ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከዓለም አቀፍ የአቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ(IAEA) ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከዓለም አቀፍ የአቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ(IAEA) ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 23/2017(ኢዜአ)፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከአለም አቀፍ የአቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ(IAEA) ዋና ዳይሬክተር ማሪያኖ ግሮሲ ጋር ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ዛሬ ጠዋት በሬይስ ኦፍ ሆፕ ጉባኤ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ከመጡት የአለም አቀፍ የአቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ(IAEA) ዋና ዳይሬክተር ማሪያኖ ግሮሲ ጋር ተገናኝተናል ብለዋል።
የአለም አቀፉ አቶሚክ ኃይል በኢትዮጵያ የሚያደርገው ድጋፍ በካንሰር ሕክምና ክብካቤ፣ የእንስሳት ጤና፣ የፀፀ ፍላይ ዝንብ ማጥፊያ፣ በኒኩለር ኢንጂነሪንግ እና የቁጥጥር ማዕቀፎች ላይ ያተኮረ ነው ሲሉም ገልጸዋል።
ውይይታችን በመካሄድ ላይ ባሉ ድጋፎች እና የወደፊት የትብብር እድሎች ላይ ያተኮረ ነበር ሲሉም አስታውቀዋል።