛ ከሆኑ የመጀመሪያው እንግዳችን ዶክተር ሰላሃዲን በማድረግ ለወላጆች ህብረት ተሞክሮን እንዲያካፍሉ እናደርጋለን " ብለዋል። በድሬዳዋ ታሪክ ከፍ ሲልም እንደ አገር በ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ1990 ዎቹ ዘመን ጀምሮ እንዲህ አይነት ዝቅተኛ ውጤት አለመምጣቱን የሚገልጹት ደግሞ የትምህርት ቤቱ አንጋፋ መምህር እዮብ ረታ ናቸው። የፊዚክስ መምህሩ እንደሚሉት የአምናው ክፍተት በሰከነ መንፈስ ታይቶ ዘንድሮ የተሻለ ሥራ ለመስራት መምህራን በጥሩ መንፈስ ጉዞ ጀምረዋል። ወላጆችም ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት መላክ ብቻ ሳይሆን የዕለት ተዕለት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው የገለጹት። "የተማሪዎች የትምህርት ቤት ቆይታ ለሰዓታት ብቻ የተወሰነ መሆኑን በመረዳት ወላጆች በስነ ምግባር የታነፀ በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማፍራት የተጀመረውን ጉዞ መደገፍ አለባቸው" በትምህርት ቤቱ የዘንድሮው የ12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪ ረደኤት ገነሙ በበኩሏ "እንደአገር በዩኒቨርሲቲዎች የተጀመረው የፈተና አሰጣጥ ኩረጃን የሚጠየፍ በራሱ ጥረት ውጤት ለማምጣት የሚተጋ ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል" ብላለች። በትምህርት ቤቱ የተጀመረው ልዩ ዕገዛ መጠናከርና መቀጠል እንዳለበት የምትገልጸው ተማሪ ረድኤት ወላጆቿ ተገቢውን ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ከመምህራን ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የልጆቻቸውን ትምህርት ሊከታተሉ እንደሚገባ አውግታኛለች። እኔም ሆንኩ የዘንድሮ ተፈታኞች ትምህርት ቤታችንንና ድሬዳዋን በውጤት ለማስጠራት ጠንክረን እያጠናን ነው ብላለች። ከገጠር ከተማ ተጉዞ የሚማረው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪ አላሙዲን አልይ በበኩሉ፤ መንግሥት የፈተና ኩረጃን ለማስቀረት የጀመረውን ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበት ነው የገለፀው። "የዘንድሮ የመምህራን ድጋፍ የተለየ ነው፤ እኛም ልዩ የጥናት ጊዜ እንዲጀመር ጫና እየፈጠርን ነው፤ ወላጆቼም በአቅማቸው እየደገፉኝ በመሆኑ ቀሪው ሥራ የኔ ጥረትና ብርታት ይሆናል፤ ልፋቴ ውጤት እንዲያስገኝ የስርቆትና የኩረጃ ሂደት መወገድ አለበት" ብሏል ተማሪ አላሙዲን። ከሳብያን ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ግቢ ለቅቄ ስወጣ ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍ ያሉኝ ትዝ አለኝ። "ለተሞክሮ የሚሆን ነገር እኔ ጋር ካለ ያለችኝን ጊዜ አብቃቅቼ ለዘንድሮው ተፈታኞች ሃሳቤን ለማካፈል ዝግጁ ነኝ" ያሉኝ በአዕምሮዬ ደጋግሞ እያቃጨለብኝ ጉዞዬን ቀጠልኩ። ለመውጫ ያህል፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ዘንድሮ በመንግሥት እና በግል 22 ትምህርት ቤቶች ከ5 ሺህ በላይ ተፈታኞች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው። እነዚህ ተፈታኞች በራሳቸው ጥረት የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ በየአቅጣጫው የተቀናጀ ድጋፍ የማድረግ ጅምር ተግባራት ተስተውለዋል፤ ይሄ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ይህን ዙሪያመለስ ድጋፍ በማጠናከር ተማሪዎቹን ለውጤት ማብቃት በሁሉም ዘንድ ለአፍታ መዘንጋት የለበትም። መድረሻውን ለማሳመር መነሻውን አድምቶ ማበጃጀት ግድ እንደሚልም እንዲሁ።
ተመድ በሶሪያ በርዕደ መሬት ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚውል የ397 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ጥሪ አቀረበ
Feb 15, 2023 8332
