ቀጥታ፡

ለዋልያዎቹ እስከ መጨረሻው ድረስ ልዩ ድጋፋችሁን ለለገሳችሁ የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ምስጋናዬ የላቀ ነው-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፤ህዳር 8/2019(ኢዜአ)፦ለዋልያዎቹ እስከ መጨረሻው ድረስ ልዩ ድጋፋችሁን ለለገሳችሁ የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች እና መላው ኢትዮጵያዊያን በሙሉ ምስጋናዬ የላቀ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ።

የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት፣ ሽንፈት ለነገው ድል የቤት ስራችንን እንድንሰራ ማሳያችን እንጂ የመጨረሻዎች መጨረሻ አይደለም።

የብሔራዊ ቡድናችን አባላት ድንቅ ጨዋታ ቢያሳዩንም የዛሬው ውጤት ግን አንዳሰብነው አልሆነም ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር፣ እስከ መጨረሻው ድረስ ልዩ ድጋፋችሁን ለለገሳችሁ የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች እና መላው ኢትዮጵያዊያን በሙሉ ምስጋናዬ የላቀ ነው።

ዋሊያዎች ከዛሬው ጨዋታ በመማር በቀጣይ በተሻለ ውጤት ሕዝባችሁን እንደምታስደስቱ ሙሉ እምነት አለኝ ፣በርቱ ሲሉም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም