ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
ቱኒዚያ እና አልጄሪያ ነጥብ ተጋርተዋል
Jul 10, 2025 46
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 3/2017(ኢዜአ)፦ በ13ኛው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ሶስት ጨዋታ ቱኒዚያ እና አልጄሪያ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል። ጨዋታው ማምሻውን በበፔሬ ጄጎ ስታዲየም ተካሄዷል። አልጄሪያ በኳስ ቁጥጥር እና የግብ እድል በመፍጠር የነበራትን ብልጫ ወደ ውጤት መቀየር አልቻለችም። መርሃ ግብሩ በአፍሪካ ዋንጫው ምንም ግብ ያልተቆጠረበት የመጀመሪያው ጨዋታ ሆኗል። ውጤቱን ተከትሎ አልጄሪያ በአራት ነጥብ ምድቡን እየመራች ነው። ቱኒዚያ በአንድ ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዛለች። በምድብ ሶስት ቦትስዋና ከናይጄሪያ ምሽት 4 ሰዓት ላይ በላርቢ ዛውሊ ስታዲየም ይጫወታሉ። የዘጠኝ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊዋ ናይጄሪያ በሶስት ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች። ካሸነፈች የምድቡን መሪነት ከአልጄሪያ ትረክባለች። ያለ ምንም ነጥብ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ የያዘችው ቦትስዋና የመጀመሪያ ድሏን ለማስመዝገብ ትጫወታለች።
የአፍሪካ ህብረት አባል አገራት የነጻ ንግድ ቀጣና ቁልፍ የማስተግበሪያ ደንቦች አፅድቀው ወደ ስራ እንዲያስገቡ ጥሪ አቀረበ
Jul 10, 2025 55
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 3/2017(ኢዜአ)፦የአፍሪካ አባል ህብረት አገራት የአህጉራዊውን ነጻ ንግድ ቀጣና ቁልፍ የማስፈጸሚያ የህግ ማዕቀፎችን በማጽደቅ ወደ ስራ እንዲያስገቡ አሳሰበ። 47ኛው የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ዛሬ በኢኳቶሪያል ጊኒ ማላቦ ተጀምሯል። ስብሰባው “ የማካካሻ ፍትህ ለአፍሪካውያንና ለዘርዓ-አፍሪካውያን” በሚል ሀሳብ እየተከናወነ ይገኛል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ የምክር ቤቱ ዋንኛ የውይይት አጀንዳ የህብረቱ የእ.አ.አ 2026 በጀት መሆኑን ገልጸዋል። ከዚህ አንጻር የህብረቱ ፕሮግራም በጀት በራስ አቅም የመሸፈን ስራ መጠነኛ ለውጥ ቢያሳይም ብዙ ስራዎች እንደሚቀሩ ተናግረዋል። ይሁንና እ.አ.አ በ2016 የህብረቱ አባል ሀገራት ወደ አፍሪካ የሚገቡ የተመረጡ እቃዎች ላይ የ0 ነጥብ 2 በመቶ ቀረጥ በመጣል የአህጉራዊውን ተቋም የፋይናንስ አቅም ማጠናከር የሚያስችለውን ውሳኔ ሀሳብ (kigali decision) ቢያፀድቁም በሚፈለገው ደረጃ እየተገበሩት እንዳልሆነ አመልክተዋል። ከህብረቱ አባል ሀገራት መካከል 17ቱ ብቻ ስምምነቱን እየተገበሩ ነው ያሉት ሊቀ መንበሩ የህብረቱን የፋይናንስ ነጻነት ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እንዲሰሩ አሳስበዋል። ሱዳን፣ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ጎንጎ፣ ሶማሊያ እና ሳሄል ቀጣናን ጨምሮ በአህጉሪቷ ያሉ የፖለቲካ አለመረጋጋቶች፣ የሰብዓዊ ቀውሶች እና የደህንነት ችግር አሁን የአፍሪካ ልማት አጀንዳ እንዳይሳካ መሰናክል ሆኖ ቀጥሏል ነው ያሉት ሊቀ መንበሩ። የአፍሪካ ህብረት የድጋፍ እና የማረጋጋት ተልዕኮ (አውሶም) የሰላም አስከባሪ ኃይል ያጋጠመው የፋይናንስ እጥረት ልዩ ትኩረት እንደሚያሻው ተናግረዋል። እነዚህ ፈተናዎች ቢኖሩም በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና በሩዋንዳ መካከል የተደረገው ስምምነት፣ የጋቦን ወደ ህገ መንግስታዊ ስርዓት መመለስ እና የጊኒ የሽግግር እቅድ ተስፋን የሚያጭሩ መልካም ለውጦች መሆናቸውን በማሳያነት ጠቅሰዋል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ከቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማህበረሰቦች፣ ከህብረቱ የሰላም እና ደህነንት ምክር ቤት እንዲሁም ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ጋር ቀጣይነት ባለው መልኩ ትብብሩን በማጠናከር የሰላም ጥረቶችን መደገፉን እንደሚቀጥል ገልጸዋል። በተጨማሪም ሊቀ መንበሩ የህብረቱ አባል ሀገራት የተቋማዊ ሪፎርም ስራን እንዲያፋጥኑንና የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ማስፈጸሚያ ደንቦችን አፅድቀው ወደ ስራ በማስገባት ለቀጣናዊ ትስስር የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ከተቋሙ ያገኘው መረጃ ያመለክታል። 47ኛው የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብስባ እስከ ነገ ይቆያል። ከምክር ቤቱ ስብሰባ ጎን ለጎን ሐምሌ 7 ቀን 2017 ዓ.ም የህብረቱ የ7ተኛ የመንፈቅ ዓመት የባለድርሻ አካላት የትብብር ስብሰባ ይደረጋል። #Ethiopian_News_Agency #Ethiopia #ኢትዮጵያ #ኢዜአ
የክልሉ መንግስት የጤና አገልግሎት ለሕብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ ተጠቃሚነቱን የሚያጎለብት ተግባር እያከናወነ ነው
Jul 10, 2025 53
ቦንጋ ፤ ሐምሌ 3/2017 (ኢዜአ)፡- የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የጤና አገልግሎት ለሕብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ ተጠቃሚነቱን ይበልጥ የሚያጎለብት ተግባር እያከናወነ መሆኑ ተገለጸ። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) በካፋ ዞን የተገነባውን የቆንዳ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል መርቀው ሥራ አስጀምረዋል። በተጨማሪም በካፋ ዞን ሳይለም ወረዳ ከ78 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የያዶታ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅና የያዶታ ጤና ጣቢያ ቀዶ ጥገና ማዕከልንም መርቀዋል ። በዚህ ወቅት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ እንዳሉት፤ የክልሉ መንግስት የዜጎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን የሚያሳድጉ በርካታ ተግባራት እያከናወነ ነው ። በተለይም ከማህበራዊ ዘርፍ ውስጥ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትንና ጥራቱን ለማሻሻል በተወሰደው እርምጃ የዛሬውን ጨምሮ ባለፉት የለውጥ ዓመታት አራት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች ተመርቀው ለአገልግሎት እንዲበቁ ተደርጓል ብለዋል። በተጨማሪም በርካታ የማስፋፊያና በግብአት የማሟላት ስራም መከናወኑን አንስተዋል። ዛሬ የተመረቀው የቆንዳ ሆስፒታል ለወረዳውና ለአጎራባች አካባቢዎች ነዋሪዎች አገልግሎት የሚሰጥ ነው ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ፤ የክልሉ መንግስት የጤና አገልግሎት ለሕብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ ተጠቃሚነቱን ይበልጥ የማጎልበት ተግባር እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። የክልሉ ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም በበኩላቸው፤ የቆንዳ የመጀመሪያ ሆስፒታል በክልሉ መንግስት 120 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ መገንባቱን ገልጸዋል። የሆስፒታሉ መገንባት ሕብረተሰቡ የተሻለ የጤና አገልግሎት እንዲያገኝ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ተናግረዋል። ዛሬ የተመረቀው የቆንዳ ሆስፒታል በሕብረተሰቡ ሲነሳ ለቆየው ጥያቄ መልስ የሰጠ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ ናቸው ። በምረቃው ሥነ-ሥርዓት ላይ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደርና የግብርና ቢሮ ሀላፊ አቶ ማስረሻ በላቸውን ጨምሮ ሌሎችም ከፍተኛ አመራሮችና የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
በዞኑ በዲጂታላይዜሽን የታገዘ አገልግሎት ለማህበረሰቡ በመስጠት የተገልጋይን እርካታ ለማረጋገጥ ትኩረት ተደርጓል
Jul 10, 2025 48
ደብረ ብርሃን ፤ ሐምሌ 3/2017(ኢዜአ)፦በሰሜን ሸዋ ዞን በዲጂታላይዜሽን የታገዘ ቀልጣፋና ፍትሃዊ አገልግሎት ለማህበረሰቡ በመስጠት የተገልጋይን እርካታ ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ። የሰሜን ሸዋ ዞን የከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ በከተሞች የኮሪደር ልማትና በዲጂታላይዜሽን አተገባበር ላይ ዛሬ ከባለድርሻ አካላት ጋር መክሯል። የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መካሻ ዓለማየሁ በውይይቱ ላይ እንደገለጹት በከተሞች ተአማኒነት ያለው አገልግሎት ለመስጠት ዲጂታላይዜሽን የአሰራር ሥርአት እየተዘረጋ ነው። የዲጂታል አሰራሩ በየደረጃው ያሉ የሲቪል ሰርቪስ ሠራተኞች ለተገልጋዩ ማህበረሰብ ግልጽና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጡ ከማድረግ ባለፈ ብልሹ አሰራርን ለማስወገድ ያግዛል ብለዋል። በአዲሱ በጀት ዓመት በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የተገልጋይን እርካታ ለመፍጠር ከሚሰራው ሥራ በተጨማሪ በከተሞችና በገጠር አካባቢዎች የኮሪደር ልማትን በማስጀመር የህብረተሰቡን አኗኗር ለማዘመን ትኩረት እንደሚሰጥም አስገንዝበዋል። የዞኑ ከተሞችና የገጠር አካባቢዎች ለማዘመን በሚሰራው ሥራም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሊወጡ እንደሚገባም አስተዳዳሪው አሳስበዋል። በዞኑ የከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ሃላፊ አቶ ብርቃብርቅ ተሾመ በበኩላቸው እንዳሉት ከተሞችን ለኑሮ፣ ለኢንቨስትመንትና ለቱሪዝም ምቹ ለማድረግ የኮሪደር ልማትን ጨምሮ የተለያዩ የልማት ተግባራት እየተከናወኑ ነው። ለዚህም በዞኑ ሥር ባለችው የሸዋ ሮቢት ከተማ የኮሪደር ልማት ግንባታ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ተጀምሮ እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰዋል። በተጨማሪም ቡልጋ፣ አረርቲና ለሚ ከተሞችን ጨምሮ በዞኑ ሥር ባሉ ዘጠኝ ከተሞች የኮሪደር ልማት ስራን ለማስጀመር የሚያስችል የጥናት ሥራ ተጠናቋል ብለዋል። የአረርቲ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽህፈት ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ መሳይ አስታጥቄ በከተማው የኮሪደር ልማት ሥራን ለመጀመር የሚያስችል ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል። ልማቱንና የህብረተሰቡን ተሳትፎ በማስመልከት ከከተማዋ ነዋሪዎች ጋር በስፋት ውይይት ተደርጎ የጋራ መግባባት ላይ መደረሱንም ጠቁመዋል። የእንሳሮ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አከበረኝ ዓለሙ በበኩላቸው እንደገለጹት ከሀገራዊ ለውጡ በፊት ተረስተው የቆዩ ከተሞች አሁን ላይ ትኩረት እያገኙ መሆናቸውን አስረድተዋል። ለዚህም የለሚ ከተማ በኢንቨስትመንት እያደገች መምጣቷ አንዱ ማሳያ ነው ያሉት አቶ አከበረኝ፣ በአዲሱ በጀት ዓመት በከተማው የኮሪደር ልማትና የዲጂታላይዜሽን አሰራርን ለመጀመር ዝግጅት መደረጉን ጠቅስዋል። በውይይቱ ላይ የዞን፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደር አመራሮች እንዲሁም ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቪየትናም ዋና ከተማ ሃኖይ አዲስ የመንገደኞች በረራ ጀመረ
Jul 10, 2025 63
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 3/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቪየትናም ዋና ከተማ ሃኖይ አዲስ የመንገደኞች በረራ ጀምሯል። በማስጀመሪያ መርሀግብሩ የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ ደንጌ ቦሩ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው የአየር መንገዱ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የቪየትናም የንግድ ተቋማት ተወካዮች ታድመዋል። አየር መንገዱ በሳምንት አራት ጊዜ የመንገደኞች በረራ የሚያደርግ መሆኑ ተገልጿል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው በዚሁ ወቅት እንዳሉት በረራው የሀገራቱን ግንኙነት የሚያጎለብት ነው። ይህ አዲስ መስመር በኢትዮጵያ እና ቪየትናም መካከል ያለውን የንግድ፣ ቱሪዝም እና የባህል ልውውጥ የሚያሳድግ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ እንዲሁም በአፍሪካ እና በደቡብ ምሥራቅ እስያ መካከል ቀጥተኛ ትስስር እንዲኖር በማድረግ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ስትራቴጂካዊ መስፋፋት በማጠናከር ዓለም አቀፍ ግንኙነትን የሚያጎለብት መሆኑን ተናግረዋል። የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ ደንጌ ቦሩ፥ አየር መንገዱ የስኬት ማሳያ የሆነ ተቋም መሆኑን ገልጸዋል። አየር መንገዱ እንደ ሀገር የተያዙ ኢኮኖሚያዊ እቅዶች እንዲሳኩ የራሱን አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን አንስተዋል። በረራው የሀገራቱን ግንኙነት በጉልህ የሚያሳድግ መሆኑን ተናግረዋል። በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመካከለኛው ምስራቅ እስያ እና ፓስፊክ ሀገራት ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል ደዋኖ ከድር በበኩላቸው አየር መንገዱ ለዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ጉልህ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ገልጸዋል። በሁለቱ ሀገራት መካከል የተጀመረው በረራ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጠቀሜታ እንዳለው አመላክተዋል።
ፖለቲካ
በዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ የተመዘገቡ ውጤታማ ስራዎች ወደ ላቀ ደረጃ የማሸጋገሩ ተግባር ይጠናከራል
Jul 10, 2025 57
ሐረር፤ሐምሌ 3/2017 (ኢዜአ)፡-በዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ የተመዘገቡ ውጤታማ ስራዎች ወደ ላቀ ደረጃ የማሸጋገሩ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በብልፅግና ፓርቲ የዋና ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ መለስ ዓለሙ ገለጹ። የብልፅግና ፓርቲ የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ በሐረር ከተማ ለሁለት ቀናት ሲያካሂደው የቆየው የ2017 እቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2018 እቅድ ተግባቦት መድረክ ዛሬ ተጠናቋል። በመድረኩ የፌደራልና የክልል የብልፅግና ፓርቲ የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ አመራሮች እንዲሁም የፓርቲው የወጣቶችና ሴቶች ክንፍ ተሳትፈዋል። በብልፅግና ፓርቲ የዋና ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ መለስ ዓለሙ በወቅቱ እንደተናገሩት፥ በ2017 በጀት ዓመት የዴሞክራሲ ባህል እሴትን ለማጠናከር የሚያስችሉ ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል። የፖለቲካ ፓርቲዎች በትብብር ከመስራት አንጻር በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በጋራ ምክር ቤቶች በመደራጀት አብሮ የመስራት ባህል እየዳበረ መምጣቱን ጠቅሰዋል። ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የተጀመሩ ስራዎች አዲስ ባህልና ልምድ እያመጡ ስለመሆኑም አንስተዋል። የጋራ ስራዎቹ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸው፤ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ለዴሞክራሲ ባህል ግንባታ በቁርጠኝነት መስራታቸውን አጎልብተው እንዲቀጥሉም አመልክተዋል። በአሁኑ ወቅት በየደረጃው ያለው የመንግስት አካላትና ሲቪል ማህበረሰብ በጋራና በቅንጅት የሚሰሩበት ጅምር ሁኔታ መፈጠሩን ጠቅሰዋል። በተለይ የወጣቶችና ሴቶች አስተዋጽኦን ለማላቅና ተሳትፏቸውን ይበልጥ ለማሳደግ ብሎም ተጠቃሚነታቸውን ለማጎልበት መድረኩ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩንም አንስተዋል። በቀጣይም ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ በተቀመጡ አቅጣጫዎች መሰረት ትኩረት ተሰጥቶ እና ባህል አድርጎ እንደሚሰራም አመላክተዋል።
የከተማው ነዋሪዎች ሰላምን ለማፅናት እያበረከቱት ያለው አስተዋጽኦ ለኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴው ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል
Jul 10, 2025 64
ደብረብርሃን ፤ ሐምሌ 3/ 2017 (ኢዜአ)፡- የደብረ ብርሃን ከተማ ነዋሪዎች ከጸጥታ ሃይሉ ጎን በመሰለፍ በአካባቢው ሰላምን ለማፅናት እያበረከቱት ያለው አስተዋጽኦ ለኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴው ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ። የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር በአካባቢው ሰላምን ለማፅናት አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት የእውቅና እና የምስጋና መርሃ ግብር አካሂዷል። በመርሃ ግብሩ ላይ የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት እንደገለጹት፤ የጸጥታ ሃይሉ ከሕብረተሰቡ ጋር በመተባበር ሰላም እንዲከበር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል። በዚህም በከተማዋ የሚካሄዱ የኢንዱስትሪ፣ የኢንቨስትመንትና የንግድ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን ጠቅሰዋል። ይህም ስራ እድል እንዲስፋፋ፣ የገቢና ሌሎች የልማት ዘርፎች ውጤታማ እንዲሆኑ ምቹ መደላድል መፍጠሩን ገልጸዋል። በከተማዋ አሁን ላይ የኮሪደር ልማትን ጨምሮ ሌሎች የመሰረተ ልማት ግንባታዎች እየተካሄዱ እንደሚገኙ አስረድተዋል። የልማት ሁሉ መሰረት የሆነውን ዘላቂ ሰላም ለማስፈን በሚደረገው ጥረት ሁሉ ሕብረተሰቡ ከጸጥታ ሃይሉ ጎን በመሰለፍ የተለመደ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥልም መልዕክት አስተላልፈዋል። የእውቅና እና የምስጋና መርሃ ግብሩ ዓላማም የከተማው ነዋሪዎች ከጸጥታ ሃይሉ ጎን በመሰለፍ የህግ ማስከበር ስራው ይበልጥ በውጤታማነት በማስቀጠሉ ሂደት ድጋፋቸውን እንዲያጠናክሩ ለማበረታታ መሆኑን ተናግረዋል። ከህግ አስከባሪዎች መካከል ሀምሳ አለቃ ሰይፈ ደምሰው በሰጡት አስተያየት፤ ሰላምን አፅንቶ በማስቀጠል ለልማት የተፈጠረው ምቹ ሁኔታ ይበልጥ ለማጠናከር ከሕብረተሰቡ ጋር ተቀናጅተወ በትኩረት እንደሚሰሩ ተናግረዋል። ሌላው የመርሃ ግብሩ ተሳታፊ ፈለቀ በየነ በበኩላቸው፤ የአካባቢውን ሰላም በማፅናት የልማት ስራዎቻቸው ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በቁርጠኝነት እንሰራለን ብለዋል። በመርሃ ግብሩ ላይ የጎዳና ላይ ትርኢቶችና ሌሎች ዝግጅቶች ተካሂደዋል።
በብሔረሰብ አስተዳደሩ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል
Jul 10, 2025 62
ሰቆጣ ፤ሐምሌ 3/2017(ኢዜአ)፦ በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራት መከናወናቸውን የብሔረሰብ አስተዳደሩ አስታወቀ። የብሔረሰብ አስተዳደሩ የተጠናቀቀው በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸምን የሚገመግምና የቀጣይ 90 ቀናት ዕቅድ ማስተዋወቂያ መድረክ በሰቆጣ ከተማ እየተካሄደ ነው። የብሔረሰብ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሃይሉ ግርማይ በመድረኩ ላይ እንደገለጹት በበጀት ዓመቱ ህብረተሰቡን ያሳተፈ የሰላምና ፀጥታ ተግባር በመካሄዱ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ ተችሏል። በልማት ሥራም ለመልካም አስተዳደር ምክንያት ሆኖ የቆየው የሰቆጣ አዳሪ ትምህርት ቤትን ጨምሮ የስርዓተ ምግብን ለማሻሻል በዓመት ከ360 ሺህ በላይ ጫጩት ማስፈልፈያ ማዕከል ግንባታ ስራን ማከናወን እንደተቻለ ገልጸዋል። በተጨማሪም የመስኖ መሰረተ ልማትን በማስፋፋት የግብርና ምርታማነት እንዲያድግ መሰራቱን ጠቁመው፣ የመኽር እርሻ ምርታማነትን ለማሳደግም በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል። በፌደራል፣ በክልልና በወረዳ በጀት እየተገነቡ ያሉ መሰረተ ልማቶች በተቀመጠላቸው ጊዜ በጥራት ተገንብተው እንዲጠናቀቁ የድጋፍና ክትትሉ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል። የአመራሩን የማስፈፀም አቅም ይበልጥ በማሳደግ በበጀት ዓመቱ የተገኙ ስኬቶችን በአዲሱ በጀት ዓመትም ለመድገም ከምንጊዜውም በላይ በቁርጠኝነት እንደሚሰራም አቶ ሃይሉ አስረድተዋል። በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የፀጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ጭምር ያልተቋረጠ የጤና አገልግሎት መስጠት መቻሉን የተናገሩት ደግሞ የብሔረሰብ አስተዳደሩ ጤና መምሪያ ሃላፊ አቶ አሰፋ ነጋሽ ናቸው። በበጀት ዓመቱ በስርዓተ ምግብ ማሻሻል እንዲሁም የወባ እና ሌሎች ተላላፊ በሽታዎችን በመከላከልና በማከም በተሰራው ስራም የከፋ ችግር ሳይደርስ ማለፉንም ተናግረዋል። የእናቶችና ህፃናት ህክምና ማዕከልን ጨምሮ 42 የጤና ፕሮጀክቶች እየተገነቡ መሆናቸውን የተናገሩት አቶ አሰፋ፤ በጤና ተቋማቱ ዜጎችን የጤና አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አስረድተዋል። የብሄረሰብ አስተዳደሩ የግብርና መምሪያ ሃላፊ አቶ አዲስ ወልዴ በበኩላቸው "በብሔረሰብ አስተዳደሩ በመስኖ ከለማው መሬት ከ700 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት ተሰብስቧል ብለዋል። ይህም የአካባቢውን ገበያ ለማረጋጋት ማገዙን ተናግረዋል። በበጋው ወቅት በ369 ተፋሰሶች ላይ ህብረተሰቡን ያሳተፈ የተፈጥሮ ሃብት ልማት ሥራ መካሄዱን ጠቁመው፣ የለሙትን ተፋሰሶች በስነ እፅዋት ዘዴ ለማጠናከርም ችግኞች መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል። በመድረኩ ላይ የክልል፣ የብሔረሰብ አስተዳደሩና የወረዳ አመራሮች ተሳትፈዋል።
የኢትዮጵያና ዛምቢያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በተለያዩ መስኮች ተጠናክሮ ቀጥሏል - አምባሳደር ሮዝ ሳካላ
Jul 10, 2025 62
አዲስ አበባ፤ሐምሌ 3/2017(ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ እና በዛምቢያ መካከል ያለው ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ ግንኙነት በተለያዩ መስኮች ተጠናክሮ መቀጠሉን በኢትዮጵያ የዛምቢያ አምባሳደር ሮዝ ሳካላ ገለጹ። በኢትዮጵያ የዛምቢያ አምባሳደር ሮዝ ሳካላ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ኢትዮጵያ እና ዛምቢያ ዘላቂ እና ዘርፈ-ብዙ ግንኙነት እንዳላቸው ገለጸዋል። ይህም ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እና በተለያዩ ዘርፎችም እያደገ መምጣቱን ተናግረዋል። በተለይም ዛምቢያ ኤምባሲዋን በኢትዮጵያ ከከፈተችበት ጊዜ አንስቶ የሁለቱ አገሮች አጋርነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎለበተ ከመምጣቱም በላይ የተለያዩ የትብብር ስራዎችም እየተጠናከረ እንደሚገኝ ተናግረዋል። እ.አ.አ በ2017 ሁለቱ ሀገራት የጋራ ኮሚሽን ማቋቋማቸውን ገልጸው፤ ይህም ተጨባጭ ጥቅሞችን ማስገኘቱን ጠቁመዋል። ሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ አቅም እንዳላቸው ገልጸው፤ ከሁለቱም ወገኖች የተውጣጡ የንግድ ባለሙያዎችን እና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን በማሰባሰብ ግንኙነታቸውን የበለጠ ለማሳደግ ጥረት መደረጉን አንስተዋል። የጋራ ኮሚሽኑ በንግድና ኢንቨስትመንት በተለይም በግብርናና በአየር ትራንስፖርት ዘርፍ ያለውን ትስስር እንደሚያጠናክር ጠቁመዋል። ዛምቢያ የአፍሪካን አንድነት ለማጎልበት እና አህጉራዊ አጀንዳዎችን ለማራመድ በተለያዩ መድረኮች በማደራጀት እና በመሳተፍ ንቁ ተሳትፎ እያደረገች መሆኑን ተናግረዋል ። አፍሪካ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ውስጥ ቋሚ ውክልና አለማግኘቷ ኢ-ፍትሃዊ ነው ብለዋል። ዛምቢያ ለቀጣናው ኢኮኖሚያዊ ውህደት ትልቅ አስተዋፅዖ እንዳደረገች ገልፀው፤ ፓን አፍሪካኒዝም እንደ መሰረታዊ መርህ እና ከእነዚህ ጥረቶች ጀርባ አንቀሳቃሽ ሃይል ሆኖ ያገለግላል ብለዋል። የአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 ለአፍሪካ በርካታ እድሎችን የሚሰጥ ወርቃማ አጀንዳ መሆኑን ገልጸው፤ በትብብር መተግበር እንደሚገባ አሳስበዋል።
የምርምር ባህልን ማሳደግና ፈጠራን ማበረታታት ቀጣይነት ላለው ሀገራዊ እድገት ወሳኝ ነው-አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ
Jul 10, 2025 80
አዲስ አበባ፤ሐምሌ 3/2017(ኢዜአ)፦ የምርምር ባህልን ማሳደግና ፈጠራን ማበረታታት ቀጣይነት ላለው ሀገራዊ እድገት ወሳኝ መሆኑን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ገለጹ። አምስተኛው ዓመታዊ የፓርላማ ጥናትና ምርምር ኮንፈረንስ "አካታችና ጠንካራ የፓርላማ ስርዓት ለሀገር በቀል እውቀትና ቀጣይነት ላለው ልማት" በሚል መሪ ሀሳብ መካሄድ ጀምሯል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ በጉባኤው መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት፥ በየዓመቱ የሚካሄደው የምርምር ጉባኤ ለእውቀት መፍለቅ፣ለምርምርና ጥናት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው። ጉባኤው ምክር ቤቱ ለተሻለ ህግ ማውጣት፣ ለውጤታማ ክትትልና ቁጥጥር እንዲሁም ለተሳካ የፓርላማ ዲፕሎማሲ የሚያስፈልገውን መረጃና ትንተና እንዲያገኝ እድል መፍጠሩን አስታውሰዋል። በምጣኔ ሃብት፣ፖለቲካ፣ማህበራዊና በቴክኖሎጂ ዘርፎች የሚደረጉ ጥናትና ምርምሮች ሀገራዊ አቅምን ለመገንባትና ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ ወሳኝ ናቸው ብለዋል። ምርምር ለማንኛውም አገራዊ ልማትና እድገት መሰረት በመሆኑ በተቋምና በሀገር ደረጃ የላቀ እድገት ለማስመዝገብ ለጥናትና ምርምር ትኩረት መስጠት ተገቢ መሆኑን አስገንዝበዋል። የምርምር ባህልን ማሳደግ፣ፈጠራን ማበረታታትና እውቀትን በተግባር ማዋል ቀጣይነት ላለው እድገት ወሳኝ መሆኑን በመጠቆም በተለይም ለህግ አውጪ አካል ስራዎች የምርምር ሚና የላቀ እንደሆነም ጠቁመዋል። ምክር ቤቱ የሚወስናቸው ውሳኔዎች፣የሚያወጣቸው ህጎችና የሚያደርገው የክትትልና ቁጥጥር ስራ ጥናትና ምርምር ላይ የተመሰረቱ እንዲሆኑ ሚናውን አጠናክሮ ይቀጥላል ያሉት። እንደ አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ገለጻ፥ የሚወጡ ህጎችን ተቀባይነት እንዲኖራቸው በጥናት ላይ የተመሰረተ የህዝብ ፍላጎት፣አስተያየትና ቅሬታን በመሰብሰብና በመተንተን በህግ አወጣጥ ሂደት ውስጥ ማካተት ያስፈልጋል። በተመሳሳይ ምክር ቤቱ መንግስት የሚሰራቸውን ስራዎች ለመከታተል፣ የበጀት አጠቃቀም ለመቆጣጠርና የመንግስት ፖሊሲዎችን ውጤታማነትን ለመገምገም ጥልቅ ትንተና ማድረግ ተገቢ ነው ብለዋል። ምክር ቤቱ ለምርምር ትኩረት በመስጠት፣የምርምር ጉባኤዎችን በማዘጋጀትና የፓርላማ የምርምር ትስስር በማቋቋም ከምርምር ተቋማት ጋር ያለውን ግንኙነት ማጠናከሩንም ገልጸዋል። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ክፍሌ(ዶ/ር) በበኩላችው፥ የቴክኖሎጂ ዕድገትን ተከትሎ የተፈጠረው የድህረ እውነት ዓለም አሉታዊ ተጽእኖ እያሳደረ እንደሚገኝ አንስተዋል። ይህን ለመቀልበስ በጥናት ምርምር ላይ የተመሰረተ ሥራ እና ጠንካራ ፓርላማ መገንባት እንደሚያስፈልግ አመላክተዋል። በምርምር ጉባኤው ጥናታዊ ፅሁፍ ያቀረቡት በጅማ ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ሳይንስ ተመራማሪ እውነቱ ሃይሉ (ዶ/ር)፥ ኢትዮጵያ ለዘመናት ፀንታ የቆየችው በራሷ ዕውቀትና እውነት ውስጥ በመኖሯ ነው ብለዋል። ምክር ቤቱ በሚያወጣቸው የህግ ማዕቀፎች ውስጥ ሀገር በቀል እውቀቶችን ማካተት አለበት ያሉት ተመራማሪው፥ የሀገር በቀል እወቀቶችን ፋይዳ ማስገንዘብም እንደሚገባ አስረድተዋል። በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የህዝብ አስተዳደርና ኢኮኖሚ መምህርና ተመራማሪ ዳንኤል በየራ በበኩላቸው፥ ከሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አካታችነት አንጻር የተገኙ ውጤቶችና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ትኩረት በማድረግ ጥናታዊ ፅሁፍ አቅርበዋል። ከግሉ ዘርፍ፣ ከትምህርት፣ ከመሰረተ ልማት፣ ከጤና አካታችነት አንጻር ውጤቶች መገኘታቸውን ጠቅሰው፥ ምክር ቤቱ ለላቀ ስኬት የክትትልና ቁጥጥር ስራውን ማጠናከር እንዳለበት ጠቁመዋል። በአምስተኛው ዓመታዊ የፓርላማ ጥናትና ምርምር ኮንፈረንስ የፓርላማ ዴሞክራሲ ሥርዓት ትግበራ መሻሻል፣የፓርላማ ተግባራትን ማጠናከር፣ የሕግ የበላይት፣አካታች አስተዳደርና ሀገረ መንግሥት ግንባታ ላይ ያተኮሩ 12 የተለያዩ ጥናታዊ ፅሁፎች በምሁራን እንደሚቀርቡ የወጣው መርሃ ግብር ያሳያል።
በተለያዩ ሀገራት በችግር ውስጥ የነበሩ ከ131 ሺህ በላይ ዜጎች ተመልሰዋል - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
Jul 10, 2025 93
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 3/2017(ኢዜአ)፦ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በ21 ሀገራት በችግር ወስጥ የነበሩ ከ131 ሺህ በላይ ዜጎች ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ሚኒስቴሩ በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመት ዋና ዋና የዲፕሎማሲ ሥራዎችን አስመልክተው ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥተዋል። ኢትዮጵያ በበጀት ዓመቱ ብሔራዊ ጥቅሟን ያስከበሩ የሁለትዮሽና ባለብዙ ወገን ግንኙነት በመፍጠር፣ ቀጣናዊ ትስስር እንዲሁም አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ትብብርን ማጠናከር የሚያስችሉ ስኬታማ የዲፕሎማሲ ስራዎች አከናውናለች ብለዋል። ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት የበለጠ ማጠናከር የሚያስችሉና ቀጣናዊ ትስስርን የሚያፋጥኑ ፍሬያማ የዲፕሎማሲ ተግባራትን ማከናወኗንም አመልክተዋል። ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያን እውነት ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስረዳት ጠንካራ የዲፕሎማሲ ሥራዎች መከናወናቸውንም አምባሳደሩ አብራርተዋል። የናይል ተፋሰስ ኮሚሽን እንዲቋቋም በማድረግ ኢትዮጵያ የፍትሃዊ ተጠቃሚነት መሻቷን በተግባር አሳይታለች ነው ያሉት። ኢትዮጵያ ከጎረቤቶቿ ጋር የህዝብ ለህዝብ ትስስርን ለማጠናከር ለ968 የተለያዩ ሀገራት ዜጎች የትምህርት እድል መስጠቷንም ቃል አቀባዩ ጨምረው ተናግረዋል። በበጀት ዓመቱ የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም የሚያስከብሩ 11 ስምምነቶች ተፈርመው በፓርላማ መፅደቃቸውንም ነው አምባሳደር ነብያት ጌታቸው የገለጹት። በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ስለ ማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውና ስለኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ በቂ ግንዛቤ በመያዝ ድጋፉን እንዲያጠናክር የሚያደርጉ ስራዎች መከናወናቸውን ጠቅሰዋል። በበጀት ዓመቱ በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ በ21 ሀገራት በችግር ውስጥ የነበሩ ከ131ሺህ በላይ ዜጎች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ መደረጉንም አስታውሰዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበጀት ዓመቱ የዜጎችን ደህንነትና ክብር የማስጠበቅ ሥራን ቀዳሚ ትኩረት ሰጥቶ መስራቱን አመልክተዋል። ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ኮንፍረንሶችን የማስተናገድ አቅሟ እያደገ መምጣቱን የጠቀሱት አምባሳደሩ፣ በቅርቡም ትላልቅ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎች ይካሄዳሉ ብለዋል። ከእነዚህም ውስጥ የተባበሩት መንግስታት ሁለተኛው የሥርዓተ ምግብ ጉባኤ እና ሁለተኛው የአፍሪካ አየር ንብረት ጉባኤ ተጠቃሽ መሆናቸውን ተናግረዋል። በአሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከተፈቀደላቸው የቪዛ ጊዜ በላይ መቆየት ከፍተኛ ተጠያቂነትን የሚያስከትል በመሆኑ ዜጎች ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባም ነው ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው ያሳሰቡት። የኢትዮጵያን ቪዛ አግኝተው የሚመጡ የሌላ ሀገር ዜጎች ከተፈቀደላቸው የቆይታ ጊዜ በላይ መቆየት በሀገሪቱ ህግ መሰረት ቅጣት የሚያሰጥ መሆኑን በመገንዘብ ጥንቃቄ እንደያደርጉም አፅንኦት ሰጥተዋል።
ምክር ቤቱ የሕግ አወጣጥ፣ የክትትልና ቁጥጥር ስራን በጥናትና ምርምር በመደገፍ ውጤታማ ተግባር እያከናወነ ነው - አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ
Jul 10, 2025 92
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 3/2017(ኢዜአ)፦ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ አወጣጥ፣ የክትትልና ቁጥጥር ስራን በጥናትና ምርምር በመደገፍ ለአካታች ልማት መሳካት የበኩሉን እየተወጣ መሆኑን የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ገለጹ። አፈ ጉባኤው ይህን ያሉት "አካታችና ጠንካራ የፓርላማ ስርዓት ለሀገር በቀል እውቀትና ቀጣይነት ላለው ልማት" በሚል በተጀመረው አምስተኛው ዓመታዊ የፓርላማ ጥናትና ምርምር ኮንፍረንስ መክፈቻ መርሃ ግብር ላይ ነው። አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ የምርምር ባህልን ማሳደግ ቀጣይነት ላለው እድገት፣ ጠንካራ ምጣኔ ሃብትና ዘላቂ እድገትን ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑንም ተናግረዋል። በመሆኑም የምርምር ኮንፍረንሱ ምክር ቤቱ ለሚያወጣቸው ፖሊሲዎች፣ ህጎችና ለሚያደርገው የክትትልና ቁጥጥር ሥራ አስተዋጽኦው ከፍተኛ እንደሆነ አንስተዋል። ምክር ቤቱ የሕግ አወጣጥ፣ የክትትልና ቁጥጥር፣ የሕዝብ ውክልና እና የፓርላማ ዲፕሎማሲ ሥራዎችን በጥናትና ምርምር የተደገፉ በማድረግ የህዝብን ጥያቄ ለመመለስ እየሰራ ነው ብለዋል። የህዝብ ቅሬታን ከመሰረቱ በጥናትና ምርምር በመለየት በሚወጡ ህጎችና ፖሊሲዎች በማካተት ዘላቂ መፍትሔ እንዲሰጣቸው እያደረገ መሆኑንም ጨምረዋል። ምክር ቤቱ በቀጣይም ከምርምር ተቋማት ጋር ያለውን የትብብር ሥራ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል። በአምስተኛው ዓመታዊ የፓርላማ ጥናትና ምርምር ኮንፍረንስ የፓርላማ ዴሞክራሲ ሥርዓት ትግበራ መሻሻል፣ የፓርላማ ተግባራትን ማጠናከር፣ የሕግ የበላይነት፣ አካታች አስተዳደርና ሀገረ መንግሥት ግንባታ ላይ ያተኮሩ 12 የተለያዩ ጥናታዊ ፅሁፎች እንደሚቀርቡ የወጣው መርሃ ግብር ያሳያል። በኮንፍረንሱ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፍተኛ አመራሮች፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኃላፊዎች፣ ምሁራንና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።
መንግስት በሁሉም መስክ የኢትዮጵያን ብልፅግና ለማረጋገጥ መሰረት የሚጥሉ ውጤታማ ተግባራትን አከናውኗል
Jul 10, 2025 77
ጎንደር፤ ሐምሌ 3/2017(ኢዜአ)፡- በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት መንግስት በሁሉም መስክ የኢትዮጵያን ብልፅግና ለማረጋገጥ መሰረት የሚጥሉ ውጤታማ ተግባራት ማከናወኑ ተገለጸ። "ጠንካራ አደረጃጀት ለሁለንተናዊ ብልፅግና " በሚል መሪ ሃሳብ የብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ የ2017 በጀት ዓመት ግምገማና የ2018 የእቅድ ትውውቅ መድረክ በጎንደር ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡ በግምገማ መድረኩ ላይ የብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ እንደተናገሩት፤ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በፓርቲው አመራር ሰጪነት ሀገርን ወደ ብልፅግና የሚያሻግሩና አለም ምስክርነቱን ጭምር የሰጠባቸው ትርጉም ያላቸው ውጤታማ ተግባራት ማከናወን ተችሏል፡፡ የኑሮ ውድነትን በመቀነስ የህዝቡን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል የሚረዱ የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብርና የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ተጠቃሽ የልማት ተግባራት መሆናቸውን አንስተዋል፡፡ የከተሞችን እድገት ለማፋጠንና የሕዝቡንም የኑሮ ዘይቤ ለማዘመን እንዲቻል በመላ ሀገሪቱ እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎች ከተሜነትን በማላበስ አዲስ ተስፋና ብርሃን የፈነጠቁ ፋና ወጊ የልማት ተግባራት መሆናቸውን ለአብነት ጠቅሰዋል፡፡ የዚህ ትውልድ አኩሪ ድልና ታሪክ የሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብም ስኬት የህዝባችን አይበገሬነትና የፓርቲያችን የአመራር ቁርጠኝነት የታየበት ነው ብለዋል፡፡ የአማራ ክልል እምቅ የተፈጥሮ ሀብት ባለቤትና በኢትዮጵያ ታሪክም ትልቅ አሻራ ያለው ነው ያሉት አቶ ፍቃዱ፤ የክልሉን ሰላም በማፅናት ልማቱን አጠናክሮ ለማስቀጠል አመራሩና ሕዝቡ ተቀናጅተው ያከናወኑዋቸው ተግባራት የሚደነቁ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ፓርቲው የሚመራው መንግስት በርካታ ውጤታማ ተግባራት ማከናወኑን ገልጸው፤ ዛሬም እንደ ትናንቱ በሕዝባችን ተሳትፎና በአመራሩ ቁርጠኛ ያልተሻገርናቸውን በድል ለመወጣት መጪው ዓመት በትጋት ለመስራት ቃል የምንገባበት ነው ብለዋል፡፡ በብልፅግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ፍሰሃ ደሳለኝ በበኩላቸው፤ የአማራ ክልል ትልቅ የመልማትና የማደግ አቅም ያለው የተፈጥሮ ጸጋዎች ባለቤት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የክልሉ ሰላም በማፅናት የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ ብልፅግና ፓርቲ የጠራና ተሻጋሪ ሃሳብ ያለው በመሆኑ ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ እየተጋ እንደሚገኝ ገልጸው፤ ፓርቲው ለሕዝቡ የገባውን ቃል አክብሮ ወደ ተግባር በማሸጋገር በኩል ሕዝባዊ አደራውን ይወጣል ብለዋል፡፡ ጎንደር የብልፅግና ትሩፋቶች ተቋዳሽ ከሆኑ የሀገራችን ቀደምት ከተሞች አንዱ ለመሆን በቅታለች ያሉት ደገሞ የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ቻላቸው ዳኘው ናቸው፡፡ በፌደራልና በክልሉ መንግስት በከተማዋ የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶች የቀደመ ገናና ስሟንና ታሪኳን ያደሰ ብሎም የኪነ ጥበብና የኪነ ህንጻ አሻራዋን በደማቁ ያጎሉ ተግባራት መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ የፓርቲው የአደረጃጀት ዘርፍ የአፈጻጸም ግምገማ መድረክ ላይ ከሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች የተውጣጡ የፓርቲው የአደረጃጃት ዘርፍ አመራሮች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ። አመራሮቹ በፌደራልና በክልሉ መንግስት እየተከናወኑ የሚገኙ የሌማት ትሩፋት፣ የኮሪደር ልማት፣ የአጼ ፋሲል አብያተ መንግስት እድሳትና የጥገና ስራ እንዲሁም የመገጭ የመስኖና የመጠጥ ውሃ ግድብ ፕሮጀክቶች ትናንት ተዘዋውረው መጎብኘታቸውን በወቅቱ ተገልጿል።

ማህበራዊ
የክልሉ መንግስት የጤና አገልግሎት ለሕብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ ተጠቃሚነቱን የሚያጎለብት ተግባር እያከናወነ ነው
Jul 10, 2025 53
ቦንጋ ፤ ሐምሌ 3/2017 (ኢዜአ)፡- የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የጤና አገልግሎት ለሕብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ ተጠቃሚነቱን ይበልጥ የሚያጎለብት ተግባር እያከናወነ መሆኑ ተገለጸ። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) በካፋ ዞን የተገነባውን የቆንዳ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል መርቀው ሥራ አስጀምረዋል። በተጨማሪም በካፋ ዞን ሳይለም ወረዳ ከ78 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የያዶታ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅና የያዶታ ጤና ጣቢያ ቀዶ ጥገና ማዕከልንም መርቀዋል ። በዚህ ወቅት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ እንዳሉት፤ የክልሉ መንግስት የዜጎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን የሚያሳድጉ በርካታ ተግባራት እያከናወነ ነው ። በተለይም ከማህበራዊ ዘርፍ ውስጥ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትንና ጥራቱን ለማሻሻል በተወሰደው እርምጃ የዛሬውን ጨምሮ ባለፉት የለውጥ ዓመታት አራት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች ተመርቀው ለአገልግሎት እንዲበቁ ተደርጓል ብለዋል። በተጨማሪም በርካታ የማስፋፊያና በግብአት የማሟላት ስራም መከናወኑን አንስተዋል። ዛሬ የተመረቀው የቆንዳ ሆስፒታል ለወረዳውና ለአጎራባች አካባቢዎች ነዋሪዎች አገልግሎት የሚሰጥ ነው ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ፤ የክልሉ መንግስት የጤና አገልግሎት ለሕብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ ተጠቃሚነቱን ይበልጥ የማጎልበት ተግባር እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። የክልሉ ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም በበኩላቸው፤ የቆንዳ የመጀመሪያ ሆስፒታል በክልሉ መንግስት 120 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ መገንባቱን ገልጸዋል። የሆስፒታሉ መገንባት ሕብረተሰቡ የተሻለ የጤና አገልግሎት እንዲያገኝ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ተናግረዋል። ዛሬ የተመረቀው የቆንዳ ሆስፒታል በሕብረተሰቡ ሲነሳ ለቆየው ጥያቄ መልስ የሰጠ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ ናቸው ። በምረቃው ሥነ-ሥርዓት ላይ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደርና የግብርና ቢሮ ሀላፊ አቶ ማስረሻ በላቸውን ጨምሮ ሌሎችም ከፍተኛ አመራሮችና የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
በክልሉ በጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች የበርካቶችን ሕይወት እየታደጉ ነው
Jul 10, 2025 49
ወላይታ ሶዶ፤ሐምሌ 3/2017 (ኢዜአ))፡-በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎ ፈቃደኛች በተከታታይ እያበረከቱት ያለው የደም ልገሳ የበርካቶችን ሕይወት እየታደጉ መሆኑ ተገለጸ። የክልሉ ጤና ቢሮ የዓለም የደም ለጋሾ ቀንን ምክንያት በማድረግ ለበጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾችና ተቋማት የምስጋና እና የእውቅና መርሃ ግብር ዛሬ በወላይታ ሶዶ ከተማ አካሂዷል። ዕውቅና ከተሰጣቸው በጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች መካከል ወጣት ሄኖክ ኮይራ በአርአያነት ተጠቅሷል። ወጣቱ በአርአያነት የተጠቀሰውም ለ65 ተከታታይ ጊዜ በበጎ ፈቃደኝነት ደም በመለገሱ ሲሆን፤ለዚህም ከክልሉ ጤና ቢሮ የዕውቅናና ምስጋና የምስክር ወረቀት እንዲሁም ሜዳሊያ ተበርክቶለታል። ወጣት ሄኖክ የሚለገሰው ደም በተለያዩ ምክንያቶች ደም የሚያስፈልጋቸውን ሰዎች ሕይወት እየታደገ መሆኑን ሲያስብ እና ሲመለከት የአዕምሮ እርካታ ከመስጠት ባለፈ ደስታ እንደሚሰማው ይናገራል። የክልሉ ጤና ቢሮ ለተከታታይ 65 ጊዜ ደም በመለገሱ የሰጠው እውቅና ልግስናውን ይበልጥ ለማጠናከር የሚያበረታታው መሆኑን ገልጿል። ሌሎችም ወጣቶች የሚተካ ደም በመለገስ የማይተካ የሰው ሕይወት ቢታደጉ በህይወታቸው ይበልጥ ደስተኛ ሊሆኑ እንደሚችሉ አስተያየት ሰጥቷል። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ሃላፊ አቶ እንዳሻው ሽብሩ በበኩላቸው፤ ወጣት ሄኖክ ኮይራን ጨምሮ በበጎ ፈቃድ ደም የሚለግሱ አካላት የበርካቶችን ሕይወት እየታደጉ በመሆናቸው ሊመሰገኑ ይገባል ብለዋል። ቢሮው የሕብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት የለጋሾች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን ተናግረዋል። በበጎ ፈቃድ ደም በመለገስ አስተዋጽኦ የሚያደርጉ አካላትን ዕውቅና የመስጠት ስራ አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ሃላፊው አስታውቀዋል።
በኢትዮጵያ ዘላቂና አካታች የምግብ ስርዓት ሽግግርን ለማሳካት የሁሉም ሚና ወሳኝ ነው
Jul 10, 2025 52
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 3/2017(ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ ዘላቂ እና አካታች የምግብ ስርዓት ሽግግርን ለማሳካት የሁሉም አካላት ሚና ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ፡፡ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ከኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር "ከራዕይ ወደ ተግባር፤ የኢትዮጵያ ዘላቂና አካታች የምግብ ስርዓት ሽግግር ጉዞ" በሚል መሪ ሀሳብ በኢትዮጵያ ሥርዓተ ምግብ ላይ ያደረገ ውይይት ተካሂዷል። በዚሁ ወቅት የመነሻ ጽሁፍ ያቀረቡት የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ፍሬው ተገኝ (ዶ/ር) እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ ለዘላቂ የልማት ግቦች ስኬት የበኩሏን አስተዋጽኦ እያደረገች ትገኛለች። ኢትዮጵያ የምግብ ስርዓት ሽግግር ትግበራን በመጀመር ግንባር ቀደም ሀገር መሆኗን ገልጸዋል። 2ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስርዓተ ምግብ ጉባኤ በኢትዮጵያ እና በጣሊያን አስተናጋጅነት ከሐምሌ 20 እስከ 22 ቀን 2017 በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ገልጸዋል። ጉባዔው በኢትዮጵያ መካሄዱ ለሀገር ገጽታ ግንባታ ትልቅ ፋይዳ ያለው መሆኑን ገልጸው፤ በተለይም ኢትዮጵያ ለጀመረችው የምግብ ስርዓት ሽግግር ጉዞ እውቅና የሚሰጥ መሆኑን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በተለይም ከለውጡ ወዲህ የምግብ ስርዓት ሽግግርን የሚያፋጥኑ የተለያዩ ብሔራዊ ፕሮግራሞችን በመቅረጽ በትኩረት እየሰራች እንደምትገኝ ይታወቃል። ለአብነትም የሌማት ትሩፋት፣ የስንዴ ልማት፣ አረንጓዴ አሻራ፣ የትምህርት ቤት ምገባ፣ ኢትዮጵያ ታምርት እንዲሁም የሰቆጣ ቃል-ኪዳን ኢንሼቲቮች ተጠቃሽ ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ የትምህርት ቤቶች ምገባ ኢኒሼቲቭ ዳይሬክተር ወይዘሮ ፍሬዓለም ሺባባው በመድረኩ የኢትዮጵያ መንግስት የሰቆጣ ቃልኪዳን እና የተማሪ ምገባ ኢኒሼቲቮችን በመውሰድ ለትውልድ ግንባታ ትልቅ ሥራ እየሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡ በዚህም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ብቻ ከ8 መቶ ሺህ በላይ ተማሪዎች በቀን ሁለት ጊዜ በመመገብ ላይ መሆኑን ተናግረው፤ በሰቆጣ ቃልኪዳንም ለትውልድ ግንባታ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የተፈጥሮ ሳይንስና ስነ ቀመር ኮሌጅ ዲን ቢቂላ ወርቅነህ (ዶ/ር) እንዳሉት፤ የኢትዮጵያ ግብርና ምርታማነት አቅምን ማሳደግ የሁሉም ሚና ነው ብለዋል፡፡ በተለይም የግሉ ሴክተር የሚጠበቅበትን መወጣት እንዳለበት አንስተው ወደ ምግብ ማቀነባበር እንዲሁም እሴትን የመጨመር ስራ መስራት እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡ የኤንቢሲ ቴሌቪዥን ዋና ስራ አስፈጻሚ ብሩክ ከበደ፤ የምግብ ስርዓት እና የምግብ ሉዓላዊነት የመገናኛ ብዙሃን ዋነኛው አጀንዳ ነው ብለዋል፡፡ በተጨማሪም መገናኛ ብዙሃን በሀገራዊ ዋና ዋና ጉዳዮች ዙሪያ በርካታ ስራዎች መስራታቸውን ጠቁመው፤ ለአብነትም የአረንጓዴ አሻራ፣ የሌማት ትሩፋት እንዲሁም በግብርና መካናይዜሽን ዙሪያ በርካታ ስራዎች መሥራታቸውን ጠቁመዋል፡፡ የኒው ላይፋ ቴን ቻሌንጅ ዴቬሎፕመንት ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ሔለን ጥላሁን በበኩላቸው የምግብ ስርዓትን አሻጋሪና አካታች ለማድረግ ወጣቶችን፣ ሴቶችን እና አካል ጉዳተኞችን አሳታፊ ማድረግ እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት የሚካሄደው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የምግብ ስርዓት ጉባዔን በስኬት ለማስተናገድ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡
የተጀመሩ የሰላምና የልማት ተግባራትን ለማጠናከር በትኩረት እየተሰራ ነው
Jul 10, 2025 55
ገንዳ ውሃ ፤ ሐምሌ 3/2017(ኢዜአ)፦ የተጀመሩ የሰላምና የልማት ተግባራትን በማጠናከር የህዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የምዕራብ ጎንደር ዞን አስተዳደር አስታወቀ። በዞኑ ባለፈው በጀት ዓመት የተሰሩ የሰላምና ልማት ስራዎችን የሚገመግምና በቀጣይ ስለሚሰሩ ተግባራት አቅጣጫ የሚያስቀምጥ መድረክ በገንዳ ውኃ ከተማ ተካሄዷል። የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ እያሱ ይላቅ እንዳሉት የዞኑን ፀጋ አሟጦ በመጠቀም የህዝቡን የሰላምና ልማትና ስራዎች ተጠቃሚ ለማድረግ በቁርጠኝነት እየተሰራ ነው። በአካባቢያቸው ያጋጠመን የጸጥታ ችግሮች ከመፍታት ጎን ለጎን ልማትን ለማፋጠንና የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት መሰራቱን አውስተዋል። ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን በተካሄደው ጥረትም የዞኑ ህዝብ የነቃ ተሳትፎ አሁን በዞኑ ለሰፈነው ሰላም ሚና መጫወቱንም አስረድተዋል። የዞኑ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ ደሳለኝ አያና በበኩላቸው በችግር ውስጥ ሆነው ተማሪዎችን ተቀብለው ያስተማሩ ትምህርት ቤቶችን በማጠናከርና በቀጣይ ያልጀመሩትን ለማስጀመር በቁርጠኝነት ይሰራል ብለዋል። በዞኑ የትምህርት ገፅታን ለማሻሻልና የትምህርት ጥራትን ለማሳደግ ከህብረተሰብ ተሳትፎና ከአጋር አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝም አብራርተዋል። ባለፈው ዓመት በርካታ የህዝብ ለህዝብ ውይይቶች ተደርገው የህዝቡን ሰላምና ልማት የማረጋገጥ ተግባር መከናወኑን የገለፁት ደግሞ በብልፅግና ፓርቲ የዞኑ ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ወይዘሮ ደመቅ አበበው ናቸው። በዞኑ አብዛኞቹ ቀበሌዎች ወደ ሰላም መመለስ መቻላቸውን አስረድተው ሰላምን በዘላቂነት በማፅናት የፀጥታና የልማት ሰራዎች በተጠናከረ ሁኔታ እንደሚሰሩም አመልክተዋል። የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ አየለ አናውጤ (ዶ/ር) እንዳሉት በክረምት ወቅት ከመደበኛ ስራዎች ጎን ለጎን የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን ማሳለጥ እንደሚገባ ጠቁመዋል። የዞኑን አንፃራዊ ሰላም ወደ ተሟላ ሰላም ለማሸጋገር የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች መመለስ እንደሚገባም አፅንኦት ሰጥተዋል። ከግምገማ መድረኩ ጎን ለጎንም የደም ልገሳ መርሃ ግብር ተካሄዷል።
ኢኮኖሚ
የአፍሪካ ህብረት አባል አገራት የነጻ ንግድ ቀጣና ቁልፍ የማስተግበሪያ ደንቦች አፅድቀው ወደ ስራ እንዲያስገቡ ጥሪ አቀረበ
Jul 10, 2025 55
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 3/2017(ኢዜአ)፦የአፍሪካ አባል ህብረት አገራት የአህጉራዊውን ነጻ ንግድ ቀጣና ቁልፍ የማስፈጸሚያ የህግ ማዕቀፎችን በማጽደቅ ወደ ስራ እንዲያስገቡ አሳሰበ። 47ኛው የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ዛሬ በኢኳቶሪያል ጊኒ ማላቦ ተጀምሯል። ስብሰባው “ የማካካሻ ፍትህ ለአፍሪካውያንና ለዘርዓ-አፍሪካውያን” በሚል ሀሳብ እየተከናወነ ይገኛል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ የምክር ቤቱ ዋንኛ የውይይት አጀንዳ የህብረቱ የእ.አ.አ 2026 በጀት መሆኑን ገልጸዋል። ከዚህ አንጻር የህብረቱ ፕሮግራም በጀት በራስ አቅም የመሸፈን ስራ መጠነኛ ለውጥ ቢያሳይም ብዙ ስራዎች እንደሚቀሩ ተናግረዋል። ይሁንና እ.አ.አ በ2016 የህብረቱ አባል ሀገራት ወደ አፍሪካ የሚገቡ የተመረጡ እቃዎች ላይ የ0 ነጥብ 2 በመቶ ቀረጥ በመጣል የአህጉራዊውን ተቋም የፋይናንስ አቅም ማጠናከር የሚያስችለውን ውሳኔ ሀሳብ (kigali decision) ቢያፀድቁም በሚፈለገው ደረጃ እየተገበሩት እንዳልሆነ አመልክተዋል። ከህብረቱ አባል ሀገራት መካከል 17ቱ ብቻ ስምምነቱን እየተገበሩ ነው ያሉት ሊቀ መንበሩ የህብረቱን የፋይናንስ ነጻነት ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እንዲሰሩ አሳስበዋል። ሱዳን፣ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ጎንጎ፣ ሶማሊያ እና ሳሄል ቀጣናን ጨምሮ በአህጉሪቷ ያሉ የፖለቲካ አለመረጋጋቶች፣ የሰብዓዊ ቀውሶች እና የደህንነት ችግር አሁን የአፍሪካ ልማት አጀንዳ እንዳይሳካ መሰናክል ሆኖ ቀጥሏል ነው ያሉት ሊቀ መንበሩ። የአፍሪካ ህብረት የድጋፍ እና የማረጋጋት ተልዕኮ (አውሶም) የሰላም አስከባሪ ኃይል ያጋጠመው የፋይናንስ እጥረት ልዩ ትኩረት እንደሚያሻው ተናግረዋል። እነዚህ ፈተናዎች ቢኖሩም በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና በሩዋንዳ መካከል የተደረገው ስምምነት፣ የጋቦን ወደ ህገ መንግስታዊ ስርዓት መመለስ እና የጊኒ የሽግግር እቅድ ተስፋን የሚያጭሩ መልካም ለውጦች መሆናቸውን በማሳያነት ጠቅሰዋል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ከቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማህበረሰቦች፣ ከህብረቱ የሰላም እና ደህነንት ምክር ቤት እንዲሁም ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ጋር ቀጣይነት ባለው መልኩ ትብብሩን በማጠናከር የሰላም ጥረቶችን መደገፉን እንደሚቀጥል ገልጸዋል። በተጨማሪም ሊቀ መንበሩ የህብረቱ አባል ሀገራት የተቋማዊ ሪፎርም ስራን እንዲያፋጥኑንና የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ማስፈጸሚያ ደንቦችን አፅድቀው ወደ ስራ በማስገባት ለቀጣናዊ ትስስር የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ከተቋሙ ያገኘው መረጃ ያመለክታል። 47ኛው የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብስባ እስከ ነገ ይቆያል። ከምክር ቤቱ ስብሰባ ጎን ለጎን ሐምሌ 7 ቀን 2017 ዓ.ም የህብረቱ የ7ተኛ የመንፈቅ ዓመት የባለድርሻ አካላት የትብብር ስብሰባ ይደረጋል። #Ethiopian_News_Agency #Ethiopia #ኢትዮጵያ #ኢዜአ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቪየትናም ዋና ከተማ ሃኖይ አዲስ የመንገደኞች በረራ ጀመረ
Jul 10, 2025 63
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 3/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቪየትናም ዋና ከተማ ሃኖይ አዲስ የመንገደኞች በረራ ጀምሯል። በማስጀመሪያ መርሀግብሩ የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ ደንጌ ቦሩ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው የአየር መንገዱ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የቪየትናም የንግድ ተቋማት ተወካዮች ታድመዋል። አየር መንገዱ በሳምንት አራት ጊዜ የመንገደኞች በረራ የሚያደርግ መሆኑ ተገልጿል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው በዚሁ ወቅት እንዳሉት በረራው የሀገራቱን ግንኙነት የሚያጎለብት ነው። ይህ አዲስ መስመር በኢትዮጵያ እና ቪየትናም መካከል ያለውን የንግድ፣ ቱሪዝም እና የባህል ልውውጥ የሚያሳድግ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ እንዲሁም በአፍሪካ እና በደቡብ ምሥራቅ እስያ መካከል ቀጥተኛ ትስስር እንዲኖር በማድረግ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ስትራቴጂካዊ መስፋፋት በማጠናከር ዓለም አቀፍ ግንኙነትን የሚያጎለብት መሆኑን ተናግረዋል። የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ ደንጌ ቦሩ፥ አየር መንገዱ የስኬት ማሳያ የሆነ ተቋም መሆኑን ገልጸዋል። አየር መንገዱ እንደ ሀገር የተያዙ ኢኮኖሚያዊ እቅዶች እንዲሳኩ የራሱን አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን አንስተዋል። በረራው የሀገራቱን ግንኙነት በጉልህ የሚያሳድግ መሆኑን ተናግረዋል። በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመካከለኛው ምስራቅ እስያ እና ፓስፊክ ሀገራት ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል ደዋኖ ከድር በበኩላቸው አየር መንገዱ ለዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ጉልህ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ገልጸዋል። በሁለቱ ሀገራት መካከል የተጀመረው በረራ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጠቀሜታ እንዳለው አመላክተዋል።
የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ ባለፉት ሁለት ዓመታት አበረታች ተግባር አከናውኗል
Jul 10, 2025 64
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 3/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ ባለፉት ሁለት ዓመታት አበረታች ተግባር ማከናወኑን የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥ እና የኢትዮጵያ ተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ የቦርድ ሊቀ መንበር ሰለሞን ደስታ ገለጹ። የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ ግንዛቤን ለማሳደግ ያለመ ወርክሾፕ ተካሂዷል። የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥ አቶ ሰለሞን ደስታ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት የሀገሪቱ የፋይናንስ ስርዓት ጤናማ፣ ለአደጋ ያልተጋለጠና የተረጋጋ እንዲሆን ፈንዱ የበኩሉን ሚና ይጫወታል፡፡ ለገንዘብ አስቀማጮች ተገቢውን ጥበቃ በማድረግ ለፋይናንስ ሥርዓቱ መረጋጋት የላቀ አስተዋጽዖ ከማበርከት ባለፈ የሀገሪቱን የፋይናንስ ዘርፍ ለማረጋጋት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸዋል። ፈንዱ ከተመሠረተበት ጊዜ አንስቶ በርካታ ሥራዎችን በማቀድ የተጣለበትን ኃላፊነት በተሟላ እና በሚፈለገው ደረጃ እየተወጣ ይገኛል ነው ያሉት። ባለፉት ሁለት ዓመታት አረቦን በመሰብሰብ ረገድ አበረታች ስራ መስራቱንም ተናግረዋል። የአባል ተቋማት ቁጥር 86 መድረሱን ተናግረው 32 ባንኮችና እና 54 ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት አባል መሆናቸውን ጠቅሰዋል። ገንዘብ አስቀማጮች እና ባለድርሻ አካላት ስለፈንዱ በቂ ግንዛቤና ዕውቀት እንዲኖራቸው መሰል መድረኮችን በማጠናከር ግንዘቤን ማስፋት እንደሚገባም ነው ያስታወቁት። የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ደሳለኝ አምባው (ዶ/ር) በበኩላቸው ፈንዱ በአጭር ጊዜ ውስጥ በርካታ ሥራዎችን በማከናወን አመርቂ ውጤቶችን ማስመዝገቡን ተናግረዋል። ፈንዱን በማደራጀት እና ለሥራ የሚያስፈልጉ የሰው ኃይል እና ሌሎች ግብዓቶችን በማሟላት ረገድ አበረታች ሥራ መስራቱን ጠቅሰዋል። በዚህም ፈንዱ ባለፉት ሁለት ዓመታት ከአባል የፋይናንስ ተቋማት 13 ነጥብ 84 ቢሊዮን ብር መነሻ እና ዓመታዊ አረቦን መሰብሰቡን ገልጸው፥ የመንግሥት ግምጃ ቤት ሰነድ ላይ ኢንቨስት በማድረግም ትርፍ እያስመዘገበ መሆኑን ጠቁመዋል። ፈንዱ በቀጣይ የአረቦን የመሰብሰብ አቅሙን እንደሚያሳድግ፣ አገልግሎቱን በቴክኖሎጂ እንደሚያዘመን እና ግንዛቤ የመፍጠር ሥራን እንደሚያጠናክር ተናግረዋል። ፈንዱ በንግድ ባንኮችም ሆነ በአነስተኛ ፋይናንስ ተቋማት ገንዘብ ለሚቆጥበው ወይም ለሚያስቀምጠው ማኅብረሰብ ዋስትና የሚሰጥ ሲሆን፣ በባንኮች ላይ ወይም ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ላይ አደጋ ቢያጋጥም፣ አስቀማጮች ካሳ የሚያገኙበት ስርዓት ነው።
የቁማ መስኖ ፕሮጀክት ለአገልግሎት መብቃት ዓመቱን ሙሉ ማምረት እንደሚያስችላቸው የሐመር ወረዳ አርብቶ አደሮች ተናገሩ
Jul 10, 2025 64
ሐመር፤ ሐምሌ 3/2017(ኢዜአ)፦ የቁማ መስኖ ፕሮጀክት ለአገልግሎት መብቃት ዓመቱን ሙሉ በማምረት ኢኮኖሚያ ተጠቃሚነታቸውን እንደሚያሳድገው የሐመር ወረዳ አርብቶ አደሮች ገለጹ። ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ መንግስት የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በሰጠው ትኩረት የመስኖ ልማት አውታሮችን የማስፋፋት ስራዎች ተከናውነዋል። ይህም አርሶ አደሮች ወቅት ሳይጠብቁ በማምረት የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸው እንዲያድግ ማገዙን የሐመር ወረዳ አርብቶ አደሮች ገልጸዋል። ለአብነትም ከ13 ዓመታት በላይ ሲጓተት የነበረው የቁማ መስኖ ፕሮጀክትን ወደ አገልግሎት በማስገባት የአርብቶ አደሩን የግብርና ሥራን ለማጠናከር ጉልህ ፋይዳ እያበረከተ ይገኛል። በ2004 ዓ.ም የግንባታ ሥራው የተጀመረው ይህ የመስኖ አውታር በተያዘለት ጊዜ ባለመጠናቀቁ የህብረተሰቡ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ሆኖ መቆየቱን ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት ችግሩ ተፈትቶ ወደ ልማት መግባታቸው ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን እንደሚያሳድገው ከተናገሩት አርብቶ አደሮች መካከል የሐመር ወረዳ የካራ-ቆርጮ ቀበሌ ነዋሪ አቶ አይላ ኩሌምፖና ወጣት ሙላ ፓርኮ የይገኙበታል። በመስኖ ፕሮጀክቱም በቆሎና ማሽላ በኩታ ገጠም እያለሙ እንደሚገኙ ገልጸዋል። የቁማ መስኖ ፕሮጀክት ክረምት ከበጋ በማምረት የምግብ ዋስትናቸውን ለማረጋገጥ እንዳገዛቸው የተናገሩት ደግሞ በወረዳው የአንጉዴ ቀበሌ ነዋሪ ወይዘሮ ጋዲ ሙጋ ናቸው። የሐመር ወረዳ መስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ቃላ ቦና በበኩላቸው የቁማ መስኖ ፕሮጀክት ከ13 ዓመታት በላይ ሲጓተት መቆየቱን አንስተዋል። ፕሮጀክቱ መጓተቱ በአካባቢው አርብቶ አደሮች ዘንድ የቅሬታ ምንጭ ሆኖ መቆየቱን ጠቅሰው፣ መንግስት ችግሩን ለመፍታት ትኩረት ሰጥቶ በመንቀሳቀሱ የፕሮጀክቱ ግንባታ ተጠናቆ ለአገልግሎት በቅቷል ብለዋል። ፕሮጀክቱ 500 ሄክታር መሬት ማልማት እንደሚያስችል የተናገሩት ደግሞ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ቢሮ የቱርሚ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት አስተባባሪ አቶ ያዘው አፈወርቅ ናቸው። የአርብቶ አደሩን የአኗኗር ሥርአት ለመቀየር እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፣ 79 ሄክታር መሬት በመስኖ የማልማት ሥራ መጀመሩን ጠቁመዋል። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ኤካል ነትር በበኩላቸው የቁማ መስኖ የአካባቢውን አርብቶ አደር ከኋላ ቀር የአስተራረስ ዘዴ በማላቀቅ በዘመናዊ እርሻ እንዲሳተፉ ዕድል ይፈጥራል ብለዋል። በቀጣይም የቁማ መስኖ ፕሮጀክት ውሀውን ከወንዙ ስቦ ለማውጣት የሚጠቀመውን የነዳጅ ፍጆታ ወደ ኤሌክትሪክ እና ወደ ሶላር የኃይል በመለወጥ በአካባቢው የመስኖ ልማቱን ለማስፋፋት እየተሰራ መሆኑንም አክለዋል። በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል 238 አነስተኛና መካከለኛ የመስኖ ተቋማት የሚገኙ ሲሆን ከ32ሺህ ሄክታር በላይ መሬትም በመስኖ እየለማ ይገኛል። በመስኖ አውታሮቹም ከ50ሺህ በላይ እማወራና አባውራዎች ተጠቃሚ መሆናቸውን ከቢሮው የተገኘው መረጃ ያሳያል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
በዞኑ በዲጂታላይዜሽን የታገዘ አገልግሎት ለማህበረሰቡ በመስጠት የተገልጋይን እርካታ ለማረጋገጥ ትኩረት ተደርጓል
Jul 10, 2025 48
ደብረ ብርሃን ፤ ሐምሌ 3/2017(ኢዜአ)፦በሰሜን ሸዋ ዞን በዲጂታላይዜሽን የታገዘ ቀልጣፋና ፍትሃዊ አገልግሎት ለማህበረሰቡ በመስጠት የተገልጋይን እርካታ ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ። የሰሜን ሸዋ ዞን የከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ በከተሞች የኮሪደር ልማትና በዲጂታላይዜሽን አተገባበር ላይ ዛሬ ከባለድርሻ አካላት ጋር መክሯል። የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መካሻ ዓለማየሁ በውይይቱ ላይ እንደገለጹት በከተሞች ተአማኒነት ያለው አገልግሎት ለመስጠት ዲጂታላይዜሽን የአሰራር ሥርአት እየተዘረጋ ነው። የዲጂታል አሰራሩ በየደረጃው ያሉ የሲቪል ሰርቪስ ሠራተኞች ለተገልጋዩ ማህበረሰብ ግልጽና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጡ ከማድረግ ባለፈ ብልሹ አሰራርን ለማስወገድ ያግዛል ብለዋል። በአዲሱ በጀት ዓመት በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የተገልጋይን እርካታ ለመፍጠር ከሚሰራው ሥራ በተጨማሪ በከተሞችና በገጠር አካባቢዎች የኮሪደር ልማትን በማስጀመር የህብረተሰቡን አኗኗር ለማዘመን ትኩረት እንደሚሰጥም አስገንዝበዋል። የዞኑ ከተሞችና የገጠር አካባቢዎች ለማዘመን በሚሰራው ሥራም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሊወጡ እንደሚገባም አስተዳዳሪው አሳስበዋል። በዞኑ የከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ሃላፊ አቶ ብርቃብርቅ ተሾመ በበኩላቸው እንዳሉት ከተሞችን ለኑሮ፣ ለኢንቨስትመንትና ለቱሪዝም ምቹ ለማድረግ የኮሪደር ልማትን ጨምሮ የተለያዩ የልማት ተግባራት እየተከናወኑ ነው። ለዚህም በዞኑ ሥር ባለችው የሸዋ ሮቢት ከተማ የኮሪደር ልማት ግንባታ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ተጀምሮ እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰዋል። በተጨማሪም ቡልጋ፣ አረርቲና ለሚ ከተሞችን ጨምሮ በዞኑ ሥር ባሉ ዘጠኝ ከተሞች የኮሪደር ልማት ስራን ለማስጀመር የሚያስችል የጥናት ሥራ ተጠናቋል ብለዋል። የአረርቲ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽህፈት ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ መሳይ አስታጥቄ በከተማው የኮሪደር ልማት ሥራን ለመጀመር የሚያስችል ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል። ልማቱንና የህብረተሰቡን ተሳትፎ በማስመልከት ከከተማዋ ነዋሪዎች ጋር በስፋት ውይይት ተደርጎ የጋራ መግባባት ላይ መደረሱንም ጠቁመዋል። የእንሳሮ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አከበረኝ ዓለሙ በበኩላቸው እንደገለጹት ከሀገራዊ ለውጡ በፊት ተረስተው የቆዩ ከተሞች አሁን ላይ ትኩረት እያገኙ መሆናቸውን አስረድተዋል። ለዚህም የለሚ ከተማ በኢንቨስትመንት እያደገች መምጣቷ አንዱ ማሳያ ነው ያሉት አቶ አከበረኝ፣ በአዲሱ በጀት ዓመት በከተማው የኮሪደር ልማትና የዲጂታላይዜሽን አሰራርን ለመጀመር ዝግጅት መደረጉን ጠቅስዋል። በውይይቱ ላይ የዞን፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደር አመራሮች እንዲሁም ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
የአፍሪካ የሥራ ዕድል ፈጠራ ፎረም እርስ በእርስ ለመማማር እና ምርቶቻችንን ለማስተዋወቅ እድል ፈጥሮልናል- አፍሪካውያን ስራ ፈጣሪ ወጣቶች
Jul 10, 2025 58
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 3/2017(ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት የተካሄደው ሶስተኛው የአፍሪካ የሥራ ዕድል ፈጠራ ፎረም እርስ በእርስ ለመማማርና ምርቶቻቸውን ለማስተዋወቅ ምቹ እድል እንደፈጠረላቸው አፍሪካውያን ስራ ፈጣሪ ወጣቶች ተናገሩ። ላለፉት ሶስት ቀናት በአዲስ አበባ ሲካሄድ የቆየው 3ኛው የአፍሪካ የሥራ ዕድል ፈጠራ ፎረም ትናንት ተጠናቋል። ከፎረሙ በተጓዳኝ በተዘጋጀው ኤግዚቢሽን ላይ ምርቶቻቸውን ያቀረቡ አፍሪካውያን ስራ ፈጣሪ ወጣቶች ለኢዜአ እንዳሉት ፎረሙ ትስስርን ለመፍጠርና ምርቶቻቸውን በተሻለ መንገድ መስራት የሚችሉበት ግብዓት ያገኙበት ነው። ከኡጋንዳ የመጣችው የኢማሮ ኢኖቬሽን መስራች ካይክራ ባርብራ እንዳለችው በግብርና ምርቶች ላይ እሴት በመጨመር ወደገበያ እያቀረበች ትገኛለች። በኢትዮጵያ በተካሄደው የሶስተኛው አፍሪካ የስራ እድል ፈጠራ ፎረም መሳተፏ ትስስርን በመፍጠር የምርት ጥራትን ለማሻሻል እንደሚያስችላት ገልፃለች። ከዚምባብዌ የመጣችው የማጅስቲክ አፍሪካ ዳይሬክተር ጌትሩድ ቻምባቲ በበኩሏ በግብርና ምርት ማቀነባበር ላይ ተሰማርታ ምርቶችን ለገበያ እያቀረበች መሆኑን ተናግራለች። የአፍሪካ የሥራ ዕድል ፈጠራ ፎረም ከገበያ ትስስር ባለፈ እርስ በእርስ ለመማማር እድል የፈጠራና ምርቶችን ለማስተዋወቅ ያስቻላት መሆኑንም ገልፃለች። ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑን የገለጹት ተሳታፊዎቹ፤ አገሪቱ በፈጣን እድገት ላይ መሆኗን መመልከታቸውንም ተናግረዋል። በኢትዮጵያ ለወጣቶች ስራ እድል ፈጠራ ምቹ የሆኑ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን አስተውለናልም ብለዋል፡፡
በማዘጋጃ ቤቱ የተጀመረው ዘመናዊ አሰራር መጉላላትን አስቀርቶልናል - የሆሳዕና ከተማ ነዋሪዎች
Jul 10, 2025 67
ሆሳዕና፤ ሐምሌ 3/2017(ኢዜአ)፦ በሆሳዕና ከተማ ማዘጋጃ ቤት በአንድ ማዕከል አገልግሎት የተጀመረው ዘመናዊ አሰራር ሲገጥማቸው የነበረውን መጉላላት እንዳስቀረላቸው ነዋሪዎች ገለጹ። የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ በበኩሉ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን የተገልጋይ እርካታን ለማምጣት የተጀመረው ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል። የሆሳዕና ከተማ ነዋሪ አቶ ሰላሙ አኒቶ ለኢዜአ እንደገለጹት፣ ከዚህ ቀደም በከተማው ማዘጋጃ ቤት ሲሰጥ የነበረው አገልግሎት ያልዘመነ በመሆኑ የተለያዩ ችግሮች ይገጥማቸው እንደነበር አስታውሰዋል። ቀደም ሲል የመረጃ አያያዙ በወረቀት ብቻ ያተኮረ በመሆኑ የፋይል መጥፋትን ጨምሮ የተለያዩ ችግሮች እየተከሰቱ ጉዳያቸውን ለማስፈጸም መጉላላት ይደርስባቸው እንደነበር ተናግረዋል። መረጃውን ለማፈላለግ በሚባክነው ጊዜና ጉልበት ነዋሪዎች ለእንግልትና ለሙስና ሲዳረጉ መቆየታቸውንም እንዲሁ። በአሁኑ ወቅት በከተማው በቴክኖሎጂ ታግዞ የተጀመረው የአንድ ማዕከል አገልግሎት ከሰው ንክኪ ውጭ መሆኑ ቀልጣፋ አገልግሎት ማግኘት ከማስቻሉ ባለፈ ይገጥማቸው የነበረን እንግልት እንዳስቀረላቸው ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም አገልግሎት ፈልጎ ወደ ማዘጋጃ ቤቱ የሚመጣ ነዋሪ የራሱን ማህደር እንኳ ለማግኘት መጉላላት ይገጥመው እንደነበር ያስታወሱት ሌላዋ የከተማዋ ነዋሪ ወይዘሮ ክብነሽ ሶዲሶ ናቸው። በአግባቡ የተሰደረ የመረጃ አያያዝ ስላልነበረ ጉዳይ ለማስፈጸም ለበርካታ ጊዜ በመመላለስ እንጉላላ ነበር ያሉት ነዋሪዋ፣ ለቅሬታቸው በቂ መልስ የሚሰጥ ሰው ባለመኖሩም ጉዳይን ከሙስና ውጭ ለማስጨረስ ይቸገሩ እንደነበር አስታውሰዋል። ማዘጋጃ ቤቱ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዲጂታል የታገዘ ዘመናዊ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ፈጣንና ተገቢ አገልግሎት ለማግኘት እንዳስቻላቸው ተናግረዋል። ጉዳያቸውን በአጭር ጊዜ መፈጸማቸውን ተናግረው፣ የመልካም አስተዳደር ችግርን በመፍታት የተጀመረው ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲጠናከርም ጠይቀዋል። በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማና ኢንደስትሪ ክላስተር አስተባባሪና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ ስንታየሁ ወልደሚካኤል ለኢዜአ እንደገለጹት፣ በክልሉ በማዘጋጃ ቤት ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለማረም ትኩረት ተሰጥቷል፡፡ በዚህም አገልግሎት አሰጣጡን የማዘመን ሥራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፣ በዚህም የሆሳዕና ከተማን ጨምሮ በክልሉ አራት ከተሞች ሙሉ በመሉ በዲጂታል የታገዘ አገልግሎት እንዲሰጡ መደረጉንና ተስፋ ሰጪ ውጤት መታየቱን ተናግረዋል። የአገልግሎት አሰጣጡ መዘመኑ ከዚህ ቀደም በተገልጋዮች ላይ ይደርስ የነበረን እንግልትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች መፍታት እንዳስቻለም ገልጸዋል። የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎትን በማዘመን የተገልጋዩን እንግልት ለመቀነስ የተጀመረው ሥራ በቀጣይም በክልሉ የተለያዩ ከተሞች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አቶ ስንታየሁ አስታውቀዋል፡፡ ዘንድሮ በክልሉ በ16 ከተሞች ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን ለህብረተሰቡ ፍትሀዊና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እየተሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡ በተለይም መሬትና መሬት ነክ አገልግሎት፣ የግንባታ ፍቃድ እንዲሁም ከልዩ ልዩ አገልግሎት የሚሰበሰብ ክፍያና መሰል አገልግሎቶችን ዲጂታላይዝድ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ነው ያስረዱት።
ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ ዘርፍ እያከናወነች ያለው ተግባር አስደናቂ ነው -የአፍሪካ የስራ ፈጠራ ፎረም ተሳታፊ ሚኒስትሮች
Jul 9, 2025 116
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 2/2017(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እድገቷን ለማፋጥን በቴክኖሎጂ ዘርፍ እያከናወነች ያለው ተግባር አስደናቂና ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ልምድ የሚወሰድበት መሆኑን በ3ኛው የአፍሪካ የስራ ፈጠራ ፎረም ተሳታፊ የሆኑ ሚኒስትሮችና የስራ ሃላፊዎች ገለጹ፡፡ የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው 3ኛው የአፍሪካ የስራ ፈጠራ ፎረም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል። በመድረኩ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ ሚኒስትሮች፣ ዲፕሎማቶች፣ የዘርፉ ምሁራን፣ ተመራማሪዎች፣ ሥራ ፈጣሪዎች እና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡ ተሳታፊዎቹ ትናንት ከሰዓት በኋላ የአድዋ ድል መታሰቢያን፣ ሳይንስ ሙዚየምንና የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋማትን ጎብኝተዋል። በጉብኝቱ ወቅት አስተያየታቸውን ከሰጡን መካከል የጋና የሠራተኛ፣ ሥራና የሥራ ስምሪት ሚኒስትር አብዱል-ራሺድ ፔልፑዎ ፤ አዲስ አበባ በፈጣን እድገት ላይ መሆኗን መመልከታቸውን ተናግረዋል። የመሰረተ ልማት ግንባታዎቹ የከተማዋን እድገት የሚያፋጥኑ መሆናቸውን ገልጸው፤ ኢትዮጵያ እድገቷን ለማፋጠን የጀመረቻቸው ተግባራት ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም ምሳሌ ናቸው ብለዋል። የደቡብ ሱዳን የሰራተኞች ጉዳይ ሚኒስትር ጀነራል ጄምስ ሆት ማይ በበኩላቸው በሳይንስ ሙዚየም ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ ዘርፍ እያከናወነች ያለውን ስራ መመልከታቸውን ነው የተናገሩት። የተመለከቷቸው ስራዎች ኢትዮጵያ ምርታማነትን ይበልጥ ለማሳደግ ዘመናዊ እርሻ ላይ ያላትን ዕቅድ የሚያሳዩ ናቸው ብለዋል። ኢትዮጵያ የጀመረቻቸው ተግባራት በአፍሪካ ከምግብ ዋስትና ጋር ተያይዘው የሚነሱ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችሉ መሆናቸውን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ሀገራት ተሞክሮ የሚሆን የልማት ስራ እያከናወነች እንደምትገኝ የገለጹት ደግሞ በማላዊ የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን ልማት ላይ የሚሰራ ድርጅት የቦርድ ሰብሳቢ ቦንፊስካ ዛሚራ ናቸው። በሳይንስ ሙዚየም በተመለከቱት ስራ መደነቃቸውን የገለጹት ቦንፊስካ፤ ተግባራቱ ኢትዮጵያን በዘርፉ ከአፍሪካ ቀዳሚ ሀገር ያደርጋታል ብለዋል።
ስፖርት
ቱኒዚያ እና አልጄሪያ ነጥብ ተጋርተዋል
Jul 10, 2025 46
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 3/2017(ኢዜአ)፦ በ13ኛው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ሶስት ጨዋታ ቱኒዚያ እና አልጄሪያ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል። ጨዋታው ማምሻውን በበፔሬ ጄጎ ስታዲየም ተካሄዷል። አልጄሪያ በኳስ ቁጥጥር እና የግብ እድል በመፍጠር የነበራትን ብልጫ ወደ ውጤት መቀየር አልቻለችም። መርሃ ግብሩ በአፍሪካ ዋንጫው ምንም ግብ ያልተቆጠረበት የመጀመሪያው ጨዋታ ሆኗል። ውጤቱን ተከትሎ አልጄሪያ በአራት ነጥብ ምድቡን እየመራች ነው። ቱኒዚያ በአንድ ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዛለች። በምድብ ሶስት ቦትስዋና ከናይጄሪያ ምሽት 4 ሰዓት ላይ በላርቢ ዛውሊ ስታዲየም ይጫወታሉ። የዘጠኝ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊዋ ናይጄሪያ በሶስት ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች። ካሸነፈች የምድቡን መሪነት ከአልጄሪያ ትረክባለች። ያለ ምንም ነጥብ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ የያዘችው ቦትስዋና የመጀመሪያ ድሏን ለማስመዝገብ ትጫወታለች።
በሴቶች አፍሪካ ዋንጫ የምድብ ሁለት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ
Jul 10, 2025 60
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 3/2017(ኢዜአ)፦ በ13ኛው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ሁለት ሁለተኛ መርሃ ግብር ዛሬ ይደረጋል። ቱኒዚያ እና አልጄሪያ ከምሽቱ 1 ሰዓት ላይ በፔሬ ጄጎ ስታዲየም ይጫወታሉ። ቱኒዚያ በመጀመሪያ ጨዋታዋ በናይጄሪያ 3 ለ 0 ስትሸነፍ አልጄሪያ ቦትስዋናን 1 ለ 0 ረታለች። ማሸነፍ ቱኒዚያ በውድድሩ የመቆየት እድሏን እንዲሰፋ ያደርጋል። አልጄሪያ ካሸነፈች ሩብ ፍጻሜ ትገባለች። የሰሜን አፍሪካ ሀገራቱ ከዚህ ቀደም 11 ጊዜ ተገናኝተው አልጄሪያ 6 ጊዜ በማሸነፍ ብልጫውን ወስዳለች። ቱኒዚያ 2 ጊዜ ስታሸንፍ 3 ጊዜ ደግሞ አቻ ተለያይተዋል። አልጄሪያ በጨዋታዎቹ 21 ግቦችን ስታስቆጥር ቱኒዚያ 14 ግቦችን ከመረብ ላይ አሳርፋለች። የምድብ ሁለት ሌላኛው ጨዋታ ምሽት 4 ሰዓት ላይ በላርቢ ዛውሊ ስታዲየም ናይጄሪያ እና ቦትስዋናን ያገናኛል። የዘጠኝ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊዋ ናይጄሪያ በመጀመሪያ የምድብ ጨዋታዋ ቱኒዚያን 3 ለ 0 በመርታት ምድቡን እየመራች ነው። በአልጄሪያ የ1 ለ 0 ሽንፈት ያስተናገደችው ቦትስዋና ያለ ምንም ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። ናይጄሪያ ካሸነፈች ወደ ሩብ ፍጻሜ የሚያስገባትን ትኬት ትቆርጣለች። ቦትስዋና በምድቡ የመጀመሪያ ድሏን ለማስመዝገብ ትጫወታለች። ሁለቱ ሀገራት እ.አ.አ በ2022 ሞሮኮ ባዘጋጀችው 12ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በምድብ ሶስት ተገናኝተው ናይጄሪያ 2 ለ 0 ማሸነፏ የሚታወስ ነው። በሞሮኮ አስተናጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው 13ኛው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ ዛሬ ስድስተኛ ቀኑን ይዟል።
ፒኤስጂ ሪያል ማድሪድን በማሸነፍ ለፍጻሜ አልፏል
Jul 10, 2025 77
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 3/2017(ኢዜአ)፦ በፊፋ ክለቦች ዓለም ዋንጫ ሁለተኛ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ፒኤስጂ ሪያል ማድሪድን 4 ለ 0 በሆነ የሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል። ትናንት ማምሻውን በሜትላይፍ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ፋቢያን ሩዊዝ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ኡስማን ዴምቤሌ እና ጎንዛሎ ራሞስ ቀሪዎቹን ጎሎች ለፈረንሳዩ ቡድን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። የመጀመሪያዎቹ ሁለት ግቦች የተቆጠሩት የሪያል ማድሪድ ተከላካዮች በሰሩት ስህተት ነው። በጨዋታው ፒኤስጂ በጨዋታው በሪያል ማድሪድ ላይ ከፍተኛ ብልጫ የወሰደ ሲሆን ተጨማሪ ግቦችን ማስቆጠር ይችል ነበር። የሪያል ማድሪዱ ግብ ጠባቂ ቲቦ ኮርቶዋ ያዳናቸው ያለቀላቸው ኳሶች ቡድኑ በሰፊ ጎል እንዳይሸነፍ አድርጎታል። ሁለቱ ግቦችን ያስቆጠረው ፋቢያን ሩዊዝ የጨዋታው ኮከብ ሆኖ ተመርጧል። የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊው ፒኤስጂ ለፍጻሜ አልፏል። በፍጻሜው ከቼልሲ ጋር ይጫወታል። የፍጻሜው ጨዋታ እሁድ ሐምሌ 6 ቀን 2017 ዓ.ም በሜትላይፍ ስታዲየም ይደረጋል። የፓሪሱ ክለብ በውድድር ዓመቱ አምስተኛ ዋንጫውን ለማንሳት ይፋለማል። የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ የክለቦቹ ባስ መንገድ ላይ በገጠመው የትራፊክ መጨናነቅ 10 ደቂቃ ዘግይቶ መጀመሩ አስገራሚ ሆኗል። ለባለንዶር ሽልማት የታጨው ኡስማን ዴምቤሌ በውድድር ዓመቱ ያስቆጠራቸውን ግቦች ወደ 35 ከፍ አድርጓል። ሪያል ማድሪድ ዓመቱን ያለ ዋንጫ አጠናቋል።
አዘጋጅ ሀገር ሞሮኮ የመጀመሪያ ድሏን አስመዝግባለች
Jul 10, 2025 59
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 3/2017(ኢዜአ)፦ በ13ኛው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ አንድ መርሃ ግብር ሞሮኮ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን 4 ለ 2 አሸንፋለች። ትናንት ማምሻውን በፕሪንስ ሙላይ አብደላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አምበሏ ጊዝላኔ ቼባክ ሶስት ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ ሰርታለች። በውድድሩ ሀትሪክ የሰራች የመጀመሪያ ተጫዋች ሆናለች። በውድድሩ ያስቆጠረቻቸውን ግቦች ወደ አራት ከፍ አድርጋለች። ያስሚን ምራቤት ለሞሮኮ ቀሪዋን ጎል በፍጹም ቅጣት ምት አስቆጥራለች። ሜርቬል ናንጉጂ እና ፍላቪን ማዌቴ ለዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። ሞሮኮ በጨዋታው በኳስ ቁጥጥር ከፍተኛ ብልጫ የወሰደች ሲሆን የተሻለ የግብ እድልም ፈጥራለች። ውጤቱን ተከትሎ አዘጋጇ ሀገር ሞሮኮ የመጀመሪያ ድሏን አስመዝግባለች። በአራት ነጥብ ደረጃዋን ከሶስተኛ ወደ ሁለተኛ ከፍ አድርጋለች። በምድቡ ሁለተኛ ሽንፈቷን ያስተናገደችው ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ያለ ምንም ነጥብ የመጨረሻው አራተኛ ደረጃ ያዛለች። በዚሁ ምድብ በተደረገው ሌላኛው ጨዋታ ዛምቢያ ሴኔጋልን 3 ለ 2 አሸንፋለች። ዛምቢያ ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ሞሮኮ ከሴኔጋል የምድብ አንድ የመጨረሻ ጨዋታዎች ናቸው።
አካባቢ ጥበቃ
ከአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ተጠቃሚነታችንን ለማሳደግ የችግኝ ተከላና እንክብካቤ ተሳትፏችንን እናጠናክራለን-የቸሃ ወረዳ ነዋሪዎች
Jul 10, 2025 53
ወልቂጤ፤ ሐምሌ 3/2017 (ኢዜአ)፦ከአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ የችግኝ ተከላና እንክብካቤ ተሳትፏቸውን እንደሚያጠናክሩ በጉራጌ ዞን የቸሃ ወረዳ ነዋሪዎች ገለጹ። በጉራጌ ዞን "በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ሃሳብ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ዛሬ በቸሃ ወረዳ ጆካ ቀበሌ ተጀምሯል። ከቀበሌው ነዋሪዎች መካከል አርሶ አደር ወርቅነሽ መንጅየ እንዳሉት፤ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የአካባቢ ስነምህዳርን እና የአፈር ለምነት በመመለስ ዘርፈ ብዙ ጥቅም እያስገኘላቸው ነው። በልማቱ እያገኙት ያለውን ጥቅም ለማሳደግ ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን በመንከባከብ ሥራውም ተሳትፏቸውን እንደሚያጠናክሩ ገልጸዋል። በተያዘው የክረምት ወቅት ለምግብነትና ለደን አገልግሎት የሚውሉ ችግኞችን መትከል ጀምረናል ያሉት አርሶ አደሯ፣ መርሃ ግብሩ ተፈጥሮን በመጠበቅና በመንከባከብ ምቹ የመኖሪያ አካባቢን ለመፍጠር ማስቻሉን ገልጸዋል። ችግኞችን መትከል ብቻ ሳይሆነ ተንከባክበን ለውጤት የማብቃት ልምድን አዳብረናል ያሉት ሌላኛው አርሶ አደር በሃሩ ፍቃዱ ፣ ከልማቱ ተጠቃሚነታቸው እያደገ በመሆኑ ዘንድሮም በችግኝ ተከላው በንቃት በመሳተፍ አሻራቸውን እያኖሩ መሆናቸውን ተናግረዋል። ደን የመንከባከብ እና ችግኞችን የመትከል ልምድ ቀደም ብሎ በአካባቢያቸው እንዳለ አስታውሰው፣ ይህን ተግባር በአረንጓዴ አሻራ መርሀግብርም አጠናክረው መቀጠላቸውን ገልጸዋል። የቸሃ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጥላሁን ሽምንሳ በበኩላቸው በወረዳው ባለፉት ዓመታት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በተተከሉ ችግኞች የአፈር ለምነት መመለሱንና ምርትና ምርታማነት መጨመሩን ተናግረዋል። በማህበረሰቡ ዘንድ ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን ተንከባክቦ የማሳደጉ ባህል እየዳበረ መምጣቱን ጠቁመው፣ የሚተከሉ ችግኞች የጽድቀት መጠንም ከ85 ከመቶ በላይ ደርሷል ብለዋል። በተያዘው የክረምት ወቅት የተለያየ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ተከላ መጀመሩን ገልጸው፣ ችግኞችን ከሰውና ከእንስሳት ንኪክ ነጻ አድርጎ ለማሳደግ ህብረተሰቡን ያሳተፈ ስራ ይሰራል ብለዋል። የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና መምሪያ ሃላፊ አቶ አበራ ወንድሙ በበኩላቸው እንዳሉት በዞኑ በአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር ከ37 ሺህ ሄክታር በሚበልጥ መሬት ላይ ችግኝ ይተከላል። በአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር የቀጣይ ትውልድን ጭምር ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አስረድተዋል። ከሚተከሉት ችግኞች ውስጥ ቡና፣ አቮካዶ፣ ሙዝ፣ ማንጎ፣ ፓፓያ እና አፕልን ጨምሮ ሌሎች ለምግብነት የሚውሉና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ይገኙበታል ብለዋል። የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ በጉራጌ ተፈጥሮን የመንከባከብና የመጠበቅ ባህል እንዳለ ገልጸው ይህም የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን አጠናክሮ ለማስቀጠል አስችሏል ብለዋል፡፡ ቀደም ሲል በአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር የተከናወኑ ሥራዎች የተራቆቱ መሬቶች መልሰው እንዲያገገሙ ማድረጋቸውን ገልጸው፣ ይህም ለዜጎች የስራ እድል እንዲፈጠርና ሃገር በቀል ዛፎች ዳግም እንዲያሰራሩ እያገዘ መሆኑን አስረድተዋል
የባህር ዳር ከተማን ጽዱና አረንጓዴ ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ-አቶ ጎሹ እንዳላማው
Jul 10, 2025 46
ባህር ዳር፤ሐምሌ 3/2017(ኢዜአ)፦የባህር ዳር ከተማን ጽዱና አረንጓዴ ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ጎሹ እንዳላማው ገለጹ። የከተማዋ አካባቢ ጥበቃ፣ጽዳትና ውበት ጽህፈት ቤት በ2017 በጀት ዓመት ያከናወናቸው የተግባር አፈጻጸም ግምገማና የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ተውውቅ መድረክ ዛሬ በባህር ዳር ከተማ ተካሂዷል። የባህር ዳር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ጎሹ እንዳላማው በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፥ከተማዋን የበለጠ ውብና ማራኪ ለማድረግ የኮሪደር ልማትን ጨምሮ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ። ከተማዋን ውብ፣ጽዱና ማራኪ በማድረግ የኢንቨስትመንት፣የቱሪዝምና የንግድ እንቅስቃሴ ማዕከል ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም አስረድተዋል። ለዚህም በከተማዋ አካባቢ ጥበቃ፣ጽዳትና ውበት ጽህፈት ቤት አዳዲስ የከተማዋን አካባቢዎች በማልማትና በመንከባከብ ውጤታማ ሥራ መከናወኑን በማሳያነት ጠቅሰዋል። በባህር ዳር ከተማ እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማትና የአረንጓዴ ልማት ሥራዎች ከተማዋ ለነዋሪው የበለጠ ምቹ እንድትሆን ማድረጉን የገለጹት ደግሞ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ሥራ አስኪያጅ አቶ ተሻገር አዳሙ ናቸው። እየተገነቡ ያሉ የአረንጓዴ ልማትና የኮሪደር ልማት ሥራዎች ባህር ዳር ከተማ ካሏት ሰፋፊ የአስፋልት መንገዶችና ሌሎች መሰረተ ልማቶች ጋር ተዳምሮ ከተማዋን ለነዋሪዎች፣ ለቱሪስትና ለኢንቨስትመንት ተመራጭ አድርጓታል ብለዋል። በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር የአካባቢ ጥበቃ ጽዳትና ውበት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ጽጌረዳ አበበ በበኩላቸው፥ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በባለሙያውና በአመራሩ ቅንጅት የከተማዋን የተፈጥሮ ጸጋ አጉልቶ ለማሳየት ተችሏል ብለዋል። በበጀት ዓመቱ የተገኘውን ተሞክሮ በማስፋትና ጉድለቶችን በማረም በቀጣይ 90 ቀናትና በአዲሱ በጀት ዓመት ከዚህ የበለጠ ለማከናወን ታቅዷል ብለዋል። በተለይም በአካባቢ ጥበቃ ላይ የወጡ ህጎችን በመፈጸምና በማስፈጸም በከተማዋ ከጣና ሐይቅና ዓባይ ወንዝ ጋር የተጣጣመ የአረንጓዴ ልማት ሥራዎች እንደሚከናወኑ አስረድተዋል። በመድረኩ የከተማዋ አመራሮች፣ የጽህፈት ቤቱ አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አስደናቂ ልማት እያከናወነች ነው - ዓለም አቀፍ የልማት አጋሮች
Jul 10, 2025 58
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 3/2017(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አስደናቂ የአካባቢ ጥብቃ ልማት እያከናወነች መሆኗን ዓለም አቀፍ የልማት አጋሮች ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የዘንድሮውን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር "በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ሃሳብ ሰኔ 20 ቀን 2017 ዓ.ም በይፋ አስጀምረዋል፡፡ በዚህም 7 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል በማቀድ በመላ ሀገሪቱ የችግኝ ተከላ እየተከናወነ ይገኛል። የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት አመራሮችና ሰራተኞች ከተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኤጀንሲ ተወካዮችና ሌሎች የልማት አጋሮች ጋር በመሆን በጉለሌ የእጽዋት ማዕከል አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ረዳት ተወካይ ዴቪድ ካርፕ፤ የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር የሚያስደንቅ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ ከተመድ የስደተኞች ጉዳይ ሃላፊዎችና ሰራተኞች ጋር በመሆን አረንጓዴ አሻራቸውን ማኖራቸውን ጠቅሰው፥ በቀጣይም ተሳትፏቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል፡፡ በኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ የምግብ ፕሮግራም ምክትል ዳይሬክተር ኬቪን ሆጅሶን በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለአየር ንብረት ለውጥ የምትሰጠው ተፈጥሯዊ ምላሽ የሚደነቅ ነው ብለዋል፡፡ በችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በመሳተፋቸው ደስታ እንደተሰማቸው ጠቁመው፤ በቀጣይም ተሳትፏቸውን እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡ የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሙሉዓለም ደስታ በበኩላቸው፤ አገልግሎቱ በመላ ሀገሪቱ የስደተኞች የመጠለያ ጣቢያዎች በሚገኙባቸው ሥፍራዎች የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። ችግኞችን ከመትከል ባሻገር እንዲጸድቁ ተከታታይ እንክብካቤዎችን እያደረገ እንደሚገኝም ገልጸዋል። የችግኝ ተከላና የእንክብካቤ ስራን ጎን ለጎን በማስኬድ የተተከሉ ዕጽዋት ለፍሬ እንዲበቁ ማድረግ እንደሚገባ የገለጹት በስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት የሴቶችና ህጻናት ቡድን መሪ ምስራቅ መሐመድ ናቸው፡፡
የድሬደዋ አስተዳደር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን ከአጎራባች ክልሎች ጋር ለማከናወን ይሰራል
Jul 10, 2025 51
ድሬደዋ፣ሐምሌ 3/2017(ኢዜአ)፡-የድሬደዋ አስተዳደር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን ከአጎራባች ክልሎች ጋር ለማከናወን እየሰራ መሆኑን የአስተዳደሩ ግብርና ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ አስታወቀ። አስተዳደሩ በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተለያዩ ችግኞች ለተጎራባች ክልሎችና ዞኖች እንደሚያሰራጭ ተገልጿል። የድሬዳዋ አስተዳደር ግብርና፣ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መሐመድ አሚን ዑመር ለኢዜአ እንዳስታወቁት፤ ከተማ አስተዳደሩ ከምስራቅ ተጎራባች ክልሎች ለሰላምና ለሁለንተናዊ ልማት በጋራ እየሰሩ ናቸው። ይህን እንቅስቃሴ በአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ይበልጥ ለማጠናከር በተሰሩ ስራዎች አበረታች ውጤቶች ተገኝተዋል ብለዋል። በተለይም ከምስራቅ ሐረርጌ ወረዳዎች እና ከሶማሌ ክልል ሲቲ ዞን ጋር በመተባበር ለድሬደዋ ከተማ የጎርፍ አደጋ መነሻ የሆኑትን የተራቆቱ ተፋሰሶች በችግኞች የማልበስ ስራ እየተከናወነ መሆኑን አስታውቀዋል። ይህን ለማጠናከርም ከቀናት በኋላ በድሬዳዋ የሚጀመረው የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ ላይ በጋራ እንደሚሳተፉ ተናግረዋል። የአስተዳደሩ የአካባቢ፣የደንና አየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን የደን ልማት ዳይሬክተር አቶ ማስረሻ ይመር በበኩላቸው በዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻ ለሶማሌ ክልል ሲቲ ዞን እና ለምስራቅ ሐረርጌ ዞን ወረዳዎች ችግኞች ይሰራጫሉ ብለዋል። ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአፋር ክልልም የተለያዩ ችግኞች ለመስጠት ዝግጅት መደረጉንም አክለዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
በህንድ የአውሮፕላን አደጋ የ204 ዜጎች ህይወት አልፏል- የሕንድ ፖሊስ
Jun 12, 2025 821
አዲስ አበባ፤ሰኔ 5/2017 (ኢዜአ)፦በህንድ የአውሮፕላን አደጋ የ204 ዜጎች ህይወት ማለፉን የሀገሪቷ ፖሊስ አስታወቀ። በሕንድ 242 መንገደኞችን ይዞ በህንድ ሰሜን ምዕራባዊ ክፍል አህመዳባድ ከተማ ከሚገኘው አውሮፕላን ማረፊያ ወደ ለንደን ጋትዊክ ለማምራት በተነሳበት ቅፅበት በአካባቢው በሚገኝ ሆስፒታል የህክምና ባለሙያዎች ማረፊያ ላይ ተከስክሷል። በቦይንግ 787-8 ድሪምላይነር አውሮፕላን ውስጥ 169 ህንዳውያን፣ 53 የብሪታኒያ ዜጎች፣ 7 ፖርቹጋላዊ እና አንድ ካናዳዊ ነበሩ። በአደጋው የተረፈ ሰው ለማግኘት የሚቻልበት እድል እጅጉን የጠበበ ነው ሲል የአህመዳባድ ፖሊስ ኃላፊ ለአሶሲዬትድ ፕሬስ ገልጾ ነበር። ይሁንና ማምሻውን በወጣ መረጃ የ40 ዓመት የህንድ እና ብሪታኒያዊ ጥምር ዜግነት ያለው ቪሽዋሽ ኩማር ራሜሽ ከአደጋው መትረፉ ተጠቁሟል። እስከ አሁን የ204 ሰዎች አስክሬን ተገኝቷል። የአውሮፕላኑ አካል የህክምና ባለሙያዎች ማረፊያ ላይ ወድቆ ቢያንስ አምስት የህክምና ተማሪዎች መሞታቸውን እና 50 ገደማ የሚሆኑት መጎዳታቸው ተገልጿል። የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት የሀዘን መግለጫ መልዕክት አደጋው ቃል ከሚገልጸው በላይ ልብ የሚሰብር ነው ሲሉ ገልጸዋል። በአደጋው ለተጎዱ በሙሉ ልባዊ ሀዘናቸውን በመግለጽ መጽናናትን ተመኝተዋል።
ኮሚሽኑ በአፍሪካ ሰላምና ደህንነት ማስፈን ዋንኛ የትኩረት አቅጣጫው አድርጎ ይሰራል- መሐሙድ አሊ ዩሱፍ
May 12, 2025 1265
አዲስ አበባ፤ግንቦት 4/2017(ኢዜአ)፡- የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን አዲሱ አስተዳደር በአፍሪካ ሰላምና ደህንነት ማስፈን ዋንኛ የፖሊሲ የትኩረት አቅጣጫው በማድረግ እንደሚሰራ የኮሚሽኑ ሊቀ-መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን አዲሱ ሊቀ-መንበር መሐመድ አሊ ዩሱፍ ከሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ጋር ዛሬ ትውውቅ እና ቆይታ አድርገዋል። ሊቀ-መንበሩ በስልጣን ጊዜያቸው ሊያሳኳቸው ስላቀዷቸው ተቋማዊ ግቦችና ቅድሚያ ሰጥተው ለመፈጸም ያሳቧቸውን ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች አስመልክቶ ገለጻ አድርገዋል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን አዲሱ አስተዳደር በሰላም፣ ደህንነት፣ ልማትና ዓለም አቀፍ ትብብር ላይ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ገልጸዋል። መሐመድ አሊ ዩሱፍ ሰላምና ደህንነት የኮሚሽኑ ዋንኛ የትኩረት ማዕከል መሆኑን አመልክተዋል። ኢ-ሕገ መንግስታዊ የመንግስት ለውጦች በአፍሪካ መረጋጋት ላይ ከፍተኛ ስጋት መደቀናቸውን ተናግረዋል። የአፍሪካ ህብረት መሰል ችግሮችን በመፍታት እንዲሁም ሰላምን በማስፈንና የዴሞክራሲ ስርዓትን በማረጋገጥ የህብረቱ አባል ሀገራትን ሉዓላዊነት እና ደህንነት መጠበቅ ላይ አበክሮ ይሰራል ነው ያሉት። ሊቀ-መንበሩ በገለጻቸው ኮሚሽኑ በዓለም አቀፍ መድረክ የአፍሪካን ድምጽ የበለጠ ለማጉላት እንደሚሻ ገልጸዋል። በዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ ውስጥ የአፍሪካ ህብረትን ሚና ማጠናከር ቁልፍ ግብ መሆኑን ጠቅሰው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ላይ ማሻሻያ እንዲደረግበት በጽኑ ሁኔታ እንደሚሟገት አመልክተዋል። ሊቀ-መንበሩ የፀጥታው ምክር ቤት አሁናዊ መዋቅር የታሪክ ኢ-ፍትሃዊነት በማለት የገለጹት ሲሆን አፍሪካ በዓለም አስተዳደር የሚገባትን ትክክለኛ ስፍራ በሚገልጽ ሁኔታ ምክር ቤቱ ማሻሻያ ሊደርግበት ይገባል ሲሉም ተናግረዋል። በሌላ በኩል በዲጂታል ኢኮኖሚና ሰው ሰራሽ አስተውሎት አማካኝነት በአፍሪካ ፈጠራ እና ዘላቂ ልማትን ማሳለጥ ሌላው የትኩረት አቅጣጫ ነው ብለዋል። የህብረቱ ኮሚሽን ከቀጣናዊ ኢኮኖሚ ማህበረሰቦች ጋር ያለውን ትብብር የበለጠ በማጠናከር ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር ወጥነት ባለው መልኩ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ሊቀ-መንበሩ በአፍሪካ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል አማካኝነት ወረርሽኝን የመከላከል ዝግጁነት እና ምላሽ አቅም ላይ ከፍተኛ ለውጥ መምጣቱንም አንስተዋል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን አዲሱ ሊቀ-መንበር መሐመድ አሊ ዩሱፍ በቀጣይ ከሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ጋር በየሶስት ወር ጊዜ ቆይታ እንደሚያደርጉ ለማወቅ ተችሏል። በየካቲት ወር 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ በተካሄደው 38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ መሐመድ አሊ ዩሱፍ ሙሳ ፋቂ ማህማትን በመተካት የኮሚሽኑ ሊቀ-መንበር ሆነው መመረጣቸው የሚታወስ ነው።
ኢትዮጵያ በባንጁል ቻርተር እና በማፑቶ ፕሮቶኮል ያላትን የአፈጻጸም ሪፖርቶች ማቅረብ ጀመረች
May 10, 2025 936
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 2/2017(ኢዜአ)፦ በፍትህ ሚኒስትር ዴኤታ በላይሁን ይርጋ የተመራ የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን በአፍሪካ የሰዎችና ህዝቦች መብቶች ቻርተር ስብሰባ ላይ እየተሳተፈ ነው። በጋምቢያ ባንጁል የአፍሪካ የሰዎችና ህዝቦች መብቶች ኮሚሽን ዋና መሥሪያ ቤት እየተካሔደ ባለው ስብሰባ ላይ በአፍሪካ የሰዎችና ህዝቦች መብቶች ቻርተር (ባንጁል ቻርተር) ወቅታዊ የኢትዮጵያ አፈጻፀምና በአፍሪካ የሴቶች መብቶች ፕሮቶኮል (ማፑቶ ፕሮቶኮል) መነሻ ወቅታዊ አፈጻፀም ላይ ልኡኩ ሪፖርቶችን ማቅረብ ጀምሯል። ሚኒስትር ዴኤታው ለኢዜአ እንደገለጹት ኢትዮጵያ በሪፖርት ዘመኑ በቻርተሩና ፕሮቶኮሉ መሰረት ያሉባትን ግዴታዎች ለመወጣትና የሰብአዊ መብቶችን ከማስጠበቅ አንጻር የተወሰዱ የፖሊሲ፣ የህግ እና ተቋማዊ እርምጃዎችን የሚመለከቱ ለውጦች ሪፖርት በዝርዝር ቀርቧል። በኮሚሽኑ መርሃ-ግብር መሰረትም ሪፖርቱን ተከትሎ ከኮሚሽነሮች ለተነሱ ጥያቄዎች ኢትዮጵያ በልዑካን ቡድኑ አማካኝነት ሰኞ ግንቦት 4 ቀን 2017 ምላሾችን ትሰጣለች ተብሎ እንደሚጠበቅም ሚኒስትር ዴኤታው ጠቁመዋል። መድረኩ ኢትዮጵያ በባንጁል ቻርተር እና በማፑቶ ፕሮቶኮል ስምምነቶች መሰረት በአገሪቱ የሰብዓዊ መብቶችን እና የፆታ እኩልነትን ለማጎልበት ያላትን ቁርጠኝነት የምታሳይበት እንደሆነም ተገልጿል።
በቱርኪዬ ኢስታንቡል በሬክተር ስኬል 6 ነጥብ 2 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ
Apr 23, 2025 1560
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 15/2017(ኢዜአ)፦በዛሬው እለት በቱርኪዬ ኢስታንቡል በሬክተር ስኬል 6 ነጥብ 2 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል። እንደ አናዶሉ የዜና ወኪል ዘገባ ዛሬ ቀትር ላይ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ የኢስታንቡል እና ጎረቤት አካባቢ ነዋሪዎች በፍርሃት የመኖሪያ ህንጻቸውን ለቀው እንዲወጡ አድርጓቸዋል። በሌላም በኩል ረፋዱ ላይ በኢስታምቡል አቅራቢያ የባህር ዳርቻ ቡዩኪክሚ የተባለ ስፍራ ላይ በሬክተር ስኬል 4 ነጥብ 9 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን አናዶሉ የዜና ወኪል የሃገሪቱን የድንገተኛ አደጋ መቆጣጠር ባለስልጣን ጠቅሶ ዘግቧል። በአደጋው ምንም የተመዘገበ ጉዳት እንዳልተከሰተ የጠቀሰው ዘገባው ነዋሪዎች የዚህ ዓይነት አጠራጣሪ ሁኔታ ሲገጥም የተጎዱ ሕንጻዎች ውስጥ እንዳይገቡ የግድ አስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር ተሽከርካሪዎችን እንዳይጠቀሙና ሌሎች የጥንቃቄ መልዕክቶችን ባለስልጣኑ ማስተላለፉም ተገልጿል። የሃገሪቱ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በቅርበት እየተከታተሉ መሆናቸውንና ለዜጎችም መልካም ሁኔታ እንዲገጥማቸው መመኘታቸው ተገልጿል። ፕሬዝዳንቱ ከሃገሪቱ የድንገተኛ አደጋ መቆጣጠር ባለስልጣንና ከሚመለከታቸው አካላት መረጃዎችን በመቀበል በቅርበት እየተከታተሉ እንደሚገኙም ተገልጿል።
ሐተታዎች
የህንድ የፈጠራ ማዕከል - ባንጋሎሩ
Jul 2, 2025 346
ቤተልሄም ባህሩ(ኢዜአ) የዴልሂና አግራ ቆይታችንን ጨርሰን ወደ ቀጣይ መዳረሻችን ባንጋሎሩ ከተማ ልንጓዝ ስንሰናዳ አብዛኛው የጋዜጠኛ ልዑክ ያሳሰበው እንደሰም የምታቀልጠውን የአግራ ፀሀይና ሙቀት በባንጋሎሩም ታገኘን ይሆን? የሚለው ነበር። ሆኖም ከዴልሂ ኢንድራ ጋንዲ አየር ማረፊያ ተነስተን ለሶስት ሰዓት ከተቃረበ በረራ በኋላ ያገኘናት ባንጋሎሩ የተለየች ሆነን አገኘናት። ባንጋሎሩ ቀዝቀዝ ባለ አየር ነበር እንግዶቿን የተቀበለችን። በዕለቱ ከክፍሎቻችን ወጥተን በጋራ ወደአየር ማረፊያ የሚወስደንን ትራንስፖርት ስንጠባበቅ ከጋዜጠኛ ቡድኑ ስድስት አባላት ከአጠገባችን እንዳልነበሩ አስተዋልን። የት ጋር እንደተነጣጠልን አላስታውስም። በዚህ ምክንያት ግን የእለቱ ጉዟችን ተሰርዞ ከተማዋን ለማየት ስንዘዋወር የማውቀው ዓይነት እንጂ የተለየ ሙቀት አላስተናገድኩም። የ13 ወር ፀጋ በመባል የምትታወቀው አገሬ ኢትዮጵያ ከዳሎል እስከ ራስ ዳሽን ባላት የመልከዓ ምድር አቀማመጥና ልዩ ልዩ የአየር ጠባይ ሙቀቱንም፣ ቅዝቃዜውንም ማወቃችን እንደዚህ ለአለ አጋጣሚ መልካም ስሜት ይፈጥራል። በተወሰነ ደረጃ በህንድ ያጋጠመኝ የአየር ባህሪ ከአገሬ ጋር ቢመሳሰልብኝ የፈጣሪንና የተፈጥሮን ስራ አጃኢብ ብዬ እንዳልፍ አድርጎኛል። ባንጋሎሩ ከተማ የቴክኖሎጂና ፈጠራ ማዕከል በመሆኗ የህንድ ሲልከን ቫሊ በመባል ትታወቃለች። ሃይማኖታዊና ታሪካዊ ስፍራዎችም ከመገለጫዎቿ መካከል ናቸው። የጠፈር ጠበብቶቹ - ባንጋሎሩ ደርሰን በመጀመሪያ ያየነው ዓለም በስፔስ ሳይንስ እየሰራች ያለችውና እያስመዘገበችው የምትገኘው ውጤት ማሳያ የሆነውን የህንድ ስፔስ ምርምር ድርጅትን ነው። ተቋሙ የህንድ መንግስት የስፔስ ዲፓርትመንት አካል ሲሆን፤ ዶክተር ቪክራም ሳራብሃይ በተሰኙ ባለራዕይ በ1962 የተወጠነና አሁን ላይ በዘርፉ ተገዳዳሪ መሆን የቻለ ነው። የተቋሙ ዓላማ የስፔስ ቴክኖሎጂዎችን በማልማትና በመተግበር ለተለያዩ አገራዊ ጥቅሞች ማዋል መሆኑን ተከትሎ የሳተላይት ማምጠቂያ መሳሪያዎችን የማምረት ስራን ጨምሮ ከአገሩ አልፎ ለሌሎች አገራትም በዘርፉ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል። የተደረገልን ገለፃ አብዛኛውን ጋዜጠኛ ያስደመመ ነበር ከገለፃ በኋላ በጋዜጠኞች የተነሳው ሃሳብም ህንድ በስፔስ ዘርፍ ያላት ልምድና ያከናወነችው ተግባር በቀጣይም ልትሰራ የወጠነቻቸው ሃሳቦች የአገሪቱን መዳረሻ የተለሙ በአገራቸው እንዲተገበር የሚናፍቁት መሆኑን ነው። ተቋሙ በዘርፉ ለተሰማሩ ኢትዮጵያዊያን የአቅም ግንባታ ድጋፍ እያደረገ መሆኑንና በቀጣይም ትብብሩን የሚያጠናክር መሆኑን ከተደረገልን ገለፃ ተገንዝበናል። በሳይንስ፣ ኢንጂነሪንግና አስተዳደር ምሁራንን በማስተማር እያበረከተ ያለው የህንድ የሳይንስ ኢንስቲትዩት በባንጋሎሩ ከጎበኘናቸው መካከል የሚጠቀስ ነው። ኢንስቲትዩቱ ከአፍሪካ የተውጣጡ ተማሪዎችን የሚያስተምርና ከተቋማት ጋርም በዘርፉ የሚሰራ ሲሆን፤ በኢትዮጵያም ከጅማ፣ በተግባር ለመቀየር ሲታትሩ የስታርት አፖችን የምርት ውጤቶቻቸውን ሲፈትሹና ሲሞክሩ ተመልክቻለሁ። በኢትዮጵያም አሁን ላይ ለስታርት አፖች በተሰጠው ትኩረትና በተፈጠረው ምቹ ስነ ምህዳር የፈጠራ ውጤቶች እያደጉና እየተበራከቱ መሆናቸው የሚታወቅ ነው። እንደ አዳማና አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ያሉ ተቋማት የተማሪዎችን ፈጠራ ወደ ውጤት ለመቀየር እየተጉ መሆኑና የስታርት አፕ ኤግዚቢሽንና የሰመር ቡት ካምፖች ፈጠራን ምን ያህል እያበራከቱ መሆናቸው በጉብኝቱ ወቅት ወደ አዕምሮዬ የመጣ የአገሬው ህዝብ በውጤት የታጀበ ጥረት ነው። ከአራት አስርት ዓመታት በላይ በባዩቴክኖሎጂ ዘርፍ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ የሚገኘው ባዮኮንም ከባላንጎሩ የጉብኝት መዳረሻችን መካከል የሆነና አስፈላጊ መድሀኒቶችን የሚያመርትና በዘርፉ ያሉ ባለሙያዎች አቅም ግንባታ ላይም እየሰራ ያለ ነው። ኢትዮጵያን ጨምሮ የአፍሪካ አገራት የአቅም ግንባታ ስልጠናው ተጠቃሚ ናቸው። ከ120 በላይ በሆኑ አገራት ለስኳርና ካንሰር ህመም የሚያገለገሉ መድሀኒቶችን በማምረትና በማሰራጨት ለህሙማን ፈውስና ለጤናው ዘርፍ ስርዓት አስተዋፅኦ እያበረከተም ይገኛል። የተቋሙ ላቦራቶሪና ዘመኑን የዋጀና ደረጃውን የጠበቀ ማምረቻ ፋብሪካን መጎብኘቴ አለም በፋርማሲዩቲካልስ ዘርፍ ያለችበትን ሁኔታ የሚያሳይ ነው። የባንጋሎሩ ቤተመንግስት - ይህን ቤተ መንግስት ማስቃኘቴን ከመጀመሬ በፊት በስፍራው ካስገረመኝ ነገር ላወጋችሁ ወደድኩ። ቤተ መንግስቱን ለመጎብኘት ያቀናነው በእለተ ሰኞ ነበር። ሆኖም ምድረ ግቢውን ቃኝተን ስለህንፃው ሰምተን ከመመለስ ውጪ ወደ ውስጥ አልዘለቅንም። ለምን? ለሚለው ምላሹ በዚህ ስፍራ "ሰኞ የእረፍት ቀን ናት" ነው። እንዴት ካላችሁ ቤተ መንግስቱ ቅዳሜና እሁድ በበርካታ ሰዎች የሚጎበኝ መሆኑን ተከትሎ በስፍራው ለሚሰሩ ሰራተኞች የእረፍት ቀናቸው ሰኞ በመሆኑ ነው። የቤተ መንግስቱ ምድረ ግቢ ሰፊና ልምላሜ የተላበሰ ሲሆን፤ የሚያምርና ለዓይን የሚስብ ኪነ ህንፃ ያለው ነው። አሰራሩና ውጥኑም እንደሚከተለው ነው። በዎዲየር ስርወ መንግስት ንጉስ ቻማራጃ ዋዲያር ወደ እንግሊዝ ባደረጉት ጉዞ በለንደን ዊንሶር ግንብ ይደነቃል። ተደንቆም አልቀረ የባንጋሎሩ ቤተ መንግስትን በተመሳሳይ ሁኔታ ይገነባል። ይህ ቤተ መንግስት በተወሰነ መልኩ የመካከለኛው ዘመን የኖርማንሲና የእንግሊዝ ግንቦችን ይመስላል። ቪድሃና ሶውዳ የካራንታካ ህግ አውጪ አካል መናገሻ በጉብኝታችን ያየነው ሌላው መዳረሻ ስፍራችን ነው። የህግ አውጪና የህግ መወሰኛ ምክር ቤት የያዘው ይህ ህንፃ ህንድ ነፃነቷን ካገኘች በኋላ በራሷ መሀንዲስ የሰራችው የመጀመሪያው ህንፃ መሆኑ ተገልፆልናል። የህንፃ ግንባታ ጥበብ ማሳያ፣ የፖለቲካ መናገሻ እንዲሁም የባህል ማሳያ ተደርጎም ይወሰዳል። እንደአጠቃላይ በቆይታዬ የተመለከትኩት የመሰረተ ልማት ግንባታ፣ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ፈጠራ ማበረታቻ እንዲሁም የአረንጓዴ ልማት ስራ ኢትዮጵያ እያከናወነች ካለው የኮሪደር ልማትና ስታርት አፕን የማበረታታት ብሎም የሳይንስና ቴክኖሎጂ ስነ ምህዳር ምቹነት ስራዎች ጋር ተመሳሳይነት ያለው መሆኑን ነው። በህንድና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ግንኙነት ዘመናትን የተሻገረ፤ ለሁለት ሺህ ዓመታት የዘለቀ መሆኑን የታሪክ መዛግብት ያሳያል። የህንድና ኢትዮጵያ ግንኙነት በአክሱም ስርወ መንግስት ኢትዮጵያና ህንድ በአዱሊስ ወደብ በኩል የንግድ ልውውጥ ሲያደርጉ እንደነበር የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ። በወቅቱ ኢትዮጵያ ቅመማ ቅመምና ሐርን ከህንድ ትገበይ ነበር። ህንድ ደግሞ ወርቅና የዝሆን ጥርስን ከኢትዮጵያ ትሸምት ነበር። ህንድ ከንግድ ልውውጥ ባሻገር በኢትዮጵያ ኪነ ህንፃ ግንባታ ላይ አሻራዋን አኑራለች። በኢትዮጵያ በትምህርት ዘርፍም ትልቅ አበርክቶ ያላት አገር ናት። ህንድ ነፃነቷን ካገኘችበት እኤአ 1948 አንስቶ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩት ኢትዮጵያና ህንድ ሌላው የሚያመሳስላቸው ነገር ሆኖ ያገኘሁት የአምራች ዘርፉን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ እያከናወኑ ያሉት ንቅናቄ ነው። ህንድ እ.አ.አ ከ2014 ጀምሮ የአምራች ዘርፉን ለማበረታታት "ሜድ ኢን ኢንዲያ" በሚል ለአስር ዓመት የተገበረችውና በርካታ ለውጥ የተመዘገበበት ንቅናቄ በኢትዮጵያ ከ2014ዓ.ም ጀምሮ እየተተገበረ ካለውና የሃገር በቀል ምርቶች እና አምራቾችን ማጠናከር፣ የኢንዱስትሪያል ማህበረሰብ ግንባታን ማሳደግ ፣ ምቹ የቢዝነስ ከባቢ መፍጠር እና የጥናት እና ምርምር ችግር ፈቺነትን ማሳደግን ዓላማ ካደረገው የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ጋር የተመሳሰለ ነው። ንቅናቄ በኢትዮጵያ መተግበሩ ዓመታዊ የዘርፍ ዕድገት፣ የማምረት አቅም አጠቃቀምና ገቢ ምርት በመተካት በኩል ጉልህ ሚና እየተወጣ መሆኑም ይታወቃል። በህንድ ተዘዋውሬ በተመለከትካቸው ከተማዎች ባሉ ጎዳናዎች ከታዘብኩት ነገር ሰዎች ከሱቅ ለሚገበያዩት ነገር ሳይቀር በዲጂታል መንገድ ክፍያ መፈፀማቸውን ነው። በባጃጅና በሞተር የትራንስፖርት አገልግሎት ለማግኘትም ጭምር ሞባይሉን በመጠቀም “ይህ ቦታ የት ነው?” ሳይል ያሻዎት ስፍራ መድረስም ሌላው ትዝብቴ ነው። ይህ ነገር በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ትኩረት አግኝተው እየተሰራባቸው ካሉት የዲጂታል ክፍያና ዲጂታል ክህሎት ማሳደጊያ መርሃ ግብር ጋር የሚመሳሰል ሆኖ አግኝቼዋለሁ። በቆይታችን ልክ እንደአትሌቶቻችን ሁሉ በዓለም አደባባይ የኢትዮጵያን ስም ከፍ አድርጎ የሚያስነሳውን ኢትዮጵያ አየር መንገድ ዝናና ክብር ለማስተዋል ችያለሁ። ፀጉረ ልውጥ መሆናችንን የተገነዘቡ በገበያ ማዕከላት የሚያገኙን እንዲሁም በምንጎበኛቸው ተቋማት የምንተዋወቃቸው ህንዳውያን "ከየት ናችሁ?" ብለው ሲጠይቁ፤ ለእኔና አንድ ከሌላ መገናኛ ብዙሃን የሄድን "ከኢትዮጵያዊ" ስንል የሚከተልልን ምላሽ "አሃ የኢትዮጵያ አየር መንገድ" የሚል ነው። ይህም አየር መንገዱ ስሙ ከኢትዮጵያ ተሰናስሎ የሚጠራ የአገሪቷ መታወቂያ ተቋም መሆኑን ያስገነዘበኝ ነው። ከህንዳውያን ጋር ብቻ ሳይሆን አብረን ከተጓዝን ጋዜጠኞች አንዱ "የኢትዮጵያ አየር መንገድ የእናንተ የብቻ ሳይሆን እኛንም እንደራሳችን ሆኖ እያገለገለን ያለ የጋራ አየር መንገዳችን ነው" ሲል ነው የገለፀው። ይሄ ለእኔ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአገር ኩራት ብቻ ሳይሆን መለያ ምልክትም ጭምር መሆኑን የተረዳሁበት አጋጣሚ ነው። በቀናት ቆይታዬ በእንግዳ አክባሪነታቸውና በለገሱን ፍቅርና እንክብካቤ ከአገሬ የራቅኩ ያህል ሳይሰማኝ ብቸኝነትን ሳላስተናግድ እንደውም እየናፈኳቸው እንድመለስ ላደረጉኝ ህንዳውያን በከበረ ሰላምታ ላመሰግን እወዳለሁ።
ውበትና ትጋት በህንድ
Jun 27, 2025 414
በቤተልሄም ባህሩ (ኢዜአ) በልጅነቴ እያየሁ ያደግኳቸው አብዛኛዎቹ ፊልሞች የህንድ ናቸው። ይህ ደግሞ ከአገራችን አርቲስቶች በላይ የህንድ የፊልም ተዋንያኑን ስም ለመለየት አስችሎኛል። የህፃንነት ዘመኔን የሚያስታውሱኝን ፊልሞች ከትዝታ ማህደሬ እያወጣሁ ከመተረክ በስተቀር ህንድን የማይበት አጋጣሚ ይኖራል ብዬ አስቤ አላውቅም። እነዚያን በህንድ ፊልም የማደንቃቸውን የምደመምባቸውን የህንዳውያንን ሶስት ከተሞች ለመጎብኘት ከተመረጡ ከሰሜንና ምስራቅ አፍሪካ የተውጣጡ ጋዜጠኞች መካከል መሆን ድንገቴ ሆነብኝ። እኔም ብቻ ሳይሆን አብዛኛዎቹ የጋዜጠኞች ልዑካን ህንድ ከልጅነት ትዝታቸው ጋር የተሳሰረ አንዳች ነገር አለው። ህንድ በፊልሞቿ የሚያቋት ስለመሆኑ ጉብኝቱን ተከትሎ በተካሄደው በዶርሻን የቴሌቪዥን ጣቢያ ውይይት ላይ ሲያነሱ ሰምቻለሁ። በዓለም ላይ በህዝብ ብዛቷ ቀዳሚዋ ህንድ የብዝሃ ባህል፣ ቋንቋና ሃይማኖት አገር ናት። በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኪነ ጥበብ ስራዎቿ በዓለም ላይ ትታወቃለች። ለጉብኝት ከተጋበዙት የጋዜጠኞች ቡድን መካከል አባል ሆኜ በዴልሂ፣ አግራና ባንጋሎሩ ከተሞች በተጓዝንባቸው ስፍራዎች ሁሉ የታዘብኩት ህንዳዊያን በስራና ትጋት ላይ መሆናቸውን ነው። ሁሉም ነገውን ለማሳመር የራሱን ድርሻ ለማኖር፤ ለሀገሩ እድገትና ልማት አሻራውን ለማኖር እንደሚታትር መረዳት ይቻላል። ባረፍንበት ሆቴል ያሉ ሰራተኞች፣ በገበያ ስፍራ የምናገኛቸው ሰዎች እንዲሁም በጎበኘናቸው ስፍራዎች ያሉ ሰዎች ሁሉ ለሀገራቸው እድገትና ልማት ብሎም ነጋቸውን ለማሳመር የራሳቸውን ድርሻ ለማኖር ይታትራሉ። አብሬ ከነበርኳቸው ጋዜጠኞች ጋር ስናወጋ የምናነሳው በከተማዋ በተጓዝንባቸው ጎዳናዎች የምናየው የመሰረተ ልማት ግንባታ፣ በየተቋማት የሚታትሩ ሰራተኞች እንዲሁም በንግድ የተሰማሩ ሰዎች ደፋ ቀና ማለት ለአገር የሚያደርጉትን ልፋት ነው። አንድ ቀን በጋራ ሆነን ወደገበያ ስፍራ ስናቀና በፍጥነት የሚደርሱ ምግቦች ተመግበው ለመሄድ የሚፋጠኑ ህንዳውያንን ያየ የጋዜጠኛ ቡድኑ አባል መሰል ልምድና ጊዜ አጠቃቀም በአፍሪካም ሊለመድ የሚገባውና የአህጉራችንን የስራ ባህልና እድገት የሚያረጋግጥ መሆኑን የገለጸበት ሁኔታ ለአገሬው ህዝብ ታታሪነት እንደማሳያ አድርጌ ላነሳው ወደድኩ። በሄድንባቸው አካባቢዎች ሁሉ አዲስ ሰው ሲያዩ ለማገዝ አና ስለነገሮች ለማስረዳት የሚፈጥኑ ዜጎችን ተመልክቻለሁ። በተጓዝኩባቸው ከተማዎች ያየኋቸውን ስፍራዎች ከማስታወሻዬ እየነቀስኩ ለእናንተ ላካፍል ወደድኩ። በቅድሚያ ከአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የስድስት ሰዓት ተኩል በረራ በማድረግ የመጀመሪያ መዳረሻ ያደረግናትን ዴልሂን እንቃኛለን። ዴልሂ- ታሪካዊ ህንፃዎችን ከአዲሶቹ ጋር አጣምራ የያዘች ጥንታዊ ስልጣኔን ከዘመናዊው ጋር አዋህዳ የምታንፀባርቅ ከተማ ናት። በከተማዋ በተዘዋወርንባቸው ስፍራዎች ሁሉ ከጎዳናዎቿ እስከ ህንፃዎቿ ምድረ ግቢ ድረስ በእፅዋት የተሞላችና ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ትኩረት የሰጠች መሆኗን በግልፅ ያሳየች ከተማ ናት። በዴልሂ ብቻም ሳይሆን በተዘዋወርንባቸው በሶስቱም ከተሞች ጎዳና ስንጓዝ ያየናቸው ግዙፍ ዛፎች ትናንት አገሪቷ ለእፅዋት የሰጠችው ትኩረት ዛሬ ላይ ፍሬ አፍርቶ አስተዋልኩ። ይህ ደግሞ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ባለፉት ዓመታት እየተከናወነ ያለው ተግባር እንዲሁም በኮሪደር ልማት ከተሞችን ፅዱና አረንጓዴ ለማድረግ የተጀመረው ጥረት አሁን ላይ ካመጡት ለውጥ ባለፈ ለወደፊት የሚኖራቸውንም መዳረሻ አሻግሬ ለማየት አስችሎኛል። አሰላሳዮቹ - በዴልሂ ቆይታችን በመጀመሪያ ያቀናነው ጥናቶችን በመስራትና ውይይቶችን በማድረግ በኩል አበርክቶ እያደረገ ያለውን ኦብዘርቨር ሪሰርች ፋውንዴሽን የተሰኘ አሰላሳይና ሃሳብ አመንጪዎች ቡድን (ቲንክ ታንክ ግሩፕ) ነው። ተቋሙ በአገር ውስጥ ባሉ የኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ በማተኮር የመስራት ተልዕኮን አንግቦ የተነሳ ቢሆንም አሁን ላይ ከኢኮኖሚና እድገት ባለፈ በኢነርጂ፣ አካባቢ፣ በደህንነትና ሌሎች ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ላይ በማተኮር ለፖሊሲ ግብዓት የሚሆኑና ለውሳኔ የሚጠቅሙ ሃሳቦችን በማመንጨት የአገሪቷን ህዝብና መንግስት እያገዘ ይገኛል። ከተቋሙ አባላት ጋር ባደረግነው ቆይታ ለራስ ችግር የራስ መፍትሄ ማምጣት ተገቢ ስለመሆኑ በአጽንኦት አንስተዋል። የአፍሪካ አገራት ትብብር የአህጉሪቷን ልዕልና ለማረጋገጥ ወሳኝ ጉዳይ መሆኑም ተነስቷል። የአሰላሳይና ሃሳብ አመንጪዎች ቡድን አባላቱ ጋር ያደረግነውን ቆይታ ጨርሰን በቀጣይ ያመራነው በህንድ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ ባሉ አገራት ጭምር በባቡር መንገድ መሰረተ ልማት ላይ አሻራ እያኖረ ወዳለው ራይትስ ወደተሰኘው ተቋም ነው። የህንድ የባቡር መንገድ የቴክኒካልና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት (Rail India Technical and Economic Service) የተሰኘው ይህ ተቋም ላለፉት 51 ዓመታት በባቡር መንገድ ጠበብቶች አማካኝነት በህንድና በመላው ዓለም ባሉ 62 አገራት በዘርፉ ሲሰራ ቆይቷል። የእጅ ጥበብ ገበያ - ቀጣይ መዳረሻችን ደግሞ ዲል ሃት ኢና የተሰኘው የባህላዊ አልባሳትና ጌጣጌጦች እንዲሁም የቤት ማስዋቢያዎች መገኛ ወደ ሆነው ገበያ ነው። ገበያው ባይገበዩበትም ዞረው እንዲቃኙ የሚያስገድድ አንዳች ድምቀትን የተላበሰ መሆኑን ባደረኩት ቆይታ አስተውያለሁ። የንግድ ማህበር የሆነው የህንድ ኢንዱስትሪ ኮንፌዴሬሽን (ሲአይ አይ) በዴልሂ ቆይታችን ካየናቸው ተቋማት መካከል የሚጠቀስ ነው። ተቋሙ የንግድ፣ ፖለቲካ፣ የትምህርትና የሲቪል ማህበረሰብ አመራር አባላትን በጋራ በማሰለፍ ዓለም አቀፍና የኢንዱስትሪ አጀንዳዎችን እንዲቀርፁ የሚሰራ ነው። አደጋን የሚቋቋም መሰረተ ልማት ጥምረት (CDRI) በነበረን ቆይታ ጥምረቱ ከአገራት፣ ከተባበሩት መንግስታት ኤጀንሲዎችና መርሃግብሮች፣ ከፋይናንስና የግል ተቋማት ጋር በመተባበር የአየር ንብረትና የአደጋ ስጋትን የሚቋቋም መሰረተ ልማት አስተዳደር ላይ እየሰራ መሆኑን ተገንዝበናል። ጥምረቱ የአደጋ ምላሽና መልሶ ማቋቋም፣ በተቋማትና ህብረተሰብ አቅም ግንባታ ድጋፍ ላይ ይሰራል። ጥምረቱ 46 አባል አገራትና ስምንት አጋር ድርጅቶች ያሉበት ሲሆን፤ አገራትና ዓለም አቀፍ አካላትን በማስተባበር የገንዘብና ቴክኒክ ድጋፍ የሚያደርግ የጥናትና ፈጠራዎች ውጤቶች እንዲሁም ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን የሚጋሩበትም ነው። የህንድ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዴልሂ(IIT Delhi) ሌላው የጉብኝት መዳረሻችን ነበር። ኢንስቲትዩቱ በኢንጂነሪንግና ሳይንስ ጨምሮ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በርካታ ሰዎችን አስተምሮ ያስመረቀ ሲሆን፤ የተለያዩ ሳይንቲስቶች፣ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎችና ስራ ፈጣሪዎችን ማፍራት የቻለ ተቋም መሆኑን መገንዘብ ችለናል። ብሄራዊ ሙዝየም - በኒው ዴልሂ የሚገኘው የህንድ ብሄራዊ ሙዚየም በአገሪቱ ያለ ትልቁ ሙዚየም ሲሆን፤ በጉብኝታችን ወቅት ለዘመናት የቆየች ቅሪተ አካልን ጨምሮ፣ የተለያዩ የጥበብ ውጤቶችና የታሪክ አሻራ ማሳያ ስራዎችን ቀርበው ይጎበኙበታል። በዴልሂ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተደረገልን የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባባልና ውይይት ህንድና አፍሪካ የጠነከረ ቁርኝት ያላቸውና በንግድ አጋርነትት በቀዳሚነት የሚጠቀሱ መሆኑ ተመላክቷል። በተደረገልን ገለፃ ህንድና የአፍሪካ የንግድ መጠን 100 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ነው። ህንድ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፣ ፋርማሲዩቲካል ፣ አውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪዎች ፣ ማዕድን እና የባንክ ዘርፎችን ያላት የአፍሪካ ኢንቨስትመንት ወደ 75 ቢሊዮን ዶላር ገደማ መድረሱም ተገልጿል። ኢትዮጵያም ከህንድ ጋር ለዘመናት የዘለቀ ወዳጅነት ያላትና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷም ረጅም ዓመታትን ያስቆጠረ መሆኑ ተነስቷል። ሁለቱ አገራት ያላቸው ግንኙነት በንግድና ኢንቨስትመንት ላይ ያተኮረ ብቻ ሳይሆን በባህል ትስስር ጭምርም የተጋመደ መሆኑ ተመላክቷል። ለወደፊቱም ኢትዮጵያን ጨምሮ ከአህጉሪቱ ካሉ አገራት ጋር የምታደርገው ትብብርና ወዳጅነት ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑም ተነስቷል። አግራ- የህንድ ታሪክ፣ ባህልና ኪነ ህንፃ መገለጫ በሆነችው አግራ ተገኝተን የጎበኘነው ህንድ ስትነሳ ስሙ ተያይዞ የሚነሳውን ታጅ መሃልን ነው። ታጅ መሃል በእምነ በረድ የተሰራ ውብ ኪነ ህንፃ ሲሆን፤ ንጉስ ሻህ ጃሃን ከሌሎች ሚስቶቹ ሁሉ አስበልጦ ለሚወዳት ሚስቱ ሙምታዝ መሀል ክብር ሲል የገነባው ድንቅ የእጅ ስራ ውጤት ነው። ታጅ መሃልን ስንጎበኝ የነበረው ሙቀት ሀይለኛ ቢሆንም ላባችን እየተንቆረቆረ ንጉሱ ለፋርስ ልዕልቷ ሚስቱ የነበረውን ፍቅር በተመለከተ በአስጎብኚያችን የሚሰጠንን ማብራሪያ ስናደምጥና የፍቅር ሃያልነትን ስናደንቅ ነበር። በዴልሂ ከጉብኝታችን ባሻገር በኢንዲያን ጌትና በገበያ ቦታዎች እንዲሁም በከተማዋ ጎዳናዎች ተዘዋውረን የህዝቡን ፍቅርና ተባባሪነት አይተናል። በተለይ ቦታ የጠፋን መሄድ ያሰብንበት ቦታ እንዳለ የሚያመላክት ፍንጭ በግርታችን ያስተዋሉ ከመሰላቸው "እዚህ መሄድ ፈልገህ ነው ይህን እዚህ ማግኘት ትችላለህ" የሚል ጥቁምታ በመስጠት እንግዳ ተቀባይነትና ሰው አክባሪነታቸውን ይገልፁልሃል። በዴልሂና አግራ የነበረንን ጉብኝትና ትዝታ እያሰላሰልን ቀጣይ መዳረሻ ያደረግናት ባንጋሎሩ ከተማን ነው። ባንጋሎሩ ቀጣይ ትረካችን ይሆናል።
ስራዋን በውጤታማነት በማስቀጠል ለሌሎች ወጣቶችም መትረፍ የቻለችው ወጣት
May 22, 2025 945
ብርሃኑ ፍቃዱ - ከሰቆጣ ኢዜአ በ2013 ዓ.ም የልብስ ስፌት ስራ የጀመረችው ወጣት ማህደር አስማረ፤ ነዋሪቷ በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ ሰቆጣ ከተማ ነው። ስራዋን በውጤታማነት የቀጠለችው ወጣት ከአንድ የልብስ ስፌት መኪና ተነስታ ወደ ሶስት የልብስ ስፌት መኪና የደረሰች ሲሆን ካፒታሏንም ከዓመት ዓመት በማሳደግ ላይ ትገኛለች። ስራዋን ለመጀመርም ባጠራቀመችው አነስተኛ ገንዘብ ቤት ተከራይታ ነበር። ከልብስ ስፌት መኪናው በተጨማሪ የሌዘርና የጥልፍ ማሽኖችን በማስመጣት የፋሽንና ዲዛይን ስራና ማሰልጠኛ ማዕከል በመክፈት ለሌሎች ወጣቶች መትረፍ የቻለችበትን አቅም ገንብታለች። የማሰልጠኛ ማዕከሉን ለመክፈት እስከ 500 ሺህ ብር ወጪ ማድረጓን የገለፀችው ወጣት ማህደር፤ 30 ተማሪዎችን ተቀብላ አጫጭር ስልጠና ለመስጠት የምዝገባና ሌሎች የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን አጠናቃለች። "ውጤታማ ለመሆን ጠንክሮ ከመስራት ውጪ ሴትነቴም ሆነ ሌላ ምንም የሚያግደኝ ነገር የለም" የምትለው ወጣት ማህደር ፤ የፋሽንና ዲዛይን ማሰልጠኛ ማዕከልን ከማስፋት ባለፈ በቀጣይ የጨርቃ ጨርቅ ማምረቻ ፋብሪካ ለመገንባት አቅዳ እየሰራች መሆኑን ገልፃለች። ወጣት መሰረት ጌታቸው በማህደር የልብስ ስፌትና የፋሽንና ዲዛይን ማሰልጠኛ ማዕከል ከባለፈው ዓመት ጀምሮ የስራ እድል ተጠቃሚ ሆናለች። ከድርጅቱ በቂ የልብስ ስፌት ሙያ፣ ልምድና እውቀት መቅሰሟንና ለዚህም ማህደር እውቀቷንና ልምዷን ሳትሰስት በማከፈሏ ብቁ ሰራተኛ እንድትሆን አድርጋታለች ። የማሰልጠኛ ማዕከሉ በከተማዋ መከፈቱ በተለይም ሴቶችና ወጣቶችን በዘርፉ ሰልጥነው የሙያ ባለቤት በመሆን ሰርተው የሚለወጡበት እድል የከፈተ ነው በማለት ትገልጻለች። ከወጣት ማህደር ጊዜን በአግባቡ መጠቀምና ጠንክሮ መስራትንና ቁርጠኝነትን ትምህርት ወስጃለሁ ያለችው ወጣት መሰረት ፤ በልብስ ስፌት ዘርፍ ላይም ውጤታማ ለመሆን እየተጋች መሆኑን ትናግራለች። የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ስራና ስልጠና መምሪያ ሃላፊ ዲያቆን ኪዳነ ማርያም ገብረህይወት፤ ወጣቶች የአካባቢያቸውን ፀጋ ለይተው ከተንቀሳቀሱ ውጤታማ እንደሚሆኑ ወጣት ማህደር ትልቅ አርአያ ናት ይላሉ። ለአብነትም እንደ ወጣት ማህደር ያሉ ታታሪ ወጣቶችን በስፋት ለማፍራት በስራ እድል ፈጠራ ላይ በማተኮር እየተሰራ እንደሚገኝ ያስረዳሉ። የወጣቷን አርአያነት ለማስፋት በቀጣይ የብድር፣ የመስሪያና መሸጫ ቦታና ሌሎች ድጋፎችን በማድረግ እንደሚያበረታቱ አረጋግጠዋል። ወጣቶች በተሰማሩበት የስራ ዘርፍ ውጤታማ እንዲሆኑ ድጋፍና ክትትል በማድረግ በባለፉት ወራት ለ11 ሺህ ሰዎች የስራ እድሉ ተጠቃሚ መሆናቸውንም አውስተዋል።
የኢትዮጵያ የእናቶች ሞትን ምጣኔ ቅነሳ ስኬቶች እና ቀሪ የቤት ስራዎች
May 13, 2025 1062
የዓለም የጤና ድርጅት (ደብሊውኤችኦ) የ2025 ዓለም የጤና ቀንን እ.አ.አ አፕሪል 7, 2025 አክብሯል። የዘንድሮው ዓመት የቀኑ መሪ ሀሳብ “ የእናቶች እና ህጻናት ጤና ጥበቃ፣ ለመጻኢው ብሩህ ጊዜ” የሚል ነው። የዓለም የጤና ጉዳዮች የበላይ አካል የሆነው ደብሊውኤችኦ መሪ ሀሳቡን መሰረተ በማድረግ ዓመቱን ሙሉ የእናቶች እና ህጻናት ጤና ጥበቃ አስመልክቶ ንቅናቄ ያደርጋል። በኢትዮጵያም የዓለም የጤና ቀን ሚያዚያ 19 ቀን 2017 ዓ.ም አዲስ አበባ በሚገኘው እንጦጦ ፓርክ “ ከቃል ያለፈ የተግባር ምላሽ” በተሰኘ ሁነት ተከብሯል። በአከባበሩ ላይ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተወካዮች፣ የጤና ሰራተኞች፣ ቤተሰቦች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል። የጤና ሚኒስቴር፣ የዓለም ጤና ድርጅት እና ቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሁነቱን በጋራ አዘጋጅተውታል። በእንጦጦ ፓርክ የነበረው የዓለም የጤና ቀን አከባበር ሁነቱን አስቦ ከመዋል ያለፈ ትልቅ ትርጉም ያለው ነው ሲል የዓለም ጤና ድርጅት ኢትዮጵያ ለእናቶች እና ህጻናት ሞት ቅነሳ ያላትን ቁርጠኝነት ማሳየቷን ገልጿል። የእናቶች እና ህጻናት ጤና የጤና ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የሰብዓዊ መብት፣ የማህበራዊ ልማት እና የብሔራዊ ልማት ጉዳይም ጭምር እንደሆነ የዘንድሮው የዓለም የጤና ቀን አከባበር ያሳየ እንደሆነ ተገልጿል። እንደ ዓለም የጤና ድርጅት መረጃ ከሁለት አስርት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ከ100 ሺህ እናቶች መካከል ከ400 በላይ የሚሆኑት ህይወታቸውን ያጡ ነበር። ኢትዮጵያ ይሄን አሃዝ በመቀየር የራሷን ታሪክ ፅፋለች። በአሁኑ ሰዓት የእናቶች ሞት ምጣኔ ከ100 ሺህ እናቶች ወደ 195 ዝቅ ብሏል። ቁጥሩ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱ ኢትዮጵያ በጤናው ስርዓት፣ የሰው ኃይል ስልጠና እና የአገልግሎት አቅርቦት ላይ እያደረገች ያለውን ዘላቂ ኢንቨስትመንት እንደሚያሳይ ድርጅቱ ገልጿል። ይሁንና አሁንም በኢትዮጵያ በየአመቱ በአማካይ 8 ሺህ ገደማ እናቶች በወሊድና ከወሊድ ጋር በተገናኘ ችግር እንደሚሞቱ መረጃው ያመለክታል። በእናቶች እና ህጻናት ጤና ጥበቃ እየተደረገው ያለው ዓመታዊ ንቅናቄ ለለውጦች እውቅና ከመስጠት ባለፈ ቀሪ የቤት ስራዎች ማጠናቀቅ እንደሚገባ የሚያመላክት ነው። የኢትዮጵያ መንግስት የሰው ኃይል ስልጠናን በማስፋት፣ የእናቶች እና ህጻናት ክብካቤን ማሻሻል፣ በዲጂታል መሳሪያዎች አማካኝነት የአገልግሎት አሰጣጥን ማጠናከር ላይ መልካም ስራዎች ቢያከናውንም አሁንም የአገልግሎት ተደራሽነት ላይ በትኩረት መስራት እንዳለበት ድርጅቱ አሳስቧል። የጤና መሰረተ ልማቶችን ማስፋፋት እና የሰለጠነ የሰው ኃይል ቁጥርን መጨመር ሌሎች ትኩረት የሚያሻቸው ጉዳዮች ናቸው ብሏል። የእናቶችና ጨቅላ ህፃናት ሞት ቅኝትና ምላሽ ስርዓትን ማጠናከር ሌላኛው በድርጅቱ የቀረበ ምክር ሀሳብ ነው። የዓለም የጤና ድርጅት ተወካይ ዶክተር ቤጆይ ናምቢያር በዓለም አቀፍ ደረጃ በተለይም በማደግ ላይ በሚገኙ ሀገራት ያለው የእናቶች እና ህጻናት ሞት አሳሳቢ እንደሆነና ጠንካራ ምላሽ እንደሚያስፈልገው አመልክተዋል። በዘላቂ ልማት ግቦች እ.አ.አ በ2030 ከ100 ሺህ እናቶች የሚሞቱን ወደ 70 ዝቅ የማድረግ ግብ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሀገራት ለማሳካት እየሄዱበት ያለው ርቀት አመርቂ አለመሆኑ ተገልጿል። ኢትዮጵያ ከተቀመጠው ግብ አንጻር ብዙ ስራዎችን ማከናወን እንደሚገባት የዓለም የጤና ድርጅት አስታውቋል። ይሁንና ኢትዮጵያ በዓለም የፋይናንስ ፈተናዎች እና አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል በግልጽ ያሳየች ሀገር መሆኗ ተገልጿል። ዓለም በተግባር የታገዘ ምላሽ ከሰጠ መከላከል የሚቻሉ የእናቶች እና ህጻናትን ሞት ማስቀረት ሊሳካ የማይችል ህልም አይደለም። ከእንጦጦ ፓርክ ጎዳናዎች አንስቶ በሀገሪቷ ክፍሎች በሚገኙ የጤና ማዕከላት የእናቶች እና ህጻናትን ሞትን ለመቀነስ የሚወሰዱ እያንዳንዱ እርምጃዎች የወደፊቱን የዓለም መጻኢ ጊዜ ብሩህ የማድረግን ራዕይን የሚያሳካ ነው ሲል የዓለም የጤና ድርጅት ጽሁፉን ቋጭቷል።
ትንታኔዎች
የፓን አፍሪካኒዝም ንቅናቄ አሻራ ያረፈበት የኢትዮ-ታንዛንያ ወዳጅነት
Dec 17, 2024 3288
የመጀመሪያው የኢትዮጵያ እና ታንዛንያ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባ ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል። የታንዛንያ የውጭ ጉዳይ እና ምሥራቅ አፍሪካ ትብብር ሚኒስትር አምባሳደር ማሕሙድ ታቢት ኮምቦ በስብስባው ላይ ለመሳተፍ ትናንት አዲስ አበባ ገብተዋል። ስብስባው የኢትዮጵያ እና ታንዛንያ የሁለትዮሽ ትስስር እና የጋራ ትብብር የማጠናከር ዓላማ የያዘ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በነበሩበት ወቅት በየካቲት ወር 2016 ዓ.ም ከታንዛንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከነበሩት ጃንዋሪ ማካምባ ጋር ባደረጉት የሁለትዮሽ ውይይት የኮሚሽኑን ስብስባ ለማካሄድ ከስምምነት መድረሳቸው አይዘነጋም። የኢትዮጵያና ታንዛንያ የሁለትዮሽ ወዳጅነት በቅርበት ለመረዳት የፓን አፍሪካኒዝም ንቅናቄን ማየት ግድ ይላል። የመላው ጥቁር ሕዝቦች ንቅናቄ የሆነው ፓን አፍሪካኒዝም ጅማሮ በ19ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ። የፓን አፍሪካኒዝም መሰረት የሆነችው ኢትዮጵያ የንቅናቄው ፋና ወጊ በመሆን ወሳኝ ሚና ተጫውታለች። የፓን አፍሪካኒዝም እሳቤ ላይ ከኢትዮጵያ ጋር አብረው በመቆም ትግል ሲያደርጉ ከነበሩት አገራት መካከል ታንዛንያ ትገኝበታለች። በፓን አፍሪካኒዝም ትግል ውስጥ ስማቸው በቀዳሚነት ከሚጠቀሱ መሪዎች መካከል ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ እና የታንዛንያው የቀድሞ ፕሬዝዳንት ጁሊዬስ ኔሬሬ ተጠቃሽ ናቸው። መሪዎቹ ለአፍሪካ አገራት ከቅኝ አገዛዝ መውጣት ትልቅ ሚና በመጫወት ሕያው አሻራቸውን አሳርፈዋል። የኢትዮጵያና ታንዛንያ የሁለትዮሽ ግንኙነት በእነዚህ መሪዎች ጊዜ የተጀመረ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ። አገራቱ በጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጣር ግንቦት 25 ቀን 1963 የቀድሞ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (በአሁኑ መጠሪያው የአፍሪካ ኅብረት) መቋቋሙ ሲበሰር መስራች አባል አገራት ነበሩ። ኢትዮጵያና ታንዛንያ በየአገራቱ ኤምባሲያቸውን በይፋ በመክፈት የሁለትዮሽ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ለማጠናክር እየሰሩ ይገኛሉ። አገራቱ የሁለትዮሽ ትብብራቸውን ለማጠናከር የሚያስችላቸው በርካታ አቅሞች አሉ። ኢትዮጵያ እና ታንዛንያ ባላቸው የቁም እንሥሳት ኃብት ከአፍሪካ በቀዳሚነት የሚጠቀሱ አገራት ናቸው። ሁለቱ አገራት በሚያደርጓቸው የጋራ ምክክሮች ይሄን ሰፊ ኃብት በመጠቀም የንግድ እና ኢኮኖሚ ትስስር ማጠናከር እንደሚገባ በተደጋጋሚ ጊዜ ያነሳሉ። ግብርና፣ የሰብል ምርት፣ የኤሌክትሪክ ኃይል፣ የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ እና አቪዬሽን ከሁለቱ አገራት የትብብር መስኮች መካከል በዋናነት ይጠቀሳሉ። የኢትዮጵያ አቪዬሽን አካዳሚ በርካታ ታንዛንያውያን ፓይለቶች እና ኢንጂነሮችን አሰልጥኖ አስመርቋል። አቪዬሽንም የሁለቱ አገራት ቁልፍ የትብብር መስክ በሚል ይነሳል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በየካቲት ወር 2016 ዓ.ም በታንዛንያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወቃል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከታንዛንያ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሁሉ ሀሰን ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል። አገራቱ በወቅቱ በባህልና ኪነ-ጥበብ፣ በግብርና እንዲሁም በኤሌክትሪክ ኃይል ንግድ ላይ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቶቹ የሁለቱ አገራት ትብብር ይበልጥ ለማጠናክር ትልቅ ፋይዳ አላቸው። የዛሬው የኢትዮጵያ እና ታንዛንያ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባም የስምምነቶችን አፈፃጸም በመገምገም ትግበራውን ማፋጠን የሚያስችል አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል። ከሰሞኑ የምሥራቅ አፍሪካ ከፍተኛ ኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት አካል የሆነው ከኬንያ ወደ ታንዛንያ የተዘረጋው የኤሌክትሪክ መስመር የሙከራ የኃይል አቅርቦት መጀመሩ ይታወቃል። የቀጣናው ከፍተኛ ኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ (ሃይዌይ) ፕሮጀክት የመጀመሪያው የኃይል ትስስር ኢትዮጵያና ኬንያን ያስተሳሰረ መሆኑ ይታወሳል። የፕሮጀክቱ ሁለተኛ ክፍል ደግሞ ከኬንያ ወደ ታንዛኒያ የተዘረጋ ሲሆን የኤሌክትሪክ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ ተጠናቆ የሙከራ ኃይል አቅርቦት መጀመሩን የውኃና ኢኒርጂ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል። ይህ ቀጣናዊ የኃይል ትስስር በተመጣጣኝ ዋጋ አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት በማረጋገጥ በሀገራት መካካል ትብብርን እና የጋራ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የሚያስችል ነው። የኃይል አቅርቦት መጀመሩ ከኢትዮጵያ እና ታንዛንያ አልፎ በቀጣናው ያለውን ትስስር ለማፋጠን ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ይታመናል። ሁለቱ አገራት በቅርቡ ወደ ትግብራ ምዕራፍ የገባው የናይል የትብብር ማዕቀፍ ስምምነትን በአገራቸው ፓርላማ ማጽደቃቸው ይታወቃል። ስምምነቱ በናይል ተፋስስ የውኃ ኃብትን ፍትሃዊ እና ምክንያታዊ በሆነ መልኩ በበጋራ ለመጠቀም የሚያስችል ነው። አገራቱም በውኃ ኃብት ያላቸውን ትብብር ይበልጥ የሚያጠናክር ነው። የፓን አፍሪካኒዝም ንቅናቄ ያስተሳሰራቸው ኢትዮጵያ እና ታንዛንያ የሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ትብብራቸውን ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ ማሸጋግር የሚያስችሉ ሰፊ እድሎች ከፊታቸው ይጠብቃቸዋል።
ከተለምዷዊ ዲፕሎማሲያዊ ትብብር የተሻገረው የኢትዮ-አልጄሪያ ወዳጅነት
Dec 16, 2024 2752
የኢትዮ-አልጄሪያ ግንኙነት ታሪካዊ ነው፡፡ታሪካዊነቱ በዘመንም፣ በጸና ወዳጅነትም ይለካል።ትናንት ማምሻውን የሀገሪቷ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሕመድ አታፍ የሀገሪቷን ፕሬዝዳንት አብደልማጂድ ቴቡኔን መልክዕት ይዘው አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወቃል። ዛሬ ማለዳ ደግሞ ሚኒስትሩ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር ጋር ተወያይተዋል። በውይይቱም ሁለቱ ሀገራት ያላቸውን የፀና ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ተናግረዋል። የፕሬዝዳንት አብደልማጂድ ቴቡኔን መልዕክትም ተቀብለዋል። ጉብኝቱን አስመልክቶ የሰሜን አፍሪካዊቷ አልጄሪያ እና የኢትዮጵያን ወዳጅነት የትመጣ እና ሂደት በወፍ በረር እንቃኝ። የኢትዮ-አልጀሪያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ሰባት አስርት ዓመታትን ተሻግሯል። ሁለቱ ሀገራት ከመደበኛ ዲፕሎማሲያዊ ትብብር የተሻገረ ወንድማማችነትና ወዳጅነት መስርተዋል። የፈረንሳይ ቅኝ ተገዥ የነበረችው አልጄሪያ በአውሮፓዊያኑ 1960ዎቹ መባቻ ነጻነቷን ለመቀዳጀት ትንቅንቅ ላይ በነበረችበት ዘመን ኢትዮጵያ አጋርነቷን አሳይታለች። ይህን ደግሞ በኢትዮጵያ የአልጄሪያ አምባሳደር የነበሩት ኤልሃምዲ ሳላህ ‘አልጀሪያ የኢትዮጵያን ውለታ አትረሳውም’ ሲሉ በአውሮፓውያኑ 2022 ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልፀው ነበር። አልጀሪያ በ1962(በአውሮፓዊያኑ) ነበር ከፈረንሳይ ቅኝ ግዛት ነጻነቷን ያረጋገጠችው። ከዚህ ዘመን ጀምሮ ሁለቱ ሀገራት ወዳጅነታቸውን መሰረቱ። የአፍሪካ አንድነት ድርጅት እንዲመሰረት እና የፓን አፍሪካኒዝም እንዲያብብ ንቅናቄ አድርገዋል። በ1960ዎቹ መጨረሻም ይፋዊ ዲፕሎማሲ ግንኙነታቸውን በይፋ ጀመሩ። አልጄሪያ የቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት(የአሁኑ የአፍሪካ ሕብረት) መገኛ በሆነችው ኢትዮጵያ ኤምባሲዋን በ1976(እ.ኤ.አ) ከፈተች። ኢትዮጵያም በ2016 ኤምባሲዋን በአልጀርስ ከፍታለች። ሁለቱ ሀገራት በአውሮፓዊያኑ 2014 በግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ንግድ፣ ባህል እና በተለያዩ መስኮች ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር የሚያስችል የጋራ ኮሚቴ ፈጥረዋል። ሁለቱ ሀገራት በንግድ፣ ኢንቨስትመንት ጥበቃ እና ማስተዋወቅ እንዲሁም ተደራራቢ ታክስ ማስቀረትን ጨምሮ ከ20 በላይ የትብብር መስኮች በጋራ መስራት ስምምነት ተፈራርመዋል። ከሁለትዮሽ ባሻገርም ቀጣናዊ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ የትብበር መስኮች ያላቸውን ትብብር የማጠናከር ፍላጎት አላቸው። ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በነበሩበት ወቅት በመስከረም ወር 2017 ዓ.ም በኒውዮርክ በተካሄደው 79ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ጎን ለጎን ከአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር መወያየታቸው ይታወቃል። በዚሁ ውይይት ኢትዮጵያ እና አልጄሪያ በአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን አልፎም በዓለም የሰላም እና ደህንነት ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ከስምምነት ላይ መድረሳቸው ይታወሳል። አምስተኛውን የኢትዮ-አልጄሪያ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባ በቅርብ ጊዜ ለማከናወን የተጀመረውን ዝግጅት ለማፋጠን ተስማማተዋል። አልጄሪያ የአፍሪካ ሕብረት የሰላም እና የጸጥታ ምክር ቤት ከአውሮፓዊያኑ ጃንዋሪ 2024 አንስቶ የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባል ሆና በመስራት ላይ ትገኛለች። ይህም ሁለቱ ሀገራት በባለብዝሃ ወገን የዲፕሎማሲ መድረክ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ የሚያጎለብት ነው። አልጄሪያ በአውሮፓዊያኑ በ2021 የአረብ ሊግ ሊቀመንበር በነበረችበት ወቅት ተቋሙ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የተዛባ አረዳድ ለማስተካከል እና ሚዛናዊ እይታ እንዲኖረው ጥረት አድርጋለች። የኢትዮ-አልጄሪያ የሁለትዮሽ ትብብር የሚያጠናክሩ የጉብኝት ልውውጦች እና ውይይቶች እያደጉ መጥተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በነሐሴ ወር 2014 ዓ.ም በአልጄሪያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወቃል። በወቅቱም ከአልጄሪያው ፕሬዝዳንት አብደልማጂድ ቴቡኔ ጋር ተወያይተው ነበር።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የኢትዮ-አልጄሪያ ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረ ታሪካዊ በሁለትዮሽ ትብብር ይበልጥ ማጠናከር የሚቻለባቸው ዘርፎች እንዳሉ ገልጸው ነበር። ከዚህ ጊዜ ጀምሮም በሀገራቱ መካከል የጉብኝት ልውውጦች እና ውይይቶች እየጨመሩ መጥተዋል። ለአብነትም በአውሮፓዊያኑ በ2021 የያኔው የአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ራምታኔ ላማምራ በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት አድርገው ነበር፤ የሁለትዮሽ ትብብር ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውም አይዘነጋም። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ደግሞ በሩሲያ ሶቺ በጥቅምት ወር 2017 ዓ.ም ከተካሄደው የመጀመሪያው የአፍሪካ-ሩሲያ የትብብር ፎረም የሚኒስትሮች ስብስባ ጎን ለጎን ከአልጄሪያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሕመድ አታፍ ጋር መክረዋል። በውይይታቸውም የጋራ ተጠቃሚነትን በሚያስጠብቁ ቀጣናዊና አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር። እናም ሁለቱ ሀገራት በተለያዩ የትብብር መስኮች ግንኙነታቸውን ማጎልበት ቀጥለዋል። በአልጄሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙክታር መሀመድ ዋሬ በቅርቡ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለአልጄሪያው ፕሬዝዳንት አብዱልመጂድ ቴቡኔ ሲያቀርቡ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና የፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴን ልባዊ ሰላምታ እና የወዳጅነት መልዕክት ለፕሬዝዳንቱ ማቅረባቸው የሚታወስ ነው። ዛሬ ደግሞ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ የሚገኙት የአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሕመድ አታፍ የፕሬዝዳንት አብደልመጂድ ቴቡኔን መልዕክት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አድርሰዋል። የሚኒስትር አሕመድ አታፍ ጉብኝት ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያለው እና የኢትዮ-አልጀሪያ ሁለትዮሽ ወዳጅነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ የሚደረገው ጥረት አካል ስለመሆኑ የአልጄሪያ ዜና አገልግሎት ዘግቧል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሕመድ አታፍ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ጋርም ተወያይተዋል። በውይይቱ በሁለትዮሽ እና አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው። ሚኒስትሮቹ በውይይታቸው አገራቱ በተለያዩ ዘርፎች ያላቸውን ትስስር በማጠናከር እና አዳዲስ የትብብር አድማሶችን በመፈለግ አጋነታቸውን ለማጎልበት እንደሚሰሩ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ እና አልጄሪያ የጋራ ሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብስባን በቅርቡ ለማድረግ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። እናም ኢትዮጵያና አልጄሪያ ከተለምዷዊ ዲፕሎማሲያዊ ትብብር የተሻገረ ነው። ሁሉን አቀፍ በሆኑ የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት ባደረጉ ትብብር መስኮች እየተወዳጁ ነው። የስትራቴጂካዊ አጋርነት ደረጃ እየጎለበተ ይመስላል። የአገራቱ መጻዒ የትብብር ጊዜ ብሩህ እና ፍሬያማ እንደሚሆን አያጠራጥርም።
ቀጣና ዘለል አንድምታ ያለው የአንካራው ስምምነት
Dec 13, 2024 2934
የአፍሪካ ቀንድ ፖለቲካ አንድምታ ከቀንዱ ሀገራት የተሻገረ ነው። የቀጣናው ሀገራት ትስስርና ትብብርም እንደዚያው። በነዚህ ሀገራት መካከል የሚፈጠር መቃረን የሚያሳድረው ተጽዕኖም አድማስ ዘለል ነው። በቅርቡ በኢትዮጵያና ሶማልያ መካከል ተፈጥሮ የነበረው የግንኙነት መሻከር ከሁለቱ ሀገራት ባሻገር በቀጣናው ስውርና ገሀድ ፍላጎት ያላቸው የውጭ ኃይሎችን ያሳሰበና ያስጨነቀ ጉዳይ መሆኑ እሙን ነው። በቱርክዬ ርዕሰ ከተማ አንካራ የተደረሰው የኢትዮ-ሶማልያ ሥምምነት ግን ለበርካቶች እፎይታን ይዞ መጥቷል። ከኢትዮጵያና ሶማልያ ጋር መልካም ወዳጅነት ያላት ቱርክዬ የሁለቱን አገራት ለማሸማገል ጥረት ከጀመረች ውላ አድራለች። ምንም እንኳ ጥረትና ድካሟ በተደጋጋሚ ሳይሳካ ቢቆይም ካለፈ ሐምሌ 2016 ዓ.ም ጀምሮ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት በሚኒስትሮች ደረጃ ለማረቅ ተግታለች። በሦስተኛው ዙር በሁለቱ ሀገራት መሪዎች ደረጃ የተደረገው ድርድር ግን ፍሬ አፍርቶላታል። ቱርክዬ እየተገነባ ባለው የብዝሃ-ዋልታ ዓለም ውስጥ ጎልተው እየወጡ ካሉ ኃያላን ሀገራት መካከል አንዷ ናት። በአፍሪካ ውስጥ ያላት ተፅዕኖ ፈጣሪነትም እያደገ መምጣቱ ይታወቃል-በተለይ በአፍሪካ ቀንድ። ቱርክዬ ከኢትዮጵያ ጋር ያላት ታሪካዊና ዘርፈ ብዙ ትስስር ጠንካራ የሚባል ነው። ቱርክዬ ከቻይና ቀጥላ በኢትዮጵያ ግዙፍ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ያፈሰሰች ሀገር ናት። ከኢኮኖሚያዊ ቁርኝቱ ባሻገር ሁለቱ አገራት በፖለቲካዊና ማኅበራዊ እንዲሁም ስትራቴጂያዊ በሆኑ ጉዳዮች ያላቸው ትብብርም የላቀ ነው። ቱርክዬ ከሶማልያ ጋር ያላት አጋርነትም እየተጠናከረ የመጣ ነው። እናም የሁለቱ ሀገራት አለመግባባት ለቱርክዬ ሳንካ ነበር። ስለዚህ የሁለቱ ሀገራት አለመግባባት በአንካራው ድርድር ዲፕሎማሲያዊ እልባት ማግኘቱ ለፕሬዝዳንት ኤርዶሃን ወሳኝ እርምጃ ሆኖላቸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የሶማልያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ በአንካራ ተገኝተው ያደረጉት ውይይት የቀንዱን ውጥረት አርግቧል። ስምምነቱ በሁለቱ ሀገሮች መካከል የተፈጠሩ አለመግባባቶችን በውይይት በመፍታት ግንኙነታቸውን ወደ አዲስ የትብብር ምዕራፍ ለመውሰድ የሚያስችል እንደሆነም ተገልጿል። በሶማልያ በኩል ኢትዮጵያ አስተማማኝ፣ ደህንነቱ የተረጋገጠ እና ዘላቂነት ያለው የባሕር በር የማግኘት መብትን ዕውቅና ለመስጠት እና በዚህ ጉዳይ ላይ አብሮ ለመስራት መስማማት ችላለች። በተመሳሳይ ኢትዮጵያም የሶማልያን የግዛት አንድነት ለማክበር የነበራትን የቆየ አቋም አጽንታለች። ሁለቱ ሃገራት የኢትዮጵያን የባሕር በር ፍላጎት እውን ለማድረግ በቀጣይ አራት ወራት በቱርክዬ አስተባባሪነት ዝርዝር ቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ ምክክር ለማካሄድ ተስማምተዋል። መሪዎቹ በመግለጫቸው ኢትዮጵያ በሶማልያ የባሕር ዳርቻ በኩል ዘላቂ እና ደኅንነቱ የተጠበቀ የወደብ አማራጭ በምታገኝበት ዙሪያ የቴክኒክ ውይይቶችን ለመጀመር ይሁንታቸውን ሰጥተዋል።ይህ የወደብ አማራጮችን በስፋት ለመጠቀም ለምትፈልገው ኢትዮጵያ ትልቅ እርምጃ ተደርጎ የሚወሰድ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመግለጫቸው፤ ቱርክ በአፍሪካ ቀንድ ሠላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ለምታደርገው አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል። የኢትዮጵያና የሶማልያ ሕዝቦች በቋንቋ፣ በባህል እና በጉርብትና ብቻ ሳይሆን በደም የተሳሰሩ ወንድማማቾች እና እህታማማች ሕዝቦች መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አውስተዋል። ይልቁንስ ሶማልያን ከአሸባሪዎች ለመከላከልና ሠላሟን ለማረጋገጥ ሲባል በሺዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል አባላት በከፈሉት መስዋዕትነት ጭምር የተሳሰረ መሆኑን ነው ግልጽ ያደረጉት። ኢትዮጵያ ለጋራ ሠላምና ልማት ከሶማልያ ጋር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል። የሶማልያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድም ለዚህ ሀቅ ጠንካራ እማኝነታቸውን ሰጥተው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ለአገሪቱ ሠላም መጠበቅ ለዓመታት የከፈለውን ዋጋ መቼም አይዘነጋም ሲሉ የሚገባውን ክብር አጎናጽፈውታል። ሶማልያ የኢትዮጵያ እውነተኛ ወዳጅ ሆና ትቀጥላለች ሲሉም አረጋግጠዋል። ሁለቱ ሀገራት በቀጣይም ሠላምን ለማፅናት በሚያደረጉት ጥረት መንግሥታቸው ቁርጠኛ መሆኑን ተናግረዋል። በጥቅሉ የአንካራው የአቋም መግለጫ የሁለቱን አገራት የጋራ አሸናፊነት ያንጸባረቀ ነው። ለዘመናት በተለይም ላለፉት ሦስት አሥርት ዓመታት ፈጽሞ የተዘነጋ እና የማይታሰብ ይመስል የነበረውን የኢትዮጵያን የባሕር በር ጉዳይ በድፍረት ዓለም አቀፍ አጀንዳ ለማድረግ ያስቻለ ነው። የኢትዮጵያ የባሕር በር ማግኘት ከሃገር አልፎ ለቀጣናው ሁለንተናዊ ትስስር ጭምር ወሳኝ መሆኑ መግባባት የተደረሰበት ሆኗል። በተለያዩ አሰራሮች እና አግባቦች፣ በሠላማዊ መንገድ እና በሰጥቶ መቀበል መርህ ኢትዮጵያ አስተማማኝ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ዘላቂ የባሕር በር ሊኖራት እንደሚገባ መግባባት የፈጠረ ነው። ይህን ሥምምነት ዕውን ለማድረግ በዝርዝር ቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ ቀጣይ ድርድሮች በማካሄድ በአጭር ጊዜ ውስጥ ገቢራዊ ለማድረግ ተጨባጭ እርምጃዎችን ለመውሰድ መግባባት ችለዋል። በዚህ ረገድ ቱርክዬ ሂደቱን ለማሳለጥ እና ለማገዝ ኃላፊነት መውሰዷ ደግሞ ዘላቂነት እንዲኖረው እንደ መልካም ዕድል የሚወሰድ ነው። ኢትዮጵያና ሶማልያ በአንካራ የደረሱት ስምምነት ከአውሮፓ ኅብረት እስከ አፍሪካ ኅብረት እንዲሁም ከምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) እስከ ተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማትና አገራት አድናቆት የቸሩት ሆኗል። ይህ ስምምነት የሁለት አገራት ስምምነት ብቻ አይደለም። የጥይት ድምጽ የማይሰማባት አፍሪካ የመፍጠር ህልም አካልም ጭምር ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። የውዳሴው መነሻና መድረሻውም ደግሞ ስምምነቱ የአፍሪካ ቀንድን ከግጭት አዙሪት ወጥቶ ወደ ዘላቂ ሠላምና መረጋጋት ብሎም ወደ አህጉራዊ ትብብር የሚወስድ መሆኑ ነው። በእርግጥም ሥምምነቱ የፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ከመባቱ በፊት ለቀንዱ አገራት የቀረበ ሥጦታ ነው። እናም የአንካራው ስምምነት ከኢትዮጵያና ከሶማልያ ባለፈ አንድምታው ቀጣናውን የተሻገረ በመሆኑ የአፍሪካውያንና የወዳጅ ሀገራት በቅን መንፈስ የተቃኘ ድጋፍ ያሻዋል። ሠላም!
ህዳሴ - በመስዋዕትነት የተገነባ ነገ
Nov 2, 2024 4053
ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ከፕሮጀክት ባለፈ የኢትዮጵያውያን በጋራ የመቻል ትምህርት ነው። የወል ዕውነታቸው፣ የወል አቅማቸው፣ የጋራ ተስፋቸው በግልጽ የተንጸባረቀበት የአይበገሬነት ምልክት ጭምር ነው። ኢትዮጵያውያን ነጋቸውን እንዴት በጋራ መገንባት እንደሚችሉ በሚገባ ያሳዩበት ዳግማዊ አድዋ ነው - ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ። አድዋ ቀደምት ኢትዮጵያውያን ለነጻነት የተዋደቁበት ደማቅ የታሪክ ምዕራፍ ሲሆን ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ደግሞ ለኢኮኖሚ ሉአላዊነት የደም ዋጋ የተከፈለበት የትውልዱ የብሄራዊነት ማሳያ ነው። ህዳሴን ዕውን ለማድረግ ኢትዮጵያ ከሴራ ዘመቻዎች እስከ ዛቻና ማስፈራሪያዎች የደረሱ እንቅፋቶችን አልፋለች። በተለይም የግድቡ ግንባታ ወደማይቀበለስበት ደረጃ በደረሰባቸው ያለፉት 6 ዓመታት ፈተናዎቹ በርትተው ነበር። ለህዳሴው ግድብ ግንባታ የሚያስፈልጉ ግብዓቶች ተጓጉዘው እንዳይደርሱ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ምርት እንዳያመርቱና እንዳያቀርቡ በተለየዩ ቦታዎች ጥቃቶች ይሰነዘሩ ነበር። ቢሆንም ግን የማያባሩ የኢትዮጵያ ጠላቶችን የተንኮል ወጥመዶች በጣጥሶ ለማለፍ ኢትዮጵያውያን አይተኬ ህይወታቸውን ጭምር ገብረው ነገን ዛሬ መስራትን በህዳሴ ዕውን አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሕዳሴ ግድብ አሁን የደረሰበት ደረጃ እንዲደርስ በርካታ መስዋዕትነት መከፈሉን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ሁሌም በጋራ የመልማት እሳቤ ማዕከል መሆኗን ገልጸው፤ታላቁ ህዳሴ ግድብም በኢትዮጵያዊያን ብርቱ ልጆች ከአፍሪካ ለአፍሪካ የተሰጠ ገጸ በረከት እንዲሁም ጣፋጭ ፍሬውም ከኢትዮጵያ ባለፈ ለተፋሰሱ አገራትም ብስራት መሆኑን ነው ያስረዱት። የታላቁ የኢትዮጵየ ህዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ በበኩላቸው ፕሮጀክቱ አኩሪ ደረጃ ላይ ለመድረስ ኢትዮጵያውያን ከገንዘብ፣ ጉልበትና እውቀታቸው ባሻገር የህይወት መስዋዕትነት የከፈሉበት ፕሮጀክት መሆኑን ጠቁመዋል።
ልዩ ዘገባዎች
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 2596
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 2334
ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
የአርሶ አደሮችን ጓሮና ኑሮ የለወጡ ቁጥሮች- “30-40-30”
Nov 15, 2024 3777
ለዛሬው ትውልድ ምግብ፣ ለመጪው ትውልድ ደግሞ ቅርስና ውርስ የሚሆን ሃብት የሰነቀው የ"30-40-30" ኢኒሼቲቭ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አርሶ አደሮች መንደር ተገኝቶ ስለ ’30-40-30’ አሃዞች አርሶ አደሮችን የሚጠይቅ ካለ የቁጥሮችን ትርጓሜና ስሌት በቅጡ መረዳት ይችላል። እነዚህ ቁጥሮች በገጠራማው የክልሉ አካባቢዎች አባውራዎች ዘንድ ሕይወትም፣ አስተሳስብም ለውጠዋልና። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኅላፊ አቶ ዑስማን ሱሩር የ’30-40-30’ ኢኒሼቲቭ የተጠነሰሰው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭን በመመርኮዝ ስለመሆኑ ያስታውሳሉ። እነዚህ ቁጥሮች የተራ አሃዝ ስያሜ ሳይሆኑ በክልሉ ግብርና ወደ እመርታ ለማስፈንጠር የተቀየሱና ትውልድ ተሻጋሪ ዓላማ የሰነቁ ናቸው። በ2014 ዓ.ም ጀምሮ እያንዳንዱ የክልሉ አርሶ አደር በሶስት ዓመታት ውስጥ ቢያንስ 100 የፍራፍሬ ዛፎች አልምቶ እንዲጠቀም መሰረት የሆኑም ናቸው። በኢኒሼቲቩ የለሙ ፍራፍሬዎች የአርሶ አደሩን ኑሮ ማሻሻል ያለሙ፣ 'ለዛሬው ትውልድ ምግብ፣ ለመጪው ትውልድ ደግሞ ቅርስና ውርስ ናቸው' ይላሉ። የምግብና ስነ-ምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ፣ ገቢ ምንጭ ማድረግ፣ ስራ ዕድል መፍጠር፣ ገበያ ማረጋጋት፣ ለኤክስፖርትና ለኢንዱስትሪዎች ግብዓት ማቅረብን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ ዓላማዎችም አሏቸው። በእያንዳንዱ አባውራ ጓሮ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲለማና ተጠቃሚ እንዲሆን ለማስቻል የተወጠነ ነው። በዚህም በ'30-40-30'ን እያንዳንዱ አባወራ ጓሮውን እንደየአካባቢው ስነ-ምህዳር በሙዝ፣ በፓፓያ፣ በማንጎ፣ በቡና፣ በአቮካዶና በሌሎች ፍራፍሬ ችግኞች እንዲያለማ ተደርጓል። 'ያልተሄደበትን መንገድ በመሄዳችን በትግበራ ሂደቱ ፈተናዎች ነበሩ' የሚሉት ሃላፊው፤ ዛሬ ላይ ግን የ30-40-30 ኢኒሼቲቭ ፍሬ የቀመሱትን ሁሉ አስተሳስብ ለውጧል ይላሉ። ኢኒሼቲቩ ባልተለመዱ አካባቢዎች የፍራፍሬ መንደሮች የተፈጠሩበት፣ የአርሶ አደሩ ኑሮና ጓሮ የተለወጠበት፣ የይቻላል አስተሳስብ የተፈጠረበት እንደሆነ ይናገራሉ። በክልሉ የ30-40-30 ኢኒሼቲቭ በመተግበር ከሴፍቲኔት የተላቀቁና ኑሯቸውን ያሻሻሉ አረሶ አደሮች ለዚህ ምስክር ናቸው። በስልጤ ዞን ውልባረግ ወረዳ ቶዴ ጠመዳ ነዋሪዎች አቶ ሀምዛ አሊዬ እና ባለቤታቸው አናጃ ኢሳ በሴፍትኔት ታቅፈው ሲረዱ የቆዩ ሲሆን በ30-40-30 ጓሯቸውን በቡና በማልማታቸው ዛሬ ገቢም፣ ምግብም ችለዋል። በ500 የቡና ችግኝ ድጋፍ ጀምረው በየዓመቱ እያሳደጉ ዛሬ ላይ ቡናቸውን ለቅመው በመሸጥ ገቢ ማመንጨትና ነሯቸውን መደጎም ችለዋል። ጓሯቸውን በማልማታቸውም ከሴፍትኔት መላቀቅ ብቻ ሳይሆን ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ያላቸው ማህበራዊ ህይወት እንዲሻሻል ስለማድረጉም ገልጽው፤ በቀጣይነትም ሌሎች ፍራፍሬዎችን ለማልማት ተዘጋጅተዋል። በውልባረግ ወረዳ ቢላዋንጃ ባቢሶ ቀበሌ ነዋሪው አቶ ኢክማላ መሀመድ እና ልጃቸው መካ ኢክማላ ደግሞ አካባቢውን ያልተለመደ የሙዝ መንደር በማድረግ ኑሯቸውን እንዳሻሻሉ ይናገራሉ። የ30-40-30 ንቅናቄ ሲጀመር በአካባቢው "ሙዝ አይለማም" በሚል የተሳሳተ እሳቤ ቅር እያላቸው ችግኞችን ወስደው የተከሉ ቢኖሩም በርካቶች በእምቢታ ጸንተው እንደነበር አስታውሰዋል። በሂደት ውጤቱ ሲታይ ግን የልማቱ ተሳታፊዎች በዝተው በውጤትና የስኬት መንገድ ላይ መቀጠላቸውን ተናግረዋል። ከሳዑዲ አረቢያ የ10 ዓመታት የስደት ቆይታ በኋላ የተመለሰው ልጃቸው መካ ኢክማላ የስደት አስከፊነትን በማንሳት ተፈጥሮ በሰጠችን ጸጋ ሳንጠቀም በመቆየታችን ይቆጨናለ ይላል። የ30-40-30 ንቅናቄም ወጣቶች ከስደት ይልቅ በጓሯቸው ሰርተው መለወጥ እንደሚችሉ ዐይን የገለጠ እና የአስተሳሰብ ለውጥም ያመጣ ስለመሆኑ ይናገራል። በሀድያ ዞን ሻሸጎ ወረዳ ዶዕሻ ጎላ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ይቴቦ ሽጉጤ፤ ኢኒሼቲቩን በመጠቀም ከሌሎች አርሶ አደሮች ጋር የሙዝ መንደር መስርተዋል። የክላስተር ሙዝ መንደራቸው በሶስት ዓመታት ውስጥ የቤተሰባቸው ኑሮ እንዲሻሻል ያደረገና በቀላሉ ጸጋን ተጠቅሞ መለወጥ እንደሚቻል ያረጋገጠ ስለመሆኑም ገልጸዋል። የስልጤ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና መምሪያ ሃላፊ አቶ ሙበራ ከማል፤ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በሚል ንቅናቄ በርካቶች በተለይም በፍራፍሬና ቅመማ ቅመም ልማት ተሳትፈው ውጤታማ መሆናቸውን ተናግረዋል። በአካባቢ ያሉ ጸጋዎችን በመለየት የቡና፣ የሙዝና የአቮካዶ ክላስተር በማልማት ከፍጆታ አልፈው ለማዕከላዊ ገበያ እየቀረቡ ስለመሆኑም ይናገራሉ። በሀድያ ዞን የሻሸጎ ወረዳ ግብርና ፅህፈት ቤት ሃላፊ ዶክተር ወንዱ መለሰ፤ የ30-40-30 የፍራፍሬ ልማት ከፍተኛ ለውጥ መምጣቱን ተናግረዋል። በሙዝ ክላስተር አርሶ አደሮች በትብብር ሰርተው እንዲለወጡ ያስቻለ መሆኑን ገልጸው፤ አርሶ አደሮችም ውጤቱን በማየት ወደተጨማሪ ልማት እየገቡ ይገኛሉ ብለዋል። የ30-40-30 ኢኒሼቲቩ 'ጥረት ካለ ስኬት እንዳለ ማሳየት የተቻለበት እና የግብርናው ዘርፍ አንኳር መሰሶዎችን ዕውን ለማድረግ ተስፋ ሰጭ ውጤት የተገኘበት መሆኑን አቶ ዑስማን ይገልጻሉ። በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች የግብዓት ፍላጎት በመጨመሩ ተደራሽነቱን ለማሳደግ ጥረት እየተደረገ ይገኛልም ብለዋል። የ30 40 30 የፍራፍሬ ልማት ፕሮጀክት አንድ አርሶ ወይም አርብቶ አደር በመጀመሪያ ዓመት 30፣ በሁለተኛው ዓመት 40 እና በሶስተኛ ዓመት 30 የፍራፍሬ ችግኞችን በመትከል ተጠቃሚ የሚሆንበት መርሃ ግብር መሆኑ ይታወቃል።
መጣጥፍ
በቻይና ይህም አለ!
Jul 8, 2025 178
በአብነት ታደሰ በርግጥ ከዓለማችን የጥንት ስልጣኔ ምድሮች አንዷ ናት- ቻይና። በታሪክ ገጾች ‘የግኝት ምድር’(Land of Invention) የሚል ተቀፅላ የሰፈረላት የሺህ ዘመናት ባለታሪክ ሀገር። የጥንት ቻይኖች አያሌ ‘ግኝቶችን’ ለዓለም አካፍለዋል። ወረቀት ፈብርከው ዘመናቸውን ጽፈዋል፣ ማተሚያ ቁስ ፈጥረው አትመዋል፤ ኮምፓስ ፈልስመው አቅጣጫ ጠቁመዋል።በ221 ዓመተ-ዓለም አንድ ወጥ ስርወ መንግስት መስርተው በሀገረ መንግስት የታሪክ ዑደት ከፍታንም ዝቅታንም አይተዋል። በቻይና አያሌ ስርወ መንግስታት ተፈራርቀዋል። ቻይናውያን ክፉውንም ደጉንም ችለው አልፋዋል። የሕዝቡ ጽናት፣ ጥበብ፣ ቱባ ባህል፣ ታሪክና ብልሃት በቻይና ግንብ ይመሰላል። ግንቡም ዝም ብሎ የጡብ ክምር አይደለም፤ የመሰረተ-ጽኑነታቸው ትዕምርት(symbol) እንጂ። ሲሶውን ሕዝቧ በያንግትዝ ወንዝ ተፋሰስ ጉያ አቅፋ፣ ጥንተ ማንነቷን ሸክፋ ዕልፍ ዘመናትን ተሻግራለች። የቻይና ስርወ መንግስታት ከስመው የዛሬዋ ኮሚኒስት ሪፐብሊክ ቻይና ከተመሰረተች ገና አንድ ምዕተ ዓመቷ ነው። ቅድመ ልደተ ክርስቶት በ221 ዓመተ-ዓለም የተመሰረተው ወጥ-ስርዎ መንግስት በመልከ ብዙ ምክንያቶች ተዳከመ። በፈረንጆቹ 1912 የመጨረሻው የቻይና ስርዎ መንግስት ተንኮታኮተ። ዘመናዊቷ የቻይና ሪፐብሊክ በዚህ ዘመን ተመሰረተች። ዳሩ ለውጡ አልጋ በአልጋ አልሆነም። ለሺህ ዘመን የጽኑ ስርዓተ መንግስት ባለቤቷ ሀገር ቻይና በአስከፊ የእርስ በርስ ጦርነት ታመሰች። ወረራንም፣ ዕልቂትንም አስተናገደች። በዘመኑ ማኦ ዘዶንግ የሚባል ባለራዕይ መሪ በቻይና ምድር ተነሳ። አርቆ አሰበ፤ ሀሳቡንም አሰረጸ፤ በዓላማ ጸንቶ ክፉ ዘመን ተሻገረ። ማኦ እና ተከታዮቹ ለቻይና ትንሳኤ ታተሩ። በጽናት ታገሉ። ለመስዕዋትነት ቆርጠው ተነሱ፤ ዋጋም ከፈሉ። በአውሮፓዊኑ ዘመን አቆጣጣር በ1949 የዛሬዋን የቻይና ሕዝባዊ ኮሚኒስት ሪፐብሊክ መሰረተ። ሃሳቡን ወደ ፖሊሲ ቀየረ፤ ተገበረውም። ቻይናን በኢንዱስትሪና ግብርና ምርት በንቅናቄ የማስፈንጠር ፕሮግራምንም (Great Leap Forward) ገቢራዊ አደረገ። ሆኖም ፖሊሲው በአንዴ ፍሬ አላፈራም። በወቅቱ በተፈጥሯዊና በሌሎች ምክንያቶች ቻይና በረሀብ ጠኔ ተመታች። ቻይናዊያን ተራቡ፤ ጎረቤት ሀገራትን ደጅ ጠኑ፤ ታላቁን ረሀብ መሻገር ያልቻሉ በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ቻይናዊያን በረሀብ አለቁ። በቻንግሻ የሚገኘው የማኦ ዘዶንግ ግዙፍ ሐውልት መራራ ጽዋን ተጎነጩ። የሀገሪቷ መሪ ማኦ ዘዶንግ በወቅቱ ፈተና ተስፋ ሳይቆርጥ ሀገር አሻጋሪ ፖሊሲውን ገቢራዊ አደረገ። ልመናን ለትውልድ ላለማውረስ፣ ንቅዘትን(ሙስናን) ነውር የሚያደርግ ስርዓት አጸና። ስራን ወንጌል፤ ሙስናን ወንጀል ያደረገ ጽኑ ስርዓተ መንግስት ገነባ። ከራሷ አልፋ ለዓለም የተረፈችዋን የዛሬዋን ቻይና በጽኑ መሰረት ላይ አነበረ። የዛሬዋ ቻይና ከዓለማችን ቁንጮ ልዕለ ሃያል ሀገራት አንዷ ናት። ከራሷ አልፋ ለዓለም ተርፋለች፤ የቻይና ቴክኖሎጂ ምጥቀትና ርቀት ዓለም ጉድ አሰኝቷል። በቅርቡ ሀገረ ቻይናን ከጎበኙ ጋዜጠኞች አንዷ ሆኜ ‘መልክዓ ቻይና’ን በወፍ በረር ቃኘሁ። በዚህ ማስታወሻዬ በቻይና የቴክኖሎጂ ልህቀትና ምጥቀት ላይ ብቻ አተኩራለሁ። ከ1 ነጥብ 4 ቢሊዮን በላይ ህዝብ ባላት፣ በ14 ሀገራት በምትዋሰነው፣ በአንድ ኮሚኒስት ፓርቲ በምትመራው ሀገር ቻይና በነበረኝ የ15 ቀናት ቆይታ ቻይና እንደ ጥንተ ታሪኳ ሁሉ በዘመኑ የቴክኖሎጂና ፈጠራ ላይ ያላትን የመራቀቅ ጥግ ታዘብኩ። ዛሬን ብቻ ሳይሆን ነገን የመቅደም እሽቅድድሟ ‘አጃይብ’ ያሰኛል። በሀገሪቷ ርዕሰ መዲና ቤጂንግ እና በማዕከላዊ ቻይዋ በምትገኘው የሁናን ግዛት ዋና ከተማ ቻንግሻ ምልከታዬ ቻይና ’ከተባለላት በላይ’ የቴክኖሎጂ ምጥቀቷ አስደንቆኛል። ምናልባትም የመጀመሪያ ጉዞዬ መሆኑም ነገሩን በአንክሮት እንድመለከት ሳያስገድደኝ አልቀረም። የሀገሪቷ ርዕሰ መዲና ቤጂንግ እና ጥንታዊቷ ቻንግሻ ከ22 ሚለዮን የሚልቅ ህዝብ በጉያዋ የታቀፈችው ታላቋ ቤጂንግ ከተማ ከዓለማችን ግንባር ቀደም የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የባህል፣ የቱሪዝምና የዲፕሎማሲ ማዕከላት አንዷ ናት። የአዲስ አበባ እህት ከተማ በዚህ ወቅት ሞቃታማ አየር ጸባት አላት። ቤጂንግ የ21ኛው ክፍል ዘመን የኪነ ህንፃና ክትመት ቴክኖሎጂ ያበበች ብቻ አይደለችም፤ ይልቁኑም በዛፎች ሀመልማላዊ ገጽታ የተላበሰች ውብ መዲና እንጂ። በሕንፃዎችም፣ በዛፎችም የተደነነች ከተማ። በተፈጥሮ የበቀሉ የሚመስሉ ሰማይ ታካኪ ሕንጻዎች፤ የመንገድ መሰረተ ልማት ስፋት፣ ጽዳትና ጥራት ‘ኩልል’ ያለች፣ ‘ምልል’ የምታደርግ ከተማ ያደርጋታል። ቤጂንግ ከተማ ከዘመናችን አስደናቂ የቴክኖሎጂ ውጤቶች አንዱ በሆነው የሰው ሰራሽ አስተውሎት(አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ) ሕይወትና ኑሮን እንዴት እንዳቃለለ የቤጂንግ የዕለት ከዕለት ክዋኔ ሁነኛ ማሳያ ነው። ቻይኖች በሰው ሰራሽ አስተውሎት ተጠበዋል፤ መጠበብ ብቻም ሳይሆን ኑባሬያቸውን ሰው ሰራሽ አስተውሎት መር አድርገዋል። ከሮቦት መስተንግዶ እስከ ሰው ሰራሽ ፀሐይ መራቀቅ ይስተዋላል። ካረፍኩበት ሆቴል (15ኛ ወለል ላይ ከሚገኘው መኝታ ክፍሌ) ሆኜ ያዘዝኩት ምግብ በቅጽበት አስተናጋጇ ‘ከች’ ብላ ትደውላለች። ፍጥነቷ ስትገረም፤ አስተናጋጆች ሮቦቶች መሆናቸውን ስትመለከት ይበልጥ ትደነቃለለህ። በክፍሌ ውስጥ ማብሪያ ማጥፊያ ስጫን መጋረጃው ሲከፈት መደንገጤን አልሸሽግም፣ ከምሽቱ 3 ሰዓት ፀሐይ አለመጥለቋን ስመለከት ‘የቻይና ሰው ሰራሽ ፀሐይ ወጣች እንዴ?’ ማለቴ አልቀረም። በነገራችን ላይ የቻይና የሰው ሰራሽ ፀሐይ ሳይንሳዊ ፈጠራ ሁለት ግዜ ተሞክሮ ያለምንም እንከን እንደሚሰራ ነግረውናል። የሰው ሰራሽ ፀሐዩ ሃይድሮጅን እና ዱተሪየም ጋዞችን እንደ ሀይል ማመንጫ ነዳጅነት በመጠቀም ንጹህ ኢነርጂን ለማመንጨት ታስቦ ዲዛይን እንደተደረገና ሰው ሰራሽ ፀሐይ በርሐን ከተፈጥሮ ፀሐይ 13 እጥፍ ያክል ሙቀት እንደሚያመነጭም ሰምተን ተደንቀናል። የቻይና ሰው ሰራሽ ፀሐይ ፕሮጀክት የሥራ ሰዓትን ከ13 ሰዓት ወደ 24 ሰዓት ለመጨመርና ምርታማነትን ለማሳደግ ግብ የሰነቀ ነው። በቻይና በሰዉ ቅርፅ የተሰሩ ሮቦቶች በእግር ኳስ ጨዋታዎች ተወዳጅነት አትርፈዋል። ቤጂንግ የሚገኘው ሂዩማኖይድ የተሰኘ የሮቦት ቡድን የሰራቸው ሮቦቶች አመርቂ ውጤት ከራቀው የሀገሪቷ እግር ኳስ ቡድን ይልቅ የሀገሬውን ቀልብ እንደሳቡ ይነገራል። በሰው ሰራሽ አስተውሎት በታገዘ የሮቦቶች ውድድር አያሌ ቻይናዊያን ይታደማሉ። ሮቦቶቹ በጨዋታ መሐል ቢወድቁ በራሳቸውን ይነሳሉ፤ ቢጎዱም ከሜዳ የሚወጡበት ስርዓት ተዘርግቷል። የታላቋ ቻይና ሰዎች ቴክኖሎጂን ከችግር መፍቻነት ወደ መዝናኛነትም አልቀውታል። በሀገራችን እንደ አዲስ ቴክኖሎጂ በንግዱ ስርዓት ውስጥ እየተዋወቀ ያለው የፈጣን ምላሽ መለያ ወይም ኪው አር ኮድ(Quick Response code) በቻይና ዕለታዊ ከዋኔዎች ቅንጦት አይደለም። በቻይና ማንኛውም ግልጋሎት በዚህ በዲጂታል ስርዓት ይከወናል። እንደሌሎች ስልጡን ሀገራት ሁሉ በንክኪ የሚደረግ ገንዘብ ዝውውር ቀርቷል። በቤጂንግ ጎዳናዎች በኪው አር ኮድ(QR Code) በሚንቀሳቀሱ ሞተር ሳይክሎችን በየመንገዱ ተሰድረዋል፤ የፈለገ መንገደኛ ሳይክሎችን በመጠቀም ወደ ፈለገበት ስፍራ ተንቀሳቅሶ ክፍያውን በኪው አር ኮድ ከፍሎ ይሄዳል። ሌላውም እንዲሁ። በአዲስ አበባ መኖሪያ ሰፈሬ የነበሩ ሳይክሎኝ ከደጃችን ደብዛቸው እንደጠፋ ሳስብ በቻይኖች ብልሃት፣ ታማኝነትና የከተሜነት ልህቀት ቀናሁ። በርግጥ በቻይና ኪው አር(QR) ኮድ ለተገለገልንበት መክፈያ ብቻ ሳይሆን ለልመናም መዋሉን ሲመለከቱ ፈገግ ሊሉ ይችላሉ። በቻይና ይህም አለ በማለት። በርግጥ በቤጂንግ የሰው እጅ ከሚያይ ይልቅ ጆሮቸውን ቢቆጥርጣቸው የሚሰሙ የማይመስሉ አዛውንቶች ሳይቀር በስራ ላይ ተጠምደው ይስተዋላሉ። ከቻይናውያን ጋር ለመግባባት በተለይም በንግድ ማዕከላት የቻይንኛ ቋንቋ መረዳት ግድ ይላል። “ሃው ማቺ፣ ጉዳ ጉዳ፤ ሺሼ፣ ኢ፣ አር…” እና መሰል ቃላት ማወቅ ይበጃል። ከዚህ ባለፈ በምልክት መግባባት አልያም በቋንቋ ተርጓሚ መተግበሪያ መጠቀም ያሻል። የቻይና ሰራሽ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ምርቶች በራሳቸው ብራንድ፣ ቋንቋና መልክ እየተመረቱ በተመጣጣሽ ዋጋ ለህዝቦቿ ተደራሽ እየተደረጉ ነው። የቻይና የራስ-በቅነት ጥረት ያስቀናል። በቴክኖሎጂ፣ በባሕልና በኢኮኖሚ ተጽዕኖ ተላቀው በራሳቸው ለመቆም የሄዱበት ርቀት ግሩም ነው። ግብይቶች በራሳቸው ገንዘብ ብቻ ይከወናል። በወቅቱ ምንዛሬ አንድ የአሜሪካ ዶላር ሰባት የቻይና ገንዘብ(ዩዋን) ነው። ከምዕራባዊያን ማህበራዊ ትስስር ገጾች(ለምሳሌ ፌስቡክ፣ ቴሌግራም፣ ዩቲዩብ፣ ቲክቶክ) በሕግ በማገድ የራሳቸውን መተግበሪያ አበልጽገው ገቢራዊ አድርገዋል። ‘ዊቻት’ የተሰኘው መተግበሪያ ሁሉም ቻይናውያን መገልገያ ነው። ከቤጂንግ ሌላ ያስደነቀችኝ ጥንታዊቷ ቻንግሻ ከተማ ነች። ቻንግሻ ስመ-ብዙ ነች። ከሶስት ሺህ ዓመታት በላይ ዕድሜ ጠገቧ የሁናን ግዛት ርዕሰ መዲና ቻንግሻ ‘የከዋክብት ከተማ’ ትሰኛለች። በነገራችን ላይ ማኦ ዘዶንግ ትውልዱ ሁናን ግዛት ውስጥ ነው። ቻንግሻ በስራ ከተማነቷ ‘የማታንቀላፋው መዲና’ ትባላለች። በመዝናኛ ስፍራነቷ ‘የተዝናኖት መነሃሪያ’ የሚል ተቀጥላ ስም አላት። ‘የሚዲያ ጥበብ’ ስፍራም ትሰኛለች። በኢንዱስትሪ፣ በጥንታዊ ሐውልቶች፣ አብያተ መቅደሶች፣ ታሪካዊ ስፍራዎች መገኛ በመሆኗ በቱሪስቶች ተወዳጅ ከተማ ናት። ትናንትና ዛሬን ያዋደደች፣ ታሪክና ባህል ባዛነቀችዋ ቻንግሻ የአምስት ቀናት ቆይታዬ ብዙ ገጽታዋ አስደምሞኛል። የሻንግ ወንዝን ተንተርሳ፣ በተራራማ፣ በሜዳማና ኮረብታማ መልክዓ ምድር በማዛነቅ የተቆረቆረች በመሆኗ የስብት ማዕከል ሆናለች። እንደ ቤጂንግ በደን የተከበበች፣ በዘመነኛ ሰማይ ጠቀስ ሕንፃዎች እና በታሪካዊ ኪነ ሕንጻዎች የተጌጠች ከተማ ናት። ከዚህ ባሻገር የአምራች ኢንዱስትሪዎች መናገሻም ናት። የምቹ ከተሜነትና ጠንካራ የስራ ባህል በግላጭ የሚስተዋልባት ከተማ። የዓለማችን ገዙፉ በጣም ሞቃታማ አየር ጸባይ ባላት ቻንግሻ ሌት ከቀን ይሰራል። ፋብሪካዎቿ አይተኙም። ሌትና ቀኑ የሚታወቀው በሰዓት ብቻ እንጂ የስራና የንግድ ድባቡ እኩል ነው። ብርሃናማዋ ቻንግሻ ‘የቻይዊያን መስቀል’ በተሰኘው በቀይ በተቀለመው መስቀልም ትታወቃለች። በርግጥ ከዓለማችን ግዙፍ ማማዎች አንዱ የሆነው ሕንጻም መገኛ ናች። በጥቅሉ የቻይና ጉብኝት ትዝብቴ የገናና ታሪክ ባለቤቷ ሀገር ከባድ ውጣ ውረዶችን አልፋ ዛሬ ዓለምን እየቀደመች መሆኑን ሳስብ፤ እንደቻይና ሁሉ የሺ ዘመናት ገናና ታሪክና አኩሪ ገድል ያላት ኢትዮጵያስ የሚል ተጠየቅ እንዳውጠነጥን አድርጎኛል። ቻይናዊያን የዘመን የፈተና ቋጠሮዎቻቸውን ፈታተው ከዛሬ ከፍታ ሰገነት ላይ ወጥተዋል። ከዛሬም በበለጠ ነገን በጽኑ መሰረት ላይ እየገነቡ ነው። እኛስ? ብዬ ሳስብ በቁጭትና በተስፋ ተዋጥኩ! ሰላም!
በ17ኛው የብሪክስ ጉባኤ ላይ መሪዎቹ ምን አሉ?
Jul 7, 2025 150
በ17ኛው የብሪክስ ጉባኤ ላይ መሪዎቹ ምን አሉ? 17ኛው የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ በብራዚል ሪዮ ዴጄኔሮ እየተካሄደ ይገኛል ጉባኤው እየተካሄደ የሚገኘው “ ሁሉን አቀፍ እና ዘላቂ የደቡብ ንፍቀ ዓለም” በሚል መሪ ሀሳብ ነው። በጉባኤው ላይ ተሳታፊ የሆኑ የብሪክስ አባል እና አጋር ሀገራት መሪዎች እና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች በዓለም አንገብጋቢ እና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ሀሳባቸውን ሰንዝረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ብሪክስ ከጠንካራ አዲስ ሀሳብ ተነስቶ ለዓለም አቀፍ ለውጥ የሚሰራ ብርቱ ኃይል ወደመሆን ተሸጋግሯል። ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት የጋራ ደኅንነትን እና ሁሉን አካታች ብልጽግናን ለማምጣት በሚያስችል ሁኔታ አፋጣኝ ማሻሻያ ማድረግ አለባቸው። በብሪክስ አዳዲስ አባላት መጨመራቸው የጋራ ድምፃችን የበለጠ ይጠናከራል። የጋራ አላማችን የበለጠ ይጠራል። አቅማችንም ይሰፋል። እንደ ብሪክስ አባልነቷ ኢትዮጵያ እነዚህ ጥረቶች እንዲሳኩ በተለይም በአለምአቀፍ ውሳኔ ሰጪ መድረኮች ለአዳዲስ ገበያዎች እና በማደግ ላይ ላሉ ሀገራት ሰፋ ያለ ውክልና በሚገኝበት ሁኔታ ላይ በንቃት አስተዋፅኦ ታደርጋለች። የብራዚል ፕሬዝዳንት ሉዊስ ኢግናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ የዓለምን የአስተዳደር ስርዓትን ለመቀየር የሚያስችል መሰረተ ልማትና የጋራ ትብብራችንን ማጠናከር ይገባል። ብሪክስ ለ21ኛው ክፍለ ዘመን የሚሆን አዲስ የብዝሃ ዓለም አስተዳደር የመፍጠር ቁልፍ ሚና አለው። ከጦርነት ይልቅ ሰላም ላይ መዋዕለ ንዋይን ማፍሰስ ትርፋማ ያደርጋል። የበለጸጉ ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ቃል የገቡትን ገንዘብ መስጠት አለባቸው። የቻይና ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኪያንግ ብሪክስ በዓለም ፍትሃዊ እና መርህን ያከበረ የዓለም ስርዓት እንዲፈጠር የመሪነት ሚናውን መወጣት አለበት። ለብሪክስ ሀገራት የኢኮኖሚ እድገት ልማት ትልቅ ድርሻ ያለው የእድገት ምሰሶ ነው። በብሪክስ ሀገራት መካከል ያለውን የባህል ልውውጥ እና የጋራ መማማር የበለጠ ማሳደግ ይገባል። ብሪክስ በዓለም ደረጃ ያሉ ግጭቶች በውይይት እና በንግግር እንዲፈቱ በማድረግ የሰላም ኃይል መሆኑን በተጨባጭ ማሳየት ይኖርበታል። የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን (በበይነ መረብ) ሊበራሊዝም መር የሆነው የዓለም የሉላዊነት አስተዳደር ስርዓት ጊዜው አልፎበታል፤ አዲስ የባለብዝሃ የዓለም ስርዓት እያቆጠቆጠ ነው። በማደግ ላይ የሚገኙ ሀገራት በራሳቸው ገንዘብ የመገበያያት ልምምዳቸውን ማጠናከር አለባቸው። የብሪክስ ሀገራት በተፈጥሮ ሀብት፣ ሎጅስቲክስ፣ ንግድ፣ ፋይናንስ እና በሌሎች መስኮች ያላቸውን ትብብር ማጠናከር አለባቸው። በሚሸፍነው መልክዐ ምድር፣ በያዘው የህዝብ ብዛት እና በዓለም ኢኮኖሚ ውስጥ ባለው ድርሻ ብሪክስ ትልቅ ኃይል ሆኗል። የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ዓለም አቀፍ ተቋማት የደቡብ ንፍቀ ዓለምን ፍትሃዊ ውክልና በሚያረጋገጥ መልኩ ሁሉን አቀፍ ሪፎርም ሊደረግበት ይገባል። የ21 ክፍለ ዘመን ሶፍትዌር በ20ኛ ክፍለ ዘመን የታይፕ ራይተር ማሽን ላይ ግልጋሎት ሊሰጥ አይችልም። የሰው ልጅ እና የዓለማችን የምንግዜውም ትልቅ ስጋት ሽብርተኝነት ነው። ሽብርተኝነት መከላከል እና ማውገዝ የሁሉም የጋራ ኃላፊነት ነው። የሰው ሰራሽ አስተውሎት ኃላፊነት በተሞላበት መልኩ መጠቀም እና ማስተዳደር በጣም አስፈላጊ ነው። ህንድ በዓለም ደረጃ ያሉ አለመግባባቶች በዲፕሎማሲ፣ በሰላም እና በንግግር እንዲፈቱ በቁርጠኝነት ትሰራለች። የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ስሪል ራማፎሳ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ወቅታዊ የዓለም ነባራዊ ሁኔታን መሰረት ያደረገ አፋጣኝ ማሻሻያ ያስፈልገዋል። ብሪክስ ዓለም አቀፍ የጂኦ ፖለቲካ ውጥረቶችን ለመፍታት፣ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን እና አሳታፊ የደህንነት ማዕቀፎችን ማረጋገጥ የሚያስችል የጋራ አሰራር መፍጠር አለባቸው። ደቡብ አፍሪካ የብሪክስ የፀረ-ሽብርተኝነት ስትራቴጂ ውጤታማ በሆነ ሁኔታ ለመተግበር ቁርጠኛ ናት። የብሪክስ መስፋት ንግድ ፣ ቴክኖሎጂ ሽግግር እና አረንጓዴ ኢኮኖሚን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች አዳዲስ የትብብር አማራጮችን ይፈጥራል። የኢንዶኔዥያ ፕሬዝዳንት ብራቦዎ ሱቢያንቶ ብሪክስ በደቡብ-ለደቡብ ሰላም፣ ደህንነት፣ ሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ የዓለም ጤና እና የከባቢ አየር ትብብር ወሳኝ ሚና እየተጫወተ ነው፡፡ የዓለም የብዝሃ ወገን ተቋማት እኩልነትን ይበልጥ የሚያረጋግጥ ለውጥ ያስፈልጋቸዋል። በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ አማካኝነት በብሪክስ እና በምዕራቡ ዓለም መካከል ሚዛናዊ ትብብር መፍጠር ይገባል። በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ኢ-ፍትሃዊ አካሄድ እና ጦርነት እንደ አማራጭ መጠቀም ሊቆም ይገባል። ዓለም አቀፍ ፍትህ እና ሰላምን ማስፈን ጊዜ ሊሰጠው የማይገባ ጉዳይ ነው። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ዓለም ከምንጊዜውም በላይ ሰላም ያስፈልጋታል። ግጭቶችን በውይይት እና በንግግር መፍታት አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው። የሰውን ህይወት እና ኢኮኖሚ በፍጥነት እየቀየረ ያለውን የሰው ሰራሽ አስተውሎትን ለእኩይ አላማ እንዳይውል በከፍተኛ ኃላፊነት እና ጥንቃቄ መጠቀም ይገባል። ብዝሃ ዓለም የባለብዝሃ ወገን አስተዳር ስርዓት ያስፈልገዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት እና የዓለም የፋይናንስ መዋቅርን ጨምሮ የዓለም የአስተዳደር ስርዓት ከጊዜው ጋር ተራማጅ መሆን አለበት። በማደግ ላይ የሚገኙ ሀገራት በዓለም ኢኮኖሚ እና አስተዳደር ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎ የበለጠ ማሳደግ ይገባል። ሁለተኛ ቀኑን የያዘው 17ኛው የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።