የወቅቱ የካራባኦ ካፕ አሸናፊ ማንችስተር ሲቲ ከኖርዊች ሲቲ ጋር ይጫወታል - ኢዜአ አማርኛ
የወቅቱ የካራባኦ ካፕ አሸናፊ ማንችስተር ሲቲ ከኖርዊች ሲቲ ጋር ይጫወታል
አዲስ አበባ፤ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ):- የእንግሊዝ ካራባኦ ካፕ ሶስተኛ ዙር መርሐ ግብር ዛሬ ይጠናቀቃል።
ምሽት 3 ሰዓት ከ30 ላይ ማንችስተር ሲቲ ከኖርዊች ሲቲ በኢትሃድ ስታዲየም ይጫወታሉ።
ባለሜዳው ማንችስተር ሲቲ የወቅቱ የዋንጫ ባለቤት ነው።
በእንግሊዝ ሻምፒዮንሺፕ (ሁለተኛ የሊግ እርከን) የሚገኘው ኖርዊች ሲቲ በሁለተኛው ዙር ካርዲፍ ሲቲን 2 ለ 1 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር ተሸጋግሯል።
ሁለቱም ቡድኖች ከዚህ ቀደም በካራባኦ ካፕ አምስት ጊዜ የተገናኙ ሲሆን ማንችስተር ሲቲ በሶስቱ ሲያሸንፍ በቀሪ ሁለት ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል።
ቡድኖቹ ለመጨረሻ ጊዜ በውድድሩ ላይ የተገናኙት እ.አ.አ በ2007 ነው።
በወቅቱ በሶስተኛው ዙር ባደረጉት ጨዋታ በጆርጅ ሳማራስ ጎል ማንችስተር ሲቲ 1 ለ 0 አሸንፏል።
ማንችስተር ሲቲ ዘጠኝ ጊዜ ዋንጫውን በማንሳት ከሊቨርፑል (10 ዋንጫ) በመቀጠል የውድድሩ ስኬታማ ክለብ ነው።
ኖርዊች ሲቲ እ.አ.አ በ1962 እና በ1985 ውድድሩን አሸንፏል።
በተጨማሪም እ.አ.አ በ1973 እና 1975 ለፍጻሜ ደርሶ ሽንፈት አስተናግዷል።
ማንችስተር ሲቲ ጨዋታውን የማሸነፍ ሰፊ የቅድሚያ ግምት አግኝቷል።
የ28 ዓመቱ ሩበን ሪካርዶ ጨዋታውን በዋና ዳኝነት ይመሩታል።