ቀጥታ፡

ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴየተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤዎችን እየተቀበሉ ነው

አዲስ አበባ፤ ህዳር 8/2019 (ኢዜአ)፦ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴየተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤዎችን እየተቀበሉ ነው

እስካሁንም የቆጵሮስ፣ የቼክ ሪፐብሊክ እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች አምባሳደሮች የሹመት ደብዳቤ ተቀብለዋል፡፡

በመርሐ ግብሩ ከአፍሪካ፣ ከእስያ፣ ከመካከለኛው ምሥራቅ፣ ከአውሮፓ እና ከካሪቢያን ሀገራት የተወከሉ ተሿሚ አምባሳደሮች በክብር ዘብና በማርሽ ባንድ ሥነ ሥርዓት ታጅበው ደብዳቤያቸውን በማቅረብ ላይ ይገኛሉ፡፡

በዚህም የሰሜን ኮርያ፣ የተባበሩት አረብ ኢመሬትስ፣ የቆጵሮስ፣ የቼክ ሪፐብሊክ፣ አየርላንድ፣ ህንድ፣ ኦስትሪያ፣ ኖርዌይ፣ ፊንላንድ፣ ማልታ፣ ቻድ፣ ደቡብ ኮርያ፣ ጣልያን፣ ባርባዶስ፣ ሉክሰምበርግ እና ግሪናዳ ሀገራት የሹመት ደብዳቤያቸውን ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም