ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ከድንገተኛ የሕክምና ወጪና የኢኮኖሚ ጫና ታድጎናል -- በድሬዳዋ ተጠቃሚዎች
Nov 18, 2026 39
ድሬዳዋ፤ ህዳር 9/2019 (ኢዜአ)--በድሬዳዋ የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ተጠቃሚዎች በሁሉም የሕክምና ተቋማት የተሟላ የጤና አገልግሎት ማግኘታቸው ከድንገተኛ የሕክምና ወጪና የኢኮኖሚ ጫና እንደታደጋቸው ገለጹ። በድሬዳዋ አስተዳደር በገጠር እና በከተማ የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ተጠቃሚዎች ቁጥር እያደገ በመምጣቱ ፍትሃዊ የጤና ተደራሽነትና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ተችሏል። በስተዳደሩ በማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድን አገልግሎት ተጠቃሚ የሆኑ ነዋሪዎች ለኢዜአ እንደገለጹት፣ የጤና መድህን በተለይ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎችን ጤናማና አምራች ዜጋ እንዲሆኑ አስችሏል። በገንደቆሬ ጤና ጣቢያ ሕክምናቸውን ሲከታተሉ ከነበሩት መካከለ አቶ ስዩም በቀለ እንዳሉት፤ በማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን በሁሉም ደረጃ ባሉ የጤና ተቋማት የሕክምና አገልግሎት እያገኙ ነው። ከዚህ በፊት የሕክምና አገልግሎት ለማግኘት የገንዘብ ዕጥረት እንደነበረባቸው አስታውሰው፣ የጤና መድህን አባል በመሆናቸው በማንኛውም ወቅት ያለችግር መታከም መቻላቸውን ተናግረዋል። ቤተሰቦቻቸውም ሕመም ሲገጥማቸው ከጤና ጣቢያ ጀምሮ አስከ ሆስፒታል ደረስ በቅብብሎሽ የፈለጉትን ሕክምና ማግኘታቸው ጤናቸውን በአግባቡ ለመጠበቅና አምራች ለመሆን እንዳስቻላቸው ነው የገለጹት የጤና መድህን አገልግሎት ከሰጠን እፎይታ ባለፈ ጤናማና አምራች እንድንሆን እያገዘን ነው ያሉት ደግሞ ሌላው ተጠቃሚ አቶ አብደላ ሙሜ ናቸው። በአዲስ ከተማ ጤና ጣቢያ ሲታከሙ ከነበሩት የጤና መድህን ተጠቃሚዎች መካከል ወይዘሮ አስራት ወልደፃዲቅ እና አቶ ቢኒያም አበራ የጤና መድህን አባል መሆናቸው የዓመታት ችግራቸውን እንደፈታላቸው ተናግረዋል። አልፎ አልፎ በጤና ተቋማት ከሚያጋጥም የመድኃኒት እጥረት ችግር በስተቀር በቅብብሎሽ አስከ ከፍተኛ ሆስፒታል ድረስ በመሄድ መታከም መቻላቸው የኢኮኖሚ ጫና እንዳቃለለላቸው ገልጸዋል። የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ከተጀመረ ወዲህ በድሬዳዋ የጤና አገልግሎት ተደራሽነት በማስፋት ጤናማ ማህበረሰብ ለመፍጠር እየተቻለ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ በአስተዳደሩ ጤና ቢሮ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አስተባባሪ ሲስተር ሜሪ አምዴ ናቸው። በአሁን ወቅት በማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን መታቀፍ ካለባቸው 91 በመቶዎቹ ተካተው አስፈላጊውን የሕከምና አገልግሎት እያገኙ መሆናቸውን ተናግረዋል። የማህበረሰብ ጤና መድህን አገልግሎት በተለይ ከፍለው መታከም የማይችሉትን የህብረተሰብ ክፍሎች ከችግር መታደጉን የገለጹት አስተባባሪዋ፣ የህብረተሰቡን የእርስ በእርስ መረዳዳትና ትስስርን እያጠናከረ መሆኑንም ተናግረዋል። በተያዘው በጀት ዓመትም የጤና መድህን አባላትን ቁጥር በማብዛት የሚሰጠውን የጤና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት ከማሳደግ ባለፈ ጤናማ እና አምራች ዜጋ የመፍጠር ሥራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
ኢትዮጵያ በመደመር እሳቤ ሀገራዊ አቅሞችንና ዓለምአቀፍ ትብብሮችን በማቀናጀት ወረርሽኞችን ቀድሞ የመከላከል አቅሟን እያጎለበተች ነው
Nov 18, 2026 47
አዲስ አበባ፤ ህዳር 9/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በመደመር እሳቤ ሀገራዊ አቅሞችንና ዓለምአቀፍ ትብብሮችን በማቀናጀት ወረርሽኞችን ቀድሞ የመከላከል እና ከተከሰተም ፈጥኖ የመቆጣጠር አቅሟን እያጎለበተች መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ገለጹ። 21ኛው ዓለም አቀፍ የፓንዳሚክ ፈንድ ቦርድ ስብሰባ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል። የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ በዚሁ ወቅት፤ ኢትዮጵያ በመደመር እሳቤ ሀገራዊ አቅሞችንና ዓለምአቀፍ ትብብሮችን በማቀናጀት ወረርሽኞችን ቀድሞ የመከላከል እና ከተከሰተም ፈጥኖ የመቆጣጠር አቅሟን እያጎለበተች ትገኛለች ብለዋል። የበሽታዎች ቅኝት፣ የላቦራቶሪ አቅምንና የአደጋ ጊዜ ምላሽ ዝግጁነትን ለማሳደግ ያለመ "የኢትዮጵያ ወረርሽኝ ዘርፈ-ብዙ መከላከል ዝግጁነት እና ምላሽ ፕሮጀክት" በስፋት እየተተገበረ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል። ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት የኢትዮጵያን የጤና፣ የግብርና እና የገንዘብ ሚኒስቴሮች እንዲሁም ዓለምአቀፍ ተቋማትን በጋራ ያስተሳሰረ መሆኑን አንስተዋል። ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያ ወደፊት ሊከሰቱ የሚችሉ ድንገተኛ የጤና አደጋዎችንና ወረርሽኞችን በራሷ አቅም ቀድማ ለመከላከል እና ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የምታደርገውን ጥረት እያገዘ እንደሚገኝ ተናግረዋል። የሰው እና የእንስሳት ላቦራቶሪዎችን በካርታ የመለየት፣ መመሪያዎችን የማዘጋጀት እና የበሽታ አምጪ ተህዋስያንን ዘረ-መል የመመርመር አቅምን እንደሚያሳድግም ጠቁመዋል። በሺዎች ለሚቆጠሩ የዘርፈ-ብዙ ባለሙያዎች ስልጠና በመስጠት የተሳሳቱ መረጃዎችን መመከት የሚያስችል የአደጋ ጊዜ ተግባቦት ስርዓት በመዘርጋት ህብረተሰቡን የመጠበቅ ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል። የጤናው ዘርፍ ስራዎች በብቸኝነት ሳይሆን ከሀገር ውስጥ እስከ ዓለም አቀፍ አጋሮች እንዲሁም ማህበረሰቡን በማቀናጀት በማስተባበር እየተከናወኑ መሆኑን አንስተዋል። የጤና አጠባበቅ ስርዓትን ለማጠናከር በላቦራቶሪዎች አቅም ግንባታ፣ በሰለጠነ የሰው ሃይል ዝግጅት፣ በድንገተኛ አደጋ ምላሽ ሰጪዎች ስልጠና እንዲሁም በቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓቶች ላይ ሰፊና አስተማማኝ ስራዎች መሰራታቸውን ጠቁመዋል። በኢትዮጵያ የተከናወኑ የጤና ስራዎች ውጤታማና አበረታች መሆናቸውን የገለጹት ሚኒስትሯ፣ ኢትዮጵያ በመደመር እሳቤ የማይበገር የጤና ስርዓት እየገነባች መሆኑን አመላክተዋል።
ጤናማ ኅብረተሰብ የመፍጠር ጉዟችን በቀልጣፋ አገልግሎትና ዘመኑን በዋጀ ስርዓት መከናወን አለበት- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Nov 18, 2026 65
አዲስ አበባ፤ ህዳር 9/2019 (ኢዜአ)፦ ጤናማ ኅብረተሰብ የመፍጠር ጉዟችን በቀልጣፋ አገልግሎትና ዘመኑን በዋጀ ስርዓት መከናወን አለበት ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልእክት ዛሬ በባሕር ዳር ከተማ በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘውን ምድረ ገነት ጠቅላላ ሆስፒታልን ጎብኝተናል ብለዋል። ከዚህ ቀደም ተቋርጦ የቆየው ይህ ግንባታ፣ ከስድስት ወራት በፊት በአዲስ ውል እንደገና ተጀምሮ ወደ መጠናቀቂያው ደርሷል ነው ያሉት። ይህ ባለ አምስት ወለል ዘመናዊ የጤና ተቋም ግንባታ ሲጠናቀቅ ወረቀት አልባ የጤና መረጃ ሥርዓት የሚመራ መሆኑን ጠቁመው፤ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ከሕክምና አገልግሎት ጋር በማቀናጀት የተሻለ የጤና አገልግሎት የሚሰጥ ይሆናል ብለዋል። የጤና ተቋማትን በአቅም፣ በቴክኖሎጂና በአገልግሎት ማሳደግ ጤናማ ኅብረተሰብን ለመገንባት የምናደርገው ቁርጠኛ ጥረት አካል ነው ሲሉም ገልጸዋል። S
ኢትዮጵያ የገነባችው የመከላከያ ሰራዊት አቅም ለቀጣናው ሰላምና መረጋጋት ትልቅ አቅም ነው
Nov 18, 2026 85
አዲስ አበባ፤ ህዳር 9/2019(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በመደመር መንግሥት የገነባችው የመከላከያ ሰራዊት አቅም ሀገራዊ ጥቅምን ከማስጠበቅ ባለፈ ለቀጣናው ሰላምና መረጋጋት ትልቅ አቅምና ተጽዕኖ እየፈጠረ መሆኑን በመከላከያ ሰላም ማስከበር ማዕከል የዓለም አቀፍ ሰላም ማስከበር ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ገዛኸኝ ፈቃዱ ገለጹ። የመደመር መንግሥት የሀገርን ሉዓላዊነትና ብሔራዊ ጥቅም በአስተማማኝ መሰረት ላይ ለማቆም ካከናወናቸው የሪፎርም ስራዎች መካከል የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን በአዲስ መልክ ማደራጀትና ማዘመን ዋነኛው ነው። ሰራዊቱን ከማንኛውም የፖለቲካ ወገንተኝነት በማላቀቅ ሕገ-መንግስታዊ ተልዕኮውን በብቃት የሚወጣ ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራትም ተከናውነዋል። በዘመናዊ ወታደራዊ ቴክኖሎጂ፣ በሰው ኃይል ስልጠናና በተቋማዊ አደረጃጀት ረገድ የተከናወኑ ውጤታማ ተግባራት የሰራዊቱን የመፈጸምና የመከላከል አቅም ወደ ላቀ ደረጃ አሸጋግረውታል። ይህ በመደመር መንግሥት የተገነባው ጠንካራና ዘመናዊ ወታደራዊ አቅም የኢትዮጵያን ሰላም ከማስጠበቅ ባለፈ ለቀጣናው ሰላምና መረጋጋት ዋስትና እንደሆነ ያነጋገርናቸው የዘርፉ ከፍተኛ አመራሮች ገልጸዋል። ብርጋዴር ጄኔራል ገዛኸኝ ለኢዜአ እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ ሰራዊቷን በከፍተኛ ሁኔታ በማደራጀት፣ በስልጠናና በአቅም ግንባታ የማድረግ አቅሙን በከፍተኛ ደረጃ ገንብታለች። በሀገር ውስጥ የተፈጠረው ይህ ጠንካራ ወታደራዊ አቅም ሀገራዊ ሰላምን ከማስፈን ባለፈ፣ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ተሳትፎና ተጽዕኖ በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያሳድገው ጠቁመዋል። ሰራዊቱ ይህንን የገነባውን አቅም በዘመናዊ ቴክኖሎጂና በእውቀት ይበልጥ በማጠናከር በሰላም ማስከበር ዘርፍ ያለውን የመሪነት ሚና ማስቀጠል እንዳለበትም አመልክተዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ኮሌጅ የፖሊሲና ስትራቴጂ ጉዳዮች ቡድን መሪ ሌተናል ኮሎኔል አራጋው ገብረመድህን በበኩላቸው፣ መከላከያ ሰራዊቱ በቴክኖሎጂ፣ በስልጠናና በሰው ኃይል ቁጥር እየዘመነ መምጣቱን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ከኮሪያ እስከ አፍሪካ ሀገራት ድረስ በሰላም ማስከበር የካበተ ታሪክ እንዳላት ያስታወሱት ሌተናል ኮሎኔል አራጋው፣ አሁን የተገነባው ዘመናዊ የሰራዊት አቅም ሰላምን ከሀገር ውስጥ አልፎ ለጎረቤት ሀገራትና ለዓለም ለማስጠበቅ ሙሉ ብቃት እንዳለው አስረድተዋል። የኢትዮጵያን የሰላም ማስከበር አስተዋጽኦና የሰራዊቱን አቅም በጥናትና በመጽሐፍ በመሰነድ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዩኒቨርሲቲዎችና የምርምር ተቋማት በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በደቡብ ምሥራቅ ኦሮሚያ ዞን የቱሪዝም መስህቦችን በማልማትና በማስተዋወቅ ሰፊ ተግባራት እየተከናወኑ ነው
Nov 18, 2026 114
ሮቤ ህዳር 09/2019 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ምሥራቅ ኦሮሚያ ዞን የተፈጥሮ፣ ታሪካዊና ባህላዊ መስህቦችን በማልማትና በማስተዋወቅ የጎብኝዎች ቁጥርና የዘርፉ ገቢ እያደገ መምጣቱን የዞኑ ቱሪዝም ጽህፈት ቤት አስታወቀ። ባለፈው በጀት ዓመት 1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ቱሪስቶች አካባቢውን የጎበኙ ሲሆን፣ በዘንድሮው ዓመት ደግሞ ከ2 ነጥብ 1 ሚሊዮን በላይ ቱሪስቶችን በመሳብ ከሶስት ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ለማግኘት ታቅዶ ወደ ሥራ ተገባቷል። የደቡብ ምሥራቅ ኦሮሚያ ዞን የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ፣ የሶፍ ኡመር ዋሻ፣ ድሬ ሼህ ሁሴንና ሌሎች በርካታ የተፈጥሮ፣ ታሪካዊና ባህላዊ መስህቦች መገኛ በመሆኑ በሀገሪቱ የቱሪዝም እምቅ አቅም ካላቸው አካባቢዎች አንዱ ነው። በተለይም የባሌ ተራሮች ልዩ የተፈጥሮ ሥነ-ምህዳርና የዱር እንስሳት ሀብት፣ የሶፍ ኡመር ዋሻ ልዩ የተፈጥሮ ገጽታና የድሬ ሼህ ሁሴን ታሪካዊና ሃይማኖታዊ እሴቶች አካባቢውን ለቱሪዝም ልማት ምቹ ከሚያደርጉት ዋና ዋና ሀብቶች መካከል ይጠቀሳሉ። የደቡብ ምሥራቅ ኦሮሚያ ዞን ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ደጀኔ ሚልኬሳ እንዳሉት፤ በዞኑ የሚገኙ የቱሪዝም መስህቦችን ለማልማት፣ መሠረተ ልማቶችን ለማሻሻልና የአካባቢውን የቱሪዝም አቅም በስፋት ለማስተዋወቅ በተለያዩ መስኮች ሥራዎች እየተከናወኑ ናቸው። ባለፈው የበጀት ዓመት 1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ቱሪስቶች አካባቢውን የጎበኙ ሲሆን፣ በዘንድሮው ዓመት ከ2 ነጥብ 1 ሚሊዮን በላይ ቱሪስቶችን በመሳብ ከሶስት ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ለማግኘት ታቅዶ ወደ ሥራ መገባቱን ገልጸዋል። መስህቦችን ማልማት የጎብኚዎችን ቁጥር ከማሳደግ ባለፈ የአካባቢውን ነዋሪዎች የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማጠናከር፣ የሥራ ዕድል ለመፍጠርና የባህልና ታሪካዊ ቅርሶችን ለትውልድ ለማስተላለፍ ወሳኝ መሆኑንም አመልክተዋል። የባሌና አካባቢው የተለያዩ ሥነ-ምህዳሮች፣ የተፈጥሮ ሀብቶችና ታሪካዊ ቅርሶች በአንድ አካባቢ መገኘታቸውን የጠቀሱት ኃላፊው፤ እምቅ የቱሪዝም ኃብቱን ለማጎልበት ከመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር እየተሰራ ነው ብለዋል። በዞኑ ከ100 በላይ አዳዲስ የተፈጥሮ፣ ታሪካዊና ሰው ሠራሽ የቱሪዝም መስህቦች በጥናት መለየታቸውንና ለመስህቦቹ ዲጂታል ካርታ መዘጋጀቱንም በማሳያነት አንስተዋል። የመስህብ ስፍራዎችን በምርምር መለየት፣ መመዝገብና የጎብኚዎችን መረጃ ተደራሽ ማድረግ ከዘርፉ የሚገኘውን ጥቅም ለማሳደግ ወሳኝ ነው ብለዋል። በዞኑ ሰሞኑን የቱሪዝም መስህቦችን የጎበኙ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ቡድንም የአካባቢውን እምቅ ሀብት ለሀገር ውስጥና ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ጉልህ ድርሻ አለው ብለዋል። በመስክ ጉብኝቱ የሚዘጋጁ የዜና ዘገባዎች፣ ፎቶግራፎችና የቪዲዮ ምስሎች የመስህብ ስፍራዎቹን ተፈጥሯዊና ታሪካዊ ይዘት በስፋት በማሳየት የጎብኚዎችን ፍላጎት ለማነሳሳት ያግዛሉ ነው ያሉት። የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የቱሪዝም ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ገረመው መብራቱ እንዳሉት፣ ፓርኩን የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር ቱሪስቶች የጎበኙ ሲሆን ከዚህም የተሻለ ገቢ ተገኝቷል ብለዋል። በፓርኩ ውስጥ በርካታ ሐይቆች እንደሚገኙ የጠቆሙት ኃላፊው፣ ከእነዚህም ውስጥ ብዙዎቹ ክረምት ከበጋ የማይደርቁ ቋሚ ሐይቆች መሆናቸው ልዩ እንደሚያደርገውም ገልጸዋል። የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክን የጎበኙት ዴቪድ ማርሻል፣ ከዚህ በፊት በተለያየ ሀገር የተለያዩ የቱሪስት መስህቦችን የጎበኙ ቢሆንም በባሌ ባዩት እምቅ የቱሪዝም ሀብት ግን እጅግ መደነቃቸውን ገልጸዋል። የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ማራኪ እና በየትኛውም ቦታ የማይገኝ ውብ ተፈጥሯዊ ገጽታ ያለው መሆኑን አንስተዋል።
ፖለቲካ
በትግራይ ክልል የተረጋጋ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ተፈጥሯል
Nov 18, 2026 151
መቀሌ፤ ህዳር 9/2019 (ኢዜአ)፦ በትግራይ ክልል የተረጋጋ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ መፈጠሩን የክልሉ የፌደራል መንግስት ባለአደራ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ። የትግራይ ክልል የፌደራል መንግስት ባለአደራ አስተዳደር የኮሙኒኬሽን ቢሮ የአስተዳደሩን የአንድ ወር የስራ አፈፃፀም አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል። የቢሮው ኃላፊ አቶ ዳሞራ ያሕያ በሰጡት መግለጫ እንደገለፁት ባለአደራ አስተዳደሩ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ባከናወናቸው ተግባራት በክልሉ የተረጋጋ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ተፈጥሯል። ባለአደራ አስተዳደሩ ከክልል እስከ ቀበሌ ሙሉ በሙሉ መዋቅር መዘርጋቱን እና በህዝብ የተመረጡ አስተባባሪዎች ሙሉ በሙሉ ወደ መደበኛ ስራ መግባታቸውን ተናግረዋል። በዚህም ከህዝቡ ጋር የተደረጉ ውይይቶች ለክልሉ ሁለንተናዊ ለውጦች መሰረት የጣሉ መሆናቸውን ጠቁመዋል። አሁን ላይ በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች የመማር ማስተማር ሂደት መጀመሩን ተናግረዋል። የክልሉ የመንግስት ሰራተኞች ወደ ስራቸው መመለሳቸውንና ደመወዝ መክፈል መጀመሩን ጠቁመው የህዝብ አገልግሎቶች ወደ ተሟላ ስራ መሸጋገራቸውንም አመልክተዋል። ባለአደራ አስተዳደሩ በተቋቋመ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የተሰሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ጠቁመው አሁን ላይ ለቀጣይ ምርጫ ምቹ ሁኔታ መፍጠር የሚያስችሉ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አስታውቀዋል። ወጣቱን ጨምሮ መላው ህብረተሰብ ለክልሉ ሰላም መረጋገጥ እያሳየ ያለውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥል አመልክተዋል።
የኢትዮጵያና የየሀገራቸውን ሁለንተናዊ የትብብር አድማስ በማስፋት የዲፕሎማሲ ግንኙነትን ለማጎልበት እንሰራለን -የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች
Nov 18, 2026 201
አዲስ አበባ፤ ህዳር 9/2019(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያና የየሀገራቸውን ሁለንተናዊ የትብብር አድማስ በማስፋት የዲፕሎማሲ ግንኙነትን ለማጎልበት በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች ገለጹ። የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ከአፍሪካ፣ እስያ፣ መካከለኛው ምሥራቅ፣ አውሮፓና ካሪቢያን ሀገራት በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙ የ16 ሀገራት አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤ በትላንትናው እለት ተቀብለዋል። በብሔራዊ ቤተ-መንግሥት በክብር ዘብና በማርሽ ባንድ ደማቅ ሥነ-ሥርዓት ታጅቦ በተካሄደው መርሐ ግብር በኢትዮጵያ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች፣ የሰሜን ኮሪያ፣ የቆጵሮስ፣ የቼክ ሪፐብሊክ እና የአየርላንድ አምባሳደሮች የሹመት ደብዳቤቸውን ለፕሬዝዳንቱ አቅርበዋል። በተጨማሪም በኢትዮጵያ የሕንድ፣ የቻድ ሪፐብሊክ፣ የኦስትሪያ፣ የኖርዌይ፣ የፊንላንድ ሪፐብሊክ፣ የማልታ ሪፐብሊክ፣ ጣሊያን፣ የባርቤዶስ፣ ደቡብ ኮሪያ፣ የሉክሰምበርግና የግሬናዳ አምባሳደሮች የሹመት ደብዳቤያቸውን ለፕሬዝዳንቱ አቅርበዋል። የሹመት ደብዳቤቸውን ለፕሬዝዳንቱ ካቀረቡት መካከል ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉ አምባሳደሮች እንዳሉት፤ የኢትዮጵያና የየሀገራቸውን ሁለንተናዊ የዲፕሎማሲ ትብብርና ግንኙነት በማጠናከር የጋራ ተጠቃሚነትን ለማጎልበት ይሰራሉ። በኢትዮጵያ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች አምባሳደር አብደላ ሀሰን ኡባይድ ሀሰን አልሻምሲ በዚሁ ወቅት፤ ኢትዮጵያና የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ጥልቅ ወዳጅነት የገነቡ ስትራቴጂክ አጋር ሀገራት ናቸው ብለዋል። በኢትዮጵያ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች አምባሳደር በመሾማቸው ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው በመጥቀስ፤ በቆይታቸው የሀገራቱን የትብብር ብሩህ አድማስ በማስፋት የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያጎለብት ጠንካራ ግንኙነት ለመገንባት በትኩረት እንደሚሰሩ ገልጸዋል። በኢትዮጵያ የቆጵሮስ አምባሳደር ሳቫስ ቪላድሚሩ በበኩላቸው፤ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የቆጵሮስ አምባሳደር ሆኜ በመሾሜ ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶኛል ብለዋል። በቀጣይም በኢትዮጵያና በቆጵሮስ መካከል የባህል፣ የንግድና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን በማጎልበት የሀገራቱን ኢንቨስትመንት ለማጠናከር በልዩ ትኩረት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል። በኢትዮጵያና በቼክ ሪፐብሊክ መካከል በመንግሥት ለመንግሥትና በሌሎች ዘርፎች ጠንካራ የዲፕሎማሲ ትብብር እየተገነባ ነው ያሉት ደግሞ በኢትዮጵያ የቼክ ሪፐብሊክ አምባሳደር ያን ሮቼክ ናቸው። የሀገራቱን ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነትም በተለያዩ የኢንቨስትመንትና የፕሮጀክት ግንባታ ትብብር የበለጠ ለማጠናከር በትኩረት እንደሚሰሩ አስረድተዋል። በኢትዮጵያ የአየርላንድ አምባሳደር ኪያራን ማደን በበኩላቸው፤ በኢትዮጵያ በተሰጣቸው ሹመትና ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል። በቀጣይም የኢትዮጵያን ፈጣን ዕድገት በመደገፍ የአየርላንድ አልሚ ባለሀብቶች በተለያዩ የንግድና ኢንቨስትመንት አማራጮች የሚሰማሩበትን ሁኔታ ለመፍጠር በትኩረት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል። በሌላ መልኩም በቅርቡ የሀገራቱን የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር በባህል ዘርፍ ትኩረቱን ያደረገ ሁነት ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አስታውሰዋል። በኢትዮጵያ የሕንድ አምባሳደር ዴቪሽ ዑታም በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያና ሕንድን ታሪካዊና ጠንካራ የዲፕሎማሲ ወዳጅነት የበለጠ ለማጎልበት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል። የኢትዮጵያን ፈጣንና አስደናቂ ዕድገት የሚያሳልጥ የንግድና ኢንቨስትመንት የኢኮኖሚ ትብብርን ለማጎልበት ይሰራል ያሉት ደግሞ በኢትዮጵያ የኦስትሪያ አምባሳደር ፒተር ኤልስነርማካይ ናቸው።
የኢትዮጵያ የዘመኑ ሉዓላዊነት በምግብ ራስን በመቻልና በዲጂታል አቅም ይረጋገጣል - አቶ አደም ፋራህ
Nov 17, 2026 741
አዲስ አበባ፤ ህዳር 8/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የዘመኑ ሉዓላዊነት በምግብ ራስን በመቻልና በዲጂታል አቅም ይረጋገጣል ሲሉ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ ገለጹ። ዘመናዊ የእጅ አዙር ቅኝ ግዛትን (Modern neo colonialism) ለመታገል የተቋቋመው “ለሕዝቦች ነፃነት!” ዓለም አቀፍ ንቅናቄ ጠቅላላ ጉባዔ በሩሲያ ሞስኮ እየተካሄደ ነው። በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በጉባኤው ላይ እየተሳተፈ ይገኛል። አቶ አደም ፋራህ በጉባኤው ላይ ኢትዮጵያ በብሔራዊ ሉዓላዊነት፣ በልማት የራስን በራስ የመወሰን ነፃነት (Development Autonomy) እና እየተለዋወጠ በመጣው የዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥርዓት ዙሪያ ያላትን አቋም እና ምልከታ አቅርበዋል። በንግግራቸውም ኢትዮጵያ ለብሔራዊ ሉዓላዊነት፣ ለሀገራት እኩል ክብር እንዲሁም በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቻርተር እና በዓለም አቀፍ ሕግ ላይ ለተመሠረተ ፍትሐዊ ዓለም አቀፍ ሥርዓት ያላትን ጽኑ ቁርጠኝነት ዳግም አረጋግጠዋል። በንግግራቸውም ኢትዮጵያ ለብሔራዊ ሉዓላዊነት፣ ለሀገራት እኩልነት፣ እንዲሁም በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቻርተርና በዓለም አቀፍ ሕግ ላይ የተመሠረተ ፍትሐዊ ዓለም አቀፍ ሥርዓት እንዲኖር ያላትን ጽኑ አቋም አፅንኦት ሰጥተው ገልጸዋል። በዓድዋ ድል ኢትዮጵያ የቅኝ ግዛትን በመመከት እና የሕዝቦችን ነፃነትና የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት በማስከበር ረገድ ያላትን የቆየ ታሪካዊ ቅርስ አስታውሰዋል። አክለውም በዘመናችን ሉዓላዊነት አዳዲስ ወቅታዊ ፈተናዎችን መቋቋምን እንደሚጠይቅ አስገንዝበዋል። በዚህም ረገድ ኢትዮጵያ በምግብ ራስን በመቻል፣ በዲጂታል እና በመረጃ (ዳታ) አስተዳደር፣ በሳይበር ደኅንነት፣ በኢኮኖሚ ብዝኃነት እና በተቋማዊ ማሻሻያዎች አማካኝነት ስትራቴጂካዊ ነፃነቷን (Strategic Autonomy) ለማጠናከር እየሰራች እንደምትገኝ አመልክተዋል። በተጨማሪም ሀገሪቱ ሀብቷንና አቅሟን በማስተባበር ዘላቂና በራስ አቅም ላይ የተመሠረተ ልማት ለማረጋገጥ ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳዩ ግዙፍ ሀገራዊ ኢኒሼቲቮች እየተገበረች ይገኛል ነው ያሉት። የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብርን፣ የስንዴ ልማትን፣ የከተማ ኮሪደር ልማትን እና ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን በማሳያነት ጠቅሰዋል። ከዚህም ባሻገር ውጤታማ የባለብዙ ወገን ትብብር (Multilateralism)፣ በዓለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ የአፍሪካ ፍትሐዊ ውክልና መረጋገጥ፣ የጋራ ተጠቃሚነትን መሠረት ያደረጉ ዓለም አቀፍ አጋርነቶች እንዲሁም ሰላምና እርቅ ለጋራ ብልጽግና መሠረት መሆናቸውን ነው ያስገነዘቡት። ብልጽግና ፓርቲ የጉባኤው ተሳትፎ ከዲፕሎማሲያዊ ውክልና ባለፈ፤ ዓለም አቀፍ የፖለቲካ አጋርነቶችን ለማጠናከር፣ እንዲሁም በሉዓላዊነት፣ በኒዮ-ኮሎኒያሊዝም፣ በልማት ነፃነት እና ፍትሐዊ ዓለም አቀፍ ሥርዓትን በመገንባት ዙሪያ በሚደረጉ ዓለም አቀፍ ውይይቶች ላይ የኢትዮጵያን አቋም ለማስረጽ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው። በጉባዔው የምልዓተ ጉባዔ ውይይቶች፣ የክብ ጠረጴዛ ምክክሮች እና የሁለትዮሽ ንግግሮች እየተደረጉ ሲሆን፤ በማጠቃለያውም የውሳኔ ሐሳቦችና ስትራቴጂካዊ የሁለትዮሽ ስምምነቶች ይፈረማሉ ተብሎ ይጠበቃል። ብልጽግና ፓርቲ በዚህ ተሳትፎው አማካኝነት የፖለቲካ ምክክሮችን ወደ ተጨባጭ ዓለም አቀፍ ትብብር ለመቀየር፣ የኢትዮጵያን ታሪካዊ ቅርስና ወቅታዊ የልማት ተሞክሮ ለማስተዋወቅ እንዲሁም እየተለዋወጠ ባለው ዓለም አቀፍ ሥርዓት ውስጥ የሀገሪቱን ስትራቴጂካዊ ጥቅሞች ለማስከበር እንደሚሰራ ገልጿል።
ኢትዮጵያ ተቋማዊ አቅሟንና አጋርነቷን በማጎልበት በዓለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ያላትን ሚና አጠናክራ ትቀጥላለች
Nov 17, 2026 747
አዲስ አበባ፤ ህዳር 8/2019(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ተቋማዊ አቅሟንና አጋርነቷን በማጎልበት በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን የሰላም ማስከበር ሚና ይበልጥ አጠናክራ እንደምትቀጥል የኢትዮጵያ ባህር ኃይል ዋና አዛዥ ቫይስ አድሚራል ክንዱ ገዙ ገለጹ። ኢትዮጵያ ተቋማዊ አቅሟን በማዘመን፣ የሰራዊቷን ዝግጁነት ማሳደግና ቀጣናዊ ብሎም ዓለም አቀፋዊ አጋርነቷን በማስፋት በዓለም የሰላም ማስከበር ሚናዋን እንደምትወጣም አክለዋል። የኢፌዴሪ ዓለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ማሠልጠኛ ተቋምና የኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ኮሌጅ በጋራ ባዘጋጁት መድረክ፣ ኢትዮጵያ በዓለም ስርዓት ለውጥና በባለብዙ ወገን ትብብር መዳከም ተግዳሮቶች ውስጥ የሰላም ማስከበር ሚናዋን የምታስቀጥልባቸው ስትራቴጂዎች ላይ ውይይት ተካሂዷል። በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ የኢትዮጵያ ባህር ኃይል ዋና አዛዥ ቫይስ አድሚራል ክንዱ ገዙ እንዳሉት የኢትዮጵያ የሰላም ማስከበር ተሳትፎ የዓለም አቀፍ ግዴታ ብቻ ሳይሆን የሚያኮራ ብሔራዊ ታሪክና ወሳኝ ስትራቴጂካዊ ሀብት ነው። ኢትዮጵያ በ1950ዎቹ በኮሪያ ጦርነት ከተሳተፈችበት ጊዜ ጀምሮ ባለፉት ከ70 በላይ ዓመታት ውስጥ ከ180 ሺህ በላይ የሰላም አስከባሪ ኃይሎችን በተለያዩ የዓለም ክፍሎች በማሰማራት ለዓለም አቀፍ ሰላምና ደህንነት ያላትን ጽኑ አቋም በተግባር ማሳየቷን አንስተዋል። አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ተቋማዊ አቅምን ማዘመንና ፖሊሲዎችን፣ የህግ ማዕቀፎችንና የአሰራር ስርዓቶችን ከዓለም አቀፍ ደረጃዎች ጋር ለማጣጣምም እንዲሁ ይሰራል ሲሉ ገልጸዋል። ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ ከአፍሪካ ህብረት፣ ከምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) እና ከምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይል ጋር ያለው ትብብር እንደሚጠናከርና ዘላቂ የሀብት ምንጮችን ለማስፋት ትኩረት ይደረጋል ነው ያሉት። የኢትዮጵያን የወደፊት የሰላም ማስከበር ስትራቴጂ ከዓለም አቀፍ ግዴታ፣ ከአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት እንዲሁም ከሀገሪቱ የረጅም ጊዜ ብሔራዊ ደህንነት ጥቅሞች ጋር በማቀናጀት እንደሚመራም ተናግረዋል። ከመድረኩ የተገኙ ምክረ-ሃሳቦች በአግባቡ ተሰንደው የሚመለከታቸው ተቋማት በቅንጅት በመስራት ወደ ተጨባጭ ፖሊሲና ተግባራዊ መርሃ-ግብር እንዲቀይሩትም አሳስበዋል።
ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በሰላም ማስከበር ተልዕኮ ለዓለምና ለቀጣናው ሰላም ያላትን ቁርጠኝነት በተግባር አሳይታለች
Nov 17, 2026 729
አዲስ አበባ፤ ህዳር 8/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ላለፉት ሰባት አሥርት ዓመታት በሰላም ማስከበር ተልዕኮ ላይ በመሳተፍ ለዓለም አቀፍና ለቀጣናዊ ሰላምና ደኅንነት ያላትን ጠንካራ ቁርጠኝነት በተግባር ማሳየቷን የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የመከላከያ ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል አብዱራህማን እስማኤል ገለጹ። ኢትዮጵያ በሰላም ማስከበር ዘርፍ የዓለምንና የቀጣናውን ሰላም በመጠበቅ ላለፉት ሰባት አስርት ዓመታት የበኩሏን ሚና ስትወጣ መቆየቷን ጠቅሰዋል፡፡ የኢፌዴሪ ዓለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ማሠልጠኛ ተቋምና የኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ኮሌጅ በጋራ ባዘጋጁት መድረክ፣ ኢትዮጵያ በዓለም ሥርዓት ለውጥና በባለብዙ ወገን ትብብር መዳከም ተግዳሮቶች ውስጥ የሰላም ማስከበር ሚናዋን የምታስቀጥልባቸው ስትራቴጂዎች ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው። ሌተናል ጄኔራል አብዱራህማን በመድረኩ ላይ እንዳሉት፣ ኢትዮጵያ ከኮሪያ ጦርነት ጀምሮ በሰላም ማስከበር ረጅም ጊዜ የቆየ አኩሪ ታሪክ ያላት ሀገር ስትሆን፣ ይህም ለዓለም አቀፍና ለሀገራዊ ሰላምና ደኅንነት ያላትን ጠንካራ ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው። ኢትዮጵያ አኩሪ ታሪኳን ለማስቀጠል ወቅታዊውን ዓለም አቀፍ ሁኔታ በጥንቃቄ በመገምገም ተግባራዊ እርምጃዎችን እየወሰደች እንደምትቀጥል ገልጸዋል፡፡ የኢፌዴሪ ዓለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ማሠልጠኛ ተቋም አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ገዛኸኝ ፈቃዱ በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ ባለፉት ከሰባት አሥርት ዓመታት በላይ ከ180 ሺህ በላይ የሰላም አስከባሪዎችን ወደ ተለያዩ ሀገራት ማሰማራቷን ገልጸዋል። ተሳትፎዋም ከኮሪያ ጦርነት ጀምሮ በሱዳን፣ በደቡብ ሱዳንና በሶማሊያ መቀጠሉን ጠቅሰው፣ ይህ አስተዋጽኦ ኢትዮጵያ ለጋራ ደኅንነት፣ ለቀጣናዊ መረጋጋትና ለዓለም አቀፍ ትብብር ያላትን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ አመልክተዋል። ሚናውን ለማስቀጠልም ዝግጁነትን ማጠናከር፣ አቅምን ማዘመንና ዘላቂ አጋርነት መገንባት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ኮሌጅ አዛዥ ተወካይ ሠራው ደማስ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ በተለያዩ ሀገራት ወታደሮቿን በማሰለፍ ለዓለም አቀፍና ለቀጣናዊ ሰላም የበኩሏን ሚና ስትወጣ መቆየቷን ተናግረዋል። በኢትዮጵያና በአፍሪካ ኅብረት የፈረንሳይ የመከላከያ አታሼና የፈረንሳይ አምባሳደር ተወካይ ኮሎኔል ዳሚየን ሲፕሪክ በሳይበር ጥቃት፣ በመረጃ ጦርነት፣ በሰው ሠራሽ አስተውሎትና በድሮኖች አጠቃቀም እየተለወጠ የመጣው የትጥቅ ግጭቶች ባህሪ የሰላም ማስከበር ሥራን ይበልጥ ውስብስብ እያደረገው መሆኑን ገልጸዋል። ዓለም አቀፍ ሰላምና ደኅንነትን ለማስጠበቅም አዳዲስ አካሄዶች እንደሚያስፈልጉ አመልክተዋል።
ሕገወጡ ህወሓት የትግራይ ክልልን ለቆ ሲወጣ በክልሉ የመንግሥት ተቋማት ላይ ውድመትና ዝርፊያ ፈፅሟል -አቶ አሰፋ አብረሃ
Nov 17, 2026 731
አዲስ አበባ፣ሕዳር 8/2019 (ኢዜአ)፦ሕገወጡ ህወሓት የትግራይ ክልልን ለቆ ሲወጣ በክልሉ የመንግሥት ተቋማትና የአስተዳደር መዋቅሮች ላይ ውድመትና ዝርፊያ መፈፀሙን የትግራይ ክልል ባለአደራ አስተዳደር የአስተዳደርና የሕዝብ አገልግሎት ዋና አስፈፃሚ አቶ አሰፋ አብረሃ ገለፁ። አቶ አሰፋ አብረሃ ይህን ያሉት በመቐለ ከተማ ከተባበሩት መንግሥታት ልዑካን፣ ከተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና ከዓለም አቀፍ ባለድርሻ አካላት ጋር በሚካሄደው ውይይት ላይ ባደረጉት ንግግር ነው። አቶ አሰፋ በዚህ ወቅት፤ የችግሩ ተጎጂዎች ተፈናቃዮች ብቻ ሳይሆኑ፣ በትግራይ የሚኖሩ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ናቸው ብለዋል። በዚህም የመንግስት ሠራተኞችን ጨምሮ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ለከፋ ችግር መዳረጋቸውን ተናግረዋል። ለአብነትም የክልሉ ዋና ከተማ መቐለ ነዋሪዎች ከ80 እስከ 90 በመቶ የሚሆኑት የሰብዓዊ ድጋፍ ፈላጊ መሆናቸውን ጠቁመዋል። ሕገወጡ ህወሓት የትግራይ ክልልን ለቆ ሲወጣ በክልሉ የመንግሥት ተቋማትና የአስተዳደር መዋቅሮች ላይ የፈጸመውን ውድመትና ዝርፊያም አውግዘዋል። የፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት፣ የፖሊስ ኮሚሽን፣ የክልሉ ፓርላማና ሌሎች የመንግሥት ቢሮዎች በእሳት መውደማቸውን፣ የቢሮ ዕቃዎችና ሰነዶች መዘረፋቸውን፣ የመረጃ መረቦችና ኮምፒውተሮች መውድርማቸውን አስረድተዋል። በዚህም ምክኒያት የመንግሥት ተቋማት ሥራቸውን በተሟላ ሁኔታ እንዳያከናውኑ እንቅፋት መሆኑን አብራርተዋል። የክልሉ ባለአደራ አስተዳደር በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ ሰላምና ፀጥታን ማስፈን፣ የመንግሥት አስተዳደርና መሠረታዊ አገልግሎቶችን መመለስ፣ ኢኮኖሚያዊ ማገገምን ማፋጠን፣ ተፈናቃዮችን ወደ ቀዬአቸው መመለስ ብሎም ለምርጫ የሚያስፈልጉ ተቋማዊ ዝግጅቶችን ማጠናቀቅ ዋነኛ ተልዕኮዎቹ መሆናቸውንም አመልክተዋል።
ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴየተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤዎችን እየተቀበሉ ነው
Nov 17, 2026 751
አዲስ አበባ፤ ህዳር 8/2019 (ኢዜአ)፦ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴየተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤዎችን እየተቀበሉ ነው እስካሁንም የቆጵሮስ፣ የቼክ ሪፐብሊክ እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች አምባሳደሮች የሹመት ደብዳቤ ተቀብለዋል፡፡ በመርሐ ግብሩ ከአፍሪካ፣ ከእስያ፣ ከመካከለኛው ምሥራቅ፣ ከአውሮፓ እና ከካሪቢያን ሀገራት የተወከሉ ተሿሚ አምባሳደሮች በክብር ዘብና በማርሽ ባንድ ሥነ ሥርዓት ታጅበው ደብዳቤያቸውን በማቅረብ ላይ ይገኛሉ፡፡ በዚህም የሰሜን ኮርያ፣ የተባበሩት አረብ ኢመሬትስ፣ የቆጵሮስ፣ የቼክ ሪፐብሊክ፣ አየርላንድ፣ ህንድ፣ ኦስትሪያ፣ ኖርዌይ፣ ፊንላንድ፣ ማልታ፣ ቻድ፣ ደቡብ ኮርያ፣ ጣልያን፣ ባርባዶስ፣ ሉክሰምበርግ እና ግሪናዳ ሀገራት የሹመት ደብዳቤያቸውን ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የህገወጡ ህወሓት መሪዎች ከ830 በላይ ተሽከርካሪዎችን ወደ ኤርትራ ወስደዋል
Nov 17, 2026 757
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 8/2019 (ኢዜአ)፦ የሕገወጡ ሕወሓት መሪዎች ከ830 በላይ ተሽከርካሪዎችን ወደ ኤርትራ ወስደዋል አሉ የትግራይ ክልል ባለአደራ አስተዳደር የአስተዳደርና የሕዝብ አገልግሎት ዋና አስፈፃሚ አቶ አሰፋ አብረሃ፡፡ የባለአደራ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች በመቀሌ ከተማ ከተባበሩት መንግሥታት ልዑካን፣ ከተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና ከዓለም አቀፍ ባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይተዋል፡፡ አቶ አሰፋ አብረሃ በዚሁ ወቅት፤ የሕገወጡ ሕወሓት መሪዎች በኤርትራ እንደሚገኙና ከ830 በላይ ተሽከርካሪዎችን ጭነው ወደ ኤርትራ እንደወሰዱ ገልፀዋል። ተሽከርካሪዎቹ መወሰዳቸው የመንግሥት ተቋማት ሥራቸውን በተሟላ ሁኔታ እንዳያከናውኑ ከፍተኛ እንቅፋት መሆኑንም አስረድተዋል። የሕገወጡ ሕወሓት ቡድን ከሻዕቢያ ጋር በመተባበር በትግራይ ሕዝብና በክልሉ ላይ ከፍተኛ ውድመትና ኪሳራ ማድረሱን ገልጸው፤ የቡድኑ እንቅስቃሴ በክልሉ የሰላምና መረጋጋት ጥረቶች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደረ መሆኑን ገልፀዋል። ይህንንም በተመለከተ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የሕገወጡን ቡድን እንቅስቃሴ በግልፅ ሊያወግዝና በክልሉ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን አስፈላጊውን ጫና ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል። ባለአደራ አስተዳደሩ በተሰጠው የስድስት ወር የሥልጣን ጊዜ ገደብ ውስጥ ሰላምና ፀጥታን ማስፈን፣ የመንግሥት አስተዳደርና መሠረታዊ አገልግሎቶችን መመለስ ዋነኛ ተልዕኮዎቹ መሆናቸውን ገልፀዋል። በተጨማሪም ኢኮኖሚያዊ ማገገምን ማፋጠን፣ ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው መመለስና ለምርጫ የሚያስፈልጉ ተቋማዊ ዝግጅቶችን ማጠናቀቅ ቀዳሚ ተግባራት መሆናቸውንም ነው የገለጹት፡፡ ሰብዓዊ ድጋፍ ከባለአደራ አስተዳደሩ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ጉዳዮች አንዱ መሆኑን ገልጸው፤ በነሐሴ ወር በተካሄደ ግምገማ መሠረት ለትግራይ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ ፍላጎት ወደ 700 ሚሊየን ዩሮ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል። ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በትግራይ ያለውን ሰብዓዊ ቀውስ በመገንዘብ የድጋፍ ምላሹን እንዲያጠናክርና በክልሉ ሰላምና መረጋጋት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ እንቅስቃሴዎችን በግልፅ እንዲያወግዝ ጥሪ አቅርበዋል።

ማህበራዊ
የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ከድንገተኛ የሕክምና ወጪና የኢኮኖሚ ጫና ታድጎናል -- በድሬዳዋ ተጠቃሚዎች
Nov 18, 2026 39
ድሬዳዋ፤ ህዳር 9/2019 (ኢዜአ)--በድሬዳዋ የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ተጠቃሚዎች በሁሉም የሕክምና ተቋማት የተሟላ የጤና አገልግሎት ማግኘታቸው ከድንገተኛ የሕክምና ወጪና የኢኮኖሚ ጫና እንደታደጋቸው ገለጹ። በድሬዳዋ አስተዳደር በገጠር እና በከተማ የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ተጠቃሚዎች ቁጥር እያደገ በመምጣቱ ፍትሃዊ የጤና ተደራሽነትና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ተችሏል። በስተዳደሩ በማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድን አገልግሎት ተጠቃሚ የሆኑ ነዋሪዎች ለኢዜአ እንደገለጹት፣ የጤና መድህን በተለይ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎችን ጤናማና አምራች ዜጋ እንዲሆኑ አስችሏል። በገንደቆሬ ጤና ጣቢያ ሕክምናቸውን ሲከታተሉ ከነበሩት መካከለ አቶ ስዩም በቀለ እንዳሉት፤ በማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን በሁሉም ደረጃ ባሉ የጤና ተቋማት የሕክምና አገልግሎት እያገኙ ነው። ከዚህ በፊት የሕክምና አገልግሎት ለማግኘት የገንዘብ ዕጥረት እንደነበረባቸው አስታውሰው፣ የጤና መድህን አባል በመሆናቸው በማንኛውም ወቅት ያለችግር መታከም መቻላቸውን ተናግረዋል። ቤተሰቦቻቸውም ሕመም ሲገጥማቸው ከጤና ጣቢያ ጀምሮ አስከ ሆስፒታል ደረስ በቅብብሎሽ የፈለጉትን ሕክምና ማግኘታቸው ጤናቸውን በአግባቡ ለመጠበቅና አምራች ለመሆን እንዳስቻላቸው ነው የገለጹት የጤና መድህን አገልግሎት ከሰጠን እፎይታ ባለፈ ጤናማና አምራች እንድንሆን እያገዘን ነው ያሉት ደግሞ ሌላው ተጠቃሚ አቶ አብደላ ሙሜ ናቸው። በአዲስ ከተማ ጤና ጣቢያ ሲታከሙ ከነበሩት የጤና መድህን ተጠቃሚዎች መካከል ወይዘሮ አስራት ወልደፃዲቅ እና አቶ ቢኒያም አበራ የጤና መድህን አባል መሆናቸው የዓመታት ችግራቸውን እንደፈታላቸው ተናግረዋል። አልፎ አልፎ በጤና ተቋማት ከሚያጋጥም የመድኃኒት እጥረት ችግር በስተቀር በቅብብሎሽ አስከ ከፍተኛ ሆስፒታል ድረስ በመሄድ መታከም መቻላቸው የኢኮኖሚ ጫና እንዳቃለለላቸው ገልጸዋል። የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ከተጀመረ ወዲህ በድሬዳዋ የጤና አገልግሎት ተደራሽነት በማስፋት ጤናማ ማህበረሰብ ለመፍጠር እየተቻለ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ በአስተዳደሩ ጤና ቢሮ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አስተባባሪ ሲስተር ሜሪ አምዴ ናቸው። በአሁን ወቅት በማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን መታቀፍ ካለባቸው 91 በመቶዎቹ ተካተው አስፈላጊውን የሕከምና አገልግሎት እያገኙ መሆናቸውን ተናግረዋል። የማህበረሰብ ጤና መድህን አገልግሎት በተለይ ከፍለው መታከም የማይችሉትን የህብረተሰብ ክፍሎች ከችግር መታደጉን የገለጹት አስተባባሪዋ፣ የህብረተሰቡን የእርስ በእርስ መረዳዳትና ትስስርን እያጠናከረ መሆኑንም ተናግረዋል። በተያዘው በጀት ዓመትም የጤና መድህን አባላትን ቁጥር በማብዛት የሚሰጠውን የጤና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት ከማሳደግ ባለፈ ጤናማ እና አምራች ዜጋ የመፍጠር ሥራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
ኢትዮጵያ በመደመር እሳቤ ሀገራዊ አቅሞችንና ዓለምአቀፍ ትብብሮችን በማቀናጀት ወረርሽኞችን ቀድሞ የመከላከል አቅሟን እያጎለበተች ነው
Nov 18, 2026 47
አዲስ አበባ፤ ህዳር 9/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በመደመር እሳቤ ሀገራዊ አቅሞችንና ዓለምአቀፍ ትብብሮችን በማቀናጀት ወረርሽኞችን ቀድሞ የመከላከል እና ከተከሰተም ፈጥኖ የመቆጣጠር አቅሟን እያጎለበተች መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ገለጹ። 21ኛው ዓለም አቀፍ የፓንዳሚክ ፈንድ ቦርድ ስብሰባ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል። የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ በዚሁ ወቅት፤ ኢትዮጵያ በመደመር እሳቤ ሀገራዊ አቅሞችንና ዓለምአቀፍ ትብብሮችን በማቀናጀት ወረርሽኞችን ቀድሞ የመከላከል እና ከተከሰተም ፈጥኖ የመቆጣጠር አቅሟን እያጎለበተች ትገኛለች ብለዋል። የበሽታዎች ቅኝት፣ የላቦራቶሪ አቅምንና የአደጋ ጊዜ ምላሽ ዝግጁነትን ለማሳደግ ያለመ "የኢትዮጵያ ወረርሽኝ ዘርፈ-ብዙ መከላከል ዝግጁነት እና ምላሽ ፕሮጀክት" በስፋት እየተተገበረ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል። ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት የኢትዮጵያን የጤና፣ የግብርና እና የገንዘብ ሚኒስቴሮች እንዲሁም ዓለምአቀፍ ተቋማትን በጋራ ያስተሳሰረ መሆኑን አንስተዋል። ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያ ወደፊት ሊከሰቱ የሚችሉ ድንገተኛ የጤና አደጋዎችንና ወረርሽኞችን በራሷ አቅም ቀድማ ለመከላከል እና ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የምታደርገውን ጥረት እያገዘ እንደሚገኝ ተናግረዋል። የሰው እና የእንስሳት ላቦራቶሪዎችን በካርታ የመለየት፣ መመሪያዎችን የማዘጋጀት እና የበሽታ አምጪ ተህዋስያንን ዘረ-መል የመመርመር አቅምን እንደሚያሳድግም ጠቁመዋል። በሺዎች ለሚቆጠሩ የዘርፈ-ብዙ ባለሙያዎች ስልጠና በመስጠት የተሳሳቱ መረጃዎችን መመከት የሚያስችል የአደጋ ጊዜ ተግባቦት ስርዓት በመዘርጋት ህብረተሰቡን የመጠበቅ ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል። የጤናው ዘርፍ ስራዎች በብቸኝነት ሳይሆን ከሀገር ውስጥ እስከ ዓለም አቀፍ አጋሮች እንዲሁም ማህበረሰቡን በማቀናጀት በማስተባበር እየተከናወኑ መሆኑን አንስተዋል። የጤና አጠባበቅ ስርዓትን ለማጠናከር በላቦራቶሪዎች አቅም ግንባታ፣ በሰለጠነ የሰው ሃይል ዝግጅት፣ በድንገተኛ አደጋ ምላሽ ሰጪዎች ስልጠና እንዲሁም በቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓቶች ላይ ሰፊና አስተማማኝ ስራዎች መሰራታቸውን ጠቁመዋል። በኢትዮጵያ የተከናወኑ የጤና ስራዎች ውጤታማና አበረታች መሆናቸውን የገለጹት ሚኒስትሯ፣ ኢትዮጵያ በመደመር እሳቤ የማይበገር የጤና ስርዓት እየገነባች መሆኑን አመላክተዋል።
ጤናማ ኅብረተሰብ የመፍጠር ጉዟችን በቀልጣፋ አገልግሎትና ዘመኑን በዋጀ ስርዓት መከናወን አለበት- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Nov 18, 2026 65
አዲስ አበባ፤ ህዳር 9/2019 (ኢዜአ)፦ ጤናማ ኅብረተሰብ የመፍጠር ጉዟችን በቀልጣፋ አገልግሎትና ዘመኑን በዋጀ ስርዓት መከናወን አለበት ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልእክት ዛሬ በባሕር ዳር ከተማ በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘውን ምድረ ገነት ጠቅላላ ሆስፒታልን ጎብኝተናል ብለዋል። ከዚህ ቀደም ተቋርጦ የቆየው ይህ ግንባታ፣ ከስድስት ወራት በፊት በአዲስ ውል እንደገና ተጀምሮ ወደ መጠናቀቂያው ደርሷል ነው ያሉት። ይህ ባለ አምስት ወለል ዘመናዊ የጤና ተቋም ግንባታ ሲጠናቀቅ ወረቀት አልባ የጤና መረጃ ሥርዓት የሚመራ መሆኑን ጠቁመው፤ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ከሕክምና አገልግሎት ጋር በማቀናጀት የተሻለ የጤና አገልግሎት የሚሰጥ ይሆናል ብለዋል። የጤና ተቋማትን በአቅም፣ በቴክኖሎጂና በአገልግሎት ማሳደግ ጤናማ ኅብረተሰብን ለመገንባት የምናደርገው ቁርጠኛ ጥረት አካል ነው ሲሉም ገልጸዋል። S
ኢትዮጵያ ፍልሰተኞችን እንደ ልማት አጋርና የኢኮኖሚ ተዋናይ በመቁጠር ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት እየሰራች ነው
Nov 17, 2026 725
አዲስ አበባ፤ ህዳር 8/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ፍልሰተኞችን እንደ ልማት አጋርና የኢኮኖሚ ተዋናይ በመቁጠር ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት እየሰራች መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሀደራ አበራ ገለጹ። በፍልሰት ጉዳዮች ላይ ያተኮረው አራተኛው የአፍሪካ የግሉ ዘርፍ ፎረም (AFD 2026) በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው። "ቀጣዩ ምዕራፍ፤ ይበልጥ አካታች የሆነ የኢኮኖሚ ሥነ-ምህዳር መፍጠር" የፎረሙ መሪ ቃል ነው። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሀደራ አበራ ፍልሰተኞችንና ተፈናቃዮችን እንደ ዕድገት አጋርና የኢኮኖሚ ተዋናይ የሚመለከት የልማት አቅጣጫ መከተል እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥተዋል። በዚህም በሰብአዊ ድጋፍ ፈላጊነትና በተጋላጭነት ብቻ መታየት እንደሌለባቸው የገለጹት አምባሳደር ሀደራ፣ ያላቸውን ክህሎት፣ ዕውቀት፣ የሥራ ፈጠራ አቅምና ምርታማነት መጠቀም እንደሚገባ ተናግረዋል። በኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ትርጉም ያለው ተሳትፎ እንዲኖራቸው ማድረግ ራሳቸውን እንዲችሉ ከማገዙም በላይ፣ የቀጣናውን ገበያ እንደሚያጠናክርና የማምረት አቅምን እንደሚያሳድግ አመልክተዋል። ይህም ለተፈናቃዮች ብቻ ሳይሆን ለተቀባዩ ማህበረሰብም ሰፊ የኢኮኖሚ ሽግግርና የጋራ ተጠቃሚነትን እንደሚያመጣም ነው ያብራሩት። ኢትዮጵያ ለፍልሰተኞች ጥበቃና ዘላቂ መፍትሔ ያላትን ቁርጠኝነት የጠቀሱት ሚኒስትር ዴኤታው፣ የስደተኞች አዋጅ ቁጥር 1110/2019 መብታቸውን፣ የሥራ፣ የትምህርትና የመዘዋወር ነጻነትን የማስፋት ስራ ትልቅ ምዕራፍ የከፈተ ተግባር መሆኑን ተናግረዋል። በተጨማሪም መንግሥት የሥራ ዕድሎችንና የሥራ ፈቃዶችን ለማስፋት፣ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አሰጣጥን ለማቀላጠፍ፣ ብሔራዊ አገልግሎቶችን ተደራሽ ለማድረግ እንዲሁም የስደተኞችን ጉዳይ በሀገር አቀፍና በአካባቢ የልማት ማዕቀፎች ውስጥ ለማካተት እያከናወናቸው ያሉ ተግባራትን በዝርዝር አስረድተዋል። የግሉ ዘርፍ ሚና የማይተካ መሆኑን የገለጹት አምባሳደር ሀደራ፣ ከማህበራዊ ኃላፊነት ባለፈ በንግዱ ዘርፍ አዋጭ በሆነና የጋራ ተጠቃሚነትን በሚያረጋግጥ አጋርነት እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል። የአፍሪካን የኢኮኖሚ አካታችነት አጀንዳ ለማሳካት የፖሊሲ ማሻሻያዎችን ወደ ተጨባጭ የኢኮኖሚ ዕድል መቀየር፣ የግል ካፒታልና አዳዲስ የፋይናንስ አማራጮችን ስራ ላይ ማዋል፣ የስደተኞችን የሥራ ፈጠራና የገበያ ትስስር ማጠናከር፣ በክህሎትና በሥራ ዕድል ላይ ኢንቨስት ማድረግ እንዲሁም አካታች የቀጣናዊ ኢኮኖሚ ልማትን ማስፋፋት እንደሚገባም ነው ያነሱት። ለዚህም መንግሥታት፣ የንግድ ተቋማት፣ የፋይናንስ ተቋማትና የልማት አጋሮች የኢንቨስትመንት መሰናክሎችን ለማስወገድ በቅንጅት መሥራት እንዳለባቸው አሳስበዋል። ኢትዮጵያ ከዚህ ፎረም የሥራ ዕድልን የሚያሰፉ፣ በስደተኞች የሚመሩ ድርጅቶችን የሚያጠናክሩ እንዲሁም የፋይናንስና የገበያ ተደራሽነትን የሚያሻሽሉ ተግባራዊ አጋርነቶች፣ ተጨባጭ የኢንቨስትመንት ቃል ኪዳኖችና ሊተገበሩ የሚችሉ ምክረ-ሐሳቦች ይመነጫሉ እንደምትጠብቅ አምባሳደሩ ገልጸዋል። የዚህ ፎረም (AFD 2026) ስኬት የሚለካው በተፈጠሩ የሥራ ዕድሎች፣ በተጠናከሩ የንግድ ተቋማት፣ በተጨባጭ ኢንቨስትመንቶችና በተለወጡ የሰዎች ሕይወት መሆን እንዳለበትም አጽንኦት ሰጥተዋል። ፎረሙ ከ400 በላይ ልዑካንን፣ ፖሊሲ አውጪዎችንና ዓለም አቀፍ አጋሮችን በአንድ መድረክ አገናኝቷል። መድረኩ በመላው አፍሪካ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ በማጠናከር የመፈናቀል ችግርን በዘላቂነት ለመፍታትና የኢኮኖሚ አካታችነትን ለማረጋገጥ ስትራቴጂካዊ አጋርነት የሚመሰረትበትና የሐሳብ ልውውጥ የሚደረግበት አህጉራዊ መድረክ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
ኢኮኖሚ
በደቡብ ምሥራቅ ኦሮሚያ ዞን የቱሪዝም መስህቦችን በማልማትና በማስተዋወቅ ሰፊ ተግባራት እየተከናወኑ ነው
Nov 18, 2026 114
ሮቤ ህዳር 09/2019 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ምሥራቅ ኦሮሚያ ዞን የተፈጥሮ፣ ታሪካዊና ባህላዊ መስህቦችን በማልማትና በማስተዋወቅ የጎብኝዎች ቁጥርና የዘርፉ ገቢ እያደገ መምጣቱን የዞኑ ቱሪዝም ጽህፈት ቤት አስታወቀ። ባለፈው በጀት ዓመት 1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ቱሪስቶች አካባቢውን የጎበኙ ሲሆን፣ በዘንድሮው ዓመት ደግሞ ከ2 ነጥብ 1 ሚሊዮን በላይ ቱሪስቶችን በመሳብ ከሶስት ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ለማግኘት ታቅዶ ወደ ሥራ ተገባቷል። የደቡብ ምሥራቅ ኦሮሚያ ዞን የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ፣ የሶፍ ኡመር ዋሻ፣ ድሬ ሼህ ሁሴንና ሌሎች በርካታ የተፈጥሮ፣ ታሪካዊና ባህላዊ መስህቦች መገኛ በመሆኑ በሀገሪቱ የቱሪዝም እምቅ አቅም ካላቸው አካባቢዎች አንዱ ነው። በተለይም የባሌ ተራሮች ልዩ የተፈጥሮ ሥነ-ምህዳርና የዱር እንስሳት ሀብት፣ የሶፍ ኡመር ዋሻ ልዩ የተፈጥሮ ገጽታና የድሬ ሼህ ሁሴን ታሪካዊና ሃይማኖታዊ እሴቶች አካባቢውን ለቱሪዝም ልማት ምቹ ከሚያደርጉት ዋና ዋና ሀብቶች መካከል ይጠቀሳሉ። የደቡብ ምሥራቅ ኦሮሚያ ዞን ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ደጀኔ ሚልኬሳ እንዳሉት፤ በዞኑ የሚገኙ የቱሪዝም መስህቦችን ለማልማት፣ መሠረተ ልማቶችን ለማሻሻልና የአካባቢውን የቱሪዝም አቅም በስፋት ለማስተዋወቅ በተለያዩ መስኮች ሥራዎች እየተከናወኑ ናቸው። ባለፈው የበጀት ዓመት 1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ቱሪስቶች አካባቢውን የጎበኙ ሲሆን፣ በዘንድሮው ዓመት ከ2 ነጥብ 1 ሚሊዮን በላይ ቱሪስቶችን በመሳብ ከሶስት ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ለማግኘት ታቅዶ ወደ ሥራ መገባቱን ገልጸዋል። መስህቦችን ማልማት የጎብኚዎችን ቁጥር ከማሳደግ ባለፈ የአካባቢውን ነዋሪዎች የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማጠናከር፣ የሥራ ዕድል ለመፍጠርና የባህልና ታሪካዊ ቅርሶችን ለትውልድ ለማስተላለፍ ወሳኝ መሆኑንም አመልክተዋል። የባሌና አካባቢው የተለያዩ ሥነ-ምህዳሮች፣ የተፈጥሮ ሀብቶችና ታሪካዊ ቅርሶች በአንድ አካባቢ መገኘታቸውን የጠቀሱት ኃላፊው፤ እምቅ የቱሪዝም ኃብቱን ለማጎልበት ከመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር እየተሰራ ነው ብለዋል። በዞኑ ከ100 በላይ አዳዲስ የተፈጥሮ፣ ታሪካዊና ሰው ሠራሽ የቱሪዝም መስህቦች በጥናት መለየታቸውንና ለመስህቦቹ ዲጂታል ካርታ መዘጋጀቱንም በማሳያነት አንስተዋል። የመስህብ ስፍራዎችን በምርምር መለየት፣ መመዝገብና የጎብኚዎችን መረጃ ተደራሽ ማድረግ ከዘርፉ የሚገኘውን ጥቅም ለማሳደግ ወሳኝ ነው ብለዋል። በዞኑ ሰሞኑን የቱሪዝም መስህቦችን የጎበኙ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ቡድንም የአካባቢውን እምቅ ሀብት ለሀገር ውስጥና ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ጉልህ ድርሻ አለው ብለዋል። በመስክ ጉብኝቱ የሚዘጋጁ የዜና ዘገባዎች፣ ፎቶግራፎችና የቪዲዮ ምስሎች የመስህብ ስፍራዎቹን ተፈጥሯዊና ታሪካዊ ይዘት በስፋት በማሳየት የጎብኚዎችን ፍላጎት ለማነሳሳት ያግዛሉ ነው ያሉት። የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የቱሪዝም ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ገረመው መብራቱ እንዳሉት፣ ፓርኩን የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር ቱሪስቶች የጎበኙ ሲሆን ከዚህም የተሻለ ገቢ ተገኝቷል ብለዋል። በፓርኩ ውስጥ በርካታ ሐይቆች እንደሚገኙ የጠቆሙት ኃላፊው፣ ከእነዚህም ውስጥ ብዙዎቹ ክረምት ከበጋ የማይደርቁ ቋሚ ሐይቆች መሆናቸው ልዩ እንደሚያደርገውም ገልጸዋል። የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክን የጎበኙት ዴቪድ ማርሻል፣ ከዚህ በፊት በተለያየ ሀገር የተለያዩ የቱሪስት መስህቦችን የጎበኙ ቢሆንም በባሌ ባዩት እምቅ የቱሪዝም ሀብት ግን እጅግ መደነቃቸውን ገልጸዋል። የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ማራኪ እና በየትኛውም ቦታ የማይገኝ ውብ ተፈጥሯዊ ገጽታ ያለው መሆኑን አንስተዋል።
በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍሰትን በማሳደግ ኢኮኖሚውን የሚያጎለብት ተግባራት እየተከናወኑ ነው
Nov 18, 2026 120
ሐረር፤ ህዳር 09/2019 (ኢዜአ)፦ የሐረሪ ክልልን ምጣኔ ሀብት ለማሳደግ የኢንቨስትመንት ፍሰትን የሚያጠናክሩ የተለያዩ ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን የክልሉ ኢንተርፕራይዞች ልማትና ኢንዱስትሪ ቢሮ አስታወቀ። በሐረሪ ክልል ምጣኔ ሀብቱን በዘላቂነት ለማሳደግ የአምራች ኢንዱስትሪውንና የኢንቨስትመንት ዘርፉን በስፋት የማነቃቃት ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል። የክልሉ መንግሥት የኢንቨስትመንት ፍሰቱን ለማሳደግ የአሠራር ሥርዓቶችን በማዘመን፣ የመሠረተ ልማት አቅርቦትን በማሻሻልና ፈጣን አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል። በተለይም በአምራች ኢንዱስትሪ፣ በግብርና ማቀነባበሪያ፣ በአገልግሎትና በሆቴል ዘርፎች ለሚሰማሩ ባለሀብቶች የሚደረገው ድጋፍና ማበረታቻ የኢንቨስትመንት ፍላጎቱን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጨምር አድርጎታል። በተያዘው በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ብቻ ከ2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ 51 አልሚዎች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መሰጠቱም የዚሁ ጥረት አንዱ ማሳያ ነው። እነዚህ ፕሮጀክቶች ወደ ሙሉ ትግበራ ሲገቡም በክልሉ ሰፊ የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባለፈ፣ የምርትና አገልግሎት አቅርቦትን በማሳደግ የክልሉን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግሩታል ተብሎ ይታመናል። የክልሉ ኢንተርፕራይዞች ልማትና ኢንዱስትሪ ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ሰሚር አብዱላሂ እንዳገለጹት፤ ቢሮው የኢንቨስትመንት ፍሰትን በማሳደግ ኢኮኖሚውን የሚያጎለብትና የሥራ ዕድል ፈጠራን የሚያጠናክሩ ተግባራት እያከናወነ ነው። በክልሉ ለኢንቨስትመንት ዘርፉ ውጤታማና ቀልጣፋ አሰራርን በመዘርጋት ለአዳዲስ አልሚዎች የተሟላ አገልግሎት ለመስጠት በተደረገው ጥረት፤ በሩብ ዓመቱ ባጠቃላይ ለ51 አልሚዎች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መሰጠቱን ገልጸዋል። ፈቃዱ ከተሰጣቸው አልሚዎች 12ቱ በሆቴል፣ ዘጠኙ በማኑፋክቸሪንግ ሲሆኑ ቀሪዎቹ በግብርናና በሌሎች ዘርፍ ፈቃድ የተሰጣቸው መሆኑን ጠቁመው፤ ጠቅላላ የካፒታል መጠናቸውም ከ2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሆነ ገልጸዋል። በክልሉ ከዚህ ቀደም ፈቃድ ወስደው የነበሩ ፕሮጀክቶች በሩብ ዓመቱ ወደ ማምረትና አገልግሎት መስጠት በመሸጋገር ለዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል እንደፈጠሩም ጠቅሰዋል። በክትትልና ቁጥጥር ተግባራት በ58 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ላይ የእርምት እርምጃዎች መወሰዳቸውን ጠቁመዋል። በዚህም 15 ፕሮጀክቶች የቃል ማስጠንቀቂያ፣ 26 የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ፣ 10 ፕሮጀክቶች እገዳ የተጣለባቸው ሲሆን፤ የሰባት ባለሀብቶች ፕሮጀክቶች ደግሞ ፈቃዳቸው መሰረዙን አስታውቀዋል። በክልሉ ለኢንቨስትመንት ዘርፉ የሚደረገው ድጋፍና ክትትል ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ምክትል ቢሮ ሃላፊው አክለዋል።
የኢትዮጵያ ሲሚንቶ ፋብሪካዎች የማምረት አቅም ረጅም ዕድሜ የሚያገለግሉ የኮንክሪት መንገዶች ለመገንባት የሚያስችል ነው
Nov 17, 2026 661
አዲስ አበባ፤ ህዳር 8/2019(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ሲሚንቶ ፋብሪካዎች የማምረት አቅም ረጅም ዕድሜ የሚያገለግሉ የኮንክሪት መንገዶች ለመገንባት የሚያስችል መሆኑን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር አስታወቀ። ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ አስተዳደሩ ከኢትዮጵያ ሲሚንቶ አምራቾች ማኅበር ጋር በመተባበር "የኢትዮጵያ መንገድ ዘርፍ ልማት የሲሚንቶ ኮንክሪትን ለመንገድ ንጣፍ መጠቀም ያሉ ዕድሎች" በሚል መሪ ሃሳብ አውደ ጥናት አካሂዷል። የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የመንገድ ምርምር ማዕከል የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር አስተባባሪ ኢንጂነር ይታገሱ ደሳለኝ በዚህ ወቅት፤ የመንገድ መሰረተ ልማት የሀገር ዕድገት መሰረት ነው ብለዋል። በኢትዮጵያ ባለፉት ሦስት አስርት ዓመታት የተተገበሩ የመንገድ ዘርፍ ልማት መርሃ ግብሮች የከተማና ገጠር ትስስርን በማጎልበት ከፍተኛ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ እያበረከቱ መሆኑን ገልጸዋል። በቀጣይም የመንገድ ደኅንነትን የሚያረጋግጥ የሲሚንቶ ኮንክሪት መንገድ ልማት በማስፋት አዳዲስ የቴክኖሎጂ አማራጮች በሥራ ላይ እንደሚውሉ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ሲሚንቶ አምራች ፋብሪካዎች ረጅም ዕድሜ የሚያገለግል የኮንክሪት መንገድ ፕሮጀክት መገንባት የሚያስችል በቂ አቅም መፍጠራቸውን አንስተዋል። የኢትዮጵያን የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ቁጥርና የማምረት አቅም ዕድገት ታሳቢ በማድረግም የመንገድ መሰረተ ልማትና ኢንዱስትሪ ትስስርን ለማጎልበት በትኩረት እንደሚሰራ አስረድተዋል። የኢትዮጵያ ሲሚንቶ አምራቾች ማኅበር የቦርድ ሊቀ-መንበር አዱኛ በቀለ በበኩላቸው፤ የሲሚንቶ ኮንክሪት የመንገድ መሰረተ ልማት ግንባታ ጥራትን ለማስጠበቅ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው አብራርተዋል። ይህም ኢትዮጵያ በቴክኒክና በኢኮኖሚ የተመጣጠነ፣ ዘላቂና ተወዳዳሪ የመንገድ መሰረተ ልማት ግንባታ አማራጭን ለመፍጠር እንደሚያስችላት አንስተዋል። የሲሚንቶ ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ረጅም ዕድሜ በማገልገል ከፍተኛ ፋይዳ ያለው የልማት ዘርፍ ነው ያሉት ደግሞ የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ታሪኩ አለማየሁ ናቸው። ለዚህም የኢትዮጵያን የሲሚንቶ ኮንክሪት የመንገድ መሰረተ ልማት ፍላጎት ታሳቢ በማድረግ የማምረት አቅማቸውን በማሳደግ ግብዓት እንደሚያቀርቡ አረጋግጠዋል። የደርባ ሚድሮክ ሲሚንቶ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኃይሌ አሰግዴ በበኩላቸው፤ በአሁኑ ጊዜ የመንገድ መሰረተ ልማት ትስስር ለማስፋት በርካታ ፕሮጀክቶች እየተገነቡ ነው ብለዋል። የሲሚንቶ ኮንክሪት መንገድ ንጣፍ በውሃና ዝናብ በቀላሉ የማይበላሽና ረዥም ዕድሜ ያለው አማራጭ መሰረተ ልማት መሆኑንም አስረድተዋል። የሲሚንቶ ኮንክሪት መንገድ ለአስፋልት ግንባታ ከውጭ የሚገባን ግብዓት የሚያስቀር አማራጭ ዘርፍ ነው ያሉት የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮንሳልቲንግ ማኅበር የቦርድ አባል ኢንጂነር ሮቤል መርኪያ ናቸው።
15ኛው ዓለም አቀፍ የጥራጥሬና ቅባት እህሎች ኮንፍረንስና ሲምፖዚየም በአዲስ አበባ ይካሄዳል
Nov 17, 2026 123
አዲስ አበባ፤ ህዳር 8/2019 (ኢዜአ)፦15ኛው ዓለም አቀፍ የጥራጥሬና ቅባት እህሎች ኮንፍረንስና ሲምፖዚየም በአዲስ አበባ እንደሚካሂድ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ያስሚን ወሀብራቢ አስታወቁ። ሚኒስትር ያስሚን ወሀብራቢ ሁነቱን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፤ መድረኩ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ጥራጥሬና ቅባት እህሎች ላኪዎች ማህበር ጋር የሚዘጋጅ ነው። "የማይበገር ንግድ እና ዘላቂ የእሴት ሰንሰለቶች" በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ የሚካሄደው መድረክም ህዳር 15 እና 16 ቀን 2019 ዓ.ም ለሁለት ቀናት እንደሚቆይ አስታውቀዋል። በመድረኩ ከ17 ሀገራት የተውጣጡ ዓለም አቀፍ ገዢዎችን ጨምሮ ከ600 በላይ ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት መሆኑ ተናግረዋል። በኮንፍረንሱ ከ100 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ ምርት ማቅረብ የሚያስችልና ከ60 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚገመት የንግድ ለንግድ (B2B) ስምምነት ይፈረማል ተብሎ እንደሚጠበቅ አመላክተዋል። ከ15 በላይ ጥናታዊ ጽሑፎች በሚቀርቡበት መድረክ ተሳታፊዎችም የኢትዮጵያን ብሔራዊ የጥራት መንደርና የልማት ሥራዎች የሚጎበኙበት መርሃ ግብር መዘጋጀቱን ገልጸዋል። በ2018 በጀት ዓመት ከ555 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ የጥራጥሬና ቅባት እህል ምርቶች ወደ ውጭ በመላክ 570 ነጥብ 4 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ መገኘቱን ገልጸዋል። ይህም የኢትዮጵያ ሀገር በቀል የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ በወጪ ንግድ ላይ ያስገኘውን ከፍተኛ ውጤት የሚያሳይ መሆኑን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ የጥራጥሬና ቅባት እህሎች ላኪዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት ኤደኦ አብዲ በበኩላቸው፤ መድረኩ የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ አጋርነትን የሚያጎለብት የገበያ ተወዳዳሪነትን ለማሻሻል ወሳኝ ነው ብለዋል። በተጨማሪም የፋይናንስ ተደራሽነትን፣ የሎጂስቲክስ አቅርቦትንና እሴት ሰንሰለቶችን ለማሳደግ ከዓለም ባንክ፣ ከብሔራዊ ባንክ እና ከሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ሰፊ ውይይት እንደሚደረግ ገልጸዋል። ይህም የሀገር ውስጥ አምራቾችንና ላኪዎችን ከዓለም አቀፍ ገዢዎች ጋር በቀጥታ በማገናኘት የንግድ ውሎችን ለማስፋት ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥር አስታውቀዋል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
የኢትዮጵያ የሰው ሰራሽ አስተውሎት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ልማት ለአፍሪካዊያን የሚተርፍ አቅም ገንብቷል
Nov 17, 2026 547
አዲስ አበባ፤ ህዳር 8/2019(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የሰው ሰራሽ አስተውሎት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ልማት ለአፍሪካዊያን የሚተርፍ ተምሳሌታዊ አቅም ነው ሲሉ የአፍሪካ ሀገራት ሰልጣኞች ተናገሩ። የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ለተውጣጡ የዘርፉ ባለሙያዎች በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ሥራ ፈጠራ (Start-up) ዙሪያ ሥልጠና እየሰጠ ይገኛል። ኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን በማቋቋም እና "ዲጂታል ኢትዮጵያ" ስትራቴጂን በመተግበር በዘርፉ ላይ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ እያፈሰሰች ትገኛለች። ይህም ከቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ባለፈ ለአፍሪካ ሀገራት የቴክኖሎጂ መፍትሔዎችን፣ ሶፍትዌሮችንና ሥልጠናዎችን የምታቀርብ የአፍሪካ የቴክኖሎጂ ማዕከል እየሆነች መጥታለች። ኢዜአ ያነጋገራቸው ከአፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ ሰልጣኝ ባለሙያዎች እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ አህጉራዊ ትስስርን ለማጠናከርና የአፍሪካን አቅም በቴክኖሎጂ ለማሳደግ እያደረገች ያለው ጥረት የሚደነቅ ነው። ከናይጀሪያ የመጣው አባዮሚ ኦሽኖዎ፤ ስልጠናው አፍሪካውያን ከቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ባሻገር አህጉራዊ መፍትሔ የሚያፈልቁ ሙያተኞች የሚፈሩበትን ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር ገልጿል። ኢትዮጵያ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ የገነባችው አቅም እና እያከናወነቻቸው ያሉ ተግባራት ለመላው አፍሪካ ምሳሌ የሚሆኑ መሆናቸውን ጠቅሷል። በኢንስቲትዩቱ የተዘጋጀው የፓን-አፍሪካኒዝም ሰው ሰራሽ አስተውሎት የሥራ ፈጣሪዎች ሥልጠና የሰልጣኞችን የቴክኒክ ክህሎት በማሻሻል የአፍሪካን ትስስር ለማጠናከር ጉልህ ሚና እንዳለው ተናግሯል። አህጉራዊ ሥልጠናዎችን በማዘጋጀት ኢትዮጵያ በአፍሪካ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እና የዲጂታል ሽግግር የመሪነት ሚናዋን በተግባር እየተወጣች መሆኗንም አመላክቷል። ዩጋንዳዊቷ በረንጋህ ናሙቢሊ በበኩሏ፤ ኢትዮጵያ አህጉራዊ ትስስርን ለማጠናከርና የአፍሪካን የቴክኖሎጂ አቅም ለማሳደግ እያደረገች ያለው ጥረት የሚደነቅ መሆኑን ገልጻለች። ኢትዮጵያ በዘርፉ ያካበተችውን ልምድና ቴክኖሎጂ ለአፍሪካ ሀገራት ማካፈሏ አህጉራዊ የዲጂታል ትብብርን ለማጠናከር እንደሚያግዝም ተናግራለች። ከሥልጠናው ያገኘችው እውቀትና ክህሎት ወደ ሀገሯ ስትመለስ ዘርፉን ለማገዝ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥርላት አመልክታለች። ሩዋንዳዊው ጋዮስ ካይራንጋ፤ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ስታርታፖች እየሰጠች ያለው ስልጠና አፍሪካውያን የራሳቸውን መፍትሔዎች በራሳቸው እንዲፈጥሩ የሚያስችል ነው ብሏል። ኢትዮጵያ እየወሰደች ያለው ኢኒሼቲቭ አህጉሪቱ በቴክኖሎጂ እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍ የጀመረችውን ተግባር ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑን ገልጿል። ኢትዮጵያዊቷ ወለላ በቀለ በበኩሏ፤ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ከተውጣጡ ሰልጣኞች ጋር አብሬ በመሰልጠኔ በምሠራው ፕሮጀክት ላይ ገንቢ ሀሳቦችን እንዳገኝና ልምድ እንድቀስም ረድቶኛለች ብላለች። ሥልጠናው የፈጠራ ሃሳቦቻችንን ወደ ተግባራዊ የንግድ ሥራና ገበያ በመቀየር ራሳችንንም ሆነ ሀገራችንን ተጠቃሚ የምናደርግበትን ዕድል ፈጥሮልናል ነው ያለችው።
የሆለታ ግብርና ምርምር ማዕከል በአፈር አጠቃቀምና እንክብካቤ ላይ የተለያዩ ምርምሮችን እያካሄደ ነው
Nov 11, 2026 191
ሆለታ፣ ህዳር 2/2019 (ኢዜአ)፡- የሆለታ ግብርና ምርምር ማዕከል በአፈር አጠቃቀምና እንክብካቤ ላይ የተለያዩ ምርምሮችን እያካሄደ መሆኑን ገለጸ። በሆለታ ግብርና ምርምር ማዕከል የአፈር ለምነት ተመራማሪ አቶ ዘለቀ ኦብሳ እንዳሉት፤ ሆለታ ግብርና ምርምር በኮትቻ አፈር ምርምር ላይ የረጅም ጊዜ ልምድ ያለው ነው። በዚህም ኮትቻ አፈር በዝናብ ጊዜ ውሃን በብዛት መያዝ እና በበጋ ወቅት በስፋት መሰነጣጠቅ ዋነኛ ችግር መሆኑን በመለየት እንደ አፈር ማጠንፈፍ የመሳሰሉ መፍትሔዎችን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት እንደ ሀገር አሳሳቢ የሆነው የአፈር መሸርሸርን ለመታደግ በአፈር አጠቃቀምና እንክብካቤ ዙሪያ ሰፋፊ የጥናት ስራዎችን በማካሄድ ላይ ይገኛል ብለዋል። በተለይም ከህዝብ ቁጥር መጨመርና ከአጠቃቀም ጉድለት የተነሳ ከፍተኛ የአፈር መሸርሸር ስለሚኖር ለዚህ መፍትሔ የሚሆኑ ውጤቶችን ለማምጣት ተግቶ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በአፈርና ውሃ ምርምር ስር ስድስት የትኩረት መስኮች አሉት። እነዚህም በሀገር አቀፍ ደረጃ በማዕከሉ አስተባባሪነት የሚካሄደው የአፈር አሲዳማንት ምርምር፣ በአፈር ለምነት ላይ የሚካሄድ ምርምር፣ የተፋሰስ ልማት፣ የኮትቻ አፈር ጥናት እና የተፈጥሮና ማዳበሪያ ዝግጅት ላይ የሚካሄዱ ምርምሮችን እንደ አብነት አንስተዋል። ማዕከሉ ደረጃውን የጠበቀ የአፈር፣ የእፅዋትና የውሃ ምርምር ላቦራቶሪዎች እንዳሉት አንስተው በዚህም የምርምር ውጤቶቹን ለዩኒቨርሲቲዎች እና ለአርሶ አደሮች በመስጠት ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል። ለአብነትም ቀደም ሲል በውል የማይታወቀው የአፈር አሲዳማነት ችግር በአሁኑ ጊዜ ችግሩ በምርምር ተለይቶ አፈሩን በማከምና የእርሻ ስራውን በማስተካከል ምርትና ምርታማነት መጨመር መቻሉን እንደ ምርምር ውጤታቸው አንስተዋል። አፈርን በኖራ ከማከም ባለፈ አሲዳማ አፈር ተቋቁመው የተሻለ ምርት መስጠት የሚችሉ የሰብል ዝርያዎችም በምርምር ተገኝተው ለአርሶ አደሮች በመስጠት ውጤት ማስገኘታቸውን አንስተዋል።
የአርሲ ዩኒቨርሲቲ የአርሶ አደሩን ምርታማነት ለማሳደግ የሚያስችሉ የዘር ብዜት ስራዎችን እያከናወነ ነው
Nov 10, 2026 237
አዳማ፣ ህዳር 1/2019(ኢዜአ)፡-አርሲ ዩኒቨርሲቲ የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት ለሚያሳድጉ የምርጥ ዘር ብዜት ስራዎች ትኩረት መስጠቱን ገለፀ። የዩኒቨርሲቲው የግብርናና አከባቢ ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ረጋሳ አያና(ዶ/ር) ለኢዜአ እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው በተግባር ከተደገፈ የመማር ማስተማር ስራዎች በተጨማሪ የአርሶ አደሩን ምርታማነት በሚጨምሩ ተግባራት ላይ እየሰራ ነው። ዩኒቨርሲቲው የሚሰጣቸው የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎቶች ችግር ፈቺና የማሕበረሰቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ እንዲሆኑም የጥናትና የምርምር ስራዎችን በስፋት እያከናወነ እንደሚገኝ ነው የተናገሩት። በስንዴ፣ በቢራ ገብስ ፣ በጤፍ ፣ በቆሎና አጃን ጨምሮ በድንች ምርቶች ላይም ሰፋፊ የጥናት ምርምር ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልፀዋል። በተለይም ከቁሉምሳ ግብርና ምርምር ማእከል ጋር በመተባበር ለአከባቢው የአየር ፀባይ ተስማሚ የሆኑ የስንዴ ፣ገብስና የጤፍ ምርጥ ዘርን ለማውጣት እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል። በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከ1 ሺህ 400 ኩንታል በላይ የስንዴ ምርጥ ዘር በማምረት ለአከባቢው አርሶ አደሮች ተደራሽ ማድረግ መቻሉንም ነው የተናገሩት። በዘንድሮው ዓመት በ97 ሄክታር መሬት ላይ አባይ ፣ ቢፍቱና ቁሉም የተባሉ የስንዴ ምርጥ ዘርን ጨምሮ ገብስ፣ ነጭና ቀይ ጤፍ ምርት ዘር የማባዛት ስራ እየተሰራ መሆኑንም አመልክተዋል። በዘንድሮው በጀት ዓመት በስንዴ ምርጥ ዘር ብቻ ከ1 ሺህ 900 ኩንታል በላይ የምርጥ ዘር ለማግኘት ታቅዶ እየተሰራ ይገኛል ነው ያሉት። ለእቅዱ ውጤታማነት ከግብርና ምርምር ማእከላት፣ከኦሮሚያ ግብርና ቢሮና ከፌዴራል የግብርና ምርምር ማእከላት ጋር በትብብር እየሰሩ መሆኑን ጠቅሰዋል። በተለይ ዩኒቨርሲቲው በደቡብ ምስራቅ ኦሮሚያ ዞን ጥዮና አርሲ ሮቤ ወረዳዎች በአርሶ አደሩ ማሳ ላይ የስንዴ ምርጥ ዘር ብዜት እያከናወነ እንደሚገኝ ጨምረው ገልፀዋል። በአርሶ አደሩ ማሳ ላይ እየተከናወነ ያለው የዘር ብዜት ስራ ምርትና ምርታማነት በማረጋገጥ የሚፈለገውን ውጤት እንዲያመጣም ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ሙያዊ ድጋፍና ክትትል እየተደረገ መሆኑንም አስረድተዋል። በተመሳሳይ በዘንድሮው ዓመት ዩኒቨርሲው ከ800 ኩንታል በላይ የገብስ ምርጥ ዘር ለማምረት እየሰራ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የስንዴ ፣ ገብስና የጤፍ ሰብል ልማት በጥሩ ሁኔታ ምርት መያዙን ጨምረው ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ የአህጉሪቱ የቴክኖሎጂ ማዕከል መሆን የሚያስችላትን ውጤታማ ሥራዎች እያከናወነች ነው
Nov 9, 2026 648
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 30/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የአፍሪካን የሰው ሰራሽ አስተውሎት አቅም በማሳደግ የአህጉሪቱ የቴክኖሎጂ ማዕከል መሆን የሚያስችላትን ውጤታማ ሥራዎች እያከናወነች መሆኑን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ገለጹ። የፓን አፍሪካ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የንግድ ሥራ ፈጠራ ማበልፀጊያ ስልጠና ፕሮግራም መካሄድ ጀምሯል፡፡ በመርሐ ግብሩ ላይ በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ሺባታ ሂሮኖሪ እንዲሁም ከተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ ወጣት የዘርፉ ተጽእኖ ፈጣሪዎች ተገኝተዋል፡፡ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት፤ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ አጠቃላይ የኢኮኖሚ፣ የጤና፣ የግብርና እና የአስተዳደር ሥርዓቶችን በከፍተኛ ደረጃ በመቀየር ላይ ይገኛል። ኢትዮጵያ በዚህ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ እንቅስቃሴ ውስጥ ተመልካች ሳትሆን፣ በንቃት በመሳተፍ የራሷን ቴክኖሎጂ የምትገነባበትን ስትራቴጂካዊ ምርጫ ማድረጓንም አብራርተዋል። የዚህ ራዕይ ቁልፍ ምሰሶ ከሆኑት መካከል በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ የተደረገው የመደመር የሰው ሰራሽ አስተውሎት ዩኒቨርሲቲ አንዱ እንደሆነ ገልጸዋል። ዩኒቨርሲቲው በ39ኛው የአፍሪካ ሕብረት ጉባኤ የኢትዮጵያን ዲጂታል መሠረተ ልማት፣ የምርምር አቅምና የቴክኖሎጂ ብቃት ለማስፋፋት የተያዘ ስትራቴጂ አካል ሆኖ መቅረቡንና በአሁኑ ወቅት ግንባታው በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡ ዓላማውም የአፍሪካን ቀጣይ ትውልድ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሳይንቲስቶች፣ መሐንዲሶችና የሥራ ፈጣሪዎችን በስፋት ማፈራት እንደሆነ አስገንዝበዋል። ኢትዮጵያ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ኢንስቲትዩትን በማቋቋም ለወደፊቱ የቴክኖሎጂ ዓለም ትልቅ እርምጃ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ የኢንስቲትዩቱ ተልዕኮ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍ ምርምርና ልማት ማካሄድ፣ ብሔራዊ የሰው ሰራሽ አስተውሎት አቅምና ባለሙያዎችን ማፍራት፣ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ዘርፎች የሰው ሰራሽ አስተውሎት መፍትሔዎችን ማበልጸግ እንዲሁም በፖሊሲ፣ በሥነ ምግባር፣ በመረጃ አስተዳደርና በባለሙያ ልማት ዙሪያ አጠቃላይ ሥራዎችን ማከናወን እንደሆነ አስረድተዋል። ኢትዮጵያ ብሔራዊ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ፖሊሲዋን ይፋ ማድረጓ በአፍሪካ የሰው ሰራሽ አስተውሎት አስተዳደርና ፈጠራ ዘርፍ መሪ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንድትመደብ እንደሚያደርጋት ተናግረዋል። ከተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም እና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በኢንስቲትዩቱ ዋና መሥሪያ ቤት የAI Uni Pod ማዕከል መመረቁን አውስተዋል። ማዕከሉ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂንና ብሔራዊ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ፖሊሲን የሚደግፍ ከመሆኑም በላይ መንግሥትን፣ ተመራማሪዎችን፣ የግል ዘርፉን እና ወጣት ፈጣሪዎችን በአንድ ላይ የሚያሰባስብ ነው። ዘመናዊ ላቦራቶሪዎችን፣ የሮቦቲክስ መሣሪያዎችን፣ ከፍተኛ የኮምፒውተር ማስላት አቅምን፣ የዲዛይን ስቱዲዮዎችንና የትብብር ትምህርት ቦታዎችን ያካተተው ይህ ማዕከል፤ ምርምር ከሥራ ፈጠራ ጋር የሚገናኝበት፣ ሀሳቦችና የመጀመሪያ ሙከራዎች ወደ ተግባራዊ ምርት የሚቀየሩበት ዋና ስፍራ መሆኑን ገልጸዋል። አፍሪካ በዓለም ላይ በወጣቶች ቁጥር ከፍተኛ ድርሻ ያላት አህጉር ብትሆንም ማንኛዋም ሀገር የአህጉሪቱን የወደፊት የሰው ሰራሽ አስተውሎት ጉዞ በብቸኝነት መገንባት እንደማትችል ጠቁመዋል። በመሆኑም ኢትዮጵያ በጋራና በአንድነት ለመሥራት እየተጋች መሆኗን ገልጸው፣ የአፍሪካ መረጃዎች በአግባቡና በኃላፊነት በአገራት መካከል ሲጋሩ ቴክኖሎጂዎች፣ ቋንቋዎች፣ ባህላዊ አገላለጾች እና ገበያዎች በተሻለ ሁኔታ እንዲረዱ እንደሚያግዙና መሰል የሥራ ፈጠራ ማበልጸጊያ ፕሮግራሞች ወጣቶች ጎን ለጎን እንዲሠሩ ሰፊ ዕድል እንደሚፈጥሩ አመልክተዋል።
ስፖርት
ታዳጊ አትሌቶች የኢትዮጵያን የድል ጉዞ የሚያድሱ ሀገራዊ ኩራቶች ናቸው -ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Nov 18, 2026 299
አዲስ አበባ፣ኅዳር 9/2019 (ኢዜአ)፦ታዳጊ አትሌቶች የኢትዮጵያን የድል ጉዞ የሚያድሱ ሀገራዊ ኩራቶች መሆናቸውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት ታዳጊ አትሌቶቹን በአካል አግኝተው ማበረታታቸውን ገልጸዋል። ታዳጊዎቹ በአፍላ ዕድሜያቸው በዓለም መድረክ ባሳዩት ብቃትና ባስመዘገቡት ድል የሀገራቸውን ሰንደቅ ዓላማ በክብር ከፍ አድርገዋል ነው ያሉት። ይህ ውጤት ለመላው ኢትዮጵያውያን ደስታና ኩራት፣ ለታዳጊው ትውልድ ደግሞ ታላቅ ተስፋና ተምሳሌት መሆኑንም ተናግረዋል። የተመዘገበው ወቅታዊ ድል ለነገው የላቀ ስኬት መነሻና መሠረት መሆኑን የጠቆሙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ አትሌቶቹ በራሳቸው በመተማመን፣ ህልማቸውን በማሳደግና ከዛሬው ድል የበለጠ ከፍታን በማለም ለመጪዎቹ የዓለም ሻምፒዮናዎችና ኦሎምፒክ ጨዋታዎች በበለጠ ብቃት፣ ትጋትና ቁርጠኝነት እንዲዘጋጁ አሳስበዋል። መንግሥት በቀጣይ የስኬት ጉዟቸው የሚያስፈልጋቸውን ሁሉንም ዓይነት ድጋፍ እንደሚያደርግ ያረጋገጡት አቶ ተመስገን፤ አትሌቶቹ ብቃትና ችሎታቸውን በቀጣይነት እያዳበሩ የሀገራቸውን ስምና ሰንደቅ በዓለም አደባባይ በተከታታይ ከፍ ለማድረግ በጽናት ለድል እንዲሰለፉ አደራ ብለዋል።
የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ከአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውጭ ሆነ
Nov 17, 2026 596
አዲስ አበባ፤ ህዳር 9/2019 (ኢዜአ)፦ በ23 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ሁለተኛ ዙር የመልስ ጨዋታ ኢትዮጵያ በሞሮኮ 5 ለ 3 ተሸንፋለች። ማምሻውን በፕሪንስ ሙላይ ኤል ሀሰን ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ናትናኤል ሰለሞን ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ያሬድ ብሩክ ቀሪዋን የኢትዮጵያን ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል። አሚር ቦሃምዲ፣ ቃይስ ሁዱሲ ባሪ፣ ዩኑስ ኤል ባህራዊ፣ ኦስማን ማማ እና አብዱልሃማድ ማሊ የሞሮኮን ጎሎች አስቆጥረዋል። ወጣት ብሔራዊ ቡድኑ በሁለተኛው አጋማሽ የተሻለ እንቅስቃሴ አድርጓል። ውጤቱን ተከትሎ በአሰልጣኝ ዳንኤል ፀሐዬ የሚመራው የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በድምር ውጤት 6 ለ 3 ተሸንፎ ከአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውጪ ሆኗል። የሞሮኮ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ወደ መጨረሻው ዙር ማጣሪያ አልፏል። ሞሮኮ የወቅቱ ከ23 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ ናት። ከ23 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ እ.አ.አ በ2027 በግብጽ አስተናጋጅነት ይካሄዳል። በውድድሩ ላይ ግብጽን ጨምሮ ስምንት ሀገራት ይሳተፋሉ። በአፍሪካ ዋንጫው ከአንድ እስከ ሶስት የሚወጡ ብሔራዊ ቡድኖች በቀጥታ እ.አ.አ በ2028 ሎስ አንጀለስ በሚካሄደው 34ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ይሳተፋሉ። በውድድሩ አራተኛ ደረጃን ይዞ የሚያጠናቅቀው ቡድን ከሌላ አህጉር አራተኛ ደረጃን ከያዘ ቡድን ጋር ለሚደረግ የጥሎ ማለፍ (Play-off) ጨዋታ ያልፋል።
ለዋልያዎቹ እስከ መጨረሻው ድረስ ልዩ ድጋፋችሁን ለለገሳችሁ የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ምስጋናዬ የላቀ ነው-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Nov 17, 2026 670
አዲስ አበባ፤ህዳር 8/2019(ኢዜአ)፦ለዋልያዎቹ እስከ መጨረሻው ድረስ ልዩ ድጋፋችሁን ለለገሳችሁ የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች እና መላው ኢትዮጵያዊያን በሙሉ ምስጋናዬ የላቀ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ። የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት፣ ሽንፈት ለነገው ድል የቤት ስራችንን እንድንሰራ ማሳያችን እንጂ የመጨረሻዎች መጨረሻ አይደለም። የብሔራዊ ቡድናችን አባላት ድንቅ ጨዋታ ቢያሳዩንም የዛሬው ውጤት ግን አንዳሰብነው አልሆነም ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር፣ እስከ መጨረሻው ድረስ ልዩ ድጋፋችሁን ለለገሳችሁ የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች እና መላው ኢትዮጵያዊያን በሙሉ ምስጋናዬ የላቀ ነው። ዋሊያዎች ከዛሬው ጨዋታ በመማር በቀጣይ በተሻለ ውጤት ሕዝባችሁን እንደምታስደስቱ ሙሉ እምነት አለኝ ፣በርቱ ሲሉም ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሽንፈት አስተናገደ
Nov 17, 2026 90
አዲስ አበባ፤ ህዳር 9/2019 (ኢዜአ)፦ በ36ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ አራተኛ መርሐ ግብር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሞዛምቢክ 1 ለ 0 ተሸንፏል። በባህር ዳር ስታዲየም በተካሄደው የምድብ 10 ጨዋታ ስታንሊ ራቲፎ በ38ኛው ደቂቃ ግቡን አስቆጥሯል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሁለተኛው አጋማሽ የወሰደውን ብልጫ ወደ ግብ መቀየር አልቻለም። ሞዛምቢክ በመጀመሪያው አጋማሽ የግብ እድሎችን በመፍጠር ተሽላ ተገኝታለች። ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ በሶስት ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዛለች። ሞዛምቢክ በሰባት ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። በምድብ 10 ሴኔጋል በ10 ነጥብ እየመራች ነው። ሱዳን በሶስት ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። የምድብ አምስተኛ እና ስድስተኛ ጨዋታዎች በመጋቢት ወር 2019 ዓ.ም ይካሄዳሉ።
አካባቢ ጥበቃ
የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችንበዘላቂነት ለመከላከል ወሳኝ መፍትሄ ነው - ምሁራን
Nov 18, 2026 121
ሀዋሳ፤ ሕዳር 9/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በዘላቂነት ለመከላከል ወሳኝ መፍትሄ መሆኑን ምሁራን ተናገሩ። ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ከ56 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል በዘርፉ የላቀ ውጤት አስመዝግባለች። ሀገሪቱ የተራቆቱ መሬቶች ወደ ቀደመ ይዞታቸው እንዲመለሱ በማድረግና የታዳሽ ሀይል አማራጮቿን በማስፋት ለአረንጋዴ ልማት እና እድገት ያላትን ቁርጠኝነት አሳይታለች። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራም ኢትየጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ከችግር ተናጋሪነት ወደ መፍትሄ አመንጪነት በመሸጋገር ለአፍሪካና ለዓለም ምሳሌ የሚሆን ተግባር አከናውናለች። በአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ያስመዘገበቻቸው ስኬቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን ተቀባይነት እንዲያድግ በማድረጉ እ.አ.አ በ2027 የሚካሄደውን 32ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤን እንድታዘጋጅ ተመርጣለች። በጉዳዩ ላይ ኢዜአ ያነጋገራቸው የዘርፉ ምሁራንም እውቅናው የኢትዮጵያ በዘርፉ ተግቶ የመስራት ውጤት መሆኑን አንስተው፣ እንደ ሀገር እየተመዘገበ ያለውን ውጤት በቀጣይም አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል። በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የወንዶገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ መምህርና ተመራማሪ ፕሮፌሰር ፀጋዬ በቀለ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ በቁርጠኝነት ያከናወነቻቸው የአረንጓዴ አሻራ ልማትና የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች በርካታ ውጤቶችን አስገኝተዋል። በተለይ በአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር ችግኞችን የመትከልና የመንከባከብ ባህል እየጎለበተ መምጣት እንደ ሀገር የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ካለው ፋይዳ ባለፈ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባት እያስቻላት ነው ብለዋል። እንደ ፕሮፌሰር ጸጋዬ ገለጻ፣ የኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች የደን ሽፋንን በማሳደግ፣ የአፈር ለምነትን በመመለስና የውሃ አካላት አቅምን በማሳደግ ለኢኮኖሚ መሰረት የሆነውን ግብርና ውጤታማነት እያሳደገ ነው። ከዚህም ባለፈ ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ በመስኖ ልማት ዓመቱን ሙሉ በማምረት ዜጎች የምግብ ዋስትናቸውን እንዲያረጋግጡና በኢኮኖሚም ተጠቃሚ እንዲሆኑ አግዟል። በመሆኑም የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ ልማት መርሃ ግብር በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በዘላቂነት ለመከላከል ወሳኝ መፍትሄ መሆኑን ገልጸዋል። በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ግብርና ኮሌጅ የምግብ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ስነ-ምግብ ተመራማሪና መምህር ፕሮፌሰር ከበደ አበጋዝ በበኩላቸው እንዳሉት፣ እንደሀገር የተከናወኑ የአካባቢ ጥበቃ ተግባራት በስነምግብ ዘርፍ ከፍተኛ ለውጥ አምጥተዋል። በተለይ በአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር የተተከሉ ችግኞች የመሬት ለምነትና የውሃ አቅምን በመጨመር የግብርና ምርታማነትን በማሳደግ በሥርአተ ምግብ ዘርፍ ተጨባጭ ውጤት ማምጣታቸውን ገልጸዋል። ይህም ጤናው የተጠበቀ ማህበረሰብን ለመፍጠር እያገዘ ነው ያሉት ፕሮፌሰሩ፣ ኢትዮጵያ በተፈጥሮና አካባቢ ጥበቃ ያከናወነቻቸው ተግባራት ለሌሎች ምሳሌ እንዳደረጋትም ተናግረዋል። የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመቋቋም አቅም ፈጥሯል ያሉት ደግሞ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጂኦግራፊና አካባቢ ጥበቃ ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ ምስራቅ ታምሬ (ዶ/ር) ናቸው። የተራቆቱ አካባቢዎች በደን መሸፈናቸው የደረቁ ምንጮች መልሰው እንዲያገግሙና የአፈር መሸርሸርን በማስቀረት ለእርሻ ሥራ ውጤታማነት የላቀ ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ ብለዋል። ይህም ዜጎች በተለያዩ ዘርፎች ተሰማርተው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከማድረግ ባለፈ ለሀገራዊ የኢኮኖሚ ዕድገት አበርክቶው የላቀ መሆኑን ነው ያነሱት። ባለፉት ዓመታት በአረንጓዴ አሸራ መርሀግብር የተከናወኑ ተግባራት በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በዘላቂነት ለመቋቋም ፋይዳቸው የጎላ መሆኑነም አመልከተዋል።
ኢትዮጵያ አረንጓዴ ኢኮኖሚን እውን ለማድረግ እና የአየር ንብረት ተጽዕኖዎችን ለመቋቋም የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ ትቀጥላለች
Nov 17, 2026 98
አዲስ አበባ፤ ህዳር 8/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ አረንጓዴ ኢኮኖሚን እውን ለማድረግ እና የአየር ንብረት ተጽዕኖዎችን ለመቋቋም እየወሰደች ያለችውን ተግባራዊ እርምጃ አጠናክራ እንደምትቀጥል የኮፕ 32 ፕሬዝደንሲ ቡድን አባል አደፍርስ ወርቁ(ዶ/ር) ገለጹ። 31ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 31) በቱርኪዬ አንታሊያ እየተካሄደ ይገኛል። “ጉዞ ወደ ዘላቂ፣ አይበገሬነት እና ፍትሃዊነት ወደተረጋገጠበት መጻኢ ዘመን” የጉባኤው መሪ ቃል ነው። በጉባኤው ላይ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን እየተሳተፈ ይገኛል። የኮፕ 32 ፕሬዝደንሲ ቡድን አባል አደፍርስ ወርቁ(ዶ/ር) የኮፕ ፕሬዝዳንት ቡድን ጨምሮ የኢትዮጵያ ልዑክ በኮፕ 31 እና በሌሎች ጉባኤዎች ላይ የኢትዮጵያ አቋም ለጉባኤው የማሳወቅ እና የማስተባበር ስራ እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር በመቀናጀት የጋራ መኖሪያ የሆኑትን አፈር፣ ውሃ እና አየር ከጉዳት ለመጠበቅ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ በሪዮ ኮንቬንሽን አማካኝነት ዓለም አቀፍ ማህበረሰብን በማንቀሳቀስ እና አዳዲስ ስትራቴጂዎችን በመቅረጽ ረገድ ግንባር ቀደም ተሳትፎ በማድረግ ላይ ናት ብለዋል። እንደ ኢኮኖሚ፣ ጤና እና ኢነርጂ ያሉ መሰረታዊ ፖሊሲዎች ከአየር ንብረት ለውጥ አደጋ ጋር በሚጣጣም መልኩ እንዲቀረጹ እና ተግባራዊ እንዲሆኑ ሰፊ ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን ነው የገለጹት። የኢትዮጵያ ፖሊሲዎች ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ በማስተባበር ረገድ አርአያ የሚሆኑ እና ጠንካራ መሠረት የያዙ ናቸው ሲሉ ተናግረዋል። በቀጣይም አረንጓዴ ኢኮኖሚን እውን ለማድረግና የአየር ንብረት ተጽዕኖዎችን ለመቋቋም የሚደረጉ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አደፍርስ ወርቁ(ዶ/ር) አመልክተዋል።
የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ልማት እና የካርበን ልቀት ቅነሳ ስኬቶች የዓለምን ትኩረት ስበዋል
Nov 17, 2026 197
አዲስ አበባ፤ ህዳር 8/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ልማት እና የካርበን ልቀት ቅነሳ ስኬቶች የዓለምን ትኩረት መሳባቸውን የኮፕ 32 የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንሺያል ቡድን አባል አቶ ገብሩ ጀምበር ገለጹ። 31ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 31) በቱርኪዬ አንታሊያ እየተካሄደ ይገኛል። “ጉዞ ወደ ዘላቂ፣ አይበገሬነት እና ፍትሃዊነት ወደተረጋገጠበት መጻኢ ዘመን” የጉባኤው መሪ ቃል ነው። በጉባኤው ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት የኮፕ 32 የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንሺያል ቡድን አባል አቶ ገብሩ ጀምበር ሀገሪቱ በካርበን ገበያ እና በአረንጓዴ ልማት ዘርፍ እያስመዘገበች ያለችው ተጨባጭ ውጤት የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ትኩረት መሳቡን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በፓሪስ ስምምነት መሰረት ባቀደችው የልቀት ቅነሳ ግብ መሰረት፣ እስከ 2035 ከ70 በመቶ በላይ የሙቀት አማቂ ጋዝ ልቀትን ለመቀነስ እና በ2050 ወደ ዜሮ ልቀት (Net-Zero) ለመድረስ የገባችውን ቃል በተግባር እያሳየች እንደምትገኝ አመልክተዋል። በተለይም ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እስካሁን የተከለቻቸው 56 ቢሊዮን ችግኞች እና በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች እየተከናወኑ ያሉ የኮሪደር ልማት ስራዎች ለዓለም አቀፍ የልቀት ቅነሳ ግቦች ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆኑን ተናግረዋል። እነዚህ ሰፊ ስራዎች በኮፕ 32 የኢትዮጵያ ፓቪሎን ላይ በምስልና በቪዲዮ እየቀረቡ ሲሆን፣ በርካታ የዓለም ሀገራትና ድርጅቶች ኢትዮጵያ የምትናገረውን በተግባር የምትፈጽም ሀገር መሆኗን በመገንዘብ አብረዋት ለመስራት ከፍተኛ ፍላጎት እያሳዩ እንደሚገኝ ነው የገለጹት። ከዚህም ባለፈ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ እና በደን ልማት የተሰሩ ስራዎችን በሳይንሳዊ መንገድ ለመለካት የሚያስችል የ"ኤም.አር.ቪ" (MRV) ማዕቀፍ በዘመናዊ የሳተላይት መረጃዎች በማዘመን ላይ ትገኛለች ብለዋል። የግብርና፣ ደን፣ ካርታ ስራ እና ስታቲስቲክስ ተቋማት በጋራ በመቀናጀት የደን ሽፋን ለውጦችን በከፍተኛ ጥራት በመለካት ወደ ካርበን ገበያ ለማስገባት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በማጠናቀቅ ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል። በድርድር መድረኮች ላይም የኢትዮጵያ ልዑክ ቡድን ታዳጊ ሀገራትን (LDC) እና የአፍሪካ ቡድንን በመወከል የካርበን ገበያ ድርድሮችን በንቃት በመምራት ላይ መሆኑን ነው የጠቆሙት ። በየሰዓቱ ከ30 በላይ በሚካሄዱ የድርድር ክፍሎች ውስጥ የኢትዮጵያ ተወካዮች በመገኘት፣ የሀገሪቱን ጥቅም የሚያስጠብቁ ውሳኔዎች እንዲተላለፉ በከፍተኛ ኃላፊነት እየሰሩ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ከካርበን ንግድ የሚገኘውን ገቢና የሙያ ድጋፍ ለአካባቢው ማህበረሰብ በፍትሃዊነት ለማከፋፈል የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ እና የምዝገባ ስርዓት (Registry) በማዘጋጀት ለግሉ ዘርፍና ለዓለም አቀፍ አጋሮች ምቹ ሁኔታን መፍጠሯን አብራርተዋል። ይህ ቁርጠኝነት በታዳጊ ሀገራት ደረጃ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የሚደረገው ጥረት በከፍተኛ ትኩረት ከተያዘ ምን ያህል ውጤት ማምጣት እንደሚቻል ለዓለም ያሳየ መሆኑንም አንስተዋል። በአጠቃላይ በኮፕ 31 ጉባኤ የመጀመሪያዎቹ ሳምንታት በባለሙያዎች ደረጃ ሲካሄዱ የቆዩት የካርበን ገበያና የሙቀት አማቂ ጋዞች ድርድሮች አበረታች ውጤት እያሳዩ መሆናቸውን ገልጸዋል። ጉባኤው ወደ ሚኒስትሮች ደረጃ እየተሸጋገረ ሲሆን፣ በቀጣይ ቀናትም ኢትዮጵያንና ታዳጊ ሀገራትን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ገንቢ ውሳኔዎች ይተላለፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ያስመዘገበቻቸውን የአየር ንብረት ለውጥ ምላሽ ውጤቶች በዓለም አቀፍ መድረክ አቀረበች
Nov 17, 2026 210
አዲስ አበባ ፣ህዳር 8/2019 (ኢዜ )፦አበቱርክ አንታሊያ እየተካሄደ በሚገኘው 31ኛው የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (COP31) ላይ ኢትዮጵያ ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ ዝቅተኛ የካርቦን ልቀት እና የአየር ንብረት ተቋቋሚነት ያለው ኢኮኖሚ በመገንባት ረገድ ያስመዘገበቻቸውን ተጨባጭ ውጤቶችና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ይፋ አድርጋለች። በCOP31 የኢትዮጵያ ፓቪሊዮን በብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስቴር አዘጋጅነት “ከቤሌም እስከ አንታሊያ፦ ዝቅተኛ የካርቦን ልቀትና የአየር ንብረት ተቋቋሚ ኢኮኖሚ በመገንባት የኢትዮጵያ ጉዞ” በሚል መሪ ቃል በተካሄደው ከፍተኛ የግምገማ መድረክ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት እና የልማት አጋሮች ተወካዮች ተገኝተዋል። በመድረኩ ከተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች መካከል የአረንጓዴ ዐሻራ ስኬት አንዱ ሲሆን፤ በ2018 ዓ.ም ብቻ ከ8.2 ቢሊዮን በላይ ችግኞች የተተከሉ መሆኑና መርሐ ግብሩ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ የተተከሉ ችግኞች አጠቃላይ ቁጥር ከ56 ቢሊዮን በላይ መድረሱ ተገልጿል። በተጨማሪም የንጹህ ትራንስፖርት ሽግግርን በተመለከተ በሀገራችን ውስጥ የሚገኙ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቁጥር 144 ሺህ 429 መድረሱ ተመላክቷል። የፖሊሲ እና ተቋማዊ ማሻሻያዎችን በተመለከተም የካርቦን ገበያ አዋጅ መጽደቁ፣ የብሔራዊ የካርቦን መዝገብ ሥርዓት መዘጋጀቱ፣ እንዲሁም የአየር ንብረት መረጃ ማዕከል እና የተቀናጀ የክትትል፣ ሪፖርትና ማረጋገጫ ሥርዓት መዘርጋቱ እንደ ዋና ዋና ስኬቶች ተነስተዋል። በመድረኩ የቀጣይ ዓመት ታላቅ ኃላፊነት የሆነው እና ኢትዮጵያ በ2027 በአዲስ አበባ የምታስተናግደውን የCOP32 ጉባኤ በስኬት ለማካሄድ በብሔራዊ፣ በአህጉራዊ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የተቀናጀ ዝግጅት እያደረገች መሆኗ ተመላክቷል። የልማት አጋሮች፣ ዓለም አቀፍ ተቋማት እና የግሉ ዘርፍ በአየር ንብረት ፋይናንስ፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እና በተቋማዊ አቅም ግንባታ የሚያደርጉትን ድጋፍ እንዲያጠናክሩም ጥሪ ቀርቧል። በውይይቱ ላይ የተሳተፉ የዩናይትድ ኪንግደም፣ የጀርመን፣ የጋና የአፍሪካ ተደራዳሪዎች ቡድን መሪ፣ የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም እና የNDCP ከፍተኛ ተወካዮች፤ ኢትዮጵያ ከፖሊሲ ቀረጻ ባለፈ በታዳሽ ኃይል፣ በምግብ ራስን በመቻል እና በአረንጓዴ ከተማ ልማት እያሳየች ያለውን ተግባራዊ እርምጃ አድንቀዋል። ኢትዮጵያም “ከአንታሊያ ወደ አዲስ አበባ” በምታደርገው ቀጣይ ጉዞ የአየር ንብረት ቃል ኪዳኖችን ወደ ተጨባጭ ውጤት በመቀየር ለአፍሪካ እና ለዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ተቋቋሚነት ግንባታ ያላትን ቁርጠኝነት ማረጋገጧን ከብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል። #Ethiopia #COP31 #ClimateAction #GreenLegacy #COP32
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
ታዳጊ ሀገራትን ከአደጋ ለመታደግ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ አቅርቦት በአስቸኳይ ማሳደግ ይገባል - የተመድ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ
Nov 11, 2026 319
አዲስ አበባ፤ ህዳር 2/2019 (ኢዜአ)፦ ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ፋይናንስ አቅርቦት በማሳደግ ታዳጊ ሀገራትን መደገፍ እንደሚገባ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ገለጹ። ታዳጊ ሀገራት ወደ ንጹህ ኃይል የሚያደርጉትን ሽግግር እንዲያፋጥኑም ጠይቀዋል። 31ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ በቱርኪዬ አንታሊያ እየተካሄደ ይገኛል። “ጉዞ ወደ ዘላቂ፣ አይበገሬነት እና ፍትሃዊነት ወደተረጋገጠበት መጻኢ ዘመን” የጉባኤው መሪ ቃል ነው። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በጉባኤው ላይ ባደረጉት ንግግር የበለጸጉ እና ከፍተኛ በካይ ጋዝ የሚለቁ ሀገራት የበከሉትን ያህል ካሳ በመክፈል ለታዳጊ ሀገራት የሚውል 1.3 ትሪሊዮን ዶላር የአየር ንብረት ፋይናንስ እንዲያቀርቡ ጠይቀዋል። እንዲሁም የዓለም አቀፍ የሙቀት አማቂ ጋዞች ልቀትን በየዓመቱ በስድስት በመቶ መቀነስ እንዳለባቸው ገልጸዋል። የአየር ንብረት ቀውሱ እየቀደመን ነው ያሉት ጉቴሬዝ፤ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሊከሰት የሚችለውን አስከፊ አደጋ ለመግታት የሚያደርገው እንቅስቃሴ በጣም አዝጋሚ መሆኑን አመልክተዋል። አሁን ያሉት ብሔራዊ የአየር ንብረት ቃልኪዳኖች ሙሉ በሙሉ ቢተገበሩ እንኳ በዓመት ከሚያስፈልገው የልቀት ቅነሳ መጠን አንድ ሶስተኛውን ብቻ ነው ማሳካት የሚችሉት ብለዋል። አሁን ያለው አካሄድ ከቀጠለ እስከ ክፍለ ዘመኑ መጨረሻ የዓለም ሙቀት ከ2.5 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚጨምር የጠቆሙት ዋና ፀሐፊው፤ ይህም ሊመለሱ የማይችሉ አስከፊ የተፈጥሮ ቀውሶችን እንደሚያስከትል አስጠንቅቀዋል። ዓለም ወደ ታዳሽ ኃይል የሚደረገውን ሽግግር ማፋጠን እና ተጋላጭ ማህበረሰቦችን ከአየር ንብረት አደጋዎች የመጠበቅ ኃላፊነቱን እንዲወጣም ነው ጥሪ ያቀረቡት ። መንግሥታት ከቃልኪዳን አልፈው በተግባር የተደገፉ እርምጃዎችን እንዲወስዱ አሳስበዋል። ዋና ፀሐፊው የበለጸጉና በካይ ጋዝ የሚለቁ ሀገራት ለአየር ንብረት ቀውሱ ተገቢውን ኃላፊነት እንዲወስዱ እና የታዳጊ ሀገራትን አቅም የሚያጠናክር የፋይናንስ ድጋፍ እንዲጨምሩ ጠይቀዋል። በተጨማሪም መንግሥታት የነዳጅ ኩባንያዎች ከፍተኛ ትርፍ ላይ ታክስ በመጣል በአየር ንብረት ጉዳት ለደረሰባቸው ሀገራት ድጋፍ እንዲያውሉ አሳስበዋል። በካዮች ተገቢውን ካሳ መክፈል አለባቸው ሲሉ ተናግረዋል። ታዳጊ ሀገራት ያለ ተጨማሪ የኢኮኖሚ ጫና ወደ ንጹህ ኃይል መሸጋገር እንዲችሉ፤ ተመጣጣኝ የፋይናንስ አቅርቦትን፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርን፣ ጠንካራ የዝግጁነት እርምጃዎችን እና የተቀናጀ ዓለም አቀፍ ትብብርን ያካተተ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጉቴሬዝ ጥሪ አቅርበዋል።
ኮፕ 31 ቃል ኪዳኖች ወደ ተጨባጭ ውጤት የሚቀየሩበት የተግባር ጉባኤ ሊሆን ይገባል
Nov 9, 2026 714
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 30 /2019 (ኢዜአ)፦ 31ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 31) በንግግርና በቃል ኪዳኖች ላይ ብቻ ሳይወሰን ተጨባጭ ውጤት የሚመጣበት የተግባር ጉባኤ መሆን እንዳለበት የኮፕ 31 ፕሬዝዳንትና የቱርኪዬ የአካባቢ፣ የከተማ ልማትና የአየር ንብረት ለውጥ ሚኒስትር ሙራት ኩሩም ገለጹ። 31ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ጉባኤ (COP31) በቱርኪዬ አንታሊያ አስተናጋጅነት ዛሬ ተጀምሯል። “ጉዞ ወደ ዘላቂ፣ አይበገሬነት እና ፍትሃዊነት ወደተረጋገጠበት መጻኢ ዘመን” የጉባኤው መሪ ቃል ነው። በጉባኤው ላይ ኢትዮጵያ ተሳትፎ እያደረገች ትገኛለች። የኮፕ 31 ፕሬዚዳንት ሙራት ኩሩም፣ ጉባኤው ቀደም ሲል የተገቡ የቃል ኪዳን ስምምነቶችን ወደ ተጨባጭ ውጤት የሚቀይር (Implementation COP) እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል። በአሁኑ ወቅት የጂኦፖለቲካ ውጥረቶች፣ የኢኮኖሚ አለመረጋጋትና እየከፋ የመጣው የአየር ንብረት ጉዳት ተደራራቢ ፈተናዎች እንደሆኑ መግለጻቸውን የቲአርቲ ወርልድ ዘገባ ያመለክታል። የአየር ንብረት ፖሊሲ አሁን ላይ የልማት፣ የምግብ፣ የኢነርጂ፣ የከተማ ልማትና የጤና ፖሊሲ አካል መሆኑን አንስተዋል። በመሆኑም ቱርኪዬ ኮፕ 31 በውይይት፣ በስምምነትና በተጨባጭ እርምጃዎች ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ትሻለች ያሉት ሚኒስትሩ የአንታሊያ ጥሪም ልዩነቶች በተበራከቱበት ወቅት በዚህ ወቅት ውይይትን ማሳደግ፣ የተሸረሸረውን እምነት ዳግም መመለስና የተገቡ ቃል ኪዳኖችን ከሕዝቦች የዕለት ተዕለት ሕይወት በማስተሳሰር መተግበር እንደሚገባ ነው ያሳሰቡት። በተጨማሪም ሚኒስትሩ እስከ እ.አ.አ 2035 ድረስ የኤሌክትሪክ ኃይል ከዓለም አቀፍ የኢነርጂ አጠቃቀም የሚይዘውን ድርሻ ወደ 35 በመቶ ለማሳደግ ያለመ "የ35-በ-35 ዓለም አቀፍ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ቃል ኪዳን" ይፋ አድርገዋል። እንዲሁም ያደጉ ሀገራት በማደግ ላይ ለሚገኙ ሀገራት በየዓመቱ እስከ 300 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ የአየር ንብረት ፋይናንስ ለማቅረብ የገቡትን ቃል ኪዳን እንዲፈጽሙ አሳስበዋል። በጉባኤው የድርድር ሂደቱን በበላይነት እየመሩ ያሉት የአውስትራሊያ የአየር ንብረት ለውጥና ኢነርጂ ሚኒስትር ክሪስ ቦወን ናቸው። ሚኒስትሩ አስቸኳይ እርምጃ ካልተወሰደ የዓለም ሙቀት መጨመር በፓሪስ ስምምነት ከተቀመጠው የ1 ነጥብ 5 ዲግሪ ሴልሺየስ ገደብ ሊያልፍ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። ይሁን እንጂ ሀገራት በአንድነትና በቁርጠኝነት ከተንቀሳቀሱ አሁንም የሙቀት መጠኑን ወደ ነበረበት መመለስ እንደሚቻል ገልጸዋል። ባለፈው ዓመት ለንጹሕ ኢነርጂ የተደረገው ዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንት 2.2 ትሪሊዮን ዶላር በመድረስ ከነዳጅና ከከሰል ዘርፍ በእጥፍ ቢበልጥም፣ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት አሁንም የፋይናንስ ድጋፍ ለማግኘት እየተፈተኑ መሆናቸውን ቦወን ጠቁመዋል። የአየር ንብረት ፋይናንስ ይበልጥ የሚያስፈልጋቸው ሀገራት አሁንም አነስተኛውን ድጋፍ እያገኙ መሆናቸውን በመጥቀስ ፍትሃዊና ፈጣን የፋይናንስ አቅርቦት እንዲኖር ጥሪ አቅርበዋል። በዚህም መሰረት ሚኒስትሮቹ በተግባር ላይ ያተኮሩ የመፍትሔ እርምጃዎችን የሚያፋጥኑ ውሳኔዎች ላይ በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን አስታውቀዋል። ይህም በጉባኤው ወቅት ትኩረት የሚሰጣቸው ተግባራት በፍጥነት ወደ መሬት እንዲወርዱ ለማስቻል የተነደፈ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ኃላፊ ሲሞን ስቲል፤ ኮፕ 31 ግቦችን ከማስቀመጥ ባሻገር የታዳሽ ኢነርጂ አቅርቦትን ለማሳደግ፣ የኤሌክትሪክ አውታሮችን ለማጠናከር እና የሚቴን ጋዝ ልቀትን ለመቀነስ የሚያስችሉ ተግባራዊ እርምጃዎችን መውሰድ አለበት ብለዋል። በሚቴን ጋዝ መቀነስና በኤሌክትሪክ ኃይል አጠቃቀም ላይ የሚወሰዱ እርምጃዎች ከታቀደው የአለም ሙቀት ላይ 0 ነጥብ 5 ዲግሪ ሴልሺየስ ለመቀነስ እንደሚረዱም የቲአርቲ ዘገባ ያመለክታል። 31ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 31) እስከ ህዳር 11 2019 ዓ.ም ይቆያል።
በምርጫ ወቅት የምንገባውን ቃል ተግብረን ማሳየት ይኖርብናል-የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች
Nov 7, 2026 398
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 27/2019 (ኢዜአ):- በምርጫ ወቅት የምንገባውን ቃል ተግብረን ማሳየት ይኖርብናል ሲሉ የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለጹ። 2ኛው የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባዔ "ዕድገትን መምራት ፖለቲካ ፓርቲዎች እንደ የአፍሪካ መጻኢ ኢኮኖሚ መሃንዲሶች" በሚል መሪ ሀሳብ በዓድዋ ድል መታሰቢያ መካሄዱን ቀጥሏል። ኢትዮጵያ በጉባኤው ከመደመር ፍልስፍና የተቀዳውን የፖለቲካ ፓርቲ የለውጥ አስተዳደር ልምዷን አቅርባለች። ከዚህም ባሻገር በአፍሪካ ምርጫ ከማሸነፍ ወደ ኢኮኖሚ ሽግግር በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ የፓናል ውይይት ተደርጓል። የላይቤሪያ አንድነት ፓርቲ ሊቀ መንበር ሉተር ትራፕህ (ዶ/ር) የሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ወረቀት ላይ ያለ ፕሮግራም መልካም መሆኑን ገልጸዋል። ነገር ግን ትግበራ ላይ የተለየ መሆኑን ገልጸው፤ ይሄ አይነት አካሄድ መቆም አለበት ብለዋል። ከዚህ አንፃር የኢትዮጵያ የብልፅግና ፓርቲ የዜጎችን የኢኮኖሚ ፍላጎት ታሳቢ ያደረገ አጀንዳ ቀርፆ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን በግልፅ ማሳየቱን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ምክትል ሥራ አስፈፃሚ ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር)፤ የምርጫ የመጨረሻ ግብ ሥልጣን መያዝ መሆኑን የለበትም ብለዋል። የምርጫው ውጤት የዜጎችን ህይወት በመሰረታዊነት የሚያሻሽል የኢኮኖሚ ሽግግር የሚፈጥር መሆን እንዳለበት ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በመደመር ፍልስፍና እየተመራች ግልጽ ፖሊሲና ፍኖተ ካርታ በማዘጋጀት መሰረታዊ ለውጥ አስመዝግባለች ብለዋል። የጋና ብሔራዊ ዲሞክራሲያዊ ኮንግረንስ ሊቀ መንበር ጆን አሴዱ ንኬቲህ ብልፅግና ፓርቲ የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ የሚመክሩበትን መድረክ በማዘጋጀቱ ምስጋና አቅርበዋል። በአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ ወቅት የምንገባውን ቃል ወደ መሬት ተግብረን ማሳየት ይኖርብናል ብለዋል። የኢኮኖሚ ፕሮግራሞችን በማጥራት፣ ያለንን የተፈጥሮ ሀብት በመለየት የሚተገበር ርዕዮት መቅረፅ እንደሚገባ ገልጸዋል። የኮቲዲቯር አይቮሪያን ፖፑላር ፍሮንት ፖርቲ ፕሬዝዳንት ፓስካል አፊ ጉይሳን፤ በምርጫ ያሸነፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሀገራቸውን ኢኮኖሚ ማሸጋገር አለባቸው ብለዋል። የፖለቲካ ፓርቲዎች ግልፅና የሀገራቱን ነባራዊ ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ የኢኮኖሚ ፕሮግራም ከሌላቸው በምርጫ መሳተፍ እንደማይገባቸው ገልጸዋል። ፓርቲዎች በዜጎች ተጠቃሚነትና ዲሞክራሲ ግንባታ የህዝብን ፍላጎት የሚያንጸባርቅ ርዕዮት ሊኖራቸው ይገባል ብለዋል። የቡሩንዲ የዲፌንስ ኦፍ ዲሞክራሲ ብሔራዊ ምክር ቤት ዋና ጸሀፊ ሪቨሪያን ንዲኩሪዮ አፍሪካውያን በትብብር የኢኮኖሚ ፖሊሲ መገንባት እንዳለባቸው ገልጸዋል። ተዓማኒነት ያለው፣ የሚለካና ሊተገበር የሚችል የፖለቲካ ርዕዮት ዓለም እንዲቀርጹም አሳስበዋል። አፍሪካ የምኞት ሀይቅ ሆና መቀጠል የለባትም ያሉት ዋና ጸሀፊው፤ ዕቅዶች ከምኞት አልፈው ገቢራዊ መደረግ እንዳለባቸው ገልጸዋል።
በአፍሪካ ስልጣንን ኢ-ህገ መንግስታዊ በሆነ መንገድ ለመቆጣጠር መሞከር ለአለመረጋጋትና ግጭት የሚጋብዝ ነው
Nov 6, 2026 924
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 27/2019 (ኢዜአ)፦ በአፍሪካ ስልጣንን ኢ-ህገ መንግስታዊ በሆነ መንገድ ለመቆጣጠር መሞከር ለአለመረጋጋትና ግጭት የሚጋብዝ መሆኑን የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሀሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። 2ኛው የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባዔ "ዕድገትን መምራት ፖለቲካ ፓርቲዎች እንደ የአፍሪካ መጻኢ ኢኮኖሚ መሃንዲሶች" በሚል መሪ ሀሳብ በዓድዋ ድል መታሰቢያ መካሄድ ጀምሯል። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሀሙድ አሊ ዩሱፍ እንደገለጹት፤ በአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች በህዝብና በተቋማት መካከል ድልድይ በመሆን ማገልገል አለባቸው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለአፍሪካ ለውጥ ለፈጠሩት የፖለቲካ ራዕይ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል። የአፍሪካ ሕብረት አጀንዳ 2063 የዲሞክራሲ አስተዳደር ስርዓት በአሕጉሪቱ የተቀናጀ የፖለቲካ ስርዓት መፍጠር እንዳለባቸው መደንገጉን ገልጸዋል። በአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች በፖሊሲ የተደገፈ የሕዝብ አገልግሎት መስጠት አለባቸው ያሉት የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ከዚህም ባለፈ በህዝብና ተቋማት መካከል ድልድይ መሆን እንዳለባቸው ገልጸዋል። መሪ ፓርቲዎች ህገ መንግስታዊ አስተዳደር የመነጨ ተዓማኒ ምርጫ ማዘጋጀት አለባቸው ብለዋል። በፓርቲዎች መካከል ውይይትና ንግግር ወሳኝ መሆኑን ገልጸው፤ በአፍሪካ ስልጣንን ኢ- ሕገ መንግስታዊ በሆነ መንገድ ለመቆጣጠር መሞከር ተገቢ አይደለም ብለዋል። ይህም ለግጭትና አለመረጋጋት የሚጋብዝ መሆኑን ጠቅሰው፣ የአፍሪካ ሕብረት ኢ -ሕገ መንግስታዊ አካሄዶችን በፅኑ እንደሚያወግዝ ገልጸዋል።
ሐተታዎች
ምድረ ቀደምቷ ኢትዮጵያ፤ ከታሪካዊ የአየር ንብረት የፍትሕ ጥያቄ እስከ ኮፕ-32 ጉባኤ ዝግጅት
Nov 18, 2026 114
ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ!! የዘመናችን ፈታኝና ዐበይት ክስተት እየሆነ የመጣ የአየር ንብረት ለውጥ ሳይንሳዊ መሰረቱም ከሁለት መቶ ዓመታት በላይ የተሻገረ ታሪክ አለው። ለዚህም በ19ኛው ክፍለ ዘመን የሙቀት መጠበቂያ ጋዞች (Greenhouse Gases) በምድር ሙቀት ሚዛን ላይ የሚያሳድሩትን ተፅዕኖ የሚመለከቱ ሳይንሳዊ ጥናቶች ተጀምረዋል። በተለይም የኢንዱስትሪ አብዮት በአውሮፓ ከተስፋፋ በኋላ የድንጋይ ከሰል፣ የነዳጅና የጋዝ አጠቃቀም መጨመር፣ የደን ጭፍጨፋና ከኢንዱስትሪ የሚወጡ የካርበን ልቀት የዓለምን የአየር ንብረት ስርዓት ቀስ በቀስ እየበከሉት መጥተዋል። የዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ቀውስ በኢንዱስትሪ ከበለፀጉ ሀገራት የሚመነጭ ቢሆንም የችግሩ ገፈት ቀማሾች ዝቅተኛ የኢኮኖሚና አደጋውን የመላመድ አቅማቸው አነስተኛ የሆኑ ታዳጊ ሀገራት መሆናቸው ጉዳቱን የከፋ ያደርገዋል። የሰዎችን ስደት በማባባስ የምግብ ዋስትናን፣ የጤና ሥርዓት፣ የውሃ አቅርቦትና መሰል ከፍተኛ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ጉዳት እያስከተለ ይገኛል። በተለይም የአፍሪካ ቀንድ አርሶና አርብቶ አደር፣ የባሕር ዳርቻና የደሴት ሀገራት፣ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የከተማ ነዋሪዎች፣ ሴቶች፣ ሕጻናት፣ አዛውንቶችና አካል ጉዳተኞችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዋስትና ቅርቃር ውስጥ በመክተት ቀላል የማይባል ተፅዕኖ ያስከትላል። በቅርቡ በኔፓል የተከሰተው የጎርፍ መጥለቅለቅ፣ የምስራቅ አፍሪካ የኤልኒኖ ድርቅ፣ በላቲንና ሰሜን አሜሪካ፣ በእስያና ሌሎች ሀገራት የሚከሰቱ አውሎ ነፋሶችና የእሳት አደጋዎች የአየር ንብረት ለውጥ ላይ አፋጣኝ መፍትሔ መውሰድ እንደሚያስፈልግ አመላካች ናቸው። ለዚህም በካርበነ ልቀት ቅነሳ መርህ የታዳሽ ኃይል ማስፋፋት፣ የንጹህ ትራንስፖርት ማበረታታት፣ የደን ጥበቃና የካርቦን ልቀት በመቀነስ የለውጥ መላመድ ምኅዳርን የሚያጎለብቱ የድርቅ መቋቋም ግብርና፣ የውሃ አስተዳደር፣ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓትና አደጋ መቋቋም የሚችል የመፍትሔ አቅጣጫ ስልቶችን መገንባት ያስፈልጋል። የኪሳራና ጉዳት ካሳ (Loss and Damage)፣ የአየር ንብረት ፋይናንስ፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርና የአቅም ግንባታ ስልቶችም የአየር ንብረት ለውጥ መፍትሔ መሰረታውያን ናቸው። የአየር ንብረት ዲፕሎማሲም በአንድ ጊዜ የተፈጠረ ሳይሆን በሳይንሳዊ ምርምር፣ በዓለም አቀፍ ውይይትና በሕጋዊ ስምምነቶች የተገነባ ረጅም ሂደት ነው። እ.አ.አ ከ1979–2026 በተለያዩ ሀገራት ከተሞች የተካሄዱት ዓለምአቀፍ የአየር ንብረት ዲፕሎማሲ መድረኮችም የሂደቱን ታሪካዊ የጉዞ ምዕራፎች ያመላክታሉ። በዚህም እ.ኤ.አ. 1979 በጄኔቫ ስዊዘርላንድ የመጀመሪያው የዓለም የአየር ንብረት ጉባኤ ሳይንሳዊ ግንዛቤን ለማሳደግ ሁነኛ መሰረት ጥሎ ያለፈ መድረክ ነበር። እ.ኤ.አ. በ1988 በጄኔቫ የዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ተጠሪ ቡድን (IPCC) በመመስረቱም ዓለምአቀፍ ሳይንሳዊ ግምገማ ለማካሄድ ተቋማዊ መሰረትን ፈጥሯል። በብራዚሏ ሪዮ ዴ ጄኔሮ እ.ኤ.አ. 1992 የጸደቀው የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ማዕቀፍ ስምምነትም (UNFCCC) ለዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ቀውስ መፍትሔ የሚያመላክት የሕግ መሰረት ጥሏል። በጀርመን መዲና በርሊንም እ.ኤ.አ. 1995 የመጀመሪያው የስምምነት ወገኖች ጉባኤ (COP1) ተካሂዷል። በጃፓን ኪዮቶ እ.ኤ.አ. 1997 የተካሄደው 3ኛው የስምምነት ወገኖች ጉባኤ (COP3) የኪዮቶ ፕሮቶኮልን በማፅደቅ የካርበን ልቀት ቅነሳ ግዴታዎችን ወደ ዓለምአቀፍ ስምምነት አምጥቷል። በሞሮኮ ማራካሽ እ.ኤ.አ. 2001 የተካሄደው 7ኛው የስምምነት ወገኖች ጉባኤ (COP7) የኪዮቶ ፕሮቶኮል ተግባራዊ እንዲሆን የሚያስችሉ ደንቦችን አስጸድቋል። በዴንማርክ ኮፐንሃገን እ.ኤ.አ. 2009 የተካሄደው 15ኛው የስምምነት ወገኖች ጉባኤ (COP15) አዲስ ዓለምአቀፍ የአየር ንብረት ስምምነት ለመፍጠር ታላቅ ጥረት የተደረገበት ታሪካዊ መድረክ ነበር። በፈረንሳይ መዲና ፓሪስ እ.ኤ.አ. 2015 የተካሄደው 21ኛው የስምምነት ወገኖች ጉባኤም (COP21) የፓሪስ ስምምነትን በማፅደቅ ለዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ትብብር አዲስ ምዕራፍ ከፍቷል። በዩናይትድ ኪንግደም ግላስጎው እ.ኤ.አ. 2021 የተካሄደው 26ኛው የስምምነት ወገኖች ጉባኤ (COP26) የግላስጎው የአየር ንብረት ስምምነትን በማፅደቅ የዓለም አቀፍ የልቀት ቅነሳ ጥረቶች እንዲጠናከሩ አድርጓል። በግብፅ ሻርም ኤል ሼክ እ.ኤ.አ. 2022 የተካሄደው 27ኛው የስምምነት ወገኖች ጉባኤ (COP27) በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ ለሚደርሱ ኪሳራና ጉዳቶች የሚውል ፈንድ ለመመስረት ታሪካዊ ስምምነት ላይ መደረሱ ይታወሳል። የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች በዱባይ እ.ኤ.አ. 2023 ያስተናገደችው 28ኛው የስምምነት ወገኖች ጉባኤ (COP28) የፓሪስ ስምምነትን የመጀመሪያ ዓለምአቀፍ የአፈጻጸም ግምገማ (Global Stocktake) አከናውኗል። እ.ኤ.አ. 2024 በአዘርባጃን ባኩ የተካሄደው 29ኛው የስምምነት ወገኖች ጉባኤ (COP29) በአዲስ ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ፋይናንስ ግብ ላይ ታሪካዊ ውሳኔን አሳልፏል። እ.ኤ.አ. 2025 በቤለም ብራዚል የተካሄደው 30ኛው የስምምነት ወገኖች ጉባኤም (COP30) የአማዞን ደን ጥበቃንና የአየር ንብረት ቃል ኪዳኖችን ወደ ተግባር የማሸጋገር አጀንዳን በማስቀደም ታሪካዊ ምዕራፍ አስመዝግቧል። የዘንድሮው 31ኛው የስምምነት ወገኖች ጉባኤም (COP31) የቱርክዬን አስተናጋጅነት ከአውስትራሊያ የድርድር አመራር ጋር በማጣመር በአንታሊያ ተካሂዷል። ኢትዮጵያም ታሪካዊውን ዓለምአቀፍ የአየር ንብረት ዲፕሎማሲ መድረክ በ2027 በአዲስ አበባ 32ኛው የስምምነት ወገኖች ጉባኤ (COP32) ለማስተናገድ ቅብብሎሹን በአንታሊያ ተረክባለች። መድረኩን በብቃት ለማስተናገድ ቀደም ብላ መዘጋጀት ጀምራለች። 32ኛውን የኮፕ ጉባኤ እንደ ሀገር ያስመዘገበቻቸውን እመርታዊ የአየር ንብረት ለውጥ ቅነሳ ተነሳሽነቶች ለዓለም የምታሳይበት ሁነኛ ጉባኤ ይሆናል። በዚህም የኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ (Cradle of Humanity)፣ የቡና መገኛ (Origin of Coffee)፣ አረንጓዴ ዐሻራ (Green Legacy)፣ ጥንታዊ ስልጣኔ (Ancient Civilization)፣ አዲስ አበባና ከተሜነት፣ የዲፕሎማሲ ማዕከል (Diplomatic Hub)፣ የአሸናፊዎች ምድር (Land of Champions) እንዲሁም የታዳሽ ኃይል (Clean Energy) ልማት ስምንት ብሔራዊ የገጽታ ግንባታ ጭብጦች ጎልተው ይገለጣሉ። በሰው ልጅ የመጀመሪያው ፍጥረት የዘር ሀረግ አመጣጥም በኢትዮጵያ መሆኑን ሚሊዮን ዓመታት ዕድሜን በማስቆጠር በአፋር ክልል የተገኙት የሉሲ እና ሰላም ቅሪተ አካልም ሕያው የታሪክ ምስክሮች ናቸው። የቡናን ታሪክ ከጥንታዊ ደኖቿ በማፍለቅ ከሺህ ዘመናት በፊት ጀምሮ ማጣጣም የጀመረችው ኢትዮጵያ ዛሬም ድረስ ለወደፊት የሚሻገር የዓለም የቡና ባህል ሥርዓትና የጣዕም ሃብት ምንጭ ናት። በጥንታዊ ሥልጣኔና ቅርስ በኩልም ከአክሱም ሐውልቶች እስከ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፣ ከኃይማኖታዊ ቅርሶች እስከ ባሕላዊ እሴቶች ድረስ የሺህ ዘመናት ሥልጣኔ ኢትዮጵያን ተምሳሌት አድርገዋታል። በአዲስ አበባ የተከናወነው እና እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ የከተማ ልማትም የአሁኑ ትውልድ የራሱን የሥልጣኔ ታሪክ ዐሻራ በማሳረፍ ውብ፣ ጽዱና ኢትዮጵያን የሚመጥን የከተሜነት ምኅዳር እየገነባ ነው። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሃሳብ አመንጪነት በግንቦት 18 ቀን 2011 ዓ.ም የተጀመረው የአረንጓዴ ዐሻራ ብሔራዊ መርሃ ግብር የአረንጓዴ ኢኮኖሚን መገንባት የሚያስችል መሰረት እየጣለ ነው። በውሃ፣ በነፋስ፣ በጸሐይ፣ በጂኦተርማልና ሌሎች አማራጮች ከሀገር ውስጥ የተሻገረ የኤሌክትሪክ ሀይል ለምስራቅ አፍሪካ በማቅረብ አፍሪካዊት የታዳሽ ኃይል ማዕከል የሚያሰኟትን አመርቂ ውጤቶች አስመዝግባለች። በፓን-አፍሪካ እሳቤም ኢትዮጵያ የጥቁር ሕዝቦች የነጻነት ቀንዲል፣ የአንድነት ተምሳሌትና የኩራት ምንጭነቷን ምስጋና ለቅድመ አያቶችና በዓድዋ ሰንሰለታማ ተራሮች በተግባር አስመስክራለች። ጀግኖች አትሌቶች በዓለም አቀፍ የውድድር መድረክ ደግመው ደጋግመው የተጎናጸፉት ደማቅ የአሸናፊነት ድል ስምና ዝናዋን በዓለም አደባባይ ከፍ አድርጓል። በአጠቃላይ በእነዚህ የታሪክ፣ የሥልጣኔና የአረንጓዴ ልማት ትሩፋቶች ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ እና ታላቅ ርዕይ የሰነቀችው ኢትዮጵያ በአዲስ አበባው የኮፕ-32 ጉባኤ በታሪካዊ ገድልነት በጉልህ የምታሳያቸው የብሔራዊ ኩራት ማኅደሮች ናቸው። በዚህም በአፍሪካ ተምሳሌትነቷን ለዓለም በማረጋገጥ ለሀገራዊ ገጽታ ግንባታ፣ ለአየር ንብረት ዲፕሎማሲ የበላይነት እንዲሁም ለዓለም ሀገራት በተሞክሮነትና በመልካም ልምድነት በኩራት በማቅረብ የዲፕሎማሲ ከፍታዋን ይበልጥ ታጸናለች።
የመደመር እሳቤ፡ የትላልቅ ውጥኖች ስኬት ምስጢር
Nov 17, 2026 89
የመደመር መንግሥት እና እሳቤ የተበታተነ አቅምን በማሰባሰብ፣ ሀገር በቀል እውቀቶችን መሠረት በማድረግ እና የሕዝብ ተሳትፎን በማስተባበር ግዙፍና ስትራቴጂካዊ ሀገራዊ ውጥኖችን ማሳካት እንደሚቻል በተግባር ያሳየ ፍልስፍና ነው። ይህ እሳቤ ወረቀት ላይ ብቻ የቀረ ሳይሆን፣ ውስን ሀገራዊ ሃብትን በአንድ ላይ በማቀናጀት አዳዲስ የሥራ ባህሎችንና ተጨባጭ ውጤቶችን ማምጣት የቻለ እሳቤ መሆኑን በተለያዩ ዘርፎች የተመዘገቡ ስኬቶች ያረጋግጣሉ። የመደመር እሳቤ ዋና ግብ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ ሲሆን፣ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑት ተግባራት የሀገሪቱን የልማት ምዕራፍ ወደ ላቀ ደረጃ አሸጋግረዋል። በኢኮኖሚ እና በመሠረተ-ልማት ዘርፎች የታዩት ተጨባጭ ማሳያዎች የመደመር እሳቤ ያለውን ትልቅ የማስፈጸም አቅም በግልጽ ያሳያሉ። በሀገሪቱ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከውጭ የሚገባውን ስንዴ ሙሉ በሙሉ በማስቀረት ኢትዮጵያን የአፍሪካ ትልቁ የስንዴ አምራች ያደረገው የስንዴ ልማት እመርታ እና በሕዝብና መንግሥት ትብብር ግንባታው የተከናወነው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የዚሁ እሳቤ ፍሬዎች ናቸው። በተጨማሪም ከ56 ቢሊዮን በላይ ችግኞች የተተከሉበት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር፣ የከተሞችን ገጽታ የቀየረው የኮሪደር ልማት እንዲሁም በአጭር ጊዜ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ መዳረሻዎችን የገነቡት የ“ገበታ ለሸገር”፣ “ገበታ ለሀገር” እና “ገበታ ለትውልድ” ፕሮጀክቶች የመደመር ስልታዊ አካሄድ ግዙፍ ውጥኖችን በአጭር ጊዜ ማጠናቀቅ እንደሚችል ማረጋገጫዎች ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አዲሱ የመደመር መንግሥት ምስረታ ወቅት ባደረጉት ንግግር፣ ይህንን እሳቤ ይበልጥ የሚያጠናክሩ ቁልፍ ሐሳቦችን አንስተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምንጩን የሚረሳ ወንዝ እንደሚደርቅ ሁሉ፣ መሠረቱንና ሀገራዊ እሳቤውን በመጣል የሚጀመር የሥልጣኔ ጉዞ ሩቅ ሊጓዝ እንደማይችል ገልጸው፤ ባለፉት ዓመታት የኢትዮጵያዊነት መሠረት የሆነውን የመደመር እሳቤን በተሟላ ሁኔታ ወደ ሥራ ማስገባት መቻሉን አብራርተዋል። አዲሱ የመደመር መንግሥት የሀገር ውስጥ እሴቶችን ከውጭው ጠቃሚና ተራማጅ ዕውቀት ጋር በማዋሃድ አዲስ የኢትዮጵያ ሥልጣኔ ለመገንባት እንደሚሠራ አስምረውበታል። በተጨማሪም በትናንቱ ንግግራቸው የመደመር ፖለቲካዊ ባህሪ ልዩነቶችን አቀናጅቶ የጋራ ውጤት መፍጠር መሆኑን በመጥቀስ፣ በምርጫ ውድድር ውስጥ የፓርቲዎች ማሸነፍና መሸነፍ ቢኖርም እንኳ ውጤቱ ሲደመር ኢትዮጵያ አሸናፊ እንጂ ተሸናፊ ልጆች የሌሏት ሀገር መሆኗን ማሳየት ነው ብለዋል። ባለፉት ዓመታት ከተናጠል ዘርፍ ወደ ብዙሃ ዘርፍ በመሸጋገር በዲጂታል ቴክኖሎጂ፣ በግብርና፣ በኮሪደርና ቱሪዝም ልማት የተመዘገቡት አስደናቂ ውጤቶች ሁሉ የተናጠል አቅሞችን በማቀናጀት (Synergy) የመጡ መሆናቸውን አስገንዝበዋል። በአጠቃላይ የመደመር መንግሥት ዛሬ ላይ ቆሞ የተሻለ ነገን እያየ፣ አዳዲስ ዕድሎችን ወደ ውጤት በመቀየር እና የጀመራቸውን ግዙፍ ስራዎች በተከታታይነት በማስቀጠል ታላቅ ሀገር የመገንባት ርዕዩን አፅንቶ የሚቀጥል ነው።
ወንጪ - ደንዲ ኢኮ ቱሪዝም፦ የነዋሪዎችን ሕይወት በተጨባጭ የቀየረው የልማት ትሩፋት
Nov 16, 2026 286
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሃሳብ አመንጪነት በገበታ ለሀገር ፕሮጀክት የተገነባው የወንጪ የቱሪዝም ልማት፣ የአካባቢውን መሠረተ ልማቶች በማሟላት የነዋሪዎችን የኑሮ ደረጃ ከመሠረቱ ከመቀየር ባለፈ ከፍተኛ የቱሪስት ፍሰት እንዲመዘገብ እያደረገ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡ በተፈጥሮ ጸጋ የታደለችው ነገር ግን በመሠረተ ልማት እጦት ተጋርዳ ለዘመናት በዝምታ ውስጥ የቆየችው ውቧ ወንጪ፣ ዛሬ ገጽታዋ ተቀይሮ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ጎብኚዎችን ቀልብ የምትገዛ ደማቅ የቱሪዝም ማዕከል ሆናለች። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ራዕይና ሃሳብ አመንጪነት እውን የሆነው የገበታ ለሀገር የልማት ፕሮጀክት፣ ለወንጪ ተፈጥሯዊ ውበት ዘመናዊ ድምቀትን ከማላበስ ባለፈ የነዋሪዎቿን የዘመናት እንግልት የቀረፈ የታሪክ ምዕራፍ ሆኗል። ቀደም ሲል የመንገድ፣ የመብራትና የንጹሕ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ባለመሟላቱ የአካባቢው ማህበረሰብ ለእንግልት ተዳርጎ እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ አስታውሰዋል። ዛሬ ግን ያ ጨለማ ተገፎ በብርሃንና በልማት መተካቱንም ነው የገለጹት፡፡ የፕሮጀክቱ ተጠቃሚና የአካባቢው ነዋሪ አቶ ተስፋዬ ወልደጊዮርጊስ፣ ህይወታቸው በባህላዊ እርሻና በከባድ ጉልበት ሥራ ብቻ ተወስኖ ለዓመታት በድካም ማለፉን ያስታውሳሉ። አሁን ግን በፕሮጀክቱ ትሩፋት አማካኝነት ዘመናዊ መኖሪያ ቤትና የተሻሻሉ የግብርና ግብአቶች ተሟልተውላቸው የኑሮ ዘይቤያቸው ከመሠረቱ መለወጡን ይጠቅሳሉ። በፕሮጀክቱ አማካኝነት መንግሥት ዘመናዊ ቤት በመሥራት ብሎም ላም በመግዛት ህይወታቸውን ዳግም እንዳቋቋመላቸው በጥልቅ የደስታ ስሜትና ምስጋና ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም ወደ አምቦና ወሊሶ በእግርና በፈረስ ለመጓዝ ቀናት የሚፈጅ አድካሚ ጉዞ ያደርጉ እንደነበር ጠቅሰው፣ ዛሬ በተዘረጋው የአስፋልት መንገድ በቀላሉ ወደሚፈልጉት አካባቢ በምቾት መጓዝ መቻላቸውን ተናግረዋል። ሌላው የአካባቢው ነዋሪ አቶ ሸለመ አብዲሳ በበኩላቸው፤ የልማት ፕሮጀክቱ ለወንጪ ህዝብ እንደ ሁለተኛ ዕድሜ እንደሆነ ይገልጻሉ። ከዚህ ቀደም በማገዶ እንጨት ጭስ እየታፈኑ ምግብ ያበስሉ እንደነበር አስታውሰው አሁን ላይ በፕሮጀክቱ አማካኝነት ከአስቸጋሪ የኑሮ ዘይቤ ተላቀው፣ በኤሌክትሪክ ኃይልና በምቹ መኖሪያ ቤት ስልጡን ኑሮ እየመሩ መሆናቸውን አብራርተዋል። በተጨማሪም የመሠረተ ልማቱ መሟላት አካባቢውን በተለይ በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት በህዝብና በተሽከርካሪ የተሞላ የንግድና የቱሪዝም ማዕከል እንዳደረገው በደስታ ተናግረዋል። ወንጪ ዓመቱን ሙሉ ለምለም የሆነ፣ ፍል ውሃዎችና የበርካታ ተፈጥሮ ሀብት ባለቤት ብትሆንም፣ ቀደም ሲል በመሠረተ ልማት እጦት ሳትታወቅ መቆየቷን የአካባቢው ተወላጅና የሥራ ዕድል የተፈጠረለት ወጣት ጸጋዬ ተረፋ ያስታውሳል። አሁን ላይ ግን የመንገድ፣ የመብራትና የውሃ አገልግሎቶች በመሟላታቸው የጀልባ ሽርሽር፣ የፈረስ ግልቢያና ሌሎች የቱሪዝም አገልግሎቶች ተስፋፍተው ለአካባቢው ወጣቶችና ነዋሪዎች ሰፊ የሥራ ዕድልና የገቢ ምንጭ መፍጠራቸውን ገልጿል። ወንጪ ዛሬ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ቱሪስቶችን ቀልብ እየሳበች መምጣቷን ጠቁሞ፣ የቱሪስት ፍሰቱ ከዓመት ዓመት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑንም ተናግሯል።
በሕብረ ቀለማት ያሸበረቀው ፍል ውሃ- አለሎበድ
Nov 12, 2026 451
በሰለሞን ብርሀኑ (ሰመራ - ኢዜአ) እየተዝናኑ ይታከሙበታል፤ እየታከሙም ይዝናኑበታል - የተፈጥሮ ችሮታ በተለገሰው የአለሎበድ ፍል ውሃ። ፍል ውሃው የአፋር ክልል መናገሻ ከሆነችው ሰመራ ከተማ በ20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ነው የሚገኘው። በአውሳ ረሱ ዞን ዱብቲ ወረዳ ደበሊና ሃሊባይሪ ቀበሌ ተንጣሎ የሚታየው ፍል ውሃ በሕብረ ቀለማት ያሸበረቀና የተዋበ የቱሪስት መዳረሻም ነው። ከመሬት ውስጥ እየተፍለቀለ የሚወጣው ውሃ ሥፍራውን ከሚያውደው እንፋሎቱ ጋር ተዳምሮ አካባቢውን ልዮ ውበት አጎናጽፎታል። በአካባቢው አጠራር አለሎበድ የሚባለው ይሄ የፍል ውሃ ሥፍራ በቀለማት ያሸበረቀ ከመሆኑ የተነሳ የቱሪስትን ቀልብ ይይዛል። በዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚነገረው ከሆነ የውሃው ትኩሳት እስከ 97 ዲግሪ ሴልሽየስ እንደሚደርስ ይነገርለታል። የፍል ውሃ ምድሩ በጀብደኛ ቱሪስቶች እጅግ ተመራጭና የሚወደድ መሆኑን ያዩት ሁሉ ይመሰክራሉ። አለሎበድን ከሌሎች የተፈጥሮ ውሃ ምንጮች የሚለየው ከምድር ውስጥ በሚመነጨው ሙቀት የሚሞቀው ውሃ በተለያዩ ጉድጓዶች ተከማችቶ መገኘቱ ነው። የአለሎበድ ፍል ውሃ ሙቀት በአማካይ እስከ 97 ዲግሪ ሴልሽየስ የሚደርስ ሲሆን የውሃ ጥርቅሞቹ በአረንጓዴ፣ ሰማያዊ፣ ቢጫና ቡናማ ቀለማት አሸብርቀውና ተሰናስለው ሲታዩ ሌላኛው ድምቀቱ ይሆናሉ። አለሎበድን ከሚያስደንቁ የተፈጥሮ ክስተቶች መካከል ሌላኛው ደግሞ ከምድር ውስጥ የሚያወጣው እንፋሎት ነው። ከመሬት ሥር የሚወጣው ውሃ ሙቀት ከፍተኛ በመሆኑ በውሃው ላይ የሚፈጠረው እንፋሎት ወደ አየር ይወጣል። በተለይም አላሎበዳ ስፖውተር (Allalobeda Spouter) የተሰኘው ፍል ውሃ ከስድስት እስከ 30 ሜትር የሚደርስ ከፍታ ላይ ሲወነጨፍ ይታያል።ክስተቱ በምድር ውስጥ ያለው ሙቀት ውሃን በማሞቅ ግፊት እንዲፈጠር እና ውሃው በጠባብ መውጫ በኩል ወደ ላይ እንዲወጣ ከሚያደርገው የተፈጥሮ ሂደት ጋር እንደሚያያዝ የከርሰ ምድር ባለሞያዎች ያስረዳሉ። አለሎበድ የሚገኝበት አካባቢ የቀይ ባሕርና የኤዴን ባሕረ ሰላጤ የስብራት መስመሮች ከታላቁ የስምጥ ሸለቆ ጋር በሚገናኙበት ልዩ የምድር አቀማመጥ ውስጥ የሚገኝ መሆኑም ይነገራል። በዚህ የምድር አቀማመጥ ምክንያት የምድር ንጣፍ በተለያዩ ስብራቶች የተከፋፈለ ሲሆን ከምድር ጥልቅ ክፍል የሚመነጨው ሙቀት ወደ ላይኛው ክፍል እንዲደርስ ምቹ ሁኔታ ፈጥሮለታል። በአለሎበድ የተካሄዱ የጂኦፊዚክስና የጂኦኬሚስትሪ ጥናቶችም ከምድር ውስጥ የሚመነጭ እንፋሎትን የያዘ የጂኦተርማል ሥርዓት መኖሩን ያመለክታሉ። ይህም አካባቢው ከቱሪዝም ባሻገር ለጂኦተርማል ኃይል ምርምርና ልማት ያለውን አቅም ያሳያል። የአለሎበድ ፍል ውሃ በአካባቢው ነዋሪዎች ዘንድ ለምግብ ማብሰያነትና ለመታጠቢያነት ጭምር የሚገለገሉበት ሲሆን በርካታ የውጭና የሀገር ውስጥ ቱሪስቶችም ወደአካባቢው እየመጡ ይጎበኙታል። ከዳሎል ባለቀለም የተፈጥሮ ገጽታ፣ ከኤርታሌ እሳተ ገሞራና ከአፋምቦ ሐይቅ በተጨማሪ አለሎበድ የአፋር ክልሉ የቱሪዝም መስህብ ሆኖ የሚያገለግል ትልቅ ሃብት ነው። የቱሪዝም ሀብቱን በሚገባ ለመጠቀም ግን የመንገድ መሠረተ ልማትን ማሻሻል ያስፈልጋል። ዘመናዊ የጎብኚዎች ማረፊያና የመረጃ ማዕከላትን ማዘጋጀትም እንዲሁ ወሳኝ መሆኑ ይታመናል። ሲያዩት የተመልካችን ቀልብ በመሳብ አንዳች የሀሴት ስሜት የሚፈጥረው ይህ ስፍራ ከልማት ርቆ ቆይቷል። የክልሉ ጸጋ የሆነውን ይህን የተፈጥሮ ሀብት አልምቶ መጠቀም ከተቻለ አንድ የቱሪስት መዳረሻ ሆኖ የማገልገል አቅም ከፍተኛ ነው። ውበቱ ሊገልጥና ፈዋሹነቱንም በይፋ ሊያውጅ እየተንደረደረ ያለውን አለሎበድ በማልማት ጠቀሜታውን ለማጉላት ትኩረት መሰጠቱ ተገልጿል። የገበታ ለሀገር ኘሮጀክት አካል የሆነውና በአፋር ክልል አዋሽ ብሔራዊ ፓርክ አቅራቢያ የሚገኘው "ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ሲመረቅ ይሄም ስፍራ በቀጣይ እንደሚለማ ተመላክቷል። የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በክልሉ የቱሪስት መዳረሻዎችን ለይቶ ከማልማት አኳያ አለሎበድ ፍል ውሃን ለቀጣይ በዕቅድ መያዙን በዚህ ወቅት ይፋ አደርገዋል። እናም በቀጣይ አለሎበድ ፍል ውሃ ሲገነባ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት በገበታ ለሀገር ፕሮጀክት ከተገነባው የኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ እና ሌሎችም የቱሪስት መስህቦች ጋር ተዳምረው የአፋርን የቱሪስት መዳረሻነት ከፍ ያደርጋሉ። ይህም የአካባቢው ነዋሪዎች በዘርፉ ተጠቃሚ ከማደረግ ባለፈ የክልሉን ገቢ በማሳደግ በኩልም ሚናው የላቀ እንደሚሆን ሳይታለም የተፈታ ነው።
ትንታኔዎች
የሰሊጥ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ እና የጤና ጸጋዎች
Nov 18, 2026 114
የሰሊጥ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ እና የጤና ጸጋዎች ሰሊጥ በዓለም ላይ ካሉ የቅባት እህሎች አንዱ ሲሆን፣ ኢትዮጵያም የሰብሉ መገኛና በዓለም አቀፍ ደረጃ ዋነኛ አምራችና ላኪ ሀገር ነች። በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ "ነጭ ወርቅ" በመባል የሚታወቀው ሰሊጥ፣ ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት ከመሆኑም ባለፈ ለሰው ልጅ ጤናና ስነ-ምግብ ያለው ጠቀሜታ እጅግ የላቀ መሆኑን የጤና ባለሙያዎች ይናገራሉ። የሰሊጥ ሰበል ሞቃታማና ከፊል-ደረቅ የአየር ንብረት የሚፈልግ ሰብል ሲሆን ከ25° ዲግሪ ሴልሺየስ እስከ 35°ዲግሪ ሴልሺየስ ባለው የሙቀት መጠን ውስጥ በተሻለ ሁኔታ ያድጋል። ለሰሊጥ ከዓመታዊ የዝናብ መጠን አንጻር ከ450 እስከ 650 ሚሊ ሜትር ዝናብ ይፈልጋል። ይሁን እንጂ ሰብሉ ድርቅን የመቋቋም አቅም ያለው በመሆኑ አነስተኛ ዝናብ ባለባቸው አካባቢዎችም ይለማል። ሰሊጥ በባህሪው ሞቃታማና ከፊል ቆላማ አካባቢዎችን የሚወድ ሲሆን፣ ከባህር ጠለል በላይ ከ500 እስከ 1,250 ሜትር ከፍታ ባላቸው አካባቢዎች በስፋት ይበቅላል። የግብርና ባለሙያዎች እንደሚገልጹት ውኃ አዘል፣ ለስላሳ እንዲሁም የሸክላና የአሸዋ ቅልቅል ያለው አፈር ለሰሊጥ ልማት እጅግ ተስማሚ ነው። ኢትዮጵያ ደግሞ ለሰሊጥ ልማት እጅግ ተስማሚ የሆነ የአየር ንብረትና ሰፊ ለም መሬት አላት። በኢትዮጵያ ሰሊጥ በዋናነት ከሚመረትባቸው አካባቢዎች መካከል ሁመራ፣ መተማ፣ ቋራ፣ አርማጭሆ እና ጎንደር ዙሪያ እንዲሁም ምዕራብ ኦሮሚያ ፣ ጋምቤላና ፓዌ የሚጠቀሱ ናቸው። በኢትዮጵያ በየዓመቱ በሰሊጥ ልማት የሚሸፈነው መሬት እንደየአየር ሁኔታውና ወቅታዊ ሁኔታዎች ቢለዋወጥም በአማካይ ከ500,000 እስከ 600,000 ሄክታር ይደርሳል። የኢትዮጵያ ሰሊጥ ልማት በአብዛኛው በዝናብ ላይ የተመሰረተ ሲሆን በአነስተኛ የአርሶ አደር መሬትና በሰፋፊ የግል እርሻዎች ላይ ይከናወናል። ይሁን እንጂ ሰሊጥ ሲደርስ የመበተን ባህሪ ስላለው ምርቱን በወቅቱ በሰው ኃይል መሰብሰብ ከፍተኛ ጥንቃቄ ይጠይቃል። የአየር ንብረት መዛባት፣ የተባይ ስርጭትና የዘመናዊ ቴክኖሎጂ እጥረት በሰሊጥ ልማት የሚስተዋሉ ዋና ዋና ተግዳሮቶች ናቸው። ከተወሰኑ ጊዜያት ወዲህ ሰሊጥ አምራች አካባቢዎች ምርቱን በኮምባይነር ታግዞ የመሰብሰብና የመውቃት ልምድ እየጎለበተ መምጣቱ ችግሩ እየተቃለለ እንዲመጣ አድርጎታል። ሰሊጥ ባለው ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ከሚያስገኘው የውጭ ምንዛሬ በተጨማሪ ለሥራ ዕድል ፈጠራም ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው። ከምርት ዝግጅት ጀምሮ እስከ ማቀነባበር፣ ማሸግ እና ንግድ ድረስ በርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል ያገኙበታል። በተለይም በምርት ስብሰባ ወቅት ለሚሰማሩ ጊዜያዊ ሠራተኞች ትልቅ የገቢ ምንጭ ነው። ከዚህም ባሻገር ለምግብ ዘይት ማምረቻዎች እና ለተለያዩ የምግብ ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎች ዋነኛ ግብአት ነው። በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚገኘው ዓመታዊ የሰሊጥ ምርት እንደየዓመቱ የዝናብ ሁኔታ የሚለያይ ቢሆንም በአማካይ ከ2 ነጥብ 5 እስከ 3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል አካባቢ እንደሚደርስ መረጃዎች ያሳያሉ። ከአጠቃላይ የሰሊጥ ምርት ውስጥ አብዛኛው ለውጭ ገበያ የሚቀርብ ሲሆን የሀገር ውስጥ ፍጆታ በጣም አነስተኛ ነው። በዚህም ኢትዮጵያ በዓለም ከፊት ከሚገኙ የሰሊጥ ላኪ ሀገራት አንዷ ናት። ሰሊጥ በኢትዮጵያ የውጭ ንግድ ውስጥ ከቡና ቀጥሎ ከፍተኛውን የውጭ ምንዛሬ የሚያስገኝ ቁልፍ ሰብል ነው። ከዚህም የተነሳ ነጭ ወርቅ እየተባለ ሲጠራም ይስተዋላል። ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ካሉ ቀዳሚ የሰሊጥ ላኪ ሀገራት ተርታ ወስጥ ነው የምትመደበው። ምርቱ በዋናነት የሚላከውም ወደ ቻይና፣ እስራኤል፣ ቱርክ፣ ጃፓንና መካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ነው። የሰሊጥ ልማት ከዘር እስከ አጨዳና መውቂያ ድረስ ከፍተኛ የሰው ኃይል የሚጠይቅ በመሆኑ በየዓመቱ በመቶ ሺዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች ጊዜያዊና ቋሚ የሥራ ዕድል ይፈጥራል። ሰሊጥ ለኢንዱስትሪ ግብዓትነት ካለው ጠቀሜታ አንጻር በሀገር ውስጥ ለሚገኙ የዘይት መጭመቂያ ፋብሪካዎች፣ ለዳቦ ቤቶችና ለጣፋጭ ምግብ አምራቾች እንደ ግብአት ሆኖ ያገለግላል።ከቅርብ ጊዜ ወዲህም ሰሊጥን በጥሬው ከመላክ ይልቅ እሴት ጨምሮ (ለምሳሌ ታሂኒ እና የሰሊጥ ዘይት በማምረት) ወደ ውጭ የመላክ ጥረቶች ተጀምሯል። ሰሊጥ ከምግብነት አንጻር ያለው ፋይዳ በተመለከተም ሰብሉ በንጥረ-ነገር የበለጸገ በመሆኑ በኢትዮጵያም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ በተለያዩ የምግብ ዓይነቶች ውስጥ ይካተታል። ሰሊጥ ከ45% እስከ 55% የሚደርስ ከፍተኛ የቅባት (ጤናማ ስብ) ይዘት ያለው ሲሆን፣ በፕሮቲን (20 እስከ 25%)፣ በፋይበር፣ በካልሲየም፣ በብረት (Iron)፣ በማግኒዚየም፣ በዚንክ እና በቫይታሚን "B" እና "E" የበለጸገ ነው። ከምግብነት አኳያ በኢትዮጵያ ባህላዊ አመጋገብ ሰሊጥ ተቆልቶና ተፈጭቶ በተለያየ መልክ ለምግብነት ይውላል። በተለይም በጾም ወቅት ዋነኛ የፕሮቲንና የኃይል ምንጭ ነው። በዳቦ፣ በኩኪስና በተለያዩ ጣፋጭ ምግቦች ላይ ሲነሰነስም ለምግቡ ልዩ ጣዕምና መዓዛ ይሰጣል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ሰሊጥ ተፈጭቶ "ታሂኒ" (Tahini) የተባለ ለምግብ ማጣፈጫነት የሚያገለግል ክሬም ይሰራበታል፤ እንዲሁም "ሃልቫ" (Halva) ለተሰኘው ጣፋጭ ምግብ ዋና ግብዓት ነው። የሰሊጥ ዘይት ለምግብ ማብሰያነትና ለሰላጣ ማጣፈጫነት እጅግ ተመራጭ ነው። ከሕክምናና ጤና አንጻር ያለው ጠቀሜታ በተመለከተም ሰሊጥ በውስጡ በያዛቸው ልዩ ፀረ-ኦክሲዳንቶች ማለትም ሴሳሚን እና ሴሳሞሊን አማካኝነት ለተለያዩ የጤና እክሎች መከላከያና መድኃኒትነት ሆኖ ያገለግላል። በዚህም ሰሊጥ የልብ ጤናን ይጠብቃል። በተለይ በውስጡ የሚገኙት ጤናማ ቅባቶች በደም ውስጥ ያለውን ጎጂ ኮሌስትሮል (LDL) በመቀነስ የልብ ህመምንና የደም ቧንቧ መጥበብን ለመከላከል ጠቀሜታ አላቸው። ሰሊጥ በማግኒዚየም የበለጸገ በመሆኑ የደም ቧንቧዎችን በማስፋት ከፍተኛ የደም ግፊትን ለመቀነስነና ለመቆጣጠር ይረዳል። በውስጡ የያዘው ከፍተኛ መጠን ያለው ካልሲየም፣ ፎስፈረስ እና ዚንክ ለአጥንት እድገትና ጥንካሬ ወሳኝ ነው። በጤና ላይ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በዕድሜ መግፋት ምክንያት የሚመጣን የአጥንት መሳሳት ይከላከላል። እንዲሁም የምግብ መፈጨት ሥርዓትን ያስተካክላል። በፋይበር የበለጸገ በመሆኑ የሆድ ድርቀትን ከመከላከል ባለፈ የአንጀት ጤናንም ይጠብቃል። በተለይ ጥቁር ሰሊጥ በብረት (Iron) ማዕድን የበለጸገ በመሆኑ ቀይ የደም ሴሎችን ለማምረትና የደም ማነስን ለመከላከል ይረዳል። እንዲሁም የስኳር በሽታን በመቆጣጠር በኩል ሚናው የላቀ ነው። ዝቅተኛ የካርቦሃይድሬትና ከፍተኛ የፕሮቲንና ጤናማ ስብ ይዘት ስላለው በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ሚዛን ለመጠበቅ ይረዳል። በተጨማሪ የሰሊጥ ዘይት ቆዳን ለማለስለስ፣ ከፀሐይ ጨረር ለመከላከልና ቁስልን ቶሎ ለማዳን በባህላዊም ሆነ በዘመናዊ የመዋቢያ ኢንዱስትሪዎች ውስጥ በስፋት ጥቅም ላይ ይውላል። የኢትዮጵያ ሰሊጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ ካለው ተፈላጊነት አንጻር ምርታማነትን በዘመናዊ ግብርና ማሳደግና እሴት ጨምሮ ወደ ውጭ መላክ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በከፍተኛ ደረጃ ያሳድገዋል። በሀገር ውስጥም አጠቃቀሙን ማስፋትና ዜጎችም ሰሊጥን በምግባቸው የመጠቀም ባህላቸውን ማሳደግ ለጤናና ስነ-ምግብ መሻሻል ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል። በመሆኑም ልማቱን በማስፋፋትና በማዘመን ምርታማነትን ለማሳደግ ከሚደረገው ጥረት በተጨማሪ እሴት ጨምሮ ለገበያ ለማዋል የሚደረጉ የተቀናጁ ጥረቶች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል።
የሥራ ፈጠራ ለሁለንተናዊ የኢኮኖሚ ዕድገት
Nov 17, 2026 97
የሥራ ፈጠራ ሳምንት (Global Entrepreneurship Week - GEW) በየዓመቱ በህዳር ወር አጋማሽ ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ (ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ200 በላይ ሀገራት ውስጥ) የሚከበር ትልቅ የስራ ፈጠራ ንቅናቄ ነው። የሳምንቱ መከበር ዋና ዓላማዎችም የስራ ፈጠራ ባህልን ማሳደግ፡ በተለይ ወጣቶችና ሴቶች አዳዲስ የንግድ ሀሳቦችን ወደ ተግባር እንዲቀይሩ ማነሳሳት፣ ግንኙነት መፍጠር፣ ስራ ፈጣሪዎችን ከባለሀብቶች (Investors)፣ ከአማካሪዎች (Mentors) እና ከመንግስት አካላት ጋር ማገናኘት፣ እውቀትና ክህሎት ማጋራት ሲሆኑ፤ በዚሁም ስለ ንግድ አመራር፣ ስለ ቴክኖሎጂ አጠቃቀም እና ስለ ገበያ ትስስር ስልጠናዎችን መስጠት ዋናዎቹ ናቸው። የዚህ አመት የዓለም አቀፉ የሥራ ዕድል ፈጠራ ሳምንት (መሪ ሐሳብ "ግንኙነቶችን መፍጠር፣ እድገትን ማፋጠን" (Building Connections, Accelerating Growth) ወይም "አብሮ መገንባት" (Together We Build) በሚሉ ሐሳቦች ላይ ያተኮረ ነው። በዓለም አቀፉ የሥራ ዕድል ፈጠራ አውታር (Global Entrepreneurship Network - GEN) የሚዘጋጀው የሳምንቱ አከባበር የዘንድሮው መርሐ ግብር ትኩረት ከተደረገባቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል አንዱ የሥነ-ምህዳር ትስስር ነው ። ይህም ሥራ ፈጣሪዎችን ከባለሀብቶች፣ ከአማካሪዎች እና ከተመራማሪዎች ጋር በማገናኘት ጠንካራ የንግድ ሥነ-ምህዳር መፍጠር ነው። ሌላው የቴክኖሎጂ እና ፈጠራ ሲሆን አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን እና ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም አዳዲስ የንግድ ሐሳቦችን ማሳደግ ይሆናል። እንዲሁም አካታችነት ሌላው የትኩረት አቅጣጫ ሲሆን፡- ወጣቶችን፣ ሴቶችን እና በገጠር አካባቢ ያሉ ሥራ ፈጣሪዎችን በንግዱ ዘርፍ በስፋት ማሳተፍን የተመለከተ ነው። ሌላው ዘላቂነት ሲሆን ይህም የአካባቢ ጥበቃን እና አረንጓዴ ልማትን ያገናዘቡ የንግድ ሥራዎችን ማበረታታት ይሆናል። ሳምንቱም ሀገር በቀል የፈጠራ ሐሳቦችን በማበረታታት እና የገበያ ትስስር በመፍጠር በተለያዩ ሁነቶች እንደሚከበር የወጡ መረጃዎች ያመላክታሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለ በኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ የልማት መስኮች፣ ኢኒሼቲቮች እና ኢንዱስትሪዎች የሚፈጠሩ የስራ እድሎች ሀገራዊ ስራ አጥነትን ለመቀነስ ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ። የስራ እድል ከሚፈጠሩባቸው ዘርፎች አንዱ ግብርና ሲሆን ግብርና የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት እንደመሆኑ ከፍተኛውን የስራ እድል ይይዛል። ዝርዝር መስኮቹም የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት፣ የአትክልትና ፍራፍሬ እርሻ፣ የግብርና ግብዓት አቅርቦት፣ የዘር ብዜት እና የግብርና ምርቶች እሴት ሰንሰለት ናቸው። ሀገራዊ ትኩረት ተሰጥቶት እየተተገበረ ያለው የሌማት ትሩፋትም የቤተሰብን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ እና የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦትን ለማሳደግ የተጀመረ ኢኒሼቲቭ ሲሆን በዚህም ለወጣቶችና ሴቶች ሰፊ የስራ እድል ተፈጥሯል። በዘርፉ የስራ እድል እየተፈጠረባቸው ካሉ መካከል የዶሮ እርባታ የእንቁላልና የስጋ፣ የወተት ላሞች እርባታና ወተት ማቀነባበር፣ የንብ ማነብ የማር ምርት እና የዓሳ እርባታ ዋናዎቹ ናቸው። በተመሳሳይ አረንጓዴ አሻራ እና አካባቢ ጥበቃ ሲሆን ይህ ዘርፍም ወቅታዊ እና ቋሚ የስራ እድሎችን በመፍጠር ይታወቃል። በዘርፉ የሚፈጠሩ የስራ እድሎችም የችግኝ ማፍላት፣ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎች፣ የደን ጥበቃ እና የእንስሳት መኖ ልማት ናቸው። ኢንዱስትሪ (ማኑፋክቸሪንግ እና ኮንስትራክሽን) ሌላው የስራ እድል የሚፈጠርበት ዘርፍ ሲሆን የኢንዱስትሪ ፓርኮች፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች እንዲሁም የኮንስትራክሽን ዘርፉ ከግብርና ቀጥሎ ከፍተኛ የስራ እድል ይፈጥራሉ። የዘርፉ ዋና የስራ መስኮች፦ ጨርቃጨርቅና አልባሳት፣ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች፣ የምግብና መጠጥ ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች፣ የኮንስትራክሽን ግብዓት ማምረቻ እና የህንጻ ግንባታ ይጠቀሳሉ። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሐሳብ አመንጪነት ተቀርጾ ስልጠና እየተሰጠበት ያለው የኢትዮ ኮደርስና ዲጂታል ኢኮኖሚ ኢኒሼቲቭም በቀጥታ ስራ ከመቅጠር ይልቅ ወጣቶች በዓለም አቀፍ እና በሀገር ውስጥ የዲጂታል ገበያ ተወዳዳሪ ሆነው ስራ እንዲፈጥሩ ወይም እንዲቀጠሩ የሚያስችል ክህሎት ይሰጣል። ዘርፉ በሶስት ዓመት ውስጥ 5 ሚሊዮን ወጣቶችን በፕሮግራሚንግ፣ በዳታ ሳይንስ እና በዲጂታል ማርኬቲንግ የማሰልጠን እቅድ ሲሆን፤ ይህም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች በርቀት እና በሀገር ውስጥ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የስራ እድል እንዲያገኙ መንገድ ይከፍታል። ዋና የስራ መስኮችም ሶፍትዌር ማበልጸግ፣ ዳታ አናሊሲስ፣ ዲጂታል ግብይት እና የቢዝነስ ፕሮሰስ አውትሶርሲንግ ናቸው። ሌላው ሆቴል እና ቱሪዝም ዘርፍ ሲሆን በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች የተገነቡ አዳዲስ የቱሪስት መዳረሻዎች (እንደ ገበታ ለሸገር እና ገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች) ዘርፉን በከፍተኛ ሁኔታ አነቃቅተውታል። ዋና የስራ መስኮቹም የሆቴልና ሪዞርት መስተንግዶ፣ አስጎብኚነት፣ የባህል እደ-ጥበብ ውጤቶች ሽያጭ እና የትራንስፖርት አገልግሎት ናቸው። በየዓመቱ የሚከበረው የስራ ፈጠራ ሳምንት፣ ሀገሪቱ ያላትን ሰፊ የወጣት ኃይል ወደ ምርታማነት ለመቀየር እና የስራ አጥነት ችግርን ለመቅረፍ ለምታደርገው ጥረት ትልቅ አቅም የሚፈጥር መድረክ ነው። በተለይም በሀገሪቱ እየተተገበረ ካለው የዲጂታል ኢትዮጵያ ራዕይ እና የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ጋር ተያይዞ፣ ሳምንቱ የሚከተሉትን ቁልፍ ፋይዳዎች ያስገኛል፦ ወጣቶችና ምሩቃን "ስራ ጠባቂ" ከመሆን ይልቅ "ስራ ፈጣሪ" እንዲሆኑ የሚያነሳሱ የልምድ ልውውጦች እና ውይይቶች ይካሄዱበታል። አዳዲስ የንግድ ሀሳብ ያላቸው ጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች ከባንኮች፣ ከማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት፣ ከግል ባለሀብቶች እና ከፖሊሲ አውጪዎች ጋር በቀጥታ የሚገናኙበትን ዕድል ያመቻቻል። ሴቶች እና በክልል ከተሞች የሚገኙ ወጣቶች በቴክኖሎጂ፣ በግብርና እና በአገልግሎት ዘርፎች አዳዲስ ፈጠራዎችን ይዘው እንዲወጡ የክህሎት ስልጠና እና የማማከር ድጋፍ እንዲያገኙ ያግዛል። በአጠቃላይ የስራ ፈጠራ ሳምንት በኢትዮጵያ ውስጥ ምቹ የስራ ፈጠራ ምህዳር ለመገንባት፣ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ለማሳደግ እና ሀገራዊ የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማፋጠን እንደ ዋነኛ አነቃቂ ኃይል ሆኖ ያገለግላል።
የኢትዮጵያን እውነተኛ የኢኮኖሚ ቁመና የገለጠው አዲሱ GDP ስሌት
Nov 16, 2026 301
የአንድ ሀገር ኢኮኖሚ ጤናማነት እና የእድገት አቅጣጫ የሚመዘነው በተጨባጭ እና ወቅታዊ መረጃ ላይ በተመሠረተ መለኪያ ነው። ፖሊሲ አውጪዎች ትክክለኛ ውሳኔ እንዲያሳልፉም ሆነ ባለሀብቶች የገበያውን ስፋት እንዲረዱ ሳይንሳዊ የኢኮኖሚ ቆጠራ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። ይህ መለኪያ ካልተስተካከለ የሀገሪቱን እውነተኛ የኢኮኖሚ ቁመና ማወቅ አስቸጋሪ ይሆናል። ኢኮኖሚ በተፈጥሮው ተለዋዋጭ በመሆኑ በየጊዜው አዳዲስ ዘርፎችን እየፈጠረ እና ቅርፁን እየቀየረ ይሄዳል።የቴክኖሎጂ መስፋፋት፣ የከተሞች እድገት እና የአገልግሎት ዘርፉ መጠናከር የኢኮኖሚውን መዋቅር በፍጥነት ይለውጣሉ።በዚህ ጊዜ ቀደም ሲል የነበሩ የመለኪያ ዘዴዎች አሁናዊውን እውነታ በሙሉ አቅማቸው ማሳየት ይሳናቸዋል። በዚህ ምክንያት አገራት የኢኮኖሚያቸውን ትክክለኛ ልክ ለማወቅ የመለኪያ መነሻቸውን በየአምስት እስከ አስር ዓመቱ ማዘመን ዓለም አቀፋዊ አሰራር ሆኗል።አዲስ የኢኮኖሚ ቅርፅን በአሮጌ መለኪያ መመዘን ብዙ የልማት ውጤቶችን ከመዝገብ ውጭ እንዲቀሩ ያደርጋል። ስለሆነም የስሌት ማሻሻያ ማድረግ ወቅቱ የሚጠይቀው አስፈላጊ እርምጃ ነው። ይህንን ዓለም አቀፋዊ አሰራር በመከተል ኢትዮጵያ የአጠቃላይ ሀገራዊ ምርት (GDP) መለኪያዋን በማዘመን ከ2019 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን አዲስ ስሌት በቅርቡ አስተዋውቃለች።በብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ትብብር የተዘጋጀው ይህ ማሻሻያ፣ ለዘጠኝ ዓመታት ሲያገለግል የነበረውን የ2008 ዓ.ም. መነሻ ዓመት ተክቷል። በዚህ አዲስ ስሌት መሠረት የአገሪቱ የ2018 በጀት ዓመት አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት 210 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ተረጋግጧል።አዲሱ ስሌት እንደ ዲጂታል ፋይናንስ፣ ካፒታል ገበያ፣ የበጋ መስኖ ልማት እና የኮሪደር ልማት ያሉ ዘመናዊ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎችን በሙሉ አቅማቸው አካቷል። በቅርቡ በተካሄዱ የግብርና፣ የኢኮኖሚ ድርጅቶች እና የቤተሰብ ጥናቶች ላይ በመመሥረት መዘጋጀቱ ደግሞ መረጃውን ይበልጥ ተአማኒ ያደርገዋል። በዚህም የሀገሪቱ ትክክለኛ የኢኮኖሚ አቅም ታይቶ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ካሉ ግዙፍ ኢኮኖሚዎች መካከል አምስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን አረጋግጣለች። በፖሊሲ ቀረጻ እና በልማት ዕቅድ ዝግጅት ረገድም አዲሱ ስሌት የማይተካ ሚና ይጫወታል። መንግሥት የእያንዳንዱን ዘርፍ ትክክለኛ ድርሻ ሲያውቅ ሀብትን በፍትሐዊነት ለማከፋፈል ይረዳዋል። በተጨማሪም የታክስ አሰባሰብ አቅምን ከሰፊው ኢኮኖሚ አንጻር በመመዘን፣ መደበኛ ባልሆነ መንገድ የሚንቀሳቀሱ ንግዶችን ወደ ሕጋዊ ሥርዓት ለማስገባት ግልጽ መነሻ ይሆናል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያ ከአበዳሪ ተቋማት እና ከልማት አጋሮች ጋር የምታደርገውን ድርድር አቅም ከፍ ማድረጉ ሌላው ትልቅ አንድምታ ነው። የአጠቃላይ ሀገራዊ ምርት መጠን ማደግ የውጭ ብድር ከጂዲፒ ጋር ያለውን ጥምርታ ዝቅ በማድረግ፣ አገሪቱ ለልማት ፕሮጀክቶች የሚሆን ተጨማሪ ፋይናንስ እና የውጭ ኢንቨስትመንት የመሳብ ዕድሏን ያሰፋዋል።በአጠቃላይ ይህ ማሻሻያ ለኢትዮጵያ ቀጣይ የብልጽግና ጉዞ ትክክለኛ መሠረት የሚጥል ወሳኝ ምዕራፍ ነው።
አዲስ አበባ፡ስምና ግብር የታረቁባት የአፍሪካ መዲና
Nov 15, 2026 597
ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ ከ140 ዓመታት በኋላ አቧራዋን አራግፋ እንደ ስሟ የፈካችው አዲስ አበባ የአዲስ አበባ ከተማ የቀድሞ ገጽታ ስሟ ከግብሯ የቀደመበት፣ ተግባርና ሥራ ያልተባበሩበት ነበር። አንዲት ከተማ ስሟን ለመምሰል ስንት ዘመን ይፈጅባት ይሆን? አዲስ አበባ ከተመሠረተች 140 ዓመት ብታስቆጥርም አበባነቷ በገጽታዋ መታየት የጀመረው ግን ባለፉት ጥቂት ዓመታት ነው። በአሁኑ ወቅት አዲስ አበባ በኮሪደር ልማትና በወንዝ ዳርቻ ልማት እንደ ስሟ አብባና ፈክታ እየተስተዋለች ነው። ከተማዋ ሰው ተኮር የልማት ሥራዎችን በማከናወን ስሉጥ ከተማነቷን የበለጠ እያስመሰከረች፤ ዲጂታል መሠረተ ልማት በማስፋት ለነዋሪዎቿም ሆነ ለጎብኚዎቿ ምቹ መሆኗን እያረጋገጠች ትገኛለች። ዜጎች ካልተመቸና ከተጨናነቀ አኗኗር ተላቀው በምቹ የመኖሪያ አካባቢ እንዲኖሩ በማድረግ ጤናማነታቸው እየተጠበቀና ምርታማነታቸው እያደገ ይገኛል። አቧራዋን ያራገፈችበት ዘመን የመደመር መንግሥት ለከተማዋ የሰጠው ትኩረት ገጽታዋን ቀየረ። ሁለት ትላልቅ ሥራዎች ለውጡን መሩት፤ እነርሱም የወንዝ ዳርቻ ልማትና የኮሪደር ልማት ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተደጋጋሚ እንደገለጹት፤ የኮሪደር ልማት ከተማንና ገጠርን እኩል እየቀየረ ያለና የከተሞችን ገመና የገለጠ ነው። እርሳቸው እንደተናገሩት ከተሞች ከዚህ ቀደም ሕይወት በሰቆቃ የሚገፋባቸው የመከራ ዳሶች፣ ንግድና አገልግሎት የማይሳለጥባቸው መተራመሻዎች ነበሩ። ፋይናንስ፣ ትራንስፖርት፣ መዝናኛና ታሪክ የማይተሳሰሩባቸው መንደሮችም ነበሩ። በኮሪደርና በወንዝ ዳርቻ ልማቶች ከተሞች የዘመናዊ ከተማ መልክ መያዝ በመጀመራቸው ለመኖሪያ የተመቹ፣ ለንግድና ለኮንፈረንስ የተስማሙ፣ ቢያስጎበኟቸው የማያሳፍሩና ተምሳሌት ተደርገው የሚጠቀሱ እየሆኑ መጥተዋል። ዛሬ ኢትዮጵያ ''የአፍሪካ ውብ አበባ'' ተብላ ብትጠራ እውነታ እንጂ ባዶ ሙገሳ ተደርጎ አይወሰድም። የአዲስ አበባ አዲስ ገጽታ በውጭ ዜጎች እንዴት ይገለጻል? የአዲስ አበባ ከተማ ለውጥ ለዓይን የሚሞላ በመሆኑ የከተማዋን ጽዳት፣ ውበትና ፍካት የተመለከተ ሁሉ የሚመሰክረው ሀቅ ሆኗል። ለረጅም ዓመታት በከተማዋ የኖሩት የሩሲያው አምባሳደር ኤቭጌኒ ቴሬኪን ከዚህ ቀደም አዲስ አበባ የአፍሪካ ዲፕሎማሲ መናገሻ ብትሆንም የከተማነት ገጽታ ግን ከአሁኑ ጋር የተቃረነ እንደነበር ያነሳሉ። ባለፉት ጥቂት ዓመታት በከተማዋ የተመዘገበው ለውጥ ግን የከተማዋን ዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ ማዕከልነት በተግባር የገለጠ መሆኑን አረጋግጠዋል። የከተማዋን ለውጥ ለከተማዋ ነዋሪ ብቻ ሳይሆን ለእነሱም የኩራት ምንጭ ነው ብለዋል። የኢንዶኔዥያው የቀድሞ አምባሳደር አል ቡስራ ባስኑር በበኩላቸው ስለአዲስ አበባ ለውጥ እማኝነታቸውን የገለጹት ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ የነበረው የከተማዋ ገጽታና አሁን የታየው ለውጥ የማይታመን ሲሉ ነው። የአዲስ አበባ የአሁን መልክ ማሳያ ሰፋፊና ምቹ መንገዶች ጽዱና ውብ ከተማ አድርገዋታል። የአዲስ አበባ ውበት ፈክቶና ደምቆ አሁን ላይ ከተማዋን ከኒው ዮርክና ከጄኔቫ ጋር ማወዳደር የሚያስችል ቁመና ላይ ትገኛለች ሲሉ የተናገሩት የዴንማርኩ አምባሳደር ሱነ ክሮግስትሩፕ ናቸው። የሮማኒያ አምባሳደር ጁሊያ ፓታኪ በኮሪደር ልማት ከተማዋ ሰፋፊ መንገዶች፣ ምቹ የእግረኛ መንገዶችና መናፈሻዎች ያሏት ዘመናዊ ከተማ መሆኗን ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። ከተማዋን ሊጎበኙና ዓለም አቀፍ ጉባዔዎችን ሊታደሙ የመጡ የውጭ ሀገር ዜጎችም የአዲስ አበባን ውበትና ለውጥ እጅን በአፍ የሚያስጭን ለሌሎች ተምሳሌት የሚሆን አርአያ ተግባር መሆኑን በተደጋጋሚ ያስረዳሉ። የከተማዋ ውብ መልክ የመጽሐፍ ምስክርነትና የዓለም እውቅና የአዲስ አበባ ከተማ የትናንትና የዛሬ ንጽጽር በመጽሐፍም ተመዝግቧል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህና ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተገኙበት በግንቦት 2018 ዓ.ም., በአራት ደራሲያንና ዓለም አቀፍ ምሁራን ተጽፎ የተመረቀው ''The Remaking of Addis Ababa: Transformation from 2020–2025'' የተሰኘው መጽሐፍም አዲስ አበባ ከ2012 እስከ 2017 ዓ.ም. (2020–2025) ባሉት ዓመታት ውስጥ ያስመዘገበችውን ፈጣን የከተማ ልማት፣ የመሠረተ ልማት ግንባታና የአረንጓዴ ሽግግር ዳሷል። መጽሐፉ ቀደም ሲል የተጎሳቁሉትና ንጽህና ያልነበራቸው አካባቢዎች ዛሬ እንዴት በዘመናዊ የኮሪደር እና የወንዝ ዳርቻ ልማቶች፣ በሰፋፊ መንገዶችና በአረንጓዴ መናፈሻዎች እንደተተኩ በመረጃ አስደግፎ ያሳያል። መጽሐፉ ከተማዋ ከማይመች አኗኗር ተላቃ ለአየር ንብረት የማይበገር፣ ጽዱና ዘመናዊ የ''ስማርት ሲቲ'' ገጽታን እንዴት እንደተላበሰችም ይዳስሰል። የአዲስ አበባ ከተማዋ ገጽታ የምሁራን ምስክርነት ያገኘ ብቻ ሳይሆን ዓለም አቀፍ እውቅናና ሽልማቶችንንም የተቸረው ነው። አዲስ አበባ በኮሪደርና በወንዝ ዳርቻ ልማት፣ በአረንጓዴ ስፍራዎችና በዘመናዊ የሕዝብ ትራንስፖርት ባመጣችው ሰው ተኮር ለውጥ በጥቅምት 2019 ዓ.ም. (ኦክቶበር 2026) በUN-Habitat እና በቻይና መንግሥት የሚዘጋጀውን የ2026 የሻንሃይ ዓለም አቀፍ የዘላቂ ከተማ ልማት ሽልማት ከ92 ተወዳዳሪ ከተሞች ልቃ አሸንፋለች። ከዚህም በተጨማሪ በ2026 የአየር ንብረት ለውጥን በመቋቋም አቅሟ ከአፍሪካ አንደኛ ከዓለም ሁለተኛ ደረጃን ስትይዝ፣ ቀደም ሲልም የሴኡል ስማርት ሲቲ ሽልማትን በማግኘት ስኬቷን በዓለም አቀፍ መድረክ አስመስክራለች። የአፍሪካ አዲሲቷ አበባ አዲስ አበባ የአፍሪካ ኅብረትና የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት መናገሻ ከተማ እንደመሆኗ ከዚህ ቀደም የአህጉሪቷን ስብሰባዎች ስታስተናግድ ኖራለች። አሁን ግን ለውጧ የዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ ማዕከልነቷን አጉልቶ በርካታ ጉባዔዎችን እንድታስተናግድ አስችሏታል። የከተማዋ ለውጥ ዓለም አቀፍ የስበት ማዕከልነቷን በማሳደጉ በ2018 በጀት ዓመት ብቻ ከተማዋ ከ200 በላይ ዓለም አቀፍና አህጉር አቀፍ ስብሰባዎችን አስተናግዳለች። ከአምስት ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎች ያሏት፣ ከባሕር ጠለል በላይ 2 ሺሕ 355 ሜትር ላይ የምትገኘው አዲስ አበባ አሁን ከስሟ ጋር እየተገናኘች ነው። ከ140 ዓመታት በፊት አዲስ አበባ ተብላ ስትሰየም የተመኘችው ውበት ዛሬ በተግባር ተገልጧል። ከተማዋ አቧራዋን አራግፋ፣ በኮሪደር እና በወንዝ ዳርቻ ልማት ታድሳ ስሟንና ግብሯን አስታርቃለች። ትናንት በመንገደኞች ዓይን ይታይ የነበረው የከተማዋ ድካም ተረስቶ፣ ዛሬ የዓለም መሪዎች የሚያደንቋትና መጻሕፍት የሚመሰክሩላት የአፍሪካ ኩራት ሆናለች። አዲስ አበባ ዛሬ ስሟን የመሰለች፣ ለነዋሪዎቿ የምትመችና ለመጪው ትውልድ የምትተርፍ እውነተኛ የአፍሪካ አበባ ሆና ፈክታለች። ታሪክ በመጻሕፍት፣ ዓለም በሽልማት፣ ዲፕሎማቶችም በአድናቆት የመሰከሩለት የአዲስ አበባ ዳግም ልደት ዛሬ በገሃድ እየታየ ነው። ለዘመናት ''ስንት ዓመት ይፈጅባት ይሆን?'' ብለን የጠየቅንላት ከተማ ዛሬ መልሱን በተግባር ሰጥታናለች። አዲስ አበባ ዛሬ እንደ ስሟ አዲስና ውብ አበባ ሆናለች። አዲስ አበባ ለአፍሪካና ለዓለም ውብ መሆኗን በተግባር ገልጣለች፤ ራሷን በገጸ በረከትነት ሞሽራለች። ዓለም ዓይኖቹን እርሷ ላይ በመጣል ታላላቅ ጉባዔዎችን ለማድረግ ቀጠሮ ይዟል፤ አሁንም እያደረገ ነው። አዲስ አበባም በደስታ እጇን ዘርግታ እንግዶቿን ትቀበላለች። ስምና ግብሯ ተጣጥመው ዘመናትን ይሻገራሉና።
ልዩ ዘገባዎች
ከዓባይ እስከ ቀይ ባሕር
Oct 9, 2026 1326
ነጋሪ መጽሔት የዓባይ ውሃ አጠቃቀምና የኢትዮጵያን የባሕር በር ፍላጎት በስፋት ተንትናለች። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም በመደመር መንግሥት ምሥረታ ላይ፣ “የኢትዮጵያ ሥልጣኔ ያለ ባሕር በር እውን ሊሆን አይችልም” በማለት ሀገሪቱ የባሕር መዳረሻ እንድታገኝ በትጋት እንደሚሠሩ አረጋግጠዋል። ይህ ጥረት በሰላማዊ ውይይት፣ በጋራ ተጠቃሚነትና በ“ሰጥቶ መቀበል” መርሕ እንደሚመራ በማስገንዘብ፣ ጉዳዩን ከአፍሪካ ቀንድ፣ ከቀይ ባሕርና ከመካከለኛው ምሥራቅ እየተለወጡ ካሉ የጂኦፖለቲካና የኢኮኖሚ ሁኔታዎች ጋር አያይዘው አቅርበዋል። መጽሔቷም በመስከረም 2019 ዓ.ም. እትሟ “የኢትዮጵያ የትንሳኤ መንገድ፡ ከዓባይ እስከ ቀይ ባሕር ፖለቲካ የዘለቀው ፍጥጫ” በሚል ርዕስ ባቀረበችው ትንታኔ፣ የውሃ ሀብት፣ የባሕር መዳረሻ፣ የዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮችና የቀጣናዊ ደኅንነት ጉዳዮች በሀገራት መካከል ባለው የኃይል አሰላለፍ ላይ ያላቸውን ተጽዕኖ ዳስሳለች። እንደ መጽሔቷ ትንታኔ፣ ዓባይና ቀይ ባሕር በተፈጥሮ የተለያዩ የውሃ አካላት ቢሆኑም፣ በዘመናዊው የጂኦፖለቲካ ስሌት ውስጥ በውሃ አጠቃቀም፣ በኢኮኖሚያዊ ጥቅም፣ በባሕር መዳረሻና በደኅንነት ጉዳዮች የተሳሰሩ ናቸው። የዓባይ ወንዝ ለኢትዮጵያና ለተፋሰሱ ሀገራት ለኃይልና የልማት ጥቅም ሲኖረው፣ ቀይ ባሕር ደግሞ አፍሪካን፣ እስያንና አውሮፓን የሚያገናኝ ወሳኝ የዓለም አቀፍ የንግድና የባሕር መተላለፊያ ነው። በተለይም የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ፣ የዓባይ ውሃን በፍትሐዊነትና በጋራ ተጠቃሚነት የማስተዳደር ጥያቄና የኢትዮጵያ የባሕር በር ፍላጎት በቀጣናው የፖለቲካና የደኅንነት ስሌቶች ላይ የሚያሳድሩትን ተጽዕኖ መጽሔቷ በስፋት ተንትናለች። የ1929 እና የ1959 የውሃ ስምምነቶች የላይኛውን ተፋሰስ ሀገራትን ጥቅም በበቂ ሁኔታ እንዳልተካተቱ በመግለጽ፣ የወንዙ ውሃ አጠቃቀም በፍትሐዊነት፣ በትብብርና በጋራ ጥቅም ላይ በተመሠረተ ማዕቀፍ መመራት እንዳለበት አመልክታለች። ኢትዮጵያ በ1993 ዓ.ም በኋላ የባሕር በር መዳረሻዋን ማጣቷን ተከትሎ፣ ጉዳዩ ከኢኮኖሚያዊ ጥቅም ባለፈ ከብሔራዊ ደኅንነትና ከረጅም ጊዜ የልማት ፍላጎት ጋር እንደተያያዘ መጽሔቷ አትታለች። የባሕር በር መዳረሻ ማግኘት የንግድ ወጪን ለመቀነስ፣ የወደብ አማራጮችን ለማስፋትና የኢኮኖሚ ዕድገትን ለመደገፍ ወሳኝ መሆኑንም አብራርታለች። በሌላ በኩል፣ ቀይ ባሕር ከእስያ፣ ከአፍሪካና ከአውሮፓ የንግድ መስመሮችን የሚያገናኝ ስትራቴጂካዊ የባሕር መተላለፊያ በመሆኑ፣ በአካባቢው ያለው የደኅንነት ሁኔታ ከአካባቢያዊ ግንኙነቶች ባለፈ ዓለም አቀፋዊ የንግድ ፍሰትን ይነካል። መጽሔቷ የቀይ ባሕር የጂኦፖለቲካ አስፈላጊነት ከስዊዝ ቦይና ከባብ-ኤል መንደብ የባሕር መተላለፊያ ጋር በማያያዝ የዳሰሰች ሲሆን፣ በአካባቢው የሚካሄዱ የኃይል ፉክክሮች የንግድና የደኅንነት ስጋቶችን እንደሚያባብሱ ተንትናለች። መጽሔቷ በትንታኔዋ የኢትዮጵያን የባሕር በር ፍላጎት ከቀጣናው ሀገራት የፖለቲካ አቋሞች ጋር በማያያዝ የተለያዩ ትንታኔዎችን አቅርባለች። ሆኖም እነዚህ በመጽሔቷ የቀረቡ የፖለቲካ ትንታኔዎች ሲሆኑ፣ የተጠቀሱ አቋሞችንና ክሶችን ከተረጋገጡ እውነታዎች መለየት ያስፈልጋል። መጽሔቷ በዓባይ ውሃ አጠቃቀምና በባሕር መዳረሻ ጉዳይ ዙሪያ የሚነሱ አለመግባባቶች በግጭት ሳይሆን በውይይት፣ በድርድርና በጋራ ተጠቃሚነት መርሕ መፍትሔ ማግኘት እንዳለባቸው አጉልታለች። የውሃ ሀብትን በፍትሐዊነት ማስተዳደርና የባሕር መዳረሻ ጉዳይን በሰላማዊ ስምምነት መፍታት ለቀጣናዊ መረጋጋት፣ ለኢኮኖሚ ትብብርና ለዘላቂ ልማት ወሳኝ መሆናቸውን በትንታኔዋ አመልክታለች። የመጽሔቱ ሊንክ https://www.ena.et/web/negari/w/negari_9696604
ከአዲሱ መንግስት ምን ይጠበቃል?
Oct 5, 2026 1164
ትልቅ ሀገር- ትልቅ ህዝብ- ታላቅ ርእይ አዲስ የሚመሰረተው መንግስት በሀገሪቷ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን የማስቀጠል፤ በተለይም የተጀመሩ ግዙፍ ሀገራዊ የልማት ፕሮጀክቶችን ለስኬት ማብቃት ትልቁ የቤት ስራ ነው የሚሆነው። በከተሞች እየተከናወነ ያለውን የኮሪደር ልማትና የስማርት ሲቲ ግንባታ፣ የዲጂታል አገልግሎቶችን የማስፋት፣ የአረንጓዴ አሻራ ልማትን ማስቀጠል ሌላኛው ሀገራዊ ሃላፊነት ነው የሚሆነው። የኢትዮጵያ ልማት በከተሞች ጋር ብቻ የሚወሰን ባለመሆኑ በገጠር አካባቢዎች የተጀመሩ የገጠር ትራንስፎርሜሽን የልማት ስራዎችንም ማስቀጠል የግድ ይላል። የገጠር ትራንስፎርሜሽን ዋነኛ ዓላማም የገጠሩን ህዝብ አኗኗር ማዘመን፣ የመሠረተ ልማትና የመሰረታዊ አገልግሎት ተደራሽነትን ማሻሻል፣ የገጠር ኢኮኖሚን ማጠናከርና የገጠር ነዋሪዎችን ከዘመናዊ የምርትና የገበያ ሥርዓት ጋር ማስተሳሰር መሆን አለበት። ኢትዮጵያ በተፈጥሮ፣ በታሪክ፣ በባህልና በሃይማኖት የበለፀገች ሀገር በመሆኗ አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎችን መፍጠር፣ ያሉትን የመጠበቅና የማልማት እንዲሁም ታሪካዊና ተፈጥሯዊ ሀብቶችን መጠበቅ፣ የቱሪስት ቆይታን ማራዘምና ከቱሪዝም ጋር የተሳሰሩ የስራ እድሎችን የማስፋት ጉዳይ የአዲሱ መንግስት ዋነኛ ትኩረት ሆኖ ይቀጥላል። በግብርናው ዘርፍም በምርትና ምርታማነት፣ በመስኖ ልማት፣ በስንዴ፣ በሌማት ትሩፋት፣ በቡና፣ በሆርቲካልቸርና በሌሎችም የግብርና ዘርፎች የተጀመሩ ስራዎች በዘላቂነት እንዲቀጥሉ ማድረግ ይጠበቃል። ከምርት መጨመር ባሻገር የግብርና ምርቶችን ማቀነባበር፣ የገበያ ትስስርን ማሻሻል፣ የማከማቻና የመጓጓዣ ስርዓትን ማዘመን እና የአርሶ አደሩን ገቢ የማሳደግ ጉዳይ ትኩረት ይፈልጋል። የምርትና ምርታማነት መጨመር በመጨረሻም ከውጭ የሚገቡ የምግብ ምርቶችን በመተካት፣ የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥና የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ አቅም በማሳደግ ከተረጅነት ለመውጣት የሚደረገውን ጥረት ማሳካት ይጠበቅበታል። የማዕድን ልማት፣ ዲጂታላይዜሽንና የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን የማዘመን ጉዳይም ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ይሆናል። የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር የምርትና የገበያ አቅርቦትን ማሳደግ፣ የአቅርቦት ሰንሰለትን ማሻሻል፣ ህገወጥ የገበያ አሰራሮችን መቆጣጠርና የዜጎችን የመግዛት አቅም ማሻሻል ይጠበቃል። የኑሮ ውድነት ችግር በአንድ መፍትሄ የሚፈታ ባለመሆኑ የገቢ፣ የምርት፣ የገበያና የፋይናንስ ፖሊሲዎችን በተቀናጀ መልኩ ማስኬድ ያስፈልጋል።
የአካታች ሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት ፅኑ መሰረት
Oct 5, 2026 891
መስከረም 25/2019 (ኢዜአ):- አዲሱ የመንግስት ምስረታ - አካታች የፖለቲካ ስርአት ግንባታ መሰረት ትልቅ ሀገር- ትልቅ ህዝብ- ታላቅ ርእይ በምክር ቤት አብላጫ መቀመጫ ያገኘው ብልጽግና ፓርቲ መንግስት የመመስረት ሃላፊነት ያለበት በመሆኑ በዛሬው እለት ይሄው የሚከናወን ይሆናል። በፓርላማው የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች መቀመጫ ያገኙ በመሆኑ የፖለቲካ ክርክሮችና የሃሳብ ብዝሃነት የሚስተናገዱበት እንደሚሆንም ይጠበቃል። በኢትዮጵያ አካታችና አሳታፊ የፖለቲካ ስርአት ግንባታ መሰረት ያኖረው አዲሱ የመንግስት ምስረታ ሂደት የክልሎች ተጠናቆ በዛሬው እለት የፌዴራል መንግስት ምስረታ እውን ይሆናል። ባለፉት ዓመታት የተመዘገበው የአካታችነት ስኬት የመንግሥት ከፍተኛ የአመራር እርከኖች፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤትና የፍትህ ተቋማት አመራሮች ላይ የተፎካካሪ ፓርቲ ተወካዮችን፣ የሴቶችንና የወጣቶችን ፍትሃዊ ስብጥር በተግባር ማሳየት ያስቻለ ነው። ከባለፉት አምስት አመታት ተሞክሮ በመነሳትም የዘንድሮው ምርጫ በብዙ መስፈርቶች ዴሞክራሲያዊ፣ አሳታፊ እና አካታች መሆኑን በተግባር ያሳየና የሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት ፅኑ መሰረት ያኖረ ሆኗል። በተቋማዊ አካታችነትና ሀገራዊ መግባባትን ለመፍጠር በተወሰዱ እርምጃዎችም ጉልህ ውጤቶች ተመዝግበዋል። ሁሉንም የፖለቲካና የኅብረተሰብ ክፍሎች ያቀፈው ሀገራዊ የምክክር ሂደት በሀገሪቷ የቆዩ ልዩነቶችን በምክክር ለመፍታት አዲስ ምእራፍ የከፈተ ሆኗል። ከዚህ ጎን ለጎን የጽንሰ-ሐሳብ፣ የቋንቋና የባህል ስብጥሮችን ያከበሩ የትምህርትና የባህል ፖሊሲዎች መተግበራቸው፣ ዜጎች በቋንቋቸው የመማርና አገልግሎት የማግኘት መብታቸው እንዲሰፋ በማድረግ ረገድም ትልቅ ስኬት ታይቷል። በመሆኑም በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አብላጫ ድምፅ ያገኘው የብልፅግና ፓርቲ የሚያቋቁመው አዲሱ መንግስት በቀጣይ ሁለንተናዊ አካታችነትን በማረጋገጥ ረገድ ብዙ እንደሚሰራ ይጠበቃል። ገዢው ፓርቲ መወዳደር የሚችልባቸውን አካባቢዎች በመተው ለተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች እድሉን መስጠቱ በምክር ቤቱ የተለያዩ ድምፆች እንዲስተጋቡ ምቹ ሁኔታ የፈጠረ ሆኗል። በመሆኑም ጠቅላላ ምርጫው የፖለቲካ ተሳታፊነትንና ውክልናን በማስፋት ረገድ ጉልህ ውጤቶች የተመዘገቡበት ነበር ማለት ይቻላል። በተጨማሪም በውሳኔ ሰጪነትና በፖለቲካ ውድድር ውስጥ የሴቶች፣ የወጣቶችና የልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፎ እንዲያድግ በመደረጉ ህዝባዊ ወካይነት ያለው የምርጫ ሂደትን ለማከናወን አስችሏል። ምርጫ አስተዳደሩንና አሰራሩን አሳታፊና ፍትሃዊ በማድረግ ረገድ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኩል የታዩት እርምጃዎች ሌላው የአካታችነት ማሳያዎች ናቸው። የድምፅ መስጫ ጣቢያዎችን ተዳራሽ ማድረግ፣ ለአካል ጉዳተኞች ምቹ የሆኑ የምርጫ ግብዓቶችን ማዘጋጀት እና በምርጫ ታዛቢነት የሲቪክ ማህበራትን፣ የሀገር ውስጥና የውጪ ምርጫ ታዛቢዎችን ማሳተፍ ተችሏል። ይህም የህብረተሰቡ ልዩ ልዩ ክፍሎች ያለምንም ገደብ የመምረጥ መብታቸውን እንዲጠቀሙና በሂደቱ ላይ ያላቸው እምነት እንዲጎለብት አድርጓል። በመሆኑም በዛሬው እለት የሚመሰረተው መንግሥት ልዩ ልዩ የፖለቲካና የማህበረሰብ ክፍሎችን ድምፅ በማስተናገድና ሀገራዊ መግባባትን በመፍጠር ጠንካራ የሀገረ መንግስት ግንባታ መሰረት የሚያኖር እንደሚሆን ይጠበቃል።
የመደመር መንግሥት-የብሔራዊ ጥቅም ዘብ
Oct 5, 2026 904
ኢትዮጵያ ዛሬ አዲስ መንግሥት ትመሠርታለች።ይህ መንግሥት የዛሬውን ትውልድ ብቻ ሳይሆን፤የመጪውንም ትውልድ ፍላጎት በጽኑ መሠረት ላይ የሚያቆም ሥራ የሚሠራ ነው። አዲሱ መንግሥት ትልቅ የሕዝብ አደራ የሚቀበልና የነገዋን ኢትዮጵያ በከፍታ ላይ የሚያስቀምጥ እንደሚሆን እሙን ነው። ኢትዮጵያ በታሪኳ እጅግ ውስብስብ የሆኑ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ ፈተናዎች አልፋ ዛሬ አዲስ የምዕራፍ ላይ ትገኛለች። አዲሱ መንግስት ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን፣ ሉዓላዊነቷን እና የሕዝቦቿን የጋራ እድገት ለማረጋገጥ ባደረገችው ያላሰለሰ ጥረት ውስጥ ቀጣይ ጉዞዋን በተሻለ መልኩ የሚያስቀጥል መንግሥት ይሆናል። ይህ ታሪካዊ ጉዞ በቀላሉ የተገኘ አልነበረም። ሕዝቡ የወደፊት ዕጣ ፈንታውን በቃላት ሳይሆን በተግባር ለመወሰን፣ መብቱን በድምፁ በመጠቀም ታሪካዊ አደራውን ለመወጣት ውስብስብ ፈተናዎችን አልፏል። በፈተና ውስጥ አልፎ የሰጠው ድምፅ ተራ የምርጫ ሂደት ሳይሆን፤ የሀገርን ሕልውና የማስከበር፣የብሔራዊ ጥቅምን የማስጠበቅ እና ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለች ሀገር የማስረከብ ጽኑ ፍላጎት መግለጫ ነበር። ዛሬ የሚመሠረተው አዲስ መንግሥት የዚሁ የሕዝብ አደራና የጽናት ውጤት ነው።ይህ የመደመር መንግሥት የሀገሪቱን ታሪካዊ፣ ተፈጥሯዊ እና ቀጣናዊ ጥቅሞች ያስከብራል፤ የኢትዮጵያን የሉዓላዊ ድንበር እና የወደፊት ሕልውና በጠንካራ ዲፕሎማሲና በውስጥ አንድነት ይጠብቃል። የዛሬዎቹን አጣዳፊ ጥያቄዎች ለመመለስ ብቻ ሳይሆን፣ መጪው ትውልድ የሚተማመንባት፣ በኢኮኖሚ የበለጸገች እና ብሔራዊ ጥቅሟን የምታስጠብቅ ሀገር መንግስት ይመሰርታል። ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን በሁለት ውኃዎች ላይ አድርጋ በጽናት እየተንቀሳቀሰች ትገኛለች። የአባይን ውኃ ለሁለንተናዊ እድገቷ መጠቀም ጀምራለች፤ ሕዳሴንም ጨርሳ የማድረግ አቅሟን አረጋግጣለች።ይህ ጉዞ ቀላል አልነበረም፤ሀገሪቱ በውስጥና በውጭ በርካታ ፈተናዎችን፣ ተፅዕኖዎችንና ጫናዎችን አልፋ ነው እዚህ ደረጃ ላይ የደረሰችው። ዛሬ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን የበለጠ የሚያስከብርላትን የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ አንሥታ ጉዳዩን ዓለም አቀፍ አጀንዳ አድርጋዋለች። የመደመር መንግሥት ኢትዮጵያ ኢ-ፍትሐዊና ባልተገባ መልኩ ያጣችውን የባሕር በሯን እንድታገኝ በትክክለኛው መንገድ ይጓዛል፤ ግቡንም ያሳካል። ዛሬ የሚመሠረተው አዲስ መንግሥት ለነገዋ ኢትዮጵያ ጠንካራ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ መደላደል የሚፈጥር ነው፤ የሀገሪቱን የባሕር በር ፍላጎት፣የዓባይ ወንዝ ፍትሐዊ ተጠቃሚነት፣የውስጥ ደኅንነትና የኢኮኖሚ ነፃነት አፅንኦት ሰጥቶ ማስጠበቅ ነው።ልዩነቶችን በማቀናጀትና አቅሞችን በመደመር የሀገርን ሕልውና አስተማማኝ ማድረግም ሌላው ከመደመር መንግስት የሚጠበቅ ነው። ከምንም በላይ ኢትዮጵያ የበርካታ ዘመናት ታሪካዊ ጠላቶቿንና ተላላኪዎቻቸውን እኩይ ሴራ ትበጣጥሳለች።የውስጥና የውጭ ጫናዎችን በህዝቦቿ ጽናት፣የአንድነት መንፈስና የማይናወጥ ሀገራዊ ወኔ እያሸነፈች ትቀጥላለች።ለነፃነቷና ሉዓላዊነቷ ሳትበገር በማንኛውም ጊዜና ሁኔታ ወደ ላቀ የልማት፣ የብልፅግናና የዕድገት ከፍታ ወደ ፊት መገስገሷን ትቀጥላለች። ዛሬ የሚመሰረተው አዲሱ የመደመር መንግሥትም የሕዝቡን ተስፋና እምነት ወደ መሬት በማውረድ፣የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም አክብሮና አስከብሮ ለመጪው ትውልድ የምትመችና በጽኑ መሠረት ላይ የተገነባች ሀገርን የማስረከብ ታሪካዊ ኃላፊነት አለበት።
መጣጥፍ
ምሽት አድማቂው - ጬሞ
Nov 13, 2026 190
ምሽት አድማቂው - ጬሞምሽት አድማቂው - ጬሞ (በቀደሰ ተክሌ - ኢዜአ ሚዛን አማን ቅርንጫፍ) ሰው ጥበቡ ዘርፈ ብዙ፤ አበላሉ፣ አጋጌጡና አለባበሱ ሁሉ የራሱ የሆነ ልዩ የጥበብ ቀለምና ውበት ያለው ነው። ፋብሪካ ከመፈጠሩ፤ ሳይንስም ከመስፋፋቱ በፊት የሰው ልጅ በራሱ መላ ምግቡን ከሽኖ ይመገብ ነበር። ያ ከጥንት ጀምሮ የሚጠቀምበት ባህላዊ የአመጋገብና ምግብ ዝግጅት ሥርዓት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ መስፋፋት ምክንያት ወደ ፋብሪካ ውጤቶች እየተቀየረ ቢመጣም ጨርሶ ግን አልጠፋም። በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የሚገኙት ቤንቾች ተፈጥሯዊ ይዘትን የጠበቁ ባህላዊ ምግቦችን በማዘጋጀት ይታወቃሉ። አረንጓዴው ምድራቸው ያበቀላቸው ስራስሮች ከቺ ጎደሬና ሌሎችም በብዛት ለምግብነት የሚገለገሏቸው ናቸው። ከበቆሎ ፍሬ በእጅ ተደቆሱ የሚዘጋጀው "ዳንጋላ" ፣ ኪጆና መሰል ምግቦችም በባህላዊ መንገድ ተዘጋጅተው ሲቀርቡ "ጬሞ" በተሰኘ ትኩስ መጠጥ ይታጀባሉ። በቤንቾች ቀዬ የሚገኘው የተፈጥሮ ቡና ተክል ፍሬው ተለቅሞ ለማዕከላዊ ገበያ ከመቅረብ አልያም ለአካባቢ ፍጆታ ከመዋል ያለፈ ትርጉም አለው። የቤንች እናቶች ቅጠሉን በወጉ ሰብስበው በሸክላ ምጣድ ክሽ አድርገው በማድረቅ ለሌላ አገልግሎት ያዘጋጃሉ። የደረቀውን የቡና ቅጠል አድቅቀው በማፍላት የዶሮ ዓይን የመሰለ ቡና ወይም በእነሱ አጠራር "ጬሞ"ን ያዘጋጃሉ። የቡና ቅጠል ቡና ውይም ጬሞን ለየት የሚያደርገው በብዙ የጓሮ ቅመማ ቅመሞች ታጅቦ መዘጋጀቱ ነው። ለአብነትም ነጭ ሽንኩርት፣ በሶብላ፣ ድምብላል፣ ኮሰረት፣ ጤናአዳም፣ ኮረሪማ፣ ሚጥሚጣ ወይም ደቆ የመሳሰሉት ጬሞን ጬሞ ከሚያሰኙ ግብአቶች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው። እነዚህ የጬሞ ግብአቶች በማሽን የተፈጩ አልያም እሴት ተጨምሮባቸው የተቀመሙ የፋብሪካ ውጤቶች አይደሉም። ከራሳቸው ጓሮ ተክለው ጬሞን ሲያፈሉ እለቱን ቀንጥሰው በትኩሱ የሚጨምሯቸው እንጂ። ይህ መሆኑ ደግሞ ከጬሞው ተፈጥሯዊ ጣዕምና የንጥረ ነገር ይዘቶችን በቀጥታ ለማግኘት የሚያስችል ዕድልን ይፈጥራል። ከዚህ የተነሳ ጬሞ እንደ ትኩስ መጠጥ ከማገልገል ያለፈ ጥቅም ያለው ሆኖ ተገኝቷል። ለጉንፋን፣ ደረቅ ሳል፣ ብርድና መሰል ሕመሞች ሁነኛ ባህላዊ መድኃኒት ተደርጎ ይወሰዳል። ይህ ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ያለው ጬሞ በቤንቾች ምድር ይዘወተራል። እንግዳ ቢመጣ ከእርጎና ኪዥ (አይብ)፣ ከጎደሬ፣ ከቺናና ሌሎች ከበቆሎ ከሚዘጋጁ ምግቦች ጋር ጬሞ አብሮ ይቀርባል። ለአራሹ አባወራ ወደ እርሻ ቦታ ለመያዝ በሚያመች እቃ ተወስዶለት ይጠጣል። ለሐዘንና ደስታ፣ ለደቦና መሰል ሰዎች በኅብረት በሚሰበሰቡባቸው ስፍራዎችም ጬሞን አፍልቶ ማቅረብ በቤንቾች ባህል የተለመደ ነው። ይህ ሥርዓት ከገጠር ተሻገሮ በከተማም እየተለመደ መምጣቱ ደግሞ ይበል የሚያሰኝ ነው። ጬሞ በሚዛን አማን ከተማ ውስጥ የፈጠረው የምሽት ትዕይንት ደግሞ ለየት ያለ ነው። መሸት ሲል ቀን በጫማ መጥረግ ሥራና ሌሎች አገልግሎቶች ተይዘው የዋሉ የጎዳና ዳር ቦታዎች ከ12 ሰዓት በኋላ ተራውን ጬሞ ለሚያፈሉ እንስቶች ይለቃሉ። ከጬሞ ባሻገር ንፍሮ፣ ጎደሬ፣ ከቺ እና ሌሎች የስራስር ምግቦች ተዘጋጅተው ወደ አደባባይ ይወጣሉ። ቀን በተለያዩ ሥራዎች የዋለ ሰው ወደ ቤት ከመግባቱ በፊት በከተማዋ ከጫፍ እስከ ጫፍ ከተዘጋጇ የጬሞ ቦታዎች አንዱ ላይ አረፍ ይላል። የሚዛን አማን ጎዳና ኮሪደሮች የምሽት ድባብ የሚደምቀው በጬሞ ነው። ጓደኛ ሲገናኝ ጬሞ ልጋብዝህ የሚባባልበት፣ ጬሞ ቦታ እንገናኝ ተብሎ የሚቀጠርበት መገናኛ፣ ወግ መጫወቻና ጊዜ ማሳለፊያ ምቹና ተመራጭ ስፍራም እየሆነ መጥቷል። ከጬሞ ጋር አብረው የሚቀርቡ ባህላዊ ምግቦች መኖራቸው ደግሞ ለከተማዋ ነዋሪ ትልቅ ጥቅም ይሰጣል። ድሃው በአነስተኛ ዋጋ ጬሞና ንፍሮ በልቶ ጠግቦ የሚያድርበትን ምቹ ዕድል መፍጠር የቻለ ተግባር ነው ማለት ይቻላል። እንደዚህ አይነት ሀገር በቀል ምርቶች ላይ የተመረኮዘ የአመጋገብ ሥርዓት ለጤና ጠቃሚ በኢኮኖሚም ትርጉም ያለው በመሆኑ አደባባይ አውጥቶ የመጠቀሙ ባህል ሊጠናከር ይገባል እንላለን። ሰላም!
የማይቆራረጠው የመረጃ መረብ
Nov 10, 2026 290
የአፋር ምድር በእምቅ የተፈጥሮ ሃብት፣ በቅርስና ታሪክ፣ በቱሪዝም መስህብነት የሚጠቀስ አካባቢ መሆኑ ይታወቃል። የአፋሮች ውብ ባህሎችና የአኗኗር ዘይቤዎች፣ አልባሳት፣ የምግብና ሌሎችም ልዩ መገለጫዎችና የካበቱ እሴቶች የሚያስደንቁ ናቸው። የአዋሽ ወንዝ በክልሉ የመስኖ ልማት በረከት ሆኖም እያገለገለ ይገኛል። የአፋር ክልል ጥጥ የሚለማበት፣ ለአትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም ለቴምር ምርት እምቅ አቅም ያለው መሆኑም ይታወቃል። በአፋሮች ዘንድ ከትውልድ ትውልድ የተላለፉ፣ የሕዝቡን ጠንካራ አብሮነትና ማኅበራዊ ትስስር የሚገልጹ እሴቶችም ልዩ ስፍራ አላቸው። በአፋር ሕዝብ ዘንድ ልዩ ቦታ የሚሰጠው “ዳጉ” እየተባለ የሚጠራው የመረጃ ልውውጥ ከእነዚህ እሴቶች መካከል በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል። የማይቆራረጠውና እሴቱ ተጠብቆ ዘመናትን የዘለቀው የመረጃ መረብ “ዳጉ” የመረጃ ልውውጥ ብቻ ሳይሆን የማኅበራዊ ሕይወት ትስስር መሰረት፣ የእርስ በርስ ቁርኝት ሰንሰለት፣ የአብሮነት ካስማና የትብብር መገለጫቸው ጭምር ነው። በዳጉ የመረጃ ልውውጥ ሥርዓት ውስጥ ሰዎች በመንገድ፣ በገበያ፣ በጉዞ ላይ ወይም በሌላ ማኅበራዊ ግንኙነት ሲገናኙ የሰሙትንና ያዩትን አስፈላጊ መረጃ የሚለዋወጡበት የመረጃ ሰንሰለታቸው ነው። የዳጉ ልዩነት ሰዎች የሚያውቋቸው ወዳጆቻቸውን ብቻ ሳይሆን በመንገድ ላይ የሚያገኟቸውን እንግዶችም ጭምር የመረጃ ልውውጡ አካል ማድረጉ ነው። ሁለት ሰዎች በመንገድ ሲገናኙ እርስ በርሳቸው የሰሙትን፣ ያዩትንና ከሚመጡበት አካባቢ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በመጠያየቅ የመረጃ ልውውጥ ያደርጋሉ። በአፋር ሕዝብ ዘንድ የዳጉ ውይይት የሚጀምርባቸው ጥያቄዎችም ልዩ ትርጉም አላቸው። ከእነዚህም መካከል "ጆሮህ ምን ሰማ?" እና "ዓይንህ ምን አየ?" የሚሉ ጥያቄዎች ይጠቀሳሉ። እነዚህ ጥያቄዎች የሚያመለክቱት መረጃው ከየት እንደመጣ፣ በማን እንደተሰማና በምን ዓይነት ማስረጃ ላይ እንደተመሠረተ ለማወቅ ሚያስችሉ ናቸው። በዚሁ መሰረትም ዳጉ በአፋሮች ዘንድ ከጥንት እስከ ዛሬ የመረጃ መለዋወጫና የማህበራዊ መገለጫ እሴት ሰንሰለት ሆኖ ቀጥሏል። የዳጉ ዋና ዋና ይዘቶችና የመረጃ ሽፋን በአንድ የሕይወት ዘርፍ ብቻ የተገደበ አይደለም። ከግለሰብ ሕይወት እስከ ማኅበረሰብ አጠቃላይ ጉዳዮች ድረስ የሚዘልቅ ሰፊ የመረጃ ሽፋን አለው። በመረጃ ልውውጡ ከሰዎች አልፎ ከእንስሳት በተለይም ከግመሎቻቸው የውሃ እና የግጦሽ ሁኔታ ጋር የተገናኘ ሊሆን ይችላል። የደኅንነት መረጃን መሰረት በማድረግም ስለ ግጭት፣ ስለ አደጋ፣ ስለ የመንገድ ሁኔታና ስለ ሌሎች ሊያስጠነቅቁ የሚችሉ ክስተቶች መረጃ መለዋወጥ የግድ ይላቸዋል። በማህበረሰቡ ዘንድ አዳዲስ ክስተቶች ካሉ፤ የሰርግ እና የለቅሶ ጉዳይና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችም በዳጉ የመረጃ ስርአት የሚቃኙ ይሆናል። በዳጉ የሚረሳ ጉዳይና የሚናቅ መረጃ ባለመኖሩ የእንስሳት የገበያ ዋጋ፣ የምርት ሁኔታ፣ የንግድና ሌሎችም ሁኔታዎች ሊቃኙ ይችላሉ። የአካባቢው የአየር ሁኔታ ተቃኝቶ ዝናብ ስለመኖሩ፣ የጎርፍና ሌሎች ተያያዥ ክስተቶችም ካሉ መረጃው ከአንዱ ጥቅ ወደ ሌላው ጥግ በዳጉ ይደርሳል። የዳጉ ዋነኛ መርህ፡ እውነት፣ ታማኝነትና ኃላፊነት ሲሆን መረጃን ማስተላለፍ ብቻ ሳይሆን የመረጃውን ትክክለኛነትና ምንጩን ማረጋገጥ የግድ ነው። በዳጉ ሥርዓት ውስጥ አንድ ሰው የሰማውን መረጃ ከየት እንደሰማ፣ ከማን እንደተቀበለና ምንጩ ምን እንደሆነ በተሟላ መልኩ የማስተላለፍ ሃላፊነት አለበት። ሐሰተኛ ወይም ያልተረጋገጠ መረጃ ማስተላለፍ በአፋር ባህላዊ ሥርዓት እንደ ከባድ ጥፋት ይቆጠራል። የዳጉን ሥርዓት መጣስም ከባህላዊው የማኅበረሰብ ሕግ ከሆነው ማዳዓ (Mada'a) ጋር በተያያዘ የማኅበረሰቡን ተጠያቂነት ሊያስከትል ይችላል። በዳጉ መርህ መሰረት እውነትን ማስቀደም፣ የመረጃ ምንጭን መግለጽ (መረጃው ከየትና ከማን እንደተገኘ) እንዲሁም ለማኅበረሰቡ ጠቃሚ የሆኑ መረጃዎችን ሳይደብቁ ለሌሎች ማካፈል የግድ ይላል። በመሆኑም ዳጉ የመረጃ ልውውጥ ብቻ ሳይሆን የጠንካራ ማህበራዊ ግንኙነት መሰረት፣ የህዝቡ የሞራልና ስነ ምግባር እሴት መገለጫ ነው ማለት ይቻላል። የዳጉ ሥርዓት ከመረጃ ልውውጥ ባሻገር ሰዎች የሚጠያየቁበት፣ በችግሮቻቸው ዙሪያ ተነጋግረው የሚረዳዱበትም ነው። ለምሳሌ አንድ አርብቶ አደር በሌላ አካባቢ የውሃ ምንጭ መኖሩን ወይም የግጦሽ መሬት መገኘቱን ካወቀ፣ ይህንን መረጃ ለሚያገኘው ሌላ ሰው ያስተላልፋል። ይህም የእንስሳትን ጤና፣ የቤተሰቦችን ኑሮና የማኅበረሰቡን የምግብ ዋስትና ለመጠበቅ ይረዳል። ዳጉ ከሌሎች ባህላዊ የአፋር ማኅበራዊ ተቋማትም ጋር ተያይዞ ይሠራል። ለምሳሌ ዳጉ በማኅበረሰቡ ውስጥ የሚገኝን መረጃ የማሰባሰብና የማስተላለፍ ሚና ሲኖረው፣ አዳ (Adda) የባህላዊ አስተዳደርና ውሳኔ ሰጪነት ሚና ይወጣል። በተጨማሪም ኤዶ (Edo) የግጦሽና የተፈጥሮ ሀብት ሁኔታን ቀድሞ የሚመረምር ባህላዊ ሥርዓት ነው። እነዚህ ሥርዓቶች ተደጋግፈው ለአርብቶ አደሩ የኑሮ ውሳኔዎች ድጋፍ ይሰጣሉ። ዳጉ በዋናነት የመረጃ ልውውጥ ሥርዓት ሲሆን ማዳዓ ደግሞ የአፋር ባህላዊ ሕግና ሥርዓት ነው። የግጭት አፈታት የማኅበረሰብ ሥርዓትና የተጠያቂነት ጉዳዮች ከማዳዓ ጋር ይያያዛሉ። ዳጉ የሚያቀርበው መረጃም በእንዲህ ያሉ ማኅበራዊ ውሳኔዎች ላይ ጠቃሚ መሠረት ሊሆን ይችላል። በዳጉ የቀድሞ የመረጃ ልወውጥ ከአንድ አካባቢ ወደ ሌላ አካባቢ በሰው ለሰው ግንኙነት፣ በጉዞና በቀጥታ ውይይት ይተላለፍ የነበር መሆኑ ይታወቃል። አሁን ላይ ግን የሞባይል ስልክና የዘመናዊ መገናኛ ቴክኖሎጂዎች መስፋፋት የዳጉን የመረጃ ልውውጥ አቅም አስፍተውታል። ሰዎች በአካል ሳይገናኙ ስለ የተለያዩ አካባቢዎች ሁኔታ በስልክ መረጃ መለዋወጥ ይችላሉ። በዘመናዊው የመረጃ መለዋወጫ መንገድ ቢታገዝም የዳጉ መሠረታዊ ባህላዊ መርሆች ግን የተከበሩና የተጠበቁ ናቸው። የመረጃ ምንጭን ማረጋገጥ፣ እውነትን ማስቀደምና ለማኅበረሰቡ ኃላፊነት መውሰድ የዳጉ መሠረታዊ እሴቶች ሆነው ቀጥለዋል። በመሆኑም ዳጉ ከአንድ ትውልድ ወደ ሌላ ትውልድ የተላለፈ የአፋር ሕዝብ የእውቀት ሀብት ነው። በዚህ ሥርዓት ውስጥ ወጣቶች ከአዛውንቶች ብዙ ይማራሉ፤ ልምድን፣ የአካባቢ እውቀትንና ማኅበራዊ ኃላፊነትን ይቀስማሉ። የአፋር አዛውንቶች በሕይወት ያካበቱትን ልምድ ለወጣቶች በማካፈል የዳጉን ሥርዓት እንዲጠብቅና እንዲያስቀጥል ያግዛሉ። የአፋር ሕዝብ ዳጉ በዓለም ላይ ካሉ ልዩ ባህላዊ የመረጃ ልውውጥ ሥርዓቶች መካከል የሚጠቀስ የማንነት መገለጫ ነው። ዘመናዊው ዓለም በኢንተርኔትና በዲጂታል ቴክኖሎጂ መረጃን በሰከንዶች ማስተላለፍ በቻለበት ዘመን፤ ዳጉ ከዘመናት በፊት በሰው ለሰው ግንኙነት የተገነባ የመረጃ መረብ መሆኑ የሚያስደንቅ ነው። በመሆኑም ይህንን እምቅ ሃብት ጠብቆ ለትውልድ ማስተላለፍና የሀገር ሃብት አድርጎ መጠቀም ያስፈልጋል።