አርእስተ ዜና
የአፍሪካ አህጉራዊ የኃይል ቋት ስርዓትን የመፍጠር ግብ በትክክለኛ ምዕራፍ ላይ ይገኛል - የአፍሪካ ህብረት
Jul 3, 2025 38
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 25/2017(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ አህጉራዊ የኃይል ቋት ስርዓትን የመፍጠር ራዕይ በትክክለኛ ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ የአፍሪካ ህብረት አስታወቀ። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የመሰረተ ልማት እና ኢነርጂ ዳይሬክተር ካሙጊሻ ካዛውራ የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ ንግድ ቀጣና አካል የሆነው አህጉራዊ ነጠላ የኤሌክትሪክ ኃይል ገበያ ዘላቂ የኃይል ልማት ማረጋገጥን አላማ ያደረገ መሆኑን ለኢዜአ ገልጸዋል። የተቀናጀ የኤሌክትሪክ ኃይል ገበያ በመፍጠር በአፍሪካ በመኖሪያ ቤቶች፣ በንግድ ተቋማት እና ኢንዱስትዎች ዘላቂ፣ ተአማኒ፣ ተወዳዳሪ እና ተመጣጣኝ ኢነርጂ ማቅረብ እንደሚያስችል አመልክተዋል። በዚህ ረገድም የአፍሪካ ሀገራት ከጎረቤቶቻቸው ጋር ትስስር ለመፍጠር እየተገበሯቸው ያሉ ፕሮጀክቶችን አድንቀዋል። ኢትዮጵያ ከሱዳን፣ ጅቡቲ እና ኬንያ ጋር የፈጠረችው የኃይል መስተጋብር የአፍሪካ ነጠላ የኤሌክትሪክ ኃይል ትግበራ ማሳያ እንደሆነ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ የኃይል ቋት አካል መሆኗን ገልጸው ቋቱ ሀገራትን በማስተሳሰር ቁልፍ ሚና እየተጫወተ ነው ብለዋል ዳይሬክተሩ። ኬንያ ከታንዛንያ ጋር የኃይል ስርዓቷን ለማስተሳሰር እያከናወነች እንደምትገኝና ይህም በቀጣይ ከደቡባዊ አፍሪካ የኃይል ቋት የኤሌክትሪክ ግብይት ለማድረግ እንደሚያስችል ገልጸዋል። በቀጣይ የምስራቅ አፍሪካ የኃይል ቋትን ከደቡባዊ አፍሪካ የኃይል ቋት ጋር የማገናኘት እቅድ መያዙን ጠቁመዋል። እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ፤ አህጉራዊ ነጠላ የኤሌክትሪክ ኃይል ገበያው ውሃ፣ ፀሐይ፣ ንፋስ እና የታዳሽ ኃይሎችን ጨምሮ ለሁሉም የኃይል ምንጮች ትኩረት እና እውቅና የሚሰጥ ነው። የኃይል አማራጮቹ የአፍሪካ የኃይል ስርዓት ማስተር ፕላን አካል እንደሆኑ ገልጸው ይህም አህጉራዊ ነጠላ የኤሌክትሪክ ኃይልን እውን ለማድረግ የሚያስችል ቁልፍ ምሰሶ መሆኑን አመልክተዋል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ከአፍሪካ ልማት ባንክ እና የዓለም ባንክ ግሩፕ ጋር በመሆን በተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት “Mission 300” የተሰኘ ኢኒሼቲቭ ይፋ ያደረጉ ሲሆን ኢኒሼቲቩ ለአፍሪካውያን የኤሌክትሪክ ተደራሽነት ማስፋትን ያለመ ነው። ኢኒሼቲቩ እ.አ.አ በ2030 300 ሚሊዮን የአፍሪካ ዜጎችን በኤሌክትሪክ የማስተሳሰር ውጥን አለው ነው ያሉት ዳይሬክተሩ። የአፍሪካ ልማት ባንክ፣ የአውሮፓ ህብረት፣ የጀርመን መንግስት እና ሌሎች የልማት አጋሮች ለኢኒሼቲቩ ድጋፍ እያደረጉ እንደሚገኝ ጠቁመዋል። የአፍሪካ ነጠላ የኤሌክትሪክ ኃይል ገበያ በአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት የኢነርጂ ደህንነትን እና ዘላቂነትን ለማረጋገጥ እንዲሁም ተወዳዳሪነትን የማሳደግ እቅም እንዳለው ታምኖበታል። #Ethiopian_News_Agency #Ethiopia #ኢትዮጵያ #ኢዜአ
በቦረና ዞን እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች የአርሶና አርብቶ አደሩን ህይወት በተጨባጭ በመቀየር ላይ ይገኛሉ
Jul 2, 2025 87
አዲስ አበባ፤ሰኔ 25/2017(ኢዜአ):-በቦረና ዞን እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ስራዎች የአርሶና አርብቶ አደሩን ህይወት በተጨባጭ በመቀየር ላይ መሆናቸውን በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ከፍያለው ተፈራ ገለጹ። የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ እና የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በቦረና ዞን እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።   በጉብኝቱም በክላስተር እየለማ የሚገኝ የስንዴ ክላስተር፣ የቀበሌ አስተዳደር የስራ እንቅስቃሴ፣ የቦረና ከብቶች ማድለቢያ ቦታን ጨምሮ በግንባታ ላይ የሚገኘውን የቦረና ባህል ማዕከልን ጎብኝተዋል። በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ከፍያለው ተፈራ ጉብኝቱን አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ፤ በቦረና ዞን እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች የህብረተሰቡን ህይወት በተጨባጭ እየቀየሩ ይገኛሉ ብለዋል። በክላስተር እየለማ የሚገኘው የስንዴ ምርትም አካባቢው ላይ የስንዴ ምርታማነት እያደገ ለመሆኑ ማሣያ ነው ብለዋል። ዞኑ ከዚህ ቀደም ተከሰቶ ከነበረው ድርቅ በማገገም ምርታማነትን በተጨባጭ እያረጋገጠ እንደሚገኝም ጠቁመዋል። በኦሮሚያ ክልል በቅርቡ ተግባራዊ የተደረገው የቀበሌ አስተዳደር መዋቅር ህዝቡ በቅርበት አገልግሎት እንዲያገኝ ማስቻሉን ተናግረዋል። በቦረና ዞን ደረጃቸውን የጠበቁ የቀበሌ አስተዳደር ጽህፈት ቤቶች ወደ ስራ የገቡ ሲሆን፥ የአርብቶ አደሩን እንግልት በመቀነስ የመልካም አስተዳደር ችግሮች በፍጥነት እንዲቀረፉ ማስቻሉን ጠቁመዋል።   የቦረና ዞን ዋና አስተዳዳሪ አብዱልሰላም ዋሪዮ በበኩላቸው፥ በዞኑ ከሁለት ወራት በፊት በተጀመረው የክረምት ወራት የግብርና ልማት 135 ሺህ ሄክታር መሬት በተለያዩ የዘር ዓይነቶች መሸፈኑን ገልጸዋል። ከዚህ ውስጥም ከ56 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በክላስተር እየለማ መሆኑን ጠቅሰው፥ 5 ሺህ ሄክታር በስንዴ ምርት የተሸፈነ መሆኑን ጠቁመዋል። ስንዴ፣ ቦሎቄ፣ ጤፍ፣ ማሾ እና ሌሎችም ሰብሎችን ማልማት መቻሉን በመግለፅ፥ ከዚህም 1 ነጥብ 9 ሚሊዮን ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ ተናግረዋል። የቦረና ዞን አሁን ላይ በተሻለ ምርታማነት ላይ እንደሚገኝ አስረድተው፥ የአርብቶ አደሩ የስራ ባህል እየተቀየረ መሆኑን ጠቁመዋል።   በቦረና ዞን የድሬ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት ጃተኒ ቦሩ እና አብዱላሂ ቆዳ ስንዴን በክላስተር በማልማት ምርታማ በመሆን ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል። በመንግሥት በኩል ምርጥ ዘርን ጨምሮ የተለያዩ ግብዓት እየቀረበላቸው በመሆኑ ምርታማነትን እያሳደገልን ነው ብለዋል። በዱቡሉቅ ወረዳ አኖሌ ቀበሌ ነዋሪዎች ኖሌ ኮርማ እና ሮባ ጎዳና የቀበሌ አስተዳደር ከመኖሪያቸው በአቅራቢያ መቋቋሙ እንግልትን እንዳስቀረላቸው ተናግረዋል።    
በአማራ ክልል ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን በላይ ችግኞች ለተከላ ተዘጋጅተዋል
Jul 2, 2025 81
ባህርዳር ሰኔ 25/2017 (ኢዜአ) ፡-በአማራ ክልል ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን በላይ ችግኞች መዘጋጀታቸውን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው የተፈጥሮ ሃብት ልማትና አጠቃቀም ዳይሬክተር አቶ እስመለዓለም ምህረት፤ ለክረምቱ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተደረገውን አጠቃላይ ዝግጅት በተመለከተ ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል።   በማብራሪያቸውም በክልሉ ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርጋ ግብር ከ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን በላይ ችግኞች ለተከላ መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል። ከእነዚህ መካከል 20 ሚሊዮን የሚሆነው የቡና እና ለምግብነት የሚውሉ የተለያዩ የፍራፍሬ ችግኞች መሆናቸውንም ተናግረዋል። ለችግኝ ተከላው ቀደም ብሎ መሬት በመለየት የጉድጓድ ቁፋሮ እና ሌሎች አስፈላጊ ዝግጅቶች መደረጋቸውን አንስተው ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል አሻራውን ለማኖር እንዲዘጋጅ ጥሪ አቅርበዋል። የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ ልማት በሀገር አቀፍ ደረጃ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአዲስ አበባ በይፋ መጀመሩን ተከትሎ በአማራ ክልልም ተጀምሯል።   በክልሉ በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞንና በባህርዳር ከተማ አስተዳደር የችግኝ ተከላ መከናወኑን አስታውሰው በሌሎች አካባቢዎችም በተጠናከረ መልኩ ይቀጥላል ብለዋል። በምዕራብ ጎጃም ዞን የሰከላ ወረዳ አርሶ አደር ገደፋዬ ሞገስ እና በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን የጓጉሳ ወረዳ አርሶ አደር አለማሁ አድማስ፤ የተራቆቱ አካባቢዎችን በመትከልና በመንከባከብ የድርሻችንን ለመወጣት ተዘጋጅተናል ሲሉ ተናግረዋል። ጥቅሙን በአግባቡ በመረዳቸው በዘንድረው የክረምት ወቅትም የሚተክሏቸውን ችግኞች በባለቤትነት ተንከባክበው ለማሳደግ መዘጋጀታቸው አስታውቀዋል። በክልሉ ባለፈው ዓመት የክረምት ወቅት ከተተከሉት ከ1 ነጥብ 4 ቢሊዮን በላይ ችግኞች ከ82 በመቶ በላይ መፅደቁን ከቢሮው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
በሚቀጥሉት አስር ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የአገሪቱ አካባቢዎች ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ-ኢንስቲትዩቱ
Jul 2, 2025 54
አዲስ አበባ፤ሰኔ 25/2017(ኢዜአ):-በሚቀጥሉት አስር ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የአገሪቱ አካባቢዎች ብዙ ቦታዎች ላይ ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ። ኢንስቲትዩቱ ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው በሚቀጥሉት አስር ቀናት ለክረምት ዝናብ መፈጠር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ይበልጥ እየተስፋፉና እየተጠናከሩ ይቀጥላሉ። በደቡብ ምዕራብ፣ምዕራብ፣ሰሜን ምዕራብ፣ሰሜን፣ መካከለኛው እና ሰሜን ምስራቅ የአገሪቱ ክፍሎች ላይ የተሻለ የዝናብ መጠንና ሥርጭት እንደሚኖር አሃዛዊ የትንበያ መርጃዎች እንደሚያሳዩ ተጠቁሟል። በተለይ በደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ሰሜን ምዕራብና መካከለኛ የአገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ ብለዋል። አልፎ አልፎ በውሃ አካላትና አካባቢ በምዕራብ፣ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ እና መካከለኛው የአገሪቱ አካባቢዎች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚሊ ሜትር በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ሊኖራቸው እንደሚችል ገልጸዋል። በተወሰኑ አካባቢዎች ላይ ነጎድጓዳማና በረዶ አዘል ዝናብ እና የዝናቡ ጥንካሬም ለረጅም ሰዓታት ያለማቋረጥ ዝናብ ሊኖር እንደሚችል በመግለጫው ተመላክቷል። በክረምቱ ወቅት የሚዘንበው ዝናብ በአመዘኙ አዎንታዊ ሚና የሚኖረው መሆኑ ተገልጿል። ይህም አስቀድሞ ለተዘሩ ሰብሎች፣ ለመኽር ሰብሎች፣ ለቋሚ ተክሎችና የጓሮ አትክልት የውሃ ፍላጎት ለማሟላት በኩል መልካም አጋጣሚ የሚፈጥር መሆኑ ተገልጿል። አብዛኛው የአገሪቱ ተፋሰሶች ላይ ከመጠነኛ እስከ ከፍተኛ የገጸ ምድር የውሃ ፍሰት ይኖራቸዋል፤ነገር ግን አልፎ አልፎ የሚኖረው ከባድ ዝናብ ጎርፍ ሊያስከትል ስለሚችል ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ ተመላክቷል። በሌላ በኩል በመጪው አስር ቀናት የቀኑ ከፍተኛ ሙቀት በአፋር፣ በምስራቅ አማራ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ምዕራብ እና ደቡብ ምስራቅ የአገሪቱ ሥፍራዎች ላይ ከ26 እስከ 41 ዲግሪ ሴልሺዬስ በላይ ሙቀት እንደሚኖራቸው ትንበያው ያሳያል።
የአየር ኃይል ሶስተኛ አየር ምድብ የስፖርት ውድድር ተጠናቀቀ
Jul 2, 2025 69
ድሬዳዋ፣ሰኔ 25/2017(ኢዜአ)፦በኢፌዴሪ አየር ኃይል ሶስተኛ አየር ምድብ ለሁለት ሳምንት ሲካሄድ የሰነበተው የስፖርት ውድድር ማምሻውን ተጠናቀቀ። በምድቡ ከሰኔ 11 ቀን 2017 ጀምሮ በተለያዩ የስፖርት አይነቶች ሲካሄድ የሰነበተው ውድድር ዛሬ ማምሻውን በተደረገ የእግር ኳስ ጨዋታ ተጠናቋል ። በወንዶች በተካሄደው የፍፃሜ ጨዋታ የሶስተኛ አየር ምድብና የሆርሞድ ጤና ቡድን መደበኛውን የጨዋታ ጊዜ ያለምንም ጎል ተለያይተዋል። አሸናፊውን ለመለየት በተሰጡ የፍፁም ቅጣት ምቶች ሆሮሞድ አራት ለአንድ በሆነ ውጤት አሸናፊ ሆኗል። ከወንዶች እግር ኳስ በተጨማሪም በምድቡ የተለያዩ ክፍሎች መካከል የአትሌቲክስ፣ የመረብ ኳስ ፣የእጅ ኳስና ሌሎች ውድድሮች በሁለቱም ፆታ የተካሄዱ ሲሆን ለአሸናፊዎቹ ሽልማት ተበርክቷል። ለአሸናፊዎች የተዘጋጀውን የዋንጫና ሌሎች ሽልማቶች የሰጡት የኢፌድሪ አየር ኃይል ሶስተኛ ምድብ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ደረጀ ቡሽሬ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ናቸው። ዋና አዛዡ ኮሎኔል ደረጀ ቡሽሬ በወቅቱ እንደተናገሩት፥ ስፖርት የሠራዊቱን አካላዊ ብቃትና ስነ ልቦናዊ ጥንካሬ በማዳበር የትኛውንም ግዳጅ በታላቅ ብቃት እንዲወጣ እያገዘ ይገኛል ። እየተጠናቀቀ በሚገኘው በጀት አመት ምድቡ በተለያዩ ተልዕኮዎቹ ውጤታማ ተግባራት ማከናወኑንም ጠቅሰዋል። በውድድሩ የከተማው አምስት የጤና ቡድኖች መሳተፋቸው ሠራዊቱ ከማህበረሰቡ ጋር ያለውን ሁለንተናዊ ትስስር እንዲጠናከር አጋጣሚ የተፈጠረበት መሆኑን አንስተዋል ። ዛሬ ማምሻውን በተካሄደው የፍፃሜ ጨዋታ የከተማው የስፖርት ቤተሰቦች በስፍራው ተገኝተው ውድድሩን ተመልክተዋል።
የሚታይ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ፖርቹጋል ፖርቶ አዲስ በረራ ጀመረ
Jul 2, 2025 89
አዲስ አበባ፤ሰኔ 25/2017(ኢዜአ):-የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ፖርቹጋል ፖርቶ አዲስ በረራ ጀምሯል። አየር መንገዱ ወደ ፖርቶ በሣምንት አራት ጊዜ በረራ እንደሚያደርግ ተገልጿል። አየር መንገዱ ወደ ፖርቹጋል ፖርቶ ከተማ የሚያደርገውን በረራ አስመልክቶ ዛሬ ማምሻውን የማስጀመሪያ መርኃ ግብር ተከናውኗል። በመርኃ ግብሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው፣ በኢትዮጵያ የፖርቹጋል አምባሳደር ልዊሳ ፍራጎሶ እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው በዚሁ ጊዜ፥ አየር መንገዱ ወደ ፖርቶ የሚያደርገው በረራ ፖርቹጋልን ከአፍሪካ ጋር ለማስተሳሰር እንደሚያግዝ ተናግረዋል። ወደ አውሮፓ ለሚጓዙ መንገደኞች የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችለውም ነው የገለጹት። በኢትዮጵያ የፖርቹጋል አምባሳደር ልዊሳ ፍራጎሶ በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያ እና ፖርቹጋል ረዥም ዘመናትን ያስቆጠረ ወዳጅነት እንዳላቸው ተናግረዋል። አየር መንገዱ ወደ ፖርቶ የጀመረው በረራም የሀገራቱን ወዳጅነት በኢኮኖሚና ህዝብ ለህዝብ ትስስር ለማጠናከር እንደሚያግዝም አውስተዋል። አየር መንገዱ ዛሬ ያስጀመረውን በረራ ጨምሮ ከ145 በላይ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎችን እየሸፈነ ይገኛል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2035 ዓመታዊ ገቢውን ወደ 25 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ለማድረግና በዓመት 67 ሚሊዬን መንገደኞችን ለማጓጓዝ ራዕይ አስቀምጦ እየሰራ ይገኛል።
ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የምግብና መድሃኒት ደህንነትና ጥራት ምርመራ አቅም እየገነባች ነው-ዶክተር መቅደስ ዳባ
Jul 2, 2025 79
አዲስ አበባ፤ሰኔ 25/2017(ኢዜአ):-ኢትዮጵያ ደህንነቱ የተረጋገጠ የመድሀኒትና የምግብ አቅርቦትን ለማስፋት ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ ላብራቶሪና የጥራት ምርመራ ስርዓትን እያስፋፋች መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ገለጹ። የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን ከዓለም አቀፍ አክሪዲቴሽን ቦርድ አይሶ 17025/2012 በመድሃኒት ጥራት ምርመራና የህክምና መገልገያ መሳሪያ ጥራት ምርመራ ያገኘውን እውቅና ይፋ አድርጓል።   የእውቅና መርሃ-ግብሩን አስመልክቶ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ባስተላለፉት መልእክት መንግስት ጥራቱን የጠበቀ የጤና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ በርካታ ተግባራት እያከናወነ ነው ብለዋል። እንዲሁም ደህንነቱ የተረጋገጠ የመድሃኒትና የምግብ አቅርቦትን ለማስፋት እና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ ላብራቶሪና የጥራት ምርመራ ስራም የትኩረት አቅጣጫ ተሰጥቶታል ነው ያሉት። በዚህም ውጤት መመዝገቡን ያነሱት ሚኒስትሯ በሀገሪቱ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪና ተአማኒ የሆኑ የህክምና መሳሪያና የምግብ ምርመራ ስርዓትን መዘርጋት እንደተቻለ አስታውቀዋል። ይህም በህክምናው ዘርፍ የነበሩ ጉድለቶችን ለማረምና ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት ለመስጠት አስቻይ ሁኔታን መፍጠሩን አመልክተዋል። የተፈጠረው አስቻይ ሁኔታ በጤናው ዘርፍ እየተመዘገበ ያለውን ሀገራዊ ስኬት ለማስቀጠል አይነተኛ ሚና እንዳለው ሚኒስትሯ ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን የተሰጠው እውቅና በዘርፉ ለጥራት ፍተሻ የተሰጠውን ትኩረት የሚያረጋግጥ መሆኑን አንስተዋል፡፡ በቀጣይም ይህን መሠል የጥራት ፍተሻ ስራ ለጤናው ዘርፍ ውጤታማነት ወሳኝ በመሆኑ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል ብለዋል።   የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሔራን ገርባ በበኩላቸው፥ ተቋሙ የተለያዩ የለውጥ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ለህብረተሰቡ የሚቀርቡ የምግብና ጤና ግብአቶች ጥራት፣ የቁጥጥር ስራውን በቴክኖሎጂ መደገፍና የሰው ኃይል ልማት ስራ በሪፎርሙ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት መሆናቸውን አንስተዋል። የተካሄደው ሪፎርም ኢትዮጵያ በዘርፉ የአፍሪካ የልህቀት ማእከል እንድትሆን የሚደረገውን ጥረት የሚያግዝ ስለመሆኑ አብራርተዋል። በቅርቡ ከዓለም አቀፍ አክሪዲቴሽን ቦርድ አይሶ 17025/2012 በመድሀኒትና በህክምና መሳሪያ ደህንነትና ጥራት ቁጥጥር እውቅና መገኘቱ ለተሻለ ትጋትና ስራ የሚያነሳሳ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
40 የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ባለሙያዎች ዓለም አቀፍ የምስክር ወረቀት አገኙ
Jul 2, 2025 110
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 25/2017(ኢዜአ)፦ በአቪዬሽን ሴኪዩሪቲ ጥራት ቁጥጥርና አደጋ አስተዳደር የሰለጠኑ 40 የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ባለሙያዎች ዓለም አቀፍ የምስክር ወረቀት ማግኘታቸውን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አስታወቀ። አገልግሎቱ ለኢዜአ በላከው መረጃ እንዳመለከተው፤ በኢትዮጵያ አጠቃላይ የአቪዬሽን ሴኪዩሪቲ ስራዎችን በበላይነት ለመምራት በአዋጅ ኃላፊነት የተሰጠው ተቋሙ ከዓለም አቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት (ICAO) ጋር በመተባበር በአቪዬሽን ሴኪዩሪቲ ጥራት ቁጥጥርና በአቪዬሽን አደጋ አስተዳደር ዙሪያ ስልጠና የወሰዱ 40 ባለሙያዎች ዓለም አቀፍ የምስክር ወረቀት እንዲያገኙ ማድረጉን ገልጿል። የዓለም አቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ከ12 ዓመታት በኋላ በኢትዮጵያ የአቪዬሽን ሴኪዩሪቲ አሰራሮች ላይ ባደረገው ኦዲት ሀገራችን ምንም ዓይነት የሴኪዩሪቲ ስጋት እንደሌለባት ማረጋገጡን አስታውሷል። ይህን ተከትሎም ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የሲቪል አቪዬሽን ደኅንነት ዋና መምሪያ ጋር በተፈጠረው መልካም ግንኙነትና ትብብር ስልጠናው ከዓለም አቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት በመጡ ባለሙያዎች ከሰኔ 9 እስከ ሰኔ 24 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ተሰጥቷል። ዓለም አቀፍ የምስክር ወረቀቱ አየር መንገዱ ተደራሽ በሚሆንባቸው ሀገራት ሁሉ የአቪዬሽን ሴኪዩሪቲ የጥራት ቁጥጥር ተግባራትን ለማካሄድ የሚያስችል መሆኑን የገለጹት ከዓለም አቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት የመጡት አሰልጣኞች፤ ባለሙያቹ ስልጠናውን በስኬት ማጠናቀቃቸውን ጠቁመዋል። ስልጣኞች ያገኙት ዕውቀት ተቋሙ ሀገራዊ ተልዕኮውን በላቀ ብቃት ለመፈፀም የሚያስችለው ከመሆኑም ባለፈ፤ ኢትዮጵያን ለአቪዬሽን ደህንነት ዘርፍ እየሰጠች ያለችው ልዩ ትኩረት ጉልህ ማሳያ ተደርጎም ሊወሰድ እንደሚችል የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አመልክቷል። የአቪዬሽን ደህንነት ጠንካራ የጥራት ቁጥጥር ትግበራ እና የአደጋ ምላሽ አሰጣጥ ዝግጁነት የእያንዳንዱ የዓለም አቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት አባል ሀገራት ኃላፊነት መሆኑን ያስታወቀው አገልግሎቱ ፤ ይህም የአቪዬሽን ኢንዱስትሪውን ደኅንነት በዓለም አቀፍ ስታንዳርድ መሰረት ለማረጋገጥ እንደሚያስችል ገልጿል፡፡ በስልጠናው የተገኘውን ዕውቀት፣ ክህሎት እና የአስተሳሰብ ለውጥ በቀጣይ በአቪዬሽን ደህንነት ዘርፍ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለመሆን ለተያዘው ራዕይ እና አጠቃላይ ተቋማዊ ስትራቴጂ ግብዓት አድርጎ በማዋል የኢትዮጵያ አየር መንገድን ተመራጭነት ይበልጥ በማሳደግ ሀገራዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ፋይዳ እንደሚኖረው አገልግሎቱ ለኢዜአ በላከው መረጃ አስታውቋል።
በመዲናዋ የስድስተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 95 በመቶው ወደ ቀጣይ ክፍል ተሸጋግረዋል
Jul 2, 2025 74
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 25/2017(ኢዜአ)፦ በመዲናዋ በ2017 ዓ.ም የስድስተኛ ክፍል ከተማ አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ከ75 ሺህ በላይ የሚሆኑት ወደ ቀጣዩ ክፍል መሸጋገራቸውን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ። የፈተና ውጤቱን ይፋ መደረግ አስመልክቶ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) መግለጫ ሰጥተዋል። ኃላፊው በመግለጫቸው በትምህርት ዘመኑ 79 ሺህ 34 ተማሪዎች የስድስተኛ ክፍል ከተማ አቀፍ መልቀቂያ ፈተናውን መውሰዳቸውን ገልጸዋል። ፈተናውን ከወሰዱት ተማሪዎች መካከል 75 ሺህ 85 ወይም 95 በመቶ የሚሆኑት 50 እና ከዚያ በላይ አማካይ ውጤት በማስመዝገብ ወደ ቀጣዩ የክፍል ደረጃ መሸጋገራቸውን አመላክተዋል። ከተማ አስተዳደሩ ለትምህርት ዘርፉ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ ሲሰራ መቆየቱን አመልክተው፥ ይህም ለውጤቱ መገኘት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ተናግረዋል። ተፈታኝ ተማሪዎች ከዚህ በታች የተቀመጡ ማስፈንጠሪያዎችን በመጠቀም ከዛሬ ጀምሮ ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ ተገልጿል። ሊንክ https://aa6.ministry.et/#/result እና የቴሌግራም ቦት @emacs_ministry_result_qmt_bot

Pulse Of Africa

POA English

POA English

Pulse Of Africa - English Language

Your news, current affairs and entertainment channel

Join us on

POA Arabic

POA Arabic - عربي

Pulse Of Africa - Arabic Language

قناتكم الاخبارية و الترفيهية

Join us on

ፖለቲካ
ሰላምና ልማት ፀንቶ እንዲቀጥል የደሴ ከተማ ነዋሪ ሕዝብ በሰልፍ የሰጠው ድጋፍ የሚበረታታ ነው
Jul 2, 2025 89
ደሴ ፤ ሰኔ 25/2017(ኢዜአ)፡- የደሴ ከተማ ነዋሪ ሕዝብ የአካባቢው ሰላምና ልማት ፀንቶ ይበልጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል በሰልፍ የሰጠው ድጋፍ የሚበረታታ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ሰላምና ደህንነት መምሪያ አስታወቀ፡፡ ሰላምና ልማትን የሚደግፍ እንዲሁም ፅንፈኝነትን የሚያወግዝ ሕዝባዊ ሰልፍ ባለፈው እሁድ በደሴ ከተማ መከሄዱ ይታወቃል። የሰልፉ ተሳታፊ ነዋሪ ሕዝብ በወቅቱ የመንግስትን የልማት እቅዶች በመደገፍና የሰላም ጥረቶች በማገዝ የድርሻውን እንደሚወጣ ገልጸዋል። ከምንም በላይ ሰላምና ልማታችንን አጥብቀን እንሻለን ሲሉም ባስተላለፉት መልዕክት አረጋግጠዋል።   የደሴና አካባቢው ሰላም አስተማማኝ የሆነው በሕዝቡ ትብብርና በፀጥታ አካላት ትጋት መሆኑንና ተጠናክሮ እንዲቀጥልም እንደሚደግፉም አመላክተዋል። ነዋሪው ሕዝብ በሰልፉ ያስተላለፈውን መልዕክት አስመልክቶ ኢዜአ ያነጋገራቸው የደሴ ከተማ ሰላምና ደህንነት መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ሰይድ የሱፍ ፤ የከተማው ሕዝብ ባካሄደው ሰልፍ ልማትን በመደገፍና ፅንፈኝነትን በማውገዝ ሰላምን ለማፅናት ከመንግስት ጎን የተሰለፈ መሆኑን ማረጋገጡን ተናግረዋል።   በተለይ መንግስት አስተማማኝ ሰላም ያስፈን፣ ህግ ያስከብር፣ ያለ ስጋት ወጥተን እንግባ፣ ልማታችን ተጠናክሮ ይቀጠል፣ ልጆቻችን ይማሩ የሚሉ መልዕክቶችን ማስተላለፉ አመራሩ ይህንን በቁርጠኝነት ለማስፈፀም ይበልጥ ያነሳሳው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በቀጣይም ሕብረተሰቡን በሚካሄዱ የሰላም ማስፈን ስራዎች በንቃት በማሳተፍ በሰላምና ልማት ላይ የበኩሉን እንዲወጣ የሚያበረታቱ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል። በድጋፍ ሰልፉ ለተነሱ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት የከተማ አስተዳደሩ ከመቼውም ጊዜ በላይ ቁርጠኛና ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡ ከአጎራባች ዞኖችና ወረዳዎች ጋር በቅንጅት በመስራት ህግ የማስከበር ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡  
በድጋፍ ሰልፉ ሕዝቡ ያስተላለፈው መልዕክት አመራሩ ለዘላቂ ሰላምና ልማት በቁርጠኝነት ይበልጥ እንዲተጋ መነሳሳትን የፈጠረ ነው
Jul 2, 2025 101
ጎንደር፤ ሰኔ 25/2017(ኢዜአ)፡- በድጋፍ ሰልፉ ሕዝቡ ያስተላለፈው መልዕክት እና የሰጠው እውቅና አመራሩ ለዘላቂ ሰላም መፅናትና ልማት ቀጣይነት ከፊት ሆኖ በመምራት በቁርጠኝነት ይበልጥ እንዲተጋ መነሳሳትን የፈጠረ ነው ሲሉ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ተናገሩ፡፡ በቅርቡ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ሰላምን የሚደግፍና ፅንፈኝነትን የሚያወግዝ ሕዝባዊ ሰልፍ መካሄዱ ይታወሳል፡፡ ሕዝባዊ ሰልፉ ከተካሄደባቸው መካከል ጎንደር ከተማ አንዱ ሲሆን፤ የሰልፉ ተሳታፊ ነዋሪዎች በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ጎንደር በከፍተኛ የልማት ሥራ ላይ እንደምትገኝ በማመልከተ ሰላሙንና ልማቱን ለማስቀጠል ከመቼውም ጊዜ በላይ ቁርጠኞች እንደሆኑ ተናግረዋል። ከተማዋ ያገኘችው ዘርፈ ብዙ የልማት እድሎች ለህዝቡ የዘመናት የልማት ጥያቄ መሰረታዊ ምላሽ የሚሰጡ በመሆናቸው ለሰላም ዘብ በመቆም ልማቱን ለማስቀጠል የድርሻቸውን ለማበርከት መዘጋጀታቸውን አረጋግጠዋል፡፡ ይህንን አስመልክቶ ኢዜአ ያነጋገራቸው የጎንደር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ደብሬ የኋላ እንደገለጹት፤ ሕዝቡ የሰላሙም የልማቱም ባለቤት በመሆን ያበረከተው አስተዋጽኦ ለከተማው ሰላም መረጋገጥና ለልማቱ ስኬታማነት የጎላ ፋይዳ አለው፡፡   ጎንደር ታሪኳን ያደሰ አቧራዋንም ያራገፈ ውበቱዋንም የገለጠ የልማት፣ የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም ተግባራት እየተከናወኑ ስለመሆኑ በድጋፍ ሰልፉ ሕዝቡ ለመንግስት እውቅና የሰጠበት ታሪካዊ ዕለት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ''ሕዝቡ ሰላምና ልማትን አጥብቆ እንደሚሻና ይህን ለማደናቀፍ የሚሹ የጥፋት ተላላኪዎችን እንደሚያወግዝ ጥብቅ መልዕከት አስተላልፏል'' ያሉት ምክትል ከንቲባዋ፤ አመራሩ ከመቼውም ጊዜ በላይ ሕዝቡን ለማገልገል ዝግጁ እንዲሆን ያደረገም ነው ብለዋል፡፡ የከተማው ነዋሪ ሕዝብ በራሱ ተነሳሽነት በመኖሪያ አካባቢው እራሱን በማደራጀት ሰላሙን ለማረጋገጥ የወሰዳቸው እርምጃዎች ሰላም ፈላጊነቱንና ቁርጠኝነቱንም በድጋፍ ሰልፉ ማረጋገጡን ተናግረዋል፡፡ የመንግስት ህግን የማስከበር ተግባር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሕዝቡ በድጋፍ ሰልፉ ያስተላለፈው መልዕክት ትልቅ ትርጉም አለው ያሉት ምክትል ከንቲባዋ፤ የፀጥታ መዋቅሩ ሕዝቡ የሰጠውን ተልዕኮና ሃላፊነት በብቃት እንዲወጣ ያደረጋል ሲሉ ገልጸዋል፡፡ በፌዴራሉና በክልሉ መንግስት ድጋፍ በከተማው የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶች ለሕዝቡ ፍትሃዊ የመልማት ጥያቄ አጥጋቢ ምላሽ የሚሰጡ መሆናቸውን ጠቁመው፤ አመራሩ እነዚህ የልማት ፕሮጀክቶች ለፍጻሜ እንዲበቁ ሌት ተቀን ለመስራት ዝግጁ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢንሼቲቭና አመራር ሰጪነት በከተማው እየተካሄዱ የሚገኙት የኮሪደር ልማት ስራ፤ የአጼ ፋሲል አብያተ መንግስት እድሳትና ጥገና እንዲሁም የመገጭ የመስኖና የመጠጥ ውሃ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ሕዝቡ አዎንታዊ ድጋፍ ከሰጣቸው የልማት ስራዎች ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል፡፡ ሕዝቡ ልማቱን አጥብቆ ከመደገፍ አንጻር የኮሪደር ልማት ስራው ስኬታማ እንዲሆን በገንዘቡ፣ በእውቀቱና በጉልበቱ ጭምር ላበረከተው አስተዋጽኦ ከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ እውቅና የሚሰጠው መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ በውጭና በሀገር ውስጥ የሚገኙ የአካባቢው ተወላጆችና ባለሀብቶች ጭምር ከተማ አስተዳደሩ ባዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ ቴሌቶን በመሳተፍ ልማቱን በገንዘብ ለመደገፍ ያሳዩት ተሳትፎም ጎንደር ወደ ቀደመ ገናና ታሪኳና ስሟ እንድትመለስ በር የከፈተ ነው ሲሉ አውስተዋል፡፡ የድጋፍ ሰልፉ አመራሩ በጊዜ የለኝም መንፈስ የሕዝቡን ጥያቄዎች ለመመለስ በላቀ ፍጥነትና ጥራት እንዲሁም ቁርጠኝነት በተግባር በማስመስከር ሀገርና ሕዝብን የማሻገር ታሪካዊ ሃላፊነቱን እንዲወጣ ታላቅ የቤት ስራ የሰጠ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ባለፈው እሁድ ጎንደር ከተማን ጨምሮ በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች በተካሄዱት ሰልፎች ሕዝቡ ከያዛቸው መፈክሮች መካከል "ክልላችንን የሰላምና የልማት ማዕከል ለማድረግ እንረባረባለን፤ ለሠላም ዘብ እንቆማለን፣ ፅንፈኝነትን እናወግዛለን፣ መንግስት ህግን በማስከበር የዜጎችን ሠላም ሊያስጠብቅ ይገባል የሚሉ ይገኙበታል፡፡
በሞባይል ባንኪንግ ማጭበርበር ወንጀል የተሳተፉ ከ80 በላይ ዋነኛ ወንጀለኞች በሕግ ተጠያቂ ተደርገዋል
Jul 1, 2025 161
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 24/2017(ኢዜአ)፦ በሞባይል ባንኪንግ ማጭበርበር ወንጀል የተሳተፉ ከ80 በላይ ዋነኛ ወንጀለኞችን በሕግ ተጠያቂ ማድረጉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ። የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ ዘርፍ የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም እና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት ተካሂዷል። የወንጀል ምርመራ የኦፕሬሽን ዋና መምሪያ ኃላፊና የወንጀል ምርመራ ቢሮ ኃላፊ ተወካይ አቶ ሙሊሳ አብዲሳ በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ ተግባራትን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በሙስና፣ በህገ ወጥ የሰዎችና የጦር መሳሪያ ዝውውር፣ በኮንትሮባንድና አደንዛዥ ዕጽ ዝውውር የተጠረጠሩ ሰዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል በህግ ተጠያቂ መደረጋቸውን አስታውቀዋል። ኮሚሽኑ ሕግን ለማስከበር በወሰደው እርምጃ 1 ሺህ ተጠርጣሪዎች ላይ የተለያየ መጠን ያለው የቅጣት ውሳኔ መተላለፉን አንስተዋል። በሞባይል ባንኪንግ ማጭበርበር የተሳተፉ ተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ በማድረግና የምርመራ መዝገብ በማጠናቀቅ ለጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ቀርቦ ክስ እንዲመሰረትባቸው መደረጉን ተናግረዋል። እነዚህ ተጠርጣሪዎች ሀሰተኛ መታወቂያና በርካታ ሲም ካርዶችን በመጠቀም፣ ሆቴሎችና ማረፊያ ቤቶችን በመከራየት ዜጎችን በማጭበርበር ላይ ተሰማርተው የነበሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል። በዚህም በድርጊቱ ላይ የተሳተፉ ከ80 በላይ ዋነኛ ወንጀለኞች ላይ ምርመራ አድርጎ ክስ በመመስረት ወደ ማረሚያ ቤት እንዲወርዱ መደረጉንም አብራርተዋል። ከሀገር ውስጥና ከውጭ ኃይሎች ጋር በማበር በሽብር ወንጀል የተሳተፉ ተጠርጣሪዎችን ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት እንዲሁም ከመከላከያ ሰራዊት ጋር በመሆን ለሕግ የማቅረብ ሥራ መከናወኑንም አስረድተዋል። በዚህም ከ450 በላይ ተጠርጣሪዎች በሰነድና በሰው ማስረጃ በማጣራት ክስ እንዲመሰረትባቸው የተደረገ ሲሆን በህግ ተጠያቂ መሆናቸውንም ገልጸዋል። በኮንትሮባንድና ሕገ ወጥ ጦር መሳሪያ ዝውውር ላይ የተሳተፉ 143 ተጠርጣሪዎች ለሕግ መቅረባቸውን ጠቁመው ካናቢስ፣ ኮኬይንን ጨምሮ የተለያየ መጠን ያላቸው አደንዛዥ ዕጾች ዝውውር ወንጀል የተሳተፉ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ውለው ተጠያቂ ተደርገዋል ብለዋል። እንደ ኃላፊው ገለጻ በበጀት ዓመቱ ከ6 ሺህ በላይ የምርመራ መዝገቦች ምርመራ ተጠናቆ ለፍትህ ሚኒስቴር የተላከ ሲሆን በዚህም በሀገርና በህዝብ ላይ ጉዳት በማድረስ የተጠረጠሩ ግለሰቦች ተጠያቂ እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። አቶ ሙሊሳ አክለውም በዘረ መል/DNA/ ምርመራ ዘርፍም ከ300 በላይ የምርመራ ጉዳዮች መቅረባቸውን አስታውሰው ወቅቱንና ጥራቱን በጠበቀ መልኩ ምርመራ ተከናውኖ የተገኘው ውጤት ለሚመለከተው አካል ተደራሽ ተደርጓል ብለዋል። አጭበርባሪዎች ከባንክ የተደወለ በማስመሰል እያጭበረበሩ መሆኑን የገለጹት ሃለፊው ከባንክ ተደውሎ የሚሰጥ ምንም ዓይነት የባንክ አገልግሎት እንደሌለ ዜጎች ሊገነዘቡ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል። ዜጎች የሚስጥር ቁጥራቸውን ለሶስተኛ ወገን አሳልፈው መስጠት የለባቸውም ያሉት አቶ ሙሊሳ ህብረተሰቡ የአጭበርባሪዎች ሰለባ እንዳይሆን ሊጠነቀቅ እንደሚገባ አመልክተዋል።
ክልሉን የሰላም፣ የልማትና የመቻቻል ተምሳሌት ለማድረግ በተከናወኑ ተግባራት የተገኙ ውጤቶችን ማስቀጠል ይገባል - አቶ አደም ፋራህ
Jul 1, 2025 128
ወላይታ ሶዶ ፤ሰኔ 24/2017 (ኢዜአ)፡-የደቡብ ኢትዮጵያ ክልልን የሰላም፣ የልማትና የመቻቻል ተምሳሌት ለማድረግ በተከናወኑ ተግባራት የተገኙ ውጤቶችን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ሲሉ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ ገለጹ። ''ጠንካራ ክልላዊ አንድነትና አብሮነት ለዘላቂ ሠላምና ብልጽግና" በሚል መሪ ሃሳብ ክልል አቀፍ የሠላም፣ የልማት እና የአንድነት ኮንፈረንስ በወላይታ ሶዶ ከተማ ተካሄዷል።   በወቅቱም አቶ አደም ፋራህ እንዳሉት፤ በክልሉ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ዘርፎች እየተመዘገበ ያለውን ውጤት አጠናክሮ ለማስቀጠል ተደጋግፎ መስራት ይገባል። ኮንፈረንሱ በክልሉ ሰላም፣ ልማትና አንድነት ላይ አዎንታዊ ለውጥ በማምጣትና የህዝቡን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ የመልካም አስተዳደር ጉዳዮችን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ የሚያግዝ መሆኑንም ጠቁመዋል። በቀጣይ ጊዜያት ከፋፋይ ትርክቶችን በማስወገድ በመደመር ዕሳቤ ወንድማማችነት እና እህትማማችነትን አጠናክሮ በማስቀጠል የብልጽግና ጉዞን ማፋጠን ያስፈልጋል ብለዋል። የጋራ ማንነትን የሚያጎለብቱ ህብረ-ብሔራዊነትን ለማረጋገጥ ያለፈውን ቅሬታ በይቅርታ አልፎ ለወደፊት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል። ጠንካራ ክልላዊ ተቋማትን ፈጥሮ በብቁ አመራር እንዲመሩ በማድረግ ብልሹ አሰራርን እና ሙስናን የሚጸየፍ ትውልድ መፍጠር እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል። የተለያዩ የልማት ኢኒሼቲቮችን ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር የክልሉን ብልጽግና ለማረጋገጥ መትጋት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።   የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ በበኩላቸው ከክልሉ ምስረታ ማግስት ጀምሮ አብሮነትን የሚያጸኑ የጋራ ትርክቶችን ለማስረጽ የተሰራው ስራ ውጤት ማስመዝገቡን ተናግረዋል። ክልሉ ካለው የመልማት አቅም አንፃር ያልተሻገርናቸው በርካታ ነገሮች አሉ ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በሁሉም መስክ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ መትጋት እንደሚገባ አሳስበዋል። ''ጠንካራ ክልላዊ አንድነትና አብሮነት ለዘላቂ ሠላምና ብልጽግና" በሚል መሪ ሃሳብ በወላይታ ሶዶ ከተማ ሲካሄድ የቆየው ክልል አቀፍ የሠላም፣ የልማት እና የአንድነት ኮንፈረንስ ዛሬ ተጠናቋል።
ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ የሥራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ የሦስት አገራት አምባሳደሮችን አሰናበቱ
Jun 30, 2025 243
አዲስ አበባ፤ሰኔ 23/2017(ኢዜአ)፦የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ በኢትዮጵያ የሥራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ የካናዳ፣የስዊዲንና የሳኡዲ አረቢያ አምባሳደሮችን አሰናበቱ። ፕሬዝዳንቱ ያሰናበቱት የካናዳ አምባሳደር ጆሽዋ ታባህ፣የስዊድን አምባሳደር ሃንስ ሄንሪክና የሳኢዲ አረቢያ አምባሳደር ፋሃድ አልሁማያዳኒ (ዶ/ር) ናቸው። ፕሬዝዳንት ታዬ ሦስቱም አምባሳደሮቹ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከአገራቱ ጋር በተለያዩ መስኮች የሁለትዮሽ ግንኙነትና ትብብር እንዲጠናከር ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።   በተለይም የንግድና የኢንቨስትመንት ግንኙነት እንዲሳለጥ እንዲሁም በሌሎች የልማት የትብብር ዘርፎች ግንኙነቱ እንዲጠናከር ላደረጉት አስተዋጽዖም ምስጋናቸውን አቅርበዋል። አምባሳደሮቹ በሌሎች መስኮች ለአብነትም በመልሶ ማልማት ሥራዎች ጉልህ አስተዋጽኦ መደረጉን አንስተው፥ትብብሮች በቀጣይም ሊጠናከር እንደሚገባ ጠይቀዋል። በቀጣይ በተለይም ውጤታማ የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቶች ይበልጥ ሊጠናከሩ እንደሚገባ ጥሪ ማቅረባቸውን ውይይቱን የተከታተሉት የፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አምባሳደር ትዝታ ሙሉጌታ ለኢዜአ ገልጸዋል። አምባሳደሮቹ በበኩላቸው፥ በኢትዮጵያ ቆይታቸው አገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር በርካታ ሥራዎች መሥራታቸውንና በዚህም አመርቂ ውጤት መገኙቱን ጠቅሰዋል። የካናዳ አምባሳደር ጆሽዋ ታባህ በቆይታቸው የካናዳና ኢትዮጵያን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ለማስፋት የሚያስችሉ ውጤታማ ሥራዎች መከናወናቸውን ጠቅሰዋል።   በተመሳሳይ የስዊድን አምባሳደር ሃንስ ሄንሪክ በቆይታቸው የኢትዮጵያ መንግሥት ቅድሚያ በሰጠባቸው መስኮች ትብብር በማድረግ አበረታች ሥራዎች ማከናወናቸውን አስረድተዋል። አምባሳደሮቹ በተለይም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች እየተዘመገቡ ያሉ ውጤቶች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውንና መሰል ሥራዎችን ሊያጠናክር እንደሚገባ ተናግረዋል። በቀጣይም ግንኙነቱ ይበልጥ እንዲጠናከር የበኩላቸውን አስተዋጽዖ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል።
በቀበሌ ደረጃ መንግስታዊ አገልግሎት ተደራሽ መደረጉ ቀልጣፋ አገልግሎት ከማስገኘቱ ባለፈ የልማት ተሳታፊነታችንን እያሳደገ ነው -ነዋሪዎች
Jun 30, 2025 134
ጭሮ ፤ ሰኔ 23/2017(ኢዜአ)፦ በምዕራብ ሀረርጌ ዞን በቀበሌ ደረጃ መንግስታዊ አገልግሎት ተደራሽ በመደረጉ ለአስተዳደራዊ ጉዳዮቻቸው ፈጣን ምላሽ ከማስገኘቱ ባለፈ የልማት ተሳታፊነታቸው እያደገ መምጣቱን የዞኑ ዶባ ወረዳ ነዋሪዎች ገለጹ። በዞኑ በአዲስ መልክ ለተዘረጋው የቀበሌ አስተዳደር አገልግሎት መስጫ የሚውሉ ጽህፈት ቤቶች ግንባታ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እየተደረጉ ነው። ነዋሪዎቹ በሰጡት አስተያየት ለህብረተሰቡ ቅርብ የሆኑ የቀበሌ መዋቅሮች ከዚህ ቀደም ትኩረት በማጣታቸው አገልግሎት ፍለጋ እስከ ወረዳ ማዕከላት ሲመላለሱ ቆይተዋል። በአሁኑ ወቅት የቀበሌ ፅህፈት ቤቶች በዘመናዊ መልኩ ተገንብተው ሙሉ አገልግሎት እያገኙ መሆኑን የተናገሩት በወረዳው የባቱ ቀበሌ ነዋሪ ኢብራሂም ሁሴን ናቸው።   በጤና፣ በትምህርት፣ በግብርና እና መሰል ጉዳዮች አገልግሎት ፍለጋ እስከ ወረዳ ማዕከል ድረስ ሲመላለሱ እንደነበር ያነሱት አስተያየት ሰጪው አሁን ላይ እነዚህን አገልግሎቶች በአካባቢያቸው በሚገኝ ቀበሌ ጽህፈት ቤት በቅርበት አገልግሎት ማግኘት ጀምረዋል። ከዚህ ቀደም በወረዳ ደረጃ ብቻ የሚያገኙትን የመሬት ነክ እና ግብርና አገልግሎቶችን በቀበሌ ማግኘታቸው የልማት ተሳታፊነታቸውን እያሳደገ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ ሌላኛው አስተያየት ሰጪ አህመድ ኢብሮ ናቸው። ይህም የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮቻቸውን በማቃለል በአካባቢያቸው በሚከናወኑ የልማት ስራዎች ውስጥ ተሳትፏቸው እንዲጨምር ማድረጉንም ተናግረዋል። በብልጽግና ፓርቲ የዶባ ወረዳ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሙዘይን ከማል እንዳሉት በወረዳው የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ በተጀመረው የቀበሌ አገልግሎት ማጠናከር ስራ ህብረተሰቡ በቅርበት አገልግሎት እንዲያገኝ ማድረግ ተችሏል። ሙሉ አገልግሎቶች ለህብረተሰቡ በቅርበት እንዲሰጡ በመደረጉም አርሶ አደሩ ከግብርና ስራው እንዳይስተጓጎል ሁሉንም መንግስታዊ አገልግሎት በቅርበት እንዲያገኝ ማድረጉን ተናግረዋል። በምዕራብ ሐረርጌ ዞን በሚገኙ 15 ወረዳዎችና አምስት ከተሞች የቀበሌ አደረጃጀቶችን በማጠናከር 3 ሺህ 522 ባለሙያዎች ተመድበው አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ወይዘሮ ኢክራም ጠሀ ናቸው።   በዚህም 512 የቀበሌ ፅህፈት ቤቶች በዘመናዊ መልኩ እንዲገነቡ መደረጉን አመልክተዋል።  

ማህበራዊ
ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የምግብና መድሃኒት ደህንነትና ጥራት ምርመራ አቅም እየገነባች ነው-ዶክተር መቅደስ ዳባ
Jul 2, 2025 79
አዲስ አበባ፤ሰኔ 25/2017(ኢዜአ):-ኢትዮጵያ ደህንነቱ የተረጋገጠ የመድሀኒትና የምግብ አቅርቦትን ለማስፋት ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ ላብራቶሪና የጥራት ምርመራ ስርዓትን እያስፋፋች መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ገለጹ። የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን ከዓለም አቀፍ አክሪዲቴሽን ቦርድ አይሶ 17025/2012 በመድሃኒት ጥራት ምርመራና የህክምና መገልገያ መሳሪያ ጥራት ምርመራ ያገኘውን እውቅና ይፋ አድርጓል።   የእውቅና መርሃ-ግብሩን አስመልክቶ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ባስተላለፉት መልእክት መንግስት ጥራቱን የጠበቀ የጤና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ በርካታ ተግባራት እያከናወነ ነው ብለዋል። እንዲሁም ደህንነቱ የተረጋገጠ የመድሃኒትና የምግብ አቅርቦትን ለማስፋት እና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ ላብራቶሪና የጥራት ምርመራ ስራም የትኩረት አቅጣጫ ተሰጥቶታል ነው ያሉት። በዚህም ውጤት መመዝገቡን ያነሱት ሚኒስትሯ በሀገሪቱ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪና ተአማኒ የሆኑ የህክምና መሳሪያና የምግብ ምርመራ ስርዓትን መዘርጋት እንደተቻለ አስታውቀዋል። ይህም በህክምናው ዘርፍ የነበሩ ጉድለቶችን ለማረምና ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት ለመስጠት አስቻይ ሁኔታን መፍጠሩን አመልክተዋል። የተፈጠረው አስቻይ ሁኔታ በጤናው ዘርፍ እየተመዘገበ ያለውን ሀገራዊ ስኬት ለማስቀጠል አይነተኛ ሚና እንዳለው ሚኒስትሯ ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን የተሰጠው እውቅና በዘርፉ ለጥራት ፍተሻ የተሰጠውን ትኩረት የሚያረጋግጥ መሆኑን አንስተዋል፡፡ በቀጣይም ይህን መሠል የጥራት ፍተሻ ስራ ለጤናው ዘርፍ ውጤታማነት ወሳኝ በመሆኑ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል ብለዋል።   የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሔራን ገርባ በበኩላቸው፥ ተቋሙ የተለያዩ የለውጥ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ለህብረተሰቡ የሚቀርቡ የምግብና ጤና ግብአቶች ጥራት፣ የቁጥጥር ስራውን በቴክኖሎጂ መደገፍና የሰው ኃይል ልማት ስራ በሪፎርሙ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት መሆናቸውን አንስተዋል። የተካሄደው ሪፎርም ኢትዮጵያ በዘርፉ የአፍሪካ የልህቀት ማእከል እንድትሆን የሚደረገውን ጥረት የሚያግዝ ስለመሆኑ አብራርተዋል። በቅርቡ ከዓለም አቀፍ አክሪዲቴሽን ቦርድ አይሶ 17025/2012 በመድሀኒትና በህክምና መሳሪያ ደህንነትና ጥራት ቁጥጥር እውቅና መገኘቱ ለተሻለ ትጋትና ስራ የሚያነሳሳ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በመዲናዋ የስድስተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 95 በመቶው ወደ ቀጣይ ክፍል ተሸጋግረዋል
Jul 2, 2025 74
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 25/2017(ኢዜአ)፦ በመዲናዋ በ2017 ዓ.ም የስድስተኛ ክፍል ከተማ አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ከ75 ሺህ በላይ የሚሆኑት ወደ ቀጣዩ ክፍል መሸጋገራቸውን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ። የፈተና ውጤቱን ይፋ መደረግ አስመልክቶ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) መግለጫ ሰጥተዋል። ኃላፊው በመግለጫቸው በትምህርት ዘመኑ 79 ሺህ 34 ተማሪዎች የስድስተኛ ክፍል ከተማ አቀፍ መልቀቂያ ፈተናውን መውሰዳቸውን ገልጸዋል። ፈተናውን ከወሰዱት ተማሪዎች መካከል 75 ሺህ 85 ወይም 95 በመቶ የሚሆኑት 50 እና ከዚያ በላይ አማካይ ውጤት በማስመዝገብ ወደ ቀጣዩ የክፍል ደረጃ መሸጋገራቸውን አመላክተዋል። ከተማ አስተዳደሩ ለትምህርት ዘርፉ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ ሲሰራ መቆየቱን አመልክተው፥ ይህም ለውጤቱ መገኘት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ተናግረዋል። ተፈታኝ ተማሪዎች ከዚህ በታች የተቀመጡ ማስፈንጠሪያዎችን በመጠቀም ከዛሬ ጀምሮ ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ ተገልጿል። ሊንክ https://aa6.ministry.et/#/result እና የቴሌግራም ቦት @emacs_ministry_result_qmt_bot
በክልሉ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ
Jul 2, 2025 71
ቦንጋ ፤ ሰኔ 25/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በዘንድሮ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሀ ግብር የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራት በተጠናከረ መልኩ እንደሚከናወኑ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ገለፁ። ክልል አቀፍ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሃግብር በቦንጋ ከተማ ተካሂዷል። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በወቅቱ እንደገለጹት በዘንድሮ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሀ ግብር የህብረተሰቡን ችግር የሚፈቱና ተጠቃሚነታቸውን በበለጠ የሚያረጋግጡ ተግባራት ይከናወናሉ፡፡   የክረምት ወራት በጎ ፍቃድ አገልግሎቶች የማህበረሰቡን ኑሮ የሚቀይሩና ተጠቃሚነታቸውን በተጨባጭ የሚያረጋግጡ ሥራዎች የሚከናወኑበት መሆኑን ጠቁመው ይኽው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል። ''በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ'' በሚል መሪ ሀሳብ የሚካሄደው የዘንድሮው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በልዩ ትኩረት እንደሚመራም አስታውቀዋል። የክልሉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ ገነት መኩሪያ በበኩላቸው በዘንድሮው የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት በ14 መስኮች ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስራዎች እንደሚከናወኑ ተናግረዋል ።   የአረጋዊያንና አቅመ ደካሞች መኖሪያ ቤት እድሳትና መልሶ ግንባታ፣ የአካባቢ ንጽህና ጥበቃ፣ ችግኝ ተከላ ፣ ደም ልገሳ፣ የማጠናከሪያ ትምህርት መስጠት ከሚከናወኑ ስራዎች መካከል እንደሚገኙበት ጠቅሰዋል ።
አዋጁ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪትን በአግባቡ በመምራት የዜጎችን ክብርና ጥቅም የሚያስጠብቅ ነው-ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል
Jul 2, 2025 109
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 25/2017(ኢዜአ)፦የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አዋጅ ወደ ተለያዩ ሀገራት የሚደረጉ የሥራ ስምሪቶችን በአግባቡ በመምራት የዜጎችን ክብርና ጥቅም ማስጠበቅ የሚያስችል መሆኑን የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለፁ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ትናንት ባካሄደው 41ኛ መደበኛ ስብሰባው የኢትዮጵያ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አዋጅን መርምሮ አጽድቋል፡፡ አዋጁ ዜጎች መብታቸው፣ ደህንነታቸው እና ክብራቸው እንዲጠበቅ የሚያደርግ እንዲሁም ኢትዮጵያ ከዘርፉ ማግኘት ያለባትን ብሔራዊ ጥቅም እንድታገኝ የሚያስችል ነው።   የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ለኢዜአ እንደገለጹት፥ አዋጁ የውጭ ሀገር ስራ ስምሪትን በተመለከተ ዝርዝር ድንጋጌዎችን አካትቷል። ባለፉት የለውጥ ዓመታት ትኩረት ከተሰጣቸው ጉዳዮች አንዱ ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ መሆኑን ጠቅሰው፥ አዋጁም ይህንኑ ታሳቢ በማድረግ መዘጋጀቱን ገልጸዋል። ከዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ አኳያ የዜጎች ደህንነትና የሀገር ጥቅም መነሻ እና መዳረሻ እንዲሆኑ ማድረግን የተመለከተ ነው ብለዋል። አዋጁ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን በማስቀረት ረገድ ጉልህ ሚና እንዳለው በመጥቀስ፥ በውጭ ሀገራት መስራት የሚፈልጉ ዜጎችም ክብራቸውና ጥቅማቸው ተጠብቆ በህጋዊ መንገድ እንዲሄዱ ያደርጋል ነው ያሉት። በውጭ ሀገር ሥራ ላይ ሊሰማራ የሚችል ዜጋ የሥራ መደቡ የሚጠይቀውን የትምህርት ዝግጅት፣ ከፍተኛ የዘርፍ እውቀት፣ የሙያና የሥራ ልምድ እንዲኖራቸው የሚያስችል እንደሆነ ጠቅሰዋል። በሚቀጠሩበት የሥራ መስክ አግባብ ካለው የምዘና ማዕከል የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማስረጃ እንዲያገኙ የሚያደርግ ስለመሆኑም አብራርተዋል። ጠንካራ የሆነ የስልጠናና የማብቃት ስርዓት አንዱ ወሳኝ ጉዳይ ነው ያሉት ሚኒስትሯ፥ ዜጎች በራስ መተማመናቸውና የመደራደር አቅማቸው እንዲያድግ በማድረግ ረገድም አዋጁ ጉልህ ሚና ይኖረዋል ብለዋል። አዋጁ የዘርፉ ተዋንያን ጠንካራ አደረጃጀትና የአሰራር ስርዓት እንዲኖራቸው የሚያደርግ መሆኑን ጠቁመዋል።  
ኢኮኖሚ
የአፍሪካ አህጉራዊ የኃይል ቋት ስርዓትን የመፍጠር ግብ በትክክለኛ ምዕራፍ ላይ ይገኛል - የአፍሪካ ህብረት
Jul 3, 2025 38
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 25/2017(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ አህጉራዊ የኃይል ቋት ስርዓትን የመፍጠር ራዕይ በትክክለኛ ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ የአፍሪካ ህብረት አስታወቀ። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የመሰረተ ልማት እና ኢነርጂ ዳይሬክተር ካሙጊሻ ካዛውራ የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ ንግድ ቀጣና አካል የሆነው አህጉራዊ ነጠላ የኤሌክትሪክ ኃይል ገበያ ዘላቂ የኃይል ልማት ማረጋገጥን አላማ ያደረገ መሆኑን ለኢዜአ ገልጸዋል። የተቀናጀ የኤሌክትሪክ ኃይል ገበያ በመፍጠር በአፍሪካ በመኖሪያ ቤቶች፣ በንግድ ተቋማት እና ኢንዱስትዎች ዘላቂ፣ ተአማኒ፣ ተወዳዳሪ እና ተመጣጣኝ ኢነርጂ ማቅረብ እንደሚያስችል አመልክተዋል። በዚህ ረገድም የአፍሪካ ሀገራት ከጎረቤቶቻቸው ጋር ትስስር ለመፍጠር እየተገበሯቸው ያሉ ፕሮጀክቶችን አድንቀዋል። ኢትዮጵያ ከሱዳን፣ ጅቡቲ እና ኬንያ ጋር የፈጠረችው የኃይል መስተጋብር የአፍሪካ ነጠላ የኤሌክትሪክ ኃይል ትግበራ ማሳያ እንደሆነ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ የኃይል ቋት አካል መሆኗን ገልጸው ቋቱ ሀገራትን በማስተሳሰር ቁልፍ ሚና እየተጫወተ ነው ብለዋል ዳይሬክተሩ። ኬንያ ከታንዛንያ ጋር የኃይል ስርዓቷን ለማስተሳሰር እያከናወነች እንደምትገኝና ይህም በቀጣይ ከደቡባዊ አፍሪካ የኃይል ቋት የኤሌክትሪክ ግብይት ለማድረግ እንደሚያስችል ገልጸዋል። በቀጣይ የምስራቅ አፍሪካ የኃይል ቋትን ከደቡባዊ አፍሪካ የኃይል ቋት ጋር የማገናኘት እቅድ መያዙን ጠቁመዋል። እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ፤ አህጉራዊ ነጠላ የኤሌክትሪክ ኃይል ገበያው ውሃ፣ ፀሐይ፣ ንፋስ እና የታዳሽ ኃይሎችን ጨምሮ ለሁሉም የኃይል ምንጮች ትኩረት እና እውቅና የሚሰጥ ነው። የኃይል አማራጮቹ የአፍሪካ የኃይል ስርዓት ማስተር ፕላን አካል እንደሆኑ ገልጸው ይህም አህጉራዊ ነጠላ የኤሌክትሪክ ኃይልን እውን ለማድረግ የሚያስችል ቁልፍ ምሰሶ መሆኑን አመልክተዋል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ከአፍሪካ ልማት ባንክ እና የዓለም ባንክ ግሩፕ ጋር በመሆን በተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት “Mission 300” የተሰኘ ኢኒሼቲቭ ይፋ ያደረጉ ሲሆን ኢኒሼቲቩ ለአፍሪካውያን የኤሌክትሪክ ተደራሽነት ማስፋትን ያለመ ነው። ኢኒሼቲቩ እ.አ.አ በ2030 300 ሚሊዮን የአፍሪካ ዜጎችን በኤሌክትሪክ የማስተሳሰር ውጥን አለው ነው ያሉት ዳይሬክተሩ። የአፍሪካ ልማት ባንክ፣ የአውሮፓ ህብረት፣ የጀርመን መንግስት እና ሌሎች የልማት አጋሮች ለኢኒሼቲቩ ድጋፍ እያደረጉ እንደሚገኝ ጠቁመዋል። የአፍሪካ ነጠላ የኤሌክትሪክ ኃይል ገበያ በአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት የኢነርጂ ደህንነትን እና ዘላቂነትን ለማረጋገጥ እንዲሁም ተወዳዳሪነትን የማሳደግ እቅም እንዳለው ታምኖበታል። #Ethiopian_News_Agency #Ethiopia #ኢትዮጵያ #ኢዜአ
በቦረና ዞን እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች የአርሶና አርብቶ አደሩን ህይወት በተጨባጭ በመቀየር ላይ ይገኛሉ
Jul 2, 2025 87
አዲስ አበባ፤ሰኔ 25/2017(ኢዜአ):-በቦረና ዞን እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ስራዎች የአርሶና አርብቶ አደሩን ህይወት በተጨባጭ በመቀየር ላይ መሆናቸውን በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ከፍያለው ተፈራ ገለጹ። የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ እና የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በቦረና ዞን እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።   በጉብኝቱም በክላስተር እየለማ የሚገኝ የስንዴ ክላስተር፣ የቀበሌ አስተዳደር የስራ እንቅስቃሴ፣ የቦረና ከብቶች ማድለቢያ ቦታን ጨምሮ በግንባታ ላይ የሚገኘውን የቦረና ባህል ማዕከልን ጎብኝተዋል። በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ከፍያለው ተፈራ ጉብኝቱን አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ፤ በቦረና ዞን እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች የህብረተሰቡን ህይወት በተጨባጭ እየቀየሩ ይገኛሉ ብለዋል። በክላስተር እየለማ የሚገኘው የስንዴ ምርትም አካባቢው ላይ የስንዴ ምርታማነት እያደገ ለመሆኑ ማሣያ ነው ብለዋል። ዞኑ ከዚህ ቀደም ተከሰቶ ከነበረው ድርቅ በማገገም ምርታማነትን በተጨባጭ እያረጋገጠ እንደሚገኝም ጠቁመዋል። በኦሮሚያ ክልል በቅርቡ ተግባራዊ የተደረገው የቀበሌ አስተዳደር መዋቅር ህዝቡ በቅርበት አገልግሎት እንዲያገኝ ማስቻሉን ተናግረዋል። በቦረና ዞን ደረጃቸውን የጠበቁ የቀበሌ አስተዳደር ጽህፈት ቤቶች ወደ ስራ የገቡ ሲሆን፥ የአርብቶ አደሩን እንግልት በመቀነስ የመልካም አስተዳደር ችግሮች በፍጥነት እንዲቀረፉ ማስቻሉን ጠቁመዋል።   የቦረና ዞን ዋና አስተዳዳሪ አብዱልሰላም ዋሪዮ በበኩላቸው፥ በዞኑ ከሁለት ወራት በፊት በተጀመረው የክረምት ወራት የግብርና ልማት 135 ሺህ ሄክታር መሬት በተለያዩ የዘር ዓይነቶች መሸፈኑን ገልጸዋል። ከዚህ ውስጥም ከ56 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በክላስተር እየለማ መሆኑን ጠቅሰው፥ 5 ሺህ ሄክታር በስንዴ ምርት የተሸፈነ መሆኑን ጠቁመዋል። ስንዴ፣ ቦሎቄ፣ ጤፍ፣ ማሾ እና ሌሎችም ሰብሎችን ማልማት መቻሉን በመግለፅ፥ ከዚህም 1 ነጥብ 9 ሚሊዮን ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ ተናግረዋል። የቦረና ዞን አሁን ላይ በተሻለ ምርታማነት ላይ እንደሚገኝ አስረድተው፥ የአርብቶ አደሩ የስራ ባህል እየተቀየረ መሆኑን ጠቁመዋል።   በቦረና ዞን የድሬ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት ጃተኒ ቦሩ እና አብዱላሂ ቆዳ ስንዴን በክላስተር በማልማት ምርታማ በመሆን ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል። በመንግሥት በኩል ምርጥ ዘርን ጨምሮ የተለያዩ ግብዓት እየቀረበላቸው በመሆኑ ምርታማነትን እያሳደገልን ነው ብለዋል። በዱቡሉቅ ወረዳ አኖሌ ቀበሌ ነዋሪዎች ኖሌ ኮርማ እና ሮባ ጎዳና የቀበሌ አስተዳደር ከመኖሪያቸው በአቅራቢያ መቋቋሙ እንግልትን እንዳስቀረላቸው ተናግረዋል።    
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ፖርቹጋል ፖርቶ አዲስ በረራ ጀመረ
Jul 2, 2025 89
አዲስ አበባ፤ሰኔ 25/2017(ኢዜአ):-የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ፖርቹጋል ፖርቶ አዲስ በረራ ጀምሯል። አየር መንገዱ ወደ ፖርቶ በሣምንት አራት ጊዜ በረራ እንደሚያደርግ ተገልጿል። አየር መንገዱ ወደ ፖርቹጋል ፖርቶ ከተማ የሚያደርገውን በረራ አስመልክቶ ዛሬ ማምሻውን የማስጀመሪያ መርኃ ግብር ተከናውኗል። በመርኃ ግብሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው፣ በኢትዮጵያ የፖርቹጋል አምባሳደር ልዊሳ ፍራጎሶ እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው በዚሁ ጊዜ፥ አየር መንገዱ ወደ ፖርቶ የሚያደርገው በረራ ፖርቹጋልን ከአፍሪካ ጋር ለማስተሳሰር እንደሚያግዝ ተናግረዋል። ወደ አውሮፓ ለሚጓዙ መንገደኞች የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችለውም ነው የገለጹት። በኢትዮጵያ የፖርቹጋል አምባሳደር ልዊሳ ፍራጎሶ በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያ እና ፖርቹጋል ረዥም ዘመናትን ያስቆጠረ ወዳጅነት እንዳላቸው ተናግረዋል። አየር መንገዱ ወደ ፖርቶ የጀመረው በረራም የሀገራቱን ወዳጅነት በኢኮኖሚና ህዝብ ለህዝብ ትስስር ለማጠናከር እንደሚያግዝም አውስተዋል። አየር መንገዱ ዛሬ ያስጀመረውን በረራ ጨምሮ ከ145 በላይ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎችን እየሸፈነ ይገኛል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2035 ዓመታዊ ገቢውን ወደ 25 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ለማድረግና በዓመት 67 ሚሊዬን መንገደኞችን ለማጓጓዝ ራዕይ አስቀምጦ እየሰራ ይገኛል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የህዝቡን ፍትሃዊ የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው -- ርእሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ
Jul 2, 2025 57
ወላይታ ሶዶ፤ ሰኔ 25/2017 (ኢዜአ) --በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የህዝቡን ፍትሃዊ የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ገለጹ፡፡ የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት የ2018 ዓ.ም በጀት ማከፋፈያ ቀመር ሂደት ላይ ተግባቦት ለመፍጠር ያለመ የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ ተካሂዷል፡፡   የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ በዚህ ወቅት እንደገለጹት በክልሉ ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል እና የልማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራት በትኩረት እየተከናወኑ ነው። የክልሉን ህዝብ አዳጊ ፍላጎቶችን ለማሟላት እና ፍትሃዊ የልማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በበጀት ቀመር ላይ ተግባቦት መፍጠር እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል። በዚህም የ2018 ዓ.ም በጀት ከመወሰኑ በፊት ከተለያዩ ምንጮች የተሰበሰቡ መረጃዎችን መሰረት በማድረግ የበጀት ቀመሩን ለመስራት መግባባት ላይ መድረስ በማስፈለጉ መድረኩ መዘጋጀቱን ገልጸዋል። የክልሉ ብሄረሰቦች ምክር ቤት በበጀት ቀመሩ ላይ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ማከናወኑን ጠቅሰው መግባባት የተደረሰበት መረጃ ለክልሉ ምክር ቤት ይቀርባል ብለዋል፡፡   የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አዳማ ቲምጳዬ በበኩላቸው በ2018 በጀት ዓመት ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍልና የልማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ መረጃዎችን የማደራጀት ስራ መሰራቱን ገልጸዋል። መድረኩ በሁሉም መዋቅር አመራሮች ዘንድ ግልጽነትና መግባባት በመፍጠር የኢኮኖሚን አቅምን መሠረት ያደረገ የበጀት ቀመር ተግባራዊ ለማድረግ የሚያግዝ ነው ብለዋል፡፡ ግልጽና ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል እንዲኖር የ2018 በጀት ቀመር የማዘጋጀትና የማደራጀት ስራ ሲሰራ መቆየቱን የተናገሩት ደግሞ የክልሉ ፕላን እና ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፈቃደስላስ ቤዛ ናቸዉ። የዘንድሮውን የበጀት ቀመር የማዘጋጀቱ ስራ እየተገባደደ ባለው በጀት ዓመት የተስተዋሉ ችግሮችን በመቅረፍ ለበጀት ቀመር ዝግጅት መረጃዎችን የማናበብና የማጥራት ተግባር የተከናወነበት መሆኑንም ገልጸዋል። ለዚህም ስራ ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ ያሉ የሶስት ዓመት መረጃዎችን የማመሳከር ስራ መሰራቱንም አክለዋል። በመድረኩ የክልል፣የዞኖች እና የ3ቱ ሪጂዮፖሊስ ከተሞች ባለድርሻዎች ተገኝተውበታል።  
ቪዲዮዎች
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
40 የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ባለሙያዎች ዓለም አቀፍ የምስክር ወረቀት አገኙ
Jul 2, 2025 110
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 25/2017(ኢዜአ)፦ በአቪዬሽን ሴኪዩሪቲ ጥራት ቁጥጥርና አደጋ አስተዳደር የሰለጠኑ 40 የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ባለሙያዎች ዓለም አቀፍ የምስክር ወረቀት ማግኘታቸውን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አስታወቀ። አገልግሎቱ ለኢዜአ በላከው መረጃ እንዳመለከተው፤ በኢትዮጵያ አጠቃላይ የአቪዬሽን ሴኪዩሪቲ ስራዎችን በበላይነት ለመምራት በአዋጅ ኃላፊነት የተሰጠው ተቋሙ ከዓለም አቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት (ICAO) ጋር በመተባበር በአቪዬሽን ሴኪዩሪቲ ጥራት ቁጥጥርና በአቪዬሽን አደጋ አስተዳደር ዙሪያ ስልጠና የወሰዱ 40 ባለሙያዎች ዓለም አቀፍ የምስክር ወረቀት እንዲያገኙ ማድረጉን ገልጿል። የዓለም አቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ከ12 ዓመታት በኋላ በኢትዮጵያ የአቪዬሽን ሴኪዩሪቲ አሰራሮች ላይ ባደረገው ኦዲት ሀገራችን ምንም ዓይነት የሴኪዩሪቲ ስጋት እንደሌለባት ማረጋገጡን አስታውሷል። ይህን ተከትሎም ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የሲቪል አቪዬሽን ደኅንነት ዋና መምሪያ ጋር በተፈጠረው መልካም ግንኙነትና ትብብር ስልጠናው ከዓለም አቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት በመጡ ባለሙያዎች ከሰኔ 9 እስከ ሰኔ 24 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ተሰጥቷል። ዓለም አቀፍ የምስክር ወረቀቱ አየር መንገዱ ተደራሽ በሚሆንባቸው ሀገራት ሁሉ የአቪዬሽን ሴኪዩሪቲ የጥራት ቁጥጥር ተግባራትን ለማካሄድ የሚያስችል መሆኑን የገለጹት ከዓለም አቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት የመጡት አሰልጣኞች፤ ባለሙያቹ ስልጠናውን በስኬት ማጠናቀቃቸውን ጠቁመዋል። ስልጣኞች ያገኙት ዕውቀት ተቋሙ ሀገራዊ ተልዕኮውን በላቀ ብቃት ለመፈፀም የሚያስችለው ከመሆኑም ባለፈ፤ ኢትዮጵያን ለአቪዬሽን ደህንነት ዘርፍ እየሰጠች ያለችው ልዩ ትኩረት ጉልህ ማሳያ ተደርጎም ሊወሰድ እንደሚችል የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አመልክቷል። የአቪዬሽን ደህንነት ጠንካራ የጥራት ቁጥጥር ትግበራ እና የአደጋ ምላሽ አሰጣጥ ዝግጁነት የእያንዳንዱ የዓለም አቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት አባል ሀገራት ኃላፊነት መሆኑን ያስታወቀው አገልግሎቱ ፤ ይህም የአቪዬሽን ኢንዱስትሪውን ደኅንነት በዓለም አቀፍ ስታንዳርድ መሰረት ለማረጋገጥ እንደሚያስችል ገልጿል፡፡ በስልጠናው የተገኘውን ዕውቀት፣ ክህሎት እና የአስተሳሰብ ለውጥ በቀጣይ በአቪዬሽን ደህንነት ዘርፍ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለመሆን ለተያዘው ራዕይ እና አጠቃላይ ተቋማዊ ስትራቴጂ ግብዓት አድርጎ በማዋል የኢትዮጵያ አየር መንገድን ተመራጭነት ይበልጥ በማሳደግ ሀገራዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ፋይዳ እንደሚኖረው አገልግሎቱ ለኢዜአ በላከው መረጃ አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ስልጠና አካዳሚ ለአፍሪካ ሀገራት ተመራጭ የስልጠና ማዕከል እየሆነ ይገኛል - የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን በለስልጣን
Jul 1, 2025 132
አዲስ አበባ፤ሰኔ 24/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የስልጠና አካዳሚ ለበርካታ የአፍሪካ ሀገራት ቀዳሚ ተመራጭ የስልጠና ማዕከል እየሆነ እንደሚገኝ የኤር ናቪጌሽን ሬጉሌሽን አገልግሎት ዳይሬክተር እና የአካዳሚው ተጠባባቂ ዳይሬክተር ልዑልሰገድ ጉልላት ገለጹ። ዳይሬክተሩ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ አካዳሚው ለአቪዬሽን ኢንዱስትሪው ውጤታማነት ባለሙያዎችን በማፍራት ላይ ይገኛል ብለዋል። ለበርካታ ዓመታት በአየር ትራፊክ ቁጥጥር፣ በኮሙኒኬሽን እና ናቪጌሽን ሰርቪላንስ (CNC) ዘርፍ በአገሪቱ የተለያዩ ክልሎች ብቁ የአቪዬሽን ባለሙያዎችን በማሰማራት ላይ መሆኑንም ጠቅሰዋል።   በዚህ ዓመት ብቻ ከ86 በላይ ባለሙያዎችን በንድፈ ሃሳብና በተግባር የተደገፈ ስልጠና በመስጠት ወደ ሥራ ማስገባቱን አንስተዋል። አካዳሚው የሚሰጠው ስልጠና ከሀገር አልፎ ለጎረቤት ሀገራትና ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ውጤታማ ስልጠና እየሰጠ ተፈላጊነቱን እያሳደገ ይገኛል ብለዋል። በቅርቡ ከጅቡቲ፣ ከሶማሊያ እንዲሁም ከኮሞሮሶና ሌሎች ሀገራት የመጡ የአቪዬሽን ሰልጣኞችን ማሰልጠኑን ተናግረዋል። በርካታ የአፍሪካ ሀገራት በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን የስልጠና አካዳሚ ሙያተኞቻቸውን ለማሰልጠን ጥያቄ እያቀረቡ እና ተመራጭ እያደረጉት መሆኑን ተናግረዋል። አካዳሚው በአፍሪካ ትልቅ ስምና ተቀባይነት እንዳለው በማንሳት፥ ይበልጥ ቀጣናውን ለማስተሳሰር በርካታ ተግባራትን በትኩረት እያከናወነ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።   በአካዳሚው አሰልጣኝ እና ዋና የአየር ተቆጣጣሪ ቤተልሔም ሞላ በበኩላቸው፥ ስልጠናው የዓለም አቪዬሽን ኢንዱስትሪ በደረሰበት ደረጃ ልክ እየተሰጠ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በተግባር እና በንድፈ ሀሳብ የተደገፈው ስልጠና ሰልጣኞች ተግባራዊ የሆነ በቂ እውቀት የሚያገኙበት እና በአቪዬሽን ኢንዱስትሪው ውጤታማ የሚያደርጋቸው ነው ብለዋል። ባለፉት ሰባት ወራት በብቁ አሰልጣኞች በንድፈ ሀሳብና በተግባር የተደገፈ ስልጠና መውሰዱን የገለጸልን ደግሞ ከድሬዳዋ የመጣው ምንተስኖት አለማየሁ ነው።   በአቪዬሽን ዘርፉ በተሰማራበት ሙያ ለማገልገል ካለው ተነሳሽነት በተጨማሪ፥ በስልጠናው ያገኘው እውቀት ትልቅ አቅም እንደፈጠረለትም ተናግሯል።        
ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 በዲጂታል ስርዓቱ ከፍተኛ ውጤት አስገኝቷል-ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር)
Jul 1, 2025 129
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 24/2017 (ኢዜአ)፦ባለፉት አምስት አመታት ሲተገበር የቆየው ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 በዲጂታል ስርዓቱ ውጤት አስገኝቷል ሲሉ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ(ዶ/ር) ገለጹ። ሚኒስትሩ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳሉት የአንድን ሀገር ሁለንተናዊ እድገት ማረጋገጥ የሚቻለው የአሰራር ስርዓትን በሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም በኢኖቬሽን ሲደገፍ ነው። ኢትዮጵያም ወደ ዲጂታል ስርዓት መግባት የሚያስችላትን የህግ ማዕቀፍ እንዲሁም ስትራቴጂ በማዘጋጀት ወደ ስራ እንደገባች ገልጸዋል። በተጨማሪም ወደ ዲጂታል ስርዓቱ መግባት የሚያስችሉ መሰረተ ልማቶች ተሟልተው ተግባራዊ መደረግ መጀመራቸውን አስታውቀዋል። ስትራቴጂው ከሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያና የ10 አመት መሪ የልማት ዕቅድ ስትራቴጂዎች እንዲሁም ከአፍሪካ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ ጋር ተሳስሮ ሲተገበር መቆየቱንም ገልጸዋል። ባለፉት አመታት ተግባራዊ ሲደረግ የቆየው የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ከአንድ ወር በኋላ እንደሚጠናቀቅ ገልፀው በቀጣይ 2030 ድረስ ተግባራዊ የሚደረገው የ5 አመት ስትራቴጂ እየተዘጋጀ እንደሚገኝ ነው የጠቀሱት። ባለፉት አምስት አመታት ሲተገበር የቆየው ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ በሳይንስ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፉ ላይ አመርቂ ውጤቶች እንደተመዘገቡቡት ሚኒስትሩ አስታውቀዋል። ባለፉት አምስት አመታት የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት በመዘርጋት፣ የዲጂታል አገልግሎት በማስፋት እንዲሁም የዲጂታል መታወቂያ ተደራሽ ከማድረግ አኳያ ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸው አንስተዋል። የመንግስትን የአሰራር ስርዓት ከማዘመን ጋር በተያያዘ የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025ን እውን ለማድረግ ከተሰሩ ስኬታማ ስራዎች መካከል መሆኑን ገልፀዋል። ማዕከሉ በአንድ ጣራ ስር የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የተለያዩ የመንግስት አገልግሎቶችን በማጣመር አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡ በቀጣይም የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ወደ ክልል ከተሞች በማስፋት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል።        
በክልሉ በዲጅታል ቴክኖሎጂ በመታገዝ በተቋማት የአገልግሎት አሰጣጡን የማሻሻል ስራ በስፋት እየተከናወነ ነው
Jul 1, 2025 186
ሀዋሳ ፤ሰኔ 24/2017 (ኢዜአ) ፡-በዲጅታል ቴክኖሎጂ በመታገዝ በእውቀትና ክህሎት የዳበሩ ባለሙያዎችን በማፍራት በተቋማት የአገልግሎት አሰጣጡን የማሻሻል ስራ በስፋት እየተከናወነ መሆኑን የሲዳማ ክልል ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ አስታወቀ። የሲዳማ ክልል ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ በክልሉ ለዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ሰጥቷል፡፡   የክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስን የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አሰፋ ጉራቻ፤ አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻልና የተገልጋዮችን ፍላጎት ለማሟላት የሚያስችሉ አሰራሮች ተግባራዊ እየተደረጉ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም ተጨባጭ ለውጥ መምጣቱን አንስተው ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በተደረገ የዳሰሳ ጥናት የተገልጋዮች እርካታ ከ47 በመቶ ወደ 66 ነጥብ 3 በመቶ ከፍ ማለቱ ተመላክቷል። ለመሻሻሉ ምክንያት የማዘጋጃ ቤቶች፣ ትራንስፖርት፣ የገቢዎችን ጨምሮ 7 የተለያዩ ሴክተሮችን የአገልግሎት ክፍተቶች በመለየት በቴክኖሎጂ ጭምር የታገዘ አሰራር በመዘርጋት መሆኑን አስረድተዋል። በቀጣይም አገልግሎት አሰጣጡን ይበልጥ ለማጠናከር በድጅታል ቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራር በመዘርጋት በእውቀትና በክህሎት የዳበረ አገልጋይ የመፍጠር ትኩረት ይደረጋል ሲሉ አረጋግጠዋል። ለተመደቡበት የሥራ ዘርፍ ቃላቸውን ጠብቀውና ሃላፊነት ወስደው የማገልገል ችግር ያለባቸው አመራርና ሰራተኞች ሲያጋጥሙ በአሰራሩ መሰረት እርምጃ የሚወሰድ መሆኑንም ተናግረዋል።   የሲዳማ ክልል ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት ዳይሬክተር ወይዘሮ ታደለች ዮሐንስ፤ በቢሮው እየተደረጉ ያሉ የአሰራር ማሻሻያዎች እንዲሁም የድጋፍና ክትትል ስራዎች ለውጥ ማምጣታቸውን አንስተዋል። በዚህም የአገልጋዮች አቅም እየዳበረ የተገልጋዮች እርካታም እየተሻሻለ መምጣቱን ተናግረዋል።፡ በሥልጠናው ከ240 በላይ የዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡    
ስፖርት
የአየር ኃይል ሶስተኛ አየር ምድብ የስፖርት ውድድር ተጠናቀቀ
Jul 2, 2025 69
ድሬዳዋ፣ሰኔ 25/2017(ኢዜአ)፦በኢፌዴሪ አየር ኃይል ሶስተኛ አየር ምድብ ለሁለት ሳምንት ሲካሄድ የሰነበተው የስፖርት ውድድር ማምሻውን ተጠናቀቀ። በምድቡ ከሰኔ 11 ቀን 2017 ጀምሮ በተለያዩ የስፖርት አይነቶች ሲካሄድ የሰነበተው ውድድር ዛሬ ማምሻውን በተደረገ የእግር ኳስ ጨዋታ ተጠናቋል ። በወንዶች በተካሄደው የፍፃሜ ጨዋታ የሶስተኛ አየር ምድብና የሆርሞድ ጤና ቡድን መደበኛውን የጨዋታ ጊዜ ያለምንም ጎል ተለያይተዋል። አሸናፊውን ለመለየት በተሰጡ የፍፁም ቅጣት ምቶች ሆሮሞድ አራት ለአንድ በሆነ ውጤት አሸናፊ ሆኗል። ከወንዶች እግር ኳስ በተጨማሪም በምድቡ የተለያዩ ክፍሎች መካከል የአትሌቲክስ፣ የመረብ ኳስ ፣የእጅ ኳስና ሌሎች ውድድሮች በሁለቱም ፆታ የተካሄዱ ሲሆን ለአሸናፊዎቹ ሽልማት ተበርክቷል። ለአሸናፊዎች የተዘጋጀውን የዋንጫና ሌሎች ሽልማቶች የሰጡት የኢፌድሪ አየር ኃይል ሶስተኛ ምድብ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ደረጀ ቡሽሬ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ናቸው። ዋና አዛዡ ኮሎኔል ደረጀ ቡሽሬ በወቅቱ እንደተናገሩት፥ ስፖርት የሠራዊቱን አካላዊ ብቃትና ስነ ልቦናዊ ጥንካሬ በማዳበር የትኛውንም ግዳጅ በታላቅ ብቃት እንዲወጣ እያገዘ ይገኛል ። እየተጠናቀቀ በሚገኘው በጀት አመት ምድቡ በተለያዩ ተልዕኮዎቹ ውጤታማ ተግባራት ማከናወኑንም ጠቅሰዋል። በውድድሩ የከተማው አምስት የጤና ቡድኖች መሳተፋቸው ሠራዊቱ ከማህበረሰቡ ጋር ያለውን ሁለንተናዊ ትስስር እንዲጠናከር አጋጣሚ የተፈጠረበት መሆኑን አንስተዋል ። ዛሬ ማምሻውን በተካሄደው የፍፃሜ ጨዋታ የከተማው የስፖርት ቤተሰቦች በስፍራው ተገኝተው ውድድሩን ተመልክተዋል።
ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቀለ 
Jul 2, 2025 74
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 25/2017(ኢዜአ)፦ በፊፋ የክለቦች ዓለም ዋንጫ የጥሎ ማለፍ የመጨረሻ መርሃ ግብር ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ሞንቴሬይን 2 ለ 1 አሸንፏል። ትናንት ከእኩለ ሌሊት በኋላ በሜርሴዲስ- ቤንዝ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የጊኒው አጥቂ ሴርሁ ጉይራሲ በ14ኛው እና በ24ኛው ደቂቃ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥሯል። ሜክሲኳዊው አጥቂ ጀርመን ቤርቴራሜ በ48ኛው ደቂቃ ሞንቴሬይን ከሽንፈት ያልታደገቸውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል። በጨዋታው ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ተጨማሪ ግቦችን ሊያስቆጥርባቸው የሚችልባቸውን እድሎች አልተጠቀመም። የጊኒው አጥቂ ሴርሁ ጉይራሲ የጨዋታው ኮከብ ሆኖ ተመርጧል። ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ሩብ ፍጻሜውን የተቀላቀለ የመጨረሻው ቡድን ሆኗል። በሩብ ፍጻሜው ከሪያል ማድሪድ ጋር ይገናኛል ። ማድሪድ ትናንት ማምሻውን ጁቬንቱስን 1 ለ 0 አሸንፏል። የጥሎ ማለፍ መርሃ ግብሮች የተጠናቀቁ ሲሆን የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች ሰኔ 27 እና 28 ቀን 2017 ዓ.ም ይደረጋሉ። ፓልሜራስ ከቼልሲ፣ ፒኤስጂ ከባየር ሙኒክ፣ ፍሉሜኔንሴ ከአል ሂላል እና ሪያል ማድሪድ ከቦሩሲያ ዶርትሙንድ በሩብ ፍጻሜው የሚደረጉ ጨዋታዎች ናቸው።
ሪያል ማድሪድ ጁቬንቱስ በማሸነፍ ለሩብ ፍጻሜ አልፏል
Jul 2, 2025 80
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 24/2017 (ኢዜአ)፦ በፊፋ የክለቦች ዓለም ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ማለፍ ተጠባቂ መርሃ ግብር ሪያል ማድሪድ ጁቬንቱስን 1 ለ 0 አሸንፏል። ማምሻዉን በሃርድ ሮክ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የ21 ዓመቱ አጥቂ ጎንዛሎ ጋርሺያ በ54ኛው ደቂቃ ከትሬንት አሌክሳንደር አርኖልድ የተሻገረለትን ኳስ በግሩም ሁኔታ በግንባሩ ገጭቶ በማስቆጠር ሎስ ብላንኮሶቹን አሸናፊ አድርጓል። ተስፈኛው ወጣት አጥቂ ጋርሺያ በውድድሩ ያስቆጠራቸውን ግቦች ብዛት ወደ ሶስት ከፍ አድርጓል። ሪያል ማድሪድ በጨዋታው የተሻለ ኳስ ቁጥጥር የነበረው ሲሆን ለግብ የቀረቡ እድሎችንም መፍጠር ችሏል። ጉዳት ላይ የነበረው ኪሊያን ምባፔ ተቀይሮ በመግባት በዓለም ዋንጫው የመጀመሪያ ተሳትፎውን አድርጓል። ጁቬንቱስ በመልሶ ማጥቃት ግብ ለማስቆጠር ወደ ሜዳ ይዞ የገባው የጨዋታ ስልት ውጤታማ አልነበረም። ውጤቱን ተከትሎ ሪያል ማድሪድ የሩብ ፍጻሜ ትኬቱን ቆርጧል። ከቦሩሲያ ዶርትሙንድ እና ሞንቴሬይ አሸናፊ ጋር ይጫወታል። በጥሎ ማለፉ የመጨረሻ መርሃ ግብር ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ከሞንቴሬይ ከሌሊቱ 10 ሰዓት ላይ በሜርሴዲስ-ቤንዝ ስታዲየም ይጫወታሉ።
የአውሮፓ ስመ ገናናዎቹ  ሪያል ማድሪድ እና ጁቬንቱስ ጨዋታ ተጠባቂ ነው 
Jul 1, 2025 116
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 24/2017 (ኢዜአ)፦ በፊፋ ክለቦች የዓለም ዋንጫ የጥሎ ማለፍ መርሃ ግብር የመጨረሻ ቀን ውሎ ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ። ምሽት 4 ሰዓት ላይ በሀርድ ሮክ ስታዲየም ሪያል ማድሪድ ከጁቬንቱስ የሚያደርጉት ጨዋታ የዓለም እግር ኳስ አፍቃሪያን ቀልባቸውን ጥለውበታል። የአምስት ጊዜ የፊፋ ክለቦች ዓለም ዋንጫ አሸናፊው ሪያል ማድሪድ በምድብ ስምንት በሰባት ነጥብ የምድቡ መሪ በመሆን ማጠናቀቁ ይታወቃል። በውድድሩ የመጀመሪያ ተሳትፎውን እያደረገ የሚገኘው ጁቬንቱስ በምድብ ሰባት ስድስት ነጥብ በማግኘት ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ወደ ጥሎ ማለፉ ገብቷል። የአውሮፓ ኃያላኑ ሪያል ማድሪድ እና ጁቬንቱስ በሁሉም ውድድሮች እስከ አሁን 21 ጊዜ ተገናኝተዋል።   ሪያል ማድሪድ 10 ጊዜ በማግኘት ውስን ብልጫ ወስዷል። ጁቬንቱስ 9 ጊዜ ሲያሸንፍ 2 ጊዜ አቻ ተለያይተዋል። በ21ዱ ጨዋታዎች ሪያል ማድሪድ 26 ግቦችን ሲያስቆጥር ጁቬንቱስ 25 ግቦችን ከመረብ ላይ አሳርፏል። ሁለቱ ክለቦች ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኙት እ.አ.አ በ2017 በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ፍጻሜ ነበር። በካርዲፍ በተካሄደው ጨዋታው ሪያል ማድሪድ 4 ለ 1 በማሸነፍ ዋንጫውን አንስቷል። በአውሮፓ እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ ትልቁ የክለቦች ባላንጣነት ማሳያ ተደርጎ የሚጠቀሰው የቡድኖቹ ፍልሚያ ሁሌም ጠንካራ እና እልህ አስጨራሽ ፉክክር የሚደረግበት ነው። ሪያል ማድሪድ እና ጁቬንቱስ የየሊጋቸውን ዋንጫ በተመሳሳይ 36 ጊዜ በማንሳት የበላይነቱን ይዘዋል። በአውሮፓ መድረክ ሪያል ማድሪድ 15 ጊዜ የሻምፒዮንስ ሊጉን ዋንጫ ከፍ በማድረግ ስኬታማ መሆን የቻለ ክለብ ነው። ጁቬንቱስ ሁለት ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን አንስቷል። የእግር ኳስ ባለሙያዎች ከወቅታዊ ብቃት አንጻር ሪያል ማድሪድ ጁቬንቱስን በጠባብ የግብ ልዩነት ሊያሸንፍ ይችላል የሚል ግምታቸውን አስቀምጠዋል። በጥሎ ማለፍ የመጨረሻ መርሃ ግብር ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ከሞንቴሬይ ከሌሊቱ 10 ሰዓት ላይ በሜርሴዲስ ቤንዝ ስታዲየም ይጫወታሉ።   ቦሩሲያ ዶርትሙንድ በሰባት ነጥብ የምድብ ስድስት መሪ፣ ሞንቴሬይ በምድብ አምስት በአምስት ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዘው ጥሎ ማለፍ ገብተዋል። ሁለቱ ክለቦች እርስ በእርስ ሲገናኙ የአሁኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። የሁለቱ ጨዋታ አሸናፊዎች በሩብ ፍጻሜው ይገናኛሉ። በአሜሪካ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው የፊፋ ክለቦች ዓለም ዋንጫ ፒኤስጂ፣ ባየር ሙኒክ፣ ቼልሲ፣ ፓልሜራስ፣ አል ሂላል እና ፍሉሜኔንሴ እስከ አሁን ሩብ ፍጻሜውን የተቀላቀሉ ክለቦች ናቸው።
አካባቢ ጥበቃ
በአማራ ክልል ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን በላይ ችግኞች ለተከላ ተዘጋጅተዋል
Jul 2, 2025 81
ባህርዳር ሰኔ 25/2017 (ኢዜአ) ፡-በአማራ ክልል ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን በላይ ችግኞች መዘጋጀታቸውን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው የተፈጥሮ ሃብት ልማትና አጠቃቀም ዳይሬክተር አቶ እስመለዓለም ምህረት፤ ለክረምቱ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተደረገውን አጠቃላይ ዝግጅት በተመለከተ ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል።   በማብራሪያቸውም በክልሉ ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርጋ ግብር ከ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን በላይ ችግኞች ለተከላ መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል። ከእነዚህ መካከል 20 ሚሊዮን የሚሆነው የቡና እና ለምግብነት የሚውሉ የተለያዩ የፍራፍሬ ችግኞች መሆናቸውንም ተናግረዋል። ለችግኝ ተከላው ቀደም ብሎ መሬት በመለየት የጉድጓድ ቁፋሮ እና ሌሎች አስፈላጊ ዝግጅቶች መደረጋቸውን አንስተው ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል አሻራውን ለማኖር እንዲዘጋጅ ጥሪ አቅርበዋል። የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ ልማት በሀገር አቀፍ ደረጃ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአዲስ አበባ በይፋ መጀመሩን ተከትሎ በአማራ ክልልም ተጀምሯል።   በክልሉ በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞንና በባህርዳር ከተማ አስተዳደር የችግኝ ተከላ መከናወኑን አስታውሰው በሌሎች አካባቢዎችም በተጠናከረ መልኩ ይቀጥላል ብለዋል። በምዕራብ ጎጃም ዞን የሰከላ ወረዳ አርሶ አደር ገደፋዬ ሞገስ እና በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን የጓጉሳ ወረዳ አርሶ አደር አለማሁ አድማስ፤ የተራቆቱ አካባቢዎችን በመትከልና በመንከባከብ የድርሻችንን ለመወጣት ተዘጋጅተናል ሲሉ ተናግረዋል። ጥቅሙን በአግባቡ በመረዳቸው በዘንድረው የክረምት ወቅትም የሚተክሏቸውን ችግኞች በባለቤትነት ተንከባክበው ለማሳደግ መዘጋጀታቸው አስታውቀዋል። በክልሉ ባለፈው ዓመት የክረምት ወቅት ከተተከሉት ከ1 ነጥብ 4 ቢሊዮን በላይ ችግኞች ከ82 በመቶ በላይ መፅደቁን ከቢሮው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
በሚቀጥሉት አስር ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የአገሪቱ አካባቢዎች ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ-ኢንስቲትዩቱ
Jul 2, 2025 54
አዲስ አበባ፤ሰኔ 25/2017(ኢዜአ):-በሚቀጥሉት አስር ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የአገሪቱ አካባቢዎች ብዙ ቦታዎች ላይ ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ። ኢንስቲትዩቱ ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው በሚቀጥሉት አስር ቀናት ለክረምት ዝናብ መፈጠር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ይበልጥ እየተስፋፉና እየተጠናከሩ ይቀጥላሉ። በደቡብ ምዕራብ፣ምዕራብ፣ሰሜን ምዕራብ፣ሰሜን፣ መካከለኛው እና ሰሜን ምስራቅ የአገሪቱ ክፍሎች ላይ የተሻለ የዝናብ መጠንና ሥርጭት እንደሚኖር አሃዛዊ የትንበያ መርጃዎች እንደሚያሳዩ ተጠቁሟል። በተለይ በደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ሰሜን ምዕራብና መካከለኛ የአገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ ብለዋል። አልፎ አልፎ በውሃ አካላትና አካባቢ በምዕራብ፣ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ እና መካከለኛው የአገሪቱ አካባቢዎች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚሊ ሜትር በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ሊኖራቸው እንደሚችል ገልጸዋል። በተወሰኑ አካባቢዎች ላይ ነጎድጓዳማና በረዶ አዘል ዝናብ እና የዝናቡ ጥንካሬም ለረጅም ሰዓታት ያለማቋረጥ ዝናብ ሊኖር እንደሚችል በመግለጫው ተመላክቷል። በክረምቱ ወቅት የሚዘንበው ዝናብ በአመዘኙ አዎንታዊ ሚና የሚኖረው መሆኑ ተገልጿል። ይህም አስቀድሞ ለተዘሩ ሰብሎች፣ ለመኽር ሰብሎች፣ ለቋሚ ተክሎችና የጓሮ አትክልት የውሃ ፍላጎት ለማሟላት በኩል መልካም አጋጣሚ የሚፈጥር መሆኑ ተገልጿል። አብዛኛው የአገሪቱ ተፋሰሶች ላይ ከመጠነኛ እስከ ከፍተኛ የገጸ ምድር የውሃ ፍሰት ይኖራቸዋል፤ነገር ግን አልፎ አልፎ የሚኖረው ከባድ ዝናብ ጎርፍ ሊያስከትል ስለሚችል ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ ተመላክቷል። በሌላ በኩል በመጪው አስር ቀናት የቀኑ ከፍተኛ ሙቀት በአፋር፣ በምስራቅ አማራ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ምዕራብ እና ደቡብ ምስራቅ የአገሪቱ ሥፍራዎች ላይ ከ26 እስከ 41 ዲግሪ ሴልሺዬስ በላይ ሙቀት እንደሚኖራቸው ትንበያው ያሳያል።
በአረንጓዴ አሻራ በንቃት በመሳተፍ ሌሎች የማህብረሰብ ክፍሎች ተሳትፏቸውን እንዲያጠናክሩ እንሰራለን -የምክር ቤት አባላት
Jul 2, 2025 52
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 25/2017(ኢዜአ)፦በእረፍት ጊዜያቸው ወደ ተመረጡበት አካባቢ ሲሄዱ በአረንጓዴ አሻራ በንቃት በመሳተፍ ሌሎች የማህብረሰብ ክፍሎች ተሳትፏቸውን እንዲያጠናክሩ አበክረው እንደሚሰሩ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ገለጹ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ ሰኔ 20/2017 ዓ.ም በይፋ ማስጀመራቸው ይታወቃል። "በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ሃሳብ በሚካሄደው በዘንድሮው አረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር በአገር አቀፍ ደረጃ 7 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል ይሆናል። ይህንን ተከትሎ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የአረንጓዴ አሻራ መረሃ-ግብር መካሔድ ጀምሯል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት አረንጓዴ አሻራን አስመልክቶ ለኢዜአ በሰጡት አስተያየትም ዜጎች በአረንጓዴ አሻራ መረሃ-ግብር በመሳተፍ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በሚደረገውን ጥረት የበኩላቸውን እየተወጡ ይገኛሉ። ዜጎች በአረንጓዴ አሻራ መረሃ-ግብር እያደረጉ ያለውን ተሳትፎ የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡ አባላቱ በእረፍት ጊዜያቸው ከማህበረሰቡ ጋር በመሆን በአካባቢያቸው በአረንጓዴ አሻራ መረሃ-ግብር የነቃ ተሳትፎ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል አዲሷ አሰፋ እንደገለጹት፤ ችግኝ መትከል ከሚሰጠው ዘርፈ ብዙ ጥቅም በተጨማሪ ለምግብ ሉዓላዊነት መረጋገጥ ትልቅ ጠቀሜታ አለው፡፡ በመሆኑም ማህበረሰቡ በአረንጓዴ አሻራ ላይ ያለውን ተሳትፎ ይበልጥ በማጠናከር ውጤቱን ማሳደግ እንደሚገባም አመልክተዋል፡፡   በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት ስራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል ኡስታዝ ካሚል አሊ በበኩላቸው፤ አረንጓዴ አሻራ ለሁለንተናዊ አገራዊ እድገት ወሳኝ በመሆኑ ዜጎች በአረንጓዴ አሻራ መረሃ-ግብር ላይ ተሳትፏቸውን ማጠናከር አለባቸው ብለዋል፡፡ በዚህ ረገድ በቀጣይ ወደ ተመረጡበት አካባቢያቸው ሲመለሱ ከተጣለባቸው ኃላፊነት ጎን ለጎን ህዝቡ በአረንጓዴ አሻራ መረሃ-ግብር ይበልጥ ተሳትፎ እንዲጠናከር እንደሚሰሩ ገልጸዋል።   በምክር ቤቱ የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል ወጌ ቁፋ አረንጓዴ አሻራ ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ተመናምኖ የቆየውን የደን ሃብት ወደ ነበረበት በመመለስ ረገድ ጉልህ አስተዋጽኦ አበርክቷል ብለዋል። በመሆኑም ህዝቡ በአረንጓዴ አሻራ ላይ ያለውን ተሳትፎ እንዲጨምር ህዝቡን በማስተባበርና አብሮ በመትከል አገራዊ ሃላፊነታቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል።   ባለፉት አመታት በተከታታይ ተግባራዊ በተደረገው በአረንጓዴ አሻራ መረሃ-ግብር እየተገኙ ያሉ ውጤቶችን ዘላቂ ማድረግ የሁሉም ዜጋ ሃላፊነት ነው ያሉት ደግሞ በምክር ቤቱ የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል ሙሉነሽ ነሞሬ ናቸው። በመሆኑም ማህበረሰቡ ለአረንጓዴ አሻራ መረሃ-ግብር ያለውን ተነሳሽነት በመጨመር ያለውን ተሳትፎ እንዲያጎላ ጥሪ አቅርበዋል።    
የአካባቢ መራቆት የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቋቋም ችግኝ ከመትከል ባለፈ ለእንክብካቤ ሥራ ትኩረት ሰጥተናል
Jul 2, 2025 60
ወሊሶ፤ ሰኔ 25/2017(ኢዜአ)፡-የአካባቢ መራቆት የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቋቋም ችግኝ ከመትከል ባለፈ ለእንክብካቤ ሥራ ትኩረት መስጠታቸውን ኢዜአ ያነጋገራቸው የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ነዋሪዎች ገለጹ። በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የዘንድሮው አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ወንጪ ወረዳ የክልሉ መንግስት ሀላፊዎች እና የአካባቢው ነዋሪዎች በተገኙበት ተጀምሯል። በችግኝ ተከላው ላይ የተሳተፉትና አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡት የአካባቢው ነዋሪዎች በአካባቢው መራቆት ምክንያት ለተለያዩ ችግሮች ተጋልጠው መቆየታቸውን አስታውሰዋል። ከአካባቢው ነዋሪዎች መካከል አቶ ሀይሉ ጉልቲ በወንጪ ወረዳ የችግኝ ተከላ የተካሄደበት "ቱሉ ሶንቆሌ" ተራራ ከዓመታት በፊት በደን የተሸፈነ ነበር ብለዋል። ተራራው በጥቂት ዓመታት ውስጥ ተራቁቶ አፈሩም በጎርፍ እየተጠረገ ሲቸገሩ መቆየታቸውን ጠቅሰው፣ ባለፉት የበጋ ወራት ተራራውን መልሶ ለማልማት የጠረጴዛ እርከን ሲሰሩ መቆየታቸውን ተናግረዋል። በተራራውና በአካባቢው የገጠመውን የመሬት መራቆት መልሶ እንዲያገግም የተለያየ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን እየተከሉ መሆናቸውንና ለተተከሉ ችግኞች የሚያደርጉትን እንክብካቤ እንደሚያጠናክሩ ተናግረዋል።   አቶ ሽፈራው ጎቡ በበኩላቸው የተራቆተ መሬት ተመልሶ አረንጓዴ እንዲለብስ ችግኝ መትከል ብቻ በቂ ባለመሆኑ ሌሎች የአካባቢው ነዋሪዎችን ጭምር በማስተባበር ለተተከሉ ችግኞች እንክብካቤ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል። "ችግኝ መትከል ብቻውን በቂ ስላልሆነ የእንክብካቤ ሥራውም በቂ ትኩረትን ይሻል" ያሉት ደግሞ አቶ ወርቅነህ ታደሰ ናቸው።   "ችግኝ ተክሎ መሄድ ብቻ ሳይሆን እንዲጸድቅ እያንዳንዱ ሰው ሀላፊነቱን መወጣት አለበት፤ የተተከሉ ችግኞች ሁሉ ለፍሬ እንዲበቁ የበኩላችንን እንወጣለን'' ሲሉም አከልዋል። አቶ ታደለ ድንቁ እና ወይዘሮ ወገኔ ድንቁም የሌሎቹን ሃሳብ የሚጋሩ ሲሆን በአካባቢያቸው የተተከሉ ችግኞች እንዲድቁም የሚጠበቅባቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።   ችግኝ የሚተከለው ለዛሬው ትውልድ ብቻ ሳይሆን ለመጪው ጭምር በመሆኑ የተተከለ ችግኝ ፍሬ እንዲያፈራ ሁሉም ሰው መንከባከብ አለበት ብለዋል።    
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
በህንድ የአውሮፕላን አደጋ የ204 ዜጎች ህይወት አልፏል- የሕንድ ፖሊስ
Jun 12, 2025 543
አዲስ አበባ፤ሰኔ 5/2017 (ኢዜአ)፦በህንድ የአውሮፕላን አደጋ የ204 ዜጎች ህይወት ማለፉን የሀገሪቷ ፖሊስ አስታወቀ። በሕንድ 242 መንገደኞችን ይዞ በህንድ ሰሜን ምዕራባዊ ክፍል አህመዳባድ ከተማ ከሚገኘው አውሮፕላን ማረፊያ ወደ ለንደን ጋትዊክ ለማምራት በተነሳበት ቅፅበት በአካባቢው በሚገኝ ሆስፒታል የህክምና ባለሙያዎች ማረፊያ ላይ ተከስክሷል። በቦይንግ 787-8 ድሪምላይነር አውሮፕላን ውስጥ 169 ህንዳውያን፣ 53 የብሪታኒያ ዜጎች፣ 7 ፖርቹጋላዊ እና አንድ ካናዳዊ ነበሩ።   በአደጋው የተረፈ ሰው ለማግኘት የሚቻልበት እድል እጅጉን የጠበበ ነው ሲል የአህመዳባድ ፖሊስ ኃላፊ ለአሶሲዬትድ ፕሬስ ገልጾ ነበር። ይሁንና ማምሻውን በወጣ መረጃ የ40 ዓመት የህንድ እና ብሪታኒያዊ ጥምር ዜግነት ያለው ቪሽዋሽ ኩማር ራሜሽ ከአደጋው መትረፉ ተጠቁሟል። እስከ አሁን የ204 ሰዎች አስክሬን ተገኝቷል። የአውሮፕላኑ አካል የህክምና ባለሙያዎች ማረፊያ ላይ ወድቆ ቢያንስ አምስት የህክምና ተማሪዎች መሞታቸውን እና 50 ገደማ የሚሆኑት መጎዳታቸው ተገልጿል። የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት የሀዘን መግለጫ መልዕክት አደጋው ቃል ከሚገልጸው በላይ ልብ የሚሰብር ነው ሲሉ ገልጸዋል። በአደጋው ለተጎዱ በሙሉ ልባዊ ሀዘናቸውን በመግለጽ መጽናናትን ተመኝተዋል።
ኮሚሽኑ በአፍሪካ ሰላምና ደህንነት ማስፈን ዋንኛ የትኩረት አቅጣጫው አድርጎ ይሰራል- መሐሙድ አሊ ዩሱፍ
May 12, 2025 1105
አዲስ አበባ፤ግንቦት 4/2017(ኢዜአ)፡- የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን አዲሱ አስተዳደር በአፍሪካ ሰላምና ደህንነት ማስፈን ዋንኛ የፖሊሲ የትኩረት አቅጣጫው በማድረግ እንደሚሰራ የኮሚሽኑ ሊቀ-መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን አዲሱ ሊቀ-መንበር መሐመድ አሊ ዩሱፍ ከሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ጋር ዛሬ ትውውቅ እና ቆይታ አድርገዋል። ሊቀ-መንበሩ በስልጣን ጊዜያቸው ሊያሳኳቸው ስላቀዷቸው ተቋማዊ ግቦችና ቅድሚያ ሰጥተው ለመፈጸም ያሳቧቸውን ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች አስመልክቶ ገለጻ አድርገዋል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን አዲሱ አስተዳደር በሰላም፣ ደህንነት፣ ልማትና ዓለም አቀፍ ትብብር ላይ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ገልጸዋል። መሐመድ አሊ ዩሱፍ ሰላምና ደህንነት የኮሚሽኑ ዋንኛ የትኩረት ማዕከል መሆኑን አመልክተዋል። ኢ-ሕገ መንግስታዊ የመንግስት ለውጦች በአፍሪካ መረጋጋት ላይ ከፍተኛ ስጋት መደቀናቸውን ተናግረዋል።   የአፍሪካ ህብረት መሰል ችግሮችን በመፍታት እንዲሁም ሰላምን በማስፈንና የዴሞክራሲ ስርዓትን በማረጋገጥ የህብረቱ አባል ሀገራትን ሉዓላዊነት እና ደህንነት መጠበቅ ላይ አበክሮ ይሰራል ነው ያሉት። ሊቀ-መንበሩ በገለጻቸው ኮሚሽኑ በዓለም አቀፍ መድረክ የአፍሪካን ድምጽ የበለጠ ለማጉላት እንደሚሻ ገልጸዋል። በዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ ውስጥ የአፍሪካ ህብረትን ሚና ማጠናከር ቁልፍ ግብ መሆኑን ጠቅሰው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ላይ ማሻሻያ እንዲደረግበት በጽኑ ሁኔታ እንደሚሟገት አመልክተዋል። ሊቀ-መንበሩ የፀጥታው ምክር ቤት አሁናዊ መዋቅር የታሪክ ኢ-ፍትሃዊነት በማለት የገለጹት ሲሆን አፍሪካ በዓለም አስተዳደር የሚገባትን ትክክለኛ ስፍራ በሚገልጽ ሁኔታ ምክር ቤቱ ማሻሻያ ሊደርግበት ይገባል ሲሉም ተናግረዋል። በሌላ በኩል በዲጂታል ኢኮኖሚና ሰው ሰራሽ አስተውሎት አማካኝነት በአፍሪካ ፈጠራ እና ዘላቂ ልማትን ማሳለጥ ሌላው የትኩረት አቅጣጫ ነው ብለዋል። የህብረቱ ኮሚሽን ከቀጣናዊ ኢኮኖሚ ማህበረሰቦች ጋር ያለውን ትብብር የበለጠ በማጠናከር ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር ወጥነት ባለው መልኩ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ሊቀ-መንበሩ በአፍሪካ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል አማካኝነት ወረርሽኝን የመከላከል ዝግጁነት እና ምላሽ አቅም ላይ ከፍተኛ ለውጥ መምጣቱንም አንስተዋል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን አዲሱ ሊቀ-መንበር መሐመድ አሊ ዩሱፍ በቀጣይ ከሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ጋር በየሶስት ወር ጊዜ ቆይታ እንደሚያደርጉ ለማወቅ ተችሏል። በየካቲት ወር 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ በተካሄደው 38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ መሐመድ አሊ ዩሱፍ ሙሳ ፋቂ ማህማትን በመተካት የኮሚሽኑ ሊቀ-መንበር ሆነው መመረጣቸው የሚታወስ ነው።
ኢትዮጵያ በባንጁል ቻርተር እና በማፑቶ ፕሮቶኮል ያላትን የአፈጻጸም ሪፖርቶች ማቅረብ ጀመረች
May 10, 2025 792
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 2/2017(ኢዜአ)፦ በፍትህ ሚኒስትር ዴኤታ በላይሁን ይርጋ የተመራ የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን በአፍሪካ የሰዎችና ህዝቦች መብቶች ቻርተር ስብሰባ ላይ እየተሳተፈ ነው። በጋምቢያ ባንጁል የአፍሪካ የሰዎችና ህዝቦች መብቶች ኮሚሽን ዋና መሥሪያ ቤት እየተካሔደ ባለው ስብሰባ ላይ በአፍሪካ የሰዎችና ህዝቦች መብቶች ቻርተር (ባንጁል ቻርተር) ወቅታዊ የኢትዮጵያ አፈጻፀምና በአፍሪካ የሴቶች መብቶች ፕሮቶኮል (ማፑቶ ፕሮቶኮል) መነሻ ወቅታዊ አፈጻፀም ላይ ልኡኩ ሪፖርቶችን ማቅረብ ጀምሯል።   ሚኒስትር ዴኤታው ለኢዜአ እንደገለጹት ኢትዮጵያ በሪፖርት ዘመኑ በቻርተሩና ፕሮቶኮሉ መሰረት ያሉባትን ግዴታዎች ለመወጣትና የሰብአዊ መብቶችን ከማስጠበቅ አንጻር የተወሰዱ የፖሊሲ፣ የህግ እና ተቋማዊ እርምጃዎችን የሚመለከቱ ለውጦች ሪፖርት በዝርዝር ቀርቧል። በኮሚሽኑ መርሃ-ግብር መሰረትም ሪፖርቱን ተከትሎ ከኮሚሽነሮች ለተነሱ ጥያቄዎች ኢትዮጵያ በልዑካን ቡድኑ አማካኝነት ሰኞ ግንቦት 4 ቀን 2017 ምላሾችን ትሰጣለች ተብሎ እንደሚጠበቅም ሚኒስትር ዴኤታው ጠቁመዋል። መድረኩ ኢትዮጵያ በባንጁል ቻርተር እና በማፑቶ ፕሮቶኮል ስምምነቶች መሰረት በአገሪቱ የሰብዓዊ መብቶችን እና የፆታ እኩልነትን ለማጎልበት ያላትን ቁርጠኝነት የምታሳይበት እንደሆነም ተገልጿል።
በቱርኪዬ ኢስታንቡል በሬክተር ስኬል 6 ነጥብ 2 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ
Apr 23, 2025 1417
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 15/2017(ኢዜአ)፦በዛሬው እለት በቱርኪዬ ኢስታንቡል በሬክተር ስኬል 6 ነጥብ 2 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል። እንደ አናዶሉ የዜና ወኪል ዘገባ ዛሬ ቀትር ላይ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ የኢስታንቡል እና ጎረቤት አካባቢ ነዋሪዎች በፍርሃት የመኖሪያ ህንጻቸውን ለቀው እንዲወጡ አድርጓቸዋል። በሌላም በኩል ረፋዱ ላይ በኢስታምቡል አቅራቢያ የባህር ዳርቻ ቡዩኪክሚ የተባለ ስፍራ ላይ በሬክተር ስኬል 4 ነጥብ 9 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን አናዶሉ የዜና ወኪል የሃገሪቱን የድንገተኛ አደጋ መቆጣጠር ባለስልጣን ጠቅሶ ዘግቧል። በአደጋው ምንም የተመዘገበ ጉዳት እንዳልተከሰተ የጠቀሰው ዘገባው ነዋሪዎች የዚህ ዓይነት አጠራጣሪ ሁኔታ ሲገጥም የተጎዱ ሕንጻዎች ውስጥ እንዳይገቡ የግድ አስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር ተሽከርካሪዎችን እንዳይጠቀሙና ሌሎች የጥንቃቄ መልዕክቶችን ባለስልጣኑ ማስተላለፉም ተገልጿል። የሃገሪቱ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በቅርበት እየተከታተሉ መሆናቸውንና ለዜጎችም መልካም ሁኔታ እንዲገጥማቸው መመኘታቸው ተገልጿል። ፕሬዝዳንቱ ከሃገሪቱ የድንገተኛ አደጋ መቆጣጠር ባለስልጣንና ከሚመለከታቸው አካላት መረጃዎችን በመቀበል በቅርበት እየተከታተሉ እንደሚገኙም ተገልጿል።
ሐተታዎች
የህንድ የፈጠራ ማዕከል - ባንጋሎሩ
Jul 2, 2025 62
ቤተልሄም ባህሩ(ኢዜአ) የዴልሂና አግራ ቆይታችንን ጨርሰን ወደ ቀጣይ መዳረሻችን ባንጋሎሩ ከተማ ልንጓዝ ስንሰናዳ አብዛኛው የጋዜጠኛ ልዑክ ያሳሰበው እንደሰም የምታቀልጠውን የአግራ ፀሀይና ሙቀት በባንጋሎሩም ታገኘን ይሆን? የሚለው ነበር። ሆኖም ከዴልሂ ኢንድራ ጋንዲ አየር ማረፊያ ተነስተን ለሶስት ሰዓት ከተቃረበ በረራ በኋላ ያገኘናት ባንጋሎሩ የተለየች ሆነን አገኘናት። ባንጋሎሩ ቀዝቀዝ ባለ አየር ነበር እንግዶቿን የተቀበለችን። በዕለቱ ከክፍሎቻችን ወጥተን በጋራ ወደአየር ማረፊያ የሚወስደንን ትራንስፖርት ስንጠባበቅ ከጋዜጠኛ ቡድኑ ስድስት አባላት ከአጠገባችን እንዳልነበሩ አስተዋልን። የት ጋር እንደተነጣጠልን አላስታውስም። በዚህ ምክንያት ግን የእለቱ ጉዟችን ተሰርዞ ከተማዋን ለማየት ስንዘዋወር የማውቀው ዓይነት እንጂ የተለየ ሙቀት አላስተናገድኩም። የ13 ወር ፀጋ በመባል የምትታወቀው አገሬ ኢትዮጵያ ከዳሎል እስከ ራስ ዳሽን ባላት የመልከዓ ምድር አቀማመጥና ልዩ ልዩ የአየር ጠባይ ሙቀቱንም፣ ቅዝቃዜውንም ማወቃችን እንደዚህ ለአለ አጋጣሚ መልካም ስሜት ይፈጥራል። በተወሰነ ደረጃ በህንድ ያጋጠመኝ የአየር ባህሪ ከአገሬ ጋር ቢመሳሰልብኝ የፈጣሪንና የተፈጥሮን ስራ አጃኢብ ብዬ እንዳልፍ አድርጎኛል። ባንጋሎሩ ከተማ የቴክኖሎጂና ፈጠራ ማዕከል በመሆኗ የህንድ ሲልከን ቫሊ በመባል ትታወቃለች። ሃይማኖታዊና ታሪካዊ ስፍራዎችም ከመገለጫዎቿ መካከል ናቸው። የጠፈር ጠበብቶቹ - ባንጋሎሩ ደርሰን በመጀመሪያ ያየነው ዓለም በስፔስ ሳይንስ እየሰራች ያለችውና እያስመዘገበችው የምትገኘው ውጤት ማሳያ የሆነውን የህንድ ስፔስ ምርምር ድርጅትን ነው። ተቋሙ የህንድ መንግስት የስፔስ ዲፓርትመንት አካል ሲሆን፤ ዶክተር ቪክራም ሳራብሃይ በተሰኙ ባለራዕይ በ1962 የተወጠነና አሁን ላይ በዘርፉ ተገዳዳሪ መሆን የቻለ ነው። የተቋሙ ዓላማ የስፔስ ቴክኖሎጂዎችን በማልማትና በመተግበር ለተለያዩ አገራዊ ጥቅሞች ማዋል መሆኑን ተከትሎ የሳተላይት ማምጠቂያ መሳሪያዎችን የማምረት ስራን ጨምሮ ከአገሩ አልፎ ለሌሎች አገራትም በዘርፉ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል። የተደረገልን ገለፃ አብዛኛውን ጋዜጠኛ ያስደመመ ነበር ከገለፃ በኋላ በጋዜጠኞች የተነሳው ሃሳብም ህንድ በስፔስ ዘርፍ ያላት ልምድና ያከናወነችው ተግባር በቀጣይም ልትሰራ የወጠነቻቸው ሃሳቦች የአገሪቱን መዳረሻ የተለሙ በአገራቸው እንዲተገበር የሚናፍቁት መሆኑን ነው። ተቋሙ በዘርፉ ለተሰማሩ ኢትዮጵያዊያን የአቅም ግንባታ ድጋፍ እያደረገ መሆኑንና በቀጣይም ትብብሩን የሚያጠናክር መሆኑን ከተደረገልን ገለፃ ተገንዝበናል።   በሳይንስ፣ ኢንጂነሪንግና አስተዳደር ምሁራንን በማስተማር እያበረከተ ያለው የህንድ የሳይንስ ኢንስቲትዩት በባንጋሎሩ ከጎበኘናቸው መካከል የሚጠቀስ ነው። ኢንስቲትዩቱ ከአፍሪካ የተውጣጡ ተማሪዎችን የሚያስተምርና ከተቋማት ጋርም በዘርፉ የሚሰራ ሲሆን፤ በኢትዮጵያም ከጅማ፣ በተግባር ለመቀየር ሲታትሩ የስታርት አፖችን የምርት ውጤቶቻቸውን ሲፈትሹና ሲሞክሩ ተመልክቻለሁ። በኢትዮጵያም አሁን ላይ ለስታርት አፖች በተሰጠው ትኩረትና በተፈጠረው ምቹ ስነ ምህዳር የፈጠራ ውጤቶች እያደጉና እየተበራከቱ መሆናቸው የሚታወቅ ነው። እንደ አዳማና አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ያሉ ተቋማት የተማሪዎችን ፈጠራ ወደ ውጤት ለመቀየር እየተጉ መሆኑና የስታርት አፕ ኤግዚቢሽንና የሰመር ቡት ካምፖች ፈጠራን ምን ያህል እያበራከቱ መሆናቸው በጉብኝቱ ወቅት ወደ አዕምሮዬ የመጣ የአገሬው ህዝብ በውጤት የታጀበ ጥረት ነው።   ከአራት አስርት ዓመታት በላይ በባዩቴክኖሎጂ ዘርፍ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ የሚገኘው ባዮኮንም ከባላንጎሩ የጉብኝት መዳረሻችን መካከል የሆነና አስፈላጊ መድሀኒቶችን የሚያመርትና በዘርፉ ያሉ ባለሙያዎች አቅም ግንባታ ላይም እየሰራ ያለ ነው። ኢትዮጵያን ጨምሮ የአፍሪካ አገራት የአቅም ግንባታ ስልጠናው ተጠቃሚ ናቸው። ከ120 በላይ በሆኑ አገራት ለስኳርና ካንሰር ህመም የሚያገለገሉ መድሀኒቶችን በማምረትና በማሰራጨት ለህሙማን ፈውስና ለጤናው ዘርፍ ስርዓት አስተዋፅኦ እያበረከተም ይገኛል። የተቋሙ ላቦራቶሪና ዘመኑን የዋጀና ደረጃውን የጠበቀ ማምረቻ ፋብሪካን መጎብኘቴ አለም በፋርማሲዩቲካልስ ዘርፍ ያለችበትን ሁኔታ የሚያሳይ ነው። የባንጋሎሩ ቤተመንግስት - ይህን ቤተ መንግስት ማስቃኘቴን ከመጀመሬ በፊት በስፍራው ካስገረመኝ ነገር ላወጋችሁ ወደድኩ። ቤተ መንግስቱን ለመጎብኘት ያቀናነው በእለተ ሰኞ ነበር። ሆኖም ምድረ ግቢውን ቃኝተን ስለህንፃው ሰምተን ከመመለስ ውጪ ወደ ውስጥ አልዘለቅንም። ለምን? ለሚለው ምላሹ በዚህ ስፍራ "ሰኞ የእረፍት ቀን ናት" ነው። እንዴት ካላችሁ ቤተ መንግስቱ ቅዳሜና እሁድ በበርካታ ሰዎች የሚጎበኝ መሆኑን ተከትሎ በስፍራው ለሚሰሩ ሰራተኞች የእረፍት ቀናቸው ሰኞ በመሆኑ ነው። የቤተ መንግስቱ ምድረ ግቢ ሰፊና ልምላሜ የተላበሰ ሲሆን፤ የሚያምርና ለዓይን የሚስብ ኪነ ህንፃ ያለው ነው። አሰራሩና ውጥኑም እንደሚከተለው ነው። በዎዲየር ስርወ መንግስት ንጉስ ቻማራጃ ዋዲያር ወደ እንግሊዝ ባደረጉት ጉዞ በለንደን ዊንሶር ግንብ ይደነቃል። ተደንቆም አልቀረ የባንጋሎሩ ቤተ መንግስትን በተመሳሳይ ሁኔታ ይገነባል። ይህ ቤተ መንግስት በተወሰነ መልኩ የመካከለኛው ዘመን የኖርማንሲና የእንግሊዝ ግንቦችን ይመስላል።   ቪድሃና ሶውዳ የካራንታካ ህግ አውጪ አካል መናገሻ በጉብኝታችን ያየነው ሌላው መዳረሻ ስፍራችን ነው። የህግ አውጪና የህግ መወሰኛ ምክር ቤት የያዘው ይህ ህንፃ ህንድ ነፃነቷን ካገኘች በኋላ በራሷ መሀንዲስ የሰራችው የመጀመሪያው ህንፃ መሆኑ ተገልፆልናል። የህንፃ ግንባታ ጥበብ ማሳያ፣ የፖለቲካ መናገሻ እንዲሁም የባህል ማሳያ ተደርጎም ይወሰዳል።   እንደአጠቃላይ በቆይታዬ የተመለከትኩት የመሰረተ ልማት ግንባታ፣ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ፈጠራ ማበረታቻ እንዲሁም የአረንጓዴ ልማት ስራ ኢትዮጵያ እያከናወነች ካለው የኮሪደር ልማትና ስታርት አፕን የማበረታታት ብሎም የሳይንስና ቴክኖሎጂ ስነ ምህዳር ምቹነት ስራዎች ጋር ተመሳሳይነት ያለው መሆኑን ነው። በህንድና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ግንኙነት ዘመናትን የተሻገረ፤ ለሁለት ሺህ ዓመታት የዘለቀ መሆኑን የታሪክ መዛግብት ያሳያል። የህንድና ኢትዮጵያ ግንኙነት በአክሱም ስርወ መንግስት ኢትዮጵያና ህንድ በአዱሊስ ወደብ በኩል የንግድ ልውውጥ ሲያደርጉ እንደነበር የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ። በወቅቱ ኢትዮጵያ ቅመማ ቅመምና ሐርን ከህንድ ትገበይ ነበር። ህንድ ደግሞ ወርቅና የዝሆን ጥርስን ከኢትዮጵያ ትሸምት ነበር። ህንድ ከንግድ ልውውጥ ባሻገር በኢትዮጵያ ኪነ ህንፃ ግንባታ ላይ አሻራዋን አኑራለች። በኢትዮጵያ በትምህርት ዘርፍም ትልቅ አበርክቶ ያላት አገር ናት። ህንድ ነፃነቷን ካገኘችበት እኤአ 1948 አንስቶ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩት ኢትዮጵያና ህንድ ሌላው የሚያመሳስላቸው ነገር ሆኖ ያገኘሁት የአምራች ዘርፉን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ እያከናወኑ ያሉት ንቅናቄ ነው። ህንድ እ.አ.አ ከ2014 ጀምሮ የአምራች ዘርፉን ለማበረታታት "ሜድ ኢን ኢንዲያ" በሚል ለአስር ዓመት የተገበረችውና በርካታ ለውጥ የተመዘገበበት ንቅናቄ በኢትዮጵያ ከ2014ዓ.ም ጀምሮ እየተተገበረ ካለውና የሃገር በቀል ምርቶች እና አምራቾችን ማጠናከር፣ የኢንዱስትሪያል ማህበረሰብ ግንባታን ማሳደግ ፣ ምቹ የቢዝነስ ከባቢ መፍጠር እና የጥናት እና ምርምር ችግር ፈቺነትን ማሳደግን ዓላማ ካደረገው የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ጋር የተመሳሰለ ነው። ንቅናቄ በኢትዮጵያ መተግበሩ ዓመታዊ የዘርፍ ዕድገት፣ የማምረት አቅም አጠቃቀምና ገቢ ምርት በመተካት በኩል ጉልህ ሚና እየተወጣ መሆኑም ይታወቃል። በህንድ ተዘዋውሬ በተመለከትካቸው ከተማዎች ባሉ ጎዳናዎች ከታዘብኩት ነገር ሰዎች ከሱቅ ለሚገበያዩት ነገር ሳይቀር በዲጂታል መንገድ ክፍያ መፈፀማቸውን ነው። በባጃጅና በሞተር የትራንስፖርት አገልግሎት ለማግኘትም ጭምር ሞባይሉን በመጠቀም “ይህ ቦታ የት ነው?” ሳይል ያሻዎት ስፍራ መድረስም ሌላው ትዝብቴ ነው። ይህ ነገር በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ትኩረት አግኝተው እየተሰራባቸው ካሉት የዲጂታል ክፍያና ዲጂታል ክህሎት ማሳደጊያ መርሃ ግብር ጋር የሚመሳሰል ሆኖ አግኝቼዋለሁ። በቆይታችን ልክ እንደአትሌቶቻችን ሁሉ በዓለም አደባባይ የኢትዮጵያን ስም ከፍ አድርጎ የሚያስነሳውን ኢትዮጵያ አየር መንገድ ዝናና ክብር ለማስተዋል ችያለሁ። ፀጉረ ልውጥ መሆናችንን የተገነዘቡ በገበያ ማዕከላት የሚያገኙን እንዲሁም በምንጎበኛቸው ተቋማት የምንተዋወቃቸው ህንዳውያን "ከየት ናችሁ?" ብለው ሲጠይቁ፤ ለእኔና አንድ ከሌላ መገናኛ ብዙሃን የሄድን "ከኢትዮጵያዊ" ስንል የሚከተልልን ምላሽ "አሃ የኢትዮጵያ አየር መንገድ" የሚል ነው። ይህም አየር መንገዱ ስሙ ከኢትዮጵያ ተሰናስሎ የሚጠራ የአገሪቷ መታወቂያ ተቋም መሆኑን ያስገነዘበኝ ነው። ከህንዳውያን ጋር ብቻ ሳይሆን አብረን ከተጓዝን ጋዜጠኞች አንዱ "የኢትዮጵያ አየር መንገድ የእናንተ የብቻ ሳይሆን እኛንም እንደራሳችን ሆኖ እያገለገለን ያለ የጋራ አየር መንገዳችን ነው" ሲል ነው የገለፀው። ይሄ ለእኔ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአገር ኩራት ብቻ ሳይሆን መለያ ምልክትም ጭምር መሆኑን የተረዳሁበት አጋጣሚ ነው። በቀናት ቆይታዬ በእንግዳ አክባሪነታቸውና በለገሱን ፍቅርና እንክብካቤ ከአገሬ የራቅኩ ያህል ሳይሰማኝ ብቸኝነትን ሳላስተናግድ እንደውም እየናፈኳቸው እንድመለስ ላደረጉኝ ህንዳውያን በከበረ ሰላምታ ላመሰግን እወዳለሁ።
ውበትና ትጋት በህንድ
Jun 27, 2025 273
በቤተልሄም ባህሩ (ኢዜአ) በልጅነቴ እያየሁ ያደግኳቸው አብዛኛዎቹ ፊልሞች የህንድ ናቸው። ይህ ደግሞ ከአገራችን አርቲስቶች በላይ የህንድ የፊልም ተዋንያኑን ስም ለመለየት አስችሎኛል። የህፃንነት ዘመኔን የሚያስታውሱኝን ፊልሞች ከትዝታ ማህደሬ እያወጣሁ ከመተረክ በስተቀር ህንድን የማይበት አጋጣሚ ይኖራል ብዬ አስቤ አላውቅም። እነዚያን በህንድ ፊልም የማደንቃቸውን የምደመምባቸውን የህንዳውያንን ሶስት ከተሞች ለመጎብኘት ከተመረጡ ከሰሜንና ምስራቅ አፍሪካ የተውጣጡ ጋዜጠኞች መካከል መሆን ድንገቴ ሆነብኝ። እኔም ብቻ ሳይሆን አብዛኛዎቹ የጋዜጠኞች ልዑካን ህንድ ከልጅነት ትዝታቸው ጋር የተሳሰረ አንዳች ነገር አለው። ህንድ በፊልሞቿ የሚያቋት ስለመሆኑ ጉብኝቱን ተከትሎ በተካሄደው በዶርሻን የቴሌቪዥን ጣቢያ ውይይት ላይ ሲያነሱ ሰምቻለሁ። በዓለም ላይ በህዝብ ብዛቷ ቀዳሚዋ ህንድ የብዝሃ ባህል፣ ቋንቋና ሃይማኖት አገር ናት። በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኪነ ጥበብ ስራዎቿ በዓለም ላይ ትታወቃለች። ለጉብኝት ከተጋበዙት የጋዜጠኞች ቡድን መካከል አባል ሆኜ በዴልሂ፣ አግራና ባንጋሎሩ ከተሞች በተጓዝንባቸው ስፍራዎች ሁሉ የታዘብኩት ህንዳዊያን በስራና ትጋት ላይ መሆናቸውን ነው። ሁሉም ነገውን ለማሳመር የራሱን ድርሻ ለማኖር፤ ለሀገሩ እድገትና ልማት አሻራውን ለማኖር እንደሚታትር መረዳት ይቻላል።   ባረፍንበት ሆቴል ያሉ ሰራተኞች፣ በገበያ ስፍራ የምናገኛቸው ሰዎች እንዲሁም በጎበኘናቸው ስፍራዎች ያሉ ሰዎች ሁሉ ለሀገራቸው እድገትና ልማት ብሎም ነጋቸውን ለማሳመር የራሳቸውን ድርሻ ለማኖር ይታትራሉ። አብሬ ከነበርኳቸው ጋዜጠኞች ጋር ስናወጋ የምናነሳው በከተማዋ በተጓዝንባቸው ጎዳናዎች የምናየው የመሰረተ ልማት ግንባታ፣ በየተቋማት የሚታትሩ ሰራተኞች እንዲሁም በንግድ የተሰማሩ ሰዎች ደፋ ቀና ማለት ለአገር የሚያደርጉትን ልፋት ነው። አንድ ቀን በጋራ ሆነን ወደገበያ ስፍራ ስናቀና በፍጥነት የሚደርሱ ምግቦች ተመግበው ለመሄድ የሚፋጠኑ ህንዳውያንን ያየ የጋዜጠኛ ቡድኑ አባል መሰል ልምድና ጊዜ አጠቃቀም በአፍሪካም ሊለመድ የሚገባውና የአህጉራችንን የስራ ባህልና እድገት የሚያረጋግጥ መሆኑን የገለጸበት ሁኔታ ለአገሬው ህዝብ ታታሪነት እንደማሳያ አድርጌ ላነሳው ወደድኩ። በሄድንባቸው አካባቢዎች ሁሉ አዲስ ሰው ሲያዩ ለማገዝ አና ስለነገሮች ለማስረዳት የሚፈጥኑ ዜጎችን ተመልክቻለሁ። በተጓዝኩባቸው ከተማዎች ያየኋቸውን ስፍራዎች ከማስታወሻዬ እየነቀስኩ ለእናንተ ላካፍል ወደድኩ። በቅድሚያ ከአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የስድስት ሰዓት ተኩል በረራ በማድረግ የመጀመሪያ መዳረሻ ያደረግናትን ዴልሂን እንቃኛለን። ዴልሂ- ታሪካዊ ህንፃዎችን ከአዲሶቹ ጋር አጣምራ የያዘች ጥንታዊ ስልጣኔን ከዘመናዊው ጋር አዋህዳ የምታንፀባርቅ ከተማ ናት። በከተማዋ በተዘዋወርንባቸው ስፍራዎች ሁሉ ከጎዳናዎቿ እስከ ህንፃዎቿ ምድረ ግቢ ድረስ በእፅዋት የተሞላችና ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ትኩረት የሰጠች መሆኗን በግልፅ ያሳየች ከተማ ናት። በዴልሂ ብቻም ሳይሆን በተዘዋወርንባቸው በሶስቱም ከተሞች ጎዳና ስንጓዝ ያየናቸው ግዙፍ ዛፎች ትናንት አገሪቷ ለእፅዋት የሰጠችው ትኩረት ዛሬ ላይ ፍሬ አፍርቶ አስተዋልኩ። ይህ ደግሞ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ባለፉት ዓመታት እየተከናወነ ያለው ተግባር እንዲሁም በኮሪደር ልማት ከተሞችን ፅዱና አረንጓዴ ለማድረግ የተጀመረው ጥረት አሁን ላይ ካመጡት ለውጥ ባለፈ ለወደፊት የሚኖራቸውንም መዳረሻ አሻግሬ ለማየት አስችሎኛል። አሰላሳዮቹ - በዴልሂ ቆይታችን በመጀመሪያ ያቀናነው ጥናቶችን በመስራትና ውይይቶችን በማድረግ በኩል አበርክቶ እያደረገ ያለውን ኦብዘርቨር ሪሰርች ፋውንዴሽን የተሰኘ አሰላሳይና ሃሳብ አመንጪዎች ቡድን (ቲንክ ታንክ ግሩፕ) ነው። ተቋሙ በአገር ውስጥ ባሉ የኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ በማተኮር የመስራት ተልዕኮን አንግቦ የተነሳ ቢሆንም አሁን ላይ ከኢኮኖሚና እድገት ባለፈ በኢነርጂ፣ አካባቢ፣ በደህንነትና ሌሎች ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ላይ በማተኮር ለፖሊሲ ግብዓት የሚሆኑና ለውሳኔ የሚጠቅሙ ሃሳቦችን በማመንጨት የአገሪቷን ህዝብና መንግስት እያገዘ ይገኛል። ከተቋሙ አባላት ጋር ባደረግነው ቆይታ ለራስ ችግር የራስ መፍትሄ ማምጣት ተገቢ ስለመሆኑ በአጽንኦት አንስተዋል። የአፍሪካ አገራት ትብብር የአህጉሪቷን ልዕልና ለማረጋገጥ ወሳኝ ጉዳይ መሆኑም ተነስቷል። የአሰላሳይና ሃሳብ አመንጪዎች ቡድን አባላቱ ጋር ያደረግነውን ቆይታ ጨርሰን በቀጣይ ያመራነው በህንድ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ ባሉ አገራት ጭምር በባቡር መንገድ መሰረተ ልማት ላይ አሻራ እያኖረ ወዳለው ራይትስ ወደተሰኘው ተቋም ነው። የህንድ የባቡር መንገድ የቴክኒካልና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት (Rail India Technical and Economic Service) የተሰኘው ይህ ተቋም ላለፉት 51 ዓመታት በባቡር መንገድ ጠበብቶች አማካኝነት በህንድና በመላው ዓለም ባሉ 62 አገራት በዘርፉ ሲሰራ ቆይቷል።   የእጅ ጥበብ ገበያ - ቀጣይ መዳረሻችን ደግሞ ዲል ሃት ኢና የተሰኘው የባህላዊ አልባሳትና ጌጣጌጦች እንዲሁም የቤት ማስዋቢያዎች መገኛ ወደ ሆነው ገበያ ነው። ገበያው ባይገበዩበትም ዞረው እንዲቃኙ የሚያስገድድ አንዳች ድምቀትን የተላበሰ መሆኑን ባደረኩት ቆይታ አስተውያለሁ። የንግድ ማህበር የሆነው የህንድ ኢንዱስትሪ ኮንፌዴሬሽን (ሲአይ አይ) በዴልሂ ቆይታችን ካየናቸው ተቋማት መካከል የሚጠቀስ ነው። ተቋሙ የንግድ፣ ፖለቲካ፣ የትምህርትና የሲቪል ማህበረሰብ አመራር አባላትን በጋራ በማሰለፍ ዓለም አቀፍና የኢንዱስትሪ አጀንዳዎችን እንዲቀርፁ የሚሰራ ነው። አደጋን የሚቋቋም መሰረተ ልማት ጥምረት (CDRI) በነበረን ቆይታ ጥምረቱ ከአገራት፣ ከተባበሩት መንግስታት ኤጀንሲዎችና መርሃግብሮች፣ ከፋይናንስና የግል ተቋማት ጋር በመተባበር የአየር ንብረትና የአደጋ ስጋትን የሚቋቋም መሰረተ ልማት አስተዳደር ላይ እየሰራ መሆኑን ተገንዝበናል። ጥምረቱ የአደጋ ምላሽና መልሶ ማቋቋም፣ በተቋማትና ህብረተሰብ አቅም ግንባታ ድጋፍ ላይ ይሰራል። ጥምረቱ 46 አባል አገራትና ስምንት አጋር ድርጅቶች ያሉበት ሲሆን፤ አገራትና ዓለም አቀፍ አካላትን በማስተባበር የገንዘብና ቴክኒክ ድጋፍ የሚያደርግ የጥናትና ፈጠራዎች ውጤቶች እንዲሁም ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን የሚጋሩበትም ነው።   የህንድ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዴልሂ(IIT Delhi) ሌላው የጉብኝት መዳረሻችን ነበር። ኢንስቲትዩቱ በኢንጂነሪንግና ሳይንስ ጨምሮ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በርካታ ሰዎችን አስተምሮ ያስመረቀ ሲሆን፤ የተለያዩ ሳይንቲስቶች፣ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎችና ስራ ፈጣሪዎችን ማፍራት የቻለ ተቋም መሆኑን መገንዘብ ችለናል። ብሄራዊ ሙዝየም - በኒው ዴልሂ የሚገኘው የህንድ ብሄራዊ ሙዚየም በአገሪቱ ያለ ትልቁ ሙዚየም ሲሆን፤ በጉብኝታችን ወቅት ለዘመናት የቆየች ቅሪተ አካልን ጨምሮ፣ የተለያዩ የጥበብ ውጤቶችና የታሪክ አሻራ ማሳያ ስራዎችን ቀርበው ይጎበኙበታል። በዴልሂ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተደረገልን የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባባልና ውይይት ህንድና አፍሪካ የጠነከረ ቁርኝት ያላቸውና በንግድ አጋርነትት በቀዳሚነት የሚጠቀሱ መሆኑ ተመላክቷል። በተደረገልን ገለፃ ህንድና የአፍሪካ የንግድ መጠን 100 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ነው።   ህንድ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፣ ፋርማሲዩቲካል ፣ አውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪዎች ፣ ማዕድን እና የባንክ ዘርፎችን ያላት የአፍሪካ ኢንቨስትመንት ወደ 75 ቢሊዮን ዶላር ገደማ መድረሱም ተገልጿል። ኢትዮጵያም ከህንድ ጋር ለዘመናት የዘለቀ ወዳጅነት ያላትና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷም ረጅም ዓመታትን ያስቆጠረ መሆኑ ተነስቷል። ሁለቱ አገራት ያላቸው ግንኙነት በንግድና ኢንቨስትመንት ላይ ያተኮረ ብቻ ሳይሆን በባህል ትስስር ጭምርም የተጋመደ መሆኑ ተመላክቷል። ለወደፊቱም ኢትዮጵያን ጨምሮ ከአህጉሪቱ ካሉ አገራት ጋር የምታደርገው ትብብርና ወዳጅነት ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑም ተነስቷል። አግራ- የህንድ ታሪክ፣ ባህልና ኪነ ህንፃ መገለጫ በሆነችው አግራ ተገኝተን የጎበኘነው ህንድ ስትነሳ ስሙ ተያይዞ የሚነሳውን ታጅ መሃልን ነው። ታጅ መሃል በእምነ በረድ የተሰራ ውብ ኪነ ህንፃ ሲሆን፤ ንጉስ ሻህ ጃሃን ከሌሎች ሚስቶቹ ሁሉ አስበልጦ ለሚወዳት ሚስቱ ሙምታዝ መሀል ክብር ሲል የገነባው ድንቅ የእጅ ስራ ውጤት ነው። ታጅ መሃልን ስንጎበኝ የነበረው ሙቀት ሀይለኛ ቢሆንም ላባችን እየተንቆረቆረ ንጉሱ ለፋርስ ልዕልቷ ሚስቱ የነበረውን ፍቅር በተመለከተ በአስጎብኚያችን የሚሰጠንን ማብራሪያ ስናደምጥና የፍቅር ሃያልነትን ስናደንቅ ነበር። በዴልሂ ከጉብኝታችን ባሻገር በኢንዲያን ጌትና በገበያ ቦታዎች እንዲሁም በከተማዋ ጎዳናዎች ተዘዋውረን የህዝቡን ፍቅርና ተባባሪነት አይተናል። በተለይ ቦታ የጠፋን መሄድ ያሰብንበት ቦታ እንዳለ የሚያመላክት ፍንጭ በግርታችን ያስተዋሉ ከመሰላቸው "እዚህ መሄድ ፈልገህ ነው ይህን እዚህ ማግኘት ትችላለህ" የሚል ጥቁምታ በመስጠት እንግዳ ተቀባይነትና ሰው አክባሪነታቸውን ይገልፁልሃል። በዴልሂና አግራ የነበረንን ጉብኝትና ትዝታ እያሰላሰልን ቀጣይ መዳረሻ ያደረግናት ባንጋሎሩ ከተማን ነው። ባንጋሎሩ ቀጣይ ትረካችን ይሆናል።    
ስራዋን በውጤታማነት በማስቀጠል ለሌሎች ወጣቶችም መትረፍ የቻለችው ወጣት
May 22, 2025 820
ብርሃኑ ፍቃዱ - ከሰቆጣ ኢዜአ በ2013 ዓ.ም የልብስ ስፌት ስራ የጀመረችው ወጣት ማህደር አስማረ፤ ነዋሪቷ በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ ሰቆጣ ከተማ ነው። ስራዋን በውጤታማነት የቀጠለችው ወጣት ከአንድ የልብስ ስፌት መኪና ተነስታ ወደ ሶስት የልብስ ስፌት መኪና የደረሰች ሲሆን ካፒታሏንም ከዓመት ዓመት በማሳደግ ላይ ትገኛለች። ስራዋን ለመጀመርም ባጠራቀመችው አነስተኛ ገንዘብ ቤት ተከራይታ ነበር። ከልብስ ስፌት መኪናው በተጨማሪ የሌዘርና የጥልፍ ማሽኖችን በማስመጣት የፋሽንና ዲዛይን ስራና ማሰልጠኛ ማዕከል በመክፈት ለሌሎች ወጣቶች መትረፍ የቻለችበትን አቅም ገንብታለች።   የማሰልጠኛ ማዕከሉን ለመክፈት እስከ 500 ሺህ ብር ወጪ ማድረጓን የገለፀችው ወጣት ማህደር፤ 30 ተማሪዎችን ተቀብላ አጫጭር ስልጠና ለመስጠት የምዝገባና ሌሎች የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን አጠናቃለች። "ውጤታማ ለመሆን ጠንክሮ ከመስራት ውጪ ሴትነቴም ሆነ ሌላ ምንም የሚያግደኝ ነገር የለም" የምትለው ወጣት ማህደር ፤ የፋሽንና ዲዛይን ማሰልጠኛ ማዕከልን ከማስፋት ባለፈ በቀጣይ የጨርቃ ጨርቅ ማምረቻ ፋብሪካ ለመገንባት አቅዳ እየሰራች መሆኑን ገልፃለች። ወጣት መሰረት ጌታቸው በማህደር የልብስ ስፌትና የፋሽንና ዲዛይን ማሰልጠኛ ማዕከል ከባለፈው ዓመት ጀምሮ የስራ እድል ተጠቃሚ ሆናለች።   ከድርጅቱ በቂ የልብስ ስፌት ሙያ፣ ልምድና እውቀት መቅሰሟንና ለዚህም ማህደር እውቀቷንና ልምዷን ሳትሰስት በማከፈሏ ብቁ ሰራተኛ እንድትሆን አድርጋታለች ። የማሰልጠኛ ማዕከሉ በከተማዋ መከፈቱ በተለይም ሴቶችና ወጣቶችን በዘርፉ ሰልጥነው የሙያ ባለቤት በመሆን ሰርተው የሚለወጡበት እድል የከፈተ ነው በማለት ትገልጻለች። ከወጣት ማህደር ጊዜን በአግባቡ መጠቀምና ጠንክሮ መስራትንና ቁርጠኝነትን ትምህርት ወስጃለሁ ያለችው ወጣት መሰረት ፤ በልብስ ስፌት ዘርፍ ላይም ውጤታማ ለመሆን እየተጋች መሆኑን ትናግራለች። የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ስራና ስልጠና መምሪያ ሃላፊ ዲያቆን ኪዳነ ማርያም ገብረህይወት፤ ወጣቶች የአካባቢያቸውን ፀጋ ለይተው ከተንቀሳቀሱ ውጤታማ እንደሚሆኑ ወጣት ማህደር ትልቅ አርአያ ናት ይላሉ።   ለአብነትም እንደ ወጣት ማህደር ያሉ ታታሪ ወጣቶችን በስፋት ለማፍራት በስራ እድል ፈጠራ ላይ በማተኮር እየተሰራ እንደሚገኝ ያስረዳሉ። የወጣቷን አርአያነት ለማስፋት በቀጣይ የብድር፣ የመስሪያና መሸጫ ቦታና ሌሎች ድጋፎችን በማድረግ እንደሚያበረታቱ አረጋግጠዋል። ወጣቶች በተሰማሩበት የስራ ዘርፍ ውጤታማ እንዲሆኑ ድጋፍና ክትትል በማድረግ በባለፉት ወራት ለ11 ሺህ ሰዎች የስራ እድሉ ተጠቃሚ መሆናቸውንም አውስተዋል።      
የኢትዮጵያ የእናቶች ሞትን ምጣኔ ቅነሳ ስኬቶች እና ቀሪ የቤት ስራዎች
May 13, 2025 934
የዓለም የጤና ድርጅት (ደብሊውኤችኦ) የ2025 ዓለም የጤና ቀንን እ.አ.አ አፕሪል 7, 2025 አክብሯል። የዘንድሮው ዓመት የቀኑ መሪ ሀሳብ “ የእናቶች እና ህጻናት ጤና ጥበቃ፣ ለመጻኢው ብሩህ ጊዜ” የሚል ነው። የዓለም የጤና ጉዳዮች የበላይ አካል የሆነው ደብሊውኤችኦ መሪ ሀሳቡን መሰረተ በማድረግ ዓመቱን ሙሉ የእናቶች እና ህጻናት ጤና ጥበቃ አስመልክቶ ንቅናቄ ያደርጋል። በኢትዮጵያም የዓለም የጤና ቀን ሚያዚያ 19 ቀን 2017 ዓ.ም አዲስ አበባ በሚገኘው እንጦጦ ፓርክ “ ከቃል ያለፈ የተግባር ምላሽ” በተሰኘ ሁነት ተከብሯል። በአከባበሩ ላይ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተወካዮች፣ የጤና ሰራተኞች፣ ቤተሰቦች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል። የጤና ሚኒስቴር፣ የዓለም ጤና ድርጅት እና ቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሁነቱን በጋራ አዘጋጅተውታል። በእንጦጦ ፓርክ የነበረው የዓለም የጤና ቀን አከባበር ሁነቱን አስቦ ከመዋል ያለፈ ትልቅ ትርጉም ያለው ነው ሲል የዓለም ጤና ድርጅት ኢትዮጵያ ለእናቶች እና ህጻናት ሞት ቅነሳ ያላትን ቁርጠኝነት ማሳየቷን ገልጿል። የእናቶች እና ህጻናት ጤና የጤና ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የሰብዓዊ መብት፣ የማህበራዊ ልማት እና የብሔራዊ ልማት ጉዳይም ጭምር እንደሆነ የዘንድሮው የዓለም የጤና ቀን አከባበር ያሳየ እንደሆነ ተገልጿል። እንደ ዓለም የጤና ድርጅት መረጃ ከሁለት አስርት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ከ100 ሺህ እናቶች መካከል ከ400 በላይ የሚሆኑት ህይወታቸውን ያጡ ነበር። ኢትዮጵያ ይሄን አሃዝ በመቀየር የራሷን ታሪክ ፅፋለች። በአሁኑ ሰዓት የእናቶች ሞት ምጣኔ ከ100 ሺህ እናቶች ወደ 195 ዝቅ ብሏል። ቁጥሩ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱ ኢትዮጵያ በጤናው ስርዓት፣ የሰው ኃይል ስልጠና እና የአገልግሎት አቅርቦት ላይ እያደረገች ያለውን ዘላቂ ኢንቨስትመንት እንደሚያሳይ ድርጅቱ ገልጿል። ይሁንና አሁንም በኢትዮጵያ በየአመቱ በአማካይ 8 ሺህ ገደማ እናቶች በወሊድና ከወሊድ ጋር በተገናኘ ችግር እንደሚሞቱ መረጃው ያመለክታል። በእናቶች እና ህጻናት ጤና ጥበቃ እየተደረገው ያለው ዓመታዊ ንቅናቄ ለለውጦች እውቅና ከመስጠት ባለፈ ቀሪ የቤት ስራዎች ማጠናቀቅ እንደሚገባ የሚያመላክት ነው። የኢትዮጵያ መንግስት የሰው ኃይል ስልጠናን በማስፋት፣ የእናቶች እና ህጻናት ክብካቤን ማሻሻል፣ በዲጂታል መሳሪያዎች አማካኝነት የአገልግሎት አሰጣጥን ማጠናከር ላይ መልካም ስራዎች ቢያከናውንም አሁንም የአገልግሎት ተደራሽነት ላይ በትኩረት መስራት እንዳለበት ድርጅቱ አሳስቧል። የጤና መሰረተ ልማቶችን ማስፋፋት እና የሰለጠነ የሰው ኃይል ቁጥርን መጨመር ሌሎች ትኩረት የሚያሻቸው ጉዳዮች ናቸው ብሏል። የእናቶችና ጨቅላ ህፃናት ሞት ቅኝትና ምላሽ ስርዓትን ማጠናከር ሌላኛው በድርጅቱ የቀረበ ምክር ሀሳብ ነው። የዓለም የጤና ድርጅት ተወካይ ዶክተር ቤጆይ ናምቢያር በዓለም አቀፍ ደረጃ በተለይም በማደግ ላይ በሚገኙ ሀገራት ያለው የእናቶች እና ህጻናት ሞት አሳሳቢ እንደሆነና ጠንካራ ምላሽ እንደሚያስፈልገው አመልክተዋል። በዘላቂ ልማት ግቦች እ.አ.አ በ2030 ከ100 ሺህ እናቶች የሚሞቱን ወደ 70 ዝቅ የማድረግ ግብ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሀገራት ለማሳካት እየሄዱበት ያለው ርቀት አመርቂ አለመሆኑ ተገልጿል። ኢትዮጵያ ከተቀመጠው ግብ አንጻር ብዙ ስራዎችን ማከናወን እንደሚገባት የዓለም የጤና ድርጅት አስታውቋል። ይሁንና ኢትዮጵያ በዓለም የፋይናንስ ፈተናዎች እና አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል በግልጽ ያሳየች ሀገር መሆኗ ተገልጿል። ዓለም በተግባር የታገዘ ምላሽ ከሰጠ መከላከል የሚቻሉ የእናቶች እና ህጻናትን ሞት ማስቀረት ሊሳካ የማይችል ህልም አይደለም። ከእንጦጦ ፓርክ ጎዳናዎች አንስቶ በሀገሪቷ ክፍሎች በሚገኙ የጤና ማዕከላት የእናቶች እና ህጻናትን ሞትን ለመቀነስ የሚወሰዱ እያንዳንዱ እርምጃዎች የወደፊቱን የዓለም መጻኢ ጊዜ ብሩህ የማድረግን ራዕይን የሚያሳካ ነው ሲል የዓለም የጤና ድርጅት ጽሁፉን ቋጭቷል።
ትንታኔዎች
የፓን አፍሪካኒዝም ንቅናቄ አሻራ ያረፈበት የኢትዮ-ታንዛንያ ወዳጅነት
Dec 17, 2024 3032
የመጀመሪያው የኢትዮጵያ እና ታንዛንያ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባ ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል። የታንዛንያ የውጭ ጉዳይ እና ምሥራቅ አፍሪካ ትብብር ሚኒስትር አምባሳደር ማሕሙድ ታቢት ኮምቦ በስብስባው ላይ ለመሳተፍ ትናንት አዲስ አበባ ገብተዋል። ስብስባው የኢትዮጵያ እና ታንዛንያ የሁለትዮሽ ትስስር እና የጋራ ትብብር የማጠናከር ዓላማ የያዘ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በነበሩበት ወቅት በየካቲት ወር 2016 ዓ.ም ከታንዛንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከነበሩት ጃንዋሪ ማካምባ ጋር ባደረጉት የሁለትዮሽ ውይይት የኮሚሽኑን ስብስባ ለማካሄድ ከስምምነት መድረሳቸው አይዘነጋም። የኢትዮጵያና ታንዛንያ የሁለትዮሽ ወዳጅነት በቅርበት ለመረዳት የፓን አፍሪካኒዝም ንቅናቄን ማየት ግድ ይላል። የመላው ጥቁር ሕዝቦች ንቅናቄ የሆነው ፓን አፍሪካኒዝም ጅማሮ በ19ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ። የፓን አፍሪካኒዝም መሰረት የሆነችው ኢትዮጵያ የንቅናቄው ፋና ወጊ በመሆን ወሳኝ ሚና ተጫውታለች።   የፓን አፍሪካኒዝም እሳቤ ላይ ከኢትዮጵያ ጋር አብረው በመቆም ትግል ሲያደርጉ ከነበሩት አገራት መካከል ታንዛንያ ትገኝበታለች። በፓን አፍሪካኒዝም ትግል ውስጥ ስማቸው በቀዳሚነት ከሚጠቀሱ መሪዎች መካከል ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ እና የታንዛንያው የቀድሞ ፕሬዝዳንት ጁሊዬስ ኔሬሬ ተጠቃሽ ናቸው። መሪዎቹ ለአፍሪካ አገራት ከቅኝ አገዛዝ መውጣት ትልቅ ሚና በመጫወት ሕያው አሻራቸውን አሳርፈዋል። የኢትዮጵያና ታንዛንያ የሁለትዮሽ ግንኙነት በእነዚህ መሪዎች ጊዜ የተጀመረ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ። አገራቱ በጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጣር ግንቦት 25 ቀን 1963 የቀድሞ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (በአሁኑ መጠሪያው የአፍሪካ ኅብረት) መቋቋሙ ሲበሰር መስራች አባል አገራት ነበሩ። ኢትዮጵያና ታንዛንያ በየአገራቱ ኤምባሲያቸውን በይፋ በመክፈት የሁለትዮሽ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ለማጠናክር እየሰሩ ይገኛሉ። አገራቱ የሁለትዮሽ ትብብራቸውን ለማጠናከር የሚያስችላቸው በርካታ አቅሞች አሉ። ኢትዮጵያ እና ታንዛንያ ባላቸው የቁም እንሥሳት ኃብት ከአፍሪካ በቀዳሚነት የሚጠቀሱ አገራት ናቸው። ሁለቱ አገራት በሚያደርጓቸው የጋራ ምክክሮች ይሄን ሰፊ ኃብት በመጠቀም የንግድ እና ኢኮኖሚ ትስስር ማጠናከር እንደሚገባ በተደጋጋሚ ጊዜ ያነሳሉ። ግብርና፣ የሰብል ምርት፣ የኤሌክትሪክ ኃይል፣ የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ እና አቪዬሽን ከሁለቱ አገራት የትብብር መስኮች መካከል በዋናነት ይጠቀሳሉ። የኢትዮጵያ አቪዬሽን አካዳሚ በርካታ ታንዛንያውያን ፓይለቶች እና ኢንጂነሮችን አሰልጥኖ አስመርቋል። አቪዬሽንም የሁለቱ አገራት ቁልፍ የትብብር መስክ በሚል ይነሳል።   ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በየካቲት ወር 2016 ዓ.ም በታንዛንያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወቃል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከታንዛንያ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሁሉ ሀሰን ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል። አገራቱ በወቅቱ በባህልና ኪነ-ጥበብ፣ በግብርና እንዲሁም በኤሌክትሪክ ኃይል ንግድ ላይ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቶቹ የሁለቱ አገራት ትብብር ይበልጥ ለማጠናክር ትልቅ ፋይዳ አላቸው። የዛሬው የኢትዮጵያ እና ታንዛንያ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባም የስምምነቶችን አፈፃጸም በመገምገም ትግበራውን ማፋጠን የሚያስችል አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።   ከሰሞኑ የምሥራቅ አፍሪካ ከፍተኛ ኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት አካል የሆነው ከኬንያ ወደ ታንዛንያ የተዘረጋው የኤሌክትሪክ መስመር የሙከራ የኃይል አቅርቦት መጀመሩ ይታወቃል። የቀጣናው ከፍተኛ ኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ (ሃይዌይ) ፕሮጀክት የመጀመሪያው የኃይል ትስስር ኢትዮጵያና ኬንያን ያስተሳሰረ መሆኑ ይታወሳል። የፕሮጀክቱ ሁለተኛ ክፍል ደግሞ ከኬንያ ወደ ታንዛኒያ የተዘረጋ ሲሆን የኤሌክትሪክ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ ተጠናቆ የሙከራ ኃይል አቅርቦት መጀመሩን የውኃና ኢኒርጂ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል። ይህ ቀጣናዊ የኃይል ትስስር በተመጣጣኝ ዋጋ አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት በማረጋገጥ በሀገራት መካካል ትብብርን እና የጋራ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የሚያስችል ነው። የኃይል አቅርቦት መጀመሩ ከኢትዮጵያ እና ታንዛንያ አልፎ በቀጣናው ያለውን ትስስር ለማፋጠን ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ይታመናል። ሁለቱ አገራት በቅርቡ ወደ ትግብራ ምዕራፍ የገባው የናይል የትብብር ማዕቀፍ ስምምነትን በአገራቸው ፓርላማ ማጽደቃቸው ይታወቃል። ስምምነቱ በናይል ተፋስስ የውኃ ኃብትን ፍትሃዊ እና ምክንያታዊ በሆነ መልኩ በበጋራ ለመጠቀም የሚያስችል ነው። አገራቱም በውኃ ኃብት ያላቸውን ትብብር ይበልጥ የሚያጠናክር ነው። የፓን አፍሪካኒዝም ንቅናቄ ያስተሳሰራቸው ኢትዮጵያ እና ታንዛንያ የሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ትብብራቸውን ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ ማሸጋግር የሚያስችሉ ሰፊ እድሎች ከፊታቸው ይጠብቃቸዋል።    
ከተለምዷዊ ዲፕሎማሲያዊ ትብብር የተሻገረው የኢትዮ-አልጄሪያ ወዳጅነት 
Dec 16, 2024 2573
የኢትዮ-አልጄሪያ ግንኙነት ታሪካዊ ነው፡፡ታሪካዊነቱ በዘመንም፣ በጸና ወዳጅነትም ይለካል።ትናንት ማምሻውን የሀገሪቷ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሕመድ አታፍ የሀገሪቷን ፕሬዝዳንት አብደልማጂድ ቴቡኔን መልክዕት ይዘው አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወቃል። ዛሬ ማለዳ ደግሞ ሚኒስትሩ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር ጋር ተወያይተዋል። በውይይቱም ሁለቱ ሀገራት ያላቸውን የፀና ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ተናግረዋል። የፕሬዝዳንት አብደልማጂድ ቴቡኔን መልዕክትም ተቀብለዋል። ​ ጉብኝቱን አስመልክቶ የሰሜን አፍሪካዊቷ አልጄሪያ እና የኢትዮጵያን ወዳጅነት የትመጣ እና ሂደት በወፍ በረር እንቃኝ። የኢትዮ-አልጀሪያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ሰባት አስርት ዓመታትን ተሻግሯል። ሁለቱ ሀገራት ከመደበኛ ዲፕሎማሲያዊ ትብብር የተሻገረ ወንድማማችነትና ወዳጅነት መስርተዋል። የፈረንሳይ ቅኝ ተገዥ የነበረችው አልጄሪያ በአውሮፓዊያኑ 1960ዎቹ መባቻ ነጻነቷን ለመቀዳጀት ትንቅንቅ ላይ በነበረችበት ዘመን ኢትዮጵያ አጋርነቷን አሳይታለች። ይህን ደግሞ በኢትዮጵያ የአልጄሪያ አምባሳደር የነበሩት ኤልሃምዲ ሳላህ ‘አልጀሪያ የኢትዮጵያን ውለታ አትረሳውም’ ሲሉ በአውሮፓውያኑ 2022 ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልፀው ነበር። ​​​ አልጀሪያ በ1962(በአውሮፓዊያኑ) ነበር ከፈረንሳይ ቅኝ ግዛት ነጻነቷን ያረጋገጠችው። ከዚህ ዘመን ጀምሮ ሁለቱ ሀገራት ወዳጅነታቸውን መሰረቱ። የአፍሪካ አንድነት ድርጅት እንዲመሰረት እና የፓን አፍሪካኒዝም እንዲያብብ ንቅናቄ አድርገዋል። በ1960ዎቹ መጨረሻም ይፋዊ ዲፕሎማሲ ግንኙነታቸውን በይፋ ጀመሩ። አልጄሪያ የቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት(የአሁኑ የአፍሪካ ሕብረት) መገኛ በሆነችው ኢትዮጵያ ኤምባሲዋን በ1976(እ.ኤ.አ) ከፈተች። ኢትዮጵያም በ2016 ኤምባሲዋን በአልጀርስ ከፍታለች። ሁለቱ ሀገራት በአውሮፓዊያኑ 2014 በግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ንግድ፣ ባህል እና በተለያዩ መስኮች ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር የሚያስችል የጋራ ኮሚቴ ፈጥረዋል። ሁለቱ ሀገራት በንግድ፣ ኢንቨስትመንት ጥበቃ እና ማስተዋወቅ እንዲሁም ተደራራቢ ታክስ ማስቀረትን ጨምሮ ከ20 በላይ የትብብር መስኮች በጋራ መስራት ስምምነት ተፈራርመዋል። ከሁለትዮሽ ባሻገርም ቀጣናዊ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ የትብበር መስኮች ያላቸውን ትብብር የማጠናከር ፍላጎት አላቸው። ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በነበሩበት ወቅት በመስከረም ወር 2017 ዓ.ም በኒውዮርክ በተካሄደው 79ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ጎን ለጎን ከአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር መወያየታቸው ይታወቃል። በዚሁ ውይይት ኢትዮጵያ እና አልጄሪያ በአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን አልፎም በዓለም የሰላም እና ደህንነት ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ከስምምነት ላይ መድረሳቸው ይታወሳል። አምስተኛውን የኢትዮ-አልጄሪያ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባ በቅርብ ጊዜ ለማከናወን የተጀመረውን ዝግጅት ለማፋጠን ተስማማተዋል። ​​​ አልጄሪያ የአፍሪካ ሕብረት የሰላም እና የጸጥታ ምክር ቤት ከአውሮፓዊያኑ ጃንዋሪ 2024 አንስቶ የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባል ሆና በመስራት ላይ ትገኛለች። ይህም ሁለቱ ሀገራት በባለብዝሃ ወገን የዲፕሎማሲ መድረክ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ የሚያጎለብት ነው። አልጄሪያ በአውሮፓዊያኑ በ2021 የአረብ ሊግ ሊቀመንበር በነበረችበት ወቅት ተቋሙ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የተዛባ አረዳድ ለማስተካከል እና ሚዛናዊ እይታ እንዲኖረው ጥረት አድርጋለች። የኢትዮ-አልጄሪያ የሁለትዮሽ ትብብር የሚያጠናክሩ የጉብኝት ልውውጦች እና ውይይቶች እያደጉ መጥተዋል። ​​​ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በነሐሴ ወር 2014 ዓ.ም በአልጄሪያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወቃል። በወቅቱም ከአልጄሪያው ፕሬዝዳንት አብደልማጂድ ቴቡኔ ጋር ተወያይተው ነበር።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የኢትዮ-አልጄሪያ ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረ ታሪካዊ በሁለትዮሽ ትብብር ይበልጥ ማጠናከር የሚቻለባቸው ዘርፎች እንዳሉ ገልጸው ነበር። ​​​ ከዚህ ጊዜ ጀምሮም በሀገራቱ መካከል የጉብኝት ልውውጦች እና ውይይቶች እየጨመሩ መጥተዋል። ለአብነትም በአውሮፓዊያኑ በ2021 የያኔው የአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ራምታኔ ላማምራ በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት አድርገው ነበር፤ የሁለትዮሽ ትብብር ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውም አይዘነጋም። ​​​ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ደግሞ በሩሲያ ሶቺ በጥቅምት ወር 2017 ዓ.ም ከተካሄደው የመጀመሪያው የአፍሪካ-ሩሲያ የትብብር ፎረም የሚኒስትሮች ስብስባ ጎን ለጎን ከአልጄሪያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሕመድ አታፍ ጋር መክረዋል። በውይይታቸውም የጋራ ተጠቃሚነትን በሚያስጠብቁ ቀጣናዊና አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር። እናም ሁለቱ ሀገራት በተለያዩ የትብብር መስኮች ግንኙነታቸውን ማጎልበት ቀጥለዋል። በአልጄሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙክታር መሀመድ ዋሬ በቅርቡ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለአልጄሪያው ፕሬዝዳንት አብዱልመጂድ ቴቡኔ ሲያቀርቡ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና የፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴን ልባዊ ሰላምታ እና የወዳጅነት መልዕክት ለፕሬዝዳንቱ ማቅረባቸው የሚታወስ ነው። ዛሬ ደግሞ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ የሚገኙት የአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሕመድ አታፍ የፕሬዝዳንት አብደልመጂድ ቴቡኔን መልዕክት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አድርሰዋል። የሚኒስትር አሕመድ አታፍ ጉብኝት ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያለው እና የኢትዮ-አልጀሪያ ሁለትዮሽ ወዳጅነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ የሚደረገው ጥረት አካል ስለመሆኑ የአልጄሪያ ዜና አገልግሎት ዘግቧል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሕመድ አታፍ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ጋርም ተወያይተዋል። በውይይቱ በሁለትዮሽ እና አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው። ሚኒስትሮቹ በውይይታቸው አገራቱ በተለያዩ ዘርፎች ያላቸውን ትስስር በማጠናከር እና አዳዲስ የትብብር አድማሶችን በመፈለግ አጋነታቸውን ለማጎልበት እንደሚሰሩ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ እና አልጄሪያ የጋራ ሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብስባን በቅርቡ ለማድረግ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። ​ እናም ኢትዮጵያና አልጄሪያ ከተለምዷዊ ዲፕሎማሲያዊ ትብብር የተሻገረ ነው። ሁሉን አቀፍ በሆኑ የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት ባደረጉ ትብብር መስኮች እየተወዳጁ ነው። የስትራቴጂካዊ አጋርነት ደረጃ እየጎለበተ ይመስላል። የአገራቱ መጻዒ የትብብር ጊዜ ብሩህ እና ፍሬያማ እንደሚሆን አያጠራጥርም።
ቀጣና ዘለል አንድምታ ያለው የአንካራው ስምምነት
Dec 13, 2024 2787
    የአፍሪካ ቀንድ ፖለቲካ አንድምታ ከቀንዱ ሀገራት የተሻገረ ነው። የቀጣናው ሀገራት ትስስርና ትብብርም እንደዚያው። በነዚህ ሀገራት መካከል የሚፈጠር መቃረን የሚያሳድረው ተጽዕኖም አድማስ ዘለል ነው። በቅርቡ በኢትዮጵያና ሶማልያ መካከል ተፈጥሮ የነበረው የግንኙነት መሻከር ከሁለቱ ሀገራት ባሻገር በቀጣናው ስውርና ገሀድ ፍላጎት ያላቸው የውጭ ኃይሎችን ያሳሰበና ያስጨነቀ ጉዳይ መሆኑ እሙን ነው። በቱርክዬ ርዕሰ ከተማ አንካራ የተደረሰው የኢትዮ-ሶማልያ ሥምምነት ግን ለበርካቶች እፎይታን ይዞ መጥቷል። ከኢትዮጵያና ሶማልያ ጋር መልካም ወዳጅነት ያላት ቱርክዬ የሁለቱን አገራት ለማሸማገል ጥረት ከጀመረች ውላ አድራለች። ምንም እንኳ ጥረትና ድካሟ በተደጋጋሚ ሳይሳካ ቢቆይም ካለፈ ሐምሌ 2016 ዓ.ም ጀምሮ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት በሚኒስትሮች ደረጃ ለማረቅ ተግታለች። በሦስተኛው ዙር በሁለቱ ሀገራት መሪዎች ደረጃ የተደረገው ድርድር ግን ፍሬ አፍርቶላታል። ቱርክዬ እየተገነባ ባለው የብዝሃ-ዋልታ ዓለም ውስጥ ጎልተው እየወጡ ካሉ ኃያላን ሀገራት መካከል አንዷ ናት። በአፍሪካ ውስጥ ያላት ተፅዕኖ ፈጣሪነትም እያደገ መምጣቱ ይታወቃል-በተለይ በአፍሪካ ቀንድ። ቱርክዬ ከኢትዮጵያ ጋር ያላት ታሪካዊና ዘርፈ ብዙ ትስስር ጠንካራ የሚባል ነው። ቱርክዬ ከቻይና ቀጥላ በኢትዮጵያ ግዙፍ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ያፈሰሰች ሀገር ናት። ከኢኮኖሚያዊ ቁርኝቱ ባሻገር ሁለቱ አገራት በፖለቲካዊና ማኅበራዊ እንዲሁም ስትራቴጂያዊ በሆኑ ጉዳዮች ያላቸው ትብብርም የላቀ ነው። ቱርክዬ ከሶማልያ ጋር ያላት አጋርነትም እየተጠናከረ የመጣ ነው። እናም የሁለቱ ሀገራት አለመግባባት ለቱርክዬ ሳንካ ነበር። ስለዚህ የሁለቱ ሀገራት አለመግባባት በአንካራው ድርድር ዲፕሎማሲያዊ እልባት ማግኘቱ ለፕሬዝዳንት ኤርዶሃን ወሳኝ እርምጃ ሆኖላቸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የሶማልያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ በአንካራ ተገኝተው ያደረጉት ውይይት የቀንዱን ውጥረት አርግቧል። ስምምነቱ በሁለቱ ሀገሮች መካከል የተፈጠሩ አለመግባባቶችን በውይይት በመፍታት ግንኙነታቸውን ወደ አዲስ የትብብር ምዕራፍ ለመውሰድ የሚያስችል እንደሆነም ተገልጿል። በሶማልያ በኩል ኢትዮጵያ አስተማማኝ፣ ደህንነቱ የተረጋገጠ እና ዘላቂነት ያለው የባሕር በር የማግኘት መብትን ዕውቅና ለመስጠት እና በዚህ ጉዳይ ላይ አብሮ ለመስራት መስማማት ችላለች። በተመሳሳይ ኢትዮጵያም የሶማልያን የግዛት አንድነት ለማክበር የነበራትን የቆየ አቋም አጽንታለች። ሁለቱ ሃገራት የኢትዮጵያን የባሕር በር ፍላጎት እውን ለማድረግ በቀጣይ አራት ወራት በቱርክዬ አስተባባሪነት ዝርዝር ቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ ምክክር ለማካሄድ ተስማምተዋል። መሪዎቹ በመግለጫቸው ኢትዮጵያ በሶማልያ የባሕር ዳርቻ በኩል ዘላቂ እና ደኅንነቱ የተጠበቀ የወደብ አማራጭ በምታገኝበት ዙሪያ የቴክኒክ ውይይቶችን ለመጀመር ይሁንታቸውን ሰጥተዋል።ይህ የወደብ አማራጮችን በስፋት ለመጠቀም ለምትፈልገው ኢትዮጵያ ትልቅ እርምጃ ተደርጎ የሚወሰድ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመግለጫቸው፤ ቱርክ በአፍሪካ ቀንድ ሠላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ለምታደርገው አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል። የኢትዮጵያና የሶማልያ ሕዝቦች በቋንቋ፣ በባህል እና በጉርብትና ብቻ ሳይሆን በደም የተሳሰሩ ወንድማማቾች እና እህታማማች ሕዝቦች መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አውስተዋል። ይልቁንስ ሶማልያን ከአሸባሪዎች ለመከላከልና ሠላሟን ለማረጋገጥ ሲባል በሺዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል አባላት በከፈሉት መስዋዕትነት ጭምር የተሳሰረ መሆኑን ነው ግልጽ ያደረጉት። ኢትዮጵያ ለጋራ ሠላምና ልማት ከሶማልያ ጋር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል። የሶማልያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድም ለዚህ ሀቅ ጠንካራ እማኝነታቸውን ሰጥተው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ለአገሪቱ ሠላም መጠበቅ ለዓመታት የከፈለውን ዋጋ መቼም አይዘነጋም ሲሉ የሚገባውን ክብር አጎናጽፈውታል። ሶማልያ የኢትዮጵያ እውነተኛ ወዳጅ ሆና ትቀጥላለች ሲሉም አረጋግጠዋል። ሁለቱ ሀገራት በቀጣይም ሠላምን ለማፅናት በሚያደረጉት ጥረት መንግሥታቸው ቁርጠኛ መሆኑን ተናግረዋል። ​ በጥቅሉ የአንካራው የአቋም መግለጫ የሁለቱን አገራት የጋራ አሸናፊነት ያንጸባረቀ ነው። ለዘመናት በተለይም ላለፉት ሦስት አሥርት ዓመታት ፈጽሞ የተዘነጋ እና የማይታሰብ ይመስል የነበረውን የኢትዮጵያን የባሕር በር ጉዳይ በድፍረት ዓለም አቀፍ አጀንዳ ለማድረግ ያስቻለ ነው። የኢትዮጵያ የባሕር በር ማግኘት ከሃገር አልፎ ለቀጣናው ሁለንተናዊ ትስስር ጭምር ወሳኝ መሆኑ መግባባት የተደረሰበት ሆኗል። በተለያዩ አሰራሮች እና አግባቦች፣ በሠላማዊ መንገድ እና በሰጥቶ መቀበል መርህ ኢትዮጵያ አስተማማኝ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ዘላቂ የባሕር በር ሊኖራት እንደሚገባ መግባባት የፈጠረ ነው። ይህን ሥምምነት ዕውን ለማድረግ በዝርዝር ቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ ቀጣይ ድርድሮች በማካሄድ በአጭር ጊዜ ውስጥ ገቢራዊ ለማድረግ ተጨባጭ እርምጃዎችን ለመውሰድ መግባባት ችለዋል። በዚህ ረገድ ቱርክዬ ሂደቱን ለማሳለጥ እና ለማገዝ ኃላፊነት መውሰዷ ደግሞ ዘላቂነት እንዲኖረው እንደ መልካም ዕድል የሚወሰድ ነው። ኢትዮጵያና ሶማልያ በአንካራ የደረሱት ስምምነት ከአውሮፓ ኅብረት እስከ አፍሪካ ኅብረት እንዲሁም ከምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) እስከ ተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማትና አገራት አድናቆት የቸሩት ሆኗል። ይህ ስምምነት የሁለት አገራት ስምምነት ብቻ አይደለም። የጥይት ድምጽ የማይሰማባት አፍሪካ የመፍጠር ህልም አካልም ጭምር ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። የውዳሴው መነሻና መድረሻውም ደግሞ ስምምነቱ የአፍሪካ ቀንድን ከግጭት አዙሪት ወጥቶ ወደ ዘላቂ ሠላምና መረጋጋት ብሎም ወደ አህጉራዊ ትብብር የሚወስድ መሆኑ ነው። በእርግጥም ሥምምነቱ የፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ከመባቱ በፊት ለቀንዱ አገራት የቀረበ ሥጦታ ነው። እናም የአንካራው ስምምነት ከኢትዮጵያና ከሶማልያ ባለፈ አንድምታው ቀጣናውን የተሻገረ በመሆኑ የአፍሪካውያንና የወዳጅ ሀገራት በቅን መንፈስ የተቃኘ ድጋፍ ያሻዋል።   ሠላም!
ህዳሴ - በመስዋዕትነት የተገነባ ነገ
Nov 2, 2024 3901
ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ከፕሮጀክት ባለፈ የኢትዮጵያውያን በጋራ የመቻል ትምህርት ነው። የወል ዕውነታቸው፣ የወል አቅማቸው፣ የጋራ ተስፋቸው በግልጽ የተንጸባረቀበት የአይበገሬነት ምልክት ጭምር ነው። ኢትዮጵያውያን ነጋቸውን እንዴት በጋራ መገንባት እንደሚችሉ በሚገባ ያሳዩበት ዳግማዊ አድዋ ነው - ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ። አድዋ ቀደምት ኢትዮጵያውያን ለነጻነት የተዋደቁበት ደማቅ የታሪክ ምዕራፍ ሲሆን ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ደግሞ ለኢኮኖሚ ሉአላዊነት የደም ዋጋ የተከፈለበት የትውልዱ የብሄራዊነት ማሳያ ነው። ህዳሴን ዕውን ለማድረግ ኢትዮጵያ ከሴራ ዘመቻዎች እስከ ዛቻና ማስፈራሪያዎች የደረሱ እንቅፋቶችን አልፋለች። በተለይም የግድቡ ግንባታ ወደማይቀበለስበት ደረጃ በደረሰባቸው ያለፉት 6 ዓመታት ፈተናዎቹ በርትተው ነበር። ለህዳሴው ግድብ ግንባታ የሚያስፈልጉ ግብዓቶች ተጓጉዘው እንዳይደርሱ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ምርት እንዳያመርቱና እንዳያቀርቡ በተለየዩ ቦታዎች ጥቃቶች ይሰነዘሩ ነበር። ቢሆንም ግን የማያባሩ የኢትዮጵያ ጠላቶችን የተንኮል ወጥመዶች በጣጥሶ ለማለፍ ኢትዮጵያውያን አይተኬ ህይወታቸውን ጭምር ገብረው ነገን ዛሬ መስራትን በህዳሴ ዕውን አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሕዳሴ ግድብ አሁን የደረሰበት ደረጃ እንዲደርስ በርካታ መስዋዕትነት መከፈሉን ተናግረዋል።   ኢትዮጵያ ሁሌም በጋራ የመልማት እሳቤ ማዕከል መሆኗን ገልጸው፤ታላቁ ህዳሴ ግድብም በኢትዮጵያዊያን ብርቱ ልጆች ከአፍሪካ ለአፍሪካ የተሰጠ ገጸ በረከት እንዲሁም ጣፋጭ ፍሬውም ከኢትዮጵያ ባለፈ ለተፋሰሱ አገራትም ብስራት መሆኑን ነው ያስረዱት። የታላቁ የኢትዮጵየ ህዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ በበኩላቸው ፕሮጀክቱ አኩሪ ደረጃ ላይ ለመድረስ ኢትዮጵያውያን ከገንዘብ፣ ጉልበትና እውቀታቸው ባሻገር የህይወት መስዋዕትነት የከፈሉበት ፕሮጀክት መሆኑን ጠቁመዋል።
ልዩ ዘገባዎች
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 2358
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 2203
  ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
የአርሶ አደሮችን ጓሮና ኑሮ የለወጡ ቁጥሮች- “30-40-30”
Nov 15, 2024 3640
ለዛሬው ትውልድ ምግብ፣ ለመጪው ትውልድ ደግሞ ቅርስና ውርስ የሚሆን ሃብት የሰነቀው የ"30-40-30" ኢኒሼቲቭ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አርሶ አደሮች መንደር ተገኝቶ ስለ ’30-40-30’ አሃዞች አርሶ አደሮችን የሚጠይቅ ካለ የቁጥሮችን ትርጓሜና ስሌት በቅጡ መረዳት ይችላል። እነዚህ ቁጥሮች በገጠራማው የክልሉ አካባቢዎች አባውራዎች ዘንድ ሕይወትም፣ አስተሳስብም ለውጠዋልና። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኅላፊ አቶ ዑስማን ሱሩር የ’30-40-30’ ኢኒሼቲቭ የተጠነሰሰው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭን በመመርኮዝ ስለመሆኑ ያስታውሳሉ። እነዚህ ቁጥሮች የተራ አሃዝ ስያሜ ሳይሆኑ በክልሉ ግብርና ወደ እመርታ ለማስፈንጠር የተቀየሱና ትውልድ ተሻጋሪ ዓላማ የሰነቁ ናቸው። በ2014 ዓ.ም ጀምሮ እያንዳንዱ የክልሉ አርሶ አደር በሶስት ዓመታት ውስጥ ቢያንስ 100 የፍራፍሬ ዛፎች አልምቶ እንዲጠቀም መሰረት የሆኑም ናቸው። በኢኒሼቲቩ የለሙ ፍራፍሬዎች የአርሶ አደሩን ኑሮ ማሻሻል ያለሙ፣ 'ለዛሬው ትውልድ ምግብ፣ ለመጪው ትውልድ ደግሞ ቅርስና ውርስ ናቸው' ይላሉ። የምግብና ስነ-ምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ፣ ገቢ ምንጭ ማድረግ፣ ስራ ዕድል መፍጠር፣ ገበያ ማረጋጋት፣ ለኤክስፖርትና ለኢንዱስትሪዎች ግብዓት ማቅረብን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ ዓላማዎችም አሏቸው። በእያንዳንዱ አባውራ ጓሮ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲለማና ተጠቃሚ እንዲሆን ለማስቻል የተወጠነ ነው። በዚህም በ'30-40-30'ን እያንዳንዱ አባወራ ጓሮውን እንደየአካባቢው ስነ-ምህዳር በሙዝ፣ በፓፓያ፣ በማንጎ፣ በቡና፣ በአቮካዶና በሌሎች ፍራፍሬ ችግኞች እንዲያለማ ተደርጓል። 'ያልተሄደበትን መንገድ በመሄዳችን በትግበራ ሂደቱ ፈተናዎች ነበሩ' የሚሉት ሃላፊው፤ ዛሬ ላይ ግን የ30-40-30 ኢኒሼቲቭ ፍሬ የቀመሱትን ሁሉ አስተሳስብ ለውጧል ይላሉ። ኢኒሼቲቩ ባልተለመዱ አካባቢዎች የፍራፍሬ መንደሮች የተፈጠሩበት፣ የአርሶ አደሩ ኑሮና ጓሮ የተለወጠበት፣ የይቻላል አስተሳስብ የተፈጠረበት እንደሆነ ይናገራሉ። በክልሉ የ30-40-30 ኢኒሼቲቭ በመተግበር ከሴፍቲኔት የተላቀቁና ኑሯቸውን ያሻሻሉ አረሶ አደሮች ለዚህ ምስክር ናቸው። በስልጤ ዞን ውልባረግ ወረዳ ቶዴ ጠመዳ ነዋሪዎች አቶ ሀምዛ አሊዬ እና ባለቤታቸው አናጃ ኢሳ በሴፍትኔት ታቅፈው ሲረዱ የቆዩ ሲሆን በ30-40-30 ጓሯቸውን በቡና በማልማታቸው ዛሬ ገቢም፣ ምግብም ችለዋል። በ500 የቡና ችግኝ ድጋፍ ጀምረው በየዓመቱ እያሳደጉ ዛሬ ላይ ቡናቸውን ለቅመው በመሸጥ ገቢ ማመንጨትና ነሯቸውን መደጎም ችለዋል። ጓሯቸውን በማልማታቸውም ከሴፍትኔት መላቀቅ ብቻ ሳይሆን ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ያላቸው ማህበራዊ ህይወት እንዲሻሻል ስለማድረጉም ገልጽው፤ በቀጣይነትም ሌሎች ፍራፍሬዎችን ለማልማት ተዘጋጅተዋል። በውልባረግ ወረዳ ቢላዋንጃ ባቢሶ ቀበሌ ነዋሪው አቶ ኢክማላ መሀመድ እና ልጃቸው መካ ኢክማላ ደግሞ አካባቢውን ያልተለመደ የሙዝ መንደር በማድረግ ኑሯቸውን እንዳሻሻሉ ይናገራሉ። የ30-40-30 ንቅናቄ ሲጀመር በአካባቢው "ሙዝ አይለማም" በሚል የተሳሳተ እሳቤ ቅር እያላቸው ችግኞችን ወስደው የተከሉ ቢኖሩም በርካቶች በእምቢታ ጸንተው እንደነበር አስታውሰዋል። በሂደት ውጤቱ ሲታይ ግን የልማቱ ተሳታፊዎች በዝተው በውጤትና የስኬት መንገድ ላይ መቀጠላቸውን ተናግረዋል። ከሳዑዲ አረቢያ የ10 ዓመታት የስደት ቆይታ በኋላ የተመለሰው ልጃቸው መካ ኢክማላ የስደት አስከፊነትን በማንሳት ተፈጥሮ በሰጠችን ጸጋ ሳንጠቀም በመቆየታችን ይቆጨናለ ይላል። የ30-40-30 ንቅናቄም ወጣቶች ከስደት ይልቅ በጓሯቸው ሰርተው መለወጥ እንደሚችሉ ዐይን የገለጠ እና የአስተሳሰብ ለውጥም ያመጣ ስለመሆኑ ይናገራል።     በሀድያ ዞን ሻሸጎ ወረዳ ዶዕሻ ጎላ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ይቴቦ ሽጉጤ፤ ኢኒሼቲቩን በመጠቀም ከሌሎች አርሶ አደሮች ጋር የሙዝ መንደር መስርተዋል።   የክላስተር ሙዝ መንደራቸው በሶስት ዓመታት ውስጥ የቤተሰባቸው ኑሮ እንዲሻሻል ያደረገና በቀላሉ ጸጋን ተጠቅሞ መለወጥ እንደሚቻል ያረጋገጠ ስለመሆኑም ገልጸዋል። የስልጤ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና መምሪያ ሃላፊ አቶ ሙበራ ከማል፤ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በሚል ንቅናቄ በርካቶች በተለይም በፍራፍሬና ቅመማ ቅመም ልማት ተሳትፈው ውጤታማ መሆናቸውን ተናግረዋል። በአካባቢ ያሉ ጸጋዎችን በመለየት የቡና፣ የሙዝና የአቮካዶ ክላስተር በማልማት ከፍጆታ አልፈው ለማዕከላዊ ገበያ እየቀረቡ ስለመሆኑም ይናገራሉ። በሀድያ ዞን የሻሸጎ ወረዳ ግብርና ፅህፈት ቤት ሃላፊ ዶክተር ወንዱ መለሰ፤ የ30-40-30 የፍራፍሬ ልማት ከፍተኛ ለውጥ መምጣቱን ተናግረዋል። በሙዝ ክላስተር አርሶ አደሮች በትብብር ሰርተው እንዲለወጡ ያስቻለ መሆኑን ገልጸው፤ አርሶ አደሮችም ውጤቱን በማየት ወደተጨማሪ ልማት እየገቡ ይገኛሉ ብለዋል። የ30-40-30 ኢኒሼቲቩ 'ጥረት ካለ ስኬት እንዳለ ማሳየት የተቻለበት እና የግብርናው ዘርፍ አንኳር መሰሶዎችን ዕውን ለማድረግ ተስፋ ሰጭ ውጤት የተገኘበት መሆኑን አቶ ዑስማን ይገልጻሉ። በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች የግብዓት ፍላጎት በመጨመሩ ተደራሽነቱን ለማሳደግ ጥረት እየተደረገ ይገኛልም ብለዋል። የ30 40 30 የፍራፍሬ ልማት ፕሮጀክት አንድ አርሶ ወይም አርብቶ አደር በመጀመሪያ ዓመት 30፣ በሁለተኛው ዓመት 40 እና በሶስተኛ ዓመት 30 የፍራፍሬ ችግኞችን በመትከል ተጠቃሚ የሚሆንበት መርሃ ግብር መሆኑ ይታወቃል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 47993
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 43489
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 27882
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 25227
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ በአልሸባብ ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገለፁ
Feb 14, 2024 23478
አዲስ አበባ፤ የካቲት 6/2016 (ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ አሸባሪው አልሸባብ ከሰሞኑ በሶማሊያ በፈፀመው የሽብር ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሃዘን ገለፁ። አምባሳደር ታዬ ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት በሽብር ቡድኑ ጥቃት ምክኒያት በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት እና አካል ጉዳት ጥልቅ ሃዘን እንደተሰማቸው ገልፀዋል። በኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ እንዲሁም በራሳቸው ስም የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ለሶማሊያ መንግስት እና ህዝብ የገለጹት ሚኒስትሩ ፤ በልምምድ ወቅት ወታደራዊ መኮንኖችን ኢላማ በማድረግ የተፈፀመውን ጥቃት የወንጀል ተግባር ነው ብለዋል። የወንጀል ተግባሩን ኢትዮጵያ በፅኑ እንደምታወግዘውም ባስተላለፉት መልዕክት አስታውቀዋል። ጥቃቱ አልሸባብ የሽብር ቡድን በሶማሊያ እና በክፍለ አህጉሩ ደህንነት አደጋ መደቀኑን በግልፅ ያረጋገጠ መሆኑን በመግለፅ ፥ የአካባቢው ሀገራት በፀረ ሽብር የሚያደርጉትን ትብብር ሊያጠናክሩ እንደሚገባም አመልክተዋል። የሶማሊያን ሰላም እና ደህንነት በጋራ ለማረጋገጥ ኢትዮጵያ ትብብሯን አጠናክራ በቁርጠኛነት እንደምትቀጥልም ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት ማስታወቃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።    
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 21650
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈጸማል-ባለስልጣኑ
Apr 6, 2023 21466
አዲስ አበባ መጋቢት 28/2015(ኢዜአ)፡ በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ። የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ የሚፈፀምበትን የድርጊት መርሐ ግብር በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ተወያይቷል።   የውይይቱ ዓላማ በመዲናዋ የሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች በአሰራሩ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማስቻል መሆኑ ተነግሯል። በዚህ ወቅት የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ፤ ባለስልጣኑ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። በዚህም ቀደም ብሎ ከነዳጅ ማደያና አከፋፋይ ኩባንያዎች ጋር ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው፤ አሁን ደግሞ ለሙሉ ትግበራው ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ውይይት ተደርጓል ብለዋል። በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓቱ በአማራጭነት ለሙከራ እየተተገበረ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም ተናግረዋል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል። የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሀምሌ አንድ ጀምሮ በአስገዳጅነት እንደሚተገበርም ጠቁመዋል። በኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ሞባይል መኒ ኦፊሰር ብሩክ አድሃነ፤ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች በማድረግ ረገድ በቴሌ ብር ውጤታማ ስራ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። ለዚህም ባለፉት ዘጠኝ የሙከራ ወራት በቴሌ ብር ብቻ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈጸሙን አንስተዋል። የነዳጅ ግብይቱን በአግባቡ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መገንባቱንም እንዲሁ። የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማኅበር አባል የሆኑት አቶ ሚካኤል ገብረስላሴ እና የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ የነዳጅ ግብይት ስርዓቱ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ መሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ብለዋል። በተለይ ለነዳጅ አዳዮች ጥሬ ገንዘብ በመቁጠር የሚያባክኑትን ጊዜ ከመቅረፍ አንፃር እንዲሁም በማደያዎች የሚቀመጥ የግብይት ገንዘብ እንዳይኖር በማድረግ የደህንነት ስጋትን እንደሚፈታ ተናግረዋል። በተጨማሪም መንግስት የነዳጅ ምርት ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን ስርጭት ሂደት መረጃ እንዲኖረው እና ነጋዴዎችም ግብርና ታክስ እንዳያጭበረብሩ በማድረግ ቴክኖሎጂው ትልቅ ሚና አለው ነው ያሉት።  
ለላቀ ውጤት - የተማሪ መምህርና ወላጆች ጥምር ጥረት
Mar 27, 2023 21099
በሃብታሙ ገዜ ስልጡን የመንገድ ጠበብቶች በጥንቃቄ የከተማ ውብ ገፅታ አልበሰው ባነጿት ከዚራ አካባቢ የሚገኘው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አዳራሽ በሰው ተሞልቷል። የተሰበሰቡት ወጣት ተማሪዎች፣ የድሬደዋ አመራሮች፣ የትምህርት ዘርፍን የሚመሩ አካላትና ወላጆች በፈገግታ ተሞልተዋል። ይበልጥኑ ከወጣቶቹ ገፅታ የሚንፀባረቀው የደስታ ፈገግታ ለአዳራሹ የተለየ ብርሃን ደርቦለታል። የደስታቸው ምንጭ ደግሞ አምና የተፈተኑትን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በላቀ ውጤት አልፈው ሽልማት በመቀበል ላይ መሆናቸው ነው። የአዳራሹን የሽልማት መርሃ ግብር የሚመራው ሰው ድንገት "የዛሬው ልዩ ክስተት ከሚሸለሙት ተማሪዎቻችን መካከል ከ600 በላይ ውጤት በማምጣት ከወንድሞቿ ጋር ሦስት ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ የአንድ ቤተሰብ አባላት መገኘታቸው ነው" ሲል ተናገረ። ይሄኔ አዳራሹ በጭብጨባ ተናጋ፤ ሁሉም ተሰብሳቢ በአንድነት ቆሞ ጭብጨባውን አቀለጠው። ለሽልማት ወደ አደባባዩ የመጡት በደስታ ፀዳል የወረዙት የወላጅ ተወካይ እንጂ የድሉ ባለቤት የሆኑት እነዚህ ሦስት ተማሪዎቹ አይደሉም። በአዳራሹ የተሰባሰቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃርና የካቢኔ አባላት እንዲሁም ተሸላሚዎቹ ተማሪዎች "የዓመቱ የተለየ ክስተት የሆኑትን ተማሪዎች" ለማየት ዓይኖቻቸው ቢባዝንም አልተሳካም። ለምን ካላችሁ ተማሪዎቹ ወደ ተመደቡበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጓዛቸው ነው። የመድረኩ የድምፅ ማጉያ ባለቤትም ሆነ ተሰብሳቢዎቹ የዓመቱ ክስተት የሆኑት ኒያ ሰላሃዲን 602፤ አሊ ሰላሃዲን 556፣ አማን ሰላሃዲን 526 ያመጡት ተማሪዎች መንትዮች መሆናቸውን ቢያውቁ ኖሮ አዳራሹ ሌላ የግርምት ደስታን ባስተናገደ ነበር። ሽልማቱን ያበረከቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ተሸላሚዎች በጥረታቸው በትጋታቸው ባመጡት ውጤት መደሰታቸውን አብስረዋል። አገር በዜጎች አንድነትና መተባበር እንደሚፀናው፤ የተማሪዎች ውጤትም በተማሪዎችና በመምህራን ጥረት ብቻ ሳይሆን በወላጆች ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ጭምር የሚመጣ ነው። "በተለይ ከአንድ ቤተሰብ የበቀሉት ተማሪዎችና የዛሬው ሽልማት እና ውጤት ያስተማረን ይህንኑ ነው" ብለዋል ከንቲባው። በዚህ አደራሽ ውስጥ የሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰነ-መምህራን ታድመዋል። እንደ ድሬደዋ አስተዳደር ከተፈተኑት ከ3 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎች መካከል በቀጥታ ያለፉት 250 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። ለመጣው ውጤት ተሞጋሹም ተወቃሹም የዘርፉ አመራሮች፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና ወላጆች ናቸው። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉካ መሐመድ "ለመጣው ዝቅተኛ ውጤት በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ያለነው በሙሉ ተጠያቂዎች ነን" ብለዋል። ኃላፊዋ ሌላውም ከዚህ ትምህርት መውሰድ እንዳለበት ነው የገለጹት። እንደ አስተዳደሩም የትምህርት አመራሮች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራንና ወላጆች ያካተተ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩን አውስተዋል። በመንግስት የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ከኩረጃ ነፃ ለማድረግ የተወሰደው እርምጃ ተማሪዎች በጥረታቸውና በብቃታቸው የልፋታቸውን ውጤት እንዲያገኙ ያስቻለ ነው። የፈተና አሰጣጡና ውጤቱ እንደአገር ያለንበትን አዘቀት አስተምሮ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ፤ ብቁና በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማዋለድም ጥርጊያ መንገድ ሆኖ አልፏል ማለት ይቻላል። መንግስት የትምህርት ጥራትን ከታችኛው እርከን ጀምሮ ለማረጋገጥም በዘርፉ ሙሁራን ጥልቅ ጥናት ላይ ተመስርቶ ያዘጋጀውን የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት ቀርጾ ዘንድሮ እስከ 8ተኛ ክፍል ተግባራዊ አድርጓል። ለመማር ማስተማሩ መጻህፍት ተዘጋጅተው ለመምህራን ስልጠና በመስጠትም ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። በሚቀጥለው ዓመትም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው። በሽልማት ሥነስርዓቱ ላይ እንደታየው ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች ሚና የጎላ ነው። ወላጆች ተገቢውን ድጋፍ እና ጥብቅ ክትትል ካደረጉ የሚፈልገው ለውጥና ውጤት ማምጣት ይቻላል። ወይዘሮ ሙሉካ በአትኩሮት ከገለጹት ሃሶቦች መካከል ዋናዎቹን ሰበዞች መዝዤ፤ "ተጠያቂዎቹ እኛው ነን" የሚለውን ሃሳብ አንግቤ ለድሬዳዋና ለአገር ከፍ ሲል ለዓለም ህዝብ ጭምር በየዘርፉ ታላላቅ ሙሁራን ወደ አፈሩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሁ። ድንገት ሃሳቤን ቀለበስኩት። መነሻዬ የወላጆች ኃላፊነት እና ድጋፍ መሆኑን መርሳት ዞሮ ዞሮ የምፅፈው መዳረሻ መርሳት ይሆንብኛል ብዬ ነው። እናም ወደ ሦስቱዎቹ፤ የዓመቱ ክስተቶች አባት አመራሁ። ድሬዳዋን ለሁለት እኩሌታ የሚከፍላትን የደቻቱን ድልድይ ተሻግሬ ወደአንድ የግል የሕክምና አገልግሎት መስጫ ሆስፒታል ገባሁ። አምሮ በተሰናዳው ሆስፒታል ውስጥ ሙያዊ ኃላፊነታቸው እየተወጡ አገኘኋቸው፤ የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍን። የውጤታማ ተማሪዎቹ ወላጅ ናቸው፤ በ1970 ዎቹ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መዝለቅ በመርፌ ቀዳዳ የመሹለክ ያህል በሚቆጠርበት ዘመን በከፍተኛ ማዕረግ አልፈው በቀሰሙት ዕውቀትና ጥበብ የሰዎችን ሕይወት እየታደጉ ይገኛሉ። ዶክተር ሰላሃዲን ለትምህርት ጥራት መውደቅ ወደ ዩኒቨርሲቲ በስርቆትና ኩረጃ የመግባት ዝንባሌዎች እንደሆኑና ይሄም ሁሌም የሚያንገበግባቸው ጉዳይ መሆኑን አጫወቱኝ። መንግስት በተለይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ባልደረቦቻቸው በሁለተኛ ደረጃ የፈተና አሰጣጥ ላይ የወሰዱት እርምጃ አስደስቷቸዋል። "በተለይ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ከሚያሳልፉት ጊዜ በበለጠ ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸው ጊዜ ይበልጣል። ከሁሉም ነገር በላይ ለትምህርት ትኩረት ማድረጋቸውን መከታተልና መደገፍ የኛ ፋንታ ነው፤ አንዴ መስመር ከያዙ የሚመልሳቸው ችግር አይኖርም" ይላሉ። ሦስቱ ልጆቻቸውን በዚህ መንገድ በመደገፍ እና ከትምህርት ቤታቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ አስችለዋል። 604 ያመጣችው ስኮላርሽፕ ሺፕ አግኝታ ወደ ውጭ ሄዳለች፤ ሁለቱ ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው። "ለልጆቼ የፈለጉትን የማድረግ አቅም ቢኖረኝም ያለትምህርት የሚፈጠር አንዳች ነገር እንደሌለ ገብቷቸው ለውጤት በቅተዋል" ይላሉ ዶክተር ሰላሃዲን። ብዙ የመስራት እንጂ ብዙ የመናገር ዝንባሌ የማይታይባቸው እኚህ የታታሪዎች አባት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራት በሚደረግ ጥረት የወላጆች ክትትልና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ነው በአፅንኦት ያሳሰቡት። "የሽልማቱ መርሃ ግብር ወደሌላ አካባቢ በሄድኩበት አጋጣሚ በመካሄዱ ሳልገኝ ቀረሁ፤ በጣም የቆጨኝና ቅር ያለኝ ዕለት ሆኖ አልፏል" ብለዋል። እሳቸውን ጨምሮ አንቱ የተሰኙ ሙሁራን ያፈራው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ፍቃዱ ሰንበቶ፤ የማርያም ሰፈር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ኢጀታ መኮንን ካለፈው ክፍተት በመማር ዘንድሮ የተሻለ ውጤት እንዲመጣ የተማሪዎች አመለካከት ላይ ለውጥ እና እችላለሁ የሚል መርህ የማስረጽ ሥራ ተሰርቷል ብለውኛል። ለውጤቱ ቀዳሚ ባለቤት ተማሪዎች ቢሆኑም ከወላጆቻቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ የማካካሻና ለፈተና ዝግጁ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ነው ርዕሳነ መምህራኑ የገለጹት። ቅኝቴን በመቀጠል ሽቅብ ወደ ሳብያን ሁለተኛ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት አመራሁ። ይህ ትምህርት ቤት በከተማዋ ካሉት ትምህርት ቤቶች በውጤታማነት እና በብዛት ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማሳለፍ ረገድ ወደር አልነበረውም፤ ባለፉት ዓመታት። ከተመሠረተ 22 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ ትምህርት ቤት በምክትል ርዕሰ መምህርነት የሚመሩት አቶ በፍቃዱ ወልደሰማያትን አገኘኋቸው። ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተናቸው ከ800 በላይ ተማሪዎች መካከል ያለፉት 20 ናቸው። የመጣው ውጤት ያለንበትን ደረጃ ፍንትው አድጎ ያሳየን መሆኑን ተከትሎ መሠረታዊ የሆኑት ችግሮች በጋራ ተነቅሰው ለመጪው ጊዜ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ ተገብቷል። አቶ በፍቃዱ እንዳሉት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ትምህርት ቤቱን ሞዴል ትምህርት ቤት ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን ለዘንድሮው ተፈታኞች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ነው። እነዚህን ሥራዎች የተማሪ፣ መምህርና ወላጅ ህብረት በቅርበት እንዲከታተል ተደርጓል። ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች የቅርብ ክትትልና ደጋፍ መሠረታዊ ጉዳይ ነው የሚሉት አቶ በፍቃዱ፣ ለዚህ ጉዳይ ትምህርት ቤቱ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ነው የገለጹት። "በተለይ ወላጆች በትምህርት ውጤታማነት ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ልክ እንደ ዶክተር ሰላሃዲን አይነት ቤተሰቦች ተሞክሮ የማስፋት ሥራ ለመስራት ትምህርት ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል" ብለዋል። "ፍቃደኛ ከሆኑ የመጀመሪያው እንግዳችን ዶክተር ሰላሃዲን በማድረግ ለወላጆች ህብረት ተሞክሮን እንዲያካፍሉ እናደርጋለን " ብለዋል። በድሬዳዋ ታሪክ ከፍ ሲልም እንደ አገር በ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ1990 ዎቹ ዘመን ጀምሮ እንዲህ አይነት ዝቅተኛ ውጤት አለመምጣቱን የሚገልጹት ደግሞ የትምህርት ቤቱ አንጋፋ መምህር እዮብ ረታ ናቸው። የፊዚክስ መምህሩ እንደሚሉት የአምናው ክፍተት በሰከነ መንፈስ ታይቶ ዘንድሮ የተሻለ ሥራ ለመስራት መምህራን በጥሩ መንፈስ ጉዞ ጀምረዋል። ወላጆችም ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት መላክ ብቻ ሳይሆን የዕለት ተዕለት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው የገለጹት። "የተማሪዎች የትምህርት ቤት ቆይታ ለሰዓታት ብቻ የተወሰነ መሆኑን በመረዳት ወላጆች በስነ ምግባር የታነፀ በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማፍራት የተጀመረውን ጉዞ መደገፍ አለባቸው" በትምህርት ቤቱ የዘንድሮው የ12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪ ረደኤት ገነሙ በበኩሏ "እንደአገር በዩኒቨርሲቲዎች የተጀመረው የፈተና አሰጣጥ ኩረጃን የሚጠየፍ በራሱ ጥረት ውጤት ለማምጣት የሚተጋ ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል" ብላለች። በትምህርት ቤቱ የተጀመረው ልዩ ዕገዛ መጠናከርና መቀጠል እንዳለበት የምትገልጸው ተማሪ ረድኤት ወላጆቿ ተገቢውን ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ከመምህራን ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የልጆቻቸውን ትምህርት ሊከታተሉ እንደሚገባ አውግታኛለች። እኔም ሆንኩ የዘንድሮ ተፈታኞች ትምህርት ቤታችንንና ድሬዳዋን በውጤት ለማስጠራት ጠንክረን እያጠናን ነው ብላለች። ከገጠር ከተማ ተጉዞ የሚማረው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪ አላሙዲን አልይ በበኩሉ፤ መንግሥት የፈተና ኩረጃን ለማስቀረት የጀመረውን ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበት ነው የገለፀው። "የዘንድሮ የመምህራን ድጋፍ የተለየ ነው፤ እኛም ልዩ የጥናት ጊዜ እንዲጀመር ጫና እየፈጠርን ነው፤ ወላጆቼም በአቅማቸው እየደገፉኝ በመሆኑ ቀሪው ሥራ የኔ ጥረትና ብርታት ይሆናል፤ ልፋቴ ውጤት እንዲያስገኝ የስርቆትና የኩረጃ ሂደት መወገድ አለበት" ብሏል ተማሪ አላሙዲን። ከሳብያን ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ግቢ ለቅቄ ስወጣ ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍ ያሉኝ ትዝ አለኝ። "ለተሞክሮ የሚሆን ነገር እኔ ጋር ካለ ያለችኝን ጊዜ አብቃቅቼ ለዘንድሮው ተፈታኞች ሃሳቤን ለማካፈል ዝግጁ ነኝ" ያሉኝ በአዕምሮዬ ደጋግሞ እያቃጨለብኝ ጉዞዬን ቀጠልኩ። ለመውጫ ያህል፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ዘንድሮ በመንግሥት እና በግል 22 ትምህርት ቤቶች ከ5 ሺህ በላይ ተፈታኞች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው። እነዚህ ተፈታኞች በራሳቸው ጥረት የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ በየአቅጣጫው የተቀናጀ ድጋፍ የማድረግ ጅምር ተግባራት ተስተውለዋል፤ ይሄ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ይህን ዙሪያመለስ ድጋፍ በማጠናከር ተማሪዎቹን ለውጤት ማብቃት በሁሉም ዘንድ ለአፍታ መዘንጋት የለበትም። መድረሻውን ለማሳመር መነሻውን አድምቶ ማበጃጀት ግድ እንደሚልም እንዲሁ።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 47993
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 43489
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 27882
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 25227
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
መጣጥፍ
የዋጋ ንረት ምን ማለት ነው?
Jun 30, 2025 174
የዋጋ ንረት በንፅፅር ለምሳሌ አምና 26 በመቶ ዘንድሮ 14 በመቶ ሲሆን ምን ማለት ነው? ለምሳሌ የአንድን የ100 ብር ዕቃ ወስደን ብንመለከት ካቻምና ከነበረበት 100 ብር አምና 126 ብር ሆኖ ነበር ማለት ነው። ስለዚህ የዕቃው ዋጋ በአመት ብር 26 ጨምሯል ማለት ነው። በተመሳሳይ መንገድ አምና 100 ብር ዋጋ ያለው ዕቃ ዘንድሮ 14 በመቶ ካደገ ዘንድሮ 114 ብር ይሆናል ማለት ነው። በዚህ ስሌት የዕቃው ዋጋ ካምና ወደ ዘንድሮ የጨመረው በ14 ብር በመሆኑ አምና ከጨመረበት ብር 26 ጋር ሲነፃፀር ጭማሪው ቀንሷል ማለት ነው። ዋጋን ያየን እንደሆነ ግን 100 ብር የነበረ ዕቃ 114 በመሆኑ ጨመረ እንጂ አልቀነሰም። የዋጋ ንረት ጨመረ የሚባለው ደግሞ ለምሳሌ አምና 26 በመቶ የጨመረው ዘንድሮ 14 በመቶ ሳይሆን 30 በመቶ ቢሆን የጨመረው አምና 100 ብር የነበረው ዕቃ ዘንድሮ 114 ሳይሆን 130 ብር ይሆናል ማለት ነው። ይህ አምና ከጨመረበት የ26 ብር ይበልጣል ማለት ነው። ስለዚህ ካቻምና 100 ብር የነበረው ዕቃ አምና 26 ብር ጨምሮ 126 ከሆነ በኋላ ዘንድሮም 14 ብር ስለጨመረ በቀላል ቀመር ዘንድሮ 140 ብር ሆኗል ማለት ነው። ስለዚህ በሁለት አመታት የዕቃው ዋጋ 40 ብር ጨምሯል። የዕቃው ዋጋ አልቀነሰም በየአመቱ የጨመረበት ምጣኔ ግን ካምና ዘንድሮ ያነሰ ነው። ይህ ነው የዋጋ ንረት ቀነሰ ማለት። ዋጋ ቀነሰ ማለትስ ምን ማለት ነው? ዋጋ ቀነሰ የሚለውን ከማየት በፊት የዋጋ ንረት የለም ማለት ምን እንደሆነ በዛው 100 ብር ዋጋ ባለው ዕቃ እንመልከት። ይህ ባለፈው አመት ብር 100 የነበረ ዕቃ ዘንድሮም እዛው 100 ብር ላይ ቢቆይ የዋጋ ንረት ዜሮ ነው። ስለዚህ የዕቃው ዋጋ አልተለወጠም ማለት ነው። ዋጋ ቀነሰ ማለት ግን የዋጋ ንረት ከዜሮ በታች ይሆናል ማለት ነው። በምሳሌው ለማስረዳት አምና 100 ብር ዋጋ ያለው ዕቃ ዘንድሮ 90 ብር ቢሆን የዋጋ ንረቱ ወይም ለውጡ ከዜሮ በታች 10 በመቶ ነው። በዚህ ግዜ የዋጋ ንረት ቀነሰ ሳይሆን ዋጋ ቀነሰ ይባላል። እነዚህ ሶስቱ የዋጋ ለውጦች ለሸማቾችና ለአምራቾች ምን ማለት ናቸው? ለሸማቾች ከሁሉም የሚመረጠው ዋጋ ሲቀንስ ማለትም 100 ብር የነበረው ዕቃ 90 ብር ሲሆን ነው። በሁለተኛ ደረጃ ተመራጩ ዋጋ ንረት ሳይኖር አምና 100 ብር የነበረው ዕቃ ዘንድሮም ሳይለወጥ በዜሮ ንረት 100 ብር ላይ ሲቆይ ነው። ሶስተኛው የተሻለ አማራጭ አምና 100 ብር የነበረ ዕቃ ዘንድሮ በ26 በመቶ ጨምሮ ብር 126 ከሚሆን በ14 በመቶ ጨምሮ ብር 114 ሲሆን ነው። ይህ ሶሰተኛው አማራጭ በሁለቱም ዋጋ ስለሚጨምር በትንሽ የጨመረው ተመራጭ ይሆናል ማለት ነው። ከአምራቾች አንፃር ሲታይ ከላይ ለሸማቾች የተሻለ አማራጭ በቅደም ተከተል ያስቀምጥነውን ገልብጠው ማንበብ ነው። አሁን ብሔራዊ ባንክ እያለ ያለው የዋጋ ንረት ወይም አመታዊ ጭማሪው ቢበዛ ከ10 በመቶ እንዳይበልጥ የሚረዳ የገንዘብ ፖሊሲ እተገብራለሁ ነው። የባንኩ አላማ የዋጋ ንረት ዜሮ ወይም ከዜሮ በታች እንዲሆን ሳይሆን 1) ከ10 በመቶ በታች እንዲሆን ሲሆን 2) የትረጋጋና ተገማች እንዲሆን ነው። የተረጋጋ ማለት ከወር ወር ወይም ካመት አመት ዋጋ የሚለወጥበት ሁኔታ በጣም የተራራቀ ያልሆነ ማለት ነው። ለምሳሌ ካንዱ ወር ወደ ቀጣይ ወር ጭማሪው 0.5 በመቶ ሆኖ በቀጣይ ወር ደግሞ የ5 በመቶ ጭማሪ ከዚያም በቀጣይ ወር ከዜሮ በታች የ2 በመቶ ወርሃዊ ለውጥ ቢመዘገብ ያልተረጋጋ ወይም ተገማች ያልሆነ የዋጋ ለውጥ አለ ማለት ነው። ሰለዚህ የተረጋጋና ተገማች የዋጋ ለውጥ እንዲኖር ማድረግ የባንኩ ሁለተኛው አላማ ነው ማለት ነው። ብሔራዊ ባንክ በጣም ዝቅተኛ የዋጋ ንረት ወይም ከዜሮ በታች የዋጋ ለውጥ እንዴት ያየዋል ብለን ያየን እንደሆነ ነገሩ እንዲህ ነው። ቅድም ከላይ እንዳየነው የዋጋ ንረት ከሸማቾችና ካአምራቾች አንፃር የሚታየው በተቃራኒ መንገድ ነው። ስለሆነም ምንም እንኳን የዋጋ ንረት በጣም ዝቅተኛ ወይም ከዜሮ በታች ቢሆን ለሸማቾች ጥሩ ቢሆንም አምራቾችን ግን የማያበረታታ ስለሚሆን ማምረት ያቆማሉ ሠራተኛ ይቀንሳሉ አጠቃላይ የኢኮኖሚው እንቅስቃሴ ይገታና ጭራሽ ከምርት እጥረት የተነሳ የዕቃዎች ዋጋ መናር ይከሰታል ሥራ አጥነት ይበዛል። ስለዚህ መንግስት ሥራ እንዲፈጠር ኢኮኖሚ እንዲነቃቃም ስለሚፈለግ የተረጋጋና ዝቅተኛ ሸማቹን የማይጎዳ አምራቹንም የሚያበረታተ የዋጋ ሁኔታ እንዲኖር ይሰራል ማለት ነው። ለአንድ ኢኮኖሚ ትክክለኛው የዋጋ ንረት ስንት ነው? ይህ ጥያቄ ሊመለስ የሚገባው ግን ከባድ ነው። ይህን ጥያቄ ለመመለለስ ከሚረዱት ሁኔታዎች አንዱ ኢኮኖሚው ያለበት ደረጃ ነው። ምን ማለት ነው በጣም ባደገና የበለጠ የማደግ እድሉ ጠባብ ለሆነ ኢኮኖሚ 1 በመቶ ወይም 2 በመቶ የዋጋ ንረት ከፍተኛ ሊሆን ይችላል። በአንፃሩ ደግሞ ገና የማደግ እምቅ አቅም ላለውና በማደግ ላይ ላለ ሀገር ነጠላ አሃዝ የዋጋ ንረት እንደ ሁኔታው የሚለያይ ሆኖ ተመራጭ ሊሆን ይችላል። ስንት ነው የሚለው ግን በሳይንሳዊ መንገድ መረጋገጥ አለበት። ለምሳሌ የሀገራችንን threshold inflation or optimal inflation level ለማወቅ እኔን ጨምሮ የባንኩ ሠራተኞች በሳይንሳዊ መንገድ ለማወቅ ተሞክሯል። በኔ ጥናት 7 በመቶ ሲሆን በሌሎቹም ከዚሁ ያልራቀ ውጤት እንዳለ አይቻለው የመረጃ አጠቃቀምና የሜቶዶሎጂ ልዩነቱ እንዳለ ሆኖ ማለቴ ነው። ሰለዚህ በነዚህ ጥናት መሰረት ብሔራዊ ባንክ የነጠላ አሃዝ የዋጋ ንረት አላማ አድርጎ መንቀሳቀሱ ትክክለኛ አቅጣጫ ነው ማለት ነው ለኛ ኢኮኖሚ። ለማጠቃለል የዋጋ ንረት ምንነትን በተመለከተ ያለውን ውዥምብር ለማጥራት ይህ አጭር መግለጫ ያግዛል ብዬ እያመንኩ የበለጠ መብራራት ካለበት ወይም ጥያቄ ካለ አንባቢዎች በአስተያየት መስጫው ላይ ማሰቀመጥ ትችላላችሁ። አቶ ፈቃዱ ደግፌ የብሔራዊ ባንክ ም/ገዥ
የሺህ ሀይቆች ምድር
Jun 24, 2025 438
የሺህ ሀይቆች ምድር (በራሔል አበበ) በርካታ መገለጫዎች አሏት። የሺህ ሀይቆች መፍለቂያ። አረንጓዴ ምድር። 75 በመቶ የአገሪቱ ገፀ-ምድር በደን የተሸፈነ። የአምስት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ሕዝብ መኖሪያ። በአውሮፓ ከበለጸጉ አገራት አንዷ። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለስምንት ተከታታይ ዓመታት በዓለም ቁጥር አንድ የደስተኞች አገር በመባል የተሰየመች ሰሜን አውሮፓዊት አገር - ፊንላንድ። በፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋባዥነት በአዲስ አበባ የአገሪቱ ኤምባሲ አስተባባሪነት በቅርቡ ፊንላንድን የመጎብኘት ዕድል አግኝቼ ነበር። በጉብኝቱ ኢትዮጵያን ጨምሮ የኬኒያ፣ ታንዛኒያ፣ ናይጄሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ሴኔጋል፤ ሞዛምቢክ እና ዛምቢያ ጋዜጠኞች ተሳትፈናል። የአገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር ከኢትዮጵያ ጋር ተመሳሳይ ነው። ምንም እንኳን የትም አገር ስሄድ ቀድሜ መረጃ የማየት ልምድ ቢኖረኝም በመጀመሪያው ዕለት ለእራት ስንወጣ ያየሁት በምሽት ያልተለመደ የፀሐይ ፍካት ግን እራቱ ቁርስ እንዲመስለኝ አድርጓል። ከዚያ በኋላ ለመድሁት። በእርግጥ በአንድ ወቅት በስፔንም ፀሐይ እስከ እኩለ ሌሊት የማትጠልቅበትን ክስተት ተመልክቻለሁ። በፊንላንድ ያየሁት ግን ተለየብኝ። ፀሐይ ፈጽሞ ለጨረቃ ቦታ መልቀቅ አትፈልግም። ምሽቱ የሚደምቀው በመብራት ሳይሆን በፀሐይ ነው። ሌሊቱ ብርሀን ነው። ሰማይ አይጠቁርም። በየዕለቱ ሳይጨልም ይነጋል። በዚህ ወቅት በተለያዩ የአውሮፓና የአሜሪካ አገራት ሰማይ ላይ የሚታየው ሰሜናዊ የቀለማት የብርሀን ፀዳል ሌላው የፊንላንድ መድመቂያ ነው። የሰሜን አውሮፓ/ኖርዲክ አገራት በተፈጥሮ የታደሉ ናቸው። እኔ ደግሞ የተፈጥሮ አድናቂ ነኝ። ያለማጋነን በፊንላንድ ተፈጥሮ ከነክብሯ ተጠብቃ አይቻለሁ። ንጹህ አየሯ የዚህ ውጤት ነው። አድናቆቴ የጀመረው ከኤርፖርት እስካረፍኩበት ሆቴል 15 ኪሎ ሜትር ያህል በመኪና ስንጓዝ የከተማዋን አረንጓዴነትና የምድሪቱን ልምላሜ ስመለከት ነበር። በጉብኝቴም በተግባር አረጋገጥሁ። የአገሪቱ አብዛኛው መሬት በደንና በውሃ ተሸፍኗል። በዋና ከተማዋ ሄልሲንኪና በዙሪያዋ በሚገኙ ውብ ደኖች መሀል ስንጓዝ መሬቱ ለም ስለመሆኑ ዓይን ብቻ ሳይሆን እግርም ምስክር ነው። ሲራመዱ የመሬቱ ምቾትና እንደ ስፖንጅ ስምጥ ስምጥ ማለት ለምነቱን ይናገራል። በሄልሲንኪ ሴኔት እና ካንሳላስቶሪ አደባባዮች እንደእኛዎቹ አራት እና ስድስት ኪሎ አደባባዮች ናቸው። ቤተ-መንግስት፣ ዩኒቨርሲቲ፣ ፓርላማ፣ ቤተ-መጽሐፍት እና ቤተክርስቲያንን አጎራብተው ይዘዋል። የሄልሲንኪ ሕንጻዎች እንደ ሌሎች የአውሮፓ አገራት ውብና የሥነ-ሕንጻ ጥበብ የሚታይባቸው ናቸው። የነዋሪዎች ቁጥር አነስተኛ በመሆኑ ከተማዋ አልተጨናነቀችም። በአስፋልትና ደረጃውን በጠበቀ ኮብልስቶን የተሰራው የከተማዋ አውራ ጎዳና ከዘመናዊ ተሽከርካሪዎች በተጨማሪ የህዝብ አውቶቡስና የኤሌክትሪክ ባቡር ያስተናግዳል። ለአውሮፓ ከተሞች አዲስ የሆነ ሰው ኮብልስቶኑ የእግረኛ መንገድ መስሎት መሐል የመኪና መንገድ ላይ ሊገኝ ይችላል። እኔም የተረፍሁት እንዲህ አይነቱን የመኪና መንገድ በአንድ ወቅት በኢጣልያ በማየቴ ነበር። የተፈጥሮ ውበት ደምቆ የሚታይባት ፊልናልድ ሲልቨር በርች የተሰኘው ብርማ ቀለም ቅርፊት ያለው ዛፍ እና ቡናማ ድብ ብሔራዊ መለያዎቿ ናቸው። በረጃጅሞቹ ዛፎች መሐል ከእንስሳት ባሻገር ስትሮበሪና እንጉዳይን ጨምሮ ለምግብነት የሚውሉ የተለያዩ ዕጽዋት ይገኛሉ። በፊንላንድ ብዙ አይነት የእንጆሪ/ስትሮበሪ ዝርያ አለ። ወቅቱ ፍሬ የሚደርስበት አልነበረም እንጂ ከጫካዎቹ መሐል ገብቶ በተለያዩ የስትሮበሪ ፍሬዎች ቅርጫት ሞልቶ መውጣት የተለመደ መሆኑን ተረድቻለሁ። ፊንላንድ የሺህ ሀይቆች ምድር ተብላም ትሞካሻለች። ለቁጥር የሚያዳግቱ በበርካታ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሀይቆችና የውሀ አካላት ከተፈጥሮ ሀብቶቿ መካከል ናቸው። ለጉብኝት በሄድኩባቸው አካባቢዎች ሁሉ የሚቀርብልኝን ኩልል ያለ ንጹህ የመጠጥ ውሃ በፍቅር ነበር የምጠጣው። ግዴታ ካልሆነ የፋብሪካ ውሃ በፊንላንድ ቦታ የለውም። ንጹህ የተፈጥሮ የምንጭ ውሃ ከቧንቧ ይቀዳል። ጽድት ከማለቱ ጣዕሙ። ፊኒሾች ለባህልና ቅርስ ትልቅ ቦታ አላቸው። በተለይ ከተፈጥሮ ጋር ያላቸው ቁርኝት አስገራሚ ነው። በአብዛኛው አፍሪካ ውስጥ የሚነገር አፈ-ታሪክና ተረት በፊንላንድም ከተፈጥሮ በተለይም ከዛፎችና ከእንስሳት ጋር ተያይዞ ሲተረትና የመድረሻቸው መነሻ እንደሆነ ሲነገር ተደንቄያለሁ። በጉብኝታችን በአንዱ ቀን ኑኪሲኦ ብሔራዊ ፓርክ ሄድን። ይህ ደግሞ እጅግ የተለየ ተፈጥሮን ማያ ስፍራ ነው። በረዣዥም ዛፎች መሐል ካደረግነው ጉዞ በኋላ የቀረበልን ባህላዊው የፊንላንድ የሳውና እና የዋና ግብዣ ነበር። ሳውና የፊንላንድ ባህል ነው። በእንግሊዝኛ ቋንቋ መዝገበ ቃላት ውስጥ ያለ የፊኒሽ ቃል “ሳውና” እንደሆነ ይነገራል። ዛሬ በዓለም ላይ በተለይም በባለኮከብ ሆቴሎች በስፋት የምናገኘው ሳውና መነሻው ፊንላንድ ናት። በርካታ የሳውና ስፍራዎች ከመኖራቸው የተነሳ የሳውና ቁጥር በአገሪቱ ከተመዘገቡ መኪኖች ቁጥር ይበልጣል ይባላል። ግብዣውን ሁላችንም በደስታ ነበር የተቀበልነው። በባህሉ መሰረት ሳውና ውስጥ በቅጠል እየተጠበጠብን ከፍተኛ ሙቀት ሲሰማን ከፊት ለፊት ባለው ቀዝቃዛ የተፈጥሮ ሀይቅ ውስጥ በመግባት ዋና የሚችል ዋኝቶ የማይችል ደግሞ በመነከር ሰውነቱን አቀዝቅዞ እንደገና ወደሳውናው ይመለሳል። የተለየ ነው።     የጉብኝቱ ዋና አስተባባሪ አና ላሚላ ትባላለች። የ35 ዓመት የስራ ልምድ ያላት ብስል ዲፕሎማት ናት። በተለያዩ አገራት ፊንላንድን ወክላ ሰርታለች። አሁንም በአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስትራቴጂክ ኮሙኒኬሽን ኃላፊ አምባሳደር ነች። ትክክለኛ የኮሙኒኬሽን ሰው ናት። አንቺ ያልኳት በአንቱታ ላርቃት ባለመፈለጌ ነው። ለነገሩ ስትታይም የ35 ዓመት ወጣት እንጂ የ35 ዓመት የስራ ልምድ ያላት አትመስልም። አንድ ቀን አን “መኮንን” በሚለው የአያቴ ስም እየጠራችኝ ስምሽ እኮ የፊኒሽ/የፊንላንድ ነው ይህን ታውቂያለሽ? ከእኛ ጋር ዝምድና ይኖርሽ ይሆን?" አለችኝ ፈገግ ብላ። "ኸረ በፍፁም ኢትዮጵያዊት ነኝ" አልኳት። ትክክል ነበረች። አጭር የፅሁፍ መልዕክት የመለዋወጥ ሀሳብን ለመጀመሪያ ጊዜ ለዓለም ያስተዋወቀው “ማቲ መኮንን” የተባለ ፊንላንዳዊ ኢንጂኒየር ነው። የቴክኖሎጂ ነገር ከተነሳ አብዛኞቻችን ከተንቀሳቃሽ ስልክ ጋር ስንተዋወቅ የያዝነው ኖኪያ የፊንላንድ ምርት ነው። የመኮንንን ሀሳብ ለመጀመሪያ ጊዜ በተንቀሳቃሽ ስልክ አማካኝነት ለዓለም ይፋ ያደረገውም ኖኪያ ነው። አሁንም ኖኪያ በኔትወርክ ዝርጋታ ጭምር እየሰራ ያለ ግዙፍ የቴሌኮም ተቋም ነው። ኢትዮጵያና ፊንላንድ የረዥም ዓመታት የሁለትዮሽ ግንኙነት ያላቸው አገራት ናቸው። ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸው 66 ዓመታትን ተሻግሯል። ፊንላንድ ከኢትዮጵያ ጋር ከእርዳታና ትብብር ባሻገር በተለያየ መስክ በጋራ ትሰራለች። በጉብኝቴ ወቅት ያገኘኋቸው የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኤሌና ቫልቶነን ይህን ግንኙነት የማሳደግ ፍላጎት መኖሩን ነግረውኛል። ከንግድና ኢንቨስትመንት በተጨማሪ ኖኪያን ከመሰሉ ኩባንያዎች ጋር የሚደረግ የቴክኖሎጂና የዕውቀት ሽግግር እጅግ አስፈላጊ መሆኑንና በአገሪቱ ቴክኖሎጂ መዘመኑን የተረዳሁት በአገሪቱ ብሔራዊ የሚዲያ ተቋም ይሌ ያለማንም እርዳታ ዜና ቀርጾ የሚያሰራጭ ሰው አልባ ሮቦትድ የስቱዲዮ ቴክኖሎጂ ስመለከት ነበር። ፊንላንድ በትምሕርት ጥራትም ስሟ በቀዳሚነት ይነሳል። በአገሪቱ ከ800 በላይ፤ በመዲናዋ ደግሞ 40 የሚጠጉ ቤተ-መጻሕፍት አሉ። ከአገሪቱ ፓርላማ አቅራቢያ የሚገኘውና አገሬው የእኩልነት ተምሳሌት ነው የሚለው የሄልሲንኪ ግዙፉ ማዕከላዊ ቤተ-መጽሐፍት ኦዲ ይባላል። በውስጡ በርካታ አገልግሎቶችን ይዟል። ንባብ ብቻ ሳይሆን የተለያዩ የባህልና ፈጠራ ታለንቶችን ያስተናግዳል። ከልጅ እስከ አዋቂ ለሁሉም ቦታ አለው።   ፊንላንድ ዜጎቿ በደስታ ግብር የሚከፍሉባት አገር መሆኗን የአገሪቱ የታክስ አስተዳደር ሲናገር በኩራት ነው። ግብር መሰወር፤ ክፈሉ ብሎ በየግዜው መቀስቀስን የመሳሰሉ ነገሮች እዛ ቦታ የላቸውም። የኩባንያም ሆነ የግለሰብ ግብር ከፋዮች በታማኝነት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት በወቅቱ እንደሚወጡ አስተዳደሩ ይገልጻል። ይህም የዜጎች ፍላጎትን ለማሟላት በተሰራ ስራ የተፈጠረ መሆኑን የተመለከትኳቸው ተቋማት ሃላፊዎች ይገልጻሉ። ዜጎች በመንግስት ላይ ከፍተኛ እምነት አላቸው። በፊንላንድ የዜጎች ደስተኝነት የሰላምና ነጻነት መገለጫ እንደሆነ ምሁራኖቻቸው በጥናት ስራዎቻቸው ጭምር ይመሰክራሉ። የደስታቸው ምንጭ ነጻና ጥራት ያለው ትምሕርት፣ በአካባቢ ጥበቃ፤ በፍትህና እኩልነት፤ በበጎ አድራጎት ተግባር፤ የእናቶችና ህጻናት ጤናን ጨምሮ አርአያ የሚሆኑ ጠንካራ የማሕበራዊ ደህንነትና ትስስር ስራዎች የመጡ ውጤቶች እንደሆኑ ይገለጻሉ። በጾታ እኩልነት ሴቶች በሁሉም መስክ ጥሩ ስፍራ አላቸው። በፖለቲካውም ከወንዶች ተቀራራቢ ቦታ እንዳላቸው የአገሪቱን ፓርላማ ስንጎበኝ ተረድቻለሁ። ከ200 የምክር ቤት አባላት 91ዱ ሴቶች ናቸው። የዚህ ሁሉ ድምር ውጤት ፊንላንድ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የደስተኛ አገራት ደረጃ ላይ ለስምንት ተከታታይ ዓመታት የከፍታ ስፍራዋን ሳትለቅ በቁጥር አንድ ላይ እንድትቆይ አድርጓታል። ዜጎቿ በቀጣዩ ዓመትም ለዘጠነኛ ጊዜ የዓለም የደስተኞች አገር ሆና ትቀጥላለች የሚል እምነት አላቸው።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም