ኢዜአ - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በዩጋንዳ አቻው ተሸነፈ
Oct 7, 2024 31
አዲስ አበባ፤ መስከረም 27/2017 (ኢዜአ) :- የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በ24ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ከዩጋንዳ አቻው ጋር ባደረገው የመጀመሪያ ጨዋታ 3 ለ 0 ተሸንፏል። በምድብ 2 የምትገኘው ኢትዮጵያ ሁለተኛ ጨዋታዋን መስከረም 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከደቡብ ሱዳን ጋር በኪኖንዶኒ ሙኒሲፓል ካውንስል ስታዲየም ከቀኑ 1 ሰዓት ላይ ታደርጋለች። በዚሁ ምድብ ዛሬ ቀን ላይ በተካሄደ ጨዋታ ብሩንዲ ደቡብ ሱዳንን 1 ለ 0 አሸንፋለች። በታንዛንያ የሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ትናንት መጀመሩ ይታወቃል። በምድብ 1 ትናንት በተደረጉ ጨዋታዎች ሱዳን ጅቡቲን 3 ለ 1 እንዲሁም ኬንያ አዘጋጇን ታንዛያን 2 ለ 1 አሸንፈዋል። የማጣሪያ ውድድሩ እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2017 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን በውድድሩ ለፍጻሜ የሚደርሱ ሁለት ሀገራት ለአፍሪካ ዋንጫ ያልፋሉ።
የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በዩጋንዳ አቻው ተሸነፈ
Oct 7, 2024 31
አዲስ አበባ፤ መስከረም 27/2017 (ኢዜአ) :- የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በ24ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ከዩጋንዳ አቻው ጋር ባደረገው የመጀመሪያ ጨዋታ 3 ለ 0 ተሸንፏል። በምድብ 2 የምትገኘው ኢትዮጵያ ሁለተኛ ጨዋታዋን መስከረም 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከደቡብ ሱዳን ጋር በኪኖንዶኒ ሙኒሲፓል ካውንስል ስታዲየም ከቀኑ 1 ሰዓት ላይ ታደርጋለች። በዚሁ ምድብ ዛሬ ቀን ላይ በተካሄደ ጨዋታ ብሩንዲ ደቡብ ሱዳንን 1 ለ 0 አሸንፋለች። በታንዛንያ የሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ትናንት መጀመሩ ይታወቃል። በምድብ 1 ትናንት በተደረጉ ጨዋታዎች ሱዳን ጅቡቲን 3 ለ 1 እንዲሁም ኬንያ አዘጋጇን ታንዛያን 2 ለ 1 አሸንፈዋል። የማጣሪያ ውድድሩ እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2017 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን በውድድሩ ለፍጻሜ የሚደርሱ ሁለት ሀገራት ለአፍሪካ ዋንጫ ያልፋሉ።
በክልሉ በጀትን ለታለመለት ዓላማ በማዋል ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ልማት ይረጋገጣል-ቢሮው
Oct 7, 2024 41
ሀዋሳ፤ መስከረም 27/2017(ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል በጀትን ለታለመለት ዓላማ በማዋል ፈጣንና ቀጣይነት ያለውን ልማት ለማረጋገጥ የተለያየ ተግባር እየተከናወነ መሆኑን የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ አስታወቀ። የክልሉ 7ኛ ዙር የፋይናንስ ሴክተር ጉባዔ ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ተጀምሯል። በጉባዔው ላይ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አራርሶ ገረመው የፋይናንስ ሴክተሩ የመንግስት የልማት ስትራቴጂና የልማት ጥያቄዎችን እውን ለማድረግ ቁልፍ መሣሪያ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል ብለዋል። በዚህ ረገድ የክልሉ መንግስት ባለፉት አራት ዓመታት ዘርፉን በፍትሃዊነትና በውጤታማነት በመምራትና በማስተዳደር በክልሉ ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ልማት እንዲረጋገጥ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ገልፀዋል። በዚህም ለዓመታት ሲንከባለሉ የመጡ ዕዳዎችን ከመቀነስ ባሻገር በመንግሥት የግዥ ሥርዓት ላይ የሚታዩ የአፈጻፀም ጉድለቶችን ለማስተካከል መቻሉንም አክለዋል። በዚህም የህዝብና የመንግስት ሀብትን ከብክነት መታደግ ተችሏል ብለዋል። በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ረገድ የነበሩ ውስንነቶችን በመቅረፍና የክልሉን ገቢ በማሳደግ ወጪን በራስ የመሸፈን አቅም መጨሩንም አመላክተዋል። እንዲሁም ከተለያዩ ምንጮች የሚገኙ ሀብቶችን ለልማት እንዲውሉ መሰራቱንም አስረድተዋል። በ2016 በጀት ዓመት ብቻ 4 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ለካፒታል ፕሮጀክቶች በማዋል ስኬታማ ተግባር መከናወኑን ዶክተር አራርሶ አውስተዋል። በቀጣይም ቢሮው ለፋይናንስ የህግ ማዕቀፎች ተግባራዊነት አበክሮ እንደሚሰራ ገልጸው ለዚህ እውን መሆን ጉባዔው ወሳኝነት እንዳለውም አመልክተዋል። በጉባኤው ላይ የተገኙት የክልሉ መንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ አብርሃም ማርሻሎ በበኩላቸው በክልሉ ያለውን ውስን ሀብት በአግባቡ ለመምራት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል። በክልሉ ውጤታማ የፋይናንስ ስርዓትን በመዘርጋት የተሻለ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል። በተለይም የክልሉ ኢኮኖሚ የሚያመነጨውን ሀብት አሟጦ በመሰብሰብ የተገኘውን ገቢ ግልፅና ተጠያቂነት ያለው አሰራር በመዘርጋት ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ስራ እየተሰራ መሆኑን አክለዋል። ሆኖም በዘርፉ አልፎ አልፎ የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮችን በማስወገድ በቀጣይ የተሻለ ስራ ለመስራት የሚያስችል አቅጣጫ እንደሚቀመጥም አረጋግጠዋል። በሴክተር ጉባኤው ላይ የፋይናንስ ዘርፍ ያለፈው ዓመት አፈፃፀም እና የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ምክክር ተደርጓል። ለሁለት ቀናት በሚካሄደው ጉባኤ ላይም የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በየነ በራሳና የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ደምሴ ዱላቻን ጨምሮ የክልል፣ የዞን፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች እየተሳተፉ ነው።
በክልሉ የተከናወኑ ፍትሃዊ የመንገድ ልማት ተደራሽነትን የማረጋገጥ ተግባራት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ያደርጋሉ
Oct 7, 2024 47
ሀዋሳ፤ መስከረም 27/2017(ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል ፍትሃዊ የመንገድ ልማት ተደራሽነት ለማረጋገጥና የትራንስፖርት አገልግሎት ለማሳለጥ በተከናወኑ ተግባራት የተገኙ ውጤቶች ህብረተሰቡን ተጠቃሚ እንደሚያደርጉ የክልሉ መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ገለፀ። ቢሮው በዓመታዊ የሴክተር ጉባኤው በበጀት አመቱ ትኩረት በተሰጣቸው ጉዳዮች ላይ በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ መክሯል። የቢሮው ኃላፊ አቶ ታምሩ ታፌ እንደገለጹት፤ በክልሉ ፍትሃዊ የመንገድ ልማት ተደራሽነትን የማረጋገጥ ተግባራት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ናቸው። በክልሉ የተከናወኑ የመንገድ ልማት ስራዎች የትራንስፖርት አገልግሎቱን የሚያሳልጡና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴውን በማፋጠን ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ መሆናቸውን ገልጸዋል። በትራንስፖርት ረገድ የተሳለጠ አገልግሎት በመስጠት የተገልጋዩን እርካታ ለማረጋገጥና የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ በአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት ብቃት ማረጋገጫ አሰጣጥ ላይ ትኩረት ተደርጎ መሰራቱን ተናግረዋል። በዚህም በክልሉ የሚገኙ 13 የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት በቴክኖሎጂ የታገዘ ስልጠና እንዲሰጡና የብቃት ማረጋገጫ አሰጣጡ ተገቢውን አሰራር ተከትሎ እንዲከናወን መደረጉን ገልፀዋል። በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀልና ትራፊክ አደጋ መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ካሳ ጨቦ የትራፊክ አደጋ እያስከተለ ያለውን ቀውስ ለመከላከል ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በክልሉ ከ48 ሺህ በላይ ባለሁለት እግር ሞተር ሳይክሎች መኖራቸውን የጠቀሱት ምክትል ኮሚሽሩ አብዛኛው የትራፊክ አደጋ የሚመዘገበው በሞተር ሳይክሎች መሆኑን ገልጸዋል። ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት በተደረገ ጥረትም የትራፊክ አደጋን እና ወንጀልን በመከላከሉ ረገድ ውጤታማ ስራ መሰራቱን ተናግረዋል። የሀዋሳ ከተማ መንገድ ልማትና ትራንስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ አዳነ አየለ በበኩላቸው በከተማዋ የትራንስፖርት አገልግሎት ፍትሃዊ እንዲሆን ተስፋ ሰጪ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ገልጸዋል። በከተማው በሚገኙ ሁለት መናኸሪያዎች በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት በመስጠት ከታሪፍ በላይ ማስከፈልና ትርፍ መጫንን ጨምሮ የተሳፋሪ እንግልት እንዲቀንስ መደረጉን አስረድተዋል። በከተማዋ የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎትን ተደራሽ የማድረግ ተግባራት መከናወናቸውን የገለጹት ኃላፊው በዚህም አበረታች ውጤት መመዝገቡን አክለዋል። በመድረኩም በተገኙ ውጤቶችና በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ውይይት ተደርጎ ከባለድርሻ አካላት ጋር የግብ ስምምነት መደረሱም ተገልጿል።
በአገልግሎት ዘመንዎ የላቀ ስኬት እንዲኖርዎት እመኛለሁ-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Oct 7, 2024 40
አዲስ አበባ፤መስከረም 27/2017(ኢዜአ)፦በአገልግሎት ዘመንዎ የላቀ ስኬት እንዲኖርዎት እመኛለሁ ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ለፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ እንኳን ደስ አለዎት አስተላለፉ። በዚህ ትልቅ የኃላፊነት ቦታ ሀገራችንን በቅንነት፣በጥበብ እና በጥልቅ የዓላማ ስሜት እንደሚያገለግሉ ሙሉ ዕምነት አለኝ ነው ያሉት። አቶ ተመስገን አክለውም፥ በአገልግሎት ዘመንዎ የላቀ ስኬት እንዲኖርዎት እመኛለሁ ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው መልዕክት አስተላልፈዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ በተጨማሪም ላለፉት ስድስት ዓመታት ኢትዮጵያን በፕሬዝደንትነት ላገለገሉት ሣሕለ ወርቅ ዘውዴ ላበረከቱት የላቀ አገልግሎት ምስጋናዬን ለማቅረብ እወዳለሁ ብለዋል፡፡
ፖለቲካ
ማሰልጠኛ ማዕከሉ ብቃት ያለው ወታደር ለማውጣት እያከናወነ ያለው ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል አለበት -ሌተናል ጄኔራል ዓለምሸት ደግፌ
Oct 7, 2024 92
ሀዋሳ ፤መስከረም 27/2017(ኢዜአ)፦ የብላቴ ኮማንዶና አየር ወለድ ማሰልጠኛ ማዕከል የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር የሚችል ብቃት ያለው ወታደር ለማውጣት እያከናወነ ያለው ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ሌተናል ጄኔራል ዓለምእሸት ደግፌ አስታወቁ። የተኩስ አመራር ሃላፊና የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹሙ ከፍተኛ ወታደራዊ አማካሪ ሌተናል ጄኔራል ዓለምሸት ደግፌ የብላቴ ኮማንዶና አየር ወለድ ማሰልጠኛ ማዕከልን የሥራ እንቅስቃሴ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል። በጉብኝቱ ላይ ሌተናል ጄኔራል ዓለምሸት እንዳሉት፣ የብላቴ ኮማንዶና አየር ወለድ ማሰልጠኛ ማዕከል የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚያስጠብቅና በወታደራዊ ዲሲፕሊን የታነጸ ብቁ ሠራዊት በማፍራት ረገድ ትልቅ አስተዋጾ እያደረገ ነው። ማሰልጠኛ ማዕከሉ የሚያሰለጥናቸውን ወታደሮች በአካል ብቃት፣ በስልትና በወታደራዊ ትምህርት በማነጽ ለሀገር ክብር የቆሙ በርካታ ጀግኖችን ማፍራት እንደቻለ ገልጸዋል። ከአካል ብቃት አንስቶ እስከ ስልት ወረዳ ያለውን የስልጠና ሂደት ተዘዋውረው እንደጎበኙ የተናገሩት ሌተናል ጄኔራል ዓለምእሸት፤ በጉብኝቱም ሰልጣኞቹ ጥሩ ስልጠና እንደወሰዱ መረዳታቸውን ተናግረዋል። ማዕከሉ ከአካል ብቃት አንስቶ እስከ ስልት ድረስ ለሚሰጣቸው ስልጠናዎች ምቹ የማሰልጠኛ ስፍራዎችን በማዘጋጀት ሰልጣኞቹ ብቁ ወታደር ሆነው እንዲወጡ ለማድረግ እያከናወነ ያለው ሥራ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጠቁመዋል። "ታሪካዊ ጠላቶቻችን አስተባባሪነት የውስጥ ታጣቂ ሽፍቶችን በመጠቀም ሀገራችንን ለማተራመስ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ እንደማይሳካላቸው የሠራዊታቸው አቋም አመላካች ነው" ብለዋል። የውጭ ሀይሎች ፍላጎት በፍጹም የሚሳካ እንዳልሆነ የገለጹት ሌተናል ጄነራሉ፣ "በማሰልጠኛው ያየነው ስልጠናና የሰልጣኞች አቅም የጥፋት ሀይሎች ተልዕኮ እንደማይሳካ አመላካች መሆኑን ተናግረዋል። በብላቴ ኮማንዶና አየር ወለድ ማሰልጠኛ ስልጠና ከወሰዱ ውስጥ መሰረታዊ ወታደር ነጻነት ታከለ እንዳለችው በማዕከሉ ላለፉት አራት ወራት ስልጠና መውሰዷን ተናግራለች። “ይህም በስነ ልቡናና በአካል ብቃት እንድጎለበት አድርጎኛል፤ አሁን ብቁ በመሆኔ ለሚሰጠኝም ማንኛውንም ግዳጅ በብቃት ለመወጣት ዝግጁ ነኝ” ብላለች። ሌላው አስተያየት ሰጪ መሰረታዊ ወታደር ዮናስ ሞሲሳ ማሰልጠኛ ከገባሁ በኋላ ሥነልቦናዬንና አካል ብቃቴን የሚያሳድጉ ስልጠናዎችን ወስጂያለሁ ብሏል። የብላቴ ኮማንዶና አየር ወለድ ማሰልጠኛ ማዕከል ትናንት ሁለተኛ ዙር መሰረታዊ ወታደሮችን አስልጥኖ ማስመረቁ የሚታወስ ነው። ማዕከሉ የኮማንዶ፣ የአየር ወለድ ማሰልጠኛ፣ የልዩ ሃይል ጸረ ሽብር ማሰልጠኛና የአመራር ማሰልጠኛ ትምህርት ቤቶችን በማደራጀት የተሰጠውን ግዳጅ በብቃት እየተወጣ የሚገኝ ማሰልጠኛ ማዕከል መሆኑም ተገልጿል።
ሀገራዊ ምክክሩ በኢትዮጵያ በሁሉም መስክ ሰላምን ለማረጋገጥ የተያዘው ቁርጠኝነት ማሳያ ነው -ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ
Oct 7, 2024 117
አዲስ አበባ፤መስከረም 27/2017(ኢዜአ)፦ሀገራዊ ምክክሩ በኢትዮጵያ በሁሉም መስክ ሰላምን ለማረጋገጥ የተያዘው ቁርጠኝነት ማሳያ ነው ሲሉ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴን ተናገሩ ። 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ይገኛል። በዚሁ ጊዜ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሆነው ተሰይመዋል። ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ለሁለቱ ምክር ቤቶች መክፈቻ ባደረጉት ንግግር፤ በአገሪቱ በሁሉም መስክ ሰላምን የማረጋገጥ ስራ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ብለዋል። በዚህም የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ስራ በሁሉም መስክ ሰላምን ለማረጋገጥ የተያዘው ቁርጠኝነት ማሳያ ነው ሲሉ ተናግረዋል። በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ኮሚሽኑ የቅድመ ዝግጅት ምዕራፉን አጠናቆ ወደ ስራ ገብቷል ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ ኮሚሽኑም በአዲስ አበባና በሌሎች ክልሎች ግብዓትና ጥያቄዎች ማሰባሰብ መቻሉን ተናግረዋል፡፡ እነዚህ ጥረቶች በቀጣይ በሀገረ መንግስት ግንባታ ላይ የሚኖራቸው ጉልህ ሚና ከፍተኛ ነው ሲሉ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል። እጅግ መሰረታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ አካታች አገራዊ ምክክር በማካሄድ የተሻለ አገራዊ መግባባት ለመፍጠር እየተሰራ ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ ይህም በአገሪቱ የመቀራረብና የመተማመን ስራን ለመስራት ያግዛል ነው ያሉት። እንዲሁም እየተሸረሸሩ ያሉ ማህበራዊ እሴቶችን ለማደስ የሚያስችሉ ስርዓትን ለመዘርጋት ያስችላል ብለዋል። ይህም ኢትዮጵያ ሁላችንንም እንድትመስል የሚደረገው ጥረት አጋዥ በመሆኑ ኮሚሽኑ የታለመለትን ዓላማ እንዲያሳካ የሁላችንንም ጥረት ይጠይቃል ብለዋል።
ኢትዮጵያ በሰጥቶ መቀበል መርህ አማራጭ የወደብ እና የባህር በር ለማግኘት የጀመረችው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል - ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀስላሴ
Oct 7, 2024 150
አዲስ አበባ፤መስከረም 27/2017 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በሰጥቶ መቀበል መርህ አማራጭ የወደብ እና የባህር በር ለማግኘት የጀመረችው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ ገለጹ። የኢትዮጵያን ወዳጆች እና አጋሮች የማበርከትና የማብዛት ስራም በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል። 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ዛሬ ተካሄዷል። ፕሬዝዳንት አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ለሁለቱ የፌዴራል መንግሥት ምክር ቤቶች ዓመታዊ ሥራቸውን መጀመራቸውን በማብሰር የፌዴራል መንግሥቱን ዓመታዊ ዕቅድ አቅርበዋል። በዲፕሎማሲው ረገድ ከጎረቤት አገሮች ጋር ያለንን ሁለንተናዊ ግንኙነቶችን በማጠናከር አገራዊ ጥቅሞችን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በሰላምና በጸጥታ ጉዳይ በኢኮኖሚ ጉዳዮች በቀጣናዊ ትስስር የጋራ ጥቅም የሚያስገኙ ስራዎች ትኩረት እንደተሰጣቸውም አመልክተዋል። ኢትዮጵያ ሰጥቶ በመቀበል መርህ አማራጭ የወደብ እና የባህር በር እንድታገኝ በሰጥቶ መቀበል መርህ የተጀመረው ጥረት መሰረት ያደረገ የመግባቢያ ስምምነት ከሶማሊያላንድ ጋር መፈረሙን ተናግረዋል። በዚህ ምክንያት የተፈጠረውን አላስፈላጊ የዲፕሎማሲ ትኩሳት ለማርገብ እና የአገርን ስም ለማጠልሸት የሚካሄደውን ዘመቻ ለመከላከል በርካታ ስራዎች መከናወናቸውን ነው የገለጹት። ኢትዮጵያ በቀጣናው በጋራ የመልማት እና በጋራ የማደግ ፍላጎቷን እውን ለማድረግ የጀመረችውን ጥረት አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ያላትን ተደማጭነት በማስፋት ዘላቂ ብሔራዊ ጥቅሞቿን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ጉልህ ስራዎች መከናወናቸውንና ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል። በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እንዲሰፍን በተለይም የሱዳን ግጭት እንዲፈታ ኢትዮጵያ የጀመረችው ግልጽና ተከታታይነት ያለው የሰላም ዲፕሎማሲ ስራ እንደሚቀጥልም ነው ያብራሩት። ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ደህንት እንዲረጋገጥ ጉልህ ተሳትፎ እንደምታደርግም ጠቅሰዋል። በሁለትዮሽ ግንኙነት ብሔራዊ ጥቅሞችን በማስጠበቅ ከቻይና ጋር ያለንን ግንኙነት በወቅቶች የማይለውጥ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ከፍ እንዲል መደረጉን አንስተዋል። ፓለቲካዊ፣ ወታደራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አቅም ካላቸው የባህረ ሰላጤው አገራት ጋር ጠንካራ ግንኙነት ለመፍጠር መቻሉንም አንስተዋል። ኢትዮጵያ የብሪክስ ሙሉ አባል መሆኗ ሚዛናዊ ግንኙነት እንዲኖራትና ዘርፈ ብዙ ትሩፋቶችን ለማግኘት እንደሚያስችላትም አንስተዋል። በባለ ብዝሃ ወገን የዲፕሎማሲ መድረክ የኢትዮጵያ ተደማጭነት እና በጎ ተጽእኖ ፈጣሪነት የሚያሳድጉ ጉልህ ስራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል። በቀጣይ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ማጠናከር እና አዳዲስ ስትራቴጂካዊ አጋሮችን የመፍጠር ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው ያመለከቱት። ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሕብረት እና ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ያላትን ትብብር ለማጠናከር ትሰራለች ብለዋል። የኢትዮጵያን ወዳጆች እና አጋሮች የማበርከትና የማብዛት ስራ በትኩረት እንደሚሰራበትም አመልክተዋል።
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ደኅንነት አስተማማኝ እንዲሆንና የጋራ ልማት ለማረጋገጥ በትኩረት ትሰራለች-ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀስላሴ
Oct 7, 2024 103
አዲስ አበባ፤ መስከረም 27/2017(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ደኅንነት አስተማማኝ እንዲሆንና የጋራ ልማት ለማረጋገጥ በትኩረት እንደምትሰራ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀስላሴ ገለጹ፡፡ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል፡፡ በዚሁ ጊዜ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሆነው ተሰይመዋል። ፕሬዝዳንቱ በመክፈቻ ንግግራቸው፤ የአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ደህንነት አስተማማኝ እንዲሆን ኢትዮጵያ ብርቱ ጥረት ማድረጓን ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ሰላምና ደህንነት በማረጋገጥ በጋራ መልማት እንዲሁም በቀጣናዊ ትስስር ላይ ትኩረት ያደረጉ ሥራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በሰጥቶ መቀበል መርህ አማራጭ ወደብና የባህር በር ተጠቃሚ ለመሆን ከሶማሌላንድ ጋር የመግባቢያ ስምምነት መፈረሙን አንስተዋል፡፡ ይሁን እንጂ ከዚህ ጋር በተያያዘ የተፈጠረውን ዲፕሎማሲያዊ ትኩሳት ለማርገብ በርካታ ሥራዎች ተሰርተዋል ብለዋል፡፡ በተጨማሪም ኢትዮጵያ በቀጣናው ያላትን ተደማጭነት በማስፋት በቀጣናው ብሔራዊ ጥቅሟን ማስከበር የሚያስችሉ ሥራዎች መከናወናቸውንም ገልጸዋል፡፡ በሱዳን የተከሰተው ግጭት በሰላማዊ መንገድ እልባት አግኝቶ በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እንዲሰፍን ኢጋድና የአፍሪካ ህብረት ከሚያደርጉት ጥረት በተጨማሪ ኢትዮጵያም ግልጽና ተከታታይ የሰላም ዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ እያደረገች መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በሁለትዮሽ ግንኙነት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸውን አንስተው፤ ከቻይና ጋር ያለውን ግንኙነት በወቅቶች የማይለዋወጥ ስትራቴጂያዊ አጋርነት ማሸጋገር ተችሏል ብለዋል፡፡ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ወታደራዊ አቅም ካላቸው የባህረ ሰላጤው ሀገራት ጋር ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መፍጠር መቻሉንም ጠቁመዋል፡፡ የኢትዮጵያን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ወደ መደበኛና ከፍ ወዳለ ደረጃ በማሸጋገር ነባር ስትራቴጂያዊ ግንኙነቶችን ማጠናከርና አዳዲስ ግኑኝነት መፍጠር ተችሏል ብለዋል፡፡ በባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ የኢትዮጵያ ተደማጭነትና ተጽፅኖ ፈጣሪነት እንዲጎለብት መደረጉን ገልጸው፤ ኢትዮጵያ የብሪክስ ሙሉ አባል እንድትሆን የተከናወኑ ተግባራትንም ለአብነት አንስተዋል፡፡ በቀጣይም የአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ደኅንነት አስተማማኝ እንዲሆንና የጋራ ልማት ለማረጋገጥ በትኩረት ይሰራል ብለዋል። የኢትዮጵያን ወዳጆች የማብዛት ሥራም በስፋት እንደሚከናወን ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ የእንኳን ደስ ያለዎት መልዕክት አስተላለፉ
Oct 7, 2024 89
አዲስ አበባ፤ መስከረም 27/2017(ኢዜአ)፦የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ፕሬዝዳንት ሆነው በመሾማቸው የእንኳን ደስ ያለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል። ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሆነው በመሾምዎ እንኳን ደስ ያለዎት ሲሉ አስፍረዋል። በቀጣይ የስራ ዘመናቸውም ፕሬዝዳንቱ መልካም የስራ ጊዜ እንዲሆንላቸው ከንቲባዋ ምኞታቸውን ገልጸዋል።
አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ
Oct 7, 2024 134
አዲስ አበባ፤መስከረም 27/2017 (ኢዜአ) ፡- አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሆነው ተሹመዋል። የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሆነው የተሾሙት አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ቃለ-መሐላ ፈጽመዋል። 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ይገኛል። አምባሳደር ታዬ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሆነው ከመሾማቸው በፊትም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው በማገልገል ላይ ነበሩ፡፡
አቶ አገኘሁ ተሻገር በሩሲያ ሴናተር ኒኮላይ ቪላዲሚሮቭ ከተመራ የልዑክ ቡድን ጋር ተወያዩ
Oct 7, 2024 83
አዲስ አበባ፤ መስከረም 27/2017(ኢዜአ)፡- የፌዴሬሸን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር በሩሲያ ሴናተር ኒኮላይ ቪላዲሚሮቭ ከተመራው የልዑክ ቡድን ጋር ተወያይተዋል። አቶ አገኘሁ ኢትዮጵያ እና ሩሲያ የረጅም ዘመን የታሪክና የባህል ግንኙነት እንዳላቸው አስታውሰው የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን ገልጸዋል። ቀደም ሲል ሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ መፈራረማቸውና ስምምነቱ ፈጥኖ ወደ ተግባር እንዲገባ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ አመልክተዋል። ምክር ቤቱ በብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች አስተዳደር ዙሪያ ከሩሲያ ጋር የልምድ ልውውጥ ማድረግ እንደሚፈልግ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በአቅም ግንባታ፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የሩሲያን ድጋፍ እንደማይለያት የጠቀሱት አቶ አገኘሁ በብሪክስ አባል ሀገራት የሚወሰኑ ውሳኔዎችን ተግባራዊ ለማድረግ ኢትዮጵያ ተግታ እንደምትሰራም ነው የገለጹት። የሩሲያና የዩክሬን ጦርነት በሰላማዊ መንገድ በውይይት እንዲፈታ የኢትዮጵያ ምኞት እንደሆነም ተናግረዋል። የሩሲያው ሴናተር ኒኮላይ ቪላዲሚሮቭ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ በላይ ለሩሲያ ጠንካራ ወዳጅ ሀገር መሆኗን ገልጸዋል። ሩሲያ በትምህርት፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ በባህል ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥልም አመልክተዋል። የሩሲያን ትምህርት ቤት በኢትዮጵያ የመክፈት ፍላጎት እንዳለም አንስተዋል። ሩሲያ የብሪክስ አባል ሀገራት ሰብሳቢ በመሆኗ አባላቱ በትብብርና በቅንጅት እንዲሰሩ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደምታደርግ ተናግረዋል። በውይይቱ ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከፍተኛ አመራሮች፣ የቋሚ ኮሚቴ አባላትና የጽህፈት ቤቱ የማኔጅመንት ቡድን መገኘቱን ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
የፌዴሬሽን ምክር ቤት የድጎማ በጀትና የጋራ ገቢዎች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ለምክር ቤቱ በሚቀርቡ የውሳኔ ሃሳቦች ላይ ውይይት አካሄደ
Oct 7, 2024 85
አዲስ አበባ፤ መስከረም 27/2017 (ኢዜአ)፡- የፌዴሬሽን ምክር ቤት የድጎማ በጀትና የጋራ ገቢዎች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ለምክር ቤቱ በሚቀርቡ የውሳኔ ሃሳቦች ላይ ምክክር አድርጓል። ቋሚ ኮሚቴው እየተወያየ የሚገኘው ምክር ቤቱ ነገ ለሚያካሂደው 6ኛ የፓርላማ ዘመን 4ኛ የሥራ ጊዜ፣ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ቀርበው በሚፀድቁ የውሳኔ ሃሳቦች ላይ ነው። ውይይቱ የተመራው በቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ሽመልስ አብዲሳ ነው። አቶ ሽመልስ በ2017 በጀት ዓመት የሚያከናውናቸው ዝርዝር ተግባራት የተካተቱበት እቅድ እንዲቀርብ በጠየቁት መሠረት የቋሚ ኮሚቴው ፀሐፊ አቶ ኃይሉ ኢፋ እቅዱን አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል። በቋሚ ኮሚቴው አባላት የተሰጡ ግብዓቶች ጠቃሚዎች በመሆናቸው ለምክር ቤቱ በሚቀርበው የቋሚ ኮሚቴው የውሳኔ ሃሳብ ላይ እንዲካተት አቶ ሽመልስ ማሳሰባቸውን ከፌዴሬሽን ምክር ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ፖለቲካ
ማሰልጠኛ ማዕከሉ ብቃት ያለው ወታደር ለማውጣት እያከናወነ ያለው ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል አለበት -ሌተናል ጄኔራል ዓለምሸት ደግፌ
Oct 7, 2024 92
ሀዋሳ ፤መስከረም 27/2017(ኢዜአ)፦ የብላቴ ኮማንዶና አየር ወለድ ማሰልጠኛ ማዕከል የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር የሚችል ብቃት ያለው ወታደር ለማውጣት እያከናወነ ያለው ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ሌተናል ጄኔራል ዓለምእሸት ደግፌ አስታወቁ። የተኩስ አመራር ሃላፊና የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹሙ ከፍተኛ ወታደራዊ አማካሪ ሌተናል ጄኔራል ዓለምሸት ደግፌ የብላቴ ኮማንዶና አየር ወለድ ማሰልጠኛ ማዕከልን የሥራ እንቅስቃሴ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል። በጉብኝቱ ላይ ሌተናል ጄኔራል ዓለምሸት እንዳሉት፣ የብላቴ ኮማንዶና አየር ወለድ ማሰልጠኛ ማዕከል የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚያስጠብቅና በወታደራዊ ዲሲፕሊን የታነጸ ብቁ ሠራዊት በማፍራት ረገድ ትልቅ አስተዋጾ እያደረገ ነው። ማሰልጠኛ ማዕከሉ የሚያሰለጥናቸውን ወታደሮች በአካል ብቃት፣ በስልትና በወታደራዊ ትምህርት በማነጽ ለሀገር ክብር የቆሙ በርካታ ጀግኖችን ማፍራት እንደቻለ ገልጸዋል። ከአካል ብቃት አንስቶ እስከ ስልት ወረዳ ያለውን የስልጠና ሂደት ተዘዋውረው እንደጎበኙ የተናገሩት ሌተናል ጄኔራል ዓለምእሸት፤ በጉብኝቱም ሰልጣኞቹ ጥሩ ስልጠና እንደወሰዱ መረዳታቸውን ተናግረዋል። ማዕከሉ ከአካል ብቃት አንስቶ እስከ ስልት ድረስ ለሚሰጣቸው ስልጠናዎች ምቹ የማሰልጠኛ ስፍራዎችን በማዘጋጀት ሰልጣኞቹ ብቁ ወታደር ሆነው እንዲወጡ ለማድረግ እያከናወነ ያለው ሥራ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጠቁመዋል። "ታሪካዊ ጠላቶቻችን አስተባባሪነት የውስጥ ታጣቂ ሽፍቶችን በመጠቀም ሀገራችንን ለማተራመስ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ እንደማይሳካላቸው የሠራዊታቸው አቋም አመላካች ነው" ብለዋል። የውጭ ሀይሎች ፍላጎት በፍጹም የሚሳካ እንዳልሆነ የገለጹት ሌተናል ጄነራሉ፣ "በማሰልጠኛው ያየነው ስልጠናና የሰልጣኞች አቅም የጥፋት ሀይሎች ተልዕኮ እንደማይሳካ አመላካች መሆኑን ተናግረዋል። በብላቴ ኮማንዶና አየር ወለድ ማሰልጠኛ ስልጠና ከወሰዱ ውስጥ መሰረታዊ ወታደር ነጻነት ታከለ እንዳለችው በማዕከሉ ላለፉት አራት ወራት ስልጠና መውሰዷን ተናግራለች። “ይህም በስነ ልቡናና በአካል ብቃት እንድጎለበት አድርጎኛል፤ አሁን ብቁ በመሆኔ ለሚሰጠኝም ማንኛውንም ግዳጅ በብቃት ለመወጣት ዝግጁ ነኝ” ብላለች። ሌላው አስተያየት ሰጪ መሰረታዊ ወታደር ዮናስ ሞሲሳ ማሰልጠኛ ከገባሁ በኋላ ሥነልቦናዬንና አካል ብቃቴን የሚያሳድጉ ስልጠናዎችን ወስጂያለሁ ብሏል። የብላቴ ኮማንዶና አየር ወለድ ማሰልጠኛ ማዕከል ትናንት ሁለተኛ ዙር መሰረታዊ ወታደሮችን አስልጥኖ ማስመረቁ የሚታወስ ነው። ማዕከሉ የኮማንዶ፣ የአየር ወለድ ማሰልጠኛ፣ የልዩ ሃይል ጸረ ሽብር ማሰልጠኛና የአመራር ማሰልጠኛ ትምህርት ቤቶችን በማደራጀት የተሰጠውን ግዳጅ በብቃት እየተወጣ የሚገኝ ማሰልጠኛ ማዕከል መሆኑም ተገልጿል።
ሀገራዊ ምክክሩ በኢትዮጵያ በሁሉም መስክ ሰላምን ለማረጋገጥ የተያዘው ቁርጠኝነት ማሳያ ነው -ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ
Oct 7, 2024 117
አዲስ አበባ፤መስከረም 27/2017(ኢዜአ)፦ሀገራዊ ምክክሩ በኢትዮጵያ በሁሉም መስክ ሰላምን ለማረጋገጥ የተያዘው ቁርጠኝነት ማሳያ ነው ሲሉ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴን ተናገሩ ። 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ይገኛል። በዚሁ ጊዜ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሆነው ተሰይመዋል። ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ለሁለቱ ምክር ቤቶች መክፈቻ ባደረጉት ንግግር፤ በአገሪቱ በሁሉም መስክ ሰላምን የማረጋገጥ ስራ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ብለዋል። በዚህም የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ስራ በሁሉም መስክ ሰላምን ለማረጋገጥ የተያዘው ቁርጠኝነት ማሳያ ነው ሲሉ ተናግረዋል። በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ኮሚሽኑ የቅድመ ዝግጅት ምዕራፉን አጠናቆ ወደ ስራ ገብቷል ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ ኮሚሽኑም በአዲስ አበባና በሌሎች ክልሎች ግብዓትና ጥያቄዎች ማሰባሰብ መቻሉን ተናግረዋል፡፡ እነዚህ ጥረቶች በቀጣይ በሀገረ መንግስት ግንባታ ላይ የሚኖራቸው ጉልህ ሚና ከፍተኛ ነው ሲሉ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል። እጅግ መሰረታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ አካታች አገራዊ ምክክር በማካሄድ የተሻለ አገራዊ መግባባት ለመፍጠር እየተሰራ ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ ይህም በአገሪቱ የመቀራረብና የመተማመን ስራን ለመስራት ያግዛል ነው ያሉት። እንዲሁም እየተሸረሸሩ ያሉ ማህበራዊ እሴቶችን ለማደስ የሚያስችሉ ስርዓትን ለመዘርጋት ያስችላል ብለዋል። ይህም ኢትዮጵያ ሁላችንንም እንድትመስል የሚደረገው ጥረት አጋዥ በመሆኑ ኮሚሽኑ የታለመለትን ዓላማ እንዲያሳካ የሁላችንንም ጥረት ይጠይቃል ብለዋል።
ኢትዮጵያ በሰጥቶ መቀበል መርህ አማራጭ የወደብ እና የባህር በር ለማግኘት የጀመረችው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል - ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀስላሴ
Oct 7, 2024 150
አዲስ አበባ፤መስከረም 27/2017 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በሰጥቶ መቀበል መርህ አማራጭ የወደብ እና የባህር በር ለማግኘት የጀመረችው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ ገለጹ። የኢትዮጵያን ወዳጆች እና አጋሮች የማበርከትና የማብዛት ስራም በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል። 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ዛሬ ተካሄዷል። ፕሬዝዳንት አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ለሁለቱ የፌዴራል መንግሥት ምክር ቤቶች ዓመታዊ ሥራቸውን መጀመራቸውን በማብሰር የፌዴራል መንግሥቱን ዓመታዊ ዕቅድ አቅርበዋል። በዲፕሎማሲው ረገድ ከጎረቤት አገሮች ጋር ያለንን ሁለንተናዊ ግንኙነቶችን በማጠናከር አገራዊ ጥቅሞችን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በሰላምና በጸጥታ ጉዳይ በኢኮኖሚ ጉዳዮች በቀጣናዊ ትስስር የጋራ ጥቅም የሚያስገኙ ስራዎች ትኩረት እንደተሰጣቸውም አመልክተዋል። ኢትዮጵያ ሰጥቶ በመቀበል መርህ አማራጭ የወደብ እና የባህር በር እንድታገኝ በሰጥቶ መቀበል መርህ የተጀመረው ጥረት መሰረት ያደረገ የመግባቢያ ስምምነት ከሶማሊያላንድ ጋር መፈረሙን ተናግረዋል። በዚህ ምክንያት የተፈጠረውን አላስፈላጊ የዲፕሎማሲ ትኩሳት ለማርገብ እና የአገርን ስም ለማጠልሸት የሚካሄደውን ዘመቻ ለመከላከል በርካታ ስራዎች መከናወናቸውን ነው የገለጹት። ኢትዮጵያ በቀጣናው በጋራ የመልማት እና በጋራ የማደግ ፍላጎቷን እውን ለማድረግ የጀመረችውን ጥረት አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ያላትን ተደማጭነት በማስፋት ዘላቂ ብሔራዊ ጥቅሞቿን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ጉልህ ስራዎች መከናወናቸውንና ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል። በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እንዲሰፍን በተለይም የሱዳን ግጭት እንዲፈታ ኢትዮጵያ የጀመረችው ግልጽና ተከታታይነት ያለው የሰላም ዲፕሎማሲ ስራ እንደሚቀጥልም ነው ያብራሩት። ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ደህንት እንዲረጋገጥ ጉልህ ተሳትፎ እንደምታደርግም ጠቅሰዋል። በሁለትዮሽ ግንኙነት ብሔራዊ ጥቅሞችን በማስጠበቅ ከቻይና ጋር ያለንን ግንኙነት በወቅቶች የማይለውጥ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ከፍ እንዲል መደረጉን አንስተዋል። ፓለቲካዊ፣ ወታደራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አቅም ካላቸው የባህረ ሰላጤው አገራት ጋር ጠንካራ ግንኙነት ለመፍጠር መቻሉንም አንስተዋል። ኢትዮጵያ የብሪክስ ሙሉ አባል መሆኗ ሚዛናዊ ግንኙነት እንዲኖራትና ዘርፈ ብዙ ትሩፋቶችን ለማግኘት እንደሚያስችላትም አንስተዋል። በባለ ብዝሃ ወገን የዲፕሎማሲ መድረክ የኢትዮጵያ ተደማጭነት እና በጎ ተጽእኖ ፈጣሪነት የሚያሳድጉ ጉልህ ስራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል። በቀጣይ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ማጠናከር እና አዳዲስ ስትራቴጂካዊ አጋሮችን የመፍጠር ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው ያመለከቱት። ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሕብረት እና ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ያላትን ትብብር ለማጠናከር ትሰራለች ብለዋል። የኢትዮጵያን ወዳጆች እና አጋሮች የማበርከትና የማብዛት ስራ በትኩረት እንደሚሰራበትም አመልክተዋል።
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ደኅንነት አስተማማኝ እንዲሆንና የጋራ ልማት ለማረጋገጥ በትኩረት ትሰራለች-ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀስላሴ
Oct 7, 2024 103
አዲስ አበባ፤ መስከረም 27/2017(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ደኅንነት አስተማማኝ እንዲሆንና የጋራ ልማት ለማረጋገጥ በትኩረት እንደምትሰራ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀስላሴ ገለጹ፡፡ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል፡፡ በዚሁ ጊዜ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሆነው ተሰይመዋል። ፕሬዝዳንቱ በመክፈቻ ንግግራቸው፤ የአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ደህንነት አስተማማኝ እንዲሆን ኢትዮጵያ ብርቱ ጥረት ማድረጓን ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ሰላምና ደህንነት በማረጋገጥ በጋራ መልማት እንዲሁም በቀጣናዊ ትስስር ላይ ትኩረት ያደረጉ ሥራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በሰጥቶ መቀበል መርህ አማራጭ ወደብና የባህር በር ተጠቃሚ ለመሆን ከሶማሌላንድ ጋር የመግባቢያ ስምምነት መፈረሙን አንስተዋል፡፡ ይሁን እንጂ ከዚህ ጋር በተያያዘ የተፈጠረውን ዲፕሎማሲያዊ ትኩሳት ለማርገብ በርካታ ሥራዎች ተሰርተዋል ብለዋል፡፡ በተጨማሪም ኢትዮጵያ በቀጣናው ያላትን ተደማጭነት በማስፋት በቀጣናው ብሔራዊ ጥቅሟን ማስከበር የሚያስችሉ ሥራዎች መከናወናቸውንም ገልጸዋል፡፡ በሱዳን የተከሰተው ግጭት በሰላማዊ መንገድ እልባት አግኝቶ በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እንዲሰፍን ኢጋድና የአፍሪካ ህብረት ከሚያደርጉት ጥረት በተጨማሪ ኢትዮጵያም ግልጽና ተከታታይ የሰላም ዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ እያደረገች መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በሁለትዮሽ ግንኙነት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸውን አንስተው፤ ከቻይና ጋር ያለውን ግንኙነት በወቅቶች የማይለዋወጥ ስትራቴጂያዊ አጋርነት ማሸጋገር ተችሏል ብለዋል፡፡ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ወታደራዊ አቅም ካላቸው የባህረ ሰላጤው ሀገራት ጋር ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መፍጠር መቻሉንም ጠቁመዋል፡፡ የኢትዮጵያን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ወደ መደበኛና ከፍ ወዳለ ደረጃ በማሸጋገር ነባር ስትራቴጂያዊ ግንኙነቶችን ማጠናከርና አዳዲስ ግኑኝነት መፍጠር ተችሏል ብለዋል፡፡ በባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ የኢትዮጵያ ተደማጭነትና ተጽፅኖ ፈጣሪነት እንዲጎለብት መደረጉን ገልጸው፤ ኢትዮጵያ የብሪክስ ሙሉ አባል እንድትሆን የተከናወኑ ተግባራትንም ለአብነት አንስተዋል፡፡ በቀጣይም የአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ደኅንነት አስተማማኝ እንዲሆንና የጋራ ልማት ለማረጋገጥ በትኩረት ይሰራል ብለዋል። የኢትዮጵያን ወዳጆች የማብዛት ሥራም በስፋት እንደሚከናወን ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ የእንኳን ደስ ያለዎት መልዕክት አስተላለፉ
Oct 7, 2024 89
አዲስ አበባ፤ መስከረም 27/2017(ኢዜአ)፦የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ፕሬዝዳንት ሆነው በመሾማቸው የእንኳን ደስ ያለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል። ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሆነው በመሾምዎ እንኳን ደስ ያለዎት ሲሉ አስፍረዋል። በቀጣይ የስራ ዘመናቸውም ፕሬዝዳንቱ መልካም የስራ ጊዜ እንዲሆንላቸው ከንቲባዋ ምኞታቸውን ገልጸዋል።
አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ
Oct 7, 2024 134
አዲስ አበባ፤መስከረም 27/2017 (ኢዜአ) ፡- አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሆነው ተሹመዋል። የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሆነው የተሾሙት አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ቃለ-መሐላ ፈጽመዋል። 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ይገኛል። አምባሳደር ታዬ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሆነው ከመሾማቸው በፊትም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው በማገልገል ላይ ነበሩ፡፡
አቶ አገኘሁ ተሻገር በሩሲያ ሴናተር ኒኮላይ ቪላዲሚሮቭ ከተመራ የልዑክ ቡድን ጋር ተወያዩ
Oct 7, 2024 83
አዲስ አበባ፤ መስከረም 27/2017(ኢዜአ)፡- የፌዴሬሸን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር በሩሲያ ሴናተር ኒኮላይ ቪላዲሚሮቭ ከተመራው የልዑክ ቡድን ጋር ተወያይተዋል። አቶ አገኘሁ ኢትዮጵያ እና ሩሲያ የረጅም ዘመን የታሪክና የባህል ግንኙነት እንዳላቸው አስታውሰው የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን ገልጸዋል። ቀደም ሲል ሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ መፈራረማቸውና ስምምነቱ ፈጥኖ ወደ ተግባር እንዲገባ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ አመልክተዋል። ምክር ቤቱ በብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች አስተዳደር ዙሪያ ከሩሲያ ጋር የልምድ ልውውጥ ማድረግ እንደሚፈልግ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በአቅም ግንባታ፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የሩሲያን ድጋፍ እንደማይለያት የጠቀሱት አቶ አገኘሁ በብሪክስ አባል ሀገራት የሚወሰኑ ውሳኔዎችን ተግባራዊ ለማድረግ ኢትዮጵያ ተግታ እንደምትሰራም ነው የገለጹት። የሩሲያና የዩክሬን ጦርነት በሰላማዊ መንገድ በውይይት እንዲፈታ የኢትዮጵያ ምኞት እንደሆነም ተናግረዋል። የሩሲያው ሴናተር ኒኮላይ ቪላዲሚሮቭ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ በላይ ለሩሲያ ጠንካራ ወዳጅ ሀገር መሆኗን ገልጸዋል። ሩሲያ በትምህርት፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ በባህል ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥልም አመልክተዋል። የሩሲያን ትምህርት ቤት በኢትዮጵያ የመክፈት ፍላጎት እንዳለም አንስተዋል። ሩሲያ የብሪክስ አባል ሀገራት ሰብሳቢ በመሆኗ አባላቱ በትብብርና በቅንጅት እንዲሰሩ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደምታደርግ ተናግረዋል። በውይይቱ ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከፍተኛ አመራሮች፣ የቋሚ ኮሚቴ አባላትና የጽህፈት ቤቱ የማኔጅመንት ቡድን መገኘቱን ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
የፌዴሬሽን ምክር ቤት የድጎማ በጀትና የጋራ ገቢዎች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ለምክር ቤቱ በሚቀርቡ የውሳኔ ሃሳቦች ላይ ውይይት አካሄደ
Oct 7, 2024 85
አዲስ አበባ፤ መስከረም 27/2017 (ኢዜአ)፡- የፌዴሬሽን ምክር ቤት የድጎማ በጀትና የጋራ ገቢዎች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ለምክር ቤቱ በሚቀርቡ የውሳኔ ሃሳቦች ላይ ምክክር አድርጓል። ቋሚ ኮሚቴው እየተወያየ የሚገኘው ምክር ቤቱ ነገ ለሚያካሂደው 6ኛ የፓርላማ ዘመን 4ኛ የሥራ ጊዜ፣ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ቀርበው በሚፀድቁ የውሳኔ ሃሳቦች ላይ ነው። ውይይቱ የተመራው በቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ሽመልስ አብዲሳ ነው። አቶ ሽመልስ በ2017 በጀት ዓመት የሚያከናውናቸው ዝርዝር ተግባራት የተካተቱበት እቅድ እንዲቀርብ በጠየቁት መሠረት የቋሚ ኮሚቴው ፀሐፊ አቶ ኃይሉ ኢፋ እቅዱን አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል። በቋሚ ኮሚቴው አባላት የተሰጡ ግብዓቶች ጠቃሚዎች በመሆናቸው ለምክር ቤቱ በሚቀርበው የቋሚ ኮሚቴው የውሳኔ ሃሳብ ላይ እንዲካተት አቶ ሽመልስ ማሳሰባቸውን ከፌዴሬሽን ምክር ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ማህበራዊ
በአገልግሎት ዘመንዎ የላቀ ስኬት እንዲኖርዎት እመኛለሁ-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Oct 7, 2024 40
አዲስ አበባ፤መስከረም 27/2017(ኢዜአ)፦በአገልግሎት ዘመንዎ የላቀ ስኬት እንዲኖርዎት እመኛለሁ ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ለፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ እንኳን ደስ አለዎት አስተላለፉ። በዚህ ትልቅ የኃላፊነት ቦታ ሀገራችንን በቅንነት፣በጥበብ እና በጥልቅ የዓላማ ስሜት እንደሚያገለግሉ ሙሉ ዕምነት አለኝ ነው ያሉት። አቶ ተመስገን አክለውም፥ በአገልግሎት ዘመንዎ የላቀ ስኬት እንዲኖርዎት እመኛለሁ ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው መልዕክት አስተላልፈዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ በተጨማሪም ላለፉት ስድስት ዓመታት ኢትዮጵያን በፕሬዝደንትነት ላገለገሉት ሣሕለ ወርቅ ዘውዴ ላበረከቱት የላቀ አገልግሎት ምስጋናዬን ለማቅረብ እወዳለሁ ብለዋል፡፡
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ለፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀስላሴ የእንኳን ደስ ያለዎት መልዕክት አስተላለፉ
Oct 7, 2024 39
አዲስ አበባ፣መስከረም 27/2017(ኢዜአ)፦የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሐማት አዲስ ለተሾሙት የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀስላሴ የእንኳን ደስ ያለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ሙሳ ፋኪ በመልዕክታቸው፥ የቀድሞዋ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በነበራቸው የስራ ሃላፊነት ለሰጡት ታሪካዊ እና በሳል አመራር አድናቆታቸውንም ገልፀዋል፡፡ ሊቀመንበሩ አክለውም ኢትዮጵያ ዴሞክራሲ እና ዘላቂ ልማትን ለማስፈን በምታደርገው ጥረት የአፍሪካ ህብረት ድጋፍ ማድረጉን እንደሚቀጥል ማረጋገጣቸውን ከህብረቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ከተማ አስተዳደሩ ለትምህርት ዘርፉ የሰጠውን ትኩረት አጠናክሮ ይቀጥላል-ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Oct 7, 2024 64
አዲስ አበባ፤ መስከረም 27/2017(ኢዜአ)፦ ከተማ አስተዳደሩ ለትምህርት ዘርፉ የሰጠውን ትኩረት አጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡ ከንቲባዋ በ2016 የትምህርት ዘመን በ 12ኛ ክፍል አገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች በተደረገ የእውቅናና የሽልማት መርሃ ግብር ላይ የሜዳሊያ እና የትምህርት መርጃ ቁሳቁሶችን አበርክተዋል። በመርሃ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ ተማሪዎች፣ የተማሪ ቤተሰቦችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመርሃ ግብሩ ላይ ተማሪዎቹን ልፋታችሁ ፍሬ አፍርቶ ለዚህ በመብቃታችሁ እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል። የዕውቅናና ሽልማት መርሃ ግብሩ ዋና አላማ ከፍተኛ ውጤት ያመጡትን ተማሪዎች ለማበረታታ በአንፃራዊነት ዝቅተኛ ውጤት ያስመዘገቡት በርትተው ከሰሩ የማይቻል ነገር አለመኖሩን በማሳየት መልዕክት ለማስተላለፍ ነው ብለዋል። በመዲናዋ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ተማሪዎች ቁጥር ከአመት አመት እያደገ መምጣቱን ገልጸው፤ ለዚህ ውጤት መገኘት ከተማ አስተዳደሩ ለትምህርት ዘርፉ የሰጠውን ትኩረት በአብነት አንስተዋል፡፡ ከተሰሩ የማሻሻያ ስራዎች ውስጥ ትምህርት ቤቶችን ከአዋኪ ድርጊቶች ማራቅ፤ የምገባ ማዕከላትን ማስፋትና የፈተና አሰጣጡ በቴክኖሎጂ የተደገፈ እንዲሆን መደረጉን ጠቅሰዋል፡፡ በቀጣይም ከተማ አስተዳደሩ ለትምህርት ዘርፉ የሰጠውን ትኩረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። ዕውቅና የተሰጣቸው ተማሪዎች እውቀታቸውን ከዚህ በላይ በማስፋት ለአገር የሚጠቅሙ ስራዎችን እንዲሰሩ አደራ ብለዋል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ በ2016 የትምህርት ዘመን 21 ነጥብ 4 በመቶ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ማምጣታቸውን ተናግረዋል፡፡ ዘንድሮው ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ተማሪዎች ቁጥር ከ2015 የትምህርት ዘመን ጋር ሲነጻጸር የአምስት በመቶ ብልጫ እንዳለው ገልጸዋል፡፡ ለተማሪዎች ውጤት መሻሻል መሰረቱ ከተማ አስተዳደሩ፣ የትምህርት ተቋማትና የትምህርት ማህበረሰቡ ተቀናጅተው መስራታቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ከተሸላሚ ተማሪዎች መካከል ከገላን የወንዶች 2ኛ ደረጃ አዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪ ናትናዔል ዘሪሁን 518 ነጥብ ማምጣቱን ተናግሯል፡፡ ለዚህ የበቃው ወላጆቹና መምህሮቹ ከሚያደርጉለት ድጋፍ በተጨማሪ በግሉ ጠንክሮ ማጥናት በመቻሉ መሆኑን ገልጿል፡፡ የኦዝሊያን ካቶሊክ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዋ ሲፈኔ ተክሉ በበኩሏ፤ 575 ውጤት ማስመዝገቧን ተናግራለች፡፡ የወላጆቿ እገዛ ፣ የመምህራኖቿ ድጋፍ እና የራሷ የግል ጥረት ለውጤት እንዳበቃት ገልጻለች፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለቀድሞዋ ፕሬዝዳንት ሣሕለ ወርቅ ዘውዴ ምስጋና አቀረቡ
Oct 7, 2024 85
አዲስ አበባ፤ መስከረም 27/2017(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያን በፕሬዝዳንትነት ላገለገሉት ሣሕለ ወርቅ ዘውዴ በኢትዮጵያ መንግሥት ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የለውጡ አንዱ ዓላማ ሥርዓትን ማጽናት ነው። የሥራ ኃላፊዎች በሕግ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በተሰጣቸው ጊዜ ይወጣሉ ብለዋል። ሌሎች ደግሞ በተራቸው እነርሱን ተክተው ሀገራዊ ዓላማን በትውልድ ቅብብል ከግብ ያደርሳሉ ሲሉም ገልጸዋል። የሀገር ግንባታ የሚሳካው በዚህ መንገድ ነው። ላለፉት ስድስት ዓመታት ኢትዮጵያን በፕሬዝዳንትነት ላገለገሉት ሣሕለ ወርቅ ዘውዴ በኢትዮጵያ መንግሥት ስም ምስጋናዬን አቀርባለሁ ብለዋል። ዛሬ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሆነው ኃላፊነት የተቀበሉት አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ ሀገርና ሕዝብን በላቀ ሁኔታ የሚያገለግሉበት የኃላፊነት ዘመን እንዲሆንላቸው መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።
ኢኮኖሚ
በክልሉ በጀትን ለታለመለት ዓላማ በማዋል ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ልማት ይረጋገጣል-ቢሮው
Oct 7, 2024 41
ሀዋሳ፤ መስከረም 27/2017(ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል በጀትን ለታለመለት ዓላማ በማዋል ፈጣንና ቀጣይነት ያለውን ልማት ለማረጋገጥ የተለያየ ተግባር እየተከናወነ መሆኑን የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ አስታወቀ። የክልሉ 7ኛ ዙር የፋይናንስ ሴክተር ጉባዔ ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ተጀምሯል። በጉባዔው ላይ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አራርሶ ገረመው የፋይናንስ ሴክተሩ የመንግስት የልማት ስትራቴጂና የልማት ጥያቄዎችን እውን ለማድረግ ቁልፍ መሣሪያ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል ብለዋል። በዚህ ረገድ የክልሉ መንግስት ባለፉት አራት ዓመታት ዘርፉን በፍትሃዊነትና በውጤታማነት በመምራትና በማስተዳደር በክልሉ ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ልማት እንዲረጋገጥ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ገልፀዋል። በዚህም ለዓመታት ሲንከባለሉ የመጡ ዕዳዎችን ከመቀነስ ባሻገር በመንግሥት የግዥ ሥርዓት ላይ የሚታዩ የአፈጻፀም ጉድለቶችን ለማስተካከል መቻሉንም አክለዋል። በዚህም የህዝብና የመንግስት ሀብትን ከብክነት መታደግ ተችሏል ብለዋል። በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ረገድ የነበሩ ውስንነቶችን በመቅረፍና የክልሉን ገቢ በማሳደግ ወጪን በራስ የመሸፈን አቅም መጨሩንም አመላክተዋል። እንዲሁም ከተለያዩ ምንጮች የሚገኙ ሀብቶችን ለልማት እንዲውሉ መሰራቱንም አስረድተዋል። በ2016 በጀት ዓመት ብቻ 4 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ለካፒታል ፕሮጀክቶች በማዋል ስኬታማ ተግባር መከናወኑን ዶክተር አራርሶ አውስተዋል። በቀጣይም ቢሮው ለፋይናንስ የህግ ማዕቀፎች ተግባራዊነት አበክሮ እንደሚሰራ ገልጸው ለዚህ እውን መሆን ጉባዔው ወሳኝነት እንዳለውም አመልክተዋል። በጉባኤው ላይ የተገኙት የክልሉ መንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ አብርሃም ማርሻሎ በበኩላቸው በክልሉ ያለውን ውስን ሀብት በአግባቡ ለመምራት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል። በክልሉ ውጤታማ የፋይናንስ ስርዓትን በመዘርጋት የተሻለ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል። በተለይም የክልሉ ኢኮኖሚ የሚያመነጨውን ሀብት አሟጦ በመሰብሰብ የተገኘውን ገቢ ግልፅና ተጠያቂነት ያለው አሰራር በመዘርጋት ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ስራ እየተሰራ መሆኑን አክለዋል። ሆኖም በዘርፉ አልፎ አልፎ የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮችን በማስወገድ በቀጣይ የተሻለ ስራ ለመስራት የሚያስችል አቅጣጫ እንደሚቀመጥም አረጋግጠዋል። በሴክተር ጉባኤው ላይ የፋይናንስ ዘርፍ ያለፈው ዓመት አፈፃፀም እና የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ምክክር ተደርጓል። ለሁለት ቀናት በሚካሄደው ጉባኤ ላይም የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በየነ በራሳና የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ደምሴ ዱላቻን ጨምሮ የክልል፣ የዞን፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች እየተሳተፉ ነው።
በክልሉ የተከናወኑ ፍትሃዊ የመንገድ ልማት ተደራሽነትን የማረጋገጥ ተግባራት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ያደርጋሉ
Oct 7, 2024 47
ሀዋሳ፤ መስከረም 27/2017(ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል ፍትሃዊ የመንገድ ልማት ተደራሽነት ለማረጋገጥና የትራንስፖርት አገልግሎት ለማሳለጥ በተከናወኑ ተግባራት የተገኙ ውጤቶች ህብረተሰቡን ተጠቃሚ እንደሚያደርጉ የክልሉ መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ገለፀ። ቢሮው በዓመታዊ የሴክተር ጉባኤው በበጀት አመቱ ትኩረት በተሰጣቸው ጉዳዮች ላይ በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ መክሯል። የቢሮው ኃላፊ አቶ ታምሩ ታፌ እንደገለጹት፤ በክልሉ ፍትሃዊ የመንገድ ልማት ተደራሽነትን የማረጋገጥ ተግባራት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ናቸው። በክልሉ የተከናወኑ የመንገድ ልማት ስራዎች የትራንስፖርት አገልግሎቱን የሚያሳልጡና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴውን በማፋጠን ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ መሆናቸውን ገልጸዋል። በትራንስፖርት ረገድ የተሳለጠ አገልግሎት በመስጠት የተገልጋዩን እርካታ ለማረጋገጥና የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ በአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት ብቃት ማረጋገጫ አሰጣጥ ላይ ትኩረት ተደርጎ መሰራቱን ተናግረዋል። በዚህም በክልሉ የሚገኙ 13 የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት በቴክኖሎጂ የታገዘ ስልጠና እንዲሰጡና የብቃት ማረጋገጫ አሰጣጡ ተገቢውን አሰራር ተከትሎ እንዲከናወን መደረጉን ገልፀዋል። በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀልና ትራፊክ አደጋ መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ካሳ ጨቦ የትራፊክ አደጋ እያስከተለ ያለውን ቀውስ ለመከላከል ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በክልሉ ከ48 ሺህ በላይ ባለሁለት እግር ሞተር ሳይክሎች መኖራቸውን የጠቀሱት ምክትል ኮሚሽሩ አብዛኛው የትራፊክ አደጋ የሚመዘገበው በሞተር ሳይክሎች መሆኑን ገልጸዋል። ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት በተደረገ ጥረትም የትራፊክ አደጋን እና ወንጀልን በመከላከሉ ረገድ ውጤታማ ስራ መሰራቱን ተናግረዋል። የሀዋሳ ከተማ መንገድ ልማትና ትራንስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ አዳነ አየለ በበኩላቸው በከተማዋ የትራንስፖርት አገልግሎት ፍትሃዊ እንዲሆን ተስፋ ሰጪ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ገልጸዋል። በከተማው በሚገኙ ሁለት መናኸሪያዎች በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት በመስጠት ከታሪፍ በላይ ማስከፈልና ትርፍ መጫንን ጨምሮ የተሳፋሪ እንግልት እንዲቀንስ መደረጉን አስረድተዋል። በከተማዋ የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎትን ተደራሽ የማድረግ ተግባራት መከናወናቸውን የገለጹት ኃላፊው በዚህም አበረታች ውጤት መመዝገቡን አክለዋል። በመድረኩም በተገኙ ውጤቶችና በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ውይይት ተደርጎ ከባለድርሻ አካላት ጋር የግብ ስምምነት መደረሱም ተገልጿል።
ግብርን በታማኝነትና በወቅቱ በመክፈል የልማት እንቅስቃሴን ለማገዝ ዝግጁ ነን -የንግዱ ማህበረሰብ አባላት
Oct 7, 2024 51
ዲላ፤ መስከረም 27/2017(ኢዜአ)፦ ግብራችንን በታማኝነትና በወቅቱ በመክፈል በከተሞች የልማት እንቅስቃሴን ለማገዝ ዝግጁ ነን ሲሉ በጌዴኦ ዞን የዲላ ከተማ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ገለጹ። የጌዴኦ ዞን አስተዳደር በዲላ ከተማ የገቢ አሰባሰብና የግብይት ደረሰኝ አሰጣጥ ዙሪያ ከግብር ከፋዩችና ባለድርሻ አካላት ጋር በዲላ ከተማ ውይይት አካሂዷል። አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት እንዳሉት ግብርን በወቅቱና በታማኝነት በመክፈል ለልማት እንቅስቃሴ መጠናከር የሚጠበቅባቸውን ይወጣሉ። በዚህም በከተማዋ የሚስተዋለው ተስፋ ሰጪ የልማት እንቅስቃሴ ዳር እንዲደርስ ተሳትፏቸውን እንደሚያጠናክሩ አረጋግጠዋል። የጌዴኦ ዞን የንግድ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሻለቃ አረጋኸኝ አሰፋ እንዳሉት ውይይቱ በገቢ ግብር ያሉ ውስንነቶችን በመቅረፍ ተቀራርቦ ለመስራት የሚያስችል ነው። በዲላ ከተማ ግብይትን በደረሰኝ የመፈጸም ልምድ ዝቅተኛ መሆኑን ጠቅሰው "ይህንን ለመቀየር መስራት አለብን" ብለዋል። "በተለይ ግብራችንን በታማኝነትና በወቅቱ በመከፈል በኮሪደርና መልሶ ልማት እንዲሁም በመሰረተ ልማት ዝርጋታ የሚከናወኑ የልማት እንቅስቃሴዎችን ከዳር ለማድረስ የበኩላችንን እንወጣለን" ሲሉ አረጋግጠዋል። በህገወጥ ንግድ በተለይ በኮንትሮባንድና በጎዳና ንግድ ላይ አስተዳደሩ እርምጃ እንዲወስድ የጠየቁት ደግሞ አቶ ሲራጅ መሐመድ ናቸው። ግብራቸውን በታማኝነት በመክፈል በከተማው ልማት ላይ የድርሻቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል። አቶ በየነ ፍልቱ በበኩላቸው ከተሞች ከፍተኛ የሆነ የልማት እንቅስቃሴ እየታየባቸው መሆኑን ጠቅሰው ግብርን በወቅቱ በመክፈል ለልማቱ መሳለጥ የበኩላቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል ። የዲላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ዳንኤል ሽፈራው በበኩላቸው በከተማው የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ የገቢ አቅምን አማጦ ለመሰብሰብ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። ህገ ወጥነትንና ሌብነትን በጋራ መከላከል እንደሚገባ ጠቅሰው በተለይ የንግዱ ማህበረሰብ ግብይትን በደረሰኝ ብቻ በመፈጸም ሃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት አሳስበዋል። የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶክተር ዝናቡ ወልዴ በበኩላቸው ግብር መክፈል ለጋራ ልማትና እድገት ወጣኝ መሆኑን ጠቅሰዋል። ይሁንና በከተሞች ለታክስ ህግ ተገዥ አለመሆን በተለይ ግብይትን በደረሰኝ አለመፈጸም በስፋት የሚስተዋል በመሆኑ በዞኑ የሚፈለገውን ልማት ማረጋገጥ አዳጋች እንዳደረገው አንስተዋል። ለከተሞች እድገት የውስጥ ገቢ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው የንግዱ ማህበረሰብ ግብይቱን በታማኝነት በመክፈል ሃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት አሳስበዋል። በተለይ በተያዘው ዓመት ከ2 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ በመሰብሰብ የዞኑን 75 በመቶ ወጭ በውስጥ አቅም ለመሸፈን ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል። ለስኬታማነቱ የንግዱ ማህበረሰብ ተሳትፎውን ማጠናከር እንዳለበት አመልክተዋል። በመድረኩ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት፣ የባህልና የሃይማኖት መሪዎች እንዲሁም የዞንና የከተማው የሥራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል።
በ2016 በጀት አመት የተሻለ የታክስ ተገዥነት ላስመዘገቡ 550 ታማኝ ግብር ከፋዮች እውቅና ሊሰጥ ነው
Oct 7, 2024 73
አዲስ አበባ፤መስከረም 27/2017(ኢዜአ)፦ በ2016 በጀት አመት የተሻለ የታክስ ተገዥነት ላስመዘገቡ 550 ታማኝ ግብር ከፋዮች መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም እውቅና ይሰጣል። የዕውቅና መርሃ ግብሩን አስመልከቶ የገቢዎች ሚኒስትር አይናለም ንጉሴ እና የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ በጋራ መግለጫ ስጥተዋል። ዕውቅናው በ2016 በጀት አመት በህግ ተገዥነትና ግብርን በወቅቱ በመክፈል የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ አካላት የሚሰጥ መሆኑን ኃላፊዎቹ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል። የገቢዎች ሚኒስትር አይናለም ንጉሴ የአገር ምጣኔ ሀብት ከሚያመነጨው አንጻር የሚሰበሰበውን ገቢ ለማሳደግ የህግ ማዕቀፎችን በማሻሻልና አሰራርን በማዘመን በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል። ከአመት ወደ አመት የሚሰበሰበው የገቢ መጠን እያደገ መምጣቱን ገልጸው በ 2016 በጀት አመት ለመሰብሰብ ከታቀደው 529 ቢሊዮን ብር ውስጥ 512 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ መቻሉን ተናግረዋል። ግብር ከፋዮች ግብርን በወቅቱና በታማኝነት በማሳወቅና በመክፈል ያሳዩት ሚና ለገቢው ማደግ ከፍተኛ አበርክቶ እንዳለው አንስተዋል። በመሆኑም በፌዴራል ደረጃ የታክስ ህግን በማክበርና በወቅቱ ግብርን በመክፈል የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ 550 ግብር ከፋዮች መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም ዕውቅና እንደሚሰጥ ገልጸዋል። የዕውቅናው አላማ ለአገራቸው ግብርን በታማኝነት የሚከፍሉትን በማበረታታት ለሌሎች አርአያ እንዲሆኑ ለማድረግ መሆን ጠቅሰዋል፡፡ የሚሰጠው ዕውቅና የወርቅ፣ ፕላቲኒየምና የብር በሚል ሶስት ደረጃዎች እንዳሉትም አስታውቀዋል። ዕውቅናው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራን ተከትሎ የሚሰበሰበውን ገቢ በማሳደግ የተያዘውን እቅድ ለማሳካት የሚረዳ ንቅናቄ ለመፍጠር ያግዛል ብለዋል ሚኒስትሯ። የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ በበኩላቸው ዕውቅናው ለሌሎች ተነሳሽነትን በመፍጠር የህግ ተገዥነትና ታማኝነትን ለማረጋገጥ እንደሚያግዝ ተናግረዋል። የዚህ አመት የታማኝ ግብር ከፋዮች ዕውቅና ለ6ኛ ጊዜ የሚሰጥ ነው።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በዓለም አቀፍ የሮቦት ኦሊምፒያድ ውድድር ላይ ይሳተፋሉ
Oct 4, 2024 217
አዲስ አበባ፤ መስከረም 24/2017(ኢዜአ):- ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በሕዳር ወር በተርኪዬ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የሮቦት ኦሊምፒያድ ውድድር ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሚሳተፉ ተገለጸ። ኦሊምፒያዱ ወጣቶች የሮቦት ፈጠራ ስራቸውን በማቅረብ የሚሳተፉበት ውድድር መሆኑ ተመላክቷል። ለዚህ አለም አቀፍ ውድድር ኢትዮጵያን በመወከል የሚሳተፈው የሮቦቲክ የፈጠራ ውጤት የማወዳደር መርሃ ግብር በተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዛሬ ተካሂዷል። በአዲስ አበባና ክልል ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ የስቲም ፓወር ማዕከል ተማሪዎች በግብርና፣ በጤና፣ በኢንዱስትሪ፣ ከተማ ግብርና እና ሌሎች ዘርፎች ላይ ያተኮሩ 37 የሮቦቲክስ የፈጠራ ውጤቶችን ለውድድሩ አቅርበዋል። ከእነዚህ መካከል ከኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ስቲም ማዕከል በኢንዱስትሪ፣ በግብርና እንዲሁም በጤና ዘርፈ ብዙ አገልግሎት የሚሰጥ የሮቦት ፈጠራ ውጤት ያቀረበው ቡድን ኢትዮጵያን በመወከል በውድድሩ እንዲሳተፍ ተመርጧል። የቡድኑ ተወካይ የ11ኛ ክፍል ተማሪ በረከት አሰፋ ኢትዮጵያ በኢንዱስትሪ፣ በሕክምና እንዲሁም በግብርና የምታከናውነውን ተግባር ለማቀላጠፍ የሮቦት የፈጠራ ውጤቱን ለመስራት እንደተነሳሳ ገልጿል። ተማሪዎቹ በተርኪዬ በሚካሄደው የአለም ሮቦት ኦሊምፒያድ ውድድር በዲጂታል ዘርፍ ሀገራቸውን ለማስጠራት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል። የስቲም ፓወር ድርጅት የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ስሜነው ቀስቅስ(ዶ/ር) ኢትዮጵያን በመወከል በዓለም ሮቦት ኦሊምፒያድ ውድድር ላይ የሚሳተፉ ተማሪዎች ለማዘጋጀት በ40 የስቲም ፓወር ማዕከላት ስልጠናው መሰጠቱን ተናግረዋል። ከእነዚህ መካከል በችግር ፈቺነቱና ለዓለም አቀፍ መድረክ ብቁ በመሆኑ የተመረጠውና ኢትዮጵያን ወክሎ የሚሳተፈው የፈጠራ ውጤት ለውድድሩ ከመቅረቡ በፊት ለገበያ ብቁ የማድረግ የማሻሻያ ስራ ይከናወናል ብለዋል። ኢትዮጵያ በውድድሩ መሳተፏ የቴክኖሎጂና ፈጠራ አቅሟን የምታሳይበትና ለተማሪዎች አለም አቀፍ እድሎች የሚፈጠሩበት እንደሚሆን አመልክተዋል። የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ይሽሩን አለማየሁ(ዶ/ር) ኢትዮጵያ ዲጂታል ምጣኔ ሃብትን እውን ለማድረግ ለፈጠራና ምርምር ምቹ ሁኔታዎችን የማመቻቸት ስራ እያከናወነች ትገኛለች ብለዋል። የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን(ዩኤንሲኤ) ዋና ፀሐፊ ክላቨር ጋቴቴ በበኩላቸው አፍሪካ በቴክኖሎጂ ከአለም ጋር ለመወዳደር ለዲጂታል ትምህርት ትኩረት መስጠት እንዳለባት አስገንዝበዋል። በወጣቶች ላይ የፈጠራ ክህሎትን ለማሳደግ የሚከናወኑ ተግባራት አጀንዳ 2063ን እውን በማድረግ የአፍሪካን ብልጽግና ለማረጋገጥ መሰረት የሚጥሉ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። የ2024 ውድድር እንደ አውሮፓውያኑ ዘመን አቆጣጠር ከህዳር 28 እስከ 30/2024 በተርኪዬ ይካሄዳል። በውድድሩ ላይ ከ80 ሀገራት በላይ እንደሚሳተፉ ተመላክቷል። የዓለም ሮቦት ኦሊምፒያድ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2004 የተጀመረ ውድድር ነው።
በጋምቤላ ክልል የኮደርስ ስልጠናን ሰኬታማ ለማድረግ ባለድርሻ አካላት በትብብር ሊሰሩ ይገባል
Oct 4, 2024 189
ጋምቤላ፤ መስከረም 24/2017 (ኢዜአ)፦ በጋምቤላ ክልል የኮደርስ ስልጠናን ስኬታማ ለማድረግ በየደረጃው የሚገኙ የአመራር አካላትና ባለድርሻዎች በትብብር ሊሰሩ እንደሚገባ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አለሚቱ ኡሞድ አስገነዘቡ ። በጋምቤላ ከተማ "የአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ'' የክልል ዕቅድ ማስጀመሪያ ሥነ ስርዓት ዛሬ ተካሂዷል። በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አለሚቱ ኡሞድ በማስጀመሪያ ሥነ ስርዓቱ ላይ እንደገለጹት፤ በአገር ደረጃ የተያዘው የዲጂታላይዜሽን ስልጠና መርሃ ግብር በክልሉ የተሳካ እንዲሆን በየደረጃው የሚገኙ የአመራር አባላትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በትብብር ሊሰሩ ይገባል። የዲጂታላይዜሽን ክህሎት ዘመኑ የሚጠይቀውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ለማሳለጥ ዓይነተኛ ሚና ይጫወታል ብለዋል። በክልልም ሆነ በአገር ደረጃ የታለመውን የልማትና የብልጽግና ጉዞ እውን ለማድረግ የዲጂታል ክህሎት የታጠቀ የሰው ሃይል ማፍራት ወቅቱ የሚጠይቀው ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል። በመሆኑም የአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያን ኮደርስ ኢኒሼቲቭን በክልሉ ውጤታማ ለማድረግ የተቀናጀ ጥረት እንደሚጠይቅም አስገንዝበዋል። ስለሆነም ለሶስት ዓመታት በሚቆየው የኮደርስ የስልጠና መርሃ ግብር ላይ በክልሉ 47 ሺህ 247 ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ግብ ተጥሎ ወደ ተግባር መገባቱን አብራርተዋል። እቅዱን ለማሳካት ከክልል እስከ ወረዳ የሚገኙ የአመራር አካላት ወጣቱ የስልጠናው ተጠቃሚ እንዲሆን ያላሰለሰ ጥረት ሊያደርጉ እንደሚገባ ርዕሰ መስተዳድሯ አሳስበዋል። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ጋትሉዋክ ሮን በበኩላቸው፤ ስልጠናው ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ የሚያደርግ በመሆኑ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል። በተለይም ወጣቱ በዚህ የኮደርስ ኢኒሼቲቭ ስልጠና ላይ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ የዕድሉ ተጠቃሚ ሊሆን እንደሚገባ አስገንዝበዋል። የክልሉ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኮሚሽነር አቶ ፖል ገሪ ፤ ኢኒሼቲቩን ለማሳካት የተጠናከረ የቅስቀሳና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በማከናወን ዜጎች የዕድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በትኩረት ይሰራል ብለዋል። በኢኒሼቲቩ ማስጀመሪያ ሥነ ስርዓቱ ላይ የክልል፣ የዞንና የወረዳ የአመራር አካላትና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ የተደረገው የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስና የኢትዮጵያ መንግስታት የሚተገበር ሲሆን፤ በአገር አቀፍ ደረጃ አምስት ሚሊዮን ወጣቶች በኦንላይን የኮዲንግ ስልጠና ለመውሰድ ያስችላቸዋል። ስልጠናው በዌብ ፕሮግራሚንግ፣ በአንድሮይድ ማበልፀግ፣ ዳታ ሳይንስ እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መሠረታዊ የዲጂታል ክህሎት ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰጥ ነው።
የፓን አፍሪካ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኮንፍረንስ በቀጣዩ ሳምንት በአዲስ አበባ ይካሄዳል
Oct 2, 2024 273
አዲስ አበባ፤ መስከረም 22/2017(ኢዜአ):- ሶስተኛው የፓን አፍሪካ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኮንፍረንስ መስከረም 28 እና 29 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አስታወቀ። ኢኒስቲትዩቱ ያዘጋጀው ኮንፍረንስ “ለአፍሪካ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ተጨማሪ አቅም መፍጠር” በሚል መሪ ሀሳብ በአድዋ ድል መታሰቢያ ይካሄዳል። ኮንፍረንሱ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍ የሚገኙ ባለድርሻ አካላትን ትብብር፣ ኢኖቬሽንና የእውቀት ሽግግር ማጎልበት አላማ ማድረጉን የኢኒስቲትዩቱ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ዘውዴ ለኢዜአ ገልጸዋል። በኮንፍረንሱ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ምሁራን በአፍሪካ በዘርፉ ያሉ ጠቀሜታዎች፣ ፈተናዎች እና ቀጣይ መፍትሔዎችን የሚያመላክቱ ሳይንሳዊ ጽሁፎችን እንደሚያቀርቡ አመልክተዋል። በጥናታዊ ጽሁፎቹ ቴክኖሎጂው በጤና፣ ግብርና፣ ትምህርት፣ ፋይናንስ፣ ዲጂታል አገልግሎቶች እና በተለያዩ መስኮች ያለውን ጠቀሜታ እንደሚዳሰስ ተናግረዋል። ዓለም አቀፍ ሁኔታን ባገናዘበ መልኩ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የአፍሪካን ችግሮች በአፍሪካዊ መፍትሔዎች መፍታት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ምክክር እንደሚደረግም ነው ዳይሬክተሩ የገለጹት። ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ከተካሄዱት ሁለት ኮንፍረንሶች የተገኙ ተሞክሮዎችን እንደሚገመገሙም ጠቅሰዋል። ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ያላትን ተሞክሮዎች በፎረሙ ላይ እንደምታቀርብም እንዲሁ። በኮንፍረንሱ ላይ የአገር ውስጥ እንዲሁም አህጉር አቀፍ ዓለም አቀፍ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ተቋማት፣ተመራማሪዎች፣ ስራ ፈጣሪዎች እና ተማሪዎች እንደሚሳተፉበት ጠቁመዋል። የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ ቴክኖሎጂው በአገሪቷ እንዲታወቅ፣ ግንዛቤ እንዲኖር እንዲሁም ዳታን መሰረት ያደረጉ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂዎች ለኢትዮጵያ ጥቅም እንዲሰጡ ለማስቻል እየሰራ ይገኛል ብለዋል። በዘርፉ ጥናትና ምርምር በማድረግ ተጠቃሚነትን የማሳደግ እና ለጀማሪ አልሚዎች ምቹ ምህዳርን የመፍጠር ስራዎች በማከናወን የልህቀት ማዕከል ለመሆን እየሰራ መሆኑን በመግለጽ። ኢትዮጵያ የሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂዎችን ለስማርት ሲቲ ፕሮጀክት፣ አገርኛ ቋንቋዎችን የማሽን ቋንቋ ለማድረግ፣ ለስማርት ፍርድ ቤቶች፣ ግብርና፣ ጤና፣ ፋይናንስ፣ ወንጀልን መከላከልና በተለያዩ መስኮች ጥቅም ላይ እያወለች መሆኑን ተናግረዋል። በቀጣይ በዘርፉ ኢትዮጵያን ይበልጥ ተጠቃሚ የማድረግ ስራ በትኩረት እንደሚከናወን አክለዋል።
የሕንድ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በተለያዩ የቴክኖሎጂ መስኮች ለመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው ገለጹ
Oct 2, 2024 306
አዲስ አበባ፤ መስከረም 22/2017(ኢዜአ):- የሕንድ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በተለያዩ የቴክኖሎጂ መስኮች ለመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው አስታወቁ። በሕንድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጉዳይ ፈጻሚ አምባሳደር ብዙነሽ መሰረት ዋና ተቀማጭነቱን በሕንድ ካደረገው የዓለም የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ማህበር(WASME) ልዑክ ጋር ተወያይተዋል። አምባሳደር ብዙነሽ በማህበሩ ስር ለሚገኙ የሕንድ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ስላሉ የኢንቨስትመንት እና የንግድ እድሎች ገለጻ አድርገዋል። ኢትዮጵያ በዲጂታል ትራንስፎሜሽን አጀንዳ አማካኝነት “ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025” ስትራቴጂን ተግባራዊ እያደረገች እንደምትገኝ አምባሳደሯ ገልጸዋል። ስትራቴጂው የዲጂታል እድሎችን በመጠቀም ኢትዮጵያን ወደ ዘላቂ እና ዲጂታል ኢኮኖሚ መንገድ መምራት የሚያስችል ነው ብለዋል። የኢትዮጵያ መንግስት በውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመት እና በማበረታቻ ማዕቀፎች ሰፋፊ ማሻሻያዎችን እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል። የዓለም የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ማህበር ከፍተኛ አማካሪ እና የልዑኩ መሪ ኢንጂነር ራሜሽ ኩማር የኢትዮጵያ እና ሕንድ የሁለትዮሽ ትብብር ማጠናከር የሚያስችሉ በርካታ አቅሞችን መጠቀም እንደሚገባ ገልጸዋል። የሕንድ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች በሳይበር ደህንነት፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ በሶፍትዌር ማበልጸግ፣ በኤሌክትሮኒክስ አስተዳደር፣ በኢንተርኔት ኔትወርክ ስርዓት፣ የምናባዊ እውነታ ቴክኖሎጂ እና ሌሎች ተያያዥ መስኮች ላይ የመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው አመልክተዋል። የዓለም የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ማህበር በኢትዮጵያ የንግድ እና ኢንቨስትመንት እድሎች ለመመልከት የንግድ ልዑኩን ወደ ኢትዮጵያ የመላክ እቅድ እንዳላው መግለጹን ኢዜአ ሕንድ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘው መረጃ ያመለክታል። ማህበሩ እ.አ.አ በ1980 የተቋቋመ ሲሆን ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች እድገት እና ልማት የሚሰራ ድርጅት ነው።
ስፖርት
የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በዩጋንዳ አቻው ተሸነፈ
Oct 7, 2024 31
አዲስ አበባ፤ መስከረም 27/2017 (ኢዜአ) :- የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በ24ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ከዩጋንዳ አቻው ጋር ባደረገው የመጀመሪያ ጨዋታ 3 ለ 0 ተሸንፏል። በምድብ 2 የምትገኘው ኢትዮጵያ ሁለተኛ ጨዋታዋን መስከረም 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከደቡብ ሱዳን ጋር በኪኖንዶኒ ሙኒሲፓል ካውንስል ስታዲየም ከቀኑ 1 ሰዓት ላይ ታደርጋለች። በዚሁ ምድብ ዛሬ ቀን ላይ በተካሄደ ጨዋታ ብሩንዲ ደቡብ ሱዳንን 1 ለ 0 አሸንፋለች። በታንዛንያ የሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ትናንት መጀመሩ ይታወቃል። በምድብ 1 ትናንት በተደረጉ ጨዋታዎች ሱዳን ጅቡቲን 3 ለ 1 እንዲሁም ኬንያ አዘጋጇን ታንዛያን 2 ለ 1 አሸንፈዋል። የማጣሪያ ውድድሩ እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2017 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን በውድድሩ ለፍጻሜ የሚደርሱ ሁለት ሀገራት ለአፍሪካ ዋንጫ ያልፋሉ።
የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በዩጋንዳ አቻው ተሸነፈ
Oct 7, 2024 31
አዲስ አበባ፤ መስከረም 27/2017 (ኢዜአ) :- የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በ24ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ከዩጋንዳ አቻው ጋር ባደረገው የመጀመሪያ ጨዋታ 3 ለ 0 ተሸንፏል። በምድብ 2 የምትገኘው ኢትዮጵያ ሁለተኛ ጨዋታዋን መስከረም 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከደቡብ ሱዳን ጋር በኪኖንዶኒ ሙኒሲፓል ካውንስል ስታዲየም ከቀኑ 1 ሰዓት ላይ ታደርጋለች። በዚሁ ምድብ ዛሬ ቀን ላይ በተካሄደ ጨዋታ ብሩንዲ ደቡብ ሱዳንን 1 ለ 0 አሸንፋለች። በታንዛንያ የሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ትናንት መጀመሩ ይታወቃል። በምድብ 1 ትናንት በተደረጉ ጨዋታዎች ሱዳን ጅቡቲን 3 ለ 1 እንዲሁም ኬንያ አዘጋጇን ታንዛያን 2 ለ 1 አሸንፈዋል። የማጣሪያ ውድድሩ እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2017 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን በውድድሩ ለፍጻሜ የሚደርሱ ሁለት ሀገራት ለአፍሪካ ዋንጫ ያልፋሉ።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከ20 ዓመት በታች ዋንጫ ዛሬ የመጀመሪያ የማጣሪያ ጨዋታዋን ታደርጋለች
Oct 7, 2024 79
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 27/2017 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በ24ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታውን ዛሬ ዩጋንዳ ጋር ያደርጋል። የሁለቱ አገራት ጨዋታ ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ በአዛም ኮምፕሌክስ ስታዲየም ይደረጋል። 24ኛው የአፍሪካ ከ20 ዓመት በታች ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ውድድር ትናንት በታንዛንያ ተጀምሯል። በማጣሪያ ውድድሩ ላይ ዘጠኝ አገራት ተሳታፊ ሆነዋል። ኢትዮጵያ በማጣሪያው በምድብ 2 ከዩጋንዳ፣ ብሩንዲና ደቡብ ሱዳን ጋር ተደልድላለች። በአሰልጣኝ ስዩም ከበደ የሚሰለጥነው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የመጀመሪያ ጨዋታውን ዛሬ ያከናውናል። 20 ተጫዋቾችን የያዘው ስብስብ ቅዳሜ አርብ መስከረም 24 ቀን 2017 ዳሬሰላም መግባቱ ይታወቃል። ተጫዋቾቹ ላለፉት ሁለት ቀናት በታንዛንያ ልምምዳቸውን አድርገዋል። ቡድኑ ከጨዋታው በፊት የመጨረሻ ልምምዱን ትናንት በኪኖንዶኒ ሙኒሲፓል ካውንስል ስታዲየም ማድረጉን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። በ46 ዓመቱ ማቲያስ ሉሌ የሚመራው የዩጋንዳ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን 20 ተጫዋቾችን ይዞ ዝግጅቱን ሲያደርግ ቆይቷል። በምድብ 2 ሌላኛው መርሃ ግብር ደቡብ ሱዳን ከብሩንዲ ከቀኑ 10 ሰዓት በኪኖንዶኒ ሙኒሲፓል ካውንስል ስታዲየም ይጫወታሉ። በማጣሪያው በምድብ አንድ ታንዛንያ፣ ሩዋንዳ፣ ሱዳን፣ ጅቡቲና ኬንያ በምድብ አንድ ተደልድለዋል። በዚሁ ምድብ ትናንት በተደረጉ ጨዋታዎች ሱዳን ጅቡቲን 3 ለ 1 እንዲሁም ኬንያ ታንዛያን 2 ለ 1 አሸንፈዋል። የማጣሪያ ውድድሩ እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2017 ዓ.ም ይቆያል። በሴካፋ ዞን ማጣሪያ ለፍጻሜ የሚደርሱ ሁለት ሀገራት ለአፍሪካ ዋንጫ ያልፋሉ። በአፍሪካ ከ20 ዓመት በታች ዋንጫ 12 ሀገራት እንደሚሳተፉ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) አስታውቋል።
የአፍሪካ ከ20 ዓመት በታች ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ውድድር ዛሬ ይጀመራል
Oct 6, 2024 142
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 26/2017 (ኢዜአ)፦ የ24ኛው የአፍሪካ ከ20 ዓመት በታች ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ውድድር ዛሬ በታንዛንያ ይጀመራል። በማጣሪያ ውድድሩ ላይ ዘጠኝ አገራት ይሳተፋሉ። ኢትዮጵያ በማጣሪያው በምድብ 2 ከዩጋንዳ፣ ብሩንዲና ደቡብ ሱዳን ጋር ተደልድላለች። በአሰልጣኝ ስዩም ከበደ የሚሰለጥነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመጀመሪያ ጨዋታውን ነገ ከዩጋንዳ ጋር ያደርጋል። 20 ተጫዋቾችን የያዘው ስብስብ ከትናንት በስቲያ ዳሬሰላም መግባቱ ይታወቃል። ቡድኑ የመጀመሪያ ልምምዱን ትናንት ኪጋምቦኒ በሚገኘው የታንዛንያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የስልጠና ማዕከል ማድረጉን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። በማጣሪያው በምድብ አንድ ታንዛንያ፣ ሩዋንዳ፣ ሱዳን፣ ጅቡቲና ኬንያ በምድብ አንድ ተደልድለዋል። የውድድሩ አዘጋጅ ታንዛንያ ከኬንያ ዛሬ ከቀኑ 10 ላይ በኪኖንዶኒ ሙኒሲፓል ካውንስል ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። በዚሁ ምድብ ሱዳን ከጅቡቲ ከምሽቱ 12 ሰዓት በአዛም ኮምፕሌክስ ይጫወታሉ። የማጣሪያ ውድድሩ እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2017 ዓ.ም ይቆያል። በሴካፋ ዞን ማጣሪያ ለፍጻሜ የሚደርሱ ሁለት ሀገራት ለአፍሪካ ዋንጫ ያልፋሉ። በአፍሪካ ከ20 ዓመት በታች ዋንጫ 12 ሀገራት ይሳተፋሉ።
አካባቢ ጥበቃ
በአዲስ አበባ የተሰማው የመሬት ንዝረት ፈንታሌ ላይ በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ ሳቢያ የተከሰተ መሆኑ ተገለጸ
Oct 7, 2024 182
አዲስ አበባ፣ መስከረም 26/2017(ኢዜአ)፦በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች የተሰማው የመሬት ንዝረት ፈንታሌ ላይ በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ ሳቢያ የተከሰተ መሆኑን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂዮፊዚክስ እና ስፔስ ሳይንስ ዳይሬክተር ዶክተር ኤሊያስ ሌዊ ገለጹ። ዶክተር ኤሊያስ ለኢቲቪ እንደገለጹት ዛሬ ምሽት 2፡10 ገደማ በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች የተሰማው የመሬት ንዝረት ፈንታሌ ላይ በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ ሳቢያ የተከሰተ ነው። እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ ከ 20 ሰዓታት በፊት ወደ 165 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ፈንታሌ ተራራ አካባቢ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 4 ነጥብ 9 የተመዘገበ መሆኑን ገልጸዋል። ይሄ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተትም ሞገዱ በመሬት ውስጥ ተጉዞ በመምጣት በአዲስ አበባና አካባቢው መሰማቱን ተናግረዋል። ተመሳሳይ የመሬት መንቀጥቀጥ በአካባቢው በተደጋጋሚ ሲከሰት የቆየ መሆኑን ገልጸው ዛሬ የተከሰተውም የዚሁ አካል መሆኑንና እንደማያሰጋ አስረድተዋል።
በደቡብ እና የደቡብ ምሥራቅ የሀገሪቷ አካባቢዎች በሁለተኛው የዝናብ ወቅታቸው የተጠናከረ ዝናብ ይጠበቃል
Oct 2, 2024 281
አዲስ አበባ፤መስከረም 22/2017(ኢዜአ)፦በደቡብ እና የደቡብ ምሥራቅ የሀገሪቷ አካባቢዎች በሁለተኛው የዝናብ ወቅታቸው የተጠናከረ ዝናብ የሚጠበቅ መሆኑን የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስትቲዩት አስታወቀ። የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስትቲዩት በቀጣዮቹ ቀናት የሚጠበቁ የአየር ሁኔታ ትንበያ መረጃዎችን በተመለከተ ለኢዜአ የፅሁፍ ማብራሪያ ልኳል። በዚህም መሰረት በቀጣዮቹ አስር ቀናት የሚጠበቀው እርጥበት እድገታቸውን ላልጨረሱና ለቋሚ ተክሎች ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር መሆኑ አስታውቋል። ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት ደቡባዊው የሀገሪቱ ክፍሎች ለሚኖሩ አርብቶ አደሮችና ከፊል አርብቶ አደሮችም ለግጦሽ ሳርና ለመጠጥ ውሃ አቅርቦት ጠቀሜታ አለው ተብሏል። በምዕራብ እና በደቡብ ምዕራብ የአገሪቱ አካባቢዎች ያለው ዝናብ ቀጣይነት እንደሚኖረው በኢንስቲትዩቱ ትንበያ ተመላክቷል። በደቡብ እና የደቡብ ምሥራቅ ኢትዮጵያ በተጠናከረ ሁኔታ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው እንደሚሆንም አስታውቋል። የበጋው ደረቅ፣ ፀሐያማና ነፋሻማ የአየር ጠባይ ጎልቶ እየታየ በመሆኑ የሌሊቱና የማለዳው ቅዝቃዜ በሀገሪቱ የሰሜን አጋማሽ ክፍሎች እንደሚጨምርም ይጠበቃል። የምዕራብና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቷ አካባቢዎች ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ሊኖር እንደሚችልም ተመላክቷል። በአብዛኛው ባሮ አኮቦ የታችኛውና የመካከለኛው አባይ፣ ኦሞ ጊቤ፤ ስምጥ ሸለቆ ተፋሰሶች ላይ እስከ ከፍተኛ የሚደርስ የእርጥበት መጠን የሚኖር ይሆናል። በዚህም የከርሰ ምድርና የገፀ ምድር የውኃ ሀብትን ከማጎልበት አንጻር የጎላ ጠቀሜታ የሚኖረው ሲሆን የመስኖም ሆነ የሀይል ማመንጫ ግድቦችን የውኃ መጠን ከፍ እንደሚያደርግ ተገምቷል። የታችኛውና የመካከለኛው ዋቤ ሸበሌ እና የገናሌ ዳዋ በአንጻሩ መጠነኛ የሆነ የእርጥበት መጠን እንደሚያገኙም ይጠበቃል።
በክልሉ በአረንጓዴ አሻራ የተተከሉ ችግኞችን የጽድቀት መጠን ለማሳደግ የችግኝ እንክብካቤ ሥራ እየተሰራ ነው ---ቢሮው
Oct 1, 2024 317
ባህር ዳር፤ መስከረም 21/2017 (ኢዜአ)--በአማራ ክልል በዘንድሮ የክረምት ወቅት በአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር የተተከሉ ችግኞችን የጽድቀት መጠን ለማሳደግ የአረምና የኩትኳቶ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው የተፈጥሮ ሃብት ልማት ጥበቃና አጠቃቀም ዳይሬክተር አቶ እስመለዓለም ምህረት ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በክረምት ወቅት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተለያዩ ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያላቸው ችግኞች ተተክለዋል። በዚህም ህብረተሰቡን በማስተባበር 169ሺህ 361 ሄክታር መሬት በችግኝ መሸፈኑን ጠቅሰው፤ የተተከሉ ችግኞችን የፅድቀት ምጣኔን 85 በመቶ ለማድረስ የእንክብካቤ ሥራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ካለፈው ነሐሴ ወር 2016 ዓ.ም መጨረሻ ጀምሮ የአረምና የኩትኳቶ ሥራ እየተከናወነ መሆኑንም ተናግረዋል። እስካሁን በተደረገ ጥረትም በየአካባቢው ያሉ አርሶ አደሮችን በማስተባበር ከ51 ሺህ ሄክታር በሚበልጥ መሬት ላይ የተተከለን የዋንዛ፣ ዝግባ፣ ወይራ፣ ኮሶ፣ ባህር ዛፍ፣ አካሽያ ዲከረንስና ሌሎች ችግኞችን የማረምና የመኮትኮት ሥራ መከናወኑን ገልጸዋል። ለተተከሉ ሁሉም ችግኞች የመጀመሪያ ዙር የአረምና የኩትኳቶ ሥራ በተያዘው ወር ሙሉ በሙሉ ለማከናወን ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ገልፀዋል። የእርጥበታማ ጊዜው ከማለፉ በፊት አርሶ አደሩ ቀሪውን ችግኝ የማረምና የመኮትኮት ተግባሩን አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም አሳስበዋል። በምዕራብ ጎጃም ዞን የሰከላ ወረዳ ነዋሪ አርሶ አደር አላምረው ፈንቴ በሰጡት አስተያየት፤ የተተከሉ ችግኞችን ተንከባክቦ ለማሳደግ የሁሉም ሀላፊነት ነው። ቀደም ሲል የደንን ጥቅም በአግባቡ ባለማወቅ ደን ሲጨፈጨፍ መቆየቱን አስታውሰው፣ ባለፉት ዓመታት በአረንጓዴ አሻራ ልማት ባከናወኗቸው ስራዎች ችግኝን መትከልና ተንከባክቦ ማሳደግ ህይወትን ማስቀጠል መሆኑን መገንዘባቸውን ገልጸዋል። በመሆኑም ዘንድሮ በክረምት ወቅት በግልና በወል መሬቶች የተከሏቸውን ችግኞች የመንከባከብ ሥራ እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል። በደቡብ ጎንደር ዞን የፋርጣ ወረዳ አርሶ አደር እሱባለው ካሴ በበኩላቸው የደን መመንጠርን ከመከላከል ባለፈ ለችግኝ ተከላ በተሰጠው ትኩረት በአካባቢያቸው የተራቆቱ መሬቶች ቀድሞ ወደነበረው ልምላሜያቸው መመለሳቸውን ገልጸዋል። በአካባቢው ከሌሎች አርሶ አደሮች ጋር በመቀናጀት በክረምት በአረንጓዴ አሻራ የተተከሉ ችግኞችን የማረምና የመኮትኮት ሥራ እያከናወኑ መሆናቸውን ገልጸዋል። በክልሉ በ2015 ዓ.ም የክረምት ወቅት በአረንጓዴ አሻራ ከተተከሉ ችግኞች 80 በመቶ ያህሉ ፀድቀው በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ከቢሮው የተገኘ መረጃ ያመለክታል።
የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከልማትም ባለፈ የዲፕሎማሲ ስኬትና የቀጣናዊ ትስስር መሰረት እየሆነ ነው
Sep 28, 2024 438
አዲስ አበባ፤ መስከረም 18/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከልማትም ባለፈ የዲፕሎማሲ ስኬትና የቀጣናዊ ትስስር መሰረት እየሆነ መምጣቱን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ፈቲ ማሀዲ (ዶ/ር) ገለጹ። የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በተጠናከረና በተሳካ መልኩ የቀጠለ የልማት ፕሮግራም መሆኑ ይታወቃል። በ2015 ዓ.ም በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር በተተክለው 7 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኞች በተደረገው የዳሰሳ ጥናት 90 በመቶ መጽደቃቸው የታወቀ ሲሆን በተጠናቀቀው ዓመትም በሀገር አቀፍ ደረጃ 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር መሬት ተዘጋጅቶ የአረንጓዴ አሻራ አርፎበታል። በዚሁ ሁኔታ በመንግስት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ ልማት በተጠናከረ መልኩ የሚቀጥል ይሆናል። በዚሁ ጉዳይ ላይ ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ፈቲ ማሀዲ(ዶ/ር) ፤ መርሃ ግብሩ ከሀገራዊ ስኬትም የተሻገረ ፋይዳ እንዳለው አንስተዋል። የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከልማትም ባለፈ የዲፕሎማሲና የቀጣናዊ ትስስር መሰረት እየሆነ መምጣቱን ገልጸዋል። በልማት ፕሮግራሙ ሂደት በዘርፉ ከተሰማሩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በትብብር ለመስራትም ጥሩ አጋጣሚ እየፈጠረ መሆኑን አንስተዋል። የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ልማት በቅጡ የተረዱ ዓለም አቀፍ ተቋማትም ጥቅሙን በመገንዘብ ምስክርነት የሰጡ መሆኑ አንስተዋል። የጎረቤት አገራትንና ቀጣናውን ጭምር ተጠቃሚ የማድረግ ዓላማ የሰነቀው የልማት ሂደት የጋራ ተጠቃሚነትና የዲፕሎማሲ ስኬት እያመጣ መሆኑንም ዶክተር ፈቲ ተናግረዋል። የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ልማት ቀጣናዊ የልማት ትስስርን የሚፈጥር በመሆኑ ሁሉም በምሳሌነት ሊወስዱት የሚገባ ስኬታማ ከንውን መሆኑን አንስተዋል። በምክር ቤቱ የውጭ ግንኙትና የሰላም ጉዳዩች ቋሚ ኮሚቴ አባል ሳዲግ አደም፤ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ትኩረት ተሰጥቶት ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል። በሂደቱም ስኬት እየተመዘገበና ተጨባጭ ጠቀሜታም እያመጣ መሆኑን ተናግረዋል። የዘንድሮው የአረጓዴ አሻራ መርሃ ግብር “የምትተክል ሀገር የሚያጸና ትውልድ” በሚል መሪ ሀሳብ በስኬት መከናወኑ ይታወቃል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
ኤጀንሲው ታዳሽ ኃይልን በሦስት እጥፍ ለማሳደግ እየሰራ ነው
Sep 24, 2024 715
አዲስ አበባ ፤መስከረም 14/2017 (ኢዜአ)፦ዓለም አቀፍ ኢነርጂ ኤጀንሲ ታዳሽ ኃይልን በሦስት እጥፍ ለማሳደግ እየሰራ መሆኑን የሮይተርስ ዘገባ አመለከተ ። የኤጀንሲው ሪፖርት እ.ኤ.አ. በ2030 ዓለም አቀፍ የታዳሽ ኃይልን በሦስት እጥፍ በማሳደግ የነዳጅ ፍጆታን በመቀነስ የአየር ንብረት ለዉጥ ግቡን ማሳካት እንደሚቻል አመልክቷል። በአየር ንብረት ለውጥ ላይ እርምጃ ለመውሰድ በኒውዮርክ የአየር ንብረት ሳምንት ላይ ለታደሙ ከመንግሥት እና ከንግዱ ዘረፍ ለተውጣጡ ኃላፊዎች ሪፖርት ማቅረቡን ዘግቧል። በዱባይ አምና በተካሄደው COP 28 የአየር ንብረት ጉባኤ 200 የሚጠጉ ሀገራት እንደ የንፋስና ፀሀይ ያሉ የታዳሽ ኃይሎችን በሦስት እጥፍ በማሳደግ በ2050 ዜሮ የካርበን ልቀት ላይ ለመድረስ መስማማታቸውን ዘገባው አስታውሷል። አገራት በ2030 ስምምነቱን ሙሉ በሙሉ በመተግበር ጥቅም ላይ ለማዋል 25 ሚሊዮን ኪሎ ሜትር የኤሌክትሪክ መስመሮችን ለመገንባት እና ለማዘመን የተቀናጀ ጥረት ማድረግ እንዳለባቸውም አንስቷል። በዚህም በ2030 ዓለም 1 ሺህ 500 ጊጋዋት የኃይል ማከማቻ አቅም እንደሚያስፈልጋት ሮይተርስ በዘገባው ጠቅሷል። አገራት በCOP 28 የኃይል አጠቃቀምን የሚረዱትን የኃይል ቆጣቢ እርምጃዎችን በእጥፍ ለማሳደግ ቃል የገቡ ሲሆን፤ዉጤታማነቱ መንግሥታት ለፖሊሲዎቻቸዉ ቅድሚያ እንዲሰጡ መጠየቃቸውን አመላክቷል። በፓሪስ የአየር ንብረት ስምምነት መሰረት የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት ሀገራት ታዳሽና የኢነርጂ ውጤታማነት ግቦችን በአገራዊ ዕቅዳቸው ውስጥ ማካተት አለባቸው ሲል ዓለም አቀፉ ኢነርጂ ኤጀንሲ ማሳሰቡን ዘገባው ያመለክታል። ከዓለም አቀፉ የኢነርጂ ዘርፍ የተለቀቀው የልቀት መጠን ባለፈው ዓመት ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱንም ዘገባው አንስቷል። የታዳሽ ኃይል አቅምን በሶስት እጥፍ ማሳደግና የኃይል አጠቃቀምን ለመቀነስ የኃይል ቆጣቢ እርምጃዎችን በእጥፍ ማሳደግ በአሥር ዓመታት መጨረሻ የዓለም ሙቀት አማቂ ጋዝ ልቀትን በ10 ቢሊየን ሜትሪክ ቶን ሊቀንስ ይችላል ተብሎ ከሚጠበቀው ጋር ሲነጻጸር መሆኑን ሪፖርቱን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል።
የሱዳንን ግጭት ለማስቆም አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድ ተጠየቀ
Sep 24, 2024 564
አዲስ አበባ ፤መስከረም 14/2017 (ኢዜአ)፦የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ እና የአሜሪካ መሪዎች የሱዳንን ግጭት ለማስቆም አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድ ማሳሰባቸውን ሱዳን ትሪቡን ከዋሽንግተን ዘግቧል። የሁለቱ አገራት ፕሬዘዳንቶች በሱዳን ጉዳይ ላይ ትናንት ውይይት ማድረጋቸውን ዘገባው ጠቁሟል። የተባበሩት ዓረብ ኢምሬቶች ፕሬዘዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ እና የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን ከውይይታቸው በኋላ በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል። መሪዎቹ በመግለጫቸው በሰላማዊ ሰዎች ላይ እደረሰ ባለው መፈናቀል ረሀብና ጭካኔ የተሞላበት ግጭት ቆሞ ዘላቂ መፍትሄ ሊበጅለት ይገባል ማለታችውን ዘግቧል። "ለሱዳን ግጭት ምወታደራዊ መፍትሄ የለም" ያለው መግለጫው ጦርነቱ ባስቸኳይ እንዲቆም፣ ወደ ፖለቲካዊ ውይይት እንዲመለስ እና በሲቪል የሚመራ አስተዳደር እንዲሸጋገር ጥሪ አቅርቧል። በዳርፉር እየተባባሰ የመጣው ብጥብጥም እንዳሳሰባቸው መሪዎቹ መግለጻቸውን ዘገባው አመልክቷል። ሁለቱም ወገኖች ግጭት አቁመው ወደ ድርድር የማይመጡና የዓለም አቀፉን የሰብዓዊ ህግ የማያከብሩ ከሆነ የተለያዩ ማዕቀቦችን ከመጣል ጀምሮ በዘር ማጥፋት ወንጀል በዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል ተጠያቂ እንዲሆኑም ጠይቀዋል። ሰላማዊ ዜጎችን በተለይም ሴቶችን፣ ህጻናትን እና አረጋውያንን መጠበቅ ከምንም በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር መሆኑንም አዘስገንዝበዋል። በግጭት መስመሮች የእርዳታ አቅርቦትን ለማመቻቸት ሰብዓዊ ፋታዎች እንዲፈጠሩ የሁለቱ አገራት መሪዎች መጠየቃቸውን ሱዳን ትሪቡን በዘገባው አመልክቷል።
የዓለም ፋይናንስ አሰራር ጥልቅ ማሻሻያ ያስፈልገዋል - አንቶኒዮ ጉተሬዝ
Sep 23, 2024 645
አዲስ አበባ፤ መስከረም 13/2017 (ኢዜአ):- የዓለም ፋይናንስ አሰራር ጥልቀት ያለው ማሻሻያ እንደሚያስፈልገው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ገለጹ። የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ነባራዊውን ዓለም የሚያንጸባርቅ መሆን አለበት ብለዋል። ከ79ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ጎን ለጎን የዋና ፀሐፊው አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ኢኒሼቲቭ የሆነው የመጪው ጊዜ ጉባዔ (Summit of the Future) በኒውዮርክ እየተካሄደ ይገኛል። የባለብዙ ወገን የዲፕሎማሲ አሰራር የእይታ ለውጥ ማምጣት፣ የተገቡ ቃልኪዳኖችን መፈጸምና የረጅም ጊዜ ችግሮችን መፍታት ላይ የጉባዔው ዋንኛ ማጠንጠኛ ጉዳዮች ናቸው። የተመድ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በጉባኤው ላይ የተሰበሰብነው የባለብዝሃ ወገን ስርዓትን ከተጋረጠበት የሕልውና አደጋ ለመታደግ ነው ብለዋል። ጉባኤው ዓለም አቀፍ ተቋማት የተመድ ቻርተር እሴቶችን መሰረት ባደረገ መልኩ ይበልጥ ሕጋዊ፣ ፍትሐዊና ውጤታማ መሆን የሚያስችላቸው ጥልቅ ማሻሻያዎች በሚያደርጉበት ሁኔታ ላይ ሀሳቦችን እንዲያነሳ ጠይቀዋል። የ21ኛው ክፍለ ዘመን ፈተናዎች የ21 ክፍለ ዘመንን መፍትሔዎች ይሻሉ ያሉት ዋና ፀሐፊው ሁሉን አሳታፊና ለሰብዓዊነት ቅድሚያ የሚሰጡ ማዕቀፎች እንደሚያስፈልጉ አመልክተዋል። በበርካታ ውስብስብና አሳሳቢ ፈተናዎችና ስጋቶች እያለፈች የምትገኘው ዓለም የገጠሟት ዘርፈ ብዙ ተግዳሮቶች በዘላቂ ልማት ላይ አሉታዊ ተጽእኖዎችን ማሳደሩን ነው የገለጹት። ይህም በማደግ ላይ የሚገኙ አገራት እድገት ላይ ጋሬጣ እንደሆነ ተናግረው ይህ ፍትሐዊ ካልሆነው የፋይናንስ አቅርቦት ጋር ተዳምሮ ተደራራቢ ጫናዎችን መፍጠሩን አመልክተዋል። በቅኝ ግዛት ዘመን የተዘረጋው የዓለም የፋይናንስ ስርዓት የአገራቱን የዘላቂ ልማት ትልሞችና ፈተናዎች ባማከለና ከወቅቱን የዓለም ኢኮኖሚ ሁኔታ ጋር በተጣጣመ መልኩ ጥልቅ ማሻሻያ ሊደረግበት እንደሚገባ አስገንዝበዋል። የፋይናንስ ስርዓቱን ለመለወጥ የተጀመሩ ተስፋ ሰጪ ስራዎች ማስቀጠል እንደሚያስፈልግም አጽንኦት ሰጥተዋል። የተመድ የጸጥታው ምክር ቤትም ሁለን አሳታፊና አካታች ያደረገ ፍትሐዊ ለውጥ ማድረግ እንዳለበት ገልጸው የአፍሪካ፣ እስያ፣ ፓሲፊክና ላቲን አሜሪካ በምክር ቤቱ ውክልና ሊያገኙ ይገባል ነው ያሉት። ዓለም አቀፍ የትብብር መድረክን ፍትሃዊ፣ አሳታፊና ትስስርን አጎልባች እንዲሆን ቁርጠኝነት የተሞላባቸውን እርምጃዎች መውሰድ እንደሚያስፈልግ አክለዋል። ትናንት በመጪው ዘመን ጉባዔ መክፈቻ ቀን አገራት ዓለም አቀፍ የዲጂታል ማዕቀፍና የቀጣይ ትውልድ የመርሆዎች መግለጫን ያካተተ ታሪካዊ የተባለለት ‘Pact for the future’ (የቀጣይ ዘመን ስምምነት) ማጽደቃቸው የሚታወስ ነው። ጉባዔው የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ዛሬ ማምሻውን ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።
በአፍሪካ በዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ የተጠረጠሩ ከ25 ሺህ በላይ ሰዎች ተለዩ
Sep 16, 2024 822
አዲስ አበባ፤ መስከረም 6/2017(ኢዜአ)፡- የዓለም ጤና ድርጅት ከዘንድሮው የፈረንጆቹ አዲስ ዓመት መጀመሪያ ጀምሮ በዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ የተጠረጠሩ ከ25 ሺህ በላይ ሰዎች በሽታ መለየታቸውን አስታወቀ። የአፍሪካ በሽታ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ማዕከል (ሲዲሲሲ) በበኩሉ ለዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ ምላሽ 600 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያሰባስብ የስፑትኒክ ዘገባ አመለክቷል። ከጥር 1 እስከ መስከረም 8/ 2024 ድረስ ከ720 በላይ በበሽታው ምክንያት ሞት መመዝገቡን ተገልጿል። እንደ ዓለም ጤና ድርጅት እስከ መስከረም 8/2024 በአፍሪካ ከበሽታው ጋር የተያያዙ 5ሺህ 789 የበሽታ ምልክቶች በቤተ ሙከራ ሲረጋገጥ 32 ሰዎች መሞታቸውን ዘገባው አመልክቷል። በሽታው በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን፤ በአገሪቱ ከበሽታው ጋር በተያያዘ ከተጠረጠሩ 21 ሺህ 835 ጉዳዮች 717 ሰዎች መሞታቸውን በዘገባው ተጠቅሷል። የዓለም ጤና ድርጅት የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወረርሽኝ በአገሪቱ ምሥራቃዊ ክፍልና በአጎራባች አገሮች የሚያደርሰውን ጉዳት ከፍ አድርጎ መገምገሙን አመላክቷል። ድርጅቱ የወረርሽኙ ጉዳት በናይጄሪያና በሌሎች የምዕራብ፣ የመካከለኛው እና የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት መጠነኛ እንደሆነ መታሰቡንና በአፍሪካ እና በተቀረው ዓለም ስላለው ሁኔታ ተመሳሳይ ግምገማ መስጠቱንም በዘገባው ተገልጿል። እንደ ስፑትኒክ ዘገባ በአጠቃላይ ከጥር 1/2022 እስከ ሐምሌ 31/2024 በዓለም ከዝንጀሮ ፈንጣጣ ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ 103ሺህ 48 የተረጋገጡ ጉዳዮች፤ 229 ሞትን ጨምሮ በ121 አገራት ተመዝግበዋል። የአፍሪካ በሽታ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ማዕከል (ሲዲሲ) በበኩሉ ለዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ ምላሽ 600 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያሰባስብ ገልጿል። የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ዣን ካሴያን ገንዘቡ ከአፍሪካ ህብረት ሀገራት፣ ከልማት አጋሮች፣ ከበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ከግሉ ዘርፍ ለማሰባሰብ እንደታቀደ አመልክተዋል። እንደ ጋቪ እና ዘ ፓንዴሚክ ፈንድ ካሉ ድርጅቶች ጋር ውይይት እየተካሄደ መሆኑንና ፤ የቴክኖሎጂ ዝውውሮች የክትባት ወጪዎችን 90በመቶ ሊቀንስ እንደሚችል ዳይሬክተሩ መግለጻቸውን ዘገባው አመልክቷል። በተጨማሪም የምዕራቡ ዓለም ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ትምህርት መውሰዱንና በዝንጀሮ ፈንጣጣ ወረርሽኝም አፍሪካን እንዳልተዉ ማሳየት እንደሚጠበቅበት ማስገንዘባቸውን አንስቷል። ገንዘብ የማሰባሰብ ጥረት የዓለም ጤና ድርጅት ባለፈው ወር በዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ ዓለም አቀፍ ድንገተኛ የጤና አደጋ መሆኑን ካወጀ በኋላ የመጣ መሆኑን በዘገበው ተጠቅሷል።
ሐተታዎች
ኢሬቻና የበዓሉ ታዳሚዎች
Oct 5, 2024 207
ከገዳ ሥርዓት እሴቶች አንዱ የሆነው የኢሬቻ በዓል ዘንድሮ "ኢሬቻ ለባህላችን ሕዳሴ" በሚል መሪ ሀሳብ በሆራ ፊንፊኔ ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ በድምቀት ተከብሯል። በአባመልካና በአባገዳዎች ምርቃት በተጀመረው በዓል ላይ በርካታ ብሔር ብሔረሰቦችና የውጭ ሀገራት ዜጎች ተገኝተዋል። የበዓሉ ታዳሚዎች እንደሚሉት ኢሬቻ በአሁን ወቅት እያደገ ከኢትዮጵያ አልፎ በዓለም እየታወቀ በመሆኑ መደሰታቸውን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ገልፀዋል፡፡ በበዓሉ ላይ ያገኘናቸው ወይዘሮ ትዕግስት መኮንን እንደገለፁት፤ ኢሬቻ የኢትዮጵያ ሕብር የሚገለጥበት ጌጥ በመሆኑ ልንኮራበትና ይበልጥ ልናጎለብተው ይገባል ሲሉ ተናግረዋል። የሕዝብን አንድነት የሚያጠናክር ኃብት የሆነውን የኢሬቻ በዓል እሴቱ ሳይበረዝ ለትውልድ እንዲተላለፍ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊሰራ ይገባል ነው ያሉት። በዓሉ በደማቅ ሥነ-ሥርዓት የተጠናቀቀ በመሆኑ መደሰታቸውን ገልጸው፤ ለቀጣይ ዓመት በተመሳሳይ መልኩ በዓሉን ለማክበር ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ሌላው ታዳሚ መብራቱ ቶሎሳ እንደገለፀው፤ ሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል የኢትዮጵያ ሕዝብ ትስስርንና አንድነትን እያጠናከረ ነው፡፡ ከአገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን ከአገር ውጭ የሚመጡ እንግዶች በጋራ ተሰባስበው የሚገናኙበት ታላቅ ሁነት መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ ሌላኛው አስተያየት ሰጪ ተሬሳ አያና በበኩሉ፤ ከኢሬቻ ክብረ-በዓል በኋላ ሕብረታችንን አጠናክረን በሰላም መኖራችንን ማስቀጠል አለብን ብሏል። የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት የከተማዋን ገጽታ እንደቀየረው በመግለጽ፤ በቀጣይ እጅ ለእጅ ተያይዘን የአገራችንን ሰላምና ብልፅግና ለማረጋገጥ ቁርጠኛ መሆን አለብን ሲልም አክሏል። መምህር ሎሜ ገብረማርያም፤ ኢሬቻ ለተከታታይ ዓመት ማክበራቸውን ገልጸው፤ የዘንድሮ ዓመትም ድባብ ከከተማው አዲስ ገጽታ ጋር ተዳምሮ አስደሳች መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ሌላኛዋ አስተያየት ሰጪ ልብነሽ ስንታየሁ በበኩሏ፤ የኢሬቻ በዓል ሁሉም ያለውን ለብሶ አምሮና አጊጦ የሚወጣበትና ባህሉን በአንድነት በመሆን የሚያስተዋውቅበት መሆኑን ገልጻለች፡፡
የምስጋና ድምጾች ጎልተው የሚሰሙበት - ኢሬቻ
Oct 4, 2024 183
የምስጋና ድምጾች ጎልተው የሚሰሙበት - ኢሬቻ ኢሬቻ ለፈጣሪ ምስጋና የሚቀርብበት በዓል ነው፡፡ ኢሬቻ በሰውና በፈጣሪው እንዲሁም በሰውና በፍጥረታት መካከል ለሚኖረው የተፈጥሮ ህግ በአፋን ኦሮሞ “ሰፉ” ተገዢነቱን የሚገልፅበት ክብረ በዓል ነው፡፡ የተፈጥሮ ህግ እንዳይዛባ እስካሁን ላቆያቸው ፈጣሪ በጋራ ሆነው ለዋቃ ምስጋና የሚያቀርቡበት ነው፡፡ ከተፈጥሮ ጋር ያለውን ግንኙነት ወይም ትስስር የሚያድስበት በዓል ነው፡፡ ኢሬቻ የምስጋና በዓል ነው፤ ከክረምት ወቅት መለያየትና መራራቅ በኋላ ሰዎች በአብሮነት ብርሃን ለማየት ያበቃቸውን ፈጣሪ የሚያመሰግኑበት። ስለ ሰላምና አንድነት የሚዘመርበት፣ ስለመጪው ጊዜ መልካም ምኞት የሚገለጥበት፣ ሁሉን ላደረገ ፈጣሪ ምስጋና የሚቸርበት የአብሮነት በዓል ነው። በልመናው፣ በምርቃቱ፣ በምስጋናው ሁሉ ሀዬ! ሀዬ! ሀዬ! (አሜን! አሜን! አሜን!) የሚሉ ድምፆች ይስተጋባሉ። የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል መስከረም 25 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሆራ ፊንፊኔ እንዲሁም በማግስቱ እሑድ መስከረም 26 ቀን በቢሾፍቱ ሆራ ሀርሰዲ ይከበራል። ኢሬቻ ለሁለት ትላልቅ ምክንያቶች የሚከበር ሲሆን ፈጣሪ ለሰው ልጅ ላደረገው መልካም ነገር ምስጋና ለማቅረብ ብሎም ወደ ፊት እንዲሆንለት ለሚፈልገው ነገር ፈጣሪን ለመማጸን ነው፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ከባዱን የክረምት ወራት በሙሉ ጤንነት ላሸጋገረው ዋቃ/ፈጣሪን መልካ በመውረድ ያመሰግናል፡፡ ሁሉን የፈጠረውን አምላክ፣ ሁሉን አሳልፎ ለዚያ ያበቃውን ፈጣሪ፣ በንፁህ ልቦና ወደ መልካ ወርዶ ያመሰግናል፡፡ ዓመቱም የሠላም፣ የፍቅር፣ የስኬትና የብልጽግና እንዲሆንለትም ይለምናል፡፡ በዚህ ወቅት እርስ በርስም እንኳን ለቢራ /ፀደይ ወቅት/ አደረሳችሁ በመባባል ደስታውን ይገልጽበታል፡፡ ኢሬቻ በዓመት ሁለት ጊዜ የሚከበር ሲሆን ኢሬቻ መልካ እና ኢሬቻ ቱሉ በመባልም ይታወቃሉ፡፡ ኢሬቻ መልካ በወርኃ መስከረም በመልካ/በውኃ ዳርቻ ላይ የሚከበር በዓል ነው፡፡ ኢሬቻ መልካ የሚከበረው በመስከረም ወር ከመስቀል በዓል በኋላ ሲሆን፤ የክረምት ወራት የዝናብ፣ የደመና፣ የጭቃና የረግረግ ወቅት አልፎ ለፈካው ወራት በመብቃቱ ለፈጣሪ ምስጋና የሚቀርብበት ነው። የኦሮሞ ህዝብ በክረምት ወራት ዝናብ ለሰጠውና በሰላም ወደ ጸደይ ላሸጋገረው ዋቃ/ፈጣሪ ምስጋና ያቀርባል፡፡ በቀጣይም ቡቃያው ከየትኛውም የተፈጥሮ አደጋ ተጠብቆ፤ በሰላም ወደ ጎተራው እንዲገባ ፈጣሪን የሚማጸንበት ነው፡፡ ሁለተኛው ኢሬቻ ቱሉ ሲሆን ይህም የሚከናወነው የበጋው ወራት ተገባዶ የበልግ / የአርፋሳ ወቅት ሲገባ ነው፡፡ በአቅራቢያ በሚገኙ ተራራማ ቦታዎች ላይ በመውጣት ለመጪው ክረምት ዝናብ ስጠን፣ ወራቱን የአዝመራ ጊዜ አድርግልን፣ በማለት ፈጣሪን ይለምናሉ፡፡ ''እርጥበት አትንፈገን፣ ወቅቶች ጊዜያቸውን ጠብቀው ይምጡ፤ የዝናብ ንፋስ ስጠን'' በማለት ለፈጣሪ ተማጽኖ የሚቀርብበት ነው። "ይህን ተራራ የፈጠርክ ፈጣሪ ወቅቱን የሰላም አድርግልን፣ የሰላም ዝናብ አዝንብልን፣ ጎርፍን ያዝልን፣ የተዘራው ፍሬ እንዲያፈራ እንለምንሃለን" እያለ በኢሬቻ ቱሉ ላይ ፈጣሪውን ይለምናል፡፡ በኢሬቻ በዓል የፈጣሪ ምህረት፣ ዕርቅ፣ እዝነት እና በዓሉ የሰላም በዓል እንዲሆን ኦሮሞ ፈጣሪውን ይጠይቃል፤ ይማፀናል፤ ለተደረገለትም ነገር ሁሉ ያመሰግናል። የኢሬቻ በዓል ከገዳ ሥርዓት መገለጫ ሲሆን፤ በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ለዘመናት ሲከበር የቆየ በዓል ነው። ኢሬቻ አብሮነትን በማጠናከር ፈጣሪያቸውን ለማመስገን የወጡ ሰዎች በንፁህ ልቦና ፈጣሪያቸውን አመስግነው ተደስተው የሚመለሱበት፣ አንድነታቸውንና ወንድማማችነታቸውን የሚያጠናክሩበት ነው። በኢሬቻ ከተለያየ ስፍራ የሚመጡ ተሳታፊዎች ያለምንም ልዩነት፣ በፍቅርና በአንድነት ፈጣሪን ያመሰግናሉ፡፡ ኢሬቻ የኦሮሞን አንድነትና የብሔር ብሔረሰቦች ወንድማማችነት ከማጠናከር አንፃር ምቹ መድረክ ነው፡፡ ኢሬቻ ከመድረሱ በፊት አባገዳዎችና የሃገር ሽማግሌዎች በየአከባቢው እየሄዱ በማህበረሰቡ መካከል ቅሬታና አለመግባባት ካለ እንዲፈታ፣ ይቅር እንዲባባሉ፣ ደም የተቃባ ካለ ጉማ /ካሳ/ እንዲከፍል ያደርጋሉ፡፡ ይህም እርቅ ሳያወርዱ ቂም ይዞ ለምስጋና ወደ ኢሬቻ መሄድ የተከለከለ ስለሆነ ነው፡፡ ኢሬቻ በንፁህ ልቦናና በንፁህ አእምሮ፣ ያለ ቂምና ቁርሾ ተኬዶ ሠላም የሚሰበክበት፣ ለምስጋና መልካ ከተወረደ በኃላም አባገዳዎች እርስ በርሳችሁ ይቅር ተባብላችኃል? እርስ በርሳችሁ ሠላም ናችሁ? ከፍጥረታትና ከፈጣሪ ጋር ሠላም አውርዳችኃል? ብለው ይጠይቃሉ፡፡ ምናልባት በየአከባቢው እርቅ ሳያወርድ የመጣ ካለ እንኳን በዚህ ወቅት ይቅርታ በመጠያየቅ ምስጋናውን አቅርቦ ይሄዳል፡፡ ለምስጋና እርጥብ ሳር ይዞ የሚወጣ ሰው ቂምና ጥላቻን አስወግዶ፣ ሠላምን፣ ወንድማማችነትን፣ ፍቅርን፣ አንድነትን፣ ተስፋን፣ ብልፅግናንና መልካም ምኞትን ይሰብካል፤ ያውጃል፡፡ ከፈጣሪው ለተሰጠው ስጦታ እውቅና ይሰጣል፤ ያመሰግናል፡፡ በፍጥረታትና በፈጣሪ መካከል ያለውን ትስስር ያደንቃል፡፡ ሲያመሰግንም ለቤተሰብ፣ ለጎረቤት፣ ለአጠቃላይ ለሰው ልጅ፣ ለሀገር ሠላምና ፍቅር በመመኘት ይዘምራል፤ ያመሰግናል፤ ይለምናል፡፡ ይህ ደግሞ ኢሬቻ የእርቅና የሠላም ተምሳሌት መሆኑን ያመለክታል፡፡ ከዚህ የምንረዳው ኢሬቻ የሠላምና የእርቅ መድረክ መሆኑን ነው፡፡ ለዚህ ነው ኦሮሞ ሰው እርስ በርሱ ከታረቀ ፈጣሪም ይታረቀዋል ብሎ የሚያምነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ኢሬቻ ምርቃት የሚሰጥበትና የሚቀበሉበት ስፍራም ነው፡፡ ኢሬቻ እሴቶች የሚጎሉበት መድረክም ነው። ለአብነትም በዘመናዊ መንገድ በተዘጋጁ የባህል አልባሳት ደምቆ መታየት የኢሬቻ መልክ ነው። በዚህም ለባህል አልባሳትና ጌጣጌጥ አምራቾች ገበያ እንዲሁም ለበርካቶች የስራ ዕድል በመፍጠር አዎንታዊ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። በተጨማሪም ለቱሪዝም ኢንዱስትሪ ዕድገት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው፡፡
"ልጅ እያላችሁ እናታችሁን አገልግሉ ስታድጉ ለአገራችሁ ዘብ ሁኑ" የሚለውን የአባታቸውን ምክር ተቀብለው ለኢትዮጵያ ዘብ የቆሙት ሶስቱ ወንድማማቾች
Oct 4, 2024 201
ጋሻው ሲሳይ፣ ዘመድኩን ሲሳይና ዘላለም ሲሳይ ይባላሉ፤ ትውልድና ዕድገታቸው አርሲ አሰላ ነው። ወንድማማቾቹ የወታደር ልጆች ወጥቶ አደሮች ናቸው፤ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ለመጠበቅ የቆረጡ ጀግኖች። አባታቸው የቀድሞ ሰራዊት አባል በመሆን ለኢትዮጵያ ሉአላዊነት ዘብና አለኝታ ሆነው አገልግለዋል። የአባታቸውን ታሪክ እና ገድል እንዲሁም ስለሀገር ፍቅር እየሰሙ ያደጉት ልጆቻቸውም መከላከያ ሰራዊትን በመቀላቀል በብርሸለቆ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ተመርቀዋል። አባታቸው ገና ከልጅነት ጀምሮ "ልጅ እያላችሁ እናታችሁን አገልግሉ ስታድጉ ለአገራችሁ ዘብ ሁኑ" በሚል ምክር የእናትና የሀገርን ተምሳሌታዊ ቁርኝት እያስረዱ እንዳሳደጓቸው ይናገራሉ። የዘመድኩንና የዘላለም ታላቅ የሆነው ጋሻው ሲሳይ ለሀገር ዘብ መቆምን ከአባቴ ተምሬ በመወሰኔ እጅግ ደስተኛ ነኝ ይላል። የአገር ምልክት የሆነውን የክብር ልብስ ለብሶ ኢትዮጵያን ከመጠበቅ የበለጠ የሚያኮራ ነገር እንደሌለም ይናገራል። የእርሱ ተከታይ ዘመድኩን ሲሳይ፤ የአባታቸውን ገድል ለማስቀጠል መከላከያ ሰራዊትን መቀላቀሉን ገልጿል። ዘላለም ሲሳይ በበኩሉ፤ ለሀገር ክብር መቆም እንደሚያስከብር በመጥቀስ ለኢትዮጵያ በውትድርና መስክ መሰለፍ የልጅነት ህልሙ እንደነበር አስታውሷል። ሶስቱ ወንድማማቾች የሀገር ፍቅር እንዲኖራቸውና የሀገራቸውን ዳር ድንበር እንዲያስከብሩ መርቀው ለሸኟቸው አባታቸው ምስጋና አቅርበዋል። ስልጠናውን በብቃትና ሙያዊ ስነምግባርን በተላበሰ አግባብ ማጠናቀቃቸውን ገልፀው፤ የሚሰጣቸውን ሀገራዊ ግዳጅ ሁሉ በብቃትና በሀላፊነት ለመወጣት ቁርጠኛ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። ኢትዮጵያን አክብሮ ከማስከበር በላይ ጀግንነት ባለመኖሩ ወጣቶች መከላከያ ሰራዊትን በመቀላቀል የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ መሆናቸውን እንዲያረጋግጡ ጥሪ አቅርበዋል።
ልብ ሊባል የሚገባው የልብ ህመም
Oct 2, 2024 274
"ልብ ሊባል የሚገባው የልብ ህመም "አሳሳቢነትና መፍትሔዎቹ በልብ ሕክምና ባለሙያዎች አንደበት። በዓለም ላይ በተለይም አፍሪካን ጨምሮ በታዳጊ ሀገራት የልብ፣ የደምሥርና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች የሚያስከትሉት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የጤና እክል ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል። በኢትዮጵያም በልብ፣ በደምሥርና ተላላፊ ባልሆኑ የበሽታ አይነቶች በርካታ ዜጎች በየቀኑ ለህልፈት እየተዳረጉ መሆኑን ባለሙያዎቹ ያነሳሉ። ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድረግ፣ ሱስ አምጪ ንጥረ ነገሮች፣ ስኳርና ጨው አብዝቶ መጠቀም ተላላፊ ላልሆኑ በሽታዎች የሚያጋልጡ መሰረታዊ ምክንያቶች ናቸው። ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉ የሕክምና ሙያተኞች የልብና የደምሥር በሽታዎችን አስቀድሞ መከላከል እንደሚቻል ያስረዳሉ፡፡ ነገር ግን በሽታዎቹ ስር ከሰደዱ በኋላ በህመምተኞቹ ላይ የሚያስከትሉት ወጪና ስቃይ ከፍተኛ ነው ብለዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የልብ ሐኪም ዶክተር ደጁማ ያደታ፤ የልብ ህመም በዓለም ላይ ቁጥር አንድ ገዳይ በሽታ መሆኑን ተናግረዋል። በኢትዮጵያም በለጋ የዕድሜ ክልል የሚገኙ ዜጎችን ከሚያጠቃ የጉሮሮ ቁስለት ህመም ጋር ተያይዞ የሚከሰት የልብ ህመም አሳሳቢነት ከፍተኛ እየሆነ መምጣቱን ገልጸዋል። በኤሊያና ኸልዝ ኬር የያኔት ሆስፒታሎች ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ግርማ አባቢ፤ የልብና የደምሥር በሽታ ከየትኛውም የህመም አይነት በላይ ለዜጎች ህልፈት መነሻ እየሆነ የመጣ አሳሳቢ የጤና እክል ነው ብለዋል። በኢትዮጵያ የልብና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመከላከልና የህክምና አገልግሎቱን ለማሻሻል በሚደረገው ጥረት የችግሩ ፍጥነትና ምላሽ የሚሰጥበት አካሄድ የተመጣጠነ አለመሆኑን ጠቅሰዋል። መንግስትም ሆነ የግሉ ዘርፍ ዜጎችን ለከፍተኛ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና እየዳረገ የሚገኘውን የልብ፣ የደምሥርና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመከላከል በሰፊው መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። የውስጥ ደዌና የአዋቂዎች የልብ ሐኪም የሆኑት ዶክተር ከፈለኝ ደጀኔ በበኩላቸው የልብ ህክምና እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ታዳጊ ሀገራት ዜጎች በጣም ውድ በመሆኑ ቅድመ መከላከል ላይ ትኩረት ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል። በታዝማ የውስጥ ደዌና ቀዶ ሕክምና ልዩ ማዕከል ጠቅላላ ሐኪም ዶክተር ኤልሻዳይ ሰለሞን፤ የልብ ህመም በተፈጥሮም ሆነ በሰዎች የእለት ከእለት የኑሮ ዘይቤ የሚከሰት በሽታ ነው ብለዋል። በህፃናት ላይ የሚከሰት የጉሮሮ (ቶንሲል) ህመም ኢትዮጵያን ጨምሮ የታዳጊ ሀገራት ዜጎች የልብ ሕመም ተጋላጭነት ከፍተኛ እንዲሆን ምክንያት መሆኑን ገልጸዋል። በተጨማሪም ሰዎች ጭንቀትንና የኮሊስትሮል መጠን በመቀነስ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴና የአመጋገብ ስርዓትን በማስተካከል ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን መከላከል እንደሚችሉ አስገንዝበዋል። የልብና የደምሥር የህክምና ግብዓቶች ውድ በመሆናቸው የሚያስከትሉት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና ከፍተኛ መሆኑን የአይሲኤምሲ አጠቃላይ ሆስፒታል ማርኬቲንግ ዳይሬክተር ጌታቸው ኃይለስላሴ ተናግረዋል። የልብ ህመም ድንገተኝነት ከፍተኛ በመሆኑ ዜጎች የተስተካከል የአመጋገብ ሥርዓት መከተልና የጤና ምርመራ ባህልን ማሳደግ እንደሚኖርባቸው አስገንዝበዋል። የልብ ሕክምና ጥቂት ሙያተኞች ያሉት ውስብስብ አገልግሎት ቢሆንም ከፍለው ከሚታከሙ ዜጎች ባሻገር አቅም ለሌላቸው ሰዎች በነፃ ህክምና አገልግሎት በመስጠት ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን እየተወጡ እንደሚገኙ ባለሙያዎቹ ተናግረዋል። መገናኛ ብዙሃንም የልብና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን በማስመልከት ቅድመ መከላከል ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ መስራት እንደሚጠበቅባቸው አንስተዋል። በኢትዮጵያ የልብ ማኅበር አስተባባሪነት "ልብን ለተግባር እናውል" በሚል መሪ ሃሳብ በኢትዮጵያ ለ9ኛ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ25 ጊዜ ዓለም አቀፉ የልብ ቀን በአዲስ አበባ መከበሩ ይታወሳል።
ትንታኔዎች
የመስከረም ድምቀቶች
Sep 19, 2024 763
መስከረም ዝም ብሎ ወር ብቻ አይደለም። መስከረም ለኢትዮጵያ ውበቷ፣ ቀለሟ፣ ትዕምርቷ፣ የባህር ሃሳቧ መባቻ ነው። መስከረም በባህሉ፣ በትውፊቱ፣ በኪነ እና ስነ-ቃሉ ልዩ ሥፍራ ይሰጠዋል። እንደ መስከረም ክብር፣ ሞገስ እና ፀጋ የተቸረው የትኛው ወር ይሆን? ሀገሬው ለቆንጆ ልጁ ስም ሲያወጣ ‘መስከረም’ እንጂ በሌላ ወር ሰይሞ አያውቅም። በኢትዮጵያ ምድር መስከረም ለሰው ልጅ ብቻ ሳይሆን ለእንስሳት እና አዕዋፋት ራሱ ልዩ ጊዜ ነው። 'አገር፣ ቀለም፣ ዘመን' እንደሸማው ድርና ማግ ከሚሆኑባቸው ወራት አንዱ መስከረም ነው። መስከረም አገርኛ አለባበስ፣ አገርኛ ዝማሬ፣ አገርኛ ጨዋታ፣ አገርኛ ትውፊትና ቀለም በተግባር ይታይበታል። መስከረም ሁለንተናዊ ውበቱ ድንቅ ነው፤ ትዕምርቱም ጉልህ ነው። መስከረም የብዙ ድምቀቶች መታያ ወር ነው። ዘመን መለወጫ መስከረም 1 ቀን ‘ርዕሰ ዓውደ- ዓመት’ ይሰኛል። የባህር ሐሳብ ሊቃውንት መስከረም ለምን የዘመን መለወጫ እንደሆነ ሲያትቱ “ብርሃናት /ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት/ የዓመት ዑደታቸውን በጳጉሜ ወር ጨርሰው በመስከረም ወር ስለሚጀምሩ ነው” ይላሉ። ’አበባዬ ሆይ፤ አበባዬ ሆይ’ የሚሉ ሕፃናት ተስፋና ምኞታቸውን በወረቀት ያቀልማሉ፤ የአበባ ስዕላት ይዘው በየደጃፉ ይሯሯጣሉ፤ የ’ዕደጉ’ ምርቃት ያገኛሉ፤ በደስታ ይፈነድቃሉ። በዚህ ድባብ ነው እንግዲህ መስከረም የግዑዛንም የሕይወታውያንም የነፃነት፣ የተስፋና የፍቅር ወርኅ ተደርጎ የሚናፈቀው። በመስከረም ምድር በዕንቁጣጣሽ ትፈካለች፤ በአበቦች ታጌጣለች፤ ውኆች ይጠራሉ። ሰማዩም የክብረ-ሰማይ ብርሃኑን ያጎላል። ጥቁር ደመና ጋቢ ይገፈፋል፤ ክዋክብት እንደፈንዲሻ በዲበ-ሰማይ ይደምቃሉ። ዕጽዋትና አዝዕርት እንቡጦች ይፈነዳሉ። የመብረቅ ነጎድጓድ ተወግዶ የሰላምና የሲሳይ ዝናብ ይዘንባል። በ’ዕንቁጣጣሽ’ ምድር ብቻ አይደለችም የምትዋበው። መስከረም ለሰው ልጆችም በተለይም ለወጣቶች የፍቅር፣ የእሸት እና የአበባ ወር ነው። የሰላም፣ የንጹህ አየር፣ የጤና ድባብ ያረብባል። የጋመ በቆሎ እሸት ጥብስ፤ ቅቤ ልውስ፤ ቅቤ በረካ ይናፈቃል። የተጠፋፋ ዘመድ አዝማድ ይገናኛል። ‘ሰኔ መጣና ነጣጠለን’ ብለው ወርኃ ሰኔን የረገሙ ተማሪዎች ተናፋቂያቸውን ያገኛሉና ‘መስከረም ለምለም’ ብለው ያሞካሹታል። የገበሬው የሰብል ቡቃያ ያብባል፤ እሸት ያሽታል። ጉዝጓዝ ሣር፣ ትኩስ ቡና ይሽታል። ደመራ ወመስቀል ደመራ መጨመር፣ መሰብሰብ፣ መከመር መሆኑን ሊቃውንት ይገልጻሉ፡፡ ኪዳነ ወልድ ክፍሌም በመዝገበ ቃላት መጽሐፋቸው ደመራ የሚለውን ቃል ደመረ ከሚለው የግእዝ ቃል የወጣ መሆኑን ያስነብባሉ፡፡ የበዓለ መስቀል ዋዜማ እንጨቶች የሚደመሩበት ስለመሆኑም ያስረዳሉ፡፡ መስቀል በእርሱ ላይ የተሰቀለውን ክርስቶስን ያሳስባል፡፡ ሰውና ፈጣሪን ለዘመናት ለይቶአቸው የነበረው የጠብ ግድግዳ የተናደበትና ሞት ድል የሆነበት የፍቅር ዓርማ መሆኑን የሀይማኖት አባቶች ይገልጻሉ፡፡ ንግሥት ዕሌኒ መስከረም 16 ቀን ደመራ ደምራ በጢስ ምልክት ተመርታ መስቀሉን ከተቀበረበት ለማውጣት ቁፋሮ ያስጀመረችበትን ቀን ምክንያት በማድረግም የመስቀል ደመራ በዓል ይከበራል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያንም ለመስቀል ችቦ እያበሩ በዓሉን በሆታ በእልልታ በስብሐተ እግዚአብሔር ያከብሩታል፡፡ መስከረም 16 እና 17 ቀን የሚከበረው የደመራ መስቀል በዓል ከሃይማኖታዊ አስተምህሮው ባለፈ ባህላዊ ትውፊትነቱ የጎላ በመሆኑ በአብዛኛው ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ይናፈቃል። ደመራና መስቀል የአንድነት፣ የፍቅር፣ የይቅርታ፣ አብሮነት፣ የምስጋና፣ የተስፋ… እሴቶች የሚገለጹበት ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ ክብረ-በዓል ነው። የኢትዮጵያ የመስቀል በዓል አከባበር በተባበሩት መንግሥታት የሳይንስ የትምህርት እና ባህል ተቋም መዝገብ ውስጥ በዓለም ቅርስነት ከተመዘገቡ የማይዳሰሱ ቅርሶች መካከል አንዱ ነው፡፡ መስቀል በአንዳንድ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ርዕሰ ዓውደ-ዓመት ይመስላል። በደቡብ ኢትዮጵያ መስቀል ከሃይማኖታዊ ይዘቱ ባህላዊ ጎኑ ይጎላል። መስቀልን ከሁሉም በዓላት የበለጠ ይናፍቁታል። የተራራቁ ቤተሰቦች የሚገናኙበት የፍቅር፣ የደስታና የእርቅ በዓል ነው መስቀል። በጋሞ ብሔረሰብ ባህል ለሰው ብቻ ሳይሆን ለእንስሳቱም ልዩ መኖ እንደሚቀርብላቸው ይነገራል። መስቀል በጉራጌዎች ዘንድ እንደ አውራው በዓል ይቆጠራል። ለመስቀል ዓመቱን ሙሉ ዝግጅት ይደረጋል። አባወራው ሰንጋ ለመግዛት፣ እማወራ ማጣፈጫውን ለማዘጋጀት፣ ወጣቶች ደመራና ደቦት ለማዘጋጀት፣ ልጆች ምርቃት ለመቀበል የየራሳቸውን ይዘጋጃሉ። ቤተሰብ ወዳጅ ዘመድ የሚጠያየቅበት፣ ጥላቻና ቂም በፍቅርና በይቅርታ የሚታደስበት ነው። የመስቀል በዓል በሁሉም የኢትዮጵያ አከባቢዎች በልዩ ድምቀት ከሚከበሩት በዓላት መካከል አንዱ ሲሆን እንደየአከባቢዎቹ ባህልና ትውፊት መሠረትም በተለያዩ ኃይማኖታዊና ባህላዊ ሁነቶችም ይከበራል፡፡ መስቀል የወል ክብረ በዓል ነው። የመስቀል ዕለት (መስከረም 17) በግ ይታረዳል። እህል ውሃ ቀርቦ የመንደሩ ሰው በጋራ ሲጫወት ይውላል፤ በሕብረት ይበላል። ኢሬቻ ኢሬቻ ከመስከረም ደማቅ መልኮች አንዱ ነው። የኦሮሞ ህዝብ በአንድነት የሚያከብረው ልዩና የማንነቱ መገለጫ የሆነው ኢሬቻ የምስጋና፣ የሰላምና የወንድማማችነት ምልክት ነው፡፡ በኦሮሞ ሕዝብ ባህል ዘንድ ኢሬቻ የሚከበረው ዝናብን፣ ሰላምን፣ ምርት እና የትውልድን ቀጣይነት የሚሰጥ ፈጣሪ በመሆኑ ጤናንና በረከትን የሚችረው እሱ 'ዋቃ' ወይም ፈጣሪ በመሆኑ ምስጋና ለማቅረብ ነው። የገዳ ስርዓት አንዱ አካል የሆነው ኢሬቻ የኦሮሞ ሕዝብ በረጅም ጊዜ የሕይወት ውጣ ውረድ ፈጣሪውን የሚያመሰግንብት ባህል፣ ማንነት፣ ስርዓትና ልምድ ነው። በዓመት ሁለቴ በሚከበረው ኢሬቻ በዓል በአባገዳዎች መሪነት የኦሮሞ ሕዝብ ፈጣሪን የማመስገኛና መማጸኛ ነው። የተራራ ኢሬቻ (ኢሬቻ ቱሉ) የሚከበረው የበጋው ወራት አልፎ የበልግ ዝናብ በሚጠበቅበት ወቅት ነው። በዚህም ፈጣሪ ''እርጥበት አትንፈገን፣ ወቅቶች ጊዜያቸውን ጠብቀው ይምጡ፣ የዝናብ ንፋስ ስጠን'' በማለት ይለምናሉ። የመልካ (የውኃ ዳርቻ) ኢሬቻ የሚከበረው በመስከረም ወር አጋማሽ፣ ከደመራ ወይም ከመስቀል በኋላ ባለው ቅዳሜና እሁድ ነው። ይህም በሆራ ፊንፊኔና በሆራ አር ሰዲ ይከበራል። በዚህም የክረምት ወራት የዝናብ፣ የደመናና፣ የጭቃና የረግረግ ወቅት አልፎ ለፈካው ወራት በመብቃቱ ምስጋና የሚያቀርብበት ነው። ኢሬቻ ለሰላምና ለእርቅ ትልቅ ስፍራ የሚሰጥ በዓል እንደሆነም ይታመናል። በዕለቱ ሰላም የአምላክ ስጦታ መሆኑ ይነገራል፤ ሰላም ከሁሉም ሀብት በላይ መሆኑም ይገለጻል። በዝናባማው ክረምት በጅረቶችና ወንዞች መሙላት ምክንያት ተራርቀው የነበሩ ቤተ ዘመዶች በባአሉ መከበሪያ ቦታ በባህል ልብሳቸው ድምቀው ይገናኛሉ፤ ይጠያየቃሉ። ኢሬቻ በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው የሰላምና የአብሮነት ምልክት በዓል ነው፡፡ በኦሮሞ ሕዝብ ባህላዊ አለባበሱን በማጌጥ ወደ ክብረ-በዓሉ የሚያመሩ ኢሬቻ አክባሪዎች እርጥብ ሳር እና አደይ አበባን ይይዛሉ። የኢሬቻ በዓል ሲከበር ከሚከወኑ ሥርዓቶች መካከል ሴቶች ሲቄ፣ እርጥብ ሣር እንዲሁም ጮጮ ይዘው ከፊት ሲመሩ አባ ገዳዎች ደግሞ ቦኩ፣ አለንጌ እና ሌሎችንም በበዓሉ ሥርዓት የሚፈቀዱትን ሁሉ በመያዝ ወደ ሥርዓቱ አከባበር ያመራሉ። ጊፋታ ጊፋታ በወላይታ ህዝብ ዘንድ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ታላቅ በዓል ሲሆን ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣ የአሮጌው ዓመት ማብቅያና የአዲሱ ዓመት መጀመሪያ የመሸጋገሪያ በዓል ነው፡፡ ጊፋታ ማለት ባይራ (ታላቅ)፣ መጀመሪያ እንደ ማለት ሲሆን በሌላ በኩል ጊፋታ ማለት መሻገር ማለት ነው፡፡ ይህም ከአሮጌ ወደ አዲስ፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን መሻገር የሚለውን ይገልጻል፡፡ ጊፋታ ሰዎች ብቻ ሳይሆኑ አእዋፋትና የቤት እንስሳትም ጭምር በጋራ የሚያከብሩት በዓል ነው ተብሎ ይታመናል፡፡ የወላይታ ብሔርሰብ የራሱ የሆነ የዘመን መቁጠሪያ አለው፡፡ በወላይታ የዘመን አቆጣጠር ጊፋታ የዓመቱ የመጀመሪያ ወር ስያሜ ነው፡፡ በበዓሉ “Gifaata Gazzee Abuuna Gaylle” ተብሎ ይዘፈናል፡፡ ይህም የበዓሉን ታላቅነት ለመግለጽ ስለመሆኑ ይነገራል፡፡ ጊፋታ መቃረቡ ከሚገለጽበት መንገድ አንዱ የጉልያ ሥርዓት ይጠቀሳል፡፡ ይሄም በአካባቢው ያሉ ዕድሜያቸው ከ15 እስከ 30 የሚደርሱ ወጣቶች የጉልያ ሥነ ሥርዓት ያከናወናሉ፡፡ ጉልያ ማለት ወጣቶቹ ለደመራ የሚሆን እንጨት የሚለቅሙበትና የሚያዘጋጁበት ወቅት ነው፡፡ ጊፋታ ከመከበሩ ቀደም ብሎ አካባቢን ማፅዳት፣ ቤት ማደስና የዕርቅ ሥራ ትልቅ ቦታ ከሚሰጣቸው መካከል ሲሆኑ በጊፋታ ለበዓሉ ድምቀት የሚውል ቅቤ፣ ሠንጋ በሬ፣ አልባሳት፣ ጌጣ ጌጦች፣ የስፌት፣ የሽክላ፣ የብረታ ብረት ምርቶችና ሌሎች ግባቶች የበዓሉ ድምቀት ናቸው፡፡ ግፋታ ሲሸኝ ጥቅምት በገባ በመጀመሪያው ሳምንት ማክሰኞ ሆኖ የሽኝት በሬ ታርዶ ከተበላ በኋላ ቶክ ጤላ የተባለውን ምሽት በችቦ ያባርራሉ፡፡ ዜማ በተቀላቀለበት ጩኸት ችቦ ይዘው ‹‹ኦሎ ጎሮ ባ! ሳሮ ባዳ ሳሮ ያ!›› ይላሉ፡፡ ትርጓሜውም ጊፋታ በሰላም ሄደሽ በሰላም ነይ! ማለት ነው፡፡ ዮ…ማስቃላ በጋሞዎች ዘንድ በየዓመቱ በጉጉት የሚጠበቀው «ዮ ማስቃላ» የዘመን መለወጫ በዓል በመስከረም ወር አጋማሽ ላይ ቅበላው ተከብሮ በዚሁ ወር መጨረሻ «ዮ ማስቃላ» ሽኝት በዓል በድጋሚ በድምቀት ይከበራል። መስከረም ወር የመጀመሪያው ቀን በጋሞ ዞን ”ሂንግጫ” ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ይህም አዲሱን ዓመት ለመቀበል ዝግጅት የሚደረግበት ቀን ነው። በጋሞዎች ዘንድ ዓመቱን ሙሉ ገንዘብ በመቆጠብ በዓሉን በድምቀት ለማክበር ዝግጅት ይደረጋል። ወንዶች ለበዓሉ የሚሆን ሠንጋ መግዣ፣ ለልጆች ልብስ እና ጌጣጌጥ ማሟያ፤ እናቶች ደግሞ ለቅቤ፣ ለቅመማቅመም፣ ለባህላዊ ምግቦች እና መጠጦች እህል መግዣ የሚሆን ገንዘብ ያጠራቅማሉ። በጋሞ ዞን የማስቃላ በዓል ለሰው ልጆች ብቻ ሳይሆን ለእንሳስት እና ለአዕዋፋትም ጭምር ነው ተብሎ ይታመናል፤ በዕለቱ ምግብ ከሰው አልፎ ለእንሳስት እና ለአዕዋፍም ይትረፈረፋል። ለከብቶችም የግጦሸ መሬት በየአካባቢው ይከለላል። በተለያዩ አጋጣሚዎች የተጣሉ ታርቀው፣ የተራራቁ ዘመድ አዝማድ እና ወዳጆች ተሰባስበው በዓሉን በጋራ እንዲያከብሩ ማድረግ የጋሞ ማስቃላ በዓል መገለጫ ነው። የመጨረሻው የማስቃላ ሽኝት በዓል እንደየአባወራው አቅም በፈቀደ መጠን የሚፈፀም ነው። በዚህ ዕለት ሁሉም ያለ ፆታ ልዩነት በአደባባይ ላይ ወጥተው ያኑረን እስከ ወዲያኛው እንኖራለን እያሉ ይጨፍራሉ። ከዚህ በኋላ ለመጪው ዓመት በሰላም በጤና ያድርሰን ተባብለው ፈጣሪን በመማፀን ዝግጅቱ ይቋጫል። ያሆዴ መስቀላ የክረምቱ ወራት አልፈው መስኩ በልምላሜና በአደይ አበባ ሲያሸበርቅ በሃድያዎች ዘንድ ትልቅ ዝግጅት አለ - ያሆዴ መስቀላ። “ያሆዴ“ ማለት እንደ ብሔሩ የባህል ሽማግሌዎች ትርጓሜ እንኳን ደስ አላችሁ፤ የሚል የብስራት ትርጉም ያለው ሲሆን ”መስቀላ” ማለት ደግሞ ብርሃን ፈነጠቀ ማለት ነው፡፡ በመሆኑም ያሆዴ መስቃላ ብርሃን ፈነጠቀ እንኳን ደስ አላችሁ የሚል ትርጉም አለው። በዓሉ በወርኃ መስከረም 16 የሚከበር ሲሆን ወሩ ብርሃን፣ ብሩህ ተስፋ፣ ሰላም፣ ፍቅር፣ ረድኤት፣ በረከት የሚሞላበት ተምሳሌት ወር ተደርጎ ይቆጠራል። የሃድያ አባቶች ”ከባለቤቱ የከረመች ነፍስ በያሆዴ መስቀላ ትነግሳለች“ የሚል ብሂል አላቸው። የሃድያ አባቶች እንደ ዘመን መለወጫ የመጀመሪያ ቀን አድርገው በመውሰድ ማንኛውንም ዓይነት ክስተት ከዚያ ጋር አያይዘው እንደሚቆጥሩ ይነገራል። ከመጋቢት ወር ጀምሮ ለከብቶች የግጦሽ ሳር የሚሆን ቦታ ከልሎ በማስቀመጥ የበዓሉ ቀን ከብቶች ተለቀውበት እንዲጠግቡ ይደረጋል። ይህም በአዲስ ዓመት መግቢያ እንኳን የሰው ልጅ እንሰሳትም ቢሆኑ መጥገብ እንዳለባቸውና ሆዳቸው ሳይጎድል አዲሱን ዓመት መቀበል እንዳለባቸው በመታመኑ ልዩ ትኩረት ይሰጣቸዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ዓመቱ የጥጋብ ዘመን እንዲሆን ለመመኘት ነው። ጋዜ ማስቃላ እና ዮኦ ማስቃላ የጎፋ ዞን ሕዝቦች የዘመን መለወጫ በዓላቸው ማለትም “የጎፋ ጋዜ ማስቃላ” እና “የአይዳ ዮኦ ማስቃላ”ን ያከብራሉ። የጎፋ እና ኦይዳ ህዝቦች የዘመን መለወጫ የሆኑት እነዚህ በዓላት በየዓመቱ በወርሃ መስከረም ይከበራሉ። የጎፋ ጋዜ ማስቃላ እና የኦይዳ ዮኦ ማስቃላ በዓል የተጣላ የሚታረቅበት፣ የተራበ ጠግቦ ለፈጣሪው ምስጋና የሚያቀርብበት፣ የታረዘ የሚለብስበት፣ ጥላቻ ተወግዶ ፍቅር የሚሰበክበት፣ ፍቅር፣ ደስታ፣ ተስፋ እንደ አደይ አበባ የሚፈካበትና ሁሉም ያለልዩነት የሚያከብሩበት በዓል እንደሆነ ይታመናል። መሳላ መሳላ በከንባታ፣ ጠንባሮና ዶንጋ ብሄረሰቦች ዘንድ በየዓመቱ የሚከበር በዓል ነው። በዓሉ በከምባታ ህዝብ ዘንድ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ታላቅ የዘመን መለወጫ በዓል ሲሆን የአሮጌው ዓመት ማብቅያና የአዲሱ ዓመት መጀመሪያ የመሸጋገሪያ በዓል ነው፡፡ መሳላ ማለት (ታላቅ)፣ መጀመሪያ እንደ ማለት ሲሆን በዓሉ ከአሮጌ ወደ አዲስ፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን መሻገር የሚለውን ይገልጻል፡፡ ከምባታዎች አስራ አንድ ወራት በስራ ካሳለፉ በኋላ የመጨረሻውን አንድ ወር ለበዓሉ ያውሉታል፡፡ የመጀመሪያዎቹን 15 ቀናት በበዓሉ ዝግጅት፣ ቀሪዎቹን ቀናት ደግሞ በሀሴት፣ በመዝናናት፣ በመጫወት በጋራ ያሳልፋሉ፡፡ ሄቦ የየም ብሄረሰብ የዘመን መለወጫ በዓል 'ሄቦ' ይባላል። የሄቦ በዓል በየም ብሄረሰብ ለዓመት ታቅዶና ታስቦበት የሚከበር የብሄረሰቡ ድንቅ ባህላዊ እሴት ያለው በዓል ነው፡፡ ሄቦ ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ በታላቅ ድምቀት የሚከበር ሲሆን ብሔረሰቡ የተለያዩ የበዓል ዝግጅቶችን አዘጋጅቶ ነጭ በቀይ በሆነው ባህላዊ አልባሳቱ ደምቆ በዓሉን ያከብራል። የበዓሉ የመጀመሪያ ዕለት 'ካማ ኬሳ' ይሰኛል። የዕርቅ ቀን ሲሆን በቤተሰብ ውስጥም ሆነ በዘመድ አዝማድ መካከል የተፈጠረ ቅራኔና የሰነበተ ቂም ካለ በሽማግሌዎች አማካይነት ሰላም ወርዶ እርቅ የሚፈፀምበት ነው። 'ካማ ኬሳ' በዋናነት ቂምና ቁርሾን ይዞ ወደ አዲሱ ዓመት ላለመሻገር ሲባል እንደሚፈጸምም ነው የሚገለጸው። ቂምና ቁርሾን ይዞ ወደ አዲሱ ዓመት መሻገሩ ለተለያዩ ማህበራዊ ቀውሶች ሊዳርግ እንደሚችልም በብሔረሰቡ አባላት ይታመናል። ማሽቃሮ የካፊቾ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል “ማሽቃሮ” በመባል ይታወቃል። የካፊቾ የዘመን ለውጥ የክረምት ወቅትን ተከትሎ ይከበራል። የካፋ ህዝብ የማሽቃሮ አዲስ ዓመት ከገበሬው የእርሻ ስራ ጋር የተያያዘ ሲሆን መለያውም ከመዝራት፣ ከእድገት እና ከመኸር ዑደት ጋር የተያያዘ እንደሆነ ይነገራል። የካፋ ንጉስ መቀመጫ በሆነውና በየዓመቱ በዓሉ በሚከበርበት “ቦንጌ ሻንቤቶ” በሚባለው ስፈራ በዓሉ ሲከበር በዞኑ የሚኖሩ ብሔረሰቦችን ባህላዊ እሴቶቻቸውን የሚያሳይ ስነ ስርዓት ያካሂዳሉ። ኢትዮጵያ የብዙ ሀይማኖታዊና ባህላዊ ሀብቶች መገኛ ነች። በሁሉም ማዕዘኖቿ አያሌ ቱባ ሀብቶችን የተቸረች ህብረ ብሄራዊነት የጎላባት ሀገር ነች። በዚህ ጽሁፍ የተወሰኑትን የመስከረም ድምቀቶች ዳሰስን እንጂ የኢትዮጵያ መገለጫዎች አይነተ ብዙ እሴቶቿም እጹብ ድንቅ ናቸው። በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች በወርሃ መስከረምም ይሁን በሌላ ወራት የሚከበሩ የህዝቦቿን ሀብቶች አጉልቶ ማሳየት፣ ለማህበረሰባዊ ትስስርና ለአብሮነት መጎልበት መጠቀም ይገባል። ቸር እንሰንብት
ስኬታማ የክትመት መሰረተ ልማት፤ ለጤናማ የነዋሪዎች ሕይወት
Sep 18, 2024 723
(በቁምልኝ አያሌው) ከተማ ቋሚና ሠፊ ህዝብ ሰፍሮ የሚኖርበት ቦታ ሲሆን፤ በወጣ ሕግ የሚመራና ራሱን የቻለ አስተዳደር ያለው ወሳኝ የሆኑ የከተማ ልማትና ከተሜነት ጽንሰ ሃሳቦችን ይዟል። ከተሜነት ከገጠር ወደ ከተማ በሚደረግ የሕዝብ ፍልሰት የሚከሰት የነዋሪነት ቁጥር መጨመር ውጤት መሆኑን ብዙዎች ይስማሙበታል። በከተሞች የሚኖሩ ዜጎች የቁጥር ዕድገት መኖርም ነዋሪዎች እራሳቸውን ከሚኖር ሁለንተናዊ ለውጥ ጋር አስማምተው የሚኖሩበት እሳቤ እንደሆነ ይነሳል። በሌላ በኩልም ከተሜነት የኪነ-ሕንፃ ጠበብቶች እና የከተማ ልማት አሰላሳዮች አሻራ ያረፈበት በሂደት የሚከናወን የመለስተኛና ትላልቅ ከተሞች የዘመናት የዕቅድና ተግባር ሥሪት ድምር ዉጤት መሆኑ ይገለፃል። የከተማ ልማት ደግሞ ከተማና ከተሜነትን ለነዋሪዎች የአኗኗር ዘይቤ ምቹ ማድረግ የሚያስችል የመሠረት ልማት ግንባታ ማሳለጫ ስልት መሆኑ ይታወቃል። በድምር ልኬቱም ከተሜነት ሲባል ለዜጎች ዘመናዊ አኗኗር መደላድል የሚፈጥር የድርጊትና የአስተሳሰብ ብልጽግና ሽግግር የሚለካበት የሰው ልጅ የድርጊት አሻራ እንደሆነም ይነሳል። የከተሞች ውስጠ መልክም ብዝኅ ባህል፣ እምነት፣ ማንነትና የስልጣኔ ስልትን ያቀፉ የሀገረ መንግስት ግንባታና የዕድገት መሸጋገሪያ ድልድይ ናቸው። ከዚህ ባለፈም ከተሞች የንግድና የአስተዳደር አውድማ ሆነው ሀገርን እና ህዝብን ያገለግላሉ። የስነ-ከተማ አጥኚዎች እንደሚሉትም ከተሞች ወንዝ ተከትለው በሰፊ የህዝብ ጥግግት የሚወጠኑ፤ በተማከለ አስተዳደር፣ በአብያተ መንግሥታት፣ አብያተ መቅደሶች እና ቤተ-መቅደሶቻቸው የሚታወቁ ማዕከላት ናቸው። የከተማ ፕላን ባለሙያው አማን አሰፋ (ዶ/ር) ከተሞች በየዘመናቱ የንግድ፣ የኪነ-ጥበብ እና የኃይማኖት ማዕከላት እንዲሁም የሥልጣኔ መሰረት መሆናቸውን በአንድ ወቅት ለኢዜአ ገልጸዋል። ለአብነትም ይላሉ ባለሙያው፤ "በኢንዱስትሪ አብዮት ዘመን ኃይል የመነጨው፣ ፋብሪካና የባቡር ሀዲድ የተዘረጋው በከተሞች ነው። ከተሞች በፈጠራ ጥበባቸው የሕዝብ ስበት ማዕከል ሆነዋል። ከድሕረ 20ኛው ክፍለ ዘመን እስከ ዛሬው የዲጂታላይዜሽን አብዮት ዘመንም ከተሞች የአዳዲስ ግኝት፣ የቴክኖሎጂና የዲጂታላይዜሽን አስኳል ሆነው ቀጥለዋል። በዚህም የኢንቨስመንት፣ የፋይናንስ፣ የባሕልና የዕውቀት ሜዳ ናቸው። ዘመኑን የዋጁ ኪነ-ሕንጻዎች፣ መንገዶችና የትንሿ ዓለም መልክ መገለጫዎችም ናቸው። ከጥንት እስከዛሬ ከተሞችን የዘመን መመልከቻ መስታውቶች እና አሻራ ማንበሪያ ሰሌዳዎች ሊባሉ ይችላል" ብለዋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የከተሜነት ትንበያ እንደሚያመለክተውም እ.አ.አ. በ2050 ከዓለም 70 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ በከተሞች አካባቢው ይኖራል። ይህም የካርቦን ልቀትና የኃይል ፍጆታ ፍላጎትን በማሳደግ የአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭነትን እንደሚያሳደግ አስገንዝቧል። በዚህም አሁን ባለንበት የ21ኛው ክፍለ ዘመን ዘላቂና ኃይል ቆጣቢ፣ የካርበን ልቀትን የሚቀንሱና ፈጠራ የታከለባቸው በቴክኖሎጂ የዘመኑ የስማርት ሲቲ ግንባታ ስራ ትኩረትን እየሳቡ መጥተዋል። የ2020 የስማርት ከተማ ግንባታ መረጃ እንደሚያሳየውም ሲንጋፖር፣ ሔልሲንኪ፣ ዙሪክ፣ ኦስሎ፣ አምስተርዳም፣ ኒው ዮርክ እና ሴዑል ከተሞች በቅደም ተከተል የዓለም ምርጥ ሰባት የስማርት ከተማነት ስያሜን ተችረዋል። በዚህ መነሻነት፤ ይብዛም ይነስ ሀገራት በብርሃን ፍጥነት እያደገ የመጣውን የዜጎች የከተሜነት ፍላጎት ታሳቢ በማድረግ የስማርት ሲቲ ግንባታን ተግባራዊ ለማድረግ ጥረት ያደርጋሉ። ለአህጉራችን አፍሪካ ግን ዜጎች የተሻለ ኑሮን በመሻት ከገጠር ወደከተማ የሚደረግ ፍልሰት ከኋላ ቀር የከተማ መሰረተ ልማት ግንባታ ጋር ተደማሮ ከእንቅርት ላይ ጀሮ ደግፍ ሆኖባታል። የግሎባል ፋየር ፓወር የ2024 ሪፖርትም፤ የግብጿ ካይሮ፣ የኮንጎዋ ኪኒሻሳ፣ የአንጎላዋ ሉዋንዳ፣ የሱዳኗ ካርቱም፣ የኢትዮጵያዋ አዲስ አበባ፣ የኬኒያዋ ናይሮቢ፣ የካሜሮኗ ያውንዲ እና የዑጋንዳዋ ካምፓላ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ የሚኖርባቸው ርዕሰ መዲኖች መሆናቸውን አመላክቷል። የዓለም መፃዒ እጣ ፋንታ ይወሰናል የሚል እምነት የተጣለበት የአፍሪካ ፈጣን የህዝብ ቁጥር ዕድገትም ለስራ ብቁ የሆነ የሰው ሃይል የማምጣቱን ያህል ግን በከተሞች ላይ ጫናው እያየለ መምጣቱ ተደጋግሞ ይነሳል። ለዚህም የቀደምት ሥልጣኔና ከተሜነት አካል የሆነችው አፍሪካ በፈጥነት እያደረገ የመጣውን የህዘብ ቁጥር ታሳቢ ያደረገ የስማርት ሲቲ እና የከተማ መሰረተ ልማት ግንባታን ማሳለጥ የሚያጠያይቅ ጉዳይ አይደለም። በአህጉሪቷም ‘የምንፈልጋትን አፍሪካ‘ በሚል መርህ እ.አ.አ ከ2013 እስከ 2063 የሚዘልቅ አጀንዳ 2063 የሚመራበት የሀምሳ ዓመታት የልማት ዕቅድ እየተሰራበት ይገኛል። በሁሉን አቀፍ ዕድገትና ዘላቂ ልማት የበለጸገች አፍሪካን መፍጠር፣ በፓን አፍሪካኒም እሳቤና በአፍሪካ ሕዳሴ ራዕይ አማካኝነት የተሳሰረና ፖለቲካዊ አንድነት ያለው አህጉር እውን ማድረግ እና የአፍሪካን መልካም አስተዳደር የሰፈነበት፣ የሰብአዊ መብቶችና የሕግ የበላይነት የሚከበርበት፣ ፍትሕ የነገሰበትና ዴሞክራሲያዊ አህጉር ማድረግ። እንዲሁም ሰላሙንና አንድነቱ የጠበቀ አፍሪካን መፍጠር፣ ጠንካራ የባህል ማንነት፣ የጋራ ቅርስና እሴቶች ያሉት ጠንካራ ማህበረሳባዊ የሞራል መሰረት የፈጠረ አፍሪካን ማየት፣ የአፍሪካ ልማት ዜጎችን ማዕከል ያደረገ፣ ሕዝብን በተለይም የወጣቶችና ሴቶችን አቅም የሚጠቀምና ለሕጻናት ክብካቤ ትኩረትን የሰጠ እንዲሆን ማድረግ እና ጠንካራ፣ አንድነቱን የጠበቀ፣ የማይበገርና በዓለም መድረክ ተጽዕኖ ፈጣሪና አጋር የሆነ አፍሪካን መፍጠርም ሰባቱ የአህጉሪቷ አጀንዳ 2063 ዓላማ እና ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫዎች ናቸው። በሁሉን አቀፍ ዕድገትና ዘላቂ ልማት የበለጸገች አፍሪካን መፍጠርም ከሰባቱ የአህጉሪቷ 2063 አጀንዳዎች ዓላማ እና የትኩረት መስክ ውስጥ በተሟላ የመሰረተ ልማት ግንባታ ለዜጎች ምቹ የሆኑ ከተሞችን የመፍጠር አካል ነው። በቅርቡም "ዘላቂ የክትመት ምጣኔ ለአፍሪካ ትራንስፎርሜሽን አጀንዳ 2063" በሚል መሪ ሀሳብ ከነሐሴ 29 እስከ ጳጉሜን 1 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በአዲስ አበባ የመጀመሪያውን የአፍሪካ ከተሞች ፎረም ተካሂዷል። የሀገራት መሪዎች፣ ምሁራን፣ የተቋማት እና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በዚህ ፎረም ላይ ለአህጉሪቷ ከተሞች ዕድገት ሳንካ የሆኑ ቁልፍና ወሳኝ ችግሮችን መፍትሔ መስጠት የሚያስችሉ ምክረ ሃሳቦች ቀርበው ምክክር ተደርጎባቸዋል። በዚህም አህጉራዊ ወንድማማችነትን በማጠናከር ለዜጎች ኑሮ ምቹ የሆኑ ዘመናዊ ከተሞችን በመገንባት የአፍሪካን ከተሞች የዕድገት አቅጣጫና ትስስር የሚያጠናክር ሆኖ ተጠናቋል። ኢትዮጵያም ባስተናገደችው ፎረም ላይ ከአክሱም፣ ሐረር፣ ጎንደር፣ አዲስ አበባ እና መሰል ጥንታዊ ከተሞቿ የሚመነጨውን የከተሜነት ጽንሰ ሃሳብና እስከ አሁናዊ የኮሪደር ልማት የክትመት ዕድገትና የገጽታ ስራዎችን በተሞክሮነት አጋርታለች። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በአፍሪካ ከተሞች ፎረም መክፈቻ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ኢትዮጵያ የአፍሪካን ዘላቂ የክትመት ሽግግር ለማሳካት በቁርጠኝነት እየሰራች እንደምትገኝ አረጋግጠዋል። በፎረሙ መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ የአህጉሪቷ ከተማ ከንቲቦች የነዋሪዎችን ሁለንተናዊ ለውጥ ማረጋገጥ የሚችል ፈጠራ የታከለበት መሰረተ ልማት ማሳለጥ ያስፈልጋል ብለዋል። የአፍሪካ ከተሞችን ዕድገት ለማሳለጥ የእርስ በርስ ትብብርና የልምድ ልውውጥ ማህልን ማዳበር ይገባል ያሉት ደግሞ የዩኤን ሃቢታት ዋና ዳይሬክተር አና ክለውዲያ ሮስባች ናቸው። የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በፎረሙ በተሰናዳው የከተማ ልማት ፋይናንስ አማራጭ የፓናል ውይይት ላይ ኢትዮጵያ ዘመናዊ ክትመትን ዕውን ለማድረግ የተከተለችው የግሉን ዘርፍ ያሳተፈ የፋይናንስ አማራጭ ስኬት እየተመዘገበበት መሆኑን አብራርተዋል። መዲናዋን ቀድመው የሚያውቋት አንጋፋው ዲፕሎማት የቀድሞ የሴራሊዮን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፕሮፌሰር ዴቪድ ፍራንሲስ፣ በቻይና ሳውዝኢስት ዩኒቨርሲቲ የኪነ-ሕንፃ ፕሮፌሰር ዋንግ ዢንግፒንግ እና በፈረንሳይ ዓለም አቀፍ ትብብር ተቋም የሰሃራ በታች የክትመት ጉዳዮች ተመራማሪ ሲና ሽልመር(ዶ/ር) ኢትዮጵያ አዲስ አበባን ለማደስ ያከናወነችው የኮርደር ልማት ስራ "አዲስ አበባ አዲስ ሆናብናለች" ብለዋል። የአፍሪካ ከተሞች የነዋሪዎችን ፍላጎት፣ የከተማነት መስፈርትና ገጽታን ከግምት ውስጥ አስገብተው የተመሰረቱ አይደሉም። የከተሞቹ ምስረታም የሰው ልጆችን ሁለንተናዊ ደኅንነት፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ የልማት ፍላጎት ካለመረዳት በሚመነጭ የከተማ ፕላን ስሪት ጋር የተያያዘ መሆኑም ይነሳል። በዚህም ከተሞች የፖለቲካል ኢኮኖሚ ማዕከል እንዲሁም የዜጎች የስራ ዕድልና ቴክኖሎጂ ፈጠራ መናኸሪያ መሆናቸውን ታሳቢ ያደረገ ውበት፣ ጽዳትና ለኑሮ ምቹ መዋቅራዊ ዲዛይን ማላበስ ያስፈልጋል። በአፍሪካም ሆነ በኢትዮጵያ በቂ የከተማ ልማት ማዕቀፍ እና ሕግጋት አለመኖር ለዘመናዊ የከተማ ልማት ዲዛይን ግንባታ ማነቆዎች መካከል ዋነኛው እንደሆነ ይነሳል። በተለይም ይህ ጉድለት ከፍተኛ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ፣ የተጠጋጋ የማኅበረሰብ አኗኗርን የያዙ ትልልቅ የአህጉሪቷ ከተሞችን ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ሥነ-ምህዳራዊ ማዕከልነት የተዛባ እንዲሆን ያደርጋል። የኢትዮጵያ ከተሞችም ለነዋሪዎች ሁለንተናዊ ለውጥ ምቹ ምኅዳር መፍጠር የሚያስችሉ ዕድሎችን የተጎናጸፉ ሆነው ሳለ በገደምዳሜው ረጅም የዕድሜ ጥንታዊነት፣ ስምና ዝና ብቻ ታቅፈው ቆይተዋል። በቅርቡ በመዲናዋ የተከናወነው የኮሪደር ልማት ስራ ግን ስሟን ሳትመስል ለቆየችው አዲስ አበባ "ለነዋሪዎቿ ምቹነትን፤ ለእንግዶቿ አግራሞት" የፈጠረ የአጭር ጊዜ አስደናቂ የልማት ክስተት ሆኖ ተመዝግቧል። መንግስት አዲስ አበባን እንደ ስሟ “አዲስ እና አበባ ማድረግ ” በሚል መርህ የከተማዋን ገጽታ ለመቀየር ቅድሚያ ሰጥቶ የተለያዩ ስራዎችን አከናውኗል። ከእነዚህም መካከል የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ኢኒሼቲቭ የሆኑት የገበታ ለሸገር ፕሮጀክቶች ተጠቃሽ ሲሆኑ፤ አሁን ላይ ደግሞ ከተማዋን ወደ ተሻለ ገጽታ እየቀየረ ያለው የኮሪደር ልማት በመከናወን ላይ ይገኛል። የኮሪደር ልማቱ በዚህም የመንገድ አውታሮች የማስፋፋት ስራ፣ ዘመናዊ የመብራት ዝርጋታ፣ ለከተማው ተጨማሪ ውበት የሚሰጡ የመንገድ ዳር የአረንጏዴ ልማት ስራዎች፣ ዘመናዊ የፍሳሽ ማስወገጃ ስርዓት፣ ምቹ የእግረኛና የብስክሌት መንገድ፣ ያረጁ ህንጻዎች ጥገና እና ማስዋብ በዋናነት እየተከናወኑ ካሉ ስራዎች ውስጥ ይገኙበታል። የኮሪደር ልማቱ ከ4 ኪሎ ፒያሳና፣ ከ4 ኪሎ አደባባይ በእንግሊዝ ኤምባሲ መገናኛ፣ ከሜክሲኮ ሳር ቤት በጎተራ ወሎ ሰፈር አደባባይ፣ ከ4 ኪሎ በመስቀል አደባባይ ቦሌ ድልድይ እና ከመገናኛ እስከ አዲስ አፍሪካ ኮንቬንሽን ማዕከል ይሸፍናል። በመጀመሪያው ምእራፍ የተመረቁ የኮሪደር ልማቱ ስፍራዎችም ከወዲሁ አዲስ አበባን የውበት ካባ አጎናጽፈዋታል። የኮሪደር ልማቱ በግብንታ ሂደትም አዲስ እይታና አስተሳሰብን ያመጣ ነው። በተጨማሪም የኮሪደር ልማቱ ከዚህ ቀደም ፕሮጀክቶችን በተቀመጠላቸው ጊዜና ጥራት ከማጠናቀቅ አኳያ ሲነሱ ለነበሩ ጥያቄዎችም ምላሽ የሰጠ ሆኗል። የኮሪደር ልማቱ ይዞት የመጣው ሌላኛው እድል ደግሞ ከተማዋ የተደራጀና ዘመናዊ የአደጋና ወንጀል ምላሽ አሰጣጥ ስርዓት እንዲኖራት ማስቻል ነው። የኮሪደር ልማቱ በሚያልፍባቸው አካባቢዎች የሚገጠሙ ዘመናዊ የደህንነት ካሜራዎችና ምቹ የተሽከርካሪ መንገዶች ወንጀል የመከላከል አቅምን ከማጎልበት ባሻገር ለድንገተኛ አደጋዎች ፈጣን ምላሽ መስጠት ያስችላሉ። ከወዲሁ በመጀመሪያው ምዕራፍ ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት የሆኑ የኮሪደር ልማት ስራዎችም በሌሎች ከተሞች ስናያቸው ሩቅ የሚመስሉ የስማርት ከተማ ሃሳቦችን በተግባር ያሳዩ ሆነዋል። በአጠቃላይ የኮሪደር ልማት ስራው ብዙ ትምህርት የተወሰደበት፣ ማድረግ እንደሚቻል የታየበት፣ የህብረተሰቡ የልማት ጥማት እና ተባባሪነት የታየበት፣ ኢትዮጵያ በራሷ ልጆች፣ በራሷ ሃብት ሃገር መቀየር የሚያስችል አቅም እንዳላት የታየበት ነው። በዚሁ መነሻነትም እንደ ጥንታዊቷ ጎንደር፣ ውቢቷ ሀዋሳ እና የቱሪስት ማረፊያዋ ቢሾፍቱ ያሉ የኢትዮጵያ ታላላቅና መካከለኛ ከተሞችም የአዲስ አበባን ውብ ገጽታ የኮሪደር ልማት ተሞክሮ ወስደው እየሰሩበት ይገኛል። በቀጣይም የከተሞች ጽዳትና ውበት የነዋሪዎችን አካላዊ፣ አዕምሯዊና ሞራላዊ ዕድገት የሚበይኑ የሁሉ አቀፍ ማዕከል መሆናቸውን ታሳቢ በማድረግ ዘመናዊ ዕቅድን ከተግባር ያዋደደ ስራ ማሳለጥ ይጠይቃል። ኢትዮጵያን የሁለንተናዊ የልማት ብርሃን አድማስ፤ የአፍሪካዊያን የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ በልጆቿ ብርቱ ክንዶች ትጋትና ትብብር ድል ይቀዳጁ መልዕክታችን ይሁን።
አረንጓዴ አሻራ ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ የሥራ ዕድል ፈጠራ
Aug 30, 2024 1376
በክፍሌ ክበበው (ኢዜአ) በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ምዕራፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር በ2011 ዓ.ም ነበር የተጀመረው። በዚሁ በመጀመሪያው ዙር የአረንጓዴ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር 23 ሚሊዮን ህዝብ ተሳትፎ ከ4 ነጥብ 7 ቢሊዮን በላይ ችግኞች መተከላቸውን የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። በዚህም በመርሃ ግብሩ እስከ 2014 ዓ.ም ድረስ በሕዝብ ተሳትፎ ለአራት ዓመታት በተካሄደው የመጀመሪያው ምዕራፍ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃግብር 20 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ 25 ቢሊዮን ችግኞችን መትከል በስኬት ተጠናቋል። የመጀመሪያው ዙር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ሐምሌ 22 ቀን 2011 ዓ.ም የተጀመረው “40 ዛፍ በነፍስ ወከፍ” በሚል መሪ ሀሳብ ሲሆን፤ በአንድ ጀምበር 200 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ ከ353 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል እ.ኤ.አ በሐምሌ 2017 በሕንድ የአካባቢ ጥበቃ ዘመቻ በ12 ሰዓታት 66 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ተይዞ የነበረውን የዓለም ክብረወስን ኢትዮጵያ መረከብ ችላለች። የኢትዮጵያ አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከመጀመሪያው ምዕራፍ አንስቶ ከዓመት ዓመት የኅብረተሰቡን ተሳትፎን እያሳደገ በስኬት እየተጠናቀቀ ከዚህ ደርሷል። በ2015 ዓ.ም መተግበር በጀመረው በሁለተኛው ምዕራፍ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር 25 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል የታቀደ ሲሆን፤በተለይ ለምግብነት የሚውሉ ተክሎች ትኩረት እንደተሰጠ መረጃዎች የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል። ከዚህም ባሻገር ችግኞችን ለጎረቤት አገራት በመስጠት ኢትዮጵያ ችግኞችን በመትከል ዓለም ዓቀፍ ፈተና የሆነውን የአየር ንብረት ለውጥ ለመቅረፍ እያደረገች ያለው እንቅስቃሴ አርዓያነቷን ያሳየችበት መሆኑ ዓለም ዓቀፍ ተቋማት የመሰከሩለት ሀቅ ነው። በዘንድሮው ለስድስተኛ ጊዜ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በአንድ ጀንበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ 615 ነጥብ 7 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል የአረንጓዴ አሻራ ሥራው በስኬት መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዕለቱ አብስረዋል። ይኸው የችግኝ ተከላ መርሃግብር ነሐሴ 17 ቀን 2017 ዓ.ም “የምትተክል ሀገር፤ የሚያጸና ትውልድ” በሚል መሪ ሀሳብ የተካሄደው ለጥምር ደን፣ ለምግብነት እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን የመትከል ለአረንጓዴ ልማት እና ለአረንጓዴ አካባቢ መላ ኢትዮጵያውያን ለትውልድና ለዓለም የሚተርፍ በስኬት ተጠናቋል። “ያሰብነውን ሳናሳካ ጀምበር የሚጠልቅብን አይደለንም” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ በአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ የተሳተፉ 29 ነጥብ 1 ሚሊዮን ዜጎች በ318 ነጥብ 4 ሄክታር በሚሸፍኑ ሥፍራዎች ላይ ችግኞችን መትከላቸውን ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እንዳሉት በአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር እስካሁን ባለው ሂደት 39 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኞች መተከላቸውን ጠቅሰው፤ በአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የተከልናቸውን ችግኞች ሲደመሩ ወደ 40 ቢሊዮን ይደርሳሉ ፡፡ ይህ ስኬት ለአየር ንብረት ለውጥ ሚዛን ለመጠበቅ፣ የአፈር መራቆትን ለመመከት እና የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ እንዲሁም ምድራችንን አረንጓዴ ለማልበስ እና ልምላሜን ለመመለስ ሳንበገር ሰርተናል ብለዋል። በዘንድሮ ዓመት የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ከ7 ቢሊዮን በላይ ችግኞች የሚተከሉ ሲሆን፤ ከዚህ ውስጥ ከ50 በመቶ በላይ የሚሆነው ለምግብነት፣ ለመድሐኒትነትና የአፈር መሸርሸርን ለመከላከል እና የተቀረው ደግሞ ለውበትና ለአከባቢ ጥበቃ የሚውል መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል። እንደሳቸው ገለጻ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ የአየር ንብረትን በማሻሻል እና ብዝሃ ህይወትን በመደገፍ ኢትዮጵያን የሚጠቅም ብቻ ሳይሆን፤ ወደፊት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሚደረጉ የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች አርአያነት ያለው ተግባር መሆኑን ሁሉም ኢትዮጵያዉያንን እና ዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ የሚያስማማ ነው። የተተከሉት ችግኞች ሲጸድቁ ስነምህዳሩን ከማሻሻል፤ የአፈር መሸርሸርና መከላትን ከመከላከል እንዲሁም የሥራ ዕድልን ለበርካቶች ከመፍጠር አኳያ ጠቀሜታቸው ከፍተኛ ነው። የተጎዳና የተራቆተ አካባቢ ላይ የሚኖሩ የኅብረተሰብ ክፍሎች አካባቢያቸውን ለምግብነት እና ለአየር ንብረት ለውጥ በደን ለማልበስ በሚደረግላቸው ቴክኒካዊ ድጋፍ ተጠቅመው አኗኗራቸውን ለመለወጥ ያስችላል። የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሚገኙ ምንጮች እንዲጎለብቱ፣ ድርቅን ለመቋቋም የሚያስችል አረንጓዴ ምህዳር እንዲፈጠር የድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ገባሮች እንዲጠናከሩ እያደረገ መሆኑን እና ጎርፍን በመከላከል፣ የአፈር መከላትን በማስቀረት፣ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው። ከዚህም በተጨማሪ የአረንጓዴ አሻራ እና የተፋሰስ ልማቱ በተራቆቱ አካባቢዎች የደን ሀብት መልሶ እንዲያገግምና ደርቀው የነበሩ ምንጮች መልሰው እንዲመነጨናና የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር እያገዘ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባለፉት ዓመታት ችግኞች በመተከላቸው የአፍሪካ ኩራት የሆነው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከሚጠበቀው በላይ ውሃ መያዙን ገልጸው፤ ግድቡን ከደለል ለመታደግ፣ በቂ ዝናብ፣ ምግብና መድሃኒት ለማግኘት በዓባይ ተፋሰስ አካባቢዎች በቀጣይ ችግኞችን አብዝቶ መትከል ይጠበቅብናል፣ ይህም የታችኛው የተፋሰሱ ሀገሮችም በቂ ውሃ እንዲያገኙም ያስችላል ብለዋል። የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በአፈር ደለል እንዳይሞላ፣ በአካባቢው ሥነ ምህዳሩን ለመጠበቅ እና ረጅም ዓመት አገልግሎት መስጠት እንዲችል በተፋሰሱ ዙሪያ ችግኞች በቀጣይነት መትከል ይገባል። የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር በተፋሰስ ልማት ምንጮችን በማጎልበት እየለማ ያለው የውሃ ሀብትም የአካባቢውን ሥነ ምህዳር ለመጠበቅ ተጨማሪ አቅም ሆኗል። በግብርና ልማት በአገር አቀፍ ደረጃ በበጋ መስኖ ልማት የበጋ ስንዴ፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርት እንዲጨምር በማድረግ የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ እና የሥራ ዕድልን በመፍጠር የበከሉን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል፡፡ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በተፋሰስ ልማት እየለማ ያለው የውሃ ሀብትም የአካባቢውን ሥነ ምህዳር ለመጠበቅ ተጨማሪ አቅም ሆኖ ለግብርና ልማት እና የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባሻገር ለጎረቤት አገራትም ጭምር የሚተርፍ ሆኗል። በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃግብር ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ እና የሥራ ዕድል ፈጠራ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ትንበያዎች ያመላክታሉ።እ.ኤ.አ. በ 2012 የተመሰረተው እና በብሪታኒያ ዕርዳታ የሚደገፈው ኤፍኤስዲ አፍሪካ ለወደፊቷ አፍሪካ ፋይናንስን ለመስራት የሚተጋ የልማት ኤጀንሲ ባወጣው አዲስ የትንበያ ሪፖርት እንደሚያመለክተው በአረንጓዴ ኢኮኖሚ እ.ኤ.አ. በ2030 ከሦስት ሚሊዮን በላይ ቀጥተኛ ሥራዎችን መፍጠር የሚያስችል ነው። ኤፍኤስዲ አፍሪካ በአረንጓዴ ኢኮኖሚ በአፍሪካ የፋይናንስ ገበያዎች ውስጥ ያሉ የሥርዓት ተግዳሮቶችን ለመፍታት መጠነ ሰፊ እና የረጅም ጊዜ ለውጥን ለመፍጠርን ዓላማ አድርጎ የሚንቀሳቀስ ነው።ባለፈው ወር መጨረሻ ይፋ ባደረገው ትንበያ በ2030 አሥራ ሁለት "አረንጓዴ" ንዑስ ዘርፎች ያለውን አዲስ ቀጥተኛ የስራ ዕድል የሚተነብይ "በአፍሪካ የአረንጓዴ ሥራዎች ትንበያ " በሚል ርዕስ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን ዘገባ የፈጠራ ሥራዎችን ከሚደግፈው ሾርትሊስት (Shortlist) ከተባለው ተቋም ጋር አሳትመዋል። እ.አ.አ በ2030 በአህጉሪቱ እስከ 3 ነጥብ 3 ሚሊዮን የሚደርሱ በታዳሽ ኃይል ዘርፍ በተለይም ከአብዛኛዎቹ በፀሐይ ኃይል አዳዲስ ቀጥተኛ ሥራዎች እንደሚፈጠሩ በትንበያ ሪፖርቱ አመልክቷል።በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ውስጥ በዋና ዋና የአረንጓዴ እሴት ሰንሰለቶች ማለትም በካርቦን ንግድ፣ በተፈጥሮ ሀብት ልማት እና በታዳሽ ኃይል ያለውን የሰው ኃይል ፍላጎት ለመጀመሪያ ጊዜ በጥልቀት የተተነተነው ጥናቱ ለአምስት አገሮች፤ ኢትዮጵያ፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ኬኒያ፣ ናይጄሪያ እና ደቡብ አፍሪካ ያተኮረ ዝርዝር ትንበያ አውጥቷል። በዚህም ኢትዮጵያ ከሃይድሮ ኤሌክትሪክ 33 ሺህ ሥራዎች ቀዳሚ ቀጣሪ እንደምትሆን በተቋማቱ ጥናት ተካቷል። በዚሁ ጥናት ከ377 ሺህ በላይ በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች የታገዘ የስማርት ግብርና ቴክኖሎጂ ልማት እና ግብርና እና ተፈጥሮ እስከ 700 ሺህ የሚደርሱ ሥራዎችን እንደሚፈጥርም በሪፖርቱ ተጠቅሷል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ በፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት መካከለኛ ገቢ ያላት ሀገር ለመሆን ጠንካራ ቁርጠኝነትን እያሳየች መሆኑን ኤፍኤስዲ አፍሪካ (FSD Africa) በዘገባው ጠቅሷል። በኢትዮጵያ ዝቅተኛ የካርቦን ኢነርጂ ልማትን በማረጋገጥ፣ ሰፊ የደን ክምችቷን በመጠበቅ እና ግብርናዋ የአየር ንብረትን የመለማመድ እና የመቋቋም አቅምን ማሳደግ በቀዳሚነት የሚጠቀስ ነው። ኢትዮጵያ ሀገራችን በአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና የተገኘበት እና የአየር ንብረት ለውጥ ለመከላከል ያላትን ቁርጠኝነት የታየበት እና ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ የሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ያለውና አበርክቶው የላቀ በመሆኑ ኢትዮጵያዉያን ይህንን እየዳበረ የመጣውን በአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ኢትዮጵያን አረንጓዴ በማልበስ፣ የለማች፣ ያደገችና የበለጸገች አገር ለተተኪው ትውልድ የማስረከቡን ባሕል በበለጠ ሊያጸኑት ይገባል።
10 ሄክታር ማሳን ወደ ፍራፍሬ ደን የለወጡ ብርቱ አርሶ አደር
Aug 27, 2024 1400
የድሬዳዋ ሕዝብ በተወለዱበት ቀዬ ስም ''ጀማል በዴሳ'' ሲላቸው የንግዱ ማኅበረሰብ ደግሞ ቀደም ብሎ በነበራቸው ጠንካራ የጫት ንግድ እንቅስቃሴ "ጀማል ቁጩ"ይላቸዋል። በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር መልካ ጀብዱ አካባቢ ሰፊ ማሳ ላይ አትክልትና ፍራፍሬ የሚያለሙት እኚህ ብርቱ አርሶ አደር ትክክለኛ ስማቸው አቶ ጀማል አህመድ ዚያድ ይባላል። ከምስራቅ ሐረርጌ ወደ ድሬዳዋ ያመሩት ጀማል አህመድ ከ12 ዓመታት በፊት 100 ፍሬ ፓፓያ በመትከል ነበር የፍራፍሬ ልማትን አሐዱ ብለው የጀመሩት። የፓፓያውን ፍሬያማነትና ይዛላቸው የመጣውን የኢኮኖሚ ትሩፋት በማየት 15 ሺህ ፍሬ ፓፓያ በመትከል የምርት መጠናቸውን አሳድገዋል። አርሶ አደር ጀማል በዚህ ሳይገቱ ሁሉንም ዓይነት የፍራፍሬ ዛፎች በማልማት ዛሬ ላይ ከ10 ሄክታር በላይ ማሳን በዓይነትና በብዛት የፍራፍሬ ቋሚ ተክሎች በመሸፈን ማሳቸውን ጫካ አስመስለውታል። በተጨማርም ሰብልና የፍራፍሬ ዛፎችን እንዲሁም ስኳር ድንችን አጣምረው እያለሙ ነው። ጥቅጥቅ ደን ከመሰለው የጀማል ማሳ ብርቱካንን ጨምሮ የፍራፍሬ ምርቶች በየቀኑ ድሬዳዋና አካባቢው ወደሚገኙ ሆቴሎችና መሰል አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች በቀጥታ ይሰራጫሉ። ለምግብነት ከሚውሉ ቋሚ ሰብሎች በተጨማሪም ለከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት የሚውሉ ልዩ ልዩ ችግኞችን በሳይንሳዊ ዘዴ በማዘጋጀትም ችግኝ ለሚፈልጉ ደንበኞቻቸው በማቅረብ ላይ ይገኛሉ። በመልካ ጀብዱ በሚገኘው የጀማል አትክልትና ፍራፍሬ ልማት ለ24 ሰዎች ቋሚ የሥራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን፤ አርሶ አደሩ በዓመት ከ13 እስከ 15 ሚሊዮን ብር ገቢ እንደሚያገኙ ይገልጻሉ። ጀማል የግብርና ኢንቨስትመንታቸውን ከድሬዳዋ ባሻገር በሌሎች የምስራቅ ኢትዮጵያ አካባቢዎች ለማስፋት እንቅስቃሴ ጀምረዋል። የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጣና ድሬዳዋን ልክ እንደ ዱባይ የንግድ መዳረሻ የመሆን እድል ፈጥሮላታል የሚሉት አርሶ አደር ጀማል፤ ከግብርና ሥራቸው ባሻገር በዓለም አቀፍ ንግድ ውስጥ ለመሰማራትም ፈቃድ ወስደዋል። የግብርና ሥራቸው ሌሎች የአካባቢው በርካታ አርሶ አደሮች በአትክልትና ፍራፍሬ በማልማት የተሻለ ሕይወት እንዲመሩ ምክንያት መሆናቸውን ጀማል ያነሳሉ። በድሬዳዋና አካባቢው የከርሰ-ምድር ውኃን በአጭር ጥልቀት ቆፍሮ ማግኘት ይቻላል የሚሉት ጀማል፤ በፀሐይ ኃይል የሚሰራ የውኃ ፓምፕን ጨምሮ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን ለማኅበረሰቡ ቢቀርቡ፤ አርሶ አደሮች ከራሳቸው አልፈው ለአገር የሚተርፍ ምርት ማግኘት እንደሚችሉ ይናገራሉ። ከራሳቸው ጥረት ባሻገር ከከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አንስቶ በከፍተኛ አመራሮች በኩል ትልቅ ድጋፍና ዕገዛ እንደተደረገላቸው ገልጸው፤ በተለይም በግብርና ባለሙያዎች ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የግብርና፣ ውኃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ምክትል ኃላፊ መሐመድ አሚን፤ ጀማል በራስ ተነሳሽነት ውጤታማ የሆኑ የሞዴሎች ሞዴል አርሶ አደር ናቸው ይላሉ። በተለይም ከመደበኛ ሰብሎች ባሻገር አትክልትና ፍራፍሬ በማልማት የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ እንደሚቻል ማሳያ ብርቱ አርሶ አደር እንደሆኑ መስክረዋል። ከራሳቸው አልፈው ለሌሎች አርሶ አደሮች ልምድና ተሞክሯቸውን በማጋራትም ትልቅ ሚና እየተወጡ መሆኑን ጠቅሰዋል። ከምግብ ሰብሎች ባሻገር ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ችግኞችን በማልማት ለከተማው የራሳቸውን አበርክቶ እየተጫወቱ መሆኑን ገልፀው፤ በዚህ ዓመት ብቻ ከ100 ሺህ በላይ ችግኞችን ማዘጋጀታቸውን ጠቁመዋል። ድሬዳዋ በብርቱካን፣ በመንደሪን፣ በሮማን፣ በአምበሾክና በሌሎች ፍራፍሬ ዓይነቶች በጣም የታወቀች እንደነበረች አስታውሰው፤ ከተማ አስተዳደሩ ይህን ነባር ስም ዳግም ለመመለስ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም የተለያዩ የአትክልትና ፍራፍሬ ክላስተሮች ተደራጅተው በስፋት እየለሙ መሆኑን ጠቅሰው፤ እስካሁን ጀማልን የመሰሉ ከ300 በላይ አርሶ አደሮች በፍራፍሬ ምርት መሰማራታቸውን አመልክተዋል። የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጣና መከፈቱ ለዚህ ተጨማሪ ዕድል መሆኑን ጠቅሰው፤ በየዓመቱ የሚመረተውን የፍራፍሬ ምርት ጥራት በማሳደግ ለውጭ ገበያ ተደራሽ ለመሆን እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
ልዩ ዘገባዎች
ያ ሆዴ የአዲስ ብርሃን ተስፋ
Sep 21, 2024 720
በማሙሽ ጋረደው ከሆሳዕና የኢዜአ ቅርንጫፍ ከብት የሚጠብቁ ህፃናት አዲስ ዓመት እየመጣ ስለመሆኑ ማብሰሪያ ከነሐሴ አጋማሽ ጀምሮ የዋሽንት /የገምባቡያ/ ድምፅ ማሰማት ይጀምራሉ። በመስከረም ከጉምና ጭጋግ ፀለምት ጨለማ የሚወጣበትና ምድሩ በአበባ ሀምራዊ ቀለም የሚታጀብበት ወቅት በመሆኑ በሀዲያ ብሄር ዘንድ ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ወቅት ነው። ያ ሆዴ የሀዲያዎች አዲስ የዘመን መለወጫ በዓል መባቻ ነው። ያ ሆዴ ማለት በሀዲያዎች ዘንድ “ብርሃን ሆነ፣ መስቀል መጣ፣ ገበያው ደራ፣ በይፋ ተበሰረ ብሎም እንኳን ደስ አላችሁ” የሚል ስያሜ እንዳለውም ይነገራል። “ያ ሆዴ " በሀዲያ ካሉ እሴቶችና ወጎች እንዲሁም ክንዋኔዎች መካከል አንዱ ሲሆን፤ አንድነት፣ መቻቻል፣ ለውጥን ለማሳለጥ፣ አብሮነትና ሰላም ለማጠናከርም ከፍተኛ ሚና እንዳለው ይወሳል። የሀዲያ አገር ሽማግሌ አቶ መንገሻ ሂቤቦ እንዳጫወቱን ከሆነ ከነሐሴ አጋማሽ ጀምሮ ከብት የሚጠብቁ ህፃናት አዲስ ዓመት መምጣቱን የዋሽንት /የገምባቡያ/ ድምፅ በማሰማት አዋጅ ማብሰር ይጀምራሉ። ይህም የበዓሉ መቅረብን ለማሳሰብና ለማስታወቅ የሚደረግ ነው። በዓሉ ብርሃን፣ብሩህ ተስፋ፣ ሰላም፣ ፍቅር፣ ረድኤት በረከት የሚሞላበት ተምሳሌታዊ ወር ተደርጎ ይታመናል። ያ ሆዴ በሀዲያ ዘንድ ልዩ ስፍራ የሚሰጠው በዓል ነው። በዓሉ ከመድረሱ በፊት ሁሉም የቤተሰብ አባላት በዓሉን ለማድመቅ የየራሳቸው ድርሻ አላቸው። ለምሳሌ አባት ለእርድ የሚሆን ከብት በማቅረብ፣ እናት ደግሞ ሌሎች የቤት ስራዎች በማከናወንና ልጆችም ልዩ ልዩ የስራ ድርሻቸውን በመወጣት በዓሉን ያከብራሉ። “አባቶች አብሮነታቸውን ከሚያጠናክሩባቸው ማህበራዊ እሴቶች መካከል አንዱ ቱታ /ሼማታ/ ነው” ይላሉ የሀዲያ አገር ሽማግሌ አቶ መንገሻ፤ ይህም ከአራት አስከ ስምንት አባላትን ይዞ የሚደራጅ የስጋ ማህበር ነው። የማህበሩ አባላት ግንኙነት ያላቸው የሚተሳሰቡ የኢኮኖሚ አቅማቸውም ተቀራራቢነት ያለው ሲሆን፤ በዓሉ ከመድረሱ በፊት በጋራ ገንዘብ ማስቀመጥ ይጀምራሉ። ለስጋ መብያ የሚሆን ቆጮ ብሎም ለአተካና የሚሆን ቡላ በማዘጋጀት ከጥቅምት እሰከ ጥር ባሉት ወራት ውስጥ እንሰት በመፋቅ እናቶች በቡድን ተሰባስበው ዝግጅታቸውን ማከናወን ይጀምራሉ። በተጨማሪም ዊጆ |የቅቤ እቁብ| በመግባት ቅቤ በማጠራቀም ለበዓሉ አስፈላጊ የሆኑ ቅመማ ቅመሞችን በማዘጋጀት ኃላፊነታቸውን ይወጣሉ። የዳጣ፣ የአዋዜ ዝርያዎችንና ለበዓሉ ማድመቂያ የሚሆኑ ባህላዊ የሆኑ መጠጦችን ጭምር ያዘጋጃሉ። ልጃገረዶች በዓሉ እንዲደምቅ ቤት መደልደል፣ የተለያዩ ቀለማትን በመጠቀም የግርግዳ ቅርጻ ቅርጾችን በመስራት እንዲሁም ግቢ በማጽዳት የማሳመር ስራቸውን ያከናውናሉ። ወጣት ወንዶች ለማገዶ የሚያገለግል በአባቶች ተለይቶ የተሰጣቸውን እንጨት ፈልጠው እንዲደርቅ ያደርጋሉ። ጦምቦራ ለደመራ የሚሆን ችቦ በማዘጋጀት ግዴታቸውን ይወጣሉ። የሀዲያ ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ባለሙያ ወይዘሮ አመለወርቅ ሃንዳሞ እንደሚሉት፤ በዓሉን ለማክበር በአገር ውስጥ የሚገኙ የአካባቢው ተወላጆች ወደ ቤተሰቦቻቸው በመመለስ አብሮነት ለማክበር ከእሩቅም ከቅርብም ይሰበሰባሉ። ይህም በዓሉ ለአብሮነትና ለሰላም ያለውን ፋይዳ የላቀ ያደርገዋል። ዓመቱን ሙሉ ለበዓሉ የሚደረጉ ዝግጅቶችና የስራ ክፍፍሎች ልዩ ትርጉም ያላቸው ናቸው። ከዚህ በተጨማሪ “ወጣቶች የትዳር አጋራቸውን የሚመርጡበት በመሆኑ በዓሉን ልዩ ድባብ ይሰጠዋል” ይላሉ ወዘሮ አመለወርቅ። የበዓሉ ዋዜማ /ፉሊት ሂሞ/ ወጣቶች ያዘጋጁትን ጦምቦራ /የደመራ ችቦ/ የአካባቢውን ነዋሪዎች በሚያዋስን ቦታ ላይ ይሰራሉ። እናቶች ከቡላ፣ ቅቤና ወተት የሚያዘጋጁት ጣፋጭ የሆነ እና ጣት የሚያስቆረጥመውን አተካና በማዘጋጀት የበዓሉን ዋዜማ/ፉሊት ሂሞን/ ያደምቁታል። የበዓሉ አመሻሽ ዋዜማ ላይ ወጣቶች “ያ ሆዴ ያ ሆዴ “በማለት ይጨፍራሉ። ይህም ለበዓሉ “የእንኳን አደረሳችሁ” መልእክት አለው። በዋቸሞ ዩኒቨርስቲ የአገር በቀል እውቀቶች ምርምር ዳይሬክተር አቶ እያሱ ጥላሁን “ይህ በዓል የሚሰጠው የስራ ክፍፍል፣ የሰላምና አብሮነት ዕሴቶች ለጠንካራ ዕድገት፣ ነገን በተስፋ ለመመልከት ወሳኝ ነው” በማለት ይገልጹታል። በወቅቱ ወጣቶች በአካባቢው እየዞሩ በመጫወት ከአባቶች ምርቃት ይቀበላሉ። የአካባቢው ነዋሪዎች ደመራው በተዘጋጀበት ቦታ ማምሻውን ይሰባሰቡና አባቶች ደመራውን የሚያቀጣጥሉበትን ችቦ በመያዝ ልጆችን በማስከተል ዓመቱ የብርሃን፣ የሰላም፣ የአብሮነት፣ የመተሳሰብ እንዲሆን ፈጣሪያቸውን በመማጸን ደመራውን ይለኩሳሉ። ደመራው ተቀጣጥሎ እንዳለቀ በእድሜ ከፍ ወዳሉ አባወራ ቤት እንደሚሰባሰቡ ነው አቶ እያሱ የተናገሩት። የእርድ ስርዓቱ በሚከናወንበት ቤት ደጃፍ አባላቱ ቤተሰቦቻቸውን በመያዝ በአንድነት በመሰባሰብ የጋቢማ ስርዓት ይከናወናል። ይህም እድሜ ጠገብ ሽማግሌዎች ቅቤ እና ወተት በሚታረደው በሬ ላይ እያፈሰሱ” ለምለም ሳር "በመያዝ በሬውን እያሻሹ አዲሱ ዓመት ለህዝብ እና መንግስት የሰላም ዓመት የሚመኙበት መንገድ ነው። ልጆች ለወግ ለማዕረግ የሚበቁበት፣ መካኖች የሚወልዱበት፣ የተዘራው ለፍሬ የሚበቃበት ዓመት እንዲህን ፈጣሪያቸውን ይማፀናሉ። በሦስተኛው ቀን የቱታው አባላትና የአካባቢ ሰዎች ተጠርተው በአባቶች ምርቃት ተደርጎ በአንድነት ሆነው ምክክር በማድረግ ለቀጣይ ዓመት የሚሆን እቅድ በማዘጋጀት ተጨዋውተው ይለያያሉ። “በየቤቱ የሄደው ቅርጫ በፍጹም ለብቻ አይበላም” ያሉት አቶ እያሱ፤ በየአከባቢው የሚገኙ አቅመ ደካሞችን አፈላልጎ ማብላትና ማጠጣት በማከናወን በዓሉን በጋራ ያሳልፋሉ። ይህም በዓሉ አንዱ ለአንዱ ያለውን ወዳጅነትና አብሮነትን በማጠናከር ትስስርን የማጉላት አቅሙ ከፍተኛ ነው። በሌላ በኩል ተጣልቶ የከረሙ ነዋሪዎች ከተገኙ በሰከነ መንፈስ በመነጋገር እርቀ ሰላም በማውረድ በንጹህ ህሊና፣ በአዲስ ምዕራፍ፣ በአዲስ ተስፋና በአዲስ መንፈስ አዲሱን ዓመት ይጀምራሉ። ይህም “ባህሉ በዜጎች መካከል የሰላምና አብሮነት ምሰሶ መሆኑን ያመለክታል” ያሉት አቶ እያሱ፤ በንጹህ ልቦና በብርሃንና በተስፋ መጪውን ዘመን ለማሳለፍ እንዲቻል ጉልህ ሚና እንዳለው አጽንኦት ይሰጡታል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 20357
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 23132
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት። እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
በጂንካ ከተማ የተመረተው 23 ኪሎ ግራም የሚመዝነው የስኳር ድንች "በአፍሪካ ትልቁ ስኳር ድንች" በሚል ተመዘገበ
Mar 13, 2023 13804
ጂንካ መጋቢት 4/2015 (ኢዜአ):- በጂንካ ከተማ ደሙዝ ሰፈር የተመረተው እና 23 ኪሎ ግራም የሚመዝነው ስኳር ድንች በአፍሪካ የድንቃ ድንቆች መዝገብ "በአፍሪካ ትልቁ ስኳር ድንች" በሚል መመዝገቡ ተገለጸ። በአዲስ አበባ በተካሄደው የእውቅና ስነስርዓት ላይ የአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ስራ አስኪያጅ አቶ አሸናፊ አለም ለስኳር ድንቹ ባለቤት አቶ ኢሳያስ ጊዜአለው የእውቅና ምስክር ወረቀት አስረክበዋል። ከዚህ ቀደም በአፍሪካ 10 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች መቅረቡን አቶ አሸናፊ ለኢዜአ ገልጸዋል። “ነገር ግን 23 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች በአፍሪካ ደረጃ ሲቀርብ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው” ብለዋል። በዓለም የድንቃ ድንቅ መዝገብ 37 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች መመዝገቡንና በደሙዝ ሰፈር የተገኘው ስኳር ድንች በ14 ኪሎ ግራም ዝቅ ብሎ ከዓለም የ”ሁለተኛነት” ደረጃ ላይ እንደሚያስቀምጠው አመልክተዋል። የስኳር ድንቹ ባለቤት አቶ ኢሳያስ ጊዜያለው ስኳር ድንቹ በአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ላይ በመስፈር የኢትዮጵያን ስም በማስጠራቱ መደሰታቸውን ገልጸዋል። ስኳር ድንቹ እውቅና እንዲያገኝ የዜና ሽፋን ለሰጠው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ምስጋቸውን አቅርበዋል። ኢዜአ የካቲት 19 ቀን 2015 ዓ.ም “በጂንካ ከተማ ደሙዝ ሰፈር 23 ኪሎ ግራም የሚመዝን አንድ የስኳር ድንች መመረቱ ተገለጸ” በሚል መዘገቡ የሚታወስ ነው።
መጣጥፍ
"ጊፋታ" - የአዲስ ተስፋ ብስራትና የአብሮነት ተምሳሌት!
Sep 22, 2024 714
(በፋኑኤል ዳዊት ከሀዋሳ ኢዜአ ቅርንጫፍ) "ዮዮ ጊፋታ" ለጊፋታ በዓል እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን ማለት ነው። ዮዮ ጊፋታ በሚሰማበት ጊዜ በወላይታ ተወላጆች ዘንድ የሚፈጠረው ወደአዲስ ዘመን መሻገርና አዲስ ተስፋን የሚጭር ስሜት ነው። የዮ ጊፋታ ወላይታዎች አዲሱን ዓመት ለመቀበል በአዲስ ተስፋና ብስራት ከያሉበት ተሰባስበው በአብሮነት የሚያከብሩት በዓል ነው። በዓሉ ያለፈውን ዓመት ስኬትና ክፍተት በመገምገም የሚመጣውን ዘመን በተሻለ እምርታ ለመቀበል በሚያስችል የመንፈስ መነቃቃትም ይከበራል። "ጊፋታ" የአዲስ ተስፋ ብስራትና የአብሮነት ተምሳሌት የሆኑ ልዩ ቀለማትን አካቶ በአብሮነት የሚከበር በዓልም ነው። የወላይታ ተወላጆች በያሉበት ዓመቱን ሙሉ በሥራ ካሳለፉ በኋላ ወደየአካባቢያቸውና ወደወላጆቻቸው ተመልሰው በዓሉን በአብሮነት ያከብሩታል። ሰላምና አንድነታቸውን ለማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ከአባቶችና ወላጆች እንዲሁም ከሀገር ሽማግሌዎች ምክርና ምርቃት የሚወሰድበት ነው። በመሆኑም ጊፋታ በየዓመቱ በተወላጆቹ ዘንድ በጉጉት ይጠበቃል። በዓሉ ወደ መልካም ነገር የመሸጋገርያ ቀን ተደርጎም ይወሰዳል። በተለይ በዓሉ አዲስ ዘመንን መቀበልን ስለሚያበስር ይቅርታ፣ አብሮነት እንዲሁም በጋራ ተሰባስቦ ማክበር የበዓሉ ልዩ ዕሴቶች ናቸው። በመሆኑም በጊፋታ በዓል ወቅት የተጣላው ይታረቃል። ሰላምን ያወርዳል። አሮጌውን ዓመት በመሸኘት አዲሱን ዓመት በተስፋ ብርሃን መቀበል የተለመደ ነው። ወላይታዎች በሚያካሂዱት የዘመን መቁጠሪያ መሰረት የሚከበረው "ጊፋታ" ታላቅ፣ በኩር ወይም የመጀመሪያ የሚልና መሰል ትርጓሜ አለው። በተለያዩ የጊዜ ክፍልፋዮች ዘመንን በመቁጠር የበዓሉ ቀን የሚወሰን ቢሆንም የክረምት ጭጋግ መውጫ ወቅት ተከትሎ በዓሉ ይከበራል። በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የታሪክና ቅርስ ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ ዶክተር አበሻ ሽርኮ ጊፋታ የመጀመሪያ እንደማለት ሲሆን በዓሉም የወላይታ አባቶች እንዳስቀመጡት የክረትም ጭጋግ ወቅት መውጣትና ብርሃን የሚታይበት ወቅትን መነሻ አድርገው እንደሚያከብሩት ተናግረዋል። ዶክተር አበሻ እንዳሉት በዓሉ ከአሮጌው ወደ አዲሱ ዓመት የሚሸጋገሩበት፣ አዲስ ተስፋ የሚሰነቅበት እንዲሁም ለልማትና ለሰላም የሚነሱበት በመሆኑ “የሰላም ተምሳሌት” ተደርጎ ይከበራል። በበዓሉ የተጣላ ይታረቃል፣ በክረምቱ ምክንያት የተጠፋፋም ይገናኛል፣ አቅም ያለው የሌለውን ይደገፋል። በዓሉ ተሰባስበው በጋራ ማደግ እንደሚቻል የሚመከርበት ሲሆን ተበድሮ ያልከፈለ ካለም ችግሩ ተመክሮበት መፍትሄ ይሰጠዋል። በአጠቃላይ በዓሉ አዲሱን ዓመት በተስፋና በአብሮነት ለመቀበል ስንቅ የሚያዝበት ጭምር ነው። ጊፋታ ሲከበር በዓመቱ ሰርቶ ስኬታማ የሆነና በተሻለ የመራ ሲወደስ በአንጻሩ ውጤታማ ያልሆነው ከሌላው ተሞክሮ የሚወስድበት መሆኑን የተናገሩት ዶክተር አበሻ፣ በዓሉ ዕሴት ለማህበራዊና ኢኮኖሚ እንዲሁም ሰላምን በመገንባት ልማትና ብልጽግናን ለማፋጠን ወሳኝ መሆኑን ነው የተናገሩት። የወላይታ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ሃላፊ አቶ ምህረቱ ሳሙኤልም በበኩላቸው ጊፋታ በወላይታዎች ዘንድ ከዘመን ወደዘመን ከመሻገር ባለፈ የአዲስ ተስፋና ለቀጣይ የልማት ሥራዎች መሰረት የሚጣልበት ነው ይላሉ። በተለይም ጊፋታ ሰርቶ መለወጥንና በራስ ባህል መኩራትን እንደሚያበረታታ ጠቁመው ለዚህም ተወላጆቹ የመንፈስ ጥንካሬን እንደሚላበሱ ነው የገለጹት። በጋራ የሚመከርበትና የስኬት መነሻ ተደርጎም ይወሰዳል። በወላይታ ዘንድ ጊፋታ ሲደርስ ልዩነትን ፈትቶ እርቅ ማውረድ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው። አቶ ምህረቱ እንደሚሉት ይህም በዓሉ የአብሮነትና የሰላም እሴቶች እንዳሉት ማሳያ ነው። በዓሉ ለሰላም ፣ አብሮነትና ልማትን ለማጠናከር ካለው ፋይዳ በመነሳት የአሁኑ ትውልድ ሀገር በቀል ዕውቀቱንና ትውፊቱን ከመጠቀም በላፈ ለትውልድ ጠብቆ እንዲያቆየው ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት የዞኑ አስተዳደር ከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሰቲና የቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመቀናጀት የጊፋታ በዓል ባህላዊ እሴቶች ይበልጥ እንዲተዋወቁና በዓሉም ዓለም አቀፍ ቅርስ ሆኖ በዩኔስኮ በማይዳሰሱ የሰው ልጅ ወካይ ቅርሶች መካከል እንዲመዘገብ ለማስቻል ተስፋ ሰጪ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል። የሶዶ ከተማ ነዋሪ ወይዘሮ አበበች ኤካሶ እንዳሉት ጊፋታ የሰላምና ዕርቅ እንዲሁም ቤተሰብ፣ ወዳጅ ዘመድ እና ጎረቤት የሚጠያየቅበት በዓል ነው። በዚህም አብሮነትና ሰላም ይጠነክራል፤ በሂደቱም አንዱ ከሌላው የስኬት ልምድን ይቀስማል፤ ከድክመቱም ይማራል። በበዓሉ ላይ ከሚከናወኑ ሁነቶች መካከል በዋናነት የአባቶች ምርቃትን የጠቀሱት ወይዘሮ አበበች ወጣቶች ነገአቸው የሰመረ እንዲሆን በአባቶች ይመረቃሉ። ልጆች በበዓሉ ወቅት ወደቤተሰቦቻቸው እንዲሰባሰቡ ከሚያደርጋቸው ምክንያቶች አንዱ ይሄው የምረቃ ሥነስርአት እንደሆነም ነው የገለጹት። ምረቃው ሲካሄድ በዓመቱ ሰርቶ የተሳካለትን በማሞገስና ያልተሳካለትን ደግሞ በመምከር ለቀጣይ በአዲስ ተስፋ ለስራ እንዲነሳሱ ይደረጋል። በመሆኑም “ጊፋታ የአዲስ ተስፋ ብስራት“ ተደርጎ ይወሰዳል። በምድር ስትኖር “ወልደህ ከወግ ማዕረግ ለማድረስ፣ ሰርተህ ለስኬት መብቃትና ልቀህ መታየት ትመኛለህ ያሉት ወይዘሮ አበበች ጊፋታ ከእነዚህ ሁሉ ጋር የተያዘ ስለሆነ በተለይም ድህነትና ኋላ ቀርነትን ለማሸነፍና በራሱ የሚኮራ ትውልድ ከማፍራት አንጻር ልዩ ትርጉም እንዳለው ነው የገለጹት። የወላይታ ሀገር ሽማግሌ አቶ ሚልክያስ ኦሎሎ በበኩላቸው እንዳሉት የጊፋታ በዓል የአዲስ ተስፋ ብስራት ነው። እሳቸው እንዳሉት የበዓሉ ዕሴት አዲስ ዘመንን በቂምና ቁርሾ መቀበልና መሻገር አይቻልም። በመሆኑም በግለሰብ ብቻ ሳይሆን በመንግስትና ህዝብ መካከል እንኳ ችግሮችና አለመግባባቶች ቢኖሩ በዓሉን የሚቀበሉት ተነጋግሮ ችግሮችን በመፍታትና በዕርቅ ነው። ይህም ቀጣይ ጊዜን በአብሮነትና በሰላም ለማሳለፍ ጉልህ ሚና አለው። ለእዚህም ነው ጊፋታ የአዲስ ተስፋ ብስራትና የአብሮነት ተምሳሌት የሚያደርገው። "በዓሉ ዓመቱን ሙሉ በተለያዩ ክዋኔዎች የሚታሰብ ነው" ያሉት አቶ ሚልክያስ በተለይም ለሰላምና ለአብሮነት የሚሰጠው ቦታ ልዩ መሆኑን ነው የገለጹት። ይህም ሰላማዊ አካባቢ በመፍጠር ዜጎች ልማት ላይ እንዲያተኮሩ ያደርጋል ባይ ናቸው። የወላይታ ዞንም ሰላማዊ ሆኖ ልማቱ ላይ ብቻ እንዲያተኮር የጊፋታ ዕሴት የጎላ አስተዋጾ እንዳለው ጠቁመው፣ በአሁኑ ወቅት ትውልዱ ባህሉን ይበልጥ እንዲያውቅና እንዲረዳ እየተደረጉ ያሉ ጥረቶች መጠናከር እንዳለባቸው ተናግረዋል። የወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ "ጊፋታ" በዓል በተለያዩ ክዋኔዎች ታጅቦ በድምቀት እየተከበረ ነው። ዮዮ ጊፋታ!
መውሊድ - የአብሮነትና የሰላም ተምሳሌት
Sep 15, 2024 914
መውሊድ አል-ነቢ፣ መውሊድ አን-ነቢ፣ መውሊዲ ሸሪፍ፣ ሚላድ፣ ኢድ ሚላድ ኡን ነቢ፣ ኢድ አል-መውሊድ …ይህ ሁሉ የነብዩ መሐመድ (ሰዐወ) የልደት ቀን መጠሪያ ነው። መውሊድ የሚከበረው በረቢዓል አወል ወር በ12ኛው ቀን አንዳንድ ሀገራት ደግሞ በ17ኛው ቀን መሆኑ ይነገራል። መውሊድ በመኖሪያ ቤት፣ በመስጊድና በታላላቅ እስላማዊ ማዕከላት ነብዩ በተወለዱበት በረቢየል አወል ወር አሥራ ሁለተኛው ቀን፣ ወይም ነብዩ በተወለዱበት ወር ውስጥ በሚገኝ ሰኞ፣ ወይም በማንኛውም ወር በሚገኝ ሰኞ ቀን ይከበራል። ዘንድሮም 1 ሺህ 499ኛው የነብዩ መሐመድ (ሰዐወ) ልደት (መውሊድ) በዓል በትውፊቱ መሠረት በተለያዩ መንፈሳዊ ዝግጅቶች “የሰላሙ ነብይ” በሚል መሪ ሃሳብ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል። በዓሉ ''የሰላሙ ነብይ'' በሚል መሪ ሃሳብ መከበሩ ሰላም ያለውን ከፍተኛ ዋጋ ከማሳየትም በላይ በእስልምና ለሰላም የሚሰጠው ትኩረት ምን ያህል የገዘፈ እንደሆነ የሚያሳይ ነው። በመውሊድ በዓል የነብዩ ታሪክ፣ የእስልምና አመጣጥና ሀዲሶች ይነበባሉ። በተጨማሪም ቁርዓን በመቅራት፣ የውዳሴ ግጥሞችን በማቅረብ፣ ጣፋጭ ምግቦችን በማዘጋጀትና ለአቅመ ደካሞች ማዕድ በማጋራት እንዲሁም ስጦታ በመለዋወጥ ነው የሚከበረው። በገጠር የመውሊድ ሥርዓት በአብዛኛው ከሦስት ተከታታይ ቀናት በላይ የሚከበር ሲሆን በተለይ በቀደምት ታላላቅ እስላማዊ ማዕከላት በዓሉ በልዩ ውበት እና ድባብ ይከበራል። በብዙ አገሮች መውሊድ ሲከበር በጥንት ጊዜ የተጻፉ ሀይማኖታዊ ይዘት ያላቸው የግጥም መጽሐፍት የሚነበቡ ሲሆን፣ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ሀገሮች ደግሞ በራሳቸው ሊቃውንት የተዘጋጁ የውዳሴ ግጥሞችን በዜማ በማቅረብ በዓሉን ያድምቃሉ። በግጥሞቹ ውስጥ ስለ ነቢዩ ውልደትና ዕድገት፣ ስለ ቤተሰቦቻቸው ታሪክ፣ ስለተለያዩ አስገራሚ ክንዋኔአቸው፣ ስለ አርቆ አስተዋይነታቸው፣ ስለታላቅነታቸው፣ ስለመጀመሪያው ራዕይ፣ ስለ ቀደምት ተከታዮቻቸው፣ ወዘተ ይዳሰሳል። መውሊድ ሲከበር ሰደቃ አለ፤ በዚህም ሀብታምና ድሃ ይገናኛሉ፤ የፈጣሪን ውዴታ በምጽዋዕት ከማግኘት ባሻገር የማኅበራዊ ግንኙነትና ትስስር ይጠናከራል። መውሊድ ወንድማማችነትና አብሮነት የሚያንፀባርቅበትም ነው። መውሊድ መንዙማ በስፋት ከሚተገበርባቸው በዓላት አንዱ ነው። መውሊድና መንዙማ ጥብቅ ትስስር አላቸው። መንዙማ ማመስገን ወይም ማወደስ ማለት ነው። ይዘቱም ፈጣሪ የሚመሰገንበት፣ ነቢዩ የሚሞገሱበት፣ የእስልምና ትምህርት የሚሰጥበት፣ ታላላቅ ሰዎች ገድላቸውና ተዓምራቸው የሚነገርበት፣ የተማፅኖ ጸሎት የሚደረግበት ነው። በኢትዮጵያ እነዚህ የመውሊድ ክንዋኔዎች በትግራይ ነጃሽ፣ በሆጂራ ፎቂሳ፣ በሰሜን ወሎ ዳና፣ በደቡብ ወሎ ጃማ ንጉሥ፣ በባሌ በድሬ ሸኽ ኹሴን፣ በጅማ በቁባ አባረቡ፣ በደንግላ እና በሌሎችም አካባቢዎች በስፋት ይከናወናሉ። የዘንድሮ ዓመት የመወሊድ በዓል የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት የተቋቋመበት 50ኛ ዓመት በዕለተ መውሊድ በመሆኑ በዓሉ ድርብ በመሆኑ በተለየ ዝግጅት ነው እየተከበረ የሚገኘው። የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ሥራ አስፈጻሚ አባልና የመውሊድ በዓል አብይ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሸይኽ አብዱልሐሚድ አህመድ እንደገለጹት፤ የመጅሊሱን 50ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ በታላቁ አንዋር መስጂድ የመውሊድ በዓል በተለያዩ ስርዓተ ክዋኔ በደማቅ መርሃ ግብር ተከብሯል። ከዚህም በተጨማሪ የረቢዕል አወል ወር እስኪጠናቀቅ ድረስ የሚሰጡ ትምህርቶችና ደዕዋዎች (ስብከቶች) “የሰላሙ ነቢይ፡” ከሚል መሪ ሃሳብ እንዲሆን በምክር ቤቱ የመውሊድ ዓቢይ ኮሚቴ ውሳኔ ተላለፎ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። በዚሁም መሰረት የሰላም ግንባታ ሥራዎችን በመደገፍ፤ ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ በማድረግ ህዝበ ሙስሊሙ አስተዋጽኦውን አጠናክሮ እንዲቀጥል የሚያስችለውን ብርታትና ቁርጠኝነት የሚሰንቅበት በዓል ሆኖ እየተከበረ መሆኑን አንስተዋል። የሰላምና የአብሮነት ምልክት ለሆነው ለዚህ መልካም ዓላማ መሳካት ያለ ልዩነት በጋራ በመተሳሰብ፤ በእዝነት የነብዩን መልካም ስራዎች መስራት እንደሚገባ አስረድተዋል። የሃይማኖቱ አባቶችም ከመዕመኑ ጋር በመሆን በጸሎት፣ ቁርዓን በመቅራትና ሐዲሶችን በማንበብ ለሀገር ሰላምና ለህዝቦች አንድነት መጸለይና በማስተማርን የየዕለት ተግባራቸው ሊያደርጉት እንደሚገባ አንስተዋል። በርግጥም የዘንድሮው የመውሊድ በዓል ድርብ በዓል ነው። መጅሊስ የተቋቋመው የዛሬ 50 ዓመት በመውሊድ ዕለት ነበርና። መልካም በዓል!