ናይጄሪያ ለግማሽ ፍጻሜ አለፈች

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 11/2017(ኢዜአ)፦ በ13ኛው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ናይጄሪያ ዛምቢያን 5 ለ 0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት  አሸንፋለች።

ማምሻውን በላርቢ ዛውሊ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኦሲናቺ ኦሃሌ፣ ኢስተር ኦኮሮንኮ፣ ቺንዌዱ ልሄዙ፣ ኦሉዋቶሲን ዴምሂን እና ፎላሼድ ጃሚሉሲ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

በጨዋታ ናይጄሪያ በተጋጣሚዋ ላይ ከፍተኛ ብልጫ ወስዳ ተጫውታለች።

ውጤቱን ተከትሎ የዘጠኝ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊዋ ናይጄሪያ ግማሽ ፍጻሜውን የተቀላቀለች የመጀመሪያዋ ሀገር ሆናለች።

በግማሽ ፍጻሜው ከደቡብ አፍሪካ እና ሴኔጋል አሸናፊ ጋር ትጫወታለች።

በሁለተኛው የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ አዘጋጇ ሞሮኮ እና ማሊ ምሽት 4 ሰዓት ላይ በፕሪንስ ሙላይ አብደላ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም