በካራባኦ ካፕ ማንችስተር ዩናይትድ ከብራይተን ጋር ይጫወታል - ኢዜአ አማርኛ
በካራባኦ ካፕ ማንችስተር ዩናይትድ ከብራይተን ጋር ይጫወታል
አዲስ አበባ፤ መስከረም 6/2019 (ኢዜአ):- በእንግሊዝ ካራባኦ ካፕ ሶስተኛ ዙር ዛሬ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
በኦልትራፎርድ ስታዲየም ምሽት አራት ሰዓት ላይ ማንችስተር ዩናይትድ ከብራይተን ጨዋታቸውን ያከናውናሉ።
ሁለቱም ቡድኖች የውድድሩ ጉዟቸውን ሶስተኛ ዙር ላይ ይጀምራሉ።
ከዚህ ቀደም ባደረጓቸው ሶስት ጨዋታዎች ማንችስተር ዩናይትድ በሁለቱ ድል ሲቀናው አንድ ጊዜ አቻ ተለያይተዋል።
እ.አ.አ በ2020 ለመጨረሻ ጊዜ በተገናኙበት የአራተኛ ዙር መርሐ ግብር ማንችስተር ዩናይትድ 3 ለ 0 አሸንፏል።
ስኮት ማክቶሚናይ፣ ሁዋን ማታ እና ፖል ፖግባ በወቅቱ ግቦቹን ለዩናይትድ ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ናቸው።
ማንችስተር ዩናይትድ ስድስት ጊዜ ውድድሩን አሸንፏል።
በአንጻሩ ብራይተን በካራባኦ ካፕ ትልቁ ውጤቱ እ.አ.አ 1978/79 የውድድር ዓመት ሩብ ፍጻሜ የደረሰበት ነው።
ኤቨርተን ከዎልቭስ እና ፍሊትውድ ከሼፍልድ ዩናይትድ በተመሳሳይ ምሽት 3 ሰዓት ከ45 ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ኮቨንተሪ ሲቲ ከአስቶንቪላ ምሽት አራት ሰዓት ላይ በኮቨንተሪ ቢውልዲንግ ሶሳይቲ አሬና ይጫወታሉ።