ኢዜአ - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ለመሳተፍ አምስት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ዝግጅት እያደረጉ ነው
Nov 29, 2023 23
አዲስ አበባ ፤ህዳር 19/2016 (ኢዜአ):-በኢትዮጵያ የአገር ውስጥና የውጭ ድርጅቶች ለመሳተፍ ከፍተኛ ፍላጎት ባሳዩበት የካፒታል ገበያ ቀዳሚ የሆኑ አምስት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተለይተው ዝግጅት እያደረጉ መሆኑ ተገለጸ። የካፒታል ገበያውን በተያዘው ዓመት ለማስጀመር የሚያስችል አብዛኛው ሥራ መጠናቀቁም ተገልጿል። ኢትዮጵያም ባደጉት አገራት በስፋት እየተተገበረ ያለውን የካፒታል ገበያን ወደ ሥራ ለማስገባት አዋጅ 1248/2013 አፀድቃ ወደ ሥራ ለመግባት እንቅስቃሴ ጀምራለች። የካፒታል ገበያ የኢትዮጵያን ማክሮ ኢኮኖሚ ሚዛን በማስተካከል የጎላ ሚና እንደሚኖረውና ለግልም ሆነ ለድርጅቶች በቂ የሥራ ማንቀሳቀሻ ገንዘብ ለማስገኘት እንደሚያግዝ ይገለጻል። በተጨማሪም የኢትዮጵያ ምጣኔ ኃብት በማይዋዥቅ መልኩ በዘላቂነት እንዲያድግ የፋይናንስ አገልግሎት ዘርፉን አስቻይ ሁኔታ ለማስፋትና ቁጠባን ለማበረታታት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ይነገራል። በኢትዮጵያም አዋጁ ከፀደቀ በኋላ የካፒታል ገበያውን ለመጀመር የሚያስችል የተለያዩ እንቅስቃሴዎች በመደረግ ላይ መሆኑ ይታወቃል። እንቅስቃሴውን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ከፍተኛ የሕግ አማካሪ ሰለሞን ዘውዴን አነጋግሯል። አቶ ሰለሞን እንዳሉትም በኢትዮጵያ በርካታ የውጭና የአገር ውስጥ ባለሃብቶች በገበያው ለመሳተፍ ከፍተኛ ፍላጎት በማሳየት ላይ ናቸው። ከፍተኛ ፍላጎት የታየበት የካፒታል ገበያ ለማስጀመር የሚያስችል የመጨረሻ ምዕራፍ ዝግጅት እየተደረገም እንደሆነም ተናግረዋል። አሁን ላይ አምስት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ወደ ገበያው ለመግባት ዝግጅት እያደረጉ ሲሆን የኬንያ፣ የናይጄሪያና የደቡብ አፍሪካ ኩባንያዎችም በካፒታል ገበያው ለመሳተፍ ፍላጎት ማሳየታቸውን አንስተዋል። የተለዩ የመንግሥት የልማት ድርጅቶችም ይሁን ፍላጎት ያሳዩ የውጭ ኩባንያዎች አጠቃላይ የዝግጅት ሥራዎች ሲጠናቀቁ ወደ ሥራ እንደሚገቡ ገልፀዋል። አሁን ላይ የመመሪያ ማዘጋጀት፣ የግንዛቤ መስጨበጫና የተሳታፊ ድርጅቶች ልየታ ሥራ እየተከናወነ ሲሆን፤ ወደ ካፒታል ገበያው የሚገባውን ድርጅት ግለሰብና ባለሃብት ማስተዳደር የሚችል የሕግ ማዕቀፍ ተዘጋጅቶ በቅርቡ ወደ ሥራ ለማስገባት እየተሰራ ነው ብለዋል። የካፒታል ገበያው አከናዋኝ፣ የኢንቨስትመንት ባንክ፣ የውክልና አስተዳዳሪዎች፣ የጋራ ኢንቨስትመንት ባንክ ሥራ አስኪያጅን ጨምሮ በካፒታል ገበያው አገልግሎት ለሚሰጡ 15 ዘርፎችም ፈቃድ መስጠት የሚያስችሉ መመሪያዎች መዘጋጀታቸውንም ነው የተናገሩት። በተያዘው ዓመት የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን አጠናቆ የካፒታል ገበያን ወደ ሥራ ለማስገባት እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል። የካፒታል ገበያው በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንትና ቁጠባን ከማሳደጉ ባሻገር የዲጂታል ግብይትን በማፋጠን በኩል ሰፊ አስተዋጽዖ እንደሚኖረውም ጠቁመዋል። ለኢንቨስተሮች ሥጋቶችን የሚቀንስ፣ ለኩባንያዎችና ገንዘብ ለሚያስፈልጋቸው ደግሞ ተጨማሪ የፋይናንስ ጥቅም እንዲያገኙ ወይም የባንክ ብድር ዓይነት ድጋፍ እንዲያገኙ እንደሚያደርግ እንዲሁ። አዳዲስ የሥራ ዕድሎች እንዲፈጠሩ እንደሚያደርግም ነው የተናገሩት። የካፒታል ማርኬት ተሳታፊ የሚባሉ ደላሎች፣ ነጋዴዎች፣ የኢንቨስትመንት ባንኮች፣ ሌሎች የፈንዱን ፍሰት የሚያግዙ ተዋንያን ናቸው። ለአገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት ለማንቀሳቀስ ከፍተኛ ጥቅም እንዳለው የሚታመንበት የካፒታል ገበያ እውን እንዲሆን ሁሉም የበኩሉን መወጣት እንዳለበት አብራርተዋል።
በምስራቅ ሸዋ ዞን 121 ሺህ ሄክታር መሬት በበጋ መስኖ ስንዴ ለምቷል
Nov 29, 2023 29
አዳማ፤ህዳር 19/2016 (ኢዜአ)፦ በምስራቅ ሸዋ ዞን 121 ሺህ ሄክታር መሬት በኩታገጠም በበጋ መስኖ ስንዴ መልማቱን የዞኑ ግብርና ጽሕፈት ቤት ገለፀ። የምስራቅ ሸዋ ዞን ግብርና ጽሕፈት ቤት ምክትል ሃላፊ አቶ አብነት ዘገየ ለኢዜአ እንደገለፁት በዞኑ በዘንድሮው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት 350 ሺህ ሄክታር ለማልማት ታቅዶ ስራው ተጀምሯል። በእስከ አሁኑ ሂደት 192 ሺህ ሄክታር መሬት መታረሱን የገለፁት አቶ አብነት፤ እስከ ትናንት ድረስ 121 ሺህ ሄክታር መሬት በኩታ ገጠም ታርሶ በዘር መሸፈኑን ተናግረዋል። የበጋ መስኖ ስንዴ ልማቱን 95 በመቶ የሚሆነውን በሜካናይዜሽንና በኩታ ገጠም ለማልማት ታቅዶ ወደ ስራ እንደተገባም ገልጸዋል። በዚህም እስከ አሁን በዘር የተሸፈነው 121 ሺህ ሄክታር በሜከናይዜሽንና በኩታ ገጠም መልማቱን አመልክተዋል። ምክትል ሃላፊው በዘንድሮው የበጋ መስኖ ስንዴ ከዞኑ 14 ነጥብ 4 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማግኘት መታቀዱን ተናግረዋል። ከግብዓት አቅርቦት አንጻርም ለዘንድሮው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት 350 ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያና ምርጥ ዘር መቅረቡን ገልጸዋል። በዞኑ የአደኣ ወረዳ ግብርና ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሮቢ ያዴሳ በበኩላቸው በወረዳው 2 ሺህ ሄክታር መሬት በበጋ መስኖ ስንዴ የማልማት ስራ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል። በዚህም ለአርሶ አደሩ የስንዴ ምርጥ ዘር፣ የአፈር ማዳበሪያና የእርሻ ትራክተር በተመጣጣኝ ዋጋ እየቀረበ መሆኑንም ጠቁመዋል። በወረዳው በመስኖ ስንዴ ልማት ከተሰማሩ አርሶ አደሮች መካከል አቶ ከተማ ሽፈራው ከአካባቢው አርሶ አደር ጋር በመሆን በኩታ ገጠም በ4 ሄክታር መሬት ላይ ስንዴ እያለሙ መሆኑን ተናግረዋል። 'በዋናነት የአካባቢው አርሶ አደሮች ለስንዴ ልማቱ በራሳቸው በባለሙያ ታግዘው ያለሙትን ምርጥ ዘር በመጠቀም በሜካናይዜሽን እያለሙ መሆናቸውንም አክለዋል። አርሶ አደር መኮንን ሽብሩ በበኩላቸው በግማሽ ሄክታር መሬት ላይ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት እያከናወኑ መሆኑን ጠቅሰዋል። በዘንድሮው በጋ በሜካናይዜሽንና ኩታ ገጠም በማልማታቸው የተሻለ ምርት እንደሚያገኙ ተስፋ መሰነቃቸውንም አስረድተዋል።
የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በክልሉ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ውይይት እያካሄዱ ነው
Nov 29, 2023 36
አዲስ አበባ ፤ህዳር 19/2016 (ኢዜአ):- የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በክልሉ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ውይይት እያካሄዱ ይገኛል። በመድረኩ ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ ባስተላለፉት መልእክት በክልሉ በተፈጠረው ግጭት እና አለመረጋጋት የተነሳ ከወትሮው በተለይ ሁኔታ መከናወን ያለባቸው የልማት ስራዎች መስተጓጎላቸውን ጠቁመዋል። በመከላከያ ሠራዊትና በክልሉ የፀጥታ ኃይል፣ አጠቃላይ አመራሩና ሰላም ወዳዱ ህዝብ በቅንጅት በሰሩት ስራ አብዛኛው የክልሉ አካባቢዎች አንፃራዊ ሰላም ሰፍኗል ብለዋል። የክልሉን ሰላም ለማረጋገጥና ወደ ልማት ስራዎች ለመመለስ ባለን ጽኑ ፍላጎት በተከታታይ የግንዛቤ ማሳደግ ስራዎች መስራታችንም አሁን ለተገኘው አንጻራዊ ሰላም ከፍተኛ አስተዋፅዖ አበርክቷል ሲሉ ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል። የተገኘውን አንጻራዊ ሰላም ለማጽናት ይቻል ዘንድ ወቅቱን እና ሁኔታዎችን ያገናዘበ የጋራ አመራር የመስጠትና የማረጋገጥ ተግባር ከመላው አመራር እንደሚጠበቅ የጠቆሙት ርዕሰ መስተዳድሩ ህዝቡ ካለበት ችግር ውስጥ በፍጥነት ለማውጣት ከወትሮው የተለየ ስራ ይጠይቃል ብለዋል። ከሰሞኑ ከህዝቡ ጋር በተደረጉ የውይይት መድረኮች የተገኙ ገንቢ እና ተራማጅ ሀሳቦችን በተጨባጭ ወደ ተግባር በመቀየር የክልሉን የሰላም፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት ይኖርብናል ነው ያሉት። ድክመቶች ሳይደገሙ በአዲስ መታደስና ታሪክ መጻፍ እንደሚገባም መግባባት ላይ መደረሱን ከክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ከአንድ ሚሊየን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ አገር ውስጥ ገብቷል
Nov 29, 2023 48
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 19/2016 (ኢዜአ)፡- ለ2016/17 የምርት ዘመን ለመግዛት ከታቀደ 23 ሚሊየን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ እስከ አሁን ከአንድ ሚሊየን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ አገር ውስጥ መግባቱን የግብርና ሚኒስቴር ገለጸ። የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሶፊያ ካሳ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፤ በምርት ዘመኑ ከ23 ነጥብ 3 ሚሊየን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ለመግዛት ታቅዷል። እስካሁን 14 ነጥብ 79 ሚሊየን ኩንታል ኤን ፒ ኤስ ዝርያና ዩሪያ የአፈር ማዳበሪያ ግዥ መፈጸሙን ጠቁመው ከተገዛው ውስጥ ከአንድ ሚሊየን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ አገር ውስጥ መጓጓዙን ገልጸዋል። እስከ ታህሳስ ወር መጀመሪያ አካባቢ ተጨማሪ 1 ነጥብ 7 ሚሊየን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ጂቡቲ እንደሚደርስ ጠቁመው በዚህ ዓመት የአፈር ማዳበሪያ በፍጥነት ወደ አገር ውስጥ እየገባ እንደሚገኝ ተናግረዋል። መንግሥት የዓለም ከፍተኛ የማዳበሪያ ጭማሪና የአርሶ አደሩን የመግዛት አቅም ከግምት በማስገባት ከፍተኛ ድጎማ ሲያደርግ መቆየቱን ጠቅሰው ባለፉት ሦስት ዓመታት የ52 ቢሊየን ብር ድጎማ ማድረጉን ተናግረዋል።
የ5-ጂ ሞባይል ኔትዎርክ መስፋፋት የዲጂታል ልማትን ከማፋጠን ባለፈ ሀገራዊ የምጣኔ ኃብት እድገትን ለማረጋገጥ ሚናው የላቀ ነው
Nov 29, 2023 32
አዲስ አበባ ፤ህዳር 19/2016 (ኢዜአ):- በኢትዮጵያ የአምስተኛው ትውልድ (5-ጂ) የሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎት መስፋፋት የዲጂታል ልማትን ከማፋጠን ባለፈ ሀገራዊ የምጣኔ ኃብት እድገትን ለማረጋገጥ ሚናው የላቀ መሆኑን የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ገለጹ። ኢትዮ-ቴሌኮም የአምስተኛውን ትውልድ (5-ጂ) የሞባይል ኔትዎርክ በጅግጅጋ ከተማ በይፋ አስጀምሯል። የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ፤ በማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት በዓለም ላይ እጅግ ፈጣን የሚባለውን የአምስተኛው ትውልድ (5-ጂ) የሞባይል ኔትዎርክ ኢትዮጵያ መጠቀም ጀምራለች ብለዋል። የአምስተኛው ትውልድ (5-ጂ) ኔትዎርክ ተጠቃሚ ከሆኑ የዓለም አገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗንም ጠቅሰዋል። የ5-ጂ ኔትዎርክ ቀደም ሲል በአዲስ አበባ እና አዳማ በይፋ መጀመሩን አስታውሰው፤ አሁን ላይ በሱማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ በመጀመሩ እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል። በኢትዮጵያ የማስፋፋት ሥራው በልዩ ትኩረት እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰው፤ በቀጣይም ተጠናከሮ ይቀጥላል ሲሉ ተናግረዋል። የአምስተኛው ትውልድ (5-ጂ) የሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎት የማስፋፋት ሥራ ለዲጂታል ኢትዮጵያ እውን መሆን የላቀ አስተዋጽዖ እንዳለውም ገልፀዋል። የ5-ጂ ኔትዎርክ አገልግሎት በጅግጅጋ ከተማ መጀመሩም የንግድና የመረጃ ሥርዓቱን ለማሳለጥና የመንግሥትን አገልግሎት አሰጣጥ የሚያቀላጥፍ መሆኑን ጠቅሰዋል። የሱማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ-መስተዳድር ኢብራሂም ኡስማን፤ የቴክኖሎጂው እውን መሆን በክልሉ ለተጀመሩ የልማት ሥራዎች መፋጠን እንዲሁም በተለያዩ ሴክተሮች ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሚያግዝ መሆኑን ገልፀዋል። በጅግጅጋ ኢዜአ ካነጋገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች መካከል ወይዘሮ ራሁ ጠይብካስ እና አብዱረዛቅ ሐሰን የአምስተኛው ትውልድ (5-ጂ) የሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎት መጀመር በንግዱም ይሁን በሌሎች አገልግሎቶች ተጠቃሚ የሚያደርግ በመሆኑ ተደስተናል ብለዋል። የ5-ጂ የኔትዎርክ አገልግሎት በተለይም ለስማርት ሲቲ፣ ስማርት ትራንስፖርት፣ የትምህርት ሥርዓት፣ ለጤና፣ ለውሃ፣ የግብርና ልማት፣ ለንግድና የፋይናንስ ሴክተር፣ ለኢንዱስትሪ፣ ለስማርት የመንግሥት አስተዳደር እና ሌሎችም ሴክተሮች የላቀ አበርክቶ እንዳለው ይነገራል።
ፖለቲካ
የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በክልሉ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ውይይት እያካሄዱ ነው
Nov 29, 2023 36
አዲስ አበባ ፤ህዳር 19/2016 (ኢዜአ):- የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በክልሉ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ውይይት እያካሄዱ ይገኛል። በመድረኩ ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ ባስተላለፉት መልእክት በክልሉ በተፈጠረው ግጭት እና አለመረጋጋት የተነሳ ከወትሮው በተለይ ሁኔታ መከናወን ያለባቸው የልማት ስራዎች መስተጓጎላቸውን ጠቁመዋል። በመከላከያ ሠራዊትና በክልሉ የፀጥታ ኃይል፣ አጠቃላይ አመራሩና ሰላም ወዳዱ ህዝብ በቅንጅት በሰሩት ስራ አብዛኛው የክልሉ አካባቢዎች አንፃራዊ ሰላም ሰፍኗል ብለዋል። የክልሉን ሰላም ለማረጋገጥና ወደ ልማት ስራዎች ለመመለስ ባለን ጽኑ ፍላጎት በተከታታይ የግንዛቤ ማሳደግ ስራዎች መስራታችንም አሁን ለተገኘው አንጻራዊ ሰላም ከፍተኛ አስተዋፅዖ አበርክቷል ሲሉ ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል። የተገኘውን አንጻራዊ ሰላም ለማጽናት ይቻል ዘንድ ወቅቱን እና ሁኔታዎችን ያገናዘበ የጋራ አመራር የመስጠትና የማረጋገጥ ተግባር ከመላው አመራር እንደሚጠበቅ የጠቆሙት ርዕሰ መስተዳድሩ ህዝቡ ካለበት ችግር ውስጥ በፍጥነት ለማውጣት ከወትሮው የተለየ ስራ ይጠይቃል ብለዋል። ከሰሞኑ ከህዝቡ ጋር በተደረጉ የውይይት መድረኮች የተገኙ ገንቢ እና ተራማጅ ሀሳቦችን በተጨባጭ ወደ ተግባር በመቀየር የክልሉን የሰላም፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት ይኖርብናል ነው ያሉት። ድክመቶች ሳይደገሙ በአዲስ መታደስና ታሪክ መጻፍ እንደሚገባም መግባባት ላይ መደረሱን ከክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
አምባሳደር ሽፈራው ገነቲ በዜጋ ዲፕሎማሲ ዙሪያ ከባህሬን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ እና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር አምባሳደር ዶ/ር መሀመድ አሊ ባሀዛድ ጋር ተወያዩ
Nov 29, 2023 43
አዲስ አበባ ፤ህዳር 19 / 2016 (ኢዜአ):- በባህሬን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቆንስል ጄኔራል አምባሳደር ሽፈራው ገነቲ ከባህሬን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ እና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር አምባሳደር ዶ/ር መሀመድ አሊ ባሀዛድ ጋር በዜጎች ጉዳይ እና ባህሬን በኢትዮጵያ የውክልና አድማስ እንዲኖራት በሚቻልበት መንገድ ላይ ተወያዩ። ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት የባህሬንን የሥራ ስምሪት ህግን በተቃረነ መልኩ የታዩ የተወሰኑ እንቅስቃሴዎችን ቆንስላ ጄኔራል ጽህፈት ቤቱ ማስተካከያ ማድረጉን ገልፀዋል። አሁን ላይ የዜጎች ጉዳይ በቆንስላ ጄኔራል ጽህፈትቤቱ ባለሙያዎች ብቻ እየተሰራ መሆኑን አምባሳደር ሽፈራው በውይይቱ አንስተዋል ። በህገወጥ መንገድ ያለመኖሪያ ፍቃድ የሚኖሩ ዜጎች የመኖሪያ ፍቃድ አግኝተው የሚሰሩበትን ሁኔታ እንዲመቻችና በህገወጥ መንገድ በእየቤቱ እየዞሩ ገንዘብ የሚመነዝሩላቸውንም ለማስቀረት የባህሬን መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል። በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት በማሳደግ በሰራተኛ ስምሪት፣ የንግድና ቱሪዝም ዘርፍ ትብብርን ማጠናከር እንዲሁም አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረትና የብዙ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች መቀመጫ በመሆኗ የባህሬን ንጉሳዊ መንግስት ውክልና እንዲኖረው ጠይቀዋል። ረዳት ሚኒስትሩ አምባሳደር ዶ/ር መሀመድ አሊ ባሀዛድ በበኩላቸው ከኢትዮጵያዊያን ዜጎች ጋር በተያያዘ ሲስተዋሉ የነበሩ ችግሮች መኖራቸውን በማስታወስ፣ ችግሮቹን ለመቅረፍ ቆንስል ጄኔራል ጽህፈት ቤቱ በኩል የተወሰዱትን እርምጃዎችን አድንቀዋል። ባህሬን በቀጣይ በአዲስ አበባ ኤምባሲ ለመክፈት የሚያስችል ጥናት የምታደርግ መሆኗን ገልፀዋል። ጥናቱ አልቆ ወደ ሥራ እስከሚገባ የክብር ቆንስላ ህጉን ተከትሎ እንደምትሰይም መናገራቸውን ከውጥ ጉዳይ ሚስቴር ማህበራዊ ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ልዑካን ቡድናቸው የኢትዮ- ቼክ የትብብር መስኮች ጋር የተያያዙ ስፍራዎችን ጎበኙ
Nov 29, 2023 58
አዲስ አበባ፤ህዳር 19/2016(ኢዜአ):-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ልዑካን ቡድናቸው የኢትዮ- ቼክ የትብብር መስኮች ጋር የተያያዙ ስፍራዎችን ጎብኝተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩና ልዑካን ቡድናቸው በቼክ ሪፐብሊክ ቆይታቸው እንደ ግብርና፣ ቱሪዝም እና ባሕል ባሉ በመስፋፋት ላይ ካሉ የኢትዮ- ቼክ የትብብር መስኮች ጋር የተያያዙ ስፍራዎችን መጎብኘታቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ብሔራዊ አርበኝነትን መፍጠር የሚያስችል አሰባሳቢ ትርክት መገንባት ያስፈልጋል- አቶ ኦርዲን በድሪ
Nov 28, 2023 55
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 18/2016 (ኢዜአ)፡- ብሔራዊ አርበኝነትን መፍጠር የሚያስችል አሰባሳቢ ትርክት መገንባት እንደሚያሰፈልግ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለጹ። ርዕሰ መስተዳድሩ በአርባ ምንጭ የስልጠና ማዕከል እየተሰጠ በሚገኝው የአቅም ግንባታ ስልጠና መድረክ ላይ ተገኝተው ከመንግስት አመራሮች ጋር ውይይት አካሂደዋል። በውይይት መድረኩ ላይ ርዕሰ መስተዳድሩ እንዳሉት የተዛቡ ትርክቶችን በማስተካከል ብሔራዊ አርበኝነትን መፍጠር የሚያስችል አሰባሳቢና የጋራ ትርክት መገንባት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። ሀገራዊ ብልጽግናን እውን ማድረግ የሚያስችል የሃሳብና የተግባር አንድነት መፍጠርም የስልጠናው ዓላማ መሆኑን አስረድተዋል። አገራዊ ኢኮኖሚያዊ፣ የሰላምና ደህንነት፣ የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ፣ የጊዜና ቴክኖሎጂ አጠቃቀም እንዲሁም ትኩረት የሚሹ አገራዊ፣ ቀጣናዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ አመራሩ በቂ ግንዛቤ በመያዝ የጋራ አቋም እንዲፈጠር የሚያደርጉ መሆናቸውን ተናግረዋል። ይህም ለዘመናት ሲንከባለሉ የመጡ የኢትዮጵያ እዳዎችን በመቅረፍ ወደ ምንዳና ሃብት ለመቀየር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አንስተዋል። ህዳር 14 የተጀመረው ስልጠናም እስከ ህዳር 26 ድረስ እንደሚቆይ የተገለፀ ሲሆን በስልጠናው ላይም ከሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደር የስራ ሀላፊዎች እየተሳተፉ መሆናቸውን ከሀረሪ ክልል መንግስት ኮሚኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል ።
ኢትዮጵያ እና ቼክ ሪፐብሊክ በመከላከያ ዘርፍ የቆየ ትብብራቸውን በማስፋት በግብርና፣ በማዕድን ልማት እና ቱሪዝም ትብብራቸውን ለማጠናከር ወሰኑ
Nov 28, 2023 160
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 18/2016 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ እና ቼክ ሪፐብሊክ በመከላከያ ዘርፍ የቆየ ትብብራቸውን በማስፋት በግብርና፣ በማዕድን ልማት እና ቱሪዝም ትብብራቸውን ለማጠናከር ወስነዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቼክ ሪፐብሊክ መንግስት ጽሕፈት ቤት በጠቅላይ ሚኒስትር ፔትር ፊያላ በይፋዊ አቀባበል ሥነ ሥርዓት አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ሁለቱ መሪዎች ባካሄዱት የሁለትዮሽ ውይይትም በመከላከያ ዘርፍ የቆየ ትብብራቸውን በማስፋት በግብርና፣ በማዕድን ልማት እና ቱሪዝም ትብብራቸውን ለማጠናከር መወሰናቸው ተገልጿል። የቼኩ ጠቅላይ ሚኒስትር ባለፉት ቅርብ ሳምንታት ኢትዮዽያን በመጎብኘት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ጋር ውይይት አድርገው እንደነበር የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሙስናና ብልሹ አሠራርን ለመከላከል ህብረተሰቡን ያሳተፈ ትግል ይደረጋል
Nov 28, 2023 82
አርባ ምንጭ፤ህዳር 18/2016 (ኢዜአ):-በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሙስናና ብልሹ አሠራርን ለመከላከል የህብረተሰብን ተሳትፎ ማጠናከር ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን የክልሉ ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ገለጸ ። “ሙስና የጋራ ጠላታችን ነው በህብረት እንታገል” በሚል መሪ ሀሳብ 20ኛው ዓለም አቀፍ የፀረ- ሙስና ቀን በአርባምንጭ ተከብሯል። የክልሉ ስነ-ምግባርና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሶፎኒያስ ደስታ በዚህ ጊዜ እንዳሉት ሙስናና ብልሹ አሰራር የመከላከል ስራው ከግብ እንዲደርስ የህብረተሰብ ተሳትፎ ወሳኝ ሚና አለው። በመሆኑም ትግሉ የተፈለገውን ውጤት እንዲያመጣ ኮሚሽኑ የህዝብ ተሳትፎን ማጠናከር ላይ አትኩሮ እየተሰራ እንደሚገኝ ነው የገለጹት። ''ሙስናና ብልሹ አሠራር የክልሉን ዕድገትና ልማት በመግታት በዜጎች ተጠቃሚነት ላይ አሉታዊ ጫና የሚያሳድር የጋራ ጠላታችን ነው'' ያሉት ኮሚሽነሩ "ሙስናን በመከላከል ረገድ ባለቤት የሆነውን ማህበረሰብ በማሳተፍ ጠንካራ ትግል ለማድረግ እየተሠራ ይገኛል" ብለዋል። በትምህርት ቤቶች፣ በሃይማት ተቋማት፣ ሲቪክ ማህበራት በኩል ሰፊ የግንዛቤ ሥራ እየተከናወነ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡ ይህን ለማጠናከር የተጀመረው ተግባር ውጤት እያመጣ መሆኑን ጠቁመው ባለፉት 3 ወራት ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ፣ በመሬት አስተዳደር፣ በግዥና ሌሎች ዘርፎች ከ10 በላይ ጥቆማዎች ቀርበው የማጣራት ስራ እየተካሄደ እንደሚገኝ ጠቁመዋል። ሙስናና ብልሹ አሠራርን ለማስወገድ ህዝብና መንግስት ተቀናጅተው መስራት እንዳለባቸው የገለጹት ደግሞ በኮሚሽኑ የትምህርትና ስልጠና ባለሙያ አቶ ፋሲል ጌታቸው ናቸው፡፡ በመንግስት ተቋማት የግዥ፣ የአገልግሎት አሰጣጥ፣ የገቢ ግብር፣ የትምህርት ማስረጃ አሰጣጥ፣ የመሬት አስተዳደር ስርአት፣ የኢንቨስትመንት ፈቃድና ሌሎች ለሙስና ተጋላጭ በሆኑ ዘርፎችና ተቋማት ሙስና እንዳይፈጸም ክትትል እየተደረገ መሆኑንም ገልጸዋል። ሙስናን መዋጋት የህልውና ጉዳይ በመሆኑ በመከላከሉና ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ ከማድረግ አንጻር ተቋማቱ ከህብረተሰቡ ጋር ተቀናጅተው መሥራት እንደሚገባቸው ጠቁመዋል፡፡ በአርባ ምንጭ ከተማ የኦሞ ባንክ ሠራተኛ የሆኑት አቶ ታከለ ምትኩ፣ መገናኛ ብዙሃን በሙስና አስከፊነትና መከላከሉ ላይ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ በመስጠት እንዲሁም ችግሮችን መርምሮ በማጋለጥ የበኩላቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል። በተቋማቸውም ሆነ በአከባቢያቸው ከብልሹ አሠራርና ሙስና ጋር በተያያዘ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለሚመለከተው ክፍል በመጠቆም የበኩላቸወን እንደሚወጡም ጠቁመዋል፡፡
ኦስትሪያ በማዕድን፣ በታዳሽ ሃይል፣ በግብርና እና በእንስሳት እርባታ ዘርፎች ከኢትዮጵያ ጋር መተባበር እንደምትፈልግ አስታወቀች
Nov 28, 2023 70
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 18/2016 (ኢዜአ) ፦ ኦስትሪያ በማዕድን፣ በታዳሽ ሃይል፣ በግብርና እና በእንስሳት እርባታ ዘርፎች ላይ ከኢትዮጵያ ጋር መተባበር እንደምትፈልግ አስታውቃለች። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከኦስትሪያ መራሄ መንግስት ልዩ ተወካይ ፒተር ላውንስኪ-ቲፈንታል ጋር ተወያይተዋል። በውይይታቸውም ኦስትሪያ ከኢትዮጵያ ጋር በማዕድን፣ ታዳሽ ኃይል፣ ግብርና እና በሌሎች ዘርፎች ትብብር ማድረግ እንደምትፈልግ የሀገሪቱ መራሄ መንግስት ልዩ ተወካይ ፒተር ላውንስኪ-ቲፈንታል ገልጸዋል፡፡ ውይይቱ በሁለትዮሽ ግንኙነት፣ በኢኮኖሚያዊ እድሎች እና የጋራ ጠቀሜታ ባላቸው ቀጣናዊ ልማቶች ላይ ያተኮረ መሆኑን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ይጠቁማል። አምባሳደር ምስጋኑ በአዲስ አበባ የሚገኘው የኦስትሪያ ኤምባሲ የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማስቀጠል አበረታች ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል። ልዩ ተወካይ ፒተር በበኩላቸው ኦስትሪያ ከኢትዮጵያ ጋር የረጅም ጊዜ ወዳጅነት እንዳላት ገልፀው እንደ ማዕድን፣ ታዳሽ ሃይል፣ ግብርና እና የእንስሳት እርባታ ባሉ ዘርፎች ለመተባበር ፍላጎት እንደላት ተናግረዋል፡፡
አንጎላ ከኢትዮጵያ ጋር በግብርናው ዘርፍ በትብብር መስራት እንደምትፈልግ ፕሬዝዳንት ጆአዎ ማኑዌል ጎንካልቬስ ሎሬንኮ ገለጹ
Nov 28, 2023 91
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 18/2016 (ኢዜአ) ፡-አንጎላ ከኢትዮጵያ ጋር በግብርናው ዘርፍ በትብብር መስራት እንደምትፈልግ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ጆአዎ ማኑዌል ጎንካልቬስ ሎሬንኮ ገለጹ። አምባሳደር ፍርቱና ዲበኮ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለአንጎላ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ጆአዎ ማኑዌል ጎንካልቬስ ሎሬንኮ አቅርበዋል ። በስነ ስርዓቱ ላይ ኢትዮጵያ በንግድ ፣በግብርና በቱሪዝም እና በኢንቨስትመንት ዘርፎች ከአንጎላ ሪፐብሊክ ጋር በቅርበት መስራት እንደምትፈልግ አምባሳደር ፍርቱና ለፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል ። ፕሬዝዳንቱ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በግብርናው ዘርፍ ከፍተኛ ውጤት እያስመዘገበች እንደምትገኝ ገልፀው፤ በትብብር መስራት እንደሚፈልጉ መግለፃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ፖለቲካ
የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በክልሉ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ውይይት እያካሄዱ ነው
Nov 29, 2023 36
አዲስ አበባ ፤ህዳር 19/2016 (ኢዜአ):- የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በክልሉ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ውይይት እያካሄዱ ይገኛል። በመድረኩ ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ ባስተላለፉት መልእክት በክልሉ በተፈጠረው ግጭት እና አለመረጋጋት የተነሳ ከወትሮው በተለይ ሁኔታ መከናወን ያለባቸው የልማት ስራዎች መስተጓጎላቸውን ጠቁመዋል። በመከላከያ ሠራዊትና በክልሉ የፀጥታ ኃይል፣ አጠቃላይ አመራሩና ሰላም ወዳዱ ህዝብ በቅንጅት በሰሩት ስራ አብዛኛው የክልሉ አካባቢዎች አንፃራዊ ሰላም ሰፍኗል ብለዋል። የክልሉን ሰላም ለማረጋገጥና ወደ ልማት ስራዎች ለመመለስ ባለን ጽኑ ፍላጎት በተከታታይ የግንዛቤ ማሳደግ ስራዎች መስራታችንም አሁን ለተገኘው አንጻራዊ ሰላም ከፍተኛ አስተዋፅዖ አበርክቷል ሲሉ ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል። የተገኘውን አንጻራዊ ሰላም ለማጽናት ይቻል ዘንድ ወቅቱን እና ሁኔታዎችን ያገናዘበ የጋራ አመራር የመስጠትና የማረጋገጥ ተግባር ከመላው አመራር እንደሚጠበቅ የጠቆሙት ርዕሰ መስተዳድሩ ህዝቡ ካለበት ችግር ውስጥ በፍጥነት ለማውጣት ከወትሮው የተለየ ስራ ይጠይቃል ብለዋል። ከሰሞኑ ከህዝቡ ጋር በተደረጉ የውይይት መድረኮች የተገኙ ገንቢ እና ተራማጅ ሀሳቦችን በተጨባጭ ወደ ተግባር በመቀየር የክልሉን የሰላም፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት ይኖርብናል ነው ያሉት። ድክመቶች ሳይደገሙ በአዲስ መታደስና ታሪክ መጻፍ እንደሚገባም መግባባት ላይ መደረሱን ከክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
አምባሳደር ሽፈራው ገነቲ በዜጋ ዲፕሎማሲ ዙሪያ ከባህሬን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ እና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር አምባሳደር ዶ/ር መሀመድ አሊ ባሀዛድ ጋር ተወያዩ
Nov 29, 2023 43
አዲስ አበባ ፤ህዳር 19 / 2016 (ኢዜአ):- በባህሬን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቆንስል ጄኔራል አምባሳደር ሽፈራው ገነቲ ከባህሬን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ እና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር አምባሳደር ዶ/ር መሀመድ አሊ ባሀዛድ ጋር በዜጎች ጉዳይ እና ባህሬን በኢትዮጵያ የውክልና አድማስ እንዲኖራት በሚቻልበት መንገድ ላይ ተወያዩ። ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት የባህሬንን የሥራ ስምሪት ህግን በተቃረነ መልኩ የታዩ የተወሰኑ እንቅስቃሴዎችን ቆንስላ ጄኔራል ጽህፈት ቤቱ ማስተካከያ ማድረጉን ገልፀዋል። አሁን ላይ የዜጎች ጉዳይ በቆንስላ ጄኔራል ጽህፈትቤቱ ባለሙያዎች ብቻ እየተሰራ መሆኑን አምባሳደር ሽፈራው በውይይቱ አንስተዋል ። በህገወጥ መንገድ ያለመኖሪያ ፍቃድ የሚኖሩ ዜጎች የመኖሪያ ፍቃድ አግኝተው የሚሰሩበትን ሁኔታ እንዲመቻችና በህገወጥ መንገድ በእየቤቱ እየዞሩ ገንዘብ የሚመነዝሩላቸውንም ለማስቀረት የባህሬን መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል። በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት በማሳደግ በሰራተኛ ስምሪት፣ የንግድና ቱሪዝም ዘርፍ ትብብርን ማጠናከር እንዲሁም አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረትና የብዙ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች መቀመጫ በመሆኗ የባህሬን ንጉሳዊ መንግስት ውክልና እንዲኖረው ጠይቀዋል። ረዳት ሚኒስትሩ አምባሳደር ዶ/ር መሀመድ አሊ ባሀዛድ በበኩላቸው ከኢትዮጵያዊያን ዜጎች ጋር በተያያዘ ሲስተዋሉ የነበሩ ችግሮች መኖራቸውን በማስታወስ፣ ችግሮቹን ለመቅረፍ ቆንስል ጄኔራል ጽህፈት ቤቱ በኩል የተወሰዱትን እርምጃዎችን አድንቀዋል። ባህሬን በቀጣይ በአዲስ አበባ ኤምባሲ ለመክፈት የሚያስችል ጥናት የምታደርግ መሆኗን ገልፀዋል። ጥናቱ አልቆ ወደ ሥራ እስከሚገባ የክብር ቆንስላ ህጉን ተከትሎ እንደምትሰይም መናገራቸውን ከውጥ ጉዳይ ሚስቴር ማህበራዊ ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ልዑካን ቡድናቸው የኢትዮ- ቼክ የትብብር መስኮች ጋር የተያያዙ ስፍራዎችን ጎበኙ
Nov 29, 2023 58
አዲስ አበባ፤ህዳር 19/2016(ኢዜአ):-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ልዑካን ቡድናቸው የኢትዮ- ቼክ የትብብር መስኮች ጋር የተያያዙ ስፍራዎችን ጎብኝተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩና ልዑካን ቡድናቸው በቼክ ሪፐብሊክ ቆይታቸው እንደ ግብርና፣ ቱሪዝም እና ባሕል ባሉ በመስፋፋት ላይ ካሉ የኢትዮ- ቼክ የትብብር መስኮች ጋር የተያያዙ ስፍራዎችን መጎብኘታቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ብሔራዊ አርበኝነትን መፍጠር የሚያስችል አሰባሳቢ ትርክት መገንባት ያስፈልጋል- አቶ ኦርዲን በድሪ
Nov 28, 2023 55
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 18/2016 (ኢዜአ)፡- ብሔራዊ አርበኝነትን መፍጠር የሚያስችል አሰባሳቢ ትርክት መገንባት እንደሚያሰፈልግ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለጹ። ርዕሰ መስተዳድሩ በአርባ ምንጭ የስልጠና ማዕከል እየተሰጠ በሚገኝው የአቅም ግንባታ ስልጠና መድረክ ላይ ተገኝተው ከመንግስት አመራሮች ጋር ውይይት አካሂደዋል። በውይይት መድረኩ ላይ ርዕሰ መስተዳድሩ እንዳሉት የተዛቡ ትርክቶችን በማስተካከል ብሔራዊ አርበኝነትን መፍጠር የሚያስችል አሰባሳቢና የጋራ ትርክት መገንባት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። ሀገራዊ ብልጽግናን እውን ማድረግ የሚያስችል የሃሳብና የተግባር አንድነት መፍጠርም የስልጠናው ዓላማ መሆኑን አስረድተዋል። አገራዊ ኢኮኖሚያዊ፣ የሰላምና ደህንነት፣ የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ፣ የጊዜና ቴክኖሎጂ አጠቃቀም እንዲሁም ትኩረት የሚሹ አገራዊ፣ ቀጣናዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ አመራሩ በቂ ግንዛቤ በመያዝ የጋራ አቋም እንዲፈጠር የሚያደርጉ መሆናቸውን ተናግረዋል። ይህም ለዘመናት ሲንከባለሉ የመጡ የኢትዮጵያ እዳዎችን በመቅረፍ ወደ ምንዳና ሃብት ለመቀየር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አንስተዋል። ህዳር 14 የተጀመረው ስልጠናም እስከ ህዳር 26 ድረስ እንደሚቆይ የተገለፀ ሲሆን በስልጠናው ላይም ከሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደር የስራ ሀላፊዎች እየተሳተፉ መሆናቸውን ከሀረሪ ክልል መንግስት ኮሚኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል ።
ኢትዮጵያ እና ቼክ ሪፐብሊክ በመከላከያ ዘርፍ የቆየ ትብብራቸውን በማስፋት በግብርና፣ በማዕድን ልማት እና ቱሪዝም ትብብራቸውን ለማጠናከር ወሰኑ
Nov 28, 2023 160
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 18/2016 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ እና ቼክ ሪፐብሊክ በመከላከያ ዘርፍ የቆየ ትብብራቸውን በማስፋት በግብርና፣ በማዕድን ልማት እና ቱሪዝም ትብብራቸውን ለማጠናከር ወስነዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቼክ ሪፐብሊክ መንግስት ጽሕፈት ቤት በጠቅላይ ሚኒስትር ፔትር ፊያላ በይፋዊ አቀባበል ሥነ ሥርዓት አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ሁለቱ መሪዎች ባካሄዱት የሁለትዮሽ ውይይትም በመከላከያ ዘርፍ የቆየ ትብብራቸውን በማስፋት በግብርና፣ በማዕድን ልማት እና ቱሪዝም ትብብራቸውን ለማጠናከር መወሰናቸው ተገልጿል። የቼኩ ጠቅላይ ሚኒስትር ባለፉት ቅርብ ሳምንታት ኢትዮዽያን በመጎብኘት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ጋር ውይይት አድርገው እንደነበር የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሙስናና ብልሹ አሠራርን ለመከላከል ህብረተሰቡን ያሳተፈ ትግል ይደረጋል
Nov 28, 2023 82
አርባ ምንጭ፤ህዳር 18/2016 (ኢዜአ):-በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሙስናና ብልሹ አሠራርን ለመከላከል የህብረተሰብን ተሳትፎ ማጠናከር ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን የክልሉ ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ገለጸ ። “ሙስና የጋራ ጠላታችን ነው በህብረት እንታገል” በሚል መሪ ሀሳብ 20ኛው ዓለም አቀፍ የፀረ- ሙስና ቀን በአርባምንጭ ተከብሯል። የክልሉ ስነ-ምግባርና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሶፎኒያስ ደስታ በዚህ ጊዜ እንዳሉት ሙስናና ብልሹ አሰራር የመከላከል ስራው ከግብ እንዲደርስ የህብረተሰብ ተሳትፎ ወሳኝ ሚና አለው። በመሆኑም ትግሉ የተፈለገውን ውጤት እንዲያመጣ ኮሚሽኑ የህዝብ ተሳትፎን ማጠናከር ላይ አትኩሮ እየተሰራ እንደሚገኝ ነው የገለጹት። ''ሙስናና ብልሹ አሠራር የክልሉን ዕድገትና ልማት በመግታት በዜጎች ተጠቃሚነት ላይ አሉታዊ ጫና የሚያሳድር የጋራ ጠላታችን ነው'' ያሉት ኮሚሽነሩ "ሙስናን በመከላከል ረገድ ባለቤት የሆነውን ማህበረሰብ በማሳተፍ ጠንካራ ትግል ለማድረግ እየተሠራ ይገኛል" ብለዋል። በትምህርት ቤቶች፣ በሃይማት ተቋማት፣ ሲቪክ ማህበራት በኩል ሰፊ የግንዛቤ ሥራ እየተከናወነ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡ ይህን ለማጠናከር የተጀመረው ተግባር ውጤት እያመጣ መሆኑን ጠቁመው ባለፉት 3 ወራት ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ፣ በመሬት አስተዳደር፣ በግዥና ሌሎች ዘርፎች ከ10 በላይ ጥቆማዎች ቀርበው የማጣራት ስራ እየተካሄደ እንደሚገኝ ጠቁመዋል። ሙስናና ብልሹ አሠራርን ለማስወገድ ህዝብና መንግስት ተቀናጅተው መስራት እንዳለባቸው የገለጹት ደግሞ በኮሚሽኑ የትምህርትና ስልጠና ባለሙያ አቶ ፋሲል ጌታቸው ናቸው፡፡ በመንግስት ተቋማት የግዥ፣ የአገልግሎት አሰጣጥ፣ የገቢ ግብር፣ የትምህርት ማስረጃ አሰጣጥ፣ የመሬት አስተዳደር ስርአት፣ የኢንቨስትመንት ፈቃድና ሌሎች ለሙስና ተጋላጭ በሆኑ ዘርፎችና ተቋማት ሙስና እንዳይፈጸም ክትትል እየተደረገ መሆኑንም ገልጸዋል። ሙስናን መዋጋት የህልውና ጉዳይ በመሆኑ በመከላከሉና ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ ከማድረግ አንጻር ተቋማቱ ከህብረተሰቡ ጋር ተቀናጅተው መሥራት እንደሚገባቸው ጠቁመዋል፡፡ በአርባ ምንጭ ከተማ የኦሞ ባንክ ሠራተኛ የሆኑት አቶ ታከለ ምትኩ፣ መገናኛ ብዙሃን በሙስና አስከፊነትና መከላከሉ ላይ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ በመስጠት እንዲሁም ችግሮችን መርምሮ በማጋለጥ የበኩላቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል። በተቋማቸውም ሆነ በአከባቢያቸው ከብልሹ አሠራርና ሙስና ጋር በተያያዘ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለሚመለከተው ክፍል በመጠቆም የበኩላቸወን እንደሚወጡም ጠቁመዋል፡፡
ኦስትሪያ በማዕድን፣ በታዳሽ ሃይል፣ በግብርና እና በእንስሳት እርባታ ዘርፎች ከኢትዮጵያ ጋር መተባበር እንደምትፈልግ አስታወቀች
Nov 28, 2023 70
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 18/2016 (ኢዜአ) ፦ ኦስትሪያ በማዕድን፣ በታዳሽ ሃይል፣ በግብርና እና በእንስሳት እርባታ ዘርፎች ላይ ከኢትዮጵያ ጋር መተባበር እንደምትፈልግ አስታውቃለች። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከኦስትሪያ መራሄ መንግስት ልዩ ተወካይ ፒተር ላውንስኪ-ቲፈንታል ጋር ተወያይተዋል። በውይይታቸውም ኦስትሪያ ከኢትዮጵያ ጋር በማዕድን፣ ታዳሽ ኃይል፣ ግብርና እና በሌሎች ዘርፎች ትብብር ማድረግ እንደምትፈልግ የሀገሪቱ መራሄ መንግስት ልዩ ተወካይ ፒተር ላውንስኪ-ቲፈንታል ገልጸዋል፡፡ ውይይቱ በሁለትዮሽ ግንኙነት፣ በኢኮኖሚያዊ እድሎች እና የጋራ ጠቀሜታ ባላቸው ቀጣናዊ ልማቶች ላይ ያተኮረ መሆኑን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ይጠቁማል። አምባሳደር ምስጋኑ በአዲስ አበባ የሚገኘው የኦስትሪያ ኤምባሲ የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማስቀጠል አበረታች ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል። ልዩ ተወካይ ፒተር በበኩላቸው ኦስትሪያ ከኢትዮጵያ ጋር የረጅም ጊዜ ወዳጅነት እንዳላት ገልፀው እንደ ማዕድን፣ ታዳሽ ሃይል፣ ግብርና እና የእንስሳት እርባታ ባሉ ዘርፎች ለመተባበር ፍላጎት እንደላት ተናግረዋል፡፡
አንጎላ ከኢትዮጵያ ጋር በግብርናው ዘርፍ በትብብር መስራት እንደምትፈልግ ፕሬዝዳንት ጆአዎ ማኑዌል ጎንካልቬስ ሎሬንኮ ገለጹ
Nov 28, 2023 91
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 18/2016 (ኢዜአ) ፡-አንጎላ ከኢትዮጵያ ጋር በግብርናው ዘርፍ በትብብር መስራት እንደምትፈልግ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ጆአዎ ማኑዌል ጎንካልቬስ ሎሬንኮ ገለጹ። አምባሳደር ፍርቱና ዲበኮ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለአንጎላ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ጆአዎ ማኑዌል ጎንካልቬስ ሎሬንኮ አቅርበዋል ። በስነ ስርዓቱ ላይ ኢትዮጵያ በንግድ ፣በግብርና በቱሪዝም እና በኢንቨስትመንት ዘርፎች ከአንጎላ ሪፐብሊክ ጋር በቅርበት መስራት እንደምትፈልግ አምባሳደር ፍርቱና ለፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል ። ፕሬዝዳንቱ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በግብርናው ዘርፍ ከፍተኛ ውጤት እያስመዘገበች እንደምትገኝ ገልፀው፤ በትብብር መስራት እንደሚፈልጉ መግለፃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ማህበራዊ
ኢትዮጵያን ከመድኃኒት እና የህክምና ግብዓቶች ጥገኝነት ለማላቀቅ የአገር ውስጥ አምራቾችን መደገፍ ይገባል
Nov 29, 2023 41
አዲስ አበባ፤ ህዳር 19/2016 (ኢዜአ) የመድኃኒት እና የህክምና ግብዓቶች ፍላጎትን ለማሟላትና የውጪ ጫናን ለመቀነስ ለአገር ውስጥ አምራቾች ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡ የጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከዘርፉ አጋር አካላት ጋር በመሆን በቅሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ በሚገኙ የመድኃኒት እና የህክምና ግብዓት አምራቾችን የመስክ ምልከታ አድርጓል። በመስክ ምልከታው ላይ ጤና ሚኒስትርን ጨምሮ የምግብና መድኀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን እና ሌሎች አጋር አካላት ተሳትፈዋል። በኢንዱስትሪ ፓርኩ የሚገኙ ሶስት የመድኃኒትና የህክምና ግብዓት አምራቾች የተጎበኙ ሲሆን፣ አሁን የሚገኙበትን ደረጃና በዘርፉ ያሉባቸውን ተግዳሮቶች ለቋሚ ኮሚቴው አቅርበዋል። የኢትዮጵያ መድኃኒትና ህክምና ግብዓት አምራቾች ማህበር ፕሬዘዳንት ዶ/ር ዳንኤል ዋቅቶላ የአገር ውስጥ አምራቾች የአገር ውስጥ ፍላጎትን ከሟሟላት ባሻገር ኢትዮጵያን በዘርፉ ቀዳሚ ለማድረግ ከግሉ ዘርፍ ከፍተኛ ፍላጎት መኖሩን ለኮሚቴው አባላት ገልጸዋል። አያይዘውም በፓርኮች የመሠረተ-ልማት አለመሟላትና የአገልግሎት ውድነት፣ ለመድኃኒት ማምረት ጥቅም ላይ የሚውሉ ግብዓቶች የታክስ ጫና፣ የመንግሥት የግዢ ሥርዓት የአገር ውስጥ አምራቾችን የሚያበረታታ አለመሆኑ በምንፈልገው ልክ እንዳንሰራ አድርጎናል ብለዋል። ጠንካራ የውጪ ጫናዎችን የሚቋቋም የጤና ሥርዓት ለመገንባት መንግሥት የገበያ ዕድሎችን ከማመቻቸት ጀምሮ ለዘርፉ ተገቢውን ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ ለቋሚ ኮሚቴው አስገንዝበዋል። የቅሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ በበኩሉ 187 አልሚዎች ለመቀበል የሚያስችል አቅም እንዳለው የገለፀ ሲሆን ከ200 ሜጋ ዋት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል፣ የውሃ፣ የአንድ ማእከል አገልግሎት በማቅረብ ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡ የጤና ማህበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ወርቀሰሙ ማሞ ባስተላለፉት መልዕክት አምራቾች እያደረጉት ያለው ጥረት አስደሳችና ሊበረታታ የሚገባው መሆኑን ገልፀዋል። የውጪ ምንዛሬ እና የጉምሩክ እንዲሁም የፖሊሲ ችግሮችን ለመቅረፍ የጤናው ዘርፍ ተገቢውን ትኩረትና ድጋፍ ሊያደርግ እንደሚገባ ጠቁመዋል። ልዩነቶችን ሁለቱንም ወገን ተጠቃሚ በሚያደርግ መልኩ በውይይት ለመፍታት ቋሚ ኮሚቴው እንደሚሰራ ገልጸዋል። የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ፍሬሕይወት አበበ በበኩላቸው መስሪያ ቤታቸው በ2016 ዓ.ም ከ97 በላይ በሚሆኑ ምርቶች ላይ የአገር ውስጥ አምራቾች ብቻ በአቅርቦት እንዲሳተፉ መደረጉን ገልፀው፤ የአገር ውስጥ ምርት ጉዳይ ኢትዮጵያን ከውጪ ጥገኝነት ማለቀቅ በመሆኑ አብረን እንሰራለን ብለዋል። የኢንዱስትሪና የማዕድን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላትም በመስክ ምልከታው ላይ መሳተፋቸውን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
የትምህርት ሚኒስቴር 10 ነጥብ 6 ሚሊየን መጽሐፍቶችን ለክልሎች አሠራጨ
Nov 28, 2023 62
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 18/2016 (ኢዜአ)፡- የትምህርት ሚኒስቴር ካሳተመው 20 ነጥብ 6 ሚሊየን የመማሪያ መጽሐፍት መካከል 10 ነጥብ 6 ሚሊየን የሚሆኑት ለክልሎች መሠራጨታቸውን ገለፀ። 32ኛው የትምህርት ጉባዔ በሶማሌ ክልል በጅግጅጋ ከተማ እየተካሄደ ነው። በትምህርት ሚኒስቴር በስትራቴጂክ ጉዳዮች ሥራ አስፈጻሚ የዕቅድና በጀት ዝግጅትና ክትትል ግምገማ ቡድን መሪ እሸቱ ገላዬ፤ "የትምህርት ዘርፍ ሪፎርም ሥራዎች አፈጻጸም" በተመለከተ ለጉባዔው ሪፖርት አቅርበዋል። የአዲሱ ሥርዓተ-ትምህርት ፖሊሲ ተግባራዊ ለማድረግ የመጽሐፍት አቅርቦት ተግዳሮቶችን ለመፍታትም የትምህርት ሚኒስቴር የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን መጽሐፍት እንዲሁም ክልሎች የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎችን መጽሐፍት እንዲያሳትሙ መግባባት ላይ መደረሱን ገልፀዋል። በዚህም በተያዘው በጀት ዓመት የትምህርት ሚኒስቴር 20 ነጥብ 6 ሚሊየን መጽሐፍትን ማሳተሙን ገልጸው፤ ከዚህ ውስጥ 10 ነጥብ 6 ሚሊየኑ ወደ አገር ውስጥ ገብቶ ለክልሎች መከፋፈሉን ተናግረዋል። ቀሪዎቹ 10 ሚሊየን መጽሐፍትም ከጅቡቲ ወደብ ወደ አገር ውስጥ በመጓጓዝ ላይ መሆኑን ጠቁመዋል። በበጀት ዓመቱ ከመንግሥትና ከኅብረተሰቡ 22 ቢሊየን ብር በማሰባሰብ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ከ 2 ነጥብ 7 ሚሊየን በላይ ከቅድመ አንደኛ እስከ 8ኛ ክፍል ተማሪዎችን በትምህርት ቤት ምገባ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ጠቁመዋል። የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል በክረምቱ ወቅት ተጀምሮ በነበረው "ትምህርት ለትውልድ " በሚል ንቅናቄ የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ የሚያስችል ለውጥ መመዝገቡን ገልፀዋል። በንቅናቄውም ክልሎች ሰፊ ሥራ መሥራታቸውን ያነሱት የቡድን መሪው፤ 14 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር የሚሆን ኃብት መሰብሰቡን ጠቁመዋል። በዚህም በተለያዩ ክልሎች የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች፣ የአንደኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መገንባታቸውን ጠቁመዋል። ዩኒቨርሲቲዎችን በተልዕኮና የትኩረት አቅጣጫ መሠረት የመለየት ሥራ መከናወኑን ጠቁመው፤ የአፕላይድ፣ የምርምርና የአጠቃላይ ዩኒቨርሲቲዎች መሆናቸውንም ገልፀዋል። ዩኒቨርሲቲዎችም ከትኩረት መስካቸው አንጻር የትምህርት ፕሮግራሞችን በመቅረጽ ወደ ተግባር መግባት መጀመራቸውን ተናግረዋል። ለዚህም የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲና የኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲዎች ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል፡፡ ጉባዔው ነገ ኅዳር 19 ቀን 2016 ዓ.ም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በመምከር ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ የሁሉም አካላት ተሳትፎ ወሳኝ ነው
Nov 28, 2023 61
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 18/2016 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት የሁሉም አካላት የጋራ ርብርብ እንደሚያስፈልግ የሰላም ሚኒስትሩ ብናልፍ አንዷለም ገለጹ። በሰላም ሚኒስቴር የተዘጋጀው የሰላም ምክር ቤት ሁለተኛ ጉባዔ በአዲስ አበባ ተካሂዷል። በመድረኩ የሰላም ሚኒስትሩ ብናልፍ አንዷለምን ጨምሮ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት እና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶክተር ዲማ ነገዎ፣ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተወካዮች ተሳትፈዋል። የሰላም ሚኒስትሩ ብናልፍ አንዷለም በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የሰላም ሥራ የሁሉንም አካላት ርብርብ እና ጥረት የሚጠይቅ ሥራ ነው። የሰላም ምክር ቤቱም ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍሎች በማካተት ሁሉም የራሱን አስተዋጽዖ እንዲያበረክት የሚያስችል መሆኑን ጠቁመዋል። በኢትዮጵያ የተለያዩ ግጭቶች መከሰታቸውን አስታውሰው ከእነዚህ የግጭት አዙሪቶች እና ከደረሱ ጉዳቶች ትምህርት በመውሰድ ለሰላም አማራጭ ቅድሚያ መስጠት እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል። ማንኛውም ጥያቄ ያለው አካል በሰላማዊ መንገድ ቁጭ ብሎ በመነጋገር ለብዙ ችግሮች መፍትሔ ማምጣት ይቻላል ያሉት ሚኒስትሩ፤ ይህም የመንግሥት ጽኑ አቋም መሆኑን ተናግረዋል። መገናኛ ብዙኃን ለሰላም ግንባታ ሥራ ቁልፍ መሳሪያ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ በኢትዮጵያም የተረጋጋ ሰላም እንዲመጣ አዎንታዊ ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አመላክተዋል። የውይይቱ ተሳታፊዎችም የተጀመሩ የሰላም ግንባታ ሥራዎችን አጠናክሮ መቀጠል ይገባል ብለዋል። ሰላም እንዳይሰፍንና ቅሬታዎች እንዲባባሱ እየሰሩ ያሉ አካላት ተጠያቂ መሆን እንዳለባቸው ገልፀዋል። የአንድ ቀን ጥፋት በርካታ ጉዳት የሚያመጣ በመሆኑ እለት ተለት በሰዎች ስነ-ልቦና ላይ መሠራት እንዳለበት ጠቁመዋል።
በቴክኒክና ሙያ ሥልጠና የሙያ ማማከርና የድጋፍ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል መመሪያ ይፋ ሆነ
Nov 28, 2023 53
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 18/2016 (ኢዜአ)፡-የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በቴክኒክና ሙያ ሥልጠና የሙያ ማማከርና የድጋፍ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል መመሪያ ይፋ አደረገ። የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መመሪያው የጀርመን የልማት ተራድኦ ድርጅት (ጂ አይ ዜድ) እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ነው ተብሏል። መመሪያው በዘርፉ የመማር ማስተማር ሂደቱን የሚያሻሽልና ተማሪዎች ያላቸውን ክህሎት አውጥተው እንዲጠቀሙ ትልቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑንም ነው የተመላከተው። የሥራና ክህሎት ሚኒስትር አማካሪ ተሾመ ለማ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት፤ መመሪያው ተማሪዎች ሙያዊ ክህሎታቸውን ተጠቅመው ውጤታማ ሥራ ፈጣሪ እንዲሆኑ ያግዛቸዋል ብለዋል። ወጣቶች በዕውቀት፣ በልምድ፣ በራስ አገዝ የሥራ ክህሎት ብቁ እንዲሆኑ፣ የሥራ ፈጠራ ስትራቴጂዎችን እንዲያጤኑና ውሳኔ ሰጪነት ላይ ያላቸውን ልምድ እንዲያዳብሩም ያስችላል ነው ያሉት። በጀርመን የልማት ተራድኦ ድርጅት (ጂ አይ ዜድ) የኢትዮ-ጀርመን የትምህርትና ሥልጠና መርሃ-ግብር አስተባባሪ አሊ ሙሃመድ ካሃን በበኩላቸው፤ መመሪያው በቴክኒክና ሙያ ሥልጠና የሚያልፉ ወጣቶችንና ሥራ ፈጣሪዎችን ይበልጥ ውጤታማ ያደርጋቸዋል ሲሉ ገልፀዋል።
ኢኮኖሚ
በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ለመሳተፍ አምስት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ዝግጅት እያደረጉ ነው
Nov 29, 2023 23
አዲስ አበባ ፤ህዳር 19/2016 (ኢዜአ):-በኢትዮጵያ የአገር ውስጥና የውጭ ድርጅቶች ለመሳተፍ ከፍተኛ ፍላጎት ባሳዩበት የካፒታል ገበያ ቀዳሚ የሆኑ አምስት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተለይተው ዝግጅት እያደረጉ መሆኑ ተገለጸ። የካፒታል ገበያውን በተያዘው ዓመት ለማስጀመር የሚያስችል አብዛኛው ሥራ መጠናቀቁም ተገልጿል። ኢትዮጵያም ባደጉት አገራት በስፋት እየተተገበረ ያለውን የካፒታል ገበያን ወደ ሥራ ለማስገባት አዋጅ 1248/2013 አፀድቃ ወደ ሥራ ለመግባት እንቅስቃሴ ጀምራለች። የካፒታል ገበያ የኢትዮጵያን ማክሮ ኢኮኖሚ ሚዛን በማስተካከል የጎላ ሚና እንደሚኖረውና ለግልም ሆነ ለድርጅቶች በቂ የሥራ ማንቀሳቀሻ ገንዘብ ለማስገኘት እንደሚያግዝ ይገለጻል። በተጨማሪም የኢትዮጵያ ምጣኔ ኃብት በማይዋዥቅ መልኩ በዘላቂነት እንዲያድግ የፋይናንስ አገልግሎት ዘርፉን አስቻይ ሁኔታ ለማስፋትና ቁጠባን ለማበረታታት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ይነገራል። በኢትዮጵያም አዋጁ ከፀደቀ በኋላ የካፒታል ገበያውን ለመጀመር የሚያስችል የተለያዩ እንቅስቃሴዎች በመደረግ ላይ መሆኑ ይታወቃል። እንቅስቃሴውን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ከፍተኛ የሕግ አማካሪ ሰለሞን ዘውዴን አነጋግሯል። አቶ ሰለሞን እንዳሉትም በኢትዮጵያ በርካታ የውጭና የአገር ውስጥ ባለሃብቶች በገበያው ለመሳተፍ ከፍተኛ ፍላጎት በማሳየት ላይ ናቸው። ከፍተኛ ፍላጎት የታየበት የካፒታል ገበያ ለማስጀመር የሚያስችል የመጨረሻ ምዕራፍ ዝግጅት እየተደረገም እንደሆነም ተናግረዋል። አሁን ላይ አምስት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ወደ ገበያው ለመግባት ዝግጅት እያደረጉ ሲሆን የኬንያ፣ የናይጄሪያና የደቡብ አፍሪካ ኩባንያዎችም በካፒታል ገበያው ለመሳተፍ ፍላጎት ማሳየታቸውን አንስተዋል። የተለዩ የመንግሥት የልማት ድርጅቶችም ይሁን ፍላጎት ያሳዩ የውጭ ኩባንያዎች አጠቃላይ የዝግጅት ሥራዎች ሲጠናቀቁ ወደ ሥራ እንደሚገቡ ገልፀዋል። አሁን ላይ የመመሪያ ማዘጋጀት፣ የግንዛቤ መስጨበጫና የተሳታፊ ድርጅቶች ልየታ ሥራ እየተከናወነ ሲሆን፤ ወደ ካፒታል ገበያው የሚገባውን ድርጅት ግለሰብና ባለሃብት ማስተዳደር የሚችል የሕግ ማዕቀፍ ተዘጋጅቶ በቅርቡ ወደ ሥራ ለማስገባት እየተሰራ ነው ብለዋል። የካፒታል ገበያው አከናዋኝ፣ የኢንቨስትመንት ባንክ፣ የውክልና አስተዳዳሪዎች፣ የጋራ ኢንቨስትመንት ባንክ ሥራ አስኪያጅን ጨምሮ በካፒታል ገበያው አገልግሎት ለሚሰጡ 15 ዘርፎችም ፈቃድ መስጠት የሚያስችሉ መመሪያዎች መዘጋጀታቸውንም ነው የተናገሩት። በተያዘው ዓመት የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን አጠናቆ የካፒታል ገበያን ወደ ሥራ ለማስገባት እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል። የካፒታል ገበያው በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንትና ቁጠባን ከማሳደጉ ባሻገር የዲጂታል ግብይትን በማፋጠን በኩል ሰፊ አስተዋጽዖ እንደሚኖረውም ጠቁመዋል። ለኢንቨስተሮች ሥጋቶችን የሚቀንስ፣ ለኩባንያዎችና ገንዘብ ለሚያስፈልጋቸው ደግሞ ተጨማሪ የፋይናንስ ጥቅም እንዲያገኙ ወይም የባንክ ብድር ዓይነት ድጋፍ እንዲያገኙ እንደሚያደርግ እንዲሁ። አዳዲስ የሥራ ዕድሎች እንዲፈጠሩ እንደሚያደርግም ነው የተናገሩት። የካፒታል ማርኬት ተሳታፊ የሚባሉ ደላሎች፣ ነጋዴዎች፣ የኢንቨስትመንት ባንኮች፣ ሌሎች የፈንዱን ፍሰት የሚያግዙ ተዋንያን ናቸው። ለአገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት ለማንቀሳቀስ ከፍተኛ ጥቅም እንዳለው የሚታመንበት የካፒታል ገበያ እውን እንዲሆን ሁሉም የበኩሉን መወጣት እንዳለበት አብራርተዋል።
በምስራቅ ሸዋ ዞን 121 ሺህ ሄክታር መሬት በበጋ መስኖ ስንዴ ለምቷል
Nov 29, 2023 29
አዳማ፤ህዳር 19/2016 (ኢዜአ)፦ በምስራቅ ሸዋ ዞን 121 ሺህ ሄክታር መሬት በኩታገጠም በበጋ መስኖ ስንዴ መልማቱን የዞኑ ግብርና ጽሕፈት ቤት ገለፀ። የምስራቅ ሸዋ ዞን ግብርና ጽሕፈት ቤት ምክትል ሃላፊ አቶ አብነት ዘገየ ለኢዜአ እንደገለፁት በዞኑ በዘንድሮው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት 350 ሺህ ሄክታር ለማልማት ታቅዶ ስራው ተጀምሯል። በእስከ አሁኑ ሂደት 192 ሺህ ሄክታር መሬት መታረሱን የገለፁት አቶ አብነት፤ እስከ ትናንት ድረስ 121 ሺህ ሄክታር መሬት በኩታ ገጠም ታርሶ በዘር መሸፈኑን ተናግረዋል። የበጋ መስኖ ስንዴ ልማቱን 95 በመቶ የሚሆነውን በሜካናይዜሽንና በኩታ ገጠም ለማልማት ታቅዶ ወደ ስራ እንደተገባም ገልጸዋል። በዚህም እስከ አሁን በዘር የተሸፈነው 121 ሺህ ሄክታር በሜከናይዜሽንና በኩታ ገጠም መልማቱን አመልክተዋል። ምክትል ሃላፊው በዘንድሮው የበጋ መስኖ ስንዴ ከዞኑ 14 ነጥብ 4 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማግኘት መታቀዱን ተናግረዋል። ከግብዓት አቅርቦት አንጻርም ለዘንድሮው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት 350 ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያና ምርጥ ዘር መቅረቡን ገልጸዋል። በዞኑ የአደኣ ወረዳ ግብርና ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሮቢ ያዴሳ በበኩላቸው በወረዳው 2 ሺህ ሄክታር መሬት በበጋ መስኖ ስንዴ የማልማት ስራ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል። በዚህም ለአርሶ አደሩ የስንዴ ምርጥ ዘር፣ የአፈር ማዳበሪያና የእርሻ ትራክተር በተመጣጣኝ ዋጋ እየቀረበ መሆኑንም ጠቁመዋል። በወረዳው በመስኖ ስንዴ ልማት ከተሰማሩ አርሶ አደሮች መካከል አቶ ከተማ ሽፈራው ከአካባቢው አርሶ አደር ጋር በመሆን በኩታ ገጠም በ4 ሄክታር መሬት ላይ ስንዴ እያለሙ መሆኑን ተናግረዋል። 'በዋናነት የአካባቢው አርሶ አደሮች ለስንዴ ልማቱ በራሳቸው በባለሙያ ታግዘው ያለሙትን ምርጥ ዘር በመጠቀም በሜካናይዜሽን እያለሙ መሆናቸውንም አክለዋል። አርሶ አደር መኮንን ሽብሩ በበኩላቸው በግማሽ ሄክታር መሬት ላይ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት እያከናወኑ መሆኑን ጠቅሰዋል። በዘንድሮው በጋ በሜካናይዜሽንና ኩታ ገጠም በማልማታቸው የተሻለ ምርት እንደሚያገኙ ተስፋ መሰነቃቸውንም አስረድተዋል።
ከአንድ ሚሊየን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ አገር ውስጥ ገብቷል
Nov 29, 2023 48
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 19/2016 (ኢዜአ)፡- ለ2016/17 የምርት ዘመን ለመግዛት ከታቀደ 23 ሚሊየን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ እስከ አሁን ከአንድ ሚሊየን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ አገር ውስጥ መግባቱን የግብርና ሚኒስቴር ገለጸ። የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሶፊያ ካሳ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፤ በምርት ዘመኑ ከ23 ነጥብ 3 ሚሊየን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ለመግዛት ታቅዷል። እስካሁን 14 ነጥብ 79 ሚሊየን ኩንታል ኤን ፒ ኤስ ዝርያና ዩሪያ የአፈር ማዳበሪያ ግዥ መፈጸሙን ጠቁመው ከተገዛው ውስጥ ከአንድ ሚሊየን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ አገር ውስጥ መጓጓዙን ገልጸዋል። እስከ ታህሳስ ወር መጀመሪያ አካባቢ ተጨማሪ 1 ነጥብ 7 ሚሊየን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ጂቡቲ እንደሚደርስ ጠቁመው በዚህ ዓመት የአፈር ማዳበሪያ በፍጥነት ወደ አገር ውስጥ እየገባ እንደሚገኝ ተናግረዋል። መንግሥት የዓለም ከፍተኛ የማዳበሪያ ጭማሪና የአርሶ አደሩን የመግዛት አቅም ከግምት በማስገባት ከፍተኛ ድጎማ ሲያደርግ መቆየቱን ጠቅሰው ባለፉት ሦስት ዓመታት የ52 ቢሊየን ብር ድጎማ ማድረጉን ተናግረዋል።
በኢንዱስትሪ ፓርኮችና በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና ውስጥ የሚገኙ የኢንቨስትመንት አማራጮች ለፈረንሳይ አምራች ተቋማት ቀረቡ
Nov 29, 2023 42
አዲስ አበባ ፤ኀዳር 19 / 2016 (ኢዜአ):-በኢንዱስትሪ ፓርኮችና በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና ውስጥ የሚገኙ የኢንቨስትመንት አማራጮች ለፈረንሳይ አምራች ተቋማት መቅረባቸው ተገለጸ። በኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ ኢንቨስትመንቶች ላይ ለመሰማራት ፍላጎት ላላቸው የፈረንሳይ አምራች ኩባንያዎችና ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች እንዲሁም በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና ያሉ ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮች ቀርበዋል። የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ እና የኢንቨስትመንት ምክትል ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን አማራጮቹ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል። የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ኮርፖሬኑ በሚያስተዳድራቸው የኢንቨስትመንት ማዕከሎች በርካታ አዋጭና ምቹ አማራጮች መኖራቸውን ጠቁመው በዋናነትም በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና የንግድና የሎጂስቲክ ዘርፍ እንዲሁም በባህርዳርና ጅማ በአግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፍ ያልተነኩ እምቅ እድሎች እንዳሉ አሳውቀዋል። ዋና ስራ አስፈፃሚው አክለውም በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ በአግሮፕሮሰሲግ ዘርፍ የተሰማራው ግዙፉ የፈረንሳይ የብቅል አምራች ኩባንያ ሱፍሌ ኢትዮጵያ በውጪ ምንዛሪ ታስገባው የነበረውን ምርት ሙሉ በሙሉ በማስቀረት በኩል ሚናው ከፍተኛ እንደሆነ ተናግረዋል። ድርጅቱ ከ50 ሺ በላይ ለሚሆኑ አርሶ አደሮች የገበያ ትስስር መፍጠሩን በማስታወስ ኮርፖሬሽኑ በፓርኮቹ በተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች ለመሰማራት ፍላጎቱ ላላቸው አዳዲስ ኩባንያዎች አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል። በመድረኩ በኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚገኙ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ፤ የተገነቡና ለአምራቾች የቀረቡ አስቻይ መሰረተ ልማቶችን ፤ ምቹ የኢንቨስትመንት ፖሊሲዎችንና ማበረታቻዎችን እንዲሁም መሰል ዝርዝር ኢንቨስትመንት ተኮር ጉዳዮችን የተመለከተ ዝርዝር ሰነድ ቀርቦ ማብራሪያ ተሰጥቶበታል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
የ5-ጂ ሞባይል ኔትዎርክ መስፋፋት የዲጂታል ልማትን ከማፋጠን ባለፈ ሀገራዊ የምጣኔ ኃብት እድገትን ለማረጋገጥ ሚናው የላቀ ነው
Nov 29, 2023 32
አዲስ አበባ ፤ህዳር 19/2016 (ኢዜአ):- በኢትዮጵያ የአምስተኛው ትውልድ (5-ጂ) የሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎት መስፋፋት የዲጂታል ልማትን ከማፋጠን ባለፈ ሀገራዊ የምጣኔ ኃብት እድገትን ለማረጋገጥ ሚናው የላቀ መሆኑን የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ገለጹ። ኢትዮ-ቴሌኮም የአምስተኛውን ትውልድ (5-ጂ) የሞባይል ኔትዎርክ በጅግጅጋ ከተማ በይፋ አስጀምሯል። የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ፤ በማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት በዓለም ላይ እጅግ ፈጣን የሚባለውን የአምስተኛው ትውልድ (5-ጂ) የሞባይል ኔትዎርክ ኢትዮጵያ መጠቀም ጀምራለች ብለዋል። የአምስተኛው ትውልድ (5-ጂ) ኔትዎርክ ተጠቃሚ ከሆኑ የዓለም አገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗንም ጠቅሰዋል። የ5-ጂ ኔትዎርክ ቀደም ሲል በአዲስ አበባ እና አዳማ በይፋ መጀመሩን አስታውሰው፤ አሁን ላይ በሱማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ በመጀመሩ እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል። በኢትዮጵያ የማስፋፋት ሥራው በልዩ ትኩረት እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰው፤ በቀጣይም ተጠናከሮ ይቀጥላል ሲሉ ተናግረዋል። የአምስተኛው ትውልድ (5-ጂ) የሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎት የማስፋፋት ሥራ ለዲጂታል ኢትዮጵያ እውን መሆን የላቀ አስተዋጽዖ እንዳለውም ገልፀዋል። የ5-ጂ ኔትዎርክ አገልግሎት በጅግጅጋ ከተማ መጀመሩም የንግድና የመረጃ ሥርዓቱን ለማሳለጥና የመንግሥትን አገልግሎት አሰጣጥ የሚያቀላጥፍ መሆኑን ጠቅሰዋል። የሱማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ-መስተዳድር ኢብራሂም ኡስማን፤ የቴክኖሎጂው እውን መሆን በክልሉ ለተጀመሩ የልማት ሥራዎች መፋጠን እንዲሁም በተለያዩ ሴክተሮች ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሚያግዝ መሆኑን ገልፀዋል። በጅግጅጋ ኢዜአ ካነጋገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች መካከል ወይዘሮ ራሁ ጠይብካስ እና አብዱረዛቅ ሐሰን የአምስተኛው ትውልድ (5-ጂ) የሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎት መጀመር በንግዱም ይሁን በሌሎች አገልግሎቶች ተጠቃሚ የሚያደርግ በመሆኑ ተደስተናል ብለዋል። የ5-ጂ የኔትዎርክ አገልግሎት በተለይም ለስማርት ሲቲ፣ ስማርት ትራንስፖርት፣ የትምህርት ሥርዓት፣ ለጤና፣ ለውሃ፣ የግብርና ልማት፣ ለንግድና የፋይናንስ ሴክተር፣ ለኢንዱስትሪ፣ ለስማርት የመንግሥት አስተዳደር እና ሌሎችም ሴክተሮች የላቀ አበርክቶ እንዳለው ይነገራል።
አብርሆት ቤተመጻሕፍት የቴክኖሎጂ እና የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ሰልጣኞችን ተቀበለ
Nov 28, 2023 52
አዲስ አበባ፤ ህዳር 18/2016 (ኢዜአ)፦ የአብርሆት ቤተመጻሕፍት አምስተኛ ዙር የቴክኖሎጂ እና የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ሰልጣኞችን ዛሬ ተቀብሏል። ለሰልጣኞቹም የቤተመጻሕፍቱ ዳይሬክተር ኢንጂነር ውብአየሁ ማሞ አቀባበል ያደረጉ ሲሆን የእንኳን ደህና መጣቹ መልእክትም አስተላልፈዋል። አብርሆት ቤተመጻሕፍት ቀደም ሲልም በአራት ዙሮች 500 ሰልጣኞችን የተቀበለ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን በአሁኑ ዙር የከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ መስፈርቱን ያሟሉ 200 ተማሪዎችን በመቀበል ለ4 ወራት የሚሰጠውን ስልጠና እንዲቀላቀሉ ተደርጓል። እነዚህ ተማሪዎች በቆይታቸው Data Structure ፣ Algorithm እንዲሁም የ Arteficial Intelligence ስልጠና እንደሚወስዱ ተገልጿል። ሰልጣኞቹ የተማሩትን የቴክኖሎጂ እውቀት በመጠቀምም ችግር ፈቺ አንዲሁም አለምአቀፋ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚያስችላቸው መሆኑን አብርሆት ቤተመጻሕፍት ለኢዜአ የላከው መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮ-ቴሌኮም አምስተኛው ትውልድ (5ጂ) የኢንተርኔት ኔትወርክ አገልግሎት በጅግጅጋ ከተማ አስጀመረ
Nov 28, 2023 68
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 18/2016 (ኢዜአ) ፡- ኢትዮ-ቴሌኮም አምስተኛው ትውልድ (5ጂ) የኢንተርኔት ኔትወርክ አገልግሎት በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ አስጀምሯል። አገልግሎቱን የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ በይፋ አስጀምረውታል። በመርሃ ግብሩ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ኢብራሒም ኡስማንን ጨምሮ ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል። አገልግሎቱ በአገሪቱ በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት አሰጣጥን ይበልጥ በማዘመን ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በእጅጉ ያግዛል ተብሏል። የ (5ጂ) የኔትወርክ አገልግሎት ወደ ሌሎች የአገሪቱ አካባቢዎችም ተደራሽ የማድረግ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ አረጋግጠዋል። ኢትዮ-ቴሌኮም ከዚህ ቀደም የ (5ጂ) የኢንተርኔት ኔትወርክ በአዲስ አበባና በአዳማ ከተማ ማስጀመሩ ይታወሳል።
የታዳሽ ኃይል አማራጮችን በመጠቀም በሚቀጥሉት አራት ዓመታት 35 በመቶ የገጠሩን ህዝብ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዷል
Nov 27, 2023 72
ሆሳዕና ፤ ህዳር 17/2016 (ኢዜአ)፦ በሚቀጥሉት አራት ዓመታት የታዳሽ ኃይል አማራጮችን በመጠቀም 35 በመቶ የገጠር ህዝብን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ገለጸ። ሚኒስቴሩ በአማራጭ ሀይል የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ያዘጋጀው ስልጠና ዛሬ በሆሳዕና ከተማ ተጀምሯል። በመድረኩ መክፈቻ ላይ በሚኒስቴሩ የገጠር ኢነርጂ ቴክኖሎጂ ልማትና ሽግግር የስራ ሂደት ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃኑ ወልዱ እንዳሉት፤ የታዳሽ ኃይል አማራጭን በመጠቀም የገጠሩን የሀገሪቱ ክፍል የኤሌክትሪክ ሀይል ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው። በዚህም በሚቀጥሉት አራት ዓመታት 150 ማይክሮ ሀይድሮ ሶላሮች ተገንብተው ለአገልግሎት የሚበቁ ሲሆን ይህም 35 በመቶ የሚሆኑ የገጠር ነዋሪዎችን የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላል ብለዋል። በዚህም እንቅስቃሴ አነስተኛ የሰላር ግሪድ አማራጮችን ጭምር በየአካባቢው እንዲደርስ በማድረግ በተለያየ መንገድ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ ጥረት መጀመሩን ጠቁመዋል። ከዚህ ቀደምም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች 10 የሶላር ሚኒ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን በመተግበር በገጠር የሚኖረውን ማህበረሰብ በመስኖ ልማት፣ በአግሮ ፕሮሰሲንግና በሌሎች ዘርፎች ተጠቃሚ ማድረጉን አስታውሰዋል። ከኤሌክትሪክ አገልግሎት በተጨማሪም ማህበረሰቡ በሌሎች ልማታዊና ተዛማጅ ዘርፎች ላይ ተሰማርቶ ተጠቃሚነቱን እንዲያሳደግ ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ላይ መሆኑንም አስረድተዋል። ይህን ዕቅድ ከግብ ለማድረስ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አጋር አካላትን በማስተባበር ጠንካራ ስራ በመስራት ላይ እንደሚገኝ አስታውቀዋል። ከመድረኩ ተሳታፊዎች መካከል በኦሮሚያ ክልል ውሃና ኢነርጂ ቢሮ የኢነርጂ ባለሙያ አቶ ቢቂላ ታምሩ የታዳሽ ኃይል አማራጭን በማስፋት በክልሉ ገጠር አካባቢዎች ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል። ለአብነትም በክልሉ ሰበታና ፈንታሌ አካባቢዎች የውሃና የፀሀይ ታዳሽ ኃይል አማራጮችን በመጠቀም ኃይል ለማመንጨት በተሰራው ስራ ማህበረሰቡን ከመብራት አገልግሎት በተጨማሪ በሌሎችም ዘርፎች ተጠቃሚ ለማድረግ መቻሉን አክለዋል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በሀድያ ዞን ግቤ ወረዳ በሚገኘው የለመሬ ተፋሰስን በመጠቀም የማይክሮ ሀይድሮ ፓወር ፕሮጀክት ግንባታ የመስመር ዝርጋታ ስራ ብቻ እንደሚቀረው የተናገሩት ደግሞ በዞኑ ውሃና ኢነርጂ መምሪያ የኢነርጂ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ደለለኝ ጌሚሶ ናቸው። ፕሮጀክቱ ከ300 በላይ የአካባቢውን አባወራና እማዎራዎች የኤሌክትሪክና የአነስተኛ ኢንዱስትሪዎች አገልግሎቶች ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተናግረዋል። ለ10 ቀናት በሚሰጠው ስልጠና ላይ ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ የዘርፉ ባለሙያዎች እየተሳተፉ ነው።
ስፖርት
ፌዴሬሽኑ ለክልሎችና ክለቦች ማጠናከሪያ ከ2 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር በላይ ማበረታቻ ሽልማት ሰጠ
Nov 27, 2023 80
መቀሌ ፤ ህዳር 17/2016 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለክልሎችና ክለቦች አትሌቲክስ እንቅስቃሴ ማጠናከሪያ ከ2 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር በላይ ማበረታቻና ሽልማት ሰጠ። ፌዴሬሽኑ በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የሚውል የሁለት ሚሊዮን ብርም ድጋፍ አድርጓል። ፌዴሬሽኑ ሽልማቱንና ድጋፉን ያደረገው በመቀሌ ከተማ ባካሄደው 27ኛ ጠቅላለ ጉባዔ ማጠቃለያ ላይ ነው። ድጋፉ የተሰጠው ስምንት ክለቦች፣ ሁሉም ክልሎችና ሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች በዘርፉ ያደረጉትን እንቅስቃሴ በመገምገም መሆኑ ተመላክቷል። በዚህም ከፍተኛው 300 ሺህ ብር፣ ዝቅተኛው ደግሞ 40 ሺህ ብር ለክለቦቹ እና ለክልሎቹ ተሰጥቷቸዋል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ለክለቦቹና ለክልሎቹ የማበረታቻ ሽልማትና ድጋፍ የተደረገው አትሌቲክስን ለማስፋፋትና ለማጠናከር የሚያደርጉትን ጥረት ለማገዝ መሆኑን ተናግራለች። በእያንዳንዱ ክልልና ከተማ አስተዳደር የሚገኙ የስፖርት አመራሮችና አሰልጣኞች ለዘርፉ ልማት የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ እንዲያጠናክሩም አሳስባለች። የክለቦች፣ የክልሎችና የከተማ አስተዳደር የስፖርት አመራሮችና አሰልጣኞች ፌዴሬሽኑ የሰጣቸውን ድጋፍ የውስጥ አቅማቸው ለማጎልበትና ተተኪ አትሌቶች በፕሮጀክት አቅፈው ለማሰልጠን እንደሚረዳቸው ለኢዜአ ገልጸዋል። ይህ በእንዲህ እያለ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የሁለት ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ ድጋፉን ከረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ተቀብለዋል። አቶ ጌታቸው ፌዴሬሽኑ ላደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን በማቅረብ ኢትዮጵያውያን በድርቁ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
የአበበች ጎበና በጎ አድራጎት ድርጅት በማርሻል አርት ስፖርት ያሰለጠናቸውን ወጣቶችና ታዳጊዎች አስመረቀ
Nov 26, 2023 190
አዲስ አበባ፤ ህዳር 16/2016 (ኢዜአ)፦የአበበች ጎበና በጎ አድራጎት ድርጅት ለሁለት ዓመታት በማርሻል አርት ስፖርት ያሰለጠናቸውን 32 ወጣቶችና ታዳጊዎች አስመረቀ። የታዳጊዎችና ወጣቶቹ ስልጠና ድርጅቱ ባመቻቸው በጎ ፈቃደኛ የማርሻል አርት ባለሙያ የተከናወነ ሲሆን ስልጠናውን አጠናቀው በዛሬው እለት ለምርቃት በቅተዋል። ተመራቂዎቹ በስልጠናው የአካል ብቃትና የስነ ልቦና ዝግጁነት እንዲኖራቸው በማድረግ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ የሰጣቸው መሆኑን ገልጸዋል። ከተመራቂዎቹ መካከል ድንቁ ረጋሳ፣ ነብዩ ዳንኤል እና ቅድስት ረጋሳ የስልጠናው እድል ስለተመቻቸላቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል። በቀጣይ በዚህ ስፖርት ተሻለ ደረጃ ለመድረስ እንደሚሰሩና ሌሎች ወጣቶችንም ለማሰልጠን ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። በአበበች ጎበና በጎ አድራጎት ድርጅት የማርሻል አርት ስፖርትን በበጎ ፈቃደኝነት እያሰለጠነ የሚገኘው ኢንትርናሽናል ኢንስትራክተር አብዱልቃድር ረጌሶ፤ ስፖርቱ በተለይ ለወጣቶችና ታዳጊዎች በብዙ መልኩ ጠቃሚ መሆኑን አስረድቷል። የነገ ሀገር ተረካቢ ወጣቶችን በሥነልቦና፤ በአካል ብቃትና በራስ መተማመን እንዲያድጉ ለማድረግ የድርሻውን አስተዋጽኦ በማድረጉ ደስተኛ መሆኑንም ገልጿል። በድርጅቱ የልጆች መምሪያ ጉዳይ ኃላፊ ወይንሸት ዳምጠው፤ ድርጅቱ ታዳጊ ህፃናትና ወጣቶችን ከማሳደግና ከማስተማር ባለፈ ስፖርታዊ ሥልጠናዎችን ሲሰጥ እንደነበር ገልፀዋል። በቀጣይም እንዲህ ዓይነቱ ስፖርት ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ገልጸው የዛሬ ተመራቂዎችም የማርሻል አርት ስፖርትን በማሳደግ የደርሻቸውን እንዲያደርጉ አስገንዝበዋል። የአበበች ጎበና በጎ አድራጎት ድርጅት በ1972 ዓ.ም በክብር ዶክተር አበበች ጎበና አማካኝነት የተመሰረተ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከ220 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት አጸደቀ
Nov 26, 2023 89
መቀሌ፤ ህዳር 16/2016(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 27ኛ መደበኛ ጉባኤ ለ2016 ዓመት ከ220 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት በማፅደቅ ተጠናቀቀ። ፌዴሬሽኑ ላለፉት ሁለት ቀናት ባካሄደው ጉባኤው ያጸደቀው በጀት ለስልጠና እንዲሁም ለስፖርታዊ ውድድሮች ማካሄጃ ጭምር የሚውል መሆኑ ተመላክቷል። በዚህም ለወጣቶች የፕሮጀክት ስልጠና ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ የጉባኤው ተሳታፊዎች ተስማምተዋል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ “ሃገራችንን በዓለም አደባባይ ኢትዮጵያን ይበልጥ ከፍ ለማድረግና የዘርፉን የገቢ ምንጭነት ለማሳደግ ከክልሎች ፌዴሬሽኖች ጋር በተቀናጀ አግባብ እንሰራለን “ ብላለች። በጉባኤው መዝጊያ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት በበኩላቸው የኢትዮጵያ ህዝብ የሚጠብቀውን ውጤት የሚያመጡ አትሌቶችን በብዛት ለማፍራት ክልሎች ከፌዴራል ጋር ተቀናጅተው ሊሰሩ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። ስፖርት ለአገር ሰላምና ፍቅር እንዲሁም አንድነትና ልማት መረጋገጥ ዓይነተኛ መሳሪያ በመሆኑ አሰልጣኞችና አመራሮች ለተግባራዊነቱ ግንባር ቀደም ሊሆኑ እንደሚገባም አሳስበዋል። በተጨማሪም ለበጀት አጠቃቀምና ለስፖርት ስነ ምግባር ትኩረት መሰጠቱን አምባሳደር መስፍን አስታውቀዋል ። በጉባኤው የተሳተፉት የክልሎች አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች አመራሮች በበኩላቸው በሃገሪቱ ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ የሚያግዝ የወዳጅነት ውድድር ለማካሔድና ተተኪ ወጣቶችን ለማፍራት በትኩረት እንደሚሰሩ ገልጸዋል። በጉባኤው የሁሉም ክልሎች የስፖርት አመራሮችና አስልጣኞች ተሳትፈዋል ።
የኢትዮጵያን ክብርና መልካም ገፅታ የሚያጎሉ አትሌቶች እንዲበራከቱ የሚደረገው ጥረት መጠናከር አለበት-አቶ ጌታቸው ረዳ
Nov 25, 2023 599
መቀሌ ፤ ህዳር 15/2016(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያን ክብርና መልካም ገፅታ ከፍ የሚያደርጉ እውቅ አትሌቶችን የማበራከቱ ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል ሲሉ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ ገለጹ። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፈዴሬሽን 27ኛ መደበኛ ጉባዔ በመቀሌ ከተማ መካሄድ ጀምሯል። አቶ ጌታቸው በጉባዔው መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት የኢትዮጵያን መልካም ገፅታና ክብር ከፍ የሚያደርጉ እውቅ አትሌቶች እንዲበራከቱ የሚደረገው እንቅስቃሴ መጎልበት አለበት። ክልሎች "ለዘርፉ ልዩ ትኩረት ሰጥተን እንቅስቃሴ ማድረግ ይገባናል" ብለዋል። ለዚህም በክልሎች አትሌቶች በብዛት የሚያፈሩ የአትሌቲክስ መንደሮችን መገንባትና አስልጣኞችን ማፍራት ወሳኝነት እንዳለው አመልክተዋል። በክልሉ ስለ ስፖርትና ልማት ማውራት መጀመሩ ትልቅ እመርታ መሆኑንም ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል። የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት በበኩላቸው፤ ስፖርት የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነትና ልማት ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል። ለስፖርት ልዩ ትኩረት በመስጠት የኢትዮጵያ አምባሳደሮች የሚሆኑ ወጣት አትሌቶችን ማፍራት እንደሚጠበቅም ተናግረዋል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ፤ ክልሎች ከፌዴሬሽኑ ጋር ተቀናጅተው ወጣቶች ኢትዮጵያዊ አስተሳሰብ ይዘው እንዲቀረፁና ለስፖርቱ እድገት ቁልፍ ሚና እንዲጫወቱ ጠይቃለች። እስከ ነገ የሚቆየው ጉባዔ በ2015 በጀት ዓመት ሥራ አፈፃፀምና በ2016 በጀት ዓመት እቅድና በጀት ላይ በመወያየት ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
አካባቢ ጥበቃ
አፍሪካ በተ.መ.ድ የአየር ንብረት ጉባዔ /ኮፕ 28/ የጋራ አጀንዳዋን በአንድ ድምፅ ታሰማለች
Nov 28, 2023 57
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 18/2016 (ኢዜአ) ፡- አፍሪካ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ጉባዔ /ኮፕ 28/ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል "አንድ ድምፅ" ታሰማለች ሲል አፍሪካ ኅብረት ገለፀ። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ጉባዔ (ኮፕ 28) በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፤ በዱባይ ከነገ በስቲያ ይጀመራል። በጉባዔው የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የተደረሱ ስምምነቶችና ድንጋጌዎች ተግባራዊነታቸው ምን ላይ እንደደረሰ ይገመግማል። ጎን ለጎን አገራት የአየር ንብረት ለማቋቋም በተለይም የታዳሽ ኃይል አማራጮችን በማስፋት እየተሰሩ ያሉ ሥራዎች ምክክር ይደረግባቸዋል። ታዳጊ አገራት በአየር ንብረት ለውጥ የሚደርስባቸውን አደጋ ለመቋቋምና የኃይል ሽግግር እንዲያደርጉ የሚያስችሉ የፋይናንስ አቅርቦት ላይም ጉባዔው ትኩረት ያደርጋል ተብሏል። በተጨማሪም የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል አገራት አዲስ የትብብር ማዕቀፍ ሊፈጥሩ እንደሚችሉም ጉባዔው ከወዲሁ ትልቅ ግምት ተሰጥቶታል። ጉባዔውን በማስመልከት ኢዜአ ያነጋገራቸው የአፍሪካ ሕብረት የግሪን ዎል ኢንሼቲቭ ዳይሬክተር ኢልቪስ ፖል፤ አፍሪካ አጀንዳዋን በጉባዔው በአንድ ድምፅ ታሰማለች ብለዋል። ጉባዔው ከዚህ ቀደም በአህጉሪቱ የአየር ንብረት ለውጥ ለመቋቋም የተደረሱ ስምምነቶች ወደ ተግባር ለመቀየርና በዘርፉ የፋይናንስ አቀርቦትን ለማስፋት ዕድል እንደሚፈጥር ገልፀዋል። የአፍሪካ ሕብረት የግብርና፣ የገጠር ልማት፣ የብሉ ኢኮኖሚና የዘላቂ አካባቢ ኮሚሽነር አምባሳደር ጆሴፋ ሳኮ፤ አፍሪካ በጉባዔው በንቃት ትሳተፋለች ብለዋል። በተለይም በቅርቡ በኬንያ ናይሮቢ በተካሄደው የአፍሪካ ሕብረት የአየር ንብረት ጉባዔ በጋራ የተያዙ አቋሞች አፍሪካ በጉባዔው ውጤታማ ተሳትፎ እንዲኖራት መሠረት ይጥላል ብለዋል። ይህንንም ተከትሎ አፍሪካ በጉባዔው የአየር ንብረት ለውጥ መቋቋም ቀዳሚ አጀንዳዋ ታደርጋለች ነው ያሉት። አፍሪካ ምንም እንኳን የበካይ ጋዝ ልቀቷ አነስተኛ ቢሆንም በአየር ንብረት ለውጥ አህጉሪቱ ድርቅ፣ ጎርፍና መሰል የተፈጥሮ አደጋዎች እያስተናገደች ትገኛለች። አፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ የደረሰባትን ጉዳት ለመቋቋምና ወደ ታዳሽ ኃይል ሽግግር እንድታደርግ የፋይናንስ ድጋፍ ማፈላለግ ሌላኛው አጀንዳዋ እንደሚሆን አንስተዋል። የዓለም ሙቀት የመጨመር ምጣኔ በአማካይ ከ1 ነጥብ 5 እስከ 2 ዲግሪ ሴሊሽየስ ለማድረግ የተደረሰው የፓሪስ ሥምምነት እውን ለማድረግ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2030 የዓለም የበካይ ጋዝ የልቀት ምጣኔ ከ28 እስከ 40 በመቶ መቀነስ እንዳለበት የተባበሩት መንግሥታት ደርጅት መረጃ ያሳያል። በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ዱባይ ኅዳር 20 የሚጀምረው የመንግሥታቱ ድርጅት የአየር ንብረት ጉባዔ (ኮፕ 28) እስከ ታህሳስ 2 ቀን 2016 ዓ.ም ይቆያል።
በክረምቱ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከተተከሉ ችግኞች ውስጥ 60 በመቶ በጥምር ግብርና የለሙ ናቸው--ዶክተር ግርማ አመንቴ
Nov 26, 2023 131
ሀዋሳ ፤ህዳር 16/2016 (ኢዜአ)፦ በሁለተኛው ምዕራፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከተተከሉ ችግኞች መካከል 60 በመቶ የሚሆኑት በጥምር ግብርና የለሙ መሆናቸውን የግብርና ሚንስትሩ ዶክተር ግርማ አመንቴ ገለጹ። ህብረተሰቡ ለተተከሉ ችግኞች ተገቢውን እንክብካቤ እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል። ሚኒስትሩ ባለፈው የክረምት ወቅት በሲዳማ ክልል በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለተተከሉ ችግኞች እየተደረገ ያለውን የእንክብካቤ ሥራ ዛሬ በመስክ ጎብኝተዋል። በጉብኝቱ ወቅት ዶክተር ግርማ ለኢዜአ እንዳሉት፤ በመንግስት አቅጣጫ መሠረት በሁለተኛው ምዕራፍ ከሚተከሉ ችግኞች መካከል 60 በመቶ የሚሆኑት በጥምር ግብርና እንዲለሙ ተደርጓል። በእዚህም ፍራፍሬና የእንስሳት መኖን በጥምር ለማልማት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል። ከሚተከሉ ችግኞች 60 በመቶውን በጥምር ግብርና እንዲለማ የተደረገበት ምክንያት የግብርና ምርትና ምርታማነትን በዘላቂነት ለማሳደግ ታስቦ መሆኑንም አስረድተዋል። ቀሪዎቹ የተተከሉ ችግኞች ለደን ልማትና ለከተማ ውበት የሚያገለግሉ መሆናቸውንም ዶክተር ግርማ ገልጸዋል። “በክረምቱ ለተተከሉ ችግኞች በህዝብ ተሳትፎ እየተደረገ ባለ የእንክብካቤ ሥራ የተሻለ የጽድቀት መጠን ላይ ይገኛሉ” ብለዋል። "የጥምር ግብርና በአርሶ አደሩ ማሳ ላይ የሚሰራና አርሶ አደሩም ጥቅሙን እስካየ ድረስ በየቀኑ የማረም፣ ውሃ የማጠጣትና የመንከባከብ ሥራ ስለሚሰራ የጽድቀት መጠኑ ከፍ ይላል" ብለዋል። በዚህ ረገድ በሲዳማ ክልልም ሆነ እንደአገር የተሰራው ሥራ መልካም መሆኑን ጠቅሰው፤ በበጋ ወራትም የችግኝ እንክብካቤ ሥራው ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል። የሲዳማ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ መምሩ ሞኬ በበኩላቸው እንዳሉት፣ በክልሉ በአረንጓዴ አሻራ የተያዘውን መርሃ ግብር ለማሳካት እየሰራ ነው። በክልሉ ባለፈው ዓመት ብቻ ስነ ምህዳርን መሠረት ባደረገ መልኩ 306 ሚሊዮን የተለያየ ጥቅም የሚሰጡ ችግኞች መተከላቸውን ጠቁመዋል። የጥምር ግብርና ልማትን ለማሳካት ለቡና፣ ፍራፍሬ እና እንስሳት መኖ ልማት ትኩረት መሰጠቱንም አስታውሰዋል። በክልሉ የተተከሉ ችግኞች የጽድቀት መጠን በአማካይ ከ85 በመቶ በላይ መሆኑን ገልጸው፣ ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን ለችግኞች የሚደረገው የእንክብካቤ ሥራ ቀጣይ እንደሚሆን አመልክተዋል። በሲዳማ ክልል ሸበዲኖ ወረዳ የሞርቾ ነጋሽ ቀበሌ አርሶ አደር ጦና ጦምራ በሰጡት አስተያየት ስልጠና ወስደው የጥምር ግብርና ሥራ መጀመራቸውን ገልጸዋል። ባላቸው አነስተኛ መሬት ላይ የተሻሻሉ የአቮካዶ ችግኞችን ከቡናና እንሰት ጋር አቀናጅተው ማልማታቸውን ገልጸዋል። ለመጀመሪያ ጊዜ ካለሙት አቦካዶ 25 ኩንታል ለይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ በማቅረብ 87 ሺህ ብር ገቢ ማግኘታቸውን ተናግረዋል። በቀጣይ ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ 580 የአቮካዶ ችግኞችን በመትከል እየተንከባከቡ መሆናቸውንም ጠቁመዋል።
የግብርና ሚኒስትሩና የሲዳማ ክልል አመራሮች ችግኞችን ተንከባከቡ
Nov 26, 2023 83
አዲስ አበባ ፤ኅዳር 16/ 2016/ (ኢዜአ)፦ የግብርና ሚኒስትሩና የሲዳማ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በአዋሳ የታቦር ተራራ ላይ የተተከሉ ችግኞችን ተንከባከቡ ፡፡ የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በወቅቱ እንዳሉት ለአረንጓዴ አሻራ የተጣለውን ግብ ለማሳካት በክረምት ወቅት የተተከሉ ችግኞችን ጽድቀት በቅርበት መከታተልና መንከባከብ ይገባል ። ማህበረሰቡም ሆነ ተቋማት በክረምት ወቅት የተከሏቸውን ችግኞች የመንከባከብና ውሃ የማጠጣት ስራ አጠናክረው መቀጠል ይኖርበቸዋል ነው ያሉት ። ሚኒስትሩ በሲዳማ ክልል በሚኖራቸው ቆይታ በእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ፕሮጀክት (LFSDP) ድጋፍ የተከናወኑና ሌሎች ልማት ስራዎችን እንደሚጎበኙ ከግብርና ሚኒስቴር ማህበራዊ ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
በአኝዋሃ ብሔረሰብ ዞን ያለውን የተፈጥሮ ደን በባዮስፌር ሪዘርቭነት ለማስመዝገብ የሚያስችል ጥናት ተጠናቀቀ
Nov 25, 2023 98
ጋምቤላ፤ ህዳር 15/2016(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በአኝዋሃ ብሔረሰብ ዞን ያለውን የተፈጥሮ ደን በባዮስፌር ሪዘርቭነት ለማስመዝገብ የሚያስችል ጥናት መጠናቀቁን የክልሉ አካባቢ ጥበቃና አየር ንብረት ለውጥ ቢሮ አስታወቀ። ደኑን በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት( ዩኔስኮ) በባዮስፌር ሪዘርቭነት ለማስመዝገብ በተካሄደው ጥናት ዙሪያ የባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት የምክክር መድረክ ዛሬ በጋምቤላ ከተማ ተካሄዷል። የቢሮ ኃላፊዋ ወይዘሮ መሠረት ማቲዎስ በምክክር መድረኩ ላይ እንዳሉት፤ የአኝዋሃ ብሔረሰብ ዞን በተፈጥሮ ሃብት የበለፀገ አካባቢ ነው ብለዋል። ይህንን እምቅ የተፈጥሮ ሃብት በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት( ዩኔስኮ) በባዮስፌር ሪዘርቭነት ለማስመዝገብ ጥናት መጠናቀቁን ተናግረዋል። ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚን ለመገንባት ለተጀመረው ጥረት መሳካት በዞኑ ያለውን የተፈጥሮ ደን ማስመዝገብ ጠቀሜታው ጉልህ መሆኑን አብራርተዋል ። ቢሮው የተፈጥሮ ደኑ በድርጅቱ እንዲመዘገብ ለሚደረገው ጥረት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ኃላፊዋ አረጋግጠዋል። የአኝዋሃ ባዮስፌር ሪዘርቭ አጥኚ ድርጅት አማካሪ ፕሮፌሰር ቂጤሳ ሁንዴራ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት የአኝዋሃ ዞን የተፈጥሮ ደን በብዝሃ ሃብቱ እጅግ የበለፀገ ነው ብለዋል። ሃብቱ በድርጅቱ ቢመዘገብ ኢትዮጵያ ያላት የተፈጥሮ ሀብት ተጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ ከማድረግ ባለፈ፤ የጥናትና የምርምር ማዕከል ሆኖ እንዲያገለግል ያስችላል ብለዋል። የአኝዋሃ ባዮስፌር ሪዘርቭ አማካሪ ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ቶሌራ አብርሃም በበኩላቸው ደኑን በድርጅቱ እንዲመዘገብ የሚያደርግ ብዝሃ ህይወት ያለበት አካባቢ መሆኑን ተናግረዋል። በተለይም አካባቢው ከአንድ ሺህ የሚበልጡ የእፅዋትና የተለያዩ እንስሳት ዝርያዎችን በውስጡ አምቆ የያዘ የተፈጥሮ ሃብት መሆኑን ተናግረዋል። የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የሰው ልጅ አኗኗር ከተፈጥሮ ጋር የተቆራኘ በመሆኑ የተፈጥሮ ሃብቱን በመጠበቅና በመንከባከቡ ረገድ የኅብረተሰቡ ተሳትፎ ወሳኝ ነው ብለዋል። ጥናቱ የተካሄደው ''መልካ ኢትዮጵያ'' የተባለ ሃገር በቀል ድርጅት ከአኝዋሃ ዞን አስተዳደር ጋር በመተባበር መሆኑም ተመላክቷል። ድርጅቱ የማጃንግ የተፈጥሮ ደንን በማጥናት በባዮስፌር ሪዘርቭነት እንዲመዘገብ ማድረጉ ይታወሳል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
ኢጋድ ና ሱዳን በሀገሪቱ የተፈጠረውን ቀውስ በሚረግብበት ሁኔታ ላይ ለመምክር ተስማሙ
Nov 27, 2023 96
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 17/2016(ኢዜአ)፡- ኢጋድ ና ሱዳን በሀገሪቱ የተፈጠረውን ቀውስ በሚረግብበት ሁኔታ ላይ ለመምክር ተስማሙ። የሱዳን ሉአላዊ የሽግግር መንግስት ሊቀመንበር አብዱልፈታህ አልቡርሃን እና የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ሊቀመንበር ወርቅነህ ገበየሁ በሱዳን ቀውስ ላይ አስቸኳይ ምክክር ለማድረግ መስማማታቸውን የሱዳን መንግስት አስታወቀ፡፡ አል ቡርሃን በሀገሪቱ የተፈጠረውን ቀውስ ለመፍታት በሚቻልበት ጉዳይ ላይ ከኢጋድ ሊቀመንበር ወርቅነህ ገበየሁ ጋር ለመምከር ፍላጎታቸውን ያሳዩት ከጅቡቲው ፕሬዝዳንት እስማኤል ኦማር ጌሌ በተወያዩበት ወቅት ነው፡፡ አልቡርሃን እና የኢጋድ ሊቀመንበር ምክክራቸውን በሳውዲ አረቢያ እንደሚያደርጉ የተገለፀ ሲሆን የሱዳን ታጣቂ ሃይሎችና ፈጠኖ ደራሽ ሃይሉ በምክክሩ እንደሚገኙም የሱዳን መንግስት መግለጫ አመልክቷል፡፡ በመግለጫው የኢጋድ አስቸኳይ ጉባኤ የሱዳንን አሁናዊ የግጭት ሁኔታ እንዲፈታ ከሁሉም አካላት ስምምነት ላይ ተደርሷል ብሏል፡፡ የአፍሪካ ህብረት የሰላምና የፀጥታ ምክር ቤት ቅዳሜ እለት ባወጣው መግለጫ በሱዳን ያለውን ግጭት አውግዞ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በሀገሪቱ የተኩስ አቁም እንዲደረግ መጠየቁን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
ፓኪስታን የብሪክስ/BRICS/ አባል ለመሆን ጥያቄ አቀረበች
Nov 25, 2023 99
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 14/2016 (ኢዜአ) ፦ ፓኪስታን የብሪክስ አባል ሀገራትን ለመቀላቀል ጥያቄ ማቅረቧን የፓኪስታን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ። ብሪክስ ለታዳጊ አገራት ጠቃሚ ቡድን መሆኑንም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አመልክቷል። የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ሙምታዝ ዛህራ ባሎክ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ ፓኪስታን የብሪክስ አባል ለመሆን ጥያቄ ማቅረቧን አረጋግጠዋል። ሀገሪቱ የቡድኑ አባል ለመሆን ጥያቄ ያቀረበችው ቡድኑ ግልጽነት የተሞላበት፣ ብዙሃኑን ያቀፈና አካታች በመሆኑ መሆኑንም ቃል አቀባይዋ ተናግረዋል። በዚህም ፓኪስታን የቡድኑ አባል ብትሆን በቀጣይ ለሚፈጠረው አለም አቀፍ ትብብር ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖራት አብራርተዋል። ፓኪስታን ከብዙዎቹ የብሪክስ አባል ሀገራት እንዲሁም ከአዳዲሶቹ ጥያቄ ያቀረቡ አገራት ጋር ወዳጅነት እንዳላት መግለጻቸውን ዥንዋ አስነብቧል። ቃል አቀባይዋ አክለውም “ቡድኑ ፓኪስታን ያቀረበችው የአባልነት ጥያቄ የትብብርና አብሮ የመለወጥ ፍላጎት የያዘ ጥያቄ መሆኑን መሰረት አድርጎ ቀና ምላሽ እንደሚሰጠን ተስፋ እናደርጋለን" ብለዋል። ብሪክስ በአሁኑ ወቅት በብራዚል፣ ሩሲያ፣ ህንድ፣ ቻይና እና ደቡብ አፍሪካ የተካተቱበት የኢኮኖሚ ቡድን ሲሆን በነሀሴ ወር በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው 15ኛው የቡድኑ የመሪዎች ጉባኤ የኢትዮጵያን፣ የኢራንን፣ የአርጀንቲናን፣ የግብፅን፣ የሳዑዲ አረቢያንና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶችን የአባልነት ጥያቄ መቀበሉ ይታወሳል።
አፍሪካ ከአጋር አከላት ጋር በትብብርና በጋራ ተጠቃሚነት ለመስራት ዝግጁ ናት - ሙሳፋቂ መሃመት
Nov 21, 2023 133
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 11/2016 (ኢዜአ)፦ አፍሪካ በሁሉም ዘርፍ ካሉ አጋር አከላት ጋር በትብብርና በጋራ ተጠቃሚነት ለመስራት ዝግጁ ናት ሲሉ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙሳፋቂ መሃመት ተናገሩ። በጀርመን በርሊን በተካሄደው የ'ኮምፓክት ዊዝ አፍሪካ' ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙሳፋቂ መሃመት አፍሪካ የጋራ ተጠቃሚነት ለሚያረጋግጡ ተግባራት በሯ ክፍት ነው ብለዋል። በአህጉሪቷ ያለውን የኢንቨስትመንት ሀብት በሁለትዮሽ ትብብር በማሳደግ የጋራ ተጠቃሚነትንና ብልጽግናን ለማረጋገጥ ዝግጁ ነን ሲሉም ነው ያረጋገጡት። የአፍሪካ ሀገራት እንደ ጀርመንና ቻይና ካሉ ሀገራት ጋር ሚዛኑን በጠበቀ የሁለትዮሽ ተጠቃሚነት እየሰሩ መሆኑንም አውስተው ''ኮምፓክት ዊዝ አፍሪካ' ጉባኤም በዚህ ረገድ ጉልህ ሚና እንደሚጫወት ተናግረዋል። እንደ አህጉር በኢንቨስትመንት መዳረሻዎችና በሌሎች መስኮች የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታትም አጋር አካላት በትብብር መስራት እንደሚገባቸው ማመልከታቸውን አፍሪካን ኒውስ ዘግቧል። በ2017 የጀርመን የጂ20 ፕሬዝዳንትነት ዘመን የተጀመረው የጂ20 'ኮምፓክት ዊዝ አፍሪካ' ጉባኤ ለውጥ ተኮር በሆኑ የአፍሪካ ሀገራት፣ በጂ 20 አጋሮች ብሎም ከእነዚህ ባሻገር ባሉ አካላት መካከል የንግግር እና የትብብር መድረክ ሆኗል።
የአፍሪካ የመሬት ፖሊሲ ጉባኤ በአዲስ አበባ ይካሄዳል
Nov 20, 2023 164
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 10/2016 (ኢዜአ) ፦ አምስተኛው የአፍሪካ የመሬት ፖሊሲ ጉባኤ በኢትዮጵያ ተባባሪ አዘጋጅነት ከነገ ጀምሮ ለተከታታይ አራት ቀናት በአዲስ አበባ ይካሄዳል። ጉባኤው “ቀጣይነት ያለው የመሬት አስተዳደር ለአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ፈጣን ትግበራ” በሚል መሪ ሀሳብ በአፍሪካ ሕብረት አዳራሽ እንደሚካሄድም ተጠቁሟል። ጉባኤውን የአፍሪካ የመሬት ፖሊሲ ማዕከል፣ የተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን፣ የአፍሪካ ልማት ባንክ ግሩፕ እንዲሁም የኢትዮጵያ መንግሥት በተባባሪነት እንዳዘጋጁት ተመልክቷል። የአፍሪካ ሀገራትን የመሬት ፖሊሲ ትግበራን በመረጃ፣ ክህሎትና እውቀት ማሳደግ በሚችሉ አጀንዳዎች ላይ መምከር የጉባኤው አላማ እንደሆነም የተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን መረጃ ያመላክታል። ተግባራዊ የተደረጉ የመሬት ፖሊሲ ልምዶችን በመጠቀም ትስስርን መፍጠርና ልምድ መለዋወጥ እንዲሁም የአህጉሪቱን የመሬት ፖሊሲ አቅም ማሳደግም የጉባኤው ሌላኛው አላማ መሆኑ ተመልክቷል።
ሐተታዎች
ኢሬቻ የአብሮነት ማሰሪያ ሐረግ
Oct 6, 2023 655
ኢሬቻ የአብሮነት ማሰሪያ ሐረግ (አሸናፊ በድዬ) ኢሬቻ የምስጋና በዓል ነው፤ ከክረምት ወቅት መለያየትና መራራቅ በኋላ ሰዎች በአብሮነት ብርሃን ለማየት ያበቃቸውን ፈጣሪ የሚያመሰግኑበት። ስለ ሰላምና አንድነት የሚዘመርበት፣ ስለመጪው ጊዜ መልካም ምኞት የሚገለጥበት፣ ሁሉን ላደረገ ፈጣሪ ምስጋና የሚቸርበት የአብሮነት በዓል ነው። በልመናው፣ በምርቃቱ፣ በምስጋናው ሁሉ ሀዬ! ሀዬ! ሀዬ! (አሜን! አሜን! አሜን!) የሚሉ ድምፆች ይስተጋባሉ። "ሀዬ! ሀዬ! ሀዬ! ሀዬ! የእውነትና የሰላም አምላክ! ከስህተትና ከክፉ ነገሮች ሁሉ ጠብቀን! ለምድራችን ሰላም ስጥ! ለወንዞቻችን ሰላም ስጥ! ከጎረቤቶቻችን ጋር ሰላም ስጠን! ለሰውም ለእንስሳቱም ሰላም ስጥ!" በማለት ይመረቃል። ሕዝቡም ይሁንልን ይደረግልን ሲል "ሀዬ! ሀዬ! ሀዬ!" ይላል። የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል መስከረም 26 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሆራ ፊንፊኔ እንዲሁም በማግስቱ እሑድ መስከረም 27 ቀን በቢሾፍቱ ሆራ ሀርሰዲ ይከበራል። የክራምት ወራት እንዳበቃ የሚከበረው "ኢሬቻ መልካ" (በውሃ ዳርቻ የሚከበር) ሲሆን በዓመቱ አጋማሽ ላይ የሚከበረው "ኢሬቻ ቱሉ" ደግሞ በተራራማ ቦታ የሚከበር ነው። ኢሬቻ መልካ የሚከበረው በመስከረም ወር ከመስቀል በዓል በኋላ ሲሆን፤ የክረምት ወራት የዝናብ፣ የደመና፣ የጭቃና የረግረግ ወቅት አልፎ ለፈካው ወራት በመብቃቱ ምስጋና የሚቀርብበት ነው። ኢሬቻ ቱሉ የሚከበረው የበጋው ወራት አልፎ የበልግ ዝናብ በሚጠበቅበት ወቅት ነው። በዚህም ፈጣሪ ''እርጥበት አትንፈገን፣ ወቅቶች ጊዜያቸውን ጠብቀው ይምጡ፤ የዝናብ ንፋስ ስጠን'' በማለት ለፈጣሪ ተማጽኖ የሚቀርብበት ነው። "ይህን ተራራ የፈጠርክ ፈጣሪ ወቅቱን የሰላም አድርግልን፣ የሰላም ዝናብ አዝንብልን፣ ጎርፍን ያዝልን፣ የተዘራው ፍሬ እንዲያፈራ እንለምንሃለን" እያለ በኢሬቻ ቱሉ ላይ ፈጣሪውን ይለምናል፡፡ በኢሬቻ በዓል የፈጣሪ ምህረት፣ ዕርቅ፣ እዝነት እና በዓሉ የሰላም በዓል እንዲሆን ከላይ በተጠቀሰው መልኩ ኦሮሞ ፈጣሪውን ይጠይቃል፤ ይማፀናል፤ ለተደረገለትም ነገር ሁሉ ያመሰግናል። የኢሬቻ በዓል ከገዳ ሥርዓት ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያለው ሲሆን፤ በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ለዘመናት ሲከበር የቆየ በዓል ነው። በዓሉ በዋናነት በአዲስ አበባ ሆራ ፊንፊኔ፤ በቢሾፍቱ ከተማ በሆራ ሀርሰዲ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ ታድሞ የሚከበር ቢሆንም በተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖችና ወረዳዎች በድምቀት ይከበራል። የኦሮሞ ሕዝብ ምድርን እና ሰማይን ለፈጠረው ፈጣሪ "ዋቃ" ምስጋናውን ለማድረስ የኢሬቻ በዓልን ያከብራል ይላሉ አባገዳዎች። የኦሮሞ ሕዝብ በዕድሜ ልዩነት ሳይገደብ የኢሬቻ በዓልን ለዘመናት በጋራ፣ በአንድነትና በፍቅር ሲያከብር ቆይቷል። በዝናባማው የክረምት ወቅት በጅረቶችና ወንዞች መሙላት ምክንያት ተራርቆ የቆየው ዘመድ አዝማድ በኢሬቻ በዓል ማክበሪያ ሥፍራ ይገናኛል፤ ይጠያየቃል፤ ናፍቆቱንም ይወጣል። አባቶች ክረምት በለሊት ይመሰላል ይላሉ። ለሊት ደግሞ ጨለማ ነው። ጨለማው ሲነጋ ደግሞ ብርሃን ነው፤ ብርሃን ደግሞ ውበት ነው፤ መታያና መድመቂያም ነው። ለዚህ ነው በኢሬቻ በዓል አከባበር ላይ ሁሉም ውብ የባህል ልብሱን በመልበስ በደስታ በዓሉን ለማክበር የሚመጣው። ሕዝቡ በዓሉ ወደሚከበርበት ሥፍራ የሚሄደው በተናጠል ሳይሆን በሕብረትና በአንድነት ነው፡፡ ለዚህ ነው ኢሬቻ የአንድነትና የአብሮነት በዓል ነው የሚባለው። በኢሬቻ ልዩነት የለም፤ ፀብ የለም፤ ክፋት የለም፤ ይልቁንም ምስጋና ይጎርፋል፤ ፍቅር ይሰፍናል፤ አብሮነት ያብባል። ኢሬቻ በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው የሰላምና የአብሮነት ምልክት ሲሆን፤ የኢሬቻ በዓልን ለማክበር የሚወጣው ታዳሚም እንደ እርጥብ ሣር ወይም አበባ ያለ እርጥብ ነገር በእጁ ይዞ የበዓሉን ስነ-ስርዓት ያከናውናል። ይህን የሚያደርገውም "ፈጣሪያችን ሆይ አንተ ያፀደቅከው ነው አብቦ ፍሬ ያፈራው፤ ለዚህም እናመሰግንሃለን" በማለት የፈጣሪን መልካምነት ለማሳየት ነው። በሌላ በኩል እርጥብ ሣር የልምላሜ ምልክት በመሆኑ የመልካም ምኞት መግለጫም ጭምር በመሆኑ ነው በኢሬቻ በዓል እርጥብ ሣር የሚያዘው። የኦሮሞ ሕዝብ ለሰላም ትልቅ ሥፍራ ይሰጣል። ሰላም ካለ ሁሉም ነገር አለ ብሎም ያምናል። በምርቃቱም "ቡና ፊ ነጋአ ሂንደቢና" ብሎ ይመራረቃል። ቡናና ሰላም አያሳጣችሁ ማለት ነው። ለዚህም ነው በኢሬቻ በዓል ለመላው የሰው ልጅ ሰላምና ደኅንነት ፈጣሪ የሚለመነው። ሳል ይዞ ስርቆት፤ ቂም ይዞ ፀሎት እንዲሉ አበው በኢሬቻ የተጣላ ታርቆ፣ ቂሙን ረስቶ በንጹህ ልቦና ፈጣሪ ንጹህ ወዳደረገው የውሃ አካል ይሄዳል፤ በዚያም ፈጣሪውን ያመሰግናል። የኢሬቻ በዓል ሲከበር ከሚከወኑ ሥርዓቶች መካከል ሴቶች ሲቄ፣ እርጥብ ሣር እንዲሁም ጮጮ ይዘው ከፊት ሲመሩ አባ ገዳዎች ደግሞ ቦኩ፣ አለንጌ እና ሌሎችንም በበዓሉ ሥርዓት የሚፈቀዱትን ሁሉ በመያዝ ወደ ሥርዓቱ አከባበር ያመራሉ። ኦ ያ መሬሆ…………………መሬሆ መሬሆ………………… መሬሆ ያ ዋቃ ኡማ ሁንዳ መሬሆ…………………ያ መሬሆ መሬሆ………………… መሬሆ ያ ዋቃ ለፋ ኡምቴ መሬሆ………………… ያ መሬሆ መሬሆ………………… መሬሆ ያ ዋቃ መልካ ኡምቴ መሬሆ………………… ያ መሬሆ መሬሆ………………… መሬሆ እያሉ ያመራሉ። የሁሉ ፈጣሪ፣ ምድርን የፈጠርክ፣ ወንዙን የፈጠርክ . . . ምስጋና ለአንተ ይሁን በማለት ያመሰግናሉ፤ ይዘምራሉ። የኢሬቻ በዓል ሥነ-ሥርዓት በአባመልካ ተከፍቶ በአባ ገዳዎች ተመርቆ ከተጀመረ በኋላ መላው ሕዝብ በአንድነት ሥርዓቱን ያከናውናል። ኢሬቻ ሁሉም በጋራ የሚያከብረው፣ የሁሉም ማጌጫ፣ መድመቂያ እና የአብሮነት መገለጫ ነው። ብሔር ብሔረሰቦች የሚታወቁበትን ባህላዊ ልብስ በመልበስ በቋንቋቸው ፈጣሪን እያመሰገኑ በዓሉን በአንድነት ያከብራሉ። ለዚህም ነው ኢሬቻ ከኦሮሞ ሕዝብ አልፎ የመላው ኢትዮጵያውያን በዓልና መገለጫ ነው የሚባለው። በርካታ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን የሆራ ፊንፊኔ እና የሆራ ሀርሰዲ በዓላት ላይ ለመታደም ወደ አገር ቤት ይመጣሉ። የውጭ አገራት ጎብኚዎችና እንግዶችም በትዕይንቱ ይታደማሉ። ለአብነትም ባሳለፍነው ዓመት ከኬንያ አገር የመጡ ልዑካን በዚህ በዓል ላይ በመታደም የበዓሉን ትልቅነት እና የኢትዮጵያውያን የአብሮነት መገለጫ መሆኑን መመስከራቸው ይታወሳል። በዚህ ዓመትም የሦስት ጎረቤት አገራት ልዑካን በዚህ በዓል ላይ እንደሚታደሙ የተገለጸ ሲሆን፤ የኬንያ፣ ሩዋንዳ እና ታንዛኒያ አገራት ተወካዮች እንደሚታደሙ ይጠበቃል። አያሌ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳዎች ያሉት ይህ የምስጋና በዓል እውነተኛ ወንድማማችነት የሚታይበት፣ አንድነት የሚጎላበት፣ አብሮነት የሚጠናከርበት፣ ሰላምና ተስፋ የሚታወጅበት ትልቅ አገራዊ እሴት ነው። በባህል አልባሳትና ጌጣጌጦች፣ ባህላዊ ምግቦችና ሌሎች ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ግለሰቦችና ተቋማት ኢሬቻና መሰል የአደባባይ በዓላትን እንደመልካም የገበያ አማራጭ ይጠቀሙባቸዋል። ኢሬቻ ባህላዊ አልባሳትና ቁሳቁሶች በስፋት የሚተዋወቁበት ታላቅ መድረክ ነው። በእርግጥም ይህንን ውብ የጋራ እሴት ጠብቆ ለትውልድ ማስተላለፍ ያስፈልጋል። ኢሬቻ የምስጋና በዓል ነውና በምስጋና እንደጀመርን በምስጋናና ምርቃት እንሰነባበት። "ሀዬ! ሀዬ! ሀዬ! ከመጥፎ ነገር ጠብቀን! ንጹህ ዝናብ አዝንብልን! ከእርግማን ሁሉ አርቀን! እውነትን ትቶ ከሚዋሽ አርቀን! ከረሃብ ሰውረን! ከበሽታ ሰውረን! ከጦርነት ሰውረን! ሀዬ! ሀዬ! ሀዬ! (አሜን! አሜን! አሜን!)
"በገበታ ለትውልድ" የሚለማው የደንቢ ሀይቅ
Oct 4, 2023 615
"በገበታ ለትውልድ" ስለሚለማው የደንቢ ሰው ሰራሽ ሃይቅ ምን ያህል ያውቃሉ? (በቀደሰ ተክሌ ከሚዛን አማን) ደንቢ ሃይቅ ሰው ሰራሽ ሃይቅ ሲሆን በእኛ የዘመን ቀመር በ1970ዎቹ የተሠራ ነው። በተፈጥሮ መስህቦች የተከበበው የደንቢ ሰው ሰራሽ ሃይቅ ለአካባቢው ብርሃንን ይፈነጥቅ ዘንድ የተሰራውን የቀድሞ የደንቢ ኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድብን ተከትሎ የተፈጠረ ሃይቅ ነው። የደንቢ ሃይቅ ለአካባቢው ማህበረሰብ ባለውለታ ነው፤ የመጀመሪያውን የኤሌክትሪክ ብርሃን ያገኙበት ነውና። ኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድቡ ከመልክዓ ምድሩ ጋር እንዲስማማ ተደርጎ የተገነባ በመሆኑ ውሃው ከላይ ወደ ታች በሁለት ምዕራፍ ቁልቁል እንዲወረወር ዕድልን ፈጥሮለታል። የመጀመሪያው የኤሌክትሪክ ሃይልን ለማመንጨት በዝግታ የሚወርደው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ሃይል አመንጭቶ ሲወጣ እጅግ ውብ የሆነ ፏፏቴን ፈጥሮ ወደ ታች የሚወርደው ነው። የደንቢ ፏፏቴ ከሃይቁ ወረድ ብሎ ስለሚገኝ "ደንቢ ሃይቅና ፏፏቴ" እየተባለ ይጠራል። ሃይቁን አይቶ ፏፏቴውን ሳያዩ መመለስ የማይቻል ነገር ነው። የደንቢ ፏፏቴ ከላይ ከዓለት ዓለት እየተጋጨ ሲወረወር የሚያሰማውን በግርማ ሞገስ በታጀበ ድምጽ፤ በተራራ ቀበቶ ተገምዶ ወደ ማረፊያ ቦታው ሲምዘገዘግ በለመለመው መስክ ላይ አሻግረው የሚቃኙት የተፈጥሮ ውበት ነው። ያሻው ወደ ተራራው ጫፍ ጠጋ ብሎ እንደ ጢስ በሚተነው የውሃ አካል ፊቱን እያስመታ አልያም ከሃይቁ ፊት ለፊት ራቅ ብሎ ተቀምጠው እየተመለከቱ መንፈስን የሚያድሱበት ውብ የፏፏቴ ሥፍራ ነው። ከላይኛው የግድቡ አናት ወደ ታችኛው ለመውረድ 640 ደረጃዎችን አቆልቁሎ መጓዝን ይጠይቃል። ይህ ትዕይንት ደግሞ የደንቢ ሃይቅ ሌላኛው መስህብ ነው። የደረጃዎቹን የመውጣትና የመውረድን ድካም አረንጓዴ ካባ የደረበው የሥፍራው ልምላሜ እንዲዘነጋ ያደርጋል። የደንቢ ሃይቅ አካባቢ ቀልብን ስቦ ድካምና ሌላ ሃሳብን አስትቶ ሃሴትን የሚያጎናጽፍ የተፈጥሮ ፀጋን የታደለ ነው። የደንቢ ሃይቅና ፏፏቴ ግርማ ሞገስ ምስጢሩ የአካባቢው ደን ነው። በረጃጅም እድሜ ጠገብ የሃገር በቀል ዛፎች የተከበበ ነው። በእምቅ ደኑ ውስጥ የሚገኙ አዕዋፋት ለሚገባ ለሚወጣው ሁሉ እንደየ ፀጋቸው ያዜማሉ። ጉሬዛዎችና ጦጣዎች ከዛፍ ወደ ዛፍ እየዘለሉ እጅ ይነሳሉ። ይህ አካባቢ የተጎናጸፈው የቱሪዝም ፀጋ ከብዙዎች ዐይን ርቆ ቆይቷል። አሁን ግን በቃ ብሎ ሚሊዮኖች ሊጎበኙት ጊዜው ተቃርቧል። አካባቢው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምሥረታን ተከትሎ ወደ ሥፍራው ጎራ ለሚሉ ሚኒስትሮችና የሃገር መሪዎች የማስተዋወቅ ሥራ በመሠራቱ "የገበታ ለትውልድ" ፕሮጀክት አንዱ አካል ሊሆን ችሏል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ቦታው ድረስ በመሄድ፣ በማየትና ለዓለም ጭምር በማስተዋወቅ የደንቢ ሎጅ ግንባታን የመሠረት ድንጋይ አስቀምጠዋል። በመድረኩ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የሚለማው የደንቢ ሃይቅ ሎጅ ፕሮጀክት በአንድ ዓመት ተኩል የጊዜ ገደብ ውስጥ የሚጠናቀቅ ነው። በተጨማሪም በደንቢ ሃይቅ ሎጅ አቅራቢያም ሌላው በጠቅላይ ሚኒስትሩ የመሰረት ድንጋይ የተቀመጠለት የአየር ማረፊያ ግንባታ ፕሮጀክት ይበልጥ አካባቢውን የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የሚያስችል ነው። የሎጅ ግንባታው ተጠናቆ ወደ ሥራ ሲገባ፤ ደንቢ ላይ ያረፈ ጎብኚ ከ40 በላይ የሚፍለቀለቁ የዑሲቃ ፍል ውሃ ቦታዎችን፣ የጋርንናንሳ ተራራን እና ሌሎች የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ የቤንች ሸኮ ዞን የተፈጥሮ ፀጋዎችን በቅርብ ርቀት መጎብኘት ይችላል። የቤንች ሸኮ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ እና የፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ሃላፊ አቶ ሳሙኤል አሰፋ በርካታ የቱሪዝም ሃብቶችን በዙሪያው አቅፎ የያዘው ደንቢ በቅርቡ የቱሪዝም ኢኮኖሚ አነቃቂ ሃይል ይሆናል የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በነደፉት የ"ገበታ ለትውልድ" ፕሮጀክት ሲለማ ከሃገር ውስጥ ባሻገር ከሃገር ውጭ በርካታ ጎብኚዎችን በማስተናገድ የውጭ ምንዛሬ የሚገኝበት ፕሮጀክት መሆኑንም ሳይዘነጉ። እንደዚህ አይነት ሃገራዊ ፕሮጀክቶች በአካባቢያቸው የተለመዱ አለመሆናቸውን ጠቅሰው የመንግስትን እይታና በአካባቢው ያለውን ሃገራዊ አቅም ወደ ኢኮኖሚ ለመቀየር ትልቅ ትርጉም ያለው መሆኑንም አድንቀዋል። የቤንች ሸኮ ዞን በርካታ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ መስህብ ሃብቶች እንዳሉት ገልጸው የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ያለውን ወደ ዓለም አቀፍ ገበያ ለመቀላቀል መንግስት የከፈተውን መልካም አጋጣሚ መጠቀም እንደሚገባ ነው የጠቆሙት። ከአንድ ዓመት ተኩል በፊት መሠረት ተቀምጦለት እየተገነባ ያለውን የሚዛን አማን ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ግንባታን መልካም አጋጣሚውን ለመጠቀም አንዱ ዕድል እንደሆነም ጠቅሰዋል። ፕሮጀክቶቹ ሲጠናቀቁ ለመጎብኘት የሚመጡ እንግዶችን ቆይታ ለማራዘም እና ወደውት ተደስተው እንዲመለሱ ለማስቻል ከወዲሁ በቂ ዝግጅት እናደርጋለን ያሉ ሲሆን በቅርብ ርቀት ያሉ የቱሪስት መዳረሻዎችን ምቹ የማድረግ ሥራም በትኩረት ይከናወናል ብለዋል። የሚዛን አማን ከተማ ነዋሪው አቶ ያሬድ ካንጃ ደንቢ በቅርብ ርቀት ቢገኝም ያልለማ በመሆኑ ብዙዎች የመጎብኘት ዕድል እንዳላገኙ ተናግረዋል። ደንቢ ሃይቅ እና ፏፏቴ ከሃይቅነትና የቱሪስት መስህብነት ባሻገር በሥራ ዕድል ፈጠራም ጭምር ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ አለው ነው ያሉት። የሎጁ መገንባት የዞኑን የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ወደ ዓለም ገበያ ያስገባል የሚል ተስፋ መሰነቃቸውንም አቶ ያሬድ አልሸሸጉንም። "እንደ አካባቢው እምቅ የተፈጥሮ ሃብት አቅም አንጻር ይህ ጅምር ነው፤ በቀጣይ በርካታ ፕሮጀክቶችን እንጠብቃለን" ብለዋል።
የብርቅዬዎችን አምባ በዩኔስኮ መዝገብ ላይ እናቆይ!
Sep 30, 2023 832
በመሐመድ ረሻድ ባሌ ሮቤ(ኢዜአ) ኢትዮጵያ የብዙ ሕብረ ብሔራዊ ባህልና ማንነት ያሏቸው ሕዝቦች ሀገር ነች። የተፈጥሮ ገፅታዋ በልዩነት ውስጥ አንድነትን፣ በብዝሃነት ውስጥ ህብረትን አጎናጽፏታል። ከህዝቦቿ ጥምር ውበት ባለፈ ተፈጥሮ ያደላት የበርካታ ጸጋዎች ባለቤትም ናት። መስራት የሚገባውን ያክል ሳይሰራበት ቢቆይም አሁን ላይ እነዚህን ተፈጥሯዊ ሃብቶች የቱሪዝም ኢንዱስትሪውን ለማሳደግና የዘርፉን ተጠቃሚነትም ለማሳደግ እየተሰራባቸው ይገኛል። በዚህ ረገድ ሥሙ በቀዳሚነት ጎልቶ የሚነሳው ባለብዙ የተፈጥሮ ውበት ባለቤት የሆነውና "አንድ ፓርክ ብዙ ዓለማት (One Park Many World)" ተብሎ የሚታወቀው የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ አንዱና ዋነኛው ማሳያ ነው። በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ባሌ ዞን የሚገኘው ይህ ብሔራዊ ፓርክ ከአዲስ አበባ በ411 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል። በድንቅ የተፈጥሮ ጸጋ የታደለው ይህ ስፍራ እንኳን ደህና መጣችሁ የሚያሰኝ ሃሴትን የሚሞላ ግርማ ሞገስን የተላበሰ ነው። ፓርኩ በሀገራችን ከሚገኙ 27 ብሄራዊ ፓርኮችና ሌሎች ጥብቅ ደን ስፍራዎች አንዱ ነው። በውስጡ በርካታ የብዝሃ-ህይወት ሃብትን የያዘና የጎብኚዎችን ቀልብ የሚስብ ነው። የደጋ አጋዘን፣ቀይ ቀበሮ፣ትልቁ ፍልፈል፣ የሳነቴ አምባ፣ የሀረና ጥቅጥቅ ደን ፓርኩ ከሚታወቅባቸው ብርቅዬዎች መካከል በዋነኞቹ ናቸው። የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በ2 ሺህ 150 ካሬ ኪሎ ሜትር ስፋት ላይ ተከልሎ የተመሰረተው በ1962 ዓ.ም ሲሆን በውስጡ ከ1 ሺህ 600 በላይ የተለያዩ የእጽዋት ዝርያዎች፣ ከ78 ዓይነት በላይ አጥቢ የዱር እንስሳት እና 300 የሚደርስ ዝርያ ያላቸው አዕዋፍን ይዟል። ከነዚህ መካከል 32 የእጽዋት ዝርያዎች እና በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙ 31 ብርቅዬ የዱር እንስሳት እንደሚገኙበትም ከብሔራዊ ፓርኩ ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያስረዳል፡፡ ጥቂት ስለ ብሔራዊ ፓርኩ ጸጋዎች፦ ⦁ የሰማይ ላይ ደሴት(The Island in the Sky) - የሳነቴ አምባ የሳነቴ አምባ የተፈጥሮ ድንቅ ስራ የሚታይበት የፓርኩ ልዩ ገፅታ የሚንፀባረቅበት ነው። ስፍራው በአፍሪካ ካሉት ፕላቶዎች በስፋቱ 17 በመቶ የሚሸፍን ሜዳማና ትልቁ የአፍሮ አልፓይን አምባ ወይም የሰማይ ላይ ደሴት(The Island in the Sky) ነው፡፡ ይህ ውርጫማ ስፍራ የከፍተኛ ተራራዎች መገኛ ሲሆን፤ በሀገራችን በከፍታው ሁለተኛ የሆነውና ከባህር ጠለል በላይ 4ሺህ 377 ሜትር ከፍታ ያለው የቱሉ ዲምቱ ተራራ መገኛም ነው፡፡ የሳነቴ አምባ ከመልክዓ ምድሩ አቀማመጥ ባሻገር የዝናብ ውኃን የመሰብሰብና የማጥራት አቅም ያለው ድንቅ መልክዓ ምድር ነው። በተለይ በአካባቢው የሚገኙ የባሌ ፍልፈሎች ከጠላቶቻቸው ለማምለጥ ሲሉ የሚሰሯቸው እልፍ ጉድጓዶች ውኃው ወደ ከርሰ ምድር እንዲሰርግ ከፍተኛውን ሚና ይወጣሉ። ይህም ከ40 የሚበልጡ ጅረቶች ከፓርኩ እንዲፈልቁ ምክንያት ሆኗል። ጅረቶቹ አቅማቸውን በማሰባሰብ እንደ ዋቤ ሸበሌ፣ ገናሌ፣ ዌልመልና ዱማል የመሳሰሉ ትላልቅ ወንዞችም መነሻ ቦታ ነው፡፡ ከዚህ የተነሳ ሳነቴ የ'ውኃ ጋን' የሚል ስያሜንም እንዲያገኝ ምክንያት ሆኗል። ከሳነቴ አምባ የሚፈልቁት እነዚህ ድንበር ተሻጋሪ ወንዞች በዞኑ የደሎ መናና ሀረና ወረዳ ለሚገኙ የአርብቶ አደር ማህበረሰብ የዘመናዊ መስኖ ልማት ምንጭ እየሆኑም መጥተዋል። በተለይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) የግንባታ ሥራውን ከሶስት ዓመት በፊት ያስጀመሩትና ተጠናቆ ለአገልግሎት ሲበቃ ከ11 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ የማልማት አቅም ያለው የዌልመል ዘመናዊ የመስኖ ልማት ፕሮጄክት አንዱ ማሳያ ነው። ኢትዮጵያን ጨምሮ በኬንያና ሶማሊያ የሚኖረው ከ30 ሚሊዮን በላይ ህዝብ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ህልውው ከዚህ አካባቢ በሚፈልቁ ተፋሰሶች ላይ የተመሰረተ መሆኑን በብሔራዊ ፓርኩ የዱር እንስሳት ክትትልና የምርምር ቡድን መሪ አቶ ሴና ገሼ ያስረዳሉ። ⦁ "የሀረና የተፈጥሮ ደን ሀብት" የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በሀገራችን በጥቅጥቅ ደን ሽፋኑ ከያዮ ደን ቀጥሎ የሁለተኛነትን ስፍራ የያዘው የሀረና የተፈጥሮ ደን ሀብት መገኛም ነው፡፡ ደኑ የፓርኩን 1ሺህ ካሬ ኪሎ ሜትር ገደማ ይሸፍናል፡፡ ከሀገራችን አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ለካርቦን ንግድ ታጭተው ህብረተሰቡ ከዘርፉ ተጠቃሚ እንዲሆን እያገዙ ከሚገኙ የሀገራችን ድንቅ ደኖች ውስጥም አንዱ ሆኗል። የሀረና የተፈጥሮ ደንን በአሳታፊ የደን ልማት አስተዳደር አርሶ አደሩን በ38 የደን ማህበራት በማደረጃት ባለፉት አራት ዓመታት በተከናወኑ ሥራዎች ከ179 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ከከርቦን ንግድ ሽያጭ መገኘቱን በኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት የባሌ ዞን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የዕቅድ ክትትል የሥራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ቀነዓ ያደታ ይገልጻሉ። የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በውስጡ ባሉት የእጽዋት እና የእንስሳት ብዝሃ ህይወት ሲታይ ከዓለም በ34ኛ፣ ከአፍሪካ ደግሞ በ12ኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በተለይ ፓርኩ በውስጡ ከሚገኘው እጽዋትና የእንስሳት ብዝሃ ህይወት በተጓዳኝ ለአዕዋፍ ዝርያ ካለው ምቹ ሁኔታ የተነሳ “Bird Site International” የተሰኘ ዓለም አቀፍ ድርጅት "በዓለም ከሚገኙ ምቹ የአዕዋፍ መገኛዎች አንዱ ስለመሆኑም አብነቱን ይሰጣል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ከላይ የተጠቀሱ እውናታዎችን ጨምሮ ሌሎች የፓርኩ እምቅ አቅሞችን ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት እ.ኤ.አ. በ2009 በጊዜያዊ መዝገቡ ላይ ማስፈሩም ይታወሳል። መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ በርካታ ባለድርሻ አካላት ባለፉት ዓመታት ቅርሱ በቋሚነት በዩኔስኮ እንዲመዘገብ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ መቆየታቸውን የፓርኩ ኃላፊ አቶ ሻሚል ከድር ያስታውሳሉ። በተለይ ፓርኩ በድርጅቱ በቋሚ የቅርስ መዝገብ ላይ እንዳይሰፍር ማነቆ ሆነው ከቆዩት መካከል ልቅ ግጦሽ፣ የሰደድ እሳት፣ ህገ ወጥ ሰፈራ ሲሆኑ፤ ችግሮቹ አሁንም ያልተሻገርናቸውና የሁሉንም ትኩረት የሚሹ ናቸው ይላሉ። በተለይ በፓርኩ አልፎ አልፎ የሚያጋጥመው ሰደድ እሳት የብርቅዬ የዱር እንስሳትን መኖሪያና ምግባቸውን ስለሚያሳጣቸው በቀጣይነት በትኩረት ሊሰራበት እንደሚገባም ያስረዳለሁ። ⦁ "ፓርኩን ለማቆየት የተከፈለ የህይወት መስዋዕትነት" ይህ የብርቅዬዎች አምባ ተጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ በተላይም የባሌ ህዝብ፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አያሌ መስዋዕትነት ከፍለዋል። በተለይ በ2007 ዓ.ም ፓርኩ ላይ ተነስቶ የነበረው የሰደድ እሳት በባሌ ህዝብ ዘንድ የማይረሳ ጠባሳ ጥሎ ማለፉን ነው አቶ ሻሚል ያስታወሱት። በግንዛቤ ማነስ ጭምር ግለሰቦች ለከብቶቻቸው የተሻለ መኖ ለማግኘት በማሰብና ለማር ቆረጣ በፓርኩ ክልል ውስጥ እሳት በመለኮስ ያስነሱትን ቃጠሎ ከሌሎች ጓደኞቹ ጋር ለማጥፋት ጥረት ሲያደርግ ህይወቱን ያጣውን የፓርኩን ሰራተኛና የአካባቢ ተቆርቋሪ ወጣት ቢኒያም አድማሱን በማሳያነት አቅርበዋል፡፡ ወጣቱ የተፈጥሮ ሀብት ጀግና በሚል በፓርኩ ውስጥ የማስታወሻ ሀውልት ቆሞለታል። እንዲሁም በተጠናቀቀው የ2015 ዓ.ም የበጀት ዓመት የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን ባካሄደው ዓመታዊ ግምገማ የተፈጥሮ ሀብት ጀግና ለሆነው ለቢኒያም አድማሱ ቤተሰቦች ዕውቅናና ሽልማት ሰጥቷል። እንዲያም ሆኖ ግን ጠባሳው በብዙ የአካባቢ ተቆርቋሪዎች ዘንድ ሁሌም የሚታወስ ነው፡፡ ይህ በብዝሃ ህይወት ስብጥሩና በአያሌ ጸጋዎች የተንበሸበሸው የብርቅዬዎች አምባ በቅርቡ በሳውዲ አረቢያ ሪያድ ተካሂዶ በነበረው 45ኛው የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የዓለም ቅርስ ጉባኤ ላይ በኢትዮጵያ ሁለተኛው ታላቅ የተፈጥሮ ቅርስና በዓለም ደግሞ 11ኛው ቅርስ በመሆን በቋሚነት መመዝገቡ ሁሉንም የአገሪቱን ዜጎች አስደስቷል። ፓርኩ በዓለም ቅርስነት መመዝገቡ ለቅርሱ የሚደረግለትን ጥበቃ ለማጠናከርና መስህብነቱን ለመጨመር እድል እንደሚፈጥር የዞኑ ባህልና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ሮብዳ ጃርሶ ይገልጻሉ። እንዲሁም ፓርኩ በዩኔስኮ እውቅና ማግኘቱ የቱሪስት ፍሰቱን በማሻሻል ከቱሪዝም የሚገኘውን ዓመታዊ ገቢ በማሳደግ ሀገርና ሕዝብ ከዘርፉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዕድል የሚፈጥር ነው ይላሉ። ቅርሱን በዩኔስኮ ማስመዝገብ ብቻውን ግብ አይደለም ያሉት ወይዘሮ ሮብዳ ህብረተሰቡ ተንከባክቦ ለዛሬ ያቆየውን ቅርስ በዘላቂነት መጠበቁ ላይ እንዲበረታም አሳስበዋል። በፓርኩ ላይ የሚደርሰውን ሰው ሰራሽ ጫና ሊቀነሱ የሚያስችሉ ፕሮጀክቶችን በመቅረፅ ገቢራዊ እያደረጉ ከሚገኙ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት መካከል የፍራንክፈርት ዞሎጂካል ሶሳይቲ ድርጅት የባሌ ዞን ቅርንጫፍ አስተባባሪ አቶ አብዱርቃድር ኢብራሂም የፓርኩ የጥበቃ ሥራ የአካባቢውን ማህበረሰብ ያሳተፈ መሆን እንዳለበት ይናገራሉ። በተለይ በፓርኩ አጎራባች የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በፓርኩ ላይ እያደረሱሷቸው ያሉ ጫናዎችን ለመቀነስ ህይወታቸውን የሚመሩበት ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ተጽዕኖውን መቀነስ እንደሚቻል ያምናሉ። ፓርኩን በዩኔስኮ ቋሚ መዝገብ ላይ ለማስፈር የተደረገው የተቀናጀ ጥረት እንዳለ ሆኖ ይሄው ገጽታውና ክብሩ ተጠብቆ እንዲቆይ ከፍተኛ ጥረትና ቁርጠኝነትን እንደሚጠይቅም በአጽኖኦት ያስረዳሉ። ከአካባቢው ነዋሪዎች መካከል ወይዘሮ ነፊሳ መሐመድ እንዳሉት ፓርኩን ለመጎብኘት ለሚመጡ የሀገር ውስጥና የውጭ አገር ጎብኝዎች የዕደ ጥበብ ቁሳቁሶችን በመሸጥ በሚያገኙት ገቢ ህይወታቸውን እየመሩ ናቸው። እንደሳቸው እምነት በአሁኑ ወቅት ፓርኩ በቋሚነት በዓለም ቅርስነት በመመዝገቡ ለቅርሱ የሚያደርጉትን ጥበቃ ይበልጥ እንዲያጠናክሩ መነሳሳትን የሚፈጥር ነው። የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ መምህርና በአካባቢ ሳይንስ ላይ ምርምር የሚያደርጉት አቶ አልይ መሐመድ እንዳሉት በፓርኩ አካባቢ የሚኖሩ የማህበረሰብ ክፍሎች ከፓርኩ በሚፈለገው ደረጃ ተጠቃሚ ቢሆኑ የጥበቃውን ሥራ በእጅጉ ያቃልላል የሚል እምነት አላቸው። ይህ ደግሞ የባለቤትነት ስሜትን በሚፈለገው ደረጃ እንዲያዳብሩ የሚያደርግም ነው። በመሆኑም በፓርኩ ላይ እየደረሰ የሚገኘውን ጫና ለመቀነስ የአካባቢውን ማህበረሰብ ከብሔራዊ ፓርኩ በኢኮ-ቱሪዝምና ተያያዥ ጉዳዮች ተጠቃሚ በማድረግ የባለቤትነት አስተሳሰብን ማጎልበት እንደሚያስፈልግም ያስረዳሉ። በተለይ ለማህበረሰቡ አማራጭ የግጦሽና የሰፈራ ቦታ፣ የማገዶ፣ የኃይል አቅርቦትና ሌሎች አማራጮች በቀጣይ እንዲቀርቡለት የማድረግ ስራ ቢሰራ በፓርኩ ላይ የሚደርሰውን ጫና ትርጉም ባለው መልኩ መቀነስ እንደሚቻልም ይመክራሉ። ከሀገር አልፎ የዓለም ቅርስ የሆነውን የብርቅዬዎች አምባ የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በዩኔስኮ ቋሚ መዝገብ ውስጥ ለማቆየት የሚያግዙ ሥራዎችን ከወዲሁ አቅደው እየሰሩ መሆኑን የፓርኩ ኃላፊ አቶ ሻሚል ያስረዳሉ። ብሔራዊ ፓርኩን በሚያዋስኑ ወረዳዎች የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ስለብዝሃ ህይወት ጥቅምና ተጓዳኝ ጉዳዮች በቂ ግንዛቤ አግኝተው በጥበቃው የድርሻቸውን እንዲወጡ ተከታታይነት ያለው የግንዛቤ ማዳበሪያ ሥራዎች እየተከወኑ መሆናቸውንም ገልጸዋል። የዓለም ቅርስ የሆነው የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ብዝሃ ህይወትን በዘላቂነት መንከባከብና መጠበቅ የሚያስችሉ ሀገር በቀልና ዘመናዊ አሰራሮችን ተግባራዊ በማድረግ ፓርኩን በድርጅቱ ቋሚ መዝገብ ውስጥ ከማቆየት ባለፈ ከዘርፉ የሚገኘውን ዘላቂ ጥቅም ለማረጋገጥ ሁሉም የድርሻውን በቁርጠኝነትና በፅናት ሊወጣ ይገባል።
አንጮቴ፣ ጩምቦና መስቀል በምዕራብ ኦሮሚያ
Sep 27, 2023 786
አንጮቴ፣ ጩምቦና መስቀል በምዕራብ ኦሮሚያ በአቤኔዘር ፈለቀ (ከነቀምቴ ኢዜአ) ወርሃ መስከረም ምድር በአደይ አበባ ፈክታ የምትደምቅበት፣ የአዕዋፍት ዝማሬ በተለየ ቅላጼ የሚደመጥበት፣ አርሶ አደሩ የልፋቱን ዋጋ ከደጅ-ከማሳው የበቆሎ፣የአተር፣ የባቄላ ወዘተ እሸት የሚቋደስበት፤ በክረምቱ ዝናብ ከአፍ እስከ ገደባቸው ሞልተው 'ከእኔ ወዲያ ላሳር' በሚል የሰዎችን እንቅስቃሴ ገድበው የቆዩ ድፍርስ ወንዞች ጎለውና ጠርተው ሰው ከወዳጅ ዘመዱ የሚገናኝበት "መስከረም ሲጠባ አደይ ሲፈነዳ እንኳን ሰው ዘመዱን ይጠይቃል ባዳ" ተብሎ የተቀነቀነለት የኢትዮጵያዋን የአዲስ ዓመት ብስራት የሚበሰርበት ነው። በመስከረም ወር ከሚከበሩ ሃይማኖታዊና ባህላዊ በዓላት አንዱ የደመራና የመስቀል በዓል ነው። መስቀል በተለይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት የሚከበር አውዳመት ነው። በተለይ የመስቀል ዋዜማ የሆነው የደመራ በዓል የእምነቱ ተከታዮች ችቦ ለኩሰው በደመቀ ሥነሥርዓት የሚያከብሩት ሲሆን፤ ከትውልድ ቀያቸው ርቀው የሚገኙና ኑሯቸውን ከኢትዮጵያ ውጭ ያደረጉ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሚሰባባሰቡበት፣ የተለያዩ አገሮች ቱሪስቶች የሚታደሙበት ነው። በዓሉ የእምነቱ ተከታዮች በየአካባቢያቸው የእምነቱ ተከታይ ካልሆኑ ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ጋር ተሰባስበው በአንድነትና በአብሮነት ለአውዳመቱ የተዘጋጀውን እና ቤት ያፈራውን ባህላዊ ምግቦችን በጋራ የሚቋደሱበት መጠጦች እየተጎነጩ በድምቅት የሚያከብሩት ነው። ለደመራና ለመስቀል እንደ የአካባቢው ወግና ሥርዓት የተለያዩ ባህላዊ ምግቦች ይዘጋጃሉ፤ ለአብነትም በጉራጌ ሕዝብ ዘንድ መስቀልና ክትፎ ያላቸውን ባህላዊ ትስስር ማንሳት ይቻላል። በምዕራብ ኦሮሚያ በወለጋና አካባቢው አንጮቴና ጩምቦ ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ለመስቀል በተለያየ መልክ ተሰናድተው ለምግብነት የሚቀርቡ ባህላዊ ምግቦች ናቸው። አንጮቴ እንደ ድንችና ሌሎች የሥራስር አትክልት ከመሬት ውስጥ ተቆፍሮ ወጥቶ በተለያዩ ዓይነት ተዘጋጅቶ በአዘቦቱ ቀን ለክብር እንግዳ፤ እንደመስቀል ላሉ ክብረ-በዓላት ደግሞ ከቤተሰብ፣ ዘመድ ወዳጅ በአብሮነት የሚቋደሰው ባህላዊ ምግብ ነው። በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ ጩምቦ ወይም 'ጮሮርሳ' በሚል ስያሜ የሚታወቀው ባህላዊ ምግብ ደግሞ ከአፍለኛ የቀይ ጤፍ በልዩ የአዘገጃጀት ሥርዓት ተዘጋጅቶ በተነጠረና ለሰውነት ተስማሚ በሆነ ለጋ ቅቤ የሚዘጋጅ ሲሆን በአዘቦቱ ቀን ለክብር እንግዳ፤ እንደ መስቀል ላሉ ክብረ-በዓላት ደግሞ ማህበረሰቡ ተጠራርቶ በአብሮነት የሚቋደሰው ነው። ወይዘሮ አጌ መንግሥቱ በነቀምቴ ከተማ አስተዳደር የኦሮሞን ባህላዊ ምግቦች አሰናድተው ለተጠቃሚው ህብረተሰብ በአካባቢው ባህል፣ ወግና ሥርዓት መሰረት የሚያቀርቡ የ'ኬኛ የኦሮሞ ባህላዊ ምግብ ማዕከል' ባለቤት ናቸው። እሳቸው እንዳሉት ለመስቀል በዓል ከሚቀርቡ ባህላዊ ምግቦች አንጮቴ አንዱና ዋነኛው ነው። አንጮቴና መስቀል የማይነጣጠሉ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው ብለዋል። እንደ ወይዘሮ አጌ ገለጻ አንጮቴን የተለየ የሚያደርገው ምርቱ በወርሃ መስከረም የሚደርስ በመሆኑ ማህበረሰቡ በመስቀል በዓል በጋራ ከሚቋደሰው እሸት አንዱ ስለሆነ ከደመራና መስቀል ክብረ-በዓላት ጋር የቆየ ባህላዊና ተለምዷዊ ትስስር ያለውና እንደ መስቀል በዓል ሁሉ ክብር የሚሰጠው ባህላዊ ምግብ መሆኑ ነው። አንጮቴ የአካል ጉዳት የደረሰበት ሰው የተጎዳው "ሰውነቱ ቶሎ እንዲጠገን ያደርጋል" ተብሎ ስለሚታመን ለፈውስነት እንዲሁም ለአራሶች ለወገብ መጠገኛነት፣ ገና ምግብ ለሚጀምሩ ጨቅላ ህፃናት ከምጥን እህል ጋር ተሰናድቶ ለዕድገትና ለአጥንት ጥንካሬ በገንቢነቱ ስለሚረዳና በተለየ ሁኔታ ለምግብነት ስለሚውል ከህብረተሰቡ ጋር ለዘመናት የዘለቀ ትስስር ያለው ባህላዊ ምግብ ነው። የመስቀል በዓልን በጥጋብ ማሳለፍ ዓመቱ በሙሉ የጥጋብ ዘመን ይሆናል ተብሎ ስለሚታመን በመስቀል በዓል ጠግቦ መብላት በማህበረሰቡ ዘንድ የተለመደ መሆኑን አንስተው፤ያለው ለሌለው በማካፈልም በመጠራራት ጭምር ጩምቦና አንጮቴን የመሳሰሉ ባህላዊ ምግቦችን በጋር በመቋደስ የደመራና መስቀል በዓልን በአብሮነት ያከብራል ይላሉ። የነቀምቴ ከተማ ነዋሪዎች ወይዘሮ ባጩ ተስፋዬ፣ አንጮቴ ተወዳጅ እና ተዘውታሪ የባህል ምግብ መሆኑና አዘውትረው እንደሚመገቡት ይገልጻሉ። የአንጮቴ ምርት ሳይበላሽ ለሁለት ለሶስት ዓመታት መሬት ውስጥ የመቆየት ባህርይ እንዳለውም ያስረዳሉ። መሬት ውስጥ ከሁለት ዓመት በላይ የቆየ አንጮቴም "ጉቦ" በመባል የሚታወቅ ሲሆን፤ ይህ ምርት በማህበረሰቡ ይበልጥ ተፈላጊ ነው ይላሉ። ወይዘሮ ባጩ አያይዘውም አርሶ አደሩም ሆነ ባለሃብቶች አንጮቴን በስፋት አልምተው ምርቱ በሁሉም ማህበረሰብ ዘንድ እንዲለመድ የማስተዋወቅ ስራ ቢሰራበት አንጮቴ ገበያ ተኮር ከሆኑ ምርቶች አንዱና ዋነኛው ሊሆን እንደሚችል ያላቸውን እምነት ይገልጻሉ። ሌላዋ የከተማዋ ነዋሪ ወይዘሮ አሼቴ ግርማ ተወልደው ያደጉት ገጠር ሲሆን፤ አንጮቴን ከመዝራት ጀምሮ በአሰራሩም ያደጉበት ስለሆነ የተለየ ፍቅር እንዳላቸው ያስረዳሉ። አንጮቴን ከገብስና ከአጃ እህል ጋር ደባልቆ በማስፈጨት ከወተት ጋር አፍልተው ልጆቻቸውን እያጠጡ ማሳደጋቸውንም እንዲሁ። የልጆቻቸው በሽታ መከላከል አቅምና ጥንካሬም ከፍተኛ እንደነበረም ያስታውሳሉ። የምስራቅ ወለጋ ዞን ባህልና ቱሪዝም ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አንዳርጌ ገለታ በአካባቢያቸው አንጮቴ፣ ጩምቦና ከደመራና መስቀል በዓል ጋር ጠንካራ ትስስር ያላቸው መሆኑን ያስረዳሉ። በአካባቢው በበዓላት ወቅት የተለያዩ ባህላዊ ምግቦች የሚዘወተሩ ቢሆንም፤ በመስቀል በዓል ግን እንደ አንጮቴና ጩምቦን በማህበረሰቡ ዘንድ ጥቅም ላይ የሚውል ባህላዊ ምግብ የለም ይላሉ። አቶ አንዳርጌ እንዳሉት ጽህፈት ቤቱ እነዚህን ባህላዊ ምግቦች ለማስተዋወቅና ለቀጣይ ትውልድ ለማሻገር ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ ተቋማትና አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ ነው። የመስቀል በዓልን ምክንያት በማድረግ በአካባቢው በሚከናወኑ ሕዝባዊ ኹነቶች አንጮቴ ዋና ምግብ ሆኖ እንዲቀርብ ዝግጅት ተደርጓል። አንጮቴ ድርቅና በሽታን ተቋቁሞ ጥሩ ምርት የሚሰጥና ሳይበላሽ ለረጅም ጊዜ መቆየት የሚችል የምግብ ዓይነት በመሆኑ፤ ይህን ምርት የማላመድና የማስተዋወቁ ስራ ትኩረት እንዲያገኝ በማድረጉ በኩል የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
ትንታኔዎች
ከገበታ ወደ ገበያ
Sep 24, 2023 628
(ሰለሞን ተሰራ) ኢትዮጵያ ከ10 ሺ ዓመታት በፊት ከኒዮሊቲክ አብዮት ዘመን ጀምሮ የበርካታ አዝእርትና እንስሳት ሀብት መፍለቂያ ሆና ዛሬ ላይ ደርሳለች። ከዚያ ዘመን ጀምሮ የአገራችን ገበሬ በስራ ያካበተውንና በተፈጥሮ የተሰጠውን ችሎታ በመጠቀም ዘመናዊና ቴክኖሎጂ በወለዳቸው መሳሪያዎች ሳይታገዝ፣ በየጊዜው የአፈሩ ለምነት እየቀነሰ ከሄደው መሬትና ባህላዊ የአስተራረስ ዘዴ ጋር እየታገለ ቁጥሩ እየናረ የሚሄደውን ህብረተሰብ ከመመገብ ወደ ኋላ ብሎ አያውቅም። ግብርናው ከቀደሙት ጊዜያት በተለየ ሁኔታ ትኩረት ባገኘበት በዚህ ዘመንም ከተደቀኑበት እጅ ጠምዛዥ ጉዳዮች ጋር ግብግብ ውስጥ ነው። የአየር ንብረት ለውጥ፣ ድርቅ፣ የፖለቲካና የገበያ አለመረጋጋት፣ የዕውቀትና የቴክኖሎጂ ውስንነት፣ የተፈጥሮ አደጋ፣ የዘርፉ ኢንቨስትመንት አለመዳበር የዘርፉ ተግዳሮት ሆነው ቀጥለዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን በ78ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ባደረጉት ንግግር በተለይ የአየር ንብረት ለውጥን ተጽእኖ በሚገባ አመላክተዋል። የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ በተለይ በአፍሪካና በሌሎች በማደግ ላይ ያሉ አገራት ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ቀውስ ሁሉን አቀፍ መፍትሄ እንዲበጅ እየሰራች መሆኗን ተናግረዋል። በተለይ ኢትዮጵያዊያን ከጫፍ ጫፍ እየተሳተፉበት ያለው የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር የዚህ ቁርጠኝነት ማሳያ መሆኑን አንስተዋል። በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ ላለፉት ተከታታይ አራት ዓመታት በሰራችው ስራ በአካባቢ ጥበቃና በግብርናው ዘርፍም ውጤት ማግኘቷ እሙን ነው። ነገር ግን ፈተናዎቹን በድል ለመሻገር የሚደረጉ ጥረቶችና በዘርፉ የተገኙ አበረታች ውጤቶች እንደተጠበቁ ሆነው አሁንም ዘርፉን በሰለጠነ የሰው ሃይል፣ በተደራጀ የግብርና መሳሪያና ማቀነባበሪያ በመደገፍ አገርና ህዝብ ከግብርናው ዘርፍ ማግኘት ያለባቸውን ጥቅም እንዲያገኙ ለማስቻል ብዙ መስራት ይጠይቃል። በተለይ የግብርና ሜካናይዜሽንን ከማስፋፋትና ዘመናዊ የግብርና ግብዓቶችን በበቂ ሁኔታ ከማቅረብ አኳያ መንግስት እየሰጠ ያለው ትኩረት የበለጠ መጠናከርና ማደግ ይኖርበታል። የግብርናና የገጠር ልማት የፋይናንስና ብድር አቅርቦትን ማጠናከር እንዲሁም የአካባቢና ስነ ምህዳር ጥበቃ ስራዎችን በዘላቂነት መተግበር ያሻል። በተለይ ኢትዮጵያ በልዩ ትኩረት እየሰራችበት ያለውን የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ ጉዳይ ከዚህ ቀደም የነበረውን የግብርና አሰራር በመቀየርና አማራጮችን በማማተር እውን ማድረግ ይጠይቃል። ኢትዮጵያ በዝናብ ወይም በመስኖ መልማት የሚችል ያልተነካ ሰፊ መሬት እንዳላት የሚታወቅ ሲሆን ይህን ያልታረሰ መሬት በአግባቡ በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ አንዱ አማራጭ ነው። መረጃዎች እንደሚያሳዩት ግብርናው ከ34 በመቶ በላይ የጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት ድርሻ ይዟል፡፡ በተጨማሪም ዘርፉ 79 በመቶ የሚሆኑ ዜጎች መተዳደሪያ ሲሆን በተመሳሳይ 79 በመቶ የሚሆነውን የውጭ ንግድ ገቢ በመሸፈንና ለአገር ውስጥ ኢንቨስትመንትና ገበያ የጥሬ እቃ አቅራቢ በመሆንም ይታወቃል። መንግስት በግብርናው ዘርፍ የወሰዳቸው የሪፎርም ስራዎችና ግብርናን ከአረንጓዴ አሻራ ጋር በማስተሳሰር የሰራቸው ስራዎች ፍሬ ማፍራት ጀምረዋል። በተለይ የስንዴ ምርታማነትን በማሳደግ ከራስ ፍጆታ አልፎ ለውጭ ገበያ ለማቅረብ የተሰራው ስራ ቀዳሚ ተጠቃሽ ነው። ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት ብቻ የስንዴ ምርታማነቷን በ27 በመቶ ማሳደግ መቻሏ ስንዴ ከመሸመት ወደ መላክ የመሸጋገሯ ማረጋገጫ ሆኗል። በጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ አህመድ የተጀመረው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ በዚህ ረገድ የሚታይ ለውጥ እያሳየ ሲሆን በተሰራው ውጤታማ ስራ ባለፈው በጀት ዓመት ኢትዮጵያ ከውጭ ስንዴ አላስገባችም። በዚህም 1 ቢሊዮን ዶላር ማዳን መቻሏን የግብርና ሚኒስትሩ ዶክተር ግርማ አመንቴ በቅርቡ ማሳወቃቸው ይታወሳል። ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት 15 ነጥብ 4 ሚሊዮን ቶን ስንዴ ያመረተች ሲሆን በተያዘው ዓመት ደግሞ ምርቱን ወደ 19 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቶን ለማሳደግ እቅድ ተይዞ እየተሰራ ይገኛል። ይህንኑ ግብ ለማሳካት ደግሞ የስንዴ ማሳዋን በማሳደግ 5 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በስንዴ ሰብል ለመሸፈን እየሰራች ነው። ከዚህ ውስጥ በመስኖ የሚለማ ስንዴን በ2 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ላይ በመዝራት በመስኖ የሚለማውን ስንዴ በ54 በመቶ ለማሳደግ እየሰራች ነው። ይህ ደግሞ በቀጣይ ከሀገር ውስጥ ፍጆታ ባለፈ ምርቱን ለውጭ ገበያ ለማቅረብ እንደሚያስችል ዶክተር ግርማ አመንቴ ተናግረዋል። የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ያወጣው ሪፖርት እንደሚያመላክተው የግብርናው ዘርፍ በአስር ዓመቱ የልማት ዕቅድ የመጀመሪያዎቹ 3 ዓመታት (2013-2015) በዋና ዋና ተግባራት ከዕቅድ በላይ ዕድገት አስመዝግቧል። በዚህም ዘርፉ በ2013 ከነበረበት 5 ነጥብ 1 በመቶ በ2014 ወደ 5 ነጥብ 8 በመቶ ያደገ ሲሆን በ2015 ደግሞ 6 ነጥብ 3 በመቶ እድገት አስመዝግቧል። ግብርናውን ለማሳደግ ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዘው የሰብል ምርት ሲሆን ለዘርፉ ማደግ 65 ነጥብ 5 በመቶ አስተዋጽኦ አበርክቷል። ደን ልማት 8 ነጥብ 6 በመቶ እንዲሁም የእንሰሳት ሃብት ልማቱ 25 ነጥብ 9 በመቶ ድርሻ ይዘዋል። በ2015 ዓ.ም ጠቅላላ 627 ሚሊዮን ኩንታል ሰብል ለማምረት ታቅዶ ከተቀመጠው ግብ በላቀ ደረጃ 639 ሚሊየን ኩንታል ምርት ማግኘት ተችሏል። ከበጋ ስንዴ ልማት ጎን ለጎን በቅርብ ጊዜ የተጀመሩ የቡና፣ አቮካዶና አኩሪ አተር የመሳሳሉት ትላልቅ የግብርና ልማት ስራዎች በተመሳሳይ ውጤት ታይቶባቸዋል። የአዝርት፣ የአትክልት፣ ፍራፍሬና ስራስር ምርት ከፍተኛ የዕድገት ሽግግር የታየባቸው ናቸው። በአረንጓዴ አሻራ፣ በሌማት ትሩፋትና በከተማ ግብርና ተሞክሮ ሊወሰድበት የሚችል አፈጻጸም መመዝገቡ በሪፖርቱ ተመላክቷል። ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋትን የስንዴ ምርት ከውጭ ገበያ ስትገዛ የኖረች ሲሆን በተለይም በተለያዩ ጊዜያት የሚፈጠሩ ዓለም አቀፍ ተግዳሮቶች አቅርቦቱን ሲያስተጓጉሉት ቆይተዋል። አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ የስንዴና የገብስ ምርትን በሀገር ውስጥ ምርት መተካት የቻለች ሲሆን የሩዝ ፍላጎቷን ደግሞ 50 በመቶ መሸፈን ችላለች። በስንዴ ምርታማነት የተገኘውን ተሞክሮ ወደሌሎች ሰብሎች በማስፋት የገቢ ምርቶችን በቀጣይ ለመተካት በትኩረት እየተሰራበት ይገኛል። ይህንን ለማሳካት መንግሥት ለዘርፉ የሰጠው ትኩረት የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ እንደሚሆን ይታመናል። በተለይ ለግብርና ዘርፉ የተሻለ በጀት መመደቡ፣ እስካሁን ለመጣውና ለወደፊትም ይመጣሉ ተብለው ለሚታሰቡ ለውጦች ትልቅ ምክንያት ነው። ለምሳሌ የ2015 ዓ.ም. በአገሪቱ ለተለያዩ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ልማት ከተመደበው 786 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በጀት ውስጥ፣ ለግብርናው ዘርፍ 34 በመቶ የሚሆን በጀት ተመድቧል። ይህ ደግም ከለውጡ በፊት ከአሥር በመቶ ያልበለጠ በጀት ጋር ሲነፃፀር እጅግ ከፍተኛ ያደርገዋል። በተጨማሪም መንግሥት ለኩታ ገጠምና ለመስኖ እርሻ ከፍተኛ ትኩረት መስጠቱ፣ ሙሉ በሙሉ በዝናብ ላይ ጥገኛ የሆነውን የግብርና ስራ በመስኖ የታገዘ እንዲሆንና አርሶ/አርብቶ አደሩ በዓመት ከአንድ ጊዜ በላይ እንዲያመርት ማድረጉ ውጤቱን ጉልህ አድርጎታል። እንደ ስንዴ፣ በቆሎ፣ ሩዝ፣ ቡና፣ አቦካዶ ሁሉ በግብርና ሚኒስቴር ከተያዙና በልዩ ትኩረት ከሚከናወኑ ዕቅዶች አንዱ የማር ምርትን ማሳደግ ሲሆን፣ በአሥር ዓመቱ የልማት ዕቅድ ውስጥ እንደተመላከተውም የማር ምርትን በማዘመን ምርቱን ለማሳደግ በስፋት ይሰራል። በኢትዮጵያ ለማር ምርት ተስማሚ የሆነ አግሮ ኢኮሎጂና ብዛት ያላቸው ዕፅዋት መኖራቸው የሚመረተው ማር የተፈጥሮ ጥራት እንዲኖረው ያግዛል። ይህንኑ ዕምቅ ሀብት ትኩረት ሰጥቶ ማልማት ከተቻለ ከ500 ሺሕ ቶን በላይ ማርና ከ50 ሺሕ ቶን በላይ ሰም ማምረት እንደሚቻል ባለሙያዎች ያስረዳሉ። የኢትዮጵያ እንስሳት ሀብት ኢንስቲትዩት ባወጣው መረጃ በሀገሪቱ አለ ተብሎ ከሚገመተው ሰባት ሚሊዮን የንብ መንጋ ውስጥ 90 በመቶው በባህላዊ ቀፎ ውስጥ የሚገኝ ነው። የንብ መንጋዎቹ በባህላዊ ቀፎ ከመኖራቸው በተጨማሪ በጫካ መገኘታቸው ሃብቱ ለአገር ዕድገት በሚፈለገው ልክ እንዳይውል አድርጎታል። ያም ቢሆን ባለፈው ዓመት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የተጀመረው “የሌማት ትሩፋት” ለማር ምርት ትኩረት የሰጠ በመሆኑ ዘመናዊ የንብ ማነብ ዘዴ እንዲስፋፋ ተደርጓል። በዚህም የማር ምርታማነትን በዓመት ወደ 98 ሺህ ቶን ማሳደግ መቻሉ በቅርቡ መገለጹ ይታወሳል። ምርቱን በእጥፍ ለማሳደግ እቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑም እንዲሁ። ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የማር ምርት የማምረት አቅም ካላቸው አሥር ሀገሮች አንዷ በመሆኗ ሃብቱን ለማልማት ሁሉም ሊረባረብ ይገባል። በአጠቃላይ መንግሥት ለአረንጓዴ ልማት/አሻራ፣ ለአፈርና አካባቢ ጥበቃ የሰጠው ትኩረት ሁሉን አቀፍ የግብርና ዕድገት እንዲመጣ መሠረት ሆኗል። በተጨማሪም መንግስት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሌማት ትሩፋትና ምግባችን ከደጃችን መርሐ ግብር ኅብረተሰቡ የከተማ ግብርናን እንዲያስፋፉ በገጠርም ሆነ በከተማ ያከናወነው ተግባር ውጤት አስመዝግቧል። በአጠቃላይ ባለፉት አምስት ዓመታት ዘርፉን ለማዘመን የተከናወኑ የልማትና የሪፎረም ሥራዎች ግብርናውን ከአዝጋሚ ጉዞ በማውጣት ወደ ፈጣንና አስተማማኝ ጉዞ ማሸጋገር ችለዋል። ኢትዮጵያ አሁንም አያሌ ያልተነኩ ዕምቅ ሀብቶች ያሏት መሆኗን እንደ እድል በመውሰድ ቀጣይነት ያለው እድገት ማስመዝገብ ይጠበቅባታል። ይህን ማድረግ ስትችል የግብርና ሽግግር ይረጋገጣል። ግብርናውን ለማሻገር ደግሞ በፋይናንስ፣ በግብአት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በሰለጠነ የሰው ሀይል ልማት ላይ በትኩረት መስራት ያሻል። ወጣቱ ግብርናን እንደ ንግድ (Agri-Bussiness) ማየትና በዚያው ልክ መስራት ይጠበቅበታል። በዚህ ልክ በርብርብ ሲሰራ ግብርናን በማሸጋገር ገበታን ከመሙላት ወይም ከፍጆታ አልፎ ገበያን ማማተር ይቻላል።
ኢትዮጵያ እና መስከረም
Sep 22, 2023 627
(በአየለ ያረጋል) መቼስ ሀገሬው መስከረምን ሲናፍቅ ‘ለብቻ’ ነው። በባህሉ፣ በትውፊቱ፣ በስለ-ምኑ፣ በኪነ-ቃሉ እና ስነ-ቃሉ ልዩ ሥፍራ ይሰጠዋል ለመስከረም። እንደ መስከረም ክብር፣ ሞገስ እና ፀጋ የተቸረው የትኛው ወር ይሆን? ማንም! ሀገሬው ለቆንጆ ልጁ ስም ሲያወጣ ‘መስከረም’ እንጂ በሌላ ወር ሰይሞ ያውቃል? አያውቅም። በኢትዮጵያ ምድር መስከረም ለሰው ልጅ ብቻ ሳይሆን ለእንስሳት እና አዕዋፋት ራሱ ልዩ ጊዜ ነው። ‘ኢትዮጵያ ነይ በመስከረም…’ እንዲሉ መስከረም ለኢትዮጵያ ውበቷ፣ ቀለሟ፣ ትዕምርቷ፣ የባህር ሃሳቧ መባቻ ነው። ተናፋቂው መስከረም ዝም ብሎ ወር ብቻ አይመስልም። እውቁ ሠዓሊ እና ባለቅኔ ገብረክርስቶስ ደስታ መስከረምን “… በሽቱ መዓዛህ ለውጠው ዓመቱን፤ ይታደስ ያረጀው ፍጥረት ሌላ ይሁን…” ሲል የአዲስ ተስፋና መንፈስ መሻቱን አሳይቷል። ተወዳጇ ድምፃዊት እጅጋየሁ ሽባባው ደግሞ “… መስከረም ለምለሙ፣ መስከረም ለምለሙ፣ ብሩህ ዕንቁጣጣሽ ደስታ ለዓለሙ…” ትለዋለች መስከረምን ስታዜመው። እንደየ ንፍቀ ክበቡ ዓመታት በወራት ሲመነዘሩ የራሳቸው መልክና መገለጫ አላቸው። ኢትዮጵያም ከጎርጎሮሳዊያኑ የዘመን ቀመር በሰባት ዓመት ከስምንት ወራት ልዩነት ያለው የራሷ የዘመን ቀመር አላት። ኢትዮጵያ ብቸኛዋ ባለ 13 ወራት ሀገር ነች። ወራቱም መጸው(መኸር)፣ ሐጋይ(በጋ)፣ ፀደይ(በልግ) እና ክረምት በሚል በአራት ወቅቶች ይከፈላሉ። ወቅቶቹም የራሳቸው ጸባይ፣ ክዋኔ፣ ትውስታና ትዕምርት ይቸራቸዋል። እያንዳንዱ ወርም እንደዚሁ። ከዘመን መባቻው መስከረም እስከ ማዕዶተ-ዘመኗ ጳጉሜን ወራቱ በሰማይና በምድሩ ተፈጥሯዊ፣ ባህላዊና መንፈሳዊ ውቅራቸው ግላዊ ገጽታ ይነበብባቸዋል። የወራቱ ቅላሜ እና ሕብርነት ልዩ መልክዓ-ኢትዮጵያን ይፈጥራል። ‘የ13 ወር ፀጋ’ የሚለው መጠሪያም በ‘ምድረ ቀድምት’ እስኪተካ ድረስ ለብዙ አሥርት ዓመታት መለያ ሆኖ ዘልቋል። ይህን መለያ ስም ያወጡት እና የኢትዮጵያ ቱሪዝም አባት የሚሰኙት አቶ ኃብተሥላሴ ታፈሠ “ኢትዮጵያ የ13 ወራት ፀሐይ ባለቤት ናት። ስያሜው ከምንም የፖለቲካና ሃይማኖት ጋር ንክኪ የለውም” ብለው ነበር። የኢትዮጵያ ወራት ስያሜ ከመልክና ግብራቸው ይመነጫል። የወራት መባቻው መስከረም እንደዛው። ሊቃውንት መስከረምን ሲፈትቱት መስ - 'ዐለፈ፤ ከረመ' ይሉትና “ክረምቱን ማስከረሚያ፤ የጥቢ መባቻ" ወርኅ ሲሉ ያመሰጥሩታል። መስከረም ዘመን ያስረጃል፤ አዲስ ሕይወትና ተስፋ ደግሞ ይደግሳል። አንዳንዴም ይህ ወር ዘመን መለወጫ፣ ዕንቁጣጣሽ፣ ቅዱስ ዮሐንስ ተብሎም ይጠራል፡፡ 'አገር፣ ቀለም፣ ዘመን' እንደሸማው በድርና ማግነት ከሚሰባረቅባቸው ወራት አንዱ መስከረም ነው። መስከረም አገርኛ አለባበስ፣ አገርኛ ዝማሬ፣ አገርኛ ጨዋታ፣ አገርኛ ትውፊትና ቀለም በመስከረም በዓላት በተግባር ይታያል። መስከረም ሁለንተናዊ ውበቱ ድንቅ ነው፤ ትዕምርቱም ጉልህ ነው። የመልክዓ-መስከረም ድምቀት ማሳያዎች ዘመን መለወጫ በኢትዮጵያ ዘመን ስሌት ቀለበት መስከረም 1 ቀን ዘመን ይለወጣልና። የዘመን መለወጫ በዓል ‘ርዕሰ ዓውደ- ዓመት’ ይሰኛል። የባህር ሐሳብ ሊቃውንት መስከረም ለምን የዘመን መለወጫ እንደሆነ ሲያትቱ “ብርሃናት /ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት/ የዓመት ዑደታቸውን በጳጉሜ ወር ጨርሰው በመስከረም ወር ስለሚጀምሩ ነው” ይላሉ። በመስከረም ሌሊቱ ከቀኑ እኩል ነው። ደራሲ ካሕሳይ ገብረእግዚአብሔር “ቀዳማይ፣ ርዕሰ ክራሞት፣ መቅድመ አውርኅ፣ ርዕሰ ዐውደ-ዓመት፣ የክረምት ጫፍ መካተቻ፣ የመፀው መባቻ” ይሉታል ወርኃ መስከረምን። እናም ዘመነ ማዕዶቷን፤ ወርኅ ተውሳኳን ‘ጳጉሜን’ ተሻግሮ መስከረምን መሳም ይጓ'ጓ'ል። የመስከረም ጥባት በአያሌው ይሻታል። 'መስከረም ሲጠባ ወደ አገሬ ልግባ …’ እንዲሉ የተሰደዱት በአዲስ ዓመት መባቻ የአገራቸውን አፈር ለመሳም ያማትራሉ። ’አበባዬ ሆይ፤ አበባዬ ሆይ’ የሚሉ ሕፃናት ተስፋና ምኞታቸውን በወረቀት ያቀልማሉ፤ የአበባ ስዕላት ይዘው በየደጃፉ ይሯሯጣሉ፤ የ’ዕደጉ’ ምርቃት ያገኛሉ፤ በደስታ ይንቦጫረቃሉ። በዚህ ድባብ ነው እንግዲህ መስከረምን የግዑዛንም የሕይወታውያንም የነፃነት፣ የተስፋና የፍቅር ወርኅ ተደርጎ የሚናፈቀው። የብዙ ሺህ ዘመናት ባለታሪኳ ኢትዮጵያ ተፈጥሯዊ አዱኛ ሳይርቃት በእርስ በርስ ጦርነት፣ በጠላት ፍላፃዎች እና በድንቁርና ብዛት... ሰንኮፎቿ ሳይነቀሉ በመልከ-ብዙ ምስቅልቅሎሽ ውስጥ ዛሬ ደርሳለች። ጊዜው የኢትዮጵያን መስከረም ያስናፍቃል። ዕንቁጣጣሽ መስከረም በአደይ አበባ የሚያሸበርቅ ወር ነው። የነገረ-ዕንቁጣጣሽ የትመጣ መልከ-ብዙ አተያዮች ይጠቀሳሉ። ለምሳሌ “ዕንቁ – ዕፅ አመጣሽ” ብሎ የአበባ መፈንዳት ለማመላከት እንደሆነ የሚጠቅሱ አሉ። ንግሥት ሳባ /አዜብ/ ወደ ንጉሥ ሰሎሞን የእጅ መንሻ ይዛ ስትሄድ ንጉሡም “ዕንቁ ለጣትሽ ጌጥ ይሁንሽ” በሚል ቀንና ከሌሊት የሚያበራ ቀለበት ስለሰጣት ነው የሚል አፈታሪክም ይነገራል። የስያሜው መነሻ ያም ሆነ ይህ መስከረም ለመልክዓ-ምድሩ፣ ለሰውና ለእንስሳት ሁሉ ‘ፍስሐ ወተድላ’ የሆነ ወር ነው። በመስከረም ምድር በዕንቁጣጣሽ ትፈካለች፤ በአበቦች ታጌጣለች፤ ውኆች ይጠራሉ። ሰማዩም የክብረ-ሰማይ ብርሃኑን ያጎላል። ጥቁር ደመና ጋቢ ይገፈፋል፤ ክዋክብት እንደፈንዲሻ በዲበ-ሰማይ ይደምቃሉ። ዕጽዋትና አዝዕርት እንቡጦች ይፈነዳሉ። የመብረቅ ነጎድጓድ ተወግዶ የሰላምና የሲሳይ ዝናብ ይዘንባል። እንስሳት የጠራ ውሃ እየጠጡ፣ ለምለም ሳር እየነቸረፉ ይቦርቃሉ። እርሻ የከረሙ በሬዎች፣ ጭነት የከረሙ አህዮች መስከረም አንጻራዊ የእፎይታ ወራቸው ነው። ነጎድጓድ በአዕዋፋት ዝማሬ ይተካል። ንቦች አበባ ይቀስማሉ፤ ቀፏቸውን ያደራሉ። ቢራቢሮ ሳትቀር ‘በመስከረም ብራ ከኔ በላይ ላሳር..’ ብላ ትከንፋለች። በ’ዕንቁጣጣሽ’ ምድር ብቻ አይደለችም የምትዋበው። መስከረም ለሰው ልጆችም በተለይም ለወጣቶች የፍቅር፣ የእሸት እና የአበባ ወር ነው። የሰላም፣ የንጹህ አየር፣ የጤና ድባብ ያረብባል። የጋመ በቆሎ እሸት ጥብስ፤ ቅቤ ልውስ፤ ቅቤ በረካ ይናፈቃል። የተጠፋፋ ዘመድ አዝማድ ይገናኛል። ‘ሰኔ መጣና ነጣጠለን’ ብለው ወርኃ ሰኔን የረገሙ ተማሪዎች ተናፋቂያቸውን ያገኛሉና ‘መስከረም ለምለም’ ብለው ያሞካሹታል። የገበሬው የሰብል ቡቃያ ያብባል፤ እሸት ያሽታል። ጉዝጓዝ ሣር፣ ትኩስ ቡና ይሽታል። ደመራ ወመስቀል ሊቃውንት የደመራን የትመጣን ሲፈትቱ ‘ደመረ፣ ተሰባሰበ’ ይሉታል። ጎረቤት፣ የሩቅ የቅርብ ዘመድ አዝማድ ተደምሮ የሚከውነው ነውና። ነገረ መስቀሉ እምነቱ፣ ባህሉ፣ ትውፊቱ ብዙ ነው። መስቀል በሃይማኖተ-አበው ሀተታ ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ለማዳን፣ ለፍጡር የሰው ልጆች ያለውን ጥልቅ ፍቅር የገለጸበት ዓርማ ነው። በዚህም መስቀልን አማኝ ምዕመናን እና ካህናት የደኅንነትና የእምነት ምልክታቸው፤ የርኩስ መንፈስ ማባረሪያ መሳሪያቸው አድርገው ይመለከቱታል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መስከረም 10 ቀን ‘ተቀጸል ጽጌ’ በሚል የክርስቶት መስቀል ግማድ (ቀኝ እጁ ያረፈበት ክፋይ) ከኢየሩሳሌም ተነስቶ ኢትዮጵያ የገባበትን ቀን ታከብረዋለች፤ መስከረም 17 ቀን ደግሞ መስቀሉ የተገኘበትን። መስከረም 16 እና 17 ቀን የሚከበረው የደመራ መስቀል በዓል ከሃይማኖታዊ አስተምህሮው ባለፈ ባህላዊ ትውፊትነቱ የጎላ በመሆኑ በአብዛኛው ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ይናፈቃል። ደመራና መስቀል የአንድነት፣ የፍቅር፣ የይቅርታ፣ አብሮነት፣ የምስጋና፣ የተስፋ… እሴቶች የሚገለጹበት ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ ክብረ-በዓል ነው። ደመራ እና መስቀል በዓላት ሃይማኖታዊ የአደባባይ በዓል ቢሆንም እንደየ አካባቢው ባህል፣ መንፈሳዊነት፣ ትውፊት፣ ዕውቀት አገርኛ ህብር ጥበባት የሚጎሉበት፣ አገር የውበት አክሊል የምትደፋበት ዕለት ነው። መስቀል የዓለማችን የማይዳሰስ የኢትዮጵያ ወካይ ቅርስ መዝገብ ሥር ሰፍሯል። በመስቀል አገርኛ ቀለም ይጎላል። 'አገር፣ ቀለም፣ ዘመን' እንደሸማው በድርና ማግነት ይሰባረቃሉ። የባህር ማዶ ጎብኚዎች በአግራሞትና መደነቅ ሲናገሩ ይደመጣሉ። የዕንቁጣጣሽ ተከታይ የመስከረም መልክ ነው መስቀል። የደመራ አደማመር እና ማብራት ሥነ-ሥርዓት በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች ተመሳሳይ እንዳልሆነ ደራሲ ካሕሳይ ገብረእግዚአብሔር ይተርካሉ። በትግራይ፣ በጎንደር፣ በወሎ፣ በዋግኸምራ፣ በአዊና በከፊል ጎጃም ደመራ ማታ ላይ ተደምሮ ንጋት ላይ ይለኮሳል። በከፊል ጎጃም፣ በሸዋ፣ በአዲስ አበባ፣ በጉራጌ፣ በጋሞ፣ በወላይታና ሌሎች የደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች ደግሞ እንደየ አካባቢው ተለምዶ መስከረም 16 ከእኩለ ቀን ጀምሮ እስከ አመሻሽ ድረስ ደመራው ይለኮሳል። መስቀል በአንዳንድ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ርዕሰ ዓውደ-ዓመት ይመስላል። በደቡብ ኢትዮጵያ መስቀል ከሃይማኖታዊ ይዘቱ ባህላዊ ጎኑ ይጎላል። ጉራጌዎች፣ ጋሞዎችና ሌሎችም መስቀልን ከሁሉም በዓላት የበለጠ ይናፍቁታል። የተራራቁ ቤተሰቦች የሚገናኙበት የፍቅር፣ የደስታና የእርቅ በዓል ነው መስቀል። በጋሞ ብሔረሰብ ባህል በዋዜማው ሰው ቢሞት እንኳን በሌሊት ተወስዶ ይቀበራል እንጂ ለቅሶ እንደማይለቀስ ይነገራል፤ ለሰው ብቻ ሳይሆን ለእንስሳቱም ልዩ መኖ እንደሚቀርብላቸው ይነገራል። ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ እንደሚባለው በጋሞዎች ደግሞ ‘ለመስቀል ያልሆነ ዱንጉዛ ይበጣጠስ’ በሚመስል መልኩ የባህል ልብስ አለባበስ እንደሚዘወተር መምህር ካሕሳይ (በሕብረ-ብዕር ድርሰታቸው) ጽፈዋል። መስቀል በጉራጌዎች ዘንድ እንደ አውራው በዓል ይቆጠራል። ለመስቀል ዓመቱን ሙሉ ዝግጅት ይደረጋል። አባወራው ሰንጋ ለመግዛት፣ እማወራ ማጣፈጫውን ለማዘጋጀት፣ ወጣቶች ደመራና ደቦት ለማዘጋጀት፣ ልጆች ምርቃት ለመቀበል የየራሳቸውን ይዘጋጃሉ። ቤተሰብ ወዳጅ ዘመድ የሚጠያየቅበት፣ ለትዳር የደረሱ ሚስት የሚያጩበትና የሚመርጡበት ጥላቻና ቂም በፍቅርና በይቅርታ የሚታደስበት ነው። በጉራጌዎች ዘንድ መስቀል ትልቅ ቦታ ይቸረዋል። መስቀል እንደየአካባቢውና ባህሉ የሚናፈቅበት ዕልፍ ገጽታዎች አሉት። ለምሳሌ እኔ በተወለድኩበት ገጠራማ አካባቢ ያለውን በወፍ በረር እንቃኘው! በደመራ ዋዜማ ቀናት ልጆች ተራራ ለተራራ፣ ወንዝ ለወንዝ፣ ቋጥኝ ለቋጥኝ በልጅነት ወኔና ስስት በመዞር ለደመራ የሚሆን እንጨት፣ አደይ አበባ፣ ደቦት(ችቦ) ያጠራቅማሉ። ልክ መስከረም 16 አመሻሽ ከብቶች ወደ ግርግም ከገቡ የመንደሩ ወጣቶች ወደ ‘አፋፍ’ ይወጣሉ። ደመራ ወደሚደመርባት ሥፍራ። ሁሉም የአንድ ዕድር አባላት ቤተሰብ ተወካዮች ባሉበት እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት የደመራው ሥራ ይጠናቀቃል። ደመራው ሲጠናቀቅ ወደየ ቤታችን እንበታተናለን። (አዲስ አበባን ጨምሮ በከተሞች እንደሚደረገው በመስከረም 16 አመሻሽ ደመራው አይለኮስም። ይልቁኑ መስከረም 16 ለ17 አጥቢያ ጀምሮ ይለኮሳል እንጂ።) ለመስከረም 17 አጥቢያ ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ጀምሮ ሁሉም ሰው ከየቤቱ ደቦቱ (ችቦውን) እየለኮሰ ‘እዮሃ ደመራ’ እያለ ወደ ደመራው ሥፍራ ይተማል። እንደየ ግለሰቡ ቤት እስከ ሦስት ኪሎ ሜትር ድረስ መጓዝ ሊጠይቅ ይችላል። የመስከረም እኩሌታ አረንጓዴያማ ውብ ማሳ ከየቤቱ ከሚወጡ የችቦ እሳት ነበልባል ብርሃን ይታጀባል። ከሌሎች አጎራባች የመንደር ደመራዎች ቀድሞ ለመለኮስ ጉጉቱ የትየለሌ ነው። ከቤት እስከ ደመራው ሥፍራ እስኪደርሱ ድረስ ሰዎችን፣ በረት ያሉ ከብቶቹንና የጓሮ አዝመራውን ጨምሮ ሕይወታዊያንን በሙሉ “እንጎረጎባህ፤ እንጎረጎባችሁ” ይባላል። የተጠያቂው ሰው ምላሽ ደግሞ “ዓመት ዓመቱን ያድርስህ” የሚል ይሆናል። ከደመራ ግጥም ተዘውታሪ ስንኞች መካከልም፡- “እዮሃ አበባዬ፣ መስከረም ጠባዬ፣ እዮሃ አረሬ አረሬ፣ መስቀል ጠባ ዛሬ፣ በሸዋ በትግሬ…” የሚለው ይጠቀሳል። ከደመራው ሥፍራ ስንደርስ የ’እንጎረጎባህ!’ ድምፆች ይበረታሉ። የ’ዓመቱን ያድርስህ’ መልስ ካልሆነም እኩይ አፀፋ ይኖራል። ሁሉም ከተሰባሰበ በኋላ ደመራን የሚያሞካሹና የአዲሱን ዓመት መልካምነት የሚመኙ ‘እዮሃ አበባዬ” ግጥሞች እየተደረደሩ ደመራው ሦስት ጊዜ እንቧለሌ ይዞራል። በዕድሜ ታላቅ እና የተከበረ ሰው በቅድሚያ ደመራውን ይለኩሳል። ቀጥሎ ሁሉም ወደ ደቦቱን(ችቦውን) ወደ ደመራው ውስጥ ያስገባል። ደመራውም ይቀጣጠላል። የእሳቱ ነበልባል በመስከረም የንጋት ውርጭና ብርድ ላይ ያይላል። ሁሉም በደመራው ዙሪያ ተኮልኩሎ የክረምት ወራት ትዝታ ይነሳል፤ ሹፈት፣ ቀልድና ቁምነገር በየፈርጁ ይሰለቃል። ሌሊቱ የአህያ ሆድ እስኪመስል ይቀጥላል። የተጣላም ይታረቃል። የደመራው አምድ (ምሰሶ) አወዳደቅ ለማየት ሁሉም በጉጉት ይጠብቃል። ምሰሶው ወደ ምሥራቅ ከወደቀ የጥጋብ ዓመት፤ ወደ ምዕራብ ከሆነ ግን የችጋር ዓመት ተደርጎ ይታመናል። ከደመራው ሁነቶች አንዱ ባህሉ የበቆሎ እሸት ናፍቆት ነው። የደመራው ምሰሶ ከወደቀ በኋላ በአቅራቢያ ካለ የበቆሎ ማሳ በቆሎ እሸት ይመጣል። በመስቀል ደመራ ፍም ተጠብሶ ይበላል። ባለበቆሎው ሰው ዓመታዊ ደንብ ስለሆነ የበቆሎ ማሳዬ ተጎዳብኝ ብሎ አይቆጣም። ከደመራው ዓመድ ግንባራችን ላይ መስቀለኛ ምልክት ማድረግ እና ‘የዛሬ ዓመት አድርሰኝ’ ስለት ይቀጥላል። ሰማዩ የአህያ ሆድ ሲመስል ልጆች በደቦ ወደ መንደር ለመንደር በመዞር ‘እንጎረጎባችሁ’ እንላለን። የቤቱ ባለቤትም በሳህን፣ ጣሳ ወይም ሌላ ዕቃ ጤፍ ዱቄት ይሰጣል። የሰበሰብነውን ዱቄት ይዘን ወደ ደመራው ሥፍራ እንመለሳለን። በደመራው ጉባዔ ተወስኖ ከዕድሩ ለተመረጠች ቀጭን እመቤት (ባለሙያ ሴት) ዱቄት ይሰጣትና በ17 ምሽት ለሚኖረው የእራት ሰዓት ዝግጅት በአነባበሮ መልክ ዱቄት አብኩታና ጋግራ ታቀርባለች። መስቀል የወል ክብረ በዓል ነው። የመስቀል ዕለት (መስከረም 17) በግ ይታረዳል። እህል ውሃ ቀርቦ የመንደሩ ሰው በጋራ ሲጫወት ይውላል፤ በሕብረት ይበላል። ለመስቀል የተጣላ ጎረቤት ይታረቃል። ልጆች በሕብረት ይቦርቃሉ። የመስቀል ትዝታ በእኛ መንደር ይናፈቃል። ሁሉም እንደየ ቀየው ትውፊት እና ልማድ ይህን ሁነት ይናፍቃል….!! ጊፋታ ጊፋታ/ ግፋታ ማለት ትርጉሙ በኩር ወይም ታላቅ ማለት ሲሆን በለኬላ ትርጓሜው መሻገር ማለት ነው፡፡ በወላይታ ብሔረሰብ አዲስ ዓመት አንድ ብሎ የሚጀመርበት የአዲስ ዓመት መግቢያና የብርሃን ጊዜ ማብሰሪያ ነው፡፡ ከአሮጌ ወደ አዲስ፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን መሻገር የሚለውንም ይገልጻል፡፡ ጊፋታ የዓመቱ የመጀመሪያ ወር ስያሜ ነው፡፡ በወላይታ ብሔረሰብ ዘንድ መስከረም ወር በገባ ከቀን 14 እስከ 20 መካከል የሚውለው እሑድ አዲሱን ዓመት የሚቀበሉበር ዕለት ይሆናል፡፡ በዓሉ የሚውልበት እሑድ ስሙም ‹‹ሹሃ ወጋ›› የእርድ እሑድ ይባላል፡፡ እሑድ የአዲስ ቀን ብሥራትም ነው፡፡ ቀጣዮቹ የሳምንቱ ቀናት የየራሳቸው ስያሜና አከባበር አላቸው። ለአብነት ‹‹ጋዜ ኦሩዋ›› ማንሳት ይቻላል። የአዲስ ዓመት አራተኛ ቀን ነው። የሰፈሩ ወጣቶች በየመንደሩ በታዋቂ የአገር ሽማግሌዎች ደጅ ተሰባስበው የግፋታ በዓል ባህላዊ ጨዋታ የሆነውን ጋዜ በጋራ ሆነው ‹‹ሀያያ ሌኬ›› እያሉ ትከሻ ለትከሻ ተቃቅፈው የሚጫወቱበትና ልጃገረዶችን ሎሚ በመለመን የሚፈልጓትን የሚመርጡበት ጨዋታ የሚጫወቱበት ቀን ነው፡፡ በዕለቱ ልጃገረዶች አንድ ላይ ሆነው በየቡድን ቁጭ ብለው ወንዴና ሴቴን ከበሮ እየመቱ ‹‹ወላወላሎሜ›› እያሉ የሚመርጡትን ወንድ ሎሚ በመስጠት የሚመርጡበት፣ እንዲሁም ሴቶች ለሚዜነትና ለጓደኝነት ከመረጧት ሴት ጋር በጥርስ አንድ ሎሚን ለሁለት የሚከፋፈሉበትና ስማቸው ሲጠራሩ ‹‹ሎሜ ሎሜ›› የሚባባሉበት ጨዋታ የሚጫወቱበት ዕለት ጋዜ ኦሩዋ ነው፡፡ ግፋታ ሲሸኝ ጥቅምት በገባ በመጀመሪያው ሳምንት ማክሰኞ ሆኖ የሽኝት በሬ ታርዶ ከተበላ በኋላ ቶክ ጤላ የተባለውን ምሽት በችቦ ያባርራሉ፡፡ ዜማ በተቀላቀለበት ጩኸት ችቦ ይዘው ‹‹ኦሎ ጎሮ ባ! ሳሮ ባዳ ሳሮ ያ!›› ይላሉ፡፡ ትርጓሜውም ጊፋታ በሰላም ሄደሽ በሰላም ነይ! ማለት ነው፡፡ ዮ …ማስቃላ በጋሞዎች ዘንድ በየዓመቱ በጉጉት የሚጠበቀው «ዮ ማስቃላ» የዘመን መለወጫ በዓል በመስከረም ወር አጋማሽ ላይ ቅበላው ተከብሮ በዚሁ ወር መጨረሻ «ዮ ማስቃላ» ሽኝት በዓል በድጋሚ በድምቀት ይከበራል። መስከረም ወር የመጀመሪያው ቀን በጋሞ ዞን ”ሂንግጫ” ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ይህም አዲሱን ዓመት ለመቀበል ዝግጅት የሚደረግበት ቀን ነው። ጋሞዎች ዓመቱን ሙሉ ገንዘብ በመቆጠብ በዓሉን በድምቀት ለማክበር ዝግጅት ይደረጋል። ወንዶች ለበዓሉ የሚሆን ሠንጋ መግዣ፣ ለልጆች ልብስ እና ጌጣጌጥ ማሟያ፤ እናቶች ደግሞ ለቅቤ፣ ለቅመማቅመም፣ ለባህላዊ ምግቦች እና መጠጦች እህል መግዣ የሚሆን ገንዘብ ያጠራቅማሉ። በጋሞ ዞን የማስቃላ በዓል ለሰው ልጆች ብቻ ሳይሆን ለእንሳስት እና ለአዕዋፋትም ጭምር ነው ተብሎ ይታመናል፤ በዕለቱ ምግብ ከሰው አልፎ ለእንሳስት እና ለአዕዋፍም ይትረፈረፋል። ለከብቶችም የግጦሸ መሬት በየአካባቢው ይከለላል። በተለያዩ አጋጣሚዎች የተጣሉ ታርቀው፣ የተራራቁ ዘመድ አዝማድ እና ወዳጆች ተሰባስበው በዓሉን በጋራ እንዲያከብሩ ማድረግ የጋሞ ማስቃላ በዓል መገለጫ ነው። በጋሞ ብሔረሰብ የሚከበረው የማስቃላ በዓል በሶፌ ሥርዓት የታጀበ ነው። የቀደመው ዓመት ማስቃላ በዓል ከተከበረ በኃላ የተጋቡ ሙሽሮች ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ ማምሻውን በአደባባይ ከመላው ሕብረተሰብ ጋር የሚቀላቀሉበት እና ሁለቱም ተጋቢ ቤተሰቦች አንድ ላይ ሆነው ደስታቸውን የሚገልፁበት ሥርዓት ነው። የመጨረሻው የማስቃላ ሽኝት በዓል ነው፤ ይህ ሥርዓት እንደየአባወራው አቅም በፈቀደ መጠን የሚፈፀም ነው። በዚህ ዕለት ሁሉም ያለ ፆታ ልዩነት በአደባባይ ላይ ወጥተው ያኑረን እስከ ወዲያኛው እንኖራለን እያሉ ይጨፍራሉ። ከዚህ በኋላ ለመጪው ዓመት በሰላም በጤና ያድርሰን ተባብለው ፈጣሪን በመማፀን ዝግጅቱ ይቋጫል። ያሆዴ መስቀላ የክረምቱ ወራት አልፈው መስኩ በልምላሜና በአደይ አበባ ሲያሸበርቅ በሃድያዎች ዘንድ ትልቅ ዝግጅት አለ - ያሆዴ መስቀላ። “ያሆዴ“ ማለት እንደ ብሔሩ የባህል ሽማግሌዎች ትርጓሜ እንኳን ደስ አላችሁ፤ የሚል የብስራት ትርጉም ያለው ሲሆን ”መስቀላ” ማለት ደግሞ ብርሃን ፈነጠቀ ማለት ነው፡፡ በመሆኑም ያሆዴ መስቃላ ብርሃን ፈነጠቀ እንኳን ደስ አላችሁ የሚል ትርጉም አለው። በዓሉ በወርኃ መስከረም 16 የሚከበር ሲሆን ወሩ ብርሃን፣ ብሩህ ተስፋ፣ ሰላም፣ ፍቅር፣ ረድኤት፣ በረከት የሚሞላበት ተምሳሌት ወር ተደርጎ ይቆጠራል። የሃድያ አባቶች ”ከባለቤቱ የከረመች ነፍስ በያሆዴ መስቀላ ትነግሳለች“ የሚል ብሂል አላቸው። የሃድያ አባቶች እንደ ዘመን መለወጫ የመጀመሪያ ቀን አድርገው በመውሰድ ማንኛውንም ዓይነት ክስተት ከዚያ ጋር አያይዘው እንደሚቆጥሩ ይነገራል። በዓሉ ከመድረሱ በፊት ሁሉም የቤተሰብ አባላት በዓሉን ለማድመቅ የየራሳቸው ድርሻ አላቸው። በብሔሩ አባቶች አብሮነታቸውን ከሚያጠናክሩባቸው ማኅበራዊ እሴቶች መካከል አንዱ ቱታ/ሼማታ/ሲሆን ይህ ማለት በዓሉን ምክንያት በማድረግ የተደራጀ ቋሚ የሆነ ከአራት እስከ ስምንት አባላትን የያዘና በሥጋ ቅርጫ የተደራጀ ማኅበር ነው። የዚህ ማኅበር አባላት ግንኙነት ያላቸው የሚተሳሰቡ የኢኮኖሚ አቅማቸውም ተቀራራቢነት ያለው ሲሆን በመቀናጀት የበዓሉ እለት ከመድረሱ በፊት በጋራ ገንዘብ ማስቀመጥ ይጀምራሉ፤ በበዓሉ ወቅትም ለእርድ የሚሆን በሬ መግዣ ገንዘብ እንዳይቸገሩና በዓሉን በደስታ እንዲያሳልፉ ሕብረታቸው ትልቅ ሚና ይጫወታል። ከመጋቢት ወር ጀምሮ ለከብቶች የግጦሽ ሳር የሚሆን ቦታ ከልሎ በማስቀመጥ የበዓሉ ቀን ከብቶች ተለቀውበት እንዲጠግቡ የሚደረግ ሲሆን በአዲስ ዓመት መግቢያ እንኳን የሰው ልጅ እንሰሳትም ቢሆኑ መጥገብ እንዳለባቸው እንዲሁም የጥጋብ ዘመን እንዲሆን በብሔሩ በዓሉ ለሰው ብቻ ሳይሆን እንሰሳትም ሆዳቸው ሳይጎድል አዲሱን ዓመት መቀበል እንዳለባቸው በመታመኑ ልዩ ትኩረት ይሰጣቸዋል። ኢሬቻ ኢሬቻ ከመስከረም ደማቅ መልኮች አንዱ ነው። ኢሬቻ የዘመነ መፀው መጀመሪያ ሁነት ነው። የኢሬቻ ክብረ በዓል ኢሬቻ ቢራ (መልካ) በሐይቆች ወይም በወንዞች ዳር የሚከበር ነው። ከክረምት ወደ መፀው መሸጋገርን ምክንያት በማድረግ የሚከወን የምስጋና በዓል ነው። በኦሮሞ ዘንድ ለዘመናት የሚከበር እና ከገዳ ሥርዓት ጋር የተቆራኘ እንደሆነ ይነገራል። ኢሬቻ ከመስቀል በኋላ ይከበራል። በቢሾፍቱ ከተማ የሚከበረው የ'ሆራ አርሰዲ' እንዲሁም ‘ሆራ ፊንፊኔ’ ከፍተኛ ሕዝብ ቁጥር በታደመበት በድምቀት ይከበራል። በሌሎችም የኦሮሚያ አካባቢዎች በተለያዩ ክዋኔዎች እንዲሁ ይከበራል። ኢሬቻ ለፈጣሪ (ዋቃ) የክረምት ወቅትን በማሳለፉ፣ ወይንም ወደ አዲስ ዓመት በማሸጋገሩ የሚቀርብ ምስጋና ነው። ‹‹ዋቃ›› ፍጥረተ ዓለምን ያስገኘውና ሒደቱንም የሚያስተናብረው አንድ አምላክ ማለት ነው፡፡ ‹‹ኢሬቻ ሰላም ነው፣ ሰላም ጥልቅ ትርጉም አለው፣ ሰው ከሰው ጋር፣ ሰው ከራሱ ጋር፣ ሰው ከተፈጥሮ ጋርና ሰው ከፈጣሪው ጋር ሰላም ሊኖረው ይገባል፤›› የሚለው ጽንሰ ሐሳብ የክብረ በዓሉ ጭብጥ ነው፡፡ ለሕዝቡና ለአገሩ ምርቃትና መልካም ምኞት የሚገለጽበትም ነው-ኢሬቻ። ታዲያ ማንኛውም ሰው ወደ በዓሉ ሥፍራ ሲሄድ አለባበሱን ማሳመር ይጠበቅበታልኢሬቻ ከመስቀል በኋላ ይከበራል። በቢሾፍቱ ከተማ የሚከበረው የ'ሆራ አርሰዲ' እንዲሁም ‘ሆራ ፊንፊኔ’ ከፍተኛ ሕዝብ ቁጥር በታደመበት በድምቀት ይከበራል። በሌሎችም የኦሮሚያ አካባቢዎች በተለያዩ ክዋኔዎች እንዲሁ ይከበራል። ኢሬቻ እንደ ዕንቁጣጣሽ በመስከረም ጥባት ውሃ ጎድሎ፣ የተራራቀ ዘመድ አዝማድ የሚገናኝበት ነው። በተለያዩ ጸሐፍት እንደተጠቀሰው፣ ኢሬቻ አንድም ‘ዋቃ’ ከብርድና መብረቅ፣ ከጎርፍ፣ ከአውሎ ነፋስ እና መሰል የክረምት ተፈጥሯዊ ክስተቶች ጠብቆ ወደ ብራ እና ፀሐያማው የመፀው ወቅት በሰላም ስላሸጋገረ፣ አንድም በዋቃ ፈቃድ ዝናብ ዘንቦ፣ መሬቱ ረስርሶ፣ አዝመራው ለምልሞ፣ መልካም ፍሬ በመታየቱ፣ እሸት በመስጠቱ ስለማያልቀው ቸርነቱ ለማመስገን ነው። ከክረምቱ ጨለማ ወደ ብርሃን የማለፍ ብሥራት ነው ኢሬቻ። በሌላ በኩል ደግሞ መጪው አዲሱ ዓመት የተባረከና የተቀደሰ፣ የደስታና የብልፅግና፣ የተድላና ፍስሃ ይሆን ዘንድ መልካም ምኞትን የመግለጫ በዓልም ነው። በኢሬቻ ክዋኔ አባ ገዳዎችና የሕዝብ መሪዎች ይመርቃሉ። በኦሮሞ ሕዝብ ባህላዊ አለባበሱን በማጌጥ ወደ ክብረ-በዓሉ የሚያመሩ ኢሬቻ አክባሪዎች እርጥብ ሳር እና አደይ አበባን ይይዛሉ። ከኢሬቻ ክብረ-በዓል የምርቃት ስንኞች መዘን እንሰናበት። “… ለምድራችን ሰላም ስጥ! ለወንዞቻችን ሰላም ስጥ! ከጎረቤቶቻችን ጋር ሰላም ስጠን! ለሰውም ለእንስሳቱም ሰላም ስጥ! ከእርግማን ሁሉ አርቀን! ከረሃብ ሰውረን! ከበሽታ ሰውረን! ከጦርነት ሰውረን! ሀዬ! ሀዬ! ሀዬ! (አሜን! አሜን! አሜን!)
ያሆዴ- የአዲስ ተስፋና ልምላሜ ምልክት
Sep 22, 2023 755
(በማሙሽ ጋረደው ከሆሳዕና) ያሆዴ የሃድያ ብሔር የአዲስ ዘመን መሸጋገሪያ በዓል ነው። በዓሉ ሲከበር ቂምና ቁርሾ ተወግዶ ያለፈው ዓመት መልካምና በጎ ያልሆነ ሁኔታ ታይቶ ለቀጣይ ስኬት አዲስ ተስፋና ልምላሜ ሰንቆ የሚሻገሩበት በዓልም እንደሆነ ይነገራል። ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡ የሃድያ ዞን አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ሃላፊ አቶ ታምሬ ኤርሚያስ እንዳሉት ሃድያ የራሱ የሆነ የጊዜ አቆጣጠር ባህል፤ ልማድ፤ ወግና ስርዓት አለው። ለዚህም እንደ ማሳያ በብሔሩ ዘንድ በከፍተኛ ድምቀት የሚከበረውን የያሆዴ ክብረ በዓል ለአብነት ጠቅሰዋል። በዓሉ የአዲስ ተስፋና ልምላሜ ምልክት ተደርጎ እንደሚወሰድ የተገለጸ ሲሆን በተለይም የሚመጣው ዘመን የስኬት እንዲሆን እያንዳንዱ ካለፈው ዓመት ስኬትና ውድቀት ልምድ እየቀመረ ሃገር ሰላም እንዲሆን ተመራርቀው በደስታ እየተበላ፤ እየተጠጣ የሚከበር በዓል መሆኑንም ተናግረዋል። በብሔሩ ዘንድ ልዩ ቦታ የሚሰጠው የያሆዴ ክብረ በዓል አሮጌውን ዓመት ሸኝተው አዲሱን ዓመት የሚጀምሩበትም ነው። በዓሉ ከነሐሴ አጋማሽ ጀምሮ በተለያዩ ክዋኔዎች የሚከበር ሲሆን በዓሉ መቅረቡን ታዳጊ ልጆች በተለያዩ ገላጭ በሆኑ ድርጊቶች እንደሚያበስሩ አቶ ታምሬ ተናግረዋል። በተለይም ታዳጊዎቹ ያሆዴ መድረሱን ለማብሰር ከነሐሴ አጋማሽ ጀምሮ እስከ ጳጉሜ መጨረሻ ድረስ በብሔሩ አጠራር ገምባቡያ ወይም (ዋሽንት) በመጠቀም የተለያዩ ጥዑመ ዜማዎችን በማሰማት በዓሉ መቅረቡን ያበስራሉ። በሃድያ ብሔር ዘንድ የአዲስ ዘመን ብስራት “ያሆዴ" የብሩህ ተስፋ፣ የሠላም፣ የፍቅር፣ የረድኤት፣ የበረከት ተምሳሌት ተደርጎ የሚወሰድ በዓል መሆኑንም አመልክተዋል። ይህም የሆነበት ምክንያት በመስከረም ሰውና እንስሳ ከዶፍ ዝናብ፣ ከውርጭ፣ ከጤዛና ከጭቃ፣ ከጉም፤ ከጭጋግና ጽልመት ነጻ ይሆናሉ። ምድሩ በሃምራዊ ቀለም ደምቆ ያሸበርቃል። ፀሐይ ሙሉ ገላዋን ገልጣ ጸዳሏን ትሰጣለች። በመሆኑም በስራ የደከመ ሰውነት ዘና፣ የታመመ ቀና ይልበታል፣ ልጅ አዋቂ የደስታ ነጋሪቱን ይጎስማል፣ የፍቅር ጽዋ ይጠጣል፣ የአእምሮ እርካታ ይነግሳል፣ በሁሉም ነገር ደስታ ይሰፍናል ወርሃ መስከረም በጥጋብና ደስታ ይጀመራል ። በዓሉ ከመግባቱ በፊት የራሱ የሆነ የሥራ ክፍፍል ኖሮት ቅድመ ዝግጅት የሚደረግበት መሆኑን ያነሱት ሃላፊው የቤተሰብ አባላት ሁሉም በየድርሻቸው ሃላፊነታቸውን እየተወጡ እንደሚጠብቁት ተናግረዋል። ለአብነትም ለበዓሉ መድመቅ በዓሉ ከመድረሱ ሦስትና አራት ወራት በፊት በአንድ ቤት ውስጥ የሚኖሩ የቤተሰብ አባላት የሚወጡት ድርሻ አላቸው። የሃድያ አባቶች የያሆዴን የዘመን መለወጫ በዓል የሚያከብሩት በቅንጅት አማካኝነት ከአራት እስከ ስድስት ሰው በመሆን ተቀናጅተው ሰንጋ በመግዛት ነው። ለበዓሉ ሰንጋ መግዣ የሚሆን ገንዘብ ማስቀመጥ የሚጀምሩትም ቀደም ብለው ነው ። እናቶች በዓሉ ከመቃረቡ ከሦስትና እና አራት ወራት በፊት ለበዓሉ የሚሆን ቅቤ ለማጠራቀም በሚገቡት (ዊጆ) በተሰኘ ዕቁብ ቅቤ ማከማቸት ይጀምራሉ። በተጨማሪም ለስጋ መብያና ለአተካና መስሪያ የሚሆን እንሰት በመለየትና በመፋቅ፣ ቆጮ፣ ሜሬሮና፣ ቡላን ጨምሮ የሚጠጣ ቦርዴ፣ ቃሪቦ፣ ጠጅ፣ ብርዝ የማዘጋጀት የድርሻቸውን ይወጣሉ። የደረሱ ልጃገረዶች የቤቱን ወለል ቆፍረው ይደለድላሉ፣ የተለያዩ ውበት የሚሠጡ ቀለማትንና የተለያዩ ኖራዎችን በመጠቀም የቤቱን የውስጥና የውጭ ግርግዳን በመቀባት ያስውባሉ። ወጣቶች ከነሐሴ መግቢያ ጀምሮ አባቶቻቸው የሚመርጡላቸውን ዛፍ፣ ግንድ ቆርጠው ለምግብ ማብሰያና ለደመራ የሚሆን ችቦ የማዘጋጀት ኃላፊነታቸውን እየተወጡ ይቆያሉ። ከመስከረም መግቢያ ጀምሮ ያሉ የቅዳሜ ገበያዎች ስያሜ (መቻል ሜራ ) የእብድ ገበያ በመባል ይጠራሉ።እነዚህ የግብይት ቀናት ከዚህ ቀደም እንደነበሩ የግብይት ቀናት በተረጋጋ መንገድ የሚተገበሩ ባለመሆኑና በጠዋት ቆሞ በጊዜ የሚበተን ገበያ በመሆኑ (መቻል ሜራ) የእብድ ገቢያ የሚል ስያሜ አሰጥቶታል ነው ያሉት አባቶች ሰንጋ ገዝተው ለመብላት ባደራጁት (ቱታ) ቅንጃ አማካኝነት ያጠራቀሙትን ገንዘብ በመያዝ ወደ መቻል ሜራ (እብድ ገበያ) በመሔድ የሚፈልጉትን ሰንጋ ገዝተው ይመለሳሉ። ገንዘብ ያላስቀመጡና በወቅቱ ማግኘት የማይችሉ አባወራዎች በዓሉን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተደስተው እንዲያሳልፉ ሌላኛው አማራጭ (ሃባ) በመባል የሚታወቅና ምንም ገንዘብ የሌላቸው ሰዎች ለበዓሉ የሚሆን ሰንጋ በብድር የሚወስዱበት በብሔሩ ተወላጆች ዘንድ የኖረ የመተጋገዝና የመተሳሰብ እሴት አንዱ ነው። የሚፈልጉትን ሰንጋ ከመረጡ በኋላ እህል በሚደርስበት በታህሳስና በጥር ለመክፈል በዱቤ ይወስዳሉ። የበሬ ነጋዴውም ያለ ማንገራገር ሰንጋውን በመስጠት ወቅቱ ሲደርስ ገንዘቡን ለመውሰድ ተስማምቶ ይሰጥና ወቅቱን ጠብቆ ገንዘቡን ይወስዳል። በትውስት ተወስዶ ገንዘብ ያልከፈለ አባወራ ለቀጣይ የዘመን መለወጫ አይደርስም ተብሎ በብሔሩ ዘንድ ስለሚታመን በተስማሙበት ወቅት ገንዘቡን የመስጠት ግዴታቸው የተጠበቀ ነው። ሌላኛው አስተያየት ሰጪ የመምሪያው ባለሙያ አቶ ይዲድያ ተስፋሁን እንዳሉት በዓሉ ያለው ለሌለው አካፍሎ በጋራ የሚበላበትና ወደ አዲስ ዘመን በጠንካራ አብሮነት የሚሻገሩበት ነው። በመሆኑም የያሆዴ በዓል በዜጎች መካከል ጠንካራ አንድነትና አብሮነትን መሰረት ያደረጉ ዕሴቶች ያሉበት መሆኑን አንስተው ለትውልድ ግንባታ የሚሆኑ ዕሴቶችን አጎልብቶ መጠቀም እንደሚገባ ተናግረዋል ። ለበዓሉ ዋዜማ ከሚዘጋጁ ሁነቶች መካከል አተካና ልዩ ቦታ የሚሰጠው ነው። አተካና በተለይም ለዚህ በዓል ከዚህ ባሻገር ለትልልቅ እንግዶች ከሚዘጋጁ ምግቦች መካከል አንዱ ነው። አተካና ከወተት፣ ከቅቤ፣ አይብና ቡላ የሚዘጋጅና በበዓሉ የምግብ ፍላጎትን የሚከፍት ተበልቶ የማይጠገብ በእናቶች የሚዘጋጅ ጣፋጭ ምግብ ነው። የበዓሉ ዋዜማ አተካን ሂሞ (የአተካና ምሽት) የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን በዓሉን ለማክበር ከሩቅም ከቅርብም የተሰበሰበ ቤተሰብና እንግዶች በናፍቆት የሚመገቡት ምግብ ነው። በዚሁ ዕለት በአካባቢው ትልቅ የሚባል አባወራ (አዛውንት) ቤት ችቦ (ሳቴ ) ተዘጋጅቶ ማምሻውን አባቶች ወይም የሃገር ሽማግሌዎች የማቀጣጠያ (ጦምቦራ) ደመራ ማቀጣጠያ ይዘው ይወጣሉ። ከዚያም የአካባቢው ማህበረሰብም የሃገር ባህል ልብስ ለብሰው እንዲሁም ወጣቶች ተሰብስበው ያሆዴ ይጨፍራሉ። የሃገር ሽማግሌዎች ይመርቃሉ፤ ከዚያም የተዘጋጀውን ችቦ በእሳት ለኩሰው ያበራሉ። ይህም አዲስ ዘመን መግባቱን ማብሰርና ዓመቱ የብርሃን ዓመት እንዲሆን መልካም ምኞት የሚገለፅበት ነው። ደመራው ከተቀጣጠለ በኃላ ወጣቶች ያሆዴ (ኦሌ) ጭፈራ ሲጫወቱ ያነጋሉ። ይህ ጭፈራ ከያሆዴ በዓል ውጭ አይጨፈርም። ወጣት ደመቀ አባቴ የሆሳዕና ከተማ ነዋሪ ሲሆን ስለ በዓሉ አስተያየቱን ሲሰጥ ''በአባቶች ደመራው ከተቀጣጠለ በኃላ እኛ ወጣቶች ያሆዴ ....ያህዴ....ሆያ ሆ... /ኦሌ/ ጭፈራ እየተጫወትን እናነጋለን፤'' ይህ ጭፈራ ከያሆዴ በዓል ውጭ ስለማይጨፈር በዓሉን ቀን በጉጉት እንደሚጠብቁት ተናግሯል። ተራርቀው የቆየ ወዳጅ ዘመድ ተሰብስቦ ያለምንም ልዩነት ችግርም ካለ በዕርቅና ሰላምን በማውረድ የሚመጣው ዘመን የልምላሜና የስኬት እንዲሆን ተመራርቀው የሚለያዩበት በዓል በመሆኑ በተስፋ የሚጠብቁት እንደሆነ ነው ወጣቱ የሚናገረው። የበዓሉ እለት ለዕርድ የተዘጋጀው ሠንጋ ከቀረበ በኃላ የባህል ሽማግሌዎች (ጋቢማ ) ሥርዓት ያከናውናሉ። ክዋኔውም የበሬውን ሻኛ በለጋ ቅቤና በሠርዶ ሳር በመቀባትና ወተት በማፍሰስ ይከናወናል። ይህም በሚከናወንበት ወቅትም ክፉ ቀን አይምጣ፣ ርሃብ ሰቀቀን ይጥፋ፣ ጥጋብ ይስፈን፣ በአካባቢው በሃገሩ ጥጃ ይቦርቅ፣ ልጅ ይፈንጭበት፣ አገር ሰላም፣ ገበያ ጥጋብ ይሁን፣ ሰማይና ምድሩ ይታረቁን በማለት (ፋቴ) ዳግም ምርቃት ፈጽመው በሬው ይጣልና የዕርድ ሥርዓት ይካሔዳል። በዕለቱም ከታረደው ሥጋ ቅምሻ በጋራ ይበሉና ቀሪውን ለማህበሩ (ለቱታ) አባላት ክፍፍል ይፈፀማል። ከእርድ ሥርዓቱ በኃላ በማግስቱ ልጆች ወደ ወላጆቻቸው ዘራሮ የሚባል አበባ ይዘው እየጨፈሩ ያስማሉ -ይመረቃሉ የመስቀል አበባ እንደሚኖር ኑሩ ይባባላሉ፤ ከስጋውም ፣ከቦርዴውም ፣ ከአተካናውም የሚመገቡበት ክዋኔ (ሚክራ) በመባል ይታወቃል። ትዳር የያዙ ሴት ልጆችም ከባሎቻቸው ጋር ሆነው ወደ ወላጆቻቸው ምግብ ሰርተው፣ የሹልዳ ስጋና (ዘራሮ) አደይ አበባ ጭምር ይዘው የሚሔዱበት እንዲሁም ያላገቡ ወጣቶች ለትዳር የሚሆናቸውን አጋር የሚፈልጉበትና የሚያጩበት ባህልም ያለው ነው ያሆዴ ክብረ በዓል። ከእርድ ስነ ስርዓቱ በኋላ ከሶስት ሳምንታት እስከ ወር ለሚሆን ጊዜ የመጠያየቂያና የመረዳጃ ወቅት ይሆናል። የያሆዴ በዓል ያሉ ዕሴቶች ለህዝብ ትስስር፣ ጠንካራ የስራ ባህልና ዘላቂ ሰላም ግንባታ ያላቸውን ሚና ለማላቅ በልዩ ትኩረት ሊሰራ እንደምገባ የሚያነሱት በዋቸሞ ዩኒቨርስቲ የህዝብ ግንኙነትና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የአቶ ዳንኤል ገዴ በዚህ ላይ በአከባቢው ያሉ የማህበረሰብ ልምዶችና ወጎች ለትውልድ እንዲሸጋገሩ መስራትና የሃገር በቀል ዕውቀትን ማጠናከር እንደምገበባ ተናግረዋል። በዚህ ረገድ የዋቸሞ ዩኒቨረሲቲ የሃድያን ብሔር የዘመን አቆጣጠር ታሪክ : ባህልና ቋንቋ እንዲሁም ሌሎች ዕሴቶች ተሰንደው እንዲቀመጡና ለማስተማሪያነት እንዲውሉ ለማስቻል በጥናትና ምርምርና የተደገፈ ስራ በመስራት ላይ መሆኑን አመላክተዋል። በተጨማሪም ባህሉ ይበልጥ እንዲታወቅና በዩኔስኮ ተመዝግቦ ለአካባቢው ማህበረሰብ የሚገባውን ጥቅም እንዲያመጣና ከቱሪዝም አንጻር ሚናውን እንዲጫወት ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛል ብለዋል።
የመኔ ሸድዬ ባሮ - የጠንካራ የስራ ባህል፣ የአብሮነትና የሰላም ተምሳሌት
Sep 20, 2023 1323
በሽመልስ ጌታነህ (ኢዜአ) የመኔ ሸድዬ ባሮ የካፈቾ ብሄር ከአሮጌው ዘመን ወደ አዲሱ የሚሸጋገሩበት፣ የአዲስ ዘመን ብስራትና የዘመን መለወጫ በዓል ነው። በዓሉ የጠንካራ የስራ ባህል፣ የአብሮነትና የሰላም ተምሳሌት በዓል እንደሆነ ይነገርለታል። በዚህም የካፋ ብሄር ለዘመናት የገነባውና ጠንካራ የስራ ባህል፤ ተፈጥሮን የመጠበቅና የመንከባከብ እንዲሁም ከተለያዩ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ጋር ተቻችሎና ተፈቃቅሮ የሚኖር ሲሆን ቱባ ዕሴቱ ዛሬም ላለው ትውልድ መሰረት መሆኑን ያምኑበታል። የተለያዩ የታሪክ ድርሳናት እንደሚያሳዩት ከሆነ የካፋ ህዝብ ጠንካራ ንጉሳዊ ሥርዓት የነበረው፤ የታሪክና የቱባ ባህል ባለቤትም ነው። ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የታሪክ ባለሙያና የሀገር ሽማግሌ አቶ አሰፋ ገብረማሪያም የካፈቾ ብሄር ዘመን መለወጫ በሃገሬው አጠራር ''የመኔ ሸድዬ ባሮ'' በዓል የካፋ ህዝብ ከሚያከብራቸው በርካታ በዓላት ውስጥ ትልቅ ሥፍራ የሚሰጠው መሆኑን አፅንኦት ሰጥተው ይናገራሉ። በዓሉ ያለውን ግዝፈት ሲያመለክቱ በሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በውጭ ፀሐፍት ጭምር “ታላቁ በዓል ወይም (ግሬት ፌስቲቫል)” ተብሎ እንደሚጠራም ተናግረዋል። በዓሉ ታሪካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ዳራ ያለው ሲሆን ከጥንት ካፋ ንጉስ ጀምሮ በየአመቱ በድምቀት የሚከበር በዓል እንደሆነም ጠቁመዋል። የካፋ ህዝብ ከ14ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ከጎሳ መሪነት አንስቶ ጠንካራ የመንግስት መዋቅር የነበረው ታላቅ ህዝብ እንደሆነ ያነሱት አቶ አሰፋ፣ በዚህም በዓሉ በዘመኑ የነበሩ መንግስታት በዓል እንደነበረም አብራርተዋል። ዓመታዊ የሥራ አፈፃፀም የሚገመገምበት ጥሩ የሠራና የተሻለ አፈጻጸም ያስመዘገበ የሚሸለምበትና ለበለጠ ሥልጣን የሚታጭበት፤ ሰነፉ ደግሞ የሚወቀስበትና ስልጣኑ የሚነጠቅበት ታላቅ በዓልም ነው ብለዋል። ይህም በብሄሩ ዘንድ ለዘመናት የተሻገረ የጠንካራ የሥራ ባህል ግንባታ መሰረት ሆኖ የቆየ መሆኑን አንስተዋል። ይህ ሁሉ ሲከናወን በማህበረሰባዊ የህግ ተገዥነት መሰረት መሆኑ የተለየ እንደሚያደርገው ገልጸው ከሁሉ በፊት ሰላምን በማስቀደም መንግስትንና ህግን ማክበር እንዲሁም ህግ የሚመራው ህዝብ የበላይ መሆኑን አመላካች ሥርዓት መሆኑን አንስተዋል። በዓሉ ከአዝመራ ጋር የተያያዘ የዘመን አቆጣጠርን ተከትሎ እንደሚከበርም የታሪክ ባለሙያው አቶ አሰፋ ይገልጻሉ። እንደ ታሪክ ተመራማሪው ገለጻ የካፋ ህዝብ አብዛኛው አርሶ አደር አልፎም አርብቶ አደር ሲሆን ለአዝመራ የተለየ ትኩረት ይሰጣል፤ በዓሉ ሊከበር 77 ቀናት ሲቀሩት ህዝቡ የአዲስ ዘመን መለወጫ ብሎ ሃምሌ አንድ አዝመራውን እንደሚጀምርም ጠቁመዋል። የአዝመራ ወቅት ሊገባደድ 25 ቀናት ሲቀሩት (ከሼ ዋጦ) ብሎ አዝመራውን ያጠናቅቃል። ወቅቱም ጨለማው አልፎ በብርሃን የሚተካበት፤ ክረምቱ ለበጋ ቦታውን የሚለቅበት በመሆኑ አዲስ አመት መድረሱን ያሳውቃል። ያን ጊዜ በጥንት የካፋ ምክርቤት ከሚገኙ ሰባት የሚክረቾ አባላት ውስጥ አንዱ የሆነው አዲዬ ራሾ ፤ የንጉሱ መቀመጫ በሆነው ቦንጌ ሸምበቶ በዓሉን ለማክበር ከየአቅጣጫው ለሚመጣው ህዝብ መንገዶችን በማፅዳት እና ለወንዞች ድልድይ በማበጀት በዓሉ መድረሱን ያበስራል። ያን ጊዜ በዓሉን ለማክበር ህዝብ ከያለበት አቅጣጫ ወደ ቦንጌ ሸምበቶ ይተማል። ህዝቡ በቦንጌ ሸምበቶ ከተሰበሰበ በኋላም ንጉሱ በተገኙበት የእያንዳንዱ ወራፌ ራሾ ሥራ ይገመገማል፤ ጥሩ ሥራ የሠራ ጠንካራ መሪ ይሸለማል፤ ለበለጠ ስልጣንም ይታጫል፤ ሀላፊነቱን በተገቢ ሁኔታ ያልተወጣው ደግሞ ይመከራል፣ ይወቀሳል አልፎም ስልጣኑን ይነጠቃል። ዛሬም ሀገራችን ይህ አይነቱን ጠንካራ የሥራ ባህል አብዝታ ትሻለች፤ እንዲህ አይነት ሀገር በቀል ዕውቀቶች ትውልዱን በጠንካራ ሥነ-ምግባርና የሥራ ባህል ለመገንባት ትልቅ ድርሻ አላቸው። በተጨማሪም በዓሉ ቅሬታዎችን ለመፍታትና ሰላምን ለማጠናከር ትልቅ አስተዋፅኦ አለው ፤ ቂምና ጥላቻን ይዞ ወደ ንጉሱ ፊት መቆምም ይሁን ወደ አዲሱ ዓመት መሻገር ነውር ተደርጎ የሚወሰድ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ወደ በዓሉ ከመምጣቱ አስቀድሞም ይሁን በበዓሉ ወቅት የተጣላ ይታረቃል፤ ጥላቻም በፍቅር ይተካል ብለዋል የታሪክ ተመራማሪው። እንዲህ አይነቱ ሀገር በቀል ዕውቀት ጠንካራ ባህል ለመገንባት፤ ቅራኔዎችን በሰላም ለመፍታትና ማህበራዊ ግኑኝነቶችን ለማጠናከር ትልቅ ፋይዳ ስላላቸው በትምህርት ሥርዓት ውስጥ አካቶ ማስተማርና ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ ይገባል ሲሉም ሃሳባቸውን አካፍለዋል። ሌላኛው የሀገር ሽማግሌና የካፋ፣ጫራ እና ናኦ የባህል ምክርቤት አባል አቶ ፀጋዬ ገብረማሪያም እንደሚሉት የካፋቾ ''የመኔ ሸድዬ ባሮ'' በዓል ማህበራዊ ግንኙነትን በማጠናከሩ ረገድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው በዓል ነው። ምክንያቱ ደግሞ፣ በዓሉን ለማክበር በአካባቢው ያሉ፣ በሌሎች የሃገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ እንዲሁም ባህር ማዶ የሚገኙ የአካባቢው ተወላጆች የሚሰበሰቡበት ታላቅ በዓል ስለሆነ ነው ብለዋል። በዚህም የተራረቀ የሚገናኝበት፤ የተጠፋፋ የሚጠያየቅበት ሲሆን ህዝቡ በአንድ ላይ ተሰብስቦ በንጉሱ ተመርቆ፣ በልቶ ጠጥቶ እንዲሁም ተጫውቶ ወደ ቀጣዩ አመት በደስታና በታላቅ ተስፋ የሚሸጋገርበት እንደሆነም አብራርተዋል። ይህ ባህል በተለያዩ ምክንያቶች ከ120 ዓመታት በላይ ሳይከበር እንደቆየ የገለፁት አቶ ፀጋዬ ገብረማሪያም ዳግም መከበር ከጀመረበት ስምንት ዓመታት ወዲህ የነበረውን ታሪክና ባህል በሚያስቀጥል መልኩ በየዓመት በድምቀት እየተከበረ መሆኑንም አንስተዋል። ወጣቱ ትውልድ ባህሉንና ታሪኩን አውቆ እንዲኖርና እንዲያስቀጥል ግንዛቤ የመፍጠርና የማስተማር ሥራ በሰፊው እየተሠራ እንደሆነም ገልፀዋል። ከዚህ ባለፈም ባህሉንና ታሪኩን ለማስቀጠል የባህል ምክር ቤቱ የወረዳ የባህል ምክር ቤቶችን የማጠናከር፣ ታሪካዊ ቅርሶችን የመሰብሰብና የማደራጀት ሥራ እየሠራ ነውም ብለዋል። በዓሉ አንድነትን የሚያጠናክር፣ ጠንካራ የሥራ ባህልን የሚያበረታታ እና የተፈጥሮ ጥበቃን የሚያጠናክር በመሆኑ ከካፋ ብሔረሰብ በዓልነቱ ባለፈ የሀገርና የአለም ቅርስና ሀብት እንዲሆን ሰፊ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባም አቶ ፀጋዬ አሳስበዋል። የካፋቾ ዘመን መለወጫ በዓል (የመኔ ሸድዬ ባሮ) መሠረቱን ሳይለቅ ለትውልድ እንዲተላለፍ በዞን ደረጃ እየተሠራ መሆኑን የገለፁት የካፋ ዞን ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ሃላፊ አቶ ተሾመ አምቦ ዘንድሮም ለዘጠነኛ ጊዜ በአደባባይ ለማክበር ሰፊ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል። በዓሉ በሁሉም የካፋ ህዝብ በጋራ ያለምንም ልዩነት የሚከበር ታሪካዊ በዓል ሲሆን አለም አቀፋዊ እውቅና አግኝቶ በዩኔስኮ እንዲመዘገብ ለማስቻል ከተለያዩ ምሁራንና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በመሆን የተለያዩ ጥናቶች እየተሠሩ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ በበዓሉ ንጉሱ የተራቡትን የሚመግቡበት (ጮንጎ) የተሰኘ ስርዓት የሚፈፀምበትና የተጣሉ የሚታረቁበት ስርዓት እንደሚፈፀም የገለፁት አቶ ተሾመ አሁንም በዓሉ በየዓመቱ ሲከበር ይህ ሥርዓት ይከወናል ብለዋል። ቀጣይ ይህን በዓል በሰፊው አስተዋውቆ ወደ ቱሪዝም በማሳደግ ህዝቡ ከዘርፉ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆን የሚያስችሉ ሥራዎች እንደተጀመሩም ሃላፊው ገልፀዋል። የዘንድሮው የ2016 ዓ.ም የካፊቾ ዘመን መለወጫ በዓል በቦንጋ ከተማ ከመስከረም 12 እስከ መስከረም 13/2016 ዓ.ም በፓናል ውይይትና በተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች በደማቅ ሁኔታ እንደሚከበርም ጠቁመዋል።
ልዩ ዘገባዎች
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 5575
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 10542
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት። እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
በጂንካ ከተማ የተመረተው 23 ኪሎ ግራም የሚመዝነው የስኳር ድንች "በአፍሪካ ትልቁ ስኳር ድንች" በሚል ተመዘገበ
Mar 13, 2023 3993
ጂንካ መጋቢት 4/2015 (ኢዜአ):- በጂንካ ከተማ ደሙዝ ሰፈር የተመረተው እና 23 ኪሎ ግራም የሚመዝነው ስኳር ድንች በአፍሪካ የድንቃ ድንቆች መዝገብ "በአፍሪካ ትልቁ ስኳር ድንች" በሚል መመዝገቡ ተገለጸ። በአዲስ አበባ በተካሄደው የእውቅና ስነስርዓት ላይ የአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ስራ አስኪያጅ አቶ አሸናፊ አለም ለስኳር ድንቹ ባለቤት አቶ ኢሳያስ ጊዜአለው የእውቅና ምስክር ወረቀት አስረክበዋል። ከዚህ ቀደም በአፍሪካ 10 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች መቅረቡን አቶ አሸናፊ ለኢዜአ ገልጸዋል። “ነገር ግን 23 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች በአፍሪካ ደረጃ ሲቀርብ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው” ብለዋል። በዓለም የድንቃ ድንቅ መዝገብ 37 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች መመዝገቡንና በደሙዝ ሰፈር የተገኘው ስኳር ድንች በ14 ኪሎ ግራም ዝቅ ብሎ ከዓለም የ”ሁለተኛነት” ደረጃ ላይ እንደሚያስቀምጠው አመልክተዋል። የስኳር ድንቹ ባለቤት አቶ ኢሳያስ ጊዜያለው ስኳር ድንቹ በአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ላይ በመስፈር የኢትዮጵያን ስም በማስጠራቱ መደሰታቸውን ገልጸዋል። ስኳር ድንቹ እውቅና እንዲያገኝ የዜና ሽፋን ለሰጠው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ምስጋቸውን አቅርበዋል። ኢዜአ የካቲት 19 ቀን 2015 ዓ.ም “በጂንካ ከተማ ደሙዝ ሰፈር 23 ኪሎ ግራም የሚመዝን አንድ የስኳር ድንች መመረቱ ተገለጸ” በሚል መዘገቡ የሚታወስ ነው።
ዶክተር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ እውቅና አገኙ
Mar 9, 2023 4843
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 30/2015 የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ በሩዋንዳ ኪጋሊ በተካሄደው በአፍሪካ ዓለም አቀፍ የጤና አጀንዳ ኮንፈረንስ (AHAIC)2023 ላይ እውቅና ተሰጣቸው። ሚኒስትሯ በሩዋንዳ ኪጋሊ ትላንት በተካሄደው Africa Health Agenda International Conference (AHAIC) 2023 ላይ የተበረከተላቸውን Women in Global Health Award የእውቅና ሽልማት በተወካያቸዉ በኩል ተቀብለዋል። እውቅናው በጤና ልማት ውስጥ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በመቋቋምና በመፍታት፣ የጤና አገልግሎት ጥራትና ፍትሀዊ ተደራሽነት እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ሽፋን ላይ ትኩረት ሰጥተው ለሚሰሩ አመራሮች የሚሰጥ መሆኑም ተመላክቷል። ለመጪዎቹ ትውልዶች አርዓያ ለሆኑ የአፍሪካ ሴት መሪዎች የሚሰጠው ሽልማቱ የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰም ለዜጎች የተሻለና ዘላቂ ጤናን ለማምጣት በሚደረግ ጥረት ውስጥ ላበረከቱት የላቀ የመሪነት ሚና ከአምሪፍ ሄልዝ አፍሪካ እውቅናውን አግኝተዋል።
መጣጥፍ
“ዮ-ማስቃላ''- ሁሉም የሚደሰትበት በዓል
Sep 23, 2023 797
በሳሙኤል አየነው የሰላም፣ የአብሮነት፣ የፍቅር፣ የመቻቻልና የአንድነት ተምሳሌት የሆነው የጋሞ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል “ዮ-ማስቃላ” ከወርሃ መስከረም አጋማሽ ጀምሮ በተለያዩ ባህላዊ ሁነቶች በድምቀት ይከበራል ። በተለያየ ምክንያት በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ተራርቀው የነበሩ ወገኖች ወደ የአካባቢያቸው በመመለስ ከቤተሰቦቻቸው ብሎም ከቀየው ህብረተሰብ ጋር አብረው የሚያከብሩት የዓመቱ ታላቅ በዓል ነው ። ታዲያ በዓሉን በድምቀት ለማክበር ወንዶች ሰንጋ በሬ ለመግዛት እንዲሁም ለትዳር አጋሮቻቸውና ለልጆቻቸው ልብስና ጌጣ ጌጥ የሚሆን ገንዘብ መቆጠብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ሴቶችም ለባህላዊ ምግቦች፣ ለቅመማ ቅመም፣ ለቅቤና ለባህላዊ መጠጦች እህል ግዥ የሚሆን ገንዘብ ዓመቱን ሙሉ ሲቆጥቡ ይከርማሉ። መስከረም ወር ከገባበት ዕለት አንስተው ወንዶችም ሆኑ ሴቶቹ በቆጠቡት ገንዘብ በየፊናቸው ለበዓሉ የሚሆኑ ቁሳቁሶችን ማቅረብ ይጀምራሉ። ይህም የዝግጅት ጊዜ “እንግጫ” በመባል ይጥራል። በ”ዮ--ማስቃላ” ጊዜ አብሮነት እንጂ ግለኝነት የሚባል ነገር በጋሞዎች ዘንድ ፈጽሞ አይታሰብም፤ አብሮ እርድ ማካሄድ፣ አብሮ መመገብ፣ አብሮ መጠጣት፣ አብሮ መጫወት የጋሞዎች መገለጫ ነው። እንደ ሌሎቹ በዓላት ሁሉ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ወገኖችም በዓሉን እንዴት እናሳልፍ የሚል ስጋት አያድርባቸውም። ምክንያቱም የሌለውም ካለው ጋር አብሮ የሚቋደስበት፣ የሚደሰትበት፣ የሚተሳሰብበትና የሰብአዊነት ልክ የሚንጸባረቅበት ልዩ ድባብ ያለው በዓል ነውና ዮ-ማስቃላ ። የጋሞ የሀገር ሽማግሌ አቶ አመሌ አልቶ ስለ “ዮ--ማስቃላ” በዓል በትንሹ እንዲያወጉን ጠይቀናቸው በዓሉ ለሰው ልጆች ብቻ ሳይሆን እንስሳትና አዕዋፋት ሁሉ የሚደሰቱበት እንደሆነ ነግረውናል። በአካባቢው ቋንቋ ተፈጥሮ ሁሉ በዓሉን በደስታ እንደሚያሳልፍ ለመግለጽ “ካፎስ ካናስ ማስቃላ” በማለት የሚገለጽ ስሆን “ለሰው ብቻ ሳይሆን ለእንስሳትም መስቀል ነው” እንደማለት ነው ብለዋል። በዓሉ ከመድረሱ ከሶስት ወራት አስቀድሞ በየአካባቢው ለእንስሳት የግጦሽ ሥፍራ ተከልሎ የሚዘጋጅ ሲሆን ችቦው በሚለኮስበት በደመራው ዕለት የቤት እንስሳት በሙሉ በዚያው የሚሰማሩ ይሆናል። ዓመቱን ሙሉ ሲያርሱ የነበሩ የእርሻ መሣሪያዎችም በበዓሉ ጊዜ ታጥበውና በቅቤ ታሽተው በክብር ይቀመጣሉ። ክብር ለሰው ልጆች ብቻ ሳይሆን ለእንስሳትና ለእርሻ መሣሪያዎችም ይሰጣል። በባህሉ መሠረት ችቦ በሚወጣበት ሰዓት አባት የራሱን ችቦ ለኩሶ የቤቱን ምሰሶ፣ የከብቶችን ጋጣና የበር ጉበኖችን ግራና ቀኝ በችቦው ጫፍ በማነካካት ወደ ውጭ ካወጣ በኋላ ወንድ ልጆች የየራሳቸውን ችቦ ተራ በተራ እየለኮሱ አባታቸውን ተከትለው “ዮ---ማስቃላ” እያሉ ወደ ደመራ ቦታ ያመራሉ። ከዚያም አባት በቅድሚያ ችቦውን ከለኮሰ በኋላ ልጆች ደግሞ ተከትለው ደመራውን ይለኩሳሉ። ከዚህ ፕሮግራም መልስ ወደ ቤት ተመልሰው የተዘጋጀውን ገንፎ በአንድ ወጭት ላይ “ዮ--ማስቃላ”እያሉ ሁሉም የቤተሰብ አባላት፣ ዘመድ አዝማድና ጎረቤት ተሰባስበው በጋራ ይመገባሉ። በ”ዮ--ማስቃላ” በዓል በዋናነት እርድ የሚከወን ሲሆን ቁርጥ፣ ጎረድ ጎረድ፣ ክትፎና የወጣ ወጥ ዓይነቶች ተሠርተው ለምግብነት ይቀርባሉ። ከባህላዊ ምግቦች ደግሞ የገብስ ቅንጬ፣ የቆጮና ገብስ ውህድ ቂጣ፣ የቡላ ፍርፍር፣ ሀረግ ቦዬ፣ እንዲሁም ከመጠጥ አይነቶች ደግሞ ቦርዴ፣ ጠላ፣ የማርና የቦርዴ ጠላ ውህድና ሌሎች ተወዳጅ ምግቦችና መጠጦች ይዘጋጃሉ። በ”ዮ--ማስቃላ” በዓል ዕለት የሚቀራረቡ ጎረቤታሞች በጋራ ሆነው አማካይ በሆነ ሥፍራ ላይ የእርድ ሥነሥርዓት ያከናውናሉ። የእርድ ሥነ-ሥርአቱም በደመራው ዕለትና ማግስት እንደ ህብረተሰቡ ይሁንታ የሚፈጸም ይሆናል። ከማግስቱ ጀምሮ የተዘጋጀውን ሥጋ በጋራ እየበሉና እየጠጡ የበዓሉን ድባብ የሚያስቀጥሉ ሲሆን “ዱንግዛ” በተሰኘው የጋሞ ባህላዊ ጥበብ ልብስ ደምቀው በጌጣጌጥ አሸብርቀው ሁሉም በየአደባባዩ በባህላዊ ጫዋታዎች እየተደሰተ በዓሉን ያከብራል። ሰላም፣ ፍቅር፣ አንድነትና አብሮነት ካለ በአዲሱ ዓመት ምድሪቱ ተገቢውን ምርት እንደምትሰጥ ሁሉም ሰው በተሰማራበት መስክ ውጤታማ እንደሚሆን ይታመናል። ከዚም የተነሳ በአሮጌው ዓመት ሃዘን ላይ የነበሩ ወገኖች ሙሉ በሙሉ ሀዘናቸውን በመተው በአዲስ መንፈስ ወደ መደበኛው ህይወት ይመለሳሉ። የተጣሉ ወገኖች ቂም ይዘው አዲስ ዓመትን መሻገር በጋሞዎች ዘንድ ነውር በመሆኑ በባህላዊ ሸንጎ ሥርአት /ዱቡሻ/ በጋሞ አባቶች አሸማጋይነት እርስ በርስ ተነጋግረው በመታረቅ አዲሱን ዓመት በጋራ ያበስሩታል። በሌላ መንገድ “ዮ..ማስቃላ” በዓል ተጠብቆ ወጣቶች የሚተጫጩበት፣ የተጫጩት ደግሞ ጋብቻ የሚከውኑበት እንዲሁም ያገቡት በየገበያው ዕለት “ሶፌ” የሚባል ሥነ-ሥርዓት በማከናወን በማህበራዊ ህይወት ማህበረሰቡን በይፋ የሚቀላቀሉበት መሆኑን ጋሽ አመሌ አውግተውናል። ጋሞዎች ከሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ጋር በመሆን በአብሮነት ለሁለት ሳምንታት በደስታ ካሳለፉ በኋላ ወደ ግብርና ሥራቸው በመመለስ ቀደም ሲል በክብር ያስቀመጧቸውን የእርሻ መሣሪያዎች በማንሳት ወደ እርሻ ሥራ ይገባሉ። እስከ ታህሳስ ወር መውጫ ድረስ የበዓሉ ድባብ ሳይጠፋ ይቆይና በመጨረሻም የመሰናበቻ ድግስ ወይም “ጮዬ ማስቃላ” በማዘጋጀት በህብረት ከተመገቡና ከጠጡ በኋላ የዓመት ሰው ይበለን፣ ዓመቱ የሰላም፣ የጤና፣ የበረከት ይሁን በማለት በመመራረቅ “ዮ--ማስቃላ”ን ይሸኛሉ። በዓሉ የህዝቡን ሰላም ፣አንድነትና አብሮነት የሚያንጸባርቅ ልዩ በዓል ነው በማለት የጋሞ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ሃላፊ አቶ ሞናዬ ሞሶሌ የጋሞ የሀገር ሽማግሌ የሆኑት የአቶ አመሌ አልቶን ሃሳብ ይጋራሉ። ባህላዊ እሴቱ ከትውልድ ወደ ትውልድ ተጠብቆ እንዲቆይ “ዮ--ማስቃላ” ትልቅ ድርሻ አለው። የባህል እሴቶች ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፉ በጥናትና ምርምር በማስገፍና የቋንቋና ባህል አውደ ጥናት በየዓመቱ እየተደረገ እንደሆነም ነግረውናል። አባቶች በልዩነት ውስጥ ያለንን አንድነት እንዳቆዩልን ሁሉ ወጣቶችም ኢትዮጵያዊ ለዛ ያላቸው የጋራ እሴቶች ሳይበረዙና ሳይከለሱ ጠብቀው ለትውልድ የማስተላለፍ ሃላፊነት አለባቸው የሚለውን የንግግራቸው ማሳረጊያ አድርገዋል።
የዕልፍ ሕጻናትን ዕጣ ፈንታ ከሞት ወደ ሕይወት የለወጠው ወጣት ላሌ ላቡኮ
Sep 8, 2023 1197
በሀገራችን በርካታ አካባቢዎች የታዳጊዎችን ተስፋና ህልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የሚገዳደሩ ከባህላዊ እምነት ጋር የተቆራኙ አይነተ ብዙ ጎጂ ባህላዊና ልማዳዊ ድርጊቶች እና ክዋኔዎች አሉ። ለአብነትም ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የተለመደው እና ከህጻናት ጥርስ አበቃቅል ጋር የተያያዘው ’ሚንጊ' የሚሰኘው ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት ይጠቀሳል። በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣቸዋል። ከዚህ ጋር በማገናኘትም የሚወለዱ ህጻናት የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ከሆነ እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥመዋል። ይህ ልማድ “ሚንጊ” ተብሎ የሚጠራ ሲሆን አያሌ ህጻናትን ቀጥፏል። ይህ ብቻም ሳይሆን የማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። ሚንጊ ተብለው የተፈረጁ ህጻናት በማህበረሰቡ ዘንድ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… እንደሚያመጡ ስለሚቆጠር ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል ዕጣ ይገጥማቸዋል። ሚንጊንና መሰል በየማህበረሰቡ ዘንድ ለዘመናት የተለመዱ ጎጂ ድርጊቶችን ለማስቀረት እና ማህበረሰብ አቀፍ ለውጥ ለማምጣት ግን ውስብስብ እና ጊዜ የሚጠይቅ ጉዳይ ነው። ላሌ ላቡኮና መሰል ብርቱና አርቆ አሳቢ ሰዎች ግን ባደጉበት ብርቱ ጥረት የማህብረሰብን አስተሳስብ በመለወጥ ለዘመናት ለሚከወኑ ውስብስብ ችግሮችን መፍትኤ መስጠት ችለዋል። ላሌ ላቡኮ በተወለደበት ቀዬ እና አባል በሆነበት ደመ ከልብ ሆነው የሚቀሩ ህጻናትን ዕጣ ፈንታ ከወንዝ፣ ከገደልና ከጫካ ከመጣል ተርፈው ለወግና ማዕረግ እንዲበቁ አስችላል። በአጉል ባህል ሕይወታቸውን የሚነጠቁ ዕልፍ አዕላፍ ህጻናት ነፍስ እንዲዘሩ በማድረግ ትውልድ ያሻገረ፣ ማህበረሰብን የለወጠ አርበኛ ነው። ላሌ ላቡኮ ይህን ነባር ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት ለመቃወምና መፍትሄ ለማምጣት ያነሳሳው ሁለት እህቶቹን ጨምሮ ምንም ነፍስ ያላወቁ ሕጻናት በሚንጊነት ተፈርጀው ሲቀጠፉ በማየቱና በመስማቱ እንደሆነ ይናገራል። ከ17 ዓመታት በፊት ‘ኦሞ ቻይልድ’ በሚል ባቋቋመው ድርጅት 'ሚንጊ' የተባሉ 58 ሕፃናትን ከገዳዮች ፈልቅቆ ከሕልፈት ወደ ሕይወት ለውጧል፣ ለቁም ነገር ለማብቃትም እያስተማራቸው ይገኛል። እህቶቹን ጨምሮ የትውልድ መንደሩ ሕጻናትን ሕይወት ለመቀጠፍ የዳረጋቸው የሚንጊ ድርጊት የሚፈጸመው፣ በማህበረሰቡ ዕውቀት ማነስ ነው ብሎ ያምናል። በዚህም ይህን አስከፊ ድርጊት እና አስተሳሰብ ለመቀየር ቆርጦ በመነሳቱ ቤተሰቡን ጨምሮ ከማህበረሰቡ መገለል እስከ ማስፈራሪያ ጥቃቶች አስተናግዷል። እርሱ ግን ፈተናዎች ሳይበግሩት በዓላማው ጸንቶ፣ ትዕግስትና ብልሃት ተላብሶ ሸውራራ ማህበረሰብ አቀፍ አመለካከቶችን መስበር ችሏል። የሚንጊ ባህል አሁንም ሙሉ ለሙሉ እንዳልተቀረፈ የሚናገረው ላሌ፣ ስር ነቀል የአስተሳስብ ለውጥ ለማምጣት ለህብረተሰቡ አሁንም ብርቱ ግንዛቤ የመፍጠር ስራዎች እንደሚገቡ ገልጿል። ላሌ በመሰረተው ድርጅት ከሚማሩ ሕጻናት ባሻገር ከ300 በላይ ህጻናት ከቤተሰባቸው ዘንድ ሆነው ለመማር እንዲችለኩ ማድረጉንም ይናገራል። ሕፃናቱን ከሞት አፋፍ ታድጎ ከራሳቸው ሕልውና ባለፈ ለቁም ነገር እንዲበቁና ለሀገርና ለወገን የሚበጁ ሰዎች እንዲሆኑ በመስራቱ አዕምራዊ እርካታ እንደሚሰማው ይገልጻል። ላሌ የሚንጊን ጎጂ ድርጊት ከመታደጉ በተጨማሪ በደቡብ ኦሞ ትምህርት ቤት ገንብቶ ከ700 በላይ ተማሪዎችን እያስተማረ ይገኛል። ናሽናል ጂኦግራፊ፣ ቴድ ቶክ፣ የሰብዓዊ መብቶች ተቋም እና የበጎ ሰው ሽልማት ድርጅት የላሌን ትውልድ የመታደግ ተግባር ዕውቅና ከሰጡት ወስጥ ይጠቀሳሉ።