ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
የግብርና ምርምር ውጤቶች የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የጎላ ሚና እያበረከቱ ነው
Jan 16, 2026 29
አዲስ አበባ፤ ጥር 8/2018(ኢዜአ)፦ በምርምር የታገዙ ቴክኖሎጂዎችን ለአርሶ አደሩ በማቅረብ በግብርናው ዘርፍ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ እንዲሁም የምግብና ሥርዓተ-ምግብ ሁኔታን ማሻሻል መቻሉን የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት አስታወቀ። በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ (ፎረም) ተካሂዷል። የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ንጉሴ ደቻሳ (ፕ/ር) እንደገለጹት፤ ተቋሙ የምርት ማነቆ የሆኑ ችግሮችን በመለየት በሽታን የሚቋቋሙና ምርታማነትን የሚጨምሩ ዝርያዎችንና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን የማፍለቅና የማስተዋወቅ ሥራዎችን በስፋት እያከናወነ ይገኛል ብለዋል። ይህም ከምግብ ዋስትና ባለፈ ለኢንዱስትሪ ግብዓት የሚሆኑና ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን ለማሳደግ እንዲሁም የገቢ ምርቶችን ለመተካት አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን ጠቁመዋል። ኢንስቲትዩቱ ምርምሮችን ከሥነ-ምህዳርና ከማህበራዊ ተቀባይነት ጋር በማጣጣም የአፈር ለምነትን፣ የውኃ አጠቃቀምንና የባለሙያዎችን አቅም ማሳደግ ላይ ትኩረት ማድረጉንም ኃላፊው አብራርተዋል። በስዊዘርላንድ የበርን ዩኒቨርሲቲ ቡድን መሪ የሆኑት ዘሪሁን ታደለ (ፕ/ር)፤ በጤፍ ምርምር ዘርፍ ከኢንስቲትዩቱ ጋር በመሆን ለአርሶ አደሩ ያቀረቧቸው የተሻሻሉ ዝርያዎች በተለያዩ ሥነ-ምህዳሮች ውጤታማ መሆናቸውን ገልጸዋል። በአሜሪካ የሄልዝ ሜድና ፋርም ቢዝ ሥራ አስኪያጅ ሙሉ አየለ (ዶ/ር)፤ ግብርናውን ለማዘመን አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ያለውን ፋይዳ በመጥቀስ በኢትዮጵያ የተጀመሩ ሥራዎች መጠናከር እንዳለባቸው አመልክተዋል። በናይጄሪያ ዓለም አቀፍ የትሮፒካል ግብርና ተመራማሪ መላኩ አየለ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ በባዮቴክኖሎጂና በሥራስር ተክሎች ላይ የሚከናወኑ ምርምሮችን በኢትዮጵያ ለመተግበር ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ በኢትዮጵያ በስንዴ ምርት የታየው ስኬታማ ሥራ በሌሎችም ሰብሎች ሊደገም እንደሚገባ ጠቁመዋል። የሶር አፍሪካ ፋርም ሥራ አስኪያጅ ወጣት አንገፉ ባናታ፤ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ ከተረፈ ምርቶች የዶሮ ምግብና የተፈጥሮ የአፈር ማዳበሪያ በማምረት ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን ተናግሯል፡፡ ሌሎች ወጣቶችን በማሰልጠን ተጠቃሚ በማድረግ ላይ መሆኑን አክሏል፡፡ በመድረኩ ማጠቃለያ የግብርና ተዋናዮች በቅንጅት በመሥራትና የመረጃ ልውውጥን በማሳለጥ ለዘርፉ እመርታዊ ለውጥ እንዲመጣ መሥራት እንደሚገባ ተመላክቷል።
ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከሶስት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰበትን ድል አስመዘገበ
Jan 16, 2026 40
አዲስ አበባ፤ ጥር 8 /2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ15ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ኢትዮ ኤሌክትሪክ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን 2 ለ 1 አሸንፏል። ማምሻውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ እዮብ ገብረማርያም እና ሀሰን ሁሴን የማሸነፊያ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፏል። ቢኒያም ካሳሁን ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቸኛውን ጎል አስቆጥሯል። ከሶስት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ25 ነጥብ ደረጃውን ከአምስተኛ ወደ አራተኛ ከፍ አድርጓል። በውድድር ዓመቱ አራተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ17 ነጥብ ከነበረበት 12ኛ ደረጃ ወደ 13ኛ ዝቅ ብሏል።
የነርቭ ዘንግ ክፍተት በሽታን ለመከላከል የሚያስችሉ ተግባራት ተጠናክረው ቀጥለዋል
Jan 16, 2026 75
አዲስ አበባ፤ ጥር 8/2018(ኢዜአ)፦የህጻናት ሞትና ዘላቂ የአካል ጉዳት የሚያስከትለውን የነርቭ ዘንግ ክፍተት በሽታ ለመከላከል የሚያስችሉ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸውን ዶክተር መቅደስ ዳባ ገለጹ፡፡ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ላለፉት ስድስት ዓመታት ከኒውትሪሽን ኢንተርናሽናል እና ከሌሎች የዘርፉ ተዋናዮች ጋር በመሆን የነርቭ ዘንግ ክፍተት በሽታን ለመከላከል የሚያስችል ጥናት ያከናወነ ሲሆን፤ በአዮዲን እና በፎሊክ አሲድ የበለጸገ ጨው በሽታውን ለመከላከል መፍትሄ መሆኑን እንዳረጋገጠም ተገልጿል። የጤና ሚኒስቴርና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ጨውን በአዮዲን እና በፎሊክ አሲድ የማበልፀግ ፕሮግራም ብሔራዊ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ይፋ አድርገዋል፡፡ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ የጥቃቅን ንጥረ ነገሮች (ማይክሮ ኒውትረንትስ ) እጥረት በዜጎች ጤና ላይ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር ጠቅሰዋል፡፡ ከንጥረ ነገር እጥረት ጋር በተያያዘ ከሚመጡ በሽታዎች መካከል በህጻናት ላይ ዘላቂ የአካል ጉዳት የሚያስከትለው የነርቭ ዘንግ ክፍተት አንዱ መሆኑን አንስተዋል፡፡ መንግስት የእናቶችን እና የህጻናትን ጤና ለመጠበቅ ከምግብ እና ስርዓተ ምግብ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን የመቀጨጭ፣ የመቀንጨር እና የጥቃቅን ንጥረ ምግቦች እጥረትን ለመፍታት በርካታ ተግባራት ሲያከናውን መቆየቱን ገልጸዋል፡፡ ከእነዚህ መካከል እናቶች በቅድመ ወሊድ ክትትል ወቅት ፎሊክ አሲድን ከአይረን እንክብሎች ጋር በማሰናሰል እንዲወሰዱ እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ ይህ እንዳለ ሆኖ አሁንም እናቶች በእርግዝና ወቅታቸው ፎሊክ አሲድን ከአይረን እንክብሎች ጋር እንዲወስዱ በማድረግ ረገድ ክፍተቶች እንደሚስተዋሉ ተናግረዋል፡፡ ችግሩንም ለመፍታት ጨውን በሁለት ንጥረ ነገሮች ማለትም (በአዮዲን እና በፎሊክ አሲድ) የማበልፀግ የጥናት ውጤት ዛሬ ይፋ መደረጉ ትልቅ እርምጃ ነው ብለዋል። የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል በበኩላቸው፤ አምራች ኢንዱስትሪዎች ጤናው የተጠበቀ ማህበረሰብ ለመፍጠር እየተከናወኑ ላሉ ስራዎች አጋዥ አቅም መሆናቸውን ተናግረዋል። በዚህ ረገድ ጨውን በአዮዲንና በፎሊክ አሲድ የማበልፀግ የጥናት ውጤት ይፋ መደረጉ ወሳኝ እርምጃ መሆኑን ጠቁመዋል። ፋብሪካዎች በአዮዲንና በፎሊክ አሲድ የበለፀገ ጨው እንዲያመርቱ ተገቢውን ስታንዳርድ ማውጣት፣ ለማህበረሰቡ ግንዛቤ ማስጨበጥ እና ተከታታይነት ያለው የምርምር ስራ ሊጠናከር ይገባል ሲሉ አሳስበዋል። የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ እንዳለው መኮንን በበኩላቸው፤ ተቋማቸው ሁሉም ዜጋ በአዮዲን እና በፎሊክ አሲድ የበለፀገ ጨው እንዲጠቀም የተያዘው ግብ እንዲሳካ የሚጠበቅበትን ሀገራዊ ኃላፊነት እንደሚወጣ አረጋግጠዋል፡፡ ጨውን በአዮዲን እና በፎሊክ አሲድ የማበልፀግ ስራ የማህበረሰቡን ጤና ከማስጠበቅ ባሻገር የምግብ አምራች ኢንዱስትሪዎች በሚያመርቷቸው ምግቦች ላይ ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን እንዲያካትቱ ያስችላል ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሳይ ኃይሉ የነፍሰ ጡሮች በመጀመሪያዎቹ 28 የእርግዝና ቀናት ፎሊክ አሲድ በአግባቡ አለመውሰድ ለነርቭ ዘንግ ወይም የቱቦ ህመም መንስኤ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ይህም ጨቅላ ህጻናትን ለሞት ወይም ለእድሜ ልክ የአካል ጉዳትና ለአዕምሮ እክል እንደሚዳርግ አንስተዋል፡፡ ኢንስቲትዩቱ ላለፉት ስድስት ዓመታት ከኒውትሪሽን ኢንተርናሽናል እና ከሌሎች የዘርፉ ተዋናዮች ጋር የነርቭ ዘንግ ክፍተት በሽታን ለመከላከል የሚያስችል ጥናት ማከናወኑን ተናግረዋል፡፡ በጥናቱ መሰረት በአዮዲን እና በፎሊክ አሲድ የበለጸገ ጨው የነርቭ ዘንግ ክፍተት በሽታን ለመከላከል መፍትሄ መሆኑን ማረጋገጥ ችለናል ብለዋል፡፡ የቀድሞ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የያዳም ፋውንዴሽን ሊቀ መንበር አቶ ደመቀ መኮንን በበኩላቸው፤ በጥናቱ የተመለከተውን አወንታዊ ውጤት ወደ መሬት ማውረድ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡ የጥናት ግኝቱ በሀገራችን ያለውን እውቀትና የሰው ኃይል በመጠቀም ችግር ፈቺ የምርምር ውጤት ማፍለቅ እንደምንችል ማሳያና ለነገው ሀገር ተረካቢ ትውልድ ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ ነው ብለዋል፡፡ ከነርቭ ዘንግ ክፍተት በሽታ ጋር ተያይዞ የሚከሰተውን ችግር ለመፍታት ኢትዮጵያ የሄደችበት ርቀት የሚበረታታ መሆኑን የተናገሩት የኒውትሪሽን ኢንተርናሽናል የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ትርንጎ ክንፈገብርኤል ናቸው፡፡ የጥናት ውጤቱን ወደ ተግባር ለመቀየር ለሚሰራው ስራ ውጤታማነት ኒውትሪሽን ኢንተርናሽናል የበኩሉን እንደሚወጣ አረጋግጠዋል፡፡
ድርጅቱ በኢትዮጵያ በግብርና፣ በቴክኖሎጂ፣ በትምህርት፣ በጤና፣ በስራ ዕድል ፈጠራ እና ድህነት ቅነሳ ዘርፎች አበረታች ስራዎችን አከናውኗል
Jan 16, 2026 40
አዲስ አበባ፤ ጥር 8/2018(ኢዜአ)፦ ቢግ ዊን ፊላንትሮፒ ግብረ ሰናይ ድርጅት በኢትዮጵያ በተለይም በግብርና፣ በቴክኖሎጂ፣ በትምህርት፣ በጤና፣ በስራ ዕድል ፈጠራ እና ድህነት ቅነሳ ዘርፎች አበረታች ስራዎች ማከናወኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከቢግ ዊን ፊላንትሮፒ ግብረ ሰናይ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ከሰተብርሃን አድማሱ ጋር ተወያይተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት ግብረ ሰናይ ድርጅቱ በኢትዮጵያ በተለይም በግብርና፣ በቴክኖሎጂ፣ በትምህርት፣ በጤና፣ በስራ ዕድል ፈጠራ እና ድህነት ቅነሳ ዘርፎች አበረታች ስራዎችን ማከናወኑን ገልጸዋል። ድርጅቱ ከመንግሥት ጋር በትብብር በሰቆጣ ቃል ኪዳን አተገባበርና በሌሎች የልማት ሥራዎች እያከናወናቸው በሚገኙ ተግባራት ዙሪያ ከዋና ሥራ አስፈፃሚው ጋር ምክክር ማድረጋቸውን አመልክተዋል። የአዲስ አበባን ተሞክሮ ወደ ክልሎች ለማስፋፋት የተያዘውን ኢኒሼቲቭ፣ (የቀዳማይ ልጅነት የስኬላፕ ፕሮግራም) እንዲሁም የሶስተኛው የወጣቶች ስራ ዕድል ፈጠራ ኢኒሼቲቭ አካል የሆነውና በአማራ ክልል የተጀመረውን የዲጂታል ንቃተ ህሊና ማስፋትን በተመለከተ መወያየታቸውንም ተናግረዋል። በቀጣይም ትብብሩን ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር በተጀመሩ እና በሌሎች አዳዲስ ዘርፎች በጋራ ለመስራት ከስምምነት ላይ መደረሱንም ጠቁመዋል።
የጥምቀት በዓል በዩኔስኮ የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ የተመዘገበ የከተማችን አንዱ የድምቀት ምንጭና የዓለም ሀብት ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Jan 16, 2026 59
አዲስ አበባ፤ ጥር 8/2018 (ኢዜአ)፦ የጥምቀት በዓል በዩኔስኮ የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ የተመዘገበ የከተማችን አንዱ የድምቀት ምንጭና የዓለም ሀብት ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። ከንቲባ አዳነች አቤቤ የጥምቀት በዓል ሃይማኖታዊ እሴቱን በጠበቀና ፍፁም ባማረ መልኩ በሁሉም ስፍራዎች እንዲከበር ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አባቶች እና የጥምቀት በዓል አዘጋጅ ኮሚቴ ጋር በቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ዙሪያ ተወያይተዋል። በውይይቱም አጠቃላይ ዝግጅቱ በተሳካ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑን ለመመልከት መቻሉን ተናግረዋል። ከንቲባዋ የጥምቀት በዓል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች ብቻ ሳይሆን፣ በርካታ ዓለም አቀፍ ጎብኚዎች የሚታደሙበትና በዩኔስኮ የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ የተመዘገበ የከተማችን አንዱ የድምቀት ምንጭና የዓለም ሀብት ነው ብለዋል። ከተማ አስተዳደሩ፣ እንደ ሌሎች ሃይማኖታዊ የአደባባይ በዓላት ሁሉ የጥምቀት በዓልም በታላቅ ድምቀትና በሰላም እንዲጠናቀቅ የሚያደርገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
ፖለቲካ
ብልጽግና ፓርቲ በሁሉም ዘርፎች የህዝብን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የጀመራቸውን ተግባራት ያጠናክራል - አቶ አደም ፋራህ
Jan 16, 2026 74
ሆሳዕና፤ ጥር 8/2018(ኢዜአ)፡- ብልጽግና ፓርቲ በየዘርፉ የህዝብን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የጀመራቸውን ተግባራት እንደሚያጠናክር የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንትና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ አደም ፋራህ ገለጹ። በሆሳዕና ከተማ ሲካሄድ የቆየው የፓርቲው የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም መድረክ በሥራ ዕድል ፈጠራ እና ገበያን ለማረጋጋት የተሰሩ ሥራዎችን በመገምገም ተጠናቋል፡፡ አቶ አደም ፋራህ በመድረኩ እንደገለጹት፣ የብዝሀ ዘርፍ ኢኮኖሚ አቅጣጫን ተግባራዊ በማድረግ ተጨባጭ ውጤት ተገኝቷል። ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራን ተግባራዊ በማድረግ የዜጎችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚነት ለማስፋት በተከናወኑ ተግባራት ባለፋት 6 ወራት ተስፋ ሰጪ ውጤት ተመዝግቧል ብለዋል፡፡ የተገኙ ድሎችን ለማላቅ ግብርና፣ ማኑፋክቸሪንግና የሥራ ዕድል የሚያስገኙ የቴክኖሎጂ አማራጮችን በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡ የሥራ አጥ ልየታን፣ ነባር ኢንተርፕራይዞችን የማጠናከርና የብቃት ምዘና ተቋማት ሥራ በጥራት እንዲከናወን በልዩ ትኩረት መምራት እንደሚገባም አስገንዝበዋል። ገበያን ለማረጋጋት በተሰሩ ሥራዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻሎች እንዳሉ ገልጸው ይህን ለማጠናከር የምርት አቅርቦትን ለማሳደግ በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡ ለዚህም የግብይት ማዕከላትን የማስፋት፣ የምርት ጥራትን የማስጠበቅ፣ ህብረት ስራ ማህበራትን የመደገፍና የፓርቲው የአንድ ግብ የሆነውን ደረጃውን የጠበቀ ዘመናዊ የግብይት ማዕከል በአንድ ከተማ ግንባታ ስራን ማጠናከር እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡ በአጠቃላይ ብልጽግና ፓርቲ በተለያዩ ዘርፎች የህዝብን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የጀመራቸውን ተግባራት ያጠናክራል ሲሉም ገልጸዋል። ለዚህም በየዘርፉ ባለፉት ስድስት ወራት የተገኙ ስኬቶችን በማላቅና ለሚገጥሙ ተግዳሮቶች የመፍትሔ አቅጣጫ በማስቀመጥ የሚፈለገውን ውጤት ለማስመዝገብ የአመራሩ ቁርጠኝነት አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል። በመድረኩ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ኃላፊዎችና የወጣቶች ክንፍ አመራሮች ተሳትፈዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
አሰባሳቢና ገዢ ትርክት በማስረጽ ረገድ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች ሚና መጎልበት አለበት
Jan 16, 2026 66
ሐረር ፤ ጥር 8/2018 (ኢዜአ)፡- በሐረሪ ክልል አሰባሳቢና ገዢ ትርክት በማስረጽ ረገድ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች ሚናቸውን ማጎልበት እንደሚገባቸው ተመለከተ። በሐረሪ ክልል የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች እና የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች ሚናቸውን ማጠናከር በሚቻሉባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሄዷል። የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሔኖክ ሙሉነህ፣ መልካም እሴቶች እንዲጎለብቱ እና ህዝቡ በክልሉ በሚከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የሚያደርገውን ተሳትፎ ለማሳደግ ያስቻሉ ስራዎች ሲከናወኑ ቆይተዋል ብለዋል። በተለይም የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ ፅንፈኛ ሀይሎች በማህበረሰቡ መካከል የሚነዙትን የጥላቻና ሀሰተኛ መረጃዎችን በመከላከል አሰባሳቢና ገዢ ትርክቶች እንዲሰርጹ በማድረግ ረገድ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ተናግረዋል። በተለይም አፍራሽ የሆኑ ፕሮፓጋንዳዎችን ቀድሞ በመከላከል የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም ማስጠበቅና ሕብረ ብሄራዊነት እንዲሰርፅና እንዲፀና በትኩረት ይሰራል ብለዋል። የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ባለሙያዎች እና ማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች በክልሉ በሁሉም ዘርፎች ለተመዘገቡ ውጤቶች አስተዋጽኦ ማበርከታቸውንም አንስተዋል። በተጨማሪም የህዝብ ሰላምና አንድነት እንዲጎለብትና የልማት ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አዎንታዊ ሚናቸውን እንዲያጠናክሩ አስገንዝበዋል። በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የክልሉ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ቶፊቅ መሀመድ በበኩላቸው፤ የክልሉ ህዝብ የሚታወቅበት የሰላም፣ መቻቻልና አብሮነት እሴቶች እንዲጎለብቱ በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ እየተከናወኑ የሚገኙ አበረታች ተግባራትን ማጠናከር ያስፈልጋል ብለዋል። የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች በተለይም የጋራ የሚያደርጉ ሀገራዊ እሴቶችን በማጠናከርና ገዢ ትርክትን በመገንባት ሰላምና ልማት እንዲጠናከር እያበረከቱ የሚገኘው ተግባር ይበልጥ መጎልበት አለበት ብለዋል። የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎችም የሚያስተላለፉት መልዕክት ሀገርን የሚገነባ፣ ከጥላቻ ይልቅ ፍቅርን የሚሰብክ እንዲሁም ህብረተሰቡ በልማት እንቅስቃሴው ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆን የሚያስችሉ ሊሆኑ ይገባል ነው ያሉት።
ከኢትዮጵያ ጋር ያለንን የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር እንሰራለን -አምባሳደሮች
Jan 15, 2026 109
አዲስ አበባ፤ ጥር 7/2018 (ኢዜአ)፡ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰሩ በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች ገለጹ። ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙ የ 14 ሀገራት አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤ ተቀብለዋል። የሹመት ደብዳቤያቸውን ለፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ያቀረቡትም የኪርጊስታን፣ ጣልያን፣ ሞሪሺየስ፣ ዛምቢያ፣ጀርመን፣ ጆርዳን፣ ኒውዝላንድ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ቡሩኪና ፋሶ፣ ሞዛምቢክ፣ ኬንያ፣ቤላሩስ፣ ፊሊፒንስ፣ ላቲቪያ ሀገራት አምባሳደሮች ናቸው። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው በሰጡት ማብራሪያ የሹመት ደብዳቤያቸውን ካቀረቡ ሀገራት መካከል 11ዱ ተቀማጭነታቸው በአዲስ አበባ መሆኑን ገልጸዋል። አምባሳደሮቹ ከፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ጋር ከፍተኛ ውጤት እየተመዘገበበት ባለው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ እንዲሁም በንግድ እና ኢንቨስትመንት በሚሰማሩባቸው መስኮች ላይ መወያየታቸውን ገልጸዋል። በተጨማሪም የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅሞች በሚያስከብሩ ስራዎች ዙሪያ ምክክር ማድረጋቸውን ነው የተናገሩት። በውይይቱ አምባሳደሮቹ በኢትዮጵያ እየተመዘገበ ላለው ለውጥ አድናቆት መስጠታቸውን ጠቁመው፥ ሀገሮቻቸው ከኢትዮጵያ ልምድና ተሞክሮ መውሰድ እንደሚፈልጉ መናገራቸውን አንስተዋል። በኢትዮጵያና በሀገራቱ መካከል የሁለትዮሽ ግንኙነትን ለማጠናከር እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል ነው ያሉት። በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙት የጣልያን አምባሳደር ሴም ፋብሪዚ በትምህርት፣ በክህሎት፣ በሳይንሳዊ እና በባህል ትብብር ዙሪያ እንደሚሰሩ ገልጸዋል። በሚኖራቸው ቆይታ ጣልያን ለኢትዮጵያ ጠንካራ ወዳጅ መሆን የምትችልባቸውን መንገዶች ለማየት እንደሚጥሩ ጠቁመዋል። አዲስ የተሾሙት የዛምቢያ አምባሳደር አልበርት ሙቻንጋ በበኩላቸው በግብርና ማለትም በተሻሻሉ የሰብል ዝሪያዎች ላይ ልምድ በመለዋወጥ እና በስፋት በመተግበር ምርታማነትን ለማሻሻል እንደሚሰሩ ገልፀዋል። የኬንያ አምባሳደር ጋልማ ሙክሄ በኢትዮጵያ እና በኬንያ መካከል ያለውን ታሪካዊ የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር እና ለማሳደግ እንደሚሰሩ ገልጸዋል። በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በመከላከያ እና በሌሎች በርካታ ዘርፎች ላይ ይህን ግንኙነት ለማጠናከር በጋራ እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል። የደቡብ ሱዳን አምባሳደር ባክ ቫለንቲኖ የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ለማጠናከር በትኩረት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል። ይህንንም በኢትዮጵያ ከሚገኙ ሌሎች አካላት ጋር በቅርበት እንደሚሰሩ አመላክተዋል:: የፊሊፒንስ አምባሳደር ማሬ ቻርሎቴ በቀጣዩ አመት ሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩበትን የምስረታ በአላቸውን እንደሚያከብሩም ተናግረዋል። በሁለቱ አገራት መካከል በፖለቲካ፣በኢኮኖሚ እና በህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ጠንካራ ትብብር ለመፍጠር እንደሚሰራ አመላክተዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤ ተቀበሉ
Jan 15, 2026 111
አዲስ አበባ፤ ጥር 7/2018 (ኢዜአ)፡- ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙ የ14 ሀገራት አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤ ተቀብለዋል። የሹመት ደብዳቤያቸውን ለፕሬዚዳንት ታዬ ያቀረቡት፤ የደቡብ ሱዳን፣ ጣልያን፣ ሞሪሺየስ፣ ዛምቢያ፣ ጀርመን፣ ጆርዳን፣ ኒውዝላንድ፣ ቡርኪና ፋሶ፣ ሞዛምቢክ፣ ኬንያ፣ ቤላሩስ፣ ፊሊፒንስ፣ ኪርጊስታን እና የላቲቪያ አምባሳደሮች ናቸው። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው በሰጡት ማብራሪያም፤ የሹመት ደብዳቤያቸውን ካቀረቡ ሀገራት መካከል 11ዱ ተቀማጭነታቸው በአዲስ አበባ መሆኑን አስታውቀዋል። ከፍተኛ ውጤት እየተመዘገበበት ባለው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ እንዲሁም ሀገሮቻቸው በንግድ እና ኢንቨስትመንት በሚሰማሩባቸው መስኮች ላይ አምባሳደሮቹ ከፕሬዚዳንት ታዬ ጋር መወያየታቸውንም ገልጸዋል። በተጨማሪም የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅሞች በሚያስከብሩ ሥራዎች ዙሪያ ምክክር ማድረጋቸውን ጠቅሰዋል። በውይይቱ አምባሳደሮቹ በኢትዮጵያ እየተመዘገበ ያለውን ለውጥ ማድነቃቸውንም አንስተዋል። በኢትዮጵያና በሀገራቱ መካከል የሁለትዮሽ ግንኙነትን ለማጠናከር እንደሚሠሩም አረጋግጠዋል ነው ያሉት።
የአውሮፓ ሕብረት እና አባል አገሮቹ የኢትዮጵያ አስተማማኝ አጋሮች ናቸው - ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር)
Jan 15, 2026 90
አዲስ አበባ፤ ጥር 7/2018(ኢዜአ)፦የአውሮፓ ሕብረትና አባል አገሮቹ የኢትዮጵያ አስተማማኝ አጋሮች መሆናቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) ገለጹ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በአውሮፓ የውጭ ጉዳይ አገልግሎት የፖለቲካ ጉዳዮች ምክትል ዋና ፀሐፊ ኡሎፍ ስኩጊን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት የንግድና ኢንቨስትመንት ትብብራቸውን ለማጠናከር የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ በውይይታቸውም የአውሮፓ ሕብረትና አባል አገሮቹ የኢትዮጵያ አስተማማኝ አጋሮች መሆናቸውን የገለጹት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ግንኙነቱ በጋራ ዕሴቶች እና ተስፋዎች ላይ የተመሰረተ ወሳኝ አጋርነት መሆኑንም አንስተዋል። ኢትዮጵያ ለቀጣናዊ ውህደት የምታደርገውን ጥረት ያነሱት ሚኒስትሩ እንቅስቃሴው ከአውሮፓ ህብረት ግሎባል ጌትዌይ ኢኒሼቲቭ(Global Gateway initiative) ጋር የሚጣጣም መሆኑን ገልጸው በቀጣናው ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ውህደትን ለማሳደግ ያላትን ቁርጠኝነትም ተናግረዋል። እየተከናወነ ያለው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ በፈጠረው ምቹ የኢንቨስትመንት ዕድል የአውሮፓ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የበለጠ የኢንቨስትመንት ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። ኡሎፍ ስኩጊን በበኩላቸው ህብረቱ ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች የሚያደርገውን ድጋፍና ስትራቴጂያዊ አጋርነት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡ ኢትዮጵያ የኮፕ 32 አስተናጋጅ ሆና በመመረጧ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን የኢትዮጵያን የልማት ውጥኖች ከግብ ለማድረስ ህብረቱ አስፈላጊውን ትብብር ያደርጋል ብለዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ እደሚያመለክተው በውይይታቸው ሁለቱም ወገኖች በጋራ ጥቅም ላይ በሚያተኩሩ ጉዳዮች አብረው ለመስራት ተስማምተዋል።
የክልሉን የልማት አቅም ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር ሰላምን ማጽናት ቀዳሚ ተግባር ነው
Jan 15, 2026 74
አዲስ አበባ፤ጥር 7/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል ያለውን ሰፊ የልማት አቅም ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር በሁሉም አካባቢዎች ሰላምን ማጽናት ቀዳሚ ተግባር በማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ እሸቱ የሱፍ (ዶ/ር) ገለፁ። በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና በአማራ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ትብብር የተዘጋጀው የፓናል ውይይት "ሰላምን ማጽናት፤ፀጋን ለማልማት"በሚል መሪ ሃሳብ በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው። የአማራ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ እሸቱ የሱፍ (ዶ/ር) በክልሉ የተከናወኑ "የሰላምና ፀጥታ ስራዎችና እምርታዎች" በሚል ርዕስ የመወያያ ጽሁፍ አቅርበዋል። በጽሁፋቸው በክልሉ ሰላምን ለማጽናት የተከናወኑ ተግባራት ተጨባጭ ውጤት እያመጡ መሆኑን ጠቅሰው፤ የተገኙ የሰላም እመርታዎችን ጠብቆ ማስቀጠል ለልማት ስራዎች መሳካት ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል። የህዝቡን ደህንነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የተከናወኑ ስራዎች በክልሉ ልማትን ለማፋጠን ወሳኝ በመሆናቸው ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል። በክልሉ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ህብረተሰቡ ከመንግሥት ጎን በመሰለፍ ያበረከተው አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል። ክልሉ ያለውን ሰፊ የልማት አቅም ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር በሁሉም አካባቢዎች ሰላምን ማጽናት ቀዳሚ ተግባር በማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አረጋግጠዋል። የአማራ ክልል ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ እንድሪስ አብዱ በበኩላቸው፤ "የክልሉ ፀጋዎችና የኢንቨስትመንት አማራጮች” በሚል ርዕስ የመነሻ ጽሁፍ አቅርበዋል። በጽሁፋቸውም ክልሉ ለኢንቨስትመንት ምቹ የሆኑና ያልተነኩ በርካታ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ፀጋዎች ባለቤት መሆኑን ገልጸዋል። በክልሉ ለማዕድን፣ ለቱሪዝም፣ ለእንስሳት ሀብት ልማት፣ ለውሃ እና ለመሬት ልማት ምቹ የሆኑ በርካታ ዕድሎች መኖራቸውን አብራርተዋል። የክልሉ የሥነ-ምህዳር አወቃቀርና ምቹ የአየር ንብረት ለግብርና ዘርፍ ዕድገት እምቅ አቅም እንዳለው ጠቁመዋል። በዓለም አቀፍ ደረጃ በቅርስነት የተመዘገቡ ታሪካዊ ቦታዎች፣ ተፈጥሯዊ መስህቦች እና የማይዳሰሱ ሃይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶች የክልሉ የቱሪዝም ሀብት መገለጫ ናቸው ብለዋል። እነዚህን ሀብቶች በተገቢው መንገድ በማልማት የቱሪዝም ዘርፉን የኢኮኖሚ ምሰሶ ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ አመላክተዋል። በክልሉ የሚገኙ የከበሩ ማዕድናት፣ የኮንስትራክሽን ግብዓቶች እና ለኢንዱስትሪ ልማት አመቺ ሁኔታዎች ለኢንቨስትመንት መዳረሻ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። እነዚህን የተፈጥሮ ፀጋዎችና የኢንቨስትመንት አማራጮች በአግባቡ በመጠቀም የክልሉን አልፎም የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ማሳደግ ይቻላል ብለዋል፡፡ በዚህ ረገድ የግል ባለሀብቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን በማንሳት የክልሉ መንግስት ለባለሀብቶች አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል። የአማራ ክልል ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ ደመቀ ቦሩ (ዶ/ር) በበኩላቸው "የአማራ ክልል የልማት ተስፋዎችና የህዝብ ተጠቃሚነት" በሚል ርዕስ ባቀረቡት ጽሁፍ ክልሉ የረጅም፣ የመካከለኛ እና የአጭር ዘመን እቅድ አዘጋጅቶ ወደ ተግባር መግባቱን ተናግረዋል። በዚህም በ2027 የአማራ ክልል በመሠረታዊ ኢንዱስትሪ ምርቶች የራሱን ፍላጎት የሸፈነ እና የተሳካ የመዋቅራዊ ሽግግር በማድረግ የክልሉን ሁለንተናዊ እድገት ለማረጋገጥ በማቀድ እየተሰራ ነው ብለዋል። በ2042 ክልሉ በዓለም አቀፍ ደረጃ በቴክኖሎጂ ተወዳዳሪ የሆነ የዘመናዊ ኢኮኖሚ ባለቤት እና የበለጸገ ማሕበረሰብ ሆኖ ማየት የዕቅዱ አካል መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ የክልሉን ሠላምና ደህንነት እንዲሁም የህግ የበላይነት ማረጋገጥ፤ የተቋማትን የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም መገንባት ስትራቴጂክ ጉዳይ ነው ብለዋል። ክልላዊ ወጎችን፣ ዕሴቶችን እና ባህሎችን በማዳበር በሥነ-ምግባር የታነፀ ትውልድ ማፍራትንም እንዲሁ። በተጨማሪ ሣይንሳዊ ዕውቀትን የማሕበረሰብ እሴት እና የኢኮኖሚ ዕድገት መሠረት ማድረግ፤ ምርታማነትንና ቅልጥፍናን በማሳደግ ጥራት ያለው ኢኮኖሚ መገንባት ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የብልጽግና ፓርቲ እቅድ እና እሳቤዎች ተጨባጭ ውጤት እየተገኘባቸው ነው- አቶ አደም ፋራህ
Jan 15, 2026 96
ሆሳዕና፤ ጥር 7/2018(ኢዜአ)፦የብልጽግና ፓርቲ እቅድ እና እሳቤዎች በሁሉም አካባቢዎች እየተተገበሩ ተጨባጭ ውጤት እየተገኘባቸው መሆኑን የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንትና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርአት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ ገለጹ። የፓርቲው የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወራት ሥራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ሲሆን የፓርቲው ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። አቶ አደም ፋራህ በዚሁ ወቅት ከክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የቀረበው የፓርቲው ሥራ አፈፃፀም የሚያመለክተው የብልጽግና ፓርቲ እቅድ እና እሳቤዎች በሁሉም አካባቢዎች የህዝብ ቅቡልነት በማግኘት እየተተገበሩ ናቸው ብለዋል፡፡ ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ለፓርቲው ስራዎች ውጤታማነት የሚረዳ የተናበበ እቅድ የማዘጋጀት እንዲሁም የፓርቲውን እሳቤ በመረዳት በስነ ምግባር የሚፈፅም ጠንካራ አመራር ለማብቃት በተሰራው ስራ መሻሻሎች መታየታቸውንም ገልጸዋል። በአገልግሎት አሰጣጥ ረገድም ከህዝቡ ዘንድ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ተደራሽነትን በማስፋት ውጤት እየተገኘ መሆኑን ተናግረዋል። በተጨማሪም የኮሪደር ልማት ስራ እና የሌማት ትሩፋትን ጨምሮ ሌሎች የፓርቲውን እሳቤዎች በመተግበር ህዝቡ ተባባሪ ሆኖ በመስራቱ ተጨባጭ ውጤቶች ተገኝተዋል ብለዋል። በሁሉም አካባቢዎች ልማትን የማፋጠን እና መልካም አስተዳደር የማስፈን ስራዎች አሁንም በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥሉ ገልጸው የህዝቡን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በፓርቲው የተያዙ ሁሉን አቀፍ የእድገትና ትራንፎርሜሽን አጀንዳዎችን ለማሳካት አመራሩ በትኩረት መስራት እንዳለበትም አስገንዝበዋል፡፡ በመድረኩ ላይ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ የክልሎችና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊዎችና የወጣት ክንፍ አመራሮች እየተሳተፉ ነው፡፡
ሀገራዊ ምክክር ለጠንካራ ሀገር መንግስት ግንባታ መሠረት ነው
Jan 15, 2026 110
አዲስ አበባ፤ ጥር 7/2018(ኢዜአ)፦ ሀገራዊ ምክክር ለዘላቂ ሰላም መስፈንና ለጠንካራ ሀገር መንግስት ግንባታ መሠረት መሆኑን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አዝመራ አንደሞ ገለፁ። በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ትብብር “ሰላምን ማጽናት፤ ፀጋን ለማልማት” በሚል መሪ ሃሳብ የተዘጋጀ የፓናል ውይይት በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። በመድረኩ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አዝመራ አንደሞ “ሀገራዊ ምክክር እና የሰላም ግንባታ” በሚል ርዕስ የመወያያ ጽሁፍ አቅርበዋል። በጹሁፋቸውም በኢትዮጵያ ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታትና ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ የሀገራዊ ምክክር ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል። ሀገራዊ ምክክሩ ቅቡልነት ያለው ጠንካራ ሥርዓተ-መንግስት ለመገንባት፣ የማያግባቡ ጉዳዮች ላይ በመመካከር ለመግባባትና የዲሞክራሲ ሥርዓትን ለማፅናት ወሳኝ ነው ብለዋል። ለዚህም የተቋቋመው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የችግሩን ጥልቀትና ባህሪ በመገንዘብ ከሌሎች ሀገራት በተሻለ መንገድና ሥነ ዘዴ ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጠንካራ ተቋማትን በመገንባት፣ ማህበራዊ ትስስርን በማጠናከርና አዲስ ማህበራዊ ውልን በመፍጠር ልዩነቶችን ወደ ትብብር መቀየር ለዘላቂ ሰላም አይተኬ ሚና እንዳለውም ተናግረዋል። ሀገራዊ ምክክር ፈጣን መፍትሄ ሳይሆን፤ ረጅም ጊዜ የሚፈልግ ኢንቨስትመንት እንደሆነ ጠቁመው፤ ምክክሩ የሰላም ግንባታ መሣሪያ ብቻ ሳይሆን የሀገር ግንባታ መሠረት መሆኑን አስረድተዋል። ሁሉም ኢትዮጵያውያን ይህን ታሪካዊ ዕድል በመጠቀም የወደፊት እጣ ፈንታቸውን እንዲወስኑና ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠር የድርሻቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል።

ማህበራዊ
የነርቭ ዘንግ ክፍተት በሽታን ለመከላከል የሚያስችሉ ተግባራት ተጠናክረው ቀጥለዋል
Jan 16, 2026 75
አዲስ አበባ፤ ጥር 8/2018(ኢዜአ)፦የህጻናት ሞትና ዘላቂ የአካል ጉዳት የሚያስከትለውን የነርቭ ዘንግ ክፍተት በሽታ ለመከላከል የሚያስችሉ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸውን ዶክተር መቅደስ ዳባ ገለጹ፡፡ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ላለፉት ስድስት ዓመታት ከኒውትሪሽን ኢንተርናሽናል እና ከሌሎች የዘርፉ ተዋናዮች ጋር በመሆን የነርቭ ዘንግ ክፍተት በሽታን ለመከላከል የሚያስችል ጥናት ያከናወነ ሲሆን፤ በአዮዲን እና በፎሊክ አሲድ የበለጸገ ጨው በሽታውን ለመከላከል መፍትሄ መሆኑን እንዳረጋገጠም ተገልጿል። የጤና ሚኒስቴርና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ጨውን በአዮዲን እና በፎሊክ አሲድ የማበልፀግ ፕሮግራም ብሔራዊ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ይፋ አድርገዋል፡፡ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ የጥቃቅን ንጥረ ነገሮች (ማይክሮ ኒውትረንትስ ) እጥረት በዜጎች ጤና ላይ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር ጠቅሰዋል፡፡ ከንጥረ ነገር እጥረት ጋር በተያያዘ ከሚመጡ በሽታዎች መካከል በህጻናት ላይ ዘላቂ የአካል ጉዳት የሚያስከትለው የነርቭ ዘንግ ክፍተት አንዱ መሆኑን አንስተዋል፡፡ መንግስት የእናቶችን እና የህጻናትን ጤና ለመጠበቅ ከምግብ እና ስርዓተ ምግብ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን የመቀጨጭ፣ የመቀንጨር እና የጥቃቅን ንጥረ ምግቦች እጥረትን ለመፍታት በርካታ ተግባራት ሲያከናውን መቆየቱን ገልጸዋል፡፡ ከእነዚህ መካከል እናቶች በቅድመ ወሊድ ክትትል ወቅት ፎሊክ አሲድን ከአይረን እንክብሎች ጋር በማሰናሰል እንዲወሰዱ እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ ይህ እንዳለ ሆኖ አሁንም እናቶች በእርግዝና ወቅታቸው ፎሊክ አሲድን ከአይረን እንክብሎች ጋር እንዲወስዱ በማድረግ ረገድ ክፍተቶች እንደሚስተዋሉ ተናግረዋል፡፡ ችግሩንም ለመፍታት ጨውን በሁለት ንጥረ ነገሮች ማለትም (በአዮዲን እና በፎሊክ አሲድ) የማበልፀግ የጥናት ውጤት ዛሬ ይፋ መደረጉ ትልቅ እርምጃ ነው ብለዋል። የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል በበኩላቸው፤ አምራች ኢንዱስትሪዎች ጤናው የተጠበቀ ማህበረሰብ ለመፍጠር እየተከናወኑ ላሉ ስራዎች አጋዥ አቅም መሆናቸውን ተናግረዋል። በዚህ ረገድ ጨውን በአዮዲንና በፎሊክ አሲድ የማበልፀግ የጥናት ውጤት ይፋ መደረጉ ወሳኝ እርምጃ መሆኑን ጠቁመዋል። ፋብሪካዎች በአዮዲንና በፎሊክ አሲድ የበለፀገ ጨው እንዲያመርቱ ተገቢውን ስታንዳርድ ማውጣት፣ ለማህበረሰቡ ግንዛቤ ማስጨበጥ እና ተከታታይነት ያለው የምርምር ስራ ሊጠናከር ይገባል ሲሉ አሳስበዋል። የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ እንዳለው መኮንን በበኩላቸው፤ ተቋማቸው ሁሉም ዜጋ በአዮዲን እና በፎሊክ አሲድ የበለፀገ ጨው እንዲጠቀም የተያዘው ግብ እንዲሳካ የሚጠበቅበትን ሀገራዊ ኃላፊነት እንደሚወጣ አረጋግጠዋል፡፡ ጨውን በአዮዲን እና በፎሊክ አሲድ የማበልፀግ ስራ የማህበረሰቡን ጤና ከማስጠበቅ ባሻገር የምግብ አምራች ኢንዱስትሪዎች በሚያመርቷቸው ምግቦች ላይ ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን እንዲያካትቱ ያስችላል ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሳይ ኃይሉ የነፍሰ ጡሮች በመጀመሪያዎቹ 28 የእርግዝና ቀናት ፎሊክ አሲድ በአግባቡ አለመውሰድ ለነርቭ ዘንግ ወይም የቱቦ ህመም መንስኤ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ይህም ጨቅላ ህጻናትን ለሞት ወይም ለእድሜ ልክ የአካል ጉዳትና ለአዕምሮ እክል እንደሚዳርግ አንስተዋል፡፡ ኢንስቲትዩቱ ላለፉት ስድስት ዓመታት ከኒውትሪሽን ኢንተርናሽናል እና ከሌሎች የዘርፉ ተዋናዮች ጋር የነርቭ ዘንግ ክፍተት በሽታን ለመከላከል የሚያስችል ጥናት ማከናወኑን ተናግረዋል፡፡ በጥናቱ መሰረት በአዮዲን እና በፎሊክ አሲድ የበለጸገ ጨው የነርቭ ዘንግ ክፍተት በሽታን ለመከላከል መፍትሄ መሆኑን ማረጋገጥ ችለናል ብለዋል፡፡ የቀድሞ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የያዳም ፋውንዴሽን ሊቀ መንበር አቶ ደመቀ መኮንን በበኩላቸው፤ በጥናቱ የተመለከተውን አወንታዊ ውጤት ወደ መሬት ማውረድ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡ የጥናት ግኝቱ በሀገራችን ያለውን እውቀትና የሰው ኃይል በመጠቀም ችግር ፈቺ የምርምር ውጤት ማፍለቅ እንደምንችል ማሳያና ለነገው ሀገር ተረካቢ ትውልድ ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ ነው ብለዋል፡፡ ከነርቭ ዘንግ ክፍተት በሽታ ጋር ተያይዞ የሚከሰተውን ችግር ለመፍታት ኢትዮጵያ የሄደችበት ርቀት የሚበረታታ መሆኑን የተናገሩት የኒውትሪሽን ኢንተርናሽናል የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ትርንጎ ክንፈገብርኤል ናቸው፡፡ የጥናት ውጤቱን ወደ ተግባር ለመቀየር ለሚሰራው ስራ ውጤታማነት ኒውትሪሽን ኢንተርናሽናል የበኩሉን እንደሚወጣ አረጋግጠዋል፡፡
ድርጅቱ በኢትዮጵያ በግብርና፣ በቴክኖሎጂ፣ በትምህርት፣ በጤና፣ በስራ ዕድል ፈጠራ እና ድህነት ቅነሳ ዘርፎች አበረታች ስራዎችን አከናውኗል
Jan 16, 2026 40
አዲስ አበባ፤ ጥር 8/2018(ኢዜአ)፦ ቢግ ዊን ፊላንትሮፒ ግብረ ሰናይ ድርጅት በኢትዮጵያ በተለይም በግብርና፣ በቴክኖሎጂ፣ በትምህርት፣ በጤና፣ በስራ ዕድል ፈጠራ እና ድህነት ቅነሳ ዘርፎች አበረታች ስራዎች ማከናወኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከቢግ ዊን ፊላንትሮፒ ግብረ ሰናይ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ከሰተብርሃን አድማሱ ጋር ተወያይተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት ግብረ ሰናይ ድርጅቱ በኢትዮጵያ በተለይም በግብርና፣ በቴክኖሎጂ፣ በትምህርት፣ በጤና፣ በስራ ዕድል ፈጠራ እና ድህነት ቅነሳ ዘርፎች አበረታች ስራዎችን ማከናወኑን ገልጸዋል። ድርጅቱ ከመንግሥት ጋር በትብብር በሰቆጣ ቃል ኪዳን አተገባበርና በሌሎች የልማት ሥራዎች እያከናወናቸው በሚገኙ ተግባራት ዙሪያ ከዋና ሥራ አስፈፃሚው ጋር ምክክር ማድረጋቸውን አመልክተዋል። የአዲስ አበባን ተሞክሮ ወደ ክልሎች ለማስፋፋት የተያዘውን ኢኒሼቲቭ፣ (የቀዳማይ ልጅነት የስኬላፕ ፕሮግራም) እንዲሁም የሶስተኛው የወጣቶች ስራ ዕድል ፈጠራ ኢኒሼቲቭ አካል የሆነውና በአማራ ክልል የተጀመረውን የዲጂታል ንቃተ ህሊና ማስፋትን በተመለከተ መወያየታቸውንም ተናግረዋል። በቀጣይም ትብብሩን ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር በተጀመሩ እና በሌሎች አዳዲስ ዘርፎች በጋራ ለመስራት ከስምምነት ላይ መደረሱንም ጠቁመዋል።
የጥምቀት በዓል በዩኔስኮ የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ የተመዘገበ የከተማችን አንዱ የድምቀት ምንጭና የዓለም ሀብት ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Jan 16, 2026 59
አዲስ አበባ፤ ጥር 8/2018 (ኢዜአ)፦ የጥምቀት በዓል በዩኔስኮ የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ የተመዘገበ የከተማችን አንዱ የድምቀት ምንጭና የዓለም ሀብት ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። ከንቲባ አዳነች አቤቤ የጥምቀት በዓል ሃይማኖታዊ እሴቱን በጠበቀና ፍፁም ባማረ መልኩ በሁሉም ስፍራዎች እንዲከበር ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አባቶች እና የጥምቀት በዓል አዘጋጅ ኮሚቴ ጋር በቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ዙሪያ ተወያይተዋል። በውይይቱም አጠቃላይ ዝግጅቱ በተሳካ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑን ለመመልከት መቻሉን ተናግረዋል። ከንቲባዋ የጥምቀት በዓል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች ብቻ ሳይሆን፣ በርካታ ዓለም አቀፍ ጎብኚዎች የሚታደሙበትና በዩኔስኮ የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ የተመዘገበ የከተማችን አንዱ የድምቀት ምንጭና የዓለም ሀብት ነው ብለዋል። ከተማ አስተዳደሩ፣ እንደ ሌሎች ሃይማኖታዊ የአደባባይ በዓላት ሁሉ የጥምቀት በዓልም በታላቅ ድምቀትና በሰላም እንዲጠናቀቅ የሚያደርገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
በሲዳማ ክልል ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የተተገበሩ የልማት ሥራዎች ውጤት አምጥተዋል
Jan 16, 2026 45
ሐዋሳ፤ ጥር 8/2018 (ኢዜአ)፡- በሲዳማ ክልል ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የተተገበሩ የልማት ሥራዎች ውጤት ማምጣታቸውን የክልሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው ኃላፊ ወሰንየለህ ስምኦን በሰጡት መግለጫ፤ ክልሉ በተቀናጀ መንገድ የ100 ቀናት ዕቅድ በማዘጋጀት ወደ ተግባር መግባቱንና በዚህም የሕዝብን ተጠቃሚነት ያሳደጉ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል። በክልሉ የግብርናውን ዘርፍ በማዘመን የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ያስቻሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ጠቁመው፤ ይህን የማጠናከር ሥራም የቀጣይ ትኩረት መሆኑን አመላክተዋል። የቱሪዝም ሀብቱ ለኢኮኖሚው ዕድገት የሚገባውን ሚና እንዲያበረክት የማልማት፣ የመጠበቅና የማስተዋወቅ ሥራ እየተሠራ ነው ብለዋል። በማኅበራዊ ልማት ዘርፍ በርካታ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ያደረጉ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውንም ገልጸዋል። የንጹህ መጠጥ ውኃ ሽፋንን በተያዘው ዓመት ወደ 70 በመቶ ለማሳደግ ግብ ተይዞ እየተሠራ ነው ብለዋል። ከገጠር ተደራሽ መንገድ ግንባታ አንጻር ባለፉት 5 ዓመታት ከ1 ሺህ 100 በላይ ኪሎ ሜትር መገንባቱንና ይህን ውጤት የማስቀጠል ሥራ ትኩረት እንደተሰጠው አስታውቀዋል። የኮሪደር ልማት ሥራዎች የማኅበረሰቡን የሥራ ባህልና ዘመናዊነት እያሳደጉ ስለመሆናቸውም አንስተዋል። የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክርው የተያዘውን ግብ ማሳካት እንዲችሉ የክትትል ሥርዓት መዘርጋቱን ጠቅሰው፤ ተልዕኮን በአግባቡ በማይወጡ የአመራር አካላት ላይ የእርምት ርምጃ እንደሚወሰድ ተናግረዋል።
ኢኮኖሚ
የኢትዮጵያን ምርት በዩናይትድ ኪንግደም የማስተዋወቅና ኢንቨስትመንት የመሳብ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል
Jan 16, 2026 48
አዲስ አበባ፤ ጥር 8/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያን ምርት በዩናይትድ ኪንግደም የማስተዋወቅና ኢንቨስትመንትን የመሳብ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ። በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና በአምራቾቹ ትብብር በተዘጋጀ የማስተዋወቂያ መድረክ ላይ ጤፍ-ሊ(Teff-Ly) የተሰኘ ከጤፍ የተሠራ የወተት ምርት ይፋ ሆኗል። በመድረኩ የንግድ ማህበረሰቡ፣ ከሚዲያ፣ ከእንስሳት ተዋጽኦዎች ነፃ በሆኑ ምግቦች ምርት እና ግብይት ውስጥ የሚሳተፉ ኢንዱስትሪዎች አባላት እና የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ተሳትፈዋል። በዚሁ ወቅት በብሪታንያና ሰሜን አየርላንድ የኢፌዴሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ብሩክ መኮንን እንዳሉት ጤፍ በኢትዮጵያ ከምግብነት ባለፈ የባህል መገለጫ ሆኖ የሚታይ ነው። ጤፍ በንጥረ ምግብ የበለፀገ ሰብል መሆኑን የገለጹት አምባሳደር ብሩክ ጤፍ-ሊ ወተት ምርት ጤፍ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ትስስር ለዓለም ለማስተዋወቅ የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል። በለንደን የኢትዮጵያ ኢምባሲ ምክትል ሚሲዮን መሪ አምባሳደር ሌሊሳ ብርሃኑ በበኩላቸው ለኢዜአ እንደገለጹት በዩናይትድ ኪንግደም ያሉ ኢትዮጵያውያን ሀገራቸውን በንግድና በባህል ልውውጥ እያስተዋወቁ የሚገኙ የባህል አምባሳደር ናቸው። ኤምባሲው በተለያዩ መድረኮች የኢትዮጵያን ምርት የማስተዋወቅና ኢንቨስትመንት ወደ ሀገር የመሳብ ስራ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል። የኦሪጅናል ጤፍ-ሊ ምርት በቢዝነስ ዘርፍ አዲስ እሳቤን ወደ ተግባር ያመጣ እና ኢትዮጵያን ለማስተዋወቅም ትልቅ አቅም የሚሆን ነው ብለዋል። ኤምባሲው የዳያስፖራው የንግድና ኢንቨስትመንት ተሳትፎን ለማሳደግ በኢትዮጵያ ያሉ ሪፎርምና ህጎችን የማሳወቅ ስራ እየሰራ ይገኛል። ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ የቴክኖሎጂና እውቀት ሽግግር እንዲሁም የውጭ ምንዛሬ ግኝትና የስራ እድል ፈጠራ ላይ አስተዋፅኦ እያደረጉ መሆኑንም ተናግረዋል። የኢትዮ-እንግሊዝ የንግድ ምክር ቤት ተመስርቶ በእንግሊዝ ይፋ መደረጉንና በኢትዮጵያም መሰል መድረክ እንደሚከናወን ገልፀዋል። በስኮትላንድ የሚገኙ ዳያስፖራዎች በሪል ስቴት ዘርፍ ለመሰማራት ፍቃድ ማውጣታቸውን አንስተው በጨርቃጨርቅና ፋሽን ኢንዱስትሪም ለመሳተፍ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን አስረድተዋል። ኦሪጅናል ጤፍ-ሊ የተሰኘው ከጤፍ የተሰራ የወተት አምራች ድርጅት መስራች ዮሴፍ ብርሃኔ ምርቱ አዲስ መሆኑን አንስተው ጤፍ ከኢትዮጵያ ጋር የተቆራኘ መሆኑን ለዓለም እንደሚያስተዋውቅ ተናግረዋል። ምርቱ በዩናይትድ ኪንግደም ተመራጭ እየሆነ መምጣቱን አንስተው፥ በቀጣይ ምርቱን በኢትዮጵያ ለማስተዋወቅ መታቀዱን ገልፀዋል። ይህም የሥራ ዕድልን የሚፈጥርና እሴት የተጨመረበት ምርትን ለዓለም ገበያ በማቅረብ የውጭ ምንዛሬን ማግኘት እንደሚያስችል አብራርተዋል።
በክልሉ ከ7 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ አዲስ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን መሳብ ተችሏል
Jan 16, 2026 53
ወላይታ ሶዶ፤ ጥር 8/2018(ኢዜአ)፡- በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በስድስት ወራት ውስጥ ከ7 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ፕሮጀክቶችን መሳብ እንደተቻለ የክልሉ እንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ። በኮሚሽኑ የስድስት ወራት ሥራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ላይ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ መሪሁን ፍቅሩ(ዶ/ር) በክልሉ ኢንቨስትመንትን ለማሳደግ በተደረገ ጥረት የአልሚዎች ቁጥር እያደገ መጥቷል። በከተማም ሆነ በገጠር የኢንቨስትመንት ዘርፉን ለማሳካት የፖሊሲና የአሰራር ማዕቀፎችን ከማውጣት ባለፈ ለኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ድጋፍና ክትትል መደረጉን አንስተዋል። በተጨማሪም የኢንቨስትመንት መሬት ወስደው ለረምጅም ዓመታት ሳያለሙ በቆዩ ፕሮጀክቶች ላይ የሚወሰደው እርምጃ እየተጠናከረ መምጣቱን ተናግረዋል። ለፕሮጀክቶች ከብድር አቅርቦት ጋር በተያያዘ የተስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል። የክልሉ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር አጸደ አይዛ በበኩላቸው ባለፉት 6 ወራት ምቹ የኢንቨስትመንት አካባቢ ለመፍጠር በተሰራው ሥራ የአልሚዎች ተሳትፎ እየጨመረ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ 7 ነጥብ 62 ቢሊየን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ 194 አዳዲስ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን ለመሳብ መቻሉን ጠቁመዋል። ከእነዚህ ውስጥ 109ኙ በኢንቨስትመንት ፈቃዳቸው መሰረት ወደ ሥራ እንደገቡና ለ20 ሺህ ዜጎች ጊዜያዊ እና ቋሚ የሥራ ዕድል መፍጠራቸውን ጠቅሰዋል። ፈቃድ ወስደው ሥራ ባልጀመሩ 49 ፕሮጀክቶች ላይ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ፤ የ13 ፕሮጀክቶች ደግሞ ፈቃድና ውላቸው እንዲሰረዝ መደረጉን እንዲሁም በሌሎች 19 ፕሮጀክቶች ላይ የተለያዩ እርምጃዎች ተወስደዋል ብለዋል። በዚህም ከ13 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ ወደ መሬት ባንክ እንዲገባ መደረጉን ኮሚሽነሯ አመልክተዋል። የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴውን ለማሳካት የህግ ማዕቀፎችንና መመሪያዎችን በማዘጋጀት ዘርፉን በአግባቡ ለመምራት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል። ክልሉ ያለውን የኢንቨስትመንት አቅም በማስተዋወቅ የህዝቡን ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ የሚደረገው ቅንጅታዊ ሥራም ይጠናከራል ብለዋል።
የአውሮፓ ህብረት ከኢትዮጵያ ጋር በተለያዩ ዘርፎች የሚያደርገውን ትብብር አጠናክሮ ይቀጥላል
Jan 16, 2026 70
አዲስ አበባ፤ ጥር 8/2018(ኢዜአ)፡- የአውሮፓ ህብረት ከኢትዮጵያ ጋር በተለያዩ ዘርፎች የሚያደርገውን ትብብር አጠናክሮ እንደሚቀጥል በአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ አገልግሎት የፖለቲካ ጉዳዮች ምክትል ዋና ፀሐፊ ኦሎፍ ስኩግ ገለጹ። የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ በአውሮፓ የውጭ ጉዳይ አገልግሎት የፖለቲካ ጉዳዮች ምክትል ዋና ፀሐፊ ኦሎፍ ስኩግ ጋር ትናንት ተወያይተዋል። ምክትል ዋና ፀሐፊው ከኢዜአ ጋር ቆይታ ባደረጉት ቆይታ፥ ከፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ ጋር በአውሮፓ ህብረት እና በኢትዮጵያ መካከል ስላለው ግንኙነት ገንቢ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል። የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን ገልጸው፤ በቀጣይም በንግድ እና ኢንቨስትመንት ዘርፎች በትብብር እንደሚሰራ ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ሽግግር በዘላቂ የልማት ግቦች እያደረገች ያለውን ውጤታማ ጥረት በመደገፍ የበኩሉን አስተዋጽኦ ያደርጋል ብለዋል። ህብረቱ ከሀገራት ጋር ያለውን የሁለትዮሽ የኢኮኖሚና የልማት ትብብር ከማጠናከር ባለፈ ቀጣናዊ ትስስርን የሚያበረታታ ግሎባል ጌትዌይ የተሰኘ ኢኒሼቲቭ እየተገበረ መሆኑንም ገልጸዋል።
በድሬደዋ አስተዳደር በግማሽ በጀት አመት ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቧል
Jan 16, 2026 49
ድሬደዋ፣ ጥር 8/2018(ኢዜአ)፡- በድሬደዋ አስተዳደር ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ያህል ገቢ አሟጦ ለመሰብሰብ እየተከናወነ የሚገኘው ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን የአስተዳደሩ ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልሰላም መሐመድ ተናገሩ፡፡ የድሬደዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልሰላም መሐመድ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን እንደገለፁት፤ ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በተከናወኑ የቴክኖሎጂና የዘመናዊ አሠራር ሪፎርሞች በአስተዳደሩ ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ያህል ገቢ ለመሰብሰብ እያስቻለ ይገኛል። ከለውጡ በፊት ይሰበሰብ የነበረው የአስተዳደሩ ዓመታዊ ገቢ ከአንድ ቢሊዮን ብር እንደማይበልጥ ጠቅሰው ከለውጡ በኋላ ገቢው ከስድስት ቢሊዮን ብር በላይ ማደጉን ገልጸዋል ። ለአብነትም በዘንድሮ ግማሽ በጀት አመት ብቻ ከቀጥታና ቀጥታ ካልሆኑ ታክሶች፤ ታክስ ካልሆነ ገቢዎችና ከማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ከአራት ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አንስተዋል። የተገኘው ገቢ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃጸር የ39 በመቶ ወይም ከ1 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር በላይ ብልጫ እንዳለው አንስተዋል። ገቢን አሟጦ የመሰብሰቡ ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን ጠቅሰው ይሄም በአስተዳደሩ የሚገኘውን ማህበረሰብ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በተገቢው መንገድ ለመመለሰ እያስቻለ መሆኑን ገልፀዋል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
የግብርና ምርምር ውጤቶች የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የጎላ ሚና እያበረከቱ ነው
Jan 16, 2026 29
አዲስ አበባ፤ ጥር 8/2018(ኢዜአ)፦ በምርምር የታገዙ ቴክኖሎጂዎችን ለአርሶ አደሩ በማቅረብ በግብርናው ዘርፍ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ እንዲሁም የምግብና ሥርዓተ-ምግብ ሁኔታን ማሻሻል መቻሉን የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት አስታወቀ። በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ (ፎረም) ተካሂዷል። የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ንጉሴ ደቻሳ (ፕ/ር) እንደገለጹት፤ ተቋሙ የምርት ማነቆ የሆኑ ችግሮችን በመለየት በሽታን የሚቋቋሙና ምርታማነትን የሚጨምሩ ዝርያዎችንና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን የማፍለቅና የማስተዋወቅ ሥራዎችን በስፋት እያከናወነ ይገኛል ብለዋል። ይህም ከምግብ ዋስትና ባለፈ ለኢንዱስትሪ ግብዓት የሚሆኑና ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን ለማሳደግ እንዲሁም የገቢ ምርቶችን ለመተካት አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን ጠቁመዋል። ኢንስቲትዩቱ ምርምሮችን ከሥነ-ምህዳርና ከማህበራዊ ተቀባይነት ጋር በማጣጣም የአፈር ለምነትን፣ የውኃ አጠቃቀምንና የባለሙያዎችን አቅም ማሳደግ ላይ ትኩረት ማድረጉንም ኃላፊው አብራርተዋል። በስዊዘርላንድ የበርን ዩኒቨርሲቲ ቡድን መሪ የሆኑት ዘሪሁን ታደለ (ፕ/ር)፤ በጤፍ ምርምር ዘርፍ ከኢንስቲትዩቱ ጋር በመሆን ለአርሶ አደሩ ያቀረቧቸው የተሻሻሉ ዝርያዎች በተለያዩ ሥነ-ምህዳሮች ውጤታማ መሆናቸውን ገልጸዋል። በአሜሪካ የሄልዝ ሜድና ፋርም ቢዝ ሥራ አስኪያጅ ሙሉ አየለ (ዶ/ር)፤ ግብርናውን ለማዘመን አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ያለውን ፋይዳ በመጥቀስ በኢትዮጵያ የተጀመሩ ሥራዎች መጠናከር እንዳለባቸው አመልክተዋል። በናይጄሪያ ዓለም አቀፍ የትሮፒካል ግብርና ተመራማሪ መላኩ አየለ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ በባዮቴክኖሎጂና በሥራስር ተክሎች ላይ የሚከናወኑ ምርምሮችን በኢትዮጵያ ለመተግበር ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ በኢትዮጵያ በስንዴ ምርት የታየው ስኬታማ ሥራ በሌሎችም ሰብሎች ሊደገም እንደሚገባ ጠቁመዋል። የሶር አፍሪካ ፋርም ሥራ አስኪያጅ ወጣት አንገፉ ባናታ፤ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ ከተረፈ ምርቶች የዶሮ ምግብና የተፈጥሮ የአፈር ማዳበሪያ በማምረት ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን ተናግሯል፡፡ ሌሎች ወጣቶችን በማሰልጠን ተጠቃሚ በማድረግ ላይ መሆኑን አክሏል፡፡ በመድረኩ ማጠቃለያ የግብርና ተዋናዮች በቅንጅት በመሥራትና የመረጃ ልውውጥን በማሳለጥ ለዘርፉ እመርታዊ ለውጥ እንዲመጣ መሥራት እንደሚገባ ተመላክቷል።
ማዕከሉ የኢትዮጵያና ኮሪያ ሪፐብሊክን ግንኙነት ከማጠናከር ባለፈ ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 መሳካት ጉልህ ሚና ይኖረዋል
Jan 16, 2026 56
አዲስ አበባ፤ ጥር 8/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ እና ኮሪያ ሪፐብሊክ ትብብር እውን የሆነው የኢንፎርሜሽን ተደራሽነት ማዕከል ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ መሳካት ጉልህ ሚና እንደሚኖረው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ(ዶ/ር) ገለጹ። በኢትዮጵያ የኮሪያ ሪፐብሊክ አምባሳደር ካንግ ጁንግ በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ ዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ውጤታማ እንዲሆን ኮሪያ ሪፐብሊክ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደምታደርግ አረጋግጠዋል። የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከኮሪያ ሪፐብሊክ የቴክኖሎጂና አይ ሲ ቲ ሚኒስቴር እንዲሁም ከኮሪያ ሪፐብሊክ ብሄራዊ የኢንፎርሜሽን ማህበረሰብ ኤጀንሲ ጋር በመተባበር ያቋቋመውን የኢንፎርሜሽን ተደራሽነት ማዕከል በይፋ አስመርቋል። ማዕከሉ ዲጂታል ክህሎትን የሚያሳድጉ ስልጠናዎችን መስጠት እና በኮምፒውተር ሳይንስና አይ ሲቲ ዙሪያ የሚማሩ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የተግባር ልምምድ እንዲያደርጉ እንደሚያስችልም ተመላክቷል። ማዕከሉ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ልማት ማዕከልን ያካተተ ሲሆን በዘርፉ ጥናትና ምርምር የሚያካሄዱ የደህረ ምረቃ ተማሪዎች ምርምራቸውን እንዲያካሂዱ ምቹ አውድ የፈጠረ መሆኑም ተጠቅሷል። ማዕከሉ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ያሉ ስታርታፖች የፈጠራ ሀሳባቸውን ወደ መሬት ማውረድ የሚችሉበት ድጋፍ የሚያገኙበት ሲሆን ጥናትና ምርምሮችን እንዲሁም ፈጠራን ማበረታታት ማዕከሉ ከተቋቋመባቸው ዓላማዎች መካከል ይገኙበታል። የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ(ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ በኢትዮጵያ አካታች የዲጂታል ስርዓት ለመገንባት ሀገራዊ ግብ ተይዞ እየተሰራ ነው። ግቡን ለማሳካት ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ወደ ስራ መግባቱን ጠቅሰው፥ ለስትራቴጂው ስኬት በዘርፉ የአቅም ግንባታ፣ ፈጠራና የዲጂታል ክህሎቱ ያደገ የሰው ኃይል ወሳኝ መሆኑን አመልክተዋል። ለዚህ ደግሞ በኢትዮጵያ እና ኮሪያ ሪፐብሊክ ትብብር ዛሬ ለምረቃ የበቃው ማዕከል ለዲጂታል 2030 ስትራቴጂ መሳካት የላቀ ሚና አለው ብለዋል። ማዕከሉ ኢትዮጵያና ኮሪያ ሪፐብሊክ ያላቸው ጠንካራ ትብብር መገለጫ መሆኑንም ገልጸዋል። በኢትዮጵያ የኮሪያ ሪፐብሊክ አምባሳደር ካንግ ጁንግ በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ መንግሥት የዲጂታል ኢኮኖሚ በመገንባት የዜጎችን ህይወት ለመለወጥ የጀመረው ጉዞ የሚደነቅ መሆኑን ተናግረዋል። ኮሪያ ሪፐብሊክ በዲጂታል ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ዝግጁ ናት ያሉት አምባሳደሩ በመስኩ ያለንን ልምድ ለኢትዮጵያ ለማካፈል ዝግጁ ነን ብለዋል። በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ኃብት ልማት፣ሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ቤተልሔም ላቀው(ዶ/ር) እንደገለጹት፤ በኢትዮጵያ ዲጂታል ሥርዓት ግንባታ ውስጥ በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ኃይል አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰዋል። በዚህ ረገድ የማዕከሉ ወደ ስራ መግባት የዲጂታል ክህሎቱ የዳበረ ትውልድ ለማፍራት አዎንታዊ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል። በመስኩ የሚከናወኑ ተግበራት ውጤት እንዲያመጡ በሕግ የማስደገፉ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉንም አብራርተዋል። የኮሪያ ሪፐብሊክ የብሔራዊ ኢንፎርሜሽን ማህበረሰብ ኤጀንሲ ፕሬዝዳንት ጆንግ ሱንግ ህዋንግ በበኩላቸው፤ ኤጀንሲው በተለይ ሰው ሰራሽ አስተውሎት በአፍሪካ እንዲስፋፋ የአቅም ግንባታን ጨምሮ የተለያዩ ድጋፎችን ተደራሽ ለማድረግ ወጥኖ እየተንቀሳቀሰ ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ ተመራጭ ከሆኑ የቴክኖሎጂ መዳረሻዎች መካከል አንዷ ናት ያሉት ፕሬዝዳንቱ ኤጀንሲው በዚህ ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።
በፍርድ ቤቶቹ የዲጂታል አሰራር ተግባራዊ መደረጉ መሰረታዊ የስራ ለውጥ ማምጣት አስችሏል
Jan 16, 2026 63
ሰቆጣ ፤ ጥር 8/2018 (ኢዜአ)፡-በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር በሚገኙ ፍርድ ቤቶች የዲጂታል አሰራር ተግባራዊ መደረጉ መሰረታዊ ለውጥ እንዲመጣ ማስቻሉን የአስተዳደሩ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስታውቋል። የከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት አቶ ጌታነህ ጥጋቡ ለኢዜአ እንደገለፁት፤ ፍርድ ቤቶች ካሁን ቀደም የነበራቸው አሰራር በወረቀት ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት አስቸጋሪ ነበር። በፋይል የተቀመጠ የባለጉዳዮች መዝገብ ለመጥፋት፣ በዝናብና በተባይ ለመበላሸትና ለሌሎች ችግሮች ይጋለጥ እንደነበርም አውስተዋል። ዘንድሮ ከፍተኛ ፍርድ ቤቱን ጨምሮ የወረዳ ፍርድ ቤቶች የዲጂታል አሰራርን በመተግበራቸው ቀደም ሲል ይከሰት የነበረውን ችግር ሙሉ በሙሉ ማስቀረት መቻሉን ገልጸዋል። የመረጃ ልውውጡም ሆነ የውሳኔ አሰጣጡ በዲጂታል የታገዘ በመሆኑ የስራ ቅልጥፍናን፣ ፍትሃዊነትንና ተአማኒነት ያለው እንዲሆን ማስቻሉን ተናግረዋል። ቀደም ሲል ባለጉዳዮች በይግባኝ ምክንያት ወደ ደሴና ባህር ዳር በመመላለስ ያገኙ የነበረውን አገልግሎት አሁን ላይ የዲጂታል ስርአቱ ባሉበት ወረዳ ሆነው ተገቢውን ፍትህ የሚያገኙበት እድል ፈጥሯል ብለዋል። በተለይም የተዘረጋው የዲጂታል ስርዓት በድምጽ የሚሰጠውን ፍርድ ወደ ፅሁፍ በፍጥነት የሚቀይር በመሆኑ የዳኞችን ጫና ጭምር ያቃለለ መሆኑን ተናግረዋል። ፍርዱ ቤቱ የራሱ የሆነ ድረ ገፅ በማልማትም ባለጉዳዮች ከቀጠሮ ጀምሮ እስከ ፍርድ ያለውን ጉዳያቸውን ባሉበት ሆነው እንዲከታተሉና እንዲያውቁ እድል የፈጠረ ነው ብለዋል። የዋግ ኸምራ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ የወንጀል ዳኛ የሆኑት አቶ ሙሉጌታ መሰለ በበኩላቸው፤ የዲጂታል አሰራር ተግባራዊ ከተደረገ ወዲህ ፈጣን የዳኝነት አገልግሎት እንድንሰጥ አስችሏል ብለዋል። በተለይም ግልፀኝነት የተላበሰ የፍርድ ሂደት እንዲፈጠር በማስቻሉ የውሳኔ ጥራትና ተአማኒነት ላይ አበረታች ለውጥ እንዲመጣ ማስቻሉን አስረድተዋል። በወረቀት በነበረበት ወቅት የፍርድ ሂደት የድምፅ ቅጅ በእጅ እንደገና ስለሚፃፍ አንድን ጉዳይ ውሳኔ ለመስጠት እስከ ሶስት ወር ይፈጅ እንደነበር ጠቅሰው አሁን በሳምንት ውሳኔ መስጠት ተችሏል ብለዋል። በሰቆጣ ከተማ የግል ጠበቃና የህግ አማካሪ የሆኑት አቶ እዝራ ደረጀ፤ ፍርድ ቤቶች የዲጂታላይዜሽን አሰራር ስርዓትን መከተላቸው ፍትህን ተደራሽ ለማድረግ ትልቅ አስተዋፅኦ ያለው ነው ብለዋል። በተለይም የግል ጠበቆች ተወዳዳሪና ውጤታማ ስራ እንዲያከናውኑ ከማስቻሉም ባለፈ ደንበኞቻቸውን ካላስፈላጊ ወጭ በማላቀቅ ካሉበት ቦታ ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ማስቻሉን አስረድተዋል።
በክልሉ የሚገኙ የቴክኒክ እና ሙያ ተቋማት በቴክኖሎጂ የታገዘ የመማር ማስተማር ስራ ላይ ማተኮር ይጠበቅባቸዋል -ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን
Jan 15, 2026 162
አሶሳ፤ ጥር 7/2018(ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ የቴክኒክ እና ሙያ ተቋማት በቴክኖሎጂ የታገዘ የመማር ማስተማር ስራ ላይ ማተኮር እንዳለባቸው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ገለጹ። የአሶሳ ግብርና ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጅ ከ70 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ያስገነባው የተሻሻለ የመስኖ አውታር ቴክኖሎጂ ተመርቆ ወደ ስራ ገብቷል። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በወቅቱ እንደተናገሩት፤ የቴክኒክ እና ሙያ ተቋማት በቴክኖሎጂ የታገዘ የመማር ማስተማር ስራ በማከናወን ስራ ፈጣሪ ዜጎችን ማፍራት ላይ ማተኮር አለባቸው። የአሶሳ ግብርና ኮሌጅም በሰለጠኑበት ሙያ ብቁ የሆኑ ሰልጣኞችን ለማፍራት የጀመረውን ጥረት ማጠናከር እንዳለበት አስገንዝበዋል። ከዚህም በተጨማሪ ኮሌጁ ዘመናዊ የግብርና መካናይዜሽንን በማስፋት አርሶአደሩን ተጠቃሚ ለማድረግ እያከናወናቸው የሚገኙ የምርምር ስራዎች መቀጠል እንዳለባቸው ተናግረዋል። ኮሌጁ የሚያፈልቃቸው አዳዲስ የግብርና ቴክኖሎጂዎችም የኮሌጁን መማር ማስተማር ስራ ከማገዝ በተጨማሪ ለአርሶአደሩ ተሞክሮ እንደሚሆኑም ገልጸዋል። የአሶሳ ግብርና ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጅ ዲን አቶ ሙስጠፋ ያሲን በበኩላቸው፤ ኮሌጁ የግብርናውን ዘርፍ የሚደግፉ የሰለጠኑ ባለሙያዎችን ለማፍራት አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እያስተዋወቀ መሆኑን ተናግረዋል። ዛሬ ወደ ስራ የገባው የመስኖ አውታር የተለያዩ አትክልቶችን በማልማት ለመማር ማስተማር እና ለቴክኖሎጂ ሽግግር የሚያግዝ መሆኑን አንስተዋል። በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የኮሌጁን የሥራ እንቅስቃሴ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
ስፖርት
ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከሶስት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰበትን ድል አስመዘገበ
Jan 16, 2026 40
አዲስ አበባ፤ ጥር 8 /2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ15ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ኢትዮ ኤሌክትሪክ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን 2 ለ 1 አሸንፏል። ማምሻውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ እዮብ ገብረማርያም እና ሀሰን ሁሴን የማሸነፊያ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፏል። ቢኒያም ካሳሁን ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቸኛውን ጎል አስቆጥሯል። ከሶስት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ25 ነጥብ ደረጃውን ከአምስተኛ ወደ አራተኛ ከፍ አድርጓል። በውድድር ዓመቱ አራተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ17 ነጥብ ከነበረበት 12ኛ ደረጃ ወደ 13ኛ ዝቅ ብሏል።
ሀዲያ ሆሳዕና ወደ አሸናፊነት ተመልሷል
Jan 16, 2026 54
አዲስ አበባ፤ ጥር 8 /2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ15ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ሀዲያ ሆሳዕና ምድረገነት ሽሬን 3 ለ 1 አሸንፏል። በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኤልያስ አሕመድ እና ሱራፌል ተመስገን በጨዋታ፣ ብሩክ በየነ በፍጹም ቅጣት ምት የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል። ተካልኝ ደጀኔ ለምድረገነት ሽሬ ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል። ከሁለት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ሀዲያ ሆሳዕና በ20 ነጥብ ደረጃውን ከ15ኛ ወደ 9ኛ ከፍ አድርጓል። በሊጉ አምስተኛ ድሉንም አስመዝግቧል። በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ስድስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ምድረገነት ሽሬ በ17 ነጥብ ከነበረበት 13ኛ ደረጃ ወደ 14ኛ ዝቅ ብሏል።
ነጌሌ አርሲ እና ወላይታ ድቻ አቻ ተለያዩ
Jan 16, 2026 54
አዲስ አበባ፤ ጥር 8/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ15ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ነገሌ አርሲ እና ወላይታ ድቻ አንድ አቻ ተለያይተዋል። በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ገ/መስቀል ዱባለ በ83ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ግብ ነገሌ አርሲ መሪ ሆኗል። ሸገር ከተማ እና ፋሲል ከነማ ነጥብ ተጋሩ በፕሪሚየር ሊጉ ነጌሌ አርሲ ከወላይታ ድቻ ሸገር ከተማ ከፋሲል ከነማ የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ይጠበቃሉ ካርሎስ ዳምጠው በ94ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት ያስቆጠረው ግብ ለወላይታ ድቻ አንድ ነጥብ አስገኝቷል። ውጤቱን ተከትሎም አዲስ አዳጊው ነገሌ አርሲ በ26 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል። ከሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነትም ወደ አንድ ዝቅ የማድረግ ዕድል ሳይጠቀምበት ቀርቷል። በሊጉ አምስተኛ ተከታታይ ድሉን የማስመዝገብ ሙከራውም አልተሳካም። ወላይታ ድቻ በ13 ነጥብ 17ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኝ ሲሆን፤ ቡድኑ ባለፉት አራት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም።
ሸገር ከተማ እና ፋሲል ከነማ ነጥብ ተጋሩ
Jan 16, 2026 57
አዲስ አበባ፤ ጥር 8/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ15ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ሸገር ከተማ እና ፋሲል ከነማ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል። በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የፋሲል ከነማው የአማካይ ተጫዋች አቤኔዘር ዮሐንስ በ72ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል። ውጤቱን ተከትሎ ሸገር ከተማ በ15 ነጥብ 16ኛ ደረጃን ይዟል። ቡድኑ ባለፉት ስድስት የሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም። ፋሲል ከነማ በ26 ነጥብ ደረጃውን ከሶስተኛ ወደ ሁለተኛ ከፍ አድርጓል። ከሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነትም ወደ አንድ ዝቅ የማድረግ እድል ሳይጠቀምበት ቀርቷል።
አካባቢ ጥበቃ
በብሔረሰብ አሥተዳደሩ በሞዴል መንደሮች የገጠር ኮሪደር ልማት ሥራ ይከናወናል
Jan 16, 2026 54
ሰቆጣ፤ ጥር 8/2018 (ኢዜአ)፡- የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር በሰባት ሞዴል መንደሮች የገጠር ኮሪደር ልማት ሥራ ለማከናወን ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አስታወቀ። በአሥተዳደሩ የገጠር ኮሪደር ልማትን ለማሳካት ያለመ የንቅናቄ መድረክ ዛሬ በሰቆጣ ከተማ ተካሂዷል። የብሔረሰብ አሥተዳደሩ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የመንገድ መምሪያ ኃላፊ ፀጋው እሸቴ በዚሁ ወቅት፤ ከዚህ ወር መጨረሻ ጀምሮ ወደ ተግባር የሚገባው የገጠር ኮሪደር ልማት በሕዝብ ተሳትፎ ታጅቦ ይከናወናል ብለዋል። በሁሉም ወረዳዎች ሰባት ሞዴል መንደሮችን በመለየት የገጠር ኮሪደር ልማት እንደሚከናወን የገለጹት ደግሞ የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ግብርና መምሪያ ኃላፊ አዲስ ወልዴ ናቸው። በገጠር ኮሪደር ልማት ቅንጅታዊ አሠራርን በመከተል የአርሶ አደሩን ኑሮ ለማሻሻል እንደሚሠራ ጠቁመዋል።
በአስተዳደሩ የተከናወነው የተፋሰስ ልማት ስራ አርሶ አደሮች ከተረጂነት እንዲወጡ አስችሏል
Jan 16, 2026 57
ድሬዳዋ፤ ጥር 8/2018 (ኢዜአ)፡-በድሬዳዋ አስተዳደር ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ የተፋሰስ ልማት ሥራዎች ከተረጂነት ለመውጣት እንዳስቻላቸው አርሶአደሮች ተናገሩ። በተፋሰሱ እና በሌሎች የገጠር ልማቶች በተከናወነው ስራ በመታገዝ ዘንድሮ ከ38 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች ከተረጂነት ወደ አምራችነት እንደሚሸጋገሩ አስተዳደሩ አስታውቋል ። ባለፉት ዓመታት የተሰሩት ልማቶች የተፈጥሮ ሃብት ይዞታን በመመለስ፣ የጎርፍ ችግርን በመከላከልና ምንጮችን በመመለስ ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ማስቻሉን ዘንድሮ በተጀመረው የተፋሰስ ልማት እየተሳተፉ የሚገኙ አርሶአደሮች ለኢዜአ ገልጸዋል። ከአርሶ አደሮቹ መካከል የገንደ ሪጌ ቀበሌ ነዋሪ አቶ ሱልጣን ፈጃል እንደገለፁት፤ ተፋሰሱ ተጨማሪ የእርሻ መሬትና ውሃን እንዲጠቀሙ በማስቻሉ በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ተሰማርተው ህይወታቸውን ለመለወጥ አስችሏቸዋል። ቀደም ብለው ዓልምተው የነበረው ብርቱካን ባለፈው ሳምንት ተሰብስቦ ከ900 ሺህ ብር በላይ ገቢ ማግኘታቸውን እንደአብነት አንስተዋል። ከብርቱካን በተጨማሪ ሽንኩርት፣ ሃባብና ሎሚ እያመረቱ ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል። .የኡሉል ሞጆ ቀበሌ አርሶአደር ወይዘሮ ሐሊማ መሐመድ በበኩላቸው፣የተፋሰስ ልማቱ ለግብርና ስራ ምቹ ሁኔታ በመፍጠሩ አርሶአደሩ በምንጭና በዝናብ ውሃ በዓመት ከሁለት ጊዜ በላይ እያመረተ መሆኑን ተናግረዋል። ይሄን የመሰለ የተፈጥሮ ፀጋና ጉልበት እያለን ለልመና እጅ አንዘረጋም ያሉት አርሶአደር ሐሊማ፤ ከራሳችን አልፈን ለተቸገሩ ለመርዳት ጠንክረን እየሰራን እንገኛለን ብለዋል። በተፋሰስ ልማትና በሌማት ትሩፋት በተፈጠሩላቸው እድሎችና ድጋፎች በመታገዝ ከተረጂነት ወደ አምራችነት በመሸጋገር ከልማታዊ ሴፍትኔት መውጣታቸውን የገለፁት ደግሞ ሌላው የኡሉል ሞጆ ቀበሌ አርሶአደር ኡስማን መሐመድ ናቸው። የቀበሌው ህብረተሰብ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት የመሸጋገርን መርህ ለማሳካት በተፋሰስ ልማትንም ሆነ በሌሎች ስራዎች እየተጋ መሆኑን አንስተዋል። የድሬዳዋ አስተዳደር ግብርና፣ ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ኑረዲን አብደላ፤ ባለፉት ዓመታት በድሬዳዋ የገጠር ቀበሌዎች በሚገኙ 57 ሺህ ሄክታር የተራቆቱ ተፋሰሶች ላይ የተለያዩ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል። በተከናወኑት ተግባራት ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ በአነስተኛ መስኖ ልማት በመሰማራት አበረታች ውጤት መገኘቱን የገንደ ሪጌ ገጠርን በአብነት ጠቅሰው አስረድተዋል። እንደ ኃላፊው አቶ ኑረዲን ገለፃ እየተከናወኑ የሚገኙ አበረታች የገጠር ልማቶች ከተረጂነት ወደ አምራችነት የመሸጋገሩን ጉዞ ስኬታማ ያደርጉታል። በዘንድሮ በጀት አመት 38 ሺህ በልማታዊ ሴፍትኔት የታቀፉ አርሶአደሮችና አርብቶአደሮች ወደ አምራችነት ይሸጋገራሉ ብለዋል።
በዞኑ የተቀናጀ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ በ631 ተፋሰሶች ላይ እየተካሄደ ነው
Jan 16, 2026 56
ወልዲያ ፤ ጥር 8/2018 (ኢዜአ)፡-በሰሜን ወሎ ዞን የተቀናጀ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ በ631 ተፋሰሶች ላይ እየተካሄደ መሆኑን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ። በመምሪያው የተፈጥሮ ሃብት ባለሙያ አቶ ጋሻው አለሙ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ባለፉት አመታት የተከናወነው የተቀናጀ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ ደርቀው የነበሩ ምንጮች እንደገና በመፍለቃቸውና የከርሰ ምድርና ገጸ-ምድር የውሃ አቅም በመጨመሩ አርሶ አደሩ በስራው በንቃት እንዲሳተፍ አድርጓል። የተቀናጀ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎች የአፈር ለምነትን በማሳደጉና የውሀ አማራጮች መስፋታቸው ለመስኖ ልማት ስራው ስኬት ተጨማሪ አቅም መፍጠራቸውን ገልጸዋል። ስራዎቹ ተራቁተው የነበሩ ተራሮችን ወደ ልምላሜ በመመለሳቸው አርሶ አደሩ በመኖ ልማትና በንብ ማነብ ስራ በመሰማራት ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት እንዳስቻለው ተናግረዋል። በዘንድሮው የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ 380 ሺህ 493 አርሶ አደሮች 631 ተፋሰሶችን እያለሙ መሆኑን አስረድተዋል። በዘንድሮው የአፈርና ውሃ እቀባ ልማት ስራም 443 ሺህ 77 ሄክታር መሬት ላይ የማሳና የተራራ ላይ እርከንና ሌሎች ስነ አካላዊ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኝ ገልጸዋል። በዞኑ የመቄት ወረዳ የ029 ቀበሌ ነዋሪ አቶ አባቡ ዋለልኝ፣ ባለፉት ዓመታት ከተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራ ያገኘናቸውን ጥቅሞች ዘንድሮም ለማስቀጠል በትጋት እየሠራን ነው ብለዋል። ባለፉት ዓመታት የተፈጥሮ ሃብት ልማት ስራዎች አካባቢዎች አገግመው ለእንስሳት መኖ፣ ንብ ማነብና ሌሎች ስራዎች ጥቅም በመስጠታቸው ዘንድሮ በራሳቸው ተነሳሽነት ለስራ መውጣታቸውን ተናግረዋል። ባለፉት አምስትና ስድስት ዓመታት ባከናወኗቸው የተፈጥሮ ሃብት ልማት ስራዎች ዘርፈ-ብዙ ጥቅሞችን አግኝተንበታል ያሉን ደግሞ በላስታ ወረዳ የጠልፈጢት ቀበሌ ነዋሪ አቶ ታደሰ ዳምጤ ናቸው። በዚህም በጓሮአቸው በአነስተኛ መስኖ አትክልት በማልማት፣ መኖ በማጨድ በእንስሳት እርባታና ማድለብ ስራ በመሰማራት ተጨማሪ ሃብት ለማፍራት እንዳስቻላቸው አስረድተዋል። በዞኑ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተሰራው የተፈጥሮ ሃብት ልማት ስራ የዞኑን የደን ሽፋን ከ20 በመቶ በላይ ማድረሱን ከመምሪያው የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
በአካባቢ ጥበቃ ልማት የተሠሩ ሥራዎች ጤናማ ትውልድ ለማፍራት ከፍተኛ ፋይዳ አላቸው
Jan 16, 2026 60
አዲስ አበባ፤ ጥር 8/2018 (ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ በአካባቢ ጥበቃና አረንጓዴ ልማት የተሠሩ ሥራዎች ጤናማ ትውልድ ለማፍራት የጎላ ፋይዳ እንዳላቸው በዓለም አቀፍ የጤና ተቋማት የሚሠሩ የጤና ባለሙያዎች ገለጹ። የኢትዮጵያ የሕጻናት ሄማቶሎጂና ኦንኮሎጂ ማኅበር የምሥረታ መርሐ-ግብር በአዲስ አበባ ተካሂዷል። በመርሐ-ግብሩ የተሳተፉ የጤና ባለሙያዎች ለኢዜአ እንዳሉት፤ በኢትዮጵያ የተከናወኑ የአካባቢ ጥበቃና የአረንጓዴ ልማት ሥራዎች ጤናን ለመጠበቅ፣ ለስፖርታዊ እንቅስቃሴ እና ለማኅበራዊ ግንኙነቶች ያላቸው ፋይዳ ከፍተኛ ነው። በአውስትራሊያ የጤና ባለሙያ የሆኑት ብሮንዊን ማክናማራ (ዶ/ር) በአዲስ አበባ ከተማ በአካባቢ ንጽህና፣ አረንጓዴ ቦታዎችና ፓርኮችን በማስፋፋት ረገድ ከዚህ ቀደም ከሚያውቁት የተለየ ለውጥ ማየታቸውን ተናግረዋል። የፕላስቲክና የኬሚካል ውጤቶች የጤና ጉዳት የሚያስከትሉ በመሆኑ ብክለትን ለመከላከል እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችንም አድንቀዋል። የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች ለጤና አጠባበቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ያስረዱት ደግሞ የቶሮንቶ ዩንቨርሲቲ ፕሮፌሰር ሺላ ዋይትዝማን ናቸው። አረንጓዴና ንጹህ አካባቢ ጤናን ለመጠበቅ ከሚያስችሉ ጉዳዮች አንዱ መሆኑን ገልጸው፤ በሽታን አስቀድሞ መከላከል ከማከም የተሻለ ነው ብለዋል። በ’ፒውር ኧርዝ’ የምሥራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ፍሬው ከፍያለው በአካባቢ ጥበቃ ተሟጋችነትና ወጣቶችን በማሳተፍ የጽዳት ሥራዎች ላይ ለበርካታ ዓመታት እየሠሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የአፍሪካ ህብረት እና ጃፓን ትብብራቸውን ለማጽናት ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ
Jan 14, 2026 109
አዲስ አበባ፤ ጥር 6/2018(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ህብረት እና ጃፓን በባለብዙ ወገን መድረኮች ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር እንደሚሰሩ አስታወቁ። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ከጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አያኖ ኩኒሚትሱ ጋር በህብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ተወያይተዋል። የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር የአፍሪካ ህብረት እና ጃፓን ከሶስት አስርት ዓመታት በላይ ያስቆጠረ ትብብር እንዳላቸው አውስተው በጃፓን አፍሪካ ልማት ዓለም አቀፍ ፎረም (ቲካድ) ማዕቀፍ ያላቸውን ግንኙነት አንስተዋል። በዮካሃማ በነሃሔ ወር 2017 ዓ.ም የተካሄደው ዘጠነኛው የጃፓን አፍሪካ ልማት ዓለም አቀፍ ፎረም(ቲካድ) በሁለቱ ወገኖች አጋርነት ውስጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው መሆኑን አመልክተዋል። ውይይቱ የሁለትዮሽ ትብብሩን የበለጠ ማጠናከርን ያለመ ነው። ጃፓን ለአፍሪካ የበሽታ መከላከል እና መቆጣጠር ማዕከል (African CDC) እያደረገች ያለው ድጋፍ እንዲሁም የአፍሪካ ዘላቂ እድገት እና ትስስር ለሚደግፉ የመሰረተ ልማት ስራዎች እያፈሰሰች ያለው መዋዕለ ንዋይ እያደገ መምጣቱ ተመላክቷል። የጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አያኖ ኩኒሚትሱ ዘጠነኛው የጃፓን አፍሪካ ልማት ዓለም አቀፍ ፎረም (ቲካድ) በስኬት መካሄዱን አድንቀዋል። 10ኛው ቲካድ በአፍሪካ እንዲካሄድ ጃፓን ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ጋር በቅርበት ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗን አመልክተዋል። ሀገራቸው የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና (AfCFTA) እና የአፍሪካ የመሠረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም (ፒዳ) ጨምሮ የአፍሪካ ህብረት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ቁልፍ ኢኒሼቲቮች መደገፏን እንደምትቀጥል ገልጸዋል። በሌላ በኩል ሚኒስትር ዴኤታዋ በዓለም አስተዳደር ውስጥ እያደገ የመጣውን የአፍሪካ ሚና በማንሳት የአፍሪካ ህብረት በቡድን 20 ቋሚ አባል መሆኗ ትልቅ ሽግግር መሆኑን ተነግረዋል። ባለስልጣናቱ በአፍሪካ ህብረት እና ጃፓን የከፍተኛ ደረጃ የምክክር መድረክ እና ቲካድ አማካኝነት ትብብራቸውን የበለጠ ለማጠናከር እና የባለብዙወገን ዲፕሎማሲ እንዲጸና በጋራ እንደሚሰሩ መግለጻቸውን ኢዜአ ከህብረቱ ያገኘው መረጃ ያመለክታል። የአፍሪካ ህብረት እና ጃፓን እ.አ.አ በ1993 አጋርነት መመስረታቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ። ሰላም እና ደህንነት፣ ኢኮኖሚ፣ ልማት፣ ንግድ፣ ጤና ፣ ግብርና፣ ቴክኖሎጂ እና የአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ከሁለቱ ወገኖች የትብብር መስኮች መካከል ይጠቀሳሉ።
ውኃ ለአፍሪካ የኅልውና ጉዳይ ነው - መሐሙድ አሊ ዩሱፍ
Jan 12, 2026 199
አዲስ አበባ፤ ጥር 4/2018 (ኢዜአ)፦ ውኃ ሁሉንም ዘርፍ የሚነካ አህጉራዊ የኅልውና ጉዳይ መሆኑን የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። 51ኛው የአፍሪካ ሕብረት የቋሚ ተወካዮች ኮሚቴ (PRC) መደበኛ ስብሰባ ከዛሬ ጀምሮ የሕብረቱ ዋና መቀመጫ በሆነችው አዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል። ስብሰባው"ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ስርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል የአፍሪካ ሕብረት ባዘጋጀው የ2026 መሪ ሐሳብ የሚደረግ ነው። በስብሰባው ላይ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ፣ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ መንበር አምባሳደር ሳልማ ማሊካ ሃዳዲ፣ የአፍሪካ ሕብረትና የሕብረቱ ተቋማት አመራሮች፣ የሕብረቱ አባል ሀገራት አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ተሳትፈዋል። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ የዘንድሮው የአፍሪካ ሕብረት ትኩረቱን ያደረገው በውኃ ላይ መሆኑን ገልጸዋል። ውኃ በሁሉም አይነት እጅጉን ወሳኝ የሆነ ሀብት እና የኅልውና ጉዳይ መሆኑን ገልጸው፤ አህጉራዊ ግቦቹን ለማሳካት ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት አስገንዝበዋል። በብራዚል ቤለም የተካሄደው 30ኛው የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 30) ትኩረት ከተሰጣቸው አጀንዳዎች መካከል አንዱ መሆኑንም አመልክተዋል። ኢትዮጵያ በምታዘጋጀው 32ኛው የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 32) ውኃ አንዱ አጀንዳ እንደሚሆንም ተናግረዋል። ሊቀ መንበሩ ኢትዮጵያ ኮፕ 32ን ለማዘጋጀት በመመረጧ በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ ያሉ ሲሆን፤ ለጉባኤው ስኬታማነት ሕብረቱ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል። በሌላ በኩል ሰላም እና ደኅንነት የአፍሪካ አንገብጋቢ አጀንዳ መሆኑን የገለጹት ሊቀ መንበሩ ሱዳን፣ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ሊቢያን በማሳያነት ጠቅሰዋል። ኢ-ሕገመንግሥታዊ ለውጦች አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሳቸውን ጠቅሰው፤ ሀገራት ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን እንዲያከብሩ አሳስበዋል። የአፍሪካ ሕብረት ተቋማዊ ሪፎርም እና ኢኮኖሚያዊ ትሥሥርን ጨምሮ ለአህጉራዊ አጀንዳዎች እየሠራ እንደሚገኝም አስታውቀዋል። አህጉራችን ፈተናዎች ቢኖሩባትም በጋራ ከቆምን እናልፋቸዋለን ሲሉም በአጽንኦት ገልጸዋል። የዛሬው ስብስባ የካቲት 4 እና 5 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚካሄደው 48ኛው የአፍሪካ ሕብረት የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ እንዲሁም የካቲት 7 እና 8 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚከናወነው 39ኛው የሕብረቱ የመሪዎች ጉባኤ የሚቀርቡ ረቂቅ አጀንዳዎች ላይ ይወያያል ተብሎ ይጠበቃል። 51ኛው የአፍሪካ ሕብረት የቋሚ ተወካዮች ኮሚቴ ስብሰባ እስከ ጥር 22 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን፤ የኮሚቴው መደበኛ ስብስባ ለዋናው ጉባኤ እንደ ይፋዊ የዝግጅት ስብስባ የሚያገለግል ነው። የአፍሪካ ሕብረት የቋሚ ተወካዮች ኮሚቴ የሕብረቱን ቋሚ ተወካዮችና የአባል ሀገራቱን አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ያቀፈ መሆኑ ይታወቃል።
51ኛው የአፍሪካ ሕብረት የቋሚ ተወካዮች ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ ዛሬ ይጀመራል
Jan 12, 2026 236
አዲስ አበባ፤ ጥር 4/2018 (ኢዜአ)፦ 51ኛው የአፍሪካ ሕብረት የቋሚ ተወካዮች ኮሚቴ (PRC) መደበኛ ስብሰባ ከዛሬ ጀምሮ የህብረቱ ዋና መቀመጫ በሆነችው አዲስ አበባ መካሄድ ይጀምራል። ስብሰባው "ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ስርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል የአፍሪካ ህብረት ባዘጋጀው የ2026 መሪ ሃሳብ የሚደረግ ነው። የዘንድሮው መሪ ሀሳብ ጭብጥ በአፍሪካ የውሃ ደህንነትና ንጽህና አጠባበቅ ላይ ትኩረቱን አድርጓል። በስብሰባው ላይ የአፍሪካ ሕብረትና የሕብረቱ ተቋማት አመራሮች፣የሕብረቱ አባል አገራት አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች እንደሚሳተፉበት ኢዜአ ከህብረቱ ያገኘው መረጃ ያመለክታል። ስብስባው የካቲት 4 እና 5 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚካሄደው 48ኛው የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ እንዲሁም የካቲት 7 እና 8 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚከናወነው 39ኛው የሕብረቱ የመሪዎች ጉባኤ የሚቀርቡ ረቂቅ አጀንዳዎች ላይ ይወያያል ተብሎ ይጠበቃል። በተጨማሪም ኮሚቴው በአፍሪካ ሕብረት ስር የሚገኙ የተለያዩ ተቋማትን የአፈጻጸም እንዲሁም ሕብረቱ እ.አ.አ በ2025 ያካሄዳቸውን ስብሰባዎች የተመለከቱ ሪፖርቶችን ያደምጣል። ሰላም እና ደህንነት፣ የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣናን ጨምሮ የኢኮኖሚ ትስስር፣ የተቋማዊ ሪፎርሞች እና የበጀት እቅዶችን የተመለከቱ የቴክኒክ ሰነዶችንም ያዘጋጃል። ኮሚቴው በ2026 የአፍሪካ ህብረት መሪ ሀሳብ ላይ ምክረ ሀሳቦችን ያቀርባል ተብሎ ይጠበቃል። 51ኛው የአፍሪካ ሕብረት የቋሚ ተወካዮች ኮሚቴ ስብሰባ እስከ ጥር 22 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል። የኮሚቴው መደበኛ ስብስባ ለዋናው ጉባኤ እንደ ይፋዊ የዝግጅት ስብስባ የሚያገለግል ነው። የአፍሪካ ሕብረት የቋሚ ተወካዮች ኮሚቴ የሕብረቱን ቋሚ ተወካዮችና የአባል አገራቱን አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ያቀፈ ነው።
የቻይና አፍሪካ ትብብር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቷል
Jan 8, 2026 209
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 30/2018(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ማሕሙድ አሊ ዩሱፍ ከቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ጋር ውይይት አካሄዱ። ውይይቱ እያደገ የመጣው የቻይና አፍሪካ ትብብርን ማጠናከር ላይ ያለመ ነው ተብሏል። ቻይና የአፍሪካ እውነተኛ አጋር መሆኗን የገለፁት የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፤ በጋራ ተጠቃሚነት ላይ ያተኮረው ፖሊሲ ጠንካራ ወዳጅነት እንዲፈጠር ማድረጉን ገልፀዋል። የቻይና አፍሪካ ግንኙነት በተለያዩ የትብብር ማዕቀፎች እያደገ መምጣቱንም ተናግረዋል። ከውይይቱ በኋላ ባወጡት የጋራ መግለጫ፤ ሁለቱ ወገኖች የዓለም ደቡባዊ ቀጣና (Global South) ሀገራትን መብትና ጥቅም ለማስከበር፣ የሉዓላዊነትን ክብር ለመጠበቅ እና ዓለም አቀፍ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት በጋራ ለመሥራት መስማታቸውን አስታውቀዋል። በውይይቱ ወቅት የቻይናን የአምስት ዓመት የልማት ዕቅድ ከአፍሪካ ኅብረት የ2063 አጀንዳ ሁለተኛው የዐሥር ዓመት ትግበራ ጋር በማጣጣም ዘመናዊነትን ለማምጣት በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ምክክር መደረጉ ተገልጿል። በዚሁ መሠረት የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና (AfCFTA) ስምምነቶችን ጨምሮ፣ ቻይና ያቀረበቻቸውን ዓለም አቀፍ የደኅንነትና የልማት ተነሳሽነቶች በጋራ ለመደገፍ ከስምምነት መድረሳቸውን ኢቢሲ ዘግቧል። በተጨማሪም የተፈረሙ የትብብር ስምምነቶችን በተግባር በመተርጎም እና የንግድ ልውውጥን በማሳደግ ያላቸውን ቁርጠኝነት በጋራ መግለጫቸው አረጋግጠዋል።
ሐተታዎች
እኩል አጋርነትን መፍጠር፤ አዲሱ የአፍሪካ እና ጣልያን የትብብር ምዕራፍ
Dec 30, 2025 565
የአፍሪካ እና ጣልያን ግንኙነት የጀመረው በ19ኛው ክፍለ ዘመን ማብቂያ ላይ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ። ጣልያን እ.አ.አ በ1947 የተፈራረመቻቸው የሰላም ስምምነቶች ቅኝት ግዛት እና የአንድ አካል የፖለቲካ የበላይነት እንዲያከትም አድርጓል። በድህረ ቅኝ ግዛት ዘመን ጣልያን ከአፍሪካ ጋር ያላት ግንኙነት ከቅኝ አገዛዝ የሁለትዮሽ ትስስር ወደ የኢኮኖሚ ትብብር ተሸጋግሯል። ወቅቱ አፍሪካውያን ሉዓላዊነታቸውን የበለጠ ያረጋገጡበትና ጣልያን ከአፍሪካ ጋር በአዲስ መልክ አጋርነቷን ያደሰችበት ነበር። ከቅኝ ግዛት በኋላ የአፍሪካ እና የጣልያን ትብብር በባህል መስክ ላይ ብቻ የተገደበ ነው። የንግድ እና የቴክኒክ ትብብሩ ውስን ነበር። እ.አ.አ ከ1990ዎቹ መግቢያ አንስቶ የአፍሪካ እና ጣልያን ስትራቴጂክ አጋርነት እያበበ የመጣበት ጊዜ ነበር ማለት ይቻላል። የዲፕሎማሲ ሚሲዮኖች እና የንግድ ቢሮዎች መጨመር እንዲሁም የኢኮኖሚ ትብብር አድማስ መስፋት የትብብሩ መገለጫ ሆኗል። ዘመናዊው የአፍሪካ እና ጣልያን አጋርነት ከእርዳታ ወደ የጋራ እድገት ምዕራፍ መሸጋገር ችሏል። የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲው የሁለቱን ወገኖች የንግድ እና የኢንቨስትመንት ትብብር አጠናክሯል። የልማት ትብብሩ እርዳታን ከመለገስ ወጥቶ እድገት ተኮር ሆኗል። ከደህንነት ጋር በተያያዘም የፍልሰት አስተዳደር እና ሽብርተኝነት መዋጋት አንዱ የትብብር መገለጫ ነው። የጣልያን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ የአፍሪካ እና ጣልያን የባለፈው ጊዜ የነበሩ ፈተናዎች እውቅና በመስጠት አሁን ላይ የሁለቱን ወገኖች የጋራ ፍላጎት ማስጠበቅ ላይ ትኩረቱን አድርጓል። የፖሊሲው ሰነድ “ ዋጋ እና ክብርን ማዕከል ያደረገ” ዲፕሎማሲ በሚልው እሳቤው ከአፍሪካ ጋር ላለው ወዳጅነት ከፍተኛ ግምት እንደሚሰጥ አስቀምጧል። እ.አ.አ በ2024 በሮም የተካሄደው የጣልያን-አፍሪካ ጉባኤ ላይ በቅርብ ጊዜያት ከነበሩ ከፍተኛ መድረኮች መካከል ይጠቀሳል። በጉባኤው ላይ የ45 የአፍሪካ ሀገራት ተወካዮች፣ የአፍሪካ ህብረት እና የአውሮፓ ህብረት መሪዎች፣ ዓለም አቀፍ ተቋማት እና የልማት አጋሮች ተሳትፈዋል። ጉባኤው የተካሄደበት ዓመት ጣልያን የቡድን ሰባት አባል ሀገራት ሊቀ መንበር የነበረችበት ወቅት ሲሆን ጣልያን ከአፍሪካ ጋር ያላትን ትብብር ማጠናከር የውጭ ጉዳይ ፖሊሲዋ አንኳር ትኩረት ሆኗል። የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ በወቅቱ ጉባኤውን የአፍሪካ እና ጣልያን ትብብርን በአዲስ መልክ የበየነና ትብብሩ እኩል በቆሙ ወገኖች መካከል ያለ ትስስር እንደሆነ አንስተዋል። ሜሎኒ የሰጪ እና ተቀባይ ዘመን እንዳበቃና የጋራ እድገት እና የጋራ ፍላጎት ላይ የተመረኮዘ ግንኙነት አዲሱ የትብብር ምዕራፍ እንደሆነም ተናግረዋል። በወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር የነበሩት ሙሳ ፋቂ ማህማት የጣልያንን አዲሱን የፖሊሲ ለውጥ ያደነቁ ሲሆን አፍሪካ ከቃል ባለፈ እውነተኛ አጋርነትን ትፈልጋለች ብለዋል። የፖሊሲ ሽግግሩ ፍትሃዊነትን ያረጋገጠ እና እኩልነትን መሰረት ያደረገ ዓለም መፍጠርን ያማከለ መሆን እንዳለበትም አንስተዋል። ጣልያን የገባቻቸውን ቃሎች ወደ ተግባር መቀየር አለባት ሲሉም ማህማት ተናግረው ነበር። በጉባኤው ላይ ይፋ ከተደረጉ ቁልፍ ማዕቀፎች አንዱ የማቴይ እቅድ (The Mattei Plan) ይገኝበታል። የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ይፋ ያደረጉት የማቴይ ፕላን ጣልያን ከአፍሪካ ጋር ያላት የኢኮኖሚ እና የልማት ትብብር ማጠናክርን ያለመ ነው። የ5 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዩሮ የስትራቴጂክ ማዕቀፉ በጣልያኑ የብሄራዊ የዘይት እና ነዳጅ ኩባንያ መስራች ኤነሪኮ ማቴይ የተሰየመ ነው። ኩባንያው ከአፍሪካ ጋር ከአጭር ጊዜ እርዳታ የረጅም ጊዜ የኢኮኖሚ ትብብርን በማስቀደም እየሰራ እንደሚገኝ ተመላክቷል። የአፍሪካን የኢኮኖሚ እድገት መደገፍ፣ የስራ እድሎችን ማስፋት፣ አፍሪካን የአውሮፓ የኢነርጂ አቅራቢ አጋር የማድረግ ስራን ማስተዋወቅ፣ ለአፍሪካውያን የኢኮኖሚ ችግሮች መፍትሄ በመስጠት ኢ-መደበኛ ፍልሰትን ከምንጩ ማድረቅ እንዲሁም ከበጎ አድራጎት የተላቀቀ የጋራ ተጠቃሚነት እና ትብብርን መፍጠር የእቅዱ አበይት አላማዎች ናቸው ። ለአራት ዓመታት የሚቆየው የማቴይ እቅድ በአፍሪካውያን በበጎ መልኩ የታየ ሲሆን እቅዱ ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር ጠንካራ የፖለቲካ ቁርጠኝነት እንደሚያስፈልግ ተነስቷል። እ.አ.አ በ2023 የአፍሪካ እና የጣልያን የንግድ ልውውጥ 59 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዩሮ መድረሱን ይፋዊ መረጃዎች ያመለክታሉ። የንግድ ልውውጡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቷል። የአፍሪካ ሀገራት በዋናነት የተፈጥሮ ጋዝ፣ ድፍድፍ ነዳጅ፣ የብረታ ብረት እና ማዕድናት ምርቶች እንዲሁም ለኢንዱስትሪ ምርቶች የሆኑ ጥሬ እቃዎችን ወደ ጣልያን ይልካሉ። ጣልያን የኢንዱስትሪ ማሽን እና መሳሪያ፣ እሴት የተጨመረባቸው እቃዎች እና የማኑፋክቸሪንግ ምርቶች እንዲሁም የኤሌክትሪክ እቃዎች ወደ አፍሪካ ከምትላካቸው ምርቶች መካከል ተጠቃሽ ናቸው። አጠቃላይ የንግድ ምጣኔው ሲታይ ጣልያን በገቢ አብዛኛውን ድርሻ ትይዛለች። ንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ ተፈጥሮ ሀብት፣ ኢነርጂ፣ መሰረተ ልማት፣ ትራንስፖርት፣ ትምህርት፣ ምርምር፣ ጤና፣ ቴክኖሎጂ፣ የፍልሰት አስተዳደር፣ ደህንነት እና አስተዳደር ከአፍሪካ እና ጣልያን የትብብር መስኮች መካከል ይገኙበታል። የ2026 የአፍሪካ-ጣልያን ጉባኤ በየካቲት ወር አጋማሽ 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት ዋና መቀመጫ እና የአህጉሪቷ መዲና ናት። ይህም ጉባኤውን የአፍሪካ ዋንኛ የዲፕሎማሲ አጀንዳ ያደርገዋል። ኢትዮጵያ በታሪክ በፓን አፍሪካ ፖለቲካ ውስጥ የመሪነት ሚና ያላት ሀገር ናት። በአሁኑ ሰዓትም በርካታ ቀጣናዊ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ሁነቶችን እያዘጋጀች ትገኛለች። የሁለቱን ወገኖች አጋርነት የበለጠ ያጠናክረዋል ተብሎ ይጠበቃል። የማቴይ እቅድ ትግበራ፣ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ትብብር፣ የአፍሪካን ተሰሚነት መጨመር፣ ፍልሰትን ጨምሮ በጋራ ጉዳዮች ላይ ጠንካራ አቋም መያዝ፣ የአጋርነት እና የመግባቢያ ስምምነቶች የአፍሪካ-ጣልያን ጉባኤው ውጤቶች ናቸው። የአፍሪካ-ጣልያን ጉባኤ ካለፈው ታሪካዊ ግንኙነቶች ፣ እያደገ ከመጣው የኢኮኖሚ ትብብር እና የጋራ ፈተናዎችን የመፍታት ቁርጠኝነት አኳያ በአፍሪካ እና በጣልያን መካከል አዲስ የትብብር ምዕራፍ የሚከፍት እንደሆነ ታምኖበታል። የአፍሪካ ዲፕሎማሲ ማዕከል በሆነችው አዲስ አበባ የሚደረገው ጉባኤ አፍሪካ መር አጋርነት ለመፍጠር እና የአፍሪካን ተሰማኒነት ለመጨመር መልካም አጋጣሚን የሚፈጥር ነው።
አፍሪካውያን ሀገር በቀል አሰልጣኞች ጎልተው የታዩበት የአፍሪካ ዋንጫ !
Dec 28, 2025 502
35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በሞሮኮ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ይገኛል።24 ሀገራት በስድስት ምድቦች ተከፍለው ጨዋታቸውን እያደረጉ ነው። በውድድሩ ላይ ከሚሳተፉ 24 ሀገራት 12ቱ በአፍሪካውያን የሚሰለጥኑ ናቸው። የአዘጋጇ ሀገር ሞሮኮ አሰልጣኝ ዋሊድ ሬግራጉዊ ከዛው ከሀገራቸው ናቸው። የ50 ዓመቱ አሰልጣኝ በ22ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ ሞሮኮን ለግማሽ ፍጻሜ አድርሰዋል።ሀገሪቷ በዓለም ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜ የደረሰች የመጀመሪያዋ አፍሪካዊ ሀገር ሆናለች። ከእ.አ.አ 2022 አንስቶ ብሄራዊ ቡድኑን እየመሩት የሚገኙት ሬግራጉዊ ሞሮኮን ከግማሽ ክፍለ ዘመን በኋላ የአፍሪካ ዋንጫ ባለቤት የማድረግ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል። የወቅቱ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ ኮትዲቭዋር አሰልጣኝ የ41 ዓመቱ የቀድሞ የብሄራዊ ቡድኑ ተጫዋች ኤመርሰን ፋኤ ነው። ፋኤ እ.አ.አ በ2023 በኮትዲቭዋር አስተናጋጅነት በተካሄደው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ቡድኑን በመምራት ዋንጫውን እንዲያነሳ አድርጓል። በውድድሩ መሐል በውጤት ማጣት የተሰናበቱትን ፈረንሳዊውን አሰልጣኝ ጂን-ሉዊስ ጋሴት በመተካት በጊዜያዊነት አሰልጣኝ የተሾመው ፋኤ ቡድኑን ለዋንጫ ማብቃቱ አስወድሶታል። በዘንድሮው ውድድር ዋንጫውን ለማንሳት የቅድሚያ ግምት ከተሰጣቸው ሀገራት ተርታ የተመደበችው ሴኔጋል አሰልጣኝ የ41 ዓመቱ የቀድሞ የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ፓፔ ታው ነው። ፓፔ ታው በተጫዋችነት ዘመኑ ለሴኔጋል ባደረጋቸው 16 ጨዋታዎች አምስት ግቦችን አስቆጥሯል። አሰልጣኙ ሴኔጋል ለ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ እንድታልፍ አድርጓል። ከሶስት ዓመት በፊት በአልጄሪያ በተካሄደው የሰባተኛው የአፍሪካ አገራት ሻምፒዮና(ቻን) ሴኔጋል ዋንጫውን ስታነሳ የቡድኑ አሰልጣኝ ሆኖ መርቷል። የሰባት ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊዋ ግብጽ የምትሰለጥነው በቀድሞ ኮከቧ ሆሳም ሀሰን ነው። በተጫዋችነት ዘመኑ በአፍሪካ ዋንጫ 11 ግቦችን አስቆጥሯል። በ177 ጨዋታዎች 69 ግቦችን ከመረብ ላይ በማሳረፍ የብሄራዊ ቡድኑ የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ነው። ሆሳም ሀሰን የአፍሪካ ዋንጫን ሶስት ጊዜ በተጫዋችነት በማንሳት ስኬታማ አሰልጣኝ ነው። ሌላኛው የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ካሜሮን አሰልጣኝ የ56 ዓመቱ ዴቪድ ፓጉ ነው። ካሜሮናዊው አሰልጣኝ የተሾሙት ከሰሞኑ ነው። ቤልጂየማዊውን አሰልጣኝ ማርክ ብራይስን በመተካት ቡድኑን እንዲመሩ ኃላፊነት ተጠሎባቸዋል። በካሜሮን እግር ኳስ ባላቸው የታክቲክ መረዳት እና ብቃት የሚሞካሹት ፓጉ ቡድኑን አንድ በማድረግ የተሻለ ውጤት ያመጣሉ የሚል እምነት ተጥሎባቸዋል። ሌላኛው የውድድሩ ተሳታፊ ሀገር ዛምቢያ ናት።የ48 ዓመቱ የዛምቢያ ብሄራዊ ቡድን የቀድሞ ተከላካይ ሞሰስ ሲቾኔ የቡድኑ የወቅቱ ዋና አሰልጣኝ ናቸው። ከእ.አ.አ 2022 እስከ 2024 በጊዜያዊነት እና በረዳት አሰልጣኝነት ያገለገሉት ሲቾኔ በ2025 ዋና አሰልጣኝ ሆነው ተሾመዋል። ምስራቅ አፍሪካን በውድድሩ ከሚወክሉ ሶስት ሀገራት መካከል አንዷ ሱዳና ናት። ጋናዊው ጀምስ ክዌሲ አፒያ የቡድኑ አሰልጣኝ ናቸው። አፒያ ከእ.አ.አ 2023 አንስቶ ቡድኑን እያሰለጠኑ ይገኛሉ። የጋቦን አሰልጣኝ ቲዬሪ ሞዩማ የብሄራዊ ቡድኑ የተከላካይ መስመር ተጫዋች ነበር። ለ11 ዓመታት ለጋቦን ተጫውተዋል። ከእ.አ.አ 2023 አንስቶ ብሄራዊ ቡድኑን በአሰልጣኝነት እየመሩ ይገኛል። የ44 ዓመቱ ደቡብ አፍሪካዊ ሞሬና ራሞሬቦሊ የቦትስዋና ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ናቸው። ከእ.አ.አ 2025 አንስቶ ቡድኑን እያሰለጠኑ ይገኛል። ሞሬና ከዚህ ቀደም የደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ነበሩ። የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ቡርኪናፋሶ አሰልጣኝ የቀድሞ የብሄራዊ ቡድን የአማካይ ተጫዋች ብራማ ትራኦሬ ነው። አሰልጣኙ ከእ.አ.አ ማርች 2024 አንስቶ ቡርኪናፋሶን እየመራ ይገኛል። ትራኦሬ ቡድኑ የተሻለ ውጤት እንዲያመጣ የማድረግ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል። የአንድ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ የሆነችው ቱኒዚያ አሰልጣኝ የቀድሞ የቡድኑ የተከላከይ መስመር ተጫዋች ሳሚ ትራቤልሲ ናቸው። የ57 ዓመቱ አሰልጣኝ ለቱኒዚያ ብሄራዊ ቡድን ለ10 ዓመታት በተጫዋችነት አገልግሏል። ብሄራዊ ቡድኑን ከእ.አ.አ 2025 ቱኒዚያን እየመራ ይገኛል። በአፍሪካ ደቡባዊ ክፍል የምትገኘው ሞዛምቢክ በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ከሚሳተፉ ሀገራት መካከል አንዷ ናት። ፍራንቺስኮ ኩዌሪዮል ኮንዴ ጁኒየር (ቺኩዊኒዮ ኩንዴ) የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ናቸው። የ60 ዓመቱ አንጋፋ አሰልጣኝ ለሞዛምቢክ ለ15 ዓመታት በተጫዋችነት አገልግለዋል። ለሀገራቸው በ43 ጨዋታዎች 12 ግቦችን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። ኩንዴ ከእ.አ.አ 2021 አንስቶ ብሄራዊ ቡድኑን እያሰለጠኑ ይገኛሉ። የናይጄሪያ አሰልጣኝ የሆነው ኤሪክ ቼሌ የኮትዲቭዋር፣ ማሊ እና ፈረንሳይ ጥምር ዜግነት ያላቸው አሰልጣኝ ናቸው። ይሁንና ቼሌ የአፍሪካ የዘር ግንድ ቢኖራቸውም በፈረንሳይ መወለዳቸው የውጭ ሀገር ዜጋ ውስጥ እንዲካተት አድርጎታል። የአፍሪካውያን አሰልጣኞች በአፍሪካ ዋንጫ የማሰልጠን ምጣኔ ከሌሎቹ ወቅቶች አንጻር የአሁኑ የተሻለ ነው ማለት ይቻላል። ይህም ሀገር በቀል አሰልጣኞች እየተሰጣቸው ያለውን ትኩረት ያሳያል። 12 ሀገራት በውጭ ሀገር ዜጎች ይሰለጥናሉ። በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ አፍሪካውያን የሚያሰለጥኗቸው ወይስ የውጭ ሀገር ዜጋዎች የሚመሯቸው ሀገራት ዋንጫውን ያነሳሉ? የሚለው ጉዳይ ትኩረትን ስቧል።
የኢትዮጵያ ዲጂታል ዘመን
Dec 22, 2025 723
የኢትዮጵያ ዲጂታል ዘመን የዲጂታል ቴክኖሎጂ የተጀመረው በ20ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ። በወቅቱ የኤሌክትሮኒክ መሳሪዎችን ተጥቅሞ መረጃን በመተንተን እና መረጃን እንደ ልዩ ገጽታ በመጠቀም እና መለያ ቁጥር (ኮድ) በመስጠት አገልግሎት ላይ ይውል ነበር። ከዛ ጊዜ በኋላ በርካታ የኮምፒዩተር ፕሮግራሞች እና ማሽኖች ተፈብርከው ጥቅም ላይ መዋል ጀምረዋል። እ.አ.አ በ1946 በአሜሪካ የፔንሲሊቫኒያ ዩኒቨርሲቲ ጥቅል አገልግሎት የሚሰጥ የመጀመሪያውን የኤሌክትሮኒክ ዲጂታል ኮምፒዩተር በመስራት የዲጂታል ዘመን ጅማሮን አበሰረ። ከእ.አ.አ 1943 እስከ 45 ባለው ጊዜ ውስጥ የተሰራው ይህ ኮምፒዩተር ባለቤቶች ጆን ማውችሊ እና ጄ ፕሬስፐርት ኤከርት ናቸው። በ150 ኪሎ ዋት ኃይል የሚሰራው ኮምፒዩተር በሴኮንዶች ውስጥ በርካታ ስራዎችን ያከናውን ነበር። ኮምፒውተሩ በወቅቱ በነበሩ ባለሙያዎች ማርሽ ቀያሪ እና መሰረት ጣይ የሚል ስያሜ አግኝቷል። የዘመናዊ የዲጂታል ስርዓቶች ምሰሶ ነው የሚባለው ኢንተርኔት የተጀመረው እ.አ.አ በ1960ዎቹ መጀመሪያ ነበር። “አርፓኔት” የተሰኘ የአሜሪካ የጥናት ፕሮጀክት ኮምፒዩተሮችን ዘመኑ ከደረሰበት የኔትወርክ ስርዓቶች ጋር በማገናኘት የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲጀመር ምክንያት ሆኗል። እንግሊዛዊው የኮምፒዩተር ሳይንቲስት ቲም በርነርስ ሊ እ.አ.አ 1969 “ወርልድ ዋይድ ዌብ” (WWW) በመፍጠር ትስስርን ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ አሸጋግሯል። ድረ ገጾችን በመፍጠር እና በህዝብ ደረጃ የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲሰፋ ወሳኝ ሚና ተጫውቷል። ዲጂታል ቴክኖሎጂ ከኮምፒዩተር መሰራት ተነስቶ ወደ ዓለም አቀፍ የትስስር መሰረተ ልማትነት የተቀየረ ሲሆን በየዕለት ተዕለት የሰዎች ኑሮ፣ማህበራዊ መስተጋብር፣ ንግድ እና የመንግስታት አሰራር ላይ ከፍተኛ ለውጥ ከማምጣት ባለፈ ዘርፎች በቴክኖሎጂ እንዲቃኙ አድርጓል። ዓለም ላይ አሁን ካለው ህዝብ 73 በመቶ የሚሆነው ህዝብ ኢንተርኔት ተጠቃሚ ነው። የዲጂታል ኢኮኖሚ የዓለምን ጥቅል ዓመታዊ ምርት (ጂዲፒ) የ15 በመቶ ድርሻን እንደሚያግዝ የተለያዩ ጥናቶች ያመለክታሉ። ሞባይል ለኢንተርኔት መስፋፋት የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳል። ሀገራት እ.አ.አ 2025 በሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ ክላውድ ኮምፒዩቲንግ፣ ኔትወርኪንግ እና ለሌሎች ትራንስፎርሜሽ ስራዎች ያወጡት ኢንቨስትመንት ከአራት ትሪሊዮን ዶላር በላይ እንደሚልቅም ይገመታል። በአፍሪካ የሞባይል የገንዘብ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ቁጥር ከ480 ሚሊዮን በላይ ተሻግሯል። ዲጂታል ስርዓቱን የሚያሳልጡ መሰረተ ልማቶች እና የዳታ ማዕከላት በአፍሪካ መንግስታት እና የልማት አጋሮች ትብብር እየተገነቡ ነው። ዲጂታል ኢኮኖሚ ለኢኮኖሚ እድገት፣ ለትምህርት እና ክህሎት፣ ለመንግስት የአሰራር ውጤታማት፣ ለፋይናንስ አካታችነት እና ኮሙኒኬሽን ጉልህ አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል። ኢትዮጵያ ከእ.አ.አ 2020 በፊት የዲጂታል ምህዳሯ የተገደበ ነው ማለት ይቻላል። ዝቅተኛ የኢንተርኔት አገልግሎት ተደራሽነት፣ ለቴሌኮም አገልግሎት ከፍተኛ ክፍያ ወጪ የሚወጣበት እና በቴሌኮም አገልግሎት የመንግስት ብቻ የበላይነት የሚታይበት ነበር። ከለውጡ በኋላ መንግስት የቅድሚያ ትኩረት ከሰጣቸው ዘርፎች አማካኝነት ዲጂታል ተጠቃሽ ነው። የዲጂታል ዘርፍ ከብዝሃ የኢኮኖሚ ምንጮች አንዱ ሆኖ ነው።ዲጂታላይዜሽን ለኢኮኖሚ ዕድገት ያለውን ሚና ከግምት ውስጥ በማስገባት ለሁሉም ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ ይገኛል። ኢትዮጵያ ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግ አካታች የሆነ የዲጂታላይዜሽን ስትራቴጂ በማዘጋጀት ወደ ትግበራ ካስገባች ሰነባብታለች። ኢትዮጵያ ከእ.አ.አ 2020 አንስቶ ለአምስት ዓመታት የሚቆይ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ በማዘጋጀት ስተገብር ቆይታለች። ስትራቴጂው የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ እና መንግስታዊ አገልግሎቶችን ዲጂታል የማድረግ አላማ ያደረገ ነው። በዚህም 900 ገደማ የሚሆኑ መንግስታዊ አገልግሎቶች ዲጂታላይዝድ ሆነዋል።3000 የሚሆኑ የዲጂታል አገልግሎት ሰጪዎች ፈቃድ አግኝተዋል። የፋይዳ መታወቂያ ኢኒሼቲቭ አማካኝነት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች የዲጂታል መታወቂያ ባለቤት ሆነዋል። የሞባይል እና ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች በከፍተኛ መጠን ጨምሯል። የአራተኛ እና አምስተኛው ትውልድ የኢንተርኔት አገልግሎት እየሰፋ መጥቷል።የዲጂታል ክህሎትም ተስፋ ሰጪ እድገት ታይቶበታል። የቴሌኮም ዘርፉ ለውጭ ክፍት እንዲሆን መንግስት ባስቀመጠው የፖሊሲ አቅጣጫ መሰረት ሳፋሪኮም ኩባንያ የቴሌኮም አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን “ምፔሳ” የተሰኘ የሞባይል የገንዘብ አገልግሎት እየሰጠም ይገኛል። የመንግስት የዲጂታል ፖሊሲዎች እና የህግ ማዕቀፎች ለዘርፉ ምቹ ምህዳር በመፍጠር ትስስር እንዲሰፋ እና አገልግሎቶች እንዲዘምኑ አስችሏል። ኢትዮጵያ ከአምስት በፊት የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በማቋቋም በርካታ ስራዎችን አከናውናለች። ባለፉት አራት ተከታታይ ዓመታት በክረምት መርሃ ግብር (ሰመር ካፕም) ወጣቶች ሲማሩ እንደቆዩ አውስተው በዘርፉ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ ትምህርት እየተሰጠ መሆኑን አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት መረጃ ያሳያል። ሁሉንም ዘርፍ የሚነካው አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በግብርና፣ጤና፣ አገልግሎት እና ሌሎች ዘርፎች ላይ በመግባት ስራን እያቀላጠፈ ይገኛል። በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አማካኝነት የሚሰበሰቡ ዳታዎች ለመንግስት እና ግል ተቋማት አገልግሎት ላይ እየዋሉ እንደሚገኝም ተገልጿል። መንግስት ወጣቶች በሰው ሰራሽ አስተውሎት አማካኝነት ሀገርን አልፎም ዓለምን የሚጠቅሙ ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያቀርቡ የሚያደርገውን ድጋፍ እያደረገ ይገኛል። ቴሌብር፣ መሶብ እና ዘመንን ጨምሮ ያሉ የዲጂታል አገልግሎቶች የዘርፉን እድገት በማሳለጥ ወሳኝ ሚና ተጫውተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት የዲጂታል 2030ን ስትራቴጂ ይፋ አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ የታለመለትን ግብ አሳክቶ መጠናቀቁን ገልጸዋል።ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 በይፋ ያበሰሩ ሲሆን ተደራሽነትን ማስፋት፣ለዜጎች እኩል እድል መፍጠር እንዲሁም በዜጎችና ተቋማት መካከል መተማመንን ማጎልበት ደግሞ የስትራቴጂው ቁልፍ መሰረታዊ ትልሞች መሆናቸውን አመልክተዋል። ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ተደራሽ፣ ፍትሃዊ እና አስተማማኝ የዲጂታል ምህዳር መፍጠር ላይ ትኩረት ያደረገ ነው ብለዋል።ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ም ባለፉት አምስት ዓመታት የተከናወኑ ተግባራትን መሰረት በማድረግ መዘጋጀቱን አንስተዋል። ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ሦስት ቁልፍ ትልሞች እንዳሉት የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ እነዚህም ተደራሽነትን ማስፋት፤ እኩል እድል ማመቻቸትና በተቋማትና ህዝብ መካከል መተማመንን መፍጠር መሆናቸውን አብራርተዋል። ትልሞቹ እንዲሳኩም በተለይ የህዝብ ዲጂታል መሠረተ ልማት ማስፋት ላይ ትልቅ ስራ እንደሚከናወን ጠቁመው፤ ይህም ዲጂታል ቴክኖሎጂ ሰው ተኮር ሆኖ የዜጎችን ኑሮ እንዲያሻሽል ትልቅ አቅም ይፈጥራል ብለዋል። በአጠቃላይ በዲጂታል ኢትዮጵያ የሚከናወኑ ስራዎች የመደመር መንግስት በቀለለ ቢሮክራሲ ታላላቅ ስትራቴጂዎችን እውን ለማድረግ ከያዘው ግብ ጋር የተሳሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል። ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 እንዲሳካም ሁሉም በትብብር መስራት እንዳለበት ነው ጥሪ ያቀረቡት። የዲጂታል 2030 ስትራቴጂ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ እንደገለጹት፥ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 በቴሌኮም ዘርፍ በርካታ ውጤቶች የተመዘገቡበት ነው። ለአብነትም የሞባይል ደንበኞች ቁጥርን 97 ሚሊዮን ማድረስ የተቻለ ሲሆን፣ ከዚህም ውስጥ 57 ሚሊዮኑ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ሆነዋል ሲሉ አንስተዋል። ዋና ስራ አስፈጻሚዋ አክለው እንደገለጹት፥ አንድ ሺህ ሰላሳ ከተሞችም የ4ጂ ኔትወርክ ተደራሽ ሆነዋል ነው ያሉት። በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ የሞባይል ተጠቃሚ ደንበኞች ቁጥር 128 ሚሊዮን የሚደርስ ሲሆን፣ የ5ጂ ኔትወርክ ሽፋንን 100 ከተሞች ይደርሳል ብለዋል። በ2030 የዲጂታል ክፍያን ከአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት አንጻር አሁን ካለበት ከሰባት እጥፍ በላይ እንዲያድግም በልዩ ትኩረት ይሰራል ሲሉም አረጋግጠዋል።ዲጂታል 2030 ስትራቴጂ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት፣ አካታችነት እና ማህበራዊ ለውጥ ቁልፍ ምሰሶ ነው። ስትራቴጂው በሚገባ ከተተገበረ፣ በቂ የዲጂታል መሰረተ ልማቶች ከተገነቡ እና ዜጎች በንቃት ከተሳተፉ ኢትዮጵያ በዲጂታል ዘመን ትሩፋቶች ተጠቅማ ትልሞቿን ማሳካት እንደምትችል አያጠራጥርም።
መልካምነት ይከፍላል..!!!
Dec 11, 2025 877
መልካምነት ይከፍላል...!!! በማስረሻ ሀብታሙ (ኢዜአ-ወላይታ ሶዶ ቅርንጫፍ) መልካም ስነ ምግባርና ባህሪ ከራስ ባለፈ ቤተሰብን ያኮራል፤ ከዚህ ከፍ ሲልም ለማህበረሰብ ግንባታና ለሀገር የሚኖረው ፋይዳ የጎላ ነው። ሌብነትና ሙስናን ለመከላከልም እንዲሁ አስተዋጾ አለው። በመልካም ስነምግባር ታንጾ ያደገ ሰው በላቡና በወዙ ጥሮ ግሮ ያፈራውን እንጂ የሌሎች የሆነን ሀብትና ንብረት አይመኝም። ዛሬ የራሱ ያልሆነውን ንብረት በሀሰት ምሎና ተገዝቶ ለመውሰድና ለመክበር የሚጥር ሰው በበዛበት በዚህ ዘመን ላይ ወድቆ ያገኙትን ንብረት ለባለቤቱ ለመመለስ "ገንዘብ የጣለ" እያለ በአደባባይ ባለቤቱን የሚያፈላለግ ሰው ሲገጥም ግርምትን ከማጫር ባለፈ እንዲህ አይነት ሰውም አለ ወይ? ያስብላል። ነገሩ የተከሰተው በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ገረሴ ዙሪያ ወረዳ ኮሻሌ ቀበሌ ነው። በአካባቢው ባህልና እምነት የሰው ገንዘብም ሆነ ንብረት ያለአግባብ መውሰድ "ጎሜ" ወይም እንደ "ሀጥያት" ተደርጎ ይቆጠራል። በኮሻሌ ቀበሌ ተወልደው ያደጉት አርሶ አደር ሴዳ ጋርዜ በዚህ ባህልና እምነት ውስጥ ያደጉ ቢሆንም በቤተሰባቸው በመልካም ስነ ምግባር ታንጸው ማደጋቸው አሁን ላላቸው ታማኝነትና ቅንነት ትልቁን ድርሻ ይይዛል። አርሶ አደሩ ታማኝነታቸውን በተግባር ጭምር በማሳየታቸው ከመንግስት ጭምር እውቅና ተችሯቸዋል። ነገሩ እንዲህ ነው አንድ ቀን ገበያ ውለው ሲመለሱ በመንገዳቸው ላይ ተጠቅልሎ የታሰረ ነገር ይመለከታሉ። መሬት ወድቆ ያገኙት ነገር እስሩን ፈትው ሲያዩ በርከት ያለ የገንዘብ ኖት ነው። ለማመን እያቃታቸው ገንዘቡን መቁጠር ጀመሩ። በላስቲክ የተጠቀለለው ብር 30 ሺህ ነበር። የራሳቸው ያልሆነውን ገንዘብ ይዞ ወደ ቤት መግባት የህሊና እዳ መስሎ ስለታያቸው አማራጭ ያሉትን አደረጉ፡፡ የገንዘቡ ትክክለኛ ባለቤት ከተገኘ በሚል "ገንዘብ የጠፋበት! ገንዘብ የጠፋበት" እያሉ በአደባባይ ጽምጻቸውን ከፍ አድርገው መጠየቅ ጀመሩ። የሰማቸው ሁሉ ግራ ስለተጋባ ቀረብ ብሎ ሊጠይቃቸው ይቅርና ጤነኛ ሰውም አድርጎ አላያቸውም። የገንዘቡ ባለቤት እኔ ነኝ የሚል ትክክለኛ ሰውም ባለመገኘቱ ልፋታቸው ድካም ብቻ ሆነ። የያዙትን 30 ሺህ ብር ይዘው ወደ ቤታቸው ለመሄድ ተገደዱ። በአካባቢው የገበያ ቀን በሳምንት አንድ ቀን ብቻ ነው። እናም የገንዘቡን ባለቤት ለማግኘት እስከ ሳምንት ድረስ መቆየት ግድ ሆኖባቸው። ባለቤቱ ይገኛል ወይስ አይገኝም በሚል ሀሳብ ሳምንቱን አሳለፉ። ቀጣይ የገበያ ቀን ሲደርስም ገንዘቡን እንጨት ላይ አስረው በማንጠልጠል "ገንዘብ የጠፋበት! ገንዘብ የጠፋበት" አያሉ በገበያ ስፍራ በመዘዋወር ዳግም የጠፋበትን ሰው ማፈላለግ ጀመሩ። ገንዘቡ የእኔ ነው፤ ጠፍቶብኛል እያለ የሚመጣ ሰው ቢበዛም ትክክለኛውን የገንዘብ መጠንና ምልክቱን የሚጠራ ሰው አለመኖሩ ግን ፍለጋቸውን አድካሚ አድርጎታል። የገንዘቡን ባለቤት አግኝተው እስኪያስረክቡ ድረስ ተስፋ አልቆረጡም፤ “ገንዘብ የጠፋበት፣ ገንዘብ የጠፋበት...” እያሉ ገበያውን ከዳር ዳር ዞሩ። የኋላ ኋላ ግን ድካማቸው በከንቱ አልቀረም። በስተመጨረሻ ትክክለኛውን የገንዘብ መጠን ከእነምልክቱ እና ቦታው የሚናገር አንድ ግለሰብ ተገኘ። ከገንዘቡ ባለቤት ጋር ከተወያዩ በኋላ ገንዘቡ ወድቆ ወዳገኙበት ስፍራ ይዘው በመሄድ የያዙትን ገንዘብ መሬት ላይ ጥለው ራሱ ባለቤቱ ምሎ እንዲያነሳ ያደርጋሉ። በእዚህ ሁኔታ ወደቆ ያገኙትን ገንዘብ በታማኝነት ያስረከቡት አቶ ሴዳ ለዚህ መልካም ተግባራቸው ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በቅርቡ እውቅና ተችሯቸዋል። የእሳቸው መልካም ተግባር መረጃ የደረሰው ኮሚሽኑም የአርሶ አደሩን አርአያነት ለሌላው ለማስተማር አፈላልጎ ያገኛቸዋል፡፡ ህዳር 26 ቀን 2018 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማ 22ኛው ዓለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀንን ሲያከብር በማጠቃለያው ላይ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አለማየሁ ባውዲ በተገኙበት የእውቅና ምስክር ወረቀትና የ15 ሺህ ብር ስጦታ አበርክቶላቸዋል፡፡ የክልሉ ስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነርና የሙስናና ብልሹ አሰራር መከላከል ዘርፍ ኃላፊ አቶ አማኑኤል አብደላ ከቤተሰብ ጀምሮ በትምህርት ቤቶች በዜጎች ስነ ምግባር ላይ አበክሮ መስራት እንዲህ ያሉ ዜጎችን በብዛት ለማፍራት የሚያስችል መሆኑን ነው የገለጹት። ታማኝ የሆኑ ሰዎች ሲበራከቱ ደግሞ ሀገርና ህዝብን የሚጎዳውን ሙስና ለመከላከል ጠቀሜታው የጎላ መሆኑንም ተናግረዋል፡ እንደ አርሶ አደር ሴዳ ጋርዜ በስነ ምግባር የታነጸ ትውልድ የሚገነባው ከቤት ጀምሮ በሚሰራ ሥራ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው ኮሚሽኑ ትውልድን በስነ-ምግባር ለማነጽ የጀመረውን ስራ ለማጠናከር በሚሰራው ሥራ እንደ አርሶ አደሩ ያሉ ታማኞች ጠቀሜታቸው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል። በክልሉ የተቋቋመው የጸረ ሙስና ግብረ ኃይልም በጸረ ሙስና ትግሉ ላይ በልዩ ትኩረት እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል። ህብረተሰቡም ታማኝነትን ባህሉ ከማድረግ ባለፈ የጸረ ሙስና ትግሉን በመደገፍ ሀገራዊ ግዴታውን እንዲወጣም ነው ያሳሰቡት። የአርሶ አደር ሴዳ ጋርዜ መልካም ተግባርና ታማኝነትም ለብዙዎች ምሳሌ ይሆናል። በተለይ ያለፉበትን ለማግኘትና በአቋራጭ ለመክበር የሚሯሯጡ ሰዎች ከእሳቸው መልካም ተግባር ሊማሩ ይገባል። የሰው ሀብት ወስዶ ከመክበር ይልቅ በታማኝነት ከምናቆየው ንጹህ ህሊና ይበልጥ አትራፊ እንሆናለን። ለሰዎች መልካም መስራት ክብርና ዋጋ የሚያሰጥ መሆኑንም የእኚህ አርሶ አደሩ ተሞክሮ ያሳያልና እንደእሳቸው ለሰራነው መልካም ተግባር ዋጋ እንዲከፈለን ታማኝነትን የህይወታችን መርህ ማድረግ አለብን። መልካምነት ቢቆይም እንኳ በራሱ ይከፍላልና።
ትንታኔዎች
ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ዋንጫ
Jan 2, 2026 532
ክፍል ሁለት የቀጠለ የኢትዮጵያ ዘጠነኛ ተሳትፎ በአህጉራዊው መድረክ እ.አ.አ 1982 ኢትዮጵያ በሊቢያ አስተናጋጅነት በተካሄደው 13ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለዘጠነኛ ጊዜ ተሳትፎዋን ማድረግ ቻለች። በውድድሩ ላይ አሁንም ስምንት አገራት ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ በምድብ ሁለት ከአልጄሪያ፣ዛምቢያና ናይጄሪያ ጋር ተደልድላ ጨዋታዎቿን አድርጋለች። በምድብ ጨዋታዎቹ በናይጄሪያ 3 ለ 0 እንዲሁም በዛምቢያ 1 ለ 0 የተሸነፈች ሲሆን ከአልጄሪያ ጋር ያለ ምንም ግብ አቻ ተለያይታለች። ኢትዮጵያ በምድቧ አንድ ነጥብ ብቻ በመያዝ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች። በፍጻሜው ጨዋታ ጋና ሊቢያን በመለያ ምት በማሸነፍ ለሶስተኛ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን አንስታለች። ኢትዮጵያ ከ31 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካው ዋንጫ የተመለሰችበት ታሪካዊ ሁነት ኢትዮጵያ ከ13ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በኋላ በአህጉራዊው የእግር ኳስ ውድድር መድረክ ለመሳተፍ ሶስት አስርት ዓመታታን መጠበቅ ግድ ሆኖባታል። በነዚህ 30 ዓመታት ጊዜ ውስጥ 15 የአፍሪካ ዋንጫ ውድድሮች ተካሄደዋል። እ.አ.አ በ2013 በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ከ31 ዓመት በኋላ ወደ ውድድሩ ዳግም ተመለሰች። ኢትዮጵያ ወደ አፍሪካ ዋንጫው ያለፈችበት መንገድ ልብ አንጠልጣይ ነበር። ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2012 በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ ከሱዳን ጋር ባደረገችው የመጨረሻ ዙር የደርሶ መልስ ጨዋታ በመጀመሪያ ዙር ኦምዱርማን ላይ 5 ለ 3 በሆነ ውጤት ተሸንፋለች። ሱዳን ጨዋታውን ያሸነፈችው በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች በተቆጠሩ ሁለት አጨቃጫቂ የፍጹም ቅጣት ምት በግቦች ነበር። ጥቅምት 4 2004 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም ለሚደረገው የመልስ ጨዋታ በስታዲየሙ ዙሪያ ከእኩለ ሌሊት ጀምሮ በርካታ ተመልካች ተሰልፎ ነበር። ጨዋታው በመጀመሪያው አጋማሽ ያለ ምንም መጠናቀቁ በስታዲየሙ የተገኘውን ተመልካች ጭንቅ ውስጥ ከቶ ነበር። ጭንቀቱ በስታዲየሙ ላሉት ብቻ ሳይሆን በቴሌቪዥን መስኮት ለሚከታተሉት በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንም ነበር። በሁለተኛው አጋማሽ የተሻለ እንቅስቃሴ ያደረጉት ዋልያዎቹ አዳነ ግርማ ባስቆጠራት ግብ መሪ መሆን ቻሉ። ይሁንና ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫው ለመሳተፍ አንድ ተጨማሪ ጎል ያስፈልጋታል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አጥቂ ሳላዲን ሰዒድ ወሳኟን ሁለተኛ ግብ ከመረብ ላይ አሳረፈ። ግቡ ሲቆጠር በስታዲየሙ ተመልካቾች ላይ የነበረው ስሜት በከፍተኛ ደስታ የተሟላ ሲሆን ስሜታቸውንብ በእንባ የገለጹም ነበሩ። ጨዋታው በድምር ውጤት 5 ለ 5 ተጠናቆ ከሜዳ ውጪ ብዙ ባስቆጠረ በሚል ኢትዮጵያ ከ31 ዓመት በኋላ ዳግም ወደ አፍሪካ ዋንጫ መመለስ ቻለች። ከጨዋታው በኋላ በአዲስ አበባ ስታዲየም፣በመስቀል አደባባይና በመዲናዋ የተለያዩ አውራ ጎዳናዎች፣መንደሮችና የተለያዩ አካባቢዎች እንዲሁም በመላው ኢትዮጵያ ባሉ ክፍሎች የነበረው የደስታ ስሜትና ፈንጠዝያ የሚረሳ አልነበረም። በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንም የደስታው ተቋዳሽ ነበሩ። ኢትዮጵያን ከ31 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫው እንድትመለስ ያደረጉት አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ነበሩ። ደቡብ አፍሪካ ባዘጋጀችው 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ 16 አገራት በስድስት ምድብ ተከፍለው ጨዋታቸውን አድርገዋል። ኢትዮጵያም በምድብ ሶስት ከቡርኪናፋሶ፣ናይጄሪያና ዛምቢያ ጋር ተደልድላ ጨዋታዋን አድርጋለች። በመጀመሪያ ጨዋታዋ ኢትዮጵያ ከዛምቢያ ጋር አንድ አቻ ተለያይታለች። አዳነ ግርማ በ65ኛው ደቂቃ ለኢትዮጵያ ግቡን አስቆጥሯል። በሁለተኛው ጨዋታ ኢትዮጵያ በቡርኪናፋሶ የ4 ለ 0 ሽንፈት አስተናግዳለች። በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ ኢትዮጵያ በናይጄሪያ 2 ለ 0 ተሸንፋለች። ውጤቶቹን ተከትሎ ኢትዮጵያ በአንድ ነጥብ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ ይዛ ከምድቧ ሳታልፍ ቀርታለች። ኢትዮጵያ ከ31 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ብትመለስም በውድድሩ ላይ ያስመዘገበችው ውጤትና ያሳየችው ብቃት የእግር ኳስ ቤተሰቡን ያስደሰተ አልነበረም። ይሁንና ብሔራዊ ቡድኑ ከደቡብ አፍሪካ ሲመለስ በአዲስ አበባ ስታዲየም በበርካታ ደጋፊዎች አቀባበል ተደርጎለታል። በፍጻሜው ጨዋታ ናይጄሪያ ቡርኪናፋሶ 1 ለ 0 በማሸነፍ የአፍሪካን ዋንጫን ለሶስተኛ ጊዜ አንስታለች። ኢትዮጵያ ለመጨረሻ ጊዜ የተሳተፈችበት የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ ለመጨረሻ ጊዜ በአፍሪካ ዋንጫ የተሳተፈችው እ.አ.አ በ2021 ካሜሮን ባዘጋጀችው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ነበር። ከስምንት ዓመታት በኋላ ወደ ውድድሩ የተመለሰችው ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከአዘጋጅ አገር ካሜሮን፣ቡርኪናፋሶና ኬፕቨርዴ ጋር ተደልድላ ጨዋታዋን አድርጋለች። ኢትዮጵያ በመጀመሪያ የምድብ ጨዋታዋ በኬፕቨርዴ 1 ለ 0 ተሸንፋለች። በሁለተኛው ጨዋታ ዋልያዎቹ በአዘጋጇ አገር ካሜሮን 4 ለ 1 ተሸንፈዋል። በጨዋታው ኢትዮጵያ አጥቂው ዳዋ ሁቴሳ በአራተኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ግብ መሪ መሆን ብትችልም ቪንሰንት አቡበከርና ቶኮ ኢካምቢ በተመሳሳይ ሁለት ግቦችን በማስቆጠር የማይበገሩትን አንበሶች አሸናፊ አድርገዋል። በወቅቱ በአሰልጣኝ ውበቱ የተመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመጨረሻ የምድብ ጨዋታዋ ከቡርኪናፋሶ ጋር አንድ አቻ ተለያይታለች። ለብሔራዊ ቡድኑ ብቸኛዋን ግብ ያስቆጠረው ጌታነህ ከበደ በፍፁም ቅጣት ምት ነበር። ኢትዮጵያ በምድቡ አንድ ነጥብ ብቻ በማግኘት ከምድቧ የመጨረሻውን ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። የኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ በቁጥሮች ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ የ11 ጊዜ ተሳትፎ ኢትዮጵያ 31 ጨዋታዎችን አድርጋ 8ቱን ስታሸንፍ 19 ጊዜ ተሸንፋለች። አራት ጊዜ ደግሞ አቻ ወጥታለች። በነዚህ 31 ጨዋታዎች ኢትዮጵያ 33 ግቦችን ስታስቆጥር 67 ጎሎችን አስተናግዳለች። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ በሰፊ ግብ ያሸንችባቸው ጨዋታዎች ሁለት ናቸው። እ.አ.አ በ1962 ራሷ አዘጋጅታ ራሷ በወሰደችው ሶስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ቱኒዚያና ግብጽን በተመሳሳይ 4 ለ 2 አሸንፋለች። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫው በሰፊ የግብ ልዩነት የተሸነፈችው እ.አ.አ በ1970 ሱዳን ባዘጋጀችው ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሲሆን በወቅቱ በኮትዲቭዋር 6 ለ 1 በሆነ ውጤት ተረታለች። ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ በውድድሩ ተሳትፎዋ ከፍተኛ ግብ ያስተናገደችበት ሲሆን 12 ጎሎች ተቆጥረውባታል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎዋ ከፍተኛ ግቦችን ያስቆጠረችባቸው ውድድሮች እ.አ.አ በ1952 እና በ1968 በቅደም ተከተል ሶስተኛውንና ስድስተኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ባዘጋጅበት ወቅት ነው። በነዚህ ውድድሮች ላይ በተመሳሳይ ስምንት ግቦችን አስቆጥራለች። ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን ሶስት ጊዜ አዘጋጅታለች። ኢትዮጵያውያኖቹ አጥቂዎች ሉቺያኖ ቫሳሎና መንግስቱ ወርቁ በአፍሪካ ዋንጫ ላይ በተመሳሳይ 8 ግቦችን በማስቆጠር በአፍሪካ ዋንጫ የምንጊዜም የከፍተኛ ግብ አግቢዎች ዝርዝር ውስጥ 21ኛ እና 22ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። እንደ መውጫ ኢትዮጵያ ሞሮኮ እየተካሄደ በሚገኘው 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ አትሳተፍም። የአፍሪካ እግር ኳስ መስራችና ፈር ቀዳጅ እየተባለች የምትጠራው ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ ተሳትፎዎቿ ከሰሜን፣ደቡብና ምዕራብ አፍሪካ አገራት ጋር ብርቱ ፉክክር በማድረግ መልካም የሚባል ውጤት አስመዝግባለች። ይሁንና ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በአፍሪካ ዋንጫ ያላት ተሳትፎ እየተቀዛቀዘ መጥቶ ብሔራዊ ቡድኑ ከምድቡ ማለፍ እየተሳነው ነው። የስፖርት ቤተሰቡና ተንታኞች ጠንካራ ብሔራዊ ቡድን መገንባት አለመቻሉ፣የእግር ኳስ እድገቱ ወደ ኋላ መቅረቱ፣ የአጥቂ መስመሩ ክፍል የአጨራረስ ድክመት፣ ለወጣት ተጫዋቾች እድል አለመስጠት፣የአሰልጣኞች በየጊዜው መለዋወጥ፣ለእገር ኳሱ የሚሰጠው ትኩረት የሚጠበቀውን ያህል አለመሆኑና እግር ኳሱ በስፖርቱ ባለፉ ሰዎች አለመመራቱን ጨምሮ በርካታ ምክንያቶች ይቀመጣሉ። ጠንካራና ተወዳዳሪ ቡድን የመገንባት ስራ ትኩረት ያሻዋል። ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2029 የሚካሄደውን 37ኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ለማስተናገድ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥያቄ ማቅረቧ የሚታወቅ ነው። በዚህም ውድድር ኢትዮጵያን ወክሎ የሚሳተፍ ጠንካራና አሸናፊ ብሔራዊ ቡድን መገንባት የሚያስችል "ሮድ 2029" የታዳጊዎች እግር ኳስ የስልጠና ፕሮጀክት ተጀምሯል፡፡ “ሮድ 2029"ን ለማሳካት ከኢትዮጵያ ከሁሉም አካባቢዎች 85 ብቃት ያላቸው ታዳጊዎች ተመርጠው ለዘጠኝ ወራት ስልጠና ወስደው ብቃት ያላቸው ተመርጠዋል፡፡ ከእነዚህ ታዳጊዎች መካከል 26ቱ በብቃታቸው ተመርጠው የ"ሮድ 2029" ግብን ማሳካት የሚያስችል የክፍል ውስጥ እና የሜዳ ላይ ስልጠና እየወሰዱ መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። ታዳጊዎቹ ኢትዮጵያ በህዳር ወር ባስተናገደችው ከ17 ዓመት በታች የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ የእግር ኳስ ማህበር ምክር ቤት ዞን (ሴካፋ) ተሳትፎ አድርጓል። የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን በውድድሩ ላይ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ በሞሮኮ በሚካሄደው 16ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማለፉ ይታወቃል። "ሮድ 2029" የታዳጊዎች እግር ኳስ የስልጠና ፕሮጀክት በአሜሪካዊ እና ኢትዮጵያዊ አሰልጣኞች ጥምረት የሚካሄድ ሲሆን በኢትዮጵያ ዓለም የደረሰበትን ዘመናዊ ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል። በዲጂታል አማራጮች ተደግፎ በንድፈ ሀሳብና በተግባር የሚሰጥ ሥልጠና መሆኑን በማንሳት፤ በእስካሁኑ ሂደት ተስፋ ሰጭ ውጤት ታይቶበታል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የ2029 የአፍሪካ ዋንጫ ለማዘጋጀት እንድትመረጥ የቴክኒክ ጉዳዮችን ጨምሮ የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑንን ፌዴሬሽኑ አመልክቷል። ታዳጊዎችን እግር ኳስ ልማት፣ የስፖርት መሰረተ ልማቶች ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን እንዲያሞሉ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች እና የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች መስፋት ተስፋ ሰጪ ጅማሮዎች ነው። መንግስት የጀመራቸው ስራዎች በተጠናከረ መልኩ መቀጠል ይኖርባቸዋል። አጠቃላይ የእግር ኳሱ እደግት የስፖርት ባለድርሻ አካላትን የጋራ ትብብር ይጠይቃል። ተስፋ ሰጪ እና ብርሃን ፈንጣቂ ጅማሮዎችን ነገ ኢትዮጵያ በአፍሪካ እና በዓለም መድረክ በእግር ኳሱ ስኬታማ ለመሆን መሰረት የሚጥሉ ናቸው።
የአፍሪካ እግር ኳስ ፈር ቀዳጇ ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ዋንጫ
Jan 1, 2026 471
ክፍል አንድ እንደ መነሻ እ.አ.አ የካቲት 8 ቀን 1957 በአፍሪካ እግር ኳስ ውስጥ ታሪካዊ ከሚባሉ ቀናት ውስጥ አንዱ ነው። በካርቱም ግራንድ ሆቴል ሱዳን፣ኢትዮጵያ፣ግብጽና ደቡብ አፍሪካ የአፍሪካን እግር ኳስ በበላይነት የሚመራውን ተቋም ለመመስረት ምክክር ላይ ናቸው። አህጉሪቷን የሚወክለው ኮንፌዴሬሽን ለማቋቋም መነሻ የሆነው ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር(ፊፋ) እ.አ.አ በ1956 በፖርቹጋል ሊዝበን ባካሄደው ዓመታዊ ኮንግረስ ላይ የአፍሪካ አገራት ተወካዮች ከሌሎች አህጉራዊ የእግር ኳስ ማህበራት ጋር ያደረጓቸው መደበኛ ምክክሮች ናቸው። በካርቱም የተሰበሰቡት አራት አገራት የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን በይፋ መሰረቱ። ግብጻዊውን አብደል አዚዝ አብደላ ሳሌምን በሙሉ ድምጽ የካፍ የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት አድርገው መረጡ። ካፍን ያቋቋሙት አገራት እ.አ.አ በ1957 የአፍሪካ ዋንጫ በሱዳን እንዲካሄድ ወሰኑ። የመጀመሪያውን የካፍ መተዳደሪያና የውድድር ደንቦች ያዘጋጁት አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ናቸው። የኢትዮጵያ የመጀመሪያ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎና የፎርፌ ውጤት የመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ እ.አ.አ ከየካቲት 10 እስከ 16 1957 በሱዳን ካርቱም ተካሄዷል። በውድድሩ ላይ ሱዳን፣ኢትዮጵያና ግብጽ ተሳታፊ ነበሩ። በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ማንችስተር ሲቲ ከሰንደርላንድ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ ተጠባቂ ነው አስቀድሞ በአፍሪካ ዋንጫ ላይ ትሳተፋለች ተብሎ የነበረው ደቡብ አፍሪካ ከአገሪቷ በነበረው የአፓርታይድ የዘር መድሎ ምክንያት ከውድድሩ ውጪ ሆናለች። ደቡብ አፍሪካ ከውድድሩ ውጪ የሆነቸው በአፓርታይድ ሕግ ነጮች ሙሉ በሙሉ በነጭ ወይም በሙሉ የተገነባ ብሔራዊ ቡድን እንጂ መቀላቀል አንችልም በማለታቸው ምክንያት ነው። በዚህም ምክንያት ከደቡብ አፍሪካ ጋራ በግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዋን ልታደርግ የነበረችው ኢትዮጵያ 2 ለ 0 በፎርፌ በማሸነፍ ለፍጻሜው አልፋለች። በሌላኛው የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ግብጽ ሱዳንን 2 ለ 1 በማሸነፍ ለፍጻሜ አለፈች። እ.አ.አ የካቲት 16 1957 በካርቱም ዓለም አቀፍ ስታዲየም በተደረገው የፍጻሜ ጨዋታ ግብጽ ኢትዮጵያን 4 ለ 0 በማሸነፍ ታሪካዊውን የአፍሪካ ዋንጫ አነሳች። አራቱንም ግቦች ያስቆጠረው የፊት መስመር ተጫዋቹ መሐመድ ዲያብ አል-አታር ሲሆን በአፍሪካ ዋንጫ ፍጻሜ አራት ግቦችን ያስቆጠረ የመጀመሪያው ተጫዋችና በአምስት ግቦች የመጀመሪያው የውድድሩ ኮከብ ግቢ አግቢ በመሆን ድርብ ታሪክ ጽፏል። ኢትዮጵያ በመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎዋ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች። በመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ ምንም የማጣሪያ ውድድር አልተደረገም። በመጀመሪያ የአፍሪካ ዋንጫ የተሳተፉት የኢትዮጵያ ተጫዋቾች ግብ ጠባቂ ሚካኤል ጊላ ተከላካዮች አየለ ተሰማ፣መኩሪያ ከበደ አስፋው፣አዳሙ ዓለሙ፣አዳል ተክለስላሴ አማካዮች ናስር በርሄና ሳሙኤል ዘውዴ አጥቂዎች አብርሃም ባይሩ፣አምደስላሴ ነጸረ፣አስፋው ብርሃኔና ከበደ መታፈሪያ ናቸው። በአፍሪካ ዋንጫና እግር ኳስ ፈር ቀዳጅ ከሆኑ አገራት መካከል አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎዋን በሱዳን አሀዱ ብላ ጀመረች። የኢትዮጵያ ሁለተኛ ተሳትፎ ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ1959 በግብጽ በተካሄደው ሁለተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ አድርጋለች። ሱዳን ሌላዋ በውድድሩ ላይ የተሳተፈች አገር ናት። የውድድሩ ፎርማት በአገራቱ መካከል እርስ በእርስ በሚደረጉ ጨዋታዎች የተሻለ ውጤት ያስመዘገበው ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ የሚያነሳበት ነበር። በዚሁ መሰረት ኢትዮጵያ በውድድሩ ባደረገቻቸው ጨዋታዎች በግብጽ 4 ለ 0፤ በሱዳን 1 ለ 0 ተሸንፋለች። በፍጻሜው ግብጽ ሱዳንን 2 ለ 1 በማሸነፍ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን አንስታለች። ኢትዮጵያ ብቸኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ያነሳችበት ታሪካዊ አጋጣሚ ሶስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ የተካሄደው በኢትዮጵያ አዘጋጅነት እ.አ.አ በ1962 ነው። የአፍሪካ ዋንጫ ውድድሩ ቀደም ብለው ከተካሄዱት ሁለት የአፍሪካ ዋንጫዎች ለየት የሚያደርገው አራት አገራት ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፉበት ነው። ኢትዮጵያ የውድድሩ አዘጋጅ በመሆኗ ሀገራችን በቀጥታ ለውድድሩ ስታልፍ ፤ በተመሳሳይ የግብፅ ቡድንም የ1959 የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ዋንጫ አሸናፊ ቡድን ስለነበር በቀጥታ ለ3ኛ የአፍሪካ ዋንጫ ሲያልፉ ዩጋንዳና ቱኒዚያ የማጣሪያ ጨዋታ አድርገው ለአፍሪካ ዋንጫ አልፈዋል። በሶስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ የነበሩት አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ሲሆኑ ውድድሩን ያስተናገደው ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ስታዲየም(የአሁኑ አዲስ አበባ ስታዲየም) ነበር። ኢትዮጵያ በግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዋ ቱኒዚያን 4 ለ 2 አሸንፋለች። አጥቂው ሉቺያኖ ቫሳሎ በ32ኛው በፍጹም ቅጣት ምት ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ ያስቆጠረችው የመጀመሪያ ግቧ ሆኖ ተመዝግቧል። ቫሳሎ በ75ኛው ደቂቃ በጨዋታ ግብ አስቆጥሯል። አጥቂው መንግስቱ ወርቁ እና ግርማ ተክሌ ቀሪዎችን ግቦች ለኢትዮጵያ ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። በሌላኛው የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ግብጽ ዩጋንዳን 2 ለ 1 በማሸነፍ ለፍጻሜው ከኢትዮጵያ ጋር ደረሰች። በፍጻሜው ጨዋታ አሊ መሐመድ ባዳዊ አብደል ፋታህ በ35ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት በግብ ግብጽን መሪ ማድረግ ችላ ነበር። ከእረፍት መልስ ግርማ ተክሌ በ74ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያን አቻ አድርጋለች። በ75ኛው ደቂቃ አሊ መሐመድ ባዳዊ አብደል ፋታህ በድጋሚ ግብጽን መሪ ያደረገች ግብ አስቆጠረ። አጥቂው መንግስቱ ወርቁ በ84ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያን በድጋሚ አቻ አደረገ። ጨዋታው በመደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ሁለት አቻ በሆነ ውጤት በመጠናቀቁ ጨዋታው ወደ ጭማሬ ሰዓት አምርቷል። በጭማሬ 30 ደቂቃው ኢታሎ ቫሳሎ በ101ኛው እና መንግስቱ ወርቁ በ118ኛው ደቂቃ ባስቆጠራቸው ግቦች ኢትዮጵያ 4 ለ 2 በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ አህጉራዊውን ዋንጫ ከፍ አድርጋለች። በፍጻሜው ጨዋታ ሁለት ግቦች ያስቆጠረው አጥቂው መንግስቱ ወርቁ በአጠቃላይ በውድድሩ ላይ ሶስት ጎሎችን ከመረብ ላይ በማሳረፍ ኮከብ ግብ አግቢ ሆኖ ጨርሷል። ለመጀመሪያ ጊዜ ስድስት አገራት የተሳተፉበት የአፍሪካ ዋንጫ የኢትዮጵያ ቀጣዩ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ እ.አ.አ በ1963 በጋና አስተናጋጅነት በተካሄደው አራተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ነው። በውድድሩ ለመጀመሪያ ጊዜ ስድስት ብሔራዊ ቡድኖች የተሳተፉ ሲሆን በሁለት ምድብ እያንዳንዳቸው ሶስት አገራት ተደልድለው ጨዋታቸውን አድርገዋል። የውድድሩ ፎርማት በየምድቡ አንደኛ ሆኖ የጨረሰ አገር ወደ ፍጻሜው እንዲሁም ሁለተኛ የወጡ አገራት ለደረጃው ያለፉበት ነበር። ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከአዘጋጅ አገር ጋና ቱኒዚያ ጋር ተደልድላች። በአክራ ስፖርት ስታዲየም ኢትዮጵያ ከጋና ጋር ባደረገችው ጨዋታ 2 ለ 0 ተሸንፋለች። በሁለተኛ ጨዋታዋ ኢትዮጵያ አጥቂው መንግስቱ ወርቁ ሁለት እንዲሁም ግርማ ተክሌና ግርማ ተስፋዬ ባስቆጠሯቸው አንድ አንድ ግቦች ቱኒዚያን 4 ለ 2 አሸንፋለች። ኢትዮጵያ ከምድቡ ሁለተኛ ሆና በማጠናቀቋ ለደረጃ ጨዋታ የቀረበች ሲሆን በግብጽ 3 ለ 0 ተሸንፋለች። በፍጻሜው ጋና ሱዳንን 3 ለ 0 በማሸነፍ ዋንጫውን አነሳች። ኢትዮጵያ ለአምስተኛ ተከታታይ ጊዜ የተሳተፈችበት የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ1965 በቱኒዚያ አስተናጋጅነት በተካሄደው አምስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለተከታታይ አምስተኛ ጊዜ ተሳትፋለች። በውድድሩ ላይ ስድስት አገራት ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከቱኒዚያና ሴኔጋል ጋር ተደልድላለች። በመጀመሪያ የምድብ ጨዋታዋ በቱኒዚያ 4 ለ 0 ተሸንፋለች። ኢትዮጵያ በሁለተኛው የምድብ ጨዋታዋ በሴኔጋል 5 ለ 1 ተሸንፋለች። በጨዋታው ለኢትዮጵያ ብቸኛዋን ግብ ያስቆጠረው ሉቺያኖ ቫሳሎ በፍጹም ቅጣት ምት ነበር። በፍጻሜው ጋና ቱኒዚያን 3 ለ 2 በማሸነፍ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ የአፍሪካን ዋንጫ ማንሳት ችላለች። ኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ ያዘጋጀችው የአፍሪካ ዋንጫ እ.አ.አ 1968 የተካሄደውን ስድስተኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ያዘጋጀችው ኢትዮጵያ ነበረች። ውድድሩን ያስተናገደው ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ስታዲየም(የአሁኑ አዲስ አበባ ስታዲየም) ነበር። በሻምፒዮናው ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ስምንት አገራት ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከኮትዲቭዋር፣አልጄሪያና ዩጋንዳ ጋር የተደለደለች ሲሆን ሶስቱንም የምድብ ጨዋታዎቿን አሸንፋለች። በመጀመሪያ ጨዋታዋ ኢትዮጵያ ግርማ አስመሮም ተስፋይ በጨዋታና ሉቺያኖ ቫሳሎ በፍጹም ቅጣት ምት ባስቆጠሯቸው ግቦች ዩጋንዳን 2 ለ 1 አሸንፋለች። ኢትዮጵያ በሁለተኛ ጨዋታዋ በኩረጽዮን ገብረሕይወት ባስቆጠራት ግብ ኮትዲቭዋርን 1 ለ 0 ረታለች። በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ ኢትዮጵያ አጥቂው መንግስቱ ወርቁና ሸዋንግዛው አጎናፍር በጨዋታ እንዲሁም ሉቺያኖ ቫሳሎ በፍጹም ቅጣት ምት ባስቆጠሯቸው ግቦች አልጄሪያን 3 ለ 1 በማሸነፍ ከምድቧ አንደኛ በመውጣት ለግማሽ ፍጻሜው አልፋለች። ኢትዮጵያ በግማሽ ፍጻሜው ጨዋታዋን ያደረገችው ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋር ነበር። ራውል አልበርት ኪዱሙ ማንታንቱ በሶስተኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን መሪ አድርጎል። ሊኦን ሙንጋሙኒ በ16ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ የኮንጎን መሪነት ወደ 2 ለ 0 ከፍ አድርጓል። ሉቺያኖ ቫሳሎ በ25ኛው ደቂያ ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያን ወደ ጨዋታው እንድትመለስ አድርጓል። መንግስቱ ወርቁ በ65ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያን አቻ አድርጓል። መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በአቻ ውጤት መጠናቀቁ ጨዋታው ወደ ጭማሪ 30 ደቂቃ አመራ። በጭማሬ ሰዓቱ ሊኦን ሙንጋሙኒ በ100ኛው ደቂቃ ያስቆጠራትን ግብ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን አሸናፊ በማድረግ ወደ ፍጻሜው እንድታልፍ አድርጎታል። ኢትዮጵያ ለደረጃው ባደረገችው ጨዋታ ላውረን ፖኩ ባስቆጠራት ግብ 1 ለ 0 ተሸንፋ ለሁለተኛ ጊዜ ባዘጋጀችው ውድድር አራተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። ኢትዮጵያ ከፍተኛ ግብ ያስተገደችበት ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሱዳን እ.አ.አ 1970 ሱዳን ባዘጋጀችው ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ ለሰባተኛ ጊዜ በአህጉራዊው የውድድር መድረክ ተሳትፋለች። በውድድሩ ላይ ስምንት አገራት ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከኮትዲቭዋር፣ካሜሮንና ሱዳን ጋር ተደልድላለች። ኢትዮጵያ በምድብ የመጀመሪያ ጨዋታዋ በሱዳን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት ተረታለች። በሁለተኛው ጨዋታም በካሜሮን 3 ለ 2 የተሸነፈች ሲሆን መንግስቱ ወርቁ ለኢትዮጵያ ሁለቱንም ግቦች ከመረብ ላይ አሳርፏል። በመጨረሻው የምድብ ጨዋታ ኢትዮጵያ በኮትዲቭዋር 6 ለ 1 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት ተሸንፋለች። መንግስቱ ወርቁ ለኢትዮጵያ ብቸኛዋን ግብ ከመረብ ላይ ያሳረፈ ተጫዋች ነበር። በዚህ ጨዋታ አጥቂው ላውረን ፖኩ አምስት ግቦችን አስቆጥሯል። ውጤቶቹን ተከትሎ ኢትዮጵያ በምድቡ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ ይዛ ያጠናቀቀች ሲሆን በውድድሩ 12 ግቦችን ተቆጥረውባታል። በፍጻሜው ሱዳን ጋናን 1 ለ 0 በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን አንስታለች። ኢትዮጵያ ከስድስት ዓመታት ቆይታ በኋላ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ ስምንተኛ ተሳትፎዋን ለማድረግ ስድስት ዓመት መጠበቅ ነበረባት። እ.አ.አ በ1976 ራሷ ለሶስተኛ ጊዜ ባዘጋጀችው የአፍሪካ ዋንጫ በድጋሚ ወደ ውድድር ተሳትፎ ተመልሳለች። በውድድሩ ላይ አሁንም የተሳተፉ አገራት ቁጥር ስምንት ነበር። ኢትዮጵያ በውድድሩ በምድብ አንድ ከግብጽ፣ዩጋንዳና ጊኒ ጋር ተደልድላለች። በመጀመሪያው የምድብ ጨዋታ ኢትዮጵያ በሰለሞን ሽፈራውና ተስፋዬ ስዩም ግቦች ዩጋንዳን 2 ለ 0 አሸንፋለች። በሁለተኛ ጨዋታዋ ኢትዮጵያን በጊኒ የ2 ለ 1 ሽንፈት አጋጥሟታል። ሰለሞን ሽፈራው ኢትዮጵያን ከሽንፈት ያልታደገችውን ብቸኛ ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል። በመጨረሻ የምድብ ጨዋታዋ ኢትዮጵያ ከግብጽ ጋር አንድ አቻ ተለያይታለች። መሐመድ አሊ ለኢትዮጵያ ግቧን ያስቆጠረ ተጫዋች ነው። ውጤቶቹን ተከትሎ ኢትዮጵያ በአራት ነጥብ ከምድቧ ሶስተኛ ደረጃን ይዛ በማጠናቀቋ ወደ ግማሽ ፍጻሜው ማለፍ ሳትችል ቀርታለች። በፍጻሜው ሞሮኮ ጊኒን በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን ማንሳት ቻለች። ይቀጥላል ….
ብክነትን መቀነስ የኃይል አቅርቦትን ማሳደግ፤ የአፍሪካ የኢነርጂ ውጤታማነት አጀንዳ
Dec 8, 2025 1124
አፍሪካ በዓለማችን በታዳሽ ኃይል እምቅ ሀብቶችን የያዘች አህጉር ናት። የዓለም 60 በመቶ የፀሐይ ኃይል ሀብት የሚገኘው በአፍሪካ ነው። አህጉሪቱ ከፀሐይ በየዓመቱ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ቴራዋት ሰዓት ኢነርጂ የማመንጨት አቅም አላት። ይሁንና በፀሐይ የምታመነጨው ኃይል ድርሻ አነስተኛ መሆነን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን (ኢሲኤ) የእ.አ.አ 2023 ጥናት ያመለክታል። የዓለም ባንክ ተቋም የሆነው ዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን በበኩሉ አፍሪካ 25 በመቶ የዓለም የንፋስ ኃይል አቅም ያላት ሲሆን 180 ሺህ ቴራ ዋት ሰዓት ማመንጨት እንደምትችል ይገልጻል። ይሁንና በዓለም ላይ በዘርፉ ያላት ድርሻ ከአንድ በመቶ በታች መሆኑን ያነሳል። ሃይድሮ ፓወር የአፍሪካ ሌላኛው የኢነርጂ ሀብት ማሳያ ነው። የአህጉሪቷ ወንዞች እና ተፋሰሶች በየዓመቱ 1 ሺህ 500 ቴራ ዋት ሰዓት የማመንጨት አቅም ቢኖራም ጥቅም ላይ የዋለው 10 በመቶውን ብቻ ነው። የናይል ተፋሰስ፣ የኮንጎ ተፋሰስ እና የዛምቤዚ ተፋሰሶችን የያዘችው አፍሪካ ከፍተኛ የሃይድሮ ፓወር አቅሟን መጠቀም አልቻለችም ይላል የዓለም አቀፉ የታዳሽ ኃይል ኢነርጂ ኤጀንሲ ጥናት። ወደ ምስራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ ያለው የእንፋሎት ኃይል ሌላኛው ትልቅ እድል ነው። የአፍሪካ የእንፋሎት (ጂኦተርማል) አቅም ከ15 እስከ 20 ጊጋዋት መሆኑን የአፍሪካ ኢነርጂ ምክር ቤት መረጃ ያሳያል። አፍሪካ ከዓለም የኢነርጂ ምርት ውስጥ ከአራት በመቶ በታች እንዲሁም በታዳሽ ኃይል ደግሞ ከ1 ነጥብ 6 በመቶ ያነሰ ድርሻ እንዳላት መረጃዎች ያመለክታሉ። የአፍሪካ የኢነርጂ ምህዳር ሁለት ተጻራሪ እውነታዎችን የያዘ ነው። አህጉሪቷ የዓለምን 17 በመቶ ህዝብ ብትይዝም በዓለም የኢነርጂ አጠቃቀም ያላት ድርሻ ከአራት በመቶ በታች ነው። በአሁኑ ሰዓት 600 ሚሊዮን ገደማ የሚሆን የአፍሪካ ህዝብ የኤሌክትሪክ ኃይል እንደማያገኝ መረጃዎች ያመለክታሉ። 21 በመቶ አፍሪካውያን ብቻ ንጹህ የማብሰያ ነዳጅ እና ቴክኖሎጂዎችን ያገኛሉ። ባህላዊ የምግብ ማብሰያ አማራጮች ለጤና አሉታዊ ተጽእኖ የሚያሳድሩ ናቸው። በአፍሪካ ከከተሜነት መስፋፋት እና ከፈጣን የህዝብ እድገት ጋር በተያያዘ የኢነርጂ ፍላጎት በፍጥነት እየጨመረ ይገኛል። እ.አ.አ በ2040 የአፍሪካ ህዝብ 2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ህዝብ እንደሚያልፍ ትንበያዎች ያሳያሉ። በተለይም የህዝብ ብዛት መጨመሩ በኢነርጂ አቅርቦት ላይ ጫና ያሳድራል። ከእ.አ.አ 2014 እስከ 2023 የአፍሪካ የታዳሽ ኢነርጂ በእጥፍ አድጎ ከ32 ነጥብ 5 ጊጋ ዋት ወደ 62 ነጥብ 1 ጊጋ ዋት ማደጉ መልካም የሚባል እምርታ መሆኑን የዓለም አቀፉ የታዳሽ ኃይል ኢነርጂ ኤጀንሲ ይገልጻል። የአፍሪካ ሌላኛው ፈተና የምትጠቀመውን ኢነርጂ የብክነት ምጣኔ ነው። በበቂ ሁኔታ ባልተደራጀው የኢነርጂ ስርዓት ምክንያት አፍሪካ በየዓመቱ በቢሊዮን ዶላሮች የሚገመት ገንዘብ ታጣለች። እንደ ዓለም አቀፉ የኢነርጂ ኤጀንሲ መረጃ ከሆነ አፍሪካ የኢነርጂ አጠቃቀሟን የምታሻሽል ከሆነ 30 በመቶ የኢነርጂ ወጪዋን መቀነስ ትችላለች። ይህም የአፍሪካ መንግስታት ለማህበራዊ ልማት የሚያወጡትን በጀት እንደሚያሳድግ እና አዲስ የኃይል ማመንጫዎችን ሳትገነባ የካርቦን ልቀትን መቀነስ የምትችልበትን እድል ይፈጥርላታል። ኢትዮጵያ ከወራጅ ወንዞች በአመት 124 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ ያላት ሲሆን ከ36 እስከ 40 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር የከርሰ ምድር የውሃ ሃብት እንዳላት የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል። ከገፀ ምድር የውሃ ሃብቷ 83 በመቶ የሚገኘው ከተከዜ፣ ባሮ፣ አባይና ጊቤ ኦሞ ወንዞች ነው። አንዱ የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚመነጨው ካላት የውሃ ሀብት ነው። ኢትዮጵያ በውሃ፣ በፀሐይ፣ በነፋስ እና በጂኦ-ተርማል የኃይል አማራጮች በአጠቃላይ ከ300 እስከ 400 ጊጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳላት መረጃዎች ያሳያሉ። በ10 ዓመት መሪ ልማት እቅዱ ኢትዮጵያ አሁን እያመነጨች ያለውን 4 ሺህ 818 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ወደ 17 ሺህ ሜጋ ዋት ለማሳደግ አቅዳለች። ከለውጡ በኋላ በኢነርጂው ዘርፍ ያለውን አቅም ለመጠቀም የተለያዩ የማሻሻያ ስራዎች ተከናውነዋል። ከስራዎቹ መካከል ለሶስት አስርት ዓመታት ስራ ላይ የነበረውን የኢነርጂ ፖሊሲ ማሻሻል ይገኝበታል። ፖሊሲው ከ2013 ዓ.ም አንስቶ የማሻሻያ ዝግጅት ሲደረግበት ቆይቷል። የፖሊሲ ማሻሻያው የተዘጋጀው አሁን ያለውን ሀገራዊ፣ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፍ ነባራዊ እውነታ መሰረት ባደረገ መልኩ ነው። ለኢነርጂ ፖሊሲው ማሻሻል ምክንያቶች ከሆኑት መካከልም ከሀገር በቀል ኢኮኖሚ፣ ከአረንጓዴ ልማት፣ ከ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድና ከዘላቂ የልማት ግቦች ጋር ማጣጣም በማስፈለጉ እንደሆነም የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመረቀው የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብም በአፍሪካ ግዙፉ የኢነርጂ ፕሮጀክት ሲሆን ለቀጣናው እና ለአፍሪካ ሀገራት ትልቅ አቅምን ይዞ መጥቷል። ከፖሊሲው ትኩረት አንዱ ከአገር ውስጥ የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነት ለጎረቤት አገራት ኃይል በማቅረብ ቀጣናዊ ትስስርን ማጠናከር እንደሆነም በሰነዱ ላይ ሰፍሯል። በ10 ዓመቱ የመሪ ልማት እቅዱም ዜጎችን በስፋት የአሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ የማድረግ ግብ ተይዟል። ከዚህ ባሻገር በእቅዱ ኢትዮጵያ የቀጣናው ሀገራትን በኃይል የማስተሳሰር ዕቅድ ሰንቃ እየሰራች ትገኛለች። በእቅዱ ለጎረቤት አገራት እየቀረበ ያለውን 2 ሺህ 803 ጊጋ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ወደ 7 ሺህ 184 ጊጋ ዋት ሰዓት የማሳደግ ውጥን ተይዟል። የአፍሪካ የኢነርጂ አጠቃቀምን ለማሻሻል እና ብክነትን ለመቀነስ የተቀናጀ ምላሽ የመስጠት ጉዳይ ጊዜ የማይሰጠው ነው። የአፍሪካ ህብረት ያዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የኢነርጂ ውጤታማነት ኮንፍረንስ (Energy Efficiency Conference) ታህሳስ 2 እና 3 ቀን 2018 ዓ.ም በህብረቱ ዋና መቀመጫ በአዲስ አበባ ይደረጋል። ኮንፍረንሱ እ.አ.አ በ2024 በአዘርባጃን ባኩ በተካሄደው 29ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ-29) ይፋ የተደረገው የአፍሪካ ኢነርጂ ውጤታማነት ጥምረት ማዕቀፍ ስር የሚካሄድ ነው። የጥምረቱ ማዕቀፍ በአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መጽደቁ ይታወቃል። “የአፍሪካ የኢነርጂ ውጤታማነት አጀንዳን በስትራቴጂካዊ አጋርነት ውጤታማ ማድረግ” የኮንፍረንሱ መሪ ሀሳብ ነው። አህጉራዊው ሁነት የተዘጋጀው የአፍሪካ ህብረት ልዩ ተቋም በሆነው የአፍሪካ ኢነርጂ ኮሚሽን እና በኢትዮጵያ መንግስት ትብብር ነው። ኮንፍረንሱ የኢነርጂ ውጤማነትን በማረጋገጥ የአፍሪካ ኢኮኖሚ እድገት፣ ዘላቂ ልማት እና ለአየር ንብረት ለውጥ የተግባር ምላሽ አቀጣጣይ ሞተር የማድረግ አላማ ያለው መሆኑ ተገልጿል። የአፍሪካ ኢነርጂ ኮሚሽን ዋና ዳይሬክተር ራሺድ አሊ አብደላ ኮንፍረንሱን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት የኢነርጂ ውጤማነት የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ዋንኛ ሀብት ነው ሲሉ ተናግረዋል። የኢነርጂ ውጤማነት የኃይል ብክነት፣ የካርቦን ልህቀት እና ወጪ ለመቀነስ እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ እድገት ለማረጋገጥ እንደሚያስችል ገልጸዋል። ኮንፍረንሱ የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ አመራሮች፣ ሚኒስትሮች፣ የኢንዱስትሪ መሪዎች፣ የፋይናንስ ተቋማት፣ የግሉ ዘርፍ፣ የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት ፣ ተመራማሪዎች እና ባለሙያዎችን በአንድ መድረክ የሚያገናኝ ነው። ባለድርሻ አካላቱ በአፍሪካ ዘላቂ የኢነርጂ ትራንስፎርሜሽንን ለማፋጠን የሚያስችሉ ውጤታማ የኢንቨስትመንት አማራጮችና ፖሊሲዎች ላይ በመምከር ቀጣይ ስራዎች ላይ የጋራ አቅጣጫ እንደሚያስቀምጡ ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። የአፍሪካ ከፍተኛ እና በሰፊው ጥቅም ላይ ያልዋለ የታዳሽ ኢነርጂ አቅም በቀጣይ የዓለም የኢነርጂ ሽግግር እና አቅርቦት ውስጥ ትልቅ ሚና የሚጫወት ነው። የኢነርጂ አቅሙን ትሩፋቶች የመጠቀም ጉዳይ አነስተኛ ነው ማለት ይቻላል። ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ያላቸውን የታዳሽ ኃይል ምንጭን ለመጠቀም እየወሰዷቸው የሚገኟቸው እርምጃዎች ተስፋ ሰጪ ናቸው። የኢነርጂ ውጤታማነትን ማሳደግ፣ የተቀናጁ ፖሊሲዎች፣ የተቀናጀ ቀጣናዊ የኃይል ቋቶችን መፍጠር፣ የኢነርጂ ፋይናንስን ማሳደግ እና የመንግስታት የፖለቲካ ቁርጠኝነት የአፍሪካ ኢነርጂ አቅሞች ወደ ዘላቂ ልማት፣ የኢነርጂ ደህንነት የማረጋገጥ፣ የአየር ንብረትን የሚቋቋም ጠንካራ ኢኮኖሚ መገንባትን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ ትሩፋቶች ይዞ ይመጣል።
ማድያት እና ህክምናው
Sep 29, 2025 3455
ማድያትን ለማከም አስቸጋሪ መሆኑንና በታካሚዎች ላይም የሥነ ልቡና እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ጫና ሊያመጣ የሚችል መሆኑን የቆዳ ሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ። ስለ ማድያት መንስዔ፣ ስለሚከሰትበት የሰውነት ክፍል፣ ማድያት ያለበት ሰው ማድረግ ስላለበት ጥንቃቄ፣ ቆዳን ስለሚያስቆጣ ሠርካዊ ልማድ እና ሕክምናውን በተመለከተ በራስ ደስታ ዳምጠው መታሰቢያ ሆስፒታል የቆዳ እና አባላዘር በሽታዎች ስፔሻሊስት ዶክተር አደራጀው ብርሃን ከኢዜአ ቆይታ አድርገዋል። በማብራሪያቸውም፤ በቆዳ ውስጥ ያሉ ቀለም አምራች ኅዋሶች(ሴሎች) ከመጠን በላይ ቀለም ሲያመርቱ ማድያት ተከሰተ እንደሚባል ገልጸዋል። ለዚህም መንስዔው የተፈጥሮ ተጋላጭነት ከተለያዩ ቀስቃሽ ምክንያቶች ጋር የሚያደርጉት መሥተጋብር መሆኑን አስረድተዋል። 👉 የማድያት መንስዔ ምንድን ነው? 1ኛ. የሆርሞን ለውጥ፡- በእርግዝና ወቅት ወይም የወሊድ መቆጣጠሪያ ሲጠቀሙ የሚኖር የሆርሞን ለውጥ ማድያት እንዲከሰት ወይም እንዲባባስ ያደርጋል ይላሉ የሕክምና ባለሙያው። 2ኛ. የፀሐይ ጨረር፡- ከልክ ያለፈ ፀሐይ ቀለም አምራች ኅዋሶች(ሴሎች) በብዛት ቀለም እንዲያመርቱ ስለሚያነቃቃ፤ የፀሐይ ጨረር ዋነኛ ቀስቃሽ እና አባባሽ ምክንያት መሆኑንም ገልጸዋል። 3ኛ. የዘር ሐረግ፡- በቤተሰብ ውስጥ ማድያት ካለ በዘር የመተላለፍ ዕድሉ ከፍተኛ መሆኑንም ይናገራሉ። 4ኛ. የቆዳ ዓይነት፡- ጥቁሮች (ከቡናማ እስከ ጥቁር የቆዳ ቀለም ያላቸው) ንቁ ቀለም አምራች ሴሎች ስላሏቸው ለማድያት የሚኖራቸው ተጋላጭነት ከፍተኛ መሆኑን ነው የተናገሩት። 5ኛ. ሌሎች መንስዔዎች፡- ሙቀት (የሚታዩ እና የማይታዩ ጨረሮች እንዲሁም የምድጃ እሳት)፤ የተለያዩ መድኃኒቶችና የመዋቢያ ምርቶች፤ የእንቅርት ዕጢ ህመሞች እንዲሁም ጭንቀት ማድያት እንዲከሰት ወይም እንዲባባስ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል መሆናቸውንም የሕክምና ባለሙያው አስገንዝበዋል። 👉 ማድያት በየትኛው የቆዳ ክፍል ላይ ይከሰታል? ማድያት ከሚከሰትበት የቆዳ እና የሰውነት ክፍሎች አንጻር በሁለት ከፍሎ ማየት እንደሚቻል ዶክተር አደራጀው አንስተዋል። እነሱም 1ኛ. ከሚከሰትበት የቆዳ ክፍል አንጻር፡- ማድያት በውስጠኛውም ሆነ በላይኛው የቆዳ ክፍሎች ላይ ወይም በሁለቱም ላይ ሊከሰት ይችላል ብለዋል። 2ኛ. ከሚከሰትበት የሰውነት ክፍሎች አንጻር፡- የሕክምና ባለሙያው እንዳሉት 60 በመቶ ማድያት ግንባር፣ ጉንጭ፣ አፍንጫ፣ የላይኛው ከንፈር እና አገጭ ላይ ይከሰታል ብለዋል። 30 በመቶው ደግሞ ጉንጭ እና አፍንጫ ላይ እንዲሁም 10 በመቶው የአገጭ መስመርን ተከትሎ እንደሚከሰት አስረድተዋል። በሌላ በኩል አልፎ አልፎ ከፊት የሰውነት ክፍሎች በተጨማሪ በደረት፣ አንገት እና ክንድ ላይ የሚከሰትበት ሁኔታ መኖሩንም ጠቁመዋል። 👉 የማድያት ባሕርይ ማድያት የቆዳ ቀለም ለውጥ ያመጣል፤ በግራና በቀኝ የፊት ክፍል ይወጣል። የማሳከክ ወይም የህመም ስሜት እንደሌለውም ዶክተር አደራጀው አስረድተዋል። • ማድያት በላይኛው የቆዳ ክፍል ላይ ሲከሰት፡- ነጣ ወይም ጠቆር ያለ ቡናማ የሆነ የቆዳ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይ አመላክተዋል። • ማድያት በውስጠኛው የቆዳ ክፍል ላይ ሲከሰት፡- ሰማያዊ ግራጫ ወይም ጠቆር ያለ ግራጫ የቆዳ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይ አንስተዋል። • ማድያት በሁለቱም የቆዳ ክፍሎች ላይ ሲከሰት፡- የተቀላቀለ የቡናማ እና ግራጫ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይም ባለሙያው አብራርተዋል። 👉 ማድያት ያለበት ሰው ምን ዓይነት ጥንቃቄዎችን ማድረግ ይገባዋል? 1ኛ. ወርቃማ ጥንቃቄ፡- • ተከታታይና ጥብቅ የሆነ የፀሐይ መከላከያ መጠቀም ይገባል ይላሉ የሕክምና ባለሙያው። በዚህም መሠረት ከቤት ከመውጣት ከ20 እስከ 30 ደቂቃ ቀደም ብሎ የፀሐይ መከላከያ ክሬሞችን መቀባትና በሁለት ሠዓት ልዩነት እየደረቡ መቀባት። • በሌላ በኩል ከ4 እስከ 10 ሠዓት ያለው የፀሐይ ሙቀት ለቆዳ ህመም አጋላጭ መሆኑን በመገንዘብ ከፀሐይ መከላከያ ክሬም በተጨማሪ ጥላና ኮፍያን መጠቀም እንደሚገባ መክረዋል። 2ኛ. ቆዳን የሚያስቆጣ የቆዳ እንክብካቤ (መስተካከል ያለበት ልማድ)• ቆዳን የሚያስቆጡ መታጠቢያዎች(ሳሙናን ጨምሮ ሌሎችም) እንዲሁም መዋቢያዎችና የሚቀቡ ነገሮች (ኮስሞቲክስን ጨምሮ ሌሎችም) አለመጠቀም ይገባል ይላሉ። • ለቆዳ ተስማሚ የሆኑ ማለስለሻዎችን በደንብ መጠቀም እንደሚገባም ይመክራሉ። 3ኛ. በሐኪም የታዘዙ መድኃኒቶችን በአግባቡ መጠቀም • በሐኪም የታዘዘ መድኃኒትን በአግባቡ(ሳያቆራርጡ) መጠቀም እንደሚመከር ያስረዱት ዶክተር አደራጀው፤ እንደ ማድያቱ እና እንደ ሰዎቹ ቆዳ ዓይነት መድኃኒቱ ለውጥ የሚያሳይበት ጊዜ ስለሚለያይና ከ8 እስከ 12 ሣምንት ሊወስድ ስለሚችል ታግሶ በደንብ ቢጠቀሙ መልካም ነው ይላሉ። 4ኛ. የተለያዩ የሕክምና አማራጮችን መጠቀም• የሕክምና ባለሙያው እንደሚመክሩት፤ በዘርፉ ያሉ የተለያዩ የሕክምና ዓይነቶችን ለምሳሌ እንደ ኬሚካል ፒልስ፣ የቆዳ ሕክምና እና ማይክሮ ኒድሊንግ ያሉትን በሐኪም ምርመራ መሠረት መጠቀም ይገባል። 5ኛ. ከወሊድ መቆጣጠሪያ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ የተከሰተ ማድያት ከሆነ ከሕክምና ባለሙያ ጋር በመመካከር ሌላ አማራጭ መጠቀም እንደሚገባም አንስተዋል። እንዲሁም ጭንቀትን መቀነስ እንደሚገባ መክረዋል። 👉 የማድያት ሕክምናን በተመለከተ የማድያት ሕክምና በጣም አስቸጋሪ ከሚባሉትና ረጂም ጊዜ ከሚወስዱ እንዲሁም በመመላለስ ከሚያስቸግሩ የቆዳ ሁኔታዎች አንዱ መሆኑን ዶክተር አደራጀው ገልጸዋል። በሕክምና ማድያቱ የጠፋላቸው ሰዎች መኖራቸውን አረጋግጠው፤ በሌላ በኩል በሕክምና ሂደት የማድያቱ ሁኔታ ከነበረበት እየቀነሰ ለውጥ የሚታይበት ሁኔታ አለ ብለዋል። ይህን ለውጥ የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ማስቀጠል እንደሚገባም ይመክራሉ። እንክብካቤው ከተቋረጠ ግን ማድያቱ እንደገና የሚመለስበት ሁኔታ መኖሩን አስገንዝበዋል። 👉 የማድያት ሕክምና አማራጮች የሚቀቡ መድኃኒቶች፣ የሚዋጡ መድኃኒቶች፣ ሌሎች የሕክምና አማራጮች(ኬሚካል ፒልስ፣ የቆዳ ሕክምና እና ማይክሮ ኒድሊንግ)፣ የፀሐይ መከላከያ አማራጮችን በአግባቡ አዘውትሮ መጠቀም እንደሚገባ ይመክራሉ።
ልዩ ዘገባዎች
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 3093
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 1966
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 1/2018(ኢዜአ)፡- በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 7785
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 6270
ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
መጣጥፍ
ዕድሜ ያልገደበው የልማት አርበኝነት
Jan 14, 2026 155
ዕድሜ ያልገደበው የልማት አርበኝነት ብርቱዎች ነገን በማሰብ ሁሌም ታትረው ይሰራሉ፤ ይደክማሉ፤ ይጥራሉ…ለቀጣዩ ትውልድም ጥሪት በማስቀመጥ አሻራቸውን ያኖራሉ። አገር የምትገነባው በትውልድ ቅብብሎሽ ነው። “አባት ያበጀው፤ ለልጅ ይበጀው” እንደሚባለው ልጆች ከአባቶቻቸው ያገኙትን ጥሪት በአዲስ እውቀትና አሰራር ለአገር እድገት በሚበጅ መልኩ አጠናክረው መጠቀማቸው አይቀርም። “ዕድሜ ጸጋ ነው” የሚለው አባባል አንዳንዴ በዕድሜ ብንገፋም ጠንክረን ከሰራን ብዙ ነገር እናያለን ከሚለው ጋር የተያያዘ ነው። በሰቆጣ ከተማም እድሜ ሳይገድባቸው በልማት ውጤታማ የሆኑ ግለሰቦች ለዚህ ማሳያ ናቸው። የከተማዋ ነዋሪ የ67 ዓመቱ አቶ ብርሃኑ አወቀ እና የ83 ዓመቱ የዕድሜ ባለፀጋ አቶ ታደሰ አዳነ ዕድሜያቸው ቢገፋም ጠንክሮ ከተሰራ ውጤታማ መሆን እንደሚቻልና ዕድሜ ጸጋ ሆኖ ብዙ ለውጥ ማየት እንደሚቻል ማሳያ ናቸው። ግለሰቦቹ ከዕድሜ ብዛት ጉልበቴ ደከመ፣ አይኔ ፈዘዘ፣ እጄም ተሳሰረ…ሳይሉ ጊዜያቸውን በደን፣ በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ሥራ በማሳለፍ ለወጣቶች የልማት አርአያነት ያለው ተግባር እየፈጸሙ ነው። አቶ ብርሃኑ አወቀ በሰቆጣ ከተማ ዳርቻ የሚገኝ አለቱ ያገጠጠና የተራቆተ አካባቢን ከሌላ አካባቢ ለም አፈር በማምጣትና በመደልደል አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም ደን በማልማት ውጤታማ ስራ እያከናወኑ ነው። ከመንግስት ሥራ በጡረታ ከወጣሁ ጀምሮ ጠንክሬ በመስራት የምለወጥበትን ሥራ ማሰብ ስነበረብኝ፤ የቆሻሻ መጣያ ሆኖ ለዘመናት የቆየን ጭንጫ መሬት ጠርጌና ደልድዬ ማልማት ችያለሁ ይላሉ ወደኋላ መልስ ብለው የተነሱበትን ሁኔታ ሲያስታውሱ። ግማሽ ሄክታር በማይሞላ መሬት ላይ ፓፓያ፣ ሙዝ፣ ዘይቱና፣ ጌሾ፣ ቡና፣ ማንጎና አቮካዶ አልምተዋል። በተጨማሪም ቆስጣ፣ ቲማቲም፣ ጥቅል ጎመንና ሽንኩርት በማምረት ከቤት ፍጆታ ባለፈ ለገበያ በማቅረብ ተጨማሪ ጥሪት አፍርተዋል። ጊዜን በአግባቡ ተጠቅሞ ተግቶ መስራት ከተቻለ ሀብት ማፍራትና ህይወትንም መለወጥ እንደሚቻል የገለጹት አቶ ብርሀኑ፣ ወጣቱም ከእሳቸው የሥራ ትጋት በመማር በአካባቢው ያለውን ፀጋ ለይቶ በማልማት ሊጠቀም ይገባል ሲሉ ይመክራሉ። ሌላው የ83 ዓመቱ የዕድሜ ባለፀጋ አቶ ታደሰ አዳነ ባለፉት 18 ዓመታት በተሰማሩበት የአትክልትና ደን ልማት ሥራ የአካባቢያቸውን ገጽታ ቀይረዋል። የዕድሜ ዘመናቸውን በውትድርናና በመንግስት ሠራተኝነት በማገልገል ሃገራዊ ግዳጃቸውን ሲወጡ ነው የቆዩት። ከመንግስት ሥራ በጡረታ ከተገለሉ በኋላም ቤት ውስጥ መቀመጥን አልመረጡት። አካፋና ዶማቸውን ይዘው ባላቸው ትንሽ መሬት ላይ ጌሾ፣ ዘይቱና እና ማንጎ በማልማት ምርቱን ከቤት ውስጥ ፍጆታ ባለፈ ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ ሆነዋል። በአካባቢያችን ያሉ ፀጋዎችን በአግባቡ ለይተን ማልማት ከቻልን ድህነትን ማስወገድ የሚከብድ አይሆንም ያሉት አቶ ታደሰ፣ የተራቆተና በጎርፍ የተጎዳን መሬት በማልማት አካባቢውን ሳቢና ማራኪ ማድረጋቸውን ነው የገለጹት። ወጣቱም ከእሳቸው አርአያነት ያለው ተግባር በመማር በአካባቢው እጁ ላይ ባለ ሀብት ሰርቶ መለወጥ እንደሚቻል በተግባር ማሳየት እንዳለበት መክረዋል። የዋግኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ግብርና መምሪያ የአትክልትና ፍራፍሬ መስኖ ውሃ አጠቃቀም ቡድን መሪ አቶ ደሳለኝ አዳነ እንደገለጹት፤ በብሔረሰብ አስተዳደሩ 24ሺህ 847 አርሶ አደሮች በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ተሰማርተዋል። ከአርሶ አደሮቹ መካከል ዕድሜ ሳይገድባቸው ወደ ልማት የገቡ አረጋዊያን እያከናወኑት ያለው የግብርና ልማት ሥራ ለወጣቱ ትልቅ ትምህርት እንደሚሆንም ተናግረዋል። ከእነሱ ልምድ በመውሰድ በዞኑ ወጣቶች፣ ሴቶችና አረጋዊያን በጓሮና ባላቸው መሬት ላይ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲያለሙ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው ይህም በዞኑ የሚስተዋለውን የስርዓተ ምግብ ችግር ለማሻሻል ያግዛል ብለዋል።
ከማላጋ እስከ አፍሪካ ዋንጫ፤ የሞሮኮው አዲስ እንቁ ብራሂም ዲያዝ
Jan 13, 2026 173
የግል ክህሎት፣ ፈጣን አስተሳሰቡ እና በጠባብ ክፍተቶች ውስጥ ሰብሮ የመግባት አቅሙ ሙገሳ እንዲጎርፍለት አድርጓል። አንድ ለአንድ ሲገናኝ ተከላካዮችን በፈጣን አካላዊ ቅልጥፍና እና በድንገት አቅጣጫ በመቀየር የሚያልፍበት መንገድ እንዲሁም የመፍጠር አቅሙ የተመልካቾችን ቀልብ የሚይዝ ነው። የአማካይ እና የአጥቂ መስመርን በማገናኘት እና በአስገራሚ ሁኔታ አጭር ኳሶችን በማቀበልም የተዋጣለት ተጫዋች ነው ማለት ይቻላል። በቦታ አያያዙ የእግር ኳስ ልኅቀቱ ከፍተኛ ነው የሚል አድናቆት ከእግር ኳስ ባለሙያዎች አግኝቷል። ኳስን ሲያንከባልልም ለዐይን ይስባል። ከክህሎቱ እና ከማራኪ እንቅስቃሴው ባለፈ ወደ ኋላ እየመለሰ ተከላካዮችን ያግዛል፣ ኳስ ይነጥቃል። ይህ ተጫዋች የ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ክስተት የሆነው የሞሮኮው ብራሂም ዲያዝ ነው። የ26 ዓመቱ የሪያል ማድሪድ የክንፍ መስመር ተጫዋች ዲያዝ በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ አምስት ጨዋታዎችን አድርጎ አምስት ግቦችን በማስቆጠር የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን እየመራ ነው። አዘጋጇ ሞሮኮ በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ መክፈቻ ኮሞሮስን 2 ለ 0 ስታሸንፍ የውድድሩን የመጀመሪያ ግብ አስቆጥሯል። ብራሂም አብዱልቃድር ዲያዝ የተወለደው እ.አ.አ ኦገስት 3 ቀን 1999 በስፔን ማላጋ ግዛት ነው። እናቱ ስፔናዊ አባቱ ሞሮኳዊ ናቸው። ዲያዝ ያደገው በማላጋ ነው። እግር ኳስንም በአንዳሉሺያዊቷ ከተማ ሲጫወት ቆይቷል። በ16 ዓመቱ ካደገበት ማላጋ በመውጣት እ.አ.አ በ2015 ወደ ማንችስተር ሲቲ ወጣት አካዳሚ በ200 ሺህ ፓውንድ ወጪ ተዘዋወረ። ዲያዝ እ.አ.አ ሴፕቴምበር 21 ቀን 2016 በካራባኦ ካፕ (በቀድሞ አጠራሩ ሊግ ካፕ) ማንችስተር ሲቲ ከስዋንሲ ሲቲ ባደረገው ጨዋታ በ80ኛው ደቂቃ በኬሌቺ ኢናቺዩ ተቀይሮ በመግባት ለውኃ ሰማያዊዎቹ የመጀመሪያ ጨዋታውን አድርጓል። የመጀመሪያውን ጨዋታ ካደረገ ከሶስት ቀናት በኋላ ከማንችስተር ሲቲ ጋር ለሶስት ዓመታት የሚያቆየውን ፕሮፌሽናል ኮንትራት ተፈራርሟል። እ.አ.አ ኖቬምበር 21 ቀን 2017 ማንችስተር ሲቲ ከፌይኖርድ ሮተርዳም ጋር ባደረገው የሻምፒዮናስ ሊግ ጨዋታ ላይ የመጀመሪያ የአውሮፓ መድረክ ጨዋታውን ማድረግ ችሏል። በወቅቱ ብራሂም ስተርሊን መደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ በጭማሪ ሰዓት ላይ ነበር ተቀይሮ የገባው። ዲያዝ በውኃ ሰማያዊዎቹ ማልያ ቋሚ አሰላለፍ ውስጥ ገብቶ የተጫወተው እ.አ.አ ዲሴምበር 19 ቀን 2017 ነው። ማንችስተር ሲቲ ከሌስተር ሲቲ በካራባኦ ካፕ ጨዋታ ላይ ለ88 ደቂቃዎች ተሰልፎ ተጫውቷል። እ.አ.አ ጃንዋሪ 20 ቀን 2018 ማንችስተር ሲቲ ኒውካስትል ዩናይትድን 3 ለ 1 ባሸነፈበት ጨዋታ በሊጉ የመጀመሪያ ጨዋታውን አድርጓል። በወቅቱ ማንችስተር ሲቲ የሊጉን ዋንጫ ያነሳ ሲሆን፤ በውድድር ዓመቱ አራት ጨዋታዎች ላይ ብቻ ተሳትፎ ያደረገው ብራሂም ዲይዝ የሜዳሊያ ሽልማት አግኝቷል። እ.አ.አ ኦገስት 5 ቀን 2018 ማንችስተር ሲቲ ቼልሲን 2 ለ 0 ባሸነፈበት የኮሙዩኒቲ ሺልድ ጨዋታ ላይ በፊል ፎደን ተቀይሮ በመግባት ለ15 ደቂቃዎች ተጫውቷል። ዲያዝ እ.አ.አ 2018/19 ማብቂያ ላይ ማንችስተር ሲቲ ፉልሃምን 2 ለ 0 ባሸነፈበት ጨዋታ ሁለት ግቦችን ከመረብ ላይ በማሳረፍ የመጀመሪያ ግቦቹን ለሲቲ አስቆጥሯል። በማንችስተር ሲቲ ያለው ውል እ.አ.አ 2019 ሊጠናቀቅ በተቃረበበት ወቅት ስሙ ከዝውውር ጋር በስፋት ይነሳ ነበር። ዲያዝ እ.አ.አ ጥር 2019 በ17 ሚሊዮን ዩሮ ከማንችስተር ሲቲ ወደ ሪያል ማድሪድ ተዘዋወረ። ለስድስት ዓመታት የሚያቆየውን ውልም ፈርሟል። የክንፍ ተጫዋቹ የመጀመሪያ ጨዋታውን በነጮቹ ማልያ ያደረገው እ.አ.አ ጥር 9 ቀን 2019 ሪያል ማድሪድ ሌጋኔን በስፔን ጥሎ ማለፍ ዋንጫ 3 ለ 0 ባሸነፈበት ወቅት ነው። ከአራት ቀናት በኋላ በስፔን ላሊጋ ሪያል ማድሪድ ሪያል ቤቲስን 2 ለ 1 ባሸነፈበት ጨዋታ ተቀይሮ በመግባት በሊጉ የመጀመሪያ ጨዋታውን አድርጓል። የመጀመሪያ ግቡን ለማስቆጠር ሶስት ወራትን ጠብቋል። እ.አ.አ ግንቦት 12 ቀን 2019 ሪያል ማድሪድ በላሊጋው በሪያል ሶሲዬዳድ 3 ለ 1 ሲሸነፍ ብቸኛውን ጎል አስቆጥሯል። በወቅቱ ዲያዝ ስድስት ጨዋታዎች ላይ በላሊጋው የተጫወተ ሲሆን፤ በመጀመሪያ ዓመቱ የሊጉን ዋንጫ አንስቷል። ሪያል ማድሪድ እ.አ.አ በ2021/21 የውድድር ዓመት ብራሂም ዲያዝ ወደ ኤሲ ሚላን በውሰት ማምራቱን ይፋ አደረገ። ዲያዝ ሚላን እ.አ.አ መስከረም 27 ቀን 2020 ክሮቶኔን 2 ለ 0 ባሸነፈበት ጨዋታ የመጀመሪያ ግቡን ከመረብ ላይ አሳርፏል። እ.አ.አ ግንቦት 2021 ኤሲ ሚላን ጁቬንቱስን 3 ለ 0 ሲያሸንፍ ያስቆጠረው ግብም ተጠቃሽ ነው። ዲያዝ በኤሲ ሚላን የውሰት ውሉ ሲያበቃ በድጋሚ ለሁለት ዓመታት በውሰት የሚቆይበት ስምምነት ሪያል ማድሪድ ከጣልያኑ ክለብ ጋር የተፈራረመ ሲሆን፤ ውሉ ሚላን ተጫዋቹን የማቆየት መብት ሰጥቶታል። እ.አ.አ መስከረም 15 ቀን 2021 ኤሲ ሚላን በሻምፒዮንስ ሊጉ የ3 ለ 2 ሽንፈት ሲያስተናግድ የመጀመሪያ የአውሮፓ መድረክ ግቡን አስቆጥሯል። በ2023 ኤሲ ሚላን ቶተንሃም ሆትስፐርስን በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ጥሎ ማለፍ 1 ለ 0 ሲያሽንፍ ብቸኛውን ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል። እ.አ.አ በ2023 ሰኔ ወር ላይ ሪያል ማድሪድ ዲያዝ ከኤሲ ሚላን የሶስት ዓመታት የውሰት ቆይታ በኋላ ወደ ክለቡ መመለሱን አሳውቋል። ተጫዋቹ በኤሲ ሚላን ቆይታው 91 ጨዋታዎችን አድርጎ 13 ግቦችን ከመረብ ጋር አገናኝቷል። ዲያዝ ወደ ሪያል ማድሪድ ከተመለሰ በኋላ ኮንትራቱን እስከ 2027 አራዝሟል። እ.አ.አ መስከረም 27 ቀን 2023 ወደ ክለቡ ከተመለሰ በኋላ ሪያል ማድሪድ ላስ ፓልማስን 2 ለ 0 ባሸነፈበት ጨዋታ ግብ አስቆጥሯል። የክንፍ መስመር ተጫዋቹ ሪያል ማድሪድ በሀገር ውስጥ እና በአውሮፓ መድረክ በሚያደርጋቸው ጨዋታዎች ላይ ግብ በማስቆጠር እና ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ በማቀበል ትልቅ አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል። ዲያዝ እስከ አሁን ለሪያል ማድሪድ ባደረጋቸው 129 ጨዋታዎች 20 ግቦችን ከመረብ ላይ አሳርፏል። ከነዚህም ውስጥ 13ቱ በላሊጋው ያስቆጠራቸው ናቸው። ከክለብ ወጣ ስንል የተጫዋቹን የብሔራዊ ቡድን ቆይታ እናገኛለን። ዲያዝ በታዳጊነቱ በተለያዩ የእድሜ እርከኖች ለስፔን ወጣት ቡድኖች ተጫውቷል። እ.አ.አ በ2016/17 የውድድር ዘመን ለስፔን ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በ16 ዓመቱ ተሰልፎ መጫወት ችሏል። በተለይም አዘርባጃን እ.አ.አ በ2017 ባዘጋጀችው 15ኛው የአውሮፓ ከ17 ዓመት በታች ዋንጫ ላይ ያሳየው ድንቅ ብቃት አድናቆት አስችሮታል። በዚያ ቀጥለው በነበሩ ዓመታትም ለስፔን ከ19 እና ከ21 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድኖች ተጫውቷል። ብራሂም ዲያዝ በስፔን ታዳጊና ወጣት ቡድኖች ላይ በአጠቃላይ 28 ጨዋታዎችን አድርጎ ስድስት ግቦችን አስቆጥሯል። የስፔን ታዋቂ የስፖርት ጋዜጣ ማርካ እ.አ.አ ጥር 23 ቀን 2023 ለሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን መጫወት ማቀዱን የሚመለከት ዘገባ ይዞ ወጥቷል። ከዜግነቱ ጋር በተያያዘ ያሉ አንዳንድ የአስተደዳር ጉዳዮች በወቅቱ መፍትሄ አግኝተዋል። ይሁንና ኮትዲቯር እ.አ.አ በ2023 ባዘጋጀችው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የሞሮኮው አሰልጣኝ ዋሊድ ሬግራጉዊ ከተጫዋቹ ጋር በተደረገ የቅድሚያ ስምምነት ለተጫዋቹ ጥሪ አልተደረገለትም። ዲያዝ እ.አ.አ መጋቢት 10 ቀን 2024 ለሞሮኮ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለሀገሪቷ ብሔራዊ መጫወት እንደሚፈልግ በይፋ ማሳወቁን ማርካ በወቅቱ ዘግቧል። ጥያቄውም ተቀባይነት አገኘ። በወቅቱ የሞሮኮ አሰልጣኝ ዋሊድ ሬግራጉዊ ብሔራዊ ቡድኑ ከአንጎላ እና ሞሪታኒያ ጋር ለነበረበት የወዳጅነት ጨዋታ ለዲያዝ ጥሪ አድርገውለታል። እ.አ.አ መጋቢት 22 ቀን 2024 ሞሮኮ አንጎላን 1 ለ 0 ባሸነፈችበት ጨዋታ ለብሔራዊ ቡድኑ የመጀመሪያ ጨዋታውን አድርጓል። እ.አ.አ ጥቅምት 6 ቀን 2024 ሞሮኮ ለ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ከጋቦን ጋር ባደረገችው ጨዋታ 4 ለ 1 ስታሸንፍ የመጀመሪያ ግቡን ለሞሮኮ ማስቆጠር ቻለ። እ.አ.አ ሕዳር 15 ቀን 2024 ሞሮኮ በማጣሪያው ጋቦንን 5 ለ 1 ስትረታ ሁለት ግቦችን ከመረብ ላይ ማሳረፍ ችሏል። ከሶስት ቀናት በኋላ ሞሮኮ ከሌሴቶ ጋር ባደረገችው የአፍሪካ ዋንጫ የመጨረሻ የማጣሪያ ጨዋታ 7 ለ 0 ስታሸንፍ ሶስት ግቦችን በማስቆጠር በሀገሩ ማልያ የመጀመሪያ ሀትሪኩን ሰርቷል። እ.አ.አ ጥቅምት 2025 ሞሮኮ ራባት ላይ ኮንጎ ሪፐብሊክን 1 ለ 0 በማሸነፍ በስፔን ከዚህ ቀደም በብሔራዊ ቡድን ደረጃ ተይዞ የነበረውን 15 ተከታታይ ጨዋታዎችን የማሸነፍ ክብረ ወሰን በመስበር ወደ 16 ማድረስ ችላለች። በዚህ ታሪካዊ ጨዋታ ላይ ዲያዝ ተሰልፎ ተጫውቷል። የሞሮኮ ተከታታይ የማሸነፍ ጉዞ 19 ጨዋታዎች ደርሶ የነበረ ሲሆን በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ከማሊ ጋር አንድ አቻ ስትለያይ አብቅቷል። ሞሮኮ ለ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በማጣሪያ ብታልፍም አስቀድማ ውድድሩን እንድታዘጋጅ እድል አግኝታ የነበረው ጊኒ በዝግጅት ማነስ ምክንያት በአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ከሁለት ዓመት በፊት አዘጋጅነቷ ተነጥቆ ለሞሮኮ ተሰጥቷል። ሞሮኮ የዘንድሮውን ውድድር በደማቅ ሁኔታ እያካሄደች ትገኛለች። በውድድሩ ላይ ጎልተው ከታዩ ተጫዋቾች መካከል ብራሂም ዲያዝ ተጠቃሽ ነው። በአፍሪካ ዋንጫው እስከ አሁን ባደረጋቸው አምስት ጨዋታዎች አምስት ግቦችን አስቆጥሯል። በተሰለፈባቸው በእያንዳዱ ጨዋታዎች ጎሎችን ከመረብ ላይ አሳርፏል። ለሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን በአምስት የአፍሪካ ዋንጫ ተከታታይ ጨዋታዎች ግብ ያስቆጠረ የመጀመሪያው ተጫዋች በመሆን አዲስ ታሪክ ጽፏል። ሞሮኮ በሩብ ፍጻሜው ማሊን 2 ለ 0 ስታሸንፍ የመጀመሪያውን ጎል አስቆጥሯል። ሀገሩ ወደ ግማሽ ፍጻሜ እንድታልፍ ትልቅ ሚና ተጫውቷል። የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱንም እየመራ ይገኛል። ሞሮኮ በዚሁ ግስጋሴዋ ከቀጠለች ዲያዝ የውድድሩ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ እና ኮከብ ተጫዋች የመሆን እድሉ ሰፊ ነው። ሞሮኮ በግማሽ ፍጻሜው ከናይጄሪያ ጋር ረቡዕ ጥር 6 ቀን 2018 ዓ.ም በፕሪንስ ሙላይ አብደላ ስታዲየም ታደርጋለች። ዲያዝ በዚህ ጨዋታ ላይ ልዩነት ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል። አንዳንድ የእግር ኳስ ተንታኞች ብራሂም ዲያዝ እ.አ.አ በ2026 ወጥነት ያለው ብቃት ማሳየት ከቻለ የአፍሪካ ኮከብ ተጫዋችነት ሽልማቱን የሚወስድበት የለም እያሉ ይገኛሉ። ሞሮኳውያን በተጫዋቹ ፍቅር ልባቸው ከንፏል። በየጨዋታው ዲያዝ ዲያዝ እያሉ ከፍተኛ ድጋፍ እና ሙገሳ እየሰጡት ይገኛሉ። እሱም በድንቅ ብቃቱ ምላሽ እየሰጣቸው ነው። በተወለደበት ማላጋ ከተማ የጀመረው የእግር ኳስ ሕይወት በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ የበለጠ አብቧል። የሞሮኮው አዲሱ ኮከብ ብራሂም ዲያዝ ቀጣይ የእግር ኳስ ሕይወት በስኬት እና በድል የደመቀ እንደሚሆን ከአሁኑ ድንቅ ብቃቱ ተነስቶ መናገር ይቻላል።