ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
በበጀት ዓመቱ ያለፉት ወራት በአምቦ ከተማ ከ9 ሺህ ለሚልቁ ወጣቶች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል
Feb 17, 2026 31
አምቦ፤ የካቲት 10/2018 (ኢዜአ)፦ በበጀት ዓመቱ ያለፉት ወራት ከ9 ሺህ ለሚበልጡ ወጣቶች የሥራ ዕድል መፈጠሩን የአምቦ ከተማ አሥተዳደር የሥራ ዕድል ፈጠራ እና ክኅሎት ጽሕፈት ቤት ገለጸ። የሥራ ዕድሉ የተፈጠረው በከተማ ግብርና፣ በአገልግሎት ዘርፍ፣ በኮንስትራክሽን እና ሌሎችም መሆኑን የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ እሸቱ አበራ ለኢዜአ ተናግረዋል። በዚህም መሠረት በግብርና ዘርፍ ለተሰማሩት ወጣቶች 20 ሺህ 554 ሔክታር መሬት እንዲሁም በአገልግሎት ለተሰማሩት ለመሥሪያና ለመሸጫ የሚሆኑ 37 ሼዶች ተገንብተው መተላለፋቸውን አብራርተዋል። ከሥራ ፈጠራው ጎን ለጎን ለ591 ኢንተርፕራይዞች 156 ሚሊየን ብር የገበያ ትሥሥር መፈጠሩንም ጠቁመዋል። የሥራ ዕድል የተመቻቸላቸው ወጣቶችም እስካሁን ከ318 ሚሊየን ብር በላይ በባንክ መቆጠባቸውን ገልጸዋል። በበጀት ዓመቱ ለ13 ሺህ ወጣቶች በተለያዩ ዘርፎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ እየተሠራ መሆኑንም አስገንዝበዋል።
የአፋር ክልልን ተፈጥሯዊ ፀጋ በመጠቀም ስንዴን በስፋት የማልማቱ ሥራ ቀጥሏል
Feb 17, 2026 46
አዲስ አበባ፤ የካቲት 10/2018 (ኢዜአ)፡- በአፋር ክልል ያለውን ሰፊ ለም መሬትና የውኃ አማራጮች በመጠቀም ስንዴን በስፋት የማልማቱ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ አስታወቀ። የስንዴን ምርታማነት ለመጨመርም ለአካበቢው የአየር ሁኔታ የተመቸ የዘር ማላመድ ሥራ በሰርቶ ማሳያና በከፊል አርብቶ አደሮች ማሳ ላይ በስፋት እየተካሄደ መሆኑን ነው በቢሮው የእርሻ ዘርፍ ኃላፊ አሕመድ አሚን የገለጹት። በዚህም መሠረት በዘንድሮው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት 1 ሺህ 442 ሔክታር ላይ ዝርያን የማላመድ ሥራ እየተሠራ መሆኑን ለኢዜአ አረጋግጠዋል። ይህም የዘር አቅርቦትን በራስ ዐቅም ለመሸፈንና የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የተያዘው ግብ እንዲሳካ ዕድል የሚፈጥር መሆኑን አመላክተዋል። ከስንዴ ምርት ባለፈ ሱፍና ሩዝን በሰፊው በማላመድ ተስፋ ሰጪ ውጤቶች እየታዩ መሆኑን ጠቁመዋል። የግብዓት አቅርቦት ዘርፍ ኃላፊ ሃሩን አሊ በበኩላቸው፤ የስንዴ ዘር ብዜት ከማካሄድ ባለፈ በማዳበሪያና ሌሎች የግብርና ግብዓቶች አቅርቦት ረገድ ተስፋ ሰጪ ሥራዎች እየተሠሩ ነው ብለዋል። የስንዴ ዘርን በማላመድ ሥራ ለ15 ሺህ ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠሩን ያስታወቁት ደግሞ በቢሮው የሰብል ልማት ዳይሬክተር ሃመዱ መሐመድ ናቸው።
ብልፅግና ፓርቲ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ታሪክ የዜጎችን እኩል ተሳትፎና ውሳኔ ሰጪነት እውን ማድረግ የቻለ ህብረ ብሄራዊ ፓርቲ ነው- ርእሰ መስተዳድር ሙስጠፋ ሙሁመድ
Feb 17, 2026 69
ጅግጅጋ፤ የካቲት 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልፅግና ፓርቲ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ታሪክ የዜጎችን እኩል ተሳትፎና ውሳኔ ሰጪነት እውን ማድረግ የቻለ ህብረ ብሄራዊ ፓርቲ መሆኑን የሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሐመድ ገለጹ። የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ መወዳደሪያ ምልክቱን (የስንዴ ነዶ) እና ማኒፌስቶውን በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ለህዝቡ አስተዋውቋል። በዚሁ መድረክ ላይ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ርእሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሐመድ፤ ብልፅግና በኢትዮጵያ ፖለቲካ ታሪክ የዜጎችን እኩል ተሳትፎና ውሳኔ ሰጪነት እውን ማድረግ የቻለ ህብረ ብሄራዊ ፓርቲ መሆኑን ገልጸዋል። በኢትዮጵያ ፖለቲካ የዳር ተመልካችነት ቀርቶ እኩል ተሳትፎና ውሳኔ ሰጭነት የተረጋገጠበት፣ በሀገሩ ጉዳይ ሁሉም ያገባኛል ብሎ የሚሰራበትና የመሪነት እድል የሚያገኝበት አካታች የዴሞክራሲ ስርአት መፍጠሩን ተናግረዋል። ፓርቲው በተለይም በሶማሌ ክልል ሁለንተናዊ የልማት ስራዎች እንዲከናወኑና የህዝብ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ በመስራት የሚጨበጥ ውጤት ስለማስመዝገቡም ገልጸዋል። በመሆኑም በዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ ብልጽግናን መምረጥ፣ የልማት ስራዎችን ማስቀጠልና የህዝብ ተጠቃሚነትን ይበልጥ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ አስረድተዋል። በመርሃ-ግብሩ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የፓርቲው ደጋፊዎችና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።
በሻምፒዮንስ ሊግ ጥሎ ማለፍ ማጣሪያ ቤኔፊካ ከሪያል ማድሪድ ሞናኮ ከፒኤስጂ የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ይጠበቃሉ
Feb 17, 2026 52
አዲስ አበባ፤ የካቲት 10/2018 (ኢዜአ)፦ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ማጣሪያ የመጀመሪያ ዙር መርሐ ግብር ዛሬ እና ነገ ይካሄዳል። በስታዲዮ ዳ ሉዝ ምሽት አምስት ሰዓት ላይ ቤኔፊካ ከሪያል ማድሪድ ይጫወታሉ። በሻምፒዮንስ ሊጉ አዲስ ፎርማት ቤኔፊካ 24 እና ሪያል ማድሪድ ዘጠነኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል። ሁለቱ ቡድኖች በቅርቡ በውድድሩ ላይ አድርገውት በነበረው ጨዋታ ቤኔፊካ 3 ለ 2 አሸንፏል። ይህም ቤኔፊካን ወደ ጥሎ ማለፍ እንዲገባ ያደረገ ሲሆን፤ ሪያል ማድሪድ በቀጥታ ወደ ጥሎ ማለፍ እንዳይገባ ምክንያት ሆኗል። ጆዜ ሞውሪኒዮ ቀድመው ያሰለጠኑትን ሪያል ማድሪድ በድጋሚ ይገጥማሉ። በሌላኛው መርሐ-ግብር ሞናኮ ከፒኤስጂ በሉዊስ ሁለተኛ ስታዲየም ምሽት አምስት ሰዓት ላይ ይጫወታሉ። ሞናኮ በሊግ እርከን የውድድር ምዕራፍ 21ኛ፣ ፒኤስጂ 11ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል። ፒኤስጂ የወቅቱ የሻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊ ነው። በሌሎች መርሐ-ግብሮች ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ከአትላንታ ምሽት አምስት ሠዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። ጋላታሳራይ ከጁቬንቱስ ምሽት 2 ሰዓት ከ45 ላይ ይጫወታሉ። የመልስ ጨዋታዎች በቀጣይ ሳምንት ይደረጋሉ። በማጣሪያው የሚሳተፉት ክለቦች በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ አዲሱ የውድድር ፎርማት ከ9ኛ እስከ 24ኛ ደረጃ ይዘው ያጠናቀቁ ናቸው። ከ36 ክለቦች መካከል በስምንት ጨዋታዎች የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ስምንት ቡድኖች በቀጥታ ወደ ጥሎ ማለፉ ገብተዋል። አርሰናል፣ ባየር ሙኒክ፣ ሊቨርፑል፣ ባርሴሎና፣ ማንችስተር ሲቲ፣ ቼልሲ፣ ቶተንሃም ሆትስፐርስ እና ስፖርቲንግ ሊዝበን በቀጥታ ጥሎ ማለፉን የተቀላቀሉ ቡድኖች ናቸው።
የኤፍኤ ካፕ አምስተኛ ዙር ድልድል ይፋ ሆነ
Feb 16, 2026 68
አዲስ አበባ፤ የካቲት 9/2018 (ኢዜአ)፦ የኤፍኤ ካፕ አምስተኛ ዙር እጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ማምሻውን ተከናውኗል። በዚሁ መሰረት ማንስፊልድ ታውን ከአርሰናል፣ ኒውካስትል ዩናይትድ ከማንችስተር ሲቲ፣ ዎልቭስ ከሊቨርፑል እና ሬክስሃም ከቼልሲ ይጫወታሉ። ሊድስ ዩናይትድ ከኖርዊች ሲቲ፣ ፉልሃም ከሳውዝሃምፕተን፣ ዌስትሃም ዩናይትድ ከማክስፊልድ እና ብሬንትፎርድ አሸናፊ እንዲሁም ሰንደርላንድ ከፖርት ቫሌ እና ብሪስቶል ሲቲ አሸናፊ ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። የኤፍኤ ካፕ አምስተኛ ዙር መርሐ-ግብር የካቲት 28 እና 29 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል።
ፖለቲካ
ብልፅግና ፓርቲ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ታሪክ የዜጎችን እኩል ተሳትፎና ውሳኔ ሰጪነት እውን ማድረግ የቻለ ህብረ ብሄራዊ ፓርቲ ነው- ርእሰ መስተዳድር ሙስጠፋ ሙሁመድ
Feb 17, 2026 69
ጅግጅጋ፤ የካቲት 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልፅግና ፓርቲ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ታሪክ የዜጎችን እኩል ተሳትፎና ውሳኔ ሰጪነት እውን ማድረግ የቻለ ህብረ ብሄራዊ ፓርቲ መሆኑን የሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሐመድ ገለጹ። የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ መወዳደሪያ ምልክቱን (የስንዴ ነዶ) እና ማኒፌስቶውን በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ለህዝቡ አስተዋውቋል። በዚሁ መድረክ ላይ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ርእሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሐመድ፤ ብልፅግና በኢትዮጵያ ፖለቲካ ታሪክ የዜጎችን እኩል ተሳትፎና ውሳኔ ሰጪነት እውን ማድረግ የቻለ ህብረ ብሄራዊ ፓርቲ መሆኑን ገልጸዋል። በኢትዮጵያ ፖለቲካ የዳር ተመልካችነት ቀርቶ እኩል ተሳትፎና ውሳኔ ሰጭነት የተረጋገጠበት፣ በሀገሩ ጉዳይ ሁሉም ያገባኛል ብሎ የሚሰራበትና የመሪነት እድል የሚያገኝበት አካታች የዴሞክራሲ ስርአት መፍጠሩን ተናግረዋል። ፓርቲው በተለይም በሶማሌ ክልል ሁለንተናዊ የልማት ስራዎች እንዲከናወኑና የህዝብ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ በመስራት የሚጨበጥ ውጤት ስለማስመዝገቡም ገልጸዋል። በመሆኑም በዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ ብልጽግናን መምረጥ፣ የልማት ስራዎችን ማስቀጠልና የህዝብ ተጠቃሚነትን ይበልጥ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ አስረድተዋል። በመርሃ-ግብሩ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የፓርቲው ደጋፊዎችና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።
ለሕዝባችን የገባነውን ቃል፣ ሕዝባችንን ከጎናችን በማሰለፍ በብቃትና በውጤት ፈጽመናል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Feb 16, 2026 109
አዲስ አበባ፤ የካቲት 9/2018(ኢዜአ)፦በ6ኛው አገራዊ ምርጫ ለሕዝባችን የገባነውን ቃል፣ ሕዝባችንን ከጎናችን በማሰለፍ በብቃትና በውጤት ፈጽመናል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። የብልፅግና ፓርቲ የ7ኛው አገራዊና ከተማ አቀፍ ጠቅላላ ምርጫ ማኒፌስቶን እና የምርጫ ምልክት የሆነው "የስንዴ ነዶ" በአዲስ አበባ ደረጃ ይፋ ተደርጓል። ምርጫ ለአንድ አገር ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ መሠረታዊ ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች የሕዝብ ሉዓላዊነት የሚገለጽበትና ሕዝብ በድምፁ መንግሥት የሚመሠርትበትም ሂደት ነው ሲሉም ገልጸዋል። በ6ኛው አገራዊ ምርጫ ለሕዝባችን የገባነውን ቃል፣ ሕዝባችንን ከጎናችን በማሰለፍ በብቃትና በውጤት ፈጽመናል ብለዋል። በ7ኛው ዙርም ለሕዝባችን ቃል የምንገባው፣ ከተመረጥን ያለምነውን ሁለንተናዊ ብልፅግና ሌት ተቀን በመሥራት ያለምንም መሸራረፍ እንፈጽማለን ሲሉ ገልጸዋል። የብልፅግና ፓርቲ ማኒፌስቶ ትናንትን ማከሚያ፣ ዛሬን በአግባቡ መጠቀሚያ፣ ነገን መተለሚያና ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት አገር ማሻገሪያ መመሪያችን ነው ብለዋል። የምርጫ መወዳደሪያ ምልክታችን የሆነው የስንዴ ነዶም የመደመር፣ የአንድነት፣ የተባብሮ መሥራት፣ የምርታማነት፣ የተምሳሌትነት፣ የልዕልና እና የሉዓላዊነት መገለጫ ነው ሲሉ አስረድተዋል። ይህም በሁላችን፣ ከሁላችን፣ ለሁላችን ብልፅግናን የምናረጋግጥበት ምልክታችን ነው ያሉት ከንቲባዋ ስለሆነም ፣ ብልፅግና ቃሉን ይጠብቃል፤ ቃሉን ይፈጽማል፤ ሕዝቡን የሉዓላዊ ሥልጣን ባለቤት ያደርጋል ብለዋል። ዛሬ የብልፅግና ፓርቲያችንን የ7ኛው አገራዊና ከተማ አቀፍ ጠቅላላ ምርጫ ማኒፌስቶን እና የምርጫ ምልክታችን የሆነውን "የስንዴ ነዶ" በአዲስ አበባ ደረጃ ይፋ አድርገናል ብለዋል።
በሁሉም መስክ የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማሳደግ በተሰራው ሥራ ውጤት ተመዝግቧል
Feb 16, 2026 75
ዲላ፤ የካቲት 9/2018 (ኢዜአ):-በሁሉም መስክ የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማሳደግ በተሰራው ሥራ ውጤት መመዝገቡን የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ አስታወቀ። "በሴቶች ተሳትፎ የፀናችና የበለፀገች ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ቃል የሴቶች ክንፍ የውይይት መድረክ በዲላ ከተማ እየተካሄደ ነው። የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ሥራ አስፈጻሚ መላኬ አለማየሁ በወቅቱ እንዳሉት፤መንግስት ከለውጡ ዓመታት ወዲህ ለሴቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ቅድሚያ ሰጥቶ በመስራቱ ስኬት ለማስመዝገብ ተችሏል። በተለይ የፖለቲካ ተሳትፏቸውን ከማረጋገጥ ባሻገር ሴቶች ከጠባቂነት ተላቀው የራሳቸውን ገቢ እንዲያመነጩ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት ተገኝቷል ነው ያሉት። ሴቶች የህብረተሰቡ ግማሽ አካል ከመሆናቸው ባለፈ ለሰላም እሴት ግንባታ ድርሻቸው የጎላ መሆኑ አንስተው፤ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ፍጹም ሰላማዊ፣ ነጻና ፍትሃዊ እንዲሆን የሴቶች ተሳትፎ ወሳኝ ነው ብለዋል። "ሴቶች በምርጫው በነቂስ በመሳተፍ ዴሞክራሲያዊ ልምምድን ልናጠናክር ይገባናል " ነው ያሉት። በዞኑ ሴቶች በከተማ ግብርና፣ በሌማት ቱሩፋትና መሰል የልማት ሥራዎች ያላቸው ተሳትፎ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ያሸጋገራቸው መሆኑን ያነሱት ደግሞ የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ (ዶ/ር) ናቸው። ምርጫ የዴሞክራሲያዊ ሀገር አንድ መገለጫ መሆኑን አንስተው ሴቶች በዘንድሮ ጠቅላላ ምርጫ ንቁ ተሳታፊ በመሆን የፀናችና የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመገንባት በሚደረግ ጥረት የድርሻቸውን እንዲወጡ አመልክተዋል። በብልጽግና ፓርቲ የዲላ ከተማ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የርዕዮተ ዓለም ዘርፍ ኃላፊና የሴቶች ክንፍ ከፍተኛ አመራር የካቲት ጥላሁን በበኩላቸው፤ ሴቶች ጠንካራ የመሪነት አቅማቸውንና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸውን እንዲያረጋግጡ በተደረገ ጥረት ውጤት ተገኝቷል ብለዋል። በቀጣይም ይህን ውጤት አጠናክሮ ለማስቀጠል የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው፣ ለ7 ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰኬታማነት ሴቶች ተሳትፏቸውን እንዲያጠናክሩ ጠይቀዋል። በመድረኩ ከፓናል ውይይት በተጨማሪ የእግር ጉዞ የተካሄደ ሲሆን በየደረጃው ያሉ የሴቶች ክንፍ አባላትና አመራሮች እንዲሁም ተጽዕኖ ፈጣሪና ታዋቂ ሴቶችም ተሳትፈዋል።
የኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ሂደት ጠንካራ መሰረት ይዞ እንዲቀጥል የበኩላችንን እንወጣለን- የምክር ቤት አባላት
Feb 16, 2026 68
አርባምንጭ፤የካቲት 9/2018 (ኢዜአ) :- የኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ሂደት ጠንካራ መሰረት ይዞ እንዲቀጥል የበኩላችንን እንወጣለን ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት አባላት ገለጹ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ ባደረገው መርሃ ግብር መሰረት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የሚካሄድ ይሆናል። በዚህም መሰረት በቅድመ ምርጫው የፓርቲዎች የእጩዎች ምዝገባ በመካሄድ ላይ ሲሆን በቀጣይነት የመራጮች ምዝገባ ለማካሄድ የሚያስችሉ ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑ ይታወቃል። በመሆኑም የኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ሂደት ጠንካራ መሰረት ይዞ እንዲቀጥል፤ በምርጫው ሂደት የበኩላቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ኢዜአ ያነጋገራቸው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት አባላት ገልጸዋል። ከምክር ቤቱ አባላት መካከል ወይዘሮ ዓለምገነት ላቀው፤ ጠቅላላ ምርጫውን ሰላማዊ፣ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ለማድረግ አስቻይ ሁኔታዎች መኖራቸውን አንስተዋል። በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እኩል ውድድር የሚካሄድበትን አውድ ለመፍጠር እያደረገ ያለውን ዝግጅት አድንቀዋል። የፖለቲካ ፓርቲዎችም በምርጫው ፍትሃዊ፣ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ፉክክር ለማድረግ ከወዲሁ እያደረጉት ያለው ዝግጅት መልካም ጅምር መሆኑን አንስተዋል። ሌሎች የምክር ቤት አባላት አቶ ደስታ አዶ እና አቶ ማሙሽ ሲማያ፤ ለምርጫው ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሂደት ከምርጫ ቦርድ በተጨማሪ ፓርቲዎች ለሰላምና ፍትሃዊ ውድድር ያላቸው ቁርጠኝነት እንዲሆም የህዝቡን ጠንካራ ተሳትፎ የግድ መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም ለምርጫው ስኬትና የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ሂደት የሁሉም አካላት ጥረትና ትብብር እንዳለ ሆኖ እንደ ምክር ቤት አባልነታቸው የድርሻቸውን አስተዋጽኦ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት ለማምጣት የምታደርገው ጥረት የሚደነቅ ነው
Feb 16, 2026 119
አዲስ አበባ፤ የካቲት 9/2018(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋትን ለማምጣት የምታደርገውን ጥረት እንደሚያደንቁ በኢትዮጵያ የዩናይትድ ኪንግደም አምባሳደር ዳረን ዌልች ገለጹ፡፡ ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት ያላትን ፍላጎት እንደሚረዱም አምባሳደር ዳረን ዌልች አስታውቀዋል፡፡ በኢትዮጵያ የዩናይትድ ኪንግደም አምባሳደር ዳረን ዌልች ከፐልስ ኦፍ አፍሪካ (ፒኦኤ) ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፤ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው የሁለትዮሽ ትብብር በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ መጥቷል። በቅርቡ የዩናይትድ ኪንግደም የኮመንዌልዝ፣ የልማት እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ይቬት ኩፐር የመጀመሪያውን የአፍሪካ ጉብኝት በኢትዮጵያ መጀመራቸውን አስታውሰዋል፡፡ ይህም የሀገራቱ ወቅታዊ ግንኙነት እያደገ ለመምጣቱ ትልቅ ማሳያ መሆኑን ጠቅሰው፤ በዚሁ ወቅትም የሀገራቱን የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስምምነቶች መፈረማቸውን አብራርተዋል። በኢትዮጵያ ሰፊ የኢንቨስትመንት አቅም መኖሩን ጠቁመው፤ ይህንን ዕድል ወደ ተግባር ለመለወጥ እንደሚሰራ ተናግረዋል። አምባሳደሩ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን የምታደርገውን ያላሰለሰ ጥረትና የምትከፍለውን መስዋዕትነትም አድንቀዋል፡፡ በተለይም ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሀገሯ ሶማሊያ ሰላምና መረጋጋት እየከፈለች ለሚገኘው መስዋዕትነት ያላቸውን አክብሮት ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ ለሶማሊያ እያከናወነች ያለው ተግባር የሀገሪቷን ታላቅነትና ለጎረቤቶቿ የምትሰጠውን ታላቅ ስፍራ የሚያሳይ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ሰፊ የልማት አቅም ያለው የአፍሪካ ቀንድ ወደ ሰላምና መረጋጋት እንዲመጣ ኢትዮጵያ ወሳኝ ሚና እንዳላትም ጠቅሰዋል። ቀጣናው ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታና ሰፊ ጥቅም እንዳለው ጠቅሰው፤ ኢትዮጵያ ለቀጣናው ሰላምና ፀጥታ ወሳኝ ሚና እንደምትጫወት ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰፊ የህዝብ ቁጥር ያላት፣ ፈጣን ኢኮኖሚያዊ እድገት እያስመዘገበች ያለች እና ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት በጎ አስተዋጽኦ የምታበረክት ሀገር ናት ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት የምታደርገውን ጥረት እንደሚረዱ ገልጸው፤ የባህር በር ለማግኘት የያዛቸውን ሰላማዊና ዲፕሎማሲያዊ መንገዶች አጠናክራ እንድትቀጥል ጠቁመዋል። ዩናይትድ ኪንግደም ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት ወደ ኢንቨትመንት እና ንግድ ግንኙነት ለማሳደግ እየሰራች ስለመሆኑም አብራርተዋል ::
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ አዋጆችን በማጽደቅ ተጠናቀቀ
Feb 16, 2026 81
አሶሳ፤ የካቲት 9/2018(ኢዜአ)፦ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት 2ኛ የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ አዋጆችን በማጽደቅ ተጠናቋል። ምክርቤቱ በዛሬ ውሎው የክልሉን ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና ዋና ኦዲት መስሪያ ቤት ሪፖርት በማድመጥ አጽድቋል። በመቀጠልም የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማህበር አደረጃጀትና የመስኖ አውታር አስተዳደር ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ያጸደቀ ሲሆን አዋጁ ዘላቂነት ያለው የመስኖ ውሃ አጠቃቀምን ለማጎልበት እና የመስኖ አውታሮችን ደህንነት ለመጠበቅ የሚያግዝ መሆኑን የምክር ቤቱ አባላት ገልጸዋል። በተጨማሪም አርሶአደሩ በመስኖ እርሻ እያከናወነ በሚገኘው የግብርና ስራ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ አዋጁ አይነተኛ ሚና እንደሚኖረው ተነስቷል። ምክር ቤቱ የክልሉን ፍትህ ቢሮ ማቋቋሚያ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ያፀደቀ ሲሆን በዲስፒሊን እና ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ምክንያት ከዳኝነት የተሰናበቱ ዳኞችን ስንብትም ተቀብሎ አጽድቋል።
በምርጫ ወቅት ለሚነሱ ቅሬታዎች በሕግ ላይ የተመሠረተ አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት በትኩረት ይሰራል
Feb 16, 2026 117
አዲስ አበባ፤ የካቲት 9/2018(ኢዜአ)፦ በምርጫ ወቅት ለሚነሱ ቅሬታዎች በሕግ ላይ የተመሠረተ አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት በትኩረት እንደሚሰራ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ቴዎድሮስ ምህረት አስታወቁ። የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር በመተባበር፣ በምርጫ ጉዳዮች ቅሬታ አፈታት ዙሪያ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና ለፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች ስልጠና መስጠት ጀምሯል። ለአራት ተከታታይ ቀናት በሚቆየው ስልጠና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዘርፉ ምሁራን፣ በምርጫ ቦርድ ባለሙያዎች እና በሰበር ሰሚ ዳኞች የሚሰጥ ሲሆን በሶስት ዙር 150 ዳኞች እንደሚሳተፉ ተገልጿል። በዚሁ ጊዜ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ቴዎድሮስ ምህረት፤ ዳኞች የዜጎችን የፍትሕ አገልግሎት ጥራት በማሻሻል ኃላፊነታቸውን በሚገባ እየተወጡ እንደሚገኙ ተናግረዋል። በምርጫ ሂደት ለሚነሱ ቅሬታዎች አፋጣኝ የፍትሕ ምላሽ አሰጣጥ ሥርዓትን በመፍጠር በኩልም ዳኞች ትልቅ አስተዋፅኦ አላቸው ብለዋል። ምርጫ ዜጎች የሚመራቸውን አካል የሚመርጡበት ታላቅ ሀገራዊ ሂደት ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ ሂደቱ ፍትሃዊ፣ ነፃ እና ገለልተኛ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የተቋማት ሚና ከፍተኛ መሆኑንም አስገንዝበዋል። በቀጣይ በምርጫ ሂደት የሚነሱ ቅሬታዎችን በሕግ ላይ የተመሰረተ አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት እንደሚሰራ ነው ፕሬዚዳንቱ ያረጋገጡት። ለዚህም ዳኞች ለምርጫው ስኬታማነት የሚኖራቸውን ድርሻ ለማላቅ ሂደቱን ማስገንዘብ የሚያስችል ስልጠና መስጠት እንዳስፈለገ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ሃይሉ በበኩላቸው፤ ቦርዱ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለማካሄድ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ምርጫው ፍትሃዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የተቀመጡ የሕግ ድንጋጌዎች ላይ በቂ ግንዛቤ መያዝ አስፈላጊ መሆኑንም ተናግረዋል። በተለይም በቅሬታ አቅራቢና በቅሬታ ፈቺ አካላት መካከል ወጥ የሆነ መረዳት ለመፍጠር ስልጠናው ጉልህ ፋይዳ እንደሚኖረው አንስተዋል።
የፖለቲካ ፓርቲዎች በጠቅላላ ምርጫው ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ውድድር ለማድረግ የሚያስችል የተሟላ ዝግጅት እያደረጉ ነው
Feb 16, 2026 109
ሀዋሳ፤ የካቲት 9/2018 (ኢዜአ):-በሲዳማ ክልል የሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ውድድር ለማድረግ የሚያስችል የተሟላ ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን ገለጹ። በመጪው ግንቦት ወር የሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ነጻ፣ ፍትሀዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ እንዲካሄድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረገ ነው። በምርጫው ዝግጅት ላይ ኢዜአ ያነጋገራቸው በሲዳማ ክልል የሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምርጫው ፍትሀዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ሠላማዊ እንዲሆን የበኩላቸውን ለመወጣት እየሰሩ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ ለዚህም በአሁኑ ወቅት በምርጫው ለሚወዳደሩ እጩዎቻቸውና አባሎቻቸው ግንዛቤያቸውን የማሳደግ ሥራ እያከናወኑ መሆናቸውን ነው የገለጹት። ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የሲዳማ አንድነት ፓርቲ (ሲአፓ) ሊቀ መንበር አቶ ለማ ሆያቶ፤ምርጫ ቦርድ የእጩዎች ምዝገባ በዲጂታል ሥርዐት እንዲከናወን ማድረጉ እንግልትን ያስቀረና የሚበረታታ መሆኑን ተናግረዋል። የምርጫው ሂደት ፍትሃዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ሠላማዊ እንዲሆን ፓርቲው የሚጠበቅበትን እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል። አባላቶቻቸውና ዕጩዎቻችው ዴሞክራሲያዊና ፍትሀዊ የምርጫ ሂደትን ጠብቀው እንዲንቀሳቀሱ ግንዛቤያቸውን ከማሳደግ ባለፈ ለሰላምና ትብብር ትኩረት ሰጥተው እንዲንቀሳቀሱ እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል። የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ፓርቲ በደቡብ ቀጠና ሲዳማ ክልል ማስተባበሪያ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ወይዘሮ ሀረገወይን ዘሪሁን፤ያለውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም በምርጫው ለመሳተፍ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅትም እስከ ታችኛው መዋቅር በመውረድ የዕጩ ምልመላ፣ የዕጩዎች ምዝገባና ሌሎች ሥራዎችን ያለተግዳሮት በማከናወን ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል። ምርጫው የዴሞክራሲ ሥርዐት ግንባታ የሚጠናከርበት መሆኑን ገልጸው፣ በአሁን ወቅት ዕጩዎቻቸው የምርጫን መሠረታዊ ዓላማዎች ተረድተው እንዲንቀሳቀሱ የማስገንዘብ ሥራ እየሰሩ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። በብልጽግና ፓርቲ የሲዳማ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊና የክልሉ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ኤርሚያስ፤ ለምርጫው አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ምርጫው ነፃ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ሠላማዊና በሁሉም ዘንድ ቅቡልነት ያለው እንዲሆን አስቻይ ሁኔታዎችን የመፍጠር ሥራ በትኩረት እየተከናወነ መሆኑንም ነው ያስታወቁት። በክልሉ በሁሉም የምርጫ ክልሎችና የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ፓርቲዎች በነጻነት ተንቀሳቅሰው እንዲወዳደሩ ሁኔታዎችን የማመቻቸት ሥራ እየተከናወነ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡ እንደ አቶ ተስፋዬ ገለጻ፤ የሲዳማ ክልል ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የፓርቲዎችና የመንግስት ግንኙነት ጤናማ እንዲሆንና ቅራኔዎች ሲኖሩም ፈጥነው እንዲፈቱ እየተጫወተ ያለው ሚና የላቀ ነው። በዞንና በወረዳ ደረጃም የጋራ ምክር ቤቶች እንዲቋቋሙ በማድረግ ፓርቲዎች ለምርጫው ሠላማዊና ዴሞክራሲያዊነት በጋራ የሚመክሩበትና ችግሮችን የሚፈቱበት መድረክ መፈጠሩን ገልፀዋል፡፡
ፖለቲካ
ብልፅግና ፓርቲ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ታሪክ የዜጎችን እኩል ተሳትፎና ውሳኔ ሰጪነት እውን ማድረግ የቻለ ህብረ ብሄራዊ ፓርቲ ነው- ርእሰ መስተዳድር ሙስጠፋ ሙሁመድ
Feb 17, 2026 69
ጅግጅጋ፤ የካቲት 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልፅግና ፓርቲ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ታሪክ የዜጎችን እኩል ተሳትፎና ውሳኔ ሰጪነት እውን ማድረግ የቻለ ህብረ ብሄራዊ ፓርቲ መሆኑን የሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሐመድ ገለጹ። የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ መወዳደሪያ ምልክቱን (የስንዴ ነዶ) እና ማኒፌስቶውን በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ለህዝቡ አስተዋውቋል። በዚሁ መድረክ ላይ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ርእሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሐመድ፤ ብልፅግና በኢትዮጵያ ፖለቲካ ታሪክ የዜጎችን እኩል ተሳትፎና ውሳኔ ሰጪነት እውን ማድረግ የቻለ ህብረ ብሄራዊ ፓርቲ መሆኑን ገልጸዋል። በኢትዮጵያ ፖለቲካ የዳር ተመልካችነት ቀርቶ እኩል ተሳትፎና ውሳኔ ሰጭነት የተረጋገጠበት፣ በሀገሩ ጉዳይ ሁሉም ያገባኛል ብሎ የሚሰራበትና የመሪነት እድል የሚያገኝበት አካታች የዴሞክራሲ ስርአት መፍጠሩን ተናግረዋል። ፓርቲው በተለይም በሶማሌ ክልል ሁለንተናዊ የልማት ስራዎች እንዲከናወኑና የህዝብ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ በመስራት የሚጨበጥ ውጤት ስለማስመዝገቡም ገልጸዋል። በመሆኑም በዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ ብልጽግናን መምረጥ፣ የልማት ስራዎችን ማስቀጠልና የህዝብ ተጠቃሚነትን ይበልጥ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ አስረድተዋል። በመርሃ-ግብሩ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የፓርቲው ደጋፊዎችና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።
ለሕዝባችን የገባነውን ቃል፣ ሕዝባችንን ከጎናችን በማሰለፍ በብቃትና በውጤት ፈጽመናል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Feb 16, 2026 109
አዲስ አበባ፤ የካቲት 9/2018(ኢዜአ)፦በ6ኛው አገራዊ ምርጫ ለሕዝባችን የገባነውን ቃል፣ ሕዝባችንን ከጎናችን በማሰለፍ በብቃትና በውጤት ፈጽመናል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። የብልፅግና ፓርቲ የ7ኛው አገራዊና ከተማ አቀፍ ጠቅላላ ምርጫ ማኒፌስቶን እና የምርጫ ምልክት የሆነው "የስንዴ ነዶ" በአዲስ አበባ ደረጃ ይፋ ተደርጓል። ምርጫ ለአንድ አገር ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ መሠረታዊ ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች የሕዝብ ሉዓላዊነት የሚገለጽበትና ሕዝብ በድምፁ መንግሥት የሚመሠርትበትም ሂደት ነው ሲሉም ገልጸዋል። በ6ኛው አገራዊ ምርጫ ለሕዝባችን የገባነውን ቃል፣ ሕዝባችንን ከጎናችን በማሰለፍ በብቃትና በውጤት ፈጽመናል ብለዋል። በ7ኛው ዙርም ለሕዝባችን ቃል የምንገባው፣ ከተመረጥን ያለምነውን ሁለንተናዊ ብልፅግና ሌት ተቀን በመሥራት ያለምንም መሸራረፍ እንፈጽማለን ሲሉ ገልጸዋል። የብልፅግና ፓርቲ ማኒፌስቶ ትናንትን ማከሚያ፣ ዛሬን በአግባቡ መጠቀሚያ፣ ነገን መተለሚያና ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት አገር ማሻገሪያ መመሪያችን ነው ብለዋል። የምርጫ መወዳደሪያ ምልክታችን የሆነው የስንዴ ነዶም የመደመር፣ የአንድነት፣ የተባብሮ መሥራት፣ የምርታማነት፣ የተምሳሌትነት፣ የልዕልና እና የሉዓላዊነት መገለጫ ነው ሲሉ አስረድተዋል። ይህም በሁላችን፣ ከሁላችን፣ ለሁላችን ብልፅግናን የምናረጋግጥበት ምልክታችን ነው ያሉት ከንቲባዋ ስለሆነም ፣ ብልፅግና ቃሉን ይጠብቃል፤ ቃሉን ይፈጽማል፤ ሕዝቡን የሉዓላዊ ሥልጣን ባለቤት ያደርጋል ብለዋል። ዛሬ የብልፅግና ፓርቲያችንን የ7ኛው አገራዊና ከተማ አቀፍ ጠቅላላ ምርጫ ማኒፌስቶን እና የምርጫ ምልክታችን የሆነውን "የስንዴ ነዶ" በአዲስ አበባ ደረጃ ይፋ አድርገናል ብለዋል።
በሁሉም መስክ የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማሳደግ በተሰራው ሥራ ውጤት ተመዝግቧል
Feb 16, 2026 75
ዲላ፤ የካቲት 9/2018 (ኢዜአ):-በሁሉም መስክ የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማሳደግ በተሰራው ሥራ ውጤት መመዝገቡን የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ አስታወቀ። "በሴቶች ተሳትፎ የፀናችና የበለፀገች ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ቃል የሴቶች ክንፍ የውይይት መድረክ በዲላ ከተማ እየተካሄደ ነው። የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ሥራ አስፈጻሚ መላኬ አለማየሁ በወቅቱ እንዳሉት፤መንግስት ከለውጡ ዓመታት ወዲህ ለሴቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ቅድሚያ ሰጥቶ በመስራቱ ስኬት ለማስመዝገብ ተችሏል። በተለይ የፖለቲካ ተሳትፏቸውን ከማረጋገጥ ባሻገር ሴቶች ከጠባቂነት ተላቀው የራሳቸውን ገቢ እንዲያመነጩ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት ተገኝቷል ነው ያሉት። ሴቶች የህብረተሰቡ ግማሽ አካል ከመሆናቸው ባለፈ ለሰላም እሴት ግንባታ ድርሻቸው የጎላ መሆኑ አንስተው፤ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ፍጹም ሰላማዊ፣ ነጻና ፍትሃዊ እንዲሆን የሴቶች ተሳትፎ ወሳኝ ነው ብለዋል። "ሴቶች በምርጫው በነቂስ በመሳተፍ ዴሞክራሲያዊ ልምምድን ልናጠናክር ይገባናል " ነው ያሉት። በዞኑ ሴቶች በከተማ ግብርና፣ በሌማት ቱሩፋትና መሰል የልማት ሥራዎች ያላቸው ተሳትፎ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ያሸጋገራቸው መሆኑን ያነሱት ደግሞ የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ (ዶ/ር) ናቸው። ምርጫ የዴሞክራሲያዊ ሀገር አንድ መገለጫ መሆኑን አንስተው ሴቶች በዘንድሮ ጠቅላላ ምርጫ ንቁ ተሳታፊ በመሆን የፀናችና የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመገንባት በሚደረግ ጥረት የድርሻቸውን እንዲወጡ አመልክተዋል። በብልጽግና ፓርቲ የዲላ ከተማ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የርዕዮተ ዓለም ዘርፍ ኃላፊና የሴቶች ክንፍ ከፍተኛ አመራር የካቲት ጥላሁን በበኩላቸው፤ ሴቶች ጠንካራ የመሪነት አቅማቸውንና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸውን እንዲያረጋግጡ በተደረገ ጥረት ውጤት ተገኝቷል ብለዋል። በቀጣይም ይህን ውጤት አጠናክሮ ለማስቀጠል የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው፣ ለ7 ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰኬታማነት ሴቶች ተሳትፏቸውን እንዲያጠናክሩ ጠይቀዋል። በመድረኩ ከፓናል ውይይት በተጨማሪ የእግር ጉዞ የተካሄደ ሲሆን በየደረጃው ያሉ የሴቶች ክንፍ አባላትና አመራሮች እንዲሁም ተጽዕኖ ፈጣሪና ታዋቂ ሴቶችም ተሳትፈዋል።
የኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ሂደት ጠንካራ መሰረት ይዞ እንዲቀጥል የበኩላችንን እንወጣለን- የምክር ቤት አባላት
Feb 16, 2026 68
አርባምንጭ፤የካቲት 9/2018 (ኢዜአ) :- የኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ሂደት ጠንካራ መሰረት ይዞ እንዲቀጥል የበኩላችንን እንወጣለን ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት አባላት ገለጹ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ ባደረገው መርሃ ግብር መሰረት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የሚካሄድ ይሆናል። በዚህም መሰረት በቅድመ ምርጫው የፓርቲዎች የእጩዎች ምዝገባ በመካሄድ ላይ ሲሆን በቀጣይነት የመራጮች ምዝገባ ለማካሄድ የሚያስችሉ ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑ ይታወቃል። በመሆኑም የኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ሂደት ጠንካራ መሰረት ይዞ እንዲቀጥል፤ በምርጫው ሂደት የበኩላቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ኢዜአ ያነጋገራቸው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት አባላት ገልጸዋል። ከምክር ቤቱ አባላት መካከል ወይዘሮ ዓለምገነት ላቀው፤ ጠቅላላ ምርጫውን ሰላማዊ፣ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ለማድረግ አስቻይ ሁኔታዎች መኖራቸውን አንስተዋል። በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እኩል ውድድር የሚካሄድበትን አውድ ለመፍጠር እያደረገ ያለውን ዝግጅት አድንቀዋል። የፖለቲካ ፓርቲዎችም በምርጫው ፍትሃዊ፣ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ፉክክር ለማድረግ ከወዲሁ እያደረጉት ያለው ዝግጅት መልካም ጅምር መሆኑን አንስተዋል። ሌሎች የምክር ቤት አባላት አቶ ደስታ አዶ እና አቶ ማሙሽ ሲማያ፤ ለምርጫው ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሂደት ከምርጫ ቦርድ በተጨማሪ ፓርቲዎች ለሰላምና ፍትሃዊ ውድድር ያላቸው ቁርጠኝነት እንዲሆም የህዝቡን ጠንካራ ተሳትፎ የግድ መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም ለምርጫው ስኬትና የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ሂደት የሁሉም አካላት ጥረትና ትብብር እንዳለ ሆኖ እንደ ምክር ቤት አባልነታቸው የድርሻቸውን አስተዋጽኦ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት ለማምጣት የምታደርገው ጥረት የሚደነቅ ነው
Feb 16, 2026 119
አዲስ አበባ፤ የካቲት 9/2018(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋትን ለማምጣት የምታደርገውን ጥረት እንደሚያደንቁ በኢትዮጵያ የዩናይትድ ኪንግደም አምባሳደር ዳረን ዌልች ገለጹ፡፡ ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት ያላትን ፍላጎት እንደሚረዱም አምባሳደር ዳረን ዌልች አስታውቀዋል፡፡ በኢትዮጵያ የዩናይትድ ኪንግደም አምባሳደር ዳረን ዌልች ከፐልስ ኦፍ አፍሪካ (ፒኦኤ) ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፤ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው የሁለትዮሽ ትብብር በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ መጥቷል። በቅርቡ የዩናይትድ ኪንግደም የኮመንዌልዝ፣ የልማት እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ይቬት ኩፐር የመጀመሪያውን የአፍሪካ ጉብኝት በኢትዮጵያ መጀመራቸውን አስታውሰዋል፡፡ ይህም የሀገራቱ ወቅታዊ ግንኙነት እያደገ ለመምጣቱ ትልቅ ማሳያ መሆኑን ጠቅሰው፤ በዚሁ ወቅትም የሀገራቱን የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስምምነቶች መፈረማቸውን አብራርተዋል። በኢትዮጵያ ሰፊ የኢንቨስትመንት አቅም መኖሩን ጠቁመው፤ ይህንን ዕድል ወደ ተግባር ለመለወጥ እንደሚሰራ ተናግረዋል። አምባሳደሩ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን የምታደርገውን ያላሰለሰ ጥረትና የምትከፍለውን መስዋዕትነትም አድንቀዋል፡፡ በተለይም ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሀገሯ ሶማሊያ ሰላምና መረጋጋት እየከፈለች ለሚገኘው መስዋዕትነት ያላቸውን አክብሮት ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ ለሶማሊያ እያከናወነች ያለው ተግባር የሀገሪቷን ታላቅነትና ለጎረቤቶቿ የምትሰጠውን ታላቅ ስፍራ የሚያሳይ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ሰፊ የልማት አቅም ያለው የአፍሪካ ቀንድ ወደ ሰላምና መረጋጋት እንዲመጣ ኢትዮጵያ ወሳኝ ሚና እንዳላትም ጠቅሰዋል። ቀጣናው ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታና ሰፊ ጥቅም እንዳለው ጠቅሰው፤ ኢትዮጵያ ለቀጣናው ሰላምና ፀጥታ ወሳኝ ሚና እንደምትጫወት ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰፊ የህዝብ ቁጥር ያላት፣ ፈጣን ኢኮኖሚያዊ እድገት እያስመዘገበች ያለች እና ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት በጎ አስተዋጽኦ የምታበረክት ሀገር ናት ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት የምታደርገውን ጥረት እንደሚረዱ ገልጸው፤ የባህር በር ለማግኘት የያዛቸውን ሰላማዊና ዲፕሎማሲያዊ መንገዶች አጠናክራ እንድትቀጥል ጠቁመዋል። ዩናይትድ ኪንግደም ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት ወደ ኢንቨትመንት እና ንግድ ግንኙነት ለማሳደግ እየሰራች ስለመሆኑም አብራርተዋል ::
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ አዋጆችን በማጽደቅ ተጠናቀቀ
Feb 16, 2026 81
አሶሳ፤ የካቲት 9/2018(ኢዜአ)፦ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት 2ኛ የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ አዋጆችን በማጽደቅ ተጠናቋል። ምክርቤቱ በዛሬ ውሎው የክልሉን ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና ዋና ኦዲት መስሪያ ቤት ሪፖርት በማድመጥ አጽድቋል። በመቀጠልም የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማህበር አደረጃጀትና የመስኖ አውታር አስተዳደር ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ያጸደቀ ሲሆን አዋጁ ዘላቂነት ያለው የመስኖ ውሃ አጠቃቀምን ለማጎልበት እና የመስኖ አውታሮችን ደህንነት ለመጠበቅ የሚያግዝ መሆኑን የምክር ቤቱ አባላት ገልጸዋል። በተጨማሪም አርሶአደሩ በመስኖ እርሻ እያከናወነ በሚገኘው የግብርና ስራ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ አዋጁ አይነተኛ ሚና እንደሚኖረው ተነስቷል። ምክር ቤቱ የክልሉን ፍትህ ቢሮ ማቋቋሚያ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ያፀደቀ ሲሆን በዲስፒሊን እና ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ምክንያት ከዳኝነት የተሰናበቱ ዳኞችን ስንብትም ተቀብሎ አጽድቋል።
በምርጫ ወቅት ለሚነሱ ቅሬታዎች በሕግ ላይ የተመሠረተ አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት በትኩረት ይሰራል
Feb 16, 2026 117
አዲስ አበባ፤ የካቲት 9/2018(ኢዜአ)፦ በምርጫ ወቅት ለሚነሱ ቅሬታዎች በሕግ ላይ የተመሠረተ አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት በትኩረት እንደሚሰራ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ቴዎድሮስ ምህረት አስታወቁ። የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር በመተባበር፣ በምርጫ ጉዳዮች ቅሬታ አፈታት ዙሪያ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና ለፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች ስልጠና መስጠት ጀምሯል። ለአራት ተከታታይ ቀናት በሚቆየው ስልጠና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዘርፉ ምሁራን፣ በምርጫ ቦርድ ባለሙያዎች እና በሰበር ሰሚ ዳኞች የሚሰጥ ሲሆን በሶስት ዙር 150 ዳኞች እንደሚሳተፉ ተገልጿል። በዚሁ ጊዜ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ቴዎድሮስ ምህረት፤ ዳኞች የዜጎችን የፍትሕ አገልግሎት ጥራት በማሻሻል ኃላፊነታቸውን በሚገባ እየተወጡ እንደሚገኙ ተናግረዋል። በምርጫ ሂደት ለሚነሱ ቅሬታዎች አፋጣኝ የፍትሕ ምላሽ አሰጣጥ ሥርዓትን በመፍጠር በኩልም ዳኞች ትልቅ አስተዋፅኦ አላቸው ብለዋል። ምርጫ ዜጎች የሚመራቸውን አካል የሚመርጡበት ታላቅ ሀገራዊ ሂደት ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ ሂደቱ ፍትሃዊ፣ ነፃ እና ገለልተኛ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የተቋማት ሚና ከፍተኛ መሆኑንም አስገንዝበዋል። በቀጣይ በምርጫ ሂደት የሚነሱ ቅሬታዎችን በሕግ ላይ የተመሰረተ አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት እንደሚሰራ ነው ፕሬዚዳንቱ ያረጋገጡት። ለዚህም ዳኞች ለምርጫው ስኬታማነት የሚኖራቸውን ድርሻ ለማላቅ ሂደቱን ማስገንዘብ የሚያስችል ስልጠና መስጠት እንዳስፈለገ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ሃይሉ በበኩላቸው፤ ቦርዱ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለማካሄድ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ምርጫው ፍትሃዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የተቀመጡ የሕግ ድንጋጌዎች ላይ በቂ ግንዛቤ መያዝ አስፈላጊ መሆኑንም ተናግረዋል። በተለይም በቅሬታ አቅራቢና በቅሬታ ፈቺ አካላት መካከል ወጥ የሆነ መረዳት ለመፍጠር ስልጠናው ጉልህ ፋይዳ እንደሚኖረው አንስተዋል።
የፖለቲካ ፓርቲዎች በጠቅላላ ምርጫው ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ውድድር ለማድረግ የሚያስችል የተሟላ ዝግጅት እያደረጉ ነው
Feb 16, 2026 109
ሀዋሳ፤ የካቲት 9/2018 (ኢዜአ):-በሲዳማ ክልል የሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ውድድር ለማድረግ የሚያስችል የተሟላ ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን ገለጹ። በመጪው ግንቦት ወር የሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ነጻ፣ ፍትሀዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ እንዲካሄድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረገ ነው። በምርጫው ዝግጅት ላይ ኢዜአ ያነጋገራቸው በሲዳማ ክልል የሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምርጫው ፍትሀዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ሠላማዊ እንዲሆን የበኩላቸውን ለመወጣት እየሰሩ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ ለዚህም በአሁኑ ወቅት በምርጫው ለሚወዳደሩ እጩዎቻቸውና አባሎቻቸው ግንዛቤያቸውን የማሳደግ ሥራ እያከናወኑ መሆናቸውን ነው የገለጹት። ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የሲዳማ አንድነት ፓርቲ (ሲአፓ) ሊቀ መንበር አቶ ለማ ሆያቶ፤ምርጫ ቦርድ የእጩዎች ምዝገባ በዲጂታል ሥርዐት እንዲከናወን ማድረጉ እንግልትን ያስቀረና የሚበረታታ መሆኑን ተናግረዋል። የምርጫው ሂደት ፍትሃዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ሠላማዊ እንዲሆን ፓርቲው የሚጠበቅበትን እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል። አባላቶቻቸውና ዕጩዎቻችው ዴሞክራሲያዊና ፍትሀዊ የምርጫ ሂደትን ጠብቀው እንዲንቀሳቀሱ ግንዛቤያቸውን ከማሳደግ ባለፈ ለሰላምና ትብብር ትኩረት ሰጥተው እንዲንቀሳቀሱ እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል። የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ፓርቲ በደቡብ ቀጠና ሲዳማ ክልል ማስተባበሪያ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ወይዘሮ ሀረገወይን ዘሪሁን፤ያለውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም በምርጫው ለመሳተፍ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅትም እስከ ታችኛው መዋቅር በመውረድ የዕጩ ምልመላ፣ የዕጩዎች ምዝገባና ሌሎች ሥራዎችን ያለተግዳሮት በማከናወን ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል። ምርጫው የዴሞክራሲ ሥርዐት ግንባታ የሚጠናከርበት መሆኑን ገልጸው፣ በአሁን ወቅት ዕጩዎቻቸው የምርጫን መሠረታዊ ዓላማዎች ተረድተው እንዲንቀሳቀሱ የማስገንዘብ ሥራ እየሰሩ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። በብልጽግና ፓርቲ የሲዳማ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊና የክልሉ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ኤርሚያስ፤ ለምርጫው አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ምርጫው ነፃ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ሠላማዊና በሁሉም ዘንድ ቅቡልነት ያለው እንዲሆን አስቻይ ሁኔታዎችን የመፍጠር ሥራ በትኩረት እየተከናወነ መሆኑንም ነው ያስታወቁት። በክልሉ በሁሉም የምርጫ ክልሎችና የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ፓርቲዎች በነጻነት ተንቀሳቅሰው እንዲወዳደሩ ሁኔታዎችን የማመቻቸት ሥራ እየተከናወነ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡ እንደ አቶ ተስፋዬ ገለጻ፤ የሲዳማ ክልል ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የፓርቲዎችና የመንግስት ግንኙነት ጤናማ እንዲሆንና ቅራኔዎች ሲኖሩም ፈጥነው እንዲፈቱ እየተጫወተ ያለው ሚና የላቀ ነው። በዞንና በወረዳ ደረጃም የጋራ ምክር ቤቶች እንዲቋቋሙ በማድረግ ፓርቲዎች ለምርጫው ሠላማዊና ዴሞክራሲያዊነት በጋራ የሚመክሩበትና ችግሮችን የሚፈቱበት መድረክ መፈጠሩን ገልፀዋል፡፡
ማህበራዊ
በዞኑ አርብቶ አደር አካባቢዎች የትምህርት ተደራሽነትን ለማስፋትና ጥራትን ለማስጠበቅ በተሰሩ ሥራዎች ለውጥ እየመጣ ነው
Feb 16, 2026 68
ሐመር፤ የካቲት 9/2018(ኢዜአ)፡-በደቡብ ኦሞ ዞን አርብቶ አደር አካባቢዎች የትምህርት ተደራሽነትን ለማስፋትና ጥራትን ለማስጠበቅ እየተደረጉ ያሉ ጥረቶች ውጤት እያመጡ መሆናቸውን የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ። በዞኑ ሐመር ወረዳ ሻንቆ ቀለማ ቀበሌ ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጭ የተገነባ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ዛሬ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል። የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቱን ዛሬ መርቀው የከፈቱት የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የተያዘውን ራዕይ ለማሳካት ትምህርት ወሳኝ መሆኑን ነው ያነሱት። መንግስትና የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ በአርብቶ አደሩ አካባቢ የትምህርት ተደራሽነትን ለማስፋትና ጥራትን ለማረጋገጥ እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቁመው በዚህም ለውጦች እየተመዘገቡ ነው ብለዋል ። ዛሬ የተመረቀው ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት በአርብቶ አደሩ አካባቢ የትምህርት ተሳትፎን ለማሳደግ ለተጀመረው ሥራ አንድ የለውጥ እርምጃ እንደሆነም ጠቅሰዋል። ቀደም ሲል በአርብቶ አደሩ አካባቢ የትምህርት ተሳትፎ አነስተኛ እንደነበር አስታውሰው፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአርብቶ አደሩ አካባቢ የትምህርት ተደራሽነትን ለማስፋት በተደረገ የተቀናጀ ርብርብ ለውጥ ታይቷል ብለዋል። ለዚህም አርብቶ አደሩ ከቅድመ መደበኛ ጀምሮ ልጁን ማስተማር መጀመሩን በማሳያነት ጠቅሰዋል። የሐመር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ጋርሾ በበኩላቸው እንዳሉት ዛሬ የተመረቀው ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ከታችኛው የትምህርት እርከን ጀምሮ ብቁ ተማሪዎችን ለማፍራት ያግዛል። የወረዳው አስተዳደር ለትምህርት ቤቱ አስፈላጊ ግብአቶችን በማሟላት ትምህርት ቤቱ የተጣለበትን ተልዕኮ እንዲወጣ ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል። ለሕንፃ ግንባታው ድጋፍ ካደረጉት መካከል የሴንተር ኦፍ ኮንሰርን ድርጅት የሕፃናት ጥበቃና ትምህርት አስተባባሪ አቶ አማኑኤል ማቴዎስ ለትምህርት ቤቱ ግንባታ ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ መደረጉን ገልፀዋል። ግንባታው ሁለት መማሪያ ክፍሎች፣ አንድ ቢሮ እና ስቶር ከነ ሙሉ መማሪያ ቁሳቁስ ያካተተ መሆኑን አንስተው ለተማሪዎች ሙሉ የደምብ ልብስ ድጋፍ መደረጉንም ተናግረዋል። በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ የዞኑና የወረዳ አስተዳደር የሥራ ሃላፊዎችና የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
በክልሉ በተፈጥሮ አካላዊ የጤና ችግር ኖሮባቸው የሚወለዱ ህፃናት ተገቢውን ህክምና እንዲያገኙ እየተደረገ ነው
Feb 16, 2026 56
ባህርዳር፤ የካቲት 9/2018 (ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል በተፈጥሮ አካላዊ የጤና ችግር ኖሮባቸው የሚወለዱ ህፃናት ተገቢውን ህክምና እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ። ቢሮው ‘‘በላቀ ተነሳሽነት ለኢትዮጵያ ልጆች’’ በሚል መሪ ቃል ችግሩን መከላከል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከአጋር አካላት ጋር የመከረበት መድረክ በባህርዳር ከተማ ተካሂዷል። የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ አበበ ተምትሜ በወቅቱ እንደገለጹት በተፈጥሮ አካላዊ የጤና ችግር ኖሮባቸው የሚወለዱ ህፃናት ችግርን ለመከላከል የባለድርሻ አካላት ትብብር ያስፈልጋል። በሽታው ሲያጋጥም ታክሞ የሚድን መሆኑን ለህብረተሰቡ በማስተማር ከችግሩ ጋር ተያይዞ የሚወለዱ ህፃናትን በቀላሉ ወደ ህክምና በማምጣት እንዲድኑ መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል። ጥናቶች እንደሚያመላክቱት የቆልማማ ዕግር ችግር ከሚወለዱ አንድ ሺህ ህፃናት መካከል በአንዱ ላይ እንዲሁም የላንቃና የከንፈር መሰንጠቅ ደግሞ ከ627 ህፃናት በአንዱ ላይ የሚከሰት መሆኑን ጠቅሰዋል። ካለፉት ሁለት ዓመታት ጀምሮ ከ2 ሺህ 300 በላይ የቆልማማ ዕግር ችግር ያላቸውን ህፃናት በማፈላለግ ተከታታይነት ያለው ህክምና እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑን አመልክተዋል። በተጨማሪም በየዓመቱ የከንፈርና የላንቃ መሰንጠቅ ችግር ያለባቸውን 300 ህፃናት በጤና ተቋማት ህክምና አግኝተው እንዲድኑ መደረጉን ጠቅሰዋል። በክልሉ የካቲት 19 ቀን 2018 ዓ.ም በደሴ ከተማ በሰላም ጠቅላላ ሆስፒታል እንዲሁም በየካቲት 23 ቀን 2018 ደግሞ በባህር ዳር ከተማ ጋምቢ ቲችንግ ሆስፒታል የከንፈርና የላንቃ መሰንጠቅ ህክምና በዘመቻ እንደሚሰጥ አመላክተዋል ። በጤና ሚኒስቴር የስፔሻሊቲና ተሃድሶ አገልግሎት ዴስክ ኃላፊ አቶ ኤርምያስ ሙላቱ በበኩላቸው በተፈጥሮ የጤና ችግር ያለባቸውን ህጻናት በሀገር ደረጃ ተገቢውን ህክምና አግኝተው እንዲድኑ እየተሰራ ነው። ህክምና የሚሰጠውም ከጡንቻና ከአጥንት ጋር ተያይዞ የነርቭ ዘንግ ክፍተት ላለባቸው፣ የከንፈርና ላንቃ መሰንጠቅ፣ የዕድገት ውሱንነት፣ የቆልማማ እግር ችግርና ሌሎች በሽታዎች መሆኑን ተናግረዋል። ችግሩን በዘላቂነት ለመከላከልም ከእርግዝና በፊትና በዕርግዝና ወቅት እናቶች የህክምና ክትትል ማድረግ እንዳለባቸው ጠቁመው ከወለዱ በኋላም ችግሩ ሲታወቅ ፈጥኖ በማሳከም ማዳን እንደሚገባ አሳስበዋል። ጤና ሚኒስቴርም ክልሉ ችግሩን ለመከላከል በሚያደርገው እንቅስቃሴ ሁሉ አስፈላጊውን ድጋፍና ዕገዛ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል። በመድረኩም ከጤና ሚኒስቴር፣ ከክልሉ ጤና ቢሮ፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ሃላፊዎች፣ ባለሙያዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
በነቀምቴ ከተማና አካባቢው የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትና የሳኒቴሽን አገልግሎትን ለማሳለጥ የተቀናጀ ጥረት እየተደረገ ነው
Feb 16, 2026 59
ነቀምት፤ የካቲት 9/2018 (ኢዜአ)፡- በነቀምቴ ከተማና አካባቢው የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትና የሳኒቴሽን አገልግሎትን ለማሳለጥ የተቀናጀ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት አስታወቀ። የከተማ አስተዳደሩ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ጽህፈት ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ ገላና መኮንን፤ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ በከተማዋ በተለይም በመጠጥ ውሃ እና ሳኒቴሽን ዙሪያ የተከናወኑ ተግባራትን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በማብራሪያቸውም የከተማዋን ህዝብ ብዛት ታሳቢ ባደረገ መልኩ የመጠጥ ውሃ አቅርቦትና ሳኒቴሽን አገልግሎትን ለማሻሻል የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት በነቀምቴ የዲጋ፣ ጫንጮ እና ሀዲያ የውሃ ግድቦችን አቅም በመደመር ለነዋሪዎች የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ተደራሽ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል። የሳኒቴሽን አገልግሎትን ለማሳለጥም በክልሉ መንግስት በጀት የሳኒቴሽን ፕሮጀክት ግንባታ እየተካሄደ ስለመሆኑ አንስተው ይህም የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድን በማሳለጥ ለከተማዋ ውበትና ፅዳት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በነቀምቴ ከተማ የውሃ እና ፍሳሽ ፅህፈት ቤት የውሃ ምርት እና ጥራት ዳይሬክተር ወይዘሮ ሙሉነሽ በቀለ፤ ለከተማዋ ነዋሪዎች የመጠጥ ውሃ አቅርቦትና ተደራሽነት ላይ በተቀናጀ መልኩ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በተለይ የውሃ አቅርቦትን ከማሳደግም ባለፈ በውሃ ውስጥ የሚገኙ ማዕድናት መብዛት እና ማነስ የሚያደርሰውን የጤና ችግር መፍታት በሚያስችል መልኩ ከአጋር ድርጅቶች ጋር እየሰራን እንገኛለን ብለዋል። ከውሃ አቅርቦትና ተደራሽነት ጋር በተገናኘ ኢዜአ ያነጋገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች የውሃ ጥራትና አቅርቦት ከፍተኛ መሻሻል በማሳየቱ መደሰታቸውን ገልጸዋል። ከነዋሪዎቹ መካከል ወይዘሮ አያልነሽ ታደሰ፤ ከዚህ በፊት በቂ የሆነ የውሃ አቅርቦትና ስርጭት ስላልነበር ለችግር፣ እንግልትና ወጪ ይዳረጉ እንደነበር አንስተዋል። አሁን ላይ ግን እነዚህ ችግሮች እየተቃለሉ ከፍተኛ መሻሻል ስለመኖሩ ተናግረዋል። የከተማዋ ነዋሪዎች አቶ አበራ ነጋሳ እና አቶ ደሞዜ ተስፋ፤ የውሃ አቅርቦትና ስርጭት ችግሩን ለመፍታት የተከናወኑ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ገልጸዋል። በከተማዋ የውሃ አቅርቦትን በማሻሻል ረገድ የሚታይ ለውጥ መምጣቱን ገልጸው ቀጣይነት እንዲኖረውም ነዋሪዎቹ ጠይቀዋል።
በክልሉ የመማር ማስተማር ሥራን በቴክኖሎጂ በመደገፍ ብቁና ተወዳዳሪ ዜጎችን ለማፍራት ትኩረት ተደርጓል
Feb 16, 2026 120
ሆሳዕና፤የካቲት 9/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመማር ማስተማር ሥራን በቴክኖሎጂ በመደገፍ ብቁና ተወዳዳሪ ዜጎችን ለማፍራት የተጀመረው ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገለጸ። ቢሮው በሁለተኛው ግማሽ ዓመት የዘርፉ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በሆሳዕና ከተማ አካሂዷል፡፡ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ እንዳሉት፤ በክልሉ በቴክኖሎጂ የታገዘ የመማር ማስተማር ሥራን ለማስፋት ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ ነው። በዚህም ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋ ለመፍጠር ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በተለያየ ደረጃ ባሉ ትምህርት ቤቶች በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዙ ትምህርቶችን በመስጠት ተማሪዎች አስፈላጊውን ዕውቀትና ክህሎት እንዲጨብጡ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡ ጊዜው የዲጂታል ቴክኖሎጂ በመሆኑ የመማር ማስተማር ሥራውን በቴክኖሎጂ መደገፍ ፍትሀዊ ተወዳዳሪነትን ለማስፈን ያለው ጠቄሜታ የጎላ በመሆኑ ለዘርፉ ትኩረት መሰጠቱን ነው አቶ አንተነህ ያመለከቱት፡፡ ለዚህም ስኬት በትምህርት ቤቶች የኮምፒውተር ቤተ ሙከራዎችን ጨምሮ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ግብዓቶችን የማደራጀት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን አቶ አንተነህ ገልጸዋል፡፡ በመድረኩ በክልሉ በተማሪዎች ውጤት ላይ የታየውን መሻሻል ለማስቀጠል የሚያስችል መግባባት ላይ መደረሱን ጠቁመው ለዚህም በተለይ የቴክኖሎጂ ተደራሽነት ላይ ጠንካራ ሥራዎች ይሰራሉ ብለዋል። ከመድረኩ ተሳታፊዎች መካከል የስልጤ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሹኩራላ አወል በበኩላቸው፤ በዞኑ የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል በሚሰሩ ሥራዎች ላይ የተስተዋሉ ተግዳሮቶችን በዘላቂነት ለመፍታት በጥናት የተደገፈ ሥራ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡ በዚህም ከተማሪ ወላጆች፣ መምህራን እና ከሌሎች ባለድርሻዎች ጋር በቅርበት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው ውጤትን መሰረት ያደረገ ክትትልና ድጋፍ ላይ እየተሰራ መሆኑንም አንስተዋል። በተለይም የመማር ማስተማር ስራውን በቴክኖሎጂ ለማገዝ አስፈላጊ ግብአቶች ተደራሽ የማድረግ ሥራዎች ትኩረት እንደተሰጣቸው ነው ያብራሩት። በዞኑ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የተጀመረው የትምህርት ቤቶችን ደረጃ የማሻሻል ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል ያሉት ደግሞ ሌላው የጉባኤው ተሳታፊ የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ መብራቴ ወልደማርያም ናቸው፡፡ በዚህም በዘንድሮው ዓመት ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ ሀብት ማሰባሰብ የተቻለ ሲሆን በተለይም የመማር ማስተማር ስራውን በቴክኖሎጂ ለማስደገፍ ግብአቶች የማሟላት ስራ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ብለዋል። በተጨማሪም አዳዲስ የቅድመ አንደኛ ትምህርት ቤቶችን ግንባታ ሥራ ማስፋፋትም ልዩ ትኩረት የተሰጠው መሆኑን ጠቅሰዋል። በመድረኩ የቢሮው፣ የዞን፣ የልዩ ወረዳ፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ የዘርፉ ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ነው፡፡
ኢኮኖሚ
በበጀት ዓመቱ ያለፉት ወራት በአምቦ ከተማ ከ9 ሺህ ለሚልቁ ወጣቶች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል
Feb 17, 2026 31
አምቦ፤ የካቲት 10/2018 (ኢዜአ)፦ በበጀት ዓመቱ ያለፉት ወራት ከ9 ሺህ ለሚበልጡ ወጣቶች የሥራ ዕድል መፈጠሩን የአምቦ ከተማ አሥተዳደር የሥራ ዕድል ፈጠራ እና ክኅሎት ጽሕፈት ቤት ገለጸ። የሥራ ዕድሉ የተፈጠረው በከተማ ግብርና፣ በአገልግሎት ዘርፍ፣ በኮንስትራክሽን እና ሌሎችም መሆኑን የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ እሸቱ አበራ ለኢዜአ ተናግረዋል። በዚህም መሠረት በግብርና ዘርፍ ለተሰማሩት ወጣቶች 20 ሺህ 554 ሔክታር መሬት እንዲሁም በአገልግሎት ለተሰማሩት ለመሥሪያና ለመሸጫ የሚሆኑ 37 ሼዶች ተገንብተው መተላለፋቸውን አብራርተዋል። ከሥራ ፈጠራው ጎን ለጎን ለ591 ኢንተርፕራይዞች 156 ሚሊየን ብር የገበያ ትሥሥር መፈጠሩንም ጠቁመዋል። የሥራ ዕድል የተመቻቸላቸው ወጣቶችም እስካሁን ከ318 ሚሊየን ብር በላይ በባንክ መቆጠባቸውን ገልጸዋል። በበጀት ዓመቱ ለ13 ሺህ ወጣቶች በተለያዩ ዘርፎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ እየተሠራ መሆኑንም አስገንዝበዋል።
የአፋር ክልልን ተፈጥሯዊ ፀጋ በመጠቀም ስንዴን በስፋት የማልማቱ ሥራ ቀጥሏል
Feb 17, 2026 46
አዲስ አበባ፤ የካቲት 10/2018 (ኢዜአ)፡- በአፋር ክልል ያለውን ሰፊ ለም መሬትና የውኃ አማራጮች በመጠቀም ስንዴን በስፋት የማልማቱ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ አስታወቀ። የስንዴን ምርታማነት ለመጨመርም ለአካበቢው የአየር ሁኔታ የተመቸ የዘር ማላመድ ሥራ በሰርቶ ማሳያና በከፊል አርብቶ አደሮች ማሳ ላይ በስፋት እየተካሄደ መሆኑን ነው በቢሮው የእርሻ ዘርፍ ኃላፊ አሕመድ አሚን የገለጹት። በዚህም መሠረት በዘንድሮው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት 1 ሺህ 442 ሔክታር ላይ ዝርያን የማላመድ ሥራ እየተሠራ መሆኑን ለኢዜአ አረጋግጠዋል። ይህም የዘር አቅርቦትን በራስ ዐቅም ለመሸፈንና የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የተያዘው ግብ እንዲሳካ ዕድል የሚፈጥር መሆኑን አመላክተዋል። ከስንዴ ምርት ባለፈ ሱፍና ሩዝን በሰፊው በማላመድ ተስፋ ሰጪ ውጤቶች እየታዩ መሆኑን ጠቁመዋል። የግብዓት አቅርቦት ዘርፍ ኃላፊ ሃሩን አሊ በበኩላቸው፤ የስንዴ ዘር ብዜት ከማካሄድ ባለፈ በማዳበሪያና ሌሎች የግብርና ግብዓቶች አቅርቦት ረገድ ተስፋ ሰጪ ሥራዎች እየተሠሩ ነው ብለዋል። የስንዴ ዘርን በማላመድ ሥራ ለ15 ሺህ ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠሩን ያስታወቁት ደግሞ በቢሮው የሰብል ልማት ዳይሬክተር ሃመዱ መሐመድ ናቸው።
ኢትዮጵያ በሜጋ የልማት ፕሮጀክቶች ያመጣችው ለውጥ አስደናቂ ነው - ልዑል ሎንኮኬላ ዲላሚኒ
Feb 16, 2026 98
አዲስ አበባ፤ የካቲት 9/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በታላቁ የሕዳሴ ግድብና በሌሎች ሜጋ የልማት ፕሮጀክቶች ያመጣችው ለውጥና ያስመዘገበችው ስኬት አስደናቂ መሆኑን የኢስዋቲኒ ኪንግደም የተፈጥሮ ኃብትና ኃይል ሚኒስትር ልዑል ሎንኮኬላ ዲላሚኒ ገለጹ። ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብም ኢትዮጵያ ከራሷ አልፎ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራትን በኃይል ለማስተሳሰር ያላትን ቁርጠኝነት በተግባር ያረጋገጠችበት ነው ብለዋል። 39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ “ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ ተካሂዷል። በጉባኤው የኢስዋቲኒ ኪንግደም የተፈጥሮ ኃብትና ኃይል ሚኒስትር ልዑል ሎንኮኬላ ዲላሚኒ ለኢዜአ እንዳሉት፤ በአፍሪካ የውኃ መሰረተ ልማት ማስፋፋት ይበልጥ ትኩረት ይፈልጋል ብለዋል። ያለ ውኃ ልማት የምንፈልጋትን አፍሪካ እውን ማድረግ አይቻልም ያሉት ሚኒስትሩ የአፍሪካ ሀገራት በቂ በጀት በመመደብ በውኃ ላይ ያላቸውን ኢንቨስትመንት ከፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል። ኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብን በራሷ አቅም ገንብታ ለውጤት ማብቃቷ እንዳስደነቃቸውም ገልጸዋል። ግድቡ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች አፍሪካ አገራትም የሚተርፍ የፕሮጀክት አፈጻጸሙም በምሳሌነት የሚወሰድ መሆኑን ጠቅሰዋል። ግድቡ ኢትዮጵያ አፍሪካን በኃይል ለማስተሳሰር ያላትን ቁርጠኝነት ያረጋገጠችበት ስኬታማ ፕሮጀክት መሆኑን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ከኃይል መሰረተ ልማት ባሻገር በመንገድ እና ሌሎች የልማት መስኮች አርዓያ የሚሆን ለውጥ ማስመዝገቧን አንስተዋል። ከስምንት ዓመት በፊት ኢትዮጵያ መጥቼ ነበር፤ ኢትዮጵያ እንደዚህ አልነበረችም፤ አሁን ግን በሁሉም የልማት መስኮች ተጨባጭ ውጤቶችን አምጥታለች ሲሉም ገልጸዋል። በአዲስ አበባ ቆይታቸው በተመለከቱት ለውጥና የልማት ጉዞ መደነቃቸውንም ተናግረዋል። በኢትዮጵያ እየተመዘገበ ያለው ውጤት የአመራሩን የገዘፈ ሚና የሚመሰክር ነው ያሉት ሚኒስትሩ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም በአብነት የሚጠቀስ ነው ብለዋል።
በክልሉ አዳዲስ ባለሀብቶችን በመሳብና ተኪ ምርቶችን በማምረት ውጤት ተመዝግቧል
Feb 16, 2026 63
ባህር ዳር፤ የካቲት 9/2018 (ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ባለፉት ስድስት ወራት አዳዲስ ባለሀብቶችን በመሳብና ተኪ ምርቶችን በማምረት ውጤት መመዝገቡን የክልሉ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው ሃላፊ አቶ እንድሪስ አብዱ እንደገለጹት በክልሉ ዘርፉን ለማሳደግ የ25 ዓመት አሻጋሪ የልማት እና የ5 ዓመት ስትራቴጅክ ዕቅድ ታቅዶ እየተተገበረ ነው። በዚህም ባለፉት ስድስት ወራት አዳዲስ ባለሀብቶችን በመሳብና ተኪ ምርቶችን በማምረት ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል። በበጀት አመቱ ስድስት ወራት 183 ቢሊዮን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ ከ1 ሺህ 800 በላይ አዳዲስ ባለሃብቶችን ወደ ክልሉ መሳብ መቻሉን ጠቅሰዋል። ለባለሃብቶቹ ቦታ ከማመቻቸት ባለፈ ፈጥነው ወደ ስራ እንዲገቡ በማድረግ የቅርብ ክትትልና ድጋፍ እየተደረገ ነው ብለዋል። በክልሉ ተኪ ምርቶችን በማምረት ሰፊ ስራ መሰራቱን አንስተው በግማሽ ዓመቱ ከ321 ሺህ ቶን በላይ የኢንዱስትሪ ተኪ ምርቶችን በማምረት ከ366 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ማዳን መቻሉን ተናግረዋል። እንዲሁም 43 ሺህ ቶን የተለያዩ ምርቶችን ለውጭ ገበያ በማቅረብ ከ112 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ገቢ መገኘቱን አብራርተዋል። የኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅምም ከ59 በመቶ ወደ 62 በመቶ በላይ ማሳደግ እንደተቻለ ጠቅሰው፤ በዘርፉ ከ47 ሺህ ለሚበልጡ ወገኖች የስራ እድል ተፈጥሯል ብለዋል። በዘርፉ የአገልግሎት አሰጣጡን ማሻሻል መቻሉን ጠቁመው በተለይም በርካታ አገልግሎቶችን በባህር ዳርና ደሴ ከተሞች ወደ ሞሶብ አንድ ማዕከል በማስገባት ባለሃብቶች ቀልጣፋና ፈጣን አገልግሎት እንዲያገኙ መደረጉን ጠቅሰዋል። በቀጣይ በዘርፉ የባለድርሻ አካላትን ቅንጅት ከማሳደግ ባለፈ የተገኙ ስኬቶችን የማጠናከርና የተስተዋሉ ድክመቶችን የማስተካከል ስራ በትኩረት እንደሚከናወን አመላክተዋል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
ኢትዮጵያ የዲጂታል ክፍያ ምህዳር በመፍጠር ለአፍሪካ የዲጂታል ስርዓት ሽግግር ሚናዋን እየተወጣች ነው
Feb 16, 2026 82
አዲስ አበባ፤ የካቲት 9/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የዲጂታል ክፍያ ምህዳር በመፍጠር ለአፍሪካ የዲጂታል ስርዓት ሽግግር ሚናዋን እየተወጣች መሆኑን በተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ጸሐፊ ክላቨር ጋቴቴ ገለጹ፡፡ የአፍሪካ ቢዝነስ ፎረም 2026 "የአፍሪካን የወደፊት ተስፋ በገንዘብ መደገፍ፣ የሥራ ዕድልና ኢኖቬሽን ለዘላቂ ሽግግር" በሚል መሪ ሀሳብ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ተካሂዷል። የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ጸሐፊ ክላቨር ጋቴቴ በዚሁ ወቅት፤ አፍሪካ ሁሉን አቀፍ ሽግግር ለመጀመር ዝግጅት ላይ ሳትሆን ቀደም ብላ ወደ ሂደቱ መግባቷን ገልጸዋል። የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ከ1 ነጥብ 5 ቢሊየን በላይ ሕዝብን ያቀፈ አንድ የገበያ ማዕከል የፈጠረ መድረክ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በአፍሪካ የዲጂታል ግብይት ሥርዓት መስፋፋትና የስታርትአፕ ንቅናቄ እያደገ መምጣቱን ገልጸው፤ በኢትዮጵያ ያለውን የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት በምሳሌነት ጠቅሰዋል፡፡ በኢትዮጵያ በሺዎች የሚቆጠሩ ነጋዴዎችና ወኪሎች በዲጂታል ሥርዓት እየተሳተፉ መሆኑን በማንሳት፤ የአፍሪካን አካታች የዲጂታል ሽግግር የሚያንጸባርቅ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አፍሪካ እሴት የተጨመረባቸውን ምርቶች ለውጭ ገበያ ማቅረብ መጀመሯ ትልቅ ስኬት መሆኑን ገልጸው፤ የአረንጓዴ ኃይል፣ የዲጂታል ሥርዓትና ክህሎትን በፋይናንስ መደገፍ ይገባል ብለዋል፡፡ የአፍሪካ አሕጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣናን ሙሉ በሙሉ መተግበር የግድ ይላል ያሉት ዋና ጸሐፊው፤ የውስጥ የገቢ አቅምን ማሳደግና ፈጠራን ማጎልበት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን በፖሊሲ ትንተና፣ በትብብርና በሌሎችም መስኮች አስፈላጊውን እገዛ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑንም ዋና ጸሐፊው አረጋግጠዋል። በአረብ ባንክ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ልማት ዋና ጸሐፊ ፋቲማ ፋሩክ (ዶ/ር)፥ አፍሪካ እምቅ ሀብት ያላት የወጣቶች ሀገር መሆኗን ገልጸዋል፡፡ የአረብ ባንክ ባለፉት አምስት አሥርት ዓመታት በአረብ ካፒታል እና በአፍሪካ ቀዳሚ የልማት ትኩረቶች መካከል ድልድይ ሆኖ ሲያገልግል ቆይቷል ብለዋል፡፡ ባንኩ ከሰሀራ በታች ላሉ የአፍሪካ ሀገራት የፋይናንስ አቅርቦት እየፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የአፍሪካ ፋይናንስ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሳማይላ ዙባይሩ በበኩላቸው፤ በአፍሪካ የሚከናወነው አካታች ሽግግር ሰፊ የሥራ ዕድል ይፈጥራል ብለዋል፡፡ የሥራ ዕድል ፈጠራ የሽግግር ውጤት መሆኑን በማንሳት፤ ኢንዱስትሪ ደግሞ ልማትን በማፋጠን ከተማን እንደሚያሳድግ ገልጸዋል፡፡ በአምራችና አገልግሎት ዘርፎች የመንግሥትና የግል አጋርነትን ማጠናከር እንደሚገባ ጠቅሰው፤ ባንኮች ለልማት ፋይናንስ ድጋፍ ዝግጁ መሆን አለባቸው ነው ያሉት፡፡ ባንኮች ፕሮጀክቶችን ለመደገፍ ዝግጁ ናቸው ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፤ ደረጃውን የጠበቀ የአደጋ ቅነሳ የፋይናንስ ምደባ ማድረግ ላይ እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ የዲጂታላይዜሽን ስኬት በፈጠራና የቴክኖሎጂ ክህሎት የበለጸገ የሰው ሃብት ለማፍራት ትልቅ ዕድል ፈጥሯል
Feb 16, 2026 84
አዲስ አበባ፤ የካቲት 9/2018(ኢዜአ):- የኢትዮጵያ የዲጂታላይዜሽን ስኬት በፈጠራና የቴክኖሎጂ ክህሎት የበለጸገ የሰው ሃብት ለማፍራት ዕድል መፍጠሩን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ኮምፒውቴሽናል ሳይንስ ኮሌጅ ገለጸ። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ኮምፒውቴሽናል ሳይንስ ኮሌጅ 80ኛውን ዓለም ዓቀፍ የኮምፒውተር ቀንን አስመልክቶ የመጀመሪያው የስማርት ሲስተም ሶሊዩሽን ጉባኤ አካሂዷል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዲጂታላይዜሽን መሠረተ ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ወንደሰን ሙሉጌታ፤ ኮሌጁ ካለፉት አርባ ዓመታት ጀምሮ በኮምፒውተር ሳይንስ ትምህርት ብቁ ሙያተኞችን እያፈራ ይገኛል ብለዋል። የዓለም ዓቀፍ የኮምፒውተር ቀን ዝግጅቱም ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ የደረሰችበትን ዕድገት በመቃኘት የተወዳዳሪነት አቅምን ለማሳየት እንደሚረዳ ገልጸዋል። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የራስ ገዝነት አስተዳደር የማሻሻያ እርምጃዎች የኮሌጁን የቴክኖሎጂ አቅም በማጎልበት ለኮምፒውተር ሳይንስ የጥናትና ምርምር ሥራ ዕድገት ምቹ ዕድሎችን እንደፈጠረ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ የተወዳዳሪነት አቅም ግስጋሴ በዕውቀትና ክህሎት የበቃ የሰው ሃይል ለማፍራት ምቹ መደላድል እየተፈጠረ እንደሚገኝ አንስተዋል። በዩኒቨርሲቲው የኮምፒዩተር ሳይንስ ትምህርት ክፍል ኃላፊ አምሳለ ዘላለም (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ለኢትዮጵያ ዲጂታላይዜሽን ሥርዓት አቅም የሚሆን የሰው ሃብት እያፈሩ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ለዚህም በዘርፉ የላቀ ልምድና ተሞክሮ ካላቸው አካላት ጋር በመተባበር ለኢትዮጵያ የዲጂታልና ኢኖቬሽን ልማት የበኩላቸውን ገንቢ ሚና እየተወጡ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ኮምፒዩተር ሳይንስ ትምህርት ክፍል ረዳት ፕሮፌሰር ዳግማዊ ለማ፤ ''የኮምፒዩተር ዕድገት በኢትዮጵያ ከየት ወደ የት'' በሚል የመነሻ ጽሑፋቸው የኢትዮጵያ የዲጂታል ልማት ዕድገት እያስመዘገበ ነው ብለዋል። በቀጣይም ፈጣን ዕድገት በሚያስመዘግበው የዲጂታል ዓለም ውስጥ ተወዳዳሪ በቴክኖሎጂ መስክ የላቀ ዕውቀትና ክህሎት የተላበሰ የሰው ሃይል የማፍራት ስራ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ኢትዮጵያ በየቀኑ የመሪነት ብቃቷን የምታሳይ ሀገር ሆናለች
Feb 16, 2026 86
አዲስ አበባ፤ የካቲት 9/2018(ኢዜአ):-ኢትዮጵያ ሰው ሰራሽ አስተውሎትን ጨምሮ በሁሉም መስክ በየቀኑ የመሪነት ብቃቷን የምታሳይ ሀገር ሆናለች ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት ረዳት ዋና ፀሐፊ እና የተመድ የልማት ፕሮግራም የአፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር አሁና ኢዚያኮንዋ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና በተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በቲምቡክቱ ኢኒሼቲቭ አማካኝነት የተቋቋመውን የሰው ሰራሽ አስተውሎት የዩኒቨርሲቲ የፈጠራ ማዕከል (AI UniPod) በይፋ አስጀምረዋል። የተባበሩት መንግሥታት ረዳት ዋና ፀሐፊ እና የተመድ የልማት ፕሮግራም የአፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር አሁና ኢዚያኮንዋ፥ የሰው ሰራሽ አስተውሎት የዩኒቨርሲቲ ፈጠራ ማዕከል “AI UniPod” በይፋ ሥራ መጀመሩ የአፍሪካን እያደገ የመጣ በራስ መተማመን የሚያሳይና ህልማችንን እውን ያደረገ ነው ብለዋል። በአፍሪካ ያላመረትነውን እንድንጠቀም ያመረትነውን ደግሞ ለሌላው እንድንሰጥ ሲደረግ መቆየቱን አውስተዋል። አሁን ለውጥ እየመጣ ነው ያሉት ዳይሬክተሯ፥ ቴክኖሎጂን የምናይበት መንገድ እየተቀየረ ነው፤ ለዚህም አፍሪካ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍ ተጠቃሚ ብቻ ሳትሆን ፈጣሪ፣ ቀራጭና መሪ እንድትሆን እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል። ይህም ለሁሉን አቀፍና ቀጣይነት ላለው ልማት የሚበጅ ቁልፍ እርምጃ መሆኑን ገልጸዋል። የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ በተጠናቀቀ ማግስት ይህ ማዕከል መከፈቱ የአፍሪካ መሪዎች በአጀንዳ 2063 ያስቀመጡትን የፈጠራ፣ የቴክኖሎጂና የሰው ሃይል ልማት ግብ እንደሚያንጸባርቅ አንስተዋል። እንደ “AI UniPod” ያሉ ተነሳሽነቶች ተግባራዊ የፈጠራ ስራዎች እንዴት ለልማት መፍትሄ እንደሚሆኑ የሚያሳዩ መሆናቸውንም ጠቁመዋል። ማዕከሉ በኢትዮጵያ መንግሥትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የጋራ ተሳትፎ እውን መሆኑን በመጥቀስ፥ ለዚህም ምስጋና አቅርበዋል። ኢትዮጵያ በየቀኑ የመሪነት ብቃቷን የምታሳይ ሀገር መሆኗን በማንሳት፥ እንዲህ አይነት ስትራቴጂካዊ ስራዎችን እንድናሳካም የሀገሪቱ መንግሥትና ተቋማት ወሳኝ ሚና መጫወታቸውን ጠቅሰዋል። የማዕከሉ ዓላማ ሰው ሰራሽ አስተውሎት አፍሪካን ይለውጣል ወይ የሚለው ሳይሆን አፍሪካን እንዴት መለወጥና ምን ፋይዳ ማምጣት አለበት የሚለው ላይ ያተኮረ መሆኑን ተናግረዋል። የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በመላው አፍሪካ በአካዳሚው፣ በመንግስትና በገበያው መካከል ያለውን ክፍተት ለመሙላት የፈጠራ ማዕከላት ላይ ኢንቨስት እያደረገ ነው ብለዋል። ከእንግዲህ የምርምር ስራዎች መደርደሪያ ላይ ተቀምጠው አይቀሩም ያሉት ሀላፊዋ፥ ይልቁንም በተግባር ተተርጉመው ህዝባችን የሚጠቅሙበት ወሳኝ ጉዞ መጀመሩን ጠቁመዋል። ዛሬ የተመረቀው የሰው ሰራሽ አስተውሎት የዩኒቨርሲቲ ፈጠራ ማዕከል መሰረቱን ኢትዮጵያ አድርጎ አህጉራዊ ሚና እንዲኖረው መታቀዱን ገልጸዋል። የአየር ንብረት ለውጥን፣ የምግብ ዋስትናን፣ ንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦትን በሚመለከት አፍሪካ ያላትን እምቅ አቅም ለመጠቀም እንደዚህ ያሉ ማዕከላት ወሳኝ መሆናቸውንም አፅንኦት ሰጥተዋል።
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አፍሪካ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ምርምርና ቴክኖሎጂ ፈጠራ መሪ እንድትሆን ይሠራል
Feb 16, 2026 94
አዲስ አበባ፤ የካቲት 9/2018(ኢዜአ)፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አፍሪካ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ምርምርና ቴክኖሎጂ ፈጠራ መሪ እንድትሆን የበኩሉን ሚና እንደሚወጣ የዩኒቨርሲቲው ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ክፍሌ(ዶ/ር) ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና በተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በቲምቡክቱ ኢኒሼቲቭ አማካኝነት የተቋቋመውን የሰው ሰራሽ አስተውሎት የዩኒቨርሲቲ የፈጠራ ማዕከል (AI UniPod) በይፋ አስጀምረዋል። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ክፍሌ(ዶ/ር)፥ የሰው ሰራሽ አስተውሎት የዩኒቨርሲቲ ፈጠራ ማዕከሉ ሥራ መጀመር በኢትዮጵያ ዲጂታል ምርምር ጉዞ ውስጥ ትልቁ ብሔራዊ ምዕራፍ ነው ብለዋል። በተቀናጀ አጋርነት እውን የሆነው ይህ ማዕከል ሀገራችን በሰው ሰራሽ አስተውሎት ምርምርና ልማት ያላትን አቅም እንደሚያጠናክርም ጠቁመዋል። ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከሀገሪቱ ቀዳሚ የምርምር ተቋምነቱና ካለበት ኃላፊነት ጋር ቀጥታ የሚጣጣም ነው ብለዋል። ዩኒቨርሲቲው ይህ የፈጠራ ማዕከል በዕውቀት ላይ የተመሰረተና ቀጣይነት ያለው እንዲሆን የአካዳሚክ መሰረትን፣ የምርምር እውቀትንና የሰው ኃይልን እንደሚያቀርብም ጠቁመዋል። ሰው ሰራሽ አስተውሎት የቴክኖሎጂ ዘርፍ ብቻ ሳይሆን፣ ምህንድስናን፣ ግብርናን፣ ጤና ሳይንስንና የመንግስት ፖሊሲን የሚያስተሳስር ዘርፈ-ብዙ መስክ እንደሆነም ጠቅሰዋል። አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በእነዚህ ዘርፎች የድህረ-ምረቃ ስልጠናዎችን እያስፋፋ እንደሚገኝ ጠቁመው በሰው ሰራሽ አስተውሎት የመጀመሪያውን የዶክትሬት ዲግሪ መርሃ-ግብር በመጀመር ምሁራንን እያፈራ ነው ብለዋል። የዚህ ማዕከል መመሥረት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ አጀንዳዎች፣ በተለይም ከዲጂታል ኢትዮጵያና ከብሔራዊ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ፖሊሲ ጋር የተቆራኘ መሆኑን አንስተዋል። ሰው ሰራሽ አስተውሎትን በግብርና ዘርፍ መረጃን መሰረት ያደረገ የሰብል ክትትልና የአየር ንብረት ለውጥ መቋቋም አቅምን ማሳደግ፣ በጤና ዘርፍ የበሽታ ምርመራና የሕክምና ጥራትን ማሻሻል፣ በትምህርት መስክ ደግሞ የመማር ማስተማር ሂደቱን ውጤታማ የሚያደርጉ የቴክኖሎጂ ትንታኔዎችን መጠቀም ይገባል ነው ያሉት። ዛሬ ሥራ የጀመረው የፈጠራ ማዕከልም የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክና ምርምር ስርዓት አካል ሆኖ እንደሚያገለግል አንስተዋል። የማዕከሉን እንቅስቃሴዎች ከድህረ-ምረቃ ምርምሮች ጋር በማስተሳሰር፣ የአእምሯዊ ንብረት መብቶችን ባከበረ መልኩ የፈጠራ ውጤቶች ወደ ገበያ የሚወጡበትን መንገድ እናመቻቻለን ነው ያሉት። አፍሪካ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍ ያላት ተሳትፎ ከተጠቃሚነት ወደ አምራችና አበርካችነት ሊሸጋገር እንደሚገባ ጠቁመዋል። የአፍሪካን መረጃዎችና ቋንቋዎች ያላካተቱ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ስርዓቶች ፋይዳቸው አነስተኛ በመሆኑ የራስን የምርምር አቅም መገንባት ስትራቴጂካዊ ጉዳይ ነው ብለዋል። አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፈጠራና የምርምር ስነ-ምግባርን የተከተሉና አህጉራዊ እውነታን ያገናዘቡ የሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂዎችን በማበልጸግ ረገድ የበኩሉን እንደሚወጣ አረጋግጠዋል።
ስፖርት
በሻምፒዮንስ ሊግ ጥሎ ማለፍ ማጣሪያ ቤኔፊካ ከሪያል ማድሪድ ሞናኮ ከፒኤስጂ የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ይጠበቃሉ
Feb 17, 2026 52
አዲስ አበባ፤ የካቲት 10/2018 (ኢዜአ)፦ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ማጣሪያ የመጀመሪያ ዙር መርሐ ግብር ዛሬ እና ነገ ይካሄዳል። በስታዲዮ ዳ ሉዝ ምሽት አምስት ሰዓት ላይ ቤኔፊካ ከሪያል ማድሪድ ይጫወታሉ። በሻምፒዮንስ ሊጉ አዲስ ፎርማት ቤኔፊካ 24 እና ሪያል ማድሪድ ዘጠነኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል። ሁለቱ ቡድኖች በቅርቡ በውድድሩ ላይ አድርገውት በነበረው ጨዋታ ቤኔፊካ 3 ለ 2 አሸንፏል። ይህም ቤኔፊካን ወደ ጥሎ ማለፍ እንዲገባ ያደረገ ሲሆን፤ ሪያል ማድሪድ በቀጥታ ወደ ጥሎ ማለፍ እንዳይገባ ምክንያት ሆኗል። ጆዜ ሞውሪኒዮ ቀድመው ያሰለጠኑትን ሪያል ማድሪድ በድጋሚ ይገጥማሉ። በሌላኛው መርሐ-ግብር ሞናኮ ከፒኤስጂ በሉዊስ ሁለተኛ ስታዲየም ምሽት አምስት ሰዓት ላይ ይጫወታሉ። ሞናኮ በሊግ እርከን የውድድር ምዕራፍ 21ኛ፣ ፒኤስጂ 11ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል። ፒኤስጂ የወቅቱ የሻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊ ነው። በሌሎች መርሐ-ግብሮች ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ከአትላንታ ምሽት አምስት ሠዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። ጋላታሳራይ ከጁቬንቱስ ምሽት 2 ሰዓት ከ45 ላይ ይጫወታሉ። የመልስ ጨዋታዎች በቀጣይ ሳምንት ይደረጋሉ። በማጣሪያው የሚሳተፉት ክለቦች በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ አዲሱ የውድድር ፎርማት ከ9ኛ እስከ 24ኛ ደረጃ ይዘው ያጠናቀቁ ናቸው። ከ36 ክለቦች መካከል በስምንት ጨዋታዎች የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ስምንት ቡድኖች በቀጥታ ወደ ጥሎ ማለፉ ገብተዋል። አርሰናል፣ ባየር ሙኒክ፣ ሊቨርፑል፣ ባርሴሎና፣ ማንችስተር ሲቲ፣ ቼልሲ፣ ቶተንሃም ሆትስፐርስ እና ስፖርቲንግ ሊዝበን በቀጥታ ጥሎ ማለፉን የተቀላቀሉ ቡድኖች ናቸው።
የኤፍኤ ካፕ አምስተኛ ዙር ድልድል ይፋ ሆነ
Feb 16, 2026 68
አዲስ አበባ፤ የካቲት 9/2018 (ኢዜአ)፦ የኤፍኤ ካፕ አምስተኛ ዙር እጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ማምሻውን ተከናውኗል። በዚሁ መሰረት ማንስፊልድ ታውን ከአርሰናል፣ ኒውካስትል ዩናይትድ ከማንችስተር ሲቲ፣ ዎልቭስ ከሊቨርፑል እና ሬክስሃም ከቼልሲ ይጫወታሉ። ሊድስ ዩናይትድ ከኖርዊች ሲቲ፣ ፉልሃም ከሳውዝሃምፕተን፣ ዌስትሃም ዩናይትድ ከማክስፊልድ እና ብሬንትፎርድ አሸናፊ እንዲሁም ሰንደርላንድ ከፖርት ቫሌ እና ብሪስቶል ሲቲ አሸናፊ ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። የኤፍኤ ካፕ አምስተኛ ዙር መርሐ-ግብር የካቲት 28 እና 29 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል።
አርሰናል በኤፍኤ ካፕ ወደ አምስተኛ ዙር አለፈ
Feb 15, 2026 129
አዲስ አበባ ፤ የካቲት 8/2018 (ኢዜአ)፡- በእንግሊዝ ኤፍኤ ካፕ የአራተኛ ዙር መርሐ-ግብር አርሰናል ዊጋን አትሌቲክን 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል። ማምሻውን በኤምሬትስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኖኒ ማዱዌኬ፣ ጋብርኤል ማርቲኔሊ፣ ጋብርኤል ጄሱስ እና የዊጋን አትሌቲኩ ጃክ ሃንት በራሱ ላይ የማሸነፊያ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። በጨዋታው ላይ አርሰናል ከፍተኛ ብልጫ ወስዶ ተጫውቷል። ሁለት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን ያቀበለው ኤበረቺ ኤዘ የጨዋታው ኮከብ ሆኖ ተመርጧል። ውጤቱን ተከትሎ አርሰናል ወደ አምስተኛ ዙር አልፏል። አርሰናል የኤፍኤ ካፕ ዋንጫን 14 ጊዜ በማንሳት ስኬታማው ክለብ ነው። በሊግ ዋን የሚገኘው የአንድ ጊዜ የውድድሩ አሸናፊ ዊጋን አትሌቲክ የኤፍኤ ካፕ ጉዞው አራተኛ ዙር ላይ ተገቷል። ዛሬ በተደረጉ ሌሎች ጨዋታዎች ፉልሃም፣ ሊድስ ዩናይትድ፣ ሰንደርላንድ እና ዎልቭስ ተጋጣሚዎቻቸውን በማሸነፍ ወደ አምስተኛ ዙር አልፈዋል።
ማንችስተር ሲቲ በኤፍኤ ካፕ ወደ አምስተኛ ዙር አለፈ
Feb 14, 2026 113
አዲስ አበባ ፤ የካቲት 7/2018 (ኢዜአ)፡- በእንግሊዝ ኤፍኤ ካፕ የአራተኛ ዙር መርሐ-ግብር ማንችስተር ሲቲ ሳልፎርድ ሲቲን 2 ለ 0 አሸንፏል። ማምሻውን በኢትሃድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ማርክ ጌሂ እና የሳልፎርድ ሲቲው አልፊ ዶሪንግተን በራሱ ላይ የማሸነፊያ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። አዲስ ፈራሚው ማርክ ጌሂ በሲቲ ማልያ የመጀመሪያ ጎሉን አስቆጥሯል። ውጤቱን ተከትሎ ማንችስተር ሲቲ ወደ አምስተኛ ዙር አልፏል። በሊግ ቱ(አራተኛ ዲቪዚዮን) የሚገኘው ሳልፎርድ ሲቲ የኤፍኤ ካፕ ጉዞው አራተኛ ዙር ላይ ተገቷል።
አካባቢ ጥበቃ
በምስራቅ ቦረና ዞን በመጪው ክረምት የሚተከሉ ችግኞች እየተዘጋጁ ነው
Feb 16, 2026 95
ነገሌ ቦረና፤ የካቲት 9/2018(ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ቦረና ዞን በመጪው ክረምት የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር የሚተከሉ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች እየተዘጋጁ ነው። ምስራቅ ቦረና በአብዛኛው የእንስሳት እርባታ የሚካሄድበት ቆላማ፣ ዝናብ አጠር እና ደረቃማ ዞን እንደሆነ ይታወቃል። የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ፣ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን መትከል፣ የውሃ አማራጮችን ለይቶ መጠቀምና ከእንስሳት እርባታ ጎን ለጎን መስኖን ማስፋት የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ መንግስት እያከናወናቸው ካሉ ተግባራት መካከል ይጠቀሳል። የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ኩልሌ ሸና ፤በዞኑ ከለውጡ ዓመታት ወዲህ ተግባራዊ የተደረገው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በሰው ሰራሽ እና በተፈጥሮ አዳጋዎች ሳቢያ የተራቆቱ አካባቢዎችን መልሶ ለማልማት እያስቻለ ነው ብለዋል። በዘንድሮው ዓመትም በ6 ሺህ ሔክታር መሬት ላይ ሁለንተናዊ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። ለመጪው ክረምት በዞኑ በሚገኙ ዘጠኝ ወረዳዎች የደን፣ የጥላ ዛፍ ፣ የእንስሳት መኖና የፍራፍሬ ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። በዞኑ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተተከሉ ችግኞችን ለመጠበቅና ለመንከባከብ ሰፊ ስራ ተሰርቷል ያሉት ምክትል ኃላፊው በዚህም አብዛኛው ችግኝ መጽደቁን ጠቅሰዋል፡፡ በተለይም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የተተከሉ የጽድ፣ ግራቪሊያ፣ ማንጎ፣ ፓፓያ፣ የእንስሳት መኖ እና የደንና የጥላ ዛፎች በተሻለ ሁኔታ መጽደቃቸውንም ለአብነት አንስተዋል። በዞኑ ሊበን ወረዳ የጎቢቻ ነዋሪ ሀጂ ቀራርሳ ጉራቻ፤ ባለፉት አመታት በደኖች ላይ በደረሰ ጉዳት ድርቅና የአካባቢ መራቆት ሲያስከትል መቆየቱን ያስታውሳሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተለያዩ ችግኞችን በመትከል የተፈጥሮ ሀብቱን መልሶ ለመተካት እየተደረገ ካለው ጥረት ባሻገር ችግኞቹን መትከልና መንከባከብ ለተሻለ ውጤት እንደሚያበቃ ነው የጠቀሱት። አቶ አብዲ ሮባ የዚሁ ወረዳና ቀበሌ ነዋሪ ሲሆኑ በየአመቱ በአካባቢው በሚከሰተው ድርቅ የወንዞችና ምንጮች መድረቅ፤ የእንስሳት መኖና የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ላይ ችግር እንደሚያጋጥም ገልጸዋል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተግባራዊ በተደረገው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ማህበረሰቡ የተሻለ ግንዛቤ ለመያዝ መቻሉንና ለውጥ መመዝገቡን ነው የገለጹት። በዚህም ማሕበረሰቡ ችግኞችን ከመትከል ባለፈ እንክብካቤም እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በተያዘው ዓመትም በተመሳሳይ መልኩ በመርሃ ግብሩ በመሳተፍ ዘላቂ ልማትና የምግብ ዋስትናን በሚያረጋግጡ ስራዎች ላይ የማተኮር እቅድ እንዳላቸው ጠቁመዋል፡፡ በምስራቅ ቦረና ዞን በ9 ወረዳዎች ባለፈው አመት በአረንጓዴ አሻራ ከተተከለው ችግኝ ውስጥ ከ75 በመቶ በላይ መጽደቁን መረጃዎች ያመለክታሉ።
ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ያስመዘገበችውን ስኬት አዲስ አበባ በራሷ ትናገራለች
Feb 15, 2026 98
አዲስ አበባ፤ የካቲት 8/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ያስመዘገበችውን ስኬት አዲስ አበባ በራሷ ትናገራለች ሲሉ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ፡፡ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሃሙድ አሊ ዩሱፍ የ39ኛው የመሪዎች ጉባኤ መጠናቀቅን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ለመቋቋም በአረንጓዴ አሻራ ለተመዘገበው ስኬት እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ያሳዩት ቁርጠኝነት በተግባር የሚታይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በአረንጓዴ አሻራ የተመዘገበውን ውጤት የአዲስ አበባ ከተማ በራሷ ትናገራለች ያሉት ኮሚሽነሩ፤ ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ በማዘጋጀት የአፍሪካ አቋም ለማሳወቅ ማጣቀሻ የሚሆን ሰነድ መጽደቁን ተናግረዋል፡፡ ጉባኤው በአየር ንብረት ፋይናንስ፣ ተጽዕኖን በመቋቋምና በሀይል ሽግግር የአፍሪካን ድምጽ የሚያንጸባርቅ አቋም የተያዘበት መሆኑን አንስተዋል፡፡ አፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ የበካይ ጋዝ ልቀት ተጽዕኖ ከ4 በመቶ እንደማይበልጥ በማንሳት፤ በብክለት የምትጎዳው ግን የላቀ ነው ብለዋል፡፡ በመሆኑም የአፍሪካ ሕብረት አባል ሀገራትን የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን መቋቋም የሚያስችል የማገገሚያ ዕቅድ እንዲያወጡ መደገፍ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡
የተፋሰስ ልማት ሥራው አርብቶ አደሩ ከእንስሳት እርባታ ጎን ለጎን በእርሻ ዘርፍ እንዲሰማራ ያግዛል
Feb 15, 2026 119
ሠመራ፤ የካቲት 8/2018 (ኢዜአ)፡- በአፋር ክልል የሚከናወነው የተፋሰስ ልማት ሥራ አርብቶ አደሩ ከእንስሳት እርባታ ጎን ለጎን በእርሻ ዘርፍም እንዲሰማራ ያግዛል ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር አወል አርባ ተናገሩ። የአፋር ክልል የ2018ዓ.ም የተፋሰስ ልማት ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር "የተቀናጀ ማኅበረሰብ አቀፍ የተፋሰስ ልማት ለምግብ ሉዓላዊነነት ስኬት" በሚል መሪ ሐሳብ በአውሲ ረሱ ዞን አደአር ወረዳ ተጀምሯል። ርዕሰ መሥተዳድር አወል በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የተፋሰስ ልማት ሥራዎችን ማጠናከር አርብቶ አደሩ ሕብረተሰባችን ከሚታወቅበት የኑሮ መሠረት ጎን ለጎን በእርሻ ሥራ እንዲሰማራ ጉልህ ድርሻ ይኖረዋል። የተፋሰስ ልማቱ በድርቅና ሌሎች አደጋዎች ምክንያት እየተመናመነ የመጣውን የተፈጥሮ ሀብት በመመለስ ሕብረተሰቡ የምግብ ሉዓላዊነቱን እንዲያረጋግጥና ከተረጂነት እንዲወጣ ያስችላል ብለዋል። በተለይም የተራቆቱ አካባቢዎች እንዲያገግሙና ምርታማ እንዲሆኑ በማድረግ አርብቶ አደሩ ከእንስሳት እርባታ ጎን ለጎን የእርሻ ሥራውን በማሳደግ፤ ለእንስሳቱ መኖ፣ ለራሱም የምግብ ፍጆታውን እንዲሸፍን የሚያስችለው መሆኑን ተናግረዋል። በዘንድሮው የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ከ200 ሺህ በላይ ሰዎችን በማሳተፍ ከ52 ሺህ ሔክታር በላይ የተፋሰስ ልማት ሥራ እንደሚከናወን ተገልጿል።
የበልግ እርሻን ቀድመው የሚጀምሩ አካባቢዎች በሚቀጥሉት አስር ቀናት የሚኖረውን የርጥበት ሁኔታ በአግባቡ ሊጠቀሙበት ይገባል
Feb 13, 2026 108
አዲስ አበባ፤ የካቲት 6/2018(ኢዜአ)፦ የበልግ እርሻን ቀድመው የሚጀምሩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በሚቀጥሉት አሥር ቀናት የሚኖረውን የርጥበት ሁኔታ በአግባቡ እንዲጠቀሙበት ኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ገለጸ። የኢትዮጵያ ሜቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ከየካቲት 4 እስከ የካቲት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ባሉት አሥር ቀናት የሚኖረውን የአየር ሁኔታ ትንበያ ይፋ አደርጓል፡፡ ኢንስቲትዩቱ ለኢዜአ በላከው መግለጫ፣ የበልግ እርሻ እንቅስቃሴ ቀድመው የሚጀምሩ አካባቢዎች የሚገኘውን እርጥበት በአግባቡ እንዲጠቀሙበት አሳስቧል። በሚቀጥሉት አሥር ቀናት በደቡብ ምዕራብ፣ በስምጥ ሸለቆና አዋሳኝ አካባቢዎች ላይ አነስተኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖር ገልጿል፡፡ በተጨማሪም በመካከለኛውና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን እንደሚጨምር አመልክቷል፡፡ በጋምቤላ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅና በደቡብ ምስራቅ አካባቢዎች የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ32 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ እንደሚቀጥል ተቋሙ ጠቁሟል። በቀጣይ የሚኖረው የአየር ሁኔታ ለቋሚ ተክሎች የተሻለ እድገት እንዲያገኙ ያግዛል፣ ለአርብቶ አደሩ የግጦሽ ሳርና የመጠጥ ውሃ አቅርቦትን ለማሻሻል ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር እንዲሁም ለበልግ እርሻ ማሳን ቀድሞ ለማዘጋጀትና የአፈር ውስጥ እርጥበትን ለማሻሻል እንደሚረዳም ጠቅሷል፡፡ ሆኖም የእርጥበት መጠን ለሰብል ዝርያ የሚበቃ ባለመሆኑና ደረቅ አየር ሁኔታም ስለሚስተዋል አርሶ አደሩ ይህንን ተገንዝቦ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ኢንስቲትዩቱ አሳስቧል። በሚቀጥሉት አሥር ቀናት በአብዛኞቹ ተፋሰሶች ላይ ደረቃማ የአየር ሁኔታ የሚጠበቅ በመሆኑ የገጸ-ምድር ውሃ ፍሰት ሊቀንስ እንደሚችል ተገልጿል። በተለይም በባሮ አኮቦ፣ በኦሞ ጊቤ፣ በስምጥ ሸለቆና በገናሌ ዳዋ ተፋሰሶች ላይ ዝቅተኛ የውሃ ፍሰት እንደሚኖር የተገለጸ ሲሆን በውሃ አጠር አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎች ውሃን ከብክነትና ከብክለት እንዲከላከሉ፣ እንዲሁም አማራጭ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት መንገዶችን እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀርቧል። በሚቀጥሉት አሥር ቀናት ለበልግ እርሻ ዝግጅትና ለቋሚ ተክሎች እንክብካቤ አመቺ ቢሆኑም ለዝርያ የሚበቃ ዝናብ ባለመኖሩና የውሃ መጠን ሊቀንስ ስለሚችል አስፈላጊው ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ ተመላክቷል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
ዘመናትን የተሻገረው የኢትዮጵያ እና የቱርክዬ ታሪካዊ አጋርነት
Feb 16, 2026 145
የኢትዮጵያ እና ቱርኪዬ ግንኙነት ክፍለ ዘመናትን ያስቆጠረ ነው። የአፍሪካ ጥንታዊ ስልጣኔ ባለቤት የሆነችው ኢትዮጵያ ኦቶማን ኢምፓየርን ጨምሮ በታሪክ ከመካከለኛው ምስራቅ እና አውሮፓ ጋር ታሪካዊ ግንኙነት ነበራት። ኦቶማን ኢምፓየር ለዘመናዊቷ ቱርክዬ መሰረት ጥሎ አልፏል። በ20ኛ ክፍለ ዘመን መግቢያ ላይ የተጀመረው የሀገራቱ ወዳጅነት በዲፕሎማሲ እና ንግድ ልውውጥ ላይ የተመረኮዘ ነው። ቱርክዬ አፍሪካን እንደ ስትራቴጂካዊ አጋር የምትቆጥር ሲሆን አፍሪካ ህብረትን ጨምሮ ቁልፍ አህጉራዊ ተቋማት የሚገኙባት እና የአፍሪካ መዲና ኢትዮጵያ የዚህ ትብብር አካል ናት። ኢትዮጵያ እና ቱርክዬ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን የጀመሩት እ.አ.አ 1896 መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ። የመጀመሪያ የኦቶማን-ቱርክዬ ቆንስላ ጽህፈት ቤት እ.አ.አ በ1912 በሐረር ከተማ ተከፍቷል። ቱርክዬ ከሰሃራ በታች የመጀመሪያውን ኤምባሲ የከፈተችው በኢትዮጵያ ሲሆን ወቅቱም እ.አ.አ በ1926 ነበር። ኢትዮጵያ በቱርክዬ ኤምባሲዋን የከፈተችው እ.አ.አ በ1933 ነው። ያለፉት ሁለት አስርት ዓመታት የኢትዮጵያ እና የቱርክዬ ግንኙነት ከፍተኛ እድገት ያሳየበት ነው። ኢኮኖሚ የሁለቱ ሀገራት አጋርነት ምሰሶ እንደሆነ ይጠቀሳል። የቱርክዬ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በማኑፋክቸሪንግ፣ በጨርቃ ጨርቅ፣ በግንባታ እና በግብርና ማቀነባበሪያ ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ተሰማርተው ይገኛሉ። ቱርክዬ በኢትዮጵያ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ ካላቸው ሀገራት መካከል በዋናነት ትጠቀሳለች። የሀገራቱ የንግድ ግንኙነትም እየዳበረ መጥቷል። ከኢኮኖሚ ባሻገር ፖለቲካ፣ ደህንነት፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢንዱስትሪ እና ባህል ሌሎች የትብብር መስኮች ናቸው። ባለፉት 10 ዓመታት በሁለቱ ሀገራት መካከል የከፍተኛ ባለስልጣናት የጉብኝት ልውውጦች ተደርገዋል። የቱርክዬ ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶዋን እ.አ.አ በ2015 በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን ጉብኝቱ የሀገራቱን የሁለትዮሽ ትስስር ማጠናከርን ያለመ ነው። እ.አ.አ በ2017 የቀድሞ ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ በቱርክዬ ጉብኝት በማድረግ ኢትዮጵያን በመወከል በቱርክዬ-አፍሪካ ቢዝነስ ፎረም ላይ ተሳትፈዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እ.አ.አ በ2021 በቱርክዬ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን በወቅቱ ሀገራቱ በተለያዩ ዘርፎች የትብብር ስምምነቶች መፈራረማቸው ይታወሳል። ውሃ፣ ወታደራዊ ትብብር እና ፋይናንስ ከስምምነቶቹ ትኩረቶች መካከልም ይገኙበታል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት የተደረገው ኢትዮጵያና ቱርክዬ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩበት 125ኛ ዓመት ላይ መሆኑ ልዩ ትርጉም የሚሰጠው ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክት የተፈረሙት ስምምነቶች የግንኙነቱን መጠናከር እንደሚያመለክቱ ገልጸዋል። ለኢትዮጵያ የልማት እና መረጋጋት ጉዞ ቱርክዬ የምታደርገውን ድጋፍም አድንቀዋል። የቱርክዬ መንግስት እና ህዝብ ያደረገልንን የወሳኝ ጊዜ ትብብር ሀገራችን ኢትዮጵያ መቼም አትረሳውም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅቱ በነበራቸው ቆይታ። የቀድሞው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እ.ኤ.አ በ2021 በቱርክዬ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን በወቅቱ አዲስ የተገነባውን የኢትዮጵያ ኤምባሲም መርቀዋል። የቱርክዬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እ.አ.አ በ2024 ኢትዮጵያን በመጎብኘት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ከመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መክረዋል። የከፍተኛ ባለስልጣናቱ ጉብኝት የሀገራቱን የግንኙነት መጠናከር የበለጠ የሚያጎለብቱም ናቸው። ኢንዱስትሪ እና ማኑፋክቸሪንግ፣ መሰረተ ልማት፣ የንግድ ብዝሃነትን ማስፋት፣ መከላከያ እና ደህንነት፣ ቱሪዝም እና ባህል ሀገራቱ ትብብራቸውን ሊያሰፉባቸው እየሰሩባቸው ከሚገኙ መስኮች መካከል ይጠቀሳሉ። የኢትዮጵያ እና የቱርክዬ አጋርነት በጋራ ፍላጎቶች፣ ተራማጅ በሆኑ ሀሳቦች፣ በጋራ ኢኮኖሚ ተጠቃሚነት እና እየተለወጡ ያሉ የዓለም እውነታዎችን ባማከለ ሁኔታ የበለጠ እየተጠናከረ መጥቷል። በልማት ጎዳና ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ እና ቱርክዬ ከአፍሪካ ጋር ያላት ትስስር የሁለቱን ሀገራት ስትራቴጂካዊ ትብብር የበለጠ ጥልቀት የሚሰጥ ነው። ሁለቱ ሀገራት በፍጥነት እየተለዋወጠ በሚገኘው ቀጣናዊ እና የዓለም ምህዳር ውስጥ ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ለማጠናከር እየሰሩም ይገኛሉ።
የአፍሪካ ህብረት እና የአፍሪካ ልማት ባንክ አጋርነታቸውን ለማደስ ቁርጠኛ መሆናቸውን ገለጹ
Feb 16, 2026 63
አዲስ አበባ፤ የካቲት 9/2018(ኢዜአ):- የአፍሪካ ህብረት እና የአፍሪካ ልማት ባንክ የአህጉሪቱን የፋይናንስ መዋቅር ማጠናከርን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ያላቸውን አጋርነት በአዲስ መልክ ለማደስ እንደሚሰሩ አስታወቁ። 39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በህብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ተካሂዷል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ከጉባኤው ጎን ለጎን ከአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ሲዲ ኡልድ ታህ(ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል። የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር ባንኩ ለአፍሪካ ቁልፍ የትኩረት መስኮች እያደረገ ያለውን ጠንካራ ድጋፍ ያደነቁ ሲሆን ለአፍሪካ ልማት ፈንድ 11 ቢሊን ዶላር ተጨማሪ ገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን መልካም የሚባል እርምጃ መሆኑን አመልክተዋል። ሊቀመንበሩ እና የባንኩ ፕሬዝዳንት ከእዳ፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና የደህንነት ፈተናዎች ባለፈ የፋይናንስ አቅርቦት የአፍሪካ አበይት ፈተና መሆኑን በምክክራቸው ወቅት ገልጸዋል። ሁለቱ ወገኖች የፕሮጀክት ዝግጅት ትብብርን ለማጠናከር፣ የአንድ ትሪሊን የአሜሪካን ዶላር የአፍሪካ ካፒታል ማሰባሰብ፣ የአፍሪካ የብድር ምዘና ኤጀንሲን ማጎልበትና ጠንካራ የአፍሪካ የፋይናንስ ስርዓት መገንባት ጉዳዮች ላይ መክረዋል። በውይይቱ የአፍሪካ ህብረት እና የአፍሪካ ልማት ባንክ አጋርነታቸውን በአዲስ መልክ ለማደስ ተሠማመተዋለ። በዓመት ሁለት ጊዜ ለመወያያት እና በአፍሪካ ፋይናንስ ላይ የከፍተኛ ደረጃ ምክክር ለማካሄድ እቅድ መያዛቸውንም ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ዘጠነኛው የአፍሪካ ቢዝነስ ፎረም ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄድ ይጀምራል
Feb 16, 2026 127
አዲስ አበባ፤ የካቲት 9/2018 (ኢዜአ):- ዘጠነኛው የአፍሪካ ቢዝነስ ፎረም ከዛሬ ጀምሮ በአዲስ አበባ ይካሄዳል። የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ኢሴኤ) ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ሁነቱን አዘጋጅተውታል። “የአፍሪካን መጻኢ ጊዜ በፋይናንስ መደገፍ፤ ሥራ እና ኢኖቬሽን ለዘላቂ ትራንስፎርሜሽን” የፎረሙ መሪ ሐሳብ ነው። የአፍሪካ ቢዝነስ ፎረም በአፍሪካ የልማት እና የኢኮኖሚ እድገት ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን በማድረግ በየዓመቱ የሚካሄድ ከፍተኛ አኅጉራዊ የምክክር መድረክ መሆኑን ኢዜአ ከኢሲኤ ያገኘው መረጃ ያመለክታል። አኅጉራዊው መድረክ የአፍሪካ መሪዎች፣ ባለሀብቶች፣ የግሉ ዘርፍ ተዋንያንና የልማት አጋሮችን በአንድ መድረክ ያገናኛል። ፎረሙ አጋርነትና የኢንቨስትመንት መጠንን ማሳደግ በተለይም የመንግሥት እና የግል የተቀናጀ የፋይናንስ አቅርቦትን ጨምሮ የተለያዩ የፋይናንስ አማራጮችን ማስፋት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ይወያያል። የሥራ ዕድል፣ ምቹ የኢኖቬሽን ሥነ-ምኅዳር እና የአፍሪካን የፈጠራ ዐቅም አሟጦ መጠቀም በፎረሙ ላይ ምክክር ከሚካሄድባቸው አጀንዳዎች መካከል ይጠቀሳሉ። በተለይም የዲጂታል ኢንዱስትሪዎች፣ የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች እንዲሁም እየሰፋ ያለው የአፍሪካ የፈጠራ ዘርፍ ትኩረት ተሰጥቶታል። በፎረሙ የተለያዩ ኢኒሼቲቮችና ማዕቀፎች ይተዋወቃሉ። የወጣቶችን የኢኖቬሽን ሥራ ከፋይናንስ አቅርቦት ጋር የሚያስተሣሥር የአፍሪካ የወጣቶች አይበገሬነትና ትራንስፎርሜሽን ማዕቀፍ ይፋ ይሆናል። በኢሲኤ የበለጸገውና የመንግሥት እና የግሉ ዘርፍ የፋይናንስ ቃል ኪዳኖችን ትግበራ የሚከታተልና የሚቆጣጠር ሥርዓትም በፎረሙ ይፋ ሆኖ ወደ ትግበራ ይገባል። ለሁለት ቀናት በሚቆየው ሁነት ላይ የአፍሪካ ሀገራት የመሪዎች የምክክር መድረኮችና የባለሙያዎች ውይይቶች ይደረጋሉ። አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችና የፈጠራ ባለሙያዎችን ከባለሀብቶች እና ፋይናንስ አቅራቢዎች ጋር የሚያገናኝ ዐውደ-ርዕይም ይካሄዳል። ሁነቶቹ ቃል ኪዳኖችን ወደ ተጨበጡ የኢኮኖሚ ፕሮጀክቶች ለመቀየር አስተዋጽዖ እንደሚያደርጉም ተመላክቷል። የአፍሪካ ቢዝነስ ፎረም በዘላቂ ልማት ግቦችና በአጀንዳ 2063 የተቀመጡ ግቦች እንዲሳኩ ስትራቴጂካዊ ሚናውን እየተወጣ እንደሚገኝም በመረጃው ተመላክቷል። የኢዜአ የዲጂታል ሚዲያ ገጾች https://linktr.ee/ENADigitalክቷል።
አፍሪካ በቅኝ ግዛት ዘመን የተፈጸመባት በደል የታሪክ ዕውቅና እና የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት የምትጠይቅበት ነው - የጋና ፕሬዚዳንት
Feb 15, 2026 116
አዲስ አበባ፤ የካቲት 8/2018 (ኢዜአ)፦አፍሪካ በቅኝ ግዛት ዘመን የተፈጸመባት በደል የታሪክ ዕውቅና እና የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት የምትጠይቅበት መሆኑን የጋና ፕሬዚዳንት እና የአፍሪካ የፋይናንስ ተቋማት ሻምፒዮን ጆን ድራማኒ ማሃማ ገለጹ። ”ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ ለሁለት ቀናት የተካሄደው 39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ በስኬት ተጠናቋል። ከሕብረቱ የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን የጋና ፕሬዚዳንትና የአፍሪካ የፋይናንስ ተቋማት ሻምፒዮን ጆን ድራማኒ ማሃማ "የቅድመ አያቶች ዕዳ፣ ዘመናዊ ፍትሕና የአፍሪካውያን ምክንያታዊ የአንድነት ውክልና" በሚል መሪ ሃሳብ መነሻ መግለጫ ሰጥተዋል። ፕሬዝዳንቱ በመግለጫቸው፤ በአፍሪካ ለተፈጸመው በደል ስርዓታዊ ማካካሻና በዓለም ዓቀፍ ተቋማት ላይ ለምታቀርበው ፍትሀዊ የውክልና ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽ ሊሰጥ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። በትራንስ-አትላንቲክ የባሪያ ንግድ በአፍሪካውያን ላይ የተፈጸመው ግፍ በሰው ልጅ ታሪክ የታየ ከፍተኛው ኢ-ፍትሀዊ በደል መሆኑን አስታውሰዋል። ይህ ኢ-ፍትሀዊ በደል ዓለም አቀፍ ዕውቅና ሊሰጠው ይገባል ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ ዕውቅና መስጠት መከፋፈል ሳይሆን የሞራል ድፍረትና ፍትሕን የማረጋገጥ የመጀመሪያው እርምጃ ነው ብለዋል። የአክራ ዳግም ማስጀመር የተሰኘው አሕጉራዊ ንቅናቄ አፍሪካ በውጭ ያላትን የእርዳታ ጥገኝነት ለማስቆም ያለመ መሆኑን ገልጸዋል። በተለይም በኮቪድ-19 ወቅት አፍሪካ ክትባት በማግኘት ረገድ የመጨረሻ ተሰላፊ የነበረችበትን አሳዛኝ ሁኔታ በማስታወስ፣ አህጉሪቱ የራሷን የጤና እና የፋይናንስ ተቋማት በራሷ አቅም መገንባት እንዳለባት ገልጸዋል። የማካካሻ ፍትህን ጥያቄን በተመለከተም ጥያቄው ከገንዘብ ክፍያ ባለፈ የታሪክ መዝገብን የማስተካከልና የተዘረፉ ቅርሶችን የመመለስ ጉዳይ እንደሚጨምር ጠቁመዋል። አፍሪካ እና የካሪቢያን ሀገራት በዚህ ጉዳይ ላይ በአንድ ድምፅ ለመቆም መስማማታቸውን ገልጸዋል። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኩል የባሪያ ንግድ በሰው ልጅ ላይ እንደተፈጸመ ወንጀል እውቅና እንዲያገኝ ግፊት እንደሚደረግ አስታውቀዋል።
ሐተታዎች
የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ
Feb 14, 2026 88
በሙሴ መለሰ የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ (Assembly of Heads of State and Government) የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ የፖሊሲ እና የውሳኔ ሰጪ አካል ነው። ይህ አካል ከሁሉም አባል ሀገራት የተውጣጡ የመንግስታት ወይም የሀገራት መሪዎችን ያቀፈ ሲሆን፣ የህብረቱን የጋራ ፖሊሲዎች የመቅረፅ እና የቀጣይ አቅጣጫዎችን የመወሰን ስልጣን ተሰጥቶታል። በአፍሪካ ህብረት ድረ-ገጽ ላይ በቀረበው መረጃ መሰረት፣ የጉባኤው ዋና ተግባራት የሚከተሉት ናቸው፦ የፖሊሲ አቅጣጫዎች፦ የህብረቱን የጋራ ፖሊሲዎች መወሰን፣ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች መለየት እና ዓመታዊ የሥራ መርሐ-ግብሮችን ያጸድቃል። ውሳኔ አሰጣጥ፦ በአህጉራዊ ሰላም፣ ጸጥታ እና ልማት ላይ የመጨረሻ ውሳኔዎችን ያሳልፋል። ክትትልና ግምገማ፦ የህብረቱን ፖሊሲዎች እና ውሳኔዎች አፈጻጸም መከታተል፣ እንዲሁም አባል ሀገራት ግዴታቸውን መወጣታቸውን ያረጋግጣል። ሹመቶች፦ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር፣ ምክትል ሊቀመንበር እና ኮሚሽነሮችን ይሾማል። ጣልቃ ገብነት፦ በአባል ሀገራት ውስጥ የጦር ወንጀል፣ የዘር ማጥፋት ወይም በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ሲያጋጥሙ ጣልቃ የመግባት ውሳኔ ያሳልፋል። ክትትልና ግምገማ: የህብረቱን አካላት እና የስራ አፈጻጸም ይገመግማል። በጀት እና መዋቅር፦ የህብረቱን በጀት ማጽደቅ፣ እንዲሁም የኮሚሽኑን አደረጃጀት እና ደንቦችን መወሰን። የጉባኤው አወቃቀር እና የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት አባልነት፦ ጉባኤው የሁሉንም 55 አባል ሀገራት መሪዎች ወይም ሕጋዊ ተወካዮቻቸውን ያቀፈ ነው። የውሳኔ አሰጣጥ፦ ውሳኔዎች የሚሳለፉት በስምምነት (Consensus) ሲሆን፣ ስምምነት ላይ መድረስ ካልተቻለ ግን በሁለት ሦስተኛ (2/3) ድምፅ ይወሰናሉ። የአሰራር ጉዳዮች ደግሞ በቀላል አብላጫ ድምፅ ይጸድቃሉ። ምልዓተ ጉባኤ (Quorum)፦ ማንኛውንም ስብሰባ ለማካሄድ ቢያንስ ሁለት ሦስተኛው የአባል ሀገራት ተወካዮች መገኘት አለባቸው። የጉባኤው ቢሮ (Bureau) ጉባኤው በየዓመቱ የሚመረጥ አንድ ሊቀመንበር እና ሌሎች አራት አባላት (ምክትል ሊቀመንበሮች) ያሉት ቢሮ አለው። ይህ ቢሮ የአህጉሪቱን አምስቱንም ቀጣናዎች (ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብ እና መካከለኛ አፍሪካ) ተዋጽኦ የጠበቀ መሆን ይኖርበታል። የጉባኤው አሠራር እና መደበኛ ያልሆኑ ስብሰባዎች መደበኛ ስብሰባ፦ ጉባኤው ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ መደበኛ ስብሰባ ያደርጋል። ልዩ ስብሰባ (Extraordinary Session)፦ ማንኛውም አባል ሀገር ጥያቄ አቅርቦ በሁለት ሦስተኛ አባል ሀገራት ድጋፍ ካገኘ በማንኛውም ጊዜ ልዩ ስብሰባ ሊጠራ ይችላል። ውሳኔዎችን ተግባራዊ ማድረግ፦ ጉባኤው ያሳለፋቸው ውሳኔዎች በአባል ሀገራት ተፈጻሚ መሆናቸውን የመከታተል እና የማረጋገጥ ኃላፊነት አለበት። የህብረቱ ከፍተኛ አመራሮች የኮሚሽኑ ሊቀመንበር፦ መሐሙድ አሊ ዩሱፍ (ጅቡቲ) እ.አ.አ በየካቲት 2025 ተመርጠው በአሁኑ ወቅት የህብረቱን የዕለት ተዕለት ሥራዎች የሚመራውን ኮሚሽን እየመሩ ይገኛሉ። ምክትል ሊቀመንበር፦ አምባሳደር ሰልማ ማሊካ ሃዳዲ (አልጄሪያ) የኮሚሽኑ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው በማገልገል ላይ ናቸው። በተለያዩ ዘርፎች የሚሰሩ ስድስት ኮሚሽነሮች በህብረቱ የስራ አስፈጻሚ ክንፍ በሆነው ኮሚሽን እየሰሩ ነው። 39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ “ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ይገኛል። ከፍተኛው የውሳኔ ሰጪ አካል የሆነው ጉባኤው በተለያዩ አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።
ያስተማራቸውን ማህበረሰብ ያልዘነጉ የቦረና ቅን ልቦች
Jan 25, 2026 554
የሆስፒታሎችን የሕክምና ቁሳቁስ ፍላጎት በመገንዘብ አሳድጎ ያስተማራቸውን ማህበረሰብ ያልዘነጉ የቦረና ቅን ልቦች። ዶክተር አብዱራህማን ሮኔ ይባላሉ። ትውልድና ዕድገታቸው በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ተልተሌ በተሰኘ አካባቢ ነው። የቀለም ትምህርት በሀገር ቤት ከተከታተሉ በኋላ ወደ ሀገረ አሜሪካ በማቅናት ኑሯቸውን በዚያው አድርገዋል። ለበርካታ ዓመታት ሕይወታቸውን በአሜሪካን ሀገር እየመሩ የሚገኙት ዶክተር አብዱራህማን ከሁለት ዓመታት በፊት ለቤተሰብ ጥየቃ ወደ ትውልድ አካባቢያቸው ቦረና አቀኑ። የጉዟቸው ዓላማ ለዓመታት የናፈቋቸውን ቤተሰቦቻቸውን ለመጠየቅ ብቻ እንደነበር ያስታውሳሉ። በቤተሰብ ጥየቃ ቆይታቸውም በቦረና ዞን ተልተሌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልን የሚጎበኙበት አጋጣሚ ተፈጠረ። ጉብኝታቸውም ሆስፒታሉ በኪነ-ሕንፃ የተዋበ መሆኑን ነገር ግን የህክምና ግብዓት እጥረት ያለበት ሆኖ ማግኘታቸውን ይናገራሉ። በተልተሌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ምልከታቸው በሕክምና ቁሳቁስ እጥረት ምክንያት ታካሚዎች ሲቸገሩ ማየታቸው የወቅቱ አሳዛኝ ትውስታ እንደነበርና ይህን እጥረት ወደ አሜሪካን ሀገር ሲመለሱ የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው መወሰናቸውን አስታውሰዋል። ዶክተር አብዱረሃማን በተልተሌ አካባቢ ተወልደውና አድገው ለሕክምና ባለሙያነት ያበቃቸውን ትምህርት የቀሰሙ ሰው በመሆናቸው በሆስፒታሉ የተመለከቱት የሕክምና ቁሳቁስ እጥረት የሺዎችን ሕይወት የሚታደግ ሰብዓዊ ፕሮጀክት የሚቀረጽበት ሃሳብ እንዲወለድ ምክንያት ሆኗል። ከዚያም የራሳቸውን የሕክምና ሙያ ዕውቀትና በውጭ ያካበቱትን ግንኙነት በመጠቀም መነሻቸውን ባለፈው ዓመት ለተልተሌ እና ሜጋ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች ዘመናዊ የሕክምና ቁሳቁስ በድጋፍ ማበርከታቸውን ገልጸዋል። በዚህ ዓመትም የሞያሌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልን ጨምሮ ለሶስት ትላልቅ የጤና ተቋማት ዘመናዊ ሕክምና መሳሪያዎችን አበርክተዋል። እነኚህ የሕክምና መሳሪያዎች አሳድጎ ያስተማራቸውን ማህበረሰብ ያስታወሱበት በጎ ተግባር መሆኑን ተናግረዋል። በተለያዩ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንም ያስተማራቸውን ማህበረሰብ በማስታወስ መንግስት የዜጎችን የሕክምና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት ለማስፋት የሚያደርገውን ጥረት እንዲያግዙ ጥሪ አቅርበዋል። ሌላኛው በአሜሪካን ሀገር በሕክምና ሙያ የሚያገለግሉት ዶክተር ዋቆ ዳደቻ በበኩላቸው፤ ሁሉም ዜጋ በትብብር መስራት ከቻለ የማህበረሰብን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል ይቻላል ይላሉ። ይህ የሆስፒታሎችን የሕክምና ቁሳቁስ እጥረት ለማሟላት የሚደረገውን ተሳትፎ ሁሉም በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ዜጎች ሊማሩበት የሚገባ በጎ ተግባር መሆኑን ገልጸዋል። በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መንግስት የሕክምና ተቋማትን ጥራትና ደረጃ ለማሻሻል የሚያደርገውን ጥረት በማገዝ አሳድጎ ያስተማራቸውን ማህበረሰብ ማሰብ እንደሚኖርባቸው አስገንዝበዋል። የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አብዱልቃድር ገልገሎ፤ በውጭ የሚኖሩ የሕክምና ሙያተኞች የሚያደርጉት የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ በአርዓያነት የሚወሰድ ነው ብለዋል። በዶክተር አብዱራህማን መሪነት ለቦረና አካባቢ ሆስፒታሎች የተደረገው የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍም የተቋማቱን የጤና አገልግሎት ጥራት በማስጠበቅ በኩል ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን በመግለጽ። በቀጣይም በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የህዝባቸውን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት በማገዝ በኩል የበኩላቸውን ገንቢ ሚና እንዲጫወቱ ጥሪ አቅርበዋል።
እኩል አጋርነትን መፍጠር፤ አዲሱ የአፍሪካ እና ጣልያን የትብብር ምዕራፍ
Dec 30, 2025 893
የአፍሪካ እና ጣልያን ግንኙነት የጀመረው በ19ኛው ክፍለ ዘመን ማብቂያ ላይ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ። ጣልያን እ.አ.አ በ1947 የተፈራረመቻቸው የሰላም ስምምነቶች ቅኝት ግዛት እና የአንድ አካል የፖለቲካ የበላይነት እንዲያከትም አድርጓል። በድህረ ቅኝ ግዛት ዘመን ጣልያን ከአፍሪካ ጋር ያላት ግንኙነት ከቅኝ አገዛዝ የሁለትዮሽ ትስስር ወደ የኢኮኖሚ ትብብር ተሸጋግሯል። ወቅቱ አፍሪካውያን ሉዓላዊነታቸውን የበለጠ ያረጋገጡበትና ጣልያን ከአፍሪካ ጋር በአዲስ መልክ አጋርነቷን ያደሰችበት ነበር። ከቅኝ ግዛት በኋላ የአፍሪካ እና የጣልያን ትብብር በባህል መስክ ላይ ብቻ የተገደበ ነው። የንግድ እና የቴክኒክ ትብብሩ ውስን ነበር። እ.አ.አ ከ1990ዎቹ መግቢያ አንስቶ የአፍሪካ እና ጣልያን ስትራቴጂክ አጋርነት እያበበ የመጣበት ጊዜ ነበር ማለት ይቻላል። የዲፕሎማሲ ሚሲዮኖች እና የንግድ ቢሮዎች መጨመር እንዲሁም የኢኮኖሚ ትብብር አድማስ መስፋት የትብብሩ መገለጫ ሆኗል። ዘመናዊው የአፍሪካ እና ጣልያን አጋርነት ከእርዳታ ወደ የጋራ እድገት ምዕራፍ መሸጋገር ችሏል። የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲው የሁለቱን ወገኖች የንግድ እና የኢንቨስትመንት ትብብር አጠናክሯል። የልማት ትብብሩ እርዳታን ከመለገስ ወጥቶ እድገት ተኮር ሆኗል። ከደህንነት ጋር በተያያዘም የፍልሰት አስተዳደር እና ሽብርተኝነት መዋጋት አንዱ የትብብር መገለጫ ነው። የጣልያን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ የአፍሪካ እና ጣልያን የባለፈው ጊዜ የነበሩ ፈተናዎች እውቅና በመስጠት አሁን ላይ የሁለቱን ወገኖች የጋራ ፍላጎት ማስጠበቅ ላይ ትኩረቱን አድርጓል። የፖሊሲው ሰነድ “ ዋጋ እና ክብርን ማዕከል ያደረገ” ዲፕሎማሲ በሚልው እሳቤው ከአፍሪካ ጋር ላለው ወዳጅነት ከፍተኛ ግምት እንደሚሰጥ አስቀምጧል። እ.አ.አ በ2024 በሮም የተካሄደው የጣልያን-አፍሪካ ጉባኤ ላይ በቅርብ ጊዜያት ከነበሩ ከፍተኛ መድረኮች መካከል ይጠቀሳል። በጉባኤው ላይ የ45 የአፍሪካ ሀገራት ተወካዮች፣ የአፍሪካ ህብረት እና የአውሮፓ ህብረት መሪዎች፣ ዓለም አቀፍ ተቋማት እና የልማት አጋሮች ተሳትፈዋል። ጉባኤው የተካሄደበት ዓመት ጣልያን የቡድን ሰባት አባል ሀገራት ሊቀ መንበር የነበረችበት ወቅት ሲሆን ጣልያን ከአፍሪካ ጋር ያላትን ትብብር ማጠናከር የውጭ ጉዳይ ፖሊሲዋ አንኳር ትኩረት ሆኗል። የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ በወቅቱ ጉባኤውን የአፍሪካ እና ጣልያን ትብብርን በአዲስ መልክ የበየነና ትብብሩ እኩል በቆሙ ወገኖች መካከል ያለ ትስስር እንደሆነ አንስተዋል። ሜሎኒ የሰጪ እና ተቀባይ ዘመን እንዳበቃና የጋራ እድገት እና የጋራ ፍላጎት ላይ የተመረኮዘ ግንኙነት አዲሱ የትብብር ምዕራፍ እንደሆነም ተናግረዋል። በወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር የነበሩት ሙሳ ፋቂ ማህማት የጣልያንን አዲሱን የፖሊሲ ለውጥ ያደነቁ ሲሆን አፍሪካ ከቃል ባለፈ እውነተኛ አጋርነትን ትፈልጋለች ብለዋል። የፖሊሲ ሽግግሩ ፍትሃዊነትን ያረጋገጠ እና እኩልነትን መሰረት ያደረገ ዓለም መፍጠርን ያማከለ መሆን እንዳለበትም አንስተዋል። ጣልያን የገባቻቸውን ቃሎች ወደ ተግባር መቀየር አለባት ሲሉም ማህማት ተናግረው ነበር። በጉባኤው ላይ ይፋ ከተደረጉ ቁልፍ ማዕቀፎች አንዱ የማቴይ እቅድ (The Mattei Plan) ይገኝበታል። የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ይፋ ያደረጉት የማቴይ ፕላን ጣልያን ከአፍሪካ ጋር ያላት የኢኮኖሚ እና የልማት ትብብር ማጠናክርን ያለመ ነው። የ5 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዩሮ የስትራቴጂክ ማዕቀፉ በጣልያኑ የብሄራዊ የዘይት እና ነዳጅ ኩባንያ መስራች ኤነሪኮ ማቴይ የተሰየመ ነው። ኩባንያው ከአፍሪካ ጋር ከአጭር ጊዜ እርዳታ የረጅም ጊዜ የኢኮኖሚ ትብብርን በማስቀደም እየሰራ እንደሚገኝ ተመላክቷል። የአፍሪካን የኢኮኖሚ እድገት መደገፍ፣ የስራ እድሎችን ማስፋት፣ አፍሪካን የአውሮፓ የኢነርጂ አቅራቢ አጋር የማድረግ ስራን ማስተዋወቅ፣ ለአፍሪካውያን የኢኮኖሚ ችግሮች መፍትሄ በመስጠት ኢ-መደበኛ ፍልሰትን ከምንጩ ማድረቅ እንዲሁም ከበጎ አድራጎት የተላቀቀ የጋራ ተጠቃሚነት እና ትብብርን መፍጠር የእቅዱ አበይት አላማዎች ናቸው ። ለአራት ዓመታት የሚቆየው የማቴይ እቅድ በአፍሪካውያን በበጎ መልኩ የታየ ሲሆን እቅዱ ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር ጠንካራ የፖለቲካ ቁርጠኝነት እንደሚያስፈልግ ተነስቷል። እ.አ.አ በ2023 የአፍሪካ እና የጣልያን የንግድ ልውውጥ 59 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዩሮ መድረሱን ይፋዊ መረጃዎች ያመለክታሉ። የንግድ ልውውጡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቷል። የአፍሪካ ሀገራት በዋናነት የተፈጥሮ ጋዝ፣ ድፍድፍ ነዳጅ፣ የብረታ ብረት እና ማዕድናት ምርቶች እንዲሁም ለኢንዱስትሪ ምርቶች የሆኑ ጥሬ እቃዎችን ወደ ጣልያን ይልካሉ። ጣልያን የኢንዱስትሪ ማሽን እና መሳሪያ፣ እሴት የተጨመረባቸው እቃዎች እና የማኑፋክቸሪንግ ምርቶች እንዲሁም የኤሌክትሪክ እቃዎች ወደ አፍሪካ ከምትላካቸው ምርቶች መካከል ተጠቃሽ ናቸው። አጠቃላይ የንግድ ምጣኔው ሲታይ ጣልያን በገቢ አብዛኛውን ድርሻ ትይዛለች። ንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ ተፈጥሮ ሀብት፣ ኢነርጂ፣ መሰረተ ልማት፣ ትራንስፖርት፣ ትምህርት፣ ምርምር፣ ጤና፣ ቴክኖሎጂ፣ የፍልሰት አስተዳደር፣ ደህንነት እና አስተዳደር ከአፍሪካ እና ጣልያን የትብብር መስኮች መካከል ይገኙበታል። የ2026 የአፍሪካ-ጣልያን ጉባኤ በየካቲት ወር አጋማሽ 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት ዋና መቀመጫ እና የአህጉሪቷ መዲና ናት። ይህም ጉባኤውን የአፍሪካ ዋንኛ የዲፕሎማሲ አጀንዳ ያደርገዋል። ኢትዮጵያ በታሪክ በፓን አፍሪካ ፖለቲካ ውስጥ የመሪነት ሚና ያላት ሀገር ናት። በአሁኑ ሰዓትም በርካታ ቀጣናዊ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ሁነቶችን እያዘጋጀች ትገኛለች። የሁለቱን ወገኖች አጋርነት የበለጠ ያጠናክረዋል ተብሎ ይጠበቃል። የማቴይ እቅድ ትግበራ፣ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ትብብር፣ የአፍሪካን ተሰሚነት መጨመር፣ ፍልሰትን ጨምሮ በጋራ ጉዳዮች ላይ ጠንካራ አቋም መያዝ፣ የአጋርነት እና የመግባቢያ ስምምነቶች የአፍሪካ-ጣልያን ጉባኤው ውጤቶች ናቸው። የአፍሪካ-ጣልያን ጉባኤ ካለፈው ታሪካዊ ግንኙነቶች ፣ እያደገ ከመጣው የኢኮኖሚ ትብብር እና የጋራ ፈተናዎችን የመፍታት ቁርጠኝነት አኳያ በአፍሪካ እና በጣልያን መካከል አዲስ የትብብር ምዕራፍ የሚከፍት እንደሆነ ታምኖበታል። የአፍሪካ ዲፕሎማሲ ማዕከል በሆነችው አዲስ አበባ የሚደረገው ጉባኤ አፍሪካ መር አጋርነት ለመፍጠር እና የአፍሪካን ተሰማኒነት ለመጨመር መልካም አጋጣሚን የሚፈጥር ነው።
አፍሪካውያን ሀገር በቀል አሰልጣኞች ጎልተው የታዩበት የአፍሪካ ዋንጫ !
Dec 28, 2025 819
35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በሞሮኮ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ይገኛል።24 ሀገራት በስድስት ምድቦች ተከፍለው ጨዋታቸውን እያደረጉ ነው። በውድድሩ ላይ ከሚሳተፉ 24 ሀገራት 12ቱ በአፍሪካውያን የሚሰለጥኑ ናቸው። የአዘጋጇ ሀገር ሞሮኮ አሰልጣኝ ዋሊድ ሬግራጉዊ ከዛው ከሀገራቸው ናቸው። የ50 ዓመቱ አሰልጣኝ በ22ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ ሞሮኮን ለግማሽ ፍጻሜ አድርሰዋል።ሀገሪቷ በዓለም ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜ የደረሰች የመጀመሪያዋ አፍሪካዊ ሀገር ሆናለች። ከእ.አ.አ 2022 አንስቶ ብሄራዊ ቡድኑን እየመሩት የሚገኙት ሬግራጉዊ ሞሮኮን ከግማሽ ክፍለ ዘመን በኋላ የአፍሪካ ዋንጫ ባለቤት የማድረግ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል። የወቅቱ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ ኮትዲቭዋር አሰልጣኝ የ41 ዓመቱ የቀድሞ የብሄራዊ ቡድኑ ተጫዋች ኤመርሰን ፋኤ ነው። ፋኤ እ.አ.አ በ2023 በኮትዲቭዋር አስተናጋጅነት በተካሄደው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ቡድኑን በመምራት ዋንጫውን እንዲያነሳ አድርጓል። በውድድሩ መሐል በውጤት ማጣት የተሰናበቱትን ፈረንሳዊውን አሰልጣኝ ጂን-ሉዊስ ጋሴት በመተካት በጊዜያዊነት አሰልጣኝ የተሾመው ፋኤ ቡድኑን ለዋንጫ ማብቃቱ አስወድሶታል። በዘንድሮው ውድድር ዋንጫውን ለማንሳት የቅድሚያ ግምት ከተሰጣቸው ሀገራት ተርታ የተመደበችው ሴኔጋል አሰልጣኝ የ41 ዓመቱ የቀድሞ የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ፓፔ ታው ነው። ፓፔ ታው በተጫዋችነት ዘመኑ ለሴኔጋል ባደረጋቸው 16 ጨዋታዎች አምስት ግቦችን አስቆጥሯል። አሰልጣኙ ሴኔጋል ለ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ እንድታልፍ አድርጓል። ከሶስት ዓመት በፊት በአልጄሪያ በተካሄደው የሰባተኛው የአፍሪካ አገራት ሻምፒዮና(ቻን) ሴኔጋል ዋንጫውን ስታነሳ የቡድኑ አሰልጣኝ ሆኖ መርቷል። የሰባት ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊዋ ግብጽ የምትሰለጥነው በቀድሞ ኮከቧ ሆሳም ሀሰን ነው። በተጫዋችነት ዘመኑ በአፍሪካ ዋንጫ 11 ግቦችን አስቆጥሯል። በ177 ጨዋታዎች 69 ግቦችን ከመረብ ላይ በማሳረፍ የብሄራዊ ቡድኑ የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ነው። ሆሳም ሀሰን የአፍሪካ ዋንጫን ሶስት ጊዜ በተጫዋችነት በማንሳት ስኬታማ አሰልጣኝ ነው። ሌላኛው የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ካሜሮን አሰልጣኝ የ56 ዓመቱ ዴቪድ ፓጉ ነው። ካሜሮናዊው አሰልጣኝ የተሾሙት ከሰሞኑ ነው። ቤልጂየማዊውን አሰልጣኝ ማርክ ብራይስን በመተካት ቡድኑን እንዲመሩ ኃላፊነት ተጠሎባቸዋል። በካሜሮን እግር ኳስ ባላቸው የታክቲክ መረዳት እና ብቃት የሚሞካሹት ፓጉ ቡድኑን አንድ በማድረግ የተሻለ ውጤት ያመጣሉ የሚል እምነት ተጥሎባቸዋል። ሌላኛው የውድድሩ ተሳታፊ ሀገር ዛምቢያ ናት።የ48 ዓመቱ የዛምቢያ ብሄራዊ ቡድን የቀድሞ ተከላካይ ሞሰስ ሲቾኔ የቡድኑ የወቅቱ ዋና አሰልጣኝ ናቸው። ከእ.አ.አ 2022 እስከ 2024 በጊዜያዊነት እና በረዳት አሰልጣኝነት ያገለገሉት ሲቾኔ በ2025 ዋና አሰልጣኝ ሆነው ተሾመዋል። ምስራቅ አፍሪካን በውድድሩ ከሚወክሉ ሶስት ሀገራት መካከል አንዷ ሱዳና ናት። ጋናዊው ጀምስ ክዌሲ አፒያ የቡድኑ አሰልጣኝ ናቸው። አፒያ ከእ.አ.አ 2023 አንስቶ ቡድኑን እያሰለጠኑ ይገኛሉ። የጋቦን አሰልጣኝ ቲዬሪ ሞዩማ የብሄራዊ ቡድኑ የተከላካይ መስመር ተጫዋች ነበር። ለ11 ዓመታት ለጋቦን ተጫውተዋል። ከእ.አ.አ 2023 አንስቶ ብሄራዊ ቡድኑን በአሰልጣኝነት እየመሩ ይገኛል። የ44 ዓመቱ ደቡብ አፍሪካዊ ሞሬና ራሞሬቦሊ የቦትስዋና ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ናቸው። ከእ.አ.አ 2025 አንስቶ ቡድኑን እያሰለጠኑ ይገኛል። ሞሬና ከዚህ ቀደም የደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ነበሩ። የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ቡርኪናፋሶ አሰልጣኝ የቀድሞ የብሄራዊ ቡድን የአማካይ ተጫዋች ብራማ ትራኦሬ ነው። አሰልጣኙ ከእ.አ.አ ማርች 2024 አንስቶ ቡርኪናፋሶን እየመራ ይገኛል። ትራኦሬ ቡድኑ የተሻለ ውጤት እንዲያመጣ የማድረግ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል። የአንድ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ የሆነችው ቱኒዚያ አሰልጣኝ የቀድሞ የቡድኑ የተከላከይ መስመር ተጫዋች ሳሚ ትራቤልሲ ናቸው። የ57 ዓመቱ አሰልጣኝ ለቱኒዚያ ብሄራዊ ቡድን ለ10 ዓመታት በተጫዋችነት አገልግሏል። ብሄራዊ ቡድኑን ከእ.አ.አ 2025 ቱኒዚያን እየመራ ይገኛል። በአፍሪካ ደቡባዊ ክፍል የምትገኘው ሞዛምቢክ በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ከሚሳተፉ ሀገራት መካከል አንዷ ናት። ፍራንቺስኮ ኩዌሪዮል ኮንዴ ጁኒየር (ቺኩዊኒዮ ኩንዴ) የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ናቸው። የ60 ዓመቱ አንጋፋ አሰልጣኝ ለሞዛምቢክ ለ15 ዓመታት በተጫዋችነት አገልግለዋል። ለሀገራቸው በ43 ጨዋታዎች 12 ግቦችን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። ኩንዴ ከእ.አ.አ 2021 አንስቶ ብሄራዊ ቡድኑን እያሰለጠኑ ይገኛሉ። የናይጄሪያ አሰልጣኝ የሆነው ኤሪክ ቼሌ የኮትዲቭዋር፣ ማሊ እና ፈረንሳይ ጥምር ዜግነት ያላቸው አሰልጣኝ ናቸው። ይሁንና ቼሌ የአፍሪካ የዘር ግንድ ቢኖራቸውም በፈረንሳይ መወለዳቸው የውጭ ሀገር ዜጋ ውስጥ እንዲካተት አድርጎታል። የአፍሪካውያን አሰልጣኞች በአፍሪካ ዋንጫ የማሰልጠን ምጣኔ ከሌሎቹ ወቅቶች አንጻር የአሁኑ የተሻለ ነው ማለት ይቻላል። ይህም ሀገር በቀል አሰልጣኞች እየተሰጣቸው ያለውን ትኩረት ያሳያል። 12 ሀገራት በውጭ ሀገር ዜጎች ይሰለጥናሉ። በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ አፍሪካውያን የሚያሰለጥኗቸው ወይስ የውጭ ሀገር ዜጋዎች የሚመሯቸው ሀገራት ዋንጫውን ያነሳሉ? የሚለው ጉዳይ ትኩረትን ስቧል።
ትንታኔዎች
ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ዋንጫ
Jan 2, 2026 949
ክፍል ሁለት የቀጠለ የኢትዮጵያ ዘጠነኛ ተሳትፎ በአህጉራዊው መድረክ እ.አ.አ 1982 ኢትዮጵያ በሊቢያ አስተናጋጅነት በተካሄደው 13ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለዘጠነኛ ጊዜ ተሳትፎዋን ማድረግ ቻለች። በውድድሩ ላይ አሁንም ስምንት አገራት ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ በምድብ ሁለት ከአልጄሪያ፣ዛምቢያና ናይጄሪያ ጋር ተደልድላ ጨዋታዎቿን አድርጋለች። በምድብ ጨዋታዎቹ በናይጄሪያ 3 ለ 0 እንዲሁም በዛምቢያ 1 ለ 0 የተሸነፈች ሲሆን ከአልጄሪያ ጋር ያለ ምንም ግብ አቻ ተለያይታለች። ኢትዮጵያ በምድቧ አንድ ነጥብ ብቻ በመያዝ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች። በፍጻሜው ጨዋታ ጋና ሊቢያን በመለያ ምት በማሸነፍ ለሶስተኛ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን አንስታለች። ኢትዮጵያ ከ31 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካው ዋንጫ የተመለሰችበት ታሪካዊ ሁነት ኢትዮጵያ ከ13ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በኋላ በአህጉራዊው የእግር ኳስ ውድድር መድረክ ለመሳተፍ ሶስት አስርት ዓመታታን መጠበቅ ግድ ሆኖባታል። በነዚህ 30 ዓመታት ጊዜ ውስጥ 15 የአፍሪካ ዋንጫ ውድድሮች ተካሄደዋል። እ.አ.አ በ2013 በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ከ31 ዓመት በኋላ ወደ ውድድሩ ዳግም ተመለሰች። ኢትዮጵያ ወደ አፍሪካ ዋንጫው ያለፈችበት መንገድ ልብ አንጠልጣይ ነበር። ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2012 በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ ከሱዳን ጋር ባደረገችው የመጨረሻ ዙር የደርሶ መልስ ጨዋታ በመጀመሪያ ዙር ኦምዱርማን ላይ 5 ለ 3 በሆነ ውጤት ተሸንፋለች። ሱዳን ጨዋታውን ያሸነፈችው በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች በተቆጠሩ ሁለት አጨቃጫቂ የፍጹም ቅጣት ምት በግቦች ነበር። ጥቅምት 4 2004 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም ለሚደረገው የመልስ ጨዋታ በስታዲየሙ ዙሪያ ከእኩለ ሌሊት ጀምሮ በርካታ ተመልካች ተሰልፎ ነበር። ጨዋታው በመጀመሪያው አጋማሽ ያለ ምንም መጠናቀቁ በስታዲየሙ የተገኘውን ተመልካች ጭንቅ ውስጥ ከቶ ነበር። ጭንቀቱ በስታዲየሙ ላሉት ብቻ ሳይሆን በቴሌቪዥን መስኮት ለሚከታተሉት በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንም ነበር። በሁለተኛው አጋማሽ የተሻለ እንቅስቃሴ ያደረጉት ዋልያዎቹ አዳነ ግርማ ባስቆጠራት ግብ መሪ መሆን ቻሉ። ይሁንና ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫው ለመሳተፍ አንድ ተጨማሪ ጎል ያስፈልጋታል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አጥቂ ሳላዲን ሰዒድ ወሳኟን ሁለተኛ ግብ ከመረብ ላይ አሳረፈ። ግቡ ሲቆጠር በስታዲየሙ ተመልካቾች ላይ የነበረው ስሜት በከፍተኛ ደስታ የተሟላ ሲሆን ስሜታቸውንብ በእንባ የገለጹም ነበሩ። ጨዋታው በድምር ውጤት 5 ለ 5 ተጠናቆ ከሜዳ ውጪ ብዙ ባስቆጠረ በሚል ኢትዮጵያ ከ31 ዓመት በኋላ ዳግም ወደ አፍሪካ ዋንጫ መመለስ ቻለች። ከጨዋታው በኋላ በአዲስ አበባ ስታዲየም፣በመስቀል አደባባይና በመዲናዋ የተለያዩ አውራ ጎዳናዎች፣መንደሮችና የተለያዩ አካባቢዎች እንዲሁም በመላው ኢትዮጵያ ባሉ ክፍሎች የነበረው የደስታ ስሜትና ፈንጠዝያ የሚረሳ አልነበረም። በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንም የደስታው ተቋዳሽ ነበሩ። ኢትዮጵያን ከ31 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫው እንድትመለስ ያደረጉት አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ነበሩ። ደቡብ አፍሪካ ባዘጋጀችው 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ 16 አገራት በስድስት ምድብ ተከፍለው ጨዋታቸውን አድርገዋል። ኢትዮጵያም በምድብ ሶስት ከቡርኪናፋሶ፣ናይጄሪያና ዛምቢያ ጋር ተደልድላ ጨዋታዋን አድርጋለች። በመጀመሪያ ጨዋታዋ ኢትዮጵያ ከዛምቢያ ጋር አንድ አቻ ተለያይታለች። አዳነ ግርማ በ65ኛው ደቂቃ ለኢትዮጵያ ግቡን አስቆጥሯል። በሁለተኛው ጨዋታ ኢትዮጵያ በቡርኪናፋሶ የ4 ለ 0 ሽንፈት አስተናግዳለች። በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ ኢትዮጵያ በናይጄሪያ 2 ለ 0 ተሸንፋለች። ውጤቶቹን ተከትሎ ኢትዮጵያ በአንድ ነጥብ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ ይዛ ከምድቧ ሳታልፍ ቀርታለች። ኢትዮጵያ ከ31 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ብትመለስም በውድድሩ ላይ ያስመዘገበችው ውጤትና ያሳየችው ብቃት የእግር ኳስ ቤተሰቡን ያስደሰተ አልነበረም። ይሁንና ብሔራዊ ቡድኑ ከደቡብ አፍሪካ ሲመለስ በአዲስ አበባ ስታዲየም በበርካታ ደጋፊዎች አቀባበል ተደርጎለታል። በፍጻሜው ጨዋታ ናይጄሪያ ቡርኪናፋሶ 1 ለ 0 በማሸነፍ የአፍሪካን ዋንጫን ለሶስተኛ ጊዜ አንስታለች። ኢትዮጵያ ለመጨረሻ ጊዜ የተሳተፈችበት የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ ለመጨረሻ ጊዜ በአፍሪካ ዋንጫ የተሳተፈችው እ.አ.አ በ2021 ካሜሮን ባዘጋጀችው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ነበር። ከስምንት ዓመታት በኋላ ወደ ውድድሩ የተመለሰችው ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከአዘጋጅ አገር ካሜሮን፣ቡርኪናፋሶና ኬፕቨርዴ ጋር ተደልድላ ጨዋታዋን አድርጋለች። ኢትዮጵያ በመጀመሪያ የምድብ ጨዋታዋ በኬፕቨርዴ 1 ለ 0 ተሸንፋለች። በሁለተኛው ጨዋታ ዋልያዎቹ በአዘጋጇ አገር ካሜሮን 4 ለ 1 ተሸንፈዋል። በጨዋታው ኢትዮጵያ አጥቂው ዳዋ ሁቴሳ በአራተኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ግብ መሪ መሆን ብትችልም ቪንሰንት አቡበከርና ቶኮ ኢካምቢ በተመሳሳይ ሁለት ግቦችን በማስቆጠር የማይበገሩትን አንበሶች አሸናፊ አድርገዋል። በወቅቱ በአሰልጣኝ ውበቱ የተመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመጨረሻ የምድብ ጨዋታዋ ከቡርኪናፋሶ ጋር አንድ አቻ ተለያይታለች። ለብሔራዊ ቡድኑ ብቸኛዋን ግብ ያስቆጠረው ጌታነህ ከበደ በፍፁም ቅጣት ምት ነበር። ኢትዮጵያ በምድቡ አንድ ነጥብ ብቻ በማግኘት ከምድቧ የመጨረሻውን ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። የኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ በቁጥሮች ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ የ11 ጊዜ ተሳትፎ ኢትዮጵያ 31 ጨዋታዎችን አድርጋ 8ቱን ስታሸንፍ 19 ጊዜ ተሸንፋለች። አራት ጊዜ ደግሞ አቻ ወጥታለች። በነዚህ 31 ጨዋታዎች ኢትዮጵያ 33 ግቦችን ስታስቆጥር 67 ጎሎችን አስተናግዳለች። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ በሰፊ ግብ ያሸንችባቸው ጨዋታዎች ሁለት ናቸው። እ.አ.አ በ1962 ራሷ አዘጋጅታ ራሷ በወሰደችው ሶስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ቱኒዚያና ግብጽን በተመሳሳይ 4 ለ 2 አሸንፋለች። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫው በሰፊ የግብ ልዩነት የተሸነፈችው እ.አ.አ በ1970 ሱዳን ባዘጋጀችው ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሲሆን በወቅቱ በኮትዲቭዋር 6 ለ 1 በሆነ ውጤት ተረታለች። ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ በውድድሩ ተሳትፎዋ ከፍተኛ ግብ ያስተናገደችበት ሲሆን 12 ጎሎች ተቆጥረውባታል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎዋ ከፍተኛ ግቦችን ያስቆጠረችባቸው ውድድሮች እ.አ.አ በ1952 እና በ1968 በቅደም ተከተል ሶስተኛውንና ስድስተኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ባዘጋጅበት ወቅት ነው። በነዚህ ውድድሮች ላይ በተመሳሳይ ስምንት ግቦችን አስቆጥራለች። ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን ሶስት ጊዜ አዘጋጅታለች። ኢትዮጵያውያኖቹ አጥቂዎች ሉቺያኖ ቫሳሎና መንግስቱ ወርቁ በአፍሪካ ዋንጫ ላይ በተመሳሳይ 8 ግቦችን በማስቆጠር በአፍሪካ ዋንጫ የምንጊዜም የከፍተኛ ግብ አግቢዎች ዝርዝር ውስጥ 21ኛ እና 22ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። እንደ መውጫ ኢትዮጵያ ሞሮኮ እየተካሄደ በሚገኘው 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ አትሳተፍም። የአፍሪካ እግር ኳስ መስራችና ፈር ቀዳጅ እየተባለች የምትጠራው ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ ተሳትፎዎቿ ከሰሜን፣ደቡብና ምዕራብ አፍሪካ አገራት ጋር ብርቱ ፉክክር በማድረግ መልካም የሚባል ውጤት አስመዝግባለች። ይሁንና ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በአፍሪካ ዋንጫ ያላት ተሳትፎ እየተቀዛቀዘ መጥቶ ብሔራዊ ቡድኑ ከምድቡ ማለፍ እየተሳነው ነው። የስፖርት ቤተሰቡና ተንታኞች ጠንካራ ብሔራዊ ቡድን መገንባት አለመቻሉ፣የእግር ኳስ እድገቱ ወደ ኋላ መቅረቱ፣ የአጥቂ መስመሩ ክፍል የአጨራረስ ድክመት፣ ለወጣት ተጫዋቾች እድል አለመስጠት፣የአሰልጣኞች በየጊዜው መለዋወጥ፣ለእገር ኳሱ የሚሰጠው ትኩረት የሚጠበቀውን ያህል አለመሆኑና እግር ኳሱ በስፖርቱ ባለፉ ሰዎች አለመመራቱን ጨምሮ በርካታ ምክንያቶች ይቀመጣሉ። ጠንካራና ተወዳዳሪ ቡድን የመገንባት ስራ ትኩረት ያሻዋል። ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2029 የሚካሄደውን 37ኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ለማስተናገድ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥያቄ ማቅረቧ የሚታወቅ ነው። በዚህም ውድድር ኢትዮጵያን ወክሎ የሚሳተፍ ጠንካራና አሸናፊ ብሔራዊ ቡድን መገንባት የሚያስችል "ሮድ 2029" የታዳጊዎች እግር ኳስ የስልጠና ፕሮጀክት ተጀምሯል፡፡ “ሮድ 2029"ን ለማሳካት ከኢትዮጵያ ከሁሉም አካባቢዎች 85 ብቃት ያላቸው ታዳጊዎች ተመርጠው ለዘጠኝ ወራት ስልጠና ወስደው ብቃት ያላቸው ተመርጠዋል፡፡ ከእነዚህ ታዳጊዎች መካከል 26ቱ በብቃታቸው ተመርጠው የ"ሮድ 2029" ግብን ማሳካት የሚያስችል የክፍል ውስጥ እና የሜዳ ላይ ስልጠና እየወሰዱ መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። ታዳጊዎቹ ኢትዮጵያ በህዳር ወር ባስተናገደችው ከ17 ዓመት በታች የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ የእግር ኳስ ማህበር ምክር ቤት ዞን (ሴካፋ) ተሳትፎ አድርጓል። የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን በውድድሩ ላይ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ በሞሮኮ በሚካሄደው 16ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማለፉ ይታወቃል። "ሮድ 2029" የታዳጊዎች እግር ኳስ የስልጠና ፕሮጀክት በአሜሪካዊ እና ኢትዮጵያዊ አሰልጣኞች ጥምረት የሚካሄድ ሲሆን በኢትዮጵያ ዓለም የደረሰበትን ዘመናዊ ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል። በዲጂታል አማራጮች ተደግፎ በንድፈ ሀሳብና በተግባር የሚሰጥ ሥልጠና መሆኑን በማንሳት፤ በእስካሁኑ ሂደት ተስፋ ሰጭ ውጤት ታይቶበታል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የ2029 የአፍሪካ ዋንጫ ለማዘጋጀት እንድትመረጥ የቴክኒክ ጉዳዮችን ጨምሮ የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑንን ፌዴሬሽኑ አመልክቷል። ታዳጊዎችን እግር ኳስ ልማት፣ የስፖርት መሰረተ ልማቶች ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን እንዲያሞሉ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች እና የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች መስፋት ተስፋ ሰጪ ጅማሮዎች ነው። መንግስት የጀመራቸው ስራዎች በተጠናከረ መልኩ መቀጠል ይኖርባቸዋል። አጠቃላይ የእግር ኳሱ እደግት የስፖርት ባለድርሻ አካላትን የጋራ ትብብር ይጠይቃል። ተስፋ ሰጪ እና ብርሃን ፈንጣቂ ጅማሮዎችን ነገ ኢትዮጵያ በአፍሪካ እና በዓለም መድረክ በእግር ኳሱ ስኬታማ ለመሆን መሰረት የሚጥሉ ናቸው።
የአፍሪካ እግር ኳስ ፈር ቀዳጇ ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ዋንጫ
Jan 1, 2026 893
ክፍል አንድ እንደ መነሻ እ.አ.አ የካቲት 8 ቀን 1957 በአፍሪካ እግር ኳስ ውስጥ ታሪካዊ ከሚባሉ ቀናት ውስጥ አንዱ ነው። በካርቱም ግራንድ ሆቴል ሱዳን፣ኢትዮጵያ፣ግብጽና ደቡብ አፍሪካ የአፍሪካን እግር ኳስ በበላይነት የሚመራውን ተቋም ለመመስረት ምክክር ላይ ናቸው። አህጉሪቷን የሚወክለው ኮንፌዴሬሽን ለማቋቋም መነሻ የሆነው ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር(ፊፋ) እ.አ.አ በ1956 በፖርቹጋል ሊዝበን ባካሄደው ዓመታዊ ኮንግረስ ላይ የአፍሪካ አገራት ተወካዮች ከሌሎች አህጉራዊ የእግር ኳስ ማህበራት ጋር ያደረጓቸው መደበኛ ምክክሮች ናቸው። በካርቱም የተሰበሰቡት አራት አገራት የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን በይፋ መሰረቱ። ግብጻዊውን አብደል አዚዝ አብደላ ሳሌምን በሙሉ ድምጽ የካፍ የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት አድርገው መረጡ። ካፍን ያቋቋሙት አገራት እ.አ.አ በ1957 የአፍሪካ ዋንጫ በሱዳን እንዲካሄድ ወሰኑ። የመጀመሪያውን የካፍ መተዳደሪያና የውድድር ደንቦች ያዘጋጁት አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ናቸው። የኢትዮጵያ የመጀመሪያ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎና የፎርፌ ውጤት የመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ እ.አ.አ ከየካቲት 10 እስከ 16 1957 በሱዳን ካርቱም ተካሄዷል። በውድድሩ ላይ ሱዳን፣ኢትዮጵያና ግብጽ ተሳታፊ ነበሩ። በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ማንችስተር ሲቲ ከሰንደርላንድ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ ተጠባቂ ነው አስቀድሞ በአፍሪካ ዋንጫ ላይ ትሳተፋለች ተብሎ የነበረው ደቡብ አፍሪካ ከአገሪቷ በነበረው የአፓርታይድ የዘር መድሎ ምክንያት ከውድድሩ ውጪ ሆናለች። ደቡብ አፍሪካ ከውድድሩ ውጪ የሆነቸው በአፓርታይድ ሕግ ነጮች ሙሉ በሙሉ በነጭ ወይም በሙሉ የተገነባ ብሔራዊ ቡድን እንጂ መቀላቀል አንችልም በማለታቸው ምክንያት ነው። በዚህም ምክንያት ከደቡብ አፍሪካ ጋራ በግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዋን ልታደርግ የነበረችው ኢትዮጵያ 2 ለ 0 በፎርፌ በማሸነፍ ለፍጻሜው አልፋለች። በሌላኛው የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ግብጽ ሱዳንን 2 ለ 1 በማሸነፍ ለፍጻሜ አለፈች። እ.አ.አ የካቲት 16 1957 በካርቱም ዓለም አቀፍ ስታዲየም በተደረገው የፍጻሜ ጨዋታ ግብጽ ኢትዮጵያን 4 ለ 0 በማሸነፍ ታሪካዊውን የአፍሪካ ዋንጫ አነሳች። አራቱንም ግቦች ያስቆጠረው የፊት መስመር ተጫዋቹ መሐመድ ዲያብ አል-አታር ሲሆን በአፍሪካ ዋንጫ ፍጻሜ አራት ግቦችን ያስቆጠረ የመጀመሪያው ተጫዋችና በአምስት ግቦች የመጀመሪያው የውድድሩ ኮከብ ግቢ አግቢ በመሆን ድርብ ታሪክ ጽፏል። ኢትዮጵያ በመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎዋ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች። በመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ ምንም የማጣሪያ ውድድር አልተደረገም። በመጀመሪያ የአፍሪካ ዋንጫ የተሳተፉት የኢትዮጵያ ተጫዋቾች ግብ ጠባቂ ሚካኤል ጊላ ተከላካዮች አየለ ተሰማ፣መኩሪያ ከበደ አስፋው፣አዳሙ ዓለሙ፣አዳል ተክለስላሴ አማካዮች ናስር በርሄና ሳሙኤል ዘውዴ አጥቂዎች አብርሃም ባይሩ፣አምደስላሴ ነጸረ፣አስፋው ብርሃኔና ከበደ መታፈሪያ ናቸው። በአፍሪካ ዋንጫና እግር ኳስ ፈር ቀዳጅ ከሆኑ አገራት መካከል አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎዋን በሱዳን አሀዱ ብላ ጀመረች። የኢትዮጵያ ሁለተኛ ተሳትፎ ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ1959 በግብጽ በተካሄደው ሁለተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ አድርጋለች። ሱዳን ሌላዋ በውድድሩ ላይ የተሳተፈች አገር ናት። የውድድሩ ፎርማት በአገራቱ መካከል እርስ በእርስ በሚደረጉ ጨዋታዎች የተሻለ ውጤት ያስመዘገበው ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ የሚያነሳበት ነበር። በዚሁ መሰረት ኢትዮጵያ በውድድሩ ባደረገቻቸው ጨዋታዎች በግብጽ 4 ለ 0፤ በሱዳን 1 ለ 0 ተሸንፋለች። በፍጻሜው ግብጽ ሱዳንን 2 ለ 1 በማሸነፍ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን አንስታለች። ኢትዮጵያ ብቸኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ያነሳችበት ታሪካዊ አጋጣሚ ሶስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ የተካሄደው በኢትዮጵያ አዘጋጅነት እ.አ.አ በ1962 ነው። የአፍሪካ ዋንጫ ውድድሩ ቀደም ብለው ከተካሄዱት ሁለት የአፍሪካ ዋንጫዎች ለየት የሚያደርገው አራት አገራት ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፉበት ነው። ኢትዮጵያ የውድድሩ አዘጋጅ በመሆኗ ሀገራችን በቀጥታ ለውድድሩ ስታልፍ ፤ በተመሳሳይ የግብፅ ቡድንም የ1959 የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ዋንጫ አሸናፊ ቡድን ስለነበር በቀጥታ ለ3ኛ የአፍሪካ ዋንጫ ሲያልፉ ዩጋንዳና ቱኒዚያ የማጣሪያ ጨዋታ አድርገው ለአፍሪካ ዋንጫ አልፈዋል። በሶስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ የነበሩት አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ሲሆኑ ውድድሩን ያስተናገደው ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ስታዲየም(የአሁኑ አዲስ አበባ ስታዲየም) ነበር። ኢትዮጵያ በግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዋ ቱኒዚያን 4 ለ 2 አሸንፋለች። አጥቂው ሉቺያኖ ቫሳሎ በ32ኛው በፍጹም ቅጣት ምት ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ ያስቆጠረችው የመጀመሪያ ግቧ ሆኖ ተመዝግቧል። ቫሳሎ በ75ኛው ደቂቃ በጨዋታ ግብ አስቆጥሯል። አጥቂው መንግስቱ ወርቁ እና ግርማ ተክሌ ቀሪዎችን ግቦች ለኢትዮጵያ ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። በሌላኛው የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ግብጽ ዩጋንዳን 2 ለ 1 በማሸነፍ ለፍጻሜው ከኢትዮጵያ ጋር ደረሰች። በፍጻሜው ጨዋታ አሊ መሐመድ ባዳዊ አብደል ፋታህ በ35ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት በግብ ግብጽን መሪ ማድረግ ችላ ነበር። ከእረፍት መልስ ግርማ ተክሌ በ74ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያን አቻ አድርጋለች። በ75ኛው ደቂቃ አሊ መሐመድ ባዳዊ አብደል ፋታህ በድጋሚ ግብጽን መሪ ያደረገች ግብ አስቆጠረ። አጥቂው መንግስቱ ወርቁ በ84ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያን በድጋሚ አቻ አደረገ። ጨዋታው በመደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ሁለት አቻ በሆነ ውጤት በመጠናቀቁ ጨዋታው ወደ ጭማሬ ሰዓት አምርቷል። በጭማሬ 30 ደቂቃው ኢታሎ ቫሳሎ በ101ኛው እና መንግስቱ ወርቁ በ118ኛው ደቂቃ ባስቆጠራቸው ግቦች ኢትዮጵያ 4 ለ 2 በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ አህጉራዊውን ዋንጫ ከፍ አድርጋለች። በፍጻሜው ጨዋታ ሁለት ግቦች ያስቆጠረው አጥቂው መንግስቱ ወርቁ በአጠቃላይ በውድድሩ ላይ ሶስት ጎሎችን ከመረብ ላይ በማሳረፍ ኮከብ ግብ አግቢ ሆኖ ጨርሷል። ለመጀመሪያ ጊዜ ስድስት አገራት የተሳተፉበት የአፍሪካ ዋንጫ የኢትዮጵያ ቀጣዩ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ እ.አ.አ በ1963 በጋና አስተናጋጅነት በተካሄደው አራተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ነው። በውድድሩ ለመጀመሪያ ጊዜ ስድስት ብሔራዊ ቡድኖች የተሳተፉ ሲሆን በሁለት ምድብ እያንዳንዳቸው ሶስት አገራት ተደልድለው ጨዋታቸውን አድርገዋል። የውድድሩ ፎርማት በየምድቡ አንደኛ ሆኖ የጨረሰ አገር ወደ ፍጻሜው እንዲሁም ሁለተኛ የወጡ አገራት ለደረጃው ያለፉበት ነበር። ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከአዘጋጅ አገር ጋና ቱኒዚያ ጋር ተደልድላች። በአክራ ስፖርት ስታዲየም ኢትዮጵያ ከጋና ጋር ባደረገችው ጨዋታ 2 ለ 0 ተሸንፋለች። በሁለተኛ ጨዋታዋ ኢትዮጵያ አጥቂው መንግስቱ ወርቁ ሁለት እንዲሁም ግርማ ተክሌና ግርማ ተስፋዬ ባስቆጠሯቸው አንድ አንድ ግቦች ቱኒዚያን 4 ለ 2 አሸንፋለች። ኢትዮጵያ ከምድቡ ሁለተኛ ሆና በማጠናቀቋ ለደረጃ ጨዋታ የቀረበች ሲሆን በግብጽ 3 ለ 0 ተሸንፋለች። በፍጻሜው ጋና ሱዳንን 3 ለ 0 በማሸነፍ ዋንጫውን አነሳች። ኢትዮጵያ ለአምስተኛ ተከታታይ ጊዜ የተሳተፈችበት የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ1965 በቱኒዚያ አስተናጋጅነት በተካሄደው አምስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለተከታታይ አምስተኛ ጊዜ ተሳትፋለች። በውድድሩ ላይ ስድስት አገራት ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከቱኒዚያና ሴኔጋል ጋር ተደልድላለች። በመጀመሪያ የምድብ ጨዋታዋ በቱኒዚያ 4 ለ 0 ተሸንፋለች። ኢትዮጵያ በሁለተኛው የምድብ ጨዋታዋ በሴኔጋል 5 ለ 1 ተሸንፋለች። በጨዋታው ለኢትዮጵያ ብቸኛዋን ግብ ያስቆጠረው ሉቺያኖ ቫሳሎ በፍጹም ቅጣት ምት ነበር። በፍጻሜው ጋና ቱኒዚያን 3 ለ 2 በማሸነፍ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ የአፍሪካን ዋንጫ ማንሳት ችላለች። ኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ ያዘጋጀችው የአፍሪካ ዋንጫ እ.አ.አ 1968 የተካሄደውን ስድስተኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ያዘጋጀችው ኢትዮጵያ ነበረች። ውድድሩን ያስተናገደው ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ስታዲየም(የአሁኑ አዲስ አበባ ስታዲየም) ነበር። በሻምፒዮናው ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ስምንት አገራት ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከኮትዲቭዋር፣አልጄሪያና ዩጋንዳ ጋር የተደለደለች ሲሆን ሶስቱንም የምድብ ጨዋታዎቿን አሸንፋለች። በመጀመሪያ ጨዋታዋ ኢትዮጵያ ግርማ አስመሮም ተስፋይ በጨዋታና ሉቺያኖ ቫሳሎ በፍጹም ቅጣት ምት ባስቆጠሯቸው ግቦች ዩጋንዳን 2 ለ 1 አሸንፋለች። ኢትዮጵያ በሁለተኛ ጨዋታዋ በኩረጽዮን ገብረሕይወት ባስቆጠራት ግብ ኮትዲቭዋርን 1 ለ 0 ረታለች። በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ ኢትዮጵያ አጥቂው መንግስቱ ወርቁና ሸዋንግዛው አጎናፍር በጨዋታ እንዲሁም ሉቺያኖ ቫሳሎ በፍጹም ቅጣት ምት ባስቆጠሯቸው ግቦች አልጄሪያን 3 ለ 1 በማሸነፍ ከምድቧ አንደኛ በመውጣት ለግማሽ ፍጻሜው አልፋለች። ኢትዮጵያ በግማሽ ፍጻሜው ጨዋታዋን ያደረገችው ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋር ነበር። ራውል አልበርት ኪዱሙ ማንታንቱ በሶስተኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን መሪ አድርጎል። ሊኦን ሙንጋሙኒ በ16ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ የኮንጎን መሪነት ወደ 2 ለ 0 ከፍ አድርጓል። ሉቺያኖ ቫሳሎ በ25ኛው ደቂያ ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያን ወደ ጨዋታው እንድትመለስ አድርጓል። መንግስቱ ወርቁ በ65ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያን አቻ አድርጓል። መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በአቻ ውጤት መጠናቀቁ ጨዋታው ወደ ጭማሪ 30 ደቂቃ አመራ። በጭማሬ ሰዓቱ ሊኦን ሙንጋሙኒ በ100ኛው ደቂቃ ያስቆጠራትን ግብ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን አሸናፊ በማድረግ ወደ ፍጻሜው እንድታልፍ አድርጎታል። ኢትዮጵያ ለደረጃው ባደረገችው ጨዋታ ላውረን ፖኩ ባስቆጠራት ግብ 1 ለ 0 ተሸንፋ ለሁለተኛ ጊዜ ባዘጋጀችው ውድድር አራተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። ኢትዮጵያ ከፍተኛ ግብ ያስተገደችበት ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሱዳን እ.አ.አ 1970 ሱዳን ባዘጋጀችው ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ ለሰባተኛ ጊዜ በአህጉራዊው የውድድር መድረክ ተሳትፋለች። በውድድሩ ላይ ስምንት አገራት ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከኮትዲቭዋር፣ካሜሮንና ሱዳን ጋር ተደልድላለች። ኢትዮጵያ በምድብ የመጀመሪያ ጨዋታዋ በሱዳን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት ተረታለች። በሁለተኛው ጨዋታም በካሜሮን 3 ለ 2 የተሸነፈች ሲሆን መንግስቱ ወርቁ ለኢትዮጵያ ሁለቱንም ግቦች ከመረብ ላይ አሳርፏል። በመጨረሻው የምድብ ጨዋታ ኢትዮጵያ በኮትዲቭዋር 6 ለ 1 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት ተሸንፋለች። መንግስቱ ወርቁ ለኢትዮጵያ ብቸኛዋን ግብ ከመረብ ላይ ያሳረፈ ተጫዋች ነበር። በዚህ ጨዋታ አጥቂው ላውረን ፖኩ አምስት ግቦችን አስቆጥሯል። ውጤቶቹን ተከትሎ ኢትዮጵያ በምድቡ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ ይዛ ያጠናቀቀች ሲሆን በውድድሩ 12 ግቦችን ተቆጥረውባታል። በፍጻሜው ሱዳን ጋናን 1 ለ 0 በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን አንስታለች። ኢትዮጵያ ከስድስት ዓመታት ቆይታ በኋላ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ ስምንተኛ ተሳትፎዋን ለማድረግ ስድስት ዓመት መጠበቅ ነበረባት። እ.አ.አ በ1976 ራሷ ለሶስተኛ ጊዜ ባዘጋጀችው የአፍሪካ ዋንጫ በድጋሚ ወደ ውድድር ተሳትፎ ተመልሳለች። በውድድሩ ላይ አሁንም የተሳተፉ አገራት ቁጥር ስምንት ነበር። ኢትዮጵያ በውድድሩ በምድብ አንድ ከግብጽ፣ዩጋንዳና ጊኒ ጋር ተደልድላለች። በመጀመሪያው የምድብ ጨዋታ ኢትዮጵያ በሰለሞን ሽፈራውና ተስፋዬ ስዩም ግቦች ዩጋንዳን 2 ለ 0 አሸንፋለች። በሁለተኛ ጨዋታዋ ኢትዮጵያን በጊኒ የ2 ለ 1 ሽንፈት አጋጥሟታል። ሰለሞን ሽፈራው ኢትዮጵያን ከሽንፈት ያልታደገችውን ብቸኛ ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል። በመጨረሻ የምድብ ጨዋታዋ ኢትዮጵያ ከግብጽ ጋር አንድ አቻ ተለያይታለች። መሐመድ አሊ ለኢትዮጵያ ግቧን ያስቆጠረ ተጫዋች ነው። ውጤቶቹን ተከትሎ ኢትዮጵያ በአራት ነጥብ ከምድቧ ሶስተኛ ደረጃን ይዛ በማጠናቀቋ ወደ ግማሽ ፍጻሜው ማለፍ ሳትችል ቀርታለች። በፍጻሜው ሞሮኮ ጊኒን በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን ማንሳት ቻለች። ይቀጥላል ….
ብክነትን መቀነስ የኃይል አቅርቦትን ማሳደግ፤ የአፍሪካ የኢነርጂ ውጤታማነት አጀንዳ
Dec 8, 2025 1463
አፍሪካ በዓለማችን በታዳሽ ኃይል እምቅ ሀብቶችን የያዘች አህጉር ናት። የዓለም 60 በመቶ የፀሐይ ኃይል ሀብት የሚገኘው በአፍሪካ ነው። አህጉሪቱ ከፀሐይ በየዓመቱ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ቴራዋት ሰዓት ኢነርጂ የማመንጨት አቅም አላት። ይሁንና በፀሐይ የምታመነጨው ኃይል ድርሻ አነስተኛ መሆነን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን (ኢሲኤ) የእ.አ.አ 2023 ጥናት ያመለክታል። የዓለም ባንክ ተቋም የሆነው ዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን በበኩሉ አፍሪካ 25 በመቶ የዓለም የንፋስ ኃይል አቅም ያላት ሲሆን 180 ሺህ ቴራ ዋት ሰዓት ማመንጨት እንደምትችል ይገልጻል። ይሁንና በዓለም ላይ በዘርፉ ያላት ድርሻ ከአንድ በመቶ በታች መሆኑን ያነሳል። ሃይድሮ ፓወር የአፍሪካ ሌላኛው የኢነርጂ ሀብት ማሳያ ነው። የአህጉሪቷ ወንዞች እና ተፋሰሶች በየዓመቱ 1 ሺህ 500 ቴራ ዋት ሰዓት የማመንጨት አቅም ቢኖራም ጥቅም ላይ የዋለው 10 በመቶውን ብቻ ነው። የናይል ተፋሰስ፣ የኮንጎ ተፋሰስ እና የዛምቤዚ ተፋሰሶችን የያዘችው አፍሪካ ከፍተኛ የሃይድሮ ፓወር አቅሟን መጠቀም አልቻለችም ይላል የዓለም አቀፉ የታዳሽ ኃይል ኢነርጂ ኤጀንሲ ጥናት። ወደ ምስራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ ያለው የእንፋሎት ኃይል ሌላኛው ትልቅ እድል ነው። የአፍሪካ የእንፋሎት (ጂኦተርማል) አቅም ከ15 እስከ 20 ጊጋዋት መሆኑን የአፍሪካ ኢነርጂ ምክር ቤት መረጃ ያሳያል። አፍሪካ ከዓለም የኢነርጂ ምርት ውስጥ ከአራት በመቶ በታች እንዲሁም በታዳሽ ኃይል ደግሞ ከ1 ነጥብ 6 በመቶ ያነሰ ድርሻ እንዳላት መረጃዎች ያመለክታሉ። የአፍሪካ የኢነርጂ ምህዳር ሁለት ተጻራሪ እውነታዎችን የያዘ ነው። አህጉሪቷ የዓለምን 17 በመቶ ህዝብ ብትይዝም በዓለም የኢነርጂ አጠቃቀም ያላት ድርሻ ከአራት በመቶ በታች ነው። በአሁኑ ሰዓት 600 ሚሊዮን ገደማ የሚሆን የአፍሪካ ህዝብ የኤሌክትሪክ ኃይል እንደማያገኝ መረጃዎች ያመለክታሉ። 21 በመቶ አፍሪካውያን ብቻ ንጹህ የማብሰያ ነዳጅ እና ቴክኖሎጂዎችን ያገኛሉ። ባህላዊ የምግብ ማብሰያ አማራጮች ለጤና አሉታዊ ተጽእኖ የሚያሳድሩ ናቸው። በአፍሪካ ከከተሜነት መስፋፋት እና ከፈጣን የህዝብ እድገት ጋር በተያያዘ የኢነርጂ ፍላጎት በፍጥነት እየጨመረ ይገኛል። እ.አ.አ በ2040 የአፍሪካ ህዝብ 2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ህዝብ እንደሚያልፍ ትንበያዎች ያሳያሉ። በተለይም የህዝብ ብዛት መጨመሩ በኢነርጂ አቅርቦት ላይ ጫና ያሳድራል። ከእ.አ.አ 2014 እስከ 2023 የአፍሪካ የታዳሽ ኢነርጂ በእጥፍ አድጎ ከ32 ነጥብ 5 ጊጋ ዋት ወደ 62 ነጥብ 1 ጊጋ ዋት ማደጉ መልካም የሚባል እምርታ መሆኑን የዓለም አቀፉ የታዳሽ ኃይል ኢነርጂ ኤጀንሲ ይገልጻል። የአፍሪካ ሌላኛው ፈተና የምትጠቀመውን ኢነርጂ የብክነት ምጣኔ ነው። በበቂ ሁኔታ ባልተደራጀው የኢነርጂ ስርዓት ምክንያት አፍሪካ በየዓመቱ በቢሊዮን ዶላሮች የሚገመት ገንዘብ ታጣለች። እንደ ዓለም አቀፉ የኢነርጂ ኤጀንሲ መረጃ ከሆነ አፍሪካ የኢነርጂ አጠቃቀሟን የምታሻሽል ከሆነ 30 በመቶ የኢነርጂ ወጪዋን መቀነስ ትችላለች። ይህም የአፍሪካ መንግስታት ለማህበራዊ ልማት የሚያወጡትን በጀት እንደሚያሳድግ እና አዲስ የኃይል ማመንጫዎችን ሳትገነባ የካርቦን ልቀትን መቀነስ የምትችልበትን እድል ይፈጥርላታል። ኢትዮጵያ ከወራጅ ወንዞች በአመት 124 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ ያላት ሲሆን ከ36 እስከ 40 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር የከርሰ ምድር የውሃ ሃብት እንዳላት የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል። ከገፀ ምድር የውሃ ሃብቷ 83 በመቶ የሚገኘው ከተከዜ፣ ባሮ፣ አባይና ጊቤ ኦሞ ወንዞች ነው። አንዱ የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚመነጨው ካላት የውሃ ሀብት ነው። ኢትዮጵያ በውሃ፣ በፀሐይ፣ በነፋስ እና በጂኦ-ተርማል የኃይል አማራጮች በአጠቃላይ ከ300 እስከ 400 ጊጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳላት መረጃዎች ያሳያሉ። በ10 ዓመት መሪ ልማት እቅዱ ኢትዮጵያ አሁን እያመነጨች ያለውን 4 ሺህ 818 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ወደ 17 ሺህ ሜጋ ዋት ለማሳደግ አቅዳለች። ከለውጡ በኋላ በኢነርጂው ዘርፍ ያለውን አቅም ለመጠቀም የተለያዩ የማሻሻያ ስራዎች ተከናውነዋል። ከስራዎቹ መካከል ለሶስት አስርት ዓመታት ስራ ላይ የነበረውን የኢነርጂ ፖሊሲ ማሻሻል ይገኝበታል። ፖሊሲው ከ2013 ዓ.ም አንስቶ የማሻሻያ ዝግጅት ሲደረግበት ቆይቷል። የፖሊሲ ማሻሻያው የተዘጋጀው አሁን ያለውን ሀገራዊ፣ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፍ ነባራዊ እውነታ መሰረት ባደረገ መልኩ ነው። ለኢነርጂ ፖሊሲው ማሻሻል ምክንያቶች ከሆኑት መካከልም ከሀገር በቀል ኢኮኖሚ፣ ከአረንጓዴ ልማት፣ ከ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድና ከዘላቂ የልማት ግቦች ጋር ማጣጣም በማስፈለጉ እንደሆነም የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመረቀው የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብም በአፍሪካ ግዙፉ የኢነርጂ ፕሮጀክት ሲሆን ለቀጣናው እና ለአፍሪካ ሀገራት ትልቅ አቅምን ይዞ መጥቷል። ከፖሊሲው ትኩረት አንዱ ከአገር ውስጥ የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነት ለጎረቤት አገራት ኃይል በማቅረብ ቀጣናዊ ትስስርን ማጠናከር እንደሆነም በሰነዱ ላይ ሰፍሯል። በ10 ዓመቱ የመሪ ልማት እቅዱም ዜጎችን በስፋት የአሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ የማድረግ ግብ ተይዟል። ከዚህ ባሻገር በእቅዱ ኢትዮጵያ የቀጣናው ሀገራትን በኃይል የማስተሳሰር ዕቅድ ሰንቃ እየሰራች ትገኛለች። በእቅዱ ለጎረቤት አገራት እየቀረበ ያለውን 2 ሺህ 803 ጊጋ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ወደ 7 ሺህ 184 ጊጋ ዋት ሰዓት የማሳደግ ውጥን ተይዟል። የአፍሪካ የኢነርጂ አጠቃቀምን ለማሻሻል እና ብክነትን ለመቀነስ የተቀናጀ ምላሽ የመስጠት ጉዳይ ጊዜ የማይሰጠው ነው። የአፍሪካ ህብረት ያዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የኢነርጂ ውጤታማነት ኮንፍረንስ (Energy Efficiency Conference) ታህሳስ 2 እና 3 ቀን 2018 ዓ.ም በህብረቱ ዋና መቀመጫ በአዲስ አበባ ይደረጋል። ኮንፍረንሱ እ.አ.አ በ2024 በአዘርባጃን ባኩ በተካሄደው 29ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ-29) ይፋ የተደረገው የአፍሪካ ኢነርጂ ውጤታማነት ጥምረት ማዕቀፍ ስር የሚካሄድ ነው። የጥምረቱ ማዕቀፍ በአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መጽደቁ ይታወቃል። “የአፍሪካ የኢነርጂ ውጤታማነት አጀንዳን በስትራቴጂካዊ አጋርነት ውጤታማ ማድረግ” የኮንፍረንሱ መሪ ሀሳብ ነው። አህጉራዊው ሁነት የተዘጋጀው የአፍሪካ ህብረት ልዩ ተቋም በሆነው የአፍሪካ ኢነርጂ ኮሚሽን እና በኢትዮጵያ መንግስት ትብብር ነው። ኮንፍረንሱ የኢነርጂ ውጤማነትን በማረጋገጥ የአፍሪካ ኢኮኖሚ እድገት፣ ዘላቂ ልማት እና ለአየር ንብረት ለውጥ የተግባር ምላሽ አቀጣጣይ ሞተር የማድረግ አላማ ያለው መሆኑ ተገልጿል። የአፍሪካ ኢነርጂ ኮሚሽን ዋና ዳይሬክተር ራሺድ አሊ አብደላ ኮንፍረንሱን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት የኢነርጂ ውጤማነት የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ዋንኛ ሀብት ነው ሲሉ ተናግረዋል። የኢነርጂ ውጤማነት የኃይል ብክነት፣ የካርቦን ልህቀት እና ወጪ ለመቀነስ እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ እድገት ለማረጋገጥ እንደሚያስችል ገልጸዋል። ኮንፍረንሱ የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ አመራሮች፣ ሚኒስትሮች፣ የኢንዱስትሪ መሪዎች፣ የፋይናንስ ተቋማት፣ የግሉ ዘርፍ፣ የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት ፣ ተመራማሪዎች እና ባለሙያዎችን በአንድ መድረክ የሚያገናኝ ነው። ባለድርሻ አካላቱ በአፍሪካ ዘላቂ የኢነርጂ ትራንስፎርሜሽንን ለማፋጠን የሚያስችሉ ውጤታማ የኢንቨስትመንት አማራጮችና ፖሊሲዎች ላይ በመምከር ቀጣይ ስራዎች ላይ የጋራ አቅጣጫ እንደሚያስቀምጡ ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። የአፍሪካ ከፍተኛ እና በሰፊው ጥቅም ላይ ያልዋለ የታዳሽ ኢነርጂ አቅም በቀጣይ የዓለም የኢነርጂ ሽግግር እና አቅርቦት ውስጥ ትልቅ ሚና የሚጫወት ነው። የኢነርጂ አቅሙን ትሩፋቶች የመጠቀም ጉዳይ አነስተኛ ነው ማለት ይቻላል። ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ያላቸውን የታዳሽ ኃይል ምንጭን ለመጠቀም እየወሰዷቸው የሚገኟቸው እርምጃዎች ተስፋ ሰጪ ናቸው። የኢነርጂ ውጤታማነትን ማሳደግ፣ የተቀናጁ ፖሊሲዎች፣ የተቀናጀ ቀጣናዊ የኃይል ቋቶችን መፍጠር፣ የኢነርጂ ፋይናንስን ማሳደግ እና የመንግስታት የፖለቲካ ቁርጠኝነት የአፍሪካ ኢነርጂ አቅሞች ወደ ዘላቂ ልማት፣ የኢነርጂ ደህንነት የማረጋገጥ፣ የአየር ንብረትን የሚቋቋም ጠንካራ ኢኮኖሚ መገንባትን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ ትሩፋቶች ይዞ ይመጣል።
ማድያት እና ህክምናው
Sep 29, 2025 3768
ማድያትን ለማከም አስቸጋሪ መሆኑንና በታካሚዎች ላይም የሥነ ልቡና እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ጫና ሊያመጣ የሚችል መሆኑን የቆዳ ሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ። ስለ ማድያት መንስዔ፣ ስለሚከሰትበት የሰውነት ክፍል፣ ማድያት ያለበት ሰው ማድረግ ስላለበት ጥንቃቄ፣ ቆዳን ስለሚያስቆጣ ሠርካዊ ልማድ እና ሕክምናውን በተመለከተ በራስ ደስታ ዳምጠው መታሰቢያ ሆስፒታል የቆዳ እና አባላዘር በሽታዎች ስፔሻሊስት ዶክተር አደራጀው ብርሃን ከኢዜአ ቆይታ አድርገዋል። በማብራሪያቸውም፤ በቆዳ ውስጥ ያሉ ቀለም አምራች ኅዋሶች(ሴሎች) ከመጠን በላይ ቀለም ሲያመርቱ ማድያት ተከሰተ እንደሚባል ገልጸዋል። ለዚህም መንስዔው የተፈጥሮ ተጋላጭነት ከተለያዩ ቀስቃሽ ምክንያቶች ጋር የሚያደርጉት መሥተጋብር መሆኑን አስረድተዋል። 👉 የማድያት መንስዔ ምንድን ነው? 1ኛ. የሆርሞን ለውጥ፡- በእርግዝና ወቅት ወይም የወሊድ መቆጣጠሪያ ሲጠቀሙ የሚኖር የሆርሞን ለውጥ ማድያት እንዲከሰት ወይም እንዲባባስ ያደርጋል ይላሉ የሕክምና ባለሙያው። 2ኛ. የፀሐይ ጨረር፡- ከልክ ያለፈ ፀሐይ ቀለም አምራች ኅዋሶች(ሴሎች) በብዛት ቀለም እንዲያመርቱ ስለሚያነቃቃ፤ የፀሐይ ጨረር ዋነኛ ቀስቃሽ እና አባባሽ ምክንያት መሆኑንም ገልጸዋል። 3ኛ. የዘር ሐረግ፡- በቤተሰብ ውስጥ ማድያት ካለ በዘር የመተላለፍ ዕድሉ ከፍተኛ መሆኑንም ይናገራሉ። 4ኛ. የቆዳ ዓይነት፡- ጥቁሮች (ከቡናማ እስከ ጥቁር የቆዳ ቀለም ያላቸው) ንቁ ቀለም አምራች ሴሎች ስላሏቸው ለማድያት የሚኖራቸው ተጋላጭነት ከፍተኛ መሆኑን ነው የተናገሩት። 5ኛ. ሌሎች መንስዔዎች፡- ሙቀት (የሚታዩ እና የማይታዩ ጨረሮች እንዲሁም የምድጃ እሳት)፤ የተለያዩ መድኃኒቶችና የመዋቢያ ምርቶች፤ የእንቅርት ዕጢ ህመሞች እንዲሁም ጭንቀት ማድያት እንዲከሰት ወይም እንዲባባስ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል መሆናቸውንም የሕክምና ባለሙያው አስገንዝበዋል። 👉 ማድያት በየትኛው የቆዳ ክፍል ላይ ይከሰታል? ማድያት ከሚከሰትበት የቆዳ እና የሰውነት ክፍሎች አንጻር በሁለት ከፍሎ ማየት እንደሚቻል ዶክተር አደራጀው አንስተዋል። እነሱም 1ኛ. ከሚከሰትበት የቆዳ ክፍል አንጻር፡- ማድያት በውስጠኛውም ሆነ በላይኛው የቆዳ ክፍሎች ላይ ወይም በሁለቱም ላይ ሊከሰት ይችላል ብለዋል። 2ኛ. ከሚከሰትበት የሰውነት ክፍሎች አንጻር፡- የሕክምና ባለሙያው እንዳሉት 60 በመቶ ማድያት ግንባር፣ ጉንጭ፣ አፍንጫ፣ የላይኛው ከንፈር እና አገጭ ላይ ይከሰታል ብለዋል። 30 በመቶው ደግሞ ጉንጭ እና አፍንጫ ላይ እንዲሁም 10 በመቶው የአገጭ መስመርን ተከትሎ እንደሚከሰት አስረድተዋል። በሌላ በኩል አልፎ አልፎ ከፊት የሰውነት ክፍሎች በተጨማሪ በደረት፣ አንገት እና ክንድ ላይ የሚከሰትበት ሁኔታ መኖሩንም ጠቁመዋል። 👉 የማድያት ባሕርይ ማድያት የቆዳ ቀለም ለውጥ ያመጣል፤ በግራና በቀኝ የፊት ክፍል ይወጣል። የማሳከክ ወይም የህመም ስሜት እንደሌለውም ዶክተር አደራጀው አስረድተዋል። • ማድያት በላይኛው የቆዳ ክፍል ላይ ሲከሰት፡- ነጣ ወይም ጠቆር ያለ ቡናማ የሆነ የቆዳ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይ አመላክተዋል። • ማድያት በውስጠኛው የቆዳ ክፍል ላይ ሲከሰት፡- ሰማያዊ ግራጫ ወይም ጠቆር ያለ ግራጫ የቆዳ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይ አንስተዋል። • ማድያት በሁለቱም የቆዳ ክፍሎች ላይ ሲከሰት፡- የተቀላቀለ የቡናማ እና ግራጫ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይም ባለሙያው አብራርተዋል። 👉 ማድያት ያለበት ሰው ምን ዓይነት ጥንቃቄዎችን ማድረግ ይገባዋል? 1ኛ. ወርቃማ ጥንቃቄ፡- • ተከታታይና ጥብቅ የሆነ የፀሐይ መከላከያ መጠቀም ይገባል ይላሉ የሕክምና ባለሙያው። በዚህም መሠረት ከቤት ከመውጣት ከ20 እስከ 30 ደቂቃ ቀደም ብሎ የፀሐይ መከላከያ ክሬሞችን መቀባትና በሁለት ሠዓት ልዩነት እየደረቡ መቀባት። • በሌላ በኩል ከ4 እስከ 10 ሠዓት ያለው የፀሐይ ሙቀት ለቆዳ ህመም አጋላጭ መሆኑን በመገንዘብ ከፀሐይ መከላከያ ክሬም በተጨማሪ ጥላና ኮፍያን መጠቀም እንደሚገባ መክረዋል። 2ኛ. ቆዳን የሚያስቆጣ የቆዳ እንክብካቤ (መስተካከል ያለበት ልማድ)• ቆዳን የሚያስቆጡ መታጠቢያዎች(ሳሙናን ጨምሮ ሌሎችም) እንዲሁም መዋቢያዎችና የሚቀቡ ነገሮች (ኮስሞቲክስን ጨምሮ ሌሎችም) አለመጠቀም ይገባል ይላሉ። • ለቆዳ ተስማሚ የሆኑ ማለስለሻዎችን በደንብ መጠቀም እንደሚገባም ይመክራሉ። 3ኛ. በሐኪም የታዘዙ መድኃኒቶችን በአግባቡ መጠቀም • በሐኪም የታዘዘ መድኃኒትን በአግባቡ(ሳያቆራርጡ) መጠቀም እንደሚመከር ያስረዱት ዶክተር አደራጀው፤ እንደ ማድያቱ እና እንደ ሰዎቹ ቆዳ ዓይነት መድኃኒቱ ለውጥ የሚያሳይበት ጊዜ ስለሚለያይና ከ8 እስከ 12 ሣምንት ሊወስድ ስለሚችል ታግሶ በደንብ ቢጠቀሙ መልካም ነው ይላሉ። 4ኛ. የተለያዩ የሕክምና አማራጮችን መጠቀም• የሕክምና ባለሙያው እንደሚመክሩት፤ በዘርፉ ያሉ የተለያዩ የሕክምና ዓይነቶችን ለምሳሌ እንደ ኬሚካል ፒልስ፣ የቆዳ ሕክምና እና ማይክሮ ኒድሊንግ ያሉትን በሐኪም ምርመራ መሠረት መጠቀም ይገባል። 5ኛ. ከወሊድ መቆጣጠሪያ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ የተከሰተ ማድያት ከሆነ ከሕክምና ባለሙያ ጋር በመመካከር ሌላ አማራጭ መጠቀም እንደሚገባም አንስተዋል። እንዲሁም ጭንቀትን መቀነስ እንደሚገባ መክረዋል። 👉 የማድያት ሕክምናን በተመለከተ የማድያት ሕክምና በጣም አስቸጋሪ ከሚባሉትና ረጂም ጊዜ ከሚወስዱ እንዲሁም በመመላለስ ከሚያስቸግሩ የቆዳ ሁኔታዎች አንዱ መሆኑን ዶክተር አደራጀው ገልጸዋል። በሕክምና ማድያቱ የጠፋላቸው ሰዎች መኖራቸውን አረጋግጠው፤ በሌላ በኩል በሕክምና ሂደት የማድያቱ ሁኔታ ከነበረበት እየቀነሰ ለውጥ የሚታይበት ሁኔታ አለ ብለዋል። ይህን ለውጥ የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ማስቀጠል እንደሚገባም ይመክራሉ። እንክብካቤው ከተቋረጠ ግን ማድያቱ እንደገና የሚመለስበት ሁኔታ መኖሩን አስገንዝበዋል። 👉 የማድያት ሕክምና አማራጮች የሚቀቡ መድኃኒቶች፣ የሚዋጡ መድኃኒቶች፣ ሌሎች የሕክምና አማራጮች(ኬሚካል ፒልስ፣ የቆዳ ሕክምና እና ማይክሮ ኒድሊንግ)፣ የፀሐይ መከላከያ አማራጮችን በአግባቡ አዘውትሮ መጠቀም እንደሚገባ ይመክራሉ።
ልዩ ዘገባዎች
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 3429
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 2262
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 1/2018(ኢዜአ)፡- በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 8060
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 6548
ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
መጣጥፍ
የኢትዮጵያ ዐሻራ ከዓድዋ - እስከ አፍሪካ ኅብረት
Feb 14, 2026 156
በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የፖለቲካ፣ የታሪክ እና ዲፕሎማሲ ምኅዳር ውስጥ ልዩ ስፍራ እና ተጽዕኖ ያላት ሀገር ናት። የጥንታዊ ሥልጣኔዎች ባለቤት የሆነችው ኢትዮጵያ፤ በቅኝ ያልተገዛች ብቸኛ የአፍሪካ ሀገር ከመሆኗ ባሻገር ለፓን አፍሪካኒዝም ንቅናቄ መስፋፋት ትልቅ ሚና ተጫውታለች። ይህንም ታሪክ ይዘክራል። 39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ዛሬ ይጀመራል አይበገሬነት፣ ሉዓላዊነት እና የፓን አፍሪካ መንፈስ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ውስጥ ካሳረፈቻቸው ዐሻራዎች መካከል በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ። በዘመናዊው ዓለምም በአፍሪካ አጀንዳዎች ላይ ወሳኝ ሚና እየተጫወተች ትገኛለች። ኢትዮጵያ የአፍሪካ የነጻነት እና ማንነት ተምሳሌት ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ1896 በዓድዋ ጦርነት በጣሊያን ኃይሎች ላይ የተቀዳጀችው ድል በአፍሪካ እና በጥቁር ሕዝቦች ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠው ነው። አብዛኛው የአፍሪካ አኅጉር በቅኝ ግዛት ውስጥ በነበረበት ወቅት ኢትዮጵያ ያስመዘገበችው ድል ሉዓላዊነቷን ከማስጠበቅ ባለፈ በአፍሪካ እና በአፍሪካ ዳያስፖራ የነጻነት ትግሎች እንዲቀጣጠሉ አድርጓል። በተለይም ከ20ኛው ክፍለ ዘመን በኋላ ለነበሩ እንቅስቃሴዎች ወሳኝ ሚና ተጫውቷል። ይህ ታሪካዊ ዐሻራ ኢትዮጵያን የጥቁሮች ኩራት፣ ትግል እና ራስን የመቻል ምልክት እንድትሆን አስችሏታል። የአፍሪካ የዲፕሎማሲ መዲና አዲስ አበባ የአፍሪካ ኅብረት ዋና መቀመጫ መሆኗ ኢትዮጵያ የአኅጉሪቷ የዲፕሎማሲ ማዕከል ሆና እንድትቀጥል አስችሏል። እ.አ.አ በ1963 የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (የአሁኑ የአፍሪካ ኅብረት) ታሪካዊ ምሥረታ የተካሄደው በኢትዮጵያ ነው። ኢትዮጵያ ከድርጅቱ መሥራች ሀገራት መካከል አንዷ ናት። ይህም የአፍሪካ የጋራ የፖለቲካ ድምጽ እንድትሆን ምክንያት ሆኗል። የአፍሪካ ኅብረት፣ የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ኢሴኤ) እና ዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ ተቋማት የሚገኙባት ኢትዮጵያ፤ በዲፕሎማሲው ምክክር እና ውሳኔ ሰጪነት ውስጥ ያላትን ማዕከላዊ ሚና የበለጠ የሚያጠናክር ነው። የፓን አፍሪካኒዝም ድምጽ ኢትዮጵያ በቅኝ አለመገዛቷ ለፓን አፍሪካኒዝም እንቅስቃሴ ሥር መስደድ ወሳኝ ነው። በፓን አፍሪካኒዝም እሳቤ ለአፍሪካ አንድነት እና የጋራ ምላሽ አጥብቃ ስትሞግትም ቆይታለች። በአፍሪካ ኅብረት እና በተለያዩ መድረኮች ኢትዮጵያ የአፍሪካ ችግሮች በአፍሪካውያን መፈታት አለባቸው የሚለውን እሳቤ ለማስረጽ አበክራ እየሠራች ትገኛለች። ኢትዮጵያ የአፍሪካ ተኮር መፍትሔዎች ከቃላት ባለፈ በአኅጉራዊ የትሥሥር አጀንዳዎች፣ ሰላም እና ደኅንነት ማዕቀፎች እንዲሁም የፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ፈተናዎች እንዲፈቱ ድጋፏን በመስጠት ቁርጠኝነቷን አሳይታለች። የአፍሪካ አኅጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነትንም በፍጥነት አጽድቃ ወደ ሥራ ማስገባቷ የዚሁ አንድ ማሳያ ነው። ሰላም ማስከበር እና ቀጣናዊ መረጋጋት ኢትዮጵያ በቀጣናዊ ሰላም እና መረጋጋት ስትራቴጂካዊ ሚና እየተወጣች ነው። በዚህም መሠረት ለተባበሩት መንግሥታት እና የአፍሪካ ኅብረት የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ከፍተኛ አስተዋጽዖ በማድረግ ከአፍሪካ ሀገራት ቀዳሚውን ድርሻ ትይዛለች። ሶማሊያ፣ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳንን ጨምሮ ግጭት ባለባቸው የአፍሪካ ሀገራት ወታደሮቿን በመላክ ለሰላም እና ደኅንነት ያላትን ሚና በተግባር ገልጣ አሳይታለች። የተባበሩት መንግሥታትም ኢትዮጵያ በሰላም ማስከበር እየተወጣች ላለው ሚና ምሥጋናውን ማቅረቡ ይታወቃል። ኢትዮጵያ በቀጣናው ሀገራት ያሉ ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ የተወጣችው የእርቅ እና የዲፕሎማሲ ሚናም ተጠቃሽ ነው። የኢኮኖሚ እድገት እና ቀጣናዊ ትሥሥር ኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በአፍሪካ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገቡ ካሉ ሀገራት መካከል በዋናነት ትጠቀሳለች። በ2017 ዓ.ም ማብቂያ የተመረቀው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እና በግንባታ ላይ የሚገኘው ኮይሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከግዙፍ መሠረተ ልማትነታቸው ባለፈ ቀጣናዊ ትሥሥር በማረጋገጥ ረገድ ወሳኝ ሚና አላቸው። ሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያ ቀጣናዊ የኢነርጂ የስኅበት ማዕከል እንድትሆን አድርጓታል። ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሀገራት የምትሸጠው ኢነርጂ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ትብብርን የሚያሳልጥ ነው። የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መንገድን ጨምሮ የመንገድ መሠረተ ልማቶች እና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ኢትዮጵያን የቀጣናዊ ትሥሥር ማዕከል እንድትሆን እያደረጓት ነው። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት እየተከናወነ ያለው አረንጓዴ ዐሻራም፤ ኢትዮጵያን የአረንጓዴ ትብብር እና የአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ተምሳሌት ማድረግ ችሏል። በአጠቃላይ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ አጀንዳ የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች ትገኛለች። የባህል እና የሥልጣኔ አስተዋጽዖ ኢትዮጵያ ጥንታዊ ታሪክ፣ ቱባ ባህል እና ብዝኃነት መገለጫዋ ናቸው። የቋንቋ ብዝኃነት በአፍሪካ ውስጥ ገራገር የዲፕሎማሲ ኃይል (Soft Power) እንዲኖራት አስተዋጽዖ አድርጓል። የኢትዮጵያ የሀገርነት ታሪክ እና የሥልጣኔ ትርክት አፍሪካ ያሏትን ጥልቅ የታሪክ ሥሮች ይበልጥ አጉልቶ የሚያሳይ ነው። የኢትዮጵያ ብዝኃ ማንነቶች፣ ሀገር በቀል ዕውቀቶች እና አስደማሚ የሥነ-ሕንጻ ሥራዎች በአፍሪካ ባህል እና ሥልጣኔ ውስጥ ያላቸው ሚና ትልቅ ነው። ኢትዮጵያ አሁንም በአፍሪካ አንድነት እና መረጋጋት ውስጥ እንደ ቁልፍ ምሰሶ ትታያለች። በአኅጉሪቱ ውስጥ ያላት ድርሻ በታሪክ ሥር የሰደደ እና አሁን ባለው ዘመን በዲፕሎማሲ፣ በሰላም ግንባታ እና ልማት ሥራ በግልጽ ጎልቶ ይታያል። ኢትዮጵያ የአፍሪካ የፖለቲካ መዲና እንዲሁም የአይበገሬነት እና የነጻነት ምልክት ናት። አፍሪካ አንድነቷን ለማረጋገጥ፣ የተረጋጋ አኅጉር ለመፍጠር እና በራስ ዐቅም ነገሮችን የመከወን ጉዞ ትልም ውስጥ የኢትዮጵያ ድርሻ ቁልፍ ነው። 39ኛው የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ “ዘላቂ የውኃ ኑረትና ንጽህና ሥርዓት፤ ለአጀንዳ 2063 ስኬት” በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬና ነገ በኅብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ይካሄዳል። ጉባዔው ኢትዮጵያ አኅጉራዊ የፖለቲካ እና ዲፕሎማሲያዊ መድረክ መሆኗን ዳግም የምታሳይበት ነው።
"ጉማታ" በረከትን የመጋራት እሴት!!
Feb 6, 2026 266
"ጉማታ" በረከትን የመጋራት እሴት!! በያንተስራ ወጋየሁ -ዲላ ቀን ቀንን እየወለደ ጊዜ ሳያቋርጥ እንደ ዥረት መፍሰሱን አያቆምም። ትናንት አዲስ የነበረው አሮጌው የሚባልበት፣ ዛሬ አዲስ ሆኖ ነገ አሮጌ ለመባል ይሮጣል። ወቅቶች ይፈራረቃሉ፣ ይመሻል፣ ይነጋል፣ ትናንት ለዛሬ፣ ዛሬ ለነገ እንዲህ እንዲህ እየተቀባበሉ ዘመን ዘመንን እየተካ ዛሬ ላይ ተደርሷል። በጥምር ግብርናውና በቡናው የሚታወቀው ጌዴኦ ትናንትን ሸኝቶ ዛሬን እንደ አዲስ ለመቀበል ሽር ጉድ እያለ ነው። በክረምቱ የተዘራው ሰብል ተሰብስቦ ወደ ጎተራ እንዳስገባ ጌዴኦ አዲስ ዓመቱን ‹‹ዳራሮ››ን ይቀበላል። ዳራሮ የተጣላ የሚታረቅበት፣ ቂም የያዘ ቂምና ቁርሾውን የሚተውበት፣ ወጣቶች የሚተጫጩበት፣ አዛውንቶች ወደ ሽምግልና የሚሸጋገሩበት እሴቶችን በውስጡ የያዘ ነው። "ያገኘሁትን ምርት ብቻዬን አልበላም" ብሎ የሚያምነው የጌዴኦ አርሶ አደር ካመረተው ምርት ለመሪው፣ ልጆች ለወላጆችና ለአሳዳጊዎቻቸው፣ አዲስ ተጋቢዎች ለአማቾቻቸው፣ ቂም የያዘ ሰው እንዲሁ የተቀየመውን ሰው ይቅርታ ለመጠየቅ ጉማታ ይዘው ይሄዳሉ። "ጉማታ" በጌዴኦ ዘመን መለወጫ ወቅት የሚፈጸም ስጦታ ነው። ጉማታ በቤት ውስጥ ተዘጋጅቶ ወደ ታላላቆች ቤት ወይም ወደ ማኅበረሰቡ አደባባይ የሚወሰድ በመሆኑ፣ የግለሰብን ደስታ ወደ ማህበረሰባዊ ደስታ የሚቀይር ድልድይ ነው። በአጠቃላይ ጉማታ ከሌለ የዳራሮ በዓል ሙሉ አይሆንም። ጉማታ የጌዴኦን ሕዝብ አንድነት የሚያጸና፣ ትውልድን ከትውልድ የሚያስተሳስር ሀገር በቀል እሴት ነው። በዳራሮ በዓል አከባበር ውስጥ "ጉማታ" እጅግ አስፈላጊና ትልቅ ትርጉም ያለው ባህላዊ የክብር ስጦታ የመስጠት ሥርዓት ነው። "ጉማታ" ማለት በቀጥታ ትርጉሙ "ስጦታ" ማለት ቢሆንም፣ በጌዴኦ ባህል ግን ከስጦታ በላይ ነው። ምስጋናን፣ ፍቅርን፣ አክብሮትንና በረከትን የመጋራት መገለጫ ነው። የጌዴአ ባህላዊ የባሌ ስርዓት መሪ ሆነው የሚሰየሙት አባ ገዳ ለህዝብ ከመጸለይ፣ ከማስታረቅና ክፉን በማውገዝ ህዝቡ ተፈጥሮን እንዲንከባከብ ከማስተማር ውጭ አይዘሩም፣ አይነግዱም፣ አልፎም እንሳስትን አያረቡም፡፡ የዳራሮ በዓልን ተከትሎ ህዝቡ የሚያቀርብላቸውን "ጉማታ" በመቀበል ባህላዊ የመሪነት ሚናቸውን በአግባቡ ከመወጣት ውጪ። ኑሮው ከጥምር እርሻ ጋር የተቆራኘው የጌዴኦ ሕዝብ ዘርቶ ካጨደው፣ አርብቶ ካገኘው ከብት፣ አንቦ ከቆረጠው ማር፣ ከሁሉም በአይነት በአይነቱ ሸክፎ ዳራሮ ወደ ሚከበርበት ሶንጎ (አደባባይ) ይተማል። ለጉማታ ከሚቀርቡ ከፍተኛ ዋጋ ያላቸው ስጦታዎች አንዱ ማር ነው። ማር በጌዴኦ ዘንድ የጣፋጭ ዘመንና የጤና ምልክት ተደርጎ ይወሰዳልና ዋናው ስጦታ ነው። ጌዶኦዎች ቡና፣ ቅቤና ባህላዊ ምግቦች፣ የቁም እንስሳት በግና ስንጋ እንዲሁም ገንዘብ በመያዝ በበዓሉ ውስጥ የጉማታ ስርዓት ሲደርስ ተሽቀዳድመው ለአባ ገዳው በመስጠት ምርቃት ይቀበላሉ። "ጉማታ" የተቀበለው ሰው የሚመርቀው ምርቃት በሰጪው ሕይወት ላይ ትልቅ ለውጥ እንደሚያመጣ ይታመናልና ከስጦታው ይልቅ ምርቃቱ ትልቅ ዋጋ አለው። "ያገኘሁትን ምርት ብቻዬን አልበላም" ብሎ የሚያምነው ጌዴኦ በረከትን ማካፈል ለቀጣዩ ዓመት ተጨማሪ በረከት እንደሚያገኝ ስለሚያውቅ ጉማታ መስጠት የዘመናት ቅርሱ ነው። ጉማታ ከአባ ገዳና ከባህል ሽማግሌዎች ባለፈ አርሶ አደሩ ከማጋኖ (ከፈጣሪ) ያገኘውን በረከት ለሚወዳቸውና ለሚያከብራቸው ሰዎች የሚያቀርብበት መንገድ መሆኑን የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ (ዶ/ር) ገልጸዋል። ልጆች ለወላጆቻቸውና ለቤተሰብ አባላት ላሳደጓቸውና ለሰጧቸው ምርቃት ምስጋናቸውን ለመግለጽ ጉማታ ይዘው ይሄዳሉ። በቅርቡ ጋብቻ የመሠረቱ ወጣቶች ወደ አማቾቻቸው ቤት ጉማታ ይዞ በመሄድ ዝምድናቸውን ያጠናክራሉ። በዓመቱ ውስጥ ቅሬታ ወይም ቂም ካለ፣ በዳራሮ ወቅት ጉማታ ይዞ በመሄድ ይቅርታ ይጠየቃል። ጉማታ የሰውን ልብ ለማለስለስና አዲስ ዓመትን በሰላም ለመጀመር ያገለግላል ተብሎ ስለሚታመን። ጉማታ በቤት ውስጥ ተዘጋጅቶ ወደ ታላላቆች ቤት ወይም ወደ ማህበረሰቡ አደባባይ የሚወሰድ በመሆኑ፣ የግለሰብን ደስታ ወደ ማህበረሰባዊ ደስታ የሚቀይር ድልድይ ስለመሆኑም ነው ዋና አስተዳዳሪው የጠቆሙት። በአጠቃላይ ጉማታ ከሌለ የዳራሮ በዓል ሙሉ አይሆንም። ጉማታ የጌዴኦን ሕዝብ አንድነት የሚያጸና፣ ትውልድን ከትውልድ የሚያስተሳስር ሀገር በቀል እሴት ነው። ይህም የመደጋገፍ እሴትን ከማጠናከር በተጓዳኝ ህዝቡ የመንግስት ገቢን እንዲሁም በማህበረሰብ ተሳትፎ ለሚከናወኑ የልማት ሥራዎች ግንባር ቀደም ተሳታፊ እንዲሆን መሰረት የጣለ ነው ይላሉ። የዘንድሮው ዳራሮ ከቤት በተለይም ከአባ ገዳው መኖሪያ አንስቶ በሶንጎዎችና በየደረጃው በሚገኙ መዋቅሮች በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት ጭምር እየተከበረ መሆኑን ያነሱት አስተዳዳሪው ጉማታም ዋናው የበዓሉ እሴት ሆኖ እየተከበረ ነው ብለዋል። ባህልና ማንነትን በማስጠበቅና በማዳበር፣ ባህሉ ወደ ወጣቶች እንዲተላለፍ በማበረታታት እንዲሁም የጌዴኦ ባህልን ለሌሎች ህዝቦች ለማስተዋወቅና የማህበረሰብ አንድነትና ባህላዊ እሴትን ለማጠናከር እያገለገለ ያለው የጌዴኦ ዘመን መለወጫ ዳራሮ ጥር 29 እና 30 በዲላ ከተማ ይከበራል። የዳራሮ በዓል የጌዴኦን ሕዝብ የሥራ ባህል፣ የተፈጥሮ ጥበቃ ዕውቀትና የሰላም እሴት ለዓለም የሚያሳይ ትልቅ አጋጣሚ ነው። ይህ በዓል በተለይ የጌዴኦ የባህላዊ መልክዓ ምድር (Cultural Landscape) በዩኔስኮ (UNESCO) በዓለም ቅርስነት መመዝገቡን ተከትሎ፣ አሁን ላይ ከቤትና ከአደባባይ አልፎ ዓለም አቀፋዊ ትኩረት እያገኘ ያለ ታላቅ እሴት ሆኗል። የዓመት ሰው ይበለን!!