ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ነገ ለምክር ቤቱ ማብራሪያ እና ምላሽ ይሰጣሉ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ነገ ለምክር ቤቱ ማብራሪያ እና ምላሽ ይሰጣሉ

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 25/2017(ኢዜአ):- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ነገ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመገኘት ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 42ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ያደርጋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በስብሰባው ላይ የመንግስት የ2017 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፃም አስመልክቶ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ ይሰጣሉ።
ምክር ቤቱ የፌዴራል መንግሥት የ2018 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት እንደሚያፀድቅ ለኢዜአ በላከው መረጃ አመልክቷል።
በስብሰባው ላይ ጥሪ የተደረገላቸው ተጋባዥ እንግዶች፤ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች ይገኛሉ።