የአፍሪካ የታዳጊ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሶስተኛ ቀን ውሎ - ኢዜአ አማርኛ
የአፍሪካ የታዳጊ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሶስተኛ ቀን ውሎ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 11/2017 (ኢዜአ)፦ ናይጄሪያ አቢኩታ እየተካሄደ ያለው የአፍሪካ ከ20 እና 18 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚሳተፉባቸው አምስት የፍጻሜ ውድድሮች ዛሬ ይካሄዳሉ።
ከቀኑ 6 ሰዓት ከ55 በ400 ሜትር ሴቶች ከ18 ዓመት በታች ፍፃሜ ገነት አየለ እና ባንቻአለም ቢክስ ይሳተፋሉ።
ምሽት 12 ሰዓት ከ55 በሚደረገው የ100 ሜትር መሰናክል ሴት ከ20 ዓመት በታች ፍፃሜ ትዕግስት ባንቲይደሩ ኢትዮጵያን ወክላ ትወዳደራለች።
በ400 ሜትር ሴቶች ከ20 ዓመት በታች ፍፃሜ ከምሽቱ 1 ሰዓት 30 ላይ የሚካሄድ ሲሆን አጃይባ አሊዬ ትሳተፋለች።
ከምሽቱ 2 ሰዓት ከ20 ላይ በ3000 ሜትር ወንዶች ከ18 ዓመት በታች ፍፃሜ አብርሃም ገብረእግዚአብሔር የሚወዳደር ይሆናል።
ምሽት 2 ሰዓት ከ40 ላይ በሚደረገው የ4x100 ሜትር ሴት ከ20 ዓመት በታች ፍፃሜ ሰላማዊት ኮከብ፣ ደሚቱ ሽፈራሁ፣ አጃይባ አሊዬ እና ትግስት ባንቲይደሩ ተሳታፊ ናቸው።
በውድድሩ ኢትዮጵያ የመጀመሪያ የወርቅ ሜዳልያ እየጠበቀች ነው።
ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው እስከ አሁን ሶስት የብር እና ሶስት የነሐስ በድምሩ ስድስት ሜዳሊያዎች ማግኘቷን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመለክታል።