የስራ ቡድኖች የአጀንዳ ምክረሃሳቦቻቸውን ለሚያደራጀው ቡድን እያቀረቡ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የስራ ቡድኖች የአጀንዳ ምክረሃሳቦቻቸውን ለሚያደራጀው ቡድን እያቀረቡ ነው
አዲስ አበባ ፤ነሐሴ 8 /2018(ኢዜአ)፦የስራ ቡድኖች ሁሉም ቡድኖች ያዘጋጇቸውንና የተስማሙባቸውን ምክረ-ሀሳቦች እንዲያናብብ፣ እንዲያጣጥም እና እንዲያደራጅ ለተቋቋመው እና 120 አባላት ላሉት ቡድን በማቅረብ ላይ ናቸው፡፡
ይህ ቡድን ከስምንቱ ባለ 500 አባላት የስራ ቡድን በተመረጡ 15 አባላት የተዋቀረ ሲሆን መግባባት የተደረሰባቸውን የሁሉንም አጀንዳዎች ምክረሃሳቦች አዳምጦ የሚያጣጥም፣ በሚቀርቡ ሀሳቦች መካከል መጣረስ እንዳይኖር ጥንቃቄ የሚያደርግና ለጠቅላላ ሀሳቦቹ ወጥነት በመፍጠር 4ሺ አባላት ላሉት ዋናው ጉባኤተኛ አደራጅቶ የሚያቀርብ ነው፡፡
ቡድኑ በአሁኑ ሰዓት ከእያንዳንዱ የስራ ቡድን የመጡ ምክረሃሳቦችን በማዳመጥ ላይ መሆኑን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታውቋል፡፡