የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ከአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውጭ ሆነ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ከአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውጭ ሆነ
አዲስ አበባ፤ ህዳር 9/2019 (ኢዜአ)፦ በ23 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ሁለተኛ ዙር የመልስ ጨዋታ ኢትዮጵያ በሞሮኮ 5 ለ 3 ተሸንፋለች።
ማምሻውን በፕሪንስ ሙላይ ኤል ሀሰን ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ናትናኤል ሰለሞን ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ያሬድ ብሩክ ቀሪዋን የኢትዮጵያን ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል።
አሚር ቦሃምዲ፣ ቃይስ ሁዱሲ ባሪ፣ ዩኑስ ኤል ባህራዊ፣ ኦስማን ማማ እና አብዱልሃማድ ማሊ የሞሮኮን ጎሎች አስቆጥረዋል።
ወጣት ብሔራዊ ቡድኑ በሁለተኛው አጋማሽ የተሻለ እንቅስቃሴ አድርጓል።
ውጤቱን ተከትሎ በአሰልጣኝ ዳንኤል ፀሐዬ የሚመራው የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በድምር ውጤት 6 ለ 3 ተሸንፎ ከአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውጪ ሆኗል።
የሞሮኮ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ወደ መጨረሻው ዙር ማጣሪያ አልፏል።
ሞሮኮ የወቅቱ ከ23 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ ናት።
ከ23 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ እ.አ.አ በ2027 በግብጽ አስተናጋጅነት ይካሄዳል።
በውድድሩ ላይ ግብጽን ጨምሮ ስምንት ሀገራት ይሳተፋሉ።
በአፍሪካ ዋንጫው ከአንድ እስከ ሶስት የሚወጡ ብሔራዊ ቡድኖች በቀጥታ እ.አ.አ በ2028 ሎስ አንጀለስ በሚካሄደው 34ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ይሳተፋሉ።
በውድድሩ አራተኛ ደረጃን ይዞ የሚያጠናቅቀው ቡድን ከሌላ አህጉር አራተኛ ደረጃን ከያዘ ቡድን ጋር ለሚደረግ የጥሎ ማለፍ (Play-off) ጨዋታ ያልፋል።