መነሻ - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
ከለውጡ ወዲህ ለሀገር መከታና ደጀን የሆነውን የሀገር መከላከያ ሰራዊት ለማጠናከር በመንግስት ቁርጠኛ አቋም ተወስዶ እየተሠራ ነው--ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
Apr 1, 2023 47
አርባ ምንጭ፣ መጋቢት 23/2015(ኢዜአ)፦ ከለውጡ ወዲህ ለሀገር መከታና ደጀን የሆነውን የሀገር መከላከያ ሰራዊት ለማጠናከር በመንግስት ቁርጠኛ አቋም ተወስዶ እየተሠራ መሆኑን የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገለጹ። በለውጡ ማግስት በልዩ ትኩረት የተጀመረውን ሪፎርም በማጠናከር የሰራዊቱን ህይወት የሚለውጡ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አመልክተዋል። የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በጋሞ ዞን ምዕራብ አባያ ወረዳ ለደቡብ ዕዝ አገልግሎት የሚሰጡ ዘመናዊ ግንባታዎችን ዛሬ አስመርቋል። ከግንባታው መካከል የኮርና ሻለቃ ጠቅላይ የሠራዊት መኖሪያ ካምፕ ይገኝበታል። በምረቃው ላይ የተገኙት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እንዳሉት፤ ከለውጡ ወዲህ ለሀገር መከታና ደጀን የሆነውን የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ለማጠናከር በመንግስት ቁርጠኛ አቋም ተወስዷል። በተለይም የሀገርን ዳር ድንበርና የህዝብ ሠላም ለማደፍረስ የሚንቀሳቀስን ኃይል ለሚመክት ሰራዊት የተሻለ ቦታ ማዘጋጀት ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል። ባለፉት ሁለት አመታት የሰራዊቱን ህይወት የሚለውጡ የአቅም ግንባታ ሥራዎች በመከላከያ ጠቅላይ መምሪያ በልዩ ትኩረት መከናወናቸውን ገልጸው፤ ዛሬ የተመረቀው የኮርና ሻለቃ ጠቅላይ መምሪያ አንዱ ማሳያ መሆኑን ለአብነት አንስተዋል። እንደሀገር የመጣውን የለውጥ ሂደት ያልፈለገው ኃይል መልኩን እየቀያየረ የሀገርን ሰላም ለመናድ ያደረገውን ሙከራ ለማክሸፍ ሰራዊቱ ያበረከተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ተናግረዋል። በተለይም በህዝቦች መካከል ግጭት ለመፍጠርና ግጭት በማባባስ ሀገር ለማፍረስ የተደረገውን ጥረት በማምከን ረገድ ሰራዊቱ ሃላፊነቱን በብቃት መወጣቱን ገልጸዋል። አንዳንዶች ያልተፈለገ መርዝ በህዝብ መካከል ከረጩና ለውጭ ኃይል ጭምር በር ከከፈቱ በኋላ ሰራዊቱን በወገንተኝነትና በብሄር ፍረጃ ይከሳሉ በማለት ገልጸው፤ ይህን ለማስቀረት ሀገርን የሚወክል ሰራዊት ለመገንባት ውጤታማ ስራ መሰራቱን ተናግረዋል። የሀገርን ህልውና ለማስቀጠል ሠራዊቱ ጠንካራ ዝግጅት ያለው መሆኑን ገልጸው፤ ሰራዊቱ የክፉ ቀን ምሽግና የሀገር አለኝታ ነው ብለዋል። ሀገርን ለመጠበቅ በተጠንቀቅ ላይ የሚገኘውን የሀገር መከላከያ ሰራዊት ስም ለማጠልሸትና ለማፍረስ መጣደፍ የጠላትነት ተግባር መሆኑንም አስገንዝበዋል። ሰራዊቱ የታነጸበት ጀግንነት ዲሲፒሊንና ህዝባዊ ወገንተኝነት በዓለም አቀፍ ደረጃ የተመሰከረ መሆኑን ተናግረዋል። መከላከያ ሰራዊቱ ከግዳጅ በሚመለስበት ወቅት ማረፊያ እንዲኖረው ለማስቻል የሚሰሩ ሥራዎች በልዩ ትኩረት የሚቀጥል መሆኑን ተናግረው ሁሉም የሚጠበቅበትን ርብርብ ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል። በሪፎርሙ በ10 ዓመት መሪ ዕቅድ እንደተመላከተው ሰራዊቱ በዘመናዊ ካምፕ እንዲኖር የማድረግ ግብ ተጥሎ እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል። የመከላከያ መሀንዲስ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል ደስታ አቢቼ በበኩላቸው ሀገር የገጠማትን ፈተና እንድትሻገር እያደረገ እንደሆነ አመልክተዋል። በዓለም አቀፍ ተልዕኮ አንጻር በቱሪኪዬ በደረሰው ርዕደ መሬት የደረሰውን አደጋ ለመቀልበስ ሰብአዊ ስራ ላይ በመሳተፍ ወደር የሌለው አጋርነት ማሳየቱን ተናግረዋል። ከለውጡ ማግስት ጀምሮ የሰራዊቱን አቅም ከፍ ለማድረግ ግዳጅን በብቃት ከመወጣት ባሻገር ህይወት ለዋጭ ተግባራት ላይ በማተኮር እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፤ ዘመናዊ አገልግሎት ሰጪ ፕሮጀክቶች ግንባታ በመካሄድ ላይ መሆኑን ተናግረዋል። በመርሃ ግብሩ ላይ የመከላከያ መኮንኖች የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ዘውዴና የጋሞ ሀገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል።
የነዳጅ ግብይቱን ወደ ዲጂታል በመቀየር በአቅርቦትና ስርጭት ላይ የሚታዩ ችግሮችን ለማቃለል እየተሰራ ነው
Apr 1, 2023 26
ጋምቤላ፣ መጋቢት 23 ቀን 2015 (ኢዜአ) በሀገሪቱ ሁሉም አካባቢዎች የነዳጅ ግብይቱን ወደ ዲጂታል በመቀየር በነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት ላይ የሚታዩ ችግሮችን ለማቃለል እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታወቀ። ባለስልጣኑ ከጋምቤላ ክልል የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር በነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት መመሪያዎችና ሌሎችም ጉዳዮች ዙሪያ በጋምቤላ ከተማ ተወያይቷል። የባለስልጣኑ የነዳጅ ውጤቶች ግብይት ስታንዳርድ ጥናትና ምርምር ዳይሬክተር አቶ ለሜሳ ቱሉ በውይይቱ ላይ እንዳሉት፤ ነዳጅ በከፍተኛ የውጪ ምንዛሬ እየመጣ ቢሆንም በአቅርቦትና በስርጭት ችግር ለብክነት እየተዳረገ ነው። በነዳጅ ላይ በተካሄደ ከፍተኛ ቁጥጥር የነዳጅ ኮንትሮባንድን 70 በመቶ ያህል መቀነሰ መቻሉን ጠቅሰው፤ አሁንም በተለያዩ አካባቢዎች የቤንዚን ኮንትሮባንድ ንግድ መኖሩን ጠቁመዋል። ችግሩን ለማስቀረት በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች የነዳጅ ግብይት ሰንሰለቱን ሙሉ በሙሉ ዲጂታል በማድረግ በነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት የሚታየውን ክፍተት ለመሙላት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የዲጂታል ግብይቱ በሙከራ ደረጃ በአዲስ አበባ መተግበር መጀመሩን ጠቁመው፤ ከግንቦት ወር 2015 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም ክልሎች ስራ ላይ የሚውል ይሆናል ብለዋል። ከዚህም በተጨማሪ በቦቲዎችና በማደያዎች ላይ የርቀት መቆጣጠሪያ መሳሪያ (ጂፒኤስ) በመግጠም የአቅርቦቱንና የስርጭቱን ሂደት ለመቆጣጠር እየተሰራ እንደሆነ ገልጸው፤ እስካሁን ከሶስት ሺህ በሚበልጡ ቦቲዎች ላይ ጂፒኤስ መገጠሙን ጠቁመዋል። ከክልሉ ባለድርሻ አካላት በነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት መመሪያ ዙሪያ ውይይት ማድረግ ያስፈለገው የጠራ ግንዛቤ በመፍጠር የክትትልና ቁጥጥር ስራውን ለማጠናከር በማለም እንደሆነ ተናግረዋል። የክልሉ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኢንጂነር ኡሌሮ ኦፒዮው በበኩላቸው የነዳጅ የጥቁር ገበያ እየተስፋፋ መሆኑን ተናግረዋል። ለጥቁር ገበያ መስፋፋት ዋነኛው ምክንያት ማደያ በሌለባቸው አካባቢዎች ለችርቻሮ በበርሜል ተቀድቶ መሄዱ እንደሆነ ገልጸው፤ በዚህ ሁኔታ ነዳጅ ከተመኑ በላይ በእጥፍ በመሸጡ እንደሆነ አመልክተዋል። አሁን ላይ ችግሩን ለመከላከል እየተደረገ ባለው የክትትልና የቁጥጥር ስራ በጀሪካንና በበርሜል በህገ ወጥ መንገድ ይዘው የተገኙ አካላትን በህግ ተጠያቂ የማድረግ ስራ እየተከናወነ ነው ብለዋል። በጋምቤላ ከተማ ከትናንት ጀምሮ ለሁለት ቀናት በቆየው የውይይት መድረክ ከክልል እስክ ወረዳ የሚገኙ የንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ፣ የጽህፈት ቤት አመራሮች፣ ባለሙያዎችና የማደያ ባለንብረቶች ተሳትፈዋል።
በድሬዳዋ አስተዳደር የጎርፍ አደጋን ለመከላከል የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ - ከንቲባ ከድር ጁሃር
Apr 1, 2023 26
ድሬዳዋ፣ መጋቢት 23/2015(ኢዜአ)፦ በድሬደዋ አስተዳደር ጎርፍን በዘላቂነት ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተጀመሩ ስራዎች በትኩረት እንደሚሰሩ ከንቲባ ከድር ጁሃር አስታወቁ። በከንቲባው የተመራ የአስተዳደሩ ካቢኔ አባላት በጎርፍ የተጎዱ መሠረተ ልማቶችን ዛሬ ተዘዋውረው ተመልክተዋል። በጎርፉ የደረሰውን ጉዳት መልሶ ለማቋቋምና ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን አካላት ለመለየት ኮሚቴ ተዋቅሯል። ከምልከታው በኋላ በአስተዳደሩ ባለፉት 15 ዓመታት ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የጎርፍ አደጋን ለመቀነስና ለመከላከል በሶስት ደረቅ ወንዞች ላይ የተሰሩት የመከላከያ ግንቦች ተጨባጭ ለውጥ እያመጡ መሆናቸውን ከንቲባ ከድር ጁዋር ገልጸዋል። በተለይም በገጠር ቀበሌዎች ለ10 ዓመታት የተከናወኑ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ሥራዎች ጎርፍ በማሳዎች ላይ ሲያደርስ የነበረውን ችግር በማቃለል ውሃውን ለመስኖ ልማት ማዋል ተችሏል ብለዋል። በአስተዳደሩ እየተሰሩ ያሉትን ስራዎች በማጠናከር የጎርፍ አደጋን ለመከላከል የተቀናጀ ስራ እንደሚሰራ ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት እየጣለ የሚገኘው ዝናብ ያስከተለው ጎርፍ በከተማው የመጠጥ ውሃ መሠረተ ልማቶች፣ በጎርፍ መውረጃ ቦዮች፣ በጎርፍ መከላከያ ግንቦችና ማሳዎች ላይ ጉዳት ማድረሱን ጠቁመዋል። ጉዳት የደረሰባቸውን መሰረተ ልማቶች መልሶ ለመጠገንና የጎርፍ አደጋን ለመከላከል አስተዳደሩ ኮሚቴ አዋቅሮ መፍትሄ የሚሆኑ ስራዎች ይከናወናሉ ብለዋል። የድሬዳዋ መንገዶች ባለስልጣን ስራ አስኪያጅ አቶ ብሩክ ወርቅነህ የጎርፍ ስጋት ያለባቸውን የማህበረሰብ ክፍሎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ከተቋቋመው ኮሚቴ ጋር በመሆንም በጎርፍ የተበላሹና የተሰበሩ መሠረተ ልማቶችን መልሶ የመጠገን ስራ ይከናወናል ብለዋል። የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የምስራቅና መካከለኛ ኦሮሚያ ሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት ማዕከል በምስራቅ የአገሪቱ ክፍል እየጣለ የሚገኘው ዝናብ ጎርፍ ሊያስከትል ስለሚችል ነዋሪዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ማሳሰቡ ይታወሳል።
መምህራን ትውልድን በመልካም ሥነ-ምግባርና በእውቀት ለማነጽ የሚያከናውኑትን ተግባር አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ ቀረበ
Apr 1, 2023 29
አዲስ አበባ መጋቢት 23/2015(ኢዜአ)፦ መምህራን ትውልድን በመልካም ሥነ-ምግባርና በእውቀት ለማነጽ የሚያከናውኑትን ተግባር አጠናክረው እንዲቀጥሉ የኦሮሚያ ክልል ጠየቀ። የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ከመጋቢት 18 እስከ 23 ቀን 2015 ዓ.ም "የትምህርት ለውጥ ከመምህራን ይጀምራል" በሚል መሪ ሃሳብ የመምህራን ሳምንት ማጠቃለያ መርሃ-ግብር አካሂዷል። በመርሃ ግብሩ ከቅድመ መደበኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለሚያስተምሩ መምህራን በጡረታ የተገለሉትን ጨምሮ ለአመራሮች የሜዳሊያ፣ የገንዘብ ሽልማትና የሰርተፊኬት እውቅና ተሰጥቷል። በእውቅና መርሃ ግብሩ በዘንድሮው አገር አቀፍ ፈተና ላይ ተማሪዎች ጥሩ ውጤት እንዲያመጡ ለሰሩ የትምህርት ማህበረሰብ አካላት እውቅናና ሽልማት ተሰጥቷል። የክልሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ክላስተር አስተባባሪ አቶ አብዱልሃኪም ሙሉ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት መምህራን አዲሱን ትውልድ በማነጽና የአገር ግንባታ ላይ በመሳተፍ ኃላፊነታቸውን መወጣት ይጠበቅባቸዋል። ''የሁሉም ሙያዎች መፍለቂያ መነሻ የሆነውን የመምህርነት ተግባር እውቅና መስጠት አገርን ማክበር በመሆኑ ለመምህራን ትልቅ ክብር ይገባቸዋል'' ነው ያሉት። በዚህም መሰረት ክልሉ ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ ለመምህራን የእውቅና ሽልማት በመስጠት ለባለሙያዎቹ ያለውን ክብር ማሳየቱን ገልጸዋል። የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር በሪሶ ቶላ በበኩላቸው የሁሉም ሙያዎች ቀዳሚ የሆነው መምህርነት በመሆኑ ለባለሙያው ትልቅ ክብር መስጠት ተገቢ ነው ብለዋል። ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዲከታተሉና እውቅትን እንዲገበዩ መምህራን ኃላፊነታቸውን ለመወጣት በርካታ ተግባራትን እያከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል። በክልሉ የሚገኙ መምህራንን አቅም ለማሳደግ እንዲሁም ምቹ የኑሮ ሁኔታ እንዲፈጠርላቸው ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ሲሉም ጠቁመዋል። እውቅናና ሽልማት የተሰጣቸው መመምህራን በበኩላቸው የተሰጠው እውቅና ለበለጠ ሥራ የሚያነሳሳቸው መሆኑን ጠቁመዋል። ለመምህራን ትኩረት መሰጠቱ የትውልድና አገር ግንባታ ላይም ትልቅ መነቃቃት ይፈጥራል ብለዋል።
ባለፉት ስምንት ወራት ለታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ተሰብስቧል
Apr 1, 2023 37
አዲስ አበባ መጋቢት 23/2015 (ኢዜአ) ባለፉት ስምንት ወራት ለታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን የግድቡ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት ገለጸ። የጽህፈቱ ቤት የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኃይሉ አብርሃም ለኢዜአ እንደገለጹት ሕዝቡ ለግድቡ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ቀጥሏል። ሕዝቡ በቦንድ ሽያጭና ስጦታ፣ በ8100 አጭር የጽሁፍ መልዕክት፣ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የስጦታ አካውንትና በሌሎች የድጋፍ ማሰባሰቢያ መርኃ-ግብር ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል። ይህንንም ተከትሎ ባለፉት ስምንት ወራት ከተለያዩ የገቢ ማሰባሰቢያ መንገዶች ከ1 ቢሊዮን 41 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን ነው ያረጋገጡት። ሕዝቡ የሚያደርገው ድጋፍ እንዲጎለብት በተለይም ባለፉት ሦስትና አራት ዓመታት በተሰራው ሥራ አበረታች ውጤት መመዝገቡን ገልጸዋል። በዚህም የግድቡ ግንባታ በመልካም የአፈጻጸም ደረጃ ላይ መሆኑን ገልጸው ግድቡ በፍጥነት እንዲጠናቀቅ ድጋፉ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ነው ያሉት። ከመጋቢት 16/2015 ዓ.ም ጀምሮ የገቢ ማሰባሰቢያ ለአንድ ወር የሚቆይ ንቅናቄ መጀመሩን ገልጸዋል። በዚህም 100 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱን ገልጸው ኅብረተሰቡ በመርኃ ግብሩ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን ጠይቀዋል። ጽህፈት ቤቱ የተለያዩ መርኃ ግብሮችን በማዘጋጀት ሕዝቡ ለግድቡ ግንባታ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።
ፖለቲካ

የሀገር ሠላም በአስተማማኝ መሠረት ላይ ጸንቶ እንዲቀጥል ሠራዊቱ ሚናውን አጠናክሮ ይቀጥላል- ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
Apr 1, 2023 121
አርባምንጭ መጋቢት 23/2015(ኢዜአ)፦የሀገር ሠላም በአስተማማኝ ጠንካራ መሠረት ጸንቶ እንዲቀጥል ሠራዊቱ ሚናውን በበለጠ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገለጹ። መከላከያ ሚኒስቴር በጋሞ ዞን ምዕራብ ዓባያ ወረዳ ያስገነባው ዘመናዊ አገልግሎቶችን ያካተተ የኮርና ሻለቃ መምሪያ ካምፕ ዛሬ ተመርቋል። የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት እንዳሉት በተለያየ መልኩ የሀገርን ሠላም ለመናድ የሚደረጉ ፍላጎቶች አሉ። የሀገር ሠላም በጠንካራ መሠረት ላይ ታንፆ እንዲቆም ሠራዊቱ ኃላፊነቱን በበለጠ ብቃት እንደሚወጣም ገልጸዋል። ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ የተገኘውን ሠላም ማጠናከር እንደሚገባ ገልጸው፤ ይሔንን ለማጽናትም ሠራዊቱ እየከፈለ ያለው መስዕዋትነት ሊደገፍ ይገባል ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል። ሠራዊቱ ተልዕኮውን በበለጠ ብቃት እንዲወጣ የሚደረጉ ሁለንተናዊ የግንባታ ሥራዎችም በልዩ ትኩረት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ አረጋግጠዋል።
ከለውጡ በኋላ የተገኘውን ድልና ስኬት ለማስቀጠል ያለመ የድጋፍ ሰልፍ ነገ በመላው ኦሮሚያ ይካሄዳል--የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ
Apr 1, 2023 66
አዲስ አበባ መጋቢት 23/2015(ኢዜአ)-- ከለውጡ በኋላ የተገኘውን ድልና ስኬት ለማስቀጠል ያለመ የድጋፍ ሰልፍ ነገ በመላው ኦሮሚያ እንደሚካሄድ የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ። በኦሮሚያ ክልል በነገው እለት የሚካሄደውን የድጋፍ ሰልፍ አስመልክቶ የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀይሉ አዱኛ ለኢዜአ መግለጫ ሰጥተዋል። አቶ ሀይሉ አዱኛ እንደተናገሩት፤ የድጋፍ ሰልፉ የሚካሄደው ከመጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም ወዲህ በክልሉ የተመዘገቡ ድልና ስኬቶችን ጠብቆ ለማስቀጠል ነው። ከለውጡ በኋላ ባለፉት አምስት ዓመታት በክልሉ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በማሕበራዊና በሌሎች ዘርፎችከፍተኛ ለውጦች ተመዝግበዋል ብለዋል። ስለሆነም በነገው እለት በክልሉ ሁሉም ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች በሚደረገው የድጋፍ ሰልፍ ህዝቡ ድልና ስኬቶችን ለማስቀጠል ቁርጠኝነቱን ያረጋግጣል ብለዋል። በድጋፍ ሰልፉ በነዚህ የለውጥ ዓመታት ያጋጠሙና ወደ ፊትም የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን በአብሮነትና በወንድማማችነት ለመሻገር ቃል የሚገባበት መሆኑንም አስረድተዋል። ሰሞኑን በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ስኬቶችን ማስቀጠል ላይ ያተኮሩ ውይይቶች መደረጋቸውን ያስታወሱት አቶ ሀይሉ፤ በውይይቶቹም ህዝቡ በለውጡ ተጠቃሚ መሆን እንደቻለ አንስቷል ብለዋል። በተለይም በወንድማማችነት፣ በአንድነትና በእኩልነት እንዲሁም በአገር ልማት ላይ ለመሳተፍ ለውጡ በር ከፋች እንደነበረ በውይይቱ ላይ በስፋት መነሳቱን ተናግረዋል። በቀጣይም የክልሉ ሕዝብ ጽንፈኝነትና አክራሪነትን በመታገል በትብብርና በአንድነት በመነሳት ትኩረቱን በልማትና በሰላም ላይ ማድረግ እንዳለበት አስገንዝበዋል። ሰላማዊ ሰልፉን በተሳካ መንገድ ለማካሄድ የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን ዝግጅት ሁሉ ማጠናቀቁን በመግለጽ የክልሉ ሕዝብም የሰልፉ ተሳታፊ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል። የድጋፍ ሰልፉን ለማስተባበር ወጣቶች፣ በጎ ፈቃደኞችና የጸጥታ አካላትም አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጋቸውን ገልጸዋል። የድጋፍ ሰልፉ ነገ መጋቢት 24 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋት 12 ሰዓት ጀምሮ መካሄድ እንደሚጀምርም ተናግረዋል።
ታላቁ ህዳሴ ግድብ በኢትዮጵያዊያን የተባበረ ክንድ የመገባደጃ ምዕራፍ ላይ ደርሷል -- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን
Mar 31, 2023 100
አዲስ አበባ መጋቢት 22/2015(ኢዜአ)፦ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በኢትዮጵያውያን የተባበረ ክንድ የመገባደጃ ምዕራፍ ላይ መድረሱን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ፡፡ አቶ ደመቀ መኮንን የሚመሩት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የግድቡ ግንባታ አፈፃፀምና የመሰረት ድንጋይ የተቀመጠበትን 12ኛ ዓመት በዓል አከባበር በተመለከተ ምክክር አድርጓል፡፡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እንዳሉት፤ ኢትዮጵያዊያን ያለ ልዩነት የግድቡ ግንባታ ከተጀመረበት እለት ጀምሮ ድጋፍ ሲያደርጉ መቆየታቸውን አስታውሰዋል፡፡ ይህም ኢትዮጵያን ከፍ የሚያደርግ አበረታች ውጤት የተመዘገበበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የግድቡ የመሰረት ድንጋይ ከተቀመጠበት ጊዜ ጀምሮ 18 ቢሊዮን ብር በተለያዩ መንገዶች መሰብሰቡን ገልጸው፤ ኢትዮጵያውያንና ፕሮጀክቱን የሚመሩ አካላት ለትውልድ የሚሸጋገር የሚያኮራ ስራ አከናውነዋል ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያውያን ላለፉት 12 ዓመታት በገንዘብ፣ በጉልበት፣ በእውቀትና በሌሎች አግባቦች አስተዋጽኦ በማድረግ ግንባታው በመገባደጃ ምዕራፍ ላይ እንዲደርስ ማድረጋቸውንም ገልጸዋል፡፡ ይሀም "ኢትዮጵያውያን ስናብር ምን ያህል አቅም እንዳለን የሚያሳይ ነው" ብለዋል፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን የግድቡ ግንባታ እስኪጠናቀቅ ከሚያደርጉት ድጋፍ ባሻገር በተግባር በሚለካ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ መሳታፍ እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል፡፡ የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የመሰረት ድርጋይ የተቀመጠበትን በዓል ስናከብር በዲፕሎማሲው መስክ የተጀመሩ ውጤቶችንም ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።፡ ኢትዮጵያ የተጀመረው የሶስትዮች ድርድር በአፍሪካ ማዕቀፍ እንዲቀጥል ፍላጎት እንዳላት ገልጸው፤ አንድን አካል ብቻ ተጠቃሚ የሚያደርግ የኋልዮሽ አካሄድ ተቀባይነት የለውም ብለዋል፡፡ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮጀክት መሆኑንም ነው የተናገሩት፡፡ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ በበኩላቸው ኢትዮጵያውያን ለግድቡ ግንባታ ሲያበረክቱት የነበረው አስተዋጽኦ "ትውልድ የሚያኮራ የነገ ታሪክ ነው" ብለዋል፡፡ በቀጣይም ግድቡ እስኪጠናቀቅ የሚያደረገው ሁለንተናዊ ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ የግድቡ ግንባታ አሁን የደረሰበት ደረጃ ኢትዮጵያ በብዙ ፈተናዎች ውስጥ ሆና የፈጸመችው ታሪካዊ ድል መሆኑን የተናገሩት ደግሞ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ ሚኒስቴር ተስፋዬ በልጂጌ ናቸው፡፡ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከኢትዮጵያ ባለፈ ቀጣናውን በኃይል የሚያስተሳስር የአፍሪካውያን ፕሮጀክት መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
የሚቀረጸው የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ አማራጭ አገርን ከግጭት አዙሪት አውጥቶ አዲስ ምዕራፍ ለመክፈት ያስችላል - ፍትህ ሚኒስቴር
Mar 31, 2023 76
ሚዛን አማን መጋቢት 22/2015 (ኢዜአ) አዲስ የሚቀረጸው የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ አማራጭ አገርን ከግጭት አዙሪት በማውጣት አዲስ ምዕራፍ ለመክፈት እንደሚያስችል የፍትህ ሚኒስቴር አስታወቀ። የፍትህ ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ዓለምአንተ አግደው በሚዛን አማን አተማ እየተካሄደ ባለው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጉባዔ ላይ እንዳመለከቱት፣ መንግሥት ከለውጡ ማግስት ጀምሮ አገራዊ ፈተናዎችን ተቋቁሞ ለማለፍ እየሰራ ነው። የቆዩ በደሎች፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እና ቁርሾዎችን በተጠያቂነት እንዲሁም በዕርቅና በይቅርታ በመዝጋት ከግጭት አዙሪት ወጥቶ አዲስ ምዕራፍ ለመክፈት አዲስ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ለመቅረጽ እንቅስቃሴ መጀመሩን ገልጸዋል። ለዚህም የፖሊሲ ግብዓቶችን የማሰባሰብ ሥራ እየተሰራ መሆኑን የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታው፣ ለሽግግር ፍትህ መሳካት ሁሉም አካላት ርብርብ እንዲያደረጉ ጠይቀዋል። ከለውጡ ማግስት ከሀገር ውስጥና ከውጭ የገጠሙን ፈተናዎች ብዙ ዋጋ እንዳስከፈሉ የገለጹት አቶ ዓለምአንተ፣ "በሰሜኑ የነበረው ጦርነት በሰላም ስምምነት መቋጨቱ ብስለት የተሞላበትና የአመራር ጥበብ የታየበት" ነው ብለዋል። "ስምምነቱ ኢትዮጵያን አሸናፊ ከማድረግ ባሻገር ታሪካዊ ጠላቶችን አንገት ያስደፋና እኩይ ዓላማቸውን ያመከነ ነው" ብለዋል። መንግስት የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታትና ሙስናን ለመታገል በቁርጠኝነት የጀመራቸው ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ መረባረብ እንደሚገባም ሚኒስትር ዴኤታው ገልጸዋል። "ወሳኝ የአገር ግንባታ ምዕራፍ ውስጥ በመሆናችን ለለውጡ ስኬትና አገራዊ ወንድማማችነት መጎልበት በትኩረት መስራት ያስፈልጋል" ብለዋል። የአገራዊ የምክክር ኮሚሽን ሥራዎችን ለመደገፍና ለማጠናከር ሁሉም ትኩረት እንዲሰጥም አቶ ዓለምአንተ ጠይቀዋል። በተለይ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ፣ ግጭቶች በዘላቂነት ተፈትተው ሰላምን ለማስፈንና የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ሂደት እንዲጠናከር የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የጎላ ሚና እንዲጫወቱ አሳስበዋል። የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጅማ ዲልቦ በበኩላቸው፣ "እንደ አገር ያጋጠሙ ስብራቶችና ያልተሻገርናቸው ፈተናዎችን ለማስወገድ የጋራ ጥረት ያስፈልጋል" ብለዋል። የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አገራዊ ጉዳዮች ላይ በአዎንታዊ ጎን ተረባርበው እንዲሰሩ ማስቻል የባለሥልጣኑ የሁልጊዜ ተግባር መሆኑንም አመልክተዋል። አገራዊ ስኬቶችን አጠናክሮ ለማስቀጠልም ሆነ ያልተሻገርናቸውን ፈተናዎች በድል ለማለፍ ሁሉም ሀገር ወዳድ ዜጎች በጋራ እንዲቆሙ ጠይቀዋል። ፍትህ ሚኒስቴር የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ አማራጮችን ላይ ያተኮሩ ውይይቶችን በአዲስ አበባ እና በክልሎች እያካሄደ ስለመሆኑ በቅርቡ ማስታወቁ የሚታወስ ነው።
የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች የሕዝብና መንግስትን ጥቅም በማይጎዳ መልኩ መረጃን ተደራሽ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል- ዋና እንባ ጠባቂ ዶክተር እንዳለ ኃይሌ
Mar 31, 2023 83
አዲስ አበባ (ኢዜአ) መጋቢት 22/2015 የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች የሕዝብና መንግስት ጥቅም በማይጎዳ መልኩ መረጃን ተደራሽ ማድረግ እንደሚገባቸው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ዋና እንባ ጠባቂ ዶክተር እንዳለ ኃይሌ ገለጹ፡፡ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትና የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም በጋራ በመሆን ከፌደራል ተቋማት ለተወጣጡ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ሲሰጡት የነበረው ስልጠና ተጠናቋል፡፡ በማጠናቀቂያ መርሐግብሩ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ዋና እንባ ጠባቂ ዶክተር እንዳለ ኃይሌ፤ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያዎችም ትክክለኛ መረጃን ለዜጎች ተደራሽ የማድረግ ግዴታ እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡ ለሕዝብ ተደራሽ የሚሆኑ መረጃዎች ደግሞ የሕዝብን ሰላምና ደህንነት የማያውኩ፣ የወጣቶችን ጤና የማይጎዱና ዜጎችን ለግጭት የማይዳርጉ መሆን እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች የሕዝብና መንግስት ጥቅም በማይጎዳ መልኩ መረጃን ተደራሽ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች መረጃን ለሕዝብ ተደራሽ በማድረግ ረገድ ያለባቸውን ክፍተት ለመሙላት የሚጠበቅበትን ድጋፍ ያደርጋል ነው ያሉት ዶክተር እንዳለ። የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጸሚ አቶ ሰይፈ ደርቤ በበኩላቸው ሰልጣኞች ያገኙትን እውቀት ተጠቅመው ተቋማቸውን በቅንነት ማገልገል እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡ ኢዜአ ከዚህ ቀደም ለተለያዩ ተቋማት መሰል ስልጠና መስጠቱን ጠቅሰው፤በቀጣይም ይህንኑ ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥል አመልክተዋል፡፡ ሰልጣኞቹ በቀጣይ ያገኙትን ክህሎት ይበልጥ ለማዳበር ሊሰሩ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡ በስልጠናው የተሳተፉ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች በበኩላቸው በስልጠናው የተሻለ እውቀትና ክህሎት ማግኘታቸውን ተናግረዋል፡፡ በዚህም ቀጣይም እውቀት ላይ የተመሰረተ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡
በኢትዮጵያ በግጭት ውስጥ የነበሩ ቡድኖችን ወደ ሰላማዊ ህይወት ለመመለስ እየተሰራ ነው
Mar 31, 2023 95
ባህር ዳር መጋቢት 22/2015 (ኢዜአ) በኢትዮጵያ በግጭት ውስጥ የነበሩ ቡድኖችን ወደ ሰላማዊ ህይወት በመመለስ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት እየተሰራ መሆኑን የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ገለጹ። ኮሚሽኑ የተደረሰው የሰላም ስምምነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ዛሬ በባህር ዳር ከተማ የምክክር መድረክ አካሂዷል። አምባሳደር ተሾመ ቶጋ መድረኩን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት፣ በአገሪቱ የመተማመን ፖለቲካ ለማስፈን መንግስት የተለያዩ ኮሚሽኖችን አቋቁሞ እየሰራ ነው። በእዚህም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል በነበረው ጦርነትና በግጭቶች ምክንያት የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ የማቋቋም፣ ተፈናቃዮችን ወደ አካባቢያቸው የመመለስና ሌሎች ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል። ኮሚሽኑም በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በተፈጠሩ ግጭቶች የተሳተፉ ተዋጊ ቡድኖችን ወደ ሰላማዊ ህይወት ለመመለስ እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል። "በእዚሀም ግንዛቤ በመፍጠር ቡድኖቹ ትጥቅ ፈትተው የአቅም ግንባታ ስልጠና እንዲወስዱና በሚፈልጉት የሥራ መስክ እንዲሰማሩ የመልሶ ማቋቋም ሥራ ይሰራል" ብለዋል። ይህም ለአገር ዘላቂ ሰላም፣ ልማትና ዴሞክራሲ ግንባታ ያለውን ፋይዳ በመገንዘብ ባለድርሻ አካላት በቀና ልብ እንዲተግብሩት አምባሳደር ተሾመ ጠይቀዋል። "በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በነበሩ ግጭቶችና የሰላም እጦት ምክንያት በህዝቡ ላይ ስጋት እንዳለ እንገነዘባለን" ያሉት ኮሚሽነሩ፣ ይሄን ስጋት ለመቀነስ በሁሉም አካባቢዎች ትጥቅ የማስፈታት ሥራ እንደሚሰራ አመልክተዋል። "በዚህም ከመደበኛ የፀጥታ ተቋማት ውጭ ያሉ ቡድኖችን ትጥቅን በማስፈታት ምንም ዓይነት የጸጥታ ችግር እንዳይፈጠር ማድረግ፣ ችግር ቢፈጠር እንኳ በክልል ፖሊስና በፌደራል የፀጥታ ሃይሎች መቆጣጠር የመንግስት ሃላፊነት ይሆናል" ብለዋል። አምባሳደር ተሾመ እንዳሉት በመልሶ ማቋቋም ሥራው የቀድሞ ተዋጊዎች፣ ጉዳት የደረሰባቸው አረጋውያን፣ የተዋጊ ልጆች የሚካተቱ ይሆናል። በሰሜን ኢትዮጵያ የነበረው ጦርነት በክልሉ ሰብዓዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውስ ማስከተሉን የገለጹት ደግሞ የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ጌታቸው ጀንበር ናቸው። ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽኑ በተሰጠው ሃላፊነት ቡድኖችን ትጥቅ ከማስፈታት ሥራ ጎን ለጎን የተፈናቀሉ ዜጎችን የሰላም ተስፋ ለማለምለም መስራት እንዳለበት ገልጸዋል። በዚህም የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ በመገንባት፣ የተፈናቀሉትን በማቋቋምና ሌሎች ተያያዥ ስራዎችን በማከናወን ዜጎች ደህንነታቸው ተጠብቆ ሰርተው የሚኖሩበትና የሚለወጡበት ሁኔታ መፍጠር እንደሚገባ አመልክተዋል። በምክክር መድረኩ ላይ የአማራ ክልል ባለስልጣናት፣ የኮሚሽኑ አመራሮችና አባላት እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኮሞሮስ ኅብረት ፕሬዝዳንት አዛሊ አሱማኒን ተቀብለው አነጋገሩ
Mar 31, 2023 125
አዲስ አበባ መጋቢት 22/2015(ኢዜአ)፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የኮሞሮስ ኅብረት ፕሬዝዳንት አዛሊ አሱማኒን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ "የኮሞሮስ ኅብረት ፕሬዝዳንት አዛሊ አሱማኒን ዛሬ በቢሮዬ ተቀብዬ በሁለትዮሽ፣ በክልላዊ እና በባለ ብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ተወያይተናል" ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል። ኢትዮጵያ ከኮሞሮስ ጋር ላላት ግንኙነት ትልቅ ቦታ ትሰጣለች፤ በተለያዩ መስኮች ያለውን ትብብር ለማጠናከርም ትሠራለች ብለዋል።

ማህበራዊ
በድሬዳዋ አስተዳደር የጎርፍ አደጋን ለመከላከል የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ - ከንቲባ ከድር ጁሃር
Apr 1, 2023 26
ድሬዳዋ፣ መጋቢት 23/2015(ኢዜአ)፦ በድሬደዋ አስተዳደር ጎርፍን በዘላቂነት ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተጀመሩ ስራዎች በትኩረት እንደሚሰሩ ከንቲባ ከድር ጁሃር አስታወቁ። በከንቲባው የተመራ የአስተዳደሩ ካቢኔ አባላት በጎርፍ የተጎዱ መሠረተ ልማቶችን ዛሬ ተዘዋውረው ተመልክተዋል። በጎርፉ የደረሰውን ጉዳት መልሶ ለማቋቋምና ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን አካላት ለመለየት ኮሚቴ ተዋቅሯል። ከምልከታው በኋላ በአስተዳደሩ ባለፉት 15 ዓመታት ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የጎርፍ አደጋን ለመቀነስና ለመከላከል በሶስት ደረቅ ወንዞች ላይ የተሰሩት የመከላከያ ግንቦች ተጨባጭ ለውጥ እያመጡ መሆናቸውን ከንቲባ ከድር ጁዋር ገልጸዋል። በተለይም በገጠር ቀበሌዎች ለ10 ዓመታት የተከናወኑ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ሥራዎች ጎርፍ በማሳዎች ላይ ሲያደርስ የነበረውን ችግር በማቃለል ውሃውን ለመስኖ ልማት ማዋል ተችሏል ብለዋል። በአስተዳደሩ እየተሰሩ ያሉትን ስራዎች በማጠናከር የጎርፍ አደጋን ለመከላከል የተቀናጀ ስራ እንደሚሰራ ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት እየጣለ የሚገኘው ዝናብ ያስከተለው ጎርፍ በከተማው የመጠጥ ውሃ መሠረተ ልማቶች፣ በጎርፍ መውረጃ ቦዮች፣ በጎርፍ መከላከያ ግንቦችና ማሳዎች ላይ ጉዳት ማድረሱን ጠቁመዋል። ጉዳት የደረሰባቸውን መሰረተ ልማቶች መልሶ ለመጠገንና የጎርፍ አደጋን ለመከላከል አስተዳደሩ ኮሚቴ አዋቅሮ መፍትሄ የሚሆኑ ስራዎች ይከናወናሉ ብለዋል። የድሬዳዋ መንገዶች ባለስልጣን ስራ አስኪያጅ አቶ ብሩክ ወርቅነህ የጎርፍ ስጋት ያለባቸውን የማህበረሰብ ክፍሎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ከተቋቋመው ኮሚቴ ጋር በመሆንም በጎርፍ የተበላሹና የተሰበሩ መሠረተ ልማቶችን መልሶ የመጠገን ስራ ይከናወናል ብለዋል። የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የምስራቅና መካከለኛ ኦሮሚያ ሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት ማዕከል በምስራቅ የአገሪቱ ክፍል እየጣለ የሚገኘው ዝናብ ጎርፍ ሊያስከትል ስለሚችል ነዋሪዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ማሳሰቡ ይታወሳል።
መምህራን ትውልድን በመልካም ሥነ-ምግባርና በእውቀት ለማነጽ የሚያከናውኑትን ተግባር አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ ቀረበ
Apr 1, 2023 29
አዲስ አበባ መጋቢት 23/2015(ኢዜአ)፦ መምህራን ትውልድን በመልካም ሥነ-ምግባርና በእውቀት ለማነጽ የሚያከናውኑትን ተግባር አጠናክረው እንዲቀጥሉ የኦሮሚያ ክልል ጠየቀ። የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ከመጋቢት 18 እስከ 23 ቀን 2015 ዓ.ም "የትምህርት ለውጥ ከመምህራን ይጀምራል" በሚል መሪ ሃሳብ የመምህራን ሳምንት ማጠቃለያ መርሃ-ግብር አካሂዷል። በመርሃ ግብሩ ከቅድመ መደበኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለሚያስተምሩ መምህራን በጡረታ የተገለሉትን ጨምሮ ለአመራሮች የሜዳሊያ፣ የገንዘብ ሽልማትና የሰርተፊኬት እውቅና ተሰጥቷል። በእውቅና መርሃ ግብሩ በዘንድሮው አገር አቀፍ ፈተና ላይ ተማሪዎች ጥሩ ውጤት እንዲያመጡ ለሰሩ የትምህርት ማህበረሰብ አካላት እውቅናና ሽልማት ተሰጥቷል። የክልሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ክላስተር አስተባባሪ አቶ አብዱልሃኪም ሙሉ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት መምህራን አዲሱን ትውልድ በማነጽና የአገር ግንባታ ላይ በመሳተፍ ኃላፊነታቸውን መወጣት ይጠበቅባቸዋል። ''የሁሉም ሙያዎች መፍለቂያ መነሻ የሆነውን የመምህርነት ተግባር እውቅና መስጠት አገርን ማክበር በመሆኑ ለመምህራን ትልቅ ክብር ይገባቸዋል'' ነው ያሉት። በዚህም መሰረት ክልሉ ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ ለመምህራን የእውቅና ሽልማት በመስጠት ለባለሙያዎቹ ያለውን ክብር ማሳየቱን ገልጸዋል። የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር በሪሶ ቶላ በበኩላቸው የሁሉም ሙያዎች ቀዳሚ የሆነው መምህርነት በመሆኑ ለባለሙያው ትልቅ ክብር መስጠት ተገቢ ነው ብለዋል። ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዲከታተሉና እውቅትን እንዲገበዩ መምህራን ኃላፊነታቸውን ለመወጣት በርካታ ተግባራትን እያከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል። በክልሉ የሚገኙ መምህራንን አቅም ለማሳደግ እንዲሁም ምቹ የኑሮ ሁኔታ እንዲፈጠርላቸው ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ሲሉም ጠቁመዋል። እውቅናና ሽልማት የተሰጣቸው መመምህራን በበኩላቸው የተሰጠው እውቅና ለበለጠ ሥራ የሚያነሳሳቸው መሆኑን ጠቁመዋል። ለመምህራን ትኩረት መሰጠቱ የትውልድና አገር ግንባታ ላይም ትልቅ መነቃቃት ይፈጥራል ብለዋል።
በጎ ፈቃደኛ ሐኪሞች የአዕምሮ እድገት ውስንነት ላለባቸው ህፃናት ነፃ የልብ ሕክምና አገልግሎት ሰጡ
Apr 1, 2023 41
አዲስ አበባ መጋቢት 23/2015 (ኢዜአ) በጎ ፈቃደኛ ሐኪሞች ከዲቦራ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር የአዕምሮ እድገት ውስንነት ላለባቸው 100 ህፃናት ነፃ የልብ ሕክምና አገልግሎት ሰጡ። የፋውንዴሽኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ ወይዘሮ ቤኪ አባዱላ እንደገለጹት፤ ከግልና ከመንግስት የህክምና ተቋማት በመጡ በጎ ፍቃደኛ ሃኪሞች ለአዕምሮ እድገት ውስንነት ላለባቸው ህፃናት ነፃ የልብ ሕክምና አገልግሎት ተሰጥቷል። በፋውንዴሽኑ የአዕምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ከ1ሺህ 500 በላይ ህፃናትና ታዳጊዎች ተመዝግበው የተለያዩ አገልግሎት እያገኙ መሆኑን ገልጸዋል። የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከሚሰጡ ዜጎችና ድርጅቶች ጋር በመተባበር ለአዕምሮ እድገት ውስንነት ላለባቸው የጤና፣ የትምህርትና የሰብዓዊ መብት አገልግሎት እየተሰጠ ነው ብለዋል። በዛሬው ዕለትም ከፍለው መታከም ለማይችሉ የአዕምሮ እድገት ውስንነት ላለባቸው ህፃናት ነፃ የልብ ሕክምና አገልግሎት ተሰጥቷል ብለዋል። ፋውንዴሽኑ በለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ እያስገነባ ያለውን ትምህርት ቤት በማጠናቀቅ ላይ መሆኑን ገልጸው፤ በዘንድሮ ዓመትም በትምህርት ቤቱ ውስጥ የፊዚዮቴራፒ፣ የሙያና ሕይወት ክህሎት ሥልጠና መጀመሩን ገልጸዋል። የፋውንዴሽኑ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ዶክተር ሔዋን ሙሉጌታ በበኩላቸው፤ ተቋሙ ከዚህ ቀደም የተለያዩ ዘመቻዎችን በማካሄድ 600 ለሚደርሱ የአዕምሮ እድገት ውስንነት ላለባቸው ታዳጊዎች የዓይንና ከአንገት በላይ ሕክምና ሰጥቷል። ፋውንዴሽኑ በቀን ለ30 የአዕምሮ እድገት ውስንነት ላለባቸው ህፃናት የፊዚዮቴራፒ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በዛሬው ዕለትም ሰባት በሚደርሱ በጎ ፈቃደኛ ሐኪሞች 100 ለሚደርሱ የአዕምሮ እድገት ውስንነት ላለባቸው ታዳጊዎች የልብ ሕክምና መስጠቱን ተናግረዋል፡፡ እንደ ምክትል ሥራ አስኪያጇ ገለጻ የአዕምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ህጻናት ለልብ ህመም ተጠቂ በመሆናቸው ህመሙ እንዳለባቸው አስቀድሞ በመለየት ህክምናውን እንዲያገኙ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል። በበጎ ፈቃድ ከተሳተፉ ሐኪሞች መካከል ዶክተር ሚካኤል ጥላሁን አንዱ ሲሆኑ የአዕምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ህፃናት እንደ ሌሎች ሰዎች የጤና አገልግሎት የማግኘት መብት አላቸው፡፡ ይህም የሚሆነው ሁሉም መተባበርና መተጋገዝ ሲችል መሆኑን ጠቅሰው፤ ሕብረተሰቡ በተለይ ደግሞ የጤና ባለሙያዎች የአዕምሮ እድገት ውስንነት ላለባቸው ዜጎች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በመስጠት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ዲቦራ ፋውንዴሽን በአቶ አባዱላ ገመዳ በ2011 ዓ.ም. ተመስርቶ የአዕምሮ እድገት ውስንነት ላለባቸውና ለሌሎች ዜጎች የተለያዩ አገልግሎቶችን እየሰጠ ይገኛል።
የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን የቤት ጥያቄ ለመመለስ ሁሉን አቀፍ ጥረት እየተደረገ ነው -ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Apr 1, 2023 41
አዲስ አበባ መጋቢት 23/2015(ኢዜአ)፦ "የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የቤት ጥያቄን ለመመለስ ሁሉን አቀፍ ጥረት በመደረግ ላይ ይገኛል" ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ። ከንቲባ አዳነች በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ለአቅመ ደካሞች፣ ለአረጋውያንና ለአካል ጉዳተኞች እንዲሁም ለልማት ተነሺዎች 200 ቤቶችን አስረክበዋል። በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎችም ማዕድ አጋርተዋል። ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት፤ ከተማ አስተዳደሩ የዜጎችን የቤት ችግር ለማቃለል የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ ነው። ይህንንም ተከትሎ በመንግስትና በግል አጋርነት እስካሁን 20ሺህ ቤቶች መገንባታቸውን አንስተዋል። አሁን ላይ ደግሞ የ120ሺህ ቤቶች ግንባታ መጀመሩን ገልጸው፤ የነዋሪውን የቤት ፍላጎት ለማሟላት ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል። በአዲስ አበባ ያለውን ሀብት በፍትሃዊነት የማከፋፈል ግዴታ አለብን ያሉት ከንቲባ አዳነች፤ ዜጎችን በእኩል የማገልገል ኃላፊነታችን ተጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት። አዲስ አበባን እንደ ስሟ አዲስ ለማድረግ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ በመጠቆም። ዛሬ የቤት ቁልፍ ከተረከቡት መካከል የጉለሌና አራዳ ክፍለ ከተማ የልማት ተነሺዎች እንደሚገኙበት ገልጸዋል። በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የቤት ቁልፍ ከተረከቡት መካከል የሁለት ልጆች እናት የሆኑት ወይዘሮ ውዴ መኬ "ታማሚ ልጅ ይዤ አውላላ ሜዳ ላይ ወድቄ ነበር፤ ዛሬ ግን ቤት በማግኘቴ በጣም ተደስቻለሁ" ብለዋል። በደረሰበት የመኪና አደጋ እግሮቹን ያጣው ወጣት ነብያት አሉላ ጫማ በመጥረግ አምስት ቤተሰቡን እያስተዳደረ መሆኑን ተናግሯል። "የነበርኩበት ቤት ለኑሮ እጅግ አስቸጋሪ ነበር፤ ከመንግስት ያገኘሁት የቤት ስጦታ ሕይወቴን ለመቀየር መሰረት የሚሆን ነው" ብሏል። ዛሬ ለአቅመ ደካሞችና ለልማት ተነሺዎች የተከፋፈለው ቤት የተገነባው በባለሀብቶች ድጋፍ ሲሆን ስድስት ብሎኮች ያሉት ነው።
ኢኮኖሚ
የነዳጅ ግብይቱን ወደ ዲጂታል በመቀየር በአቅርቦትና ስርጭት ላይ የሚታዩ ችግሮችን ለማቃለል እየተሰራ ነው
Apr 1, 2023 26
ጋምቤላ፣ መጋቢት 23 ቀን 2015 (ኢዜአ) በሀገሪቱ ሁሉም አካባቢዎች የነዳጅ ግብይቱን ወደ ዲጂታል በመቀየር በነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት ላይ የሚታዩ ችግሮችን ለማቃለል እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታወቀ። ባለስልጣኑ ከጋምቤላ ክልል የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር በነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት መመሪያዎችና ሌሎችም ጉዳዮች ዙሪያ በጋምቤላ ከተማ ተወያይቷል። የባለስልጣኑ የነዳጅ ውጤቶች ግብይት ስታንዳርድ ጥናትና ምርምር ዳይሬክተር አቶ ለሜሳ ቱሉ በውይይቱ ላይ እንዳሉት፤ ነዳጅ በከፍተኛ የውጪ ምንዛሬ እየመጣ ቢሆንም በአቅርቦትና በስርጭት ችግር ለብክነት እየተዳረገ ነው። በነዳጅ ላይ በተካሄደ ከፍተኛ ቁጥጥር የነዳጅ ኮንትሮባንድን 70 በመቶ ያህል መቀነሰ መቻሉን ጠቅሰው፤ አሁንም በተለያዩ አካባቢዎች የቤንዚን ኮንትሮባንድ ንግድ መኖሩን ጠቁመዋል። ችግሩን ለማስቀረት በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች የነዳጅ ግብይት ሰንሰለቱን ሙሉ በሙሉ ዲጂታል በማድረግ በነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት የሚታየውን ክፍተት ለመሙላት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የዲጂታል ግብይቱ በሙከራ ደረጃ በአዲስ አበባ መተግበር መጀመሩን ጠቁመው፤ ከግንቦት ወር 2015 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም ክልሎች ስራ ላይ የሚውል ይሆናል ብለዋል። ከዚህም በተጨማሪ በቦቲዎችና በማደያዎች ላይ የርቀት መቆጣጠሪያ መሳሪያ (ጂፒኤስ) በመግጠም የአቅርቦቱንና የስርጭቱን ሂደት ለመቆጣጠር እየተሰራ እንደሆነ ገልጸው፤ እስካሁን ከሶስት ሺህ በሚበልጡ ቦቲዎች ላይ ጂፒኤስ መገጠሙን ጠቁመዋል። ከክልሉ ባለድርሻ አካላት በነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት መመሪያ ዙሪያ ውይይት ማድረግ ያስፈለገው የጠራ ግንዛቤ በመፍጠር የክትትልና ቁጥጥር ስራውን ለማጠናከር በማለም እንደሆነ ተናግረዋል። የክልሉ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኢንጂነር ኡሌሮ ኦፒዮው በበኩላቸው የነዳጅ የጥቁር ገበያ እየተስፋፋ መሆኑን ተናግረዋል። ለጥቁር ገበያ መስፋፋት ዋነኛው ምክንያት ማደያ በሌለባቸው አካባቢዎች ለችርቻሮ በበርሜል ተቀድቶ መሄዱ እንደሆነ ገልጸው፤ በዚህ ሁኔታ ነዳጅ ከተመኑ በላይ በእጥፍ በመሸጡ እንደሆነ አመልክተዋል። አሁን ላይ ችግሩን ለመከላከል እየተደረገ ባለው የክትትልና የቁጥጥር ስራ በጀሪካንና በበርሜል በህገ ወጥ መንገድ ይዘው የተገኙ አካላትን በህግ ተጠያቂ የማድረግ ስራ እየተከናወነ ነው ብለዋል። በጋምቤላ ከተማ ከትናንት ጀምሮ ለሁለት ቀናት በቆየው የውይይት መድረክ ከክልል እስክ ወረዳ የሚገኙ የንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ፣ የጽህፈት ቤት አመራሮች፣ ባለሙያዎችና የማደያ ባለንብረቶች ተሳትፈዋል።
ባለፉት ስምንት ወራት ለታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ተሰብስቧል
Apr 1, 2023 37
አዲስ አበባ መጋቢት 23/2015 (ኢዜአ) ባለፉት ስምንት ወራት ለታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን የግድቡ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት ገለጸ። የጽህፈቱ ቤት የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኃይሉ አብርሃም ለኢዜአ እንደገለጹት ሕዝቡ ለግድቡ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ቀጥሏል። ሕዝቡ በቦንድ ሽያጭና ስጦታ፣ በ8100 አጭር የጽሁፍ መልዕክት፣ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የስጦታ አካውንትና በሌሎች የድጋፍ ማሰባሰቢያ መርኃ-ግብር ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል። ይህንንም ተከትሎ ባለፉት ስምንት ወራት ከተለያዩ የገቢ ማሰባሰቢያ መንገዶች ከ1 ቢሊዮን 41 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን ነው ያረጋገጡት። ሕዝቡ የሚያደርገው ድጋፍ እንዲጎለብት በተለይም ባለፉት ሦስትና አራት ዓመታት በተሰራው ሥራ አበረታች ውጤት መመዝገቡን ገልጸዋል። በዚህም የግድቡ ግንባታ በመልካም የአፈጻጸም ደረጃ ላይ መሆኑን ገልጸው ግድቡ በፍጥነት እንዲጠናቀቅ ድጋፉ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ነው ያሉት። ከመጋቢት 16/2015 ዓ.ም ጀምሮ የገቢ ማሰባሰቢያ ለአንድ ወር የሚቆይ ንቅናቄ መጀመሩን ገልጸዋል። በዚህም 100 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱን ገልጸው ኅብረተሰቡ በመርኃ ግብሩ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን ጠይቀዋል። ጽህፈት ቤቱ የተለያዩ መርኃ ግብሮችን በማዘጋጀት ሕዝቡ ለግድቡ ግንባታ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተሻሻሉ አሰራሮችንና የመካናይዜሽን ቴክኖሎጂዎችን በማስተዋወቅ አርሶ አደሩን ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑን ገለጸ
Apr 1, 2023 34
ጎንደር፣ መጋቢት 23 ቀን 2015 (ኢዜአ) የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተሻሻሉ የግብርና አሰራሮችን በመተግበርና የመካናይዜሽን ቴክኖሎጂዎችን በማስተዋወቅ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሳተፉ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑን አስታወቀ፡፡ በዩኒቨርሲቲው የግብርና እና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ዶክተር ካህሌ ጀምበሬ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ ዩኒቨርሲቲው በማዕከላዊና ምዕራብ ጎንደር ዞኖች በበጋ መስኖ ስንዴ ልማቱ እየተሳተፉ ለሚገኙ 2 ሺህ አርሶ አደሮች ድጋፍ እያደረገ ነው፡፡ ዩኒቨርሰቲው በመካናይዜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ በምዕራብ ደንቢያ ወረዳ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማቱ ለሚሳተፉ አርሶ አደሮች በሶስት ትራክተሮች የታገዘ 75 ሄክታር ኩታ ገጠም መሬት ለአርሶ አደሮች ማስረከብ ችሏል። በጎንደር ዙሪያ ወረዳ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማቱ ለሚሳተፉ አርሶ አደሮች ቴክኖሎጂውን በማስተዋወቅ በቀጣይ ዓመት በትራክተር ለማረስ የሚያስችሉ አሰራሮች ማመቻቸቱን ነው ዶክተር ካህሌ የገለጹት፡፡ ዩኒቨርሲቲው በማዕከላዊና ምዕራብ ጎንደር ዞኖች አርሶ አደሮቹ እያለሙት ላለው 700 ሄክታር መሬት ከ1 ሺህ 200 ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ በማሰራጨት ተጠቃሚ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ባቋቋማቸው አራት የምርምር ጣቢያዎች በመታገዝ የአካባቢውን ስነ-ምህዳር የተላመዱ ምርታማ የስንዴ ዝርያዎችን በመለየት አንድ ሺህ ኩንታል ምርጥ ዘር ለአርሶ አደሩ ማቅረቡን አመልክተዋል፡፡ በተሻሻሉ አሰራሮች ታግዞ በስንዴ ሰብል ከለማው መሬትም 31 ሺህ ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ ነው ዶክተር ካህሌ የጠቆሙት። የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማቱ የእርሻ ትራክተሮችንና ግብዓቶች በወቅቱ በማቅረብ እያገዘ እንደሚገኝ የተናገሩት የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ግብርና መምሪያ የመስኖ ስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ሃውልቱ ታደሰ ናቸው፡፡ ዩኒቨርሲቲው ከአንድ ሺህ ኩንታል በላይ ምርጥ ዘርና ከ600 ኩንታል በላይ ማዳበሪያ በዞኑ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማቱ ለተሳተፉ አርሶ አደሮች በማቅረብ ለመርሐግብሩ መሳካት ድጋፍ ማበርከቱን ተናግረዋል፡፡ በምዕራብ ደንቢያ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት አርሶ አደር ታምራት ጎሹ በበኩላቸው ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በአንድ ሄክታር መሬት እያካሄዱት ላለው የስንዴ ልማት በትራክተር በማረስ እንዳገዛቸው ገልጸዋል። ሌላው የዚሁ ወረዳ ነዋሪ አርሶ አደር ቢክስ ሞላ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ባቀረበላቸው አንድ ኩንታል ማዳበሪያና 30 ኪሎ ምርጥ ዘር በግማሽ ሄክታር መሬት የበጋ መስኖ ስንዴ ማልማታቸውን ተናግረዋል፡፡ ካለሙት መሬት 20 ኩንታል ምርት እንደሚጠብቁ ጠቅሰው፤ ምርቱን ከሰበሰቡ በኋላም በወረዳው ለሚገኘው የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበር ለማስረከብ ስምምነት ማድረጋቸውን አመልክተዋል፡፡ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የዘንድሮ የበጋ ወራት 14 ሺህ ሄክታር መሬት በስንዴ ሰብል እየለማ እንደሚገኝና ከ500 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠበቅ ከዞኑ ግብርና መምሪያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ታላቁ ሕዳሴ ግድብ የአካባቢውን አገራት በኃይል ለማስተሳሰር ያስችላል -- የቀድሞ የሱዳን የመስኖ ሚኒስትር ኦስማን አል-ቶም ሃማድ
Apr 1, 2023 37
አዲስ አበባ መጋቢት 23/2015(ኢዜአ)፦ታላቁ ሕዳሴ ግድብ የአካባቢውን አገራት በኃይል ለማስተሳሰር ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው የቀድሞ የሱዳን የመስኖ ሚኒስትር ኦስማን አል-ቶም ሃማድ ገለጹ። የቀድሞ የሱዳን የመስኖ ሚኒስትሩ ኦስማን አል-ቶም ሃማድ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ በታችኛው የተፋሰሱ አገራት ላይ የሚደርሰውን የጎርፍ መጥለቅለቅ በመቆጣጠርና የውሃ ፍሰቱን በማስተካከል ትልቅ ጠቀሜታ አለው። በተለይም ሱዳን የውሃ ፍሰቱን በመቆጣጠር አገሪቱ ከሚገጥማት የጎርፍ አደጋ ይታደጋታል ብለዋል። ጎን ለጎንም ተከታታይ ድርቅ በሚከሰትበት ወቅት ግድቡ ክስተቱን በመቋቋም የራሱ አዎንታዊ አበርክቶ እንደሚኖረው ገልጸዋል። የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ከዲዛይን ጀምሮ እስከ አተገባበሩ ድረስ በጥንቃቄ እየተገነባ ያለ ግድብ መሆኑንም ጠቅሰዋል። ይህም ብቻ ሳይሆን ግድቡ ለጎረቤት አገራት የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት አገራቱ እርስበርስ እንዲተሳሰሩ ያስችላል ነው ያሉት። በመሆኑም የአካባቢው አገራት ለጋራ ጥቅም መተባበር ጠቃሚ መሆኑን አንስተዋል። ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ በውሃ ጉዳይ ተባብረው ከሚሰሩ ሌሎች አገራት ተሞክሮ መቀመር እንዳለባቸውም አሳስበዋል። ይህንንም ተከትሎ የአካባቢው አገራት ግድቡን ብቻ ሳይሆን በሌሎችም የልማት መስኮች ላይ የጋራ ትብብር ያስፈልጋል ብለዋል። በጋራ ለመሥራትና ፕሮጀክቶችን ለመቅረጽ የአገራቱ የፖለቲካ ቁርጠኝነት እንደሚያስፈልግ በመግለጽ። በጋራ የሚካሄዱ ፕሮጀክቶች የጋራ የሆኑ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና አካባቢያዊ ግቦችን ለማሳካት እንደሚያስችል ጠቁመዋል። የጋራ የልማት ፕሮጀክቶቹ የፋይናንስ ድጋፍ እንዲያገኙም በጋራ መሥራት እንዳለባቸው ጠቁመዋል። አገራቱ በሦስትዮሽ ማዕቀፍ በሚያካሂዱት ውይይት የሦስቱን አገራት ፍላጎት የሚያረጋግጥ ሥምምነት ላይ እንደሚደረስ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓት የመፈጸም አሰራር በሙከራ ደረጃ ተግባራዊ መሆን ጀመረ
Mar 31, 2023 71
አዲስ አበባ መጋቢት 22/2015(ኢዜአ) የነዳጅ ግብይትን በዲጂታል የክፍያ ስርዓት የመፈጸም አሰራር በሙከራ ደረጃ በአዲስ አበባ ተግባራዊ መሆን ጀመረ፡፡ የዲጂታል ክፍያው ትግበራ የተጀመረው በነዳጅ ድጎማ ስርዓት ተጠቃሚ የሆኑትን ጨምሮ በሁሉም ተሽከርካሪዎች ላይ መሆኑም ተገልጿል። የክፍያ ስርዓቱን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዶክተር ዓለሙ ስሜ፣ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ገብረመስቀል ጫላ፣የኢትዮጰያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ሳህረላ አብዱላሂ እና የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ በይፋ አስጀምረዋል። የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትሩ ዶክተር ዓለሙ ስሜ የነዳጅ ግብይት ስርዓት መዘመን ለትራንስፖርት አገልግሎት መሳለጥ ሚናው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም ከነዳጅ አቅርቦት ጋር ተያይዘው የሚፈጠሩ ህገ-ወጥነትን ለመቆጣጠርና ለመከላከል እንደሚያግዝ ተናግረዋል፡፡ ዛሬ በሙከራ ደረጃ የተጀመረው ይህ አገልግሎት በአጭር ግዜ ውስጥ በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች ተደራሽ እንደሚሆን ጠቁመዋል። የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ገብረመስቀል ጫላ በበኩላቸው መንግስት በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ከሚያስገባቸው ግብዓቶች ውስጥ ነዳጅ አንዱና ዋነኛው መሆኑን ገልጸዋል። ይሁንና የነዳጅ አጠቃቀምና ስርጭት እንደ አገር ክፍተቶች ያሉበት ከመሆኑ ባሻገር ፍትሃዊ ተደራሽነት ላይም ጫና ማሳደሩን ገልጸዋል። በተጨማሪም ግብይቱ ለህገ-ወጥነት ተጋላጭ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በመሆኑም የዲጂታል ግብይት ስርዓቱ በዘርፉ የሚነሱ ችግሮችን በመቅረፍ ረገድ የጎላ ሚና እንደሚኖረው ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ስርዓት ከተጀመረ ስምንት ወራትን ማስቆጠሩን አስታውሰዋል። በድጎማ ስርዓቱ የሚጠቀሙ አሽከርካሪዎችም የነዳጅ ግብይታቸውን በቴሌ-ብር እንዲፈጽሙ መደረጉን ጠቅሰው፤ ይህንን መነሻ በማድረግ ለሁሉም ተሽከርካሪዎች የዲጂታል የነዳጀ ግብይት ስርዓት ተዘርግቷል ነው ያሉት። መንግስት ለነዳጅ ብቻ በዓመት ከ4 ቢሊዬን ዶላር በላይ ወጪ እንደሚያወጣ ገልጸው ግብይቱ ወደ ዲጂታል መደረጉ ለቁጥጥር ስርዓቱ የጎላ ሚና አለው ብለዋል። የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን በማድረግ ረገድ አበረታች ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በተለይም በተለያዩ ዘርፎች የቴሌ-ብር ግብይት መፈጸም መጀመሩ የዜጎችን ኑሮ ከማቃለሉ ባሻገር የገንዘብ ዝውውሩ ከእጅ ንኪኪ የጸዳና እንዲሆን አስችሏል። ዛሬ በሙከራ ደረጃ የተጀመረው ይህ የዲጂታል የነዳጅ ግብይት ስርዓትም ዲጂታል ኢኮኖሚን በማረጋገጥ ረገድ ፈር ቀዳጀ እንደሚሆን ተስፋ ተጥሎበታል። ለዚህም አገልግሎቱ ሳይቆራረጥ በቀላሉ የሚሰጥበት አማራጮችን በማስፋት ተደራሽ እንዲሆን ይደረጋል ብለዋል ዋና ስራ አስፈጻሚዋ። በቴሌ ብር አማካኝነት የሚከናወነው የታለመለት የነዳጅ ድጎማም የቁጥጥር ስርዓቱን እንዳሻሻለው ጠቁመዋል፡፡ ዲጂታል የነዳጅ ግብይቱን ከቴሌ ብር በተጨማሪ በሌሎች የዲጂታል አማራጮችን ለማስፋት ከባንኮች ጋር የማስተሳሰር ስራ እየተከናወነ መሆኑም ተነስቷል።
የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ሰው ሰራሽ አስተውሎት በተለያዩ ተቋማት ስራ ላይ እንዲውሉ እየሰራ ነው- የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር
Mar 31, 2023 67
አዲስ አበባ መጋቢት 22/2015 (ኢዜአ)፦ የሰው ሰራሽ አስተውሎት በተለያዩ ተቋማት ስራ ላይ እንዲውሉ እየሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ወርቁ ጋቸና ገለጹ። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እያከናወናቸው ያሉ ስራዎችን ጎብኝተዋል። በኢንስቲትዩቱ የተከናወኑ በርካታ ስራዎችን በተመለከተ ዋና ዳይሬክተሩ ኢንጅነር ወርቁ ጋቸና ለቋሚ ኮሚቴ አባላቱ ገለጻ አድርገውላቸዋል። ዋና ዳይሬክተሩ በገለጸቸው የደህንነት፣ የጤና፣ የፋይናንስ፣ የትምህርትና ሌሎት አገልግሎቶች የተሳለጡና ጥራታቸውን የጠበቁ ለማድረግ የተለያዩ ሲስተሞች ለምተው ተግባራዊ መሆን መጀመራቸውን ተናግረዋል። በስማርት ሲቲ ግንባታ በተለያዩ የመዲናዋ አካባቢዎች በሺዎች የሚቆጠሩ የደህንነት ካሜራዎች ተተክለው አገልግሎት እየሰጡ መሆኑንም እንዲሁ። የጤናውን ዘርፍ አገልግሎት ለማዘመን ደግሞ በዘውዲቱ መታሰቢያና በየካቲት 12 ሆስፒታሎች የስኳር በሽታን ልየታና ምርመራ ማደረግ የሚያስችል ሲስተም ለምቶ የሙከራ ትግበራው ተጠናቋል ብለዋል። የፋይናንስና የትምህርት ዘርፉም በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተደገፈ እንዲሆን ተመሳሳይ ስራዎች መከናወናቸውን አብራርተዋል። ዘርፉን በሰው ሃይል ለማጠናከር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በመተባበር ከተለያዩ አገራት በማስመጣት እንዲያስተምሩ እየተደረገ መሆኑንም ጠቅሰዋል። በተለያዩ ተቋማት የሰው ሰራሽ አስተውሎት ስራ ላይ እንዲውል ኢንስቲትዩቱ እየሰራ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል። የቋሚ ኮሚቴው የመስክ ቡድን አስተባባሪ ፋናዬ መለሰ፤ የኢንስቲቱዩቱ ጅምር ስራዎች የሚደነቁ መሆናቸውን ገልጸዋል። የሰው ሰራሽ አስተውሎትን በተቋማት ጥቅም ላይ ለማዋል የተያዘው እቅድም ሊበረታታ ይገባል ነው ያሉት። የሰው ሰራሽ አስተውሎት በኢትዮጵያ ለተጀመሩ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎችና የለውጥ ጉዞ አጋዥ መሆኑንም ቋሚ ኮሚቴው በቅጡ ተገንዝቧል ብለዋል። በመሆኑም የኢንስቲትዩቱን ስራዎች ውጤታማነት ለማስቀጠል ምክር ቤቱ በቀጣይነት እገዛ የሚያደርግ መሆኑን አረጋግጠዋል።
በማደግ ላይ ያሉ አገሮች ለአካታች ዲጂታል ኢኮኖሚ ትግበራ ትኩረት ሰጥተው ካልሰሩ እኤአ በ2025 ከ1 ትሪሊየን ዶላር በላይ ገቢ ሊያጡ ይችላሉ- ተመድ
Mar 27, 2023 181
አዲስ አበባ መጋቢት 18/2015(ኢዜአ)፦ በማደግ ላይ ያሉ አገሮች ለአካታች የዲጂታል ኢኮኖሚ ትግበራ ትኩረት ሰጥተው ካልሰሩ እኤአ በ2025 ከአገር ውስጥ ዓመታዊ ምርታቸው ከ1 ትሪሊየን ዶላር በላይ ገቢ ሊያጡ እንደሚችሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ "የፈጠራና ቴክኖሎጂ ለፆታ እኩልነት" በሚል መሪ ሃሳብ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ውይይት አካሂዷል። የድርጅቱ የሰብአዊ ጉዳዮች የኢትዮጵያ አስተባባሪ ዶክተር ካትሪን ሶዚ፤ የዲጂታል ዘመን ሥራዎችን ቀላል በማድረግ በተለይም ሴቶችና ህፃናትን ተጠቃሚ ሊያደርጉ የሚችሉ በርካታ ዕድሎችን ይዞ መጥቷል ብለዋል። በዓለም ላይ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች አሁንም ከኢንተርኔት ተደራሽነት ውጭ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ ተደራሽነቱን ማስፋት አስፈላጊ ነው ሲሉ ገልጸዋል። አካታች የዲጂታል ስትራቴጂ ተግባራዊ አለማድረግ በማኅበራዊና የምጣኔ ሃብት እድገት ላይ ተጽዕኖው ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው፤ አገሮች በቀጣይ ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ ይገባል ነው ያሉት። አፍሪካን ጨምሮ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው አገሮች ባለፉት አሥርት ዓመታት ለአካታች ኢንተርኔት ትኩረት ባለመስጠታቸው ከዓመታዊ የአገር ውስጥ ምርታቸው 1 ትሪሊየን ዶላር ማጣታቸውን ተናግረዋል። በመሆኑም መንግሥታት ክፍተቱን ለመሙላት ለአካታች የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ትኩረት ሰጥተው ካልሰሩ እ.ኤ.አ በ2025 1 ነጥብ 5 ትሪሊዮን ዶላር ሊያጡ ይችላሉ ሲሉ ግምታቸውን አስቀምጠዋል። የክህሎትና እውቀት ክፍተት፣ የኢንተርኔት ዋጋ አቅምን ያገናዘበ አለመሆን፣ ፆታዊ ትንኮሳ፣ የመጠቀሚያ መሳሪያዎች እጥረት የዘርፉ ፈተናዎች መሆናቸውን ዶክተር ካትሪን ገልጸዋል። በ2025 ኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታዋን የተሳካ ለማድረግ ስትራቴጂ ቀርፃ እየሰራች መሆኑን ጠቅሰው፤ ዕቅዱ የተሳካ እንዲሆን አስፈላጊው ሁሉ ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል። በመድረኩ ላይ የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ፤ በኢትዮጵያ በቴሌኮም ዘርፉ እየተወሰዱ ያሉ የለውጥ ሥራዎችና የተገኙ ውጤቶችን አብራርተዋል። በ2025 ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ሁሉንም ባሳተፈ መልኩ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል። በተለይም የሴቶችን የዲጂታል አቅም ለማሳደግ ክህሎትና እውቀት ላይ ትኩረት ያደረጉ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልጸዋል። በተጨማሪም በሴቶችና በወንዶች መካከል ያለውን የዲጂታል ተጠቃሚነት ዕድልና ክህሎት ልዩነት ለማጥበብ እንደ አገር ጥናት እየተካሄደ መሆኑን አስረድተዋል። በቀጣይም መሰል ተግባራት ተጠናክረው የሚቀጥሉ መሆኑን ጠቅሰው፤ ዲጂታል ኢትዮጵያ እውን ይሆናል ብለዋል።
አካታች የዲጂታል ምጣኔ ሀብትን እውን ለማድረግ እውቀትና ክህሎትን ማሳደግ ላይ እየተሰራ ነው
Mar 27, 2023 177
አዲስ አበባ መጋቢት 18/2015 (ኢዜአ) ፦ ኢትዮጵያ አካታች የዲጂታል ምጣኔ ሀብትን እውን ለማድረግ እውቀትና ክህሎት ላይ ትኩረት አድርጋ እየሰራች መሆኑ ተገለጸ። አለም አቀፍ የሴቶች ቀን በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የሴቶችን የዲጂታል ተጠቃሚነት ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት በማድረግ ተከብሯል። በዚሁ ጊዜ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ በኢትዮጵያ በቴሌኮም ዘርፉ እየተወሰዱ ያሉ ሪፎርሞችን አብራርተዋል። ኢትዮጵያ ተግባራዊ እያደረገች ባለችው ዲጂታል 2025 መርሃ-ግብር ሴቶች ቴክኖሎጂን በሚፈለገው ደረጃ እንዳይጠቀሙ ካደረጉ ችግሮች ውስጥ የዲጂታል ክህሎትና እውቀት ማነስ አንዱ መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም የሴቶችን የዲጂታል አቅም ለማሳደግ ክህሎትና እውቀት ላይ ትኩረት ያደረጉ ተግባራትን በማከናወን አካታች ምጣኔ ሀብትን ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በተጨማሪም በሴቶችና በወንዶች መካከል የዲጂታል ዕውቀት ልዩነትን ለማጥበብ እንደ ሀገር ጥናት እየተካሄደ መሆኑን አስረድተዋል። በቀጣይ በጥናቱ ግኝት መሰረት እስትራቴጂ በመቅረጽ ሴቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ ይሰራል ብለዋል። የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ኢትዮጵያ በዲጂታል 2025 የያዘቻቸውን እቅዶች ለማሳካት ድጋፍ እንደሚያደርግ በመድረኩ ላይ የተገኙት የድርጅቱ ተወካይ ገልጸዋል። በዓለም አቀፍ ደረጃ አካታች ዲጅታል መርሃ ግብሮችን ባለመተግበር በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሴቶች ከኢንተርኔት ተደራሽነት ውጭ እንደሆኑ በመድረኩ ተነግሯል።
ስፖርት
ሁለተኛ ዙር የደርባ ሚድሮክ ሲሚንቶ ወንዶች ቮሊቦል ፕሪሚየር ሊግ በባህርዳር ከተማ ተጀመረ
Apr 1, 2023 33
አዲስ አበባ መጋቢት 23/2015 (ኢዜአ)፦ ሁለተኛ ዙር የደርባ ሚድሮክ ሲሚንቶ ወንዶች ቮሊቦል ፕሪሚየር ሊግ በባህር ዳር ከተማ ዛሬ ተጀምሯል። በባህር ዳር ሚሊኒየም ሜዳ ከቀትር በፊት የስምንተኛ ሳምንት ሁለት ጨዋታዎች ተደርገዋል። ባህር ዳር ከተማ ብሔራዊ አልኮልን 3 ለ 2 እንዲሁም ሙገር ሲሚንቶ መቻልን 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል። በስምንተኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ከቀኑ ዘጠኝ ሰአት መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ይጫወታሉ። የፕሪሚየር ሊጉ ከ8ኛ እስከ 11ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከመጋቢት 23 እስከ 29/2015 በባህር ዳር ከተማ እንደሚካሄዱ የኢትዮጵያ ቮሊቦል ፌዴሬሽን አስታውቋል። ከ12ኛ ሳምንት እስከ 14ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ደግሞ በአዲስ አበባ በማካሄድ ውድድሩን ለማጠናቀቅ መታቀዱንም ፌዴሬሽኑ አስታውቋል። ከአንደኛ እስከ ሰባተኛ የነበሩት የውድድር መርሐ-ግብሮች በወላይታ ሶዶና ሮቤ ከተሞች መካሄዳቸው የሚታወስ ነው። በደርባ ሚድሮክ ሲሚንቶ ወንዶች ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ስምንት ክለቦች ተሳታፊ ናቸው።
የወርልድ ቴኳንዶ ዓለም አቀፍ የዳኝነት የአሰልጣኞች ስልጠና መሰጠት ተጀመረ--የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር
Apr 1, 2023 27
አዲስ አበባ መጋቢት 23/2015 (ኢዜአ)፦ የወርልድ ቴኳንዶ ዓለም አቀፍ የዳኝነት የአሰልጣኞች ስልጠና ዛሬ በአዲስ አበባ መሰጠት መጀመሩን የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀው ይህ ስልጠና የኢትዮጵያ ወርልድ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ከዓለም አቀፉ የወርልድ ቴኳንዶ ጋር በመተባበር መሆኑ ተገልጿል። በስልጠናው መክፈቻ ላይ የዓለም አቀፉ የወርልድ ቴኳንዶ ሊቀ-መንበር ጁንግ ሲዮክ ዮ፣ የዓለም አቀፍ ወርልድ ቴኳንዶ የዳኞች ሊቀ-መንበር አማን ሞራስ፣ የኢትዮጵያ ወርልድ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ዳዊት አስፋው እንዲሁም የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈጻሚ አባላት ተገኝተዋል፡፡ ስልጠናው በንድፈ ሃሳብና በተግባር የተደገፈ ሲሆን ከሳዑዲ አረቢያ፣ ከደቡብ ሱዳን፣ ከኮትዲቯር፣ ከሩዋንዳና ኢትዮጵያ የመጡ ሰልጣኞች ይሳተፉበታል፡፡ ስልጠናውን አጠናቀው የሚሰጠውን ፈተና ያለፉ ሰልጣኞች የዓለም አቀፍ የቴኳንዶ ዳኝነት ሰርተፊኬት እንደሚሰጣቸው የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር በማህበራዊ ትስስር ገጹ ያወጣው መረጃ ያመላክታል። ዓለም አቀፍ የቴኳንዶ የዳኝነት የአሰልጣኞች ስልጠናው እስከ መጋቢት 26/2015 ዓ.ም ድረስ እንደሚቆይ ተገልጿል።
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በ17ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታዎች ዛሬ ወደ ውድድር ይመለሳሉ
Apr 1, 2023 33
አዲስ አበባ መጋቢት 23/2015 (ኢዜአ)፦ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ17ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታዎች ከዛሬ ጀምሮ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ስታዲየም ይካሄዳሉ። ፕሪሚየር ሊጉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከጊኒ ባደረገው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ምክንያት ለሶስት ሳምንት ተቋርጦ ነበር። ውድድሩ በ17ኛ ሳምንት ተስተካካይ መርሐ-ግብር ሲመለስ መቻል ከአዳማ ከተማ ከቀኑ 9 ሰአት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። በፕሪሚየር ሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ መቻል በ23 ነጥብ 5ኛ እንዲሁም አዳማ ከተማ በ21 ነጥብ 12ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። በሌላኛው መርሐ-ግብር ሲዳማ ቡና ከሀዲያ ሆሳዕና ከምሽቱ 12 ሰአት ይጫወታሉ። ሲዳማ ቡና በ19 ነጥብ 13ኛ እንዲሁም ሀዲያ ሆሳዕና በ21 ነጥብ 9ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። የ17ኛ ሳምንት ተስተካካይ መርሐ-ግብር ነገም ቀጥሎ ሲውል ፋሲል ከነማ ከወላይታ ዲቻ ከቀኑ 9 ሰአት እንዲሁም የፕሪሚየር ሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮ ኤሌትሪክ ከምሽቱ 12 ሰአት ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። ተስተካካይ መርሐ-ግብሩ እስከ መጋቢት 26/2015 ይቆያል። ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 17ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በድሬዳዋ ስታዲየም ለማካሄድ ቀን ተቆርጦለት ነበር። በድሬዳዋ ከተማ በጣለው ከባድ ዝናብ ሜዳው በመበላሸቱና በቀላሉ ሊያገግም ባለመቻሉ አንድ የ17ኛ ሳምንት ጨዋታ ከተካሄደ በኋላ አወዳዳሪው አካል ያለውን ነባራዊ ሁኔታ በማየት ቀሪ የከተማው የመጨረሻ ጨዋታዎች መሰረዛቸውን ማሳወቁ የሚታወስ ነው። የፕሪሚየር ሊጉ አክሲዮን ማህበር ውሳኔውን ተከትሎ በባህርዳር፣ አዳማና ሐዋሳ ከተሞች ያሉ ስታዲየሞች ፕሪሚየር ሊጉን ለማጫወት ያላቸውን ዝግጁነት መገምገሙ አይዘነጋም። በዚሁ መሰረት ከ17ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታዎች እስከ 27ኛ ሳምንት ውድድሩ በቅደም ተከተል በመጀመሪያ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየምና በቀጣይ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እንዲካሄዱ አክሲዮን ማህበሩ መወሰኑ ይታወቃል። የፕሪሚየር ሊጉን የደረጃ ሰንጠረዥ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ35 ነጥብ ይመራል። ባህር ዳር ከተማና ኢትዮጵያ መድን በተመሳሳይ 30 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበላልጠው ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል። አርባ ምንጭ ከተማ፣ኢትዮ ኤሌትሪክና ለገጣፎ ለገዳዲ ከ14ኛ እስከ 16ኛ ደረጃን ይዘው ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛሉ።
12 የመደመር ትውልድ የመዝናኛና የስፖርት ማዘውተሪያ ማዕከላት በመጪው ሰኔ ወር ለአገልግሎት ይበቃሉ-ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Mar 30, 2023 110
አዲስ አበባ መጋቢት 21/2015 (ኢዜአ) በመዲናዋ ከ “መደመር ትውልድ” መጽሐፍ ሽያጭ በሚገኝ ገቢ የሚገነቡት 12 የሕጻናትና ወጣቶች የመጫወቻና የስፖርት ማዘውተሪያ ማዕከላት ግንባታቸው በመጪው ሰኔ ወር ተጠናቆ አገልግሎት እንደሚጀምሩ የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። በአዲስ አበባ በ11ዱም ክፍለ ከተሞች የስፖርት ማዘውተሪያና የመጫወቻ ማዕከል ግንባታ የማስጀመሪያ መርሐ-ግብር ዛሬ ተከናውኗል። የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ቆሼ አካባቢ ቴኒስ ሜዳ፣ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ፈረንሳይ የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳና በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሁለት የስፖርት ማዘውተሪያና የመጫወቻ ማዕከላት ግንባታ የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል። ከንቲባዋ በዚህ ወቅት ባደረጉት ንግግር ከ“መደመር ትውልድ” መጽሐፍ የሚገኘው ገቢ ለወጣቶችና ሕጻናት የመዝናኛ ስፍራዎችን ለመገንባት እንዲውል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ መፅሐፉን በስጦታ ማበርከታቸውን አስታውሰዋል፡፡ መጽሐፉ ትውልድ ቀረጻ ላይ ያተኮረ መሆኑን ያነሱት ከንቲባዋ፤ ሽያጩ የሚካሄደውም በሚሰበሰበው ገቢ ትውልድ የሚቀረፅባቸውን ማዕከላት ለመገንባት ነው ብለዋል። በዛሬው ዕለትም 12 የመደመር ትውልድ የስፖርት ማዘውተሪያና የመጫወቻ ማዕከላት ግንባታ መጀመሩን ጠቅሰው፤ በመጪው ሰኔ ወር ግንባታቸው እንደሚጠናቀቅ ጠቁመዋል። ያለፉት ትውልዶች በዘመናቸው ከፈጸሟቸው መልካም ተግባራትና ጉድለቶች የተሻለች ሀገር የሚገነባ ትውልድ ለመፍጠር ሃሳብና ምቹ ስፍራ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። በአእምሮና በአካል የዳበረ ሀገሩን የሚወድ ጠንካራ ትውልድ ለመገንባት በተጀመረው ፕሮጀክት ባለፉት የለውጥ ዓመታት በርካታ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች መገንባታቸውን ገልጸዋል። በቀጣይም በመደመር እሳቤ በሀገሩ የሚኮራ እና ህብረ ብሔራዊ አንድነቱን የሚያስጠብቅ ትውልድ ለማፍራት ከአምስት ሺህ ያላነሱ የስፖርት እና የመዝናኛ ስፍራዎችን እንሰራለን ብለዋል፡፡ ለልጆች የተሻለች ኢትዮጵያን ለመገንባት እንዲሁም በስፖርትና ሥነ-ምግባር የተካኑ የነገ ሀገር ተረካቢዎችን ለማፍራት ሁሉም በትኩረት እንዲሰራ ጥሪ አቅርበዋል። የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ በላይ ደጀን በበኩላቸው ባለፉት ሁለት ዓመታት የከተማ አስተዳደሩ በሰጠው ትኩረት 235 የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ተገንበተው ለአገልግሎት ክፍት መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎቹም የፋት-ሳል፣ እግር ኳስ፣ እጅ ኳስ፣ መረብ ኳስ፣ ቅርጫት ኳስ፣ ቮሊቦልና ጠረጴዛ ቴኒስን ያካተቱ ናቸው ብለዋል።
አካባቢ ጥበቃ
በጣና ሐይቅ ላይ 1ሺህ 250 ሄክታር ስፍራ ሸፍኖ የነበረ የእምቦጭ አረም መወገዱ ተገለጸ
Apr 1, 2023 35
ባህር ዳር፣ መጋቢት 23/2015(ኢዜአ)፦ በጣና ሐይቅ ላይ 1ሺህ 250 ሄክታር ስፍራ ሸፍኖ የነበረ የእምቦጭ አረም መወገዱን የጣና ሐይቅና ሌሎች የውሃ አካላት ጥበቃና ልማት ኤጀንሲ አስታወቀ። በሐይቁ ዙሪያ የሚኖሩ አርሶ አደሮች አረሙን ለማስወገድ ዘላቂ መፍትሔ እንዲበጅ ጠይቀዋል። የአማራ ክልልና የዞን የስራ ኃላፊዎችና የግብርና ቢሮ ሰራተኞች የእምቦጭ አረም ማስወገድ ስራ ዛሬ አከናውነዋል። የኤጀንሲው ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ዘላለም ልየው እንደገለጹት፤ በዘንድሮ ዓመት ብቻ በጣና ሐይቅ 2ሺህ ሄክታር የሚሸፍን ቦታ በእምቦጭ አረም ተወሯል። በደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ እንዲሁም በምዕራብ ጎጃም ዞኖች በሚገኙ 35 ቀበሌዎች አረሙን የማስወገድ ስራ በሕዝብ ጉልበትና በ10 ማሽኖች በመታገዝ የተቀናጀ ስራ መሰራቱን ተናግረዋል። ባለፉት ሶስት ወራት የአካባቢውን ሕብረተሰብ በማሳተፍ በተደረገው ጥረት በሐይቁና በሐይቁ ዳርቻ 1ሺህ 250 ሄክታር ላይ የነበረ የእምቦጭ አረም ማስወገድ መቻሉንም ነው አቶ ዘላለም የጠቆሙት። የእምቦጭ አረም ማስወገድ ስራ ውጤት እያመጣ እንደሆነና፤ በቀጣይ የእምቦጭ አረም ከሐይቁ የማስወገድ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። ባለድርሻ ተቋማትም የበኩላቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ኃይለማርያም ከፍያለው በበኩላቸው የጣና ሐይቅን ብዝሃ ህይወት በዘላቂነት መጠበቅ ለአንድ ተቋም ብቻ የሚሰጥ እንዳልሆነ ተናግረዋል። ለሐይቁ ደህንነት ዋነኛ ፀር የሆነውን የእምቦጭ አረምን ለማስወገድ ቢሮው ከኤጀንሲው ጋር ተቀናጅቶ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል። የሐይቁን ደህንነት በዘላቂነት ለመጠበቅ ሁሉም በእኔነት ስሜት የእምቦጭ አረምን በመከላከል የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል። በፎገራ፣ ሊቦ ከምከምና ደራ ወረዳዎች በእምቦጭ አረም ከተወረረው 75 በመቶ የሚሆነውን ስፍራ ከአረሙ ማጽዳት መቻሉን የገለጹት ደግሞ የደቡብ ጎንደር ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አዲስ ተፈራ ናቸው። ቀሪውን አረም በቀጣይ ወራት ለማስወገድ በወረዳዎቹ የሚገኙ አርሶ አደሮችና አመራሮች በቅንጅት እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።
የዓባይ ተፋሰስን ደህንነት በዘላቂነት ለመጠበቅ የባለድርሻ አካላት ርብርብ ያስፈልጋል-የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር
Mar 31, 2023 52
ባህር ዳር መጋቢት 22/2015 (ኢዜአ) የዓባይ ተፋሰስን ደህንነት በዘላቂነት ለመጠበቅና የሕዳሴውን ግድብ ከደለል ለመታደግ ባለድርሻ አካላት መረባረብ እንዳለባቸው የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አብርሀም አዱኛ ገለጹ። የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን እና የጣናን ሐይቅ ደህንነት መጠበቅ በሚቻልበት ላይ ያተኮረና ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት አውደጥናት ዛሬ በባህር ዳር ከተማ ተካሂዷል። ሚኒስትር ዴኤታው በአውደ ጥናቱ ላይ እንዳሉት፣ ሚኒስቴሩ የዓባይ ተፋሰስ የውሃ አስተዳደርን በአዲስ በማዋቀር የሪፎርም ሥራ እየሰራ ይገኛል። "አገሪቱ በርካታ የውሃ ሃብት ቢኖራትም የውሃ ሃብት አያያዝና ደህንነትን በዘላቂነት መፍታት ባለመቻሉ በአንድ በኩል የውሃ አቅርቦት በሌላ በኩል የጎርፍ መጥለቅለቅ ችግር እየተከሰተ ይገኛል" ብለዋል። ችግሩ በዘላቂነት እንዲፈታ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴርን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማት የተሳተፉበት ጥናት በአሁኑ ወቅት መጠናቀቁን ዶክተር አብርሀም ገልፀዋል። የዓባይ ተፋሰስ ሲታሰብ የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ፣ ጣና ሐይቅ እና ሌሎች የዓባይ ተፋሰሶችን ደህንነት መጠበቅ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑንም አመልክተዋል። የዓባይ ተፋሰስን ደህንነት በዘላቂነት ለማስጠበቅና ግድቡን ከደለል ለመታደግ በመንግስት ከሚደረገው ጥረት ጎን ለጎን የባለድርሻ አካላት ድጋፍ ወሳኝ በመሆኑ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል። "የዓባይ ተፋሰስ በቆዳ ሽፋን የአገሪቱን 20 በመቶ፣ ከአገሪቱ የህዝብ ቁጥር 30 በመቶ፣ ከሃገሪቱ የውሃ ሃብት 45 በመቶ ይሸፍናል" ያሉት ደግሞ የዓባይ ተፋሰስ አስተዳደር ቢሮ ዋና ሃላፊ አቶ የወንድወሰን መንግስቱ ናቸው። ከተፋሰሱ ውስጥ ጣና ሐይቅ እና ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሰፊውን ቦታ እንደሚይዙ ጠቁመው፤ "የተፋሰሱ አካባቢ ለእርሻ፣ ለእንስሳት እርባታና ለዓሣ ማስገር ሥራ በመዋሉ ለጉዳት እየተጋለጠ ይገኛል" ብለዋል። በተፋሰሱ ዙሪያ በተቀናጀ የአካባቢ ጥበቃ ሥራ ክፍተት በመኖሩ ቦታው ለተፈጥሮ ሃብት መራቆት መዳረጉን የገለጹት ሃላፊው፣ "ይህም ጣናን ጨምሮ ተፋሰሶች በደለልና በሌሎች በካይ ኬሚካሎች እንዲሞሉ እያደረገ ነው" ብለዋል። በመሆኑም በተፋሰሱ ዙሪያ ለመጠቀም በሚደረገው ግብግብ ልክ ለደህንነቱ መጠበቅም ባለድርሻ አካላት በትኩረት እንዲሰሩ አሳስበዋል። እንደ ዓባይ ተፋሰስ አስተዳደር ቢሮ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የአጭር፣ የመካከለኛ እና የረጅም ጊዜ እቅድ ተነድፎ እየተሰራ ሲሆን እስካሁን የጣና ሐይቅን ከደለል መሞላት ለመታደግ በገባር ወንዞች አካባቢ የችግኝ ተከላ ሥራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውን ገልጸዋል። በጣና ሐይቅ ተግዳሮቶች ዙሪያ መነሻ ጽሁፍ ያቀረቡት የዓባይ ተፋሰስ የአካባቢ ጥበቃ ባለሙያ አቶ አህመድ ታደለ እንዳሉት፣ ለጣና ሐይቅ ተግዳሮት ዋነኛ ምክንያት በየአካባቢው ያሉ ባለድርሻ አካላት ሃላፊነታቸውን መወጣት አለመቻል ነው። በጣና ሐይቅ ዙሪያ የሚኖረው ህዝብ የተፈጥሮ ሃብት ያላግባብ እንዲመናመን ማድረጉ ለአፈር መሸርሸርና ጣና በደለል እንዲሞላ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል። "ችግሩን ለመፍታት በየአካባቢው ህብረተሰቡን በማስተማር ግንዛቤውን ከማሳደግ ባለፈ ለሐይቁ ዘላቂ ደህንነት የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ማድረግ ያስፈልጋል" ብለዋል። በአውደ ጥናቱ ላይ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የዘርፉ የሥራ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
በምሥራቅ ባሌ ዞን የድርቅ ተጋላጭነትን መቀነስ ታሳቢ ያደረገ 155ሺህ ሄክታር መሬትን የሸፈነ የተፋሰስ ልማት ስራ መሰራቱ ተገለጸ
Mar 26, 2023 186
መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ) በምሥራቅ ባሌ ዞን የድርቅ ተጋላጭነትን መቀነስ ታሳቢ ያደረገ 155 ሺህ ሄክታር መሬትን የሸፈነ የተፋሰስ ልማት ስራ መሰራቱን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ። በዞኑ ባለፉት ሁለት ወራት ሲካሄድ የነበረው የአፈርና ውኃ ጥበቃ ሥራ መጠናቀቁን ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል። የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት እንደገለጸው ባለፉት ሁለት ወራት በተከናወነው የአፈርና ውኃ ጥበቃ ስራ 155ሺህ ሄክታር መሬት የሸፈነ የተፋሰስ ልማት ስራ ተከናውኗል። የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ከድር ይሳቅ በተቀናጀ የአፈርና ውኃ ጥበቃ የተከናወኑ ሥራዎች የድርቅ ተጋላጭነትን በመቀነስ በኩል ጉልህ አስታዋጽኦ እያበረከቱ ነው። በዞኑ ስምንት ወረዳዎች ከ155ሺህ ሄክታር መሬትን በመሸፈን በተከናወነው በዚህ ሥራ 3ሺህ ሄክታር መሬትን ከእንስሳት ንክኪ ማካለልን ጨምሮ የችግኝ ዝግጅት፣ 20ሺህ ኪሎ ሜትር የማሳና የተራራ ላይ እርከን ስራ፣ የግጦሽ መሬት ልማትና ሌሎች የድርቅ ተጋላጭነትን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል። አቶ ከድር እንዳሉት፣ በዞኑ በተደጋጋሚ እየተሰሩ የሚገኙ የተቀናጀ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራዎች የድርቅ ተጋላጭነትን ከመቀነስ በተጓዳኝ የሥራ ዕድል ምንጭ እንዲሆኑ ከ4ሺህ የሚበልጡ ወጣቶችን በዘርፉ ማደራጀት ተጀምሯል። በዞኑ የዳዌ ቃቸን ወረዳ የግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መሐመድ አሚን እንዳሉት፣ በአካባቢያቸው በተደጋጋሚ እያጋጠመ የሚገኘውን የድርቅ ተጋላጭነት ለመቀነስ ለተፈጥሮ ኃብት ጥበቃ ትኩረት ተሰጥቷል። በወረዳው የተቀናጀ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ የተከናወነባቸው ተፋሰሶች በዘላቂነት እንዲጠበቁ ከ30 የሚበልጡ ወጣቶችን በተፈጥሮ ኃብት ማህበራት እንዲደራጁ ተደርጓል ብለዋል። ወጣቶቹ ከእንስሳት ንክኪ በተከለሉና በተፈጥሮ ኃብት በተሸፈኑ አካባቢዎች ውስጥ የንብ ማነብ፣ የእንስሳት መኖ ልማት፣ ሌሎች የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ሥራዎችን እንደሚያከናውኑ ነው የገለጹት። በዳዌ ቃቸን ወረዳ በአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ ከተሳተፉ ነዋሪዎች መካከል አቶ ያህያ አብዱልወሃብ በሰጡት አስተያየት፣ የተቀናጀ የአፈርና ውሀ ጥበቃ ሥራዎች የድርቅ ተጋላጭነትን እንደሚቀንሱ በማመን በስራው መሳተፋቸውን ተናግረዋል። በተለይ ዘንድሮ በአካባቢያቸው በተከናወኑ ሥራዎች ላይ ወጣቶች እንዲደራጁ መደረጉ ሥራውን ውጤታማ ያደርገዋል ነው ያሉት። ወጣት ሙክታር መሐመድ በበኩሉ፣ በሰው ሰራሽ ተጽእኖ የተነሳ አካባቢያቸው ተራቁቶ እንደልብ ይፈሱ የነበሩ ወንዞች በመድረቃቸው ለድርቅ መጋለጣቸውን አስታውሰዋል። ባለፉት ዓመታት በተከናወኑት የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራዎች የተራቆተው አካባቢ አረንጓዴ እየለበሰ መምጣቱ ተስፋ እየሰጣቸው መሆኑን ነው የገለጹት። በአሁኑ ወቅት ከሌሎች 15 የአካባቢያቸው ወጣቶች ጋር የተፈጥሮ ኃብት ጥበቃ ማህበራት በመደራጀት በንብ ማነብና የእንስሳት መኖ እየተሳተፈ መሆኑን አመልክቷል።
በአማራ ክልል በዘንድሮው የበጋ ወራት በ331 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የአፈር እና ውሃ ጥበቃ ስራ ተከናውኗል - የክልሉ ግብርና ቢሮ
Mar 24, 2023 292
ሰቆጣ መጋቢት 15 ቀን 2015(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል በዘንድሮው የበጋ ወራት በ331 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የአፈር እና ውሃ ጥበቃ ስራ መከናወኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ። በክልሉ በበጋው ወቅት የተከናወኑ የተፈጥሮ ሃብት ልማት ስራዎችን እንዲጠብቁ ለአርሶ አደሮች በባለቤትነት የማስረከብ መርሐግብር በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ደሃና ወረዳ ሽመላ ቀበሌ ጋውሳ ተፋሰስ ዛሬ ተካሂዷል። የአማራ ክልል የግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶክተር አልማዝ ጊዜው የክልሉን የተቀናጀ የተፈጥሮ ሃብት ልማት ስራዎች ውጤታማ ለማድረግ ከ14 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የዞንና ቀበሌ ባለሙያዎች የክህሎት ስልጠና መሰጠቱንና 34 ሺህ የሚደርሱ የስራ መሳሪያዎች ለዞኖች መከፋፈላቸውን ለኢዜአ ገልጸዋል። በክልሉ 8 ሺህ 548 ተፋሰሶች ላይ የተፈጥሮ ሃብት ልማት ሥራዎች ለማከናወን ታቅዶ፤ በ8 ሺህ 596 ተፋሰሶች ላይ ስራዎቹ መካሄዳቸውን አመልክተዋል። በልማቱ በ331 ሺህ ሄክታር ላይ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎች መከናወናቸውንና በስራዎቹ ከ4 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ አርሶ አደሮች መሳተፋቸውን ጠቁመዋል። የተፈጥሮ ሃብት ልማት በዘላቂነት በማከናወን የዜጎችን ሕይወት ለመቀየር የሚያስችሉ ተግባራት ለማከናወን መታሰቡን ነው ዶክተር አልማዝ ያስረዱት። በቀጣይም የለሙ ተፋሰሶችን በስነ ሕይወታዊ ዘዴዎች የመሸፈንና የኢኮኖሚ ምንጭ የሚሆኑትን የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ላይ በትኩረት ይሰራል ብለዋል። የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አዲስ ወልዴ እንዳሉት፤ በአስተዳደሩ በ277 ተፋሰሶች ውስጥ የሚገኝ 4 ሺህ 927 ሄክታር መሬት ላይ የተፈጥሮ ሃብት ልማት ስራዎች ተካሄዷል። በልማቱም ከ82 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች መሳተፋቸውንና በዞኑ ባለፉት ዓመታት የተካሄዱት ተፋሰሶች የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት እንዳሳደጉትም ገልጸዋል። በተለይም በተራራ ላይ የተሰሩ የጠረጴዛ እርከኖች ለበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውንና ስራዎቹን በቀጣይም ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል። ኢዜአ ያነጋገራቸው በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ደሃና ወረዳ የሚገኙ አርሶ አደሮች በአካባቢያቸው ባለፉት ዓመታት በወረዳው በተካሄዱት የተፈጥሮ ሃብት ልማት ስራዎች በመሳተፍ የእርሻ መሬታቸውን ለም አፈር በማሳ ውስጥ በማስቀረት ምርታማነታቸውን ማሳደግ መቻላቸውን ገልጸዋል። ዘንድሮ የተካሄዱት የተፈጥሮ ሃብት ልማት ሥራዎች በአግባቡ እንዲጠበቁና እንዲያገግሙ በየአካባቢያቸው የተፈጥሮ ሃብት ኮሚቴ ተዋቅሮ ስራ መጀመሩን ተናግረዋል። በአማራ ክልል በዘንድሮው ዓመት በተከናወኑ የተቀናጀ የተፈጥሮ ሃብት ልማት ስራዎች ሶስት ቢሊዮን ብር የሚገመት የጉልበት አስተዋጽኦ መደረጉን የክልሉ ግብርና ቢሮ መረጃ ያመለክታል'።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
ተመድ በሶሪያ በርዕደ መሬት ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚውል የ397 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ጥሪ አቀረበ
Feb 15, 2023 630
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 8/2015 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሓፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በሶሪያና ቱርክ ድንበር አቅራቢያ በደረሰው ርዕደ መሬት ሳቢያ ከቤታቸው የተፈናቀሉ ሶሪያውያንን ለማገዝ የ397 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ጥሪ አቀረቡ። ዋና ጸሓፊው ጥሪውን ያቀረቡት ባሳለፍነው ሳምንት በቱርክና በሶሪያ ድንበር አቅራቢያ በደረሰው ርዕደ መሬት ሳቢያ ከቤታቸው የተፈናቀሉ አምስት ሚሊዮን የሚጠጉ ሶሪያውያንን ለማገዝ ነው። በኒውዮርክ በሰጡት መግለጫ ሶሪያውያኑን ለማገዝ የተጠቀሰው የገንዘብ መጠን ለሶስት ወራት ጊዜ ብቻ የሚበቃ መሆኑን ጠቅሰው የሚመለከታቸው ሁሉ የድርሻቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል። ከአደጋው በኋላ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 50 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር አስቸኳይ ድጋፍ ማቅረቡን ገልጸው ተጨማሪ እገዛዎች አሁንም እንደሚያስፈልጉ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። በድርጅቱ ስር የሚገኙ የተለያዩ ተቋማትና አጋር አካላት በጋራ በሚያቀርቡት ገንዘብ፤ አስቸኳይ ድጋፍ ለሚፈልጉ ሶሪያውያን የመጠለያ፣ የጤና፣ የምግብ እንዲሁም ሌሎች አስቸኳይ ድጋፎች እንደሚደረጉ አብራርተዋል። ተመሳሳይ የድጋፍ ማዕቀፍ በቱርክ ድንበር ለሚገኙ ዜጎች እየተጠናቀቀ እንደሚገኝም ዋና ጸሓፊው ተናግረዋል።
በተርኪዬ በመሬት መንቀጥቀጥ ለደረሰው ጉዳት ጥልቅ ሀዘን የተሰማው መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ
Feb 6, 2023 629
አዲስ አበባ ኢዜአ ጥር 29/2015፦በደቡባዊ ተርኪዬ በተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት፣ የአካል ጉዳት እና የንብረት መውደም የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ። ሚኒስቴሩ በሀዘን መግለጫው በአደጋው ህይወታቸውን ስላጡት ዜጎች የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጾ፤ ጉዳት የደረሰባቸውም በቶሎ እንዲያገግሙ የመልካም ምኞት መልዕክቱን አስተላልፏል። በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ኢትዮጵያ ከቱርኪዬ መንግሥት እና ህዝብ ጎን የምትቆም መሆኗን መገለጹን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ከባህረ-ሰላጤው ሀገራት ጋር ያለውን ኢኮኖሚያዊ ትስስር እያሳደገው እንደሚገኝ ተገለጸ
Dec 20, 2022 622
አዲስ አበባ ታኅሳስ 11/2015 (ኢዜአ) አህጉራዊው የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና አፍሪካ ከባህረ-ሰላጤው ሀገራት ጋር ያላትን የንግድ ግንኙነትና ኢኮኖሚያዊ ትስስር እያሳደገው እንደሚገኝ ተመላከተ። የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ከአፍሪካ ጋር ያላት የንግድ ትስስር ከባህረ-ሰላጤው ሃገራት መካከል በቀዳሚነት እንደሚጠቀስም ተገልጿል። የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ዋና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዊሊያም ስቴንሀውስ ከሲ ጂ ቲ ኤን ጋር በነበራቸው ቆይታ የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ በተለይም ዱባይ የአፍሪካን ንግድና ኢንቨስትመንት በተመለከተ ዋና ማዕከል ሆናለች ብለዋል። በዱባይ 25ሺህ ገደማ የአፍሪካ ካምፓኒዎች እንደሚንቀሳቀሱ አመልክተው ይህም ሀገሪቱ በነጻ የንግድ ቀጣናው የቢዝነስ አጋር እንድትሆን አስችሏታል ነው ያሉት። አፍሪካውያን ባለሃብቶች የግብይት ማዕከላቸውን በተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ በማድረግና ምርቶችን ወደ አህጉሪቷ በማስገባት በነጻ ንግድ ቀጣናው ስር የገልፍ ሀገራትን ኢኮኖሚያዊ ትስስር እያሳደጉት እንደሚገኝም አስገንዝበዋል። የዱባይ ወደብ በአፍሪካ ያለው ተደራሽነት መስፋፋትም አፍሪካ ከባህረ ሰላጤው ሀገራት ጋር የሚኖራትን የሎጀስቲክስ አቅርቦት እንደሚያሳድግ በመረጃው ተመላክቷል። ከገልፍ ሀገራት ጋር ያለው ግንኙነት ከኢኮኖሚያዊ ትስስር ባለፈ ዲፕሎማሲያዊና ወንድማማችነትን መሠረት ያደረገ ነው ያሉት ደግሞ በተባበሩት አረብ ኤሜሬት የኢትዮጵያ ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሱሌማን ደደፎ ናቸው። አምባሳደሩ እንደሚሉት ከመካከለኛው ምስራቅ መነሻቸውን ያደረጉ ባለሃብቶችና የቢዝነስ ሰዎች ከምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ጋር በልዩ ልዩ ዘርፎች ግንኙነታቸውን እያጠናከሩ ይገኛል። እ.አ.አ በጥር 2021 ተግባራዊ መሆን የጀመረው የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ከአጀንዳ 2063 ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ ነው። የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና የአህጉሪቱን ወሳኝ የኢኮኖሚ ዘርፎች ማለትም የዲጂታል ንግድ፣ የኢንቨስትመንት ትስስርና ሌሎች የንግድ ግንኙነቶችን በነጻ የንግድ ቀጣና ለማከናውን የተካሄደ ስምምነት ነው።
የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎዛ የገዢው ፓርቲ ኤ ኤን ሲ መሪ በመሆን በድጋሚ ተመረጡ
Dec 19, 2022 593
አዲስ አበባ ታኅሳስ 10/2015 (ኢዜአ) ፦የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ገዢውአፍሪካን ናሽናል ኮንግረስ(ኤ.ኤን.ሲ) ፓርቲን በድጋሚ እንዲመሩ ተመረጡ። ፕሬዚዳንት ራማፎሳ በሁለተኛ ዙር እንደሚያሸንፉ ከምርጫው በፊት ሰፊ ግምት ተሠጥቷቸው እንደነበር የፓርቲውን ኃላፊዎች ጠቅሶ የዘገበው ኤንቢሲ ነው። በፓርቲው ስር ድምጽ ሊያገኙ ይችላሉ በሚል እውቅና ከተሰጣቸው ሌሎች እጩዎች ከፍተኛውን ድምጽ በማግኘት መመረጣቸውም በመረጃው ተመልክቷል። ፕሬዚዳንት ራማፎሳ አሁን የገዢው ፓርቲ ሊቀመንበር ሆነው መመረጣቸውን ተከትሎ ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ፓርቲውን የሚመሩ ይሆናል።
ሐተታዎች
ለላቀ ውጤት - የተማሪ መምህርና ወላጆች ጥምር ጥረት
Mar 27, 2023 129
በሃብታሙ ገዜ ስልጡን የመንገድ ጠበብቶች በጥንቃቄ የከተማ ውብ ገፅታ አልበሰው ባነጿት ከዚራ አካባቢ የሚገኘው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አዳራሽ በሰው ተሞልቷል። የተሰበሰቡት ወጣት ተማሪዎች፣ የድሬደዋ አመራሮች፣ የትምህርት ዘርፍን የሚመሩ አካላትና ወላጆች በፈገግታ ተሞልተዋል። ይበልጥኑ ከወጣቶቹ ገፅታ የሚንፀባረቀው የደስታ ፈገግታ ለአዳራሹ የተለየ ብርሃን ደርቦለታል። የደስታቸው ምንጭ ደግሞ አምና የተፈተኑትን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በላቀ ውጤት አልፈው ሽልማት በመቀበል ላይ መሆናቸው ነው። የአዳራሹን የሽልማት መርሃ ግብር የሚመራው ሰው ድንገት "የዛሬው ልዩ ክስተት ከሚሸለሙት ተማሪዎቻችን መካከል ከ600 በላይ ውጤት በማምጣት ከወንድሞቿ ጋር ሦስት ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ የአንድ ቤተሰብ አባላት መገኘታቸው ነው" ሲል ተናገረ። ይሄኔ አዳራሹ በጭብጨባ ተናጋ፤ ሁሉም ተሰብሳቢ በአንድነት ቆሞ ጭብጨባውን አቀለጠው። ለሽልማት ወደ አደባባዩ የመጡት በደስታ ፀዳል የወረዙት የወላጅ ተወካይ እንጂ የድሉ ባለቤት የሆኑት እነዚህ ሦስት ተማሪዎቹ አይደሉም። በአዳራሹ የተሰባሰቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃርና የካቢኔ አባላት እንዲሁም ተሸላሚዎቹ ተማሪዎች "የዓመቱ የተለየ ክስተት የሆኑትን ተማሪዎች" ለማየት ዓይኖቻቸው ቢባዝንም አልተሳካም። ለምን ካላችሁ ተማሪዎቹ ወደ ተመደቡበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጓዛቸው ነው። የመድረኩ የድምፅ ማጉያ ባለቤትም ሆነ ተሰብሳቢዎቹ የዓመቱ ክስተት የሆኑት ኒያ ሰላሃዲን 602፤ አሊ ሰላሃዲን 556፣ አማን ሰላሃዲን 526 ያመጡት ተማሪዎች መንትዮች መሆናቸውን ቢያውቁ ኖሮ አዳራሹ ሌላ የግርምት ደስታን ባስተናገደ ነበር። ሽልማቱን ያበረከቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ተሸላሚዎች በጥረታቸው በትጋታቸው ባመጡት ውጤት መደሰታቸውን አብስረዋል። አገር በዜጎች አንድነትና መተባበር እንደሚፀናው፤ የተማሪዎች ውጤትም በተማሪዎችና በመምህራን ጥረት ብቻ ሳይሆን በወላጆች ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ጭምር የሚመጣ ነው። "በተለይ ከአንድ ቤተሰብ የበቀሉት ተማሪዎችና የዛሬው ሽልማት እና ውጤት ያስተማረን ይህንኑ ነው" ብለዋል ከንቲባው። በዚህ አደራሽ ውስጥ የሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰነ-መምህራን ታድመዋል። እንደ ድሬደዋ አስተዳደር ከተፈተኑት ከ3 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎች መካከል በቀጥታ ያለፉት 250 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። ለመጣው ውጤት ተሞጋሹም ተወቃሹም የዘርፉ አመራሮች፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና ወላጆች ናቸው። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉካ መሐመድ "ለመጣው ዝቅተኛ ውጤት በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ያለነው በሙሉ ተጠያቂዎች ነን" ብለዋል። ኃላፊዋ ሌላውም ከዚህ ትምህርት መውሰድ እንዳለበት ነው የገለጹት። እንደ አስተዳደሩም የትምህርት አመራሮች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራንና ወላጆች ያካተተ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩን አውስተዋል። በመንግስት የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ከኩረጃ ነፃ ለማድረግ የተወሰደው እርምጃ ተማሪዎች በጥረታቸውና በብቃታቸው የልፋታቸውን ውጤት እንዲያገኙ ያስቻለ ነው። የፈተና አሰጣጡና ውጤቱ እንደአገር ያለንበትን አዘቀት አስተምሮ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ፤ ብቁና በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማዋለድም ጥርጊያ መንገድ ሆኖ አልፏል ማለት ይቻላል። መንግስት የትምህርት ጥራትን ከታችኛው እርከን ጀምሮ ለማረጋገጥም በዘርፉ ሙሁራን ጥልቅ ጥናት ላይ ተመስርቶ ያዘጋጀውን የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት ቀርጾ ዘንድሮ እስከ 8ተኛ ክፍል ተግባራዊ አድርጓል። ለመማር ማስተማሩ መጻህፍት ተዘጋጅተው ለመምህራን ስልጠና በመስጠትም ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። በሚቀጥለው ዓመትም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው። በሽልማት ሥነስርዓቱ ላይ እንደታየው ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች ሚና የጎላ ነው። ወላጆች ተገቢውን ድጋፍ እና ጥብቅ ክትትል ካደረጉ የሚፈልገው ለውጥና ውጤት ማምጣት ይቻላል። ወይዘሮ ሙሉካ በአትኩሮት ከገለጹት ሃሶቦች መካከል ዋናዎቹን ሰበዞች መዝዤ፤ "ተጠያቂዎቹ እኛው ነን" የሚለውን ሃሳብ አንግቤ ለድሬዳዋና ለአገር ከፍ ሲል ለዓለም ህዝብ ጭምር በየዘርፉ ታላላቅ ሙሁራን ወደ አፈሩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሁ። ድንገት ሃሳቤን ቀለበስኩት። መነሻዬ የወላጆች ኃላፊነት እና ድጋፍ መሆኑን መርሳት ዞሮ ዞሮ የምፅፈው መዳረሻ መርሳት ይሆንብኛል ብዬ ነው። እናም ወደ ሦስቱዎቹ፤ የዓመቱ ክስተቶች አባት አመራሁ። ድሬዳዋን ለሁለት እኩሌታ የሚከፍላትን የደቻቱን ድልድይ ተሻግሬ ወደአንድ የግል የሕክምና አገልግሎት መስጫ ሆስፒታል ገባሁ። አምሮ በተሰናዳው ሆስፒታል ውስጥ ሙያዊ ኃላፊነታቸው እየተወጡ አገኘኋቸው፤ የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍን። የውጤታማ ተማሪዎቹ ወላጅ ናቸው፤ በ1970 ዎቹ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መዝለቅ በመርፌ ቀዳዳ የመሹለክ ያህል በሚቆጠርበት ዘመን በከፍተኛ ማዕረግ አልፈው በቀሰሙት ዕውቀትና ጥበብ የሰዎችን ሕይወት እየታደጉ ይገኛሉ። ዶክተር ሰላሃዲን ለትምህርት ጥራት መውደቅ ወደ ዩኒቨርሲቲ በስርቆትና ኩረጃ የመግባት ዝንባሌዎች እንደሆኑና ይሄም ሁሌም የሚያንገበግባቸው ጉዳይ መሆኑን አጫወቱኝ። መንግስት በተለይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ባልደረቦቻቸው በሁለተኛ ደረጃ የፈተና አሰጣጥ ላይ የወሰዱት እርምጃ አስደስቷቸዋል። "በተለይ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ከሚያሳልፉት ጊዜ በበለጠ ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸው ጊዜ ይበልጣል። ከሁሉም ነገር በላይ ለትምህርት ትኩረት ማድረጋቸውን መከታተልና መደገፍ የኛ ፋንታ ነው፤ አንዴ መስመር ከያዙ የሚመልሳቸው ችግር አይኖርም" ይላሉ። ሦስቱ ልጆቻቸውን በዚህ መንገድ በመደገፍ እና ከትምህርት ቤታቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ አስችለዋል። 604 ያመጣችው ስኮላርሽፕ ሺፕ አግኝታ ወደ ውጭ ሄዳለች፤ ሁለቱ ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው። "ለልጆቼ የፈለጉትን የማድረግ አቅም ቢኖረኝም ያለትምህርት የሚፈጠር አንዳች ነገር እንደሌለ ገብቷቸው ለውጤት በቅተዋል" ይላሉ ዶክተር ሰላሃዲን። ብዙ የመስራት እንጂ ብዙ የመናገር ዝንባሌ የማይታይባቸው እኚህ የታታሪዎች አባት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራት በሚደረግ ጥረት የወላጆች ክትትልና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ነው በአፅንኦት ያሳሰቡት። "የሽልማቱ መርሃ ግብር ወደሌላ አካባቢ በሄድኩበት አጋጣሚ በመካሄዱ ሳልገኝ ቀረሁ፤ በጣም የቆጨኝና ቅር ያለኝ ዕለት ሆኖ አልፏል" ብለዋል። እሳቸውን ጨምሮ አንቱ የተሰኙ ሙሁራን ያፈራው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ፍቃዱ ሰንበቶ፤ የማርያም ሰፈር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ኢጀታ መኮንን ካለፈው ክፍተት በመማር ዘንድሮ የተሻለ ውጤት እንዲመጣ የተማሪዎች አመለካከት ላይ ለውጥ እና እችላለሁ የሚል መርህ የማስረጽ ሥራ ተሰርቷል ብለውኛል። ለውጤቱ ቀዳሚ ባለቤት ተማሪዎች ቢሆኑም ከወላጆቻቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ የማካካሻና ለፈተና ዝግጁ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ነው ርዕሳነ መምህራኑ የገለጹት። ቅኝቴን በመቀጠል ሽቅብ ወደ ሳብያን ሁለተኛ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት አመራሁ። ይህ ትምህርት ቤት በከተማዋ ካሉት ትምህርት ቤቶች በውጤታማነት እና በብዛት ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማሳለፍ ረገድ ወደር አልነበረውም፤ ባለፉት ዓመታት። ከተመሠረተ 22 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ ትምህርት ቤት በምክትል ርዕሰ መምህርነት የሚመሩት አቶ በፍቃዱ ወልደሰማያትን አገኘኋቸው። ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተናቸው ከ800 በላይ ተማሪዎች መካከል ያለፉት 20 ናቸው። የመጣው ውጤት ያለንበትን ደረጃ ፍንትው አድጎ ያሳየን መሆኑን ተከትሎ መሠረታዊ የሆኑት ችግሮች በጋራ ተነቅሰው ለመጪው ጊዜ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ ተገብቷል። አቶ በፍቃዱ እንዳሉት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ትምህርት ቤቱን ሞዴል ትምህርት ቤት ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን ለዘንድሮው ተፈታኞች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ነው። እነዚህን ሥራዎች የተማሪ፣ መምህርና ወላጅ ህብረት በቅርበት እንዲከታተል ተደርጓል። ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች የቅርብ ክትትልና ደጋፍ መሠረታዊ ጉዳይ ነው የሚሉት አቶ በፍቃዱ፣ ለዚህ ጉዳይ ትምህርት ቤቱ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ነው የገለጹት። "በተለይ ወላጆች በትምህርት ውጤታማነት ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ልክ እንደ ዶክተር ሰላሃዲን አይነት ቤተሰቦች ተሞክሮ የማስፋት ሥራ ለመስራት ትምህርት ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል" ብለዋል። "ፍቃደኛ ከሆኑ የመጀመሪያው እንግዳችን ዶክተር ሰላሃዲን በማድረግ ለወላጆች ህብረት ተሞክሮን እንዲያካፍሉ እናደርጋለን " ብለዋል። በድሬዳዋ ታሪክ ከፍ ሲልም እንደ አገር በ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ1990 ዎቹ ዘመን ጀምሮ እንዲህ አይነት ዝቅተኛ ውጤት አለመምጣቱን የሚገልጹት ደግሞ የትምህርት ቤቱ አንጋፋ መምህር እዮብ ረታ ናቸው። የፊዚክስ መምህሩ እንደሚሉት የአምናው ክፍተት በሰከነ መንፈስ ታይቶ ዘንድሮ የተሻለ ሥራ ለመስራት መምህራን በጥሩ መንፈስ ጉዞ ጀምረዋል። ወላጆችም ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት መላክ ብቻ ሳይሆን የዕለት ተዕለት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው የገለጹት። "የተማሪዎች የትምህርት ቤት ቆይታ ለሰዓታት ብቻ የተወሰነ መሆኑን በመረዳት ወላጆች በስነ ምግባር የታነፀ በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማፍራት የተጀመረውን ጉዞ መደገፍ አለባቸው" በትምህርት ቤቱ የዘንድሮው የ12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪ ረደኤት ገነሙ በበኩሏ "እንደአገር በዩኒቨርሲቲዎች የተጀመረው የፈተና አሰጣጥ ኩረጃን የሚጠየፍ በራሱ ጥረት ውጤት ለማምጣት የሚተጋ ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል" ብላለች። በትምህርት ቤቱ የተጀመረው ልዩ ዕገዛ መጠናከርና መቀጠል እንዳለበት የምትገልጸው ተማሪ ረድኤት ወላጆቿ ተገቢውን ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ከመምህራን ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የልጆቻቸውን ትምህርት ሊከታተሉ እንደሚገባ አውግታኛለች። እኔም ሆንኩ የዘንድሮ ተፈታኞች ትምህርት ቤታችንንና ድሬዳዋን በውጤት ለማስጠራት ጠንክረን እያጠናን ነው ብላለች። ከገጠር ከተማ ተጉዞ የሚማረው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪ አላሙዲን አልይ በበኩሉ፤ መንግሥት የፈተና ኩረጃን ለማስቀረት የጀመረውን ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበት ነው የገለፀው። "የዘንድሮ የመምህራን ድጋፍ የተለየ ነው፤ እኛም ልዩ የጥናት ጊዜ እንዲጀመር ጫና እየፈጠርን ነው፤ ወላጆቼም በአቅማቸው እየደገፉኝ በመሆኑ ቀሪው ሥራ የኔ ጥረትና ብርታት ይሆናል፤ ልፋቴ ውጤት እንዲያስገኝ የስርቆትና የኩረጃ ሂደት መወገድ አለበት" ብሏል ተማሪ አላሙዲን። ከሳብያን ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ግቢ ለቅቄ ስወጣ ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍ ያሉኝ ትዝ አለኝ። "ለተሞክሮ የሚሆን ነገር እኔ ጋር ካለ ያለችኝን ጊዜ አብቃቅቼ ለዘንድሮው ተፈታኞች ሃሳቤን ለማካፈል ዝግጁ ነኝ" ያሉኝ በአዕምሮዬ ደጋግሞ እያቃጨለብኝ ጉዞዬን ቀጠልኩ። ለመውጫ ያህል፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ዘንድሮ በመንግሥት እና በግል 22 ትምህርት ቤቶች ከ5 ሺህ በላይ ተፈታኞች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው። እነዚህ ተፈታኞች በራሳቸው ጥረት የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ በየአቅጣጫው የተቀናጀ ድጋፍ የማድረግ ጅምር ተግባራት ተስተውለዋል፤ ይሄ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ይህን ዙሪያመለስ ድጋፍ በማጠናከር ተማሪዎቹን ለውጤት ማብቃት በሁሉም ዘንድ ለአፍታ መዘንጋት የለበትም። መድረሻውን ለማሳመር መነሻውን አድምቶ ማበጃጀት ግድ እንደሚልም እንዲሁ።
ውጣ ውረድ የማይበግረው አጋርነት
Mar 17, 2023 371
በሰለሞን ተሰራ ኢትዮጵያ በሥልጣኔ ቀደምትና ታሪካዊት ሀገር ነች። ቅሉ ከውጭ ሀገራት ያላትን ዘመናዊው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ቅኝት የጀመረችው በ19ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ መሆኑ በታሪክ ይጠቀሳል። በተለይም ኢጣሊያ በአውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ1896 በአድዋ እንዲሁም በድጋሚ በ1935 ያደረገችው የግፍ ወረራ ኢትዮጵያ የዓለምን ፖለቲካ በቅጡ አሰላለፍ ተረድታ አጋር ሀገራትን እንድትሻ ዐይኗን ገልጦላታል። በዚህም ድኅረ-አድዋ ድል በርካታ ሀገራት ከኢትዮጵያ ጋር መደበኛ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መስርተዋል። የወቅቱ ልዕለ-ኃያል ሀገር አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷ የተመሰረተውም በዳግማዊ አፄ ምኒልክ እና በፕሬዝዳንት ሩዝቬልት መንግሥት ተወካይ ሮበርት ስኪነር መካከል በፈረንጆቹ አቆጣጠር 1903 በተደረሰው የንግድ አጋርነት ስምምነት ነበር። ድኅረ-ስምምነቱም በፈረንጆቹ በ1909 የአሜሪካ ሌጋሲዮን በአዲስ አበባ የተመሰረተ ሲሆን ሆፍማን ፊሊፕ የተባሉት ቋሚ መልዕክተኛ የአሜሪካ ቆንስላ ተሿሚ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለአፄ ምኒልክ አቅርበዋል፡፡ ከ120 ዓመታት በላይ ዕድሜ ያስቆጠረው የኢትዮ-አሜሪካ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በጽኑ ወዳጅነትና የጋራ ጥቅሞች ላይ የተመሰረተ እንደነበር ይወሳል፡፡ ሀገራቱ ጥቅማቸውን በጠበቀ መልኩ የመሰረቱት ግንኙነት ሰላምን፣ መረጋጋትን እና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለማምጣት ታሳቢ ያደረገ መሆኑም አይዘነጋም፡፡ የፋሽስት ኢጣሊያ ወረራን ተከትሎ ቆንስላዋን የዘጋችው አሜሪካ፤ ኢትዮጵያ በአርበኞቿ ትግል ነፃነቷን ስታረጋግጥ በፈረንጆቹ አቆጣጠር በነኅሴ 1943 በድጋሚ ቆንስላዋን በመክፈት ግንኙነቷን አስቀጥላለች። በተመሳሳይ ወቅት ኢትዮጵያ በአሜሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ የቆንስላ ቢሮ ከፍታ ዕውቁን ዲፕሎማት ብላታ ኤፍሬም ተወልደመድኅንን በቋሚ መልዕክተኛነት ሾማለች። በአውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ1952 የተደረገው 'ፖይንት ፎር' የተሰኘው የተቋማት ቴክኒክ ድጋፍ ስምምነት ለሁለቱ ወዳጅ ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ይበልጥ መሰረት የጣለ እንደሆነ የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ፡፡ በዚህ ስምምነትም የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የአውራ ጎዳና ባለሥልጣን እና የኢትዮጵያ ካርታ ሥራ ድርጅት በአሜሪካ መንግሥት ድጋፍ ተቋቁመዋል። የሁለትዮሽ ግንኙነቱ አድማሱን እያሰፋ፣ ሥር እየሰደደ ቀጥሎ ኢትዮጵያ ጦር ሠራዊቷን እንድታጠናክር በአነስተኛ የጦር መሳሪያዎች፣ ተሽከርካሪዎችና ወታደራዊ ሥልጠናዎች ተጨባጭ አጋርነት አሳይታለች። የደርግ ወታደራዊ መንግሥት ሥልጣን በተቆጣጠረ ማግስት ግን በዘመኑ በነበረው ዓለም አቀፋዊ ርዕዮተ- ዓለም ልዩነት ሳቢያ የሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ሻክሮ ሌላ መልክ ያዘ። በተለይም የደርግ ሊቀ-መንበር የነበሩት ሌተናል ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም ወደ ሶቪየት ሕብረት አቅንተው የጦር መሳሪያ ድጋፍ መፈራረማቸው አለመግባባቱን ይበልጥ አባባሰው። በዚህም አሜሪካ በኤርትራ የነበረውን የቃኘው ሻለቃ ጣቢያዋን ዘግታ ወጣች። ሀገራቱ ግንኙነታቸውን ከአምባሳደር ደረጃ በማውረድ በጉዳይ አስፈጻሚ ሲገናኙ ቆይተዋል፡፡ ኢሕአዴግ ወደ ሥልጣን ሲመጣ የሀገራቱ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ቀድሞ ወደነበረበት የአምባሳደር ደረጃ በመመለስ ከአሜሪካ ጋር የነበረው ግንኙነት መልሶ እንዲያንሰራራ አድርጎታል፡፡ ባለፉት 30 ዓመታት አሜሪካ በጤና፣ በሰብዓዊ ድጋፍ፣ በመልካም አስተዳደርና በዴሞክራሲ ተቋማት ግንባታ ላይ በምታደረገው ድጋፍ በመታገዝ በጋራ ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡ ከሦስት ዓመታት ወዲህ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ አሜሪካ መርህን ያልተከተለ አካሄድ በሀገራቱ መካከል የነበረውን ወዳጅነትና አጋርነት ላይ ጥቁር ጥላ ማጥላቱ አይዘነጋም፡፡ ነገር ግን ባለፉት ሦስት ዓመታት በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ሻክሮ የቆየውን ግንኙነት በማደስ የነበረውን ጠንካራ ወዳጅነት በድጋሚ የሚያጸኑ ጅማሮዎች ተስተውለዋል። በተለይም ጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ.ም. በአፍሪካ ሕብረት መሪነት የተደረሰውን የሰላም ሰምምነት ተከትሎ የሀገራቱ መቃቃር እየረገበ ሲሆን የአሜሪካ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ኢትዮጵያን በተደጋጋሚ እየጎበኙ ነው፡፡ ይህን ተከትሎ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ከትናንት በስቲያ አዲስ አበባ የገቡት የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን፤ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ እና ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ተነጋግረዋል። አንቶኒ ብሊንከን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ያደረጉት ውይይት ዘርፈ-ብዙ አጋርነትን ለማጠናከር መግባባት የተደረሰበት እንደነበርም በሁለቱም ወገኖች ተገልጿል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ውይይቱ በተለያዩ የሀገር ውስጥ፣ ቀጣናዊ እና የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ እንደሆነና በኢትዮጵያ እና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል ያለውን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ስምምነት የተደረሰበት እንደሆነ አስታውቀዋል። ኢትዮጵያ በሰላም ስምምነቱ ላይ እያስመዘገበች ያለችው ስኬት ተቀባይነት ማግኘቱንም ጠቅሰዋል። በኢኮኖሚው መስክ በተለይም በግብርና እና በቀጣናዊ መረጋጋት ላይ ባተኮሩ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በመስጠት መነጋገራቸውን በመልዕክታቸው ጠቁመዋል። በተመሳሳይ አንቶኒ ብሊንከን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ባደረጉት በሁለትዮሽና በቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ በትኩረት መክረዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ሚኒስትሮቹ ለረዥም ዘመን የዘለቀውን የኢትዮ-አሜሪካ ትብብር እና አጋርነት ለማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ተነጋግረዋል። በኢትዮጵያ አዲስ የመረጋጋትና የሰላም ምዕራፍ መከፈቱን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ለአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን አብራርተውላቸዋል። የሰላም ምዕራፍ የበለጠ እንዲጠናከርና የሰመረ እንዲሆን ከዚህ ባለፈም የሀገሪቱን በጎ ገጽታ እንዲላበስ መንግሥት በቁርጠኝነት እንደሚሰራም አረጋግጠዋል። የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ ሀገራዊ ኢኮኖሚያዊ እምርታ እንዲመጣ ለሰላም ስምምነቱ ተፈፃሚነት መንግሥት አሁንም ቁርጠኛና ጠንካራ ፍላጎት እንዳለው ጠቅሰው፤ በመልሶ ግንባታ እና መልሶ ማቋቋም ተግባር የአሜሪካ መንግሥት እንዲደግፍም ጠይቀዋል፡፡ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በበኩላቸው፤ የሀገራቱ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሻገር አሜሪካ በትብብር መንፈስ እንደምትሰራ እና አሜሪካ ሁለንተናዊ ድጋፏን እንደምታጠናክር አረጋግጠዋል። አሜሪካ ለድርቅ ተጎጂዎች እና ለስደተኞች የምታደርገው ድጋፍ አለመቋረጡ የሁለቱ ሀገራት አብሮነት ተጠናክሮ መቀጠሉን ይጠቁማል፡፡ የብሊንከን የአፍሪካ ጉብኝት ከኢትዮጵያ መጀመሩም ዛሬም ኢትዮጵያ በአሜሪካ መንግሥት ዐይን ያላትን ቀዳሚ ሥፍራ ያመለክታል። አንቶኒ ብሊንከን የሰላም ትግበራ ሂደቱ በመልካም ሁኔታ ላይ መሆኑን ጠቁመው፤ የበለጠ እንዲጠናከር የአሜሪካ መንግሥት ሁለገብ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት የሁለቱን ሀገራት ሁለንተናዊ ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ቁርጠኛ መሆኑን ማረጋገጡን አስታውቀዋል። ኢትዮጵያ በአካባቢው ሰላምና መረጋጋት እንዲመጣ እያደረገች ያለውን ጥረት አሜሪካ በአድናቆት እንደምትመለከተውና የሚበረታታ መሆኑን ብሊንከን ገልጸዋል። የብሊንከንን ጉብኝት ተከትሎ አሜሪካ 331 ሚሊየን ዶላር ተጨማሪ የሰብዓዊ ድጋፍ ለኢትዮጵያ እንደምታደርግ አረጋግጣለች። ድጋፉም በተለያዩ ምክንያቶች ለተፈናቀሉ ወገኖች ነፍስ አድን ሰብዓዊ ድጋፍ የሚውል መሆኑ ተገልጿል።
የሴቶች ቀን ሲታሰብ
Mar 8, 2023 550
የሴቶች ቀን ሲታሰብ የሰው ልጅ ሕይወትን ቀላል ባደረጉ የፈጠራ ስራዎቻቸው የምናስባቸው እንስቶች በቀዳሚነት ይነሳሉ። በተለያዩ መስኮች አሻራቸውን ያሳረፉ እንስቶች ቁጥራቸው ከፍተኛ ቢሆንም በዚህ ጽሑፋችን ግን በኬሚስትሪና ፊዚክስ ዘርፍ በአለም አቀፍ ደረጃ ባበረከቱት አስተዋጽኦ በኖቤል ሽልማት እውቅና የተሰጣቸውን የየዘመኑ ፈርጦች እንዳስሳለን። ከነዚህ ፈርጦች መካከል በኬሚስትሪ ዘርፍ የኖቤልን ሽልማትን ከሴቶች ቀዳሚ በመሆን በቀዳሚነት ያሸነፉት ሜሪ ኩሪ ይወሳሉ። ይልቁንም እ.አ.አ በ1903 በኬሚስትሪ ዘርፍ የተቀበሉትን የኖቤል ሽልማት በድጋሚ በ1911 በመሸለም ብቸኛነት ስማቸው ይነሳል። በ1967 በፖላንድ ዋርሶ የተወለዱት ማሪ ኩሪ ለዘመናዊው የሳይንስና ኬሚስትሪ ዘርፍ ውለታን ከዋሉ ስመጥር ተመራማሪዎችና በጨረራ ህክምና ፈጠራ የዘርፉ ፈር ቀዳጅ በመሆን የአለምን የራዲዮአክቲቪቲ እይታን የቀየሩ ጀግና ናቸው። የሜካኒካልና ኤሮስፔስ ተመራማሪዋ ፍራንሲስ አርኖልድ ደግሞ በህክምናናና በታዳሽ ኃይል ዘርፍ አሻረቸውን በጉልህ ካኖሩ ተመራማሪዎች መካከል ይጠቀሳሉ። አሜሪካዊቷ ፍራንሲስ ለታዳሽ ኃይል እና ለፋርማሲ አገልግሎት የሚውል አዲስ ኢንዛይም በምርምር በማግኘት በዘረፉ አሻራቸውን አኑረዋል። ለዚህም አስተዋጽኦዋ እ.አ.አ በ2018 በኬሚስትሪ ዘርፍ የኖቤልን ሽልማት አሸንፈዋል። የኤድስን ስርጭትን በመከላከል ረገድ ሰፊ አበርክቶ ያላቸው የህክምና ተመራማሪዋ ፍራንሶዝ ባሪሲኖሲም የሴቶች ቀን ሲታሰብ ከሚወሱ አንስቶች አንደኛዋ ናቸው። ባሪሲኖሲ የኤች አይቪ ኤድስን ከገዳይ በሽታነት መታከምና መቆጣጠር ወደ ሚችል በሽታነት ለመቀየር የኤች አይቪ ኤድስ ምርመራን በማላቅ ረገድ ሚናቸው የጎላ እንደሆነ ይወሳል። በ1947 በፓሪስ ከተማ የተወለዱት ባሪሲኖሲ “ሳይንስን ለሰው ልጆች ጥቅም እንዲውል እንሰራለን” በሚለው አባባላቸው ይታወቃሉ። ኤድስን በመከላከል ላደረጉት አስተዋጽኦም በፊዚዮሎጂ/ሕክምና ዘርፍ እ.አ.አ በ2008 የኖቤል ሽልማትን አግኝተዋል። ያለ ህክምና ትምህርት የሚሊዮኖችን ሕይወት በታደገው የወባ በሽታ መከላከያ ፈጠራቸው አለም እውቅና የተሰጣቸው ቱ ዩዩ በሴቶች ቀን የምናመሰግናቸው ሌላኛዋ ተመራማሪ ናቸው። ቻይናዊቷ ቱ ዩዩ ባህላዊውን የወባ በሽታ መከለከያ ህክምና ወደ ዘመናዊ በመቀየርና በማስተዋወቅ ነው ስመ ገናና የሆኑት። የወባ በሽታን በመከላከል ረገድ በአለም አቀፍ ደረጃ ጉዙፍ አሻራቸውን ላስቀመጡት ተመራማሪ ባለውለታነት እ.አ.አ በ2015 በፊዚዎሎጂ/ ህክምና ዘርፍ ሳይንስ ምድብ የመጀመሪያዋ ቻይናዊት በመሆን የኖቤል ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። የሰው ልጆችን ሕይወት ካቀለሉ አለም አቀፍ ፈጠራዎች መካከል የተጠቀሱትን ጨምሮ በሌሎችም ዘርፎች የሴቶች ተሳትፎ የጎላ መሆኑ ይታወቃል።
ሴትነት እና እናትነት
Mar 8, 2023 847
(አየለ ያረጋል) እስኪ መላ ስጪኝ መላ ካንቺ ይገኛል እኔማ ወንድ ነኝ ይደናገረኛል… (የማኅበረሰቡ ቃላዊ ግጥም) ሴትነት እናትነትን ለመግለጽ ቀርቶ በጥቂቱ ለመረዳት የ’እናት ልብ’ መታደል የሚሻ ይመስላል። ጥቂት ወንዶች ይህን ጸጋ ይቸራሉ። ልክ እንደ ዶክተር ይሁኔ አየለ። የስነ-ምግብ ሳይንቲስቱ ዶክተር ይሁኔ አየለ ‘እናት’ በሚል ርዕስ ባሳተሙት ድንቅ መጽሐፍ የሴትነት እና እናትነትን ከፍታ በ’ኩርሽም’ ቃላት ተራቀውበታል። የሴቶች ቀንን (ማርች-8) ሰበብ በማድረግ ይህን ጽሑፍ ሳዘጋጅ መታሰቢያነቱ እናትን አስበው በ‘እናትነት’ ቅን ልቦና ‘እናትን’ ላበረከቱልን ዶክተር ይሁኔ አየለ ነው። ‘እናት፤ የሴት ልጅ ስንክሳር፤ ከቤተሰባዊ ሕይወት እስከ ሐልዮመንበርት’ በሚል ርዕስ በቅርቡ ባሳተሙት (በ406 ገፆች በተቀነበበ) አርበ ጠባብ መጽሐፍ ሴትነትን ከዘፍጥረት እስከ አሁን ዘመናትን ዋጅተው፣ እናትነትን ከሴትነት ዘንቀው፣ የእናትነት ጸጋን ከነባራዊ ሃቅ ጋር አሰነናስለው፣ የእናትነትን ልዕለ-ተፈጥሮ አርቅቀው፣ የዓለምን ክብር-ነሽነት ከነገረ-ሃይማኖት እስከ ነገረ-ባህልና ፍልስፍና ፈትተው፣ የማኅበረሰቡን ምልከታ ዝንፈት እና ሚዛን ጉድለት ከማኅበራዊ እስከ ፖለቲካዊ መገለጫዎች አዛምደው አቅርበውታል። ዶክተር ይሁኔ አየለ “እናት” በተሰኘ እናት የሆነ መጽሐፋቸው እናትነትን በልኩ ነጽረውታል። ሴትነት በኢትዮጵያ የአስተሳሰብ ሰለባነቱን፣ ነገረ-ሴትነትን ከንጽረተ-ሴትነት ቃኝተውታል። በእሳቤ ሚዛን ሰለባነት ዓለም ውስጥ ከንግስት ማክዳ እስከ ንግስት ፉራ፣ ከሰብለ ወንጌል እስከ ድል ወንበራ፣ … ብርቱ ኢትዮጵያዊት ሴቶችን ሕይወት ጨልፈውታል። የሴትነትን ጸጋዎች ጨልፈው በሴትነት ላይ የሚፈጸሙ የሀበሻ ግፎችን ተንትነውበታል። ሴቶች የማኅበረሰቡ ግፍ ሰለባዎች፣ የማኅበራዊ ፍትህ ጉድለት ሰለባዎች እንደሆኑ በቅጡ ገልጸውታል። ዳሩ ሴትነት ጀግና እና ብልህ፣ የቤተሰብ መሰረት፣ የደስታና እልልታ እናት፣ ቃል ኪዳንና ክብር ጠባቂ እንደሆነ ገልጸዋል። “ሴት ልጅ ባለብዙ ጸጋዎች ናት። ከጸጋዎቿ መካከል ጀግንነት እና ብልሃት ይጠቀሳሉ። … ሴት ልጅ ባህልን ፈጥራ የማኅበራዊነትን ማስተሳሰሪያ ገመዶች ገምዳ አስተሳስራ ማኅበረሰብን የተከለች ሥርዓት ናት። … ቤተሰብ የአንድ ማኅበረሰብ የመጀመሪያ ተቋም ነው። የተቋሙ ባለሥልጣን (እመቤት) ሴት ናት። ያቺ ሴት እናት ናት። ቤተሰብ የስብዕና መሰረት የሚባለው እናትን ምሰሶ አድርጎ ነው” (ገጽ-285) ሴት ልጅ መለኛ መሆኗን ማኅበረሰባችን ቢያምንም ሴትነትን ግን እንዳላከበረ አሉታዊ ይትባህልና ኪነተ- ቃሉን ዘይቤ ያወሳሉ። በእርግጥ የእናትን ምቹነት እና ዋጋ ከፋይነት የሚያትቱ የአማርኛ ተረትና ምሳሌዎችም አሉ። ለምሳሌ ዳንኤል አበራ “የአማርኛ ተረትና ምሳሌዎች” በሚለው መጽሐፋቸው “እናት ትረገጣለች እንደመሬት፤ እናት ለልጄ ልጅ ለነገዬ፤ እናቷን አይተህ ልጅቷን አግባ፤ እናት የሌለው ልጅ እንደ ጌሾ፤ ሳይበላ የበላ ሳይናገር ዋሾ…” የሚሉ ምሳሌያዊ ንግግሮችን አስፍረዋል። መላኩ ይርዳው የተባሉ ጸሐፊ ‘ደቦ ቅጽ-፩’ ከተሰኘው የ60 ደራሲያን ሥራዎችን ያካተተ መጽሐፍ ውስጥ ‘የሴትነት ጸጋ’ በሚል በጻፉት መጣጥፍ ሴትነትን ከፍቅር፣ ከጥበብ፣ ከብልሃትና ልዕልና ጋር አቆራኝተውታል። “ሴት ልጅ ቅኔ ናት፤ ከተባለላት፣ ከተጻፈላት፣ ከተዜመላት በላይ የረቀቀች ረቂቅ ቅኔ ናት። እስከዛሬ ከያኒያን ስለሴት ከተራቀቁት፣ ከተጠበቡት ሁሉ እኔ ለማውቃት ሴት ሁሉ የሚመጥኑ ሆነው አልታዩኝም። የሴትነት ጸጋው ብዙ ነውና የሴትን ትክክለኛ ማንነት መርምረን አጥንተን የደረስንበት ውስጠ-ስሪቷን አጥንተን የተረዳነው አይመስለኝም።… ከታላቅነቷ፣ ከብልሃቷ፣ ከረቂቅነቷ፣ ከመግዛት አቅሟ፣ ከርህራሄዋ፣ ከሰላማዊነቷ ከሌሎችም አያሌ በረከቶች አንጻር ለሴት ልጅ የተደረገላት፣ የተነገረላትና የሆነላት ሁሉ ያንስብኛል” ኃይሉ ገብረዮሐንስ (ገሞራው) ስለሴት ልጅ ጭቆና የታገለ እና ስለክብሯ የዘመረ ምሁር ነው። ስለሴት ልጅ ስቃይና ሰቆቃ አትቷል። ‘በናቴኮ ሴት ነኝ’ በሚለው መጽሐፉ ስንኞች እንምዘዝ! …. ግማሽ አካሏ ወንድ በትምክህት ቢከዳት ጧ! ብላ አለቀሰች አዛኝ ቢደርስላት፣ … ብሶት ተጫጭኗት ምንም ሰው አልሆነች በቀቢጸ ተስፋ ሕላዌንም ጠላች ያገሬ ጭቁን ሴት መድኅን መላ ያጣች….! ‘ሔዋንያት የትውልድ ፋብሪካዎች ናቸው፤ እነሱ ባይኖሩ ዓለም ባዶ ትሆን ነበር’ እንዲል ፈላስፋው ሶቅራጥስ። ስለሴት (ግማደ ሰቧ ፍጡር) ግፍና በደል ገሞራው እንዲህ ይላል። “መራራ ጭቆና በሰፈነበት ምዝብር ሕብረተሰብ ውስጥ ታፍነው የሚኖሩ ሔዋንያት ብሶታቸው፣ ፍዳቸው፣ በደላቸው፣ ጭንቀታቸውና መከራቸው እንደ ሰማዕታት ገድል እጥፍ ድርብ ነው…. አጉል ልማድ፣ ኋላቀር ባሕልና አድሃሪ ሕገ-ማኅበረሰብ ከከንቱ አስተሳሰቦች ጋር ተዳምሮ በአንድነት በመመሳጠር ዘርዓ ሔዋንን ሲጫወቱባቸው ሲያሾፉባቸው ኑረዋል” (ገጽ-23) በሥነ-ሕይወት ሳይንስና በትምህርተ-ጄነቲክስ (አካለ ሕላዌ) ሴቶችን ከወንዶች የሚያሳንስ ምንም አይነት አካላዊ ተሰጥኦ እንደሌለ ተረጋግጧል። ታሪክና ተረክ ግን ወገንተኛ መሆኑን ገሞራው ይናገራል። ተረክና ተረት አልባሌ ታሪክ የሚፈጥሯቸው አርበኞች ሁሉ በፆታቸው ተባዕት በመሆናቸው፤ በሴቶች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ በማሳደሩ ሊኖራቸው የሚችለው ዕድገት ላይ ትልቅ ደንቃራ ሆኖ መቆየቱን ይገልጻል። “የታሪክን ሁኔታዎችን የመመንዘር ትርጓሜያዊ አንጻር የታሪክን ትዕይንቶች ብንመረምር አንደርድሮ የሚያደርሰን ሴቶች ከወንዶች የከፋ ባህሪያዊ ድክመት እንዳለባቸው ከሚያሳይ ሥዕል ላይ ነው።” በሚት(ተለጣጭ ተረክ) ላይ የሚራቀቁት አቶ ቴዎድሮስ ገብሬ (በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፎክለር መምህር) ‘ተረኮች እማዊ ሳይሆን አባዊ ናቸው’ በማለት ይህን ጉዳይ ያጠናክሩታል። “በሚት ውስጥ ገነው ከሚታዩ አበይት ማኅበራዊና ባህላዊ እውነታዎች መሃል አንዱ ፆታዊ ወገንተኝነት ነው። የሰማናቸው፣ ያነበብናቸው ሚታዊ ተረኮች በእጅጉ አባዊ ለሆኑ ሥርዓቶች (ፓትሪያርካል ሲስተምስ) ያደሩ፣ በአብዛኛው በተባዕት ተጋዳሊያን የተሞሉ ናቸው” ይላል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዶክተር ይሁኔ (በገፅ-401) ስለሰው ማንነት ቀረጻ በተመለከተ ከጥንት እስከ ዛሬ አከራካሪ የሆኑ ፈላስፎችን ክርክር ያነሳሉ። ይኸውም የሰው ልጅ ‘ማን ቀረጸኝ? ተፈጥሮ ወይስ ተሞክሮ?’ የሚለውን መከራከሪያ ጽንሰ-ሃሳብ ይፈትሻሉ። በዚህም “ሰዎች ሲፈጠሩ የሰውየውን ችሎታ ይዘው ነው” እና “የሰዎች ማንነት የሚቀረጸው ከውልደት በኋላ በተሞክሮ ወይም ከአካባቢ ጋር በሚኖራቸው መስተጋብር ነው” የሚሉትን ሃሳቦች ወስደው ከእናት ሚና ጋር ያዛምዱታል። እናም እናት ‘በየትኛውም መደብ ልጅን አሳምራ ትቀርጻለች’ የሚል ድምዳሜ ሰጥተዋል። “በየትኛውም መንገድ በሰው ልጅ ላይ የእናት ቀራፂነት ስለሚኖር ከተጽዕኖዋ ማምለጥ የሚቻል አይመስለኝም።… አካባቢም ሰውን ይሰራዋል የሚሉትም ከውልደት በፊትም ሆነ በኋላ ከተፈጥሮ ጋር የሚደረገው ውስብስብ መስተጋብር ‘ሰው’ በመሆን ላይ ጉልህ ሚና ይጫወታል” ይላሉ። በዚህ እሳቤ ሰው የወላጆቹም፤ የአካባቢውም ውጤት መሆኑን በግልጽ እንረዳለን” ይላሉ። ሴቶች ከጥንት እስከ ዛሬ በኢትዮጵያ ማኅበረ-ባህላዊ እንዲሁም ለሰላምና ዕርቅ እሴቶች ጉልህ ሚና አላቸው። ሴቶች ያልተሳተፉበት ዘርፍ የለም። ከመሪነት፣ ጥበበኝነት፣ ከአገር ድንበር ጠባቂነትና የዲፕሎማሲያዊ ሚና… መጥቀስ ይቻላል። ሴቶች በሁሉም ማኅበረሰብ ዘንድ በሰላምና ግጭት አፈታት ግንባር ቀደም ተሰሚነት አላቸው። ለአብነትም ሀደ ሲንቄ፣ በሶማሌ-ሔር፣ በሲዳማ-ያካ፣ በራያ ማኅበረሰብ ዱበርቲዎች፣ በስልጤ-ሴረን ባህል መጥቀስ ይቻላል። ከሰሞኑ ባከበርነው የአድዋ ድል የኢትዮጵያ ሴቶች ውለታ በወፍ በረር ማውሳት ይቻላል። የኢትዮጵያ ሴቶች ከሌላው ዓለም ሴቶች በተለየ የራሳቸው ቀለም ያላቸው፣ የአመራር ልምድ ያዳበሩ፣ የመወዳደሪያ ስነ-ልቦና ያላቸው፣ ችለው አሸንፈው ያሳዩ ናቸው። ሴቶች ድሉን በማስመዝገብ የተጫወቱትን ሚና ያህል፣ ገድላቸው በታሪክ በሚገባ አልተወሳም። ዶክተር አልማው ክፍሌ የተባሉ የታሪክ ምሁር በአንድ ወቅት ሚዲያ ላይ ቀርበው “በአድዋ ጦርነት ዘማቾች 75 በመቶ ሴቶች ነበሩ” ሲሉ ሰምቻለሁ። በአድዋ ጦርነት ሴቶች በተለያዩ ሙያዎች ተመድበው ከካምፕ እስከ ጦር ሜዳ ከመመገብ እስከ ማጀገን፣ ከማከም እስከ መዋጋት ድንቅ ሚና ተወጥተዋል። ድርብ ድርብርብ ኃላፊነት ይዘው የዘመቱ፣ ለወንዶችም ልብ፣ ሞራልና ወኔ አቀባዮች ነበሩ። እቴጌ ጣይቱን መሰል የአድዋ ሴት የጦር ፊታውራሪዎች በርካታ ናቸው። ጸሐፌ ትእዛዝ ገብረሥላሴ ወልደአረጋይ ‘ታሪክ ዘመን ዘዳግማዊ ምኒልክ’ በተሰኘው መጽሐፋቸው የሴቶችን ሚና በተመለከተ እንዲህ ይላሉ፡- “እንዲህም እየሆነ፣ አጤ ምኒልክ ባዳራሹ እቴጌ ጣይቱ በእልፍኝ ባለሟሎችዎን ወይዛዝርቱን ይዘው ግብሩ አንድ ቀን ሳይጎድል፣ ይዘምታሉ። ከዘመቻ ላይ ጠጁ ማሩ አለመጉደሉ፣ ስለምንድነው ያልህ እንደሆነ ይህን ታሪክ መመልከት ነው። በስድስት ድንኳን እንጀራው ሲጋገር ሲያድር፣ በአራት ድንኳን ወጡ ሲሠራ ሲያድር፣ ጠጁ በቀንድ በኮዳ ደግሞ ሦስት መቶ ስድስት መቶ የሚሆን ገንቦኛ ሲጓዝ ግብሩ ይጎድል ይመስልሀል” (ገጽ-241) ደራሲ በዕውቀቱ ሥዩም ‘ከአሜን ባሻገር’ በተሰኘ መጽሐፉ ‘ሴቶች በዋሉበት’ በሚል ርዕስ የኢትዮጵያ ሴቶች ተጋድሎና ሚና “ከቁስ ባሻገር ከልብ ያቀርባሉ” ይላቸዋል። “ሴቶች ባዋላጅነት ከነበራቸው የማይተናነስ ሚና በጦር ሜዳ ተጫውተዋል። እናቶቻችን በጦር ወቅት፣ መሳሪያ ያቀርቡ ነበር። ምግብ ያቀርቡ ነበር። ሃሳብ ያቀርቡ ነበር። ልብ ያቀርቡ ነበር። ደስታ ያቀርቡ ነበር። ኧረ ምኑ ቅጡ። ሴቶች ባንድ በሙቀጫ ዙሪያ፣ ማኅበረሰቡን ኬሚስት፣ ገጣሚና የፖለቲካ ተንታኝ ሆነው ማገልገላቸውን ልብ እንበል” ይላል። (ገጽ-138) ዶክተር ይሁኔ (በገጽ-14) በበኩላቸው እናቶችን ሩህሩሆች፣ አጉራሽና አልባሽ፣ የችግር ቤዛዎች፣ ሕይወት ዑደት አስቀጣዮች፣ የሕይወት መድኅኖች፣ ባለብዙ ጸጋዎች፣ መልካም ባህሪ አውራሾች፣… በማለት ገልጸውታል። መላ ሴቶችንም በእናቶች አተያይ ማየት እንደሚገባም እንዲሁ። “እናትነት መልካም ገጽታዎችን ደራርቦ የያዘ የሴት ልጅ ትልቅ መገለጫ ነው። እናትነት ከፍ ያለ ሥልጣን ነው። እናትነት ጥልቅና ሰናይ ባህሪያት የሚፈልቁበት ምንጭ ነው። እናትነት የደግነት፣ የጥራት፣ የልህቀትና ተፈላጊነት ማሳያ ተምሳሌት ነው። እናትነት ሞት የማያደበዝዘው ኃያል መንፈስ ነው። እናትነት ከባድ ተጽዕኖ ፈጣሪነት ነው። … እናትነት የሰላም፣ የመልካም ግንኙነትና እንክብካቤ መፍለቂያ አድባር ናት። እናትነት ሰፊና ጥልቅ የሕይወት ትምህርት ቤት ነው። እናትነት ሌሎች ከስቃይ ነፃ እንዲሆኑ፣ ምቾት እንዲሰማቸው በሚደረግ ትግል ውስጥ ዋጋ እየከፈሉ መኖር ነው” በመቀጠልም የኢትዮጵያ እናቶችን ‘ጠቃሚ ነገር ሰጪዎች’ ይላቸዋል። “እናቶች ሰው የመሆኛ ቅመሞች የሚጨለፍባቸው ባህር ናቸው። … ሕይወታዊ ስሪታችን ብዙ ጠቃሚ ነገሮችን የወሰደው ከእናት ነው። ከእናት የምናገኘው ‘ማይቶኮንድሪያ’ (ማይቶኮንድሪያ የኃይል ማመንጫ ክፍል ሲሆን የምንመገበው ምግብ እየተቃጠለና ወደ አስፈላጊው ኃይል እየተቀየረ ሕይወትን ያንቀሳቅሳል) የምግብ ማቃጠያ ምድጃ ወይም ኃይል ማመንጫ ቤት ሆኖ ያገለግላል። … ብዙ መልካም ስብዕና መገለጫዎች ምንጫቸው የእናት ፍቅር፣ የመልካም ስብዕና እና የርህራሄ ምንጭ ነው” (ገጽ- 61) ኢያሱ በካፋ ‘የኢያሱ በካፋ ወጎች’ በተሰኘው መጽሐፉ እናትነትን ማህጸንን፣ ምግብን፣ ትንፋሽን፣ ደም፣ ሥጋን እና ነፍስን ሰጥተው በረቂቅ ተፈጥሮ ሰውን ከመውለድ ባለፈ ፍቅራቸውን ዘላለማዊ ገደብ አልባ እና ዕልቆ-ቢስ እንደሆነ እንዲህ ገልጾታል። “እናትነት ነፍስን ማካፈል ነው፤ እናትነት የማይደበዝዝ ዘላለማዊ ፍቅር መስጠት ነው፤ እናትነት ከራስ ሕልውና ይበልጥ ለልጅ ማሰብ ነው፤ እናትነት ፍፁም ወረት አልባ መሆን ነው። እናት ለልጇ ያላት ፍቅር አይነጥፍም፤ አይለወጥም። ለእናት ልጇ ሁሌም ልጇ ነው” (ገጽ-4) እናትነት በቃላት ለመግለጽ እንደሚከብድ፤ በውለታ ማካካስ ይከብዳል። የእናት ውለታዋን መክፈል የሚችል ልጅ የለም። የእናት ፍቅርን ለመግለጽም በርካቶች አንደበታቸው ይተሳሰራል፤ ቃላት ይነጥፍባቸዋል፤ ስሜታቸውን መግራት ይሳናቸዋል። ድምፃዊ እሱባለው ይታየው(የሺ) ‘ይናገራል ፎቶ’ በሚል እናትና አባቱን በገለጸበት ሙዚቃ የመጨረሻው ማጠንጠኛው ‘እወድሻለሁ/እወድሃለሁ’ ያለው፤ እንዲሁም ድምፃዊት ብዙነሽ በቀለ ‘እናት ውለታዋ’ በተሰኘ ዘፈኗ ውስጥ (ዜማና ግጥም ጋዜጠኛ ሰለሞን ተሰማ)፤ “ወላጅ እናት እኮ ፍፁም በመንፈሷ፣ ልጇን ትወዳለች አብልጣ ከራሷ” እያለች በሚስረቀረቅ ድምጿ የምታንጎራጉረው ለዚህ ይመስላል። ዕውቁ የቋንቋ ሊቅ የሻው ተሰማ (የኮተቤው) ‘የጥቁር አፈር ትሩፋቶች’ በተሰኘው መጽሐፉ (ገጽ-79) ‘መቀነትሽን አጥብቂ’ በሚል ርዕስ ባሰፈረው ረዘም ያለ ግጥም ሁለት አንጓዎች ብቻ ስንመዝ የእናትነት ውለታን መመለስ እንደሚሳን፤ የእናትነት ግብሯ ‘እናት’ የሚለው ቃል በራሱ እንደሚያንስባት ያትታል። … “ለዚህ ወሮታሽ አጸፋ፤ እናት ይልሻል አገሩ፤ እኔም እናቴ ብልሽ መች ሊመጥንሽ ዳሩ። … እናትነት ምጡቅ ነው፤ እናት ከመባል ይልቃል፤ የግብርሽ ስንክሳር ዚቁ፤ በስያሜ መች ያልቃል”… በማለት ይገልጸዋል። መውጫ ዶክተር ይሁኔ የሴት እና እናትን የነገዋን መንገድ ከሳይንስ አተያይ አንጽረው፤ ከማኅበረ-ፖለቲካ፤ ከማኅበረ-ባህል ከፍታዋ አመሳክረው፤ እናትና ሀገርን መጋመድ አመስጥረው መልእክታቸውን እንደ መውጫ አስፍረዋል። ለስንበት አንድ አንቀጽ እንወርውር!! “የእናት ሀገር ህልውና ከእናቶች ሕይወት ጋር በቀጥተኛ ተዛምዶ አለው። የሰመረ ትውልድ ሊቀጠል የሚችለው በጥሩ ሁኔታ በተገነባ የእናቶች አቅም ነው። የእናቶች አቅም ሲገነባ የራሳቸውን አቅም ያውቃሉ፤ ምርጫቸውን በራሳቸው ይወስናሉ፤ እንዲሁም ለሚመጣው ማኅበራዊ ለውጥ የራሳቸውን አሻራ ያሳርፋሉ። ስለሆነም የእናቶችን አቅም ማጎልበት ትውልድን ማጎልበት ነው። እናቶች ላይ መሥራት ትውልድ ላይ መሥራት ነው”
ትንታኔዎች
የአየር ንብረት ፋይናንስ-አፍሪካውያን ገፍተው ያልሄዱበት መንገድ
Feb 18, 2023 638
/በገዛኸኝ ደገፉ/ የአፍሪካ ቀንድ ከ40 ዓመታት ወዲህ ተከስቶ አያቅም የተባለለትን የድርቅ አደጋ እያስተናገደ ይገኛል፡፡ በዚህም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የሰብዓዊ ዕርዳታ ፈላጊ ሆነዋል። የድርቁ አደጋ የከፋበት የአፍሪካ ቀንድ ይሁን እንጂ አብዛኞቹ የአፍሪካ ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥ አሉታዊ ተጽዕኖዎችን ተሸክመዋል። በተጨማሪም የከተሞች መስፋፋትና የከተሜነት የኑሮ ዘይቤን እያስተናገደች ባለችው አፍሪካ የኃይል እጥረት፣ በቂ የመሰረተ ልማት አውታሮች ዝርጋታ አለመኖር፣ ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረግ ፍልሰት፣ ሥራ አጥነት ብሎም የወንጀሎች መስፋፋት አሕጉሪቱን ክፉኛ እየፈተኗት ይገኛሉ። የገጠር መሬት ምርታማነት መቀነስ ከገጠር ወደ ከተማ ለሚደረገው ፍልሰት አንደኛው ገፊ ምክንያት ሲሆን ለመሬቱ ምርታማነት መቀነስ ሰበብ ተደርጎ በዋናነት የሚጠቀሰው ደግሞ የአየር ንብረት ለውጥና የበረሃማነት መስፋፋት የሚወልዳቸው የውኃ ኃብት መቀነስና ለተከታታይ ዓመታት የሚዘልቁት የድርቅ አደጋዎች መሆናቸው ጉዳዩን ይበልጥ አወሳስቦታል። እንደ አህጉር ከ4 በመቶ ያነሰ የካርቦን ልቀት ያላት አፍሪካ 65 በመቶ የሚሆነው ህዝቧ የችግሩ ቀጥተኛ ገፈት ቀማሽ መሆን ከጀመሩ ዓመታት ተቆጥረዋል። ከዚህ ችግር ሙሉ ለሙሉ መውጣት ባይቻልም ትርጉም ባለው ደረጃ መቀነስ እንዲቻል አህጉሪቱ ያላትን የተፈጥሮ ኃብትና ወጣት የሰው ኃይል በማስተሳሰር ለውጥ ማምጣት ግድ ይላታል። በአፍሪካ የማይቀረውን የከተሞች መስፋፋትም ሆነ የህዝቦቿን የመልማትና የመለውጥ ፍላጎት ማሟላት ካለባት የአየር ንብረት ፋይናንስን የበለፀጉ ሀገራት ገቢራዊ ሊያደርጉት ይገባል። የአየር ንብረት ፋይናንስ (Climate Finance) የአካባቢ፣ ብሔራዊ ወይም ድንበር ተሻጋሪ ፋይናንስን የሚመለከት ሲሆን ከሕዝብ፣ ከግል እና ከአማራጭ የገንዘብ ምንጮች የተውጣጣ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቅረፍ እና ለማስተካከል የሚወሰዱ እርምጃዎችን የሚደግፍ ዓለም አቀፍ ስምምነት ነው። የኪዮቶ ፕሮቶኮል እና የፓሪስ ስምምነት ደግሞ ሰፊ የገንዘብ አቅም ካላቸው አገራት አነስተኛ የኃብት አቅም ላላቸው እና ይበልጥ ተጋላጭ ለሆኑ አገራት የገንዘብ ድጋፍ እንዲደረግ የሚጠይቅ ስምምነት ነው። ስምምነቱ “የጋራ ግን ደግሞ ልዩነት ያለው ኃላፊነትና አቅም” በሚለው መርህ መሰረት ያደጉ አገሮች አዳጊ አገራትን ለመርዳት የገንዘብ ምንጮችን እንዲያቀርቡ ይጠይቃል። ፋይናንሱ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቀነስ ወሳኝ ድጋፍ እንደሚሆን ታምኖበታል። ምክንያቱም ልቀትን በከፍተኛ ሁኔታ ለመቀነስ ላቅ ያለ የኢንቨስትመንት አቅም የሚጠይቅ በመሆኑ። በተመሳሳይ ከአሉታዊ የአየር ንብረት ተጽዕኖዎች ጋር ለመላመድ እና ተለዋዋጭ ጫናዎችን ለመቀነስ የአየር ንብረት ፋይናንስ ከፍተኛ የገንዘብ አቅም ይጠይቃል። ከጥቂት አሥርት ዓመታት በፊት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተዘጋጅቶ የቀረበው የምእተ ዓመቱ የልማት ግብ ሰነድም ሆነ በቅርቡ በሚጠናቀቀው ዘላቂ የልማት ግቦች ላይ ለጉዳዩ ከፍ ያለ ትኩረት ቢሰጠውም እስካሁን ግን የፈየደው ነገር የለም። አፍሪካ የአየር ንብረት ተጽዕኖዎችን ለመላመድ ዓመታዊ 41 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር የፋይናንስ ክፍተት ይገጥማታል። ይህን ክፍተት ለመሙላት አዲስ አበባ እያስተናገደች ባለችው 36ኛው የአፍሪካ መሪዎች ጉባዔ ላይ የአየር ንብረት ፋይናንስ ገቢራዊ ማድረግን ቀዳሚ ትኩረታቸው መሆን እንዳለበት የአንድ ዘመቻ (ONE Campaign) አጽንኦት ሰጥቶ ምክረ ሃሳቡን ሰንዝሯል። የአፍሪካ ኅብረት እና የምስራቅ አፍሪካ የአንድ ዘመቻ ዳይሬክተር ዶሪን ኒኒናሃዝዌ የአፍሪካ መሪዎች የአየር ንብረት ለውጥን ለመላመድ ፋይናንስ ድጋፍን በማረጋገጥ የአየር ንብረት ለውጥን አስከፊ ተጽዕኖ የመቋቋም አቅም እንዲገነቡ መክረዋል። አፍሪካ ባልፈጠረችው የአየር ንብረት ለውጥ ህዝቦቿ ለከፋ ጥቃት እየተዳረጉ ይገኛሉ። ስለዚህ የአፍሪካ መሪዎች የበለጸጉ አገሮች የገቡትን የማላመድ ፋይናንስ ድጋፍ ቃል እንዲፈጽሙ ከማግባባት ባለፈ ማሳሰብ ይኖርባቸዋል ብለዋል። ይህ ማለት እኤአ ከ2020 እስከ 2025 በዓመት 100 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚገመተውን ግብ የማሳካት ተግባር የሚጠይቅ ነው። ከዚህ ባሻገር በቀጣዮቹ ዓመታት በተጨመሩ መዋጮዎች የሚስተዋሉ ጉድለቶችን መፍታት እና በግብጿ ሻርም ኤል ሼክ ከተማ ባስተናገደችው COP-27 ላይ በተደረሰው ስምምነት መሰረት ለመላመድ በእጥፍ ፋይናንስን የማቅረብ ቁርጠኝነት የማቅረቢያ ዕቅድ ሊነድፉ ይገባል ነው ያሉት። የአፍሪካ አገሮች ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ፣ ከሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት እና ከአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖዎች ጋር ሲታገሉ ቢቆዩም አሁን ላይ “አፍሪካ በአፈፃጸሙ ላይ መጠነኛ መሻሻል አሳይታለች” ብለዋል። እናም በ36ኛው የመሪዎቹ ጉባዔ የተገኙ ስኬቶች እና የጠፉ ዕድሎች እንዲሁም የድርጅቱን ዓላማዎች ለማሳካት በአየር ንብረት ፋይናንስ በጥልቀት መክረው ለተሻለ ስኬት ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል። የዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (IOM) ዋና ዳይሬክተር አንቶኒዮ ቪቶሪኖ በአየር ንብረት ምክንያት የሚፈጠሩ መፈናቀልን ለመግታት የተሻሻሉ የመላመድ እና የተጽዕኖ ቅነሳ ተነሳሽነት ገቢራዊ ለማድረግ በአገራት መካከል ጠንካራ አጋርነትን መፍጠር ወሳኝ መሆኑን ያሰምሩበታል። በተለይ በአፍሪካ ቀንድ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ በተፈጥሮ ሃብት ላይ ኑሯቸውን መሰረት ባደረጉ ህዝቦች ላይ አውደ-ተኮር መላመድ እና የመቋቋም አቅም ግንባታ መፍጠር ይገባል። ለዚህ ደግሞ መላመድን የሚደግፉ ፋይናንስ ለማግኘት የሚረዱ መመሪያዎች ይበልጥ የተፍታቱ መሆን ይኖርባቸዋል ሲሉ ቪቶሪኖ ይሞግታሉ። ከ 36ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ በተጓዳኝ በተካሄደው ከፍተኛ የውይይት መድረክ (High-Level Forum) ላይ ዳይሬክተሩ እንዳሉት በሻርም ኤል ሼክ በተካሄደው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ መላመድን፣ መከላከልን እና ዝግጁነትን ለማሻሻል ዓለም አቀፍ ትብብር ማጎልበት ልዩ ትኩረት መሰጠቱን አውስተዋል። የመንግሥታቱ ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥን አስመልክቶ ያወጣቸው የስምምነት ማዕቀፎች (United Nations Framework Convention on Climate Change (UNFCCC)) በርካታ ዝርዝርና ሚዛናዊ አካሄዶችን የያዙ ናቸው። ያም ሆኖ አተገባበራቸው እዚህ ግባ የማይባል በመሆኑ የሚታሰበውን ያህል ለውጥ ማምጣት ሳይችል ቀርቷል። በዚህም ቦረና ዞንን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ ቀንድ ህዝቦች ለከፋ የምግብ እጥረት ተጋልጠዋል። የአየር ንብረት መዛባት፣ የሙቀትና የባህር ጠለል መጨመር፣ ጎርፍ፣ ድርቅ እንዲሁም ያልተገመቱ ተፈጥሯዊ አደጋዎችን ለመቀነስ የአየር ንብረት ፋይናንስ ዓይነተኛ አማራጭ እንደሆነ ብዙዎቹ ይስማሙበታል። ዳሩ ግን አገራትን፣ አህጉርን፣ ዓለምን እንዲሁም መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ዓለም አቀፍ ተቋማትና ግዙፍ ኩባንያዎችን ያስተሳስራል የተባለለት የአየር ንብረት ፋይናንስ በቅጡ ገቢራዊ ማድረግ ባለመቻሉ የአፍሪካ ቀንድን ጨምሮ በርካታ ህዝቦች ዳፋውን ለመጋፈጥ ተገደዋል። የአየር ንብረት ፋይናንስን በመተግበር በመስኩ የተጎጂዎችን ቁጥር ሊቀንሱና የዓለምን ሥነ-ምህዳር ከተቻለ ወደ ቀድሞው ሊመልሱ አሊያም አሁን ባለበት አረጋግተው ሊያቆዩ የሚያስችሉ በርካታ አማራጮች ተግባራዊ ሊደረጉ ይገባል። ለአብነትም ለድሃ ሃገራት አርሶ አደሮች የግብርና ምርቶች ተገቢውን ዋጋ በመክፈል የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን እንዲቋቋሙ ማድረግ ከአማራጮቹ መካከል አንዱ ተደርጎ የሚወሰድ ነው። ግዙፎቹ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ለሚያስወግዷቸው በካይ ጋዞች ተመጣጣኝ የጤና ሥርዓት በመዘርጋት የታዳጊ ሃገራት ዜጎችን የጤና አገልግሎት ማሻሻል ሌላው አማራጭ ነው። የተፈጥሮ ኃብቶችን የሚጎዱ የኢንዱስትሪ ዘርፎች ተፈጥሮን በሚንከባከቡ ዘዴዎች መተካት እንዲሁም ብክለትን የሚያስቀሩ የምርት ሂደቶች መለማመድ ጥቂቶቹ የመፍትሄ አማራጮች ተደረገው የሚወሰዱ ናቸው። በፓሪስ ከተደረሰውን የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት ቀደም ብሎ በፈረንጆቹ 1994 ዓለም አቀፍ የአካባቢ ጥበቃ ተቋም (Global Environment Facility-GEF) COP-16 ዓለም አቀፍ ጉባዔ በኋላ በ2010 አረንጓዴ የአየር ንብረት ፈንድ (Green Climate Fund-GCF) እንዲሁም በ2001 ደግሞ ልዩ የአየር ንብረት ለውጥ ፈንድ (Special Climate Change Fund-SCCF) እና የመላመድ ፈንድ (Adaptation Fund-AF) የተባሉ ማዕቀፎች የተዘጋጁ ቢሆንም ስለጉዳዩ የሚያስረዱ ተከታታይ ስብሰባዎች ከማዘጋጀት በዘለለ ብዙ ርቀት መጓዝ ሳይችሉ ቀርተዋል። በቅርቡ በአለም ባንክ አሰባሳቢነት በኬንያ ናይሮቢ ተዘጋጅቶ በነበረው የአህጉሪቱን መሪዎች ባለሃብቶችንና ምሁራንን ባካተተውና “One Planet Summit” በተሰኘ መሰል ጉባዔ ላይም አፍሪካውያን ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ የሚገጥማቸውን ችግሮች ተከላክለው ሁለንተናዊ ዕድገታቸውን እንዲያፋጥኑ ካስፈለገ የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም የምጣኔ ኃብት ፖሊሲ አዘጋጅተው መተግበር እንደሚኖርባቸው መግባባት ላይ የተደረሰ ቢሆንም አሁንም ጥያቄ ያስነሳው አፈጻጸሙ ስለመሆኑ ብዙ ተብሎለታል። ክላይሜት ፖሊሲ ኢኒሽየቲቭ የተባለ ድርጅት ይፋ ያደረገው ሪፖርት እንደሚያመለክተው አፍሪካ እንደ ፈረንጆቹ የጊዜ ቀመር ከ 2020 እስከ 2030 ባሉት አሥር ዓመታት 2 ነጥብ 8 ትሪሊየን የአሜሪካ ዶላር አሊያም በየዓመቱ ከ2 መቶ ሃምሳ ቢሊየን ዶላር በላይ የሚያስፈልጋት ሲሆን አህጉሪቱ ከዘርፉ እያገኘችው ያለው ገንዘብም ከሚያስፈልጋት 12 በመቶውን ወይም 30 ቢሊየን ዶላር ብቻ ስለመሆኑ አስነብቧል። አፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥን ተቋቁመው ሊሰሩ የሚችሉ በርካታ ተግባራት እንዳሏት የሚያትተው ሪፖርቱ ከአየር ንብረት ፋይናንስ የሚገኘው ገንዘብ በትራንስፖርት፣ በኃይል ልማት፣ በኢንዱስትሪ ብሎም በግብርና፣ በአፈርና በደን ኃብት አጠቃቀም ውጤታማ በሆነ መንገድ ከዋለ የአህጉሪቱን የተፈጥሮ ኃብቶች መንከባከብ ከማስቻሉም ባለፈ ላቅ ያለ ፋይዳ ይኖራዋል ብሏል። ይህ ሲሆን የሥራ ዕድል በመፍጠር የሥራ አጥ ቁጥርን በመቀነስ ለአህጉሪቱ ሰላምና መረጋጋት ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖው ያስረዳል። ላለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ ገቢራዊ እየተደረገ የሚገኘው የአረንጓዴ አሻራን የማስፋፋትና የተጎዱ አካባቢዎችን የማከም ሥራ እንዲሁም አይቀሬ የሆኑትን ከተሜነትና የማምረቻ ኢንዱስትሪዎች መስፋፋት ታሳቢ ያደረጉ የአየር ንብረት ፖሊሲዎች ተግባራዊ መደረጋቸው ለአፍሪካ ሃገራት እየፈጠረው ያለው በጎ ተጽዕኖ በግልጽ እየታየ ነው። ይህ የኢትዮጵያ ጥረት ግን በአየር ንብረት ፋይናንስ እንዲደገፍ አገራዊና የተቀናጀ አሕጉራዊ ጥረት ማድረግን ይጠይቃል። ከአጠቃላይ የአፍሪካ አገራት መካከል ደቡብ አፍሪካ፣ ኢትዮጵያ፣ ናይጄሪያ እና ግብጽ ብቻ 151 ቢሊየን ዶላር ከአየር ንብረት ንብረት ፋይናንስ ማግኘት እንደሚኖርባቸው የክላይሜት ፖሊሲ ኢኒሽየቲቭ ሪፖርቱ ይገልጻል። ለዚህ ደግሞ ኢትዮጵያ በመጭው የCOP-28 ጉባዔ የራሷንና የአፍሪካን ፍላጎት የሚያስጠብቁ የፋይናንስ ትልሞችን የመንደፍ ተሳትፎ ማድረግ ይጠበቅባታል፡፡ የ COP-27 ጉባዔ ለአፍሪካ ያስገኘውን ውጤት እና አንድምታ የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ የመሪዎች ኮሚቴ ሰብሳቢ እና አስተባባሪ በሆኑት በኬንያው ፕሬዝዳንት ሰብሳቢነት በኅብረቱ የአዲስ አበባ ጉባዔ ላይ በጥልቀት ይገመግማል ተብሎ ይጠበቃል። እዚህ ላይ ኢትዮጵያ ጥረቷን የሚያጎለብት የገንዘብ ድጋፍ ለማግኘት ጠንካራ ተሳትፎ ልታደርግ ይገባል። የአፍሪካ አገራት ገፍተው ረጅም ርቀት ያልሄዱበት የአየር ንብረት ፋይናንስ እና ሌሎች የድጋፍ አማራጮችን በፍትሃዊነትና በምክንያታዊነት በመጠቀም የአየር ንብረት ተጽዕኖን የሚቋቋሙበት ጠንካራ አቅም ሊገነቡ ግድ ይላቸዋል። በእርግጥም አፍሪካውያን መሪዎች በሚያደርጉዋቸው ስብሰባዎች በየማዕዝናቱ በድርቅ ሳቢያ ለምግብ እጦት የተዳረጉ ህዝቦቻቸውን የሚታደጉበት ሁነኛ የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኙበትን ዘዴ ነድፈው ረጅም ርቀት ሊጓዙ ይገባል። ”
ዛሬ የሚጀመረው 36ኛው የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ በተለያዩ አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል
Feb 18, 2023 602
"የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና መቀላጠፍ" በሚል መሪ ሃሳብ የሚካሄደው የዘንድሮ የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2019 ወደ ሥራ የገባውንና 1 ነጥብ 4 ቢሊየን ሕዝብ በንግድ ለማስተሳሰር የታለመውን የንግድ ቀጣና ይበልጥ ተግባራዊ ማድረግ በሚቻልበት ጉዳይ ላይ ይመክራል። በተለይም ደግሞ የጋራ የጉምሩክ ሥርዓትና ወጥ የታሪፍ አስተዳደር በአህጉሪቷ ለመተግበር ትኩረት ይደረግበታል ተብሏል። ሌሎችም የእርስ በርስ የንግድ ግንኙነትን የሚያቀጭጩ አሰራሮች ነቅሶ በማውጣት የተሳለጠ የንግድ ሥርዓት ለመፍጠር ምክክር አድርገው አቅጣጫ እንደሚያስቀምጡ ይጠበቃል። የአፍሪካ የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ በአፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ የተከሰተው ድርቅና ረሃብ እንዲሁም በዩክሬንና በሩስያ ጦርነት ምክንያት አደጋ ላይ የወደቀው የአህጉሪቱ የምግብ ዋስትና ችግር እልባት በሚሰጡ ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ምክክር ያደርጋል ተብሏል። በተለይም ደግሞ የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም የግብርና ሥራ ለማሳለጥና በአህጉሪቱ ዘመናዊ የእርሻ ሥራ በሚስፋፋባቸው ሁኔታዎች ላይ ውይይት እንደሚደረግ ተጠቁሟል። ይህም በዘላቂነት የአህጉሪቱን የምግብ ፍላጎት በራስ አቅም ለመሸፈን የሚደረገውን ጥረት የሚያግዝ ይሆናል ተብሏል። በመሆኑም የዛሬው ጉባዔ ትኩረቱ በዚሁ የምግብ ዋስትና ሁኔታ ላይ እንደሚሆን ብዙ ግምት ተሰጥቶታል። የአፍሪካ የ2063 አጀንዳ አፈጻጸም ባለፉት አሥር ዓመታት በአፍሪካ ሰላምና ደኅንነት ለማረጋገጥ እንዲሁም የበለጸገች አፍሪካን ለመገንባት የተጣለውን የረዥም ጊዜ ዕቅድ ከግምት በማስገባት የተሰሩ ሥራዎች ይገመግማል ተብሏል። ለቀጣይ አሥር ዓመታት በተለያዩ ዘርፎች ላይ ትኩረት ሊደረግባቸው በሚችሉ አንኳር ጉዳዮች ላይ ምክክር ተደርጎ አቅጣጫ እንደሚቀመጥም ነው የተገለጸው። በተለይም ደግሞ ዋና ዋና የሚባሉ ስኬቶችን በመገምገምና ያጋጠሙ ችግሮችን በመለየት መጪውን አሥር ዓመት የተሻለ ለመፈጸም የሚያስችል የትግበራ ማዕቀፍ እንደሚዘጋጅ ይጠበቃል። ከዚህም ባሻገር አፍሪካ በፋይናንስ ራሷን እንድትችል እየተደረገ ያለውን ጥረትም ትልቅ ሥፍራ ይሰጠዋል ተብሎ ይጠበቃል። ለአብነትም የኅብረቱ ሰላም ፈንድ የሚደረገው የአባል አገራት መዋጮና አገራት ከታክስ ገቢያቸው ለኅብረቱ በማዋጣት አጠቃላይ የኅብረቱን ወጪ በራስ አቅም ለመሸፈን የሚደረገውም ጉዳይ ምክክር ሊደረግበት የሚችል ጉዳይ ሊሆን ይችላል። በአፍሪካ ሰላምና ደኅንነት ማረጋገጥ በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ በቻድ፣ በካሜሮን፣ ኒጀር፣ በናይጄሪያ አካባቢው ከጽንፈኝነት ጋር በተያያዘ በርካታ የጸጥታ ችግሮች እየተከሰቱ ሲሆን ይህም ለበርካቶች ሞትና መፈናቀል ምክንያት ሆኗል። በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምስራቃዊ ክፍልም የትጥቅ ትግል መቀስቀሱ የተዘገበ ሲሆን ይህም አገሪቱን ከሚያዋስኑ አገራት ጋርም አለመረጋጋት ፈጥሯል። በሰሜን ሞዛምቢክ ያለው የጸጥታ ችግርም አሁንም እልባት ያላገኘ ጉዳይ ነው። ደቡብ ሱዳንና ኢትዮጵያ የሰላም ስምምነት ትግበራ ሂደት ላይ ናቸው፤ ሱዳን ሕዝባዊ አስተዳደር ለመመሥረት የሽግግር ትግበራ ላይ ናት። በመሆኑም የአፍሪካ ኅብረት በእነዚህና በሌሎች የጸጥታ ጉዳዮች ላይ ምክክር ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።
ዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ - የአፍሪካ የዘመናት ፈተና
Feb 13, 2023 605
በረከት ሲሳይ በርካታ የአፍሪካ አገራት ነፃነታቸውን ከተቀዳጁበት ከ1960ዎቹ ጀምሮ እስካሁን እልባት ካልተገኘላቸው አፍሪካዊ ጉዳዮች መካከል ዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ አንዱ ነው። ለዚሁ ጉዳይ በርካታ መነሾ ቢኖሩትም ቅኝ ግዛቱ የፈጠራቸው ፖለቲካዊ ስንጥቃቶች፣ ድህነትና ሌሎች ማኅበራዊ ምስቅልቅሎሽ ለእነዚህ የጸጥታ ችግሮች በአብዛኛው የሚነሱ ምክንያቶች ናቸው። በአህጉሪቱ ላለፉት 40 እና 50 ዓመታት መቋጫ በሌለው መልኩ እዚህም እዚያም የሚነሱ ግጭቶችና ጦርነቶች ለአያሌዎች ሞትና የአካል ጉዳተኝነት ለገሚሱ ደግሞ ለዘመናት ከኖረበት ቀዬ እንዲሰደድ ምክንያት ሆነዋል። በብዙ ጥረት የተገነቡ መሰረተ-ልማቶች ወደ ፍርስራሽነት እንዲለወጡና በሂደት ላይ ያሉ የዘመናዊ አገር ግንባታ ሂደቶች እንዲስተጓጎሉና በፈተናዎች እንዲታጀቡ አድርጓል። ይህንኑ ኢኮኖሚያዊ ኪሣራ በሚያሳይ መልኩ፤ የዓለም የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) ከሁለት ዓመታት በፊት ያወጣው ሪፖርት እንደሚያሳየው፤ በአፍሪካ የሚከሰቱ የጸጥታ ችግሮች በየዓመቱ የአገራቱን አጠቃላይ አገራዊ ምርት (ጂ ዲ ፒ) እድገት ከ4 በመቶ እስከ 6 በመቶ እንዲቀንስ ያደርገዋል ይላል። በተለይም ደግሞ በኢኮኖሚው ላይ የሚከሰቱ ችግሮች ተጽዕኖ ዓመታትን የሚዘልቅ በመሆኑ ተደራራቢና ድግግሞሽ ያሏቸው ችግሮች እንዲበራከቱ በር ከፍቷል። በእነዚህ ድርብርብ ውጥንቅጦች በአህጉሪቱ በከባድ ድህነት የሚኖሩ ዜጎች ህይወት ይበልጡኑ እንዲወሳሰብባቸውና ለከፋ ማኅበራዊ ችግር እንዲጋለጡ እያደረገ ነው። ከዚህም ባለፈ የጸጥታ ችግሮች በአፍሪካ ሳያባሩ መቀጠላቸው ዛሬም ጉዳዩን በአንክሮ እንድንመለከተው ያስገድደናል። ይህንን በሚያስረግጥ መልኩ ያለፈው የፈረንጆች ዓመት (2022) ግጭቶች የተስተዋሉበት ዓመትና በዘንድሮ ዓመት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩ ተመላክቷል። በሰላም ስምምነት የተቋጨውን በኢትዮጵያ ተከስቶ የነበረውን ጦርነት ጨምሮ እስካሁን እልባት ያልተገኘላቸው የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎና የደቡብ ሱዳን የጸጥታ ችግሮች ተጠቃሽ መሆናቸውን ነው የአፍሪካ የደኅንነት ተቋም ሪፖርት የሚያሳየው። ከዚህ ጎን ለጎን በሳሀል፣ በቻድ ሃይቅ ሸለቆ፣ በምስራቅ አፍሪካና በሰሜን ሞዛምቢክ ጸጥታን የሚያውክ የጽንፈኝነት እንቅስቃሴ መኖሩንም አመላክቷል። ከዚህ ጎን ለጎን በቡርኪና ፋሶ፣ በጊኒ፣ ማሊ፣ ሱዳን፣ ቻድ፣ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ጅቡቲ፣ ጊኒ ቢሳው፣ ማዳጋስካርና ኒጀር የተሳካና ያልተሳካ የመፈንቅለ-መንግሥት (ኢ-ሕገ-መንግሥታዊ) ሙከራ መካሄዱንና የፖለቲካ አለመረጋጋት እንደተስተዋለባቸው ነው ሪፖርቱ ያወሳው። መንግሥታዊ የአስተዳደር ግድፈቶች፣ ምርጫን ተከትሎ የሚቀሰቀስ አለመግባባትና ሌሎችም በአህጉሪቱ ላለፉት ሁለት ዓመታት የተከሰቱ የጸጥታና የደኅንነት ችግሮች ለተያዘው የፈረንጆች ዓመትም ትልቅ ሥጋት መሆኑን ነው ያነሳው። አፍሪካ ኅብረት በበርካታ አገሮች የጸጥታ ችግሮች እንዲቆሙና እንዲረጋጉ በማድረግ አዎንታዊ ሚና መጫወቱ ተገልጿል። ለአብነትም በኢትዮጵያ በዘላቂነት ግጭትን ለማቆም የተደረሰው የሰላም ስምምነት ተጠቃሽ ሲሆን በሌሎችም አገራት ወደ ተሻለ ፖለቲካዊ መረጋጋት እንዲመጡ ትልቅ ሥራ ሰርቷል። ይህም ሆኖ አሁንም ድረስ ዘላቂ ሰላም በማረጋገጥ በኩል በርካታ ሥራ እንደሚቀር ነው የተገለጸው። በተለይም ደግሞ በምዕራብ ሳሀል ያለው ከአልቃይዳና ከአይ ኤስ ጋር ግንኙነት ያለው ጽንፈኛ ቡድን በአካባቢው የፈጠረው አለመረጋጋት፣ ከማሊ የፈረንሳይ ጦር መውጣትና ማሊ ራሷ ከሳሀል ቡድን አምስት የጸጥታ መዋቅር መውጣቷም ሌላው የአህጉሪቷና የአካባቢው ራስ ምታት ሆኗል። የቻድ ሃይቅ ሸለቆ አካባቢ (በኒጀር፣ ቻድ፣ በካሜሮንና ናይጄሪያ) የሚስተዋለው የቦኮሃራምና ሌሎች የጽንፈኝነት እንቅስቃሴ፣ በምስራቃዊ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ራሱን ኤም23 በማለት የሚጠራው ቡድን ከማዕከላዊ መንግሥት ጋር ጦር መማዘዙ እንዲሁም በሰሜን ሞዛምቢክ ያለው በመንግሥትና በተቃዋሚ መካከል የተቀሰቀሰው የሽምቅ ውጊያ አሁንም አለመቆሙ፤ የአፍሪካ ኅብረት ጸጥታን በተመለከተ በዚህ ዓመት ትኩረት ሊያደርግበት የሚገባ ጉዳይ መሆኑን ነው የእንግሊዙ ቻም ሃውስ የተሰኘው የጥናት ተቋም መረጃ የሚያመለክተው። በተያዘው የፈረንጆች ዓመት በተለያዩ ደረጃ የሚካሄዱ 17 ብሔራዊ ምርጫ መኖራቸውንና ይህንንም ተከትሎ ሊከሰቱ የሚችሉ የድኅረ-ምርጫ ፖለቲካዊ ግጭቶችን በማስቀረት ረገድ አፍሪካ ኅብረት አዎንታዊ ሚና መጫወት እንደሚጠበቅበትም ተመላክቷል። የአፍሪካ ኅብረት ቀጣይ አቅጣጫስ? አፍሪካ ኅብረት በበርካቶች አይን ሲታይ ምንም እንኳን የፖሊሲና የስትራቴጂ ችግር ባይኖርበትም ከአፈጻጸም ጋር በተያያዘ በበርካታ ጉዳዮች ላይ ችግሮች ተስተውሎበታል። ለዚህም ተቋሙ ካለበት የፋይናንስና ሌሎች ተያያዥ የቴክኒክ ችግሮች በተጓዳኝ በዋነኛነት አባል አገራት በኅብረቱ ቻርተር በመመራት ረገድ በርካታ ክፍተቶች መኖራቸው መረጃዎች ያሳያሉ። በተለይም በጸጥታና ደኅንነት ምክር ቤት በኩል የሚወስናቸው ስምምነቶች ገቢራዊ አለመሆናቸው ትልቅ ክፍተት ሲሆን ምክር ቤቱም በቅርቡ ያደረገው ስብሰባ ይህንኑ አጋልጧል። ይህም አፍሪካ ኅብረት በአህጉሪቱ መልካም አስተዳደርና ዴሞክራሲ እንዲጎለብት በማድረግ ረገድ ያለው ቁርጠኝነት ልዩ ትኩረት የሚሻ መሆኑን አመላክቷል። ለአብነትም እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2020 የጥይት ድምፅ የማይሰማባት አህጉር ለመፍጠር ያቀደው ዕቅድ ምንም እንኳን ዕቅዱ ከጅምሩም ቢሆን ያለው ነባራዊ ሁኔታና የግጭቶች የመስፋፋት አዝማሚያ ከግምት በማስገባት ሊሳካ እንደማይችል በርካታ የመስኩ ተንታኞች ቢናገሩም ኅብረቱ በዚህ ረገድ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት አልቻለም። ለዚህም ደግሞ በቀዳሚነት ምንም እንኳን የአባል አገራት የፖለቲካ ቁርጠኝነት ማነስ ትልቁን ድርሻ ቢይዝም የሚወስዳቸው እርምጃዎች ሳይሸራረፉ ተግባራዊ ለማድረግ መቸገሩን ነው የሚያሳዩት። በአፍሪካ በሰላምና ጸጥታ ጉዳዮች ላይ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችሉ ሥራዎች በቁርጠኝነት መሥራት ይገባል። በተለይም ደግሞ አፍሪካ ኅብረት በቅርቡ ዳግም የከለሰውን በአህጉሪቱ የጥይት ድምፅ ለማጥፋት የወጣውን ፍኖተ- ካርታና እንዲሁም የክትትልና የግምገማ ማዕቀፍ ፈጥኖ ወደ ሥራ ማስገባት ይኖርበታል። ይህንንም ተከትሎ በጸጥታና የደኅንነት ምክር ቤቱ ያቋቋመውን የባለሙያዎች ቡድን የያዘ ማዕቀብ ለመጣል የሚሰራው ንዑስ ኮሚቴም በአግባቡ መጠቀም አለበት። አሁን ላይ በአህጉሪቱ ለጸጥታ መስፈን ሥጋት በሚሆኑና በሚያቆጠቁጡ ጉዳዮች ላይ እልባት ለመስጠት መረባረብ እንዳለበት ነው የሚጠቀሰው። በተመሳሳይ የሚወስዳቸው እርምጃዎችም በባህሪያቸው ተከታታይነትና ወጥነት ያላቸው እንዲሁም ችግሮች ከተፈጠሩ በኋላ ሳይሆን ከመፈጠራቸው በፊት አስቀድሞ መከላከልና ማክሸፍ ላይ ሊረባረብ እንደሚገባ ነው የሚያነሱት። ከዚህ በተጓዳኝ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታን ለማፋጠን የሚያስችሉ የአገራትን የፖለቲካ እንቅስቃሴ መደገፍና በዘላቂነት ዴሞክራሲ ባህል እንዲሆን የሚያስችሉ ሥራዎችን መደገፍ እንዳለበትም ነው የሚነሳው። በተለይም ደግሞ ወጣቶችን ያሳተፉ የዴሞክራሲ ግንባታ ሥራዎች በስፋት መሠራት እንዳለበት ነው የሚጠቀሱት። ከዚህ ጎን ለጎንም የአፍሪካ የእርስ በርስ መገማገሚያ መድረክም (ፒር ሪቪው ሜካኒዝም) በተለይም መልካም አስተዳደርና የዴሞክራሲ ሥርዓት እንዲጎለብት በማድረግ ረገድም አበርክቶው ከፍ እንዲል መሠራት ይጠይቃል። የሰላም ሥራውን ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችለውን የሰላም ፈንድም ማሰባሰብ እንዳለበትም ነው የሚነሳው። ባሳለፍነው የፈረንጆች ዓመት አጋማሽ ላይ የሰላም ፈንዱ አጠቃላይ ገቢ 328 ሚሊየን ዶላር የደረሰ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 22 አባል አገራት ሙሉ በሙሉ እንዲሁም አምስት አገራት ደግሞ በከፊል የሚጠበቅባቸውን መዋጮ አዋጥተዋል። በሌላ በኩል 28 አባል አገራት ደግሞ መዋጮውን መክፈል አለመቻላቸውን ነው የአፍሪካ ኅብረት የሰላምና ደኅንነት ሪፖርት የሚያመለክተው። በመሆኑም አፍሪካ ኅብረት አባል አገራት የሚያዋጡትን ገንዘብ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ እንዲጨርሱ ቅስቀሳ ማድረግን በአፍሪካ ጥላ ሥር በተለያዩ አገራት የሚያንቀሳቅሰውን የሰላም ሥራ ውጤታማ ማድረግ ይገባዋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት(ተ.መ.ድ) የጸጥታ ምክር ቤት ጉዳይ ላለፉት 15 ዓመታት በአፍሪካ መሪዎች በስፋት የተቀነቀነው አፍሪካ በጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ ሊኖራት ይገባል የሚለው ጉዳይም አፍሪካ ኅብረት በዘንድሮ ጉባዔው ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው። ምክር ቤቱ ከሚመለከታቸው ጉዳዮች ውስጥ ከ70 በመቶ በላይ የሚሆኑት አፍሪካን የተመለከቱ መሆናቸውና ይህም ሆኖ በምክር ቤቱ ውስጥ አፍሪካ አለመወከሏ የፍትሃዊነት ጥያቄ ሲያስነሳ ቆይቷል። በርካታ የአፍሪካ መሪዎች እንዲሁም ኅብረቱን በሊቀ-መንበርነት የመሩት እስከ ወቅቱ ሊቀ-መንበር የሴኔጋሉ ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል ድረስ ጥሪያቸውን በተለያዩ መድረኮች አሰምተዋል። አሁን አሁን ላይም ጥያቄውን ምንም እንኳን የሩቅ ምስራቆቹ ጃፓንና ቻይና እንዲሁም ሕንድ አስቀድመው ቢቀበሉትም በተለይም አንዳንድ የምዕራብ አገራት ያሏቸውን የሃሳብ እቀባ በማንሳት ጉዳዩን እንዲጋሩት በማድረግ አፍሪካ ትልቅ ስኬት አግኝታለች። ይህም ሆኖ አሁንም አፍሪካ ስንት መቀመጫ ይኑራት? እንዲሁም ድምፅን በድምፅ የመሻር መብት ይሰጣት ወይስ አይሰጣት? የሚለው ጉዳይ ላይ ክርክሮቹ እንደቀጠሉ ነው። በዘንድሮ ጉባዔው ኅብረቱ በእነዚህ ጉዳይ ላይ ተወያይቶ ወደ መጨረሻ ምዕራፍ ላይ የሚደረስበትን ውሳኔ ያስተላልፋል ተብሎ ይጠበቃል። ይህንንም ማድረግ ከተቻለ በአፍሪካ ቀደምት መሪዎች ሲቀነቀን የቆየውን "አፍሪካዊ መፍትሔ ለአፍሪካ ችግሮች" የሚለውን ብሂል እውን ለማድረግና አህጉሪቷ ላይ ዘላቂ ሰላምና ደኅንነትን ለማስፈን በሚደረገው ጥረት ላይ አዎንታዊ አበርክቶ እንደሚኖረው ታምኖበታል።
ጠንካራ አንድነት - ለዘላቂ ሰላም መሰረት!
Feb 3, 2023 543
በእንግዳው ከፍያለው (ባህር ዳር ኢዜአ) በረጅም እንጨት ጫፍና ጫፍ በገመድ ታስረው የተንጠለጠሉ ቋጠሮዎችን ተሸክማ ከጓደኞቿ ጋር ገበያ እየሄደች ነበር የተገናኘነው። ወጣት ማሪማ ሜካ ትባላለች፤ ዕድሜዋ ከሃያ ዓመት አያልፍም። በእንጨቱ አንደኛው ጫፍ 10 ሊትር አረቄ የያዘ ጀሪካን፤ በሌላኛው ጫፍ ደግሞ ሌላ ቋጠሮ በማንጠልጠል ተሸክማለች። ሸክሙን በትካሸዋ ላይ ጣል እድርጋ ፈጠን እያለች ስትራመድ ላየ በፊቷ ላይ አንዳች የብርታትና የጽናት መንፈስን ያነባል። እንደእኔ ለአካባቢው እንግዳ የሆነ ሰው “ሴት ልጅ እንዴት ይህን ያህል ክብደት ተሸክማ ትጓዛለች?” ብሎ ራሱን ሊጠይቅ ይችላል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የማንዱራ ወረዳ ነዋሪዋ ወጣት ማሪማ ግን ሸክሙ እንደ ኩበት ቀሏት ይሁን ጽናቱን ፈጣሪ ሰጥቷት ባላውቅም በደስታ ወደ ፊት መራመዷን ቀጥላለች። “የኛ ችግር የምንይዘው ሸክም ሳይሆን የጸጥታ ስጋት ነበር” የምትለው ወጣቷ ባለፉት ዓመታት በኛ ላይ የደረሰው አስከፊ ሰቆቃና መከራ ለጠላትም እንዲገጥመው አልመኝም በማለት ትናገራለች። ባለፉት ዓመታት በአማራና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች አዋሳኝ ወረዳዎች ሲከሰት የነበረው ግጭት የሁለቱን ክልሎች ህዝቦች ለሞት፣ ለስደት፣ ለንብረት መውደም እንዲሁም ለተለያዩ ችግሮች ዳርጓቸው መቆየቱ የቅርብ ትውስታ ነው። አካባቢው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሚገነባበት፣ ሰፋፊ የእርሻ ኢንቨስትመንት፣ የስኳር ፕሮጀክቶችና ሌሎች የኢንዱስትሪ ልማቶች ያሉበትና ለመተግበር የታቀደበት በመሆኑ የውጭ ሃይሎች ግጭት እንዲነሳ እጃቸውን ሊያስገቡ እንደሚፈልጉ ሳይታለም የተፈታ ነው። ወጣት ማሪማ ግጭት በተከሰተባቸው በነዚያ አስከፊ ጊዜያት የነበረውን ሁኔታ፣ የደረሰውን ጉዳት፣ በተከፈለው መስዋዕትነት የመጣውን ሰላም በሚያስታውስ የተስፋ ስሜት "ጸረ ሰላም ሃይሎች ያስነሱት ግጭት ለዘመናት በአንድነት የኖረውን የሁለቱ ክልሎች ህዝቦች ተስፋ አጨልሞት ነበር፤ በሰላም እጦት ሁሉም ህዝብ ጫካ ገብቶ ኑሮውን ከዱር አውሬ ጋር ያደረገበት የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው" ትላለች። በአሁኑ ወቅት ጸረ ሰላም ሃይሎችና ተባባሪዎቻቸው የፈጠሩት ሰው ሰራሽ ችግር ሊፈታ መቻሉ እፎይታን መፍጠሩን ትገልጻለች። በወቅቱ ሕክምና፣ መድሃኒትና ሌሎች የጤና መጠበቂያ ቁሶች ባለመኖራቸው ህጻናትና ሴቶችን ጨምሮ በወባ እና ሌሎች በሽታዎች ሕይወታቸውን ያጡ ወገኖች እንዳሉ በመጥቀስ፤ በአሁኑ ወቅት የጸጥታ አካላትና ሰላም ፈላጊ የአካባቢው ተወላጆች ከመንግሰት ጋር በመሆን ባደረጉት ጥረት የነበረው ግጭት ተወግዶ በአካባቢው ሰላም ሰፍኗል። ይህም ለማሪማና ለአካባቢው ነዋሪዎች እፎይታን በማጎናጸፉ በጣም ደስተኛ ናቸው። የተገኘውን ሰላም ተከትሎ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ማንዱራ ወረዳ ተነስታ በአማራ ክልል አዊ ዞን ቻግኒ ከተማ በመምጣት ለመገበያየት በቅታለች። ከጓደኞቿ ጋር ከቻግኒ ከተማ የሚፈልጉትን ገዝተው ወደ አካባቢያቸው ወስደው በትርፍ ለመሸጥ ምቹ ሁኔታም ተፈጥሮላቸዋል። በቻግኒ ከተማ የቅዳሜ ገበያ የተለያዩ የንግድ እንቅስቃሴዎች ይካሄዳሉ። በርበሬ፣ የተለያዩ የጥራጥሬ፣ የቅባትና የአገዳ ምርቶች ለሽያጭ ይቀርባሉ። አልባሳት፣ የሴቶች ጌጣጌጥ እና የንጽህና መጠበቂያ ቁሶች እንዲሁም ሌሎች የኢንዱስትሪና የግብርና ምርቶች ንግድ ልወውጥ የሚካሄድባት ከተማ መሆኗን በነበረኝ የአጭር ጊዜ ቆይታ አስተውያለሁ። ገበያተኛው የተፈጠረውን ሰላም በማጣጣም ላይ መሆኑን በገበያው ውስጥ ከሚያሳየው መስተጋብር መረዳት ቀላል ነው። እኔም ይሄን በተደጋጋሚ ታዝቢያለሁ። ከህዝቡ ፊት ያነበብኩት በግጭቱ የተነሳ በደረሰው ችግር ምክንያት ቁርሾና ቂም በቀል ውስጥ መግባትን ሳይሆን የሰላምና እርስ በርስ መዋደድና የመደጋገፍ ስሜትን ነው። ይሄን ደግሞ በቻግኒ ከተማ በሚካሄደው የቅዳሜ ገበያ መስተጋብር ላይ ተገኝቶ ማረጋገጥ ይቻላል። ገበያው የሁለቱም ክልሎች ህዝቦች ያላቸውን ይዘው መጥተው በነጻነት የሚገበያዩበት ነው። አሁን በሰላም ተገበያይቶ ወደ ቤት የሚመለስበት ሁኔታ በመፈጠሩ ለወጣት ማሪማ እና እንደ እሷ ላሉ ወጣቶች ደስታና እፎይታን ሰጥቷል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን የማንዱራ ሚሊሻ የሆኑት አንመይ አልቤም በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ተፈጥሮ የነበረውን የሰላም መታጣት ችግር ዛሬ መፈታት በመቻሉ በነጻነት ያለስጋት ለመገበያየት መብቃቱን አስረድቷል። "ያ አሰቃቂና የእልቂት ጊዜ አልፎ ተገናኝተንና እርስ በርስ ተገበያይተን በሰላም ወደየቤታችን እንመለሳለን ብሎ ማሰብ እንደ ከንቱ ህልም ነበር" ይላል የነበረውን ሁኔታ ሲያስታውስ። “ሚሊሻ እንደመሆኔ ከፌዴራልና ከክልሎች የጸጥታ ሃይሎች ጎን በመሰለፍ ግጭት ቀስቃሾችን ለመፋለም ጨካ ለጫካ ያሳለፍነው ጊዜ መቼም አይረሳኝም” ያለው ሚሊሻ አንመይ፣ ስንቶች በሕክምና፣ በመድሃኒትና ምግብ እጦት ህይወታቸው ማለፉን አንስቷል። "አማሟቴን አሳምረው" እንደሚባላው በወጉ መሞትና መቅበር ትልቅ ጸጋ መሆኑን የገለጸው አንዳች የሀዘን ስሜት ውስጥ በመግባት ነው። አሁን ላይ ሁሉም የደረሰውን ጉዳት በመርሳት የተገኘውን ሰላም አጠናክሮ ለማስቀጠል እየተንቀሳቀሰ ነው። የሁለቱ ክልል ህዝቦች ቂም በቀልን ትተን በጋራ የምንሰራበት ወቅት ላይ መድረሳችን ህዝቡ ከጥንት ጀምሮ ያለው የመተሳሰብ፣ የአብሮነትና አንድነት የመንፈሰ ጠንካራነት ማሳያ እንደሆነም ነው የገለጸው። በእርግጥም የማንዱራ ሚሊሻው እንዳለው በአካባቢያቸው ትምህርት ቤቶች በመከፈታቸው ህጻናት ያለስጋት በመማር ላይ ናቸው። የጤና ተቋማትም የተለመደውን የሕክምና አገልግሎት እየሰጡ ነው። በሰላም እጦት ተዘግተው የነበሩ መንገዶች በመከፈታቸውም ሁሉም ተሯሩጦ ኑሮውን ለማሸነፍ ላይ ታች እያለ ነው። ባለሃብቶችም በክረምቱ በግብርናው መስክ ተሰማርተው ማልማት ችለዋል። የጸጥታ ስጋት ተወግዶ ሌሎች የልማት ሥራዎች ሲተገበሩ ማየት ትልቅ ስኬት ነው። በአማራ ክልል አዊ ብሔረሰብ አስተዳደር የቻግኒ ከተማ ነዋሪ አቶ ሲራጅ አዲስ እንዳሉት ግጭት በነበረበት ወቅት በአካባቢው የኢንቨስትመንትና የንግድ እንቅስቃሴ ተዳክሞ ነበር። እሱ ቀርቶ በሰላም ውሎ ለማደር ጊዜው ከባድ ነበር ይላሉ። "የተገኘው ሰላም በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች እና በህብረተሰቡ የጋራ ጥረት በመሆኑ ሰላሙ አስተማማኝና ዘላቂ እንዲሆን ሁላችንም የበኩላችንን መወጣት ይኖርብናል" ብለዋል። አሁን ላይ ያለፈውን የመከራ ጊዜ፣ በሞት የተለየውን ወገን፣ የወደመውን ሀብትና ንብረት በመርሳት በተገኘው ሰላም በጋራ ሰርቶ ራስንና አካባቢውን ለመለወጥ መትጋት እንደሚገባ ነው የመከሩት። ያለፈን በደልና ቅሬታ በእርቅና በይቅርታ በማለፍ ነገን ብሩህ ለማድረግ መትጋት አለብን በማለትም ነው ያስገነዘቡት። አቶ ሲራጅ እንዳሉት በአሁኑ ወቅት የጉሙዝ ማህበረሰብ ወደ ቻግኒ መጥቶ ያለውን ሽጦ የሚፈልገውንም ገዝቶ ይሄዳል፤ እነሱም ወደ መተከልና ማንዱራ በመሄድ ያላቸውን ይሸጣሉ፤ የፈለጉትንም ገዝተው የሚመጡበት ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል። ይሄን አብሮነት በማጠናከር ሁለንተናዊ የጋራ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሰላምን ማጽናት ላይ ጠንክሮ መስራት ይገባል። በአማራም ሆነ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ችግር ሲፈጥሩ የነበሩ ወንጀለኞችን አጋልጦ ለህግ ማቅረብ ያስፈልጋል። አሁንም የጥፋት ተልዕኮ ይዘው ችግር ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱትን አደብ እንዲገዙ ማድረግ ተገቢ ነው። ወንጀለኛን ለህግ አጋልጦ መስጠትን ከተለማመድን ነገም አካባቢውን የጦር ቀጣና ለማድረግ የሚፈልጉ የጥፋት ሃይሎች መግቢያ ቀደዳ አይኖራቸውም ይላሉ። ሃገር በአንድ ወገን ብቻ ሳይሆን በሁሉም ዜጎች የተባበረ ክንድ ትገነባለች፤ ደህንነቷም ድንበሯም ይጠበቃል። ለዛሬው ትውልድ የደረሰችውም የብዙዎች ዋጋ ተከፍሎባት እንደመሆኑ በጋራ በሰላምና በአብሮነት ይሄንኑ ማስቀጠል የግድ ይላል። በተለይም የሰላም ጉዳይ ቅድሚያ ትኩረት የሚወስድ እንደመሆኑ አካበቢን የመጠበቅ የነቃ ተሳትፎን ወሳኝ ነው። ኢትዮጵያ ልታለማውና ልትጠቀምበት የምትችለው ገና ብዙ ያልሰራችበት ሃብት ባለቤት መሆኗ የአንዳንድ ሃይሎችን ቀልብ መሳቡ የሚጠበቅ ነው። ሰላሟ ሲረጋገጥ የዜጎች ደህንነት ሲከበር የተጀመረው የእድገት ጉዞ መፋጠኑ የማይቀር በመሆኑ ሁሉም የድርሻውን መወጣት ይኖርበታል።
ልዩ ዘገባዎች
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 182
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 366
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት። እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
በጂንካ ከተማ የተመረተው 23 ኪሎ ግራም የሚመዝነው የስኳር ድንች "በአፍሪካ ትልቁ ስኳር ድንች" በሚል ተመዘገበ
Mar 13, 2023 474
ጂንካ መጋቢት 4/2015 (ኢዜአ):- በጂንካ ከተማ ደሙዝ ሰፈር የተመረተው እና 23 ኪሎ ግራም የሚመዝነው ስኳር ድንች በአፍሪካ የድንቃ ድንቆች መዝገብ "በአፍሪካ ትልቁ ስኳር ድንች" በሚል መመዝገቡ ተገለጸ። በአዲስ አበባ በተካሄደው የእውቅና ስነስርዓት ላይ የአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ስራ አስኪያጅ አቶ አሸናፊ አለም ለስኳር ድንቹ ባለቤት አቶ ኢሳያስ ጊዜአለው የእውቅና ምስክር ወረቀት አስረክበዋል። ከዚህ ቀደም በአፍሪካ 10 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች መቅረቡን አቶ አሸናፊ ለኢዜአ ገልጸዋል። “ነገር ግን 23 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች በአፍሪካ ደረጃ ሲቀርብ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው” ብለዋል። በዓለም የድንቃ ድንቅ መዝገብ 37 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች መመዝገቡንና በደሙዝ ሰፈር የተገኘው ስኳር ድንች በ14 ኪሎ ግራም ዝቅ ብሎ ከዓለም የ”ሁለተኛነት” ደረጃ ላይ እንደሚያስቀምጠው አመልክተዋል። የስኳር ድንቹ ባለቤት አቶ ኢሳያስ ጊዜያለው ስኳር ድንቹ በአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ላይ በመስፈር የኢትዮጵያን ስም በማስጠራቱ መደሰታቸውን ገልጸዋል። ስኳር ድንቹ እውቅና እንዲያገኝ የዜና ሽፋን ለሰጠው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ምስጋቸውን አቅርበዋል። ኢዜአ የካቲት 19 ቀን 2015 ዓ.ም “በጂንካ ከተማ ደሙዝ ሰፈር 23 ኪሎ ግራም የሚመዝን አንድ የስኳር ድንች መመረቱ ተገለጸ” በሚል መዘገቡ የሚታወስ ነው።
ዶክተር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ እውቅና አገኙ
Mar 9, 2023 671
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 30/2015 የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ በሩዋንዳ ኪጋሊ በተካሄደው በአፍሪካ ዓለም አቀፍ የጤና አጀንዳ ኮንፈረንስ (AHAIC)2023 ላይ እውቅና ተሰጣቸው። ሚኒስትሯ በሩዋንዳ ኪጋሊ ትላንት በተካሄደው Africa Health Agenda International Conference (AHAIC) 2023 ላይ የተበረከተላቸውን Women in Global Health Award የእውቅና ሽልማት በተወካያቸዉ በኩል ተቀብለዋል። እውቅናው በጤና ልማት ውስጥ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በመቋቋምና በመፍታት፣ የጤና አገልግሎት ጥራትና ፍትሀዊ ተደራሽነት እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ሽፋን ላይ ትኩረት ሰጥተው ለሚሰሩ አመራሮች የሚሰጥ መሆኑም ተመላክቷል። ለመጪዎቹ ትውልዶች አርዓያ ለሆኑ የአፍሪካ ሴት መሪዎች የሚሰጠው ሽልማቱ የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰም ለዜጎች የተሻለና ዘላቂ ጤናን ለማምጣት በሚደረግ ጥረት ውስጥ ላበረከቱት የላቀ የመሪነት ሚና ከአምሪፍ ሄልዝ አፍሪካ እውቅናውን አግኝተዋል።
መጣጥፍ
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 618
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼
ሽሬ ወአክሱም (የአልፎ ሂያጁ ማስታወሻ)
Jan 25, 2023 654
ሽሬ ወአክሱም (የአልፎ ሂያጁ ማስታወሻ) አየለ ያረጋል (ኢዜአ) መዳረሻዬ ሽሬ እንዳስላሴ ነው። ለዘገባ ሥራ ከባህርዳር- ጎንደር- ደባርቅ- ሸሬ መንገድ ከሚዲያ ባልደረቦች ጋር እየተጓዝኩ ነው። የጥምቀት ሙሽራዋ ጎንደር እየተኳኳለች ነበር። ደባርቅ ከመድረሴ በፊት ዳባት ትገኛለች-የደጃች አያሌው ብሩ ቁርቁር ከተማ። ደጃች አያሌው ትውልዳቸው በጌምድር ጋይንት ቢሆንም ግዛታቸውና ኑሯቸው ዳባት ነበር። ሞገደኛው ደጃዝማች አያሌው ብሩ በጎንደር ማኅበረሰብ ዘንድ ዝናቸው የናኘ ነው። ደጃዝማች አያሌው በ20ኛው ክፍለ ዘመን መባቻ (ከልጅ ኢያሱ እስከ አጼ ኃይለሥላሴ ዘመነ-መንግሥት) ታሪካዊ ክንውኖች ጉልህ ተሳትፎ አላቸው። አንዷን ብቻ ልምዘዝ። ራስ ተፈሪ ‘ንጉሠ-ነገሥት አጼ ኃይለሥላሴ’ ደጃች አያሌው የቅርብ ዘመዳቸውን ራስ ጉግሳ ወሌ ብጡልን (የንግሥት ዘውዲቱን ባለቤት) ወግተው የጎንደር ግዛት ‘ራስ’ ተብለው ለመሾም ቃል ቢገባላቸውም፤ ተልዕኳቸውን ተወጥተው ቃሉ ባለመፈጸሙ ደጃዝማቹ ከአጼው ጋር መቀያየማቸው አልቀረም። በዚህም:- "አያሌው ሞኙ፣ ሰው አማኙ ሰው አማኙ፣ የአያል ጠመንጃ፣ ስሟን እንጃ ስሟን እንጃ…” በማለት የጎንደር አዝማሪ አዚሟል። ዛሬም ይህ ግጥም የብዙ ባህላዊ ዘፈኖች አዝማች ነው። ደጃች አያሌው ብሩ ደፋር ናቸው ይባላል። ከአጼ ኃይለሥላሴ ጋር ቢቀያየሙም በ1928 ዓ.ም ፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ ሲመጣ ቅድሚያ ለአገሬ ብለዋል። ‘የተደበቀው ማስታወሻ’ በተሰኘው የዶክተር ሀራልድ ናይስተሮም (ትርጉም ገበየሁ ተፈሪ እና ደሳለኝ አለሙ) መጽሐፍ እንደተጠቀሰው ደጃች አያሌው “ንጉሡ እንደኛ ሰው ናቸው። ኢትዮጵያ ግን የሁላችንም ናት" ብለው ጦራቸውን መርተው በሽሬ ግንባር ዘምተዋል። ጉዟችን ቀጥሏል። ደባትን እያለፍን ነው። ‘እንኳን ደህና መጡ፤ ወደ ጭና ታሪካዊቷ ሥፍራ’ የምትለዋን ታፔላን በስተግራ እያየን ወደ ደባርቅ ገሰገስን። የሰሜን ተራሮች የብርድ ወጨፎ ያረሰረሳትን ደባርቅን ከማለፋችን ሊማሊሞ ጠመዝማዛ ቁልቁለት ተቀበለን። አስፈሪ የሊማሊሞ መልክዓ ምድር የደጋው ሰሜን ውርጭ እና የተከዜ በርሃ ኬላ ነው። ባለቅኔው ጸጋዬ ገብረመድህን “የሰማይ የምድሩ ኬላ፣ የየብስ የጠፈሩ ዋልታ አይበገር የዐለት ጣራ፣ አይመክተው መከታ ሊማ-ሊሞ አድማስ ሰበሩ፣ በጎማ ፈለግ ይፈታ? በትሬንታ እግር ይረታ?…” ብሎ የመኪና መንገድ ተገንብቶበት በማየቱ ግርምቱን የተቀኘለትም ለዚህ ይመስላል። ከሊማሊሞ ቁልቁለት በኋላ አዲ-አርቃይ፣ ዛሪማ፣ ማይፀብሪ እና ሌሎች የጠለምት ወረዳ ከተማዎችን አልፈን፤ የዋልድባ ረባዳማ አካባቢዎችን ተሻግረን ተከዜ ወንዝ ደረስን። የዚህን መንገድ እና ተከዜ ወንዝን ሳስብ የሀዲስ ዓለማየሁ ትዝታ አስተከዘኝ። የፋሺስት ኢጣሊያ ወራሪ ጦር የወገንን ጦር ፊት ለፊት መቋቋም ሲሳነው በሰው ልጆች ላይ ተደርጎ የማያውቅ መርዝ በጅምላ የፈጀበት አሳዛኝ ታሪክ ነበር። በተከዜ ወንዝ ውሃን በመመረዝ የወገን ጦር ያለቀበት ሥፍራ ነው። የተከዜ ሸለቆ በኢትዮጵያዊያን ደምና አጥንት ዋጋ የተከፈለበት ነው። ሀዲስ ዓለማየሁ በአንድ ዕለት የተመለከቱትን እንዲህ ጽፈውታል። “የተከዜ ውሀ እመሻገሪያው ላይ ሰፊና ፀጥ ያለ ነው። ታዲያ ያ ሰፊ ውሀ፤ ገና ከሩቅ ሲያዩት ቀይ ቀለም በከባዱ የተበጠበጠ ይመስላል። “ምን ነገር ነው፤ ምን ጉድ ነው?” እየተባባልን ቀረብ ስንል መሻገሪያው በቁሙም በወርዱም ከዳር እስከ ዳር ሬሳ ሞልቶበት የዚያ ሬሳ ደምና ፈርስ ነው። የሰው ሬሳ፣ የፈረስ እና የበቅሎ ሬሳ፣ ያህያ ሬሳ፣ ያውሬ ሬሳ፥ ሬሳ ብቻ! እግር ከራስ ራስ ከእግር እየተመሰቃቀለ እየተደራረበ ሞልቶበት፥ የዚያ ሁሉ ሬሳ ደምና ፈርስ ነው”። ይሉናል። ቀጥለውም “በእውነቱ እንዲህ ያለውን መሳሪያ ምንም ጠላት ቢሆን በሰው ላይ ለማዋል የሚጨክን ሰው፥ ሰብዓዊ ስሜት የሌለው፣ አለት ድንጋይ የተፈጠረበት መሆን አለበት፤ እንዲህ ያለውን መሳሪያ በሰው ላይ ማዋል ሰብዓዊ ህሊና ሊሸከመው የማይችል እጅግ ከባድ መሆኑን ዓለም ሁሉ ያወቀውና ያወገዘው በመሆኑ የኢጣሊያ መንግሥት በኢትዮጵያ ላይ ከማድረጉ በቀር “ሌላ መንግሥት በሌላ አገር ላይ አደረገ’ ሲባል ተሰምቶ የሚያውቅ አይመስለኝም” ብለዋል። ከተከዜ ባህር ማዶ ጉዞዬ ያገኘኋት ሌላዋ ታሪካዊ ሥፍራ እንዳባጉና ናት። እንዳባጉና የወገን ጦር ትልቅ ገድል የፈጸመበት ነው። ጀግኖች አባቶቻችን የጠላት ታንክ ሳያስፈራቸው የጠላት ጅምላ ጨራሽ ቦምብ ጣይ አውሮፕላን ተቋቁመው ጠላትን ድባቅ የመቱበት፤ ወደ አክሱም እንዲያፈገፍግ ያደረጉበት ሥፍራ ነው። “የጠላት ቦምብ ጣይ አውሮፕላን በጦር ሜዳው ትንንሽ ቦምቦች አውቶማቲክ ጠመንጃ ይተኩስ ነበር። አቢሲኒያኖች ደግሞ ከጠላት ጋር ግብግብ ገጥመው ጉዳይም አልሰጡትም ነበር…” ይላል ዶክተር ሀራልድ ‘የተደበቀው ማስታወሻ’ በተሰኘ መጽሐፉ። ይህ አካባቢ በሀገር ፍቅር የነደዱ ኢትዮጵያዊያን ደም ያፈሰሱበት፣ አጥንት የከሰከሱበት፤ ለኢትዮጵያ መስዕዋትነት የከፈሉበት ነው። ይህ የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር ዋጋ የተከፈለበት ቀጣና ነው። ቀኑ ተገባዷል። ጉዟችን እንደቀጠለ ነው። እኔም የማሽላ ማሳዎችን ግራ ቀኝ እየተመለከትኩ ለዕለቱ መዳረሻችን ወደሆነችው ሽሬ ከተማ ገባን። ሽሬ በትግርኛ ‘ሽረ’ ሲሉት ይደመጣሉ። በእርግጥ ሽሬን ለመጀመሪያ ጊዜ መርገጤ ነው። ዕለቱም ጥር ሥላሴ ነው። ሽሬ በጥር ሥላሴ ትደምቃለች፤ ሙሉ ስሟም ሽረ እንዳስላሴ ነው። የሽሬ ሥላሴ ጠበል ሽሬ ደርሰን ማረፊያችንን ያዝን። ጊዜው በጣም አልመሸምና ከተማዋን በቀላሉ መቃኘት ይቻላል። ሽሬ ሰፊና ደማቅ የዞን ከተማ ናት። ከመካከላችን የአንደኛው ባለሙያ ቤተሰቦች ሽሬ ነበሩና አስጠሩን። ለሥላሴ ጠበል ግብዣ። ባል እና ሚስቱ ከልክ በላይ መስተንግዶ አደረጉልን። ‘ጠብ እርግፍ አድርገው አስተናገዱን’ ማለት ይቀላል። እንግዳ መቀበል ነባር ኢትዮጵያዊ እሴታችን ቢሆንም ጦርነት ውስጥ ለቆየ አካባቢ የተለየ መልክ ነበረው። እንግዳ አቀባበላቸው በእርግጥም የመሃል አገር ሰው የናፈቃቸው ይመስላል። የተትረፈረፈ እህልና ውሃ አቅርበው በ’ብሉልን፤ ጠጡልን’ ተማጽኗቸው የተነፋፈቀ ቤተ-ዘመድ ግብዣ አስመሰሉት። የሥላሴው ጠበል የሸሬ ጠላ ቀረበ። የሸሬ ጠላ ሳስታውስ ፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላ ታወሱኝ። የወቅቱ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምሀሩ ፕሮፌሰር ሽብሩ በዘመነ ደርግ በዕድገት በሕብረት ዘመቻ ተማሪዎቻቸውን ይዘው ሽሬ ዘምተው ነበር። በወቅቱ ታዲያ የሸሬ ጠላ ፍቅር ይዟቸው በየጊዜው ሲኮመኩሙ የተመለከቱ ሰዎች ‘ፕሮፌሰሩ ከጠፉ የሚገኙት ጠላ ቤት ነው’ ሲባሉ እንደነበር ‘ከጉሬ ማርያም እስከ አዲስ አበባ’ በተሰኘው ግለ ታሪካቸው አስፍረዋል። ከግብዣ መልስ ከማረፊያ ሆቴል ላይ ሆኜ ከተማዋን ስቃኛት ከጦርነት ድባቴ የተላቀቀች ይመስላል። የአመሻሽ ሕዝቡ እንቅስቃሴም ሆነ እስከ ሌሊቱ አጋማሽ የሚሰሙ የመዝናኛ ቤቶች ሙዚቃዎች የከተማዋን አሁናዊ መልክ የገለጠልኝ ነበር። ንጋት ላይ በቁርስና ቡና ሰዓታት ከሰዎች ጋር መስተጋብሬ ጀመረ። በጦርነት አዙሪት የከረመችው ሽሬና አካባቢው ኑሮ እጅጉን የከበደ ነበር። መልከ-ብዙ ማህበራዊ ቀውሶች አስተናግደዋል። አሁናዊ ምላሻቸው “ተመስገን፤ ያ ሁሉ አለፈ” የሚል ነው። ገበያው ተረጋግቷል፤ ማህበራዊ ኑሮ ተመልሷል። ድህረ-ሰላም ስምምነት ለሽሬ ነዋሪዎች ሁለንተናዊ እፎይታን አንብሯል። ከቀናት በኋላ በአክሱም የታዘብኩትም እንዲህ ነው። ኑሮን ያቀለለው የተቋማት አገልግሎት ጅማሮ በመጀመሪያ ዘገባ ስራዬ መሰረተ ልማትን አገልግሎት ቃኘሁ። ባንክ፣ ቴሌ፣ ሆስፒታል… መሰሎቹን። ተጠቃሚዎችንም፣ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ስራ ሃላፊዎችንም አነጋገርሁ። ከሰላም ስምምነቱ ማግስት ጀመሮ ተቋማቱ ወደስራ መመለሳቸው ከሁለንተናዊ ችግር እንደታደጋቸው ያነሳሉ። በትራንስፖርት እየተንቀሳቀሱ፣ በኤሌክተሪክ ስራዎቻቸውን እየከወኑ ነው። ለሁለት ዓመታት የተቋረጠው አገልግሎት አቅርቦት እና የአገልግሎት ፈላጊዎች ፍላጎት ግን አሁንም ሙሉ በሙሉ ተመጣጣኝ እንዳልሆነ የተጠቃሚዎችም፤ የአገልግሎት ሰጭዎችም ሀሳብ ነው። በሽሬ ስሁል ሆስፒታል የተመለከትኳቸው፤ ያነጋገርኳቸው፤ ከታዳጊዎች እስከ አዛውንት ዕድሜ ያሉ ህሙማን የሰላም አየር ማግኘታቸው የሕይወታቸው ዑደት እንዲቀጥል አድርጓል። ድንገተኛም ሆነ ነባር ህመም ያለባቸው ሰዎች በነጻ እየታከሙ ነው ያገኘኋቸው። ሰላም ከሌለ መታከም ቀርቶ በቅጡ ማስታመም፤ በወጉ መቀበርም እንደማይቻል ገልጸውልናል። የጤና፣ የባንክና የቴሌኮም አገልግሎት የግብዓት ክፍተቶች የማሟላት ሰራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም በፌዴራል ደረጃ በየተቋማቱ የተመደቡ አስተባባሪዎች አረጋግጠውልኛል። የጸጥታ አካሉና የህብረተሰቡ ትብብርም የሚያስቀና እንደሆነ ግለሰቦችም፤ የጸጥታ አካላትም ነግረውኛል። አክሱም ጺዮን ማርያም፣ ሽሬ ስላሴ ንግስ፣ የጥምቀት በዓላት ከሶስት ዓመታት በኋላ በአደባባይ ታቦት ወጥቶ ተከብሯል። የፌዴራል ፖሊስ ተወካዮችም ይህንኑ ነው ያረጋገጡልኝ። የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከከተማ ነዋሪዎች ጋር ያላቸው ግንኙነት ቤተሰባዊ የሆኑ ይመስላል። እንቅስቃሴያቸውም የሰላማዊ ቀጠና መልክ ያለው ነው፤ ዩኒፎርም ከመልበሳቸው በስተቀር ጀሌያቸውን ይንቀሳቀሳሉ። ይህ ደግሞ መተማመን ከመፍጠር ባለፈ ጦርነት ውስጥ ለቆየ ማህበረሰብ ከስነ ልቦና ጫና እንዲላቀቅ አይነተኛ ሚና እንደላው ይሰማኛል። ኢ-መደበኛ የሽሬና አክሱም ወጎች ያረፍኩበት ሆቴል ባለቤት ‘አደይ’ ተግባቢ ናቸው። ደግ እናት ይመስላሉ። ከገባን ጀምሮ ‘ጠላ ተጎንጩ፤ ቡና ጠጡ’ ጭንቃቸው ነው። ሁለት ቀን ቡና አስፈልተውልናል፤ ጠላ አቅርበው ዘክረውናል። ይህ ሁሉ ሲሆንም ለከተማው እንግዳ መሆናችንን እንጂ ስለሙያችንም ሆነ ስለሌላ ማንነታችን አያውቁም ነበር። ብዙ መጨዋወትና ውሎ አዳር በኋላ ነው ጋዜጠኛ ስለመሆናችን ያወቁት። አደይ ተጨዋች ናቸው። አማርኛ ያዝ ቢያደርጋቸውም ጨዋታቸው ‘ኩርሽም’ ነው- ተሰምቶ የማይሰለች። በአጋጣሚ ‘ሰለክላካ’ ስለምትባለዋ ታሪካዊ ሥፍራ ጠይቄያቸው እያወጋን ነበር። ‘እንደእናንተ ወጣቶች ሳለን ‘ሰለክላካን ያላዬ ሸዋን ያመሰግናል’ ይባል ነበር። ታዲያ አንድ የሸዋ ሰው መጣና ሰለክላካን አየና ‘በቃ ይቺ ናት’ ሰለክላካ’ ብሎ ተገረመ” ብለው አሳቁን። (የፍቅር እስከ መቃብር መሪ ገጸ-ባህሪው ‘በዛብህ’ ወደ ዲማ ጊዮርጊስ ሄዶ ‘የዲማ መልኳ እና ዝናዋ’ ተጣርሶበት እንደተገረመበት ቅጽበት መሆኑ ነው)። አደይ የተጀመረው ሰላም ፍጹም ምሉዕ ሆኖ ወደ ቀደመ ኢትዮጵያዊ መልካችን የምንመለስበት ጊዜ እንዲመጣ ይሻሉ። ከጦር-ነት ወደ ሰላም-ነት! ቆንጂዬዋ ፊዮሪ የኮሌጅ ተማሪ ነበረች። በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ጀምሮ በኋላም በጦርነት ሳቢያ ትምህርቷን ካቆመች ሦስት ዓመታት ሆኗታል። ጦርነቱ ከቆመ በኋላ የጀበና ቡና ጀምራለች። ደንበኞቿ ሰብሰብ ብለን እንቀመጣለን። ፊዮሪ ከስኒ ማቅረቢያዋ ላይ አነስተኛ ጀበናዋን፤ የሚያማምሩ ስኒዎቿን እና መዓዛው ከሚያውድ የዕጣን ማጨሻዋ ጋር ሰድራ ይዛ ትቀርባለች። ከመካከላችን ካለው ጠረጴዛ ላይ ታስቀምጥና እርሷም ወንበር ይዛ ከመካከላችን ትቀመጣለች። ቡናው እስኪሰክን ጨዋታዋን ታስኮመኩመናለች። ቡናው ከሰከነ በኋላ ቡናዋን ቀድታ ለእያንዳንዳችን በእጃችን እያነሳች ትሰጣለች። በሽሬ ቡና የሚቀርበው በዚህ መልክ ነው። ለፊዮሪ እና መሰሎቿ ጦርነቱ ክፉ ጠባሳ መጣሉ፤ ተስፋቸው ላይ መጥፎ አሻራ ማስቀመጡን ታነሳለች። አሁን ግን ብሩህ ተስፋ ሰንቃለች። ስለነገዋም “ሰላሙ ይዝለቅልን፤ ትምህርቴን ለመቀጠል እመኛለሁ” ትላለች። አክሱም ከሽሬ በስተሰሜን 60 ኪሎ ሜትር ይርቃል። ከሽሬ አክሱም ስንንቀሳቀስ ከጥምቀት ዕለት በስተቀር ገበሬው የግብርና ሥራዎቹን እየከወነ ነበር። አርሶ አደሩ ያርሳል፤ መስኖውን ያለማል። የተዘራውን ውሃ ያጠጣል። የበቀለ ቡቃያውን ይኮተኩታል። ከጦርነት ወደ ልማት መዞሩን ዐይኔ ታዝቧል። በጥምቀት ዋዜማ፤ የከተራ በዓል ዕለት ሁለት ጎራማይሌ የረፋድ ትዕይንቶችን ላንሳ። ከአክሱም ከተማ ወደ አድዋ እና ሽሬ መገንጠያ አካባቢ ሰፊ የቀንድ ከብት ገበያ ነበር። እውነተኛ የዓመት በዓል ገበያ መልክ ያለው ትዕይንት ነበር። በተለይም የፍየል ዋጋ በተመጣጣኝ ዋጋ እየተገበያዩ እንደነበር ሰምቻለሁ። ታሪካዊቷን አክሱም ከተማ ለመጨረሻ ጊዜ የረገጥኳት/የተሳለምኳት ከአራት ዓመት በፊት በ2011 ዓ.ም ይመስለኛል። ከገበያው ቀጥሎ በታቦተ-ጽዮን መገኛዋ ርዕሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ደጅ፣ በጥንታዊያኑ የአክሱም ሐውልት መገኛ አደባባይ ነበር። ከጽዮን በስተምዕራብ በአርባቱ እንሰሳ በኩል፤ በቅዱስ ያሬድ ዋርካ… አድርጌ በጽዮን ዋናው በር ደረስኩ። ማራኪ የአክሱም የኮብልስቶን መንገዶች ኦና ናቸው። የወትሮው ግርግር ናፍቋቸዋል። ከጽዮን ቅጥር ግቢ በዋናው በር በስተውጭ አነስተኛ እና ብቸኛ ዋንዛ በኮብልስቶን መሃል ነበረች። ዛሬም ለምልማ አለች። በዚህ አካባቢ ድሮ የነጭ ጎብኚ ጋጋታ፣ የጽዮን ደጅ ጠኚ ምዕመን… የተጨናነቀ ነበር። እንደ ድሮው የፎቶ አንሺ ግርግር፣ የአክሱም መስቀል ቀርጸው የሚሸጡ ወጣቶች ጫጫታ የለም። ይልቁንም እርጥባን የሚሹ አቅመ ደካሞችና ህፃናት ነበሩ። ጦርነት የሥፍራዋን መልክ አጠይሞታል። ያም ሆኖ ከተማዋ የንግድ እንቅስቃሴ ሙሉ በኩሉሄ ባይባልም ወደነበረበት እየተመለሰ ነው። የግልም ሆነ የመንግሥት ባንኰች ሥራ ከጀመሩ ሰነባብተዋል። ከአክሱም ሐውልት ወደ ሌላ ሰፈር አቀናሁ። ትርሐስ ገና ታዳጊ ልጅ ነች። ጠይም፤ ስርጉድ፣ ሳቂታና ተረበኛ አይነት ልጅ ነች። እንደ ሽሬዋ ፊዮሪ መንገድ ዳር የጀበና ቡና እየሰራች ነው። ከሩቅ የመጣን እንግዶች መሆናችንን ስታውቅ፤ ደስታዋ ከገጿ ይነበብ ነበር። ያለፉ ጊዜያትን ሰቆቃ አጫወተችን። ስለቀጣይ ዕጣ ፈንታዋ እና ዕቅዷ ስታወራ ትቆይና “የሰው ልጅ ግን በጣም ከሃዲ ነው። ከወራት በፊትኮ ስለቢዝነስ አላስብም ነበር። መቼ እሞታለሁ እንጂ” ብላ ራሷን ትወቅሳለች። ወደ ሰማይ አንጋጣ ፈጣሪዋን ታመሰግናለች። ጦርነት ተራውንም ሕዝብ ለመልከ-ብዙ ቀውስ ዳርጎት እንደቆየ ታነሳለች። ዛሬ ሁሉ አልፎ ሰላም መውረዱ ለመጨዋወት መብቃቷ ለእርሷ ትልቅ ብሥራት ነው። ይህ ለትርሐስ ብቻ ሳይሆን ለመላው አክሱማዊያን መሆኑ እሙን ነው። አክሱም ከተማ በመከላከያ ሠራዊት ቁጥጥር ሥር ከዋለችበት ጊዜ ጀምሮ በከተማዋ በሻለቃ አዛዥነት የተሰማራ የፌደራል ፖሊስ አባልም ያጋጠመውን አሳዛኝ ገጠመኞች አጫውቶኛል። ጦርነቱ ቢራዘም ኖሮ በተራው ሕዝብ ላይ ምን ያህል የከፋ ጉዳት ይደርስ እንደነበር በአሳዛኝ ሁኔታ ገልጾልኛል። አክሱሞች ያን ሁሉ አልፈው ሰላም አየር ነፍሶ፣ ከስጋት ቆፈን ተላቀው ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ ተመልሰዋል። የዛሬ ሳምንት ሰርክ(11 ሰዓት) ላይ አክሱም የከተራ በዓል በድምቀት አክብራለች። ታቦተ-ጽዮን ወደ ባህረ- ጥምቀቱ ስትወርድ፤ ወግና ሥርዓቱ ተጠብቆ፣ ሕዝቡ በሀበሻ ነጫጭ አልባሳት፣ ካህናት በልብሰ ተክህኖ ደምቀው … እየተከወነ ነበር። አንዲት እናት ለአማርኛ ተናጋሪ በቀረበ አነጋገር እያለቀሱ ታቦት እየሸኙ ነው። ትኩር ብዬ ሳያቸውም ዕንባቸው ዱብ ዱብ ይላል። “ከዚያ ሁሉ መከራ አልፎ ለዚህ በቃን፤ ተመስገን” እያሉ እልልታውን ያቀልጡታል። በደስታ እያነቡ ነበር። ይህ ስሜት የብዙኃኑ አክሱማዊያን እናቶች እንደሆነ መገመት ቀላል ነው። አክሱም በኮቪድ እና በኋላም በጦርነቱ ምክንያት ባህረ-ምቀት ታቦት ወጥቶ ሲከበር ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር። ከወትሮው በተለየ ድምቀትና ውበት በሰላምና በደስታ፤ በአደባባይ እልልታና ሆታ በማክበራቸው ልዩ ስሜት ፈጥሮባቸዋልና! እናም በአክሱም የከተራ ሆነ የበዓለ-ጥምቀት ክብረ-በዓላት በሰላም ስምምነቱ ማግስት በድምቀት ተከውኖ አለፈ። የሃይማኖት አባቶቹም ሆኑ ምዕመኑ በሰጡት ቃለ መጠይቅም የዘንድሮው ክብረ-በዓል ካለፉት ዓመታት ነባራዊ ሁኔታ ጋር እያነጻጸሩ፤ ትልቅ ብሥራትና መልክ እንዳለው ገልጸዋል። ሰላም እንዲጸና፤ ነባር ኢትዮጵያዊ አንድነትና መተባበር እንዲመለስ ጽኑ መሻታቸውን ነግረውናል። በበጎ ቀን የማውቃትን አክሱም፤ ከረዥም ጊዜ በኋላ አሁናዊ መልኳን ታዝቤ፤ የነገ ትዝታ ሰንቄ ተመለስኩ!! ሰላም ለኢትዮጵያ!!