ቀጥታ፡

በተጠባቂው ጨዋታ ማንችስተር ሲቲ እና  ቼልሲ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 26/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ20ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ማንችስተር ሲቲ እና ቼልሲ ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ ተጠናቋል።

ማምሻውን በኢትሃድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቲጃኒ ራይንደርስ በ42ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ጎል ማንችስተር ሲቲን መሪ አድርጓል።

ኢንዞ ፈርናንዴዝ በ94ኛው ደቂቃ ላይ ከመረብ ባሳረፈው ግብ ቼልሲ አቻ ወጥቷል።

ባለሜዳው ማንችስተር ሲቲ በኳስ ቁጥጥር እና ኢላማ የጠበቁ ሙከራዎችን በማድረግ የተሻለ ነበር።

ውጤቱን ተከትሎ ማንችስተር ሲቲ በ42 ነጥብ ደረጃውን ከሶስተኛ ወደ ሁለተኛ ከፍ አድርጓል።

ከሊጉ መሪ አርሰናል ጋር ያለው የነጥብ ልዩነት ወደ ስድስት ከፍ ብሏል። 

ቼልሲ በ31 ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዟል።

ዛሬ በተደረጉ ሌሎች ጨዋታዎች ሊድስ ዩናይትድ አንድ አቻ ሲለያይ፣ የፉልሃም እና ሊቨርፑል ጨዋታ ሁለት አቻ ተጠናቋል።

ብሬንትፎርድ ኤቨርተንን 4 ለ 2፣ ኒውካስትል ዩናይትድ ክሪስታል ፓላስን 2 ለ 0 አሸንፈዋል።

ቶተንሃም ሆትስፐርስ እና ሰንደርላንድ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

የዛሬ ጨዋታዎችን ተከትሎ የ20ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ተጠናቋል።

የ21ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከታህሳስ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም