የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሽንፈት አስተናገደ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሽንፈት አስተናገደ
አዲስ አበባ፤ ህዳር 9/2019 (ኢዜአ)፦ በ36ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ አራተኛ መርሐ ግብር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሞዛምቢክ 1 ለ 0 ተሸንፏል።
በባህር ዳር ስታዲየም በተካሄደው የምድብ 10 ጨዋታ ስታንሊ ራቲፎ በ38ኛው ደቂቃ ግቡን አስቆጥሯል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሁለተኛው አጋማሽ የወሰደውን ብልጫ ወደ ግብ መቀየር አልቻለም።
ሞዛምቢክ በመጀመሪያው አጋማሽ የግብ እድሎችን በመፍጠር ተሽላ ተገኝታለች።
ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ በሶስት ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዛለች።
ሞዛምቢክ በሰባት ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።
በምድብ 10 ሴኔጋል በ10 ነጥብ እየመራች ነው። ሱዳን በሶስት ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።
የምድብ አምስተኛ እና ስድስተኛ ጨዋታዎች በመጋቢት ወር 2019 ዓ.ም ይካሄዳሉ።