ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አዋጅን አፀደቀ

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 24/2017(ኢዜአ)፦ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አዋጅን አፅድቋል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት የምክር ቤቱን 41ኛ መደበኛ ስብሰባ አካሂዷል።


 

በዚህም የኢትዮጵያ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት አዋጅን መርምሮ በሙሉ ድምጽ አፅድቋል።

በዚሁ ወቅት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ ስራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ(ዶ/ር) አዋጁ የዜጎችን ደህንነት፣ ብቃትና ተወዳዳሪነት ማጎልበት የሚያስችል ነው ብለዋል።


 

እንዲሁም ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን በመከላከል ዜጎች በሕጋዊ መንገድ ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው ሲሉም አክለዋል።

ምክር ቤቱ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 1389/2017 አድርጎ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም