ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
በትምህርት ቤቶች እና በወላጆቻችን በተደረገልን ድጋፍና ክትትል ስኬታማ ሆነናል -ተማሪዎች
Sep 17, 2026 9
ወልድያ፣ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ):- በትምህርት ቤቶች እና በወላጆቻችን የተደረገልን ድጋፍ ስኬታማ በመሆን ትምህርታችንን ለመቀጠል አስችሎናል ሲሉ የሰሜን ወሎ ዞን ተማሪዎች ገለጹ። በሰሜን ወሎ ዞን በተጠናቀቀው የትምህርት ዘመን በመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተናዎች ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች የእውቅናና ሽልማት መርሃ-ግብር አካሂዷል። በሰሜን ወሎ ዞን የ12ኛ ክፍልና የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ለኢዜአ እንዳሉት፤ በትምህርት ቤቶችና በወላጆች የተደረገልን የቅርብ ክትትልና ድጋፍ ጥሩ ውጤት አምጥተን ለቀጣይ ትምህርት እርከን እንድንዘጋጅ አግዞናል። ከዚህ ውስጥም በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና 567 ነጥብ 44 ያመጣው የቆቦ ከተማ «ዕውቀት ጮራ» ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ መንገሻ ሞላ፤ በወልድያ ዩኒቨርሲቲ በተመቻቸው የአዳሪ ትምህርት ቤት እድል ተጠቃሚ መሆኑን ነው የሚናገረው። በዚሁ ወቅት በተለይ በመምህራን በተደረገለት ድጋፍ ጠንክሮ በመስራት ለከፍተኛ ትምህርት የሚያበቃውን ውጤት ለማስመዝገብ እንዳስቻለው ነው የሚናገረው። በቀጣይም የሕግ ትምህርት በመከታተል ያስተማረውን ማህበረሰብ የማገልገል ህልም እንዳለው ነው የገለፀው። በተመሳሳይ በዚሁ ትምህርት ቤት በ12ኛ ክፍል ፈተና 544 ነጥብ 67 በማምጣት ከፍተኛ ውጤት ያመጣው ተማሪ ኃየሎም አስረስ፤ በወላጆች፣ በትምህርት ማህበረሰቡና በመንግስት በተደረገለት ድጋፍ ጥሩ ውጤት ላመጣ ችያለሁ ነው የሚለው። በሌላ በኩል ተማሪ ብሩህ ሄኖክ በ6ኛ ክፍል የዞን ፈተና 97 ነጥብ 5 ያስመዘገበ ሲሆን ተማሪ ሳምራዊት ሀብተየስ ደግሞ 83 ነጥብ 5 ውጤት ማስመዝገባቸውን ይገልፃሉ። ለዚህም የመምህራን እንዲሁም የቤተሰብ ድጋፍ ለውጤቱ ትልቅ ድርሻ እንዳለው ገልፀው የተሻለ ተስፋ ሰንቀን ትምህርታችንን እንድንቀጥል አድርጎናል ነው የሚሉት። የሰሜን ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ ወንድወሰን አክሊሉ እንደገለጹት፤ በዞኑ በ2018 ትምህርት ዘመን 825 ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት አምጥተዋል። ውጤቱ ባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከተመዘገበው ጋር ሲነፃፀር የ7 በመቶ እድገት እንዳለው ነው የገለጹት። ለውጤቱ መመዝገብም የትምህርት ቤቶች ልዩ ድጋፍ፣ የቤተ-መጽሐፍትና የኮምፒውተር ግብአቶች መሟላት አስተዋጽኦ ማድረጉን ነው የጠቀሱት። በአዲሱ የ2019 የትምህርት ዘመንም የኦንላይን ፈተና ዝግጅቶችን ጨምሮ የማጠናከሪያ ሥራዎችም በተሻለ መልኩ እንደሚቀጥሉ ነው ያረጋገጡት።
የወቅቱ የካራባኦ ካፕ አሸናፊ ማንችስተር ሲቲ ከኖርዊች ሲቲ ጋር ይጫወታል
Sep 17, 2026 18
አዲስ አበባ፤ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ):- የእንግሊዝ ካራባኦ ካፕ ሶስተኛ ዙር መርሐ ግብር ዛሬ ይጠናቀቃል። ምሽት 3 ሰዓት ከ30 ላይ ማንችስተር ሲቲ ከኖርዊች ሲቲ በኢትሃድ ስታዲየም ይጫወታሉ። ባለሜዳው ማንችስተር ሲቲ የወቅቱ የዋንጫ ባለቤት ነው። በእንግሊዝ ሻምፒዮንሺፕ (ሁለተኛ የሊግ እርከን) የሚገኘው ኖርዊች ሲቲ በሁለተኛው ዙር ካርዲፍ ሲቲን 2 ለ 1 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር ተሸጋግሯል። ሁለቱም ቡድኖች ከዚህ ቀደም በካራባኦ ካፕ አምስት ጊዜ የተገናኙ ሲሆን ማንችስተር ሲቲ በሶስቱ ሲያሸንፍ በቀሪ ሁለት ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል። ቡድኖቹ ለመጨረሻ ጊዜ በውድድሩ ላይ የተገናኙት እ.አ.አ በ2007 ነው። በወቅቱ በሶስተኛው ዙር ባደረጉት ጨዋታ በጆርጅ ሳማራስ ጎል ማንችስተር ሲቲ 1 ለ 0 አሸንፏል። ማንችስተር ሲቲ ዘጠኝ ጊዜ ዋንጫውን በማንሳት ከሊቨርፑል (10 ዋንጫ) በመቀጠል የውድድሩ ስኬታማ ክለብ ነው። ኖርዊች ሲቲ እ.አ.አ በ1962 እና በ1985 ውድድሩን አሸንፏል። በተጨማሪም እ.አ.አ በ1973 እና 1975 ለፍጻሜ ደርሶ ሽንፈት አስተናግዷል። ማንችስተር ሲቲ ጨዋታውን የማሸነፍ ሰፊ የቅድሚያ ግምት አግኝቷል። የ28 ዓመቱ ሩበን ሪካርዶ ጨዋታውን በዋና ዳኝነት ይመሩታል።
የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ከሩዋንዳ ጋር ይጫወታል
Sep 17, 2026 31
አዲስ አበባ፤ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ):- ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ጨዋታዋን ከሩዋንዳ ጋር ዛሬ ታደርጋለች። ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም በታንዛንያ አስተናጋጅነት መካሄድ ጀምሯል። በውድድሩ ላይ ዘጠኝ ሀገራት በሶስት ምድብ ተከፍለው ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በምድብ አንድ ከአዘጋጇ ታንዛንያ እና ሩዋንዳ ጋር ተደልድሏል። ብሔራዊ ቡድኑ የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታውን ዛሬ ከቀኑ ስምንት ሰዓት ከሩዋንዳ አቻው ጋር ያደርጋል። በአሜሪካዊው አሰልጣኝ ቤንጃሚን ዚመር የሚመራው ብሔራዊ ቡድን በሐምሌ ወር 2018 ዓ.ም ከተጀመረው ብሔራዊ ምልመላና ምዘና( National Camping) አንስቶ ዝግጅቱን ሲያደርግ ቆይቷል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለታንዛንያው የሴካፋ ማጣሪያ ውድድር መጀመሪያ ላይ የ40 ተጫዋቾችን ጊዜያዊ ስም ዝርዝር ይፋ አድርጎ ነበር። በአሁኑ ወቅት አሰልጣኝ ቤንጃሚን ዚመር ስብስቡን ወደ 25 ተጫዋቾች በመቀነስ ልምምዱን ሲያደርግ ቆይቶ ወደ ስፍራው አቅንቷል። በአንድሬ ካሳ ምቡንጎ የሚመራው የሩዋንዳ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም ባደረገው የመጀመሪያ ጨዋታ በአዘጋጇ ታንዛንያ 3 ለ 0 ተሸንፏል። የሩዋንዳ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በበጀት እጥረት ምክንያት ቡድኑ በውድድሩ ላይ እንደማይሳተፍ አስታውቆ የነበረ ቢሆንም፣ ከሀገሪቷ ስፖርት ሚኒስቴር ጋር በተደረገ ስምምነት ውሳኔው ተቀይሮ ውድድሩ ሊጀመር የአንድ ሳምንት እድሜ ሲቀረው መሳተፉ ተረጋግጧል። የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የማጣሪያ ጉዞውን በድል ለመጀመር ይጫወታል። በአንጻሩ የሩዋንዳ አቻው ወደ ግማሽ ፍጻሜ ለማለፍ ያለውን ተስፋ ለማለምለም እጅጉን ወሳኝ ነው። በቤንጃሚን ዚመር የሚመራው ታዳጊ ቡድን ሁለተኛ የምድብ ጨዋታውን መስከረም 9 ቀን 2019 ዓ.ም ከአዘጋጇ ታንዛንያ ጋር ያደርጋል። ቡድኑ ወደ ግማሽ ፍጻሜ የሚገባው ከምድቡ አንደኛ ወይም ከሶስቱ አጠቃላይ ምድቦች ምርጥ ሁለተኛ ሆኖ ካጠናቀቀ ብቻ ነው። በምድብ ሁለት ዩጋንዳ፣ ሱዳን እና ጅቡቲ እንዲሁም በምድብ ሶስት ደቡብ ሱዳን፣ ኬንያ እና ብሩንዲ ይገኛሉ። የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በጋና እ.አ.አ በ2027 ለሚካሄደው ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ በማጣሪያ ውድድሩ የፍጻሜ ተፋላሚ መሆን ይኖርበታል። ከየቀጣናው ሁለት ሀገራት ለአፍሪካ ዋንጫው ያልፋሉ። ብሔራዊ ቡድኑ በጋና በሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ብሔራዊ ቡድኑ ካለፈ እና ግማሽ ፍጻሜ መድረስ ከቻለ በዛው ዓመት በአዘርባጃን እና ኡዝቤኪስታን ጣምራ አዘጋጅነት ለሚካሄደው ከ20 ዓመት በታች የፊፋ ዓለም ዋንጫ ማለፉን ያረጋግጣል። ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም በ20 ዓመት የአፍሪካ ዋንጫ ሁለት ጊዜ ተሳትፋለች። እ.አ.አ በ1993 በሞሪሺየስ በተካሄደው እንዲሁም እ.አ.አ በ2001 ራሷ ባዘጋጀችው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ተሳትፋለች። የሴካፋ ዞን ማጣሪያ እስከ መስከረም 15 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።
የተማሪዎች ምገባ አያሌ ትሩፋቶች
Sep 17, 2026 120
በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ466 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ህጻናት በትምህርት ቤት የምገባ ፕሮግራም ተጠቃሚ መሆናቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ። የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራሞች የምግብ አማራጭ ብቻ ሳይሆኑ በትምህርት፣ በጤና እና በኢኮኖሚያዊ መረጋጋት ላይ ያላቸው አዎንታዊ ተጽእኖ እጅግ የገዘፈ ነው። መርሃ ግብሩ የተማሪዎችን የመማር ምጣኔ በመጨመር በተቃራኒው መጠነ ማቋረጥን በእጅጉ በመቀነስ ረገድ ጉልህ ፋይዳ አለው። ፕሮግራም በተለይም በአደጋ ተጋላጭና ድርቅ ባለባቸው አካባቢዎች ወደ ትምህርት ገበታ የሚመጡ ልጆችን ቁጥር እንዲጨምር ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጓል። ተማሪዎች በቀን ውስጥ የሚያገኙት የተመጣጠነ ምግብ በክፍል ውስጥ ያላቸውን የንቃት፣ የማስታወስ እና የትምህርት መቀበል አቅም በማሳደግ የትምህርት ውጤታቸውን በከፍተኛ ደረጃ አሻሽሏል። የኢትዮጵያ የህብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት (EPHI) እና የዓለም የምግብ ድርጅት መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ ምገባው ህጻናት ከስድስቱ የምግብ ምድቦች የተውጣጡ አልሚ ምግቦችን እንዲያገኙ በማድረግ የተመጣጠነ ምግብ እጥረትንና የጤና አደጋን ይቀንሳል። የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦቱ የህጻናትን አጠቃላይ አካላዊ እድገት፣ የበሽታ መከላከል አቅም (Immunity) እና የአዕምሮ ጤና በመጠበቅ ጤናማ ትውልድ እንዲፈጠር የሚያስችል ነው። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዓለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) እ.አ.አ በ2030 ሁሉም ህጻናት የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኙ አቅዶ እየሰራ ይገኛል። በአፍሪካ ደረጃ ከ100 ሚሊዮን በላይ ህጻናት የተለያዩ የትምህርት ቤት ምገባ መርሃ ግብሮች ተጠቃሚ እንደሆኑ መረጃዎች ያሳያሉ። በኢትዮጵያም የትምህርት ቤቶች ምገባ መርሃ ግብር በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ህጻናትን ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የተማሪዎች ምገባ መርሃ ግብር ከ9 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ተማሪዎች በቀን ሁለት ጊዜ አገልግሎቱን እያገኙ መሆኑን ገልጸው፤ ሀገሪቱ የምትመግበው ህጻናት ቁጥር ከአንዳንድ ሀገራት የህዝብ ቁጥር ጋር የሚስተካከል መሆኑን መግለጻቸው ይታወሳል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ታዳጊ ህፃናት ትምህርት ቤት መሄድ ሲገባቸው በዳቦ ምክንያት እንዳይስተጓጎሉ ማድረግ ሊተኮርበት የሚገባ ዋነኛ የሀገር ግንባታ ጉዳይ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል። በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደረጃ የምገባ ኤጀንሲ በማቋቋም ተማሪዎችን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ የማድረግ ዘላቂ ተግባር በስኬት በመከናወን ላይ ይገኛል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ በመዲናዋ በሚገኙ በመንግሥት ትምህርት ቤቶች ከቅድመ-አንደኛ እስከ መካከለኛ ደረጃ ለሚማሩ አንድ ሚሊየን የሚጠጉ ተማሪዎች በቀን ሁለት ጊዜ (ቁርስ እና ምሳ) በነፃ ይመገባሉ። ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተሞክሮ በመነሳት ይህ ስራ በፈረንሳይ ፓሪስ እና በብራዚል ሪዮ ዲ ጄኔሮ በተከናወኑ ዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ተወዳድረው አሸናፊ በመሆን የሜላን ፓክት ሽልማት (Milan Pact Award) ተቀዳጅቷል። እ.አ.አ በ2022 በብራዚል ሪዮ ዲ ጄኔሮ በተካሄደው 8ኛው የዓለም አቀፍ የከተሞች የምግብ ፖሊሲ ስምምነት ጉባኤ ላይ የተበረከተው ይህ ታሪካዊ የሜላን ፓክት ሽልማት፣ አዲስ አበባ መርሃ ግብሩን በዘላቂነትና በተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት ዘርፍ እጅግ ውጤታማ በሆነ መንገድ በመምራቷ የተሰጠ ነው። በተጨማሪም እ.አ.አ በ2021 በጣሊያን ሮም በተካሄደው የዓለም ሥነ ምግብ ኮንፈረንስ እና በሚላን የምገባ ፎረም ላይ መዲናዋ የምገባ ፎርም ምርጥ ተሞክሮ በሚል እውቅና አግኝታለች። እነዚህ ዓለም አቀፍ ሽልማቶች የተሰጡት መርሃ ግብሩ የተማሪዎችን የምገባ ችግር ከመቅረፍ ባለፈ፣ ከተማዋ የምግብ ስርዓትን በዘላቂነት በመምራትና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን እናቶች በህብረት ስራ ማህበራት በማደራጀት ማህበራዊ ፍትህና የኢኮኖሚ ነፃነት እውን እንዲሆን በማድረጓ ነው። የአዲስ አበባ አርአያነት ያለው ተግባር አሁን ላይ ወደ ክልሎች እና ከተሞች በስፋት እየተዳረሰ ይገኛል፤ እንደ ኬንያ ያሉ የአፍሪካ ሀገራት የልዑካን ቡድኖችም መዲናዋን በመጎብኘት ልምድ እየቀሰሙ ይገኛሉ። የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት (EPHI) የተማሪዎች የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦትን የተመለከተ አዲስ የስነ ምግብ መጽሐፍ አዘጋጅቶ ተግባራዊ አድርጓል። ከንቲባ አዳነች አቤቤ መርሃ ግብሩ ተማሪዎች በኢኮኖሚ አቅም ማነስ ምክንያት ይሰማቸው የነበረውን የስነ-ልቦና ጫናና የድፍረት ማጣት ሙሉ በሙሉ በመቅረፍ ማህበራዊ ፍትህ ማረጋገጡን በአንድ ወቅት ገልጸዋል። ምግብ በማብሰልና በማቅረብ ሂደት ላይ ከ25 ሺህ በላይ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው እናቶች በህብረት ስራ ማህበራት ተደራጅተው ቋሚ የገቢ ምንጭ እንዲያገኙ በማድረግ የሴቶችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አቅም ገንብቷል። የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ በሀገር አቀፍ የተማሪዎች የምገባ መርሃ ግብሩ አብዛኛው በጀት በሀገር ውስጥ አቅም እና በመንግስት የሚሸፈን ነው። መርሃ ግብሩ ከተጀመረ ወዲህ በተለይም ድርቅና የአየር ንብረት ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የተማሪዎች ምዝገባ በ10 በመቶ እንዲጨምር እና የትምህርት ማቋረጥ ምጣኔ በእጅጉ እንዲቀንስ አድርጓል። ትምህርት ቤቶች የወጪ ጫናቸውን እንዲቀንሱ በትምህርት ቤቶች ግቢ ውስጥ የጓሮ አትክልት ልማት፣ የዶሮ እና የወተት ከብቶች እርባታ እንዲጀመር ተደርጓል። ኢትዮጵያ ይሄን መርሃ ግብር የምግብ አቅርቦትን ተደራሽ ማድረግ ብቻ ሳይሆን የሀገርን የረጅም ጊዜ የሰው ሀብት (Human Capital) መገንቢያ ስትራቴጂ አድርጋ እየሰራች ይገኛል። የምገባ ፕሮግራሙ ከትምህርት ተደራሽነትና ውጤታማነት ባሻገር ህጻናት በጤናማ አካልና አእምሮ እንዲያድጉ በማድረግ ለሀገር አቀፍ የጤና ጥበቃ ስራዎች ትልቅ አበርክቶ እያበረከተ ይገኛል። በምገባ ማዕከላት ዙሪያ የሚደረጉ የንፅህና አጠባበቅና የደህንነት ትምህርቶች ተማሪዎች በለጋ እድሜያቸው ጤናማ የኑሮ ዘይቤዎችን እንዲላመዱና የግል ንፅህናቸውን እንዲጠብቁ አቅም እየፈጠረ ይገኛል። በአጠቃላይ የምገባ ፕሮግራም በትምህርት ላይ እያሳረፈ ካለው በጎ አሻራ ባለፈ ምርታማ ትውልድ ለመፍጠር እና ለአንድ ሀገር እድገት እና ልማት ያለው አስተዋጽኦ ጉልህ ነው። በዚህ ረገድም ኢትዮጵያ በስኬት ጎዳና እና ለሌሎች አርአያ በሚሆን ተምሳሌታዊ ተግባር በግንባር ቀደምትነት የምትነሳ ሀገር ናት።
ማንችስተር ዩናይትድ ከካራባኦ ካፕ ውድድር ተሰናበተ
Sep 17, 2026 132
አዲስ አበባ፤ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ካራባኦ ካፕ የሶስተኛ መርሐ ግብር ብራይተን ማንችስተር ዩናይትድን 3 ለ 2 አሸንፏል። ትናንት ማምሻውን በኦልድትራፎርድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሼ ሌሲ እና ሜሰን ማውንት ባስቆጠሯቸው ጎሎች ማንችስተር ዩናይትድ 2 ለ 0 መምራት ችሎ ነበር። ቻራላምፖስ ኮስቱላስ፣ ፓስካል ግሮስ እና ማክሲም ዲካይፐር ከመረብ ላይ ባሳረፏቸው ጎሎች ብራይተን አሸናፊ ሆኗል። የግሮስ እና ዲካይፐር ጎሎች ከእረፍት መልስ የተቆጠሩ ናቸው። ውጤቱን ተከትሎ ብራይተን ወደ አራተኛው ዙር አልፏል። የስድስት ጊዜ የውድድሩ አሸናፊ የሆነው ማንችስተር ዩናይትድ በሶስተኛው ዙር ተሰናብቷል። በሌሎች መርሐ ግብሮች አስቶንቪላ ኮቨንተሪ ሲቲን 3 ለ 1፣ ኤቨርተን ዎልቭስንና ፍሊትውድ ሼፍልድ ዩናይትድን በተመሳሳይ 1 ለ 0 በማሸነፍ ቀጣዩን ዙር ተቀላቅለዋል። የካራባኦ ካፕ የሶስተኛ ዙር መርሐ ግብር የወቅቱ የዋንጫ ባለቤት ማንችስተር ሲቲ እና ሌስተር ሲቲ ነገ በሚያደርጉት ጨዋታ ይጠናቀቃል።
ፖለቲካ
ግብፅ የ21ኛውን ክፍለ ዘመን የዓባይ ተፋሰስ እውነታ መቀበል አለባት - አምባሳደር ተሾመ ቶጋ
Sep 17, 2026 221
ዓባይ ወንዝ የተፋሰሱ ሀገራት የሚጋሩትና በዓለም አቀፍ ደረጃ ግንባር ቀደም ከሆኑ ድንበር ተሻጋሪ የውሃ ሀብቶች ውስጥ የሚመደብ ነው። ግብፅ በወንዙ ፍሰት ላይ ምንም ዓይነት አስተዋጽኦ ሳታበረክት የታችኛው ተፋሰስ ዋና ተጠቃሚ ሆና ቆይታለች። ኢትዮጵያ ደግሞ፣ የዓባይ ወንዝ የውሃ ፍሰት 86 በመቶ ድርሻ አላት። በግብፅ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት ተሾመ ቶጋ በ«ፐልስ ኦፍ አፍሪካ» (Pulse of Africa) መድረክ ላይ “Egypt Must Align Its Nile Strategies with the Realities of 21st Century” በሚል ርዕስ ባሰፈሩት ጽሑፍ፤ ግብፅ በወንዙ አጠቃቀም ላይ “ታሪካዊ መብቶች አሉኝ” በሚል አቋም ለረጅም ጊዜ መያዟን አመልክተዋል። እንደ አምባሳደሩ ገለጻ፣ ግብፅ የላይኛው ተፋሰስ ሀገራት ይሁንታ በሌለበት የቅኝ ግዛት ስምምነቶች ላይ የሙጥኝ ማለቷ ከዘመኑ ዓለም አቀፍ የውሃ ሕግ መርሆዎች ጋር የሚስማማ ማዕቀፍ ለመዘርጋት ትልቅ ዕንቅፋት ሆኗል። እ.አ.አ በ1959 የተፈረመው የቅኝ ግዛት ውል የዓባይን አጠቃላይ የውሃ ድርሻ የሌሎች ተፋሰስ ሀገራትን ባላሳተፈ መልኩ ለግብፅና ሱዳን ብቻ የሰጠ መሆኑን አምባሳደሩ አውስተዋል። መሰረታዊ መነሳት ያለበት ጥያቄ «ግብፅ በዓባይ ወንዝ ላይ ያላት ፍላጎት ሳይሆን፣ ያ ፍላጎት የሌሎችን የተፋሰስ ሀገራት ፍትሐዊ መብቶችና የልማት ትልሞችን በሚጎዳ መልኩ መፈጸም አለበት ወይ?» የሚለው ነው ብለዋል። የሕዝብ ቁጥር ዕድገት፣ የአየር ንብረት መዛባት፣ የምግብ ዋስትና ስጋቶች እና አዳዲስ የኢነርጂ ፍላጎቶች የዓባይ ወንዝ አስተዳደርን መሰረታዊ በሚባል ሁኔታ መቀየራቸውን አንስተዋል። የዓባይን ወንዝ በቀድሞ ታሪካዊ ውሎች ብቻ መመልከት ከእውነታው የራቀ እና ዘላቂ መፍትሔ ሊያመጣ የማይችል አካሄድ መሆኑን ገልጸዋል። አምባሳደሩ በጽሑፋቸው እንዳመላከቱት፣ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያ የውስጥ አቅሟን አስተባብራ የልማት ግቦቿን ማሳካት እንደምትችል ያረጋገጠ ትልቅ ምዕራፍ ነው። ይህ ፕሮጀክት በወንዙ ላይ የነበረውን የኃይል ሚዛን እና ስትራቴጂካዊ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ መለወጡንም አመልክተዋል። ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ ተጨማሪ ልማት ማካሄድ የለባትም የሚሉ ሀሳቦች ተቀባይነት እንደሌላቸው ጠቅሰው፤ የፋይናንስ ክልከላዎችን በመጠቀም የኢትዮጵያን የልማት ፕሮጀክቶች ማስተጓጎል ፈጽሞ የማይቻል መሆኑን የሕዳሴው ግድብ በተግባር ማሳየቱን ገልጸዋል። አሁን ያለው ብቸኛው ዘላቂ መፍትሔ የሁሉንም ተፋሰስ ሀገራት ፍላጎት የሚያስተናግድ ዲፕሎማሲያዊ እና ፖለቲካዊ ማዕቀፍ መፍጠር መሆኑን አስገንዝበዋል። እንደ ቻይና ያሉ ሀገራት ድንበር ተሻጋሪ ወንዞችን ከጎረቤቶቻቸው ጋር በውይይትና በድርድር እንደሚያለሙት ሁሉ፣ የዓባይ ተፋሰስ ሀገራትም ልዩነቶቻቸውን በሰላማዊ መንገድ ማስተዳደር እንደሚችሉ የሌሎች ወንዞች ተሞክሮዎችን በመጥቀስ አምባሳደሩ አብራርተዋል። የተፋሰሱ ሀገራት እ.አ.አ በ2010 ይፋ ባደረጉት እና እ.አ.አ በ2024 በሕጋዊ መንገድ ጸድቆ ሥራ ላይ በዋለው አካታች የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት (CFA) አማካኝነት እያደረጉት ያለው ጥረት የላይኛው የተፋሰሱን ሀገራት ፍላጎትና ልማት መከበር እንዳለበት የሚያሳይ ነው ብለዋል። የፍትሐዊ ተጠቃሚነት ጉዳይ ከግድቡ ወይም ከኢትዮጵያና ግብፅ የሁለትዮሽ ግንኙነት የዘለለና የዘመኑን የኢኮኖሚና የውሃ አስተዳደር እውነታ ከግምት ውስጥ ያስገባ ነው። የእ.አ.አ 1993ቱ የጋራ መግባቢያ ስምምነት እና የእ.አ.አ 2015ቱ የመርሆዎች መግለጫ ስምምነት (Declaration of Principles) ኢትዮጵያ ሰላማዊ መፍትሔዎችን ለመፈለግ ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳዩ መሆናቸውን በጽሑፋቸው ጠቅሰዋል። ኢትዮጵያውያን እና ግብፃውያን ጥልቅ ታሪካዊና ባህላዊ ትስስር እንዳላቸው አምባሳደሩ ገልጸው፤ ዓባይን እንደ ጠብ መጫሪያ ሳይሆን የሕዝቦች ማስተሳሰሪያ ድልድይ በማድረግ መጠቀም እንደሚገባ ተናግረዋል። አምባሳደሩ እንዳብራሩት፣ የኢትዮጵያ የሰላም እና የትብብር መንፈስ እንደ ድክመት ወይም መብትን አሳልፎ እንደ መስጠት ሊወሰድ አይገባም። ኢትዮጵያ ድህነትን የማስወገድ፣ የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚነትን የማረጋገጥ እና ለኢኮኖሚ የመጠቀም ሕጋዊ መብት አላት። ከዚህ ጎን ለጎንም በታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ላይ ጉዳት በማያደርስ መልኩ የውሃ ሀብቷን በፍትሐዊነት ለመጠቀም ትሰራለች ነው ያሉት። የዓባይ ወንዝ ተጠቃሚነት ጉዳይ በአሸናፊነትና በተሸናፊነት ላይ የተመሰረተ የውድድር መልክ መያዝ እንደሌለበትና ትክክለኛው አካሄድ በጋራ ትብብር መንፈስ መስራት መሆኑ ተገልጿል። ኢትዮጵያና ግብፅ በሃይድሮሎጂ፣ በአየር ንብረት ለውጥ ምላሽ፣ በድርቅና አውሎ ነፋስ አደጋዎች መከላከል፣ በግብርና ምርታማነት እና በኤሌክትሪክ ኃይል ንግድ በጋራ መስራት የሚችሉባቸው እድሎች እንዳሉ አምባሳደሩ አንስተዋል። ሀገራቱ በሃይድሮፓወር እና በውሃ ሀብት አስተዳደር በትብብር መስራት እንደሚችሉም አመልክተዋል። የኢነርጂ ንግድ፣ የኢንቨስትመንት ትስስር እና የቀጣናው ኢኮኖሚያዊ ትስስር ሁለቱ ሀገራት ወንዙን እንደ የጋራ የልማት ዕድል እንዲጠቀሙበት ትልቅ አቅም የሚፈጥር ነው ብለዋል። ግብፅ የ21ኛውን ክፍለ ዘመን የዓባይ ተፋሰስ እውነታ መቀበል እንዳለባትም ነው የተናገሩት። አሁን የሚያስፈልገው ግጭት ሳይሆን፣ በሉዓላዊ መብት፣ በፍትሐዊ አጠቃቀም፣ በጋራ መከባበር እና በጋራ ብልጽግና መርሆዎች ላይ የተመሰረተ አዲስ የፖለቲካ መግባባት መፍጠር ነው ብለዋል አምባሳደሩ። ዓባይ የአንድ አካል ብቸኛ ባለቤትነት የሚንጸባረቅበት ሊሆን አይገባም ያሉት አምባሳደሩ፤ የወደፊት የጋራ ዕጣ ፈንታ የሚገነባው በጋራ ኃላፊነት እና ትብብር ብቻ መሆኑን ገልጸዋል።
በዞኑ የዘላቂ ሰላም ግንባታ ፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ
Sep 16, 2026 370
ገንዳውኃ፣ መስከረም 6/2019 (ኢዜአ):- በምዕራብ ጎንደር ዞን ህብረተሰቡን በማሳተፍ እየተከናወኑ ያሉ የዘላቂ ሰላም ግንባታ፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ። ዞኑ "አርቆ ማየት፣ አልቆ መስራት" በሚል መሪ ሀሳብ ለሶስት ቀናት ሲያካሂድ የቆየውን የ2018 የበጀት ዓመት የስራ እቅድ ግምገማ እና የ2019 የዕቅድ ትውውቅ መድረክ ዛሬ አጠናቋል። የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ እያሱ ይላቅ በወቅቱ እንደገለጹት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ህብረተሰቡን በማሳተፍ የተከናወኑ የዘላቂ ሰላም ግንባታ፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል በቅንጅት ይሰራል። በያዝነው በጀት ዓመት የአገልግሎት አሰጣጥን በማቀላጠፍና የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎችን በማፋጠን የሕዝቡን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ በበለጠ ትኩረት እንደሚሰራ አመላክተዋል። የአገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል ለህብረተሰቡ የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን የማስፋፋት ስራ እንደሚከናወን ጠቁመዋል። ህብረተሰቡን በባለቤትነት በማሳተፍ እየተከናወኑ ያሉ የዘላቂ ሰላም ግንባታ ስራዎችም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል። በብልፅግና ፓርቲ የዞኑ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ እንዳለው ማሩ በበኩላቸው፤ በፓርቲው አመራር ሰጪነት የዞኑን ሰላምና ልማት አጠናክሮ ለማስቀጠል ይበልጥ በትጋት ይሰራል ብለዋል። ዞኑ ለግብርና ልማት ያለውን ከፍተኛ አቅም በአግባቡ ለመጠቀም በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራርን ማስፋፋት ላይ በትኩረት ይሰራል ያሉት ደግሞ የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አንዳርጌ ጌጡ ናቸው። ለዚህም የግብርና ቴክኖሎጂ፣ የምርጥ ዘርና የማዳበሪያ አቅርቦት በወቅቱ ማሰራጨት ላይ ቅንጅታዊ ተግባራት እንደሚጠናከሩ አመልክተዋል። በተጨማሪም የመስኖ ልማትን ለማስፋፋት የውሃ መሳቢያ ቴክኖሎጂዎችን በስፋት ለማስተዋወቅና ለማዳረስ በትኩረት እንደሚሰራ አስታውቀዋል። በመድረኩ በተጠናቀቀው በጀት አመት የተሻለ አፈፃፀም ላሳዩ ወረዳና ከተማ አስተዳደሮች የእውቅና ሽልማት ተሰጥቷል።
የኢትዮጵያ ማንሰራራት የአፍሪካን ሕዳሴ ያበስራል - የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
Sep 15, 2026 865
ኢትዮጵያ አዲሱን ዓመት ብሔራዊ ጥቅሞቿን በማስቀደምና የአፍሪካውያን እውነተኛ ድምፅ በመሆን ጀምራዋለች። በዓለም አቀፍ ተለዋዋጭ የጂኦፖለቲካ ውጥረት ውስጥ ጽኑና ገለልተኛ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲን በመከተል የብሪክስ አባል መሆን የቻለችው ኢትዮጵያ፣ በሕንድ ኒው ዴልሂ በተካሄደው 18ኛው የብሪክስ መሪዎች ጉባኤ ላይ አህጉራዊ አርአያነቷንና ስትራቴጂካዊ ተሰሚነቷን በተግባር አስመስክራለች። “ጽናትን፣ ፈጠራን፣ ትብብርን እና ዘላቂነትን መገንባት” በሚል መሪ ቃል የተካሄደው ይህ ጉባኤ፣ ኢትዮጵያ ከአባልና አጋር ሀገራት ጋር ያላትን ሁለገብ ትስስር ወደ ላቀ ከፍታ ያሸጋገረና ፍትሃዊና አካታች ዓለም አቀፍ ሥርዓት እንዲገነባ ያላትን ቁርጠኝነት በግልጽ ያሳየ ምዕራፍ ሆኗል። ኢትዮጵያ በጉባኤው መድረክ ላይ ባነጸባረቀችው አቋም፣ ሀገራት ቀውሶች ከመከሰታቸው በፊት የመቋቋም አቅም ሊገነቡ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥታለች። በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ባደረገችው ጥረት ከውጭ ለእርዳታ ከሚገባ የስንዴ ጥገኝነት ሙሉ በሙሉ መላቀቋን ይፋ ያደረገች ሲሆን የብሪክስ የሰብል ልውውጥ ማዕቀፍ (BRICS Grain Exchange) እንደ አምራችም ሆነ አቅራቢ ሆና ለመሳተፍ ዝግጁ መሆኗን አረጋግጣለች። በመድረኩ ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂና ፈጠራ ዘርፍ የዲጂታል መሠረተ ልማት፣ ዲጂታል መታወቂያ፣ የክፍያ ሥርዓቶች እና አስተማማኝ የመረጃ ልውውጥ አውታሮችን በስፋት እየገነባች መሆኗን አስገንዝባለች። ለአፍሪካ የነገውን የቴክኖሎጂ ዘመን በባለቤትነት ለመምራት የሚያስችለውን «የመደመር ሰው ሠራሽ አስተውሎት ዩኒቨርሲቲ» እያቋቋመች መሆኗን በመግለጽ፣ ከብሪክስ ተቋማት ጋር በጋራ ለመሥራት ያላትን ዝግጁነት አረጋግጣለች። አፍሪካ የበርካታ ማዕድናት ሀብት ባለቤት መሆኗን በማስታወስም፣ የማዕድን ሀብት ለኢነርጂ ሽግግር፣ ለላቀ ማኑፋክቸሪንግ እና ለዲጂታል ኢኮኖሚ ወሳኝ መሆኑን ኢትዮጵያ አንጸባርቃለች። የብሪክስ አባል ሀገራት የካፒታል፣ የቴክኖሎጂ እና የገበያ አማራጭ በመያዛቸው እነዚህን ሀብቶች አቀናጅቶ ለመጠቀምና በጥሬ ሀብቱ ላይ እሴት ለመጨመር ትልቅ እድል እንደሚፈጥር አመልክታለች። ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ የማምረት አቅሟን እያስፋፋች መሆኗን፣ እንዲሁም በማዕድናት፣ በታዳሽ ኢነርጂ እና እያደገ ባለው የኢንዱስትሪ አቅም ላይ አጋርነቶችን ለመፍጠር ዝግጁ መሆኗን አረጋግጣለች። በተጨማሪም የኢትዮጵያ አየር መንገድ አፍሪካን ከዓለም ጋር የሚያገናኝ ትልቅ ዕድል መሆኑን፣ ለጎረቤት ሀገራት የሚደረገው የኃይል አቅርቦት እና አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ መሆኗ ለአህጉራዊና ዓለም አቀፍ ትስስር ያላትን አበርክቶ በግልጽ በማስመዝገብ መድረኩን ተጠቃማበታለች። ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ስርዓት ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሪፎርም እያከናወነችና የውጭ ዕዳዋን ለማሸጋሸግ እየሰራች መሆኗን ገልጻ፤ በፈተና ውስጥ ለሚገኙ ኢኮኖሚዎች የዕዳ አከፋፈል ሂደት ፈጣን፣ ግልጽ እና ተገማች መሆን እንዳለበት አሳስባለች። እንዲሁም በማደግ ላይ የሚገኙ ሀገራት በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ውስጥ ያላቸው ውክልና ፍትሃዊ፣ ተደማጭነታቸውን ያረጋገጠ እና ተጨባጭ ውጤት የሚያመጣ መሆን እንዳለበት ጠንካራ ጥሪ አቅርባለች። በጉባኤው ባደረገችው ንቁ ተሳትፎም ሀገራችን የዓለም ንግድ ድርጅት አባል እንድትሆን፣ በዓለም አቀፍ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት (ICAO) ምክር ቤት ተጨማሪ መቀመጫ እንድታገኝ፣ እንዲሁም የዓለም አቀፉ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤን (COP32) በአዲስ አበባ እንድታዘጋጅ ድጋፍ አግኝታለች፤ የኒው ዴቨሎፕመንት ባንክ (NDB) ቢሮ በአዲስ አበባ እንዲከፈት እና ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች ወደ ስምምነት የሚቀይር «የብሪክስ አስተባባሪ» እንዲቋቋም ያቀረበቻቸው ምክረ ሀሳቦች ሰፊ ተቀባይነት አግኝተዋል። ከብሪክስ መድረክ ጎን ለጎን ከተከናወኑ ሰፊ የዲፕሎማሲ ሥራዎች መካከል ከዓለም መሪዎች ጋር የተደረጉት ውይይቶች ሀገራዊ ጥቅሞችን ከማስጠበቅና አጋርነትን ከማጠናከር አንፃር ትልቅ ስኬት የተመዘገበባቸው ነበሩ። ከሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በኢትዮጵያና ሩሲያ መካከል ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት ተደርጓል። ውይይቱ በመከላከያና ደኅንነት፣ በንግድና ኢንቨስትመንት፣ በትምህርት፣ ቴክኖሎጂ እንዲሁም በባህልና ሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት መስኮች ያለውን ትብብር ለማሳደግ የጋራ ቁርጠኝነት የተረጋገጠበት ነበር። በተጨማሪም ለኮፕ 32 በሚደረገው ዝግጅት፣ በአየር ንብረት ለውጥ እና በልማት ግቦች ዙሪያ ትብብራችንን ለማጠናከር የሚያስችል ስምምነት መፍጠር ተችሏል። ከሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ጋርም በመከላከያ ትብብር ማሳደግ፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በአቅም ግንባታ እና በማዕድን ልማት ዙሪያ ውይይት የተደረገ ሲሆን፤ የዘመናት ታሪካዊ ትስስራችንን ወደተግባራዊ የኢኮኖሚና ልማት ምዕራፍ ማሸጋገር ተችሏል። በተጨማሪም ከማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሂም ጋር በኢንቨስትመንት፣ ቱሪዝም፣ የታዳሽ ኃይል አጋርነትና በአምራች ዘርፍ ተሞክሮዎች ዙሪያ ውይይት ተደርጎ ለሀገር ውስጥ ልማት የሚሆን ትልቅ በር ተከፍቷል። ከአቡ ዳቢ አልጋ ወራሽ ልዑል ሼህ ኻሊድ ቢን ሙሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር በብሪክስ ቅድመ-አጀንዳዎችና በሁለገብ ትብብር ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን፤ ከኢራኑ ፕሬዚዳንት መስዑድ ፔዜሽኪያን ጋርም በቀይ ባሕር አካባቢ ወቅታዊ ሁነቶች እና በቀጣናው የደኅንነት መረጋጋት እንዲሁም በወል ተጠቃሚነት ላይ የተመሠረተ የንግድ፣ የኢኮኖሚና ልማት ልውውጦቻችንን ይበልጥ ለማስፋፋት በጋራ ለመሥራት ስምምነት ላይ ተደርሷል። በአጠቃላይ፣ ኢትዮጵያ በ18ኛው የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ያከናወነቻቸው ስትራቴጂካዊ የዲፕሎማሲ ሥራዎችና ያስመዘገበቻቸው ተጨባጭ ውጤቶች የሀገሪቱን የረጅም ጊዜ የዲፕሎማሲና የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን እውን የሚያደርጉ ወሳኝ ምሶሶዎች ናቸው። መንግሥት በዚህ ታሪካዊ መድረክ ኢትዮጵያ የብሪክስ አባልነቷን በመጠቀም ስትራቴጂካዊ ጥቅሟን በድፍረት የምትጠይቅ፤ ለአፍሪካ ልማት፣ ሰላም እና ፍትሃዊ ዓለም አቀፍ ትብብር የቆመች አስተማማኝ አጋር መሆኗን በተግባር አስመስክሯል። የኢትዮጵያ ማንሰራራት የአፍሪካን ሕዳሴ ያበስራል!
በመደመር መንግሥት በሳል ዲፕሎማሲ ዓቅም የተመዘገበ የብሪክስ ድል
Sep 15, 2026 747
ኢትዮጵያ በረጅም የዲፕሎማሲ ታሪኳ የገነባችውን ልምድ ከዘመኑ ዓለም አቀፍ ለውጦች ጋር በማጣጣም፣ብሔራዊ ጥቅሟን በማስቀደምና ከተለያዩ የዓለም ኃይሎች ጋር አጋርነቷን በማስፋት በሳል የውጭ ግንኙነት አካሄድ እየተከተለች ትገኛለች። የዚህ አካሄድ ጉልህ ውጤት ማሳያ ደግሞ ኢትዮጵያ የብሪክስን ጥምረት መቀላቀሏ ነው። ይህ ስኬት ግን የጥምረቱ አባል በመሆኗ ብቻ የሚያበቃ አይደለም። ኢትዮጵያ በመድረኩ የራሷን ብሔራዊ አጀንዳ በጥምረቱ የጋራ አቋም እንዲያገኝ ማድረግ መቻሏ ዋናው የዲፕሎማሲ ውጤት ሆኗል። ይህን የዲፕሎማሲ አቅጣጫ በመቅረጽና በመምራት የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሚና ወሳኝ ነው። ኢትዮጵያ የብሪክስ ቡድንን ለመቀላቀል ፍላጎቷን በመግለጽ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ቀጥተኛ እና ታሪካዊ የዲፕሎማሲ መሪነት በነሐሴ 2015 ዓ.ም በደቡብ አፍሪካ በነበረው 15ተኛው የብሪክስ ጉባዔ ላይ ጥያቄዋ ተቀባይነትን አግኝቶ፣ በጥር 2016 ዓ.ም በይፋ መቀላቀሏ ይታወሳል፡፡ አሁን ላይ ከ11 የብሪክስ አባል ሀገራት ውስጥ አንዷ ሆና በዚህ ማዕቀፍ ውስጥ የራሷን ጉልህ ሚና እየተጫወተች ትገኛለች። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ በተለዋዋጭ የዓለም ሥርዓት ውስጥ ከአንድ የኃይል ጎራ ጋር ብቻ ሳትወግን ከተለያዩ ዓለም አቀፍ የትብብር መድረኮች ጋር በጋራ ጥቅም ላይ የተመሠረተ ግንኙነት መፍጠር እንዳለባት ባስቀመጡት አቅጣጫ መሰረት ዓለም አቀፍ የትብብርና የተፅዕኖ አድማሷን እያሰፋች ነው። የብሪክስ አባልነትም ከዚህ ስትራቴጂያዊ አቅጣጫ የመነጨ ነው። ኢትዮጵያ በብሪክስ ውስጥ መግባቷ ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካና የዲፕሎማሲ ጥቅም የሚያመጣውን አቅም በመለየት፣ አጀንዳውን ከኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ ብሔራዊ ጥቅም ጋር የተሳሰረ ስትራቴጂያዊ የዕይታ ለውጥ ውጤት ነው። ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል እንድትሆን ከዲፕሎማሲያዊ ጥረት በተጨማሪ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከቻይና፣ ከሩሲያ ከሕንድና ከሌሎች የብሪክስ አባል ሀገራት መሪዎች ጋር ባደረጉት ከፍተኛ የመሪዎች ዲፕሎማሲና ኢትዮጵያ ለዓለም ያበረከተችውን ታሪካዊ ሚና በቀጥታ ማስረዳታቸው ወሳኝ ሚና ተጫውቷል። ኢትዮጵያ በብሪክስ ያላት የነቃ ተሳትፎና የድል የጉዞ አሁንም ቀጥሏል። ከመስከረም 2 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ በህንድ በተካሄደው 18ኛው የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ አጀንዳዎቿን አሰምታለች። ብሔራዊ መሻቷን ገልጻለች። ድሎችን ተቀዳጅታለች። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በጉባኤው ባደረጉት ንግግር ለችግሮች የማይበገር ፅኑ ሥርዓት እየገነባች መሆኗን አስረድተዋል። ኢትዮጵያ በምግብ ሉዓላዊነት በስንዴ ምርት ያስመዘገበችውን ስኬት፣ በጤና፣ በዲጂታል ሽግግርና በሰው ሰራሽ አስተውሎት ያላትን አቅም በማሳደግ ራሷን የመቻልና ለወደፊት የመዘጋጀት አቅሟን እያጠናከረች መሆኗን ጠቁመዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ18ኛው የብሪክስ ጉባኤ የኢትዮጵያን የባሕር በር ጉዳይ እያደገ ካለው ገዙፍ ኢኮኖሚዋና የህዝቧ ፍላጎት አኳያ አጣዳፊ ምላሽ የሚሻ ስትራቴጂያዊ የብሔራዊ ጥቅም አጀንዳ መሆኑን በግልጽ አቅርበዋል። ይህ ኢትዮጵያ የራሷን ወሳኝ ብሔራዊ ጥያቄዎች በምትሳተፍባቸው ዓለም አቀፍ መድረኮች ሁሉ በተቀናጀ መልኩ ለማስገንዘብና ምላሽ እንዲያገኙ የምትከተለውን የዲፕሎማሲ አቅጣጫ ፍሬያማነት ያሳያል። የመሪዎቹ ጉባኤ 140 የጋራ አቋሞችን የያዘ የኒው ዴልሂ መግለጫ በማውጣት ሲጠናቀቅ ኢትዮጵያም በድል ተመልሳለች። በብሪክስ ኒው ዴልሂ የአቋም መግለጫ ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉን የንግድ ድርጅት ለመቀላቀል የምታደርገውን ጥረት ጥምረቱ በጽኑ እንደሚደግፍ በድጋሚ አረጋግጧል። በዓለም አቀፍ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ምክር ቤት ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረት ብቸኛ እጩ በመሆን ተጨማሪ መቀመጫ እንድታገኝ የሚደረገውን ጥረት በጽኑ እንደሚደግፍም አመላክቷል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉን የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ኮፕ 32 ለማዘጋጀት የጀመረችውን ተነሳሽነትና ዝግጅት እንደሚደግፉ የብሪክስ አባል ሀገራት መሪዎች በጋራ መግለጫቸው አረጋግጠዋል። በነገራችን ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በህነዱ የብሪክስ ጉባኤ ከአባልና አጋር ሀገራት መሪዎች ጋር በሁለትዮሽ የሀገራቱ ትብብር ዙሪያ ፍሬያማ ውይይቶችን ያካሄዱ ሲሆን፤ በንግድና ኢንቨስትመንት፣ በመከላከያ መስኮችና በዲጂታላይዜሽን ዙሪያ ሊኖሩ ስለሚችሉ ትብብሮች በጥልቀት መወያየታቸው ሌላኛው ስኬት ነው። የብሪክስ አባልነት ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዕድልም ነው። በተያያዘም የብሪክስ አባል በመሆኗ አሁን ላይ ተሰሚነቷ ከማደጉም በላይ በፋይናንስ፣ ኢንቨስትመንት እና መሰል የዕድገት መሰረተ ልማት ትብብሮች ላይ አማራጮችን አበርክቶላታል። ለዚህም ኢትዮጵያ የኒው ዴቨሎፕመንት ባንክን በአባልነት መቀላቀሏ ለሀገራዊ የልማት ፋይናንስ፣ ለመሠረተ ልማት ድጋፍ እና ለማክሮ-ኢኮኖሚ መረጋጋት አማራጭ የገንዘብ ምንጮችን ለማግኘት የሚያስችላትና ከደቡብ ደቡብ የፋይናንስ ሥርዓቶች ጋር የሚኖራትን ትስስር የሚያጠናክር ነው። ኢትዮጵያውያን ወጣቶችም በተለያዩ የብሪክስ የወጣቶች ማዕቀፍ ውስጥ በስራ ፈጠራ፣ በጤና፣ በትምህርት፣ በአካባቢ ጥበቃ፣ ሳይንስ እና መሰል መስኮች ላይ በንቃት እየተሳተፉ የሚገኝ ሲሆን፣ እየተፈጠሩ በሚገኙ የኢንቨስትመንት እድሎችም በርካታ የስራ እድሎች እየተፈጠረለቸው ይገኛል፡፡ በተጨማሪም ከአባል እና አጋር ሀገራቱ ወጣቶች ጋር ትስስር የመፍጠርና ልምድ ልውውጥ የማድረግ ዕድሎችን አስገኝቶላቸዋል፡፡ ኢትዮጵያ የባንኩ የአፍሪካ ቢሮ በአዲስ አበባ እንዲቋቋም ያላትን ዝግጁነት መግለጿም የብሪክስን አባልነት ወደ ተጨባጭ የኢኮኖሚ ትስስር ለመቀየር ያላትን ፍላጎት ያሳያል። የኢትዮጵያ የብሪክስ አባልነት ስኬታማ ጉዞ በዓለም አቀፍ ለውጥ መካከል በተለያዩ የትብብር መድረኮች በመሳተፍ ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስገኘት በትጋትና በተፅዕኖ ፈጣሪነት እየሰራች መሆኗን ያሳያል። ብሪክስ የኢትዮጵያ ጥያቄዎች የሚሰሙበት፣ አጋርነቶችን የምትገነባበት፣ ብሔራዊ ጥቅምን በማስከበር ዓለም አቀፍ ተፅዕኖ የምትፈጥርበት፣ አፍሪካን በመወከል አጀንዳዎቿን የምታራምድበት መድረክም ሆኗል።
የኢጋድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባውን ዛሬ ያካሂዳል
Sep 15, 2026 838
አዲስ አበባ፤ መስከረም 5/2019 (ኢዜአ)፦ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የሚኒስትሮች ምክር ቤት 74ኛው አስቸኳይ ስብሰባውን ዛሬ በጅቡቲ ያደርጋል። በስብሰባው ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እና የኢጋድ አባል ሀገራት ተወካዮች ይሳተፋሉ። በስብሰባው አባል ሀገራት በቀጣናው ያለውን የጸጥታና የደህንነት ሁኔታ እና እየተከናወኑ ያሉ ቀጣናዊ ጥረቶችን በመገምገም ለሰላም፣ መረጋጋትና ትብብር ያላቸውን የጋራ አቋም እንዲያጠናክሩ መልካም አጋጣሚ እንደሚፈጥር ኢዜአ ከኢጋድ ሴክሬተሪያት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። በተጨማሪም ምክር ቤቱ የድርጅቱን ተልዕኮ እና በቀጣናው ቅድሚያ በሚሰጣቸው ጉዳዮች ላይ የሚያደርገውን ድጋፍ እና የኢጋድ ስምምነትን (IGAD Treaty) ተፈጻሚነት ማጠናከርን ጨምሮ በዋና ዋና ተቋማዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራል። ስብሰባው የኢጋድ አባል ሀገራት በቀጣናው የሚገኙ ተግዳሮቶችን በጋራ ለመቅረፍ እንዲሁም ለሕዝቦቻቸው ሰላም፣ መረጋጋትና ብልጽግናን ለማረጋገጥ ያላቸውን ጽኑ ቁርጠኝነት የሚያረጋግጡበት እንደሆነም ተገልጿል። የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከኢጋድ ቁልፍ የፖሊሲ አደረጃጀቶች መካከል አንዱ ሲሆን፣ የድርጅቱን ሥራዎች በመምራትና በአባል ሀገራት መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር ረገድ ጉልህ ሚና የሚጫወት ነው።
በማእከላዊ ጎንደር ዞን የሰላምን አማራጭ የተቀበሉ የቀድሞ ታጣቂዎች የልማት አርበኛና የሰላም አምባሳደር ሆነው እየሰሩ ነው
Sep 14, 2026 989
ጎንደር፤ መስከረም 4/2019 (ኢዜአ)፡- በማእከላዊ ጎንደር ዞን የመንግስትን የሰላምን አማራጭ የተቀበሉ የቀድሞ ታጣቂዎች የልማት አርበኛና የሰላም አምባሳደር ሆነው እየሰሩ መሆኑን የዞኑ አስተዳደር ገለጸ። በአማራ ክልል የማዕከላዊ ጎንደር ዞን "አርቆ ማየት፣ አልቆ መሥራት" በሚል መሪ ቃል ያለፈው በጀት ዓመት አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል። በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አወቀ አስፈሬ፤ በበጀት ዓመቱ በተለይም በሰላምና ፀጥታ ዙሪያ ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ በፀጥታ አካላት የተከናወኑ ተግባራት ውጤት አምጥተዋል ብለዋል። በተሳሳተ መንገድ ጫካ ገብተው የነበሩ ታጣቂዎች የሰላምን አማራጭ ተቀብለው እንዲመጡ መደረጉን አንስተው በርካቶች የተሃድሶ ስልጠና ወስደው ህብረተሰቡን በመቀላቀል የልማት አርበኛና የሰላም አምባሳደር ሆነው እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል። የቀድሞ ታጣቂዎቹ በተለያዩ የልማት ስራዎች ላይ በመሰማራት የራሳቸውንና የቤተሰባቸውን ህይወት ለመለወጥ ብሎም የበደሉትን ሕዝብ ለመካስ እየሰሩ ይገኛሉ ብለዋል። በአስተዳደሩ በኩል አስፈላጊው እገዛ እየተደረገ መሆኑን አንስተው ሌሎችም ጫካ የሚገኙ ታጣቂዎች የጥፋትን መንገድ ትተው የሰላምን አማራጭ በመቀበል ህዝባቸውን እንዲቀላቀሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። በዞኑ ከሰላምና ፀጥታ ባሻገር በግብርና፣ በኢንዱስትሪ በማህበራዊ አገልግሎት እንዲሁም በመሰረተ ልማት ግንባታ ዙሪያ አበረታች ውጤቶች መታየታቸውን ገልጸዋል። በዞኑ 22 ትምህርት ቤቶችን በመገንባት ለአዲሱ የትምህርት ዘመን ለአገልግሎት ዝግጁ መደረጋቸውን ጠቁመው፤ በግንባታ ላይ የሚገኙ 44 ትምህርት ቤቶችን ለማጠናቀቅም በትጋት እየተሠራ ይገኛል ብለዋል። በብልፅግና ፓርቲ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፋሲል ሰንደቁ፤ ባለፈው በጀት ዓመት 7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ በስኬት ማጠናቀቅ መቻሉ ትልቅ ስኬት መሆኑን ተናግረዋል። የማዕከላዊ ጎንደር ዞን የሴቶችና ሕፃናት ማኅበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ቀኑ ቢያድጎ በበኩላቸው፤ የሴቶችን፣ ወጣቶችንና የአካል ጉዳተኞችን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት ተከናውነዋል ነው ያሉት። በ2019 በጀት ዓመትም ማኅበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የኢኮኖሚና ማኅበራዊ የልማት ሥራዎችን ለማከናወን መታቀዱን አስረድተዋል። ለተከታታይ ሁለት ቀናት በሚካሄደው የውይይት መድረክ የዞን፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደሮች አመራሮች በመሳተፍ ላይ ናቸው።
በሪፎርም ሥራዎች የተመዘገቡ ስኬቶች ኢትዮጵያን በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ሁለንተናዊ ማንሠራራት ማሸጋገር አስችለዋል
Sep 14, 2026 1042
አዲስ አበባ፤ መስከረም 4/2019 (ኢዜአ)፡- ባለፉት ዓመታት በሪፎርም ሥራዎች የተመዘገቡ ስኬቶች ኢትዮጵያን በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ሁለንተናዊ ማንሠራራት ማሸጋገር ያስቻሉ መሆናቸውን የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ገለጹ። የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት "በማንሠራራት ወደ ልዕልና" በሚል የፓናል ውይይት መድረክ አካሂዷል። በፓናል ውይይቱ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እውነቴ አለነ፣ የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ አዝመራው አንደሞ፣ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ኃይማኖት ዘለቀ፣ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ፣ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሰይፈ ደርቤ ተገኝተዋል። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እውነቴ አለነ በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት 2018 ዓ.ም የሀገሪቱ የማንሠራራት አቅም በተጨባጭ የታየበትና ፈተናዎች ወደ ዕድል እና ስኬት የተቀየሩበት ዓመት ነበር። የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ መጠናቀቁ ለሀገሪቱም ሆነ ለአፍሪካ ትልቅ አብነት መሆኑን ገልጸዋል። በበጀት ዓመቱ በየዘርፉ የተመዘገቡ አመርቂ ውጤቶች ኢትዮጵያውያን የጽናት እና የአይበገሬነት ተምሳሌት መሆናቸውን በተግባር ያስመሰከሩበት እንደነበርም አክለዋል። ሀገራዊ የምክክር ጉባኤው በስኬት መጠናቀቁም ትውልዱ በታሪክ ሲዘክረው የሚኖር ድል መሆኑን አብራርተዋል። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አዝመራው አንደሞ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያውያን በነፃነት ሀሳብ ከማመንጨት እስከ ማደራጀት፣ ማቀናጀትና ለሀገር የሚጠቅሙ ምክረ-ሀሳቦችን ለማመንጨት የሄዱበት ርቀት የተዋጣ ሀገራዊ ምክክር እንዲካሄድ አስችሏል። ሀገራዊ የምክክር ጉባኤው የማያግባቡ ጉዳዮችን በምክክር የመፍታት ባህልና ልምምድ እንዲጎለብት መሠረት መጣሉን አብራርተዋል። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ኃይማኖት ዘለቀ፣ ባለፉት ስምንት ዓመታት በመገናኛ ብዙኃን ዘርፍ ስኬታማ የሪፎርም ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል። አዲሱ የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ከመቆጣጠር ይልቅ ሚዲያዎችን የሚደግፍ፣ የሚከታተልና አቅም የሚገነባ ተቋም እንዲሆን ማስቻሉንም ጨምረው አብራርተዋል። የመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በተለይ የመገናኛ ብዙኃንን አቅም በመደገፍ ረገድ ውጤታማ ሥራ እያከናወነ መሆኑን አንስተዋል። በአሁኑ ወቅትም አዲስ የልህቀት ማዕከል በማቋቋም ጭምር በተለይ የባለሙያዎችን የዘርፍ ጋዜጠኝነት አቅም ለማዳበር እየሠራ ስለመሆኑም ተናግረዋል። በዚህም የመቆጣጠርና የመደገፍ ሥራን ሚዛን አስጠብቆ በመሄድ ረገድ የተሻለ ሥራ መከናወኑን ጠቅሰው፤ ይህም መገናኛ ብዙኃን ብሔራዊ ጥቅምን አክብረው እንዲሠሩ በማድረግ ረገድ መሻሻሎች እንዲመዘገቡ ማድረጉን ጠቅሰዋል። የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ፤ የሀገሪቱን የማንሠራራት ሥራዎችን ወደ ላቀ ደረጃና ልዕልና ለማሸጋገር ሁለት መሠረታዊ ተግባራት እንደሚከናወኑ አንስተዋል። የመጀመሪያው ኢትዮጵያ የገባችውን ቃል የምትፈጽም ሀገር መሆኗን የሚያሳይ አወንታዊ የሀገር ምስል (Brand) መገንባት መሆኑን ጠቁመው፤ ሁለተኛው ደግሞ ዜጎች በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የሚሰባሰቡበትንና ቀጣይነት ያለው ስኬት መሠረት የሚጥል የጋራ ሀገራዊ ትርክት መፍጠር እንደሆነ ገልጸዋል። ይህን በማሳካት ረገድ ደግሞ የመገናኛ ብዙኃንና የኮሙኒኬሽን ተቋማት ትልቅ ሚና እንዳላቸው አውስተዋል። ከዚህ አኳያ የመገናኛ ብዙኃን ዲጂታል ሚዲያን ታሳቢ ባደረገ መልኩ አሠራራቸውን በመቀየር ሕዝብን ለሀገራዊ ራዕይ ማሰባሰብ ላይ በቀጣይነት ሥራት እንደሚጠበቅባቸውም አስገንዝበዋል።
18ተኛው የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ የሁለተኛ ቀናት ቆይታ
Sep 14, 2026 943
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ልዑካቸው ከመስከረም 2 /2019ዓ.ም ጀምሮ በተካሔደው 18ተኛው የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ ላይ መሳተፋቸው ይታወሳል፤ መስከረም 3 ቀን፣ 2019 ዓ.ም የጉባዔው ሁለተኛ ቀን ‘‘ጽናትን፣ ፈጠራን፣ ትብብርን እና ዘላቂነትን መገንባት’’ በሚል መሪ ቃል የብሪክስ አባል እና አጋር ሀገራት መሪዎች እንዲሁም የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች በተሳተፉበት የተካሔደ ሲሆን፣ ጥምረቱ 140 የጋራ አቋሞችን የያዘ (የኒው ዴልሂ መግለጫ) በማውጣትም የመሪዎቹ ጉባኤ ተጠናቋል። የብሪክስ ኒው ዴልሂ የአቋም መግለጫ የዓለም አቀፍ አስተዳደር ማሻሻያ፣ ዓለም አቀፍ እና ቀጣናዊ ሰላም፣ ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገት እንዲሁም የህዝብ ለህዝብ ትሥሥርን ያካተቱ ዐበይት ጉዳዮች ላይ የአባል ሀገራቱን የጋራ አቋም ያንጸባረቀ ሲሆን ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉን የንግድ ድርጅት ለመቀላቀል የምታደርገውን ጥረት ጥምረቱ በጽኑ እንደሚደግፍ በድጋሚ አረጋግጧል፤ በዓለም አቀፍ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ምክር ቤት ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረት ብቸኛ እጩ በመሆን ተጨማሪ መቀመጫ እንድታገኝ የሚደረገውን ጥረት በጽኑ እንደሚደግፍም አመላክቷል። በተጨማሪም ሀገሪቱ የዓለም አቀፉን የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ኮፕ 32 ለማዘጋጀት የጀመረችውን ተነሳሽነትና ዝግጅት እንደሚደግፉ በጋራ መግለጫቸው አረጋግጠዋል። ጥምረቱ 19ኛውን የብሪክስ ጉባኤ በቻይና አስተባባሪነት እንዲዘጋጅም በጋራ አጽድቋል። ከመሪዎቹ ጉባኤ ጎን ለጎን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከአባልና አጋር ሀገራት መሪዎች ጋር በሁለትዮሽ የሀገራቱ ትብብር ዙሪያ ፍሬያማ ውይይቶችን ያካሄዱ ሲሆን፤ በንግድና ኢንቨስትመንት፣ በመከላከያ መስኮች ትብብር፣ በዲጂታላይዜሽን ዙሪያ ሊኖሩ ስለሚችሉ ትብብሮች በጥልቀት ተወያይተዋል። በድኅረ ጉባኤ ለመሪዎች በተደረገው የእራት ግብዣ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከተለያዩ የብሪክስ አባል እና አጋር ሀገራት መሪዎች ጋር የታደሙ ሲሆን፤ የሁለት ቀናት የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤን አጠናቅቀው ተመልሰዋል። ለበለጠ ወቅታዊ መረጃ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ማኅበራዊ የሚድያ ገጾች ይከታተሉ:- ድኅረ ገፅ: https://pmo.gov.et/ ፌስቡክ: https://web.facebook.com/PMOEthiopia ኤክስ(ትዊተር): https://x.com/PMEthiopia ዩትዩብ: https://youtube.com/@officeoftheprimeminister-e1878... #PMOEthiopia

ማህበራዊ
በትምህርት ቤቶች እና በወላጆቻችን በተደረገልን ድጋፍና ክትትል ስኬታማ ሆነናል -ተማሪዎች
Sep 17, 2026 9
ወልድያ፣ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ):- በትምህርት ቤቶች እና በወላጆቻችን የተደረገልን ድጋፍ ስኬታማ በመሆን ትምህርታችንን ለመቀጠል አስችሎናል ሲሉ የሰሜን ወሎ ዞን ተማሪዎች ገለጹ። በሰሜን ወሎ ዞን በተጠናቀቀው የትምህርት ዘመን በመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተናዎች ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች የእውቅናና ሽልማት መርሃ-ግብር አካሂዷል። በሰሜን ወሎ ዞን የ12ኛ ክፍልና የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ለኢዜአ እንዳሉት፤ በትምህርት ቤቶችና በወላጆች የተደረገልን የቅርብ ክትትልና ድጋፍ ጥሩ ውጤት አምጥተን ለቀጣይ ትምህርት እርከን እንድንዘጋጅ አግዞናል። ከዚህ ውስጥም በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና 567 ነጥብ 44 ያመጣው የቆቦ ከተማ «ዕውቀት ጮራ» ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ መንገሻ ሞላ፤ በወልድያ ዩኒቨርሲቲ በተመቻቸው የአዳሪ ትምህርት ቤት እድል ተጠቃሚ መሆኑን ነው የሚናገረው። በዚሁ ወቅት በተለይ በመምህራን በተደረገለት ድጋፍ ጠንክሮ በመስራት ለከፍተኛ ትምህርት የሚያበቃውን ውጤት ለማስመዝገብ እንዳስቻለው ነው የሚናገረው። በቀጣይም የሕግ ትምህርት በመከታተል ያስተማረውን ማህበረሰብ የማገልገል ህልም እንዳለው ነው የገለፀው። በተመሳሳይ በዚሁ ትምህርት ቤት በ12ኛ ክፍል ፈተና 544 ነጥብ 67 በማምጣት ከፍተኛ ውጤት ያመጣው ተማሪ ኃየሎም አስረስ፤ በወላጆች፣ በትምህርት ማህበረሰቡና በመንግስት በተደረገለት ድጋፍ ጥሩ ውጤት ላመጣ ችያለሁ ነው የሚለው። በሌላ በኩል ተማሪ ብሩህ ሄኖክ በ6ኛ ክፍል የዞን ፈተና 97 ነጥብ 5 ያስመዘገበ ሲሆን ተማሪ ሳምራዊት ሀብተየስ ደግሞ 83 ነጥብ 5 ውጤት ማስመዝገባቸውን ይገልፃሉ። ለዚህም የመምህራን እንዲሁም የቤተሰብ ድጋፍ ለውጤቱ ትልቅ ድርሻ እንዳለው ገልፀው የተሻለ ተስፋ ሰንቀን ትምህርታችንን እንድንቀጥል አድርጎናል ነው የሚሉት። የሰሜን ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ ወንድወሰን አክሊሉ እንደገለጹት፤ በዞኑ በ2018 ትምህርት ዘመን 825 ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት አምጥተዋል። ውጤቱ ባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከተመዘገበው ጋር ሲነፃፀር የ7 በመቶ እድገት እንዳለው ነው የገለጹት። ለውጤቱ መመዝገብም የትምህርት ቤቶች ልዩ ድጋፍ፣ የቤተ-መጽሐፍትና የኮምፒውተር ግብአቶች መሟላት አስተዋጽኦ ማድረጉን ነው የጠቀሱት። በአዲሱ የ2019 የትምህርት ዘመንም የኦንላይን ፈተና ዝግጅቶችን ጨምሮ የማጠናከሪያ ሥራዎችም በተሻለ መልኩ እንደሚቀጥሉ ነው ያረጋገጡት።
ከ46 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው 12 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ ላይ የማታለል ወንጀል ፈጽሞ ከሀገር የተሰወረው ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ዋለ
Sep 16, 2026 471
አዲስ አበባ ፤መስከረም 6/2019 (ኢዜአ)፦ከ46 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸውን 12 የBYD Seagull ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በመሸጥ ገንዘቡን ለተበዳይ ሳያስረክብ ከባድ የማታለል ወንጀል በመፈጸም ከሀገር የተሰወረው ግለሰብ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ። ተጠርጣሪው ከኢትዮጵያ ወጥቶ በታይላንድ፣ በሲንጋፖር፣ በፊሊፒንስና በኢንዶኔዥያ ሀገራት ከሕግ ተጠያቂነት ለማምለጥ ሲዘዋወር ከቆየ በኋላ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከኢንተርፖል ጋር በመተባበር በግለሰቡ ላይ ዓለም አቀፍ የቀይ ማስታወቂያ (Red Notice) እንዲወጣበት በማድረግ በኢንዶኔዥያ ኢንተርፖል መስከረም 3 ቀን 2019 ዓ.ም በኢንዶኔዥያ ሀገር በቁጥጥር ሥር ውሎ መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም ለኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ተላልፎ ተሰጥቷል። ሰልማን መሀመድ በተጠረጠሪው ወንጀል ፖሊስ የምርመራ መዝገብ አደራጅቶ ያጠናቀቀ ሲሆን ከዚህ ወንጀል በተጨማሪም በሌሎች ሁለት ከባድ የማታለል ወንጀሎች ተጠርጥሮ ተጨማሪ ምርመራ እየተጣራበት መሆኑንም ገልጿል። የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በተለያዩ የሽብር ወንጀሎችና በሌሎች ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች የሚፈለጉ ወንጀለኞችን በቁጥጥር ሥር አውሎ ሕግ ፊት ለማቅረብ ከሀገራት የፖሊስ ተቋማትና ከኢንተርፖል ጋር በትብብር እየሠራ ሲሆን ይህንንም አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል። ለዚህ ኦፕሬሽን መሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ለአዲስ አበባ ፖሊስ፣ ለኢንዶኔዥያ ፖሊስ እና ለዓለም አቀፉ የፖሊስ ኅብረት ድርጅት (ኢንተርፖል) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ምስጋና አቅርቧል።
በአፋር ክልል የቅድመ-መደበኛ ትምህርት ቤቶችን ተደራሽ ለማድረግ ከአጋር አካላት ጋር የሚደረግ የቅንጅት ስራ ይጠናከራል
Sep 16, 2026 355
ሰመራ፣መስከረም 6/2019 (ኢዜአ) ፡- በአፋር ክልል የቅድመ-መደበኛ ትምህርት ቤቶችን ተደራሽ ለማድረግ ከአጋር አካላት ጋር የሚደረገው የቅንጅት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ። የክልሉ ትምህርት ቢሮ በአይሳኢታ ከተማ አስተዳደር ኘላን ኢንተርናሸናል በተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት ወጪ የተገነባን የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት አስመርቆ ወደ ስራ አስገብቷል። በምረቃ ሰነ ሰርዓቱ ላይ የተገኙት የአፋር ክልል ትምህርት ቢሮ ኀላፊ ሙሳ አደም እንደተናገሩት የአርብቶ አደሩን የትምህርት ተደራሸነትና ጥራት ለማረጋገጥ ባለ ድርሻ አካላትን ባሳተፈ መልኩ እየተሰራ ነው። በዚህም በክልሉ 35 ቅድመ መደበኛና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እየተገነቡ መሆኑን ተናግረዋል። በተለይም የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች መስፋፋት ሕጻናት ለመደበኛው ትምህርት የተለያዩ ክህሎቶችን እንዲያዳብሩና ተነሳሽነታቸው እንዲጨምር የሚያደርግ መሆኑን አብራርተዋል። በዚህም ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት የቅድመ-መደበኛ ትምህርት ቤቶችን ተደራሽነት የማስፋፋት ስራ እየተካሄደ መሆኑን ጠቁመው ዛሬ የተመረቀው ትምህርት ቤትም የዚሁ አካል መሆኑን አስታውቀዋል ። የአይሳኢታ ከተማ አስተዳደር ተወካይ አቶ አሚን ያሲን በበኩላቸው የትምህርት ቤቱ ግንባታ የህፃናትን በቅርበት የመማር እድል ያሰፋል ብለዋል። ከተማ አስተዳደሩ በዘርፉ ከአጋር አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል ። በኘላን ኢንተርናሽናል የአፋር ቅርንጫፍ ተወካይ አቶ መሐመድ አህመድ በበኩላቸው እንደተናገሩት ድርጅቱ ለትምህርት ዘርፉ መሻሻል በግብአት አቅርቦትና በሌሎች አገዛ እያደረገ ነው ብለዋል። በአይሳኢታ ከተማ አስተዳደር ለሚገኘው ሲንብሌ ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ግንባታ 10 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር ወጪ መደረጉን አስታውቀዋል። በምረቃ ሰነ ሰርዓቱ ላይ የከተማ አስተዳደሩ የስራ ኀላፊዎችና ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
ጥራት ያለው የህክምና አገልግሎት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል
Sep 16, 2026 142
ደሴ፤ መስከረም 6/2019 (ኢዜአ)፡-የጤና ተቋማትን ደረጃ በማሻሻልና አሰራርን በቴክኖሎጂ በመደገፍ ጥራት ያለው የህክምና አገልግሎትን ተደራሽ የማድረግ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር ገለጸ። የዞኑ ጤና መምሪያ በደሴ ከተማ ለህብረተሰቡ የተሻለ የህክምና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ያለመ መድረክ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር እያካሄደ ይገኛል። የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ መኮነን በመድረኩ እንደገለጹት፤ የጤና ተደራሽነትን በማስፋትና የተቀላጠፈ የህክምና አገልግሎት በመስጠት ጤንነቱ የተጠበቀ አምራች ዜጋ ለመፍጠር እየተሰራ ነው። ለተገልጋዩ ህብረተሰብ ጥራቱን የጠበቀ የሕክምና አገልግሎት ለመስጠት የጤና ተቋማትን ደረጃ ማሻሻል ቁልፍ ተግባር ተደርጎ እየተተገበረ መሆኑንም ተናግረዋል። ለዚህም ባለፉት ዓመታት በዞኑ የጤና ተቋማትን ተደራሽነት በማስፋት፣ ደረጃቸውን በማሻሻልና የህክምና ግብዓቶችን በማሟላት ለዜጎች ጥራት ያለው የህክምና አገልግሎት ለመስጠት በተደረገው ጥረት ውጤት ተመዝግቧል። በቀጣይም አገልግሎቱን ይበልጥ በማዘመንና ዲጂታል በማድረግ የተገኘውን ውጤት አጠናክሮ ለማስቀጠል እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል። የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ጌታቸው በለጠ በበኩላቸው፤ በሽታዎችን ቀድሞ በመከላከልና አክሞ በማዳን ላይ ያተኮረውን የጤና ፖሊሲ ተግባራዊ መደረጉ ጥራት ያለው የሕክምና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ አስችሏል ብለዋል። በተለይም እናቶች በጤና ተቋማት በሰለጠኑ ባለሙያዎች ታግዘው እንዲወልዱ በማድረግ፣ በወሊድ ወቅት የሚያጋጥመውን የሞት ምጣኔ ለመቀነስ መቻሉን ገልጸዋል። በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በግንባታ ላይ ከነበሩ 80 ጤና ተቋማት ውስጥ ግማሽ ያህሉ ተጠናቀው አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውም አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ ሰፊ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው ብለዋል። "አገልግሎቱን በቴክኖሎጂ ጭምር በማስደገፍና የውስጥ ግብዓት በማሟላት ለህብረተሰቡ ጥራት ያለው የህክምና አገልግሎት እየተሰጠ ነው" ያሉት ደግሞ የወግዲ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ አቶ ሁሴን ሙሉጌታ ናቸው። በአዲሱ በጀት ዓመትም የህብረተሰቡን ጤንነት በመጠበቅ አምራች ዜጋ ለመፍጠር የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው የጠቀሱት። ለሁለት ቀናት በሚቆየው በዚህ መድረክ የዞን፣ የወረዳ፣ የከተማ አስተዳደር፣ የሆስፒታልና የጤና ተቋማት አመራሮች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ኢኮኖሚ
የቱሪዝም ትንሳኤን ያበሰረው የመደመር እሳቤ
Sep 16, 2026 402
ኢትዮጵያ አስደማሚ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ የቱሪዝም ሀብቶች ባለቤት ናት ። የጎብኚዎችን ቀልብ የሚስቡ ደጋግመው ቢያዩዋቸው ፣ ቢታደሙባቸው የማይሰለቹ ተጠንተውም የማያልቁ ፀጋዎች ቢኖሯትም ለዘመናት በወጉ ሳትገልጣቸው የሚጠበቀውን ያክልም ሳይጎበኙ ሳይተዋወቁም ቆይተዋል። ይህን ባለማድረጓ ደግሞ ከዕልፍ የቱሪዝም ጸዋጋዎቿ ሳትቋደስ ዘመናትን ተሻግራለች። “በታሪክም ሆነ በተፈጥሮ ጸጋዎች ከኛ ጋር ሊወዳደሩ የማይችሉ ብዙ ሀገራት ከኢንዱስትሪው ብዙ አትርፈዋል። እኛ ግን እንቁዎቻችንን ደብቀን ታሪካችንን አቧራ አልብሰን ለዘመናት ቆይተናል።” የመደመር መንግሥት መጽሐፍ ገጽ 259 ዛሬ ግን ይህ ታሪክ እየተቀየረ ነው። ከመደመር መንግሥት አምስት ወሳኝ የኢኮኖሚ ምሰሶዎች አንዱ በሆነው ቱሪዝም ቅርሶችንና ወሳኝ ፀጋዎችን ከቁስ ወደ ቁርስ እየለወጠ፣ ኢትዮጵያን እየገለጠ እንዲመጣ እየተደረገ ነው። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአራት ኪሎ ቤተመንግስት “ሀ” ተብሎ የተጀመረው አዳዲስ የቱሪስት መዳረሻ ልማት በገበታ ፕሮጀክቶች አማካኝነት ወደ ሁሉም የሃገራችን ክፍሎች ተዳርሷል። በኢትዮጵያ ትኩረት ተነፍጓቸው የነበሩት የሀገራችን የቱሪዝም ሀብቶች በመደመር መንግሥት ቅድሚያ ተሰጥቷቸው ትንሳኤያቸው ተበስሯል። ለዘመናት አቧራ ለብሰው የኖሩ ዕንቁ የቱሪዝም ሀብቶች አቧሯቸው እየተራገፈ ነው። ከዳሎል እስከ ስሜን ተራሮች ማራኪ ተፈጥሯዊ መስህቦች ይበልጥ ለዓለም እየተዋወቁ ነው። አዳዲስ ተፈጥሯዊ ፀጋዎችም በቱሪዝም ልማት ኢኒሼቲቮች የመገለጥና የመታወቅ ዕድል አግኝተዋል። የመደመር እሳቤ የምናብ ከፍታና የመፈጸም ልክ አንዱ ጉልህ ማሳያ የቱሪዝሙ ዘርፍ ፕሮጀክቶች ናቸው። ከነዚህ ኢኒሼቲቮችም መካከል አንዱ ከቤተ መንግስት እደሳት ጀምሮ አዲስ አበባን እንደ ስሟ አዲስ ያደረጋት የገበታ ለሸገር ፕሮጀክት ነው። የገበታ ለሸገር ፕሮጀክት የቱሪዝም አብዮትን በመቀስቀስ የአንድነት ፓርክን፣ እንጦጦና ወዳጅነት ፓርክና ሌሎች ተያያዥ ፕሮጀክቶችን ዕውን አድርጓል። ዛሬ ላይ አዲስ አበባን አዲስ መልክ አጎናጽፎ፤ የነተቡ ሰፈሮች ወደ ውብ መልኮች ተቀይረው የሚሊዮኖች ጎብኚዎች መዳረሻ ሆነዋል። ከገበታ ለሸገር በመቀጠል የኢትዮጵያን አዳዲስ መልኮች የገለጠው ኢኒሸቲቭ ደግሞ የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት ነው። ገበታ ለሀገር ከኦሮሚያ ክልል የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ወንጪን፣ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዳውሮና ኮንታን የሸፈነው ኮይሻን፣ከአማራ ክልል የጣናን ምዕራባዊ ዳርቻ የተንተራሰችውን ጎርጎራን ውብ አድርጓል። እነዚህ ፕሮጀክቶች የኢትዮጵያን አይነተ ብዙ ታሪክ፣ ተፈጥሮንና ባህል በመግለጥ ለኢትዮጵያ ተጨማሪ ሞገስና ድምቀት ሆነዋል። ከገበታ ለሀገር ቀጥሎ ገቢራዊ የተደረገው የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት አድማሱ በሶማሌ ክልል ሸበሌ ሪዞርትን፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የደንቢ ኢኮ ሎጅን፣ በአማራ ክልል የሐይቅ ሎጎ ሪዞርትን፣ በአፋር ክልል የኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ እንዲሁም የአርባምንጭ ኮንፈረንስ ሪዞርትን እውን አድርጓል። ከገበታ ለሸገር እስከ ገበታ ለትውልድ ፕሮጀክቶች ባሻገር የመደመር መንግስት ታሪካዊ ቅርሶችን የመጠበቅ፣ እሴት ጨምሮ የመግለጥ አኩሪ ስራዎችንም አከናውኗል። ለዚህ ደግሞ ከብሔራዊ ቤተ መንግስት ጀምሮ ጥንታዊ አብያተ መንግስታት፣ ታሪካዊ፣ ሃይማኖታዊና ባህላዊ ቅርሶች ተጠግነዋል። የባለፉት ጥቂት ዓመታት የቱሪዝም ዘርፍ ለውጦች የኢትዮጵያን ገጽታ ያስተዋወቁ፤ በየአካባቢው ተስፋና ልማትን የፈነጠቁ፣ ዘመን ተሻጋሪ ስራዎች ናቸው። እነዚህ ፕሮጀክቶች በኢትዮጵያ የዕድገትና የብልጽግና ታሪክ ውስጥ በደማቁ የሚጻፉ አንቀጾች ሆነው ለትውልድ የተኖሩ ዓሻራዎች ናቸው።
የኢትዮጵያና እስራኤል ትብብር ወደ ላቀ ምዕራፍ ተሸጋግሯል-አምባሳደር አብርሃም ንጉሴ (ዶ/ር)
Sep 16, 2026 356
አዲስ አበባ፤መስከረም 6/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያና እስራኤል ሁሉን አቀፍ ትብብር መጠናከር የሀገራቱን ግንኙነት ወደ ላቀ ምዕራፍ ማሸጋገሩን በእስራኤል የኢትዮጵያ አምባሳደር አብርሃም ንጉሴ (ዶ/ር) ገለጹ። አምባሳደሩ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤የሁለቱ አገራት ግንኙነት ጥልቅ ታሪካዊ መሠረት ያለው መሆኑን ገልጸዋል። ግንኙነቱ አሁን ላይ በመንግሥታት ትብብር፣በኢንቨስትመንት፣በቴክኖሎጂ እና በሰዎች አቅም ግንባታ ላይ የተመሠረተ ሁሉን አቀፍና ዘመናዊ አጋርነት ላይ መድረሱን አመልክተዋል። ኢትዮጵያ እና እስራኤል ከጥንት ጀምሮ የነበራቸው ልዩ ታሪካዊ ግንኙነት ዛሬ ለደረሰበት ጠንካራ የሁለትዮሽ አጋርነት እንዳበቃቸው ተናግረዋል። በአዲስ አበባ የሚገኘው የእስራኤል ኤምባሲ የሁለቱን አገራት የረጅም ጊዜ ግንኙነት ለማጠናከርና ለማስፋት በተለያዩ ዘርፎች በስፋት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን አስረድተዋል። የሁለቱ አገራት አበይት የትብብር መስኮች አንዱ የሆነው ግብርና፤ የእስራኤል ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ኩባንያዎችን በመገንባት ዘመናዊ የግብርና ቴክኖሎጂዎችንና ባለሙያዎችን ወደ ሀገር ውስጥ እንዲያስገቡ መልካም አጋጣሚን መፍጠሩን ነው ያነሱት። የእስራኤል ኩባንያዎች በፍራፍሬና በአትክልት ልማት ላይ የተሰማሩባቸውን በቢሾፍቱ አካባቢ የሚገኙ የግብርና ስራዎች በማሳያነት ጠቅሰዋል። በዘርፉ ያለው ትብብርና ኢንቨስትመንት ኢትዮጵያ አቮካዶን ጨምሮ የግብርና ምርቶቿን ወደ አውሮፓ እና እስያ ገበያዎች የምታቀርብበትን አቅም እንዲያድግ አስተዋጽኦ አድርጓል ብለዋል አምባሳደር አብርሃም። በተጨማሪም የኢትዮጵያ ማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ለውጭ ባለሀብቶች፣ እስራኤላውያንን ጨምሮ ምቹ ሁኔታዎችን እየፈጠረ መሆኑን አመልክተዋል። የውጭ ባለሀብቶችን በመሳብ ረገድ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው የገለጹት አምባሳደሩ፤ የተደረጉት ማሻሻያዎች ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ስራ ለመጀመር እና የኢንቨስትመንት ዕድሎችን ለመመልከት እያገዟቸው እንደሚገኙ ተናግረዋል። የማዕድን አቅምን ጨምሮ የኢትዮጵያ ተፈጥሮ ሀብቶች ተጨማሪ የእስራኤል ኢንቨስትመንቶችን መሳብ የሚያስችሉ መሆናቸውን ነው ያስረዱት። የእስራኤል ኩባንያዎች ወርቅን ጨምሮ በተለያዩ ማዕድናት ፍለጋና ማምረት ስራዎች ላይ ተሰማርተው እንደሚገኙ ጠቁመዋል። ጤና ሁለቱ አገራት ትብብራቸውን እያሰፉባቸው ካሉ ዘርፎች መካከል አንዱ መሆኑን የገለጹት አምባሳደሩ፤ የእስራኤል ሀኪሞች ከኢትዮጵያ የህክምና ባለሙያዎች ጋር በመቀናጀት የአቅም ግንባታን ጨምሮ በተለያዩ መርሃ ግብሮች ላይ በትብብር እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል። በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ መስኮች፣በተለይም በሳይበር ደህንነት ዙሪያ ያለውን ትብብር አምባሳደሩ አንስተዋል። እስራኤል የሳይበር ደህንነት ተግዳሮቶችን በመቅረፍ ረገድ ያከማቸችውን ልምድ ለኢትዮጵያ ለማካፈል እንደምትሻም ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገትን የሚያፋጥን የሕልውና ጥያቄ ነው
Sep 16, 2026 492
አዲስ አበባ፤ መስከረም 6/2019 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገትን የሚያፋጥን ጠንካራ መሰረት ያለው የሕልውና ጥያቄ መሆኑን የኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አብዱልበር ሸምሱ ገለጹ። የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነትን በሴራ ማጣት በትራንስፖርት፣ በሎጂስቲክስና በወደብ አገልግሎት የገቢና ወጪ ንግድ ሥርዓት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እያደረሰ ይገኛል። በየዓመቱም በቢሊዮን የሚቆጠር የውጭ ምንዛሬ እንድትከፍል በማስገደድ በአጠቃላይ የኢኮኖሚ ዕድገትና እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያስከተለ ነው። ይህም የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት የሀገርን ተፈጥሯዊ፣ መልክዓ ምድራዊ፣ ስትራቴጂካዊና ሕጋዊ የባሕር በር ባለቤትነት ለማስመለስ ያነሱትን ጥያቄ ምክንያታዊነት ያጎላዋል። ኢንጂነር አብዱልበር ሸምሱ ለኢዜአ እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ በባሕር ላይ የሎጂስቲክስና ትራንስፖርት እንቅስቃሴ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን የሚያጎለብት ጠንካራ አቅም የገነባች ሀገር ናት። በባሕር ላይ የንግድ መስመር፣ የሎጂስቲክስና ትራንስፖርት እንቅስቃሴም በትላልቅ መርከቦች፣ ብቁ የመርከብ ካፒቴኖችና በዳበረ መዋቅር የሚከናወኑ ተግባራት የኢትዮጵያን አቅም የሚያሳዩ ናቸው ብለዋል። የኢትዮጵያ የባሕር በር ማጣት የሚያስቆጭ ነው ያሉት ዋና ሥራ አስፈፃሚው፤ ይህም በባሕር ላይ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እንዳለው አንስተዋል። ኢትዮጵያ ለሺህ ዘመናት ስትጠቀምባቸው ከነበሩት የቀይ ባሕር ሉዓላዊ ወደቦቿ እንድትገለል የተፈጸመባት ታሪክ ይቅር የማይለው በደል በዘርፉ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያሳደረባት መሆኑን ገልጸዋል። የባሕር በር አለመኖሩም ኢትዮጵያን በወደብ ኪራይ፣ በሸቀጦች የወጪና ገቢ እንቅስቃሴ መዘገየት በመፍጠርና ቀጥተኛ ተፅዕኖ በማሳደር የኢኮኖሚ ዕድገትን እየጎተተ መሆኑን አስረድተዋል። የባሕር በር ባለቤትነትም በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ የወደብ አገልግሎት የሚያጋጥሙ ተፅዕኖዎችን በማስቀረትና የኢኮኖሚ ዕድገትን በማፋጠን ለዜጎች የሕይወት መሻሻል መሠረት መሆኑን አብራርተዋል። የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄም በወደብ አገልግሎት የሚያጋጥሙ የትራንዚት መጨናነቅን፣ የገቢና ወጪ ምርት መዘግየትንና የወደብ ኪራይን ለማስቀረት ጠንካራ የኢኮኖሚ መሠረት ያለው መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም የኢትዮጵያን ታሪካዊ፣ ሕጋዊ፣ መልክዓ ምድራዊና ተፈጥሯዊ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገትን የሚያፋጥን የህልውና ጉዳይ መሆኑን አስረድተዋል። የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ በሚደረገው ጥረትም ሁሉም ዜጋ በትብብርና በንቁ ተሳትፎ የድርሻውን መወጣት እንዳለበት አስገንዝበዋል።
በባሕርዳር ከተማ ከ61 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ ወደ ሥራ ተገብቷል
Sep 16, 2026 151
ባህር ዳር ፤መስከረም 6/2019 (ኢዜአ)፦በአዲሱ በጀት ዓመት ከ61 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር አቅዶ ወደ ሥራ መግባቱን የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ሥራና ክህሎት መምሪያ አስታወቀ። የመምሪያው ኃላፊ አቶ ዘመነ አሰፋ እንደገለጹት፤ ለወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠር አንዱ የልማት ቁልፍ ተግባር ተደርጎ እየተሠራበት ነው። በዚህም በበጀት ዓመቱ ከ61 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መጀመሩን ነው የገለጹት። የሥራ ዕድሉ በከተማ ግብርና፣ በኮንስትራክሽን፣ በእንጨትና ብረታ ብረት፣ በሌሎች ዕድገት ተኮር ዘርፎች እንዲሁም በውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ዘርፎች መሆኑን አስረድተዋል። የከተማ አስተዳደሩ ከአጋር ተቋማት ጋር በመተባበር ወደ ሥራ ለሚገቡ ወገኖች ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ብድር፣ ከ230 ሄክታር በላይ መሬት፣ 124 ሼዶችና 124 ኮንቴይነሮችን ማመቻቸቱን ነው የተናገሩት። በበጀት ዓመቱ 2 ሺህ 767 አዳዲስ ኢንተርፕራይዞችን በዶሮ፣ በወተት፣ በጨርቃ ጨርቅና ሌሎች ዘርፎች በማደራጀት ወደ ሥራ ለማስገባት መታቀዱንም ጠቁመዋል። የ"እናንዬ፣ አስማረችና ጓደኞቻቸው" የዓሣ ምርት ማኅበር ሥራ አስኪያጅ ወይዘሮ እናንዬ ታምሩ በበኩላቸው፤ ባለፈው ዓመት 70 አባላትን በማቀፍ በዓሣ ልማት ዘርፍ ተደራጅተው ሥራ መጀመራቸውን ተናግረዋል። ማኅበራቸው በቀን እስከ 20 ኪሎ ግራም ዓሣ በማዘጋጀትና ለገበያ በማቅረብ አባላቱን ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል። የ"አዲሴና ምሕረት" የዶሮ እርባታ ሽርክና ማኅበር ሥራ አስኪያጅ ወይዘሮ አዲሴ አብረሃም፤ በየዙሩ 1 ሺህ ጫጩቶችን በማስመጣትና በማሳደግ ለተጠቃሚዎች እያሰራጩ እንደሚገኙ ተናግረዋል። ዘርፉ አዋጭ በመሆኑ ሌሎች ወጣቶችም ተደራጅተው ወደ ሥራ በመግባት የራሳቸውንና የቤተሰባቸውን ኑሮ ለመለወጥ መሥራት እንዳለባቸው ገልጸዋል። የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ሥራና ክህሎት መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ከ55 ሺህ በላይ የሥራ ዕድሎችን በመፍጠር ከዕቅድ በላይ ስኬታማ አፈጻጸም ማስመዝገቡን መግለጹ ይታወሳል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት የወሰደችው ስትራቴጂካዊ እርምጃ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቷን በተግባር የሚያረጋግጥ ነው
Sep 16, 2026 700
አዲስ አበባ፤ መስከረም 6/2019 (ኢዜአ)፦የሰው ሰራሽ አስተውሎትና የቴክኖሎጂ ሽግግር የዓለምን ኢኮኖሚ በከፍተኛ ሁኔታ እየቀየረ ባለበት በዚህ ወቅት፣ ኢትዮጵያ ለዘርፉ የሰጠችው ከፍተኛ ትኩረትና ስትራቴጂካዊ እርምጃ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቷን የሚያረጋግጥ መሆኑን የምጣኔ ሀብት ባለሙያው አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ ገለጹ፡፡ ኢትዮጵያ ከምትከተላቸው ብዝሃ ኢኮኖሚ ዘርፎች መካከል አንዱ የሆነው የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ መስክ በተከናወኑ ሰፊ ሥራዎች በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ውስጥ ተጨባጭ ለውጦች እየተመዘገቡ ይገኛል። በዚህ የለውጥ ጉዞ ውስጥ ሀገሪቱ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ልማትና አጠቃቀም በአህጉሪቱ ቀዳሚ በመሆን ጠንካራ የመሪነት ሚና እየተወጣች ትገኛለች። ይህንን የቴክኖሎጂ አብዮት ከማፋጠን ባለፈ አህጉራዊ ተደራሽነቱን ለማስፋት በተከናወኑት ተጨባጭ ተግባራት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ህብረት የሰው ሰራሽ አስተውሎት እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ መሪ ሆነው መሾማቸው ይታወቃል። ይህም ኢትዮጵያ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና በፈጠራ ሥራዎች ያስመዘገበችውን ድል ከማሳየቱም በላይ፣ ቀጣይነት ያለው የቴክኖሎጂ ልማት እውን እንዲሆን አርዓያነት ያለው መሰረት ጥሏል። በዚህም ሀገሪቱ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ያላት አቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን በማረጋገጥ፣ ለአፍሪካ የዲጂታል ሉዓላዊነትና ብልጽግና ትልቅ ተስፋን ፈጥሯል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕንድ ኒው ዴልሂ በተካሄደው 18ኛው የብሪክስ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ዲጂታል መታወቂያን፣ የክፍያ ሥርዓቶችን እና የመረጃ ልውውጥን ያካተተ ዲጂታል የሕዝብ መሠረተ ልማት እየተገነባና የመረጃ ደህንነት ማዕቀፎች መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል። በተጨማሪም የቀጣዩ ትውልድ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ አብዛኛውን የሰው ልጅ የሚያገለግል፣ በርካታ ቋንቋዎችን የሚረዳ፣ ማኅበረሰቦችን የሚያካትትና ሰፊ እውቀትን ያቀፈ መሆን እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል። የምጣኔ ሀብት ባለሙያው አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፣ በአሁኑ ወቅት የዓለም አቀፍ ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በዋናነት በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ ነው። በተለይም ወጣቱ ትውልድ ሙሉ በሙሉ ወደ ዲጂታል አሰራር መሸጋገሩ የቴክኖሎጂ ሽግግሩ ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል። ከጥቂት ዓመታት በፊት በዲጂታል መንገድ ይከናወን የነበረው የገንዘብ ልውውጥ 10 በመቶ ብቻ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ላይ ግን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ጨምሮ አብዛኞቹ ባንኮች እስከ 90 በመቶ የሚሆነውን የገንዘብ እንቅስቃሴ በዲጂታል መንገድ እያከናወኑ መሆኑን በአብነት ጠቅሰዋል። ኢትዮጵያ የሰው ሰራሽ አስተውሎትን (AI) እንደ አንድ ዋነኛ የመወዳደሪያ አቅም እና ስትራቴጂ በመውሰድ በከፍተኛ ትኩረት እየሰራችበት እንደምትገኝ አንስተዋል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ደረጃ ለሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ትልቅ ትኩረት የሰጠች ሀገር መሆኗንም ተናግረዋል። በአትዮጵያ አብዛኛው የሕብረተሰብ ክፍል የቴክኖሎጂ ክህሎትን በቀላሉ መቅሰም የሚችል ወጣት የሰው ሀይል በመሆኑ፣ ኢትዮጵያን "የአፍሪካ ሲሊኮን ቫሊ" የማድረግ ትልቅ አቅም እንዳለውም ጠቁመዋል። በተለይም የ5 ሚሊዮን ኮደሮች የስልጠና ፕሮግራም ወጣቶች ወደ ሥራ ሲገቡ ለሀገሪቱ የቴክኖሎጂ መነቃቃት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክትም ተናግረዋል። በቀደመው የኢኮኖሚ አካሄድ ብቻ ውጤታማ መሆን የማይቻል በመሆኑ በቴክኖሎጂና በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ላይ በባለቤትነት መሥራት ለነገዋ ኢትዮጵያ ወሳኝ እንደሆነ አብራርተዋል።
አኩቴክ ዲያግኖስቲክ የህክምና ቱሪዝም ማዕከልነት ግብ ለማሳካት ተጨማሪ አቅም የሚፈጥር ነው
Sep 15, 2026 408
አዲስ አበባ፤ መስከረም 5/2019 (ኢዜአ)፦ አኩቴክ ዲያግኖስቲክ ሀገሪቱን የህክምና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የተያዘውን ግብ ለማሳካት ተጨማሪ አቅም የሚፈጥር መሆኑን የአኩቴክ ዲያግኖስቲክ ዋና ዳይሬክተር ሄኖክ ታደሰ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በቅርቡ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የሥራ እንቅስቃሴ መመልከታቸው ይታወሳል። በዚሁ ወቅት እንዳሉት፣ አኩቴክ (ACCU-TECH) ዲያግኖስቲክ ላቦራቶሪ የሀገሪቱን የጤና ዘርፍ ወደ ከፍተኛ ምዕራፍ የሚያሸጋግር እና ለዘርፉ ልዩ መለያ እና አቅም ነው። ዘመናዊው ላቦራቶሪ በአንድ ጊዜ በርካታ ናሙናዎችን በመቀበል ለተወሰነ ጊዜ ሳምፕሎችን በጥንቃቄ ማቆየት የሚያስችል አቅም እንዳለውም ተናግረዋል። የአኩቴክ ዲያግኖስቲክ ዋና ዳይሬክተር ሄኖክ ታደሰ ለኢዜአ እንዳሉት፣ ስያሜው "አኩ" ትክክለኛነትን እና "ቴክ" ቴክኖሎጂን የሚወክል ሲሆን፣ የሚጠቀማቸው ዘመኑን የዋጁ ቴክኖሎጂዎች የምርመራ ውጤቶች ጥራት እንዲኖራቸው ያስችላሉ። ይህ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ዘመናዊ ላቦራቶሪ ወደ ውጭ ሀገር ተልከው ይሠሩ የነበሩ የላቦራቶሪ ምርመራዎችን በማስቀረት ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወትም ገልጸዋል። የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ከሪቲና ፋርማሲዩቲካል ጋር በመተባበር የተቋቋመው ላቦራቶሪ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሙሉ በሙሉ አውቶሜትድ የሆነ ነው ብለዋል። ላቦራቶሪው በምርመራ ሂደቶች ላይ የሚታዩ የውጤት መዘግየቶችንና የውጭ ምንዛሬ ወጪዎችን ለማስቀረት ጉልህ ሚና እንዳለውም ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም እስከ 68 በመቶ የሚደርሱ ስህተቶች ሊከሰቱ እንደሚችሉ አንስተው፣ አሁን ያለው ሲስተም ይህንን ዲጂታላይዝ በማድረግ ስህተቱን ወደ ዜሮ እንደሚያወርደው አስረድተዋል። ላቦራቶሪው በርካታ ናሙናዎችን በአንድ ጊዜ የመመርመር ብቃት ያለው ከመሆኑ ባሻገር ናሙናዎችን በጥንቃቄ የሚያቆይ መሆኑንም ተናግረዋል። ማሽኖቹ ከሰው ሰራሽ አስተውሎት (አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ) ጋር የተገናኙ በመሆናቸው ሥራን በቀላሉና በፍጥነት እንዲያከናውኑ ማስቻሉን አንስተዋል። በቀጣይም አገልግሎቱን በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ አካባቢዎች ተደራሽ ለማድረግ በድሮን ናሙና መሰብሰብ የሚያስችል ተግባር ለማከናወን እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። ላብራቶሪው ሀገሪቱን የህክምና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የተያዘውን ግብ ለማሳካትም ተጨማሪ አቅም እንደሚሆን ተናግረዋል።
የመደመር አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዩኒቨርሲቲ አፍሪካ የነገውን የቴክኖሎጂ ዘመን በባለቤትነት እንድትመራ ትልቅ ሚና ይጫወታል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
Sep 12, 2026 466
አዲስ አበባ፤ መስከረም 2/2019 (ኢዜአ):- አፍሪካ የነገውን የቴክኖሎጂ ዘመን በባለቤትነት እንድትመራ የመደመር አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዩኒቨርሲቲ ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። 18ኛው የብሪክስ ጉባኤ ዛሬ በህንድ ኒው ዴልሂ መካሄድ ጀምሯል። በጉባኤው ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ንግግር አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው ዓለም አቀፍ ቀውሶች የሚያስከትሉት ጉዳት በአንድ ዘርፍ ላይ ብቻ ሳይወሰኑ ተደራራቢ መስተጓጎል እንደሚፈጥሩ ገልጸዋል። ሀገራት ቀውሶች ከመከሰታቸው በፊት የመቋቋም አቅም ሊገነቡ እንደሚገባ ጠቅሰው፤ በዚህ ረገድም ኢትዮጵያ ፈተናን መቋቋም የሚያስችሉ ስርዓቶችን እየገነባች እንደምትገኝ ተናግረዋል። መንግስት በምግብ ዋስትና ላይ ባከናወነው ተግባር ኢትዮጵያ ከውጭ ከሚገባ ስንዴ ጥገኝነት ሙሉ በሙሉ ወጥታ ራሷን መቻሏን ጠቅሰዋል። በመሆኑም ሀገሪቱ ለታቀደው የብሪክስ የሰብል ልውውጥ ማዕቀፍ (BRICS Grain Exchange) እንደ አምራችም ሆነ አቅራቢ ሆና ለመሳተፍ ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል። በጤናው ዘርፍም የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ትልቅ ትምህርት መስጠቱን ነው የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ። ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ የሚያጋጥሙ ቀውሶችን ለመቋቋም የሀገር ውስጥ የማምረት አቅሟን እያሳደገች እንደምትገኝ ገልጸው፤ የፋርማሲዩቲካልና የመድኃኒት ማምረቻዎችንም እያስፋፋች መሆኗን ጠቁመዋል። በቴክኖሎጂው ዘርፍ ዲጂታል መሠረተ ልማት፣ ዲጂታል መታወቂያ (Digital ID)፣ የክፍያ ሥርዓቶች እና የመረጃ ልውውጥ በስፋት እየተገነቡ መሆናቸውን አንስተዋል። መረጃዎች ደህንነታቸው በተጠበቀ መልኩ በሕግ አግባብ ጥቅም ላይ እንዲውሉ እየተደረገ እንደሚገኝ ጠቅሰው፤ ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ይህንን ለውጥ የበለጠ እንደሚያጠናክረው አመልክተዋል። በቀጣዩ ትውልድ ሰው ሰራሽ አስተውሎት ይበልጥ ሰዎችን ማገልገል፣ ብዙ ቋንቋዎችን መረዳት እና ሰፊ የሰው ልጅ እውቀት ማካተት እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል። አፍሪካ የነገውን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘመን በባለቤትነት ለመምራት የምርምር፣ የኮምፒውቲንግ አቅም፣ ክህሎት እና ተቋማት እንደሚያስፈልጋት አስገንዝበዋል። ኢትዮጵያ እየገነባች ያለችውም የመደመር አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዩኒቨርሲቲም አፍሪካ የወጠነችውን ግብ የማሳካት አላማ እንዳለው አመልክተዋል። ኢትዮጵያ አፍሪካን የሚወክል የቴክኖሎጂ አቅም ለመገንባት ከብሪክስ ተቋማት ጋር በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳላትም ገልጸዋል። በተጨማሪም ሰዎችን ማዕከል ያደረገ የኤአይ አስተዳደር መደገፍ እንዳለበት እና ጥሩ አስተዳደር ከብቃት ጋር ሊጣጣም እንደሚገባ አሳስበዋል።
ስፖርት
የወቅቱ የካራባኦ ካፕ አሸናፊ ማንችስተር ሲቲ ከኖርዊች ሲቲ ጋር ይጫወታል
Sep 17, 2026 18
አዲስ አበባ፤ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ):- የእንግሊዝ ካራባኦ ካፕ ሶስተኛ ዙር መርሐ ግብር ዛሬ ይጠናቀቃል። ምሽት 3 ሰዓት ከ30 ላይ ማንችስተር ሲቲ ከኖርዊች ሲቲ በኢትሃድ ስታዲየም ይጫወታሉ። ባለሜዳው ማንችስተር ሲቲ የወቅቱ የዋንጫ ባለቤት ነው። በእንግሊዝ ሻምፒዮንሺፕ (ሁለተኛ የሊግ እርከን) የሚገኘው ኖርዊች ሲቲ በሁለተኛው ዙር ካርዲፍ ሲቲን 2 ለ 1 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር ተሸጋግሯል። ሁለቱም ቡድኖች ከዚህ ቀደም በካራባኦ ካፕ አምስት ጊዜ የተገናኙ ሲሆን ማንችስተር ሲቲ በሶስቱ ሲያሸንፍ በቀሪ ሁለት ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል። ቡድኖቹ ለመጨረሻ ጊዜ በውድድሩ ላይ የተገናኙት እ.አ.አ በ2007 ነው። በወቅቱ በሶስተኛው ዙር ባደረጉት ጨዋታ በጆርጅ ሳማራስ ጎል ማንችስተር ሲቲ 1 ለ 0 አሸንፏል። ማንችስተር ሲቲ ዘጠኝ ጊዜ ዋንጫውን በማንሳት ከሊቨርፑል (10 ዋንጫ) በመቀጠል የውድድሩ ስኬታማ ክለብ ነው። ኖርዊች ሲቲ እ.አ.አ በ1962 እና በ1985 ውድድሩን አሸንፏል። በተጨማሪም እ.አ.አ በ1973 እና 1975 ለፍጻሜ ደርሶ ሽንፈት አስተናግዷል። ማንችስተር ሲቲ ጨዋታውን የማሸነፍ ሰፊ የቅድሚያ ግምት አግኝቷል። የ28 ዓመቱ ሩበን ሪካርዶ ጨዋታውን በዋና ዳኝነት ይመሩታል።
የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ከሩዋንዳ ጋር ይጫወታል
Sep 17, 2026 31
አዲስ አበባ፤ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ):- ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ጨዋታዋን ከሩዋንዳ ጋር ዛሬ ታደርጋለች። ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም በታንዛንያ አስተናጋጅነት መካሄድ ጀምሯል። በውድድሩ ላይ ዘጠኝ ሀገራት በሶስት ምድብ ተከፍለው ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በምድብ አንድ ከአዘጋጇ ታንዛንያ እና ሩዋንዳ ጋር ተደልድሏል። ብሔራዊ ቡድኑ የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታውን ዛሬ ከቀኑ ስምንት ሰዓት ከሩዋንዳ አቻው ጋር ያደርጋል። በአሜሪካዊው አሰልጣኝ ቤንጃሚን ዚመር የሚመራው ብሔራዊ ቡድን በሐምሌ ወር 2018 ዓ.ም ከተጀመረው ብሔራዊ ምልመላና ምዘና( National Camping) አንስቶ ዝግጅቱን ሲያደርግ ቆይቷል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለታንዛንያው የሴካፋ ማጣሪያ ውድድር መጀመሪያ ላይ የ40 ተጫዋቾችን ጊዜያዊ ስም ዝርዝር ይፋ አድርጎ ነበር። በአሁኑ ወቅት አሰልጣኝ ቤንጃሚን ዚመር ስብስቡን ወደ 25 ተጫዋቾች በመቀነስ ልምምዱን ሲያደርግ ቆይቶ ወደ ስፍራው አቅንቷል። በአንድሬ ካሳ ምቡንጎ የሚመራው የሩዋንዳ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም ባደረገው የመጀመሪያ ጨዋታ በአዘጋጇ ታንዛንያ 3 ለ 0 ተሸንፏል። የሩዋንዳ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በበጀት እጥረት ምክንያት ቡድኑ በውድድሩ ላይ እንደማይሳተፍ አስታውቆ የነበረ ቢሆንም፣ ከሀገሪቷ ስፖርት ሚኒስቴር ጋር በተደረገ ስምምነት ውሳኔው ተቀይሮ ውድድሩ ሊጀመር የአንድ ሳምንት እድሜ ሲቀረው መሳተፉ ተረጋግጧል። የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የማጣሪያ ጉዞውን በድል ለመጀመር ይጫወታል። በአንጻሩ የሩዋንዳ አቻው ወደ ግማሽ ፍጻሜ ለማለፍ ያለውን ተስፋ ለማለምለም እጅጉን ወሳኝ ነው። በቤንጃሚን ዚመር የሚመራው ታዳጊ ቡድን ሁለተኛ የምድብ ጨዋታውን መስከረም 9 ቀን 2019 ዓ.ም ከአዘጋጇ ታንዛንያ ጋር ያደርጋል። ቡድኑ ወደ ግማሽ ፍጻሜ የሚገባው ከምድቡ አንደኛ ወይም ከሶስቱ አጠቃላይ ምድቦች ምርጥ ሁለተኛ ሆኖ ካጠናቀቀ ብቻ ነው። በምድብ ሁለት ዩጋንዳ፣ ሱዳን እና ጅቡቲ እንዲሁም በምድብ ሶስት ደቡብ ሱዳን፣ ኬንያ እና ብሩንዲ ይገኛሉ። የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በጋና እ.አ.አ በ2027 ለሚካሄደው ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ በማጣሪያ ውድድሩ የፍጻሜ ተፋላሚ መሆን ይኖርበታል። ከየቀጣናው ሁለት ሀገራት ለአፍሪካ ዋንጫው ያልፋሉ። ብሔራዊ ቡድኑ በጋና በሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ብሔራዊ ቡድኑ ካለፈ እና ግማሽ ፍጻሜ መድረስ ከቻለ በዛው ዓመት በአዘርባጃን እና ኡዝቤኪስታን ጣምራ አዘጋጅነት ለሚካሄደው ከ20 ዓመት በታች የፊፋ ዓለም ዋንጫ ማለፉን ያረጋግጣል። ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም በ20 ዓመት የአፍሪካ ዋንጫ ሁለት ጊዜ ተሳትፋለች። እ.አ.አ በ1993 በሞሪሺየስ በተካሄደው እንዲሁም እ.አ.አ በ2001 ራሷ ባዘጋጀችው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ተሳትፋለች። የሴካፋ ዞን ማጣሪያ እስከ መስከረም 15 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።
ማንችስተር ዩናይትድ ከካራባኦ ካፕ ውድድር ተሰናበተ
Sep 17, 2026 132
አዲስ አበባ፤ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ካራባኦ ካፕ የሶስተኛ መርሐ ግብር ብራይተን ማንችስተር ዩናይትድን 3 ለ 2 አሸንፏል። ትናንት ማምሻውን በኦልድትራፎርድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሼ ሌሲ እና ሜሰን ማውንት ባስቆጠሯቸው ጎሎች ማንችስተር ዩናይትድ 2 ለ 0 መምራት ችሎ ነበር። ቻራላምፖስ ኮስቱላስ፣ ፓስካል ግሮስ እና ማክሲም ዲካይፐር ከመረብ ላይ ባሳረፏቸው ጎሎች ብራይተን አሸናፊ ሆኗል። የግሮስ እና ዲካይፐር ጎሎች ከእረፍት መልስ የተቆጠሩ ናቸው። ውጤቱን ተከትሎ ብራይተን ወደ አራተኛው ዙር አልፏል። የስድስት ጊዜ የውድድሩ አሸናፊ የሆነው ማንችስተር ዩናይትድ በሶስተኛው ዙር ተሰናብቷል። በሌሎች መርሐ ግብሮች አስቶንቪላ ኮቨንተሪ ሲቲን 3 ለ 1፣ ኤቨርተን ዎልቭስንና ፍሊትውድ ሼፍልድ ዩናይትድን በተመሳሳይ 1 ለ 0 በማሸነፍ ቀጣዩን ዙር ተቀላቅለዋል። የካራባኦ ካፕ የሶስተኛ ዙር መርሐ ግብር የወቅቱ የዋንጫ ባለቤት ማንችስተር ሲቲ እና ሌስተር ሲቲ ነገ በሚያደርጉት ጨዋታ ይጠናቀቃል።
በካራባኦ ካፕ ማንችስተር ዩናይትድ ከብራይተን ጋር ይጫወታል
Sep 16, 2026 220
አዲስ አበባ፤ መስከረም 6/2019 (ኢዜአ):- በእንግሊዝ ካራባኦ ካፕ ሶስተኛ ዙር ዛሬ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ። በኦልትራፎርድ ስታዲየም ምሽት አራት ሰዓት ላይ ማንችስተር ዩናይትድ ከብራይተን ጨዋታቸውን ያከናውናሉ። ሁለቱም ቡድኖች የውድድሩ ጉዟቸውን ሶስተኛ ዙር ላይ ይጀምራሉ። ከዚህ ቀደም ባደረጓቸው ሶስት ጨዋታዎች ማንችስተር ዩናይትድ በሁለቱ ድል ሲቀናው አንድ ጊዜ አቻ ተለያይተዋል። እ.አ.አ በ2020 ለመጨረሻ ጊዜ በተገናኙበት የአራተኛ ዙር መርሐ ግብር ማንችስተር ዩናይትድ 3 ለ 0 አሸንፏል። ስኮት ማክቶሚናይ፣ ሁዋን ማታ እና ፖል ፖግባ በወቅቱ ግቦቹን ለዩናይትድ ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ናቸው። ማንችስተር ዩናይትድ ስድስት ጊዜ ውድድሩን አሸንፏል። በአንጻሩ ብራይተን በካራባኦ ካፕ ትልቁ ውጤቱ እ.አ.አ 1978/79 የውድድር ዓመት ሩብ ፍጻሜ የደረሰበት ነው። ኤቨርተን ከዎልቭስ እና ፍሊትውድ ከሼፍልድ ዩናይትድ በተመሳሳይ ምሽት 3 ሰዓት ከ45 ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። ኮቨንተሪ ሲቲ ከአስቶንቪላ ምሽት አራት ሰዓት ላይ በኮቨንተሪ ቢውልዲንግ ሶሳይቲ አሬና ይጫወታሉ።
አካባቢ ጥበቃ
ኢትዮጵያ ዘላቂና የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም አረንጓዴ ኢኮኖሚ የመገንባት ራዕይዋን ውጤታማ በሆነ መልኩ አጠናክራ ቀጥላለች
Sep 15, 2026 310
አዲስ አበባ፤ መስከረም 5/2019 (ኢዜአ):- ኢትዮጵያ ዘላቂና የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም አረንጓዴ ኢኮኖሚ የመገንባት ራዕይዋን ውጤታማ በሆነ መልኩ አጠናክራ መቀጠሏን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትሩ አለሙ ስሜ (ዶ/ር) ገለጹ። ሚኒስትሩ ይህንን የገለጹት በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው የኖርዲክ-አፍሪካ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ (Nordic Africa EV Summit) ጉባኤ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ነው። ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መሪነት አረንጓዴና የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም የልማት ስትራቴጂን በሀገራዊ የልማት ዕቅዷ ማዕከል አድርጋ እየሰራች ትገኛለች። የአረንጓዴ አሻራ፣ የታዳሽ ኃይል ማስፋፋት፣ የአረንጓዴ ከተማ ልማት እና ዝቅተኛ የካርቦን ልቀት ያለው ኢኮኖሚ የመገንባት ጥረት ኢትዮጵያ የልማት አቅጣጫዋን ለመለወጥ ያላትን ቁርጠኝነት ያሳያል ብለዋል። የሀገሪቱ የረጅም ጊዜ የአየር ንብረት ስትራቴጂ የትራንስፖርት ዘርፉን ከካርቦን ነፃ ማድረግን ዋነኛ መንገድ አድርጎ ማስቀመጡንም ጠቁመዋል። የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን፣ የሕዝብ ትራንስፖርትን፣ የአረንጓዴ ከተማ ኮሪደሮችን እና ንፁህ የትራንስፖርት ሥርዓቶችን ከታዳሽ ኃይል አቅም ጋር የማዋሃድ ሥራ እየተከናወነ መሆኑንም አብራርተዋል። ይህ ጥረት ከአካባቢ ጥበቃ ባለፈ የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን፣ የኃይል ደህንነት፣ የቴክኖሎጂ ፈጠራ፣ የኢንዱስትሪ ልማት እና የዜጎችን የኑሮ ጥራት የማሻሻል አጀንዳ መሆኑን አስገንዝበዋል። የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የቴክኖሎጂ፣ ኢኖቬሽን፣ ግንኙነት እና መሠረተ ልማት ክፍል ዳይሬክተር ሮበርት ታማ ሊሲንጌ በበኩላቸው፤ በአፍሪካ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን የመጠቀምና የማምረት አጠቃላይ አዝማሚያ እየጨመረ መምጣቱን ገልጸዋል። አህጉሪቱ ኃይል በማመንጨት ላይ ብቻ ሳትወሰን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በማምረት ለሀገር ውስጥ ገበያ እንዲሁም ወደ አውሮፓና እስያ ለመላክም መስራት እንዳለባት ገልጸው፤ ሀገራት ተሽከርካሪዎቹን ለማስገባት የሚያስችሉ ማበረታቻዎችንና የተሟላ ስነ-ምህዳር በመፍጠር ላይ እንደሚገኙ አብራርተዋል። የኖርዲክ-አፍሪካ ኢቪ ሳሚት ሮድ ቱ አፍሪካ የሀሳብ መሪ ሚከል ቤከር አከርቪክ እንደተናገሩት፤ ከተሞችን ከካርቦን ነፃና ንፁህ አየር እንዲኖር ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል። በትራንስፖርት ዘርፍ የሚፈጠረው የልቀት መጠን ከፍተኛ በመሆኑ፣ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን አሰራር መተግበር በኢኮኖሚ ደረጃ ብቻ ሳይሆን ለአካባቢ ጥበቃም እውነተኛ ትራንስፎርሜሽን እንደሚያመጣ አስረድተዋል።
ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም፣ አረንጓዴ እና ዘላቂ የትራንስፖርት ስርዓትን ለመገንባት በቁርጠኝነት እየሰራች ነው
Sep 15, 2026 266
አዲስ አበባ፤ መስከረም 5/2019 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም፣ አረንጓዴ እና ዘላቂ የትራንስፖርት ስርዓትን ለመገንባት በቁርጠኝነት እየሰራች መሆኑን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) ገለፁ። ሚኒስትሩ ይህንን የገለጹት በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው የኖርዲክ-አፍሪካ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ (Nordic Africa EV Summit) ጉባኤ ላይ ነው። ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መሪነት አረንጓዴና የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም የልማት ስትራቴጂን በሀገራዊ የልማት ዕቅዷ ማዕከል አድርጋ እየሰራች ትገኛለች። የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር፣ የታዳሽ ኃይል ማስፋፋትና ዝቅተኛ ካርቦን ያለው ኢኮኖሚ የመገንባት ጥረት የዚሁ ቁርጠኝነት ማሳያ መሆናቸውን አብራርተዋል። የትራንስፖርት ዘርፉን ከካርቦን ነፃ ማድረግ ለዘላቂ ኢኮኖሚ ግንባታ ከሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት አንዱ መሆኑን አመልክተው፤ ሀገሪቱ ይህንን ውሳኔ ወደ ተግባር ለመቀየር የኤሌክትሪክ ህዝብ ትራንስፖርት፣ የአረንጓዴ ከተሞች ኮሪደር እና የፅዱ አየር ትራንስፖርት ስርዓትን ከታዳሽ ኃይል አቅሟ ጋር አስተስስራ እየገነባች እንደሆነ ገልፀዋል። የኤሌክትሪክ ትራንስፖርት ሽግግር ለአካባቢ ጥበቃ ብቻ ሳይሆን ለኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን፣ ለኃይል ዋስትና፣ ለቴክኖሎጂ ፈጠራና ለዜጎች የህይወት ጥራት መሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ጠቁመዋል። ተሽከርካሪዎችን ብቻ ወደ ሀገር ማስገባት የኤሌክትሪክ ትራንስፖርት ምህዳርን ሙሉ በሙሉ ሊፈጥር እንደማይችል አመልክተው፤ የተሟላ ውጤት ለማስመዝገብ መሰረተ ልማቶችና አሰራሮች ማሟላት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ በዚህም የቻርጅ ማድረጊያ መሰረተ ልማቶችን ማስፋፋትና የዲጂታል አሰራርን መዘርጋት፣ ሁለንተናዊ ስታንዳርዶችን ማዘጋጀት፣ የሰለጠነ የሰው ኃይል ማፍራት (ኢንጂነሮችንና ቴክኒሻኖችን ማሰልጠን) እንዲሁም የባትሪዎችን መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል ስርዓት መዘርጋት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡ በመሆኑም የተቀናጀ ስርዓት መገንባት፣ ከቴክኖሎጂ ገዢነት ወደ ሀገር ውስጥ አቅም ግንባታ መሸጋገር እንዲሁም ቀጣናዊና አህጉራዊ ትብብርን ማጠናከር እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል። ኢትዮጵያና አፍሪካ ከኖርዲክ ሀገራት አዎንታዊ ተሞክሮዎችን እንደሚወስዱ የጠቆሙት ሚኒስትሩ፤ ሆኖም የአፍሪካ መፍትሔዎች የአህጉሪቱን እውነታና የትራንስፖርት ፍላጎት ያገናዘቡ መሆን እንዳለባቸው አፅንኦት ሰጥተዋል። አፍሪካ ወደ ኤሌክትሪክ ሞቢሊቲ የምታደርገው ሽግግር የኢንዱስትሪ ልማት ሞተር እንጂ ለውጭ ምርቶች ሌላ ገበያ መዳረሻ ብቻ መሆን እንደሌለበት አስገንዝበዋል፡፡ አፍሪካውያን በጠቅላላው የእሴት ሰንሰለት ውስጥ እንዲሳተፉ የሀገር ውስጥ ገጣጣሚዎችንና አምራቾችን ማጠናከር፣ በምርምርና ልማት ላይ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ እንዲሁም ድንበር ተሻጋሪ የትራንስፖርት ስርዓቶችን ማስተሳሰር እንደሚገባ ገልፀዋል። ለዚህ ትራንስፎርሜሽን የመንግስት ሀብት ብቻውን በቂ አለመሆኑን ጠቁመው፤ በመንግስታት፣ በልማት አጋሮች፣ በንግድ ባንኮችና በግል ባለሀብቶች መካከል ጠንካራ አጋርነት መፍጠር እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። ጉባኤው ከውይይት ባለፈ ወደ ተግባራዊ እርምጃዎች የሚወሰዱበት፣ ግልጽ ግቦች የሚቀመጡበት እንዲሁም የልማትና ቴክኖሎጂ አጋሮች ትብብር የሚጠናከርበት መድረክ እንደሚሆን እምነታቸውን ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ አረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር አፍሪካ ለችግሮቿ መፍትሔ ማቅረብ እንደምትችል ማረጋገጫ ነው
Sep 13, 2026 506
አዲስ አበባ፤መስከረም 3 /2019 (ኢዜአ):-የኢትዮጵያ አረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር አፍሪካ ለችግሮቿ መፍትሔ ማቅረብ እንደምትችል ማረጋገጫ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ገለጹ። ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ የአየር ንብረት ለውጥን በመቋቋም፣ ሥነ-ምህዳርን በመመለስና ዘላቂ ልማትን በማረጋገጥ ለአፍሪካና ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አርዓያ የሚሆን ተግባር እያከናወነች መሆኑንም ተናግረዋል። በተባበሩት መንግሥታት የኢኮኖሚክ ኮሚሽን የአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛ ባለሙያ ዮሴፍ አምሃ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንዳሉት፤ የአረንጓዴ ዐሻራ ኢኒሼቲቭ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቋቋም ወሳኝ ነው። ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር ከከባቢ አየር የሚለቀቁ ሙቀት አማቂ ጋዞችን በመያዝ ለሥነ-ምህዳር ጥበቃ ገንቢ ሚና እየተወጣች መሆኑን ገልጸዋል። መርሃ ግብሩ ለአርሶ አደሩ፣ ለወጣቶችና ለሴቶች የሥራ ዕድል በመፍጠር የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ያረጋግጣል ብለዋል። የፓን አፍሪካ አየር ንብረት ፍትህ ጥምረት ዋና ዳይሬክተር ሚቲካ ምወንዳ (ዶ/ር)፤ የአረንጓዴ ዐሻራ ሀገራት ችግራቸውን በራሳቸው አቅም ለመፍታት ሊወስዱት የሚገባ ምርጥ ተሞክሮ መሆኑን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር ያስመዘገበችው ስኬት አፍሪካ ለችግሮቿ መፍትሔ ማቅረብ እንደምትችል ያሳየ ነው ብለዋል። በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ የአየር ንብረት ሻምፒዮንና የአፍሪካ የግሬት ግሪን ዋል ኢኒሼቲቭ አምባሳደር ታቢ ጆዳ፤ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር በጠንካራ አመራር የታጀበ ውጤታማ ሥራ መሆኑን ገልጸዋል። መንግሥት ፕሮግራሙን ከንግግር ባለፈ መሬት ላይ የሚታይና ሚተረጎም ድንቅ ኢኒሼቲቭ ነው ብለዋል። በአፍሪካ ልማት ባንክ የአፍሪካ አየር ንብረትና ልማት ልዩ ፈንድ አስተዳዳሪ ጀምስ ኪንያንጊ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ እርምጃዎችን በመቅረጽና በተግባር ረገድ ለአፍሪካውያን አርዓያ መሆኗን ገልጸዋል።
በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ስኬታማ ሥራ ተከናውኗል
Sep 10, 2026 408
የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር በ2011 ዓም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት በይፋ መጀመሩ ይታወቃል። መርሃ ግብሩ እንደ ሀገር ያጋጠሙ በርካታ የዘላቂ ልማት ተግዳሮቶችን የመሬት መጎሳቆል የደንና ብዝሃ ህይወት መጨፍጨፍ፣ የውሃ አካላትን መድረቅና በደለል መሞላት ለመከላከል ታስቦ ወደ ሥራ መገባቱ ይታወቃል። በዚህም በመጀመሪያው ምዕራፍ 50 ቢሊዮን ችግኝ በማህበረሰብ ተሳትፎ ለመትከል ታቅዶ ነበር። ኢትዮጵያ ባለፉት ስምንት የመርሃ ግበሩ የትግበራ ዓመታት 56 ነጥብ 8 ቢሊዮን ችግኞችን፤ በዚህ ዓመት ብቻ ደግሞ 8 ነጥብ 2 ቢሊዮን ችግኝን በመትከል በዓለም ላይ አዲስ ታሪክ ፅፋለች። አጠቃላይ ከተተከሉ ችግኞች ከ3 ቢሊዮን በላይ የሚሆኑት በአንድ ጀምበር የተተከሉ መሆናቸው በዓለም ላይ ትልቅ የችግኝ ተከላ ሆኖ ተመዝግቧል። ከተተከሉ ችግኞች 60 በመቶ የሚሆኑት የጥምር ደን ግብርና (የፍራፍሬ፣ የቡና፣ የመኖ ዝርያዎች) ሲሆኑ 35 በመቶ የደን ዝርያ ናቸው። ይህ ታላቅ የልማት ድል የተሳካው ከላይ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እስከ ታችኛው የመንግስት አደረጃጀት ለመርሃ ግብሩ በተሰጠው ቁርጠኛ አመራር ነው። በየዓመቱ ከ25 ሚሊየን በላይ ዜጎች በችግኝ ተከላ ተሳትፈዋል። እስካሁን በተሠራው ሥራ በየዓመቱ ይፈጸም የነበረው የደን ጭፍጨፋ ከ92 ሺህ ወደ 27 ሺህ ሄክታር እንዲቀንስ አስችሏል። በእርሻ ማሳ የአፈር መከላት በዓመት በሄክታር ከ130 ቶን ወደ 54 ቶን ቀንሷል። አረንጓዴ ዐሻራ በየዓመቱ ወደ ውሃ አካላት የሚገባ የአፈር ደለል ከ1 ነጥብ 9 ቢሊዮን ቶን ወደ 208 ሚሊዮን ቶን ዝቅ እንዲል አስችሏል። በመርሃ ግብሩ ለ2 ነጥብ 6 ሚሊዮን ወጣቶችና ሴቶች አረንጓዴ ሥራ ተፈጥሮላቸዋል። በበርካታ አካባቢዎች የፍራፍሬና የደን ክላስተር እየተፈጠረ አርሶ አደሮች የላቀ የኢኮኖሚ አቅም እንዲገነቡ እያስቻለ ነው። ኢትዮጵያ ግዙፍ የልማት መርሃ ግብር ቀርጻ መተግበር እንደምትችል ትልቅ ተሞክሮ የተወሰደበትና ለዓለም ያሳየችበትም ነው። ከዚህም ባለፈ ሀገራችን ዓለም እየተፈተነችበት ላለው የአየር ንብረት ለውጥ ተግባራዊ መፍትሔ በመስጠት ምሳሌ መሆኗን ያሳየችበት ነው።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
በቀጣናው ያሉ ፈተናዎችን በዘላቂነት ለመፍታት የሀገራት የጋራ ቁርጠኝነት ወሳኝ ነው - ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር)
Sep 15, 2026 495
አዲስ አበባ፤ መስከረም 5/2019 (ኢዜአ)፦ በቀጣናው እያጋጠሙ የሚገኙ ፈተናዎች በዘላቂነት እንዲፈቱ የአባል ሀገራት አብሮነትና የጋራ ቁርጠኝነት ወሳኝ መሆኑን የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ገለጹ። የኢጋድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት 74ኛው አስቸኳይ ስብሰባውን ዛሬ በጅቡቲ አካሂዷል። በስብሰባው ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እና የኢጋድ አባል ሀገራት ተወካዮች ተሳትፈዋል። በቀጣናው ሰላም እና ጸጥታ እንዲሁም በሌሎች አበይት ጉዳዮች ላይ ምክክር ተደርጓል። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ በቀጣናው እያጋጠሙ ያሉ ፈተናዎችን በዘላቂነት ለመቋቋም የአባል ሀገራት አብሮነትና የጋራ ቁርጠኝነት ወሳኝ ነው። በኢጋድ ሴክሬታሪያት በኩል የተከናወኑ የልማትና የሰላም ሥራዎች አበረታች ውጤቶችን እያስገኙ መሆናቸውን በመግለጽ፣ ተቋሙ ለቀጣናው ህዝቦች ብልጽግና መረጋገጥ የጸና አቋም እንዳለው አመልክተዋል። ምንም እንኳን የተለያዩ ጂኦፖለቲካዊ ፈተናዎች ቢኖሩም፣ የኢጋድ ሴክሬታሪያት ያለፉት ስድስት ወራት አፈጻጸም አበረታች የሚባል መሆኑን ተናግረዋል። በቀጣናዊ መሠረተ ልማት እና የጤና ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶችን ያነሱት ዋና ፀሐፊው፤ የቀጣናው የከርሰ ምድር ውሃ መረጃ ሥርዓት የአገልግሎት ተደራሽነት የላቀ ውጤት ማስመዝገቡን ጠቁመዋል። እንዲሁም የቀጣናው ዓለም አቀፍ የጤና ሽፋን መረጃ ጠቋሚ (ኢንዴክስ) ከ60 ወደ 65 በመቶ ከፍ ማለቱንና ይህም እ.አ.አ በ2027 70 በመቶ ለማድረስ የተያዘውን እቅድ ለማሳካት የሚያስችል መሆኑን ነው ያነሱት። በሌላ በኩል ሱዳን ወደ ኢጋድ ሙሉ አባልነቷ መመለሷ የቀጣናውን ትብብርና አንድነት ይበልጥ እንደሚያጠናክረው ገልጸዋል። ዋና ፀሐፊው እ.አ.አ ጁላይ 2026 ወደ ሱዳን ባቀኑበት ወቅት የኢጋድ የሱዳን ልዑክ ቢሮ በድጋሚ በይፋ መከፈቱን አስታውሰው ይህ እርምጃ ከቀጣናው ሕዝቦች ጋር ያለውን ቀጥተኛና ዘላቂ ትስስር አጠናክሮ የሚያስቀጥል መሆኑን አመላክተዋል። ኢጋድ ከአፍሪካ ሕብረት፣ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኤጀንሲዎች እና ከሌሎች ስትራቴጂካዊ አጋሮች ጋር ያለው ግንኙነት ለቀጣናው ዘላቂ ልማት ወሳኝ ነው ብለዋል። አጋርነቱ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትን አቅም በማጠናከር ረገድ የጎላ ድርሻ እንደሚያበረክትም ነው ያነሱት። በቀጣይ ሊከሰቱ የሚችሉ የአየር ንብረት ለውጥ አደጋዎችን የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓትን በማጠናከር ለመቋቋም የሚያስችሉ አሰራሮች እየተቀረፁ መሆናቸውን ተናግረዋል። ሀገራት የኤልኒኖ (El Niño) የአየር ንብረት መዛባት የሚያስከትለውን ስጋት ለመቀነስ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከር እንዳለባቸው አሳስበዋል። በሌላ በኩል ቀጣናውን ከሰው ሰራሽ አስተውሎት ጋር ለማስተሳሰርና በቴክኖሎጂ የታገዘ የልማት መሠረት ለመጣል የተጀመሩ ስራዎች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን ገልጸዋል። ስብሰባው የቀጣናውን ሰላም፣ ደህንነት እና ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማፋጠን በሚያስችሉ ሀገራዊና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ በመምከርና ውሳኔዎችን በማሳለፍ መጠናቀቁን ኢዜአ ከኢጋድ ሴክሬተሪያት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። የኢጋድ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ከተቋሙ ቁልፍ የፖሊሲ አደረጃጀቶች መካከል አንዱ ሲሆን፣ የድርጅቱን ሥራዎች በመምራትና በአባል ሀገራት መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር ረገድ ጉልህ ሚና የሚጫወት ነው።
አፍሪካ በዓለም ፊት ቦታ ለማግኘት አትማጸንም ፤ ይልቁንም የሚገባትን ስፍራ በባለቤትነት እየያዘች ነው
Sep 9, 2026 489
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ):- አፍሪካ በዓለም ፊት ቦታ ለማግኘት አትማጸንም ፤ የሚገባትን ስፍራ እና ክብር በራሷ እያረጋገጠች ነው ሲሉ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። የአፍሪካ ህብረት ቀን ዛሬ እየተከበረ ይገኛል። የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ቀኑን በማስመልከት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ሊቀ መንበሩ የአፍሪካ ህብረት ቀን እ.አ.አ በ1999 የቀድሞ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ለመተካት ይፋዊ ውሳኔ የተላለፈበት የሰርጥ ድንጋጌ (Sirte Declaration) የሚታወስበት እንደሆነ ገልጸዋል። በዚያን ወቅት የአፍሪካ መሪዎች አህጉራዊ ትስስርን ለማፋጠን እና የአፍሪካን ድምጽ በዓለም አቀፍ መድረክ ከፍ ለማድረግ የአፍሪካ ህብረትን ለመመስረት ወሳኝ እና ታሪካዊ እርምጃ የወሰዱበት ምዕራፍ ነው ብለዋል። የዘንድሮው የአፍሪካ ህብረት ቀን ለአህጉሪቱ እጅግ ልዩ ትርጉም ባለው ወቅት ላይ እየተከበረ እንደሚገኝ አውስተዋል። ከጥቂት ቀናት በፊት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ የአፍሪካን እውነተኛ ቁመና እና ትክክለኛ መጠን የሚያሳይ የዓለም ካርታ አጠቃቀምን የሚደግፍ፣ በአፍሪካ መሪነት የቀረበ የውሳኔ ሀሳብ አፅድቋል። በቶጎ ሃሳብ አመንጪነትና በአፍሪካ ህብረት ድጋፍ እውን የሆነው ይህ እርምጃ ከቀላል የካርታ ማስተካከያ በላይ ትርጉም አለው ብለዋል ሊቀ መንበሩ። አፍሪካ በዓለም ፊት እንዴት እንደምትታይ ትኩረት የሚሰጠው መሆኑን እና አፍሪካ ራሷን የምትገመግምበትንና የምታሳይበትን ትርክት ራሷ መቅረጽ እንዳለባት አበክሮ የሚያስታውስ ነው። ይህ ውሳኔ አፍሪካ በዓለም ፊት በምን መልኩ መታየት እንዳለባት ከማሳየቱም በላይ፤ አፍሪካ ራሷን የምትመዝንበትንና እውነታዋን ለዓለም የምታሳይበትን ትርክት በራሷ መቅረጽ እንዳለባት በግልጽ የሚያሳይ መሆኑን ነው ያነሱት። የአፍሪካ እጣ ፈንታ የሚወሰነው በአፍሪካውያን የራሳቸው እይታ ነው። አፍሪካን በእውነተኛ ቁመናዋ፣ኃይሏ እና አቅሟ የምንመለከትበት ጊዜ አሁን ነው ብለዋል። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር አያይዘውም ካርታውን የማስተካከል እርምጃ አፍሪካ ወደ ላቀ የጋራ ራዕይ የምታደርገው አህጉራዊ ጉዞ አካል መሆኑን አንስተዋል። ይህም በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጠና (AfCFTA) አማካኝነት የኢኮኖሚ ትስስር ማጠናከርን፣ ሰላም እና ፀጥታን ማረጋገጥን፣ ዘላቂ ልማትን እውን ማድረግን እና በዓለም አቀፍ ውሳኔ ሰጪ አካላት ውስጥ የአፍሪካን ተሳትፎ ማሳደግን እንደሚያካትት በዝርዝር አስረድተዋል። የአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 የተሳሰረች፣ የበለጸገች እና ሰላማዊት አፍሪካን ለመገንባት የማዕዘን ድንጋይ ሆኖ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል። ሰላም እና ፀጥታን ማረጋገጥ፣ የኢኮኖሚ ትስስርን በማፋጠን እና የአፍሪካን ዓለም አቀፍ ተሰሚነት መጨመር የአፍሪካ ህብረት ቀዳሚ ትኩረቶች ናቸው ብለዋል። አፍሪካ በዓለም ፊት እውቅና ለማግኘት አትለምንም፤ ይልቁንስ በዓለም አቀፍ መድረክ የሷ የሆነውን ትክክለኛ ስፍራ በራሷ ባለቤትነት እየያዘች ነው። አሁን የሚጠበቅብን ይህንን ጠንካራ እምነት ወደ ህብረት፣ ሀብትና ብልጽግና፣ ሰላም እና ተደማጭነት መለወጥ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ሊቀመንበሩ አፍሪካ የምታስመዘግበው እድገት በዓለም አቀፍ መድረኮች በሚኖራት ውክልና ብቻ ሳይሆን፣ በዜጎቿ ላይ የኑሮ ጥራት መሻሻል ጭምር መለካት እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል። በዚህም መሰረት የአፍሪካ ህብረት የ2026 ዓመት ትኩረቱን በዘላቂ የንጹህ ውሃ አቅርቦት እና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አገልግሎት ላይ ማድረጉ፣ ህብረቱ አህጉራዊ ራዕዮችን ከዕለት ተዕለት የዜጎች ህይወት ጋር ለማያያዝ ያለውን ጽኑ ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ አመልክተዋል። በአፍሪካ ህብረት ቀን አከባበር አባል ሀገራት፣ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማህበረሰቦች፣ የአፍሪካ ተቋማት፣ የግሉ ዘርፍ፣ የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ ሴቶች እና ወጣቶች ተባብረው ይበልጥ የተሳሰረች፣ በራሷ አቅም የምትተማመን እና የራሷን እጣ ፈንታ በራሷ መወሰን የምትችል አፍሪካን እንዲገነቡ ሊቀመንበሩ ጥሪ አቅርበዋል። የምንፈልጋት አፍሪካ የሚለውን አህጉራዊ ራዕይ እውን ለማድረግ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ እና የሰርት ድንጋጌ ለቀጣዩ የአፍሪካ ትውልድ ዘላቂ የትምህርት እና የዕድገት መሰረት ሆኖ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። የነገዋ አፍሪካ በካርታ ላይ ብቻ የተሻለ ውክልና ያላት ብቻ ሳትሆን፤ በዓለም አቀፍ መድረክ ሉዓላዊነቷ የጸና፣ ጠንካራ ውስጣዊ አንድነት ያላት፣ ለህዝቦቿም ዘላቂ ብልጽግናን የምታጎናጽፍ አህጉር መሆን ይኖርባታል ነው ያሉት። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ለመላው አፍሪካውያን እና በውጭ ሀገር ለሚገኙ የአፍሪካ ዳያስፖራዎች ሰላማዊ እና የትብብር መንፈስ የተሞላበት የአፍሪካ ህብረት ቀን እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
የአፍሪካ ህብረት እና አሜሪካ አጋርነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ
Sep 4, 2026 679
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ)፡- የአፍሪካ ህብረት እና አሜሪካ ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን እና ሁሉን አቀፍ ትብብራቸውን የበለጠ ለማላቅ እንደሚሰሩ አስታወቁ። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሺያን ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። ውይይቱ በአፍሪካ ህብረትና አሜሪካ መካከል ያለውን ለረጅም ጊዜ የቆየ አጋርነት ማጠናከር እና በአህጉሪቱ ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር የአፍሪካና አሜሪካን ትብብር ታሪካዊ መሆኑን አውስተው በህብረቱ፣ በአባል ሀገራት እና በአሜሪካ መካከል የሁለቱንም ወገኖች ጥቅም በሚያስጠብቅ መልኩ ጠንካራ አጋርነት መገንባት እንደሚገባ አሳስበዋል። በምስራቅ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ሱዳን እየተደረጉ ላሉ አፍሪካ መር የሰላም ጥረቶች አሜሪካ እያደረገች ላለው ገንቢ አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሺያ በበኩላቸው አፍሪካ አሜሪካ ቀዳሚ ትኩረት የምትሰጣት አህጉር እንደሆነች ገልጸዋል። የጋራ ፍላጎቶችንና ግቦችን ከህብረቱ ኮሚሽንና ከአባል ሀገራት ጋር በመሆን ለማሳካት ያላቸውን ጽኑ ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል። በንግድ እና ኢንቨስትመንት፣ በመሰረተ ልማት ዝርጋታ፣ በዲፕሎማሲ፣ እንዲሁም በሰላምና ጸጥታ ያለውን ትብብር ማጠናከር እንደሚገባም አመልክተዋል። በውይይቱ ላይ በሱዳን ጉዳይ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ፣ የሰብአዊ እርዳታ ያለ ገደብ እንዲገባ እና በሲቪሎች የሚመራ ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ሂደት እንዲጀመር አጽንዖት ተሰጥቷል። በአፍሪካ ባለቤትነት የሚመሩ የሰላም ጥረቶች እና አሜሪካ የምትደግፋቸው የሰላም ሂደቶች በተቀናጀ መልኩ ለመተግበር ከስምምነት ላይ ተደርሷል። በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በመሰረተ ልማት እና በሰላም መስኮች የሁለቱን ወገኖች ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችሉ የትብብር መስኮች ተገምግመዋል። ሁለቱ ወገኖች በአፍሪካ ህብረትና በአሜሪካ ስትራቴጂክ ኢንቨስትመንት ማዕቀፍ ውስጥ የተደረጉ ስምምነቶችን ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። በሊቢያ ጉዳይ ዘላቂ የፖለቲካ መፍትሄ ማግኘት እንደሚያስፈልግም ተነስቷል። የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር እና ረዳት ሚኒስትሩ የሁለቱን ወገኖች ስትራቴጂካዊ አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከርና የትብብር አድማሱን ለማስፋት የጋራ ቁርጠኝነታቸውን መግለጻቸውን ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያ 76ኛውን የዓለም ጤና ድርጅት ስብሰባ ታስተናግዳለች
Aug 5, 2026 1980
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 29/2018 (ኢዜአ)፦ 76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ ስብሰባ (RC76) ከነሐሴ 18 እስከ 22 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። ስብሰባው ከዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ጽሕፈት ቤት ጋር በመተባበር የሚዘጋጅ ነው። በዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና መረጃ መሠረት፣ ስብስባው የቀጣናውን የጤና አጀንዳዎች ላይ መምከርና አህጉራዊ ትብብርን ማጠናከርን ያለመ ነው። የ47ቱ የአፍሪካ ቀጣና አባል አገራት የጤና ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ የዓለም አቀፍ ጤና መሪዎች፣ የልማት አጋሮች፣ ለጋሾችና የዓለም ጤና ድርጅት ተወካዮችን ጨምሮ ከ600 በላይ ተወካዮች በስብስባው ላይ ይሳተፋሉ። የስብሰባው ተሳታፊዎች በቀጣናዊ የጤና አቅዶች ላይ የተመዘገቡ ውጤቶችን የሚገመግሙ ሲሆን በአዳዲስ ስትራቴጂዎችና የውሳኔ ሀሳቦች ላይ ይመክራሉ። እንዲሁም የጤና ሥርዓቶችን ለማጠናከር፣ ሁለንተናዊ የጤና ሽፋን ተደራሽነትን ለማስፋፋት፣ የጤና ደህንነትን ለማሻሻልና የአደጋ ጊዜ ዝግጁነትን ለማሳደግ የሚረዱ የጋራ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። በኢትዮጵያ፣ በአፍሪካ ህብረትና በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) የዓለም ጤና ድርጅት ተወካይ ፕሮፌሰር ፍራንሲስ ካሶሎ፤ ስብሰባው አባል አገራት የቀጣናውን የጤና አጀንዳ እንዲቀርጹ፣ አጋርነታቸውን እንዲያጠናክሩ እና በመላው አፍሪካ ጤናማ፣ አስተማማኝና ጠንካራ ማህበረሰቦችን የመገንባት ሂደት ለማፋጠን ትልቅ እድል የሚሰጥ ነው ብለዋል። ተወካዩ አክለውም የኢትዮጵያ ስብሰባውን ማስተናገድ፤ ለቀጣናዊ ወንድማማችነትና ለጋራ ትብብር ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል። ይህ አህጉራዊ ጉባኤ የኢትዮጵያን የጤና ሥርዓት ስኬቶች፣ በተለይም መሰረታዊ የጤና አገልግሎቶችን በማስፋፋትና በቅርቡ በክልል የተከሰተውን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ተከስቶ የነበረውን የማርበርግ ቫይረስ በመቆጣጠር ረገድ የተመዘገቡ ውጤቶችን ለማሳየት ዕድል እንደሚፈጥር መረጃው አመልክቷል። ስብስባው የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) መቀመጫ የሆነችው አዲስ አበባ፣ የዲፕሎማሲ ማዕከልነቷን በመጠቀም ለጋራ የጤና ፈተናዎች የተቀናጀ አህጉራዊ ምላሽ ለመስጠት ስትራቴጂካዊ መድረክ እንድትሆን ያደርጋታል። በስብስባው ላይ የቴክኒክ ውይይቶች፣ አውደ ርዕዮች ፣ የሁለትዮሽ ስብሰባዎችና የሕዝብ ግንኙነት ስራዎች የሚካሄዱ ሲሆን፣ እነዚህም በአፍሪካ ተቋማት መካከል የጤናው ዘርፍ የፈጠራ ስራዎችንና የእውቀት ልውውጥን የሚያጎሉ እንደሚሆኑ ተገልጿል። የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ የቀጣናዊ ጽሕፈት ቤቱ የበላይ አካል ሲሆን፤ በየዓመቱ በመሰብሰብ የቀጣናውን የጤና ፖሊሲ ይወስናል፣ የድርጅቱን ሥራዎች ይገመግማል፣ እንዲሁም በመላው አህጉሪቱ ለሚከናወኑ የጤና ተግባራት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን አጀንዳዎች ያስቀምጣል።
ሐተታዎች
ጤናማ ዜጋ አምራች ሀገር፤ የመደመር መንግሥት የጤና ፖሊሲ ትሩፋት
Sep 15, 2026 314
አዲስ አበባ፤ መስከረም 5/2019 (ኢዜአ):-ኢትዮጵያ ነገን ታሳቢ ባደረገ መልኩ የተገበረችው አዲስ የጤና ፖሊሲ የመደመር መንግስት ቃልን በተግባር የመተርጎም ብቃትን ከሚያመላክቱ ትሩፋቶች መካከል ተጠቃሽ ነው። የመደመር መንግስት ባለፉት ስምንት ዓመታት ትኩረት ከሰጠባቸው ዘርፎች መካከል ማህበራዊ ልማት ዘርፉ ተጠቃሽ ነው። በዚሀ ዘርፍ ከሚመደቡት መካከል ደግሞ የጤና ዘርፉ ተጠቃሽ ሲሆን የኢትዮጵያ ህዝብ ፍትሃዊ እና ተደራሽ የጤና አገልግሎት ማግኘት የሚችልበትን ዕድል ለመፍጠር የፖሊሲ ማሻሻያ ማድረግን ጨምሮ የጤና መሰረተ ልማት ግንባታ እና የሰለጠነ የጤና ባለሙያ አቅም ግንባታ ላይ ውጤታማ ተግባራት አከናውኗል። ቅድሚያ መከላከል ላይ ትኩረት ያደረገውን የጤና ፖሊሲ በመከለስ ለአክሞ ማዳንም ትኩረት እንዲሰጥ መደረጉን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መንግስት ባለፉት ዓመታት በዘርፉ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ በርካታ ሆስፒታሎች ተገንብተው ወደ ስራ እንዲገቡ ማድረጉንና በዚህም በዘርፉ ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውን መግለጻቸው ይታወሳል። የመደመር መንግስት የህብረተሰቡ ጤና በተሟላ መልኩ ሲጠበቅ ምርታማነት ላይ ሊያመጣ የሚችለውን አዎንታዊ ሚና በሚገባ በመረዳት ከጤና መሰረተ ልማት ባሻገር ህብረተሰቡ አስቀድሞ ጤናውን ለሚጠብቅባቸው መሰረተ ልማቶች ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል። ለዚህ ነው በአሁኑ ወቅት አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ያሉ የኮሪደር ልማትና የወንዝ ዳርቻ ልማት ላይ በትኩረት እየሰራ የሚገኘው ይህ የመንግስት ጥረት እንደተጠበቀ ሆኖ የግል ዘርፉም የህብረተሰቡን ጤና ከመጠበቅ እና ለፖሊሲው ውጤታማነት በኩሉን ድርሻ መወጣት የሚችልበት ዕድል ተፈጥሯል። ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ የተገበረችው አዲስ የጤና ፖሊሲ እና በዘርፉ የወሰደቻቸው ውጤታማ እርምጃዎች አይበገሬ የጤና ስርዓት መዘርጋት አስችሏታል። መንግስት ጤናው የተጠበቀ ማህበረሰብ ለሀገር እድገትና ብልፅግና ወሳኝ መሆኑን በመገንዘብ ባለፉት ዓመታት ውጤታማ የፖሊሲ ማሻሻያ እርምጃዎች በመውሰዱ የጤና ቱሪዝም ተወዳዳሪነትን የሚያሳድጉ ስኬቶች ተመዝግበዋል። ከለውጡ በፊት ኢትዮጵያ ስትከተል የቆየችው በሽታ መከላከል ላይ ብቻ ያተኮረው የጤና ፖሊሲ፣ በጤና አገልግሎት አሰጣጥና የተቋማት ግንባታ እንዲሁም በዘርፉ ቴክኖሎጂ ከመጠቀም አንጻር ክፍተት ይታይበት ስለነበር ውጤታማነቱ ላይ የራሱን ተግዳሮት ደቅኖ ቆይቷል። የመደመር መንግስት የጤናው ዘርፍ ፖሊሲ ምሉዕ የሚሆነው በሽታ መከላከል ላይ ብቻ በማተኮር ሳይሆን አክሞ ማዳንንም የፖሊሲው የትኩረት ማዕከል ማድረግ ሲቻል መሆኑን በማመነ ፖሊሲው ይህንን ባካተተ መልኩ እንዲሻሻል አድርጓል። በተጨማሪም አዲስ አበባን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ማድረግ የሚያስችሉ ለጤና መሰረተ ልማት ግንባታ ለአካታች የጤና አገልግሎት ለጤና ፋይናንስ እና ለቴክኖሎጂ አጠቃቀም ውጤታማነት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ በመሰራቱ በመንግስትም ሆነ በግል ዘርፉ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ያካተቱ በርካታ የጤና መሰረተ ልማቶች ተገንብተው ወደ አገልግሎት እንዲገቡ ተደርጓል። ለዚህም ይመስላል በአዲስ አበባ ከተማ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን በማዘመን፣ በማስፋፋትና ጥራቱን በማሳደግ ደረጃውን የጠበቀና ዘመናዊ የህክምና አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉ መሳሪያዎችን በማስገባት የጤናውን ዘርፍ ለማዘመን እየተሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ መናገራቸው። በጤው ዘርፍ የአገልግሎትን ጥራት፣ ተደራሽነትና ፍትሐዊነትን ማረጋገጥ ቁለፍ ጉዳይ ነው። የመደመር መንግስት እነዚህን ችግሮች ለማቃለል ለአዳዲስ ሆስፒታሎች እና ጤና ጣቢያዎች ግንባታ እንዲሁም ለነባሮቹ የጤና ተቋማት የማሻሻያ እና የማዘመን ተግባራት በመከናወናቸው በአገልግሎት ጥራት ተደራሽነትና ፍትሃዊነትን ከማረጋገጥ አንጻር ውጤቶች ተመዝግበዋል። በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የህክምና ተቋማትን በዘመናዊ የህክምና ግብዓት ማደራጀትና አቅማቸውን ማሳደግ ፍትሃዊ እና ተደራሽ የሆነ እንዲሁም አስተማማኝ የህክምና አገልግሎት በመስጠት የጤና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የተያዘውን ርዕይ ለማሳካት አይነተኛ ሚና ይኖረዋል። ባለፉት ስምንት ዓመታት በጤና ዘርፍ የነበሩ ክፍተቶችን መቅረፍ የሚያስችሉ ተግባራት መከናወናቸውን የሚገልጹት የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ በዚህም የመንግስት የጤና ተቋማት ቁጥርና የሀገር ውስጥ ምርት ድርሻ ማደጉን በመጥቀስ የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድን ሽፋን እና የዜጎች ተጠቃሚነት ማሳደግ መቻሉን ለዘርፉ ዕድገት ጥሩ ማሳያ ነው። ባለፉት ስምንት ዓመታት በዘርፉ በተከናወኑ ተግባራት እምርታ መመዝገቡን የመድሃኒት፣ የክትባት እና የህክምና ግብዓቶች ምርት አቅርቦት እና ቁጥጥር መጨመሩን እንዲሁም በጤና ፋይናንስ ስርዓት ላይ የተመዘገበውን ለውጥ በማሳያነት ይጠቅሳሉ። ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በተለይ በጤናው ዘርፍ የተከሰቱ ዓለም አቀፍ ወረርሽኞችንና በዘርፉ የተስተዋሉ ተግዳሮቶችን ወደ ዕድል በመቀየር አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ ችላለች። በዚህም የወረርሽኝ ልየታ እና ቁጥጥር፣ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና ክብካቤ፣ የጤና ባለሙያዎችን ማብቃትና ቁጥራቸውን ማሳደግ፣ የዲጂታል ጤና እና በዘርፉ የተከናወኑ ልዩ ልዩ የበጎ አድራጎት ተግባራት በጤና ዘርፉ የተመዘገቡ ስኬቶች መሆናቸውን ሚኒስትሯ መጥቀሳቸው ለተፈጠረው አቅም ጥሩ ምሳሌ ነው። የመደመር መንግስት ለማህበራዊ ልማት በተለይም ለጤናው ዘርፍ በሰጠው ትኩረት ምክንያት በርካታ ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል። እነዚህ በዘርፉ የተከናወኑ ውጤታማ ተግባራት ለጤና ዲፕሎማሲ ዘርፍ እመርታ አበርክቷቸው ከፍተኛ መሆኑን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር መቅደስ ዳባ የገለጹ ሲሆን፤ ይህም ኢትዮጵያ የተለያዩ የዘርፉ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎችን እንድታስተናግድ ተመራጭ እንዳደረጋት እና ከአፍሪካ በቀዳሚነት ተመርጣ ዓለም አቀፍ የጤና ድርድሮችንና ንግግሮችን እንድትመራ እንዳስቻላትም እንዲሁ።
የሰው ተኮር ፕሮጀክቶች እመርታ፤ የአረጋውያን በረከት፣ የታዳጊዎች የተስፋ ማዕድ
Sep 14, 2026 409
ሀገር በታሪክ ሰሪዎችና ባለውለታዎች ጀግኖች አባቶች ገድል፣ በነገ ተስፋዎች ጽናት ትገነባለች፤ በጠንካራ ተቋማትና ተስፋን በሰነቁ ፕሮጀክቶች ትጸናለች። የመደመር መንግሥት የዜጎችን ማኅበራዊና ምጣኔ-ሀብታዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከነደፋቸው ውጥኖች መካከል ሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶች ይጠቀሳሉ። ሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶች የአቅመ ደካሞችን ቤት በማደስ፣ በተማሪዎች ምገባ እና በወጣቶች ሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ ብቻ የተመረኮዙ አይደሉም፤ ይልቁንስ የሀገር ባለውለታዎች ካስማ፣ የነገ ተስፋዎች ማገር ናቸው። የመደመር መንግሥት ማኅበራዊ ፍትሕ ማስፈን ቀዳሚ አጀንዳው ሲያደርግ፣ የትናንት የሀገር ጀግኖች ውለታ በመመለስ እና ለነገ ታዳጊዎች ብርሃን በመፈንጠቅ ነው። በኢትዮጵያ በከተማና ገጠር፣ በአዛውንቶችና ወጣቶች መካከል አንዳችም ልዩነት ሳይፈጠር የአካባቢያቸውን የመልማት ጸጋ አውጥቶ መጠቀም የሚያስችሉ የዜጎች ሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶች ተደራሽ ሆነዋል። በትምህርት ቤቶች የተማሪዎች ምገባ አዲስ አበባ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና የተቸረው ውጤት አስመዝግባለች፤ ሌሎች ክልሎችም ብዙ ተምረውበታል። መንግሥት በመዲናዋ በ2018 ዓ.ም በትምህርት ቤቶች ምገባ መርሃ ግብር 976 ሺህ 702 ተማሪዎች በቀን ሁለት ጊዜ ቁርስና ምሳ መመገብ የሚያስችል ሥርዓት በማንበር ህዝባዊነቱን በተግባር ገልጧል። ሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች ኢኒሼቲቩን እንደ ትምህርት በመውሰድ የትምህርት ቤት የተማሪዎች ምገባ መርሃ ግብር በመጀመር የተማሪዎችን ከትምህርት ገበታ የማቋረጥ ምጣኔ ቀንሰዋል፤ የተማሪዎችን ትኩረት በመሰብሰብ ለውጤታማ መማር ማስተማር ሂደት መሰረት ጥለዋል። የደጃዝማች ወንድይራድ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ ናታኒም በላይ፣ በትምህርት ቤት የተማሪዎች ምገባ መርሃ ግብር በመጀመሩ ትምህርቱን በሙሉ ትኩረት ሳያቋርጥ የሚማርበት ዕድል ማግኘቱን ገልጿል። በትምህርት ቤቶች የምገባ መርሃ ግብር መጀመሩ ለእናቶች የሥራ ዕድል በመፍጠር ገቢ ማግኘትና የአዕምሮ እርካታ እያገኙ መሆኑን የገለጹት ደግሞ በአፄ ነአኩቶ ለአብ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማሪዎች መጋቢ ወይዘሮ መሰረት እንዳለ ናቸው። በአዲስ አበባ 30 የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከላትን በማቋቋም ራሳቸውን መመገብ ለማይችሉ አቅመ ደካማ ዜጎች የተመጣጠነ ምግብ የሚያገኙበት ምቹ ምኅዳር ተፈጥሯል። የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ 30ኛውን የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ሥራ ሲያስጀምሩ፣ የነዋሪዎችን ሕይወት ለመለወጥና ለኑሮ ምቹ አካባቢን መፍጠር ዋና አጀንዳቸው መሆኑን ተናግረዋል። የምገባ ማዕከላትን ማስፋፋት አቅመ ደካማ ወገኖችን ከመመገብ ባለፈ ለነዋሪዎቻችን ያለንን ክብር የምናሳይበትና ለዜጎች የሥራ ዕድል የምንፈጥርበት ነው ብለዋል። ሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶች በመዲናዋ ማኅበራዊ ፍትሕን በማንገስ የኢትዮጵያን ብልጽግና ማረጋገጥ እንደሚያስችሉ ተናግረዋል። ሀገር ላጸኑ የሃገር ባለ ውለታዎች አባቶችና እናቶች በንጹህ፣ ጽዱና ምቹ ቤት የተደላደለ ሕይወት እንዲመሩ ተደርጓል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ታኅሣሥ 2016 የአዋሬ መንደር የጋራ መኖሪያ ህንፃ አሰርተው ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ወገኖች አስተላልፈዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅቱ ሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶች በአጭር ጊዜ ለውጥ የሚያመጡ፣ የዜጎችን የአኗኗር ዘይቤ የሚያሻሽሉ እና ሀገር የሚያሻግሩ መሆናቸውን ገልጸዋል። አዋሬን እንደ ምሳሌ በመጥቀስ፤ ዕውቀት፣ ሀብትና ጉልበት ተሰናስለው ለሀገርና ሕዝብ ካስማና ማገር የሚሆኑ ተጨባጭ ውጤቶች ማምጣት እንደሚቻል አስረድተዋል። "እንሠራለን፣ ኢትዮጵያን እንቀይራለን፣ ኢትዮጵያን እናበለጽጋለን" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ውብ ኢትዮጵያን ለትውልድ ለማስረከብ ዕድሉ በኢትዮጵያውያን እጅ ላይ እንዳለ አረጋግጠዋል። የአቅመ ደካሞችን ቤት መጠገን፣ አለፍ ሲልም አዳዲስ ምቹና ዘመናዊ የመኖሪያ መንደሮችን ከተሟላ የመንገድ፣ የውሃ፣ መብራትና መሰል መሠረተ ልማት ጋር ሰርቶ ማስረከብ የመደመር መንግሥት መገለጫ ሆኗል። በመዲናዋ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ወገኖች ተሰርተው የተላለፉ ቤቶች ተጠቃሚ የሆነው ወጣት ታምራት ተመስገን የአካል ጉዳተኛ በመሆኑ በርካታ ፈተናዎችን ማስተናገዱን ገልጿል። ይሁን እንጂ አዲስ በተረከበው ቤት እንደ ልብ መንቀሳቀስና ሕይወቱን ማሻሻል የቻለበት ዕድል እንደተፈጠረለት ገልጿል። በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ቤታቸው የታደሰላቸው እናት ወይዘሮ ታየሁ መኮንን "ቤት ነው ለማለት እንኳን በማያስደፍር" ቤት ውስጥ ይኖሩ እንደነበር አስታውሰዋል። በሸራና በላስቲክ ከተጠጋገነ፣ የግድግዳው አፈር ከሚናድ ቤት ውስጥ መቆየታቸውን አስታውሰው፣ "ቤቴ በመታደሱ 'ቤቱ እላዬ ላይ ይደረመሳል' ከሚል ሰቀቀን ተላቅቄ፣ ያለ ሀሳብ ጎኔን ማሳረፍ ችያለሁ" ብለዋል። በነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል ከጎዳና ሕይወት ወደ ለውጥ አብነት የተሸጋገሩ ወጣት ልጃገረዶች እልፍ ናቸው። ማዕከሉ በአስከፊ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ ለነበሩ ሴቶች አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ሕክምና በማድረግ፣ ዘላቂ የሕይወት ክህሎት ሥልጠና በመስጠት ሕይወታቸውን የሚያሻሽሉበት ተቋም ነው። ማዕከሉ በ2016 ዓ.ም ሥራ ከጀመረ በኋላ በአምስት ዙሮች ሦስት ሺህ 259 ሴቶችን በማሰልጠን ወጣቶች ተስፋ እንዳላቸውና ለለውጥ ቅርብ እንደሆኑ በተግባር አሳይቷል። በነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል በ2018 ዓ.ም በአምስተኛ ዙር በዶሮ እርባታ ሥልጠና ወስዳ የተመረቀችው ትዕግስት ፀጋዬ፣ ማዕከሉ ከጎዳና ሕይወት ወጥታ ጠንካራ ስብዕና መገንባት የሚያስችል አቅም እንደፈጠረላት ተናግራለች። በማዕከሉ የቤት አያያዝ ሥልጠና የወሰደችው መሰረት አበራ በበኩሏ፣ ከጎዳና ላይ ከነበረችበት አሰልቺ ሕይወት ተላቃ ጠንካራ የራስ መተማመን በመገንባት ነገን የምታልም ሴት እንዳደረጋት ገልጻለች።
የጭስ አልባው ኢንዱስትሪ ትንሳኤ፡ የመደመር እሳቤ ትሩፋት
Sep 13, 2026 595
ኢትዮጵያ ሺህ ዘመናትን የተሻገሩ ታሪካዊ፣ ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊና ተፈጥሯዊ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶችን በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) አስመዝግባለች። በዓለም የሚዳሰስ ቅርስነት ዝርዝር ከሰፈሩ የኢትዮጵያ ቅርሶች መካከል የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፣ የአጼ ፋሲለደስ አብያተ መንግሥታት፣ የአክሱም ሐውልቶች፣ የሐረር ጀጎል ግንብ፣ የጢያ ትክል ድንጋይ፣ የአዋሽና የኦሞ ሸለቆዎች፣ የኮንሶ ባህላዊ መልክዓ ምድር፣ የጌዴኦ ባህላዊ መልክዓ ምድር፣ የራስ ዳሽንና የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርኮችና ሌሎችም ይገኙበታል። በማይዳሰስ ቅርስነት ከሰፈሩ የኢትዮጵያ ቅርሶችም የመስቀል ደመራ በዓል፣ ፊቼ-ጫምባላላ፣ የገዳ ሥርዓት፣ ጥምቀት፣ ሹዋሊድ፣ የሶማሌ ባህላዊ የዳኝነት ሥርዓት፣ የወላይታ ጊፋታና የመሳሰሉት ሕያው ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊና ማኅበረሰባዊ ትውፊቶችን ያካትታሉ። እነዚህ ኢትዮጵያውያን ለዓለም ሕዝብ ያበረከቷቸው የመስህብ ሀብቶችም ለሀገር የኢኮኖሚ ዕድገት፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በገጽታ ግንባታና ለአካባቢ ልማት የሚያበረክቱት ዕድል በቀላሉ የሚታይ አይደለም። የመደመር መንግሥትም ይህንን የኢትዮጵያውያንን ሰፊ የቱሪዝም አቅም በመረዳት፣ ቱሪዝምን በብዝኅ ዘርፍ የኢኮኖሚ ዕድገት ዕይታው ውስጥ ትኩረት ከሰጣቸው የልማት መስኮች አንዱ አድርጎታል። በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያውም ቱሪዝም ከአምስቱ የብዝኅ የኢኮኖሚ አዕማድ አንዱ እንዲሆን በመደረጉ ዘርፉ የሚያስገኘው ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ የበለጠ ትኩረት እንዲያገኝ አድርጓል። ይህም ዘርፉ ከነበረበት ተለምዷዊና አዝጋሚ ዕድገት የሚላቀቅበትን ዘመናዊ የቱሪዝም መዳረሻ መሠረተ ልማቶችን በመገንባት፣ ነባር ቅርሶች በማደስና በመጠገን ውጤታማ ሥራ ተሰርቷል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሐሳብ አመንጪነት በገበታ ለሸገር፣ በገበታ ለሀገርና በገበታ ለትውልድ የመስህብ መዳረሻ ልማት የቱሪዝሙን ዘርፍ ማንሰራራት ያበስሩ ፕሮጀክቶች እውን ሆነዋል። ለአብነትም በገበታ ለሸገር በአዲስ አበባ የተገነቡ የወዳጅነት፣ አንድነትና የእንጦጦ ፓርኮች፤ የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማት የመዲናዋን ዓለም አቀፍ ገጽታ መቀየር ያስቻለ ምቹ ምኅዳር ፈጥረዋል። በገበታ ለሀገርና ለትውልድ የመዳረሻ ልማት ፕሮጀክትም ጎርጎራ፣ ወንጪ፣ ኮይሻ፣ ሐላላ ኬላ፣ ደንዲ ኢኮ ሎጂ፣ አርባ ምንጭ ኮንፈረንስ ሪዞርት፣ ሎጎ፣ ሸበሌ ሪዞርት፣ ኒን ሊ ፓልም ሎጂ እና የመሳሰሉት እንዲገነቡ አስችሏል። ይህም የመደመር መንግሥት የኢትዮጵያን የከተማና ገጠር የቱሪዝም መዳረሻ አሰናስሎ በማልማት ለሀገር የኢኮኖሚ ዕድገት የሚያበረክተውን ገንቢ ሚና መወጣት የሚችልበትን ከፍተኛ ዕድል ከፍቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቅርቡ በቱሪዝም ጉዳዮች ላይ ከኤንቢሲ ኢትዮጵያ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳሉት፤ በቱሪዝም ዘርፍ የተከናወኑ የልማት ሥራዎች የሀገሪቱን የቱሪዝም መስህብ ስፍራዎች በማስፋፋትና የመዳረሻ ብዝሃነትን በማሳደግ ተጨባጭ ውጤቶች ተመዝግበዋል። በተለይም ለዘርፉ በተሰጠው ትኩረት የኢኮኖሚ መነቃቃትን በመፍጠር በሥራ ዕድል ፈጠራም ጭምር ከአምስቱ የብዝሃ ዘርፍ የኢኮኖሚ ማሻሻዮች መካከል አንዱ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም የጎብኚዎች ፍሰትን በመጨመርና የቆይታ ጊዜ በማራዘም የቱሪዝም ብዝኅ እመርታዊ ውጤቶች በየአካባቢው ኢኮኖሚን በማነቃቃት የገጠርና የከተማ ልማትን ለማስተሳሰር አዲስ ዕድል ፈጥረዋል ብለዋል። የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ እንደገና አበበ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የመደመር መንግሥት የቱሪዝም መዳረሻ ልማትና የቅርስ ዕድሳት ውጤታማ ሥራ የዘርፉን ዳግም ውልደት ያበሰሩ ለውጦችን አምጥቷል ብለዋል። ይህም የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ጎብኝዎችን የቆይታ ጊዜ በማራዘም ዘመናዊና የተሰናሰለ የከተማና ገጠር የመስህብ መዳረሻና እንቅስቃሴ እንዲፈጠር ማስቻሉን ገልጸዋል። የቱሪዝም አስጎብኚ ድርጅቶች እንደሚሉትም፤ የኢትዮጵያ መጠነ ሰፊ የመዳረሻ ልማትና የቅርስ ጥበቃ ውጤታማ ሥራ ለቱሪስቶች መዳረሻና ጉብኝት ምቹ ምኅዳርን በመፍጠር የሀገርን ገጽታ የገለጡ ናቸው። የታላቁ የኢትዮጵያ አስጎብኚ ድርጅቶች ማኅበር ምክትል ፕሬዝዳንት እንቁ ሙሉጌታ እንደገለጹት፤ የቱሪዝም መሠረተ ልማት መስፋፋት የቱሪዝም ፍሰቱን በማሳደግ ተጠቃሚነትን እያሳደገ ነው። የኤደን ላንድ ቱር ኤንድ ትራቭል ባለቤት እንዳልካቸው የምሩ፤ ለቱሪዝም ልማት የተሰጠው ትኩረት አማራጭ የመዳረሻ ስፍራዎች በማስፋፋት ለመስህብ መዳረሻ ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል። የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ጎብኝዎች እንደሚሉትም፤ በኢትዮጵያ ታሪካዊ፣ ባህላዊ፣ ሃይማኖታዊና ተፈጥሯዊ መስህቦችን መጎብኘት የሚያስችሉ ውጤታማ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል። ከዓለም አቀፍ ጎብኝዎች መካከል ጀርመናዊው ሉካስ ኩፕፈርናጌል፤ ኢትዮጵያ በአዲስ አበባና ሌሎች አካባቢዎች የገነባቻቸው አስደማሚ የቱሪዝም መዳረሻዎች ሀገሪቱን አፍሪካዊት ግንባር ቀደም የቱሪስት ማዕከል የሚያደርጉ ናቸው ብለዋል። ሌላኛዋ አስተያየት ሰጪ የሀገር ውስጥ ጎብኚ ምሕረት አሰፋ በበኩላቸው፤ የለሙት የቱሪዝም መዳረሻዎች የሀገርን ገጽታ የቀየሩ፣ ውብ፣ ጽዱና ዓለም አቀፍ የመስህብ ተወዳዳሪነትን የሚያጎለብቱ መሆናቸውን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በታሪክ፣ በሃይማኖት፣ በባህልና በተፈጥሮ የታደለችውን ሀብት ወደ ኢኮኖሚያዊ አቅም የመቀየር ሥራ በስፋት እያከናወነች ይገኛል። የመደመር መንግሥት ቱሪዝምን የብዝኅ የኢኮኖሚ አዕማድ አካል በማድረግ የገነባቸው ማራኪ የመዳረሻ ስፍራዎች የዘርፉን ማንሰራራት በማጽናት ለኢኮኖሚ ዕድገት የሚያበረክተውን አቅም ለማጎልበት ያለመ ነው። ቀጣዩ የዘርፉ ጉዞም የኢትዮጵያን ቅርስና ተፈጥሯዊ ጸጋ በመጠበቅ የመዳረሻ ብዝኅነትን በማስፋፋትና የአገልግሎት ጥራትን በማሳደግ ቱሪዝምን ከተስፋ ወደ ተጨባጭ የኢኮኖሚ ውጤት የሚያሻግር ይሆናል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የጥቁር ሕዝቦች የመቻል ተምሳሌት
Sep 9, 2026 420
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የጥቁር ሕዝቦች የመቻል ተምሳሌት መጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም የኢትዮጵያውያን የጋራ ቃል ኪዳን የታሰረባት ታሪካዊ ክስተት ናት። ዕለቷም የዓባይን የሺሕ ዘመናት ገደብ የሌለው ጉዞ በጉባ ተራሮች ግርጌ ልጓም ለማበጀት የታሰረች ቀለበት ሆና ተመዝግባለች። ኢትዮጵያውያን ቃል ኪዳናቸውን ባሰሩ ማግስት የግብፅና ሌሎች ታሪካዊ የኢትዮጵያ ጠላቶች ጩኸትና የጥፋት ሴራ በግልጽ መታየት ጀመረ። በተለይም ግብፅ ኢትዮጵያ ውስጣዊ መረጋጋት እንዳይኖራት የውስጥ ታጣቂዎችን ከመደገፍ ጀምሮ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በራፍ ጭምር የሀሰት ክሶችን እስከማሰማት የደረሰ የሺሕ ዘመናት ዓባይን በብቸኝነት የመጠቀም አባዜዋን አንጸባርቃለች። ትብብርን ከፅናት አሰናስለው የቀጠሉት ኢትዮጵያውያን ለአሥራ አራት ዓመታት የታላቁ ሕዳሴ ግድብን የማደናቀፍ የታሪካዊ ጠላቶችን ሴራ በጋራ በመመከት ለፍጻሜ አብቅተውታል። የሀገርን ሉዓላዊነት በጽናት የማስከበር የአርበኝነት ተጋድሎን ከዓድዋ ጀግኖች የወረስን እኛ ኢትዮጵያውያን በጉባ ተራሮች ግርጌ በደም፣ በላብ፣ በዕንባና በውኃ ጠብታ ታላቁ የሕዳሴ ግድብን በዓባይ ላይ አንጸናል። ጳጉሜን 4 ቀን 2017 ዓ.ም የአዲስ ዓመት ዋዜማም ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን በማጠናቀቅ ለፍጻሜ በማድረስ አብስሯል። ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሺሕ ዘመናት የልማት ጥማትን በማርካት የብልፅግና ፍኖት ብስራት ሆኗል። ታላቁ ሕዳሴ ግድብ ለሌላ የልማት ዕቅድ ወጋገን የፈነጠቀ የንጋት ሐይቅ ፈጥሯል። ግድቡ በኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝቦቿ ትብብር ብቻ ያለ አንዳች የውጭ ድጋፍና ብድር ለፍጻሜ መብቃቱም ለአፍሪካውያን የመቻል ትዕምርት ሆኗል። በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ብስራት በጉባ ተራሮች ግርጌ የከተሙ የምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ሀገራት መሪዎች የመሰከሩት ጥሬ ሐቅም ይህ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በምረቃው ዕለት እንደገለጹት፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የጥቁር ሕዝቦችን የታሪክ ክብር ያደሰና ለአፍሪካውያን የመቻል ውጤት ነው። በወቅቱም የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያን የብልፅግና ጎህ ያበሰረ፣ ቀጣናዊ የኃይል ትስስርና የጋራ ዕድገት መንገድ የጠረገ ፓን-አፍሪካኒዝም ፕሮጀክት መሆኑን መግለጻቸው ይታወሳል። የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅ አፍሪካውያን አንጡራ ሀብታቸውን በራሳቸው አቅምና ጥረት በማልማት ታላላቅ የልማት ገድሎችን መፈጸም እንደሚችሉ ያመላከተ የጥቁር ሕዝቦች ሁሉ የኩራት ምንጭ መሆኑንም ጠቁመዋል። የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር እና የክብር እንግዳ መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ታላቁ ሕዳሴ ግድብ የታዳሽ ኃይል ሽግግርን በማፋጠን የአፍሪካውያንን የጋራ ምኞት የሚያሳካ ህያው ምልክት ነው ማለታቸው ይታወሳል። የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅና ለምረቃ መብቃትም የኢትዮጵያውያንን ለአንድ ሀገራዊ የልማት ርዕይ በጋራ የመቆም ውጤታማነትን በተግባር ለዓለም የገለጠ ፓን-አፍሪካኒዝም ፕሮጀክት መሆኑን መስክረዋል። በዚሁ ወቅት የተገኙት የጅቡቲ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ዑመር ጌሌ በበኩላቸው እንደገለጹት፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የዘመናዊው ዓለም የአፍሪካውያን የኩራት ምንጭ የሆነ የልማት ድል መሆኑንና መላውን ዓለም ያስደነቀ የኢትዮጵያ ስኬትና የወዳጆቿ የጋራ ሀብት ነው። ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ብሔራዊ ፕሮጀክት ብቻ ሳይሆን አስደማሚ የፓን-አፍሪካኒዝም መግለጫ ፕሮጀክት ነው ያሉት ደግሞ በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ምረቃ ላይ የታደሙት የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ናቸው። የኢትዮጵያውያን ብሔራዊ ፕሮጀክት የሆነው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ስኬት አፍሪካውያን በተባበረ ክንድ አቅማቸውን በመጠቀም የራሳቸውን ዕድል በራሳቸው መወሰን እንደሚችሉ ትምህርት ያስተላለፈ ነው ሲሉም መግለጻቸው ይታወሳል። ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ የምህንድስና ልህቀትም አህጉሪቱ ለብልፅግናዋ የሚረዱና ሁለንተናዊ ለውጥ የሚያመጡ ሁነኛ የልማት ፕሮጀክቶችን በራሷ አቅም የመገንባት ብቃት እንዳላት ማረጋገጫ ነው። በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ምረቃ ላይ የተገኙት የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ እንደተናገሩት፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አህጉራዊ ትብብርና ግንኙነትን የሚያጠናክር የወንድማማችነት ምልክት ነው። ፕሬዝዳንቱ አክለውም ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሁላችንንም ተጠቃሚ የሚያደርግ የጋራ ጉዳያችን ነው በዚህም ዕድለኞች ነን ሲሉ መግለጻቸውም ይታወሳል። ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ "ለእኛ እንደ አንድ ፕሮጀክት ሳይሆን ሀላፊነትን የምንጋራበት ነው" ያሉት ፕሬዝዳንቱ አፍሪካውያን ከተባበርን ስኬቶችን ማስመዝገብ እንደምንችል ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል። የላይኛውና የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት መበልጸግ የሚችሉት በጋራ እንደ አንድ ማህበረሰብ በመስራት ነው። ውሃና ሌሎች ተፈጥሯዊ ሀብቶች በድንበር የተወሰኑ ሳይሆኑ የወደፊት እጣ ፈንታችንን የሚወስኑ ናቸው ብለዋል። የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት በበኩላችው እንደሚሉት፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የአንድነት እና የመስዋዕትነት ምልክት ነው። ግድቡ ፕሮጀክት ብቻ ሳይሆን የአንድነትና የመስዋዕትነት ምልክት ነው፡፡ የግድቡ ግንባታ እውን መሆን ህዝብ ከተባበረ እና ለአንድ ዓላማ በአንድነት ከቆመ ምን መስራት እንደሚችል ማሳያ መሆኑን ነው ያነሱት ፕሬዝዳንቱ፤ ይህም ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ የኩራት ምንጭ ነው ማለታቸው ይታወሳል። ፕሬዝዳንቱ አክለውም ግድቡ የኃይል ፍላጎትን ከማሳካት ባለፈ ለልጆቻችን የምንመኘውን የበለጸገ ሀገርና አህጉር ለማስረከብ እድል የሚፈጥር ነው ብለዋል። ይህ በታሪክ ድርሳናት ሰፊውን ድርሻ የሚይዘው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ስኬት የኢትዮጵያዊያን የቃል ኪዳናቸው ማህተም ሆኖ ለዘላለም ይኖራል።
ትንታኔዎች
የተማሪዎች ምገባ አያሌ ትሩፋቶች
Sep 17, 2026 120
በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ466 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ህጻናት በትምህርት ቤት የምገባ ፕሮግራም ተጠቃሚ መሆናቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ። የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራሞች የምግብ አማራጭ ብቻ ሳይሆኑ በትምህርት፣ በጤና እና በኢኮኖሚያዊ መረጋጋት ላይ ያላቸው አዎንታዊ ተጽእኖ እጅግ የገዘፈ ነው። መርሃ ግብሩ የተማሪዎችን የመማር ምጣኔ በመጨመር በተቃራኒው መጠነ ማቋረጥን በእጅጉ በመቀነስ ረገድ ጉልህ ፋይዳ አለው። ፕሮግራም በተለይም በአደጋ ተጋላጭና ድርቅ ባለባቸው አካባቢዎች ወደ ትምህርት ገበታ የሚመጡ ልጆችን ቁጥር እንዲጨምር ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጓል። ተማሪዎች በቀን ውስጥ የሚያገኙት የተመጣጠነ ምግብ በክፍል ውስጥ ያላቸውን የንቃት፣ የማስታወስ እና የትምህርት መቀበል አቅም በማሳደግ የትምህርት ውጤታቸውን በከፍተኛ ደረጃ አሻሽሏል። የኢትዮጵያ የህብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት (EPHI) እና የዓለም የምግብ ድርጅት መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ ምገባው ህጻናት ከስድስቱ የምግብ ምድቦች የተውጣጡ አልሚ ምግቦችን እንዲያገኙ በማድረግ የተመጣጠነ ምግብ እጥረትንና የጤና አደጋን ይቀንሳል። የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦቱ የህጻናትን አጠቃላይ አካላዊ እድገት፣ የበሽታ መከላከል አቅም (Immunity) እና የአዕምሮ ጤና በመጠበቅ ጤናማ ትውልድ እንዲፈጠር የሚያስችል ነው። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዓለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) እ.አ.አ በ2030 ሁሉም ህጻናት የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኙ አቅዶ እየሰራ ይገኛል። በአፍሪካ ደረጃ ከ100 ሚሊዮን በላይ ህጻናት የተለያዩ የትምህርት ቤት ምገባ መርሃ ግብሮች ተጠቃሚ እንደሆኑ መረጃዎች ያሳያሉ። በኢትዮጵያም የትምህርት ቤቶች ምገባ መርሃ ግብር በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ህጻናትን ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የተማሪዎች ምገባ መርሃ ግብር ከ9 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ተማሪዎች በቀን ሁለት ጊዜ አገልግሎቱን እያገኙ መሆኑን ገልጸው፤ ሀገሪቱ የምትመግበው ህጻናት ቁጥር ከአንዳንድ ሀገራት የህዝብ ቁጥር ጋር የሚስተካከል መሆኑን መግለጻቸው ይታወሳል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ታዳጊ ህፃናት ትምህርት ቤት መሄድ ሲገባቸው በዳቦ ምክንያት እንዳይስተጓጎሉ ማድረግ ሊተኮርበት የሚገባ ዋነኛ የሀገር ግንባታ ጉዳይ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል። በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደረጃ የምገባ ኤጀንሲ በማቋቋም ተማሪዎችን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ የማድረግ ዘላቂ ተግባር በስኬት በመከናወን ላይ ይገኛል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ በመዲናዋ በሚገኙ በመንግሥት ትምህርት ቤቶች ከቅድመ-አንደኛ እስከ መካከለኛ ደረጃ ለሚማሩ አንድ ሚሊየን የሚጠጉ ተማሪዎች በቀን ሁለት ጊዜ (ቁርስ እና ምሳ) በነፃ ይመገባሉ። ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተሞክሮ በመነሳት ይህ ስራ በፈረንሳይ ፓሪስ እና በብራዚል ሪዮ ዲ ጄኔሮ በተከናወኑ ዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ተወዳድረው አሸናፊ በመሆን የሜላን ፓክት ሽልማት (Milan Pact Award) ተቀዳጅቷል። እ.አ.አ በ2022 በብራዚል ሪዮ ዲ ጄኔሮ በተካሄደው 8ኛው የዓለም አቀፍ የከተሞች የምግብ ፖሊሲ ስምምነት ጉባኤ ላይ የተበረከተው ይህ ታሪካዊ የሜላን ፓክት ሽልማት፣ አዲስ አበባ መርሃ ግብሩን በዘላቂነትና በተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት ዘርፍ እጅግ ውጤታማ በሆነ መንገድ በመምራቷ የተሰጠ ነው። በተጨማሪም እ.አ.አ በ2021 በጣሊያን ሮም በተካሄደው የዓለም ሥነ ምግብ ኮንፈረንስ እና በሚላን የምገባ ፎረም ላይ መዲናዋ የምገባ ፎርም ምርጥ ተሞክሮ በሚል እውቅና አግኝታለች። እነዚህ ዓለም አቀፍ ሽልማቶች የተሰጡት መርሃ ግብሩ የተማሪዎችን የምገባ ችግር ከመቅረፍ ባለፈ፣ ከተማዋ የምግብ ስርዓትን በዘላቂነት በመምራትና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን እናቶች በህብረት ስራ ማህበራት በማደራጀት ማህበራዊ ፍትህና የኢኮኖሚ ነፃነት እውን እንዲሆን በማድረጓ ነው። የአዲስ አበባ አርአያነት ያለው ተግባር አሁን ላይ ወደ ክልሎች እና ከተሞች በስፋት እየተዳረሰ ይገኛል፤ እንደ ኬንያ ያሉ የአፍሪካ ሀገራት የልዑካን ቡድኖችም መዲናዋን በመጎብኘት ልምድ እየቀሰሙ ይገኛሉ። የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት (EPHI) የተማሪዎች የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦትን የተመለከተ አዲስ የስነ ምግብ መጽሐፍ አዘጋጅቶ ተግባራዊ አድርጓል። ከንቲባ አዳነች አቤቤ መርሃ ግብሩ ተማሪዎች በኢኮኖሚ አቅም ማነስ ምክንያት ይሰማቸው የነበረውን የስነ-ልቦና ጫናና የድፍረት ማጣት ሙሉ በሙሉ በመቅረፍ ማህበራዊ ፍትህ ማረጋገጡን በአንድ ወቅት ገልጸዋል። ምግብ በማብሰልና በማቅረብ ሂደት ላይ ከ25 ሺህ በላይ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው እናቶች በህብረት ስራ ማህበራት ተደራጅተው ቋሚ የገቢ ምንጭ እንዲያገኙ በማድረግ የሴቶችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አቅም ገንብቷል። የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ በሀገር አቀፍ የተማሪዎች የምገባ መርሃ ግብሩ አብዛኛው በጀት በሀገር ውስጥ አቅም እና በመንግስት የሚሸፈን ነው። መርሃ ግብሩ ከተጀመረ ወዲህ በተለይም ድርቅና የአየር ንብረት ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የተማሪዎች ምዝገባ በ10 በመቶ እንዲጨምር እና የትምህርት ማቋረጥ ምጣኔ በእጅጉ እንዲቀንስ አድርጓል። ትምህርት ቤቶች የወጪ ጫናቸውን እንዲቀንሱ በትምህርት ቤቶች ግቢ ውስጥ የጓሮ አትክልት ልማት፣ የዶሮ እና የወተት ከብቶች እርባታ እንዲጀመር ተደርጓል። ኢትዮጵያ ይሄን መርሃ ግብር የምግብ አቅርቦትን ተደራሽ ማድረግ ብቻ ሳይሆን የሀገርን የረጅም ጊዜ የሰው ሀብት (Human Capital) መገንቢያ ስትራቴጂ አድርጋ እየሰራች ይገኛል። የምገባ ፕሮግራሙ ከትምህርት ተደራሽነትና ውጤታማነት ባሻገር ህጻናት በጤናማ አካልና አእምሮ እንዲያድጉ በማድረግ ለሀገር አቀፍ የጤና ጥበቃ ስራዎች ትልቅ አበርክቶ እያበረከተ ይገኛል። በምገባ ማዕከላት ዙሪያ የሚደረጉ የንፅህና አጠባበቅና የደህንነት ትምህርቶች ተማሪዎች በለጋ እድሜያቸው ጤናማ የኑሮ ዘይቤዎችን እንዲላመዱና የግል ንፅህናቸውን እንዲጠብቁ አቅም እየፈጠረ ይገኛል። በአጠቃላይ የምገባ ፕሮግራም በትምህርት ላይ እያሳረፈ ካለው በጎ አሻራ ባለፈ ምርታማ ትውልድ ለመፍጠር እና ለአንድ ሀገር እድገት እና ልማት ያለው አስተዋጽኦ ጉልህ ነው። በዚህ ረገድም ኢትዮጵያ በስኬት ጎዳና እና ለሌሎች አርአያ በሚሆን ተምሳሌታዊ ተግባር በግንባር ቀደምትነት የምትነሳ ሀገር ናት።
የቱሪዝም ትንሳኤን ያበሰረው የመደመር እሳቤ
Sep 16, 2026 402
ኢትዮጵያ አስደማሚ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ የቱሪዝም ሀብቶች ባለቤት ናት ። የጎብኚዎችን ቀልብ የሚስቡ ደጋግመው ቢያዩዋቸው ፣ ቢታደሙባቸው የማይሰለቹ ተጠንተውም የማያልቁ ፀጋዎች ቢኖሯትም ለዘመናት በወጉ ሳትገልጣቸው የሚጠበቀውን ያክልም ሳይጎበኙ ሳይተዋወቁም ቆይተዋል። ይህን ባለማድረጓ ደግሞ ከዕልፍ የቱሪዝም ጸዋጋዎቿ ሳትቋደስ ዘመናትን ተሻግራለች። “በታሪክም ሆነ በተፈጥሮ ጸጋዎች ከኛ ጋር ሊወዳደሩ የማይችሉ ብዙ ሀገራት ከኢንዱስትሪው ብዙ አትርፈዋል። እኛ ግን እንቁዎቻችንን ደብቀን ታሪካችንን አቧራ አልብሰን ለዘመናት ቆይተናል።” የመደመር መንግሥት መጽሐፍ ገጽ 259 ዛሬ ግን ይህ ታሪክ እየተቀየረ ነው። ከመደመር መንግሥት አምስት ወሳኝ የኢኮኖሚ ምሰሶዎች አንዱ በሆነው ቱሪዝም ቅርሶችንና ወሳኝ ፀጋዎችን ከቁስ ወደ ቁርስ እየለወጠ፣ ኢትዮጵያን እየገለጠ እንዲመጣ እየተደረገ ነው። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአራት ኪሎ ቤተመንግስት “ሀ” ተብሎ የተጀመረው አዳዲስ የቱሪስት መዳረሻ ልማት በገበታ ፕሮጀክቶች አማካኝነት ወደ ሁሉም የሃገራችን ክፍሎች ተዳርሷል። በኢትዮጵያ ትኩረት ተነፍጓቸው የነበሩት የሀገራችን የቱሪዝም ሀብቶች በመደመር መንግሥት ቅድሚያ ተሰጥቷቸው ትንሳኤያቸው ተበስሯል። ለዘመናት አቧራ ለብሰው የኖሩ ዕንቁ የቱሪዝም ሀብቶች አቧሯቸው እየተራገፈ ነው። ከዳሎል እስከ ስሜን ተራሮች ማራኪ ተፈጥሯዊ መስህቦች ይበልጥ ለዓለም እየተዋወቁ ነው። አዳዲስ ተፈጥሯዊ ፀጋዎችም በቱሪዝም ልማት ኢኒሼቲቮች የመገለጥና የመታወቅ ዕድል አግኝተዋል። የመደመር እሳቤ የምናብ ከፍታና የመፈጸም ልክ አንዱ ጉልህ ማሳያ የቱሪዝሙ ዘርፍ ፕሮጀክቶች ናቸው። ከነዚህ ኢኒሼቲቮችም መካከል አንዱ ከቤተ መንግስት እደሳት ጀምሮ አዲስ አበባን እንደ ስሟ አዲስ ያደረጋት የገበታ ለሸገር ፕሮጀክት ነው። የገበታ ለሸገር ፕሮጀክት የቱሪዝም አብዮትን በመቀስቀስ የአንድነት ፓርክን፣ እንጦጦና ወዳጅነት ፓርክና ሌሎች ተያያዥ ፕሮጀክቶችን ዕውን አድርጓል። ዛሬ ላይ አዲስ አበባን አዲስ መልክ አጎናጽፎ፤ የነተቡ ሰፈሮች ወደ ውብ መልኮች ተቀይረው የሚሊዮኖች ጎብኚዎች መዳረሻ ሆነዋል። ከገበታ ለሸገር በመቀጠል የኢትዮጵያን አዳዲስ መልኮች የገለጠው ኢኒሸቲቭ ደግሞ የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት ነው። ገበታ ለሀገር ከኦሮሚያ ክልል የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ወንጪን፣ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዳውሮና ኮንታን የሸፈነው ኮይሻን፣ከአማራ ክልል የጣናን ምዕራባዊ ዳርቻ የተንተራሰችውን ጎርጎራን ውብ አድርጓል። እነዚህ ፕሮጀክቶች የኢትዮጵያን አይነተ ብዙ ታሪክ፣ ተፈጥሮንና ባህል በመግለጥ ለኢትዮጵያ ተጨማሪ ሞገስና ድምቀት ሆነዋል። ከገበታ ለሀገር ቀጥሎ ገቢራዊ የተደረገው የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት አድማሱ በሶማሌ ክልል ሸበሌ ሪዞርትን፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የደንቢ ኢኮ ሎጅን፣ በአማራ ክልል የሐይቅ ሎጎ ሪዞርትን፣ በአፋር ክልል የኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ እንዲሁም የአርባምንጭ ኮንፈረንስ ሪዞርትን እውን አድርጓል። ከገበታ ለሸገር እስከ ገበታ ለትውልድ ፕሮጀክቶች ባሻገር የመደመር መንግስት ታሪካዊ ቅርሶችን የመጠበቅ፣ እሴት ጨምሮ የመግለጥ አኩሪ ስራዎችንም አከናውኗል። ለዚህ ደግሞ ከብሔራዊ ቤተ መንግስት ጀምሮ ጥንታዊ አብያተ መንግስታት፣ ታሪካዊ፣ ሃይማኖታዊና ባህላዊ ቅርሶች ተጠግነዋል። የባለፉት ጥቂት ዓመታት የቱሪዝም ዘርፍ ለውጦች የኢትዮጵያን ገጽታ ያስተዋወቁ፤ በየአካባቢው ተስፋና ልማትን የፈነጠቁ፣ ዘመን ተሻጋሪ ስራዎች ናቸው። እነዚህ ፕሮጀክቶች በኢትዮጵያ የዕድገትና የብልጽግና ታሪክ ውስጥ በደማቁ የሚጻፉ አንቀጾች ሆነው ለትውልድ የተኖሩ ዓሻራዎች ናቸው።
የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ የከፍታ ጉዞ ማሳያ - ብሪክስ
Sep 13, 2026 873
''የብሪክስ ጉባዔ የጋራ ትብብርን ወደ የጋራ እሴት፣ ጽናት እና ዘላቂ ዕድገት የመለወጥ ሰፊ አቅምና ቁርጠኝነት አለው" በማለት ነው የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ18ኛው የብሪክስ ጉባዔ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር። 18ኛው የብሪክስ ጉባኤ የጥምረቱ አባል ሀገራት መሪዎች በተገኙበት “ጽናትን፣ ፈጠራን፣ ትብብርንና ዘላቂነትን መገንባት” በሚል መሪ ሀሳብ በህንድ ኒውዴልሂ እየተካሄደ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የልዑክ ቡድናቸው በዚሁ ዓለም አቀፍ ተጽዕኖ በሚፈጥረው ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ። ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የልዑክ ቡድናቸው የብሪክስ ጉባኤ ተሳትፎ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው። ብሪክስ ለአፍሪካ ቀጣና እና በተለይም ለኢትዮጵያ በርካታ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ እና የጂኦ-ፖለቲካዊ ጥቅሞችን የሚያስገኝ አዲስ የዓለም ስርዓት እየተፈጠረበት የሚገኝ ጥምረት ነው። የብሪክስ ጥምረት ለኢትዮጵያ የውጭ ኢንቨስትመንት ፍሰት ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው። በዚህም እንደ ቻይና፣ ህንድ እና ሩሲያ ካሉ ታላላቅ ሀገራት ወደ ኢትዮጵያ የሚመጣውን የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት በተለይም በማኑፋክቸሪንግ፣ በግብርና እና በኢነርጂ ዘርፍ በማሳደግ በኩል አይነተኛ አማራጭ የኢንቨስትመንት መንገድ ነው። ጥምረቱ ለኢትዮጵያ ከሚያስገኘው ትሩፋት አንጻር ሲታይ የውጭ ምንዛሬ እጥረትን በመቅረፍ፤ ከብሪክስ አባል ሀገራት ጋር በሚደረጉ የንግድ ልውውጦች የሀገር ውስጥ ገንዘብን የመጠቀም ዕድልን ስለሚፈጥር፣ የውጭ ምንዛሬ ግኝት እጥረትን ከመቀነስ አኳያም እንዲሁ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው። ኢትዮጵያ በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ዕቅዷ ኢኮኖሚዋን በመሠረታዊነት ለሚያሳድጉ መሠረተ ልማት ግንባታ እና ማስፋፊያ እንዲሁም ለቴክኖሎጂ ሽግግር ልዩ ትኩረት ሰጥታ እየሠራች ትገኛለች። ከዚህ አኳያ ብሪክስ የመንገድ፣ የባቡር፣ የኃይል ማመንጫዎችና ዲጂታል ቴክኖሎጂ እና መሰል የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች የሚሆን የፋይናንስ ድጋፍ በማመቻቸት በኩል ኢትዮጵያ ለያዘችው ግብ ስኬት ከፍተኛ ጠቀሜታ የሚያስገኝ ጥምረት ነው። ባለፉት ዓመታት ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲው ዘርፍ ላሳካቻቸው ውጤቶች የዓለም አቀፍ ግንኙነቷን የቃኘችበት አዲስ አካሄድ ተጠቃሽ ነው። ከእነዚህ ስኬቶች መካከል ደግሞ በብሪክስ ጥምረት ውስጥ አባል የሆነችበት መንገድ አንዱ ሲሆን፤ ይህ የብሪክስ ጥምረት ለኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ተፅዕኖ ፈጣሪነት የራሱን ሚና በመጫወት ኢትዮጵያ በቀጣናው እና በአህጉሪቷ ያላትን መሪነትና ዲፕሎማሲያዊ የበላይነት በማጠናከር በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ድምፅ እንድታጎላ እና ተጽዕኖ ፈጣሪነቷ እንዲያድግ እያስቻለ መሆኑም በተጨባጭ ታይቷል። የብሪክስ ጥምረት በአፍሪካ አለፍ ሲልም በጥምረቱ አባል ሀገራት መካከል ተመጣጣኝ ልማት እንዲኖር እና ሀገራቱ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ትብብራቸውን እንዲያጠናክሩ አስቻይ ምህዳር እየፈጠረም ይገኛል። በተለይ አፍሪካ ያላትን የተፈጥሮ ሀብት በማልማት የኢኮኖሚ ዕድገቷን እንድታፋጥን አማራጭ የፋይናንስ ምንጭ መሆን የሚያስችለውን አደረጃጀት እና አሰራር እየዘረጋም ይገኛል። ይህ የጥምረቱ አዳዲስ አደረጃጀት እና አሰራር አዲሱ የልማት ባንክ እንዲወለድ አስችሏል። በዚህ ባንክ አማካኝነት የአፍሪካ ሀገራት ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት እና ከዓለም ባንክ ጥብቅ መስፈርቶች ነፃ በሆነ መንገድ ለተለያዩ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች አማራጭ የፋይናንስ ምንጭ ወይም ብድር እንዲያገኙ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል። በጥምረቱ አማካኝነት የተፈጠረው አዲሱ የልማት ባንክ የአፍሪካ ሀገራት በራሳቸው ሀገራዊ ገንዘብ እና ከአሜሪካ ዶላር ተጽእኖ ውጪ ከታላላቅ የብሪክስ ሀገራት ጋር የንግድ ልውውጥ እንዲያከናውኑ በር እየከፈተ ይገኛል። በተጨማሪም አፍሪካ በዓለም አቀፍ የፖለቲካ እና ኢኮኖሚ የውሳኔ መድረኮች ላይ ያላትን ተፅዕኖ ፈጣሪነት በማሳደግ፣ ፍትሐዊ የሆነ የዓለም አቀፍ ስርዓት እንዲፈጠር እያስቻለ መሆኑም የአደባባይ ምስጢር ከሆነ ሰነባብቷል። ይህ የብሪክስ ጥምረት መመስረት፣ መስፋፋትና መጠናከር በዓለም የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ስርዓት ላይ በርካታ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጦችንና አንድምታዎችን እያስከተለ ይገኛል። የብሪክስ ጥምረት ተመስርቶ እየፈጠረ ያለው ዓለም አቀፍ የፖለቲካ ተጽዕኖ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የምዕራባውያን ሀገራት በዓለም ፖለቲካ ላይ የነበራቸውን የበላይነት በመገዳደር፣ ሥልጣንና ውሳኔ ሰጪነት ለተለያዩ የአህጉራት ኃይሎች እንዲከፋፈል፣ በዓለም አቀፍ ተቋማት ላይ የአሰራር እና የአደረጃጀት ማሻሻያ ጥያቄዎች ጎልተው እንዲሰሙ የማድረግ አቅም እየፈጠረ ነው። በተጨማሪም የብሪክስ ጥምረት አባል ሀገራት በንግድ ልውውጣቸው ወቅት በራሳቸው ሀገራዊ ገንዘቦች የመጠቀም ዝንባሌያቸው በመጨመሩ፣ የአሜሪካ ዶላር በዓለም ንግድና መጠባበቂያ ክምችት ላይ ያለውን ፍጹም የበላይነት በማዳከም፤ አዲሱ ልማት ባንክ የብሪክስ የድንገተኛ የገንዘብ ድጋፍ ማዕቀፍ የምዕራባውያኑን ጥብቅ የፖለቲካ መስፈርቶች ሳይከተሉ ለታዳጊ ሀገራት ፕሮጀክቶች ፋይናንስ እንዲያቀርቡ ብሎም የብሪክስ አባል ሀገራት የዓለምን ከፍተኛ የነዳጅ፣ የጋዝ፣ የብረታ ብረት እና የግብርና ምርቶች አቅርቦት የሚቆጣጠሩ በመሆናቸው፣ በዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮች እና የዋጋ ውሳኔዎች ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እንዲያሳድሩ የውሳኔ ሰጪነት አቅማቸውን እያሳደገ መጥቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጉባኤው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ኢትዮጵያም ሆነች አፍሪካ ያላቸውን የመልማት አቅም ለመጠቀም አማራጭ የልማት ፋይናንስ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተዋል። ለዚህ ደግሞ የብሪክስ ጥምረት ይዞት የመጣውን ዕድል በውል አንስተዋል። ለዚህም ነው በብሪክስ አባል ሀገራት ዘንድ ሀብት፣ ቴክኖሎጂ እና ሰፊ ገበያ አለን፤ አሁን ያለው መልካም ዕድል እነዚህን አቅሞች በማስተሳሰር የላቀ እሴት መፍጠር እና ይህ እሴት ደግሞ ሀብቱ በሚገኝበት ቦታ መመረት እንዲችል ማድረግ ነው ሲሉ ያመላከቱት። ኢትዮጵያ በማዕድን ልማት፣ በታዳሽ ኃይል እና እያደገ በሚገኘው የኢንዱስትሪ መሠረቷ ላይ እነዚህን አጋርነቶች ለመገንባት ዝግጁ መሆኗን ያረጋገጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በአሠራር ሥርዓቶቻችን ውስጥ ጽናትን መገንባት፣ የሰው ሰራሽ አስተውሎት የአህጉራችንን ፍላጎት እንዲያገለግል ማድረግ፣ አስተማማኝ የዕዳ እፎይታ ሒደትን ማሳደግ እንዲሁም የአየር ንብረት ጥበቃ ሥራዎችን ከኢኮኖሚ ሽግግር ጋር ማስተሳሰር ከጥምረቱ የሚጠበቅ መሆኑንም ነው ያነሱት። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ የብሪክስ ጉባዔ የጋራ ትብብርን ወደ የጋራ እሴት፣ ጽናት እና ዘላቂ ዕድገት የመለወጥ ሰፊ አቅምና ቁርጠኝነት አለው። የጥምረቱ አቅም ከተናጠል አካሄድ ይልቅ ትብብርና ለጋራ እሴት መጎልበት ያለውን ዕድል ያመላክታል። ኢትዮጵያ ለኮቪድ እና ኤልኒኖን ጨምሮ ለዓለም የኢኮኖሚ እና የንግድ ስርዓት መመሰቃቀል እጅ ሳትሰጥ፤ ይልቁንም መሰል ቀጣናዊ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ችግሮችን ወደ ዕድል በመቀየር፤ ለችግሮች የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባት ባከናወነቻቸው ተግባራት ጽናትን ገንዘቧ እያደረገች ትገኛለች። ለዚህም ነው "አካታች ዓለም አቀፍ አስተዳደር እና ባለ ብዙ ወገን ትብብርን ማጠናከር” በሚል አጀንዳ ላይ ትኩረት ባደረገው የጉባኤው የመጀመሪያ ቀን ውሎ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ችግሮች ከመፈጠራቸው አስቀድሞ ጽናትን ማጠናከር እና የአስተዳደር ስርዓት አካል የማድረግን መሠረታዊ ጠቀሜታ የገለጹት። ይህ ጽኑ ስርዓት ግንባታ ኢትዮጵያ በፈታኝ ሁኔታዎች ውስጥ እንድትበረታ ማስቻሉን ለማሳያነት አቅርበዋል። ኢትዮጵያ ከውጭ ከሚገባ የስንዴ ጥገኝነት ተላቃ በምግብ ራሷን መቻሏን አንስተዋል። በጤና ቅድመ መከላከል ፖሊሲ አካል ሆኖ የሕክምና ቁሳቁሶችና መድኃኒቶች ማምረትን፣ የዲጂታል ስርዓት ሽግግርንና ደኅንነቱ የተጠበቀ አጠቃቀም የማስፈን አበይት ተግባራት መከናወናቸውን ነው አጽንኦት የሰጡት። በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ የጀመረችው የመደመር አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዩኒቨርሲቲ አፍሪካ የነገውን የቴክኖሎጂ ዘመን በባለቤትነት እንድትመራ ትልቅ ሚና የሚጫወት መሆኑን የገለጹት። በእነዚህና መሰል የልማት ትብብሮች ከጥምረቱ አባል ሀገራት ጋር አብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆኗንም ነው ያረጋገጡት። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ ጥምረቱ የተቋቋመበትን ዓላማ እና መርህ በተጨባጭ እውን እያደረገች እንደምትገኝ በመጠቆም፤ ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት እና የዲጂታል ስርዓት ማሻሻያ ባከናወነቻቸው አመርቂ ትግበራዎች፣ በታዳሽ ኃይል መስፋፋት እና የኢንዱስትሪ መሠረት ልማቶቿ፣ በግብርና ስርዓት ማሻሻያ እየተመዘገቡ ያሉ የምግብ ሉዓላዊነት መረጋገጥ ብሎም ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ግዙፍ የአየር መንገድ ግንባታ የአኅጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ንግድ ትሥሥርን ለማስፋፋት በምታደርገው ጥረት በጥምረቱ ለሚነሱ ተያያዥ የውይይት አጀንዳዎች መሪ ተዋናይ መሆን እንደሚያስችላትም አንስተዋል። ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የልዑክ ቡድናቸው የብሪክስ ጉባኤ ተሳትፎ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው መሆኑ እሙን ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጉባኤው እያደረጉት ካለው ተሳትፎ ጎን ለጎን ቀጣናዊና ዓለም አቀፍ ትብብሮችን በሚያጠናክሩ አጀንዳዎች ላይ ከተለያዩ የብሪክስ ስብስብ አባል ሀገራት መሪዎች ጋር ውጤታማ የሁለትዮሽ ውይይቶችን አድርገዋል። በዚህም ከህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ፣ ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን፣ ከቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ፣ ከቪየትናም ጠቅላይ ሚኒስትር ሌ ሚን ሁንግ፣ ከካዛኪስታን ፕሬዚዳንት ቃሲም ጆማርት ቶካዬቭ፣ ከአቡ ዳቢ አልጋ ወራሽ ከልዑል ሼህ ኻሊድ ቢን ሙሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያ፣ ከማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሂም፣ ከኢራኑ ፕሬዚዳንት መስዑድ ፔዜሽኪያ እንዲሁም ከሌሎች መሪዎች ጋር የሁለትዮሽ ትብብርን በሚያጠናክሩ አጀንዳዎች ላይ ውጤታማ ውይይቶችን አካሂደዋል። የውይይቶቹ ማጠንጠኛም የጥምረቱን አባል ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነትን በሚያበረታቱ እንደ ኢንቨስትመንት፣ ቀጣናዊ ጉዳዮች፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ የአቅም ግንባታና ክህሎት፣ ቱሪዝም፣ የማዕድን ልማት እና ወደ ኮፕ 32 በሚደረገው ጉዞ ላይ ሊኖሩ ስለሚችሉ ትብብሮች ላይ ያተኮሩ እንደነበሩ ተመላክቷል።
ከታሪክ ዘካሪነት ወደ ታሪክ ሰሪነት፤ የአዲሱ ትውልድ የሜጋ ፕሮጀክቶች ግንባታ አብዮት
Sep 13, 2026 566
የአንድ ሕዝብ የነፃነት ድል የሚያበቃው በድል ማግስት በሚተረክ የታሪክ መዛግብት ብቻ አይደለም። በሌላ የታሪክ ገጽ ላይ አዲስ ድል መጎናፀፍ ሲቻል የቀደመውን ድል ትርጉምና ምልዑነት የበለጠ ያጎላዋል። ዓድዋ የክንደ ብርቱ ቅድመ አያቶች የሀገርን ሉዓላዊ ነፃነት የማስጠበቅ አኩሪ የድል ምልክት ነው። የድል ምልክትነቱም ለጭቁኑ የዓለም ጥቁር ሕዝቦች ፅናትና የነፃነት ጎህን በመቅደድ፣ ለአሁኑ ትውልድ ደግሞ የይቻላል መንፈስን አጎናፅፏል። ጀግንነትንና አልበገር ባይነትን ከቅድመ አያቶቹ የወረሰው የአሁኑ ትውልድም በሌላ የታሪክ ገጽ በጉባ ተራሮች ግርጌ በዓባይ የዘመናት ዥረት ላይ ታላቁን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በመገንባት የራሱን ታሪክ ጽፏል። የሕዳሴ ምረቃ የተበሰረባት ጳጉሜ 4 ቀን 2017 ዓ.ም ዕለትም የኢትዮጵያን አፍሪካዊት የብልፅግና ተምሳሌትነት የሚበይኑ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች የተበሰሩባት ድርብ ታሪካዊት ዕለት ሆና ተመዝግባለች። በሕዳሴ የይቻላል መንፈስን የተጎናፀፈችው ኢትዮጵያም በኃይል፣ በግብርና፣ በአቪዬሽን፣ በጋዝ፣ በማዕድንና በሌሎች ዘርፎች ወደ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች ግንባታ ተሸጋግራለች። የጉባ ብስራቶችም የአንድ ፕሮጀክት ወይም ዘርፍ ስኬት ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ ሀብቷን በራሷ አቅም በማልማት የብልፅግና ጉዞዋን ለማስፋት የምታደርገው የልማት ጉዞ ሕያው ምልክት ናቸው። የመደመር መንግሥት አፍሪካዊት የብልፅግና ተምሳሌት ኢትዮጵያን በራሷ ልጆች የመቅረጽ ራዕይም ከዓድዋ ነፃነትን፣ ከሕዳሴ የልማት ድልን፣ ከጉባ ተራሮች ግርጌ ብስራትን በመሰነቅ ታሪክን ከመዘከር ወደ አዲስ ታሪክ መጻፍ ተሸጋግሯል። ይህም ሕዳሴ ግድብ በአንድ የታሪክ ምዕራፍ ብቻ ተከትቦ የሚቀር የትውልድ ዓርማ ሳይሆን ለሚቀጥሉት ትውልዶች የመፈጸም አቅምና የይቻላል መንፈስ የሚያስተላልፍ ቅርስ መሆኑን ያሳያል። የአንድ ግዙፍ የትውልዱ ብሔራዊ ፕሮጀክት ምረቃም የሌሎች ሜጋ ፕሮጀክቶችን ውልደት በማብሰር ኢትዮጵያ በአዲስ የስኬት ምዕራፍ እየተስፈነጠረች መሆኗን ያመላክታል። የጉባ ብስራት የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ፣ የጋዝ፣ የነዳጅ ማጣሪያና የማዳበሪያ ፋብሪካዎች፣ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ እንዲሁም የ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ አብነቶች ናቸው። ኃይልን ከግብርና፣ ኢንዱስትሪን ከአቬየሽን ያሰናሰሉት የጉባ ብስራት ግዙፍ ፕሮጀክቶችም በዚህ የልማት ጉዞ ቀጣዩን ምዕራፍ መጻፍ ጀምረዋል። ይህም ኢትዮጵያ ሜጋ ፕሮጀክቶችን የምታልም ሀገር ብቻ ሳትሆን የመፈጸም አቅም ያላት መሆኗን የሚያሳይ አዲስ የልማት ምዕራፍ ነው። በመደመር መንግሥት ውልደት ማግስት ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊና በፖለቲካዊ ዘርፎች ያስመዘገበቻቸው እመርታዎች ሀገርን ከመዋቅራዊ ስብራት ወደ ማንሰራራት ያሸጋገሩ ድሎች ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጳጉሜ 4 ቀን 2017 ዓ.ም ታሪካዊቷ ዕለት እንዳሉት፤ ሕዳሴ ያስገኘው ወኔና ተስፋ የነገዋን ኢትዮጵያ ብሩህ አድማስ የሚያበስሩ ፕሮጀክቶችን ለማስፈጸም መንገድ ከፍቷል። በዚህም በጥቂት ዓመታት ውስጥ ለሰላማዊ ዓላማ የሚውል የኒውክሌር ፕላንት፣ የጋዝ፣ የነዳጅ ማጣሪያና የአፈር ማዳበሪያ ፋብሪካዎች፣ እንዲሁም 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን የመኖሪያ ቤቶች እንደሚገነቡ ማብሰራቸው ይታወሳል። እነዚህ ግዙፍ የልማት ዕቅዶች በቁጥር የሚገለጹ ፕሮጀክቶች ብቻ አይደሉም። ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብቷን ከራሷ የመፈጸም አቅም ጋር በማሰናሰል የነገን ሀገራዊ ተስፋ የሚያመላክቱ የልማት አቅጣጫዎች ናቸው። የመደመር መንግሥት ግዙፍ ሀገራዊ የልማት ትልሞችም የኢትዮጵያን ሁሉን አቀፍ የማንሰራራት ምዕራፍ በማብሰር፣ የሀገርን ብልፅግና የሚቀርጹ እመርታዎች የተገኙባቸው ናቸው። ከእነዚህ መካከል የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ የአየር ማረፊያ የፕሮጀክት ግንባታ ብስራት አንዱ ነው። ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅም ኢትዮጵያ በአቪዬሽን ዘርፍ ያላትን አህጉራዊና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት በማጎልበት፣ በኢኮኖሚ፣ በቱሪዝምና በዲፕሎማሲ ዘርፎች አዳዲስ ዕድሎችን የሚከፍት ቁልፍ መሠረተ ልማት ይሆናል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የፕሮጀክቱን ግንባታ ባስጀመሩበት ወቅት እንዳሉት፣ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲጠናቀቅ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ የአቪዬሽን ዘርፍ ተወዳዳሪነት የሚያሳድግ ነው። በዚህ መነፅር ሲታይም የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ የአየር ማረፊያ ፕሮጀክት የአቪዬሽን ፕሮጀክት ብቻ አይሆንም። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ያላትን የአቪዬሽን መሪነት በማላቅ፣ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን የሚያጎለብት ስትራቴጂካዊ ኢንቨስትመንት ይሆናል። የቢሾፍቱ አየር ማረፊያ ግዝፈትና ዝማኔ ኢትዮጵያን የአቪዬሽን፣ የቱሪዝምና የዲፕሎማሲ ማዕከል የማድረግ ከፍተኛ አቅም አለው ያሉት ደግሞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ናቸው። ይህም ሕዳሴ ግድብ ያስተዋወቀው የታላቅ ሀገር ግዙፍ ፕሮጀክትን የመፈጸም ባህል ከኃይል ዘርፍ ወደ አቪዬሽንና ሌሎች ስትራቴጂካዊ የልማት መስኮች እየተስፋፋ መሆኑን ያመላክታል። ሌላኛው የኢትዮጵያን የማንሰራራት አቅጣጫ የሚበይነው ግዙፍ ፕሮጀክትም የተፈጥሮ ጋዝና የአፈር ማዳበሪያን በሀገር ውስጥ የማምረት ትልም ነው። የኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብት ከመሬት ሥር ተደብቆ የሚቀር ሳይሆን፣ የምርት፣ የኢንዱስትሪና የኢኮኖሚ ልማት መሠረት የማድረግ አዲስ የዕድገት አቅጣጫ ሆኗል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክትን ባስጀመሩበት ወቅት፣ የኢትዮጵያ የጋዝ ምርት ፕሮጀክት የኃይል አቅርቦትን ከግብርና ምርታማነት ጋር ያሰናሰለ ነው ብለዋል። ይህም የኦጋዴን የተፈጥሮ ጋዝ የኃይል አቅርቦትን ከማሟላት ባሻገር፣ የኢትዮጵያን የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጉዞ በስፍራው ለሚገነባው የአፈር ማዳበሪያ ፋብሪካ ግብዓትነት ያገለግላል። በዚህ አተያይም ጋዝን ማልማት የኃይል ፍላጎትን ከማሟላት ባሻገር፣ የግብርና ምርታማነትን፣ የኢንዱስትሪ ምርትንና የሀገር ውስጥ ግብዓት አቅርቦትን የሚያጠናክር የተሰናሰለ ስልታዊ የልማት አቅም ይፈጥራል። የመደመር መንግሥት ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ለብዝኅ ክፍለ ኢኮኖሚ ዕድገት የሰጠው ትኩረትም ኢትዮጵያን በግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን፣ ቱሪዝምና ዲጂታል ዘርፎች በስኬት ምሕዋር እንድትገባ አድርጓታል። ይህም የኢትዮጵያን ማዕድን ከጥሬ ዕቃ ላኪነት ወደ እሴት የታከለበትና ፈጠራ ያለበት የምርት ሰንሰለት የሚሸጋገርበትን ወሳኝ ዕድል ፈጥሯል። የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ሃብታሙ ተገኘ፣ የካሉብ ፋብሪካ የተፈጥሮ ጋዝ ማጣራትና ወደ ፈሳሽነት የመቀየር የማዕድን ልማት ለተሽከርካሪና ፋብሪካ አማራጭ የኃይል ምንጭ ማቅረብ የሚያስችል ነው ብለዋል። ይህ ተፈጥሮ ሀብትን በጥሬ ዕቃነት ከመሸጥ ይልቅ በማቀነባበርና በማልማት የበለጠ እሴት ለማስገኘት የተያዘውን አቅጣጫ ያመላክታል። የመደመር መንግሥት ሀገር በቀል የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያም የግሉን ዘርፍ በማሳተፍና ዓለም አቀፍ ባለሀብቶችን በመሳብ፣ አዳዲስ የልማትና የኢንቨስትመንት ዕድሎችን ከፍቷል። ለዚህም ነው የዳንጎቴ ግሩፕ ባለቤትና መሥራች አሊኮ ዳንጎቴ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሪፎርም በኢኮኖሚው ውስጥ ጤናማ ውድድርና ቀልጣፋ አሠራር እንዲፈጠር አድርጓል ብለዋል። ከሕዳሴ ግድብ እስከ አቪዬሽን፣ ከተፈጥሮ ጋዝ እስከ ማዳበሪያ ድረስ ገሃድ የገለጠው የኢትዮጵያ ማንሰራራትም ከማለም ወደ መፈጸም፣ ከመፈጸምም ወደ ዘላቂ የልማት አቅም ለመሸጋገር የሚደረገውን ጉዞ ያመላክታል። የዓድዋ ድል የኢትዮጵያውያንን አንድነትና የጋራ አቅም ለዓለም ታሪክ ያሳየ ድል እንደነበር ሁሉ፣ ሕዳሴ ግድብም ያንኑ የጋራ አቅም በዘመናዊ ልማት ላይ የገለጠ አዲስ ታሪካዊ ክስተት ሆኗል። የኢትዮጵያውያን አንድነት የዓድዋን ድል ካቀዳጀ፣ ያው በሕብር የተሸመነ አንድነትም ሕዳሴን እውን አድርጓል። ሕዳሴ የተስፋ ብርሃን ካበራ፣ ያ ተስፋም በሌሎች የልማት ሜጋ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ ሆኖ እየቀጠለ ነው። ይህ የይቻላል መንፈስ ከፕሮጀክት ወደ ፕሮጀክት የሚጓዝ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያውያን ስለነገ ሀገራቸው ያላቸውን እምነት የሚያድስ የልማት ብስራት ነው። ሕዳሴ ግድብ የተጀመረውን የተስፋ ጉዞ አዲስ አቅጣጫ አስይዞታል። የሚቀጥለው ታላቅ ተግባር ደግሞ ይህን የመፈጸም አቅም ወደ ዘላቂ ምርታማነት፣ የሥራ ዕድል፣ የዜጎች ተጠቃሚነትና የተሻለ ኑሮ መቀየር ነው። እናም የሕዳሴ ግድብ ብስራት በግድቡ የውሃ ሙሌት ብቻ የሚያበቃ ሳይሆን፣ በኢትዮጵያውያን የጋራ ህልም፣ በሀገራዊ አንድነትና በመፈጸም አቅም የሚቀጥል የልማት ብስራትን ፈንጥቋል።
ልዩ ዘገባዎች
በታዳጊው የተሰራችው መኪና
Jun 17, 2026 13364
ለአዳዲስ ፈጠራ የማይታክተው ልጅዓለም ንጉሱ ትውልድና እድገቱ በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ወረዳ ፀመራ ቀበሌ ነው። ከሕጻንነቱ ጀምሮ ፈትቶ መግጠምና አፍርሶ መስራትን እየተለማመደ የመጣው ልጅዓለም፤ ከቤት እስከ ትምህርት ቤት ያልተቋረጠ ፈጠራውን አጠናክሮ ቀጥሏል። ከዚህ ቀደም ለሚማርበት ፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከወዳደቁ ቁሶች የተለያዩ ቅርፃ ቅርፆችን በመስራት የፈጠራ አሻራውን አኑሯል። በትምህርትና በፈጠራ ሥራው ገፍቶበት አሁን ላይ የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ልጅዓለም እንጨት ገጣጥሞ መኪና በመስራት ያለውን የጥበብና ፈጠራ ክህሎት አሳይቷል። በታዳጊው የተሰራችውና በፔዳል የምትነዳው መኪና ሁለት ሰዎችን የማያዝ አቅም አላት። በቀጣይ ተጨማሪ ቁሶችን በማቅረብና በተለያየ መንገድ የሚያግዘው ካገኘ መኪናዋ በዲናሞ እንድትንቀሳቀስ ለማድረግ መዘጋጀቱን ተናግሯል። የተሽከርካሪውን አካል የገጣጠመው በአካባቢው አጠራር "እንቋ" የተሰኘ ዛፍ እንጨትን በመጠቀም ሲሆን የተሽከርካሪውን እግር ለማዘጋጀት ደግሞ የዋርካ ዛፍ ተጠቅሟል። በዚህም መሰረት የልጅዓለም መኪና የመብራትና የመሪ ስራዋ ተጠናቆ ሁለት ሰዎችን ጭና መንቀሳቀስ እንደምትችል በተግባር አሳይቷል። "በቀጣይ የሚያግዘኝና የሚደግፈኝ ካገኘሁ በዲናሞ የሚሰራ ተሽከርካሪ ለመስራት ዝግጁ ነኝ" ያለው ጥበበኛው ተማሪ ወደ ፊት ለሀገሬ ብዙ የመፍጠር ህልም አለኝ ብሏል። የፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ግርማ ጌቴ፤ ከዚህ በፊት ተማሪ ልጅዓለም በትምህርት ቤቱ የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎች እንዳሉት አስታውሰው ትምህርቱንም ፈጠራውንም አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል። የፈጠራ ክህሎቱን፣ ተሰጥኦውንና ፍላጎቱን ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ ተከታትያለሁ ያሉት መምህሩ የሳይንስ ትምህርቱንና የግል ክህሎቱን ደምሮ ለአዳዲስ ሥራዎች እየተጋ መሆኑን አንስተው፣ የመኪና ፈጠራውም ይህንኑ በተግባር ያሳየበት ነው ብለዋል። የግብዓት አቅርቦት ድጋፍ ከተደረገለት የተሻለና ውጤታማ ሥራ መስራት እንደሚችል ገልጸው ለሚፈጥሩ ወጣቶች በጥሩ ምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን ተናግረዋል። በእንጨት የተገጣጠመችው መኪና በሁላችንም ድጋፍ የዲናሞ፣ የብረትና ሌሎች አስፈላጊ ቁሶች ከተሟሉላት በታዳጊው ጥበብ የተሻለች መኪና ሆና ልትሰራ ትችላለች ሲለም እምነታቸውን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 22505
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 15527
በዮሐንስ ደርበው በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 21275
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
መጣጥፍ
የአፍሪካ የልማት መሰረትና የሰላም ማስከበር አውራ - ኢትዮጵያ
Sep 16, 2026 176
ኢትዮጵያ ነፃነቷን አስከብራ የኖረች ሀገር ከመሆኗ ባሻገር፣ ለአህጉሩ ሀገራት የነፃነት፣ የልማትና የሰላም ማስከበር ጥረቶች ታሪካዊና መዋቅራዊ መሰረት በመጣል ግንባር ቀደም ሚና ስትጫወት ቆይታለች። ሀገሪቱ ለአፍሪካ አንድነት፣ ለቀጣናዊ ትስስርና ለሰላም ማስከበር ያበረከተችው አስተዋጽኦም የላቀ ነው። የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ገቢር ነበብ ሆኖ፣ ለጎረቤት አገራት ቅድሚያ በመስጠት፣ በጋራ ልማትና በጋራ ተጠቃሚነት መርህ የሚመራ ነው። አገሪቱ በአፍሪካ አህጉር በሚከናወኑ የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የመሠረተ ልማት ትስስር፣ የሰላም ማስከበርና ተዛማጅ ሁለንተናዊ መስኮች የምትጫወተው የፊት አውራነትና የመሪነት ሚና በተጠናከረ ሁኔታ ቀጥሏል። የኢነርጂ እጥረት የአፍሪካ አገራት የኢኮኖሚ ዕድገት ዋነኛ ማነቆ መሆኑን የተረዳችው ኢትዮጵያ፣ ግዙፍ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን በመገንባትና ጥቅም ላይ በማዋል አህጉራዊ አርአያነቷን እያስመሰከረች ትገኛለች። በዚህ ረገድ የላቀ ምሳሌ የሚሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ፣ የአገሪቱን የኃይል ፍላጎት ከመሙላት ባለፈ ለጎረቤት አገራትም አስተማማኝ የኃይል ምንጭ በመሆን ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ትስስርን በጥብቅ መሠረት ላይ ጥሏል። ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ለሱዳን፣ ለጅቡቲ እና ለኬንያ የኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብ የቀጣናውን የኢነርጂ ፍላጎት ከመሙላት ባለፈ፣ ዘላቂ የኃይል ልማት ትስስርን በተግባር እያረጋገጠች ትገኛለች። በተጨማሪም ከታንዛኒያ፣ ከሩዋንዳ፣ እንዲሁም ከሌሎች የምስራቅ አፍሪካና የአፍሪካ ቀንድ አገራት ጋር የኃይል መስመሮችን ለመዘርጋትና ትስስሩን የበለጠ ለማስፋፋት በትጋት እየሰራች ትገኛለች። የኢትዮጵያ የኃይል ልማት ፖሊሲ ያጋራ ተጠቃሚነትንና አብሮ ማደግን መሰረት ያደረገ በመሆኑ ጎረቤት አገራት የታዳሽ ሃይል ተጠቃሚ እንዲሆኑ የድርሻዋን ማበርከቷን ቀጥላለች። ኢትዮጵያ የቀጣናው የሎጅስቲክስና የትራንስፖርት ዋና ማዕከል በመሆንም አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ትስስርን እያጠናከረች ትገኛለች። የሀገሪቱ ተቋማዊ አምባሳደር የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ አፍሪካን ከእስያ፣ አውሮፓ፣ አሜሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ ጋር በማያያዝ ረገድ የማይተካ ሚና የሚጫወት ወሳኝ የትራንስፖርት አውታር ሆኗል። በተጨማሪም ከጂቡቲ፣ ኬንያ እና ሱዳን ጋር የተዘረጉት የትራንስፖርትና የሎጀስቲክስ መሰረተ ልማቶች፣ ኢትዮጵያ ከጎረቤቶቿና ከቀጣናው አገራት ጋር ያላትን የንግድና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በጥራትና በፍጥነት ለማሳለጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛሉ። የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ ልማትም ከሀገራዊና ቀጣናዊ ወሰኖች የተሻገረ ግብ በመሰነቅ፣ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖዎችን ለመቋቋም እና የተፈጥሮ ሀብትን ለመታደግ ያለመ ግዙፍ ስትራቴጂካዊ እርምጃ ነው። ይህ ታላቅ የልማት ኢንሼቲቭ ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ያላትን ጠንካራ ቁርጠኝነት በተግባር ያረጋገጠ ሲሆን፣ የፓሪስ የአየር ንብረት ስምምነትንና የተባበሩት መንግሥታት የዘላቂ ልማት ግቦችን (SDGs) ከማሳካት አንጻር በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ እውቅናና አድናቆት ተችሮታል። የአባይ ወንዝ መነሻ የሆነችው ኢትዮጵያ፣ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብሯ አማካኝነት የታችኞቹ የተፋሰሱ አገራት በጎርፍና በደለል እንዳይጠቁ ከመጠበቋም በላይ፣ የጋራ የውሃ ሀብትን በዘላቂነት ለመንከባከብና ለመጠበቅ በትጋት እየሠራች ትገኛለች። ይህ ጥረት የወንዙን ዓመታዊ የውሃ ፍሰት በመጠበቅና የአፈር መሸርሸርን በመቀነስ ለቀጣናው አገራት ዘላቂ ጥቅም የሚያረጋግጥ ተግባራዊ እርምጃ ነው። ኢትዮጵያ በቀጣናዊና አህጉራዊ የሰላም ማስከበር ስራዎች ውስጥ የአንበሳውን ድርሻ በመውሰድ አሁንም በግንባር ቀደምትነት እየሠራች ትገኛለች። በተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና በአፍሪካ ኅብረት ጥላ ሥር በሶማሊያ (AMISOM/ATMIS)፣ በደቡብ ሱዳን፣ በኮንጎና በሌሎችም የአህጉሪቱ የግጭት ቀጣናዎች የሰላም አስከባሪ ኃይሎችን በማሰማራት ረገድ የኢትዮጵያን ያህል ከፍተኛ መስዋዕትነት የከፈለና አስተዋጽኦ ያደረገ አገር የለም ለማለት ይቻላል። ኢትዮጵያ በተለይም በሶማሊያ የሚንቀሳቀሰውን አል-ሸባብን የመሳሰሉ ሽብርተኛ ቡድኖች ላይ ጠንካራ ወታደራዊ እርምጃ በመውሰድ ሽብርተኝነትን በግንባር ቀደምትነት እየታገለች ትገኛለች። የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት አባላት የሶማሊያ መንግሥት ተቋማት እንዲጠናከሩና ቀጣናው ሙሉ በሙሉ ከሽብር ስጋት ነፃ እንዲሆን በጀግንነት፣ በውጤታማነትና በላቀ ቁርጠኝነት የተጣለባቸውን አገራዊና አህጉራዊ ኃላፊነት እየተወጡ ይገኛሉ። የአፍሪካን አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና (AfCFTA) ስምምነት በማጽደቅና በተግባር ላይ በማዋል ረገድም ኢትዮጵያ የጎላ ተሳትፎ እያደረገች ትገኛለች። አህጉራዊ የንግድ ውሎችና ግዴታዎች ሙሉ በሙሉ ተፈጻሚ እንዲሆኑ፣ እንዲሁም የጉምሩክ አሠራሮች የተቀላጠፉና ዘመናዊ እንዲሆኑ በትጋት እየሠራች ነው። ለፓን-አፍሪካኒዝም እሴቶች መጠናከር፣ ለአህጉሪቱ የኢኮኖሚ ነፃነትና ሉዓላዊነት መረጋገጥ የኢትዮጵያ የታሪክና የፖሊሲ ካፒታል ጠንካራ መሠረት ሆኗል። በአጠቃላይ፣ አገሪቱ የአፍሪካ የልማት ምሰሶና የሰላም ማስከበር ግንባር ቀደም መሪ በመሆን ታሪካዊና አህጉራዊ ኃላፊነቷን በተጠናከረ ሁኔታ እየተወጣች ትገኛለች። በአጠቃላይ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግስታት የኢኮኖሚ ኮሚሽን (UNECA) መቀመጫ በመሆን የአህጉሪቱን እውነተኛ ትረካዎችና የመረጃ ልውውጥ በግንባር ቀደምትነት የምታስተጋባ "የአፍሪካ ድምፅ" ስትሆን፣ እንደ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ባሉ የታዳሽ ኃይል ፕሮጀክቶቿና ለጎረቤት ሀገራት በምታቀርበው ንጹህ ኤሌክትሪክ የቀጣናውን የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ሽግግርና የኢንዱስትሪ እንቅስቃሴ ትደግፋለች። በተጨማሪም በባቡር፣ በአውራ ጎዳናዎች፣ በቴሌኮም፣ በኢትዮጵያ አየር መንገድ እና በኢጋድ (IGAD) በኩል አህጉራዊ የመሰረተ ልማትና የንግድ ትስስርን በማጠናከር፣ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና (AfCFTA) ስምምነትን ከመደገፍ ባሻገር በሰላም ማስከበርና በቀጣናዊ ድርድሮች ረገድ የምትጫወተው ሚና ለዘላቂ ልማትና ሰላም ትልቅ ዋስትና ሆኗል።
በሕብር የተሸመነ አንድነት፤ የኢትዮጵያ ጥንካሬ የወል እውነት
Sep 15, 2026 300
አዲስ አበባ፤ መስከረም 5/2019 (ኢዜአ):-በሕብር የተሸመነ አንድነት፤ የኢትዮጵያ ጥንካሬ የወል እውነት የኢትዮጵያ የረጅም ዘመናት የሀገረ መንግሥት ግንባታ የታሪክ ምዕራፎች ከዜጎቿ በሕብር የተሸመነ አንድነት የሚመነጭ ነው። በዚህ የረጅም ዘመናት የታሪክ ጉዞም የኢትዮጵያውያን ብዝኅ ማንነቶች፣ ቋንቋዎች፣ ሃይማኖቶች፣ ባሕሎችና ልዩ ልዩ እሴቶች በአንዲት የኢትዮጵያ ማዕቀፍ ሥር ተሳስረውና ተሰናስለው የዘለቁ ውድ ሀብቶች ናቸው። የኢትዮጵያውያን በሕብረ ብሔራዊ አንድነት የተሸመነ እውነትም ከሀገር መለያነት ባሻገር በዜጎች መካከል ለዘመናት የተገነባ የጋራ ሕይወት ውጤት ነው። በሕብር የተሸመነው ይህ ማኅበራዊ እሴት በልዩነት ውስጥ የእኛነት፣ በብዝሃነት ውስጥ የአንድነት፣ በተለያዩ ማንነቶች ውስጥ የኢትዮጵያዊነት የጋራ እሴት አሸብርቆ ይታያል። ይህን የጋራ እውነት በማጠናከር ለቀጣዩ ትውልድ ማሸጋገርም በራሱ መንገድ ብቻ የሚፈጸም አይደለም። የጋራ ታሪክ፣ እሴትና ሀገራዊ ምልክትን በማስተሳሰር አሰባሳቢና የጋራ ትርክትን መገንባትም ይጠይቃል። የአሰባሳቢ ትርክት ግንባታ የተለያዩ ማንነቶችን ማጥፋት ሳይሆን፤ በልዩነቶች መካከል የጋራ እሴቶችን በማጉላት ለአንድ ሀገራዊ ዓላማ መሰለፍ የሚያስችል ቀጣይነት ያለው የአስተሳሰብ ውቅር ነው። በዚህ ሂደት የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የጋራ ታሪካቸውን በመረዳት፣ የጋራ እሴቶቻቸውን በማጎልበትና የጋራ የወደፊት ራዕይን በመጋራት ከእኔ ወደ እኛ የሚያመራ ሀገራዊ አስተሳሰብን ያጎለብታሉ። ለዚህም ሀገራዊ ምክክር ጉልህ ሚና አለው። የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤም ለዘመናት የተስተጋቡ የአለመግባባት ትርክቶችን በአሳታፊና አካታች የሃሳብ የበላይነት ለማረቅ ሁነኛ መሰረት ጥሏል። የምክክር ጉባኤው ምክረ ሃሳብ ውጤቶችም የመቀራረብና የአንድነት መንፈስን በማጎናጸፍ ኢትዮጵያውያን ቀጣይነት ላለው ጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ የሚተባበሩበትን ታሪካዊ ዕድል ፈጥሯል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በምክክር ጉባኤ ማስጀመሪያ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ምክክር ከእኔነት ወደ እኛነት ሀገራዊ ማዕቀፍ የሚያመራ ሁነኛ የአሰባሳቢ ትርክት ግንባታ መንገድ ነው ብለዋል። የምክክር ጉባኤውም ለሀገርና ለጋራ ጥቅም ቅድሚያ በመስጠት የጋራ ሀገራዊ አስተሳሰብን ለማጠናከር መሰረት የሚጥል መሆኑን አስገንዝበዋል። የምክክር መድረኩም የታሪክን፣ የአጋጣሚንና የዕድልን ማዝለቀቅ ለፈለጉ ሰዎች፤ በዚያ ብዕርና ብራና ላይ ሀገርን የሚታደግ፣ የሚገነባና ለዘመናት የሚታወስ ታሪክ ለመጻፍ ዕድል የሚሰጥ ነው ብለዋል። ይህም ሀገራዊ የምክክር ጉባኤው የምክረ ሃሳብ ውጤቶች ከአንድ የምክክር መድረክ በላይ ለጋራ ሀገራዊ እሴትና የወደፊት ራዕይ ግንባታ ወሳኝ ዕድል የሚፈጥር ታሪካዊ ሂደት መሆኑን ያመላክታል። ኢትዮጵያ በሕዝቦቿ አንድነትና ትብብር የጋራ ታሪክን ወደ የጋራ የወደፊት ራዕይ ለመለወጥ የሚያስችሏት በርካታ አጋጣሚዎችን ያሳለፈች ታላቅ ሀገር ናት። ከእነዚህ መካከል የዓድዋ ድል አንዱ ምልክት ነው። የዓድዋ ድል በአንድ ዘመን በተፈጸመ ወረራ ላይ የተገኘ ወታደራዊ ድል ብቻ አይደለም። በሕብር የተሸመኑ ኢትዮጵያውያን የሀገርን ሉዓላዊ ነጻነት ለማስጠበቅ በአንድ ዓላማ የተሰለፉበት የጋራ ታሪካዊ የወል እውነት ነው። የዓድዋ ድል በኢትዮጵያና ሕዝቦቿ ሕብረ ብሔራዊ አንድነት የደምና አጥንት መስዋዕትነት ደማቅ ቀለም ተሸምኖ የተጻፈ የነጻነት ታሪክ ነው። በዚህ የታሪክ ገጽ የግል ልዩነቶቻቸውን በይደር የያዙ ኢትዮጵያውያን የሀገርን ጥቅም ከግል ጥቅም በተሻገረ ዕይታ በመመልከት ከአራቱም ማዕዘናት ለጋራ ዓላማ ተሰልፈው ድልን የተጎናጸፉበት ክስተት ሆኗል። ይህ የዓድዋ ትርክት ለዛሬው ትውልድ የሚያስተላልፈው ዋና መልዕክትም የሀገርን ጉዳይ በማስቀደም ለጋራ ዓላማ መሳካት ሕብረ ብሔራዊ አንድነት የተሸመነ ሀገራዊ ትብብር ወሳኝ አቅም መሆኑን ነው። የዓድዋ አርበኝነትን በልማት የትብብር መንፈስ የተላበሰው አዲሱ ትውልድም በጉባ ተራሮች ግርጌ በፈጸመው ታላቅ ገድል ታላቁን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በመገንባት የራሱን ታሪክ ጽፏል። የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫም በትብብር፣ በመደጋገፍና በዜጎች የጋራ ርብርብ የተገነባ መሆኑ የዘመኑና የቀጣይ ትውልድ የጋራ ሀገራዊ አሰባሳቢ ትርክት መገንቢያ ፕሮጀክት ለመሆን በቅቷል። በፕሮጀክት ግንባታ ሂደትም የአራቱም ማዕዘናት የኢትዮጵያ ሕዝቦች ያላቸውን በማዋጣት በጋራ ተሰልፈዋል፤ የሀገር ጉዳይ ሲሆን የጋራ ዓላማ ልዩነት እንደማይገድባቸውም በተግባር አስመስክረዋል። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)፤ ኢትዮጵያ በትርክት መዛባት ምክንያት የበዙ ውድ ዋጋዎችን ስትከፍል መቆየቷን አስታውሰዋል። በዚህም የመደመር መንግሥት የትናንት ቁርሾዎችን በንግግር፣ በውይይትና በምክክር መፍትሔ በመስጠት አሰባሳቢና የወል ትርክትን ለመገንባት የሚያስችል መሰረት መጣሉን አስገንዝበዋል። ለዚህም እኩልነትን፣ አካታችነትንና አሳታፊነትን ማዕከል ያደረገ አሰባሳቢና የወል ትርክት እየተገነባ መሆኑን አጽንኦት የሰጡት። የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳይ አማካሪ ሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በበኩላቸው፤ ንዑሳን፣ አካባቢያዊ፣ ተቋማዊና ሌሎች የትርክት ዓይነቶች የሰው ልጆች ጠባይና ተፈጥሯዊ መሆናቸውን ገልጸዋል። ንዑሳን ትርክቶችንም ሀገር እንደ ትምህርትና ፕሮጀክት በማድረግ ልታበረታታቸው አይገባም ያሉት አማካሪ ሚኒስትሩ፤ የሀገር መሰረታዊ ማዕከል የወል እውነት ነው ብለዋል። በሀገር ደረጃ ሁሉንም የሚያስተሳስር የወል ትርክት ቀዳሚ ሊሆን እንደሚገባ ማስገንዘባቸውም አስተሳሳሪ ትርክት ግንባታ ትኩረት የሚሻ መሆኑን አስረጂ ነው። ኢትዮጵያ በረጅም የታሪክ ጉዞዋ ሕዝቦቿን በማስተሳሰር የወል ትርክት መገንባት የሚያስችሉ በርካታ አጋጣሚዎችን ያስተናገደች ሀገር ናት። ለዚህም ከሩቁ የዓድዋ ድልን፣ ከቅርቡ ደግሞ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን መጥቀስ ይቻላል። እነዚህን ታሪካዊ አጋጣሚዎችም ለጋራ የወል ትርክት ግንባታ በመጠቀም ለዛሬ ብሎም ለነገ ሀገራዊ ራዕይ ስኬትና አንድነት አይተኬ ሚና አላቸው። ለዚህም ነው የኢትዮጵያን የጋራ ታሪክና እሴቶች ወደ የጋራ የወደፊት ራዕይ ማሸጋገር፣ ብዝሃነትን እያከበሩ አንድነትን ማጠናከር የወል ትርክት ዋነኛ እሳቤ መሆኑን የሚያስረዱት አማካሪ ሚኒስትሩ። ዓድዋ የነጻነት የጋራ ትርክት፤ ሕዳሴ ደግሞ የልማትና የራስ መተማመን የጋራ ትርክት ውጤት ሆኗል። ይህም የአንዱ ትውልድ ቅርስ የነጻነት እሴት ሲያስተላልፍ፣ ሌላው ደግሞ የዛሬውን ትውልድ በጋራ ራዕይ በማሰባሰብ የነገን የዕድገትና ብልፅግና ምኞት ተልሟል። የመደመር እሳቤም በእኛነት መርህ ላይ ተመሥርቶ ብዝሃነትን እንደ ስጋት ሳይሆን እንደ የጋራ ብልፅግና አቅም በመመልከት፣ የጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ የማዕዘን ድንጋይ አድርጎ እየሰራበት ነው። በዚህም የዓድዋ ድል ይህንን ታሪክ ያስተማረን ሲሆን፣ የሕዳሴ ግድብ ደግሞ በዘመናችን በተግባር የተገለጠ የአሰባሳቢ ትርክት ግንባታ የወል እውነት ማዕከልነትን ቀርጿል።