ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዝ ለአዲሱ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
Sep 11, 2026 69
አዲስ አበባ፤መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦ የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዝ ለ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአውስትራሊያ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት መግለጫ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ በአውስትራሊያ ማህበራዊ እና ባህላዊ ሕይወት ውስጥ ያለውን ትልቅ ስፍራ አንስተዋል። በዓሉ ከደማቅ ባህላዊ ትውፊቶቹ ባሻገር፣ የኢትዮጵያን ጥልቅ ታሪክና ማንነት አጉልቶ የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል። በዓሉ ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች ተሰባስበው የቆዩ እሴቶቻቸውን ይበልጥ የሚያጸኑበት፣ እንዲሁም የጋራ ትስስራቸውን የሚያጠናክሩበት ልዩ ወቅት መሆኑንም ጠቁመዋል። ኢትዮጵያውያን በአውስትራሊያ መሬት ላይ ሆነው የትውልድ ግንዳቸውን ጠብቀው ማክበራቸው ለአውስትራሊያ ብዝሃነት ትልቅ እሴት እንደሆነ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ይህ ድርጊት ማህበረሰቡ በአውስትራሊያ ታሪክ ውስጥ እየጻፈው ላለው አዲስ ምዕራፍ ትልቅ ማሳያ መሆኑን አንስተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዝ አዲሱ ዓመት ለኢትዮጵያውያን ሁሉ የሰላም፣ የብልጽግና እና የደስታ እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል።
በጎነት የሰብዓዊ ክብር መሠረት፤ የመደመር መንግሥት የሰው ተኮር ልማት የተስፋ አድማስ
Sep 11, 2026 108
በጎነት ከኢትዮጵያውያን የዕለት ተዕለት ኑሮና እንቅስቃሴ ጋር በጥብቅ የተሳሰረ፣ ከራስ ቀንሶ ለሌሎች መድረስ የሚገለጽበት ከፍ ያለ ሰብዓዊ እሴት ነው። በጎነት የግለሰብን ችግር ብቻ የሚያቃልል ተግባር አይደለም። የዜጎችን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ክፍተቶችን በመሙላት አብሮነትን፣ መተሳሰብንና የጋራ ኃላፊነትን የሚያጠናክር የማህበራዊ ኃላፊነት ውልም ነው። ''ሃምሳ ሎሚ ለሃምሳ ሰው ጌጡ፤ ለአንድ ሰው ሸክሙ” እንዲል የሀገር ብሂል ሰዎች በአንድነት ቆመው ለአንድ መልካም ዓላማ ከተባበሩ ለመፍታት የማይቻል ችግር እንደሌለ በተግባር የሚያሳዩ ብዙ አብነቶች አሉ። በተለይም በሰው ተኮር ልማትና በበጎ ፈቃድ የሚከናወኑ የቤት ግንባታና እድሳት ሥራዎች ችግርን ከመቅረፍ ባለፈ የሰዎችን ሰብዓዊ ክብር የሚመልሱ የተስፋ ምንጭ ተግባራት ሆነዋል። ባለፉት ዓመታት በሀገር አቀፍም ሆነ በአዲስ አበባ በበጋና ክረምት ሰው ተኮር የበጎ ፈቃድ መርሃ ግብሮች በርካታ ዜጎችን ከማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉስቁልና ወደ ልዕልና እንዲሸጋገሩ አስችሏል። ከእነዚህ የሰው ተኮር ተግባራት ተጠቃሚ ከሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች መካከል በመኖሪያ ቤት ችግር ምክንያት ኑሯቸው በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ የነበሩ ነዋሪዎች ይገኙበታል። ቤት ለአንድ ሰው የመኖሪያ ቦታ ብቻ አይደለም። ይልቁንም የዜጎችን የደህንነት፣ የክብር፣ የመረጋጋትና ዘላቂ የተስፋ ወጋገን የሚያቆራኝ መሰረታዊ ጉዳይ ነው። ስለዚህ ለአንድ ቤተሰብ የሚገነባ ወይም የሚታደስ ቤት ከግንባታ ዕቃና ከግድግዳ በላይ ትርጉም አለው፤ የተሰበረ ተስፋን ይጠግናል፣ የተረሳ ክብርን ይመልሳል፣ ለነገም አዲስ እድል ይከፍታል። በአዲስ አበባ በበጎ ፈቃደኞች፣ በባለሀብቶችና በመንግሥት የጋራ ጥረት ቤት ተገንብቶላቸው እፎይታን ያገኙ ነፍሶችም በርካቶች ናቸው። ወይዘሮ መስከረም ሰለሞን እንደሚሉት፤ ከዓመታት በፊት ከሁለት ልጆቻቸው ጋር ፒያሳ አካባቢ ለሰው ልጅ ክብርን በማይመጥን ጎስቋላ ቤት ውስጥ ሕይወትን ይመሩ ነበር። በተለይም ክረምት በመጣ ቁጥር የጎርፍና የዝናብ ፍሳሽ አደጋ በከፍተኛ ጭንቀት እንዲያሳልፉ ያስገድዳቸው እንደነበር አስታውሰዋል። በሳር ቤት አካባቢ በተሰራላቸው ዘመናዊ የመኖሪያ መንደር የተሰጣቸው የመኖሪያ ቤት አዲስ የሕይወት ተስፋን እንዳጎናጸፋቸው አስረድተዋል። ይህንም ለመኖር ከማይመች ቦታ ወጥቼ ወደ አማረ ቤት በመግባቴ እንደገና የመወለድ ያህል ታላቅ ደስታ ተሰምቶኛል ሲሉ ገልጸዋል። እንደ ወይዘሮ መስከረም ታሪክ ሁሉ የሌሎች ነዋሪዎች የቤት ግንባታና ዕድሳት ሥራዎች ተሞክሮ የሚያሳየው የቁሳዊ እፎይታ ብቻ ሳይሆኑ ሰብዓዊ ክብርን የሚያጎናጽፉ የተስፋ ውጤቶች መሆናቸውን ነው። በአንድ ወቅት ከፎቅ ላይ ባጋጠማት የመውደቅ አደጋ ሳቢያ የአካል ጉዳት ያጋጠማት ታሪክ ሙሉጌታ፤ በአዲስ አበባ በኪራይና በመንግሥት ቤት ከቤተሰቧ ጋር ሕይወትን ስትገፋ እንደነበር ገልጻለች። የአካል ጉዳተኛ ከሆነች በኋላ ቀደም ሲል ትኖርበት የነበረው ቤትና አካባቢ ከቦታ ቦታ እንደልብ ለመንቀሳቀስ አስቸጋሪ እንደነበር በማስታወስ፤ ከቤተሰቧ ጋር ይኖሩበት ከነበረው ባምቢስ አካባቢ ወደ ሳር ቤት አካባቢ የመኖሪያ ቤት ማግኘቷ በሕይወት ዘመን ያገኘሁት ትልቅ የተስፋ ስጦታዬ ነው ብላለች። ቤቱ እንደልብ መንቀሳቀስ የሚያስችል፣ መሠረታዊ የመኖሪያነት መስፈርቶች የተሟላላት መሆኑ ሕይወቴን በትልቅ እፎይታ እንድመራ አስችሎኛል ስትል ተናግራለች። በሰው ተኮር ፕሮጀክት የሚገነቡ ቤቶች የሚያመጡት ለውጥ ለአካል ጉዳተኞች ብቻ የሚወሰን አይደለም። በቤት ውስጥ ልጆች፣ አረጋውያን፣ የሀገር ባለውለታዎችና መላ ቤተሰብ እንዲሁም የተሻለ ኑሮን ለመፍጠር የሚታገሉ እናቶችና አባቶችም የዚህ ተግባር ተጠቃሚዎች ናቸው። በዚህም በጎነት የአንድን ሰው ዛሬ ከማሻሻል ባለፈ የአንድ ቤተሰብን ነገ የሚቀርጽ ኃይል መሆኑን ያሳያል። ወይዘሮ ጽጌሬዳ ጎበና ፤ ለረጅም ዓመታት ፒያሳ አካባቢ ለመኖር ምቹ ባልሆነ ቤትና ሰፈር ከአንድ ልጃቸው ጋር ይኖሩ ነበር። በፒያሳ አካባቢ የሕይወት ቆይታ ዘመናቸውም ልዩ ድጋፍ የምትሻው ልጃቸው እንደልቧ መንቀሳቀስ የማትችልበትን በርካታ የሰቆቃ ጊዜያት እንዳሳለፈች አስታውሰዋል። በዚህ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ እያሉ በሳር ቤት አካባቢ አዲስ ቤት ማግኘታቸው እንደገና የመወለድ ያህል ትልቅ እፎይታን እንደቸራቸው ገልጸዋል። የተሰጣቸው ቤት ለልጃቸው እንቅስቃሴ ምቹ ከመሆኑ ባለፈ ዘመናዊ የአኗኗር ዘይቤን እንዲከተሉ ያስቻለ ታላቅ የሕይወት ብስራት መሆኑን ገልጸዋል። እነዚህ ታሪኮች የሚያስረዱት አንድ ቤት ሲታደስ ግድግዳና ጣሪያ ብቻ አለመሆኑን ነው። ከቤቱ ጋር የነዋሪው ተስፋ፣ የቤተሰቡ መረጋጋትና የሰው ልጅ ክብርም አብሮ ይታደሳል። በዚህም በጎነት የችግር መፍቻ ብቻ ሳይሆን ከጊዜ ጊዜ የተስፋ ማስፈንጠሪያና ሰብዓዊ ክብር ማጎናጸፊያ ተግባር እየሆነ መጥቷል። በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ቤታቸው ከታደሰላቸው መካከል ታየሁ መኮንን እንደሚሉት፤ ቀደም ሲል ይኖሩበት የነበረው ቤት 'ቤት ነው ለማለት እንኳን አያስደፍርም' ነበር። ዛሬ ግን ታሪካቸው ተቀይሯል። በበጎ ፈቃደኞች አማካኝነት የመኖሪያ ቤት ችግራቸው ተቀርፎ፣ 'ቤቴ በመታደሱ ያለ ሀሳብ ጎኔን ማሳረፍ ችያለሁ' ሲሉም ወይዘሮ ታየሁ ገልጸዋል። ይህ አንድ ነዋሪ ያገኘው የቤት ለውጥ ብቻ አይደለም። ከዓመታት የጭንቀት ኑሮ ወደ መረጋጋት የተሸጋገረ ሕይወት ነው። ከስጋት ወደ እፎይታ፣ ከተስፋ መቁረጥ ወደ ተስፋ የተደረገ ጉዞ ነው። ለበርካታ ዓመታት በማይመች ቤት ኑሮ ሲገፉ እንደቆዩ የገለጹት ወይዘሮ ዘውዲቱ ገብረማርያም ደግሞ፤ አሁን ላይ ቤታቸው በመታደሱ ደስ ብሏቸው የሚኖሩበትን ዕድል እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል። በሰው ተኮር የልማት መርሃ ግብር አቅመ ደካማ ወገኖችን ለመደገፍ የሚከናወኑ ተግባራትም የበርካቶችን ተስፋ የሚያለመልም አስደናቂ ተግባር መሆኑን ገልጸዋል። እነዚህ የነዋሪዎች ምስክርነቶች በጎነት በተግባር ሲገለጽ የሰውን ክብር እንደሚያጎናጽፍ፣ የተሰበረ ተስፋን እንደሚያድስና ለነገ የሚያስብ ሕይወትን እንደሚፈጥር ያረጋግጣሉ። በተለይም እናቶች፣ አረጋውያን፣ አቅመ ደካሞችና የሀገር ባለውለታዎች የሚያገኙት ድጋፍ በቁሳዊ እርዳታ ብቻ የሚመዘን ሳይሆን 'እናንተም የዚህ ሀገር ክብር ናችሁ' የሚልን ሰብዓዊ መልዕክትን ያስተላልፋል። በዚህ ረገድ የመደመር መንግሥት ሰው ተኮር ልማትን እንደ የልማት ፖሊሲ አቅጣጫ በመያዝ የዜጎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ክፍተቶች በመሙላት ተስፋን የሚያለመልሙ ተግባራትን እያጠናከረ ይገኛል። የቤት ግንባታና ዕድሳት፣ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶችና ሌሎች ሰው ተኮር መርሃ ግብሮችም ይህንኑ አቅጣጫ በተግባር ከሚያሳዩ ተጨባጭ ለውጦች መካከል ይጠቀሳሉ። አስተያየት ሰጪዎቹ ዛሬ ላይ ውብና ጽዱ በሆነ ቤት የሚኖሩበት ዕድል የተፈጠረው መንግሥት፣ ባለሀብቶችና ሌሎች በጎ ፈቃደኞች ባከናወኑት መልካም ተግባር በመሆኑ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። በአዲስ አበባ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት አረጋውያንን፣ አቅመ ደካሞችና የሀገር ባለውለታዎችን አመቺ መጠለያ እንዲያገኙ ለማድረግ የሚሰሩ ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉም መልዕክት አስተላልፈዋል። በእርግጥም የበጎነት ዋጋው በሚሰጠው የቁሳቁስ መጠን ብቻ አይለካም። በሰው ልብ ውስጥ በሚፈጥረው ተስፋና በሕይወት ላይ በሚያመጣው ለውጥ ይመዘናል። የተሰራው ቤት ለአንዲት እናት የእፎይታ ምንጭ፣ ለአንድ አረጋዊ የክብር መገኛ፣ ለአካል ጉዳተኛ ደግሞ በራስ መተማመንና ነፃነት መገለጫ ይሆናሉ። ይህም ሰው ተኮር ልማት ማለት ትልልቅ ፕሮጀክቶችን መገንባት ብቻ ሳይሆን፣ የአንድ ዜጋን የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል፣ የአንድ ቤተሰብን ተስፋ ማደስና የአንድን ሰው ክብር ማስመለስ ጭምር መሆኑን ያሳያል። በጎነት ከአንድ ሰው ወደ ሌላው የሚሸጋገር ቀላል የመልካም ተግባር መገለጫ ቢመስልም በጋራ ሲተገበር ማኅበረሰብን የመለወጥ ታላቅ ኃይል አለው። የእነዚህ ነዋሪዎች ታሪክም ይህንኑ ያረጋግጣል። ከተስፋ መቁረጥ ወደ ተስፋ፣ ከስጋት ወደ እፎይታ፣ ከአስቸጋሪ ኑሮ ወደ የተሻለ ኑሮ የተሸጋገሩ ሕይወቶችን ያሳያል። ስለሆነም በጎነትን እንደ የአንድ ጊዜ ዘመቻ ሳይሆን እንደ የማኅበረሰብ የጋራ እሴት ማጠናከር፣ ተጋላጭ የሆኑ ወገኖችን መደገፍና ሰው ተኮር ልማትን ማስቀጠል የጋራ ኃላፊነት ነው። ዛሬ የተሰራ ቤት ከግድግዳ በላይ ነው። የነገ ተስፋ መሰረት ነው። ዛሬ የተዘረጋ የበጎነት እጅም ከአንድ ሰው የሚተርፍ ለብዙዎች የሚደርስ የሰብዓዊነት ብርሃን ነው።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ አዲስ ዓመትን በማስመልከት ማዕድ አጋሩ
Sep 11, 2026 66
አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦ከንቲባ አዳነች አቤቤ አዲስ ዓመትን በማስመልከት በልደታ ተስፋ ብርሃን ምገባ ማዕከል ማዕድ አጋርተዋል። በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት በማዕከሉ ምገባ ዘወትር የሚከናወን ቢሆንም፣ በዛሬው ዕለት በበዓሉ ምክንያት የተገኘነው ለእናንተ ያለንን አክብሮት፣ ፍቅርና ቤተሰባዊነት ለመግለፅ ነው ብለዋል። አዲሱ ዓመት የበለጠ የምንደጋገፍበትና የምንበለፅግበት እንዲሆን እመኛለሁ በማለት መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
በአዲሱ ዓመት ለሀገራችን ዕድገት በትጋት እንሰራለን
Sep 11, 2026 68
ደሴ ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦ አዲሱ ዓመት አንድነታችንን ጠብቀን ሰላምና ልማታችንን በተሻለ መልኩ ለማረጋገጥ በትጋት የምንሰራበት ዓመት ነው ሲሉ በደቡብ ወሎ ዞን የሀርቡ ከተማ አስተዳደር ነዋሪዎች ገለፁ። የከተማዋ ነዋሪዎች በአዲሱ ዓመት ለሀገርና ለከተማቸው ሰላምና ልማት በቁርጠኝነት ለመስራት ማቀዳቸውን ነው የተናገሩት። የከተማዋ ነዋሪ ወይዘሮ ዚነት ሁሴን ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት፤ በአዲሱ ዓመት የከተማዋን ሰላምና እድገት ለማስቀጠል በሚደረገው ጥረት ውስጥ በመሳተፍ የበኩሌን አስተዋጽኦ ለማበርከት ተዘጋጅቻለሁ ብለዋል። አዲሱ ዓመት የተሻለች ኢትዮጵያን የምናይበት ዓመት ይሆናል ብለው ተስፋ ማድረጋቸውን ገልጸዋል። የአካባቢያቸውን ጸጥታ በጋራ ከመጠበቅ ጎን ለጎን በትምህርት፣ በጤና እና በመሰረተ ልማቶች ግንባታ ላይ ንቁ ተሳትፎ ለማድረግ ማቀዳቸውን ተናግረዋል። ሌላው የሀርቡ ከተማ ነዋሪ አቶ ሁሴን የሱፍ በበኩላቸው፤ አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የጤና፣ የመከባበርና የአንድነት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል። በዓሉን በፍቅርና በደስታ እያከበሩ መሆኑን ጠቁመው፤ በአዲሱ ዓመት አንድነታችንን ጠብቀን ለከተማችን ሰላም፣ ልማትና ሁለተናዊ ብልጽግና በትጋት የምንሰራበት ሊሆን ይገባል ነው ያሉት። በአዲሱ ዓመት ጥሩ ተስፋ ሰንቀን አንድነታችንንና የአካባቢያችንን ሰላም የምናስቀጥልበት ነው ያሉት ደግሞ አቶ መሀመድ እንድሪስ ናቸው። ከባለፈው ዓመት ድክመቶቻችን ተምረን ጥንካሬዎችን በማስቀጠል ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽግና የድርሻችንን ለመወጣት ከወዲሁ ተዘጋጅተናል ብለዋል። የከተማዋን ዘላቂ ሰላም ለማስጠበቅ እና የልማት ስራዎችን ለማፋጠንም ከመንግስትና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት ለመስራት መዘጋጀታቸውን ነው የተናገሩት፡፡
አዲስ የተስፋ ብርሃን የፈነጠቀበት- አዲስ ዓመት
Sep 11, 2026 78
መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦ አዲስ የተስፋ ብርሃን የፈነጠቀበት አዲስ ዓመት የኢትዮጵያውያን አዲስ ዓመት (መስከረም 1) የዓመት መለወጫ ብቻ ሳይሆን የተፈጥሮ መታደስ፣ የሰላም፣ የፍቅርና የይቅርታ መገለጫ ተደርጎ የሚወሰድ ታላቅ ህዝባዊ በዓል ነው። በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር መሠረት አዲሱ ዓመት የሚጀምረው የክረምቱ ድቅድቅ ጨለማና ዝናብ አልፎ፣ ሰማዩ ጠርቶ፣ ምድሩ በብርሃንና በአደይ አበባ በሚሸፈንበት በመስከረም ወር መጀመሪያ ላይ ነው። «እንቁጣጣሽ» የሚለው ስያሜ «እንቁ ዕጣ ለአንቺ» ወይንም “እንኳን ደህና መጣሽ” በማለት በከበሩ ዕንቁዎች የተደረገ አቀባበል ጋር ተያይዞ የተሰየመ ስለመሆኑም ይነገራል። በአዲስ ዓመት ክረምቱ አልፎ መስከረም ሲጠባ አበቦች ያብባሉ፣ ጥርት ያሉ ወንዞች ይታያሉ፤ ምድር በአረንጓዴ ውበት ታሸበርቃለች። የተፈጥሮ ማሸብረቅን ተከትሎም የሰዎችም ህይወትና ተስፋ አዲስ የሚሆንበት ምልክት መሆኑ ይነሳል። በአሮጌው ዓመት የነበሩ ቅሬታዎች፣ ጥላቻዎችና አለመግባባቶች ተወግደው አዲስ ምዕራፍ የሚከፈትበት፣ ዘመድ ከዘመድ የሚጠያየቅበትና ይቅር የሚባባልበት ወርቃማ ጊዜም መሆኑ ይነገራል። በአዲስ ዓመት መባቻ በየቤት ደጃፍና በየመንደሩ «ችቦ» ይበራል፤ የችቦው መበራት ጨለማውን አሮጌ ዓመት ሽኝተን፣ በብርሃን የተሞላውን አዲስ ዓመት መቀበላችንን የሚያመላክትም ነው። «እዮሃ መስከረም ጠባ...» እየተባለም ይዜምለታል። በበዓሉ ዕለት ጠዋት ልጃገረዶች ባህላዊ አልባሳታቸውን ለብሰው፣ ከበሮ በመምታት «አበባዮሽ» እያሉ በየቤቱ በመዘዋወር የእንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞት በማቅረብ በስጦታና ሙገሳ እንዲሁም በምርቃት የሚሸኙበት ነው። ወንዶች ልጆች ደግሞ በአደይ አበባና በተፈጥሮ ምስሎች ያሸበረቁ ስዕሎችን በወረቀት ላይ በመሳል «እንኳን አደረሳችሁ» በማለት ለጎረቤትና ለዘመድ አዝማድ ያበረክታሉ። በእለቱ የሀገር ባህል ምግብ ተዘጋጅቶ ቤተሰብ፣ ዘመድና ጎረቤት በአንድ ላይ ይሰበሰባል፤ የቡና ስነ-ስርዓት ተካሂዶ በእንቁጣጣሽ የተቆረጠው አደይ አበባና ሳር ይጎዘጎዛል በዚህ መልኩም ክብረ በዓሉ ይቀጥላል። በዚሁ መሰረትም የዘንድሮውን አዲስ ዓመት ኢትዮጵያዊያን በታላቅ ደስታና ተስፋ ተቀብለው በማክበር ላይ ይገኛሉ። የኢትዮጵያ ማንሰራራት በብዙ መልኩ የተገለጠበትና ዘለቄታዊ መሰረቶች የተጣሉበት 2018 ዓ.ም ተጠናቆ ወደ 2019 ዓ.ም ስንሸጋገር ያለፉትን ስኬቶች በማጠናከርና ጉድለቶችን ለመሙላት በመዘጋጀት ነው። እንደ ሀገር እየተከናወኑ ያሉ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎችን በማስቀጠልና የተጀመሩትን ታላላቅ ሜጋ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው እቅድ መሰረት ለስኬት ለማብቃት በመትጋት መሆንም ይኖርበታል። አዲስ የተስፋ ብርሃን በፈነጠቀበት አዲስ ዓመት አዲስ አስተሳሰብ በመሰነቅ ከመቼውም ጊዜ በላይ ለዘላቂ ሰላምና ለልማት በመነሳት መሆን ይኖርበታል። በአዲስ ዓመት የመስከረም ብርሃን ለኢትዮጵያ የሰላም፣ የፍቅር፣ የብልፅግና እና የከፍታ ዘመን ይዞ እንዲመጣ እንመኛለን! መልካም አዲስ ዓመት!
ፖለቲካ
አዲሱ አመት የመከላከያ ሠራዊታችን አቅም ይበልጥ የሚጠናከርበት ዓመት ይሆናል - ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
Sep 11, 2026 191
አዲስ አበባ ፤ጳጉሜን 5 /2018 (ኢዜአ)፦አዲሱ ዓመት የመከላከያ ሠራዊታችን አቅም ይበልጥ የሚጠናከርበትና ዝግጁነቱ የሚያድግበት ዓመት ይሆናል ሲሉ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገለፁ፡፡ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብና ለመከላከያ ሠራዊት አባላት ለ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፈዋል። ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ባስተላለፉት መልዕክት፤ 2018 በርካታ ፈተናዎች የተጋፈጥንበት ዓመት ቢሆንም፣ የመከላከያ ሠራዊቱ የተቀመጡ ሀገራዊ ግቦችንና ዕቅዶችን በተቀናጀ አሠራር በማሳካት የተሰጠውን ኃላፊነት በከፍተኛ ብቃት የተወጣበት ዓመት ነበር ብለዋል። በተጠናቀቀው ዓመት የሠራዊቱ ዋና ትኩረት የሀገርን ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ፣ ህዝብን መጠበቅና የልማት ጉዞዎችን ከዕንቅፋት መከላከል እንደነበር ጠቁመው፤ በዚህም በተለያዩ አካባቢዎች መረጋጋት በመፍጠር ህዝቡ ወደ መደበኛ ኑሮው እንዲመለስ መደረጉን አስረድተዋል። አክለውም ዘላቂ ሰላም በወታደራዊ አቅም ብቻ የማይረጋገጥ በመሆኑ ህዝቡ ለሰላም የሚያበረክተውን ሚና ማጠናከር እንደሚገባ አመልክተዋል። በሌላ በኩል 2018 ዓ.ም የመከላከያ አቅምን ከዘመኑ ጋር ለማዛመድ ከአናሎግ ወደ ዲጂታል አሠራር የመሸጋገር፣ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን የመታጠቅ፣ የምድርና የአየር ኃይል አቅምን የማሳደግ እንዲሁም የመከላከያ ኢንዱስትሪን በሀገር ውስጥ ምርቶች የማጠናከር ሰፊ ሥራ የተሠራበት ዓመት መሆኑን ገልፀዋል። በመጪው 2019 ዓ.ም የመከላከያ ሠራዊቱ ሁለት ዋና ዋና ትኩረቶች ይኖሩታል ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፤ የመጀመሪያው የሀገርን ሰላም፣ ደህንነትና ሉዓላዊነት ማስጠበቅ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ የሠራዊቱን የማድረግ አቅም፣ የሰው ኃይል፣ የሥልጠና፣ የመሠረተ ልማት እና የመከላከያ ኢንዱስትሪ ልማት ሥራዎችን ወደተሻለ ደረጃ ማሸጋገር እንደሆነ አስታውቀዋል። አዲሱ ዓመት የመከላከያ ሠራዊታችን አቅም ይበልጥ የሚጠናከርበትና ዝግጁነቱ የሚያድግበት ዓመት ይሆናል ሲሉም አክለዋል፡፡ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፤ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ፣ ለጀግናው የመከላከያ ሠራዊት አመራሮች፣ መኮንኖች፣ ወታደሮችና ሲቪል ሠራተኞች መልካም አዲስ ዓመት እንዲሆን ተመኝተው፤ አዲሱ ዘመን ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም፣ ለህዝባችን ደህንነትና ብልፅግና፣ ለሰራዊታችን የበለጠ አቅም፣ ዝግጁነትና ስኬት የሚያመጣ ዓመት ይሁንልን ሲሉም መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡
ሀገራዊ የምክክር ጉባዔ በስኬት መጠናቀቁ ለኢትዮጵያ አዲስ ምዕራፍ ከፋችና የተስፋ ብርሃን ያበሰረ ነው
Sep 10, 2026 403
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ አካታችና አሳታፊ የሆነው ሀገራዊ የምክክር ጉባዔ በስኬት መጠናቀቁ ለኢትዮጵያ አዲስ ምዕራፍ ከፋችና የተስፋ ብርሃን ያበሰረ መሆኑን የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ገለጹ። የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በቀሪው የሥራ ጊዜው መጠናቀቅ ያለባቸውን ቀሪ ተግባራት እንደሚያከናውን አስታውቋል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ በ2018 በዓመቱ የተከናወኑ ዓበይት ተግባራትን እና በቀሪው የሥራ ጊዜ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን አስመልክተው ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸው 2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ስኬታማ ሆኖ ማለፉን ተናግረው፤ ከስኬቶች መካከል ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ በስኬት መጠናቀቁ ተጠቃሽ መሆኑን ተናግረዋል። ከሐምሌ 8 እስከ ነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ.ም በተካሄደውና አራት ሺህ ተመካካሪዎች በተሳተፉበት ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ላይ በስምንት መሠረታዊ አጀንዳዎች ላይ ሰፊና ጥልቅ ምክክር መደረጉን አስታውሰው፤ በበርካታ ጉዳዮች ላይ ስምምነትና መግባባት ላይ መደረሱን ገልጸዋል። ስለሆነም የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር በአሳታፊነት እና በአካታችነት በበርካታ ሀገራዊ እና መሠረታዊ በሆኑ አጀንዳዎች ላይ መክረው በመግባባት መከናወኑ የ2019 አብሳሪ እና አዲስ ምዕራፍ ከፋች ነው ብለዋል። ይህ ስኬት ታሪክ ቀያሪ እና ተስፋ ሰጪ ውጤት ሙሉ የሚሆነው በአዲሱ የ2019 ዓ.ም እና ቀጥለው በሚኖሩ በርካታ አዳዲስ ዘመኖች ውጤታማነቱን አጠናክረን ስንቀጥል ብቻ ነው ብለዋል። በመሆኑም ኮሚሽኑ በቀሪው የሥራ ጊዜው የምክክሩን ውጤት ከግብ ለማድረስ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ተናግረዋል። በዚሁ መሠረት በኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅ መሰረት ሌሎች መጠናቀቅ ያለባቸውን ቀሪ ተግባራት ያከናውናል ብለዋል። እነሱንም አንደኛ የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ሂደቶችን፣ በምክክሮቹ የተገኙ ምክረ ሐሳቦችን ተግባር ላይ ሊውሉ የሚችሉበትን መንገድ የሚገልጽ ሰነድ በማዘጋጀት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ለአስፈጻሚ አካል እና ሌሎች ለሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት በቅርቡ እንደሚያቀርብ ገልጸው፤ ይህንም ለሕዝብ ይፋ ያደርጋል ሲሉ ጠቅሰዋል። በሁለተኛ ደረጃ በሀገራዊ ምክክሮች የተገኙ ምክረ ሐሳቦችን መንግሥት በተግባር ላይ ለማዋል እንዲችል ግልጽ እና ተጨባጭ ኮሚሽኑን ማገዝ የሚያስችለውን ስትራቴጂ በመንደፍ ላይ ይገኛል ብለዋል። በሦስተኛነት የምክረ ሐሳቦቹን አፈጻጸም ለመከታተል የሚያስችል ሥርዓት እና ዘዴዎችን ማዘጋጀት እና ማደራጀት እንደሆነም አመላክተዋል። በአራተኛነት በክልሎች፣ በከተማ አስተዳደሮች እና በፌደራል ደረጃ ሊታዩ የሚገባቸውን ልዩነቶች ከኢትዮጵያ ሕዝብ እና ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር ማጠናቀቅ እንደሆነ ጠቅሰዋል። አምስተኛው ሂደቶችን ግልጽ ለማድረግ፣ ግንዛቤ ለመፍጠር እና የምክክር ባህል ሆኖ እንዲቀጥል የሚያስችሉ የሕዝብ ግንኙነት እና የመገናኛ ብዙሃን ሥራዎችን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። እነዚሁ ቀሪ ተግባራት እንዲሳኩ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ በየደረጃው ያሉ የመንግሥት አካላት፣ የሃይማኖት፣ የሲቪክ፣ የከፍተኛ ትምህርት እና የመገናኛ ብዙሃን ሌሎች ተቋማት እና ማህበራት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ምሁራን እና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት የእስካሁኑን ስኬታማ አስተዋጽኦቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ሰላምና ልማቷ የተረጋገጠ ኢትዮጵያን ለትውልድ ለማሻገር የጋራ ትብብር ያስፈልጋል- የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች
Sep 10, 2026 369
አዳማ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፡-የኢትዮጵያን ዘላቂ ሰላምና ልማት ዕውን በማድረግ ለነገው ትውልድ ለማስተላለፍ የሁሉም አካላት የተቀናጀ ጥረትና አገራዊ ትብብር ወሳኝ መሆኑን ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ገለጹ። በሀገሪቱ አሁን ላይ የተያዙ የልማትና የሰላም ጥረቶች ፍሬ እንዲያፈሩ የፖለቲካ ልዩነቶችን ወደ ጎን በማለት በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ አብሮ መስራት ወሳኝ መሆኑን በተደጋጋሚ የሚገለጽ ጉዳይ ነው። ጳጉሜ 5 «የነገ ቀን»ን አስመልከተው ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት በአዳማ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እንዳሉት የኢትዮጵያን ዘላቂ ሰላምና ልማት ዕውን በማድረግ ለነገው ትውልድ ለማስተላለፍ የሁሉም አካላት የተቀናጀ ጥረትና አገራዊ ትብብር ወሳኝ ነው። ከአስተያየት ሰጪዎች መካከል የአብን ሥራ አስፈጻሚና የኦሮሚያ ክልል አስተባባሪ አቶ ሀብታሙ ተሰማ፤ የጳጉሜን ቀናት በልማትና በመልካም አስተዳደር ተግባራት እንዲታሰቡ መደረጉ ሕዝባዊ ተግባቦትን ከማጎልበቱም በላይ ለነገው ትውልድ የተሻለች ሀገር ለማስረከብ ጉልህ አስተዋጽኦ አለው። ሀገር በትውልድ ቅብብሎሽ የምትቀጥል በመሆኗ፣ መጻኢ ዕድሏን ብሩህ ለማድረግ በተለይም የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ባለቤትነት ማረጋገጥ አስፈላጊ መሆኑን አቶ ሀብታሙ ገልጸዋል። የመደመር መንግሥት ካከናወናቸው ተግባራት መካከል የታላቁ ሕዳሴ ግድብ፣ የአረንጓዴ አሻራ፣ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዕድገትና የኮሪደር ልማትን ጨምሮ በመሠረተ ልማት ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶች ከዛሬ ባለፈ የነገውን ትውልድ ታሳቢ ያደረጉ መሆናቸውን አንስተዋል። በተለይም የመረጃ ሀብትን ከመጠበቅ ጎን ለጎን ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂን በመጠቀም የመንግሥት አገልግሎትን ለማዘመን በተጀመረው ሥራ፣ እንደ መሶብ ያሉ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት እየተስፋፉ እንደሚገኙ አክለው ገልጸዋል። የባህር በር አጀንዳ እና የኢትዮ ኮደርስ ሥልጠና ፕሮጀክትም ትውልዱ ከመጪው ዘመን ቴክኖሎጂ ጋር እንዲራመድ የሚያስችሉና የኢትዮጵያ መንግሥት ነገን አርቆ የሚያይበት ማሳያ መሆናቸውን አቶ ሀብታሙ አብራርተዋል። ስለሆነም ዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ልማቷ የተረጋገጠባትን ኢትዮጵያ ለነገው ትውልድ ለማስረከብ ሁሉም ወገን የበኩሉን ኃላፊነት ሊወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል። የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጀት (መኢአድ) የምስራቅ ሸዋ ዞን አስተባባሪ አቶ ተድላ በቀለ በበኩላቸው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የጳጉሜ ቀናት የሀገርን መልካም እሴቶች በሚገነቡ የተለያዩ ሁነቶች መከበራቸው በጎ ጎን እንዳለው ገልጸዋል። በመደመር መንግሥት በተጨባጭ የሚታዩ ልማቶች የተመዘገቡ ቢሆንም፣ ዘላቂ ሰላም ከማስፈን፣የዜጎች ደህንነት ከመጠበቅ፣ ከህብረተሰቡ የመልማት ፍላጎትና ከመሰረተ ልማት እጥረቶች የተነሳ ከመንግስትና ከህዝቡ ብዙ መስራት እንደሚጠበቅ አስታውቀዋል። በተለይም ህዝብን ለምሬት የሚዳርጉ ብልሹ አሰራሮችና ሙስናን ቅድሚያ ሰጥቶ መታገል እንደሚገባ ጠቁመው፤ ለዚህም በየደረጃው ያለው ባለድርሻ አካል የበኩሉን አስተዋጽኦ በማድረግ ነገን ብሩህ ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል። ገዥው መንግስትም ከመልካም ተሞክሮዎችና ካጋጠሙት ፈተናዎች ትልቅ ትምህርት በመውሰድ እና በሆደ ሰፊነት በመታገስ ለዜጎች የሚታይ ተስፋን በመሰነቅ የነገን ሰላም ለማስፈን ሊረባረብ ይገባል ነው ያሉት። ለ2019 አዲስ ሕይወት ራሳችንን ማዘጋጀትና ለነገ የተሻለ ማኅበራዊ መስተጋብር፣ እውነተኛ ወንድማማችነት እና ዘላቂ ሰላም ለመገንባት በቁርጠኝነት መነሳት ያስፈልጋልም ብለዋል።
አፍሪካ በዓለም ፊት ቦታ ለማግኘት አትማጸንም ፤ ይልቁንም የሚገባትን ስፍራ በባለቤትነት እየያዘች ነው- መሐሙድ አሊ ዩሱፍ
Sep 10, 2026 396
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ):- አፍሪካ በዓለም ፊት ቦታ ለማግኘት አትማጸንም ፤ የሚገባትን ስፍራ እና ክብር በራሷ እያረጋገጠች ነው ሲሉ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። የአፍሪካ ህብረት ቀን ተከብሯል።። የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ቀኑን በማስመልከት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ሊቀ መንበሩ የአፍሪካ ህብረት ቀን እ.አ.አ በ1999 የቀድሞ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ለመተካት ይፋዊ ውሳኔ የተላለፈበት የሰርጥ ድንጋጌ (Sirte Declaration) የሚታወስበት እንደሆነ ገልጸዋል። በዚያን ወቅት የአፍሪካ መሪዎች አህጉራዊ ትስስርን ለማፋጠን እና የአፍሪካን ድምጽ በዓለም አቀፍ መድረክ ከፍ ለማድረግ የአፍሪካ ህብረትን ለመመስረት ወሳኝ እና ታሪካዊ እርምጃ የወሰዱበት ምዕራፍ ነው ብለዋል። የዘንድሮው የአፍሪካ ህብረት ቀን ለአህጉሪቱ እጅግ ልዩ ትርጉም ባለው ወቅት ላይ እየተከበረ እንደሚገኝ አውስተዋል። ከጥቂት ቀናት በፊት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ የአፍሪካን እውነተኛ ቁመና እና ትክክለኛ መጠን የሚያሳይ የዓለም ካርታ አጠቃቀምን የሚደግፍ፣ በአፍሪካ መሪነት የቀረበ የውሳኔ ሀሳብ አፅድቋል። በቶጎ ሃሳብ አመንጪነትና በአፍሪካ ህብረት ድጋፍ እውን የሆነው ይህ እርምጃ ከቀላል የካርታ ማስተካከያ በላይ ትርጉም አለው ብለዋል ሊቀ መንበሩ። አፍሪካ በዓለም ፊት እንዴት እንደምትታይ ትኩረት የሚሰጠው መሆኑን እና አፍሪካ ራሷን የምትገመግምበትንና የምታሳይበትን ትርክት ራሷ መቅረጽ እንዳለባት አበክሮ የሚያስታውስ ነው። ይህ ውሳኔ አፍሪካ በዓለም ፊት በምን መልኩ መታየት እንዳለባት ከማሳየቱም በላይ፤ አፍሪካ ራሷን የምትመዝንበትንና እውነታዋን ለዓለም የምታሳይበትን ትርክት በራሷ መቅረጽ እንዳለባት በግልጽ የሚያሳይ መሆኑን ነው ያነሱት። የአፍሪካ እጣ ፈንታ የሚወሰነው በአፍሪካውያን የራሳቸው እይታ ነው። አፍሪካን በእውነተኛ ቁመናዋ፣ኃይሏ እና አቅሟ የምንመለከትበት ጊዜ አሁን ነው ብለዋል። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር አያይዘውም ካርታውን የማስተካከል እርምጃ አፍሪካ ወደ ላቀ የጋራ ራዕይ የምታደርገውን አህጉራዊ ጉዞ አካል መሆኑን አንስተዋል። ይህም በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጠና (AfCFTA) አማካኝነት የኢኮኖሚ ትስስር ማጠናከርን፣ ሰላም እና ፀጥታን ማረጋገጥን፣ ዘላቂ ልማትን እውን ማድረግን እና በዓለም አቀፍ ውሳኔ ሰጪ አካላት ውስጥ የአፍሪካን ተሳትፎ ማሳደግን እንደሚያካትት በዝርዝር አስረድተዋል። የአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 የተሳሰረች፣ የበለጸገች እና ሰላማዊት አፍሪካን ለመገንባት የማዕዘን ድንጋይ ሆኖ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል። ሰላም እና ፀጥታን ማረጋገጥ፣ የኢኮኖሚ ትስስርን በማፋጠን እና የአፍሪካን ዓለም አቀፍ ተሰሚነት መጨመር የአፍሪካ ህብረት ቀዳሚ ትኩረቶች ናቸው ብለዋል። አፍሪካ በዓለም ፊት እውቅና ለማግኘት አትለምንም፤ ይልቁንስ በዓለም አቀፍ መድረክ የሷ የሆነውን ትክክለኛ ስፍራ በራሷ ባለቤትነት እየያዘች ነው። አሁን የሚጠበቅብን ይህንን ጠንካራ እምነት ወደ ህብረት፣ ሀብትና ብልጽግና፣ ሰላም እና ተደማጭነት መለወጥ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ሊቀመንበሩ አፍሪካ የምታስመዘግበው እድገት በዓለም አቀፍ መድረኮች በሚኖራት ውክልና ብቻ ሳይሆን፣ በዜጎቿ ላይ የኑሮ ጥራት መሻሻል ጭምር መለካት እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል። በዚህም መሰረት የአፍሪካ ህብረት የ2026 ዓመት ትኩረቱን በዘላቂ የንጹህ ውሃ አቅርቦት እና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አገልግሎት ላይ ማድረጉ፣ ህብረቱ አህጉራዊ ራዕዮችን ከዕለት ተዕለት የዜጎች ህይወት ጋር ለማያያዝ ያለውን ጽኑ ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ አመልክተዋል። በአፍሪካ ህብረት ቀን አከባበር አባል ሀገራት፣ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማህበረሰቦች፣ የአፍሪካ ተቋማት፣ የግሉ ዘርፍ፣ የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ ሴቶች እና ወጣቶች ተባብረው ይበልጥ የተሳሰረች፣ በራሷ አቅም የምትተማመን እና የራሷን እጣ ፈንታ በራሷ መወሰን የምትችል አፍሪካን እንዲገነቡ ሊቀመንበሩ ጥሪ አቅርበዋል። የምንፈልጋት አፍሪካ የሚለውን አህጉራዊ ራዕይ እውን ለማድረግ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ እና የሰርት ድንጋጌ ለቀጣዩ የአፍሪካ ትውልድ ዘላቂ የትምህርት እና የዕድገት መሰረት ሆኖ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። የነገዋ አፍሪካ በካርታ ላይ ብቻ የተሻለ ውክልና ያላት ብቻ ሳትሆን፤ በዓለም አቀፍ መድረክ ሉዓላዊነቷ የጸና፣ ጠንካራ ውስጣዊ አንድነት ያላት፣ ለህዝቦቿም ዘላቂ ብልጽግናን የምታጎናጽፍ አህጉር መሆን ይኖርባታል ነው ያሉት። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ለመላው አፍሪካውያን እና በውጭ ሀገር ለሚገኙ የአፍሪካ ዳያስፖራዎች ሰላማዊ እና የትብብር መንፈስ የተሞላበት የአፍሪካ ህብረት ቀን እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለአፍሪካ ሕብረት ቀን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
Sep 9, 2026 558
አዲስ አበባ ፤ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ)፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለ24ኛ የአፍሪካ ሕብረት ቀን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ(ዶ/ር) ኢትዮጵያ ከቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ጀምሮ እስከ አሁኑ የአፍሪካ ሕብረት ድረስ በአህጉሪቱ ጉዞ ውስጥ ጽኑ ድምፅ ሆና የቆየችና አሁንም ያለች ሀገር ነች፤ አዲስ አበባም የአህጉራዊ ሕብረታችን መኖሪያ ሆና ታገለግላለች ብለዋል።
ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን በማጠናከር ለሀገር ዕድገት መትጋት ይገባል
Sep 9, 2026 513
ባህር ዳር፤ ጳጉሜ 4/2018(ኢዜአ)፦ ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን በማጠናከር ለሀገር ዕድገት መትጋት ይገባናል ሲሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል ማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር) ገለጹ። በክልሉ የሚገኙ የማህበራዊ ዘርፍ ተቋማት የህብር ቀንን በባህር ዳር ከተማ በድምቀት እያከበሩ ነው። የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር ) በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፤ የህብር ቀን የሀገሪቱን ብዝሃነት፣ አብሮነትና አንድነት የምናስብበት ታላቅ ዕለት ነው። ዕለቱን ስናስብ የጋራ ትርክትን በማጎልበት ለአገር እድገትና ብልጽግና በቅንጅት የመቆም ባህልን የምናጎለብትበት ነው ሲሉም አመልክተዋል። "በጋራ ስንቆም እንበረታለን" ያሉት አስተባባሪዋ፣ አብሮነታችን ለጠላት እሳት፣ ለወዳጅ ደግሞ የብረት አጥር ለመሆን የሚያስችል ነው ብለዋል። አክለውም ዕለቱን ስናስብ በማዳመጥ፣ በመከባበርና በመተባበር ለህብረ ብሔራዊ አንድነት መጠናከር የድርሻችንን በመወጣት መሆን አለበት ነው ያሉት። በአዲሱ ዓመትም የተግባር ሰው በመሆን ሰላምና ልማትን በማረጋገጥ የህዝቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባም አንስተዋል። የብሔር፣ የቋንቋና የሃይማኖት ልዩነቶች ሳይገድቡ ሕብረ ብሔራዊነትን ለሀገር ግንባታ በመጠቀም መስራት እንደሚገባም ነው የተናገሩት። የክልሉ ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ብርቱካን ሲሳይ በበኩላቸው፤ ዕለቱ የብዝሃነት መገለጫና የተሰናሰለ አንድነታችን ማሳያ ነው ብለዋል። የጳጉሜን ቀናትን ስናከብር ያለፈውን የምንገመግምበት፣ አብሮነትና የጋራ ጽናት በህብር የምናሳይበት ለቀጣይ ሥራ መነሳሳትን የፈጠረ ነው ሲሉም ተናግረዋል። በተጨማሪም ዕለቱ ማዕድ በማጋራት፣ ደም በመለገስ፣ ነፃ ህክምና በመስጠትና ለልጆች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ በማበርከት መከበሩ ለተተኪው ትውልድ መልካም መሰረት የሚጥል መሆኑን አስረድተዋል።
ሀገራዊ አንድነትን የሚያጠናክር አስተሳሳሪ የወል ትርክት ግንባታ ውጤት እያስመዘገበ ነው
Sep 9, 2026 561
አዲስ አበባ ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦የኢትዮጵያን ዘርፈ ብዙ ብዝሃነትና ህብረ ብሔራዊነት መሠረት ያደረገ፣ ሀገራዊ አንድነትን የሚያጠናክር አስተሳሳሪ የወል ትርክት የመገንባት ተግባር ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን የሕገ መንግሥትና ፌዴራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ኃይለኢየሱስ ታዬ (ዶ/ር) ገለጹ። ህብረ ብሔራዊነትን ማጎልበት ሀገራዊ አንድነትን፣ ሰላምንና የልማት ዕድገትን ለማጠናከር ወሳኝ መሆኑንም ነው ዋና ዳይሬክተሩ የተናገሩት። ኢትዮጵያ በህብረ ብሔራዊነት የደመቀች ለሀገራዊ እሴቶች እና ግቦች የሚተጉ እንዲሁም በጋራ እጣ ፈንታ የተሳሰሩ ህዝቦች ያሏት ሀገር ናት። ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት ኃይለኢየሱስ ታዬ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ የኢትዮጵያን ብዝሃነት እና ህብረ ብሔራዊነት ለወል ትርክት ግንባታ በማዋል አስተሳሳሪ ትርክት ከመገንባት አኳያ ውጤቶች ተመዝግበዋል። ኢትዮጵያ ህብረ ብሔራዊ ብዝሃነት ያላት ሀገር መሆኗን ጠቁመው፤ ይህንን ብዝሃነት በተገቢው መንገድ ማስተናገድ የጋራ ሀገራዊ ማንነትን ለመገንባት መሠረት መሆኑንም አክለዋል። በዚህም ባለፉት ዓመታት የኢትዮጵያ ህብረ ብሔራዊነት በተገቢው በመመራቱ ለሀገር ጥንካሬ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ ጠቁመዋል። ህብረ ብሔራዊነት አንዱ የሀገራዊ ትርክት ግንባታ ማዕከል መሆኑን ገልጸው፤ ሁሉም ቋንቋዎች፣ ባህሎችና ማንነቶች ለሀገር ግንባታ ወሳኝ መሆናቸውን ተናግረዋል። አሰባሳቢ ትርክት በሀገራዊ ስኬቶች፣ በልማትና በሀገሪቷ ህብረ ብሔራዊነት ላይ ሊመሠረት እንደሚችልም ነው ጨምረው የገለጹት። የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን አከባበር የኢትዮጵያ ህብረ ብሔራዊነት ጎልቶ የሚታይበት ብቻ ሳይሆን ሀገራዊ አንድነት የሚጠናከርበት መሆኑን ጠቁመዋል። ማዕከሉ የኢትዮጵያ ህብረ ብሔራዊነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ግንዛቤ በመፍጠር በኩል በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝም አስታውቀዋል። የፌዴራል ሥርዓቱ የሚጠይቀው ዕውቀት፣ ክህሎትና አስተሳሰብ እንዲጎለብትም በርካታ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል። ፌዴራሊዝም በብዝሃነት የተገነባች ሀገር ውስጥ የተለያዩ ማንነቶችን አሳታፊ በሆነ መንገድ ለማስተናገድና የጋራ ሀገር ግንባታን ለማጠናከር ጠቃሚ ሥርዓት መሆኑንም ተናግረዋል። አክለውም የፌዴራሊዝም ሥርዓቱ የተለያዩ አካባቢዎች ራሳቸውን በራሳቸው እንዲያስተዳድሩና አካባቢያቸውን እንዲያለሙ ዕድል በመስጠት የልማት አቅሞችንና ፍላጎቶችን ለማስታረቅ አግዟል ብለዋል። የኢትዮጵያ ህዝብ በብዝሃነት ውስጥ አብሮ የመኖር ልምድ ማካበቱንና ይህንን የአብሮነት እሴት ወደ ሀገራዊ የጋራ እሴትነት ለማሸጋገር በተከናወኑ ተግባራት በርካታ ውጤቶች መመዝገባቸውን ጠቁመው፤ ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል። ስለሆነም ህብረ ብሔራዊነትን ከፌዴራሊዝም እና ከዴሞክራሲ እንዲሁም ከልማትና ከሀገራዊ እሴቶች ጋር በማጣመር የጋራ ሀገራዊ ማንነትና አንድነትን ለማጠናከር በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል።

ማህበራዊ
የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዝ ለአዲሱ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
Sep 11, 2026 69
አዲስ አበባ፤መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦ የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዝ ለ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአውስትራሊያ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት መግለጫ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ በአውስትራሊያ ማህበራዊ እና ባህላዊ ሕይወት ውስጥ ያለውን ትልቅ ስፍራ አንስተዋል። በዓሉ ከደማቅ ባህላዊ ትውፊቶቹ ባሻገር፣ የኢትዮጵያን ጥልቅ ታሪክና ማንነት አጉልቶ የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል። በዓሉ ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች ተሰባስበው የቆዩ እሴቶቻቸውን ይበልጥ የሚያጸኑበት፣ እንዲሁም የጋራ ትስስራቸውን የሚያጠናክሩበት ልዩ ወቅት መሆኑንም ጠቁመዋል። ኢትዮጵያውያን በአውስትራሊያ መሬት ላይ ሆነው የትውልድ ግንዳቸውን ጠብቀው ማክበራቸው ለአውስትራሊያ ብዝሃነት ትልቅ እሴት እንደሆነ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ይህ ድርጊት ማህበረሰቡ በአውስትራሊያ ታሪክ ውስጥ እየጻፈው ላለው አዲስ ምዕራፍ ትልቅ ማሳያ መሆኑን አንስተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዝ አዲሱ ዓመት ለኢትዮጵያውያን ሁሉ የሰላም፣ የብልጽግና እና የደስታ እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ አዲስ ዓመትን በማስመልከት ማዕድ አጋሩ
Sep 11, 2026 66
አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦ከንቲባ አዳነች አቤቤ አዲስ ዓመትን በማስመልከት በልደታ ተስፋ ብርሃን ምገባ ማዕከል ማዕድ አጋርተዋል። በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት በማዕከሉ ምገባ ዘወትር የሚከናወን ቢሆንም፣ በዛሬው ዕለት በበዓሉ ምክንያት የተገኘነው ለእናንተ ያለንን አክብሮት፣ ፍቅርና ቤተሰባዊነት ለመግለፅ ነው ብለዋል። አዲሱ ዓመት የበለጠ የምንደጋገፍበትና የምንበለፅግበት እንዲሆን እመኛለሁ በማለት መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
በአዲሱ ዓመት ለሀገራችን ዕድገት በትጋት እንሰራለን
Sep 11, 2026 68
ደሴ ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦ አዲሱ ዓመት አንድነታችንን ጠብቀን ሰላምና ልማታችንን በተሻለ መልኩ ለማረጋገጥ በትጋት የምንሰራበት ዓመት ነው ሲሉ በደቡብ ወሎ ዞን የሀርቡ ከተማ አስተዳደር ነዋሪዎች ገለፁ። የከተማዋ ነዋሪዎች በአዲሱ ዓመት ለሀገርና ለከተማቸው ሰላምና ልማት በቁርጠኝነት ለመስራት ማቀዳቸውን ነው የተናገሩት። የከተማዋ ነዋሪ ወይዘሮ ዚነት ሁሴን ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት፤ በአዲሱ ዓመት የከተማዋን ሰላምና እድገት ለማስቀጠል በሚደረገው ጥረት ውስጥ በመሳተፍ የበኩሌን አስተዋጽኦ ለማበርከት ተዘጋጅቻለሁ ብለዋል። አዲሱ ዓመት የተሻለች ኢትዮጵያን የምናይበት ዓመት ይሆናል ብለው ተስፋ ማድረጋቸውን ገልጸዋል። የአካባቢያቸውን ጸጥታ በጋራ ከመጠበቅ ጎን ለጎን በትምህርት፣ በጤና እና በመሰረተ ልማቶች ግንባታ ላይ ንቁ ተሳትፎ ለማድረግ ማቀዳቸውን ተናግረዋል። ሌላው የሀርቡ ከተማ ነዋሪ አቶ ሁሴን የሱፍ በበኩላቸው፤ አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የጤና፣ የመከባበርና የአንድነት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል። በዓሉን በፍቅርና በደስታ እያከበሩ መሆኑን ጠቁመው፤ በአዲሱ ዓመት አንድነታችንን ጠብቀን ለከተማችን ሰላም፣ ልማትና ሁለተናዊ ብልጽግና በትጋት የምንሰራበት ሊሆን ይገባል ነው ያሉት። በአዲሱ ዓመት ጥሩ ተስፋ ሰንቀን አንድነታችንንና የአካባቢያችንን ሰላም የምናስቀጥልበት ነው ያሉት ደግሞ አቶ መሀመድ እንድሪስ ናቸው። ከባለፈው ዓመት ድክመቶቻችን ተምረን ጥንካሬዎችን በማስቀጠል ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽግና የድርሻችንን ለመወጣት ከወዲሁ ተዘጋጅተናል ብለዋል። የከተማዋን ዘላቂ ሰላም ለማስጠበቅ እና የልማት ስራዎችን ለማፋጠንም ከመንግስትና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት ለመስራት መዘጋጀታቸውን ነው የተናገሩት፡፡
አዲስ የተስፋ ብርሃን የፈነጠቀበት- አዲስ ዓመት
Sep 11, 2026 78
መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦ አዲስ የተስፋ ብርሃን የፈነጠቀበት አዲስ ዓመት የኢትዮጵያውያን አዲስ ዓመት (መስከረም 1) የዓመት መለወጫ ብቻ ሳይሆን የተፈጥሮ መታደስ፣ የሰላም፣ የፍቅርና የይቅርታ መገለጫ ተደርጎ የሚወሰድ ታላቅ ህዝባዊ በዓል ነው። በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር መሠረት አዲሱ ዓመት የሚጀምረው የክረምቱ ድቅድቅ ጨለማና ዝናብ አልፎ፣ ሰማዩ ጠርቶ፣ ምድሩ በብርሃንና በአደይ አበባ በሚሸፈንበት በመስከረም ወር መጀመሪያ ላይ ነው። «እንቁጣጣሽ» የሚለው ስያሜ «እንቁ ዕጣ ለአንቺ» ወይንም “እንኳን ደህና መጣሽ” በማለት በከበሩ ዕንቁዎች የተደረገ አቀባበል ጋር ተያይዞ የተሰየመ ስለመሆኑም ይነገራል። በአዲስ ዓመት ክረምቱ አልፎ መስከረም ሲጠባ አበቦች ያብባሉ፣ ጥርት ያሉ ወንዞች ይታያሉ፤ ምድር በአረንጓዴ ውበት ታሸበርቃለች። የተፈጥሮ ማሸብረቅን ተከትሎም የሰዎችም ህይወትና ተስፋ አዲስ የሚሆንበት ምልክት መሆኑ ይነሳል። በአሮጌው ዓመት የነበሩ ቅሬታዎች፣ ጥላቻዎችና አለመግባባቶች ተወግደው አዲስ ምዕራፍ የሚከፈትበት፣ ዘመድ ከዘመድ የሚጠያየቅበትና ይቅር የሚባባልበት ወርቃማ ጊዜም መሆኑ ይነገራል። በአዲስ ዓመት መባቻ በየቤት ደጃፍና በየመንደሩ «ችቦ» ይበራል፤ የችቦው መበራት ጨለማውን አሮጌ ዓመት ሽኝተን፣ በብርሃን የተሞላውን አዲስ ዓመት መቀበላችንን የሚያመላክትም ነው። «እዮሃ መስከረም ጠባ...» እየተባለም ይዜምለታል። በበዓሉ ዕለት ጠዋት ልጃገረዶች ባህላዊ አልባሳታቸውን ለብሰው፣ ከበሮ በመምታት «አበባዮሽ» እያሉ በየቤቱ በመዘዋወር የእንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞት በማቅረብ በስጦታና ሙገሳ እንዲሁም በምርቃት የሚሸኙበት ነው። ወንዶች ልጆች ደግሞ በአደይ አበባና በተፈጥሮ ምስሎች ያሸበረቁ ስዕሎችን በወረቀት ላይ በመሳል «እንኳን አደረሳችሁ» በማለት ለጎረቤትና ለዘመድ አዝማድ ያበረክታሉ። በእለቱ የሀገር ባህል ምግብ ተዘጋጅቶ ቤተሰብ፣ ዘመድና ጎረቤት በአንድ ላይ ይሰበሰባል፤ የቡና ስነ-ስርዓት ተካሂዶ በእንቁጣጣሽ የተቆረጠው አደይ አበባና ሳር ይጎዘጎዛል በዚህ መልኩም ክብረ በዓሉ ይቀጥላል። በዚሁ መሰረትም የዘንድሮውን አዲስ ዓመት ኢትዮጵያዊያን በታላቅ ደስታና ተስፋ ተቀብለው በማክበር ላይ ይገኛሉ። የኢትዮጵያ ማንሰራራት በብዙ መልኩ የተገለጠበትና ዘለቄታዊ መሰረቶች የተጣሉበት 2018 ዓ.ም ተጠናቆ ወደ 2019 ዓ.ም ስንሸጋገር ያለፉትን ስኬቶች በማጠናከርና ጉድለቶችን ለመሙላት በመዘጋጀት ነው። እንደ ሀገር እየተከናወኑ ያሉ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎችን በማስቀጠልና የተጀመሩትን ታላላቅ ሜጋ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው እቅድ መሰረት ለስኬት ለማብቃት በመትጋት መሆንም ይኖርበታል። አዲስ የተስፋ ብርሃን በፈነጠቀበት አዲስ ዓመት አዲስ አስተሳሰብ በመሰነቅ ከመቼውም ጊዜ በላይ ለዘላቂ ሰላምና ለልማት በመነሳት መሆን ይኖርበታል። በአዲስ ዓመት የመስከረም ብርሃን ለኢትዮጵያ የሰላም፣ የፍቅር፣ የብልፅግና እና የከፍታ ዘመን ይዞ እንዲመጣ እንመኛለን! መልካም አዲስ ዓመት!
ኢኮኖሚ
የሀዋሳ ከተማ የተቸረችውን የተፈጥሮ ሀብት በአግባቡ አልምቶ ለመጠቀም በተከናወኑ ተግባራት ውጤት ተመዝግቧል
Sep 10, 2026 243
ሀዋሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ የሀዋሳ ከተማ የተቸረችውን የተፈጥሮ ሀብት በአግባቡ አልምቶ ለመጠቀምና ለህዝብ ጥቅም ለማዋል በተከናወኑ ተግባራት ውጤት መመዝገቡን ከንቲባ ጥራቱ በየነ ገለጹ፡፡ የሀዋሳ ሐይቅ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት ግንባታ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት የምስጋናና የዕውቅና መርሀ ግብር እየተካሔደ ነው። ''ሀዋሳ ታመሰግናችኋለች'' በሚል መሪ ቃል የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች በተገኙበት ነው መርሃ ግብሩ እየተካሔደ የሚገኘው። የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ እንደገለጹት በ2018 በጀት ዓመት የታቀዱ ተግባራት በቅንጅት ተከናውነው ውጤት ያስገኙበት ነው። ከተማዋ የተቸረችውን የተፈጥሮ ሀብት በአግባቡ አልምቶ ለመጠቀምና ለህዝብ ጥቅም ለማዋል የተደረገው ጥረት ተስፋ ሰጪ ውጤት ማስመዝገቡን አንስተዋል። ከእነዚህም አንዱ የሐይቅ ዳር ልማት ፕሮጀክት መሆኑን አንስተው በመንግስትና በአጋር አካላት ተሳትፎ ግንባታው እየተፋጠነ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል። ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ የከተማዋን ገጽታና ውበት እንዲሁም ተወዳዳሪነትና ተመራጭነትን በማሳደግ ረገድ ትርጉም ያለው ውጤት እንደሚኖረው ተናግረዋል። በዚህ የልማት ሥራ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እያበረከቱ የሚገኙ አካላትን ያመሰገኑት ከንቲባው የዛሬው የምስጋናና ዕውቅና መርሀ ግብር የተዘጋጀው ተሳትፎውን የበለጠ ለማጠናከር መሆኑን አስረድተዋል። በመርሀ ግብሩ ላይ የክልሉና የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ አባላት፣ባለሀብቶች፣የሀገር ሽማግሌዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በግንባታ ላይ ያሉ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች ለነገዋ ኢትዮጵያ ጠንካራ መሰረት የሚያኖሩ ናቸው- ወጣቶች
Sep 10, 2026 125
ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በግንባታ ላይ ያሉ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች ለነገዋ ኢትዮጵያ ጠንካራ መሰረት የሚያኖሩ መሆኑን በሀዋሳ ከተማ ኢዜአ ያነጋገራቸው ወጣቶች ገለጹ። ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቁን ተከትሎ ሌሎች የሀገርን እድገትና ብልጽግና ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች በመከናወን ላይ ይገኛሉ። በግንባታ ላይ ያሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ኢትዮጵያን በላቀ መልኩ ወደ ፊት የሚያራምዱ እና ለቀጣዩ ትውልድ ብሩህ ተስፋ የሰነቁ መሆናቸው ይታመናል። የነገዋን ኢትዮጵያ የሚወስኑት እነዚህ የልማት ፕሮጀክቶች ከሀገራዊ ፋይዳም የተሻገረ ቀጣናዊና አህጉራዊ ጠቀሜታ የሚኖራቸው ናቸው። ከግዙፍ ፕሮጀክቶቹ መካከል የቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ፣ የኒውኩለር ማብላያ፣ የጋዝ ፋብሪካ፣ ማዳበሪያ ፋብሪካ፣ የ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ይጠቀሳሉ። እነዚህ ግዙፍ ፕሮጀክቶችና ሌሎችም እየተከናወኑ ያሉ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች የነገዋ ኢትዮጵያ ፅኑ መሰረትና የትውልዱ ብሩህ ተስፋ የሚሆኑ ናቸው። በሌላ በኩል ወጣቱን ትውልድ በቴክኖሎጂ ተጠቃሚ በማድረግ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንዲሆን ለማስቻል እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች የነገዋን ኢትዮጵያ ለመገንባት መሰረት የሚጥሉ ናቸው። በፖለቲካና ዲፕሎማሲ መስኮች የሚከናወኑ ሀገራዊ ጉዳዮችም የነገዋን የበለጸገች ኢትዮጰያ ለመገንባት ተስፋ የተሰነቀባቸው መሆኑን መግለፅ ይቻላል። ከዚሁ ጋር በተገናኘ ኢዜአ ያነጋገራቸው የሀዋሳ ከተማ ወጣቶች በመደመር መንግስት እየተከናወኑ ያሉ ሀገራዊ ኢንሼቲቮችና ግዙፍ ፕሮጀክቶች የነገዋ ኢትዮጵያ ጠንካራ መሰረቶች መሆናቸውን ተናግረዋል። ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል ወጣት በቃሉ መሠረት፤ ታላቁ የህዳሴ ግድብ፣ የጉባ ብስራቶች፣ የገበታ ፕሮጀክቶች፣ የኮሪደር ልማት ሥራዎችና ሌሎች ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ዛሬን ብቻ ሳይሆን ነገንም ጭምር ታሳቢ ያደረጉ መሆናቸውን አንስቷል። የኢትዮጵያ የወደፊት እጣ ፈንታ ላይ ለመወሰን በተለይም የወጣቶች ጠንካራ ተሳትፎ አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሶ በዲጂታል ዘርፍ ግንባር ቀደም ተሳታፊ የሚሆንበት መደላድል መፈጠሩ ጥሩ ጅምር መሆኑን ተናግሯል። ሌላኛው ወጣት ኃይለኢየሱስ ታምራት፤ በመደመር መንግስት እየተከናወኑ ካሉ ነገን ታሳቢ ያደረጉ ተግባራት መካከል የጠንካራ ተቋማት ግንባታ ሥራዎች ኢትዮጵያን ሊያሻግሩ የሚችሉ ናቸው ብሏል፡፡ ለአብነት በስኬት መከናወን የቻለው ሀገራዊ ምክክር በመነጋገር ላይ የተመሰረተ አዲስ የፖለቲካ ምዕራፍን የከፈተ ፣ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በዕኩልነት ለነገይቱ ኢትዮጵያ ሀሳብ ያዋጣበት መሆኑን ገልጿል፡፡ ወጣት ትዕግስት ፍስሀ በበኩሏ የመደመር መንግስት የኢትዮጵያ የህልውናና የነገ እጣ ፈንታ የሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮችንም በመተግበር በኢኮኖሚ የተሻለ ተወዳዳሪ የሆነች ሀገር ለመገንባት እየሰራ መሆኑን ተናግራለች፡፡ የባህር በር ባለቤትነትን ለማረጋገጥ አሁን ላይ እየተከናወኑ ያሉ ዓለም ዓቀፍ መርህን መሰረት ያደረጉ እንቅስቃሴዎች ኢትዮጵያን ከፍ የሚያደርጉ ተግባራት መሆናቸውን ጠቅሳለች፡፡ የባህር በር ባለቤትነት ለነገይቱ ኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ አንድምታ ያለው መሆኑን የተናገረችው ወጣት ትዕግስት፣ ለበርካታ ወጣቶች የሥራ ዕድል በመፍጠርና ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞች በማስገኘት ረገድ ትልቅ ተስፋ የሚጣልበት ተግባር መሆኑን አመላክታለች፡፡ መንግስት በሁሉም ዘርፎች እያከናወናቸው ያሉ ስኬታማ ተግባራት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የበኩላቸውን እንደሚወጡ ወጣቶቹ አረጋግጠዋል፡፡
በኢትዮጵያ እየተመዘገበ ያለው ፈጣን እድገት በትውልዱ ዘንድ ብሩህ ተስፋ እና የላቀ ተነሳሽነት ፈጥሯል
Sep 10, 2026 122
ጂንካ፤ ጷግሜን 5/2018 (ኢዜአ፡-በኢትዮጵያ በየዘርፉ እየተመዘገበ ያለው ፈጣን እድገትና ለውጥ በትውልዱ ዘንድ ብሩህ ተስፋ እና የላቀ ተነሳሽነትን መፍጠሩን የጂንካ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ። በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የተገነቡና በግንባታ ላይ ያሉ ሜጋ ፕሮጀክቶቹ የአሁኑን ትውልድ ብቻ ሳይሆን የመጪውን ብሩህ ጊዜ ታሳቢ ያደረጉ ስለመሆናቸውም ነዋሪዎቹ ተናግረዋል። "የነገ ቀን" ጳጉሜን-5 በሀገሪቱ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል፡፡ ቀኑን አስመልክቶ ኢዜአ በጂንካ ከተማ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች እንዳሉት ኢትዮጵያ በአጭር ጊዜ ውስጥ እያስመዘገበች ያለው ፈጣን እድገትና ለውጥ ትውልዱ በነገዋ ኢትዮጵያ ቀን ብሩህ ተስፋ እንዲሰንቅ የላቀ ተነሳሽነት ፈጥሯል፡፡ ከነዋሪዎቹ መካከል የጂንካ ሁለተኛና መሰናዶ ትምህርት ቤት መምህር ሀብታሙ አያሌው እንዳሉት ሀገራችን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በግብርናው፣ በኢንዱስትሪ፣ በቴክኖሎጂና በቱሪዝም ዘርፎች ተጨባጭ የሆነ ፈጣን እድገት አስመዝግባለች። በሀገሪቱ የተገነቡና እየተገነቡ ያሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች ለነገዋ ኢትዮጵያና ለዜጎቿ ብሩህ ተስፋ መሆናቸውን ገልጸው፣ የሕዳሴው ግድብ፣ የቢሸፍቱ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት፣ የአረንጓዴ ልማት ሥራዎችና ሌሎች ግዙፍ ፕሮጀክቶች ሀገራዊ እድገትን በማፋጠን በየዘመኑ ትውልድን ተጠቃሚ ያደርጋሉ ብለዋል። በተለይ በአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር፣ በቱሪዝም ዘርፍ፣ በዲጂታል ኢትዮጵያ እና በገበታ ለሀገርና ለትውልድ የተከናወኑ ስኬታማ የልማት ተግባራት ተጨባጭ ለውጥ ያመጡና በትውልዱ ዘንድ ተነሳሽነትን የፈጠሩ ናቸው ብለዋል። ሌላው የከተማው ነዋሪ አቶ ታምራት ምናስ፣ በኢትዮጵያ በመከናወን ላይ ያሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች እና ዲጂታል ቴክኖሎጂ ለዜጎች ብዙ ተስፋና ዕድሎች ይዘው መጥተዋል ብለዋል። በሴራ ያጣነውን የባህር በር ባለቤትነት የማስመለስ ጥረትን ጨምሮ ኢትዮጵያ ያላትን ሀብት በማልማት ከድህነት እንድትወጣ በተከናወኑ ሥራዎች እየተመዘገበ ያለው ውጤት በትውልዱ ዘንድ ተስፋን የሚያጭር ነው ብለዋል። በአሁኑ ወቅት በየዘርፉ እየተመዘገቡ ያሉ ስኬቶች መጪው ዘመን ለኢትዮጵያ ብሩህ እንደሆና ያሳያሉ ያሉት አቶ ታምራት፣ የኢትዮጵያን አድገት በላቀ ተነሳሽነት እና ትጋት ለማስቀጠል የበኩላቸውን ለመወጣት ዝግጁነታቸውን አረጋግጠዋል። ወጣት በቃህኝ ጥላሁን በበኩሉ በኢትዮጵያ እየተከናወኑ ያሉ ትላልቅ ግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች በወጣቱ ዘንድ ተስፋን ያጫሩ እና ለነገ ተነሳሽነቱን የያሳደጉ ናቸው ብሏል። ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የተከናወኑ ሥራዎችና በመከናወን ላይ ያሉ ተግባራት ከሀጋራዊ ፋይዳቸው ባለፈ በተለይ ወጣቱን ከቴክኖሎጂ ጋር በማስተዋወቅ ተጠቃሚ እያደረጉ መሆናቸውን ተናግሯል። ወጣቱ በዲጂታል ኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ አቅሙን ከማሳደግ ባለፈ ለሥራ ዕድል ፈጠራ በማዋል ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነቱን እያሳደገ ጭምር መምጣቱንም ገልጿል። ኢትዮጵያ የተሻለች፣ የበለጸገች እና በቴክኖሎጂ ራሷን የቻለች ሀገር ለማድረግ ዛሬ እየተሰሩ ያሉ ሥራዎች የሀገሪቱን የነገ ብሩህ ተስፋ እያለመለሙ በመሆኑ መጠናከር እንዳለባቸው ተናግሯል።
የሞጆ ሎጂስቲክስ ማዕከል የኢትዮጵያ የብልፅግና ጉዞ ማብሰሪያ፣ የቀጣናው ማስተሳሰሪያ እና የመደመር እሳቤ ፍሬ ማሳያ ነው
Sep 10, 2026 172
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ የሞጆ ሎጂስቲክስ ማዕከል የኢትዮጵያ የብልፅግና ጉዞ ማብሰሪያ፣ የቀጣናው ማስተሳሰሪያ እና የመደመር እሳቤ ፍሬ ማሳያ መሆኑን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሞጆ የሎጂስቲክስ ማዕከል ማስፋፊያ መርቀው በይፋ ሥራ አስጀምረዋል። በመርሀ ግብሩ ላይ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ፣ የኢፌዴሪ ጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ የሞጆ የሎጂስቲክስ ማዕከል የሀገራችን የደም ስር ነው። የትራንስፖርትና የሎጂስቲክስ አገልግሎት ችግሮችን መፍታት የሚያስችል የማዕዘን ድንጋይ መሆኑን ገልጸዋል። ማዕከሉ የሁለንተናዊ ልማትና ብልፅግና ማረጋገጫ የመደመር መንግሥት ስኬት አይነተኛ ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዘርፉን ማነቆ በተመለከተ የሰጡት አቅጣጫ ፍሬ ማፍራቱ ማሳያ ነው ብለዋል። የሞጆ ሎጂስቲክስ ማዕከል የኢትዮጵያ የብልፅግና ጉዞ ማብሰሪያ፣ የቀጣናው ማስተሳሰሪያ እና የመደመር እሳቤ ፍሬ መሆኑን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ የአፍሪካ የሎጂስቲክ ማዕከል እናደርጋታለን ያሉት ቃል በተግባር እውን እንዲሆን ያስችላል ያሉት ሚኒስትሩ፤ በማዕከሉ ሁለት የባቡር መስመሮች መዘርጋታቸውን ተናግረዋል። የወጭና ገቢ ንግድ ዕቃዎችን የሚያስተናግዱ መጋዘኖች የያዘና በአንድ ጊዜ በርካታ የጭነት አገልግሎት መስጠት ያስችላል ብለዋል። አርሶ አደሮች ምርታቸው ሳይበላሽ ለውጭ ገበያ ማቅረብ የሚችሉበትን ዕድል መፍጠሩን ተናግረዋል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
የመንግስታዊ አገልግሎቶችን በማዘመን የህዝብን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቷል
Sep 10, 2026 213
ድሬዳዋ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ የመንግስታዊ አገልግሎቶችን በማዘመን የህዝብን የልማትና የመልካም አስተዳደር ተጠቃሚነት በላቀ ደረጃ ለማሳደግ ትኩረት መሰጠቱን የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ገለጹ። ጳጉሜን 5 "የነገ ቀን" በሚል ስያሜ በድሬዳዋ አስተዳደር በፈጠራና በቴክኖሎጂ ዘርፍ የተመዘገቡ እምርታዎችን የሚያመላክት የፓናል ውይይትና በአውደ ርዕይ ተካሂዷል። ከንቲባ ከድር ጁሃር በወቅቱ እንደተናገሩት፣ የዲጂታል መሠረተ ልማቶችን ተደራሽ በማድረግ የነገዋን ታላቅ አገር የመገንባቱ ጉዞ በተጨባጭ ውጤቶች እውን እየሆነ ነው። የተሻለች እና የበለፀገች አገር ለትውልድ ለማስረከብ በየደረጃው የሚደረገው ርብርብ ተጠናክሮ መቀጠሉንም ከንቲባው ተናግረዋል። በተለይ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ክህሎትን የጨበጠ የሲቪል ሰርቪስ ሠራተኛ በመገንባት ፈጣንና ቀልጣፋ የመንግስት አገልግሎቶችን ተደራሽ በማድረግ የነዋሪውን የልማት እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ እየተመለሰ መሆኑን ገልጸዋል። ባለፈው አንድ ዓመት በከተማ አስተዳደሩ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እየተሰጡባቸው ባሉ አከባቢዎች አዎንታዊ ለውጦች እየተመዘገቡ መሆናቸውን ለአብነት አንስተዋል። በአስተዳደሩ ዲጂታል የአሰራር ሥርዓትን በላቀ ደረጃ ለማሳደግ በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች፣ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ እና በግል ተቋማት የተጀመሩ የፈጠራና የቴክኖሎጂ የምርምር ሥራዎች የነገዋን ታላቅ አገር ለመገንባት መደላድል እየፈጠሩ ይገኛሉ ብለዋል። በድሬዳዋ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ዘመናዊ፣ ቀልጣፋና ከሙስና የፀዳ አገልግሎት በመስጠት የተገልጋይ እርካታን ለማሳደግ የተጀመሩ ስራዎች ይጠናከራሉ ብለዋል። የነገ ቀን በድሬዳዋ ሲከበር ከመድረክ በተጨማሪ በአረጋዊያን መጦሪያ ማዕከል ለሚገኙ አቅመ ደካሞች ከንቲባው ማዕድ ያጋሩ ሲሆን የድሬዳዋ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራርም ተጎብኝቷል። በስነስርዓቱ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈጉባኤ አብዲ ሙክታር፣ በብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ፣ የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች፣ የኃይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።
ዲጂታል ኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማሳደግ አገልግሎት አሰጣጥና የሥራ ዕድል እያሰፋ ነው
Sep 10, 2026 181
ጅግጅጋ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ) ፦ዲጂታል ኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማሳደግ አገልግሎት አሰጣጥን እያቀላጠፈና የሥራ እድልን እያሰፋ መሆኑን የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ኡስማን ገለጹ። የጳጉሜን 5 "የነገ ቀን" በሚል ስያሜ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች እየተከበረ ሲሆን በሶማሌ ክልል ደረጃም ቀኑ በጂግጂጋ ከተማ በተለያዩ ዲጂታል የንቅናቄ መርሃ-ግብሮች ተከብሯል። በመርሃ-ግብሩ ላይ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም እንደገለጹት፤ በክልሉ በቴክኖሎጂና በሰው ኃይል ልማት ላይ በስፋት በመስራት ሁለንተናዊ እድገትን በዘላቂነት ለማስመዝገብ እየተሰራ ነው። በተለይ ዲጂታል አገልግሎትን በማስፋፋት ለአገልግሎት አሠጣጥ፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራና ለክልሉ የኢኮኖሚ አቅም መጠናከር ትኩረት ተሰጥቶ በመሰራቱ አበረታች ውጤቶች ተገኝቷል ብለዋል። ዲጂታል ኢትዮጵያን ማረጋገጥ በቴክኖሎጂ፣ በፋይናንስ፣ በትራንስፖርትና በሌሎችም ዘርፎች አሰራርን በማዘመን ለቀጣይ ትውልድ የተሻለች ሀገር ለማስረከብ ከፍተኛ ድርሻ እንዳለውም አስረድተዋል። ለዚህም ስኬት የተቋማት የማስፈጸም አቅምን መገንባት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸው፣ በክልሉ ተቋማትን በቴክኖሎጂ አቅርቦትና በሰው ኃይል የማደራጀት ሥራው ትኩረት እንደተሰጠው ገልጸዋል። ለአብነትም በክልሉ የመንግሥት አገልግሎቶችን ለማቀላጠፍ 13 መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫዎች መገንባታቸውን ጠቁመዋል። ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ እንዳሉት መንግሥት ለዲጂታል መሠረተ ልማት ግንባታ ዘርፍ የሠጠው ልዩ ትኩረት የነገን የሀገሪቱን አድገት ለማፋጠን የሚያግዝ ነው። በዲጂታል ዘርፍ የኢትዮ ኮደርስ፣ የስታርትአፕ እና የዲጂታል ክህሎት ንቅናቄዎች የዜጎችን አቅም በመገንባት ረገድ ምቹ ሁኔታ እየፈጠሩ ይገኛሉ ሲሉም ገልጸዋል የክልሉ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ መሀመድ አሊ በበኩላቸው እንዳሉት ፤ በክልሉ የዲጂታልና የፈጠራ ክህሎትን ለማዳበር ዘርፈ ብዙ ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ። በተለይም በክልሉ በስፋት እየተሰጠ ያለው የ“ኢትዮ ኮደርስ” ሥልጠና የወጣቶችን ቴክኖሎጂ የመጠቀም አቅም በከፍተኛ ደረጃ እያሳደገው መሆኑን ተናግረዋል። ይህም ቴክኖሎጂን ጥቅም ላይ በማዋል የመንግሥትን አገልግሎቶች ለማዘመን ፣ የስራ ዕድል ለመፍጠርና የሀገርን ልማት በማፋጠን በኩል ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው አስገንዝበዋል። በጅግጅጋ ከተማ በተካሄደው በዚህ መርሃ - ግብር ላይ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ ባለድርሻ አካላት፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ ወጣቶችና የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።
የቴክኖሎጂ ልማትና ተጠቃሚነትን የማጠናከር ጉዳይ የነገ መዳረሻን ለመወሰን የሚያስችል ቁልፍ ተግባር ነው
Sep 10, 2026 95
ባህርዳር ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ የቴክኖሎጂ ልማትና ተጠቃሚነትን የማጠናከር ጉዳይ የነገ መዳረሻን ለመወሰን የሚያስችል ቁልፍ ተግባር መሆኑን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ገለጹ። ጳጉሜን 5 (የነገ ቀን) የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደን ጨምሮ ሌሎችም ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች በተገኙበት ተከብሯል። በመርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ፤ የቴክኖሎጂ ልማትና ተጠቃሚነትን የማጠናከር ጉዳይ የነገ መዳረሻን ለመወሰን የሚያስችል ቁልፍ ተግባር መሆኑን ገልጸዋል። የዛሬ ችግሮቻችን በጋራ በመፍታት የነገውን መዳረሻችንን የምንተልምበት ጊዜው አሁን ነው ያሉት ርእሰ መስተዳድሩ በተለይም ቴክኖሎጂን መፍጠር፣ በመቅዳትና በስፋት መጠቀም ይገባናል ብለዋል። በተጨማሪም ማህበረሰባዊ ካፒታልን፣ ገንዘብን፣ የአካባቢ ጸጋን በማልማት ጥቅም ላይ የማዋል ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ሲሉ ተናግረዋል። የክልሉ ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ባንችዓምላክ ገብረማርያም፤ የዲጂታል ሲቪል ሰርቪስ ግንባታን ዕውን በማድረግ ነገን የተሻለ ለማድረግ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል። በዲጂታል ኢትዮጵያ ትግበራዎች ውስጥ አንዱ የሆኑው የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ለዚህ ጥሩ ማሳያ መሆኑን አንስተው ይበልጥ የማስፋትና ተደራሽነቱን የማብዛት ስራ ይሰራል ብለዋል።
በአፋር ክልል ዲጂታል አገልግሎትን የማስፋፋት ቅንጅታዊ ተግባራት ይጠናከራሉ
Sep 10, 2026 315
ሰመራ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ዲጂታል አገልግሎትን በማስፋፋት የህዝብ እርካታ ለማሳደግ የተጀመሩ ቅንጅታዊ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የአፋር ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የመሬት ቢሮ ኀላፊ አቶ ኡመር ኑር ተናገሩ። የጳጉሜን 5 "የነገው ቀን" በአፋር ክልል ሠመራ ከተማ "ለተቀናጀ አገልግሎት ወደ ዲጂታል መንግሥት" በሚል መሪ ቃል፣ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በተለያዩ መርሃ ግብሮች ድምቀት ተከብሯል። በዕለቱ የተገኙት የአፋር ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የመሬት ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡመር ኑር እንዳሉት፤ "የነገ ቀን" ሲከበር በዲጂታል አሰራር የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን በማቀላጠፍ የህዝብ እርካታን ለማሳደግ ቁርጠኝነትን በማሳየት መሆን አለበት። በክልሉ የተቀናጀ የዲጂታል አገልግሎትን በመተግበር የመንግሥት አገልግሎት ጥራትንና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ልዩ ትኩረት መሰጠቱን አመልክተዋል። በተደመረ አቅምና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ታግዞ የሥራ ዕድል ፈጠራና ሀገራዊ ዕድገትን ለማፋጠን በአብሮነትና በቁርጠኝነት መንቀሳቀስ ወሳኝ መሆኑንም በአፅንኦት ገልጸዋል። ዲጂታል አገልግሎትን በማስፋፋት የህዝብ እርካታን ለማሳደግ የተጀመሩ ቅንጅታዊ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸው፣ በዚህም የነገን ቀን የተሻለ ለማድረግ ይሰራል ብለዋል። የክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ መሐመድ አህመድ በበኩላቸው፤ በክልሉ በዲጂታል የታገዘ የመንግስት አገልግሎት በስፋት እየተተገበረ መሆኑን ገልጸው፣ ይህም የበለጸገችና ጠንካራ ሀገርን ለመገንባት ተጨማሪ አቅም ይፈጥራል ብለዋል። በክልሉ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን በማስፋፋት ቀልጣፋና ዘመናዊ አሠራር መዘርጋት መቻሉን ጠቁመዋል። በዲጂታል የታገዘ ዘመናዊ አሰራር መተግበሩ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚታዩ ህገ-ወጥና የተዝረከረኩ አሠራሮችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት ከፍተኛ አቅም ፈጥሯል ብለዋል። በክልል ደረጃ የሚሰጡ ማናቸውም አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ መታገዛቸው ውጤታማ ተግባራት ለማከናወን እያስቻለ መሆናቸውን ጠቁመዋል። የ"ነገው ቀን" አከባበር መርሃ ግብር ላይ የሴክተር መሥሪያ ቤቶች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎችና የመንግሥት ሠራተኞች ተገኝተዋል።
ስፖርት
ማንችስተር ዩናይትድ እና ባየር ሙኒክ ድል ቀንቷቸዋል
Sep 11, 2026 87
አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ትናንት ማምሻውን አራት ጨዋታዎች ተካሄደዋል። በኦልትራፎርድ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ማንችስተር ዩናይትድ ሳባህን 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል። ማትያስ ኩንያ፣ ብሩኖ ፈርናንዴዝ፣ ቤንጃሚን ሼሽኮ እና ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ ግቦቹን አስቆጥረዋል። ባለሜዳው ማንችስተር ዩናይትድ ብልጫ ወስዶ ተጫውቷል። የአዘርባጃኑ ሳባህ በውድድሩ ላይ ሲሳተፍ የአሁኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። በሌላኛው መርሐ ግብር ባየር ሙኒክ ቦዶ ግሊምትን 5 ለ 0 ረትቷል። ማይክል ኦሊሴ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ጀማል ሙሲያላ፣ ሃሪ ኬን እና አልፎንሶ ዴቪስ ቀሪዎቹን ጎሎች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። የጀርመኑ ክለብ በመጀመሪያ አጋማሽ ከተጋጣሚው ፈተና ቢገጥመውም በሁለተኛው ክፍለ ጊዜ ግቦቹን በማስቆጠር ማሸነፍ ችሏል። በሻምፒዮንስ ሊጉ ለመጀመሪያ ጊዜ እየተሳተፈ የሚገኘው የጣልያኑ ክለብ ኮሞ አርቢ ላፕዚግን 4 ለ 1 አሸንፏል። ሌንስ ስላቪያ ፕራግን 3 ለ 2 ማሸነፍ ችሏል። ትናንት አስቀድመው በተደረጉ ጨዋታዎች ፊነርባቼ ከሮማ ፣ ፒኤስቪ ከሻካታር ዶኔስክ በተመሳሳይ አንድ አቻ ተለያይተዋል። ጨዋታዎቹን ተከትሎ የመጀመሪያ ዙር መርሐ ግብር ተጠናቋል። ሁለተኛ ዙር የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች በጥቅምት ወር 2019 ዓ.ም መግቢያ ይካሄዳሉ።
ፊነርባቼ ከሮማ፣ ፒኤስቪ ከሻካታር ዶኔስክ ያደረጓቸው ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀቁ
Sep 10, 2026 209
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሊግ ምዕራፍ ጨዋታዎች መካሄዳቸውን ቀጥለዋል። ማምሻውን በሱክሩ ሳራኮግሉ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ፊነርባቼ እና ሮማ ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል። አርቺ ብራውን ለፊነርባቼ፣ ብራያን ክሪስታንቴ ለሮማ ግቦቹን አስቆጥረዋል። በፊሊፕስ ስታዲየም በተደረገው ሌላኛው መርሐ ግብር ፒኤስቪ አይንድሆቨን ከሻካታር ዶኔስክ አንድ አቻ ተለያይተዋል። ሰርጂኖ ዴስት ለፒኤስቪ ግቧን ሲያስቆጥር ግሊከር ሜንዶዛ የሻካታርን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ባየር ሙኒክ ከቦዶ ግሊምት እና ማንችስተር ዩናይትድ ከሳባህ: የዕለቱ ተጠባቂ መርሐ ግብሮች
Sep 10, 2026 156
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ):- የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሊግ ምዕራፍ የመጀመሪያ ዙር መርሐ ግብር ዛሬ ይጠናቀቃል። ባየር ሙኒክ የኖርዌውን ቦዲ ግሊምት ምሽት አራት ሰዓት ላይ በአሊያንዝ አሬና ስታዲየም ያስተናግዳል። የስድስት ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ባለቤቱ ባየርን ባለፈው የውድድር ዓመት እስከ ግማሽ ፍጻሜ ደርሷል። በሻምፒዮንስ ሊጉ የሊግ ምዕራፍ ለሁለተኛ ጊዜ የሚሳተፈው ቦዶ ግሊምት ባለፈው የውድድር ዓመት 16 ውስጥ ገብቷል። ቦዶ ግሊምት በጉዞው ማንችስተር ሲቲ፣ አትሌቲኮ ማድሪድ እና ኢንተር ሚላን ያሸነፈበት መንገድ በእግር ኳስ አፍቃሪያን አድናቆት አስችሮታል። በዛሬውም ጨዋታም ሙኒክን ይፈትነዋል ተብሎ ይጠበቃል። በሌላኛው መርሐ ግብር ማንችስተር ዩናይትድ ከሳባህ ምሽት አራት ሰዓት ላይ በኦልድትራፎርድ ስታዲየም ይጫወታሉ። የሶስት ጊዜ የሻምፒዮንስ ሊግ ሻምፒዮኑ ማነችስተር ዩናይትድ ከእ.አ.አ 2023/24 የውድድር ዓመት በኋላ ወደ አውሮፓ መድረክ ተመልሷል። እ.አ.አ በ2017 የተመሰረተው የአዘርባጃኑ ሳባህ ለመጀመሪያ ጊዜ በሻምፒዮንስ ሊጉ ተሳትፎ ያደርጋል። በሌሎች መርሐ ግብሮች በሻምፒዮንስ ሊጉ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሳተፈው የጣልያኑ ኮሞ ከአርቢ ላይፕዚግ እና ስላቪያ ፕራግ ከሌንስ በተመሳሳይ ምሽት አራት ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። ፊነርባቼ ከሮማ እና ፒኤስቪ አይንድሆቨን ከሻካታር ዶኔስክ በተመሳሳይ ምሽት 1 ሰዓት ከ45 ላይ ይጫወታሉ።
ባርሴሎና ሻምፒዮንስ ሊጉን በድል ጀምሯል
Sep 10, 2026 210
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ባርሴሎና ፌይኖርድን 5 ለ 1 ረትቷል። ማምሻውን በካምፕ ኑ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ራፊንሃ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ላሚን ያማል፣ ካሪም አዲዬሚ እና ጋብርኤል ጄሱስ ቀሪዎቹን ጎሎች ለባርሳ ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። ሴም ስቴጅን ለፌይኖርድ ብቸኛውን ግብ አስቆጥሯል። በጨዋታው ባርሴሎና ፍጹም የበላይነት ወስዷል። የባርሴሎናው አምበል ራፊንሃ በዘንድሮው የውድድር ዓመት ያስቆጠራቸውን ጎሎች ብዛት ስምንት አድርሷል። የካታላኑ ክለብ ዘንድሮ ያደረጋቸውን አምስት ጨዋታዎች ያሸነፈ ሲሆን 22 ጎሎችን ከመረብ ጋር አገናኝቷል። ቡድኑ በጠንካራ ጅማሮው ቀጥሏል። በሌላኛው መርሐ ግብር ስቱትጋርት ቫይኪንግን 3 ለ 1 አሸንፏል። በኤምኤችፒ አሬና በተደረገው ጨዋቻ ኤርሜዲን ዴሚሮቪች ሶስት ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ ሰርቷል። የ28 ዓመቱ ቦስኒያዊ አጥቂ በዘንድሮው ሻምፒዮንስ ሊግ ሀትሪክ የሰራ የመጀመሪያ ተጫዋች ሆኗል። ዝላትኮ ትሪፒች ለኖርዌው ክለብ ብቸኛውን ጎል አስቆጥሯል።
አካባቢ ጥበቃ
በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ስኬታማ ሥራ ተከናውኗል
Sep 10, 2026 137
የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር በ2011 ዓም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት በይፋ መጀመሩ ይታወቃል። መርሃ ግብሩ እንደ ሀገር ያጋጠሙ በርካታ የዘላቂ ልማት ተግዳሮቶችን የመሬት መጎሳቆል የደንና ብዝሃ ህይወት መጨፍጨፍ፣ የውሃ አካላትን መድረቅና በደለል መሞላት ለመከላከል ታስቦ ወደ ሥራ መገባቱ ይታወቃል። በዚህም በመጀመሪያው ምዕራፍ 50 ቢሊዮን ችግኝ በማህበረሰብ ተሳትፎ ለመትከል ታቅዶ ነበር። ኢትዮጵያ ባለፉት ስምንት የመርሃ ግበሩ የትግበራ ዓመታት 56 ነጥብ 8 ቢሊዮን ችግኞችን፤ በዚህ ዓመት ብቻ ደግሞ 8 ነጥብ 2 ቢሊዮን ችግኝን በመትከል በዓለም ላይ አዲስ ታሪክ ፅፋለች። አጠቃላይ ከተተከሉ ችግኞች ከ3 ቢሊዮን በላይ የሚሆኑት በአንድ ጀምበር የተተከሉ መሆናቸው በዓለም ላይ ትልቅ የችግኝ ተከላ ሆኖ ተመዝግቧል። ከተተከሉ ችግኞች 60 በመቶ የሚሆኑት የጥምር ደን ግብርና (የፍራፍሬ፣ የቡና፣ የመኖ ዝርያዎች) ሲሆኑ 35 በመቶ የደን ዝርያ ናቸው። ይህ ታላቅ የልማት ድል የተሳካው ከላይ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እስከ ታችኛው የመንግስት አደረጃጀት ለመርሃ ግብሩ በተሰጠው ቁርጠኛ አመራር ነው። በየዓመቱ ከ25 ሚሊየን በላይ ዜጎች በችግኝ ተከላ ተሳትፈዋል። እስካሁን በተሠራው ሥራ በየዓመቱ ይፈጸም የነበረው የደን ጭፍጨፋ ከ92 ሺህ ወደ 27 ሺህ ሄክታር እንዲቀንስ አስችሏል። በእርሻ ማሳ የአፈር መከላት በዓመት በሄክታር ከ130 ቶን ወደ 54 ቶን ቀንሷል። አረንጓዴ ዐሻራ በየዓመቱ ወደ ውሃ አካላት የሚገባ የአፈር ደለል ከ1 ነጥብ 9 ቢሊዮን ቶን ወደ 208 ሚሊዮን ቶን ዝቅ እንዲል አስችሏል። በመርሃ ግብሩ ለ2 ነጥብ 6 ሚሊዮን ወጣቶችና ሴቶች አረንጓዴ ሥራ ተፈጥሮላቸዋል። በበርካታ አካባቢዎች የፍራፍሬና የደን ክላስተር እየተፈጠረ አርሶ አደሮች የላቀ የኢኮኖሚ አቅም እንዲገነቡ እያስቻለ ነው። ኢትዮጵያ ግዙፍ የልማት መርሃ ግብር ቀርጻ መተግበር እንደምትችል ትልቅ ተሞክሮ የተወሰደበትና ለዓለም ያሳየችበትም ነው። ከዚህም ባለፈ ሀገራችን ዓለም እየተፈተነችበት ላለው የአየር ንብረት ለውጥ ተግባራዊ መፍትሔ በመስጠት ምሳሌ መሆኗን ያሳየችበት ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ማጠናቀቂያ የችግኝ ተከላ አካሄዱ
Sep 10, 2026 125
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ):- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ማጠናቀቂያ የችግኝ ተከላ አካሂደዋል። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት እንደገለጸው በዘንድሮው ዓመት «ተስፋን እንትከል» በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ የነበረውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ማጠናቀቂያ ነው የችግኝ ተከላ ያካሄዱት። የ2018 ዓ.ም የችግኝ ተከላ መጠናቀቅን ስናበስር የተተከለው እያንዳንዱ ችግኝ የሕብረታችን፣ የሕዳሴያችንና የዘላቂ እድገታችን ሕያው ምልክት መሆኑን በማስታወስ መሆኑንም አስታውቋል። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በጽኑ አንድነታችንና በጋራ ጥረታችን የታነጸች፣ የበለጸገችና ብሩህ ኢትዮጵያን ለማየት ሙሉ ተስፋ ሰንቀን ወደፊት እንገሰግሳለን ሲልም መልእክት አስተላልፏል።
የአየር ንብረት ለውጥ በማኅበረሰብ ጤና ላይ ሊያሳድር የሚችለውን ተፅዕኖ ለመከላከል የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው
Sep 9, 2026 181
አዲስ አበባ ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦የአየር ንብረት ለውጥ በማኅበረሰብ ጤና እና ስነ-ምግብ ላይ ሊያሳድር የሚችለውን ተፅዕኖ ለመከላከል የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሳይ ሀይሉ ገለጹ። የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኢትዮጵያ አረንጓዴ ዐሻራ መርሀ ግብር በጤና እና በስነ-ምግብ መጠበቅ ላይ ያለውን ሚና በተመለከተ የምርምር ጉባኤ የዘርፉ ተዋናዮች በተገኙበት እያካሄደ ይገኛል። ዶክተር መሳይ ሀይሉ በመድረኩ እንደተናገሩት፤ ከተለያዩ የህብረተሰብ ጤና ፈተናዎች መካከል ከውሃ ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች እንደሚገኙበት ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን ለመሻገር እየወሰደቻቸው ያሉ የፖሊሲ እርምጃዎች ትልቅ ሚና አላቸው ብለዋል። ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር በቢሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞችን መትከሏ ተስማሚ የአካባቢ አየር ንብረት እንዲኖር አድርጓል ብለዋል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ አረንጓዴ ትራንስፖርትን ለማበረታታት የወሰደቻቸው የፖሊሲ እርምጃዎች የአየር ብክለትን በመቆጣጠር የማኅበረሰብን ጤና ለመጠበቅና ስነ-ምግብን ለማሻሻል የራሳቸው አበርክቶ እንዳላቸው ገልጸዋል። ኢንስቲትዩቱ በአረንጓዴ ልማት ላይ የሚሰሩ ስራዎችን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ በማጥናት የደን ልማትና ንጹህ መጓጓዣ የመፍጠር እርምጃዎች ከአየር ንብረት ጋር ተያያዥነት ያላቸውን የበሽታ ጫናዎች እንደሚቀንሱ፣ የአየር ጥራትን እንደሚያሻሽሉ እና የስነ-ምግብ ክትትልን እንዴት እንደሚያጠናክሩ በጥናት የማረጋገጥ ስራ እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል። ኢንስቲትዩቱ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የሚሰሩ ስራዎች በጤናው ዘርፍ ያላቸውን አበርክቶ በምርምር ስራዎች ለመፈተሽና በቀጣይ በሚሰሩ ተግባራት ላይ ከተለያዩ ተቋማት ጋር ያለውን የትብብር ስራ ለማጠናከር መድረኩ መዘጋጀቱን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፈጠነ ተሾመ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ተቋሙ በመረጃ ላይ የተመሰረቱ የአየር ፀባይ ትንበያዎችን በመተንተንና በማደራጀት ለጤናው ዘርፍና ለልዩ ልዩ ጥቅሞች እንዲውሉ ተደራሽ እያደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ኢንስቲትዩቱ ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የተገናኙ መረጃዎችን በመለዋወጥ የማህበረሰብ ጤና እንዲጠበቅ ትብብሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። ለበሽታ ክትትል፣ ለአደጋ ዝግጁነት እና ለቅድመ ማስጠንቀቂያ የሚረዱ የአየር ንብረት መረጃዎችን በወቅቱና በቀጥታ ለማድረስ ተግቶ ይሰራል ነው ያሉት።
የኢትዮጵያውያን ኅብር በውጤት የተገለጠበት - አረንጓዴ አሻራ
Sep 9, 2026 229
(በሙሴ መለሰ) ኢትዮጵያ ባለፉት አሥርት ዓመታት የደን መመናመን፣ የአፈር መሸርሸር፣ የለም መሬት እየቀነሰ መምጣት እና ተደጋጋሚ ድርቅን ጨምሮ እጅግ አስቸጋሪና ተደራራቢ የአየር ንብረት ለውጥ ፈተናዎች ይገጥሟት ነበር። ይህ የስነ-ምህዳር መዛባት በሚሊዮን የሚቆጠሩ አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮችን ህይወትና የምግብ ዋስትና አደጋ ላይ ጥሎት ቆይቷል። በተለይም በቆላማ እና ከፊል አርብቶ አደር በሆኑት የሀገሪቱ አካባቢዎች የውሃ ምንጮች መድረቅ እና የግጦሽ መሬቶች መውደም ሰብአዊ ህይወቶችንና የቁም እንስሳትን ለአደጋ አጋልጧል። የብዝሃ ህይወት መመናመን ሌላኛው ፈተና ተደርጎ የሚወሰድ ሲሆን፣ ይህ የተፈጥሮ ሀብት መመናመን በሀገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገትና ልማት ጎዳና ላይ ትልቅ ተግዳሮት ሆኖ ቆይቷል። ኢትዮጵያ ይሄን የአየር ንብረት ለውጥ በዘላቂነት ለመከላከል እና የተፈጥሮ ሀብትን ለመጠበቅ ከቃል ያለፈ የተግባር ስራ ከጀመረች ዓመታት ተቆጥረዋል። የዚህ ሀገራዊ ስራ አበይት መገለጫ ከሆኑ ብሔራዊ ኢኒሼቲቮች መካከል “አረንጓዴ አሻራ” ተጠቃሽና ግንባር ቀደም መርሃ ግብር ነው። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት በ2011 ዓ.ም የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር፣ የደን መመናመንን ለመግታትና ሥነ-ምህዳርን ለመመለስ የተጀመረ ታላቅ ሀገራዊ ንቅናቄ ነው። ይህ ስራ ዛፍ የመትከል ዘመቻ ብቻ ሳይሆን፣ ኢትዮጵያውያን በአንድነትና በህብር በመቆም በጋራ የሰሩበት ታላቅ ህብረተሰባዊ አቅም የታየበት ማረጋገጫም ሆኗል። ሀገሪቱ እ.አ.አ በ2027 የሚካሄደውን ታላቁን የዓለም አቀፍ አየር ንብረት ጉባኤ (ኮፕ 32) በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ እንድታስተናግድ መመረጧ፣ በአረንጓዴ ልማት ያሳየችው የህብርና የአንድነት ጉዞ ያስገኘው ትልቅ ዓለም አቀፋዊ ድል ነው። በአረንጓዴ አሻራ ስኬት ትልቁ መገለጫ የህዝቦች የጋራ ትብብር እና ተደጋግፎ መስራት መሆኑን በተግባር ለማሳየት ተችሏል። የኢትዮጵያ የደን ሽፋን በ2010 ዓ.ም ከነበረበት 17.2 በመቶ በጥቂት ዓመታት ውስጥ ማለትም በ2017 ዓ.ም ወደ 23.6 በመቶ ማደግ ችሏል። እስካሁን ከ54 ቢሊዮን በላይ ችግኞች የተተከሉ ሲሆን፣ በየዓመቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች በአንድነት በመሳተፍ ለአየር ንብረት ተጋላጭ የነበሩ አካባቢዎች አረንጓዴ ለብሰው እንዲለወጡ አድርገዋል። በብራዚል ቤለም በተካሄደው 30ኛው የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ የአፍሪካ ተደራዳሪዎች ቡድን ኢትዮጵያን የኮፕ 32 አስተናጋጅ አድርጎ በሙሉ ድምፅ መምረጡ የህብር እና የአንድነት ውጤት ነው። የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ስኬት የተለካው ችግኝ በመትከል ብቻ ሳይሆን፣ ህዝብና መንግስት በህብር ተክሎ የማሳደግና የመንከባከብ ባህልን በማዳበር ሲሆን የተተከሉ ችግኞች የመጽደቅ ምጣኔ ከ85 በመቶ በላይ ሆኗል። ይህ ሂደት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ከአቮካዶ፣ ማንጎና ፓፓያ የመሳሰሉ የፍራፍሬ ችግኞች መተከል ጋር ተያይዞ የግብርና ምርታማነትን ያሳደገ ሲሆን፣ ለብዙ ዜጎች የሥራ ዕድል ፈጥሯል። መርሃ-ግብሩ ከደን ዛፍ ችግኝ ባለፈ የምግብ እና የከተማ ውበት መሰረት የሆኑትንም ያካተተ በመሆኑ ውጤቱን የላቀ አደርጎታል። የግብርና ምርታማነት እንዲጨምርም ጉልህ አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል። አረንጓዴ አሻራ የአየር ንብረት ለውጥን ለመዋጋት የተደረገ የአካባቢ ጥበቃ ስራ ብቻ ሳይሆን፣ ሕዝቦች በአንድነትና በህብር ሲሰለፉ ሀገራቸውንና መልክዓ ምድራቸውን መቀየር እንደሚችሉ ለዓለም ያሳዩበት ታላቅ ማረጋገጫ ነው።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
አፍሪካ በዓለም ፊት ቦታ ለማግኘት አትማጸንም ፤ ይልቁንም የሚገባትን ስፍራ በባለቤትነት እየያዘች ነው
Sep 9, 2026 176
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ):- አፍሪካ በዓለም ፊት ቦታ ለማግኘት አትማጸንም ፤ የሚገባትን ስፍራ እና ክብር በራሷ እያረጋገጠች ነው ሲሉ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። የአፍሪካ ህብረት ቀን ዛሬ እየተከበረ ይገኛል። የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ቀኑን በማስመልከት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ሊቀ መንበሩ የአፍሪካ ህብረት ቀን እ.አ.አ በ1999 የቀድሞ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ለመተካት ይፋዊ ውሳኔ የተላለፈበት የሰርጥ ድንጋጌ (Sirte Declaration) የሚታወስበት እንደሆነ ገልጸዋል። በዚያን ወቅት የአፍሪካ መሪዎች አህጉራዊ ትስስርን ለማፋጠን እና የአፍሪካን ድምጽ በዓለም አቀፍ መድረክ ከፍ ለማድረግ የአፍሪካ ህብረትን ለመመስረት ወሳኝ እና ታሪካዊ እርምጃ የወሰዱበት ምዕራፍ ነው ብለዋል። የዘንድሮው የአፍሪካ ህብረት ቀን ለአህጉሪቱ እጅግ ልዩ ትርጉም ባለው ወቅት ላይ እየተከበረ እንደሚገኝ አውስተዋል። ከጥቂት ቀናት በፊት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ የአፍሪካን እውነተኛ ቁመና እና ትክክለኛ መጠን የሚያሳይ የዓለም ካርታ አጠቃቀምን የሚደግፍ፣ በአፍሪካ መሪነት የቀረበ የውሳኔ ሀሳብ አፅድቋል። በቶጎ ሃሳብ አመንጪነትና በአፍሪካ ህብረት ድጋፍ እውን የሆነው ይህ እርምጃ ከቀላል የካርታ ማስተካከያ በላይ ትርጉም አለው ብለዋል ሊቀ መንበሩ። አፍሪካ በዓለም ፊት እንዴት እንደምትታይ ትኩረት የሚሰጠው መሆኑን እና አፍሪካ ራሷን የምትገመግምበትንና የምታሳይበትን ትርክት ራሷ መቅረጽ እንዳለባት አበክሮ የሚያስታውስ ነው። ይህ ውሳኔ አፍሪካ በዓለም ፊት በምን መልኩ መታየት እንዳለባት ከማሳየቱም በላይ፤ አፍሪካ ራሷን የምትመዝንበትንና እውነታዋን ለዓለም የምታሳይበትን ትርክት በራሷ መቅረጽ እንዳለባት በግልጽ የሚያሳይ መሆኑን ነው ያነሱት። የአፍሪካ እጣ ፈንታ የሚወሰነው በአፍሪካውያን የራሳቸው እይታ ነው። አፍሪካን በእውነተኛ ቁመናዋ፣ኃይሏ እና አቅሟ የምንመለከትበት ጊዜ አሁን ነው ብለዋል። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር አያይዘውም ካርታውን የማስተካከል እርምጃ አፍሪካ ወደ ላቀ የጋራ ራዕይ የምታደርገው አህጉራዊ ጉዞ አካል መሆኑን አንስተዋል። ይህም በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጠና (AfCFTA) አማካኝነት የኢኮኖሚ ትስስር ማጠናከርን፣ ሰላም እና ፀጥታን ማረጋገጥን፣ ዘላቂ ልማትን እውን ማድረግን እና በዓለም አቀፍ ውሳኔ ሰጪ አካላት ውስጥ የአፍሪካን ተሳትፎ ማሳደግን እንደሚያካትት በዝርዝር አስረድተዋል። የአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 የተሳሰረች፣ የበለጸገች እና ሰላማዊት አፍሪካን ለመገንባት የማዕዘን ድንጋይ ሆኖ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል። ሰላም እና ፀጥታን ማረጋገጥ፣ የኢኮኖሚ ትስስርን በማፋጠን እና የአፍሪካን ዓለም አቀፍ ተሰሚነት መጨመር የአፍሪካ ህብረት ቀዳሚ ትኩረቶች ናቸው ብለዋል። አፍሪካ በዓለም ፊት እውቅና ለማግኘት አትለምንም፤ ይልቁንስ በዓለም አቀፍ መድረክ የሷ የሆነውን ትክክለኛ ስፍራ በራሷ ባለቤትነት እየያዘች ነው። አሁን የሚጠበቅብን ይህንን ጠንካራ እምነት ወደ ህብረት፣ ሀብትና ብልጽግና፣ ሰላም እና ተደማጭነት መለወጥ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ሊቀመንበሩ አፍሪካ የምታስመዘግበው እድገት በዓለም አቀፍ መድረኮች በሚኖራት ውክልና ብቻ ሳይሆን፣ በዜጎቿ ላይ የኑሮ ጥራት መሻሻል ጭምር መለካት እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል። በዚህም መሰረት የአፍሪካ ህብረት የ2026 ዓመት ትኩረቱን በዘላቂ የንጹህ ውሃ አቅርቦት እና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አገልግሎት ላይ ማድረጉ፣ ህብረቱ አህጉራዊ ራዕዮችን ከዕለት ተዕለት የዜጎች ህይወት ጋር ለማያያዝ ያለውን ጽኑ ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ አመልክተዋል። በአፍሪካ ህብረት ቀን አከባበር አባል ሀገራት፣ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማህበረሰቦች፣ የአፍሪካ ተቋማት፣ የግሉ ዘርፍ፣ የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ ሴቶች እና ወጣቶች ተባብረው ይበልጥ የተሳሰረች፣ በራሷ አቅም የምትተማመን እና የራሷን እጣ ፈንታ በራሷ መወሰን የምትችል አፍሪካን እንዲገነቡ ሊቀመንበሩ ጥሪ አቅርበዋል። የምንፈልጋት አፍሪካ የሚለውን አህጉራዊ ራዕይ እውን ለማድረግ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ እና የሰርት ድንጋጌ ለቀጣዩ የአፍሪካ ትውልድ ዘላቂ የትምህርት እና የዕድገት መሰረት ሆኖ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። የነገዋ አፍሪካ በካርታ ላይ ብቻ የተሻለ ውክልና ያላት ብቻ ሳትሆን፤ በዓለም አቀፍ መድረክ ሉዓላዊነቷ የጸና፣ ጠንካራ ውስጣዊ አንድነት ያላት፣ ለህዝቦቿም ዘላቂ ብልጽግናን የምታጎናጽፍ አህጉር መሆን ይኖርባታል ነው ያሉት። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ለመላው አፍሪካውያን እና በውጭ ሀገር ለሚገኙ የአፍሪካ ዳያስፖራዎች ሰላማዊ እና የትብብር መንፈስ የተሞላበት የአፍሪካ ህብረት ቀን እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
የአፍሪካ ህብረት እና አሜሪካ አጋርነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ
Sep 4, 2026 468
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ)፡- የአፍሪካ ህብረት እና አሜሪካ ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን እና ሁሉን አቀፍ ትብብራቸውን የበለጠ ለማላቅ እንደሚሰሩ አስታወቁ። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሺያን ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። ውይይቱ በአፍሪካ ህብረትና አሜሪካ መካከል ያለውን ለረጅም ጊዜ የቆየ አጋርነት ማጠናከር እና በአህጉሪቱ ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር የአፍሪካና አሜሪካን ትብብር ታሪካዊ መሆኑን አውስተው በህብረቱ፣ በአባል ሀገራት እና በአሜሪካ መካከል የሁለቱንም ወገኖች ጥቅም በሚያስጠብቅ መልኩ ጠንካራ አጋርነት መገንባት እንደሚገባ አሳስበዋል። በምስራቅ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ሱዳን እየተደረጉ ላሉ አፍሪካ መር የሰላም ጥረቶች አሜሪካ እያደረገች ላለው ገንቢ አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሺያ በበኩላቸው አፍሪካ አሜሪካ ቀዳሚ ትኩረት የምትሰጣት አህጉር እንደሆነች ገልጸዋል። የጋራ ፍላጎቶችንና ግቦችን ከህብረቱ ኮሚሽንና ከአባል ሀገራት ጋር በመሆን ለማሳካት ያላቸውን ጽኑ ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል። በንግድ እና ኢንቨስትመንት፣ በመሰረተ ልማት ዝርጋታ፣ በዲፕሎማሲ፣ እንዲሁም በሰላምና ጸጥታ ያለውን ትብብር ማጠናከር እንደሚገባም አመልክተዋል። በውይይቱ ላይ በሱዳን ጉዳይ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ፣ የሰብአዊ እርዳታ ያለ ገደብ እንዲገባ እና በሲቪሎች የሚመራ ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ሂደት እንዲጀመር አጽንዖት ተሰጥቷል። በአፍሪካ ባለቤትነት የሚመሩ የሰላም ጥረቶች እና አሜሪካ የምትደግፋቸው የሰላም ሂደቶች በተቀናጀ መልኩ ለመተግበር ከስምምነት ላይ ተደርሷል። በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በመሰረተ ልማት እና በሰላም መስኮች የሁለቱን ወገኖች ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችሉ የትብብር መስኮች ተገምግመዋል። ሁለቱ ወገኖች በአፍሪካ ህብረትና በአሜሪካ ስትራቴጂክ ኢንቨስትመንት ማዕቀፍ ውስጥ የተደረጉ ስምምነቶችን ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። በሊቢያ ጉዳይ ዘላቂ የፖለቲካ መፍትሄ ማግኘት እንደሚያስፈልግም ተነስቷል። የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር እና ረዳት ሚኒስትሩ የሁለቱን ወገኖች ስትራቴጂካዊ አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከርና የትብብር አድማሱን ለማስፋት የጋራ ቁርጠኝነታቸውን መግለጻቸውን ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያ 76ኛውን የዓለም ጤና ድርጅት ስብሰባ ታስተናግዳለች
Aug 5, 2026 1775
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 29/2018 (ኢዜአ)፦ 76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ ስብሰባ (RC76) ከነሐሴ 18 እስከ 22 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። ስብሰባው ከዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ጽሕፈት ቤት ጋር በመተባበር የሚዘጋጅ ነው። በዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና መረጃ መሠረት፣ ስብስባው የቀጣናውን የጤና አጀንዳዎች ላይ መምከርና አህጉራዊ ትብብርን ማጠናከርን ያለመ ነው። የ47ቱ የአፍሪካ ቀጣና አባል አገራት የጤና ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ የዓለም አቀፍ ጤና መሪዎች፣ የልማት አጋሮች፣ ለጋሾችና የዓለም ጤና ድርጅት ተወካዮችን ጨምሮ ከ600 በላይ ተወካዮች በስብስባው ላይ ይሳተፋሉ። የስብሰባው ተሳታፊዎች በቀጣናዊ የጤና አቅዶች ላይ የተመዘገቡ ውጤቶችን የሚገመግሙ ሲሆን በአዳዲስ ስትራቴጂዎችና የውሳኔ ሀሳቦች ላይ ይመክራሉ። እንዲሁም የጤና ሥርዓቶችን ለማጠናከር፣ ሁለንተናዊ የጤና ሽፋን ተደራሽነትን ለማስፋፋት፣ የጤና ደህንነትን ለማሻሻልና የአደጋ ጊዜ ዝግጁነትን ለማሳደግ የሚረዱ የጋራ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። በኢትዮጵያ፣ በአፍሪካ ህብረትና በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) የዓለም ጤና ድርጅት ተወካይ ፕሮፌሰር ፍራንሲስ ካሶሎ፤ ስብሰባው አባል አገራት የቀጣናውን የጤና አጀንዳ እንዲቀርጹ፣ አጋርነታቸውን እንዲያጠናክሩ እና በመላው አፍሪካ ጤናማ፣ አስተማማኝና ጠንካራ ማህበረሰቦችን የመገንባት ሂደት ለማፋጠን ትልቅ እድል የሚሰጥ ነው ብለዋል። ተወካዩ አክለውም የኢትዮጵያ ስብሰባውን ማስተናገድ፤ ለቀጣናዊ ወንድማማችነትና ለጋራ ትብብር ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል። ይህ አህጉራዊ ጉባኤ የኢትዮጵያን የጤና ሥርዓት ስኬቶች፣ በተለይም መሰረታዊ የጤና አገልግሎቶችን በማስፋፋትና በቅርቡ በክልል የተከሰተውን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ተከስቶ የነበረውን የማርበርግ ቫይረስ በመቆጣጠር ረገድ የተመዘገቡ ውጤቶችን ለማሳየት ዕድል እንደሚፈጥር መረጃው አመልክቷል። ስብስባው የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) መቀመጫ የሆነችው አዲስ አበባ፣ የዲፕሎማሲ ማዕከልነቷን በመጠቀም ለጋራ የጤና ፈተናዎች የተቀናጀ አህጉራዊ ምላሽ ለመስጠት ስትራቴጂካዊ መድረክ እንድትሆን ያደርጋታል። በስብስባው ላይ የቴክኒክ ውይይቶች፣ አውደ ርዕዮች ፣ የሁለትዮሽ ስብሰባዎችና የሕዝብ ግንኙነት ስራዎች የሚካሄዱ ሲሆን፣ እነዚህም በአፍሪካ ተቋማት መካከል የጤናው ዘርፍ የፈጠራ ስራዎችንና የእውቀት ልውውጥን የሚያጎሉ እንደሚሆኑ ተገልጿል። የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ የቀጣናዊ ጽሕፈት ቤቱ የበላይ አካል ሲሆን፤ በየዓመቱ በመሰብሰብ የቀጣናውን የጤና ፖሊሲ ይወስናል፣ የድርጅቱን ሥራዎች ይገመግማል፣ እንዲሁም በመላው አህጉሪቱ ለሚከናወኑ የጤና ተግባራት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን አጀንዳዎች ያስቀምጣል።
ኢትዮጵያ የማዕድን ሀብቷን ቀጣዩ የኢኮኖሚዋ ምሰሶ እያደረገች ነው- ሲኤንኤን
Aug 4, 2026 1430
የሲኤንኤን ጋዜጠኛ ቪክቶሪያ ሩቢዳሪ በኢትዮጵያ ላይ በሚያተኩረው ዘገባዋ በሀገሪቱ ኮረብቶች ያለውን ወርቅ ጨምሮ ከፍተኛ የብረት ማዕድናት አምራች ለመሆን እያደረገች ያለውን ጥረት መመልከቷን ተናግራለች። በዘገባዋ ኢትዮጵያ በማዕድን ዘርፍ ከፍተኛ የሃይል ሚዛን መሆን እንደምትፈልግ ገልጻ፤በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኘው ኩርሙክ የወርቅ ፕሮጀክት በኢትዮጵያ የማዕድን ኢንቨስትመንቶች ውስጥ በዋናነት የሚጠቅስ መሆኑን ተናግራለች። በምዕራብ ኢትዮጵያ አረንጓዴ ከለበሱት ከፍተኛ የኮረብታ ስፍራዎች ላይ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ዶላሮችን የሚያስገኙ ከፍተኛ የወርቅ ሀብቶች እንዳሉ እና አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች ብቅ እያሉ መሆኑን ትናገራለች። በሺዎች የሚቆጠሩ የግንባታ ባለሙያዎች እና ማዕድን አውጪዎች በኢትዮጵያ ግዙፍ የሆነውን የወርቅ ማዕድን ፋብሪካ ግንባታ እያከናወኑ እንደሚገኝ ገልጻለች። በስፍራው የሚገኙ የማዕድን እና ጂኦሎጂ ባለሙያዎች የወርቅ ማዕድኑን የማጣራት ስራ እያከናወኑ መሆኑን ገልጻለች። ጋዜጠኛዋ የወርቅ ማጣራት እና ምርት ሂደቱን በተመለከተ ከባለሙያዎች ማብራሪያ ማግኘቷንም አመልክታለች። ወርቁን የማግኘት ሂደቱ እጅጉን ፈታኝ እና አድካሚ እንደሆነ ገልጻ፥ይሁንና ልፋቱ ትልቅ ጠቀሜታ የሚያስገኝ መሆኑን ተናግራለች። የወርቁን ግብአት ውጪ ሀገር ልኮ ከማጣራት ይልቅ በኩርሙክ የወርቅ ማዕድን ፋብሪካ የራሱ ማጣሪያ ፕላንት እንዳለው በጉብኝቷ ወቅት መረዳቷን አመልክታለች። የሲኤንኤኗ ጋዜጠኛ ቪክቶሪያ ሩቢዳሪ ወርቅ የሀገሪቷ ዋና የወጪ ንግድ ገቢ ምንጭ እየሆነ መምጣቱን ገልጻለች። ባለፈው ዓመት በወርቅ የተገኘው የወጪ ንግድ ገቢ ከፍተኛ መሆኑን ተናግራለች። ይህም የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ውጥኖች በግልጽ የሚያሳይና ኢትዮጵያ የማዕድን ሀብቷን ቀጣዩ የኢኮኖሚዋ ምሰሶ እያደረገች እንደምትገኝ ሲኤንኤን በዘገባው አስረድቷል።
ሐተታዎች
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የጥቁር ሕዝቦች የመቻል ተምሳሌት
Sep 9, 2026 171
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የጥቁር ሕዝቦች የመቻል ተምሳሌት መጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም የኢትዮጵያውያን የጋራ ቃል ኪዳን የታሰረባት ታሪካዊ ክስተት ናት። ዕለቷም የዓባይን የሺሕ ዘመናት ገደብ የሌለው ጉዞ በጉባ ተራሮች ግርጌ ልጓም ለማበጀት የታሰረች ቀለበት ሆና ተመዝግባለች። ኢትዮጵያውያን ቃል ኪዳናቸውን ባሰሩ ማግስት የግብፅና ሌሎች ታሪካዊ የኢትዮጵያ ጠላቶች ጩኸትና የጥፋት ሴራ በግልጽ መታየት ጀመረ። በተለይም ግብፅ ኢትዮጵያ ውስጣዊ መረጋጋት እንዳይኖራት የውስጥ ታጣቂዎችን ከመደገፍ ጀምሮ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በራፍ ጭምር የሀሰት ክሶችን እስከማሰማት የደረሰ የሺሕ ዘመናት ዓባይን በብቸኝነት የመጠቀም አባዜዋን አንጸባርቃለች። ትብብርን ከፅናት አሰናስለው የቀጠሉት ኢትዮጵያውያን ለአሥራ አራት ዓመታት የታላቁ ሕዳሴ ግድብን የማደናቀፍ የታሪካዊ ጠላቶችን ሴራ በጋራ በመመከት ለፍጻሜ አብቅተውታል። የሀገርን ሉዓላዊነት በጽናት የማስከበር የአርበኝነት ተጋድሎን ከዓድዋ ጀግኖች የወረስን እኛ ኢትዮጵያውያን በጉባ ተራሮች ግርጌ በደም፣ በላብ፣ በዕንባና በውኃ ጠብታ ታላቁ የሕዳሴ ግድብን በዓባይ ላይ አንጸናል። ጳጉሜን 4 ቀን 2017 ዓ.ም የአዲስ ዓመት ዋዜማም ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን በማጠናቀቅ ለፍጻሜ በማድረስ አብስሯል። ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሺሕ ዘመናት የልማት ጥማትን በማርካት የብልፅግና ፍኖት ብስራት ሆኗል። ታላቁ ሕዳሴ ግድብ ለሌላ የልማት ዕቅድ ወጋገን የፈነጠቀ የንጋት ሐይቅ ፈጥሯል። ግድቡ በኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝቦቿ ትብብር ብቻ ያለ አንዳች የውጭ ድጋፍና ብድር ለፍጻሜ መብቃቱም ለአፍሪካውያን የመቻል ትዕምርት ሆኗል። በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ብስራት በጉባ ተራሮች ግርጌ የከተሙ የምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ሀገራት መሪዎች የመሰከሩት ጥሬ ሐቅም ይህ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በምረቃው ዕለት እንደገለጹት፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የጥቁር ሕዝቦችን የታሪክ ክብር ያደሰና ለአፍሪካውያን የመቻል ውጤት ነው። በወቅቱም የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያን የብልፅግና ጎህ ያበሰረ፣ ቀጣናዊ የኃይል ትስስርና የጋራ ዕድገት መንገድ የጠረገ ፓን-አፍሪካኒዝም ፕሮጀክት መሆኑን መግለጻቸው ይታወሳል። የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅ አፍሪካውያን አንጡራ ሀብታቸውን በራሳቸው አቅምና ጥረት በማልማት ታላላቅ የልማት ገድሎችን መፈጸም እንደሚችሉ ያመላከተ የጥቁር ሕዝቦች ሁሉ የኩራት ምንጭ መሆኑንም ጠቁመዋል። የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር እና የክብር እንግዳ መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ታላቁ ሕዳሴ ግድብ የታዳሽ ኃይል ሽግግርን በማፋጠን የአፍሪካውያንን የጋራ ምኞት የሚያሳካ ህያው ምልክት ነው ማለታቸው ይታወሳል። የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅና ለምረቃ መብቃትም የኢትዮጵያውያንን ለአንድ ሀገራዊ የልማት ርዕይ በጋራ የመቆም ውጤታማነትን በተግባር ለዓለም የገለጠ ፓን-አፍሪካኒዝም ፕሮጀክት መሆኑን መስክረዋል። በዚሁ ወቅት የተገኙት የጅቡቲ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ዑመር ጌሌ በበኩላቸው እንደገለጹት፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የዘመናዊው ዓለም የአፍሪካውያን የኩራት ምንጭ የሆነ የልማት ድል መሆኑንና መላውን ዓለም ያስደነቀ የኢትዮጵያ ስኬትና የወዳጆቿ የጋራ ሀብት ነው። ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ብሔራዊ ፕሮጀክት ብቻ ሳይሆን አስደማሚ የፓን-አፍሪካኒዝም መግለጫ ፕሮጀክት ነው ያሉት ደግሞ በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ምረቃ ላይ የታደሙት የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ናቸው። የኢትዮጵያውያን ብሔራዊ ፕሮጀክት የሆነው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ስኬት አፍሪካውያን በተባበረ ክንድ አቅማቸውን በመጠቀም የራሳቸውን ዕድል በራሳቸው መወሰን እንደሚችሉ ትምህርት ያስተላለፈ ነው ሲሉም መግለጻቸው ይታወሳል። ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ የምህንድስና ልህቀትም አህጉሪቱ ለብልፅግናዋ የሚረዱና ሁለንተናዊ ለውጥ የሚያመጡ ሁነኛ የልማት ፕሮጀክቶችን በራሷ አቅም የመገንባት ብቃት እንዳላት ማረጋገጫ ነው። በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ምረቃ ላይ የተገኙት የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ እንደተናገሩት፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አህጉራዊ ትብብርና ግንኙነትን የሚያጠናክር የወንድማማችነት ምልክት ነው። ፕሬዝዳንቱ አክለውም ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሁላችንንም ተጠቃሚ የሚያደርግ የጋራ ጉዳያችን ነው በዚህም ዕድለኞች ነን ሲሉ መግለጻቸውም ይታወሳል። ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ "ለእኛ እንደ አንድ ፕሮጀክት ሳይሆን ሀላፊነትን የምንጋራበት ነው" ያሉት ፕሬዝዳንቱ አፍሪካውያን ከተባበርን ስኬቶችን ማስመዝገብ እንደምንችል ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል። የላይኛውና የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት መበልጸግ የሚችሉት በጋራ እንደ አንድ ማህበረሰብ በመስራት ነው። ውሃና ሌሎች ተፈጥሯዊ ሀብቶች በድንበር የተወሰኑ ሳይሆኑ የወደፊት እጣ ፈንታችንን የሚወስኑ ናቸው ብለዋል። የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት በበኩላችው እንደሚሉት፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የአንድነት እና የመስዋዕትነት ምልክት ነው። ግድቡ ፕሮጀክት ብቻ ሳይሆን የአንድነትና የመስዋዕትነት ምልክት ነው፡፡ የግድቡ ግንባታ እውን መሆን ህዝብ ከተባበረ እና ለአንድ ዓላማ በአንድነት ከቆመ ምን መስራት እንደሚችል ማሳያ መሆኑን ነው ያነሱት ፕሬዝዳንቱ፤ ይህም ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ የኩራት ምንጭ ነው ማለታቸው ይታወሳል። ፕሬዝዳንቱ አክለውም ግድቡ የኃይል ፍላጎትን ከማሳካት ባለፈ ለልጆቻችን የምንመኘውን የበለጸገ ሀገርና አህጉር ለማስረከብ እድል የሚፈጥር ነው ብለዋል። ይህ በታሪክ ድርሳናት ሰፊውን ድርሻ የሚይዘው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ስኬት የኢትዮጵያዊያን የቃል ኪዳናቸው ማህተም ሆኖ ለዘላለም ይኖራል።
የፀጥታና ደህንነት ተቋማት በመጠናከራቸው ኢትዮጵያን የማትበገርና የጸናች ሀገር አድርጓታል
Sep 8, 2026 264
የፀጥታና ደህንነት ተቋማት በመጠናከራቸው ኢትዮጵያን የማትበገርና የጸናች ሀገር አድርጓታል ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷን፣ ሰላሟንና የሕዝቦቿን ደህንነት ለማስጠበቅ ባለፉት ዓመታት በጸጥታና ደህንነት ዘርፍ በተቋማዊ አደረጃጀት፣ በሕግ፣ በሙያዊ አቅም ግንባታ፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂና በተቀናጀ አሠራር ያካሄደቻቸው ሪፎርሞች የጸጥታ አቅሟን እንድታሳድግ አስችለዋል። በዚህም የፖሊስና የመረጃ ተቋማት የሚመሩበት የሕግ ማዕቀፍና ተቋማዊ አደረጃጀቶችን ከማጠናከር ባሻገር፣ ተቋማቱ የዘመኑን የጸጥታ ተግዳሮቶች መመከት የሚያስችላቸውን አቅም እንዲገነቡ ተደርጓል። በመከላከያ ዘርፍም የሠራዊቱን አደረጃጀትና የማድረግ አቅም ማጎልበት፣ የቴክኖሎጂ አቅሙን ማጠናከር የሪፎርሙ የትኩረት አቅጣጫዎች ነበሩ። በዚህም የምድር ጦርን ጨምሮ የአየር ኃይልና የባሕር ኃይል አቅምን ማጠናከር እንዲሁም ከዘመናዊ የሰራዊት አሠራር ጋር የሚሄድ የወታደራዊ አቅም መገንባት በዚሁ አቅጣጫ ተካትቷል። በቅርቡ በሃዋሳ በተካሄደ የኮማንዶ ምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንዳሉት፣ ኢትዮጵያ የሀገሪቱን ደህንነት ከማስጠበቅ ባለፈ በቀጣናውና በአፍሪካ ሰላምና ብልጽግና ላይ አስተዋፅዖ ማድረግ የሚችል በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ ኤሊት የጦር ኃይል ለመገንባት እየሠራች ነው። በምድርና በአየር የነበረውን ወታደራዊ ሥልጠና ወደ ባሕር ማስፋፋትን ጨምሮ፣ የጦር ኃይሉን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ማጠናከርና የተለያዩ የውጊያ አቅሞችን ማሳደግ የሠራዊቱን ዘመናዊነት ለማረጋገጥ ከተወሰዱ አቅጣጫዎች መካከል መሆናቸውን መጠቆማቸው ይታወሳል። በተመሳሳይ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ በ45ኛው የፅናት ኮርስ የኮማንዶ ምረቃ መርሃ ግብር ላይ እንዳሉት፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሉዓላዊነትና ብሔራዊ ጥቅምን ለማስከበር የተጠናከረ ወታደራዊ አቅም እንዲኖረው ተሰርቷል። የቴክኖሎጂ ግኝቶችን የታጠቅንበት ዘመን ላይ ነን ያሉት ፊልድ ማርሻሉ፣ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ውስጥና የውጭ ጠላቶች እንደማይችሏት ገልጸዋል። የጸጥታ ተቋማት በተናጠል ከመሥራት ይልቅ በቅንጅት እንዲሠሩ ማድረግም በሪፎርሙ የተሰጠው ትኩረት ሌላው አቅጣጫ ነው። የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል፣ የኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽነሮችና የሰላምና ፀጥታ ኃላፊዎች ሀገራዊ የጋራ የፀጥታ መድረክ ላይ እንደገለጹት፣ የፌዴራል፣ የክልልና የከተማ የጸጥታ ተቋማት በጋራ በማቀድ፣ በመቀናጀትና ልምድ በመለዋወጥ የጋራ የጸጥታ ተልዕኮዎችን የሚያከናውኑበት አሠራር ተጠናክሯል። ይህ የተቀናጀ አሠራር በተለያዩ ብሔራዊ ዝግጅቶችና የሀገራዊ ጸጥታ ተልዕኮዎች ወቅት የተቋማትን የጋራ አቅም ለመጠቀም መሠረት መሆኑ በቀደመ ማብራሪያዎች ጠቁመዋል። የሳይበር ደህንነት የሀገራዊ ደህንነት አካል እየሆነ መምጣቱ የሪፎርሙ አንድ አካል እንዲሆን ተደርጓል። በዚህ ረገድ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሃሚድ አምስተኛው ዙር ብሔራዊ የሳይበር ታለንት የሰመር ካምፕ ማስጀመሪያ መርሃግብር ላይ እንደገለጹት፤ አስተዳደሩ ተቋማዊ አቅሙን በማሳደግ ወሳኝ የመረጃ መሠረተ ልማቶችን ከሳይበር ጥቃቶች ለመጠበቅ የሰው ኃይል ልማት፣ የዝግጁነት አቅምና የተቋማት ትብብርን ማጠናከር ላይ በትኩረት እየሰራ ይገኛል። የሳይበር ደህንነት የሀገሪቱን ዲጂታል ሽግግር ለማረጋገጥ ወሳኝ በመሆኑ በዘርፉ ብቁ የሰው ኃይል ማፍራትና የተቋማትን ዝግጁነት ማጠናከር ቀዳሚ ትኩረት ነው ብለዋል። በአጠቃላይ በሀገሪቱ የጸጥታና ደህንነት ዘርፉ የተከናወኑት ሪፎርሞች የጸጥታና ደህንነት ሥርዓቱን በተቋማዊ አደረጃጀት፣ በሙያዊ ብቃት፣ በቴክኖሎጂና በቅንጅታዊ አሠራር ለማጠናከር ያለመ ሲሆን፣ ይህም ሀገሪቱ የራሷን የጸጥታ አቅም በማሳደግ ሉዓላዊነቷን፣ ሰላሟንና ብሔራዊ ጥቅሟን በበለጠ አቅም ለማስጠበቅ ያላትን ብቃት አጠናክሯል።
በልጆቿ ፀንታ የኖረች ሀገር
Sep 8, 2026 455
በብርሀኑ ፍቃዱ (ሰቆጣ ኢዜአ) የውጪ ወራሪን በጀግኖች አባቶቻችን ክቡር መስዋዕትነትና በጸና ተጋድሎ በማክሸፍ፣ ኢትዮጵያን በትውልድ ቅብብሎሽ አጽንቶ አሁን ላለንበት ማድረስ ተችሏል። ለአብነትም የጣሊያን ወራሪ ኃይል በጥንት አባቶቻችን ተጋድሎ ሽንፈትን ተከናንቦ መመለሱ ለኢትዮጵያዊያን ድልና ለመላው ጥቁር ህዝብ የነፃነት ፋኖስ ሆኖ ሲዘከር ይኖራል። "የአይቻልም" መንፈስን በ"ይቻላል" ለውጠው ያሳዩት እነዚህ ጀግኖች፣ ለጥቁር ህዝቦች የነፃነት ጮራ የፈነጠቁ፣ እኩልነትን ያበሰሩ፣ የሀገር ፍቅርና ጽናትን ለልጅ ልጆቻቸው ያወረሱ እንዲሁም ታሪክን በወርቅ ቀለም የጻፉ ናቸው። የዛሬው ባለታሪኮቻችን ሻለቃ ባሻ ሞገስ የማነብርሃን እና መቶ አለቃ አበባው ገብረ እግዚአብሔር ለሀገራቸው ሉዓላዊነት መከበር በጽናት ታግለው ያሳለፉትን የተጋድሎ ታሪክ «የጽናት ቀን»ን ምክንያት በማድረግ እንደሚከተለው እናስቃኛችኋለን። በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በሰቆጣ ወረዳ «ቃፋ ሚካኤል» በተባለ መንደር ነዋሪ የሆኑ ሻለቃ ባሻ ሞገስ የማነብርሃን፣ ከ1960 ዓ.ም ጀምሮ ለ22 ዓመታት ክቡር በሆነው የውትድርና ሙያ ሀገራቸውን አገልግለዋል። "ጀግንነትን፣ አሸናፊነትን እና ለሀገር አንድነት መስዋዕት መክፈልን ከአባቴ ከሻለቃ የማነብርሃን የወረስኩት አኩሪ ታሪክ በመሆኑ፣ እኔም ለሀገሬ ክብር በጽናት ተዋድቄያለሁ" ሲሉ ይገልጻሉ። የውትድርና ሕይወታቸውን በቀብሪ ደሃር ማሰልጠኛ ማዕከል የጀመሩት ሻለቃ ባሻ ሞገስ፤ በዳሎል፣ ምፅዋ፣ ከረን፣ ሙሳቤት፣ ቃሮራ፣ አፋበት፣ ናቅፋ እና በሌሎች የኤርትራ ቆላማና ደጋማ አካባቢዎች የተሰጣቸውን ግዳጅ በጽናት ተወጥተዋል። "የወጣትነት እድሜዬን ክቡር የሆነውን የሀገር መከላከያ ሠራዊት በመቀላቀል ሀገር የሰጠችኝን ግዳጅ በጽናት ተወጥቻለሁ" ያሉት ሻለቃ ባሻ ሞገስ፤ ሀገርን በውትድርና የማገልገል እድል ማግኘት ታላቅ ዕድልና ክብር መሆኑን ገልጸዋል። ኢትዮጵያን የመሰለች ጥንታዊት ሀገር ሉዓላዊነቷ፣ አንድነቷና ክብሯ እንዲጠበቅ አባቶቻችንም ሆኑ እኛ ዋጋ ከፍለናል፤ የአሁኑ ትውልድም ሉዓላዊነቷን አጽንቶ ለመዝለቅ ወቅቱ የሚጠይቀውን መስዋዕትነት ለመክፈል ዘብ መቆም አለበት ሲሉ ይመክራሉ። አሁን ያለው የሀገር መከላከያ ሠራዊት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ፣ በሰው ኃይል አቅምና ትጥቅ፣ ከሳይበር እስከ መካናይዝድ ልቆ የተደራጀ በመሆኑ ከኢትዮጵያ አልፎ ለቀጠናው ዘብ የሚሆን አስተማማኝ ኃይል መሆኑን እያየን ነው ብለዋል። "ሀገራችን የባሕር በር አልባ መሆኗ ያስቆጨኛል፤ ዕድሜ ልኬን ለሀገሬ ዘብ ብቆም ምኞቴ ነው" ያሉት ሻለቃ ባሻ ሞገስ፤ ወጣቱ ትውልድ የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ የተጀመረውን ተግባር በሰላማዊ መንገድ ለማሳካት መስራት እንዳለበት አሳስበዋል። ሌላው የከተማዋ ነዋሪ መቶ አለቃ አበባው ገብረ እግዚአብሔር በበኩላቸው፤ «ታላቋን ሶማሊያ» ለመመስረት በሚል በጦር የሰከረው የዚያድ ባሬ መንግሥት በእብሪት ተነሳስቶ ሀገራችንን በወረረበት ወቅት በ18 ዓመታቸው የቀድሞውን የሀገር መከላከያ ሠራዊት መቀላቀላቸውን ያወሳሉ። "ወላጅ አባቴ የሀገር መከላከያ ሠራዊት የቀድሞ አባል ነበር" ያሉት መቶ አለቃ አበባው፤ እሳቸውና ታናሽ ወንድማቸው የአባታቸውን አሻራ በመከተል የመከላከያ ሠራዊቱን መቀላቀላቸውን ተናግረዋል። የ10ኛ፣ 19ኛ፣ እና 82ኛ ልዩ ኮማንዶ ክፍለ ጦሮች አባል በመሆን በሕክምና ሙያቸው ሠራዊቱን ለ12 ዓመታት ማገልገላቸውን ጠቁመው፤ ውትድርና ጽናትን፣ የሀገር ፍቅርን እና ከራስ በፊት ለወገን መስዋዕት መሆንን የሚጠይቅ የተከበረ ሙያ መሆኑን ገልጸዋል። ከሰራዊት አባልነት ከተገለሉም በኋላ ባካበቱት የሕክምና ሙያ በሰቆጣ ጤና ጣቢያና በተፈራ ኃይሉ ሆስፒታል ተቀጥረው ህዝባቸውን ያገለገሉ ሲሆን፣ የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ በመሆንም ሰርተዋል። "ለዘመናት ያዘንኩበት የባሕር በር ጉዳይ አሁን ላይ የትውልዱና የመንግሥት አጀንዳ ሆኖ መነሳቱ አስደስቶኛል" ያሉት መቶ አለቃ አበባው፤ ይህም የሀገራችንን የቀደመ ገናናነት የሚመልስ በመሆኑ ለስኬቱ በአንድነት መሰለፍ ይገባል ብለዋል። የአሸናፊነትና የጀግንነት ወኔ ከጥንት ጀምሮ ያለና የሚቀጥል መሆኑን አሁን ላይ የመከላከያ ሠራዊት ዘመኑን የዋጀ አደረጃጀትና የቴክኖሎጂ አቅም በማየት መገንዘብ ይቻላል ብለዋል። ወጣቱ ትውልድ ጸንታ የተከበረች ሀገሩን በአንድነትና በፍቅር ሉዓላዊነቷን ጠብቆ ለመጪው ትውልድ ማስተላለፍ እንዳለበት መክረዋል።
የስኬት መገለጫና የውጤት ማሳያዎች
Aug 28, 2026 618
አዲስ አበባ ነሀሴ 22/2018 (ኢዜአ) የስኬት መገለጫና የውጤት ማሳያዎች በኢትዮጵያ ባለፉት አምስት ዓመታት ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ እድገት ለማስመዝገብና የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ (Homegrown Economic Reform) እቅዶችን በመተግበር በበርካታ ዘርፎች መሠረታዊ ለውጦችን እና ስኬቶችን ማስመዝገብ ተችሏል። በግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ በዲጂታል (አይሲቲ)፣ በማዕድን እና በቱሪዝም ዘርፎች የተመዘገቡት ስኬቶች የሀገሪቱን ምጣኔ ሀብታዊ አቅም ከማሳደግ ባሻገር የወደፊት ዘላቂ እድገት መሠረት ያኖሩ መሆኑን መናገር ይቻላል። በመሆኑም በአምስቱ ዋና ዋና ሴክተሮች የመጡ ውጤቶችና የተመዘገቡ ስኬቶችን በወፍ በረር እንቃኛለን። 1. በግብርና ዘርፍ የስንዴ ምርትና የውጭ ኤክስፖርት: የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት መስፋፋት ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናዋን ለማረጋገጥ የሚያስችል መሰረት አስቀምጧል። ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የስንዴ ምርትን ወደ ውጭ ሀገር መላክ የቻለችበትን እመርታዊ ስኬትም አሳይቶናል። የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭን በመተግበር በወተት፣ በእንቁላል፣ በዶሮና የማር ምርት እንዲሁም በአትክልት፣ ፍራፍሬ፣ ሩዝና ሻይ ልማትም ባለፉት አምስት አመታት እመርታዊ ለውጥ ተመዝግቧል። አርሶ አደሩ የመሬትና የውሃ ሀብቶችን አቃፊ በሆነ መንገድ በመጠቀም በዓመት ሁለትና ሶስት ጊዜ ማምረት የሚችልበት አሰራር ተዘርግቷል። በዚህም የቤተሰብ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ ሁነኛ የገቢ ምንጭ የሆነበትን እድል ፈጥሯል። ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ በምግብ ራስን የመቻል አቅም በመገንባት ላይ ይገኛል። በተለይም ደግሞ የቡና ምርታማነትና ጥራት በማደጉ ምክንያት በኤክስፖርት ዘርፍ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ማገኘት ተችሏል። በዘርፉ በቀጣይም የግብርናውን ዘርፍ ይበልጥ በዘመናዊ ቴክኖሎጂና በሜካናይዜሽን በማስደገፍ ምርታማነትን የማሳደግ ጥረት ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል። የመስኖ መሠረተ ልማቶችን በማስፋፋት የዝናብ ጥገኝነትን ለመቀነስ መጣር እንዲሁም የግብርና ምርቶችን ጥራት በማሻሻልና በማቀነባበር ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶችን ዋጋ ማሳደግ ተገቢ ይሆናል። 2. የኢንዱስትሪ ዘርፍ ሀገራዊ የአምራች ኢንዱስትሪ ንቅናቄ በመፍጠር ቀደም ሲል ተቆልፈው የነበሩና በዝቅተኛ አቅምያመርቱ የነበሩ ፋብሪካዎች ወደ ሙሉ የማምረት አቅማቸው እንዲመለሱ ተደርጓል። የሀገር ውስጥ የምርት ፍላጎትን በመሸፈን ለውጭ ሀገር ምርቶች ይወጣ የነበረውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ወጪም መቀነስ አስችሏል። ለሀገር ውስጥና ለውጭ ባለሀብቶች ምቹ የህግና የአሰራር ሁኔታዎችን በመፍጠር በርካታ ኢንቨስትመንቶችን መሳብ ተችሏል። ከተገነቡት የተቀናጁ የግብርና ማቀነባበሪያ ፓርኮች (IAIPs) ጋር አርሶ አደሩን በማስሳሰር የግብአትና የምርት ትስስር እንዲጠናከር ተደርጓል። የአምራች ዘርፉ መስፋፋት ለብዙ ሺህ ዜጎች፣ በተለይም ለወጣቶች የሥራ እድል መፍጠር የታቸለበት ሆኗል። በቀጣይም የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በኃይል፣ በሎጂስቲክስና በግብአት አቅርቦት ሙሉ በሙሉ በመደገፍ ኤክስፖርትን ማሳደግ። የአምራች ኢንዱስትሪዎች 80% እና ከዚያ በላይ የሀገር ውስጥ ጥሬ ዕቃዎችን እንዲጠቀሙ ማበረታታት፣ በህዝብና በግል አጋርነት (PPP) አማካኝነት በትልልቅ የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች ላይ የግሉን ዘርፍ አሳትፎ ማስፋፋት ትኩረት የሚደረግበት ይሆናል። 3. የዲጂታል (አይሲቲ) ዘርፍ የ"ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" ስልት ስኬቶችን በማስቀጠል ወደ "ዲጂታል 2030" እቅድ መሸጋገር ተችሏል። በ"መሶብ" የአንድ ማዕከል አገልግሎት እና በሌሎች ፖርታሎች አማካኝነት ህዝባዊ አገልግሎቶችን በበይነ-መረብ (Online) የመስጠት ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል። የዜጎችን መረጃ ማዕከላዊ የሚያደርግና ለፋይናንስ እንዲሁም ለሌሎች አገልግሎቶች መሠረት የሆነውን የፋይዳ መታወቂያ ፕሮጀክት በላቀ መልኩ ማሳካት ተችሏል። የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን የኮደር ስልጠናም የዜጎችን የዲጂታል ክህሎት ለማሳደግ ታላቅ ሀገራዊ የስልጠና መርሃ ግብር ተዘርግቶ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል።የዲጂታል አገልግሎቶች መዘርጋታቸው የፊት ለፊት ግንኙነትን በመቀነስ ሌብነትንና ብልሹ አሰራርን በመከላከል የኢንቨስትመንት ምህዳሩን አሳልጧል። የቴሌኮም ዘርፍ ውድድር: የቴሌኮም ዘርፉን ክፍት ማድረግን ተከትሎ የኢንተርኔትና የኔትወርክ ተዳራሽነትንና ጥራትን በየገጠሩ የማስፋት ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል። የዲጂታል ክፍያ ሥርዓቶችን እና የባንክ አገልግሎቶችን ይበልጥ ዘመናዊና የተቀናጁ ማድረግም አስፈላጊ ይሆናል። የሀገሪቱን የዲጂታል መሠረተ ልማት ከሳይበር ጥቃቶች የመጠበቅ አቅምን ማጠናከር። 4. የማዕድን ዘርፍ በዘርፉ ይስተዋል የነበረውን ኮንትሮባንድና ህገ-ወጥ ንግድ በመግታት ህጋዊ አሰራርና ቁጥጥር እንዲሰፍን ተደርጓል። የህግና መመሪያዎች ማሻሻያ በማድረግ የማዕድን ዘርፉን ለውጭና ሀገር ውስጥ ኢንቨስትመንት ማራኪ የሚያደርጉ የፖሊሲ ማሻሻያዎች ተደርገዋል። የወርቅ፣ የከሰል ድንጋይ፣ የሲሚንቶ ግብአቶችና የከበሩ ድንጋዮች ምርትን በማሳደግ ዘርፉ የሀገሪቱ ዋነኛ የውጭ ምንዛሬ ማግኛ እንዲሆን ተሰርቷል። በተለይም የከሰል ድንጋይ ምርትን በሀገር ውስጥ አምርቶ በመተካት ለፋብሪካዎች ግብአት ማቅረብ ተችሏል። 5. የቱሪዝም ዘርፍ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ( ዶ/ር)አነሳሽነት የተጀመሩት "ገበታ ለሸገር"፣ "ገበታ ለሀገር" እና "ገበታ ለትውልድ" ፕሮጀክቶች በመላ ሀገሪቱ በርካታ አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎችን መገንባት ተችሏል። በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች የተከናወኑ የኮሪደር ልማቶች የከተሞችን ውበትና ለኑሮ ምቹነት ከመጨመራቸው ባሻገር ለከተማ ቱሪዝም ትልቅ እድል ፈጥረዋል። አዲስ አበባ በርካታ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎችንና ኮንፈረንሶችን ባካሄደችበት የዲፕሎማሲና የኮንፈረንስ ማዕከልነቷን አጠናክራለች። የሀገሪቱን ታሪካዊና ባህላዊ ቅርሶች የመጠበቅ፣ የማደስና ለጎብኚዎች ምቹ የማድረግ ስራዎች በስፋት ተከናውነዋል። በድምሩ ባለፉት አምስት ዓመታት በግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ በዲጂታል፣ በማዕድን እና በቱሪዝም ዘርፎች የተመዘገቡት ስኬቶች ሀገሪቷን ወደ ተሻለ የኢኮኖሚ ምዕራፍ ማሸጋገር አስችለዋል። በመሆኑም እነዚህን ስኬቶች አጠናክሮ ለማስቀጠል የታቀዱትን የወደፊት ስትራቴጂካዊ አቅጣጫዎች በተቀናጀ መልኩ መተግበር፣ የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ እና የግሉን ዘርፍ አሳታፊነት ማሳደግ በቀጣይ አዲስ የሚመሰረተው መንግስት ዋነኛ የቤት ስራ ይሆናል።
ትንታኔዎች
የዲጂታል አብዮት ለነገዋ ኢትዮጵያ
Sep 9, 2026 235
በኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት የታየው የቴክኖሎጂ ለውጥ የዛሬን ፈታኝ ሁኔታዎች ከመቅረፍ ባለፈ፣ ኢትዮጵያን ወደ ዘመናዊው የዲጂታል ምህዳር በፍጥነት እያሸጋገራት ይገኛል። የፖሊሲ ማሻሻያዎች፣ የዲጂታል መሰረተ ልማት ግንባታዎች እና የተቋማት ማጠናከሪያ ስራዎች ለዚሁ አገራዊ የነገ ትራንስፎርሜሽን በምሳሌነት የሚጠቀሱ ዋና ዋና እርምጃዎች ናቸው። መንግስት የዲጂታል ዘርፉን የሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት ምሶሶ በማድረግ የነደፈውን "ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" ስትራቴጂ በስኬት ማጠናቀቁ፣ 2030 ዲጂታል ስትራቴጂን መጀመሩ ሀገሪቱን በቴክኖሎጂው ዘርፍ ወደ አዲስ የወደፊት ምዕራፍ እንድትገባ ያስቻለ መሰረታዊ ለውጥ አምጥቷል። የቴሌኮም ዘርፉ ለውጭ ኢንቨስትመንት ክፍት መደረጉ፣ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መግባትና የኢትዮ ቴሌኮም መዘመን ለኢንተርኔት ተደራሽነት መስፋፋት ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጓል። በተለይም የ5G ቴክኖሎጂ አገልግሎት በስፋት መጀመሩ ሀገሪቱን በምስራቅ አፍሪካ በቴክኖሎጂ ተጠቃሚነትና በመሰረተ ልማት ዝግጁነት ቀዳሚ ያደረጋት ሲሆን፣ ይህም ለነገው ፈጣን የመረጃ ልውውጥ እና ለቀጣይ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል። የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቱ መዘመን በፋይናንስ ዘርፉ ላይ አብዮታዊ ለውጥ በማምጣት የነገዋን ስማርት ኢኮኖሚ መደላደል ጥሏል። እንደ ቴሌብር ያሉ የዲጂታል ክፍያ አማራጮች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ያለ ባንክ ሂሳብ በስልካቸው ብቻ ግብይት እንዲፈጽሙ በማድረግ ለአካታች ዲጂታል ኢኮኖሚ ትልቅ አቅም ሆነዋል። ይህ የፋይናንስ ቴክኖሎጂ ምህዳር መስፋፋት ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በቀላሉ የዲጂታል ክፍያዎችን እንዲቀበሉና የፋይናንስ ተደራሽነታቸው እንዲያድግ ያስቻለ ሲሆን፣ መደበኛ ያልሆነውን የግብይት ስርዓት ወደ ዘመናዊና ግልጽ የነገ ዲጂታል ስርዓት የመቀየር ሂደቱን አፋጥኖታል። በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ረገድ የኢትዮጵያ ሰውሰራሽ አስተውሎት ኢንስቲትዩት መቋቋም የሀገሪቱን ታላቅ የነገ ራዕይ ለዓለም አሳይቷል። ኢንስቲትዩቱ በጤናው ዘርፍ የካንሰርና የሳምባ በሽታዎችን ቀድሞ የሚያውቁ የኤአይ ውጤቶችን በማበልጸግ ህይወትን የማዳን ስራ እያከናወነ ይገኛል። በተመሳሳይ በግብርናው ዘርፍ የአፈር ለምነትንና የሰብል በሽታን በቴክኖሎጂ የመለየት ስራዎች እየተከናወኑ ሲሆን፣ ይህም ለነገዋ ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትና ማረጋገጥና ለምርታማነት ማደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። ሌላው ትልቅ የለውጡ ስኬት የሀገር በቀል ቋንቋዎችን በዲጂታል አለም ተወዳዳሪ ለማድረግ የተሰሩ የቋንቋ ፕሮሰሲንግ (NLP) ስራዎች ናቸው። ይህም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች በዘመናዊ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎች ውስጥ እንዲካተቱ በማድረግ ለነገው ትውልድ የባህል እና የእውቀት መተላለፊያ ምቹ መንገድ ፈጥሯል። ከዚሁ ጎን ለጎን የ"ፋይዳ" (Fayda) ብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ፕሮጀክት የዜጎችን መረጃ በማደራጀት ለነገው ዘመናዊ የአገልግሎት አሰጣጥ አስተማማኝ የመረጃ መሰረት ጥሏል። ይህም ለባንክ፣ ለጤናና ለሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶች ቀልጣፋ አሰራርን ፈጥሯል። በአሁኑ ወቅት ዜጎች እንደ ፓስፖርት ማደስ፣ የንግድ ፈቃድ ማውጣትና ግብር መክፈል ያሉ አገልግሎቶችን ከቤታቸው ሆነው በኢንተርኔት ማከናወን መቻላቸው የነገዋን አሰራር ዛሬ ማሳያ ሲሆን፣ የሳይንስ ሙዚየም ደግሞ የነገዎቹን ፈጣሪዎች አቅም የሚያበለጽግ ማዕከል ሆኗል። በተጨማሪም በዲጂታል ክህሎት ግንባታ ረገድ ለወጣቶችና ለባለሙያዎች የሚሰጡ የስልጠና ፕሮግራሞች በስፋት እየተካሄዱ ይገኛሉ። ይህም ኢትዮጵያ በነገው ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ መድረክ ብቁ እና ተወዳዳሪ የሆነ የሰው ኃይል እንድታፈራ ዘላቂ መሰረት እየጣለ ነው።
ነገን በብልሃት ማነጽ - የዲጂታል 2030 ስትራቴጂ
Sep 9, 2026 195
(በሙሴ መለሰ) ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት የጀመረችውን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ አጠናክራ ለመቀጠል እና ከጊዜው ፈጣን የቴክኖሎጂ እድገት ጋር ለመራመድ “የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030” ስትራቴጂን በይፋ አድርጋለች። ታኅሣሥ 11 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ የተደረገው ይህ ታላቅ አገራዊ ዕቅድ፤ ሀገሪቱ በቴክኖሎጂው ዓለም ከተመልካችነት ይልቅ ተሳታፊና መሪ የምትሆንበትን አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ነው። ይህ አዲስ ስትራቴጂ ከቁጥሮች እና ከኢኮኖሚያዊ ስኬቶች ባሻገር፣ ዛሬን ከመቅረጽ ባለፈ ነገን ከመገንባት እና ለቀጣይ ትውልድ አሻራ ከማስቀመጥ አንጻር ሰፊና ጥልቅ ፋይዳ ያለው ሀገራዊ ትልም ነው። በዲጂታል ዘመን የመረጃ ሉዓላዊነት ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ ነው ። በዚህ ዘርፍ የሚያጋጥም ጥገኝነት የሃገር ደህንነት ላይም የራሱን አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳረፉ አይቀርም። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በዚህ ዙሪያ መረጃ የዚህ ዘመን ስትራቴጂካዊ ሀብት እና ጠንካራ ሀገረ መንግሥት የሚገነባበት ቁልፍ የሉዓላዊነት ምሰሶ ነው ማለታቸው ይታወሳል። የተዋሰ አሊያም በውጭ አካላት ላይ ጥገኛ የሆነ መረጃ ሀገራዊ መሻታችንን ማሳካት ስለማያስችል፤ የፖሊሲ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የራስን መረጃ በራስ አቅም መሰብሰብ እና መተንተን ወሳኝ ግብዓት ነውም ብለዋል። የዲጂታል 2030 ስትራቴጂ ከወረቀት ባለፈ በህዝብና በሀገር ላይ የሚኖረው ተጨባጭ ማሳያ በአጭር ጊዜ ውስጥ መሬት የረገጠ እውነታ ነው። ለአብነት ያህል፣ በዓለም ሁለተኛውና ለአፍሪካ የመጀመሪያው የሆነው የሰው ሰራሽ አስተውሎት ዩኒቨርሲቲ ግንባታ መጀመሩ እና ከዩኤንዲፒ ጋር በመተባበር የተመረቀው 'AI UniPod' ማዕከል ለወጣቶች የተፈጠረ ትልቅ የቴክኖሎጂ መሠረት ነው። ተቋማቱ ከሀገር ውስጥ አልፎ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ተማሪዎች ነፃ የትምህርት ዕድል በማመቻቸት ላይ መሆናቸው፣ ኢትዮጵያ የአህጉሪቱ የፈጠራ ማዕከል ሆና እንድትቀጥል የሚያስችላት የትውልድ አሻራ ነው። የሞባይል ተጠቃሚዎችን ቁጥር 128 ሚሊዮን ለማድረስ እንዲሁም የ5G ኔትወርክ ተደራሽነትን ሙሉ በሙሉ እውን ለማድረግ የተነደፈው ዕቅድ፣ በከተማና በገጠር መካከል የነበረውን የዲጂታል ክፍተት በማጥበብ የመረጃ እኩልነትን የሚያረጋግጥ ትልቅ ምዕራፍ ነው። እንደ ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ከመሳሰሉ መሠረተ ልማቶች ጋር ተቀናጅቶ የሚሰራው ይህ እቅድ፣ የዜጎችን ተደራሽነት በማስፋት እኩል እድል የሚፈጥር አሰራርን ይዘረጋል። ይህ የዲጂታል መረብ መስፋፋት የዜጎችን ኑሮ በጥራት ከማሻሻል ባለፈ አገልግሎቶች በፍጥነት እንዲቀላጠፉ ትልቅ አቅም ይፈጥራል። የመንግሥት አገልግሎቶችን ሙሉ በሙሉ ወረቀት አልባ ለማድረግ የሚከናወነው አሰራር ግልጽነትን በማስፈን በዜጎችና በተቋማት መካከል መተማመንን ያጎለብታል። ዲጂታል 2030 ስትራቴጂ የዛሬን ስኬት ብቻ ሳይሆን የወደፊቱን ትውልድ አዕምሮ በዕውቀትና በፈጠራ ብርሃን በመቅረጽ የሀገርን የሰው ሀብት በዘላቂነት የሚያለማ የዕድገት ምሰሶ ነው። ስትራቴጂው ካነጣጠረባቸው ቁልፍ ነጥቦች መካከል ተደራሽነትን ማስፋት፣ እኩል እድል መፍጠር እና በዜጎችና ተቋማት መካከል መተማመንን ማጎልበት ይገኙበታል። ግልጽነት የሰፈነበት፣ ከወረቀትና ከቢሮክራሲ የጸዳ አሰራር መዘርጋቱ ዜጎች በሀገራቸው ተቋማት ላይ ያላቸውን እምነት ያጠናክራል። ይህ ደግሞ ማህበራዊ መተሳሰርን አጠናክሮ ለአንድነትና ለጋራ ብልጽግና መሰረት የሚጥል ትውልድ ተሻጋሪ ስራም ነው። በሚሊዮን የሚቆጠሩ የዲጂታል ሥራ ዕድሎችን ለወጣቶች ማመቻቸት የወጣቶችን ፈጠራ ወደ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም መቀየር ያስችላል። ወጣቱ በዲጂታል ንግድ፣ በሶፍትዌር ልማት እና በዲጂታል አገልግሎቶች ላይ ተሰማርቶ በራሱ ጥረት እያደገ ሲሄድ፣ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ መሠረት የጸና ይሆናል። የዲጂታል ኢኮኖሚ እያደገ ሲሄድ የሳይበር ደህንነት እና የመረጃ ጥበቃ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ። የዲጂታል 2030 ስትራቴጂ የሳይበር ደህንነት መሠረተ ልማቶችን ማጠናከሩን እንደ ዋና ዕቅድ ይዞ መንቀሳቀሱ ዜጎችና ተቋማት በአስተማማኝ ዲጂታል ምህዳር ውስጥ እንዲኖሩ ያስችላል። ቴክኖሎጂ የሉዓላዊነት ሌላኛው መገለጫ በመሆኑ፣ የህዝብ ዲጂታል መሠረተ ልማትን ማስፋት ወሳኝ ነው። መረጃዎች በውጭ አካላት ቁጥጥር ስር ሲሆኑ የሀገር ደህንነት አደጋ ላይ ይወድቃል። የዲጂታል 2030 ስትራቴጂ የመረጃ ደህንነትን በአስተማማኝ ሁኔታ ለመጠበቅ የሚያስችል አቅም በመፍጠር ለነገው ትውልድ የባለቤትነት ስሜት ያጎናጸፋል። ወጣቶች በሮቦቲክስ፣ በዳታ ሳይንስ እና በሶፍትዌር ልማት ላይ ሲሰማሩ፣ ችግሮችን በፈጠራ ሃሳብ የሚፈቱ አዳዲስ ጅምሮች ይፈጠራሉ። ይህም የወጣቱን የእውቀት አቅምና ክህሎት ወደ ተጨባጭ ኢኮኖሚያዊ ውጤት በመቀየር ለቀጣዩ ትውልድ ራሱን የቻለ የኢኮኖሚ መሠረት ይጥላል። የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ስኬት ከተቀናጀ የመደመር እሳቤ ጋር የሚተሳሰር ነው። ነገን የተረጋጋ ሰላምና ኢኮኖሚያዊ ብልጽግና የምናረጋግጥበት ሁነኛ መንገድም ጭምር ።
የስንዴ አብዮት፦ የኢትዮጵያ ማንሰራራት አብነት
Sep 6, 2026 567
ኢትዮጵያ ዓመታዊ የስንዴ ፍላጎቷ ከ107 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ነው። ይህንን ፍላጎት ለማሟላት ለዓመታት ከ700 ሚሊዮን ዶላር እስከ 1 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ ውድ የውጭ ምንዛሬ ለስንዴ ግዢ ስታወጣ ቆይታለች። ከዚህ ቀደም ሀገሪቱ ከዓመታዊ ፍላጎቷ መሸፈን የምትችለው ከ25 እስከ 30 በመቶ የሚሆነውን ብቻ ሲሆን፣ ቀሪውን በውጭ ግዢ ትሸፍን ነበር። በተለይም የዩክሬንና የሩሲያ ጦርነት በዓለም አቀፍ ደረጃ 30 በመቶ የሚሆነውን የስንዴ አቅርቦት በማወኩ ኢትዮጵያ ከባድ የአቅርቦት ፈተና ውስጥ እንድትገባ አድርጓት ነበር። ይህንን የረጅም ጊዜ ተግዳሮት በዘላቂነት ለመቅረፍ መንግሥት የበጋ መስኖ ስንዴ ልማትን በስፋት በመተግበር፣አሲዳማ መሬቶችን በኖራ በማከም እና ረግረጋማ ቦታዎችን በቴክኖሎጂ በማድረቅ ታሪካዊ ለውጥ ለማምጣት እርምጃዎችን ወስዷል። በኩታ ገጠም እርሻና በዘመናዊ ማሽነሪዎች አጠቃቀም የታጀበው ይህ የልማት አብዮት ፍሬ አፍርቶ፣ ኢትዮጵያ ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ ከውጭ የምታስገባውን የንግድ ስንዴ ሙሉ በሙሉ አቁማለች። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በስንዴ ልማት የተመዘገበው ስኬት ከውጭ ማስገባትን ማቆም ላይ ብቻ ሳይወሰን፣ ሀገሪቱ ወደ ውጭ መላክ (ኤክስፖርት ማድረግ) የሚያስችል አቅም እንዳላት ያሳየ መሆኑን አመልክተዋል። በዚህም መሠረት የካቲት 5 ቀን 2015 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን በይፋ የስንዴ ኤክስፖርት የተጀመረ ሲሆን፣ ለዚህ ስኬታማነት የተለያዩ ክልሎች ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል። ብሔራዊ የማክሮ ኢኮኖሚና የኤክስፖርት ኮሚቴ ሀገሪቱ የሀገር ውስጥ ፍጆታዋን ሸፍና 32 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ለውጭ ገበያ ማቅረብ የሚያስችል አቅም እንዳላት አረጋግጦ፣የ2.9 ሚሊዮን ኩንታል የውል ስምምነቶች ከረድኤትና ከሀገር ውስጥ ድርጅቶች ጋር ተፈራርሟል። ከሀገር ውስጥ አቅርቦት ባሻገር ኢትዮጵያ በ2015 ዓ.ም ለኬንያ ስንዴ ለመላክ ስምምነት የፈረመች ሲሆን፣ ጅቡቲም ከኢትዮጵያ ስንዴ መግዛት እንደምትፈልግ ገልጻ ከኢትዮጵያ የስንዴ ልማት ብዙ ተሞክሮ እንደምትወስድ አመላክታለች። የአፍሪካ ልማት ባንክ ስንዴ ከውጭ እንደማታስገባ እና ምርቷን ለጎረቤት ሀገራት ማስተላለፍ መጀመሯን በማድነቅ ለአህጉሪቱ እንደ ትልቅ የዕድገት ተሞክሮ አቅርቧል። የአሜሪካ የውጭ ግብርና ቢሮ ሪፖርቶችም በኢትዮጵያ የስንዴ ምርት ዘርፍ ትልቅ እመርታ እያሳየ መምጣቱን ጠቅሰው፣መንግሥት የመስኖ ልማትና የግብርና ኤክስቴንሽን ድጋፍ በማጠናከሩ ሀገሪቱ ከፍተኛ ምርት ማምረቷን አረጋግጠዋል። የኢትዮጵያ ዓመታዊ የስንዴ ምርት ከ290 እስከ 340 ሚሊዮን ኩንታል (ከ29 እስከ 34 ሚሊዮን ቶን) በላይ መድረሱ ኢትዮጵያን በአፍሪካ አህጉር ቀዳሚ የስንዴ አምራች ሀገር አድርጓታል። የስንዴ ልማቱ አርሶ አደሩን ከቀድሞው ከእጅ ወደ አፍ ኑሮ አላቆ፣ በኩታ ገጠም እርሻና በሜካናይዜሽን ታግዞ ወደ ሰፋፊ የንግድ ምርት እንዲገባ አስችሏል። የተሻሻሉ የስንዴ የሰብል ዝርያዎች መለቀቃቸው ለዚህ ውጤት ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረከተ ሲሆን፣ የምርት አቅርቦት ሰንሰለቱን ማዘመን በቀጣይነት በትኩረት እየተሠራበት ይገኛል። በምርት አቅም እና በኩታ ገጠም እርሻ የተመዘገቡት እነዚህ ሰፊ ስኬቶች፣ ሀገሪቱ በኢኮኖሚ አቅም እያደረገችው ያለውን ሁለገብ ማንሰራራት በግልጽ የሚያሳዩ አብነቶች ናቸው። ይህ ትልቅ ለውጥ ኢትዮጵያ ከድህነትና ከዕርዳታ ጥገኝነት ወጥታ የምግብ ሉዓላዊነቷን ማረጋገጥ ብቻ ሳይሆን፣ ለሌሎች አፍሪካ ሀገራትም ተስፋ የሚሰጥ አህጉራዊ አርዓያ መሆን መቻሏን አስመስክሯል። ይህ የምርት እመርታ በግብርናው ብቻ ሳይሆን፣ አጠቃላይ የሀገሪቱን ማንሰራራት የሚያረጋግጥ ትልቅ ምዕራፍ ነው። ለዘመናት በውጭ ዕርዳታና በለጋሾች ላይ ተወሰና የነበረችው ኢትዮጵያ፣ዛሬ በራሷ አቅም በመሥራት አህጉራዊ አርዓያ መሆን መቻሏ ትልቅ ስኬት ነው። የኢኮኖሚ ነፃነት እና የሉዓላዊነት ማዕቀፍን በማረጋገጥ ረገድም የስንዴ አብዮቱ የሀገርን አቅም የሚያሳይ ተምሳሌት ሆኗል። በመሆኑም በስንዴ ልማት የተገኘው ይህ ድል የግብርና ዘርፍ ስኬት ብቻ አይደለም፤ ኢትዮጵያውያን በቁርጠኝነትና በትጋት ከሠሩ ሀገርን ማሻገር እንደሚችሉ በተግባር ያረጋገጡበት ታላቅ የሀገር የማንሰራራት ማሳያ ነው።
የቡና ወጪ ንግድ እድገት - የኢትዮጵያ እመርታ አንዱ ማሳያ
Sep 5, 2026 425
ገና ወደ ውስጥ ሲገቡ ለምለም ቄጠማ በተጎዘጎዘበት ቤት እና ትኩስ በተቆላ ቡና ከደማቅ ፈገግታ ጋር አቀባበል ታደርጋለች። የቡናው ሽታ ደግሞ ልዩ መዐዛ አለው። አለምነሽ ሀብቱ ወደ ከተማ ከገባች በኋላ ድሮም የምትወደውን ቡና የሰርክ ስራዋ የእለት መተዳደሪያዋ አድርጋዋለች። ቡና ትወዳለች የአዘገጃጀት ድምቀቷንም ሌሎች ይወዱላታል። እሷ የምታዘጋጀውን የጀበና ቡና ለመጠጣት የመጣ ደንበኛዋ አትርፎ እንደወጣ እንዲሰማው የማድረግ ተሰጥኦ አላት። ቡና ትወዳለች ትጠጣለች ታጠጣለች ። እንደሷ ሁሉ ቡና ለኛ ለኢትዮጵያውያን አብሮን የሚውል፣ የሚያመሽ በብዙዎቻችን ቤት በቋሚነት የማይጠፋ ማህበራዊ መገናኛችን መመካከሪያችንም ጭምር ነው። በቡና ምርት በርካታ መሬትን ሸፍና ብዙ አርሶ አደሮችን እያሳተፈች የወጪ ንግዷን ለማሳደግ የምትጥረው ኢትዮጵያ ደግሞ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የምታገኝበት ዋንኛ የግብርና ኢኮኖሚው የጀርባ አጥንትም ነው። ባለፉት ዓመታት የቡና ምርትና ምርታማነት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ የሀገሪቱን የወጪ ንግድ ድርሻም እያሳደገ መምጣቱን የተለያዩ መረጃዎች እያሳዩ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 30ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄ ማብራሪያ ሲሰጡ ለቡና ልማት የተሰጠው ትኩረት ኢትዮጵያን በአለም ሶስተኛዋ ቡና ላኪ ሀገር እንድትሆን ማስቻሉን ማንሳታቸው ይታወሳል። በተጠናቀቀው በጀት ዓመትም ከቡና ወጪ ንግድ የተገኘው ከ3 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ኢትዮጵያ በበጀት ዓመቱ ወደ ውጭ ከላከቻቸው ምርቶች ከፍተኛው እንደነበረም አስረድተዋል። በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ከብራዚልና ከኮሎምቢያ በመቀጠል በዓለም 3ኛዋ ትልቋ የቡና ላኪ ሀገር መሆኗን እና በአፍሪካም ቀዳሚ ደረጃ ላይ መቀመጧን ገልጸዋል። የኢትዮጵያን የሀገር ውስጥ የቡና ፍጆታ ከመቻል አልፈን ለውጭ ገበያ በማቅረብ የመጣው ለውጥ የሀገራዊ የሪፎርሙ ስኬት መገለጫ ነው ማለታቸውም ይታወሳል። ይህ የአንድ ዓመት ምርት እንግዲህ ኢትዮጵያ ባለፉት 17 አመታት ቡናን ወደ ውጭ በመላክ ካገኘችው 3 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ጠቅላላ ገቢ ጋር ሲነጻጸር አስደማሚ ስኬት መሆኑ አያጠራጥርም። አረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ለቡና ኤክስፖርት እድገት ስኬት አስተዋጽኦ ማበርከቱን በወቅቱ ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቡናን ካልተከልን ፤ ካልተንከባከብን ፤ካልለቀምን፤ ካላጠብን፤ካላሸግንና ካላጓጓዝን ይህ ውጤት ሊመጣ አይችልም ብለውም ነበር። ኢትዮጵያ የአረቢካ ቡና መገኛ እንደመሆኗ የምርቱን እድገትና ዓለም አቀፍ ገበያ ላይ ተፈላጊነቱን ለማሳደግ እየተከናወኑ ባሉ ተከታታይ ስራዎች ተጨባጭ ውጤቶች ተገኝተዋል። ባለፉት ተከታታይ ዓመታት የተከናወነ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር በሌሎች ኢኮኖሚያዊ፣ አካባቢያዊና የተፈጥሮ ሥነ-ምህዳራዊ ግዙፍ አበርክቶው እንዳለ ሆኖ በቡና ምርት እድገት ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል። ለዚህ ማሳያው ደግሞ መርሃ-ግብሩ ሲጀመር በ2011 ዓ.ም. ስድስት መቶ ሺህ ችግኝ የተተከለ ሲሆን ዓመታዊ ምርቱም 5 መቶ ሺህ ሜትሪክ ቶን ነበረ። በወቅቱ የተገኘው የውጭ ምንዛሪም 738 ሚሊዮን ዶላር ነበር። ይሄ ትኩረት በመቀጠሉም የቡና ችግኝ የመትከሉ ስራ አድጎ በ2017 ዓ.ም. ላይ 1 ነጥብ 4 ሚሊዮን የደረሰ ሲሆን በዛው ዓመት 2 ነጥብ 65 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ማግኘት ተችሏል። ከላይ እንደተገለጸው የ2018 የቡና ወጪ ንግድ ገቢ 3 ነጥብ 1 መድረሱ ለዘርፉ የተሰጠውን ትኩረት እና የተመዘገበውን እመርታ የሚያሳይ ነው። ለዓመታት በዝቅተኛ ደረጃ ላይ የቆየው የቡና ወጪ ንግድ ገቢ በአጭር ጊዜ መለወጥ እና ኢትዮጵያ ወደ ተለያዩ ሃገራት ከምትልካቸው የግብርና ምርቶች ከፍተኛውን ድርሻ ይዞ መቀጠሉ ለዘርፉ ለተሰጠው ትኩረት እና ለተገኘው ውጤት አንዱ መገለጫም ነው። የኢትዮጵያ ቡና በዓለም ገበያ ላይ ተፈላጊነቱ በየጊዜው እየጨመረም ይገኛል። ጀርመን፣ አሜሪካ፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ጃፓን፣ ቤልጂየም እና ደቡብ ኮሪያ ከቀዳሚዎቹ የኢትዮጵያ ቡና ገዢዎች መካከል የሚጠቀሱ ሲሆን በቻይና እና በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የቡና ፍጆታና የመጠጣት ባህል በፍጥነት ማደጉ ለኢትዮጵያ አዳዲስ የገበያ እድሎችን ፈጥሯል። ይህ የኢትዮጵያ የእመርታ ጉዞ በቀጣይም ተጠናክሮ የሚቀጥል ብልጽግናዋንም የምታረጋግጥ የዳበረ ኢኮኖሚ ያላትና የበለጠ ጠንካራ ሀገርነቷን የምታስቀጥልበት አዲስ ምዕራፍም ነው።
ልዩ ዘገባዎች
በታዳጊው የተሰራችው መኪና
Jun 17, 2026 12987
ለአዳዲስ ፈጠራ የማይታክተው ልጅዓለም ንጉሱ ትውልድና እድገቱ በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ወረዳ ፀመራ ቀበሌ ነው። ከሕጻንነቱ ጀምሮ ፈትቶ መግጠምና አፍርሶ መስራትን እየተለማመደ የመጣው ልጅዓለም፤ ከቤት እስከ ትምህርት ቤት ያልተቋረጠ ፈጠራውን አጠናክሮ ቀጥሏል። ከዚህ ቀደም ለሚማርበት ፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከወዳደቁ ቁሶች የተለያዩ ቅርፃ ቅርፆችን በመስራት የፈጠራ አሻራውን አኑሯል። በትምህርትና በፈጠራ ሥራው ገፍቶበት አሁን ላይ የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ልጅዓለም እንጨት ገጣጥሞ መኪና በመስራት ያለውን የጥበብና ፈጠራ ክህሎት አሳይቷል። በታዳጊው የተሰራችውና በፔዳል የምትነዳው መኪና ሁለት ሰዎችን የማያዝ አቅም አላት። በቀጣይ ተጨማሪ ቁሶችን በማቅረብና በተለያየ መንገድ የሚያግዘው ካገኘ መኪናዋ በዲናሞ እንድትንቀሳቀስ ለማድረግ መዘጋጀቱን ተናግሯል። የተሽከርካሪውን አካል የገጣጠመው በአካባቢው አጠራር "እንቋ" የተሰኘ ዛፍ እንጨትን በመጠቀም ሲሆን የተሽከርካሪውን እግር ለማዘጋጀት ደግሞ የዋርካ ዛፍ ተጠቅሟል። በዚህም መሰረት የልጅዓለም መኪና የመብራትና የመሪ ስራዋ ተጠናቆ ሁለት ሰዎችን ጭና መንቀሳቀስ እንደምትችል በተግባር አሳይቷል። "በቀጣይ የሚያግዘኝና የሚደግፈኝ ካገኘሁ በዲናሞ የሚሰራ ተሽከርካሪ ለመስራት ዝግጁ ነኝ" ያለው ጥበበኛው ተማሪ ወደ ፊት ለሀገሬ ብዙ የመፍጠር ህልም አለኝ ብሏል። የፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ግርማ ጌቴ፤ ከዚህ በፊት ተማሪ ልጅዓለም በትምህርት ቤቱ የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎች እንዳሉት አስታውሰው ትምህርቱንም ፈጠራውንም አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል። የፈጠራ ክህሎቱን፣ ተሰጥኦውንና ፍላጎቱን ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ ተከታትያለሁ ያሉት መምህሩ የሳይንስ ትምህርቱንና የግል ክህሎቱን ደምሮ ለአዳዲስ ሥራዎች እየተጋ መሆኑን አንስተው፣ የመኪና ፈጠራውም ይህንኑ በተግባር ያሳየበት ነው ብለዋል። የግብዓት አቅርቦት ድጋፍ ከተደረገለት የተሻለና ውጤታማ ሥራ መስራት እንደሚችል ገልጸው ለሚፈጥሩ ወጣቶች በጥሩ ምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን ተናግረዋል። በእንጨት የተገጣጠመችው መኪና በሁላችንም ድጋፍ የዲናሞ፣ የብረትና ሌሎች አስፈላጊ ቁሶች ከተሟሉላት በታዳጊው ጥበብ የተሻለች መኪና ሆና ልትሰራ ትችላለች ሲለም እምነታቸውን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 22303
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 15333
በዮሐንስ ደርበው በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 21077
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
መጣጥፍ
በጎነት የሰብዓዊ ክብር መሠረት፤ የመደመር መንግሥት የሰው ተኮር ልማት የተስፋ አድማስ
Sep 11, 2026 108
በጎነት ከኢትዮጵያውያን የዕለት ተዕለት ኑሮና እንቅስቃሴ ጋር በጥብቅ የተሳሰረ፣ ከራስ ቀንሶ ለሌሎች መድረስ የሚገለጽበት ከፍ ያለ ሰብዓዊ እሴት ነው። በጎነት የግለሰብን ችግር ብቻ የሚያቃልል ተግባር አይደለም። የዜጎችን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ክፍተቶችን በመሙላት አብሮነትን፣ መተሳሰብንና የጋራ ኃላፊነትን የሚያጠናክር የማህበራዊ ኃላፊነት ውልም ነው። ''ሃምሳ ሎሚ ለሃምሳ ሰው ጌጡ፤ ለአንድ ሰው ሸክሙ” እንዲል የሀገር ብሂል ሰዎች በአንድነት ቆመው ለአንድ መልካም ዓላማ ከተባበሩ ለመፍታት የማይቻል ችግር እንደሌለ በተግባር የሚያሳዩ ብዙ አብነቶች አሉ። በተለይም በሰው ተኮር ልማትና በበጎ ፈቃድ የሚከናወኑ የቤት ግንባታና እድሳት ሥራዎች ችግርን ከመቅረፍ ባለፈ የሰዎችን ሰብዓዊ ክብር የሚመልሱ የተስፋ ምንጭ ተግባራት ሆነዋል። ባለፉት ዓመታት በሀገር አቀፍም ሆነ በአዲስ አበባ በበጋና ክረምት ሰው ተኮር የበጎ ፈቃድ መርሃ ግብሮች በርካታ ዜጎችን ከማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉስቁልና ወደ ልዕልና እንዲሸጋገሩ አስችሏል። ከእነዚህ የሰው ተኮር ተግባራት ተጠቃሚ ከሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች መካከል በመኖሪያ ቤት ችግር ምክንያት ኑሯቸው በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ የነበሩ ነዋሪዎች ይገኙበታል። ቤት ለአንድ ሰው የመኖሪያ ቦታ ብቻ አይደለም። ይልቁንም የዜጎችን የደህንነት፣ የክብር፣ የመረጋጋትና ዘላቂ የተስፋ ወጋገን የሚያቆራኝ መሰረታዊ ጉዳይ ነው። ስለዚህ ለአንድ ቤተሰብ የሚገነባ ወይም የሚታደስ ቤት ከግንባታ ዕቃና ከግድግዳ በላይ ትርጉም አለው፤ የተሰበረ ተስፋን ይጠግናል፣ የተረሳ ክብርን ይመልሳል፣ ለነገም አዲስ እድል ይከፍታል። በአዲስ አበባ በበጎ ፈቃደኞች፣ በባለሀብቶችና በመንግሥት የጋራ ጥረት ቤት ተገንብቶላቸው እፎይታን ያገኙ ነፍሶችም በርካቶች ናቸው። ወይዘሮ መስከረም ሰለሞን እንደሚሉት፤ ከዓመታት በፊት ከሁለት ልጆቻቸው ጋር ፒያሳ አካባቢ ለሰው ልጅ ክብርን በማይመጥን ጎስቋላ ቤት ውስጥ ሕይወትን ይመሩ ነበር። በተለይም ክረምት በመጣ ቁጥር የጎርፍና የዝናብ ፍሳሽ አደጋ በከፍተኛ ጭንቀት እንዲያሳልፉ ያስገድዳቸው እንደነበር አስታውሰዋል። በሳር ቤት አካባቢ በተሰራላቸው ዘመናዊ የመኖሪያ መንደር የተሰጣቸው የመኖሪያ ቤት አዲስ የሕይወት ተስፋን እንዳጎናጸፋቸው አስረድተዋል። ይህንም ለመኖር ከማይመች ቦታ ወጥቼ ወደ አማረ ቤት በመግባቴ እንደገና የመወለድ ያህል ታላቅ ደስታ ተሰምቶኛል ሲሉ ገልጸዋል። እንደ ወይዘሮ መስከረም ታሪክ ሁሉ የሌሎች ነዋሪዎች የቤት ግንባታና ዕድሳት ሥራዎች ተሞክሮ የሚያሳየው የቁሳዊ እፎይታ ብቻ ሳይሆኑ ሰብዓዊ ክብርን የሚያጎናጽፉ የተስፋ ውጤቶች መሆናቸውን ነው። በአንድ ወቅት ከፎቅ ላይ ባጋጠማት የመውደቅ አደጋ ሳቢያ የአካል ጉዳት ያጋጠማት ታሪክ ሙሉጌታ፤ በአዲስ አበባ በኪራይና በመንግሥት ቤት ከቤተሰቧ ጋር ሕይወትን ስትገፋ እንደነበር ገልጻለች። የአካል ጉዳተኛ ከሆነች በኋላ ቀደም ሲል ትኖርበት የነበረው ቤትና አካባቢ ከቦታ ቦታ እንደልብ ለመንቀሳቀስ አስቸጋሪ እንደነበር በማስታወስ፤ ከቤተሰቧ ጋር ይኖሩበት ከነበረው ባምቢስ አካባቢ ወደ ሳር ቤት አካባቢ የመኖሪያ ቤት ማግኘቷ በሕይወት ዘመን ያገኘሁት ትልቅ የተስፋ ስጦታዬ ነው ብላለች። ቤቱ እንደልብ መንቀሳቀስ የሚያስችል፣ መሠረታዊ የመኖሪያነት መስፈርቶች የተሟላላት መሆኑ ሕይወቴን በትልቅ እፎይታ እንድመራ አስችሎኛል ስትል ተናግራለች። በሰው ተኮር ፕሮጀክት የሚገነቡ ቤቶች የሚያመጡት ለውጥ ለአካል ጉዳተኞች ብቻ የሚወሰን አይደለም። በቤት ውስጥ ልጆች፣ አረጋውያን፣ የሀገር ባለውለታዎችና መላ ቤተሰብ እንዲሁም የተሻለ ኑሮን ለመፍጠር የሚታገሉ እናቶችና አባቶችም የዚህ ተግባር ተጠቃሚዎች ናቸው። በዚህም በጎነት የአንድን ሰው ዛሬ ከማሻሻል ባለፈ የአንድ ቤተሰብን ነገ የሚቀርጽ ኃይል መሆኑን ያሳያል። ወይዘሮ ጽጌሬዳ ጎበና ፤ ለረጅም ዓመታት ፒያሳ አካባቢ ለመኖር ምቹ ባልሆነ ቤትና ሰፈር ከአንድ ልጃቸው ጋር ይኖሩ ነበር። በፒያሳ አካባቢ የሕይወት ቆይታ ዘመናቸውም ልዩ ድጋፍ የምትሻው ልጃቸው እንደልቧ መንቀሳቀስ የማትችልበትን በርካታ የሰቆቃ ጊዜያት እንዳሳለፈች አስታውሰዋል። በዚህ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ እያሉ በሳር ቤት አካባቢ አዲስ ቤት ማግኘታቸው እንደገና የመወለድ ያህል ትልቅ እፎይታን እንደቸራቸው ገልጸዋል። የተሰጣቸው ቤት ለልጃቸው እንቅስቃሴ ምቹ ከመሆኑ ባለፈ ዘመናዊ የአኗኗር ዘይቤን እንዲከተሉ ያስቻለ ታላቅ የሕይወት ብስራት መሆኑን ገልጸዋል። እነዚህ ታሪኮች የሚያስረዱት አንድ ቤት ሲታደስ ግድግዳና ጣሪያ ብቻ አለመሆኑን ነው። ከቤቱ ጋር የነዋሪው ተስፋ፣ የቤተሰቡ መረጋጋትና የሰው ልጅ ክብርም አብሮ ይታደሳል። በዚህም በጎነት የችግር መፍቻ ብቻ ሳይሆን ከጊዜ ጊዜ የተስፋ ማስፈንጠሪያና ሰብዓዊ ክብር ማጎናጸፊያ ተግባር እየሆነ መጥቷል። በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ቤታቸው ከታደሰላቸው መካከል ታየሁ መኮንን እንደሚሉት፤ ቀደም ሲል ይኖሩበት የነበረው ቤት 'ቤት ነው ለማለት እንኳን አያስደፍርም' ነበር። ዛሬ ግን ታሪካቸው ተቀይሯል። በበጎ ፈቃደኞች አማካኝነት የመኖሪያ ቤት ችግራቸው ተቀርፎ፣ 'ቤቴ በመታደሱ ያለ ሀሳብ ጎኔን ማሳረፍ ችያለሁ' ሲሉም ወይዘሮ ታየሁ ገልጸዋል። ይህ አንድ ነዋሪ ያገኘው የቤት ለውጥ ብቻ አይደለም። ከዓመታት የጭንቀት ኑሮ ወደ መረጋጋት የተሸጋገረ ሕይወት ነው። ከስጋት ወደ እፎይታ፣ ከተስፋ መቁረጥ ወደ ተስፋ የተደረገ ጉዞ ነው። ለበርካታ ዓመታት በማይመች ቤት ኑሮ ሲገፉ እንደቆዩ የገለጹት ወይዘሮ ዘውዲቱ ገብረማርያም ደግሞ፤ አሁን ላይ ቤታቸው በመታደሱ ደስ ብሏቸው የሚኖሩበትን ዕድል እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል። በሰው ተኮር የልማት መርሃ ግብር አቅመ ደካማ ወገኖችን ለመደገፍ የሚከናወኑ ተግባራትም የበርካቶችን ተስፋ የሚያለመልም አስደናቂ ተግባር መሆኑን ገልጸዋል። እነዚህ የነዋሪዎች ምስክርነቶች በጎነት በተግባር ሲገለጽ የሰውን ክብር እንደሚያጎናጽፍ፣ የተሰበረ ተስፋን እንደሚያድስና ለነገ የሚያስብ ሕይወትን እንደሚፈጥር ያረጋግጣሉ። በተለይም እናቶች፣ አረጋውያን፣ አቅመ ደካሞችና የሀገር ባለውለታዎች የሚያገኙት ድጋፍ በቁሳዊ እርዳታ ብቻ የሚመዘን ሳይሆን 'እናንተም የዚህ ሀገር ክብር ናችሁ' የሚልን ሰብዓዊ መልዕክትን ያስተላልፋል። በዚህ ረገድ የመደመር መንግሥት ሰው ተኮር ልማትን እንደ የልማት ፖሊሲ አቅጣጫ በመያዝ የዜጎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ክፍተቶች በመሙላት ተስፋን የሚያለመልሙ ተግባራትን እያጠናከረ ይገኛል። የቤት ግንባታና ዕድሳት፣ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶችና ሌሎች ሰው ተኮር መርሃ ግብሮችም ይህንኑ አቅጣጫ በተግባር ከሚያሳዩ ተጨባጭ ለውጦች መካከል ይጠቀሳሉ። አስተያየት ሰጪዎቹ ዛሬ ላይ ውብና ጽዱ በሆነ ቤት የሚኖሩበት ዕድል የተፈጠረው መንግሥት፣ ባለሀብቶችና ሌሎች በጎ ፈቃደኞች ባከናወኑት መልካም ተግባር በመሆኑ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። በአዲስ አበባ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት አረጋውያንን፣ አቅመ ደካሞችና የሀገር ባለውለታዎችን አመቺ መጠለያ እንዲያገኙ ለማድረግ የሚሰሩ ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉም መልዕክት አስተላልፈዋል። በእርግጥም የበጎነት ዋጋው በሚሰጠው የቁሳቁስ መጠን ብቻ አይለካም። በሰው ልብ ውስጥ በሚፈጥረው ተስፋና በሕይወት ላይ በሚያመጣው ለውጥ ይመዘናል። የተሰራው ቤት ለአንዲት እናት የእፎይታ ምንጭ፣ ለአንድ አረጋዊ የክብር መገኛ፣ ለአካል ጉዳተኛ ደግሞ በራስ መተማመንና ነፃነት መገለጫ ይሆናሉ። ይህም ሰው ተኮር ልማት ማለት ትልልቅ ፕሮጀክቶችን መገንባት ብቻ ሳይሆን፣ የአንድ ዜጋን የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል፣ የአንድ ቤተሰብን ተስፋ ማደስና የአንድን ሰው ክብር ማስመለስ ጭምር መሆኑን ያሳያል። በጎነት ከአንድ ሰው ወደ ሌላው የሚሸጋገር ቀላል የመልካም ተግባር መገለጫ ቢመስልም በጋራ ሲተገበር ማኅበረሰብን የመለወጥ ታላቅ ኃይል አለው። የእነዚህ ነዋሪዎች ታሪክም ይህንኑ ያረጋግጣል። ከተስፋ መቁረጥ ወደ ተስፋ፣ ከስጋት ወደ እፎይታ፣ ከአስቸጋሪ ኑሮ ወደ የተሻለ ኑሮ የተሸጋገሩ ሕይወቶችን ያሳያል። ስለሆነም በጎነትን እንደ የአንድ ጊዜ ዘመቻ ሳይሆን እንደ የማኅበረሰብ የጋራ እሴት ማጠናከር፣ ተጋላጭ የሆኑ ወገኖችን መደገፍና ሰው ተኮር ልማትን ማስቀጠል የጋራ ኃላፊነት ነው። ዛሬ የተሰራ ቤት ከግድግዳ በላይ ነው። የነገ ተስፋ መሰረት ነው። ዛሬ የተዘረጋ የበጎነት እጅም ከአንድ ሰው የሚተርፍ ለብዙዎች የሚደርስ የሰብዓዊነት ብርሃን ነው።
የኢትዮጵያ የማዕድን ምርት እመርታ
Aug 21, 2026 1308
በሙሴ መለሰ የኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ በአገር በቀል የኢኮኖሚና የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ታግዞ፣ ባለፉት ዓመታት የታዩበትን የአሰራርና መዋቅራዊ ችግሮች በመቅረፍ ከፍተኛ የመነቃቃት ምዕራፍ ላይ ይገኛል። ዘርፉ በ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድ ውስጥ ትኩረት ከተሰጣቸው አምስት ቁልፍ የኢኮኖሚ ምሰሶዎች አንዱ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት እንደገለጹት፣ ማዕድን በብዝኃ ዘርፍ የልማት ምልከታችን ውስጥ እና በሀገሪቱ የልማት ዕቅድ ውስጥ ትኩረት ከተሰጣቸው አምስት የኢኮኖሚ ምሰሶዎች አንዱ ቁልፍ ዘርፍ ሆኖ ይቀጥላል። ባለፉት ሶስት አሥርት ዓመታት ውስጥ የማዕድን ዘርፉ ለአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) ያበረከተው አስተዋጽኦ ከ0 ነጥብ 8 በመቶ በታች የነበረ ቢሆንም፣ በአሁኑ ወቅት ግን መንግሥት ለዘርፉ በሰጠው የላቀ ትኩረት ከፍተኛ መዋቅራዊ ሽግግር እያመጣ ይገኛል። በ2018 በጀት ዓመት ከዘርፉ 5 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማግኘት ተችሏል። ይህም ከቀዳሚው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ92 በመቶ የገቢ ዕድገትና የ27 በመቶ የምርት መጠን ብልጫ ያሳየ ሲሆን፣ ምርቶቹም በዋናነት ወደ ሳውዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ አሜሪካ፣ ጀርመን እና ቻይና ተልከዋል። በወጪ ንግድ እድገት ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ ያለው የወርቅ ምርት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ስምንት ወራት 22 ነጥብ 5 ቶን ለውጭ ገበያ የቀረበ ሲሆን እስከ ዓመቱ ማብቂያ 32 ቶን ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል። በባህላዊ መንገድ የሚመረተውን የወርቅ ምርት ለማዘመንም መንግሥት የማጣሪያና ማቀለጫ ፋብሪካዎችን በመገንባት ላይ ይገኛል። የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ከውጭ የሚገቡ ስትራቴጂክ ምርቶችን በሀገር ውስጥ የመተካት ሰፊ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው። በዚህም ለድንጋይ ከሰል ግዢ ይወጣ የነበረውን የውጭ ምንዛሬ ሙሉ በሙሉ ማስቀረት የተቻለ ሲሆን፣ የሲሚንቶ ምርትም ባለፉት ስምንት ዓመታት ከነበረበት 8 ሚሊየን ቶን አሁን ላይ በዓመት ወደ 14 ሚሊየን ቶን አድጓል። ሀገሪቱ በየዓመቱ ለማዳበሪያ ግዢ የምታወጣውን 2 ቢሊየን ዶላር ለማስቀረትም የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ ተጀምሯል። በተጨማሪም በየዓመቱ ለብረት ምርት ግዢ የሚወጣውን 1 ቢሊየን ዶላር በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት የሚያስችል ግዙፍ ፋብሪካ የመገንባት ስምምነት ተፈጽሞ ወደ ስራ ተገብቷል። የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ በዘርፉ የተሰማሩ ፕሮጀክቶች ዋጋ 10 ቢሊየን ዶላር የደረሰ ሲሆን፣ ይህም ከለውጡ በፊት ከነበረውና ከ100 ሚሊየን ዶላር የማይበልጡ አነስተኛ ኢንቨስትመንቶች በከፍተኛ ደረጃ የለወጠ ስኬት ነው። የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በአፋር ክልል የሚገኘውን ግዙፍ የፖታሽ ክምችት ለማልማት ፈቃድ አግኝቶ ወደ ሥራ ገብቷል። በተጨማሪም ታንታለምን እሴት ጨምሮ ለመላክ ከአሜሪካ ኩባንያ ጋር ድርድር እየተደረገ ሲሆን፣ ለባትሪና ቴክኖሎጂ ወሳኝ የሆኑትን ሊቲየም፣ ኮባልትና ኒኬልን ለማምረት ዝግጅት ተጠናቋል። የኢንቨስትመንት ምህዳሩን ሳቢ ለማድረግ የማዕድን ፈቃድ አሰጣጥ አሰራር ቅድሚያ የመጣን ቅድሚያ ማስተናገድ በሚል መርህ እንዲመራ ተደርጓል። የወጪ ንግድ ኮንትራት ምዝገባና መላኪያ ፈቃዶች፣ እንዲሁም የካዳስተር ሲስተም ሙሉ በሙሉ ወደ ኦንላይን ኤሌክትሮኒክስ አሰራር ተሸጋግረዋል። በ2019 በጀት ዓመት ከዘርፉ 6 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት የታቀደ ሲሆን፣ የመንግሥት ስትራቴጂካዊ እቅድ እ.አ.አ. በ2030 የማዕድን ወጪ ንግድ ገቢን ከ10 ቢሊዮን ዶላር በላይ በማድረስ ኢትዮጵያን ከአፍሪካ አምስት ቀዳሚ የማዕድን አምራች ሀገራት ተርታ ማሰለፍ ነው። በዘርፉ እየተካሄደ ያለው መዋቅራዊ ሽግግር ኢትዮጵያ በውጭ ምርቶች ላይ ያላትን ጥገኝነት በመቀነስ ወደ ኢንዱስትሪ መሪነት የምታደርገውን ጉዞ ያፋጥነዋል። የወርቅ፣ የተፈጥሮ ጋዝ፣ የፖታሽ እና የቴክኖሎጂ ማዕድናት በሀገር ውስጥ እሴት ተጨምሮባቸው ለዓለም ገበያ መቅረባቸው ሀገሪቱ በዓለም አቀፍ የንግድ መድረክ ላይ የሚኖራትን ተጽዕኖ ፈጣሪነት እና ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገት ያረጋግጣል።