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 8/2015 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሓፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በሶሪያና ቱርክ ድንበር አቅራቢያ በደረሰው ርዕደ መሬት ሳቢያ ከቤታቸው የተፈናቀሉ ሶሪያውያንን ለማገዝ የ397 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ጥሪ አቀረቡ። ዋና ጸሓፊው ጥሪውን ያቀረቡት ባሳለፍነው ሳምንት በቱርክና በሶሪያ ድንበር አቅራቢያ በደረሰው ርዕደ መሬት ሳቢያ ከቤታቸው የተፈናቀሉ አምስት ሚሊዮን የሚጠጉ ሶሪያውያንን ለማገዝ ነው። በኒውዮርክ በሰጡት መግለጫ ሶሪያውያኑን ለማገዝ የተጠቀሰው የገንዘብ መጠን ለሶስት ወራት ጊዜ ብቻ የሚበቃ መሆኑን ጠቅሰው የሚመለከታቸው ሁሉ የድርሻቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል። ከአደጋው በኋላ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 50 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር አስቸኳይ ድጋፍ ማቅረቡን ገልጸው ተጨማሪ እገዛዎች አሁንም እንደሚያስፈልጉ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። በድርጅቱ ስር የሚገኙ የተለያዩ ተቋማትና አጋር አካላት በጋራ በሚያቀርቡት ገንዘብ፤ አስቸኳይ ድጋፍ ለሚፈልጉ ሶሪያውያን የመጠለያ፣ የጤና፣ የምግብ እንዲሁም ሌሎች አስቸኳይ ድጋፎች እንደሚደረጉ አብራርተዋል። ተመሳሳይ የድጋፍ ማዕቀፍ በቱርክ ድንበር ለሚገኙ ዜጎች እየተጠናቀቀ እንደሚገኝም ዋና ጸሓፊው ተናግረዋል።
ሽሬ ወአክሱም (የአልፎ ሂያጁ ማስታወሻ)
Jan 25, 2023 8224
ሽሬ ወአክሱም (የአልፎ ሂያጁ ማስታወሻ) አየለ ያረጋል (ኢዜአ) መዳረሻዬ ሽሬ እንዳስላሴ ነው። ለዘገባ ሥራ ከባህርዳር- ጎንደር- ደባርቅ- ሸሬ መንገድ ከሚዲያ ባልደረቦች ጋር እየተጓዝኩ ነው። የጥምቀት ሙሽራዋ ጎንደር እየተኳኳለች ነበር። ደባርቅ ከመድረሴ በፊት ዳባት ትገኛለች-የደጃች አያሌው ብሩ ቁርቁር ከተማ። ደጃች አያሌው ትውልዳቸው በጌምድር ጋይንት ቢሆንም ግዛታቸውና ኑሯቸው ዳባት ነበር። ሞገደኛው ደጃዝማች አያሌው ብሩ በጎንደር ማኅበረሰብ ዘንድ ዝናቸው የናኘ ነው። ደጃዝማች አያሌው በ20ኛው ክፍለ ዘመን መባቻ (ከልጅ ኢያሱ እስከ አጼ ኃይለሥላሴ ዘመነ-መንግሥት) ታሪካዊ ክንውኖች ጉልህ ተሳትፎ አላቸው። አንዷን ብቻ ልምዘዝ። ራስ ተፈሪ ‘ንጉሠ-ነገሥት አጼ ኃይለሥላሴ’ ደጃች አያሌው የቅርብ ዘመዳቸውን ራስ ጉግሳ ወሌ ብጡልን (የንግሥት ዘውዲቱን ባለቤት) ወግተው የጎንደር ግዛት ‘ራስ’ ተብለው ለመሾም ቃል ቢገባላቸውም፤ ተልዕኳቸውን ተወጥተው ቃሉ ባለመፈጸሙ ደጃዝማቹ ከአጼው ጋር መቀያየማቸው አልቀረም። በዚህም:- "አያሌው ሞኙ፣ ሰው አማኙ ሰው አማኙ፣ የአያል ጠመንጃ፣ ስሟን እንጃ ስሟን እንጃ…” በማለት የጎንደር አዝማሪ አዚሟል። ዛሬም ይህ ግጥም የብዙ ባህላዊ ዘፈኖች አዝማች ነው። ደጃች አያሌው ብሩ ደፋር ናቸው ይባላል። ከአጼ ኃይለሥላሴ ጋር ቢቀያየሙም በ1928 ዓ.ም ፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ ሲመጣ ቅድሚያ ለአገሬ ብለዋል። ‘የተደበቀው ማስታወሻ’ በተሰኘው የዶክተር ሀራልድ ናይስተሮም (ትርጉም ገበየሁ ተፈሪ እና ደሳለኝ አለሙ) መጽሐፍ እንደተጠቀሰው ደጃች አያሌው “ንጉሡ እንደኛ ሰው ናቸው። ኢትዮጵያ ግን የሁላችንም ናት" ብለው ጦራቸውን መርተው በሽሬ ግንባር ዘምተዋል። ጉዟችን ቀጥሏል። ደባትን እያለፍን ነው። ‘እንኳን ደህና መጡ፤ ወደ ጭና ታሪካዊቷ ሥፍራ’ የምትለዋን ታፔላን በስተግራ እያየን ወደ ደባርቅ ገሰገስን። የሰሜን ተራሮች የብርድ ወጨፎ ያረሰረሳትን ደባርቅን ከማለፋችን ሊማሊሞ ጠመዝማዛ ቁልቁለት ተቀበለን። አስፈሪ የሊማሊሞ መልክዓ ምድር የደጋው ሰሜን ውርጭ እና የተከዜ በርሃ ኬላ ነው። ባለቅኔው ጸጋዬ ገብረመድህን “የሰማይ የምድሩ ኬላ፣ የየብስ የጠፈሩ ዋልታ አይበገር የዐለት ጣራ፣ አይመክተው መከታ ሊማ-ሊሞ አድማስ ሰበሩ፣ በጎማ ፈለግ ይፈታ? በትሬንታ እግር ይረታ?…” ብሎ የመኪና መንገድ ተገንብቶበት በማየቱ ግርምቱን የተቀኘለትም ለዚህ ይመስላል። ከሊማሊሞ ቁልቁለት በኋላ አዲ-አርቃይ፣ ዛሪማ፣ ማይፀብሪ እና ሌሎች የጠለምት ወረዳ ከተማዎችን አልፈን፤ የዋልድባ ረባዳማ አካባቢዎችን ተሻግረን ተከዜ ወንዝ ደረስን። የዚህን መንገድ እና ተከዜ ወንዝን ሳስብ የሀዲስ ዓለማየሁ ትዝታ አስተከዘኝ። የፋሺስት ኢጣሊያ ወራሪ ጦር የወገንን ጦር ፊት ለፊት መቋቋም ሲሳነው በሰው ልጆች ላይ ተደርጎ የማያውቅ መርዝ በጅምላ የፈጀበት አሳዛኝ ታሪክ ነበር። በተከዜ ወንዝ ውሃን በመመረዝ የወገን ጦር ያለቀበት ሥፍራ ነው። የተከዜ ሸለቆ በኢትዮጵያዊያን ደምና አጥንት ዋጋ የተከፈለበት ነው። ሀዲስ ዓለማየሁ በአንድ ዕለት የተመለከቱትን እንዲህ ጽፈውታል። “የተከዜ ውሀ እመሻገሪያው ላይ ሰፊና ፀጥ ያለ ነው። ታዲያ ያ ሰፊ ውሀ፤ ገና ከሩቅ ሲያዩት ቀይ ቀለም በከባዱ የተበጠበጠ ይመስላል። “ምን ነገር ነው፤ ምን ጉድ ነው?” እየተባባልን ቀረብ ስንል መሻገሪያው በቁሙም በወርዱም ከዳር እስከ ዳር ሬሳ ሞልቶበት የዚያ ሬሳ ደምና ፈርስ ነው። የሰው ሬሳ፣ የፈረስ እና የበቅሎ ሬሳ፣ ያህያ ሬሳ፣ ያውሬ ሬሳ፥ ሬሳ ብቻ! እግር ከራስ ራስ ከእግር እየተመሰቃቀለ እየተደራረበ ሞልቶበት፥ የዚያ ሁሉ ሬሳ ደምና ፈርስ ነው”። ይሉናል። ቀጥለውም “በእውነቱ እንዲህ ያለውን መሳሪያ ምንም ጠላት ቢሆን በሰው ላይ ለማዋል የሚጨክን ሰው፥ ሰብዓዊ ስሜት የሌለው፣ አለት ድንጋይ የተፈጠረበት መሆን አለበት፤ እንዲህ ያለውን መሳሪያ በሰው ላይ ማዋል ሰብዓዊ ህሊና ሊሸከመው የማይችል እጅግ ከባድ መሆኑን ዓለም ሁሉ ያወቀውና ያወገዘው በመሆኑ የኢጣሊያ መንግሥት በኢትዮጵያ ላይ ከማድረጉ በቀር “ሌላ መንግሥት በሌላ አገር ላይ አደረገ’ ሲባል ተሰምቶ የሚያውቅ አይመስለኝም” ብለዋል። ከተከዜ ባህር ማዶ ጉዞዬ ያገኘኋት ሌላዋ ታሪካዊ ሥፍራ እንዳባጉና ናት። እንዳባጉና የወገን ጦር ትልቅ ገድል የፈጸመበት ነው። ጀግኖች አባቶቻችን የጠላት ታንክ ሳያስፈራቸው የጠላት ጅምላ ጨራሽ ቦምብ ጣይ አውሮፕላን ተቋቁመው ጠላትን ድባቅ የመቱበት፤ ወደ አክሱም እንዲያፈገፍግ ያደረጉበት ሥፍራ ነው። “የጠላት ቦምብ ጣይ አውሮፕላን በጦር ሜዳው ትንንሽ ቦምቦች አውቶማቲክ ጠመንጃ ይተኩስ ነበር። አቢሲኒያኖች ደግሞ ከጠላት ጋር ግብግብ ገጥመው ጉዳይም አልሰጡትም ነበር…” ይላል ዶክተር ሀራልድ ‘የተደበቀው ማስታወሻ’ በተሰኘ መጽሐፉ። ይህ አካባቢ በሀገር ፍቅር የነደዱ ኢትዮጵያዊያን ደም ያፈሰሱበት፣ አጥንት የከሰከሱበት፤ ለኢትዮጵያ መስዕዋትነት የከፈሉበት ነው። ይህ የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር ዋጋ የተከፈለበት ቀጣና ነው። ቀኑ ተገባዷል። ጉዟችን እንደቀጠለ ነው። እኔም የማሽላ ማሳዎችን ግራ ቀኝ እየተመለከትኩ ለዕለቱ መዳረሻችን ወደሆነችው ሽሬ ከተማ ገባን። ሽሬ በትግርኛ ‘ሽረ’ ሲሉት ይደመጣሉ። በእርግጥ ሽሬን ለመጀመሪያ ጊዜ መርገጤ ነው። ዕለቱም ጥር ሥላሴ ነው። ሽሬ በጥር ሥላሴ ትደምቃለች፤ ሙሉ ስሟም ሽረ እንዳስላሴ ነው። የሽሬ ሥላሴ ጠበል ሽሬ ደርሰን ማረፊያችንን ያዝን። ጊዜው በጣም አልመሸምና ከተማዋን በቀላሉ መቃኘት ይቻላል። ሽሬ ሰፊና ደማቅ የዞን ከተማ ናት። ከመካከላችን የአንደኛው ባለሙያ ቤተሰቦች ሽሬ ነበሩና አስጠሩን። ለሥላሴ ጠበል ግብዣ። ባል እና ሚስቱ ከልክ በላይ መስተንግዶ አደረጉልን። ‘ጠብ እርግፍ አድርገው አስተናገዱን’ ማለት ይቀላል። እንግዳ መቀበል ነባር ኢትዮጵያዊ እሴታችን ቢሆንም ጦርነት ውስጥ ለቆየ አካባቢ የተለየ መልክ ነበረው። እንግዳ አቀባበላቸው በእርግጥም የመሃል አገር ሰው የናፈቃቸው ይመስላል። የተትረፈረፈ እህልና ውሃ አቅርበው በ’ብሉልን፤ ጠጡልን’ ተማጽኗቸው የተነፋፈቀ ቤተ-ዘመድ ግብዣ አስመሰሉት። የሥላሴው ጠበል የሸሬ ጠላ ቀረበ። የሸሬ ጠላ ሳስታውስ ፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላ ታወሱኝ። የወቅቱ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምሀሩ ፕሮፌሰር ሽብሩ በዘመነ ደርግ በዕድገት በሕብረት ዘመቻ ተማሪዎቻቸውን ይዘው ሽሬ ዘምተው ነበር። በወቅቱ ታዲያ የሸሬ ጠላ ፍቅር ይዟቸው በየጊዜው ሲኮመኩሙ የተመለከቱ ሰዎች ‘ፕሮፌሰሩ ከጠፉ የሚገኙት ጠላ ቤት ነው’ ሲባሉ እንደነበር ‘ከጉሬ ማርያም እስከ አዲስ አበባ’ በተሰኘው ግለ ታሪካቸው አስፍረዋል። ከግብዣ መልስ ከማረፊያ ሆቴል ላይ ሆኜ ከተማዋን ስቃኛት ከጦርነት ድባቴ የተላቀቀች ይመስላል። የአመሻሽ ሕዝቡ እንቅስቃሴም ሆነ እስከ ሌሊቱ አጋማሽ የሚሰሙ የመዝናኛ ቤቶች ሙዚቃዎች የከተማዋን አሁናዊ መልክ የገለጠልኝ ነበር። ንጋት ላይ በቁርስና ቡና ሰዓታት ከሰዎች ጋር መስተጋብሬ ጀመረ። በጦርነት አዙሪት የከረመችው ሽሬና አካባቢው ኑሮ እጅጉን የከበደ ነበር። መልከ-ብዙ ማህበራዊ ቀውሶች አስተናግደዋል። አሁናዊ ምላሻቸው “ተመስገን፤ ያ ሁሉ አለፈ” የሚል ነው። ገበያው ተረጋግቷል፤ ማህበራዊ ኑሮ ተመልሷል። ድህረ-ሰላም ስምምነት ለሽሬ ነዋሪዎች ሁለንተናዊ እፎይታን አንብሯል። ከቀናት በኋላ በአክሱም የታዘብኩትም እንዲህ ነው። ኑሮን ያቀለለው የተቋማት አገልግሎት ጅማሮ በመጀመሪያ ዘገባ ስራዬ መሰረተ ልማትን አገልግሎት ቃኘሁ። ባንክ፣ ቴሌ፣ ሆስፒታል… መሰሎቹን። ተጠቃሚዎችንም፣ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ስራ ሃላፊዎችንም አነጋገርሁ። ከሰላም ስምምነቱ ማግስት ጀመሮ ተቋማቱ ወደስራ መመለሳቸው ከሁለንተናዊ ችግር እንደታደጋቸው ያነሳሉ። በትራንስፖርት እየተንቀሳቀሱ፣ በኤሌክተሪክ ስራዎቻቸውን እየከወኑ ነው። ለሁለት ዓመታት የተቋረጠው አገልግሎት አቅርቦት እና የአገልግሎት ፈላጊዎች ፍላጎት ግን አሁንም ሙሉ በሙሉ ተመጣጣኝ እንዳልሆነ የተጠቃሚዎችም፤ የአገልግሎት ሰጭዎችም ሀሳብ ነው። በሽሬ ስሁል ሆስፒታል የተመለከትኳቸው፤ ያነጋገርኳቸው፤ ከታዳጊዎች እስከ አዛውንት ዕድሜ ያሉ ህሙማን የሰላም አየር ማግኘታቸው የሕይወታቸው ዑደት እንዲቀጥል አድርጓል። ድንገተኛም ሆነ ነባር ህመም ያለባቸው ሰዎች በነጻ እየታከሙ ነው ያገኘኋቸው። ሰላም ከሌለ መታከም ቀርቶ በቅጡ ማስታመም፤ በወጉ መቀበርም እንደማይቻል ገልጸውልናል። የጤና፣ የባንክና የቴሌኮም አገልግሎት የግብዓት ክፍተቶች የማሟላት ሰራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም በፌዴራል ደረጃ በየተቋማቱ የተመደቡ አስተባባሪዎች አረጋግጠውልኛል። የጸጥታ አካሉና የህብረተሰቡ ትብብርም የሚያስቀና እንደሆነ ግለሰቦችም፤ የጸጥታ አካላትም ነግረውኛል። አክሱም ጺዮን ማርያም፣ ሽሬ ስላሴ ንግስ፣ የጥምቀት በዓላት ከሶስት ዓመታት በኋላ በአደባባይ ታቦት ወጥቶ ተከብሯል። የፌዴራል ፖሊስ ተወካዮችም ይህንኑ ነው ያረጋገጡልኝ። የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከከተማ ነዋሪዎች ጋር ያላቸው ግንኙነት ቤተሰባዊ የሆኑ ይመስላል። እንቅስቃሴያቸውም የሰላማዊ ቀጠና መልክ ያለው ነው፤ ዩኒፎርም ከመልበሳቸው በስተቀር ጀሌያቸውን ይንቀሳቀሳሉ። ይህ ደግሞ መተማመን ከመፍጠር ባለፈ ጦርነት ውስጥ ለቆየ ማህበረሰብ ከስነ ልቦና ጫና እንዲላቀቅ አይነተኛ ሚና እንደላው ይሰማኛል። ኢ-መደበኛ የሽሬና አክሱም ወጎች ያረፍኩበት ሆቴል ባለቤት ‘አደይ’ ተግባቢ ናቸው። ደግ እናት ይመስላሉ። ከገባን ጀምሮ ‘ጠላ ተጎንጩ፤ ቡና ጠጡ’ ጭንቃቸው ነው። ሁለት ቀን ቡና አስፈልተውልናል፤ ጠላ አቅርበው ዘክረውናል። ይህ ሁሉ ሲሆንም ለከተማው እንግዳ መሆናችንን እንጂ ስለሙያችንም ሆነ ስለሌላ ማንነታችን አያውቁም ነበር። ብዙ መጨዋወትና ውሎ አዳር በኋላ ነው ጋዜጠኛ ስለመሆናችን ያወቁት። አደይ ተጨዋች ናቸው። አማርኛ ያዝ ቢያደርጋቸውም ጨዋታቸው ‘ኩርሽም’ ነው- ተሰምቶ የማይሰለች። በአጋጣሚ ‘ሰለክላካ’ ስለምትባለዋ ታሪካዊ ሥፍራ ጠይቄያቸው እያወጋን ነበር። ‘እንደእናንተ ወጣቶች ሳለን ‘ሰለክላካን ያላዬ ሸዋን ያመሰግናል’ ይባል ነበር። ታዲያ አንድ የሸዋ ሰው መጣና ሰለክላካን አየና ‘በቃ ይቺ ናት’ ሰለክላካ’ ብሎ ተገረመ” ብለው አሳቁን። (የፍቅር እስከ መቃብር መሪ ገጸ-ባህሪው ‘በዛብህ’ ወደ ዲማ ጊዮርጊስ ሄዶ ‘የዲማ መልኳ እና ዝናዋ’ ተጣርሶበት እንደተገረመበት ቅጽበት መሆኑ ነው)። አደይ የተጀመረው ሰላም ፍጹም ምሉዕ ሆኖ ወደ ቀደመ ኢትዮጵያዊ መልካችን የምንመለስበት ጊዜ እንዲመጣ ይሻሉ። ከጦር-ነት ወደ ሰላም-ነት! ቆንጂዬዋ ፊዮሪ የኮሌጅ ተማሪ ነበረች። በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ጀምሮ በኋላም በጦርነት ሳቢያ ትምህርቷን ካቆመች ሦስት ዓመታት ሆኗታል። ጦርነቱ ከቆመ በኋላ የጀበና ቡና ጀምራለች። ደንበኞቿ ሰብሰብ ብለን እንቀመጣለን። ፊዮሪ ከስኒ ማቅረቢያዋ ላይ አነስተኛ ጀበናዋን፤ የሚያማምሩ ስኒዎቿን እና መዓዛው ከሚያውድ የዕጣን ማጨሻዋ ጋር ሰድራ ይዛ ትቀርባለች። ከመካከላችን ካለው ጠረጴዛ ላይ ታስቀምጥና እርሷም ወንበር ይዛ ከመካከላችን ትቀመጣለች። ቡናው እስኪሰክን ጨዋታዋን ታስኮመኩመናለች። ቡናው ከሰከነ በኋላ ቡናዋን ቀድታ ለእያንዳንዳችን በእጃችን እያነሳች ትሰጣለች። በሽሬ ቡና የሚቀርበው በዚህ መልክ ነው። ለፊዮሪ እና መሰሎቿ ጦርነቱ ክፉ ጠባሳ መጣሉ፤ ተስፋቸው ላይ መጥፎ አሻራ ማስቀመጡን ታነሳለች። አሁን ግን ብሩህ ተስፋ ሰንቃለች። ስለነገዋም “ሰላሙ ይዝለቅልን፤ ትምህርቴን ለመቀጠል እመኛለሁ” ትላለች። አክሱም ከሽሬ በስተሰሜን 60 ኪሎ ሜትር ይርቃል። ከሽሬ አክሱም ስንንቀሳቀስ ከጥምቀት ዕለት በስተቀር ገበሬው የግብርና ሥራዎቹን እየከወነ ነበር። አርሶ አደሩ ያርሳል፤ መስኖውን ያለማል። የተዘራውን ውሃ ያጠጣል። የበቀለ ቡቃያውን ይኮተኩታል። ከጦርነት ወደ ልማት መዞሩን ዐይኔ ታዝቧል። በጥምቀት ዋዜማ፤ የከተራ በዓል ዕለት ሁለት ጎራማይሌ የረፋድ ትዕይንቶችን ላንሳ። ከአክሱም ከተማ ወደ አድዋ እና ሽሬ መገንጠያ አካባቢ ሰፊ የቀንድ ከብት ገበያ ነበር። እውነተኛ የዓመት በዓል ገበያ መልክ ያለው ትዕይንት ነበር። በተለይም የፍየል ዋጋ በተመጣጣኝ ዋጋ እየተገበያዩ እንደነበር ሰምቻለሁ። ታሪካዊቷን አክሱም ከተማ ለመጨረሻ ጊዜ የረገጥኳት/የተሳለምኳት ከአራት ዓመት በፊት በ2011 ዓ.ም ይመስለኛል። ከገበያው ቀጥሎ በታቦተ-ጽዮን መገኛዋ ርዕሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ደጅ፣ በጥንታዊያኑ የአክሱም ሐውልት መገኛ አደባባይ ነበር። ከጽዮን በስተምዕራብ በአርባቱ እንሰሳ በኩል፤ በቅዱስ ያሬድ ዋርካ… አድርጌ በጽዮን ዋናው በር ደረስኩ። ማራኪ የአክሱም የኮብልስቶን መንገዶች ኦና ናቸው። የወትሮው ግርግር ናፍቋቸዋል። ከጽዮን ቅጥር ግቢ በዋናው በር በስተውጭ አነስተኛ እና ብቸኛ ዋንዛ በኮብልስቶን መሃል ነበረች። ዛሬም ለምልማ አለች። በዚህ አካባቢ ድሮ የነጭ ጎብኚ ጋጋታ፣ የጽዮን ደጅ ጠኚ ምዕመን… የተጨናነቀ ነበር። እንደ ድሮው የፎቶ አንሺ ግርግር፣ የአክሱም መስቀል ቀርጸው የሚሸጡ ወጣቶች ጫጫታ የለም። ይልቁንም እርጥባን የሚሹ አቅመ ደካሞችና ህፃናት ነበሩ። ጦርነት የሥፍራዋን መልክ አጠይሞታል። ያም ሆኖ ከተማዋ የንግድ እንቅስቃሴ ሙሉ በኩሉሄ ባይባልም ወደነበረበት እየተመለሰ ነው። የግልም ሆነ የመንግሥት ባንኰች ሥራ ከጀመሩ ሰነባብተዋል። ከአክሱም ሐውልት ወደ ሌላ ሰፈር አቀናሁ። ትርሐስ ገና ታዳጊ ልጅ ነች። ጠይም፤ ስርጉድ፣ ሳቂታና ተረበኛ አይነት ልጅ ነች። እንደ ሽሬዋ ፊዮሪ መንገድ ዳር የጀበና ቡና እየሰራች ነው። ከሩቅ የመጣን እንግዶች መሆናችንን ስታውቅ፤ ደስታዋ ከገጿ ይነበብ ነበር። ያለፉ ጊዜያትን ሰቆቃ አጫወተችን። ስለቀጣይ ዕጣ ፈንታዋ እና ዕቅዷ ስታወራ ትቆይና “የሰው ልጅ ግን በጣም ከሃዲ ነው። ከወራት በፊትኮ ስለቢዝነስ አላስብም ነበር። መቼ እሞታለሁ እንጂ” ብላ ራሷን ትወቅሳለች። ወደ ሰማይ አንጋጣ ፈጣሪዋን ታመሰግናለች። ጦርነት ተራውንም ሕዝብ ለመልከ-ብዙ ቀውስ ዳርጎት እንደቆየ ታነሳለች። ዛሬ ሁሉ አልፎ ሰላም መውረዱ ለመጨዋወት መብቃቷ ለእርሷ ትልቅ ብሥራት ነው። ይህ ለትርሐስ ብቻ ሳይሆን ለመላው አክሱማዊያን መሆኑ እሙን ነው። አክሱም ከተማ በመከላከያ ሠራዊት ቁጥጥር ሥር ከዋለችበት ጊዜ ጀምሮ በከተማዋ በሻለቃ አዛዥነት የተሰማራ የፌደራል ፖሊስ አባልም ያጋጠመውን አሳዛኝ ገጠመኞች አጫውቶኛል። ጦርነቱ ቢራዘም ኖሮ በተራው ሕዝብ ላይ ምን ያህል የከፋ ጉዳት ይደርስ እንደነበር በአሳዛኝ ሁኔታ ገልጾልኛል። አክሱሞች ያን ሁሉ አልፈው ሰላም አየር ነፍሶ፣ ከስጋት ቆፈን ተላቀው ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ ተመልሰዋል። የዛሬ ሳምንት ሰርክ(11 ሰዓት) ላይ አክሱም የከተራ በዓል በድምቀት አክብራለች። ታቦተ-ጽዮን ወደ ባህረ- ጥምቀቱ ስትወርድ፤ ወግና ሥርዓቱ ተጠብቆ፣ ሕዝቡ በሀበሻ ነጫጭ አልባሳት፣ ካህናት በልብሰ ተክህኖ ደምቀው … እየተከወነ ነበር። አንዲት እናት ለአማርኛ ተናጋሪ በቀረበ አነጋገር እያለቀሱ ታቦት እየሸኙ ነው። ትኩር ብዬ ሳያቸውም ዕንባቸው ዱብ ዱብ ይላል። “ከዚያ ሁሉ መከራ አልፎ ለዚህ በቃን፤ ተመስገን” እያሉ እልልታውን ያቀልጡታል። በደስታ እያነቡ ነበር። ይህ ስሜት የብዙኃኑ አክሱማዊያን እናቶች እንደሆነ መገመት ቀላል ነው። አክሱም በኮቪድ እና በኋላም በጦርነቱ ምክንያት ባህረ-ምቀት ታቦት ወጥቶ ሲከበር ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር። ከወትሮው በተለየ ድምቀትና ውበት በሰላምና በደስታ፤ በአደባባይ እልልታና ሆታ በማክበራቸው ልዩ ስሜት ፈጥሮባቸዋልና! እናም በአክሱም የከተራ ሆነ የበዓለ-ጥምቀት ክብረ-በዓላት በሰላም ስምምነቱ ማግስት በድምቀት ተከውኖ አለፈ። የሃይማኖት አባቶቹም ሆኑ ምዕመኑ በሰጡት ቃለ መጠይቅም የዘንድሮው ክብረ-በዓል ካለፉት ዓመታት ነባራዊ ሁኔታ ጋር እያነጻጸሩ፤ ትልቅ ብሥራትና መልክ እንዳለው ገልጸዋል። ሰላም እንዲጸና፤ ነባር ኢትዮጵያዊ አንድነትና መተባበር እንዲመለስ ጽኑ መሻታቸውን ነግረውናል። በበጎ ቀን የማውቃትን አክሱም፤ ከረዥም ጊዜ በኋላ አሁናዊ መልኳን ታዝቤ፤ የነገ ትዝታ ሰንቄ ተመለስኩ!! ሰላም ለኢትዮጵያ!!
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 17014
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 15735
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 12844
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 9728
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
መጣጥፍ
የአፍሪካ ዋንጫን በመሀል ዳኝነት  የመራችው ብቸኛዋ ሴት ዳኛ
Jan 28, 2024 1218
  በይስሐቅ ቀለመወርቅ እንደ መነሻ፡- በእግር ኳስ ውድድሮች የመሃል ዳኝነቱን ቦታ በብዛት የሚይዙት ወንዶች ሲሆኑ፤ አሁን ላይ አልፎ አልፎ ሴቶች ትልልቅ የእግር ኳስ ጨዋታዎችን ሲዳኙ አስተውለናል። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2022 በኳታር አስተናጋጅነት በተከናወነው 22ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ፤ ፈረንሳዊቷ ስቴፋኒ ፍራፓርት፤ ኮስታሪካ እና ጀርመን ያደረጉትን ጨዋታ በመሀል ዳኛነት መርታለች። በዚህም በወንዶች ዓለም ዋንጫ ታሪክ በመሀል ዳኝነት የእግር ኳስ ጨዋታን የመራች የመጀመሪያዋ ሴት በመሆን ታሪክ ሰርታለች ። ዘንድሮ ደግሞ በኮትዲቯር አስተናጋጅነት እየተከናወነ በሚገኘው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ሞሮኳዊቷ ቦችራ ካርቡቢ፤ ውድድሩን እንዲመሩ ከተመረጡት 32 የመሀል ዳኞች መካከል ብቸኛዋ ሴት ናት። በዚህም በውድድሩ በጊኒ ቢሳውና በናይጄሪያ መካከል የተከናወነውን ሦስተኛ የምድብ ጨዋታ፤ በመሀል ዳኝት በመምራት፤ ታሪክ ጽፋለች። የሞሮኮ ዓለም አቀፍ ማኅበር የእግር ኳስ ዳኛ የሆነችው ቦችራ ካርቡቢ፤ በወንዶችም ሆነ በሴቶች አህጉራዊ የእግር ኳስ ውድድሮች ላይ በርካታ የመጨረሻ ምዕራፍ የእግር ኳስ ጨዋታዎችን ዳኝታለች። 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫን ብቸኛ የሴት ዳኛ ሆና የመራችው ቦችራ ካርቡቢ ማናት? ቦችራ ካርቡቢ በሞሮኮ ሰሜናዊ ክፍል በምትገኘው "ታዛ" ከተማ፤ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1987 ተወለደች። የዘር ግንዷ በሰሜን ምሥራቅ ሞሮኮ ከሚገኙት ሪፊያን ከሚባሉት የበርበር ጎሳ ዝርያ ካላቸው ሕዝቦች የሚመዘዝ ሲሆን፤ ለቤተሰቦቿ አምስተኛና የመጨረሻ ልጅ ነች። ገና በልጅነቷ ለእግር ኳስ ፍቅር ያደረባት ቦችራ ካርቡቢ፤ ኳስ መጫወት የጀመረችው በአንድ ትንሽ የወጣቶች ቡድን ውስጥ ነበር። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2001 በተወለደችበት ከተማ "ታዛ"፤ ለወንዶችና ለሴቶች የእግር ኳስ ዳኝነት ሥልጠና የሚሰጥበት ትምህርት ቤት ተከፈተ ። ይኼ ትምህርት ቤት ቀልቧን የሳበው ቦችራ፤ ሥልጠናውን መውሰድ ጀመረች። "እግር ኳስን እወዳለሁ፤ ራሴንም ላስተምር ፈለኩ።ለምን አላደርገውም ብዬ ፍላጎቴን በመከተል የእግር ኳስ ጨዋታን ደንብ መማር ጀመርኩ" ስትል የእግር ኳስ ዳኝነት ትምህርት የጀመረችበትን ጊዜ ታስታውሳለች። ይኼ ድርጊቷ ካልተዋጠላቸውና፤ በበጎ ጎኑ ካልተመለከቱት ውስጥ ደግሞ፤ ወንድሞቿ ቀዳሚዎች ነበሩ። "በምኖርበት ከተማ አንድ ሴት አጭር ቁምጣ ለብሳ ከወንዶች ጋር ሥልጠና ስትወስድ መታየቷ፤ እንደ አሳፋሪ ድርጊት ስለሚታይ መነጋገሪያ ሆኜ ነበር" ትላለች። የቦችራ ካርቡቢ የዳኝነት ጉዞ እንደ አውሮፓውያን ቆጣጠር በ2007፤ ሞሮኮ ብሔራዊ የሴቶች እግር ኳስ ሻምፒዮናን ጀመረች። ይህ መሆኑ ቡችራ ካርቡቢ ብሔራዊ ዳኛ እንድትሆን ዕድል የፈጠረላት ሲሆን፤ መኖሪያዋንም ከትውልድ ሥፍራዋ "ታዛ" ወደ ሞሮኮ ሌላኛዋ ከተማ "ሚከንስ" እንድትቀይር አደረጋት። "ይህን ዕድል ማግኘቴ ቤተሰቦቼ እንዲረዱኝና ሙያዊ ለሆነ ጉዳይ እንደምሄድ እንዲያምኑ አድርጓቸዋል" በማለት የዳኝነት ሙያዋን በመጨረሻ እንደተቀበሉት ታስረዳለች። በሚከንስ ከተማ በእግር ኳስ ዳኝነት ሥልጠና ላይ እያለች፤ አንድ ቀን አባቷ መጥቶ እንደተመለከታትና፤ ወንድሞቿ ምርጫዋን ሊያከብሩላት እንደሚገባ እንደነገራቸውም ገልፃለች። የ19 ዓመት ወጣት እያለችም፤ በሞሮኮ የሴቶች አንደኛ እና ሁለተኛ የሊግ ውድድር በመዳኘት፤ የዳኝነት ሥራዋን አንድ ብላ ጀመረች። ይህ ከሆነ ከ10 ዓመት በኋላ፤ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2016 ደግሞ፤ ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ዳኛ በመሆን ራሷን ወደ ሌላ ምዕራፍ አሸጋገረች። ከሁለት ዓመት በኋላም በ2018 በጋና አስተናጋጅነት በተከናወነው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ፤ በዛምቢያና በኢኳቶሪያል ጊኒ መካከል የተደረገውን ጨዋታ በመሀል ዳኝነት አጫወተች። ይህም በአህጉራዊ የውድድር መድረክ ለመጀመሪያ ጊዜ በመሀል ዳኝነት ያጫወተችው ጨዋታ ሆኖ ተመዘገበላት። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2020፤ "ቦቶላ" እየተባለ በሚጠራው በሞሮኮ የወንዶች ከፍተኛ የሊግ ውድድር ላይ በመሀል ዳኝነት በመዳኘት፤ የመጀመሪያዋ ሴት ሆነች ። ከአንድ ዓመት በኋላም በካሜሮን አስተናጋጅነት በተከናወነው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ፤ ሴኔጋልና ግብፅ ባደረጉት የፍፃሜ ጨዋታ የቫር ዳኛ (video assistant referee) በመሆን ሰርታለች። ከዛሬ ሁለት ዓመት በፊትም የሞሮኮ የንጉሱ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታን በመዳኘትም ቀዳሚዋ ሴት ናት። አሁን ላይ እየተከናወነ ባለው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ወድድርም፤ በጊኒ ቢሳውና በናይጄሪያ መካከል የተከናወነውን ሦስተኛ የምድብ ጨዋታ በመሀል ዳኝት በመምራት፤ የመጀመሪያዋ ሰሜን አፍሪካዊት የአረብ ሴት ሆናለች። ቡችራ ካርቡቢ ከእግር ኳስ ዳኝነት ሥራዋ በተጨማሪ፤ የፖሊስ ኦፊሰር በመሆን ሀገሯን እያገለገለች ትገኛለች።      
ዕልፍ ውበት ከኮይሻ ዕልፍኝ
Dec 23, 2023 2194
ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ፣ የቱባ ውበቶች መገለጫ ናት። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንዳሉትም ፈጣሪ በሰጣት የተፈጥሮ ሀብት የታደለች ናት በተለይም በተራሮች፣ በሸለቆዎች፣ በወንዞችና በሐይቆች፣ የተሞላች ሀገር ናት። በአንድ በኩል ተፈጥሮ በብዙ ያደላት፣ ልጆቿም በትጋታቸው በየዘመናቱ ያደመቋት ብትሆንም በሌላ በኩል በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ፈተናዎች እንዲሁም በመሰረተ ልማት መጓደል ፀጋዎቿን በአግባቡ ሳታስተዋውቅና ሳትጠቀምበት ቆይታለች። ከአምስት ዓመታት በፊት የመጣውን አገራዊ ለውጥ ተከትሎ መንግስት ለብዝሃ ኢኮኖሚ በሰጠው ትኩረት ቱሪዝም አንዱ የኢኮኖሚ ምሰሶ ሆኖ ብቅ ማለቱን ተከትሎ ጸጋዎቿ እየተገለጡ ይገኛሉ። በዚህም የአገሪቱን የቱሪዝም አለኝታዎች በአግባቡ መለየትና ማልማት፣ የቱሪዝም መዳረሻዎችን መሠረተ-ልማት ማጠናከርና ተጨማሪ አዳዲስ መሠረተ-ልማቶችን መገንባት የመንግስት የትኩረት አቅጣጫዎች ሆነዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት በገበታ ለሸገርና በገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች ውጤታማ የቱሪዝም ልማት ስራዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ዕውን ሆነዋል። በገበታ ለሸገር ከተገነቡና ለአገልግሎት ከበቁ የቱሪዝም መዳረሻዎች መካከል የእንጦጦ፣ የአንድነትና የወዳጅነት ፓርኮች ይጠቀሳሉ። በወንዝ ዳርቻ ልማትም ሰፋፊ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ። በገበታ ለሀገርም ጎርጎራ፣ ወንጪ-ደንዲና ኮይሻ ፕሮጀክቶች ተጠቃሽ ናቸው። የኢትዮጵያን ውብ የተፈጥሮ ብልጽግና ሰዎች አይተው ይረኩ ዘንድ የኮይሻ ፕሮጀክት ውብ ሆኖ መሰናዳቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከሰሞኑ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አጋርተዋል።   የኮይሻ የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት የብዝኃ-ቱሪዝም ባለቤት ለሆነችው ኢትዮጵያ ተጨማሪ አቅም የሚፈጥር ነው። የኮይሻ ኢኮ-ቱሪዝም በውስጡ ከያዛቸው በርካታ ሀብቶች መካከል የጨበራ ጩርጩራ ፓርክ አንዱ ሲሆን በማራኪ ጥብቅ ደን የተሸፈነ ብሔራዊ ፓርክ ነው። በገበታ ለአገር በኮይሻ ፕሮጀክት ውስጥ ከሚለሙ የቱሪዝም መስህቦች አንዱ የሆነው ጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክ ለአረንጓዴ ቱሪዝም ሁነኛ ማሳያ የሚሆን የሀገሪቱ ታላቅ የመስህብ ስፍራ ነው። የመካከለኛው ኦሞ ሸለቆ አረንጓዴያማው ጌጥ ጨበራ ጩርጩራ ወደ 50 የሚጠጉ ከትናንሽ እስከ ትላልቅ ወንዞች መነሻ ሲሆን በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙትን ጨምሮ አያሌ የዕፅዋት ብዝኃ ሕይወትን የለበሰ ተፈጥሯዊ ፀጋ ነው። የጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክ ዝርያው እየተመናመነ የመጣው የአፍሪካ የዝሆን ዝርያን ጨምሮ እንደ ጎሽ፣ ዲፋርሳ፣ ከርከሮ፣ ሳላ እና አጋዘን ያሉ የዱር እንስሳት የሚገኙበት ነው፡፡ ፓርኩ በደን ሽፋኑ ይበልጥ ጎልቶ ስሙ የሚነሳ ሲሆን፤ በፓርኩ ውስጥ የሚያቋርጡ በርካታ ወንዞችና አምስት ሃይቆችም ይገኛሉ። በጉያው ካቀፋቸው ፏፏቴዎች መካከል ባርቦ ፏፏቴ አንዱ ሲሆን የፏፏቴው ድምጽ ለፓርኩ ተጨማሪ ድምቀት ሆኖታል። የገበታ ለአገር ፕሮጀክት አካል በሆነው የኮይሻ ፕሮጀክት ፓርኩን ለመጎብኘት የሚያስችል መሰረተ ልማት በማሟላት የአካባቢውን የቱሪዝም ተጠቃሚነት ለማሳደግ የተለያዩ ስራዎች ተከናውነዋል። የመሰረተ ልማት ግንባታዎቹ የፓርኩን ተፈጥሮ ሳይረብሽ ከፓርኩ ውጪ የሚከናወን ሲሆን ይህም ቱሪስቶች ፓርኩን በቀላሉ እንዲጎበኙት የሚያስችል ነው።   ሌላው የኮይሻ ውብት የግልገል ጊቤ ሶስት ግድብ የፈጠረውን ሰው ሰራሽ ሀይቅ ተንተርሶ የሚገኘው ሀላላ ኬላ ነው። ሀላላ ኬላ በዳውሮ ዞን በኮረብታዎች፣ ሰንሰለታማ ተራራዎችና በግልገል ጊቤ 3 የኃይል ማመንጫ ግድብ የተከበበ ስፍራ ነው። በዳውሮኛ ቋንቋ "ኬላ" ማለት የድንጋይ ካብ ማለት ሲሆን ሃላላ ኬላ በ1532 ዓ.ም ተጀምሮ በ10 የዳውሮ ነገስታት ለ200 ዓመታት የተገነባ ነው። ስያሜውንም በመጨረሻው ንጉስ ሃላላ ስም ያገኘ ሲሆን ቅርሱ 500 ዓመታትን አስቆጥሯል። ስፍራው ፀጥታ የሰፈነበት፣ የተረጋጋና መንፈስን የሚያድስ እንዲሁም ታሪክ፣ ባህልና መልከዐ ምድርን ማድነቅ ለሚፈልጉ ማረፊያና ማራኪ የቱሪስት መስህብ እንደሆነ ይነገርለታል። ሀላላ ኬላ ሪዞርት የኢትዮጵያን የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ለማጎልበትና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ መዳረሻ ለመክፈት በማሰብ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አማካኝነት በ2013 ዓ.ም ይፋ በሆነው የገበታ ለአገር ፕሮጀክት ስር ከሚገኙ የኮይሻ ቅርንጫፍ ስራዎች መካከል አንዱ ነው። በርካታ የተፈጥሮ በረከቶች በአንድ ቦታ የሚገኙበት ሀላላ ኬላ ጎብኚዎች የሚመኙት አይነት አካባቢ፤ የሚውዱት አይነት የተረጋጋ የአየር ጠባይ ያለው ነው፤ የሀላላ ኬላ ሪዞርት። ሪዞርቱ የተገነባው ኢትዮጵያ ያሏትን ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ሀብቶች በማጎልበት ማራኪነታቸውንና መስህብነታቸውን በመጨመር እንዲሁም ተደራሽነታቸውን በማስፋት ለእይታ እንዲበቁ ለማድረግ ነው። በተጨማሪም ወደ ስፍራው የሚያቀኑ ጎብኚዎች በእንቅስቃሴያቸው ሁሉ እንዲደሰቱና አዲስ ቆይታ እንዲኖራቸው ጥሩ እይታን ፈጥሮ አካባቢውን በሚገባ የሚያስተዋወቅ ነው። የሪዞርቱ ንድፈ ሀሳብ የሃላላ ኬላ ግንብና የአካባቢውን ሕዝብ ታሪክ እንዲሁም የቱሪዝም ሀብትን ከማክበርና ከመጠበቅ ጋር የተቆራኘ ነው። ቱኩል በመባል በአካባቢው ነዋሪ የሚታወቀውን ባህላዊ የስነ ሕንጻ አሰራር ጥበብ በመከተል የቤቱ ውስጣዊ ክፍል አየር በደንብ እንዲያገኝ፣ ጣሪያቸው ከፍ ብሎ ተሰርቷል። የሃላላ ኬላ ሪዞርት በሚያዚያ ወር 2015 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን ጨምሮ የተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ባለሀብቶችና እንግዶች በተገኙበት መመረቁ የሚታወስ ነው። የኮይሻ እልፍኝ ሌላው ውበት የሆነው የልማት ስራ የኮይሻ የሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ነው። የፕሮጀክቱ የግንባታ ሂደት 62 በመቶ መድረሱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ገልጸዋል፡፡ "በቅርብ ርቀት በጨበራ ጨርጩራ ብሔራዊ ፓርክ የሚገኘውን የጨበራ የዝሆን ዳና ሎጅን በምንመርቅበት በአሁኑ ወቅት የኮይሻ ግድብ ለአካባቢው የቱሪዝም ዕድል ተጨማሪ አስተዋፅኦ ያደርጋል" በማለትም በኮይሻ እልፍኝ ዕልፍ ውበት ዕልፍ ዕድል መኖሩን ተናግረዋል፡፡  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም