ቀጥታ፡

ማንችስተር ዩናይትድ ከካራባኦ ካፕ ውድድር ተሰናበተ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ካራባኦ ካፕ የሶስተኛ መርሐ ግብር ብራይተን ማንችስተር ዩናይትድን 3 ለ 2 አሸንፏል።

ትናንት ማምሻውን በኦልድትራፎርድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሼ ሌሲ እና ሜሰን ማውንት ባስቆጠሯቸው ጎሎች ማንችስተር ዩናይትድ 2 ለ 0 መምራት ችሎ ነበር።

ቻራላምፖስ ኮስቱላስ፣ ፓስካል ግሮስ እና ማክሲም ዲካይፐር ከመረብ ላይ ባሳረፏቸው ጎሎች ብራይተን አሸናፊ ሆኗል።

የግሮስ እና ዲካይፐር ጎሎች ከእረፍት መልስ የተቆጠሩ ናቸው።

ውጤቱን ተከትሎ ብራይተን ወደ አራተኛው ዙር አልፏል።

የስድስት ጊዜ የውድድሩ አሸናፊ የሆነው ማንችስተር ዩናይትድ በሶስተኛው ዙር ተሰናብቷል።




በሌሎች መርሐ ግብሮች አስቶንቪላ ኮቨንተሪ ሲቲን 3 ለ 1፣ ኤቨርተን ዎልቭስንና ፍሊትውድ ሼፍልድ ዩናይትድን በተመሳሳይ 1 ለ 0 በማሸነፍ ቀጣዩን ዙር ተቀላቅለዋል።

የካራባኦ ካፕ የሶስተኛ ዙር መርሐ ግብር የወቅቱ የዋንጫ ባለቤት ማንችስተር ሲቲ እና ሌስተር ሲቲ ነገ በሚያደርጉት ጨዋታ ይጠናቀቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም