ጤናማ ኅብረተሰብ የመፍጠር ጉዟችን በቀልጣፋ አገልግሎትና ዘመኑን በዋጀ ስርዓት መከናወን አለበት- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ - ኢዜአ አማርኛ
ጤናማ ኅብረተሰብ የመፍጠር ጉዟችን በቀልጣፋ አገልግሎትና ዘመኑን በዋጀ ስርዓት መከናወን አለበት- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
አዲስ አበባ፤ ህዳር 9/2019 (ኢዜአ)፦ ጤናማ ኅብረተሰብ የመፍጠር ጉዟችን በቀልጣፋ አገልግሎትና ዘመኑን በዋጀ ስርዓት መከናወን አለበት ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልእክት ዛሬ በባሕር ዳር ከተማ በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘውን ምድረ ገነት ጠቅላላ ሆስፒታልን ጎብኝተናል ብለዋል።
ከዚህ ቀደም ተቋርጦ የቆየው ይህ ግንባታ፣ ከስድስት ወራት በፊት በአዲስ ውል እንደገና ተጀምሮ ወደ መጠናቀቂያው ደርሷል ነው ያሉት።
ይህ ባለ አምስት ወለል ዘመናዊ የጤና ተቋም ግንባታ ሲጠናቀቅ ወረቀት አልባ የጤና መረጃ ሥርዓት የሚመራ መሆኑን ጠቁመው፤ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ከሕክምና አገልግሎት ጋር በማቀናጀት የተሻለ የጤና አገልግሎት የሚሰጥ ይሆናል ብለዋል።
የጤና ተቋማትን በአቅም፣ በቴክኖሎጂና በአገልግሎት ማሳደግ ጤናማ ኅብረተሰብን ለመገንባት የምናደርገው ቁርጠኛ ጥረት አካል ነው ሲሉም ገልጸዋል።
S